Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

‹‹የአንዳርጋቸው ጽጌን የሞት ቅጣት ሊያፀኑ የሚችሉት ፕሬዚዳንቱ ናቸው›› ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ

$
0
0

ባለፈው ዓርብ በጽሕፈት ቤታቸው ከጋዜጠኞች ጋር የተወያዩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የሞት ቅጣት ሊፀና የሚችለው በፕሬዚዳንቱ ይሁኝታ ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ላይ ያላት የመሪነት ሚና እንዳልቀነሰ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ መንግሥታቸው የአገር ውስጥ የግል ዘርፉን ለማበረታታት እየሠራ እንደሆነና የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን እያሰረ ያለው በፖለቲካ አቋማቸው የተነሳ እንዳልሆነም ገልጸዋል፡፡ የደመወዝ ጭማሪውን መጠንም ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡

ዓርብ ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ከ9፡00 ጀምሮ ከሁለት ሰዓት በላይ በፈጀው ጋዜጣዊ መግለጫቸው ከጋዜጠኞች በርካታ ጥያቄዎችን ያስተናገዱ ሲሆን፣ ከእነዚህም አንዱ ሪፖርተር የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ በድጋሚ የማይታይ ከሆነ የሞት ፍርዱ ተፈጻሚ ይሆናል ወይ? ሲል የጠየቃቸው ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሞት ፍርድ ተፈጻሚ የሚሆነው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ካፀደቁት በኋላ እንደሆነ አስታውሰው፣ ይኼን ጥያቄ መመለስ የሚችሉት ፕሬዚዳንቱ ብቻ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ የነበራት ተሰሚነትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት ስለመቀነሱ የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በደፈናው የኢትዮጵያ ተቀባይነት ቀንሷል ከማለት ይልቅ በየትኛው ዘርፍ እንደሆነ ተለይቶ ጥያቄው ቢቀርብ የተሻለ እንደሚሆን ካስረዱ በኋላ፣ በእሳቸው እምነት የኢትዮጵያ የመሪነት ሚና አሁንም እየቀጠለ ለመሆኑ ማሳያ የሚሏቸውን ጉዳዮች ጠቅሰዋል፡፡ የመጀመርያው ጉዳይ በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ላይ የአፍሪካውያንን ድምፅ ማሰማት ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ተፅዕኖ አሁንም ጉልህ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ እንደ ምሳሌም በዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር በሚመራው የአረንጓዴ ዕድገት ፎረም ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትሯ አማካይነት የቦርድ አባል ሆና መመረጧን ጠቅሰዋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2015 የሚጠናቀቀው የምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች ከተጠናቀቀ በኋላ ስለሚቀጥለው ሁኔታ አፍሪካ ያላትን ድምፅ ለማሰማት ከተወከሉት አገሮች መካከል አንዷ ኢትዮጵያ እንደሆነችም አመላክተዋል፡፡ የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት (አይሲሲ) አፍሪካ ላይ በተለየ ሁኔታ ትኩረት አድርጎ መሥራቱን ለመቃወም የተደረገውን ትግል በስኬት ለመደምደም፣ በተለይ የኬንያ ፕሬዚዳንት ክስ በሥልጣን ላይ እስካሉ ድረስ እንዳይነሳ ለማድረግ የኢትዮጵያ መሪነት ሚና ጉልህ እንደነበርም ጠቅሰዋል፡፡ ይኼን ስኬት የጠቀሱት ባለሥልጣናት ከተጠያቂነት ቢያመልጡ ደስተኛ ስለሆኑ ሳይሆን፣ የአገሮች ሉዓላዊነትና የሕዝቦች ምርጫ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ስለሆነ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እስርም የተለየ ፖለቲካ ስለሚያራምዱ የተወሰነ ውሳኔ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያንና አካባቢውን በሽብርተኝነት ለማናጋት በተቀናጀ ሁኔታ ከሚሠራው የሽብር መረብ ጋር ግንኙነት ፈጥረው በመገኘታቸው እንደሆነ አመልክተዋል፡፡ የጦማርያኑና የጋዜጠኞቹ ጉዳይም ከተመሳሳይ መረብ ጋር የተገናኘ እንደሆነ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ መንግሥታቸው የዜጎችን ሰላማዊ ኑሮ ለማረጋገጥ የሽብርተኝነት መረቡን ለመበጣጠስ የጀመረውን ስኬታማ ሥራ አጠናከሮ እንደሚቀጥልም ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ሥር ተወሽቀው የሽብር ተግባር ላይ ተሳታፊ የነበሩ ጥቂት ግለሰቦች ታሰሩ ማለት የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ታሰሩ ማለት እንዳልሆነም በመጠቆም፣ ለምርጫ 2007 ገዥው ፓርቲና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እያደረጉት ያለው ዝግጅት ሊስተጓጎል እንደማይችልም አመላክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት አቶ አንዳርጋቸውና ግንቦት 7 ብቻቸውን ኢትዮጵያ ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ከባድ እንደማይሆን ቢገባውም፣ እነዚህ የሽብር ቡድኖች የተደገፏቸውና የሚተማመኑባቸው አገሮች ጋር ከሠሩ ጉዳቱ ከባድና አካባቢያዊ ተፅዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ግን አስረድተዋል፡፡ በዚህም የተነሳ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በቁጥጥር ሥር መዋል በሽብርተኞቹ ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ ከባድ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ከአስመራ ወደ ደቡብ ሱዳን ለመዘርጋት የተሞከረው መረብ እየተበጣጠሰ ለመምጣቱ የአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ማሳያ እንደሆነም አመልክተዋል፡፡ በቅርብ ጊዜያት የጋምቤላ ንቅናቄና የኦብነግ አባላት በቁጥር ሥር መዋላቸውም የሽብር ቡድኑ አባላት የሌላ አገር ዜግነት ቢኖራቸውም፣ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም እስከነኩና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ባለው የሽብር ወንጀል እስከተካፈሉ ድረስ ዕርምጃ ከመውሰድ ኢትዮጵያን የሚያቆማት አካል እንደሌለም አስታውቀዋል፡፡ በተለያዩ ሙያዎች ውስጥና በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ በመጠለል የሽብር ወንጀል ላይ ተካፋይ ከሆኑ በኋላ ከተጠያቂነት ለማምለጥ የውጭ ኃይሎችን በተለይም ኤምባሲዎችን በመጠቀም የኢትዮጵያን መንግሥት ለመጠምዘዝ ሙከራዎች እየተደረጉ እንደሆነ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የዜጎችን ሕገ መንግሥታዊ መብት በማክበር ሕጋዊ ዕርምጃ ከመውሰድ የሚያግዳቸው ኃይል እንደሌለ አመልክተዋል፡፡

በተደጋጋሚ የፋይናንስ ችግር የለም በሚል መንግሥታቸው ቢገልጽም፣ በዚህ ችግር በተለይ የአገር ውስጥ የግሉ ዘርፍ እየተጠቃ ስለመሆኑ የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ መንግሥት ለብድር ያስቀመጠውን ገንዘብ አሟጦ ጥቅም ላይ የሚያውል አካል ባልመጣበት ሁኔታ የገንዘብ ችግር አለ ማለት ተገቢ እንደማይመስላቸው ገልጸዋል፡፡ 70 በመቶ የባንክ ብድር ለማግኘት 30 በመቶ የፕሮጀክት ወጪ ማሳየት የሚጠይቅ ሕግ ያለ ሲሆን፣ የውጭ ባለሀብቶች ይህን 30 በመቶ ማሽንን በኮላተራልነት እያቀረቡ እያለ ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች መከልከሉ አግባብነት ያለው ስለመሆኑ የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የውጭ ባለሀብቶች ፋብሪካ በመንቀል ሲመጡ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስለሚያመጣ የተፈቀደ ቢሆንም ይህን የማድረግ አቅም ያለው የአገር ውስጥ ባለሀብት እስከመጣ ድረስ መንግሥት ለአገር ውስጥ ባለሀብቱ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚያጤነውም ቃል ገብተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ መንግሥታቸው ይፋ ባደረገው የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ጭማሪ መጠን ላይ የተጠየቁ ሲሆን፣ በሐምሌ ወር መጨረሻ እስኪገለጽ ድረስ የመንግሥት ሠራተኞች በትዕግሥት እንዲጠባበቁ ጠይቀው፣ ገና የደመወዝ ጭማሪው መጠን ሳይታወቅ በአንዳንድ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ መታየቱ አሳሳቢ መሆኑን ግን ተቀብለዋል፡፡ መንግሥት የደመወዝ ጭማሪ ያደረገው ባለፉት ሁለት ዓመታት በገንዘብና በፊሲካል ፖሊሲው እንዲሁም በአስተዳደራዊ ዕርምጃዎች አማካይነት የዋጋ ግሽበቱን ኢኮኖሚያዊ ጤንነት ጋር በተጣጣመ መልኩ በአንድ አኃዝ እንዲገደብ ካደረገ በኋላ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡ የዋጋ ግሽበቱ የመንግሥት ሠራተኛውን ብቻ ሳይሆን በዝቅተኛ ደመወዝ ኑሯቸውን የሚገፉ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ እንደሚጎዳ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም፣ የዋጋ ግሽበትን ጉዳት በሚፈለገው መጠን መቀነስ ባይቻልም አነስተኛ ገቢ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ገቢያቸው እንዲጨምርና የሥራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው ለማድረግ መንግሥታቸው የተለያዩ ጥረቶችን እያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የደመወዝ ማስተካከያው የሚደረገው የመንግሥት ሠራተኞችን ኑሮ ለማሻሻል ቢሆንም፣ ስግብግብ ነጋዴዎች የሚያደርጉት የዋጋ ጭማሪ ችግር እንዳይፈጥር መንግሥት ቁጥጥር እንደሚያደርግና አደብ እንዲገዙ ለማድረግ ዕርምጃ ሊወስድ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡ ይሁንና በአሁኑ ጊዜ መንግሥት ነጋዴዎቹን የማሳመንና የማስረዳት ሥራ እየሠራ መሆኑን በመጠቆም፣ ከሕጋዊ ዕርምጃ ባለፈ ማግባባት መምረጡን አስረድተዋል፡፡ ሕጋዊ ዕርምጃ የሚወሰደው ስግብግብ ነጋዴዎች ካስገደዱ ብቻ እንደሚሆንም አመላክተዋል፡፡

 

Source: Ethiopian Reporter

ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጡት መግለጫ – ክፍል 1& &2  (ሐምሌ 11/2006 ዓ.ም)


የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ታሰሩ

$
0
0

–ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተጠቁሟል

newsየፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ምክትል ዋና ቃዲ (ምክትል ፕሬዚዳንት) ሼክ አማን ሽፋው ዓለሙ ጉቦ በመቀበል ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ሐምሌ 8 ቀን 2006 ዓ.ም. ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ያቀረበው ክስ እንደሚያስረዳው፣ ምክትል ፕሬዚዳንቱ 50,000 ብር ጉቦ ጠይቀው 10,000 ብር ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፡፡

እንደ ኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ክስ ምክትል ዋና ቃዲው፣ በሥራ ኃላፊነታቸውና ግዴታቸው ማድረግ የሚገባቸውን አላደረጉም፡፡ በመሆኑም ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት አስበው የግል ተበዳይ ናቸው የተባሉት ወ/ሮ ሮዛ መሐመድ ጁሃር፣ የጋብቻ ሰነዳቸው የሸሪዓ ስለመሆኑ ተመስክሮ እንዲሰጣቸው ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ማመልከታቸው በክሱ ተጠቅሷል፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ማስረጃውን ሊሰጣቸው ባለመቻሉ ግለሰቧ አቤቱታቸውን ለጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ማቅረባቸውም በክሱ ተገልጿል፡፡ ምክትል ዋና ቃዲው ጉዳዩን ለመጨረስ 50,000 ብር ጠይቀው፣ ከግለሰቧ ጋር ከተስማሙ በኋላ ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ከምሽቱ 11፡00 ሰዓት፣ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 ልዩ ቦታው አስኮ ነዳጅ ማደያ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ፣ ከግለሰቧ 10,000 ብር ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ክሱ በዝርዝር ያስረዳል፡፡

ተጠርጣሪው ሐምሌ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርበው የዋስትና መብታቸው ታልፎ፣ ማረሚያ ቤት እንዲቆዩና ሐምሌ 15 ቀን 2006 ዓ.ም. ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡

በክሱ ላይ የተጠቀሰው የወንጀል ሕግ ቁጥር 408(2) ከሰባት እስከ 15 ዓመታት በእስራት ሊያስቀጣ እንደሚችል ተደንግጓል፡፡

Source: Ethiopian Reporter

ለአዳማ ከተማ አዲስ ማስተር ፕላን እየተዘጋጀ ነው

$
0
0

-የ20/80 እና የ40/60 ኮንደሚኒየም ቤቶች ግንባታ ይጀመራል

daየአዳማ ከተማ አስተዳደር አዲስ ማስተር ፕላን በማዘጋጀት ላይ እንደሆነ አስታወቀ፡፡ የአዳማ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ የሱፍ ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንደገለጹት፣ መስተዳደሩ የከተማዋን ዕድገት ያገናዘበ አዲስ

ማስተር ፕላን በማዘጋጀት ላይ ነው፡፡ አዲሱ ማስተር ፕላን የመኖሪያ ክልሎች፣ የንግድ ማዕከላትና የኢንዱስትሪ ዞኖችን ያካተተ እንደሆነ የገለጹት አቶ አህመድ፣ የኒውዮርክ ዩኒቨርሲቲ የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚያደርግና የዓለም ባንክ ደግሞ ለፕሮጀክቱ ወጪ የሚውል ገንዘብ እንደሚያቀርብ አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም የአዳማ ከተማና የአሜሪካ ዴንቨር ከተማ በተለያዩ ዘርፎች ለመተባበር የሚያስችላቸውን የእህትማማች ከተሞች ስምምነት ለመፈራረም በሒደት ላይ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ አዲሱ የከተማ ማስተር ፕላን አዳማን ከዓለም አቀፍ ከተሞች ጋር የሚያስተካክላት እንደሆነ አክለው ገልጸዋል፡፡

የአዳማ ከተማ የኢትዮ፣ ጂቡቲ የባቡር መስመር ግንባታ ተከትሎ በ1908 ዓ.ም. የተቆረቆረች ነች፡፡ ‹‹የስምጥ ሸለቆዋ እንቁ›› የሚል መጠሪያ የወጣላት አዳማ ከተማ 133.6 ካሬ ኪሎ ሜትር ሥፋት ሲኖራት፣ የሕዝብ ብዛቷ 300,000 ያህል ይገመታል፡፡

የከተማዋ መስተዳደር አዳዲስ የአስፓልትና የኮብልስቶን መንገዶች በመገንባት ላይ እንደሚገኝ፣ በከተማዋ ዙሪያ የአሥር ኪሎ ሜትር የቀለበት መንገድ በመገንባት ላይ እንዳለ፣ የጎርፍ መከላከል ሥራዎችና የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች ግንባታ እየተካሄደ እንደሆነ፣ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ እየተካሄደ እንደሆነ፣ የአዳማ ከተማ የቤቶች ልማት ጽሕፈት ቤት ተወካይ አቶ ለሜሳ ቱራ ለሪፖርተር የገለጹ ሲሆን፣ ጽሕፈት ቤቱ የ20/80 እና የ40/60 የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ ለመጀመር በዝግጅት ላይ እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ መስተዳደር የጀመረውን የ20/80 እና የ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም እንደ ሞዴል በመውሰድ በአዳማ፣ በሻሸመኔና በሌሎች 38 የኦሮሚያ ከተሞች ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ እንዲደረጉ በጨፌ ኦሮሚያ (የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት) መወሰኑ ይታወሳል፡፡

በአዳማ ከተማ የቦታ መረጣ ሥራ እንደተካሄደ እንደሆነ የገለጹት አቶ ለሜሳ፣ ምን ያህል ቤቶች እንደሚገነቡና የፕሮጀክቱ ጠቅላላ ወጪ ጥናት እንደሚካሄድ አስታውቀዋል፡፡ የቤቶቹ ግንባታ በ2007 ዓ.ም. እንደሚጀመር አክለው ገልጸዋል፡፡ ቀደም ሲል መስተዳደሩ 2,769 ኮንደሚኒየም ቤቶች መገንባቱንና በ2004 ዓ.ም. ባካሄደው የቤት ፈላጊዎች ምዝገባ 16,000 ነዋሪዎች እንደተመዘገቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡

- See more at: http://satenaw.com/amharic/?p=1296#sthash.oTXKS2hD.dpuf

የአፍሪካ ነገር – የኢትዮጵያ ነገር

$
0
0

መስፍን ወልደ ማርያም

የካቲት 2006

Prof. Mesfin

መስፍን ወልደ ማርያም

በሃያኛው ምዕተ-ዓመት ላይ የታወቀ የፈረንሳይ ፈላስፋ ነበረ፤ እሱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ በነበረበት ጊዜ ከእሱ ጋር በዩኒቨርሲቲ ሁለት አፍሪካውያን አብረውት ይማሩ እንደነበሩ ይናገራል፤ እነዚህ አፍሪካውያን የፈረንሳይኛ ቋንቋን ልክ አንደፈረንሳዮች እየተናገሩ፣ እንደፈረንሳዮች እያሰቡ ከፈረንሳዮቹ ተማሪዎች ጋር እኩል በትምህርት እየጎለበቱ ነበር፤ በኋላ እነዚህ አፍሪካውያን ወደአገራቸው ተመልሰው ሥልጣን ላይ ሲወጡ ሰፊ አገራቸው ለሁለቱ የተማሩ አፍሪካውያን የማይበቃ ሆነባቸው፤ ስለዚህም አንደኛው የአገር መሪ ሆነና ሌላውን ገደለው፤ የፈረንሳዩ ፈላስፋን ያሳዘነው ትዝብት ነው።

በአለፉት ሃምሳ ዓመታት ውስጥ በአፍሪካ የታየው የሥልጣን ሽኩቻ ለብዙ የአፍሪካ አገሮች የእድገት ማነቆ ሆኖ ቆየ፤ ከአውሮፓውያን ቄሣራዊ ኃይሎች ቅኝ አገዛዝ ነጻ ሲወጡ ከፍተኛ ተስፋ የተጣለባቸው አገሮች ዛሬ ቆመው ቀርተዋል፤ በሰሜን አፍሪካ አልጂርያና ቱኒስያ እንደፈረንሳይ የሚቆጠሩ ናቸው ይባል ነበር፤ እነዚህ ትልልቅ አገሮች ለሁለት ለሁለት ሰዎች የማይበቁ ሆነው የመከራ አገሮች ሆነዋል፤ ከፈረንሳይ ጋር በአደረጉት መራራ ትግል ሕዝቦቹ የከፈሉትን መስዋእትነትና ትግላቸው አሳድሮባቸው የነበረውን የላቀ ተስፋ መሪዎቹ ዋጋ አልሰጡትም፤ (ተመስገን ደሳለኝ በፋክት ቁጥር 33 ‹‹የሕወሓት ሰማዕታት አጭር ማስታወሻ፣) በዚህም ምክንያት እነሱ ለአንድ ወንበር ሲፎካከሩና ተወዳዳሪዎቻቸውን አስረውም ሆነ ገድለው ወንበሩን ለብቻቸው ሲይዙት ቆይተዋል።

በአንድ በኩል ከወንበሩ በሚመነጨው ኃይልና ሀብት መከታን የሚያገኙ መስሏቸው በነበራቸው ተስፋ፣ በሌላ በኩል በምዕራባውያን ኃይሎች ላይ ተማምነው ሕዝባቸውን በመናቃቸው በአረብ አገሮች መሪዎች ላይ በቅርቡ በተከሰተው ወረርሺኝ ብዙዎች ከወንበራቸው ተደፍተዋል፤ የሁሉም አወዳደቅ የከፋ ውርደትን የለበሰ ቢሆንም አንደጋዳፊ ያለ አልነበረም፤ እኛስ ብንሆን በዓለም በሙሉ የተከበሩትን ንጉሠ ነገሥት እንዴት አዋርድናቸው! ያወረዷቸውስ ሰዎች በተራቸው እንዴት ተዋረዱ! ያዋረዱ ሁሉ ይዋረዳሉ፤ ሕዝብን ያዋረዱ ይዋረዳሉ፤ አገርን ያዋረዱ ይዋረዳሉ፤ የሰው ልጅን ያወረዱ ሁሉ ይዋረዳሉ።

ለጭቆናና ለክፋት ሰብአዊ መብቶችን እንደልብ እየጣሱ በጉልበተኛነት መታወቅ የራስን ታሪክ ራስን ዋቢ አድርጎ መጻፍ ነው፤ ያለፉት ባንዶች ተመችቷቸው ስለነበረ ወደፊትም የባንዶች ዕጣ-ፋንታ እንደበፊቱ ይሆናል ማለት ልበ-ደንዳናነት ብቻ ሳይሆን፣ በጥላሸት የጨለመ አእምሮ ብቻ ሳይሆን፣ በዛር ፈረስ ላይ ወጥቶ ወደገደል መጋለብ ነው፤ ከአሁን ወዲያ አገዛዙ ሲከሽፍ ሕዝቡ አብሮ ከከሸፈ በአገዛዙ ማመካኘት አይጠቅምም፤ ሕዝብ ኃላፊነትን መውሰድ አለበት፤ አገር በጥቂት ሰዎች አይገነባም፤ እያንዳንዱ ሰው የድርሻውን ኃላፊነት መቀበል አለበት፤ የእየአንዳንዱ ሰው አስተዋጽኦ አሰፈላጊ ነው።

የእያንዳንዱ ሰው ኃላፊነት ከየት የመጣ ነው? አንደኛ አያት ቅም-አያቶቻችን ይችን አገር ለመገንባትና በነጻነት ለመጠበቅ በሕይወታቸው ሳይቀር የከፈሉት ከባድ መስዋዕት እየቆረቆረን ኃላፊነትን ይጭንብናል፤ በሞታቸው ያስተላለፉልንን ኩራትና ክብር ብናጣ የምናዋርደው እነሱን ብቻ ሳይሆን ራሳችንንም ነው፤ የኃላፊነታችን አንዱ ምንጭ ይህ ነው።

ሁለተኛው የኃላፊነታችን ምንጭ ልጆቻችን ወይም የሚቀጥለው ትውልድ ነው፤ እኛ ከአባቶቻችን የወረስነውን ኩራትና ክብር መጠበቅ አቅቶን ለልጆቻችን ውርደትን እንዳናወርስ ኃላፊነት አለብን፤ ሲሆን የወረስነውን ኩራትና ክብር አዳብረንና አጠንክረን ማቆየትና ለልጆቻችን ማውረስ፣ ቢያንስ ግን የተረከብነውን ማስረከብ ግዴታችን ይሆናል፤ አለዚያ መክሸፍ ይሆናል፤ ኢትዮጵያዊነት ማንነት አይደለም ከተባለ፣ ከኋላችን በሕይወት መስዋእትነት የተረከብነውን ክደናል፤ ከፊታችንም ለልጆቻችን የምናስረክበው የጋራ እሴት የለንም፤ በወጥመድ ውስጥ እንዳለች አይጥ መንፈራፈር ብቻ ነው።

በአገርና በአገዛዝ ሥርዓት መሀከል ያለውን ገደል ማየት የማይችሉ ሰዎች የወጣቱን የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ሲያላሉት፣ የወያኔ ካድሬዎች እየተቀባበሉ ሲያራግቡት ውርደታችን የለበስነውን ክብራችንን እየገለጠ ገብቶ ራቁታችንን እያስቀረን ነው፤ ኢትዮጵያም እንደኮንጎ፣ ኢትዮጵያም እንደኒጄር፣ ኢትዮጵያም እንደመሀከለኛው አፍሪካ፣ ኢትዮጵያም እንደሩዋንዳ፣ ኢትዮጵያም እንደሱዳን፣ ኢትዮጵያም እንደሶማልያ ወደትርምስ እየዘቀጠች መሆኑን ምስክሮች ሆነን እያየን ነው፤ ምዕራባውያን ኃይሎች ለውርደታችን እንጂ ለክብራችን እንደማይጠቅሙ በኢራቅ፣በአፍጋኒሰታን፣ በፓኪስታን ለሆነው ሁሉ ምስክሮች ሆነን እያየን ነው።

ከሃምሳ ዓመታት ያህል በፊት በማናቸውም ነገር የአፍሪካ መሪዎች ሆነን የጀመርነው ሰዎች ዛሬ በዚህ ትልቅ የአፍሪካ አህጉር ኔልሰን ማንዴላ ከሚባል ትልቅ ሰው በቀር ስሙ በዓለም የሚጠራ አለመኖሩ የውርደታችንን ጥልቀት ያመለክታል፤ በኔልሰን ማንዴላ ትልቅነት ላይ ብቻ ሳይሆን በኔልሰን ማንዴላ ህልውና ላይም ኢትዮጵያ ማኅተምዋን በጉታ ዲንቃ ሃይማኖት አማካይነት ማሳረፍዋን አልዘመርንበትም፤ በአብዲሳ አጋ የአውሮፓ አርበኝነት አልዘመርንበትም፤ በዘርዓይ ደረስ የአውሮፓ አርበኝነት አልዘመርንበትም፤ በአበበ አረጋይ አርበኝነት አልዘመርንበትም፤ በበላይ ዘለቀ ስቅለት እንጂ በአርበኝነቱ አልዘመርንለትም፤ ኢትዮጵያን የጠበቋትን ልጆቿን፣ ኢትዮጵያን ያስከበሯትን ልጆቿን ታሪክ ረግጦና ችላ ብሎ ለባንዶችና ለባንዶች ልጆች ውዳሴ ከርስ የሚዘምር ትውልድ ውርደትን ይለብሳል፤ በኀልዮም ሆነ በነቢብ፣ ወይም በገቢር፣ አውቆም ይሆን ሳያውቅ አገሩንና ወገኑን ያዋረደን ማንም አያከብረውም፤ በሆዳሞች የተገነባውና የሚገነባው ሁሉ ከርሰ-መቃብር ውስጥ ይፈራርሳል።

የዛሬ ሁለት መቶ ዓመታት ግድም አንድ የአንግሊዝ ፈላስፋ ሕዝብን ስለማዶልዶም የሚከተለውን ብሎ ነበር፤ ዛሬ ለኛ የሚናገር ይመስላል፡–

ለጥሩ ዓላማም ቢሆን እንደፈለገ የሚያገላብጣቸው የተገሩ ለዘብተኛ መሣሪያዎች እንዲሆኑለት የራሱን ሕዝብ የሚያቀጭጭ ሀገረ-መንግሥት በትንንሽ ሰዎች ምንም ትልቅ ነገር ማከናወን አንደማይቻል ይገነዘባል፤ መሣሪያው በቀላሉ እንዲሠራለት ሁሉንም ነገር መስዋእት በማድረግ መሣሪያውን ፍጹም አድርጎ ሲስል  ያወደመው የሕይወት ኃይል በመጨረሻ ላይ  ለምንም ነገር አይጠቅመውም፡፡  

በእንግሊዝኛው  … a state which dwarfs its men, in order that they may be more docile instruments in its hands even for beneficial purposes, will find that with small men no great thing can really be accomplished; and the perfection of the machinery to which it has sacrificed everything will in the end avail it nothing, for want of the vital power which, in order that the machine might work more smoothly, it has preferred to banish.

በሃያ አንደኛው ምዕተ ዓመትም ኢትዮጵያ በረጅም ታሪክዋ ሲከሽፍባት የቆየውን ሥልጣንን የመግራት ብቃት ማግኘት አቅቷት ትናንት ከተፈጠሩ አገሮች ተርታ ተሰልፋ ትገኛለች፤ ይህ ውርደት የማይሰማው ባለሥልጣን ነኝ-ባይ ከነሎሌዎቹ በውርደት ባሕር እየሰመጠ ነው፤ የሚሰምጠው ሎሌዎቹን ብቻ ይዞ አይደለም።

የኢትዮጵያው ጓንታናሞ ቤይ ‹‹ ማዕከላዊ ››

$
0
0

ዳዊት ሰለሞን

maeklawi prison

ማዕከላዊ

አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሂዩማን ራይትስ ዎች እንዳለፉት አመታት ሁሉ የኢትዮጵያን መንግስት የሚያስቆጣ ባለ 70 ገጽ ሪፖርት ከሁለት ሳምንታት በፊት ይፋ አድርጓል፡፡ የተቋሙን ሪፖርት ከሌላው ጊዜ የተለየ የሚያደርገው በአንድ ርዕሰ ጉዳይ በአንድ ተቋም  በማጠንጠኑ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የወንጀል ምርመራ ማዕከሎች መካከል በአዲስ አበባ ዕምብርት በሚገኘው ማዕከላዊ ተጠርጣሪዎች ግርፋት፣ማሰቃየትና ድብደባ እንደሚፈፀምባቸው ሪፖርቱ አትቷል፡፡

አሜሪካ በሁለቱ የኒውዮርክ መንትያ ህንጻዎቿ ላይ በአልቃይዳ የተቀነባበረ ጥቃት ከተሰነዘረባት በኋላ ‹‹ሽብርተኛ›› በማለት የሰየመችውን ቡድን አባላት ከምድረ ገጽ ለማጥፋት በጆርጅ ቡሽ ፊት አውራሪነት የሽብር ቡድኑ ዋነኛ መጠለያ ያለቻችትን አፍጋኒስታንን ወረረች፡፡ በዘመቻው በቁጥጥር ስር የዋሉ የአልቃይዳ አባላትና ተጠርጣሪዎች በጄኔቭ ስምምነት መሠረት በህግ የመዳኘት መብት እንዳያገኙ ለማድረግ የቡሽ አስተዳደር ከግዛቱ ውጪ በኩባ ድንበር የሚገኘውን ጓንታናሞ ቤይን ከዛሬ አስር አመታት በፊት ከጦር ካምፕነት ወደ ማሰቃያ ማዕከልነት አሸጋገረው፡፡

‹‹በሽብርተኝነት›› ተጠርጥረው ወደ ጓንታናሞ ቤይ እንዲገቡ የተደረጉ ተጠርጣሪዎች የዜግነት ስብጥር የሚበዛበት ቢሆንም አንዳንድ መረጃዎች የሚበዙት ተጠርጣሪዎች አፍጋናዊያን፣ ኢራቃዊያን፣ የመናዊያን፣ ሊቢያዊያንና ግብጻዊያን ስለመሆናቸው ይጠቁማሉ፡፡ ከታሳሪዎቹ መካከል 99 ከመቶ ያህሉም የሙስሊም እምነት ተከታዮች ናቸው፡፡

አሜሪካ በህገ መንግስቷ ተጠርጣሪዎች ዋስትና፣ ጠበቃ፣ ጎብኚና ነጻ የፍትህ ስርዓት  እንዲያገኙ ለማድረግ ቃል የገባች ቢሆንም በጓንታናሞ ቤይ የተጣሉ ተጠርጣሪዎች ለረዥም አመታት ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እንዳይታይ፣ ጎብኚዎች እንዳያገኙ፣ ግርፋትና ስነ ልቦናዊ የሆነ ቶርቸር እንዲደርስባቸው በማድረግ ከህገ መንግስቷ የተጣረሰ ኢ ሰብአዊ ድርጊት ስትፈጽምባቸው ቆይታለች፡፡

እስረኞቹን አጋቾቻቸው እጅና እግሮቻቸውን ለ24 ሰዓታት በሰንሰለት በማሰር ሲያሰቃዩአቸው ቆይተዋል፣ በረመዳን የጾም ወቅት እስረኞቹ የሃይማኖታቸውን ትዕዛዝ ለመፈጸም ከምግብ ተከልክለው ወሩን ለማሳለፍ ቢዘጋጁም የማጎሪያው ሃላፊዎች ሀይልን በመጠቀም በቀን ለሁለት ጊዜያት ምግብ እንዲመገቡ በማድረግ ጥቃት ፈጽመውባቸዋል፡፡

የአሜሪካ መንግስት (የቡሽ አስተዳደር) ይህንን ግፍ በጓንታናሞ ቤይ ሲፈጽም የከረመው በገዛ ዜጎቹ ላይ ባይሆንም በሰብአዊ ፍጥረት ላይ የሚደርስን በደል የአገሪቱ ህዝብ በራሱ እንደደረሰ በመቁጠር የቡሽን የበቀል እርምጃ በተለያዩ መድረኮች ሲቃወም ተስተውሏል፡፡

ጥቁር አሜሪካዊው ባራክ ሁሴን ኦባማ ለፕሬዝዳንትነት ያደርጓቸው በነበሩ ቅስቀሳዎች ‹‹ጓንታናሞን›› ከተመረጡ እንደሚዘጉ መግለጻቸውም በአስገራሚ ሁኔታ የአገራቸውን ህዝብ ድጋፍ እንዲያገኙ ረድቷቸዋል፡፡ ኦባማ የማሰቃያ ማዕከሉን ለመዝጋት ፕሬዝዳንት ሆነው ከተመረጡ በኋላ እንቅስቃሴ ቢጀምሩም ከተፎካካሪዎቻቸው ጠንከር ያለ ተቃውሞ ማስተናገዳቸው አልቀረም፡፡ አሁን የኦባማ ምኞት እውን ሆኖ ጓንታናሞ ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ተዘግቷል፡፡ ፍትህ ተነፍገው የወታደሮች መጫወቻ ሆነው የቆዩ ተጠርጣሪዎችም በወታደራዊ ፍርድ ቤቶች እንዲቀርቡ ተደርገዋል፣የሚበዙትም ከአልቃይዳ ጋር ምንም አይነት የሚያገናኛቸው መስመር እንደሌለ በመረጋገጡ ከቤተሰቦቻቸው እንዲቀላቀሉ ተደርገዋል፡፡

 

      በኢትዮጵያው ጓንታናሞ ቤይስ?

የዛሬው የአፍሪካ ህብረት ህንጻ የቆመበት መሬት በዘመነ ደርግ ላቅ ያለ የስቃይ ምድር ነበር፡፡ ከርቸሌ ብዙ ሺህ ወጣት ኢትዮጵያዊያንን በልታለች፣ በወታደራዊው መንግስት ላይ ተቃውሞን ያሰሙ ዜጎች በከርቸሌ ፊደል የማይተርከውን ስቃይ አስተናግደዋል፡፡ በኢትዮጵያውያኑ የለቅሶና የደም መሬት ላይ የአፍሪካ መሪዎች አመታዊ ስብሰባቸውን ለማድረግ ሲመጡ በቻይና እርዳታ የተሰራላቸውን ህንጻ ውበት እንጂ በከርቸሌ የፈሰሰው ደም፣ የባከነው አእምሮና የተፈፀመው ግፍ አይታሰባቸውም፡፡ በዘመነ ደርግ ለከርቸሌ እስረኞችን ይመግብ የነበረው የምርመራ ማእከል ደግሞ ማዕከላዊ ነው፡፡

ማዕከላዊን በመገንባት የተቃዋሚዎቻቸውን በአደባባይ ለመገንፈል ያሰፈሰፈ ቁጣ መሸበብ የጀመሩት አጼ ኃይለስላሴ ናቸው፡፡ ንጉሱ ተማሪዎችን፣ አመጽ ያማራቸውን ወታደሮች፣ ስልጣኔ የሸተታቸውን ሰራተኞችና የባላባት ጭሰኛ መሆን የመረራቸውን ገበሬዎች በምስጢር ፖሊሶቻቸው አማካኝነት እያደኑ ማስፈራሪያና ግርፊያ ይፈጽሙባቸው እንደነበር ለዚህ ፊቸር ያናገርኳቸው ሰዎች እማኝነታቸውን ሰጥተውኛል፡፡ ደርግ የንጉሱን ወንበር በመገልበጥ ስጣኑን እንደተረከበ የተነሳበትን ተቃውሞ ለማፈን ከሁሉም የማጎሪያ ካምፖች በተሻለ ማዕከላዊን ስለመጠቀሙ በዛ ያሉ ምስክሮችን መቁጠር ይቻላል፡፡

የኢህአፓ ወጣቶች በማዕከላዊ የሚያውቁትን ምስጢር እንዲያወጡ፣ያልተያዙ ጓደኞቻቸውን እንዲጠቁሙ በሚል በወታደሮች ተደብድበዋል፣ ሴቶቹ ተደፍረዋል፣ በኤሌከትሪክ ሽቦ ተጠብሰዋል፣ ጥፍሮቻቸው በጉጠት እንዲነቀሉ ተደርገዋል፣ ሰውነታቸው ተገልብጦ ውስጥ እግራቸው በበሬ ቆለጥ ተገርፏል፡፡ ድብደባውን መቋቋም ተስኗቸው ይህችን ጨካኝ አለም የተሰናበቱ የት የሌለ ናቸው በማዕከላዊ፡፡የወቅቱ የምርመራ ሰራተኞች ብቃት የሚለካው እየገረፉና እያሰቃዩ በሚያገኙት መረጃ እንጂ መረጃውን ለማግኘት በሚጠቀሙት ፖሊሳዊ የምርመራ ጥበብ አልነበረም፡፡ይህ ጥበብም እነሆ እስካሁን ድረስ እየተወራረሰ ይገኛል፡፡

በ1983 የሰርዓት ለውጥ ተደርጎ ራሱን ነጻ አውጪ በማድረግ የሚቆጥረው ኢህአዴግ ስልጣነ መንግስቱን ሲቆናጠጥ ማዕከላዊ ዑደቱን እንዲያቋርጥ አለመደረጉን በየጊዜው ከማዕከላዊ የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡

በ1987 ዓ.ም የፀደቀው ህገ መንግስት ተጠርጣሪዎች ህገ ወጥ ለሆነ አያያዝ እንደማይደረጉ፣ ኢሰብአዊ የሆነ ጥቃት እንደማይደርስባቸው፣ በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ፣ በምርመራ ወቅት የሰጡትን የእምነት ክህደት ቃል በፍርድ ቤት መለወጥ እንደሚችሉ ቢደነግግም በማዕከላዊ እነዚህ ህገ መንግስታዊ መብቶች ሆን ተብለው እንደሚጣሱ በምርመራ ጣብያው ዘግናኝና የሰቆቃ ጊዜያትን ያሳለፉ ሰዎች ይናገራሉ፡፡

ሂዩማን ራይትስ ዎች ላወጣው ሪፖርት እማኝ እንደሆኑ የተነገረላቸው 35 በማዕከላዊ የነበሩ እስረኞችም የተናገሩት ለወራት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ መቆየታቸውን፣ በጨለማ ቤት መክረማቸውን፣ ከጠያቂዎች ጋር እንዳይገናኙ መደረጋቸውንና በምርመራ ወቅት ግርፋት፣ ማሰቃየትና ማስፈራራቶች ይፈፀምባቸው እንደነበር ነው፡፡

ከሪፖርቱ ውጪ ጀሚል አክበር፣ ስዬ አብርሃ፣ ደበበ እሸቱና ኢንጂነር ኃይሉ ሻወል በጻፏቸው መጻህፍት በማዕከላዊ የምርመራ ማእከል ቆይታቸው ለጆሮ የሚሰቀጥጡ ስቃዮችን ማለፋቸውንና መስማታቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ የመጻሕፍቱ መልእክት አንድና አንድ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የመንግስታት ለውጥ ቢደረግም ማዕከላዊ ግን የየስርዓቱን ተቃዋሚዎች፣ ጋዜጠኞችና ተቺዎች ማሰቃ በመሆኑ ቀጥሏል፡፡

      ጣውላ፣ ጨለማ ቤትና ሸራተን በማዕከላዊ

በማዕከላዊ የምርመራ ማዕከል እንዲገቡ የተፈረደባቸው ዜጎች ቆይታ ለሚያደርጉባቸው ክፍሎች ተገቢ ነው ያሏቸውን ስያሜዎች አውጥተውላቸዋል፡፡ ጨለማ ቤት እጅግ ቀዝቃዛና ዘና ብሎ ለመተኛት የማያወላዳ የተፈጥሮ አልያም የሰው ሰራሽ ብርሃን አልቦ ነው፡፡ ወደዚህ ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቀንና ሌሊት በጨለማ የሚዋጡ በመሆናቸው ሰዓት፣ ቀንና ምሽትን ለመለየት ይቸገራሉ፡፡ የቅንጅቱ ሊቀመንበር የነበሩት ኃይሉ ሻውል በቅርቡ ባሳተሙት መጽሐፍ ለ28 ቀናት ጨለማ ቤት እንዲቆዩ መደረጋቸውን በመጨረሻም መርማሪዎቹ ‹‹መብራት የሚሰራልን አጥተን ነው ይቅርታ›› በማለት አምፑል በማስገባት እንዳበሩላቸው ገልጸዋል፡፡ እንደ ሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ሪፖርት ከሆነ በዚህ ጨለማ ክፍል የቆዩ ሰዎች ጊዜያቸውን በማጠናቀቅ ወደ ውጪ ሲወጡ ለከፍተኛ የአይን ህመም ይዳረጋሉ፡፡

ጣውላ ቤት የተሻለ ስፋትና አጋር እስረኛ የሚገኝበት ከመሆኑ ባለፈ በጨለማ የተዋጠ ነው፡፡ ቤቱ ከጣውላ የተሰራ በመሆኑም ድምጽ ከየትኛው ክፍል እንደሚመጣ አይታወቅም፡፡ ይህም እስረኞቹ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እንዲያንጎረጉሩ፣ የመሰላቸውን እንዲናገሩ ይረዳቸዋል፡፡ አንደኛው እስረኛ ለመጸዳዳት ከክፍሉ ወጣ በሚልበት አጋጣሚም ከሌላው እስረኛ ጋር የሚገናኝበት፣ የሚተያይበት በመሆኑም ለታሳሪዎቹ ህይወት እንድትሸታቸው ያደርጋል፡፡ ሸራተን በማዕከላዊ የቅንጦት ክፍል ነው፡፡ የክፍሉ ስፋት በመጠኑ የሚያወላዳ ከመሆኑም በላይ የመብራት ባለቤት ነው፡፡በዛ ያሉ እስረኞች የሚገኙበት በመሆኑም በማዕከላዊ እንደ ቅንጦት ተቆጥሮ ሸራተን ለመሰኘት በቅቷል፡፡ ሸራተን የገቡ እስረኞች በአብዛኛው የምርመራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ በመሆናቸው በጨለማ ቤትና በጣውላ ቤት ያሳለፉትን መከራ እያነሱና እየጣሉ ከሌሎች ታሳሪዎች ጋር ፍርድ ቤት የሚያሳልፍባቸውን ውሳኔ ይጠባበቃሉ፡፡

 

           የመንግስት ምላሽና ሪፖርቶች

ሂዩማን ራይትስ ዎቹ በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ኢሰብአዊ ድርጊቶች እንደሚፈጸሙ ሲያጋልጥ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ የመንግስት ኃላፊዎችም ሪፖርቱን ከመንግስት ተቃዋሚዎች የተሰበሰበና እውነታውን የማያሳይ በማለት ከማጣጣል ተቆጥበው አያውቁም፡፡

የአሜሪካ መንግስት /ስቴት ዲፓርትመንት/ በሚያወጣቸው ሪፖርቶች የእስረኞች አያያዝ እንዳሳሰበው የገለጸባቸው አጋጣሚዎች በዛ ያሉ ናቸው፡፡ በ2007 ኤፕሪል በዊኪሊክስ አማካኝነት የወጣ መረጃም በኢትዮጵያ የሚገኙ እስረኞችን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተሉት የፕሪዝን ፌሎው ሺፕ መስራች ፓስታር ዳንኤል ለአሜሪካ ኤምባሲ ሰዎች መንግስት በእስረኞች ላይ ግርፋት፣ ማስፈራራትና ማሰቃየት እንደሚፈጽም መናገራቸውን አትቶ ነበር፡፡ በቅርቡ ሂዩማን ራይትስ ዎች  ላወጣው ሪፖርት የመንግስት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ሽፈራው በጽሁፍ እንዲሁም የመንግስት ኮሚኒኬሽን ምክትል ኃላፊ አቶ ሽመልስ ከማል  ለኤኤፍፒ በሰጡት ምላሽ ክሱን አጣጥለውታል፡፡

በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ቆይታ አድርገው የነበሩት ሁለቱ ስዊዲናዊያን ጋዜጠኞች ማርቲን ሺብዬና ዮሃን ፒርሰን ‹‹ፖሊስ ሁሉም ነገር የሚያልቀው በፍርድ ቤት እንደሆነ ይናገራል፣ ነገር ግን ሁሉም ነገር የሚሆነው በምርመራ ወቅት ነው፡፡ ፖሊስ በሀይል ተጠርጣሪዎች የተጠረጠሩበትን ጉዳይ መፈፀማቸውን እንዲያምኑ ያደርጋል›› ይላሉ፡፡

በሪፖርቱ ዙሪያ ለኤ.ኤፍ.ፒ በእስር ላይ ስለምትገኘው ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ የተናገሩት ወላጅ አባቷና ጠበቃዋ አቶ አለሙ ጌቤቦ ለሦስት ወራት ያህል ልጃቸውን በማዕከላዊ ማየት እንዳልቻሉ በመጥቀስ በእነዚያ 90 ቀናት ውስጥ ከቤተሰብና ከጠበቃዋ ለይተው ምን ሲፈጽሙባት እንደቆዩ እንደማያውቁ ተናግረዋል፡፡ ርዕዮትን ከሦስት ወራት በኋላ እንዲመለከቷት ሲፈቀድላቸው ተጎሳቁላ ማግኘታቸውንና ለዘጠኝ ቀናት ያህል ምግብ ሳትመገብ መቆየቷን መረዳታቸውን መስክረዋል፡፡

በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ወደ ማዕከላዊ የገቡ ሌሎች ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ከርዕዮት ጋር የሚመሳሰል ታሪክ እንዳላቸው የታሳሪዎቹ ቤተሰቦች ይናገራሉ፡፡

ፓስተር ዳንኤል በእስር ቤቶች ኢሰብአዊ ድርጊት የሚፈጽሙ መርማሪዎች መኖራቸውን መንግስት ከደረሰበት በኋላ የሚበዙትን ከስራ እንዳባረራቸው ለአሜሪካው ዲፕሎማት መናገራቸውን ዊኪሊክስ ቢዘግብም የመረጃ መረቡ ባወጣው ሪፖርት ፓስተሩ ነገሩን ለማድበስበስ ያህል እንደተናገሩት እንደቆጠረባቸው አትቷል፡፡

በምርመራ ላይ የቆዩ ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት በሚቀርቡባቸው አጋጣሚዎች በምርመራ ወቅት ድብደባ፣ ማስፈራራትና ማሰቃየት እንደደረሰባቸው የተናገሩባቸው አጋጣሚዎችም በዛ ይላሉ፡፡  ዳኞች እንዲህ አይነት የመብት ጥሰት አቤቱታ ሲቀርብላቸው ፖሊሶች ላይ ጫን ያለ እርምጃ እንዲወሰድ አለማድረጋቸው የምርመራ ውስጥ ስቃዩ እንዲቀጥል የበኩሉን አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

 

            የእኛ ኦባማ የት ነው?

የኢትዮጵያ መንግስት ኃላፊዎች የሰብአዊ መብት ተቋማት፣ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅቶች አልያም የአለም ባንክ ለሚያወጧቸው ሪፖርቶች የሚሰጧቸው ምላሾች አንድ ጫፍ የረገጡ ናቸው፡፡ የሪፖርቶቹን መውጣት ተከትሎ ጉዳዩን ለማጣራት ገለልተኛ ቡድን እንዲዘጋጅ የተደረገበት ጊዜ የለም፡፡ ጆርጅ ቡሽም እንዲህ ነበሩ፡፡ በጓንታናሞ ለሚፈጸም የሰብአዊ መብት ጥሰት ጆሮ አልነበራቸውም፡፡ ወታደሮቻቸው ሴት እስረኞችን እንደሚደፍሩ፣ ታሳሪዎችን በረመዳን የጾም ወቅት በኃይል እንዲመገቡ ማድረጋቸው፣ ተጠርጣሪዎች ለወራት ፍትህ ሳያገኙ መቆየታቸው ሲነገራቸው ለመስማት አልፈቀዱም፡፡ በፕሬዝዳንቱ እምነት እየተሰቃዩ የሚገኙት ሰዎች ሳይሆኑ ‹‹ሽብርተኞች›› ናቸው፡፡

ኦባማ ግን እንደ ቡሽ በጭፍን ጥላቻ የታወሩ አልነበሩም፡፡ ጓንታናሞ የሰብአዊ መብት ረገጣ የሚፈፀምበትና አሜሪካ ቆሜለታለሁ ለምትለው ዲሞክራሲ ተቃራኒ መሆኑን በመረዳት ጓንታናሞን ላይከፍቱት ቆለፉት፡፡

የእኛው ማዕከላዊ በእኛው ዜጎች እኛው ላይ ኢ- ህገ መንግስታዊና ኢሰብአዊ ድርጊት የሚፈፀምበት ማዕከል ነው፡፡ በጓንታናሞ አሜሪካዊያኑ የገረፉት፣ ያሰቀዩት አፍጋኑን፣ ግብጻዊውን፣ ኢራቃዊውን፣ አፍሪካዊውን ነው፡፡ በማዕከላዊ መሰቃየቱንና ህገ መንግስታዊ መብቱ እንደተጣሰበት የሚናገረው ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ ኦባማ ጓንታናሞን ስለ አሜሪካዊያን አልዘጉትም፡፡ ስለ ፍትህ እንጂ፡፡ የእኛ ኦባማ ለጊዜው እዚህ ነኝ ባይለንም የመጣ ቀን ግን ማዕከላዊን ስለእኛ ይዘጋዋል፡፡

አቶ ግርማ ሰይፉ ለአምባሳደር ጥሩነህ ዜና ደብዳቤ ጻፉ

$
0
0
(ግርማ ሰይፉ)

(ግርማ ሰይፉ)

(ዘ-ሐበሻ) በፓርላማው ውስጥ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ አባል የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ ማሩ በጥርጣሪ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ሰብዓዊ መብት አያያዝ በተመለከተ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ደብዳቤ ጻፉ። ደብዳቤው እንደወረደ ይኸው፦

ሐምሌ 11 ቀን 2006

ለክቡር አምባሳደር ጥሩነህ ዜና
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር
አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡ በጥርጣሪ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ሰብዓዊ መብት አያያዝ ይመለከታል

ክቡር ኮሚሽነር ከሐምሌ አንድ ቀን ጀምሮ በ “ወንጀል” ተጠርጥረዋል በሚል የፓርቲያችን አንድነት ለፍትህና ዲሞክራሲ (አንድነት) የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው እና የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እንዲሁም አቶ አብርሃ ደስታ ከአረና ፓርቲ እና አቶ የሺዋስ አሰፋ ከሰማያዊ ፓርቲ በፖሊስ ቁጥጥር ስር አንደሚገኙ ሰምተዋል ብዬ አምናለሁ፡፡ ይሁን አንጂ ይህን ማመልከቻ እሰከምፅፍበት ሰዓት ድረስ ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ ታሳሪዎች ከህግ አማካሪ እና ቤተሰብ ጋር በህግ በተፈቀደው ስርዓት መሰረት ሊገናኙ አልቻሉም፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ ማንም በሌለበት እና ከህግ አማካሪዎች ጋር ሳይገናኙ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተጠይቆባቸው ወደ ማእከላዊ ሄደዋል የሚል ዜና ቢወጣም አሁንም በትክክለኛ ሁኔታ ፍርድ ቤት ስለመቅረባቸው መረጃ የሚሰጥ አካል አላገኘንም፡፡ አንድ እድ ሰዎች ከምሸቱ በአንድ ሰዓት ፍርድ ቤት ቀርበዋል የሚሉም አሉ፡፡
በዚህ የተነሳም ተሳሪዎች በድብቅ ፍርድ ቤት ቀርበዋል የሚባልበት ሁኔታ እና ይልቁንም ከህግ አማከሪያቸው እንዲሁም ከቤተሰብ ጋር እንዳይገናኙ የተደረገበት ሁኔታ ለከፍተኛ ጥርጣሬ የሚያሳድር ነው፡፡ የእነዚህ ታሳሪዎች በጥርጣሬ የታያዙበትን ወንጅል እንዲያምኑ በኢትዮጵያ ህገ መንግሰትም ሆነ በህገ መንግሰት ተቀባይነት ባገኙ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሰረት ምንም ዓይነት የሀይል እርምጃ እና ህገወጥ የሆነ ምርመራ ማካሄድ አይቻለም፡፡ ሰለሆነም ክቡር ኮሚሽነር በህግ መንግሰት የተፈቀደ ሰብዓዊ መብታቸውን የተነፈጉ እነዚህ ታሳሪዎች ያሉበትን ሁኔታ መስሪያ ቤቶ ክትትል እንዲያደርግ እና ለቤተሰቦች እንዲያሳውቅ አደራ ጭምር እየጠየቅሁ፡፡ የፖሊስ አካላትም ይህን ህገወጥ ክልከላቸውን እንዲያቆሙና ለህግ ተገዢ እንዲሆን እንዲያሳሰቡልን እንጠይቃለን፡፡ በአፋጣኝ ታሳሪዎችን ሁኔታ ማወቅ በታሳሪዎች ላይ ሊደርስ ከሚችል አካላዊም ሆነ ሌላ ማንኛውም ጉዳት ለመታደግ ስለሚረዳ፣ ሀገርም ከዚህ የምትጠቀመው አንድም ነገር ስለማይኖር ክቡርነትዎ አሰፈላጊውን ትኩረት ስጥተው ኃላፊነቶን እንደሚወጡ ተሰፋ አለኝ፡፡

ከማክበር ከሠላምታ ጋር
ግርማ ሠይፉ ማሩ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል

አዲስጉዳይ ቅዳሜ ሐምሌ 12 ቀን 2006 ዓ.ም ዕትሙ (አዲስ ጉዳይ)

$
0
0

ማስታወሻ
awe

ያለፉት ሁለት ዕትሞቻችን በማተሚያ ቤት ችግር ምክንያት ቀናችንን ሳንጠብቅ እሁድ በመውጣታችን አንባቢዎቻችንን ጊዜ እንደተሻማን ቢገባንም ችግሩ የጋራችነው ብለቹ ገበያ ላይ ስንውል ለገዛቹሁንና አስተያየት ለሰጣቹን እናመሰግናለን፡፡ አዲስጉዳይ ሁልጊዜም ታማኝነቷ ለአንባቢዎቿ ነው፡፡
በሐተታ አምዳችን አገራዊ ምርጫ በተቃረበ ቁጥር በአገራችን የፖለቲካ ትኩሳቱ እየጨመረ መሄዱ የተለመደ መሆኑን የቀደሙት ምርጫዎች ምስክሮች ናቸው፡፡ ሰሞኑን የታየው የሦስት ፓርቲ አመራሮች እስር ከእዚህ ጋር ተያያዥነት እንዳለው የተለያዩ ግለሰቦችና ምሁራኖች ይናገራሉ፡፡ ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ 2007 ምርጫ ከመድረሱ በፊት የፖለቲካ ተሳትፎ ያላቸው ጨምሮ ጋዜጠኞችን በሽብተኛ ሕግ በማሰረ ምርጫውን ጠቅልሎ ለማሸነፍ እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ጨምረው ይነጋራሉ፡፡ ጉዳዩን አስመልክተን የምርጫ ዕዳዎች ምርጫ ሲቃረብ፣ውጥረቶች ሲባባሱና እስራቶች ሲበራከቱ ሲል በሽፋን ገፃችን አስፍረናል፡፡
አንድ ሀገር ተተኪ ትውልድ እንዲፈጠርባት ከተፈለገ በቤተሰብ፣በአካባቢና በትምህርት ቤት ልጆች እንዲያነቡ የሚያበረታቱ ለትውልድ ተቆርቋሪ የሆኑ ዜጎች ያስፈልጉናል፡፡ምክንያቱም ያላነበበ ትውልድ ስለራሱ፣ሰለ ሀገሩ ታሪክ የሚናገረው ያጥረዋል፡፡ በተጨማሪም የማያነብ ኀብረተሰብ እንደማይጽፍ ፣የማይጽፍ ኀብረተሰብ ደግሞ እንደማያብና ማንበብና መጻፍ፣አንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች መሆናቸውን የሚዳስስ ጹሐፍ በዐብይ ጉዳይ ገጻችን “ኢትዮጵያ ታንብብ!! የዕውቀትና ያባህል ሕዳሴ በኢትዮጵያ” በሚል ሰፊ ትንታኔ የሚሰጥ ጹሑፍ አስተናግደናል፡፡
የሰሞኑን የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እስርን አስመልክቶ የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዚደንት ከሆኑት ኢንጂነር ግዛቸው ሽፋራው እና ከሰማዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ጋር በቃለምልልስ አምዳችን ተስተናግደዋል፡፡
80 ቀን ያስቆጠረው የስድስት ጦማሪያንና የሦስት ጋዜጠኞች እስር የፍርድ ቤት ውሎና የክሳቸውን ዝርዝር የሚያመልከት በሰሞነኛ አምድ ተስተናግዷል፡፡
በአንድ ጉዳይ ገጻችን እሁድ ከምሽቱ 3፡45 እልፈቱ የተሰማው ታዋቂው የወግ ፀሐፊ፣ደራሲ፣ ጋዜጠኛና መምህር የሆኑት መስፍን ሀ/ማርያም የሕይወት ታሪካቸውን የወግ ‘አባት በወግ’ በወግ ሲሸኝ ብለን አቅርበነዋል፡፡
አምደኞቻችን፡- ዶ/ር ብርሃኔ ረዳኢ “ግራ እግርን ፍለጋ”፣ፊልፖስ ዓይናለም “የባልና ሚስት የእኩልነት መብት”፣ዳንኤል ክብረት “እንደገና እንጋባ”፣አሌክስ አብርሃም “ዘርፌ ቡቲክ!”፣በኃይሉ ገ/እግዚአብሔር “የፓርላማው ኩንግ ፉ” እና ሰሎሞን ተሰማ ጂ. “መልሳይነት”! (ትናትና እና ዛሬ) የሚሉና ሌሎች በርካታ ጹሑፎች ተስተናግደዋል፡፡ —

 

Source-  Addis Guday

ከድምፃችን ይሰማ የተላለፈ ጥሪ፦ “መንግስታዊው ‘ጥቁር ሽብር’የህዝብን የድል ችቦ አያጠፋውም!”

$
0
0

ሰኞ ሐምሌ 14/2006
demtschin yesema 2
ከቀናት በፊት በእለተ ጁምአ በታላቁ አንዋር መስጂድ በመንግስት ታጣቂዎች የተወሰደው ድንበር የለሽ ጭፍጨፋ የሙስሊሙ ህብረሰተብ ሰላማዊ ትግል በታሪኩ ሌላ መጠምዘዣ ውስጥ እንዲገባ ምክንያት እንዲሆን የሚያስገድድ ነው፡፡ በዚህ በመንግስት የደህንነት ኃይሎችና በፖሊስ ሀላፊዎች ከቀናት በፊት ታቅዶ በተወሰደ እርምጃ ከ6 ሺ በላይ የመንግስት ቅጥረኛ ሲቪል ለባሾች እንደተሳተፉበት መገለጹ ይታወሳል፡፡ ቅጥረኞቹ የተከበረው የረመዳን ወር የጁምአ ሰላት ከመሰገዱ በፊት በመስጊዱ ውጫዊ ሰሜናዊ አቅጣጫ ግርግር በማስነሳትና ከፖሊሶች ጋር ከሁለቱም አቅጣጫ ድንጋይ በመወራወር የታለመውን ውጤት ለማምጣት ሞክረዋል፡፡ በዚህም በአካባቢው የነበሩትን ጨምሮ በሁሉም አቅጣጫ የነበሩና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች የጁምአ ሰላታቸውን እንዳይፈጽሙ እክል ከመሆናቸውም በላይ እጅግ በርካታ ጾመኛ ሙስሊሞች ላይ እጅግ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ፈጽመዋል፡፡
በእለቱ በተካሄደው ጭፍጨፋ እንደተለመደው የመንግስት የጦር ሜዳ ስልት ሙስሊሙን ከሁሉም አቅጣጫ በቆረጣ ስልት ለሰላት በተቀመጠበት በመቁረጥ በነፍስ ወከፍ በያዙዋቸው ዱላዎችና የመሣሪያ ሰደፎች ርህራሄ አልባ በሆነ ሁኔታ ደብድበውታል፤ ጭፍጨፋ አድርሰውበታል፡፡ ጭፍጨፋው እድሜ፣ ጾታ፣ አስተሳሰብና፣ የአካል ሁኔታን ሳያገናዝብ ነበር የተወሰደው፡፡

ይህን ጭፍጨፋና ክስተቱ የደረሰበትን እለት ማሰብና በሌላ የታሪክ የቀን መቁጠሪያ ውስጥ መክተቱ አስፈላጊ ከመሆኑ አንጻር ለእለቱ ልዩ ስያሜ እንዲሰጠው ታምኖበታል፡፡ በዚህም መሰረት በእለቱ የተወሰደው መንግስታዊ ሽብር ‹‹ጥቁር ሽብር›› የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ ‹‹ጥቁር ሽብር›› በሰለጠነ ውይይት ከማያምን፣ ሰላማዊነትና ዲሲፒሊን ከማይገባው መንግስት የሚፈልቅ፣ ሰዎች ሳይሆኑ ዱላ ብቻ የሚናገርበት፣ ሐሳብ የሚንሸራሸርበት ሳይሆን ነውጥና ግፍ የሚሰፍንበት ሂደት ነው፡፡ ‹‹ጥቁር ሽብር›› አይናቸውን የጋረደው ጥቁር ግርዶሽ የህዝብን እውነታ እንዳይረዱ ያደረጋቸውና ብቃት የሌላቸው ኃላፊዎች የሚወስኑት፣ ሰብዓዊነት በጭካኔ ጭለማ ውስጥ የሚሰጥምበት አስከፊ ክስተት ነው፡፡ አዎን! ለሰላማዊ ሕዝብና ጥያቄ ምላሹን ዱላ ያደረገ ኃይል፣ ባልታጠቀና በእጁ ድንጋይ ባልጨበጠ ጾመኛ ሕዝብ ላይ የጥይት ቃታ የሚስብ መንግስት ከርሞም የሚነዳው በ‹‹ጥቁር ሽብር›› ብቻ ነው፡፡ ሰላማዊ ትግላችንም ከዚህ በኋላ በሚኖረው ሂደት የሐምሌ 11/2006ን አሰቃቂ የመንግስት ጭፍጨፋ የታሪክ ካስማ በማድረግ እለቱ ‹‹ጥቁር ሽብር›› ሲባል ከዚህ በኋላ ያሉ ክስተቶችም ‹‹ከጥቁር ሽብር በኋላ›› ወይም ‹‹ከጥቁር ሽብር በፊት›› እየተባሉ የሚዘገቡ ይሆናል፡፡
‹‹ጥቁር ሽብር›› ከአወሊያ መስጂድ የውድቅት ሰዓት ቀድሞም በአሳሳ በጁሙአ ሰላት ወቅት የተፈጸመ ነው፡፡ ‹‹ጥቁር ሽብር›› ጨለማ ተገን ተደርጎ በአወሊያ መስጂድ ከሁለት አመታት በፊት እንደተወሰደው፣ በጠራራ ጸሐይም በሲቪል ለባሽ ካድሬዎች አሻጥር ተከልሎ ልባቸው በተንኮል በጠቆረ ኃላፊዎች ትእዛዝ፣ በታወረ ህሊና እና አይን የሚወሰድ የአላዋቂነት ድርጊት ነው፡፡ ‹‹ጥቁር ሽብር›› እውቀት አይጠይቅም፤ ዱላና እርግጫ ብቻ ነው የሚጠይቀው፡፡ ‹‹ጥቁር ሽብር›› ህገ መንግስቱን በድቅድቅ ጨለማም ሆነ በቀትር ጸሐይ ንዶ ያሻውን የሚገድል፣ የተቀረውንም የሚያቆስል ጸያፍ ድርጊት ነው፡፡ የእለቱ ስያሜ እስከመቼውም የሚዘልቅ ሲሆን ለወደፊቱም በዚህ የ‹‹ጥቁር ሽብር›› አሻጥር ውስጥ የተሳተፉ ወንጀለኞች ለፍርድ የሚቀርቡበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን እናምናለን፡፡

ይህ በእውር ድንበር የተወሰደና ማንንም ሳይለይ ድንገት እንደደራሽ ጎርፍ የደረሰ ‹‹ጥቁር ሽብር›› ብዙዎችን በአካል ያቆስል ይሆናል፤ በተቃራኒው ግን ዱላውና ግድያው የሰዎችን ሞራል ከፍ ያደርጋል፡፡ በመብት ነጠቃ የ‹‹ጥቁር ሽብር›› ሰለባነት ማግስት የሞራል ከፍታና የአላማ ጽናት ጎልቶ ይታያል፡፡ ባለፉት ሶስት በሚጠጉ አመታት መሰል በርካታ የ‹‹ጥቁር ሽብር›› ዘመቻዎች ተፈጽውብናል፡፡ በማግስቱ ግን ሁሌም ጎልተን እንታያለን፡፡ በተደበደብን ቁጥር፣ በደሉ ባረፈብን ቁጥር ቁስላችን ከመመርቀዝ ይልቅ እየጠገገ ጥንካሬያችንን ሲያጎላው አይተናል፡፡ ሁላችንም እንደምንረዳው ኃይል የተስፋ መሟጠጥ፣ የሐሳብና ዴሞክራሲያዊነት መራቆት አይነተኛ ምክንያት ነው፡፡ ተስፋ መቁረጥ ሲናኝ ኃይል ባህሪ ይሆናል፡፡ የእኛ ትግል ግን በሰላምና ዲሲፕሊን ውስጥ እያለፈ ድልን ይቀዳጃል!
መንግሥታዊው ‹‹ጥቁር ሽብር›› የህዝብን የድል ችቦ አያጠፋውም!
ትግላችን በአላህ ፈቃድ እስከ ድል ደጃፎች ድረስ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!


“አንዳርጋቸው ጽጌን እነርሱ አሸባሪ ሲሉት እኛ ማንዴላ እንለዋለን”–አበበ ገላው በሚኒሶታ (ቪድዮ)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ባለፈው ሳምንት ለኢሳት 4ኛ ዓመት በዓል ተጋባዥ ሆኖ በሚኒሶታ የተገኘው ጋዜጠኛና አክቲቪስት አበበ ገላው ለምን የግንቦት 7 አባል ለመሆን እንደወሰነ ማብራሪያ ሰጠ። ከ15 ሺህ ዶላር በላይ በተሰበሰበት በዚህ የሚኒሶታው የኢሳት በዓል ላይ አበበ ባደረገው ንግግር “አንዳርጋቸው ጽጌን እነርሱ አሸባሪ ሲሉት እኛ በአደባባይ ማንዴላ እንለዋለን” ብሏል። በአሁኑ ወቅት በሃገር ቤት ያለው ኢትዮጵያዊ ለትግል እንደቆረጠ የገለጸው አበበ እኔንም እሰሩኝ እያለ ነው ብሏል። ንግግሩን ዘ-ሐበሻ በካሜራዋ አስቀርታዋለች ይመልከቱት።

“አንዳርጋቸው ጽጌን እነርሱ አሸባሪ ሲሉት እኛ ማንዴላ እንለዋለን” – አበበ ገላው በሚኒሶታ (ቪድዮ)

Hiber Radio: ከአንዳርጋቸው ጽጌ መታፈን በኋላ በጎንደር እና አካባቢው የአገዛዙ ሰራዊት ቁጥር እየጨመረ መሄዱ ተገለጸ

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ሐምሌ 13 ቀን 2006 ፕሮግራም

<...ከምርጫ 7 በሁዋላ በተለይ የያዙት ስልት ጠንካራ ጠንካራ የፓርቲ አባላትን በማሰር ትግሉን እናዳክመዋለን ነው ። አንድነት መዋቅራዊ ድርጅት በመሆኑ ጠንካራ አባላቱ ቢታሰሩም ትግሉ ይቀጥላል...ሕዝቡ የበለጠ በተበደለ ቁጥር ለትግል እየተነሳ ነው...>

ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው የወቅቱ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረጉት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡ)

<<...አንዳርጋቸው የሕዝብ ጀግና ነው። ለኢትዮጵያ ሕዝብ ብሎ ታላቅ መስዋዕትነት እየከፈለ ነው። እሱ የራሱን ተወጥቷል። እኛስ ነው ጥያቄው?...>> በሎስ አንጀለስ ለተቃውሞ ከወጡ አንዷ ስለ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለህብር ከሰጠችው አስተያየት (ሙሉውን ያዳምጡ)

የኢትዮጵያው አገዛዝ ኢሰብዓዊ ምርመራና የፈጠራ ፊልም ቅንብሩ በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት እንዴት ይታያል? በአቶ አንዳርጋቸው ላይ ሊቀርብ የሚችል የአገዛዙ የፈጠራ ፊልም ከወዲሁ በሕዝቡ ሳይታይ ተቀባይነት ያጣ ይመስላል(ልዩ ዘገባ )

ሌሎችም አሉ

ዜናዎቻችን

* ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታፈን በኋላ በጎንደር እና አካባቢው የአገዛዙ ሰራዊት ቁጥር እየጨመረ መሄዱ ተገለጸ

* በጦማርያኑና ጋዜጠኞች ላይ የሽብር ክስ መቅረቡ ምዕራባውያንን አስቆጣ

* አሜሪካ በግዛቷ የተመዘገቡ የመጓጓዣ አውሮፕላኖች በሰሜንና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ እንዳይበሩ አስጠነቀቀች

* ከትግራይ ክልል የመጡ ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው ሰፍረው በመገኘታቸው ከአማራ ክልል ታጣቂዎች ጋር ተጋጩ

- ተኩስ ልውውጥ እንደነበር እማኞች ገልጸዋል

* በኢትዮጵያው በስልጣን ላይ ባለው አገዛዝ በጦማሪያኑና በጋዜጠኞች ላይ የተመሰረተው የሽብር ክስ ምዕራባዊያንን አስቆጣ

* አሜሪካ በግዛቷ የተመዘገቡ አውሮፕላኖች በሰሜንና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ የአየር ክልል እንዳይበሩ አስጠነቀቀች

* የኢትዮጵያው አገዛዝ የደህንነት እና የመከላከያ ባለስልጣናት ከኤርትራ ተቃዋሚዎች ጋር ሰሞኑን ምስጢራዊ ውይይት ማድረጋቸው ተሰማ

* አንድነት ከመኢአድ ጋር ላደረገው ውህደት ለፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩ የራሱን ዕጩዎች ዛሬ በፓርቲው ም/ቤት አስመረጠ

* የሙስሊሙ ማህበረሰብ ሰላማዊ እንቅስቃሴ የሀይል ጥቃት እንደማይገታው ተገለጸ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

በአንዋር መስጊድ በተፈጠረ ግጭት የታሰሩ ፍርድ ቤት ቀርበው ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው

$
0
0

-አንድ ጋዜጠኛና አንድ የፖለቲካ ፓርቲ አባልን ጨምሮ በርካቶች መታሰራቸው ተጠቁሟል ‹‹አብዛኛዎቹ ተለቀው ለግጭቱ ምክንያት የሆኑት ብቻ ታስረዋል›› ፖሊሶች

ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ለጁምዓ (እለተ ዓርብ) ፀሎት መርካቶ በሚገኘው ታላቁ የአንዋር መስጊድ ተገኝተው የነበሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች ባሰሙት ጠንከር ያለ ተቃውሞ ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት

demtschin yesema 2በመፈጠሩ፣ የተጎዱ የዕምነቱ ተከታዮች፣ የተለያዩ ግለሰቦችና የፖሊስ አባላት መኖራቸው ተገለጸ፡፡ በግጭቱ ምክንያት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የዕምነቱ ተከታዮችና በአካባቢው በግርግሩ ወቅት የነበሩ ሰዎች በፖሊስ ታስረው አንድ ቀን ካደሩ በኋላ፣ በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ሐምሌ 12 ቀን 2006 ዓ.ም. ቀርበው ለተጨማሪ ምርመራ ጊዜ ቀጠሮ እንደተጠየቀባቸው ታውቋል፡፡

ሐምሌ 4 ቀን 2006 ዓ.ም. በተለይ ሴት የዕምነቱ ተከታዮች ከድምፅ ያልዘለለ ተቃውሞ ማሰማታቸው የተገለጸ ቢሆንም፣ የአሁኑ ከበድ ያለ እንደነበር ተገልጿል፡፡ ግጭቱ በተፈጠረበት ወቅት በቦታው የጋዜጠኝነት ሥራዋን ስትሠራ ነበረች የተባለችው የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድና ለግል ጉዳይዋ መርካቶ አካባቢ እንደነበረች በፓርቲው አመራሮች የተገለጸው የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል ወ/ት ወይንሸት ሞላን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ወደተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች መወሰዳቸው መገለጹ ይታወሳል፡፡

በተለይ መሀል መርካቶ በሚገኘው አራተኛ ፖሊስ ጣቢያ፣ ኮልፌ ፖሊስ ማሠልጠኛ፣ ማዕከላዊና ኢትዮጵያ ትቅደም ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ በርካታ ሰዎች ታስረው እንደነበር የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡

ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸውን ተጠርጣሪዎች በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት፣ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና በተለያዩ ፍርድ ቤቶች በማቅረብ ለተጨማሪ ምርመራ ጊዜ ቀጠሮ እንደተጠየቀባቸው ታውቋል፡፡

በወቅቱ በነበረው ግጭት የተፈነከቱ፣ የእጃቸው ጣቶች የተሰበሩ፣ የሚያነክሱና ራሳቸውን ስተው የወደቁ እንደነበሩ በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ገልጸው፣ የፖሊስ ተሽከርካሪዎችና የቀይ መስቀል አምቡላንሶች ወደ ሆስፒታል ሲያመላልሱ መታየታቸውን ጠቁመዋል፡፡

ታሳሪዎቹ ‹‹ፍትሕ ናፈቀን፣ ፍትሕ ይከበር፣ የዕምነት ነፃነታችን ይከበር፣ የታሰሩ ይፈቱ፣ መንግሥት በዕምነታችን ጣልቃ አይግባብን፣ የሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ይፈቱ…›› እና ሌሎች መፈክሮችን በማሰማት በአንዋር መስጊድ ግቢ ውስጥ በማሰማት ላይ እያሉ፣ ከማን እንደተወረወረ ባልታወቀ ድንጋይ ፖሊሶች መጎዳታቸውን በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ገልጸዋል፡፡

ለሥራ ወጥተው ምንም ሳያደርጉ ልጆቻቸው የት እንደደረሱ ማወቅ ያልቻሉ እናቶች፣ ቤተሰቦችና የሚመለከታቸው ወገኖች በየፖሊስ ጣቢያው ሄደው ሲጠይቁ በቂ ምላሽ አለማግኘታቸውን የገለጹ ቢሆንም፣ አንዳንዶቹ ወላጆች ደግሞ የልጆቻቸውን ስም እየተናገሩ የታሰሩበትን ፖሊስ ጣቢያ ለማወቅ መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ሐምሌ 17 ቀን 2006 ዓ.ም. በድጋሚ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡና ምናልባትም በተለይ ሳያስቡትና በወጡበት ችግሩ የገጠማቸው በዋስትና ይለቀቃሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸውም ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል፡፡

በግጭቱ ወቅት በቁጥጥር ሥር ስለዋሉት ሰዎች ብዛትና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ፣ እንዲሁም የግጭቱ ዋነኛ መነሻ ምን እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንና የፌዴራል ፖሊስ ምላሽ እንዲሰጡ የተጠየቁ ቢሆንም፣ ማብራሪያውን ለማግኘት አልተሳካም፡፡ ነገር ግን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የፖሊስ አባላት እንደገለጹት፣ በግጭቱ ወቅት ቁጥራቸው በዛ ያሉ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ነበር፡፡ ሐምሌ 14 ቀን 2006 ዓ.ም. ከበላይ ኃላፊዎች በመጣ ትዕዛዝ ሁሉም ማለት በሚባል ደረጃ ተለቀዋል፡፡ አሁን በቁጥጥር ሥር ሆነው በምርመራ ላይ የሚገኙት ለረብሻው ምክንያት የሆኑና በተደጋጋሚ ችግር ሲፈጥሩ የተገኙ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ በደንብ በመደራጀት ሕዝብ ሰላም እንዳያገኝ በተደጋጋሚ ግጭት ሲያስነሱ የተገኙ ከ14 በላይ ግለሰቦች በተፋጠነ ችሎት እየቀረቡ መሆኑንም አክለዋል፡፡

በግጭቱ ወቅት ፖሊሶች ሞተዋልና ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል ስለመባሉም ሐሰት መሆኑን ተናግረው፣ ጉዳት የደረሰባቸው እንዳሉ ግን አልካዱም፡፡ ፖሊስ ምርመራውን ጨርሶ ለዓቃቤ ሕግ ካስረከበና የሚከሰሱ ከሆነም የፍርድ ቤት ጉዳያቸው ሲጠናቀቅ፣ የግለሰቦቹን የወንጀል ድርጊትና እንቅስቃሴ ከነማስረጃው ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ አስረድተዋል፡፡

Source: Ethiopian Reporter

የባለሥልጣኑ የዳኝነት ችሎት በሦስት መዝገቦች ላይ ውሳኔ ሰጠ

$
0
0

-ጂኦቴል የሞባይል መገጣጠሚያ ሁለት ሞዴሎችን እንዳያመርት ታገደ

-ሊፋን ሞተር ላይ የቀረበው ክስ ውድቅ ሆነ

k2.items.cache.6956c787ef5259e79426818930533811_Lnsp_589ቴክኖ ሞባይል መገጣጠሚያ ፋብሪካ ሁለት የሞባይል ምርቶቹን አስመስሎ ሠርቶብኛል ያለውን ጂኦቴል የሞባይል ፋብሪካን ያልተገባ የንግድ ውድድር አድርጓል በሚል በመሠረተበት ክስ፣ ተመሳስለው የተሠሩ ናቸው የተባሉት ሁለቱ የጂኦቴል ሞባይል ቀፎዎች ምርት እንዲቆም ውሳኔ ተላለፈ፡፡

ይህንን ውሳኔ የወሰነው የሁለቱን ወገኖች ክርክር ሲመለከት የነበረው የኢትዮጵያ የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ችሎት ነው፡፡ ማክሰኞ ሐምሌ 15 ቀን 2006 ዓ.ም. የተላለፈው የፍርድ ውሳኔ መዝገብ እንደሚያመለክተው፣ ተመሳስለው የተሠሩ ናቸው የተባሉትና ከዚህ በኋላ እንዳይመረቱ ውሳኔ የተላለፈባቸው የጂኦቴል የሞባይል ቀፎ ምርቶች G340 እና G341 የተባሉት ናቸው፡፡

የክርክር መዝገቡ እንደሚያመለክተው ቴክኖ ሞባይል ጥር 17 ቀን 2006 ዓ.ም. ባቀረበው የተሻሻለ የክስ አቤቱታ ከሳሽ ቴክኖ በሚል የንግድ ምልክት ከሚያመርታቸው የሞባይል ቀፎዎች ሞዴሎች 340 እና 341 የተባሉ ምርቶች እንደሚገኙበት ይጠቅሳል፡፡ ጂኦቴል ጤናማ በሆነ የንግድ ውድድር ተግባራትን ይዞ መወዳደር ሲገባው፣ G340 እና G341 የሚባሉ የሞባይል ቀፎዎቹን ማሸጊያቸውና የስልኩን የመሸፈኛ አካል (Body) ገጽታ (Layout) በከፍተኛ ደረጃ አስመስሎ ለገበያ አቅርቧል በሚል የቀረበ ክስ ነው፡፡

ቴክኖ ሞባይል ጨምሮ እንደገለጸው፣ ለሦስት ዓመታት ያህል ከሳሽ (የቴክኖ ሞባይል) የገነባውን መልካም ዝና ሀቀኛ ባልሆነና አሳሳች በሆነ መልኩ የስልኮቹ ቀፎ ታስቦበት ከከሳሽ ምርት ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ሆነው የተመረቱ ናቸው፡፡ ይህም ስለሆነ የቴክኖ ሞባይል ደንበኞች የከሳሽን ምርት የሸመቱ እየመሰላቸው የተከሳሽን (ጂኦቴል) ምርቶች በስህተት በመሸመት ላይ ስለሆኑ በሸማች ላይ መደናገር መፍጠሩንም የክስ መዝገቡ ያመለክታል፡፡ በዚህ ክስ መሠረትም ቴክኖ ሞባይል የዳኝነት ችሎቱን ተከሳሽ ተገቢ ያልሆነውን ድርጊት እንዲያቆምለት ጠይቋል፡፡ በተጨማሪም በጂኦቴል የተመረቱት ሁለቱ ሞዴሎች ተሰብስበው እንዲወገዱ፣ በተፈጠረው መደናገር ሸማቹ ግልጽ መረጃ እንዲኖረው ለማድረግ ተከሳሽ በጋዜጣና በቴሌቪዥን ይቅርታ እንዲጠይቅ ይወሰንልኝ ብሎ ዳኝነት ጠይቋል፡፡ የጉዳት ካሳና ወጪ ኪሳራ እንዲተካለትም አመልክቷል፡፡

ጂኦቴል ለክሱ በሰጠው ምላሽ ሞዴሎቹን ከሚመለከተው የመንግሥት አካል የብቃት ማረጋገጫ በመቀበል እያመረታቸው መሆኑን ገልጿል፡፡ አያይዞም የጂኦቴል ሞባይሎች እየተመረጡ በመምጣታቸው ለከሳሽ (ቴክኖ ሞባይል) እያሳሰበው በመምጣቱ እንጂ ተከሳሽ የተጠቀመው “GEOTEL” የሚል ስለሆነ ከከሳሽ ምርቶች ጋር የተፈጠረ የመደናገር ችግር የሌለ መሆኑንና ምርቶቹን ለመለየት በግልጽ መለያውን እየጻፈ መገኘቱን ጠቅሷል፡፡ ስለዚህ የተፈጠረ መመሳሰል ባለመኖሩ ክሱ ውድቅ እንዲደረግለት አመልክቷል፡፡ ግራ ቀኙን የተመለከተው የዳኝነት ችሎት ተመሳስለው ተመረቱ የተባሉት ምርቶች እንዲቆሙ የተጠየቀው ጥያቄ ተገቢ መሆኑን አግኝቸዋለሁ ብሏል፡፡ ነገር ግን G340 እና G341 ሞዴል የሞባይል ቀፎዎች ተሰብስበው እንዲወገዱ ከሳሽ የጠየቁትን ዳኝነት በተመለከተ የአገራችን ኢኮኖሚ እንዳይባክን ጥንቃቄ ማድረግ ስለሚኖርበትና ተከሳሽም የሞባይል ቀፎዎች ማምረቱን እንዲያቆም ከተደረገ ውጤቱ ተመሳሳይነት ስለሚኖረው አልተቀበለውም፡፡

በሌላ በኩልም ከሳሽ የጉዳት ካሳ እንዲከፈል የጠየቀ ቢሆንም፣ የደረሰበት ጉዳትና የጉዳት መጠኑ በግልጽ ያልቀረበ ስለሆነ የዳኝነት ችሎቱ አልፎታል፡፡ ሆኖም ተከሳሽ በፈጸሙት ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር ተግባር በአዋጅ ቁጥር 873/2006 አንቀጽ 43/3 መሠረት አስተዳደራዊ ቅጣት መጣል ያለበት በመሆኑ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በዚሁ መሠረት የግራ ቀኙን ክርክር የተመለከተው የዳኝነት ችሎት በከሳሽ T340 እና T341 እንዲሁም የG340 እና G341 የሞባይል ቀፎዎች ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር ተግባር ነው የሚያሰኝ መመሳሰል ሁኔታ አለው ወይ? ተገቢ ካልሆነ ከሳሽ የሚገባው ዳኝነት ምንድነው? የሚሉ ጭብጦችን በመያዝ መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽ G340 እና G341 የሚባሉ ሞዴል የሞባይል ስልኮች ማምረት እንዲያቆም ወስኗል፡፡ ከሳሽ የተመረቱት G340 እና G341 ሞዴል የሞባይል ስልክ ቀፎዎች እንዲወገዱ፣ የጉዳት ካሳ ክፍያና ተከሳሽ በሚዲያ ይቅርታ እንዲጠይቅ ያቀረቡትን ዳኝነት ግን ችሎቱ አልተቀበለውም፡፡

ተከሳሽ ተመሳሳይ ሞዴል በማምረት በሸማቾች ላይ መደናገር ሊያስከትል በሚችል ሁኔታ መገኘታቸው አግባብነት ስለሌለው G340 እና G341 የሞባይል ቀፎዎች ማምረት ከጀመሩበት ወቅት ጀምሮ ውሳኔ እስከተሰጠበት ጊዜ ድረስ ባሉት ወራት ክርክር ከተነሳባቸው ሞባይሎች ሽያጭ ተሰልቶ አምስት በመቶ ለመንግሥት ገቢ እንዲያደርግም ቅጣት ጥሏል፡፡ ወጪና ኪሳራን በተመለከተ ከሳሽ ዝርዝር አቅርበው የመጠየቅ መብታቸው የተጠበቀ መሆኑን በመግለጽ መዝገቡን ዘግቷል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን የዳኝነት ችሎት ከዚህ መዝገብ በተጨማሪ በሁለት መዝገቦች ላይ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ አንደኛው አቶ ዘሪሁን አያሌው የተባሉ የግል ተበዳይ የሊፋን ተሽከርካሪዎች በመገጣጠም ለገበያ የሚያቀርበውን ያንግፋን ሞተርስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያን የከሰሱበት መዝገብ ይገኛል፡፡ የክሱ ጭብጥ እንደሚያመለክተው ከሳሽ ከተከሳሽ ሊፋን 620 አውቶማርክ የቤት መኪና እ.ኤ.አ ኖቬምበር 20 ቀን 2010 በተደረገ ሽያጭ ውል 430 ሺሕ ብር ክፍያ ፈጽመው ቢረከቡም መኪናው የአሠራር ችግር አለበት የሚል ነው፡፡ መኪናውን ከገዙበት ጊዜ ጀምሮ ለግማሽ ሰዓት ፀሐይ ሲነካው ይጮሃል፣ በዚህም ምክንያት መሽከርከር ያቆማል፣ ለማንቀሳቀስ መቀዝቀዝ ያስፈልገዋል፣ ከዚህም ሌላ መኪናው ወደፊት እየተነዳ ወደኋላ እንደሚሽከረከር የሚያሳዩ የኋላ ማርሽ መብራቶች ይበራሉ፡፡ መኪና ውስጥ ያሉ ወደኋላ እንደሚንቀሳቀስ ያሳያሉ፡፡

እነዚህ ችግሮች እየተባባሱ በመሄዳቸው ጥር 6 ቀን 2006 ዓ.ም. ተከሳሽ ጋራዥ መኪናው ተወስዶ ተሠርቷል በሚል ሲረከቡ፣ የመኪናው የኋላ ዕቃ መጫኛ ላይ ድሮ ያልነበረ የኋላ ካሜራ ተገጥሟል፣ ይህ የመኪናውን መልክ አበላሽቷል የሚል እንደነበር የክስ መዝገቡ ያመለክታል፡፡ ለዚህ ክስ የተጠየቀውም ዳኝነት ያንግፋን ሞተርስ የመኪናውን ዋጋ 430 ሺሕ ብር እንዲመልስ፣ መኪናው ባጋጠመው እክል ችግር ስለገጠመኝ በዝቅተኛ የቀን ቤት መኪና ወጪ 250 ብር ታስቦ 273 ሺሕ ብር እንዲከፈል የሚል የዳኝነት ተጠይቆበታል፡፡

ያንግፋን ሞተርስ ለክሱ መቃወሚያና አማራጭ መልስ የሰጠ ሲሆን፣ በዚህም መቃወሚያና ምላሹ ውስጥ የአዋጅ ቁጥር 685/2002 ተፈጻሚነት ለኅብረተሰቡ ወሳኝ በሆነ ዕቃዎች እንጂ መኪናን በተመለከተ ተፈጻሚ አይደለም፣ በአዋጁ አንቀጽ 28/2 መሠረት በዕቃው ላይ የተገኘውን ጉድለት ዕቃው ከተገዛ 15 ቀን ውስጥ እንዲለውጥ ወይም እንዲመለስ መጠየቅ ነበረባቸው የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ከዚህም ሌላ ከሳሽ በሽያጭ ውሉ አንቀጽ 4.3 ላይ በመኪናው ላይ ስለደረሰው ችግር በጽሑፍ ማሳወቅ እንዳለበት የተጠቀሰ ሲሆን፣ ከሳሽ ይህንን አለማድረጋቸውንና ተከሳሽ ለከሳሽ የሰጠው ዋስትና መኪናውን ከተረከበ 24 ሰዓት ያለፈ በመሆኑ ውድቅ ነው ይላል፡፡

በከሳሽ የተጠየቀው ዳኝነት ሁሉ ውድቅ እንዲሆንለት የጠየቀው ያንግፋን ሞተርስ ተከሳሽ ተመሳሳይ መኪኖችን ለሌሎች ሸማቾች እንዳይሸጥ ይወሰን በሚል ያቀረበውን ዳኝነት ጥያቄ በመቃወም፣ ሌሎች ገዢዎች መኪናውን በአግባቡ እየተጠቀሙበት ስለሆነ ከሳሽ መኪኖቹን እንዳይሸጡ ዳኝነት መጠየቅ አይችሉም ብሎ ተከራክሯል፡፡ በሁለቱም ወገኖች ምስክሮችንና መረጃዎችን አቅርበው ተከራክረዋል፡፡ የዳኝነት ችሎቱም ግራ ቀኙን በመመልከት ከሳሽ መኪናው የተገዛበት ሒሳብ ከሕጋዊ ወለድ ጋር በመኪና ጉዳት መነሻ በቀን ላወጣ የምችለው ወጪ በሦስት ዓመት ተሰልቶ ይከፈለኝ፣ ተከሳሽ ተመሳሳይ መኪና እንዳይሸጥ ይታገድ በሚል ያቀረበው ጥያቄ ተገቢነት ያለው ሆኖ አላገኘሁትም በሚል ወስኗል፡፡ ይኸውም መኪናው ከተገዛበት ጊዜ ጀምሮ ለረዥም ጊዜ አገልግሎት እየሰጠ በመቆየቱ መሆኑን አብራርቶ፣ የካሳ ጥያቄም ቢሆን ከሳሽ ያላዩትን ወጪ መጠየቃቸው ተገቢ መስሎ አልታየንም ብሏል፡፡

የከሳሽ ክስ በአዋጅ ቁጥር 813/2006 አንቀጽ 20 ሥር በንግድ ዕቃዎች ላይ ስለሚገኙ ጉድለቶች በብር የማይሸፈን በመሆኑ፣ ከሳሽ ያቀረቡትን ክስ ውድቅ አድርጓል በሚል ወስኗል፡፡ በዚህ ውሳኔ ቅር የተሰኘም በአዋጅ ቁጥር 8/3/2006 አንቀጽ 39/1 መሠረት በ30 ቀናት ለፌዴራል ይግባኝ ሰሚ አስተዳደር ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ የሚችል መሆኑን ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ ተከሳሽ ላወጣው ወጪና ኪሳራ ከሳሽን የመጠየቅ መብቱን በፌዴራል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 463 መሠረት ተጠብቋል በማለት ትዕዛዝ በመስጠት መዝገቡን ዘግቷል፡፡

የዳኝነት ችሎቱ በዕለቱ ውሳኔ የሰጠበት ሦስተኛው ጉዳይ ደግሞ በአንድ የግል ተበዳይ የቀረበ ክስ ነው፡፡ የክስ መዝገቡ የግል ተበዳይ ተማሪ ተመስገን ሸዋዬ ከሚክስ ማክስ ኤሌክትሮኒክስና ኮምፒዩተር ማዕከል አዲስና ጥቅም ላይ ያልዋለ ቶሺባ ላፕቶፕ በ14,600 ብር ገዝተው ሁለት ወር ሳያገለግል ሙሉ በሙሉ ተበላሽቶብኛል በሚል የመሠረቱት ክስ ነው አዲስ ኮምፒዩተር ሻጭ ነኝ ከሚለው ድርጅት የገዙት ላፕቶፕ በጀርባው ላይ “Factory Reconditioned” የሚል ዓርማ ያለው ነው፡፡ ሆኖም ተከሳሽ እንደሚለው አገልግሎት ላይ ያልዋለ ሁለተኛ ምርት ነው በማለት ሁለተኛ ምርት በመሸጥ አሳሳች ተግባር በመፈጸም ተገቢ ያልሆነ ትርፍና ጥቅም አግኝቷል በሚል የቀረበ ክስ ነው፡፡ ስለዚህ ተከሳሽ በገዛሁት ኮምፒዩተር ምትክ አዲስና አገልግሎት ላይ ያልዋለ ኮምፒዩተር ይቀይርልኝ ወይንም ኮምፒዩተሩን መልሼ የከፈልኩት ዋጋ ይመለስልኝ ብለው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ ተከሳሽም ለክሱ በሰጡት ምላሽ ኮምፒዩተሩ ከሳሽ የፈለጉት ፕሮግራም የተጫነበትና “Factory Reconditioned” መሆኑን በመግለጽ የሸጠላቸው መሆኑንና ምርቱ ሁለተኛ ምርት ያለመሆኑን ገልጿል፡፡ ኮምፒዩተሩን ይዘው በመጡ ጊዜ በባለሙያዎች የተረጋገጠው ብልሽቱ ያጋጠመው በአጠቃቀም ችግር መሆኑን የከሳሽ ምላሽ ያስረዳል፡፡ ከዚህም ሌላ ከሳሽ አስቀድመው በሁለት የተለያዩ ቦታዎች ኮምፒዩተሩን አስፈትተው እንደነበር መናገራቸውን ገልጸዋል፡፡

ስለዚህ ክሱ ውድቅ ይሁንልኝ ብሎ ምስክሮችን በማቅረብ አስደምጠዋል፡፡ ችሎቱም ግራና ቀኝ የቀረቡትን መከራከሪያዎች በማየትና እንዲሁም “Factory Reconditioned” ማለት ከአዲስ ኮምፒዩተር ኦርጅናል ምርት ጋር ተቀራራቢነት ኖሮት እንደ አዲስ የተሠራ እንጂ፣ ሁለተኛ ምርት ያለመሆኑን በመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ በጽሑፍና በአካል ማብራሪያ የተሰጠበት በመሆኑ፣ የከሳሽ ክስ የሕግና ማስረጃ ድጋፍ ስለሌለው ውድቅ ነው በማለት ውሳኔ በመስጠት መዝገቡን ዘግቷል፡፡ እነዚህ ሦስት ጉዳዮች የባለሥልጣኑ የዳኝነት ችሎት ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ ውሳኔ የተሰጠባቸው ናቸው፡፡

Source: Ethiopian Reporter

ኢሕአዴግ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን በሽብርተኝነት መወንጀሉን እንዲያቆም መድረክ ጠየቀ

$
0
0

medrekየኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ሰላማዊ ታጋዮችን በሽብርተኝነት መወንጀሉን እንዲያቆም ጠየቀ፡፡

መድረክ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ ኢሕአዴግ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን እያሰረና እያሰቃየ ያለው በአምባገነናዊ አገዛዝ ለመጠቀል የነበረው ምኞት ሥጋት ውስጥ መውደቁን በመረዳቱ እንደሆነ አመልክቷል፡፡

ኢሕአዴግ እያካሄደ ባለው የእስር ዕርምጃ የመድረክ አባል የሆነው የዓረና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የመድረክ ጠቅላላ ጉባዔ አባል የሆኑት አቶ አብርሃ ደስታ ከሚኖሩበትና ከሚሠሩበት መቀሌ ከተማ ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ መደረጉን መግለጫው አመልክቷል፡፡ ከሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ የታሰሩት አቶ አብርሃ በቤተሰቦቻቸውም ሆነ በጓደኞቻቸው እንዲጎበኙ አለመፈቀዱንም መግለጫው ያትታል፡፡

ከአቶ አብርሃ ደስታ በተጨማሪ የአንድነት አመራር አባላት የሆኑትን የአቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ እንደዚሁም የሰማያዊ አመራር አባል የሆኑት የአቶ የሺዋስ አሰፋን እስርም መድረክ ተቃውሟል፡፡

ገዥው ፓርቲ ከወሰደው የፖለቲካ ፓርቲ አመራርና አባላት እስር ጋር በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሚገኙ አባላቱ ለእስር፣ ስቃይና እንግልት መጋለጣቸውንም መድረክ አስታውቋል፡፡ በተለይም በትግራይና በኦሮሚያ ክልሎች የሚገኙ አባላቱ ላይ እየደረሰ ያለው እስርና ግፍ እየተስፋፋ መሄዱ፣ አገሪቱ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ጥያቄ ውስጥ እንደሚከተው አስገንዝቧል፡፡

መድረክ የኢሕአዴግ ዕርምጃ በቀጣይ ዓመት ከሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ጠቁሞ፣ ዕርምጃው አስቀድሞ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችንና እንቅስቃሴያቸውን ለማዳከም ያለመ እንደሆነ አስታውቋል፡፡ ‹‹ዕርምጃዎቹ የጠቅላይነትና ብቸኛ ገዥ ፓርቲነት ምኞት ነፀብራቆች ናቸው፤›› ያለው መግለጫው፣ የአገሪቱን ውስብስብ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮችን ለመፍታት ውይይትን የገፋ ዕርምጃ እንደማይጠቅም አመልክቷል፡፡

ፓርቲው በመጨረሻም ኢሕአዴግ በሰላማዊ መንገድ የመቃወም ሕገ መንግሥታዊ መብቶችን በመግፈፍ የሚፈጽማቸውን የማሰርና የማሰቃየት ዕርምጃዎች እንዲያቆምና ሰላማዊ ታጋዮችን በአስቸኳይ እንዲፈታ ጠይቋል፡፡

 

Source: Ethiopian Reporter

አዟሪና አከፋፋዮች ለምን አንድ ለአምስት አይደራጁም? (ጽዮን ግርማ)

$
0
0

ዮን ግርማ

ጽዮን ግርማ tsiongir@gmail.com

ጽዮን ግርማ
tsiongir@gmail.com

ከአምስት ወራት በፊት ከኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት የስልክ ጥሪ ደረሰኝ፡፡ በሞያው ውስጥ ሰንበት ብያለኹና ከአብዛኞቹ የጣቢያው ዘጋቢዎች ጋራ እንተዋወቃለን፡፡ ጥሪው የደረሰኝም በላይ ኃድጎ ከተባለ ከማውቀው ጋዜጠኛ ነበር፡፡ ለሥራ ጉዳይ በስልክ ሳይኾን በአካል መገናኘት እንደሚፈልግ ነገረኝ፡፡ ባለመመቻቸት ሳንገናኝ ቀናት ቢቆጠሩም በመጨረሻ ተገናኘን፡፡

በአካል መገናኘትን ያስመረጠው ጥብቅ ጉዳይ ከጋዜጠኝነት ሞያ ጋራ ለሚሠራ አንድ ዘጋቢ ፊልም ቃለምልልስ እንድሰጥ ነበር፡፡ በወቅቱ እንደነገረኝም፤ዘጋቢ ፊልሙ የሚሠራበት የማጠንጠኛ ሐሳብ የበርካታ ሚዛናዊ ጋዜጦች ሕትመት መቋረጥና ሥርጭት መቀነስ ዋነኛ ምክንያት፣አከፋፋዮችና አዟሪዎች በሕትመት ውጤቶቹ ላይ በተዘዋዋሪ የሚኖራቸው የይዘት ተሳትፎና በአሣታሚው ላይ ያደርሳሉ የተባለውን ጫና በሚመለከት አስተያየት እንድሰጥ ነበር፡፡

ከስድስት ዓመታት በፊት ተቋቁሞ ለአንድ ዓመት ከስድስት ወር ገበያ ላይ የቆየው ‹‹እንቢልታ ጋዜጣ›› ባለቤትና ዋና አዘጋጅ ስለነበርኩ፣ጋዜጣውም ከሕትመት ውጪ የኾነው አከፋፋዮቹና አዟሪዎቹ በጋዜጣው ላይ በፈጠሩት ጫና ምክንያት መኾኑን መረጃ ስለደረሰው ለቃለ ምልልሱ እንደመረጠኝ ነገረኝ፡፡ ከዛው ጋር በተያያዘም የጋዜጠኝነትን ነባራዊ ኹኔታ አያይዤ አስተያየቴን እንዳካፍል ጠየቀኝ፡፡

ጋዜጣው ከገበያ ውጪ ለመኾኑ በርካታ ምክንያቶች እንዳሉት ገልጬለት፤‹‹እንቢልታ ጋዜጣ›› በአከፋፋዮችና በአዟሪዎች ጫና ምክንያት ከገበያ ወጣ መባሉን ግን ከእርሱ እንደሰማሁ ነገርኩት፡፡አጠቃላይ ሐሳቡን በሚመለከት ግን፤‹‹አከፋፋዮችና አዟሪዎች ጫና ይፈጥራሉ›› የሚለው ሐሳብ ጣቢያው በሚያሠራው ዶክመንተሪ በተደጋጋሚ መነሳቱን፣አሁን ካለው ነባራዊው ሁኔታ ጋር አብሮ የማይሄድ መኾኑን፣ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እራሱ ይህን ጉዳይ ደጋግሞ መሥራቱ እንዴት እንደማይሰለቸው ተገርሜ ጠይቄው ነበር፡፡ በመጨረሻም በዚህ ጉዳይ ላይ የተሟላ አስተያየት መስጠት የሚያስችል ልምድ ቢኖረኝም ለኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ግን ለመስጠት ፈቃደኛ እንዳልሆንኩ በእርጋታ አስረድቼው ነበር፡፡የ‹‹እንቢልታ›› ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በነበርኩበት ቀደም ባለው ጊዜ ተመሳሳይ ነገር ተጠይቄ ፈቃደኛ እንዳልነበርኩ ነገርኩት፡፡

አስተያየት የማልሰጥበት ምክንያትም ኾን ተብለው ከሚዘጋጁ አስተያየት ሰጪዎች በስተቀር ያለው ተጠያቂ ለሚቀርብለት ጥያቄ የሚሰጠው ምላሽ በቴሌቭዥን ሲቀርብ እጅግ ተቆራርጦና አስተያየት ሰጪው መልስ ከሰጠበት ጥያቄ ጋራ በቀጥታ ግንኙነት እንዲኖረው ተደርጎ ሳይኾን እነርሱ እንዲተላለፍ ከሚፈልጉት ሐሳብ ጋራ አጣብቀው ይሰፉታል የሚል እምነት እንዳለኝ ነገርኩት፡፡ ይህንንም ለቃለ ምልልሱ ፈቃደኛ ብኾን ኖሮ ሊያነሳልኝ የፈለገውን ጥያቄ በምሳሌነት ጠቅሼ አስረዳሁት፡፡
ለምሳሌ ’የጋዜጠኝነት ሞያ በኢትዮጵያ ያለው ነባራዊ ሁኔታ ምን ይመስላል?’ በሚል ለጠየቀኝ ጥያቄ ልሰጠው እችል የነበረው ምላሽ፤‹‹አሁን በኢትዮጵያ ባለው ነባራዊ ሁኔታ የጋዜጠኝነት ሞያ በራሱ ነጻ አልወጣም፡፡መንግሥት ወደ ራሱ ፍላጎት በመጎተት እስረኛ አድርጎታል፤ተቃዋሚዎችም ሞያውን እንደነርሱ ፍላጎት ይስቡታል፣ባለሃብቶችም እንደሚመቻቸው ሊያሽከረክሩት ይፈልጋሉ፡፡ አንባቢውም ማንበብ የሚፈልገው ብቻ እንዲጻፍለት ይፈልጋል፡፡ በዋነኛነት ለሞያው ነጻ አለመውጣት ተጠያቂው ግን መንግሥት ነው፡፡ ምክንያቱም የእርሱ ጡጫ ስለሚጠነክር ምንም ነገር ተቋቁሞ መቀጠልን እጅግ ከባድ ያደርገዋል›› የሚል እንደነበር ነገርኩት፡፡

እርሱ ደግሞ ይሄን ሲያስተላልፈ ያውም በጨዋ መንገድ ፤‹‹አሁን በኢትዮጵያ ባለው ነባራዊ ሁኔታ የጋዜጠኝነት ሞያ በራሱ ነጻ አልወጣም፡፡‹‹ተቃዋሚዎች ሞያውን እንደነርሱ ፍላጎት ይስቡታል፣ባለሃብቶችም እንደሚመቻቸው ሊያሽከረክሩት ይፈልጋሉ፡፡ አንባቢውም ማንበብ የሚፈልገው ብቻ እንዲጻፍለት ይፈልጋል፡፡›› የሚለውን ብቻ ወስዶ እንደሚኾን በእርግጠኝነት ነገርኩት፡፡ እርሱም ከዛ በላይ ብዙ ሊለልኝ ስላልፈለገ ለስንብት ተነሳ፡፡እናም ከወራት በኋላ እኔን በጠየቀኝ ጋዜጠኛ ስምም ባይኾን በሌላ አዘጋጆች ስም በዚህ ሓሳብ ዙሪያ የሚያጠነጥን ‹‹መንታ መንገድ›› የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም ባለፈው ሣምንት በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ቀርቦ ታየ፡፡ ስለ ፊልሙ ቅድመ ዝግጅት በማወቄ ሳይኾን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ስለ ሕትመት ሚዲያው ስርጭት የቀረበው መረጃ እውነተኛውን ስዕል የሚያሳይ አይደለም ብዬ ስለማምን አስተያየቴን እንዲህ ጻፍኩ፡፡

ዘጋቢ ፊልሙ
ዘጋቢ ፊልሙ የግሉ ፕሬስ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዐት ግንባታ ያለው አስተዋጾ፣የግሉ ፕሬስ ሚና እና ነባራዊ ኹኔታ፣የፕሬስ ታሪክ፣የፕሬሱ ፈተናዎች፣የጸረ ሽብር ሕጉና ፕሬስ በሚሉ ዋና ርዕሶች ሥር ሌሎች ንዑስ ርእሶችን ለመዳሰስ ይሞክራል፡፡ይህንንም ሐሳብ ለማጠናከር በአጠቃላይ ዘጠኝ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ጋዜጠኞች እንዲሁም ሁለት ሰዎችን አስተያየት አካቷል፡፡ ርእሶቹ ለየብቻቸው በብዙ የሚያወያዩና አንዳንዶቹም ከጋዜጠኝነት መሠረታዊ መርሕ ጋራ የተሳሰሩ በመኾናቸው በተነሱት ሁሉም ሐሳቦች ላይ አስተያየት የመጻፍ ዕቅድ የለኝም፡፡ ነገር ግን የዘጋቢ ፊልሙ ማጠንጠኛና መንግሥት ሊወስደው ያሰበውን ቀጣይ እርምጃ አመላካች ነው ያልኩትን የአከፋፋዮችና የአዟሪዎችን ጉዳይ ለማንሳት እሞክራለሁ፡፡

የመንደርደሪያ ሐሳቡ አሮጌነት
ዘጋቢ ፊልሙ ወደ ተነሳበት ሐሳብ የሚያንደረድረውን አስተያየት ያስጀመረው፤የቀድሞ የፓርላማ አባል፣ በ2002 ምርጫ በቦንጋና አካባቢው ከዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ጋራ በገጠሙት የምርጫ ጦርነት ተሸንፈው በኋላም በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የተመደቡትና አሁን የሕግ ባለሞያና መምሕር መኾናቸው በተገለፀው አቶ ብርሃኑ አዴሎ ፕሬስ በአደጉት አገሮች ያለውን ሚና በማስተንተን ነው፡፡

ያለ ነጻ ፕሬስ ከሚኖር መንግሥት ይልቅ ያለ መንግሥት የሚኖር ፕሬስ እንደሚመርጥ የሚናገረው ሦስተኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ቶማስ ጀፈርሰን፤ ሕግ አውጪው፣ ሕግ ተርጓሚውና ሕግ አስፈጻሚው የመንግሥት አካላት እርስ በርሳቸው የተነጣጠሉና እርስ በርሳቸው የሚቆጣጠሩ እንዲሆኑ ሲታገል ቆይቶ፤ ሐሳብን የመግለጽ ነፃነት ለዜጎች መተኪያ የሌለው መብት ነው የሚለው እምነቱን ለማረጋገጥም ፕሬስ አራተኛው የመንግሥት አካል (The Fourth State) ኾኖ እንዲያገለግል በማድረግ ጥንካሬውን አሳይቷል፡፡ አቶ ብርሃኑም ይህንኑ የጀፈርሰን ሓሳብ አንስተው፤ ፕሬስ ባደጉት አገራት አራተኛው የመንግሥት አስፈጻሚ ክንፍ እንደኾነ በመንገር ነበር አስተያየታቸውን የጀመሩት፡፡ አቶ ብርሃኑ ግን ስንሰማው የኖርነውን የፕሬስን አራተኛ መንግሥትነት ደግመው ከመንገር ውጪ ኢትዮጵያ ውስጥ ፕሬሱ በአራተኛ መንግሥትነት እንዲያገለግል እንደ ቶማስ የታገለ መሪ መኖር አለመኖሩን ሳይነግሩን አልፈዋል፡፡

የዘጋቢ ፊልሙ ሐሳብ በኤቴቪ ተደጋግሞ ከመነሳቱና ከአስተያየት ሰጪዎቹ ውስጥ የተወሰኑት ለዓመታት በአንድ ዐይነት ጉዳይ ላይ ደጋግመው ተመሳሳይ ነገር ከመናገራቸው የተነሳ አቶ ወንደሰን መኮንን የተባሉት በመንግሥት ድጋፍ መቆሙ የሚነገርለት የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች ፕሬዝዳንት አስተያየት ሲሰጡ፤ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡ ሳይኾን የቴሌቭዥን ፕሮግራም የሚያቀርቡ አንባቢ ይመስሉ ነበር፡፡ ሐሳባቸውንም በአንድ ትንፋሽ በመደዳ ደርድረው ነበር ያጠናቀቁት፡፡
ባነሱት ሐሳብም፤የግሉ ፕሬስ ያላደገው ፕሬሱ ለኢትዮጵያ እንግዳና አዲስ ባሕል መኾኑን በመጥቀስ የዛሬ ሃያ ዓመት የሰጡትን አስተያየት ዛሬም ደግመው ለዕድገቱ መቀጨጭ እንደምክንያት ያስቀምጣሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ የግሉ ፕሬስ በጥፋት ጎዳና ላይ እየተጓዘ መኾኑን በእርግጠኝነት ተናገሩ፡፡ ለዚህም አስተዋጾ ያበረከቱት፤የሕትመት ሚዲያው አጀማመር ላይ በግንባር ቀደምትነት የተሰለፉት ጋዜጠኞች ከደርግ ሥርዐት የተረፉ መኾናቸውን ይነግሩናል፡፡ ለዚህ ንግግራቸው ማልበሻም ይኾን ዘንድ ኢቴቪ የዱሮ ጋዜጦችን ምስል አሳይቶናል፡፡ እውነት ግን ጣቢያውና መንግሥት (ኢሕአዴግ) ስለነዚህ ጋዜጦችና የደርግ ርዝራዥ ስለሚላቸው ሰዎች መቼ ነው ማውራት የሚያቆመው? ምስሉንስ መቼ ነው በሌላ የሚቀይረው? እርሱ የደርግ ርዝራዥ የሚላቸው ሰዎች (ከጥቂቶቹ በስተቀር አብዛኞቹ በደርግ ሥርዐት ወቅት ተማሪዎች ነበሩ) ይታተሙ የነበሩ ጋዜጦች እኮ በተለያ ምክንያት ከገበያ የወጡ፣ በራሱ በመንግሥት ድምጥማጣቸው እንዲጠፋ ተደርገው ከዓመታት በፊት የተዘጉ፣ ባለቤቶቻቸውና ጋዜጠኞቻቸው በእስር የተሰቃዩ፣ የተሰደዱ፣ ሞያ የቀየሩ ፣ በሕይወት የሌሉ እንዲሁም በሌላ ምዕራፍ ታስረው እስር ቤት የሚገኙ ናቸው፡፡

እንዚህን ጋዜጦች ገዢው ፓርቲና ባለሥልጣናቱ የሚያስታውሳቸውን ያህል ስንትና ስንት መስዋትዕነት የከፈሉላቸው ባለቤቶቹ እንኳን የሚያስታውሷቸው አይመስለኝም፡፡ የፕሬስ ታሪክ ሰፊና ከዓመት ዓመት የተለያየ አካሄድ የነበረው ነው፡፡ ከ1994 ዓ.ም እስከ 1997 ዓ.ም የነበረውን የፕሬስ አካሄድ ብቻ ብንመለከተው በእነዚህ ጊዜያት ትንሽ ለውጥ የታየበት፣ የነፃ ፕሬስ ተቋማትና የሕትመት ውጤቶች በቁጥር ብቻ ሳይሆን በይዘትም ለውጥ ያሳዩበት አዳዲስ ባለሞያዎች ኢንዱስትሪውን የተቀላቀሉበት፣ የጋዜጠኝነት ሞያን ለማዳበር የሚጣጣሩ ጋዜጠኞች የተፈጠሩበት፣ በዕውቀትም በክህሎትም ብቃት ያላቸው ሞያተኞች ሞያውን የተቀላቀሉበት ጊዜ ነበር፡፡ ከ97 በኃላ ደግሞ ሌላ አዲስ ባሕል ይዞ መጥቶ ተመልሶ ጠፍቷል፡፡ አሁን ደግሞ በስደትና በእስር፤ በተፅእኖ፣ በወከባና በሽብርተኝነት ዐዋጅ የተጨነቀ ፕሬስ ተፈጥሯል፡፡

ከዚህ ዘጋቢ ፊልም ያስገረመኝ ሌላው ነገር፤የፖለቲካ ፓርቲ አባላት የነበሩና የኾኑ ግለሰቦች በሕትመት ሚዲያ ላይ የሚጻፉትን ጹሑፎች ከእነ ገጻቸው በምስል እያሳየ የአቶ ብርሃኑ አዴሎን አስተያየት ያቀረበበት ክፍል ነው፡፡ እርሳቸው እንዳሉት ሚዲያው ሥነ ምግባሩን የተከተለ ሥራ ብቻ መሥራት እንጂ በፕሬስ ስም ወንጀል የኾ ድርጊት ላይ ተባባሪ በመኾን ኅብረተሰቡን ለማደናገር መሞከር አግባብ እንዳልሆነ ይገራሉ፡፡ ወንጀል ያሉት ደግሞ በፓርቲ ፖለቲካ ውስጥ ያሉ ሰዎችን እንደ አምደኛ አድርጎ በማቅረብ የእነርሱን የፖለቲካ ፍላጎትና አስተሳሰብ እንዲያንጸባርቁና በመንግሥት በኩል የመጣውን ለውጥ እንደሌለ አድርገው እንዲናገሩ በመፍቀዱ ነው፡፡

የፖለቲካ ፍላጎትና አስተሳሰብን ማንጸባረቅ፣ ‹‹ለውጥ አልመጣም›› ብሎ መከራከርን ማነው ወንጀልና ሽብርተኝነት ያደረገው? ከአንድ ሚዲያ ግዴታዎች አንዱ የተለያየ እምነትና አስተሳሰብ ያላቸውን ሰዎች ሐሳባቸውን የሚገልጹበትን መንገድ በእኩል ማመቻቸት፣ የተለያየ ሐሳብ ያላቸው ሰዎች እንዲከራከሩበት በር መክፈት ነው፡፡ ይህ ለአቶ ብርሃኑ እንዴት ወንጀል ኾኖ እንደታያቸው አልገባኝም፡፡ በዚህ አስተሳሰባቸው ሃያ አራት ሰዓት ሙሉ የኢሕአዴግን ፖለቲካዊ አስተሳሰብ እንዲህ ካሉ ዶክመንተሪዎች ጋራ እያዋዛ ተመልካቹ ላይ የሚጭነውን የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ምነው በሽብር ሳይፈርጁ ዘለሉት? ይኸው የእራሳቸውን ሐሳብ እራሱ እየጫነብን አይደል እንዴ?

የሕትመት ሚዲያው ሥርጭት
ሌላው ከዚህ ዶክመንተሪ ውስጥ ያስገረመኝ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ም/ዋና ዳሬክተር አቶ ልኡል ገብሩ የሕትመት ሚዲያ ሥርጭትን በሚመለከት ጥናት ማድረጋቸውን በመግለጽ የሰጡት አስተያየት ነው፡፡ እንዲህ ይላል፤‹‹እነዚህ የሕትመት ሚዲያዎች ከፍተኛ ቅጂ አላቸው ከተባለ አርባና አርባ አምስት ሺሕ ነው፡፡ ከአርባ አምስት ሺሕ ቅጂ ውስጥ በጣም ብዙ ሸጡ ከተባለ ሁለት ሺሕ ኮፒ ብቻ ነው የሚሸጡት፡፡ ሌላውን አርባ ሦስት ሺሕ ቅጂ መጋዘን ውስጥ ያስቀምጡታል፡፡ አንድ የሕትመት ውጤት አትራፊ የሚኾነው አንድም ማስታወቂያ ማግኘት አለበት ወይም ደግሞ የሥርጭት መጠናቸው ከአንድ መቶ ሺሕ መብለጥ አለበት›› አሉ፡፡ የአስተያየታቸው ማጠቃለያም እነዚህ የሕትመት ውጤቶች እንዲህ የሚያደርጉት ሌላ በእነርሱ በኩል የራሱን አጀንዳ ለማስፈጸም ፍላጎት ካለው አካል የገንዘብ ድጋፍ እያገኙ ነው የሚል ነው፡፡

እነዚህ የሕትመት ውጤቶች አርባ አምስት ሺሕ አሳትመው አርባ ሦስት ሺሕ መጋዘን ውስጥ እያስቀመጡ ከኾነ አቶ ልኡል በእውነትም ልክ ናቸው፡፡ እነዚህን የሕትመት ሚዲያዎች የሚያግዝ ረጅምና ፈርጣማ የኢኮኖሚ ክንድ ያለው ሌላ አካል ለመኖሩ እርግጠኛ ኾኖ መናገር ይቻላል፡፡ እውነቱ ግን ይህ አይደለም፡፡ መቼም አቶ ልኡል ይህን ጥናት ራሳቸው ሠርተውታል ተብሎ አይታመንም፡፡ በመጀመሪያ የተጠቀሰው ቁጥር በሣምንት ነው በወር? ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ በግንቦት ወር 2006 ዓ.ም ያወጣው መረጃ በስርጭት ላይ የዋሉ ጋዜጦችን ከእነ ሕትመት ብዛታቸው ይዘረዝራል፡፡በዚህ መረጃ መሠረት በሣምንት ውስጥ ከፍተኛውን የሥርጭት መጠን የያዘው መጽሔት አንድ ብቻ ነው፤ እርሱም ዐሥራ ስምንት ሺሕ ቅጂ ነው፡፡ ይህ በአራት ሳምንት ተባዝቶ በወር ቢሰላ ሰባ ሁለት ሺሕ ይመጣል፡፡ የሣምንት ሕትመታቸው በወር ተሰልቶ ሃምሳ ሺሕ ቅጂ የሚያሳትሙት ከሦስት አይበልጡም፡፡ እንግዲህ እኔ ያገኘኹት መረጃ የእርሳቸው መሥሪያ ቤት ካወጣው ሰነድ ላይ ነው፡፡ እርሳቸው ግን ከየት ነው ያገኙት?

የእርሳቸውን መረጃ እንደወረደ እንቀበለውና፤ ሁለት ሺሕ ብቻ ተሸጦ ሌላው አርባ ሦስት ሺሕ ጋዜጣ መጋዘን ያስቀምጣሉ ብለዋል፡፡ ለመሆኑ አቶ ልኡል አርባ ሦስት ሺሕ መጽሔትና ጋዜጣ ከማተሚያ ቤት ሲወጣ ብዛቱን ዐይተውት ያውቃሉ? በስንት ብር እንደሚታተምስ ያውቃሉ? አንድ የሕትመት ውጤት በጣም አትራፊ ቢኾን እንኳን ይህን ያህል ቁጥር ያለው የሕትመት ውጤት ለአንድ ጊዜ ሳይሸጥ ቢመልሰው መልሶ በእግሩ መቆም እንዴት እንደሚከብደው አያውቁም?፡፡ አሁንም እርሶ ያሉትን እንቀበልና የሕትመቱን ኪሳራ ለመሸፈን ደግሞ ከፍተኛ የኾነ የገንዘብ ዝውውር መኖር አለበት፡፡ ጋዜጠኞች የሚጠጡበትን የሻይ ሲኒ በቀለም ለይቶ ለሚያውቀው የእርስዎ መንግሥት እንዲህ ያለ የገንዘብ ዝውውር እያለ እንዴት እስካሁን ሳይደርስበት ቀርቶ ይኾን?

ለመኾኑ አቶ ልኡል በአዲስ አበባና በመላው ኢትዮጵያ ስንት አከፋፋይና ስንት አዟሪ እንዳለ ያውቃሉ? አንድ አዟሪ በከፍተኛ መጠን የሚሸጠውን ተፈላጊ የሕትመት ውጤት በቀን ስንት እንደሚሸጥ ያውቃሉ? እኔ በግሌ ባያውቁ ነው እንጂ ቢያውቁ እንዲህ አይሳሳቱም ብዬ ገመትኩሎት፡፡

መቼም ሪፖርትር ጋዜጣን ያውቁታል?ሪፖርትር ጋዜጣ ላይ ለሦስት ዓመታት በከፍተኛ ሪፖርተርነት ሠርቻለሁ እናም ጋዜጣው ዐሥረኛ ዓመቱን በኢግዚብሽን ማዕከል ሲያከብር ከመርሐ ግብሩ አንዱ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያሉትን አከፋፋዮችና አዟሪዎችን የፕሮግራሙ ተሳታፊ እንዲኾኑ መጋበዝ ነበር፡፡ እነዚህን አዟሪና አከፋፋዮች ለማግኘት ምን ስልት ተነደፈ መሰሎት? ጋዜጣውን ለማከፋፈል የሚወስዱ ንኡስ አከፋፋዮች ጋራ እየተሄደ አዟሪዎቹ ለመረከብ ሲመጡ ስማቸው እየተመዘገበ ካርድ ተሰጣቸው፡፡ በወቅቱ ከሦስት የማይበልጡ ዋና አከፋፋዮች፣ አርባ የሚኾኑ ንኡስ አከፋፋዮችና አራት መቶ የሚኾኑ አዟሪዎች ተገኙ፡፡

ከስድስት በላይ የሕትመት ውጤቶች ላይ ስለሠራኹ ሌላ በርካታ ምሳሌ ልጨምርሎት እችላለሁ፡፡ ለዛሬ ግን በዚህኛው ምሳሌ ላይ ተንተርሼ ላስረዳዎት፡፡ እነዚህ አከፋፋይና አዟሪዎች ሌላው ቀን ብዙም ገበያ ስለሌለው ከቅዳሜና እሁድ በስተቀር ሁሉም በአንድ ጊዜ አይወጡም፡፡ ቅዳሜና በትንሹ ሁለት መቶ ሃምሳ የሚኾኑት አዟሪዎች ወጥተዋል ተብሎ ይገመታል፡፡ እንደ ቦሌ፣ መገናኛ፣ አራት ኪሎ፣ ፒያሳ….. እያሉ ዋና ዋና ቦታዎች ያሉትን አዟሪዎች ያስታውሷቸው መኪናዎትን ያቁሙና ስርጭቱ ከፍተኛ ነው ያሉትን አንዱን የሕትመት ውጤት ስም ጠርተው ‹‹በቀን ስንት ተረክበህ ስንት ትሸጣለህ?›› ይበሉና ይጠይቁት፡፡ ከዛም እኔ ከምነግሮት ቁጥር ጋራ ያነጻጽሩታል፡፡ ለማንኛውም አንድ ጋዜጣ አዟሪ በአሁኑ ሰዓት ሽያጩ ከፍተኛ ነው የተባለለትን መጽሔት በቀን በትንሹ ስልሳ ይሸጣል፡፡ ሽያጩ ከፍተኛ ሲኾን ደግሞ አንድ አዟሪ እስከ አንድ መቶ ሃምሳ ሊሸጥ ይችላል፡፡ ይህን ቁጥር በሁለት መቶ ሃምሳ ብናበዛው ዐስራ አምስት ሺሕን እናገኛለን፡፡ ከዚያም በአዲስ አበባ አቅራቢያ ያሉትን ጨምሮ ወደየክልል ከተሞች ሲበተን ደግሞ የታተመውን ቁጥር ልክ ይገኛል ማለት ነው፡፡

‹‹አንድ የሕትመት ውጤት አትራፊ የሚኾነው አንድም ማስታወቂያ ማግኘት አለበት ወይም ደግሞ የሥርጭት መጠናቸው ከአንድ መቶ ሺሕ መብለጥ አለበት›› ሲሉ ሰማሁ ልበል፡፡ ሐሳቡን ልክ ኖት ቁጥሩን ግን ተሳስተዋል አቶ ልኡል፡፡ አንድ ጋዜጣም ኾነ መጽሔት ከዐሥር ሺሕ በላይ ያለ ማስታወቂያም ቢታተም ትርፍ ያመጣል፡፡ ከዛ በታች ከኾነ ደግሞ የሥራ ማስኬጃ ወጪውን አመጣጥኖ ራሱን ይችላል፡፡ ይሄም ራሱን የቻለ ስሌት አለው፡፡ እንደ ሥራ ማስኬጃው ወጪ፣ እንደ ገጽ መጡ፣ እንደ ቀለሙና እንደ ማተሚያ ቤቱ ዋጋ ወጪና ገቢው ይለያያል፡፡ እርሶ ስላላወቁ ነው እንጂ አብዛኛው ጋዜጠኛ ለስሜቱ፣ ለፍላጎቱና ለእምነቱ የሚሠራ ነው፡፡ ኑሮውን ቀረብ ብለው ቢያዩት መሳሳቶ የበለጠ ይገባዎት ነበር፡፡ ደግሞ እኮ በእርሶ አባባል ይህ የሚደረገው ሁሌም ነው፡፡ ታዲያ የት ነው የሚቀመጠው? ምን ዐይነት መጋዘን ይኾን የሚችለው? እስቲ ኤቴቪ በነካካ እጁ አንድ አርባ ሦስት ሺሕ ሕትመት የያዘ መጋዘን ያሳየን፡፡

አዟሪና አከፋፋዮች ለምን አንድ ለአምስት አይደራጁም?
የዘጋቢ ፊልሙ የመጨረሻው ማጠንጠኛ ችግሮቹን አዟሪና አከፋፋዮች ላይ የሚደመድም ነው፡፡ የሕትመት ሥርጭቱን የማከፋፈል ሥርዐት በሚመለከት ወጥ የኾነ አሠራር ስለሌለ አከፋፋዮቹ እንደፈለጋቸው የሚያሽከረክሩት ነው የሚል መልዕክትም ተላልፏል፡፡ እነዚህ አከፋፋዮች አፍራሽ ተልኮ ካላቸው ከተወሰኑት ሕትመቶች ጋራ ትስስር ስላላቸው የተወሰነው አሣታሚ እንዳይሸጥለትና ገበያ ውስጥ እንዳይቆይ የማድረግ ኃይል አላቸውም ተብሏል፡፡

‹‹በፕሬስ ውጤቶቹ ላይ ትልቅ ተጽዕኖና አፈና እየፈጠሩ ያሉት አከፋፋዮቹ ናቸው፡፡›› በማለት በዘጋቢ ፊልሙ ላይ አስተያየት የሰጡት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴታ አቶ እውነቱ ብላታ፤ እነዚህ አከፋፋዮች የፕሬሱን ይዘት ሳይቀር እየወሰኑ ሚዛናዊ የኾነው ከገበያ እንዲወጣ እንደሚያደርጉ፣ ይሄም መንግሥት ባለበት አገር በጠራራ ጸሐይ እየተፈጸመ ያለ ፀረ ፕሬስ ዕድገት መኾኑን በመግለጽ በመንግሥት በኩል ይህን ችግር መፍታት እንደሚኖርባቸው ሲናገሩ አድምጠናቸዋል፡፡

አቶ እውነቱን እኔ ብኾን የጠየኳቸው ኖሮ፤ ‹‹ለመኾኑ የትኞቹ ጋዜጠኞች በዚህ ምክንያት ከገበያ ወጡ? የትኞቹ አከፋፋዮችና አዟሪዎች ናቸው ይህ ኃይል ያላቸው?›› ብዬ እጠይቃቸው ነበር፡፡ እርግጥ ነው ከ1994 ዓ.ም እስከ 1997 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ እነ አቶ ሽመልስ ከማል በፊት ለፊትና በእጅ አዙር ኒሻን፣ ኢፍቲን፣ ኔሽንና የመሳሰሉትን ጋዜጦች በሚያሳትሙበት ጊዜ እንዲህ ያለ ምክንያት ይሰጡ ነበር፡፡ በግላቸውም ከጓደኞቻቸው ጋር ኾነው ‹‹እንዲህ ያለውን ሰንሰለት እንሰብራለን›› በማለት ይዝቱም ነበር፡፡ በ97 ምርጫም ይህ ነገር ተደጋግሞ ይነገር ነበር፡፡ ያን ግዜ የሕትመት ሚዲያው ብዛት ስለነበረው ስርጭቱም ከፍተኛ ስለነበር ወሬው እውነት ይሁን አሉባልታ ሳይታወቅ አልፏል፡፡አሁን ግን ባለሥልጣናቱ እንዳከበዱት ሳይኾን ካሉም ‹‹እነ እከሌ›› ናቸው ብሎ መጠቆም ይቻላል፡፡እስቲ እነ እከሌ በሉ፡፡

እነዚህ አከፋፋይና አዟሪዎች እኮ ከአንድ ጋዜጣ ላይ የሚያገኙት ከሽርፍራፊ ሳንቲም አይበልጥም፡፡ የእነርሱ ገቢ የሚጨምረው ሕትመቱ በተሸጠ ቁጥር ነው፡፡ እንኳን ሊያፍኑ ቀርቶ ገቢ ስለማይሞላላቸው አከራይተው ገንዘብ ሲያገኙ ያላየ አንባቢ ይኖር ይኾን? አብዛኞቹ አከፋፋይና አዟሪዎች የሕትመት ውጤት በማይወጣበትና የሥርጭት መጠኑ አነስ ያለ ሲኾንባቸው እንደ ጫማ መጥረግ፣ ሎቶሪ መሸጥና የመሳሰለውን የቀን ሥራ ሠርተው ወደ ቤታቸው የሚገቡ ናቸው፡፡

በመጨረሻ
ኤቴቪና ባለሥልጣናቱ በዚህ ዘጋቢ ፊልም ማጠቃለያ ላይ ለፕሬሱ ዕድገት ተቆርቋሪ ለመምሰል ሞክረዋል፤ ፕሬሱ ያለበትን የማተሚያ ቤት ችግር፣ የባለሞያ ችግር፣ የቢሮና የመሠረታዊ መገልገያ ዕቃዎች ችግር፣ የማስታወቂያ ችግር እንዲሁም የአዟሪና አከፋፋይ ችግር ለመፍታት የተነሳ አስመስሎ አቅርቧል፡፡ በፕሬሱ ላይ እነዚህ ሌሎች ችግሮች እንዳሉበት ማንም አይክድም፡፡ ዋናው ችግር ግን ይሄ አይደለም፡፡ መንግሥት ዋናውና መሠረታዊ የኾነውን የፕሬስ ነጻነት አንቆ ይዞ በጭፍጫፎው ላይ አዛኝ ለመምሰል የሚያደርገው ሙከራ ‹‹ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ…›› ያስመስልበታል፡፡ እንደ ባለሥልጣናቱ ገለጻ መንግሥት እነዚህን አዟሪዎችና አከፋፋዮችን በጎንዮሽ በቁጥጥር ሥር የማድረግ ፍላጎት እንዳለው አሳይቶበታል፡፡ እኔ ደግሞ ሐሳብ አለኝ፤ መንግሥት በነጻ ፕሬስ ጉዳይ እንዲህ እንቅልፍ አጥቶ ከሚያድር አከፋፋዮቹና አዟሪዎቹ ለምን በአንድ ለአምስት አደራጅቶ እርፍ አይልም?

 tsiongir@gmail.com

(ቅዳሜ ሐምሌ 12 ቀን 2006 ዓ.ም በወጣው ፋክት መጽሔት ላይ የታተመ)

በሰሜን ሸዋ መርሃቤቴና አካባቢው የተነሳው ውጥረት ተባብሷል፤ ጫካ የገቡ መሪዎች የሕዝቡን አመጽ ተቀላቅለዋል

$
0
0
(በመርሃቤቴ አካባቢ በተነሳው ግጭት ተጎድተው ሆስፒታል ከገቡት መካከል)

(በመርሃቤቴ አካባቢ በተነሳው ግጭት ተጎድተው ሆስፒታል ከገቡት መካከል)

ምኒልክ ሳልሳዊዝ እንደዘገበው፦

በሰሜን ሸዋ መርሃቢቴ እና አካባቢው ላይ የተነሳው የህዝብ እምቢተኝነት ከቀድሞው የበለጠ ተባብሶ ያለበት ሁኔታ መኖሩን ከአካባቢው የሚወጡ ዘገባዎች ጠቁመዋል። ሕዝቡ የመብራት ትራንስፎርመር መወሰዱን መሰረዙ ቢነገረውም ልታዘናጉን ነው። የከተሞቻችንን ንብረት የመጠበቅ ሃላፊነት አለብን የፌዴራል ፖሊሶች ከአካባቢያችን ይውጡልን የሚሉ ጥያቄዎችን በማንገብ መሳሪያውን ይዞ ወደ ከተማው በመውጣት አካባቢውን በውጥረት እንደሞላው ታውቋል።

የመርሃቢቴ ህዝብ አሁንም በያለበት እየተጠራራ የተደበቀውን የጦር መሳሪያ በማውጣትበመሰባሰብ መንገዶችን ተራሮችን ሸጦችን ተቆጣጥሮ ለውጊያ እየተዘጋጀ ነው። ጎረቤት ወረዳዎችም ይህንን የመሬን ህዝብ አመፅ በመደገፍ ወገናዊ ድጋፍና ትብብር ለማድረግ እየተዘጋጁና ግንኙነት እያደረጉ መሆኑን ከሚደርሱን መረጃዎች አረጋግጠናል። የየአካባቢው የወያኔ ታጣቂ ሚሊሻዎች፣ አስተዳደሮች፣ ካድሬዎች በሚያስደስት ሁኔታ ከህዝቡ ጎን ተሰልፈዋል።

እንደምኒልክ ዘገባ ከሆነ ወያኔ በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ወድቋል ወደ ማይችለው አዘቅትም ገብቷል። ህወኃትን ከነ ግሳንግስ አገዛዙ ለማስወገድ ጊዜው አሁን ነው፣ በተለያየ መንገድ ሸፍተው በጫካ የነበሩ መሬዎች ሁሉ የህዝቡን አመፅ ተቀላቅለዋል ሲል ዘገባውን ቁጭቷል።


የአሁኑ ትዉልድ ያለነጻነቱ መኖር የሚፈልግ ትዉልድ አይደለም (ግርማ ካሳ)

$
0
0

ግርማ ካሳ

Habtamu abrhayeshiwas daniel

በአንቀጽ 19፣ ንኡስ አንቀጽ 3፣ የአገሪቷ ሕገ መንግስት፣ ዜጎች ሲታሰሩ በ48 ሰዓት ዉስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ እንዳለባቸው በግልጽ ይደነግጋል። ክሱ በግልጽ ችሎት መሰማቱን ተከሳሾች የማይፈልጉ ከሆነ፣ ወይንም በአገር ደህንነት ላይ ችግር ያመጣል ተብሎ ካልታሰበ በቀር፣ በአንቀጽ 20 ፣ ንኡስ አንቀጽ 1 እንደተቀመጠው፣ ዜጎች በግልጽ ችሎት የመሰማት መብት አላቸው።

አንቀጽ 21 ንኡስ አንቀጽ 2፣ በጥበቃ ሥር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ዜጎች ከትዳር ጓደኞቻቸው፣ ከቅርብ ዘመዶቻቸው፣ ከጓደኞቻቸው፣ ከሃይማኖት አማካሪዎቻቸው፣ ከሐኪሞቻቸው እና ከሕግ አማካሪዎቻቸው ጋር የመገናኘትና በነርሱም የመጎብኘት መብት እንዳላቸው በግልጽ አስፍሯል።

እነ ሃብታሙ አያሌው ፣ ሐምሌ አንድ ቀን ነው የታሰሩት። ማእካላዊ እንደታሰሩ እንደታወቀ፣ ጠበቃዎቻቸው ሊጎበኗቸው ይሄዳሉ። «የፀረ ሽብር ኃላፊውን አናግሩ» የሚል ምላሽ ይሰጣቸዋል። እስረኞችን ማናገር ስላልቻሉ፣ ጠበቆቹን ፍርድ ቤት ይከሳሉ። የፌደራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የአራዳ ምድብ ፍ/ብሔር ችሎት የጸረ-ሽብር ግብረ ኃይል ባለስልጣናት እስረኞቹን ይዘው እንዲቀርቡ፣ ሐምሌ 6 ቀን ትእዛዝ ይሰጣል። ኮማንደር ተክላይ መብራቱ በታዘዘው መሰረት ይቀርባሉ። ታሳሪዎቹን ግን ይዘው አልመጡም። ተከሳሾቹ በሰኔ 30 ቀን 2006 ዓ.ም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በወጣ የመያዣ ትዕዛዝ፣ ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም እንደተያዙና ሐምሌ 2 ቀን 2006 ዓ.ም ፍ/ቤት ቀርበው ቀጠሮ እንደጠየቁባቸውና በህጉ መሰረት መብታቸው ተጠብቆ እንዳለ ይናገራሉ። ማስረጃ አምጡ ተብለው በተጠየቁት መሰረት፣ በነጋታው የጽሁፍ ማስረጃ ያቀርባሉ። ፍርድ ቤቱም የእስረኞች ጠበቆችን ክስ ፋይል ይዘጋል። ኮማንደር ተክላይ፣ እስረኞቹ በ48 ሰዓት ዉስጥ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን  ያሳይል ያሉትን የወረቀት ማስረጃ ቢያቀርቡም፣ እስረኞችን ያያቸው ማንም ሰው የለም። ይኸው ሐምሌ 15 ደርሰናል። ጠበቆች፣ ቤተሰብ፣ መንፈሳዊ አባቶች …አንዳቸውም እስረኞችን እስከ አሁን ማየት አልቻሉም። እስረኞቹ ምንም አይነት ሁኔታ ላይ እንዳሉ አይታወቀም።

በእስረኞች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ከመድረሱ የተነሳ፣ ሰው እንዳያያቸው ሆን ተብሎ በሚስጥርና በጨለማ ፍርድ ቤት ቀርበው፣ እንደ ተለመደው የ28 ቀን ቀጠሮ ተሰጥቶ ሊሆን ይችላል። አሊያም ኮማንደር ተክላይ አንዱን ካድሬ ዳኛ ፣ እስረኞቹ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ፣ ፎርጅድ ወረቀት እንዲጽፍ አስደርገዉትም ይሆናል የሚል ግምትም አለኝ።

በዚህም ሆነ በዚያ፣ አንድ ነገር በጣም ግልጽ የሆነ ነገር አለ። እርሱም ኢሕአዴግ ሕገ መንግስቱን በአፍጢሙ እንደደፋው ነው። ፍርድ ቤት መቀለጃ ሆኗል። «የሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ በመሞከር» እያሉ ሌሎችን ይከሳሉ። ግን ሕግ መንግስቱን እየናዱ ያሉት እነርሱ እራሳቸው ሆነዋል። ሌላዉን ሽብርተኛ እያሉ ይከሳሉ። ሕዝቡን እያሸበሩ ያሉት ግን እነርሱ ናቸው።

ይህ በአገዛዙ የምናየው፣ አይን ያወጣለት የሕግ ጥሰትና መንግስታዊ ዉንብድና ፣ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ኢሰብአዊ ግፍና ንቀት የኢሕአዴግ ስርዓት ፍጻሜ መጀመሪያ ነው።

አንድ መርሳት የሌለብን ነገር አለ። ይሄን ሁሉ የሚያደርጉት ፈርተን፣ ባርነትን አሜን ብለን ተቀብለን፣ ተስፋ ቆርጠን እንድንቀመጥ ነው። «እነ ሃብታሙን ያየህ ፣ ተማር። አርፈህ ቁጭ በል» የሚል መልእክትን ለማስተላለፍ ነው። ነገር ግን አይሰራም። የአሁኑ ትዉልድ በሌሎች አገሮች ስላለው ነጻነት ያነባል፤ ያዳምጣል፤ ያውቃል። በምንም መልኩ ነጻነቱንና መብቱን ተገፎ መኖር የሚፈልግ ትዉልድ አይደለም። ለዚህም ነው፣ ትላንት እነ እስክንደር ነጋ ቢታሰሩም ከሁሉም አቅጣጫ እሳት የላሱ ደፋር ጋዜጠኞችና ብሎገሮች ብቅ፣ ብቅ ያሉት። እንደገና ደግሞ አሁንም ጋዜጠኞችና ብሎገሮችን አሰሩ። ነገ ደግሞ ሌሎች ሁለት እጥፍ ወጥተው የነ እስክንደርን ፣ የዞን ዘጠኞችን ድምጽ ማስተጋባት ይቀጥላሉ።

ትላንት እነ አንዱዋለም አራጌ ቢታሰሩም፣ እሳት የለበሱ፣ እንደ አብርሃ ደስታ፣ ሃብታሙ አያሌው ያሉ ሰላማዊ ወጣት ፖለቲከኞች ብቅ ብለዋል። የማይፈሩ፣ ብስለት ያላቸው፣ የሰላማዊ ትግል አርበኞች !!! እንደገና አገዛዙ እነ ሃብታሙን አሰረ። ሰው ግን አይደናገጥም። ብዙዎች ሰላማዊ ትግሉን ይቀላቀላሉ። እነ ሃብታሙ ዳግማዊ አንዱዋለም ነበሩ። አሁን ደግሞ ዳግማዊ አብርሃዎች፣ ዳግማዊ የሺዋሶች፣ ዳግማዊ ሃብታሙዎች ፣ ዳግማዊ ዳንኤሎች፣ ዳግማዊ ወይንሸቶች ይወጣሉ። በምንም መልኩ አገዛዙ ለዲሞክራሲና ለነጻነት የሚሰማዉን ጩኸት ዝም ማሰኘት አይችልም። በምንም መልኩ ጥቂቶች የሚሊዮኖች ድምጽ ማፈን አይችሉም።

ጨዉ ለራስህ ስትል ጣፍጥ እንደሚባለው፣ ኢሕአዴጎች ለራሳቸው ሲሉ የሚበጀዉን በቶሎ ያደርጉ ዘንድ አስጠነቅቃለሁ። አለበለዚያ ግን አወዳደቃቸው እጅግ በጣም የከፋ ነው የሚሆነው። ከሚሊዮኖች ጋር ተጣልተው የትም አይደርሱምና።

ወደ ውሃው ትሄዱ ወይስ ውሃው ወደ እናንተ ይምጣ? –ከመኳንንት ታዬ (ደራሲና ፀሃፊ)

$
0
0

ፈላስፋ እንዲ አለ ብዬ ፅሁፌን ልጃምር ”የማሰብ ደግነቱ ነገርን ከልብ መረዳት ነው ፤መጥፎነቱም ነገርን ከልብ አለመረዳትና አለማወቅ ነው’::የማስተዋል ቁም ነገሩ ትግስትና ዝግታ ነው።መጥፎነቱም መቸኮልና መቅበዝበዝ ነው። ይህን ከአንጋረ ፈላስፋ (ከፈላስፋዎች አባባል ከጠቀስኩ ዛሬ ብዕሬን እንዳነሳ ወደገፋፋኝ አንዳች ነገር ነጥብ በነጥብ ለመጋዋዝ ልሞክር ።
river walking
ሰሞኑን አንዳች የሚያስገርም ከመባል ያለፈ ነገር በእኛ ዘንድ ተሰማ ።መቼስ መንግስታችን ልበል ከተባለ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን(የግንቦት7 ዋና ፀሃፊ) ከየመን መንግስት ላይ በዶላር መግዛቱን እውን ሆነ። ህሊናውን እንደ መጫሚያው በሚረግጥ እና የሐገር ክብር በማይሰማው ብሎም ነገን ባላገናዘበ ሁኔታ አሳልፎ ሰጣቸው ።ግድ የለም ነገ እሩቅ አደለም ።እናት ሐገር ኢትዮጲያ የትላንት ትውልድ ካላት ብድሩ ብዙ ግዜ አይወስድም።ይሁንና አሁን የገዛ ሐገሩን በሽፍትነት ስለሚያስተዳድረው የኢትዮጲያ ቅኝ ገዢ ጥያቄ ይኑረኝና ወደ ዛው ልጓዝ። በተለምዶም ሆነ ስለጥሩ መጠቃቃም የሰው ልጅ ውሃ ሊቀዳ ወደ ውሃው ይሄዳል ። ቢህ ምክንያት የሰው ልጅ በውሃው ተጠቃሚ ሆኖ(ለፈለገው ተግባር እየተጠቀመበት) ይሄው አስከዛሬ አለ። በተቃራኒው ግን ውሃው እዛው የሰው ልጅ ያለበት ድረስ ከሄደ በሰውና በንብረት ላይ የሚያደርሰው አደጋ መጠኑ ሰፊ ነው ።ለዚህ አለም በሙሉ ያለነጋሪ የሚያውቀው ህገ ልቦና የተረጎመለት አንድምታ ነው ። ስለ እርእሴ ለትርጓሜ ያህል ያህል ካልኩ እስቲ ለምን ይህን እንዳልኩ ከላይ ከተንደርደርኩበት ሃሳብ ጋር ሁኜ ወደ ታችኛው ልዝለቅ።

ሰሞኑን አንዲት ወያኔዎቹና ሽፍቶቹ የምትል አጠር ያለች መድብል በማነብበት ግዜ፤ወየነ’ማለት ሐራ(ነፃ) ለማውጣት ታገለ አደመ እንደማለት ሲሆን ወያነ ማለት ደግሞ አብዮት፤ወያናይ ማለት ደግሞ አብየተኛ ማለት እንደሆነ ባስረጂ የሚናገር ፅሁፍ አጋጠመኝ። (ትርጓሜው በትግርኛ ቋንቓ) ማለት እነደሆነ(ዶ/ር ካሳ ገ/ሂይወት እና ዳንኤል ተኸሉ ረዳ ያጤኑታል) ሲል ይገልፀዋል።በዚህም ይመስላል ማለትና ድርጊት አልተገናኘም ሲል በሽፍቶቹ እየተጠቀመ አንድ 7 የሚሆኑ የሽፍትነት ስራ የጀመሩትን እያነጋገረ ይነጉዳል አልጨረስኩትም ። ስለመፃሃፉም ልገልፅ አደለምና ጅማሬዬ፤ወደ እራሴ ከመመለሴ በፊት ወያኔ የሚለው ስም እንኳን አይገልፃችሁም ከትርጓሜ አኳያ ብሎ ሽፍቶችን ስለወሰደ አሱን ተጋርቼው ወደ ጉዞዬ ልቀጥል።

ኢትዮጲያ ደርግን የ መሰለ በቁም ሰው የሚበላ መንግስት እጅግ ውድና በአለም ዘንድ ታላቅ ነገር በመስራት ሐገራቸውንና አለምን ሊያገለግሉ የሚችሉ ልጆቿን ባደባባይ እያረደ ጥሎ እርሱ ግን በመሰሪያ ተከልሎ 17 አመት ከከረመ በሗላ ዳግም ላይመለስ ሊያሸንፋቸው በሚችለው ግን ባለሸነፋቸው ሽፍቶቶች ተከቦ ኢትዮጲያን ዳግም ለሚበላት አዲስ አውሬ አስረክቦ ከሔደ ይሄው 23 አመት ዘለቀ።በዚህ በ23 አመት የፍዳ ዘመናት ውስጥ ከነበረችበት ሳትራመድ ይሁን አልያም ከፍና ዝቅ እያለች ዛሬ በ አለም 2ኛ ደሃ ሐገር ሆና እነ ኤርትራና ሱማሌ ብሎም ጅቡቲ ብቻ በጦርነት የሚታመሱትም ይሁን በሰላም ያሉት ሳይቀድሟት ተስልፋ ይሄው አለች ።

በዚህ ሁነት እና መተላለፍ ውስጥ 23 አመት መቆየት ፤ብሎም መከፋፈልና አንድ መሆን መግደልና መሞት ውስጥ የማስተዋል እጁን ሳይነኩ መቆየታቸው ትላንት ከወደቁት ከመማር ይልቅ ወዳቂዎች ከተንጠለጠሉ በሗላ ያደርጉ የነበሩትን እኩይ ተግባር በመፈፀም የትንፋሽ የበላይነትን ለማግኘት በመሯሯጥ አለቃ እኛ ነን ሲሉ ላስተዋለ” ”የማሰብ ደግነቱ ነገርን ከልብ መረዳት ነበር ” ሲል የሚመጥናቸውን ባይሆን እንኳ ለተናጋሪው የሚስማማውን በማለት ጉዳዩን ያስረዳል።

አሮጌ አመለካከትና የበላይነት ስሜት ለማንም ቢሆን የማስተዋል ነፃነትን ስለሚገፍ በመግደል፤በመግረፍ ፤በማሰር እና በመሳሰሉት እራሱን ለመግለፅ በሞመከር ማንነት ከምንግዜውም በላይ ያወርዳል ብሎም ለነገ የሚፈራው እና የሚሰጋው ነገር እንዳለ የዛሬ ቅዠቱ ያሳያል።
እስቲ እንጋገር አቶ አንዳርጋቸው(ግ7.ዋ.ፀ) በእናንተ እጅ ሲታሰሩ ሲያዙ ሲገደሉም ሆነ ሲገረፉ የመጀመሪያው አደሉም ።በዚህ ማንም አይደነቅም። ይእልቅስ የሚደንቀው አንድን ውሃ የያዘ እንስራ ካፉ ላይ ስለተሸረፈ ውሃ ይፈሳል ወይም ይጎላል ብላችሁ ስለምታስቡት ስለ እናተ መደነቅ ግድ ይላል። እንበል፤ አንዳች ነገር ግን አዲስ ያልሆነ ይኖራል በማለት መለስ ብላችሁ አስቡ።ከእናንተ ጋር ለትግል የወጡ ስንቶች ነበሩ ፤ ስንቶቹስ ተገደሉባችሁ ?ድርጅታችሁን ከመሰረቱት ጀምሮ ለዚ እስካበቁት? (ማውሳት የፈለኩት የትግሉ ሂደት በምን ሁኔታ ላይ እንደደረሰ ስለማላውቀው ግንቦት 7 አደለም)፤ በአግባቡ ማስተዳደር ሲያቅታችሁ ለድክመታችሁ ሽፋን የሚሆን ረጅም መንገድ ስለምትጓዙት ስለ እናንተ ነው።

ታዲያ የቀደሙት ሁሉ የትግል ጓዶቻችሁ ከእናንተ መለየት ሳያቋርጣችሁ ትግላችሁን ፈፅማችሁ እዚ ከደረሳችሁ ስለምን አንድ አንዳርጋቸውን ማሰርና መግደል ትግሉን እንደሚያቐርጠው አመናችሁ? እነሆኝ ማስተዋል ማጣታችሁ መቸኮልና መቅበዝበዛችሁ አለም በግርድፉ ሲያመችሁ ነበር አሁን ግን እያለጠ ማንነታችሁን እንዲያውቅ እድል ሰጣችሁት ።ይሄ ከሰው አደለም ከእግዚያብሔር ነው።አዳርጋቸው ያለው እኮ ትላንት ከትላንት ወዲያ እናንተ ተናግራችሁ ጫካ የገባችሁበትን ቃል ነው።ታዲያ ምኑ ላይ ጥፋቱ? ፍትህ እኩልነት የዲሞክራሲ የበላይነት ስለማይታየኝ ከእናንተ ጋር አልሰራም አለ፤ ወደ የሚመቸውና የተመኘውን ፍትህና እኩልነት አመጣበታለሁ ወዳለው መስመር ተጓዘ።በእናንተ ሲሆን ደግ ነገር ነበር ። ዛሬ ደግሞ አፈሙዙ ወደ እናንተ ሲዞር አንድን ታጋይ በመያዝ የተሻለ ነገር እንደሰራቸሁ ስትናገሩ አልዘገነናችሁም።ለአብነት ያህል አቶ ስብሐት ነጋ ከላይ ከጠቀስኩት መፅሃፍ አዘጋጅ ጋር ባንድ ወቅት ያወጉትን ላስነብባችሁ።

ጠያቂ፤-…….. መሰረታዊ ልዩነት እንዳለችሁ እያወቃችሁ ነው ለንግግር የጋበዛችኃቸው?

ስብሃት ነጋ፤-…………..”እንደኛ ሁኑ አንልም።እንደኛ አልሆንክም ብለን የመታንም አንድም ድርጅት የለም…….” እያሉ በትግሉ ግዜ ከሌሎች ተወጊ ድርጅቶች ጋር ያሰለፉትን የትግል ታሪክ ሲመላለሱ ይነበባል።እሺ ይህ ከነበረ ሐሳባችሁ ዛሬስ አንዳርጋቸውን ለመያዝ ከሌላ ሐገር በእርጥባን የተገኘውን ብር ተጠቅማችሁ ስትወጡና ስትወርዱ መታየታችሁ ከማለታችሁ ጋር አይጋጭም ወይ?በቃ እንደ እናንተ አንሆንም ነው ያለው።እንደ እናንተ አልሆንም ያለሆነውን ካልመታችሁ፡ ባኢስር ላይ ያሉት ትልልቆቹና ትንንሾች ወንዶችና ሴቶች ፤ምን በሰሩ በያስርቤት ታጎሩ? አቦይ ስብሃት?ይህ ብዙ ብርቅ አደለም በእናንተ ዘንድ ። “የማስተዋል ቁም ነገሩ ትግስትና ዝግታ ነው።መጥፎነቱም መቸኮልና መቅበዝበዝ ነው”ይህ አባባል በትንሹ ይገልፃችኃልና።ግና በውኑ አንዳርጋቸውን ስትይዙ በውጭ ስለሚኖሩት ልጆቻችሁና አንባሰደሮቻችሁ ብቻ ስለሁሉም ፤ብሎም ለዲፕሎማሲ ስራ ስለመመላለሳችሁ አስባችኋል? እሱ የሚወክለው ድርጅት የቱንም ያህል መስዋትነት ከፍሎ ተመጣጣኝ ከሚባል በላይ ሊያደርስባችሁ እንደማይችል ስለምን አላወቃችሁም?እሰቲ ቆም ብላችሁ አስቡ።ሲጀመር ወደ ውሃው ትመጡ ወይስ ውሃው ወደ እናንተ ይምጣ ? ብያችሁ ነበር ።ይህ ጥያቄ በዱርና በከተማ በሰላምና በጦርነት የሚታገሉትን ይወክላል። ሕዝቡ ወደ እናንተ ጥያቄና ሓሳብ ከሚመጣ እናንተ ወደ ህዝቡ ሐሳብ ብትሔዱ ለመኖር ባትችሉ እንኳን ለማኗኗር አድሉ ይገጥማችሁ ነበር።በሐገር ውስጥ በሰላም የሚንቀሳቀሰውን ፓርቲ ሁሉ ወነጀላችሁ።ወጣት የተባለ አግዛችሁ አሰራችሁ፤ ገረፋችሁ፤ ገደላችሁ።ግን ትግሉን ማስቆም ግን አልቻላችሁም።ለዚህ ነው ውሃው ወደ እናንተ ከሚመጣ እናተ ወደ ውሃው ሒዱ የምንላችሁ።ይህ ማለት በሰላም ታጥባችሁ በሰላም ጠትታችሁ በሰላም ለመኖር የሚያበቃችሁን ንፁህ አየር እንድትነፍሱ ያደርጋችኋል።ነገር ግን በተቃራኒው ውሃው ወደ እናንተ ከመጣ ፤ከዚህ በፊት እና በቅርብ በውሃ መጥለቅለቅ ምክንያት ብዙ ሕዝባቸውን ብሎም ንብረታቸውን ያጡት ለማግኘት አንዳርጋቸውን የፈለጋችሁበትን ያህል ግዜና እሱን ልትገዙበት ያወጣችሀትን ያህል ገንዘብ ሳታወጡ ታገኛለችሁ።ባጋጣሚ ጋዳፊን (ሊቢያ)ሳዳም ሁሴን(ኢራቅ) ወዘተን እያሰባችሁ ቆዩ።ውሃው ወደ እነሱ እንዳይመጣ በኬሚካል መርዝ ሳይቀር የተጠቀሙ ነበር ግን …….ጫጩት ፊት ፈንግል አይወራም።በርግጥ አስተዳደር ያለማወቅ በራስ መተማን እዳይኖር ከሚያመጣው ጭንቀት በበመነጨ ይህ እንደሚሆን ለማንም ግልፅ ነው ።ግን እኮ አቃተን በቃን ብሎ በሰላም ማስረከቡ በክብር በላይ ክብር እንጂ ውርደት አይሆንም። ጋዳፊም ይሁን ሳዳም ወይም ሁስኒ ሙባረክ ሌሎችም ዛሬ እናንተ የምትመርበትን አብዮት ገንዘብ ስለማድረጋቸው የመጣ የመጨረሻ ጣጣ ነው ።ከሌላው አለም ገንዘብ ብቻ መሰብሰብ ሳይሆን በመምራትና በመመራት ሂደት ውስጥ ላለው ቁም ነገር የሚረዳውን እውቀት መሰብሰብም ብልህነት ነው ።ሰውንም ከመግደል እራስም ከመሞት ያድናልና።

ስለ ሐገር በጥቂቱ ፤-በዚህ ግንዘቤ ውስጥ ለህዝባችሁ ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ግራ በሚያጋበ ሁኔታ እየሰራችሁ እንደሆነ ለእናንተ ግልጸፅ ባይሆንም አለምና የኢትዮጲያ ህዝብ ይገነዘባችኋል።እናንተን እንደማይመለከት ለመግለፅ የወደድኩት ፤ያወጣችሁትን የፀረ ሽብር ሕግ አለም እየተቸበትና እየተቀለደበት እንደሆነ ብሎም በሰባአዊ መብት ተከራካሪዎች ዘንድ የአውሬነት መደብ ተሰጥቶአችሁ ስትገለፁ መቼስ አንዳርጋቸውን በያዘችሁበት(በተለይ)ሰሞን ሚዲያዎችን ተከታትላችሁ ከሆነ የደረሳችሁበትን ደረጃ ያስረግጣል።ታዲያ በዚህ ሁነት ማንን እየመራችሁ ነው?የኢትዮጲያ ህዝብስ ስንት ሚሊዮን ነው?በስልጣን ለመቆየት ትውልድን ማጥፋትን ጨምሮ ሐገርን ቆርሶ አስከመቸብቸብ ድረስ ሁሉንም አደረጋችሁ።ከላይ በተገለፀው መሰረት ሽፍትነትም ላይገልፃችሁ እየተሰናበተ ነው ።አሺ ማን ይሁን ስማችሁ?የኢትዮጲያ መንግስት? ቅኝ ገዢ?ወንበዴ ቡድን? እንደው ማን ?አስቲ ለአፍታ ያህል ተወያዩ።እናንተ ብታረጁም ቢበቃችሁም ገና ያልበቃቸው ልጆቻችሁ አሉ?የትም ይሁኑ የትም የሚኖሩት ማርስ ላይ አደለም ምድር ላይ ነው።ስለዚህ ግፍ ለእነሱ አታቆዩ።በተረፈው ከመለስ ዜናዊ በፊትና በኋላ ብዙ ከእናንተ በህይወትና በሞት የተለዩአችሁ አሉ። ያ ሆኖ እናንተ ማድረግ የምትፈልጉትን እንዳላ አገዳችሁ ሁሉ፤ አንዳርጋቸውንና ሌሎች የፖለቲካ መሪዎችን በማሰርና በመግደል ነገ የተሻለ እንደሚሆን የምታስቡ ከሆነ ከትላንትና ጀምሮ የተኛችሁ ደካሞች ናችሁ።
ቸር እንሰንብት

Sport: ይድረስ ለኢትየጵያውያን ሱዋሬዞች…

$
0
0

suarez
ሰሞኑን ከብራዚሉ የዓለም ዋንጫ ጋር ታያይዞ የሚነገረው የኡራጓዩ አጥቂ ሊዊስ ሱዋሬዝ ጉዳይ የብዙ ኢትዮጵያውያን የአፍ ማበሻ እስከ መሆን መድረሱ ያሳሰበን እኛ ሀገር ወዳዶች ከዚህ በታች ያለውን ደብዳቤ ‹ለሚመለከተው ሁሉ!› በሚል ዘንቢል ውስጥ አድርገን ልከናልና እንደሚሆን አድርጉት እንላለን፡፡

ውድ ኢትየጵያውያን ሱዋሬዞች!
መፅሃፉ ‹የራስህን የአይን ጉድፍ ሳትመለከት የሌላውን ለማየት ምነው ቸኮልክ?› ይላል፤ ለመሆኑ እንደ ሊዊዝ ሱዋሬዝ ትጥቅ አድርገው ፤ልምምድ ሰርተው፤ ሜዳ ገብተው ጨዋታ ከጀመሩ በኋላ የተጋጣሚን ትከሻ በመንከስ የበላይነትን ለማሳየት የሚሞክሩ ሰዎች በሀገራችን ስለመኖራቸው የተረጋገጠ መረጃ እስካሁን ድረስ ባይወጣም በየተሰማሩበት የሥራ መስክ ከግለሰብ እስከ መንግስት ባለስልጣን ድረስ የሚናከሱ ሰዎች ስለመኖራቸው አንከራከርም፡፡ የመንግስትን ሥልጣን ከያዙ በኋላ በየተቀመጡበት የስልጣን ወንበር ላይ ሆነው ‹እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን ፤ከኔ የተለየ አመለካከት ያለው ሁሉ አጥፊና አሻባሪ ነው› ብለው ያወጁትን የሚቀበልና የሚተገብር ሲጠፋ እንደ ሱዋሬዝ ጥርሳቸውን አሹለው የሚመጡ ባለስልጣናት ትላንትም ነበሩ፤ ዛሬም አሉ፡፡እንደ እነሱ አይነት ሱዋሬዞች ህዝብ በጾምና በጸሎት ብቻ የሚገላገላቸው ቢሆን ኖሮ የእስከዛሬው ሱባኤ በቂ ነበር፤ ግን አልሆነም፡፡
ውድ ኢትየጵያውያን ሱዋሬዞች!

በመንግስት ሥልጣን ላይ ሆነው ምንም እንኳ እንደ ሱዋሬዝ በይፋና በአደባባይ ባይናከሱም አስቀድመው ባደራጇችሁኋቸው ጭፍሮቻችሁ አማካይነት በስራና በስራ ብቻ የመለወጥ እቅድ ወጥነው የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን የማጥፋት አቅዳቸውን የሚከውኑ ሱዋሬዞች በየቦታው በየጥጋ ጥጉ ይገኛሉ፡፡ እነዚያ ሱዋሬዞች የመንጋ አስተሳሰብ ውጤት በመሆናቸው አምላካቸው በህጋዊ ንግድ ሥራ ስም የሚዘርፉት ገንዘብ ነው፤ በሚዘረፈው ገንዘብ ዙሪያ የተለየ አመለካከት የሚያራምዱትን ሁሉ በጠላትነት ለመፈረጅ አያመነቱም፡፡ ሀገሪቱ የግላቸው አድገው ስለሚቆጥሩ ባለ ፎቅና ባለ መኪና ከመሆንም አልፈው ኑሯቸውን ከነ ቤተሰባቸው በአውሮፖና በአሜሪካ ያደርጋሉ፤ በሀብቷና በገንዘቧ እንደፈለጋቸው ይሆናሉ፡፡ የፍትሀዊነት ጥያቄ ለሚያነሳባችሁ ለዚያ ሰው ወየውለት! ሱዋሬዝነታቸውን በተግባር ያሳዩታል፡፡
ውድ ኢትየጵያውያን ሱዋሬዞች!

በኪነ ጥበቡ ዘርፍም የተደራጁ ሱዋሬዞች አሉ፡፡ በሚሰሩት ሥራ የህዝብ ተቀባይነት ያገኙና የህዝቡን የልብ ትርታ የሚያስተጋቡ ሙያተኞች ከተለመደው ‹የወደድኩሽ፤ ወደድኩህ› ቅኝት ራሳቸውን ለማራቅ ሲሞክሩ የጥርስ ማስታወቂያቸውን በመልቀቅ ያስጠነቅቋቸዋል፡፡ ሙያተኞቹ የዚህን የጥርስ ማስታወቂያ ባለመረዳት በሙያቸው ማድረግ ያለባቸውንና ያመኑበትን በግጥሞቻቸው፤ በዜማዎቻቸው፤ በሥነ ሥዕል ሥራዎቻቸው፤ በፊልምና በቴአትር ሥራዎችቻው ወዘተ ህዝብ ጋር ለማድረግስ ደፋ ቀና ሲል የነሱዋሬዝ ጥርስ ከክሊኒኩ ታጥቦና ተወልውሎ ብቅ ይላል፡፡ በዚህ ሳቢያ መስራት በሚችሉበት ወቅት ሥራቸውን ያቆሙ፤ መኖር ከሚችሉበት ቀዬ የተባረሩ፤ ሀገር ለቀው የተሰደዱ ቁጥራቸው ጥቂት የሚባል አይደለም፡፡ በምትኩም አንድ አይነት ግጥምና ዜማ በሚያንጎራጉሩ የጥበብ ባለሙያ ተብዬዎች መድረኩ እንዱዲሞላ ያደርጋሉ፡፡ በየመድረኩ የሚጋበዙት እነዚህ ተመሳሳይ ቅኝትና ዜማ የሚያላዝኑ ልማታዊ አርቲስቶች የክብር አክሊል እንዲደፉ ያደርጋሉ፡፡ ከዚህ በኋላ እነሱን ለመተቸትና ሙያዊ አስተያየት ለመስጠት መነሳት ከኡራጓዩ አጥቂ ጋር በባዶ ቤት እንደመፋጠጥ ይሆናል፡፡
ውድ ኢትየጵያውያን ሱዋሬዞች!

በስፖርቱ ዘርፍ ያሉ ሱዋሬዞች ደግሞ አትሌቲክስን ከእግር ኳስ የሚለዩ አይደሉም፡፡ በስፖርት ትምህርት ሆነ በስፖርት ዘርፍ ይህ ነው የሚባል ልምድና ሙያ ሳይኖራቸው የአመራር ወንደሩ ላይ በመቀመጥ የሀገሪቱ የስፖርት ፌፋ የሆኑ ሱዋሬዞች ጥቂት አይደሉም፡፡ በስልጣን ወንበሩ ላይ በመቀመጣቸው ስፖርቱን በራሳችሁ የፖለቲካ አስተሳሰብ አንፃር ለመምራት ይተጋሉ፡፡ በዘርፉ የረጅም ጊዜ ልምድና እውቀት ያላቸው ባለሙያዎች ከስፖርቱ አካባቢ እንዲርቁ ያደርጋሉ፤ በእድል ወይ በአጋጣሚ የተገኙ የስፖርት ድሎችን እነሱን ከሀገር ሀገር ለማዞርና በየስብሰባው ለመጋበዝ በር ይከፍትላቸዋል፡፡ዘመኑ ከደረሰበት የስፖርት አመራር ፍልስፍና አንፃር ማንኛውም አይነት የስፖርት አይነት መመራት ያለበት ትምህርትና በልምድ ባካበቱ ባለሙያዎች የመሆኑ ጉዳይ ለውይይት ወደ የጠረጴዛ ሲመጣ አስቀድመው ካዘጋጃችኋቸው ታፔላዎች መሀከል የፈለጉትን እየመዘዙ በፈለጋቸው ሙያተኛ ጀርባ ላይ ይለጥፋሉ፡፡ ታፔላ አላስለጥፍም ብሎ ጀርባውን ያዞረ ሙያተኛ ካለ ችግር የለውም፤ እንደ ሱዋሬዝ ትከሻው ላይ ሳይሆን አላስነካም ያለው ጀርባው ላይ ይሰፍሩበታል፡፡ ከህዝብና ከመንግስት አላትመው ሀገር ጥሎ እንዲጠፋም ያደርጋሉ፡፡
ውድ ኢትየጵያውያን ሱዋሬዞች!

በመገናኛ ብዙሃን አካባቢ ያሉ ሱዋሬዞች ደግሞ በትከሻና ጀርባ ብቻ የሚመለሱ አይደሉም፡፡መንግስትን የጠቀሙ እየመሰላቸው ሁሉን ነገር ኳኩለውና ቀባብተው ከምታቀርቡት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጀምሮ ፅንፍ ይዘው አንዳች በጎ ነገር ለማየት አቅም እስካጡት ድረስ ሀገሪቱን የፕሮፖጋንዳ አውድማ እየሆነች መሆኗን መመስከር ግድ ነው፡፡ የልማታዊውን መንግስት ልማታዊ አጀንዳዎች ብቻ የሚያራግቡት እነዚያ ባለ ተመሳሳይ ድምፅ ዘጋቢያን በነባራዊው የህብረተሰብ የኑሮ ውጥረት ላይ የተመሰረቱ ዘገባዎችን ከመዘገብ ይልቅ ስለ ህዳሴው ዘመን መለፈፍ ብቻ ይቀናቸዋል፡፡ ለአፍታም ቢሆን ግራና ቀኝ አይመለከቱም፡፡ስለ ስኬት ብቻ ሲያወሩ ውለው ቢያድሩ አይሰለቻቸውም፡፡ ከዚህ ወጣ ያለ ዘገባ በሚዘግቡት ላይ ዘመቻ ይከፍቱባቸዋል፡፡ እነሱ ነጋ ጠባ የምታመልኩት ህገ መንግስት የሀሳብ ነፃነት የሚፈቅድና በተግባርም የሚያበረታታ መሆኑን ግን ለደቂቃም ቢሆን ማሰብ አይፈልጉም፡፡የተለየ ሀሳብ ያላቸው ድምፆችን ‹ውድቀት ናፋቂ ወይም ጦርነት አድናቂ› ብለው ያብጠለጥሏችዋል፡፡ከዚህ አለፍ ያለ መገዳደር የሚፈጥሩት ላይ የተለመደው የሱዋሬዝ ተሞክሮ ተግባራዊ ይደረግባቸዋል፡፡
ውድ ኢትየጵያውያን ሱዋሬዞች!

የተፈጠሩ ችግሮችን ተመልክቶ ማረም፤መታረም በማይችሉት ላይ ይፋዊ ይቅርታ መጠየቅ ለሱዋሬዛውያን ፈፅሞ የሚዋጥ አይደለም፡፡ ከዓመታት በፊት በመርዝ ኬሚካል ነክረው የዘሩ ዘር ጊዜው ደርሶ ሲያፈራ ይመፃደቁበታል፡፡ ለሌሎች ቀርቶ ለራሱ የማይሆን የተጣመመ ትውልድ በማፍራታቸው መፀፀት ሲገባቸው እንደ ስኬት ይቆቆጥሩታል፡፡ ድንጋይ ጠራቢ ትውልድ ከየዩኒቨርሲቲዎቻችን እንደ አሸን መፍላታቸው የነገዋ ኢትዮጵያ ህዳሴ ማሳያ አድርገው ሲያቀርቡ አይቀፋቸውም፡፡ የነገው ትውልድ ጉዳይ ያሳሰባቸው ወገኖች ‹ነገሩ እንዴት ነው› ሲሉ ጠባሳው ሊታይ የሚችል ንክሻቸውን ያሳርፉባቸዋል፡፡
ውድ ኢትየጵያውያን ሱዋሬዞች!

ሱዋሬዝ ላደረገው ንክሻ ፊፋ ጋር ተከሶ ቀርቦ ተቀጥቷል፤ የእናንተስ ቅጣት መቼና እንዴት ይሆን?
ይድረስ ለኢትየጵያውያን ሱዋሬዞች…
ይህ የቁም ነገር መፅሔት 13ኛ ዓመት ቅፅ 13 ቁጥር 182 ይድረስ ዓምድ ነው ነው

ሰሞኑን ከብራዚሉ የዓለም ዋንጫ ጋር ታያይዞ የሚነገረው የኡራጓዩ አጥቂ ሊዊስ ሱዋሬዝ ጉዳይ የብዙ ኢትዮጵያውያን የአፍ ማበሻ እስከ መሆን መድረሱ ያሳሰበን እኛ ሀገር ወዳዶች ከዚህ በታች ያለውን ደብዳቤ ‹ለሚመለከተው ሁሉ!› በሚል ዘንቢል ውስጥ አድርገን ልከናልና እንደሚሆን አድርጉት እንላለን፡፡

ውድ ኢትየጵያውያን ሱዋሬዞች!

መፅሃፉ ‹የራስህን የአይን ጉድፍ ሳትመለከት የሌላውን ለማየት ምነው ቸኮልክ?› ይላል፤ ለመሆኑ እንደ ሊዊዝ ሱዋሬዝ ትጥቅ አድርገው ፤ልምምድ ሰርተው፤ ሜዳ ገብተው ጨዋታ ከጀመሩ በኋላ የተጋጣሚን ትከሻ በመንከስ የበላይነትን ለማሳየት የሚሞክሩ ሰዎች በሀገራችን ስለመኖራቸው የተረጋገጠ መረጃ እስካሁን ድረስ ባይወጣም በየተሰማሩበት የሥራ መስክ ከግለሰብ እስከ መንግስት ባለስልጣን ድረስ የሚናከሱ ሰዎች ስለመኖራቸው አንከራከርም፡፡ የመንግስትን ሥልጣን ከያዙ በኋላ በየተቀመጡበት የስልጣን ወንበር ላይ ሆነው ‹እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን ፤ከኔ የተለየ አመለካከት ያለው ሁሉ አጥፊና አሻባሪ ነው› ብለው ያወጁትን የሚቀበልና የሚተገብር ሲጠፋ እንደ ሱዋሬዝ ጥርሳቸውን አሹለው የሚመጡ ባለስልጣናት ትላንትም ነበሩ፤ ዛሬም አሉ፡፡እንደ እነሱ አይነት ሱዋሬዞች ህዝብ በጾምና በጸሎት ብቻ የሚገላገላቸው ቢሆን ኖሮ የእስከዛሬው ሱባኤ በቂ ነበር፤ ግን አልሆነም፡፡
ውድ ኢትየጵያውያን ሱዋሬዞች!

በመንግስት ሥልጣን ላይ ሆነው ምንም እንኳ እንደ ሱዋሬዝ በይፋና በአደባባይ ባይናከሱም አስቀድመው ባደራጇችሁኋቸው ጭፍሮቻችሁ አማካይነት በስራና በስራ ብቻ የመለወጥ እቅድ ወጥነው የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን የማጥፋት አቅዳቸውን የሚከውኑ ሱዋሬዞች በየቦታው በየጥጋ ጥጉ ይገኛሉ፡፡ እነዚያ ሱዋሬዞች የመንጋ አስተሳሰብ ውጤት በመሆናቸው አምላካቸው በህጋዊ ንግድ ሥራ ስም የሚዘርፉት ገንዘብ ነው፤ በሚዘረፈው ገንዘብ ዙሪያ የተለየ አመለካከት የሚያራምዱትን ሁሉ በጠላትነት ለመፈረጅ አያመነቱም፡፡ ሀገሪቱ የግላቸው አድገው ስለሚቆጥሩ ባለ ፎቅና ባለ መኪና ከመሆንም አልፈው ኑሯቸውን ከነ ቤተሰባቸው በአውሮፖና በአሜሪካ ያደርጋሉ፤ በሀብቷና በገንዘቧ እንደፈለጋቸው ይሆናሉ፡፡ የፍትሀዊነት ጥያቄ ለሚያነሳባችሁ ለዚያ ሰው ወየውለት! ሱዋሬዝነታቸውን በተግባር ያሳዩታል፡፡
ውድ ኢትየጵያውያን ሱዋሬዞች!

በኪነ ጥበቡ ዘርፍም የተደራጁ ሱዋሬዞች አሉ፡፡ በሚሰሩት ሥራ የህዝብ ተቀባይነት ያገኙና የህዝቡን የልብ ትርታ የሚያስተጋቡ ሙያተኞች ከተለመደው ‹የወደድኩሽ፤ ወደድኩህ› ቅኝት ራሳቸውን ለማራቅ ሲሞክሩ የጥርስ ማስታወቂያቸውን በመልቀቅ ያስጠነቅቋቸዋል፡፡ ሙያተኞቹ የዚህን የጥርስ ማስታወቂያ ባለመረዳት በሙያቸው ማድረግ ያለባቸውንና ያመኑበትን በግጥሞቻቸው፤ በዜማዎቻቸው፤ በሥነ ሥዕል ሥራዎቻቸው፤ በፊልምና በቴአትር ሥራዎችቻው ወዘተ ህዝብ ጋር ለማድረግስ ደፋ ቀና ሲል የነሱዋሬዝ ጥርስ ከክሊኒኩ ታጥቦና ተወልውሎ ብቅ ይላል፡፡ በዚህ ሳቢያ መስራት በሚችሉበት ወቅት ሥራቸውን ያቆሙ፤ መኖር ከሚችሉበት ቀዬ የተባረሩ፤ ሀገር ለቀው የተሰደዱ ቁጥራቸው ጥቂት የሚባል አይደለም፡፡ በምትኩም አንድ አይነት ግጥምና ዜማ በሚያንጎራጉሩ የጥበብ ባለሙያ ተብዬዎች መድረኩ እንዱዲሞላ ያደርጋሉ፡፡ በየመድረኩ የሚጋበዙት እነዚህ ተመሳሳይ ቅኝትና ዜማ የሚያላዝኑ ልማታዊ አርቲስቶች የክብር አክሊል እንዲደፉ ያደርጋሉ፡፡ ከዚህ በኋላ እነሱን ለመተቸትና ሙያዊ አስተያየት ለመስጠት መነሳት ከኡራጓዩ አጥቂ ጋር በባዶ ቤት እንደመፋጠጥ ይሆናል፡፡
ውድ ኢትየጵያውያን ሱዋሬዞች!

በስፖርቱ ዘርፍ ያሉ ሱዋሬዞች ደግሞ አትሌቲክስን ከእግር ኳስ የሚለዩ አይደሉም፡፡ በስፖርት ትምህርት ሆነ በስፖርት ዘርፍ ይህ ነው የሚባል ልምድና ሙያ ሳይኖራቸው የአመራር ወንደሩ ላይ በመቀመጥ የሀገሪቱ የስፖርት ፌፋ የሆኑ ሱዋሬዞች ጥቂት አይደሉም፡፡ በስልጣን ወንበሩ ላይ በመቀመጣቸው ስፖርቱን በራሳችሁ የፖለቲካ አስተሳሰብ አንፃር ለመምራት ይተጋሉ፡፡ በዘርፉ የረጅም ጊዜ ልምድና እውቀት ያላቸው ባለሙያዎች ከስፖርቱ አካባቢ እንዲርቁ ያደርጋሉ፤ በእድል ወይ በአጋጣሚ የተገኙ የስፖርት ድሎችን እነሱን ከሀገር ሀገር ለማዞርና በየስብሰባው ለመጋበዝ በር ይከፍትላቸዋል፡፡ዘመኑ ከደረሰበት የስፖርት አመራር ፍልስፍና አንፃር ማንኛውም አይነት የስፖርት አይነት መመራት ያለበት ትምህርትና በልምድ ባካበቱ ባለሙያዎች የመሆኑ ጉዳይ ለውይይት ወደ የጠረጴዛ ሲመጣ አስቀድመው ካዘጋጃችኋቸው ታፔላዎች መሀከል የፈለጉትን እየመዘዙ በፈለጋቸው ሙያተኛ ጀርባ ላይ ይለጥፋሉ፡፡ ታፔላ አላስለጥፍም ብሎ ጀርባውን ያዞረ ሙያተኛ ካለ ችግር የለውም፤ እንደ ሱዋሬዝ ትከሻው ላይ ሳይሆን አላስነካም ያለው ጀርባው ላይ ይሰፍሩበታል፡፡ ከህዝብና ከመንግስት አላትመው ሀገር ጥሎ እንዲጠፋም ያደርጋሉ፡፡
ውድ ኢትየጵያውያን ሱዋሬዞች!

በመገናኛ ብዙሃን አካባቢ ያሉ ሱዋሬዞች ደግሞ በትከሻና ጀርባ ብቻ የሚመለሱ አይደሉም፡፡መንግስትን የጠቀሙ እየመሰላቸው ሁሉን ነገር ኳኩለውና ቀባብተው ከምታቀርቡት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጀምሮ ፅንፍ ይዘው አንዳች በጎ ነገር ለማየት አቅም እስካጡት ድረስ ሀገሪቱን የፕሮፖጋንዳ አውድማ እየሆነች መሆኗን መመስከር ግድ ነው፡፡ የልማታዊውን መንግስት ልማታዊ አጀንዳዎች ብቻ የሚያራግቡት እነዚያ ባለ ተመሳሳይ ድምፅ ዘጋቢያን በነባራዊው የህብረተሰብ የኑሮ ውጥረት ላይ የተመሰረቱ ዘገባዎችን ከመዘገብ ይልቅ ስለ ህዳሴው ዘመን መለፈፍ ብቻ ይቀናቸዋል፡፡ ለአፍታም ቢሆን ግራና ቀኝ አይመለከቱም፡፡ስለ ስኬት ብቻ ሲያወሩ ውለው ቢያድሩ አይሰለቻቸውም፡፡ ከዚህ ወጣ ያለ ዘገባ በሚዘግቡት ላይ ዘመቻ ይከፍቱባቸዋል፡፡ እነሱ ነጋ ጠባ የምታመልኩት ህገ መንግስት የሀሳብ ነፃነት የሚፈቅድና በተግባርም የሚያበረታታ መሆኑን ግን ለደቂቃም ቢሆን ማሰብ አይፈልጉም፡፡የተለየ ሀሳብ ያላቸው ድምፆችን ‹ውድቀት ናፋቂ ወይም ጦርነት አድናቂ› ብለው ያብጠለጥሏችዋል፡፡ከዚህ አለፍ ያለ መገዳደር የሚፈጥሩት ላይ የተለመደው የሱዋሬዝ ተሞክሮ ተግባራዊ ይደረግባቸዋል፡፡
ውድ ኢትየጵያውያን ሱዋሬዞች!

የተፈጠሩ ችግሮችን ተመልክቶ ማረም፤መታረም በማይችሉት ላይ ይፋዊ ይቅርታ መጠየቅ ለሱዋሬዛውያን ፈፅሞ የሚዋጥ አይደለም፡፡ ከዓመታት በፊት በመርዝ ኬሚካል ነክረው የዘሩ ዘር ጊዜው ደርሶ ሲያፈራ ይመፃደቁበታል፡፡ ለሌሎች ቀርቶ ለራሱ የማይሆን የተጣመመ ትውልድ በማፍራታቸው መፀፀት ሲገባቸው እንደ ስኬት ይቆቆጥሩታል፡፡ ድንጋይ ጠራቢ ትውልድ ከየዩኒቨርሲቲዎቻችን እንደ አሸን መፍላታቸው የነገዋ ኢትዮጵያ ህዳሴ ማሳያ አድርገው ሲያቀርቡ አይቀፋቸውም፡፡ የነገው ትውልድ ጉዳይ ያሳሰባቸው ወገኖች ‹ነገሩ እንዴት ነው› ሲሉ ጠባሳው ሊታይ የሚችል ንክሻቸውን ያሳርፉባቸዋል፡፡
ውድ ኢትየጵያውያን ሱዋሬዞች!

ሱዋሬዝ ላደረገው ንክሻ ፊፋ ጋር ተከሶ ቀርቦ ተቀጥቷል፤ የእናንተስ ቅጣት መቼና እንዴት ይሆን?

ይህ በቁም ነገር መፅሔት 13ኛ ዓመት ቅፅ 13 ቁጥር 182 ይድረስ ዓምድ ላይ ታትሞ የወጣ ነው

“አንዳርጋቸው ሽልማቱን መልሰህ ተቀበለኝ፤ አንበሳው የሚገባው ላንተ እንጂ ለኔ አይደለም”–ታማኝ በየነ (Video)

$
0
0

“አንዳርጋቸው ሽልማቱን መልሰህ ተቀበለኝ፤ አንበሳው የሚገባው ላንተ እንጂ ለኔ አይደለም” ይህ ቪድዮ የተገኘው ከታማኝ በየነ የምስል ክምችት ነው።

“አንዳርጋቸው ሽልማቱን መልሰህ ተቀበለኝ፤ አንበሳው የሚገባው ላንተ እንጂ ለኔ አይደለም” – ታማኝ በየነ (Video)

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸሙ አሰቃቂ የማሰቃያ (Torture) አይነቶችን በሚመለከት የተጠናቀረ ልዩ ዝግጅት (Audio)

$
0
0

በአቢይ አፈወርቅ (አውስትራሊያ -ሲድኒ)

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸሙ አሰቃቂ የማሰቃያ (Torture) አይነቶችን በሚመለከት የተጠናቀረ ልዩ ዝግጅት (Video)

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>