Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

የት ናችሁ የትግራይ ልሂቃን? –ከአንተነህ መርዕድ

$
0
0

ነሃሴ 2016
13934987_153112055123291_7181282795788322844_nበስማችሁ የተደራጀው ዘረኛና ዘራፊ ቡድን የንፁህ ኢትዮጵያን ልጆች ደም እንደጎርፍ ሲያፈስስ ምነው ድምፃችሁ ጠፋ?

የኦጋዴኖች መጨፍጨፍና ሬሳቸው በሜዳ ላይ መጎተት፣ የጋምቤላዎች በጅምላ መታረድ፣ የኦሮሞዎችና የአማራዎች በጠራራ ፀሃይ በአነጣጥሮ ተኳሽ ትግርኛ ተናጋሪ አጋዚ በየሜዳው መደፋት እንዴት ህሊናችሁን አልኮሰኮሳችሁም?

በጣት የሚቆጠሩ  ዘራፊዎች ነገን አጨልመውባችሁ ሊሄዱ ሲዘጋጁ እንዴት አልታያችሁ አለ?

ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ህልውናውን እንዲያጣና የግፍ ፅዋ እንዲጨልጥ የተገደደው መላው ኢትዮጵያዊ፤ “ከዚህ በኋላ በቃኝ፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ነፃነቴን ማግኘት አለብኝ” ብሎ መንቀሳቀስ መጀመሩን ዓለም ሲመሰክር እንዴት አልከሰትላችሁ አለ?

እስከአሁኗ ደቂቃ የኢትዮጵያ ህዝብ እባካችሁ በፍቅርና በእኩልነት እንኑር እያለ የሚያሰማው ልመናና ጩኸት ላለማስማት ምን አገዳችሁ?

ይህ ዘራፊና ዘረኛ ቡድን በስልጣን ለመቆየት ከሁሉም በላይ በትግራይ ህዝብ ዘላቂ ህልውና ላይ እንደዘመተበትና የእሱን ሃጢያት እዳ ከፋይ ሆኖ እንዲኖር እንደፈረደበት አይታታችሁም?

ከሚሞት ጥቂት የአምባገነን ቡድን ጋር በማበራችሁና ዝምታን በመምረጣችሁ እንዴት የዋህና ድሃ የትግራይ ህዝብ ሲጎዳ አልታያችሁ አለ? ህወሃት የትግራይን ህዝብ ጥቅም በዘላቂው እንደጎዳ ለመናገር አንደበታችሁን ምን ዘጋው?

አዎ! ከሌላው ኢትዮጵያዊ በተለየ የሥራ መስክ ተከፍቶላችኋል። ሁሉንም የአገሪቱን ሃብት፣ መከላከያውን፣ ደህንነቱን ስልጣኑን ሙሉ በሙሉ በተቆጣጠረው ቡድን ተጠቃሚ ሆናችኋል። ለመማርና ሳትማሩም ለትልልቅ የጥቅም ቦታዎች ያለገደብ ተሳታፊ እንድትሆኑ ተመቻችቶላችኋል። ሌላው ሲገደል፣ ሲታሰር፣ ሲዘረፍና አገሩን ጥሎ ሲሰደድ ሁሉም በር በሞኖፖል ተከፍቶላችኋል። ነገር ግን ምስኪኑ በሚሊዮን የሚቆጠረው የትግራይ ህዝብ በድህነት እያለ ከኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ ጋር የሚኖረውን ዘላቂ ጥቅሙን በጊዜያዊ ድሎታችሁ ነግዳችሁበታል።

በአጋዚ አልሞ ተኳሽ ህፃናት ኢትዮጵያውን ሲደፉ፣ ህዝቡ ሃዘን ውስጥ ተቀምጦና ዓለም ያየውን ዘግናኝ ነገር ለማመን እስኪቸገር ሲያዝን ውስኪ እየተራጫችሁ ስትጨፍሩ በምትደልቁት አተሞ ስትደነቁሩ፣ ወይም እንዳላያችሁ ፀጥታን ስትመርጡ፤ እንኳንስ የትግራይን ህዝብ የራሳችሁንም ቀጣይ ጥቅም በሚያስዘነጋ የቅዠት ዓለም ውስጥ መሆናችሁ እየታየ ነው።

በህወሃት የቅዠት ዓለም ውስጥ ሳይሆን እውነተኛዋን ትግራይን ተመልከቱ፡

  • በብዙ ሺህ ኪሎሜትር ከሚዋሰነው፣ ለዘመናት አብሮት ከኖረው፣ ከተዋለደው ከተዛመደው ከወንድሙ ከኤርትራ ህዝብ አቆራርጠውታል።
  • ከላይ ከጎንደር፣ ወሎና አፋር ድረስ በዘረኝነት በተሞላው ስግብግብነትና ትዕቢት ከአማራው፣ ከአገው፣ ከአፋሩ ደም አቃብተውታል።
  • ከሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ንብረቱንና የልጆቹን ህይወት በመንጠቅ ለያይተውታል።
  • ጋምቤላዎችን በማጨፋጨፍና በመጨፍጨፍ፣ መሬቱን በመዝረፍና ለውጭ ባለሃብቶች በመሽጥ አስሰድደውታል።
  • ኦጋዴንን ህዝብ በጅምላ ገድለውታል፤ በርሃብ ዓለም እንዳይደርስለት ቀጥተውታል።
  • መሃል አዲስ አበባና ዳር ለዳር የሚኖረውን ድሃ ህዝብ አፈናቅለው ሜዳ ላይ በመጣል እነአቦይ ሰማይ ጠቀስ ፎቅ ገንብተውበታል።
  • በዓለም ዙርያ ያሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች የህወሃት የግል ቢሮና የአንድ ዘር ተጠቃሚነትን በግልፅ በማወጅ ቀሪውን ኢትዮጵያዊ አግልለውበታል።

ይህ ሁሉ ግፍና ያልተዘረዘረው ወንጀል ምን ያህል ጊዜ ይዘልቃል ብላችሁ ብታስቡ ነው ማዕበሉን ላለማየት አሸዋ ውስጥ እራሷን እንደቀበረችው ሰጎን በጊዜያው ጥቅም ውስጥ ራሳችሁን ደብቃችሁ በማስገምገም ላይ ያለው ህዝባዊ ማዕበል አልታያችሁ ያለው? ከሁሉም የተነጠለች ትግራይ ዕድሏ ከሱዳን ጋር ብቻ እንዲሆን ወሰናችሁ ማለት ነው? የሚቻል አይደለም።

ከሃያ ዓመት በፊት ጥቂት ትዕቢት በወጠራቸው የሻዕብያ ሰዎች ኢትዮጵያውያንን የመናቅ፣ በሃብት በንብረቷ አዛዥና ናዛዥ መሆናቸው እንዴት እንዳሳወራቸው ትምህርት የሚሆነን ይመስለኛል። የኤርትራ ኤምባሲ እንደማዕከላዊ ይፈራ ነበር።የራሱ እስር ቤትና ማሰቃያ ነበረውና። “አፍሪካዊት ሲንጋፖር” የምትሆነውን ኤርትራን ለመገንባት ያለሙት ግን በኢትዮጵያ ጥሬ ሃብትና ገበያ ላይ ነበር። ቅዠት እውነት አይደለምና ከእንቅልፋቸው ሲባንኑ ወንድሞቻችን ኤርትራውያንም እኛም አሁን ካለንበት እንገኛለን። የዘሩትን ማጨድ ይሏል ይህ ነው።

የመከላከያው ተቋም ተነቃቅሎ ትግራይ ተገንብቷል። ብዙ ትልልቅ ነገሮች ከመሃል አገር እየተነቀሉ ወደትግራይ የመሄዳቸው ጉዳይ “በጠላት” የሚነገር ፕሮፓጋንዳ ሳይሆን የአለፉት ሃያ ዓምስት ዓመታት እውነታ ሲሆን በትናንቱ ዜና ደግሞ የቴሌኮሙኒኬሽን የመረጃ ቋት (ዳታ ሲስተም) ከአዲስ አበባ ተነቅሎ መቀሌ መተከሉ ስንሰማ የህወሃትን የዕብደት መጠን ከመግለፅ ባሻገር እንግዳ ባህሪ አያደርገውም። አፍ የሚችለውን እጅ ይመጥናል ይባላልና ህወሃት ግን መዋጥ የሚችለውን አይደለም እያነሳ ያለው። ይልቅስ የስስታም መጨረሻው በጎረሰው ታንቆ መሞት ነውና እናየዋለን። ለመሆኑ ለይስሙላ የተቀመጡት የፌደራል ባለስልጣናት እነኃይለማርያም  ዋና ከተማቸውንም መቀሌ እስኪሆን ነው የሚጠብቁት?

እዚህ ላይ ህዝቡ በትዝብት የገጠማትን ላካፍላችሁ።

የሚጓጓዝ ቢሆን ሁሉም በመኪና

ትግራይ ውስጥ ነበሩ አባይና ጣና። ብለዋል።

ግድ የለም ፋብሪካውም ይሂድ፣ ሁሉንም የቻሉትን ይውሰዱ። በቅዠት ዓለም ውስጥ የሚያልሟት ትግራይ አየር ላይ ነው የምትገነባው? ጥሬ እቃው፣ የሃይል አቅርቦቱ፣ ገበያው ከየት ነው? በስልጣን ጥም የተመረዙ ህወሃቶች ይህ ሁሉ እንደማይሳካ ቢያውቁትም የትግራይን ህዝብ እንደሰባዊ ጋሻ መያዣነት ለመጠቀም ነው። ለእውነተኛ የትግራይ ዘላቂ ልማት ቢያስቡት ከኢትዮጵያ ህዝብ ተለይቶ ከቶም የትግራይ ህዝብ ሊያድግ አይችልም። ከገፉበትና ድጋፍ ካገኙ ለታሪክ የሚተው ፀፀት የሚያስይዝ ህንፃ ብቻ ሆኖ ነው የሚቀረው። ለመሆኑ የትግራይ ልሂቃን ይህ እንዴት ይጠፋችኋል? ብቸኛ ተጠቃሚነታችሁ ምን ያህል ይዘልቃል ብላችሁ ታስባላችሁ? ለአፈራችሁት ሃብትና ቤተሰብ ዋስትና የሚሰጣችሁ የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ የሚሞት ስርዓት አይደለም።

የስብሃት ነጋ፣ የአባይ ወልዱ፣ የስዩም መስፍን፣ የአባይ ፀሃዬ፣ የአዜብ መስፍን፣ የብርሃነ ገብረክርስቶስ፣ የቴዎድሮስ አድሃኖም፣ ምን አለፋችሁ የትልልቆቹ ህወሃት ባለስልጣናት በቢልዮን የሚቆጠር የዘረፉት ንብረትና ቤተሰባቸው ውጭ ነው ያለው? ለምን ትግራይ ውስጥ ያንን ሃብት አላፈሰሱትም? እንደመንግስቱ ኃይለማርያም የዘረፋና የወንጀሉ ተባባሪ ጓዶቻቸውን ጥለው እብስ ለማለት ዝግጁ ናቸው። ውሃ ሃጅ ደንጋይ ቀሪ እንደሚባለው የስርዓቱ ተባባሪ ሆናችሁ ያስገደላችሁና ያስዘረፋችሁ እንደነለገሰ አስፋው ጎርፉን መጠበቅ ሊኖርባችሁ ነው። የዚች አገር ታሪክ እንደሆነ ራሱን የሚደጋግም ነው። ህወሃቶች ለአፈሰሱት የንፁሃን ደም፣ ለዘረፉት ንብረት፣ ለአደረሱት ሰቆቃ እዳ ከፋዩ እዚያው ይቀራል። የትግራይ ልሂቃንና የትግራይ ህዝብ በፍጥነት ከቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ካልቆመ የሚመጣውን ጉዳት ማሰቡ ያስፈራል።

ኦሮሞው፣ አማራው፣ ሶማሌው፣ ደቡቡ፣ ጋምቤላው፣ መሃል አዲስ አበባ፣ በአጠቃላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለዘረኛውና ዘራፊው ህወሃት ላለመገዛት መቁረጡና መንቀሳቀሱ ካልተሰማችሁ መልካም እንቅልፍ። የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ የከፋ ምንም አይደርስብኝም ብሎ ተነስቷል። ኳሷ እጃችሁ ላይ ናት። ውጤቱም እንደምርጫችሁ ይወሰናል። ፈጥናችሁ የትግራይንና የኢትዮጵያ ህዝብ ካንጃበበት መከራ ለመታደግ የትግሉ አካል ሁኑ። ህዝቡ እያለቀሰና እየጮኸ በዝምታችሁ ከቀጠላችሁ እናንተ ስታለቅሱ ሌላው በዝምታ የሚታዘባችሁ ቀን ተቃርቧል። ልቦና ይስጣችሁ።

ኢትዮጵያን የቁርጥ ቀን ልጆቿ ይታደጓታል!

መከራው በትግላችን ያበቃል!

 

 


ህወሓት/ኢህአዴግ ከስልጣን ይውረድ! የሽግግር መንግስት ይቋቋም [ከትግራይ ተወላጆች የተሰጠ መግለጫ]

$
0
0

8 ነሓሴ 2008

tplf-rotten-apple-1.jpgበአጠቃላይ ለ25 ዓመታት ሙሉ ህዝባችንን አፍኖ ሲገዛ የቆየና፣ ለ40 ዓመታት ሰላማዊ ዜጎችን እየረሸኑ አገራችንን እየዘረፉ የቆዩ ባለስልጣኖች ያሉበት ህወሓት/አህአዴግ በተለይ በዚህ ዓመት በኦሮሞና በአማራ ህዝባችን ላይ ጦርነት ከፍቷል። የአገዛዙን የግድያ ወንጀሎች እናወግዛለን፤ የህዝቡን ተቃውሞ እንደግፋለን።

ስለዚህ በአገራችን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲገነባ፣ የህዝባችን አንድነት እንዲጠናከርና የአገራችን ሉኣላዊነት እንዲከበር᎓

[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

የህብር ሬዲዮ  ነሐሴ 8 ቀን 2008 ፕሮግራም

$
0
0

habtamu05 < …እነሱ እሳትና ጭድ የሚሉት ለዓመታት እርስ በእርሱ አደባድበው ስልጣናቸው ላይ ለመቆየት የወጠኑት ሴራ ከሽፎ ዛሬ ጎንደር ላይ ባህር ዳር ላይና ደብረ ማርቆስ ላይ በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የሚፈጸመውን ግፍ እንቃወማለን ብሎ የአማራ ሕዝብ መነሳቱ በኦሮሚያም በተደረገው ተቃውሞ ላይ አማራ ወገናችን ነው ማለቱ እንቅልፍ ነስቷቸዋል ።የተባበረ ትግላችን ይቀጥላል …> አቶ ሌንጮ ባቲ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ከፍተኛ አመራር ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጋር ድርጅታቸው ስላደረገው አብሮ የመታገል ስምምነት ተጠይቀው ከሰጡት ምላሽ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

<…ይሄ ለውጥ ለሁሉም የሚመጣ በዚያች አገር ላይ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲገነባ የምናደርገው ትግል ነው… የኦሮሞና የአማራ ሕዝብ መተባበር ስርዓቱን እንቅልፍ መንሳቱን እያየን ነው። ትብብሩና የጋራ ትግሉ ለሁሉም ነጻነት የሚያመጣ ነው…>  አቶ ነአምን ዘለቀ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ከፍተና አመራር ከኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ጋር ድርጅታቸው ስላደረገው ስምምነት ከአቶ ሌንጮ ባቲ ጋር በጋራ ከሰጡት መግለጫ የተወሰደ(ቀሪውን ያዳምጡት)

<…ተቃዋሚዎች አሁን አጣዳፊ የሆኑትን እና ወደፊት ሊነሱ የሚገባቸውን ጉዳዮች በመለየት በጋራ መምከር መነጋገር አለባቸው…>  አክቲቪስት ገረሱ ቱፋ  በወቅታዊው ሁኔታ ላይ ለህብር ሬዲዮ ከአክቲቪስት መስፍን አማን ጋር ከሰጠው ቃለ መጠይቅ(ክፍል አንድ)

<…ተቃዋሚዎች በጋራ መነጋገር መጀመር አለባቸው። የተናጠል የድርድር ጥያቄ ራሳቸውን ለማዳከምና ስርዓቱ ዕድሜ እንዲገዛ የሚያደርግ በመሆኑ አማራጩ የሕዝቡን የለውጥ ጥያቄ የሚፈታ ሁሉን አቀፍ ድርድር ማድረግ እንዲደረግ መግፋት አለባቸው ሌላው ግን መረሳት የሌለበት…> አክቲቪስት መስፍን አማን በወቅታዊ ጉዳይ በጋራ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ቀሪውን ተከታተሉት)

<…ሕዝቡ እዛ አገር ላይ እየተባበረ ነው እኛ እዚህ በውጭ አገር ሕዝቡን መከተል አለብን።  ኦሮሞና አማራ በጋራ መቆም አለብን። የሚደረገው ትግል የትኛውንም ብሄር የሚያገል አይደለም። ኦሮሞ አያገልም…> አቶ ንጉሴ ርቂቱ በቬጋስ የኦሮሞ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር በከተማው የሕወሃሀት ደጋፊዎች የጠሩት ስብሰባን ለመቃወም በወጡበት ወቅት ከሰጠን ማብራሪያ (ቀሪውን ያድምጡት)

<…በቬጋስ የምንገኝም ተቃዋሚዎች በጋራ ተባብረን ይሄ ስርዓት የሚፈጽመውን ግፍ መቃወምና ተባብረን መቆማችንን ማሳየት ጭምር አለብን …> አቶ እንዳልካቸው ካሳሁን በቬጋስ የጎንደር ሕብረት የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ኦገስት 24/2016 በቬጋስ ስለተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ከሰጠን ማብራሪያ(ቀሪውን ይከታተሉ)

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በብራዚሉ/ሪዮ ዲጄኔሮ ኦሎምፒክ ላይ  ሰሞኑን ያሰመዘዘገቡት አሰገራሚ እና አሳፋሪ ገጠመኞች በአለማቀፋዊ የዜና  አውታሮች እይታ (ልዩ ጥንቅር) ሌሌችም

ዜናዎቻችን

ኮ/ል ዘውዱን የሕዝብ አደራ አለብን ለሕወሓት  አሳልፈን አንሰጥም ያሉ በጎንደር የብአዴን አመራሮች ከስልጣን ተነሱ

አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር የሕዝቡን የለውጥ ፍላጎት ተግባራዊ የማያደርግ  የተናጠል ድርድር እንዳማይቀበሉ ገለጹ

የሕወሓት/ ኢህ አዲግ አገዛዝ 2 የአሜሪካ ዘጋቢዎችን  ጨምሮ ሶስት የውጪ ሚዲያ  ጋዜጠኞችን ሰሞኑን አሰረ

ዶ/ር አረጋዊ በርሄ፣ጋዜጠኛ አብርሃ በላይን ጨምሮ የትግራይ ብሄር ተወላጅ ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች የሕወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ወርዶ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ጠየቁ

ምዕራባዊያኖች  ዜጎቹን በመግደል እና በማሸበር ላይ ለሚገኘው የሕወሓት/ኢህአዲግ  መንግስት  ጭካኔ ጆሮ ዳባ ልበስ በማለታቸው  ተብጠለጠሉ

በእስራኤል ውስጥ አንድ ኢትዮጵያኖችን የሚያገል ዘረኛ ማስታወቂያ ታላቅ ቁጣ ቀሰቀሰ

የአሜሪካው እጩ ፕ/ት ዶናል ትራምፕ “ፕ/ት ባራክ ኦባማ አሸባሪው አይሲስን ፈጥረዋል”በማለታቸው ብርቱ ትችት  ገጠማቸው

ስዊዘርላንድ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ድንበሯን አልፈው አንዳይሻገሩ አገደች

አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያን ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በሚል ብቻ ሕወሓት ኢህአዴግ በሕዝቡ ላይ የሚፈጽመውን ግፍ እያዩ እንዳላዩ መሆኑን እንዲያቆሙ ተጠየቀ

በሕቡ ስታገል ቆይቻለሁ ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሄራዊ ፓርቲ ተቃዋሚዎች በጋራ እንዲተባበሩ ጥሪ አቀርባለሁ አለ

ሰሞኑን  በልብ ህመም ሞቱ የተባሉት የቀድሞው የደ/አፍሪካ ፕ/ት ታቦ ኢምቤኬ አ/አ ውስጥ በሽምግልና ላይ መሆናቸው ተገለጸ  ሌሎችም  

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብርሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድበአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነውበእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነምበዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ፡ (ሀብታሙ ይግዛው)

$
0
0

Unity-1-741x437አስተዋይነት እና ታጋሽነት እንደ ፍራቻ በተቆጠረበት በዚህ ዘመን፣የተበደሉ ህዝቦች ይህን አመለካከት በመስበር መንገዶችን እና አገዛዙን ሲያስጨንቁ ሰንብተዋል።

እንደሚታወቀው በአማራ እና በኦሮምያ ክልሎች ውስጥ እልህ አስጨራሽ የተቃውሞ ሰልፎች ሲደረጉ ቆይተዋል። አሁንም ህዝባዊ እምቢተኝነቱ እና የተለያዩ ሰላማዊ የትግል ስልቶች በመተግበር ላይ ናቸው። በአንጻሩ የአገዛዙ ታማኝ አሽከሮች በቀጥታ አልሞ በመተኮስ ሰላማዊ ሰልፈኞችን መግደላቸውን እንደ መፍትሄ ወስድውታል።

በዚህ ወቅት አገዛዙ ሰላማዊ የሆነን ህዝብ በመግደል፤ በማሰር፤ እንዲሁም በመግረፍ ይህ ነው የማይባል በደል እያደረሰበት ይገኛል። ይህ ጸረ ህዝብ የሆነ አገዛዝ የሽብር ወንጀሉ በመላው የሀገሪቱ ህዝብ እና በአለምአቀፉ ህብረተሰብ ዘንድ በጉልህ የተጋለጠበት አረመኔ ቡድን ነው።

የህዝብ ንብረት የሆነው የመከላከያ ሰራዊት እና የፖሊስ ሀይል ከተግባራቸው ተቆጠበው ትግሉን እንዲቀላቀሉ የሚደረገው ጥረት እንዳለ ሆኖ የበርካታ ንጽሃን ደም የፈሰሰለትን ይህ ህዝባዊ መነቃቃት ከታሰበበት ዓላማ እንዲደርስ የሁላችንም ርብርብ ከመቼው በላይ አስፈላጊ የሆነበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።

ከአሁን በፊት የተደርጉት ሰላምዊ ሰልፎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የተሳኩ ቢሆኑም ስኬቱ የተጠየቀው ዋጋ  በጣም ከፍተኛ ነበር። በተለዩ የሀገሪቱ ቦታዎች የደረሰው የህይወት መጥፋት እና የአካል ጉዳት  ቀላል የሚባል አይደለም። በዚህ ረገድ የአንድም ኢትዮጵያዊ ነፍስ ቢሆን እንኳን ከባድ መሰዋትነት የሚባል ነው።

የህዝባዊ እምቢተኝነቱ ሰለባዎችን ቁጥር ለመቀነስ በቀጣይ ከአለፉት ተሞክሮዎቻችን ተምረን ለተመሳሳይ ውጤት የተሻለ መንገድን መፈለግ ግድ ብሏል። ይህ መሰረት በማድረግ ከእንግዲህ ወዲያ የሚደረጉ ማናቸውም የተቃውሞ ተግዳሮቶችን #በአንድላይ እና #በተመሳሳይ ሰዓት በተቀናጀ ሁኔታ ሊከናወኑ ይገባቸዋል።
ይህም የሆነበት ዋናው ምክኒያት አገዛዙ በተለያዩ ቦታዎች በተመሳሳይ ሰዓት የሚደረጉ የህዝብ እንቅስቃሴዎችን ለመከላከል የሚችልበት አቅም የሌለው በመሆኑ ነው። ይህ ማለት ገዥው ቡድን የትኛውንም ጦር ቢያንጋጋ ጠቅላላ ህዝብን በተመሳሳይ ሰዓት ማፈን አይቻለውም።

ስለዚህም የሰልፍ አዘጋጆች ፣የጎበዝ አለቆች፣ የውስጥ እና የውጭ አርበኞች፤ የፌስቡክ ታጋዮች፣ጦማሪዎች፣ ማህበራዊ ገጾች ፣መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም እያንዳንዳችን ይህ መልዕክት ለህዝባችን እንዲደርስ የበኩላችን ድርሻ እንድንወጣ ፤ ለተግባራዊነቱም በሙሉ አቅማችን እንድንቀሳቀስ ስል በታላቁ የኢትዮጵያ ህዝብ ስም ጥሪየን አቀርባለሁ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
ሞት ለወያኔ!
ኢትዮጵያትቅደም

የኢትዮጵያ ትንሣኤ እንዴት? ከሸግግር መንግሰት እሰከ ጠብመንጃ አፈሙዝ!!!! –ግርማ ሠይፉ ማሩ

$
0
0

 

girmaseifu32@yahoo.com, www.girmaseifu.blogspot.com

Woyane

ኢትዮጵያችን ከሰሞኑ ድርስ የዲሞክራሲ እርጉዝ የሆነች ይመስላል፡፡ በሰላማዊ መንገድ ለውጥ ለምንፈልግ ሰዎች መንግሰት የፖለቲካ ማሻሻያ በማድረግ ሁላችንም አሸናፊ ሆነን የምንወጣበት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እናገኝ ይሆን ብለን እየጠበቅን ነው፡፡ የለም ገዢው ፓርቲ አብቅቶለታል በውስጥም በስብሷል ከውጭም ጫናው በርትቷል ፈንግለን እንጥለዋለን የሚሉም አሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ አንድ ዓይነት ውጥረት ተፈጠረ በተባለ ቁጥር “የሸግግር መንግሰት” አቀንቃኞች ናቸው፡፡ እነዚህን ሶስት የዲሞክራሲ ፅንስ ማዋለጃ መንገዶችን በአጭር በአጭሩ ለማየት እሞክራለሁ፡፡ የግሌን አቋም የያዝኩበትን መስመር ትንሸ ሰፋ አድረጌ እምለከታለሁ፡፡

የሸግግር መንግሰት ማቋቋም

ይህን ሃሳብ የሚያቀነቅኑ ግለሰቦችም ሆኑ ቡድኖች ይህ ሃሳብ ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው መቼ እንደሆነ የተረዱት አይመስለኝም፡፡ የዚህ ሃሳብ ተግባራዊ መሆን የሚችለው በኢህአዴግ መቃብር ላይ ብቻ ነው ብዬ ባልፍ በቂ ነበር፡፡ የኢህአዴግ መቃብር ደግሞ ከዚህ ቀጥሎ በምንመለከተው ሁኔታ የሚሆን ሰለሚሆን “የሽግግር መንግሸት” ለብቻው የሚቆም አማራጭ አይደለም፡፡ ገዢው ፓርቲ የሸግግር መንግስት ለሚባል አካል ስልጣኑን አስረክቦ ቢለቅ እኔም የምታዘበው ይመስለኛል፡፡ ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ወግ ቢደርሳቸው የዚህን ያህል የተዓማኒነት ችግር ያለበት መንግሰት እየመራሁ ነው ከሚሉ፣ ፓርላማውም ወግ ደርሶች ጫና ቢያሳድር፣ “ፓርላማው”ን በትኖ አዲስ ምርጫ በህገ መንግሰቱ አንቀፅ 60 መሰረት እንዲከናወን ማድረግ ይችል ነበር፡፡ ለዚህ አልታደልም፡፡ ከዚህ የተለየ ህጋዊ ስርዓት “የሸግግር መንግሰት” ለመመስረት የሚስችል መንገድ የለም፡፡

በጣም ግልፅ ለመሆን ከዚህም ከዚያ በሚውጣጣ የቡድን እና ግለሰቦች ስብስብ “የሸግግር መንግስት” ይመስረት የሚሉ ሰዎች ያላቸውን የቡድን ውክልና ወይም ደግሞ ግለሰባዊ እውቅና መሰረት አድርገው ስልጣን በአቋራጭ የሚፈልጉ ናቸው፡፡ እመኑኝ እነዚህ ሰዎች በዚህ መስመር ሰልጣን ቢያገኙ ያገኙትን ስልጣን በቀጣይ በሚደረግ ምርጫ ስልጣናቸውን ቢያጡ አሜን ብለው የሚቀበሉ አይሆኑም፡፡ ሰለዚህ በእኔ እምነት “የሸግግር መንግስት ይቋቋም” በሚለው አልስማማ፡፡

ኢህአዴግ በስብሷል የስርዓት ለውጥ መደረግ አለበት

በዚህ ጉዳይ ኢህአዴጎች ባይስማሙ ብዙ ወገን ሊስማማ ይችላል፡፡ ይህን ስርዓት በስብሰሃልና ዞርበል እያልን ከሆነ በጉልበትና በጉልበት ብቻ የሚሆን ነው፡፡ ይህ ጉልበት ደግሞ አንድም በታጠቁ ኃይሎች፣ ወይም ደግሞ ህዝባዊ አመፅን ተከትሎ በሚመጣ የሰርዓት መፍረስ የሚገኝ ውጤት ነው፡፡ መንግሰት አሁን በያዘው ሁኔታ እሳቱን እያዳፈነ፣ የተዳፈነውን እሳት ግን ጭድ ስር እየደበቀ የሚቀጥል ከሆነ አይቀሬው ህዝባዊ ማዕበል እሳት ሆኖ ይበላዋል፡፡ ይህ እሳት ኢህአዴግን ብቻ ሳይሆን እኛም ከእሳቱ ብንተርፍ ወላፈኑ እይለቀንም፡፡ ይህ በሰላማዊ ሽግግር ሊታለፍ ካልቻለ ቀላል የማይባል ቀውስ በሀገራችን እንደሚያስከትል ግልፅ ነው፡፡ ይህ አማራጭ በትጥቅ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች እና ምንአልባት ህዝባዊ አመፅን በመምራት ላይ ያሉ ቡድኖች/ግለሰቦች በሚያደርጉት ስምምነት ቀጣይ የሀገሪቱ እጣ ፈንታ እንዴት ይሁን ብለው ሊነጋገሩ ይችላሉ፡፡ ኢህአዴግ-ሻቢያ- ኦነግ በለንደን እንዳደረጉት ማለት ነው፡፡ ከመንግሰት ጋር ይህ ውይይት ሊደረግ አይችልም፡፡ ሰለዚህ በዚህ አማራጭ ላይ ብዙ ማለት የሚቻል አይመሰለኝም፣ የአሸናፊዎች ፍትህ መስጫ ነው የሚሆነው፡፡ ምን አልባት በዚህ ወቅት እነዚህ አሸናፊ ኃይሎች የሚያቋቁሙት “የሸግግር መንግስት” አንደኛው ትክክለኛው አማራጭ የሚሆን ሲሆን እንደከዚህ ቀደሙ የኢህአዴግ የሽግግር መንግሰት መጪው የሸግግር መንግሰትም አግላይ ላለመሆኑ ምንም ዋስትና ሊኖረን አይችለም፡፡

ባጭሩ በሀይል የስርዓት ለውጥ ይደረግ ሲባል ኢህአዴግ ምንም ታሪክ እንደማይተርፈው መረዳት ያለበት ይሆናል፡፡ በሰፈረው ቁና መሰፈሩ ላይቀር የሚችልበት እድል ሰፊ ነው፡፡ ኢህአዴግ እና ኢህአዴጋዊያን ይህ ክፉ ቀን እንዳይመጣ ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን የፖለቲካ ማሻሻያ በማድረግ ሀገሪቱን ህዝብንም ሆነ እራሳቸውን እንዲጠብቁ መምከር እፈልጋለሁ፡፡

የፖለቲካ ማሻሻያ ማድረግ

አሁን ባለንበት ወቅት በሁሉም ወገን ተቀባይነት ማግኘት ያለበት ሃሣብ ነው ብዬ የማምነው፡፡ አሁን የደረስንበትን ቀውስ ሳናባብስ ነገር ግን ስር ነቀል የፖለቲካ ማሻሻያ በማድረግ ወደምንፈልገው ዲሞክራሲያው ስርዓት ልንሸጋገር እንችላለን የሚል እምነት አለኝ፡፡ ይህ የፖለቲካ ማሻሻያ የሚገኘው ግን አሁን የተጀመሩት ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው ቀጥለው መንግሰት በልመና/በችሮታ የሚሰጠው ሳይሆን ለዚህች ሀገር መፍትሔ የሚያመጣ መንገድ ነው ብሎ አምኖ ሲቀበለው እና በሂደቱ በቅንነት ሲሳተፍ ነው፡፡ ከመንግሰት በተፃራሪ የቆምን ሀይሎችም የእኛ ብቻ ነው ልክ ከሚለው ግትር አቋም መለሳለስ ሲችሉ እና አንበረከክነው ከሚለው አስተሳሰብ ስንወጣ ነው፡፡

ይህ የፖለቲካ ማሻሻያ ለማድረግ በዋነኝነት ከመንግሰት ውጭ ያሉ ሀይሎች ችግሩ አሁን በስራ ላይ ያለው ህገመንግሰት ተቀዶ መጣል አለበት ከሚለው ፅንፍ ወጥተወ ሰላማዊ ሽግግር ለማድረግ እንደመነሻ የሚያገለግል እጅግ ጠቃሚ የሆነ የፖለቲካ ሰነድ መሆኑን አምኖ መቀበል ያስፈልጋል፡፡ ይህ ሲሆን ገዢው ፓርቲ በተለይ (የድል አጥቢያ አርበኞች ሳይሆኑ) በትግሉ ወቅት ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈሉበት ህገመንግሰት ተቀባይነት በማግኘቱ ደስተኞች ሰለሚሆኑ ሂደቱን የተሳካ ያደርገዋል፡፡ ይህም ሆኖ ህገመንግሰቱ ሊሻሻል የሚችል መሆኑ የማሻሻያ አንቀፆች ያሉት ስለሆነ በሂደት የሚሻሻልበት ሂደት መኖሩን መቀበል ደግሞ ለተቃዋሚዎች ተሰፋን የሚያጭር ይሆናል፡፡

ይህ የፖለቲካ ማሻሻያ በሚከናወንበት ጊዜ ሁሉ አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግሰት በመደበኛ የእለት ከእለት ስራው ላይ እንዲቆይ በመስማማት ሀገሪቱ ወደ ሌላ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ እንዳትገባ በማድረግ በስልጣን ላይ ያሉትም ቢሆኑ በስልጣን ላይቀጥሉ ቢችሉ የሰነልቦና ዝግጅ ማድረጊያ ጊዜ ያገኛሉ፡፡ ከገዢው ፓርቲ ውጪ ያሉ በሀገር ውስጥም በውጭ የሚገኙ ስልጣን የሚፈልጉ ሀይሎችም ለስልጣን የሚያበቃቸውን በቂ ዝግጅት ከህዝቡ ጋር በማድረግ እራሳቸውን ለማዘጋጀት በቂ ጊዜ ያገኛሉ፡፡ ማን ስልጣኑን ይይዛል የሚለውን ህዝብ ይወስናል፡፡

የፖለቲካ ማሻሻያ ሂደቱን ሊመራ የሚችል ገለልተኛ የሆነ የሸግግር ሂደቱን የሚመራ “የሽግግር ኮሚሽን” የሚቋቋም ሲሆን ይህ ኮሚሽን በዋነኝነት በሀገሪቱ የፖለቲካ ምዕዳሩን ሊያሻሽሉ የሚችሉ ልዮልዮ ደንቦችን እና መመሪያዎችን እንዲወጡ በማድረግ፣ አፋኝ ህጎችን በመሻር/ወይም በምክር ቤቱ እንዲሻሩ በማድረግ ህዝቡ በፖለቲካው በንቃት እንዲሳተፍ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

ይህ ማሻሻያ በልመና የሚገኝ ባለመሆኑ መንግሰት ወደ ትክክለኛውም አማረጭ እሲገባ ድረስ አሁን ያለው ህዝባዊ እንቢተኝነት እና “በቃ” የሚለው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በማድረግ መንግሰት ይህን አስፈላጊ የፖለቲካ ማሻሻያ እንዲቀበል ማሰገደድ የግድ ይላል፡፡ ምንአልባትም መንግሰት በራሴ አፈታዋለሁ በሚል በሚጠራቸው “ህዝባዊ መድረኮች” ሁሉ በመገኘት ይህን የፖለቲካ ማሻሻያ እንዲያደርግ ግፊት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ መንግሰት “ሕዝባዊ” ብሎ የሚጠራች መድረኮች በአብዛኛው የፓርቲው አባላትና ጥቂት ጥቅመኞች እንደሆኑ በመረዳት በስብሰባው ላይ ሌሎች እንዲገኙ ጥረት ማድረግ ተገኝተውም ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

 

አሁን በመደረግ ላይ ያሉ እንቅስቃሴዎች መንግሰት ላይ የፈጠሩት ጫና ያለ ቢሆንም መንግሰት በተገቢው መንገድ ምላሻ ለመሰጠት በሚያስገድድ መልክ እንዳልሆኑ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ለምሣሌ ሰላማዊ ሰልፍም ሆኖ ተቃውሞ በተደረገ ማግስት መንግሰት በዚህ ተቃውሞ ላይ የተሳተፉ ዜጎችን እየገደለና በየቤቱ እየዞረ እየለቀመ በማስር ከስራ በማፈናቀል እንቅስቃሴውን ማፈን እንደ አንድ ታክቲክ እየተጠቀመ ስለሆነ ማነኛውም የህዝብ ጥያቄ (ትክክል ባይሆን) ከመንግሰት ወገን መልስ ከመስጠት አልፎ ጥያቄውን በማቅረብ የተሳተፉ ወይም የመሩ ሰዎችን ማሰረን፣ ከስራ መባረርን መቃወም ሲከፋም እንዳይታሰሩ መከላከል፡፡ ከታሰሩም በታሰሩበት ቦታ በመገኘት ተቃውሞ መቀጠል፣ እስኪፈቱ ድረስ በፈረቃ በቦታው በመገኝት ተቃውሞ ከፍ እንዲል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

መንግሰት አሁን የግድ የሚያስፈልገውን የፖለቲካ ማሻሻያ እስኪቀበል ድረስ የተቀናጀ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ህዝባዊ እንቅስቃሴው ከጊዜ ወደጊዜ አድማሱን እያሰፈ ረጅም ጊዜ የሚወሰድ የስራና ትምህርት ማቆም አድማ ማድረግ ሊጨምር ይችላል፡፡ መንግሰት በዚህ ላይ በሚሳተፉ ሰዎች ላይ በሚወሰድ እርምጅ በመቃውም ከላይ በተገለፀው መልኩ ተቃውሞን ማስፋት፡፡

በማነኛውም ጊዜ ሆነ ቦታ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በማነኛውም ዜጋ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳይደርስ ጥንቃቄ ማድረግ፤በተለያየ ምክንያት የዚህ ዓይነት ችግሮች ሲፈጠሩ ማጋለጥና ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ህዝቡ እንዲተባበር ማድረግ፡፡ መንግሰት ይህን ሰበብ በማድረግ በሰው ህይወት ላይ አደጋ እንዳያደርስ፣ በሰው ህይውት ላይ ለሚደርሱ ጉዳቶች ሃላፊነቱን እንዲወሰድ ማድረግ፡፡

ኢትዮጵያዊያን በዘርና ሃይማኖት ተቧድነው ይጣላሉ ብሎ መገመት አስቸጋሪ ቢሆን መንግሰትን ጨምሮ የተለያዩ ሀይሎች ለቡድናዊ ፍላጎታቸው ማስፈፀሚያ አንድን የህብረተሰብ ክፍል እንደሰብዓዊ ከላለ ለመጠቀም መሞከራቸው አይቀርም፡፡ ማነኛውም ህዝባዊ እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እና ኢትዮጵያዊነታችን ከብሔር ማንነታችን ጋር በምንም ሁኔታ የማይጋጭ መሆኑን ማስመስከር ይጠበቅብናል፡፡ በተለይ ኢትዮጵያዊ ልሂቃን ይህን ጉዳይ ለፖለቲካ ጥቅም ከማዋል እራሳችንን በማራቅ ታሪክ መስራት ይጠበቅብናል፡፡

ሕመም፡- አንድም ለትምህርት፤ አንድም ለሞት! –ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

$
0
0

unnamed (1)ጥንታውያን የአብነት ሊቃውንት፤ ‹ሕመም አንድም ለትምህርት፤ አንድም ለሞት ነው› ይላሉ። መታመሙን ላወቀ፣ መድኃኒቱን ለፈለገ፣ መድኃኒቱንም በትክክል ለወሰደ፣ ወስዶም ለዳነ ሰው ሕመም ለትምህርት ይሆነዋል፡፡ ሦስት ነገር ይማርበታልና፡፡ አንድም ዳግመኛ እንዳይዘው ጥንቃቄን፣ አንድም ቢይዘው ሊተርፍ የሚችልበትን መፍትሔ፣ አንድም ደግሞ ለሌላው የሚመክረው ልምድን ያተርፋል፡፡ ያለበለዚያ ግን የሕመም መጨረሻው ሞት ነውና ላንዱ ትምህርት የሆነው በሽታ፣ ሌላውን ይገድለዋል፡፡
አሁን ታመናል፡፡ ሕዝቡ የሚያነሣው ጥያቄ፣ መንግሥት የሚሰጠው ምላሽ፣ የሃይማኖት ‹አባቶች› የሚያወጡት መግለጫ፣ ማኅበራዊ ሚዲያው ከግራ ከቀኝ የሚያናፍሰው ነገር፣ ደጋፊና ተቃዋሚው ከወዲህ ወዲያ የሚሠናዘረው ዱላ፤ ሕመም ላይ መሆናችንን የሚገልጥ ነው፡፡ አሁን የሚያስፈልገን መታመሙን የሚያምን፣ መድኃኒቱን የሚፈልግና መድኃኒቱንም በተገቢው ሁኔታ የሚወስድ መንግሥትና ሕዝብ ነው፡፡
መጀመሪያ መተማመን የሚያስፈልገው ‹ችግር አለ ወይ?› የሚለው ላይ ነው፡፡ አዎን ችግር አለ፡፡ እየሆኑ ያሉት ነገሮች የሚነግሩን ችግር መኖሩን ነው፡፡ ችግሩ እነ እንትና ያነሣሡት፣ የቀሰቀሱት፣ ያደራጁት ምናምን ማለታችን ችግር መኖሩን አያስቀረውም። በሀገራችን ‹የጥያቄ ክፉ የለውም፤ የመልስ እንጂ›  ይባላል፡፡ የጥቂቶች ወይም የብዙዎች፣ የእነ አንቶኔ ወይም የነ እንትና መሆኑ ጥያቄውን አይለውጠውም። ለውጥ የሚያመጣው ለጥያቄው ተገቢውን መልስ መስጠቱ ነው። ‹በቅርቡ ያልመለሰ እረኛ፣ በሩቁ ሲባዝን ይውላል› እንደሚባለው፤ በየጊዜው ተገቢ መልስ ሳይሰጣቸው፣ ወይም ደግሞ ይዋሉ ይደሩ እየተባሉ፤ ያለበለዚያም የተፈቱ የመሰሉ ነገሮች እንደገና እያመረቀዙ መሆናቸው እየታየ ነው፡፡
በሽታው ምንድን ነው? ይኼ የምር የሆነ ውይይትና መግባባት የሚጠይቅ ነው፡፡ ለፖለቲካ ፍጆታ ወይም ለፕሮፓጋንዳ ወይም ለጊዜያዊ ድል ወይም የመሥዋዕት በግ ፍለጋ ወይም ለዶክመንተሪ ፊልም ወይም ደግሞ ለቁጣ ማብረጃ ከሚሆን ውይይት፣ መግለጫና ንግግር ያለፈ ሁሉን ዐቀፍ፣ ለመፍትሔ ብቻ የቆመና በእውነት የሚደረግን ውይይት የሚጠይቅ፡፡ አንድ ዓይነት ሰዎች ተሰብስበው አንድ ዓይነት ንግግር የሚናገሩበት ሳይሆን ልዩ ልዩ ፍላጎቶችን፣ አመለካከቶችን፣ አቋሞችንና የመፍትሔ ሐሳቦችን የሚወክሉ ወገኖች፤ ለአንዲት ሀገር ሲባል ሁሉን ዐቀፍ፣ ግን የምር የሆነ፣ ምናልባትም አንዳንዶቻችንን ሊመረን የሚችል መድኀኒት የሚፈልጉበት ውይይት ነው።  በተለመደው መንገድ መጓዛችንን ትተን አዲስ መድኃኒት በአዲስ መንገድ እንፈልግ፡፡ በተመሳሳይ መንገድ እየተጓዘ፣ የተለየ ውጤት የሚጠብቅ ሞኝ ብቻ ነውና፡፡
ከያቅጣጫው የሚሰጡ መግለጫዎች ሆድ ለባሰው ማጭድ የሚያውሱ፣ ከሚያረጋጉ ይልቅ የሚያናድዱ፣ ከሚያስታግሡ ይልቅ የሚያባብሱ፣ ከሚመክሩ ይልቅ የሚያነዝሩ ናቸው፡፡ ራሳቸው ችግር ናቸው እንጂ ችግር የሚፈቱ አይደሉም፡፡ ሌላው ቀርቶ የሃይማኖት አባቶች እንኳን የሚናገሩት ነገር ሃይማኖት ሃይማኖት የሚል አይደለም፡፡
አሁን የሚታየው የመሥዋዕት በግ ፍለጋ ነው። ማዶ ያሉትን አካላት የችግሩ መነሻና መድረሻ ማድረጉ መፍትሔ አያመጣም፡፡ እንዲያውም ጥያቄ ይፈጥራል፡፡ እዚህ አብረውት ከሚኖሩት የመንግሥት አካላት ይልቅ ማዶ ያሉትን ለምን ሰማ? እነዚያስ እዚህ ገብተው ሕዝብ እስኪቀሰቅሱ ድረስ እንዴት ዐቅም አገኙ? ሰው ውጭ ውጭ የሚያየው ቤቱ ምን ሲሆንበት ነው? መልሶ መላልሶ ችግሩ እዚሁ ነው የሚሆነው፡፡ የሚያዋጣው ወደገደለው መግባት ነው፡፡ ወደ ችግሩ፡፡
ቀጥሎ የሚነሣው ድግሞ ‹መድኃኒቱስ ምንድን ነው?› የሚለው ነው፡፡ ሁሉንም ወገኖች የሚወክለውና ለሀገሪቱ ሁነኛ መድኃኒት ለመፈለግ የሚደረገው የምር ውይይት ነው መድኃኒቱን ሊያመጣው የሚችለው፡፡
ከአንድ አቅጣጫ የሚመጣ መድኃኒት የሚያድንበት ጊዜ አብቅቷል፡፡ አሁን ሁሉን አግባብ፣ ሁሉንም ሊያድን የሚችል መድኃኒት የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ ነን፡፡ በዚህ ሂደት የሚፈራም የሚናቅም መኖር የለበትም፡፡ የሚገለል የሚጣልም መኖር የለበትም፡፡ መድኃኒት አንዳንድ ጊዜ የሚያስፈልግ እንጂ የሚፈለግ ላይሆን ይችላል፡፡ የሚያድን እንጂ የሚወደድ ላይሆን ይችላል፡፡ መድኃኒት ፍለጋው ይህንን ያገናዘበ መሆን አለበት፡፡ በዚህ ሂደት ልናድናት ቆርጠን መነሣት ያለብን ኢትዮጵያን ነው፡፡ ሥርዓቶች፣ ፖሊሲዎች፣ አደረጃጀቶች፣ አወቃቀሮች፣ ሊቀየሩ ይችሉ ይሆናል፡፡ ከጠላትነት ወደ ተነጋጋሪነት፣ ከአጥር ወደ ድልድይ፣ ከተጻራሪነት ወደ ተደጋጋፊነት መምጣት ያስፈልግ ይሆናል፡፡
በተበታተነ ሁኔታ በየአካባቢው የሚነዱትን እሳቶች ለማጥፋት ከመሯሯጥ ይልቅ ልብን ሰብሰብ አድርጎ የማያዳግም መፍትሔ መስጠቱ ነው የሚሻለው፡፡ በተለይም መንግሥት ይህ ይጠበቅበታል፡፡ እየሮጡ መስማት እየሮጡ መርሳትን ያመጣልና ቆም ብሎ ሰምቶ ቆም ብሎ መፍትሔ መስጠት ነው ብልሃቱ፡፡
ኮሶ ሲያሽር እየመረረ ነው፡፡ ወይ ሁላችን እናሸንፋለን፤ አለያም ሁላችንም እንሸነፋለን፡፡ ወይ ሁላችንም ለሕመሙ ትክክለኛውን መድኃኒት አግኝተን ተምረን እንድናለን፤ አለያም መድኃኒቱን አጥተን ሞተን እናርፋለን፡፡ ምርጫው ሁለት ነው። ሕመም አንድም ለትምህርት፣ አንድም ለሞት ነውና።
‹ሕመምተኛ ሲሻለው የዳነ ይመስለዋል፤ ሕመምተኛ ሲያቃዠው የሞተ ይመስለዋል› ይባላል፡፡ አንድ ነገር በትክክል መነሻው ሳይታወቅ፣ ችግሩም ሳይፈታ፣ በራሱ ጊዜ ጋብ አለ ማለት ሕመሙ ዳነ ማለት አይደለም፡፡ ብርድ እንዳገኘ የጉንፋን ቫይረስ ሁኔታው ሲመቻችለት እንደገና ይነሣል፡፡ ሕመምተኛው ሲሻለው የዳነ እየመሰለን ከምንተወው፣ በሚገባ ሕመሙን መርምረን ተገቢውን መድኃኒት መስጠቱ የተሻለ ነው፡፡ ዛሬ የተነሡት ነገሮች ጋብ ቢሉ እንኳን ባንድ በኩል ጥለውት የሚያልፉት ጠባሳ፣ በሌላ በኩል በትክክል ባለመፈታታቸው ምክንያት በባሰ ሁኔታ ዳግም መነሣታቸው አይቀሬ ነው፡፡ እንደምናየው ከሆነ በሀገሪቱ የሚከሰቱ ለውጦች የሰውን አስተሳሰብ፣ አነዋወር፣ መስተጋብርና አሰላለፍ እየለወጡት ነው። ዛሬ እንደትናንቱ የሆነ የለም፡፡ ነገም እንደዛሬ የሚሆን አይገኝም፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ‹በሽተኛ ሲያቃዠው የሞተ ይመስለዋል› እንደተባለው ሀገሪቱ ያለቀላት የሚመስላቸው ወገኖች፤ የሀገሪቱን ታሪክ የማያውቁ ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህ የባሰ ችግርና መከራ፣ ከዚህ የባሰ ውጥንቅጥና ፈተና አሳልፋ የምትኖር ሀገር ናት፡፡ አሳልፋ የማታልፍ ሀገር ናት፡፡ በየዘመኑ ከሕመማቸው መማር ያልቻሉ መንግሥታትና ኃይላት አልፈዋል፡፡ ኢትዮጵያ ግን አሁንም አለች፡፡
ሕመሙን ከማባባስ፣ በሕመሙ ለማትረፍም ከመሮጥ፣ ሕመሙን በትክክል አክመን ከሕመሙ እኛው ተምረን እንውጣ፡፡ ካልሆነ ግን ሞተን ለሌሎች የታሪክ መማሪያ እንሆናለን፡፡

ከሀብታሙ አያሌው ጋር ዛሬ በጤናው እና በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ስንጨዋወት አጽንኦት ሰጥቶ የተናገራቸው ጠንካራ ሀሳቦች -ኤልያስ ገብሩ ጎዳና

$
0
0
ሀብታሙ አያሌው

ሀብታሙ አያሌው

“በህዝብ ትግል የህወሃት ካምፕ ይፈርሳል፤ …አንድ በሆንን ማግስት ህወሃት እንደጥዋት ጤዛ እንደሚረግፍ አልጠራጥርም”
“የአማራውን ህዝብ እንደ ቅጥል ማርገፍ የጀመሩት ዛሬ አይደለም”
“የህወሃት ሰዎች እንደደርግ ወታደር ኮፊያቸውን ዘቅዝቀው የሚቆሙበትን መሬት በኦሮሚያ ተወላጆች ደም ስላጨማለቁት መጨረሻቸው እጅግ የከፋ እንደሚሆን ይሰማኛል”
“በዚህ ወቅት የትግራይ ህዝብ ይሄንን ጨቋኝ ስርዓት ነቅሎ ለመጣል የተለየ ታሪካዊ ሃላፊነት እንዳለበት ይሰማኛል”
ሃብታሙ አያሌው

/ከሀብታሙ አያሌው ጋር ዛሬ በጤናው እና በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ስንጨዋወት አጽንኦት ሰጥቶ የተናገራቸው ጠንካራ ሀሳቦችን እንዲህ አሰናድቼዋለሁ/

“በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች በሚገኙ በተለያዩ ቦታዎች በህወሃቶች ትዕዛዝ ሳቢያ በጥይት ተመትተው በሞቱ ወገኖቼ እጅግ ሲበዛ አዝኛለሁ። እነዚህ በግፍ በህወሃት የሞቱ ሰዎች በኢትዮጵያ ታሪክ ህያው ሰማዕት ሆነው ለዘላለም ይኖራሉ።
ወልቃይትን በሚመለከት፣ በእኔ እምነት ህዝቡ ማንነቱ እንዲረጋገጥለት ጥያቄ እያቀረብ መሆኑን አውቃለሁ። ይህን እንድረዳ ያደረገኝ አሁን የተደረገው አመጽ አይደለም። ህወሃት/ኢህአዴግ ጋር በነበርኩበት ጊዜ በከፍተኛ ምስጢር ይዞ ተግባራዊ ለማድረግ ሲንቀሳቀስ በታዘብኳቸው ጊዜ በድርጅቱ ላይ እምነት እንዳይኖረኝ ካደረጉ እኩይ ተግባሩ አንዱ የወልቃይት ጉዳይ ነበር።

የህወሃት የመስፋፋት ዘመቻ ወሎን፣ አፋርን፣ ወልቃይትን፤ አሁን ደግሞ ጎንደርንና ጎጃም ጋር ከሱዳን የሚዋሰኑበትን ሰፊ ድንበር እስከ ህዳሴው ድልድይ ድረስ አጠቃልሎ ታላቅ የሚሏትን ትግራይ ለመመስረት ያለመ ነበር። የአማራውን ህዝብ እንደቅጠል ማርገፍ የጀመሩት ዛሬ አይደለም። ይህንን ሴራ ከእነሱ ጋር እያለሁ ስለተረዳሁ ከዚያ የጥፋት ድርጅት ወጥቼ የቀድሞ አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲን በመቀላቀል በጎንደር ብቻ ሁለት ታላላቅ ሰልፎችን በመምራት እንዲህ የህዝቡ መብት እንዲከበር ብርቱ ጥረት አድርጌያለሁ። ድንበሩን/መሬቱን በተመለከተም ጥናት በማድረግ በአዲስ አበባ በፓርቲው አዳራሽ ጥናቱን ለህዝብ አቅርቤያለሁ።

የኦሮሚያ መሬት ከተማ በማስፋፋት ስም ህወሃቶች ሊቀራመቱት የያዙትን ዕቅድ የማውቅ በመሆኑ በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎችን በመምራት ትልቅ ተቃውሞ ሳደርግ ነበር።

ስለዚህ አሁን የሚሰማኝ፣ በዚህ ወቅት ህዝቡ ለትግል ተነሳስቶ በህወሃት በአደባባይ ሲገደል አልጋ ላይ የወደኩ ደካማ ብሆንም በቁጭት ከማልቀስ በቀር ሀዘኔን የምገልጽበት ነገር አጥቻለሁ።

አንድ ነገር ግን እርግጠኛ ነኝ፣ በህዝብ ትግል የህወሃት ካምፕ ይፈራርሳል። የህወሃት ሰዎች እንደደርግ ወታደር ኮፍያቸውን ዘቅዝቀው ለመለመን የሚቆሙበት መሬትን እንኳን በኦሮሚያ ተወላጆች ደም ስላጨማለቁት መጨረሻቸው እጅግ የከፋ እንደሚሆን ይሰማኛል።

በዚህ ወቅት የትግራይ ህዝብ ይሄንን ጨቋኝ ስርዓት ነቅሎ ለመጣል የተለየ ታሪካዊ ሃላፊነት እንዳለበት ይሰማኛል።
አሁንም አላለሁ፣ እመነኝ ደርግ ወድቋል፣ ኢህአዴግም ይወድቃል። ድል የህዝብ ነው። በዚህ ታሪካዊ ወቅት አማራና ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን የህወሃት አገዛዝ ለመጣል ሁሉም ኢትዮጵያዊ አንድ ሆኖ መቆም አለበት። አንድ በሆንን ማግስት ህወሃት እንደጥዋት ጤዛ እንደሚረግፍ አልጠራጥርም!

መታመሜን ተከትሎ በተለያየ መንገድ ከጎኔ ዛሬም ድረስ ለቆማችሁ በሙሉ ከልብ ዳግሜ ማመስገን እወዳለሁ። አሁን በቀን 400 ሚሊ ግራም ማደንዘዣ (ፔቲዲን) እየተወጋሁ ነው። በዚህ ሁኔታ እንዴት እንደምዘልቅ አላውቅም። ይህ ያሳስበኛል። ምን ያህል ሰውነቴን እንደሚጉዳው አላውቅም። ማደንዘዣው የጎንዮሽ ጉዳት አለው። ዛሬም ድረስ ሌላ ህክምና ስላላገኘሁ ሌላ ኢንፌክሽን ተፈጥሮ የባሰ ነገር እንዳይከሰት በመከላከል ላይ እገኛለሁ። በአብዛኛው ዐበል እና እምነት (ቅባ ቅዱስ) ነው የምጠቀመው።”

‘’ የኢትዮጵያዊኖች ተጋድሎ! ወይስ የማን ተጋድሎ ነው…..?” –ፊልጶስ

$
0
0

Woyane

ወያኔ  ኢትዮጵያን  እያፈራረሰና  ህዝቡን ‘ርስ በርስ እያባላ  ያለው  ብቻውን  አይደለም። የሀገሪቱ ጠላቶች፣  ሆድ-አደሮች፣  መሀል-ሰፋሪዎች፣  ግብዞችና  የመሳሰሉ  ሁሉ  አጋጣሚውን  ይጠቀማሉ። ሲጠቀሙም  ኖረዋል። ወያኔና  ግብረ – አበሮቻቸው  እኮ ኢትዮጵያን  የማፈርስረሱን  መረሀ-ግብር  የተቀበሉት  ከምዕራቡና  ከዐረቡ ዓለም ነው።   መርሳት  የሌለብን  ወያኔ  ከዚህ  ደርጃ  እንዲደርስ  የኛ  አስተዋ’ጾ መሆኑን  መቀበል አለብን።  ማርቲን  ሎተር  ይመስለኛል፤ ካልተጎነበስክላቸው  እነሱ  ከአንተ  ጀርባ  ላይ  አይወጡም !”ያለው።  ቁምነገሩ  ካለፈው  መማር  መቻላችን  ላይ ነው።

በርግጥ  አሁን  ብዙሀኑ  የወያኔን  “አሪወሳዊነት”  ከማንኛውም  ግዜ  በበለጠ  የተረዳበትና  የ40 ዓመት የከፈፍለህ  የቤት  ስራ ”ፉርሽ” የሆነበት ነው።   ይሁን  እንጂ  ብዙ  ድህረ-ገጾች፣  ዜና – ዘጋቢዎች፣ ዘፋኞች፣  ሰላምዊ  ሰልፎኞች፣  የፓለቲካ  ተንታኞች፣  መግለጫዎችና   የመሳሰሉት  በሚያሳዝንና በሚያሳፈር  ሁኔታ  ከወያኔ  የጎሳ  ወጥመድ   ያለመላቀቃችን ፤ አንድርምጃ  ወደፊት፣  አንድርምጃ ደግሞ  ወደ  ኋላ  መሆኑ  በግዜ  ሊታሰብበትና   ሊታረም   የሚገባ   ጉዳይ ነው። እናም  የምንናገረውንና  የምንጽፈውን  በጥንቃቄ   መመርመርና፤ ወያኔ  የማይቆፍረው  ጉድጎዳ፣  የማያፈሰው  ደም  እንደሌለ  ከምንግዜውም  የበለጠ   አሁን  መረዳት  ያስፈልጋል።

  • ”የአማራ ተጋድሎ!….. የኦሮሞ ተጋድሎ!….. የመሳሰሉ ዜናዎችና  መፈክሮች   የሚያመለክቱት አሁንም   ደም  እንደጎርፍ  እየፈሰሰና  ምድራዊን  ስቃይ  እየተቀብለን፣  ወያኔ  ካሰመረልን የጎሰኝነት  ስሜት  ያለመውጣታችን  የሚያመለከት ነው።  ለምንድን  ነው የኢትዮጵያኖች ተጋድሎ ! “ የማንለው?? ?….. እድግመዋለሁ፤ የኢትዮጵያዊኖች ተጋድሎ!” ። አማሮች እንዲህ…አድረጉ…  ኦሮሞዎች  እንዲህ ሆኑ………አደረጉ… ..ወዘተ…..እያልን ፤ በአንድ  አካባቢ  አንድ  ወጥ  ህዝብ   እንዳለ   አድርገን   ማቅረባችንና   መዘገባችን  ይቁም። በተለይም ኢሳት  (ቲቪና  ሬዲዮዎ )  የኢትዮጵያ ህዝብን ዓይና ጆሮ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ ጉዳይ ግን ቢያስብበት መልካም ነው እላለሁ።

በዚች ሰዓት ጋምቤላዎች  የከፍሉት  መሰዋ’ትነና  እየከፈሉት  ያለው  ተጋድሎ፣  የኦጋዴኖችና  አንዲሁም  በተለያየ  ግዜ  በተለያዩ  የሀገሪቱ  ግዛቶች   ከወያኔ ጋር  የሚተናናቁት ሁሉ የኢትዮጵያኖች ያውም  የዚህ ኢትዮጵያዊ ትውልድ  ተጋድሎ  እንጅ  የማን   ሊባል  ይችላል?  ካላያማ  ከወያኔ  በምን  ተለየን?  የተጀመረውን  የጸረ-ወያኔ  የጎሳ ከፋፍለህ  ግዛው  እንዴት ነው  የምናከሽፈው? “የዚያ  ጎሳ  ተጋድሎ!….. የዚህ  ጎሳ  ተጋድሎ!…..” እያልን  እንዴት  አድርገን  ነው  ትግሉን  ለህዝባዊ ፣ ለሁሉሙ  ኢትዮጵያዊ  ድል  የምናበቃው?

 

 

 

  • ሌላው የስሞኑን  ህዝባዊ  አመጽ  ያቀጣጠለው  የወልቃይት  ጉዳይ  ነው። የወልቃይት ጥያቄ የሁሉም  ኢትዮጵያዊ  ጥያቄና  ትግል  ነው። ኢትዮጵያዊ  ዜጋ  ነኝ  የሚል ሁሉ ይመለከተዋል። ይሁን  እንጂ   ወልቃይት አማራ !…” የሚለው  አባባል፣ መፈክርና  ቀረርቶ  የወያኔ  የጎሳ ስራ መስራቱን  ነው  የሚያመለክተው።  ወልቃይት …..  የጎንደር  አንዱ  ግማድ  ነው፤ ለዚህም የህይወት  መሰዋትነት  ብቻ  አይደልም፤  የዘር  ማጥፋት  ወንጀል  እየተፈጸመበት  ያለ  ህዝብ ነው። ያ  ማለት  ደግሞ  ‘’ወልቃይት – ጎንደር፤  ጎንደርኢትዮጵያ  ነው።”’  ይህም  ማለት ኢትዮጵያ  ከሌለች   – ወልቃይትጎንደር  የለም  ሁሉም  ኢትዮጵያዊ  የሚስማመው ”  በኢትዮጵያዊያን   ተጋድሎ !….” ነው።   ትግሉ  የሁሉም  ኢትዮጵያዊ  መሆኑ  በዚህ ሰዓት መዘንጋት  የሌለበት  ጉዳይ ነው።  ለመሆኑ  የሌላው  ኢትዮጵያዊ  ተጋድሎና  መሰዋትነት  የት ሊጣል  ነው?  የአብሮነት  ትግል  ባላማካሄዳችን  አይደልም  ወይ፤  ወያኔና  ሆድ-አደሮቹ ሀገራችን  የግላቸው  እቃ  አድርገው   ህዝብን  እንደቅጠል  የሚያረግፉት።

 

  • ወያኔ ለኢትዮጵያ  ጎሳዎች  ብሎ   የጫነብን  ሰንደቅ ዓላማ፤  በየተኛውም  ኢትዮጵያዊ ተቀባይነት  አለመኖሩ  ብቻ  አይደለም ፤ ነባሩ ሰንደቅ – ዓላማ   የኢትዮጵያ ህዝብ የአንድነትና   የተጋድሎ  መግለጫ   መሆኑን  እያስመሰከረ  ነው።  ስለዚህም  በህዝባዊ  አመጽ   ወቅት  የቡድን  ወይም  የድርጅት  ሰንደቅ  ዓላማ  ይዘን  መውጣታችን  ይከፋፍለናል  እንጅ  አንድ  አያደርገንም።  በርግጥ  በአንዳንድ  የደቡብ  ክፍል  የወያኔ ካድሪዎች  የአንዳንድ ድርጅቶችን “ሰንደቅ  ዓላማ”   ይዘው  በመውጣት  ህዝብን  ለመምታትና  ለመከፋፈል  እየተጠቅሙብት  ቢሆንም፤  እኛ  ግን  አንድነታችን  በተግባር  እናስመስክር። እየተከፈለ  ያለው  የህይወት  መሰዋትነት  ነው።

 

  • ሰሞኑን  ከተቀሰቀሰው  ህዝባዊ  አመጽ ጋር  አንዳንድ  ዘፋኞች  ከትግሉ  ጋር  በተያያዘ   ነጠላ ”የቅሰቀሳና  የውዳሴ”  ዜማ ለቀዋል፡:  በተለይም  ስለ  “ወልቃይት-ጎንደር፣ …….ስለ ኦሮሚያ፣….  ወዘተ።  ይሁን  እንጂ  በ’ኔ  እይታ   ዜማዎቹ  በደንብ  የታሰበባቸው  አይደሉም። ”ኢትዮጵያዊ”  አንድምታ  የላቸውም።  ተጋድሎውና  ህዝባዊ  አመጹ  የመላው  ኢትዮጵያዊ በመሆኑ  ዜማዎቹም  የሁሉንም  ኢትዮጵያዊያን   አንድነትና  ጅግንነትን  የሚያወድሱና የሚቀሰቅሱ   መሆን  ሲገባቸው  በአካባቢያቸው  ተወስነዋል።   የወያኔች  በጎሳ  ላይ  በተመሰረተ የጥላቻና  የግብዝነት  ከበሮ -ድለቃ ፤ የምን ያህል  የወርዱና  የዘቀጡ ኅሊና   ያልፈጠረባቸው  መሆናቸውን  የሚያመለክት  ሆኖ   ሳለ፤  የ’ነሱን  ፈለግ  መከተሉ   በአንድ  አፍ  ሁለት  ምላስ  …” ይሆንብናል።   ”ወልቃይት  ብረሳሽ  ቀኜን  ይርሳኝ!..!”  ከማለት  ኢትዮጵያ ….ብረሳሽቀኜን  ይርሳኝ!”  ብሎ  ቢያንጎራጉር፤  ለአንድነታችንና   ለትግላችን   የሚኖረው  ፋይዳ  ከፍተኛ   ነው።  ለወያኔም  የራስ  ምታት  ነው።  ኢትዮጵያ  እንዳትኖርና  እንድትፈራርስ   እኮ ነው  ወልቃይትና  ሌሎችም  አካባቢዎች  ለወያኔ  የተከለሉትና  ለሱዳን  እጅ  መንሻ የሚቀርቡት።  እናም  በተቻለ  መጠን   የትግል  ዜማችን  የሁላችንም  ሀገር  ልናደርጋት  መሰዋ’ት   ለምንከፍልላት  ኢትዮጵያችንና  ህዝባችን  ይሁን።

 

 

 

 

 

ያለፉትም  ሆነ  አሁን  ያሉት ”ጅግኖቻችን”  የከፈሉት  መሰዋትነትና  እየከፈሉ  ያሉት  ለኢትዮጵጵያና  ለኢትዮጵያዊያን  ነው።  ታዲያ   እነዚህን  የክብር  የኢትዮጵያዊያን  ጀግኖች  ወደ  መንደርተኛነት  ማውረድ  ምን  ይሉታል?።  ቢቻል  በዚህ ሰዓት   ዘፋኞች  በህብረት  ለሁሉም  ኢትዮጵያዊ  የሚሆን  በተለያዩ   የሀገሪቱ   ቋንቋዎች  ዜማ  ቢለቁ   ለትግሉም  ሆነ  ለአንድነታችን  የበኩላቸውን  አስተዋ’ጾ  ያደርጋሉ። በዚህ ጉዳይ ላይ በተለይም  ባህር-ማዶ የምትገኙት እንደ አለምፀሀይ  ወዳጆና  ታማኝ  በየነ ያላችሁ፤ የጥበብ ሰዎችን እንደተለመደው  ብታሰተባብሩ ”ለቀባሬው ማርዳት” ባይሆንብኝም  መለዕክቴ  ይድረሳችሁ።

 

—//—-

 

ፊልጶስ / ነሀሴ 2008 / E-mail: philiposmw@gmail.com

 


እናት ሆይ! ጀርባሽን እሚዘነችሩትን እስከ መቼ እሹሩሩ ትያለሽ? –በላይነህ አባተ

$
0
0

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

Cry-ethiopia1.jpgእናት ሆይ! የደራሲና የዘፋኝ መዋኛ ባህሩ፣ የድርሰትና የዘፈን መቅጃ ምንጩም ማህበረሰብና የማህበረሰቡ ባህል መሆኑን ልብሽ ይነግርሻል፡፡ ከማህበረሰቡ የባህል ባህር የወጣ ድርሰትና ዘፈን ከባህር እንደ ወጣ አሳ እድሜው አጭር መሆኑን ዛሬ ተነበው ነገ የማይደገሙት ድርሰቶች፣ ዛሬ ተደምጠው ነገ የማይደመጡት ዘፈኖች ያረጋግጡልሻል፡፡ የማህበረሰቡን ደስታ፣ ችግር፣ መከራና ሐዘን ያልዳሰሰ ድርሰትና ዘፈን ከባህር ውጪ እንደቆየ አሳ የሞተ መሆኑንም አእምሮሽ ያስረዳሻል፡፡ የማህበረሰቡ ችግር፣ መከራና እልቂት መንስኤ የሆኑትን ከንቱዎች እሚያወድስ ድርሰትና ዘፈን እንዲያውም እንደ ጠነባ አሳ ወዲያው እንደሚወረወር ህሊናሽ ያሳውቅሻል፡፡

እናት ሆይ! ጣሊያን ገረድ ሊያደርግሽ ሲደነፋ ቀረርቶና ፉከራዎች በዋሽንት፣ በክራር፣ በመሰንቆ፣ በበገና፣ በጸናጽል፣ በከበሮና በሌሎችም ባህላዊ መሳሪያዎች ታጅበው እንደታደጉሽ ታስታውሻለሽ፡፡ በእነዚህ ባህላዊ መሳሪያዎች የታጀቡ ቀረርቶዎችና ፉከራዎች ስንት ድንበር ጠባቂ ጀግኖች እንዳፈሩልሽ ትዝ ይልሻል፡፡ እነዚህ የጀግና መኮትኮቻ ቀረርቶዎችና ፉከራዎች በምድርሽ እንዳይሸለሉ ከሃያ አምስት አመታት በፊት በድንበር ሻጮች እንደተከለከሉም ትገነዘቢያለሽ፡፡ ድንበር ሻጮችን በመከተልም ብዙዎቹ የኪነ-ጥበብ ልጆችሽ ከቀራርቶና ከፉከራ እንደራቁ ታውቂያለሽ፡፡ አንዳንዶች ራሳቸውን የጠሉ ዘፋኞችም ቀረርቶና ፉከራን እንደ ስልጣኔ-አልባ ሕዝብ ኪነ-ጥበቦች በመቁጠር ከራሳቸው የባህል ባህር ወጥተው ከማያውቁት የባህል ባህር ገብተው እንደ ጀማሪ ዋናተኛ ሲንጨቧረቁና የባህል ተገዥ ባሪያዎች ሲሆኑም ትታዘቢያለሽ፡፡

ያለሽበት የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ዘመን ከቱርኩ፣ ከደርቡሹና ከጣሊያኑ የወረራ ዘመን የከፋ መሆኑን የተቆረጠው አንገትሽ፣ የተሸጠው ፍሪንባሽ፣ የተሰነጣጠቀው ሆድ እቃሽና የወደቀው ክብርሽ እንደሚያስረዳ ታውቂያለሽ፡፡ የዛሬው መከራሽ ካለፉት መክፋቱን በባሩድ የተረሸኑት፣ ከገደል የተወረወሩት፣ በወህኒ የተሰቃዩት፣ በርሃብ የተጨረገዱት፣ በስደት ባህር የገቡት፣ በሊቢያ የተቀሉት፣ ባረብ ታንቀው የሞቱት፣ ባፍሪካ በእሳት የጋዩትና በእስር የተንገላቱት ልጆችሽ ምስክሮች እንደሆኑ ትረጃለሽ፡፡ ታዲያ ለዚህ ከድሮው የከፋ ህመምሽ ስንት ምሁራን መድኃኒት ፍለጋ ኳተኑልሽ? ስንት አቀንቃኞች ሰቆቃሽን አቀነቀኑልሽ? በሌጣ እግርሽ ተጉዘሽ ኩበት ለቅመሽና በኩበት ጪስ ታጥነሽ እንጎቻ አነጉተሽ ያስተማርሻቸው ምሁራን ሲመረቁ የገቡትን መሐላ ዘንችረው ለምን እጀ አመድ አፋሽ አደረጉሽ? በቅኔሽና በዜማሽ እንጀራ እሚጎርሱት ካህናትና ዘፋኞችሽ ይሉኝታን ጎርድመው ለምን ፊታቸውን አዞሩብሽ?

የቆሎ ተማሪሽ ቁራሽ ሲለምንና እንደ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ በኮር አባልነት የበረዶ ስኳር(ዓይስ ክሬም) መላስ ሳይጀምር  “ያሁኑ ይባስ!” ይል እንደነበር ታስታውሻለሽ፡፡ ያሁኑ ብሶ አንዳንድ ምሁራንና ዘፋኞችሽ ካንቺ ከእናታቸው ፊታቸውን ከማዞርም አልፈው የጣሊያንን ያልተሳካ ምኞት ከሚፈጥሙት ጡት ነካሽ ልጆችሽ ጋር ቦጫጭቀውና በከረጢት ቋጥረው መቃብር ሊወስዱሽ ተሰልፈው ትመለከቻለሽ፡፡ እንዲያውም ይንጠስልሽ ብለው ልቅሶሽን ሰርግ ለማስመሰል ስለ ልማት ሲወሸክቱና ስለ ህዳሴ ሲዘፉኑ ትሰሚያለሽ፡፡ አንገትሽን ገዝግዘው የቀነጠሱትን፣ ጀርባሽን ተልትለው የሸጡትን፣ ሆድ እቃሽን ወጋግተው ወንፊት ያደረጉትና የልጆችሽን ደም እንደ ዓባይ ፏፏቴ ያፈሰሱትን “አምሳለ ሙሴ” ብለው እየደረሱና እየዘፈኑ ካንቺ አልፈው ከታሪክ፣ ከፍትህና ከእግዚአብሔር ሲጣሉም ታዳምጫለሽ፡፡ ታዲያ ካንቺ፣ ከታሪክ፣ ከፍትህና ከእግዚአብሔር ለተጣሉት ምሁሮችሽና ዘፋኞችስ ምን ምክር አለሽ? ጣልያን ገረድ ሊያደርግ ሲወርሽ መንገድ እያሳዩ ፋኖዎችሽን ካስፈጁትና ለፋኖዎችሽ ገዳዮች እንቁላል አቅራቢ ከነበሩት እርጉም ልጆችሽ ምን ተማርሽ?

እናት ሆይ! እናት ሆደ ሰፊን እያወጋሽ እስከ መቼ ባንዳን ትታገሻለሽ? እናት አትጨክንምን እየተረትሽ ጡት ነካሽ ልጆችሽን እስከ መቼ ጡት አጉርሰሽ ታድሪያለሽ፡፡ የወለደ አይጥልምን እየተረትሽ ጀርባሽን እሚዘነችሩትን እስከ መቼ እሹሩሩ ትያለሽ?

 

ነሐሴ ሁለት ሺ ስምንት ዓ.ም.

 

ይድረስ ለመላው ኢትዬጵያዊ ወገናችን ሁሉ! –በስራኤል ሃገር የጎንደር ተዎላጆች ማህበር

$
0
0

እነሆ ወሳኙ የፍልሚያና የትንቅንቁ ወቅት ላይ ደረስን!

Gonder6በባእዳን እጆች ተደግፈው፤ በስልጣን ላይ የነበረውን የደርግን ድንቁርናና አልሰማባይነት የተፈጠረውን ክፍተት ተጠቅመው ላለፉት ሃያ አምስት የመከራ ዓመታት በመንበሩ ላይ ፊጥ ያሉት የባንዳ ልጆች በመዘዙት የበቀል ጅራፍ ያልተወጋና ጠባሳው የማይገኝበት የሃገር ልጅ ይኖራል ብሎ ማሰብ በእጅጉ የዋህነት ነው ኦሮሞው፤ አማራው፤ ጉራጌው፤ ሱማሊው ፤ ትግሬው በጠቅላላ ሁሉም ኢትዬጵያዊ የእዚህ የህወሃት መርዘኛ ፖለቲካ ሰለባ ነው።  ምክኒያቱም ይህ ለኢትዬጵያዊነት የሚከፈል ልዩ ዋጋ ነው ለእነርሱም ይህ የባንዳነት ማረጋገጫቸው ነው  “ወይራ ዶግ ይወልዳል” ሆነና እነአሉላ በወጡበት ማህጸን እነመለስ እና እነ ስብሃት ወጡ፤ የኢትዬጵያዊነት መሰረት ከሆነው ከትግራይ ህዝብና መሬት ተፈለፈሉ ዘይገርም ነው ነገሩ!።

እርግጥ ነው እነዚህ  የበግ ለምድ ለብሰው የመጡ የህወሃት ተኩላዎች ራሱን የብርሃን መልዓክ እስኪመስል መቀየር ከሚችለው ክፉውና መሰሪው አባታቸው ከዲያብሎስ በተካፈሉት ጥበብ ከክፋት በቀር  አንዳች መልካም ነገር በማይገኝበት ማንነታቸው ሃገራችንን የሲዖል ምሳሌ ማድረጋቸው ህሊናቸውን ከደፈጠጡትና ለቦርጭ ከሚሮጡት ውጭ ለማንኛውም ኢትዬጵያዊ ግልጥና ግልጥ ነው። እነዚህ የሌዋታን ውላጆች በረጩት መርዝ ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የተጠቀሙበት ስልት በተለይም በሁለቱ ታላላቅ ህዝቦች  ማለትም በሰፊው የኦሮሞና የአማራ ህዝቦች መካከል ለጊዜውም ቢሆን የተሳካ መስሎ ታይቶም ነበር ይሁን እንጅ በእውነተኞቹ ኢትዬጵያዊያን ያላሰለሰ ጥረትና የላቀ መስዋዕትነት እነሆ ዛሬ ላይ ሁለቱ ወንድማማቾች የእባቦቹን መርዞች አርክሰው ከልብ የተቃቀፉበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ይህ ድል ህወሃትን ያስደነበረ ቀሪውን ኢትዬጵያዊ ደግሞ ያስፈነጠዘ ድል ነው ይህን ድል የመጠበቅ ሃላፊነት ደግሞ በእያንዳንዱ ዜጋ ትከሻ ላይ መውደቁን ልናውቅ ይገባል።

ምልክቱን በባንዲራችን ላይ ካስቀመጡለት ከሉሲፈር ጋር በደደቢት ቃልኪዳን የተጋቡት ሊዋታኖቹ ኃይልን የሚሞሉት ደግሞ ከዘንዶው ነው እነርሱ የደም ግብር ያቀርቡለታል እርሱ ጊዜያዊ ኃይል ይሰጣቸዋል ፤ ህዝብን ያደነዝዝላቸዋል የዕምነት መሪዎችን የሃሰት ትንቢት እንዲናገሩ ያስታቸዋል ከግዚአብሄር ሃሳብ ጋር ፈጽሞ የሚጣረስ ትምህርት እንዲያቀርቡ ያመቻቻቸዋል።  ይህ ዘንዶ ምንም እንኳን እስከተቀጠረለት ቀን ድረስ በዘመናት መካከል ምድራችንን ቢተናኮለም ዋናውን ሰራ የጀመረው ግን በዓድዋ ዘመቻ ጊዜ ነበር በወቅቱ በአባቶቻችን ክንድ ጅራቱ እንደተቆረጠ አመለጠ። እንደገና ከአርባ ዓመት በኃላ መርዙን ተሞልቶ እየተጎተተ የመጣው ኃይል ብዙ ዋጋ ካስከፈለን በኋላ አሁንም በአባቶቻችን ፈታኝ ትግል ተመትቶ ተመልሷል። አሁን ግን በስመ ወያኔነት ቆዳውንም ቀይሮ መርዙን በብዙ እጥፍ ጨምሮ መጥቷል። እነሆ ይህንን አስጨናቂ ዘንዶ እግዚአብሄር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይቀጣው ዘንድ ንጉሱ በደጅ ነው (መዝ 74 ፤ 13-14) “ አንተ የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ ለኢትዬጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።” ይላል። እግዚአብሄር ይህንን የህወሃት ስጋ ለብሶ የተገለጠን ዘንዶ የሚመታበት ጊዜ ላይ ነን ሁል ጊዜ ህዝብን እያስጨነቀ እያስለቀሰ እንዲኖር አይፈቅድለትም። አዎ ያንድ ነገር መነሻ እንዳለው እንዲሁ መድረሻ አለው ፤ የመዝራት ጊዜ አለ የማጨድ ጊዜ አለ። መከራን ዘሩ ምን ያጭዱ ይሆን? ፤ ውሸትን ዘሩ ምን ይሰበሰቡ ይሆን፤ ትዕቢትን ዘሩ ምን ያከማቹ ይሆን?

በአስራ ዘጠነኛው መግቢያ ዓመታቶች ላይ  አሜሪካንና ህዝቧን ህልውናቸውን አደጋ ላይ የሚጥል የወንበዴ መንጋ ምክኒያት በትርምስ  በእጅጉ ተናውጣ ነበር ይሁን እንጅ  ችግሮቻቸውን  በራሳቸው መፈታት የሚያውቁበቱ ነጮቹ ያን የጨለማ ወቅታቸውን በድርሳን ለብደው ዳግመኛ እንዳይነሳ አድርገው ቀበሩት። ታዲያ ይህንን አስጨናቂ ጊዜ ጸሃፊ Eugene Rosow ሲገልጠው “ The Born To Loss” ብሎ መጽሃፉን ሰየመው የጥፋት ልጆች እንደማለት ነው።  እነዚህ እርጉም ሃዋርያትና የጥፋት መልዕክተኞች በነዚህ ሃያ አምስት የመከራ ዓመታት የጉስቁልናን ምንነት አሳዩን ፤ የሃዘንን ዶፍ አጠገቡን፤ የውርደትን ጥግ አስጨበጡን፤ የመለያየትንም ጣራ አስነኩን ምን ያልሆንነው አለ? በጠመንጃ የገሩት ሚዲያቸው ጥቁሩን ነጭ፤ ገደሉን ሜዳ፤ ምድረበዳውን ገነት የሚልና እነርሱ መስማት የሚፈልጉትን ብቻ እንዲናገር አድርገው ቃኙት ። እናም በዚሁ በቀቀን በሆነው ሚዲያቸው የግልብጥ እያናገሩ የተራበውን ጠግበሃል፤ የመነጠውን ድሃ በልጥገሃል፤ በጠመንጃ ዘር እየፈጁ ዲሞክራሲ አሰፈንልህ እያሉ በመላገድ በታላቁና በኩሩው የኢትዬጵያ ህዝብ ላይ ተዛበቱበት ግን ይህም ያልፋል አዎ ያልፋል!  የሃፍረት ታሪካችን ቢሆንም እንኳን ግን ደግሞ የማይደገም ታሪክ ሆኖ ይመዘገባል።

ውድ ወገናችን ሆይ ዛሬ ላይ የግፉ ጽዋ ሞልቶ በአርያም ፈሧል። አባቶቻችን ወንድ ልጅ ሲፈራ ያዩት እንደሆነ ” በላ ተመልሰህ ከእናትህ ማህጸን ግባ”  ይሉታል። ወዴትስ ይኬዳል ? ከዚህ በላይስ የውርደትን ገጣባ ተሸክሞ ከምድር በላይ የመኖር ትርጉሙስ ምንድነው? ይህችን ውብ ሃገርህን እንደአባቶችህ በክብር  አስጠብቀህ ታሪክ በመስራት ለመጭው ትውልድ ታስተላልፋለህ? ወይንስ ያ መላው ጥቁር ህዝብ እንደ ትልቅ ተስፋ አንጋጦ የሚያየው ኢትዬጵያዊነት በአንተ ዘመን ያበቃለታል? እናም መምጫህ የማይታወቅ ከርታታ ሆነህ ታልፋለህ? ቆም በልና አስብ የሰው ልጅ ክብሩ ታሪኩ ነው። ሃገርህ ክብርህ ናት ሃገርህ ከሞተች ያንተም ነገር እዚያው ላይ ያበቃለታል። አባቶቻችን ከምንም በላይ ሃገር ነው ሲሉና በስንኝ ሲሸበልሏት እንዲህ እንዳሉ ተመልከት ፤-

እናት አባት ቢሞት በሃገር ይለቀሳል፤

ሃገር ከሞተ ግን ወዴት ይደረሳል?

ጥቅል ሃሳቡ ማዕረጉም ክብሩም በሃገር ነው ለማለት ነው።  ዛሬ ይህቺ የአፍሪካ ንግስት ፤ የጥቁር ህዝብ ፈርጥ፤ የረጅም ታሪክ ባለቤት ኢትዬጵያ  በባንዳና ወሮበላ የትግራይ ልጆች ታሪኳን እንዳልሆነና እንዳልነበረ ለማድረግ የመጨረሻው ጫፍ ላይ እንገኛለን ። ስለዚህም ሁላችንም ቀበቶአችንን ጠበቅ ትንፋሻችንን ዋጥ አድርገን በበቀል ከተሞሉ የባንዳ ልጆች ጋር እየተናነቁ እየወደቁም እየጣሉም ከሚገኙት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር አብረን ልንቆም ይገባል። ትግላችንን ለድል ለማብቃት የሚከተሉት መርሆዎች አስፈላጊ ናቸው ብለንም እናምናለን። ጠንካራ ዲስፕሊን፤ ከአጉል ጥላቻ የራቀ ሰፊ ልብ፤ የራሳችን ስራ በአግባቡ መወጣታችንን ማረጋገጥ እንጅ ሌሎችን የትግል አጋሮቻችን ከመወንጀል መቆጠብ፤ ወንጀለኛውን የህወሃት ቡድን ከሰፊው የትግራይ ህዝብ ነጥሎ ማየት መቻል ምክኒያቱም ቡድኑ ብቻውን ተነጥሎ እንዳይቆም የትግራይን እንደማምለጫ ምሽግ ለመጠቀም ተግቶ እየሰራ በመሆኑ በዚህ በኩል ንቁዎች  ልንሆን ይገባል።

ለተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፤-  ይህ ወቅት በአንድ ቆመን ራሳችንን እየገዛን ፤ ከየትኛውም  የግል መሻትና አጉል ምኞት በፊት ሃገርና ህዝብን በማስቀደም  በአንድ ማዕከል ስር የሚመራ ጊዜያዊ ተቋም በመፍጠርና በሳል አመራር ለመስጠት ራስን ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው። ይህ አሰራር መጠነኛም ቢሆን አሁን የሚታየውን  የቅንጅት ክፍተት በመሸፈን ገንፍሎ የወጣውን የህዝብ ብሶት ለድል ለማብቃት በእጅጉ ይረዳል ይህን ስራ በአግባቡ ለማከናወንም ያለዕረፍት ብዙ መሰራት ይጠበቅብናል ብለን እናምናለን። እንዲህ ዓይነት ተቋም መፍጠር ያላግባብ የሚባክንን የህዝብ ንብረትና ጊዜ ከመታደጉ ሌላ አቅጣጫችን ከሚያስቱት መልቲዎችም ይሰውረናል። ይህ ወቅት ከመጠላልፍ ጌም ወጥተን ከዚያ ይልቅ የጠሩ ሃሳቦችን በማፍለቅና በጠንካራ ዲስፕሊን በመታገዝ የወገንን ስቃይና ጣር ለመቀነስ ፊተኛ ሆነን በመገኘት ለቤዛነት ራሳችንን ማዘጋጀት የሚጠበቅብን ጊዜ ነው። የትግሉ ባህሪ ይህንንም ይጠይቃልና!። አዎ ይህ ወቅት ወሳኝ ወቅት ነው  እርስ በርሳችን በመቀራረብ ተደጋጋፊ የሆኑና  የተሰናሰሉ ስራዎችን በመስራት በአሸናፊነት ለመወጣት ዕረፍት የለሾች ልንሆን ይገባል።  ይህንን በህዝብ የቁጣ ማዕበል የታጀበ የአመጽ ግለት ሳይቀዘቅዝና አንዳች ደባች አዚም ጥላውን ሳይጥለበት ከመጋኞቹ ነጥቀን በህዝብ እጅ ለማስቀመጥ በመለኮታዊ ጥበብ ሳይቀር የተካንን ልንሆን ይገባል።

የ1997 ዓም ሃገር አቀፍ ምርጫ ብዙ አስተምሮን አልፎአል ። ህዝብ ዘረኞቹን  የህወሃት ወንበዴዎች ለቦታው አትመጥኑም ብሎ በካርዱ የቀጣበት ጊዜ ነበር። ይሁን እንጅ በእኛ የውስጥ ድክመትም ይሁን በምዕራባውያን የረቀቀ ተንኮል የህዝብ ትግልና መስዋዕትነት ጭቃ ላይ ተደባልቆ የብዙዎቻችንን ልብ ሰብሮ አልፎአል ያ ውድቀታችን እንዳይደገም ምን እናድርግ? ህዝብ በባዶ እጁ ወደ አደባባይ በመውጣት ዘመናዊና ገዳይ መሳሪያዎችን እስከአፍንጫው ከታጠቁ ጨካኝ የባንዳ ልጆች ጋር ፊት ለፊት እየተጋፈጠ ባለበት በዚህ ወቅት መስዋዕትነታችንን ለመቀነስ  ምን ዓይነት የረቀቁ ዘዴዎችን እንፍጠር? ይህንን አስቸጋሪ ወቅትስ እንዴት እንለፈው? ማሰብ ፤ ማሰብ አሁንም ማስብ ከዚያም በድርጊት መቋጨት ወቅቱ የሚጠብቀው ተግባራችን ነው።

በትግሉ እሳት ውስጥ ለምታልፉ ለሃገራችን  የኢትዬጵያ ልጆች፤-   ውድ ወንድሞቻችን ፤ እህቶቻችን ፤ እናቶቻቸን፤ አባቶቻችን እንዲሁም ልጆቻችን የምታልፉበትን እሳት እየተመለከትን በሚደርስባችሁ በደልና አፓርታይድን ባስናቀ የግፍ መዓት ውስጣችን እየነደደ አለን ግን አብረናችሁ ነን።አንዳንድ ጊዜስ ውጭ ሆኖ ከመቃጠል አብሮ በሳቱ ውስጥ ማለፍ ሳይሻል አይቀርም ይሁን እንጅ ውጭ ሆኖ በእሳት ውስጥ ለሚያልፈው ህዝብ ሃሳብ መስጠት ህሊናንና የሚፈትኑ የሞራል ጥያቄን የሚያጭሩ ሁኔታዎች ቢኖሩም ምንም ማድረግ አይቻልም ሃሳብ ከመስጠትና  በሚያስፈልገው አብሮ ከመቆም ውጭ ሌላ አማራጭ የለንም።

በዚህ አጭር ጽሁፍ ላማሳሰብ የምንወደው ወጣቶቹ ብሩህ የሆነውን አዕምሮአችሁን በመጠቀም እስካሁን ባደረጋችኋቸው እንቅስቃሴዎች  እንዳስደመማችሁን ልንነግራችሁ እንውዳለን  ለዚህ ምስክር የሚሆነን  በቅርቡ በአማራ በኦሮሚያ የተደረጉት ሰላማዊ ሰልፎች ናቸው እጅግ የሚያስደንቁ፤ ኢትዬጵያዊ ጨዋነትን የተሞሉ ፤ ብስለት የታየባቸው ነበሩ በዚህም ስራ ልትኰሩ ይገባል ይሁን እንጅ ባገኛችኋቸው ድሎች በመስከር ወደ ፍጻሜው ከመገስገስ እንዳትዘናጉ እጅግ ጥንቃቄ ያሻል ። የወደፊቱን  ትግላችሁንም  እንዲሁ በቅንብሮች ረቂቅነት የህዝቡን ኃይል በአግባቡ መጠቀም፤ ጥይቶችን በማክሸፍ የተጎጅውን ቁጥር በመቀነስ፤ በተለያዬ ባሉ አውራጃዎችና ወረዳዎች የማያቋርጥና የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር ጉጂሌውን ማስጨነቅ ይቻላል ይህ አሰራር በትራንስፖርት የሚሯሯጠውን የወያኔ ደም አፍሳሽ አጋንንት ለመገደብ በእጅጉ ይረዳል ሲያልፍም ጫናው ከበዛም ዱርቤቴ ለማለት ነፃ መሬት ለማግኘት ዓይነተኛ መፍትሄ ነው። ከዚህ ወዲያ ወዴት ይደረሳል? እስከመቼ ስደት? እስከመቼስ ለባንዳ ልጆች ተሽቆጥቁጠን? በቃ ምን ይደረግ ይህ ተጋድሎ በዘመናችን ሰርተነው እንድናልፍ ታሪክ የጣለብን የቤት ስራችን ነው።  እናም ጌም ስራባቸው እንጅ በከንቱ ደምህን እያፈሰሱ ለአጋንንታቸው መስዋዕት እንዲያደርጉህ አትፍቀድላቸው አንተ እኰ የዬቶር ልጅ ነህ ደግሞም ከእንግዲህ ወደ ኋላ መመለስ የባርነት ሰንሰለታችንን ለማጥበቅ እንጅ ሌላ መፍትሄ የለውም  እናም በርቱ!!!።

ለኦርቶዶክስና ፕሮቴስታንት መሪዎችና ተከታዬች፤  ይህ ወቅት በመዘናጋትና በቸልተኝነት ለህወሃት መሰሪ ፕሮፐጋንዳ ታልፈን የምንሰጥበት ጊዜ እንዳይሆን አጥብቀ የምንመረምርበት ወቅት ነው መጽሃፉም የሚለው እንኳንስ የፖለቲከኞችን መሰሪነት ትንቢትን ሳይቀር መርምሩ ነው የሚለው። እውነት ወዴት ነው? ህዝባችን ሲገደል ዝም፤ ሲታሰር ዝም፤ ሲሰደድ ዝም፤ ሃገር ያለ ሃይ ባይ ስትዘረፍ ዝም የትኛው የክርስትና መጽሃፍ ነው ይህንን የሚያስተምረን? ነው ወይስ ፍርሃትን በመንፈሳዊ ካባ መሸፈን? የዓለም መድኃኒት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ላይ የወጣበት ጥጉ ነገር እኮ እውነት ነው እንዲያውም ተልዕኮውን ሲገልጽም እውነት እኔ ነኝ ስለ እውነትም ልመሰክር መጣሁ ነው ያለው ። ታዲያ ተከታዬቹ ወዴት ነን? እውሸት በምድራችን ዙፋን ተክሎ ሲንጎራደድ የዕምነት አባቶች ምን ማለት ነው የሚጠበቅብን? ምርጥ ክራቫት አድርጎ አትሮኑ ላይ እየተጎማለሉ ፓስተር እገሌ እየተባሉ በስብከት ብልጠት የግል ዝናን ማስጠበቅ ነው እንዴ የዕምነት መሪ መሆን?። ወይስ መስቀል ጨብጦ፤ ጢምን አንዥርግጎና ረጅም ቀሚስ ለብሶ አባ መባል? ወዴት ነው እውነት ? ይህ ጥያቄአችን ከዕውነት ጋር ወግነው ዋጋ እየከፈሉ ያሉትን የዕምነት አባቶች አይመለከትም የመንፈስን ነገር ጥለው በስጋ ከገዳዬች ጋር ለተዛመዱት እንጅ!። ጀርመናዊው ፓስተር ደየትሪክ ቦንሆፈር  ለሂትለር ጥይት ደረቱን አሳልፎ የሰጠው አይሁዶች ለምን ይገደላሉ ? ሰው መግደል ኃጢአት ነው በማለቱ ነው። እንደኛው የሰማይም የምድርም አርበኛ እንደሆኑት እንደ  አቡነ ጴጥሮስ  ማለት ነው።

እያልን ያለነው ልክ እንደ ሙስሊም ወንድሞቻችን የህወሃት ሴራ ገብቶአችሁ ታገሉ፤ ለዕውነት ቁሙ፤  ለምትመሩት ህዝብ የዕውነት እረኝነታችሁን አሳዩ ነው። የስልጣኑን ወንበር ይዘው የሚዘርፉትን ፤ የዘር ማጽዳት ወንጀል የሚፈጽሙትን፤ ሃገር እየቆራረሱ የሚሸጡትን ህሊና ቢስ የሴኦል መልዕክተኞችን ፃ መንፈስ ርኩስ በሉልን ነው። ይህ የጨለማ ወቅት ያልፍና እንዳንተዛዘብ!። ዕውነተኞቹ የዕምነት መሪዎች ግን እንደ ንጉስ ኢዬሳፍጥ እናንተም የምትመሩትን ህዝብም በጾም የምትጠምዱበት ጊዜ ነው እንላለን።

ለተወደድከው የትግራይ ህዝብ፤  ወቅቱ ለሁላችንም አስተውለን የምንራመድበት ሃገርም እንደ ሃገር ህዝብም እንደ ህዝብ እንዲቀጥሉ የየድርሻችን የምንወጣበት እጅግ ወሳኝ ወቅት ላይ እንገኛለን።  በህወሃት ስም በበቀል የተደራጁት የባንዳ ልጆች ትላንትና ኢትዬጵያ የምትባል ሃገር እንድትኖረን ከጠላት ጋር የተዋደቁትን የአባቶችህን ታሪክ ለማደበስና የባዕዳን ጌቶቻቸውን የቆዬ ሃገርህንና ታሪክህን የማጥፋት ህልም ለማስፈጸም   አንተንም እንደሌባ መሸሸጊያ ዋሻ ለመጠቀም ሲል ብቻ ባቀደው ስውር የአጀንዳው ቀለበት ውስጥ እንድትገባ ተደርገሃል ይህንንም ስልት ለማስፈጸም ከቀሪው የኢትዬጵያ እህትና ወንድሞችህ መለየት አንዱ የውንብድና ዘዴው ነው  በዚህ መሰሪነቱም ቀን ከሌት እየሰራ ከወጥመዱ እንዳትላወስ ተደርገሃል ለዚህ እኩይ ገመድ መበጠሻው ስለት ደግሞ ከቀሪ የኢትዬጵያ ወንድሞችህ ጋር ማበር ነው ። የእንግዴ ልጅ ልትላቸው ይገባል።

እነዚህ የአንተ የሆነ ባህል፤ ዕምነት የሌላቸው ወሮበላ ወዲኒዎች በስምህ ከጉያህ ይውጡ እንጅ በየትኛውም መለኪያ ቢሆን አንተን ጨዋውንና እውነተኛውን የትግራይ ህዝብ ይወክላሉ ብለን አናምንም። ምንህ ይመስላቸዋል? አንተ የኢትዬጵያዊነት መሰረት ነህ እነርሱ ደግሞ ኢትዬጵያ የምትባል ሃገር የለችም የሚል ስብከት ነው ያላቸው ምክኒያቱም ኢትዬጵያ የምትባል ሃገር ከቀጠለች የዓድዋ ድል ሊታሰብ ነው፤ የእነምኒሊክ የነአሉላ የእነባልቻ የሌሎችም ጅግኖች ስም ሊታወስ ነው ይህ ደግሞ ለባንዳ ልጆችና ለጌቶቻቸው ስድብ ነው ውርደት ነው አንገት መድፋት ነው ስለዚህ የድል በዓሎቻቸን ሲከበሩ እንዳያዪ የጀግኖቻችን ስም ሲጠራ እንዳይሰሙ ኢትዬጵያ የምትባል ሃገር ትፍረስ ግልግል!። በዕምነት ነው የሚመስሉህ ? በጭራሽ! በዚህ በኩልማ  የእምነትህ መሰረት የሆነውን የኢትዬጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን አከርካሪዋን ሰብረነዋል እያሉ በየአደባባዪ በሳጥናኤል መንፈስ እየፎከሩብን ነው። እነርሱ ስልጣን ላይ ስላሉ የድህነት ቀንበር ከላይህ ተሰብሮአል? ውሸት ነው  የሃገሪቱ ሃብት የሚንከባለለው በአንድ የዘር ትሥስር በመሰሪነት ቃልኪዳን በተጋመዱ የጨለማ ሰዎች መሃከል መሆኑን ሁሉም ኢትዬጵያዊ ያውቃል ። ምናቸው ነው የተረፈህ ከክፉ ስማቸው በቀር? እናም በቃችሁ ልትላቸው ይገባሃል።

ሰፊው የትግራይ ህዝብ ሆይ እመነን የአማራ ህዝብ ይወድሃል፤ የኦሮሞ ህዝብ ይወድሃል፤ ሱማሌው፤ ጉራጌው ሌላውም እንዲሁ ይወድሃል!። አዎ እንወድሃለን። ስማን! ከእነዚህ ወንበዴዎች መለየትህን ግን አውጅ!። ከወንድሞችህም ጋር ተባብረህ ቁም!። አሉላ ጀግናችን ነው፤ ዬሃንስ የእኛ መሪ ናቸው ሌላው ቀርቶ በኢትዬጵያዊነቱ ምክኒያት ብቻ ከህወሃት ባንዳዎች ተነጥሎ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ጀግናው ኃየሎ ም የእኛ ጀግና ነው። ከአዲሱ ትውልድ የፈለቁት እነ አብርሃ ደስታ የእኛ ጀግኖች ናቸው። እነ ገ/ መድህን አርአያ፤ ስዬ አብርሃ፤ ገብሩ አስራት እና ሌሎችም ወንድሞቻችን ህወሃት ለማንም የማይጠቅም ከሃዲ ቡድን መሆኑን እየመሰከሩ ከሌለው ኢትዬጵያዊው ወገናችው ጎን ከቆሙ ውለው አድረዋል የነዚህን ልጆችህን ምክር ስማ!።  በቅርቡ ም የትግራይ ልጆች ተሰባሰበው ያወጡት መግለጫ መልካም ጅምር ነውና አብረሃቸው ልትቆም ይገባሃል።

ድል ለኢትዬጵያ ሰፊ ህዝብ!!!

እግዚአብሄር ኢትዬጵያን ይባርክ

በስራኤል ሃገር ከምንገኝ የጎንደር ተዎላጆች ማህበር

 

የትግሬ-ወያኔ የዐማራ እና የኦሮሞ ነገዶችን ሕዝብ ጨርሶ ለማጥፋት ያቀደው ሚስጢራዊ አዲስሤራ –ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

$
0
0

            ማክሰኞ ነሐሴ ፲ ቀን ፪ሺህ፰  ዓ.ም.             ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፳፪

Moresh-901.jpgላለፉት 25 ዓመታት የትግሬ-ወያኔ በሕዝብ ላይ የፈጸመው ግፍና በደል ከመጠን በላይ በመሆኑ፣ ሕዝቡን ለእምቢተኝነት አነሳስቷል። ይህ ግፍና በደል መጠን የለሽ በመሆኑ፣ በአገሪቱ ልዩ ልዩ ክፍሎች፣ በተለይም በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋ፣ በወሎ፣ በሐረርጌ፣ በአርሲና በወለጋ ክፍለ-ሀገሮች የሚኖረው ሕዝብ፣ የትግሬ-ወያኔ «ለብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ዕኩልነት» ሲል «አመጣሁት» ያለውን «ሕገ-መንግሥት» የማይቀበለው መሆኑንና፣ የዚሁ  «ሕገ-መንግሥት» ተብየ መገለጫ የሆነውን ሠንደቅ ከተሰቀለበት በማውረድ፣ ከጥንት ጀምሮ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት መገለጫ፣ የነፃነት ቀንዲል የሆነችው ሠንደቅ ከፍ-ብላ እንድትውለበልብ እያደረገ መሆኑ በግልጽ ተስተውሏል። ይህም የትግሬ-ወያኔ አመጣሁት ያለው ዕኩልነትና የነገዶች አንድነት ውሸት መሆኑን፣ ባንፃሩ ግን የትግሬ-ወያኔ የውስጥ ቅኝ ገዥ ኃይል እንደሆነ፣ በተከታታይ በተደረጉት የሕዝባዊ እንቢተኝነት ሰላማዊ ሰልፎች በግልጽ ታይቷል።

ይህ የሕዝብ አመጽ ያርበደበደው የትግሬ-ወያኔ ቡድን፣ የሚይዝ የሚጨብጠውን በማጣቱ፣ የእርሱ ምርኮኛ የሆነውንና በጥቅማጥቅም የገዛውን የትግራይ ትውልድ በነቂስ አስታጥቆ፣ በዐማራና በኦሮሞ ነገዶች ሕዝብ ላይ ለመዝመት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስተማማኝ ከሆኑ የውስጥ ምንጮቻችን ያገኘናቸው መረጃዎች ያሳያሉ። የትግሬ-ወያኔ ከሚያደርገው ሠፊ የጥፋት ዝግጅቶች ውስጥ፣ የትግራይን ትውልድ «በትግልህ ያገኘኸውን ልዩ መብትና ነፃነት፣ ትምክተኞች፣ ነፍጠኞች፣ የድሮው ሥርዓት አራማጆችና ዐማሮች ሊነጥቁህ ነውና ዐማራን ለማጥፋት ዝመት፣ ተንቀሳቀስ» በማለት፣ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምት፣ በአርማጭሆ ነዋሪዎች ላይ ክተት አውጇል። በአጠቃላይም በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋና በወሎ የዐማራ ነገድ ሕዝብ ላይ መጠነ ሠፊ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመፈጸም ዝግጅቱን አጠናቋል። በመሆኑም ሰሞኑን በጎጃምና በጎንደር የተለያዩ ከተሞችና ገጠሮች ቅጥር የነፍሰ ገዳይ ቡድኖችን በማሰማራት ሌሊት ሌሊት ወጣቱን እየፈነ ወደ ማሰቃያ እስር ቤቶቹ እያስገባ መሆኑ ታውቋል።

ይህ ድርጊቱ ፍላጎቱን ሙሉ በሙሉ ሊሳካለት እንደማይችል በመረዳት፣ በመላ ኢትዮጵያ የሚያካሂደው ሌላም ሠፊ የጥፋት ዕቅድ አቅዶ ለተግባራዊነቱ በጥድፊያ እየሠራ መሆኑ እየተሰማ ነው። ይህም መጠነ ሠፊ የሆነ ጥፋት ያነጣጠረው በዐማራና በኦሮሞ ነገዶች ሕዝብ ላይ እንደሆነ ታውቋል። የትግሬ-ወያኔ በእነዚህ ነገዶች ሕዝብ ላይ የጥፋት ተልዕኮውን ለመወጣት ያቀደው ዕቅድ፣ «በዐረብ ኢሚሪቶችና በሻዕቢያ የሚታገዙ አሸባሪዎች፣ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ እየተንቀሳቀሱ ነው» የሚለውን ሀሳብ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ፣ በተለይም ሽብርተኝነት ለመዋጋት በሚል ሸሪክ የሆነውን የምዕራቡን ዓለምና የአሜሪካንን ልብ ለማማለል እንደሆነ ይገመታል። በዚህ ረገድ በቅርብ ቀናት ውስጥ የትግሬ-ወያኔ በሐረር፣ በድሬደዋ፣ በጎንደር፣ በባሕር ዳርና መሰል ከተሞች፣ የሕዝብ ክምችት በሚበዛባቸው ቦታዎች፣ በመንግሥታዊ ተቋሞች፣ በመገናኛ አውታሮች ወዘተርፈ ፈንጅ በማፈንዳት እኩይ ዓላማውን በተግባር እንደሚያውል ውስጥ አዋቂዎች አስጠንቅቀዋል። ፈንጂዎችን ራሱ አፈንድቶ፣ «የዐማራ እና የኦሮሞ ጽንፈኞች እንዲህ አደረጉ» በማለት ለደጋፊዎቹ  የተቀነባበረ የሤራ መረጃ በማቅረብ፣ «ሕገ-መንግሥት» ተብየውን አግዶ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ወታደራዊ አገዛዝ በማወጅ፣ በሁሉም ቦታዎች ለወያኔ ጄኔራሎች የመግደልና የማሰር ሥልጣን በመስጠት በዐማራውና በኦሮሞው ነገዶች ሕዝብ ላይ መጠነ ሠፊና አሰቃቂ ዕልቂት ለመፈጸም ቁርጠኛ አቋም መያዙ ታውቋል።

በሰኔ 1980 ዓ.ም. «ነፃ ላወጣህ መጣሁ» ባለውና በራሱ ነገድ በሆነው የሀውዜን ከተማ ነዋሪ ሕዝብ ላይ ያን የመሰለ የተቀነባበረ ሤራ ሠርቶ ሕዝብ ያስጨረሰ ድርጅት፣ «ጠላቶቼ ናቸው» ባላቸው የዐማራና የኦሮሞ ነገድ ሕዝብ ላይ ይህን ዓይነቱን ድርጊት አያቅድም፣ አይፈጽምም፣ አያደርጉትም፣ አይሆንም የሚያሰኝ አመክንዮ አይኖርም። ኢትዮጵያዊ የሆኑትንና «ለትግሬ-ወያኔ ዓላማ አንገዝም፣ አባልም አንሆንም» ያሉትን የትግራይ ልጆች፣ «አባሎቼ ናቸው» የሚል የተቀነባበረ የሐሰት መረጃ፣ ለደርግ የመረጃ አካላት እያቀበለ ወገኖቹን ያስጨፈጨፈ ድርጅት ይህን አያስብም አይባልም። በሂደት እንዳስተዋልነው፣ ወያኔ «አደርገዋለሁ፣ አጠፋዋለሁ» ብሎ ያቀደውንና ያለው በተግባር ከመፈጸም ወደ ኋላ ያለበት አንድም አጋጣሚ አላየንም። ይህንም እኩይ ድርጊት አያደርገውም ለማለት የሚያስችል ምክንያት ለማቅረብ አስቸጋሪ ነው።

የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን፣ ዐማራንና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን አጠፋለሁ ብሎ አቅዶ መነሳቱ ይታወቃል። በዕቅዱ መሠረትም 5 ሚሊዮን ዐማራ አጠፋ። የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አመራርን ከሦሥት ከፈለ፥ የአገር ቤትና ስደተኛ ሲኖዶሶች እንዲሁም ገለልተኛ በሚል። የሃይማኖቱ ነባር ተቋሞችን፣ ለምሣሌ ያህል፥ የዋልድባን፣ የዝቋላ አቦን እና የማኅበረሥላሴን ገዳማትን አቃጠለ፤ ቅጥረ ግቢያቸውን መነጠረ። የሃይማኖት አባቶችን አሰደደ። ቱባ ባለሥልጣኖቹ ዐባይ ፀሐየ፤ ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ ሣሞራ የኑስ ሌሎችም በአደባባይ፣ «ዐማራና ኦርቶዶክሱን አከርካሪውን ሰብረነዋል፣» «ገድለን ቀብረነዋል» ማለታቸውን አንዘነጋም። እናም ባለፉት 25 ዓመታት ገድለው ካልጨረሱት ውስጥ የቀረውን የዐማራና የኦሮሞን ነገዶች ሕዝብ «አስቸኳይ ወታደራዊ» አገዛዝ በማወጅ ሊጨርሱት ቁርጥ ሀሳብ ማድረጋቸውን የዐማራውና የኦሮሞው ነገድ አባሎች ለአፍታም መጠራጠር አይኖርባቸውም። ስለሆነም፣ የትግሬ-ወያኔ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ወደ ጥፋት ተልዕኮው ሳይገባ፣ ዐማሮችና ኦሮሞዎች ዕቅዱን ለማክሸፍ መተባበር ይጠበቅባቸዋል።

ከሁሉም በላይ «ሺህ ጋን ቢታለብ ወይ በገሌ» እንዳለችው ድመት፣ ዐማራው በብሔርተኞቹ ድርጅቶች በቀና ስለማይታይ፣ ልጆቹ በመካከላቸው አለን የሚሏቸውን ጥቃቅን ልዩነቶች በማርገብ፣ በአንድነት በመቆም ለወገናችን መከታ መሆን ይጠበቅብናል። የዐማራው ምሁራንና ፖለቲካኞች በአንድነት መቆም፣ የአንድነት ኃይሉን ለተፈላጊው አጠቃላይ የኢትዮጵያውያን አንድነት ጽኑ መሠረት ስለሚሆን፣ የዐማራው ምሁራን በቅድሚያ የነገዳቸውን አንድነት ዕውን በማድረግ፣ በሌሎች አቻ ቡድኖችና ድርጅቶች ላይ መልካም ተጽዕኖ ማሳደር ይጠበቅባቸዋል። ይህን ለማድረግ ስበቦችን መደርደር አስፈላጊ አይደለም። በወገናችን አንገት ላይ ሳንጃ ተጥሏል፤ በግንባርና ደረቱ ላይ አፈሙዝ ተደግኗል። ስለዚህ ይህ ጊዜ አይሰጥምና በዐማራ ስም የተደራጃችሁ ድርጅቶች ከያላችሁበት «አለን» ብላችሁ በጋራ የምትሠሩበት መንገድ ካሁኑ ካልጀመራችሁ፣ ይህንም ለወገናችሁ በግልጽ ካላሳያችሁ፣ የጥፋቱ አካል እንጂ፣ የመፍትሔው አካል ናችሁ ብሎ ማኅበረሰቡም ሆነ ታሪክ  ሊያወሳችሁ እንደማይችል በእርግጠኝነት መናገር ድፍረት አይሆንም። ስለሆነም ሁላችንም ለዐማራው ኅብረትና አንድነት ኅሊናችን ከፍተን በቅንነት እንነሳ! በዚህ የመከራ ጊዜ የዐማራው ልሂቅ በአንድነት ቆሞ፣ ለወገኖቹ ቤዛ ካልሆነ ምንጊዜም ዐማራው አንድ ይሆናል ለማለት ያስቸግራል። እንኳን የአንድ ታላቅና ታሪካዊ ነገድ ልጆች ቀርቶ፣ በክረምት እባብና ጓጉንቼር በአንድ ጉድጓድ ይኖራሉ። ይህ ክፉ የወያኔ ዘመን ዐማራውን ቀርቶ፣ ዐማራና ኦሮሞውን በአንድ ካላሰላለፈ የኢትዮጵያ አንድነት ርቆ የተሰቀለ ባዶ ተስፋ ከመሆን አያልፍም።

 

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

ዐማራነት ነፃነት፣ ዕኩልነት አንድነት ነው!

ኢትዮጵያ በቆራጥና ጀግና ልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!

 

የፍራንክፈርት ከተማ ባሕርዳርንና ጎንደርን መስላ ዋለች! –ከ ኆኅተብርሃን ጌጡ

$
0
0

-ለ 25 ዓመታት የተገነባዉ የዘረኝነት ግንብ በመፈራረስ ዋዜማ ላይ


ቀኑ ዓርብ ነሐሴ 12 ቀን 2016 ነበር።  የትዕይንተ ሕዝቡ መገናኛ ማዕከል ቦታ ዋናዉ ባቡር ጣቢያ አካባቢ ነዉ። በተጠቀሰዉ የሰልፉ መጀመሪያ ሰዓት ኢትዮጵያዉያን አካባቢዉን አጥለቀለቁት። ፍራንክፈርት ከተማ በአረንጟዴ፣ ቢጫና ቀይ ኅብረ-ቀለም ባለዉ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ደምቃና ተዉባ ትታያለች። ከሁሉም የጀርመን ከተሞች በመምጣት ፍራንክፈርትን ከኢትዮጵያ  ከተሞች አንደኛዋ አስመስሏት ዉሏል። መነኮሳትና ቀሳዉስቱም ልብሰተክህኗቸዉን ደርበዉ ሰልፉን አድምቀዉታል። የሴቶች እህቶቻችንም ቁጥር ከሁልጊዜዉ በተለየ ቁጥሩ አይሎ የታየበት ብቻ ሳይሆን፣ ቁጭትና ሀገራዊ ስሜታቸዉም ከፊታቸዉ ላይ ይነበብበት የነበረ ሰልፍ ነዉ። የሰልፉ መጀመሪያ ፍራንክፈርት ዋናዉ ባቡር ጣቢያ ሆኖ፣ መዳረሻዉ ሄሰን ቲሌቪዥን ጣቢያ  ( Hessischer Rundfunk) እንዲሆን ነዉ የተዘጋጀዉ። ይህም የሆነበት ምክንያት የትዕይንተ ሕዝቡ (የሰላማዊ ሰልፉ) መደረግ ዓላማዎች ለጀርመን ሕዝብ በመገናኛ ብዙኃን እንዲተላለፍ ለማድረግ የታሰበበት እንደሆነ የሰልፉ አስተባባሪዎች በአፅንኦት ይናገራሉ። ካለፈ ተመክሮ በመነሳት ሚዲያዎች ወደ እኛ የማይመጡ ከሆነ፣ እኛ ወደ ሚዲያዎቹ በመሄድ የሰልፉ ዓላማ ወደምንኖርበት ሀገር ሕዝብ ጆሮ መድረስ ስላለበት ሂደን በራቸዉን መክፈት አለብን በሚል ዘዴ የታሰበ እንደነበር አዘጋጆቹ ጨምረዉ ይናገራሉ። የዚህ ፅሁፍ አቅራቢም የዓይን ምስክርነት ይሰጥበታል። ይህ ብቻም አይደለም። የሰላማዊ ሰልፉ መነሻና መድረሻ የቦታ ርቀት ወደ  6 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ ሲሆን በዚህ ረዥም የእግር ጉዞ ግራና ቀኝ ሰልፈኛዉን እየተመለከተ ለሚገኘዉ የከተማዋ ኗሪ በጀርመንኛና በእንግሊዘኛ ቑንቑዎች የተዘጋጁትን  የሰልፉን ዓላማዎች የሚገልፁትን መፈክሮች በበቂም ለማደል እንደታቀደ ጊዜዉ አጭር ቢሆንም የታሰበበት ሰልፍ እንደነበርና እንደተሳካም አዘጋጆቹ አበክረዉ ይናገራሉ። ይህም በመሆኑ በጀርመንኛ ቑንቑ ተፅፎ በተበተነዉ ፅሁፍ ማለትም … Wie lange werden Diktatoren, die die eigene Bevolkerung umbringen noch von Deutschland und der EU unterstutzt ???? …. የገዛ ሕዝባቸዉን ለሚገሉና ለሚጨፈጭፉ አምባገነኖች ማለትም እንደ ኢትዮጵያ ላሉ መንግሥታት የጀርመን መንግሥትና የኤዉሮፓ ህብረት እስከ መቼ ነዉ እርዳታቸዉንና ድጋፋቸዉን የሚቀጥሉት? የተሰኙ መልዕክቶች ተላልፈዋል። ይህ ዓይነቱ መልዕክትም ታክስ ከፋዩ ሕዝብ የሀገሩን መንግሥት ለምን ብሎ እንዲጠይቅ የሚያስችለዉ አቀራረብ የሰላማዊ ሰልፉ አቅም መሆኑን በተግባር ለማሳየት ተሞክሯል። በዕለቱም ምሽት በጀርመን አገር ሁለተኛዉና ትልቁ የቴሌቪዥን ጣቢያ ማለትም ZDF (Zweites Deutsches Fernsehen)  እና ሰልፉ የተካሄደበት የሄሰን ክፍለ ሀገር ዋንኛ የቴሌቪዥን ጣቢያ በሆነዉ ሄሲሼር ሩንድፉንክ (Hessischer Rundfunk)  ኢትዮጵያዉያን  ለምን ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ እንዳስፈለጋቸዉ ተገቢ በሆነ መንገድ በዜና መልክ የሚዲያ ሽፋን አግኝቶ፣ ለጀርመን ሕዝብ መቅረብ ችሏል። ዓላማዉም ይህ ነበር እንጅ ለመዋጋት አልነበረም።

ታዲያ የሰላማዊዉን ሰልፍ ዜና ላዳመጠና የሰልፉን የትዕይንተ ሕዝብ ትርጉም ምንነት ከመነሻና እስከ መዳረሻ ለተከታተለ፣ ኢትዮጵያዊ ብዙ ነገሮች በአእምሮው ብልጭ ይሉበታል። በመጀመሪያ ደረጃ ያን ያህል ረዥም መንገድ ሰልፈኛዉ ሲጟዝ ፖሊስ ግራና ቀኝ ቆሞ የመኪና መንገዶች ሰልፈኛዉ እስኪያልፍ እየተዘጉ ነዉ። ዲሞክራሲ ባደገበት አገር ሕዝባዊ ሰልፍ ከብር አለዉ። አሽባሪዎች ተብለን አልተፈረጅንም። በሻዕቢያ ተላላኪነትም አልተጠረጠርንም። የአጋዚ ጦር በቦታዉ ስላልነበር መሞት ቀርቶ መገፍተር የደረሰበት ሰልፈኛም አልነበረም። አደለም መገፍተር በግልምጫ የታየም አልነበረም። እነሱ በቦታዉ ኖረዉ ቢሆን ኖሮ፣ ፍራንክፈርት በሚገኘዉ የሕወሓት/ኢሕአዴግ ቆንስል አጠገብ ሰልፈኛዉ ሲያልፍ  አንድ ቆራጥ ወጣት ኢትዮጵያዊ የእነሱን ኦፊሴላዊ ሰንደቅ ዓላማ አውርዶ፣ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከቆንስላዉ ቢሮ  ጎን የመስቀል እርምጃ ሲወስድና ሲያዉለበልብ፣ ያለምንም ጥርጥር ቢያንስ መጠነኛ የሰዉ ሕይወት ማለፉ አይቀሬ ነበር። እና ማደግና የዲሞክራሲ ማበብ ለሰልፍም ሆነ ለሕዝባዊ ጥያቄዎች መልሱ ጥይት አይደለም። የእኛ መሪዎች የዲሞክራሲን ቃል ባፋቸዉ ደጋግመዉ ይጠሩታል እንጅ ከተግባሩ ጋር ግን አይተዋወቁም። ማወቅም አይፈልጉም።

ለሃያ አምስት ዓመታት የተገነባዉ የዘረኝነት ግንብ በመፍረስ ዋዜማ ላይ እንደሚገኝ ኢትዮጵያ ዉስጥም ሆነ በዉጭ አገር ከሚኖረዉ ሕዝባችን አንደበት የሚነገረዉ የሰሞኑ የሰላማዊ ሰልፎች መልዕክት አንድ እራሱን የቻለ የምሥራች ዜና ነዉ። በዕለቱ በፍራንክፈርቱ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ይስተጋቡ ከነበሩት መፈክሮች መካከልም …አማራም፣ ኦሮሞም አንድ ነዉ፣ የጋራ ሀገሩም ኢትዮጵያ ነች፣ ያለፈዉ አኩሪም ሆነ አሳፋሪ ታሪካችን የጋራችን እንጅ፣ የአንድ ወገን ዕዳ አይደለም፣ በየቦታዉ የሚነሱ የማንነት ጥያቄዎች በሕዝብ ይሁንታ ይፈታሉ እንጅ፣ በጫካዉ የወያኔ ሕግ አይዳኙም፣ የፖለቲካ ደመኛችን ወያኔ እንጅ፣ የትግራይ ሕዝብ ምንጊዜም ወገናችን ነዉ ወዘተ…. የተሰኙ መፈክሮች በአማርኛና በኦሮሞኛ ቑንቑዎች ሲስተጋቡ ዉለዋል። ያለምንም ጥርጥር ኢትዮጵያዊነት አሽንፎ እየወጣ ነዉ። ትናንት ለጎሪጥ በመተያየት ሁሉም በየፊናዉ ያደርገዉ የነበረዉ ሰልፍ ቀርቶ፣ ሁላችንም በኢትዮጵያዊነታችን ትዕይንተ ሕዝብ ስናደርግ ከዚህ የበለጠ ገዥዉን መደብ የሚያሸማቅቅ የፖለቲካ ድል ምን አለ?  የሃያ አምስት ዓመቱ የፖለቲካ መዘዉር ኢትዮጵያዊነት እንዲኮስስ ተደርጎ፣ በምትኩ፤ ኦሮሞነት፣ አማራነት፣ ሱማሌነት፣ ትግሬነት፣ ስልጤነት….ወዘተ እንዲነግሱ በማድረግ ኢትዮጵያዊነታችን ሆን ተብሎ  እንዲደበዝዝ  ስዉር የፖለቲካ ደባ ተሰርቷል።  ይህን ዘገባ እያዘጋጀሁ እያለሁ ጎረምሳዉ የመንግሥት የኮሜኒኬሽን ሚኒስትር አቶ ጌታቸዉ ረዳ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጥ ማለትም በእሱ አነጋገር በጣም ተናዶ፣ (… እሳትና ጭድ የሆኑ አስተሳሰቦች  ሁላችንም አንድ ነን በተለይም አማራም፣ ኦሮሞም አንድ ነዉ)  የሚለዉ የወቅቱ የኢትዮጵያዊነትን አሸንፎ የመዉጣት ድል የሚያንፀባርቀዉ መልዕክት … እንዴት አንድ ሊሆኑ ይችላሉ? በማለት በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ብስጭቱ ከፊቱ ላይ ይነበብ ነበር። ጋዜጠኞቹ ሰዉየዉን እንዴት ይመለከቱት እንደነበር ለተከታተለ ሰዉ ይህ ሰዉ በዕዉኑ ጤነኛ ነዉን? ይሉ እንደነበር ያለማጋነን ከፊታቸዉ ማንበብ ይቻላል። ጋዜጠኞቹም አሳዘኑኝ። የሚያምኑበትን ሳይሆን በእንጀራ ምክንያት መንግሥት እንዲባል የሚፈልገዉን  ማዘጋጀት ስላለባቸዉ  መግለጫዉን እየተከታተሉ ለጎሪጥ በመተያየት ይጎሻሸሙ ነበር። እንዳይሳሳቁ ካሜራዉ ያጋልጣቸዋል። የሆድ ሕመም ሆኖባቸዉ፣ የማይቻል የለም ቻሉት። እነሱም አንድ ቀን ነፃ ይወጣሉ። ሁሉም ጋዜጠኞች እስክንድር ነጋንና ተመስገን ደሳለኝን መሆን አይችሉም። እንደ ሻማ ቀልጦ ለሌሎች መብራት የመሆን መስዋዕትነት ግለሰብም ሆነ ትውልድ ቁጥሩ ገፍ አይደለም። ይህ ጥቂቶች የሚታደሉት በደም የሚፃፍ የታሪክ አሻራ ነዉ። መፅሃፉ …የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸዉ… እንደሚለዉ መሆኑ ነዉ። መስዋዕትነቱም እንደዚያዉ ነዉ። ሁሉም አይታደለዉም። አይደፍረዉምም።

የሰሞኑ በየሀገሩ የሚደረጉት ሰላማዊ ሰልፎች የሀገር ቤቱ እንቅስቃሴ ነፀብራቆች መሆናቸዉ ለሁላችንም ግልፅ ነዉ። በዉጭ የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊም የተፈጠረባት ምድር ሀገሩ ፣ የተወለደበት ቤተሰብ፣ ያደገበት ቀዪ ሁሉም አካባቢ በጥይት እየነደደ መሆኑን ጧት ማታ ያስተዉላል። በዓይን በብሌኑ እያየ ለማመን እስከሚያቅተዉ ይከታተላል። እንደ ሰዉ ለሚያስብ አርፎ መቀመጥን አይመርጥም። የወገን ደም እየፈሰሰ በር ዘግቶ መቀመጥ፣ አባባሉ እራሴንም ይጨምራል የኅሊና ቁስል እየሆነ ከመኝታ ያባንናል። በመብት ማስከበርና በነፃነት ጥያቄ ድርድር ባለመኖሩ የሕዝቡ ጥያቄ መብታችን ይከበር ነዉ። ባለብዙ ብሄረሰቧ ሀገር ባንድ ጥቂት አናሳ ቡድን ተቀፍድዳ  እየተገዛች ስለሆነ፣ ይህ ይብቃና የሁላችንም ሀገር መሆኗ በተግባር ይረጋገጥ ነዉ ጥያቄዉ። ገዥዉ መደብ ግን …የብሔረሰቦቿን መብት አስከብሮ ሀገራዊ አንድነትን የሚያጠናክር መንግሥት ከእኛ የተሻለ ሰለሌለና ስለማይመጣም ዝምብላችሁ ሰጥለጥ ብላችሁ ተገዙ…. ነዉ የሚለዉና የግል ጡሩምባዎቹ በሆኑት ኢቲቪና የኢትዮጵያ ራዲዎች ጧት ማታ የሚለፍፈዉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግሞ በኢቲቪ የምትቀርብልን ኢትዮጵያና  እኛ በዓይናችን ብሌን የምንመለከታት መሬት ላይ ያለችው ኢትዮጵያ እናንተ እንደምትነግሩንና እናንተ እንደምታቀርቧት ሆና ስለማናገኛት የጥቂቶች የምድር ገነት ለብዙኃኑ የምድር ሲኦል የሚያደርግ የዘር ፖለቲካ መርሆን አቁሙና ለእኛ ለሁላችን ሀገር የሆነች ኢትዮጵያ ትኑረን ነዉ። ይህ ዕዉን ሊሆን ከቻለ ደግሞ የጥቂቶች ሀገር መዝረፍና በሃያ አራት ሰዓት ሚሊዪነር መሆን የሚችሉበት ዘመን ለያከትም ነዉ። አናሳዉ ቡድን በትረ ሥልጣኑን ለብዙሃኑ ሊያስረክብ ነዉ። አሳዳጁ ተሰዳጅ ሊሆን ነዉ። አሳሪዉ ታሳሪ ሊሆን ሊገደድ ነዉ። አንደኛዉ የበኩር፣ ሌላኛዉ እንደ እንጀራ ልጅ መብት የመታየት መኖር ሊያከትም  ነዉ።  በገዛ ሀገሩ የመንገድ ዳር ለማኝ ሆኖ፣ የሌሎችን ፎቅ የሚቆጥርበትና ወደ ሰማይ አንጋጦ የሚመለከትበት ጊዜ ማክተሚያ ሊደርስ ነዉ። ይህ ግን በሰላም የማይታሰብ ነዉ። ግድያዉ መፍትሄም ባይሆን ለቀጣይነቱ በየቦታዉ ርችቶች እየታዩ ነዉ። አንድ ገበሬ ሽንኩርት ጭኖ ወደ ገበያ ሲገሰግስ አህያዉ ከተማዉ አካባቢ ስትደርስ ለገመችበት። ጭራሽ መንቀሳቀስ አቆመች። ይኽዉ ገበሬ የግድ ካልተራመድሽ ብሎ አህያዋን ባልተወለደ አንጀቱ በዱላ ይቀጠቅጣት ጀመር። ይህን የተመለከተ የአካባቢዉ አልፎ ሂያጅ መንገደኛ …ጌታው እንዲያዉ ለመሆኑ ሕሊና የለህም ተዉ አትቀጥቅጣት፣ ነፍሷ መዉጣት እኮ ነዉ የቀራት ሲለዉ፣  አይ ጌታየ! ኀሊናስ የለኝም ጨርሻለሁ፣  ወደ ገበያ የምወስደዉ ሽንኩርት ብቻ ነዉ የቀረኝ። እሱንም ይኽዉ መንገድ ላይ እያስቀረችዉ ነዉ..? እንዳለዉ ባለጊዜዎች የሚታያቸዉ ሟቹ ሳይሆን የደራዉ የሀገር ዘረፋ ገበያቸዉ ነዉ።

እስኪ ማን ይሙት የአንድ ሀገር ሕዝብ ከዳር እዳር ተንቃስቅሶ ለመብቱና ለነፃነቱ መከበር ከእንግዲህስ ይብቃ ብሎ የመንግሥት ለውጥ እንዲደረግ በሰላማዊ እምቢተኝነት ጥያቄ ሲያቀርብ፣ …ባለቤት የሌላቸዉ አመፆችና እንቃስቃሴዎች በየቦታዉ እየተደረጉ… ብሎ ማፌዝና ስለሆነም መንግሥት ሰላም የማስከበር ሕገመንግሥታዊ ኀላፊነት ስላለበት… በሚል መመሪያ የጅምላ ግድያ በሰላማዊ ሰልፈኛው ላይ ማድረግ ተገቢ ነበርን? ያዉም የሕዝብ ብሶት ወለደኝ ከሚለዉ ኢሕአዴግ። ደግሞስ በአንድ ሀገር እንቅስቃሴ ከሕዝብ በላይ ምንስ አለና ነዉ ባለቤታቸዉ የማይታወቁት እንቅስቃሴዎች በማለት ሕዝባቢዉን አመፅ ለማጣጣልና ቦታ ላለመስጠት መንግሥታዊ ሽወዳ የሚደረገዉና የሚቀለደዉ። በሽወዳ 25 ዓመታት አልፈዋል። ብሔረሶቦችን እርስ በርስ በማጋጨት የሥልጣን ዕድሜን ማራዘም ተችሏል። ግን አሁን ጊዜዉ አከተመ። ማጣፊያዉ አጠረ።  እንዲህ  ዓይነቱ የፖለቲካ ጨዋታ የተበላ ቁማር ሆኗል። ሕዝቡ ኦሮሞም አማራም አንድ ነዉ ብሎ ዘመረ። በቅርብ ጊዜ የምናየዉ ዕዉነታ ቢኖር ኦሮሞዉና አማራዉ ብቻ ሳይሆን አንድነታቸዉን የሚገልጹት፣ በሀገሪቱ የሦሥተኛነትን  ቁጥር ይዞ የሚገኘዉና አኩሪ ታሪክ ያለዉ የትግራይ ሕዝብም  በከንቱ የፈሰሰዉ የኦሮሞ፣ የአማራ ወንድሞቻችን ደም የእኛም ደም ነዉ ብሎ እንደሚነሳና በእሱ ስም የሚነግዱትን የፖለቲካ ነጋዴዎች አቁሙ! ከኢትዮጵያ ሕዝብ የሚነጣጥለንን ስዉር የፖለቲካ ጨዋታ ምዕራፍ ዘግታችሁ ብሔራዊ የአንድነት አጀንዳ ክፈቱ! አለበለዚያ …ዉጉዝ ከመ አርዮስ… ከእናንተ ጋር አይደለንም እንደሚላቸዉ ጥርጣሬ ሊገባን አይገባም። ይህ ዕዉን የሚሆንበትን ጊዜ ለማቃረብ ደግሞ ሁላችንም የየአቅማችንን የቤት ሥራ እንሥራ። ከፋፋይ የዘር ፖለቲካን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከፍነንና ገንዘን እንዳይነሳ አድርገን እንቅበረዉ። ማቅ እናልብሰዉ። ይጥቆር። ያንጊዜ ኢትዮጵያዊነት አብቦ ይፈካል። ኢትዮጵያዊነት ይነግሳል። የገዥዎቻችንም ዓላማ ይከሽፋል። ከሥር መሠረቱም ይናጋል። በየቦታዉ በተደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች መምሕር በቀለ ገርባም ሆነ ኮሎኔል ደመቀ ዘዉዱ ብርቅዬ የነፃነት አርበኞቻችን እንጅ፣ አሽባሪዎች አይደሉም በማለት ድምፁን ከፍ አድርጎ ያስተጋባዉም መልዕክቱ ጥልቅ የሚሆነዉ ለዚህ ነዉ። እነ እስክንድር ነጋ፣ አንዱዓለም አራጌ፣ እነ ተመስገን ደሳለኝ የሰላማዊ ትግል ቀንዲሎች እንጅ የጥፋት ዘመን  መልዕክተኞች አለመሆናቸዉን ሕዝቡ በአንደበቱ ምስክርነቱን የሚቸራቸዉም ለዚህ ነዉ። አብርሃ ደስታ ከእስር ቢፈታም በትግራይ ተወላጅነቱ ሳይወገንለት የሥርዓቱ ሰለባ ሆኖ መሰቃየቱን አብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ የማይዘነጋዉ የቅርብ ጊዜም ትዝታ ነዉ።

በሁሉም ሕዝባዊ የፖለቲካ ጥያቄዎች መንግሥት ገታራ አቑም ባይወስድ ኖሮ፣ ሀገራዊ መፍትሔዉ  በሀገሪቱ የብሔራዊ ዕርቅ መዉረድ ነበር።  ለእራሳቸዉም የመንግሥት ባለሥልጣናትም ሆነ ለሀገሪቱ መድኀንና አንድና አንድ የፖለቲካ ፈዉሱ አሁንም ብሔራዊ ዕርቅ ከሁሉም አማራጮች የቀዳሚነቱን ሥፍራ ከመዉሰድ እንደ ብቸኛ መፍትሄም ባይወሰድ (ስለዘገየ) የአማራጭነቱ ሚና ጉልህ ሥፍራ ይኖረዋል።  ግን የቤተ መንግሥቱ  ወንበር አንድ ጊዜ ከተቀመጡበት ላለመልቀቅ አዚም ያለዉ ይመስለኛል። ኀሊና ይጋርዳል። ዓይን ያዉራል። ለሕዝብ የተገባዉ ቃል ሁሉ ይረሳል። የማሰቢያ ጭንቅላትም ይደፈናል። ለዚህም ነዉ አንድ የወሎ ገበሬ በኢሕአዴግ የሥልጣን መጨበጥ ዋዜማ ሰሞን ነፃ ባወጡት የሰሜን ወሎ አካባቢ በተደረገ ስብሰባ፣…ነፃ አዉጭዎች ነን ካላችሁማ ምን ይደረግ፣ እስኪ ደግሞ እናንተን እንያችሁ… ግን እናንተም አሁን ማር ሆናችሁ ቀርባችሁን በሁዋላ እንደ ደርግ እሬት እንዳትሆኑብን… በማለት ነበር ነቢዩ ገበሬ አስቀድሞ የነገራቸዉ። ወጣም ወረደ፣አልታደልንም። ደም ካልተገበረ በሰላማዊ መንገድ መሠረታዊ  ለዉጥን ማምጣት አልተቻለም። ይህ ዕድል በ 1997 በቅንጅት ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ወቅት አመለጠ። አሁን የፖለቲካ ድርጅቶች ሳይሆኑ ሕዝብ በቃኝ ብሎ ተነሳ። ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ማሳወቅ እንጅ፣ ሕገመንግሥታዊ ፈቃድ መጠየቅ አያስፈልገንም አለ። በሕገመንግሥቱ ላይ የሰፈረዉ ሰንደቅ ዓላማም ሕዝቡ የሚቀበለዉ አይደለም ብሎ ከዳር እስከዳር የቀድሞዉን ባንዲራ ይዞ ወጣ። ባጭሩ በተዘዋዋሪ መንገድ ሕዝቡ ሕገመንግሥቱን እንደማያምንበትና እንደማይቀበለዉም መልዕክቱን አስተላለፈ። ይህ ብቻም ሳይሆን የሀገሪቱ የችግሮቹ ሁሉ ምንጭ ሕገመንግሥቱ ስለሆነ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሕገመንግሥቱን የሀገሪቱ መመሪያ ገዥ ሕግ አድርጎ እንደማይቀበለዉ አሳወቀ። ይሁን እንጅ አሁንም ቢሆን ይኽዉ እኛ በሕገመንግሥታችን የብሔር ብሔረሰቦችን መብት ለማክበር በባንዲራዉ መካከል በተለያዩ ሕብረ ቀላማት አስዉበን የብሔር ብሄረሰቦችን እኩልነት መብት በሚያስከብር መልኩ ያወጣነዉን ሕገመንግሥት በመጣስ ጠባቦችና ትምክህተኞች (ኦሮሞዎችና አማራዎች ለማለት) ጨቁነዉ ሊገዙህ ተነስተዉብሃል የሚል የማደናገሪና ከፋፋይ ቅስቀሳ ከማድረግ ወደሁዋላ እንደማይል ሳይታለም የተፈታ ነዉ። እንዲያዉ ለነገሩ …ዶሮን ሲያታልሏት… ካልሆነ፣ በዓመት አንድ ጊዜ የሰንደቅ ዓላማና የብሔረሰቦች ቀን በዓል እያከበሩ ማስጨፈር  የብሔረሰቦች እኩልነት ተከብሯል ለማለት ያስደፍራል? በዚህ መታለልም ለመገዛት አምችቷል ቢባል ማጋነን አይሆንም።

ምናልባት አንዳንድ የዋሆች የወልቃይት የአማራን የማንነት ጥያቄ ለሰሞኑ እንቃስቃሴ እንደ ምክንያት ሊቆጥሩት ይችላሉ። የወልቃይት ኗሪዎች ቀያቸዉን ከተነጠቁበት ጊዜ ጀምሮ በየማሳቸዉ እያንጎራጉሩ፣

እናንተም እረሱ እኛም እናርሳለን፣

መኽር (ሰብል) ሰብሳቢዉን አብረን እናያለን።

እያሉ የዉስጥ አንጀታቸዉ አርሮ ዓመታትን አሳልፈዋል። ግን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያጤነዉ የሚገባዉ፣ወያኔዎች ከኢትዮጵያዊነት ሌላ  የተለየ አመለካከት ከሌላቸዉ መጀመሪያዉኑ ገና ጫካ እያሉ፣ ለምን ከዉጭ አገር ጋር ወልቃይትን ወደ ትግራይ በማጠቃለል ለምሳሌ (ከሱዳን) ወሰን አስፈለጋቸዉ? መንግሥት ከሆኑ በሁዋላስ ለምን በትግራይና በጎንደር መካከል ወሰኑ ወደ ቀድሞዉ (ተከዜ) እንዲመለስ አላደረጉም? ጎንደርም፣ ትግራይም የኢትዮጵያ ግዛቶች ናቸዉ የሚል ዕምነት ቢኖራቸዉ ኖሮ፣ ይህ ጥያቄ ይህን ያህል ደም አፋሳሽ መሆን አልነበረበትም። አሁንም የተደበቀ ዓላማ እንዳላቸዉ ለአንዳፍታም መጠራጠር የማያስፈልገዉ እዉነታ ነዉ። ወጣ ወረደም ሰበቡ የወልቃይት የአማራ የማንነት ጥያቄ ሆኖ ብቅ ይበል እንጅ፣ መሬት ላይ የሚነበበዉ ዕዉነታ በሥልጣን ላይ ያለዉ መንግሥት ከደርግም እየባሰ ስለመጣ፣ ብሶት የወለደዉ ሆኖ የመጣ መንግሥት መሆኑንም ስለዘነጋ፣ የሃያ አምስት ዕድሜዉም ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ሊያደርገዉ ስላልቻለ፣ የተሰጠዉ የሙከራ ጊዜም ስላለፈ፣ የብሔራዊ ዕርቅ በሩንም ክርችም አድርጎ ስለዘጋ፣ ባጭሩ መንግሥታዊ አስተዳደሩን ስላላወቀበትም ወደ መጣበት ባይመለስም ከሥልጣን ይዉረድ  ነዉ ጥያቄዉ። በጣም የሚያስገርመዉ እኮ ሰሞኑን በየቦታዉ በሚካሄዱት የገዥዉ መደብ የአዉራ ካድሬዎችም ሆኑ የሌሎች ዉሎ ገብ ካድሬዎች  የስብሰባ መድረኮች ላይ የሚንፀባረቁት ዲስኩሮች በእኛ ጊዜ ከሞተዉ በደርግ ጊዜ የተገደለዉ ይበልጣል እየተባለ፣ የሰዉ ልጅ ሞት (ግድያ) ቁጥር/አኀዝ መብዛትና ማነስ እንዴ ዲሞክራት መንግሥትነት የመለኪያ መመዘኛ ሆኖ እየቀረበ ነዉ። አኀዝን የምንጠቀምበት ብዙዉን ጊዜ ለኢኮኖሚ ዕድገት ማነፃጸሪያነት ነበር እንጅ ለሞት የሰዉ ቁጥር ብዛት ማወዳደሪያነት እስታትስቲክስ አልነበረም። እና ይህ የጤነኝነት አካሄድ ነዉ ትላላችሁ ወገኖቼ? ገሰሰዉ እንግዳ የሚባል ፀሐፊ ይመስለኛል …ታሪክ አጉዳፊዉ የአልባንያ ደብተራ… በሚል ርዕስ ለንባብ ባበቃዉ መፅሃፍ …ደርግም፤ ወያኔም ሁለቱም ገዳይ መንግሥታት ናቸዉ። አገዳደላቸዉ ግን የተለያየ ነዉ። ደርግ ጅል መንግሥት ስለነበረ በስም ጠቅሶ እነገሌን፡ እነገሌን ገድያለሁ ብሎ ማታ በሬድዮና በተሌቪዥን መግለጫ ይሰጣል። ወያኔዎች ደግሞ እራሳቸዉ ይገሉና …እንዲያዉ ለመሆኑ ማን ይሆን የገደለዉ ብለዉ ከሟች ቤተሰቦች ዘንድ መጥተዉ፣ ዓይናቸዉን በጨዉ አጥበዉ  ለቅሶ ይደርሳሉ በማለት የዉስጥ ማንነታቸዉንም ስለሚያዉቅ ትክክለኛ ባሕርያቸዉን በሚገባ ገልጾታል። አለመታደልም ሆኖ በገደሉት ሰዉ ቁጥር ብዛትና ማነስ ካለፈዉ የተሻሉ ዲሞክራሲያዊ መንግሥትነታቸዉን እየለኩበት ነዉ።

ሀገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ አገር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችም ሆኑ ሰላማዊ ሰልፎች ዓላማቸዉ አንድና አንድ ይመስለኛል። የሕዝቦቿ እኩልነት የተረጋገጠባት፣ ሁሉም ዜጎቿ የእኛ ሀገር ናት የሚሏት ኢትዮጵያ ትገንባ ነዉ ማሳረጊያዉ። የመንግሥት ለዉጥ በተደረገ ቁጥር፣ ሥልጣን ላይ ላለዉ መንግሥት ብቻ የሚጠቅም ብቻ ሕገመንግሥት በየጊዜዉ የሚወጣባት አገር ሳትሆን፣ ሀገር የምትመራበት፣ ሕዝብ የሚተዳደርበት፣ መንግሥትም ለሀገርና ለሕዝብ ተጠያቂ የሚሆንበት እንጅ ከሀገርና ከሕዝብ በላይ ሆኖ፣ ሕዝብ ለሚያሸብር ሕገመንግሥት በተግባር ላይ የማይዉልባት ሀገር እንድትኖረን፣  ባጭሩ የአንድ አገር ሕዝብ በአፈሙዝ የሚገዛበት አገር ከመሆን ዘመን ነፃ ሆነን የመኖር መንግሥታዊ ባሕል እንገንባ ነዉ እንቃስቃሴዉ።  በትረ ሥልጣን የጨበጠዉ ወገን ደግሞ በግሉ ሚዲያዎች ከእኔ የተሻለ መንግሥት ሊመጣም ስለማይችል የእኔን የፖለቲካ ቀመር ተቀብላችሁ፣  በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ተጠምቃችሁና ቆርባችሁ  ከኖራችሁና  ከተገዛችሁ ኢትዮጵያ እንደ  ሀገር የመቀጠል ዕድሏ ሰፊ ነዉ። አለበለዚያ የሀገሪቱ ማጣፊያ ያጥራል፣ እኛም ከሌለን ሀገሪቱ ትበታተናለች እየተባልን ነዉ፣ እየተስፈራራን ያለነዉ። ሕዝቡ ግን በደማችን ነፃነታችን ይከበራል እንጅ፣  ከእናንተ በደጅ ጥናት የሚገኝ የዜግነት የመብት ከበሬታ  እንደማይገኝ እናዉቃለን እያለ ነዉ ድምፁን ከፍ አድርጎ እያስተጋባ የሚገኘዉ። ይህ የተራራቀ ፅንፈኛ አመለካከት እንዴት ይታረቅ? ነዉ ጥያቄዉ። የፍራንከፈርቱ ሰላማዊ ሰልፍ ዓላማም ከሕዝቡ ጥያቄዎች ጎን በመሰለፍ ለሚኖርበት ሀገር የተለያዩ ተቑማት መልዕክቱን ማስተላለፍ ነዉ። ይህንንም በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል። ባጭር ጊዜ ዉስጥ በተደረገ መሰናዶ ፍራንክፈርት አካባቢ ለመጀመሪያ ጊዜ ቁጥሩ በርከት ያለና ትርጉም ያለዉ ትዕይንተ ሕዝብ በማድረግ  ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን መቆሙን በተግባር አሳይቷል። ለሚኖርበት ሀገር መንግሥትና ሕዝብም ዓላማዉን በትክክል አሳዉቑል። ወሳኙ የሀገር ቤቱ ትግል መሆኑ ቢታወቅም፣ በየሀገሩ የሚደረጉ ሰላማዊ ሰልፎችም የራሳቸዉ የሆነ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸዉ ሊዘነጋ አይገባዉም።

የአዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ የህክምና ትምህርት ተማሪ ዶክተሮች የወያኔ ስርአትን አውግዘዋል

$
0
0
14079604_960460517432514_3499976317752314383_n

የአዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ የህክምና ትምህርት ተማሪ ዶክተሮች

የአዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ የህክምና ትምህርት ተማሪ ዶክተሮች በኦሮሞና በአማራ ወንድሞቻችን ላይ የወያኔ መንግስት እያደረገ ያለውና የሚካሄደው ኢ.ሰብአዊ ጭፉጨፉ አግባብ አይደለም በማለት ስርአቱን አውግዘዋል ተቃውማቸውን አሰምተዋል።

 

የትግሬዎች መንግሥት አወዳደቁና ክፋቱ! -አንዱዓለም ተፈራ

$
0
0

 

እስከመቼ cropped-eskemeche-question32

ሐሙስ ነሐሴ ፲ ፪ ቀን ፳ ፻ ፰ ዓመተ ምህረት ( 08/18/2016 )

ባሁን ሰዓት፤ በገዥነት ሕልሙ እየተንሳፈፈ ካለው የትግሬዎች ቡድን በስተቀር፤ ኢትዮጵያን አደጋ ላይ የጣላት ይሄው ቡድን፤ የውድቀት አፋፉ ላይ መሆኑ ለሁላችን ግልጽ ነው። አሁን ካለንበት ሰዓት እስከመጨረሻው ውድቀቱ ያለው ጊዜ ግን፤ በጣም የከፋና የተመሰቃቀለ ነው። ይህ የሚሆነው፤ ከፊል በዚህ ወራሪ ቡድን ተግባር ሲሆን፤ ከፊሉ ደግሞ በኛው በታጋዩ ክፍል ያለነው ለዚህ ውድቀት በማድረግና ባለማድረግ ላይ ባለው ሂደታችን ነው። በተጨማሪ ደግሞ፤ የሃያ አምስት ዓመት የዚህ ቡድን ፀረ-ኢትዮጵያ አገዛዝ፤ ሀገራችንን ለከፋ ወደፊት አዘጋጅቷታል። ሀቁን ተቀብለን ከአሁኑ መደረግ ያለበትን ካላደረግን፤ በኋላ ይሄን ብናደርግ ኖሮ ብለን የመቆጫ ሰዓት አናገኝም፤ ያኔ ሁኔታውን አንገዛውምና!

ይህ ወራሪ ቡድን፤ የመጨረሻ እስትንፋሱን የሚያወጣው በቃሬዛ ነው። ሕዝቡ አቸናፊ ሆኖ እንደሚወጣ ምንም ዓይነት ብዥታ ባይኖረንም፤ የሚከተለው ምን ይሆን? የሚለው ስጋት ሀቅ ነው። ያንን ሳጋት የበለጠ ለማክፋት ይህ የትግሬዎች ቡድን ሲጥር፤ ታጋዩ ክፍል የሚሠጠው መልስ ወሳኝ ነው። ህዝቡ ማቸነፍ የሚችለው፤ ከዚህ ቡድን በልጦ ሲገኝ ነው። ጎልብቶ ሲገኝ ነው። ጎብዞ ሲገኝ ነው። ይህ ቡድን ምን እያቀደ ነው? ብሎ ቀድሞ ሲዘጋጅ ነው። ምን ሊያደርግ ይችላል? የሚለውን ወስዶ አደናቃፊ ዝግጅቶችን ሲያሰላ ነው። አስኪ ይህ ቡድን ሊያደርጋቸው የሚችሉትን እንመልከት፤

  • እንዳየነውና እንደሰማነው፤ አልቃይዳ ወይንም አልሸባብ ወይንም አይሲስ ብሎ ታጋዩን ያልሆነ ቀለም በመቀባት፤ የውጪ ሀገሮችን ድጋፍ ለማግኘት ይጥራል። አይሆንም ማለት ሞኝነት ነው። ዛሬም ድረስ በሺር አል አሳድ ሶሪያን የሚገዛው፤ አሜሪካና አውሮፓ በከፍተኛ ድጋፍ ተቃዋሚዎቹን ቢረዱም፤ በሶቪየቶችና ቻይናዎች ድጋፍ ነው። እኒህም ሆኑ ሌሎች ሀገራት፤ ስሌታቸውን የሚያተኩሩት፤ ለኔ ሀገር ሁኔታው ምን ያስገኝልኛል? ብለው ነው።
  • ከዚህ አያይዞ፤ የውጭ ቅጥረኞች በማለት ታጋዮችን በሀገር ቤት ለማስጠላት ይሞከራል። እያደረገውም ነው። ይህ፤ ጊዜ ለመገብያ የሚጠቀምበት ዘዴ ነው። ወረሩኝ ብሎም ጦርነት በጎረቤት ሀገሮች ሊከፍት ይችላል። ይህ ሁሉ፤ የሕዝቡንና የታጋዩን እንቅስቃሴ ለማለዘብ ነው። ጊዜው አልፏል።
  • ዋናው የዚህ የትግሬዎች ቡድን አስከፊ ተግባር፥ ጉልበቱን መጠቀም ነው። ይህ እብሪተኛ ቡድን መቼም ቢሆን የሚተማመነው፤ “ጉልበቴ ከሁሉም ይበልጣል!” ብሎ ነው። አሁንም ሁሉን ነገር “በጉልበቴ እወጣዋለሁ!” ብሎ፤ አረመኔያዊ ተግባሩን ቀጥሎበታል። ነገሮችን አጢኖ መመልከት ድክመት ይመስለዋል። በሰላም ባዶ እጁን አቤቱታ ሊያሰማ የወጣውን ሕዝብ፤ እስካፍንጫው የታጠቀ አጋዚ አሰልፎ በቀጥታ በሰልፉ ላይ በመተኮስ አሁን በመቶዎች የሚቆጠሩትን እየገደለ ነው። ነገ ደግሞ በሺዎች የሚቆጠሩትን ይረሽናል። እስኪሞት ድረስ ሌላ ዕውቀት የለውም። ካልገደለ ውሎ የሚያድር አይመስለውም። ሕዝብ ቆርጦ ከተነሳ፤ መመለሻ የሌለው መሆኑን ሊረዳው አይችልም። የዚህ ቡድን መነጽር፤ የተቃወመኝን ገድዬ፤ ጉዳዩን አጠፋለሁ ነው።
  • ታጋዩን ከሕዝቡ ለመነጠል ይጥራል። ደደብ ሆኖ ነው እንጂ፤ ታጋዩ እኮ ሕዝቡ ነው! ሊገባው አይችልም። ታጋዩን ሊከፋፋል ይሞክራል። ታጋዩን እኮ፤ ከዚህ ቡድን ሕልውናና ጥፋት የበለጠ የሚያንገበግበው የለም። ለነገሩ ይህ አዲስ አይደለም። እስከዛሬ ያቆየው፤ የሕዝቡ በአንድ አለመነሳት ነበር። በዘር፣ በሃይማኖትና በጥቅም መከፋፈሉን ተክኖበታል። አሁን ግን ሕዝቡ ይህን ሁሉ ጥሶ እንዲወጣ የዚህ ቡድን ለከት የለሽ በደል አስገድዶታል።
  • “አሸባሪዎች ናቸው!” ብሎ ማላዘን የዕለት ተግባሩ ነው። ነገ ደግሞ የየሰዓት ጸሎቱ ይሆናል። ለዚህም የሃይማኖት አባቶችን አሰልፎ ያስወግዛል፣ ይማጠናል፣ ያባብላል። የቤተክህነትና የመስጊድ መሪዎችን አቅርቦ ሊናዝዝ ይቻላል። አብሮም ሆዳም የመንግሥት ሠራተኞችንና የጦር መሪዎችን አሰልፎ ሊያስወግዝ ይቻላል።
  • መላ የፌዴራልና የክልል አስተዳደራዊ መዋቅሮችን የስለላ ድርጅት ያደርጋቸዋል። እያንዳንዱን ትግሬና የስመ ኢሕአዴግ አባል ተራ ሰላይ ያደርጋል። ከታጋዩ ከድተው ወደኔ ገቡ ብሎ የውሸት ታጋዮችን በቴሌቪዥን ሊያቀርብ ይችላል። ተዘረፈ ብሎ የመንግሥትን ካዝና ወደ መቀሌ ሊያሻግረው ይችላል። ይህ ቡድን ሌብነት ኒሻኑ ነው።
  • ለመታያ የተቀነባበረ የሱ ደጋፊ ሰላማዊ ሰልፎችና ትዕይንቶች ሊያዥጎደጉድ ይችላል። በማስፈራራት፣ በመደለልና በማስገደድ ሰልፍ እንዲወጡ ሊያደርግ ይችላል። ይህን ማንም አይስተውም። ሆኖም ግን የራሱን የመንፈስ ጭንቀት እንኳን አይበርድለትም። አምባገነን መንግሥታት ሙያቸው ነው። ትናንት መንግሥቱ ኃይለማርያም አድርጎታል።
  • ሲያስበረግገው የሚያድረው የሕዝቡ ቁጣ፤ በፓልቶክ፣ በፌስቡክ፣ በሬዲዮና በድረገጾች ላይ ዘመቻውን እንዲያበዛ ያደርገዋል። መስሎት ነው። ኢንተርኔቱን ይዝጋው፤ ሕዝቡ በኢንተርኔት ሳይሆን በሚኖርበት ሀቅ ተገፋፍቶ ነው የተነሳው። ፓልቶክ ደግሞ ሕዝቡን ወደ አንድ አመጣና በትክክለኛው ጠላቱ ላይ እንዲያተኩር ረዳው እንጂ፤ ችግሩ ያስተዳደር በደል ነው። የዜና ልውውጡን ሊያግት ቢሞከርም፤ በየቦታው ያለው የሱ ግፍ ያነሳሳው ነው።
  • በማታለልና በማውገርገር የተካነው ይህ የትግሬዎች ቡድን፤ እደራደራለሁ፣ ለውጥ አደርጋለሁ፣ ሽምግልና እገባለሁ ሊል ይቻላል። ይህን እያለ ግን፤ በጎን በከፋ ሁኔታ ያው መግደሉን ይቀጥልበታል። ይህን የሚለው ጊዜ ለመግዣ ብቻ ነው። ተገዶም ቢሆን ለድርድር ቢቀርብ፤ ሥልጣኑን ማጋራት ወይንም የሰረቀውን ሀብት መመለስ አይፈልግም። ሥልጣኑን የሚያስረክበው ወድሞ ነው።

ይህ ሁሉ ተግባሩ፣ አንድ ቀና አንድ ሌሊት ሊገዛለት ቢችልም፤ በአንጻሩ ግን፤ ትግሉን በትግሬዎችና በኢትዮጵያዊያን መካከል በማድረግ፤ የትግራይን ሕዝብ ለነገ ዕልቂት ያዘጋጀዋል። ይህ እየመጣ ያለ ሀቅ ነው። በርግጥ አሁን ሊለወጥ የሚችልበት ሰዓት ነው። ይህን ደግሞ እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ።

ምንም አንኳ ይህን ፈጻሚው የትግሬዎች ቡድን ቢሆንም፤ በዚያው አኳያ፤ የታጋዩ ክፍል ጥረት፤ ሊያስተካክለው ወይንም ሊያባብሰው ይችላል። በአሁኑ ወቅት ታጋዩ ያለበት ሁኔታ አመቺ አይደለም። በርግጥ ሕዝቡ ራሱ እየመራ ያለበት ይህ እንቅስቃሴ፤ ወደፊት እንዲሄድና ለስኬት እንዲበቃ፤ መልክ መያዝ አለበት። ማዕከል ሊኖረ ይገባል። ይህ ማለት፤ አሁን ካሉት ድርጅቶች አንዱ ወይንም ሌላው ይምራው ማለት አይደለም። አሁንም መሪው በቦታው ሕይወቱን እየከፈለ ያለው ሕዝቡ ራሱ ነው። ታዲያ በውጪም ሆነ በሀገር ውስጥ ያለን የታጋዩ ክፍል ነን የምንል ሰዎች፤ እገዛችን መሆን ያለበት፤ ይህን ሕዝባዊ አካል መርዳትና ማጠናከር ነው። ለዚህ አመራር ተገዥ መሆን ነው። በየቦታው በመደረግ ላይ ያለው ሰላማዊ ሰልፍ፤ እንዲያው ከየሰማዩ ዱብ ዱብ ያለ አይደለም። ሕዝባዊ ቅንጅት አለው። ወጣቶቹ ከፍተኛውን መስዋዕትነት እየከፈሉ ያዋቀሩት የደማቸው ሐረግ ነው። ይህን ማጎልበት አለብን። የኔን ድርጅት ወይንም የኔን ድርጅት እያልን፤ ድርጅቶቻችን በሕዝቡ ላይ ለመጫን ያጎበጎብነው፤ ልጓማችንን መያዝ አለብን።

ጎንደር የተሰለፉት ወጣቶች፤ የእስልምና ተከታይ ወኪሎችና የኦሮሞ ወጣቶች ጉዳይ ጉዳያችን ነው! አሉ። የኦሮሞ ወጣቶች ተከትለው፤ ጠላታችን አማራ አይደለም ጠላታችን ወያኔ ነው! አሉ። የትግሬዎችን ቡድን አከርካሪ ሰበሩት። ይህ በተግባር መያያዝ አለበት። ጊዜውና ምቾቱ ያለን እኛ በውጭ የምንገኝ ይሄን አንድነትን የመፈለግ ጥረት ማጎልበት እንችላለን። አለዚያ፤ እንደ ግብፁ ሙባረክ ሳይሆን እንደ ሶሪያው አሳድ የተጓተተና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ብዙ ታጋዮች የሚያልቁበት ሀቅ መልበሳችን ነው። ግንቦት ሰባት የራሱን ንጉስ ለማንገስ ሲሯሯጥ፣ ኢሕአፓ የራሱን ለማንገስ ሲጣደፍ፣ ሰላማዊ የራሱን፣ መድረክ የራሱን ሲያዘጋጅ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል፤ አንድነት አጥቶ፤ ይጓተታል። ሶሪያ ውስጥ የየውጪ ሀገሮች፤ ማለትም የቱርክ፣ የሊባነን፣ የኩዌት፣ የአሜሪካ ደጋፊ ታጋዮች ተለያይተው በየበኩላቸው ባንድ በኩል፤ ሶቪየት ኢራንና ቻይና ደግሞ የአሳድን ማዕከላዊ መንግሥት ደግፈው፤ የሶርያ ሕዝብ እያለቀ እንዳለበት ሀቅ፤ ተያይዘን እንዳንሰምጥ እሰጋለሁ።

አንድነት አለመሰለፋችን ትግሉን ጎድቶታል። አንድ ጠላት አለን ብቻ ሳይሆን፤ ሁሉም ድርጅቶች ሕዝቡ የበላይና ወሳኝ ነው ብለዋል። ታዲያ ይሄን ከተቀበሉ፤ ለምን የየራሳቸውን ጥንካሬ አጉነው፤ ሌሎችን እንደሌሉ በመቁጠር ይሯሯጣሉ? ለምን ሀገርን በማስቀደም የትግሉ አካል ለመሆን ፈቃደኛ አይሆኑም? ይህ ተጠያቂነታቸውን ያጎላዋል። ይህ ትግሉን በመጎተት ያስጠይቃቸዋል። የትግሬዎች ቡድን የሚያደገውን ጥፋትና የሚያደርሰውን በደል መዘርዘሩ በቂ አይደለም። ባሁኑ ሰዓት ደግሞ፤ ሕዝቡ ደሙን እያፈሰሰ ባለበት ወቅት፤ ስለ በደሉ መዘርዘር ትርጉም አጥቷል። አሁን ትግሉ ወደፊት መሄዱንና የድል ጎዳና መቀየሱን ነው ማብሰር ያለብን። አሁን፤ የሕዝቡን ድል መዘርዘር ላይ መሆን አለብን። ይህ ግን በምኞት አይመጣም። ተጨባጭ ሥራዎችን መሥራት አለብን። ይህ ደግሞ የሚጀምረው፤ ትግሉን በአንድነት ለማድረግ ወደ አንድ በመሰባሰብ ነው። ምንም እንኳ ይህ የአንድነት ጥሪ ለፍቶ ለፍቶ የሟሸሸ ቢሆንም፤ አሁን ክፍተት ተፈጥሮ ማዕከሉ ባዶ ሲሆን፤ እንደ ትግሬዎች ቡድን ዘሎ ለሚገባ የታጠቀ ቡድን በሩን በርግደን እንዳንተው እፈራለሁ። ሕዝባዊ ድል የሚገኘው፤ ሕዝቡ ሲመራና ሲታገል ብቻ ነው። ድርጅቶች የሚታገሉት ለድርጅታቸው ነው። የሕዝብ ድርጅት ደግሞ የለንም።

ከታላቅ አክብሮታ ጋር

አክባሪያችሁ አንዱዓለም ተፈራ

 

በባሕርዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ በትግሬ-ወያኔ ግፍ የተጨፈጨፉትን እንድናውቃቸውና እንድንዘክራቸው! –ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት       

$
0
0

ሐሙስ ነሐሴ ፲፪ ቀን ፪ሺህ፰  ዓ.ም.              ቅፅ   ቁጥር ፳፭

Moresh-901.jpg

ዘረኛው የትግሬ ወያኔ የወልቃይት ጠገዴን የማንነት ጥያቄ ደግፈው በወጡ የባሕርዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ በግፍ የገደላቸው ወገኖቻችን ዝርዝር በከፊል።

«የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ፣ የእኛም የዐማራነት ጥያቄ ነው፣» ብለው እሑድ ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓም ላይ በባሕርዳር ከተማ፣ በሰላማዊ መንገድ ድምፃቸውን ለማሰማት በወጡ ዐማሮች ላይ፣ የትግሬ ወያኔ ዘረኛ ቡድን በርካታ፣ ሩቅ አሳቢ፣ ለሥራ የጓጉ፣ ላገርና ለወገን ታላቅ ተስፋ ሰንቅው የነበሩ የአያሌ ወጣቶችን ሕይዎት በግፍ ነጥቋል። በባሕርዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ ወያኔ ከገደላቸው በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች መካከል ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን የከፊሎቹን አገኝቷል።

ከሰንጠረዡ ለመረዳት እንደሚቻለው፣ በግፍ ከተገደሉትና ዝርዝራቸውን ማወቅ ከተቻለው አርባ ዘጠኝ(49) ሰዎች ውስጥ፣ ዕድሜአቸው ሰላሳና ከዚያም በላይ የሆኑት ስምንት ( 8) ብቻ ነው። አርባ አንዱ (41) በወያኔ የግፍ አገዛዝ የተወለዱና ወያኔ ሲገባ ከአምስት ዓመት ዕድሜ የማይበልጡ መሆኑ በግልጽ ይታያል።  በመሆኑም  ያለፈውን ሥርዓት የማያውቁ፣ ያልኖሩበት፣ በትህምርትም ያልተማሩት በመሆኑ የሚናፍቁት አንዳች ነገር ይኖራ ተብሎ አይታሰብም።  ወጣቶቹ ሰዎች ናቸው እና እንደማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር መልካም ነገርን፣ እንደሰው ዕኩል መታየትን፣ ጥሩና መልክ ነገሮችን የመመኘት፣ ራሳቸውን ከሌሎች አቻዎቻቸው ጋር አመዛዝኖ ለእኛ ለምን ሰብአዊ መብቶቻችን፣ ተዘዋውሮ የመሥራትና ያመኑበትን በግልጽ የመናገር፣ የመደራጀት፣ ወዘት መብትና ነፃነት እንነጠቃለን፣ ከዚህ ሁሉ በላይ ማንነታቸውን ለምን ይካዳል ብለው መጠየቃቸው ሰው ሆኖ በመፈጠራቸው ብቻ የተሰጣቸው መብት እንጂ፣ ያለፈ ሥርዓት የመናፈቅ ወይም ትምክህተኛ የመሆን ውጤት አይደለም።

በሌላም በኩል እነዚህ በወያኔ ዘመን ተወልደው፣ በርሱ የትምህርት ሥርዓት ያለፉ ወጣቶች ያነሱት የማንነት ጥያቄ ሥርዓቱ ገነባሁት ያለው «የነገዶች ዕኩልነትና ሰላም» አስገኘሁት እያለ የሚለፍፈው «ልማት» ውሸት መሆኑን ገላጭ ነው። የዘረኝነት ሥርዓቱ፣ ዐማራውን በጠላትነት ፈርጆ ያወጀበት የዘር ጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል፣ እየከፋ መምጣቱን፣ የዐማራው ወጣት ትውልድ ማንነታችን እናስከብር ብሎ በቁርጠኝነት መነሳቱን የሚያመለክት ነው። ባጭሩ ወያኔ  የወልቃይት ጠገዴን የማንነት ዕውነተኛ ጥያቄ «ያለፈው ሥርዓት ናፋቂዎች፣ ትምክህተኞች፣ ነፍጠኞች» እያለ ያልሆነ ስም የሚለጥፍባቸው ንፁሐን ዜጎች የራሱ ከፋፋይ፣ አጥፊና ዘረኛ ሥርዓት ውጤቶች፣ የዘረኛና ብልሹ አስተዳደሩ ውጤት መሆኑን፤ ይህንም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ያልተቀበለው እንደሆነ የሚያሳይ አጉሊ መነፀር ነው።

በወያኔ አጋዚ ጦርና ከሕዝቡ መሀል ለዘመናት በኖሩና የባሕርዳር ሕዝብ እንደወገን በሚያያቸው፣ እነርሱ ግን እንደጠላት ቆጥረው  ለገዳዩ ቡድን መረጃ በማቀበል በተሰማሩት የትግሬ ነገድ አባሎች የተጨፈጨፉት ሰላማዊ ዜጎች፣ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ስማቸውን ለማግኘት የቻላቸው የሚከተሉት ናቸው። ለወራት ያህል በዘለቀው ሕዝባዊ እንቢተኝነት ሕይዎታቸውን ያጡ ወገኖቻችን ስምና ማንነት እየተከታተልን የማሳወቅ ተግባራችንን በንቃት ለመወጣት የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን። 

ተራ

ቁጥር

የተገዳይ ሙሉ ስምዕድሜመኖሪያ አድራሻ
1ዕድሜዓለም ዘውዱ27ባሕር ዳር
2ገረመው አበባው25ባሕር ዳር
3ተፈሪ ባዩ16ባሕር ዳር
4ሰሎሞን አስቻለ25ባሕር ዳር
5ሙሉቀን ተፈራ27ባሕር ዳር
6አደራጀው ኃይሉ19ባሕር ዳር
7አስማማው በየነ22ባሕር ዳር
8ታዘበው ጫኔ21ባሕር ዳር
9አሥራት ካሣሁን24ባሕር ዳር
10የሽዋስ ወርቁ20ባሕር ዳር
11ብርሃን አቡሃይ29ባሕር ዳር
12ሽመልስ ታዬ22ባሕር ዳር
13አዛናው ማሙ20ባሕር ዳር
14ሢሣይ አማረ24ባሕር ዳር
15ሞላልኝ አታላይ21ባሕር ዳር
16መሣፍንት አማራ22እስቴ
17እንግዳው ዘሩ20ባሕር ዳር
18ዝናው ተሰማ19ባሕር ዳር
19ዋለልኝ ታደሰ24ባሕር ዳር
20ይታያል ካሤ25ባሕር ዳር
21እሸቴ ብርቁ37ባሕር ዳር
22ሞገስ40ባሕር ዳር
23አደራጀው ደሣለኝ30ባሕር ዳር
24አበበ ገረመው27ጢስ ዐባይ
25ማኅሌት23ባሕር ዳር
26ተስፋዬ ብርሃኑ58ባሕር ዳር
27ፈንታሁን30ባሕር ዳር
28ሰጠኝ ካሤ28ባሕር ዳር
29ባበይ ግርማ26ባሕር ዳር
30አለበል ዓይናለም28ደብረማርቆስ
31አብዮት ዘሪሁን20ባሕር ዳር
32አበጀ ተዘራ28ወረታ
33ደመቀ ዘለቀ22ወረታ
34አለበል ሃይማኖት24ወረታ
35ሰሎሞን ጥበቡ30ቻግኒ
36ፍሥሃ ጥላሁን25አዲስ አበባ


የዶ/ር መረራና በዕውቀቱ መንገድ! –በዮሴፍ ሙሉጌታ  ባባ (ዶ/ር)

$
0
0

kankokunmalimaali@gmail.com

ክፍል 13

merera

የሱጌቦ፣ የጫላ፣ የሐጎስ፣ የአበበ፣ የኦባንግ…ወዘተ የማንነት ጥያቄ አንፃራዊ ምላሽ ካገኜ ከ25 ዓመት ቦኃላ፣ ዛሬም አበበ በሶ በላጫላ ጩቤ ጨበጠፖሊማኖታዊ አስተሳሰብ ጨርሶ መርገብ እንዳልቻለ ከዝህ በፊት በግል በድፍረት ሞግቼ ነበርበአንድነት ኋይሎችና (ultra-right) በብሔርተኞች (ultra-left) መካከል ያለው ይህ ፖሊቲካዊ ጽንፍ፣ ከ1966 ዓ፣ም ጀምሮ ቁም ስቅላችን እያሳየን የሚገኝ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ አሳሳብ ደረጃ ላይ ደርሷል። ሁኔታው እንደዝህ የሚቀጥል ከሆኔ፣ በአፊሪካ ቀንድ ማኅበራዊና ሃይማኖታዊ ቀውስ ያስከትላል የሚል ስጋት አለኝ። የምዕራቡን ‹‹ዓለም›› ፖሊቲካዊ ፍልስፍና በሚገባ የተረዳ ሰው፣ ይህ እውኔታ ፈጽሞ ይጠፈዋል የሚል ግምት የለኝም። የሆነ ሆኖ፣ በኢትዮጵያ ፖሊቲካዊ ፍልስፍና ታሪክ ውስጥ፣ እነዝህን ጽንፈኛ አመለካከቶች ለማስታረቅ የደፈሩ ጥቂት ምሁራንና ጸሐፍዎች አልጠፉም።

(ሀ) ‹ያ ትውልድ›:- የሔኖክ የማነ ‹‹የዶ/ር መረራ የገመድ ላይ ጉዞ›› ‹ፖሊቲካዊ ትንተና› እንዳለ ሆኖ፣ በኢትዮጵያ ፖሊቲካዊ ፍልስፍና ታሪክ ውስጥ፣  ሁለት ጽንፈኛ አመለካከቶችን ለ‹‹ማስታረቅ›› ከፊተኛ ጥረት ካደረጉ ጥቅት ምሁራን መካከል፣ ዶ/ር መረራ ጉዲናን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል። ከዝህ በፊት ለንባብ የበቁ የምርምር ሥራዎቹ፣ በአንድነት ኋይሎችና በብሔርተኞች መካከል ያለው እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ ማብቃት እንዳለበት በግልጽ ያሳያሉ። (Merera Gudina, Ethiopia: Competing Ethnic Nationalisms and the Quest For Democracy, 1960-2000, 2002, Passim; Ethiopia: From Autocracy to Revolutionary Democracy, 1960s-2000, 2011, Passim፣ መረራ ጉዲና፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅ ጉዞና የሕይወቴ ትዝታዎች፣ 2006፣ Passim የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ሕልሞች፣ 2008፣ Passim) በተለይ፣ የኦሮሞና የአማራ ልሂቃን ፖሊቲካ፣ ብዙም ያለተንቀሳቀሰና ‹‹በዋናነት በሁለት ጫፎች ላይ ቆሞ ገመድ ከመጓተት ወደ መሃል መጥቶ የጋራ ዴሞክራትክ አጀንዳ መቅረጽ›› እንዳላስቻላቸው ዶ/ር መረራ ያሰምርበታል። (መረራ ጉዲና፣ 2008፣ ገጽ 11) የሁለቱን ልሂቃን ፖለቲካዊ ውይይት አንዱ ሌላውን የማይሰማ ‹‹የዶንቆሮዎች ውይይት (dialogue of the deafs)›› ሲል አካሄዳቸውን አጣጥሏል። (ገጽ 11፣12) ለወደፊቱ በአፊሪካ ቀንድ ለሚነሳው‹‹ግጭት/ጦርነት›› ተጠያቅዎቹ የትግራይ፣ የአማራና የኦሮሞ ልሂቃን መሆናቸውን በሚያሳይ መልኩ የሚከተለውን ሐሳብ በድፍረት ሰንዝሯል፡-

‹‹ለታሪክም፣ ለሕዝብም አስረድቼ ማብቃት የሚፈልገው  መሠረታዊ ነጥብ፣ አብዛኛው የትግራይ ልሂቃን ‹ስልጣን ወይም ሞት› ብለው ሥልጣን ላይ የሙጥኝ እስካሉ ድረስ፤ አብዛኛው የአማራ ልሂቃን በአፄዎች ዘመን የነበረውን የበላይነት መልሼ አገኛለሁ ብሎ የሚያስበውን የሕልም ፖሊቲካ እስካልተወ ድረስ፣ ብዙሃኑ  የኦሮሞ ልሂቃን ኦሮሚያን ለብቻ የማውጣቱን ሕልም እስካልተወ ድረስ ሀገራችን ከአደጋ ቀጠናና ቀውስ የምትወጣ አይመስለኝም። በሌላ ቋንቋ ለነዝህ መሠረታዊ በሽታዎቻችን መድኃኒት እስካላገኘን ድረስ ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምም ሆነ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን ፈጽሞ የምታገኝ አይመስለኝም።›› (ገጽ. 12)

ዶ/ መረራ ታሪክና ሕዝብን ለምስክርነት መጥራቱ፣ በኢትዮጵያ ፖሊቲካ ጉዳይ ተስፋ መቁረጡን ያሳያል። ‹‹ያ ትውልድ›› ካለፈው ጥፋቱ ተምሮ፣ ልዩነቱን አቻችሎና አንድነቱን ጠብቆ ኢትዮጵያን ከመበታተን ይታደጋት ይሆን? ጊዜ የሚነግረን ይሆናል!

(ለ) ‹‹የእኔ ትውልድ››፡- በአሁኑ ጊዜ ‹‹የኢትዮጵያ ታሪክን›› በተመለከተ የጋራ ግንዛቤ ያላቸውን ወጣቶች ፈልጎ ማግኘት ብርቅ እየሆነ መቷል። በተለይ፣ የአንድነት ኋይሎችና ብሔርተኞች ‹‹የሀገራችንን ታሪክ›› የሚረዱበትና የሚተነትኑበት መንገድ፣ ብሔራዊ መግባባት ላይ እንዳንደርስ ትልቅ እንቅፋት ሆኗል። ከዝህ ‹ጽንፋዊ የታሪክ ትንተና› ለመራቅ ብቸኛው መንገድ ደግሞ፣ ‹ሌላው ወገን› የሚለውን ልብ ብሎ ማዳመጥ ነው። የበለጠ ግልጽ ለማድረግ፣ የማንነት ጥያቄን ከጠባብነት፣ የሀገር አንድነት ጉዳይን ከትምክህተኝነት ጋር ብቻ አቆራኝቶ ‹መገንዘብ›፣ ወደ ፖሊቲካዊ ጽንፍ ሊያመራ ይችላል። ስለዝህ፣ በሁለቱ ጽንፈኛ አስተሳሰቦች ውስጥ ያለውን እውኔታ በትክክል ለመረዳት፣ ከዝህ ቀደም በሁለቱ ወገኖች በኩል የተደረሱትን ጥልቅ የምርምር ሥራዎች በሰከነ መንፈስ መመርመር ያስፈልጋል።

የዘመኑ (contemporary) ወጣት ጸሐፍ በእውቀቱ ሥዩም የጽፈኝነት ፈተናን ማለፍ የቻለው ይህንን በማድረጉ ይመስለኛል። በቅርቡ ለንባብ የበቃ ‹‹ከአሜን ባሻገር›› የተሰኘ ሥራው፣ ጸሐፍው ስበዛ የመጽሐፍ ትል መሆኑን ይመሰክራል። ይህ ማለት ግን ጸሐፍው የሰነዘራቸው ሐሳቦች ሁሉ ተቀባይነት አላቸው ለማለት ፈልጌ አይደለም። (እኔ ራሴ በሁለት ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ‹ጥንቃቄ› እንድያደርግ አጭር-መልዕክት (e-mail) ሰድጄለት ነበር—‹ጆሮ› ካለው ይስማ!) ይልቅ፣ እዝ ላይ ለማለት የተፈለገው የኢትዮጵያ ሕዝቦች ታሪክ በጥልቀትና በ‹ትክክል› መረዳት የሚንችለው በአንድ ወገን ብቻ የሚደረሰውን የምርምር ሥራዎች ዋብ በማድረግ ሳይሆን፣ በሌላ ወገን በኩል ያለውን ታሪካዊ-ጥያቄ በሚገባ መገንዘብ ስንችል ብቻ ነው። ሰውሻውያን እንደሚዘባርቁ ሳይሆን፣ በእውቀቱ ከ‹ቀበሌ አስተሳሰብ› ተላቆ ያንን ማድረግ የቻለ ‹ደፋር› ወጣት ነው!

ከ ‹‹ያ ትውልድ›› ዶ/ር መረራን፣ ከ ‹‹እኔ ትውልድ›› በዕውቀቱን ማንሳቴ ያለ ምክንያት አይደለም። የኢትዮጵያ ፖሊቲካዊ ፍልስፍና ታሪክን በሚገባ ለመረዳት፣ ከምርምር ዓለምም ሆነ ከሥነ-ጹሑፍ ዓለም ለብዝኃ-ዕይታ (multi-perspective) ዝንባሌ ያላቸው ብዙ መረራዎችና በእውቀቱዎች በጣም እንደሚያስፈልጉን ለማሳየት ብቻ ነው። እርግጥ ነው ለብዝኃ-ዕይታ ትኩረት የሚሰጡ ብዙ ተመራማርዎችና ጸሐፍዎች ዛሬም አሉን። ለእነኝህ ግለሰቦች ትልቅ ክብር አለኝ። ይሁን እንጅ፣ የፖሊቲካና የሃይማኖት ጽንፈኝነት ጡዘት ላይ በደረሰበት በአሁኑ ጊዜ፣ እንደዝህ ዓይነት አስተሳሰብ ያላቸው ምሁራንና ወጣቶች በብዛት ያስፈልጉናል።

በመጨረሻ፣ ለ ‹‹ያ እና አሁኑ ትውልድ›› ማስተላለፍ የሚፈልገው አንድ ‹‹መልዕክት›› አለኝ፡-

የኢትዮጵያ ፖሊቲካዊ ፍልስፍና ታሪክ በጣም ውስብስብ ነው። አንድ ወጥ አመለካከትን ሳይሆን ብዝኃ-ዕይታን (multi-perspective) ይፈልጋል። በግልብ አስተሳሰብ የችግሩ መንሥኤ ላይ መድረስ አይቻልም። የችግሩ ምንጭ በሚገባ አውቆ፣ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት፣ አንዱ ሌላውን ማዳመጥ ያስፈልጋል። መከባበር፣ መደማመጥና መነጋገር የ‹‹ስልጣኔ›› ምልክት ይመስለኛል። ከዕድሜ ልክ እንቅልፋችን ነቅተን፣ የኢትዮጵያ ፖሊቲካዊና ማኅበራዊ ችግሮችን በራሳችን እንፍታው። የሦስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት አያስፈልገንም። የምዕራቡን ‹‹ዓለም›› የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት በጣጥሰን፣ ብሔራዊ እርቅ አንፍጠር። ዳግም የቆንጨራ ‹ጨወታ› ወስጥ መግባት ትልቅ ዋጋ ያስከፍለናል። ‹የታሪክ ሒሳብ ማወራረድ› የሚለው ፈልስፍና የትም አያደረሰንም። እንደ አውሬ መበላላቱን ትተን፣ ፍቅርና መቻቻልን እንላበስ። የአስተሳሰብ ሽርሙጥናን አጥብቀን እንታገል!  የአስተሳሰብ ለውጥ ከተግባር እንደምቀድም ለማወቅ ደግሞ፣ የሚከተለውን  ግጥም ልብ ማለት በቂ ነው፡-

 

ማጭድ ይሆነን ዘንድምኒሽር ቀለጠ

ዳሩ ብረት እንጂልብ አልተለወጠ

ለሳር ያልነዉ ስለትእልፍ አንገት ቆረጠ

(ግጥም፡ በዕውቀቱ ሥዩም)

 

የመንግስት ባለሥልጣናትና የሃይማኖት መሪዎች ሆይ! ዝለዝህ ጉዳይ በደንብ አስቡበት! ስለ ‹ዶላርዝም›ና ስልጣን ብቻ ሳይሆን፣ ስለብሔራዊ እርቅም አስቡ! በሕዝቦች መካከል ጥላቻና ዘረኝነት እየዘራችሁ፣ ሰዎች ስለ ቆንጨራና ማጭድ አብዝቶ እንድያስቡ አታድርጉ። ሰውን እንኳ ባትፈሩ ለፈጣሪ ስትሉ የድሆችን አሰቃቅ ሁኔታ ተመልከቱ! ለህሊናችው ሲትሉ እውነትን ውደዱ፤ ‹‹ከባላጌ ክቡር የድሃ ስልጡን ይሻላልና›› ለመልካም ስማችው ተጠንቀቁ። ስለ ልጆቻቹ አስቡ። ለምሳሌ፤- ልጆቻቹ ‹‹የሌባ ልጅ›› ተብለው እንዳይጠሩ ከፈለጋችው ፣ ከድሆች ኪስ በወጣ ገንዘብ መኪናና ቤት አትግዙ። ወይም ‹‹የሰሙኒ-ልጅ›› ተብለው እንዳይጠሩ ከፈለጋችው፣ ለትዳራችው ታማኝ ሁኑ! ‹‹ከመጠምጠም መማር ይቅደም›› እንደሚባለው፣ ዕድሜ ልካችውን ገንዘብና ሴቶችን ከሚታሳድዱ፣ ጥበብን አብዝታችው ውደዱ። ብሔርን ወይም ኅይሞኖት እየለያችው ሰውን አትበድሉ፤ ድሆችን አትበዝብዙ፤ እንባቸው እንደ ጎርፍ ጠራርጎ እንዳይወስዳችውም ተጠንቀቁ!

   ነገር ግን፣ ሕዝባቸውን በቅንነት እያገለገሉ ያሉ ጥቂት የመንግስት ባለሥልጣናትንና የሃይማኖት መሪዎችን እንወዳቹዋለን፤ እናከብራቹዋለን፤ ዋቃዮ/እግዝአብሔር/አላህ ረዥም ዕድሜና ጤና ይስጣቸው!

በክፍል 14 ‹‹ዴሞክራሲ ‹ማሽላ› ይሁን ‹ገብስ› ገና አልታወቀም›› የሚለውን እንመለከታለን!

ቸር እንሰንብት!!          

 

 

 

 

 

እንዲህ ተፅፎ ነበር !! –መስፍን ማሞ ተሰማ

$
0
0

መንደርደሪያ፤

Gonder6ኢትዮጵያዊው የሥነፅሁፍና የምርምር ሊቅ፤ ዲፕሎማትና መምህር፤ እንዲሁም በቀዳማዊ ሃይለ ሥላሴ መንግሥት የልዩ ልዩ መሥሪያ ቤቶች ከፍተኛ ሃላፊ፤ ጋዜጠኛ፤ ደራሲ ገጣሚና ተርጓሚ ክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል በ1930ዎቹ ዓ/ም በፃፉት “ታሪክና ምሳሌ” 1ኛ መፅሐፍ ላይ (እሳቸው በ30 ዓመት የሥነ ፅሁፍ ዘመናቸው 26 መፃህፍትን አቅርበዋል) ከሚገኙት የተለያዩ ትውልድን ቀራጭና ታሪክን አስራጭ ሥራዎች ውስጥ በመንቀስ ሀገራችን አትዮጵያና እኛም ዜጎቿ ዛሬ በምንገኝበት የሕወሃት/ኢህአዴግ አፓርታይዳዊ አገዛዝ፤ ወደር አልባ ሰቆቃ፤ ግፍና ምዝበራ . . . አንፃር በእኛ በኩል (ከህወሃት/ኢህአዴግ ያልተዋለድነው) ለዜግነት/ኢትዮጵያዊነት ካለን ቁርኝትና ሃላፊነት፤ ለሀገር ነፃነትና ክብር ካለን መስዋዕትነት፤ ለባንዲራ ማተብ ካለን ፍቀርና ቀናዒነት አንፃር በዘመን ሂደት የደረስንበትን ለመመርመርና ከተቻለም ተማምሮ የጎበጠውን ለማቃናት ማስታወሻ አልያም የቀደመው ትውልድ መሥዋዕትነት መማፀኛ/ወይም መዘከሪያ ይሆን ዘንድ ታስቦ የቀረበ መሆኑ ይታወቅ ዘንዳ እንወዳለን። ይህ አቅርቦት በ’ታሪክና ምሳሌ’ 1ኛ መፅሐፍ ሙሉ ይዘት ላይ የቀረበ ቅኝት ወይም ዳሰሳም አይደለም፤ ይልቁንም በግፈኞች እየተገፋ እየተጋዘና እየተገደለም ለሚታገለው ይህ ትንታግ ኢትዮጵያዊ ወጣት ትውልድ ለሚገኝበት ዘመንና ወቅት ለትግሉ ፅናትና ለድሉ ብቃት በማስተማሪያነት ወይም በአስታዋሽነት በቀጥታ የተፃፉ የሚመስሉትን ጥቂት የመፅሐፉን ገፆች በንዑስ ማብራሪያ አጅቦ ያወረደ እንጂ። እነሆ ከበደ ሚካኤል እንዲህ ፅፈዋል፤ =የሚቀጥለውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ====

=== ፈንጂ ነው ይቅርታ ። === –አቢይ ኢትዮጵያዊ

$
0
0
Tomar
ግለሰቦች ክደው ሕዝብን ሲበድሉ፤
አምባገነኖቹ ዕድሜ ያገኛሉ።
እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ምንም ላልታጠቁ፤
በጉልበት በብረት ዛሬም ለሚጠቁ፤
በተለይ በዚህ ወቅት የሰላም እጃቸው፤
የአጋዚ ጥይት ገድሎ ለሚፈጃቸው፤
መድኃኒት ነው ፈንጂ ሕዝብን የበደሉ፤ 
አደባባይ ውጥተው
“በድለናል” ካሉ።
እናም እንደማዲንጎ በሕዝብ የተረታ፤
ይውጣና አሁኑኑ:-
ፈንጂ ይስጥ በይቅርታ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ይህን ጥሪ ስማ፤
በልቦናህ ጻፈው ማን እንደሚያቅማማ።
ልጆችህ ሲደፉ በዓጋዚ ስትደማ፤
በየስርቻው ሞልቷል ቢጠራ ‘ማይሰማ።
እሰዬን አስተውል፣እነገብሩ አሥራትን፤
ያን ታምራት ላይኔ ያስገነጠላትን።
በየመድረኩ ላይ ዛሬም የሚዋሹ፤
በዜና አንባቢነት ህሊና ያቆሸሹ።
ሞልተዋል ድርቅ የለም ለምተናል የሚሉ፤
ጉጅሌ ለበላው ጅለው የተጃጃሉ።
እነዚህን ሁሉ ሐቁ እንዲፈጃቸው፤
የእነ መሓሙድ ይቅርታ ወጥቶ ያፈንዳቸው።
እናም ሕዝቡን ስሙት አድምጡት ላንድአፍታ፤
እንደልጅ ማዲንጎ ጠይቁ ይቅርታ። 
እንደው ስንቴ ከዱን ከመካከላችን፤
መንግሥትን ወግነው አሾፉ በሕዝባችን።
በኪነት-በስፖርቱ በፖለቲካ-ስልጣን፤
በምርጫ በትግል ስንቱን ጀግና አጣን።
ይህን የሕዝብ በደል ማዲንጎ አሸንፎ፤
አስደሰተው ሕዝቡን በይቅርታው አቅፎ።
ሕዝቡ ትዕግስት አለው ሳይነጋ ይጠብቃል፤
እነማን በዳዮች እንደሆኑም ያውቃል።
እናም የበደላችሁ ያኔ ተለጥፋችሁ፤
ዛሬውኑ ይቅርታ ጠይቁ ፈጥናችሁ።
ባንዳውን ሳይጨምር፣ስንቱ ስው ተረታ???…
በሆዱ በሥልጣን ለገንዘብ ተፈታ።
ልደቱ የተባለው በቁም-ሲታይ ሞቱ፤
መሐሙድም ርካሽ ሲሆን አየን ገልቱ።
ያቺ አስቴር አወቀም ባለድምጻዊቷ ፤
ኢትዮጵያን ነው የከዳች ለስንዝር ዕርስቷ።
ንዋይ ደበበስ ቢሆን ዘምሮ ለኢትዮጵያ፤
ወዶ ገባ ሆነ ከጉጅሌ ጉያ።
ሰለሞን ተካልኝ ና ሲባል ብላልኝ ፤
እንደጅብ ይጮሃል እሱስ ይጠንባልኝ።
እነ ኃይሉ ሻወል ስንቱ ይቆጠራል፤
ወዲያው ካያለበት እንደነጋ  ይጠራል።
እናም እንደማዲንጎ በሕዝብ የተረታ፤
ይውጣና አሁኑኑ:-
ፈንጂ ይስጥ በይቅርታ።
ኃይሌስ ቢሆን ስንቴ አውቆ ተታለለ፤
ጀግና እንዳልተባለ በወቸገል-ሥም ማለ።
ፈንጂ ነው ዕውነታ ሐቅ ነው መናገር፤
ጉጅሌ ኢትዮጵያን ከፋፍሏታል በዘር።
ይኼን አትመስክሩ፤
የኢትዮጵያ ሕዝብ አውቋል፤
ግና ይቅርታችሁን ዓመታት ጠብቋል።
እናም ሕዝቡን ስሙት አድምጡት ላንድአፍታ፤
ታሪክ ሳይጠራችሁ የማታ የማታ፤
ዛሬ ቁረጡና ቆማችሁ በዕውነታ፤
እንደልጅ ማዲንጎ ጠይቁ ይቅርታ።

የተቃውሞ ሰልፍ በሜልበርን – SBS Amharic (Video)

$
0
0

የተቃውሞ ሰልፍ በሜልበርን – SBS Amharic (Video)
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ – በውጪው ሲኖዶስ የአውስትራሊያና ኒውዝላንድ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ሐሙስ ኦገስት 18 በሜልበርን ነዋሪ በሆኑ ኢትዮጵያውያን በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ተገኝተው ያደረጉት ንግግር።

ይድረስ ለአዲስ አበባና በሌሎች ዋና ዋና ከተማ ለምትኖሩ ህዝቦች –ከ ደሃብ ዘደቡብ

$
0
0

14022173_308042539547525_919601382848618367_nበአዲሰ አበባ በሌሎች ዋና ዋና ከተማ የሚኖሩ ህዝቦች

ለምን ወደ አደባባይ በመዉጣት ተቃዉሟቸዉን ማሰማት ይኖርባቸዋል ?

አዲሰ አበባ በኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉ የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች አባላት የሚኖሩባት የሃገራችን ዋና መዲና መሆኗ ግልጽ ነው

በኢትዮጵያ ዉስጥ የርስ በርስ ግጭት  ቢነሳ የሂደቱ ዋና ሠለባ ወይንም ተጠቂ የሚሆኑት በዋናነት የአዲሳበባ ነዋሪዎች ሲሆኑ በቀጣይነትም ኢትዮጵያዉያን በአብዛግናዉ ተሰባጥረዉ በሚኖሩባቸው እንደ ድሬዳዋ፣ ናዝሬት፣ አዋሳ ፣ ደብረዘይትና በመሳሰሉት ሌሎች የሃገሪቷ ዋና ዋና ከተሞች ዉስጥ የሚገኙ ህዝቦች መሆናቸው ለማንም ግልጽ ነው::

  • አለመታደል ሆኖ አሁን በስልጣን ላይ ያለው አካል እያስተዳደረ ያለበት ስልትም ይሁን ግጭቶችን ለመፍታት እየሄደበት ያለው መንገድ በሃገሪቷ ዉስጥ የርስ በርስ ግጭቶች በከፍተኛ ደረጃ እንዲስፋፉ የሚያደርጉ ናቸው :: በአዲስ አበባና በመሳሰሉት ሌሎች ዋና ዋና ከተሞች ለሚገኙ ህዝቦች ከፍተና አደጋን ደቅኖ መገኘቱን ከግምት በማስገባት ”ሳይቃጠል በቅጠል”  እንዲሉ ከአሁኑ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ ብጋምቤላ፣ በደቡብ ህዝቦችና በሌሎችም አካባቢዎች የተቀጣጠለዉን ህዝባዊ ተቃዉሞ በመቀላቀል እንዲያዉም የመሪነቱን ሚና መጫወት ግድ ይለዋል ::

 

  • ከማህበራዊ ህይወት አንጻርም ቢሆን የአዲሳበባና የሃገሪቱ ሌሎች ዋና ዋና ከተሞች ህዝቦች ለዘመናት ከኖሩበት ቀዬ እየተፈናቀሉ በምትካቸው ሌሎች የዘመኑ ባለጸጋዎች እየተተኩ ነው :: የቀድሞ ባለይዞታዎች ግን ማህበራዊ መስተጋብራቸዉን እየተነጠቁ በከተማዋ ጥጋጥጎች ለመወሽቅ የተገደዱት በዚህ ሥርዓት ዉስጥ በመሆኑ ሥርዓቱን በማስወገድ ረገድ የበኩላቸዉን ሚና ሊወጡ ግድ ይላል ::

 

  • በኢኮኖሚው መስክም ደግሞ በንግድ ዘርፍ ተሰማርተው የነበሩት ሲፈናቀሉ የነበራቸዉን የንግድ ይዞታ፣ የደንበኞችና የገበያ ድርሻ ወይንም በእንግሊዘኛዉ business የሚሉትን ተነጥቀው ሲሆን የሚሰጣቸው ካሳ ግን ትልቁን ዋጋ የሚይዘዉን የንግድ ይዞታ፣ የደንበኞችና የገበያ ድርሻ ወይንም business ያላካተተ ካሳ ነው :: በመሆኑም እየበደላቸዉ ያለዉን ሥርዓት መዋጋት ግድ ይላቸዋል :: በተጨማሪም ከመኖርያቸው የሚፈናቀሉትም ቢሆን ላባቸዉን አንጠፍጥፈው የሠሩትን ቤት ለመሬቱ ሲባል ሲነጠቁ በዋጋ ተመን ትልቁን ድርሻ የሚይዘዉን የመሬቱን ዋጋ ያላካተተ ካሳ በመሆኑ በተለይም ነጣቂዉ ወይንም አፈናቃዩ አካል መሬታቸዉን ለ ባለሃብት ተብዬዎቹ ከሚሸጥበት ዋጋ ጋር ሲነጻጸር የሰማይና የምድር ያህል የተራራቀ መሁኑ ሲታሰብ ሲልጣን ላይ ያለዉና ንብረታቸዉን መጠበቅ የሚገባዉ ግን የተገላቢጦሽ እየዘረፋቸው ያለ አካል ነዉና ሊታገሉት ግድ ይላል ::

 

  • በሥርዓቱ በመከፋታቸው ምክንያት መከፋታቸዉን ለሚመለከተው አካል ለመግለጽ ባዶ እጃቸዉን አደባባይ የሚወጡትን ህጻናት፣ ወጣቶችና፣ አዛዉንት በጥይት የሚረፈርፍ ሃይልና ነጻነትህን ተገፈህ ኑር የሚል ስርዓትን መታገስ ባርነትን ተቀብሎ እንደመኖር ይቆጠራል :: እኛ ኢትዮጵያዉያኖች ደግሞ እንኳን ከዉስጣችን በወጡ ያልሰለጠኑና ለመሰልጠንም ፍጹም ፍላጎት በሌላቸው አካላት መገዛት መገለጫችን ባለመሆኑ ሥራአቱን በጋራ ታግሎ ማስወገድ  ግድ ይላል ::

 

  • ከሁሉም በላይ ግን አያት – ቅድመ አያቶቻቸው ዋጋ ከፍለው ባቆዩለት ሃገር ላይ በዚህ በስልጣኔ ክፍለዘመን እንደ ባርያ አሳዳሪ ሥርዓት እያጋጨ፣ እያረደና እየገደለ እኔ የሚልህን ብቻ አድርግ፣ ስጭንህ ተጫን፣ ስልክህ ሩጥ፣ ስዘርፍህ አሜን በል፣ ስገልህም እንዳትጠይቀኝ የሚለዉንና ፍጹም የማይሰለጥነዉን ወዳጅ መሳይ ጠላቱን ግን ጫንቃዉ ላይ ተቀምጦ ልሽናብህ የሚለዉን አካል በቃህ ሊለዉ ይገባል  :: ብሎም ላንዴም ለወዲያኛዉ ለማስወገድ በሃገሪቱ የተለያዩ ከተሞች የተጀመረዉን ትግል ማገዝ ጊዜ ሊሰጠዉ የማይገባ ቀዳሚ ተግባሩ ሊሆን ይገባል ብዬ አምናለሁ ::

 

  • በመጨረሻም ወጣቶች የወደፊቷ ኢትዮጵያ የናንተ መኖርያ ከመሆኗ አንጻር የባርነቱ መጠን ገዝፎ ለመቀልበስ የሚጠይቀዉን የመስዋዕትነት መጠን ከፍተኛ ከማድረጉ መጠን አሁን ሰፊ እድል ተፈጥሯልና “የነብርን ጭራ አይዙም ከያዙም አይለቁም እንዲሉ ይህንን በያካባቢዉ የተቀጣጠለዉን አብዮት በማፋፋም የመሪነቱን ሚና በመወጣት ወደፊት የሚመታችሁን እንቅፋት ካሁኑ ማስወገድ ጊዜ ልትሰጡት የማይገባ ነው ብዬ አምናለሁ ::

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

ከ ደሃብ ዘደቡብ

 

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live