Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

“አዋጅ ተነገረ! ዉሻና ዝንጀሮ ተባበረ!” (ዉሻና ዝንጀሮ ያደረጉት ክርክርና በመጨረሻ ያደረጉ ቃልኪዳን) [ከተፈራ ድንበሩ]

$
0
0

unity-300x2191.jpg

ከተፈራ ድንበሩ

ውሻ፡  አንተ ዝንጀሮ ከዚህ አካባቢ ብትሔድ ይሻልሃል፤ ሂድ! ሂድ! ሂድ! ነው የምልህ! ቶሎ ከዚህ አካባቢ ባትጠፋ ቦጫጭቄ ቦጫጭቄ ነው አፈር የማደርግህ!

ዝንጀሮ፡ እስቲ ሞክር! ዋጋህን ታገኛለህ! እኔ ብቻዬን ያለሁ መሰለህ? የኔ ሠራዊት አንድ ጊዜ ቢዘምትብህ አንተን ብቻ ሳይሆን ዘመድ አዝማድህን ሁሉ ፈጅተን ነው ለአውሬ እራት የምናደርገው!

ዉሻ፡ ይኸውልሃ! ፉከራህ ሁሉ ወደፍርሃት ተለውጦ ሠራዊት ከምትላቸው ጀሌዎችህ ጋር ዛፍና ገዳላገደልን የሙጥኝ ያልከው ታዲያ ለምንድነው? እስኪ ውጡ እና ኑ! እኛና እናንተ ይለይልናል! እኛ ሁለት ሆነን እናንተ ሃያ ሆናችሁ አገር እስኪሸበር በሲቃ እያስጮህናችሁ እያሳደድን እስከገደል አፋፍ ድረስ  አደረስናችሁ፤ በራሳችሁ የምትተማመኑ ከሆነ ውጡ እስኪ! ቦቅቧቆች! ቅዘናሞች! ቂጣችሁ እስኪላጥ በየገደሉ ያንፏቀቅናችሁ እኛ ጌቶቻችሁ ነን፤ እመኑ።

ዝንጀሮ፤ አዎን የፈራነው እኮ እናንተ ውሾች እያነፈነፋችሁ ሰዎችን በኛ ላይ ስለምትጠሩብን ነው፤ እንዲህ እንድትጮኹብን ያደረጉትና እናንተን ለዚህ ዕድል ያበቋችሁ ሰዎች ናቸው እንዲህ እንድትፎክሩብን ያደረጓችሁ፤ እናንተ የምትቦርቁበት ሜዳ፤ ውሀ እየተንጣለለበት የተለያዩ እህሎች፣ አታክልቶች፣ ፍራፍሬዎች የሚመረትባቸውና ስፍር ቁጥር የሌለው የቀንድ ከብት እና ሌሎች እንሰሳት የሚረቡበትን ሜዳ ትተን በተራራማና ገደላገደል ላይ የምንኖረው ቀደም ሲል ሰዎች አሳደውን እና መድረሻ አሳጥተውን ነው እናንተን ለዚህ ያበቋችሁ። ያን ሁሉ አገር ምድር ትተንላችሁ በየቋጥኞችና ገደላገደል አፋፍ ላይ መኖራችን አንሶባችሁ ለምን አሁንም ደግሞ ታሳድዱናላችሁ?

ዉሻ ፤ የሌባ አይነደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ ይላል ሰው! ደግሞ ለምን ታሳድዱናላችሁ ትላለህ እንዴ? በየማሳው ላይ የምትሸመጥጡትን ሰብል ዘርታችሁታል? ከናንተ ተርፎና ታጭዶ የተከመረን ክምር በየአውድማው እየዘረጠጣችሁ  የምትበሉት ባለርስት ሆናችሁ ነው ወይንስ የሌብነት ሙያችሁን ለመሸፋፈን ነው?

ዝንጀሮ፡ ዘረፋ የምንገባው ቢቸግረን ነው፤ ያን ሁሉ ሜዳ እና ለም አገር ሁሉ ትተንላችሁ በየጫካው ስንኖር ፍራፍሬ እንኳ እየለቀምን እንዳንኖር ጌቶቻችሁ እንደዋርካ፣ ዝግባ፣ እንኮይ ዶቅማ፣ ያሉትን ዛፎች ሁሉ እየቆረጡ ቀጋ፣ እንጆሪ፣ አጋምና ኮሽም ሳይቀር ቁጥቋጦውን ሁሉ እየመነጠሩ ደኑን ስላጠፉት የምንበላው የምንቀምሰው አጥተን በችጋር ስናልቅ ታዲያ  ዝም ብለን ነው የምንሞተው?

ውሻ፡ እናንተ እርስበርሳችሁ እንኳ የማትስማሙ ጠባይም የሌላችሁ አስቀያሚዎች፤ እንደኛ ጠባይ ቢኖራችህ ኖሮ በየገዳላገደሉ እየተንፉዋቀቃችሁ አትኖሩም ነበር፤ እኛ ግን ታማኞች ስለሆን ኮርተን ተንቀባረን እንኖራለን።

ዝንጀሮ፡ አዎን አስቀያሚዎች ነን፤ በአስቀያሚነታችን አናፍርበትም፤ እናንተ ለጌቶቻችሁ ባሪያ በመሆን ከነሱ የተራረፈውን ፍርፋሪ እና ልፋጭ ሥጋ ተኝታችሁ እየዋጣችሁ፤ ሰው የቀዳውን ውሀ እንዲሁም የወተት ጭላጭ እና አሬራ እየጠጣችሁ ወዛሞች ትሆናላችሁ እንጂ እንዴት እንደኛ አስቀያሚ መሆን ትችላላችሁ? ያውም ቢሆን አንድ ቀን የማታስፈልጉ መሆናችሁን ሲረዳ ጌታችሁ የት እንድሚጥላችሁ እንኳ አታውቁትም። እስከዚያው ይህን የምትጨፍሩበትን የተለያዩ ሰብሎችና የሚመረትባቸውን፣ የተለያዩ እንስሳት የሚረቡበትን አገር ሁሉ ከሌሎች ጠላቶቻችን ጠብቀን ስናቆይ ዱር እየዋልን ዱር እያደርን ሐሩሩ፣ ውርጩ፣ ረሀብ፣ ጥሙ ተፈራርቆብን ነው መልካችን አስቀያሚ መሆን የቻለው፣ ቆዳችንም የገረጣው፤  በዚህ ደግሞ እንኮራለን እንጂ አናፍርበትም። መልካችን ኑሮአችንን ይመስላል፤ የድካማችንን ውጤት ባንጠቀምበትም እንደናንተ ያሉ ውሾች እና ጌቶቻችሁ እየተጠቀማችሁበት ትገኛላችሁ፤ ታዲያ ባለውለታዎች በመሆናችን መጥፎ ስምና ስድብ ይገባናል?

ዉሻ፤ አገሩን ሁሉ የጠበቁት ሰዎች ናቸው እንጂ እኛ ነን ትላላህ እንዴ? በሌላ በኩል ደግሞ ተሰደን ኖርን ትላለህ፤ አታፍርም ስትዋሽ?  ደግሞ የኛም አገር ባለቤት መሆን ያምራችኋል እንዴ? ጌቶቻችን አደላድለው ማድሪያችንን ስለሰጡን ከነሱ ጋር ሆነን  ያላችሁበትንም አስለቅቀናችሁ መድረሻ ልናሳጣችሁ እንችላለን፡፡ ደግሞ ከፍተኛ የማሽተት ችሎታ ስላለን መረጃ በወቅቱ በማቀበልና የስዎችን ደህንነት በመጠበቅ በታማኝነት ስለምናገለግል ሰው ላደረገው የአገር ጥበቃ ሁሉ የኛም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለበት።

ዝንጀሮ፡ ይህን እንድትናገር የሚያደርግህ ሆዳችሁን እየሞላችሁ ለሰው ታማኝ ሆናችሁ መኖራችሁ አርቃችሁ እንዳታስቡ ስላደረጋችሁ ነው፤ ብታስትውሉ ኖሮ በየጊዜው አገር ምድሩን በሙሉ ሊወስዱት ከመጡ ወራሪዎች ተከላክለንና ተቆጣጠረን ባናቆየው ኖሮ አሁን ሰዎችና እናንተ የምትፈነጩበት ባላገር ሁሉ የሌሎች ፍጥረታት ግዛት ሆኖ ይቀር ነበር። እናንተም የቀብሮንና የተኩላን ያህል እንኳ ችሎታ ስለሌላችሁ ተበታትናችሁ ዘራችሁ ሁሉ ይጠፋ ነበር፤ ዉሾች የተባላችሁ ፍጡራን የምታደርጉትን አታውቁትም፤ የጌቶቻችሁን ጥፋቶች ማስፈጸም ሥራ ነው ትላለህ እንዴ? ማስተዋል ቢኖራችሁ ኖሮ ውለታችንን ታደንቁት ነበር። ስውም ለራሱ ጥቅም ሲል እየተጠቀመባችሁ ስለሆነ ያላችሁበት ሕይወት ጊዜያዊና አስተማማኝ አለመሆኑን መረዳት አልቻላችሁም፤ ብታስተውል ኖሮ ለታሠሩት ዉሾች ወገኖችህ ሁሉ ትቆረቆር ነበር፣ የልጆችህና ቤተስብህም እጣፋንታ ይኸው ስለሆነ አርቀህ ብታስብ ጥሩ ነው።

ውሻ፡- የምናደርገውንማ እናውቃለን፤ ይኸው ከናንተ በተሻለ ተንቀባረን መኖራችን አይታይህም እንዴ? ይልቅ ማንነትህን አውቀህ ወደጎሬህ ብትሄድ  ይሻልሃል፡፡

ዝንጀሮ፡ አንተ ችሎ፣ ዘወትር እያሳደድከኝ መኖርህ ምን ያስደስትሃል? የምትጠብቀውን ይህን ሀብት ሁሉ ታየዋለህ እንጂ አታዝበትም፤ አትጠቀምበትም፤ ሰብሉንም እንደሆነ በፈቃድህ አትበላውም፤ ጌታሀ አንተን በየዱሩ ሲያንገላታህና ከኛ ጋር ሲያጣላህ ኖሮ በመጨረሻ ሁሉንም ምርት ከጎተራው አከማችቶ ሲሻው ይበላዋል፤ ሲሻው ሸጦና ለውጦ ይንደላቀቅበታል፤ ላንተ እንደሆነ ከፍርፋሪ በስተቀር የሚደርስህ ምንም ነገር የለም፤ ያችም ብትሆን ነፍስህን ለማቆየትና በቀጣዩ ደግሞ የጌታህን ከብቶችም ሆነ ሌሎች ፍጥረቶችን በንብረትነት ለመጠበቅ እንድትችል ወስፋትህን ለመሙላት ብቻ እንደሆነ አይታወቅህም?

ውሻ፡ እናንተ ዝንጀሮዎች ወይ አትቆፍሩ፣ ወይ አትዘሩ ወይ አታርሙ፣ ሰው ያበቀለውን እና ያመረተውን በአሳቻ ሰዓት እየሸመጠጣችሁ ከመብላት በስተቀር ምን ደግ ነገር ትሠራላችሁ? እያጠፋችሁ ከመኖር በስተቀር ምን ሥራ አላችሁ? እኛስ ጌቶቻችንን እያገለገልን እንኖራለን።

ዝንጀሮ፡ ተሳሳትክ፤ እኛኮ በአንድ በኩል ከእናንትና ከስዎች ጋር፣ በሌላ በኩል ከተፈጥሮ ጋር እየታገልን እራሳችንን ችለን ነው የምንኖረው፤ በጥርሳችሁና በአፋችሁ ጩኸት የምትኖሩ ስለሆነ የራሳችሁን ዕድል እንኳ የማታውቁ የስዎች ተቀጥላዎች ናችሁ፡፡ ጌቶቻችሁ ሲፈልጉ በሰንሰለት እያሠሯችሁ ወይም ኅሊናችሁ ተገድቦና ድምጻችሁ እንኳ እንዳይሰማ በሕይወት እያላችሁ በሳጥን ውስጥ ተቆልፎባችሁ ያለነፃነት ትኖራላችሁ፤ እኛ ዝንጀሮ የተባልነው ፍጡራን ግን ከአንድ ጫካ ወደሌላ ጫካ እየዞርን ተፈጥሮ የሰጠንን ፍራፍሪዎች እየተመገብን በነፃ እንኖራለን፤ ሰው ጫካውን እየመነጠረ ተፈጥሮ የሰጠንን እንዳንጠቀም ሲያደርገን ደግሞ ከአንድ ማሳ ወደሌላ ማሳ እየዞርን በሜዳ ላይ ያልተሰበሰበውን ሰብል ወይም ደግሞ ታጭዶ የተከመረውን ነዶ እየዘረጠጥን እንበላለን። ሰው እኛን የናቀው ሕንፃ ስለገነባ፣ ሀብት ስለሰበሰባና የጦር መሣሪያ ስለአከማቸ በዚያ ተመክቶ ይንቀናል እንጂ በተፈጥሮ እኩል ነን እናንተ ነፃነታችሁን አሳልፋችሁ ህሊናችሁን ሸጣችሁ ለሆዳችሁ የተገዛችሁ ምቀኞች ባትኖሩ ኖሮ እኛ ሙሉ ነፃነት ኖሮን እንደናንተ ያሉትን እንሰሳት የተባላችሁ ጭቁን ፍጥረታት ጭምር ነፃ እናወጣ ነበር፤ አሁንስ ቢሆን በኑሯችን ብንጎሳቆልም እንደኛ ነፃነት ያለው የት ይገኛል? አንድ ቀን በጭቁን ፍጥረታት የተባበረ ትግል የሰው ኃይል ሲዳከም መድረሻ የምታጡት እናንተ ውሾች ናችሁ፡፡ ሰው የሠራውን ሕንፃ እያያችሁ በዘበኝነት ትጠብቃላችሁ እንጂ የናንተ ስላይደለ የምትተኙት ከስብሳብ፣ የምትበሉት ከወጭት አያልፍም ይልቁንስ ብንስማማ አይሻልም? እናንተ እከብቶቻችሁ ጋ ሂዱ፤ ሰብል ሰብሉን ለኛ ብትተዉልን ምን አለ? ሰው ፍየል፤ በግ፤ ወይም ሌላ ሌላ እንሰሳዎችን ቢያርድ ምርጥ ምርጥ የሆነውን እንዲሁም ልብና ኩላሊት እንኳ ባይሰጧችሁም ሽንፍላና እንጀት እየበላችሁ ትኖራላችሁ። እናንተ ልክስክሶች ስለሆናችሁና የምትበሉትን እንኳ  ስለማትመርጡ ተጸይፈዋችሁ ነው እንጂ ሰዎች እናንተንም ከመብላት አይመሱም ነበር።

ዉሻ፦ ሽንፍላም ሆነ ልፋጭ ትበላላችሁ የምትሉን እንደናንተ ሣርና  የእንጨት ፍሬ ከመባላት ሳይሻል እንደማይቀር አጥተኸው አይመስለኝም፤ ዝናም ሲጠፋ ሣሩም ቅጠሉም ፍራፍሬውም ስለማይኖር በችጋር የምታልቁት እናንተ ናችሁ እንጂ እኛ አይደለንም። እኛ በታማኝነታችን ጦማችንን አለማደራችን አልታየህም፤  እናንተ ግን ዕድሜ ልካችሁን ስትሠጉ ነው የምትኖሩት፤  ታማኝ በመሆናችን ሳያበሉን የማያሳድሩን ሰዎች  የሚሰጡንን ክብር አታውቀውም፤ እናንተ ድሮስ ማዕርግ የት ታውቃላችሁ?

ዝንጀሮ፦ አዎን የጌቶቻችሁ ዘበኞች ስለሆናችሁ ሆዳችሁ እንዴት ሊጎድልባችሁ ይገባል? ሆዳችሁ ከጎደለባችሁማ  እንኳን ሮጣችሁ ልትናከሱ ቀርቶ ላንቃችሁ እንኳ መጮህ አይችልም፤ ይህን አገግሎት ካቆማችሁ ሰው እንደቆሻሻ እንደሚጥላችሁ አታውቁም? ሌላው ልታውቁት የሚገባው ደግሞ  እኛ ተፈጥሮ የሰጠችንን ምንም ሳንለውጥ የምንመገብ ስለሆነ ስካር ወይም የእእምሮ መቃወስ የሚባል ነገር አናውቅም፤ ሰው ግን ብዙ የተለያዩ ምግቦችን ያለቅጥ እያግበሰበሰ፤ እየቀመመ ከተፈጥሮ ሕግ ውጭ እንደሱ ነፍስ ያላቸውን ፍጥረታት ሁሉ በግፍ እየገደለ ስለሚበላና ስለሚጠጣ አእምሮው ከመደንዘዙም በላይ  ገሚሱ የማይድን በሽታ ይዞት ዕለተ ሞቱን እየተጠባበቀ በሥጋት የሚኖር ሲሆን፤ እናንተ ውሾችም ከሱ የተረፈውን ስለምትመገቡ የሰው በሽታ ይተላለፍባችኋል፤ አለቅጥ ለረዥም ጊዜ መተኛታችሁ በሽታ መሆኑ አይታውቃችሁም? እስቲ ምን የመኖር ዋስትና አላችሁ?  ዕድሜያችሁስ ምን ያህል አጭር መሆኑን ተገንዝበኸዋል? እንደኛ በአካልም በአእምሮም ጤነኛ ሆናችሁ በነፃነት እንድትኖሩ የምንላችሁን ብትሰሙና ብትተባበሩ ይጠቅማችኃል፤ ለምሳሌ እንደኛው ያሉ ፍጥረታት የሚመስሉ የጋራ ጠላት ሆነው የሚያጠቁንን ጅቦች ለመከላከል ብንተባበር ከመጠቀም በስተቀር ምን ትጎዳላችሁ?

ውሻ፡ ጅብ በእርግጥ የሁላችንም ጭቁን ፍጥረታት ጠላት ነው፤ ሆኖም ጅቦችን መቋቋም የምንችለው እኛ ውሾች የተባልን ፍጥረቶች እንጂ እናንተ ምንም ማድረግ የማትችሉ ፍጥረቶች ናችሁ፤ እናንተ ጅቦችን ተዋጉ የምትሉት ለብልጠታችሁ ነው፤ እኛ ከጅብ ጋር ጦርነት ስንከፍት እናንት ሰብሉን ለመሸምጠጥ ዕድል እንዲኖራችሁ  ስለሆነ ከናንት ጋር መተባበር አንችልም፤ አትቀልድ።

ዝንጀሮ፡ የተሳሳትከው አንተ ነህ፤ ጅብም ሆነ ሰው የናንተም የኛም ጠላቶች ናቸው፤ ሁለቱም ጠላቶቻችን ባይሆኑ ኖሮ በምድር ላይ የሚገኘው ተፈጥሮ በሙሉ ዱሩና ደኑ በሰዎች መመንጠሩ ሲቀርለት እየተስፋፋና እያፈራ ምድር በተፈጥሮዋ ተሞልታ የሁላችንም መመኪያ ትሆን ነበር፤ ደግሞ በየጫካው እየዞርን የፈለግነውን ተፈጥሮ የለገሰንን ሁሉ እንደልባችን እየተመገብን እንኖር ነበር። እኛ ዝንጀሮ የተባልን ፍጡራን ምንም እንኳ ዱር የምንኖር ቢሆንም፤ እንደናንተ በሰንሰለት ታሥሮና ለሰው በሪያ ሆኖ ከመኖር የተሻለ ሕይወት አለን፤ በዱር በገደሉ በየቁጥቁዋጦውና አረሁ ብንዘዋወርም ደኑ በኛ ቁጥጥር ሥር ስለሆነ ዋና ጠላታችን ከሆነው ሰው ነፃ ወጥተን እንደልባችን እየተዘዋወርን እንኖራለን፤ ሰው ደግሞ እኛን ለማጥቃት ቢዘምትም የምንበቀለው በድንገት በደፈጣ በምናደርገው ወረራ ነው፤ ዓመት ሙሉ የደከመበትን በአንድ ቀን ሌሊት የማውደም ልዩ ችሎታ አለን። ይህ በደፈጣ የምናደርገው ትግል የባላገር ባለቤት አድርጎናል፤ እናንተ ከጌቶቻችሁ ተለይታችሁ መኖር አትችሉም፤ አይፍፈቀድላችሁም፤ ወደዱር እንኳ ስትሄዱ ለሰው አሽከር ሆናችሁ ነው እንጂ ራሳችሁን ችላችሁ መሄድ አትችሉም፤ ምክንያቱም እናንተ የምትኖሩት ጌቶቻችሁን ለማገልግል ብቻ ስለሆነ ለሆዳችሁ የተገዛችሁ እንሰሳት ናችሁ። ሁሉንም ለራሱ ሊሰበስብ በሚያደርገው ጥረት ሰው እኛን ለመቋቋም የሚሞክረው በመሣሪያ ኃይል ብቻ ነው፤ ሆኖም፣ በጠመንጃ ሊገድለን ሲሞክር ባለን ከፍተኛ ወታደራዊ ቅልጥፍና ስለምንገለባበጥ ጥይት ሊመታን አይችልም፤ በየቦታው ከትሞ በየጊዜው አዳዲስ የመሣሪያ ክምችት እየጨመረ ያለው አቅም ስለሌለው ነው። ተባብረን ባላገሩን በሙሉ ብንቆጣጠርበት ሰው የሚያግበሰብሰውን ሀብት ሁሉ ያጣዋል፤ መሣሪያ የሚያገኝበት ምንጭ ይደርቃል፤ በመሣሪያ መጠቀም ካልቻለ ደግሞ በቀላሉ በእጃችን ሥር ወደቀ ማለት ነው።

አንድ ቀን ዝንጀሮ የተባለ ሠራዊት ሁላ ግምባር ከገጠመ እናንተ ውሾች ከጌቶቻችሁ ጋር መግቢያ አይኖራችሁም፤ እናንተ የምታመልኩት ሰው ሲጨፍርበትና ሲዘባነንበት የነበረውን ቤት ጥሎ ሲፈረጥጥ ከኛ እጅ አያመልጥም። እሱም የሠራዊታችን ተገዥ ይኖናል፤ ዛሬ ሰው የሚሰድበንና የሚንቀን ሁላችን በአንድነት ሆነን ፍርድ ስንሰጠው ነፃነት፤ እኩልነት፣ ፍትህ፣ ማለት ምን እንደሆነ ሰናሳየው፤ ዝንጀሮ መባላችን ቀርቶ እኛም የሰውን ክብር እናገኛለን፤ ይልቅስ የነፃነት ቀናችን እንዲፋጠን እኛ የምንላችሁን ብትሰሙን እና ብንደማመጥ ጥሩ ነው።

ውሻ፡ ከናንተ ጋር ሆነን ጅብን ልንዋጋ? ሞኛችሁን ፈልጉ! እናንተ ዝንጀሮዎች፤ ሰው ባያስጠጋንና በጫካ ብንኖር ኖሮ ዘራችን በጅብ ያልቅ ነበር፤ በየዛፉ ስለምትንጠላጠሉ ነው እንጂ እናንተ ነበራችህ የመጀመሪያዎቹ የጅብ ቀለቦች፤ ለመሆኑ ጅብ ምን ይበቃዋል? እነዚህን የዱር እንሰሳትም ሆነ የቤት እንሰሳትን ለመጨረስ አይመለስም።  ስለዚህ አሁንም ይህች ሐሳብህ እኛ ዱር ገብተን በጅብ ስናልቅላችሁ እናንተ ያለተቀናቃኝ እንደልባችሁ የሰውን ሰብል ለመሸምጠጥ አይደል? ሰብል ደግሞ ተሽምጥጦ ካለቀ ሰው ለኛ የሚሰጠን ስለሚያጣ በረሀብ ማለቅ አንፈልግም፤  ስለዚህ ይህ ሐሳብህ ሌላ የብልጠት ዘዴ ስለሆነ እናንተን ማመን አይቻልም፤ እናንተ ለመሆኑ ምናችሁ ይታመናል? የወለዳችሁት ልጅና አባቱ እንኳ አይተመማኑም፤ እናት ዝንጀሮ ወንድ ልጇን የገዛ አባቱ እንዳይገድልባት ደብቃ ነው የምታሳድገው፤ ልጁም የአባቱን ኮቴ ሲለካ ሲለካ እያደገ አንድ ቀን ኮቴው ከአባቱ ኮቴ ጋር እኩል መሆኑን ሲያውቅ የጅር የበላይ ለመሆን አባቱን ከመዋጋት አይመለስም፤ እኛ ግን ውሾች የተባለን ፍጡራን ምንም እንኳን እናንተ ነፃነት የምትሉት ነገር ባይኖረንም ልጆቻንንና ወገኖቻችንን በጣም እናከብራለን፤ የተሰጠንን አክብረን እንበላለን እንጂ እንደናንተ ሠርቀን ወይም ዘርፈን አንበላም።

ዝንጀሮ፤ እንደናንተ ዝንጀሮ የሚባል ፍጥረት ጭላዳ፣ ጎመር፣ ወዘተ ተባብሎ በአፍና በዘር ተለያይቶ ሳይለያይ ከጦጣና ጉሬዛ ጭምር በሠራዊት በሠራዊት ተከፋፍሎ እየተመራ ነው የሚተዳደረው፤ እንደጉሬዛ ያለው  በመንፈሳዊነት ይታወቃል፤ እንደአውራ ዶሮ ሊነጋ ሲል ደጋግሞ በመጮህ ፈጣሪውን ከማመስገኑም በላይ የቀኑን ምሥራች ለኛ ያበሥረናል፤ እያንዳንዱም ሠራዊት ወይም ጅር ደግሞ የየራሱን ባላገር ይቆጣጠራል፤ ታዲያ አንድ የዝንጀሮ መሪ በራሱ ሠራዊት ውስጥ ተቀባይነት ኖሮት መሪ መሆን የሚችለው ከማንኛውም ሌላ ዝንጀሮ ጋር ተፋልሞ ኃይለኛነቱንና ጀግንነቱን በተግባር አሳይቶ ነው እንጂ እንደናንተ ለማንም ጅራቱን እየቆላ አይደለም፤ ይህን ብታስተውል ኖሮ ጥያቄውን አትጠይቀኝም ነበር።

ዉሻ፤ በናንተ መካከል ዘወትር የሚታየውን ጠብ እና ጀብደኝነት ጀግንነት ትለዋለህ? እርስበርሳችሁ ባትጣሉ ኖሮ ለመሆኑ ምን አገር ይበቃችሁ ነበር? እኛስ ብንጣላ እንኳ ሰው በመካከላችን ገብቶ ጠበኛውን አሥሮ ስለሚያገላግለን አንጨነቅም፤ የምንጨነቀው ነገር ቢኖር አልፎ አልፎ በጭለማ ወጣ ወጣ ስንል ጅብ እንዳያጠቃን ብቻ ነው።

ዝንጀሮ፡ ሰውስ ከጅብ በምን ይለያል? ጅብ ጅብ የተባለበት ምክንያት እኮ ከመጠን ያለፈ ስለሚበላ ነው፤  እናንተ የምታመልኩት ሰው ግን መቼ በልቶ ይበቃዋል? ዘርፎ ዘርፎ እኛ ልንጠቀምበት እንችል የነበረውን ሁሉ የተፈጥሮ ሀብት ሰብስቦና አግብስብሶ በግል ሊጠቀምበት ከሚያስፈልገው በላይ እጅግ ያከማች የል? መች ይጠግባል?  እንዲየውም ከሰው ጅብ ሳይሽል ይቀራል? ምክንያቱም ጅብ እኮ ከወገኑ ጋር ተካፍሎ ይበላል። እንደሰው ያለ ክፉ እንኳን ያለ አይመስለኝም፤ ጌታህ ብቻ ስለሆነ የማይገባውን ክብር ልትሰጠው አይገባም።

ውሻ፡ ታዲያ እናንተ ከሰው ይበልጥ ደግ ነን ነው የምትለው? ምንም ቢሆን ሰው ይሻለናል፤ የናንተና የኛ አኗኗር ለየብቻ ነው፤ ባላገሩን ለብቻው ከተማውን ለብቻው ተቆጣጥሮ የሚያስተዳድረው ሰው በሌለበት እንዴት እኛና እናንተ ተስማምተን መኖር እንቻላለን?

ዝንጀሮ፡ ቀስ እያልኽ አትጠጋኝ፤ እዚያው ባለህበት ቆይ፤ እናንተ ውሾች እኮ ከኛ ጋር በአንድ ቦታ ኑሩ አላልናችሁም፤ እናንተ የምትመገቡት ሌላ እኛ የምንመገበው ሌላ፤ እንደየልማዳችን ለየራሳችን መኖር የሚከለክለን ምንም ነገር የለም፤ እኛ የእናንተን ሳንፈልግ፤ በየቀያችን፣ እናንተም በየቀያችሁ እየኖርን፣ እናንተም የኛን ሳትፈልጉ በጋራ ጠላቶቻችን ላይ የጋራ አቅዋም ብንወስድ ማን ይጎዳል?  በነዚህ ጠላቶቻችን ላይ ብንተባበር ጥንትም የራሳችን የነበረው ደኑ ተራራው፤ ሽንተረሩ ወንዛወንዙና የዱር ሀብቱ ሁሉ የናንተና የኛ የተናቅን እንሰሳት የተባልን ፍጡራን ስለሚሆን እናንተ የሚስማማችሁን እኛም የሚስማማንን እየተመገብን እናንተ እኛ ጋ ሳትደርሱ፤  እኛም የናንተን ሁሉ ሳንነካ የናንተም ሆነ የኛ ትውልድ ጦርነት አለብኝ በማለት ሳይጨነቅ በሰላም ተከባብረን መኖር እንችላለን።

ውሻ፤ አሁን ገና እውነት የምትናገር መሰለኝ። ስው እኮ እኛ ተዋግተን አንዳንዶቻችን ክፉኛ ቆስለንና ሞተን ከብቱንና ንብረቱን ብንጠብቅለትም ሰው የፈለገውን ይወረውርልናል እንጂ የደከምንበትን ከማየት በስተቀር አንጠቀምበትም፤ ጌታችን ሰው ከፈለገ  ይሸጠናል፤ ይለውጠናል፤ በማናውቅበት አገር ከዘመዶቻችን ተለይተን ስዎችን ለመጥቀም ሰላማዊ ፍጥረታትን በማጥቃት ጠላት ከማብዛት በስተቀር ምንም መብት የሚባል ነገር አናውቅም። ረሀብና በሽታ እንኳን ሲያጠቃን የመዳን ተስፋ ስለሌለን ሞታችንን ብቻ ነው የምንጠቀው፤ እንደዚህ ባለው ኑሮ ከመካከላችን አንዱ ሲጎድል ወይ ሞቶ ወይ ተሽጦ መሆኑን ተረድተን ለዛሬ ከማሰብ በስተቀር የወደፊቱን ስለማናውቀው የያንዳንዳችን ቀን እስኪደርስ መስለን እንኖራለን ። ሌላው ነገር ደግሞ የእናንተ ኑሮ በየቁጥቋጦውና ገደላ ገደሉ የሆነው የተፈጥሮ ሀብታችሁ ስለተወሰደባችሁና  ስለተሳደዳችሁ ምርጫ አጥታችሁ መሆኑን ተረድቻለሁ። ለካ ሁለታችንም ጭቁኖች ነን! ያውም የጋራ ጨቋኛችን በሆነው ሰው። የድሮውን የጥላቻ ታሪክ ትተን አሁን ያለንበትን ጭቆና በጋራ ለማስወገድ መተባበራችን የሚከፋ አይመስለኝም፡፡ ታዲያ እናንተ የኛን ሳተፈልጉ ወደኛ ሳትደርሱና እኛም ለራሳችን በሚስማማን ሁኔታ መኖር የምንችል ከሆነ ሊያስማማን ይችላል፤ ግን ሰው እኮ በጣም አዋቂና ከአቅማችን በላይ የሆነ መሣሪያ ስላለው እሱን ክደን እንዴት ሊሆንልን ይችላል?

ዝንጀሮ፦ አይ ችሎ ማደር እውነቱን መናገርህም ያሰመሰግንሃል፤ የዋህ መሆንህንም እረዳለው፤  ሆኖም እናንተ ውሾች የተባላችሁ ፍጡራን ሰው ካላሳደራችሁ ሕይወት እንደሌላችሁ ማመን የለባችሁም፤ ዋናው ነገር ይኸ ነው።  በራሳችሁ ጥረት ለኑሮአችሁ የሚያስፈልጋችሁን ማግኘት እንደምትችሉ አንተ ራስህ አሁን ተናግረከዋል፤ እናንተ የቤት እንሰሳት የተባላችሁትና እኛ የዱር አራዊት የተባልነው ዝንጀሮዎች የአንደኛችን  ወገን የሌላውን ወገን እንደጠላት አለማየታችን የመጀመሪያው ትልቅ እርምጃ ነው። ሰው በኛና በእናንተ ልዩነት ተጠቅሞ እናንተን በኛ ላይ እያዘመተ ነው ተንደላቆ የሚኖረው፤ ወደፊትም ዘራችን ከዘራችሁ ጋር ደም ተቃብቶ በጠላትነት ሲዋጋ ሰው ግን ተደላድሎ ለመኖር ነው የሚያቅደው። ወደፊት ከማሰብ ይልቅ ወደኃላ እያሰብን እና እየተጋጨን መኖር የለብንም፤ ድሮ ማ በማን ላይ የበለጠ ጉዳት አድርሷል የሚለውን ለማጣራት ብንሞክር አጣርተን ለማረጋገጥ ያስቸግረናል። እንደዚያ ብናስብ ቂምበቀል እየተወረሰ በናንተም በኛም ወገኖች መካከል ሳያቋርጥ እያጣላን ከሚኖር በስተቀር የሞቱትን አያስነሣም፤ ለወደፊቱም ሁላችንንም አይጠቅመንም፡፡  ዛሬ ያለንበትን ጭቆና በጋራ እናስወግድ ማለትህ ትልቅ እርምጃ ነው፡፡ ይህ የአስተሳሰብ ለውጥ ነው የድል በር የሚከፍትልን፡፡ አቋማችን አንድ ከሆነ እና እርስበርሳችን ላለመጣላት ከተስማማን የሰው መሣሪያ የትም አያደርሰውም፤ በመጀመሪያ ሰው የሚኖረው በኛ ልዩነትና ጠብ ላይ መሆኑን እንተማመን፤ ዘለዓለም እንሰሶች ተብለን አንኖርም፤ የእስከዛሬው ይበቃናል፤ በተባበረ ትግላችን ከሰዎች እኩል መሆናችን አይቀርም፤ ሆኖም በጋራ ለመታገል ቃለመሐላ መፈጸም አለብን። ከዚህ በኃላ ያለው ቀላል ነው።፡

ውሻ፦ እኛ እኮ እናንተን የምናሳድደው ጌቶቻችንን ፈርተን እነሱን ለማገልገል እንጂ እናንተ ዝንጀሮ የተባላችሁ ፍጡራን ምንም ልታደርጉን አትችሉም፤ ከናንተ ጋር መሠረታዊ ጠብ ሊኖረንም አይችልም፤ እኛ ከጌቶቻችን ነፃ መሆን ከቻልን በባላገር ውስጥ መኖር እናውቅበታለን፤ ከዘመዶቻችን መካከል ተኩላ የሚባል ዘር ከናንተ ጋር በጉርብትና እንደሚኖር ታውቃለህ። እናንተን ማሳደድ ስንተው ታዲያ ስው ወደባላገር እንዳይመጣ በመሣሪያው ተጠቅሞ ጉዳት እንዳያደርስብን ምን ማድረግ ይቻላል?

ዝንጀሮ፡ ቀበሮ “ሰውን ማመን ቀበሮ ነው” ያለችው ከናንተ ያነስ አቅም ያላትና የናንተው ወገን አይደለችም እንዴ ቤቷን ጫካ አድርጋ እንደኛ የምትኖረው? አትስጉ። በመጀመሪያ የውሻ ወገን ሁሉ ወራዳ ልክስክስ ተብሎ በመቃብርና ሕይወት መካከል እንዲኖር ሰው ለራሱ ጥቅም ያደረገው ተንኮል መሆኑን መረዳቱ ነው። ይህን ውሻ ለተባለ ፍጡር ሁሉ ማስረዳትና ማሳመን የናንተ ተግባር ይሆናል። ውሻ የተባለ ሁሉ ከትንሽ እስከትልቅ ሴትና ወንድ ሳይባል በሰንሰለት የታሠረውም ያልታሠረውም እንዲያምን ማድረግ አስፈላጊውን ጊዜ ወስዶ መሠራት ያለበት ትልቅ ሥራ ነው። ታዲያ ቀጥሎ በጋራ ተስማምተን አብረን እርምጃ ከመውሰዳችን በፊት ሴቶች ውሾችም ሆኑ ቡችሎች ተሳስተው አንዳች የጥላቻ ምልክት በጌቶቻቸው ላይ እንዳያሳዩ ጥንቃቄ መደረግ አለበት።

ውሻ፤– እኛ ወደን አይደለም ታማኝ ሆነን የምንኖረው፤ ምርጫ አጥተን ነው እንጂ፤ አብዛኛዎቻችን ጌቶቻችን ወደውጭ ለአገልግሎት ሊያሰማሩን ካልሆነ በስተቀር ወይ በር ተዘግቶብን ወይ ደግም በሰንሰለት ታሠረን ነው የምንኖረው፤ ታዲያ እንዴት የጋራ እርምጃ መውሰድ እንችላለን?

ዝንጀሮ፦ ዘዴማ ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ በመጀመሪያው እርምጃ እኛ ስንመጣ እንድታጠቁን ይልካችኃል፤ በዚህን ጊዜ ጩኹና ስንሸሽ ተከሉን፤ ሰው እስከማይደርስበት ዱር ድረስ ያባረራችሁን መስላችሁ በመጨረሻ እንደደመሰስናችሁ ለመምሰል ሁላችሁም ድምፃችሁን አጥፉ፤ ይህን ጊዜ ሰው ያመፃችሁበት ሳይሆን ሞታችሁ ያለቃችህ ስለሚመስለው ሌሎች ውሾች ወገኖቻችሁን ማዝመቱ አይቀርም፤ በሁለተኛው ጊዜ ሲያሰማራችሁ ጩኸቱን እየቀጠለ ዉሻ የተባለ ሠራዊት ወደፊት ወደኛ በመገስገስ የበፊተኛውን እርምጃ እየደጋገመ ከወገኑ ጋር ይደባለቃል። እኛም ለሰው ጥይት ብቻ እንደማንሸነፍ ከዚህ በፊት እንደነገርኩህ በተለመደው የደፈጣ ውጊያ ስልታችን የተለያዩ የጥቃት እርምጃዎችን ስለምንወስድበት ሰው የሚመካበት ሰው-ሠራሽ ነገር ሁሉ እንደማያድነው ያየዋል።  በምናደርገው የመረጃ ልውውጥ እና ስልታዊ አመጽ በየአቅጣጫው እንቅስቃሴያችን ሲበረታበት ትዋጉለት የነበራችሁ እናንተ ጭቁን ፍጡራን ሁሉ ትታችሁት ከገኛ ጋር ስትሆኑ መሣሪያውን መጠቀም እንኳ አቅቶት ብቻውን ይቀራል። እኛና እናንተ ጭቁኖች ሁሉ አንድነት ስንፈጥር ክዚህ ቀደም የምታደርጉት የሕይወት መስዋዕትነት ይቀራል። እነዚህ እርምጃዎች ተደጋግመው ሲፈጸሙ ሰው  ብቻውን ስለሚቀርና አብዛኛዎቻችሁን ወደኛ ለማዝመት ሲል ስለሚፈታችሁ ነፃ እየወጣችሁ ባላገር ትገባላችሁ፤ እኛም ከናንተ ጋር በመተባበር ታሥረው የቀሩትን ባለን ጥበብ ዘምተን እንፈታቸውና የሰውን ገዥነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እናስቀራለን፤ ከዚህ በኃላ ገዥና ተገዥ ሳይኖረን ሁላችንም ተከባብረን በሰላም እንኖራለን፤ ገባህ?

ውሻ፦ እውነት ነው፤ እኛ ከተባበርን ሌሎች ጠላቶቻችንን መቋቋም እንችላለን፤ ሰው የሚገለገልባቸውን በጎች፣ ፍየሎች፣ ወዘተ በማደን መኖር እናውቅበታለን።

ዝንጀሮ፦ ልብ በል፤ የናንተም ሆኑ የኛ ወገኖች በሙሉ እንዲቀባሉን እኛ ተንቀን የነበርንና በዚህ የነፃነት ጎዳና የተሠማራን ሁሉ የሌሎች የተናቁትን ፍጡራን መብትና ክብር በመጠበቅ ጥሩ ምሳሌዎች መሆን ይኖርብናል፤ አቅም አለን ብለን ደካማና አናሳ የሆኑትን የሆኑትን ፍጥረታት በፍጹም መጉዳት የለብንም፤ አንዱ ኃይላችን በሁሉም ወገኖች መታመናችን ነው፤ በተጨባጭ ጥሩ ምሳሌ እያሳየን ስንቀሳቀስ በየቦታው ውዳቂ መስለው የሚታዩት ፍጡራን ሁሉ  የቆምንላቸው መሆኑን ሲረዱ በምናደርገው የጋራ እርምጃ ሁሉ በፍላጎታቸው  ከጎናችን ይቆማሉ። ሁሉም ፍጡር አካባቢውን በነፃ ያስተዳደራል፤ የተናቁ ፍጡራን ሁሉ እንዳቅማቸው ለትግላችን ጠቃሚ አስተዋፅዖ ማድረግ ስለሚችሉ ሌሎች ፍጡራንን ሁሉ እንዳይጠላ ትንሹም ትልቁም ሴቱም ወንዱም የኛና የናንተ ወገን ሁሉ እንዲማር የማድረግ ኃላፊነት አለብን፤ አርስ በርስ በጠላትነት መተያየት ጨርሶ ቆሞ የሚቀጥሉት ትውልዶቻችን እኩልነትንና ፍቅርን ብቻ ማዳበር ይኖርባቸዋል።

ውሻ፦ የጋራ ጠላታችን የሆነውን የሰውንም መብት ማክበር አለብን ማለት ነው?

ዝንጀሮ፦ አዎን፤ የመጨረሻው ግባችን ሰውንም ነፃ ማውጣት ነው፤ እዚያ ደረጃ ላይ ለመድረስ ግን በሁላችንም በኩል የአስተሳሰብ ለውጡ የሠረጸ መሆን አለበት፤ በመጀመሪያ አሁን በላያችን ያለውን የገዥነት ኃይሉን በሙሉ አስወግደን ሰውን ከተራ ፍጡራን እኩል ማድረግ ብቻ ሳይሆን፤ እሱም ለዘመናት በራሱ ተመክቶ ሲፈጽም የነበረውን የገዥነት አቅሙ እና የበላይነት ሕልሙ ሁሉ ጠፍቶ ካለእኩልነት  ሌላ የጋራ ጥቅም እንደሌለ የሚያምንበት ሁኔታ መፈጠር ይኖርበታል። ከላይ እንደገለጽኩልህ ሰው ራሱ አልፈጸመውም እንጂ የባህል ለውጥ የሚለውን በናንተና በእኛ የተናቅን ፍጡራን ብቻ ሳይሆን ሒደቱን ጠብቆ ሰውም ራሱ የባህል ለውጡን በተግባር እንዲፈጽም ይደረጋል።

ውሻ፦ አሁን በሁሉም ነገር የተግባባን መሰለኝ፤ ስለዚህ የጋራ ቃልኪዳናችንን በቃለመሐላ ማረጋገጥ እንችላለን።

 

ቃልኪዳን

  1. እኛ የተናቅን ፍጡራን ውሻ፣ ዝንጀሮ፣ ወዘተ እየተባልን በሰው እጅ ተጨቁነን መኖራችን የመነጨው ባለመተባበራችን መሆኑን ተማምነን ከዛሬ ጀምሮ አንደኛው ወገን ሌላውን በጠላትነት እንዳያይ፣ የአንደኛችን ወገን መጠቃት የሌላው ወገን መጠቃት እንደሆነ ተማምነን ኃይላችንን ሁሉ በጋራ ጠላታችን በሆነው ሰው ላይ አዙረን ባላገሩ በሙሉ በኛ በጭቁን ፍጥረታት ቁጥጥር ሥር እስከሚውል ድረስ ማንኛውንም መስዋዕትነት በመክፈል በተፈጥሮ ላገኘነው የጋራ ነፃነታችን ለመታገል ተስማምተናል።
  2. ዋናው የጋራ ጠላታችን ሰው መሆኑን ተረድተን ማንኛውም ሰውን የሚመለከት ምሥጢር ከመኻከላችን ሳይወጣ እንዲጠበቅ ማድረግ እንዳለብን ተስማምተናል። ለጋራ መብታችንና ኅልውናችን ስንል ማናቸውንም ጠላትን የሚመለከት መረጃ በወቅቱ ለመለዋወጥ ተስማምተናል።
  3. ዋናው ጠላታችን ማናቸውንም ጥቃት በአንደኛችን ወገን ላይ ቢፈጽም ሁላችንም ባለን አቅም ሁሉ በጋራ ለመከላከልና ብሎም በማጥቃት ይህን የጋራ ጠላታቻንን ለማንበርከክ ቆርጠን ተስማምተናል።
  4. በመካከላችን መከፋፈል እንዳይፈጠር፣ ሁላችንም ነቅተን ሕፃን፣ ሴት፣ ሽማግሌ አሮጊት ጎልማሳ ሳይቀር በዚሁ ጉዳይ እንዲያምኑ በየበኩላችን የዕለት-ተዕለት ከፍተኛ ዘመቻ ለማድረግ ተስማምተናል።
  5. በያለበት ያለው ጭቁን ፍጡር ሁሉ ለአንድ የጋራ ዓላማ መቆም የሚችለው ከልብ ሲከበርና ስለመከበሩም በተግባር ሲያይ ስለሆነ፣ በችግርና በውርደት መኖራችን እንዲቀርልን እንደምንፈልግ ሁሉ ፣ እንደኛ የተጨቆኑ ፍጡራንን በሙሉ መብታቸውን አውቀንላቸውና አክብረናቸው በጋራ ነፃነቱ መንገድ እንዲያምኑና ከጭቆናው ለመላቀቅ በውዴታቸው ከጎናችን እንዲሰለፉ የየበኩላችንን ጥረት ሁሉ ለማድረግ ተስማምተናል።
  6. ከዛሬ ጀምሮ ለዘመናት በመካከላቻን የነበረው ቂም ሁሉ እንዲቆም፤ አንዱ ወገን የሌላውን ዘር በመጥላት በጥላቻ ስም መጠራራታችን እንዲቀር፤ በየትኛውም ቀበሌና መንደር አንዱ የሌላውን ስም እንዳያጠፋ፤ ሁላችንም በየበኩላችን ለጋራ መብታችንና ክብራችን በመቆም ይህንንም  አውቀን ልጆቻችንና በተሰቦቻችንን ለማስተማር ተስማምተናል።
  7. ከላይ ከተጠቀሱት ውስጥ እንደሁኔታው በሚያስፈልግበት ሁሉ በየኩላችን ዳይረክተሮችን፣ መምሪያዎችንና ቡድኖችን አቋቁመን እንዳስፈላጊነቱ ግንኙነቶችን በማድረግ ለመተባበር ተስማምተናል።
  8. አንዱ ወገን በሌላው ወገን ጣልቃ ሳይገባ፤ እያንዳንዳችን ወገኖች በውስጣችን ያለውን ጉዳይ በየራሳችን የውስጥ አመራር ለማስተዳደርና በውስጣችን አጥፊም ቢኖር በየራሳችን የውስጥ ሕግና ደንብ መሠረት እርምጃ ለመወሰድ እንደምንችል ተስማምተናል።
  9. እንደወንዝ ያሉትን የተፈጥሮ ሀብቶችና ከአንድ ዳር ወሌላ ዳር የሚወስዱ መንገዶችን በጋራና በእኩልነት የመጠቀም መብት እንዳለን ተስማምተናል።
  10. እኛ ዝንጀሮና ዉሻ የተባልን ጭቁን ፍጥረቶች ሰው እንደኛው ፍጡር መሆኑን አውቆ እስከዛሬ የፈጸመብንን በደል ተረድቶና ባደረገው ጥፋት ተጸጽቶ የሚያምንበት ደረጃ መድረሱን በጋራ ስናረጋግጥ በኛም ሆነ በማናቸውም ጭቁን ፍጥረታት ላይ ምንም ዓይነት ጥቃት ወይም የበቀል እርምጃ እንደማይወስድ ሲረጋገጥና ለፍትሕ ተገዥ ሲሆን፤ የሰው ዘር ሁሉ ከኛ ከጭቁን ፍጥረታት እኩል በነፃነት መኖር እንደሚችል እናምናለን።

 

“ሰውን ማመን ቀብሮ ነው”

 


ድር ቢያብር አንበሳ ያስር! –በተክሉ አባተ (ዶ/ር)

$
0
0

unityታሪካዊ የለውጥ ጎዳና ለኢትዮጵያ በሚል ርዕስ በአገራችን እየተደረገ ያለው የሕዝብ ተቃውሞ አስፈላጊና አበረታች እንደሆነ ሞግቻለሁ። የትግሉም ዓላማ እውነተኛና ዘላቂ ዴሞክራሲና ነጻነት ማስፈን እንደሆነም ከሕዝቡ መፈክሮች በመነሳት አትቻለሁ። በተጨማሪም መንግስትና ደጋፊዎቹ፣ ትግሉን በማካሄድ ላይ ያለው ሰፊው ሕዝብ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት ተቋማትና የመገናኛ ብዙኅን ይህን መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ልዩና ላቅ ያለ አስተዋጽዖ ማድረግ እንዳለባቸው ጠቁሜያለሁ። ሕዝቡ የትግሉ ባለቤትና ኦዲተር ሆኖ ሥራ አሥፈጻሚ አካል ወይም ልዩ ብሄራዊ ኮሚቴ መምረጥ እንዳለበትም ለማሳየት ሞክሬ ነበር። በመጨረሻም ኮሚቴው ለምንና እንዴት መመረጥ እንዳለበት ለመነሻ ያህል ጥቂት ነጥቦችን አንስቻለሁ። በዚህ ጽሑፍ ደግሞ ይህ ለውጥ አስተባባሪ ኮሚቴ እንዴት እንደሚመረጥና የትግል መርሆቹና ስልቶቹ ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ዘርዘር አድርጌ አቀርባለሁ።

እስካሁን ድረስ እንደታዘብነው ከሆነ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፍጹም ውህደት እንዲፈጥሩ መጠበቅ የሚከብድ ይመስላል። ያለው ብቸኛ አማራጭ እያንዳንዱ ፓርቲ የራሱን ምንነትና ማንነት እንደያዘ የጋራ ፕሮጀክቶችን መንደፍ ነው።: ይህም ማለት ፓርቲዎች ስማቸውንና የራሳቸውን ፕሮግራም እንደያዙ በጋራ ሊሠሯቸው የሚገቡ ጉዳዮችን አብሮ መለየትና መሥራት ነው።: ሁሉም የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ባይቻል አብዛኛው ተገናኝቶ  መወያየትና ሁሉንም የሚወክል አስተባባሪ ግብረ ኃይል ማቋቋም ወሳኝ ነው። ግብረ ኃይሉ ለውጥ እስኪመጣ ትግሉን በበላይነት ይመራል። አመቺና ውጤታማ የትግል ስልቶችን ለይቶ ለሁሉም ፓርቲና ለሕዝቡ በተለያዩ መንገዶች ይፋ ያደርጋል። የሚመረጡት የትግል ስልቶች በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች በአንድ ጊዜ ሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል። ተፈጻሚነታቸውን ይከታተላል። የቋንቋና የባህል ልዩነት ስላለ እያንዳንዱ ፓርቲ የራሱ አባላትና ደጋፊዎች የሚበዙበትን አካባቢ በዋናነት ሊያስተባብር ይችላል።

የሚመረጡት የትግል ስልቶች (ለምሳሌ የተቃውሞ ሰልፍ፣ ማእቀብ ማድረግ፣ ማግለል፣ ወዘተ) በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች አንድ ላይ መደረግ አለባቸው። ይህ ከሆነ የተቃዋሚው ጎራ ይበልጥ እየተባበረ እንደሄደ ሕዝብና መንግስት ያውቃሉ። አስገዳጅና አማራጭ ኃይል እንዳለም አመላካች ይሆናል። በሁሉም ቦታ አንድ ላይ የሚደረጉ ትግሎች የፖሊስንና የካድሬውን ስምሪት ያሳሳዋል። ይህም ሊከሰት የሚችለውን የተለመደ ግድያና ዱላ እንዲሁም አፈና በእጅጉ ይቀንሰዋል። መንግስት የፍርሃት መጠኑን እንዲጨምርና ሕዝብን እንዲያዳምጥ ያስገድደው ይሆናል።

ወሳኝ ተግባራት

ለሕዝብ ቆሜአለሁ የሚል ትክክለኛ ፓርቲ በሚከተሉት መሠረታዊ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋም ይኖረዋል ተብሎ ስለሚታሰብ አስተባባሪ ግብረ ኃይሉ በቀጣይነት የሚደረጉ ሰላማዊ ትግሎች እነዚህንና ሌሎችንም ጥያቄዎች ያማከሉ እንዲሆኑ ማድረግ ይችላል። በሌላ አባባል የትግሉ ዓላማ የኢትዮጵያዊያንን መብትና ነጻነት ማምጣትና ሁሉንም በአንድነት አቅፋ የምትሄድ ፍጹም ዴሞክራሲያዊት አገር መገንባት ነው። ይህን ዓላማ ለማሳካት ቀጥለው የተዘረዘሩትንና ሌሎችንም ጥያቄዎች ማንሳትና ለነሱም አጥጋቢ መልስ ማግኘት ወሳኝነት አለው።

  • ሕገ መንግስቱን የሚጻረሩ ሕጎች መመሪያዎችና ደንቦች ይሻሩ
  • ነጻና ገለልተኛ የፍትህ ሥርዓት ይቋቋም
  • ምርጫ ቦርድ ከመንግስት ተጽእኖ ይላቀቅ
  • ሃሳብን በነጻነት መግለጽ ይፈቀድ
  • መንግስታዊ አሸባሪነት ይቁም
  • ፓርቲዎች በነጻ የመሰብሰብና ሰልፍ የመውጣት መብታቸው ይጠበቅ
  • የፖለቲካ  እስረኞች ያለቅድመ ሁኔታ ይፈቱ
  • መንግስት በሃይማኖት ተቋማት የሚያደርገውን ጫና ያቁም
  • በሙስና የተጨማለቁ ባለሥልጣናት ለፍርድ ይቅረቡ
  • የመከላከያ ፖሊስና ደኅንነት መስሪያ ቤቶች ብሄራዊ ተዋጽኦ ይኑራቸው ለሕዝብም ይቁሙ
  • ሁሉን አቀፍ ብሄራዊ መግባባትና እርቅ  ይደረግ
  • የሽግግር መንግስት ተመስርቶ ትክክለኛና ነጻ ምርጫ ይካሄድ ወዘተረፈ

የትግል ስልቶች

ለመነሻ ያህል ወይም ለምሳሌ ይሆን ዘንድ አስተባባሪ ግብረ ኃይሉ ቀጥለው የተዘረዘሩትን የትግል ስልቶች ደረጃ በደረጃ ሥራ ላይ ሊያውል ይችላል።

  • ጥርት ያለ የትግል ቅደም ተከተልና ስልት በጋራ መንደፍና ፕሮግራሙንም በተለያዩ  ቋንቋዎች አዘጋጅቶ ለሕዝብና ለፓርቲ አባላት ማሳወቅ የትግሉን መጀመር ለማብሰርና ቆራጥነት ያለው አስተባባሪ ግብረ ኃይል እንተመሰረተ ለማሳየት ሕዝብን ሳይጨምር የሁሉም ፖለቲካ ፓርቲዎች ሥራ አመራሮች ሥራ አስፈጻሚዎችና ሌሎች የፓርቲዎች የቢሮ ሠራተኞች ያሉበት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ ማካሄድ፣ በሰልፉ ላይ እያንዳንዱ ፓርቲ አርማውንና በጋራ የሚዘጋጁትን መፈክሮች መያዝ
  • መንግስት በሰልፉ ወቅት የሚጠየቁትን ጥያቄዎች በተመለከተ መልስ የሚሰጥበት የተወሰነ ጊዜ ገደብ ማስቀመጥ
  • ሰልፉን በቪዲዮ ቀርጾ በማኅበራዊ ሚዲያዎች መልቀቅ በጽሑፍም ማዘጋጀትና መበተን
  • መንግስት በተሰጠው ጊዜ ውስጥ አጥጋቢ መልስ ካልሰጠ በዋና ዋና ከተሞች (ለምሳሌ በአዲስ አበባ፣ በናዝሬት፣ በአዋሳ፣ በጅማ፣ በዲላ፣ በነቀምት፣ በደሴ፣ በባህር ዳር፣ በጎንደር፣ በመቀሌ፣: በደብረ ማርቆስ፣ በአሰላ፣ በሐረር፣ በድሬዳዋ፣ በሰመራ፣ በጋምቤላ፣ በአሶሳ፣ ወዘተ) ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ በአንድ ቀን ውስጥ ማካሄድና የሰልፉን የአቋም መግለጫ ለመንግስት በጽሑፍ መስጠት፣ አጥጋቢ መልስ መንግስት በተወሰ ጊዜ ውስጥ እንዲሰጥ ማሳሰብ
  • መንግስት በተሰጠው ጊዜ ውስጥ አጥጋቢ መልስ ካልሰጠ በግብረ ኃይሉ አማካኝነት በጥንቃቄ በሚመረጡ ጥቂት ከገዥው ፓርቲ ጋር ግንኙነት ባላቸው ወሳኝ ተቋማት ላይ ብሄራዊ ማእቀብ መጣል፣ ማእቀቡ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ቀድሞ መወሰንና መንግስት በዚያ ጊዜ ውስጥ መልስ እንዲሰጥ ማስገደድ
  • መንግስት በተሰጠው ጊዜ ውስጥ አጥጋቢ መልስ ካልሰጠ ህዝቡ በአስተባባሪ ግብረ ኃይሉ በዝርዝር የሚቀርቡትን ሁሉንም ንብረትነታቸው የገዥው ፓርቲ የሆኑ ድርጅቶች (ባንኮችን ጨምሮ)  ላይ ማእቀብ መጣል
  • አሁንም መንግስት ለህዝብ ጥያቄ መልስ የማይሰጥ ከሆነ በመላ ኢትዮጵያ በአንድ ቀን ያመረረ ሰልፍ ማድረግ፣ መንግስት ጥያቄዎችን እንዲመልስ ዳግም ማሳሰብ
  • አጥጋቢ ምላሽ ከመንግስት እስኪገኝ ድረስ እንደአስፈላጊነቱ ስልትን እየቀያየሩ (ለምሳሌ ካድሬዎችንና ባለሥልጣናትን ከማህበራዊ ሕይወት ማግለል፣ መንግስት በሚጠራቸው ስብሰባዎች አለመገኘት ወይም ተገኝቶ ጆሮንና አፍን መዝጋት፣ ተቀማጭ ገንዘብን ከባንክ ማውጣት፣ በጭቆና ምክንያት ለታሰሩት ለተደበደቡት ለተሰደዱት ለጠፉት በህብረት ሻማ ማብራትና ሥራቸውን ለሕዝብ ማቅረብና ለውይይት ማብቃት፣ የተቀናጀ ሥራ ማቆም አድማ ማድረግ፣ ትግሉን በሁሉም የአገሪቱ ክፍል መቀጠል…
  • የስለላ ሥራ በመንግስት ባለሥልጣናትና በካድሬዎች ላይ ማካሄድና መጥፎ ሥራቸውን በተለያዩ  መንገዶች ለሕዝብ ይፋ ማድረግ
  • እውነታ ላይ የተመሰረተ የፕሮፓጋንዳ ሥራ መሥራት፣ የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ሕዝብን በመረጃ ማንቃት
  • በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የትግሉ አካል ስለሆኑ በንቃት ማሳተፍ
  • ለመንግስት የሚላኩ ውሳኔዎችን የአቋም መግለጫዎችን እንዲሁም ሥራ ላይ ያሉ የትግል ስልቶችን ለዲፕሎማቶች ማሳወቅ
  • ይህ ሁሉ ሲደረግ የመንግስት ባለሥልጣናትና ደጋፊዎች ሕዝቡን መቀላቀል ቢፈልጉ ይቅርታ እየጠየቁ እንዲቀላቀሉ ማድረግ

ማጠቃለያ

ይህ ሁሉ ሲደረግ መንግስት ዝም ብሎ አይቀመጥም።: ከአስተባባሪ ግብረ ኃይሉ እየቀደመ የማስታገሻና የማርከሻ እርምጃዎችን ሊወስድ እንደሚችል ግልጽ ነው። በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ልዩነት እንዲኖር ያደርጋል።: የትግሉን አስተባባሪዎች ሊያስር ሊያንገላታ ሊገድልም ይችላል። ሕዝቡንም ሊያስፈራራና ሊደበድብ ሊያስርም ይችላል። ይህ ሁሉ ሊመጣ እንዳለው ቀደም ብሎ መገመትና መስዋእት ለመክፈል መዘጋጀት ያስፈልጋል። ለውጥ ባጭር ጊዜም ሊመጣ ስለማይችል የተለያዩ  ስልቶችን በቀጣይነት መጠቀም ወሳኝ ነው። ሕዝብን የማንቃትና የማረጋጋት ሥራ ግን የሁል ጊዜ ተግባር ሊሆን ይገባል።

 

የፖለቲካ ፓርቲዎች ፍጹም ውህደት እንዲመጣ ከሚጥሩ ይልቅ ከላይ በተጠቀሰው መንገድ ቢጓዙ ውጤታማ ይሆናሉ። እንደ ድር ቀጥነው የሚታዩት የፖለቲካ ፓርቲዎች በወሳኝ የለውጥ ሥራዎች ላይ የሚተባበሩ ከሆነ እንደ አንበሳ አይሎ የሚታየውን መንግስትንና ታጣቂ አካሉን ሁሉ ሊያሸንፉ ይችላሉ። ድር ቢያብር አንበሳ ያስር ይባል የለ!

 

 

ማሳሰ:- ይህ ጽሑፍ የዛሬ ሁለት ዓመት ሰላማዊ ሕዝባዊ ትግል! በሚል ርዕስ ከጻፍኩት የተወሰደ ነው። ጥቂት ማሻሻያ ግን አድርጌለታለሁ!

 

ገንቢ አስተያየት ካለዎት በteklu.abate@mail.com ይላኩልኝ!

 

አዲስ አበባ : የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ

$
0
0

14102347_10206973158153743_6094082353928561593_nአዱ ገነት የምድር እምብርት ፥ የፍቅር አድባር ፥ የመተሳሰብ እና ያንድነታችን መቀነት። የህብረታችን ዜማ ፥ የውህደታችን ቅኔ ፥ ጅረት ከሚፈስበት ሰፈር ነው የተፈጠርኩት እኔ ! አዲስ አባባ ፥ እስላሙ እና ክርስቲያኑ ድርጅት ሳይሆን ህይወት ፥ ጥርነፋ ሳይሆን ኑሮ ባስተሳሰረው ፥ ታሪክ ባመሳሰለው የማንነት ፍሰት ውስጥ ባንድነት ዧ ብሎ የሚፈስ የብርሃን ጎርፍ የሚመስል ህዝብ ያለበት ከተማ! አዲስ አበባ ። አዲስ አባባ ወንድሞቼ ፥ እህቴ ፥ እናት እና አባቴ የሚኖሩበት ፥ እንዲህ ትግል ሲኖር ደግሞ ታግለው የሚሞቱባት ከተማ ነች ! የልጅነት አሻራዬን ፥ የእግሮቼን ዱካ እየለካች ያሳደገችኝ መንደሬ ያለችው እዛው አዲስ አበባ ነው ። ለፋሲካ እና ለኢድ የሁለት እምነት ድስት የተጣደባት መንደር አዲስ አበባ ነች ። የወያኔን ገበና ፍንትው አድርጋ ማንነቱን ገሃድ ያወጣች ከተማ አዲስ አበባ ነች ። አዲስ አበባ የታጋዮች ከተማ!
አዲስ አባባ የኔ ሰፈር! በተዘጉ ቤቶች ውስጥ መፅሃፍ ስናጥብ ያደርንብሽ ከተማ። ወያኔ ላይ ስናሴር የዋልንብሽ ሰፈር ። የማንተቴን ትዝታ አቅፈሽ የያዝሽ ፥ እኔን የሰራሽ ፥ የኄኖክ ደጀ ሰላም ፥ አዱ ገነት ! ከጎንሽ ቆመን እጃችንን ባናወጣም ፥ ላንቺ የሚሆን አንድ ዘለላ አንጓ ቅኔ ግን አናጣም!
አዲስ ነውና ስምሽ
አዲስ ሁኝ እባክሽ!

የዲሞክራሲ ቀለሞች –ከሽግግር እስከ ችግግር! –ዳዊት ከበደ ወየሳ (አትላንታ –አሜሪካ)

$
0
0
(ኢትዮጵያ ውስጥ በሚታተመው “አዲስ ገጽ” መጽሄት ላይ ወጥቶ የነበረ ጽሁፍ ነው)
 
በሽግግሩ መንግስት ወቅት የጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ፤ ከፓርላማው ወረድ ብሎ፤ ከቤተ መንግስቱ በአጓዳኝ፤ ወይም ወደ ግቢ ገብርኤል መሄጃ ላይ ይገኝ ነበር። ያን ሰሞን ከበአላት ወይም ቅዳሜና እሁድ በቀር የአዘቦት ቀናት በሰልፍ ይሞላሉ። ጋዜጦችና ጋዜጠኞች የየእለቱ ዘገባቸው ስለተደረጉት ዲሞክራሲያዊ ሰለሰልፎች ብቻ ሆነ። በኋላ ላይ የሰልፈኞቹ ነገር ቀስ በቀስ እየቀነሰ መጣና ነገሩ ቀዘቀዘ። ያን ሰሞን በሆነ ባልሆነ ሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉም አልታጡም።
አንድ ቀን ፓርላማው ጋር ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የተሰበሰቡ ሴቶችን የሚበትን የወያኔ ዋርድያ አጋጠመን። ሴቶቹን “ሂዱ” ሲሏቸው፤ “ዲሞክራሲያዊ መብታችን ነው። ደርግ ያፈነን አነሰና እናንተም…” እያሉ አንጃ ግራንጃ ሲፈጥሩ፤ የወያኔዎቹ አለቃ ድምጹን ከፍ አድርጎ… “ካላስ ተበተኑ!” ብሎ ንግግር ጀመረ።
 “ቧ አልግሱ! ዲሞክራሲ ተወዲኡ!” ወይም በአማርኛ ትርጓሜው “በቃ ዞር በሉ! ዲሞክራሲ አልቋል” አላቸው። ይሄንን በወቅቱ በስፍራው ሆነን የታዘብን ጥቂት ሰዎች፤ በነገሩ ስቀን አለፍን። እየቆየን ስንመጣ ግን… ‘እውነትም ንፉግ መንግስት ነው ያለን፤ ለካ ዲሞክራሲም እንደ ስኳር ሬሽን ያልቃል!’ ብለን መገረማችን አልቀረም።
 
በአጠቃላይ “የሴቶች መብት ይከበር” ከሚለው ጥያቄ ጀምሮ “የኢትዮጵያ ዳር ድንበር ቀይ ባህር ነው” እስከሚሉት መፈክሮች ድረስ ያስተናግድ የነበረው የአራት ኪሎ መንገድ ቀስ በቀስ ጭር እያለ መጣ። የሁለት አመቱ የሽግግር መንግስት ሲያበቃ የኛም ሰላማዊ ሰልፎች አበቁና ከሽግግር ወደ ችግግር በሰላም ተሻገርን። በችግግሩ ዘመን ቀስ በቀስ ወደ ሰላማዊ ኑሮ ተመለስን። ከሰላማዊ ኑሮ ወደ ሰላማዊ ትግል ስንሸጋገር ግን…  መንግስት እና የመብት ጥያቄ ምን እና ምን እንደሆኑ ገና በጠዋቱ ተረዳነ – እነዚያ ፈቃድ እና ፈቃጅ ሳያስፈልጋቸው የተደረጉ ሰላማዊ ሰልፎችም፤ የሽግግሩ መንግስት ለሁለት አመታት እራሱን እንዲያረጋጋና ግዜ እንዲገዛ ረዱት እንጂ፤ ለህዝቡ አንዳች ነገር ጠብ አላለትም።
 ———————–//—————————-
የዲሞክራሲ ቀለሞች – ከሽግግር እስከ ችግግር!
ዳዊት ከበደ ወየሳ (አትላንታ – አሜሪካ)
ethiopia
ኢህአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ… የ”አትነሳም ወይ?!” መዝሙሮች ተደምጠዋል፤ በርካታ የተቃውሞ ሰልፎች እና የስራ ማቆም አድማዎች ተደርገዋል። የተቃውሞ ሰልፉ ከመብዛቱ የተነሳ ሁሉንም መዘርዘር ያታክታል። ለምሳሌ “የአጼ ምኒልክ ሃውልት ይፍረስ” የሚሉ ሰዎች ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ። ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የሃውልቱን ዙሪያ በጥቁር ጨርቅ ሸፈኑት። ይህ ዜና ተብሎ በሬድዮ እና በቴሌቪዥን ቀረበልን።
ከዚህ በኋላ የኢህአዴግ ሹማምንት የህዝቡን የጩኸት ትርታ ለማዳመጥ ጸጥ ሲሉ፤ እኛ ደ’ሞ ‘ሃውልቱን በመድፍ እናፍርሰው ወይስ በቦንብ እንናደው ወይስ ዲሞክራሲያዊ መብቱን ጠብቀን በገመድ ጎትተን እንጣለው?’ እያሉ ብበምት የሚንሾካሾኩብን መሰለን። እንደእውነቱ ከሆነ ግን… ኦህዴድ እና ህወሃት በሃውልቱ መፍረስ ቢስማሙም፤ ኢህዴን (የአሁኑ ብአዴን) ሃሳቡን በመቃወም የራሱን ስብሰባ አደረገ። በዚህ ታሪካዊ ስብሰባ ላይ፤ “እኛ የታገልነው የምኒልክን ሃውልት ለማፍረስ ነው ወይ?” የሚል በሲቃ የታጀበ ንግግር ተደመጠ።
በዚህ ሁሉ ውዝግብ መሀል ግን… እኛ ጋዜጣችንን ለማሳተም የብርሃን እና ሰላም ማተሚያ ቤትን ደጀ ሰላም ስንጠና፤ በድንገት ታይቶ የማይታወቅ የኦሮሞ ፈረሰኞች ከኮተቤ፣ ከሱሉልታ እና ከሰላሌ ተሰባስበው… የአጼ ምኒልክ እና የእቴጌ ጣይቱን ፎቶ ከፊት ለፊት ይዘው፤ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማን እያውለበለቡ አራት ኪሎን አቋርጠው፣ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በኩል አድርገው፤ ራስ መኮንን ድልድይን ተሻግረው፤ ወደ ምኒልክ ሃውልት  ተጓዙ። ብዙዎቻችን የዚህን ጉድ መጨረሻ ለማየት ፈረሰኞቹን ተከተልናቸው። ፈረሰኞቹ አራዳን አልፈው ከአጼ ምኒልክ ሃውልት ዘንድ ሲደርሱ ሃውልቱን ክብ እየዞሩ ቀረርቶ እና ጌራርሳ እያሰሙ፤ ከጥቂት ቀናት በፊት ሃውልቱ የተሸፈነበትን ጥቁር ጨርቅ ቀደው እና ቀዳደው ጣሉት። (ይህን ለምስክርነት የምንናገረው በወቅቱ  ኢዜአ ያልዘገበው… ህዝቡ በአይኑ የታዘበው፣ የሴቶች እልልታ የወንዶች ፉጨት ያጀበው ታሪካዊ ትእይንት ስለነበር ነው)
ከዚያ በኋላ እንኳንስ ሃውልቱ ሊፈርስ ቀርቶ፤ ጭራሽ ወርቃማ እና ብርማ ቀለም እንዲቀባ አደረጉ – ህዝቡና የልጅ እያሱ ልጅ።
አጼ ምኒልክ በያዙት ጦርም ላይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ተደርጎበት፤ ቢያንስ ለብዙ ወራት ቆየ። በጨዋታችን መጀመሪያ ላይ ይህን ጉዳይ የምናነሳሳው… የህዝብን ሃያልነት ማሳያ ምስክር እንዲሆነን ጭምር ነው። ሆኖም የዲሞክራሲ ቀለም ደምቆ እንዲዋብ ህዝቡ መብቱን አውቆ ማስከበር መቻል አለበት። አስቡት። በሽግግር መንግስቱ ዘመን የአጼ ምኒልክ ሃውልት ፈርሶ ቢሆን ኖሮ፤ እንደሌኒን ሃውልት የት እንደደረሰ ላይታወቅ ይችል ነበር። ክብር ሃውልቱን ለታደጉ ጀግኖች ሁሉ ይሁን።
እንዲህ የአገር ቅርስን በሰላማዊ ሰልፍ የማስተረፍ ስራ የመሰራቱን ያህል፤ ፈገግ የሚሰኙ አይነት ሰልፎችም ተካሂደው ነበር። ከእነዚህ አንዱ ጭር ሲል የማይወደው ኢህአዴግ ያዘጋጀው የህጻናት ሰላማዊ ሰልፍ ነው። ሰልፉ በሴቶች ቢሮ በኩል አድርጎ ለአደባባይ የበቃው፤ የእናት ጡት ወተትን አስፈላጊነት ግንዛቤ ለመፍጠር በሚል ነበር። እናም አንድ ቀን የአካባቢው ትምህርት ቤቶች ተዘግተው… የህጻናት ሰልፍ አራት ኪሎን እንዲያጨናንቅ ተደረገ። የህጻናቱም ጥያቄ አንድ እና አንድ ብቻ ሆነ። አንዷ “የእናት ጡት ለህጻናት!” ስትል ሁሉም በአንድ ድምጽ “የእናት ጡት ለህጻናት” እያሉ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ግቢ ደረሱ።
ከያዙት መፈክር ጎን፤ የተዘቀዘቁ ትላልቅ የጡጦ ስዕሎች አሉ። ሁሉም ደግመው ደጋግመው “የእናት ጡት ወተት ለህጻናት፡፡” የሚለውን መፈክር እንደውዳሴ ማርያም ይደጋግሙታል። እንዲህ እንዲህ እያሉ በጠቅላዩ ሚንስትር ደጃፍ ትንሽ ቆዩ። በኋላ ላይ የቴሌቪዥን ጋዜጠኞች በስፍራው መኖራቸውን ካረጋገጡ በኋላ የጠቅላይ ሚንስትሩ ተወካይ ሽክ ብለው መጡ። እንዲህም አሉ።
 “እርግጥ ነው። ህጻናት የእናት ጡት ወተት ያስፈልጋቸዋል።” ካሉ በኋላ የጠቅላይ ሚንስትሩ ተወካይ…የእናት ጡት ወተት ለህጻናት አስፈላጊ መሆኑን አስረዱ። “አሁንም የእናት ጡት ለህጻናት አስፈላጊ መሆኑን ስለተረዳን፤ የሽግግር መንግስቱ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርግላችኋል።” ሲላቸው ከህጻናቱ ጋር የመጡት እናቶች አጨበጨቡ፤ ህጻናቶቹም ተንጫጩ። የሽግግር መንግስቱን አመስግነው ከመበተናቸው በፊት፤ ጋዜጠኞች ለአንዳንድ ህጻናት ጥያቄ አቀረብን።
“ጥያቄያቹህ የእናት ጡት ወተት ማግኘት ነው። አሁን እንደሰማነው ‘የሽግግር መንግስቱ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል’ ተብሏል። እንዴት ታዩታላቹህ?” አልናቸው።
አንደኛው ህጻን ተገርሞ እኛንም ጓደኞቹንም እያየ፤ “የሽግግር መንግስቱ ጡት አለው እንዴ?” ሲል፤ እኛም ሆንን ጓደኞቹ ዛሬም ድረስ ያልመለስነውን ጥያቄ አቀረበልን።
እንዲህ አስቀው የሚያስቁንን ሰላማዊ ሰልፎች ወደ ጎን ትተን… ወደኋላ ተመልሰን ስንመለከት ግን… ከምንወቃቀስበት ጉዳይ ይልቅ የምንሞጋገስባቸው ጉዳዮች ብዙ አሉን። ከምንም በላይ “ጨርቅ” ተብላ የተንቋሸሸች ሰንደቅ አላማችን፤ ከወደቀችበት ተነስታ ከፍ ብላ መውለብለቧ ይሰመርበት።
በሽግግሩ ዘመን… የወቅቱ የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ ቡትሮስ ቡጥሮስ ጋሊ አዲስ አበባ መጥተው ነበር። የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችም “ኢትዮጵያ ህጋዊ የባህር በር ያስፈልጋታል” የሚል መሰረታዊ ጥያቄ ያነገበ ደብዳቤ አዘጋጅተው ሰላማዊ ሰልፋቸውን ስድስት ኪሎ ላይ ጀመሩ።
ሰልፉ ተጀምሮ ገና ከግቢው እንደወጡ አንድ ተማሪ ተገደለ (ተስፋሁን ይመስለኛል የተማሪው ስም)። ይህን ተከትሎ ብዙዎች ተደበደቡ፤ አካላቸውም ጎደለ። ምሽቱን በተላለፈው ዜና፤ የተገደለው የዩኒቨርስቲ ተማሪ የቀድሞ ደርግ ኢሰፓ የነበረ መሆኑን ሳያፍሩ ተናገሩ። ከዚያ ሁሉ ሺህ ህዝብ መሃል… “ኢሰፓ የሆነውን ነጥሎ የሚገድል ጥይት አለ እንዴ?” ብለን ተገርመን ሳናበቃ፤ “እንዲያውም ሟቹ ትምክህተኛ አማራ ነበር” አሉን። ቀጥሎም የወቅቱ ፕሬዘዳንት መለስ ዜናዊ በቲቪ ቀርበው እንዲህ አሉ።
“እኛ ሰልፈኞቹን በአስለቃሽ ጢስ ብንበትናቸው ደስ ይለን ነበር። ሆኖም ከደርግ መንግስት የተረከብነው አስለቃሽ ጢስ ሳይሆን፤ ታንክ እና ሚሳየል ነው።” ብለው የመጀመሪያ ቀልዳቸውን ከምር ነገሩን። እንደሳቸው አባባል፤ “እንደውም እኛ ሰልፉን በጥይት ስለበተንን ልንመሰገን ይገባል። ደርግ ቢሆን በታንክ ይረመርማቸው ነበር” የሚል አንደምታ ያለው ንግግር ነበር – ያሰሙን።
በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የሚከፈተው የጠመንጃ ላንቃ ግን፤ በተስፋሁን ላይ ተጀመረ እንጂ አላበቃም። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ፤ ምንም ያላደረጉ ሰላማዊ ዜጎች በጠራራ ጸሃይ ጥይት እየተርከፈከፈ ተገድለዋል – “ክብር ለነሱ ይሁን” ሌላ ጉዳይ እናውጋ።
ከሽግግሩ ዘመን በኋላ “አባይ ተገንብቶ ለልማት ይዋል።” ስንል፤ በረከት ስምኦን ራሱ ቃል በቃል እንዲህ ብሎን ነበር። “በአባይ ወንዝ ላይ ግድብ ስሩ የሚሉ ቅዠታሞች አሉ። አባይ ቢገነባ ኢትዮጵያ በውሃ ተጥለቅልቃ እናልቃለን እንጂ፤ ምንም አናተርፍም።” ብሎ መግለጫ ጭምር ሰጥቶ ነበር። በኋላ ላይ የአባይ ግድብ ግንባታ ሲታወጅ፤ በረከት ስምኦን ዋና ተዋናይ ሆኖ፤ ጉዳዩን ለፖለቲካ ጥቅም ሲመነዝረው እያየን… “ወይ ግዜ” ያልንበት ወቅት እሩቅ አይደለም። በዚያም ተባለ በዚህ ግን ለሰንደቅ አላማችን ከፍ ማለትም ሆነ፤ ለአባይ መገደብ ትልቁ ምክንያት ሳያሰልስ ይታገል የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ፤ አብዮታዊ ዲሞክራሲ አለመሆኑን እነሱም ያውቁታል፤ እኛም እንመሰክራለን። በመሆኑም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ህዝባዊ መብቱን ተጠቅሞ  የዲሞክራሲው ቀለም እንዲደምቅ፤ የህዝብ ፍላጎት እንዲጠበቅ ያደረገው የኢትዮጵያ ህዝብ… ከምንም በላይ ሊመሰገን ይገባዋል።
ከሽግግር መንግስት እስከ ችግግር ዘመናችን ድረስ ብዙ አሳልፈናል። አሁንም በትዝታ ወደ ሽግግሩ መንግስት ዘመን እንውሰዳቹህ። ከሃያ አመታት በፊት ነው። ብዙዎቹ ሰልፈኞች መፈክር እያሰሙ ወደ ጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ ያመራሉ። በወቅቱ ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩት አቶ ታምራት ላይኔ ናቸው። ሰልፈኞቹ በመፈክራቸው መጀመሪያ  እና በደብዳቤያቸው መጨረሻ ላይ “የሽግግር መንግስቱን ቻርተር እንደግፋለን” የሚል ሙሻሙሾ የሚያወርዱ ከሆነ፤ የሰልፈኞቹ ተወካዮች ወደ ውስጥ እንዲገቡ ያደርጉና ያናግሯቸዋል።
ሰልፉን እራሱ ኢህአዴግ ያቀናበረው ከሆነ ደግሞ ሃያ እና ሰላሳ ሰው ያለበትም ቢሆን፤ በሬድዮ፣ በቲቪ፣ በጋዜጣም ጭምር ስለሰላማዊ ሰልፉ ብዙ ይባልለታል። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ከሚሆኑት መካከል፤ “ፓትርያርኩ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ሰላማዊ ሰልፈኞች ጠየቁ” የሚለው ዜና አንደኛው ነበር።
በምሽቱ ዜና ላይ… “ፓትርያርኩን በመቃወም ከወጡት ሰልፈኞች መካከል አንዳንዶቹ እንዲህ በማለት አስተያየት ሰጥተዋል።” ይባልና… በቃለ መጠይቁ ላይ የሚቀርቡት ሰዎች፤ “ፓትርያርኩ በደርግ ዘመን ያገለገሉ ስለሆኑ አንቀበላቸውም” ይላል አንደኛው። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ… “የደርግ ኢሰፓ አባል ናቸው” ብሎ ይከሳቸዋል። ቀጥሎ ያለው ደግሞ “ከስልጣናቸው ወርደው ለፍርድ ይቅረቡ” በማለት ይደነፋል። አቡነ መንቆርዮስም ይህን ድራማ አዘል የተቃውሞ ሰልፍ ማታ ላይ በቲቪ ሲመለከቱ ልባቸው ተሰብሮና መንፈሳቸው ተሸብሮ፤ በንጋታው ኢትዮጵያን ለቀው ወደ ጎረቤት አገር እንዲሰደዱ የተደረጉበትን፤ በ’ሳቸውም መንበር አባ ጳውሎስ እንዲተኩ የተደረገበትን ድራማ እንደትላንት የምናስታውስ ብዙዎች ነን።
በሌላ በኩል ደግሞ… የኢትዮያን ህዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች…  በማንም በምንም አይነት ተቀባይነት አይኖቻውም ነበር። ከኤርትራ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ፤ ከስራ የተባረሩ ሰራተኞች፤ ጡረታቸውን የተነጠቁ አባቶች፤ በብሄራቸው የተገፉ ዜጎች፤ ኢትዮጵያዊነትነት ከፍ አድርገው የዘመሩ የሌላ ብሔር አባሎች… የ’ነዚህ ሰዎች ጩኸት የውሃ ሽታ ሆኖ ቀርቷል። “መብታችን ይከበር” የሚሉ ድምጾች በአራት ኪሎ ጎዳና ላይ ብዙ ተደምጠዋል። አንዳንዶቹ ምላሽ ሲያገኙ፤ የተቀሩት ደግሞ ጩኸት ብቻ ሆነው ቀርተዋል። በኋላ በኋላ ላይ… የማይቀረው ህዝባዊ መዝሙር እና መፈክር የአራት ኪሎን ግቢ ሲያነቃንቀው “ጠቅላይ ሚንስትሩ ስራ ላይ ናቸው… አትጩኹ” በሚል የታጠቁ የወያኔ ሰዎች ወደላይ እየተኮሱ ጩኸቱን ይብሱን አባብሰው ሰልፍ መበተን ጀመሩ።
በጋዜጠኝነታችን የህዝቡን ድምጽ ለማሰማት፤ በስፍራው ተገኝተን ክፉና ደግ መታዘባችን አልቀረም።  ሰላማዊ ሰልፈኞች ሰፈር አቋርጠው ሲመጡ በእጃቸው መፈክር ተሸክመው፤ አንዳንዶችም ዘንባባና የዛፍ ቅጠል ይዘው ‘ሆ’ እያሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ ሰፈር ይደርሳሉ። እዚያ ሲደርሱ መጮህ ስለማይቻል ተወካዮቻቸው ወደ ውስጥ እስከሚገቡ ወይም ደብዳቤውን እስከሚያስረክቡ ድረስ፤ አገር ሙሉ ሰልፈኛ ጥላ ፍለጋ በየአጥሩ ጥግ ለሰአታት ያህል ይቀመጣል። በዚህ አይነት መሰላቸት ሰአታት ያልፉና ሰልፈኞች ወደየጉዳያቸው ይበተናሉ። ከየመንደሩ ይዘዋቸው የመጡት ቁሳቁሶች፤ የካርቶን ላይ ጽሁፎች፣ የወረቀት ስእሎች፣ የጨርቅ ላይ መፈክሮች እዚያው ይጣሉና አካባቢው እብድ የጨፈረበት ገበያ ይመስላል። ሰልፈኞቹ ከተበተኑ በኋላ ወረቀትና ጨርቁን የሚሰበስቡ ሰዎች ይመጡና ያን ሁሉ ግሳንግስ ሰብስበው ያቃጥሉታል። ልክ እንደተቃጠሉት የመፈክር ካርቶኖች… በሽግግር መንግስቱ እና ከዚያ በኋላ የተነሱ በርካታ ህዝባዊ ጥያቄዎች፤ ምላሽ ሳያገኙ ዶግ አመድ ሆነዋል። ብዙዎቹ የ”መብታችን ይከበር” ጥያቄዎች ግን ከወረቀት ባለፈ፤ በህዝብ ልብ ላይ የታተሙ በመሆናቸው በውድ ሳይሆን በግድ ተከብረዋል።
እነዚህ ተሸራርፈውም ቢሆን… ለአጭር ግዜም ቢሆን… ብልጭ ድርግም እያሉም ቢሆን… ህዝቡ እንዲከበሩለት ያደረጋቸው መሰረታዊ የመብት ጥያቄዎች… ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት፤ የመሰብሰብ እና የመደራጀት፣ በነጻ ዳኝነት ፍርድ ማግኘት፣ የሰብአዊ መብት ጥበቃ እና የህዝባዊ ስልጣን መረጋገጥ ናቸው። “እነዚህ የመብት ጥያቄዎች በተገቢው መልክ ተግባራዊ ሆነዋል” ብሎ ክርክር የሚገጥም ካለ ውሸታም እንጂ ሌላ ስም አይሰጠውም። ነገር ግን እነዚህ የዲሞክራሲ ደማቅ ቀለም የሆኑ የመብት ጥያቄዎች፤ መንግስት በቸርነቱ ሳይሆን፤ ህዝብ በእምቢ ባይነቱ ያገኛቸው የትግል ስጦታዎች ሆነዋል፤ ይህ እውነት ነው። ‘እነዚህ መብቶች በመንግስት በኩል ከመከበር ይልቅ ተሸርሽረው ተሸርሽረው እያለቁ ናቸው።’ ብንል ይህም ሌላ እውነት ነው።
እውነትን መደርደር የሚያስጣላ እና የሚያከራክር ነገር አይደለም። ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት መንግስት የሚያሳስበው ባይሆን ኖሮ፤ ሌላ ተዛማጅ እና ግራ ተራማጅ ህጎች ማውጣት ባላስፈለገው ነበር። ህገ መንግስቱ ሲረቅና ሲጻፍ ሁሉንም ወገን የሚያረካ ሆኖ አልተዘጋጀም። ቢያንስ ቢያንስ ግን… የሰው ልጅ ሰብአዊ መብቶች እንደሚከበሩ ይደነግጋል። ይህ ደግሞ በቀዳማዊ ኃይለስላሴም ሆነ በደርግ ህገ መንግስት ላይ በግልጽ የተካተተ ነው። ነገር ግን እነዚህ መሰረታዊ መብቶች በጽሁፍ እንጂ በተግባር ባልተረጋገጡባት አገር… በአሳዛኝ መልኩ ትውልድ አልፎ ትውልድ በመተካት ላይ ይገኛል። እንደእውነቱ ከሆነ… ሰብአዊ መብት፣ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት፣ የፍትህ፣ የመሰብሰብ እና የመደራጀት መብት ሙሉ ለሙሉ ያልተረጋገጠባት  አገር፤ “ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ” የሚለውን ስም ለመሸከም አቅም አይኖራትም። ይህን እያልን… መብታችን እየተበዘበዘ፤ የዲሞክራሲ ቀለም እየደበዘዘ ሊሄድ ይችል ይሆናል። ይህ ግን ለዘላለሙ አይቀጥልም። የሰው ልጅ… እስከልጅ ልጁ እየተረገጠ ሊገዛ አይችልምና… ጨለማ በጠዋት ጮራ እንደሚገፈፍ ሁሉ… የደበዘዘው የዲሞክራሲ ቀለም የሚደምቅበት ምዕራፍ ቀስ በቀስ መምጣቱ የተፈጥሮ ግዴታ ነው።
ከማጠቃለላችን በፊት የዚህን ጽሁፍ ዋና መልእክት እዚህ ላይ ለማስፈር ወደድን። ኢህአዴግ አዲስ አበባ እንደገባ ጥቂት ግዜ ቆይቶ የሽግግር መንግስት አቋቋመ። እኛም (አብዱራህማን አህመዲን እና ሙሼ ሰሙ) ጋር በመሆን “የኢትዮጵያ ወጣቶች ህብረት” የሚባል ሊግ አቋቋምን። አላማችን ወጣቱን በኢትዮጵያዊነት ዙሪያ ማሰባሰብ ነበር። እንደታሰበውም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶች ህብረቱን ተቀላቀሉ። እንቅስቃሴው አዲስ አበባን አዳረሰ። ስብሰባ የምንጠራባቸው አዳራሾች እስከአፍንጫቸው ድረስ እየሞሉ ህዝቡ በውጭ ሆኖ ስብሰባውን ይከታተል ጀመር። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ከመንግስት የምዝገባም ሆነ የስብሰባ ፈቃድ ተሰጥቶን አያውቅም። (በ’ርግጥ  ኢህአዴግ፤ በኋላ ላይ ሊጉን በጉልበት አፈረሰው) ወጣትነት ደፋር ያደርጋል። የመሰብሰብ እና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታችንን መንግስት እንዲሰጠን ስላልፈለግን እኛም በህዝብ ጉልበት መብታችንን አስከበርን። ከምንም በላይ ግን፤ “መንግስት መብት ይሰጥሃል እንጂ፤ መብትህን አያስጠብቅልህም።” የሚለው መመሪያችን ተስማምቶናል። እውነት ነው። መንግስት መብትህን በህግ እና በህገ መንግስት ላይ ጽፎ ይሰጥሃል እንጂ፤ መብትን የማስጠበቅ ሃላፊነት የሚጣለው በ’ያንዳንዱ ግለሰብ እና ማህበረሰብ ላይ ይሆናል።
መሰረታዊ መብቶቻችን በህጉ እና በህገ መንግስቱ ላይ እንዲሰፍሩ ትውልድን የተሻገረ ትግል ተካሂዷል። እነዚህን መብቶች በውድም ሆነ በግድ ተግባራዊ ስናደርግ፤ አምባገነናዊ አስተዳደር እየወደቀ፤ የዲሞክራሲ ቀለም እየደመቀ ይሄዳል። ከሽግግሩ መንግስት እስከ ችግግሩ ዘመን ድረስ የሄድንበት መንገድ… የግል እና የወል መብትን የማስጠበቅ ታሪክን የያዘ ባለብዙ ምእራፍ ታሪክ ነው። በሁሉም ምእራፎች መብታችንን ለመጨፍለቅ ጥረት ሲደረግ እንጂ ስንወድቅ አልታየንም። አሁንም ከመጨረሻው ምእራፍ በፊት የመጨረሻውን ጩኸት እየጮሁ፤ “በህግ አምላክ!” የሚሉ ደፋሮች አልታጡም። የ’ነሱ ጩኸት ከዳር እስከዳር እንዲደመጥ፤ የለኮሱት ሻማ ብርሃን እንዲሰጥ… የዲሞክራሲ ቀለሞች በብዕሮቻቸው ጫፍ እንዲደምቅ ለሚያደርጉት ትግል ህዝቡ ሊያግዛቸው ይገባል።
በአጠቃላይ ከሽግግር መንግስት እስከ ችግግር ዘመናችን ድረስ ብዙ ግዜ ወድቀን፤ ብዙ ግዜ ተነስተናል። በዚህ የቀራንዮ መንገድ ላይ ብዙዎች ወድቀው ቀሩ፣ ሌሎች መንገዳቸውን ቀየሩ። አንዳንዶች ሞቱ፤ ሌሎች ታሰሩ፤ ቀንበሩ የከበደን አገር ለቀን ተሰደድን። እንዲህም ሆኖ ከያለንበት የምንጮኸው ወድቀን እንዳልቀረን ለማብሰር ጭምር ነው። የዲሞክራሲ ቀለሞች እስከሚደምቁ ድረስ ድምጻችንን እናሰማለን። እንደዘፈን አዝማች፤ “መንግስት መብት ይሰጥሃል እንጂ፤ መብትህን አያስጠብቅልህም።” እንላለን። ጎበዝ! እንግዲህ ለራስህ እወቅበት።
(ይህ ጽሁፍ ከወራት በፊት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚታተመው አዲስ ገጽ ጋዜጣ ላይ ወጥቷል። ጽሁፉ በተዘጋጀበት ወቅት፤ በኦሮሚያ ተጀምሮ በአማራ ክልል እየተቀጣጠለ ያለው፤ ህዝባዊ አመጽ አሁን ያለበትን አይነት መልክ ገና አልያዘም። ይህ ጽሁፍ ሰሞኑን የተዘጋጀ ቢሆን ኖሮ፤ የ’ነዚህን ህዝባዊ አመጾች ቀለም ያካትት ነበር። አሁንም ቢሆን “መንግስት መብት ይሰጥሃል እንጂ፤ መብትህን አያስጠብቅልህም። መብቱን የሚያስከብረው እያንዳንዱ ዜጋ በግል፤ ህብረተሰቡን በወል ሆኖ ነው።” የሚለው ቀለም ደምቆ ወጣ እንጂ አልደበዘዘም። ስለሆነም ከትላንት እስከዛሬ በሰላማዊ መንገድ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ለነበሩ፤ በዚህ ሂደትም መስዋዕት ለሆኑ ውድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ… ይህ ጽሁፍ ለነሱ መታሰቢያ ይሁንልን። ክብር ለ’ነሱ ይሁን!)

ወያኔን ኢንቡልኑ። –ዳዊት ዳባ

$
0
0

Woyane

አገሬው በሺዎች ልጆቹን እየቀበረ፤ በአስር ሺዎች ወደማጎርያ እየተጋዘ። በሚሊዬኖች አደባባይ ወጥቶ እየታገለ ነው። አሁን ላይ መሸፋፋኛው ተገላልጦ ፍንትው ብሎ የወጣው  ታላቁ የህዘብ ጥያቄ “ የህዋዋት የበላይነት በቃ” የሚለው ነው። ይህ ማለት “የስርአት ለውጥ ነው”። ህዘብ በቃ ሲል በጠቅላላ በአገሪቷ ላይ ካሰፈኑት ፈፁም የበላይነት በተጨማሪም    ኢህአዲግ በሚለው ስብስብ ውስጥ ያለው የበላይነትና አድሏዊነት ይብቃም እያለ ነው። ይህ ድምፅ ከውጪ ብቻ አይደለም እየተሰማ ያለው።  እዛው ከውስጣቸውም እያየለ እየመጣ ነው።  አዎ የደርግን ስርአት በጦርነት አሸንፋዋል።  አሸናፊነት የሚሰጠውን ሁለንተናዊ ጉልበት ውስን ለሆኑ አመታት በተለየና በነበረው ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ ለሚዛኑ መዛባት ምክንያት አድርጎ መውሰድ ይቻል ይሆናል። ይህም እንኳ ለከት ባለው ሁኔታ ተደርጎ ቢሆን ኖሮ ነው።

ለኦሮሞዎች ድርጅት እንፍጠር ብለው ከምርኮኞች ሰርተዋል። ለአማራዎች ድርጅት እንፍጠር ብለው ደግሞ እንዲሁ ፈጥረዋል። እንዲህ እንዲህ እያሉ ለሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች   ድርጅቶች ፈጠሩ።  እነዚህ ድርጅቶች በሰዎች ነው የተሰሩት። እንዳሻቸው ጢቢ ጢቢ እንዲጫወቱባቸውና ለሀያ አምስት አመት መጠቀሚያ ሊያደርጓቸው መቻላቸው የሚሰግርም ነው። ያም ሆኖ  የፈለገውን አይነት ክትትል ግምገማና ጥቅም ይኑር። ቋንጃቸው አልተሰነኮለም። አንገታቸው ላይ ሰንሰለት አልታሰረም። ሁሌ መሳርያ የያዘ አካል ማማ ላይ ቆሞ አይጠብቃቸውም። ይህም ተደርጎ ቢሆንም እንኳ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ የትግሬ ወያኔዎች አገዛዝ  ፍፃሜ ላይ ይህ ክፍል የሚኖረው ትልቅ ሚና ቀድሞ ማየት መቻል አለመቻል ካልሆነ  ሳይታለም የተፈታ ነበር።

እነዚህ ድርጅቶች ውስጥ ድርሻ ያደረጉ ከላነሰ ምን አልባትም ከተሻለ ማህበረሰባዊ እሴት ካለው ህዘብ ውስጥ የወጡ ናቸው። የበዙት በእድሜያቸውማ ሆነ በጉልበታቸው ካሳዳሪዎቻቸው የበረቱ ናቸው። በአይምሮም ሆነ በመማር ካገኙት እውቀትም በልጠዋቸዋል። በቁጥር አጥፈዋል። በድርጅት ጥንካሬም  እንዲሁ። በአግባቡ አልተጠቀሙበትም እንጂ ከወከሉት ማህረሰብ ብዛት አኳያ ሊሰጣቸው የሚችለው ጉልበትም  የትየለሌ ነበር። እርቀን ካለነው በተሻል በቅርብ ሆነው ብልግና ቆሞ ሲሄድ አይተዋል። ወገንታዊነት ሊኖራቸው አይችልም አያማቸውም ብሎ ማሰብ የአቦይ ስበሀት ድንቁርና ብቻ ነው። ዛሬ የምናየው የነዚህ ጉዳዬች ድምር ውጤትን ነው። ከአመት በፊት ኦፒዲዬዎች የተመከሩት  ህወሀት እራሱን ችሎ  የኦሮሞን ህዘብ አፍኖ ሊገዛ በጭራሽ አይችልም። የታፈነ የኦሮሞ ህዘብ ማለት ጢቢ ጢቢ መጫወቻ  ስትሆኑ መኖር ነው። ሊገባችሁ ከቻል ቀላሉ መንገድ  ህዝቡን ልቀቁት ነበር። ከምትግመቱት በላይ ጉልበት ይሆናችሗል ነበር።  ይህ በሌሎች አጋር  ድርጅቶች ዘንድ የተወሰደ ተሞክሮ ነው።

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አነድ ጊዜ ላይ ቀለል አድርገው  አመላካችና የምታድግ ግን የማትመስል አሳብ ጣል አድርገዋል። “እንቢ ካሉ  ሌሎቹ  እራሳቸውን ችለው መንግስት መሆን ይችላሉ” የምትል።

መሳርያ የያዘው ላይ በመለጠፍ መትረፍ ይቻላል የሚለውም ህልም ነው። ጉዞው የሗልዬሽ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ጀነራሎቹ እንጂ አብዛኛው ሰራዊት የናንተ አይደለም። ህዘብ ነው። የደሀ እናት ልጆች ናቸው። የወገኖቹ ደም በመላው አገሪቱ የሚንዥረዥር። ለራሱም ያልተመቸው። ጠቀላላ የአገሩና የወገኑ ሁኔታ የሚያመው። አዎ ቁጭ ብሎ የመምከር አማራጮችን የማየት በአጠቃላይ ትግሉን በጋራ ለማድረግ በአፈናው ምክንያት ክፍተቶች አሉበት። የማይሞሉ ወይ ሊሞላቸው የማይቻለው ግን አይደሉም። ፈዛዛ ተቃዋሚ መኖሩ ነው እንጂ ድሮ በቀላሉ ሊሞላ የሚችል ነበር። አሁንም ቢሆን ሌላው ቀርቶ የጊዜ፤ አጋጣሚና ቦታ መመቻቸት በራሱ  ደህና ሁኑን ለሁሌው ሊያመጣ ይችላል። ይህ የህዘብ ትግል በሁሉም አገሪቷ ክፍል ባንድ ጊዜና ሰዓት በአገር አቀፍ ደረጃ መደረጉ አይቀርም። የዚህ አይነት ሁኔታዎች ከዛሬ ጀምሮ ሁላችንም ነፃ ነን የሚለውን መናበብና ስሜት መፍጠሩ አይቀርም። የአገሪቷ ጠቅላላ ሁኔታ የሚሻውም ይህንኑ ነው።

የኦሮሞ ተቃውሞ ጥንካሬ አንዱ መገለጫ  ስርአቱ ውስጥ ያሉ ወገኖቻቸውን መዚገብ ገልጠው የለውጡ አካል የሆነውን ካልሆነው መናገር መቻላቸው ብቻ ሳይሆን ከበዙት ጋር አስፈላጊ ሲሆን ሊደርሷቸው የመቻልን አቅም መገንባታቸው ነው። በግሌ ከአመታት በፊት የኢላሞ ሞልሞሌ ቀበሌ ሊቀመንበር ስሙ ማነው? ባለቤቱስ ማን ትባላለች? የጅ ስልኩስ? ብዬ ነበር። ምን እናድርገው? ድክመት ሆኗል። አሁንም ሊሰራ የሚቻል ነው። ቀድሞ አስቦ መስራት የብልሆች ነው። አንዳንዴ ደግሞ ግድ ሲል በዘመቻ በሳምንታት ይሰራል። ሁሉን ያቀፈ ትብብር ማቆሙም እንዲሁ።  ይህ ሀሳብ በዜጎች ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው መሰረቱ የተጣለ ነው። አንዳንዴ አሜሪካኖች ጠርተው ኑ እዚህች ላይ ፈርሙ እስኪሉ የሚጠበቅ ይመስላል።

እውነት ለመናገር ዲሞክራሲያዊት ፤ ፍትህና እኩልነት የሰፈነባት የሁሉንም ፍላጎትና ጥያቄ ማስተናገድና ብሎም መሸከም የምትችል አገር እንዲኖረን አሁን የተፈጠረውን አይነት አጋጣሚ መቼም ተፈጥሮ አያውቅም። ከወያኔ በሗላ ጦር ሀይል ፖሊቲካው ውስጥ የለም። ደርግ ጦር ነበረው። ወያኔ ጦር ይዞ ነው የገባው። አሁን ማንም ፍላጎቱን አቻችሎና ተደራድሮ፤ በዜጎች ፍላጎት ተዳኝነቶ  ካልሆነ ፍላጎቱን በጦር ሐይል መጫን የሚችልበት ሁኔታ የለም። ወያኔን ባዶ እጁን ታግሎ የጣለ ህዘብ ለትናንሽ  ባለመሳርይዋች ወይ ጉልበታሞች ይገብራል መጃጃል ነው። አጉል ፍርሀትና ጥርጣሬ ካልሆነ መጪው ጊዜ ለሁሉም ብሩህ ነው። መተባበር አብሮ መታገል ሽግግሩንም መስራት ይቻላል። {የዚችን ፓራግራፍ ይዘት የያዘ አነጋገር ረፋዱ ላይ አቶ ሌንጮ ለታ ኦ.ሜ.ኔ ላይ ያደረገው ቃለ መጠይቅ ላይ ሲጠቀም ሰማው}። በነገራችን ላይ የትብብሩ ፋይዳ ለወደፊት እነሌንጮ ድርጅታዊ ጥንካሬ ሊገነቡ ከቻሉ ካልሆነ አልታየኝም። እንደውም ጊዜው ለሚሻው ትልቅ ነገር ዝም ብሎ አፍ ማዘጊያና መከፋፈያ አድርጌ ነው የወሰድኩት።

ያም ሆኖ በሽግግሩ አዳልጦን ማጥ ውስጥ እነዳንገባ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። አይደለም ከፈላጭ ቆራጭ አንባገነን ወደዲሞካራሲያዊ ሁሌም ቢሆን መንግሰት መቀየር እንደተባለው ያው ዳይፐር መቀየር ነው። ሲቀይሩ ላለማነካከትም ሆነ ቶሎ ቶሎ በአዲስ ይቀየር የሚባለውም ለዚሁ ነው። መቀየሩ ጥሩ ግድም ሆኖ እያለ ያገለገለ ከቆሻሻ ውስጥ አውጥቶ  አድርግ አታድርግ በሚል ግብ ግብ አገሩን በሙሉ አር እንዳናናካካውም መጠንቀቁም አይከፋም። ለፈለገ ከድል በሗላ ይህም ሀሳብ ችግር የለውም። ከድል በፊት ትግሉ ውስጥ ማስሮጥ ግን ህዘብ መራራ መሰዋትነት ከፍሎ ወደፊት ያስኬደው ትግል ላይ መከፋፈያ ታኮ ይሆናል። ምንጩ ደግሞ ይታወቃል ድክመት ነው። በመጀመርያ እናሸነፍ። ከዛ ያሉ ፖለቲካዊ ፍላጎቶችና ልዩነቶች ሰላማዊ ህጋዊና መዋቅራዊ በሆነ መንገድ እንደባደብባቸው።

ጊዜው የኔን መንገድ በትንሹ። ብዙ የጋራ ስራን ግድ የሚል ነው። አገዛዙ የፈለገውን ያህል ቢዳከም ፍፃሜውን ማድረግ ብዙ ስራን ይፈልጋል። ከዛም ባጭር ጊዜ ውስጥ ሰላም መረጋጋትን ማስፈንና አልፎም ህግና ስርአት በቶሎ እንዲጠበቅ የሚያስችል ብቃት ላይ ማቀድ፤ በዝርዝር መዘጋጀትና የመተግበር ዝግጁነትን መፍጠር ደግሞ አለ። ይህን አለማድረግ እንዝላልነት ብቻ ሳይሆን አስጠያቂም ነው። በግልሰብ ደረጃ ሎተሪ ቢደርሰኝ ብሎ ከዛ ተነስቶ ማለም ወይ ማቀድ ይቻላል። በአገርና በሕዝብ ግን አንባገነን እየታገልክ ላዛውም የኛዎቹን እያወቅናቸው ፖለቲካዊ ማሻሻያ እንዲያደርጉ ሲጠብቁ መዘናጋት ሀላፊነት የጎደለው ይሆናል። ከአንዷለም ይፈታም ሆነ ፖለቲካዊ ማሻሻዬዎችን አስቀምጦ መታገያ ማድረጉ ማለፊያ ሊሆን ይችላል። ይህ አያከራክርም። ከዛ ባለፈ ሰላም የሰፈነባት የተረጋጋች ዲሞክራሲያዊ ኢትይጵያ ያለነሱ በጎ ፍቃድ አይመጣም ካልን መታገል ሳይሆን ቤተ መንግስት በር ላይ እየሄድን ምህላ መያዙ ይሻል ነበር። በዛ ላይ ልናገኝ የምንችልው ውጫው ድጋፍ ለውጡን መሸከም መቻላችን ላይ የሚታይ፤ ሊተገበር የሚችል ዝግጅት በዝርዝር አስቀምጠን ማሳመን ከመቻላችን ጋር በቀጥጣ ይገናኛል። ይሄ ሁሉ በተናጠል በሚደረግ እሩጫ ሊሰራ አይችልም። ሽግግር ግድም፤ ሀላፊነትም፤  ስራም ነው።

ዳዊት ዳባ

Saturday, August 20, 2016

dawitdaba@yahoo.com

 

 

 

 

በኢትዮጵያ ያለው ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ነውን?  ክፍል አንድ፣  –ይገረም አለሙ

$
0
0

Woyane
ህገ መንግስታዊውን ሥርዓት በሀይል ለማፈረስ የሚል ክስ  በሀገራችን ተራና የተለመደ ነገር ከሆነ አመታት ተቆጥረዋል፡፡በስፋት የታወቀው፣ ምን አልባትም የተጀመረው  በቅንጅቶች  ክስ ይመስለኛል፡፡ለሥልጣን ያሰጋሉ ተብሎ የተገመቱ ዜጎችን በዚህ እየወነጀሉ በመገናኛ ብዙሀን መናገሩንም የጀመሩት አቶ መለስ  ናቸው፡፡ ለነገሩ ከደደቢት እስከ ምንይልክ ቤተ መንግስት የተሰራ የተነገረው ሁሉ የአቶ መለስና  የአቶ መለስ ብቻ አንደሆነ ተነግሮን የለ፡፡ እናም የእኛ የሆነ የምንለውም የምንሰራውም የለንም ሁሉም በአቶ መለስ ተወጥኗል ተነግሯል የእኛ ስራ የሚሆነው  የርሳቸውን ማስቀጠል ነው በማለት አሳፋሪውን ነገር በኩራት የነገሩን ሰዎችም ህገ መንግሥታዊውን ሥርዓት በኃይል ለማፍረስ የሚለውን ውንጀላ ቀጥለውበታል፡፡  ይህም ሆነና ከወያኔ ፍላጎት በተቃራኒ የተናገረ፣ የጻፈ፣ መብቴን ያለ፣ አገዛዝ በቃኝ ያለ፣ ወዘተ ሁሉ ኦነግ፣ ግንቦት ሰባት፣ አሸባሪ፣ የኤርትራ ተላላኪ ወዘተ የሚል ሰም እየተለጠፈበት፣ ህገ መንግስታዊውን ሥርዓት በሀይል ለማፍረስ በሚል ውንጀላ  ማሰር የሥርዓቱ ዋና ተግባር ከሆነ አመታት ተቆጠሩ፡፡ይህ የሚሆነው  ግን የሚገነባም ሆነ የሚፈርስ ህገ መንግስታዊ ሥርዓት ሳኖር ነው፡፡ ሌላው ቢቀር ህገ መንግሥታዊ ሥርዓት ባለበት ሀገር ዜጎች በዘፈቀደ አይታሰሩም በሀሰት አይወነጀሉም ተቃወማችሁ ተብለው አይገደሉም፡፡

ብዙ ዝርዝር ውስጥ ሳይገባ ህገ መንግስታዊ ሥርዓት የሚለውን ቃል እንደወረደ ብንተረጉመው በህገ መንግሰት መሰረት ላይ የቆመ መንግስት ያለበት ሥርዓት ማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ ሁለት መሰረታዊ ነገሮች አሉ፤ አንደኛውና ዋናው ህገ መንግስት ሲሆን ሁለተኛው መንግስት ነው፡፡ የሁለቱ መኖር ብቻ ግን አንድን ሥርዓት ህገ መንግሥታዊ ሊያሰኘው አይችልም፡፡ ይችላል ከተባለ ደግሞ የንጉሱም የወታደራዊውም   ህገ መንግስታዊ ሥርዓት ነበር ማለት ይሆናል፡፡

በህዝብ ውይይት ተረቆ በህዝብ ይሁንታ በጸደቀ ህገ መንግስት መሰረት በዴሞክራሲያዊ ምርጫ  ስልጣን የያዘና ራሱን ለህገ መንግስቱ እያስገዛ  በህገ መንግስቱ ድንጋጌ መሰረት ሕዝብን በማስተዳደር የአምስት አመት ኮንትራቱን የሚወጣ ተጠያቂነት ያለው መንግሥት ሲኖር ነው ስርዓቱ ህገ መንግስታዊ ሊባል የሚበቃው፡፡

በኢትዮጵያችን ከእነዚህ አንዱም የሌለ በመሆኑ ነው ህገ መንግስታዊ ሥርዓት አለ ወይ? ብሎ መጠየቁ ግድ የሚሆነው፡፡ሌሎቹን ትተን አንዱንና ዋናውን  ህገ መንግሥቱን ብቻ እንኳን ነጥለን ብናይ የምናገኘው ውጤት በኢትጵያ ያለው የወያኔ ሥርአት ህገ መንግሥታዊ ሊባል የማይበቃ መሆኑን ነው፡፡ ህገ መንግሥተን አስመልክቶ የሚነሱትን የወያኔ የፖለቲካ ፕሮግራም ግልባጭ ነው ፤የሀገራችን ህዝቦች በትግላቸው የተቀዳጁት ነው ህዝብ ያልተወያየበትና ያላጸደቀው ነው፣ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰብ ህዝቦች ወደውና ፈቅደው ያጸደቁት ነው ወዘተ የሚሉትን  ላለፉት ሀያ ዓመታት የተሰሙና አሁንም ያሉ ክርክሮችን  ለግዜው አቆይተን ወያኔዎች የሚመጻደቁበትንና በመቃብራችን ላይ ካልሆነ በስተቀር አይነካም  እያሉ የሚፎክሩበትን ህገ መንግስት  ያውቁታል ወይ? ያከብሩታል ወይ? ይገዙበታል ወይ? ብለን ብንጠይቅ የምናገኘው ምላሽ አረ በፍጹም የሚል ይሆናል፡፡ ይህ ከሆነ ታዲያ ራሱ ያወጣውን ህገ መነግስት የማያከብር መንግስት የመሰረተው ሥርዓት እንደምን ህገ መነግስታዊ ስርኣት ሊባል ይበቃል የሚለው አብይ ጥያቄ  ይሆናል፡፡ በህገ መንግስቱ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለግዜው ስንተዋቸው ግን  ህገ መንግስቱን ዴሞክራሲያዊ፣ በህዝብ የጸደቀ፣ ወዘተ እያሉ ለሚያንቆለጳጳሱትና አሁን ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ህገ መንግስቱ ከጸደቀ ወዲህ የተወለደ ይመስል ራሳቸው ተሞኝተው እኛንም ተጨፎኑ እናሞኛችሁ ለሚሉን  ስለ ህገ መንግስቱ አረቃቅም ሆነ አጸዳደቅ የህገ መንግስት  ጉባኤን በሊቀመንበርነት ከመሩት ዶ/ር ነጋሶ በላይ አታውቁምና ርሳቸው ስለ ህገ መንግስቱ የተናገሩትን መለስ ብላችሁ ተመልከቱ የሚል የወገን ምክር በመለገስ ነው፡፡ ዴሞክራሲያዊ ህገ መንግሥት በማለቴ እጸጸታለሁ ማለታቸውን በማስታወስ ጭምር፡፡

አንድን ስርዓት ህገ መንግስታዊ ሊያሰኙት የሚበቁ ሌሎች ጉዳዮች ሁሉ ቀርተው በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ህገ መንግስቱን የማያከብርና ለህገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች የማይገዛ ከሆነ ያ ስርዓት ህግ መንግስታዊ ስርዓት ሊባል እንደማይበቃ ወያኔዎችም አሌ የሚሉ አይመስለኝም፡፡ ባይሆን እኛ የብሄር ብሄረሰብ ህዝቦችን መብት ያረጋገጥን፣ልማት ያመጣን፣ ሰላም ያሰፈንን በመሆናችን ስርዓታችን ህገ መንግስታዊ አይደለም ሊባል አይችልም፣ ይህን የሚሉት ምንትሶች ናቸው፣ እንዲህ ለማድረግ የሚያስቡ ናቸው ወዘተ ይሉ  ይሆናል እንጂ፡፡ (የሚሉትን መድገም አስፈላጊ መስሎ ስላልታየኝ ነው)

ሆኖም ግን ራሳቸውም ህገ መንግስቱን ለማጥቂያ መሳሪያነት የሚያውሉት እንጂ የሚገዙበትና ህዝብ የሚያስተዳድሩበት እንዳልሆነ፤ ስለሚያውቁ፣እናድርግ ቢሉም  የሥልጣን እድሜአቸው የሚያጥር መስሎ ስለሚታያቸው  ጥያቄ ሲነሳባቸው  የህገ መንግስቱን  አንቀጾች ጠቅሰው አይከራከሩም፡፡  እኛ ግን እነሆ ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን በሀይል ለማፍረስ እያላችሁ በየግዜው ዜጎችን በአሸባሪነት በጸረ ሰላምነት ወዘተ አየከሰሳችሁ የምታስሩት ህገ መንግስታዊ ሥርዓት በሌለበት ሀገር ነው፡፡ ህገ መንግሥታዊ ሥርዓት ቢኖር ሌላው ቢቀር ንጹሀን ዜጎችን በማን አለብኝነት ስም እየሰጣችሁና ወንጀል እየፈበረካችሁ፣ አባይ ምስክር እያሰለጠናችሁና ታዛዥ ዳኛ እየመደባችሁ አታስሩም ነበር፣ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ እንቦቀቅላ ህጻናት ሰልፍ ወጡ፣ እኛን ተቃወሙ ብላችሁ ገዳይ ሰራዊት ማሰማራት አትችሉም ነበር፤ብታደርጉት ደግሞ ለህግ ቀርባችሁ ተገቢ ቅጣታችሁን ታገኙ፣ ከፍ ሲልም ሥልጣናችሁን ትነጠቁ ነበር፤ ይህን ሁሉ ማድረግ የቻላችሁት መንግሥቱ ለህገ መንግሥቱ የሚገዛና ሥርዓቱ ሕገ መንግሥታዊ ባለመሆኑ ነው ብለን እንሞግታቸዋለን፡፡  ሙግታችንም እንደ እነርሱ በጡንቻ ወለድ የፕሮፓጋንዳ ዋይታ ሳይሆን  የሚመጻደቁበትን ህገ መንግሥት እየጠቀስን ይሆናል፡፡

በማስረጃነት/መከራከሪያነት የማቀርባቸውን የህገ መንግሥቱን አንቀጾች ለመለየት አስራ አንድ ምዕራፎችንና 106 አንቀጾችን የያዘውን “ሕገ መንግሥታችንን” እንደ አዲስ አነበብኩት ፡፡ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች እነርሱም እንደ ወያኔ የፕሮፓጋንዳ ጩኸት እንጂ ህጋዊ ክርክር ተግባራቸው ባለመሆኑ እንጂ ብዙ ሊሰሩባቸው ይችሉ የነበሩ አንቀጾችን የያዘ ነው፡፡ የህግ ባለሙያዎችም ከቃላት አጠቃቀሙና ከአረፍተ ነገር አሰካኩ የህግ ቋንቋ መሆን አለመሆን ጀምሮ ብዙ ሊሉበት የሚችል ሆኖ ነው የታየኝ፡፡ አንተስ እስከ ዛሬ የት ነበርክ እንዳትሉኝ ብቻ፡፡ እስቲ  አንቀጽ 39/ 1 ተመልከቱት፡ እንዲህ ይላል፤ “በዚህ ሕገ መንግሥትውስጥ ብሔር፣ ብሔረ ሰብ፣ ሕዝብ ማለት ከዚህ ቀጥሎ የተገለጸውን ባህርይ የሚያሳይ ማህበረሰብ ነው፡፡ ሰፋ ያለ የጋራ ጸባይ የሚያንጸባርቅ፣ ባህል ወይም ተመሳሳይ ልምድ ያላቸው፣ ሊግባቡበት የሚችሉበት የጋራ ቋንቋ ያላቸው፣የጋር ወይንም የተዛመደ ህልውና አለን ብለው የሚያምኑ፣ የሥነ ልቦና አንድነት ያላቸውና በአብዛኛው በተያያዘ መልክዓምድር የሚኖሩ ናቸው፡፡”

መጀመሪያ ሶስቱንም ማህበረሰብ አላቸው፣ ከዛም ለሶስቱም አንድ አይነት መግለጫ ነው የቀረበው፡፡ እንዴት ነው ነገሩ ብሔር፣ ብሔረሰብና ሕዝብ አንድና ተመሳሳይ ናቸው፣ ከሆነስ ለያይቶ፣ ስም አበጅቶ መጥራቱ ለምን አስፈለገ? ዝርዝር ውስጥ ሳይገባ የዚህ አንቀጽ አገላለጽ  ትክክል ነው፣ አይደለም በማለት ባለሙያዎች እውቀት ቢያስጨብጡን፡፤

ነገርን ነገር ያነሳዋል ሆኖ እንጂ የህገ መንግሥቱ ጉድለቶች የዚህ ጽሁፍ አጀንዳ አይደሉም፡፡የተጻፈው አለመከበሩን እንዲያም ሲል አለመታወቁን በማሳየት ህገ መንግስት በማይከበርበት ሀገር ህገ መንግሥታዊ ሥርዓት ሊኖር አይችልም የሚለውን ለማሳየት ነው ወደ ህገ መንግስት ንባብ የገባሁት፡፡ እናም ለማስረጃነት ሊቀርቡ የሚችሉት አንቀጾች በዙብኝ፤ ቀንሼ ዋና ዋና ያልኩዋቸውን ለየሁ፣እነዚህም ጥቂት የሚባሉ አልሆኑምና በአንድ ክፍል ቢካተቱ ጽሁፉን ሊያረዝሙት ሆነ፡፡ ታዲያ አንባቢን ላለመሰልቸት በድረ ገጽ የሚወጣ ጽሁፍም የተመጠነ መሆን አለበት ብየ ስለማምን በሁለት ክፍል ማድረጉን መረጥሁ፡፡

ስለሆነም በተከታዩ ጽሁፍ  በኢትዮጵያ ሕገ መንግስታዊ ሥርዓት አለን? ለሚለው ጥያቄ  ምላሹ የለም የሚል እንዲሆን የሚያበቁትን   ከበሬታ ከተነፈጋቸውና አንዳንዶቹም ከነመኖራቸው የማይታወቁ ከሚመስሉት የህገ መነግሥቱ አንቀጾች የተወሰኑትን ይዤ እመለሳለሁ፡፡ እስከዛው ግን ስለ ህገ መንግስት መከበር አለመከበር ሲነሳ አስቀድሞ ሊጠቀስ የሚገባውን፣ ህገ መንግሥቱ ስለ ራሱ የበላይነትና ተከባሪነት የደነገገውን እንይና የተጠቀሱት ምን ያህል ተፈጻሚ ሆነዋል የሚለውን ህገ መንግሥቱ ከጸደቀበት 1987 እስካሁን በሀገራችን ከሆነው ጋር በማስተያየት የየራሳችንን ብይኔ አንስጥ፡፡

አንቀጽ 9 የሕገ መንግሥት የበላይነት

9/.1  ሕገ መንግሥቱ የሀገሪቱ የበላይ ህግ ነው፤ ማንኛውም ሕግ፣ልማዳዊ አሰራር፣ እንዲሁም የመንግሥት አካል ወይንም ባለሥልጣን ውሳኔ ከዚህ ሕገ መንግሥት ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡

9./2 ማንኛውም ዜጋ የመንግሥት አካላት፣ የፖለቲካ ደርጅቶች፣ ሌሎች ማህበራት እንዲሁም ባለሥልጣኖቻቸው ሕገ መንግሥቱን የማክበርና የማስከበር፣ ለህገ መንግሥቱ ተገዢ የመሆን ኋላፊነት አለባቸው፤

በአንቀጽ 9/1 የተደነገገውን በመተላለፍ ከህገ መንግሥቱ የሚቃረኑ  አዋጆች ወጥተዋል፣ባለ-ሥልጣናት በንግግርም በድርጊትም የሚፈጽሙዋቸው ተግባራት ህገ መነግሥቱ መኖሩንም የሚያውቁ የማይመስሉ ናቸው፤ ከህገ መንግስቱ ድንጋጌ ይልቅ የባለ ሥልጣናቱ ትዕዛዝ፣ በአዋጅና በመመሪያ ከሚተላለፈው በላይ ልማዳዊ አሰራር የተንሰራፋበት ሥርዓት ነው ያለን፡፡

አንቀጽ 9/2 ላይ የሰፈረውንም ስናይ ዜጎች ተወያይተው ያረቀቁት፣ በድምጻቸው ያጸደቁትና ይሁንታቸውን የቸሩት ባይሆንም የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት እስከ ተባለ ድረስ ባይወዱትም ያከብሩታል፣እንዲሻሻል ቢታገሉም ይገዙበታል፡፡ በአንጻሩ ባለሥልጣናቱ  ሕዝቡ አንዲያከብረው ሲናገሩ በማጥቂያ መሳሪያነት ሲገለገሉት እንጂ እነርሱ አክብረውት ሲሰሩ አይሰተዋልም፡፡

በተለይ ደግሞ መሰረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ተብለው በህገ መንግሥቱ ምዕራፍ 3  በ31 አንቀጾች ከተዘረዘሩት ድንጋጌዎች አንጻር ሲመዘኑ  በህገ መንግሥት ሳይሆን ፕ/ር መስፍን በ1997 ምርጫ ወቅት አንዳሉት በህገ አራዊት የሚመሩ ነው የሚመስሉት፡፡  በህገ አራዊት የሚመራ መንግሥት ያቋቋመው ሥርዓት ደግሞ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ሊባል አይበቃም፡፡

አንድየ የማሪያም ልጅ ሞልቶ ከተረፈው አድሜ ሳይነፍገን በክፍል ሁለት ለመገናኘት ያብቃን፡፡አሜን

 

በጠራራ ጸሀይ አገር ሲዘረፍ –አቻምየለህ ታምሩ

$
0
0

TPLF 1በያዝነው የፈረንጆች ዓመት በወርሀ ጥር የወያኔ ካድሬዎችና የአገዛዙ የፕሮፓጋንዳ ተቋማት የሆኑት እነ ኤ.ቢ.ሲ.፣ ዋልታ፣ ፋና፣ ኤ.ዜ.አ. ወዘተ ትግራይ በታሪኳ ለብሔራዊ ባንክ አቀረበችው ስላሉት የወርቅ ምርት መጠን በስፋት ዘግበው ነበር። የአገዛዙ ልሳን ኢ.ቢ.ሲ. እ.አ.አ. ጥር 07 ቀን 2016 ዓ.ም. ባቀረበው ርዕሰ አንቀጽ፤ ዋልታ እ.አ.አ. ጥር 09 ቀን 2016 ዓ.ም. ባስደመጠም የዜና እወጃ ፤ ኤ.ዚ.አ. ጥር 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ባስነበበን ሪፖርት ትግራይ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ 597.7 ቶን ወርቅ [በባህላዊ መንገድ] እንዳመረተችና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንዳቀረበች ነግረውናል።

ይህንን «ልማታዊ ዜና» የሰሙ ብዙ ሰዎች «ትግራይ ከየት አምጥታ ነው ይህንን ያህል ወርቅ አምርታ ለብሔራዊ ባንክ የምታቀርበው?» በማለት ከቁጥሩ ጀርባ ያለውን የምጣኔ ሀብት ትርጉም ሳያጤኑ አጣጥለውት አልፈዋል። ሆኖም ግን ከቁጥሩ ጀርባ ወያኔ ትልቅ አገራዊ ዘረፋና ወንጀል ፈጽሟል። ወያኔ በቁጥሩ ቁማር ተጫውቶ የኢትዮጵያን የሁለት አመት ባጀት ያህል ብሔራዊ ሃብት በአንድ ግብይት ብቻ ወደ ትግራይ አሸሽቷል ወይንም አሻግሯል። ነገሩ እንዲህ ነው።

ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ 597.7 ቶን ወርቅ ከትግራይ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቀረበ ማለት በ42 ወር ውስጥ 597.7 ቶን ወርቅ ከትግራይ ለብሔራዊ ባንክ ቀረበ ማለት ነው። ይህ ማለት ትግራይ በአመት በአማካኝ 171 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቅርባ ነበር ማለት ነው። በኢትዮጵያ የንግድ ህግ መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ብቸኛው ወርቅ ገዢና አስቀማጭ ተቋም ነው። ክልሎች በየክልሉ የተመረተውን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ሲያቀርቡ ብሔራዊ ባንክ ክልሎች ላቀረቡት የወርቅ መጠን ክፍያ ይፈጽማል። ለምሳሌ ትግራይ 597.7 ቶን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ስታቀርብ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለትግራይ ክልል የ597.7 ቶን ወርቅ ክፍያ በገንዘብ ይፈጽማል። ያልቀረበ ወርቅ ሪፖርት ተደርጎ ብሔራዊ ባንክ ላልቀረበ ወርቅ እንደቀረበ ተደርጎ ክፍያ ቢፈጽም ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሀብት transfter ይኖራል ማለት ነው።

ወያኔ የነገረን ትግራይ ለብሔራዊ ባንክ ያቀረበችው 597.7 ቶን ወርቅ ማለት 597,700 ኪሎ ግራም ወርቅ ማለት ነው።ይህ ማለት ደግሞ 19,216,473 ወቄት ወርቅ ማለት ነው። ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ በነበሩት አመታት ውስጥ አማካኝ የአንድ ወቄት ወርቅ ዋጋ 1,100 የአሜሪካን ዶላር ነበር። ይህ ማለት ትግራይ አቀረበችው የተባለው 597.7 ቶን ወርቅ ዋጋ 21. 376 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይሆናል ማለት ነው።

ይህ ማለት [በወያኔ ዜና መሰረት] ትግራይ ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ላቀረበችው 597.7 ቶን ወርቅ ብሔራዊ ባንክ 21. 376 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከፍሏታል ማለት ነው። የኢትዮጵያ ያለፈው አመት ባጀት አስር ቢሊዮን ዶላር ነው። ይህ ማለት ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ ትግራይ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አቀረበችው ለተባለው 597.7 ቶን ወርቅ የተከፈላት 21. 376 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከኢትዮጵያ የሁለት አመት በጀት በላይ ነው ማለት ነው።

ዋናውና ቁልፉ ጥያቄ እውነት ትግራይ ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 597.7 ቶን ወርቅ ወይንም ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ አቅርባለች ወይ? የሚለው ነው።

ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የአለም አገሮችን የወርቅና የሌሎች ማዕድናትን አመታዊ ምርት ማስረጃ የሚሰበስበውንና የሚያደራጀውን የUnited States Geological Survey (USGS) Minerals Resources Program አመታዊ የአለም ማዕድናት ምርት ሰንጠረዥን ማየት በቂ ነው። ይህ የአሜሪካ ተቋም በአለም ላይ ያሉ ማዕድን አምራች አገሮችን የማእድን አመታዊ ምርት አሃዝ ሰብስቦ ደረጃ ያወጣና የአለም አገሮችን በማዕድን ምርት ያወዳድራል። በዚህ መስሪያ ቤት ማስረጃ መሰረት ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ በአለም ላይ በወርቅ ምርት አንደኛ ቻይና ስትሆን አመታዊ የወርቅ ምርት መጠኗ 403 ቶን ነው። ሁለተኛዋ የአለም ወርቅ አምራች አገር ደግሞ አውስትራሊያ ስትሆን አመታዊ የምርት መጠኗ ደግሞ 250 ቶን ወርቅ ነው። ሶስተኛ አሜሪካ [235 ቶን ወርቅ በአመት] ፤አራተኛ ሩስያ ፌድሬሽን [217.8 ቶን ወርቅ በአመት] ፤ አምስተኛ ፔሩ [161 ቶን ወርቅ በአመት] ፤ስድስተኛ ደቡብ አፍሪካ [160 ቶን ወርቅ በአመት]፤ ሰባተኛ ካናዳ [103 ቶን ወርቅ በአመት] ፤ ስምንተኛ ሜክሲኮ [96.7 ቶን ወርቅ በአመት] ፤ ዘጠነኛ ኡዝቤኪስታን [ 93 ቶን ወርቅ በአመት] እና ጋና [86.5 ቶን ወርቅ በአመት] በአለም ላይ አስሩ ከፍተኛ ወርቅ አምራች አገሮች ናቸው። የዚህ ምንጭ የሚከተለውን ትር መክፈትና መመልከት ይቻላል…http://www.indexmundi.com/minerals/…

ወያኔ ኢትዮጵያ ትግራይ ብቻ ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቅርባለች ያለው እውነት ቢሆን ኖሮ ኢትዮጵያ በወርቅ ምርት በአለም ደረጃ ፔሩን ቀድማ ሩስያን ተከትላ አምስተኛ ደረጃ ላይ ትሆን ነበር። ልብ በሉ ከአንድ እስከ አስር የወጡ አገሮች ሁሉ ወርቅ የሚቆፍሩት በጣም ዘመናዊ በሆነ መሰርሰሪያ ማሽን ነው። ወያኔ ግን ትግራይ በየ አመቱ 171 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቅርባለች የሚለን በባህላዊ መንገድ አምርታ ነው።

ከፍ ብዬ በለጠፍሁት የUnited States Geological Survey (USGS) Minerals Resources Program አመታዊ የወርቅ ምርት እውነተኛ ደረጃ መሰረት የኢትዮጵያ አመታዊ የወርቅ አምራችነት ደረጃ 29ኛ ሲሆን አመታዊ የወርቅ ምርቷ ደግሞ 12 ቶን ብቻ ነው። ልብ በሉ ይሄ አመታዊ የኢትዮጵያ የወርቅ ምርት ዶዶላ፣ መተከል፣ ለገደንቢና ወለጋ ሜድሮክ በዘመናዊ ቴክኖሎች ታግዞ የሚያመርተውን ይጨምራል። ወያኔ ግን የትግራይን አመታዊ ምርት ብቻ 171 ቶን ነው ይለናል።

ሜድሮክ በዶዶላ፣ በመተከል፣ በለገደንቢና በወለጋ የሚያመርታቸውን ዜሮ አድርገን ኢትዮጵያ ያመረተችውን 12ቱን ቶን ወርቅ ከትግራይ ብቻ ለብሔራዊ ባንክ የቀረበ የወርቅ መጠን አድርገን ብንወስድ፤ ብሔራዊ ባንክ ከትግራይ በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ እንደቀረበለት ተደርጎ ለትግራይ በጠቅላላ ከከፈለው 21.3 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ውስጥ በያመቱ ላልቀረበ 158 ቶን ወርቅ ክፍያ ፈጽሟል። ይህ ማለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከትግራይ ቀረበ ተብሎ ከፍያ ከፈጸመበት 597.7 ቶን ወርቅ ውስጥ ባንኩ የተረከበው ወርቅ 42 ቶብ ብቻ ነው። የተቀረው 555.7 ቶን ወርቅ ወርቁ ከትግራይ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሳይቀርብ ብሄራዊ ባንክ ግን ከትግራይ ወርቅ ሳይቀርብ ክፍያ እንዲፈጽም የተደረገበትና የአገር ሀብት ዘረፋ የተካሄደበት የውሸት ቁጥር ነው።

ይህ ማለት ብሔራዊ ባንክ ለትግራይ ከከፈለው 21.3 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ከ20 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለትግራይ የተከፈለው የአገር ሀብት ላልቀረበ የወርቅ መጠን እንደቀረበ ተደርጎ ነው ማለት ነው። ይህ ማለት ወያኔ ያልቀረበ ወርቅን አስታኮ 20 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያገር ሀብት ወደ ትግራይ wealth transfter አድርጓል ማለት ነው። ይህ ማለት የሁለት አመት የኢትዮጵያ አመታዊ በጀትን የሚያህል የአገር ሀብት ትግራይ ለብሔራዊ ባንክ ወርቅ እንዳቀረበች ተሳቦ እንድትወስድ ተደርጓል ማለት ነው። ይህ ማለት የሁለት አመታት የኢትዮጵያ አመታዊ ሀብት ወደ ትግራይ እንዲሄድ ሲባል ዘረፋ ተፈጽሟል ማለት ነው። ወገኖች this is a huge wealth transfter. ወያኔ ከጥር ወዲህም ማራኪ ቁጥር እያቀረበ የአገር ሀብት ወደ ተስፋዋ ምድሩ እያሸጋገረ ይገኛል። በሌላ ጊዜ ከሌሎች ቁጥሮች ጀርባ ስለሚፈጸም አገራዊ ዘረፋ የምለው ይኖረኛል።

የሚገርመው ትግራይ በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቀረበች በተባለ በወሩ የቀረበው ሌላ ዜና የስርዓቱ ዜና ነው። ፋና በየካቲት 11 ቀን 2008 ዓ.ም [እ.ኢ.አ.] ያቀረበው ዜና ርዕስ እንዲህ ይላል…«ለብሄራዊ ባንክ እየቀረበ ያለው ወርቅ በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ ነው።» ዜናው በዚህ ብቻ አያበቃም። ከ2004 ዓ.ም. እስከ 2008 ዓ.ም.[እ.ኢ.አ.] በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ ትግራይ ለብሔራዊ ባንክ አቀረበች እንዳልተባለ «ብሄራዊ ባንክ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በባህላዊም ሆነ በዘመናዊ መልኩ ተመርቶ የሚቀርበለት ወርቅ በእጅጉ ቀንሷል። በ2005 ለባንኩ የቀረበለት 8.1 ቶን ወርቅ ነበር። በ2006 ዓ.ም ደግሞ 7.4 ቶን ሆነ፤ በ2007ም በጣም አሽቆልቁሎ 5.4 ቶንድረስ ወርዷል።» አሉን። ይህ ሁሉ የሚሆነው ከትግራይ ብቻ ለብሔራዊ ባንክ በአመት 171 ቶን ወርቅ ቀረበ ተብሎ 20 ቢሊዮን ዶላር እንደቀላል ወደ ትግራይ transfter እንዲሆን ባደረጉ በአንድ ወር ውስጥ ነው።

አይ አንቺ አገር! ማፍያዎች የውሸት ቁጥር እየቀቀሉ ሌላውን ጾም ደፍተፍና አራቁተው የድሆችን ሀብት ወደ መንደራቸው ያግዛሉ። በአንድ ማጭበርበር ብቻ ሀያ ቢሊዮን ዶላር የአገር ሀብት ወደ መንደራቸው አሸሹ! በቁጥር ሊሸውዱን ሲሞክሩ በትንተና እንዲህ ባጋለጥናቸው ጉዳይ ብቻ ሀያ ቢሊዮን ዶላር በድብቅ ባልተወለደ አንጀታቸው ከገፈፉ ሰው ሳያውቀው የዘረፉት የአገር ሀብት ቢታወቅ ለሌላው ኢትዮጵያ ምን ያህል ያተርፉለት ይሆን?

[የግርጌ ማስታወሻ፡ ከላይ ለትንተና የተጠቀምሁባቸውን ማስረጃዎች ሁሉ ከታች ካለው የአስተያየት መስጫው ሳጥን መመልከት ይቻላል!]

ዶ/ር ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ፤ ስለ ወቅታዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁነት፤ የብሔራዊ ዕርቅ አስፈላጊነትና አካሄድን አስመልክተው ይናገራሉ

$
0
0

 

tsegaye_22“አገሪቱ ትፈርሳለች፤ ሕዝብ በሕዝብ ላይ ይነሳል የሚል ስጋት የለኝም። ይኼ እንደማይሆን እርግጠኛ ነኝ።” – ዶ/ር ጸጋዬ ረጋሳ

“ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ በአንድ መሪ የማትመራበት ጊዜ እየመጣ ነው። አንድ መሪ አይበቃትም። ሊይስተዳድራት የሚችለው ቡድን ነው” – ዶ/ር ጸጋዬ ረጋሳ


ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው! (ከይገርማል)

$
0
0

Tomar

አንዳንድ ሰዎች “ለምን ትግሬወችን ከወያኔ ጋር አዳብላችሁ ትወነጅላላችሁ?” ብለው ሲቆጡ አንዳንዴም ሲሳደቡ እያየን: እየሰማን: የጻፉትንም እያነበብን ነው:: እነዚህ ሰዎች ከሁለት የተለያዩ አቅጣጫወች የተነሱ ሊሆኑ ይችላሉ::

 

የመጀመሪያወቹ የመንግስትን አስነዋሪ: ከፋፋይ: ጨቋኝና ዘረኛ ስርአት በማውገዝ ለውጥ መምጣት አለበት ብለው የሚከራከሩና የሚታገሉ አስር የማይሞሉ ትግሬወችን ስም በመጥቀስ ትግሬን ከወያኔ ጋር ደርቦ መወንጀሉ የእኒህን የጸረ ወያኔ ትግል አራማጅ የሆኑ ትግሬወች ትግል ብላሽ የሚያስቀር ብቻ ሳይሆን በተስፋ መቁረጥ ወደወያኔ እንዲጠቃለሉ የሚገፋ ስለሚሆን የተቃውሞውን ጎራ ይጎዳል የሚሉ የዋሆች ናቸው::

 

እኒህ በመጀመሪያው ምድብ የተካተቱት ሰዎች ያልተገነዘቡት ነገር ያለ ይመስላል:: ከልብ አምነው አምባገነኖችን የሚታገሉ ሰዎች ከየትኛውም ጎራ በሚወረወር አፍራሽ እንቅስቃሴ ተበራገው መጠለያ ፍለጋ ወደዚህ ወይም ወደዚያ ሰፈር የሚያጋድሉ አይደሉም:: የሎጅክ ሰዎች ስለሆኑ ማንንም ለማስደሰትም ሆነ ለማስቀየም ብለው የሚያደርጉት ነገር አይኖርም:: የሚያደርጉት ትክክል ነው ብለው የሚያምኑበትን ብቻ ነው:: ያመኑበትን ነገር ለማድረግ የሚያስፈራቸው ነገር የለም:: የተፈጠሩት የተዛባን አመለካከት ወይም ድርጊት ለማስተካከል ስለሆነ ይህን ያመኑበትን ጉዳይ ለማስፈጸም ማንኛውንም መስዋእትነት ለመክፈል ጀርባቸውን የማያሳዩ ናቸው:: የነርሱ የሞራል እርካታ የዴሞክራሲና የፍትህ መስፈን ጉዳይ ነው:: በነዚህ ሰዎች ዘንድ ቀረቤታ: ዝምድና ወይም ጠላትነት ቦታ የለውም:: እነርሱ የሚፈልጉት ዴሞክርሲ: ፍትህና እኩልነት ሰፍኖ ማንም ይሁን ማን በሰራው ስራ በህግ እንዲመዘን ነው::

 

ሌላው  መታወቅ ያለበት ዕውነታ የትግራይ ሕዝብ ፍላጎት አስር በማይሞሉ ውክልና በሌላቸው የወያኔ ተቃዋሚወች የሚለካ አለመሆኑ ነው:: እኒህ ወያኔን እየተቃወሙ ያሉት ሰዎች ዘረኝነት ያልተጠናወታቸው: ሕገወጥ ተግባር በማንም ይፈጸም በማን ህገወጥ እስከሆነ ድረስ እንቃወማለን በማለት ለትግል የተሰለፉ ከብዙሀኑ ለየት ያለ ባህሪ ያላቸው ግለሰቦች(Exceptions) ናቸው:: ከብዙሀኑ አስተሳሰብ ያፈነገጠ አመለካከት ያላቸው ግለሰቦች በየትኛውም ቡድን ነበሩ: አሁንም  አሉ: ወደፊትም ይኖራሉ:: እኒህ በጣት የሚቆጠሩት የራሳቸው ለየት ያለ ስብዕና ያላቸው ግለሰቦች አማኙን ብዙሀን የሚወክሉ ናቸው ብሎ መውሰድ ትክክል አይሆንም::

 

በአሁኑ ጊዜ እየተካሄደ ባለው የሕዝብ የነጻነት ጥያቄ ላይ ችግር እየፈጠሩ ካሉት የለየላቸው ግለሰቦች ወይም ቡድኖች በተጨማሪ የእኛም ድርሻ ቀላል የሚባል አይደለም::

 

ከሊቅ እስከደቂቅ: ከአለቃ እስከምንዝር ያሉት ትግሬወች በማያሻማ መልኩ ትግሬና ወያኔ አንድ ነው ብለው በተደጋጋሚ ነግረውናል:: ከዚህ በላይ ምን ይበሉን? ሲነግሩን እየሰማን መቀበል ካቃተን ችግሩ የማንም ሳይሆን የራሳችን ነው:: እነሱ የሚነግሩንን ሰምተን እንዳልሰማን በተግባር እያደረጉት ያለውን አይተን እንዳላየን ስለሆንን አይደል ጅሎች: ደደብ አህያወች እያሉን ያሉት!

 

እስቲ እንዲያው በሞቴ የትኛው የትግራይ አካባቢ ነው ሰብሰብ ብሎ ወያኔን ሲቃወም የተሰማው? ደርግን ለመቃወም ያልፈራው የትግራይ ህዝብ የራሱን ልጆች ለመገሰጽ የሚፈራ ይመስላችኋል? እሽ! አዎ ፈርቶ ነውም እንበል! ከሀገር ውጪ የሚኖረው የትግራይ ህዝብስ እየተሰባሰቡ ለወያኔ ድጋፍ ከመስጠትና ወያኔን እየተቃወሙ ነው የሚሏቸውን ሁሉ ከማዋከብና ከማዋረድ ወጥተው “ሕዝብን በዘር: በቋንቋና በሀይማኖት መከፋፈሉ ይቁም! የሀገር ጥቅም ይከበር! መንግስታዊ ሙስና ይወገድ!  በትግራይ ሕዝብ ስም አይነገድ!- – -” ብለው የኢትዮጵያን ባንዲራ ለብሰው: መፈክር አንግበው አደባባይ ወጥተው የተቃውሞ ድምጽ ሲያሰሙ ታይተዋል?

 

“ወያኔን እየተቃወሙ ያሉት ጥቂት ትግሬወች እንዳይቀየሙ ስናወግዝ ወያኔን ከትግራይ ሕዝብ ለይተን መሆን ይኖርበታል” ብለው ሊመክሩን የሚነሱት ወይም “ክፉ የሚያደርጉባችሁን በበጎ መልሱላቸው” የሚሉት የግብረገብ ምሁራን የተጣለብንን የጭቆና ቀንበር የሚያጠብቁብን የወዳጅ ጠላት ከመሆን አይዘሉም::

 

ሁለተኛው ቡድን ትግሬወች አድልኦና መገለል ሳይደርስባቸው ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ጋር ተመሳስለው እየኖሩ በየአካባቢው የሚደረገውን ፀረ-ወያኔ እንቅስቃሴ እንዲሰልሉ ለማስቻል በሕዝብ አንድነት ስም የሚሰብኩ ልበ-ስውር ሰዎች የተሰባሰቡበት ነው:: ደርግ ከትግራይ ተመቶ የወጣው በወያኔ ሀይል ብቻ አልነበረም:: በወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት የነበሩት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማሪያም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪወችን ሰብስበው ሲያነጋግሩ እንዳሉት የትግራይ ሕዝብ ከገበሬ እስከምሁር ወንድ ሴት ሳይሉ ተሰባስበው በሽሬ የነበረውን የመንግስት ሰራዊት እንደጠላት ጦር እንደጨፈጨፉት ነው:: ይህ ብቻም አይደለም: በመላ ኢትዮጵያ በተለይ ደግሞ ወታደራዊ ካምፖች ባሉባቸው አካባቢወች ሁሉ እብድ መስለው: ዘበኛና ገረድ ሆነው: በሽርሙጥና ስራ ተሰማርተው – – -ነው ለወያኔ ሲሰልሉ የነበረው:: ዛሬም በዚያው ተግባራቸው ተሰልፈው ያለስጋት መረጃ እያቀበሉ እነሱ በደስታ እኛ በመከራ: እነሱ በአሰሪነት እኛ በተቀጣሪነት: እነሱ በሀብታምነት እኛ በድህነት: እነሱ በገዥነት እኛ በተገዥነት: እነሱ በመሪነት እኛ በጀሌነት- – – እንድንኖር ለማድረግ ነው ሲያዩት ልክ የሚመስል ሀሳብ እያራገቡ የምናካሂደውን የሞት ሽረት ትግል ለማደናቀፍ በስልት እየተንቀሳቀሱ ያሉት::

 

የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ የሚያበቃው በመልመጥመጥ አይደለም:: የህዝብ ትግል ዳር የሚደርሰው በፍርሀት እየራዱ: እንደቄጠማ እያረገዱ የማባበያ ቃላት በመደርደር አይደለም:: እነሱ እንደሚሉን እውነትም ደደብ አህያ ካልሆንን በስተቀር “በደም የተገኘን ስልጣን በካርድ አሳልፈን አንሰጥም! ትግሬና ወያኔ አንድ ነው! ወያኔ ከሌለ ትግሬ የለም ማለት ነው! –” እያሉ እየነገሩን ባለበት ሁኔታ “ወያኔና ትግሬ አንድ ነው የሚለው የወያኔ ወሬ ሀሰት ነው!” ብሎ ያወገዘ አንድም  የትግራይ አካባቢ ሳይኖር ካለማወላወል የሚናገሩትን ትተን ያላሉትን ብለን ለመከራከር ባልደፈርን ነበር!

 

እነ አቦይ ስብሀት ነጋ: እነ ብቸኛው ጀኔራል ሳሞራ የኑስ: ሰምና ወርቅ በሌለው አገላለጽ የወያኔን እና የትግራይን ሕዝብ አይነጣጠሌነት ቁልጭ: ቅቡጭ አድርገው ነግረውናል:: ድርጅቱም ቢሆን የትግራይ ሕዝብ እንጅ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻ አውጭ እንዳልሆነ ከሚጠራበት ስም ጀምሮ እስከሚፈጽማቸው ተግባራት ድረስ ያሉት ጭብጦች አስረጅ ናቸው::

 

ሁሌም ሳስበው ከሚረብሹኝ ነገሮች አንዱ የወልቃይት ጉዳይ ነው:: የወልቃይት ሕዝብ “ኧረ እኛ አማሮች ነን” እያሉ ሲጮሁ “እናንተ ባታውቁት ነው እንጅ ትግሬወች ናችሁ” በሚል መንፈስ በግዳጅ ወደትግራይ መካለላቸውን በመቃወማቸው የደረሰባቸውን ግፍ ሁላችንም እናውቃለን:: ይህን በ21ኛው ክ/ዘመን እየተደረገ ያለውን የወያኔ የቅኝ ገዥነት ተግባር ያወገዘ የትኛው የትግራይ አካባቢ ነው? ወልቃይት አማራ ነው የሚሉትን ወልቃይቴወች ለመቃወም “ለሀገር ሰላም ለህዝብ ፍቅር” ሊለምኑ የሚገባቸው አዛውንትና አሮጊቶች ሳይቀሩ ጠበንጃ ይዘው መውጣታቸውን የማያውቅ ማን አለ? በተቃዋሚወች ጎራ የተሰለፉት ግለሰቦች ሳይቀሩ ታሪክን መሰረት ያላደረገ የተዛነፈ ፍርድ የሚሰጡትስ ለምን ይመስላችኋል? እያሉን ያሉት እኮ ወያኔ በሀይል ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ የወልቃይትን ህዝብ እያፈናቀለ የራሴ የሚለውን ወርቅ የትግራይ ሕዝብ እንዲሰፍር አድርጎ ዲሞግራፊውን ካዛባ በኋላ “ሕዝቡ ዴሞክራሲያዊ መብቱ ተከብሮለት በድምጽ ብልጫ ወደሚፈልገው ክልል እንዲካለል ይደረግ” ነው::  እስቲ ሁላችሁም ይህን አካሄድ ልብ በሉት!

 

ክልሎች አብረው መኖር እስካልፈለጉ ድረስ ተገንጥለው የራሳቸው ሀገር ሊመሰርቱ ይችላሉ የሚል የመገንጠል መብት በሕገመንግስት ተቀምጦ እያለ ይቅርና ባይኖር እንኳ ካላንዳች ታሪካዊ መሰረትና ካለሕዝብ ፈቃድ አንድን አካባቢ ከአንዱ ክልል ወደ ሌላ ክልል  በጉልበት ማካለል ፍትሀዊ ሊሆን አይችልም::

 

በወያኔ መሰሪ አካሄድ ሀገራችን ችግር ላይ ናት:: በሕዝቡ መሀል ከአንድነት ስሜት ይልቅ የፍርሀትና የጥርጣሬ ስሜት አይሏል:: የስራ እጦቱ: ድህነቱ: የኑሮ ውድነቱ: የመልካም አስተዳደር ችግሩ: ሙስናው: የዘር ክፍፍሉ: – – – እየከፋ በመሄድ ላይ ነው:: ወያኔ ችግሩን ሁሉ እየፈታ ያለው በኃይል ነው:: ይህ ኃይል የትግራይ ሕዝብ ነው:: ምኑም ያልገባቸው ወይም ለሆዳቸው ያደሩት የሌላ ብሄር አባላትም ቀላል የማይባል ድጋፍ እያበረከቱ ነው:: የትግራይ ሕዝብ እንደህዝብ ወያኔ እንደ ድርጅት በየአገኙት አጋጣሚ ሁሉ አንድ ነን እያሉን ነው: እኛ ደግሞ “ሀሰት አንድ አይደላችሁም!!” ብለን ክርክር ገጥመናል::

 

በአማራው ክልል ያለው መለስተኛ ጦርነት ሳይባባስ መፍትሄ ይፈለግ – #ግርማ_ካሳ

$
0
0

Gonder– በሰሜን ጎንደር ዞን 145 ወታደሮች ተገድለዋል

– ከአዘዞ ካምፕብቻ 143 ወታደሮች ካምፑን ጥለው እስከነ ትጥቃችው ጠፍተዋል

ህወሃት ለሰላም በሮቹን በሙሉ ስለዘጋ፣ በሰላም የሚታገሉ፣ እንደ አንድነት ያሉ ፓርቲዎችን አግዶ፣ እንደ አንዱዋለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን ኦልባና ለሌሳ …ያሉ ሰላማዊ የፖለቲካ መሪዎችን አስሮ፣ ምርጫ መቶ በመቶ አሸነፍኩ ብሎ፣ ዜጎች ወደ ማይፈለጉት መስመር ፊታቸውን እንዲያዞሩ ገፋፍቷቸዋል።የሰላም በር ሲዘጋ የአመጽ በር ተከፍቷል። በአሁኑ ወቅት ምንም መሸፋፈን አያስፈለግም፤ በተለይም በአማራው ክልል በአሁኑ ጊዜ መለስተኛ ጦርነት ነው ያለው።

አንዳንዶች የሕዝቡን ተቃዉሞ እንደ ቀላል ይቆጥሩታል። ከሚገባውም በላይ ሕወሃትን አጎዝፈው ይመለከታሉ። ምናልባት ሕወሃቶችም ራሳችው፣ ለብሄራዊ እርቅ እስከ አሁን ድረስ በራቸውን የዘጉት፣ ለራሳቸው ከፍተኛ ግምት ስለሰጡና ህዝቡንም ስለናቁት ይሆናል ብዬ አስባለሁ።

እርግጥ ነው የህወሃት ሰራዊት መሳሪያ የታጠቀ ሃይል ነው። ያኔ ደርግ እንደነበረው ማለት ነው። ግን የመሳሪያ ብዛት በራሱ የሚፈይደው ነገር አይኖርም። መሳሪያና ትጥቅ አስፈላጊነቱ እንደተጠበቀ፣ ጦርነት የሚደረግበት አካባቢ ሁኔታ፣ የወታደሮች ሞራልና ስሜት፣ የስለላ መረጃ የመሳሰሉትን የየራሳችው ትልቅ አስተዋጾ አላቸው። እንደ ደርግ በአፍሪካ የታጠቀ ሰራዊት አልነበረም። ወደ 500 ሺህ የሚሆን ወታደር ነበር። በመሳሪያና በወታደር ብዛት ቢሆን ደርግ አይሸነፍም ነበር። ያ ጦር ግን የተሸነፈው አንደኛ ወታደሩ ስለተሰላቸና ሻእቢያና ወያኔም በቀጥታ ቅድመ መረጃዎች ያገኙ ስለነበረ ነው። ወያኔና ሻእቢያ ደርግን ያሽነፉት ተዋግተው ሳይሆን በሳቦታጅ ነበር። አሁን ያለው የሕወሃት ሰራዊትም ከደርግ ሰራዊት በምንም አይለየም፡

ሕወሃቶች አንደኛ በአማራው ክልል የታጠቁ ሃይላት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴዎች የማወቅ እድል የላቸዉም። ያ ብቻ አይደለም፡ እነማን እንደሆኑም አያውቅም።

ሁለተኛ በኮንቮይ ከአዲስ አበባ ይሁን ከመቀሌ ወታደሮች መንቀሳቀስ ሲጀምሩ በቀላሉ መረጃዎች ይወጣሉ። የአማራው ክልል መሬቶችም አስቸጋሪ እንደመሆናቸው በወታደራዊ ኮንቮዩ ላይ ጥቃቶችን በመፈጸም ወይንም መንገዶችን በመዝጋት የጦሩን እንቅስቃሴ መግታት ወይንም ማጓተት ቀላል ነው የሚሆነው።

ሶስተኛ መሬቱን የማያውቅ ወታደር፣ ከባባድ መሳሪያ ቢሸከምም ፣ ጉድጓድ ሸንተረሩን ከሚያውቅ የአካባቢው ታጣቂ ጋር መፋለሙ ለርሱ አስቸጋሪ ነው። ባዙቃዉን ተሸክሞ ወደ ላይ ሲመለከት፣ በስር ከዋሻ ብቅ ብሎ አንዱ ይጠለዋል።

አራተኛ አሁን ያለው ሰራዊት በስሜት የሚዋጋ ሰራዊት አይደለም። የሚለግም፣ በሕዝቡ ላይ መተኮስ የማይፈለግ፣ እያጉረመረመ ያለ ሰራዊት ነው። በአለቆቹ እየተሰደበ፣ የዘር ልዩነት እየተደረገበት፣ እድገትና የዉጭ ስልጠና ለአንድ ብሄረሰብ ተወላጆች ብቻ ስለሚሰጠት የተማረረ ሰራዊት ነው። እንዲህ አይነት ሰራዊት ተዋግቶ ድል ማድረግ አይደለም፣ አንድ እርምጃ መራመድ አይችልም።

አምስተኛ ቀውስና አለመረጋጋት የተፈጠረባቸው ቦታዎች አድማሳቸው በጣም የሰፋ ነው። ድፍን ሰሜን እና ደቡብ ጎንደር ( ጎንደር ከተማ፣ ዳባት፣ ደባርቅ፣ አምባ ጊዮርጊስ፣ አዘዞ፣ ማክስኚት፣ ጎርጎራ፣ አርማጭሆ፣ ዳንሻ፣ ደብረ ታቦር፣ ጋይንት፣ አዲስ ዘመን፣ አዘዞ፣ ጭዋሂት፣ ሐሙሲት፣ ሳቆጥራ፣ አለፋ፣ አይንጋ፣ ሳንጃ፣ ሙሴ ባንድ፣ ቆላ ደባ….) በምእራብ ጎጃም ዞን ( ፍኖት ሰላም፣ ማንኩሳ፣ ቡሬ፣ ጅጋና እንዳለ የዳሞት አወራጃ )፣ ምስራቅ ጎጃም ዞን ( ደብረ ማርቆስ፣ አባይ በረሃ ፣ በደጀን አርጎ ወደ ሞጣ ከዚያ ባህር ዳር በሚወስደው መንገድ በአይንጋ) ፣ በባህር ዳር ከተማ እና በጢስ አባይ ከተማ፣ በሰሜን ወሎ ሸዋ (መቄት፣ ቆቦ፣ ማጀቴ ….)፣ በአጠቃላይ በመላው የአማራ ክልል ማለት ይቻላል እንቅስቃሴና ተቃዉሞ አለ። በስንቱ ቦታ ወታደር፣ ከዚህ እዚያ እያመላለሱ ይችላሉ ? እንደ ደሴ ፣ ደብረ ብርሃን፣ ወልዲያ፣ ኮምቦልቻ፣ ሸዋ ሮቢት ባሉ ቦታዎች ህዝቡ ተቃዉሞ ለማሰማት ተዘጋጅቷል። በነዚህ ከተሞች ከፍተኛ የወታደር ክምችት አለ። ህዝቡ እንዳይወጣ ለማፈን እየተጠባበቀ ያለ። ወታደሮቹ ወደ ሌላ ቦታ ከተንቀሳቀሱ ሸዋና ወሎ እንደ ፍም እሳት መቀጣጠሉ አይቀሬ ነው።

እስከ አሁን በተደረገው መለስተኛ ጦርነት፣ ሕወሃቶች ኮሎኔል ደመቀ ዘዉዱን አፍነው ለመወሰድ ብዙ ጊዜ ሞክረው አልተሳካላቸውም። ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም ጀመሮ እስከ አሁን በሰሜን ጎንደር ዞን ብቻ (ጎጃምን እና ደቡብ ጎንደር ዞንን ሳይጨምር) ቢያንስ 145 ወታደሮች ሕይወታቸው ጠፍቷል።

በጎንደር ከተማ አሥራ ስድስት የፌዴራል ፖሊስ፣ አንድ የመከላከያ ሰራዊት፣ አንድ ሚሊሺያ፣ ስምንት ልዩ ኃይል የተገደሉ ሲሆን በአዘዞ ሶስት፣ በአይንጋ አሥራ ሶስት፣ በአምባ ጊዮርጊስ ሶስት ፣ ቆላድባና አዘዞ መሃል ላይ (ከገበሬ ማህበር ጋር በተደረገ ጦርነት) ዘጠኝ ፣ በሙሴ ባንድ ዘጠና አንድ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተገድለዋል።
በአጠቃላይ 143 ወታደሮች። (ይህ መረጃ የተገኘው በሰሜን ጎንደር በጸጥታና ደህነነት እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት አመራር አባላትን ባካተተ ስብስባ ከቀረበ ሪፖርት ነው)

አንድ መቶ አርባ አምስት ወታደሮች መገደላቸው፣ የሕወሃት ጦር ያለበትን ከፍተኛ አጣብቂኝ አንዱን ገጸታ ብቻ ነው የሚያሳየው። ትጥቃቸውን እየያዙ ሰራዊቱን ትተው፣ ህዝቡን ከቀድሞ አለቆቻቸው ለመጠበቅ የሕዝቡን ትግል የተቀላቀሉም ጥቂት አይደሉም። አዘዞ ከሚገኘው የጦር ካምፕ ብቻ ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም ጀመሮ፣ ትላንት 13 የሰራዊቱን አባል ያካተተ አንድ ጋንታን ጨመሮ፣ አንድ መቶ አርባ አንድ ወታደሮች ካምፑን ጥለው ሄደዋል። ጠፍተዋል።

የህዝብን መብት በሃይልና በጠመንጃ ማፈን አይቻልም። ህዝብ ቆርጧል። የሕወሃትን መንግስት በፊትም አልመረጥኩም፣ አሁንም እኔን አይወክልም። ይሄን መንግስት የምሸከምበት ትከሻ ከአሁን በኋላ የለኝም ብሏል።ይህ ህዝብ አንገቱን ከዚህ በኋላ አይደፋም። የዚህን ህዝብ ጥያቄ ከመስማትና ከማክበር ዉጭ ሌላ አማራጭ የለም። የዚህ ሕዝብ ጥያቄ ፍትህ፣ ሰላም፣ ልማት፣ እኩልነት፣ አንድነት ፣ ዲሞክራሲ ነው።

በመሆኑ የሕወሃት መንግስት ያለዉን ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት በማስገባት፣ ነገሮች የበለጠ ወደ ከፋ ደረጃ ከመድረሳቸው በፊት፣ ነገሮችን በማርገብ፣ ራሱን ለብሄራዊ እርቅ እንዲያዘጋጅ አሳስባለሁ። በአፋጣኝ የሚከተሉት ቢደረጉም ይጠቅማሉ ብዬ አስባለሁ፡

1. የሕሊና እስረኞች በሙሉ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ

2. የሽግግር መንግስት ወይንም ካቢኔው አገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎችን ያካተተ( መድረክ፣ ሰማያዊ፣ መኢአድ. የቀድሞ አንድነትና ኢዴፓ) የአንድነት መንግስት ይቋቋም (ጦርነት ወይንም ችግር ሲፈጠር ብዙ ጊዜ እስራኤሎች የፓርቲ ልዩነቶቻቸው ወደ ጎን አድርገው ለአገራቸው ደህነንት ሲሉ የአንድነት መንግስት ይመሰርታሉ) ከ እስራኤሎች ትምህርት ይወሰድ። ከፓርቲ ይልቅ የአገር ሰላምና ደህንነት ይቅደም።

3. አሁን ያለውን የፌዴራል አወቃቀር የሚመረመር ገለልተኛ ኮሚሽን ይቋቋም። ይሄ በዘር ላይ የተመሰረተው ፌዴራል አወቃቀር ነዉና አሁን ወዳለነብት ቀዉስ ዉስጥ የከተተን።

4. ፖሊሲ፣ ፍርድ ቤት፣ ምርጫ ቦርድ፣ የህዝብ ቆጠራ ጽ/ቤት፣ የመከላከያ ሰራዊት፣ ሜዲያው ነጻና ገለልተኛ የሚሆንበት ሁኔታ እንዲፈጠር የሚረዳ ተቃዋሚዎችና ባለሞያተኞችን ያካተተ ኮሚሽን ይቋቋም።

5. ለሁለት አመት በኋላ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ይደረግ።

“ዐማራው፣ አሁንም በዘረኛው የትግሬ ወያኔ አገዛዝ የዘር ፍጅት እየተፈጸመበት ነው!”–ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

$
0
0

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት            

ሐሙስ ነሐሴ ፲፱ ቀን ፪ሺህ፰  ..              ቅፅ ቁጥር ፳፭

  • ወያኔ አጥፍቶ ለመጥፋት የመጨረሻውን መሰናዶ እያደረገ መሆኑ ግልፅ ሆኗል

moresh.jpgየትግሬ-ወያኔ ላለፉት 25 ዓመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ፣ በተለይም በዐማራው፣ በኦሮሞው፣ በሱማሌው፣ በሐዲያው፣ በአኙዋኩ፣ በኑዌሩ፣ በከፊቾው፣ ወዘተርፈ ላይ የፈጸመው የዘር ፍጅት፣ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ ሊፈጸም ቀርቶ ለማሰብ አስቸጋሪ ነው። ግፉ ከገደቡ አልፎ በመትረፍረፉ፣ የዚህ የከፋ የዘር ፍጅት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ሰለባ የሆኑት ነገዶች ተወላጆች፣ በዳያቸው የሆነውን የትግሬ-ወያኔ በቃህ ካሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። ለዚህ ማረጋገጫውም፣ በየአካባቢው በባዶ እጃቸው እስከ አፍንጫው ከታጠቀው ገዳይ ኃይል ፊት በመቆም በተከታታይ የሚያሰሙት የተቃውሞ ድምፅና ሰላማዊ ሰልፍ በግልጽ ያሳያል።

የትግሬ-ወያኔ ትውልድ በምድጃ ዙሪያ ከአያት ቅድመ-አያቶቹ ተግቶት ያደገው የዐማራ ጥላቻ እጅግ የሠፋና ሥር የሰደደ መሆኑ ይታወቃል። ለዚህም ሥር የሰደደ ጥላቻ ዋና ማሳያው፣ ገና የትጥቅ ትግል ሲጀምር፣«የትግራይ ሕዝብ ደመኛ ጠላት ዐማራ ነው!»፣ «ወያኔ ዐማራን ሳያጠፋ አንዳችም እረፍት አይኖረውም!» የሚል »መሪ ሀሳብ» በፕሮግራሙ ነድፎ መንቀሳቀስ የጀመረ መሆኑ ነው። በዚህ ጥላቻ ላይም ተመሥርቶ፣ ዘረኛው አገዛዝ ባለፉት 25 ዓመታት ብቻ  ከ5 ሚሊዮን በላይ ዐማሮችን ከምድረ-ገጽ አጥፍቷል። ሌሎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ዐማሮች ለዘመናት ከኖሩበት አካባቢ ሀብት ንብረታቸውን ነጥቆ በማባረር ለከፍተኛ ችግር ዳርጓቸዋል፤ በቁጥር ከአንድ ሚሊዮን ተኩል የማያንሱትን ዐማሮች ከኢትዮጵያ ምድር አሰድዷል። ይህ በዐማራ ጥላቻ ተወልዶ ያደገና ዐማራን ለማጥፋት የተደራጀ ዘረኛ ቡድን፣ ካለፈው ሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ፍትኅ በጠየቁ የዐማራው ተወላጆች ላይ የዘር ፍጅት በመፈጸም ላይ መሆኑን የዓለም የመገናኛ ብዙኃን በሥፋት እየዘገቡት መሆኑ ይታወቃል።

በዚህም መሠረት ከአርባ ዓመታት በላይ የዘር ፍጅት የተፈጸመበት የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ሕዝብ፣ ያነሳው የማንነት ጥያቄ፣ የእኛም ጥያቄ ነው። ወልቃይት ጠገዴ ዐማራ ነው፣ የእነርሱ ድምፅ የእኛምን ነው፣ ብለው በባህር ዳር ከተማ እሑድ ነሐሴ 1 ቀን2008 ዓም በሰላማዊ መንገድ ድምፃቸውን ባሰሙ ንፁሐን ዜጎች ላይ ነፍሰ በላው የአጋዚ ሠራዊት፣ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ስማቸውንና አድራሻቸውን ያገኘውን የ49 (አርባ ዘጠኝ) ሰዎች የስም ዝርዝር ማውጣቱ ይታወሳል። በዚህ መግለጫም ከሐምሌ 5ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ፣ በጎንደር ክፍለ-ሀገር የተለያዩ ቦታዎች በትግሬ-ወያኔ ሰው-በላ ነፍሰ ገዳዮች በተተኮሱ ጥይቶች በጠራራ ፀሐይ ከተገደሉት እና ከቆሰሉት ዐማሮች መካከል፣ የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት መረጃ አሰባሳቢ ቡድን ለማግኘት የቻለውን ዝርዝር በሚከተሉት ሠንጠረዦች አቅርቧል።

ሠንጠረዥ 1፦ የትግሬ-ወያኔ ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓም ጀምሮ በጎንደር ክፍለ-ሀገር እና በደብረ ማርቆስ ከተማ (ጎጃም) የገደላቸው ወገኖቻችን ዝርዝሩ ከፊል ዝርዝር

ተ.ቁስምየተገደሉበት አካባቢማብራሪያ
1ዘሪሁን (ሰሎሜ)ገደብየ፣ የገጠር ቀበሌልጆች እና ሚስት ያሉት
2ባየሁቀበሌ 10፣ ጎንደር ከተማወጣት እና ከቤተሰቦቹ ጋር ይኖር የነበረ
3በለጡ መሐመድቀበሌ 20 (አዘዞ)፣ ጎንደር ከተማ
4እንጀራ ባየቀበሌ 20 (አዘዞ)፣ ጎንደር ከተማ
5የቻፖራ ወንድምጎንደር ከተማየሚታወቀው የወንድሙ ስም ነው
6ግርማቸው ከተማአርባ፣ ላይ አርማጭሆ
7ሊሻን ከበደአይምባ የገጠር ቀበሌ
8መሌአይምባ የገጠር ቀበሌ
9አዛነው ደሴኩርቢ የገጠር ቀበሌ፣ አርማጭሆገበሬ
10አራጋው መለሰኩርቢ የገጠር ቀበሌ፣ አርማጭሆገበሬ
11ሰጠኝ አድማሱደልጊ ከተማ
12ታረቀኝ ተሾመደልጊ ከተማ
13ሔኖክ አታሎደልጊ ከተማ
14ደሴ ደረሰሻውራ፣ የገጠር ቀበሌየ53 ዓመት ጎልማሣ፣ ሚስት እና ልጆች ያሉት
15ግርማቸው ሞገስሻውራ፣ የገጠር ቀበሌደከማ እናት አለችው
16ወርቁጣቁሳ፣ የገጠር ቀበሌ
17ማማየ አንጋውዳንሻ ከተማተደብድቦ የሞተ
18ፈንታ አህመድዳንሻ ከተማ
19ክንፌ ቸኮልበአከር
20ዜናደብረ ማርቆስ ቀበሌ 03ደካማ እናት ያሉት
21ሲሳይ ታከለአርማጭሆ
22ማዕረግ ብርሃንደብረ ታቦር ከተማየቤገምድር ኮሌጅ የ2ኛ ዓመት ተማሪ የነበረ፣ ቤተሰቦቹ ታች ጋይንት ደምበጣ ቀበሌ የሚኖሩ
23መምህር ተስፋየ ብርሃንቀበሌ 01፣ ደብረ ታቦር ከተማቤተሰብ አለው
24ይበልጣል ደሴቀበሌ 01፣ ደብረ ታቦር ከተማቤተሰብ አለው፤ የማስተርስ ፕሮግራም የ2ኛ ዓመት ተማሪ

ማሳሰቢያ፤

  1. በወረታ ከተማ የሞቱት ሦስት ሰዎች ብዛት ሲሆን፣ የአንደኛው ሰው ማንነቱ አልተለየም፤ የሁለቱም ስም እስካሁን ለማወቅ አልተቻለም።
  2. በአዲስ ዘመን እና ይፋግ ከተሞች የተገደሉት ሰዎች ሁለት መሆናቸው ታውቋል። ስማቸውን ግን እስካሁን ለማረጋገጥ አልተቻለም።
  3. በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሞቱት ሦስት ሰዎች  መካከል የአንደኛው ሰው በስም ሲታወቅ የቀሩት ገና አልታወቀም።
  4. በአርማጭሆ ወረዳ የተገደሉት 10 (አሥር) ሰዎች እንደሆኑ ታውቋል።

የቆሰሉ ሰዎች፦

ተ.ቁስምየቆሰለበት አካባቢማብራሪያ
1ሀብቴ ዓለሙሻውራ፣ የገጠር ቀበሌበጸና ታምሞ ለከፍተኛ ሕክምና ወደ አዲስ አበባ ሄዶ እንዲታከም ተብሏል። ሆኖም ጭንቅላቱ በጥይት ስለተመታ የመትረፍ እንድል እንደሌለው ተገልጣል።
2ይደነቅቀበሌ 20 (አዘዞ)፣ ጎንደር ከተማ
3አይሸሽም ወርቄቀበሌ 20 (አዘዞ)፣ ጎንደር ከተማ
4ምናለቀበሌ 20 (አዘዞ)፣ ጎንደር ከተማ
5ጌታቸው ሞላቀበሌ 18፣ ጎንደር ከተማ

 

ይህ ሕዝባዊ እንቢተኝነት ወያኔ የቆመበትን የሥልጣን መሠረት በማናጋቱ፣ የአገዛዙ ሥርዓት ከመጥፋቱ በፊት ጠላቴ ነው ብሎ በፈረጀው የዐማራው ነገድ ላይ የመጨረሻውን የጥፋት በትር ለማሣረፍ እየተንቀሣቀሰ ቁርጠኛ ውሳኔ ላይ የደረሰ እና በተግባርም በግልፅ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ሆኗል።  ለዚህ ተግባሩ ማሳያ ሆነው ከሚጠቀሱት ማስረጃዎች መካከለል የሚከተሉት ይገኙበታል።

አንደኛ፦ የአገሪቱን የመከላከያ ተቋሞች ከመሀል ኢትዮጵያ ነቅሎ ወደ ትግራይ ወስዷል፤

ሁለተኛ፦ የአገሪቱን የመረጃ ማዕከል ከአዲስ አበባ ነቅሎ ትግራይ አስገብቷል፤

ሦስተኛ፦ ለምትገነጠለው ትግራይ የኢኮኖሚ መሠረት የሆኑ ፋብሪካዎችን፣ ኢንዱስትሪዎችን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ ኮሌጆችን፣ መንገዶችን፣ ከተሞችን፣ መገናኛ ተቋሞችን በኢትዮጵያ ሕዝብ አንጡራ ሀብት ገንብቷል፤

አራተኛ፥ ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓም ጀምሮ በጎንደር፣ በጎጃም፣ በወሎ እና በሸዋ እንደሰደድ እሳት የተቀጣጠለው ሕዝባዊ እንቢተኝነት ሕዝቡን በመሰለል ሲያስሩና ሲያስገድሉ በነበሩት በወያኔ አባሎች ላይ በማነጣጠሩ፣ ሽብር ውስጥ የገባው ዘረኛው የትግሬ-ወያኔ ቡድን በጎንደርና በባሕርዳር ይኖሩ የነበሩ የሥርዓቱ አቀንቃኝ የሆኑትን ትግሬዎች ለይቶ በሌሊት ወደ አዲስ አበባና መቀሌ እንዲሄዱ አድርጓል።

አምስተኛ፦ በጎንደርና በጎጃም በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆችን ነጥሎ ወደ ትግራይ እንዲሄዱ አድርጓል።

እነዚህ ድርጊቶች ወያኔ በጎንደርና በጎጃም ነዋሪ በሆነው የዐማራው ነገድ ላይ ጅምላ ጨራሽ የሆነ ፍጅት ለመፈጸም የተዘጋጀ እንደሆነ የሚያመላክቱ ምልክቶች እንደሆኑ ብዙዎች ይስማማሉ። ሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት፣ «ወያኔ ዘሩን በነቂስ ከጎንደር እና ከጎጃም ማስወጣቱ ምን ሊማድረግ አስቦ ነው?» የሚለውን ጥያቄ ለአካባቢው ነዋሪዎች አቅርቦ ነበር። ላቀርብንላቸው ጥያቄዎች የአካባቢው ሰዎች የሰጡን ጠቅለል ያለ መልስ፦ «የትግሬ-ወያኔዎች በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖረውን የዐማራ ነገድ እና ከዐማራው ጋር ተሰባጥረው የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ዘር ጨራሽ በሆኑ ኬሚካሎች እና ባዮሎጂካዊ የሕዝብ መፍጃ ባክቴሪያዎችና ቫይረሶች ለመፍጀት» እንዳቀዱ ድርጊቱ አመላካች እንደሆነ ይስማማሉ። «ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?» ለሚለው ተከታይ ጥያቄ አስተያየት ሰጪዎቹ የሚከተሉን ሊያደርጉ ይችላሉ ብለው እንደሚያስቡ ይገልፃሉ።

1       በውኃ ማጠራቀሚያ ገንዳዎች እና ጉድጓዶች መርዝ ሊጨምሩ ይችላሉ፤

2       ሕዝብን በገፍ የሚጨርሱ ተዛማች በሽታዎችን ሆን ብለው ሊያራቡ ይችላሉ። ለዚህ እንደማሳያ የሚሰጡት ሰሞኑን በባሕርዳር፣ በደብረታቦር እና በሌሎችም የዐማራ ከተሞች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ከውኃ ጋር በተያያዘ ጤንነቱ የታወከ እንደሆን ይገልጻሉ። አገዛዙም ይህን አጣዳፊ በሽታ«አተት»፣ ማለትም፦ «አጣዳፊ ተቅማጥና ትውክት» ብሎ እንደሚጠራው፣ እውነቱ ግን ይህ ኮሌራ በአገሪቱ በስፋት ሆን ተብሎ እንዲዛመት መደረጉን በቁጭት ያስረዳሉ።

3       ሌላው ሊያደርጉት የሚችሉት፣ ላለፉት 25 ዓመታትም አጥብቀው ሲሠሩበት የኖሩት፣ የወያኔ ትውልድ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ቁንጮ ላይ ካልቆየ፣ አገሪቱን በነገድ ከፍፋሎ እርስ በርሳቸው በማናከስ፣ እነርሱ የአገሪቱን ሀብት ዘርፈው ጠቅለው ትግራይ በመግባት የትግራይን ረፐብሊክ መመሥረት የሚለውን የቆየ ዓላማቸውን ዕውን ማድረግ የሚለው ነው። ለዚህ ዓላማ ተግባራዊነትም የሕገመንግሥቱ አንቀጽ 39 ለዚሁ ተግባር ሲባል የተቀመመ አጥፊ ቅመም እንደሆነ ይታመናል። ይህ አንቀጽ ሆን ተብሎ የተሰነቀረው፣ ወያኔ «ለብሔር/ብሔረሰቦች» ዕኩልነት አስቦና ተጨንቆ ሳይሆን፣ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ቁንጮ ላይ መቆየት ካልቻለ፣ ወያኔ በአገር ክሕደት ተከሳሽ መሆኑን ስለሚያውቅ፣ ከዚህ ማምለጫው ብቸኛ መንገድ ትግራይ ገንጥሎ መሄድ የሚለው በመሆኑ ብቻ ነው። አንቀጹም የተቀመጠው ለዚህ እንጂ፣ ለሌሎቹ አለመሆኑን የተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች ያሳያሉ። እነዚያን ቅድመ ሁኔታዎች ባንድ ቀን ጀምበር ማሟላት የሚችለው ወያኔ ብቻ ነው።

4       ወያኔ ከነአጥፊ ኃይሉ ወደ በቀለበት ትግራይ ምድር ተጠቃሎ መግባቱን ሲያረጋግጥ፣ ሌሎች ነገዶች ኃይላቸውን አስተባብረው የጭቃ እሾህ እንዳይሆኑበት፣ በራሳቸው ችግሮች እንዲወጠሩ ማድረግ የሚችል አጥፊ ሥራዎችን ይሠራል። ሊያደርጋቸው ከሚችሉ የጥፋት እርምጃዎች መካከል የኃይል ማመንጫዎችን ማውደም፣ ድልድዮችን ማፈራረስ፣ የመገናኛ አውታሮችን መበጣጠስ፣ የአገሪቱን ሀብት አሟጦ መውሰድ፣ ሕዝብ ይከተላቸዋል ብሎ የሚያስባቸውን ሰዎች በገፍ መግደል፣ የኢኮኖሚ ተቋሞችን መውሰድ የማይችላቸውን ማውደም፣ በታላላቅ ከተሞች በተቀነባበረ ሁኔታ ፈንጂ በማፈንዳት ሕዝብ መጨረስ እና ድርጊቱን «በተቃዋሚ አሸባሪነት» በሚፈርጃቸው ክፍሎች (በተለይም በዐማራው) ላይ ማላከክ፣ ወዘተርፈ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይታሰባል። ይህን ደግሞ ወያኔ አያደርገውም አይባልም። «ውሻን በምን ፈራኸው» ሲሉት በአጥንት እንዳለው፣ በገዛ ወገኖቻቸው ላይ የሐውዜንን ወንጀል የፈጸሙ ሰዎች በሌሎች ነገዶች ላይ አይፈጽሙም ብሎ ለማሰብ ያስቸግራል።

ወያኔ አጥፍቶን ከመጥፋቱ በፊት ተቃዋሚው ኃይል የሚከተሉትን ተግባሮች በተቀናጀ መንገድ መወጣት ቢችል ጥፋቱን ፈጽሞ እንኳን ማስቆም ባይቻል መቀነስ ይቻላል።

  1. ሕዝቡ በቡድን ተደራጅቶ፣ የውኃ ማከማቻ ጋኖችን በፈረቃ በስውር እና በግልጽ መጠበቅ እና ከብክለት መከላከል፤
  2. ሕዝቡ ነቅቶ የትግሬ-ወያኔን የማፍረስ እንቅስቃሴ እንዲገታ የተቀነባበረና ተደጋጋፊ ቅስቀሳ መሥራት፤
  3. በትግሬ-ወያኔን የስለላ መዋቅር ውስጥ ያሉ ሰዎችን ምንነት እና እንቅስቃሴ ነቅቶ መጠበቅ እና ተግባራቸውን በተከታታይ ማጋለጥ፤
  4. የትግሬ-ወያኔን ሕዝብ የማጥፋት ዓላማ በተጠናከረ እና ወጥነት ባለው መልኩ ለዓለም ማኅበረሰብ ሳይሰለቹ ማሳወቅ፤
  5. በፀረ-ወያኔው ጎራ ለጊዜውም ቢሆን፣ የጎንዮሽ መጎሻሸም ትቶ፣ ሙሉ አቅሙን በትግሬ-ወያኔ ላይ በማሳረፍ፣ ኢትዮጵያ እንደ አገር ልትቀጥል የምትችልበትን መንገድ መከተል። የትግሬ-ወያኔ ክፉኛ የሚሞተው ኢትዮጵያውያን በነገድ በመከፋፈላችን ሳይሆን፣ በአንድነት በመቆማችን ስለሆነ፣ ለአንድነቱ የምንችለውን ሁሉ በቀና መንፈስ ማድረግ፤

 

 

 

ከእነዚህ በተጓዳኝ የወያኔን አገዛዝ ዕድሜ ለማራዘም በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ፣ ወያኔ አጥፊ ቡድን ነው ብለን የምናምን የሚከተሉትን ለሦስት ተከታታይ ወሮች ላለማድረግ ለራሳችን ቃል እንግባ።

አንደኛ፦ በኢትዮጵያ ኢየር መንገድ አለመጓጓዝ፣

ሁለተኛ፦ ከኢትዮጵያ የሚመጣውን እንጀራ አለመግዛት፣

ሦስተኛ፦ ወደ አገር ቤት ገንዘብ አለመላክ፣

አራት፦ ከወያኔ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው ከሚጠረጠሩ ሰዎች ጋር ያለንን ማኅበራዊ ግንኙነት ማቋረጥ፣

እነዚህን ካደረግን አገር ቤት አፈሙዝ ተደግኖባቸው ሕዝባዊ እንቢተኝነቱን ለሚያጧጡፉት ወገኖቻችን ከፍተኛ የሞራል ድጋፍ ከማድረጉም በላይ የወያኔን ኢኮኖሚያዊ አቅም ስለሚያዳክምበት፣ አሳሪውና ገዳዩ ኃይል ከሕዝብ ጎን እንዲሰለፍ ያግዛል።

በማጠቃለያም፦ በእነዚህ ወገኖቻችን ስም ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በውጭ በስደት ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ የሚያስተላልፈው ጥብቅ መልዕክት ይኖራል፥ ቢያንስ ከላይ የተጠቀሱትን አራት ተግባሮች ከመስከረም 1 ቀን 2009 ዓም ጀምሮ  እስከ ኅዳር 30 ቀን2009 ዓም ድረስ ተግባራዊ እንድናደርግ ለራሳችን ቃል እንድንገባ በአክብሮት ይጠይቃል።

 

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃል-ኪዳን ነው!

ድሉ የሠፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው!

ሞት ለትግሬ-ወያኔና ለአጋሮቹ!

– See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/20036#sthash.PrX9NLY5.dpuf

ልትጠፋ ያለች ከተማ  በሃዘን ግዜ ዳንኪራ ታበዛለች። –ከተማ  ዋቅጅራ

$
0
0

tiyሰዶም እና  ጎሞራ ሊጠፉ የቻሉበት ምክንያት ነውራቸው ሳያሳፍራቸው ዳንኪራ በማብዛታቸው ነው። በደላቸውን እንደ መላካም ነገር በመናገር፣ ሃጥያታቸውን እንደ ጽድቅ በማውራታቸው፣ ነውራቸውን በአደባባይ ያለ ህፍረት በመግለጻቸው ነበረ የጥፋት እሳት ወርዶ ያጠፋቸው። ዛሬም ገዳይ እንደ ጀግና፣ በዳይና ጨቋኝ እንደ መልካም አስተዳዳሪ፣ በመቁጠር መልሰው መላልሰው ነውራቸውን ይነግሩናል። እኛም ስንመልስ ተዉ…. ዛሬ እዩኝ እዩኝ ነገ ደብቁኝ ይመጣል፣ ግዜ ያነሳውን ግዜ ይጥለዋል፣ መግቢያ  እስቀሚጠፋባችሁ ድረስ የጭንቅ ቀን ይመጣባችኋል፣ እያለን ሰሚ ከተገኘ ከቅድመ አደጋ በፊት  ማሳሰቢያዎችን ከመናገር ውጪ ሌላ የምናደርገው ነገር የለንም።

 

ኢትዮጵያ ድፍን 25 አመት ህዝቦቿን በማጠላለፍ እርስ በራሱ እንዲጠላላና በጠላትነት እንዲተያይ  ያለ መታከት በመስራት እርጉም ሐዋርያ በመሆን በመርዝ የተለወሰ  በብሔር እና ብሔረሰቦች ስም ስብከትን በመስበክ TPLF የበላይ ሆኖ ሁል ግዜም በንግስናው ለማስቀጠል ህዝብንና አገርን በማጥፋት ተልኮአቸውን ሲከውኑ ከርመዋል። የባህር በርን አሳልፈው የሰጡ፣ ከጎንደር እስከ ጋንቤላ የሚያካልለውን ለም መሬት ለሱዳን ለመስጠት ደፋ ቀና የሚሉ፣ በድርጊታቸው ሳያፍሩ መልካም እንደሰሩ በአደባባይ ነውራቸውን ሊነግሩን የሚዳዱ ጉዶች ናቸው።

 

በኢትዮጵያ ውስጥ ህዝቡ ወያኔ አይወክለንም ብሎ በግልጽ በማመጽ ተቃውሞውን የጀመረው በ1997 አመተ ምህረት ነው። ከዛ ግዜ ጀምሮ ውስጥ ውስጡን ሲንከባለል የመጣው ተቃውሞ ዛሬ ሙሉ ኦሮሚያን  እና  ሙሉ አማራን በማካለል እንቢ ለወያኔ ብለው ተቃውሞአቸውን በማቀጣጠል ላይ ይገኛሉ። በኦሮሚያ ከ9 ወር በላይ ያለማቋረጥ ወያኔ በቃኝ ብለው ሲቃወሙ የሚሰጣቸው መልስ ግን ሞትና እስራት በመሆኑ የኦሮሞ  እናቶች ልባቸው በሃዘን ቆስሏል። ህዝባችን ሃዘን ላይ በሆነበት ሰአት የትግራይ እናቶች በወርቅ ቀለም በተጻፈ ትግራዋያን የሚል ሪባን በደረታቸው ላይ በማንጠልጠል በአሜሪካ አገር በኢትዮጵያ  ህዝብ ሃብት ይጨፍሩ ነበረ። ወዮ ለናንተ ወዮ በደሃው ሃዘን ለምትደሰቱ ለናንተ ወዮታ አለባችሁ።

 

በአማራ  ክልል የተነሳው የህዝብ ንቅናቄ የወያኔ ጀሌዎችን እና የTPLF ስር መሰረቱን ያናጋው እንቅስቃሴ ነበረ። ሰላሚዊ ሰልፍ የወጡትን ገሎ መሄድ የለመደው ደም አፍሳሹ  ወያኔ ወደ አማራው ክልልም በመግባት አፍኜ እና ገድዬ እሄዳለው ብሎ የመጣውን የTPLF ሰራዊት በጀግናው ኮሬኔል ደመቀ ዘውዴ መሪነት ለዘላለም እንዲያሸልቡ በማድረግ ለአማራው ህዝብ የትግል አርማ  ሆኖ የተነሳ የዘመኑ ቴዎድሮስ ነው። ጀግናው የጎንደርም ህዝብ ጀግናውን በመከተል በውስጣቸው የነበረውን ጀግንነት እና ለጨቋኝ አልገዛም ባይነት ወኔ ተላብሰው የTPLFን ሰራዊት አብረከረኩት። በውስጣቸው የታመቀው ጭቆና ፈነዳ የነጻነት ሻማም በኮሬኔል ደመቀ አማካኝነት በጎንደር ተለኮሰ። ጎንደር የተለኮሰው የነጻነት ሻማ ጎጃምን፣ ወሎን፣ ሸዋን በማዳረስ ሙሉ አማራን በአንድነት አስተሳስሮ አስነሳ። የአማራው እንቅስቃሴ በመሳሪያ  የታጀበ ስለነበረ  የTPLF ጦር ተብረከረከ ሞት ሞት ሸተተው ድንጋጤም ዋጠው። የወያኔ ንግስና  የታወጀው በወልቃይት በኩል ነበረ ዛሬም የወያኔ ሞት የሚበሰረውም በወልቃይት በኩል ነው። እመኑኝ ይሄ ያልተበረዘ  እውነት ነው። ጀግና  ማለት ሰይጣናዊ ተልኮውን ለማሳካት ህጻንን፣ ሴትን፣ ወጣቱን፣ አዛውንቱን፣ የንጹሃንን ደም እያፈሰሰ  እናቶችን የሚያስለቅስ ሳይሆን …. ጀግና  ማለት እውነትን አንግቦ አንባ  ገነኖችን የሚጥል ሃቀኛ ታጋይ ነው።  ይሄ ጀግንነት ደግሞ  በመላው ኢትዮጵያ  ልቦናውስጥ ያለ  ሃቅ ነው። ሃሰትን ይዞ በጉልበቱ እና በጦሩ ከተመካው ጎልያድ ይልቅ እውነትን ይዞ በእግዚአብሔር የተመካው ትንሹ ዳዊት በጠጠር እና በወንጭፍ አሸናፊ እንደሆነ አስቡ። እውነት ምን ግዜም አሸናፊ ነው። በሰራዊት እና  በፈረሰኞቹ ከሚመኩት ጥጋበኞች ይልቅ እውነትን ይዘው የሚወጡት ሰፊው የኢትዮጵያ  ህዝብ ድል በእጁ ነው።

 

የጥፋት ምልክቶች እየታዩ  ነው።

የኢትዮጵያ  እናቶች እና  ህዝብ ሃዘን ላይ ናቸው። የስራ ማቆም አድማ፣ የሃዘን ቀን አዋጅ፣ የነጻነት ተጋድሎ ቀን፣ ህዝባችን እየወደቀ  እየተነሳ ባለበት ወቅት የትግራይ ህዝብ ግን ከበሮ እየደለቁ በአደባባይ ህዝባቸውን ሰብስበው አሸንዳ እያሉ ይጨፍሩብናል። ልትጠፋ  ያለች ከተማ  እና  ህዝብ በሃዘን ወቅት ጭፈራ  ያበዛሉ ይባላል። እነሱ ይጨፍሩብናል ምክንያቱም ሞት እነሱ ጋር አልገባማ ሃዘን እነሱ መንደር የለማ ጭቆና በነሱ መንደር አይታወቅማ። ዋ ለናንተ ልቦናችሁን ላደነደናችሁ፣ ዋ ለዛች ትግራይ ከተማ፣ ዋ ለናንተ  በራችሁን ዘግታችሁ በሰው ሃዘን በደስታ ለምትጨፍሩት፣ ደስታቹሁ በሃዘን ሳቃችሁ በለቅሶ እልልታችሁ በዋይታ እንደሚቀየር  አታውቁምን? አንድ ጽሁፍ አንብቤ  ነበረ  (ለትግራይ ህዝብ ጸልዩ) የሚል አዎ በእውነት ለሚመጣባችሁ እና  ለማይቀረው መዓት ትልቅ ጸሎት ያስፈልጋችኋል።  ጸሎቱ ምህረትን ሊያመጣ የሚችለው ግን ለሚመለስ ልብ ባቻ ነው እንጂ ጥፋቱ በራፉ ላይ ደርሶባቸው ዛሬም ያልሆኑትን ትግራዋያን ጀግና እያሉ ጥፋታቸውን ለሚያፋጥኑት አይደለም።

 

ሳጠቃልለው እውነት እውነት እላችኋለው ሰዶምና ጎመራ በነውራቸው እየጨፈሩ እንደጠፉት ሁሉ ዛሬም በኢትዮጵያ  ህዝብ በአዘናቸው ሰዓት ደስታቸው በማድረግ የሚጨፍሩት ከተማና  ህዝብ ይጠፋሉ። ይሄ  የሚሆነው ስለተናገርንም አልያም ዝም ስላልንም አይደለም መሆን ያለበት እውነት ስለሆነ እንጂ። ህዝብ ከተነሳ  ሰደድ እሳት ነውና ከፊቱ ያለውን በሙሉ ጠራርጎ ያጠፋል። አበቃው።

 

 

ከተማ ዋቅጅራ

26.08.2016

Emial- waqjirak@yahoo.com

ለሁሉም ጊዜ አለው –ማስተዋል በለጠ

$
0
0

 Justice

በመላዋ ሀገራችን ለነፃነታችን እየተዋደቁ የሚገኙ ዜጎች ውድ ሕይወታቸውን እየሰው የነፃነት ቀንዲሉን በማብራት ላይ ናቸው፡፡ ታሪክ ሲዘክረው የሚኖር ታላቅ መስዋዕትነት እየከፈሉ በመሆናቸው በአልሞ ተኳሽ የወያኔ አጋዚ ጦር አንገታቸው እየተቀላና ጭንቅላታቸው እየተገመሰ ሕይወታቸውን የሚያጡ ውድ ወገኖቻችንን ነፍሳቸውን ፈጣሪ ይማርልን፡፡

በዚያን ሰሞን ካነበብኳቸው መጣጥፎች አንዱ በ16 የትግራይ ተወላጆች የተጻፈው በወያኔ ላይ የተወሰደ አቋም ነው፡፡ ኪዳነ ምሕረት ትባርካቸው፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን አንድ ወቅት ጥሩ ኢትዮጵያውያን ተጋሩን(ትግሬዎችን) መቁጠር ጀምረው የቀኝ እጅ ጣቶቻቸውን ተጠቅመው (ይመስለኛል) አንድ ሁለት ሦስት ያህል እንደተጓዙ አምስትን እንኳን መዝለል አቃታቸውና “አሥር ቢሞሉልኝ ደስ ባለኝ” ብለው ተስፋ በመቁረጥ መቁጠሩን እንደተውት አርድተውናል፡፡ አሁን 16 መድረሳቸው ተስፋን የሚያጭር ነው፡፡ እየበዙ እንደሚሄዱ ደግሞ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ዕድሉን ስላላገኙት እንጂ በቁም ነገር ከተጫወትን ኢትዮጵያውያን ተጋሩ ቁጥራቸው ከዚህ እንደሚበልጥ መገመት አይከብድም፡፡ አገዛዙ ከትግሬ አይውጣ እንጂ ወያኔ ሥልጣን ቢለቅ የሚወዱ ትግሬዎች ደግሞ ጥቂት እንደማይሆኑ መገመት ይቻላል፤ ይህን ወያኔ የተከለብንን የዘር መዘዝ ለማጥፋት ማርከሻውን በቶሎ ካላፈላለግንና በ“ሜሪቶክራሲ”(በችሎታና ዕውቀት) መተካት ካልቻልን ገና ወደፊትም ብዙ እንዳክራለን፡፡

በመሠረቱ ከኢትዮጵያዊነት በወረደ ከዚህኛው ወይም ከዚያኛው ጎሣ እየተባባሉ ማናቸውንም ዓይነት ተቃውሞን መግለጹ ዘመናዊነትን ሊገልጽና የሥልጡን ፖለቲካ መታወቂያ ሊሆን እንደማይገባው አምናለሁ፤ በሃይማኖትና በአካባቢ ልጅነት መደራጀትም እንደዚሁ ተገቢ አለመሆኑ ይገባኛል፡፡ ቢሆንም ቅሉ … ከዐማራ ተወላጆች፣ ከኦሮሞ ተወላጆች፣ ከትግራይ ተወላጆች … የምንለው ነገር ለጊዜው ጠቃሚ ሆኖ ከተገኘ ማለትም እየወረደብን ያለውን የመከራ ዶፍ ከመመከት አኳያ አንዳች ፋይዳ ካለው ቢያንስ በመርኅ ደረጃ ብደግፈው ብዙም አይከፋኝም፡፡ እናም አብላጫውን ደሜን ያገኘሁት ከሦስቱም ‹በጥባጭ‹ ዘውጎች መሆኑን ከሕይወት ተሞክሮ የተረዳሁት ማስተዋል በለጠ በዚህ መጣጥፍ ውስጥ ያለውን አስተያየት በቀናነት የምሰነዝረው አድማጭ አገኛለሁ ከሚል ትልቅ ተስፋ ነው፡፡

ታሪኬን ብዙዎች ይጋሩት ይናል ብዬ ስለማምን ስለራሴ ትንሽ ብናገር ደስ ይለኛል፡፡ መነሻየ ግምት እንጂ ጥናት አይደለም፡፡ የብዙ ጥናቶች መሠረት ለእውነት የቀረቡ ግምቶች መሆናቸውንም አንዘንጋ፡፡ እናም የእኔ ዘውጋዊ ቀመር እንደሚመስለኝ 30% ዐማራ፣ 30% ኦሮሞ፣ 30% ትግሬ እና 10% ከሌሎች ነው፤ እንዲህ የሆንኩ ያህል ይሰማኛል፡፡ እንደዚህ ስል ደግሞ የሚያምነኝ እንደማላገኝ ብቻ ሣይሆን ጥቂት የማይባሉ ሰዎች እንደሚያላግጡብኝም ይገባኛል፡፡ የእኔ እውነት መነሻ ግን ይሄውላችሁ፡፡

መልኬን አሁን ላሳያችሁ ባለመቻሌ አዝናለሁ፡፡ ትግሬ ጋ ስሆን ፊቴን ያዩና “ደምህ ወደደቡብና ወደ ኦሮሞ ይሄዳል” ይሉኛል፡፡ ኦሮሞ ጋ ስሆን “መልክህ የዐማራና የትግሬ ይመስላል” ይሉኛል፡፡ ዐማሮች ጋ ስሆን “አባትህ ከደቡብ የተቀጠሩ ወታደር ሳይኑ አይቀሩም” እያሉ ይቀልዱብኛል፡፡ እኔ ራሴን በመስተዋት ስመለከት አንዱንም የማልመስል ከሁሉም ግን ጥቂት ጥቂት እንደወሰድኩ ያህል ይሰማኛል፡፡ ትልቁ ማስረጃየ ግን ሦስቱም ዘውጎች ከየተነሱበት መጥተው የሚያልቁበት ቦታ ላይ መወለዴ ነው፡፡ አዎ፣ የአማራ፣ የትግሬና የኦሮሞ ጠቅላይ ግዛቶች የሚጫፈሩበት(overlap የሚያደርጉበት) ሥፍራ ላይ ነው የትውልድ መንደሬ፡፡ ለዚህም ነው ቁርጥ ባለ ሁኔታ ይህን ወይ ያን ልመስል ያልቻልኩት፡፡

ስለዚህ አንዱ በዐማራነቴ አህያ ቢለኝ ወይም ዛሬ ጧት በፕሮፌሰር አልማርያም መጣጥፍ ላይ እንዳነበብኩት “የአእምሮ ዘገምተኛ” ቢለኝ ወይም በኦሮሞነቴ “ሽብርተኛ”ና “ወንጀለኛ” ብባል ወይም በትግሬነቴ ዘረኛና ጎጠኛ ብባል ብዙም የሚሰማኝ አልሆንም፡፡ ሁሉን መሆን አንዳንዴ ዕዳ አንዳንዴ ደግሞ በረከትም ነው፡፡ የሆንኩትን እንድሆን የመምረጥ ዕድል ያልተሰጠኝ መሆኔ ግን በከንቱዎች ከንቱ አባባል እንዳልቆጣ ትልቅ የትግስት ጋሻ አስጨብጦኛል፡፡ ለመሆንና ላለመሆን ምርጫ ባልተሰጠኝ ሁኔታ በሆንኩት ነገር መበሳጨትም ሆነ ከሰው ጋር ትርፍ ንግግር ውስጥ መግባት ትልቅ ሞኝነት ነው፡፡

ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሣ ሰሞኑን በጻፈው መጽሐፍ የትውልድ አካባቢየና ተፈጥሮ ቀድመው ያቆራኙትን ዐማራነቴንና ኦሮሞነቴን በተመለከተ ብዙ ነገር አትቷል፡፡ የፕሮፌሰሩ ልፋትና ድካም ይገባኛል፤ በሕዝቡና በሀገሩ ሰላምንና ፍቅርን፣ ወንድማማችነትንና እትማማችነትን ለማስፈን በመፈለጉ ብዙ ርቀቶችን ተጉዞ በእምቅድመ ዘመነ ታሪክ በአዳምና ሔዋን አንድ የሆንነውን ግን የዘነጋነውን እኛን አንድ አድርጓል፡፡

በመሠረቱ ታዲያ ጥቁሮች ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሣይሆን የሰውን ዘር በሞላ በሥነ ፍጥረት አንድ ያደረገ ፈጣሪ ከአዳምና ከሔዋን አንስቶ አሁን የምንገኝበትን የሰባት ቢሊዮን የሕዝብ ቁጥር ለበረከትም ይሁን ለእርግማን እንደሰጠን ለምናምን ሰዎች የሰውን ልጅ አንድነትና የዘር ሐረግ ወጥነት ለመረዳት አንዳችም ምርምር ባላስፈለገን ነበር፡፡ ይሄ አንድ የመሆን ወይም ያለመሆን ችግር አይደለምና ዋናው እየበጠበጠን የሚገኝ ችግራችን፡፡

(እንደኔ አስተሳሰብ) የሰው ልጅ ዋና ችግር የዘር ሐረጉ መለያየት አይደለም፡፡ ትልቁ ችግር የተፈጥሮ ሀብትን በአግባቡ ከመከፋፈል አንጻር የሚታየው ኢ-ፍትሃዊነት ነው፡፡ ምክንያቶቹ የፈለገውን ያህል በቅርጽ ቢለያዩም ዋናው ችግራችን የሀብት ክፍፍል ላይ የሚፈጠር የ“ያንተ በዛ፣ የኔ አነሰ” ዓይነት መፎካከርና ያን ተከትሎ የሚፈጠር ቀውስ ነው፡፡ አንዱ በጉልበቱ ወይም በብልጠቱ ቢሊዮን ሲወስድ ሌላው መቶም አያገኝም፡፡ አንዱ ያለ የሌለ ዘዴና ብልኃቱን ተጠቅሞ ወደሀብትና ሥልጣን ማማ በአቋራጭ በመውጣት እንደካሙዙ ባንዳ ዕድሜ ልኩን ሲጎለት ይህን ቅጥፈት የታዘበ ሌላው ባለወር ተራ ደግሞ ወደዚያ ሥፍራ ለመጓዝ የንጹሓንን ደም እየገበረ ሌት ከቀን በእውኑም በህልሙም ይባዝናል፡፡ እንጂ የመለስ ዜናዊ የ17 ዓመታት ጉዞና የቢሊዮን ዶላሮች ክምችት ለእንደርታው ገበሬ ለአቶ ሐጎስ ፀጋዝኣብ የፈየደለት አንድም ነገር እንደሌለ ቢያንስ ኅሊናችን ይረዳዋል – ይህን የምለው ታዲያ አጠቃላዩን እውነታ ለመግለጽ እንጂ የመለስ ሸፋፋና ወልጋዳ አስተሳሰብና አመራር ጥቂት የማይባሉ ተጋሩ ወንድምና እህቶቼን አልጠቀመም እያልኩ አይደለም፡፡ የተጠቀመ ተጠቅሟል፤ የተጎዳም እንዲሁ፡፡

ሁላችን እናውቀዋለን፤ የሰው ልጅ ዘር አንድ ነው፡፡ ነጭና ጥቁር የመጣው ከጊዜ በኋላ እንደሆነ መጻሕፍት ይናገራሉ፡፡ የመልክና የቁመት ልዩነት እንደሆነ በማኅበረሰብ ደረጃ ይቅርና በኔ ቤትም ጎልቶ የሚታይ ግን ተዓምራዊ ያልሆነ ተራ ክስተት ነው፡፡ በኔ ቤት ለምሣሌ እኔ ወደጥቁርነት የማደላ ፉንጋ የቀይ ዳማ ስሆን አንዱ ልጄ ቆንጆ ቀይ፣ አንዱ ደግሞ ከኔ የባሰ አሻሮ ናቸው፤ ሌሎቹም እንዲሁ የተለያዬ መልክ፣ ቁመትና ጠባይ አላቸው – “ቤቴ መንገድ ዳር አለመሆኑን”ና ታማኝ የትዳር አጋር ያለኝ መሆኔን አስቡልኝ ታዲያ! (በነገራችን ላይ አንዳንድ ሸረኛ አንባቢ ምን ሊለኝ እንደሚችል እያሰብኩ ነው ከመንገድ እየወጣሁ ደረጃውን ባልጠበቀ የመነቸከ ቀልድ ላስፈግጋችሁ የምሞክረው)፡፡ እነዚህን ልዩነቶች እኔና እናታቸው አልሰጠናቸውም – ባልሰጠናቸው ልዩነት ደግሞ አይጣሉም፡፡ ስለዚህ ልዩነትን ለጠብ ማዋል የከይሲዎች ተግባር እንጂ የደግ ሰው ጠባይ አይደለምና መጠንቀቁ ጠቃሚ ነው፡፡

ይህን የልዩነት ሰበዝ በኦሮሞነትና በዐማራነት ካየነው እርግጥ ነው “ይህ ሰው ኦሮሞ ነው”፣ “ይህ ሰው ጉራጌ ነው” የምንልባቸው ልማዳዊ የሰውነት ቅርፆች ሊኖሩ እንደሚችሉ በበኩሌ እረዳለሁ፡፡ ለዚህም ነው ከፍ ሲል የኔ የሰውነት ቅርጽና የመልክ ይዘት የዚህ ወይ የዚያ ሣይሆን ድብልቅ ነው ለማለት የደፈርኩት – ለፖለቲካ ፍጆታ አይደለም፡፡ To my belief, there are some typically subtle features of ethnics if they are not mixed up and diluted through intermarriage. And, in most cases, the Ethiopian societies are said to be interwoven to the extent of not being able to be clearly and unmistakably identified as this or that ethnic group, excepting some incidents especially in remotest rural areas where there is less chance of intermingling through intermarriage.

እውነት እንነጋገር ካልን ታዲያ ከሥነ ልሣናዊ ተቀራራቢነትም ይሁን ከአካላዊ ቅርጽ አኳያ አንድ ትግሬና አንድ ዐማራ የሚለዩበትን ገጽታ(feature) ለመለየት በበኩሌ እቸገራለሁ – ተፈጥሯዊ ዝምድናቸው በጣም ያቀራርባቸዋል፡፡ ይህንን ስል ፕሮፌሰር ፍቅሬ ያለውን የኦሮሞና የአማራ ጎሣዎች የመባቀያ ተመሳሳይነት ጨብጬ ይህን እኔ የምለውንም በተጨማሪነት ለማስገንዘብ ፈልጌ እንደሆነ መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ ዐማራና ኦሮሞ አንድ መሆናቸው የሚያስደስተኝን ያህል ትግሬና ዐማራም አንድ ብቻ ሣይሆኑ እንደኔ እንዲያውም ሁለቱ ጎሣዎች ወያኔን ተመስሎ ከፋፋይ ሰይጣን በመካከላቸው ገብቶባቸው እንጂ በልይት ዘውግነት መለያየት ራሱ ይበዛባቸዋል ባይ ነኝ – በአንድ ዘውግ ሥር መመደብ ነበረባቸው እያልኩ ነው በግልጽ ዐማርኛ፡፡ የአሁኑን ባላውቅም በኔ የወጣትነት ዘመን አንድን ትግሬ ከአንድ ዐማራ ለመለየት ምናልባት በትግሬው ግምባር ላይ ይቺ 11 ቁጥር የምንላት ታርጋ ኖራ በሷ ካልለየነው በስተቀር በምንም መንገድ አይለዩም ነበር – በነገራችን ላይ የሌላቸውም አሉ (ባይገርማችሁ ባለ 11 ቁጥር ዐማራ አለ፤ 11 ቁጥር የሌለው ትግሬም አለ)፡፡ ወያኔ እንደጣዖት የሚያመልክባትን የብሶተኞች የምትመስል 11 ቁጥርን በድንበር አካባቢ ያለን ሰዎችም አለችን፡፡ ለዐይን ህመም ተብሎ ብዙዎቻችን እንቀነደብ እንደነበር የኔም ግምባር ኅያው ምሥክር ነው፡፡ በኔ አካባቢ የባህሎች መዋሃድ ስላለ የብዙ ማኅበረሰቦች አሻራ በሁሉም ሰው ላይ ይታያል፡፡

በተረፈ ግን ዱሮ ትግሬን ከዐማራ ለመለየት የሚቻልበት ዘዴ አልነበረም፡፡ መልክና ቁመናቸው፣ ሥነ ልቦናዊ ቀመራቸው፣ ሥነ ልሣናዊ ዳራቸው፣ ሃይማኖታዊ ሥርዓታቸው፣ አመጋገባቸውና አለባበሳቸው፣ እንግዳ አቀባበላቸው፣ ሰውን አክባሪነታቸው፣ ባህላቸውና ኢኮኖሚያዊ ትስስራቸው ሲታይ አንዳቸውን ከሌላኛቸው መለየት የማይቻልበት ሁኔታና ወቅት ነበር – የዛሬውን ዘመነ ጥልሚያኮስ አያድርገውና፡፡ ለምሣሌ ሁለት ኦሮሞዎች እዚህ አጠገቤ እያወሩ ነው ልበል፡፡ በዚህኛው ሌላኛው አጠገቤ ደግሞ ሁለት ትግሬዎች እያወሩ ነው ልበል፡፡ አንድ ኦሮምኛም ትግርኛም የማይችል በዐማራነት የሚታወቅ ሰው ቢያዳምጥና ከየትኛዎቹ ምን እንደተረዳ/እንደሰማ ይህ ቢጠየቅ በርግጠኝነት ከትግርኛ ተናጋሪዎቹ በአነስተኛ ግምት ወደ 25 በመቶ የሚጠጋውን ሊረዳ ሲችል ከኦሮምኛ ተናጋሪዎች ግን 5 በመቶውን እንኳን ስለመረዳቱ እጠራጠራለሁ፡፡ ታዲያ ይህን የትግሬ-ወያኔዎችን በዐማሮች ላይ መጨከን ምን አመጣው? ይህ ይመስኛለል ትልቁ የዘመናችን ዕንቆቅልሽ፡፡ ፍቺ ያጣንለት ሚሌኒየማዊ ጥያቄ ነው፡፡ ምን ዓይነት ሰይጣን በወንድማማቾች መካከል ገባ? በውነቱ በተለይ በተጋሩ ወንድሞቼ አካባቢ ይህን የምለውን እውነት የሚያስታውስ ጠፍቶ ነው ወይንስ ማስታወስ አስፈላጊ ሣይሆን ቀርቶ ይሆን? ለምን? ማንን ለመጥቀም? እነዚህን ወንድማማች ማኅበረሰቦች በማፋጀት የሚገኘው ጥቅም ምንድን ነው? ጥላቻን ዘርቶ ዐመፃን ማጨድ ማንን ነው የሚጠቅመው? ተጋድመው የተፉት ምራቅ ተመልሶ ወደራስ እንደሚመጣስ መገንዘብ እንዴት ያቅታል? አሁን በዐማሮች ላይ እየተደረገ ያለው ሊታመን የማይችል ሲዖላዊ ተዓምር ወደሰማዩ ጌታ መጮኹና መልስ ማግኘቱ ይቀራል? ያኔ ምን ይውጠናል?

የሰዎች ትክክለኛ የኅሊና ፍርድ ተዛብቶ ወደ ከፋና ከረፋ ዝቅተኛ የአስተሳሰብና የአመለካከት ደረጃ ለምን እንደሚወርድና አንዱ በአንዱ ለምን እንደሚጨክን ብዙ ጊዜ ይጠየቃል፡፡ መልሱ ደግሞ ቀላል ነው – እሱም ጥቅም ነው፡፡ ጥቅም አይደለም ጎሣና ነገድን ወንድምና እህትን ያገዳድላል፡፡ አባትና ልጅን ያባላል፡፡ ቤተ ዘመድን ያጨራርሳል፡፡ ጥቅምና ሥልጣን በጣም አደገኛ መርዝ ናቸው፡፡ “የአቦይ ስብሃት ሀብት ከሚነካ የትግራይ ሕዝብ ጥንቅር ይበል፤ የአባይ ፀሐዬ ሥልጣን ከሚሸረሸር የትግራይና ዐማራ ሕዝብ ሚና ለይቶ ይጨራረስ፡፡ መንግሥቱ ኃ/ማርያም ሥልጣኑን ከሚያጣ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ባፍ ጢሟ ትደፋ፡፡…” ይህ ነው የግለሰቦች የሥልጣንና የሀብት አምልኮ፡፡ እንጂ ሕዝብና ሕዝብ በየትም ሀገር ለጠብና ለፍጅት ተፈላልጎ አያውቅም፡፡ የዕልቂት ከበሮ የሚጎስሙ ወገኖች በሀብትና በሥልጣን ሱስ ናላቸው የዞረ ጥቂት ግለሰቦችና በሥራቸው የሚኮለኩሏቸው አጥፊ ጀሌዎች ናቸው፡፡ ይህ ዓይነቱ የትያትር መድረክ ደግሞ መጋረጃው ሲዘጋ አብሮ የሚዘጋና በሌላ የተሻለ ወይም እንደኛ እንደስካሁኑ ከሆነ የጥንቱን በሚያስመሰግን መጥፎ ታሪክ የሚተካ ነው – እስካሁን እንዲህ ነበር ወደፊትም እንዲሁ ነው፤ ክፉም ሆነ ደግ መንግሥት ወይም ሥርዓት ባለበት ለዘላለም አይኖርም፡፡ ሕዝብ ግን ዘላለማዊ ነው፡፡ እናም ውድ ኢትዮጵያውን አይዞን ይህ ወያኔዊ የጥፋት ዘመን አልፎ የፍቅርና የመተሳሰብ ዘመን በቅርብ ይመጣል፡፡ ጸሎታችን መሆን ያለበት መስዋዕትነቱ እንዲቀንስልን “ጌታ ሆይ ዕርዳን” ነው – እኛም ከክፋትና ከአጥፊነት ርቀን ታዲያ፡፡ ደግሞም በመካከላችን ጥላቻን አናባብስ፡፡ የሚተርፈን ትዝብቱ ነው፡፡ ኢትዮጵያ እንደሆነች ጠፍታ የማትጠፋ የፈጣሪ ቃል ኪዳን የሚጠብቃት ሀገር ናት – በወረት የዘረኝነትም እንበለው የትምክህተኝነት ንፋስ አንወሰድ፡፡ ከሁሉም ከሁሉም ምንም ዓይነት ጥጋብ አይፈታተነን፡፡ ብናገኝ አንኩራ፣ ብናጣም አንፍራ፡፡ “ሁሉም በርሱ ሆነ – ያለርሱ በሰማይም በምድርም ምንም አልሆነም፡፡” ስለዚህ ለምኑ እንጨነቃለን? የተወሰደ እንደሚመጣ፣ የመጣም እንደሚወሰድ አናውቅምን? ማን ነው እንደኮራ እንደደራ የኖረ? ማን ነው እንዳነሰ እንደኮሰመነ ኖሮ ከምድር የተሰናበተ? ጠቢቡ አስቀድሞ “ለሁሉም ጊዜ አለው” ብሏል፡፡

ከአዳም ጀምሮ እስካሁን ድረስ ይህ የጥቅምና የሆድ ጉዳይ የዓለም ሕዝቦችን እያፋጀ ነው፡፡ አዳምና ሔዋን ከገነት የተባረሩት፣ አቤል በወንድሙ በቃየል የተገደለው፣ ያቆብ ጭብጥ በማትሞላ ምሥር ብኩርናውን የለወጠው፣ ይሁዳ ጌታውን በሠላሣ ዲናር የሸጠው፣… በዘመናችንም ሲአይኤና ሞሳድ በዲሞክራሲ ጭምብላቸው ዓለምን እንዲህ የሚያሽቃንጡባትና እንደፈለጉ የሚፈነጥዙባት በጥቅምና ለጥቅም ሲባል ነው(ህእ! ሳውዲ ዐረቢያ ውስጥ የዴሞክራሲ ጭላንጭል የለም … በአውራ መንገዶችና በሠፈር ውስጥ ብቻዋን መሄድ የማይፈቀድላት ሴት መኪና እንኳን አትነዳም፤ ስለዴሞክራሲ ጭንቅ ጥብብ የምትለውና በዴሞክራሲ በሚመጣባት ሀገር ላይ ከማዕቀብ እስከ ጦር ማዝመት የምትደርሰው አሜሪካ የዚህች ሀገር የበላይ ጠባቂና ዘበኛ ናት – ለጥቅም ሲባል… ዕንቆቅልሽ፡፡)

… እንጂ ዐማራ ከማንም የበለጠ “አህያና ደደብ” ወይም “የአእምሮ ዘገምተኛ” ሆኖ አይደለም – ሰፊው ኦሮሞ ከትግሬ በልጦ ጠባብ ሆኖ አይደለም፡፡ ትግሬ ከማንም በልጦ ጀግናና አልሞ ተኳሽ ሆኖ አይደለም፡፡ ማዕከላዊው የግጭት መንስኤ ጥቅም ነው፡፡ በጥቅም የታወሩ ወንድሞቻችን አቅል አጡና ከምድረ ገጽ ሊያጠፉን ቆርጠው ተነሱ፡፡ ባጭሩ ይህን ሁሉ ዕልቂትና ፍጅት እያስከተለ ያለው ከፀሐይ በታች ያለ የሸርና የተንኮል ጉንጉን የተላበሰ የወያኔዎች የሀብትና የሥልጣን ጉጉትና የዓለም አቀፉ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሤራ ድምር ውጤት ነው፡፡ ከወያኔዎች ጋር ተሰልፎ ጃዝ ሲሉት እየገደለና እየዘረፈ የሚተመው የጥፋት ሠራዊት ደግሞ ከዕውቀትም ከባህልም ከሃይማኖትም የወጣ ወፍ ዘራሽ ጀሌ ነው – አብዛኛው ከእረኝነት በቀጥታ የመጣና ማኅበራዊ እንስሳነቱ የተጓደለበት ከመሆኑም ባሻገር ዐማራን እንዲጠላና ከጥላቻውም ብዛት የተነሣ በጭካኔ እንዲፈጀው ሥነ ልቦናዊ ጫና የተደረገበት አሳዛኝ ፍጡር ነው፡፡ ሳይፈልግ በተደረገበት ተፅዕኖ ምክንያት ስለሆነ ይህን ሁሉ ግፍ የሚፈጽመው ሙሉ በሙሉ በርሱ ለመፍረድም ይከብዳል፤ በዚያ ላይ የውጭ ጠላቶቻችን ለውስጥ ምንደኞች ያሸከሙት ታሪካዊ የጥፋት ተልእኮም ቀላል አይደለም – የየትኛውንም ሀገር ባለሥልጣናት ብሔራዊ ስሜት በማጥፋት የነርሱ አሽከሮች የሆኑ መሪዎችን በማፍራት የሚታወቁት የዐውሬው ልጆች ምዕራባውያንና አውሮፓውያን ካልጠፉ ወይም ሰይጣናዊ ተፈጥሯቸውን ካልቀየሩ (ይህ የማይሆን አማራጭ ነው) አለዚያም እኛ ይህን መርዝነታቸውን ነቅተንባቸው በኅብረት ካልታገልናቸውና ድል ካልነሳናቸው ደግሞ ዕረፍት እንደሌለን መረዳት ተገቢ ነው፡፡ የዘመቻቸው ጅማሮ ጥንታዊ ነው፤ ድላቸው ግን ጊዜያዊ ነው፡፡

ጥቂት ታገሱኝ – አንዲት ነገር ብቻ ትቀረኛለች፡፡ የትግራይ የወቅቱ መሣፍንትና መኳንንት ትግራይን ይዘን እንሄዳለን ቢሉ ጥርሳችንን ተነቅሰን እንስቅባቸዋለን፡፡ በርግጥም ጤነኛ ነኝ የሚል የዚህች ዓለም ዜጋ ይስቅባቸዋል፡፡ “እውነት እውነት እላችኋለሁ” ብሎ ይጀምር ነበር ክርስቶስ የመረረ እውነት ሲናገር፡፡ እኔም ልዋሰውና – እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ትግራይን መገንጠል ቢያስፈልግ ኖሮ ይቻል የነበረው የዛሬ 25 ዓመት ገደማ በ1983ዓ.ም ወርኃ ግንቦት ላይ ነበር፡፡ አሁን እጅግ መሽቷል፤ “ቢያዩኝ እስቅ፣ ባያዩኝ እሰርቅ“ የሚለው ብሂል የማይሠራበት የመጨረሻው ሰዓት ላይ ስላሉ ያን ቅዠታቸውን ዘመን ሽሮታል፡፡ “ዕድላችንን እንሞክር” የሚባልበት ጠባብ የተስፋ ጭላንጭል እንኳን የለም፡፡ አንድ የትግርኛ ብሂል ላስታውስ – ወዳማርኛ ልመልሰው ፡- “የሚበቃትን ያህል ጥሬ ከፈጨች በኋላ የማርያም በዓል ነው ትላለች” ይላል፡፡ ግሩም ብኂል ነው፡፡ በልጆች ጨዋታ ጊዜ “ጨዋታው ፈረሰ፣ ዳቦው ተቆረሰ” ሊባል ይችል የነበረው ዛሬ ሣይሆን ከዛሬ 25 ዓመታት ገደማ በፊት ነው፡፡

ወልቃይትንና አካባቢዋን ከጎንደር፣ ራያዎችን ከወሎ፣ የአባይ ግድብን ከቤንሻጉል፣ እንትናን ከአፋር … ከዘረፉና ወደ “ታላቋ የትግራይ ሪፐብሊክ” ካካለሉ በኋላ፣ ሰፊ የዐማራ ግዛትን ለሱዳን ከሸጡ በኋላ፣ የኢትዮጵያን ሀብትና ንብረት ለ40 እና 25 ዓመታት በተከታታይ ካለተቆጣጣሪ እንደልብ ከመዘበሩና ወደሚፈለጉት ቦታ ካዘዋወሩ በኋላ፣ በሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ በልዩ ልዩ ዘዴ ከምድረ ገፅ ካጠፉና እንዲሰደድም እንዲፈናቀልም እንዲራብና እንዲታረዝም ካደረጉ በኋላ፣ የኢትዮጵያን አስተዳደር በአንድ ጎሣ ቁጥጥር ሥር አውለው የሀገሪቷን አንጡራ ሀብት እንዳሻቸው ከቦጠቦጡና መዋቅሮቿን ሁሉ ካፈራረሱ በኋላ፣ የሚንቀሳቀስንም ሀብትና ንብረት ወደ አሳቻ ቦታ ካሻገሩ በኋላ… ለዚህ ሁሉ ዘመን በአንዲት ሉዓላዊት ሀገርና በአንድ ሕዝብ ላይ እንደልብ ከፈነጩ በኋላ አሁን ሲመሽ “የያዝኩትን ይዤ የራሴን ግዛት እመሠርታለሁ” የሚለው ብልጣብልጥነት ከማሣቅም ያልፋል – ወያኔ ከኢትዮጵያ የአንበሣና ዝኆኑን ድርሻ ዝቆ ወደራሱ ጎተራ ካስገባ በኋላ ለመሆኑ ለሌላው ሕዝብ ምን የቀረለት ነገር አለና ብቻውን መንግሥት መሥርቶ ከነሱ ጋር በአቻ ጉርብትና የሚኖረው? የመረጃ ቋቱ ሳይቀር ተጉዞ መቀሌ ገባ ከተባለ በኋላ ሌሎቹን እንደፍጥርጥራችሁ ብሎ “ትግራይ ሪፐብሊክ” የምትመሠረተው በየትኛው ሥሌት ነው? የዋህነት ወይንስ ድምበርን የማያውቅ ብልጠት? ሀገርን ማስተዳደርና ሀገርን መመሥረት የልጆች የቃቃ ጨዋታ አይደለም፡፡ አንድን ሀገር አፍርሶም ሌላ ሀገር መገንባት የሚታሰብ አይሆንም፡፡ ቂልነት ነው፡፡ ወይም የለዬለት ዕብደት፡፡

የወያኔዎች አጀማመር ሁሉ እንዳይሆን ነው፤ ሲጀምር ትልቅ ሀገርን እየገዙ የ”ገዛ ሀገር”ን መሬት ለባዕድ መሸጥና በነሱው አጠራር ካንዱ ‹ክልል‹ ወደሌላው ‹ክልል‹ ቁርጥራጭ መሬት እየቀደዱ መስፋት ጥንቱንም አላስፈላጊ ነበር – ሌላ ታሳቢ ተንኮል እስከሌላቸው ድረስ፡፡ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያውያን የጋራ ሀገር እስከሆነች ድረስ በግዛት መካለልና ያንንም ተከትሎ በመጣ ዕልቂት የሰውና የንብረት ውድመት መከሰት አልነበረበትም፡፡ ማንም ዜጋ የትም ሄዶ መሥራትና ሀብት ንብረት ማፍራት ስለሚችል አዲስ አከላለል ወይም ኬሌላ ግዛት የመሬት ዝርፊያ ባላስፈለገም ነበር፡፡

ወያኔ ግን የነገን ሣይሆን የዛሬን ብቻ ስለሚያስብ የሆነው ሁሉ ሳንወድ በግዳችን ሆነ፡፡ ግዴለም – “በዚሁ ይለፍ፡፡” ዋናው ነገር ግና ከዚህ ሁሉ የሰው ዕልቂትና የንብረት ውድመት በኋላ የ“ታላቋን ትግራይ ሪፐብሊክ” ለመመሥረት ማሰብ ከፍ ሲል ለመግለጽ እንደተሞከረው ዕብደት እንጂ ሌላ ሊሆን አለመቻሉን መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ወያኔዎች እንደዚህ ያለ ጅል አስተሳሰብ ውስጥ የሚገኙ ከሆነ ከፍ ሲል በዐማርኛ የጠቀስነውን የትግርኛ ብሂል ደግመን በማስታወስ ”ዝአኽለን ጥሂነን በዓል ማርያም ትብላ” ብለን እንተርትባቸዋለን፤ ወቅቱ የሀዘን ቢሆንም በለበጣ የአግራሞት ሣቅ እንፈግባቸዋለን፡፡ ይህን ቅዠት ማንም ወያኔም ይሁን የትግራይ ክፍለ ሀገር ሰው ሊያስበው አይገባም፤ አይችልምም፡፡ ሁለት ተቃራኒ ነገሮች ኅብረት የላቸውም፡፡ ብርሃንና ጨለማ በአንድ ጊዜ አይገኙም፡፡ ኢትዮጵያዊነትና ትግራዊነትም እንዲሁ፡፡ ጤናማ ተጋሩ ከዚህ ወያኔያዊ ቅዠት ባፋጣኝ ውጡና የሚሻለውን ለማድረግ ተመካከሩ፡፡ ይህ “ወርቃማ” ዕድል የዛሬ 25 ዓመት አለፈ፡፡ የፈሰሰን ውኃ ማፈስ ደግሞ አይቻልም፡፡

ይልቁንስ ለትግራይና ለተጋሩ የሚያዋጣው ብቸኛ መንገድ የሆነች መፈንቅለ መንግሥት ማድረግና ያችን ተከትሎ ጤናማ ትግሬዎች የያዙት “የክልሉ መንግሥት” ከሌሎች ጤናማ ወገኖች ጋር አዲስ ድርድር ማድረግ ነው፡፡ ለዚህም የጤናማ ትግሬዎች ሚና በጣም ወሳኝ ነው – በተለይ ወጣቱ፡፡ ይህ ሣይሆን ቀርቶ ወያኔ የትግራይን መፃዒ ዕድል እንደእስከዛሬው ሁሉ እንዲወስን ከተደረገ በርግጥም የትንቢቱ ፍጻሜ ይሆንና  ሊያስወግዱት በሚቻል ችግር ሀገራችን የማትወጣው አደጋ ውስጥ ትገባለች፡፡ ይህን እውነት አሁን ሳይመሽ በጊዜ እንዲህ ባልተለመደ ድፍረት የምናገረው ሌላውን ተውትና ከነባራዊው ዓለም ተጨባጭ ወይም ገሃድ እውነት በመነሳት የተበደለ ሲነሳ የሚያቆመው ነገር እንደሌለ በመረዳት ነው፡፡

እዚህች ላይ አንዲት ጠቃሚ ነጥብ ላንሳ፡፡ … ደጋግ ሰዎች ለፈጣሪ ከጮኹና የፈጣሪን ልብ ካራሩ ትንቢት ሊለወጥ ወይም የሚከሰት ውድመት ሊቀንስ እንደሚችል መገንዘብ ተገቢ ነውና ለፈጣሪ የቀረባችሁ ዜጎች የእንቅልፍ ሰዓታችሁን በመቀነስ ሌት ተቀን ወደፈጣሪ ጩኹ፤ እየመጣ ያለው የመከራ ዶፍ ሰው ቀርቶ ምድር አትችለውም – በዓለም ታሪክ ወደር የሌለው የወያኔዎች ዐረመኔነት የሚያስከትለው ጦስ እንዲህ በቀላሉ የሚገመት ነው ብሎ የሚያስብ ሰው ካለ ስለወንጀል ዕዳ አከፋፈል ምንም የማያውቅ የዋህ ሰው መሆን አለበት፡፡ ይህን የማይም ማስጠንቀቂያ እየተናገርኩ ያለሁት በዱባ ጥጋብ ለታበዩትና በዕብሪት ጉሽ ጠላ ለሰከሩት ወያኔዎችና መሰሎቻቸው አይደለም፤ ተፈጥሮን ተመክሮ አይመልሰውምና እነሱ መቼም ሊለወጡ አይችሉም – እንዲለወጡ የሚጠብቅም ሰው ካለ የአእምሮ ህክምና የሚያስፈልገው የለዬለት ሞኝ ነው፤  እነሱና ጋዳፊ ሊለወጡ እንደማይችሉ በበኩሌ በደንብ አውቃለሁ – ጋዳፊ ስምንት ቀን ተሸሽጎበት ከነበረው የቆሻሻ ቱቦ ወጥቶ “ምን ሆናችሁ? ሊቢያ ውስጥ ምን ተፈጠረ?” እያለ መሪው እርሱ የሆነ ያህል ቆጥሮ በባትሪ እየፈለጉት የነበሩትን ተቃዋሚዎች ለማዘዝ ቃጥቶት ነበር አሉ – ግን ወዲያው ያዙትና በመቀመጫው በኩል ሣንጃቸውን ወድውደው አንጀቱን በጣጥሰው ገደሉት – የአምባገነኖች መጨረሻ እንዲህ ነው፡፡ እኚህን መሰል ደናቁርት ከአህያ የማይሻል የማየት ችሎታ ነው ያላቸው፤ የጅልነታቸው መጠን የጨካኝነታቸውን ያህል ነው፡፡ …

እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገራችንን ከተጋረጠባት የጥፋት ዳመና ያውጣልን፤ ፍቅርና አንድነትን ይስጠን፡፡ ለሳዖል የሰጠውን ማስተዋል ለሕወሓትም ሰጥቶ ሕዝብንና አገርን እያረዱበት የሚገኙትን ጎራዴ/ሠይፍ ወደ አፎቱ እንዲያስገቡና ዕርቅና ሰላም በሀገራችን እንዲሰፍን እግዜር ይርዳን፤ ምርጫ አጥተን የምንገባበት መብታችንን የማስከበር ትግል ሁሉ ብዙ የሕይወትና የንብረት መስዋዕትነትን ይጠይቃልና የእስካሁኑ መከራችን በቃችሁ ብሎ ባፋጣኝ ምሕረቱን ይላክልን፤ አሜን፡፡

mz23602@gmail.com

ዛሬ ኦሮምያ እየተባለ የሚጠራው ምድር የማን ነው? የማይረባ ጥያቄ!!!! ሌሎችም የሰሞኑ ክስተቶች! –ሰርጸ ደስታ

$
0
0

በቅጽበት የተናደው የ25 ዓመት የዘረኝነት ግንብ
ሰሞኑን ፕሮፌሰር መስፍን ወልቃይት የማን ነው? የሚለውን ጥያቄ የማይረባ ጥያቄ ያሉበት መልዕክታቸው እጅግ አስደስቶኛል፡፡

OromiaMap12_71.jpgበ60ዎቹ ከተነሱት የጠባብ ብሔረተኝነት አራማጅ ቦድኖች አንዱ ወያኔ ዛሬ የዛን ጠባብነት ተግባር ላይ አዋለው እንጂ በ60ዎቹ የተነሱ ቡድኖች በአብዛኛው የዚሁ ልክፍት የተጠናወታቸው የሕዝብና የአገር ጉዳይ የማይገባቸው ዘረኞች ናቸው፡፡ ይሄን እውነታ ለወያኔ ብቻ ብንሰጠው ከዚያ የወረደ ጠባብነት የተፈወስን እንዳይመስለን፡፡ እውነታው ከወያኔም በከፋ ዘረኛ አስተሳሰብ ያላቸው የ60ዎቹ ቡድኖች አሉ፡፡ ይሄው የዘረኝነት መርዝ ዛሬ ሁሉንም በክሎት ስለሚሰራው እንኳን እንዳያስተውል አእምሮው መክኗል፡፡ ወያኔ የኢትዮጵያ ሕዝብ በዘረኝነት ልክፍት እንዲበከል 25 ዓመት በገዛ አገራችን ሀብት ብዙ ሠርቷል፡፡ እግዚአብሔር ግን ይህ እንዳይሆን ሕዝቡን (ከተማረውና ብልጣብልጥ ከሆነው በቀር) ከዚህ መርዝ ጠብቆታል፡፡ በደንብ አስተውሉ ዛሬ ዘረኝነት ያለው በማን ዘንድ ነው? በዲያስፖራ ወይስ በአገር ቤት? በተማረው ወይስ በተራው ሕዝብ? በትክክልም ወያኔ ዘረኛ ነው፡፡ ግን በየ አገሩ የምትኖር ራስህን በኦሮሞነት፣ አማራነት፣ ትግሬነት ወዘተ ኪስ ከተህ ሌላው አልታይ ብሎህ እጅግ የከፋ የዘረኝነት አዘቅት ውስጥ እንደገባህ ሳይታወቅ በምን ሞራል ዘረኛን የማወገዝ አቅም ይኖርሀል፡፡ የወያኔን የዘረኝነት ፕሮገራም በዋነኝነት የሚያሰፈጽምለት ማን ነው? ተማርኩ አወቅሁ የሚለው የመከነው ትውልድ አይደለም?  ተራው (መሠረታዊው በቦታው የሚኖረው) ሕዝብ ጋር እኮ ይሄ የለም፡፡ ሲሆን እኮ መማር ሌሎች አገሮችን ማየት የበለጠ ብዝሐነትን ለማስተናገድ እድል ይሰጥ ነበር፡፡ መሠረቱም መሠረታዊ ወገንተኝነት እንጂ ዘረኝነት ባልሆነ፡፡ ሰው በአእምሮው እየበሰለ ሲሄድ ጥበብን ይለብሳል፡፡ ጥበብ ደግሞ ሁሉን እንድንረዳ ታደርጋለች፡፡ የምናደርገውና የምንወስነው ነገር ሁሉ ከአመክንዮ (ሎጂክ) እንጂ ከጠባብ ስሜተኝነት አይሆንም፡፡

ዛሬ እኮ ሰማያዊ መንግስትን እናስተምራለን በስላሴ አምሳል የተፈጠረው ሁሉ ይገደናል የሚሉት የሐይማኖት አባቶች ሳይቀሩ እኮ በአደገኛ የዘረኝነት ልክፍት ውስጥ ናቸው፡፡ ዛሬ እኮ የተማረው በአብዛኛው በዘረኝነት ልክፍት ታውሯል፡፡ አሁን አኮ ለዘመናት የታፈነውን የኢትዮጵያዊነት መንፈስ እንዲፈነዳ ያደረገው እኮ የጎንደር ተራ(ተራ ግን አይደለም) ሕዝብ ነው! ተማርኩ፣ አወቅሁ የሚለውማ የወያኔ ዋነኛ የዘረኝነት መንፈስ አሰራጭ ሆኖ 25 ዓመት ሲያገለግል ነበር፡፡ ዛሬ ደርሶ አንድነትን ለመስበክ ፊት አውራሪ መሆኑ ደግሞ የሚያሳየው ተለዋዋጭነቱን ግልብነቱን፣ መካንነቱን  እንጂ መሠረታዊ ማንነቱን አይደለም፡፡

እንደ እግዚአብሔር ቸርነት እንጂ እንደዘረኛው የ60ዎቹ ትውልድማ ዛሬ ኢትዮጵያ የለችም፡፡ 25 ዓመት ሙሉ ወያኔ በስልጣን ላይ ሌሎች ደግሞ በያሉበት ሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲበታተን ብዙ ተሠራ፡፡ በተለይ ደግሞ አማራና ኦሮሞ በሚል የአገሪቱን ብዙውን ሕዝብ ለማቃረን ከፍተኛ በጀት ተመድቦለት ተዘመተ፡፡ እግዚአብሔር ግን ከላይ ሆኖ ሁሉን እስከጊዜው ይታዘብ ነበር፡፡ በመጨረሻም ዘረኞቹ ራሳቸው ባሰቡት አካሄድ የተሄደባቸው የአገርንና ሕዝብን የማፍረስ ሥራ ውጤቱ በተቃራኒው እየሆነ እራሳቸው እስከሚታዘቡት ድረስ ይሄው የ25 ዓመት ግንብ ተንዶ ዛሬ ላይ ይፋዊ አንድነት መሰበክ ጀመረ፡፡ የዛሬ 10 ወር ገደማ የአዲስ አበባውን ማስተር ፕላን ተከትሎ የኦሮሞ ወጣቶች በተናጥል (በኦሮሞነት ብቻ በሚመስል መንፈስ) ማስተር ፕላኑን ሲቃወሙ አሁን ወልቃይት የማን ነው? የሚለውን የማይረባ ጥያቄ ያሉት ፕሮፌሰሩ የዛሬ 10 ወሩን የኦሮሞ ወጣቶች ተቃውሞ  አልገባኝም በማለት መልዕክት ማስተላለፋቸውን እናስታውሳለን፡፡ በትክክልም ውጤቱ እንጂ የተቃውሞው መንፈስ የማይረባ ነበር፡፡ ውጤቱ ግን የዛሬን አንድነት የጸነሰ ነበር፡፡ ማንም ሰው በዚህ ፍጥነት 25 ዓመት ታቅዶና ያለ የሌለ ሀብት ፈሶበት የተገነባ ዘረኝነት እንዲህ ፍርስርሱ ይወጣል ብሎ አልገመትም፡፡ የወያኔውን አፈቀላጤም በብስጭት የተናገሩት ይሄንኑ ነበር፡፡ 25 ዓመት ሙሉ እሳትና ጭድ እንዲሆን ያደረግናቸው ሕዝቦች እንዴት አንድ ሆኑ? አሉን፡፡ ከዛሬ 10 ወሩ የኦሮሞ ወጣቶች ተቃውሞ በኋላም ብዙ ጭራሽ በተለይም የኦሮሞና የሌላው ሕዝብ የሚቃረንበት ድምጾች በስፋት ተሰሙ፡፡ ኦሮምያ የኦሮሞ የሚል አዲስ መፋተጊያ ተፈጠረ፡፡ ሂደቱ ሁሉ ካልደፈረሰ አይጠራም የሚባለው ነበር፡፡ ወያኔ አጋጣሚውን በደንብ ተጠቀመበት፡፡ ውጤቱ ግን የተንኮልን ጉድጓድ አርቀህ አትቆፍር ለተኮለኛ የተነገረው ምክር ነበር፡፡ ብዙ ተማርን ብለው ራሳቸውን የቆለሉ ዘረኞችም በይፋ ከማውገዝ ይልቅ ሌላ ትንታኔ እየሰጡ በመከነው አእምሮአቸው አመክኒዮ ቢስ (ሎጂክ የሌለው) ፍልስፍና ሲፈላሰፉብን ቆዩ፡፡ ሁሉም ነገር ለበጎ ነው የሚል አባባል ከብዙዎች ዘንድ አሰማለሁ እኔ አባባሉን ባልጠቀምበትም፡፡ አሁን የመጣንበት ሂደትን ግን ሳስብ ግርም ይለኛል፡፡ እግዚአብሔር ጥፋትን ወደ በጎነት መቀየር እንጅ ጥፋትን መከልከል አያስፈልገውም፡፡ ለዛም ነው መሰለኝ ከእግዚአብሔር ሲመጣ ሁሉም ነገር ለበጎ ነው የሚባለው፡፡ የዛሬ 10 ወሩ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ተከትሎ የተነሳው የኦሮሞ ወጣቶች ተቃውሞ የቱንም ያህል ዘረኝነት መንፈስ ቢመስልም ወጤቱ ማንም ሊያስበው ከሚችለው በላይ በጎ የሆነ ስኬት ሆነ፡፡ አሁን ላይ ቆሜ ሳስብ በእርግጥም በዛ ወቅት በኦሮሞ ወጣቶች የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ባይገታ ማንም ይመለከተኛል ብሎ በኢትዮጵያዊነት ሊያስቆመው የሚችል አልነበረም፡፡ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ከማይደግፉት ሰዎች አንዱም ብሆን ማስተር ፕላኑን ያስቆመውን የተቃውሞ መንፍስ ግን የማይረባ ነበር (አነጋገሬን አንሻፎ መጠቀም አይቻልም)፡፡ በወቅቱም የተሰማኝን ስሜት እንዲሁ ነው የገለጽኩት፡፡ ዛሬ በድፍረት ወልቃይት የማን ነው የሚለውን የማይረባ ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን በዛን ወቅት የኦሮምያ ተቃውሞ አልገባኝም በማለት በመለሳለስ የተቹት ወቅቱ የማይረባ ለማለት ምቹ አልነበረም፡፡ ያ አነሳሱ የማይረባ የነበረው እንቀስቃሴ የሚረባ ጽንስን ጸንሶ ዛሬ ላይ አገርንና ሕዝብን የሚታደግ ክስተት ሆኖ ተወልዶ እናየዋለን፡

ማንም ይሄንን አልገመተም!! ዛሬ ላይ ለብዙዎች ኦሮምያ የማን ነው? የሚለው የማይረባ ጥያቄ ሆኖ ትክክለኛው ጥያቄ የገባቸው ይመስለል፡፡ 25 ዓመት በማይረቡ ጥያቄዎች ስንደናበር ለጠላቶቻችን ተመቻችነትን ኖረን ነበር፡፡ አልገባንማ፡፡ የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድ አድርጎ ያሰረው ሞገሱና ኃይሉም ኢትዮጵያዊነት እንጂ ኦሮሞነት፣ አማራነት፣ ትግሬነት ….ወዘተ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊነት ነው ጉልበቱም ውበቱም፡፡ ወያኔ ኢትዮጵያዊነት አደገኛ ጠላቱ እንደሆነ ከመጀመሪያውም ሲለሚያውቅ ነበር ሕዝብን ከታላቅነቱ አውርዶ በየጎጡ የኮሰሰ ያደረገው፡፡ ልብ በሉ እኔ ኦሮሞነት አማራነት ምናምን የሚገባኝ ሰው አደለሁም፡፡ ከዛ ይልቅ ከዚህም የበዛ የህዝብ ማንነት፣ ባሕል፣ አኗኗ እሴት ይማርከኛል፡፡ አማርኛ ተናጋሪ ሁሉ አንድ ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡ ሲጀምር ከቤሰብ ጀምሮ የተለያየን ነን፡፡ ግን በተቻለ መጠን ብዛታችንን እንጂ ትንንሽነችንን አልወደውም፡፡ እኔ ከኢትዮጵያም ያለ ግዙፍነት እመኛለሁ፡፡ እንደ 60ዎች ያለ የመከነ ዘረኛ አእምሮ ባይገጥመን አይደለም ኤርትራ ሌላውም የአካባቢው ሕዝቦች በአንድ አገርነት (ሕብረ-ብሔርነት) ሊኖሩ የሚችሉበት እድሉ ነበር፡፡ ቢያንስ ዛሬ የአውሮፓ አገራት ያደረጉትን አይነት ውሕደት ከመሠሎቻቸን በተለይም ሱዳን፣ ኢትዮጵያ(ኤርትራን ጨምሮ)፣ ጂቡቲ ሶማሊያን ያካተት የአገራት ውሕደት መፍጠር የሚያስችል የሕዝቦች የአኗኗርና ባህል  መሠረት ነበር፡፡ እንዲህ በማሰብ ለአፍሪካም ጭምር አርዐያ መሆን ሲገባን ራሳችንን በመከኑ አእምሮዎች ባርነት ሥር ጣልን፡፡ የማይረቡ ጥያቄዎች እየጠየቅን እስከአሁንም የማንረባ ሆንን፡፡

የሪዮው ጀግና ፈይሳ ሌሊሳና የአዲስ አበባው ሰላማዊ ሠልፍ መቀረት 

የወያኔ ቡድን ሳምንት እሁድ በአዲስ አበባ ተጠርቶ የነበረውን ሠላማዊ ሰልፍ ሕዝቡን በማስፈራራት ሰልፉን ማስቀረቱን እንደ ትልቅ ድል አስቦት መደንፋቱን ሳያቆም ነበር ባላሰበውና ባልገመተው ቦታ በሪዮዎ የኦሎንፒክ ጎዳናዎች አንበሳውን ፈየሳን ሲያይ በድንጋጤ ከተራራነት ወደ ሸለቆነት የተቀየረው፡፡ የአዲስ አበባ ሕዝብ ሰልፍ ቢወጣ ማን ያየው ነበር?  ያው ደም የጠማቸው አጋዚዎች ሰለባ ይሆን ነበር እንጂ፡፡ የወያኔን ቡድን ግፍ ለዓለም ለማሳየት አንዱ ፈይሳን እግዚአብሔር ወገኖቹን አሳሰበው፡፡ እንዲህ ያለውን ድፍረትና ለወገን ራስን መሠዋዕት ማድረግ የሚያስችል አቅም ሥንቶቻችን እንዳለን አላውቅም፡፡ እኔ አለኝ ብዬ አላምንም፡፡ ዓለምንም ያስደመመ ጀግንንነትና ቁርጠኝነት ነው፡፡ ዛሬ ላይ አገር ቤት ራሳቸውን መሥዋዕት እያደረጉ ያሉትን ወገኖቹን ለማብና ስለነሱም ወሳኝ መስዋዕትነትን ለመክፈል ፈይሳ በጣም አስቦበት የወሰነው እንጂ በስሜት እነዳልነበርም አስተውለናል፡፡ ይሄ ከባድ ነው!! ወያኔን አከርካሪውን የሰበረ ነበር፡፡ ወደፊት ተስፋ የምናደርጋት ኢትዮጵያ ለዚህ ልጇ ምን መታሰቢያ እንደምታኖርለት አላውቅም፡፡ ለነገሩ ማን ያስታውሳል? ኢጣሊያን በረሃዎች አለምን ጉድ የሚያሰኝ ጀግንነት የፈጸሙና የጀነራልነት ማዕረግን የተቀዳጁ እንደነ አብዲስ አጋ ያሉ ጀግኖች ከጀነራልነት ወደ መቶ እልቅና የሚወርዱባት አገር ምን ውለታ አሳቢ አለባት? አጎብዳጆችና ባንዳዎች እንጂ ጀግኖች አልታሰብባት ያለች ምድር!!

የገዱ አንዳርጋቸው የሰሞኑ ጋዜታዊ መግለጫና የመንግስት ሚዲያ

በአማራ ክልል በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ከበሬታ እንዳላቸው የሚነገርላቸው የክልሉ ፕሬዘዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ይሄ ሁሉ ወጥንቅጥ በሚመሩት ክልል ሲካሄድ ዝም የማለታቸው ነገር ብዙ ብዙ ሲያስብል ቆይቶ ሰሞኑን በቴሌቪዥን ብቅ ብለው 15 ደቂቃ ገደማ ጋዜታዊ መግለጫ መስጠታቸው አንዱ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር፡፡ አቶ ገዱ ሲናገሩ በቀጥታ የሚሰማውና በተለያዩ ሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫቸው እየተጠቀሰ የሚነገረው አንዳንዴ ከነጭረሱ የሚቃረን ሆኖ ታዘብኩት፡፡ አሸባሪው ኢቢሲ አቶ ገዱ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን አሉ ብሎ ሲጠቅስ ቀዳሚው ነበር፡፡ ይሄንኑ የአሸባሪውን የኢቢሲን ነገር ጠቅሶ የጀርመኑ ሬዲዮም ዘገበው፡፡ በኃላም በተለያዩ ድረ-ገጾች ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን አስተያየቶች ሰማን፡፡ አቶ ገዱ የማያዳግም የሚል ቃል ከአንደበታቸው ሲወጣ ፈጽሞ አይሰማም፡፡ አስፈላጊውን የማስተካከያ እርምጃ እንስዳለን ነው ያሉት፡፡ አቶ ገዱ በንግግራቸው ሁሉ ኃላፊነት በተሰማውና በጥንቃቄ ሕዝብን  የማያስቆጡ ቃላቶችን እየመረጡ እንደነበር በደንብ ማስተዋል ይቻላል፡፡ አቶ ገዱ ስለ ኮሌኔል ደመቀ ሲናገሩ መጀመሪያ የኮሌኔሉን ሙሉ ሥም ጠቅሰው ከዛ ግለሰቡ የሚልን ቃል ተጠቅመዋል፡፡ አሸባሪው ኢቢሲ ገዱ የጠቀሱትን የኮሌኔሉን ሥም ቆርጦ ግለሰቡ ከሚለው ንግግራቸው አንስቶ ሊያሰማን ሞክሯል፡፡ ያም ቢሆን ገዱ አረጋግጠው የተናገሩት የኮሌኔሉ ጉዳይ የሕዝብ ጥያቄ እንዳለበት ነው፡፡ ሕዝቡንም ማክበር እንደሚገባም በመጠቆም፡፡ ገዱ በእርግጥም እንደ ኃይለማሪያምና ሙክታር በወያኔ ትዕዛዝ በሕዝብ ላይ የሚደነፉ አይደሉም፡፡ በእርግጥም እንደ ክልል አስተዳዳሪነታቸው አሁን እየሆነ ያለው ጉዳይ ያሳስባቸዋል፡፡ የገዱ ሙሉ ንግግር እንሆ

http://www.ena.gov.et/index.php/video/video/item/6654-2016-08-25-20-36-40

የወያኔን ደጋፊዎች ለእብደት የዳረጋቸው ክፉ ዘረኝነት 

አሁን ላይ እግዚአብሔር ይመስገን ነገሩ እየጠራ መጥቷል፡፡ በአለማወቅም የተሸወዱት በጸጸትና በቁጭት አውቀው ያደረጉት ደግሞ ሳይወዱ በግድ የማይወዱትን አንድነት እየሰበኩ ነው፡፡ በዛው ልክ የዘረኝነት ልክፍቱ የባረቀባቸውም ብዙዎች ናቸው፡፡ አሁን አሁን የሕወሐት ደጋፊ የነበሩ ግለሰቦች ወደ እብደቱም እየቃጣቸው ይመስላል፡፡ ሰሞኑን አንደ አንድ የሕወሐት አምላኪዎች በየማሕበራዊ ገጹ በእብደት ሲሳደቡና ሲጮሁ ተመልከትኩ፡፡ የሕወሐት ዋና የሆነቸው ሚሚ ስበሐቱን ከዚህ በፊት ሰምቼ ሰው ምን ቢያደርጉት እንደዚህ ይሆናል ብዬ ነበር፡፡ ችግሩ ለካ የእብደት ነበር፡፡ ለእንደ ሚሚ ያሉት በእርግጥም የወያኔ መውደቅ ማሳበድ አይደለም ራሳቸውን ሊያስጠፋቸው እንደሚችል እገምታለሁ፡፡ ሰሞኑን አንድ የወያኔ እንዲህ ለአደጋ መጋለጥ ያሳበዳት እብድ በየፌስቡኩ እብደቷን አሳውቃለች፡፡ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ እብደቷ ሳያንስ በዚሁ እብደቷ ሳቢያ ከአፏ በወጣው ንግግሯ ከሥራዋም ተሰናብታለች የሚል ዜናን ሰማን፡፡ ሚስኪን፡፡ ይች አሁን የዘረኝነት ልክፍት ያሳበዳት እንጂ ከወያኔው ቡድን ተጠቃሚም አትመስለኝም፡፡ ባይሆን እንደነ ሚሚ ያሉት ማበድ አይደለም ራሳቸውን ቢሰቅሉ አይገረምም፡፡ በዘረኛው ቡድን ከለላ ሥር ያለቸው ሚሚ እንኳን ከሥራ ልትታገድ ጭራሽ የሰላምና የሕዝቦች መፈቃቀር መገለጫ መድረክ በሆነው  የሪዮ ኦሎምፒክ የኢትየጵያው የኦሎሚፒክ ልዑክ አባል ሆና እንደተሳተፈች ሰማን፡፡ ለነገሩ ሮቤልን አባቱ ለዋና ከሄዱ እሷ በጅምናስቲክ ልትወዳደር ይሆናል፡፡ አሁን ደግሞ አንደ ወዳጄ አንድ ሌላ እብድ ሼር አደረገኝ፡፡  አንድ ነገር አሁንም አስጠነቅቃለሁ፡፡ ወያኔና የትግራይ ሕዝብ የተለያየ ነው፡፡ ወያኔ ከትግራይ የወጣ የወረበሎች ቡድንም ቢሆን የትግራይን ሕዝብ አይወክልም፡፡ ደጋፊዎቹና ወያኔ የሚያደርገውን መረኔነት አይቶ የትግሬ ማለት እንዲህ ነው የሚያስብል ድምዳሜ ስህተት ነው፡፡ በአጋጣሚ ለማሕበራዊ መገናኛ እዱሉ ዛሬ በብዛት ያለው ለወያኔና ደጋፊዎቹ ስለሆነ የሰፊውን የትግሬ ወካይ አስመስሎት እንዳይታይ፡፡ ለምን እንደሆነ ባይገባኝም እስካሁን የታዩት ሚሚ ስበሐቱን ጨምሮ ሶስቱም ሴቶች ናቸው፡፡

ለወያኔው በድን እየቀረበ ያለው የተሳሳተ ጥሪ

እኔ በሕይወቴ ኢትዮጵያ እንደ ወያኔ ያለ አደገኛ ቡድን ገጥሟታል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ብዙዎች ለወያኔ የብሔራዊ እርቅ ጥሪ እያቀረቡለት እሰማልሁ፡፡ በትክክል ከተረዳንው የወያነው ቡድን ይሄን ለማድረግ የማያስችሉት ችግሮች ስላሉበት እንጂ አሁን ላይ እንዲሀ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ ሌሎች ብለውት ሳይሆን ራሱ የሚያደርገው ጥሪ ነበር፡፡ ብሔራዊ እርቅ በሉት፣ ሌላ ስልጣኑን የሚሻማበት ሂደት የወያኔን ቡድን አባላት ለ25 ዓመት ሲሰሩት የነበረውን ወንጀል ስለሚያጋልጥባቸው አልፎም ለፍርድ ሊያቀርባቸው ስለሚችል አሁን የዚህ ቡድን አባላት ጭንቀት እሱ ነው፡፡ ማንም ትክክለኛ የሆነ ተፎካካሪ ወደ ስልጣን መጋራት መጥቶ ሊያልፈው የማይችል በአገርና ሕዝብ ላይ የፈጸሙትን ወንጀል አይቶ ሊያልፋቸው አይችልም፡፡ ለመሆኑ ኢትዮጵያ ዛሬ በወንጀለኞች ቡድን ሥር እንዳለች በደንብ አስተውለንዋል? እና ይሄንን ቡድን ሥልጣን አጋራኝ ማለት ራስህን አጋልጥ ወይም አባል አድርገኝ እንደማለት ነው፡፡ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ በትክክል የገለጹት መሠለኝ፡፡ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የዚህ ቡድን አባላትና ደጋፊዎች የአገርቱን ሐብት ሁሉ ለራሳቸው አድርገው እየኖሩ ነው፡፡ ሌላ ኃይል ቢመጣ ምን ብሎ ሊያልፋቸው ይችላል፡፡ ብሔራዊ ዕርቅ ምናምን የሚባለው ቀደም ብሎ ቢሆን ዕድሉ ነበር፡፡ አሁን ላይ አስቸጋሪ ነው፡፡ እርቅ ብሎ የሄ ቡድን ከተቀበለ አሁን የገባበትን አጣብቂች ለማብረድና እርቅ ብለው የቀረቡትን ለመመረብ እንደሚሆን መገመት ብልህነት ነው፡፡ ልብ በሉ በመንግስት መዋቅር ከሚታወቁትም የቡድኑ ባለስልጣናት ወጭ በወሳኝ አገሪቱንና ሕዝቦቿን ለዛሬው አረንቋ የከተቷት አደገኛ የሥውር አባላት አሉት፡፡ ለምሳሌ ስበሐት ነጋ የተባሉት ግለሰብ እስከዛሬ በሚታወቅ የመንግስት መዋቅር ውስጥ የገቡበት ዋቅት ትዝ አይለኝም፡፡ ሆኖም የአገሪቱ አራጊ ፈጣሪ መሆናቸው ግልጽ ነው፡፡ ልብ በሉ በምን መስፈረት ነው እንዲህ ያለው የወሳኝነት መብት ለስብሐት ነጋ የተሰጠው? ተብሎ ቢጠየቅ የወንጀለኛ ቡድን መሪነት አወቃቀር ባለው ሥልጣን ነው፡፡ ስለዚህ ወያኔን አሁን ላይ ብሔራዊ ዕርቅ ምናምን ብሎ መዘናጋት አደገኛ ውጤት ይኖረዋል፡፡ ጠልቼው እንዳይመስላችሁ፡፡ በግሌም ይቻል እንደሁ በሚል ጉዳዩን ሊያነሱ ከሚችሉ ጋር ለመወያየት የሞከርኩት ነበር ግን የማይታሰብ ነው፡፡ የፓርላማ አባል የነበሩት ግርማ ሰይፉ ተናግረውታል ምንም ዕድል የለም፡፡ ሽግግርም በሉት በሔራዊ ዕርቅ ሊኖር የሚችለው ከወያኔ በኋላ ነው፡፡

 

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

 

አሜን!

 

ሰርጸ ደስታ

 

 

በኢትዮጵያ ውስጥ በተከሠተው ጉዳይ ላይ የሕዝባዊ ማስታወቂያ ጥሪ

$
0
0

ከአቤቱታ አቀነባባሪ ኮሚቴ
Ethiopiaከኢትዮጵያ ውጭ የሚኖሩ የሰብእና [humanities]ና፣ የማኅበራዊ[social sciences]፣ እንዲሁም የሳይንስ [sciences] ጥናቶች ሊቃውንትና ምሁራን የሆኑት ኢትዮጵያውያን ባገራችን ውስጥ የተፈጠሩት አንገብጋቢ የፖለቲካ፣ የሰብኣዊ መብት፣ የምጣኔ-ሀብትና የማኅበራዊ ኑሮ ከፍተኛ ቀውሶች እንዲፈቱና ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ለማድረግ፣ ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሓፊ አቤቱታ ለማቅረብ፣ ከላይ የተጠቀሰው ኮሚቴ ፊርማ በማሰባሰብ ላይ ይገኛል። ኮሚቴው በውጭ የምትኖሩት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትና ምሁራን የሆናችሁ በሙሉ ከዚህ በታች በሚገኘው ድረ-ገጽ ገብታችሁ ፊርማችሁን በማስፈር ላገራችሁና ለወገኖቻችሁ ስትሉ ድጋፋችሁን በማበርከት በአቤቱታው እንድትተባበሩን በአክብሮት ይጠይቃል። የአቤቱታው ቅጂ፣ እንዳስፈላጊነቱ ተስተካክሎ፣ ለአሜሪቃ ፕሬዚደንት [USA President]፣ ለአውሮጳ አንድነት ሸንጐና[European Union Parliament] ለአውሮጳ አንድነት የሰብኣዊ መብቶች ጉዳይ ወኪል [European Union Commission for Human Rights] ይላካል። የድረ-ገጹ አድራሻ እንደሚከተለው ነው።
http://www.petitionbuzz.com/petitions/appeal-to-the-un-secretary-general

 

 

//


8ቱ በዘር የሚተላለፉ በሽታዎች

$
0
0


በቤተሰብዎ ውስጥ ስለተከሰተ የበሽታ ዝርዝር ያውቃሉ? በጣም በጉልህ ስለሚነገሩትና ስለሚታዩት በሽታዎች ያውቁ ይሆናል፡፡ ምናልባት ቅድም አያትዎ እና እህቶቻቸው የጡት ካንሰር ይዟቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተው ይሆናል፡፡ ወላጅ አናትዎ ግን ከዚህ በሽታ ነፃ ሆነው ይሆናል፡፡ ወይም ምናልባት ወላጅ አባትዎ እና ወንድማቸው የደም ብዛት ችግር ይኖራቸው ይሆናል፡፡ ወይም ምናልባት ወላጅ አባትዎ እና ወንድማቸው የደም ብዛት ችግር ይኖራቸው ይሆናል፡፡ ብዙም ትኩረት የማይሰጧቸው በቤተሰብዎ ውስጥ ያሉ የተለያዩ በሽታዎች ይኖራሉ፡፡ የተወሰኑ በሽታዎች በዘር ወደ ልጅ ወይም ወደ የልጅ ልጅ እየተላለፉ ይሄዳሉ፡፡ አንዳንዶቹ በሽታዎች በተፈጥሮ የሰውነት አወቃቀር ምክንያት የሚመጡ፤ አንዳንዶች ደግሞ ተመሳሳይ የመኖሪያ ቦታን በመጋራት፣ ተመሳሳይ ምግብ ሁሌ በመመገብ እና በመሳ ሰሉት ምክንያቶች ሊይዝዎት ይችላሉ፡፡ ከእነዚህ በዘር ከሚተላለፉ በሽታዎች ውስጥ የተወሰኑትን ከዚህ ቀጥሎ በአጭሩ እንመለከታለን፡፡
8. የጡት ነቀርሳ (ካንሰር)
የጡት ካንሰር ጂን 1 እና የጡት ካንሰር ጂን 2 በመባል የሚታወቁ በዘር የሚተላለፉ የሰውነት መዋቅሮች (ጂኖች) አሉ፡፡ የቤተሰብዎ አባላት በተለይም እናትዎ፣ እህትዎ ወይም ሴት ልጅዎ የጡት ካንሰር ተጠቂ ከሆኑ በቶሎ እርስዎም መመርመር ይኖርብዎታል፡፡
7. የማህፀን ካንሰር (ነቀርሳ)
ይህን ዓይነት ካንሰር የጡት ካንሰር ጂኖች እራሳቸውን በመለወጥ ሊያመጡት ይችላሉ፡፡ እናቶ፣ የሴት ልጅዎ ወይም እህትዎ የማህፀን ካንሰር ተጠቂ ከሆኑ እርስዎም በህይወትዎ የ 5 በመቶ በዚህ በሽታ የመያዝ ዕድል አለዎት፡፡ በሽታው ሳይባባስ በጊዜ ለማወቅ መመርመር ይበጃል፡፡
6. ከፍተኛ የደም ግፊት
ከፍተኛ የደም ግፊትን ተመርምሮ የታዘዘን መድኃኒት በተገቢው መልክ በመከታ ተል፣ ጤናማ አመጋገብ በመመገብና የሰውነት እንቅስቃሴ (ስፖርትን) በመሥራት ልንቆጣጠ ረው እንችላለን፡፡ ነገር ግን ብዙ ሰዎች በሽታ ው በጣም እስኪባባስ ድረስ እንዳለባቸው አያውቁትም፡፡ ከወላጆች አንዳቸው የደም ብዛት ተጠቂ ከሆኑ፤ በየጊዜው በመመርመር ጤናዎን መከታተል ይኖርብዎታል፡፡
5. ከፍተኛ ኮሌስትሮል
ኮሌስትሮል የምንለው በቀይ የደም ሴሎች (በደምዎ) ውስጥ የስብ ብዛትን ነው፡፡ በበዛ ቁጥር ለጤና በጣም አደገኛ ነው፡፡ የኮሌስትሮል መጠንዎን ጤናማ አመጋገብን በመከተልና ስፖርት በመስራት ሊቆጣጠሩት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን የኮሌስትሮል መጠንዎን የማይቆጣጠሩት ከሆነና ወላጅዎ ወይም ልጅዎ ከ55 ዓመታቸው በፊት ለልብ ህመም የተጋለጡ ከሆነ አደጋ ላይ እንደሆኑ ይወቁ፡፡ የኮሌስትሮል መጠነንዎን በየጊዜው ይከታተሉ፡፡
4. የስኳር በሽታ
ሁለቱም ዓይነት 1 አይነት እና 2 የሚባሉት የስኳር በሽታ አይነቶች በዘር ይተላለፋሉ፡፡ በየትኛውም ዓይነት የስኳር በሽታ ተጠቂ የሆነ የቤተሰብ አባል ካሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ የደሞን የስኳር መጠን እየተመረመሩ ይከታተሉት፡፡ ምንም እንኳን ዓይነት 1 የስኳር በሽታን እንዳይዘን ማስቀረት ባይቻልም፤ ዓይነት 2 ግን እንችላለን፡፡ ይህም የሚሆነው በጤናማ አመጋገብና ስፖርትን በመሥራት ነው፡፡
3. ግላውኮማ
ግላውኮማ በዘር የሚተላለፍ የዓይን በሽታ ነው፡፡ በቤተሰብዎ ውስጥ የግላውኮማ ችግር ካለ ጨርሶ እንዳይዝዎት ማድረግ ባይቻልም በህክምና ማዳን ግን ይቻላል፡፡
2. ድብርት
በድብርት ምክንያት የመጣ የአእምሮ ህመም በቤተሰብዎ ውስጥ ካለ ያ የታመመ ሰው በዘር ተላልፎበት ሊሆን ይችላል፡፡ አንድ ነገር ግን ልብ ይበሉ፡፡ ይህ በሽታ ሁሌ በዘር ብቻ ተላል ፎ አይዝም፡፡ በቤተሰብዎ ውስጥ ይህ በሽታ ባይኖርም እርስዎ በራሶ ሊይዝዎት ይችላል፡፡
1. አለርጂ እና አስም
አለርጂ የምንለው ለምሳሌ የአበባ የወንዴ አባላዘር ብናኝ ሲሸተን ዓይናችንን የመቆጥቆጥ እና የመቅላት፣ የመተንፈሻ አካሎቻችን ማሳከክ እና ለመተንፈስ መቸገር ዓይነት ምልክት ካሳየን አለርጂ ብለን እንጠራዋለን፡፡ ይህም አለርጂ በዘር ይተላለፋል፡፡ ከወላጅዎ አንዳቸው በአለርጂ ከተጠቁ እርስዎም 50 በመቶ የመያዝ ዕድል አሎት፡፡ ሁለቱም ወላጆቾ ደግሞ ካለባቸው የ75 በመቶ የመያዝ ዕድል አለዎት ማለት ነው፡፡ አስምም ብዙ ጊዜ ከአለርጂ ጋር በአብዛኛው ዝምድና አለው ተብሎ ይታመናል፡፡ አብዛኛዎቹ አስም ያላቸው ህፃናት አለርጂም አለባቸው፡፡ ሁለቱም ደግሞ በዘር ይተላለፋሉ፡፡
ምንጭ፡ ዘቢሄቭ ኦርግ

ህወሓት ምንም አዲስ መልዕክት የሌለው መግለጫ ዛሬ ሰጠ –ጉዳያችን

$
0
0

ለመግለጫው አጭር መልስ የሚሆነው ´´ከዝንብ ማር አይጠበቅም´´ የሚል ነው EPRDF press release is the same as ´´square one´´ expression of its failed policy for the last 25 years

የአማርኛ ፅሁፍ ከስር ይመልከቱ።
woyaneEPRDF press release of August 28,2016 is the same as ´´square one´´ expression of its failed policy for the last 25 years. It is  full of empty words. There is no single word of ´´excuse´´ for over 1000 Ethiopians killed in last seven months by the regime. The press release is expected to invite more people to protest  TPLF. Because it did´t even reason out the real situation of the country plus the possible solutions suppose to be proposed by this particular press release. In addition to that the press release, at the last statement conclusion, warns peaceful protestors and appreciate the regime´s security personnels. Such a kind of approaches of TPLF is very common for Ethiopians in the last 25 years. In short it is possible to say that this is another confirmation as dictators will make fast their last days by following poor minded advisers. The same is happening in TPLF. For your easy information about the press release, please read the below Amharic version of Gudayachn´s view and full press release of TPLF video at the end of article.
የኢትዮጵያ ሕዝብ እያገባደድነው ባለው የ2008 ዓም ለነፃነት የሚያደርገውን ትግል በአዲስ መልክ ያቀጣጠለበት ዓመት ነው።በእዚህ ዓመት ብቻ እስካሁን ትክክለኛ ቁጥሩ ባይታወቅም በኦሮምያ እና አማራ ክልሎች ብቻ በሰላማዊ ሰልፍ መብታቸውን በመጠየቃቸው ብቻ ከ1000 በላይ ኢትዮጵያውያን በጥይት አረር ተገድለዋል። በአስር ሺዎች ወደ እስር ቤት ተግዘዋል።ሌሎች አስር ሺዎች ካሉበት ቀዬ ወደ ሌላ ቦታ ተሰደዋል።
ሕዝባዊ አመፁ እያየለ መጥቶ ይህ ፅሁፍ በምፃፍበት በእዚህ ቅፅበት በጎንደር እና ጎጃም ሕዝብ የህወሓት መዋቅር የሆኑ የአስተዳደር እርከኖችን አፍርሶ እራሱን በእራሱ ጊዝያዊ የአስተዳደር መዋቅር እየዘረጋ እና መሪውን እየመረጠ መሆኑ እየተዘገበ ነው።በእዚህ ሁኔታ እያለ ነው እንግዲህ የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከስብሰባ በኃላ ደረሰበት የተባለውን ውሳኔ ዛሬ ነሐሴ 22፣2008 ዓም በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የተነበበው።
መግለጫው በእራሱ የኢህአዴግ ነው ወይ? የሚለው መሰረታዊ ጥያቄ ነው።ምክንያቱም የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ብአዴን እና ኦህዴድ ቀድሞም በህወሓት መዋቅር የመታዘዛቸው ጉዳይ እንዳለ ሆኖ በእዚህ ዓመት ይብሱን በሕዝባዊ አመፁ ሳብያ ሕልውናቸው ማክተሙን በግልፅ የታየበት ነው።ስለሆነም የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ሲባል ህወሓት እና ህወሓት ብቻውን ያሰበውን መግለጫ በሚል ስም እንዳወጣው መረዳት ተገቢ ነው።
በተሰጠው መግለጫ ላይ በመጀመርያ ክፍል ላይ ´´ውዳሴ ህወሓት´´ የተሞሉ ቃላት ብቻ ሲገኙበት።በሚልዮን የሚበሉት እና የሚጠጡት ባጡባት አገር ውስጥ ይልቁንም ረሃብ እንደ አዲስ አበባ ያሉ ታላላቅ ከተሞች ውስጥ ተማሪዎች የምግብ ድጋፍ ካልተደረገላቸው ትምህርታቸውን መቀጠል እንደማይችሉ እነዩኒሴፍ የመሳሰሉ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በገለፁበት ሁኔታ ሁሉ የኢህአዴግ መግለጫ ኢትዮጵያ እንዳደገች ለመስበክ መሞከሩ አሁንም በአስራአንደኛው ሰዓት ላይ ቆመውም ህወሓቶች ለለውጥ ሳይሆን ለበለጠ ግድያ መነሳታቸውን አመላካች ነው።
የመግለጫው ዋና እና ቁልፍ ምክንያት የኢትዮጵያን ሕዝብ አዘናግቶ የበለጠ ጦር ሕዝባዊ አመፁ ወደተነሳባቸው ቦታዎች አዝምቶ ለመጨፍለቅ እና የምዕራባውያንን ውትወታ በሆነች ለውጥ በምትመስል መግለጫ ይሄው እየሰራን ነው ለማለት የታሰበ ነው።ለእዚህም ነው የህወሓት የማኅበራዊ ሚድያ አፈቀላጤዎች  መግለጫውን በተመለከተ በእንግሊዝኛ ለመፃፍ የሚደክሙት።ሌላው አስቂኝ የመግለጫው ሂደት አሁን ኢህአዴግ የሚያደርገው ለውጥ ከአስራ አምስት ዓመት በፊት የተጀመረው አካል ነው ሲል መደመጡ ነው።ይህ ´´ ሃያ አምስት ዓመት በጥይት ስገድሉን ኖረው አሁን ደግሞ በሳቅ ገደሉን ´´የምትለዋን አባባል ያስታውሳል። ስህተት ተሰርቷል ለውጥ ያስፈልጋል ብሎ በድፍረት የለውጥ አስፈላጊነትን አፍን ሞልቶ ለመናገርም ያፈረ ስርዓት ዛሬ በህዝባዊ አመፅ ለለውጥ ተገደድኩ ይሉኛል በሚል ጭንቀት ለውጡን ከአስራ አምስት ዓመት በፊት ባቀጣጠልነው መሰረት ነው ብሎ መግለጫ ማውጣት ለምንም አይነት እርምጃ አለመዘጋጀታቹን የበለጠ ግልፅ ያደርገዋል።
ህወሓት በእዚህ መግለጫ ላይ ለችግሩ መነሻ ብሎ ያቀረባቸው ነጥቦች በእራሳቸው ደካማ እና መሰረታዊ የህወሓት የፖሊሲ ውድቀት እና ስልጣንን በብቸኝነት የመቀራመት አባዜ ያገለለ ነው።በዛሬው መግለጫ ህወሓት የአገራችን ችግር ብሎ ያቀረባቸው ችግሮች ያሉ ችግሮች ቢሆኑም ዋናው እና መሰረታዊው ችግር ከላይ እንደተጠቀሰው የህወሓት የፖሊሲ ውድቀት፣ጎጠኛ እና አድሏዊ ስርዓት መስፈን እና ስልጣንን በብቸኝነት የመቀራመት አባዜ የሚሉት ዋነኛ ናቸው።ለእነኝህ መፍትሄዎቹ ደግሞ በዋናነት ህወሓት ስልጣኑን በፍጥነት እንዲለቅ ማድረግ እና ሕዝባዊ እና የሽግግር መንግስት መመስረት ነው።ከእዚህ ያነሰ መፍትሄ ቁስል የበለጠ እንዲመረቅዝ እና ኢትዮጵያን ወደ ባሰ ማጥ ውስጥ የመክተት ግልፅ ፍላጎትን ብቻ ያመለክታል።ህወሓት በዛሬው መግለጫው ግን ችግሮች ብሎ ጉዳዩን በጥገናዊ ለውጥ ለማለፍ የሞከረበት መንገድ ችግሮቹን  የህዝብ መብዛት፣የሕዝብ ፍላጎት መጨመር፣ስልጣንን የሀብት ማከማቻ የማድረግ ሂደት በኢህአዴግ ውስጥ በመስረፁ ወዘተ ናቸው በሚሉ ቃላት ለማድበስበስ ሞክሯል።
ባጠቃላይ መግለጫውን በሶስት ክፍሎች ልንከፍለው እንችላለን።የመጀመርያው ክፍል ህወሓት እራሱን ያሞገሰበት እና ኢትዮጵያውያን ´´ምግብ በልታችሁ ያደራችሁት እኔ ስልጣን ከያዝኩ በኃላ ነው´´ ቀረሽ ሐተታ ሲሆን ሁለተኛው ችግሩን ከህወሓት የስልጣን ጥማት እና አገሪቱን በተሳሳተ የጎጥ ፖለቲካ  መከፋፈል የመጣ መሆኑን ሸሽጎ የችግሩን መነሻ በገሃድ ካሉ ግን ብቸኛ ችግሮች ካልሆኑት የስልጣን መባለግ፣የህዝብ ብዛት መብዛት እና የህዝብ አዳዲስ ፍላጎቶች በሚሉ ቃላት ሊያድበሰብስ የሞከረበት ነው።በመግለጫው የመጨረሻ ክፍል ላይ ደግሞ ሕዝባዊ አመፁን የጥፋት ኃይሎች መሆኑን ሊሰብክ ይሞክርና ከጎኑ ቆመው ሕዝብ የገደሉትን ሲያሞግስ እና አይዟችሁ በርቱ ሲል ታገኙታላችሁ። መግለጫው ባጭሩ ይሄው ነው።ለመግለጫው አጭር መልስ የሚሆነው ´´ከዝንብ ማር አይጠበቅም´´ የሚል ነው።ህወሓት ማር ሊያመነጭ አይችልም።ማር የንብ ሥራ እንጂ የዝንብ ሊሆን እንደማይችል ሁሉ።

ሙሉ መግለጫውን ለመመልከት  ይህንን ይጫኑ።

ጉዳያችን GUDAYACHN 

 www.gudayachn.com

እጅግ በጣም አስቸኳይ መልእክት –ብሥራት ደረሰ

$
0
0

 

Tomarበአሁኒቷ ቅጽበት በዐማራው አካባቢ ሕዝቡ ከወያኔ ታጣቂዎች ጋር በባዶ እጁ እየተፋለመ ይገኛል፡፡ ይህ ለዓመታት ታፍኖ የነበረ የነፃነት ጥያቄ ወቅቱን ጠብቆ አሁን በቅርብ ከሞላ ጎደል በሁሉም የጎጃምና የጎንደር አካባቢዎች ፈንድቷል፡፡ ይህ የሚያሳየው ጭቆናና ምሬት በኃይል ታፍኖ ሊቀር የማይችል መሆኑን ነው፡፡

ይሁንና ነፃነት የጠማው የኢትዮጵያ ሕዝብ በጎሣና በሃይማኖት ተወስኖ የአንዱ ንቅናቄ ለሌላኛው ባይተዋር ሊሆን እንደማይገባ ሁላችንም ማሰብ ይኖርብናል፡፡ እርግጥ ነው እስካሁን ስህተቶች አልነበሩም አንልም፡፡ ንስሃ ልንገባባቸውና ይቅርታ ልንባባልባቸው የሚገቡ ስህተቶችን ሁላችንም ስንሠራ ለመቆየታችን ትልቁ ማስረጃ የወያኔ ሥልጣን ላይ ለ25 ዓመታት ተገሽሮ ሁላችንንም ሲቀጠቅጥ መቆየቱ ነው፡፡ ብንተባበር ኖሮ 25 ዓመታትን ቀርቶ 25 ቀናትንም አራት ኪሎ ምንሊክ ቤተ መንግሥት ውስጥ ወያኔ አይቆይም ነበር – ታሪካዊ ፀፀት፡፡

ስህተት አንድ – ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የመብት ጥያቄ አንስቶ ብቻውን ሲታገል ሌላው በአብዛኛው በታዛቢ ወንበር ላይ ተቀምጦ ነበር፡፡ ያ ትልቅ ስህተት ነበር፡፡ እርግጥ ነው የሙስሊሙን ጥያቄ ከሃይማኖት አውጥቶ ወደ አጠቃላይና ሁሉንም ሊያቅፍ ወደሚችል የመታገያ መስመር ማስገባት ይቻል እንደነበር ብንጠቁም አግባብ ነው፡፡ ጥያቄዎችን ከማጥበብ ይልቅ ማስፋትና ሁሉንም አሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ ይገባል፤ ይቻላልም፡፡ ጠባብ ጥያቄዎችን መጠየቅ ለወያኔዎች የተናጠል ብትር ይዳርጋል፤ ማንም ደግሞ በተናጠል ጥያቄዎች ድልን ሊቀዳጅ አይችልም፡፡ በትልቅ ጥያቄ ፍቺ ውስጥ ብዙ ትንንሽ ጥያቄዎች ሊፈቱ እንደሚችሉ ባለመረዳት ወይም ለመረዳት ባለመፈለግ ብዙ ዘመን ተሞኝተናል – በዚህም ሰበብ ለወያኔ ምቹ ፈረስና መጋጃ ሆነን ለብዙ ዘመን ባጅተናል፡፡ ይህን ሞኝነታችንን ተረድተን ባፋጣኝ ካልተስተካከልን የሰሞኑ እንቅስቃሴም ከጊዜያዊ ጫጫታነት አያልፍም፡፡

ስህተት ሁለት – ኦሮሞ ኢትዮጵያውያን በተለይ ከዚህ ዓመት(2008) መባቻ ጀምሮ በየአካባቢያቸው ሰላማዊ ተቃውሞ ሲያደርጉና በወያኔ ቅልብ የአጋዚ ጦር እንደዐይጥ ሲጨፈጨፉ ሌላው ዳር ቆሞ ይታዘብ ነበር – የወንድሞቹ ቁስል አልተሰማውም ማለት ግን አይደለም፡፡ ለወያኔ የከፋፍለህ ግዛ ሥልት ተንበርክከን ራሳችንን በየግል ቋጠሮ በማስቀመጣችን ግን አልተባበርንም፤ በዚያም ምክንያት ወያኔ ተመቸውና በተናጠል መደቆሱን ቀጠለ፡፡ አሁንም እርግጥ ነው – የኦሮሞዎችን ጥያቄ ከኦሮሞ ግዛት መጥበብና መስፋት ጋር ብቻ ከማያያዝ ይልቅ እሱን በእርሾነት ይዞ ለትልቁ ሀገራዊ ነፃነት ሁሉም በአንድነት እንዲነሣ ቢደረግ ኖሮ ይሄኔ ይሄ በየአካባቢው የሚደረግ የቁጥ ቁጥ ትግል ባላስፈለገ ነበር፡፡ ይህችን ሒሣባዊ ቀመር እንዴት ማወቅ እንዳልቻልን ሳስበው ይገርመኛል፡፡ ጥቂት ወያኔዎች በአእምሮ ማለትም በተንኮል በተካነ አእምሮ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ይህን ያህል እንዴት ሊበልጡ እንደቻሉ ሳስበውም እንደዚሁ ይደንቀኛል፡፡ በምን አፈዘዙን?

ስህተት ሦስት – ሰሞኑን የዐማራው ሕዝብ ፀረ ወያኔ እንቅስቀሴውን ጀምሯል፡፡ የዘገዬ ቢሆንም ጅምሩ መልካም ነው፡፡ ሆኖም በተለይ በመነሻው አካባቢ ጥያቄው ልክ እንደላይኞቹ ሁሉ ጠበበና ወይም የሚጠበቀውን ያህል ሌሎችን አሳታፊ ሆኖ የተገኘ አልሆነምና ከክልሉ ውጪ ያሉትን ለመሳብ አቅም ያነሰው መሰለ፡፡ ጎንደር ላይ “የኦሮሞ ወንድሞቻችን ደም የኛም ደም ነው” በሚል ሕዝቡ በራሱ ተነሳሽነት የኦሮሞ ወንድምና እህቶቹን ሰማዕትነት ማስታወሱ አዲስ ምዕራፍ ከፍቶ ሁለቱን የወያኔ መጫወቻ ታላላቅ ብሔሮች (በእስካሁኑ ሁኔታ ማለቴ ነው) ቢያቀራርብም አሁንም ብዙ የሚቀረው ነገር እንዳለ መገንዘብ ይገባል፡፡ ወያኔዎችና ተባባሪዎቻቸው ለዘመናት የሠሩት ዕኩይ ተግባር በአንድና በሁለት የተቃውሞ ሰልፎች የሚናድ እንዳልሆነ መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡ ሁለትም ይሁኑ ከዚያ በላይ ትልልቅ ግንዶችን የሚያሸንፍ ቅርንጫፍ – ቅርንጫፉ ምንም ያህል ቀጭንና ላንቁሶም ይሁን – የግንዶቹን ሥሮች እንደምሥጥ እምሽክ አድርጎ በመብላት ግንዶቹን ከናካቴው ሊያጠፋቸው እንደሚችል እስካሁን ማንም አልተረዳም፡፡ ታላላቆችን ለማጥፋት ደግሞ አካላዊ ግዝፈት የግድ አይደለም – ብልጠትና መሠሪነት ብቻቸውን ብዙ ሚና ይጫወታሉ – በዚያ ላይ መካሪና ሁለገብ ረድኤት የሚሰጥ አጋዥ ኃይል ካለ አናሳዎች የጥፋት መንገዳቸው ቀኝ በቀኝ ነው የሚሆንላቸው፡፡ በዓለም 14.2 ሚሊዮን አካባቢ የሕዝብ ቁጥር ያላት እስራኤል የዓለምን ፖለቲካና ኢኮኖሚ በተቆጣጠሩ ምርጥ የኅቡኣን ድርጅቶች አባላት ልጆቿ አማካይነት የሰባት ቢሊዮኑን የዓለም ሕዝብ የዕለት ተለት ሕይወትና እስትንፋስ እንደምትቆጣጠርና እንደምትወስንም ለሚረዳ ዜጋ ከስድስት ሚሊዮን የፈለቁ ጥቂት አሰለጦች ከውጪ ረዳቶቻቸው ጋር ተዓምር አይሠሩም ብሎ መገመት ሞኝነት ነው፡፡ ብዛት ብቻውን አይጠቅምም – በራሱ ዋጋቢስ ነው፤ እንዲያውም ብዛት ያጃጅላል ይመስለኛል፡፡ የሌለህን እንዳለህ፣ ያልሆንከውን እንደሆንክ በሥነ ልቦና ጥጋብ እያሰከረ ተጠቂ ያደርግሃል – ብዛት፡፡ ስታንስ ግን ጠርጣራና ፈሪ ያደርግህና ከቢጤዎችህ ጋር እያቆራኘ – እንደሙጫ እያጣበቀ – ብዙ ትንግርት እንድትሠራ ያደርግሃል – ጥቂትነት፡፡ ዕድሜ ደጉ… ማንበብም ደጉ… ከብዙው ጥቂቱን አየን፡፡

ከቅርብ ቀናት ወዲህ የዐማራው ጥያቄ ለአጠቃላዩ ሀገራዊ ነፃነት የጥሪ ደወል ማሰማት ቢጀምርም ከፍ ሲል እንደተገለጸው በመነሻው አካባቢ በወልቃይት ዙሪያ ያጠነጥን ስለነበር ያ ጥያቄ ለጋሙጎፋውና ለአፋሩ ሩቅ መስሎ ሊታይ ቢችል አያስወቅስም ባይ ነኝ፤ ጥያቄው ሁሉን ቆንጣጭ ነበር ለማለት አያስደፍርም፡፡ አሁን መስተካከሉና ብሔራዊ አጀንዳ መያዙ ግን ደግ ነው፡፡ መስተካከሉን አምነን ታዲያ እንቀላቀለው፡፡ ምክንያቱም የዋናው ድል መቋጫ በዋናነት አዲስ አበባን ጨምሮ የሁሉም ሕዝብ ንቁ ተሣትፎ ነውና፡፡

ስህተት አራት – የዐማራው ጥያቄ ከጎጥና ከሸጥ አልፎ ሀገራዊ ቅርጽ ከያዘም በኋላ የመላዋ ኢትዮጵያ ሕዝብ ለጋራ ሀገራዊና ብሔራዊ ነፃነቱ በአንድነት “ሆ!” ብሎ እንዳይነሣ ያደረገው ነገር አለ፡፡ ይህን ነገር ሁነኛ የፖለቲካ ቡድች በአፋጣኝ አጥንተው መፍትሔ ካልተፈለገለት ይሄ አንዴ ወለጋ ሌላ ጊዜ ጎንደር የሚደረግ ሕዝባዊ የእምቢተኝነት ዐመፅና የነፃነት ትግል የትም አይደርስም፡፡ አዎ፣ የትም! ለሕወሓት ግን ሠርግና ምላሽ ነው፡፡ ለዚህ ጎጠኛ የአናሳዎች ቡድን መሠሪ ተንኮል መሸነፍ ይብቃን፡፡

ነፃነት ቆራጥነትንና እልህን ትፈልጋለች፡፡ ነፃነት ሸረኝነትና ተንኮልን ያዘለ ፉክክርን አትሻም – የነፃነት ፍልሚያ ውጤታማ እንዲሆን በቀናነትና በእኔ እብስ አንተ ትብስ የጋራ መግባባትና መተሳሰብ መቃኘት አለበት፡፡ ሁሉም እንደየአቅሙ በስሜትና በከፍተኛ ወኔ ከተሳተፈ የነፃነት ቀን ቅርብ ናት፡፡ ነገር ግን “ቆይ እነእንትና ይለይላቸው፣ እነሱ ሲያዳክሟቸው እኛ እንቀጥልና የመጨረሻ ግብኣተ መሬታቸውን እናሳያቸዋለን…” በሚል የማይረባ ሥልት በተናጠል መጓዝ ካለ መቼም ቢሆን ነፃነት አትገኝም፡፡ ነፃነት በእልህ አስጨራሽ የጋራ ትግል እንጂ በብልጣብልጥነትና ከጋራ ትግል በመሸሽ ልትገኝ አትችልም፡፡ በአንዱ ሞት ሌላው ነፃ እንዲወጣ ተደብቆ ወይ አሸምቆ ቢጠባበቅ ደግሞ ከኅሊናም ከሃይማኖትም አንጻር ወንጀልና ኃጢኣትም ነው፡፡ ሁሉም የድርሻውን ይወጣ፡፡ “ማን ይጠይቀኛል? ማንስ ያየኛል?” የሚሉት ጥያቄዎችም የጅል ፈሊጦች ናቸው፤ በመጀመሪያ ዋናው ጠያቂ ኅሊናችንና የሚሰውት ወገኖቻችን ነፍሳት ናቸው፡፡ ከዚህ ነጥብ አኳያ ሁሉም ዐይን ነውና እንዳንታለል፡፡

ስህተትን ለማስወገድ እንዲህ ቢደረግ ጥሩ ይመስለኛል፡-

ኦሮሞው፣ ዐማራውና ሌላው ጎሣ ሁሉ በተጀመረው መንገድ ለአንድ ዓላማ ይተባበር፡፡ የተናጠል ትግል የትም እንደማያደርስም ከልምድ ይረዳ፡፡ ጠላት አንድ ነው፡፡ የጥቃቱ ሰለባዎችም አንድ ናቸው ወይም ቢያንስ አንድ መሆናቸውን ሊረዱ ይገባቸዋል፡፡ ራሳቸውን እየለያዩ በተለያዬ ጊዜ ከሚጠቁ በአንድነት ተባብረው ከዘላለም ባርነት በአንዲት ጀምበር የዘላለም ነፃነታቸውን መጎናጸፍ ይችላሉ፡፡ እንደእስከዛሬው በመለያየትና የመቃብር ጉድጓድ እየቆፈሩ በዐፅምና ባለፉ ሰዎች የታሪክ ጠባሳ የሚጃጃሉ ከሆነ ግን ልክ  እንደስካሁኑ ለጠላታቸው ምቹ እንደሆኑ አንዱ ምዕተ ዓመት አልፎ ሌላው ይተካል፡፡ በሰው ሠራሽና በጠላት-ጠመድ የልዩነት ቦምቦች ፍንዳታ ጊዜያቸውን በከንቱ ማባከን የለባቸውም፡፡ ከዚህ ሞኝነታቸው ተምረው ብልኅነትን ገንዘባቸው ያድርጉ፡፡

ለምሣሌ የቋንቋና የሰንደቅ ዓላማ ልዩነቶች ወደ ውስጥ ገብተው ካጤኗቸው መሠረታዊ ችግሮች አይደሉም፡፡ ያገሬ ባላገርና ሕጻናት ልጆቹ በሕወሓት አልሞ ተኳሾች ጭንቅላታቸው እየተበተነ በቀያቸው ሥጋቸውን አሞራና ውሻ እየጎተተው ሳለ፣ ሕወሓት ኑሯችንን አመሰቃቅሎና ሰብኣዊ ተፈጥሯችንንም  ከእንስሳነትም በታች አውርዶ በነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ የሰቀቀን ኑሮ እየገፋን ሳለ፣ እትብቴ በተቀበረባት የገዛ ምድሬ እኔን ለመንግሥት ሥራ መቅጠሩ እንደቅንጦትና ብርቅ ይቆጠርና እንደህንድ የካስት ሲስተም ሊጨብጡኝ እንኳን እየተፀየፉኝ በምገኝበት ሁኔታ … ፖለቲከኞች ሚዛን በማይደፉ የአዛኝ ቅቤ አንጓች ዓይነት ጉንጭ አልፋ ክርክሮች ቢጠመዱ ሕዝብና ታሪክ ይቅር የማይሉት ሌላ ስህተት ነው – “ቀድሞ የመቀመጫየን” ብላለች ዝንጀሮ፡፡ ከሌላው እንቶፈንቶ ይልቅ የተበላሸን በማቃናት፣ የተሳሳተን በማረም፣ የተዛነፈን በማስተካከል … ወደ ደገኛው መንገድ እንግባና እንደቀድሟችን በቶሎ አንድ ብንሆን ሁላችን እንጠቀማለን፤ ሌላው ቀስ ብሎ ይደረስበታል፡፡

ሞኝነትንና ብልጣብልጥነትን አርቆ መቅበር ይገባል፡፡ ይህን በሕዝብ ደምና አጥንት ላይ የቆመ ከፋፋይ የወያኔ ብልሹ ሥርዓት ከሥሩ መንግሎ ከነሰንኮፉ ለመጣል ሁሉም “ሆ!” ብሎ በአንድ ወቅት መነሣት አማራጭ የሌለው የጊዜው አንብጋቢ ጉዳይ ነው – ከዳር እዳር ተነጋግሮና በጥሞና ተመካክሮ በአንድ ወቅት መነሣት!! ጎጃም የሚፈሰው ደም የአርሲው ነው፤ ወለጋ የሚፈሰው ደም የጎንደሬው ነው፡፡ የወያኔን ሤራ በጣጥሰው ካልጣሉና ሰሞኑን በተጀመረው የአንድነት መንፈስ ካልታገሉ ማንም ነፃ ሣይወጣ የወያኔ አሽከርና ደንገጡር ሆኖ የመከራ ኑሮን መግፋት ነው – እስከወዲያኛው፡፡ መጥፎ ህልም ስታልም መፍትሔው ከእንቅልፍህ መንቃት ነው – ከወያኔ ሰቆቃ ለመዳንም መፍትሔው በከፋፋይ ሤራው ላይ የማያዳግም እርምጃ ወስዶ ኅብረትን ማጽናት ነው፡፡

ያለፈ አልፏል፡፡ “ላለፈ ክረምት ቤት አይሠራም”፡፡ በእጃችን ያለችዋ ጊዜ ናት ወርቃማ ጊዜያችን፡፡ ወንድሞቻችን በጎጃምና በጎንደር እየተዋደቁ በወሎና በሸዋ እንዲሁም በአዋሣና በጋሙጎፋ የሚገኝ ሕዝብ ተኝቶ እንቅልፉን የሚደቃ ከሆነ የምትጠበቀዋ ነፃነት ቅዠት ናት – አትገኝም፡፡ ጎንደርና ባህር ዳር እየታመሱ አዲስ አበባና ናዝሬት በአሥረሽ ምቺው “ዓለማቸውን የሚቀጩ” ከሆነ የነበረችን አነስተኛ በሕይወት የመቆየት ነፃነት ራሷ ወደለዬለት ባርነት ትለወጥና ትልቁ እሥር ቤታችን – ዞን ዘጠኝ – ወደማዕከላዊ የወያኔ የ”ወንጀል ምርመራ” ዘብጥያነት ይለወጣል፡፡ ለዚህም ነው “የነብርን ጅራት አይዙም…” የሚባለው፡፡ ወያኔና የቆሰለ ነብር አንድ ናቸው፡፡ የወያኔን ተፈጥሯዊ የበቀለኛነት ስሜት አዲስ አበቤዎች በተለይ ጠንቅቀን እናውቀዋለን፡፡ ከ97 ምርጫ በኋላ ምን እንደደረሰብን እንኳንስ እኛ ሌላው ዓለምም ያውቃል፡፡ ወያኔ በየጊዜው በደም ካልዋኘ ያስተበተበው ድግምት አይሠራለትም – ትልቁ የሰይጣን ምስ ወይም ግብር ደግሞ ደም ነው፡፡ ለዚህም ነው በበቀል የሰከሩት ወያኔዎች በተለይ ዐማራውንም ሆነ ሌላውን – ዓላማቸውን የማይደግፍና የሚቃወማቸውን ትግሬም ሳይቀር – አዛዣቸው ዲያብሎስ በሉ ባላቸው ቁጥር ባልተወለደ አንጀታቸው ጭንቅል ጭንቅሉን እያሉ ለአባታቸው የሚገብሩት፡፡ እነሱ ካልጠፉ ሞታችንና አሟሟታችን እየከፋ እንጂ እየቀነሰ አይሄድም፡፡ በሰይጣን የቆረበ ሰው የተጎጂዎች አበቅቴ እስኪብት ድረስ ዘመኑ ከሚፈቅድለት የወንጀል ድርጊት ውጪ ሌላ ደግ ነገር ይሠራል ተብሎ አይጠበቅም – የባሕርዩ መገለጫ ክፋት ብቻ ነውና፡፡

ምርጫው የኛ ነው እንግዲህ፡፡ በሕዝብ መተባበር ወያኔዎች ሰሞኑን ደንግጠዋል፡፡ የድንጋጤያቸው ደረጃም ሱሪያቸው ከፊትም ከኋላም እስኪረጥብ ድረስ መሆኑን ምሥጢሩን የሚያዉቁ እየተናገሩ ነው፡፡ ይህን በጥርጣሬ ደረጃ ያለ የወያኔ መረጣጠብ ማፋጠንና የዚህን ሰው-በላ የአፓርታይድ ሥርዓት ዕድሜ በደቂቃዎች እንዲገመት ማድረግ ይቻላል፡፡ እንደዚያ የሚሆነው ግን የተጨቋኞች ዓላማና ፍላጎት አንድ ሆኖ ሁሉም በያለበት ወያኔን ሲያርበደብድ እንጂ አንዱ ከነሱ ጋር ማኪያቶ እየጠጣና ውስኪ እየጨለጠ፣ ሌላው ደግሞ በአልሞ ተኳሾች ልዩ ጥይት ጭንቅቱ እየፈረሰ አይደለም፡፡ አሁንም እርግጥ ነው – ኢትዮጵያ ኢያሪኮ እንዳልሆነች ልብ ይሏል፡፡ የኢትዮጵያ ነፃነት ካለደም እንደማትገኝ የጎንደርና የጎጃም ዐማሮች እያስመሰከሩ ነው፤ ከወያኔ ተፈጥሮ የምንረዳውም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ያልቃታል እንጂ ወያኔዎች ፈረንጆቹ ዴሞክራሲ በሚሉት ቀልድ ወይም በሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ቤተ መንግሥት እንደማይለቁ ግልጽ ነው፡፡ ስለሆነም የነሱን ፈለግ በመከተል ሁሉም በተቻለው መፋለም ይገባዋል እንጂ በጩኸት ብቻ ወያኔ አራት ኪሎን ይለቃል ማለት ዘበት ነው፡፡ የዓለም ገዢ ኃይልም ከነርሱ ጋር ስለሆነ ሰሞነኛው ጩኸታችን ቀርቶ የገፍ ዕልቂታችን እንኳን ተገቢውን ዓለም አቀፍ ትኩረት አላገኘም – ማን እንደሰው ቆጥሮን! ይሄኔ የሮበርት ሙጋቤ የክብር ዘብ የአንድ ነጭ ዚምባብዌያዊ የሣሎን ውሻን በባረቀ ጥይት አቁስሎ ቢሆን ኖሮ የነቢቢሲና ሲኤንኤን እንዲሁም የነስካይኒውስና አልጀዚራ ቲቪዎች የአንድ ሣምንት የመክፈቻ ዜና በሆነ ነበር፤ ዘርንና ምጣኔ ሀብትን መሠረት ባደረገ መልክ ዓለም ይህን ያህል አሽቃባጭ ናትና ወደ አምላካችን ብቻ እንጩህ ይልቁንስ፡፡ ከሰው ምንም አንጠብቅ፡፡ ከራሳችን ውስጥ ብዙ ሥጋዊና መንፈሣዊ ኃይል አለ፡፡ ያን እናውጣውና እንጠቀምበት፡፡ ሕዝባችንንም እናንቃው፡፡ የምንችል እናስተምረው፡፡ ከተኛበትም እንቀስቅሰውና የጥንት የጧት አያት ቅድመ አያቶቹ የሠሩትን የመሰለ ታሪክ እንዲሠራ ለዳግም ልደት እናብቃው፡፡…

ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡

ሕዝቡ ማናቸውንም ዓይነት ፖለቲከኛ በልጦ ሄዷል – ወያኔንም ተቃዋሚንም፡፡ ወያኔ ተጎልቶ ያለው ከ41 ዓመታት በፊት በነበረበት ደደቢት ላይ ነው – ሰውነታቸው በዐማራና በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ጥላቻ እንደተሞላና ገድሎ በማይረካ የበቀል ስሜት እንደተምቦገቦገ፡፡ ተቃዋሚዎች ያሉት የዛሬ 160 ዓመታት ገደማ ኢትዮጵያ የነበረችበት የዘመነ መሣፍንት ወቅት ላይ ነው – በማይጨበጥ ህልማዊ ሥልጣን እርስ በርስ ሲራኮቱ፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉም አእምሮውን የነሣው ነገር አለ፤ ሆድ ይሁን የዝናና የታዋቂነት ልክፍት በውል ለይቼ አላውቅም፡፡ ግን ግን አሁን እኔ እምለው ሁሉም ምናልባትም አብዛኛው ራሱን መፈተሸና ከሕዝብ የነፃነት ፍላጎትና የአርነት ትግል ጎን መሰለፍ የሚችልበትን ብልሃት ባፋጣኝ መቀየስ ይገባዋል ነው – በሕዝብ መበለጡን አውቆ ራሱን “ሳያስፎግር” በቶሎ ይስተካከል – በተቃዋሚነት እያምቧተሩና በሕዝብ ስም እየቀለዱ(እየነገዱም) መኖር ከእንግዲህ የሚታሰብ አይመስለኝም፡፡ አንዳንዱ ተቃዋሚ ይህን ዓይነት ሕዝብ የሚቀድምበትን የአጣብቂኝ ወቅት የጠበቀ አይመስልም – ለዚህም ነው ተደናግጦና ፈዝዞ ጥግ ጥጉን ይዞ እንደማንኛውም ተራ ዜጋ የነገሮችን አነሳስና ጡዘት እየታዘበ የሚገኘው፡፡ በየተወሰነ ወቅት ይሰጥ የነበረው መግለጫና ፉከራ(ፉገራም ቢባል ያስኬዳል) እንግዲህ ለላንቲካው ነበር ማለት ነው፡፡ አዎ፣ ትዝብትንና ምን ይሉኝን ዕንወቅ፡፡ እንደካሮት ወደታች ሣይሆን እንደሸምበቆ ወደላይ እንደግ፡፡ የአእምሮ መካንነትን እንዋጋና ጤናማ ሰው እንሁን፡፡ ያኔ ሀገራችን ትነሣለች፡፡

… ብዙ ማሰብ፣ ብዙ መሥራት፣ መጥፎ ነገሮችን መርሳት፣ ደጋግ ነገሮች ማስታወስ፣ ፍቅርንና አንድነትን መዘከር፣ ቂምንና በቀልን እርግፍ አድርጎ መተው፣ ወንድማማችነትን መስበክ፣ ጎሠኝነትን መጠየፍ፣ ሰውኛነትን ማጉላት፣ ከሕዝብ መማር፣ በሌሎች ወንጀል ንጹሕን ሰው ከመጠየቅና በሌሎች ደግ ሥራና ምሥጉን ትውፊት ምንም ያልሠሩ ሰነፎችን ማወደስን መተው፣ … በቃ … ባጭሩ ጤናማ ኅሊና ያለው ሰው መሆን …. የሁሉንም ችግር እንደራስ ችግር መቁጠር፣ የሁሉንም የነፃነት ትግል እንደራስ ትግል አምኖ በጋራ መታገል፣ ያንደኛው መክሸፍ የሌላኛውም መክሸፍ መሆኑን ከልብ መገንዘብና የጋራ ኃላፊነትን መውሰድ … ከሌሎች ብዙ አለመጠበቅ፣ የራስንም ድርሻ መወጣት … በገንዘብም በጉልበትም በዕውቀትም በጊዜም … አቅም በቻለ ሁሉ ለዚህች የጋራ ሀገራችን መስዋዕትነትን መክፈል፣ ካለመስዋዕትነት ነፃነት እንደማይገኝ መረዳት…ነፃነት እንደቡና ቁርስ ከሙዳይ ተቆንጥራ የምትሰጥ የዳቦ ፍርፋሪ ወይም ጭብጥ ቆሎ ሣትሆን የደምና የአጥንት ግብር የምትጠይቅ መሆኗን አምኖ ለሚፈለገው ግዳጅ ሁሉ ራስን ማዘጋጀት …ገና ለገና ሥልጣን አገኝ ይሆናል በሚል ከመጠን በላይና ለትዝብት በሚዳርግ ሁኔታ በሥልጣን ሱስ/አራራ አለመስገብገብ … ከሁሉም በላይ በሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ማመን … ፡፡ ወቅቱ የክተት ነው፡፡ ዐጤ ምንሊክ ወደ ዐድዋ ሲዘምቱ በዘርና በጎሣ የተከፋፈለ የውጊያ ጥሪ አላደረጉም – ይህን ዓይነት ሸንካላ ወያኔያዊ አካሄድ አያውቁትምም ነበር፡፡ ባጠፋሁ ይቅርታ … በስሜት ስትናገሪ የምታስቀይሚው ሰው ይኖራል መቼም፡፡ … ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፡፡ ለአሁኑ በቃኝ፡፡

ወይ አብረን እንሳቅ ካልሆነም አብረን እናልቅስ! (ከይገርማል)

$
0
0

unity

በየአካባቢው እየተደረጉ ያሉት ጸረ-ወያኔ እንቅስቃሴወች ክልላዊ ባህሪ መያዝ ያሳሰባቸው ግለሰቦች የሰሞኑ የአማራ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያውያን እንጅ የአማሮች መባል የለበትም ብለው ሲከራከሩ እየተደመጡ ነው:: ከኢትዮጵያዊነት ደረጃው ዝቅ ብሎ የማያውቀው አማራ ዛሬ ላይ በአካባቢው የታጠረ የሚመስል ትግል እያደረገ መሆኑ ግልጽ ነው:: “ወልቃይት የአማራ ነው! በአማራ ላይ ያነጣጠረ የዘር ምንጠራ ይቁም! የወያኔ የበላይነት ይብቃ!—” እያለ ድምጹን ከፍ አድርጎ መፈክር እያሰማ ነው:: ይህን እንዲል ያስገደደው በራሱ ላይ ያነጣጠረ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ስለተከፈተበት እንደሆነ በበኩሌ እረዳለሁ:: በህልውናው ላይ የተጀመረውን የጥፋት ዘመቻ ለመመከት ደፋ ቀና እያለ ያለው አማራ የሌሎች ወገኖቹ ህይወት አሳስቦት በኦሮሚያና በሌሎች ክልሎች የሚፈጸመውን የወያኔ የዕብሪት ጭፍጨፋ እያወገዘ ኢትዮጵያዊነቱን ማስመስከሩም አልቀረም::

 

የአማራውን ትግል ፍጹም ኢትዮጵያዊ መልክ ለመስጠት የሚደረገው ሙከራ ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን እንደሚችል መገንዘብ ተገቢ ነው:: የአማራው ትግል በሀገራችን እንደቅንጦት የሚታዩት የዴሞክራሲያዊ መብቶች ይከበሩ በማለት የሚደረግ ትግል ሳይሆን ከወያኔ የዘር ማጥፋት ዕቅድ ለማምለጥ የሚደረግ የሞት ሽረት ትግል ነው:: አማሮች በሰላም ከሚኖሩበት አካባቢ እየተለቀሙ ሲታረዱ አንድም ክልል ሀዘናቸውን የተጋራ: የተቃውሞ ድምጹን ያሰማ አልነበረም:: ወደፊት ጊዜ ፍንትው አድርጎ የሚያወጣው ሀቅ የሚጠበቅ ሆኖ አሁን ባለን ግርድፍ መረጃ መሰረት በግላጭ ከተገደሉት በተጨማሪ ሦስት ሚሊዮን ያህል አማራ ያርግ ወይ ይስረግ ሳይታወቅ ዳብዛው ጠፍቶ ቀርቷል:: ይህንን አማራ-ተኮር እልቂት ሲያቀነባብሩ ከነበሩት ወያኔወች ጎን በመሰለፍ የአማራ ወኪል ነኝ የሚለውን ብአዴንን ጨምሮ ሁሉም ክልሎች በአማሮች ላይ የተለያየ የግፍ አይነት ፈጽመዋል:: ዛሬ ላይ እኒህ የጥፋት ሰለባ የሆኑት መከረኞች እየደረሰባቸው ያለው የዘር ማጽዳት ዘመቻ እንዲገታ ተቃውሟቸውን በማሰማት ላይ ናቸው:: ከእኛ የሚጠበቀው የእነዚህ ወገኖቻችንን ስሜት ተጋርተን ጩኸታቸውን አብረን እየጮህን በደላቸው እንዲሰማ የድርሻችንን ማበርከት እንጅ በጥቃት ስሜት እየተንተከተከ ያለውን የሕዝብ እንቅስቃሴ የሚያጠፋ ቀዝቃዛ ውሀ መቸለስ አይደለም::

 

ኢትዮጵያን ከወያኔ የጭቆና አገዛዝ ነጻ ለማድረግ የሚደረገው ግብግብ በአማሮች ላይ ብቻ የተጣለ ሸክም እንዲሆን የማይፈቅዱ አማሮች መኖራቸውን አምነን መቀበል ከስህተት ያድነናል:: ስለዚህ መተያየት እንዳይፈጠርና ወደኋላ ማለትን እንዳያስከትል በሚተላለፉት መልእክቶች ላይ ጥንቃቄ ሊደረግ ተገቢ ነው:: የሚሻለው: እንቅስቃሴ በማይታይባቸው አካባቢወች የጸረ-ወያኔው የአመጽ እንቅስቃሴ እንዲጀመር አመቻችቶ ሀገራዊ ገጽታ እንዲላበስ የተቀናጀ ትግል ለማድረግ መጣር ነው::

 

እንደሚገመተው ከሆነ ዛሬ ላይ የሕዝባቸው ሰቆቃ ያንገፈገፋቸው  በብአዴን ውስጥ ያሉ የአማራ ልጆች ከወገናቸው ጋር መስዋእትነትን ለመቀበል ወስነው በጽናት እንደቆሙ ነው:: እኒያ የወያኔን የጥፋት አላማ በአማራ ላይ ሲፈጽሙና ሲያስፈጽሙ የነበሩት የቀድሞ የብአዴን አመራሮች ከታች እየተሳቡ በወጡ እውነተኛ የአማራ ልጆች የተተኩ መሆኑን የሚያሳይ የተግባር እንቅስቃሴ እንዳለ ለመገንዘብ አያዳግትም::

 

በአማራ ላይ የሚፈጸመው ሰቆቃ ያብቃ ብላችሁ የሕዝባችሁን የትግል እንቅስቃሴ ደግፋችሁ እየታገላችሁ ያላችሁ እናንተ የአማራ ልጆች ብርቱ ጥንቃቄ ልታደርጉ ይገባል:: ወያኔወች በክፋትና በተንኮል የተራቀቁ ናቸው:: ሌት ከቀን የሚያስቡት ጠላት ነው ብለው የፈረጁትን አማራ ከማጥፋት ጎን ለጎን የሕዝቡን አንድነት ሸርሽረው የተቃውሞውን እንቅስቃሴ ማርገብና ለማይጠረቃ የንዋይ ፍላጎታቸው ለብዝበዛ የተመቸ ሜዳ መፍጠር ነው:: የሚደክሙት ለዳር ድንበር መከበርና ለሀገር ብልጽግና: ለህዝብ ሰላም: ፍቅርና አንድነት አይደለም:: እነርሱን የሚያሳስባቸው  ከፈረሹበት የእርዝቅ መንበር ላይ የሚቀመጥ የልጅ ልጅ ተክተው ትግራይ-መር ኢትዮጵያን ለማስቀጠል ምን እናድርግ የሚለው ጥያቄ ብቻ ነው::

 

ይህን እነርሱ በጎ የሚሉትን አላማቸውን ለማደናቀፍ የሚነሳን ማንኛውም አካል ከማጥፋት ወደኋላ አይሉም:: ቂመኞች በመሆናቸው ይቅርታን አያውቁም:: ሽንፈትን አምኖ እንደ እንግዳ ዶሮ አንገትን ቀብሮ ከነርሱ ስር ማደር ከመጠቃት አያድንም:: በህይወት ላሉ አማራወች ይቅርና ለሞቱ አባቶቻችን ያልተኙ መርዘኞች መሆናቸውን ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት አያስፈልግም:: የሚሻለው “ከውርደት ሕይወት-የኩራት ሞት!” ይመረጣል ብሎ ከህዝብ ጎን ተሰልፎ እስከመጨረሻው ድረስ እየተፋለሙ ጥሎ መውደቅ ነው:: ነካክቶ ማፈግፈግ የረባ ነገር ሳይሰሩ ቀስ በቀስ ከምድረገጽ መጥፋትን ያስከትላል:: የሚያሸንፉን አንድ ሆነው በአንድ ልብ ስለተሰለፉ እንጅ በምናቸውም ከእኛ ስለሚበልጡ አይደለም:: ልብ አድርጉ! ይህንን የተነቃቃ የህዝብ ትግል እንዲበርድ አድርጎ ማፈግፈጉ ጉዳቱ ቀላል አይሆንም:: በቅንጅት አመራሮች የተሳሳተ አካሄድ የሕዝባችን የትግል መንፈስ የተቀዛቀዘበት ሁኔታ ተከስቶ እንደነበር ማንም አይስተውም:: አሁን ገንፍሎ እየወጣ ያለውን የሕዝብ አመጽ በአግባቡ ካልተጠቀምንበት ጭራሹኑ የተሰበረ መንፈስ ፈጥሮ ዳግም ይህን እድል የማናገኝበት ሁኔታ ሊያስከትል ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው::

 

ትግሉን ለማቀላጠፍ ዝግጁ ሆኖ መጠበቅ ኋላ ላይ ከመደናበር ያድናል:: ለዚያም ነው እስከቀበሌ ድረስ ወርዶ ሕዝብን የማንቃት: የማደራጀትና የማስታጠቅ ስራ ለይደር የሚተው የማይሆነው::  ስለሀገር አንድነትና ስለሕዝብ ነጻነት የሚጨነቁ ግለሰቦችና ፓርቲወች ድጋፋቸውን እንዲያበረክቱ ለማስቻል በራችሁን ብትከፍቱ የተሻለ ነገር አቅዶ ለመተግበር ይጠቅማል:: እናንተ ለማስተባበር ከቆረጣችሁ ጥሎ ለመውደቅ ፈክሮ የሚነሳው አማራ ድፍን ኢትዮጵያን እንደጉድ ማጥለቅለቁ የማይቀር ነው:: ይህን ለማድረግ ስትነሱ በቅድሚያ ከመሀላችሁ ተሰግስገው ለወያኔ አይንና ጆሮ ሆነው እየሰሩ ያሉትን ባንዳወች በማጽዳት መሆን አለበት::

 

አማራ ሲፈጥረው በሞራል የተገነባ ሕዝብ ነው:: ከሌላ አካባቢ መጥተው ተመሳስለው ለሚኖሩ ሰዎች ያለው ፍቅርና ክብር የተለየ ነው:: በሆነ ምክንያት ከሌላ አካባቢ ከመጡት ሰዎች ጋር የተጋጨ ያገር ሰው ቢኖር ይወቀሳል:: “የሰው አገር ሰው እንዴት ለማስቀየም ደፈርህ? ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ እኛን አምኖ እኛኑ ዘመድ አድርጎ ተጠግቶ የሚኖርን ሰው ማስቀየም ደግ ነው?” ተብሎ ውግዘት ይደርስበታል:: በዚህም የተነሳ በአማራ ክልል የሚኖሩ የሌሎች ክልሎች ኗሪወችም ሆኑ የውጭ ሀገር ሰዎች ከአካባቢው ተወላጅ በተሻለ ሁኔታ ያለሀሳብ ተከብረው በሰላም ይኖራሉ:: ይሁንና “ያልበደለ ሰው ለምን ይቀጣል!” የሚሉ ተቆጭ ሽማግሌወች በሌሉባቸው አካባቢ የሚኖሩ ዘረኞች ከሌላ አካባቢ የመጡ ናቸው በሚሏቸው ምንም ጥፋት በሌላቸው ሰላማዊ አማራወች ላይ አማራ በመሆናቸው ብቻ ሀብታቸውን ይዘርፏቸዋል: ያፈናቅሏቸዋል: አስረው ያሰቃይዋቸዋል: ይገድሏቸዋል:: ይህን ከሞራልና ከሐይማኖታዊ ባህሪይ ያፈነገጠ ወንጀል ሲሰሩ ጠያቂ ሕግ: ወቃሽ ህሊናም ሆነ የሚፈሩት አምላክ የላቸውም:: እንዲህ ያለውን የሕዝብ ሰቆቃ ማስቆም የሚቻለው አንገትን ደፍቶ በመኖር ሳይሆን ግንባር ለግንባር ገጥሞ በመፋለም ነው::

 

አማራው ከአማራ ክልል ውጭ ሲኖር በየትኛውም ደረጃ በፖለቲካ አመራርነት መሰየም ቀርቶ የግልም ሆነ የሲቭል ስራውን በሰላም ሰርቶ መኖር አልፈቀድለት ብሎ ፍዳ ሲያይ ኖሯል:: በሌላ በኩል በአማራ ክልል የሚኖሩ የሌላ ክልል ተወላጆች በክልሉ የፖለቲካ ሀላፊነት ሳይቀር ከታች እስከላይ ድረስ ተሰግስገው ያለሀሳብ እየፈረዱ እያስፈረዱ ተቀምጠዋል:: በግል ስራ የሚተዳደሩትም ቢሆኑ ከኗሪው በላይ ሆነው ስለያንዳንዱ ግለሰብ መረጃ በማቀበል ሲያሳፍኑና ሲያስገድሉ እስካሁን ድረስ ዘልቀዋል:: በዚህ የተዛባ ተግባራቸው ለማፈር ያልታደሉት እኒህ ሰዎች ይባስ ብለው በአንድ ድምጽ “አህያ: ደደብ: የማይመጥኑ—” ናቸው ብለው የአማሮችን ተግባርና ባህሪ የማይገልጽ የስድብ ስም ሰጥተው አማሮችን በማንቋሸሽ እየጠሯቸው ነው:: ከአሁን በኋላ አማራው ግፍ ተሸክሞ አህያ የሚባልበት የትግሬ ወያኔወች የሀገር ሀብት እየዘረፉ ብልጥ የሚባሉበት ጊዜ ያበቃል:: ቢችሉ ከብልጥነት ወጥተው ብልህ ለመሆን ቢሞክሩ በዋናነት ለራሳቸው ይጠቅማቸዋል::

 

አማራ ማንንም በክፉ የሚያይ ሕዝብ አይደለም:: ሌላውም እንደራሱ የሚያስብ መስሎት ለረጅም ጊዜ ለመከራ ተጋልጦ ቆይቷል:: “ሞኝ የዕለቱን ብልህ ያመቱን” እንዲሉ አማሮች የዘላለም ህይወት ለመታደል ለህሊና የማይቆረቁር በፈጣሪ ዘንድ የተወደደ ተግባር በመፈጸም ታጋሽነታቸውን ሲያሳዩ የትግሬ ወያኔወች ግን የአፍታ ህይወት አጓጉቷቸው: ትዕቢት ልቦናቸውን ሰውሮት ከህዝብ ቀምተው ህዝብን እያዋረዱ ጥለውት የሚሄዱት ሀብት ያከማቻሉ:: ከእንግዲህ በኋላ ግን ሁኔታወች መስተካከል ይኖርባቸዋል:: ከቀን ቀን ይማራል የማይባልን አጥፊ ሰው አዝሎ እሹሩሩ ማለት ጉዳት እንጅ ጥቅም የለውም:: አማሮች አሁንም ቢሆን ባለጌወችን ፈርተው ሳይሆን አምላክን ስለሚያስቡ መሰረታዊ ባህሪያቸውን ቀይረው ማንንም ለማጥፋት ወይም ለመበቀል የሚነሱ አይሆንም:: ነገር ግን ከእንግዲህ በኋላ የትግሬ ወያኔወች ከመሀላቸው ዘና ብለው ተቀምጠው መረጃ እያቀበሉ ትግሉን እንዲያከሽፉ: ጭቆናን እንዲያስቀጥሉ  ሊፈቀድላቸው አይገባም:: ” የሰው ሞኝ የለውም ብልሀቱ ይለያያል እንጅ!” አይደል የሚባለው? እኛም እንዳቅማችን ብልሀት አናጣም:: ሰላማዊ ኗሪ መስለውም ሆነ በግላጭ የጦር መሳሪያ ታጥቀው የወያኔ የመረጃና የአፋኝ ኃይል ሆነው የሚሰሩ በክልሉ የሚኖሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ባስቸኳይ ክልሉን ለቀው እንዲወጡ ይደረግ:: ይህን የሕዝቡን ትግል ለማኮላሸት የተሰገሰገን የጥፋት ኃይል በጉያ ታቅፎ ይዞ ታግለን እናሸንፋለን ማለት ከየዋህነት የዘለለ ሞኝነት ነው:: ይህ የዘረኝነት ጉዳይ አይደለም: መተኪያ የሌለው የትግል ስትራቴጅ እንጅ::

 

አማሮች አሁንም ኢትዮጵያን ይወዳሉ:: አሁንም የህዝብን በሰላም አብሮ መኖር ይፈልጋሉ:: አይደለም በአንድ ሀገርና በአንድ ሰንደቅ አላማ ስር ክፉና ደጉን ተጋርተው አብረውት ለኖሩ ሕዝቦች ይቅርና ከሌላ ሀገር ለመጣ ሰላማዊ ሰውም ቢሆን ፍቅርና ክብር የሚሰጥ ትሁትና ፈሪሀ-እግዚአብሔር ያደረበት ሕዝብ ነው: አማራ:: ሰላም የሚነሱት ወያኔወች በያዙት መንገድ እስከቀጠሉ ድረስ ግን “ለሰላም ስትሉ ሁሉንም ነገር ተውት” ማለት “በወያኔ የሚደርስባችሁን ግፍ ችላችሁ አንገታችሁን ደፍታችሁ ተቀመጡ” ማለት ነው:: ከእንግዲህ በኋላ በሀገር ልጅነት ስም ነጻነታቸውን ተገፈው በባርነት ለመኖር አይፈቅዱም:: በዚህ ምክንያት የሚደፈርስ ሰላም ካለ መደፍረሱ የግድ ይሆናል:: ሰላም በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ የሚመጣ አይደለም::

 

ካድሬወቹን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እያቀረበ “ጥያቄ ካለ በሰላማዊ መንገድ መጠየቅ ሲቻል ለአመጽ መነሳሳት አግባብ አይደለም” የሚል የማጭበርበሪያ አስተያየት የሚያሰጠው ወያኔ ከስህተቱ ቢማር ይበጀዋል:: ለሕዝብ ጥያቄ ጆሮ ሰጥቶ የሕዝቡን ፍላጎት ተከትሎ የሚሰራ ቢሆን ኖሮ አሁን እየታየ ያለው አመጽና ውድመት ባልተከሰተም ነበር:: በየአካባቢው የሚደረጉት እንቅስቃሴወች በሙሉ የሕዝብን ጥያቄ አዳምጦ ትክክለኛ ምላሽ ለመስጠት ፍላጎት ባለመኖሩ የተፈጠሩ መሆኑን ማንም አይስተውም:: ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሕዝብን ጥያቄ ያቀረቡ የሕዝብ ወኪሎች በእብሪት ስለታፈኑ ነው ተቃውሞው የተቀሰቀሰው::

 

የትግራይ ሕዝብ “ጥሩውን ጥሩ: መጥፎውን መጥፎ” ማለት ማወቅ አለበት:: ከዚያም አልፎ ጥሩውን በመደገፍ መጥፎውን ደግሞ በማውገዝ ከሌሎች ሕዝቦች ጎን ተሰልፎ አጋርነቱን መግለጽና መስዋእትነት መክፈል ይኖርበታል:: ያ ሲሆን ነው መተሳሰብ አለ ማለት የሚቻለው::

 

ኢትዮጵያውያን ክፉውንና ደጉን ተጋርተን አብረን ኖረናል:: ዛሬም ያንኑ ልማዳችንን ሳንቀይር እንደወቅታዊ ሁኔታው ወይ አብረን እንስቃለን ወይም አብረን እናለቅሳለን:: አንዳችን እየሳቅን ሌላችን የምናለቅስበት አግባብ ግን ሊኖር አይችልም::

ትንሳኤ ለኢትዮጵያ!

አዲስ አበባዎች ይነቅላሉ –ዳዊት ዳባ

$
0
0
comment symbol icon

comment symbol icon

የሌሊሳ ተግባር  ጀግንነት ነው። ድረጊቱ ትግሉ ላይ ያስገኘው ጠቀሜታ እስካሁን ከተባለለትም የላቀ  ነው። ደስታዬንና ምስጋናዬን ለመገለፅ ቃላት የለኝም ።  የኢሳት የእስፖርት ጋዜጠኛ  ወንድማገኘው እንዲሁ ምስጋና ይገባሀል። ከአምት በፊት ያን ዝግጅትህን ሳዳምጥ እጅግ አድርጌ መውደድ ብቻ ሳይሆን  አንድ ቀን የወንድም ሌሊሳ አይነት  ጀግንነት እንደሚሆን ቀድሜ  አይቼበታለው። ሰውዝ አፍሪካ ላይ የአለም ዋንጫ ሲደረግ  መልካም አጋጣሚ ነበር። “እነሱም እኛም እስፖርቱን ለፖለቲካ {ለኛ ለትግል} ላንጠቀምበት  ተስማማን “ የሚለውን ስሰማ አንጀቴ ነበር የተቃጠለው። በዚህ አይነት አስከፊ ጭቆናና ዘግናኝ አድሎ ውስጥ እየኖረ “ወገኛ ህዝብ” ብዬ ሁሉ በሆዴ ተሳድባያለው። እስፖርትና ትግል  ስል መጎልጎል የጀመርኩት ያኔውኑ ነበር። በዚህ ጊዜ ነበር የጥቁር አሜሪካኖቹን ታሪክና ሌሎች ከእስፖርት ጋር የተገናኙ የትግል ታሪኮችን ያወኩት። ልፅፍበት እያሰብኩ ሳለው ዝግጅትህን አዳመጥኩ ድንቅ ሆኖ ስላገኘሁት በጭራሽ ልንበዛበዝበት አልፈለኩም። ሌሊሳ ያን ዝግጅት መስማት አለመስማቱን የማውቀው ነገር የለም። ጠቃሚ ሀሳብ እንዲሰማና ጉልበት እንዲኖረው ተደርጎ ሲለቀቅ ግን ጊዜ ይወስድ እንደው እንጂ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ብዙ እርቀት እንደሚጓዝ  አውቃለው። ኢትዬጵያዊያን  በዚህ አይነት ታላቅ መድረክ ላይ ባይሆንም ያደርጉት ጀማምረዋል። አሁንም  ፈተናን በማውጣት የአገዛዙን የማስተዳደር አቅም ማዳከምና የማሳጣት ትግል ተደርጓል። እዚህ ትግል ላይ ከፍ ብሎ የሞራል ጥያቄ ተነስቷል። በፈለገ አይነት የከፋ ጭቆናና እየተጨፈጨፈ ቢሆንም ዜጋው ሲታገል ሊተላለፍ ስለማይገባው መስመር ሁሉ ተስብከናል። የሰው ልጅ ለነፃነቱና እራሱን ከጥቃት ለመከላከል የሚያደርገው የትኛው ተግባሩ ነው ትክክል የማይሆነው? የሚለው ጥያቄ በአይምሮዬ እንደተመላለሰ እንደከነከነኝ  አለ።

አንድ ባለንጀራዬ ትግሉ አንቀሳቃሾች ውስጥ ቅርብ ነው ብሎ ባሰበው  ወንድም በኩል ይህን የውጪ ሜዲያዎች ዝምታ አስገድደን ልንሰብረው እንችላለን ሲል አዲስ ሀሳብ ለማስረፅ መክሮ ነበር። እኔ አለው አንድ አስር ሀያ ቆራጥ ታጋዬች ካሉ እናፈላልግና በቀጣይ ሰልፍ ስንወጣ ጋዝ ወይ ምላጭ ነገር ይዘን እንውጣ። በተገቢው  ካልተስተናገድንና እውነታችን እስካልተነገረ ሌላ መጉዳት አይሆንልንም እራሳችንን ግን እንጎዳለን ብለን አዋራ እናስነሳ ሲል። አክቲቪስቱ አፍጥጦ እንደ እብድ ሲያየው ቆይቶ ምን ይበል  ጥሩ ሀሳብ አለ እየተገረመ። ግን ተግባራዊ አልሆነም። እስከዛሬም ማሰብና መፈተግበር እንጂ የማይሰበር ነገር ግን የለም። ጀግናው ሌሊሳ  ሰባበረው።

አዲስ አበባ ላይ በቅርብ ታላቅ ህዘባዊ እንቢተኛነት ይካሄዳል። የጎንደርና የጎጃም ህዘብ ላይ ጦርነት አውጀው ፍጅት እየፈፀሙ ነው። ይህንን ዝም ብለን ልናየው የሚገባ አይደለም። ህዝባዊ አመፁ እንደሰደድ እሳት አገሩን  እያዳረሰና እየተጠጋ ቢሆንም ለጊዜው ለብቻቸው ተጠቂ የሆኑት በአገር አቀፍ ደረጃ ህዘባዊ እንቢተኛነቱን ማምጣት ስላልቻልን ነው። ከሳምንት በፊት አዲስ አባባ የነበረው ጥሪ ትክክለኛ እርምጃ ነበር። ይህ ሙከራ አገዛዙን ብዙ ሚሊዬን ብር እንዳስወጣው ሰማው። ታዲያ በየሳምንቱ እሁድ እሁድ አደባባይ እየወጣን ህዘባዊ እንቢተኛነት የምናደርግብት ቀን አድርገን ብንይዘው  ስንት ሳምንታት ይህን ያህል ብር እያወጣ ሊዘልቅ ነው?።  በነገራችን ላይ ያልተካሄደው አገሩን ወታደር በወታደር ስላደረጉ በጭራሽ አይደለም። እሱን ሌላ ቦታ ሰባብረውት እየወጡ እንዳለው በገፍ ወጥቶ መና ማስቀረት ይቻላል። እንዲሁም እንደ አዲስ አበባዊነቴ ስለዚህ ህዘብ እንቢተኛነቱን በተመለከተ የሚሰጡ ፖለቲካዊ ትንታኔዎች የበዙት የሚገዙኝ ሆነው አላገኘሗቸውም። ትግሉ ከኦሮሚያ ሊሻገር አልቻለም፤ እራሱኑ ህዝባዊ እንቢተኛነቱን በተመለከተም ሲሰጡ የነበሩ ትንታኔዎች ሁሉ ትክክለኛ እልዳልነበሩ እያየን ነው። ባለፈው ጥሪ ተቃውሞው ያለተደረገበትን ምክንያት  ብዙዎች በስሱ ስለሄዱበትና ስለማይፈይድ እዚህ አላነሳውም። ትምህርት ሊወሰድበት ግን ይገባል። ያም ሆኖ ጥሪው ጊዜን ቦታና ሁኔታዎችን በአግባቡ የሰላ  ነበር። መልክቶቹ ይዘታቸውና አቀራረባቸው ድንቅ ነበር። ላሁኑ ተደረገ አልተደረገ አይደለም ዋናው ነገር፡፤ መነጋገርያ መሆኑ በራሱ በቅርብ በቀጣይ ለታቀደው እጅጉኑ አጋዥ ነው።

ሰዎቻችን ዛሬም ግድያ መፍትሄ ነው ላይ ናቸው። ምንም አይነት የአንባገነን የሀይል ከህዘብ ሀይል አይበልጥም የሚባለው ዝም ብሎ መስሏቸዋል። ተመልከቱ ሌሊሳ ብቻውን ባፍጢም ነው አፈር ውስጥ የደፋቀው። ገና ገና ነው። ህዝብ  መምዘዝ የሚችለውን ልምጭ በጣም በጥቂቱ ነው የተጠቀመው። የአዲስ አበባ ህዘብ ወደ ስድስት ሚሊዬን የሚጠጋ ነው። እራሱ  አይደለም መኪና ቢያሰለፍ ፍፃሜ ይሆናል። ታክሲዎች ስራ ሲያቆሙ መኪናዎቻቸውን እቤት የማቆም ግዴታ የለባቸውም። እንደጎንደርና ጎጃም ህዘብ እቤቱ ቢቀመጥ  አለተፈለጋችሁምና ጎሽ  ውረዱን በአለም ዘንድ ይናኛል። ህዘብ ባንድ ጊዜ አንድን ነገር ማድረግ አይችልም ከሆነ ዛሬም ክርክሩ የኦሮሞን የጎጃምና የጎንደርን ህዝብ አይቶ መማር ለሚፈልግ ከበቂ በላይ ነው። ስድስት ሚሊዮን ህዘብ ስልክ አንስቶ ቢደውል ወታደሩን ሁሉ ይደርሳል። የዛኑ ቀን መሳርያ ያዞራል። ቀን ወስኖ ተቃዋሚዎች ቢሮ በመሄድ አባል ለመሆን ቢሰለፍ እረሱን የቻለ ታላቅ ሰልፍ ይሆናል። ላስር ደቂቃ በያለበት ቢቆም ቢጨፍር ቢስቅ ችግር ነው። ገንዘቡን መከልከልና ገንዘቡን በጁ ማድረግ ይችላል። እናንተም ልጆቻችሁም ንብረታችሁም የበዛው እዛው ነው ያለው። እራሱን ለመከላከል እነዚህን ገነሮች መያዣ ሊያደርጋቸው ይችላል። ከወሰነ ወሮ ሊቀማቸው የሚቺሉ ብዙ ወሳኝ የቀበሌ ቢሮዎች አጠገቡ አሉ፡፤ አንድ አይነት መልእክት የያዘ ወረቀት ቢለጥፍ አጥርና ስልክእንጨቱ ሁሉ በመልክት ያሸበረቅል። እየተመናመነ ባለ ሀይል ማፅዳቱ ብቻ ወራቶች ይፈልጋል። በዛ ላይ የሚለቅመው መሳርያ የያዘውን ካድሬ ነው።

አንድ ቀን ጠዋት ላይ ስትነሱ መንገዶች በሙሉ በከተሜው ህዘብ ተሞልቶ ሊገኝ ይችላል፤ አዲስ አባባ ለሚገኙ ቻይናዊያን በሙሉ ለቃችሁ ውጡ ብሉ ድብዳቤ ቢልክላቸውስ፣… ተዘርዝሮ አያልቅም።

አዲስ አበባ ላይ ለውጥን ፈላጊውም ሊያንቀሳቅስ የሚችለውም ህዘብ ቁጥር የበዛ ነው። የስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን በሚሊዬን አደባባዩችን ተቆጣጥረውት የነበረው ትናንትና ነው። ህዝቡ መታገል ሳይደክመው መሪነቱን በአደራ የተረከቡ መምራት ደክሟቸው ነው ትግሉ የቀዘቀዘው። ሶስት ቀላል የመብት ጥያቄዎቻቸው ውስጥ አንዳቸውም አልተመለሱም።  ሳይገባቸው ለመከራ የተዳረጉ ንፁሀን ዜጎች ሂወት ጉዳይ ለሁላችንም የእግር እሳት ነው። ይህ የህብረተሰብ ክፍል የተደረጃና፤ ዘመኑ ባፈራቸው መገናኛዎች የተጣመረ ነው።  ስራውን ያውቀዋል። የአዲስ አበባ ካድሬዎች ከሌሎች ክልሎች ላይ ካየነው ወግንታዊነት በላይ ከህዘብቸው ጎን ለመቆም ብዙ ተጨማሪ ምክንያቶችም አሏቸው። ትናንትና በመድረክ፤ በሰማያዊ፤ በአንድነት፤ በመኢአድ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የወጣው ህዘብ ሁሉ ዛሬ በተራው ትግሉን አንቀሳቃሽ ነው።  የማቀናጀት ድክምት ካልሆነ የሚጠብቃቸውን እያወቁ አዲስ አበባ ላይ በቆራጥነት የተሰለፉ የኦሮሞ ወጣቶች ብዙውን መሬት ላይ የሚያስፈልገውን ስራ ይሸፍኑታል። የጎንደር ህብረት የዚህን ያህል ካንቀሳቀሰ በውጪ ያሉ የካሳንቺስ፤ የጎላ፤ የሽሮ ሜዳ… ማህበሮች ምስር ወጥ በሄንከን እየበሉ መበተን ብቻ ሳይሆን እራሳቸወን ወደ ለውጥ አንቀሳቃሽንት ይቀይራሉ። እንደሚታወቀው አገዛዙ ሁሌም ቆረጣ ነው። በከተማዋ ያሉ ማህበራት በተመለከተ መሪዎቻቸው ላይ ነው የሰራው። የሚያሞዳምደውም ። ሊገባቸው ያልቻለው አስተማሪውም፤ ታክሲ ነጂውም፤ ጋዜጠኛውም፤ ጥቃቅኑም… ያው ተራ ህዘብ ነው። ተራ የከተማዋ በለቤት ነው። የነዚህ ማህበራት መሪዎች ወና ስራ የህዘብን ትግል ለማውገዝ መሆኑን አባላቱም ህዝብም የለመደው ነው። በዋናነት አየሩ በለውጥ ሽታ ከታወደ በሗላ ምርጥ ጓደኛሞች በሙሉ አንዳንድ ሴል ናችሁ። በመቶ ሺ ሰሎች አዲስ አባባ ውስጥ አሉ ማለት ነው። ለአዲስ አበባዊያን ከድጋሚ ጥሪ በፊት በንቃት ሁኔታዎችን መከታተል፤ መወያየት እራስን ማዘጋጀት ሲታትሩ መጠበቅ ነው።  ይተገበራል!!!።

ብሔራዊ ጭቆና ይብቃ።

ዳዊት ዳባ።

Monday, August 29, 2016

 

 

 

 

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live