Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

የዶይቼ ቬለ የአማርኛው ስርጭት ሆን ተብሎ እየታፈነ ነው

$
0
0

የዶይቼ ቬለ የአማርኛው ስርጭት መታፈን

ኢትዮጵያ | DW.COM | 29.09.2016

የዶይቼ ቬለ የአማርኛ ስርጭት ካለፉት ጥቂት ጊዚያት ወዲህ  ሆን ተብሎ እየታፈነ ወይም እየታወከ መሆኑ  ተገለጸ። የመሥሪያ ቤቱ የቴክኒክ ባለሙያዎች እንደረሱበት፣ ስርጭቱ የሚታወክበት ቦታ እና የጊዜ ርዝመት የተለያየ መልክ አለው።

unnamed-1 ስርጭቱ ቀደም ባሉ ዓመታት ተመሳሳይ እወካ ደርሶበት የነበረ ሲሆን፣ የመብት ተሟጋቾች እወካውን የሚፈጽመው የኢትዮጵያ መንግሥት ነው በሚል መክሰሳቸው አይዘነጋም። ዶይቸ ቬለ ይህን ችግር በተመለከተ ቅሬታውን ለኢትዮጵያ መንግሥት እንደሚያቀርብ ባለስልጣናቱ ገልጸዋል።
የዶይቼ ቬለ የአማርኛ ስርጭት ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ  የድምፅ መታፈን/መታወክ ወይም ጃሚንግ እንዳገጠመው የቴክኒክ ክፍል ኃላፊዎች አስታውቀዋል። እወካው መኖሩንም በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚገኙ አድማጮቻችንም በሚልኩልን መልዕክቶች አረጋግጠውልናል። የአማርኛዉ ዝግጅት በሚሰራጩባቸዉ የአጭር ሞገድ መስመሮች ላይ እየደረሰ ያለው መታወክ ወይም ጃሚንጉ ሆን ተብሎ የሚደረግ ሳይሆን እንዳልቀረ የስርጭቱን ጥራት እና ሽፋንን የሚከታተሉት የዶይቸ ቬለ የቴክኒክ ባለሙያው ሁበርት ቻያ ገልጸዋል።
«  ከተሞክሮ ለመናገር የምንችለው፣ ይህ ረባሽ ድምፅ ወይም እወካ በተወሰነ የስርጭቱ ወቅት ስለሆነ የሚሰማው፣ ሆን ተብሎ የሚደረግ ነው ብለን እናስባለን። ይህ እወካ በተለይ፣ ለምሳሌ ዜናን ወይም እንዲሰሙ የማይፈለጉ ዘገባዎችን ይመለከታል። »
የእወካው ዓይነት የተለያየ መልክ እንዳለው ብሎም ፣ አንዳንዴ ሙሉ በሙሉ፣ ሌላ ጊዜ አለፍ አለፍ ብሎ እንደሚቋረጥ ወይም ስርጭቱን የሚረብሽ ድምፅ እንደሚሰማበት ነው ባለሙያው ያስታወቁት። ለዚህም ባለሙያው የሚሰጡት ምክንያት፣
« የሚያውክው ወገን ስርጭቱን በጠቅላላ ወይም የተወሰነውን ክፍሉን ማወክ የሚያስችለው በቂ አቅም የለውም። ስለዚህ በርግጠኝነት ውጤታማ ለመሆን የተወሰኑ ይዘቶችን ለተወሰኑ ደቂቃዎች እየመረጠ  ያውካል። »
የመታፈን ወይም የመታወክ እጣ ሲገጥመው የመጀመሪያው ጊዜ ያልሆነው የዶይቸ ቬለ የአማርኛው ስርጭት ካሁን ቀደም ለገጠመው አፈና ተጠያቂው የኢትዮጵያ መንግሥት ሳይሆን እንዳልቀረ የመብት ተሟጋቹ ድርጅት  «ሂውመን ራይትስ ዎች» ያወጣቸው ዘገባዎችም ይህንኑ  ይጠቁማሉ

ለተወሰነ ጊዜ ከአፈና ነፃ ሆኖ ከቆየው በኋላ አሁን  እንደገና ለገጠመው የመታፈን ችግር  ለስርጭቱ መታፈኑ ምክንያቱ በርግጠኝነት ይህ ነው ብሎ ለመናገር ባይቻልም፣  እንደ ዶይቸ ቬለ የአፍሪቃ ክፍል ኃላፊ ሚስተር ክላውስ ሽቴከር ግምት፣ ከጥቂት ወራት ወዲህ በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተነሳው ፀረ መንግሥት ተቃውሞ ምክንያት ሊሆን ይችላል።

« የኢትዮጵያ ባለስልጣን መሥሪያ ቤት ስርጭቱን እንዲያፍን ያነሳሳውን ምክንያት በተመለከተ ግምት ብቻ ነው ልንሰጥ የምንችለው። ይሁንና፣ ባለፈው ዓመት በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ከተነሳው እና ከ400 የሚበልጡ ሰዎች ሕይወት ካለፈበት ግጭት በኋላ የጃሚንግ እና ሆን ተብሎ የሚደረገው የማወክ ተግባር ጨምሮዋል። እና  የስርጭቱ መታወክ በመንግሥት ጭቆና ፣ እንዲሁም፣ ተጓድሎ በሚገኘው ፖለቲካዊ ተሀድሶ ሰበብ በተለይ በወጣቱ ዘንድ ስለሚታየው ቅሬታ ከምናቀርባቸው ዘገባዎች ጋር የተያያዘ ነው ብለን እንጠረጥራለን። መንግሥት በዘገባዎቹ ደስተኛ አይደለም። ነገር ግን ይህ ሚዛናዊ የሆነ የዘገባ አቀራረብ ሥራችን አንድ አካል ነው። »
ዶይቸ ቬለ የሰሞኑን የስርጭት መታወክ/ ጃሚንግን በተመለከተ፣ ካሁን ቀደም ተመሳሳይ ችግር ሲገጥመው እንዳደረገው ሁሉ፣ አሁንም ቅሬታውን  ለኢትዮጵያ መንግሥት የማቅረብ እቅድ እንዳለው ሚስተር ክላውስ ሽቴከር ገልጸዋል።
« በአዲስ አበባ የጀርመን አምባሳደር በተገኙበት አንድ ስብሰባ ወቅት የስርጭት አፈና ጃሚንግ ድጋሚ ሥራ ላይ እንደማይውል ከኮሚኒኬሽን ጉዳይ ሚንስቴር ዋስትና አግኝተን ነበር። እኔ እስከማውቀው ድረስ ስለ ጃሚንግ እንዲህ በግልጽ ሲነገር ይህ የመጀመሪያ ጊዜ ነበር። እና በቀዝቃዛው ጦርነት ጊዜ የሚሰራበት ዘዴ በዚሁ አብቅቷል ብለን ተስፋ አድርገን ነበር። ግን ይህ ቃላቸው/ዋስት አለመከበሩን ነው አሁን ያየነው። በዚህም የተነሳ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት፣ የጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል በቅርቡ በኢትዮጵያ በሚያደርጉት ጉብኝታቸው ወቅት ስለዚሁ ጉዳይ  ከከፍተኞቹ ባለስልጣናት ጋር አንስተው እንዲወያዩበት የመራሒተ መንግሥቷን ጽሕፈት ቤት እንጠይቃለን። የስርጭት አፈና/እወካ ከጊዜው ጋር የሚሄድ አይደለም። እኛ የኢትዮጵያንም መንግሥት ሆነ ሕዝብ ለመጉዳት አንፈልግም። ሚዛናዊ  የሆነ መረጃ ማቅረብ ብቻ ነው የምንፈልገው። እና በዚሁ ሥራችንም ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ወደፊት እንደማያውከን ተስፋ እናደርጋለን። »አርያም ተክሌ ሸዋዬ ለገሠ

ፈይሣ ሌሊሣ በድርጊቱና በአስተሳሰቡ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን እንደራሳችን ወገን እንድቆጥር አድርጎናል! –ኦባንግ ሜቶ

$
0
0

Lalisa Feysa

ከአንድ ወር በፊት በሪዮ ኦሎምፒክ ሁለት እጆቹን በማንሳት በኢትዮጵያ የሚፈጸመውን ግፍ የተቃወመው ፈይሣ ሌሊሣ “ሁላችንንም እንደ ኢትዮጵውያን እንድንተያይ አድርጎናል” በማለት አቶ ኦባንግ ሜቶ ገለጹ፡፡

የፈይሣን የጀግንነት ተግባር በተመለከተ አቶ ኦባንግ በሚመሩት ድርጅት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ስም ባሰራጩት መግለጫ ላይ ነበር ይህንን ሃሳብ የገለጹት፡፡ “ኦገስት 21፤ 2016ዓም ኢትዮጵያውያን አዲስ የመንፈስ መነቃቃት ሆነላቸው” በማለት የፈይሣን አኩሪ ተግባር የገለጸው መግለጫ ይህ የኦሮሞ ወጣት ለወገኖቹ ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም ድምጻችንን በዓለም ላይ እንዲሰማ አድርጎልናል ብሏል፡፡  ድርጊቱም የዓለምአቀፉን ሚዲያ ትኩረት በመሳብ በህወሃት የግፍ አገዛዝ ላይ ብርቱ ጡጫውን አሳርፏል፡፡

“በርግጥ ፈይሳ የኦሮሞ ሕዝብ ኩራት ነው” ያሉት አቶ ኦባንግ፤ “ነገርግን ፈይሣን በዋሽንግተን ዲሲ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጥ በሰማሁት ጊዜ እንዲሁም በግሌ ካገኘሁት በኋላ ከብሔር ማንነቱ በላይ እጅግ ታላቅና አስደናቂ ሰው መሆኑን ለመረዳት እያለሁ” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

“የኢትዮጵያ መንግሥት የራሱን ሕዝብ እየገደለ፣ እያሰረና እየጨቆነ ይገኛል፤ በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በጋምቤላ ያለው ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ነው፤ … እኔ ኦሮሞ ነኝ፤ ያደኩትም በኦሮሚያ ነው፤ የሕዝቤን ስቃይ በደንብ አውቃለሁ፤ መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ በጠየቁ ሰልፈኞች ላይ መንግሥት ተኩስ ከፍቶ እስካሁን ከ1000 በላይ ሰዎች ሞተዋል፤ ሌሎች ደግሞ ከአገር ለቅቀው እንዲወጡ በመደረጋቸው በሊቢያ በረሃ ታርደዋል፤ ሌሎች በጣም ብዙዎች ደግሞ በሜዲተራንያን ባሕር የባህር አውሬ ሲሳይ ሆነዋል” በማለት ፈይሣ ለጋርዲያን ጋዜጣ የተናገረውን በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል፡፡

ይህንን የፈይሣን ንግግር አቶ ኦባንግ ከራሳቸው የሕይወት ተሞክሮ ጋር አዛምደውታል፡፡ “ፈይሣ የተናገረው የራሴን ሕይወት የሚያሳይ ነው፤ ከተወለድኩበት የአኙዋክ ጎሣ በዲሴምበር 2003 ዓም 424 ወገኖቼ ከሦስት ባነሱ ቀናት ውስጥ መሬታቸውን እና የመሬት ሃብታቸውን ለመቀማት በተመኘው የህወሃት ቡድን ተጨፍጭፈዋል፤ ከዚህ አሰቃቂ ድርጊት በኋላ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን ስመለከት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ነጻ መውጣት እውን ካልሆነ አንድ ጎሣ ወይም ብሔር ብቻውን ነጻ መውጣት እንደማይችል፤ ይህም ደግሞ ለዘላቂ ነጻነትና ፍትሕ ወሳኝ መሆኑን ተገነዘብኩ፤ ይህም ግንዛቤዬ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) መቋቋም በር ከፋች ሆነ፤ አኙዋኮች በመጨፍጨፍ በቀጣይ ተመሳሳይ አመለካከትን ህወሃት/ኢህአዴግ እንደሚያራምድና በሌሎች የኢትዮጵያ ወገኖች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ እንደሚወስድ ግንዛቤ ወሰድኩ፤ ለዚህ ነው የሁሉም ነጻ መውጣት ወሳኝ መሆኑን የተረዳሁት፤ ፈይሣም እንዲሁ ህወሃት/ኢህአዴግ በፈጠረው የጎሣና የዘር ወጥመድ ውስጥ መግባት ለኢትዮጵያውያን አደገኛ ነገር መሆኑን በውል የተረዳ ነው” በማለት አቶ ኦባንግ በመግለጫው ላይ ተናግረዋል፡፡

ለማስረጃም ይህንን ጠቅሰዋል፤ ከላይ ፈይሣ መግለጫ በሰጠበት ጋዜጣ ላይ የሚከተለውን ብሎ ነበር፤ “አሁን ያለው ሁኔታ (ብሔርን እየለዩ የማጥቃት እርምጃ) በዚሁ ከቀጠለ የኢትዮጵያ ሁኔታ አደገኛ እንደሚሆን አልጠራጠርም፤ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ጣልቃ በመግባት በዚያች አገር ላይ ለውጥ እንዲመጣ መርዳት አለበት፤ እኔ በግሌ ሁኔታው በዘር ላይ ወደማነጣጠር እንዳይሄድ እፈራለሁ፤ ሁኔታው ወደከፋ ደረጃ ሳይደርስ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ጣልቃ መግባቱ የግድ ነው” ብሏል፡፡

“በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ የጠፋው ነገር ሰብዓዊነት ነው፤ በፊታችን የተጋረጠው ጦርነት እንደ እውነት የተዘራውን ውሸት መፋለም ነው” ያሉት አቶ ኦባንግ ላለፉት 25 ዓመታት ህወሃት በኢትዮጵያ ውስጥ የነዛው ጥላቻ፣ ዘረኝነት፣ መከፋፈል፣ … በብዙዎቻችን ዘንድ ሥር ሰድዶ ከሰብዓዊነት በፊት ጎሣን፣ ዘርን፣ ብሔርን፣ … በሚያስቀድም አዙሪት ውስጥ እንድንወድቅ አድርጎናል ብለዋል፡፡ ይህንን እንደምናሸንፈው የተናገሩት ኦባንግ እንደ ጋምቤላ፣ እንደ ኦሮሞ፣ እንደ አማራ፣ እንደ ሶማሊ፣ … ሆነን ሳይሆን እንደ አንድ ባለዓላማ ኢትዮጵያዊ ሆነን ህወሃት የደገሰልንን ጥፋት አልፈን መሻገር እንችላለን ብለዋል፡፡

እንዲህ እንድንሰባሰብ የፈይሣ ድል ያደፋፍረናል ያለው መግለጫ ፈይሳ ሁለተኛ ሆኖ በማሸነፍ የድል መስመሩን ሲያልፍና እጁን አጣምሮ ድምጻችንን ከፍ አደርጎ ሲያሰማልን በኢትዮጵያ ላይ የሰፈረው ጭለማ ተገፈፈ፤ የብርሃን ጭላንጭል ታየን፤ ድምጻችን ጎልቶ በዓለም ተሰማልን፤ የፈይሣ የጀግንነት ተግባር አዲስ ተስፋ በልባችን ውስጥ ፈነጠቀ፤ የውድድር መስመሩን አልፎ ድል ሲጎናጸፍ ለአንድ ወገን ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ በህወሃት/ኢህአዴግ የተመሠረተውን የዘረኝነት መሠረት አናወጠው በማለት መግለጫው ፈይሣ ለኢትዮጵውያን ያስገኘውን ድል ይጠቅሳል፡፡

ከዚህ ባለፈ መልኩ በብዙዎቻችን ላይ የተደፋውን እና አሜን ብለን የተቀበልነውን የህወሃት/ኢህዴግን የዘረኝነት ማታለያ ፈይሣ እምቢ በማለት ነጻ ሰው መሆኑን ማሳየቱ ብዙዎቻችንን ከታሰርንበት የዘር ፖለቲካ ወጥተን ለኅብረት እንድንቆም ያደፋፈረን ነው ብዬ እንዳምን ተስፋ ሰጥቶኛል በማለት አቶ ኦባንግ የግል ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡ በዚህ ብቻ አላቆሙም “ከዘርና ብሔር ልዩነታችን ባሻገር ፈይሳ ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ጀግና ነው፤ ባለፈው ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ባገኘሁት ጊዜ አገር ወዳድ፣ ትሁት፣ ተወዳጅ፤ የዓላማ ሰውና ደፋር መሆኑን ለማወቅ ችያለሁ” ብለዋል፡፡

በዚሁ መግለጫ ላይ አቶ ኦባንግ ፈይሳን ሊገጥሙት ከሚችሉት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ዋንኛውን ጠቅሰዋል፤ “ፈይሣን ህወሃት/ኢህአዴግ ባስቀመጠለት የዘር ሳጥን ውስጥ እንዲገባና ለብዙዎቻችን የትግል ተስፋ እንዳይሆን ይበልጡኑም በኦሮሞነቱ እንዲወሰን ሊያደርጉት ይሞክሩ ይሆናል፤ ሆኖም ማወቅ የሚገባን ነገር ማነው ማንነታችንን የሚወስንልን? ይኼ ነህ ብሎ የሚነግረን ወይም በዚህ የዘር ሣጥን ውስጥ ግባ ብሎ የሚደርገን ማነው? ህወሃት ያመጣው የዘር ፖለቲካ በርካታ ኢትዮጵውያንን በዚህ ዓይነት የዘር ሣጥን ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸው ከሰብዓዊነት ወደ ዘር ዝቅ ብለዋል፤ ይህንን በማድረግ ህወሃት ተሳክቶለታል ሊባል ይችላል፤ ኢህአዴግን በአንድ ዓመት የሚበልጠው ፈይሣ ለ25 ዓመታት የተዘራውን የዘር ፖለቲካ አልፎ በመውጣት ቢሳካለት አገሩ ነጻ ሆና ወደ አገሩ ተመልሶ በሩጫ ለመወዳደር እንደሚፈልግ መስማት የህወሃት የዘር ፖለቲካ ያላሰከራቸው በርካታ ፈይሣዎች እንዳሉ ያሳየ ጉልህና ተስፋ የሚሰጥ ተግባር ነው፡፡”

የፈይሣን አኩሪ ተግባር የተከተሉ በርካታዎች እየመጡ መሆናቸውን የጠቀሰው መግለጫ ከፈይሣ ሌሊሣ የድል ተግባር በኋላ ኤቢሣ እጅጉ በኪዩቤክ ካናዳ ማራቶን፤ በሪዮ ፓራኦሎምፒክ በ1500 ሜትር የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ ታምሩ ደምሴ፤ እንዲሁም በማርሻል አርትስ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሌላ ኢትዮጵያዊ ካሣ ይመር፤ በድፍረት እጃቸውን አጣምረው በማንሳት ለአገራቸውና ለወገናቸው ድምጽ ሆነዋል ብሏል፡፡

በማጠቃለያም “በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ እንደነዚህ ዓይነት ልጆች ያስፈልጓታል፤ የሞራል ልዕልናቸው የላቀ፤ ሰውን ሁሉ በሰብዓዊ ፍጡርነት የሚያዩና የሚያከብሩ አዲስ ለምንመሠርታት ኢትዮጵያ ያስፈልጉናል፤ ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ የሚሠጡ፤ የሌላው ህመምና ሥቃይ የራሳቸው አድርገው የሚወስዱ፤ የወገናቸውን መከራ በሚችሉት ሁሉ ለዓለም ለማሰማት በሕይወታቸው የሚደፍሩ ያስፈልጉናል” በማለት በአኢጋን መግለጫ ላይ የተናገሩት አቶ ኦባንግ ፈጣሪ እነ ፈይሣ፣ ኤቢሳ፣ ካሣ፣ እና ታምሩ ሕዝባቸውን የሚያገናኙ ድልድዮች ሆነው እንዲሰሩ እንዲረዳቸው ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

ይህ መግለጫ የተዘጋጀው በአኢጋን የሚዲያ ክፍል ሲሆን በኢሜይል አድራሻችን media@solidaritymovement.org ወይም አቶ ኦባንግ ሜቶን Obang@solidaritymovement.org ኢሜይል ሊያገኙ ይችላሉ፡፡

የጎባጣ አሽከር አጎንብሶ ይሄዳል….. (መርሐጥበብ ከባህር ዳር)

$
0
0

መርሐጥበብ ከባህር ዳር

 ወ/ሮ ገነት ገ/እግዚአብሔር

ወ/ሮ ገነት ገ/እግዚአብሔር

እኔማ ዘንድሮ በግርምት መሞቴ ነው፡፡ የሰው ልጅ በሚያውቀውም ሆነ በማያውቀው እየገባ መዘባረቁ የግርምቴ መነሻ ነው፡፡ የሻይ ማንኪያ ያህል መረጃ ይዞ ጭልፋ ሙሉ ወግ ማውጋት ምን የሚሉት በሽታ ነው፡፡ ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም እንዲሉ በትንሽ ነገር ሲነኩ እንደ ቆሌ ዶሮ መርገፍገፉ የሰሞኑ የአገሪቱ ካብኔ ተብየዎች ባህርይ በመሆኑ ከመደነቅ ይልቅ መገረም ነው የዕለት ቀለቤ፡፡

ሰሞኑን የአማራ ክልል ከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ በኃላፊነት የምትመራው ዲንቢጧ የሕወአት ተላላኪና የተላላው ደርጅት ብአዴን አባል ገነት ገ/እግዚአብሔር ገ/ኢየሱስ በምትፈጽመው ድርጊት በመላው አማራ ክልል የሕዝብ ጥላቻ ከማትረፏ በላይ አመኔታ የሌላት ደካማ ፍጡር መሆኗን በምትመራው ተቋምና በተለያዩ መድረኮች ሲነገራት የማትሰማና ከወድቀት የማትማር የባህር ዳር ከተማ ወጣት እያሳደነች የምታሳስርና የምታስገድል እንዲሁም በአማራ ክልል ሕዝብ ስም የምትነግድ ትውልድና ዘመን የማይረሳት ጠላት መሆኗ እየታወቀ የክልሉ መንግስት ቃል አቀባይ ተብየው ንጉሱ ጥላሁን ለክልሉ መንግስት ቃል ማቀበሉን ትቶ ለወ/ሮዋ ጥብቅና መቆሙን በራሱ የማኅበራዊ ድረ ገጽ በለቀቀው መረጃ መታዘብ ችያለሁ፡፡

የጠሉትን ማስጠላት ምን ያደርጋል በሚል ርዕስ የለቀቀው መረጃ “ወ/ሮ ገነት ሙሰኞችን አጥብቃ የምትታገል ምርጥ የሴት አመራር መሆኗን መመስከር እፈልጋለሁ፡፡ ነገር ግን በቢሮው ውስጥ ያሉ መሃንዲሶች በአጭር ጊዜ በሙስና ተዘፍቀው ሃብት በማካበት መኪና መግዛት፣ የቤት ባለቤት መሆን እና የቅንጦት ኑሮ ከማንም የኢትዮጵያ ህዝብ በላይ ለመሆን ሲባል ይህች ሴት የምትጠላውን ኪራይ ሰብሳቢነት ስለሚሰሩ ሴትነቷ ሳይገድባት ትታገላቸዋለች፣ ከስራ ታግዳለች፤ ለአብነት በቅርቡ የኮንትራክተሮችን የደረጃ ማሳደግ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች ከአንድ ኮንትራክተር እስከ 20 ሽህ ብር በመቀበል ህጉና መመሪያው የሚጠይቀውን መረጃ ሳያሟሉ ደረጃ የማሳደግ ስራ የሰሩ 4 ባለሙያዎችን ማንም ወንድ ያልደፈራቸውን እሷ ከስራ አግዳቸዋለች ታዲያ ይህችን ሴት ከዚህ በላይ ብትባልም አይገርመኝም ነገር ግን ደሃው የአማራ ህዝብ ነገ እለወጣለሁ እያለ የሚከፍለውን ግብር ሙሰኞች ሲዘርፋት ዝም ብዬ አላይም በማለቷ እንድትሸማቀቅ የሚያደርጉ የፌስ ቡክ ጀግኖች የገባችሁም ያልገባችሁም ከዚች ጀግና ሴት ራስ ላይ ብትወርዱ ጥሩ ነው፡፡ ከሚፃፈው ነገር ስነሳም ወ/ሮ ገነት ተወልዳ ያደገችው ባህር ዳር ቀበሌ 11 ሆኖ ሳለ ሌላ ታርጋ በመስጠት በሴትነት አታሸማቋት ኪራይ ሰብሳቢው ትታገልበት ይህ እውነታ ታሪክ ነው፡፡” የሚል ነው፡፡

እንደ ቃል አቀባዩ ዲስኩር ሙሰኞችን አጥብቃ የምትታገል ምርጥ የሴት አመራር መሆኗን መመስከር እፈልጋለሁ ማለቱ “የጎባጣ አሽከር አጎንብሶ ይሄዳል” የሚለውን አባባል ለጽሁፌ በርዕስነት እንድመርጥ አስገደደኝ፡፡ ለምን ቢሉ ከጌታው ከፍ ብሎ ላለመታየትና ጌታውን ላለማሳጣት ነው የሚለው አባባል ትዝ አለኝ፡፡ የንጉሱ ጠበቃነት በመረጃ ያልተደገፈ ነው፡፡

በሶማሌ አንድ አባባል አለ ልንገራችሁ። አባባሏን የሰመኋት ይህን ጦማር ስሞነጫጭር ነው፡፡ አንዲት ሶማሌ ሴት ነበረች። በሶማሌ ባህል ጋብቻ በግልጽ ካልሆነ አይፈጸምም። አንዲት ሶማሌ ከባህሉ ውጭ በድብቅ የወደደችውን ባል አገባች። ሁለቱ ተጋቢዎች  ከጊዜ በኋላ እንናገራለን በሚል ስምምነት የተጋቢ ቤተሰቦች ሳያውቁ አብረው መኖር እንደጀመሩ ባል በድንገት በመኪና አደጋ ሕይወቱ ያልፋል። ሚስት እንዴት ብላ ታልቅስ፤ ምክንያት አጣች። ‘ባሌ ነበረ’ ብላ ካለቀሰች፣ ሕጋዊ ባል አይደለም፤ ስለዚህ ‘ብልግና ነበር የምትሰሩት፤ መቼ ነው የተጋባችሁት?’ ሊባል ነው። ስለዚህ ልጅቷ ተጨንቃ ዝም አለች። በዚህ አጋጣሚ ከነበራቸው ፍየሎች አንዱ በቀበሮ ተበላና ሞተ የሚባል ወሬ በእረኛው መልዕክት ይደርሳል፡፡ ‘የኛ ፍየል እኮ በቀበሮ ተበላ ይላታል። ሚስቲቱም ምክንያት አግኝታ በዛ አለቀሰች። የልቅሶ ደረጃውን በመገንዘብ ይህን ያዩ አባትም “ልጄ ይሄ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነው!” አላት። ይባላል፡፡ የንጉሱ ወግም ከገነት ትግል ጀርባ ያለውን ድርጊት አለመገንዘቡን ያስታውሳል፡፡

በቅድሚያ ገነት ተብየዋን ግለሰብ በሚገባ አያውቃትም፡፡ የቀን እንጂ የሰው ጀግና እንደሌለውና በአንድ ድርጅት መሰባሰብ የግለሰቦች ማንነት መገለጫ እንደማይሆን እንኳን የመንግስት ቃል አቀባይ በሌላም ሙያ የተሰማራ ይዘነጋዋል የሚል ህሳቤ የለኝም፡፡ የንጉሱ ሀሳብ አላዋቂ ሳሚ ….. ነው የሆነብኝ፡፡

ግለሰቡ በቢሮው ውስጥ ያሉ መሃንዲሶች በአጭር ጊዜ በሙስና ተዘፍቀው ሃብት በማካበት መኪና መግዛት፣ የቤት ባለቤት መሆንና የቅንጦት ኑሮ እየኖሩ ያሉትን ጾታዋ ሳይገድባት ትታገላለች ያለው ሀሳብ ጅምላ አስተያየት በመሆኑ ብዙም ባልቀበለውም ድክመቱንና ሀቁን ጉዳይ ለማሳየት እሻለሁ፡፡ አቶ ንጉሱ ቆርጦ ቀጥል አመለካከትህ ብዙም ርቀት አያስጉዝህም፡፡ የአማራ ክልል አመራር ስሙ በተነሳ ቁጥር የምትሰነዝረው አስተያየት ለስልጣንህ ማቆያ የምትጠቀምበት ስትራቴጂ እንደሆነ ማስረጃ መጥቀስ አያስፈልግም፡፡ የጎንደር ቅዳሜ ገበያ በእሳት ሲጋይ ሰሜን ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ላይ ሆነህ በቪኦኤ የአማረኛ ቋንቋ ሬዲዮ ጣቢያ የሰጠኸው መግለጫ ተጠቃሽ ነው፡፡ በሌለህበትና በማታውቀው ጉዳይ መዘባረቅ በክራሞት የተላበስከው የሙያ ካባ ስለሆነ ብዙም  አይደንቀኝም፡፡ ዛሬ ደግሞ ስለ ግለሰቧ የሰጠኸው አስተያየት ብዕሬን ከወረቀት ጋር እንዳዋድድ አስገደድከኝ፡፡ ምክንያቱም ነገ ደግሞ ሌላ ላለማለትህ ዕምነት ስላጣሁብህ ነው፡፡

በእኛ አገር የጋዜጠኝነት ሙያ  የአንድ ወገን መረጃ ዜና እየሆነ አገር ማመስ ከተጀመረ ሩብ ዓመት እንዳለፈው ላንተ መንገር ለቀባሪው ማርዳት ነው የሚሆንብኝ፡፡ ሴትየዋ ብቻ የነገረችህን ተቀብለህ በቢሮው ውስጥ ያሉ መሃንዲሶች ኪራይ ሰብሳቢዎች ናቸው ማለትህ አዘንኩልህ ይህ ቀን እንዲህ ሆኖ የሚቀር መስሎህ ሁሉንም መሃንዲሶች በኪራይ ሰብሳቢዎች ቅርጫት ማስቀመጥህ ዘንግተኸው እንደሆነ እንጃ እንጂ የኮንስትራክሽን ዘርፉን የሚመራውም ኃላፊ መሃንዲስ ነው፡፡ ዳሩ ከመንግስት ቃል አቀባይ ምን ይጠበቃል፡፡

አቶ ንጉሱ ከሰጠኸው አስተያየት ተነስቼ ለአብነት ብለህ ያቀረብከው ሀሳብ “ጅል አይሙት እንዲያጫውት” የሚያሰኝ ነው፡፡ ቢሮው የኮንትራክተሮችን የደረጃ ማሳደግ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች ከአንድ ኮንትራክተር እስከ 20 ሺህ ብር በመቀበል ህጉና መመሪያው የሚጠይቀውን መረጃ ሳያሟሉ ደረጃ የማሳደግ ሥራ የሰሩ 4 ባለሙያዎችን ማንም ወንድ ያልደፈራቸውን እሷ ከስራ አግዳቸዋለች ያልከው ጉዳይ ጫፍ ይዘህ መሮጥህን ያሳያል፡፡ በቅድሚያ ምነው ዛሬ ይህን ሀሳብ ይዘህ ወጣህ ጃል? ከነገረ ቀደም በዚህ ዘርፍ ከሥራ የታገደ አይደለም አራት አንድም ባለሙያ የለም፡፡ በሥራ ተቋራጮች የደረጃ ማሳደግ ተግባር ከመመሪያ ውጭ ተደራድረዋል በሚል ተብለው የተጠረጠሩ በተለያየ የሥራ መደብና ደረጃ የሚገኙ ባለሙያዎች ከነበሩበት የሥራ መደብ አንተ እንዳወራኸው ታግደው ሳይሆን በሌላ የሥራ መደብ ተዛውረው እየሠሩ እንዳሉና እስካሁንም የተጠረጠሩበት ጉዳይ አስካሁን ዳር ሳይደርስ ባለሙያዎችም በተመደቡበት የሥራ መደብ እያገለገሉ እንደሚገኙ ልብ ትለው ይገባል፡፡

“ወዳጄ” አለ አጎቴ ታየር ወዳጄ ንጉሱ የወግህን ብዕር አልወደድኩትም፡፡ በደብዛዛ አመለካከት የወጣ ሀሳብ ከማደናቆር ውጭ ሌላ ፋይዳ የለውም፡፡ ታዲያ ይህችን ሴት ከዚህ በላይ ብትባልም አይገርመኝም ያልከው ነገር አልገባኝም ለምን አትነግረንም ቃል አቀባይነትህን ዘነጋኸው፡፡

ደሃው የአማራ ህዝብ ነገ እለወጣለሁ እያለ የሚከፍለውን ግብር ሙሰኞች ሲዘርፋት ዝም ብዬ አላይም በማለቷ እንድትሸማቀቅ የሚያደርጉ የፌስ ቡክ ጀግኖች የገባችሁም ያልገባችሁም ከዚች ጀግና ሴት ራስ ላይ ብትወርዱ ጥሩ ነው ያልከው ጉዳይ እጅግ አስጋራሚና እስስታም ባህርይን የሚያንፀባርቅ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ርካሽ ተወዳጅነት የሚፈጥረው ስሜት በመሆኑ አልተቀየምኩህም፡፡ ግለሰቧ ልውደድህ ብትልህስ በምን ቀልቧ ትወዳሃለች ጊዜውንና ቦታውን ማየት ነው እንጂ፡፡

ካቀረብከው ሀሳብ ሌላው ያስገረመኝ ጉዳይ “…ከሚፃፈው ነገር ስነሳም ወ/ሮ ገነት ተወልዳ ያደገችው ባህር ዳር ቀበሌ 11 ሆኖ ሳለ ሌላ ታርጋ በመስጠት በሴትነት አታሸማቋት ኪራይ ሰብሳቢው ትታገልበት ይህ እውነታ ታሪክ ነው፡፡” ያልከው ነው፡፡ ይህ ሀሳብ ጤንነትህን ሁሉ እንድጠራጠር ነው ያደረገረኸው

በቅድሚያ ምነው ስሟን ብቻ ጠርተህ ተውካት? ብዕርህ የፍርሃት ቀለም ለምን ይተፋል? ሌላው ትውልድ በማን ይገለጻል? በወላጅ ወይስ በቦታ? ደግሞም የግለሰቧን የትውልድ ቦታ ለማወቅ የግል ማኅደሯ ከሚገኝበት ተቋም ፈትሽ፡፡ እያሸማቀቃት እያለው ጾታዋ ሳይሆን ተግባሯ ነውና በመጀመሪያ ኪራይ ሰብሳቢነት ከመታገሏ በፊት ራሷን ከኪራይ ሰብሳቢነት ታጽዳ ያኔ የቃል አቀባይነትህ ተግባር ትፈጽማለህ፡፡ ዘመዴ ጫፍ ይዘህ አትባዝን- አበቃሁ፡፡

 

“የመለስ ልቃቂት” ሆድ እቃ ሲገለጥ”  –ሚካኤል ደርቤ (ቦስተን ማሳቹሴት)

$
0
0

 

መንደርደሪያ    

ye-meles-lekakit-standing-bookደረቅ ፖለቲካዊ መረጃዎች የተዘጋጀበት መጽሀፍ እንዲነበብ ከተፈለገ በአቀራረቡና በአፃፃፍ ስልቱ የሚያጓጓ ሊሆን ይገባል። በተለይም ስለ ዘረኛ ኋላቀርና ቆሞ ቀር የሆነውን የወያኔ ፖለቲካ መጽሐፍ ጽፎ አንባቢ መሳብ በጣም አስቸጋሪ ነው። ሩቅ ሳንሄድ  የእንግሊዝ የወያኔ መፈንጫ የሆነው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ ተከማችቶ የአይጥ መናኸሪያ የሆነውና በአስወጋጅ ኮሚቴ የተቃጠለው የውሸት አለቃ የሆነው በረከት ስምኦን የበሬ ወለደ ፕሮፖጋንዳ መጽሃፍ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። የውሸት አለቃው መጽሃፉን በውድ ዋጋ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ ቢያሳትምም፣ በሸራተን ሆቴል ውስኪና ሻምፓኝ አስከፍቶ ቢያስመርቅም፣ በታዋቂ ሆድ- አደር አርቲስቶችን ምዕራፍ እያስነቀሰ ቢያስነብብም፤ በማዕዛ ብሩ ሸገር ሬዲዮ በግድ እንዲተረክ ሙከራ ቢያደርግም መነበብ አልቻለም ከዚህ በተጨማሪ አንባቢዎች መጽሃፉን የፃፈው ሰው የደበቀው ነገር ሊኖር ይችላል፤ አሊያም ሃሰትን በእውነት ተለውሶ የተከተበ መሆን ጥርጣሬ ካሳደረ የመነበብ እድሉ ዝቅተኛ ነው። እርግጥ “ማን ያውራ የነበረ፣ ማን ያርዳ የቀበረ” የሚባል የተለመደ ሀገራዊ ብሂል ቢኖርም የወያኔን የሴራ ፖለቲካ ለማንበብ ከዚያም በላይ ትዕግስት ይጠይቃል። ወያኔ በጠላትነት መጥቶ እንደ ንብ መንጋ ኢትዮጵያን አፓርታይድ በሚመስል አሰራር ተቆጣጥሮ ያደረሰው የግፍ ግፍ የሂሳብ ስሌት ሳይሰሩ የሚያቀርቡ ሰዎች ለማውራትም ሆነ ለማርዳት የመታመን እድላቸው ጠባብ አይደለም። የሚቀርቡት መጽሀፎች በመረጃ የተጠናከሩ፤ ግራ ቀኝ  አመለካከቶችን ማገናዘብ ከቻሉ፤ በሀቅ ላይ የተመሰረቱ ትናንትናዎች ይዘው የሚነሱ ከሆነ መነበብ የሚችሉበት እድል ሰፊ ይሆናል።

ስለሆነም በአንድ በኩል ተጨባጭ መረጃዎችንና እውነታዎችን ሳይዛቡ የሚቀርቡበት፤ በሌላ በኩል ከሙያም ከፖለቲካ ልምድም በመንሳት የግል ምልከታን ሳያቅማሙና ሳይተሻሹ ለማቅረብ ከፍተኛ ድፍረት ይጠይቃል። ለምሳሌ ወያኔ ከልቡ ማውጣት ያልቻለው ገብሩ አስራት ጠቃሚ መረጃዎችን የያዘ ዳጎስ ያለ መጽሃፍ ቢያበረክትም በርካታ ሚስጥሮችን ሊሸሽግ በመሞከሩ “ከነገረን የደበቀን ይበልጣል” መባሉ መነሻው ይሄ ነው። በተለይም ኤፈርትን የመሳሰሉ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ አጥንት የጋጡ የዝርፊያ ማዕከላት “በኢትዮጵያ ያሳደሩት ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖ እዚህ ግባ አይባልም” ማለት እንኳን የገፈቱ ቀማሽ ለሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ለገብሩ የመንፈስ ልጆችም አያሳምንም። ከገብሩ አስራት ጋር “መድረክ” የሚል ድርጅት የመሰረቱን ፕሮፌሰር መረራንም ሆነ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በገብሩ አገላለጥ ከማዘን አልፈው መናደዳቸው አይቀርም።

 

“የመለስ ልቃቂት” የተባለው የኤርሚያስ ለገሰ መጽሀፍ በቅድሚያ ለመመርመር የሞከርኩት ከዚህ አንጻር ነበር። ይህንን ጽሁፍ ለመሞነጫጨር ያነሳሳኝ የመጀመሪያ ምክንያት ይሄ ነው። ያለማጋነን ከገመትኩት በላይ በበርካታ መረጃና ማስረጃዎች የታጨቀው ይህ መጽሀፍ የህዉሃት በዝርፊያ የተመሰረቱና የፋፉ ኢኮኖሚያዊ ሃይሎች ላይ መብረቃዊ ምት ያሳረፈ ነው። ፀሃፊው ኤፈርት-መር ካፒታሊዝም እያለ በተደጋጋሚ ቢገልጠውም ለእኔ ግን በዝርፊያ የገነባው ካፒታሊዝም (Crony Capitalisim) ሆኖ አግንቼዋለሁ። በሌላ በኩል ፀሃፊው የዝርፊያ ማዕከሉን በግማሽ መንገድ እንዳለ አስልቶ “ልቃቂት” ደረጃ ደርሷል ቢልም በዚህ መልኩ ለጥቂት ጊዜያቶች ከቀጠለ የአገሪቱ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ህይወት በአያሌው የሚናጋ ይሆናል። ጊዜ ከተሰጠው የኢትዮጵያ ህዝብ ስርአቱን ለመገርሰስ ከፍተኛ መስዋዕትነት የሚያስከፍል ይሆናል። ከልቃቂት ያለፈው የዝርፊያው ካፒታሊዝም (ክሮኒክ ካፒታሊዝም) በጠምንጃና በሰደፍ የፖለቲካ ስልጣንን ማቆየትንና በህዝብ ላይ ሸክሙ የሚከብድበት ሁኔታ ይፈጠራል። ከመጽሀፉ መገንዘብ የቻልኩት ነገር ቢኖር የወያኔ አገዛዝ በዝርፊያ ቁምጣን የያዘው ቢሆንም በቃን የሚል አይደለም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ ህዝብ ባደረሰባቸው አደገኛ ምት እንደተጎዱ መውሰድ ቢቻልም የቆሰለ አውሬ ሆነው የሚቀትሉበት ሁኔታ እድሉ ዝግ አይደለም። አደብ እንዲገዙ ካልተደረገ አልጠግብ ባይነታቸው በበለጠ ቁጭትና በቀል ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ሁኔታ ይፈጠራል።

የአገሪቱን ሀብት የተቆጣጠሩት የህዉሃት የብርቅ ልጆች በአንድ በኩል በሃብት ጋራ ላይ ሰማየ ሰማያት እየረገጡ የሚሄዱበት፤ በሌላ በኩል ኢትዮጵያ የሃዘን ቤትነቷ የሚቀጥል ይሆናል። ይህ እንደ አሳ ከጭንቅላቱ የገማ ስርአት ያለምንም ከልካይ የአገሪቷን አንጡራ ሃብት የሚቆጣጠርበት ሁኔታ ይፈጠራል። ፀሃፊው በመጽሐፉ እንደገለጸው ሁኔታዎች በፍጥነት ካልተቀየሩ ነገ ከነገወዲያ “የኢትዮጵያ አየር መንገድ”፣ “የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ”፣ “የኢትዮጵያ ቴሌኮሚዩኒኬሽን” የሚባሉ ተቋማት በባለቤትነትና በስም ተቀይረው የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። ዛሬ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከሰጠው ብድር 40% ያህሉን ወያኔ ኤፈርትን ለመሰሉ ዘራፊ ኩባንያዎች እንዲሰጥ ካስገደደ፤ ከአመታት በኋላ እንደ አንፀባራቂው የመቶ ፐርሰንት ምርጫ ውጤት የብድር መጠኑም ተመሳሳይ ይሆናል።

ለምሳሌ ያህል “የመለስ ልቃቂት” ገጽ 139 ላይ “ልማት ባንክ የማነው? የትግራይ አይደለምን?” በሚል ርዕስ ስር እንዳመለከተው “በዘመነ መለስ ዜናዊ” የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከሰጠው 8.5 ቢሊዮን ብር ብድር ውስጥ 5ቢሊዮን ያህል (59%) የወሰዱት የትግራይ ክልላዊ መንግስትና የዘረፋ ካፒታሊዝም እየገነባ ያለው ኤፈርት ነው። ልማት ባንኩ ዳይመንድ ጁባይል ኢዩቤልዩውን ባከበረ አመት ብቻ  ለማበደር በእቅድ ከያዘው 2.78 ቢሊዮን ብር ውስጥ 1.7 ቢሊዮን ብር (63%) የዘራፊው ቡድን ንብረት ለሆነው መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ማስፋፊያ ፕሮጀክት አስቀድሞ የተያዘና የተፈቀደ ነው። ከሁሉም የሚያሳዝነው አበዳሪም ተበዳሪም የሆነው ኤፈርት በራሱ የሰጣቸው ብቻ ሳይሆን እንደ ጆፌ አሞራ ከየቦታው የለቃቀማቸውን የኤፈርት ብድሮች የተበላሹና የማይሰበሰቡ በማለት ከአካውንቱ እንዲወጣ አድርጓል። “የመለስ ልቃቂት” የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ምዕራፎች አየር መንገዱ፣ ጉምሩክ ባለስልጣን፣ ቴሌ ኮሙዩኒኬሽን፣ መንገዶች ባለስልጣን፣ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ፣ ንግድ ባንክ፣ የፍትህ ሚኒስቴር፣ ደህንነት ቢሮ፣ መከላከያ፣ ኢምግሬሽን ቢሮ፣ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትና ኤምባሲዎች፣ የሚዲያ ትርቋማት (ኢቲቪ፣ ፋና፣ ዋልታ)…. ወዘተ በምግባር የማናቸው የሚለውን ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ ነው።

 

“የመለስ ልቃቂት ጭብጦች”

                                                                                                                                                                                 

እስከገባኝ ድረስ “የመለስ ልቃቂት” መፅሃፍ ውስጣዊ ይዘት ስመረምር ለጊዜው ሦስት ያህል ቁልፍ ጉዳዮችን ተመልክቻለሁ። እነዚህ ቁምነገሮች በተጠናጥል የቆሙ ሳይሆን አንደኛው ለቀጣዩ መሰረት ሆኖ የሚያገለግል ነው። ለዚህም ሃፍረተቢስነታቸውም ያስመሰከሩ በቂ ምክንያቶች ቀርበዋል። ወያኔዎች ከራስ በላይ ንፋስ እንደሚባለው ብሂል “ወደ ውስጥ ተመልካች” (Inward Looking) በመሆናቸው ስለደህንነት መዋቅራቸው፣ ስለ ኢኮኖሚ ሞኖፖሊያቸውና የፖለቲካ የበላይነት ለማረጋገጥ የሚሰሩት የተቀናጀ ስራ ጠቅላላውን የፖለቲካ ሃይል አሰላለፍና ጉዞ እንድንመለከት ያስችለናል። ለማንኛውም “የመለስ ልቃቂት” ዋና ዋና ጭብጦች የሚከተሉት ይመስሉኛል።

ጭብጥ አንድ፦ የመጽሃፉ መንደርደሪያና ፍሬ ሃሳብ በምዕራፍ አምስት “የማስታወሻ አስኳል” በሚል ርዕስ እናገኘዋለን። የማስታወሻው አስኳል ባለቤት ሟቹ መለስ ዜናዊ ሲሆን ኤርሚያስ “ስድስቱ የመለስ አስተምህሮዎች” በማለት ከፋፍሎ ለብቻ አቅርቦታል። እነዚህ አስተምህሮዎች መለስ ዜናዊ ድንክዬ ልጆቹንና የቤት ውስጥ ባለሟሎቹን ለማደቆን ያዘጋጀው ሰነድ ላይ እንደሚገኝ ያስገነዝባል። “የመለስ ልቃቂት” ገጽ 165- 166 ስድስቱ አስተምህሮቶችን ጭማቂ እንደሚከተለው ይገልጻል፦

 

አስተምህሮ አንድ፦“ትእምት የህዉሀት ንብረት ያልሆነ በትጥቅ ትግሉ ወቅት በተሠባሠበ ገንዘብና ንብረት በህግ የተቋቋመ                         ግብረ-ሠናይ ድርጅት ነው”

አስተምህሮ ሁለት፦“ትእምት የተቋቋመበት ተልዕኮ በመንግስትም ሆነ በባለሀብቶች ሊሸፈን የማይችል ቀዳዳ ለመድፈን

                         ነው።”

አስተምህሮ ሶስት፦  “ትእምት አመራር ስርአት በግልፅነት መርህ ላይ የተመሠረተ ነው።”

አስተምህሮ አራት፦ “ትእምት ከመንግስት ያገኘው ወይም የወሰደው ቅንጣት ሳንቲም የለም። ወደፊትም አይኖርም።”

አስተምህሮ አምስት፦ “ትእምት ኢኮኖሚውን ሊቆጣጠር፣ ባለሀብቶችን ሊያፍን ነው የተቋቋመው በማለት የሚናፈሠው

                         አሉባልታ መሠረ-ቢስ ነው”

አስተምህሮ ስድስት፦ “ትእምት በክልሎች መካከል የተመጣጠነ እድገት መኖር አለበት ብለን ያስቀመጥነውን መርህ

                           አይጻረረም”

 

ኤርሚያስ በመጽሀፉ አስኳል ላይ የመለስን አስተምህሮ ለምን በስድስት ገድቦ ለማቅረብ እንደፈለገ ግልፅ አይደለም። የማስታወሻውን አስኳል ነጥብ በነጥብ ለተመለከተ ሰው ተጨማሪ የመለስ የቅጥፈት አስተምህሮቶችን መመልከት ይቻላል። ለምሳሌ ያህል “በመለስ ልቃቂት” ገጽ 182 ላይ እንደተገለጸው መለስ ዜናዊ “ኩባንያዎቹ የወያኔን ፖለቲካዊ ስራዎች ለማከናወን ገንዘብ አይሰጡም” የሚል የጠራራ ፀሃይ ውሸት ጽፏል። ድንክዬዎቹና ባለሟሎቹ “የደንቆሮዎች ውይይት” በመሰለ የሃሳብ ውዥንብር ውስጥ ካልዳከሩ በስተቀር ህዉሃትና በተለያየ ጊዜ ጠፍጥፎ የፈጠራቸው ድርጅቶች በዘረፋ የተደራጁት ኩባንያዎች ቀጥተኛ ተጠቃሚዎች ናቸው። ከዚህ አንፃር የዝርፊያ ኩባንያዎቹ ያደረጉትና እያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ በለሆሳስ የሚታለፍ አይደለም። ፓርቲዎቹ ለሚሰሩት ስራ፣ ለአባሎቻቸው የሚከፍሉት መደለያ ገንዘብ ህዝቡን ለማፈን ለሚዘረጉት መዋቅር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የገንዘብ ምንጫቸው እነዚህ ኩባንያዎች ናቸው።

 

ያም ሆነ ይህ “የመለስ ልቃቂት” ከመጀመሪያው ምዕራፍ እስከ መጨረሻው  ገጽ ድረስ የሟቹ መለስ ዜናዊ ኑዛዜ ቃላት (“አስተምህሮ”) በቅጥፈት የተሞሉና ውሸት መሆናቸውን በመረጃ አስደግፎ ያቀርባል። በዝርዝር እንዳየሁት ከሆነ ይህ “አሳ ጎርጓሪ” የሆነ መጽሃፍ ከኢኮኖሚ ሂሳብ ባሻገር የወቅቱን የህዉሃት የፖለቲካ የበላይነት የተረጋገጠበት ነው።

ጭብጥ ሁለት፦ “የመለስ ልቃቂት” የወያኔ ሦስቱ የዘረፋ የኢኮኖሚ ሃይሎች የሆኑትን ኤፈርት፣ ትልማ(ትግራይ ልማት ማህበር) እና ማረት (ማህበረ ረድኤት ትግራይ) አስቀድሞ በታቀደና የአፓርታይድ መርሆ በሆነ መንገድ የኢትዮጵያን አንጡራ ሃብት የማግበስበስ ስራ በቅንጅትና በመደጋገፍ እንደሚፈጽሙት ያስረዳናል። በጠምንጃ የተደገፈው የወያኔ ስልጣነ መንግስት ለሦስቱ የፖለቲካል- ኢኮኖሚ ሃይሎች የተለያየ ተልዕኮ በመስጠት የኢትዮጵያንም ሆነ ከውጭ የሚመጡ እርዳታዎችን በመቀራመት ወደ ትግራይ እንዴት እያሻገረ መሆኑን መረዳት ይቻላል። የኤፈርት፣ ትልማና ማረት ጓዳ ጎድጓዳ ሲመረመር በአገሪቷ ላይ ያደረሱትና እያደረሱ ያሉት የጥፋት መጠን ምን ያህል ከፍተኛ እንደሆነ በቀላሉ መገመት ይቻላል። ርግጥም በኢትዮጵያ የሰፈነውን ኢ-ፍትሃዊነትና የተዛባ ተጠቃሚነት ለመዳሰስ የሦስቱን የፖለቲካል- ኢኮኖሚ ሃይሎች አመሰራረት፣ አደረጃጀት፣ ራዕይ፣ ተልዕኮና ተጨባጭ ተግባራት አብጠርጥሮ ማወቅ የወያኔ መሪዎች የኢኮኖሚ ራዕይ “የትግራዋይ” መሆኑን ይደርስበታል። ያለምንም ማጋነን “የመለስ ልቃቂት” ኢትዮጵያን አፓርታይድ በሚመስል መልኩ የያዙት የወያኔ መሪዎች ለሩብ ክፍለዘመን ቆዳቸውን እየቀያየሩ የሚያሳዩትን ድራማ በመረጃ አስደግፎ ያቀረበ በሳል መጽሃፍ ነው።

በተለያዩ መጽሃፍትና መጣጥፎች እንደተገለጠው የወያኔ የኢኮኖሚ አውታር ስለሆነው “ኤፈርት” ብዙ ተብሏል። ኤርሚያስ በዚህ መጽሃፍ ላይ በርካታ መረጃዎችን በመጨመር ያጠናከረው ሲሆን በአገሪቷ ህግ መሰረት የተቋቋመ መሆኑና አለመሆኑን ጥያቄ አስነስቶበታል። የፖለቲካ ፓርቲዎችና አመራሮቻቸው ላይ መነጋገር መጀመር እንዳለባቸው አስገንዝቧል። እኔም የጸሃፊውን ሃሳብ እጋራለው። ከወያኔ በኋላ የሚገነባው አዲስ ስርአት በእነዚህ የዝርፊያ ተቋማት ላይ አስቀድሞ አቋም መውሰድ እንደሚገባው አምናለሁ። የተዘረፈው የኢትዮጵያ ህዝብ ሀብት ለባለቤቱ የሚመለስበት ሁኔታ መፈጠር ይኖርበታል። በስሙ የሚነግድበት የትግራይ ህዝብም ኤፈርት፣ ትልማም ሆነ ማረት ህገ-ወጥና ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ የተቋቋሙና የኢትዮጵያን ህዝብ አጥንት በመጋጥ የፋፉ መሆኑን ተገንዝቦ ድርጅቶቹ ላይ ለሚወሰዱት እርምጃዎች ትብብር ማድረግ ይጠበቅበታል።

ጭብጥ ሦስት፦ “የመለስ ልቃቂት” የወያኔ ሦስቱ የዝርፊያ ድርጅቶች የትግራይ የህዝብን በልዩ ሁኔታ ተጠቃሚ አድርገዋል የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱን በተለያዩ ቦታዎች አሳይቷል፡፤ ይህንን ድምዳሜ በመጽሃፉ ሆድ እቃ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በጀርባ ሽፋኑም ላይ አጽንኦት ሰጥቶ አስፍሯል። ከብዙ በጥቂቱ እንዲህ ይላል፣

“ትግራይ አልተጠቀመችም የሚለው የፖለቲካ መንገድ በየትኛውም መከራከሪያ እያረጀና እያፈጀ ሄዷል። ተጠቃሚነት መለካት ያለበት በየደረጃው ነው። …. ሁሉም የትግራይ ተወላጅ ሚሊኒየር ሊሆን አይችልም። ሁሉም የትግራይ ተወላጅ የመንግስት ተቀጣሪ ሊሆን አይችልም። ሁሉም የትግራይ ተወላጅ ዩንቨርስቲና ኮሌጅ ሊገባ አይችልም።…. ትግራይ ተጠቅማለች ሲባል ሁሉም የትግራይ ወጣትና ሴት የፋብሪካ ሰራተኛ ኩባንያዎች በሆኑት አዲግራት መድሃኒት ፋብሪካ፣ አልመዳ ጨርቃጨቅ፣ በትራንስ፣ በህይወት ሜካናይዜሽን፣ መሶቦ ሲምንቶ፣ ኢዛና…. ወዘተ የመሳሰሉት ዘመናዊ ፋብሪካዎች ተቀጥረው የሚሰሩት የትግራይ ተወላጆች ናቸው” ይላል።

“የመለስ ልቃቂት” የወያኔ መሰረት የትግራይ ስለሆነች የትግራይ ህዝብ በየደረጃው እንዲጠቀም አድርጓል ትለናለች። ወያኔ ከምንም በላይ የሚፈራውና የመኖር ህልውናውን የሚያናጋው የትግራይ ህዝብ ስለሆነ ህዝቡ ቢፈልግም/ባይፈልግም የኢኮኖሚ ተጠቃሚነቱን ማረጋገጡ የማይቀር እንደሆነ ያስገነዝበናል። ትግሬዎች ለወያኔ አገዛዝ ባላቸው ቅርበትና ርቀት ልክ ተጠቃሚነታቸው እንደሚረጋገጥላቸው ኤርሚያስ እማኞችን እያቀረበ ያሳየናል።  በዚህ ማስረጃ ውስጥ ገዥዎቻችን ምን አይነት ሰዎችና ምን አይነት ባህሪ እንዳላቸው እንመለከታለን። ወያኔዎች ከኢትዮጵያ ጥቁር አፈር ስለመፈጠራቸው ሳንወድ በግድ ጥያቄ እንድናነሳ ያደርገናል።

በአጠቃላይ መልኩ ብዙ እንደተላለፉት የሚያስታውቀው “የመለስ ልቃቂት” መጽሃፍ ወያኔ የፖለቲካ ሞኖፖሊውን እያስፋፋ የሄደውን ያህል የኢኮኖሚ ሞኖፖሊውን በአስተማማኝ መሰረት ላይ እየገነቡ ነው። ለፖለቲካው ፍፁም የበላይነትና መደላድል ወሳኝ የሚሆነው ኢኮኖሚውን መቆጣጠር እንደሆነ የሚገለጥበት አባባል ትክክል መሆኑን ያረጋገጠበት ነው። አዋጁን በጆሮ ካልተባለ በስተቀር ወያኔ የገነባው የዝርፊያ ካፒታሊዝም በራሱ መናገር ጀምሯል። የንቅዘቱ ደረጃ ከወያኔ የፕሮፖጋንዳ ማሽን ከሚነዛበት ቅጥፈት በላይ ተሻግሯል። ሦስቱ የወያኔ የዝርፊያ ማዕከላት ሁሉንም እየጠቀለሉ ነባር ሀገራዊ ከበርቴዎችን ከጨዋታ ውጭ እየወጡና ከትግራይ ውጭ አዳዲሶች እንዳይወለዱ እየተደረገ ነው። ከዚህ ሁኔታ ተነስተን አገራችን ኢትዮጵያ ያለችበት የወቅቱ ሁኔታና የወደፊት እጣ ፋንታ እጅግ አሳሳቢ ሆኗል። በአድሎና መገለል ምክንያት ጨጓራው የተላጠውና ቆሽቱ ድብን ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ባልታወቀ ጊዜ ፈንድቶ የወጣ እለት ውጤቱ ምን እንደሚሆን ለመገመት ነብይ መሆን አይጠይቅም።  “የመለስ ልቃቂት” የታመቀውን የህዝብ ብሶት በንዴት ገንፍሎ ሊያወጣው እንደሚችል ሙሉ እምነት አለኝ። ከዚህ አንጻር ኤርሚያስ መጽሓፉን መታሰቢያ ያደረገለት አንጋፋው ሙሉጌታ ሉሌ በጦቢያ መጽሔት ላይ “ስም ያልወጣለት ወንጀል” በሚል ርዕስ ያቀረበው መጣጥፍ ይታወሰኛል። አንጋፋው ብዕረኛ እንደገለጠው ከሆነ አንድ በአገዛዝ ውስጥ ያለ ህዝብ ደም የሚያስተፋ ንዴትና ቁጣ ካልተሰማው መሰረታዊ ለውጥ አይመጣም ይለናል።

“መናደድ ትልቅ ነገር ነው። መናደድ ብንችል ደግሞ አንዱ የዚች አገር ማዳኛ የትግል መቅድም ይሆናል። ግን ለመናደድ ለመብሸቅና ከተቻለም እህህህ ብሎ ደም መትፋት መቻል አለብን!! በማለት ብዕረኛው ይገልፃል።

“የመለስ ልቃቂት” መናደድ የማይፈልገውን ከውስጡ ፈንቅሎ በተዋረደ ስሜት የሚናደድበት ሁኔታ ይፈጥራል። ወጣቱ አዲስ የቁጭት ስሜት ፈጥሮ ወደ ተግባር የሚገባበት “የማታገያ ሰነድ” እንዳገኘ እቆጥራለሁ።

መልካም ንባብ!!

የማለዳ ወግ…በጅዳ 3 ሽህ ታዳጊዎችን ለመታደግ መምህራን ሲተጉ … ! -ነቢዩ ሲራክ

$
0
0

* በጅዳ የኢትዮ አለም አቀፍ ት/ቤት ዘንድሮም በአደጋ ላይ
* በትውልድ ላይ መቀለድ ይቁም … !
* መምህራንና ሰራተኞችን ተቆጥተዋል

እለተ ሃሙስ መስከረም 19 ቀን 2009 ዓም ምሽት ላይ በጅዳ አለም አቀፍ ት/ቤት ዙሪያ አንድ ሰበር መረጃ አቅርቤ ነበር ። ሰበሩ መረጃ ለአመታት ከግል ጥቅማ ጥቅም ባለፈ ከሶስት ሽህ በላይ (3000) ታዳጊ ኢትዮጵያውያንን ተማሪዎች ጉዳይ “ያገባናል ” ብለው የማያውቁት መምህራን ዘንድሮ ” ያገባናል ” ብለው ከጅዳ ኮሚኒቲ አመራሮችን ጋር ስብሰባ ላይ መፋጠጣቸውን ይመለከት ነበር ። ዛሬ የምናዎጋው በስብሰባው ዙሪያ ቢሆንም እንደ መግቢያ ትናንት መምህራኑ ሲዎሱ አሞን የባጀው ግዴለሽነትና ዝምታቸውን እናዎሳለን ፤ ዛሬም ሌላ ቅን ነውና መምህራኑ ለታዳጊዎች መብት መከበር ያሳዩትን ትጋት በጨረፍታ እንቃኛለን ! የፈቀደ ይከተለኝ …

nebiyu-1-satenaw-news

አሞን የባጀው የመምህራኑ ግዴለሽነትና ዝምታ …
===========================
አዲስ አመት በመጣና በሄደ ቁጥር ሁሌም ለጅዳና አካባቢው ቀዳሚው ህመም “የትምህርት ማዕከሉ አደጋ ላይ ወደቀ !” የሚለው መረጃ ነው ፤ በእርግጥም የትምህርት ማዕከሉ ማደግ ባለበት ፍጥነት ቀርቶ ለመቀጠል አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱ የመኮላሸት አደጋው መረጃ አሳሳቢ ነው ። ይህ ላለፉት በርካታ አመታት ወላጅ ነዋሪውን ሲያመን ቢከራርምም የውስጥ ብክለቱን አሳምረው ከሚያውቁት ከመምህራን የሚሰማው ሮሮ በተናጠል ከንፈር ከመምጠጥ የዘለለ እንዳልነበር በቅርብ የምናውቅ የምንመሰክረው እውነታ ነው ። ተማሩ ተመራመሩ የተባሉት መምህራን የውስጥ ችግሩን እያወቁና ትውልድ የሚቀረጽበት ማዕከል ወዳልተፈለገ አደጋ እየተጓዘ ዝምታን መርጠው ከርመዋል ። ባንድ ወቅት ” ት/ቤቱ አስተዳደርና ኮሚኒቲው በመኖሪያ ፍቃዳችን ዝውውር ዙሪያ መጉላላት አደረሰብን !“ ብለው የማስተማር ማቆም አድማ አድርገው መብታቸውን ያስከበሩ መምህራን የታዳጊዎችን የትምህርት ማዕከልን የውስጥ ገመና ከማናችንም በላይ እያወቁትና ችግሩን ለመፍታት ቀዳሚ መሆን ሲገባቸው ፈቃደኛ ሳይሆኑ ከርመው አሳዝነው ያውቃሉ ። ከእጅ ወደ አፍ በሆነ ኑሮ ልጅ ወልደን በአሳር በመከራ የምናሳድግ ስደተኞች ልጆች ትምህርት አሰጣጥና ግዙፉ የመቀጠል ያለመቀጠል አደጋን ችግር ቀድመው ቢረዱና መድሃኒቱን ቢያውቁትም ሊያክሙት ተስኗቸው ባጅቷል … እኒሁ ተስፋ የጣልንባቸው መምህራን እንኳንስ በታዳጊዎች መማሪያ ማዕከል የመጣውን ችግር ሊቀርፉ የውስጥ ህብረት አጥተው ግዙፉን ችግር በግድ የለሽነትና በትዝምታ ማለፍ መምረጣቸው መላ ነዋሪው አስከፍቶና አሳዝኖን መክረሙም ሌላው የማይደበቅ ነጭ እውነታ ነው …

አደጋው ገዝፎ መምህራን ሲቆጡ …
==============================
ዘንድሮ ግን ነገሮች ተለዋውጠዋል ፤ በጅዳ አለም አቀፍ ት/ቤት መምህራንና ሰራተኞች በህብረት ተቆጥተው ታይቷል ፤ ምክንያታቸው ደግሞ ከሶስት ሽህ (300) በላይ ታዳጊ ተማሪዎች ትምህርት የሚገበዩበት ማዕከል እያደር የመዝቀጡ እውነታ ገንፍሎ መውጣቱ ነበር ። መምህራንና ሰራተኞች ከላይ እስከታች ፤ ከኮሚኒቲው እስከ ት/ቤቱ አስተዳደር በኢህአዴግ አደረጃጀት በተዋቀረው አመራር የውስጥ ህብረት አጥተውና ተፈራርተው ቢባጁም ዘንድሮ እንደባጁት ፈርተው መቀጠልን አልፈቀዱም ። ለአመታት አርቆ የያዛቸውን ፍርሃት ሰብረው ከመውጣት ባለፈ ተቀናጅተው ወደ ትምህርት ቤቱ ባለቤቶች ቀርበው ” ግፍ በዝቷልና ሊቆም ይገባል ” ብለው ድምጻቸውን ማስማት ጀምረዋል ። በትምህርት ማዕከሉ የሚሰራው ሸፍጥና ግፍ ” መቆም አለበት” በማለት ተቃውሞ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል ! ከሶስት ሳምንት በፊት የተቆጡት መምህራንና የት/ቤቱን ባለቤት ከሆነው የኮሚኒቲውን አመራሮች ጋር ለመምከር ደጋግመው ቢጠይቁም አመራሩ እድል አለመስጠቱ ይጠቀሳል ። ዳሩ ግን ኮሚኒቲው አሻፈረኝ ሲል የወላጅና መምህራን ህብረትን በማማከር ወደ ቆንስላው ኃላፊዎች ቀርበው ብሶታቸውን ቢያሰሙም “ ህብረታችሁን አጽንታችሁ ከተጓዛችሁ ወላጁን በማቀፍ ለውጥ እንደምታመጡ ለታዳጊዎች ማዕከል ማንሰራራትና ትንሳኤ ተስፋ ያለው በእናንተ በመምህራን ላይ ነው ” ከሚል ዲፕሎማሲዊ የኃላፊዎች ምላሽ ባለፈ ላቀረቡት ስሞታ የረባ መፍትሔ እንዳልተሰጣቸው ከአስተባባሪዎች መካከል አንድ መምህር አጫውተውኛል … በያዝነው ሳምንት ግን ሳይታሰብ የኮሚኒቲው አመራር ከመምህራኑ ጋር ለመገናኘት ፕሮግራም መያዛቸው በተነገራቸው መሰረት ሐሙስ መስከረም 19 ቀን 2009 ዓም ምሽት ተቃውሞ ጥያቄያቸውን ከትምህርት ቤቱ ባለቤት ለት/ቤቱ አስተዳደር ፤ ለት/ቤቱ ባለቤት ለጅዳ ኮሚኒቲ አመራር አባላት እና ለመንግስት ዲፕሎማቶች አቅርበዋል !

በጦፈው ስብሰባ ምን ተባለ … ?
===========================
በእርግጥም ሐሙስ ምሽት የጅዳ ኮሚኒቲ አዳራሽ መምህራንና ሰራተኛች በነቂስ ተገኝተዋል ፤ በት/ቤቱ በኩል ስብሰባው ይጀምራል ተብሎ የተነገረው ሰዓት የተወሰነ ክፍተት ቢፈጥርም ስብሰባው ዘግይቶ ጀመረ … አጀንዳ ያልያዙት የኮሚኒቲው አመራሮች ያለ አጀንዳ ስብሰባውን መምራት ሲጀምሩ እርምት ተደረገ … እናም በቀጥታ ወደ ውይይቱ ተገባ ፤ መምህራን ጥያቄያችውን አዘነቡት … እንዲያ እያለ ቀጠለ ! …በእርግጥ መረጃውን ሳዳምጠው ማመን አልቻልኩም ፤ ብዙዎች እንደኔ መገረማቸውንም ሰምቻለሁ … በጦፈው ስብሰባ የተሰማው የመምህራንና ሰራተኛ ጥያቄ ፡ ቁጣ ፡ ሮሮና ተማጽኖ በወገናዊ ስሜት የተነገረ ፤ ከዚህ ቀደም ታይቶም ሆነ ተሰምቶ የማይታወቅ ነበር ማለት ይቻላል !
…በዚሁ ስሜት ቀስቃሽ በሆነ ስብሰባ በመምህራን የት/ቤቱ ፈቃድ አለመታደስ ፣ ካለው የተማሪ ብዛት አንጻር ተጨማሪ ት/ቤት ለመከራየት እቅድ ቢኖርም ፣ ት/ቤቱን መከራየት አለመቻሉን እንኳ የሰሙት በቅርቡ መሆኑን ተናግረዋል ። ዘንድሮም ወላጅ በፈረቃ ሊያስተምር ሲወሰን ፣ በጉዳዩ ባለድርሻ መምህራን እንዲመክሩና እንዲወያዩ አለመደረጉንም አንስተዋል ። ከሽዎች የሚቆጠሩ ታዳጊዎች ትምህርት የሚቀስሙበት ማዕከል አደጋ ላይ መሆን ያስቆጣቸው መምህራን በድፍረት ” ድብቅብቁ ይቁም! ” በማለት ሞጋች ጥያቄዎችን ለኮሚኒቲው ምክር ቤት አመራሮ ች ፤ ለት/ቤቱ አስተዳደር እና ለዲፕሎማቶች ያቀረቡ ሲሆን የቀረቡት ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው :-

በመምህራንና ሰራተኞች የቀረቡት ጥያቄዎች…
==========================
* የትምህርት ቤቱ ህጋዊነት ተረጋግጦ ተማሪዎች ወላጅ ብሎም ሰራተኛው ከስጋት ነፃ ይሁን
* በሳውዲ ት/ሚኒስትር ፈቃድ ይታደስ ፣ ትምህርት ቤቱ በአስቸኳይ በቦርድ ይተዳደር
*የት/ቤቱ የተወላከፈው አስተዳደር በአግባቡ ተዋቅሮ ተጠያቂነት እና ህግና ስርአትን የተከተለ አሰራር ይኑረው
*የት/ቤቱ አስተዳደር ከዝምድና ከጎሰኝነት እና ከመሳሰሉት ነፃ ይሁን
* ማህበረሰቡ የራሱ የሆነ ት/ቤት እንዲገነባ ሁነኛ ስራ ይሰራ
* አዲስ አመት ምዝገባ ላይ የሚስተዋለው በዘመድ አዝማድና በመሳሰሉት መሆኑ ኢ-ፍትሀዊነት ነው ይቁም
* መሰረታዊ የአሰራር እና የአስተዳደር ለውጥ ይኑር
* በትምህርት ደረጃቸው ማስተርስ ያላቸው ሰራተኞች ማግኘት ያለባቸውን ቦታ ይሰጣቸው
* የኮሚኒቲው ምክር ቤት በብቃት ሀላፊነቱን ይወጣ
* ት/ቤቱ ባለቤት አልባ እና ተቆርቋሪ አጥቷል
* በማዕከሉ አላፈናፍን ያለው ” ኪራይ ሰብሳቢነት” ተነቅፏል
* “የኪራይ ሰብሳቢነት” ምንጩ ቢታወቅም ኪራይ ሰብሳቢዎች ተሸፋፍነዋል ተለይተው ይታወቁ የሚሉት ከብዙው በጥቂቱ ይጠቀሳሉ

ለመምህራኑ ጥያቄ የተሰጠው ምላሽ …
=====================
ከዚህ በላይ በመምህራኑ የቀረቡትን ጥያቄዎችና ያነሷቸውን አንኳር መሰረታዊ ጥያቄዎችም የጅዳ ኮሚኒቲ አመራሮችንጨምሮ የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር ምላሽ ሰጥተውባቸዋል። በምላሹም የኮሚኒቲው አመረሮች ” ኃላፊነታችንን ለመወጣት ወደ ኋላ አላልንም ፣ ነገር ግን መንገድ ከያዝን በኋላ ይበላሽብናል ። በተበላሸ መሰረት ላይ ስለገባን ስራው አስቸጋሪ ሁኖብናል ” ብለዋል ። … ለትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ለማፈላለግ በሚደረገው ሂደት እግር በእግር እየተከታተሉ የሚያበላሹት ” ኪራይ ሰብሳቢዎች ” እንደሚያስቸግሯቸው በሚያሳብቅ ሁኔታ በሂደቱ ተማረው ምላሽ ሰጥተዋል። በሳውዲ ትምህርት ሚኒስቴር በኩል “ ቦርድ አቋቁሙ ” ተብሎ የተጓተተበትን ሂደትና ምክንያት አጥጋቢ ምላሽ ባይሰጥም ቦርድ ለማቋቋም በቅርቡ የተጠቆሙ የቦርድ አባላት ስላሉ ኮሚኒቲው ተመራጮችን እንደሚያጸድቅ ቃል ገብተዋል ።

ባልተለመደ መልኩ የህዝብ ወገናዊነትን ያሳዩትና ፍርሃትን አስወግደው ኮሚኒቲውን የሞገቱት መምህራን በስብሰባው ላይ ብሶት ስጋታቸውን ለማቅረብ ተደራጅተው በነቂስ መገኘታቸው ይጠቀሳል ። ” የትምህርት ማዕከሉ እያደረ መዝቀጥ የለብትም ፣ አሉ ያላችኋቸውን ኪራይ ሰብሳቢዎችን አጋልጡ!” ተብለው ለተጠየቁት የኮሚኒቲ አመራሮችን በምላሻቸው “ኪራይ ሰብሳቢ” ያሏቸውን ለማጋለጥ አልደፈሩም። የኮሚኒቲው አመራሮች ት/ቤቱን ለማሰራት እየተደረገ ስላለው ጥረት ሲዘረዝሩ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ ሳውዲ በመጡ ቁጥር የነዋሪውን ብሶት ማሳዎቃቸውን አስረድተዋል ፤ ወደ ኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስቸኳይ የትብብር ደብዳቤ መላካቸውን ገልጸዋል ፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አልፎ « ትምህርት ቤት ይሰራልን!» የሚል ደብዳቤ ተልኮ ከጠቅላይ ሚኒስተሩ እጅ መግባቱንም ለተሰብሳቢው አሳውቀዋል ። በዚህ ላይ አስተያየት የሰጡት የጅዳ ቆንስል ኃላፊ አምባሳደር ውብሸት “ ከመንግስት የተጠየቀው ድጋፍ በአሁኑ ሰአት ባለው የፓለቲካ አለመረጋጋት ትኩረት ላይሰጠው ይችላል ” የሚል ግምት እንዳላቸው ጠቁመዋል ። ከአንባሳደሩ ጋር ተቀራራቢ አስተያየት የሰጡት መምህራኑና ሰራተኞች በበኩላቸው ” ነዋሪው የሚያስተባብረው ቢያገኝና ኮሚዩኒቲው ከጉቦኝነት ነፃ ከሆነ ማንንም ሳይፈልግ ማህበረሰቡ የራሱን ህንፃ ይሰራል!”ሲሉ ተናግረዋል ። በዚህም በዚያም ተብሎ የጅዳ ኮሚኒቲ አመራሮች የመምህራኑን ጥያቄ ለመመለስ በሞከሩበት ምሽት በሁለት ወር ውስጥ አዲስ ነገር እንደሚታይ ቃል በመግባት ” ጥረታችን እንዲሳካ ታገሱንም እርዱንም ” በማለት መምህራንና ሰራተኞቹን ተማጽነዋል!

የዳይሬክተር አብዱ አባ ፎጌ ዲስኩር …
======================
የኮሚኒቲው አመራሮች በፈታኝ ጥያቄዎች ሲፋጠጡ የኮሚኒቲውን አመራር ትንፋሽ ለመስጠት የት/ቤቱ ዳይሬክተር አብዱ አባ ፎጌም የተለመደ ረዠምና አደንዛዥ የማይጨበጥ ትንተናቸውን ማቅረባቸው ይጠቀሳል። ለትምህርት ቤቱ አለመቀየር ብዙው ነዋሪ ጣቱን የሚቀስርባቸው የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር አብዱ አባፎጊ የተናገሩትን ሁሉ ዙሪያ ጥምጥም ትተን ወደ ፍሬ ነገሩ ስናመራ የፈቃዱን ጉዳይ እና ተዛማጅ ጉዳዮችን በሚመለከት በሰጡት ምላሽ ” ለማስተካከል የበኩላችንን ጥረናል ፣ ወደ ሳውዲ ት/ሚኒስተር ከአመት በላይ ተመላልሰናል። ብዙ በጀት ለዚሁ ጉዳይ ወጪ አድርገናል ። በእርግጥ የተጨበጠ ነገር በማጣቴ ሰራተኛውን ሰብስቤ ማወያየት አልቻልኩም ” በማለት የተለመደ እርባና ቢስ ዲስኩር ማሰማታቸው ይጠቀሳል ።

አስተያየት ፤ የምክር ቤቱ አባል …
===================
ከኮሚኒቲና ለት/ቤቱ ቅርብ የሆኑ የኮሚኒቲ ምክር ቤት አባልን የትምህርት ማዕከሉን ለማዳን መፍትሔው ምንድነው ? ብዬ ጠይቄያቸው ዋናው እየታየ ሰው ሊናገረው የማይደፍረው የኮሚኒቲው እና ት/ቤቱ በፖለቲካ ድርጅቶት አባላት ተጽዕኖ ስር መውደቃቸው እንደሆነ አጫውተውኛል ፣ ከኮሚኒቲው ስራ አስፈጻሚዎች መካከል ( 7 ለ 3 )አብዛኛው የኢህአዴግ አባላት በመሆናቸው በውሳኔ ድምጽ አሰጣጡ ተጽዕኖ መፍጠሩን ያስረዳሉ ። ከዚህም አልፎ የኢህአዴግ አባላት የበላይ መሆን ”በት/ቤቱ ውስጥ ያለውን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ፤ ስብሰባ ሲጠራ ፤ መዋጮ ሲጠየቅና ለመሳሰሉት ድርጅታዊ ጥቅማ ጥቅሞችን ለማስፈጸም ተብሎ የትምህርት ማዕከሉ እየተጎዳ ነው ።” ካሉ በኋላ ከዚህም አልፎ በትምህርት ቤቱ ዙሪያ ገብ ላለው መሰረታዊ ችግር ተጠያቂ የሆነውን የት/ቤቱን አስተዳደር ለመቀየር የሚደረገውን እንቅስቃሴ እስካሁን የሚያሰናክለውና የማይደፈርበት ምክንያት ዳይሬክተሩና የአስተዳደር ኃላፊው የድርጅት አባላት መሆናቸው እንደሆነ ዘርዝረው አውግተውኛል ። ይህም ዛሬ ኮሚኒቲው አስቸግሮኛል ያለው ኪራይ ሰብሳቢነት ተዛማጅ ችግሮች ተጠናክሮ መቀጠል ምክንያት መሆኑን “ ስሜን አትጥቀስ ” ያሉኝ የምክር ቤት አባሉ አስረድተውኛል ! ቀጠሉና “ አንተ ስታስበው የትምህርት ቤቱ ቁንጮ አስተዳደር በኦሆድድ ፤ በህዎሃት እና በብአዴን ወፍራም ተጽዕኖ ሹሞች ተይዞ ለውጥ ለማምጣት እንዴት ይቻላል?ከዚህ ቀደም ይህን ማሰብ የዋህነት ነው፤ ለውጥ ማምጣት የሚቻለው በድርጅት ሸፋን ለውጥ እንዳይመጣ እክል የሆኑትን በማንሳት ብቻ ነው ፤ እመነኝ እስካልሆነ ድረስ ለውጥ ላለመምጣቱ ምክንያት ይህ ብቻ ነው ፤ በዚህ ምክንያት ወላጆች ሁሌም ስለጆቻችን ት/ቤት ስናስብ በስጋት ኖረናል ፤ ከሰሞኑ የነዋሪው ብሶትና የታዳጊዎች ማዕከል ጉዳይ አሳስቧቸው መምህራን እውነቱን መጋፈጥ ጀምረዋል ፡ ትልቅ ለውጥ ነው ! ድሮም ያጠፋን የእነሱ ዝምታ ነበር ። ዘንድሮ ደፍረው ለእውነትና ለህዝቡና ለታዳጊዎች መቆማቸው ትልቅ ተስፋ ነው ። እነሱ ከበረቱ ነዋሪው ይደግፋቸዋል ፤ ነዋሪው ከደገፈ ደግሞ ለውጥ አይቀሬ ነው !” ሲሉ ጥልቅና ዘርዘር ያለ አስተያየታቸውን አካፍለውኛል …
አስተያየት ፤ ዲፐሎማቱ …
========================
ሌላው በትምህርት ቤቱ ዙሪያ አስተያየታቸውን እንዲሰጡኝ የጠየቅኳቸው ስማቸው ለደህንነታቸው ሲባል እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሳውዲ የሚገኙ ዲፕሎማት ” ነቢዩ የምሰጥህን አስተያየት እንደ ዲፕሎማት ሳይሆን እንደ ዜጋ ተቀበለኝ ፤ ነዋሪው ከዚህ ቀደምም ሸህ ሁሴን አልሙዲ ይሰራሉ ብሎ በሌለ ተስፋ ፕሮጀክት ይሰራ ተብሎ ኮሚኒቲው ለሙስና ተጋልጧል ፤ አሁን ደግሞ መንግስት ት/ቤት ይስራልን የሚል ጥያቄ መቅረቡን እየሰማን ነው ፡ ይህ ትክክለኛ አካሄድ አይደለም ፤ መንግስት ትምህርት ቤት ለመስራት በጀት ይመድባል ብሎ ጊዜ ማባከን ተገቢ አይደለም !አሁን እንቅስቃሴ የጀመሩት መምህራን ከጠነከሩ ፣ ወላጅና ነዋሪው ትምህርት ቤት እንዲሰራ የሚያደራጀው ካገኘና ወላጅ ከመምህራን ጎን ከቆመ በአጭር ጊዜ ስኬት ይኖራል ! ” በማለት ሲናገሩ እስካሁን ምንም ማደረግ ያልቻለው የቆንስል መስሪያ ቤት ወደ ፊትም ምንም ማድረግ እንደማይችል ጠቁመውኛል ።

አስተያየት ፤ መምህሩ …
======================
ከስብሰባው በኋላ አስተያየታቸውን እንዲሰጡኝ የጠየቅኳቸው አንድ የስብሰባው ንቁ ተሳታፊ መምህር ” የሚሰራው ስራ አሰላችቶንና አንገሽግሾን ላቀረብነው ተደጋጋሚ መሰረታዊ ጥያቄ የተሰጠው መልስ ቀድመን የገመትነው ነው፤ አያጠግብም ! ዘንድሮ አምና አይደለም ፡ ወላጅ ከጎ ናችን ከቆመ ታዳጊ ልጆቻችን ትምህርት ቅበላ በመምህራን ጉድለት በሚከሰተውን የትምህርት ጥራት ለማካካስ ከመትጋት ባሻገር ኪራይ ሰብሳቢነትን ለማስዎገድና የበከተው አስተዳደር ብቃት ባለው አስተዳደር እንዲተካ ጥረት ከማድረግ አንመለስም ። ፍርሃቱ በቅቶናል ፤ ወላጁም ስለ ልጆቹ ከጎ ናችን ሊቆም ይገባል ” ሲሉ በስሜት አስተያየታቸውን ሲያቀብሉኝ “ጀሮ ያለው ይስማ ! ” በማለት ጭምር ነበር !

አዎ ! በጅዳ ሶስት ሽህ (3000)ታዳጊዎችን ለመታደግ መምህራን ሲተጉ ማየት ያስደስታል ፤ በትውልድ ላይ መቀለድ ይቁም !እኔም እንደሚያገባው ዜጋ ” ጀሮ ያለው ይስማ” እላለሁ !

ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ
መስከረም 21 ቀን 2009

– See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/22232#sthash.EPBrJBJT.dpuf

ዘላቂ ጉዳት የማያስከትል ለውጥ!  –አስራት አብርሃም

$
0
0
asrat abereha

አስራት አብርሃም


በአሁኑ ሰዓት የስርዓት ለውጥ እንዲመጣ የማይፈልግ ያለ አይመስለኝም፤ ሁላችንም ለውጥ እንዲመጣ እንፈልጋለን። መሰረታዊው ጥያቄ ግን ዘላቂ ጉዳት የማያስከትል፤ ሁሉንም አሸናፊ፤ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ የስርዓት ለውጥ እንዴት ማምጣት ይቻላል? የሚለው ነው። ከደርግ ወደ አሁኑ ስርዓት ለመሻገር እንደ ሀገር ብዙ አላስፋለጊ ዋጋ ከፍለናል፤ የብዙ ኢትዮጵያውያን ቤት ፈርሷል፤ በመቶ ሺዎች ህይወታቸውን አጥቷል፤ አካለ ጎደሎ ሆኗል፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ የባህር በራችን አሳልፈን እንድንሰጥ ተደርገናል፤ ይሄኛው ከደረሱብን ጉዳቶች ሁሉ የከፋ፣ ለቀጣይ ትውልዶች ሳይቀር ዋጋ የሚያስከፈል ነው። አሁን ማሰብ ያለብን እንደነዚህ ዓይነቶቹ ተጨማሪ ጉዳቶች ሳናስተናግድ እንዴት ነው ከዚህ መንግስት መላቀቅና የተሻለ ስርዓት ማምጣት የምንችለው የሚለው ጉዳይ ነው። ለዚህ የተሻለ መፍትሄ ለማግኘት በጉዳዩ ላይ በስፋትና በጥልቀት መወያየት፣ መግባባት መቻል አለብን፤ ፍላጎቶቻችን ማቀራረብና ማስማማት መቻል አለብን።

ስርዓቱን የሚቃወም ሁሉ ለውጥ ለውጥ ፈላጊ መሆኑ እውነት ቢሆንም ሁሉም ግን ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ እየታገለ ነው ማለት አይቻልም። አንዳንድ የምናያቸው ምልክቶችም የሚያሳዩት ይህኑኑ ነው። ስለመጭው ጊዜ፣ ስለሀገር አንድነት፣ ሁሉም ዜጋ በእኩልነት ስለሚኖርባት ኢትዮጵያ እያሰበ የሚታገለው ኢትዮጵያዊ ድምፁ እየሰለለ ነው፣ እዚህም እዚያም በጎጥ በተደራጁ ቡድኖች እየተዋጠ ነው ያለው። አንዳንዶች ደግሞ አንድም በተስፋ መቁረጥ አንድም ደግሞ በራራቸው መንደር በሚኖረው ጊዚያዊ ሞቅታ ልባቸው እየተሰለበ ከነበሩበት የዜግነት ከፍታ ወርደው ወደ ጎጣቸው ገብቷል፤ እርግጥ ነው በዚህ መንገድ መታገል ቀላልና ጥረት የማይጠይቅ ነው። በጎጥ ተደራጅቶ እንደፈለጉ ማውራት፣ በቀላሉ ህዝብን ማነሳሳትና ማሰለፍ ይቻላል። ዘላቂ ውጤት፣ ሰላምና አብሮነት ማምጣት ባይቻልም፤ ለራስህ ጠባብ ቡድን ጊዜያዊ ድልና ጥቅም ማግኘት እንደሚቻል በህወሀትም እያዩት ስለሆነ ሊያጓጓቸው ይችላል።

በመሆኑም እኔ በዚህ ፅሁፍ በወደፊቷ ኢትዮጵያ የሁሉም የዜግነት መብት በእኩልነት የሚረጋገጥበት፤ ተከባብሮ በፍቅርና በአንድነት መኖር ስለሚቻልበት ነው ሀሳብ መስጠት የምፈልገው። ከአሁን በፊት እንደገለፅኩት ሁላችንም በኢትዮጵያ የተገኘነው መርጠነው አይደለም፤ ተፈጥሮ ነች አንድ ላይ እንድንሆን ያደረገችኝ። መለያየት ብንችል እንኳ ሀሳባዊ ልዩነት እንጂ ከቦታው ነቅለን መሄድ የምችል አይደለንም። ስለዚህ አንድ ላይ መኖር እጣ ክፍላችን ከሆነ እንዴት ነው አብረን ሳንጎዳዳ፤ ተጠቃቅመን፤ ተደጋግፈን መኖር የምንችለው የሚለው ጉዳይ ላይ መነጋገር አለብን።

በአሁኑ ወቅት በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ሰዎች የተለያዩ ሀሳቦች እየሰጡ ነው ያሉት፤ እኔም የበኩሌን ሳቀርብ ሀሳቡን ለማዳበር ይረዳ ይሆናል በሚል እምነት ነው። ከሌሎች፤ ከሚመስሉኝ ሰዎች ጋር ሆኜ በጋራ ለመስጠት ብችል ደስ ይለኝ ነበር፤ ነገር ግን በፓርቲ ማዕቀፍ ውስጥ እንዳይሆን የነበርኩበት ፓርቲ (አንድነት) ተወስዷል። ከዓረና ከወጣሁም ቆይቻለሁ (ይሄ የምለው አንዳንድ ሰዎች አሁንም ዓረና የምመስላቸው ስላለሁ ነው) በእርግጥ ዓረና ሲታሰብ ጀምሮ የነበርኩበት፤ የፖለቲካ ጥርሴ የነቀልኩበት፤ በሁኔታዎች የማይለዋወጡ ጓደኞች ያፈራሁበት ቢሆንም በአንዳንድ አካሄዶች ላይ በነበረኝ ልዩነት ምክንያት ከፓርቲው እንደተለየሁ የሚታወቅ ነው። ከተለመደው የሀገራችን የመለያየት ባህል በተለየ ሁኔታ በሰላምና በክብር ነው የተለየሁት። ስለዚህ ከቀድሞ የአንደነት አመራሮች ጋር በግል ከማደርጋቸው ውይይቶች ውጪ በአሁኑ ሰዓት የየትኛውም ፓርቲ አባል አይደለሁም።

ወደ ዋናው ዳጉይ ስገባ፣ በመጀመሪያ ምን እናድርግ በሚለው ጉዳይ ላይ እየቀረቡ ባሉት አማራጮች ላይ የራሴን ምልከታ ላስቀምጥና ወደ መፍትሄ ሀሳብ እሻገራለሁ። በአንዳንድ ታዋቂ ሰዎችና የፖለቲካ ቡድኖች በቀዳሚነት እየቀረበ ያለው አማራጭ የሽግግር መንግስት ይመስረት የሚል ነው። የሽግግር መንግስት ጥያቄ አቶ ግርማ ሰይፉ እንዳሉት ያለህዝብ ውክልና በአቋራጭ ስልጣን የሚገኝበት መንገድ እንጂ በአሁኑ ሰዓት አዋጭ የመፍትሄ ሀሳብ አይደለም፤ ኢህአዴግም በዚህ መንገድ ወደ ድርድር ማምጣት የሚቻል አይመስለኝም፤ ይህን የሚያደርግበት አስገዳጅ ሁኔታ ውስጥ ገብቷል ብዬም አላስብም። ስለዚህ የሽግግር መንግስት የሚለው አማራጭ አሁን ባለው ሁኔታ እውን የሚሆን ነገር አይደለም፤ ከዚህም ባሻገር ደግሞ ሁሉንም ነገሮች ከዜሮ እንዲጀመር የሚያደርግ በመሆኑ ጠቃሚነቱም ያን ያህል ነው።

ሁለተኛው አማራጭ የባለአደራ መንግስት ነው። ይህ በህዝብ የተመረጠ መንግስት እስኪቋቋም ድረስ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሲቪል ተቋማት፣ ከታዋቂ ግለሰቦች፣ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጣ የባለአደራ መንግስት ተቋቁሞ ሀገሪቱን በጊዚያዊነት እንዲመራ ማድረግ ነው። እንዲህ ዓይነቱ መንግስት ሰላምና ስርዓት ለማስፈን ሰራዊቱንና የፀጥታ አካላትን እንዴት አድርጎ ሊያዛቸው እንደሚችል ግልፅ አይደለም፤ ምን ዓይነት የህግ መሰረት እንደሚኖረውም ለመገመት የሚያስቸግር ነው። ከሽግግር መንግስትም ብዙ የሚለይ አይመስልም፤ የሚለየው ነገር ቢኖር የሽግግር መንግስት በፖለቲካ ኃይሎች የሚቋቋም መሆኑ ላይ ነው።

በሶስተኛው ረድፍ የሚቀመጡት ደግሞ ከኢህአዴግ ጋራ ጥምር መንግስት መመስረት የሚፈልጉ ናቸው። ከሁሉም በላይ ይሄ አማራጭ የከፋ ይመስለኛል። አንዳንድ የስልጣን ጥማት ያላቸው የፖለቲካ መሪዎች በአቋራጭ ስልጣን እንዲያገኙ ይረዳ እንደሆነ እንጂ ወደ ለውጥ ጎደና የሚወስድ አይደለም። በአንፃሩ ገዢው ፓርቲ ራሱን ዳግም ለማጠናከር እድል የሚሰጥ ነው የሚሆነው። ከኢህአዴግ ባህርይና አሁን በሀገራችን ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ካየነው የጥምር መንግስት ጥያቄ የፖለቲካ ሽርሙጥና ነው። በእርግጥ ጥምር መንግስት መመስረት ተገቢ የሚሆንበት ሁኔታ አለ፤ ህዝባዊ ምርጫ ተካሄዶ አንዱ ፓርቲ አሸናፊ ሳይሆን ሲቀር ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ፓርቲዎች ባገኙት የህዝብ ድምፅ መሰረት ድርድር አድርገው በስምምነት የጥምር መንግስት ሊያቋቁሙ ይችላሉ። ከዚህ ውጪ የሆነ ጥምር መንግስትም እንበለው ሽግግር መንግስት ዘላቂ መፍትሄ የማያመጣ ያለህዝብ ውክልና በአቋራጭ ስልጣን ፍለጋ ነው የሚሆነው።

ስለዚህ ለእኔ የተሻለ አማራጭ የሚመስለኝ ፓርላማውን በትኖ አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ማድረግ ነው። ኢህአዴግ ከልብ ለበጎ ነገር የሚነሳ ከሆነ፣ በዚች ሀገር ሰላማዊ የሆነ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ከቆረጠ ማድረግ ያለበት በሀገሪቱ ጉዳይ ላይ ያገባናል የሚሉ፣ በሀገር ውስጥም በውጭም ያሉ፤ በሰላማዊ መንገድም በጥትቅም እየተንቀሳቀሱ የሚገኙትን ቡድኖች ሁሉ ጠርቶ ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡና በሰላም እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ ነው፤ ቀጥሎ ምርጫ ቦርድን ሙሉ ለሙሉ አፍርሶ ከሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ተነጋግሮ በስምምነትና በመተማመን አዲስ ምርጫ ቦርድ በማቋቋም፤ ነፃና ገለልተኛ ምርጫ እንዲካሄድ አድርጎ በህዝብ ለተመረጠው አካል ስልጣኑን በሰላማዊ መንገድ ማስረከብ ነው።

እዚህ ላይ መታየት ያለበት ዋናው ነገር ሁሉንም ነገር እንደአዲስ ከመጀመር ይልቅ አሁን ያሉትን የመንግስት ተቋማት ገለልተኛ ሆነው የሚሰሩበትና የሚጠናከሩበት መንገድ ነው። ለምሳሌ ጦር ሰራዊቱ ከላይ ያሉትን የጦር አዛዦች ጡረታ እንዲወጡ በማድረግ የብሄር ተዋፅኦ የጠበቀ አመራር እንዲኖረው በማድረግ ማስተካከል የሚቻል ነው። የደህንነት መስራቤቱንም እንደዚሁ፤ ሌላውም በተመሳሳይ መንገድ ማስተካካል ይቻላል። ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት ሙሉ ለሙሉ መፍረስና መቀየር ያለበት ምርጫ ቦርድ ነው፤ ከሁሉም ገለልተኛ የሆነ በሁሉም ዘንድ ተአማኒነትና ከበሬታ ያለው፤ በሰው ኃይል፤ በአደረጃጀት ጠንካራ የሆነ ምርጫ ቦርድ ማቋቋም ያስፈልጋል።

ሌላው መስማማት የሚያስፈልገው ነገር ቢኖር የህገ መንግስት ማሻሽያ ጉዳይ ነው፤ ህገ መንግስቱ ለሚደረገው የስርዓት ለውጥና እንዲኖር ለሚፈለገው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በሚያመች መልኩ መሻሻል መቻል አለበት። በሀገሪቱ ውስጥ የሚኖረው አስተዳደርም ለልማትና አስተዳደር በሚያመች መልኩ፤ የብሄረሰቦች ራሳቸውን በራሳችው የማስተዳደር መብት ሳይገፋ፤ ቋንቋቸውን ለመጠቀም፣ ባህላቸውን ለመጠበቅና ለማሳደግ እንቅፋት በማይሆን መልኩ መስተካከል አለበት። ይህ ማለት ግን አንድ ቋንቋ የሚናገር ሁሉ በአንድ ክልል መጠቃለል አለበት ማለት ላይሆን ይችላል። ይህም የሚሆነው በህዝብ ፍላጎትና ፍቃደኝነት ተመስርቶ ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ በተለያዩ አከባቢዎች ያሉት የአከላለል ጥያቄዎች በኗሪው ህዝበ ውሳኔ እንዲፈቱ በማድረግ ዘላቂ መፍትሄ እንደሚደረግባቸው መስማማት ያስፈልጋል። እዚህ ስምምነት ላይ ለመድረስ ግን መደረግ ያለባቸው ቅድመ ሁነቶች ይኖራሉ፤ ከላይ ለመግለፅ እንደፈለኩት ኢህአዴግ ስልጣኑን በህዝብ ለተመረጠ አካል ለማስረከብ ቁርጠኛ መሆኑን ማረጋገጥ መቻል አለበት። በምትኩ ለኢህአዴግ ባለስልጣናት የሚሰጥ ልዩ ልዩ ዋስትና ሊኖር ይችላል።

በነገራችን ላይ “የኢህአዴግ ባለስልጣናት ስልጣን ይልቀቁልን እንጂ በወንጀል ያለመጠየቅ ዋስትና መስጠት ይቻላል” የሚሉ አሉ። በዚህ ጉዳይ ላይ እኔ የተለየ አቋም ነው ያለኝ። “አተርፍ ባይ አጉዳይ” እንደሚባለው ወንጀልና ወንጀለኞችን ማበረታታት እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል። በግልፅ የሚታወቅ በተለይ ከሰብአዊ መብት አያያዝ ጋር የተገናኘ ወንጀል ያለባቸው ባለስልጣናት ያለመክስስ መብት ሊሰጣቸው አይገባም። በአንፃሩ ምንም ወንጀል የሌለባቸው የስርዓቱ ባለስልጣናት በሰላም የመኖር መብት ሊከበርላቸው፤ ከዚያም ባሻገር በቀሪ ህይወታቸው ሊያኖራቸው የሚችል ነገር ሊሰጣቸው ይችላል።

ዋስትና ስለመስጠት ጉዳይ መነጋገር ካለብን በእርግጥም ዋስትና የሚያስፈልገው የትግራይ ህዝብ ነው። በተለይ ከክልሉ ውጩ የሚኖረው ትግርኛ ተናጋሪ ዜጋ ከለውጥ በኋላ አሁን ካለው ስርዓት ጋር በተያያዘ ምንም ነገር እንደማይደርስበት ማረጋገጥ ያስፈልጋል። እንደማነኛውም ዜጋ በፈልገው ቦታ ተንቀሳቅሶ የመስራት፤ የመኖርና ሀብት የማፍራት መብቱ ሊጠበቅለት ይገባል። ይህ ስጋት ተገቢ ይሁንም አይሁንም ሊታይና ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው። በእርግጥም ይሄ ሀሳባዊ ስጋት አይደለም፤ በአሁኑ ሰዓት በኢህአደግ በኩልም በአንዳንድ ፅንፈኛ ኃይሎችም ተደቅኖበት ያለ ስጋት ነው። ስጋት ካለ ደግሞ አንድም የለውጡ ሂደት የሚያዘገየው ነው የሚሆነው፤ ሌላው ደግሞ የሆነ ህዝብ መስዋዕት በማድረግ የሚመጣ ለውጥ ከሞራልም ከህግም አንፃር ተቀባይነት የለውም፤ ይሄ የህወሀት መንገድ ነው። ባለፉት ዓመታት በተለያዩ ክልሎች የሚኖሩ አማርኛ ተናጋሪዎች ላይ ሲደርስ የነበረው መፈናቀል፤ ጭቆናና ስቃይ ዳግም በየትኛውም ህዝብ ላይ እንዲደርስ መመኘት የለብንም። ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለማምጣት የሚታገል ማነኛውም ኃይል አንድን ህዝብ በሌላ ህዝብ ላይ እንዲነሳ የሚያደርግ ተደጋጋሚ ስህተት አይሰራም፤ የጥላቻ፣ የፍረጃና የፍርሀት ፖለቲካም አያራምድም።

በተወሰነ መልኩ በጎንደርና በመተማ አከባቢዎች እንደተየው ዓይነት በስርዓቱ ምክንያት የትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈጠር ያልነበረበት ነው። እንዲህ ማድረጉ ለትግሉም የሚጨምረው ነገር የለም፤ በእርግጥ “ከስርዓቱ ጋር ግንኙበት ያላቸው ብቻ ናቸው ጥቃት የደረሰባቸው” የሚል ነገር ተደጋግሞ ሲነግር ሰምቻለሁ፤ በእነዚህ አከባቢዎች ከሚኖረው የትግራይ ተወላጆች ብዛት አንፃር ጉዳት የደረሰባቸው ጥቂት መሆናቸው ሲታይ የተባለው እውነትነት ሊኖረው እንደሚችል መገመት ይቻላል። ነገር ግን አንድ ግልፅ መሆን ያለበት ነገር አለ፤ አንድ ሰው ከስርዓቱ ጋር ያለው ትስስር በማስረጃ ማረጋገጥ የሚችል የተደራጀ አሰራር በሌለበት ህዝባዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ንፁሃን ሰዎች አይጎዱም ማለት አይደለም። በራሴ አቅም በተለያየ መንገድ ለማጣራት ሞክሬ የተረዳሁትም ይሄኑኑ ነው። በአጋጣሚው ንፁሃን ዜጎች ላይም ጉዳት ደርሷል። በመሰረቱ ህዝቡ በየአከባቢው እንደመሰለው እርምጃ ይውሰድ ብሎ መቀስቀስ በደርግ ጊዜ እንደነበረው ዓይነት ሁኔታ መፍጠር ነው የሚሆነው፤ በየቀበሌው ለሚገኘው አብዮት ጥበቃ ሳይቀር እንደመሰለው እርምጃ እንዲወስድ በመፈቀዱ ጉዳዩ ሀገር ከመከላከል ወደ ግል ቂም በቀል ወርዶ የብዙ ንፁሃን ህይወት ጠፍቷል። በተመሳሳይ ሁኔታ ስርዓትና ቁጥጥር የሌለው እርምጃ እንዲኖር መፍቀድ በህዝብ ላይ ጉዳት ማድረስና ስርዓት አልበኝነት እንዲነግስ ማድረግ ነው የሚሆነው። የዘር ፍጅትም የሚከተለው እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ሲፈጠር ነው።

ስርዓቱ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ማውገዝ አለብን፤ መታገልም ያስፈልጋል። በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተፈፀመው የህይወት መጥፋት እጅግ የሚያንገበግብ ነው፤ የወገን ህይወት ነው የጠፋው፤ የወገን ደም ነው የፈሰሰው፤ ይሄ መታገል ያስፈልጋል። ኃላፊነት መውሰድ ያለባቸው አካላትም ተለይተው በህግ መጠየቅ አለባቸው። ህወሀትን ይደግፋሉ በሚል መነሻ ጥረው ግረው በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ ጥቃት ማድረስ ግን ፈፅሞ ተቀባይነት ያለው ጉዳይ አይደለም። ህወሀት ባጠፋ ቁጥር የራስ ወገን በሆነ የትግራይ ህዝብ ላይ ጥቃት ማድረስ መቼም ቢሆን ተገቢነት ሊኖረው አይችልም። እንኳን ዛሬ ዓለም በሰለጠነበት፤ የሰብአዊ መብት ጉዳይ ዋነኛ አጀንዳ በሆነበት ዘመን ቀርቶ በድሮ ጊዜም ቢሆን እንዲህ ዓይነቱ ነገር ተቀባይነት አልነበረም። ለዚህ አንድ የሚገርም በአፄ ምኒልክ ዘመን የሆነ ጉዳይ ብጠቅስ ደስ ይለኛል፤ የእንደርታ ገዥ የነበሩት ደጃች አብርሃ በማመፃቸው ምክንያት በሸዋና በሌሎች አከባቢዎች በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ ጥቃት ደርሶ ነበር ይባላል፤ በዚህ ምክንያት አፄ ምኒልክ አዋጅ አውጥተው ነበር፤ እንዲህ የሚል፦

…አንድ ሰው ደጃች አብርሃ ቢከዳ እዚህ የተቀመጡትውን እኔን የሚወደኝን የትግሬ ሰወ ሁሉ ታስቀይማለህ አሉ። አባያ ወንድሙ ይታሰርበታል እንጂ ይታረዳልን። አሁንም ዳግመኛ በአደባባይ ያለውን የትግሬ ሰው የሚያስቀይም ነገር የተናረ ትቀጣለህ። አደባባይ ያለውን የትግሬ ሰው የሚያስቀይም የተናገረውን ተያይዘህ አምጣልኝ ዳኝነት ይታይልሃል።

                    (የአጤ ምኒልክ የሀገር ውስጥ ደብዳቤዎች፣ ገፅ 589)

የድሮ መሪዎቻችን ቢያንስ ፈሪሃ እግዚአብሄር የነበራቸው በመሆኑ ከአሁኖቹ በእጅጉ ይሻላሉ። የራሳቸው የሆነ ጥሩ ነገርም እንደነበራቸው የምንረዳው እንዲዚህ ዓይነቱ ነገር ስናገኝ ነው። በሌላ በእኩል ደግሞ አሁን ያለንበት ሁኔታ፣ የሞራል ድቀት ከመቼም ጊዜ የከፋ መሆኑ እንረዳለን። ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው መጠቀል አለባቸው፤ ግን ደግሞ በስርዓቱ ላይ ያነጣጠሩ እንጂ ፍፁም ህዝብ በህዝብ ላይ እንዲነሳ የሚያደርጉ መሆን የለባቸውም፤ እንደዚህ ዓይነት አሰራር በግልፅ ነው መወገዝ ያለበት። በራስ ወገን ላይ በፖለቲካ ምክንያት ጥቃት ማድረስ ዘላቂ ሰላምና አብሮነትም የሚፈጥር አይሆንም። በአንድ ወገን የሚኖርን ተቃውሞና ውግዘት በመፍራት ዝም መባል የለበትም፤ እንደህ ዓይነቱ አካሄድ አደርባይነትና እወደድ ባይነት ነው (opportunism and populism) ነው።

እስካሁን እንደታዘብኩት በዚህ ጉዳይ ላይ አፅንኦት ሰጥተው ሲናገሩ የሰማቸው ፕሮፌስር መስፍን ወልደማርያም እና ፕፎሰፌር ብርሃኑ ነጋ ይመስሉኛል። ፕሮፈሴር መስፍን ለአዲስ አድማስ በሰጡት ቃለ መጠይቅ “ወያኔን ትግሬ እያደረጉ፣ ትግሬን ሁሉ ወያኔ እያደረጉ የሚኬድበት ሁኔታ መታረም አለበት፤ አደገኛ መርዝ ነው፡፡ሀገሪቱን አደጋ ላይ የሚጥል ነው፡፡” ማለት እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ በትግራይ ህዝብ እየተደገሰ ያለው አደጋ እንደሚያሳስባቸው ተናገሯል። ፕሮፈሴር ብርሃኑ ነጋም በዴምህት ሁለተኛ ጉባኤ ላይ “ከትግራይ አብራክ የወጡና ይህን ስርዓት የሚቃወሙትን በቆራጥ ወኔ ነው የምናደንቀው” በሚል ርዕስ ባቀረቡት ንግግር የጥላቻ ፖለቲካ ስለሚያራምዱ ወገኖች እንዲህ ብሏል፦

…ለጊዜያዊ የፖለቲካ ጉልበትነት እንጠቀምበታለን ብለው የሚያስቡ አክራሪና አጥፊ ኃይሎች ትግሉን ወደ ጥላቻ ትግል ለማስቀየስ የሚሞክሩ ሊኖሩ እንደሚችሉ እናውቃለን። እንደነዚህ አይነት ጥቂት ኃይሎች በህዝቡ ትግል ውስጥ ተመሽገው የሚወስዷቸው እርምጃዎችንና የሚያካሂዷቸውን የጥላቻ መርዛማ ፕሮፓጋንዳ ህወኃት/ኢህአዴግን ስለተቃወሙ ብቻ ዝም ብለን “የህዝቡ ትግል አካላት ናቸው” ብለን የምናልፋቸው ሊሆኑ በፍጹም አይገባም። እንዲህ አይነት እኩይ ኃይሎችን ማውገዝ ብቻ ሳይሆን አስቀያሚ ገጽታቸውን በሚያሳዩበት ጊዜ ሁሉ እነሱን ማጋለጥና ከህዝቡ ፍትሀዊ ትግል ማግለል ለእውነትና ለፍትህ፤ ኢትዮጵያችንን ከተጋረጠባት አደጋ ለመታደግ፤ ብሎም ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንታገላለን የምንል ኃይሎች ሁሉ ያለማሰለስ ልንሰራው የሚገባን ስራችን ነው።

ይህ የሁሉም ኃላፊነት የሚሰማው ዜጋ አቋም ነው ሊሆን የሚገባው፤ እንደ ዜጋ ከፍ ሲል ደግሞ እንደሰው ለሰብአዊነት፣ ለእውነትና ለትክክለኛነት መቆም ያስፈልጋል። በመሰረቱም አንድን ህዝብ በጠቅላላ ማስፈራራት ውጤት የሚያመጣ ነገር አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ ህዝቡ የስርዓት ለውጥ ቢመጣ ስለሚኖረው የተሻለ ነገር በማስረዳት ነው ማሰለፍ የሚቻለው። ከለውጥ በኋላ ከህወሀት ጋር በተያያዘ ምንም የሚደርስበት ጉዳት ሊኖር እንደማይችል፤ እንደማነኛውም ዜጋ አሁን ካለው በተሻለ ሁኔታ በነፃነት ሰርቶ የመኖር መብቱ እንደሚከበርለት ማሳየት ያስፈልጋል። በተለይ ደግሞ በትግራይ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ የዘረኝነት ቅስቀሳ የሚያካሄዱ ግለሰቦችና ቡድኖች በማሻማ ሁኔታ ማውገዝና ራስን ከእነዚህ አካላት መለየት ያስፈልጋል። ከእስትራቴጂ አንፃርም የተደባለቀ ትግል ለውጤት የሚበቃ አይደለም፤ ለውጤት ቢበቃም እንኳ ዘላቂ ሰላም ሊያመጣ አይችልም፤ ሀገር ከመበታተን፤ ህዝብ ለህዝብ ከመተላለቅ የሚያድን አይደለም። አዋጪው መንገድ ኢትዮጵያ የሁላችን እንድትሆን፤ የጋራ ራዕይና ህልም መፍጠር እንጂ የተወሰነ ህዝብ በመነጠል እንዲመጣ የምንፈልገው የተሻለ ለውጥ ሊመጣ አይችልም። ጠቡ ህዝብ ለህዝብ ስለሚሆን አሸናፊ ወገን አይኖርም፤ ተያይዞ መውደቅ ነው የሚሆነው፤ የፖለቲካ ኃይላት ናቸው ሊሸናነፉ የሚችሉት፤ ህዝብ እንደህዝብ ሊሸነፍ አይችልም።

የመጣህበትን ህዝብ ከቻልክም ደግሞ በማነኛውም ህዝብ ላይ በደልና ጭቆና ሲደርስ መጮህና መታገል ተገቢ ነው። ከዚህ ባለፈ ሁኔታ የራስህን ህዝብ የተጎዳ፣ ከሌላው በተለየ ሁኔታ አደጋ ያንዣበበት በማስመሰል ፖለቲካ መስራትና የኑሮ መሰረት እንዲሆን ማድረግ ከሞራልም ከሰብአዊነትም አንፃር ተገቢ ያልሆነ አካሄድ ነው። በተለይ ለለውጥ ከሚታል ሰው የሚጠበቅ አይደለም። አብሮ ለዘላለም የሚኖር፤ ተለያየቶ ላይለያይ ህዝብ መሀል ዘላቂ ጠብና ቂም መፍጠር ተገቢ አይደለም። ስልጣን መፈለግ ኃጢአት ባይሆንም በዚህ መንገድ የሚገኝ ስልጣን ግን ቢቀር ነው የሚሻለው። ከሁሉም በላይ ደግሞ ከቋንቋ በስተቀር በዘርም፣ በኃይማኖትም፣ በባህልም፣ በመልክም አንድ ዓይነት በሆነው የትግራይና የጎንደር ህዝብ ማሀል የጥላቻ ግንብ እንዲገነባ ማድረግ ይቅር የማይባል ስህተት ነው። ለወደፊት በሚኖሩት ትውልዶች ፊትም የሚያሳፍር ኋላቀር ተግባር ነው የሚሆነው። በአጠቃላይ የትግራይና የአማራ ህዝብ ተመሳሳይ ዕጣ ክፍል ያለው፤ ተደጋግፎና ተገባብቶ ከመኖር ውጪ ሌላ አማራጭ ተፈጥሮም ታሪክም ያልሰጠው ህዝብ ነው። በመሰረቱ በሁለቱም ወገን ባሉት የስልጣን ኃይሎች እንጂ በሁለቱም ህዝብ መሀል ጥላቻ አለ ብዬ አላምንም።

የምናደርገው ትግሉ ሁሉም የሚያሳትፍ፤ ለሁሉም ተስፋ የሚሰጥ፤ በማንም ህዝብ ላይ ስጋት የማይፈጥር እንዲሆን መጣር ያስፈልጋል። እንኳን በአንድ ሀገር የሚኖር፤ በደም፣ በአጥንት፣ በታሪክ፣ በዜግነት የተሳሰረ ህዝብ ይቅርና ከአውሮፓ ድረስ መጥተው ለብዙ መቶ ዓመታት ህዝቡን በቀኝ ግዛት ይዘው ሲገዙትና ሲጨቀኑት የነበሩትን የደቡብ አፍሪካ ነጮችም የሚያቃፍ ትግል እነማንዴላ አድርጓል። ታሪክ ሰርተው፤ ለሁሉም ዜጋ በእኩልነት የሚያገለግል ስርዓት መስርተው አልፏል፤ እኛ ኢትዮጵያውያንም እንዲህ ያለ የተገባ ትግል እንዳናከሄድ የሚያግደን ነገር ምንድነው?!

 

በአዲስ አበባ “አቧሬ” አካባቢ ሁለት ሺህ ሕጋዊ ቤቶች ይፈርሳሉ –ዋዜማ ራዲዮ

$
0
0

abware-area-satenaw-newsበየካ ክፍለ ከተማ ሚስስ ሳንፎርድ ትምህርት ቤት አካባቢ የሚገኙ ሁለት ሺሕ የሚጠጉ ቤቶች በቅርብ ወራት ዉስጥ የመፍረስ አደጋ ተጋርጦባቸዋል፡፡ ከነዚህ ዉስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ሰፋፊ የግለሰብ ይዞታዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ የቀበሌ ቤቶች ናቸው፡፡ እንዲፈርሱ የዉሳኔ ሐሳብ የተሰጠባቸው የአቧሬ ሰፈሮች ሕገወጥ በመሆናቸው ሳይሆን ቦታው ለመልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች በእጅጉ በመፈለጉ ነው፡፡

በየካ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ጽሕፈት ቤት ሰራተኞች ባሳለፍነው ሳምንት በጽሑፍ የተላለፈላቸው መመሪያ እንደሚያስረዳው አቧሬና አካባቢውን በአስቸኳይ ለማልማት አቅጣጫ በመያዙ በወረዳ 6 (በቀድሞ አጠራር ቀበሌ 09) ዙርያ የሚገኙ የግል ይዞታዎችና የቀበሌ ቤቶች ቁጥርና ስፋት በዝርዝር አጥንተው በአጭር ጊዜ ዉስጥ እንዲያቀርቡ በማዕከል ኃላፊዎች ታዘዋል፡፡

በአንጻሩ የቤቶቹን መፍረስ ዉሳኔ በጥርጣሬ የሚመለከቱ በክፍለከተማ በተለያየ ኃላፊነት ደረጃ እየሰሩ የሚገኙ የዋዜማ ምንጮች በቅርብ ወራት ዉስጥ ምንም አይነት የቤት ማፍረስ ሥራ እንደማይከናወን ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ ይህም የሚሆነው ቤቶችን ለልማት ሲባል የማፍረስ ተግባር ለተቃውሞ እንቅስቃሴ በር ሊከፍት ይችላል የሚል ስጋት በካቢኔው ዘንድ በመኖሩ ነው፡፡

አገሪቱ ወደለየለት ብጥብጥ እንድታመራ የሚሹ አክራሪ ኃይሎች በዋና ከተማዋ አመጽ ለመቀስቀስ አጀንዳ አጥተዋል፤ እኛ ቤቶችን ለልማት ስናፈርስ እነርሱ እንደ ጥሩ አጋጣሚ ሊጠቀሙበት ይችላሉ የሚል ስጋት በከንቲባው ዋና የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ አቶ ተወልደ ገብረጻዲቅ ሲንጸባረቅ በተደጋጋሚ ሰምቻለሁ ይላል በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የይዞታ ጽሕፈት ቤት ዉስጥ በኦፊሰርነት የሚያገለግል ወጣት የድርጅት አባል፡፡

ቤት የማፍረስ ተግባር ዘንድሮ የማይታሰብ ነው የሚሉት ወገኖች እንደ ተጨማሪ ማስረጃ የሚያቀርቡት በ2008 መጨረሻ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቀርሳ፣ ኮንቶማና ማንጎ ሰፈሮች ዉስጥ ሕገወጥ ሰፋሪዎችን ለማንሳት በተደረገው ሙከራ የወረዳ አንድ ሥራ አስፈጻሚን ጨምሮ የነዋሪዎች ሕይወት መጥፋቱን ተከትሎ ዉጥረት መንገሱን በማስታወስ ነው፡፡ በወቅቱ በነዋሪውና በፀጥታ ኃይሎች መሐል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ከንቲባው አቶ ድሪባ ኩማ ሕገወጦችን የማፍረስ ጉዳይ ለድርድር አይቀርብም የሚል መግለጫ ቢሰጡም በዚያው ሰሞን እንዲፈርሱ ቀነ ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበሩ ሰፈሮች ለጊዜው እንዲታለፉ ለክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና ማደስ ኃላፊዎች የቃል ትዕዛዝ ተሰጥቶ ነበር፡፡

እንደ ምሳሌም የቀርሳና ኮንቱማ ሰፈሮችን የሚያዋስነውና በርካታ ሕገወጥ ሰፋሪዎች ይገኙበታል የሚባለውን የአቃቂ ቃሊቲ መንደር ለማፍረስ ግብረኃይል ተደራጅቶ፣ ቀን ተቆርጦ፣ ልዩ የፖሊስ ኃይል ተመድቦ፣ ዶዘሮች ወደ አካባቢው እንዲቀርቡ ከተደረገ በኋላ ባልታወቀ ምክንያት የማፍረስ ሂደቱ ድንገት እንዲታጠፍ ሆኗል ይላሉ የወረዳው ባልደረቦች፡፡

የዋዜማ ዘጋቢ ያናገራቸውና ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አንድ የአራዳ ክፍለ ከተማ ሰራተኛ ዉሳኔው የታጠፈው ዜጎችን በክረምት ማፈናቀል አግባብ እንዳልሆነ በካቢኔው አቅጣጫ በመያዙ ነው ሲሉ ሌሎች በመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ጽሕፈት ቤት የሚሰሩ ኦፊሰሮች ደግሞ በተቃራኒው እንዲያውም ሕገወጥ ቤቶች እንዲፈርሱ የሚመረጠው በክረምት ወቅት ነው፡፡ ይህም በበጋ ቤቶችን ማፍረስ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ ሊያርቃቸው ስለሚችል ነው ሲሉ ተጻራሪ ሐሳቦችን ያቀርባሉ፡፡

በኦሮሚያ መንግሥትን ለሰፊ ሕዝባዊ ተቃውሞ የዳረገው የተቀናጀ ማስተር ፕላን ለጊዜው እንዲታጠፈ ከተደረገ በኋላ አዲስ አበባ የተናጥል የከተማ መሪ ፕላን ለማዘጋጀት ተገዳለች፡፡ ኾኖም ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ እስከዛሬም በይፋ አላጸደቀችውም፡፡ የሕዝብ ዉይይት ተደርጎ በአስቸኳይ ይፀድቃል የተባለው መሪ ፕላን ከዛሬ ነገ እየተባለ ለወራት ሲንከባለል ቆይቷል፡፡ ያም ኾኖም አስሩም ክፍለ ከተሞች በአሁኑ ሰዓት የመሬት ጉዳዮችን እየፈጸሙ ያሉት ያልጸደቀውን የከተማዋን መሪ ፕላን መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ባይፀድቅም እየሰራንበት ነው፤ በሱ መስራት ከጀመርን ዓመት አልፎናል ይላል ለዋዜማ ሐሳቡን የገለጸ አንድ የአራዳ ክፍለ ከተማ የመሬት ባለሞያ፡፡

በአዲሱ መሪ ፕላን የከተማዋ 30 በመቶ ለአረንጓዴ ልማት የሚፈለግ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለአረንጓዴ ቦታ የተከለሉ ሥፋራዎች ዉስጥ እየኖሩ ያሉ ዜጎች በሂደት እንዲነሱ እንደሚደረግ የከተማዋ ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡ ኾኖም ቁጥራቸው በርካታ ከመሆኑ ጋር ምትክ ቦታ ለመስጠት አስተዳደሩ ፈተና እንደሚገጥመው ከወዲሁ ተሰግቷል፡፡

ባለፉት ዓመታት የከተማዋን አብዛኛዎቹን የቆረቆዙ መንደሮች በመልሶ ማልማት ለማልማት በተደረጉ እንቅስቃሴዎች በሰንጋ ተራና አካባቢው 14 ሄክታር መሬት ለፋይናንስ ተቋማትና ለ40/60 የቤት ልማት ፕሮጀክት የተላለፈ ሲሆን በልደታ ቤተክርስቲያን አካባቢ 16 ሄክታር መሬት ደግሞ ለ20/80 ቤቶች ልማት ማከናወኛ የተሰጠ ነው፡፡ በተለይ በልደታ ክፍለ ከተማ የልደታና አካባቢው መልሶ ማልማት ፕሮጀክት በመስተዳደሩም ሆነ በፌዴራል ደረጃ በስኬታማነቱ በተደጋጋሚ የሚወደስ ፕሮጀክት ነው፡፡ የግልና የመንግሥት ባንኮች ሕንጻዎችን፣ ፀሜክስ ኢንተርናሽናል እያስገነባው እንዳለው አይነት ባለ ኮከብ ሆቴል ፕሮጀክቶችን፣ ፍሊንስቶን ያስገነባውን ዘመናዊ የገበያ ማዕከል (ሞል) ተግባራዊ ማድረግ የተቻለው በዚህ እንደ ሞዴል በሚወሰድ የመልሶ ማልመት ሥራ እንደሆነ በኃላፊዎች በተደጋጋሚ ይገለጻል፡፡

ይህ የልደታ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት የኮንዶሚንየም ነዋሪዎች ከመሀል ከተማ ርቀው እንዳይሰፍሩ፣ በመካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ዜጎች መሐል መራራቅ እንዳይኖር ያደረገ ልማት እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲ አማካሪ አቶ አባይ ፀሐዬ በተደጋጋሚ ሲያሞካሹት ይሰማል፡፡ ኾኖም ተመሳሳይ የመልሶ ማልማት ስኬት ሊደገም አልቻለም፡፡ ብዙዎቹ በመልሶ ማልማት ቤቶቻቸው የፈረሱባቸው ዜጎች ከነባር ይዞታቸው ተፈናቅለው በከተማዋ ጫፍ በሚገኙና መሠረተ ልማት ባልዳሰሳቸው ሥፍራዎች እንዲሰፍሩ ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በቅርቡ የመፍረስ አደጋ የተጋረጠበት አቧሬ ሰፈር ከአንድ ሺ ካሬም የሚልቁ ሰፋፊ ይዞታዎች የሚገኙበት ሲሆን የመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ዋና መቀመጫም የሚገኘው በዚህ ወረዳ ነው፡፡ በመልሶ ማልማት ምክንያት የሚነሱ ዜጎች ይዞታቸው ምንም ያህል ሰፋፊ ቢሆን እንኳ በመኖርያ ቤት እስከተመዘገበ ድረስ በምትክነት የሚሰጣቸው የካሬ ስፋት ከ500 ሜትር ስኩዌር ካሬ በላይ እንዳይሆን መመሪያው ያዛል፡፡ ኾኖም ተነሺዎቹ ይዞታቸውን በግላቸው የማልማት ፍላጎት ካላቸውና የፋይናንስ አቅም በራሳቸው መፍጠር ከቻሉ መሪ ፕላኑ በሚያዘው መሠረት በአካባቢው ዘጠኝ ፎቅና ከዚያ በላይ የመገንባት መብት ይሰጣቸዋል፡፡ ይህ ግን ለብዙ የከተማዋ ጎስቋላ ነዋሪዎች የሚታሰብ ጉዳይ አይሆንም፡፡

ባለፉት ጥቂት አመታት ዉስጥ በልማት ስም ከፈረሱ የአዲስ አበባ ከተሞች መሐል አሜሪካን ግቢ ተጠቃሽ ነው፡፡ በአካባቢው ለ30 አመታት ነዋሪ የነበሩ ዜጎች የይዞታ ባለቤትነትን ከማረጋገጥና ከካሳ ክፍያ ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ዉዝግብ ዛሬም ሙሉ በሙሉ ምላሽ አላገኘም፡፡ ኾኖም ከአካባቢው የተነሱ ሱቆች ራሳቸውን በቡድን እያደራጁ ቁራሽ መሬቶች እየተሰጣቸው ቆይቷል፡፡

ከነዚህ አካባቢዎች በተጨማሪ አዲስ ከተማ፣ ጎጃም በረንዳ፣ ቁጭራ ሰፈር፣ ጣሊያን ሰፈርና ገዳም ሰፈር በመልሶ ማልማት የሚፈርሱና እየፈረሱ ያሉ አካባቢዎች ናቸው፡፡

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዉስጥ የሚካተተው የመስቀል አደባባይ ኢሲኤ ጀርባ 4 ሄክታር መሬት፣ አራዳ ክፍለ ከተማ ዉስጥ የሚካተተው የ አራት ኪሎ ባሻ ወልዴ ችሎት አካባቢ 24 ሄክታር መሬት በመልሶ ማልማት ተነስቷል፡፡ የባሻ ወልዴ ችሎት አካባቢ በሊዝና በምሪት ለባለሀብቶችና ለድርጅቶች የተላለፈ ሲሆን ቦታ ከወሰዱ ድርጅቶች መሐል የብአዴን ጽሕፈት ቤት ግንባታ፣ ሁለት የግል ሆስፒታሎች ግንባታ፣ የዳሽን ባንክ ቅርንጫፍ ቢሮ ግንባታ፣ የሂልኮ ኮምፒውተር ኮሌጅ ግንባታ በአመዛኙ ተጠናቋል፡፡

የባሻ ወልዴ ችሎት አካባቢ እየተከናወኑ ካሉ ፕሮጀክቶች ትልቁ በአምባሳደር ልብስ ስፌት ባለቤት በአቶ ሰኢድ መሐመድ ብርሃን እየለማ ያለው ቦታ ሲሆን ከአርበኞች ግንብ ሕንጻ ጎን ከፓርላመው ባሻገር የሚገኝ 3ሺ ካሬ ቦታ ነው፡፡ አገልግሎቱም ባለ 4 ፎቅ ሰፊ የገበያ ማዕከል ግንባታ ነው፡፡ ይህ ግንባታ ረዥም ዓመታትን የወሰደ ቢሆንም እስካሁንም አልተገባደደም፡፡ የባሻ ወልዴ ችሎት መልሶ ማልማት ቦታዎች በተፈለገው ፍጥነት አለመሄዳቸው ብቻም ሳይሆን ብዙዎቹ ቦታዎች ከፈረሱ አመታት ቢያስቆጥሩም አሁንም አለመልማታቸው የነዋሪዎች መነጋገሪያ ሆነዋል፡፡ በመሪ ፕላኑ መሰረት አካባቢው ለቤተመንግሥትና ፓርላማ ቅርብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከ4 ፎቅ በላይ መገንባትን አይፈቅድም፡፡

ተመሳሳይ ሰፊ የመልሶ ማልማት ሥራ ካከናወኑ ክፍለ ከተሞች መሐል የቂርቂስ ክፍለ ከተማ ተጠቃሽ ሲሆን ለአፍሪካ ሕብረት አዲሱ ሕንጻ ግንባታና ለኢሲኤ (የቀድሞው አፍሪካ አንድነት ድርጅት የመጀመርያ መሰብሰቢያ አዳራሽ) ማስፋፊያና ፓርክ ሲባል ኢስጢፋኖስ ጀርባ የነበሩ በርካታ ነዋሪዎችን ከቀያቸው ለማፈናቀል ተገዷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ካዛንቺስና አካባቢዋ በርካታ ባለ ኮከብ ሆቴሎች ግንባታ መከናወን የቻለውም ቦታው ለመልሶ ማልማት በመዋሉ ነው፡፡

አሁን ተመሳሳይ ሰፋፊ የሆቴል ፕሮጀክቶች ይካሄዱበታል ተብሎ የሚገመተውና የካዛንቺስ 2 መልሶ ማልማት ዘመቻ በሚል የሚታወቀውን የልማት ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ ራዲሰን ብሎ ማዶ፣ ኢንተርኮንቲነንሰታል ሆቴል ፊትለፊት፣ ኦራኤል ቤተክርስቲያን ተሻግሮ የሚገኙ ሰፈሮች ሙሉ በሙሉ እንዲነሱ ተደርጓል፡፡ ይሁን እንጂ ቦታዎቹ ከጸዱ ዘለግ ያለ ጊዜ ቢያስቆጥሩም የፈረሱት ቦታዎች እስከአሁንም ለአልሚዎች አልተላለፉም፡፡

በከተማዋ ነዋሪዎች እንደ ተደጋጋሚ ቅሬታ የሚነሳውም ይኸው ጉዳይ ነው፡፡ ድሀን በልማት ስም አፈናቅሎ መተው፣ ወቅቱን ያገናዘበ ተገቢ ካሳን አለመስጠት፣ የማኅበራዊ ምስቅልቅል የሚፈጥሩ አሰፋፈሮችን መከተል የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ለረዥም አመታት ያማረረ ጉዳይ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የፈረሱ ቦታዎች ለአመታት ያለምንም አገልግሎት ተጥረው እንዲቀመጡ መሆናቸው ግርትን የሚፈጥር ጉዳይ ነው፡፡ ይህም አንድም በመስተዳደሩ ድክመት ቦታዎቹን ለአልሚዎች በጊዜ ያለማስተላለፍ ችግር ጋር የሚያያዝ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ደግሞ አልሚዎች ቦታዎቹን አጥረው ይዞታቸውን ካስከበሩ በኋላ ለዓመታት ግንባታ ለማከናወን ሳይፈቅዱ መቆየታቸው ነው፡፡

ይዞታዎች ለአልሚዎች ሲተላለፉ የግንባታ መጀመርያ ጊዜና ማጠናቀቂያ ጊዜ በዉል ተለይተው፣ የሊዝ ዉል ፈርመው የሚገቡበት አሰራር ቢኖርም ይህ ሁኔታ ለሁሉም ዜጎች በእኩል የሚሰራ አልሆነም፡፡

በዚህ ረገድ በከተማዋ የአስተዳደር እርከን በሁሉም ደረጃ ከኤህአዴግ አባላት ሳይቀር ሰፊ ትችትና ትዝብትን የሚያስተናግዱት በሳኡዲያዊው ባለሀብት ሼክ መሀመድ አላሙዲ የተያዙ ሰፋፊ የከተማዋ ይዞታዎች ናቸው፡፡ በተለይም ከካዛንቺስ ኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል ጎን ተቆፍሮ የሚገኘው ቦታ መለስተኛ ኩሬ ፈጥሮ ለአካባቢው የጤና ጠንቅ እስከመሆን የደረሰ ሲሆን በኢንተርኮንቴኔንታል ሆቴል የሚያርፉ እንግዶች መስኮቶቻቸውን ለመክፈት እስከመቸገር መድረሳቸው ይነገራል፡፡ የሸራተን ማስፋፊያ በሚል ለጎልፍ ክለብና ልዩ ልዩ መዝናኛዎች የታጠረውና በተለምዶ ፖሊስ ጋራዥ የሚባለው ሰፊ ቦታ ማጅራት መቺዎችና ኪስ አውላቂቆች መሸሸጊያ እየሆነ እንደመጣ ነዋሪዎች ብቻም ሳይሆን የከተማዋ ፖሊስ ጽሕፈት ቤትም የሚያነሳው ጉዳይ ሆኗል፡፡ የፒያሳው ግዙፍ የመንታ ሕንጻዎች ፕሮጀክት በዲዛይን ለውጥና በሌሎች ጥቃቅን ሰበቦች የተነሳ ይህ ነው የሚባል ግንባታ ሳይካሄድበት ለ18 ዓመታት ታጥሮ መቀመጡም የከተማዋ ነዋሪ በአስተዳደሩ ላይ እምነት እንዲያጣ ካደረጉት አበይት ምክንያቶች አንዱ ነው፡፡

ዜና በጣም ይረብሻል—ኦሮምያ በእሬቻ ባዕል በደም ታጠበች

$
0
0

የኢሬቻ በዓል በማክበር ላይ በነበሩ የኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ ለማውገዝ የግድ ኦሮሞ መሆን አይጠበቅም፡፡ ያሳዝናል፤ ያናድዳል፡፡ ለነጻነት በሚደረግ ትግል የንጹሐን ዜጎች ሞት የሚጠበቅ ቢሆንም ባዶ ቄጠማን በእጃቸው ይዘው ከአምላካቸው ለአገራቸው ሰላም ሲለምኑ በነበሩ ሰዎች ላይ ይህን ዓይነት መቅሰፍት ሲወርድ በምን ቃል መግለጽ ይቻላል?
በዚህች አገር ላይ በዓልን በፌሽታና በደስታ እንዲያከብሩ የተፈቀደላቸው ከተከዜ ማዶ ያሉ ሰዎች ብቻ መሆናቸውን በግልጽ እያየን ነው፡፡
ለሞቱ ቤተሰቦች መጽናናትን እመኛለሁ፤ በአካባቢው ያላችሁ የአማራ ተወላጆች ከተጎዱ የኦሮሞ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጎን በመቆም አጋርነታችን የምናሳይበት ከዚህ ጊዜ በላይ የለም፡፡
ትግላችን መራር ቢሆንም ማሸነፋችን ግን ጥርጥር የለውም!!

 

ይህ ለሰላማዊ ህዝብ ይገባዋልን??

j0-copy-2-copy

j1-copy-2-copy

j2-copy-2-copy

j3-copy-2-copy

j4-copy-2-copy

j5-copy-2-copy

j6-copy-copy

j7-copy-copy

j8-copy-copy

j11-copy-copy-copy

j11-copy-2-copy

j12-copy-copy-copy

 

j13-copy-copy

 

j14-copy

j15-copy


አንዳንዴ ሸረሪትም በራሷ ድር ትያዛለች (ከይገርማል)

$
0
0

TPLFበ1999 ዓ.ም ይመስለኛል አንድ የደቡብ አፍሪካ ምሁር የወያኔ-መሩ ኢሕአዴግና የሀገር ቤት ሰላማዊ ተቃዋሚወች ከመጠፋፋት ፖለቲካ ወጥተው ታሪካዊት ሀገራቸውን ወደ ዴሞክራሲ: ሰላምና ብልጽግና እንዲያሸጋግሩ ሲያሳስቡ እንዲህ ብለው ነበር::

“ኔልሰን ማንዴላ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ሆነው በተመረጡ ጊዜ በሀገሪቱ በሚኖሩት ነጮች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ በርካታ ሰዎች ጎትጉተው ነበር:: ማንዴላ ግን ‘የበደለን ስርአቱ እንጅ ሰዎች አይደሉም:: ያ አስከፊ ስርአት ተመልሶ እንዳይመጣ ሁላችንም ተረባርበን አርቀን ልንቀብረው ይገባል:: ደቡብ አፍሪካ ሰፊ ሀገር ናት: ለሁላችንም ትበቃናለች::’ በማለት ሀገራቸውን ከጥፋት በመታደግ በመላው አለም ለዘላለም የሚታወስ ታሪክ አስመዘገቡ::

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀርቶ ለመላው አለም ምሳሌ የምትሆን ጥንታዊና ታሪካዊ ሀገር ናት:: የአፍሪካ ሀገሮች እንደሀገር በማይታወቁበት ጊዜ ኢትዮጵያ በንግድ: በስልጣኔና በወታደራዊ ሀይሏ ታዋቂ ነበረች:: አሁን የሚታየው ሁኔታ መታረም አለበት:: መንግስትና ተቃዋሚወች በሀገራችሁ ጉዳይ ላይ ቁጭ ብላችሁ መነጋገር ይኖርባችኋል:: ሶማሌወች ‘ከቆመ ወጣት የተቀመጠ ሽማግሌ አሻግሮ(አርቆ) ማየት ይችላል’ ይላሉ:: አፍሪካውያን ከናንተ የረጅም ጊዜ ልምድና ተሞክሮ የምንማረው ብዙ ነገር አለ::”

 

ወያኔወች በጣሊያን ፉርኖና ካልቾ አድገው መንገድ በመምራትና በስለላ ሀገራቸውን የበደሉ የባንዳ ልጆች መሆናቸውን ዶ/ሩ አላወቁም:: የጣሊያንን ባህርይ ተላብሰው በዚያው በጣሊያን ስታይል ኢትዮጵያን በዘርና በቋንቋ ከፋፍለው እየገዙን ያሉ ጸረ-ሕዝብና ጸረ ሀገር መሆናቸውን አልተረዱም:: ስለሀገርና ስለአንድነት የሚያወራ ትምክህተኛ የሚባልበት ጊዜ ላይ እንደምንገኝ:  ከአንድነት ይልቅ ልዩነት: ከሀገር በፊት ጎሳ ይቅደም የሚል መፈክር የሚያስተጋባ በስምም ሆነ በተግባር ኢትዮጵያን የማይወክል ቡድን ጥንታዊቷንና ታሪካዊቷን ሀገር በጉልበት እየገዛ እንደሆነ አልተገነዘቡም::

 

የወያኔን ድብቅ ፍላጎት ለማሳካት በሚመች መልኩ ሀገራችን ኢትዮጵያ በክልሎች ተከፋፍላ በዜጎቿ መሀል የመጠፋፋት ፖለቲካ ሲቀነቀን ኖሯል:: በመንግሥት ደረጃ በሚካሄደው የጥላቻና የዘረኝነት ሰበካ ምክንያት ከትግራይ ክልል በስተቀር ደረጃው ይለያይ እንጅ ሁሉም ክልሎች ተጠቂ ሆነዋል:: ከጥቂት ጊዚያት ወዲህ ግን ነገሮች ተገለባብጠው እንዲጠፋፉ ይቀሰቀሱ የነበሩት ጎሳወችና ሀይማኖቶች ግምባር ፈጥረው የጥፋት አራማጁን ኃይል ለጠፋው ጥፋት አንደኛ ደረጃ ተጠያቂ ያደረጉበት ሁኔታ እየታየ ነው:: አንዳንዴ ሌላውን ለማጥመድ በምትተበትበው ድር ራሷ ድር-አድሪ ሸረሪቷም ልትያዝ ትችላለች:: በወያኔወች ላይ የደረሰው ሁኔታ ይኸው ነው:: የዘር ፖለቲካ ይቅር የሚሉትን ሰዎች እያዋረዱ በሰላምና በፍቅር በአንዲት ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖር የነበረውን አንድ ሕዝብ በቋንቋና በዘር ከፋፍለው ሲያናቁሩ የኖሩት ወያኔወች ችግሩ አቅጣጫውን ቀይሮ ወደራሳቸውና ወርቅ ወደሚሉት ሕዝባቸው ፊቱን በማዞሩ በድንጋጤ መደናበር ይዘዋል:: አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማህበረሰብ ለመፍጠር እየደከሙ እንደሆነ የሚደሰኩሩት ውሸት የማይሰለቻቸው እኒህ ወመኔወች እነርሱ ይጠሩበት የነበረውን ስም ለተቃዋሚወቻቸው አሻግረው በሀገራችን ዘር-ተኮር እልቂት ለመፍጠር እና የልማትና የአንድነት እቅዳቸውን ለማበላሸት “ጸረ-ሰላም ኃይሎች” የሚሏቸው ተቃዋሚወች እንቅልፍ አጥተው ለጥፋት እንደተሰለፉባቸው አድርገው ያለሀፍረት መተርተር ይዘዋል::

 

እውነታው ግን እኒህ የወያኔ እብዶች ከስህተታቸው ተምረው ሕዝብን ከሕዝብ የሚያቀራርብ ስራ እየሰሩ አለመሆኑ ነው:: ለችግሮች ትክክለኛ መፍትሄ ክመፈለግ ይልቅ ችግሩን ለማባባስ  በእሳት ላይ ቤንዚን ማርከፍከፍ መርጠው የትግራይ ሰዎችን በሙሉ  አስታጥቀው ለጦርነት አዘጋጅተዋል:: ትግሬ የተባለን ሁሉ መሳሪያ ማስታጠቅና በወታደር ማስጠበቅ በምንም መለኪያ መፍትሄ ሊሆን አይችልም:: ለተቃውሞ የሚወጡትን ሰዎች በማሰርና በመግደል በግፍ ላይ ግፍ ይከምሩ ካልሆነ በስተቀር መፍትሄ ማምጣት አይቻልም:: እየተፈጠረ ያለውን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ የጥፋት ሀይሎች ሴራ አድርጎ ማውራትና ችግሩን ወደሌላ መግፋት ወይም በሀይል ለመፍታት መሞከር ዘላቂ ሰላም አያመጣም::

 

የትግራይ ሕዝብ በወያኔ ጊዜ የተፈጠረ አይደለም:: ወያኔ ከመፈጠሩ በፊት ከሌሎች ጎሳወች ጋር ችግሩንም ደስታውንም ተካፍሎ አብሮ የኖረ ሕዝብ ነው:: በተፈጥሮ አደጋም ይሁን በጦርነት ቢፈናቀል አቅም እንደፈቀደ የወገኖቹ ድጋፍ ተችሮት በየትኛውም ክልል ያለመሸማቀቅ ኖሯል:: በአሁኑ ጊዜ ግን ሁኔታው ተለውጦ በቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥርስ ውስጥ የገባበት ሁኔታ ይታያል:: ይኸ ሀቅ ነው:: ቢያለባብሱት መፍትሄ አይሆንም:: የትግራይ ሕዝብ በሌሎች ክልሎች ተገልሎም: ተፈርቶም: ተጠልቶም: ኮሽ ባለ ቁጥር በፍርሀት እየባነነ የሚኖር ለጥቃት የተጋለጠ ሕዝብ ሆኗል:: ለምን? ለሚለው ጥያቄ የተለያዩ መልሶች ሊኖሩ ይችላሉ:: ብዙወች የሚስማሙበት ግን ትግሬ የተባለ ሁሉ ሕወሀት ጥቅሜን የሚያስጠብቅልኝ ድርጅቴ ነው ብሎ ደግፎት ስለቆመ ነው የሚለው መልስ ነው:: ከኗሪው ጋር ተሰባጥረው  በየክልሎች የሚኖሩት ትግሬወች ሴት-ወንድ: ትንሽ-ትልቅ ሳይል መሳሪያ ታጥቀው ለወያኔ መረጃ የሚያቀብሉ ሰላዮች እንደሆኑ ነው የሚታወቀው:: ከሀገር ውጪ የሚኖሩት በበኩላቸው የወያኔ ክንፍ በመሆን ሁለንተናዊ ድጋፍ ሲያደርጉ እንጅ ሲቃወሙ አይታዩም:: በትግራይ የሚኖረው ሕዝብም ቢሆን የወያኔን ዕቅድ ለማስፈጸም ከመሰለፍ ውጪ በአጎራባች ክልሎች የሚኖረው ሕዝብ እየተፈናቀለ በምትኩ የትግራይ ተወላጆች በቦታው እንዲሰፍሩ ሲደረግ: ሰላማዊ ዜጎች ሲገደሉና በሕዝብና በሀገር ላይ በደል ሲፈጸም ድጋፍ እንጅ ተቃውሞ ሲያሰማ አልተደመጠም:: እንደ ፖለቲከኛ አንድን ሕዝብ በጅምላ በአንድ መልክ መፈረጅ ተገቢ ላይሆን ይችላል:: እውነታው ግን ይኸው ነው:: በተቃውሞው ጎራ ተሰልፈናል የሚሉ አንዳንድ ሰዎች ራሳቸው ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ወደኋላ ሲንሸራተቱ ማየት እንግዳ ነገር አይደለም:: ከሕዝብ ርቆ ወደወያኔ በመጠጋት የጥፋት ሀይልና ምሽግ ሆኖ እያገለገለ በመሆኑ ነው የትግራይ ሕዝብ ከቀሪው ኢትዮጵያዊ የመገለል እጣ እየደረሰበት ያለው:: “የትግራይ ሕዝብ ከማንም ባላነሰ በወያኔ የተበደለ ሕዝብ ነው:: ተቃውሞውን እንዳያሰማ ከፍተኛ አፈና አለበት ገሌ መሌ” የሚለው ፍሬ ከርስኪ ወሬ አይሰራም:: ከሶማሌ እስከ ጋምቤላ ከጎንደር እስከ ሞያሌ ያለው ሕዝብ እየታገለ ያለው ከአፈና ነጻ ስለሆነ ወይም የተለዩ ምቹ የመታገያ መንገዶች ስላሉት አይደለም:: ከስራ መባረሩን: ዱላውን: እስሩን: ግድያውን ችሎ ነው እየጮኸ የተቃውሞ ድምጹን እያሰማ ያለው::

 

ከክልሉ ወጥቶ በሌሎች አካባቢወች ለሚኖረው ለተራው የትግራይ ሕዝብ የበፊቱ ኑሮ ይሻለዋል ወይስ የወያኔው ጊዜ? መሳሪያ ታጥቆ  ወይም በወታደር ጥበቃ እየተደረገለት የሚኖር ሰው በነጻነት የሚኖር ሰው ነው ለማለት ይቻላል? እንዲህ ተሁኖ ኑሮስ ኑሮ ነው? በዚህ ሁኔታስ እስከመቸ መቀጠል ይቻላል? እኒህ ጥያቄወች በትግራይ ልጆች ምላሽ ሊሰጥባቸው የሚገቡ ጥያቄወች ናቸው:: የኢትዮጵያ ሕዝብ በዝባዥና ጨቋኝን እንጅ ሰላማዊ ወገኑን የሚጠላ ሕዝብ አይደለም:: የትግራይ ሕዝብ ሰልፉን አስተካክሎ ወያኔን ለመታገል መንቀሳቀስና መስዋእትነት መክፈል ሲጀምር ያን ጊዜ የጦርመሳሪያና ጠባቂ ታጣቂ ኃይል ሳያስፈልገው እንደማንኛውም ሰው በፈቀደው የሀገሪቱ ክልል ተዘዋውሮ ሰርቶ መኖር ይችላል::

 

የብሄር-ብሄረሰቦች መብት ተከብሮ ሁሉም ክልሎች በቋንቋቸው እየሰሩ ራሳቸውን በራሳቸው እያስተዳደሩ ነው ተብሎ የሚቀለድባት ኢትዮጵያ በወያኔወች መዳፍ ውስጥ ውላ እንደቆሎ እየታሸች ነው:: የወያኔወች ግፍ አንድ ሁለት ተብሎ ተቆጥሮ የሚያልቅ አይደለም:: ሌላው ቀርቶ ከትግራይ በስተቀር ሌሎች ክልሎች በራሳቸው ሰዎች እንዲተዳደሩ አልተፈቀደም:: ብሔር-ብሔረሰቦች ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ መብቱ ቢሰጥ ኖሮ እነ በረከት ስምዖን: ህላዊ ዮሴፍ: ገነት ገ/እግዚአብሔር— የአማራ ክልል መስተዳድር ውስጥ ምን ይሰሩ ነበር? ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሀገሪቱ ውስጥ ተዘዋውሮ የመኖርም ሆነ ሀብት የማፍራት መብቱ የተጠበቀ ነው በሚለው አረዳድ ከክልላቸው ወጥተው በሌሎች ክልሎች የሚኖሩትን ሰዎች በሀገር ልጅነታቸውና በሕገ-መንግሥቱ አግባብ ልክ ነው ብለን እንቀበል:: በስልጣን ላይ ተቀምጠው “ያዘው! ጣለው! ግረፈው!” እያሉ የሚቀልዱብንን በምን ስሌት ይሁን ብለን እንቀበላቸው? ትግራይ ውስጥ ከቀበሌ እስከክልል ድረስ ባሉት የፖለቲካ ስልጣኖች በአመራር ሰጭነት የተቀመጠ  የአማራ: የኦሮሞ: የደቡብ:— ሰው አለ? ሌሎች ክልሎች ለምን ከክልላቸው ውጪ ባሉ ሰዎች እንዲተዳደሩ ይደረጋል? እነ አቶ በረከት: ወ/ሮ ገነት አማራ ክልል ምን ያደርጋሉ? ወርቅነህ ገበየሁ: አባዱላና ኩማ ደመቅሳ ኦሮሚያ ክልል ምን ይሰራሉ? ለመሆኑ በረከት ስምዖን ኢትዮጵያዊ ነው? ኢትዮጵያ እንደአሜሪካ በሀገሪቱ ውስጥ በመወለድ ዜግነት ትሰጣለች ወይስ ፎርማሊቲውን አሟልቶ ዜግነት እንዲሰጠው ማመልከቻ  አቅርቦ ጥያቄው ተቀባይነት አግኝቶ ዜግነት ተሰጥቶት ነው? “አንችው ታመጭው አንችው ታሮጭው” እንደሚባለው የማንፈልገውን ዘረኝነት ከጫናችሁብን በኋላ ይሁን በቃ ራሳችንን በራሳችን እናስተዳድራለን ብለን ስንል ፊልትሮው እንደተበላሸ መኪና ትንተፋተፋላችሁ::

 

ብአዴን ሲመሰረት የቀበሌወች: የመንግሥት መ/ቤቶችና ድርጅቶች ወኪሎች የተገኙበት ስብሰባ በየቀበሌው ተደርጎ ነበር:: በአንደኛው ቀበሌ ከተሰብሳቢወቹ መሀል ብዙ ትግሬወችን የተመለከቱ አንድ አማራ “የተሰበሰብነው የአማራ ድርጅት ለመመስረት ወኪል ለመምረጥ ነው ብላችሁናል:: ታዲያ ከእኛ መሀል ያሉት ትግሬወች ምን ያደርጋሉ?” ብለው ጠይቀው ነበር:: ከሕዝቡ መሀል ተመሳስለው ተቀምጠው የነበሩ አንድ የብአዴን አመራር አባል እመር ብለው ተነስተው “የሰውን ደም እየመረመርን ፖዘቲቭ ከሆነ አማራ ኔጌቲቭ ከሆነ ሌላ የሚል ቀልድ ለመጫወት አይደለም እዚህ የተሰበሰብነው” የሚል አስገራሚ መልስ ነበር የሰጡት::

 

ወ/ሮ ገነት ገ/ እግዚአብሔር የሚባሉ የአማራ ክልል ከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ከወያኔ ጋር በመተባበር ወጣቶችን እያስገደለች ነው ተብላ ስሟ ከብዙወች መሀል በመጠቀሱ የአማራው ክልል ቃል አቀባይ አቶ ንጉሱ አዝነው ለወ/ሮይቱ የሚከላከልና የሚያሞገስ ጽሁፍ በፌስቡክ ላይ ማስነበባቸውን ሰማን:: አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለወ/ሮዋ ብቻ  ጠበቃ ሆነው የቆሙት በቀሪወቹ ላይ የተሰነዘረው ክስ ትክክል ነው ብለው ተቀብለውት ነው ወይስ ምን? ወ/ሮይቱ ተወልዳ ያደገችው ባ/ዳር ነው ይሉናል አቶ ንጉሱ:: ዶሮና ቆቅ ዝርያቸው አንድ ነው:: ነገር ግን በቤት ውስጥ የተፈለፈለች ቆቅ ዶሮ ልትሆን አትችልም:: የዘር ፖለቲካ ቀርቶ እንደሆነ ይነገረን:: የዘር ፖለቲካ ካልቀረ ግን ለማም ጠፋም ሁሉም በየራሱ ሰው ይተዳደር እንላለን:: የሆነው ሆኖ በአማራ ክልል አማራ ያልሆኑ ሰዎች በፖለቲካ አመራር ሰጭነት እንዲቀመጡ የተደረገው እነርሱን የሚተካ አማራ ማግኘት ስላልተቻለ ነው? በሌሎች ክልሎች ያለው ሁኔታስ ተመሳሳይ ነው ማለት ነው: ወይስ ምን?

 

አሁን ካለው የሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ተነስተን ስንገመግም የወያኔ የዘር ፖለቲካና የተዛባ አመራር መቋጫው እየቀረበ ይመስላል:: ብዙ ያስሄደናል ተብሎ የተጠረገው የከፋፍለህ ግዛው ጎዳና ሱር ኮንስትራክሽን እንደሰራው መንገድ እየፈራረሰ ነው:: ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት ይጠቀሙበት የነበረው መላ ከሽፏል:: በብሔር-ብሔረሰቦች መሀል የዘሩት ቂምና ጥላቻ የፈለጉትን ያህል ምርት ሳያስገኝ ደርቋል:: በፍርሀት የተሸበበው ሕዝብ ልጓሙን አውልቆ ጥሎታል:: እስከ የልጅ ልጅ ድረስ በዙፋን ቁጭ ብለን እንድንገዛ ያስችለናል ብለው የቋጠሩት ሸር ተፈቷል:: ለጻድቃን የወረወሩት ጦር ወደሀጥአን ዞሯል:: ወያኔወች ግን አሁንም ቢሆን ከስህተታቸው ሊማሩ ባለመፍቀዳቸው ከራሳቸው አልፈው በደጋፊወቻቸው ላይ አደጋ ደቅነዋል:: በእርግጠኝነት ለመናገር ወያኔ መቸም እንዳያቀጠቅጥ ሆኖ ይቆረጣል:: የወያኔን ውድቀት ተከትሎ ዜጎች በነጻነት የሚኖሩባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እውን ትሆናለች::

ትንሳኤ ለኢትዮጵያ!

 

በአምቦ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ ተቀስቅሷል

$
0
0
Oromo

ፋይል- ኦሮሞ ተቃውሞ ሰልፍ

ከተማዋ በተኩስ እሩምታ ውስጥ መሆኗን የከተማዋ ነዋሪዎች ይናገራሉ:: ተጨማሪ ሃይል ወደ አምቦ እንቅስቃሴ እያደረገ በመሆኑ
ሆሎታ
አዲስ አለም
ኦሎንኮሚ
ጊንጪ ያላችሁ መንገድ በመዝጋት በጉዞ ያለውን ሃይል ባለበት አስቁሙት የሚል መልዕክት በማስተላለፍ ላይ ናቸው:: በተያያዘ ዜና በአወዳይም የዛሬው የቢሾፍቱ ጭፍጨፋ ያስቆጣቸው የከተማዋ ነዋሪዎች አደባባይ መውጣታቸው እየተነገረ ነው

እኛ እያለቀስን..እነሱ በደስታ

$
0
0

14572192_675203989308611_2001452800520476251_nእኛ እያለቀስን
እነሱ በደስታ
እንዴት እንቻለው
ሰው በሰው ሲመታ
ጥይት መጫወቻ
ሆነ እና በአገሩ
ወገን ተገደለ
በአገር በመንደሩ
እረ እናተ ሰወች
በቃ አትግደሉብን
መሬት ፈልጋችሁ
ሰው አትጨርሱብን
ማነው ሽማግሌ
መካሪ በአገሩ
ሰው እዬሞተነው
መንግስትን እሰሩ
መግስት ገዳይ ሆኖ
እኛ እዬሞትንለት
ሊተናኮል መጣ
ኢሬቻን ይዞበት
ይህ ኩሩ ጀግናዬን
አስለቅሶት ዋለ
ገሎበት ልጇቹን
ጥሎበት በረረ
በዚህ አያበቃም
ትግላችን በወኔ
ድባቅ ሳንከተው
ይህንን ወመኔ
ከእነ ምናምቴው
ይሞታል ወያኔ
ይህ አንድነት አለን
እኛ ታላቅ ህዝቦች
ይሰማናል ሁሌም
የወገናችን ሞት።

በዛሬው የኢሬቻ በዓል በተፈጠረው ግጭት በመቶዎች የሚቆጠር ህይወት መጥፋቱን ኦፌኮ አስታወቀ

$
0
0

Sunday, October 2, 2016/ VOA Amharic

1451በዛሬው ዕለት በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ኃይቅ ለመከበር በዝግጅት ላይ የነበረውና ከኦሮሞ ክብረ በዓሎች አንዱ የሆነው ኢሬቻ በዓል መንግሥትን በተቃወሙ ወጣቶችና በመንግሥት ታጣቂዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ተቋርጦ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት ማለፉን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አስታወቀ። የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፤ ፓርቲያቸው ባጠናቀረው መረጃ ሰዎች በተኩስ፣ በአስለቃሽ ጭስ እና በመረጋገጥ ሕይወታቸው እንዳለፈ ነው። 
በርካታ የቆሰሉ ሰዎች አሁንም በሆስፒታል እንደሚገኙ አክለው የተናገሩት ዶ/ር መረራ የሟቾች ቁጥር አሁንም ሊጨምር እንደሚችል ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው በቦታው የነበሩ የዐይን እማኞች ግጭቱ የተጀመረው በበዓሉ መክፈቻ ላይ ንግግር ሊያደርጉ የነበሩ ሰዎች ላያ እና ሊሰቀል በነበረው ባንዲራ ላይ ተቃውሞ በመነሳቱ ነው።
ከግጭቱም በኋላ በርካቶች በተኩስ፣ በአስለቃሽ ጭስ፣ በመረጋገጥ እና ገደል ውስጥ ገብተው ሕይወታቸው እንዳለፈ ተናግረዋ። የተጎዱ ሰዎችን በተመለከተ እስካሁን ይህ ነው የተባለ ትክክለኛ ቁጥር ማግኘት ባይቻልም የዐይን እማኞች ተጎጂዎች 25 በሚሆኑ መኪኖች ሲወሰዱ ተመልክተናል ብለዋል።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በሰጠው መግለጫ፤ “የኢሬቻ በዓልን ባህላዊ አከባበር ጠብቆ ለማክበር የኦሮሞ ህዝብ አባገዳዎችና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ያደረጉት ሰፊ ቅድመ ዝግጅት በሁከት ፈጣሪ ኃይሎች ተስተጓጉሏል፡፡ ሁከት ፈጣሪዎቹ ባስነሱት ሁከት በተፈጠረ ግርግር በመረጋገጥ የሰው ህይወት ጠፍቷል፡፡” ብሏል። ዝርዝሩን ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ይጠብቁ። (ፎቶ፡ አንዷለም ሲሳይ)

 

መንግሥቱ ኃይለማርያም ለፍርድ ሊቀርብ ነው!

$
0
0

 

ጋ ዜ ጣ ዊ   መ ግ ለ ጫ

jusበኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ እጅግ መራር የሆነ መጠነ ሰፊ ግፍና ያልተቆጠበ ወንጀል ፈጽሞ የሕዝቡ ቁጣ ሲገነፍል ሀገር ጥሎ በመሸሽ ዚምባብዌ በምትባል ሀገር ተሸሽጎ የሚገኘው፤ የደርግ አገዛዝ መሪ የነበረው መንግሥቱ ኃይለማርያም ለፍርድ እንዲቀርብ ተጨባጭ እርምጃ እየተወሰደ ነው።

“ፍትሕ ለኢትዮጵያ ግብረ ኃይል” በመሰኘት በቅርቡ በአሜሪካ ሀገር የተቋቋመው ሕዝባዊ ድርጅት በጉዳዩ የሚያምኑ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የሚሳተፉበት ድርጅት ሲሆን ዓላማውም ማንንም ሥልጣኑን ተገን አድርጎ የሰው ሕይወት ያጠፋን ለፍርድ ለማቅረብ ሲሆን የመጀመሪያ ጥረቱ የሚያተኩረው መንግሥቱ ኃይለማርያምን ለፍርድ ማቅረብ መሆኑን አረጋግጧል።

የግብረ ኃይሉ ራዕይ ለዲሞክራሲ፤ ለሕግ የበላይነት፤ ለሰብአዊ መብት መከበር፤ ለሰላም፤ ለአንድነት በኢትዮጵያዊነት፤ ቀጣይ ለሆነና ለመላው ሕዝብ ለሚደርስ ልማት ባለማሰለስ የሚጥር አመራር በተግባር ላይ ውሎ ለማየት ነው። ዓላማውም የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት ተከስቶበት ከነበረው የአምባገነን አገዛዝ ለመላቀቅና ለዴሞክራሲ ሥርዓት የጀመረውን ትግል በማኮላሸት መንግሥቱ ኃይለማርያም ለፈጸማቸው እጅግ ብዙ ወንጀሎች ለፍርድ እንዲቀርብ በማድረግ ለወደፊቱም ማንኛውም ተመሳሳይ ግፍ የሚፈጽም የኢትዮጵያ መሪ ተጠያቂ እንደሚሆን ግልጽ መልእክት ለማስተላለፍ ነው።

እንደሚታወቀው፤ በደርግ 17 ዓመትና በኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራቲክ ግንባር (ኢሕአዴግ) 25 ዓመት ዘመነ ግፍ አገዛዝ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ኢትዮጵያውያን ተጨፍጭፈዋል። ከነሱ ውስጥ አብዛኛዎቹ ወጣቶችና ሴቶች እንደ ነበሩ የታወቀ ሐቅ ነው። እንዲሁም፤ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መንግሥት የአመራር አባላት ከነበሩት ውስጥ 60 ባለሥልጣኖችን ያለአንዳች የፍትሕ ሒደት፤ መንግሥቱ ኃይለማርያም በራሱ ፊርማ ወስኖ ያስገደለ መሆኑ በይፋ የታወቀ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ፤ እንደ ከፍተኛ ሰቆቃ ምን ጊዜም የማይዘነጋው፤ በመንግሥቱ ኃይለማርያም አመራር የተከናወነው የ“ቀይ ሽብር” እልቂት ነው። በዚሁ እጅግ አሳዛኝ ጭፍጨፋና የስቃይ ዘመቻ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን ሰለባዎች እንደ ነበሩ የታወቀ ነው። እስካሁንም ድረስ ብዙ ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች በ“ቀይ ሽብር” ጠንቅ በተጨፈጨፉባቸው የቅርብ ዘመዶችና ወገኖች ኃዘናቸው አልለቀቃቸውም። በተጨማሪም፤ በመንግሥቱ ኃይለማርያም አመራር፤ በደርግ አማካኝነት እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን በእስር፤ በወከባ፤ በድብደባና በሌሎች ልዩ ልዩ ጥቃቶች እንደ ተሰቃዩ የተረጋገጠ ነው።

ከላይ ከተጠቀሱት የደርግ ወንጀሎች በተጨማሪ፤ በኢትዮጵያ ላይ ተከስቶ የነበረው ኢዴሞክራሲያዊ የሆነ መራር የነበረ ከልክ ያለፈ አምባገነንነት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ያመነመነ፤ ጸጥታዋን ያደፈረሰና የርስ በርስ ግጭት ያመቻቸ ነበር። በዚህም ምክንያት በልዩ ልዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሱት ተቃውሞዎችና ውጊያዎች ሀገሪቱን ለከፋ እልቂትና መገነጣጠል ዳርገዋታል። ከሶማሊያ ጋር የተከሰተው ግጭትና በኤርትራም የተከናወነው ጭፍጨፋ ለሀገሪቱ መከፋፈልና እልቂት አንደኛው ምክንያት የመንግሥቱ ኃይለማርያምና የደርግ ደካማና ብልሹ አመራር እንደ ነበር የታወቀ ነው።

በመንግሥቱ ኃይለማርያም አምባገነናዊ አመራር በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ ለደረሰው ወንጀል ዋናው ተጠያቂ እሱው በመሆኑ ለፍርድ ማቅረቡ ታሪካዊ ግዴታ ነው። እስካሁንም ድረስ የኢትዮጵያን ሕዝብ ልባዊ ይቅርታ በመጠየቅ ፋንታ አጉል ጀግንነት የተንጸባረቀባቸው ጽሑፎችና መልእክቶች ማስተላለፉ አንዳችም የሕሊና ጸጸት ያልታሰማው መሆኑ ግልጽ ነው።

ስለዚህ መንግሥቱ ኃይለማርያም ለፈጸመው ወንጀል ሁሉ ለፍርድ እንዲቀርብ “ፍትሕ ለኢትዮጵያ ግብረ ኃይል” በቸሩ የኢትዮጵያ አምላክ እርዳታ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ ቆርጦ ተነስቷል። ለዚህም የተቀደሰ ተግባር ለሀገር ፍትሕ የሚቆጩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ እርዳታቸውንና ድጋፋቸውን እንዲለግሱ በትሕትና ያሳስባል።

ግፈኛው መንግሥቱ ኃይለማርያም ከፍትሕ አያመልጥም!

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!

ኢሜል ፡ FEG012009@gmail.com

መስከረም 21 ቀን 2009 ዓ.ም.

ለዘብተኞችን ማጥቃት፤ አክራሪዎችን ማብዛት –አንዱዓለም ተፈራ  –የእስከመቼ አዘጋጅ

$
0
0
ሰኞ፤ መስከረም ፳ ፫ ቀን ፳ ፱ ዓመተ ምህረት
cdo-debretsionየሃሳብ ልዩነት፤ ያለ ነገር ብቻ ሳይሆን፤ አስፈላጊም ነው። የተለያዩ ሃሳቦች መከሰት፤ አማራጮችን በመድረክ ላይ በማቅረብ፤ ልዩነቶችን እንድንመረምርና፤ በብዙኀኑ ዓይን የተሻለ የተባለውን እንድንመርጥ ዕድል ይፈጥርልናል። በነዚህ የተለያዩ ሃሳቦች ተነስቶ ርስ በርስ መወነጃጀሉ፤ አንድም እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን ባይነት ብሎም ራስን የማግዘፍ ጥንውት ነው። ሌላም ትግሉ መልክ ይዞ ወደፊት እንዳይሄድ እንቅፋት ለመሆን የተጠነሰሰ ሴራ ነው።
አክራሪዎች መኖራቸውንና የትግላችን አንዱ ገፅታ መሆኑን መቀበል አለብን። ይህ በቀኝ ይሁን በግራ፣ በፊት ይሁን በኋላ፣ ፈለግነውም ጠላነውም፤ ያለ ሀቅ ነው። ይህ የትግል አቅጣጫችን ሊቀይር ቀርቶ፤ ትኩረታችን ሊስብ አይገባውም። የሀገራችን የፖለቲካ እውነታ፤ ያደግንበትም ሆነ አሁን ያለው ተጨባጭ ሀቅ፤ መፈናፈኛ በማሣጣቱ፤ አክራሪዎች መፈጠራቸው፤ ሁኔታው የወለደው ክስተት ነው። እናም አክራሪ የምንላቸውን ለማጥቃት ወይንም ለማጥፋት ዓይኖቻችንን ከዋናው ግባችን መንቀል፤ ለራሳችን ጥቃት በሩን ለጠላት በርግደን መክፈታችን ነው። ትኩረታችን መሆን ያለበት ሰፊው ሕዝብ የሥልጣኑ ባለቤት የሚሆንበትን በመፈለግና ያን በመቀበል ላይ ነው። ብዙኀኑ የተቀበሉት ለስኬት እንዲበቃ፤ ጥረታችንን በሙሉ በዚያ ላይ ማረባረብ አለብን። በግራና በቀኝ ተፋሰሶች እያበጀን፤ ጉልበታችንን እኛው ራሳችን አናዳክም።
“አስቀድሞ መግደል አሾክሿኪውን ነው!” ብለው ቀደምቶቻችን ሲያስተምሩን፤ አሾክሿኪው የጠላት አንድ አካል መሆኑን፤ እነሱም ሆኑ ራሱ አሾክሿኪው ስለሚያምኑበትና ስለሚቀበሉት ነው። በተጨማሪም፤ እጅ ከፍንጅ መረጃው ስለተያዘ ነው። እኛ የያዝነው ግን፤ “እኔ የምለውን ያልተቀበለ፤ ‘ወያኔ’ ነው!” የሚል ጠባብ፣ ራስ ተኮር፣ እኔ ብቻ ነኝ አዋቂ ባይነትና ከሀገር በላይ ግለሰብን ወይንም የራስ ድርጅትን የሚያስቀምጥ አባዜ ነው።
ባሁኗ ሰዓት፤ በፖለቲካ ትግሉ መስክ፤ ባንድ በኩል የሀገር አንድነትን ፈላጊዎች፤ “ሀገር አቀፍ ትግል እንጂ ሌላ ምን ሲባል!” የሚል ምሽግ ሠርተናል። በሌላ በኩል ደግሞ በሀገር ውስጥ ባለው የፖለቲካ እውነታ በመመርኮዝ፤ “የለም፤ የአማራ ወጣቶችና የኦሮሞ ወጣቶች የትግሉን የበላይነት ጨብጠውታል። እናም ያን ሀቅ ተቀብለን፤ እኒህ ክፍሎች የሚቀራረቡበትንና የሚተባበሩበትን በመፈለግ፤ የወደፊቷን ኢትዮጵያ እንመሠርታታለን!” ባዮች አንድ ምሽግ ሠርተናል። ለኒህ ሁለቱ የትግል መስመሮች ጠላታችንም ግባችንም አንድ ነው። መንገዳችን ግን የተለያየ ነው። በርግጥ የትኛው የተሻለ ይሆናል የሚለውን፤ ሁለቱ ክፍሎች ቀርበን ለመነጋገር፤ አሁን ትልቅ ችግር ላይ ነን። የዜሮ ድምር ፖለቲከኞች፤ “ሌላው መታሰብ እንኳን የሌለበት ነው!” የሚል አቋም ያራምዳሉ። እንዲያውም ሁለቱም ክፍሎች በየጎራችን ጎድበን፤ አንዳችን ሌላችንን፤ ከወራሪው ፀረ-ኢትዮጵያ የትግሬዎች ቡድን የበለጠ ጠላት አድርገን በመፈረጅ፤ ለመጠፋፋት ተነስተናል።
እንግዲህ ሀቁ እንዲህ ነው። አስታራቂ ሽማግሌ ከየትም አይመጣም። እውነት የሕዝቡን ድል ፈላጊዎች ከሆን፤ ከባህላዊ ዘፈናችን አንድ ስንኝ ልዋስና፤ አስታራቂም የለን፤ እኛው እንታረቅ። የርስ በርሳችን መወነጃጀልና ጉልበታችን ለዚሁ ማጥፋት ማንን እንደሚረዳ፤ እኔ ለናንተ አልነግርም። አስቸጋሪ የሆነው ደግሞ፤ ይህ የታጋዮች በሁለት ጎራ መመሸግ፤ እየተከሰተ ያለው በቀጥታ ሳይሆን፤ በተዘዋዋሪና ትግሉን በቀጥታ በሚጎዳ መልክ ነው። መድረካችን በሳል የትግል ነጥቦችን በርጋታ የምንነጋገርበት ሕዝባዊ ስብስብ ሳይሆን፤ ፓልቶክና ፌስቡክ፣ ቲውተርና የየግል የሬዲዮ ስርጭት መሰምሮች ሆኗል።በመጀመሪያ ደረጃ፤ የፖለቲካ ልዩነት መግለጫና መነታረኪያ ባህላችን፤ ስድብ ማሽጎድጎድ ሆኗል። ብዙ በመሳደብ፤ የአቸናፊነት ሽልማት ለመቀበል መስገብገብ ይታያል። “ወያኔ!” ብሎ አንዱ ሌላውን አስቀድሞ ስለወነጀለ፤ ወንጃዩ የሕዝብ ወገን፤ ታርጋው የተለጠፈበት ደግሞ የጠላት ወገን የሆነ ይመስለዋል። አጉል ቅዠት ነው። ስድብ ስለ ቆሸሸውን የሰዳቢ አፍ ይናገራል እንጂ፤ የተሰዳቢውን ማንነት አይገልጽም። ይህ መጥፎ ባህል ነው። ይቅርብን።
አንዱ የመነጋገርያ ነጥብ የአማራውን መደራጀት የሚመለከት ነው። አማራው መደራጀት አለበት ብለው ያመኑና በዚሁ እምነታቸው የገፉ አሉ። ባለፉት ሃይ አምስት ዓመታትና አሁንም በአማራው ላይ እየደረሰበት ያለውን የዘር ማጽዳት ወንጀል በመንተራስና፤ የትግሬዎችን ቡድን የፖለቲካ ፍልስፍናና የአስተዳደር መመሪያ መረጃ በመያዝ፤ አማራው በሕልውና እንዲኖር፤ ተደራጅቶ መታገል አለበት! የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል። በሌላ በኩል ደግሞ አማራው መደራጀት የለበትም በማለት፤ “ትግሉ መካሄድ ያለበት በኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው!” የሚለውን ሃሳብ ሙጥኝ ብለው የተጣበቁ አሉ። በጄ! ይህን በተለያየ መልኩ ማየት ይቻላል። ነገር ግን፤ አንዱ ወገን የሌላውን ወገን ከመስማት ይልቅ፤ በራስ ጭንቅላት የፈጠሩትን ደጋፊ ወይንም ነቃፊ ነጥብ በማብጠልጠል፤ ከራስ ጋር ሙግት የተያዘበት ሀቅ ነግሷል። የሌላውን ነጥብ ማዳመጡ ቦታ አልተሠጠውም። አማራው ያለበት የዘር ማጽዳት አውነታ ለመቀየር፤ ማንኛውንም በማድረግ ሕልውናውን መጠበቅ እንዳለበት መረዳት ያስፈልጋል። ይህን እረዳለሁ ብሎ የተነሳን ደግሞ፤ ማንም ቢሆን ማን ሊያቆመው፣ ሊከለክለው ወይንም ሊቃወመው አይገባም። መቃወም ማለት በአማራው ላይ መዝመት ማለት ነው። ለዚህ ክፍል፤ ኢትዮጵያን ከማስብ በፊት፤ አማራው መዳን አለበት። ይህ አከራካሪ የመሆኑን አጥር ዘሏል። ስለዚህ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ መሄዱ አስፈላጊ አይደለም። ይልቁንስ ለመረዳት መጣሩ ተገቢ ነው። ኢትዮጵያ እንዴት ትድናለች የሚለው ጥያቄ ያንገበገባቸው ሰዎች፤ ታጋዮችንና በሀገሪቱ ያለውን ሀቅ፤ የምርምራቸው መነሻ ማድረግ ይገባቸዋል።
ሁለተኛው መነጋገሪያ ነጥብ፤ ኢሳትን የተመለከተ ነው። ኢሳት የራሱ ግብ ያለው የግል ተቋም ነው። ባለቤት አለው። ኢሳት የኢትዮጵያ ሕዝብ ንብረት አይደለም። ውሎ አድሮ ለንግድ የተዘጋጀ ተቋም ነው። ስለዚህ ባለቤቱ የሚያዝበት እንጂ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያዝበት ተቋም አይደለም። ይህን ማለት፤ ኢሳት መጥፎ ነው ማለት አይደለም። ነገር ግን፤ ማንም ተነስቶ ይሄን ካላደረገ ወይንም ያንን ከላደረገ የሚልበት አለመሆኑን ለማስጨበጥ ነው። ማንም ግለሰብ ይህን የግል ተቋም፤ በግሉ ሊረዳ ይችላል። ማንም ግለስብ ደግሞ፤ በግሉ ይሄን የግል ተቋም ላይረዳ ይችላል። ነገር ግን ማንም ግለሰብ፤ ከባለቤቱ በስተቀር፤ ሊያዝበት አይችልም። ይህ መታወቅ አለበት። እናም ይሄን ይዘን፤ የግሉን ተቋም ለምን ይሄን አላደረገም ብሎ መወንጀል፤ ተገቢ አይደለም። ይህ በታጋዮች መካከል ለመጣላት ምክንያት ሊሆን አይገባውም። የኢትዮጵያዊያን ንብረት ቢሆን ኖሮ፤ ለምን እንዲህ ወይንም ለምን እንዲያ አላደረገም ብለን መናገር መብታችን ይሆን ነበር። አሁን ግን መብታችን አይደለም። ከወደድን እንደግፈው፤ ካልወደድንም ደግሞ እንተወው። በቃ።
ሶስተኛው መነጋገሪያ ነጥብ ደግሞ ትግሬዎችን የተመለከተ ነው። ባሁኑ ሰዓት፤ በሀገራችን ላለው የግፍና የስቃይ ውርጅብኝ፤ ተጠያቂው ወራሪው የትግሬዎች ቡድን ነው። ይህ ወራሪ ቡድን፤ በምንም መንገድ ይሁን በምንም፤ ትግሬዎችን ወክያለሁ ብሎ፤ በኢትዮጵያዊያን ላይ ግራና ቀኝ ጥፋት፤ በተለይም ደግሞ በአማራው ላይ የዘር ማጽዳት ወንጀል እየፈጸመ ነው። ይህን የሚፈጽመው፤ በአብዛኛው ትግሬዎችን በመሣሪያነት ይዞ ነው። በርግጥ ከሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች የሆኑ አንዳንድ ሆድ አደሮች፤ በግለሰብ ደረጃ፤ በባንዳነት እየረዱት ናቸው። እኒህ ሆድ አደሮች ይሄንን በሚያደርጉበት ሰዓት፤ ሕልውናቸውን ሸጠው፤ የዚሁ የወራሪው የትግሬዎች ቡድን አካልና አምሳል ሆነው ነው። እናም እነሱ ትግሬዎችም ባይሆኑ፤ የዚህ የወራሪው የትግሬዎች ቡድን አካል ናቸው። ስለዚህ ይህን ቡድን በምንም መልኩ ብናየው የትግሬዎች ቡድን ነው። አማራውን ለማጥፋት የተነሳው ይህ የወራሪው የትግሬዎች ስብስብ ነው። ኦሮሞዎችን እየገደለ ያለው ይህ የወራሪው የትግሬዎች ቡድን ነው። አኝዋኮቹን የጨፈጨፈው ይህ የወራሪው የትግሬዎች ቡድን ነው። ኦጋዴኖቹን የበደለው ይህ የወራሪው የትግሬዎች ቡድን ነው። እና ገና ለገና ትግሬዎች ይበደሉ ይሆናል በማለት፤ በውጪ ሀገር ያሉ “ታጋይ ነን!” ባይ ትግሬዎች፤ ጥብቅና ከትግሬው ቡድን ጋር አብረው ተሰልፈዋል። አልሸሹም ዞር አሉ ነው። ጠላት የማብዛትና የማሳነስ ስልት አይደለም። አሁንም፤ ዛሬ የዘር ማጽዳት ወንጀል እየተፈጸመበት ላለው አማራና ዛሬ ለሚያልቀው የኦሮሞ ወጣት ከመቆም ይልቅ፤ ገና ለገና በትግሬዎች ንብረት ላይ ጉዳት ይደርስ ይሆናል ብሎ የሚጮኽ፤ በምንም መለኪያ ቢታይ፤ የወራሪው የትግሬዎች አጥፊ ቡድን አካል እንጂ፤ የሕዝብ ወገን አይደለም። ጠላቱንና የትግል መስመሩን ለይቶ ያልተነሳ ታጋይ፤ የያዘውን ትግል አያውቀውም፤ ድሉም ምን እንደሆነ ስለማያወቅ፤ ለድል አይበቃም።
የያዝነው የምኞትና የፍላጎት ትግል አይደለም። በቦታው ያለውን ሀቅ ተቀብሎ፤ ያን ለማስተካከል የሚደረግ ትግል ነው። ወራሪው የትግሬዎች ፀረ-ኢትዮጵያዊያን ቡድን የሚታረቅ፤ የሚሻሻል፤ የሚታረም አይደለም። መሠረታዊ እምነቱ ኢትዮጵያዊነት አይደለምና! ከዚህ ቡድን ጋር እርቅ ለማድረግ የሚፈልጉና “ብዙ ሰው እንዳያልቅ!” እያሉ የሚያላዝኑ ሰዎች፤ ጎራቸው ከዚሁ ወራሪ ቡድን ጋር ይቀራረባል። ይህ ወራሪ ቡድን፤ ከትግራይ ውጪ ለሚያልቀው ወገን ደንታ የለውም። እየገፋበትም ነው። ይህን ቡድን በምንም መልኩ ለማዳን መሞከር፤ የዚሁ ቡድን ደጋፊነት ነው። አጥሩ ግልጽ ነው። ይልቅስ በታጋዩ ወገን ያለውን እናስተካክል። ለወራሪው ቡድን አሳቢዎች ብዙ አሉ። እኛ ለሱ መጨነቁን እንተወው። በአንድነት መታገሉን እስከወደድን ድረስ፤ ወደ አንድነት የሚወስደውን መንገድ እንከተል። በታጋዩ ጎራ ያለን ሁሉ፤ ወደ አንድ ለመምጣት ያለው በር አንድ ነው። ተቀራርቦ መነጋገር። እንዴት ወይንም መቼ ወይንም የት የሚለው፤ በሁለተኛ ደረጃ የሚከተል ነው። መጀመሪያ የአንድነቱን አስፈላጊነት መቀበል ነው። ይሄን ደግሞ ያልለፈለፈለት የለም። ታዲያ ቀጥሎ መገናኘት ነው። ለዚህ ጠሪው ብዙ አድማጩ ዜሮ ለሆነበት ትንግርት፤ እግሬን አስቀድሜ አነሳለሁ። እናም ውይይቱ ትናንት መሆን ቢኖርበትም፤ ትግሉ እየተካሄደም፤ ዛሬ ይቀጥል።  

ሕወሓት የማይወድቅባቸው የትግል ሥልቶች -ነፃነት ዘለቀ

$
0
0

 

1451ባሳለፍነው እሁድ በደብረ ዘይት የእሬቻ በዓል አከባበር ላይ በአጋዚ የወያኔ ቅልብ ጦር ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችንን ነፍስ እግዚአብሔር ይማርልን፤ ከዚህች ዘግናኝ ቀን በፊትም ሆነ በኋላ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በዚሁ የወያኔ ጦር ያለቁና ወደፊትም የሚያልቁ ወንድም እህቶቻችንንና ልጆቻችንን መንግሥተ ሰማይን ያውርስልን፡፡ ፈጣሪ የነሱን መስዋዕትነት እንደአቤል ንጹሕ ደም ቆጥሮልን የነፃነታችንን ቀን ያፋጥንልን፡፡ የቤተሰባቸውንም ሆነ የሁላችንን የተሰበረ ልብ ይጠግን፡፡ አሁንስ እጅግ በጣም እየተጎዳን ነው፡፡

ወያኔ በምን እንደማይወድቅ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለይ ቁልጭ ብሎ እየታየ ነው፡፡

  1. በምንም ዓይነት መንገድ ወያኔ በጩኸት አይወድቅም፡፡ እርግጥ ነው ሰሚ ከተገኘ ጩኸት ብሶትንና ግፍን ለመግለጽ ይጠቅማል፡፡ በኛ የእስካሁኑ ሁኔታ ግን ሰሚ የለንምና ጩኸታችን አልጠቀመንም፡፡ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተሰማራው ኃይል ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለው በመሆኑ “ዐውቆ የተደበቀ ቢጠሩት አይሰማም” እንዲሉ ሆኖ ለማንም ብንጮኽ ሰሚ አናገኝምና ትርፉ ድካምና ጩኸትን በከንቱ ማባከን ነው፡፡ የኛ ደም ውኃ ይመስል በየቀኑ እንደጎርፍ እየፈሰሰ በዋና ዋና የሚዲያ አካላት በስፋትና በጥልቀት የማይዘገብበት ምክንያት ሌላ ሣይሆን ጥፋትና ውድመታችን የታዘዘው ዓለምን ከተቆጣጠረው ዋናው የአጋንንት ኃይል በመሆኑ ነው፡፡ እንጂ አንድ የስዊድን ወይም የእንግሊዝ ዜጋ የወያኔ ወንድሞች ማለትም አይሲሶች ቢገድሉት ኖሮ የሣምንታት የዜና መክፈቻቸው በሆነ ነበር፡፡ እነዚህ ጉደኞች ከአምስት መቶ ሕዝብ በላይ በጠራራ ፀሐይ የታጨደበትን አሳዛኝ ዕልቂት በመኪና ተገጭቶ የሞተ አንድ የአውሮፓ ውሻ ያህል እንኳን አልቆጠሩትም፡፡ ለይስሙላ ግን “In God we trust.” እያሉ በፈጣሪ ኅልውና ሲያላግጡ አያፍሩም፤ የሥራቸውን ይስጣቸው እንጂ ምን ይባላል፡፡ ለነገሩ ከሞላ ጎደል ሁሉም የዘሩትን እያጨዱ ነው፤ ወደፊትም ይህ የፈጣሪ ፍርድ በነሱም ላይ አይቀርም፡፡ ማንም የሥራውን ያገኛል፡፡
  2. በምንም መንገድ በሰላማዊ ሰልፍ ወያኔ አይወድቅም፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ ጊዜ ማባከኛ ነው፡፡ 25 ዓመት ተሰልፈን ያመጣነው ለውጥ የለም፡፡ “ደግሞ ጀመራቸው!” ከማስባልና እንደክፉ ዐመል የተተከለን ጠባይ ከማሳየት ውጪ ምንም አልፈየደም፡፡ ሰልፍ የሚሠራበት ሀገር አለ፤ ለኛ ግን አይሠራም፡፡
  3. በምንም መንገድ ሕወሓት በድርድር አይወድቅም፡፡ ወያኔ ዘንድ ሰጥቶ መቀበል ብሎ ነገር የለም፡፡ የወያኔ ጠባይ ጨርሶ ማጣት ወይም ጠቅልሎ መውሰድ እንጂ የቁጥ ቁጥ ነገር አይዋጥላቸውም፡፡ አንድም የሕዝብ ጥያቄ በአወንታ መልሰው የማያውቁት ጥያቄን በአግባብ መመለስን እንደመሸነፍ ስለሚቆጥሩት ነው፡፡ ለምሣሌ ሁለትና ሁለት ሲደመር ስንት እንደሚሆን ወያኔዎችን ብትጠይቋቸው ሦስት ወይም አምስት ይሉ ይሆናል እንጂ እቅጩን “አራት ነው” አይሉም፡፡ ምክንያቱም በትክክል መመለስ ጠያቂን እንደሚያስደስት ስለሚያምኑና ያንንም ለነሱ እንደሽንፈት ስለሚቆጥሩት ነገረ ሥራቸው ሁሉ ጠማማ ነው፡፡ ይህ ጠባያቸው የሚያሳየን አእምሯቸው ያልሠለጠነና በዕድገቱ ከእንስሳትም በታች መሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም ከወያኔ ጋር ተደራድሬ ሀገሬን ነፃ አወጣለሁ የሚል አካል ቢኖር ራሱም ያበደ ነው፡፡ ወይም ወያኔ ጊዜ ገዝቶ ከጭንቀቱ እስኪገላገልና አንዳች ዘዴ ፈልጎ እስኪያጠፋው በመሣሪያነት ሊያገለግል የወደደ ጊዜያዊ የሥልጣን ፍርፋሪ የሚፈልግ መሆን አለበት፡፡ እርግጥ ነው ወያኔ በጣም ሲጨነቅ ከነልደቱ አያሌውና ከነ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ዓይነቶቹ የሥልጣን ጥመኞች ጋር ሊደራደር ይችል ይሆናል፡፡ እነዚህ ወገኖች በሥልጣን አራራ የሚታሙና የሚወቀሱም በመሆናቸው ለወያኔ የተወሰነ እፎይታ ለመስጠት በመናጆነት ሊያገለግሉ ቢሞክሩ አይገርምም – ጊዜና ዕድል ከገጠማቸው ሊያውም፡፡
  4. በምንም መንገድ ወያኔ በምርጫ አይወድቅም፡፡ ይህ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ምርጫን በግልጽና በማንአለብኝነት በማጭበርበርና ኮረጆን በመገልበጥ የሚታወቁትን ወያኔዎችን በምርጫ አሸንፌ ሥልጣን እረከባለሁ ማለት ከጅብ መንጋጋ ሥጋ ለመቀማት እንደመሞከር ያለ ቂልነት ነው፡፡ በፍጹም አይታሰብም፡፡
  5. በምንም መንገድ በምዕራባውያን ተፅዕኖ አይወድቅም፡፡ ሞልቃቃ ልጃቸው ስለሆነ በጠራራ ፀሐይ ሚሊዮኖችን ቢጨፈጭፍና የዘር ማጥፋት ወንጀል ቢፈጽምም በሞራል ከማበረታታትና የገንዘብ ድጋፍ ከመለገስ በስተቀር ፊቱን የሚያዞርበት አንድም ምዕራባዊ ሀገር የለም፡፡ ምክንያቱም ከፍ ሲል ለመጥቀስ እንደተሞከረው የኢትዮጵያ ጥፋትና ውድመት የተቀነባበረው በነዚህ ልዝብ ሰይጣናት የምዕራቡ ዓለም የደኅንነት ተቋማትና በዐረቦችም ጭምር የወልና የተናጠል ድጋፍ ነውና፡፡
  6. በምንም መንገድ እዚያና እዚህ በሚደረግ ያልተቀናጀ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ወያኔ አይወድቅም፡፡ በዘርና በጎሣ እንዲሁም በሃይማኖት በተከፋፈለ ሕዝባዊ ዐመፅ ወይም የእምቢተኝነት ንቅናቄ ወያኔ ይወድቃል ማለት ዘበት ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ነገር ለወያኔ ሥራ ያበዛበት እንደሆነ እንጂ፣ የመቆያ ሥልቶችን እንዲያሰላስል ዕድል ይሰጠው እንደሆነ እንጂ፣ ትንሽ እንዲጨነቅ ያስገድደው እንደሆነ እንጂ ከአራት ኪሎ አያስወጣውም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የተነጣጠለ ትግል ለአደጋና ዕልቂት የሚጋብዝ እንጂ ውጤት የለውም፡፡
  7. በምንም መንገድ በጋዜጣዊ መግለጫና በፉከራ አይወድቅም፡፡ ወያኔዎች ምሥጥ ናቸው፡፡ ዕድሜ ለላኪዎቻቸው የትም ሆነህ ብትቃወማቸው ክንዳቸው ረጂም ነው፤ ባለህበት ይመጡልሃል፡፡ አንተን የመሰለ ሰው አስርገው ይልኩብሃል፡፡ እናም እንኳንስ በጋዜጣዊ መግለጫና በፖለቲካዊ ጫጫታ ይቅርና በተደራጀ ጦርም እነሱን ማሸነፍ አስቸጋሪ ነው፤ ጨርሶ አይቻልም እያልኩ ግን አይደለም፡፡ ገንዘባቸው፣ ስለላቸው፣በአባቶቻቸው የሚደረግላቸው የመረጃና የበጀት ድጋፍ፣ በጥቅም በዘርና በቋንቋ ሰውን መከፋፈላቸው፣ እኛን የሚመስለው የሰውነትና የቋንቋ እንዲሁም ሌላው ቅርጻቸው የኛን ትግል እጅግ ከባድና ውስብስብ ያደርገዋል፡፡ በዚያ ላይ ብዙ ተቃዋሚዎቻቸው ወያኔዎችን ይንቃሉ፡፡ እንደውነቱ ከሆነ በዋናነት ወያኔን የጠቀመው የነሱ ሸረኝነትና የኛ እነሱን መናቅ ነው፡፡ እነሱ እያደቡ ዕቅዳችንን ሁሉ ሲያከሽፉ እኛ ደግሞ ስንፎክርና በመግለጫ “ድባቅ ስንመታቸው” ይሄውና ሩብ ምዕተ ዓመት ዘለቅን – ሁነኛ የማስወገጃ ሥልቱን በቶሎ ካልነቃንበት ደግሞ ምዕተ ዓመቱን ይደፍናሉ፡፡ አሁን አሁን ግን ሕዝቡ ቀደመና መቆሚያ መቀመጫ እያሳጣቸው ይገኛል፡፡ የነሱ ተንኮል ማርከሻ ይህ ዓይነቱ መነሻው እንጂ መድረሻው በውል የማይታወቅ ሕዝባዊ ቁጣ ነው፡፡ ብልህ ሰው ታዲያ ያስፈልገናል፡፡ ይህን ሕዝባዊ እምቢተኝነት ወያኔዎች ብቻ ሣይሆኑ አለቆቻቸውም ይፈሩታል፡፡ ለምን ቢባል የሕዝብ ዐመፅ የት ጀምሮ የት እንደሚያልቅ አይታወቅም፡፡ የወያኔ ጌቶች ወያኔንና መሰል አሸባሪ ድርጅቶችን ጠፍጥፈው ሲሰሩ በርቀት መቆጣጠሪያ ሳይቀር እየተከታተሉ የሚያሸክሟቸውን ተልእኮ ተፈጻሚነት ያረጋግጣሉ፡፡ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ግን ከነሱ ዓላማና ፍላጎት ሊወጣ የሚችልበት አጋጣሚ ብዙ ስለሆነ ይፈሩታል፤ ፊት ለፊት ሊጋፈጡትም ብዙውን ጊዜ አይደፍሩም፡፡ ስለዚህ ይህን የትል ዓይነት ገፋ አድርጎ መቀጠል ተገቢ ነው፡፡
  8. በምንም መንገድ በስደተኞች ብዛትና ሀገርን ለወያኔ ለቅ በመሄድ ወያኔ አይወድቅም፡፡ ይህ ዓይነቱ ነገር ሳይዋጉ እጅን እንደመስጠት ነውና በሀገር ውስጥ ሆኖ መታገል አማራጭ የለውም፡፡
  9. በምንም መንገድ በማዕቀብና ዕቃና አገልግሎት ከሕወሓት ባለመግዛት ወያኔ አይወድቅም፡፡ ምክንያቱም በቂ የሀብት ክምችት አላቸው፤ ሁሉ በጃቸው ሁሉ በደጃቸው – ምን ሲጎድልባቸው፡፡ ሕወሓት ሀገሪቱን ላለፉት 25 ዓመታትና ከዚያም በላይ ለሚቆጠር ጊዜ በብቸኝነት ሲበዘብዝ በመክረሙ የገንዘብም ሆነ የማቴሪያል ችግር ሳይኖርበት ብዙ ዓመታትን መዋጋት የሚስችለው አቅም አጎልብቷል፡፡ ስለዚህ ከነሱ ዕቃ ባለመግዛት የምንጎዳቸው ነገር የለም፡፡
  10. በምንም መንገድ በፈቃዱ አይለቅም፡፡ ብሔራዊ ስሜት ቀርቶ የሰውነት ደረጃም የሌላቸው የለየላቸው ዕብዶችና ሰካራሞች በመሆናቸው የሀገሪቱና የሕዝቧ ችግር ገብቷቸው ሥልጣናቸውን ለሽግግርም ይሁን ለቋሚ የሕዝብ ተመራጭ መንግሥት ሊያስረክቡ አይችሉም፡፡ ትግራይንና የትግራይን ሕዝብ በሆነ ኮሮጆ ውስጥ ይዘህ “ይህን ኮሮጆ እሳት ውስጥ ከምጨምረውና ሥልጣናችሁን ከምትለቁ የትኛውን ትመርጣላችሁ?” ብለህ ብትጠይቃቸው ወያኔዎች ሥልጣናቸውን እንደሚያስቀድሙ ግልጽ ነው፡፡ ትግራይንና ተጋሩን ይቅርና በሚስትና በልጆቻቸው ሳይቀር ቁማር የሚጫወቱ የብዔል ዘቡል ደቀ መዛሙርት ናቸው፡፡ የሚገርም ተፈጥሮ እኮ ነው ያላቸው!

 

ስለዚህ መፍትሔው ምንድን ነው ቢባል መልሱ በበኩሌ እንዲህ ይመስለኛል፡፡

 

ሁሉም ከተሞችና የገጠር ቀበሌዎች በአንድ ወቅት ተባብረው በመነሣት በየአካባቢያቸው የሚመጣውን የወያኔ ጦር ቢቻል መማረክና ማስተማር፣ ያ ባይቻል አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ በቁጥጥር ሥር ማዋልና ለፍርድ ማቅረብ፡፡ ዕቃና ንብረት እየዘረፉ የሚያሸሹባቸውን መንገዶች ሁሉ መዝጋት፤ የጎበዝ አለቃ እየመረጡ ትግሉን በአንድ ጊዜ በሁሉም ሥፍራ ማጧጧፍ፡፡ የወያኔ ወታደራዊ ክንድ ከተመታ፣ በተለይም አጋዚ የሚባለው የሰይጣን መንጋ ከተበተነ ሕወሓት ምንም አቅም አይኖረውምና በፍጥነት ይፍረከረካል፡፡ ያኔ ከያካባቢው የሕዝብ ተወካዮች ተመርጠው ትልቅ ሀገራዊ ስብሰባ በማካሄድ ከታዋቂ ጤናማ ፖለቲከኞችና ታዋቂ ግለሰቦች እንዲሁም የሕዝብ እምነት ከሚጣልባቸው ተቃዋሚዎች የሚውጣጡ የአደራ መንግሥት ማቋቋም፡፡ ያ የዐደራ መንግሥት ለሁለት ዓመታት ያህል ሀገሪቱን ካረጋጋ በኋላ በእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት አዲስና ለሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል የሚያለግል ዴሞክራሲያዊ መንግሥት መመሥረት፡፡ ስንታገል ደግሞ በአንድነት እንጂ ዘርና ጎሣ፣ ሃይማኖትና ክልል ለይተን መሆን የለበትም፡፡ እንደዚያ ካደረግን የወያኔን ፈለግ እንደመከተል ያለ ከንቱነት ነው፡፡ አሮጌው ወይን በአዲስ አቅማዳ ከተገለበጠ ጥፋትን በጥፋት መተካት ነውና ካለፈ ጠመዝማዛ ሕይወታችን መማር አለብን፡፡ ስለዚህ ትግሬን ከዐማራ፣ ኦሮሞን ከሶማሌ፣ ከምባታን ከአፋር … አንዱ ከሌላው ሳይለያይ የአንዲት ሉዓላዊት ሀገር ሕዝብ ባንድ ልብና ባንድ መንፈስ መታገል ይኖርበታል፡፡ ወያኔዎች በተለይ ትግሬን ከሌላው ለመለየትና በሌሎች እንዲጎዳ በማድረግ ከነሱ ጋር ለመለጠፍ የሚያካሂዱትን የቀቢፀ ተስፋ ሸርና ተንኮል ነቅተን መጠበቅ አለብን፡፡ የወያኔን ሤራ በንቃት መከታተልና የእሳት ቃጠሏቸውን ሁሉ ሳይቀር እየተከታተልን ማጋለጥ አለብን፤ ሆን ብለው የሚጭሯቸውን ግጭቶች እየተከታተልን እውነቱን በወቅቱና አደጋ ሳያስከትሉ ይፋ ማድረግ አለብን፡፡ ሟች ይዞ ይሞታልና እነሱ ሥልጣናቸውንና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የማያደርጉት ነገር አይኖርም፡፡ እኛን ለመለያየትም የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡ መለያየትን ደግሞ እስኪያንገሸግሸን አየነው፤ ክፉኛ ጎዳን እንጂ አልጠቀመንም፡፡ መኖር ከፈልግን እንግዲህ ማድረግ ያለብን እንደዚህ ነው፡፡ ሁሌ መሞኘት የለብንም፡፡ በመሠረቱ ብልጥ ከአንዴ በላይ መብለጥ አልነበረበትም፡፡ እኛ ግን የሆንነውን ሳናውቀው ዕድሜ ልካችንን በነዚህ ሰይጣኖች ስንታለልና ስንበለጥ ኖርን፡፡

እንጂ እንዳሁኑ አካሄዳችን ከሆነ ሶማሊያና ሦርያ በስንት ጣማቸው የሚያስብል አስቀያሚ ሁኔታ እንደሚፈጠር በጣም ግልጽ ነው፤ የሚደርስልን ደግሞ እንደሌለ መረዳት ይገባል፡፡ ወያኔዎች አያያዛቸው “የምፅዓት ቀን ለምን ዘገዬ?” እያሉ ለአባታቸው ለዲያቢሎስ ከፍተኛ ተማፅኖ በማቅረብ ላይ የሚገኙ ይመስሉኛል፡፡ የታወከን ሀገር በብልሃትና በዘዴ እንደማረጋጋት ቦሃ ላይ ቆረቆር እንዲሉ በሰላም በዓልን በሚያከብር በሚሊኖች የሚቆጠር ሕዝብ ላይ ከመሬትና ከሰማይ ጥይት ማዝነብ በየትኛውም ሥሌት ትርጉም የለውም፡፡ እነዚህ ድፍን ቅሎች የጥጋብ ሞራ ሁለመናቸውን ስለጋረደው የሚያደርጉት ነገር ምን ሊያስከትል እንደሚችል ማሰብ አልቻሉም፤ ተፈጥሯቸው ሁሌም በተቃርኖ የተሞላ ነው – “እንብላ” ሲሏቸው “እንተኛ” ዓይነት፡፡ ገና ለገና የላኳቸው የጥፋት ኃይሎች በሁሉም ረገድ አይዟችሁ ስላሏቸው ብቻ ምድራችን ዐይታውም ሆነ ሰምታው የማታውቀውን የክፋት ሥራ በኢትዮጵያውያን ላይ ይፈጽማሉ፡፡ በመጨረሻው የሚያስደስተው ነገር ግና የሠሯትን ሁሉ አንድ ባንድና በዕጥፍ ድርብ ያወራርዷታል፤ ያም ቀን ደርሷል፡፡

እንደማሣረጊያ – ያገሬ ባላገር ምን አለ?

 

 

የማን ቤት ፈርሶ የማን ሊበጅ፤

ያወሬ መፈንጫ ይሆናል እንጂ፡፡

 

እባክሽ እናቴ ውለጅ መንታ መንታ፤

ቀኝ እጄ ሲመክት ግራ’ጄ ተመታ፡፡

 

እዚያ ማዶ ሆኖ አንድ ሰው ተጣራ፤

እዚህ ማዶ ሆኖ አንድ ሰው ወይ አለው፤

ጎበዝ ተጠራጠር ይህ ነገር ለኛ ነው፡፡

 


“ለማን አቤት እላለሁ?” ወ/ሮ ታደሉ ተማም – SBS Radio

$
0
0

ወ/ሮ ታደሉ ተማም፤ ደምቢዶሎ ላይ ልጃቸው ኃይሉ ኤፍሬም፤ በመንግሥት ታጣቂ ወታደሮች ጥይት የተገደለባቸው እናት ናቸው። ለሟች ልጃቸው ዳኝነት አላገኘሁም፤ ግና ፍትሕን “ከማን እጠይቃለሁ?” ይላሉ።

“ለማን አቤት እላለሁ?” ወ/ሮ ታደሉ ተማም –  SBS Radio

ምክር ይፈለግ!    [አስራት አብርሃም]

$
0
0

Asrat-Abereha2የሀገራችን ሁኔታ ከዕለት ወደ ዕለት እጅግ ወደ ባሰ ሁኔታ እየተንደረደረ ነው ያለው። ቁጭ ብለንም ልንመክርበት ይገባል። “ሰው ይሰብሰብ ምክር እንዲገኝ” የሚል የአበው አባባል አለ፤ አሁን ቁጭ ብለን መነጋገር አለብን። ከፊታችን ተደቅኖ ያለው አደጋ እንደሀገር መፍረስ እንደህዝብ መተላለቅ ነው። በዚህ ሁኔታ ከቀጠልን ህዝቡ ባልተደራጀ ሁኔታ ባዶ እጁ አደባባይ እንዲወጣ እየተደረገ የጥይት ራት ነው የሚሆነው፤ ለውጡ አይቀሬ ቢሆንም እንኳ በብዙ እልቂትና ደም መፋስስ ነው የሚሆነው። በመንግስትም በዚያ ወገንም ኃላፊነት የሚሰማው ወግን እያየን አይደለም። ስለዚህ ለእኔ የሚታየኝ ጉዳዩ ገለልተኛ በሆነ ሶስተኛ ወገን  መያዝ አለበት። ሁለቱም ወገኖች በገለልተኝነት ሊያደራድር፤ ሊያግባባ የሚችል ከሀገር ሽማግሌዎች፤ ከታዋቂ ግለሰቦችና ከኃይማኖት መሪዎች የተውጣጣ ሀገር አቀፍ ቡድን መቋቋም አለበት። ይሄ ቡድን የፖለቲካ ኃይሎች እንዲስማሙ ማድረግ እንጂ የስልጣን ፍላጎት ያለው ኃይል መሆን የለበትም፤ ይሄ የስልጣን ጉዳይ አይደለም፤ ሀገርና ህዝብ የማዳን ጉዳይ ነው። የዚህ ስብስብ ዋና ዓላማ የፖለቲካ ኃይሎች እንዲደራደሩ በማድረግ ተስማምተው ወደ ነፃና ገለልተኛ የሆነ ምርጫ የሚገቡበት መንገድ መፍጠር ነው። በባለፈው ፅሁፌ ለመግለፅ እንደሞከርኩት ድርድሩ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ስለሚደረግበት ሁኔታ፤ የህገመንግስቱ ጉዳይ፤ የፌደራል ስርዓቱ፤ ወንጀል የሌለባቸው የኢህአዴግ ባለስልጠናት በሰላም የመኖር ዋስትና የማግኘት ጉዳይ፤ በአንዳንድ አከባቢዎች ያሉትን ግጭቶች ዘላቂ መፍትሄ የሚያገኙበት ጉዳይ፤ በእነዚህና በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ ተነጋግሮ ስምምነት ላይ የሚደርስ ውይይት ያስፈልጋል። በእነዚህ ጉዳዮች ላይ መግባባት ከተቻለ ህዝባዊ ምርጫ ተደርጎ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ባገኙት የህዝብ ድምፅ መሰረት ጥምር መንግስት መመስረት ይችላሉ። አሁን ባለው ሁኔታ በሀገራችን አንድ ወጥ የሆነ ኃይል መንግስት የመሆን እድል የሚያገኝ አይመስለኝም።

ጎን ለጎን ደግሞ በተቃዋሚው ጎራ ያለውን መከፋፈልና የዓላማ መለያየት ወደ አንድ ማምጣትና ማስታረቅ ያስፈልጋል። ከመንግስት ጋር መደራደር የሚችሉ የፖለቲካ ኃይሎችም ተለይተው መታወቅ አለባቸው፤ በኦሮሚያ ያለው እንቅስቃሴ በሚመሩት የፖለቲካ ኃይሎች መግባባት ያለ ይመስላል፤ የኦሮሞ ፈርስት መሪዎች በሀገር ቤት ኦፌኮ ወኪላቸው እንደሆነ ከአሁን በፊት ተነግሯል፤ በእነ ሌንጮ ለታ የሚመራው ኦዴግን በውጭ አለ፤ በእነዚህ መሀል ብዙም መሰረታዊ ልዩነት አለ ብየ አላስብም። በመሰረቱ የኦሮሞ ህዝብ እያነሳው ያለው ጥያቄ ፍትሃዊ ነው፤ መልስ ማግኘት መቻል አለበት፤ የኦሮሞ ህዝብ በመሬቱ ተጠቃሚ መሆን አለበት፤ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብቱ ሊጠበቅለት ይገባል፤ ለኦሮሞ ህዝብ የሚመጥን ስልጣን በፌደራል መንግስት መያዝ መቻል አለበት፤ በዚህ ሀገር ብዙህነት ትርጉም እንዲኖረው ከተፈለገ ኦሮሞኛ ሁለተኛ የፌደራል መንግስት የስራ ቋንቋ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል።

በአማራ አከባቢ ያለው ጥያቄም እንደዚሁ ፍትሃዊና ተገቢ ጥያቄ ነው፤ የአማራ ህዝብ ካለፉት ስርዓቶች ጋር በማያያዝ ብዙ በደል ደርሶበታል፤ ይሄ መሆን ያልነበረበት ነው። ስለዚህ ጥቅሙንና ህልውናውን ለማስጠበቅ የሚያደርገው ትግል መደገፍ ነው ያለበት። በእርግጥ የህዝቡን ጥያቄ ለአንዳንድ ፅንፈኛ ኃይሎች መጠቀሚያ መሆኑ አልቀረም። እነዚህ ኃይሎች የአጥንቱ ክፋይ፤ የደሙ ቁራጭ ከሆነው የትግራይ ህዝብ ጋር ዘላቂ ጠብ ውስጥ ነው እየከተቱት ያሉት። ይህን አካሄድ ህወሀት የጀመረው ቢሆንም፤ በአሁኑ ዘመን በተመሳሳይ የጥላቻ ፖለቲካ የሚሄዱ ቡድኖች መፈጠራቸው አሳዛኝ ነው። የችግሩ ምንጭም የሚመስለኝ ትግሉን የሚመጥን አመራርና ድርጅት ባለመፈጠሩ ተገቢ ባልሆኑ ኃይሎች ስር በመውደቁ ነው የሚመስለኝ። በአማራ አከባቢ ያለው ህዝባዊ የትግል እንቅስቃሴ   የሚመጥን ድርጅት ያስፈልገዋል። የአማራ ልሂቃን በብሄር መደራጀት የሚፈልጉ በብሄር ቢደራጁ፤ በሀገር አቅፍ በመደራጀት የሚፈልጉም እንደዚሁ በፍላጎታቸው መደራጀት አለባቸው።

የአማራ ልሂቃን እንደሚታወቀው ከአሁን በፊት በአገር አቀፍ ደረጃ ነው መታገል ይመርጡ የነበረው፤ አሁንም ብዙዎቹ በዚሁ መንገድ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋራ በአንድነት መታገሉ የሚመርጡ ይመስለኛል። እንደማነኛውም ህዝብ በውስጡ የሚኖረው ሰው ፍላጎቱና አስተሳሰቡ ስለሚለያይ የሚያሰባስበው አጀንዳም እንደዚሁ የተለያየ ነው የሚሆነው። ለምሳሌ ሸዋውና በተለያየ ሀገሪቱ አከባቢ የሚኖረው የአማራ ተወላጅ ሰፊዋን ኢትዮጵያ ትቶ የአንዲት ወረዳ፣ የወልቃይት ጉዳይ የሚመስጠው አጀንዳ ላይሆን ይችላል፤ የወሎውም፣ የጎጃሙም እንደዚሁ። በነገራችን ላይ የጎንደሩ እንቅስቃሴም ቢሆን የወልቃይት ጉዳይ ብቻ ከሆነ አጀንዳው የትግሉ ዓላማ የሚያሳንሰው ነው የሚሆነው፤ ሲጀምር የወልቃይት ጉዳይ የወልቃይቶች ነው፤ በጎንደር የሚኖር አማራም በአድዋ የሚኖር ትግሬም የሚያገባው ነገር የለም። ሁሉንም ዜጎች በእኩልነት የሚያይ መንግስት ሲመሰረት ኗሪው ህዝብ ነው ወዴት መካለለል እንዳለበት የሚወስነው። ስለዚህ የህዝቡ ውሳኔ ተግባራዊ በማድረግ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍትሄ የሚሰጠው ጉዳይ ነው የሚሆነው። ከዚያ በኋላ ወልቃይት ወደ ጎንደር ይካለል ወደ ትግራይ ይካለል እንደጥንቱ አማርኛ እና ትግርኛ የሚናገሩ የአከባቢው ዜጎች በሰላም የሚኖሩበት ምድር ይሆናል።

በመሰረቱ የዚህ ዘመን ትውልድ ጥያቄ መሆን ያለበት ለአንድ ትልቅ ሀገር የሚመጥን፤ ሰፊውን ህዝብ የሚያሳትፍ ትልቅ አጀንዳ ቀርፆ ለታሪክም ሀገርም የሚተርፍ ታሪክ መስራት ነው። በኢትዮጵያ ያለው መሰረታዊ ጥያቄ እክልነትና ድሞክራሲ ጥያቄ ነው፤ ዓለሙም ዘመኑም የሚዋጀው ይሄንኑ ነው።  ከዚህ ወጪ ያለው መንገድ ሁሉ ኢትዮጵያ ወደ ዲሞከራሲ ሊወሰዳት አይችልም፤ በተቃራኒው ሊበታትናት፤ ሊያጠፋት ይቻላል። ይሄ ከተከሰተ ደግሞ አንዱ ብቻ ተጎጂ ሌላው ደግሞ ተጠቃሚ የሚሆንበት እድል ፈፅሞ አይኖርም። ሁሉም ነው ተጎጂ ሚሆነው።

 

የቢሸፍቱው አልቂት፤ –ይገረም አለሙ

$
0
0

161or-23

ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረውን የኢሬቻ በአል ለማክበር ኢትጵያውያን በቢሸፍቱ/.አዳማ ከተማ የከተቱት ቅድሜ መስከረም 21/ 2009 ዓም ጀምሮ ሲሆን  በማግስቱ እሁድ  ረፋዱ ላይ  በምስል ተደግፎ በማህበራዊ መገናኛ  የተሰራጨው ዜና ፈጽሞ ያልተጠበቀ ብቻ ሳይሆን ሊገመት የማይችል ነበር፡፡ በአንድ ጣራ ስር ሆነን መርዶውን ከሰማነው መካከል እድሜአቸው ስድሳውን የዘለለ አንዲት እናት ለስንቱ አናልቅስ ብለው  አንባቸውን አዘነቡት፡፡ ሌሎቻንም በየውስጣችን አለቀስን፡፡ ለደቂቃዎች ቤቱ ጸጥ ረጭ አለ፡፡ሁሉም በየራሱ ስሜት ውስጥ ሰምጦ የሚናገር ጠፋ፡፡  ዝምታው የተሰበረው ሆራ ሀይቅ ዳር የተሰበሰበ ህዝብ አይደለም ሰላማዊ ተቃውሞ ማሰማት ድንጋይ ቢወረውር ምን ጉዳት አንዳያደርስ ነው በአስለቃሽ ጭስ የሚባረረው በጥይት የሚደበደበው በሚል መልስ የለሽ ጥያቄ ነበር፡፡

ይህም ይረሳ ይሆን!

የቢሸፍቱው አልቂት በአይነቱም በብዛቱም የተለየ ከመሆኑ በቀር ለወያኔ ግድያ፣ ለእኛም ሰምቶ አይቶ እርር ድብን ማለት አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ባለፉት ሀያ አምስት አመታት በእምነት ቦታዎች፣ በት/ት ተቋማት፣ በአደባባይ፣ በእስር ቤቶች፣ ግድያዎች ተፈጽመዋል፡፡ ድርጊቱ በተፈጸመ እለትና ማግስት ከወያኔ በተቃራኒ ያለን ሁሉ እርር ድብን እያልን እንቃጠላለን፣ በምናገኘው የመገናኛ መንገድ ሁሉ ወያኔን እያወገዝን በቃ ከዚህ በኋላ እያለን አያዛትን እየፎከርን እንዲህ መሆን አለበት፣ ይህ መደረግ አለበት እንላለን፡፡ ፖለቲከኞቻችንም በዚህ ቀን እንኳን ድምጻቸው እንዲሰማ ተቃውሞአቸው እንዲበረታ ተጠራርተው በጋራ መጮሁ አልሆንልህ እያላቸው ከየጎጆአቸው ሆነው የወረቀት መግለጫ ያወጣሉ ወይንም ጥቂት ጋዜጠኞችን በቢሮአቸው ጠርተው ውግዘት ተቃውሞአቸውን ያሰማሉ፡፡ በተለያየ የዓለም ክፍል በተለይ ደግሞ በሰሜን አሜሪካና በአውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ተጠራርተው ሰልፍ በመውጣት በአልህና በቁጣ ተቃውሞአቸውን ይገልጻሉ፡፡ ከዛ ከአንድ ሳምንት በኋላ ሁሉም ይረሳል፡፡ ያለግድያ መኖር የማይችለውና ለችግሮች ሁሉ መፍትሄ፣ ለጥያቄ ሁሉ መልስ ጠመንጃውን አድርጎ የሚያምነው በዚህም ሥልጣኑን ማቆየት የቻለው ወያኔ ውሎ አድሮ ሌላ ግድያ ይፈጽማል ሌላ እልቂት ያደርሳል፡፡ ያኔ አኛም  ያንን የተለመደ የአንድ ሳምንት ቁጭትና ጩኸት እናሰማና እንረሳዋለን፡፡ በእንዲህ ሁኔታ ዙሩ ቀጥሎ  የቂሊንጦው ፍጅት በተረሳ ማግስት የቢሸፍቱው እልቂት ተፈጸመ፡፡  ያው አንደተለመደው መርዶው ከተሰማበት ቅጽበት ጀምሮ የኢትዮጵያውያን ንዴት እልህ ቁጣ ውግዘት ፉከራ  ከያቅጣጫው እየተሰማ ነው፡ ይህም ከአንድ ሳምንት በኋላ ላለመረሳቱ ግን ርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡

ለስንቱ እናልቅስ

ከላይ የገለጽኳቸው አናት በየግዜው የተፈጸሙና ያስለቀሱዋቸውን ድርጊቶች ባለመርሳታቸው ነው ለስንቱ እናልቅስ ያሉት፡፡ ፖለቲከኞቻችን ግን አብዛኛዎቹ ትግሉን ሳይሆን ቤተ መንግስቱን ናፋቂዎቹ የእኝህን እናት ያህል እንኳን  ትናንትን ያስታውሳሉ ለማለት አልደፍርም፡፡ ያ ቢሆንና ያለፈውን እየረሱ  በአዲሱ የሚጩሁ ባይሆኑ ኖሮ ከአንግዲህ በህዝብ ላይ እልቂት ሲፈጸም መቆጣትና መግለጫ ማውጣት ሳይሆን ህዝቡን ከገዳዮች  መገላገል ነው ብለው ተጠራርተው መክረውና እቅድ አውጥተው መታገል በቻሉ ነበር፡፡

ወያኔ እልቂት የሚፈጽመው ጾታ እድሜ ብሄር ሳይመርጥ ለሥልጣኔ ያሰጋኛል ባለው ላይ ሁሉ  ነው፡፡  ከየትኛውም ብሄር ይሁን የትኛውንም ኃይማኖት ይከተል ሕዝብ ያስተባብራል ለወንበራችን ያሰጋል ተብሎ የተገመተ ማናቸውም ሰው እስር ወይንም ግድያ ይደገስለታል፡፡ እንዲህ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ እየገደለ የመጣና አሁንም እየገደለ ያለ ወደ ፊትም የሚቀጥል የጋራ ጠላትን መከላከልም ሆነ ማስወገድ የሚቻለው ድር ቢያብር አንበሳ ያስር ብሎ በአንድነት በመሰለፍ ቢሆንም ለዚህ መብቃት አልተቻለም፡፡

መተባበር ባለመቻሉ፤  ወያኔዎች እየገደሉ ይኖራሉ፡፡

ጋን በጠጠር ይደገፋል አንዲሉ ሁሉም ያለውን ትንሽም ይሁን ትልቅ አቅም አስተባብሮ በየግል አቋሙ ተከባብሮና የጋራ አጀንዳ ቀርጾ ለመታገል ፈቃደኛ ባለመሆኑ  በሁሉም ዘርፍ ደካማና አነስተኛ የሆነው የተቃውሞ ጎራ ወያኔን የሚገዳደር እቅም ሊፈጥር አልቻለም፡፡ የዚህ አብዩ ምክንያት  ተደጋግሞ እንደተነገረ እንደተጻፈው  ትናንሽ ዘውድ በኪሱ  ይዞ የሚዞረው መብዛቱ ነው፡፡ በሥልጣን ጥም የናወዙ ፖለቲከኞች  በህዝብ ላይ የሚፈጸመውን አልቂት እያዩ እንኳን ከዚህ በሽታቸው ለመገላገል ሲሞክሩ አይታዩም፡፡

አደረጃጀትን የትግል ስልትን ወዘተ  ምክንያት በማድረግ መለያየቱ በትንሹም ቢሆን ምክንያት ሊሰጠው ይችላል፡፡ በተመሳሳይ የትግል ስልት በአንድ ብሄር ስም አራት አምስት ድርጅት መመስረቱ ግን ለምን የሚያሰኝ ነው፡፡ በአንድ ብሄር ስም ተለያይቶ ድርጅት ከመሰረቱ በኋላ ደግሞ የሚታየው የመጀመሪያው ጥፋት፣ ርስ በርሳቸው አለመተባበራቸው ይህም ቢቀር አለመከባበራቸው ነው፡፡ አንተም በመንገድህ እኔም በመንገዴ ከመባባል ይልቅ  አንዱ የአንዱ አደናቃፊ መሆናቸው ደግሞ ሁለተኛው ጥፋት ሲሆን  ሶስተኛው ጥፋት በኢትዮጵያዊነት ተደራጅተው በሚታገሉት ላይ ላይ ቃታ ለመሳብም ሆነ ድንጋይ ለመወርወር አቅሙ ባይኖራቸውም የሚያካሂዱት የፖሮፓጋንዳ ዘመቻ  ነው፡፡ በዚህ መልኩ ወያኔን አንታገላለን እያሉ ለወያኔ  እድሜ መራዘም መስራት፡፤

መተባበር ያለመቻል ዋናው ችግር የሥልጣን ጉዳይ መሆኑ ከታወቀ ውሎ አድሯል፡፡ ግን ሁሉም ሊቀመንበር ወይም ፕሬዝዳንት የሚባልበትን ድርጅትና ሥልጣኑን እንደያዘ ሕዝብን ከእልቂት ለመታደግና በዘላቂነት ከወያኔ አገዛዝ ለመገላገል ብሎም በድል ማግስት ሊመሰረት ስለሚገባው ስርአት ምንነትን እንዴትነት ተነጋግሮ የጋራ መርሀ ግብር ዘርግቶ ከድል አስከ ሽግግር የሚያደርስ የዘመቻ እቅድ አውጥቶ መታገል ምን ይገዳል፡፡ የቢሸፍቱው አልቂት እንደተሰማ ሌሎቹ ቢቀሩ የኦሮሞ ስም ያያዙት ድርጅቶች ወዲያውኑ ተጠራርተው ሸንጎ ይቀመጣሉ፣ ከዚህ የባሰ ምን እስኪመጣ ነው የምንጠብቀው ተባብለው የየግል ጉዳያቸውን ጥለው አንድ ሆነው ለመውጣት ይመክራሉ ብየ ጠብቄ ነበር፡፡ ግና ምን ያደርጋል ፖለቲከኞቹ በህዝብ ላይ የሚፈጸመው እልቂት ለስንቱ እናልቅስ ያሉትን እናት ያህል እንኳን  የሚሰማቸው አልሆኑምና ዛሬም እዛው የትናንት ቦታቸው ላይ እንደቆሙ ናቸው፡፡

የቢሸፍቱውን እልቂት ማውገዝ ከስሜት በላይ መሆን አለበት፡፡

እልቂቱን ተከትሎ የሚሰማው ተቃውሞ ውግዘትና ፉከራ ስሜት ብቻ ከሆነ እንደስከዛሬው ሁሉ ከሳምንት በኋላ ይረሳል፡፡የለም ከዚህ በላይ ምን እስኪሆን እንጠብቃለን ከተባለ የሚነገረው የሚጻፈው ሁሉ የሚረሳ ሳይሆን  ወደ እምነት የሚሸጋገር ይሆንና የሚከተሉት ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡

የፖለቲካ ድርጅቶች፣

ኢትዮጵያ የብዙ ብሄረሰቦች  ሀገር እንደመሆኗ በኢትዮጵያዊነት መተባበር እንደማይቻል ከልማዳችን አይተነዋል፡፡ በዚህ ዙሪያ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ፈልጎ መፍትሄ አፈላልጎ ለመነሳት ደግሞ ግዜ የለም፡፡ አማራ ግን አንድ ነው፣ ኦሮሞም አንድ ነው፣   ሌሎችም አንደዚሁ፡፡ በመሆኑም የትግል ስትራቴጂ ልዩነት እስከሌለ ድረስ በአንድ ብሄር/ብሄረሰብ ስም አራት አምስት ደርጅት መመስረት  የግለሰቦች የግል ፍላጎት ከመሆን የዘለለ ምክንያት ሊቀርብለት አይችልም፡፡ የግለሰቦችን የሥልጣን ፍላጎት ለማርካት ተብሎ ህዝብን እየፈጀ ያለው ሥርዓት ለማስወገድ የሚደረገውን ትግል ማዳከም ደግሞ በምንም መመዘኛ ተቀባይነት የለውምና ለአንድ አማራ አንድ ፓርቲ ለአንድ ኦሮሞ አንድ ፓርቲ ወዘተ እንዲሆን ለማድረግ ግዜ ሳይሰጡ መስራት፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በርግጥ ለነጻነት የሚታገሉ ድርጅቶች በወያኔ መወገድና የትግሉ ውጤት ኢትዮጵያን ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚያበቃ በመሆኑ ላይ ተስማምተው አንዱ የሌላው አንቅፋት ሳይሆን እየተናበቡ በየሚያምኑበት መንገድ ትግሉን መቀጠል፡፡

የየፓርቲዎቹ አባላትና ደጋፊዎች፤

አባልነታችሁም ሆነ ድጋፊነታችሁ በስሜት ሳይሆን በእምነትና በእውነት ላይ የተመሰረተ ይሁን፡፡ እናም ድርጅታሁ ለነጻነት ትግሉ ምን አዎንታዊ ምን አሉታዊ አስተዋጽኦ እያበረከተ አንደሆነ ፈትሹ፡፡ በአንድ ብሔረሰብ ስም አራት አምስት ድርጅት ስለተመሰረተበት ምክንያትም መርምሩ፡፡ከዛም የዓላማና የትግል ስትራቴጂ ልዩነት የሌላቸው አንድ እንዲሆኑ፣አንድ መሆን የማይችሉት ደግሞ አንዱ ለሌላው እንቅፋት ሳይሆን ተደጋገፍውና ተከባብረው እንዲሰሩ አስገድዱ፡፡

ዲያስፖራው፤

እስከ ዛሬ ስር ሰዶ የነበረው ሆድና ጀርባ የመሆንና የጎሪጥ መተያየት ሀገር ቤት ሕዝቡ ባሳየው አንድነት ረገብ ያለ ቢሆንም ገና ይቀረዋል፡፡ እናም ጨርሶ ለማስወገድ ታሪክ እየመዘዙ መነታረኩ፣ ሰልፍ ላይ የሚያዙ ሰንደቅ ዓላማዎችና የሚስተጋቡ መፈክሮች ምክንያት እየሆኑ መዋረፉ ተለያይቶ ሰልፍ መውጣትም ሆነ ማዶና ማዶ ሆኖ የማይደምቅ ጩኸት ማሰማት ከእንግዲህ መኖር የለበትም፡፡ የህዝብ ልጆች ቢሸፍቱ ላይ  በደማቸው ያቀለሙት አንድነት ከእንግዲህ በምንም በማንም አይቀለበስም፡፡ ስለሆነም የዲያስፖራው የከእንግዲህ ተግባር አንድ የሚያደርጉንን ጉዳዮች ውኃ እያጠጣን ማሳደግ እንጂ የሚያለያዩንን በመፈለግ መድክም መሆን የለበትም፡፡

ወያኔ በሥልጣን ላይ እስካለ ግድያ አይቀርም፡፡ እኛም በመጣንበት የሀያ አምስት አመት መንገድ መጓዛችንን ከቀጠልን ግድያን ማስቆምም ሆነ ከወያኔ መገላገል አይቻለንም፡፡ ስለሆነም መንገዳችንም ሆነ አካሄዳችን፣ ስራችንም ሆነ አስተሳሰባችን መለወጥ አለበት፡፡ ለለውጥ ለመብቃት ደግሞ ከተቻለ አንድ መሆን፣ካልተቻለም መደጋገፍና መተባበር፣ ይህም ካልተቻለ በአንድ ጎራ ተሰልፎ ርስ በርስ ከመጠቃቃትና አንዱ ለሌላው እንቅፋት ከመሆን መታቀብ ያስፈልጋል፡፡ ወያኔን ያወገዘ ሁሉ ተቀዋሚ ድርጅት የፈጠረ ሁሉ የነጻነት ታጋይ አይደለምና የነጻነት ትግሉ እንዳይጉዳ እውነተኛ ታጋዮች ለአጉል መስዋዕትነት አንዳይዳረጉ ስንዴውን ከእንክርዳድ ለይቶ ማወቅና መጠንቀቅም አስፈላጊ ነው፡፡

ተቀዋሚው ማድረግ ያለበትን ባለማድረግ ከዚህ በኋላ ወያኔ ጉልበት ኖሮትም ይሁን በአልሞት ባይ ተጋዳይነት በህዝብ ላይ እልቂት ቢፈጽም ከወያ ባልተናነሰ ተጠያቂ ይሆ

ሕወሓት የማይወድቅባቸው የትግል ሥልቶች –ነፃነት ዘለቀ

$
0
0

 

tplf-ethiopian-leadersባሳለፍነው እሁድ በደብረ ዘይት የእሬቻ በዓል አከባበር ላይ በአጋዚ የወያኔ ቅልብ ጦር ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችንን ነፍስ እግዚአብሔር ይማርልን፤ ከዚህች ዘግናኝ ቀን በፊትም ሆነ በኋላ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በዚሁ የወያኔ ጦር ያለቁና ወደፊትም የሚያልቁ ወንድም እህቶቻችንንና ልጆቻችንን መንግሥተ ሰማይን ያውርስልን፡፡ ፈጣሪ የነሱን መስዋዕትነት እንደአቤል ንጹሕ ደም ቆጥሮልን የነፃነታችንን ቀን ያፋጥንልን፡፡ የቤተሰባቸውንም ሆነ የሁላችንን የተሰበረ ልብ ይጠግን፡፡ አሁንስ እጅግ በጣም እየተጎዳን ነው፡፡

ወያኔ በምን እንደማይወድቅ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለይ ቁልጭ ብሎ እየታየ ነው፡፡

  1. በምንም ዓይነት መንገድ ወያኔ በጩኸት አይወድቅም፡፡ እርግጥ ነው ሰሚ ከተገኘ ጩኸት ብሶትንና ግፍን ለመግለጽ ይጠቅማል፡፡ በኛ የእስካሁኑ ሁኔታ ግን ሰሚ የለንምና ጩኸታችን አልጠቀመንም፡፡ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተሰማራው ኃይል ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለው በመሆኑ “ዐውቆ የተደበቀ ቢጠሩት አይሰማም” እንዲሉ ሆኖ ለማንም ብንጮኽ ሰሚ አናገኝምና ትርፉ ድካምና ጩኸትን በከንቱ ማባከን ነው፡፡ የኛ ደም ውኃ ይመስል በየቀኑ እንደጎርፍ እየፈሰሰ በዋና ዋና የሚዲያ አካላት በስፋትና በጥልቀት የማይዘገብበት ምክንያት ሌላ ሣይሆን ጥፋትና ውድመታችን የታዘዘው ዓለምን ከተቆጣጠረው ዋናው የአጋንንት ኃይል በመሆኑ ነው፡፡ እንጂ አንድ የስዊድን ወይም የእንግሊዝ ዜጋ የወያኔ ወንድሞች ማለትም አይሲሶች ቢገድሉት ኖሮ የሣምንታት የዜና መክፈቻቸው በሆነ ነበር፡፡ እነዚህ ጉደኞች ከአምስት መቶ ሕዝብ በላይ በጠራራ ፀሐይ የታጨደበትን አሳዛኝ ዕልቂት በመኪና ተገጭቶ የሞተ አንድ የአውሮፓ ውሻ ያህል እንኳን አልቆጠሩትም፡፡ ለይስሙላ ግን “In God we trust.” እያሉ በፈጣሪ ኅልውና ሲያላግጡ አያፍሩም፤ የሥራቸውን ይስጣቸው እንጂ ምን ይባላል፡፡ ለነገሩ ከሞላ ጎደል ሁሉም የዘሩትን እያጨዱ ነው፤ ወደፊትም ይህ የፈጣሪ ፍርድ በነሱም ላይ አይቀርም፡፡ ማንም የሥራውን ያገኛል፡፡
  2. በምንም መንገድ በሰላማዊ ሰልፍ ወያኔ አይወድቅም፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ ጊዜ ማባከኛ ነው፡፡ 25 ዓመት ተሰልፈን ያመጣነው ለውጥ የለም፡፡ “ደግሞ ጀመራቸው!” ከማስባልና ለዘመናት የተተከለን ጠባይ ከማሳየት ውጪ ምንም አልፈየደም፡፡ ሰልፍ የሚሠራበት ሀገር አለ፤ ለኛ ግን አይሠራም፡፡
  3. በምንም መንገድ ሕወሓት በድርድር አይወድቅም፡፡ ወያኔ ዘንድ ሰጥቶ መቀበል ብሎ ነገር የለም፡፡ የወያኔ ጠባይ ጨርሶ ማጣት ወይም ጠቅልሎ መውሰድ እንጂ የቁጥ ቁጥ ነገር አይዋጥላቸውም፡፡ አንድም የሕዝብ ጥያቄ በአወንታ መልሰው የማያውቁት ጥያቄን በአግባብ መመለስን እንደመሸነፍ ስለሚቆጥሩት ነው፡፡ ለምሣሌ ሁለትና ሁለት ሲደመር ስንት እንደሚሆን ወያኔዎችን ብትጠይቋቸው ሦስት ወይም አምስት ይሉ ይሆናል እንጂ እቅጩን “አራት ነው” አይሉም፡፡ ምክንያቱም በትክክል መመለስ ጠያቂን እንደሚያስደስት ስለሚያምኑና ያንንም ለነሱ እንደሽንፈት ስለሚቆጥሩት ነገረ ሥራቸው ሁሉ ጠማማ ነው፡፡ ይህ ጠባያቸው የሚያሳየን አእምሯቸው ያልሠለጠነና በዕድገቱ ከእንስሳትም በታች መሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም ከወያኔ ጋር ተደራድሬ ሀገሬን ነፃ አወጣለሁ የሚል አካል ቢኖር ራሱም ያበደ ነው፡፡ ወይም ወያኔ ጊዜ ገዝቶ ከጭንቀቱ እስኪገላገልና አንዳች ዘዴ ፈልጎ እስኪያጠፋው በመሣሪያነት ሊያገለግል የወደደ ጊዜያዊ የሥልጣን ፍርፋሪ የሚፈልግ መሆን አለበት፡፡ እርግጥ ነው ወያኔ በጣም ሲጨነቅ ከነልደቱ አያሌውና ከነፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ዓይነቶቹ የሥልጣን ጥመኞች ጋር ሊደራደር ይችል ይሆናል፡፡ እነዚህ ወገኖች በሥልጣን አራራ ሰለባነት የሚታሙና በኅብረተሰቡ ዘንድ በብርቱ የሚወቀሱም በመሆናቸው ለወያኔ የተወሰነ እፎይታ ለመስጠት በመናጆነት ሊያገለግሉ ቢሞክሩ አይገርምም – ጊዜና ዕድል ከገጠማቸው ሊያውም፡፡
  4. በምንም መንገድ ወያኔ በምርጫ አይወድቅም፡፡ ይህ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ምርጫን በማንአለብኝነትና በጀብደኝነት በማጭበርበርና ኮረጆን በመገልበጥ የሚታወቁ ወያኔዎችን በምርጫ አሸንፌ ሥልጣን እረከባለሁ ማለት ከጅብ መንጋጋ ሥጋ ለመቀማት እንደመሞከር ያለ ቂልነት ነው፡፡ ይህ በፍጹም አይታሰብም፡፡
  5. በምንም መንገድ ሕወሓት በምዕራባውያን ተፅዕኖ አይወድቅም፡፡ ሞልቃቃ ልጃቸው ስለሆነ ሰሞኑን በደብረ ዘይትና በሌሎችም አካባቢዎች እየታዘብነው እንደምንገኘው በጠራራ ፀሐይ ሚሊዮኖችን እንደዐይጥ ቢጨፈጭፍና የዘር ማጥፋት ወንጀል ቢፈጽምም በሞራል ከማበረታታትና የገንዘብ ድጋፍ ከመለገስ ባለፈ ፊቱን የሚያዞርበት አንድም ምዕራባዊ ሀገር አይኖርም፡፡ ምክንያቱም ከፍ ሲል ለመጥቀስ እንደተሞከረው የኢትዮጵያ ጥፋትና ውድመት የተቀነባበረው በነዚህ ልዝብ ሰይጣናት የምዕራቡ ዓለም የደኅንነት ተቋማትና በዐረቦችም ጭምር የወልና የተናጠል ድጋፍ ነውና፡፡
  6. በምንም መንገድ እዚያና እዚህ በሚደረግ ያልተቀናጀ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ወያኔ አይወድቅም፡፡ በዘርና በጎሣ እንዲሁም በሃይማኖት በተከፋፈለ ሕዝባዊ ዐመፅ ወይም የእምቢተኝነት ንቅናቄ ወያኔ ይወድቃል ብሎ ማሰብ የወያኔን ተፈጥሯዊ ጠባይ ካለመረዳት የሚመነጭ ሞኝነት ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ነገር ለወያኔ ሥራ ያበዛበት እንደሆነ እንጂ፣ የመቆያ ሥልቶችን እንዲያሰላስል ዕድል ይሰጠው እንደሆነ እንጂ፣ ከችግሩ መውጫ ቀዳዳ እስኪያገኝ ድረስ ለተወሰነ ጊዜ ትንሽ እንዲጨነቅ ያስገድደው እንደሆነ እንጂ ከአራት ኪሎ ቤተ መንግሥት አያስወጣውም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የተነጣጠለ ትግል ለአደጋና ዕልቂት የሚጋብዝ እንጂ ውጤት የለውም፡፡ በዘመናት የመከራ ኑሯችን የተፈተነ ሃቅ ነው፡፡
  7. በምንም መንገድ በጋዜጣዊ መግለጫና በፉከራ አይወድቅም፡፡ ወያኔዎች ምሥጥ ናቸው፡፡ ዕድሜ ለላኪዎቻቸው የትም ሆነህ ብትቃወማቸው ክንዳቸው ረጂም ነው፤ ባለህበት ይመጡልሃል፡፡ አንተን የመሰለ ሰው አስርገው ይልኩብሃል፡፡ እናም እንኳንስ በጋዜጣዊ መግለጫና በፖለቲካዊ ጫጫታ ይቅርና በተደራጀ ጦርም እነሱን በቀላሉ ማንበርከክ አስቸጋሪ ነው፤ ጨርሶ አይቻልም እያልኩ ግን አይደለም፡፡ ገንዘባቸው፣ ስለላቸው፣ በአባቶቻቸው የሚደረግላቸው የመረጃና የበጀት ድጋፍ፤ በጥቅም፣ በዘርና በቋንቋ ሰውን መከፋፈላቸው፣ እኛን የሚመስለው የሰውነትና የቋንቋ እንዲሁም ሌላው ቅርጻቸው የኛን ትግል እጅግ ከባድና ውስብስብ ያደርገዋል፡፡ በዚያ ላይ ብዙ ተቃዋሚዎቻቸው ወያኔዎችን ይንቃሉ፡፡ እንደውነቱ ከሆነ በዋናነት ወያኔን የጠቀመው የነሱ ሸረኝነትና የኛ እነሱን መናቅ ነው፡፡ እነሱ እያደቡ ዕቅዳችንን ሁሉ ሲያከሽፉ እኛ ደግሞ ስንፎክርና በመግለጫ “ድባቅ ስንመታቸው” ይሄውና ሩብ ምዕተ ዓመት ዘለቅን – ሁነኛ የማስወገጃ ሥልቱን በቶሎ ካልነቃንበት ደግሞ ምዕተ ዓመቱን ይደፍናሉ፡፡ አሁን አሁን ግን ሕዝቡ ቀደመና መቆሚያ መቀመጫ እያሳጣቸው ይገኛል፡፡ የነሱ ተንኮል ማርከሻ ይህ ዓይነቱ መነሻው እንጂ መድረሻው በውል የማይታወቅ ሕዝባዊ ቁጣ ነው፡፡ ብልህ ሰው ታዲያ ያስፈልገናል፡፡ ይህን ሕዝባዊ እምቢተኝነት ወያኔዎች ብቻ ሣይሆኑ አለቆቻቸውም ይፈሩታል፡፡ ለምን ቢባል የሕዝብ ዐመፅ የት ጀምሮ የት እንደሚያልቅ አይታወቅም፡፡ የወያኔ ጌቶች ወያኔንና መሰል አሸባሪ ድርጅቶችን ጠፍጥፈው ሲሰሩ በርቀት መቆጣጠሪያ ሳይቀር እየተከታተሉ የሚያሸክሟቸውን ተልእኮ ተፈጻሚነት ያረጋግጣሉ፡፡ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ግን ከነሱ ዓላማና ፍላጎት ሊወጣ የሚችልበት አጋጣሚ ብዙ ስለሆነ ይፈሩታል፤ ፊት ለፊት ሊጋፈጡትም ብዙውን ጊዜ አይደፍሩም፡፡ ስለዚህ ይህን የትግል ዓይነት ገፋ አድርጎ መቀጠል ተገቢ ነው፡፡
  8. በምንም መንገድ በስደተኞች ብዛትና ሀገርን ለወያኔ ለቅቆ በመሄድ ወያኔ አይወድቅም፡፡ ይህ ዓይነቱ ነገር ሳይዋጉ እጅን እንደመስጠት ነውና በሀገር ውስጥ ሆኖ መታገል አማራጭ የለውም፡፡
  9. በምንም መንገድ በማዕቀብና ዕቃና አገልግሎት ከሕወሓት ባለመግዛት ወያኔ አይወድቅም፡፡ ምክንያቱም በቂ የሀብት ክምችት አላቸው፤ ሁሉ በጃቸው ሁሉ በደጃቸው – ምን ሲጎድልባቸው፡፡ ሕወሓት ሀገሪቱን ላለፉት 25 ዓመታትና ከዚያም በላይ ለሚቆጠር ጊዜ በብቸኝነት ሲበዘብዝ በመክረሙ የገንዘብም ሆነ የማቴሪያል ችግር ሳይኖርበት ብዙ ዓመታትን መዋጋት የሚያስችለውን አቅም አጎልብቷል፡፡ ስለዚህ ከነሱ ዕቃ ባለመግዛት የምንጎዳቸው ነገር የለም፡፡ ዳሸን ቢራቸውን ባትጠጣ፣ ጨዋቸውን ባትገዛ አይጎዱም፡፡…
  10. በምንም መንገድ ወያኔ ሥልጣንን በፈቃዱ አይለቅም፡፡ ብሔራዊ ስሜት ቀርቶ የሰውነት ደረጃም የሌላቸው የለየላቸው ዕብዶችና ሰካራሞች በመሆናቸው የሀገሪቱና የሕዝቧ ችግር ገብቷቸው ሥልጣናቸውን ለሽግግርም ይሁን ለቋሚ የሕዝብ ተመራጭ መንግሥት ሊያስረክቡ አይችሉም፡፡ ትግራይንና የትግራይን ሕዝብ በሆነ ኮሮጆ ውስጥ ይዘህ “ይህን ኮሮጆ እሳት ውስጥ ከምጨምረውና ሥልጣናችሁን ከምትለቁ የትኛውን ትመርጣላችሁ?” ብለህ ብትጠይቃቸው ወያኔዎች ሥልጣናቸውን እንደሚመርጡ ግልጽ ነው፡፡ ትግራይንና ተጋሩን ይቅርና በሚስትና በልጆቻቸው ሳይቀር ቁማር የሚጫወቱ የብዔል ዘቡል ደቀ መዛሙርት ናቸው፡፡ የሚገርም ተፈጥሮ እኮ ነው ያላቸው!

 

ስለዚህ መፍትሔው ምንድን ነው ቢባል መልሱ በበኩሌ እንዲህ ይመስለኛል፡፡

 

ሁሉም ከተሞችና የገጠር ቀበሌዎች በአንድ ወቅት ተባብረው በመነሣት በየአካባቢያቸው የሚመጣውን የወያኔ ጦር ቢቻል መማረክና ማስተማር፣ ያ ባይቻል አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ በቁጥጥር ሥር ማዋልና ለፍርድ ማቅረብ፡፡ ዕቃና ንብረት እየዘረፉ የሚያሸሹባቸውን መንገዶች ሁሉ መዝጋት፤ የጎበዝ አለቃ እየመረጡ ትግሉን በአንድ ጊዜና በሁሉም ሥፍራ ማጧጧፍ፡፡ የወያኔ ወታደራዊ ክንድ ከተመታ፣ በተለይም አጋዚ የሚባለው የሰይጣን መንጋ ከተበተነ ሕወሓት ምንም አቅም አይኖረውምና በፍጥነት ይፍረከረካል፡፡ ያኔ ከያካባቢው የሕዝብ ተወካዮች ተመርጠው ትልቅ ሀገራዊ ስብሰባ በማካሄድ ከታዋቂ ጤናማ ፖለቲከኞችና ታዋቂ ግለሰቦች እንዲሁም የሕዝብ እምነት ከሚጣልባቸው ተቃዋሚዎች የሚውጣጡ ዜጎች ያሉበት የአደራ መንግሥት ማቋቋም፡፡ ያ የዐደራ መንግሥት ለሁለት ዓመታት ያህል ሀገሪቱን ካረጋጋ በኋላ በእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት አዲስና ለሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል የሚያለግል መንግሥት መመሥረት፡፡ ስንታገል ደግሞ በአንድነት እንጂ ዘርና ጎሣ፣ ሃይማኖትና ክልል ለይተን መሆን የለበትም፡፡ እንደዚያ ካደረግን የወያኔን ፈለግ እንደመከተል ያለ ከንቱነት ነው፡፡ አሮጌው ወይን በአዲስ አቅማዳ ከተገለበጠ ጥፋትን በጥፋት መተካት ነውና ካለፈ ጠመዝማዛ ሕይወታችን መማር አለብን፡፡ ስለዚህ ትግሬን ከዐማራ፣ ኦሮሞን ከሶማሌ፣ ከምባታን ከአፋር … አንዱ ከሌላው ሳይለያይ የአንዲት ሉዓላዊት ሀገር ሕዝብ ባንድ ልብና ባንድ መንፈስ መታገል ይኖርበታል፡፡ ወያኔዎች በተለይ ትግሬን ከሌላው ለመለየትና በሌሎች ጉዳት እንዲደርስበት በማድረግ ከነሱ ጋር ለመለጠፍ የሚያካሂዱትን የቀቢፀ ተስፋ ሸርና ተንኮል ነቅተን መጠበቅ አለብን፡፡ የወያኔን ሤራ በንቃት መከታተልና ሆን ብለው እሳት የሚለኩሱትን የሰውና የንብረት ቃጠሎ ጨዋታ ሁሉ ሳይቀር እየተከታተልን ማጋለጥ አለብን፤ ለመሠሪ ተልእኮ የሚጭሯቸውን ግጭቶች እየተከታተልን እውነቱን በወቅቱና አደጋ ሳያስከትሉ ይፋ ማድረግ አለብን፡፡ ሟች ይዞ ይሞታልና እነሱ ሥልጣናቸውንና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የማያደርጉት ነገር አይኖርም፡፡ እኛን ለመለያየትም የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡ መለያየትን ደግሞ እስኪያንገሸግሸን አየነው፤ ክፉኛ ጎዳን እንጂ አልጠቀመንም፡፡ መኖር ከፈልግን እንግዲህ ማድረግ ያለብን እንደዚህ ነው፡፡ ሁሌ መሞኘት የለብንም፡፡ በመሠረቱ ብልጥ ከአንዴ በላይ መብለጥ አልነበረበትም፡፡ እኛ ግን የሆንነውን ሳናውቀው ዕድሜ ልካችንን በነዚህ ሰይጣኖች ስንታለልና ስንበለጥ ኖርን፡፡

እንጂ እንዳሁኑ አካሄዳችን ከሆነ ሶማሊያና ሦርያ በስንት ጣማቸው የሚያስብል አስቀያሚ ሁኔታ እንደሚፈጠር በጣም ግልጽ ነው፤ የሚደርስልን ደግሞ እንደሌለ መረዳት ይገባል፡፡ ወያኔዎች አያያዛቸው “የምፅዓት ቀን ለምን ዘገዬ?” እያሉ ለአባታቸው ለዲያቢሎስ ከፍተኛ ተማፅኖ በማቅረብ ላይ የሚገኙ ይመስሉኛል፡፡ ዱሮውን የታወከን ሀገር በብልሃትና በዘዴ እንደማረጋጋት ቦሃ ላይ ቆረቆር እንዲሉ በሰላም በዓልን በሚያከብር በሚሊኖች የሚቆጠር ሕዝብ ላይ ከመሬትና ከሰማይ ጥይት ማዝነብ በየትኛውም ሥሌት ትርጉም የለውም፡፡ እነዚህ ድፍን ቅሎች የጥጋብ ሞራ ሁለመናቸውን ስለጋረደው የሚያደርጉት ነገር ምን ሊያስከትል እንደሚችል ማሰብ አልቻሉም፤ ተፈጥሯቸው ሁሌም በተቃርኖ የተሞላ ነው – “እንብላ” ሲሏቸው “እንተኛ” ዓይነት፡፡ ገና ለገና የላኳቸው የጥፋት ኃይሎች በሁሉም ረገድ አይዟችሁ ስላሏቸው ብቻ ምድራችን ዐይታውም ሆነ ሰምታው የማታውቀውን የክፋት ሥራ በኢትዮጵያውያን ላይ ይፈጽማሉ፡፡ በመጨረሻው የሚያስደስተው ነገር ግና – በማንም ላይ ሊደርስ በሚችል ስቃይ መደሰት ተገቢ ባይሆንም – የሠሯትን ሁሉ አንድ ባንድና በዕጥፍ ድርብ የሚያወራርዱ መሆናቸው ነው፤ ያም ቀን ደርሷል፡፡

እንደማሣረጊያ – ያገሬ ባላገር ምን አለ?

 

 

የማን ቤት ፈርሶ የማን ሊበጅ፤

ያወሬ መፈንጫ ይሆናል እንጂ፡፡

 

እባክሽ እናቴ ውለጅ መንታ መንታ፤

ቀኝ እጄ ሲመክት ግራ’ጄ ተመታ፡፡

 

እዚያ ማዶ ሆኖ አንድ ሰው ተጣራ፤

እዚህ ማዶ ሆኖ አንድ ሰው ወይ አለው፤

ጎበዝ ተጠራጠር ይህ ነገር ለኛ ነው፡፡

 

ምን ስም ይሰጠዋል? [ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት]

$
0
0

ማክሰኞ መስከረም ፳፬ ቀን ፪ሺህ፱  ..              ቅፅ ቁጥር

Moresh-901.jpgበዓለም ላይ የነበሩና ያሉ ዘረኞች፣ ግፈኞችና አምባገነኖች የተለያዩ ምክንያቶች እየፈለጉ ሕዝብ ገድለዋል፣ አስረዋል፣ አሰቃይተዋል። በዚህም ተግባራቸው፣ « ናዚ፣ ፋሽስት፣ ጨፍጫፊ፣ አረመኔ» ወዘተርፈ ተብለዋል። ከእነዚህ እጅግ በከፋ ሁኔታ የዘረኛው የትግሬ ወያኔ ቡድን በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በአጠቃላይ፣ በተናጠል ደግሞ በዐማራው፣ በኦሮሞው፣ በአኙዋኩ፣ በኑኤሩ፣ በሶማሊው፣ በአፋሩ፣ በሲዳማው ወዘተርፈ ነገዶች ላይ የሚፈጽመው ሁለንታናዊ ግፍ በምን ቃላት ሊገለጽ እንደሚችል የቋንቋ ሊቃውንት ሊያስቡበት የሚገባ ነው። ከላይ የተገለጹት የጭካኔ እና የአረመኔነት ስያሜዎች በፍፁም የወያኔን ማንነትና ዕውነተኛ ባሕሪ አይገልጹትም። ይገልጹታል ከተባለም ተለምዶአዊ በመሆኑ፣ የቃሎቹ የያዟቸው ጽንሰ ሀሳቦችና ድርጊቶቹ የሚጣጣሙ አይደሉም። በምንም ታምር ከጥንት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የኖረ በዓልን ለማክበር ቄጤማ ይዘው በተቀመጡ ሽማግሌዎች፣ ሕፃናት፣ ሴቶችና ወንዶች ላይ ከሰማይ በአውሮፕላን፣ ከምድር በመትረየስ የሞት ዶፍ ማውረድ በምንም መመዘኛ ምክንያታዊነት የለውም። እገዛዋለሁ የሚለውን ሕዝብ፣ ያውም «ለብሔር/ብሔረሰቦች እኩልነት» ቆሜአለሁ እየለ ጧት ማታ በሚምል የገዛ ወገኑን የደበደበ አረመኔ የሚባል ቡድን በዓለም ታሪክ ስለመኖሩ በእርግጠኝነት ለመናገር አይቻልም።

የትግሬ ወያኔ ፣ በሀሰት ያሰራቸውን የኅሊና እስረኞች በራሱ የፍርድ ሂደት ቢያቀርባቸው አደረጉ ያላቸውን ስለማድረጋቸው ማስረጃ ማቅረብ አልቻለም። ስለሆነም እስካሁንም የሚሠራው ትያትር ሕዝቡ ያወቀበት መሆኑን በመረዳቱ፣ በቂልንጦ፣ በጎንደርና በደብረታቦር እስር ቤቶች በቁጥጥሩ ሥር ያሉትን እስረኞች በእሳት ለኩሶ፣ ንፁሐን ዜጎችን አጠቃ፣ በአሰቃቂ ሁኔታ ጨረሰ። እስረኞችን የወባ መድኃኒት ነው ብሎ፣ ማላታይን አጠጥቶ ፈጀ። ኤች አይ ቪ ቫይረስን በመርፌ እየወጋ ሕዝብ ጨረሰ። የዐማራውን ነገድ ቁጥር ለመቀነስና ፈጽሞ ለማጥፋት ባለው ዕቅድ፣ ዐማራ ሴቶችን ለይቶ በወሊድ ቁጥጥር ስም ታማሚና መካን አደረገ። የዐማራ ወንዶችን የመራቢያ አካላቸውን እየቀጠቀጠ፣ ሰዎችን በቁማቸው ጉድጓድ ውስጥ ከቶ አሰቃየ። እንዲህ ዓይነት ፍፁም አረመኔና ፋሽስት የተባለ ቡድን ከወያኔ በቀር የኢትዮጵያ ታሪክ አያውቅም።

ግፈኛውና ዘረኛው የትግሬ ወያኔ ቡድን ባለፈው እሑድ ጥቅምት 22 ቀን 2009 ዓም በደብረ ዘይት ከተማ የእሬቻን የኦሮሞ ባህላዊ በዓል ለማክበር ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተሰበሰቡ ንፁሐን ዜጎች ላይ የፈጸመው ቃላት ሊገልጹት የማይችሉት የጅምላ ግድያና ፍጅት ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በጽኑ ያወግዛል።

ግድያው ወያኔ ለ25 ዓመታት ካደረጋቸው የሚለየው፣ ላለፉት ዘጠኝና አሥር ወራት በተከታታይ በሐረርጌ፣ በወለጋ፣ በጅማ፣ በአርሲ፣ በኢሉባቡር፣ በሸዋ፣ በጎንደር፣ በጎጃምና መሰል ክፍለሀገሮች የዘለቀው ሕዝባዊ እንቢተኝነትና የዐማራው የማንነት ትግል ገዝፎና ገፍቶ ምኒልክ ቤተመንግሥት በራፍ ላይ በመድረሱ፣ በወያኔና አሽከሮቹ ላይ የፈጠረው የፍራት መጠን ከፍተኛ መሆን በአልሞት ባይ ፍርግጫ ያላቸውን የመጨረሻ ኃይል ያሳዩበት መሆኑ ነው። ነፃነትን የተጠማ፣ ማንነቱን ለማስከበር ቆርጦ የተነሳን ሕዝብ፣ ይህ ዓይነቱ የፈሪ በትር የታጋዩን ሕዝብ ወኔ ያጎለብታል እንጂ፣ እንደማይቀንሰው የኢትዮያ ሕዝብ ደጋግሞ ለዓለም ማኅበረሰብ አሳይቷል። በመሆኑም የትግሬ ወያኔ ፍርሀት በወለደው ስሜት በእሬቻ በዓል ተሳታፊዎቹ ላይ የወሰደው ዘግናኝና ሰቅጣጭ የጅምላ ፍጅት፣ የወያኔን በቃላት ሊገለጽ የማይችል ጭካኔ ከማሳየት በቀር፣ የሥልጣን ዕድሜውን ያራዝማል ተብሎ አይታሰብም። በአንፃሩ የወያኔን ዕድሜ በእጅጉ የሚያሳጥር፣ የሕዝቡን ነባር አንድነት ወደነበረበት ደረጃ የሚመልስ ነው። እንዲያውም የትግሬ ወያኔ ጠባብና አናሳ ቡድን ለሥልጣን ዕድሜው ማራዘሚያ በኦሮሞውና በዐማራው ነገዶች መካከል በሀሰት ገንብቶት የነበረው የጥላቻ፣ የመጠራጠርና የመገፋፋት ድልድይ ይሰብራል።

ሰሞኑን ደብረዘይት ላይ የፈሰሰው የኦሮሞው፣ የዐማራውና መሰል ነገዶች ልጆች ደም፣ ትናንት ጎንደር፣ ባሕርዳር፣ ደብረታቦር፣ ደብረማርቆስ፣ ነፋስ መውጫ፣ ወረታ፣ አምባ ጊዮርጊስ፣ ደባርቅ፣ ዳንግላ፣ ኮሶ በር፣ ቡሬ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ወዘተርፈ ላይ ከፈሰሰው የዐማሮች ደም የሚለየው አንዳችም ነገር የለም። በሁሉም አካባቢዎች በወያኔ ነፍሰ ገዳዮች የፈሰሰው ደም የኢትዮጵያውያን ደም ነው። ወያኔ ከሁሉም በላይ የዐማራውንና የኦሮሞውን ልዩነት ሊያሰፋው የሚፈልገው ሁለቱ ነገዶች አንድ ከሆኑ ኢትዮጵያን ሊገዛና ሊዘርፋት እንደማይችል ስለሚያውቅ ነው። ይህንን የትግሬ-ወያኔን መሰሪ ሴራ፣ የኦሮሞውና የዐማራው ልጆች «አውቀንባችኋል» በማለት ወደ ነባሩ አንድነታችን በፍጥነት መመለስ ወያኔን አይሞቱ ሞት የሚገድለው እንደሆነ አይጠረጠርም። ስለሆነም የመከራ ጊዜአችን ለማሳጠር የሁለቱ ነገዶች አንድነት ፍቱን የወያኔ አገዛዝ ማርከሻ እንደሚሆን ተረድተን፣ ፍትሕ የተነፈጉ ፍትሕን እንዲያገኙ፣ በአረመኔዎች የተገደሉ ደማቸው ደመከልብ ሆኖ እንዳይቀር፣ ኢትዮጵያውያን በነገድ ሳይሆን፣ በዕኩልነት ላይ በተመሠረተ ኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ እንድናተኩር ያሻል።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

የኢትዮጵያ ትንሣዔ በትግላችን ዕውን ይሆናል!
Attachments area

Click here to Reply or Forward

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>