Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

ትግላችን ባለስልጣናቱ ላይም ትኩረት ያድርግ (ከይገርማል)

$
0
0

woyane-satenaw-news-4አምባገነኖች ለሕዝብና ለሀገር ራሳቸውን አሳልፈው ለመስጠት የቆሙ አስመስለው ያውሩ እንጅ እውነታው ግን በዚች ዓለም ላይ እንደራሳቸው የሚጨነቁለት ምንም እንደሌለና ለፍላጎታቸው መሳካት ማንኛውንም ነገር መስዋእት ለማድረግ የማይመለሱ መሆናቸው ነው:: በነርሱ ዘንድ ሚስት: ልጅ: ወዳጅ: ዘመድ: ሕዝብ: ሀገር ተደምረው ከነርሱ የበለጠ ሚዛን አይደፉም:: እስከተመቻቸው ድረስ ለፍላጎታቸውና ለጥቅማቸው ሲሉ ሊሸጡ ሊለውጡ ወይም መስዋእት ሊያደርጉ አያመነቱም:: የሰው ዘር የተፈጠረው እነርሱን ለማገልገል እንደሆነ አድርገው ያስባሉ:: ሰው ሲባል እነርሱ የሚሰማቸው ሰዋዊ ስሜቶች የሌለው የሚናገር እንስሳ ይመስላቸዋል:: በዚህም ምክንያት ርሀቡ: እርዛቱ: መከፋቱ: ስደቱ: መከራው: ምንም አይመስላቸውም::

 

ሲያዩዋቸው ጀግና ይመስላሉ እንጅ ሲበዛ ፈሪወች ናቸው:: ጀግኖቹ ከፊት ተሰልፈው በከፈሉት መስዋእትነት ከድል በኋላ ከጀርባ ተደብቀው በፍርሀት ሲርገፈገፉ የነበሩት ሰዎች ከፊት ይቆሙና የጀግንነት ፉከራቸውን ማዥጎድጎድ ይጀምራሉ:: ያልዋሉበትን ፈፋ እንደዋሉበት ያልፈጸሙትን ጀብድ እንደፈጸሙት አድርገው በማቅረብ በሰላ ምላሳቸው ይለፍፋሉ: ወሬ ነጋሪ ይሆናሉ:: ወንድነትን የሚፈትን ችግር ሲመጣ ግን መውጫ ቀዳዳ ፍለጋ አይኖቻቸው በጭንቀት ይቃብዛሉ::  ጀግኖችን ከውጊያ ሜዳ ጥለው በማይታመን ፍጥነት ሮጠው ከኋላ ይደበቃሉ::

 

ለእነዚህ አምባገነኖች መላዋ አለም ልትገለባበጥ የደረሰች የሚመስላቸው ችግሩ ሁሉ አፍጥጦ ወደእነሱ ሲመጣባቸው ነው:: ያን ጊዜ ይይዙት ይጨብጡት ይጠፋቸዋል:: የደረቡት የሀሰት የጀግንነት ልብስ ይወልቅና ርቃናቸውን ቆመው በወንዝ ውስጥ እንደበቀለ ፊላ በፍርሀት መንቀጥቀጥ ይጀምራሉ:: የአቶ መለስ ታሪክ የሚያሳየን ይህን እውነታ ነው:: ከቀድሞ የትግል ጓዶቻቸው እንደተረዳነው አቶ መለስ ዜናዊ ከሰራዊቱ ጀርባ ቆመው ሰራዊቱ በተኩስ የሚጠመድበትን ጊዜ ይጠብቁና የመጀመሪያዋ ጥይት “ጧ” ብላ ስትተኮስ ቀኝ ኋላ በመዞር የሦስት ቀኑን የእግር መንገድ በግማሽ ቀን ተጉዘው ከሰላም ወረዳ እያለከለኩ ይደርሱ እንደነበረ ነው:: አቶ መለስ ለውጊያ ሳይሆን ለወሬ የተፈጠሩ በመሆናቸው በጀግንነታቸው ሳይሆን በምላሳቸው የወያኔ ቁንጮ ለመሆን የበቁ ባለመጥፎ ራእይ ሰው ነበሩ::

 

በጥንት ጊዜ አንዲት ሴት ምን አይነት ባል እንደምትፈልግ በጓደኞቿ ተጠይቃ ነበር አሉ: “አፍ ያለው ያግባሽ ከብት ያለው”  ተብላ::  ጠያቂወቹ ለማለት የፈለጉት አደባባይ ውሎ ተሟግቶ የሚረታ: ተናግሮ የሚያሳምን ባል ነው የምትፈልጊው ወይስ በሀብት የደረጀ: በባለጸግነቱ የታወቀ? ለማለት ነበር:: ታዲያ ሴትዮዋ “አፍ ያለው ያግባኝ” ስትል መለሰች አሉ:: ተሟግቶ የማይረታ ተናግሮ የማያሳምን ሰው ሀብቱንስ እንዴት ሊያስጠብቅ እኔንስ እንዴት ሊያስከብር ይችላል? በሚል ሀሳብ ነበር “አፍ ያለው ያግባኝ” ልትል የበቃችው::

 

ብዙ ጊዜ አፍና ተግባር ይለያያል:: ከአንደበታቸው የተቡ ሰዎች ከተግባሩ የደከሙ የሚሆኑበት እውነታ ብዙ ነው:: ልክ እንደሟቹ ጠ/ሚኒስትር ማለት ነው:: በጦርነት ጊዜ ጓደኞቻቸውን ትተው: የተሸከሙትን ሀላፊነት ጥለው ከውጊያ ወረዳ መጭ! እንደሚሉትና በሰላም ጊዜ ስላልዋሉበት የጦር ሜዳ ተርተው እንደማይጠግቡት::

 

“ጀግና አይበረክትም!” አይደል የሚባለው! ጀግኖች ከፊት ተሰልፈው ጥለው ወድቀዋል:: አሁን በህይወት ያሉት በውጊያ ወቅት ከኋላው ረድፍ ተደብቀው ልባቸው በፍርሀት ትርክ ትርክ ስትል የነበሩ ሰዎች ናቸው:: ብርሀኑ ዘሪሁን እንዳለው የመጨረሻው ፈሪ የመጨረሻው ጨካኝ በመሆኑ በጭካኔያቸው ፍርሀታቸውን ለማስተባበል ሲሰሩ ይታያሉ:: እኒህ ፈሪና አምባገነን መሪወች የሚገድልላቸውና የሚሞትላቸው እስካለ ድረስ በሕዝብና በሀገር ላይ የሚደርሰው በደል አይታወቃቸውም:: የሚወድመው ንብረት የሚሞተው ሰው አያሳስባቸውም:: የሕዝብ ስቃይና መከራ አይሰማቸውም:: ሌላው ቀርቶ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንኳ ምንም ደንታ የላቸውም:: መርበትበትና መደናበር የሚጀምሩት ችግሩ ሁሉ ወደነርሱ ፊቱ ሲያዞር ብቻ ነው:: ያን ጊዜ ሀገር በሽብር እየተገረፈች እንደሆነ ሕዝበ-አዳም በመከራ እንደተዋጠ ፍንትው ብሎ ይታያቸዋል::

 

ትግላችን አሁን ባለው መልኩ ፋታ ሳይሰጥ ዳር እስከዳር የሚያምስ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ እነዚህ ጥቂት ፈሪና አምባገነን መሪወች ላይም ያተኮረ መሆን ይኖርበታል:: የሕወሀት እና የአጎብጓቢ ድርጅቶች ቁልፍ ሰዎች የትኩረት ማእከል መሆን አለባቸው:: አዎ ትግሉ እነርሱ ላይም ያነጣጠረ መሆን ይገባዋል:: የሚኖሩበትን ቤት በመክበብ ቢቻል ከነነፍሳቸው ይዞ መደራደሪያ ለማድረግ ተገደው እንዲወጡ በቤቶቻቸው ላይ እሳት መለኮስ ካልሆነም ቢያንስ በሰላም ተኝተው እንዳይነሱ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ቤቶቻቸውን በድንጋይ መደብደብ: ሲያልፉ ሲያገድሙ ማወክ:: እነዚህ ወሳኝ ሰዎች ኢላማ (target)መደረግ አለባቸው:: ባለስልጣኖችን mark እናድርግ:: ይህን ማድረግ በጀመርን ማግስት ድምጻችን ይሰማል:: አማላጆች መዥጎድጎድ ይጀምራሉ:: ሁሉም መውጫ ቀዳዳ የሚማትር ይሆናል:: ይህን ተከትሎ የጨለማው ጊዜ ይገፈፍና የብርሀን ዘመን ይብታል::

 

የብአዴን: የኦሕዴድ: የደሕዴን እና አጋር ድርጅቶች አባል ሆናችሁ የዘረኛውን የሕወሀት አገዛዝ የምትቃወሙ: ባርነትን የምትጸየፉ ሁሉ ይህንን አስከፊ ስርአት ለማስቀጠል ደባ የሚፈጽሙትን ሰዎች እየለያችሁ ስማቸውን እና አድራሻቸውን ለሕዝብ ይፋ በማድረግ ትግሉን አግዙ:: ሁኔታው ከተመቻቸላችሁ የሕዝብ ጠላቶች ናቸው የምትሏቸው ላይ ራሳችሁም ብትሆኑ ርምጃ መውሰድ ይኖርባችኋል::  ይህን ስታደርጉ ከቂምበቀል እና ከጥላቻ በጸዳ መልኩ በትክክል የሕዝብ ጠላቶች የሆኑትን በመለየት መሆን ይኖርበታል:: ከዚህ በተጨማሪ በሕዝብ ላይ የታቀደውን ሴራ ማጋለጥ እና በየአካባቢው የሚደረጉ ትግሎችን የሚያንቀሳቅሱ ሰዎችን ከጥቃት መከላከል ይኖርባችኋል::  የፖለቲካ አክቲቭስቶች እናንተን ጨምሮ መላው ኢትዮጵያዊን ከወያኔ አፈና ለማላቀቅ ራሳቸውን አሳልፈው ለመስጠት ከፊት የቆሙ ብርቅ ወገኖቻችሁ ናቸው:: እነርሱን ለጥቃት ማጋለጥ ወያኔን ማተበት: ሀገርን እና ሕዝብን ለመከራ መዳረግ ነው::

 

ትንሳኤ ለኢትዮጵያ!


በዕድሜዬ የማውቃቸው ሦስቱ የኢትዮጵያ መንግሥታት –አገሬ አዲስ

$
0
0

haile_mengistu_melesከዛሬ አርባ አራት ዓመት በፊትና በዃላ በኢትዮጵያ ውስጥ የራሳቸው መታወቂያ ያላቸው ሶስት አይነት መንግሥታት ተመስርተው ለማየት በቅቻለሁ።ከዛሬ አርባ አራት ዓመት በፊት የነበረው ዘውዳዊ ስርዓት፣በነገሥታት የሚመራ ስርዓት የነበረ ሲሆን የፖለቲካና የኤኮኖሚው መሰረቱ አገር በቀል የሆነ፣ከባእዳን ቁጥጥር ነጻ የሆነ በባላታዊ ስርዓትላይ መሰረት የጣለ ነበር።ኢትዮጵያም አገር ወዳድ አመለካከት ባላቸው መሪዎች ፍላጎት የምትመራ አገር ነበረች።ይህ ስርዓት ከባዕዳን ጋር የነበረው ግንኙነት የወዳጅነት ሳይሆን የእምቢ ባይነትና ባለማጎብደድ ብሎም ለቅኝ ገዢ ወራሪ ሃይል ያልተንበረከከ በመሆኑ ጠላቱ የበዛና ብቻውን የቀረ ነበር።ኢትዮጵያ ቁጥራቸው በበዛ ጠላቶች ተከባ እንድትፈራርስ ደባና ሴራ የሚመታባት አገር ነበረች።የአውሮፓውያን የመስፋፋትና የቅኝ አገዛዝ ወረራም በተደጋጋሚ ተሰንዝሮባት መሪዎቹ በሕዝባቸው ሃይልና በአላቸው የጦር መሣሪያ፣ጋሻና ጦር ብቻ በየአቅጣጫው የመጣውን ጠላት ተፋልመው ነጻነታቸውን ሳያስደፍሩ እንደ ሃገር በነጻነት ለመኖር በቅተዋል።በዚህ የትንቅንቅ ሂደት አንድ አገር ሊደርስበት የሚችለው የእድገት ደረጃ ሳይታይ መቅረቱ የሚያስገርም አይሆንም።

እድገትና ስልጣኔ ሰላምና አንድነትን ይጠይቃል።ያ በሌለበት አገር ስልጣኔ አይታሰብም።ምንም እንኳን የኤኮኖሚ እድገትና መሻሻል ባይኖርም ሕዝቡ በባዕዳን ክርን እንዳይደቆስ፣ክብርና ዜግነቱን እንዳያጣ የሚንከባከብና የሚያስከብር ስርዓት ነበር።ነገስታቱ ከወራሪ ባእዳን ጋር የሚያደርጉት ትንቅንቅ እንዳለ ሆኖ  በውስጥም የስልጣን ሽኩቻ ላይ በመሰማራታቸው የረጋ ስርዓትና ቀጣይነት ያለው እድገት ለማምጣት አልቻሉም።ዘመነ መሳፍንት ያደረሰውን ቀውስና ስብራት ለመጠገን የብዙ ጊዜ ሰላም ይጠይቅ ነበር።አጼ ቴዎድሮስ  በመሳፍንቱ የተናጋውን አንድነት በሃይል አስከበሩ፣ከውጭ ወራሪዎችም ጋር በተለይም ከእንግሊዞች በኩል የሚቃጣውን የወረራ ጉዞ በዲፕሎማሲና በጉልበት ተጠቅመው እስከሕይወተ ፍጻሜያቸው ድረስ ተከላከሉ። አጼ ዩሃንስ በቱርክና በግብጽ .በእንግሊዞች የተቀመረ ወረራ ጋር ተጋፍጠው ህይወታቸውን አሳልፈው ሰጡ፣አጼ ምኒሊክም ከውጭ ወራሪዎች ጋር የገጠማቸው ችግር ቀላል አልነበረም፤ ድንበር ጥሶ የመጣውን የጣሊያን ጦር በመቋቋምና ድል በመምታት አቅማቸውና ሁኔታው እስከፈቀደላቸው ድረስ ወደመጣበት በመመለስ ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፓ ወራሪ ሃይል በጥቁር ሕዝብና መሬት ላይ ተዋርዶ እንዲመለስና ለሌላው ጭቁን ሕዝብ የትግልና የነጻነት አርአያ እንዲሆን አድርገዋል።አልፎ አልፎ ጸጥታና ሰላም ሲሰፍን ባላቸው እውቀትና አቅም አገራቸውን ለማሳደግና የሕዝቡን ኑሮ ለማሻሻል ቦዝነው አያውቁም።ለአንድ አገር መሻሻልና እድገት የተማረ ሕዝብና እውቀት ዋና መሰረቱ ስለሆነ በዚያ መስክ ትምህርት እንዲስፋፋ የመጀመሪያውን መሰረት ጥለዋል። አገራቸው ከሰለጠነው ዓለም ጋር እንድትጓዝ ዘመናዊ አሰራሮችንና የእድገት በሮችን የከፈቱት እሳቸው ነበሩ።የስልክ መስመር፣የፖስታ አገልግሎት፣የመብራት ሃይል፣የመጓጛዣ መኪና፤ሆቴል፣ የፎቶግረራፍ ሙያ፣የባቡር መስመር፣ የባንክ አገልግሎት፣ ሆስፒታል፣የመንግስት አሰራር በካቢኔ  ሚኒስትሮች መልክ እንዲደራጅ ያደረጉት እሳቸው ናቸው።አገራቸው በጎሳ ተከፋፍላ ከምትጓዝ በአንድ አጠቃላይ ማእከላዊ መንግስት ስር እንድትተዳደር የአጼ ቴዎድሮስን ፈለግ ተከትለው በተግባር የተረጎሙ መሪ ናቸው።ይህ አካሄድ ከሌላው አገር ማእከላዊ መንግስት አመሰራረት የተለዬ አይደለም።ስልጣን እናጣለን ከሚሉት የከባቢ መልከኞችና ባላባቶች ጋር ጦር ያማዘዘ ሂደት ነበር።

እንደ አባ ጅፋር አይነቶቹ ኦሮሞውን ወገናቸውን እየለጎሙ በባርነት ከሚሸጡ ባለባቶች ጋር ያደረጉት ትግል ቀላል አልነበረም።አንዳንዶቹን በማሳመንና በማባበል ሌሎቹን ደግሞ በሃይል አንድነትን ከሚቀበሉ የጎሳ መሪዎችና ተወላጆች ጋር በመተባበር ኢትዮጵያ ዳግም እንድትነሳ አድርገዋል።ይህ የውህደትና የአንድነት እርምጃ በአንዳንዶቹ ግምት የተደረገ ወረራ ነው በማለት እስከዛሬ ድረስ ቅርሾ በመያዝ አሁን ላለንበት ወቅት ለውጩም ጠላት በር የከፈተ እንቅፋት ሆኗል።በአጼ ቴዎድሮስም ሆነ በአጼ ምኒሊክ እንዲሁም ከሳቸው በዃላ በነበሩት መሪዎች የተካሄደው አገርን የመገንባትና ድንበር የማስከበር እርምጃ እሳቸውን ተክተው ስልጣኑን የተረከቡት ንግስት ዘውዲቱና ልጅ እያሱም ቢሆኑ ምንም እንኳን በውስጥ ቀውስ ተጠምደው ለአገራቸው የረባ ነገር ሳይሰሩ በአጼ ሃይለስላሴ አድማ ተመተው ከስልጣን እስከተወገዱበት ድረስ ፈለጉን ተከትለው ተጉዘዋል።ስልጣን ከተፈሪ መኮንን (ሃይለሥላሴ) እጅ ከገባ በዃላም የተጀመረውን ለማስቀጠል አገሪቱ ሰላም አላገኘችም።በአጼ ምንሊክ ተዋርዶ የተመለሰው የጣሊያንና የነጮቹ ጎራ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ለዳግመኛ ጊዜ ወረራ አካሄደ።ከአምስት ዓመት ትግል በዃላ በዓለም የተፈጠረው ሁኔታ አግዟቸው የነጮቹ ጎራ እርስ በርሱ በጥቅም ሲጋጭ የወራሪው የጣሊያን መንግሥት ከጀርመኑ የሂትለር መንግሥት ጋር አብሮ በመቆሙ የሌሎቹ ጠላት ሆኖ በወገኖቹ ነጮች በእንግሊዞች እርዳታ ከኢትዮጵያ ተሸንፎ ለመውጣት በቃ።ንጉስ ሃይለስላሴ ከሚኒልክ ተረክበው ሊቀጥሉ የፈለጉትን የእድገት ጎዳና የውጭ ሃይሎች ለመቀልበስና ፍላጎታቸውን ለማሟላት በጦር ሜዳ ሊሳካላቸው ባለመቻሉ በስውር መንገድ እየገቡ ሙከራ ማድረጋቸውን አላቆሙም።በመሳፍንቱና በነገሥታቱ መካከል የሚነሳውን አለመግባባትና የሥልጣን ሽኩቻ እያራገቡ፣አንዱን በማወደስና በመርዳት ሌላውን በመውቀስ የተንኮል ሴራ ሲያውጠነጥኑ ኖረዋል።ያም ቢሆን ለሚፈልጉት ግብ አላደረሳቸውም። ሆኖም ግን በእርስ በርሱ ግጭት የብዙ ሰው ህይወትና የአገር ንብረት ወድሟል። አለመተማመንና ቅርሾም በመፍጠሩ ሁሉም በሙሉ ልቡ ወደአገሩ ከማተኮር ይልቅ ወደ ሚደግፈውና የከባቢ ስሜት እየገባ የራሱን አገር ነጻነት ከማስከበር ይልቅ በውጭ ሃይሎች እየተረዳ የሥልጣኑ ባለቤት ለመሆን በሚያስችለው የባንዳ ተልእኮ ውስጥ ተሰማርቶ ብዙ ጉዳት እንዳደረሰ በታሪክ ታይቷል።ይህ አድራጎት ጎልቶ የታየው በጣሊያን ወረራ ወቅት ነበር።በዚህ የጣሊያን ወረራ ከጎኑ ተሰልፈው ያገራቸውን ሰንደቅ አላማ ቀደው በጣሊያኖቹ ባንዲራ የተኩና ተሸክመው በወገኖቻቸው ላይ ግፍ የፈጸሙ ዜጎች ብዙ ናቸው።ከነሱም መሃል አሁን በስልጣን  ላይ የሚገኙት አባቶችና አያቶች ይጠቀሳሉ።ከጦር ሜዳ አንስቶ በሰላይነት የተሰማሩ እንደነበሩም ታሪካቸው ይመሰክራል።ጣሊያን የነሱን እርዳታ ባያገኝ ኖሮ አዲስ አበባ ድረስ ሰተት ብሎ ለመግባትና አገሪቱን ከሞላ ጎደል ለመቆጣጠር ባልቻለም ነበር። በቆራጥ መሪዎቹና በአገር ወዳዱ ሕዝብ መስዋእትነት የጣልያንና የባንዳዎቹ ፍላጎት ግን በአጭሩ ተቀጭቶ ኢትዮጵያም መልሳ በራሷ አገር ወዳድ መሪዎች ልትመራ ቻለች።ከዚህ የጦርነት ስብራት በዃላ አገሪቱ ለመንሰራራት ትልቅ ፈተና ገጥሟት ነበር።ጣልያንና እንግሊዝ የረጩት የልዩነት መርዝ በአንዳንዱ የአገሪቱ ዜጋ አስተሳሰብ ላይ ጎጆውን ሰርቶ አልፏል።የአንድነት  ፍላጎቱን ለማመንመንና ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ የባዕዳነትን ስሜት እንዲያስተናግድ የሚያስችለው አስተሳሰብ በአንዳንዶቹ ላይ ተጽእኖ በማድረጉ አገሪቱ በህብረት ልትገነባ የሚያስችላት ሃይል እንዳይኖራት አድርጓል።

ለአሁኑም ልዩነትና የጎጥ ፖለቲካ ስርዓት ምክንያት ሆኗል።ከውጭ ወራሪ ሃይል ጋር ከሚደረገው ትንቅንቅ በተጨማሪ በአገር ውስጥ ግጭቶች እንዲነሱ ተደርጎ  የአገር ሃብትና የሰው ሃይል ባላስፈላጊ የእርስ በርስ ግጭት እንዲመናመንና ጭራሽ ወደባሰ ድህነት እንዲያመራ ምክንያት ሆኗል።ከጣሊያን ቀጥሎ በሶማሊያ ወራሪ ሃይል ጋር ተደጋጋሚ ጦርነት ተደርጓል፣በራያና አዘቦ፣በጎጃም፣በባሌ የተደረጉት የእርስ በርስ ውጊያዎችም የአገሪቱን ሃብት በማድቀቁና የልዩነት መንፈስ በማዳበሩ በኩል የየራሳቸውን አስተዋጽኦ አድርገዋል። አንድ ጊዜ ሲበርድ ሌላ ጊዜ ሲያገረሽበት በሚሄደው የውስጥ ችግር የተወጠረው መንግሥት እፎይ ብሎ ሙሉ ለሙሉ ለልማት እንዳያተኩር እንቅፋት ሆኖበት ነበር። ከዚያም በላይ የነበረው ስርዓት ባህልና እምነቱ በቀድሞ አስተሳሰብ የተተበተበ በመሆኑ እርቆ ሊሄድ አልቻለም።ዘመናዊ አስተሳሰብና ትምህርት ለማስፋፋት የሚፈልጉት ንጉስም ከቤተክህነትና ከባላባቶች አካባቢ ብዙ ፈተናና ተቃውሞ ነበረባቸው።

የሕዝቡ ኑሮ ከፍልስፍናና ከፈጠራ ይልቅ በተፈጥሮና በመለኮታዊ ችሮታ ላይ የተመካ  ነበር።ዝናብ ሲጠፋ ይራባል፣ወንዝ እያለው በመስኖ የመጠቀም ችሎታ አላዳበረም።

እርግጥ ነው የነበረው ስርዓት ሙሉ ለሙሉ የሕዝቡን ፍላጎት የሚያሟላ ነበር ማለት አይቻልም።አገር ከመውደዱና የአገርን ነጻነት ከማስከበሩ ጎን ለጎን  አገሪቱን በሚያሻሽለው የዴሞክራሲ ጥያቄና ሰለሕዝቡ መደረግ የሚገባቸውን  በተለይም የባላባቱንና የጭሰኛውን ግንኙነት ለመቀየር የመሬትን ባለቤትነት የሚያረጋግጠውን የዜጋ መብት ያከበረ አልነበረም።ዃላ ቀር ከነበረው የባላባት ስርዓትና የምርት ግንኙነት የሚያላቅቅ የተሻለ የኤኮኖሚ መዋቅር  የሚያመቻች አገር ወለድ ተቋማትና አሠራር አላዳበረም።በመሆኑም እያደር ድህነት እንጂ መሻሻል አልታየበትም ነበር።ይህም አንዱና ዋናው የተቃውሞ መቀስቀሻ ሆነ።ተቃውሞው ሕዝቡን በሙሉ ያሳተፈ ሳይሆን በተማረውና በነቃው ዙሪያ የሚካሄድ ነበር፤ለተቀሰቀሰው ተቃውሞ ግን ጥይት አልተኮሰም፣ሰላማዊ ሰልፈኞችን በአደባባይ አልረሸነም።ግፋ ቢል አስሮና በወላጆች ምክር ከመልቀቅ ያለፈ ቅጣት አልቀጣም። የአጼ ሃይለስላሴ መንግሥት እንደዛሬዎቹ የውጭ እርዳታና ብድር አያገኝም ነበር።ለመጀመሪያ ጊዜ የመቶ አስር ሚሊዮን ዶላር  ከፍተኛ የውጭ አገር እርዳታና ብድር የተገኘው ንጉሱ ቻይናን በጎበኙበት ጊዜ ከቻይና ነበር።በተረፈ በስዊድን መንግሥት እርዳታ በደቡብ በእርሻ ስራ የልማት ዘርፎችና  ፣ከደቾች ሱካር ፋብሪካ፣ከተንዳሆ የእንግሊዞች የጥጥ እርሻ ተጨማሪ የጎላ ድርሻ  የነበራቸው የውጭ አገር ተቋማት አልነበሩም።አሜሪካ በወታደራዊ መስክ ጀርመን በፖሊስ ሰራዊት ተቋም ከሚሰጡት ድጋፍና ስልጠና ሌላ በኤኮኖሚው ዘርፍ ጎልቶ የታዬ ተሳትፎ አልነበራቸውም።የአሜሪካኖቹም እርዳታ ቢሆን ከጂኦፖለቲክ ጥቅማቸው አንጻር ነበር።

ወደ መጨረሻው ላይ በአገሩ ተወላጆች የተጀመሩ ሰፋፊ የእርሻ ስራዎች ነበሩ።እነሱም ያተኮሩት በአገር ውስጥ ገበያ በሚሆኑ ምርቶች ላይ ሳይሆን በውጭ አገር ገበያ ለሚቀርቡ ምርቶች በሰሊጥ፣ቦለቄና በመሳሰሉት ላይ በመሆኑ ከዓለም የዋጋ ግሽበት ጋር አብረው ከሰሙ፤ የተረፉትም ደርግ ስልጣኑን ሲይዝ ነጠቃቸው።

የውጭ ወራሪና ታሪካዊ ጠላቶች የተከሰተውን ችግርና ሕዝብ አለመርካት በመጠቀም የነበረውን አገር ወዳድ ስርዓት እንዲወገድ ሌት ተቀን ይሰሩ ነበር። ከነዚህም ውስጥ ወጣቱን በሃይማኖትና  በፖለቲካ መስመር ውስጥ ማሰለፍና መቀስቀስ ቀላሉና ማራኪው መንገድ ነበር።ወጣት ትውልድ አዲስ አስተሳሰብና ለዕድገት ያለው ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ ለለውጥ የተዘጋጀ የህብረተሰብ ክፍል ነው።ያንን ፍላጎቱን በሚጥም መልክ እየቀሰቀሱ ማሰለፍ ቀላሉ ዘዴ ነበር።በመጀመሪያ ወጣቱ በምእራባውያን አስተሳሰብ እንዲቀረጽ በልዩ ልዩ ዘዴ ዘመቻ ተደርጎበታል።በሙዚቃ፣በፊልም፣በአለባበስ፣..ወዘተ በዘመናዊነት ስም  ከኢትዮጵያዊነት ባህልና አስተሳሰብ እንዲርቅ ተደርጓል።የስርዓቱም ተወካዮች አንዳንዶቹ በጎና መልካሙን መለየት፣ከወቅቱም ጋር መሄድ ተስኗቸው በያዙት ዃላ ቀር መንገድ ስለቀጠሉበት ለልዩነቱና ለደረሰው ስብራት የበኩላቸውን አበርክተዋል።ለብዙ ጊዜ ውስጥ ለውስጥ እየተብላላ የቆየው ብሶትና የለውጥ ፍላጎት በውስጡ ኢትዮጵያን የመጥላትና ኢትዮጵያዊ ያለመሆንን ስሜት ለሚያራምዱት አገር በቀል ጠላቶች ቦታና እድሉን ፈጠረላቸው።

በዓለም ላይ የተከሰተው የፖለቲካ ቀውስና በተለይም በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ የአገሪቱን ሁኔታ አባብሶት የዘውዳዊ ስርዓት መዋቅሩን ለማናጋት ቻለ።ለዘመናት ሰፍኖ የኖረው አገር ወዳዱ የባላባታዊ ስርዓት ፈተና ውስጥ ገባ፤ፈተናውን ማለፍ አቅቶት ወደቀ።በለውጥ ሽፋን የወታደር አምባገነን ቡድን ቦታውን ቀማው።

ይህ የወታደር ቡድን አነሳሱ ላይ ቀናና አገር ወዳድ ነበር፣ሥልጣንም ይዞ ለመቆየት ዓላማ አልነበረውም።በዃላ ላይ ለስልጣን በሚፎካከሩ ሁለት ቡድኖች በኢሕአፓና በመኢሶን መካከል በሚደረገው ትንቅንቅ ውስጥ ገባና አንዱ አንዱን በመሆን እርስ በርሱ ተናክሶ የመኢሶንን ቡድን በመደገፍ የሚራመደው የነመንግሥቱ ሃ/ማርያም ቡድን በአሸናፊነት ስልጣኑን ጠቅሎ ያዘ።የተማሪው ትግል የወለዳቸው እነዚህ ሁለት ድርጅቶች በመጀመሪያው ላይ አንድ የነበሩ ሲሆን የሚያራምዱትም አንድ አይነት የሶሺያሊስት ዝንባሌ ያለው ፍልስፍና ነበር።ለአንዳንድ ጥያቄዎች በሚሰጠው መልስ ላይ ልዩነት ተፈጥሮ ልዩነቱን ተወያይቶ ከማሶገድ ይልቅ የጠላትነት ጎራ ተፈጠረና አንዱ ሌላውን ለማጥፋት ቆርጦ ተነሳ።ለዲሞክራሲ ለውጥ ይታገሉ የነበሩት እራሳቸው ችግርን በዲሞክራሲ መንገድ መፍታት ተሳናቸው።የአንደኛው ክንፍ  አባላት ጸረ ዲሞክራሲ የሆነውን የወታደር አምባገነን ተራማጅ አድርገው በመቀበል አብረው ለመስራት ወሰኑ።ሌላው ከዳር ሆኖ  የወታደሩን ቡድን ከውስጡ ለማፈራረስ ሌላ ዘዴ ቀመረ።የሁለቱ ቡድኖች ቀውስ በደርግ ውስጥ ሰርጎ ገባና አገር አቀፍ ቀውስ ሆነ።ደርግም በአነሳሱ ላይ ይዞት የነበረው አገር ወዳድ መልኩ ተለወጠና እየደበዘዘ የስልጣን ወዳድነት ባህሪ በተጫነው ጥቂት ቡድን በኩል ስልጣኑ መንግስቱ ሃ/ማርያም ለሚባለው ለፍላፊ፣ ጨካኝና በዝቅተኛነት ስሜት በቀልና ጥላቻ ላደረበት አምባገነን የግል ንብረት ሆነ።በውስጡና ከውጭ ለሚነሱት ጥያቄዎች ሁሉ መልሱ ጥይት ሆነ።ይኸው አምባገነን  አካሄዱ ያላማራቸው ጸባዩን  የሚያውቁት የሐርር ሶስተኛ ክ/ጦር አባላት ቤተሰቡን መያዣ አድርገው ለጥያቄ ሲፈልጉት፣ብትፈልጉ ቀቅላችሁ ብሏቸው እንጂ አልመጣም ብሎ የመለሰ፣የራሱን ስልጣን ከወለዳቸው ልጆቹ አብልጦ የሚያይና የሚመርጥ አረመኔ መሆኑን ከጧቱ ያሳዬ ነበር።ግን ይህ አባባሉ ከቤተሰቡ ይበልጥ አገሩን እንደሚወድ ተደርጎ ተመነዘረለትና አገር እስኪያጠፋና እስኪጠፋ ድረስ መብትና ስልጣን ተሰጠው።እርግጥ ነው በሱ አይፈረድበትም! መንግስቱ ሃ/ማርያም በጦሩ የነበረው ቦታ የመሳሪያ ግምጃ ቤት አላፊ ሆኖ ጥይት መቁጠርና መሳሪያ መጠገን ስለሆነ ከቃታና ከሰደፍ የበለጠ በቅርብ የሚያውቀው ችሎታና እውቀት አልነበረውም።ለፍቅርም ለጠብም የሚመዘው ያንኑ አብሮት ውሎ የሚያመሸውን ጠመንጃ ነበር።ከማን ጋር ነሽና ተሆኛለሽ ጤና ነው።ይህ ፈላጭ ቆራጭ እውቀተ ቢስ ሰው አጋጣሚ ሆኖ ባገኘው ዕድል በሕዝቡና በአገሪቱ ላይ የፈጸመው ወንጀል ሌሎቹ የቀድሞ መሪዎች የፈጸሙት ቢደመር የሱን እሩብ አይሆንም።ለአገር ይሞታሉ እንጂ አገር ገለው አላለፉም።ወጣቱን ጨፍጭፎ ለገደለበት ጥይት ዋጋ ያስከፈለ አረመኔ መንግሥት በኢትዮጵያ መሬት ላይ ሲበቅል ደርግ የመጀመሪያው ነው።ለመገንጠል ጫካ ገብተው ይታገሉ የነበሩትን “የብሔር ነጻ አውጭዎችን”ቀስፈው የያዙትን፣ለአገራችው ክብርና አንድነት ለማስከበር የተሰለፉትን የጦር መኮንኖችና ወታደሮች ጥያቄ አቀረባችሁ በማለት በጦር ሜዳ እየገደለ ሰራዊቱን መሪ አልባ አድርጎ ያስጠቃና በመጨረሻውም ከነጮች ጋር ተደራድሮ አገሪቱን አሁን ላለው አውሬ ቡድን አሳልፎ ሰጥቶ አገር ጥሎ የኮበለለ ፣ በኢትዮጵያ ሕዝብ ስነልቦና ላይ የፍርሃትና የሽብር ድባብ ያሰፈነ፣ኢትዮጵያን በታሪኳ ያላየችውን የመሪ ሽሽት ያስተዋወቀ አሳፋሪ ከንቱ ሰው ነው። ይህንን ከንቱና አሳፋሪ እንደ ጀግና ቆጥረው የሚያሞካሹት፣የፈጸመውን የአገር ክህደትና ወንጀል የሚኮሩበት የሱ ቢጤዎችና የስርዓቱ ተጠሪዎች በየአገሩ ተበትነው ሲመጻደቁ ይሰማል።የእሱ የሥራ ውጤት አገሪቱን አሁን በሥልጣን ላይ ላለው ለተገንጣዮች ቡድን አስረክቦ መሄድ ሲሆን የአገሪቱ አንድነት በባሰ አደገኛ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ከፍተኛ ድርሻ አበርክቷል።

ይህ አሁን በስልጣን ላይ ያለው ቡድን ከሃምሳ ዓመት ወዲህ በአገራችን ውስጥ ከሰፈኑት መንግሥታዊ ስርዓቶች የተለዬ፣አገር ወዳድነት ስሜት የሌለው፣ገና ከጅምሩ በውጭ ሃይሎች የተቀሰቀሰና የተረዳ፣የጣሊያንንና የሌሎቹን የኢትዮጵያ ጠላቶች ፍላጎት በተዘናጋ መልኩ ለማስፈጸም የተፈጠረ ስብስብ ነው።ይህ ስብስብ እንደጣሊያንና እንግሊዝ አገሪቱን በጎሳና በክልል ከፋፍሎ ጠንካራና አንድ አገር እንዳትሆን ሌትተቀን የሚሰራ ቡድን ነው።ለጎሳ መብትና እኩልነት ቆሜለሁ እያለ ጎሳ ከጎሳ እንዲባላና እንዲጋጭ እያደረገ ጠንካራ ብሔራዊ ስሜት እንዳይኖር የሚያደርግ የውጭ ተልእኮውን በሚገባ የሚፈጽም የባንዳ ስብስብ ነው። ኢትዮጵያ የምትባል አገር ፈርሳ ኤርትራ፣ትግሬ፣ኦሮሞ፣አማራ፣ሶማሌ፣ጋምቤላ፣አፋር፣…ወዘተ የሚሉ የመንደር መንግሥታት ተመስርተው እርስ በእርሳቸው ሲዋጉ እንዲኖሩ ቀምሮ የተነሳ ቡድን የሚቆጣጠረው መንግሥት ነው። ይህንንም በተግባር አሳይቷል፤ኤርትራን አስገንጥሎ በማግስቱ ወደ ጦርነት የሄደ ቡድን ነው።ከሌሎቹም ጋር ግብግብ ከገጠመ ውሎ አድሯል።አገር ከማፈራረሱም ጋር አገር የመበዝበዝንም ተግባር በማከናወኑ ከሌሎቹ ስርዓቶች የተለየ አድርጎታል።የመሪ ሌባ የሰፈነበት  ስርዓት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እንደዚህ ታይቶና ተሰምቶ አይታወቅም። ይገላል፣ይዘርፋል፣አገሪቱን ለውጭ አገር ጥቅምና ቁጥጥር አሳልፎ የሰጠ፣ድንበር እየቆረሰ የሚያስረክብ፣እንደመሪ ሳይሆን እንደሰውና ዜጋ ሊታይ የማይገባው የአውሬ ስብስብ ነው።

የውጭ ባላደራ መንግሥት በመሆኑ ከሌሎቹ የተለየ እውቅናና ድጋፍ አለው።ከላይ እንደተገለጸው ኢትዮጵያ እንደ አንድ ነጻ አገር እንዳትኖር ለተደረገባት የወረራ ሙከራ አጻፋውን ሰጥታ አሳፍራ የመለሰች፣ለሌሎች አገራት የትግልና የነጻነት ምሳሌ ሆና የኖረች በመሆኗ ወራሪዎች ጥርሳቸውን የነከሱባት አገር ነበረች፤ያንን በቀል በአገር በቀሉ ከሃዲ ቡድን ሊካሱ ችለዋል።ለዚህ ባለውለታ ቡድን እንኳንስ የፖለቲካ ድጋፍና የገንዘብ እርዳታ ቀርቶ ሌላም ቢያደርጉ አይከብዳቸውም።በኢትዮጵያ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች አገሮች ለሚያካሂዱት ዘረፋና ወረራ አስከባሪ ቀድሞ ደራሽ በሩ መሆኑም ውለታ እየሰራላቸው ነው።በዚህም የባንዳ ተግባሩ የሚሻውን ድጋፍ እየሰጡ በስልጣኑ ላይ እንዲቆይ ይመርጣሉ።አገር ወዳድ ሃይል በኢትዮጵያ ምድር ላይ እንዲወለድ አይሹም።ይህ የሚረዱት መንግስት ቢወድቅ፣ሰላምና ጸጥታን ለማስከበር በሚል ስም ወታደሩ ሥልጣኑን እንዲወስድ ወይም የውጭ ሃይል እንዲገባ ከማድረግ አይመለሱም፡፤ይህ ካልሆነ ኢትዮጵያ ተበታትና በተለያዩ የክልከል የጎሳ መሪዎች መዳፍ ስር ወድቃ ቁጥጥራቸውን ለማስቀጠል በሚረዳ መልኩ ቢሆን ይመርጣሉ።ለዚህ ኢራቅ ምሳሌ ናት።የኩርዲስታንና የሌላው አካባቢ መነጣጠል ያንን ያረጋግጣል።

ለሰብአዊ መብት ቆመናል እያሉ የሰው ልጅ በአደባባይ ሲረሸን፣እናት በልጇ አስከሬን ላይ ተቀምጣ እንድትዘፍን ስትገደድ፣ወጣቱ በሥራ አጥነት ተስፋ ቆርጦ ሲሰደድ እያዩና እየተጠየቁም ጆሮ ዳባ ልበስ ከማለትም አልፈው ለዚሁ ወንጀለኛ መንግሥት ተብየው ቡድን የማበረታቻ የገንዘብ እርዳታና የፖለቲካ ድጋፋቸውን መስጠቱን መርጠዋል።እዚህ ላይ ነው ማን ለምንና ለማን ጥቅም መቆሙ የሚታየው።

አሁን በስልጣን ላይ ያለው ቡድን  በስልጣን ላይ ለመቆየት ካልቻለ አገሪቱን በታትኖ ለመጥፋት እቅድ እንዳለው ከከፍተኛ ባለስልጣናቱ ውስጥ ሁለቱ ፣አባይ ጸሃዬና ስዩም መስፍን የተባሉት ወንጀለኞች በቅርቡ በሰጡት ቃለምልልስ አረጋግጠዋል።ለዚህ አመቺ የሚሆነው ደግሞ ሕዝቡ ተለያይቶ በክልልና በጎሳ ትግል ውስጥ ከተሰለፈ ነው።በዚህ ጉዞ ደግሞ ማንም አትራፊ ሳይሆን የሚጎዳበት ነው፤በአንዱ ኪሳራ ላይ ሌላው ሊጠቀምና በሰላም ሊኖር አይችልም።አገራችን የእብድ ቤት ትሆናለች ማለት ነው።ያ ሁኔታ ደግሞ የውጭ ሃይሎች ሰርገው እንዲገቡና የሚፈልጉትን እንዲያደርጉ ዕድልና በር ይከፍታል።አደጋውን ለመቀልበስ አገር ወዳዱና ለውጥ ፈላጊው ኢትዮጵያዊ ያለው ምርጫ አንድና አንድ ብቻ ነው።በጎሳ መለያየቱን ትቶ በአንድ አገር ዜግነት መቆምና ያለውን ስርዓት ማሶገድ። የውጭ አገር ጠላቶች ለሚፈልጉት የመገነጣጠል ዓላማ ሳይመች፣የተለያየ መሆኑን በሚያበስር መልኩ የተለያየ ባንዲራ ስር መሰለፉን ትቶ በአንድ ሰንደቅ ዓላማ ስር  መሰለፍ፤በውጭ አገር መንግሥታት ላይ ከመተማመን ይልቅ በራስ መተማመን።የዘመነ መሳፍንትን ጊዜ መንፈስ ከሚያንጸባርቀው የአካባቢና ጎሰኛ ፖለቲካ ወጥቶ አገር አቀፍ ፖለቲካ መንደፍና መከተል።ለተመሳሳይ የጎሳ ስብስብ ጥቅምና ስልጣን የሚካሄደውን ዝግጅትና የተናጠል ጉዞ መንቀፍና ማክሰም።የጠላትን ሃይል ለመስበር በሚችለው የትግል ስልት መሰለፍ። እስከአሁን የታየውን የመጠላለፍ ጎጂ ተግባር አሶግዶ ተመሳሳይ የሆነ ዓላማና አቋም ያላቸው በአንድ ጣራ ስር እንዲሰለፉ ማድረግ፤የተቀጣጠለውን ሕዝባዊ ትግል በመርዳት መልክ በማስያዝና በማያያዝ እንዲቀጥል፣ብሔራዊ መልክ እንዲይዝ ማድረግ።በመንግስት ላይ የተከሰተውን  የፖለቲካና የኤኮኖሚ ቀውስ እንዲፋፋም ጠንክሮ መስራት።የመንግስት ባለስልጣናትና ቤተሰቦች የአገርና የውጭ ባለሃብቶች ንብረት በሆኑትና ስርዓቱን በሚረዱ ተቋማትና የንግድ ድርጅቶች ላይ እቀባ ማስፈን። የመንግስት የለያይተህ ግዛን መመሪያ እጅ ለእጅ ተያይዞ ማክሸፍ።እወክለዋለሁ ከሚለው ሕዝብና ክልል መነጠል።በክፍተት ስርዓተአልበኝነት እንዳይከሰት ሕዝቡ በየቦታው ከሰራዊቱና ከፖሊስ ሃይሉ ወደ ሕዝቡ ከሚቀላቀሉት ጋር ሆኖ ሕግ አሰከባሪ አካል እንዲፈጥር ማድረግ። እነዚህን ተግባራት በስራ ለመተርጎም የሚችል አካል ለመፍጠር በአገር ውስጥ ሁሉን አቀፍ ጉባኤ በአስቸኳይ ማካሄድ የወቅቱ ተግባር መሆን ይኖርበታል።ሁኔታው ከእጅ ሳይወጣ በፍጥነት መፍትሔ መፈለግ አስፈላጊ ነው።በዚህ ግርግር ከሕዝቡ በስተጀርባ ሥልጣን እይዛለሁ ብሎ ማሰብና ከውጭ ሃይሎች ጋር መደራደር ዋጋ አይኖረውም።ሥልጣን ለመጨበጥ ቢቻል እንኳን ሁኔታውን ያባብሰዋል እንጂ ዘላቂ መፍትሔ አያመጣም፣ሕዝቡም አይቀበልም፤የሚቋምጡ ካሉ ባይሞክሩት ጥሩ ነው።

በአገርቤትና በውጭ አገር የሚገኙት ተቃዋሚዎች ግንኙነት መፍጠር አለባቸው።አገራችን የጥፋት ማእበል ውስጥ እንዳትገባ አገር አድን ሃይል መፍጠር ይኖርባቸዋል፤የሚፈጠረው ይህ አካል ከሁሉም የተውጣጣ ሲሆን እንደሽግግር መንግስትም ሆኖ ሊያገለግል ይችላል።

እነዚህ በአለፉት የአርባ አምስትና ከዚያም በላይ በሆኑት የዕድሜ ዓመታት ያየናቸው መንግሥታት ሲሆኑ ሶስቱም የሕዝቡን ፍላጎትና ጥያቄ መመለስ የቻሉ አይደሉም።ሦስቱም ሕዝብ መርጦና ፈቅዶ የሥልጣኑ ባለቤት ያደረጋቸው ሳይሆኑ በጉልበትና በታሪክ አጋጣሚ  ከሥልጣን ወንበር ላይ የተቀመጡ ናቸው።ሁለቱ መንግሥታት አወዳደቃቸውም ሳያምር የቀረ ሆኗል።አሁን በመውረግረግ ላይ ያለው ቡድን እንዳለፉት ሁለቱ በሕዝቡ ትግል የሚወገድበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም።

በተደጋጋሚ እንደታየው ለነዚህ ሦስት ስርዓቶች ዕድል የሰጠው የሕዝቡ አለመንቃትና አለመደራጀት፣ብሎም በአንድነት ቆሞ ወግዱ ሳይላቸው በመቅረቱ ነው።አሁን ግን ያለንበት ዘመንና የንቃተ ህሊናችንም ለነዚህ አይነቶቹ ስርዓቶች የሚመች አይደለም።እርግጥ ነው ሕብረተሰባችን ሙሉ ለሙሉ የነቃና የተደራጀ ነው አይባልም፤ግን ካሳለፈው መከራ ብዙ ትምህርት ቀስሟል።ወደተሻለ አቅጣጫ ሊመራ የሚችል የተደራጀ ጠንካራ ሃይል ባይኖረውም የሚፈልገውን ያውቃል።

አሁንም ያለፉት አይነት ስርዓቶች አይነት ለመተካት ፍላጎት ያላቸው አይጠፉም።በዘርና ባለፈ ቅርሾ ሰበብ የዘር ፖለቲካ የሚያናፍሱ አገሪቱንና ሕዝቡን ለአደጋ ሊያጋልጡበት የሚችለው ዕድል ከፍተኛ ነው።እራሳቸውን ትልቅ በማድረግም ከውጭ መንግሥታት ጋር እየተደራደሩ እራሳቸውን ለአገልጋይነት አጭተው ሕዝባቸውን መስዋእት ለማድረግ የተሰለፉም እንዳሉ አይካድም።

ከዚህና ካለፈው አይነት ስርዓት የተሻለ ለማምጣት የሚፈልጉና አገራቸው እንዳገር አንድነቷ ተጠብቆና ተከብራ የሕዝቡም ኑሮ ተሻሽሎ ማየት የሚፈልጉት እውነተኛ አገር ወዳዶችና የለውጥ ሃይሎች ሳያቅማሙ አንድነት ፈጥረው ካለፉት የተለዬ ስርዓት እንዲመሰረት መጣር አለባቸው።አገራችን ዳግመኛ ከጎሰኛ፣ ከአምባገነንና የውጭ ሃይሎች አሽከር ከሆነ ቡድን እጅ እንዳትገባ መጠንቀቅ ተገቢ ነው።

የሚመሰረተው ስርዓት፣በሕግ የበላይነት የሚያምን፣የዴሞክራቲክ መብቶችን የሚያረጋግጥ፣የዜጎችን እኩልነትና ፍትህን የሚያከብር፣በሕዝብ ተመርጦ በተወሰነ ጊዜ የሚወጣና የሚወርድ መንግሥትና መሪ እንዲኖር በሚያስችል አሰራርና ሕግ የሚመራ፣የአገሪቱን አንድነትና የሕዝቡን ልዑላዊነት የሚያስከብርና የሚያረጋግጥ መሆን ይኖርበታል።

ይህንን የሚቀበሉ ሃይሎች፣የፖለቲካ ድርጅቶች፣የሲቪክ ተቋማት፣ግለሰቦች፣የጉዳዩ ተካፋይ የሆኑ ሁሉም ዜጎች ከጎሳና ከሃይማኖት ነጻ የሆነ የሽግግር መንግሥት ለመመስረት በጋራ መምከርና መዘጋጀት የወቅቱ ተግባር መሆኑን ሊያውቁትና ሊቀበሉት ይገባል።የሽግግር መንግሥቱንም መመሪያና የአጭር ጊዜ መርሃግብር በጋራ መንደፍ ይኖርባቸዋል፤ስለሆነም ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ እንዳይሆን ነገ ዛሬ ሳይሉ አብረው ለመምከር አስቸዃይ ስብሰባ ሊጠሩ ይገባል።እንደተለመደው የስብሰባ ውድድርና መጠላለፍ እንዳይኖር ብዙሃኑ ቁጥጥር ሊያደርግባቸው ይገባል።

በተጨማሪም ህወሃት /ኢሕአዴግ ተቃውሞውን የአሸባሪዎችና የጥፋት ሃይሎች ሥራ ለማስመሰል፣እንዲሁም መውደቂያውን አስቦ በተንኮልና እኔ ከሞትኩ ከሚል እኩይ አሳብ በመነሳት በአንዳንድ ተቋማትና በግለሰቦች ላይ አደጋ በመጣልና በእሳት በማጋየት ተግባር ላይ ስለሚውል ያንን በማጋለጥና በእልህ ሕዝቡ በተመሳሳይ ተግባር ላይ እንዳይሰማራ ማስጠንቀቅ ያስፈልጋል። ማንኛውም ተቋም ከድል በዃላ ለአገሪቱና ለሕዝቡ ጥቅም በሚሰጡበት መልኩ እንዲደራጁ ማድረጉ ስለማይቀር ከውድመት ማዳን ብልህነት ነው።የሚጎዳውንና የሚጠቅመውን አስቀድሞ ማጤኑ በሳልነት ነው።በዛች አገር መሬት ላይ ያለንብረት ምንጩና መሰረቱ የአገሪቱ ሃብትና የህዝቡ ላብ ስለሆነ መውደም አይኖርበትም።

በአርባ አምስት ዓመታት ውስጥ ያየዃቸው የኢትዮጵያ መንግሥታት ጭማቂ ባህሪያት

የአጼ ሃይለሥላሴ መንግሥት     የደርግ መንግሥት              የህወሃት/ኢሕአዴግ መንግሥት

ንጉሳዊ ፈላጭ ቆራጭ ፣         ወታደራዊ አምባገነን፣                የዘረኞች አምባገነን

በፈሪሃእግዚአብሔር የሚመራ፣   በሕገጠመንጃ የሚመራ፣               በሕገአራዊት የሚመራ

ሕዝብ የሚያከብረው ፣         ሕዝብ ጠልቶት የሚፈራው፣            ሕዝብ አንቅሮ የተፋው

ለአስከሬን ክብር ያለው፣       ገሎ የጥይት ዋጋ የሚያስከፍል፣          ልጅ ገድሎ እናትን የሚደበድብ

ተቃዋሚውን በዱላ እንጂ      የጭካኔ ባህል ያዳበረ ጥያቄና          ለተቃውሞ ቦታና ዕድል የማይሰጥ፣

በጥይት የማይደበድብ         ተቃውሞ በጥይት የሚመልስ           የሚገል፣የሚያስርና የሚያሳድድ

ለሥልጣኑ ሙት                ለሥልጣኑ ሙት፣ትዕግስተቢስ፣       ለሥልጣኑ ሙት፣ዘራፊ፣አገሩን የሚሸጥ

ሕዝቡን ያስከበረ፣ካለቪዛ በአውሮፓ   የስደትን በር የከፈተ፣ሕዝቡን     ስደትን እንደሙያና ሥራ የቆጠረ

የመዘዋወር መብት ያረጋገጠ፣         ለውርደት የዳረገ               በወታደሩና በድሆች ስም የሚነግድ

ሕዝቡ በአገሩ ውስጥ ከዳር እስከዳር   ፍርሃትና ሽብር የሰፈነበት         ፍርሃትና የመበታተን አደጋ የሰፈነበት

የመንቀሳቀስ፣የመኖርና የመስራት      ከግማሽ ሚሊዮን በላይ           ጥላቻና ልዩነት የሚያራግብ                                                                                                      ወ ነጻነቱን ያረጋገጠ፣አንጻራዊ ሰላም      ወታደር አሰልፎ ጥቂት           በዘር እንጂ በዜግነት የማያምን

የሰፈነበት                   ተገንጣዮችን  መቋቋም           የአገሪቱን መከላከያ ሃይል በዘር

በስልሳ ሽህ ቋሚ ወታደር ያገሩን        አቅቶት የኮበለለ፣                 አዋቅሮ ለማዋጋትና አገር

ዳር ድንበር ያስከበረ                  በኢትዮጵያ መሪዎች               አፍርሶ ለመጥፋት የተዘጋጀ

ለአፍሪካ አንድነት መሠረት የጣለ     ታሪክ ውስጥ አሳፋሪ  የሆነ               ለባዕዳን ጥቅም የቆመ

ሙት ይዞ ይሞታል –ለምለም ጸጋው

$
0
0

lemem

ሙት ይዞ ይሞታል – ለምለም ጸጋው

አለባብሰው ቢያርሱ ባረም ይመለሱ  –ይሄይስ አእምሮ

$
0
0
አንድ የወያነ ትግሬ የአጋዚ ወታደር ፊቱን በመሸፈን ቦ ኦሮሚያ ክል ቢሸፍቱ (ደብረዘይት) ላይ ህዝቡን እንዲህ ነው የፈጀው።

አንድ የወያነ ትግሬ የአጋዚ ወታደር ፊቱን በመሸፈን ቦ ኦሮሚያ ክል ቢሸፍቱ (ደብረዘይት) ላይ ህዝቡን እንዲህ ነው የፈጀው።

ማለባበስ በጣም ጎጂ ነው፡፡ አሁን የምንገኝበት ማኅበራዊና ፖለቲካዊ አጣብቂኝ እንደእስከዛሬው ዓይነት የሽፍንፍንና የጥግንግን አካሄድን የሚያስተናግድ አይደለም – አምርሯል፡፡ አካፋን አካፋ ማለት የሚገባበት ትክክለኛ ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ አንድን እውነት ሺህ ጊዜ ብንሸፋፍነው መገለጡ አይቀርም፡፡ ሲገለጥ ደግሞ የሚያስቀይም ስዕል ጎልቶ የሚታይበት አጋጣሚ እየበዛ ይመጣና ከመገናኘት ይልቅ መለያየት የማያመልጡት አሳዛኝ ክስተት ይሆናል፡፡

በሰሞኑ የእሬቻ በዓል የተከሰተውን ከወያኔ በቀር ሁላችንም እናውቃለን፤ ወያኔዎች ግን “ጥቂት ሰዎች (ኦሮሞዎች) በተፈጠረው መጨናነቅ ተረጋግጠው” እንደሞቱ እንጂ (በውጪዎቹ stampede ሲሉ ሰምተዋልና)  በነሱው ታዛዥ “ኢትዮጵያውያን” አልሞ ተኳሽ ወያኔያዊ አልቃኢዳዎች በመትረየስና በጭስ ጋዝ እንደተረፈረፉ ሊያምኑ አይፈልጉም፡፡

ከዚህ የእሬቻ ዕልቂት ሌሎቻችን ምን እንማራለን?

ከዚህ ዕልቂት የምንማረው ነገር እጅግ ብዙ ነው፡፡ በመሠረቱ ይህ ዕልቂት በጎሣ ላይ ያነጣጠረ እንዳልሆነ ማመን እፈልጋለሁ፡፡ ኢትዮጵያውያን ለወያኔ ከፋፋይ ሥርዓት እጅ ሰጥተን ሁሉንም ነገር ወደዘር እንመነዝረዋለን እንጂ በአንዱ ሰው ውስጥ ብዙ ዘር በሚገኝበት እንደኢትዮጵያ ባለ ሀገር ውስጥ ሙከራው የለም ማለት ባይቻልም አንድን ዘር ለይቶ የማጥቃት ሙከራ እምብዝም አይሳካም፡፡ ምክንያቱም በሕዝብ የዘመናት ማኅበረሰብኣዊ ሽመና የተነሣ ማኅበረሰቡ አንዱን ሲሉት ሌላውን ነው – ኦሮሞ ሲሉት ትግሬ ነው፤ ትግሬ ሲሉት ደግሞ አማራ ነው፤ ጎንደሬ ሲሉት አርሲ ነው – ወለጋ ሲሉት ደግሞ ሲዳሞ ነው፡፡ ሁሉም ተቀያይጦ አንዱን ስትገድለው በውስጡ ሌላውም አብሮ ይሞታል፡፡ ከዐማራና ትግሬ ወላጆች የተገኙ ልጆችን ብትፈጅ ላንተ አንዱን ወይ ሌላውን የገደልክ ይመስልሃል እንጂ ሁለቱንም ነው ባንድ ጥይት የፈጀሃቸው፡፡ እንደፍቅሬ ቶሎሳ አንድ ቀደም ያለ መጣጥፍ ከሆነ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ በመዋሃዱ አንዱን ከሌላው ለመለየት የሚቻል አይደለም – ወያኔዎች ውኃና ዘይት ሊያደርጉን ቀን ከሌት ቢማስኑም ፈጣሪ በፀጋው ወተትና ውኃ አድርጎ አንዳችንን በአንዳችን ውስጥ እንደሰም አቅልጦ ውሁድ ሻማና ጧፍ አድርጎናል፤ ጊዜ ይፍጅ እንጂ ደግሞ ወያኔ ያዞረብንን ትብታብ  በአንድነት በጣጥሰን አንዲት ታሪካዊት ሀገራችንን በጋሪዮሽ የብርሃን ፀዳላችን የምናደምቅበት የነፃነት ዘመን በቅርቡ መምጣቱ አይቀርም፡፡

ቋንቋ እንደሆነ በመልመድ ወይም በመማር እንጂ በባሕርያዊ የደም ትልልፍና በሀብት ውርስ የፍርድ ሂደት ስለማይገኝ ዐማርኛ የማይችል “ዐማራ” በኦሮሞ ውስጥ ብታገኝ ወይም ትግርኛ የማይችል “ትግሬ” በኦሮሞ ውስጥ ብታገኝ ይህ ክስተት ከፍ ሲል የሰው ልጅ ዝቅ ሲል ደግሞ የኢትዮጵያውያን ልዩ መገለጫ በመሆኑ የሚያስደንቅ አይደለም፡፡ ለዚህም ነው የወያኔ የዘር ቀመር ወንዝ የማያሻግር ወፍ ዘራሽ የታሪክ አራሙቻ መሆኑ የሚነገረውና ሀገር አጥፊነቱ ዘወትር የሚገለጸው፡፡ ሰሚ በመጥፋቱ ግን ሀገርና ሕዝብ ላይ በቀላሉ ሊቀለበስ የማይችል ጉዳት እየደረሰ ነው፡፡ ደጋግ ሰዎች እየጠፉ በክፉዎች ተከበናልና አንድዬ ይሁነን፡፡

ለማለት የፈለግሁት በዚህ የእሬቻ በዓል የሞቱት ሁሉም ኢትዮጵያውያን እንጂ አንዱ ዘር ማለትም ኦሮሞ ተመርጦ እንዳልሆነ ለማስታወስ ነው፤ ይህንንም ስል የማንንም ወንጀል ለመደበቅ ሣይሆን እውነቱን ለመግለጽ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ወያኔ በዚህ ዕልቂት የፈረደብን በሁላችንም ላይ እንደሆነ መረዳት አለብን፡፡ ለነገሩ በዓሉን ለማክበር ከሁሉም ሥፍራዎችና ከሁሉም ጎሣዎች የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን በሥፍራው በመገኘታቸው የኦሮሞ ሟች ቁጥር ሊበዛ እንደሚችል ቢገመትም ሁሉም ሞቷል ማለት እንችላለን፡፡ ማንም ይሙት ማን ግን የሞተው ሰው በመሆኑ፣ በዚያም ላይ ምናልባት ሁሉም ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ስለሚገመት የሀዘኑን ምንጭ ወያኔን ሳይጨምር ሀዘኑ የሁላችንና የመላዋ ሀገራችን ነው፡፡ ነፍስ ይማር፡፡

ፍርዱ በሁላችንም ላይ ከሆነ ዘንዳ በወያኔ ላይ መነሳት ያለብን ሁላችንም በጋራ ሆነን ነው፡፡ የያዝነው መንገድ ግን እንደዚህ አይደለም ወይም አይመስለኝም፡፡ ጥቃቱ በሁላችንም ላይ የሚደርስ ሆኖ ሳለ የትግላችን አቅጣጫ ግን የተፈናጅራ (የተለያዬና ርስ በርስ የሚቃረን) ሆኖ ለኛ ተጨማሪ ዕልቂትን የሚያስከትል ለጠላቶቻችንና ለገዳዮቻችን ደግሞ ሠርግና ምላሽ ሆኖ ጮቤ የሚያስረግጣቸው ነው፡፡ በቢሊዮን ዶላሮች በሚገመት የበጀት ምደባ የማያገኙትን ከፋፋይ የትግል ሥልት በመከተላችን ወያኔዎች እኛን በጅልነታችን እንደሚያመሰግኑን አልጠራጠርም፤ በዚህ ረገድ ያጠመዱት ወጥመድ ተሳክቶላቸዋልና በጣም ዕድለኞች ናቸው፡፡

እውነቱን ለመናገር ብዙ አክራሪነት ይታየኛል፡፡ አክራሪነት ደግሞ ያለያያል እንጂ ወደ አንድ የጋራ መድረክ አያመጣም፡፡ ሕዝቡ በተለይም ወጣቱ ሰከን ማለት አለበት፡፡ አንድን የዘር ሐረግ ብቻ እየነቀሱ በዚያ ላይ ማጠንጠን መጨረሻ ጥፋት መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡ ከወያኔ ካልተማርን ፈጣሪ ራሱ ወርዶ ወንበር ዘርግቶ አያስተምረንም፡፡ “ኦሮሞና ዐማራ አንድ ሆኑ፤ ሌሎች ጎሣዎችንም በኅብረት አስተሳስረውና አማክለው ለሀገራዊ ነፃነት ፈር ቀዳጅ የጋራ ትግል ጀመሩ” ተብሎ ከመነገሩና በብዙዎች ዘንድ ከመወደሱ በሰሞኑ የእሬቻ በዓል አከባበር ላይ የታዘብነው ሁሉንም የማያካትትና ብዙኃንን ትቶ የአንድን ንቅናቄ ዓላማ ብቻ የሚያቀነቅን የትግል አቅጣጫ ትኩረት ሳቢ ነበር ማለት አይቻልም፡፡ ከስሜት ካልወጣን፣ ከጎጠኝነት ወይም ከክልላዊ የተናጠል ሩጫ ካልታቀብንና ለወል ማንነታችን ካልተጋን የጠላቶቻችን መሣሪያ እንደሆንን እንዘልቃለን፡፡

የማየው አክራሪነት ዘር ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ብዙ ወጣቶች ኦሮሞን ከኢትዮጵያ ገንጥለው የወያኔን አጀንዳ ለማራመድ ሲሞክሩ ይታያል፤ የፈረደበትን ወያኔ ልጥቀስ እንጂ ከወያኔ በማይተናነስ የዘውገኝነት አረንቋ ገብተን ዳግም እንድንዳክር የሚያስገድድ በዘረኝነት አባዜ የተለወሰ ድግስ የሚደግሱልን ወገኖች ሊኖሩ እንደሚችሉ በዚህ አጋጣሚ ባስታውስ ነውር ያለበት አይመስለኝም፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ወገኖች ሃሳባቸው በተለያዩ ከፋፋይ ድርጊቶች ይገለጻል፡፡ ወልጋዳው አካሄድ ተጠናክሮ የሚታየው በውጪ ሀገራት በተለይም እንደልብ በሚፈነጩበት በዲያስፖራው አካባቢ ቢሆንም በተለይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ይህ ወረርሽኝ ወደ ሀገር ውስጥም ገብቶ ስሜት ቆንጣጭ በሆነ ሁኔታ እያቃቃረን ይገኛል፡፡ ልብ ልንገዛና ወደኅሊናችን ልንመለስ ባለመቻላችን ሌላው ሁሉ ቀርቶ የእግዚአብሔርን ቤት እንኳን በዘርና በጎሣ እየከፋፈልን “የአቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን”፣ “የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ደብር” ወዘተ. በሚል የመንግሥተ ሰማይንና የገሃነመ እሳትን ነዋሪዎች ሳይቀር በሣቅ የሚያፈነዳ ከንቱ የማይም ትያትር የምናሳይ “ኢትዮጵያውያን” ሞልተናል፡፡ እዚህ በሀገር ቤት መቼም ከመኪና ታርጋ ጀምሮ እስከ ባንክና ሌሎች የንግድ ተቋማት ድረስ በዘር ልምሻና በፆታና ሃይማኖት ድልድል ተኮድኩደን “ወጋገን ባንክ”፣”አንበሣ ባንክ”፣ “አዋሽ ባንክ”፣ “ዳሸን ባንክ”፣ “ንብ ባንክ”፣ “ብርሃን ባንክ”፣ “እናት ባንክ” … እያልን ስንጃጃል የሚታዘበን ቢኖር የአሣራችን ብዛትና የቂልነታን መጠን ዳር ድንበር የሌለው መሆኑን በግልጽ ይረዳል፡፡ ዘመን ሲያልፍ የምናወራው ስንትና ስንት የነውር ሥራ አለን መሰላችሁ፡፡

ሰሞኑን ከታዘብኳቸው እንከኖቻችን ጥቂቶቹ፡-

ትዝብት አንድ – አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ የኢትዮጵያ ባንዴራ የዐማራ (ብቻ) አይደለችም፡፡ ይህች ባንዴራ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኦሮሞዎችና ዐማራዎች እንዲሁም ትግሬዎችና ሌሎች ጎሣዎች በመላዋ ሀገራችን ከውጭ ወራሪዎችና ከውስጥ ምንደኞቻቸው ጋር በተካሄዱ ጦርነቶች ያለቁላት የቀስተ ደመና ምሳሌ ናት፡፡ ይህች ባንዴራ ለተንኮል ሲባል ቤተ ሙከራ ውስጥ ተፈልስፎ እንደሚሰጥ ዘመን ወለድ የጠላት ፍብርክ ባንዴራ ሳትሆን እነአባመላ ዲነግዴ፣ እነጄኔራል ደምሴ ቡልቶ፣ እነቀ.ኃ.ሥላሴ፣ እነመንግሥቱ ኃ.ማርያም፣ እነደጃች ገረሱ፣ እነጄኔራል ጃጋማኬሎ፣ እነአብዲሣ አጋ፣ እነ ስንቱን የኦሮሞ ጀግና አንስቼ ልዝለቀው – እነዚህ ሁሉ የኦሮሞ የጦር አበጋዞችና የሀገር መሪ ነገሥታት የተዋደቁላት ባንዴራ ዛሬ ለአንድ ጎሣ  – ለዐማራ – በችሮታ ተሰጥታ በዚህ የተገፋ ሕዝብ ስም ስትጎሳቆል ማየት ከማሳዘኑም በላይ የታሪክን ፍርድ የሚጋብዝ ከፍተኛ ጥፋት እንደመፈጸምም ይቆጠራል፡፡ የሕዝብን የጋራ አንጡራ ሀብት ቀምቶ ለአንድ ነገድ ብቻ ማስታቀፍ ነውርና ታሪክን አለማወቅ ወይም ጨርሶ መካድ ነው፡፡ ይህ በዘመን የሾመጠረ ጠላ ሰክሮ እምቡር እምቡር ማለት ደግሞ የትም እንደማያደርስና  ውሉን የማይስተው ታሪክ ትክክለኛ መስመሩን ሲይዝ ለትዝብት እንደሚዳረግ መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ሸረኛ ሰዎች በዘረጉት የወጥመድ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ በስሜት ስካር ከመጨፈር ይልቅ ወደ እውነተኛው ታሪካችን በመመለስ በወያኔ ሤራ የላሉና የተበጣጠሱ የአብሮነታችንን ገመዶች ማጠባበቅ ይሻለናል፡፡ ስሜትና እውነት እንደሚለያዩ ካልተገነዘብን ዘመን ወለድ ስካራችን በቀላሉ አይለቀንም፡፡

ስለሆነም ወደኅሊናችን በመመለስ የጥንት የጧትን አእምሯዊና ባህላዊ የጋራ ሀብትና ንብረት አክብሮ መያዝ ይኖርብናል፡፡ ንፋስ ወደነፈሰበት ሁሉ እየዞርን አንገታችንን ማጣት አይገባንም፡፡ በአንድ በኩል ኅብረትና አንድነት ፈጠርን እያልን በሌላ በኩል የጋራ ሀብታችንን መጥላትና ወደ አንድ ጎሣ መለጠፍ ተገቢም ወቅታዊም አይደለም፡፡ በአንድ ጊዜ ሁለት መሆን አይቻልም፡፡ ለመሠሪዎች ተንኮል መንበርከክም ለተራዘመ የግፍ አገዛዝ ከመዳረግ ውጪ አንዳችም ፋይዳ የለውም፡፡ ከጎጂ መሠረት አልባ እልህ ወጥቶ ምክንያታዊና ሰብኣዊ ፍጡር መሆን ይገባል፡፡ በኦሮምኛ ትውፊት “ትናንት አልፏልና አያስጨንቅህ፤ ነገም ያንተ ላይሆን ይችላልና እጅግም አያሳስብህ፤ ዛሬ ግን በእጅህ ያለ በመሆኑ በጥበብና በማስተዋል ተጠቀምበት” የሚል በሳል ብሂል አለ፡፡ ብልኆች ይህን ብሂል አጢነው በአግባቡ ይጠቀሙበታል፤ ዝንጉዎች ግን በሰው አልባሌ ምክር እየተወሰዱ ጊዜያቸውንና አቅማቸውን በሞላ ለአሉታዊ ዓላማና ግብ ያውሉታል፤ በመጨረሻው ግን ለፀፀት መዳረጋቸው አይቀርም፡፡

በደብረ ዘይት ዕልቂት የኢትዮጵያን ንጹሕ ባንዴራ ብመለከት ኖሮ ደስታየ ወሰን ባልነበረው፡፡ የወያኔን ባንዴራና ከፋፋይ ወገኖች የደረቱልንን ቡትቶ አስወግደን በመጣል ከፍ ሲል የጠቃቀስኳቸውና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን የተሰውላትን ንጹሕ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ ብንሰቅል ኖሮ ትግላችንን በሰማንያው የኢትዮጵያ ነገድና ጎሣ ሁሉ ልናስደግፈው በቻልን ነበር፡፡ ሰይጣን ይሁን ወይም ወያኔዊ የዓመታት መርዘኛ ፕሮፓጋንዳ ያን ብልኃትና ጥበብ ሰውሮብን ለሕዝብና ለመሬቱ ባዕድ የሆነ ሌላ ባንዴራ በማሳየታችን ትግላችንን አሳነስነው፤ የሌሎችንም ድጋፍ አቀዘቀዝነው፡፡ ተገቢ አይደለም፡፡ በውጭ ሀገር በሚደረጉ ሰልፎችም ይሄው አዲስ ክስተት ይታያል፡፡ በስመ “እነእንትናን ላለማስቀየም” ሲባል እርጥብን ከደረቅ፣ ነጭን ከጥቁር መሞጀር አግባብ አይደለም – እውነቱን ልቦናችን እያወቀው – የልቦናችንን ማወቅም ሁሉም ወገን እየተረዳው አጉል መሸዋወድ ተገቢ አይደለም፡፡ ያለህን የጋራ ንብረት በመጣል አይደለም ማንነትህን የምታስጠብቀው፤ ያልነበረህን በነበረህ በመለወጥና አዲስ ማንነት በመደረት አይደለም ፍቅርና አንድነት የምታዳብረው፡፡ “ያልወለድኩት ልጅ ቢለኝ አባባ፤ አለው አፌን ዳባ፣ ዳባ” ይባላል፡፡ “የራስህ ጉዳይ ነው” እንዳትሉኝ እንጂ ለምንድን ነው እኔ የብኣዴን ተብዬውን ባንዴራ ከነቀለሙ እንኳን እስካሁን ላውቀው ያልቻልኩት? ማንም እየተነሣ የላዩ ላይ በል ባለው ቁጥር ባንዴራ እየጠፈጠፈ በየአምሳና መቶ ዓመቱ የሚያሸክመኝ ነፈዝ ከሆንኩ ምኑን ሰብኣዊ ፍጡር ሆንኩት! እንደዚያማ ከሆንኩ የኔን ነፃነት፣ የማሰብና የማገናዘብ ችሎታየን ምን ወሰደብኝ ሊባል ነው? አሜሪካውያንን ተመልከት፣ እንግሊዛውያንን ልብ በል፡፡ ማንም ሞቅ ያለው የጨረቃ ሌሊት ዕብድ ሁሉ እየመጣ ባንዴራን አይለውጥም፤ ሀገር እንደማይለወጥ ሁሉ የጥንት አባቶችና እናቶች የሞቱለት ሰንደቅ ዓላማም ግርግር በተፈጠረ ቁጥር አይቀየርም፡፡ ለዚህም ነው በባንዴራ የሚደረግ ድርድር ቅጥ ያጣ ድርድር የሚሆነውና ሰውን አስደሰትኩ ብለህ የጋራ ማንነት መገለጫህን ዋጋ ማውረድ የማይገባህ፡፡ ይታሰብበት፡፡

ማለባበስ ይቅር የምለው እንግዲህ ከነዚህ መሠረታዊ ነጥቦች በመነሳት ነው፡፡ ይህን ጉዳይ በሚመለከት ከብዙዎች ኦሮሞዎችና ሌሎች ጓደኞቼ ጋር ስንጨዋወት የተረዳሁት ሃቅም ይሄው ነው፡፡ ትግላችን እንዲሰምር ከታይታዊ የይስሙላ መተባበር ይልቅ ለእውነተኛ የመተማመንና የመዋደድ ስሜት መገዛት አለብን፡፡ ትብብራችን የስትራቴጂ ወይም የሥልት ከሆነ ቀደም ሲል እንደተናገርኩት አለባብሶ ማረስና ለዐረም ሲመለሱ መቸገር ነው፤ ማኅበራዊ ዕርቅና ስምምነት ግልብ ሳይሆን ልባዊ መሆን አለበት፤ የሚያስተማማና እየቆዬ የሚያመረቅዝ ነገር መኖር የለበትም፤ የሚያሸምቁበት ሸፍጥም ሊኖር አይገባም፤ ፍጹማዊ መግባባትና ግልጽነት በተስማሚዎች መካከል ሊሠፍን ይገባል፡፡ የዛሬ ዐርባና ሃምሳ ዓመት ያልነበረ ነገር ዛሬ መጥቶ የዛሬ ዐርባና ሃምሳ ዓመታት የነበሩ ፍጡራንን ሊከፋፍልና የሚደርስባቸው በደልና ጭቆና ላይ ልብ ለልብ ተገናኝተው እንዳይታገሉ ደንቃራ ሊፈጥርባቸው አይገባም፡፡

“ከትናንት በስቲያ እገሌ ገዝቷል፤ ከትናንት እስከዛሬ እነእገሌ እየገዙ ነው፤ ከዛሬ ጀምሮ ደግሞ የእኛ የመግዛት ተራ ነው” የሚሉት አስቂኝ ፈሊጥ ደግሞ በጭራሽ አያዛልቅም – ይህ ሥልት በዚህ በምንገኝበት የዴሞክራሲ ዘመን ለመታገያና ለማታገያነት ቀርቶ ሊሰሙት የሚያሰጠላ ያረጀ ያፈጀ ሥልት ነው፡፡ በመሠረቱ ማንም ቢገዛ ለዘመዶቹና ለጥቂት ወገኖቹ የሀብት መንገድ ይከፍት እንደሆነ እንጂ በቋንቋና በዘር ምክንያት ሁሉም አያልፍለትም፡፡ ይህ ቢሆን ኖሮ እንደትግሬ ወያኔ ዘረኛ እንዳለመኖሩ አዲስ አበባ ላይ የሚለምን አንድም የትግሬ ጎሣ አባል ባልነበረ፡፡ የአዲስ አበባን መንገዶች ሁሉ ተመልከቱ – ከትግራይ የመጡ የኔ ቢጤዎች እንደማንኛውም ጎሣ አባላት እየለመኑ ታገኟቸዋላችሁ፤ ከጠቅላላው የተጋሩ ብዛት አኳያ ያለፈለት ትግሬ ጥቂት ነው፡፡ ያላለፈለትና እንደኛው እንደብዙዎቹ መከራውን የሚበላው ትግሬ ብዙ ነው፡፡ እርግጥ ነው – እንደዬግለሰቡ አእምሯዊ ጥንካሬ የሚታይ ሆኖ አብዛኛው ወይም በጨዋ አነጋገር ጥቂት የማይባለው ትግሬ ችግሩን በሥነ ልቦናዊ ኩራት ሊያስታምምበት የሚያስችለው ብዙዎቻችን በወቅቱ በግልፅ ይታያል ብለን የምናምነው ትግሬያዊ የበላይነት የሚፈጥርለትን ባዶ ተስፋ ሊሰንቅ ይችል ይሆናል፡፡ ተስፋ ግን ሆድን አይሞላምና የመንደሬን ነዋሪ ወይዘሮ አብረኸትን ከአምባሻ ሻጭነት ወይም ወጣት ግደይን ከቁራሌነት አውጥቶ ባለፎቅ ያደረገ ትግሬ ወያኔ እስካሁን አላገኙም – እውነቴን ነው፤ ረጋ ብለን ከታዘብን ስሜትና እውነት እንደሚለያዩ ማጤን እንችላለን፡፡ ስለሆነም ይህ በዘር ላይ የተመሠረተ የአገዛዝ እሳቤ ልቦለዳዊ እንጂ እውናዊ አይደለም፡፡ እናም ወደ አቅላችን እንመለስ፡፡ ደግሞም የአሁኑን የወያኔ አገዛዝ  ለታሪክ ፍርድ ትተን ለጊዜው እንርሳውና የዱሮዎቹን አገዛዞች ብናይ ያን ያህል በዘርና በጎሣ የተመሠረቱ ናቸው ብለን የምንወቅሳቸው እንዳልነበሩ ጤናማ ኅሊና ያለን በዕድሜ አንጋፋ ሰዎች የምንፈርደው ጥሬ እውነት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የለየለት ዘረኝነት የታየው አሁን እንጂ የቀድሞዎቹ እኩል ይገድሉን፣ እኩል ይቀጠቅጡን፣ እኩል ይጨቁኑንና ያንላቱን ነበር እንጂ ለአበበና ለደቻሳ ወይም ለዘበርጋና ለሐጎስ በሚል የተለዬ ሕግ አውጥተው ከፈሪሃ እግዚአብሔር መንገድ የሚያፈነግጡ አልነበሩም፡፡ ባልነበረ ነገር አንኮነን – ቢያንስ ገሃድ የወጣና በመርህ ደረጃ የጸደቀ የአሁኑን መሰል አድልዖዊ የአገዛዝ ሥልት አልነበረም፡፡

ትዝብት ሁለት ፡- ቋንቋን በሚመለከት ደግሞ ጥቂት የምጨምረው ነገር አለኝ፡፡ ዐማርኛ መናገር የሚችል ኦሮሞ ዐማርኛን መናገር ለምን ይጠየፋል? የቋንቋና የሰው ግንኙነት እኮ የመራጃና (tool) የሰው ግንኙነት እንደማለት ነው፡፡ ቋንቋ ማለት እንግሊዝኛም በለው ቻይንኛ ወይም ዐማርኛም በለው ኦሮምኛ ከአንድ ዶማ ወይም ከአንድ ማረሻ አይለዩም፡፡ በቃ፡፡ ልዩነቱ – ልዩነት ከተባለ – ዶማው ለመቆፈሪያነት ሲውል ቋንቋው ደግሞ ለመግባቢያነት ማገለልገሉ ብቻ ነው – አንዱ ይታያል ሌላው አይታይም፤ አንዱ ቁሣዊ ነው ሌላኛው ረቂቅ የአእምሮ ሥሪት ነው፡፡ ከዚያ ውጪ “ያንተ ቋንቋ፣ የኔ ቋንቋ” በሚል ይህን ያህል ልንወራከብበትና በሥነ ልቦና ልክፍት ተጠምደን ልንፋጅበት የሚገባን አይደለም – በዚህ ረገድ ብዙ አለማወቅና ብዙ የስሜት መነዳት ይታያል፡፡ እንደኔ ቢቻል ሁላችንም ኦሮምኛ ብንችልና በርሱ ብንጠቀም ደስ ባለኝ፡፡ እንደታሪክ አጋጣሚ ሆኖ ግን ሰማንያው የኢትዮጵያ ጎሣ የሚግባባው በዐማርኛ ሆነና ቋንቋው ለራሱም ዐማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ለሚባሉትም ጥላቻን አትርፎ ቁጭ አለ – ምሥጋናና ወሮታ ማስገኘት ሲገባው፡፡ አንዳንድ ዕቃ ሳትወድ በግድ ዕዳ ያመጣብሃል፤ አንዳንድ ዕቃ ደግሞ ሸጠኸውም ሆነ አከራይተኸው ወይም አውሰኸው ጥቅም ታገኝበታለህ፡፡ ዐማርኛ ግን ለዐማሮች ያስገኘላቸው የዕልቂት ዐዋጅ ሆነ፡፡ የበሉበትን ወጪት መስበር መቼም እንደኢትዮጵያውን የሚያውቅበት የለም፡፡ …

ዐማርኛን በጋራ መግባቢያነት መጠቀም ካልፈለግን ደግሞ ከሌሎቹ አንዱን እንምረጥና እንጠቀምበት፡፡ በጎች እንኳን ሲቀላቀሉ “እምባ” ይላሉ፡፡ እኛ ደግሞ ሰዎች ስለሆንን ስንገናኝ አንድ ወይ ሁለት እንዳስፈላጊነቱም ከዚያ በላይ የወል መግባቢያ ያስፈልገናል፡፡ ዐማርኛ በታሪክ አጋጣሚ ይህን ቦታ ሊያገኝ ቻለ እንጂ ቀደምት ተናጋሪዎቹ ወረፋ ይዘውና ከንጉሥ ደጅ ጠንተው ይህን የመከራ ዕጣ ፋንታ የተቀበሉ አይመስለኝም፡፡ ታዲያ ለምን እንጠየፈዋለን? ሰዎቹንስ ባልሠሩት ሥራ ለምን እንጠላቸዋለን? ሌላ የተሻለ አማራጭ እስክናገኝ ብንጠቀምበት ምን እንጎዳለን?

አስፈላጊ ሆኖ ካገኘነው ቋንቋውን ይናገሩታል የሚባሉ ሰዎችን ግዴለም እንራቃቸው – ይህም ስህተት መሆኑ እንዳለ ሆኖ፡፡ እነሱን መጥላትና የነሱ ስለመሆኑ እንኳን በወጉ የማይታወቀውን ዐማርኛን መጥላት ግን ስህተት ነው ብቻ ሣይሆን ጤናማነት የሚጎድለው የተዛባ አመለካከት ነው፡፡ ባሏን የጎዳች መስሏት ስስ የሰውነቷን ክፍል በጋሬጣ እንደቧጨረችው ሴት መሆን ይቅርብን፡፡ ለምሳሌ ኦሮሞና ዐማራ ተባበሩ በተባለበት ማግስት እንኳን “በእናቴ ዐማራ ነኝ” የሚለው ሣተናው የባህር ማዶ ታጋይ ዐማርኛን ሲጠየፍ ይስተዋላል፡፡ ለምን? ዐማርኛ ቋንቋ ሁሉንም የኢትዮጵያ ነገዶችና ጎሣዎች አስተባብሮ ባንድ ግዛት ውስጥ ተቻችለው እንዲኖሩ ማድረጉ ስህተት ይሆን?  ይህ ዓይነቱ ጠባይ በቅጡ ካልተያዘ ጠባብነት የሚመነጭ ሲሆን በሌላም ወገን የቋንቋን ተፈጥሯዊ የኢ-ባሕርያዊነት ጠባዩን በውል ካለመገንዘብ የሚመጣ በሽታ ነው፡፡ ቋንቋና ሸሚዝ አንድ መሆናቸውን ለሚረዳ ለእንደኔ ዓይነቱ ሰው ግን ሰዎች እንኳንስ በሰዎች ቋንቋ በዝንጀሮ “ቋንቋ”ም ቢግባቡ ድንቅ ነገር እንጂ አያስከፋም፡፡… ይህቺ በቋንቋ ምክንያት ቱፍ ቱፍ የሚሉ ሰዎች በስስ ሰብኣዊ ጠባይ በመግባት መሰሎቻቸውን ወይም ቢጤዎቻቸውን በቀላሉ በማስቆጣት ለሚፈልጉት ዓላማ ለማነሳሳት እንጂ በርግጥም የቋንቋ ጉዳይ ያን ያህል ሚዛን የሚደፋ ሆኖ እንዳልሆነ ሳይገባቸው ቀርቶ አይመስለኝም፡፡

በነገራችን ላይ አንድ ቋንቋ ለብዙኃን የወል መግባቢያነት እንዲውል ሲደረግ ቋንቋውን በአፍ መፍቻነት የሚጠቀሙት ሰዎች ቁጥር ከቁብ አይጣፍም፡፡ እንደዚያ ቢሆን ኖሮ በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ የጋራ ቋንቋ ከምኞት ባለፈ ትግርኛ ሊሆን በቻለ ነበር፡፡ የዓለም ቋንቋ ደግሞ መንደሪን የሚባለውና ከአንድ ቢሊዮን ሕዝብ በላይ የሚገመት ቻይናዊ የሚናገረው ቋንቋ በሆነ ነበር፡፡ ምሥጢሩ ያለው ቋንቋው በድልድይነት ስንቶችን ያገናኛል? የሚለው ነው እንጂ “ስንቶች በአፍ መፍቻነት ይናገሩታል?” የሚለው አይደለም፤ ይህን እውነት አለማወቅ ለቋንቋ አርበኝነት በማጋለጥ ላልተፈለገ ኩርፊያና ላልተጠበቀ ጉዳት ይዳርጋል፡፡ ኅብረ ብሔራዊ በሆኑ የኛን መሰል ሀገራት ውስጥ አንድ ቋንቋ ለጋራ ቋንቋነት የሚመረጠው “ከራሴው ውጪ የማንንም ቋንቋ አልጠቀምም” በሚል በርህን በመጠርቀም ሣይሆን “የትኛው ቋንቋ በየትኞቹ ማሕበረሰቦች ዘንድ በስፋት ይነገራል?” የሚል ጥናት በመመርኮዝ ነው፡፡

ዐማርኛን ለመግደል ብለው ወያኔ ትግሬዎች ብዙ ሠሩ፤ በሥልጣን ቆይታቸው  የዐማርኛን ጥቅም በሂደት ሲረዱ ግን ዐማሮችን የማጥፋት ዋና ተልእኳቸውን ለአፍታም ሳይዘነጉ ቋንቋውን ነጥለው ለልጆቻቸውና ለካድሬዎቻቸው በደንብ ማስተማሩን ተያያዙት፡፡ እነሱ አካሄዳቸውን ሲለውጡ ሌላው የነሱን የቀደመ ፈለግ ተከትሎ ዐማርኛን ሲጠየፍና ሲያንቋሽሽ ቆይቶ በመጨረሻው ሲያጤነው አዲስ አበባ የገቡት ልጆቹ የዘበኝነትና የጽዳት ሥራ ለመያዝ እንኳን መቸገራቸውን ተገነዘበ፤ በዲግሪ ተመርቀውም አዲስ አበባ ሲመጡ ወይ እንግሊዝኛ አልቻሉ ወይ ዐማርኛ አልቻሉ ከሁለት ያጣ ጎመን እየሆኑ መቸገራቸውን ሲገነዘቡ በወያኔ የመበለጥ ሞኝነታቸውን በማሰብ አምርረው አዘኑ፡፡ ይህ ነው እንግዲህ አንዱ የወል ቋንቋ ዕንቆቅልሽ – ቋንቋውንና ተናጋሪዎቹን የመጥላትና የመውደድ ጉዳይ አይደለም ወንድሜ፡፡ ስለዚህ በምናውቀው ልሣን ሁሉ እንግባባ እንጂ የኩራት ድንበር አናብጅ፤ አንተ በዐማርኛ ላይ አፍንጫህን ብትነፋ ዐማርኛ አይጎዳም፤ አንቺ በትግርኛ ወይም በኦሮምኛ ላይ ፊትሽን ብታዞሪ እነሱ ግዑዛን ናቸውና አይጎዱም፡፡ ቋንቋ የትም ብትሄድ ወስፋትህን የምትሸነግልበት የእስትንፋስህ መሠረት የሆነ የመግባቢያ መሣሪያ እንጂ ጠላትህ ሊሆን አይችልም፡፡ ያን ቋንቋ በአፍ መፍቻነት ማንም ይናገረው ማን ላንተ ያለው ጠቀሜታ ግን ከምንም በላይ ነው፡፡ ዓለም ወደ አንድ መንደርነት እየተለወጠችና አንድነቷን እያጠናከረች በምትገኝበት የግሎባላይዜሽን ዘመን በራስህ ጠባብ ዓለም ውስጥ በምትፈጥረው ምክንያት የተነሣ ለዚህና ለዚያ ቋንቋ ያለህ አተያይ ቢንሻፈፍ ተጎጂው አንተው ብቻ ነህ፤ ኩራት እራት መሆኑ ቀርቷል ወዳጄ ልቤ – (እንደቃና ቲቪ ‹ወዳጄ ታየር› ልበልህ ይሆን?)፡፡ በወያኔ የቋንቋ ፌዴሬሽን ሳቢያ ስንቶች እንደተጎዱ እኔ ነኝ የማውቀው – መምህር ነበርኩና፡፡

ስለዚህ ግዴላችሁም ሌላ የምንተካው እስክናገኝ ድረስ ለጊዜው በዚሁ ቋንቋ – ባማርኛ –  እንጠቀም፡፡ በማይጨበጥ ምክንያት በጠላቶቻችን ተገፋፍተን ልንሰባብረው የሞከርነውን ማኅበረሰብኣዊ ድልድይ በአፋጣኝ እንጠግን፡፡ አለበለዚያ እየሞትን ነው፤ እግዜር አይበለውና በጠላቶቻችን ምክርና ሰይጣናዊ አስተምህሮ ከቀጠልን የሁላችንም ወረደ መቃብር በአጭር ጊዜ ውስጥ ይፈጸማል፡፡ የመከፋፈላችን ብሥራት ለጠላቶቻችን የደስታ ምንጭ ነው፡፡

“አገባሻለሁ ያለ ሁሉ ላያገባሽ ከባልሽ ጋር ሆድ አትባባሽ” የሚለውን የዐማርኛ ብሂልና “ይበጃል ቢሉን አህያ አረድን፤ አይበጅም ቢሉን ጠራርገን ጣልን፤ ‹(የአህያው ሥጋ) ይበጃችሁ ነበር እኮ› ቢሉንና ሄደን ብንፈልገው አጣነው” የሚለውን የኦሮምኛ ብሂል እንድታጣጥሟቸው በመጋበዝ ልለያችሁ፡፡ ለሁላችን መልካም ክራሞት፤ ለሀገራችንም ሰላምንና በአዲስ ሕዝባዊ ኢትዮጵያዊ መንግሥት ሥር መረጋጋትን ተመኘሁ፡፡

1451

ኢትዮጲያውያን ሆይ፤ ዝምታ እንደ ክህደት የሚቆጠርብት ጊዜ ላይ ነን! –ሙሉቀን ገብያው

$
0
0

6359214439124871891168943538_silenceአገራችን  ኢትዮጵያ   መስቀለኛ  መንግድ  ላይ ናት። በህዝባችን ላይ የደረሰው  የግፍ በደል  ጽዋ ሞልቶ እየፈሰሰ ነው። እንዲህም  ሆኖ ገዥው  ህወሐት ግድያውን፣ እስራቱን፣ ግርፋቱን፣ ቃጠሎውን በኢትዮጲያውያን ላይ ከመ ቼውም  በበለጠ  እጥፈ ድርብ አድርጎ ቀጥሎበታል። አዲሱ ትውልድ «በቃ አይሆንም» ብሎታል። መመለሻ ከሌለው  ስፍራ ደርሷል።

ለ 25 አመት የዘለቀው  የእስር ወጥመድ  መሰበሪያው  ደርሷል። በኢትዮጵያውያን ላይ ዘርግቶት ያለው  ፍርሃት፣ መከፋፈል፣ የእርስ በርስ ጥርጣሬ  ጥቁር ደመና እየለቀቀ ነው። የነጻነት ሽታ አየር ላይ  ነው። ነጻነትና እኩልነት ያለባት የተስፋ አገር እየቀረበችን ነው።  ኢትዮጵያውያን ሁሉ ተባብርን  ለፍጻሜው መትጋት አለብን።

ፋሽስቱ ህወሐት በብዝህዋን መገናኛ  ለሚለቅው  አታላይ ፕሮፓጋንዳ  ጆሮ  አንሰጥም ብለናል፡፡ በገዳይ  ማሽን ሰራዊቱ በሺዎቹ  ቁጠር ቢጨፈጭፈንም፤ እኛ  ግን ባዶ እጃችንን ሆነን፣ ደረታችንን ሰጥተን ያለ ፍርሃት በሰላማዊ መንግድ እንቃወመዋለን።  ወደ ኋላ አንሸሽም።  ገዳዩ ህወሐት ከጸሃይ  በታች  ያለ ነገር  ሁሉ አደርጋለው  ብሎ  እሸነግላለው  ቢልም  ያ ግዜ አልፎበታል።

ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር በአንድ ወቅት ‘ዝምታ ክህደት የሆነበት ግዜ ደርሷል’ ብሎ ነበር።

ወገኖቼ ኢትዮጵያውያን፤  ዝምታ ክህደት የሆነበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።

  • በሺዎቹ የሚቆጠሩ ወንድምና እሆች በየእለቱ  ሲረግፉ ፥ዝምታ ፤
  • በእስር ላይ ያኖራቸውን ወገኖቻችንን በህይወታችው  በእስር ግንብ  ከልሎ በጥይት ደብድቦ  አፈኖ ሲያቃጥል ፥ዝምታ፤
  • እናት አምጣ ወልዳ ያሳደገችውን፤ ደረሰልኝ ያለቸውን ልጇን ገደለው እላዩ ላይ ተቀመጭ  ብለው ሲደበድቧት ፥ዝምታ፤
  • በብዙ ሺዎቹ የሚሆኑ  ወጣቶችን አሰሮ ወደ ማጎርያ ካንፕ ወሰዶ ሲያሰቃይ ፥ዝምታ፤
  • የእሬቻን በአል ለማክበር ቢሾፍቱ የወጡ  ሰላማዊ  ወገኖችን በብዙ መቶዎች ሲገድል፥ዝምታ።   

ወገኖቼ፡ ህሊናችን፣ ሰው መሆናችን፣ የሞራል ልእልናችን፣ ኢትዮጵያዊነታችን የሚፈተንበት፤ በተለይም በአሁን ሰአት የዝምታን ግንብ የምናፈርስበት ጊዜ ላይ ነን።

ኢትዮጵያውያን ሆይ፤  ዝምታ እንደ ክህደት የሚቆጠርበት ጊዜ  ላይ  ነን፡፡

 

 

 

የኦሮሞና ኣማራ ህዝቦች ሆይ! ለወያኔ ከፋፋይ ፕሮፓጋንዳ ቀስት የኣዞ ቆዳ ይኑራችሁ! – ቦሩ በራቃ

$
0
0

 

Oromo amhara unityበርግጥ የጸረ ወያኔ ትግሉ ወደ ወሳኝ ምእራፍ ተሻግሯል። ወያኔም ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ ውስጥ ናት። በተለይም የኦሮሞና የኣማራ ህዝብ ትግል ትከሻ ለትከሻ ተደጋግፎ መፋፋም ስርኣቱን ተስፋ እንዳስቆረጠው በገሃድ እየታየ ነው። ድሮም ቢሆን ወያኔን ይህን ሁሉ እድሜ መርቆ የሰጠው የኦሮሞውና የኣማራው ልህቃን ኣለመተባበርና ኣልፎ ኣልፎም ወያኔውን ወደ ጎን በመተው እርስ በራሳቸው ላይ የማነጣጠር ችግር ነበር። ኣሁን ግን ያ ኣስነዋሪ ጊዜ እየተሻሻለ ይገኛል። ይሁንና የሁለቱም ወገን ጽንፈኞች ዛሬም ላለፉት 25 ኣመታት ለወያኔ እድሜ ማራዘሚያነት በገፀበረከትነት ያገለገለውን የከፋፋይነት ፕሮፓጋንዳ መቀጠላቸው ባይታበልም ኣብዛኛው ኣገር ቤት የሚገኘውና በትግሉ ሜዳ የተሰለፈው ህዝባችን ግን ከዚህ ኣባዜ ነጻ መሆኑን ኣረጋግጧል። ዳያስፖራው ወገናችንም ቢሆን በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ሁለት እንደ ባላንጣ የሚታዩትን ባንዲራዎች ጎን ለጎን ኣሰልፎ እጅ ለእጅ ኣየተያያዘ ወያኔ ላይ መነሳቱን በገሃድ ኣስመስክሯል።

የኦሮሞ ህዝብ ተጋድሎ ለወራት ከዘለቀ በሁዋላ የኣማራው ተጋድሎ ከጎንደር በተቀሰቀሰ ማግስት የታደሰው የሁለቱ ህዝቦች የትግል ትብብርና ኣጋርነት እንደ ድንገተኛ ካንሰር የወያኔን ኣከርካሪ ኣያደቀቀው ነው። በተለይም ባሁኑ ሰኣት ደግሞ ኦሮምያ ውስጥ በሚገኙ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ የኦሮሞና የኣማራ ብሄር ተወላጆች የትግል ኣጋርነት ቃለ መሃላ ፈፅመው በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ኣንድ ኣይነት መፈክር በወያኔ ላይ እያስተጋቡ ይገኛሉ። ወያኔ ይህ ይሆናል ብሎ ያሰበም ኣይመስልምና በጣም ተደናግጧል። ከድንጋጤውም የተነሳ ህይወት ኣድን ብሎ ያመነበትን ኣንድ ኣስቂኝ ፕሮፓጋንዳ በጥድፊያ ይዞ ብቅ ብሏል። የኦሮሞን ህዝብ ትግል ከግብፅ መንግስት ጋር ኣቆራኝቶ ማቅረብ።

ይህም ‘ኦነግ ማንነታቸው ካልታወቀ የግብጽ የፖለቲካ ሃይሎች ጋር ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲዶልት የሚያሳይ ኣዲስ ቪድዮ ኣገኘሁ’ እያለ መለፈፍ ነው። ባሁኑ ወቅት ኦሮምያ ውስጥ ከተቀጣጠለው ህዝባዊ ኣብዮት በስተጀርባ የግብፅ እጅ ኣለበት ሲል በድመት ምላሱ ምሏል ወያኔ። ለመሆኑ የተባለው ቪድዮ የምንድነው? ቪድዮውስ የመቼ ነው? ኣንድ በወቅቱ እዚያው ካይሮ በስፍራው ታድሞ የነበረ የቅርብ ወዳጄ ቪዲዮውን ወያኔ ሚድያ ላይ ከተመለከተ በሁዋላ ኣንዳጫወተኝ የወያኔ ውሸት ኣስቂኝ ነው። ነገሩ እንዲህ ነው። የተባለው ቪዲዮ በሚያዝያ ወር 2014 የተቀረጸ ነው። ግብጽ ኣገር ካይሮ ከተማ የሚኖሩ የኦሮሞ ስደተኞች በመላው የኦሮሞ ተወላጆች በያመቱ ሚያዝያ ወር ተከብሮ የሚውለውን የኦሮሞ ሰማእታት ቀን ለማክበር ኣንዲት ኣነስተኛ ኣዳራሽ ውስጥ ተሰባስበዋል። በኣሉን ያዘጋጁት የኦሮሞ ኮሚኒቲ ኣመራሮች በኣካል የሚያውቁዋቸውን ኣንዳንድ የሰብኣዊ መብት ተከራካሪ የግብጽ ተወላጆችን ዝግጅቱ ላይ ጋብዘው ነበረ። ግብጻውያኑ እንግዶች በበኣሉ ስነ ስርእት ተደምመው ንግግር ለማድረግ ጠየቁ መሰለኝ ተፈቀደላቸውና ወደ መድረኩ ወጡ። የትም ኣገር ኣንድ እንግዳ ለህዝባችን ያለውን ወገንተኝነት ሲያሳይ እንደሚደረገው ሁሉ የመድረኩ መሪዎችም ግብጻውያኑን ተጋባዦች የኦሮሞ ህዝብ የትግል ኣርማ የሆነውን የኦነግ ባንዲራ ኣለበሷቸው።

በተጋባዦቹ ግብጻውያን ለኦሮሞ ህዝብ ፍትሃዊ ትግል ያላቸውን መልካም ምኞት ለመግለጽ መድረኩ ላይ ቆመው ተናገሩ። ትግላችሁ ሰምሮ ነጻነታችሁን በቅርብ ጊዜ እንደምትጎናጸፉ ምኞታችን ነው ኣሉ። ታዳሚውም ኣጨበጨበላቸው። እንግዶቹ እንኩዋንስ የግብጽን መንግስት ሊወክሉ ይቅርን በኣገሪቷ መንግስትም ብዙ ጊዜ ጫና የሚደርስባቸው ኣይነት ናቸው። የግብፅን መንግስት ኣቅዋም ሳይሆን የራሳቸውን ምኞት ነበር የተናገሩት። ጋባዦቻቸውም የኦነግ ኣመራር ኣባላት ሳይሆኑ በኣካል የማቃቸው ተራ ስደተኞች ናቸው። በቃ የሆነው ይሄው ነው። ወያኔ ታድያ 2 ኣመት ከ6 ወር በፊት የሆነውን ነገር በዚህ ጊዜ መምዘዙና በጥብቅ የተያዘ ኣዲስ ምስጢር ፈልፍሎ ያገኘ በማስመስል የሚነዛው ያለምክንያት ኣይደለም። ለጉዳዩ ቁብ ሰጥቶት ቢሆን ኖሮ ቪዲዮው ተቀርጾ በማግስቱ ሊያገኘው እንደሚችል እርግጠኛ ነኝ ይላል ይህ ወዳጄ። በኣምባሳደርነት ያስቀመጠው የመሃመድ ድሪር ጆሮ ጠቢዎች በስደተኝነት ተመስለው ኦሮሞ ኮሚኒቲ መሃል ተሰግስገው ኣሉና ቪዲዮውን በጥቂት ሰኣታት ውስጥ እንደሚያደርሱለት የሚያጠያይቅ ኣይደለም በማለትም ያክላል። ወያኔዎቹ ግን ቪድዮውን በጥሩ ዋጋ ለመሸጥ ኣስበው 2 ኣመት ከ6 ወር ሙሉ ያቆዩት ለዚህ ኣይነት የጭንቅ ጊዜ መሆኑ ነው።

ወያኔም ሆነ ሁላችንም የምናውቀው ኣንድ እውነት ኣለ። ስርእቱን እየነቀነቀ ያለው ትግል ኣገር ቤት ነው። ታጋዩም ኣታጋዩም የኣገር ቤቱ ህዝባችን ነው። ማንኛውም የፖለቲካ መሪ ድርጅት ባሁኑ ሰኣት እንደ ሰደድ እሳት ኢትዮጵያ ውስጥ እየተንቀለቀለ ያለውን ትግል በግንባር ቀደምትነት እየመራሁ ነው ብሎ ማንንም ማሞኘት ኣይችልም። ህዝቡ በራሱ ለራሱ ኣመራር በመስጠት እየታገለ ነው። የማንኛውም የቅርብም ሆነ የሩቅ ባእድ ኣገር እርዳታም ኣልጠየቀም ኣላስፈገውምም። ኦሮምያም ሆነ ኣማራ ክልል ያለው እውነታ ይህ ነው። ወያኔም ይህንን ኣሳምሮ ያውቃል። ነገር ግን ለህዝቡ ትግል ክብር በመንፈግ ሩቅ ካሉት የፖለቲካ ኣካላት ጋር ማስተሳሰር የ25 ኣመት ልማዱ ነው። የኣምባገነኖች ባህሪይ ተመሳሳይ ነውና ህዝብ ሲያምጽባቸው ጣታቸውን ሆን ብለው ሌላ የውጭ ኣካል ላይ ይቀስራሉ። ወያኔም ባለፉት 25 ኣመታት ህዝብ ባመጸበት ቁጥር ያለማቁዋረጥ ለዚህ ኣላማ ሲጠቀምባት የኖረው ኤርትራ ነበረች። የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ ጉዳይ ምንም ጣልቃ ሳይገባ በኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ ውስጥ ግን ስሙ በግንባር ቀደምትነት ይነሳል። ወያኔ የህዝቡን የትግል ገድል ከህዝቡ ቀምቶ ኣስመራ ድረስ ልኮለት ሽእብያን ዝነኛ የኢትዮጵያ ተቃዎሞ ፖለቲካ ጎራ መሪ ኣድርጎት 25 ኣመታት ሙሉ ሹሞታል።

ይህን ያደረገው ለሁለት ምክንያቶች ነው ብዬ ኣስባለሁ። የመጀመሪያው ለህዝቡ ያለውን ኣስነዋሪ ንቀት ለማሳየት ነው። ኣቻዬ የሆነው የኤርትራ መንግስት ካልሆነ በስተቀር እኔን ስልጣኔ ላይ ሊፈታተነኝ የሚችል ሃይል ኣገር ውስጥ የለም እንደ ማለት ነው። ሁለተኛው ደግሞ ኣገር ውስጥ ህዝባዊ ተቃውሞ ሲነሳበት ኣገሬንና የኣፍሪቃን ቀንድ ቀጣና የምታተራምሰው ኤርትራ ናትና ኣንድ በሉልኝ ብሎ ለደጋፊዎቹ የውጭ መንግስታት ለማላዘን ነው። ታድያ ኣሁን ደግሞ ኣይኑን ወደ ግብጽ ጣል ያደረገበት ምክንያት ምን ይሆን ብሎ ለሚጠይቅ መልሱ ኣጭር ነው።

እንደሚታወቀው ግብፅ የኣባይን ጉዳይ ጨምሮ በኣንዳንድ ምክንያቶች የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ተደርጋ ሲወርድ ሲዋረድ በመጡ መንግስታት ስትፈረጅ ኖራለች። በተለይም የኣማራ ልህቃን በዚህ ይስማማሉ ብሎ ያምናል ወያኔ። ከግብፅ ጋር የሚደረግ ማንኛውም ኣይነት ስምምነት ጸረ-ኢትዮጵያዊ ውል ነው ተብሎ ይታመናል። ግብጽን በተመለከተ ኣማራው የከረረ ኣቅዋም ሲኖረው ኦሮሞው ደግሞ የተለሳለሰና ምናልባትም ከኣማራው የተቃረነ ኣመለካከት ይኖራቸዋል ብሎም ራሱን ኣሳምኗል። እናም ኦሮሞና ኣማራን እርስ በርሳቸው እንዲጠራጠሩና ብሎም ስርእቱን ችላ ብለው ወደተለመደው የልዩነት ጎዳናቸው ተመልሰው እንዲፋጠጡ የሚያስችል ብሎ የገመተው የቀረችው ብቸኛ ካርድ ይቺ የግብፅ ጉዳይ ናት። ግን ካርዷ ገና ከመመዘዟ እዛው ወያኔ ኪስ ውስት ኣርጅታ በልዛ ከኣገልግሎት ውጭ ሆናበታለች።

እኛ ህዝቦች ምንጊዜም ወያኔን ቀድመን መገኘት ኣለብን። ወያኔ ለምሳ ሲያስበን እኛ ኣስቀድመን ቁርሳችን ልናደርገው ይገባናል። በወያኔ ከፋፋይ ፕሮፓጋንዳ የሚታለል ካለ እየፈሰሰ ያለው የቆራጡ የህዝባችን ደም የማያንገበግበው ራስ ወዳድ ከሃዲ መሆን ኣለበት። ኦሮሞውና ኣማራው ሲተባበር ወያኔን መጣል የወራት ወይም የኣመታት ሳይሆን የቀናት ብቻ ጉዳይ ነው። ይህን እስትንፋሱን የሚያቆምበት ድል ለማሰናከል ደግሞ ህወሃት ተኝቶ ኣያድርም። እኛ ተዳክመን ከተመቻቸንለት ገና ከዚህ በላይ ብዙ ተልካሻ ሴራዎችን በመሃላችን ኣንደሚሸርብ ከወዲሁ ተገንዝበን መጠንቀቅ ኣለብን። ለወያኔ ከፋፋይ የፕሮፓጋንዳ ቀስት የኣዞ ቆዳ ሊኖረን ይገባል።

 

መጥኖ ያለመጉረስ ማጅራት ያስመታል –ፈቃዱ ቢረጋ

$
0
0

1。ባለፈው ሰሞን አቶ ያሪድ ጥበቡ መነሻቸውን አይጋ ፎረም ላይ የቀረበ ጽሁፍን መሰረት አድርገው  የሰጡት አስተያየትና ምክር፤ በየ ብዙሃን መገናኛው ስለተናኘና በESATም ቃለ መጠይቅም ስለተደረገበት፤  የሰሞን ጫጫታ ባይሆን ተመኘሁና እንድንነጋገርበት ያየሁበት አተያይ።
2。11 ወር ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ህዝብ ህዝባዌ እንቅስቃሴን ከ66ቱ የኢትዮጵያ አብዮት ጋር ተመሳሳይነቱ እየተነገረ ስለሆነና በአብዮት ፍንዳታ ዋዜማ ላይ እንደሆንን ምኞትና ስጋት ስላለ ከሆነስ ምን ይፈጠራል? ባይሆንስ ምን ይሆናል?
3。የሽግግር መንግስት ይቋቋም ኢህአዴግ ይወገድ፤ ብሔራዊ እርቅ ይደረግ፤ ባላደራ መንግስት ይቋቋም…….ወዘተ፤ የተቀዋሚ ድርጅቶች ቋሚ መፈክር ነው። ምን ማለትስ ነው? እንዲትስ ተፈጻሚ ይሆናል?
4。ለ25 አመት የተገፋባቸው ሁለት ጽንፎች፤ ጭፍን ደጋፊና ጭፍን ጥላቻ ከመሰርታዊ ሃገራዊ ጉዳያችን እያስውጡን ይሆን? መንጠልጠያቸው የሆነው የ97ቱ ምርጫ እውነተኛ ገጽታው ምን ይመስላል?
5。ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶችና መንግስታት፤የመንግስታቱ ማህበርም በሃገራችን ጉዳይ በተለየ ሁኔታ ተሰባስበው መንግስትን እየከሰሱ ነው። እነዚህ ስብስቦች ካንጀታቸው አስበውልን እንደሆነ የሚያሳይ ዓለም አቀፋዊ እውነት አለ ወይ?
ከላይ የተነሱትን ስጋቶቼን እየከፋፈልኩ ነካ ነካ ስለማደርጋቸው በስፋት ይታይ ዘንድ እጠይቃልሁ።


የአቶ ያሬድ ምክሮች

yared
መንሻ ሃስቡ በአይጋ ፎረምና በተመሳሳይ ከመንግስት ጋር ቀረቤታ ያላቸው በተለይ ለአንድ ብሄራዊ ድርጅት ጥብቅና የቆሙ  የብዙሃን መገናኛዎች፤ በሌሎች ክልሎቹ ችግር ሲነሳ በየክልሉ መንግስት ላይ ጣታቸውን መቀሰር ብቻ ሳይሆን ግለ ሰቦችን መወንጀል፤ ሃገርዊ ችግር ሲገጥምም የተለመደው አሸባሪ የውጭ ሃይሎች በሚሉት ክሳቸው ጠባብ ቅርቃር ውስጥ ገብተው ከዚያ መውጣት አለመፈለግ ወይም ያለመቻላቸው ማሳያ ነው።
 መንግስትን እንደ መነግስት ኢህአዴግን እንደ ገዢ ፓርቲ ተጠያቄ የማድረግ አቅማቸውን ማሳደግ አልቻሉም። በሌላው ተቃዋሚም ሆነ ቅር በተሰኙ ህዝቦች፤   መንግስቱ በአንድ ብሔር የበላይነት የተያዘ እንደሆነ የሚከሰሱበትን፤  አዎ መንግስቱ የኛ ነው የማለት ያህል በገጣባው ወይም  ሳያውቁት የተቀበሉት እውነት ይመስላል።
 ይህን አስመልክቶ፣በጥቅሉ መንግስት፤ በተናጠልም ኢምባሲዎች፤ ጠቅላይ ሚኔስቲር፤ ሊሎችም የሚኒስቲር መስርያ ቤቶች፤   የተቃዋሚ፣ የደጋፈ፤ የአሸባሪ፣ የተሸባሪ……….ወዘተ የሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች መገልገያ ተቋሞች ናቸው።
 ይህን አረዳድ ከጠቅላይ ሚኒስቲሩ ጀምሮ እስከ ቀበሌ ካድሪ ድረስ የተደባላለቀባቸው እንደሆነ በርክታ አብነቶችን ማንሳት ይቻላል። ጠቅላይ ሚኒስተራችን በተደጋጋሚ እኛ ኢህአዴጎች ብለው ሲናገሩ ምን ነካቸው ህገ መንግስቱን ለማስጠበቅ የተሾሙ መሆናቸውን ዘነጉት ወይ ማለታችን ስላቅ ሳይሆን የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን መግለጣችን ነው። 
ይህ ማለት የአቶ ያሬድን ምክር ቅቡል ያደርገዋል ማለት አይሆንም፡
አቶ ያሬድም ከሌላኛው ጽንፍ ቆመው በህዝቦች መካከል ሊያጢሱ የሚፈልጉት ጢስ አይሸተንም አይቆጠቁጠንም ማለት አይደለም።
 ከዮሃንስ ቤተመንግስት በአማራው ክልል መንግስት መስተዳደሮች ላይ የተሳለላቸውን ካራ እንዲገነዘቡት ማሳሰብ በሚል፤ ከግለሰብ ጽሁፍ ተነስቶ ይህን የመሰለ በህዝቦች መካከል ችግር ፈጣሬ ሃሳብ ማቅረቡ እውነት ለሃገር ታስቦ ነው ወይሰ ባልበላውም ጭሬ ልበትነው ነው?
እስኪ በተራ ቁጥር ተዘርዝረው የተሰጡ  ምክሮች እንያቸው
ምክር  1. የአጋዚያንና የፊደራል ፖሊስን ከክልሉ ማባረርና  በሚዲያ ማሳወቅ(ይላል)። ይህ ምክር ፊደራል መንግስቱ ይፍረስ ህገመንግስቱም ይሻር ማለት እንድሆነ ለክልሉ መስተዳደር የሚጠፋው አይመስለኝም፤ የህልውናው ጉዳይ ስለሆነም አይ ዲያስፖራ ብለው መሳለቃቸው  አይቀርም። በሚዴያ ይለቀቅ ማለቷ የጎረቤትህ ቤት ሲቃጠል ለኔ ብለህ ተጠንቀቅ ሆነና ሃገራችን እንደሊብያ እንደ ሲርያ የሚድያው አብዮት ሰላባ እንዳትሆን ምን ታስቦልን ይሆን? በማለት ሰጋን እንጂ፤መጠርጠራችን ያለና የሚኖር ነው። 
ምክር 2. የመከላከያ ሰራዊቱ ዳር ድንበር በማስጠበቅ ይወሰን(ይላል)። የየትኛው ሃገር ተመክሮ እንደሆነ ባይታወቅም፤ መከላከያ ጠረፍ ጠባቂ ብቻ ሳይሆን ሃገር ጠባቄም ነው። ይህ ማለትም ህገ መንግስቱን መንግስቱንና ህዝቡን መጠበቅና መከላከል ማለት ነው። ምናልባት በወንድሜ ምልከታ ሃገር ማለት የመሪት ቆዳ ስፋትና ጥበት ክሆነ እንደልዩነት አስምሮ ማለፍ ይቻላል።
ምክር 3. በበአዴን ውስጥ ተሰግሰገው የሚገኙ የህወሃት ደጋፊዎችን ማባረር(ይላል)። ይህኛው ደግሞ የሰዎችን ሰባዊ መበት የሚጥስ የመደገፍ የመቃወም መብትን የሚጣረስ እንደሆነ ልብ የተባለ አይመስልም። ካልሆነም በተመካሪዎቹ ላይ ያሎትን ንቀት ማሳያና አተራማሽ እንደሆነም ሊሰመርበት ይገባል። 
ምክር 4. ኢህአዴግ ብሒራዌ ተዋጾ እንዲኖረው ማድረግ(ይላል)። አቶ ያሬድ ብሄራዌ መገለጫቸው የአራዳው ልጅነት እንድሆነ ሲነግሩን ከርመው፤ በብሄር መደራጀት ሃገራዊ አደጋ እንደሆነ የሚሰብኩት ወንድሜ በምን ሚዛን ይሆን ይህን ለውጥ ያደረጉት? ይመስለኛል በሆነ ብሔርዌ ድርጅት ላይ ያላቸውን ጥላቻ ማሳያ ይሆናል ብሎ መገመት የሚያስነውር አይመስልኝም።
ምክር 5. ከአማራው ክልል  የተወሰዱ መሬቶችን ማስመለስ(ይላል)። ክልል የሚለው አገላለጽ በስህተተ የተጠቀሰ እንጂ የመካሪው ቋንቋ ሊሆን አችልም። መሬት ማስመለስ የሚለው አባባል እንዲት እንደሚመለስ ባያሳውቁንም የተውሰደ መሬት ካለ የመሬቱ ባለቤት ህዝቡ ስለሆነ ህዝባዊ ምላሽ ያስፈልገዋል እንጂ፤ ለአጎበር የወጣ ጠብመንጃና በፊስቡክ ቱታ የሚሆን ነገር የሚኖር አይመስለኝም። ይህን ካአቶ ያሬድ ይሰሙታል እንጂ አይነግሩም።
ምክር 6,7,8. በአንድ የግንባሩ አባል ብሄርራዊ ድርጅት ላይ የተሰነዘሩ የጥቃት መልክቶች ስለሆኑ፤ አይሆንም እንጂ እልቂትና መጠፋፋትን ጋባዝ  በመሆኑ፤ ሚሪላንድ ተቀምጦ በማን ልጅ ህይውትና መከራ ላይ ነው  አንገት መስበቅና መውረግረጉ?
ምክር 9。 በቦዘኔዎች በሰርጎ ገቦች፣ በትግራይ ተወላጆች ላይ እርምጃ እንዳይወሰዱ ጠንቅቆ መጠበቅ(ይላል)።   ለማያነበው የፊስቡክ ታዳሚ ተሰውራ የቀረበች ማላሻ እንጂ እንዴት ነው ከላይ ከደገሱለት፤ ማባረር፣ ማስወገድ ሊታደጉት የሚችሉት?። ምክሩ በአይነ ስጋ ያገኘን ብሎ ተጠናቀቀ። አሜን ብያለሁ።
፪. የአብዮት ዋዜ
የውዳጂን  ምክሮቹን መነሻ በማድረግ ከኢሳት ጋርና በእንቁ መጽሔት አብዮትን አስመልክቶ የተደርጉት ቃለ ምልልሶች  የአብዮት መጣ አዋጅ ስላለበቻው፤ ለራሳችን የአፍ ጉቦ እየሰጠን ከትግሉ መዝናጋታችን ፪፭ ዓመት ያስቆጥረ ችግራችን በመሆኑ አንድያችንን እንዳያዘናጋን  ስለፈራሁ ልናየው ፈለኩ ።
አቶ ያሬድ፣ በኢትዮጵያ የ66 አብዮት ሲፈነዳ ማንም ክሳምንት በፊትም ሆነ በኋላ እንደሚሆን የገመተ ውጫዊም ሆነ ውስጣዊ ሃይል አልነበረም። በባለቤተነት የመራው ደርጅትም ሃይልም አልነበረም። ሀገሬቱን እንደ  ሰደድ እሳት አቀጣጠላት፣ የስርአቱ ፍጻሚም ሆነ። ካሉ በኋላ አሁን የተቀሰቀስው ህዝባዊ እንቅሳቃሴ አምሳያው ነው ይሉናል።
ምናልባት ደጋግመው እንዳነሱት የጅማው አይነት ህዝባዊ አስተዳደር በየስፍራው እየተቋቋመ ሃገርዊ መንግስት የማቋቋም መፍትሄ ሃሳባቸው ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለኝ። በተረፈ በሃገሪቱ ብቃት ያለው የፖለቲካ ድርጅት እንደሌለ እንደ ወትⶂአቸው በድፍረት ተናግረዋል። ይሁን እንጂ አሁን ሃገሪቱ የተሰራችበት ፊደራላዊ አወቃቀር ለጅማው አይነት ምኞች አመቺ አይሆንምና ሌላ መፍትሄ ሃሳብ የሚጠይቀን ይሆናል።
እኔ እንደሚመስለኝ የረዥም ጊዜ ታሪክ ኖረህ አልኖረሀ ለአብዮት መፈጠር ምክንያት አይሆንም። ለአብዮት መከስት ዋንኛ ምክንያት በየሀገራቱ ያሉ  ቅራኔውች ምን ያህል እንደተቡና ለመመለስ የማይችሉበት ደረጃ ሲደርሱ፣ የስርአቱ የጀርባ አጥንቶች አብሮ መኖር ይሳናቸውል፤ አብረው መኖር ካልቻሉ ይጠፋፋሉ። ታሪክ እንደሚያሳየን ህዝቡ አቸናፊ ሆኖ ገዢው ተሽናፊ ይሆናል። በጥገና በሃይል የሚቀለበስበትም ሁኒታ እንደሚኖር ተሰምሮበት ይታለፍና፡ በየትኛውም ስፍራ እንድሚሆነው የሂደትም ህግ ስለሆነ ኢትዮጵያም በአብዮታዊ ሂደት ውስጥ እንዳለች ተቃውሚም ሆነ ደጋፊ መሆን ሳያሻ ህግ ስለሆነ ብቻ መስማማት ይቻላል።
ይህን መሰረት አድርገን አቶ ያሪድና የኢሳቱ ቃለ መጠይቅ አቅራቢ የተስማሙበት፤ የአሆኑ የህዝብ መነሳሳትና የ66ቱ አብዮት አንድና ተመሳሳይ ናቸው ስለሚሉ ምን ያህል እውነት እንደሆነ እንየው።
ሀ. በጥቅሉ የአሁኑ ህዝባዊ መነሳሳትም ሆነ የ66ቱ አብዮት አንድ የሚሆኑት ችግሮቹ እንደተነሱ መልስ ማግኘት ባለመቻላቸው እየጠጠሩ እያበጡ የመገንፈል ባህሪያቸው ፍጽም አንድ ያደርጋቸዋል።
ለ. የ66ቱ አብዮት ሃግራዊና ህዝባዊ ሲሆን፤ ይህኛው በተውሰኑ ክልሎች በወጣቱ የሚገፋ መሆኑ የተነሱ ጥያቄዎች ከህዝቡ የእለት ተእለት ህይወት ጋር ተያያዥነት ስለሌላቸው፣ በሆነ ቡድን ስብስብ ፍላጎትና አላማ ላይ የተማከለ ከመምሰል በተጨማሬ መንግስትን እንደመንግስት በማውገዝ ፈንታ የመንግስቱን አካል የሆነን አንድን ድርጅት ማውገዙ መሰረቱን ጥላቻ ስለሚያደርገው ህዝባዊ አይሆንም ማለት ነው;።
ሐ. በ66ቱ አብዮት  የነበረ መንግስትና ይህ መንግስት በስም መንግስት ከመባል ውጭ አንድ የሚያደርጋቸው አንዳችም ነገር የለም። የቀድሞው መንግስት ከዓለምም ከዝቡም ተነጥሎ ለመገፋት ቀኑን የሚጠብቅ መንግስት እንጂ አንዳችም ነገር መክቶ መቆም የማይችል በቁሙ የሞተ ነበር።
ይህኛው መንጋስት ሰፊ ህብረተ ሰባዊ መስረት ያለውና እራሱን አስተካክሎ ህዝባዊ ችግሮችን የመፍታት ህዝባዊ ያልሆኑ እንቅስቃሲሆችን የማስቆም ሃይልና ጥንካሬ አለው። ስልሆነም በውስጡ ችግር ቢፈጠር እንኳን ለህገ መንግስቱና ለሃግሬቱ ተገዢ የሆነው ወታደር የማረጋጋትና ስርአቱ እንዲቀጥል የማድረግ አቅምና ችሎታ አለው። ይህ ሰራዊት የተማረና እንክብካቢ የሚደረገለት ስለሆነ ምን ለማግኘት ነው በዚህ ስርአት ላይ ሊነሳ የሚችለው። ወይስ የፊደራላዊው መንግስት አወቃቀር ሰባዊ ክቡንና ማንነቱን ስለማያስከብርለት? ገና ያላጣጣማቸው በጅምር ላይ ያሉ ስኪቶችን ከዚህ መንግስት ይጠብቃል እንጂ ምንነቱ ባልታወቀ ስልፍና ግርግር ተደልሎ በመሰረተው ስርአት ላይ ጠብመንጃ ለማዞር የፊስ ቡክ አርበኞችና የአውሮፓና የአሚሪካ የአደባብይ ትምክተኞችና ቁማር የተበሉ ጠባቦች ጩህትን ሊያደምጥ የሚያስችለው አንዳችም ነገር የለም። በገጠርም ሆነ በከተማ የሚገኘው ህዝብ በስርአቱ ላይ ቅሪታ አለው እንዲመለስለት ይፈልጋል፤ መልሱን ግን ማግኘት የሚችለው ከማን እንድሆነ ጠንቅቆ ያውቃል። ላለፈው 25 ዓመት ድርጅት መሆን ተስኗቸው እርስ በራሳቸው ከሚጠላለፉ ድርጅቶችና ስድብን የትግሉ ስልት ካደረገ ዲያስፖራ አይጠብቅም ስልሆነም የውንድሜ ያሪድና የኢሳቱ ጋዚጠኛ ወይም ተከራካሪ የተስማሙበት ያብዮት ዋዜማ የዶሮ ወተት ነው።


 የሽግግር መንግስት ይቋቁም፤ ብሂራዊ እርቅ ይሁን።
መንሻዬ የተቃዋሚ ድርጅቶች ለ 25 አመት ያልተቋረጠ ጥሪ ስለሆነ፤ ጥሪውን ሊያስተጋባ የሚችል እውነታ አለ ወይ? ካልሆነስ መነሻው ምን ይሆን?
በርግጥ ይህን አይነት እርቅ በጥቅሉ የሚያስፈልግበት ሁኒታ እንደሚኖር መስማማት ይቻላል።
 በኛ ተጨባጭ ሁኒታ እንዴት ልናስኪደው ይቻለናል? ብሄራዌ እርቅ ለማደግ በአጠቃላይ ሃገራዊ በሚለው የቋንቋ አግባብ፣ ህዝብ ለህዝብ ተጣልቶ እንዲታረቅ የሚያስችል ሁኒታ ሲኖር የሚፈጠር የመፍትሄ ሃሳብ ነው። ይህ ሁኔታ በኛ ሃገር ሙከራዎች ቢኖሩም ምስጋና ይግባውና ህዝቡ ተዛዝኖና ተከባብሮ የኖረና የሚኖር   ስለሆነ ችግሩ የለብንም።
 ሌላው አንዱ ብሔር በሌላው ብሔር ላይ ወይም አንዱ እምነት በሌላው ላይ….ወዘተ ተነስቶ የተፋጠጠበትና፤ ውርወድ እንውረድ የተባባለ ሳይሆን፤ ለ25 ዓመት በትምክህትኞችና በጠባቦች የታቀዱ ከፋፋይ ዓላማዎችን አክስሞ፤ ዛሪ ከቀደመው በተለየ ተክብሮና አክብሮ መኖሩን እንደመርህ የተቀበል ስለሆነ አያሰጋንም። ይህን ሁኒታ ለመፍጠር የሚመኙና የሚፈልጉ የሉም ማለትም አይቻልም።
የቀረው እርቅ በተቃዋሚ ደርጅቶችና በገዢው ፓርቲ መሆኑ ነው። እነዚህ ተቃዋሚ ስብስቦች በውን እንደ ድርጅት አሉ ወይ? ካሉስ ለ25 ዓምት ምን ሰሩ የትኛውን ህዝብ አደራጁ/? ከገዢው ፓርቲ የተለየ ፕሮግራም አላቸው ወይ? በህብረት መስራት ያልቻሉት በመስመር፣ በፕሮግራም ልዩነት ነው ወይስ ኢህአዲግ ሲሳሳት ለማጉላት፤ መልካም ሲሰራ ለማራከስ፤ ምርጫ ሲቃረብ በየሚዲያው መንግስት እንዲህ ፈጸመ እንዳንሳተፍ እክል ሆነን ብሎ ለማማረር፤ የተሰጣቸውን እድልና ጊዜ እንኳን በአግባቡ መጠቀም የማይችሉ እንደሆኑ ከህዝቡ የተሰወረ አይደለም።
መንግስት በየትኛውም ታሪክና ገጠመኝ ተቃዋሚን እንዲጠናከር የተምቻቸ ሁኔታን መፍጠር አይችልም። ተገፍቶ ተገዶ የሚለቃቸው ነግሮች ይኖራሉ፤ ይህም ብቃት ያለው ተቃዋሚ ሲኖር ነው። ካቶ ያሪድ በተውሶ አባባል የኛዎቹ ተቃዋሚ ተብዬዎች ብቃት ያለው  ሰልፍ መጥራት የማይችሉ ምንምና ለምንም የማይሆኑ ናቸው። ስለሆነም እርቁ በማንና ለምን? እርቁ ከገለሰቦች ጋርና በአቁራጭ ስልጣን ፈላጊውች የሚያራምዱት ስልት ነው። ኢህአዴግም ይህን የስልጣን ተስፍኞች ጥሬ ተቀብሎ ካስተናገደ፤  የህዝብን ትግል ሊያኮላሽ ፈልጎ እንጂ መፍትሂ ፍለጋ ሊሆን እንደማይችል ሊሰመርበት ይገባል/ የጀነራል ጻድቃንና የጀነራል ጆቤም ምከር እዚህ ውስጥ ተካቶ መታየት አለበት። ስለሆነ በሁለት እግር ቁሞ የሚጠየቅ ጥያቂ ስለሆነ እራሳችሁን ፈትሹ። 16 ሁነው በወቅቱ ሁኔታ ለመነጋገር የጀመሩት ጅማሮ እንግዳ ነገር ባይሆንም መልካም ጅማሮ ነው። ይሁንና በምን መሰረት ላይ እንደተሰባሰባችሁ ልታሳውቁን ግድ የሚላችሁ ነው። 
ሁለት ጽንፎች
ጽንፈኝነት ሰዎች   በጥላቻና በንቀት በቁጭት ለራስ የሚሰጥ ግምት ላይ ተመስርቶ፤ ሚዛናዊ ወይም ሎጅክ ሳይታከልበት መኮንንና ማሞግስ ነው።
ላለፉት 25 ዓመታት ይህንን  በማራገባቸን እነደውዛችን ተላምደነው ልንላቀቀው ያልተቻለን ችግር ነው።
ጭፍን ተቃዋሚው መንግስት ምንም ስራ ምንም መቃወም አለበት። መንገድ ቢሰራ ኢኮኖሚው ቢያድግ፤ትምህርትና ጢና ቢስፋፋ፤ ተርግጠውና ተረስተው የነበሩ ህዝቦች አንገታቸውን ማቅናታቸው፤ ይህችን ሃገር በፍቅርና በኩልነት በማይናወጥ አለት ላይ ለማቆም የሚደረገው ጎንበስ ቀና አይታየውም። በውርስ የተላለፈለትን ሃገር፤ ስልጣን፤ ንብረትና፤በሊሎች ውርደትና የበታችነት መከበሩ ዳግም እንዳይመለስ ሁኖ ስለተስናበተ። ክህልሙ ባኖ እውነት ማየት ስላተቻለው ሁሌም የዛሪ 40 ዓመት እንዳስቀመጥነው ነው። በመሆኑም የቀረው ነገር በህዝቦች መሃከል ጥላቻ መንዛት ስለሆነ የሚጠልፋቸው የዋህዎች ስልሚኖሩ ያሳዝናል፤ በቀር ታሪክ ማንገዋለልና የተንጓለለውን ማስወገዷ አይቀሬ ስለሆነ ለጊዜ መተው ነው።   
ጭፍን ደጋፊውም መንግስት ሰው ገደለ፤ አድⶀአዊ ተግበር ፈጽመ፤ በሙስና ተዘፈቀ፣ በመስሎቹ ህዝቦች ላይ ከዚህ በፊት በሱ የተፈጸመበት አይነት በደልና ስቆቃ ቢፈጸምም፤ ያየውን የዳሰሰውን ሳይሆን በመንግስት መገናኛ የሚለቀቁ የተፈበረኩ  ዜናውችን ተቀብሎ ማስተጋባት እንጂ፤ የየሁት የሰማሁት ሌላ ነው፤ ይህ ከየት መጣ ብሎ አይጠይቅም። በመሆኑም ከዚህ ውጪ ያየውን አይተው የሚነግሩትን ይጠላል ከራሱም ጋር የተጣላ ይሆናል።
እንዲት ለዚህ በቃን የቆየ ታሪካዊ ዓመጣጥ ቢኖረውም በተለይ የ97 ምርጫ ውጤት ይበልጥ ያጎላው እንደሆነ ይታየኛል።
የ97 ምርጫ በማንና በማን ተካሂደ? በኢህአዲግና በቅንጅት ለመሆኑ ተለዋጭ የሊለው መልስ ነው። ኢህአዲግ ለ25 አመት ማንና ምን እንደሆነ ስለሚታወቅ፤ ብቅ ብሎ የጠፋውን ቅንጅትን እንመልከት
1。 ቅንጅት ሲመሰረት የይድረስ ይድረስ እንጂ መሰረታዊ የድርጅትን አመሰራረት መርህ ተከትሎ፤ አባል ድርጅቶቹም ሆነ ግንባሩ፣ አመስረታቸው ዋንኛ የችግሮቻቸው መቀፍቀፊያ ይሆናል።
2。 ቅንጅት ከምርጫ በፊት የቆይታ እድሚው 3 ወር ብቻ ነበረ።  በዚያን ወቅት  በነበረው የሃገሬቱ ተጨባጭ ሁኒታ የሃገሪቱን ህዝቦች ለመድረስ የሚያስችል የመገናኛ መንገድና የዜና ማስራጫው ውስን በመሆኑ ገጠሩን የኢትዮጵያ ምድር መድረስ አይቻልም ነበር። በከተማዎችም ቢሆን ጊዜው ማጠሩ ብቻ ሳይሆን፤ የድርጅት ስራ በየሆቲሉ ተቀምጦ የሚስራ ስላልሆነ አደራጆቹም ተደራጆቹም ለምዱም ሆነ ብቃቱ ስላልነበራቸው የተሳካለት ስራ አልሰሩም ነበር።
3。 ኢህአዴግም በወታደራዊ ሃይል አሽንፎ ገባ እንጂ  ፖለቲካዊ ስራ የተሰራበት ህዝባዊ መሰራት አልነበረውም። ሹማንቱና ካድሪዎቹ፤ ሬድዮና ቲሊቭዥኑ በሚያሰሙት ድለላ ተኮፈስ እንጂ እንኳን በከተማ በገጠርም ከትግራይና ከወሎ በቀር ህዝባዊ መሰረቱን እንዳይጥል፤ የደርግ አወዳደቅና የመፈረውካከሱ ፍጥነት፤ያልተጠበቀ ስለነበር ድሉን ተከትሎ ማባረር እንጂ ተረጋግቶ የፖለቲካ ስራ ለመስራት ፋታ የሚሰጥ ሁኔታ አልነበረም።
ቅንጅት ከተማዎችን እዲት አሸነፈ
.በከተማ ነዋሬ የነበረው ህዝብ በጦርነት የተሸነፈው ወታደርና ቤተ ሰቦቹ በአብዛኛው የመሸጉት ከትማ መሆኑ፤ በየመንግስታዊ መዋቅርና መስርያ ቤቶች የሚሰራው ስውና ቤተ ሰብ፤ ኢርትራ ሂደች ብሎ ያኮረፈው፤ ከህወሃት ጋር በቀጥታ ጦርነት ውስጥ ገብትው በሽንፈት ከትግሉ የተገለሉ ቤተሰቦችና የድርጅት ቅሬቶች፤ትግሬ ነገሰ ብሎ የተበሳጨው፤  ኢህአዴግ ክሃገሪቱና ከህዝቡ ደህንነት በመነሳት እርምጃውች ወስዶ  ስለነበር ተነካን ብለው የተቆጡ ሴትኛ አዳሪዎችና ወንጀለኛ ቦዘኔዎች፤ የከተማው ህዝብ ለዘመናት ማስኖ ያልተሳካለትን፤ የኢአዲግ ሰራዊትና አባላት ቀዳዳ ቁምጣ ለብሰው ገብተው በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ባለ ህንጻና ባለመኪና ሆነው በማየቱ ቅሪታ የተሰማው  ……….ወዘተ እነዚህ ዋናዎቹ ሁነው ሊሎችም ታክለውበት ኢሃዲግ ጊዜ አግኝቶ ያለሰራበት በጥላቻ አድፍጦ የሚጠባበቅ የማህበረ ሰብ ክፍል ነበር። ስለሆነም ኢሃዲግ ያላለመው ሽንፈት ውጢት ሆነ። በመሆኑም መደናገጡን ሊደብቅ አልተቻለውም አራስ ነብር ሆነ። ለጊዜ አስከፊ ቢሆንም ውለን አድረን ስናየው አራስ ነብርነቱን ወደንለታል። ለቅንጅት አስረክቦን ቢሆን ምን መሆን እንችል እንደነበር ለመገመት ያየነውን እውነት መቀበል ብቻ ነው።
 ሎቶሬ የወጣላቸው አሽንፊዎችም ስግብግብነተቸውን መቆጣጠር ተስኗቸው ሁሉንም ተመኙ። ምኞታቸውንም ተግባራዊ ለማድረግ አመጽ መጥራትን ምርጫቸው አደረጉ በቁማራቸው የበርካታ ወጣቶችን ህይውት ለማስነጠቅ ምክንያት ሆኑ።
ምን ያህል ራስ ውዳድና የስልጣን ጥመኞች እንደነበሩ በወጣቶቹ ህይውት ላይ መቆመራቸው አሳዝኗቸው ሳይሆን የራስቸው ፍላጎት ነግሶባቸው ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና አቶ ለደቱ አያሌው ሌደብቁት ያልቻሉት እውነት ሆነ። በአሸዋ ላይ በመገንባታቸው ተናዱ፤ በግልና በቡድንም ባላንጣ ሆኑ አለቀ።
  የ97ቱ ምርጫ በአግባቡ ተፈትሾ መልስ ሊሰጠው ባለመቻሉ እየተንከባለለ መጥቶ ተቃውሚችም ሌላ መስራት ሳይቻላቸው ችንፈታቸውን ባዶነታቸውን መሸፈኛ ሲያደርጉት፤ ኢሃዲግም ስለደነበረ የሆነ ኮሽታ ሲሰማ ነፍጡን ማንሳቱን ተዘውታሪ ድርጊቱ አድርጓል።
 የ97 ምርጫ ጎራ ተለይቶ የተወጋገዝንበት አንዳችን የሌላችን ህመም ሳይሰማን እየደነቆርን ያደማንበት ስለነበር በሰከነ ሁኒታ ማየት ባለማቻላችን ስር ሰዶ እዚህ አድርሶናል።
 ብሄራውና ህዝባዌ ጥላቻንም እየጨፈጨፈ ያለበት ሁኒታ ስለሆነ ከዚያ ለመውጣት መንግስት በዚህ ዙርያ በርካታ ስራ ይጠበቅበታል።
ማንም አጠፋ ማንም ወደታሪክ መዘክር መመለስ አለበት። ኢትዮጵያ በታሪኳ እንድዚህ አይንት ችግሮችን ለማስተናገድ እንግዳ አይደለችም። ትዮድሮስ፤ ምንይልክ፤ ዮኅንስ፤ ቀ.ኃ.ስ በንግስናቸው ዘመን የሚቻላቸውን በደል በህዝቦች ላይ ፈጽመዋል፤ ደርግም እንዲሁ፤ ይሁን እንጂ ሃገርና ህዝብ ነዋሪና ቀዋሚ በመሆናቸው፤ ያለፈው እንዳይደገም መጭውን ተስፋ በመሰነቅ፤ ሃገሪው እንደ ሃገር ሊያስቀጥለን ችሏል። አሁንም ጉዳዩን ወደ ህዝብ ቀርቦም ሆነ በሆነ መግባባት ሊዘጋ ይገባዋል።
አለም አቅፋዊ ድርጅቶችና የብዙሃን መገናኛዎች በኢትዮጵያ ጉዳይ
ኢትዮጵያ ውሰጥ የተፈጠረውን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ፣ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃንና ዓለም አቀፋዊ ስያሜ የተሰጣቸው የሰባዊ መብት ጉዳይ ድርጅቶችና የመንግስታቱ ድርጅትም የተለያየ አስተያየት ሲሰጡና ያገባናልም ሲሉ እየተደመጡ ነው።
ችግር ሲፈጠር ገላጋይና ሽምጋይ ማስፈለጉ ያለና የነበር ስለሆነ፣ አስፈላጊም ነው። ገላጋይ ብትር አቀባይ የሚሆንበትም ገጠመኝ ስለሚኖርም ማጅራታችንን ተመተን ጸጥ እንዳያሰኙን ሰጋን። ታሪካቸው ደግሞ እንድንፈራቸው አደረገን እንጂ መቺ ሰላምና መረጋጋት ጠልተን?።
ያገባናል ባይ ድርጅቶች እነማናቸው ምንስ ይመስላሉ?
1. UN /ተመድ/ የመንግስታቱ ድርጅት፦ በታሪኩ   ድሃ ሀገራት እርስ በርሳቸውም ሆነ ወይም በየሃገራቱ  በህዝቦች መሃክል አለመግባብት ተፈጥሮ  እልቂት ሲሆን፤ ከሃያላኑ ይሁንታን ካላገኘ ጣልቃ ገብቶ ህዝቦችን የታደገበት ሁኔታ ቢኖር ከሚጠበቅበት በጣም እጅግ የወረደና ዝቅ ያለ ነው ወይም የለም። 
ሃያላኑ ከግላቸው ጥቅምና ፍላጎት ተነስተው በአቅመ ደካማ ሃገራት ጣልቃ ገበተው የዘመናዊ መሳርያቸው መፈተሻ ሲደርጓቸው፤ ይሁንታ ሰጥቶ ለወረራቸውና ለበደላቸው ከለላ ሆነ እንጂ፤ የሰዎች መብት በመጣሱ፤ የሃገራት ልዑላዊነት በመደፈሩ ያሰማው ድምጽና ተቃውሞ የለም።
 ስለሆነም ድርጅቱ ጥርስም ድድም የሚኖረው በደካሞች ላይ እንጂ ሃያላኑን አስመልክቶ የሚያንከባልሉት ቅል ነው።
   በመሃከለኛው ምስራቅ ሀገራት ለረዥም ጊዜ የተካሄደው ጦርነትና አለመረጋጋት  ዋንኛ ምክንያቱ ፓሌስትናውያን ሃገራቸውን ተቀምተው ሃገር አልባ መሆናቸው  ብቸኛ ምክንያት ነው።
 በዚህም ሳብያ ህዝቦች ተሰደው የመከራ ህይወት እንደሚገፉና ስደተኞችን ያስጠጉ ሃገራትና አካባቤው በቦምብ እየታረሱ መሆናቸውን የመንግስታቱ ማህበር ፊቱን ያዞረበት እውነውት ነው።
 ሰሞኑን የአሚሪካ መንግስት ለነዚህ ህዝቦች መጨፍጭፍያ ቀድሞ ከመደበው ባጀት ተጨማሪ ማከሉንም UN መርጃው አለው። ምነው አበዛችሁት?  ለምን? አይልም እንዲልም መጠበቅ የለብንም።
ድሃ መንግስታት በጦር ወንጀልና በስባዊ መብት ጥሰት እየታስሩ ክስ ሲመሰረትባቸው፤ ባህር ተሻግረው በሺዎች ኪሎ ሚትር ተጉዘው የሰው ዘር የሚያጠፉትን ከላላ ሆናቸው እንጂ ለምን ብሎ አልጠየቃቸውም።
በኢራቅ ህዝብና ሃገር የተፈጸመው የአንድ እምነት ተከታይ ህዝብና የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደሆነም አልተነገረም።
 በመሆኑም የመንግስታቱ ድርጅት በአንድ ሃገር ጉዳይ ይመለከተኛል ስላለና ስለጠየቀ ብቻ፤ እንዲገባ ከመፈቀድ በፊት ሃገራቱ ማጣርያና መመዘኛ ሊያስቀምጡ ይገባል። 
2. Human right watch(HRW) የሰዎች መብት ተሟጋች ድርጅት፡ ይህ ድርጅት በ1978 ኒዮርክ ከተማ ሲመሰረት መጠርያ ስሙ Helsinki watch ሲሆን አላማና ግቡ ሰብአዊ መብት ሳይሆን በሶቭየት ህብርት መንግስት ላይ ያነጣጠረ ነበር።
ብዙም ሳይቆይ Helsinki Accord በመባል የምስራቅ አውሮፓ ሃገራትንና ሶቭየት ህብረትን፤   ሰባዊ መበት በመጣሳቸው ማጋለጥና ተጠያቂ ማድረግ መሪ ዓላማው አደረገ(የተመሰረተበት ሃገር አሜሪካ የአለም አቀፍ የስባዊ መበት ድርጅት አባል አለመሆኗ እንደተጠበቀ ሁኖ) በራሱ ዓመታዊ ዘገባ ሳይቅር፤ በ1980ዎቹ ሃገራት ዲሞክራቲክ እንዲሆኑ አንዳደረገም ይተርካል። እነዚህ ዘገባዎቹ ፖለትካዊ ተለኮ እንጂ ከሰባዊ መብት ጋር አንዳችም ግንኙነት የላቸውም።
በ1981 America watch ሁኖ በደቡብ አሜርካ በተፈጠሩ አማጽያንን ለማጥፋት ከየሃገሩ መንግስታቱ ጋር በማበር መሳርያ በማቀበልና የስለላ ስራ ሲሰራ ለመቆያቱ የታሪኩ ማህደራት ዋቢ ናቸው።
 በ1985 Asia watch በ1989 Meddle East watch በመሆን ሲያተራምስ ቆይቶ፤ በዚሁ ዓመት መጨረሻ HRW ሆነ። ብዙ የሚነገርለት የሰዎች መብት ጠባቂው ድርጅት ይህን ሲመስል፤ ዛሬ እየፈርሱ ባሉ ቀደም ሲል በፈረሱ ወደፊትም ሊያፈርሱ ባቀዱላቸው  ሃገራት እርዥም እጁ የሌለበት የለም።
 ይህ ድርጅት ለረዥም ጊዜ በኢትዮጵያ ገዳይ ላይ እየዘገበ ይገኛል። በ2009  በኢትዮጵያ ጉዳይ ባለ በርካታ ገጽ ዘገባ በVOA እንዲነበብለት ያደርጋል። የዘገባው መሃከላዊ ነጥብ ሀገሪቱን በዘር ማተራመስ ነው።
 ” ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ አነስተኛ ብሔር ሃገሪቱን እያጠፋት ነው” ይላል የእለተ አርብ የVOA ንባብ። ስለሆነም ይህም የአፍሪቃ ቀንድ ዎች(horn african wach) መሆኑ ነው::
 የሪድዮ ጣብያውም ቪኦኤን ማለቴ ነው፣ ሃገሪቱን በነውጥ ለመናጥ ከሚሰሩ ተቋማት ዋንኛና ግንባር ቀደም ነው። በመርጃ ውንጀላዬን ላጠናክር፣ 2012 ላይ ዋልድባ አካባቢ የስኳር ልማት ጀማሮን አሰመልክቶ በየፈርንጁ ሃገር የሚገኙ ዲያስፖራዎች አቧራ ለማስነሳት በሞከሩበት ወቅት፤ voa ታሪክ ሰርቶ፣ ጦርነት ፈጥሮ፤ ከበየዳ፣ ከሃሙሲት፣ ከወገራ፣ ካርማጭሆ。。。。。ወዘተ ህዝቡ ታጥቆ ለጦርነት ዋልድባ ወረደ ብሎ ሲዘግብ ነበር። አቅራቢውም አዲሱ አበበ ነው። ዘንድሮም የተፈጠረውን አለመረጋጋት የዘር ፍጅት ይሆን ዘንድ በመሻት፣ ከላይ በተጠቀሰው ዋልድባ አካባቢ ደን እየተመነጠረ ከስሎ ወደትግራይ እየተጫነ ነው በማለት ሃዲሱ ሲዘግብ፣ ምንጩም በ2012 የተጠቀመባቸው መነኩሴ እንደሆኑ ይናገራል።እጅግ ብዙ መራጃዎች ማቅረብ ይቻላል። ሬድዮ ጣቢያው በደርግ ዘመን ያገኘውን ተደማጭነት እንዴትና ለምን አላማ እየተጠቀመበት መሆኑን ማሳያ ነው።    
 ባለፈው ሰሞን የአሚሪካው ፕሪዘደንት ለመንግስታቱ ድርጅት ባሰሙት የመጨረሻ ኑዛዜ፣ ሃገሪ ለሰዎች መብት መከበር ትቆማለች ይሁን እንጂ ሰራተኛው በማህበር እንዲደራጅ አትፈቅድም የሚል ተቃርኖ ያለበትን ንግግራቸውን አደመጥን። ሰዎች ባሻችው መደራጀት ሰባዊ መብት አይደለም ማለት ይሆን?
 ለማኝኛውም  እነሱ ገነዘቡ ስላላቸው የሚነሱ ህዝባዊ ጥያቂዎች ደጉመው ያስታግሷቸዋል። እኛ 99% ነን (we are the 99%)የተሰኘውን  ሃገሪቱን ከአንዱ ዳር ወደሌላው ዳር ያዳረሰውን እንቅስቃሲ እንዲት ባሰቃቂ መልኩ እንዳኮላሹት የቅርብ ትውስታችን ነው።
 የኋላ ቀር ሃገራት ህዝባዊ ጥያቄን ለመፍታት ለማስታገስ ገንዘቡ ስለማይኖራቸው ሃልና አመጽ መጠቀም ይገደዳሉ እንጂ በባህሪ ሁሉም አንድ ናቸው።
 ለዚህም ነው የሰባዊ መብት ተቆርቋሪ ነው የሚባለው ድርጅት አይኑ ውስጥ የተማገርውን ግንድ ሳያስወግድ እሩቅ ሃገር ያሉ ችግሮችን ማየት አይችልም ተልኮውም አመሰራራቱና ስሙ አይገልጹትም የሚባለው።  
3。Amnesty international  ድርጅቱ በ1961 ሲመሰረት መነሻ ምክንያቱና አላማውም ነጻና ሰባዊ ነበር። በመሆኑም ብዙ ተከታይ ማፍራት ሲችል በአሆኑ ጊዜ አባላቱ 7ሚሊዮን እንደሆኑ ይገመታል።
የተባበሩት መንግስታት በወረቀት ላይ ያሰፈረውን UDHR አንቀጽ 19ና 18ን መሰረት ያደረገ ስራዎች መስራት እንደጀመረ፤ በተመሰረተ 5 ዓመት ባልሞላው ጊዜ  በ1967 CIA (central intellgent agency) ሰርጎ ገብነት ተተበተበ።
 ይህም በመሆኑ ድርጅቱ እንዲመሰርት ምክንያት የሆነውና መስራቹ፣ የድርጅቱ መሪ ፒተር ቢንሶን(Peter Benson) ከድርጅቱ እንዲሰናበት ተደረገ። ከዚያ በኋላም ድርጅቱን ከስለላ መረቡ ስለጸዳበትና ነጻ እንደሆነ የሚያሳይ ሰነድ የለም
1978ና በ1977 ኖቤል ፕራይስና የተመድ (UN) ፕራይስ አግኝቷል፤ ለአባላቱ መበራከትም ምክንያት ነው። አሁንም ነጻ ነው ተብሎ አይነገርም።
በ1990ዎቹ በተለያየ ሃገራት መንግስታት ላይ አቋም ወስዶ ስያወግዝና ሲኮንን፤ በየሃገራቱ የውስጥ ጉዳይ  ጣልቃ  በመግባት ቁጥር ስፍር ለሌላቸው ህዝቦች መጨፍጨፍ ዋንኛ ምክንያይት የሆኑትን መንግስታት አልወቅሰም አልኮነነም። ይባስ ብሎም የጉልበተኞቹን ጣልቃ ገብነት አስፈላጊነት ሰበከ።  በደረሰው ጥፋትም ተጸጽቶ መግላጫም አልሰጠም። አምነስቴ ኤንተርናሽናል ማለት እንዲህ ነው። (አንጎላ Angola ፤ኢስት ቲሞር east timore ፤የፐርሽያ ሰላጤ persian golf፣ርዋንዳ Ruwanda ፣የቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ former yugozlavia የሚጠቀሱ አብነቶች ናቸው።
2011 አሚሪካ በአልቃይዳ በደረስባት ጥቃት ሳቢያ ሃገራትን ስትወር፣ ሰዎች በእምነታቸው ሳቢያ ስታስር ስትገድል፤ እንደ አቡግሬብ እስር ቤት አይነት ሰቆቃ ሲፈጸም፣ ጓንታናሞ ያለፍርድ የታጎሮ እቆምላቸዋልሁ ስለሚላቸው እስረኞች፤አንድም ነገር ማለት አለመቻሉ የምንነቱ መገለጫ ሲሆን።
 ሁሌም የሚያስግርማችሁ ጉዳይ፣ ድርጅቱ  ለስዊዝ ባለስልጣናት ይህን ሰውዬ እሰሩት ብሎ ከተለመደው አሰራራ ውጭ ሂዶ ሹክ ማለቱ ነው። ሰውየውም ፕሪዝዳን ቡሽ ነው።
 ሌላ የድሃ ሃገር መሪዎች ጉዳያቸው ሂግ ፍርድ ቤት ቀርቦ ሰው ሰምቶት ጸሀይ ሞቆት እንደሆነና መቺም ተሳዳጅ እንደሆኑ ማስተዋሉ ለድርጅቱ ውስልትና ማሳያ ነው።
2014 ማይክል ብራውን የሚባል የ18 ዓመት ወጣት ሚዙሪ/ፈርግርሰን በፖሊሰ ግድያ ይፈጸምበታል፤ ግድያው ህዝባዊ መነሳስት ቀስቅሶ የመንግስትን አትኮሮት የሳባ ቀውጢ ይሆናል።
አምነስቴ ኢንተር ናሽናል በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ አሚሪካ 13 አባላት ያሉት ቡድኖቹን ያስገባል የወሰደው እርምጃ የፖሊስ ባለ ስልጣናትን ለማናገር ፈቃድ መጠየቅና፤ አማጽያኑን ወይም ስልፈኞቹን አመጽ አልባ ሰልፍ እንዲት እንደሚደረግ ላሰልጥን አለ እንጂ፤ ሰባዊ መብት መረገጡን የፖሊሶቹ በጥቁሮች ላይ የሚፈጽሙትን ግድያ አላወገዘም ።
እናም ይህ ድርጅት ነው እዚህ ሃገር እዚያኛው ደሃ ሃገር እንድንገባ መንግስታቱ ይፍቅዱልኝ የሚለን ምን ሊያደርግ?
ያለንበት ዘመን ሚድያው መንግስት ይሽራል መንግስት ይሾማል፤ ጦርትንርትም ፈጥሮ ያዋጋል፤ የህዝቦችንም አንድነትና የሃገራትን ህልውና አደጋ ላይ ይጥላል።
ባለፈው በአረቡ አብዮት ወቅት፤ በተለይ ፊስቡክ የግብጹን የታህሪር አደባባይ አብዮት እናደቀጣጠለውና እንደመራው ይታወቃል። እንቅስቃሲው ብሔራዊና ሃገርዌ ያለመሆኑን ፍጻሚው ያሳየናል። ሁሴን ሙባረክ ማርጀታቸው የእስልምና ወንድማማቾች ድርጅት እየተጠናከረ መምጣት ምእራባውያኑን እንቅልፍ አይነሳቸውም አይባልምና የፊስቡክ አብዮቱን ከኋላ ሆነው በል አላሉትም ማለት አይቻልም። በገንዘብና በተጸኖ የራሳቸውን ሰዎች ለማስመረጥ ሙከራ አደረጉ፤ ሳይሳካላቸው ቀርቶ የእስልምና ወንድማማቾች አሸነፈ።
 ለዘመናት እራሳቸው ያሰለጠኑትና ባጀት መድበው የሚያስተዳድሩትን ወታደር መፈንቅለ መንግስት አድርጎ በህዝብ የተመረጠን መንግስት አፍርሰው ፕሬዘዳንቱን አሰሩ። የግብጹ አብዮት እንዲህ ሲሆን የፊስ ቡክ ታዳሚ የነበረው ወጣት፤ዛሬ  ወይኔ ሃገሬን እየለ  ጸጉሩን እየነጨ አንገቱን ደፍቶ ያለቅሳል።
ይህን ሁኒታ ከኛ ሃገር ገጠመኝ የሚለየው ግብጾች ለውድድር የሚቀርብ ብቃት ያለው ድርጅት ኑሮአቸው እንኳን በዚህ ሁኔታ ሲጠናቀቅ የኛን የባሰ እንደሆነ መላልሰን ልናየው ይገባል።  
ስጋቲን በዚህ ተጨባጭ ምሳሌ ልቋጭ ሊቢያ በሙሃመር ጋዳፊ ዘመን ለምእራባውያን አስቸግራ እንደነበሩ ይታወቃል። በፍጹም ሊንበረከኩ ያልቻሉ መሪ ነበሩ፤  በሳቸው ዘመን ህዝቡ በኑሮው እጅግ የተመቸው ነበረ። ጣልቃ መግባት ያልቻሉ ምእራባውያን ሊያጠፉቸው ተነሱ፤ እሳቸውም አልበግሬ ሁነው የአፍሪካ ድርጅት ባለተራ ፕሬዘዳንት   ሁነው፤ እኛ አፍሪካውያን የራሳችን መገበያያ ገንዘብ ይኑረን ለዚህም ያከማቸሁት ወርቅ በነጻ ላቅርብ አሉ፤ የአሜሪካን ዶላር ውረቅት እናድርገውም አሉ።  ይህ ጉዳይ ዛሬ የምታዩትን የሊቢያን ሁኔታ ፈጠር። በዚህ ሁኔታ ወስጥ ሁሉም ከላይ የተጠቀሱ፣ ሰመ የህዝባዊ መብት ደርጅቶች ቀጥተኛ ተሳትፎ አላቸው።
ኢትዮጵያም  ባልፈው 25 ዓመት የተከተለቸው የኢኮኖሚክ ፖሊሲን ምእራባውያኑ አልተዋጠላቸውም፤ በመሆኑም ያልምከሩት ሙከራ አልነበረም።
 ሃገሪቱ በእድገትና በመለወጥ ሂደት ላይ በመሆኗ፣ የአፍሪካ ሃገራት እንድሞዴል እየተመልከቷት ነው። እና ይህ ሄደት ለምእራባውያኑ እንቅልፍ የሚነሳ በአፍሪካ መሰረት የሚያሳጣ ይሁንም አይሁንም አያሰጋቸውም ማለት ስላይደለ፤ ብንሰጋ ፍርሃት ሳይሆን ላየነው ለሰማነው ምስክርነት ስልሆነ ሃገርችን እንደፈልጉ የሚገቡባት የሚወጡባት እንዳትሆን መንግስት አለመፍቀዱ አግባብ ነው።
 መንግስትም የራሴ አጣሪዎች አሉኝ የሚለውን ታማኝነት የሊለውን ድርጅቱን ለራሱ አድርጎ፤  ሃገር በቀልና በህዝቡ የተውከል ነጻ አጣሪ ኮሚቲ ማቁቋም ግንባር ቀደም ተጋብሩ ይሆን ዘንድ መግፋትና ማስፈጸም ይኖርብናል። 
በሃገርችን እየተካሂዱ ያሉት ህዝባዊ መነሳሳቶች የሚመሩበት ወጥ ዓላምና የሚመራቸው ድርጅት ባለመኖሩ ቀጣይነታቸው አጠያያቂ ነው።
 እራሳቸውን ድርጅት ብለው የሚጠሩና በየብዙሃን መገናኛው በለው አለቀለት ያሉ ከፈርንጅ ሃገር ሆነው እንቅልፍ ያጡት፤ ትርጎም አልባ በሔራዊ እርቅ የሚሉን ምኞታቸው አንድ ነው ባቁራጭ ስልጣን። ይህ ካልሆነም በመሳርያነት አያገለግሉም ማለት አይቻልም።
የኢትዮጵያ መንግስት ህዝባዊ ጥያቄውችን መመልስ ማለት ቃል እየገቡ ችግሮች እንዲባባሱና ችግሮች ሲባባሱ፣ የሚከሰቱ ህዝባዊ ቁጣዎችን በሃይል ማፈኑ የትም እንደማያደርስ ተገንዝቦ ከህዝቡ ጋር መስራት የመጨራሻ ምርጫው መሆኑን መገንዘብ ይገባዋል።
እንደ ሃገር ለመቀጠል ያለን አንድና ብቸኛ ምርጫ ይህ ብቻ ነው። በቀር ባቋራጭ ለስልጣን ሲባል የሚቀርቡ መፍትሄ መሳል የሽግግር መንግስት፣ ባላደራ መንግስት。。。。。ወዘተ አደገኞች ናቸው። 
ኢትዮጵያ በልጆቿ እኩልነትና አንድነት ለዘላለም ትኑር!!!!!!!!

ከመቶ አመት የቤት ስራወቻችን አንዱ የሆነው የኦነግ አፍራሽ ተልእኰ (ከይገርማል)

$
0
0

Ethiopiaሕዝቡ ከዳር እስከዳር በምሬት ተነስቶ በወያኔ ላይ የሚሰነዝረውን ጡጫ እያበረታ ነው:: ወያኔም በበኩሉ “ተመጣጣኝ ርምጃ” በሚለው ጥቃት በርካታ ዜጎችን ተኩሶ እየጣለ ነው:: ለአመታት ተደክሞ በብዙ ወጪ የተገነቡ ፋብሪካወችና ድርጅቶች በአንድ ቀን እሳት እንዳልነበሩ እየሆነ ነው::  ልቡ በክፋት ለተደፈነው ወያኔ ይህ ሁሉ የሚያሳስበው አይመስልም:: እንዲያውም አለመረጋጋቱን አጥብቆ የሚፈልገው ይመስላል:: የወያኔ አውራወች ችግሩን የሚያባብስ ርምጃ ሲወስዱ እንጅ መፍትሄ ለመፈለግ ሲሰሩ አይታዩም:: እንቅስቃሴው የፈጠረው አንድ በጎ ነገር ቢኖር ወዲያና ወዲህ ሆነው በጠላትነት እንዲተያዩና እንዲጠፋፉ ሸር ሲጎነጎንባቸው የነበሩ ጎሳወች ልዩነታቸውን አጥብበው: ጥላቻቸውን ፍቀው በአንድነት መሰለፋቸው ነው:: ለብዙ አመታት ፊት ተዟዙረው የነበሩት ስልጤወችና ጉራጌወች ይቅር ተባብለዋል:: በጥርጣሬ ይተያዩ የነበሩት ኦሮሞወችና አማራወች “በወያኔ ተንኮል ነቅተናል!” ብለው እጅ ለእጅ ተያይዘው በአንድነት ቆመዋል:: ይሁን እንጅ የወያኔ ቅጅ የሆነው ኦነግ (በስም ብዙ በባህርይ ግን አንድ የሆኑ የኦሮሞ ድርጅቶች) የሚባለው ድርጅት ሰዎች ይህን የሕዝቦች አንድነት አጥፍተው በምትኩ ክፍፍልን እና ጥላቻን ለመትከል ከፍተኛ ደባ እየፈጸሙ ነው::

አቶ ጃዋር መሀመድ ሰሞኑን የተናገረው ነገር በጣም የሚረብሽ ነው:: ይህን ሰው ባልተገራ አንደበቱ ምክንያት ብዙወች ይንቁታል::  የሚናገራቸው ነገሮች የተቀመጠበትን የሀላፊነት ቦታም ሆነ የአንድ ጤነኛ ሰው ባህሪን የሚመጥኑ እንዳልሆነ ነው የሚነገረው:: ጃዋር የክርስቲያኖቹን አንገት ለሜንጫ ከተመኘ ጀምሮ በብዙወች ዘንድ ጥላቻን ያተረፈ ሰው ሆኗል:: ይህ ሰው የፖለቲካ ድርጅት አባል እንዳልሆነ ይናገራል:: ይሁን እንጅ የሚያራምደው ሀሳብ ያለጥርጥር ደም ከጠማቸው የኦነግ አባላት ውስጥ አንዱ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው::

ኦነግ የወያኔን እና የሻእቢያን እቅድ ለማስፈጸም በመቆም እጅግ ብዙ አማራውችን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለ ሀላፊነት የማይሰማው አሸባሪ ድርጅት ነው:: በንጹሀን አማሮች ላይ የተፈጸመውን  ጭፍጨፋ መቸም ቢሆን ታሪክ  የሚዘነጋው አይሆንም:: አማራወች በኦሮሞወች ላይ ከ120 አመት በፊት ፈጽመውታል በተባለው በሬ-ወለድ ጭፍጨፋ መነሻ በዚህ በሰለጠነ ዘመን የአሁኑን አማሮች በበቀል የፈጀ እጅግ የተበላሸ ኋላቀር ድርጅት ነው:: ይህ በሻእቢያ እገዛና ኢትዮጵያን እንደሀገር ማየት በማይፈልጉ ሀይሎች የተቋቋመው ድርጅት የሀገራችንን ታሪክ ለማበላሸት እና አንድነቷን አደጋ ላይ ለመጣል እረፍት አጥቶ ግፍ ሲፈጽም ኖሯል:: ለኤርትራ መገንጠል: ለኢትዮጵያ ታሪክ መጉደፍ: በኢትዮጵያውያን መሀል ልዩነት እና ጥላቻ ስር መስደድ: ለአማሮች መጨፍጨፍ እና ሀገራችን ለጥቃት ተጋላጭ እንድትሆን በማድረግ በኩል ጉልህ ድርሻ አበርክቷል:: ኦነግ ዛሬም እንኳ ከጥፋቱ ሊመለስ የማይፈቅድ ድርጅት መሆኑን በአቶ ጃዋር በኩል አስረግጦ እየነገረን ነው::

 

አቶ ጃዋር የፖለቲካን ሀ – ሁ ሳይረዳ የፖለቲካ ተንታኝ እና አክቲቭስት የሚል ስም የተሰጠው አፉ እንዳመጣ የሚናገር  ያልበሰለ ሰው እንደሆነ ብዙወች ይስማማሉ:: ለነገሩ ኦነግ ውስጥ ምራቁን የዋጠ አስተዋይ ሰው ማግኘት ከባድ ሳይሆን አይቀርም:: አቶ ጃዋር ስለኦሮሚያ የሽግግር ጊዜ ሰነድ ሲያወራ: ስለኦሮሚያ ከፖለቲካ ነጻ የሆነ የጦር ሰራዊት ምስረታ ደረቱን ነፍቶ ሲናገር የኦሮሚያን ነጻ ሀገር አይቀሬነት እያረጋገጠልን መሆኑ ነው:: ይህ ግለሰብ የኦነግን ትንፋሽ ሳይይዝ በራሱ ጊዜ ፈጥሮ ያወራል ማለት አይቻልም:: ኦነግ አሁንም የኢትዮጵያን ሕዝብ መጠፋፋት እያወጀልን ነው:: በሰላምና በፍቅር አብሮ የኖረውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሸር ለያይቶ በመሬት ይገባኛል ጥያቄ እርስ በርስ ሊያጫርስ በጽናት ቆሟል:: አቶ ጃዋር የተናገረው ነገር በተሳሳተ መልኩ እንደተተረጎመ አድርጎ በዘሀበሻ ላይ ጽፎ ያስነበበን ጽሁፍ ያንኑ የኦነግን አላማ በድጋሚ የሚያረጋግጥ ነበር:: ደስ ሲላቸው የብሔር-ብሔረሰቦች መብት የሚከበርባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን በጋራ መስርተን በአንድነት እንኖራለን የሚሉት ኦነጎች ብዙም ሳይቆዩ ‘በኢትዮጵያ ውስጥ እንቀጥል ወይስ የራሳችን ሀገር እንመስርት?’ በሚለው ጉዳይ ላይ የኦሮሞ ሕዝብ ብቻ ነው ሊወስን የሚችለው ብለው እውነተኛ ፍላጎታቸውን ያወጡታል:: አቶ ጃዋር ስለመከላከያ ሰራዊት ምስረታ ሲያወራ ምን ለማለት እንደፈለገ የማይገነዘብ ሰው አይኖርም:: በክልል ወይም በክ/ሀገር ወይም በአካባቢ በአንዲት ፌደራላዊት ሀገር ውስጥ ከሌሎች ጋር አብሮ የሚኖር ሕዝብ የአካባቢ ፖሊስ እንጅ መከላከያ ሰራዊት ሊኖረው አይችልም:: መከላከያ ሰራዊት የሀገሪቱን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ በሀገር ደረጃ የሚቋቋም ወታደራዊ ሀይል ነው::

 

የ1997 ዓ.ም ሀገር አቀፍ እና ክልላዊ ምርጫን ተከትሎ ቅንጅት አሸንፏል ብለው ያመኑት የተቃዋሚ ኃይሎች ሕብረት አመራሮች ለዴሞክራሲያዊ ስርአት የሚታገሉ መሆኑን እረስተው በምርጫ ውድድር ያሸነፈው ቅንጅት ላይ ዘምተው እንደነበር የሚረሳ አይደለም:: በውድድር ያሸነፈውን ስልጣን ትቶ ሁሉንም የሚጋብዝ የሽግግር መንግሥት እንዲመሰረት በቅንጅት ላይ ጫና ሲያደርጉ የነበሩት ተቃዋሚወች ፍላጐታቸው የተከፈተው የሰላማዊ እና የዴሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር ስርአት እውን በመሆኑ ተደስተው ዴሞክራሲያዊ ስርአቱ እንቅፋት እንዳይገጥመው በመከላከል ወደተሻለ የእድገት ደረጃ እንዲሸጋገር ለማገዝ ሳይሆን ስልጣን ለመጋራት ነበር:: ማንም ይሁን ማን በሕዝብ እስከተመረጠ ድረስ የሕዝብን ውሳኔ አክብሮ መቀበል የዴሞክራሲያዊ ስርአቱ አንድ መገለጫ መሆኑን ረስተው በሕዝብ ፈቃድ የተመረጠው ቅንጅት ላይ የጥላቻ እና የምቀኝነት ዘመቻ ሲያካሂዱ ወያኔን ጭራሽ እንደሞተ ቆጥረውት ነበር:: ከዚህ ሁሉ በኋላ ሞቷል ተብሎ የታሰበው ወያኔ በራሱ መንገድ ተጉዞ ሁሉንም በሚፈልገው መልክ ሲያስተካክል ተቃዋሚ ድርጅቶች ከርስ በርስ ንክሻ ወጥተው እንደለመዱት በየፊናቸው በወያኔ ላይ መጮህ ጀመሩ::

የዛሬው የኦነግ የጦር ሰራዊት ምስረታ ዕቅድ የመነጨውም ወያኔ እየሞተ ነው ከሚለው የተሳሳተ ስሌት የተነሳ ነው:: አሁን በየአካባቢው እየተደረገ ያለው አመጽ የወያኔን ቀብር አቅርቦታል ብለው ያመኑት ኦነጎች እውነተኛውን ፍላጎታቸውን አውጥተው ኦሮሚያን ብቻ የሚመለከት የሽግግር መንግስት ምስረታ ሰነድ ለማዘጋጀት እና የመከላከያ ሰራዊት ለመገንባት እየተዘጋጁ እንደሆነ እየነገሩን ነው:: ይህ አካሄዳቸው ትግሉን ምን ያህል ሊጎዳው እንደሚችል የተገነዘቡት አይመስልም:: በመጀመሪያ ደረጃ ወያኔ እነርሱ እንደሚያስቡት ሊሞት በጣዕር ላይ ያለ ድርጅት አይደለም:: ሌላው ደግሞ ወያኔ ‘ጉድጓዱ የተማሰ ልጡ የተራሰ’ ነው ብለን ብናስብ እንኳ የኦሮሚያ መንግስት ምስረታ ሀሳብ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ዘላቂ ሰላም የሚያመጣ ፍቱን መፍትሄ አይደለም::

 

በየጊዜው እንደምናየው በኦሮሚያ የሚደረጉ የሕዝብ አመጾች የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ሳይሆን የኦነግን ባንዲራ በመያዝ የሚደረጉ ናቸው:: የኦነግ ሰዎች ሲያወሩ ኢትዮጵያን እና ኦሮሚያን ለያይተው ነው:: ሌሎቻችንም ብንሆን ይህን አባባል የለመድነው ይመስላል:: ኢትዮጵያውያን እና ኦሮሞወች በየተቃውሞ መድረኩ የየራሳቸውን ባንዲራ ይዘው ጐን ለጐን ሲሰለፉ እያየን ነው:: ኦነግ የኦሮሚያን ካርታ ካወጣ ብዙ አመታትን አስቆጥሯል:: የኦሮሚያን የሽግግር መንግስት ሰነድ ለማርቀቅ እና የመከላከያ ሰራዊት ለመገንባት እንደታቀደም እየሰማን ነው:: የቀረው የወያኔን ውድቀት ተከትሎ የኦሮሚያን ነጻነት ማወጅ ብቻ ነው::

 

“ብቻ ወያኔ ይውደቅ” የሚሉ ኢትዮጵያዊያኖች የኦነግን አደገኛና አፍራሽ አካሄድ እየተገነዘቡ አይመስልም::  ይህ የተዛባ አመለካከት በፍጥነት ሊታረም ይገባል:: መላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የኦነጎችን እና የወያኔን አፍራሽ እንቅስቃሴ በእኩል በንቃት በመከታተል የሚሸርቡትን ሴራ ማክሸፍ ይኖርበታል:: የኦነግ ያፈጠጠ ፍላጎት ኦሮሚያን ከኢትዮጵያ መገንጠል ነው:: ይህ የመገንጠል መዘዝ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መሀል ከፈጠረው ውድመት ሽህ ጊዜ ለሚበልጥ ጉዳት የሚዳርግ: ክልሉን የጦር ቀጣና ለማድረግ በሚያስቡ ታሪካዊ ጠላቶቻችን የተሰላ ተንኮል ነው:: ከኢትዮጵያ የመቶ አመት የቤት ስራ ውስጥ አንዱ የሆነው የኦነግ እንቅስቃሴ ካልተነቃበት ሊታረም የማይችል ጥፋት የሚያስከትል ይሆናል::

 

አንዳንድ የአማራ አክቲቭስቶች የኦነግን የነጻ ሀገር ምስረታ ፍላጎት እንደአደጋ አለማየታቸው ገርሞኛል:: ለመሆኑ ኦነግ ነጻ ኦሮሚያን እንደሀገር መመስረት ቢፈልግ የቱን ይዞ የቱን ትቶ ነው? አማራው ራሴን ችየ ሀገር እመሰርታለሁ ቢልስ የትኛውን የሀገሪቱ አካባቢ ይዞ ነው:: “ብቻ ወያኔ ይውደቅ!” የሚለው አባባል ፍጹም የተሳሳተ ነው:: ኦነግ የራሱ ካርታ እንዳለው ከዚህ በፊት ባወጣቸው ሰነዶች ላይ አይተናል:: ኦሮሞወች ነጻ ሀገር ለመመስረት ከፈለጉ ይህን ፍላጎታቸውን ማንም ሊያዳፍነው አይችልም ብለው የሚሉት ሰዎች ምን እያሰቡ ነው? በዚህ ሰነድ ላይ ተስማምተዋል ማለት ነው? ወይስ የኦነግን ጉዳይ በይደር ትተን ወያኔን ከስጣልን ካስወገድን በኋላ እንመለስበታለን ተብሎ ታስቦ ነው?

 

ከኦነግ ጀርባ የተሰለፈ ጠንካራ ኃይል መኖሩ መዘንጋት የለበትም:: አሁን እየተደመጠ ያለው የግብጽ መንግሥት ለኦነግ ማንኛውንም ድጋፍ ለማድረግ ቃል እንደገባ ነው:: ግብጽ የኢትዮጵያን መዳከም እና መከፋፈል አጥብቃ የምትፈልግ መቸም ቢሆን የማትተኛልን ታሪካዊ ጠላታችን ናት:: ኦነግ ስለወደፊቱ መጨነቅ የሚፈልግ ድርጅት አይደለም:: ወያኔ በበኩሉ ለብዙ ሽህ አመታት ኢትዮጵያን በደምና በአጥንቱ አስከብሮ ያቆየውን የአንድነት ኃይሉን አከርካሪ መስበሩን በኩራት ነግሮናል:: በዚህ የዱርየ ስራቸው የሚኩራሩት የወያኔ አመራሮች የአንድነት ተሟጋቾችን አዳክመው ሀገራችንን ለጥቃት ማጋለጣቸውን የሚያስተውሉበት ዐዕምሮ ያልታደሉ መሆናቸውን አስመስክረዋል:: ወያኔ ብሔር-ብሔረሰቦችን ለማፈን ከላይ ያስቀመጣቸውን የድርጅት አመራሮች እና ሰራዊቱን ተማምኖ ሕዝብን ንቋል:: በበብሔር-ብሔረሰቦች  መሀል መተሳሰብ እንዳይኖር አድርጎ በመሀከላቸው የጥላቻ ዘር ሲዘራ ኖሯል:: ከአማራ ክልል እና ከአፋር ክልል ቆርሶ በጉልበት ወደትግራይ በማካለሉ ከአጐራባች ክልሎች ጋር ጠብ ፈጥሯል:: ኢትዮጵያ ብትፈራርስ ወያኔም ሆነ የትግራይ ሕዝብ  እንዴት ሊጠቀሙ እንደሚችሉ አይታወቅም:: “ብልህ የአመቱን ሞኝ የእለቱን” የሚለው አባባል ጊዜው አልፎበት በአዲሱ ፋሽን ሁሉም የእለቱን ናፋቂ ሆኗል:: ነገ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን እያሉ የሚጨነቁ ሰዎች ግን አልጠፉም:: አንዳንዴ ለምኑም ግድ የሌላቸው ሰዎች ያስቀናሉ:: ዞሮ ዞሮ በኢትዮጵያ ላይ እየደረሰ ላለውና ወደፊት ለሚመጣው ችግር በዋናነት ተጠያቂው ትግራይ-ወለዱ ወያኔ ነው::

 

የሰው ልጅ ትልቁ ጥንካሬ ተስፋ ነው:: እና አሁንም ከችግር የመውጫ መንገዶች ጨርሰው አልተዘጉም ብለን ተስፋ እናድርግ:: የአንዳንድ ሀገር ወዳድ ወገኖች የመንፈስ ጥንካሬ የሁላችንም ተስፋ ነው::  ስለሀገር እና ስለሕዝብ አብዝተው የሚጨነቁ ሰዎች ደከመን ሰለቸን ሳይሉ መፍትሄ ለማምጣት የሚያደርጉት ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት:: ያለፈውን እና አሁን ያለውን ሁኔታ ገምግሞ የወደፊቱን ለመተንበይ  ለአንዳንዶቻችን ከባድ ሊሆን ይችላል:: እኔ እራሴ ደርግ ከወደቀ በኋላ እንኳ የደርግን ውድቀት አምኘ መቀበል አቅቶኝ ከዛሬ ነገ ተመልሶ ይመጣል እያልሁ ሳስብ ነበር:: የወቅቱን ሁኔታ በጥሞና መገምገም ለቻለ ኢትዮጵያን የገጠማት ፈተና እጅግ ከባድ መሆኑን ይረዳል:: አይመጣም ያልነው የሚመጣበት አይሆንም ያልነው የሚሆንበት ብዙ አጋጣሚ አለ:: ፈረንጆች Expect the worst የሚሉት ለቀልድ ሳይሆን መጥፎ አጋጣሚ ከመጥፎ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ከመልካም ሁኔታ መሀልም ሊከሰት እንደሚችል ግንዛቤ ተይዞ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ሲመክሩ ነው:: ስለዚህ እያንዳንዷን ርምጃ በጥንቃቄ ካልተራመድናት በሆይ ሆይታ የሚደረግ ጉዞ ከድጡ ወደማጡ ሊከተን ይችላል:: የሚያሳስበን የአሁኑ ችግር ብቻ ሳይሆን የወደፊት ኑሯችንም ጭምር ነው::

 

ትንሳኤ ለኢትዮጵያ!


የኢትዮጵያ ጉዳዮች ውይይት መድረክ (በዳላስ)

$
0
0

ህዝብ በዓሉንና እምነቱን ተግባራዊ በሚያደርግበት ስፍራ ጥቃት መፈጸም

ከወንጀሎች ሁሉ የከፋ ወንጀል ነው!!

udj-ethiopia-demo-satenaw-newsወያኔ/ህወሐት ፤  ከፍጥረቱ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ፤ በኢትዮጵያና በህዝቧ ህልውና ላይ እየዘመተ እንዳለ የተደበቀ ጉዳይ አይደለም። ላለፉት 25 አመታት ይህ ቡድን የፈጠረውና የሚመራው የኢሕአድግ መንግስት ፤ በአገራችንና በህዝባችን ላይ ያልፈጸመው የግፍና የወንጀል አይነት የለም። የስርአቱ በደል ያላንኳኳው የህብረተሰብ ክፍል አይገኝም ። ይህ የአጥፊነቱ ተፈጥሮ ፤ ወደ ዘር ማጥፋትነት ተሸጋግሮ ፤ የአማራው፤ የኦሮሞው ፤ የኮንሶው ፤የጋምቤላው ፤ የሶማሌውና የአፋሩ ህብረተሰብ ፤ በተለያየ ወቅት ፤በዚህ ቡድን የዘር ማጥፋት ጥቃት ደርሶበታል።

በቅርቡ በቢሾፍቱ የእሬቻን በአል ለማክበር በወጣው ሰላማዊ ህዝብ ላይ የተደረገው የጅምላ ጭፍጨፋ ፤ በአይነቱ ናዚ ከፈጸመው የዘር ማጥፋት ስልት ጎን የሚያስመዘግበው ነው ። ይህ ዘግናኝና ኢ ሰብአዊ ድርጊት ፤ ታሪክ ይቅር የማይለው ፤ በ 21ኛው ክፍለ ዘመን የተፈጸመ ወንጀል ነው።  ለጠፋው የሰላማዊና የንጹሃን ዜጎች ህይወት ፤ አሁንም ተጠያቂው በስልጣን ላይ ያለው ወያኔ/ህወሐት የሚመራው ቡድን መሆኑ እሙን ነው ። ድርጊቱ በኦሮሞ ህብረተሰብ ፤ ባህል ፤ እምነት ፤ ማንነትና ታሪክ ላይ ብቻ የተቃጣ ጥቃት ሳይሆን፤ በመላ ኢትዮጵያዊያን ላይ ጭምር ነው ። በሰው ዘር ላይም የተፈጸመ ወንጀል ነው።

በመሆኑም የኢትዮጵያ ጉዳዮች ውይይት መድረክ ፤ በእሬቻ በአል ወቅት በወገን ላይ የደረሰውን ኢሰብዓዊ ጭፍጨፋ ፤ ለመጠቀም በሚቻል የመጨረሻ ቋንቋ ፤ አጥብቆ ያወግዛል ፤ ይቃወማል ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ለመቼ ሊሆን ነው? –ግርማ በላይ

$
0
0

ግርማ በላይ – gb5214@gmail.com

Oromo amhara unity“ዝምታ ወርቅ ነው” – ጥሩ አባባል ነው፡፡ “ዝም አይነቅዝም” – ይሄኛውም ግሩም አባባል ይመስላል፡፡ “በለፈለፉ በአፍ ይጠፉ” – ጠንከር ያለ ሀበሻዊ መልእክት ያለው ነው፤ ፀረ ዴምከራሲያዊነቱም እንዲሁ ከሌሎቹ አየል ይላል፡፡ አዎ፣ የሀገራችን ሥነ ቃላችንም ሆነ አጠቃላይ ባህላዊ ትውፊታችን መናገርንና ሃሳብን በነፃነት መግለጽን አያበረታታም ብቻ ሣይሆን ክፉኛ ይኮንናል፡፡ በዚህም ሳቢያ ይሉኝታ እየገነነና ሀፍረትን እየወለደ “የዝምታ የዝምታ” የሚል አንደርብ የተደገመብን ይመስል ውስጥ ለውስጥና በየመሸታ ቤቱ እየተማማን እንኖራለን፡፡ ይህ ይትበሃል ደግሞ በሌላ በኩል ለአምባገነኖች ምቹ እየሆነና ለተተኪ ደቀ መዛሙርታቸውም መድረኩን እያበጃጀ በመረረ የጭቆናና የአፈና አዙሪት እንደተዘፈቅን የመከራ ሕይወት እንድንገፋ ያደርገናል፡፡ አሣዛኝ ዕጣ፡፡ ዘመን የማይሽረው የትውልድ መርገምት፡፡ ተራማጅና ተስፋ ሰጪ ልጆቻችንን በየዘመኑ እየቀጠፈ በስ(ዕ)ለትም ሆነ በጸሎት ሊለቀን ያልቻለ መጥፎ ሾተላይ፡፡ ቤተ መንግሥት ውስጥ ያለውም፣ ወደ ቤተ መንግሥት ለመግባት ወር ተራውን የሚጠብቀው ተስፈኛም የተሸመደመዱበት አገር አጥፊ ልክፍት፡፡

በዝምታ ዙሪያ የተነገሩ ፈረንጅኛ አባባሎችን ለዚህ መጣጥፍ ፈርጥነት ብዬ ድረገፅ ስዳስስ ቤንጃሚን ፍራንክሊን ተናግሮታል የተባለ ይህን ጥቅስ ሳገኝ ከሌሎቹ ይበልጥ ሳበኝ፤“Remember not only to say the right thing in the right place, but far more difficult still, to leave unsaid the wrong thing at the tempting moment.” በግርድፉ ወዳማርኛ ሲተረጎም “በትክክለኛው ቦታና ጊዜ ትክክለኛ ነገር መናገርህን ብቻ ከቁም ነገር አትቁጠር፤ ይልቁንም ፈታኝ በሆነ ወቅት አንተ እውነት ነው የምትለውን ነገር በዝምታ ማለፍህ ትክክል እንዳልሆነ አስታውስ፡፡” ትርጉሙን አወላግጀው ከሆነ ይቅርታ፡፡

የዛሬ አራት ይሁን አምስት ዓመት ገደማ የኢትዮጵያ ነፃነት እንደሸቀጥ ከየትም ሀገር በባቡርም ይሁን በመኪና ተጭኖ ሊመጣ እንደማይችልና በተለይም ከኤርትራ ደግ ነገር መጠበቅ የዋህነት መሆኑን በቁጭት ስናገር የደረሰብኝ ውርጅብኝ አሁን ድረስ ይታወሰኛል፡፡ እኔ ብቻ ሣልሆን በአገላለጻችን ክረት እንለያይ እንደሆነ እንጂ ደምስ በለጠ የሚባል ጋዜጠኛ እንደሆነ የሚናገር አንድ ዲያስጶራና አቶ ጌታቸው ረዳ የተባለ የአንድ ድረገፅ አዘጋጅ ጨምሮ አንዳንድ ወገኖች በጊዜው በዚህ ጉዳይ ይጮኹ ነበር፡፡ ግን ሰሚ አልተገኘም፡፡ ይባስ ብሎ እነሱን በእርጋታ ከማስረዳት ይልቅ በነገር ጦር ቀንድ ቀንዳቸውን የሚመታ ነውጠኛ የድርጅት አፍቀሪ ይበዛ እንደነበር ትዝ ይለኛል – ለማንኛውም ሌላ ምርጫ ስላልነበረን “ይሁንላቸው” ብለን ዝም አልን፤ ዝምታችን ግን ዋጋ ቢስ ሆኖ እነዚያ በረሃ ወረዱ የተባሉ ነፍጥ አንጋች ወንድምና እህቶቻችን በነዚህ ሁሉ የትግል ዓመታት ከአዲስ አበባ ታክሲዎች የጥቅስ ትግል ያልዘለለ እንዲያውም ያነሰ ውጤት ማስመዝገባቸውን ስንረዳ ዝምታችንን መስበርን ወደድን፡፡ አዎ፣ “ከላይ ነው ትዛዙ ብለን ዝም አልን” ወይም “ይህም ሁሉ ያልፋል” የሚል ጥቅስ የለጠፈ ሚኒባስ ታክሲ በረሃ ወረድኩ ካለና በአሥር ዓመት ውስጥ አንድም የሙሽት ሊሆን የሚበቃ የድል ብሥራት ሊያሰማ ካልቻለ ወይም እንዲያሰማ “ካልተፈቀደለት” ታጋይ የበለጠ ሥራ ሠርቷል ቢባል ማጋነን አይደለም ፡፡ የአእምሮ ዕድገት መገለጫው አንዱ በንግግር መግባባት መቻልና አለመግባባት ቢፈጠር እንኳን በሃሳብ ተግባብቶ ላለመደራረስ በጨዋ ደንብ መለያየት ነው፤ ከዚህ ውጭ ግን በነገር ጅራፍ እየተሞሻለቁ በጎራዎች መፈራረጅ ባህላችን ሊሆን ባልተገባ ነበር፡፡ በጤናማ አካሄድ የማትስማማበት ሃሳብ እንጂ የማትግባባው ሰው ሊኖር አይገባም፡፡ ሳትስማማ ስትቀር ደግሞ “እሱ ወያኔ ነው፤ እሷ ሻዕቢያ ናት፤ እነሱ አሸባሪና ትምክህተኞች ናቸው …” እየተባባሉ በርስ በርስ ግፍትሪያ መቆራቆሱ የምክንያታዊነትና የተጠየቃዊ አመክንዮ ጉድለት ማሳያ ነው፡፡

ያኔም ሆነ አሁን የኔ አቋም እንደያኔው ነው፡፡  በማይጨበጥ ተስፋ የሕዝብን ሆድ ከመቀብተት ባለፈ ከኤርትራ አቅጣጫ የሚመጣ ነፃነትና የነፃነት ዜና ከንፋስነት አያልፍም፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ችግር የተፈጠረበት ቤት ውስጥ መፍትሔ አይገኝም፡፡ ይህ አካሄድ የሚታመን መስሏቸው ወደዚያ አካባቢ በመሄድ ሕወታቸውን ለሻዕቢያ ጊሎቲን የሰጡ ንጹሓን ዜጎችን እግዚአብሔር በምሕረቱ ይጎብኛቸው፤ ኢትዮጵያ ብዙ ልጆቿን በሻዕቢያ ዐረመኔያዊ ውሳኔ አጥታለች – ሳያቀስ በማይለቅ ያደቆነ ሰይጣን የሚምልና የሚገዘት ጠላት መቼም ወዳጅ ላይሆን ብዙ የዋሃን ዜጎቻችን ውድ ሕይወታቸውንና ውድ ጊዜያቸውን ሰውተዋል – አሁንም ድረስ፡፡ የትሮይ ፈረስ ለመሆንና ላለመሆን ከሻዕቢያ ጋር በተደረገና በሚደረግ ግብግብ የጠፋው ነፍስና የኮሰመነው ስብዕና፣ የታየው ፈተናና የጫጫው የጋመ ተስፋ ይህ ክፉ ዘመን አልፎ አዲስ ዘመን ሲተካ በተራፊዎች መነገሩ አይቀርምና ለዚያ ያብቃን፡፡ አሁንም ለጭዳነት የተዘጋጁ ወገኖቻችንን አንድ መላ ፈጥሮ ፈጣሪ ከዚያ ምድራዊ ሲዖል ያውጣልን፡፡ ለእግዚአብሔር የሚሣነው ነገር የለምና ሁለቱንም ወንድማማችና እትማማች ሕዝቦች እግር ተወርች የፊጥኝ ከታሰሩበት የእሳት ሰንሰለት ፈልቅቆ አውጥቶ ለሚፈልጉት የነፃነት ዓይነት ያብቃልን፡፡ በተረፈ አሁንም ይህን ላም አለኝ በሰማይ አንጋጣችሁ የምትጠብቁ ሞኞች ካላችሁ መጠበቁ መብታችሁ ሆኖ እውነቱን ግን አድምጡ፡፡ ሻዕቢያ ውሉን የማይስት የኢትዮጵያ ጠላት መሆኑን ካልተረዳን ሀገራችን መቼም ነፃ አትወጣም፡፡

የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ በአንድ ታጋይ መታፈን ምክንያት የነፃነት ትግሉ በአንድ ዓመት እንዳጠረ በግልጽ ተነግሮን ነበር፡፡ ስለአፈናውና አፈናውን ተከትሎ ስለወጡ የአፋኝ አሳፋኝ ድራማ ትንታኔዎች ውስጥ አንገባም፡፡ ሕዝብ እንደአጠቃላይ የዋህ ነውና የቁርጥ ቀን ልጁን የመታፈን አሳዛኝ ዜና በሆዱ ዋጥ አድርጎ ይዞ የተገባለትን ቃል በጉጉት መጠባበቁን ቀጠለ፡፡ ያ አሳዛኝ ጊዜ ካለፈ ሁለት ዓመት ከሦስት ወር ገደማ ሆነው፡፡

“ቂጣም ከሆነ ይጠፋል፤ ሽልም ከሆነ ይገፋል” ይባላልና ያን ተስፋ ብንጠብቅ ብንጠብቅ ዐርባ ምንጭ አካባቢ የሆነች ኦፕሬሽን ተከናወነች ከመባል ውጪ አንድም ነገር ሳይታይ ጊዜው ክንፍ እውጥቶ ነጎደ፡፡

ይህ ትግል ከተጀመረ አሥር ዓመታትን ሊደፍን የቀረው ጊዜ ጥቂት ነው ወይም ደፍኖም ይሆናል፡፡ የጦር ሜዳ ውሎን ያካተተ አንድ ሁለገብ ትግል ፍሬ እስኪያፈራና ተጨባጭ ውጤት እስኪያሳይ ስንት ጊዜ እንደሚያስፈልገው በውል ለይቶ ማወቅ አስቸጋሪ ነው፡፡ እርግጥ ነው- – ሎራን ካቢላ የተባለ የኮንጎ ኪንሻሳ ዲታ ተጋዳላይ በ11 ወራት ውስጥ የሞብቱ ሴሴኮን መንግሥት ገልብጦ የሀገሪቱን ዘውድ ጭኗል፤ አሁንም እርግጥ ነው – ይሄው ሰውዬ ለላኪዎቹ የገባውን ቃል ባለማክበሩ ይመስላል በገዛ ታጣቂዎቹ እንዲገደል በዝግ ችሎት ተፈርዶበት በልጁ በጆሴፍ ካቢላ እንዲተካ ተደርጓል፡፡ እንደሰብኣዊና ቁሣዊ አቅርቦቱና እንደየታጋዩ የወኔ ልዩነት እንዲሁም እንደዓለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታዎችና እንደሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች ዓይነት አንድ የነፃነት ትግል ከጥቂት ቀናትና ሣምንታት ጀምሮ እስከ ሃያና ሠላሣ ዓመታት ሊፈጅ እንደሚችል ከታሪክ መዛግብት እንገነዘባለን፡፡ ከ30 ዓመታት በላይ የፈጀው የኤርትራ “ነፃነት”ና 17 ዓመታት ያህል የጠየቀው “የትግራይ ሪፐብሊክ ነፃነት” ለዚህ አባባል ጥሩ አብነቶች ናቸው፡፡ “ሕወሓት” የሚለው መጠሪያ የአነጋገሬን ትክክለኝነት የሚያሳይ ይመስኛል፤ አጠቃላይ ዝግጅታቸውም ወደዚያ የሚያመራ ስለመሆኑ ፍንጭ ይሰጣል፡፡

የኛ ግን ከዘጠኝና አሥር ዙር ሥልጠናዎችና ተያያዥ ምረቃዎችም በኋላ እዛው በረሃ ውስጥ ነን፡፡ ምሥጢሩ ምን ይሆን? የሰው ኃይል ችግር? የገንዘብ ችግር? የዕውቀት ችግር ? የሕዝብ ድጋፍ ዕጦት? የውጊያ ሞራል ማነስ? የወኔ ችግር? የአመራር ችግር? የመሣሪያ ችግር? ወይንስ ምን?… እውነቱን እንነጋገር፡፡ መሰዳደብና መፈራረጅ የትም አያደርስም፡፡ ሕዝብ ደግሞ የዝምብ ልጃገረድ ለይቶ የሚያውቅበት የግንዛቤ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ሕዝቡ አሁን ቆርጦ የተነሣው እንዲያውም ነፃ አውጪዎቹን ራሳቸውን ነፃ ለማውጣት ነው፡፡ በሰላማዊ መንገድም ይሁን በጦር ትግትግ ሕዝቡን ከወያኔ “ነፃ ሊያወጡት” የቆረጡትን ንቅናቄዎችንና ፓርቲዎችን በሙሉ ነፃ ሣያወጣ ይህ በየአካባቢው ከወያኔ የአጋዚ ጦር ጋር የሚፋለም ሕዝብ ወደ ቤቱ የሚመለስ አይመስልም፡፡ ኢትዮጵያ የተቃርኖዎች ሀገር ናት፤ “ነፃ አውጭዎች” በዚህና በዚያ ቀያጅ አስተሳሰብና ጠንጋራ አመለካከት ተጠልፈው ሲሽመደመዱ ሕዝቡ ሊታደጋቸው ቆርጦ ተነሣ፡፡ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ እነዚህ ሁሉ በመቶዎች የሚገመቱ በሀገር ውስጥም በውጪም እንደጉንዳን የሚርመሰመሱ “ነፃ አውጭዎች”ና የሲቪክና የሃይማኖት ተቋማት በቅርብ ጊዜ ውስጥ ከየታጎሩበት እሥር ቤት ነፃ ሲወጡ ይታየኛል – በሕዝብ ትግል፡፡

ያልተቀየደ ነፃ አውጪ ጦር ቢኖረን ኖሮ ታጋዩ ጦር ሠፍሯል ከተባለበት የኤርትራ ግዛት በጥቂት ኪሎ ሜትር ሬዲየስ ውስጥ ወያኔ ያፈናቸው ወጣቶች በርሀብ፣ በዱር ዐውሬ፣ በግርፋትና በጥይት እያለቁ ባልተገኙ ነበር – ይህንንም ውሸት በሉና አስደምሙኝ፡፡ የጎንደርና የጎጃም ጠቅላይ ግዛቶች ግዳጅ የሚሰጠው አጥቶ በረሃ ውስጥ “ለሚርመሰመሰው” ነፃ አውጪ ጦር በጣም ቅርብ ናቸው፡፡ መቼም ከዐርባ ምንጭ ይልቅ መተከል ለኤርትራ በረሃዎች ሳይቀርብ አይቀርም፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ይልቅ ብር ሸለቆ ለሰሜን ኢትዮጵያ ይቀርባል፡፡ ምናልባት እኮ ወጣቱ ሆ ብሎ በወያኔ ላይ የእምቢተኝነት ዐመፅ የጀመረው ነፃ በሚባሉ የተቃውሞው ጎራ ሚዲያዎች የሚናፈሰውን የሁለገብ ትግል ቅስቀሳ አዳምጦና በዚያ ተመክቶም ሊሆን ይችላል – ስለዚህ ለሕዝባዊ መነሳሳቱ አስተዋፅዖ ያደረገ አካል ስቃይና መከራውንም ሊጋራው በተገባ ነበር(እነዚህ ሚዲያዎች ታሪክ ሲዘክረው የሚኖር ጉልኅ አወንታዊ ሚና መጫወታቸውን እዚህ ላይ መግለጽ ይኖርብኛል – ችግሩ በተግባር አለመደገፋቸው ነው)፡፡ እንግዲህ እንደንብ ከቀፎው ያወጣነው ወጣት በዐረመኔው የወያኔ አጋዚ ጦር ሲገደልና ሲሰቃይ አሁን ያልደረስንለት መቼ ልንደርስለት ነው? ሕዝብ በባዶ እጁ እየወጣ ካለቀ በኋላ ማንን ነው ነፃ የምናወጣው? አሁን ጥያቄው የነፃነት ጉዳይ ብቻ አይደለም – የተቃዋሚዎች የራሳቸው ኅልውና ጥያቄም ጭምር ነው፡፡ ከወረቀትና ከአልፎ አልፎ መግለጫ ባለፈ በርግጥም “እንዲህ እንዲህ ያለ አበረታች እንቅስቃሴ አለ ወይ?” ተብሎ ቢጠየቅ መልስ እንዳይቸግረን እፈራለሁ፡፡ ቀናት ሣምንትን፣ ሣምንታትም ወራትንና ዓመታትን እየተኩ በአበበ ተ/ሃይማኖት አነጋገር እንዲሁ እየተበሳበሱ መኖር ከተፈለገ ያ ሌላ ነገር ነው፡፡ እውነቱን መናገር ካስፈለገ ግን ከዚህ ጊዜ ሌላ ምቹ የትግል ወቅት ሊኖር ስለማይችል በረሃ የወረደና መሬት ላይ የሚታይ የነፃነት ትግል ቢኖር ኖሮ በአሁኑ ሰዓት ወያኔ ቀርቶ የሥምሪት ኃላፊዎቹ አብርኆታውያን ተብዬዎቹ ራሳቸው ሳይቀሩ ኢትዮጵያን አይረግጡም ነበር፤ ለነገሩ ለማንም ደንታ ባይኖራቸውም ሕዝባዊ ጅራፉን እነሱም እየቀመሱት ነው ፡፡

 

እንደኔ የዚህ ዕንቆቅልሽ መሠረት እንዲህ ይመስለኛል፤ ይህን ግሩም ጥቅስ እናንብ፡፡

 

የሕወሓት ከፍተኛ ልዑካን ከሻዕቢያ ተወካዮች ጋር ያደረጉትን ውይይት በተመለከተ ለሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መግለጫ ሲሰጡ፣ በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ ሻዕቢያዎች የመሣሪያ ዕርዳታ ሲጠይቋቸው፣ በተለይ ኢሳይያስ አፈወርቂ “የማይቆጣጠሩትን ድርጅት መርዳት አይቻልም፤ ዕርዳታ ሲሰጥ ከበስተጀርባው የፖለቲካ ዓላማህን የማስፈጸም አንድምታ መኖር አለበት፡፡” ብሎ እንዳለ ገልጸው ነበር፡፡ ይህ የኢሳይያስ አባባል በወቅቱ ክብደት ባይሰጠውም የሻዕቢያዎች ፍላጎት የጋራ ጠላታቸው የሆነውን ደርግን ለማዳከም ሕወሓትን ሊጠቀሙበት እንጂ ጠንክሮ ራሱን የቻለ ኃይል ሆኖ እንዲወጣ እንዳልነበር በግልጽ ያሳያል፡፡ ( አፅንዖት የተጨመረ) ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ፣ ገብሩ አሥራ፣ ገጽ 92

 

ይህ ጥቅስ ብቻውን ብዙ መጻሕፍትን ያህል ብዙ ነገር በግልጽ ይናገራል፡፡ ኤርትራ የገቡ የነፃነት ታጋዮችም የውኃ ሽታ እየሆኑ መቅረት ከዚሁ የሻቢያ ሊለወጥ የማይችል ግትር አቋም ጋር የተያያዘ ለመሆኑ ከዚህ በላይ ኅያው ማስረጃ የለም፡፡ ቀደም ሲል የወጡ “ጥቁር ጫካ” በሚል ብዕር የወጡ ጽሑፎችም ሆነ በኢሳይያስ ሣንጃ ታርደው በኤርትራ በረሃ የወደቁ ኢትዮጵያውያን ደም የሚመሰክረውም እውነት ይህንኑ ነው፡፡

በመሠረቱ የሚሳካላቸው መስሏቸው የሞቀ ቤታቸውንና የሞቀ ትዳራቸውን እርግፍ አድርገው ጥለው ወደዚያ የሄዱ ወንድሞቼንና እህቶቼን አደንቃለሁ – እኔ ላደርገው ያልደፈርኩትን በማድረጋቸው የኔን መስቀል ተሸክመዋልና እመብርሃን ከነልጇ ትራዳቸው፡፡ የእናታቸውን በወያኔ መታረድ ያስጣሉ መስሏቸው፣ የተሻለ ሌላ አማራጭም አጥተው ለከፋ አራጅ በመዳረጋቸው ግን ሊታዘንላቸው እንደሚገባ እረዳለሁና በጸሎታችን ዘወትር እናስባቸው፡፡ የኢትዮጵያ ነፃነት መቼም ቢሆን እንደተደበቀ አይቀርምና ያኔ እነዚህ ወገኖች በዚህ ሙከራቸውና ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው ባደረጉት ጥረታቸው ብቻ የግርማ ሞገስ አክሊል እንደሚጎናጸፉ አምናለሁ፡፡ እነዚህ ወገኖች ከአጋም ተጠግቶ እንደበቀለ ቁልቋል የገና ዳቦ ሆነው ከሁለት ወገን በሚደርስባቸው ስቃይ ሲያለቅሱ መኖርን የመረጡት ሌላ አማራጭ ከማጣት አንጻር መሆኑን እንረዳላቸዋለን፡፡ ነገር ግን የሻዕቢያን ተፈጥሮ ለሚያውቅና ሻዕቢያ ለኢትዮጵያ ያዘጋጀላትን የመቶ ዓመት የቤት ሥራ ለሚገነዘብ ወገን በኤርትራ በኩል መልካም ነገር ይገኛል ብሎ ማሰብ እንደማይቻል ጊዜ ራሱ በግልጽ እየነገረን ነው፡፡ ከዚህ ጊዜ በላይ ምቹ የትግል ወቅት እንዳለመኖሩ ሌላው ቀርቶ 40 እና 50 ሺህ ጦር እንዳለው የሚነገርለት ዴምህት የሚባለው ሌላው ላም አለኝ በሰማይ አሁን የት እንዳለና ምን እየሠራም እንደሆነ ከሰይጣን ምናልባትም ከእግዚአብሔር በስተቀር ማንም አያውቅም፡፡ ለዚህም ነው ይሄ ዶሮ ማታ ዓይነት ፖለቲካ እንደማያዋጣና እውነቱን መጋፈጥ ብቻ ተገቢ እንደሆነ ብዙ ወገኖች በድፍረት የሚናገሩት – (ዶክተር አሰፋ ነጋሽም አሁን ትዝ አለኝ)፡፡ ባህላችን ደግሞ አሣሪ እየሆነ ተቸገርን፡፡ “ዝም በል” እየተባለ ያደገ “ዝም በል!” ይላል እንጂ ሊያዳምጥህ አይፈልግም፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉም የስሜት አምባላይ ፈረስ እየጋለበና በራሱ ጠባብ ዓለም እየተመመ አንዱ ሌላውን ማዳመጥ አልቻለም፡፡ ደግነቱ ፈጣሪ ጥሎ እንደማይጥለን አምናለሁ እንጂ ተያይዘን ወደገደል እየገባን እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ …

ከፍ ሲል ለመግለጽ እንደተሞከረው ከቅርብ ወራት ወዲህ ሕዝቡ ራሱ ፖለቲከኞችን ሳይቀር ከየተረፈቁበት የጎጥና የሸጥ እንዲሁም ያረጀና ያፈጀ ሸውራራ አመለካከት ነፃ ሊያወጣቸው የራሱን እርምጃ መውሰድ ጀምሯል፡፡ በፊት ፊት ፊት ጡዝ ጡዝ ይል የነበረ ከውካዋ የፖለቲካ ድርጅት ሁላ ዛሬ ዛሬ በሀፍረት ጅራቱን ወትፎ ከሕዝቡ ኋላ ቱስ ቱስ ማለት ይዟል፡፡ ወደፊት ብዙ የሚታይ ነገር ያለ ይመስለኛል፡፡

ምሥረታው ከሻዕቢያም ቀደም ይላል የሚባልለት ኦነግ በዚህ በ50ዎች ዓመታት በሚቆጠር ዕድሜው አንዲትም ወረዳ ሊይዝ ያልቻለበት ምክንያት የዓላማና ግቡ ልልነት እንደሆነ ይነገራል፡፡ በአእምሮ መዳበር ያልተመሠረተ ነገር ሁሌም እንደጫጫና መጫጫቱንም ለመሸፈን ሁሌም ጉልበት እንደተጠቀመ መኖሩ የሚታወቅ ነው፡፡ የሀገራችን ፋኖዎች በሙሉ በዚህ ይታወቃሉና እማኝ መቁጠር አያስፈልግም፡፡

ኦነግ ከወያኔ ጋር ተሻርኮ አዲስ አበባ እንደገባ ያኔ በ83 ግድም እንዲህ ሆነ አሉ፡፡ አንድ አካባቢ ቡና ቤት ውስጥ ጓደኛሞች ያወራሉ – መጠጥ ላይ፡፡ በወሬያቸው መሀል ላይ አንደኛው “ኤዲያ፣ ኦነግ ማለት እኮ ደካማ ድርጅት ነው …” ሲል አጠገብ የነበረ የኦነግ አባል ሰምቶ ኖሮ ድርጅቱ “ጠንካራነቱ”ን ሳይውል ሳያድር አሳዬ፡፡ የሆነው ምንድነው – ያ ኦነግን የተቸው ሰው ቤቱ አልገባም፡፡ ተከታተሉና አርደው በድኑን በማዳበሪያ ከትተው ጉድባ ውስጥ ጣሉት፡፡ የድርጅት ዕድገትና ጥንካሬ ማለት እንዲህ ነው እንግዲህ፤ ሕዝብን ነፃ ለማውጣት የቆመ፣ ለሕዝብ የመናገርና የመጻፍ መብት የተነሣ ድርጅት ማለት እንዲህ ነው፤ ለዚህ ለዚህማ ደርግና ከርሱም በፊት የነበረው የዐፄው መንግሥት ይሻሉ አልነበረምን? “በጊዜ የጮኸ ጅብ አያሳድረኝም” ይባላል፡፡ እንደዚህ ያሉ ደመ ሞቃት ድርጅቶች ገና ከአሁኑ እንዲህ የጨከኑ ሀገራዊ ሥልጣን ቢይዙ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ ይታያችሁ፡፡ የአንድን ነገር ጅማሮ መድረሻውን ለመገመት መነሻውን ማየት ብቻ በቂ ነው፡፡ በዚህ ቅኝት የሚጓዙ ድርጅቶችና ተከታዮቻቸው ሞልተዋል – ዋጮን ለመገልበጥ ባለ በሌለ ኃይላቸው የሚጓዙ ደምባራ ፈረሶች ሕዝብን ጉዳት ላይ እንደሚጥሉ በተደጋጋሚ አይተናል፡፡ ይህ ዓይነቱ የየጁ ደብተራ ዓይነት ዕድገት በሁሉም የፖለቲካና የሃይማኖት ድርጅቶቻችን ዘንድ በስፋት የሚዘወተር ነው፡፡ ሃሳብን በሃሳብ፣ ነገርን በነገር፣ ዕውቀትን በዕውቀት፣ አመለካከትን በአመለካከት እንደመሞገት ቅኔው ጎድሎበት ቀረርቶ ጨመረበት ተብሎ እንደሚቀለድበት የፈረደበት የየጁ ደብተራ የጎፈነነ ስሜታችንን ሲቻል በግድያ ያ ሳይቻል ሲቀር በስድብና በዛቻ የምናወጣ ገልቱዎች ቁጥር ሥፍር የለንም፡፡ ይህ የውርደት እንጂ የዕድገት ምልክት አይደለም፤ የዝቅጠት እንጂ የብስለት ማሳያም አይሆንም፡፡

ለማንኛውም ኦነግም ቢሆን በእስካሁን አካሄዱ ሕዝብን አስተባብሮ የመነሣትና ለድል የማብቃት ተፈጥሯዊ ችሎታው ዝቅተኛ ነው፡፡ ከሕዝብ በሚያንስ የፖለቲካ ድርጅት ሀገርና ሕዝብ ነፃ አይወጡም፡፡ ሕዝብን በዘርና በጎሣ፣ በጎጥና በቋንቋ፣ በባንዲራና በሃይማኖት እየከፋፈሉ ወያኔን አስወግዳለሁ ማለት ቅዠት ነው፡፡ የጠገበ አንበጣ አንስተህ የተራበ መዥገር በመትከልም ነፃነትን እውን አታደርግም፡፡ የሰከነ ፖለቲካ ለማምጣት ከስሜትና ከሆይሆይታ በመራቅ በአስተውሎት መራመድን፣ ከሁሉም ጋር መመካከርንና መግባባትን ይጠይቃል፡፡

የሆኖ ሆኖ ለኔ እንደሚታየኝ ነፃነታችን በአንድዬ እጅ ናት፡፡ የነፃነት መምጣት ደግሞ የቀን ጉዳይ እንጂ ማንም ሊያስቀራት አይችልም፡፡ ሕዝቡ በጀመረው ፍልሚያ ይቀጥል፤ የበቁ አባቶች በየበዓታቸው ልባዊ ጸሎታቸውንና ምህላቸውን ያድርጉ፤ ከክፋትና ከተንኮል ርቀን ወደፈጣሪያችን እንመለስ፤ አንዱ አንዱን አይበድል፤ የተጣላንና በነገር የተቋሰልን  በይቅርታና በዕርቅ ቁስሎቻችን እንዲሽሩ እናድርግ፣ ከሁሉም በላይ ፍቅርና መተዛዘን ይኑረን፤ ነጋዴው በአንድ አዳር ለመክበር የሚያደርገውን ማተብየለሽና ይሉኝታቢስ ሩጫ አቁሞ የሸማቹን የመግዛት አቅም ይመልከት፤ሥራችንን እናክብር፣ ለትውልድና ለሀገር የመቆርቆር ነባር ልማዳችንን እንመልስ፤ ከተናጠል ሩጫ ሶበር ብለን ለጋራ ሕይወት በጋራ እናስብ፣ ሞልቶ ለማይሞላ ሆድ ስንል ሀገርንና ወገንን አንክዳ፣ አንገትም ዐይንም ይኑረን … ያኔ እግዚአብሔር ፊቱን ወደኛ ይመልስልናል፤ ያኔ በምሕረት እጆቹ ይዳብሰናል፤ ያኔ “የአንዲት ላም ወተትና የአንድ ማሣ ሰብል” ለብዙዎች የሚበቃበት የበረከት ጊዜ ይመጣልናል፡፡ በያዝነው መንገድ ከቀጠልን ግን እመኑኝ ዕድሜያችን ግፋ ቢል አምስት ወይ አሥር ዓመት ቢሆን ነው፡፡ አሁንም ቢሆን እንዳን አንቆጠርም – ካልዋሸን በስተቀር ጠፍተናል፤ እንደሀገርም ሆነ እንደሕዝብና እንደማኅበረሰብ በቁማችን ሞተናል …

መልካም አዲስ ዓመት፡፡ ዓመቱ የነፃነትና የብልጽግና ይሁንልን፡፡ በ2010 አንደኛው የመባቻ ወር ላይ “አምና ወያኔ ከሥር መሠረቱ የተነቀለበትና ነፃነታችን የተበሠረበት ዓመት ነበር” ብለን የመጀመሪያውን እውነተኛ የነፃነት ክብረ በዓል በድምቀት ለማክበር ያብቃን፡፡

የወቅቱ ፖለቲካዊ አሰላለፍና ፋይዳው –በተክሉ አባተ (ዶ/ር)

$
0
0

 

መግቢያ

gondarprotest200የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል እየሰፋና ቀጣይነቱን እያረጋገጠ ሲሄድ በውጭው ዓለም የሚገኙ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ባህርያቸውን ይበልጥ እየገለጡ መጥተዋል። ግለሰብ ተኮር እንቅስቃሴዎች ወደ ድርጅት ወይም ማኀበር ወይም ኅብረት እየተለወጡ ነው። ይበልጥ ትኩረት እየሳበ የመጣው ግን የድርጅቶቹ ብዛት ሳይሆን የተነሱበት ዓላማ ወይም ግብ ነው። የአንዳንዶች የትግል ባህርይ ከተጠበቀው በአንፃሩ ሆኖ በመገኘቱ ጥቂት በማይባሉ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ቁጣና ግርምትን ፈጥሯል። ይህን ተከትሎ ክርክሮችና ተግሳጾች በመገናኛ ብዙኃን እየወጡ ነው። እኒህ አይነት እንቅስቃሴዎች ትግሉ ምን ያህል ሰላማዊና አንድነትን የተላበሰ እንደሚሆን ካሁኑ ግርታን ፈጥረዋል። ዳሩ ግን እስካሁን ድረስ ወቅታዊ የፖለቲካ አሰላለፎችን ባህርይ ከነዓላማቸው ዘርዘር ባለ መልኩ ያቀረበ የለም።

ይህ አጭር ጽሑፍ የፖለቲካው አሰላለፍ ምን እንደሚመስልና ንጹህና ውጤታማ ሽግግር ለማምጣት ሊኖረው የሚችለውን ፋይዳ ምን ሊሆን እንደሚችል ይጠቁማል። ይህም ልዩነቶቻችንን ያለምንም መሸፋፈን በይፋ ለውይይት ለማቅረብ ሊረዳ ይችላል። እንዲህ አይነት ውይይቶችም የጋራ መግባባትና ግንዛቤ በመፍጠር ትግሉን ይበልጥ ሊያቀላጥፉ ይችላሉ።

ቀጥታ ወደዋናው ጉዳይ ከመግባቴ በፊት ቀጥለው የተዘረዘሩትን ማሳሰቢያዊ ነጥቦች ላንሳ!

  • ይህ ጽሑፍ በማኅበራዊ ሚዲያዎች እንዲሁም በቴሌቪዢንና በሬዲዮ የተደረጉ ውይይቶችንና ጽሑፎችን እንደ መረጃ ተጠቅሟል
  • ጽሑፉ ከኢትዮጵያ ውጭ የሚገኙ ስለኢትዮጵያ ሕዝባዊ ትግል ስለሚያሳስባቸው ድርጅቶች ቢሆንም ሁሉንም ለመቁጠር ዓላማ የለውም ዋና ዋናዎችን ግን ለዐብነት ይጥቅሳል
  • ጽሑፉ የሚያወግዘው ወይም የሚደግፈው ድርጅት ወይም ግለሰብ የለም። ዳሩ ግን ለምሳሌነት የቀረቡ ይኖራሉ። ይህም ቢሆን ዓላማው አንባቢያን የራሳቸውን ግምት ወይም ግንዛቤ እንዲወስዱ እንጅ አድሎ እንዲያደርጉ አይደለም
  • የጽሑፉ ዋና ዓላማ ሕዝባዊ ትግሉን ለማገዝ እየተደረጉ ያሉትን አካሄዶች ከአገራችን ጥቅም አኳያ እንድንመረምራቸው መጋበዝ ነው

ፖለቲካዊ አሰላለፎች

ጠቅለል ባለ መልኩ ስንመለከተው ፖለቲካዊ አሰላለፎች ሁለት ትይዩና የማይገናኙ ዐበይት መስመሮችን ይዘዋል። መስመሮቹ ከዚህ በፊት የሚታወቁ ቢመስሉም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ገዝፈው አካል ይዘው እየታዩ ነው። አንዱ መስመር ከሌላው በአንፃሩ የተሰመረ ስለሆነ ተቃርኗቸው ከባድ ቀውስ ሊያመጣ የሚችል ነው። ዳሩ ግን መስመሮቹ በውስጣቸው ሌሎች ተደራቢ ንዑስ መስመሮችም አሏቸው። እነዚህ ዐበይትና ንዑሳን የፖለቲካ አሰላለፎች ብዥታና ጥርጣሬ  እየፈጠሩ ስለሆነ ለሰከነ ውይይት ከዚያም መግባባት ማብቃት ይጠበቅብናል። ችላ ብለናቸው ወይም አለባብሰናቸው ብንሄድ ጠልፈው ይጥሉናል። ካሰብነው እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታም በእጅጉ ይገቱናል።

ከዚህ ቀጥሎ በግልጽ መታየት የጀመሩትን ፖለቲካዊ አካሄዶች መነሻቸውና መድረሻቸው ምን እንደሆነ ባጫሩ ላቅርብ! ከዚያም የትኛው አካሄድ አዋጭ ወይም አክሳሪ ሊሆን እንደሚችል እጠቁማለሁ።

መስመር 1 ሕብረ ብሄራዊ

ይህ መስመር መነሻውና መድረሻው ሁሉንም ብሄረሰቦች በእኩልነት አቅፋ በሰላምና በብልጽግና የምትኖር ኢትዮጵያን መመስረት ነው። በሕዝቦች መካከል ያሉትን ታሪካዊና ወቅታዊ ልዩነቶች በውይይት በመፍታት ለሁሉም እኩል ተጠያቂና አገልጋይ መንግስት  መመስረት ዋና ዓላማው ነው። በመሆኑም ልዩነቶችን አቻችሎ ሙሉ ሃይልን ያለውን መንግስትን መጣል ላይ ማሳረፍ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው ለዚህ አሰላለፍ። በዚህ መስመር ከሚጓዙ በርካታ ድርጅቶች መካከል አርበኞች ግንቦት ሰባት፣ ሸንጎ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት፣ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ፣  ኢሕአፓ ዋነኞቹ ናቸው።

መስመር 2 ብሄር ተኮር

ይህ መስመር መነሻው አንድ አይነት ሲሆን መድረሻው ግን የተለያየ ነው። በዚህ መስመር ስር ንዑሳን መስመሮች አሉ። በሕዝቦች መካከል ያሉት ታሪካዊና ወቅታዊ ልዩነቶች ትልቅ ቦታ ይሰጣቸዋል። ያለውን መንግስትን መጣል ቅድሚያ መሰጠት እንዳለበት ቢያምኑም መናበብ ግን አይታይባቸውም።በአንዱ መስመር የተሰለፉት በሌላው መስመር የተሰለፉትን በጥርጣሬና በስጋት ይመለከታሉ። በግልጽ ቃል በቃል ባይናገሩም ፉክክር ውስጥ የገቡ ይመስላሉ። በመስመር 2 እየተጓዙ ያሉት በዋናነት ኦሮሞውንና አማራውን እንደሚወክሉ የሚናገሩ ድርጅቶች ናቸው። ያላቸውን ልዩነት አጥርቶ ለማየት ይረዳ ዘንድ ጥቂት ማብራሪያ ልጨምር!

ኦሮሚያ

በውጭው ዓለም የኦሮሞን ማኅበረሰብ ከማንም ተቋም ወይም ድርጅት በላይ እያስተባበረ የሚገኘው ጃዋር ሙሐመድ በሥራ አሥኪያጅነት የሚመራው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ነው ቢባል አይጋነንም።   ይህ የሚዲያ ተቋም አንድ የፖለቲካ ድርጅት ከሚሠራው ያልተናነሰ ይሠራል። በውጭው ዓለምና ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖረውን የኦሮሞ ወገን እያገለገለና ተቀባይነትን እያተረፈ ይገኛል።

ከበርካታ ሥራዎቹ ውስጥ ክርክርና ብዥታ ያመጣው ቅርብ ጊዜ ጃዋር በሚኒሶታ ያደረገው ንግግር ነው። ብዙዎች ንግግሩ ኦሮሚያን እንደ አገር ሊመሰርት የሚችል ቻርተር እየተዘጋጀ እንደሆነና ቅርብ ጊዜም በዚሁ ላይ ለመወያየት በተለያዩ አገሮች የሚኖሩ የኦሮሞ ወገኖች ለስብሰባ እየተዘጋጁ እንደሆነ ተረድተዋል። አንዳንዶች ደግሞ የኦሮሞው ማኅበረሰብ ትግሉን በተመለከተ በመካከሉ የጠራ መግባባት እንዲኖር ለማድረግ የተዘጋጀ ሰነድ እንደሆነ ገምተዋል። ጃዋርም የሰጠው ማስተባበያ ብዥታውን የሚጨምር እንጅ የሚያብራራ አይደለም።

ያም ሆነ ይህ እየተዘጋጀ ያለው የስብሰባ ጥሪ ማስታወቂያ እጅግ ግልጽ የሆኑ ነጥቦችን አስቀምጧል። ኦሮሚያ በቅኝ ግዛት የተያዘች አገር እንደሆነች ወዘተረፈ ያትታል። ይህን በተመለከተ ዶ/ር ተድላ በጥሩ ሁኔታ ጃዋርን ሞግቷል። ምንም እንኳን ባንዳንድ መድረኮች ከአንድነት ሃይሎች ጋር አብሮ  እንደሚሠራ ለማብሰር እጅ ለእጅ ቢጨባበጥም የጃዋር የፖለቲካ መስመር ከብሄር የዘለለ እንደሆነ የሚያሳይ አሳማኝ ነገር አልታየም። እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ኦሮሚያ እንጅ ኢትዮጵያ ተኮር አይደለም። አዎ አንድ ጉዳይ ግን ማንሳት ይቻል ይሆናል! የጃዋር ንግግሮችና ጽሑፎች ሁሉ የራሱን ወይም የሚመራውን ሚዲያ አቋም እንደሚያንጸባርቁ  አይታወቅም።

አማራ

ለመጀመሪያ ጊዜ ለአማራው ደኅንነት የቆመ ድርጅት የተቋቋመው በፕሮፌሰር አስራት ተጋድሎ  ነበር።  ዓላማውም ከሌሎች የኢትዮጵያ ነገዶች ፍጹም በተለየ መልኩ ሕወሓት በአማራው ላይ የሚያደርሰውን የተቀነባበረ ግፍ ለመቋቋም ነበር። ዓላማቸውን በደንብ ሳያሳኩ ራሳቸው የግፉ ቀማሽ ሆነው ያለእድሜያቸው አርፈዋል። ከዚያ በኋላ ድርጅቱ ብሄራዊ አጀንዳ እንዲይዝ ተደርጓል። በአማራ ነገድ ስምም ድርጅት ማቋቋም የማይታሰብ ሆኗል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ስለአማራው የሚያስቡና የሚሠሩ ተቋማት ተፈጥረዋል። ዓላማቸው አማራውን «ከፈጽሞ መጥፋት» ማዳን እንደሆነ ቢያብራሩም ግባቸውና አካሄዳቸው ግን ይለያያል። ሞረሽ ወገኔ  የዐማራ ድርጅት የዐማራውን ደኅንነትና ጥቅም አስከብሮ ከሌሎች ነገዶች ጋር በእኩልነትና በአንድነት እንዲኖር እንደሚታገል አሳውቋል። በመሆኑም ይህ ድርጅት መነሻው ነገድ ቢሆንም መድረሻው ኢትዮጵያ ናት።

ቤተ ዐማራ የተባለው ድርጅት ደግሞ  መነሻውም መድረሻውም የዐማራው ነገድ ይመስላል። ልክ እንደ  ሞረሽ ወገኔ ዐማራው በእውነትም በልዩ መንግስታዊ ጥቃት ውስጥ እንደሚገኝ ያምናል። ተጨባጭ ማስረጃዎችንም ያቀርባል። ዳሩ ግን መድረሻው የዐማራን መንግስት ማቋቋም እንደሆነ ያብራራል። ዐማራው ሌት ተቀን ስለኢትዮጵያ እያሰበ ለራሱ ግን የተጠቀመው እንደሌለ ያስረዳል። እንዲያውም ኢትዮጵያዊነቱ በሌሎች ዘንድ እንደ ጠላት እንዲታይ እንዳደረገው ይሞግታል። እንዲሁም ባሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ እንደ አገር እንደሌለችና በጽንሰ ሀሳብ ብቻ እንደምትገኝ ይከራከራል። በመሆኑም ዐማራው የራሱን እድል በራሱ መወሰን እንደሚገባው ዳሩ ግን አብረው መኖር የሚፈልጉ ነገዶች ካሉ እንደሚያስተናግድ ይጠቁማል። ከዚህ ባሻገር የትግል ግባቸውና ስልታቸው ገና ፍንትው ብሎ  ያልወጣው የጎንደር ኅብረት፣ የጎጃም ኅብረት፣ የወሎ ኅብረት የሚባሉ ድርጅቶችም እየተንቀሳቀሱ ነው።

አዋጭው መስመር

ወደ ዋናው ነጥብ እንግባ! ከተዘረዘሩት የፖለቲካ መስመሮችና አሰላለፎች ውስጥ ዘላቂና ስኬታማ እንዲሁም ሰላማዊ ሽግግር ሊያስገኝ የሚችለው የትኛው ነው? ይህ ጥያቄ እጅግ ከባድ ቢሆንም የኢትዮጵያን ታሪክ እንዲሁም ወቅታዊ ክስተቶችን ግምት ውስጥ በማስገባት የራሴን ግንዛቤ ላቅርብ።

1ኛው ተመራጭ መስመር

የሕወሓትን አምባና ብሄር ገነን መንግስት በእውነተኛ ሕዝባዊና ዲሞክራሲያዊ መንግስት ለመተካት እጅግ ተወዳጁና አዋጩ መስመር የመጀመሪያው ነው።  የብሄረሰቦችን ማንነትና ምንነት አክብሮ  አንዲት ኢትዮጵያን ዳግም መመስረት ቀጥለው ስለተዘረዘሩትና ስለሌሎችም ምክንያቶች እጅግ ማራኪ ነው።

  • ኢትዮጵያዊነት እጅግ የተለመደ ጽንሰ ሀሳብ ስለሆነ የሕዝባችንን ይሁንታ ለማግኘይ እጅግ ይቀላል
  • ኢትዮጵያዊነት ሁሉም ነገዶች የሚጠለሉበት ጃንጥላ ስለሆነ ስጋትና ጥርጣሬን ያስወግዳል
  • አረመኔውን መንግስት በተባበረ ክንድ ቶሎ ለመጣል ያስችላል
  • ከድንበር ጋር በተያያዘ ሊኖር የሚችለውን አላስፈላጊ የእርስ በርስ ጦርነትን ያስቀራል
  • ከተለያዩ ነገዶች የተመሰረቱ ቤተሰቦች በአንድነትና በፍቅር ይጸናሉ
  • ችግርን በውይይትና በአንድነት ከመፍታት አኳያ ለልጅ ልጆቻችን አርአያ እንሆናለን
  • ያለንን እምቅ ሀብት ባግባቡ ለመጠቀም ያስችለናል
  • ለምሥራቅ አፍሪካና ለመላው ዓለም የሰላምና የእድገት ተምሳሌት ሆነን እንታያለን
  • በነዚህ ሁሉ ጥቅሞች የተነሳ የሞራል ልዕልና የአእምሮ ጤንነት እናገኛለን

ይህ መስመር በጽንሰ ሀሳብ ደረጃ ከሌላ ከምንም መስመር ጋር አይወዳደርም። ምጡቅና የሚታለም ነው። ዳሩ ግን መሬት ላይ ያሉ እውነታዎችን ስንመለከት ይህ መስመር ተግባራዊ የሚሆን አይመስልም። ላለፉት 25 ዓመታት ኢኮኖሚው፣ ፖለቲካው፣ ማኅበራዊ ኑሮው፣ ሃይማኖቱ፣ ትምህርቱ ወዘተ በዘር መነጽር ሲታይ ቆይቷል።  ይህም እቅድ ወጥቶለት በጀት ተይዞለት የተሠራ ነው። ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችና ታላላቅ የሚባሉ ሰዎች ሳይቀሩ ዘር  መቁጠር እየቀናቸው መጥቷል። ከዚህ በፊት በብሄራዊ ስሜታቸው የሚታወቁ  ድርጅቶችና ግለሰቦች ወደ ነገዳቸው ወረድ ማለት እንዳለባቸው አምነዋል። በመሆኑም ብሄራዊ እንጅ ብሄረሰባዊ የሆነ አካሄድ እንዲኖረን መጠየቅ ሊከብድ ይችላል።

በመሆኑም የአንድነት ሃይሉ ታላቅ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል ቢባል የከበደ አይደለም። እነዶክተር ብርሃኑ ነጋና ታማኝ በየነ ያለመታከት ልመና እስኪመስል ድረስ ነገደኞችን ብሄራዊ ስሜትና አጀንዳ እንዲኖራቸው ሲወተውቱ ማየት የተለመደ ሆኗል። ከነዚህ ምክንያቶች በመነሳት የመጀመሪያው የፖለቲካ መስመር እየቀጠነና ተከታዮች እያነሱበት የሄደ ጽንሰ ሀሳባዊ ብቻ ይመስላል። በመሆኑም  ይበልጥ ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው ሁለተኛው የፖለቲካ መስመር ሳይሆን አይቀርም።

2ኛው ተመራጭ መስመር

የመጀመሪያው መስመር አባጣና ጎርባጣ የበዛበት መስሎ ስለታየ ሳንወድ በግድ ሁለተኛውን መስመር ልንከተል ነው ማለት ነው። ይህም ነገድን መነሻ ኢትዮጵያን መድረሻ ያደረገ የፖለቲካ አወቃቀር ማለት ነው። የማንፈልገው ቢሆንም መሬት የረገጠና ጎልቶ እየወጣ ያለ አማራጭ ይመስላል። ሕወሓት ካገኛቸው ስኬቶች ውስጥ ትልቁ ሕዝብ በነገድ እንዲደራጅ እንዲተዋወቅ እንዲነጋገር ማድረጉ ነው። በተቃዋሚ ጎራ ያለነው ሳንቀር በአደባባይ እያወገዝን በተግባር ግን የምንኖረው ሆኗል ነገድ። ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል ለመናገር የሚቸግራቸው ብዙ ኦሮሞ  ወገኖቻችን አሉ። ከዚህ በፊት በብሄራዊ ስሜቱ የሚታወቀው የሰሜኑ ሕዝብ ሳይቀር በነገድ መደራጀት የውዴታ ግዴታ እንደሆነ አምኗል። ይባስ ብሎም የራሱን መንግስት መመስረት እንዳለበት የሚከራከሩ እየተነሱ ነው። ይህ እየሆነ ባለበት ሁኔታ ብሄራዊነትን ብቻ ማዕከሉ ያደረገ ሽግግር እናድርግ ማለት ምናባዊ ይመስላል። ይህ አባባል የአንድነት  ሃይሎችን እጅግ እንደሚጎዳ ይታወቃል! ግን ሃቅ ነው።

ይህ ከሆነ ከምንጠብቀውና ከምንመኘው ሁሉ በአንድ ደረጃ ዝቅ ብለን የምንወዳትንና የምንሳሳላትን ኢትዮጵያን መፈለግና ማግኘት ይጠበቅብናል። ይህም ማለት ኦሮሞውም፣ ዐማራውም፣ ሶማሌውም፣ ሌላውም ሕዝብ ራሱን የሚወክል ድርጅት ፈጥሮ ደኅንነቱንና ጥቅሙን እንዲያስከብር መፍቀድ ማበረታታ ሊያስፈልግ ነው። ዳሩ ግን ይህ የሚሆነው ኢትዮጵያ የምትባል ልዑአላዊ አገር እንዳለች ሲያምኑና በጋራ ለሚዘጋጀው ለሕገ መንግስቷም ሲገዙ ነው። የፌዴራል አይነት ሥርዓት ቢመስልም ከተለመደው ግን የተለየ ነው። መሠረቱ ነገድ ነውና! ይህን መስመር የምንከተል ከሆነ ቀጥለው የተዘረዘሩትንና ሌሎችንም ጥቅሞችን እናገኛለን። ግልጽነት ተጠያቂነት እኩልነትና ፍትሕ ወዳጅ የሆነ የሽግግር አካል ከተገኘ ይህ መስመር ደህና ሊያስኬድ ይችላል።

  • ይህ አይነት ፖለቲካዊ አወቃቀር ገሃዱን ዓለም ስለሚያንጸባርቅ ሁሉንም ነገዶች በቀላሉ ለማስተባበር ያስችላል
  • ሁሉም የሚሳተፍበት ሕገ መንግስትና ብሄራዊ መንግስት ስለሚመሰረት በነገዶች መካከል ስጋትንና ጥርጣሬን መፈራራትንም ያስወግዳል
  • ሁሉም ነገድ የራሱን ባህል ቋንቋውን ጨምሮ ማሳደግ ስለሚችልና ራሱንም በራሱ ስለሚያስተዳድር እርካታና አመኔታን ያገኛል። ይህም በሂደት ከዘር ፖለቲካ ወጥቶ በጠቅላላ የሰው ልጅ መብትና ግዴታ ላይ የተመሰረተ ሥርዓት እንዲገነባ ያበረታታዋል
  • የመገንጠልና የጦርነት ስጋቶች አይኖሩም
  • በቀላሉ ሊገነባ የሚችል ሥርዓት ስለሆነ ሽግግሩን ያፋጥናል። ባእዳን ሃይሎች እንዳይገቡ ያደርጋል

የማይፈለገው መስመር

በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ መስመር 1 ወይም መስመር 2 ለጉዟችን ካልተመረጡ እስካሁን ስንፈራውና በለሆሳስ ስናዋጋው የነበረው መዓት ይወርድብናል። ይህውም ኦሮሞው አማራውና ሌላውም ነገድ የየራሱን መንግስት መስርቶ ራሱን የቻለ አገር ይሆናል። ኢትዮጵያ የሚለው ስም በታሪክ መዛግብት ብቻ ሰፍሮ ይቀራል። ይህ ከሆነ በየነገዶች መካከል ያለውን ድንበር ለመወሰን እጅግ አስቸጋሪ ስለሚሆን የማያባራ የእርስ በርስ ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል። ይህም ለውጭ ጠላቶቻችን አጋልጦ ይሰጠናል። እድገትና ብልጽግና ቀርቶ በሰላም ወጥቶ  መግባት ላም አለኝ በሰማይ ይሆናል። ባጠቃላይ አገራችን ከሶማሊያም የባሰች ለዓለምም ጠንቅ የሆነት የምድር ሲዖል ልትሆን ትችላለች።

ማጠቃለያ

ይህ ጽሑፍ ዲያስፖራው ኢትዮጵያዊ ወገኔ ለዘላቂና ውጤታማ ሽግግር ሊያበረክተው የሚችለውን አስተዋጽዖ ከነስጋቶቹ ባጭሩ ጠቊሟል። ምንም እንኳን አገር ቤት ካለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር አኳያ ሲታይ ኢምንት ቢሆንም የሚያበረክተው አስተዋጽዖ ግን ቀላል አይሆንም። ያካበታቸው ልዩ ልዩ ካፒታሎች ለሰላማዊ ሽግግርም ሆነ ለእድገት እንዲሁም ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የላቀ ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ። ይህ ሊሆን የሚችለው ግን በተለይ የአንድነት ሃይሉ ታሪካችንን ብቻ ሳይሆን መሬት ላይ ያለውን እውነታ በሚገባ ሲተነትንና አግባብ ያለው የፖለቲካ መስመር ሲከተል ነው።  አገር ቤት ኦሮሞውና ዐማራው አንድነቱን እያጠናከረ ባለበት ሁኔታ ዲያስፖራው ወደነገድ የወረደበት ምክንያት እምብዛም አያሳምንም። በእውነት ትግላችን ለአገራችን ለምስኪኑ ሕዝባችንም ከሆነ ነገድ ዘለል ትግልን እንከተል።የመግባቢያ ሰነድ በጋራ በማዘጋጀት የነጻነት ጉዟችንን እንያያዘው!

ይህ ካልሆነ ብዙዎች ከነገዳቸው ጋር የተያያዘ ሥራና ስም እየመረጡ የግድ ብሄራዊ የአእምሮ ቅኝት ብቻ ይኑራችሁ ብሎ ለማስገደድ መሞከር ኪሳራን ያስከትላል። ይህ ፈታኝ ወቅት ነውና ሁሉም አካል በኢትዮጵያዊነት ማዕቀፍ ስር ሆኖ የራሱን እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ መንግስት እንዲመሰርት መፍቀድና ማገዝም ጥበብ ነው። ያለበለዚያ ኢትዮጵያ ወይም ሞት የምንል ከሆነ መስዋዕትነቱ ለማንም አይበጅም። ይህ ሲባል ግን ነገድ ተኮር ድርጅቶች እንደፈለጉ ይሆናል ማለት አይደለም። ሁሉም ነገር በሥርዓትና በሕግ ሊመራ ይገባዋልና! ያለበለዚያ ሊመጣ የሚችል ችግር ካለ ተጠያቂ የሚሆኑበት መንገድ ክፍት እንደሆነ መገንዘብ ያሻል።

በመጨረሻም በውጭው ዓለም የሚገኙ የአንድነትና የነገድ ተኮር ድርጅቶች ሰከን ብለው ሊያስቧቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ላንሳ! አንደኛ ብቻቸውን በምንም መልኩ የኢትዮጵያን ሕዝብ ስለማይወክሉ አገር ቤት ካሉ አቻዎቻቸው ጋር በሚቻልበት መንገድ ሁሉ አብሮ መምከርና መናበብ ያስፈልጋል። ሁለተኛ በመካከላችሁ የቱንም ያህል የሃሳብ ልዩነት ቢመጣ ባለመግባባታችሁ ተግባቡ እንጅ እርስ በርሳችሁ አትወነጃጀሉ። ሙሉ ትኩረት የጋራ ጠላትን መታገል ላይ መሆን ይገባዋል። ሦስተኛ ማንም አካል በብልጣብልጥነት ማንንም ሊሸነግል የሚችልበት ዘመን ላይ አይደለንም። እያንዳንዱ አካል ለሚሠራው ሙሉ ሃላፊነትና ተጠያቂነት አለበት። ሕዝቡ መከራ ያስተማረው ነውና ከዚህ በኋላ ለሚደናቀፍ አብዮት  ትዕግስትና ይቅርታ ያለው አይመስልምና እንጠንቀቅ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

አስተያየት ካለዎት በteklu.abate@gmail.com ይላኩ!

አልሸሹም ዞር አሉ እንዳይሆን –ሰማሀኝ ጋሹ (ዶ/ር)

$
0
0

 

Et_olf1.pngየኦሮሞ ቻርተርና ወታደራዊ ክንፍ መቋቋምን በተመለከተ የሚመክር በአትላንታ የሚካሄድ ስብሰባ ዜና እና ሰነድ ይፋ ከተደረገ በሗላ በተለያዩ ወገኖች ዘንድ ጥርጣሬና ጥያቄ አስነስቷል። ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ አቶ ጃዋርንና ፕ/ር ህዝቄልን የኦሮሞ  ቻርተርን በተመለከተ ውይይትም አካሂዷል። በውይይቱ ወቅት የመገንጠል ጥያቄዉን በተመለከተ ጥሩ ማብራርያ የተሰጠ ቢሆንም አሁንም በርካታ መልስ የሚሹ ጉዳዮች አሉ። በተለይ አትላንታ ይካሄዳል ተብሎ የታሰበዉን ስብሰባ በተመለከተ የወጣዉ መግለጫ በብዙዎች ዘንድ ያልተጠበቀ ነገር ነዉ። በጎንደር በተካሄዳዉ የተቃዉሞ ሰልፍ ወቅት ህዝቡ ‘ የኦሮሞ ደም የኛ ደም ነዉ’  ፥ ‘ በቀለ ገርባ መሪያችን ነዉ’ በማለት ለኦሮሞ ህዝብ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ ያለዉን አጋርነት ከገለፀ በሗላ በህዝቦች መካከል የነበረዉንና በህወሓት ለዘመናት የሚዘወረዉን የከፈፍልህ ግዛ  (divide and conquer)  ፖለቲካ በማዳከም ከፍተኛ የትግል አንድነት ያመጣ መሆኑ ይታወቃል። ህዝቡ ይህንን የተፈጠረዉን አንድነት የሚያጠናክር የፖለቲካ ሀይሎች የጋራ መድርክ ሲጠብቅ የተናጥል ስብሰባ መጠራቱ በብዙዎች ዘንድ ጥርጣሬ መጫሩ የሚጠበቅ ነዉ። ከዚህ አኳያ የተፈጠረዉን የህዝብ አንድነት ሊያጠናክር የሚችል ስራ ላይ ማተኮር ሲገባ የተናጠል የስብሰባ ጥሪ መጠራቱ  በጋራ ትግሉ ላይ የራሱን ተፅእኖ ማሳደሩ የማይቀር ነዉ።

 

ከዚህ የከፋዉ ደግሞ የቀረበዉ ሰነድ ስለ ህዝቡ የጋራ ትግልና የደረሰበትን ደረጃ  ጨርሶ አያነሳም።  ሰነዱ ወደፊት የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ስርአት ዉስጥ የሚኖረዉን ሚና በተመለከተም ምንም አይነት ፍንጭ ያልሰጠ ሲሆን   የኦሮሞን ህዝብ በደሴትነት ተነጥሎ የተቀመጠ ያስመስለዋል። እንደዉም ሰነዱ የኦሮሞ ህዝብ ከኢትዮጵያ ጋር ያለዉን ግንኙነት የቅኝ ግዛት አድርጎ ያቀርበዋል። የቅኝ ግዛት ትንታኔዉን (colonial thesis) በርካታ የኦሮሞ ምሁራንና ፖለቲከኞች እንደማይደግፉት እየታወቀ ሁሉንም የኦሮሞ መሪዎች ላማሰባሰብ ያለመ ሰነድ ለምን ያአንድ ወገን አቋም ብቻ ለማንፀባርቅ እንደፈለገ ግልፅ አይደለም። የኦሮሞ ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ያለዉን ግንኙነት የቅኝ ግዛት ጥያቅ እንዳልሆነ የሚያምኑትን የኦሮሞ ፖለትከኞችና ምሁራን የሚያገል ያሰመስለዋል። የኦሮሞን ህዝብ ቅኝ እንደተገዛ አድርጎ ማቅረቡ የኦሮሞ ህዝብ ከሌላዉ ህዝብ ጋር ያለዉን የባህልና የታሪክ ትስስርና የኦሮሞ ህዝብ ለኢትዮጵያ አንድነትና ህልዉና ያበረከተዉን አስተዋፅኦ የሚያሳንስ ነዉ። ከዚህም በተጨማሪ ይህን አይነቱ ትንታኔ አንዱን ማህበረሰብ ጨቋኝ ሌላዉን ተጨቋኝ በማድረግ የሚቀርበዉን የታሪክ ትንታኔ ህያዉ ሆኖ እንዲቆይ የሚፈልግ ያስመስለዋል። ይህም  እስካሁን የሄድንበትን የጋራ አለመተማመን (mutual suspicion) በማስቀጠል ልንፈጥረዉ ለምናስበዉ ዴሞክራሲያዊ ስርአት እንቅፋት ይሆናል።

 

በተለይ በኢትዮጵያን አንድነትና በግለሰብ መብት ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ስርአት እንዲቋቋም የሚፈልጉ ዜጎችን የቀድሞዉ ስርአት ናፋቅዎችና ምኒልካዉያን እየተባለ መስደብ የተለመደ ነዉ። ያሁኑን ተዉልድ የፖለቲካ አስተሳሰብ መተቸት ካስፈለገ በራሱ በትዉልዱ አስተሳሰብ ላይ ተመስርቶ መተቸት ሲገባ ከቀደሙት ስርአቶች ጋር በማያያዝ አንገት ለማስደፋት የሚደረገዉ እንቅስቃሴ ያደባባይ ሚስጥር ነዉ። የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ ከወራት በፊት ያደረገዉን የሬድዮ ዉይይት አስመልክቶ የቀድሞዉ ስርአት ናፋቂ የሚል ስድብና ዛቻ የኦሮሞ አክቲቪስቶች ነን ከሚሉ ወገኖች አስተናግዷል። ለዚህም ነዉ የአማራ ወጣቶች ሁሉም የብሄር ድርጅቶች አማራን በጠላትነት የሚፈርጁ በመሆኑ ተደራጅተን እራሳችንን እንከላከል እያሉ ያሉት። ምንም እንኳን ያለፈዉን ታሪካችንን በተመለከተ ብሄራዊ መግባባት ላይ መድረስ አስቸጋሪ ሊሆን ቢችልም እንዲህ አይነት የታሪክ ትንታኔዎችን ለፖለቲካ ፍጆታ ባለመጠቀም የተሻለ የፖለቲካ ድባብ ለመፍጠር ጥረት እንዳልተደረገ ግን ከቀረበዉ ሰነድ መረዳት ይቻላል።

 

ከዚህም በጠጨማሪ የቀረበዉ ሰነድ ባለፉት አስርተ አመታት የብሄረሰቦችን እኩልነት ለማምጣት የተሄደበትን መንገድ፥ ዉጤቱንና ችግሮቹን ሳያነሳ የኦሮሞ ህዝብ ከዛሬ አርባ አመት በፊት በነበረበት ሁኔታ እንዳለ አድርጎ ያቀርበዋል። ከሁሉም ብሄረሰቦች የተወጣጡ ወጣቶች በተማሪዎች እንቅስቅሴ ወቅት ያነሱት የመሬት ላራሹና የራስን እድል በራስ የመወሰን ጥያቄ በደቡብ ኢትዮጵያ የነበረዉን የጭሰኝነት ስርአት ያስወገደ ሲሆን ይህም ለኦሮሞ ህዝብ ታላቅ ለዉጥ አምጥቷል። ደርግም ሆነ ወያኔ ስታሊናዊ በሆነ መንገድ ችግሮቹን ለመፍታት የሄዱበት መንገድ ዉጤቱ አመርቂ ባይሆንም ሙከራዎች ግን ተደርገዋል። ይህ ሁሉ የፖለቲካ ለዉጦች በተካሄዱበት ሀገር አሁንም ቅኝ እንደተገዛን ነን የሚል እድምታ ያለዉ አቀራረብ በጣም ጨለምተኛና  ካላፈዉ ስህተቶች ተምሮ የቀረዉን የእኩልነት ጥያቅ ለማሳካት በሚያስችል መልኩ አለመቀረፁ በኢትዮጵያ ያለዉን አስቸጋሪ የፖለቲካ ሁኔታ ለመፍታት ያለዉን ቁርጠኝነት ዉሱን ያስመስለዋል።

 

የኦሮሞ መሪዎች ስብሰባ ያስፈለገበትን ምክንያት አቶ ጃዋር ሲያስረዳ ወደፊት ለሚደረገዉ የሽግግር ወቅት እያንዳንዱ ማህበረሰብ የራሱን ቻርተር አዘጋጅቶ መምጣት ስላለበት የኦሮሞን ቻርተር  ለማዘጋጀት በማስፈለጉ ነዉ ይላል። ለዚህም የደቡብ አፍሪካዉን ብሄራዊ ኮንግረስና የህንዱ ጃዋራላል ኔህሩ በትግል ወቅት እንዲህ አይነት ቻርተር አዘጋጀተዉ ነበር ሲል ያስረዳል አቶ ጃዋር። እያናንዳንዱ ማህብረስብ የራሱን ቻርተር አዘጋጅቶ ይምጣ ከተባለ  ሁሉም ብሄረሰቦች አንዳንድ ቻርተር በማዘጋጀት ሲመጡ ቢያንስ ከ 80 ያላነሱ ቻርተሮች ተዝጋጅተዉ ሊቀርቡ ነዉ ማለት ነዉ( ያዉም እያንዳንዱ ማህበረሰብ በአንድ ድርጅት ይወከላል ብለን ካሰብን ነዉ።) እንዲህ ያለ ሁኔታን እንዲኖር መፈለግ አላማዉ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ወይስ የባቢሎንን ግንብ ለመገንባት ነዉ? ሁሉም ብሄር የራሱን መብት እንዲከበር በሚል በሚያደርገዉ ፍላጎት ሁሉንም የሚያረካ መፍትሄ ማግኘት የሚክብድ ከመሆኑም በተጨማሪ የፈለገዉን ያላገኘዉ ወገን ‘የራሴን እድል በራሴ’ እወስናለሁ ወደሚል ሌላ ዙር ግጭት ይገባል። በተለይ ወታደራዊ ክንፍ ያለዉ የብሄር ድርጅት የሚበረታታ ከሆነ በጉልበት የፈለገዉን ለማድረግ ማንገራገሩ የማይቀር ነዉ። ወያኔም በ1983 ዓም ባደረገዉ የሽግግር መንግስት ምስረታ ወቅት በብሄር የተደራጁትን ብቻ ተቀብሎ ህብረ ብሄር የሆኑትን ግን አልቀበልም ነበር ያለዉ። ለዚህም የተማመነዉ የነበረዉን ጉልበት ነዉ። ኦነግንም ከሽግግሩ መንግስት እንዲወጣ ያደረገዉ ይሄዉ የወያኔ እብሪተኝነት ነዉ። አሁንም በብሄር ተደራጅታችሁ የራሳችሁን ቻርተር አዘጋጅታችሁ ኑ ማለት ተመሳሳይ አካሄድ ያለዉ ነዉ። በርካታ ማህበረሰቦችም በተለያየ ምክንያት ተደራጅተዉ  ቻርተር አዘጋጅተዉ ላይቀርቡ ይችላሉ። በዚህ ጊዜ የነዚህ ማህበረሰቦች እድል ቻርተር አዘጋጅተዉ በመጡት ሊወሰን ነዉ ማለት ነዉ? ይህስ አካሄድ ወያኔ በ1983 ካደረገዉ በምን ይለያል? ወታደራዊ ክንፍ ያላቸዉ የፖለቲካ ሃይሎች እኛ ባልነዉ ካለተስማማችሁ ዞር በሉ ቢሉ ዋስትናዉ ምንድን ነዉ? አልሸሽም ዞር አሉ እንደሚባለዉ ተመልሶ ወደ ግጭት አያስገባንም ወይ?

 

አቶ ጃዋር ያቀረባቸዉ የደቡብ አፍሪካ፤ ህንድና ቱኒዝያ ምሳሌዎች አሁን ከተጠራዉ የኦሮሞ የነፃነት (freedom) ቻርተር ጉዳይ በጣም የተለዩ ናቸዉ። በነዚህ ሃገሮች የቀረቡት የነፃነት (freedom) ቻርተሮች ሆነ ድርድሮች ሃገራዊና የሁሉንም ማህበረሰብ ፍላጎት የሚያንፅባርቁ እንጂ የአንድ ብሄርን ብቻ የሚመለከቱ አልነበሩም። እንዲሁም በህንድ የተካሄደዉ የፀረ ቅኝ ግዛት ትግልና በደቡብ አፍሪካ የተካሄደዉ የፀረ አፓርታይድ ትግል አሁን ኢትዮጵያ ዉስጥ ካለዉ የፖለቲካ ሁኔታ ጋር ያላቸው ዝምድናና እና ልዩነት በግልፅ አልቀረበም ። የምናቀርባቸዉ ምሳሌዎች ተገቢ ትርጉማቸዉን የያዙ ቢሆኑ የምናቀርበዉን ሃሳብ ተአማኒነት ያጠናክረዋል። አቶ ጃዋር ስለ ቱኒዝያ የተናገረዉም እኛ እየሄድንበት ካለው ጋር የሚገናኝ አይደለም። ከሌሎች አብዮት ከተካሄደባቸዉ የአረብ ሃገራት በተለየ የተሻለ የፖለቲካ ሽግግር በቱንዝያ የተፈጠረዉ እንደ ሊቢያና ሶርያ በሃይማኖትና በጎሳ ለመከፋፈል ባለመፍቀዳቸዉ ነዉ። ወታደራዊ ክንፍ ያላቸዉ የብሄር ድርጅቶችን የምናበረታታ ከሆነ ግን ለጊዜዉ በአንድ ጠላት ላይ ሲያተኩሩ ልዩነት የሌላቸዉ የሚመስሉ የፖለቲካ ህይሎች ያ ጠላት ከስፈራዉ ሲነሳ  እርስ በርሳቸዉ መበላላታቸዉ የማይቀር ነዉ።  ሊብያ ዉስጥ በተካሄደዉ አብዮት ወቅት ሁሉም ጎሳዎች ጋዳፊን ለመጣል ሰምና ወርቅ ሆነዉ ከሰሩ በሗላ አሁን ሁሉም በየፊናዉ  ወታደራዊ ቀጠና አቋቁሞ እየተጋጨ ሲሆን ማዕከላዊ መንግስት በስምምነት ለመመስረት አልቻሉም ።

 

በእዉነት የኢትዮጵያን የፖለቲካ ችግሮች ለመፍታት ቅንነቱና ቁርጠኝነቱ ካለ እንደ ኑክልየር ሳይንስ ዉስብስብ ስላልሆነ 80 ቻርተር ማዘጋጀት አያስፈልገዉም። የኢትዮጵያ የፖለቲካ መሰረታዊ ችግሮች እንዴት ብሄራዊ አንድነትንና የብሄር  መብትን፥  የግለሰብና የቡድን መብትን አጣጥመን እንቀጥል፥  እንዴት ብሄራዊ መግባባትን እንፍጠር፥ ዴሞክራሴያዊ ባህልና ተቋማት እንዴት እንገንባና ማህበራዊና ኤኮኖምያዊ ፍትህ እንዴት እናረጋግጥ የሚሉት ናቸዉ። እነዚህን የፖለቲካ ጥያቄዎች ለመመለስ ዋናዉ መነሻ የተናጥል አካሄድን በተቻለ መጠን በማስቀረት ሁሉም የፖለቲካ ሃይሎች በጋራ የሚመክሩበትን ሁኔታ ማመቻቸት ነዉ። ነገር ግን አሁንም የሽግግር ሂደቱን በበላይነት ለመቆጣጠር የሚካሄደዉ ፉክክር ስር የሰደደዉን የፖለቲካ ሃይሎች አለመተማመን እንዲቀጥል የሚያደርገዉ ከመሆኑም በተጨማሪ የግጭትንና የእኔ አውቅልሃለሁን የቆየ የፖለቲካ ባህል ለመለወጥ የሚኖረዉን እድል ያደበዝዘዋል።

ሥህተቶችን ሳንደግም የተሻለች ኢትዮጵያን ወደ መገንባት –ገለታው ዘለቀ

$
0
0

udj-ethiopia-demo-satenaw-newsበሚመጣው ህዳር ወር ላይ የኢትዮጵያ ልጆች የኦሮሞ ብሄር ለሂቃን ተሰብስበው በከፍተኛ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ሲባል ምክክሩን ወድጄው በስብሰባው ላይ ቢነሳ ጥሩ ነበር ብየ ባሰብኩት ላይ ለመወያየት ነው አነሳሴ። የውይይቱ አሳብ ለሁሉ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ነው በርግጥ። እነዚህ የኦሮሞ ወገኖቼ ከዚህ ስብሰባ በሁዋላ የሚያወጡት የአቋም መግለጫ የኢትዮጵያን ማህበረ ፓለቲካ ለመለወጥ ትልቅ ድርሻ ያለው የትብብር፣ የአንድነት አሳብ እንደሚሆን አምናለሁ።

በአሁኑ ሠዓት ኢትዮጵያችን በከፍተኛ ህዝባዊ ንቅናቄ እየተናጠች ነው። ምን አልባትም ይህ ዓይነቱ ህዝብ መራሽ የሆነ ሰፊ ትግል በታሪካችን አልታየም። የህዝባዊ አመፁ በከፍተኛ ሁኔታ እየገፋ ባለበት በአሁኑ ወቅት የፓለቲካ ሃይላት ሲቪክ ድርጅቶችና የሃይማኖትና የባህል መሪዎች ሁሉ ሁለት ትላልቅ የምክክር አጀንዳዎች ከፊታቸው ተደቅነዋል። በተናጠልም በጋራም በነዚህ ጉዳዮች ላይ መወያየት አለብን። አንደኛው ወቅታዊ ጉዳይ ይህ የህዝብ ትግል እንዴት ነው የሚቋጨው? እንዴት ነው የሚያልቀው? የሚለው አስቸኳይ ጉዳይ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በሽግግሩ ጊዜ ሊሰሩ የሚገባቸው ስራዎች ላይና የሽግግሩ ጊዜ ምን መምሰል እንዳለበት በመምከሩ ላይ ያተኮረ ነው።

በነዚህ ሁለት ነጥቦች ላይ ኢትዮጵያውያን ባሉን አጋጣሚዎች ብንወያይ መልካም ነው። ከፍ ሲል እንዳልኩት ትግሉ ሰፊና አስደናቂ ሲሆን በአብዛኛው አካባቢያዊ ጥያቄን እያሳየ አጠቃላይ የስርአት ለውጥን ፈላጊ ሆኖ ይታያል። የትግሉን ባህርይ ስናይ በኦሮምያ አካባቢ በአመዛኙ ሰላማዊ ህዝባዊ አመፅ ሲሆን በአማራ አካባቢ ደግሞ በሰላምም በትጥቅም የመታገል ባርይ አለው። በአሁኑ ሰአት ትግሉን የደቡብ ህዝብም የተቀላቀለው ሲሆን ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። እንግዲህ ታዲያ ይህ ትግል ሄዶ ሄዶ በምን መንገድ ይጠናቀቃል? እንዴት ነው የሚያልቀው? ህዝብ የትግሉን ድል እንዴት አድርጎ ነው የሚያየው የሚለውን ማጥናት ተገቢ ነው። ይህን እንድንጠይቅ የሚያደርገን የትግሉ ባህርይ ነው። ባለቤቱና የሚመራው ህዝቡ በመሆኑ (ይህንን ጽሁፍ ሳዘጋጅ አንዳንድ ሃይሎች እኛ ነን ትግሉን ያቀጣጠልነው ቢሉም) እንዴት ይህ ትግል ወጥ የሆነ አመራር አግኝቶ መንግስት ይለውጣል? የሚል ጥያቄ ያስነሳል። መቼም የህዝቡ ትግል ሲያይል ሊከሰት ይችላል ተብሎ ከሚጠበቀው መሃል አንዱ መፈንቅለ መንግስት ነበር። ነገር ግን በኢትዮጵያ ሁኔታ ይህ ነገር የሚከሰትበትን እድል ማየት ተገቢ ነው። ማን በማንስ ላይ ነው መፈንቅለ መንግስት የሚያደርገው። ተደረገ ቢባልስ ራሱ ሰራዊቱ ህወሃትን አይደለም ወይ የሚጠብቀው? ምን ለውጥ ይመጣል? የሚል ነው። ሌላው የዚህ የህዝብ ተቃውሞ ግፊት መንግስትን ወደ ብሄራዊ እርቅና መግባባት የመወስድ ሃይል ነበረው። ይሁን እንጂ መንግስት ለዚህ ልቡ ተሰብሯል ወይ? ስንል አይመስልም። እስካሁን ምልክቶች አይታዩም። በብሄራዊ እርቅ ዙሪያ የሚሰሩ አሉና እስቲ እነሱ እየገፉ ይሂዱና ለውጥ ካለ እናያለን። እነዚህ ጉዳዮች ካልሰሩ ታዲያ ይህ የህዝብ አመጽ እንዴት ነው ድሉን የሚጨብጠው? ብለን እንጠይቃለን። መቼም መንግስት ህዝቡ በየከተማው አምፆብኛልና ጥይት የለኝም ብሎ ወታደር አሰናብቶ የአራት ኪሎን ቤተመንግስት ነቅሎ አይሄድም። በመሆኑም ይህ የህዝብ ትግል በድል እንዲጠናቀቅ የግድ የታጠቀ ሃይል ወጥ የሆነ እዝ ያለውን ሃይል ይሻል። ይህ የታጠቀ ሃይል ህዝብ ያደከመውን መንግስት በትጥቅ ጥሎ የሚመካበትን ሃይል በቁጥጥር ስር አውሎ ሲያበቃ ነው ይህ ትግል የሚቋጨው። ይህ የታጠቀ ሃይል የሚያስፈልገው ቋፍ ላይ ያለውን መንግስት ለመናድ ብቻ ሳይሆን የሽግግር ጊዜውን ለማድረግ በመላ ሃገሪቱ የሰላም ማስከበር አገልግሎት መስጠት ስላለበት ነው። በርግጥ ይህ ሃይል ሲያሸንፍ አሁን ያለውን መከላከያና ፓሊስ በሙሉ ይበትናል ሳይሆን እነዚህን ሃይሎች በአዲስ መንፈስ አንፆ መሄድ ይኖርበታል። ትግሉ ሊቋጭ የሚችለው እንግዲህ በታጠቀና የህዝቡን ጥያቄ ባነገበ ብሄራዊ ሃይል በመሆኑ አሁን በየአካባቢው ያለውን ሃይል ወደ ወጥ እዝ በማሰባሰብ የመጨረሻውን ትግል ማድረግ ያሻልና የመጨረሻውን ትግል ለመምራት ዝግጁ ነን ሃይል አለን የሚሉ ሃይሎች ይህን ጉዳይ ማሰብ ይኖርባቸዋል። የአካባቢ ትግሎች በበቂ የተደረጉ ሲሆን አሁን ህብረብሄራዊ የሆነ ሃይል ባስቸኳይ መውጣት አለበት። በመሆኑም የታጠቁ ሃይሎች ወደ ህብረት መጥተው ህብረቱን ለህዝብ መግለፅ ይጠበቅባቸዋል። በተግባርም የኦፐሬሽን ስራዎች መጀመር አለባቸው። የኦሮሞ ለሂቃንም ሆኑ የአማራ ወዘተ. በጋራ በመነጋገር የህዝቡን ትግል በድል እንዲቋጭ እዚያም እዚያም የተበታተነውን ሃይል በአንድ ወጥ እዝ ስር አድርገው ትግሉን መምራት ካልቻሉ ኦሮሞ ለብቻው አማራ ለብቻው ወዘተ ሰራዊት ለመገንባት ከጣሩ ይህ ትግል ወደ ብዙ አቅጣጫ የመውደቅ እድል ይኖረዋል። የአንድ ብሄር የታጠቀ ሃይል ድል ቢያደርግም እንኳን ለኢትዮጵያ ጥሩ አይሆንም። ህወሃት 25 ዓመት ሙሉ የሚለው አብላጫ ታግያለሁና አብላጫ ይገባኛል አይነት ነው። በመሆኑም በተናጠል የነበረው ትግል አሁን ይጠናቀቅ ዘንድ ህብረትን ፈልጓል። ትግሉ ብሄራዊ ንቅናቄን የሚሻበት የመጨረሻ ምእራፍ ላይ ነውና መነጋገር ያስፈልጋል ነው የምላችሁ።

ሁለተኛው ወቅታዊ ጥያቄ ደግሞ ያለፈ ስህተት እንዳይደገም የሽግግር ጊዜው ምን መምሰል አለበት? በዚህ የሽግግር ጊዜ ምን ልንሰራበት ነው? የሚለው ጥያቄ ነው።

ኢትዮጵያችን ከዘውዳዊ አገዛዝ ወደ ዘመናዊ አስተዳደር መሻገር ሲያምራት የሽግግር ጊዜን የፅሞና ጊዜ አድርጋ አልወሰደችም። ወታደር ስልጣኑን ነጥቆ ወስዶ ለስሙ የሽግግር ጊዜ ቢልም በተግባር ግን የሽግግር ጊዜ አላየንም። ራሳቸው መንግስቱ “በውኑ ደርግ አለን” ብለው የኢትዮጵያን ህዝብ ቢጠይቁት እስካሁን በዚህ ጥያቄ ይሳለቃል። በህወሃት ኢህአዴግ ጊዜም እንዲሁ የሽግግር ጊዜ ሲጠበቅ ሰፊ ማህበረሰብ ያገለለ የሽግግር ጊዜ የማይባል አሳልፈን ቀረን። የኢትዮጵያን ህዝብ መሰረታዊ ጥያቄ በሚገባ የምናጤንበት ጊዜ ሳይኖረን ቀረ። ለሶስተኛ ጊዜ ተመሳሳይ ችግር ውስጥ እንዳንገባ በዚህኛው ለውጥ ጊዜ ስለ ሽግግር ዛሬ ላይ ሆነን ማሰብ አለብን። በተለይ የኢትዮጵያ ፓለቲካ አሰላለፍ ወዲያና ወዲህ በሆነበት በዚህ ልዩ ጊዜ የሽግግር ጊዜ የጽሞናና የእቅድ ጊዜ የግድ ያስፈልገናል። በዚህ የሽግግር ጊዜ የሚያስፈልገው ዋና ነገር ምንድን ነው? ካልን የስምምነት አሳብ ነው። ይህ አሳብ ኢትዮጵያውያንን ወደ አንድ የተሻለ አዲስ ኪዳን የሚወስዳቸው መሆን አለበት። በዚህ የሽግግር ሰአት ኢትዮጵያውያን ባህላዊ ኢኮኖሚያዊ ፓለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮቻቸውን እንዴት አድርገው ማስተዳደር እንደሚገባቸው በዘላቂ ጉዳይ ላይ አቋም የሚይዙበት ሰአት ነው። ኢትዮጵያውያን ብዙህ ሆነው ግን ደግሞ አንድ አገር እንዲኖራቸው ይሻሉ። ይህ ማለት እንግዲህ ይህ የፈለጉት አንድነት የሚጠይቃቸውን የመስዋእት ጥያቄ አይፈሩም ማለት ነው። ስለሆነም የስምምነቱ አጀንዳ መሆን ያለበት እንዴት አድርግን አንድ ትልቅ አገራዊ የፓለቲካ ጠገግ እንፍጠር የሚል እና በሌላ በኩል ደግሞ ባህላዊ እኩልነትን የምናሳይበትን ሲስተምና ጠገግ መፍጠር ነው። የስምምነቱ አሳብ ይህን ያዘለ ሆኖ ነገር ግን መስዋእቱን የሚያቀርበውና አሳቡን የሚያፀድቀው ህዝብ፣ ዜጎች ሁሉ መሆን አለባቸው። በዚህ በሽግግር ወቅት ሊነሳ የሚገባው አንድ ጉልህ ጉዳይ የአንድነት ትርጉም ነው። የአንድነት መገለጫዎች ምን ምን እንደሆኑ መታወቅና ስምምነት መያዝ አለበት። ይህ ጉዳይ የፓለቲካ ዶክትሪን ሳይሆን ዘመን ተሻጋሪ የሆነ መሰረታዊ የሆነ ሃገርን እንደገና የማነፅ ጉዳይ ነው።

እንደሰማነው የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች የኦሮሞን ህዝብ ህልም የሚገልፅና ኦሮሞ ምን አይነት አገር በአዲሲቷ ኢትዮጵያ እንደሚፈልግ ሊወያዩ ነው። መወያየት አሳብ ማምጣት ደግ ነገር ነው። ሌሎች ቡድኖችም እንዲሁ በየቡድኑ ምክክር እያሰቡ እንደሆነ አላውቅም። ነገር ግን ያም አለ ይህ ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የሚያስፈልገውን መስዋእቶች ሁሉ እንዳንረሳ ያስፈልጋል። የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ የፍትህ የነፃነት የእኩልነት ጥያቄ በመሆኑ ይህንን የሚያስከብር ስርአት አብሮ መምከር እንጂ የኢትዮጵያን መስዋእቶች የሚበላ ወይም የሚቀራመት መሆን የለበትም። አማራ፣ ሲዳማ ወዘተ ለየብቻ ስለመጪው ጊዜ ስለሽግግር ጊዜው የስምምነት አሳቦች መወያየት ሲያምራቸው ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የሚሆነውን መስዋእት ካላሰቡ የተሻለች አገር አንገነባም። የሽግግሩ ጊዜ ሊያነሳው የሚገባው የስምምነት አሳብ አንድ የኢኮኖሚና የፓለቲካ ማህበረሰብ መፍጠርና ባህላዊ ማንነትን ራሱን በቻለ ነፃ አስተዳደርና የባህል ፌደሬሽን ማስተዳደር ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ የብሄር ትግል አድራሽ መሆን ይኖርበታል። እስከ ሽግግሩ ጊዜ ቆይቶ ከዚያ በሁዋላ ሊሟሟ ይገባል። የብሄር ፓለተካንም አንድነትንም ይዘን ብሄራዊ ምርጫ አድርገን ወደተሻለች ኢትዮጵያ መሻገር አንችልም።መወሰን አለብን። በአዲሲቱ ኢትዮጵያም የብሄር ፓለቲካን ካልጎተትን ካልን ሃገሪቱ ብዙ ግልፅነት በሚጎድላቸው የባህል የአኮኖሚ የማህበራዊና የፓለቲካ ስርአት ውስጥ መውደቋ ይቀጥላል። ግልፅ ያልሆነ ስምምነት ይዘን ያልቆረጠና የሰሰተ ስምምነት ይዘን አዲስ ስርአት መመስረት አንችልም። ይህን የምንልበት ብዙ ምክንያቶች አሉ። ዘውግ ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የስልጣን ምንጭ ይሁን የሚሉ ሃይሎች ሊመልሷቸው ከሚገቡ ጥያቄዎች መሃል
1. የብሄር ፓለቲካ በኢትዮጵያ ብሄሮች፣ በኦሮሞ፣ በአማራ፣ በትግሬ ወዘተ. ባህልና እምነት እሴቶች ውስጥ አለ ወይ? በነዚህ ብሄሮች እሴቶች ልብና መንፈስ ውስጥ ይገኛል ወይ? ብለን ልንመረምረው ይገባል። የኢትዮጵያ ብሄሮች በሃይማኖቶቻቸውም ሆነ በባህሎቻቸው እኔ….እኔ….. እኔ ….የሚል ነገር አያበረታቱም። አብረው በሚኖሩበት አገር ውስጥ የኔ….የኔ…የኔ….የሚል እሴት የላቸውም።

ለምሳሌ የኦሮሞን የገዳ ስርአትና ሌሎች ባህሎቹን ብናይ አንድ ከኦሮሞ ብሄር ውጭ ያለ ሰው ወደ ኦሮሞ ማህበረሰብ ከሄደና አብሮ ከኖረ እንደ ኦሮሞ ነው የሚታየው። የኦሮሞ ማህበረሰብ ባህል ይህንን ሰው እንዲለይ አይፈልግም። ከገዳ ስርኣትና ከአጠቃላይ የኦሮሞ ባህል መርሆዎች የሚቀዳው የፓለቲካ እምነት የብሄር ፓለቲካ ሳይሆን ሁሉን አቀፍ የሆነ በዜግነት ላይ የተመሰረተ ፓለቲካ ነው። የኦሮሞ ህዝብ መሪዎች ነን የሚሉ ሃይሎች በዘውግ ላይ የሚመሰረት ፓለቲካ የሚያራምዱ ከሆነ የኦሮሞን ባህል እሴቶች እየሰበሩ መሆናቸውን ማጤን አለባቸው። የገዳ ሥርኣት የኦሮሞ ባህል ብቻ ሳይሆን ጌዲኦም ይህን ባህል ይከተላል። የጌዲኦ ህዝብም እንዲሁ ለባህሉ እሴቶች ይጠነቀቃል። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ብሄሮች አብረው በአንድ ገበታ ይበላሉ። አንተ ትብስ ………አንተ ትብስ……….ይባባላሉ። አይሰስቱም። ይሉኝታ አላቸው። የብሄር ፓለቲካን እሴቶች ስናይ ደግሞ ከራስ በላይ ነፋስ አይነት ልብ አለው። ራስን በራስ…….የራስን እድል በራስ…..የራስ ባህል………የራስ መሬት …..ራስ…ራስ..ራስ….ነው ጨዋታው። የብሄር ፓለቲካ ከሶሻሊስት አብዮት የተቀዳ የእኛን ባህልና ሃይማኖት የሚፃረር በመሆኑ ነው በህብረተሰቡ ዘንድ ምስቅልቅልን እንዲያመጣ ያደረገው። ይህን የሚሸከም ባህላዊም ሃይማኖታዊም መሰረት የለንም። በመሆኑም ይሄን የሃገራችንን ባህልና ሃይማኖት የሰበረ ስስታም የፓለቲካ ዶክትሪን ልንከተለው አይገባም። ራስ….ራስ…ራስ…..ከሚለው ወጥተን እኛ…እኛ…እኛ …….ወደሚል የፓለቲካ አስተሳሰብ ስንገባ ነው የአማራን ወይም የኦሮሞን ወይም የሌሎችን ብሄሮች እሴቶች የምናከብረው።
2. የዴሞክራሲ ጉዳይ። ዘውግን ለአደሲቷ ኢትዮጵያ የስልጣን ምንጭ ማድረግ ከፈለግን የዴሞክራሲ መርሆዎችን ልንረማመድባቸው ነው። ምርጫን የዜግነት መብትን ሁሉ ይጋፋብናል። ስለዚህ እንምረጥ። ዴሞክራሲን ከነሙሉ ክብሩ ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ ከተመኘን ከዘውግ ፓለቲካ መላቀቅ አለብን።
3. የብሄር ፓለቲካ ግብ ምንድን ነው? ብለን እንጠይቅ። ኢትዮጵያን የሚያክል ጠገግ እንደ ኮንትራት አድርገን ብሄርን ዘላለማዊ ጠገግ አድርገን አገር መመስረት ካማረን ከስረናል። የብሄር ፓለቲካ ችግር ይህ ነው። አካባቢያዊ ማንነትን እያጎላ ብሄራዊ ማንነትን ያኮስስና አገርን ያናጋል። ዘላቂ ግብም የለውም።
4. የአባቶች ደምና አጥንት ጉዳይ። ኦሮሞው ሲዋጋ የኖረው አሁን ወያኔ ለፈጠረው የኦሮምያ ካርታ አይደለም። ትግራይ ሄዶ ነው የሞተው። አማራው ጉራጌው ትግሬው ሁሉም ዘብ ሆኖ ሲጠብቅ የኖረው ኢትዮጵያን ነውና የአባቶች ህብረት በዚህ ትውልድ መከበር አለበት። በደምና አጥንታቸው ላይ የምንረማመድ ትውልድ እንዳንሆን።
5. የብሄር ፓለቲካ ህዝባዊ ጥያቄ አለው ወይ? ብለን እንጠይቅ። ከጥቂት ሰዎች በላይ ህዝባዊ መሰረት የለውም። ይህንን ማጥናት ይቻላል። የሁሉም ህዝብ ጥያቄ አንድ አይነት ነው። ፍትህ ነፃነት።
በርግጥ ነው ቡድንን ነጥሎ የሚያጠቃ ሲመጣ መመከት ተገቢ ነው ይሁን እንጂ በተረጋጋ መንግስት ጊዜ ዘውግ የፓለቲካ መሰላል እንዲሆን የሚሻ ኢትዮጵያዊ በጣም ጥቂት ነው።
6. የብሄር ፓለቲካ አሁን ካለችው አለም ጋር ይሄዳል ወይ? ይህን ጥያቄ መመለስ ተገቢ ነው። አለም ወዴት እያመራች ነው? ሚለውን ወጣ ብሎ ማየት ያሻል። የብሄር ፓለቲካ ፊውቸር የለውም።
7. የጋራ ሃብትና የክልል ሃብት ላይ ትልቅ ንትርክ ያመጣል። አነሰም በዛም የጋራ ሃብቶች አሉን። እነዚህን ሃብቶች በኢትዮጵያዊነት ልንወርሳቸው ነው የሚገባው። የኔ የኔ ከመጣ ሁል ጊዜም ለአገሪቱ የግጭት ሃይል መቅበራችን ነው።
8. የማንነት እሽቅድምድም። ፓለቲካ ሁል ጊዜም የፍላጎት ማእከል(center of interest) አለው። ይህን ማእከል ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ሳንሰዋ ከቀረንና የዝንባሌና ፍላጎታችን ማእከል ብሄር ከሆነ በፍትህ ላይ ልንረማመድ እንችላለን። ፍትህ እኩልነት የሚታየን ከላይ ሆነን ስናይ ነው። ከላይ ከኢትዮጵያዊነት ላይ ሆነን…..። ከስር ከየብሄራችን የምናየው እይታ የሁሉን እኩልነት አያሳየንም። ከሁሉ በላይ ችግር ጎልቶ የሚታየን የኛ የምንለው ቡድን ይሆንና የሃገርን ለዛ ያጠፋብናል። ከዚህ የተነሳ እኔ መጀመሪያ ወላይታ ነኝ ሁለተኛ ቅብጥርሴ እያልን የማንነት እሽቅድምድም ውስጥ ይከተንና ፍትህን ምስጥ ሆኖ ይበላብናል።
9. ከብሄር ፓለቲካ ተምረን ተምረን ያፈራነው እውቀት ይህ ነው ወይ? ኢትዮጵያ ጥሟታል ወይ? ብለን መጠየቅ ተገቢ ነው። እንደ ኢትዮጵያውያን ስለዚህ ስለብሄር ፓለቲካ የተማረ የለምና እናስብበት። የብሄር ፓለቲካ በማህበረሰብ ህይወት ውስጥ ምን አይነት ሃይል (energy) እንደሚፈጥር ከሌላው አለም በተሻለ ተምረናልና እናስተውል።
10. የብሄር ፓለቲካ ፓሊሲዎችን ለማውጣት ምርምር ስናደርግ ልንቆጣጠራቸው የማንችላቸው ብዙ ተለዋዋጮች (variables) አሉት። ብዙ ጥያቄ ለማኝ የሆኑ ጉዳዮችን በውስጡ የያዘ ነው።
11. የብሄር ፓለቲካ ፍትህን ዴሞክራሲን ለማምጣት እንዴት ዋስትና ሆኖ ታየን? ሆሞ ጂኒየስ ሆኖ ጭቆና አለና። በአለም ላይ በብሄር ላይ እየተደራጁ ለስልጣን መሮጥ ለብሄሮች ቢጠቅም አለም ይህን ፍልስፍና በተከተለው። አለም እንደ ጦር የሚፈራውን ፓለቲካ ልንከተል አይገባም።
12. ቅይጡን ዜጋና ኢትዮጵያዊነትን እንደ ብሄር የወሰደውን ዜጋ ምን እናድርገው? ህወሃት ስታትስቲክስ ሲሰራ ብሄሮች ሲቆጠሩ ይህ ቅይጡ ቦታ የለውም። ገማቾች እንደሚሉት ይህ ቅይጥ ከሁለትና ሶስት ብሄር የተወለደው ዜጋ በቁጥሩ ከብዙ ብሄሮች ይበልጣል። ወደፊትም ቁጥሩ እየጨመረ ይሄዳል። የብሄር ፓለቲካ ሲመጣ ይህን ማህበረሰብ ለዘብተኛ ያደረገው ሲሆን ትልቁ ችግር ይህ ህዝብ በህሊናው የተሳለ ካርታ የለውም። ከቦታ ውጭ ይጥለዋል የብሄር ፓለቲካ። የፓለቲካና የዜግነት መብቱ በጣም ይሸራረፋል። በመሆኑም በዚህች አገር የብሄርን ፓለቲካ ለማስፈን የሚጥሩ ሃይሎች ይህን ሰፊ ማህበረሰብ ያስቡለት ዘንድ ይገባል።
ለማጠቃለል ያህል በፊዚክስ ትምህርት ውስጥ አንድ ጽንሰ ሃሳብ አለ ሲባል እንሰማለን። የስበትና የግፍትሪያ ህግ (laws of attraction and repulsion) ማለት ነው። ይህ ትምህርት የሚለው ግፍትሪያም ሆነ መሳሳብ የሚኖረው በዚያ በማግኔቲክ ፊልዱ ውስጥ ብቻ ነው። ከፊልዱ ውጭ ይህ ህግ አይሰራምና ግፍትሪያውም ስበቱም አይሰራም። ምን አልባት ይህ ተዛምዶ(Analogy)ምን ያህል አሳቤን እንደሚያሳይ ባላውቅም ነገር ግን የብሄር ፓለቲካ ሲስተም ዘርግተን ከዚያ በሁዋላ ችግር የለውም ለጋራው ቤታችን በገለልተኝነት አብረን እንሰራለን ማለት ከተፈጥሮ ህግ ጋር መታገል ነው። የሃገራችን ሰው ዘር ከልጓም ይስባል ይላል። በርግጥ በዘርና በደም ፓለቲካ ሲስተም ውስጥ ገብተን ብሄራዊ ተቋማት እንገነባለን ገለልተኝነት ያብባል ማለት ዘበት ነው። ከዚህ የብሄር ፓለቲካ የስበት ፊልድ ወይም የፓለቲካ መጫወቻ ሜዳ ወጥተን የተሻለች ለሁሉ የምትሆን ኢትዮጵያን መፍጠር የምንችለው የብሄር ፓለቲካ ሲስተም ውስጥ ሆነን ሳይሆን ከዚህ ሲስተም ወጥተን በመርህ ላይ ስንቆም ነው።

እዚህ ላይ አንድ መታየት የሚገባው እውነት አለ በርግጥ። ለራሴ የተማርኩት ነገር ቢኖር በብሄር መደራጀትን በተመለከተ በሁለት መንገድ አየዋለሁ። አንዱ ማንነትን እያነጣጠረ የሚያጠቃ ሃይል ሲመጣ በርግጥ ራስን መከላከል ያሻልና ቡድኖች ማንነታችንን አታጥፉ ብለው ሊደራጁና ለነፃነት ሊታገሉ ይችላሉ። ይህ ፍትሃዊ ነው። አንድ ቡድን ተለይቶ ሲጠቃ ቢደራጅ አይደንቅም። ሁለተኛው መደራጀት በተረጋጋ አገር በመድብለ ፓርቲ ሥርአት ውስጥ በዘውግ ላይ ያተኮረ የብሄር ፓርቲ መመስረት ነው። ይህንን ነው አጥብቄ የምቃወመው። ስስታም፣ ሙሰኛ፣ አድልዎኛ የሆነ ልብ ያለው በመሆኑ ለሃገር አንድነት የማይጠቅም በመሆኑ ሁላችን ልናወግዘው ይገባል። ጎረቤት ኬንያን ጨምሮ ስዊዘርላንድን ጨምሮ በብዙ አገሮች ይህ ፓለቲካ ወንጀል የሚያስቀጣ ተደርጎ የሚወሰድ የፓለቲካ ዶክትሪን ነው። የዘር ፓለቲካ በህግ የሚያስቀጣ የሆነበት ምክንያት እነዚህ ሃገራት የዚህ ፓለቲካ ፍላጎት(motive) ወንጀል መሆኑ ስለገባቸው ነው።

በአጠቃላይ ኢትዮጵያን ወደተሻለ ስርአት ለመምራት በሽግግሩ ጊዜ ኢትዮጵያውያን አንድ ከፍ ያለ ዘመን ተሻጋሪ ስምምነት ሊያደርጉ የሚገባበት ጊዜ በመሆኑ ሃላፊነት ይሰማኛል የሚሉ ሃይላት ስምምነቱን እጅግ በሰከነ ሁኔታ ማድረግ ያሻል። አዲስ የሆነ ኪዳን ዜጎች ሁሉ ገብተው የምንቀጥልበት ሁኔታ እንዲፈጠር በስምምነት ላይ የተመሰረተ አንድነት እንድንፈጥር መጣር የሚጠበቅብን ወሳኝ ምእራፍ ላይ ነን። በመሆኑም አንደኛ ትግሉ ቶሎ እንዲጠናቀቅና ተፈላጊ ለውጥ እንዲመጣ ወጥ ንቅናቄ ማቋቋም ሁለተኛ የሽግግሩን ጊዜ ኢትዮጵያ አዲስ ኪዳን የምትገባባት ጊዜ እንዲሆን ሁላችን እንትጋ። በቅርቡ ስብሰባ የጠራው የኦሮሞ ማህበረሰብም ሆነ ሌሎች በብሄር ላይ የተመሰረተ ድርጅት ያቆሙ ሃይሎች ሁሉ ደግመው እንዲወያዩበት የሚያስፈልገው ነገር ለኢትዮጵያ ምን መስዋእት እናድርግ? በሚለው ላይ ነው። አገር የሚመሰረትባቸውን አለባዎች ሁሉ ተቀራምተን ለህብረት ዝግጁ ነን ማለት ባዶ ነገር ነው። ኢትዮጵያ የማትጨበጥ አይደለችም። የቡድኖችና የዜጎች መስዋእት ዋልታና ማገር ሆነውላት የምትኖር አገር ናት።

እግዚአብሔር የኢትዮጵያን ይባርክ።

የታላቁ ጀግና ብ/ጄኔራል ለገሰ ተፈራ ስንብት –መሳይ መኮንነን

$
0
0

legesse-tefera-satenaw-newsብ/ጄኔራል ለገሰ ተፈራ ከኢትዮጵያ አየር ሃይል የበረራ ጀግኖች መካከል አንዱ ነበሩ። የኢትዮጵያ አየር ሃይልን ከመቀላቀላቸው በፊት በ1956 ዓም ሃረር አካዳሚ በመግባት ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። በሃረር አካዳሚ ቆይታቸው ወቅት የጠለቀ የውጊያ ስልት፣ ወታደራዊ አመራር፣ የአካል ብቃትና የወታደራዊ ሳይንስ ስነምግባር በመማር በመኮንንነት ተመርቀዋል።

የኢትዮጵያ አየር ሃይል ስመጥር በሆነው የሃረር አካዳሚ ምልመላ በሚያካሂድበት ወቅት ብ/ጀኔራል ለገሰ ተፈራ ብቁ ሆነው በመገኘታቸው አየር ሃይልን ተቀላቀሉ። በ1959ዓም ትምህርታቸውን አጠናቀው የበረራ ክንፋቸውን ከገኙ በኋላ የጄር አብራሪና አስተማሪ ሆኑ። ብ/ጄኔራል ለገሰ ተፈራ በየጊዜው በሚያሳዩት የሙያ ብቃት ምክንያት ከሌሎች መካከል ተመርጠው በተዋጊ አውሮፕላን በረራ አስተማሪነት ከፍተኛ ድርሻ አበርክተዋል።

ወራሪው የሱማሊያ መንግስት የግዛት ተስፋፊነት ምኞቱን ለማሳካት ኢትዮጵያ በወረራ ጊዜ ብ/ጄኔራል ለገሰ ተፈራ ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ጀግንነት ፈጽመዋል። በዚያድባሬ ወረራ ወቅት የዘጠነኛው ስኳድሮ ተዋጊ የነበሩት ብ/ጄኔራል ለገሰ ተፈራ፣ በግላቸው አምስት የሶማሊያ አውሮፕላኖች በአየር ላይ ውጊያ በመምታት ጥለዋል። የቡድን አባሎቻቸው ከሆኑት ኮረኔል ባጫ ሁንዴ፣ ብ/ጄኔራል አሸናፊ ገ/ጻዲቅ፣ ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ፣ ሜ/ጄኔራል አምሃ ደስታና ሌሎች የኢትዮጵያ ጀግኖች ጋር በመሆን የሱማሊያን ወራሪ ሃይል ለመደምሰስ በተደረገው ጦርነት አንጸባራቂ ድል አስመዝግበዋል።
ብ/ጄኔራል ለገሰ ተፈራ በወራሪው የሱማሊያ ጦር ላይ ባደረሱት ከፍተኛ ምትና ጉዳት ኢትዮጵያ ለተጎናጸፈችው ድል ላበረከቱት የጀግንነት ስራ የህብረተሰባዊነት ኢትዮጵያ ጀግና የጦር ሜዳ ጀብዱ ሜዳሊያ ተሸላሚ ከሆኑት ሶስት ኢትዮጵያውያን መካከል አንዱ ለመሆን ችለዋል።

ከ11 ዓመት የሱማሊያ እስር ቤት ቆይታ በኋላ ወደ ሃገራቸው በመመለስ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማገልገል ባላቸው ፍላጎት ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ አየር ሃይል ተመልሰው የበረራ አስተማሪ በመሆን አገልግለዋል። ሆኖም ባደረባቸው የጤና መታወክና ሌሎች ተጨማሪ ምክንያቶች ብዙ መቀጠል አልቻሉም። ይባስ ብሎ በግንቦት 83 በተከተሰተ የመንግስት ለውጥ ምክንያት ውጥናቸው ሳይሳካ ቀርቶ ወደ አሜሪካን ተሰደዱ።
የህብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግና የጦር ሜዳ ጀብዱ ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆኑት ብ/ጄኔራል ለገሰ ተፈራ፣ ያፌት ለገሰ፣ ነጻነት ለገሰ እና ሉሊት ለገሰ የሚባሉ የሶስት ልጆች አባት ነበሩ።

አልተገናኝቶም፣ ሕዝብ ለነጻነት፤ ፖለቲከኞች ለቤተ መንግሥት፡ –ይግረም ዓለሙ

$
0
0

 

Power is the peopleየፖለቲካ ትግል የሥልጣን ትግል መሆኑ እሙን ቢሆንም  ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን መሆን በመታገል በሕዝብ ድምጽ ተመርጦ ሥልጣን መያዝን ዓላማ ካላደረጉ የቤተ መንግሥቱ ወንበር የሚሆነው ለአንድ ሰው ብቻ በመሆኑ ትግሉ የመጠላለፍ ጨዋታው የጥሎ ማለፍ ይሆንና ስልጣን ላይ ያለውን ሀይል እድሜ በማራዘም ሁሉም የሚመኙትን ወንበር ሳያገኙ ዘመናት ይቆጠራሉ፡፡

ደርግን ለማስወገድ በተደረገው ትግል የሁሉም ዓላማና ግብ በደርግ ወንበር ራስን ማስቀመጥ እንጂ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመስረትን ያስቀደመ አልነበረምና የእርስ በርሱ ትግል ደርግን በመታገል ከተከፈለው ያልተናነሰ መስዋዕትነት አስከፍሏል፡፡ መጨረሻም መስዋዕትነቱ ሁሉ መክኖ ሀገሪቱን ለወያኔ አገዛዝ ዳርጓታል፡፡

ባለፉት ሀያ አምስት ዓመታት የታየውም ከዛ ብዙም ያልተለየ  በመሆኑ ነው መስዋእትነት አንጂ ድል ለመታየት አለመቻሉ፡፡ በዚህ የተማረረውና በፖለቲከኞቹ ተስፋ የቆርጠው ህዝብ አሁን  የነጻነት ትግሉን ራሱ በራሱ ተያይዞታል፡፡  ፖለቲከኞቹ ግን የአርባ አመቶቹም ሆኑ የአስርና የሀያ አመቶቹ ( የትግል እድሜአቸው ነው) ትናንት ካሳለፉትም ሆነ ዛሬ ከሚኖሩት ተምረውና ተመክረው ዓላማቸውን ከራስ ሥልጣን መሻት ወደ ዴሞክራሲያው ስርዓት መቀየር ባለመቻላቸው የህዝቡን ትግል ሊመሩት ሊያስተባብሩት ቀርቶ እሱ በራሱ መንገድ ትግሉን ሲያቀጣጥል ወደ እነርሱ መንገድ ሊመልሱት ይዳዳቸዋል፡

በ2001 ዓም አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ እንደተመሰረተ የመጀመሪያዋ ሊቀመንበር ብርቱካን ሚደቅሳ አንድነት የሚታገለው ለሥልጣን ሳይሆን ለዴሞክራሲ ሥርዓት ነው በማለቷ ፖለቲከኞቹ ብቻ ሳይሆኑ አንዳንድ ጋዜጠኞች ጉድ በሉ ለሥልጣን የማይታገል ፓርቲ ተፈጠረ በማለት ሲሳለቁም ሲተቹም ሰምተንም አንብበንም ነበር፡፡ለዴሞክራሲ መታገልና ለሥልጣን መታገል ያላቸውን አንድነትና ልዩነት ተቺዎቹ መረዳት ተስኖአቸው ሳይሆን በሀገራችን የተለመደውና ጡረታ ሊወጣ ያልቻለው የተለየ አስተሳሰብ ይዞ ብቅ የሚልን ተረባርቦ ከመድረኩ የማጥፋት በሽታ ተጠቂዎች መሆናቸው ነበር ብርቱካን በተናገረችው ላይ ያዘመታቸው፡፡

ከዛ ወዲህ ከአርበኞች ግንቦት 7 ሰፈር የሚጻፉትም  ሆኑ የሚነገሩት በ2001 ዓም ወ/ት ብርቱካን ይዛው ከነበረውና የውስጡም የውጪውም በትብብር በአጭር ካስቀረው አስተሳሰብ ጋር አንድ አይነት ነው፡፡ ጠመንጃ አንስተው ዱር ቤቴ ብለው እየሞቱና እየገደሉ የሚታገሉት ለሥልጣን ሳይሆን ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መሆኑን ግባቸውም ወያኔን አሸንፎ ሥልጣን መያዝ ሳሆን የሽግግር መንግሥት እንዲመሰረት ማብቃት እንደሆነ ነው የሚገልጽት፡፡ በእውነቱ በዚህ መስመር ከተሰለፈ ኃይል ይህ መሰማቱ በእውነቱ ቅዱስ ዓላማ ነው፡፡

በሰላማዊ መንገድም ሆነ በትጥቅ አንታገላለን ከሚሉ መኖሪያቸውን በሀገር ውስጥም በውጪም ካደረጉ  ሌሎች ድርጅቶች አንዲህ አይነት ቃል ተስምቶ አያውቅም፡፡ የምንታገለው ወያኔን አስወግደን ሥልጣን በመያዝ ዓላማችንን ተግባራዊ ለማድረግ ነው ነው የሚሉት፡፡ማለታቸው ባልከፋ ግን በመረጡት የትግል ስልት ተንቀሳቅሰው ለሚያልሙት ሥልጣን የሚያበቃቸው ድርጅታዊ አቅምና የትግል ብቃት ሊፈጥሩ አልቻሉም፡፡ ሁሉም ለሥልጣን የሚታገሉና በህልማቸውም በእውናቸውም ምንይልክ ቤተ መንግስትን የሚያልሙ በመሆናቸው ተባብረው አንድ ጠንካራ ሀይል ሊፈጥሩ አልቻሉም፡፡በዚህም ቢያበቃ ደግ ነበር፡፡ ከመካከላቸው አንድ ሁለቱ ትንሽ መንቀሳቀስ ሲጀምሩ ወያኔ ገና ምኑም ሳይነካ በተቀደምን እኩይ መንፈስ  ጎትተው ለማስቀረት አደናቅፈው ለመጣል ይሰራሉ ያሴራሉ፡፡

ለሥልጣን መታገል ምን አንደሆነ ወያኔ በቂ ገላጭ ነው፡፡ የትግሉ ፍጻሜ ራስን ለስልጣን ማብቃት ነው፡፡ ስልጣንኑ ከያዘ በኋላም በትግል የተገኘ ሥልጣን በትግል ይጠበቃል ብሎ እኔ ታግየ ባመጣሁት እያሉ ለሌሎች እንደሚገባቸው ሳይሆን አንደሱ ችሮታ ሥልጣን እየሰጠ፣ የህዝብን የስልጣን ባለቤትነት የሚያረጋግጥ ሳይሆን የሱን እድሜ የሚያራዝም ስመ ምርጫ እያካሄደ፣ ጥያቄንም ተቃውሞንም በሀይል እየጨፈለቀ ከዴሞክራሲ ጋር ሆድና ጀርባ ሆኖ የሚኖር ነው፡፡

በአንጻሩ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን መሆን የሚታገል ሀይል፡ በሰላምም ይሁን በጠብመንጃ  ታግሎ ለድል ሲበቃ በትግል ያገኘሁት ሥልጣን ሳይል የህዝብን የሥልጣን ባለቤትነት የሚያረጋግጥና ሀገሪቱን ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርአት የሚያሸጋግር ነጻ ምርጫ እንዲካሄድ ያደርጋል፡፡ ለራሱም የህዝብን አመኔታ አግኝቶ ለመመረጥ የሚያበቃውን ጥንካሬ ይገነባል፣ተወዳድሮ ካሸነፈ ሥልጣን ይረከባል፤ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ከመነሻው የታገለለት ነውና መሰረቱ የጸና ግድግዳና ጣራው የጠነከረ ዴሞክራሲ ለመገንባት ይሰራል፣የህዝብን የሥልጣን ባለቤትነት በተግባር ያረጋግጣል፤ለመመረጥ የቀሰቀሰበትን ሲመረጥም የገባውን ቃል ገቢራዊ ለማድረግ ይተጋል፡፡ ከተሸነፈ አሸናፊውን አንኳን ደስ አለህ በማለት ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ለቀጣይ ምርጫ ራሱን ያዘጋጃል፡፡

መነሻ ዓላማውም ሆነ መድረሻ ግቡ ሥልጣን ሳይሆን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ነውና ስልጣኔን ላጣ እችላለሁ በሚል ስጋት በምርጫ ላይ ፊቱን አያዞርም፡፡አንደውም አስተማማኝ በማንምና በምንም ምክንያት ሊሸረሸር የማይችል የምርጫ ስርዐትና ተቋም እንዲኖር ያደርጋል፡፡ እናም ወንበር እስከ መቃብር ሳይል ነጻና ፍትሀዊ ምርጫ አካሂዶ ቢሸነፍ አሸናፊወውን አንኳን ደስ አለህ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓታችንን ይበልጥ ለማጠናከር በርትተህ እንደምትሰራ ጽኑ እምነት አለን እኛም አጋርነታችን አይለይህም በማለት ሥልጣኑን ያስረክባል፡፡

የአብዛኛዎች ፖለቲከኞችም ሆኑ የግል ተንቀሳቃሾች ህልምና ፍላጎት ሥልጣን በመሆኑ በርስ በርስ ፍትጊያ  የወያኔን ስልጣን እያራዘሙ አንዳቸውም የሚመኙትን ሥልጣን ከማጣታቸው በላይ ህዝቡ ከአገዛዝ ተላቆ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዳይበቃ አድርገውት ሀያ አምስት አመታት ተቆጠሩ፡፡ አሁንም የተማሩ አይመስሉም፡፡

ወያኔ የሚስተካከል ተቀዋሚውም ከራስ በላይ ሕዝብ ብሎ የሚታገል አለመሆኑ ተስፋ ያስቆረጠው፣ ግፉ ያንገፈገፈውና መስቃ የመረረው ሕዝብ ራሱን እየደራጀ ከሞት ጋር በመጋፈጥ የነጻነት ትግሉን በደም ሲያቀልመው፣ የመለያየቱን የበርሊን ግንብ ደርምሶ አንድነቱን በመስዋዕትነት ሲያደምቀው፣ እጅ ለእጅ ተያይዞ የወያኔን እሳትና ጭድ ሴራ ሲያከሽፈው፡ አብዛኛዎቹን ፖለቲከኞቹ በዚህ መስመር ማየት አልተቻለም፡፡ እንደውም  የቆረቡበት ከሚመስለው አስተሳሰባቸው ባለመላቀቅ ትግሉን ከደረሰበት ከፍታ በማውረድና የህዝቡን አንድነት በመሸርሸር በእነርሱ ቁመትና ፍላጎት መጠን ለማድረግ መድከማቸው  እነርሱም አንደ ወያኔ ከዴሞክራሲ ጋር ሆድና ጀርባ መሆናቸውን ነው የሚያሳየው፡፡

ወያኔ ሀያ አምስት አመት ምኒልክ ቤተ መንግስት ተቀምጦ አለመማሩ፣ከወዳጅም ጠላቶቼ ከሚላቸውም የሚሰነዘርለትን ምክር ትችት አስተያየት ወዘተ ባለመቀበል  አለመሻሻሉ ችግሩ ከተፈጥሮው እንደመሆኑ አነዚህም ሥልጣን ብቻ የሚያልሙ ፖለቲከኞች ሌላው ሁሉ በቀር ከሰሞኑ የህዝብ ትግል አንድትና መስዋዕትነት ለመማር አለመቻላቸው ችግራቸው ከአፈጣጠራቸው በመሆኑ ነው ለማለት ያስችላል፡፡

በተፈጥሮአቸው ከዴሞክራሲ ጋር ያልተጣሉ ወይንም በሥልጣን ጥም ያልናወዙ  ዓላማቸው ግልጽ ነው፡፡በሚሰሩትና በሚናገሩት መካከል ልዩነት አይታይም፣ጭብጨባም ሆነ ውዳሴ የወያኔ መሰሪነትም ሆነ የህዝብ ትግል መፋፋም፣የአስመሳዮች ሴራም ሆነ የትግሉ እልህ አስጨራሽ መሆን  እዛና እዚህ አንዲረግጡ አንደ እስስት አንዲለዋወጡ አያደርጋቸውም፡፡

እባካችሁ፤ተቃዋሚ ነን ባዮች ብዙ ናችሁ፡ ወንበሩ ደግሞ ካለ አንድ ሰው እንደማያስተናግድ ታውቃላችሁ፣ስለሆነም መመኘት መፈለጋችሁ እንዳለ ሆኖ ወንበሩን ማግኘት የሚቻለው በሀገሪቱ ነጻ የምርጫ ስርዓት ተፈጥሮ እኔም ተወዳድሮ ለማሸነፍ የሚያበቃ አቅም ሲኖሮኝ ነው ብላችሁ ነጻ የምርጫ ስርኣት ለመፍጠር የሚያስችል የሽግግር ግዜ ለማምጣት ለመታገል ወስኑ፡፡ በያዛችሁት መንገድ የህዝቡን የነጻነት ትግል በመጉዳት የወያኔን እድሜ ታራዝሙ ካልሆነ በስተቀር የምትመኙትን ወንበር እንደማታገኙት ሀያ አምስት አመት በበቂ አይታችኋል፡፡አሁን ደግሞ የነጻነት ትግሉ በህዝብ እጅ ገብቷልና እንኳን በእናንተ በወያኔም የሚደናቀፍ አይመስልም፡፡ እናም ለማታገኙት ሥልጣን የታሪክና የትውልድ ተጠያቂ ከመሆን የምትችሉትን ትንሽ ትንሽ አዎንታዊ አስተዋጽኦ በማድረግ የአኩሪ ታሪክ ተካፋይ ብትሆን ይበጃል፡፡


ሕወሓት መራሹ ኣገዛዝ አጣብቂኙ ስለበረታበት የኣስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ

$
0
0

stateofemeየመጨረሻው ሰዓት ነው። ወያኔ የኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ ኣውጇል። በኦሮሚያ ያለው የሕዝብ ተቃውሞ በመበርታቱ ኣላላውስ ያለው ኣጣብቂኝ ውስጥ የገባው ወያኔ ትላንትና ከሰዓት በኋላ ከሕወሓት ኣስቸኳይ ስብሰባ በኋላ ለሃይለማርያም በተሰጠው ትእዛዝ መሰረት የኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ እንዲነገር መደረጉ ወያኔ የደረሰበትን ውድቀት በገሃድ ያሳይል፤ ባለፉት ሃያ ኣምስት ኣመታት ውስጥ ኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ ሲታወጅ ይህ የመጀመሪያው ሲሆን ሃገሪቱ ከባድ ኣደጋ ውስጥ መሆኗንና ወያኔ መምራት ኣለመቻሉን የሚመሰክር ኣዋጅ መሆኑ ታውቋል።ሕዝባዊው ትግሉ ካለበት ደረጃ ከፍ ብሎና ጠንክሮ በመሄድ ላይ በመሆኑ ለነጻነት ፈላጊ ሕዝቦች ታላቅ የድል ብስራት ነው።

#MinilikSalsawi
ሕወሓት መራሹ ኣገዛዝ አጣብቂኙ ስለበረታበት የኣስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ

ከወቅቱ ህዝባዊ እምቢተኝነት ጋር ተያያዥንት ያላቸው የህግ ጉዳይወች ዳሰሳ –ማህሙድ እሸቱ ትኩዬ

$
0
0

መግብያ

ሕወሓት መራሹ ኣገዛዝ አጣብቂኙ ስለበረታበት የኣስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀእንደሚታወቀው አብዘሀኛዎቹ የኢትዮጺያ ተቃዎሚወች በሀገሪቱ ውስጥ ለሚካሃደው ማንኛውም ድርጊት ሃላፊነት መውሰድ ያለበት ህውሃት ነው የሚል እምነት አላቸው። ሆኖም ይህ እቋም ከህግ አንጻር አግባብ ነውን? ይህ ጸሃፊ በመንግስት የሚጠላውን የከፋፍለህ ግዛ መርህ ተጠምዝዞ በከፋፍለህ አጥቃ መተግበር የለበትም ብሎ ይምናል።

እርግጥ ነው አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የህውሃት ባለስልጣኖች ከእያንዳንዱ ውሳኔዎች ጀርባ መኖራቸው በስፋት ይጠቀሳል። ይህ ሁኔታ ሌሎች ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ፓርቲዎችንም ሆኑ ግለሰቦች ከተጠያቂነት አያድናቸውም። ከዚህ ጋር ተያይዞ የበላይ ትዛዝን እንደ ወንጀል ማቅለሊያነት የሚጠቅሰው የወንጀል ህግ አንቀጽ አግባብነት የሚኖረው በህግ ደንብ የአዛዥ እና ታዛዥነት ግንኙነት ባላቸው ሰውች መካከል ታዛዡ የታዘዘው ድርጊት ወንጀል መሆኑን በቅጡ መለየት የማይችል እና ትዛዙን ከመፈጸም ውጭ ሌላ አማራጭ ሳይኖረው ሲቀር ታዛዡ የበላይ ትዛዙን እንደ ወንጅል መቅለሊያነት ሊያነሳ እንደሚችል ደንግግዋል። ነግር ግን በህውሃት አመራሮች እና ሌላ ከታች ከተጠቀሱት ጉዳዩች ጋር ግንኙነት ያላቸው ፓርቲዎች እና አመራሮች ጋር ምንም አይነት ህጋዊ የሆነ የአዛዥ እና ታዛዥነት ግንኙነት በለመኖሩ (ለምሳሎ የጠ/ሚ እና ከህውሃት የተውጣጡ አማካሪዎቹ) እና ታዘው ነው ይህን ውስኔ የወሰኑት የሚባሉት የክልል ባለስልጣናት ትዛዙን አለመፈጸም የሚችሉበት አግባብ ሳላል ከዚህ የቅጣት ማቅለያ ተጠቃሚ መሆን አይችሉም። ስለሆነም ጸሀፊው ህውሃት ከሚለው ስያሜ ይልቅ ኢሃዴግ ወይም መንግስት የሚለውን ሰያሜ መርጧል።

በአሁኑ ግዜ ሀገራችን ኢትዬጺያ ከፍተኛ የሆነ አመጽ እና ህዝባዊ እምቢተኝነትን በማስተናገድ ላይ ትገኛለች። በኦሮምያ እና አማራ ክልል የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍልዎች ብዙ ሰላማዊ ሰልፍዎችን አካሂደዋል የተለያዩ አድማውችንም ( ከቤት አለመውጣት እና ገበያ ማቆም) በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።

ጠ/ሚ ሃይለማርያም አመጹን እና ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ለማስቆም የመከላከያ ሰራዊቱን ማንኛውንም አስፈላጊ ሃይል እንዲጠቀም አዘዋል። በመሆኑም በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰወችን ተገድለዋል፤ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተደብድበዋል፤ ቆስለዋል፤ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የህብረተሰብ ክፍልዎችም ታስረዋል።

እነዚህ ድርጊቶች በብዙ የሰበአዊ መብት ተሟጋች ድርጅትዎች እና አክቲቪስቶች በጣም እየተራገቡ ተተችተዋል። እጅግ አሰቃቂ እና ኢ-ሰብአዊ ተብለውም ተፈርጀዋል።

መንግስት እንዚህን ድርጊቶች ለማስተባበል የተለያዩ የመከራከርያ ሃሳቦችን ያነሳል። በፊት እንደገለጽኩት መንግስት  ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የሚከተሉትን የመከራከርያ ነጥቦችን ሲያነሳ ይስትዋላል።

1. የተቃውሞ ሰልፍዎቹ የመንግስት አካላትን እውቅና እና ፍቃድ ስላላገኙ ህጋዊ አይደሉም።
2. መንግስት በሀገሪቱ ውስጥ ሰላም እና ደህንነትን የማስፈን ሀላፊነት ያለበት በመሆኑ እና የተቃውሞው ስልፎቹ ሰላማዊ ባለመሆናቸው አስፈላጊ እርምጃወችን ወስድዋል። እርምጃወቹም ህጋዊ እና መንግስት ከተጣለበት ሀላፊነት ጋር አብረው የሚሄዱ ናቸው።
3. የተቃውሞው እና የህዝባዊ እምቢተኝነቱ  ምክንያት ሀገሪትዋ እይስመዘገበች ያለችው ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ጋር ተያያዝነት ያላቸው የልማት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በአግባቡ አለመለስ እንጂ ስርአት እና የፓሊሱ ችግሮች ውጤት አይደሉም።

ይህ ጽሁፍ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ጉዳይዎች ላይ የህግ ትንተና ለመስጠት ታልሞ የተዘጋጀ ሲሆን የሚከተሉትን የህግ ጥያቄዎች ይመልሳል ተብሎ ይጠበቃል።

1. አሁን ከለው እና ስለ-ሰላማዊ ስልፍ የሚያትተው ህግ አንጻር የሰላማዊ ሰልፍ ህጋዊ ይሆን ዘንድ የመንግስት አካሎች እውቅና ያስፈልጋልን?
2. ጠ/ሩ የመከላከያ ሰራዊቱን ሁከቱን ለማስቆም ማንኛውንም ሀይል እንዲጠቀም ሲያዙ መከተል ያለባቸውን ህገ-መንግስታዊ ቅድመ ሁኔታ እና ሂደት (procedures) ተከትለዋልን?
3. ሲጀመር የመከላከያ ሰራዊቱ ሰላማዊ ሰልፉን የማስቆም ህገ-መንግስታዊ ስልጣን አለውን?
4. የመከላከያ ሰራዊቱ ይህንን ስልጣን ያገኘበት መንገድ በህገ-መንግስቱ ላይ ከተቀመጠው ቅድመ-ሁኔታ እና ሂደት ጋር ይጣጣማልን?
5. የተወሰዱት እርምጃዎች መንግስት በሀገሪቱ ውስጥ ሰላምንና ደህንነትን ከማስፈን ሃላፊነቱ አንጻር አግባብናቸውን? አግባብነታቸውን በተላይም መንግስት አላስፊላጊ ሃይል መጠቀሙን እና አለመጠቀሙን ማን ሊወስን ይገባል? ከዚህ እንጻር ኢትዬጺያ ያጸደቀቻቸው አለማቀፍ ስምምነቶች ምን ይላሉ?
6. እውን የተቃውሞው ምክንያት የመልካም አስተደር ችግር ወይስ የፓሊሲ እና የህግ የበላይነት አለመከበር ችግር?

ክፍል አንድ

<<ስለ ሰላማዊ ሰልፍ >>
1. አሁን ከለው እና ስለ-ሰላማዊ ስልፍ ከሚያትተው ህግ አንጻር የሰላማዊ ሰልፍ ህጋዊ ይሆን ዘንድ የመንግስት አካሎች እውቅና ፍቃድ ያስፈልጋልን?

እንደሚታወቀው ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት በተለያዩ አለማቀፍ የሰበአዊ መብት ሰነዶች እውቅና ካገኙ  መሠረታዊ ዲሞክራሲያዊ መብቶች መካከል በግንባር ቀደምነት ተጠቃሽ ነው። በሃገራችን ኢትዮጲያም ይህ መብት በህጎች ሁሉ የበላይ በሆነው ህገ-መንግስት ተረጋግጧል። የኢፌዴሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 30 ላይ “ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሰሪያ ሳይዝ በሰላም የመሠብሠብ ፥ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው” በማለት ይደነግጋል።  በተጨማሪም አንቀጹ ሰላማዊ ሰልፎች የህዝብ እንቅስቃሴ ላይ ችግር እንዳይፈጥሩ ለማድረግ፤ የዲሞክራሲያዊ መብቶችንና የህዝብን የሞራል ሁኔታን እንዳይጥሱ ለማስጠበቅ አግባብ ያላቸው ሰርአቶች (regulations) ሊደነገጉ ይችላሉ ይላል።

ከላይ የተጠቀሰው አንቀጽ የመብቱን ይዘትና መብቱ ሊገደብ የሚችልበትን ምክንይቶች ከመግለጽ ውጭ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የመንግስት አካሎችን ፍቃድ ወይም እውቅናን እንደ ቅድመ ሁኔታ አላስቀመጠም። በርግጥ ህገ-መንግስት ጥቅል መርሄችን መደንገግ እንጂ ዝርዝር ሁኔታዎችን  መግለጽ አይጠበቅበትም የሚል መከራከርያ ሊነሳ ይችላል። ሆኖም ጸሃፊው ህገ-መንግስቱን  ስለ ሰብአዊ መብቶች የሚደነግገውን ክፍል (Chapter three) በተመለከተ ይህ የመከራከርያ ሃሳብ ተቀባይነት የለውም ብሎ ይምናል። ምክንያቱም በህገ-መንግስቱ የተዘረዘሩት መብቶች በምን ቅድመ–ሁኔታወች፥ በምን ምክንያቶችና መመዘኛዎች ሊገደቡ እንደሚገባ ህገ-መንግስቱ በዝርዝር ካላስቀመጠ መንግስት የፈለገውን ህግ አውጥቶ ባሻው መልኩ መብቶቹን የሚገድበበት ሁኔታ ይፈጠራል። ይህ ከሆነ ደግሞ ዜጎች ህገ-መንግስታዊ መብቶቻቸውን መተግበር የማይችሉበትና መብቶቹም በወረቀት ከመጠቀስ ውጭ መሬት ላይ ዱብ የማይሉበት ሁኔታ ይፈጠራል። በዚህ ሁኔታ ለዜጎች የሰበአዊ መብቶች ጥበቃ ማድረግ (protection of human rights) የሚለውና ህገ-መንግስት ካስፈለገበት ዋና ምክንያይቶች አንዱ የሆነውን መርህ አላማን ማሣካት ፍጹም የማይሞከር ይሆናል። ስለሆነም መብቶች በምን ቅድመ–ሁኔታወች፥ በምን ምክንያቶች ( አንቀጽ 30 ምክንየቶቹን ዠርዝርዋል) እና መመዘኛወች ሊገደቡ እንደሚገባ ሣይገለጽ ዝርዝሩ በህግ ይገለጻል (claw back clause) የሚሉት የህገ-መንግስት አንቀጾች ከሰብአዊ መብቶች ጥበቃ አንጻር ችግር እንዳለበቸው ይህ ጸሃፊ ያምናል።

ስለ ሰላማዊ ሰልፍ በዝርዝር የሚደነግገውን ህግ በተመለከተ ጸሃፊው እስካሁን ካደረገው የህግ ጥናት አንጻር ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ይለው ህግ በሽግግር መንግስቱ ጊዜ የወጣው የአዋጅ ቁጥር 3/ 1984 ( proclamation No.3 1991) ብቻ ነው። ይህን አዋጅ በግልጽም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የሚሽር ሌላ አዋጅ ሥለሌለና ከህገ-መንግስቱ ጋር የማይጣረስ በመሆኑ በህግ-መንግስቱ አንቀጽ 9(1) መሰረት አሁንም ተፈጻሚነት ይኖረዋል። አዋጁ በመግቢያው(preamble) ላይ አላማው የዲሞክራሲያዊ መብቶችን ካለምንም ገደብ ማክበርና በአግባቡ እንዲተገበሩ ሁኔታወችን ማመቻቸት መሆኑን ያትታል።

የሰላማዊ ሰልፍ የሚካሄድበትን ሂደት በተመለከተ አዋጁ እንደ ግዴታ ያስቀመጠው ቅድመ ሁኔታ ( procedural obligation)  ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ያሰበው አካል ሰላማዊ ሰልፉ በሚካሄድበት አካባቢ ለሚገኝው የአስተዳደር መስርያ ቤት ሰልፉ ከመካሄዱ ከ48 ሰአት በፊት በጹሁፍ የሰልፉን አላማ፥ ሰልፉ በየት አካባቢና መንገድ እንደሚካሄድ፥ ሰልፉን ማን እንዳደራጀው እና ከመንግስት ሰልፉን አስመልክቶ ምን እይነት ድጋፍ እንደሚፈልጉ ማሳውቅ ነው (Hence, what’s required is serving a written notice)።

አዋጁ አንቀጽ 6 ላይ  የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት የሰላማዊ ሰልፍ የማካሄድ ጥያቄው በጹሁፍ በደረሳቸው በ12 ሰአት ጊዜ ውስጥ መልስ የመስጠት ግዴታ እንዳለባቸው ከመደንገጉ በተጨማሪ ሰልፉን መከልከል እንደማይችሉ በግልጽ ያስቀምጣል። በተጨማሪ አንቀጹ ሰልፉ የሚካሄድበትን ቦታና ግዜ በተመለከተ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ከሰልፉ አስተባባሪዎች ጋር ሊደራደሩ እንደሚችሉ ያትታል። ድርድሩ በሁለቱ ወገኖች ስምምነት የሚወሰን በመሆኑ ከሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎቹ አንጻር ያለው ብቸኞ ግዴታ ሰልፍ ማድረግ እንደሚፈልጉ ማሳወቅ እንጂ ፍቃድ ማግኘት አይደለም ማለት ነው። ሰለሆነም ሰላማዊ ሰልፎቹ ከመንግስት አካላት እውቅና ወይም ፍቃድ ስላላገኙ ህጋወጥ ናቸው የሚለው ብዙ ግዜ በመንግስት በኩል የሚነሳው የመካራከርያ ሃሳብ ከህግ አንጻር ተቀባይነት የለውም።

አሁን በለው ሁኔታ መንግስት የፈለገውን ህግ አውጥቶ ያሻውን መብት መገደብ የሚችል በመሆኑ ይህ ጸሃፊ መንግስት ወደ ፊት ይህንን አዋጅ ሊሽረው እና ከመንግስት ፍቃድ ሳይገኝ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን ህገወጥ ተግባር ሊደርገው ይችላል የሚል ስጋት አለው። ለዚህም ነው ስለ ሰበአዊ መብቶች የሚደነግጉት የህገ-መንግስቱ አንቀጾች ሰብአዊ መብቶች በምን ቅድመ–ሁኔታወች፥ በምን ምክንያቶችና መመዘኛወች ሊገደቡ እንደሚገባ በዝርዝር ሊጠቅሱ ይገባል የሚለውን ነጥብ ከላይ አንክሮት ለመስጠት የፈለገው።  በተጨማሪም የመንግስት ፍቃድ ሣይሰጥ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን ህገወጥ ተግባር ሊያደርግ የሚችል አዋጅ ከወጣ አዋጁ ( ደንቡ እንደ ህገመንግስቱ አገላለጽ) ከህገ-መንግስቱ መንፈስ ጋር ከመቃረኑ በተጨማሪ ኢትዬጺያ ካጸደቀችው አለማቀፍ ስምምነቶች በተለይም ሰለ ሲቪል እና ፓለቲካል መብቾች የሚደነግገው አለማቀፍ ቃል ኪዳን ጋር ይጣረሳል። እንደዚያ ከሆነ በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 9(1) እና 13 (2) መሰረት አዋጁ ኢ-ህግ-መንግድታዊ ይሆናል ማለት ነው።

እዚህ ጋር በተግባር ሲካሄዱ የነበሩትን ሰልፎች ከላይ ከተጠቀሰው የህግ ማእቀፍ አንጻር ማየቱ ተገቢ ነው። አብዘሃኛዋቹ ሰላማዊ ሰልፎች ሰላማዊና ብዙውን ግዜ የመንግስይ ሀይሎች ሰልፎቹን በሀይል እናስቆማለን ሲሉ በወሰዱት እርምጃ ወደ ሁከትነት የተቀየሩ ቢሄንም አንዳንድ ቦታዎች ላይ በመሳርያ የታጀቡ ሰልፎች ሲካሄዱ ተስተውለዎል። ይህ ተግባር ከህገ-መንግስቱ ጋር የሚጣረስ ተግባር መሆኑን ይህ ጻሃፊ ይምናል። ሰላማዊ ሰልፎች ሁሌም ፍጹም ሰላማዊ ሊሆኑ የሚገባ ሲሆን የጸጥታ አካላት እና የሰላማዊ ሰልፎች አስተባበሪ ግለሰቦች ሰላምን ለማስፈንና የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ በጋራ ሊሰሩ ይገባል። በኢትዬጺያ ውስጥ ይህ ሲሆን የሚታየው መንግስት በጠራቸው ሰልፎች ብቻ መሆኑ እጅግ ያሳዝናል። ከዚህ ይልቅ የጽጥታ ሃይሎሽ የተቃውሞ ስልፎችን በሃይል ለማስቆም በሚሞክሩበት ሂደት ሰልፎቹ ወደ ሁከትነት የሚቀየሩበት ሁኔታ ዘውትር ይስተዋላል። ከውቅቱ ሁኔታ ጋር ተያይዞም ጠ/ር ሃይለማርያም አመጹን እና ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ለማስቆም የመከላከያ ሰራዊቱን “ማንኛውንም አስፈላጊ ሃይል” እንዲጠቀም ማዘዛቸው ይታወሳል። ማንኛውም አስፈላጊ ሃይል ማለት ምን ማለት ነው? በህገ-መንግስቱ ከተደነገጉት የሰበአዊ መብቶች እንጻር እንዴት ይታያል? ጠ/ሩ ይህን ትዛዝ ሲያዙ መከተል ያለባቸውን ህገ-መንግስታዊ ቅድመሁኔታ እና ሂደት (procedures) ተከትለዋልን?

የነዚህንና ሎሎች ተያያዥ ጉዳዬችን ትንትናን ይዘን በክፍል ሁለት በቅርቡ እንገናኝ።

ይቀጥላል…..!!

ከወቅቱ ህዝባዊ እምቢተኝነት ጋር ተያያዥንት ያላቸው የህግ ጉዳይወች ዳሰሳ. –ማህሙድ እሸቱ ትኩዬ/

$
0
0

ክፍል ሁለት

ስለ ጠቅላይ ሚኒስተሩ ትዛዝ

hailemariam_desalgn-6-satenaw-newsበክፍል አንድ ላይ እንደተገለጸው ጠ/ሩ የህዝባዊ እምቢተኝነቱንና አመጹን ለማስቆም የመከላከያ ሰራዊቱ “ማንኛውንም ሃይል” እንዲጠቀም አዘዋል። ይህ ትእዛዝ የተለያዩ የህግ ጭብጦችን (issues) ያስነሳል።

የመጀመሪያው ጥያቄ የሚሆነው ትእዛዙ በኢፌደሪ ህገ-መንግስት ክፍል ሶስት (Chapter Three) ላይ ከሰፍሩት የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ አንጻር እንዴት ይታያል የሚለው ነው። ጠ/ሩ የመከላከያ ሰራዊቱን ማንኛውንም አስፈላጊ ሀይል ተጠቅሞ አመጹንና ህዝባዊ እምቢተኝነቱ (እንደ ጠ/ሩ አገላለጽ ሁከቱን) እንዲቆጣጠር ሲያዙ በህገመንግስቱ የተጠቀሱት የሰበአዊ መብቶች እንደሚጣሱና እንደሚገሰሱ እሙን ነው።

ምንም እንኳን ሰብአዊ መብቶች በመርህ ደረጃ የማይጣሱና የማይገሰሱ የሰው ልጅ ሰው በመሆኑ ብቻ የሚያገኛቸው መብቶች ቢሆኑም አግባብነት ባለው ስርአት መሰረት በተለይም በህግ አውጭው አካል (legislative organ) በከፊል ሊገደቡ እንደሚችሉ ግልጽ ነው (limitation)። እዚህ ላይ አግባብነት ያለው ስርአት መሰረት የሚለው ሰብአዊ መብቶቹን ሊገድብ የሚችል ህግ ብቻ ማውጣት እንዳልሆነ ልብ ይላል። ጸብሃፊው ከዚህ በፌት ባወጣው ጱሁፍ ላይ (የአማረኛ ትርጉሙን በቅርቡ) በሃገራችን ውስጥ ስላለው የዘፍቀደ የሰብአዊ መብቶች አገዳደብ እና ህጎች እንዴት የመንግስት የፓለቲካ መጠቀምያ መሳሪያወች እንደሆኑ በግልጽ በማሳየቱ ሰብአዊ መብቶች እንዴት መገደብ አለባቸው የሚለውን ጉዳይ በዝርዝር መተንተኑ አስፈላጊ ሆኖ አላገኘውም።

ከያዝነው ጭብጥ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያለው ጉዳይ  የአስፈጻሚው አካል (Executive Organ) ዜጎችን የሰብአዊ መብቶቻቸውን እንዳይተገብሩ በመከልከል መብቶቹን ሙሉ በሙሉ ስለሚገድብበትና ስለሚጥስበት ሂደት ነው(derogation and suspension)። ምህንይቱም “ማንኛውንም እርምጃ” የሚለው የጠ/ሩ ትእዛዝ ሁሉም የሰብአዊ መብቶች የሚጣሱበትን አግባብ የሚፈጥርና የመከላከያ ሰራዊቱ የመብቶች ሁሉ መሰረት የሆነውን በህይወት የመኖር መብት፥ በነጻነት የመንቀሳቀስ መብት፥ ሰላሚዊ ስልፍ የማድረግ መብትና ሌሎችን ስለጣሰ ነው።

በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 93 ላይ እንደተገለጸው የህገ-መንግስታዊ ስርአቱን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ሲከሰትና በተለመደው የህግ የማስከበር ሥርአት ለመቋቋም የማይቻል ሲሆን የፍደራል መንግስቱ የሚኒስተሮች ምክርቤት የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በመደንገግ ሰብአዊ መብቶችን መሉ በሙሉ በመገደብ በዜጎች እንዳይተገበሩ ሊያደርግ ይችላል (derogation and suspension)።

አንቀጹ የአስቸኳይ ግዜ እዋጅ ህጋዊነት ይኖረው ዘንድ ቅድመ ሁኔታወችን ይስቀመጠ ሲሆን አዋጁ በሚኒስተሮች ምክር ቤት በታወጀ በ48 ሰአት ውስጥ ለህዝብ ተወካዩች ምክርቤት መቅረብ እንዳለበትና የምክር ቤቱን ሁለት ሶስተኛ የድጋፍ ድንጽ ማግኘት እንዳለበት ( የህዝብ ተወካይወች ምክር ቤት ስራ ላይ ካልሆነ በ15 ቀን ውስጥ መቅረብ አለብት) ሊቆይ የሚችለውም ለ6 ወር ብቻ እንደሆነ ይጠቅሳል።  በተጨማሪም አንቀጹ ኢሰብአዊ አያያዝን(prohibition against inhuman treatment) የሚከለክለውን የህገመንግስት እንቀጽ 18 እና ሌሎች ( 25, 39(1)(2)) በማንኛውም መልኩ በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ሊጣሱ እንደማይችሉ በግልጽ ያስቀምጣል። እዚህ ጋር በህይወት የመኖር መብት በግልጽ ባይጠቀስም የህግ-መንግስቱ ክፍል ሶስት ( Chapter 3) ላይ የተጠቀሱት የሰበአዊ መብቶች ኢትዮጲያ ከጽደቀቻቸው አለማቀፍ ስምምነቶች ጋር በተጣጣመ መልኩ መተርጎም አለባቸው በሚለው የህገ-መንግስት አንቀጽ 13(2) አማካኝነት በህይወት የመኖር መብት በአስቸካይ ግዜ አዋጅ ሊጣስ እንደማይችል ሊታወቅ ይገባል።

የጠቅላይ ሚኒስተሩን ትእዛዝ ከላይ ከተገለጸው የህግ-ማእቀፍ አንጻር መገምገሙ ተገቢ ነው። እንደሚታወቀው የጠቅላይ ሚኒስተሩ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብለው “ሁከቱን ለማስቆም የመከላከያ ሰራዊቱ ማንኛውንም ሃይል እንዲጠቀም አዝዣለሁ” ከማለት ውጭ ውሳኔው በሚኑስተሮች ምክርቤት የተወሰነ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ስለመሆኑ የተነገረ ነገር የለም። ውሳኔው በ48 ሰአት ግዜ ውስጥም ሆነ በ15 ቀን ውስጥ ለህዝብ ተወካዩች ምክርቤት ቀርቦ 2/3 ድምጽ አላገኘም። በተጨማሪም ውሳኔው ከላይ የተጠቀሱትን በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ሊጣሱ የማይችሉ መብቶችን ከለላ ባልሰጠ መልኩ በማንኛውም ሃይል መጠቀም ሂደት ውስጥ እንዲጣሱ ተደርጎ የተወሰነ ውሳኔ ነው። ስለሆነም ውሳኔው የህግ መሰረት የለለው የሰበአዊ መብቶችን በማናለብኝና በዘፈቀደ የሚጥስ በህገ-መንግስቱ የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔዎችና ሂደቶች (procedures) ያልተከተለ ኢ-ህግ መንግስታዊ ውሳኔ ነው ማለት ነው።

ሌላው እዚህ ጋር መነሳት ያለበት ጉዳይ የመከላከያ ሰራዊቱ አመጹንና ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ማስቆም የሚችልበትን የህግ-አግባብ መመርመር ይሆናል። በዋናነት የመከላከያ ሰራዊቱ ስልጣን ድንበርን በመጠበቅ የሃገር ሉአላዊነትን ማስከበር መሆኑ እሙን ነው። ለዚህም ነው ኢፌድሪ ህገ–መንግስት ስለ መከላከያ ሰራዊ መርሆች በሚደነግገው አንቀጽ 87 ላይ የመከላከያ ሰርልዊቱ ስልጣን የሀገርን ሉአላዊነት ማስከበር መሆኑን በግል የጠቀስው።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የሀገርን ሉአላዊነት ማስከበር በብዙ መልኩ መተርጎም የሚችል ሰፊ ሀስብ (vague) በመሆኑ የመከላከያ ሰራዊቱን አመጹንና ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ለማስቆም የሚያግደው ነገር የለም የሚል መከራከርያ ሊነሳ ይችላል። ሆኖም ሁሉም አግባብነት ያላቸው የህገ መንግስት አንቀጾችን ስናይ በመርህ ደረጃ የመከላከያ ሰራዊቱ ስልጣን ድምበር ከመጠበቅ ጋር የተቆራኘ መሆኑን እንግነዘባለን።

እንደሚታወቀው ሃገራችን ኢትዮጺያ የፌደራል መንግስት አወቃቀርን የምትከተል ሀገር ናት። በዚህ የፌደራል ስርአት ውስጥ ክልሎች የራሳቸው በህገ-መንግስቱ የተረጋገጠ ስልጣን አላቸው። ስለ ክልሎች ስልጣን የሚያትተው የኢፌድሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 52(2) (ሰ) አማካኝነት ክልሎች የክልላቸውን ሰላምና ጸጥታ የማስጠበቅ ስልጣን እንዳላቸው በግልጽ ይጠቅሳል።

የፌደራሉን መንግስት ስልጣን የሚዘረዝረው አንቀጽ በበኩሉ በአንቀጽ 51(14) ላይ የፌደራል መንግስቱ “ከክልሎች አቅም በላይ የሆነ የጸትታ መደፍረስ ሲያጋጥም በክልሉ መንግስት ጥያቄ መሰረት የሀገሪቱን የመከላከያ ሃይል ያሰማራል” ይላል።  የህገመንግስቱ አንቀጽ 87 የመከላከያ ሰራዊቱ የሀገርን ሉአላዊነት ከመጠበቅ በተጨማሪ በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ መሰረት የሚሰጡትን ተግባራት እንደሚፈጽም ያትታል። በተጨማሪም ህገ-መንግስቱ በአንቀጽ 62(9) ላይ የፌደሬሽን ምክርቤቱን ተግባር ሲዘረዝር ክልሎች ህገመንግስቱን በመጣሥ የህገመንግስታዊ ስርአቱን አደጋላይ የጣሉ እንደሆነ የፌደራል መንግስቱ ጣልቃ እንደሚገባ ይገልጻል።

ሌላው እነዚህን ህገ-መንግስታዊ መርሆችን ለመተግበር የወጣውና የፌደራል መንግስቱ በክልሎች የመከላከያ ሰራዊቱን በማሰማራት ጣልቃ የሚገባበትን ሥርአት የሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 359/1995( proclamation no. 359/2003) የፌደራል መንግስቱ በክሎች ላይ ጣልቃ የሚገበብትን ሶስት አግባቦች አስቀምጧል።  እነሱም፦
1. ክልሎች ከአቅም በላይ የጸጥታ ችግር ሲጋጥማቸውና የፌደራል መንግስቱን እርዳታ ሲጠይቁ።
2. ክልሎች ህገመንግስቱን በመጣስ የህገመንግስታዊ ስርአቱን አደጋላይ የጣሉ እንደሆነ።
3.  በክልሎች ውስጥ ከባድ የሰብአዊ ጥሰት ሲኖር ናቸው።
በክልሎች ጥያቄ ከሚካሄደው የፌደራል መንግስት ጣልቃ ገብነት ውጭ በሁለትና ሶስት ላይ በተጠቀሱት ሌሎቹ የፌደራል መንግስቱ መካላከያ ሰራዊቱን ወደ ክልሎች በሚያማራበት አግባቦች እንደ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ማውጅና ለፌደሬሽን ምክርቤቱ ሪፓርት የማቅረብ ያሉ ግዴታ  (procedural obligations) አለበት።

ከዚህ የህግ ማእቀፍ አንጻር ጠቅላይ ሚኒስተሩ የመከላከያ ሰራዊቱን በኦሮምያና አማራ ክልል የሚካሄደውን አመጽ እንዲያስቆም ያዘዙበት መንገድ አግባብነቱ እጅግ በጣም አጠያያቂ ነው። ይህ ጸሃፊ እስከሚያስታውሰው ደረስ የአማራም ሆነ የኦሮምያ ክልል የፌደራል መንግስቱ መከላከያ ሰራዊቱን እዞ ሀከቱን እንዲያስቄም አልጠየቁም። ጉዳዩም ክልሎች ህገ መንግስቱን በመጣስ ህገመንግስታዊ ስርአቱን አደጋ ላይ የከተቱበት ውይም ትልቅ የሰበአዊ ጥሰት የፈጸሙበት ሳይሆን ህዝብ ያመጸበትና አልገዛም ያለበት (እንደ መንግስት እገላለጽ ጥቂቶች ሁከት የፈጠሩበት) ሁኔታ ነው። ስለሆነም የፌደራል መንግስቱ የመከላከያ ሰራዊቱን በክልሎች እንዲያሰማራ ማሟላት ያለበትን ቅድመ-ሁኔታ አያሟላም። ያሟላል እንኳን ቢባል የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ስላልታወጀና ለፌደሬሽን ምክር ቤት መቅረብ ያለበት ተከታታይ ሪፓር ሳይቀርብ በአስፈጻሚው አካል ብቻ የተወሰነ ውሳኔ በመሆኑ የህግ መሰረት የለለው ኢ-ህግ መንግስታዊ ውሳኔ ነው ማለት ነው።

እንግዲህ በዚህ የዘፈቀደና ኢ-ህግ መንግስታዊ አመጽ የማስቆም ሂደት ውስጥ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰወችን ተገድለዋል፤ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተደብድበዋል፤ ቆስለዋል፤ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የህብረተሰብ ክፍልዎችም ታስረዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጥይቄ እነዚህ እርምጃዎች መንግስት በሀገሪቱ ውስጥ ሰላምንና ደህንነትን የምስፈን ሃላፊነቱ አንጻር አግባብናቸውን? አግባብነታቸውን በተላይም መንግስት አላስፊላጊ ሃይል መጠቀሙን እና አለመጠቀሙን ማን ሊወስን ይገባል? ከዚህ እንጻር ኢትዬጺያ ያጸደቀቻቸው አለማቀፍ ስምምነቶች ምን ይላሉ?

የነዚህንና ሌሎች ተያያዝ ጉዳዬች ትንተናን ይዘን በቅርቡ በክፍል ሶስት (3) እንገናኝ

ይቀጥላል……..!

ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፤ ስለ ወቅታዊው የኢትጵያ ፖለቲካዊ ቀውስ ሂደትና የኢትዮጵያዊ ማንነት ጉዳይ ይናገራሉ።

$
0
0


ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፤ ስለ ወቅታዊው የኢትጵያ ፖለቲካዊ ቀውስ ሂደትና የኢትዮጵያዊ ማንነት ጉዳይ ይናገራሉ።
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፤ ስለ ወቅታዊው የኢትጵያ ፖለቲካዊ ቀውስ ሂደትና የኢትዮጵያዊ ማንነት ጉዳይ ይናገራሉ።

ኢትዮጵያ ታማለች !!! –ከተማ ዋቅጅራ

$
0
0

ethiopia-3-satenaw-newsየታመመችው ኢትዮጵያ የምትባለዋ አገር ናት። አገር ከታመመ ደግሞ በውስጧ የሚኖሩ ልጆቿን ማቀፍ መንከባከብ አትችልም። ወገኔ ሆይ ኢትዮጵያ ታማለች የሰው ያለህ የወገን ያለህ ትላለች። ህመሟን የሚያስታምማት ደግፎ ቀና የሚያደርጋት ሰው ትፈልጋለች ህመሟን አስታሞ አክሞ የሚያድናት ህዝብ ትፈልጋለች። የት ናችሁ የኢትዮጵያ ወዳጆች ኸረ ወደት ናችሁ የሰው ያለህ እያለች ስትጣራ ተበታትነን ሁሉም በየፊናው በህመሟ የምንቀልድ በዛን። የወገን ያለህ ብላ ስትጣራ እኛም ሌላ ህመም ሆንባት ቀና አርጉኝ ስትል እንድትሞት እንጫናት ጀመር ተንከባከቡኝ ስትል እየገፋናት አታስፈልጊንም አልናት ለህመሜ የሚደርስ እና የደረሰልኝ ማን ነው ብላ ተኝታለች አስታሞኝ ለህመሜሜ ደርሶ የሚያድነኝ ማን ይሆን ብላ ትጣራለች። ወገኖቼ እውነት ኢትዮጵያ ታማላች።
አገር ስትታመም በውስጧ ያቀፈቻቸው ልጆቿ በታላቅ ስቃይ ይመታሉ ታላቅም መከራ ይደርስባቸዋል በውስጧ ያሉትን ሰብስባ መያዝ ስለማትችል ከጉያዋ ወጥተው ወደ በአድ አገር ይሰደዳሉ። ልጆቿን የመመለሱም ሆነ የመከልከሉ አቅም አይኖራትም ምክንያቱም ስለታመመች።
ከህመሟ ሊታደጋት ካጎነበሰችበት ቀና ሊያደርጋት ከተኛበት ሊያነሳት ብዙዎች ቢደክሙም ከህመሟ እንዳታገግም ካጎነበሰችበት ቀና እንዳትል ከተኛችበት እንዳትነቃ የሚተጉ የውስጥ እና የውጪ ጠላቶች እንዳሉ እሙን ነው።
አገር ስትታመም ጩኸት ይበረታል በውስጥም ጩኸት …ከአገርም ተሰዶም ጩኸት፣ በአገር ቤትም ለቅሶ… ተሰዶም ለቅሶ፣ በአገርም ሞት… ተሰዶም ሞት፣ በአገር ቤትም ውርደት… ተሰዶም ውርደት ይሆናል ምክንያቱም የሁላችንንም ጩኸት የምትሰማ የሁላችንንም እንባ የምታብስ የሁላችንንም ሞት የምትታደግ አገራችን ስለታመመች መከራችንን መሸፈን አትችልምና ነው።
በወለጋ፣ በጎንደር፣በሐረር፣በባህር ዳር፣ በአንቦ፣ በደብረማርቆስ፣ በሱልልታ፣ በወልቃይት፣ በአርሲ፣ በኮንሶ፣በባሌ፣ በአገው፣ በሰላሌ፣ ፣ በአንድ ላይ ሆነው ህዝባችን ተነስተው ድምጻቸውን ማስተጋባት ጀመሩ በደላቸውን መናገር ጀመሩ ህመማቸውን መግለጽ ጀመሩ ችግራቸውን ማስተጋባት ጀመሩ የተሰጣቸው ምላሽ ግን ጥይት፣ የተሰጣቸው መልስ ግን ድብደባ፣ የተሰጣቸው ምላሽ ግን እስራት ነው። ምክንያቱም አገር ስለታመመች።
ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣ ሁመራ ለ25 አመት ከዛም በላይ በህዝባችን ላይ የዘር ማጥፋት እርምጃ ተወስዶብናል አሁን ግን ህዝባችን ላይ የሚወሰደው የዘር ማጥፋትም ሆነ ከመሬቱ የማፈላቀል ስራ እና ወንጀሎችን በዝምታ አናልፍም የተፈጸመብንን ግፍ እናጋልጣለን ብለው በተነሱበት ሰአት የተሰጣቸው መልስ ጥይት፣ ድብደባ፣ እስራት የማስፈራሪያ ዛቻ ነው። ምክንያቱም አገር ስለታመመች።
ይባስ ብሎ ጆሮን ጭው የሚያስብል ዜና ከወደ ደብረ ዘይት እና ከወደ ጋንቤላ ተሰምቷል። የደብረ ዘይቱ የኢሬቻን በአል በማክበር ላይ ባሉ ኢትዮጵያዊያን ለይ የተወሰደው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ታሪክ የማይረሳው ነው። ከ670 ንጹሃን ዜጎቿን በወያኔ አጋዚ በመጨፍጨፋቸው ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ ታላቅ ቁጣን በመቀስቀሱ ህዝቡ ወያኔን በመፋለም ላይ ይገኛል። ሌላው ደሞ ድንበር ጥሰው በመጡ የሱዳን ዜጎች አገር ሰላም ነው በሚኖሩ ዜጎች ላይ ከ280 በላይ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ በጥይት ተደብድበው በአገራቸው ተገደሉ ህጻናት እና ሴቶች ታፍነው ተወሰዱ ሃብት ንብረታቸው ከውጪ በመጡ ታጣቂዎች ተዘረፉ ይሄ ሁሉ ዘግናኝ እና ውርደት የተሞላበት ድርጊት ሲደረግ ከመንግስት የሚሰጠው መልስ እጅግ ያሳፍራል ህዝቡን ለታላቅ በቀል ያነሳሳል በህዝባችን ሞት እና መከራ ላይ የሚያደርጉት ነገር በቁስል ላይ ጨው የመነስነስ ያህል ነው። ከአገር ቢሸሽም ሞትና ውርደት በአገር ቤትም ሞትና ውርደት መድረስ ከጀመረ ሰነባብቷል። ምክንያቱም አገረ ኢትዮጵያ ስለታመመች።
ኢትዮጵያን ህዝቦቿን ለማጥፋት ለሚሯሯጡ ቅጣቱን ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ለማዳን ለሚተጉ የአሸናፊነት ኃይሉን እንደሚጎናጸፉ እሙን ነው።
ሳጠቃልለው እግዚአብሔር በትላልቅ ጉባዬ እና በኃይላቸው በሚመኩ መሃል ተገልጦ አያውቅም በተናቁት እና እራሳቸውን ዝቅ ባደረጉት መሃል ነው ሃይሉን የሚገልጠው። ትልቁ ጎልያድ ለመጣል እረኛው እና ትንሹን ዳዊትን ነው የተመረጠው። እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነጻ ለማውጣት የመረጠው ባህር ላይ የተጣለው ኮልታፋው ሙሴን ነው። ሰማይና ምድርን በቃሉ የዘረጋው ክርስቶስ የተወለደው በቤተ መንግስት ሳይሆን በግርግም ነው። ቀድመውም መወለዱን ያዩት ነገስታቶች አልያም ባለስልጣኖች ሳይሆን የተናቁት እረኞች ናቸው። ዛሬም ኢትዮጵያ አገራችን ታማለች እንጂ አልሞተችም በአለም ደረጃ እና በግለሰቦች አመለካከት የተዋረደች እና የተናቀች ብትሆንም በእግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠች እና የተወደደች አገር ናት። የወደዳት እና የመረጣት እግዚአብሔር ግዜው ሲደርስ ጠላቶቿን እንደ ዳዊት በጠጠር የምታሸንፍ አገር ናት። ስለ ኢትዮጵያ በእግዚአብሔር ዘንድ የተነገረው ትንቢቱ ሲፈጸም። የናቋት እና ያንቋሸሿት ሁሉ በእግዚአብሔር በትር ካልተመቱ እና ከቆዩ እያዩት ከአለም ሁሉ ከፍ ከፍ ስትል ይመለከታሉ። ያኔ ልጆቿን በእቅፏ ትሰበስባለች ያኔ የናቋትም ያንቋሸሿትም ከአሸናፊዎች ሁሉ በላይ ስትሆን ያፍራሉ። ይሄንን ሊቃወም አልያም ሊያሸንፍ የሚችል የትኛውም የምድር ሃይል የለም ምክንያቱም ከእግዚአብሔር ስለሆነ። ኢትዮጵያ ታማ እንጂ ሞታ አታውቅም። ከህመሟ ድና ልጆቿን የምትሰበስብበት ግዜ ቅርብ ነው።
እስከዛው ግን በህመሟ እና በልጆቿ ስቃይ የሚሳለቁ ይበዛሉ።
ከተማ ዋቅጅራ
11.10.2016
Email- waqjirak@yahoo.com

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>