Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

የወልቃይት ጥየቄ ሕገ መንግሥታዊነት፤ –ይገረም አለሙ

$
0
0

welkeit - satenaw

የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ መነሳት የጀመረበት ገዜ ጠያቂዎቹ እንደሚሉት ከወያኔ የሥልጣን እድሜ በላይ ነው፡፡ ስሙን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ብሎ ዓላማውን ተግራይን ነጻ ማውጣት አደርጎ የተነሳው ቡድን በለስ ቀንቶት ትግራይን መቆጣጠር ሲችል ቢያንስ በሁለት ምክንያቶች ወደ ቀሪው የኢትዮጵይ ክፍል መስፋፋትን ነው የመረጠው፡፡ አንደኛው ምክንያት ማሸነፍ ከተቻለ በትግራይ ሳይወሰኑ ማእከላዊ ሥልጣን ለመያዝ ሁለተኛው ደግሞ “ነጻ ሊያወጧት የታገሉላትን” ትግራይ ግዛት ለም መሬቶቸን በማጠቃለል ማስፋት ናቸው፡፡ የትግራይ አጎራባጅ የሆኑት ለም የጎንደርና የወሎ ወረዳዎች በወረራ የተያዙት ወያኔ ምንይልክ ቤተ መንግሥት ሳይደርስ ነው፡፡ ይህን ወረራ ዜጎች በዝምታ አልተመለከቱም በእሽታ አልተቀበሉም፣ ነገር ግን ወያኔ አንደም በጡንቻ ሁለትም በህግ ሽፋን በወሰዳቸው የማሰር የመግደልና የመሰወር ርምጃ ተቃውሞውን ለማዳን ችሎ ነበር፡፡

ነገር ግን የመብት ጥያቄ በጠመንጃ የማያዳፍኑት፣ ግንባር ቀደም ጥያቄ አቅራቢዎችንም በመግደል  የማያጠፉት በመሆኑ ይሄው ዛሬ የተዳፈነው ተገልጦ፣ በሀይል የተረገጠ የመሰለው ፈንቅሎ፣ገለን ቀብረነዋል ያሉት ህይወት ዘርቶ ህዝቡን በአንድ ደምጽ  ለተቃውሞ ያነሳሳ በአንጻሩ ገዢዎችን ያሸበረ ለመሆን በቅቷል፡፡

የጥያቄው መሰረት ወልቃይት ጠገዴ ወደ ትግራይ  መካለሉ ሆኖ የጥያቄው አቀራረብ እና  የሚሰጠው ምላሽ ግን የተለያየ መልክ እየያዘ ብዙ ዘርፎች አውጥቷል፡፡ በጠያቂዎች በኩል ሕገ መንግሥታዊ መብታችንን ነው የጠየቅነው፣በሕገ መንግሥቱ መሰረት ምላሽ ይሰጠን፣በማለት እስከ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አቤት ሲሉ ተጠያቂዎቹ  በአሁኑ ወቅት ምላሽ ያላገኘ የማንነት ጥያቄ የለም ፣የወልቃይት ጥያቄ ጸረ ህገ መንግሥት ነው ከማለት አልፈው ጥያቄውን ለማዳፈን የሀይል ርምጃ መውሰደን  ነው የመረጡት፡፡ ህገ መንግሥታዊ  የመብት ጥያቄ ሲቀርብ ትክክል ነው ብሎ ምላሽ ለመስጠትም ሆነ ህገ ወጥ ነው ለማለት ጠመንጃ ማንሳት ሳይሆን ህገ መንግስቱን መሰረት ማድረግ ነበር የሚገባው፡፡

ስለ ፌዴራል አከላል የሚገልጸው የህገ መንግሥቱ አንቀጽ 46/1 “ ክልሎች የሚዋቀሩት በሕዝብ አሰፋፈር ፣ ቋንቋ፣ ማንነት እና ፈቃድ ላይ በመመስረት ነው፣” ይላል፡፡በተገለጸት  መስፈርች መካከል እና ወይም  የሚል ቃል ባለመኖሩ አለበለዛም  እነዚህን ባገናዘበ መልኩ ተብሎ ባለመገለጹ  ክልሎች ሲዋቀሩ አራቱም መስፈርቶች በሥራ ላይ መዋል ይኖርባቸዋል፡፡ነገር ግን አሁን ያለው አከላለል የተሰራው  አነዚህን መስፈርቶች ባሟላ ሳይሆን የህውኃትን ፍላጎት ባማከለ ሁኔታ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ መስፈርቶቹን በሙሉ ስራ ላይ ማዋል አንደማይቻል የክልሎችን  ይዘት በአንክሮ  ማየት ብቻ ይበቃል፡፡

የወልቃይትን ጥያቄ ከዚህ የህገ መንግሥቱ አንቀጽ አንጻር ሲታይ፤

በህገ መንግሥቱ የሰፈሩት አራት መስፈርቶች ተግባራዊ አለመሆናቸውን  በተናጠል አንያቸው፤

በሕዝብ አሰፋፈር፤

አሰፋፈር ሲባል  ሰፋሪውን ሰውና የሚሰፈርበትን መሬት የሚመለከት ይመስለኛል፡፡ ከዚህ አንጻር ሕገ መንግሥቱ ወደ ወጣበት  1987 ተመልሰን  የወልቃይት ጠገዴን አካባቢ አሰፋፈር ስናስታውስ የምናገኘው የነዋሪውም ሆነ የመሬቱ አሰፋፈር ቤጌምድር ጎንደር እንደነበረ ነው፡፡ የመሬቱ አቀማመጥም ሆነ የአካባቢው ህብረተሰብ ባህል፣ ሥነ-ልቦና ፣ ትስስር ወዘተ ከትግራይ ይልቅ  ለትናንቱ ጎንደር ለዛሬው አማራ ሚዛን ይደፋል፡፡ የወልቃይትን ወደ ትግራይ መከለል የሚቃወሙ ወገኖች  የሚያቀርቡትና  ተቃውሞውን የሚቃወሙት ወገኖች በማስረጃ ሊቋቋሙት ያልቻሉት በኢትያጵያ ታሪክ ትግሬ ሰዉ አንጂ ትግራይ መሬቱ ተከዜን ተሸግሮ አያውቅም የሚለው መከራከረያ የህዝቡን የቀደመ አሰፋፈር እንዴትነት የሚያሳይ ነው፡፡  በተለያየ መንገድና ሁኔታ ከቦታ ቦታ ተንቀሳሶ የሚደረግ ሰፈራ አካባቢውን የእኔ ለማለት አያበቃም፡፡ በህገ መንግሥቱ የተገለጹትን መስፈርቶች ባላሟላ መልኩ ወልቃይት ወደ ትግራይ መስተዳድር ከተጠቃለለ በኋላ በርካታ የትግራይ ተወላጆች በአካባቢው እንዲሰፍሩ የተደረገው  የህዝቡን አሰፋፈር ቅድመ ይዘት በመለወጥ የሚነሳውን ጥያቄ ለመከላከል መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ የወልቃይት ጉዳይ በሕዝበ ውሳኔ አይፈታም የሚለው መከራከሪያ የሚነሳውም ህገ መንግስቱ ስራ ላይ ከዋለ በኋላ በሀይል በተካሄደ ሰፈራ ከነዋሪዎቹ ሰፋሪዎቹ አንዲበልጡ በመደረጉ   ነው፡፡

ቋንቋ፤

ይህ መስፈርት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አከላል አብይ መገለጫ ነው፡፡ ይሁን አንጂ በህገ መንግሥቱ የተገለጹ መስፈርቶች አስከመኖራቸው ተርስተው  ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም ይባል እንጂ  አከላለሉ ይህንንም  ያሟላ ላለመሆኑ የደቡብ ክልልን ማየት ብቻ ይበቃል፡፡ደቡብ የሚባል ቋንቋም ሆነ  “ብሔር ብሔረሰብ ህዝብ” የለም፡፡ ወልቃይት ላይ ስንመለስም የአካባቢው ሰዎች እንደሚናገሩት ሌሎችም የምርምርም ሆነ የአይን ምስክርነት ሲሰጡ እንደሚሰሙት በአካባቢው  አማርኛ ትግረኛ አረብኛ (በእኩል ደረጃም ባይሆን ) ይነገራል፡፡  ይህ ከሆነ  አንድን ሶስት ቋንቋ የሚናገር ሰው የግድ ወደ አንድ ብሔር ማስጠጋት ሲፈለግ ከግለሰቡ ምርጫ ውጪ በሌላ ሀይል ሊወሰን አይችልም፡፡ ፈቃድ ደግሞ በህገ መንግስቱ የተገለጸ አንድ መስፈርት ነው፡፡ የዚህ አብይ ችግር ደግሞ አማራ ትግሬ የሚባል ክልል መፈጠሩ ነው፡፡

ማንነት፣

የሰዎች የማንነት መታወቂያቸው ብሄራቸው /ጎሳቸው፣  የብሄሩ መለያ ደግሞ  ቋንቋ  በሆነበት ሥርዓት  እንደ ወልቃይቴ ያለ ከአንድ በላይ ቋንቋ የሚናገር ማህበረሰብ  ያለ ፈቃዱና ፍላጎቱ  ቋንቋውን ስለመናገሩ ብቻ የዚህኛው ወይንም የዛኛው ብሄር ነህ ተብሎ ሲጫንበት አድራጎቱ የጉልበት እንጂ የህግ አይሆንም፡፡በጉልበት የተፈጸመ ነገር ደግሞ ተግባራዊ ሆኖ የሚቆየው ገዢው ጠንካራ ተገዢው  ደካማ እስከሆነ ድረስ ብቻ ነው፡፡ለሁሉም ግዜ አለውና ነገሮች ሲለወጡ ጥያቄው እንዲህ ፈታኝ ይሆናል፡፡

ትግረኛ መናገራችን ብቻ ትግሬ አያደረገንም የሚሉት ተከራካሪዎች በደስታ ግዜ የምንዘፍነው፣ በሀዘን ግዜ የምናለቅሰው፣  በስር ቋንቋችን በአማርኛ ነው፡፡ ወግ ባህላችን፣ አሰራር ልምዳችን የአማራ እንጂ የትግሬ አይደለም ይላሉ፡፡ ከዚህ አለፍ ብለውም ወያኔ የፈለገው እኛን ሰዎቹን ሳይሆን ለም መሬታችንን ነው፡፡  መሬታችንን የትግራይ ለማድረግ  ነው የግድ ትግሬ ሁኑ የተባልነው በማለት ክርክራቸውን ያጠናክራሉ፡፡ የፌዴራል አከላለሉ ዜጎችን በብሔር/ጉሳ የማይከፋፍል  ቢሆንና የክልሎቹ መጠሪያም በብሔር /ጎሳ ባይሆን ይህ ጥያቄ ባልተነሳ ነበር፡፡  በጎሳ/በብሔር ስም የሚጠራ ክልል ፈጥሮ ከፈቃቸዳው ውጪ የዜጎች ማንነት  በባለሥልጣኖች ተወስኖ አንተ አማራ ነህ አንተ ትግሬ ነህ ወዘተ ማለት ቢዘገየም የሚያስገኘው ውጤት እየታየ ነው፡፡

ፈቃድ፤

ለፌዴራል አከላለል ፈቃድ አንዱ መስፈርት ሆኖ ቢገለጽም የአፈጻጸሙ እንዴትነት ግልጽ አይደለም፡፡ ፈቃድ የሚጠየቀው ማነው? እንዴት ነው የሚጠየቀው? ጠያቂውስ ክልሉ ወይንስ ፌዴራል መንግሥቱ? ክልል ነው ቢባል በሁለት ክልሎች መካከል ያለ የወልቃይት አይነቱ ጉዳይ እንዴት ይሆናል ? ፈቃድ የሚለው መስፈርት ያልተብራራ በመሆኑ አፈጻጸሙ አንዴትም ይሁን በማን የአካባቢው ነዋሪ ፈቃደኝነት የማይታለፍ  እንደውም ወሳኙ መስፈርት ነው፡፡ በህገ መንግሥቱ የተገለጹት ሶስት መስፈርቶች  ተሟልተው የማይገኙ በመሆናቸው የነዋሪውን ፈቃድ መጠየቅ ሌሎቹን ጉድለቶች ሁሉ ያሟላል፣ ይሸፍናል፡፡ ነገር ግን ገዢዎች በህዝብ ፈቃድ ፍላጎታቸንን አናሳካም ብለው ገና ሳይሞክሩት ስለሚፈሩት ተግባራዊ አያደርጉትም፡፡ ተግባራዊ የማያደርጉትን ለምን ህገ መንግሥት ውስጥ ይጽፋሉ የሚል ጥያቄ ማንሳት ስለ ገዢዎች አለማወቅ ይሆናል፡፡

በጥቅሉ በሀገራችን የተከናወነው የፌዴራል አከላለል ሌሎች ችግሮቹ እንደተጠበቁ ሆነው በህገ መንግሥቱ የሰፈሩትን  መስፈርቶች አንኳን ያላሟላ ነው፡፡ በዚህ መልኩ የተሰራውና ክልሎችን በብሄር/ብሔረሰብ ስም አንዲጠሩ ያደረገው  ፌዴራላዊ አከላለል  ( ደቡብ የሚባል ብሄርም ብሄረሰብም ህዝብም አለመኖሩን ልብ ይሏል) ትግራይና አማራ የተባሉትን ክልሎች  ለመለየት የሄደበት መንገድ መሬቱን አንጂ ነዋሪውን ያላማከለ ፣ የወያኔን ፍላጎት እንጂ ህገ መንግሥቱን መሰረት ያላደረገ  በመሆኑ ነው ጥያቄው  ከላይ በመጠኑ ለማሳየት እንደተሞከረው አንዱንም የህገ መንግሥቱን መስፈርቶች አልተከተለም፡፡  ለአመታት ያላባራውና አሁን ገንፍሎ የወጣው፡፡

የወልቃይት ችግር አንዴት ይፈታል፡፡

ጥያቄው በተጠያቂዎቹ በኩል የተለያየ ስምና ፍረጃ ቢሰጠውም በዚህ ጽሁፍ ለማሳየት አንደተሞከረው ህገ መንግሥታዊ ጥያቄ ነው፡፡ በመሆኑም ትናንት በከላዩ ጉልበተኛነትና በተከላዩ ደካማነት የተፈጠረውን ህገ መንግሥቱን ያላከበረ አከላለል  በህገ መንግስቱ የሰፈሩትን አራት መስፈርቶች ባገናዘበ ሁኔታ ማስተካከል አንዱ መፍትሄ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለወያኔ አንደም ሽንፈት ሁለትም ለትግራይ ትልቅ የኢኮኖሚ መሰረት የሆኑ ቦታዎችን ማጣት ስለሚሆን ተግባራዊነቱ አይታሰቤ ነው፡፡ ሁለተኛው መፍትሄ  መሬት ላይ ያለውን አከላለል በሚያጸና መልኩ ህገ መንግሥቱን መቀየር ነው፡፡ ይህ ቢሆን ህግ  ወደ ኋላ ተመልሶ አይሰራም የሚለው ለህገ መንግስት መስራት አለመስራቱ የባለሙያዎች ምላሽ የሚያሻ ሆኖ  ጥያቄው ህገ መንግስታዊ ነው የሚለውን ክርክር ያስቀረው ካሆነ በስተቀር የወያኔን ፍላጎት የሚያስቀጥል አንጂ የህዝቡን ጥያቄ የማይመልስ በመሆኑ ፋይዳ አይኖረውም፡፡ ስለሆነም መፍትሄው አንድና አንድ ነው፡፡ ወያኔዎች ለወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች የሚሰጡት “ይህ ሊሆን የሚችለው በመቃብራችን ላይ ብቻ ነው” የሚሉት ምላሽ ነው በአስተማማኝ ወደ ዴሞክራሲ ሊያደርሰን የሚችለው መፍትሄ፡፡ በግልጽ አነጋገር ከአገዛዝ ወደ ህገ መንግሥታዊ ሥርዓት መሸጋገር፡፡

 


      ይድረስ ለታጋዩ ሕዝባችን (1) –ፍርዱ ዘገዬ (ከአዲስ አበባ)

$
0
0

 

MESSAGEአንደኛ – የማንም ንብረት ቢሆን በተያዘው የሕዝባዊ እምቢተኝነት ሰበብ ማቃጠሉና ማውደሙ ጠቃሚም ተገቢም አይደለም – መራራው የትግል ጉዟችን ብዙ ማስተዋልና ብዙ ማሰላሰል ያለበት ይሁን፡፡ በርግጥ በእስካሁኑ ሁኔታ የዐማራው ትግል ብስለትና ጨዋነት የተሞላበት መሆኑና ልዩ ጥንቃቄ መደረጉ የሚያስመሰግን ነው፡፡ አንዳንዴ የምናየውን የሚቃጠል ወይ የሚወድም ንብረትን ግን ወደ ሕዝብ ሀብትነት ለውጦ ለነጻነት ትግሉ እንዲጠቅም ማድረግ ይቻላል፡፡ ለምሣሌ የዳሸን ቢራን መኪና ወይም የወያኔዎችን ማናቸውንም ከሀገርና ከሕዝብ የዘረፉትን ንብረት ከማውደም በሕዝብ ቁጥጥር አውሎ ለትግሉ ስኬት እንዲያገለግል ማድረግ ይቻላል፡፡ መኪናውን ለዕቃና መሣሪያ ማመላለሻ ቢያውሉት የሚያስከፋ አይደለም፡፡ በመነመነ የሀገር ሀብት በእልህ እየተነሳሱ ቢያቃጥሉና ቢያወድሙ የገዛ ንብረትን እንደማውደም ነውና ሊመከርም ሊበረታታም አይገባውም፡፡

መደረግ ያለበት ጥንቃቄ ግን መረሳት የለበትም፡፡ እነዚህ ሰዎች የመጨረሻ ከይሲ ስለሆኑ የሚበሉና የሚጠጡ ነገሮች ላይ በተለይ በጣም መጠንቀቅ ይገባል፡፡ ጭራቅ ለሰው አያዝንም፡፡ ጭራቅ በሰው ሀዘን የሚደሰት ዐረመኔ ፍጡር ነው፡፡ ወያኔዎች ደግሞ የመጨረሻ ጭራቅና ጨካኞች እንደመሆናቸው ሕዝብን ለመፍጀት የማያደርጉት ነገር የለም – በዚያን ሰሞን በአንድ የጎንደር አካባቢ የውኃ ጎተራ(ጋን) በመርዝ ሊበክሉ እንደነበር ሰምተናልና ከተጨማሪ ጥቃት ራሳችንን ለመከላከል ነቅተን መጠበቅ አለብን – በየትም ቦታ ያለን ዜጎች እንጠንቀቅ፤ ሥራም እንከፋፈልና ግዳጃችንን ባግባብ እንወጣ፡፡ ስለዚህ የሚያዙ ንብረቶችን በዐዋቂና ሲቻል በቤት እንስሳት (ሌላ አማራጭ ስለሌለ እንጂ ይህም ያሳዝናል) በመሞከር አገልግሎት ላይ ማዋል ይገባል፡፡ መኪናና የመሳሰሉ ንብረቶችን ግን ለትግሉ ማዋል ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም፡፡

ሁለተኛ – የመሣሪያ ችግር ብዙም አንገብጋቢ አይመስለኝም፡፡ ወጣቱ እየተደራጀ የወያኔ ሠራዊት ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመፈጸም መሣሪያ መቀማት፣ ግምጃ ቤቶችን በግልም በቡድንም መዝረፍ… ስለሚቻል በቀውጢ ሰዓት የመሣሪያ ችግር እስከዚህም ነው፡፡ ችግር ሊሆን ይችል የነበረው የወኔ ማጣት ነበር፡፡ ይህ ችግር ደግሞ የተፈታ ይመስለኛልና መበርታት ነው፡፡ የቆረጠ አንድ ሰው ብዙ ጀብድ ይሠራል፡፡

ሦስተኛ – ጎጃምና ጎንደር ሲጠነክር ሌሎች ዳተኛ ሆነዋል፡፡ ይህ እጅግ አደገኛ ነገር ነው፡፡ ሁሉም መነሣት አለበት፡፡ ችግራችንና ብሶታችን እኩል እንደመሆኑ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ፣ ከደቡብ እስከ ሰሜን ሁሉም በአንዴ ተነስቶ ወያኔን እስከወዲያኛው መደምሰስ አለበት፡፡ ወያኔዎች የመጨረሻ ፈሪዎች ናቸው፡፡ ሁሉም በአንዴ ቢነሳባቸው ሽንታቸውን እየረጩ ነው በእግር አውጪኝ የሚሸሹት፡፡ በዚህ ይታወቃሉ፡፡ በሀሽሽና በአነቃቂ ዕፆች እየተደፋፈሩ፣ በሳቦታጅና በከሃዲ የደርግ ጦር አዋጊዎች ሸፍጥና በሱዳን ደንቃራና መተት እንዲሁም በጠላት ድጋፍና በሕዝባዊ ኩርፊያ ምክንያት ክፍት ቤተ መንግሥት አግኝተው በቀላሉ መግባት ስለቻሉ ብቻ ጀግኖች መስለዋችሁ ከሆነ ስህተት ነው – እንደዚያ ያለ ወርቃማ ዕድል ባገኝ እኔና ስምንቱ ልጆቼም ኢትዮጵያን መቶ ዓመት ልንገዛ እንችላለን፡፡ ጀግናው በርግጥም ጊዜ እንጂ እነሱ አይደሉም፡፡ ዕንቆቅልሹ ይፈታ፡፡ አፍዝ አደንግዙም ማርከሻው ባፋጣኝ ተፈልጎለት ከእሥራችን እንፈታ፡፡

ስለዚህ በተለይ ወሎና ሸዋ በአፋጣኝ ተነስቶ መንገዶችን መዘጋጋት አለበት፡፡ ብዙ ነገር እንዳያሸሹ የሸዋና የወሎ መንገዶች በቶሎ መዘጋት አለባቸው፤ ሁሉም በያካባቢው ያሉትን መንገዶች ቢዘጋ ብዙ ጉዳት አይደርስም፡፡ አደጋን መከላክል ደግሞከሩቅ ነው፡፡ ከሰንዳፋና ከሱልልታ ጀምሮ መንገዶችን ጥርቅም እያደረጉ በመዝጋት መፈናፈኛ ቢያሳጧቸው ምንም አያመጡም፡፡ ይህ ደግሞ በጣም ቀላል ነው፡፡ አሥር ቆራጥ ወጣቶች አንድ ኦራል ሙሉ ወታደር ሊማርኩ ይችላሉ፡፡ መጠነኛ ወታደራዊ ሥልጠና ግን ማግኘት ይኖርባቸው ይሆናል፡፡ በተረፈ ግን አንድ ፍልስጥኤም ምን ያህል የጀብድ ሥራ እንደሚሠራ የምናውቅ ሰዎች አንድ ቆራጥ ኢትዮጵያዊ ከልቡ ከተነሣ ምን ያህል ወደርየለሽ የጀግንነት ተግባር ሊፈጽም እንደሚችል እንገነዘባለን፤ በጎጃምና በጎንደር እያየንም ነው፡፡

አራተኛ – የአዲስ አበባ ከእምቢተኝነቱ ማዕድ አለመሳተፍ ለበጎ ነው፡፡ አዲስ አበባ እስካሁን ብትሳተፍ የክፍለ ሀገራቱ እንቅስቃሴ ይታፈን ነበር፡፡ ስለዚህ በእስካሁኑ ሁኔታ የሸገር መተኛት ብዙም መጥፎ አይመስለኝም፡፡ አዲስ አበባ የመጨረሻው የወያኔዎች ህቃታ መውጫ ናት፡፡ ከአሁን በኋላ ግን ሁሉም በአንዴ በመነሣት ሊረባረብባቸው ይገባል – ጊዜ የለንም፡፡ በሰሞኑ የሕዝብ እንቅስቃሴ አካሄድ ሁሉም ከተረባረበ ወያኔን ለማጥፋት አንድ ወርም በጣም ብዙ ጊዜ ነው፡፡

ማድረግ የሚገባው በሁሉም ሥፍራ ወጥሮ ማጣደፍ ነው፡፡ መቼም እርግጠኛ ነኝ 50 ሚሊዮኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ በጸረ ወያኔ እንቅስቀሴው በንቃት ቢሳተፍ ይህን ሕዝብ ጨፍጭፎ መጨረስ የሚችል አጋዚ አይኖርም፡፡ እስካሁን የኖሩት በማስፈራራት እንጂ በርግጥም የሚፈራላቸው ኃይል ኖሯቸው አይደለም፡፡ ዛፍ ላይ ወይም ፎቅ ውስጥ ተደብቆ በአጉሊ መነጽር በሚመራ ልዩ ጠብመንጃ የንጹሓንን አናት መበርቀስ የዕይታንና የማነጣጠርን ብልሃት እንጂ ጀግንነትን የሚጠይቅ ትልቅ ሥራ አይደለም፡፡ በዚህ የ“ሥራ” መስክ ቢሰለጥን የ5 ዓመት ሕጻንም ብዙ ጥፋትና ውድመት ሊያስከትል ይችላል፡፡ ስለሆነም ሁላችንም ሳንፈራ ለጋራ ነፃነታችን በአንዴ ብንነሣ ይሳካልናል፡፡ እኔ መቼም በጎጃምና በጎንደር እንዴት እንደኮራሁ ቃላት አይገልጹትም፡፡ አዲስ አበባ እስኪመጣ በጣም ጓጉቻለሁ፡፡ አንድ አስተባባሪ ኃይል በኅቡዕ ተፈጥሮ ይህ ለጊዜው የሚጎመዝዝ በኋላ ግን የፍሬው ጥፍጥና በልጅ ልጆቻችን እየደመቀ የሚሄድ ተግባር በቶሎ መጀመር ይኖርበታል፡፡

አምስተኛ –  በዚህ ሕዝባዊ ትግል የፖለቲካ ፓርቲዎች ጎልቶ አለመውጣት ወይም የአንዳንዶቹ እንደመትረየስ የሚንደቀደቅ አፍ በስማም እንደተባለበት ሰይጣን ጸጥ ረጭ ማለት ለበጎ ነው፡፡ ምክንያቱም ሕዝቡ በትግሉ የሚያመጣውን ነፃነት ከአሁን በኋላ ማንም እንደፈለገ ሊቸረንና ሊነሣን አይችልምና፡፡ እስካሁን የተጎዳነው ሕዝብ ልክ እንዳሁኑ በስፋትና በጥልቀት በባለቤትነትም ስሜት የመራው ሕዝባዊ አብዮት ስላልነበረን ነው፤ በዚህም ሳቢያ የሕዝብን የነፃነት ባለቤትነት ማጣጣም አልቻልንም፡፡ በደርግ መነሻ አካባቢ እርግጥ ነው እንዳሁኑ ባይሆንም የተወሰነ ሕዝባዊ ተሣትፎ እንደነበርና በኋላ ግን የሕዝቡ አብዮት በወታደር እንደተጠለፈ እናውቃለን፡፡ የማይሙ ደርግ የሥልጣን ጠለፋ ስህተት ነበርና ለባሰ ውድቀት ዳርጎን አለፈ፡፡

ወያኔም የተነሣው በአንድ አካባቢ ሕዝብ በመሆኑና መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ባለማቀፉ የሆነው ሁሉ ሆኖ ለዚህ በቃን፡፡ አሁን ግን የፈጣሪ ተዓምር ተጨምሮበት ባልታሰበ አቅጣጫ በፈነዳ የብሶት ኒዩክሌር ሀገራችን ከነዚህ መርዘኛ የኮብራና የአናኮንዳ እባቦች በቅርቡ ነፃ ልትወጣ የነፃነት ምጥ ተፋፍሞ ይገኛል፡፡ የምትወለደው ነፃነት ለኔም ትጠቅመኛለች የሚል ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ይተባበርና ካለብዙ መስዋዕትነት እምዬ ኢትዮጵያን “እንኳን ማርያም ማረችሽ” ለማለት እንብቃ፡፡ ሁሉም ወደየኅሊናው ከተመለሰና ከተባበረ ይህ ታሪካዊ ድርጊት እጅግ በጣም ቀላል ነው፡፡ ከፍርሀት ቆፈን መውጣት ብቻ ነው መፍትሔው፡፡

ስድስተኛ – በዚህ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ለመሣተፍ ምንም ዓይነት ቅድመ ሁኔታ አናብጅ፡፡ ሙሰኛም ሳይቀር ተጸጽቶና ከልቡ አዝኖ የበደለውን ሕዝብ ለመካስ ቆርጦ ይነሣ፡፡ ክፉ ሥራውን ሕዝብ እንደሚያውቅ ሁሉ  በነፃነት ትግሉ የሚያበረክተውን በግልጽ የሚመዘግብለት ሕዝብ የፊትና የአሁን ተግባሩን በማመዛዘን ይቅርታ ያደርግለታልና በካፈርኩ አይመልሰኝ በጥፋት ድርጊቱ አይቀጥል፡፡ ዜጎችም ከከንቱ ብቀላና ከተንኮል አስተሳሰብ እንታቀብ፤ ጤናማ ኅሊና ይኑረን፤ አጥፊ ሲጸጸትም ምሕረት የማድረግ ባህልን እናዳብር፡፡ ሰው የገደለም ቢሆን በእውነት አልቅሶና ሀገሬንና ሕዝቤን በድያለሁ ብሎ በዚህ ወሳኝ ወቅት ወደ ነፃነቱ ጎራ በመቀላቀል ከጥፋቱ ጋር የሚመጣጠን መልካም የነፃነት ተጋድሎ ካደረገ ቢሰዋ እንኳ ሕዝቡ ይቅርታውን ይቸረውና ቀሪ ትውልዱ አንገቱን ቀና አድርጎ እንዲሄድ ምቹ ሁኔታ ይፈጠርለታል፡፡ መጥፎው ነገር ወንጀልን በወንጀል እያደሱ መጓዝ ነው፡፡ ኅሊናችንን እንጠብ፣ የነፍሳችንን መንገድ እናስተካክል፡፡ ተበልቶ ለእዳሪ፣ ተጠጥቶ ለሽንት ለሚሆን የሞተ እህል ውሃ ብለን ዘላለማዊነታችንን ባጭሩ አንቅጨው፡፡ ለእህል ውኃ የሚኖሩ እንስሳት ብቻ እንጂ ሰዎች ሊሆኑ አይገባም፡፡ ከእንስሳትም እኮ ለሰው የሚያዝኑና ለሆዳቸው የማያድሩ እንስፍስፎች አሉ – ለምሣሌ ዶልፊን ለሰው አዛኝና አልቃሽ ነው፡፡ ካሳዘንከው ጅብ እንኳን ሳይበላህ አዝኖልህ ሊምርህ ይችላል፡፡ ሰው እንደወያኔ ከጅብ ካነሰ ምን ይባላል? ከጅብና ከወያኔ ማነስ ትልቅ የተፈጥሮና የሥነ ሕይወታዊ ቀመር ችግር  ነው፡፡

ሰባተኛ – አጋዚዎችና አንዳንድ በወያኔ ፍቅር ያበዱ ትግሬዎችን እንዲሁም ከየትኛውም ጎሣ የተገኙ ሆዳም ጅቦችን  እንጠንቀቅ፡፡ ፍቅር መጥፎ ነው፡፡ ፍቅር ያሳብዳል፡፡ ፍቅር ሎጂክና ምክንያታዊነትን የማያውቅ ደደብ ፍጡር ነው፡፡ እርግጥ ነው ፍቅር ዓይነቱ ብዙ ስለሆነ ሁሉም ፍቅር በዚህ እኔ በምለው የፍቅር ጎራ ውስጥ ይካተታል ማለት አይደለም፡፡ የዘርና የጎሣ ፍቅር፣ የሆድ ፍቅር፣ በዓላማና በጥቅም ትስስር የሚመሠረት ፍቅር… እጅግ አደገኛ ነውና ወቅቱ እስኪያልፍ አንደበታችንን ሰተር፤ የምንናገረው ከማን ጋር እንደሆነ ማወቅ፣ ፀጉረ ልውጥን መከታተል… ይገባል እንጂ ልባችንን ለማንም ለማናውቀው ሰው ሁላ መስጠት ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፤ በሚያልፍ ጊዜ የማያልፍ ክፉ ነገር እንዳንሸምት ጥንቃቄ እናድርግ፡፡

ስምንተኛ – በጥቅሉ ይህች ጊዜ እግዜር የፈቀደልን የሽልማት ጊዜ ናት፡፡ ካልተጠቀምንባት ግን እንደዋዛ ልታልፍ ትችላለች፡፡ ካለፈችን ደግሞ  ዳግመኛ ላናገኛት እንችላለን (ሰሜን ኮሪያን ያዬ በነጻነት ትግል አያላግጥም – እያንዳንድሽ ዘላለምሽን የወያኔ ባርያ ሆነሽ ትቀሪያታለሽና ዋ! ብያለሁ፡፡) ይህችን ዕድል ዳግም ካላገኘናት የወያኔን ግፍና በደል በምንም ዓይነት ተዓምር አንችለውም፡፡ የወያኔን የብቀላ ብትር የቻለ ፍጡር እስካሁን በምድር አልተገኘም፡፡ ወያኔ እንኳስ በሕይወት የሚገኝን ፍጡር የሞተን ሰው አጥንትና የዘመናት ዐፅም ከመቃብር ቆፍሮ እያወጣ በጨንገር የሚገርፍ ልዩ የአጋንንት መንጋ ነው፡፡ እነፕሮፌሰር አሥራትን የገደለ … እነሀብታሙ አያሌውን በቁም ስቅል እየገደለ ያለ ዐውሬ ከአሁን በኋላ ስድስት ወር እንኳን ሥልጣን ላይ ቢቆይ በተለይ አንድም ዐማራ በሕይወት አይተርፍም ቢባል ከፈጠጠው እውነታ አኳያ ብዙም ማጋነን አይደለም፡፡ ይህን ሁሉም ይረዳ፡፡ አሁን ደግሞ ዐማራና ኦሮሞ በመቀራረባቸው ምክንያት ወያኔዎች መርዝ እንደበላ ውሻ ጨርቃቸውን ጥለው አብደዋልና ኦሮሞም ሆነ ዐማራ ዕድላችሁ አንድና አንድ ነው – መጥፋት፡፡ ስለዚህ ሁልሽም ይህን የዲያብሎስ ግሪሣ በአንድ ጊዜ ገጥመሽ አስወግጅ፡፡ ስትፎካከሪ ከርመሽ ወያኔ በረዳቶቹ በነዚያ የአጋንንት ጭፍሮች አማካይነት እንደባብ አፈር ልሶ ነፍስ ከዘራ ወዮልሽ፡፡ እነሱም የሚመጻደቁት የድመት ነፍስ እንዳላቸው ስለሚያምኑ ነው፡፡

እነዚያ የዐድዋ ተሸናፊ ሉሲፈራውያን የሩዋንዳ ሕዝብ እርስ በርሱ ከተጨፋጨፈ በኋላ ያለ አንዳች ይሉኝታ በዕብሪት ምን ነበር ያሉት? አዎ፣ እኔ ላስታውስህ – “እንደሚጨፋጨፉ አስቀድመን እናውቅ ነበር!” ነው ያሉት፡፡ ምን ማለት ነው? አልነግርህም፡፡ አልግርሽም፡፡ ግን ጠንቀቅ እንበል፡፡ ትዕቢት የሰይጣን ዋናው መገለጫ መሆኑን ግን እንረዳ፤ ጥጋበኛው ሕወሓትም ትምክህቱንና ዕብሪቱን ያገኘው ከነሱው ከጌቶቹ ነው፡፡ የወያኔን ጌቶች ማመን ቀብሮ ነውና “እገሌ ይደርስልናል” ማለቱ በፍጹም አያዋጣም፡፡

አዳኛችን አንድ ነው – እግዚአብሔር፡፡ ነፃ አውጫችን አንድ ነው – እኛው ራሳችን፡፡ ከሩዋንዳዎች መማር አለብን፡፡ ከሦርያዎች መማር አለብን፡፡ ከሶማያሊውያን መማር አለብን፡፡ ከየመኖች መማር አለብን፡፡ … እነዚህና ሌሎቹም እንደኛው እልከኛ የዘረኝነትና የጎሰኝነት ሾተላይ ገጥሟቸው ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰባቸው እናውቃለን፤ እነማን እንደሚያጨፋጭፏቸውም አሣምረን እናውቃለን፡፡ ለአብነት ነጫጭባዎቹ ቢፈልጉ ሦርያ በአንድ አዳር ሰላም ልታገኝ ትችላለች፡፡ ነገር ግን ወዲያ ማዶና ወዲህ ማዶ ያሉ ከአንድ ግንድ የተገኙ ለይምሰል ግን የማይዋደዱ የሚመስሉ የሉሲፈር ልጆች በእጅ አዙር( ፈረንጆቹ proxy war በሚሉት) እየተዋጉ የመሣሪያ መፈተሻ አድርገዋት ቀሩ – ያሳዝናል – እኛ ግን የደጉ አምላክ ልጆች ነንና ከዚህ ብዙ ልንማር ይገባናል፡፡ ወያኔዎች ደግሞ እንኳንስ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ለትግራይ ክፍለ ሀገር ሕዝብም የማይመለሱ የእፉኝት ልጆች ናቸው – ከሥልጣንና እንደመዥገር ከተጣበቁበት ሀብት አንጻር የሚመጣባቸውን ሁሉ የእናታቸውን ልጅ ሳይቀር በጭካኔ ይገድላሉ፤ ከመግደላቸው በፊት በሚያደርጉበት ዐረመኔያዊ ተግባርም ይዝናናሉ፡፡ ከነዚህ ሰዎች ጋር ድርድር የሚባል ነገር ደግሞ የማይታሰብ ነው፡፡ ወደ መቃብር ካልወረዱና ተራራ እሚያህል ድንጋይ ካልተጫነባቸው ልታምኗቸው አትችሉም፡፡ … ውርድ ከራስ፡፡ በጎሠኝነት ዥዋዥዌ የምትዋልሉ የትግራይ ሰዎች ካላችሁ አቋማችሁን ፈትሹ – ከሚሰምጠው የወያኔ መርከብም ባፋጣኝ ውረዱ – የወያኔ ታይታኒክ መርከብ መስመጫዋ ደርሷልና ሚናችሁን ለዩ፡፡

የተኛችሁ ተነሱ፤ ያንቀላፋችሁ ንቁ፡፡ በዚህ ሰሞን አዲስ አበባን ጨምሮ ሁሉም የሀገራችን ክፍል ለመጨረሻው አርማጌዴዎን ይነሳ፡፡ የወሎና የሸዋ መንገዶች ይዘጋጉ፡፡ ያኔ መሸሻቸው ሁሉ ሲዘጋ የሚሆኑትን እናያለን … የዚያ ሰው ይበለን፡፡ እደግመዋለሁ – ወሎና ሸዋ ከእንቅልፋችሁ ንቁ፡፡ ወለጋ፣ አዋሣ፣ ሐረር፣ ጋሙጎፋ፣ አርሲ፣ ትግራይ፣ አፋር፣ … ሁሉም በአንዴ መነሣትና የማይቀረውን ነጻነቱን መጎናጸፍ አለበት – በራስ የትግል መስዋዕትነት የሚመጣን ነጻነት ደግሞ የሚቀማ ምንም ምድራዊ ኃይል የለም፡፡

ኢትዮጵያ በውድ ልጆቿ ትግል ነፃ ትወጣለች፤ እግዚአብሔር ከኛ ጋር ይሁን፡፡ አሜን፡፡

ግርግር ለሌባ ያመቻል –አገሬ አዲስ

$
0
0

Woyaneበእሳት በተቀጣጠለ ቤት ሳቢያ በሚነሳ የሰፈር ግርግር አሳቱን ለማጥፋትና እቃ ለማዳን በሚል ሰበብ ሌባ ሰርጎ እንደሚገባና በቀውጢ ውስጥ በሚታመስ አገር ውስጥ በሚነሳ ግብግብ አጋርና ተቆርቋሪ መስሎ ለማጥቃትና የራሱን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚመጣ ጠላት እንደሚኖር ተደጋግሞ ታይቷል።ለዚህም ነው ባገራችን ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባበታል ወይም ግርግር ለሌባ ያመቻል የሚለው አባባል የተቀረጸው። በችግር ወቅት በእውነት የሰው ልጅ ጉዳት ተሰምቷቸው የቻሉትን ለማድረግ የሚጥሩና ሌላውንም እየቀሰቀሱ ለተጎዳ እርዳታ እንዲደረግ የሚጠይቁ እንዳሉ ሁሉ ለተጎዳው አሳቢና እርዳታ አቅራቢ መስለው ለእርዳታ የተሰበሰበውን የሚሰርቁና ለራሳቸው ጥቅም የሚያውሉ ሊኖሩ እንደሚችሉ ማሰብ ብልህነት ነው።
በሕዝባዊ ትግልም ውስጥ የሕዝቡን ትግል ያበሩና የረዱ መስለው የራሳቸውን ፍላጎት ለማስከበር የሚራወጡ እንደማይጠፉ በተደጋጋሚ ታይቷል፤አሁንም እየታዬ ነው።በአለፉት ዓመታት የኢትዮጵያ ሕዝብ በገጠመው ችግር ጀርባ የተጠቀሙ እንዳሉ አይዘነጋም።ተደጋግሞ በተከሰው ድርቅ ምክንያት ሕዝብ ለርሃብና በሽታ ተጋልጦ እንደቅጠል ሲረግፍ በዚያ ተገን እርዳታ የሰጡ መስለው የተሰጠውን እርዳታ ለግላቸው ያዋሉ ግለሰቦችና ድርጅቶች እንደነበሩ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፤ አሁንም መኖራቸው አይካድም።
የ1964-66ቱ የድርቅ መቅሰፍት ጠባሳው ሳይደርቅ ታሪክ እራሱን ይደግማል እንደተባለው ከአስር ዓመት በዃላ የዛሬ ሰላሳ ሁለት ዓመት በ1974-76 እ.ኢ.አ. (በፈረንጆቹ 1984 ዓ.ም.)በአገራችን ከፍተኛ የድርቅ መቅሰፍት እንዳለ ይፋ በወጣበት ጊዜ በስልጣን ላይ የነበረው የደርግ ስርዓትም ለዚያ የሚሆን ቅድመዝግጅት ባለማድረጉ የብዙ መቶ ሽህ ሕዝብ ህይወት እንደጠፋ የምናውቀውና ለወደፊቱም ታሪክ መዝግቦ ያስቀመጠው ኢትዮጵያውያንን እስከዛሬ ድረስ ለሃፍረት የዳረገ ሁኔታ ነበር።በዚያን ጊዜ ለተቸገሩ ወገኖቻችን እርዳታ እንሰበስባለን ብለው የተነሱ ብዙ የውጭአገር ድርጅቶችና ኢትዮጵያኖች በያሉበት ተንቀሳቅሰው ነበር።በውጭ አገር ከተነሳሱት ድርጅቶች መካከል ሻእቢያና ወያኔ በጫካ በነበሩበት ጊዜ ከጎናቸው በመቆም እርዳታ ሲያደርጉ የነበሩ በሃይማኖትና በሰብአዊ መብት ድርጅት ስም የሚንቀሳቀሱ አውሮፓውያን ነበሩ።እነዚህ ድርጅቶች በዚህ የድርቅ እርዳታ ሰበብ ከሕዝብ የተሰበሰበውን እርዳታ ብዙውን ድርሻ በሥራ ማስኪያጃና በመሳሰሉት ወጭዎች ሰበብ ለራሳቸው ገቢ ሲያደርጉ የተረፈውን ለሚረዷቸው ተገንጣይ ሃይሎች የጦርነት ባጀት መሟያ አድርገውታል። ለተራበው ሕዝብ ተላከ የተባለው እርዳታም በአገራቸው ፋብሪካ በገፍ ተዘጋጅቶ ለገበያ ቀርቦ ገዥ ያጣ፣ደረቅ እሽግ የክፉ ቀን ወይም የጦር ሜዳ ምግብ ነበር።ከአውሮፓ የተላከውን እርዳታ ከቦታው ለማድረስም የአውሮፓውያኑ የመርከብና የአውሮፕላን አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች ተጠቅመዋል።ይህን ከፍተኛ ወጭ ለማዳንና ሕዝቡም የለመደውን እህል እንዲመገብ፣የቀረበላቸውን ሃሳብ አልተቀበሉትም።የቀረበው ሃሳብ በአጎራባች አገሮችና በሌላው የኢትዮጵያ ክፍለሃገር የሚመረተውን ገዝቶ በማቅረብ ለተቸገረው በቅርበትና ባስቸኳይ እርዳታው ሊደርስ ይችላል የሚል ነበር። በተጨማሪም አስቸኳይ እርዳታ ከማድረጉም ጎን ለጎን ለወደፊቱ ድርቅ ቢከሰትም እርሃብ ዳግም እንዳይከሰት በሚረዳው መልኩ ገንዘቡ ጥቅም ላይ ይዋል የሚል ሃሳብ ተሰንዝሮ ነበር።ሆኖም ግን የታያቸውና የዘረጉት እቅድ በእርዳታ ስም በተዘዋዋሪና በቀጣይነት የሚጠቀሙበትን በመሆኑ ለቀረበላቸው አስተያየት ትኩረትም አልሰጡትም። ከሕዝቡ የተሰበሰበው በመቶ ሚሊየን የሚቆጠረው ገንዘብ በሃይማኖት ተቋማት፣በካቶሊክና በፕሮቴስታንት እንዲሁም መንግሥታዊ ባልሆኑት ድርጅቶች(NGO)ካዝና ውስጥ ገብቶ ለፈለጉት ተግባር አውለውታል።በደሃው የኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ዕቅዳቸውን አሳኩበት፤ተገንጣዮችንና አስገንጣዮችን አጎለበቱበት።የካቶሊክ ተቋማቱ ከታሪካዊ ትስስራቸው የተነሳ ከተገንጣዮች ጋር የነበራቸው ግንኙነትና የሰጡት እርዳታ የሚገርመን ባይሆንም በዚህ በሰዎች ህይወት ጀርባ የተከናወነው ሸፍጥና ዘረፋ በደሃው የትግራይ ሕዝብ ስም ጭምር የተደረገ በመሆኑ እራሳቸው ለትግራይ ሕዝብ መብትና ነጻነት እንታገላለን ብለው የተነሱትም አሁን በሥልጣን ላይ የተቀመጡት የህወሃት አባላት ተቋዳሾች በመሆናቸው የወንጀሉ ተካፋዮች ነበሩ። በካቶሊኮቹ ብቻ ሳይሆን በፕሮቴስታንቱም በኩል እንዲሁ በኦሮሞ ነጻ አውጭ ድርጅት በኩል የተደረገው እርብርቦሽ ያንኑ የሚመስል ነበር። አሁንም ቢሆን በዚያው ቀጥሎበት ይገኛል። በይበልጥ ቅስም የሰበረው ደርግ አስረኛ ዓመቱን ለማክበር ሲል በዚያ በፈታኝና ቀውጢ ሰዓት በሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ወጭ አውጥቶ ድል ያለ ፌስታ ማዘጋጀቱ ነው።ምንም እንኳን ሃላፊነት የነበረውና ለሕዝብ የሚጨነቅ አለመሆኑ ቢታወቅም በመንግሥት ደረጃ ያለ አካል አገሩ በዓለም አቀፍ ደረጃ በርሃብ ታውቆ የውጩ ሲረባረብ ያንን ያህል ክህደትና ጭካኔ የተሞላበት ምግባር ላይ መዋሉ እስከመቼውም በታሪክ ይቅርታ የሚባልለት አይደለም።ያም ብቻ ሳይሆን በሚገቡ የእርዳታ ስጦታዎች ማለትም በምግብ፣በመድሃኒትና በገንዘብ ላይ ቀረጥ በማስቀመጥ ከፍተኛ ገንዘብ ሰብስቦ ለጦር መሳሪያ ግዥና ለባለሥልጣኖቹ ኪስ ማብቃቱም ሌላው አሳፋሪና ኢሰብአዊ ምግባር ነበር።
በስደት በሚኖሩ ኢትዮጵያኑም ዙሪያ ይህንኑ የመሰለ አውሬነትና እራስ ወዳድነት የተንጸባረቀበት ሁኔታ ነበር።እኔ የማውቀውን ብናገር፤በሆላንድ ውስጥ የነበርነው የደረሰውን ችግር በሚመለከት የሚቻለንን ለማድረግና እርዳታ ለመሰብሰብ ስንነሳ በተጓዳኝ ሌሎች ጥቂት ኢትዮጵያውያን እንዲሁ እርዳታ እንሰበስባለን ብለው ተነሱ።ተቀራርቦ ለመስራት የተደረገው ጥረት ሳይሳካ በተነሱበት መንገድ ቀጥለው በተለይም ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ከአገሩ ዜጎች ጋር የተጋቡ በመሆናቸው የደቹን ህብረተሰብ ለመሳብና ለማሳመን በመቻላቸው ሌሎቻችን ከሰበሰብነው በላይ ገንዘብ ለመሰብሰብ ቻሉ። በእኛ በኩል የሰበሰብናትን በድምጽ ብልጫ ውሳኔ ተወስኖ ያደርስልናል ለተባለው ድርጅት ተሰጠ።በሌሎቹ በኩል ግን “ሌባ ሲሰርቅ ይስማማል ሲካፈል ይጣላል” እንደሚባለው ሆነና በክፍፍሉ ላይ ጭቅጭቅ ተነሳ፤መፈነጋገል ተጀመረና ግብግብ ገጠሙ። አንዱ በራሱ ስም መኪና ገዛበት፤ይኸው ሰው ከሌላው ጋር በድራግ ሱስ የተለከፈ ስለነበር በዛው በድራግ ግዢ ገንዘቡን አባከኑት።ሌላው የዋህ ብቻውን አጨብጭቦ ቀረ።ቢወጣ ቢወርድ የሚሰማው አጣ። የሚገርመው ነገር፣በድሆቹ ስም ይህን ያደረጉት ሰዎች አንዳቸውም አልተባረኩም፤ሁለቱ ለጡረታ ሳይበቁ በድንገተኛ በሽታ ሞቱ፤ አንዱም ኑሮ ሳይሳካለት ቀረና የወለደውን ልጅ ስሞ ሳይጠግበውና ለቁም ነገር ሳያበቃው አገር ጥሎ ጠፋ። በእብሪት ተነፍቶ የነበረው ደርግም ቅሌት ተከናንቦ ፈራረሰ።የኢትዮጵያ ሕዝብ እምባ በከንቱ ደርቆ አይቀርም፤ ይዋል ይደር እንጂ ግፍ የሰሩበትን ዋጋ ያስከፍላል።
ይህንን እንደምሳሌ ያቀረብኩት አሁን ኢትዮጵያ ባለችበትና ሕዝብ በሚሳተፍበት ትግል ዙሪያና በእርዳታ ስም በመከናወን ላይ ያለው የመሽቀዳደምና በስም የመነገድ ምግባር በመከሰቱ ከዚህ አይነት ደረጃ ላይ ሊደርስ እንደሚችል በመገመት ነው።
ሕዝብ ለዴሞክራሲ ስርዓት መስፈን፣ለመብቱና ለአገሩ አንድነት በሚዋደቅበትና መስዋዕት በሚከፍልበት በአሁኑ ጊዜ በልዩ ልዩ ስም ትግሉን እንመራለን፣ እንረዳለን፣የትግሉ አጋርና አካል ነን፡ የሚሉ ተነስተው የሚያደርጉት ሽኩቻና መስገብገብ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ በማጤን በአፋጣኝ እንዲወገድ ለማሳሰብ ነው።
ሕዝቡ ኢትዮጵያ ወይም ሞት ብሎ በአንድ ሰንደቅ ዓላማ ስር ተሰልፎ ሲታገል የዚያ ተጻራሪ የሆነ የመገንጠልን ቅኝት የሚቃኙና የነሱን ጥቅም ለማስጠበቅ የተነሱ አስመሳዮች ይህን የሕዝብ ትግል ቆልምመው ለራሳቸው ፍላጎት ለማዋል የሚቅበጠበጡ ስላሉ ከሚያደርጉት ጸረ ኢትዮጵያ እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ ማስገደድና ለነሱም እርዳታም የሚያደርጉ የዋህ አገር ወዳዶች ሁኔታውን እንዲያጤኑት ለማሳሰብ ነው።አንዳንዶቹ ድርጅቶች እነሱ የማይቆጣጠሩት ህዝባዊ እንቅስቃሴና ትግል ቢሰናከል ይመርጣሉ።ለእነሱ ትግል ማለት ለተነሱበት የማይታወቅ ዓላማ ማጎብደድና የጠየቁትን ድጋፍ ሳይጠራጠሩ መስጠት ነው።አፍ አላቸው ያምታታሉ፣የሰውን ደካማ ስነልቦና ፈልቅቀው ስለሚያውቁ ይጠቀሙበታል።በዘፈኑ፣በትያትሩ፣በቀልዱ፣በከባቢ ስሜቱ፣በጥቅም ሰንሰለት ተብትቦ በማሰር… የሚቃወማቸውን በማስፈራራቱና በሃሰት ስብእና በሚነካ ዘመቻ የፈለጉትን ከማድረግ አይመለሱም፤በተወሰነም ደረጃ ተሳክቶላቸዋል።ግን አብሯቸው ማምሸቱ ያጠራጥራል።የጊዜ ጉዳይ ነው ይጋለጣሉ።
ጎን ለጎንም በራሱ ሃይል ተነሳስቶ ትግል በሚያደርገው ሕዝብ ስም፣በተለይም በአማራው ማህበረሰብ ስም ሞረሽ ፣ቤተአማራ፣ዳግማዊመአድ…ወዘተ የተባሉ እርስ በርሳቸው የሚሻኮቱ የተለያዩ ድርጅቶች አቋቁመው የገንዘብ እርዳታ በመሰብሰብ ላይ የተሰማሩ ቡድኖች ተመስርተዋል። አነሳሳቸው ቀና ቢመስልም በዚህ መልክና ብዛት ስር የሚያደርጉት ተለያይቶ ጉዞ ወደፊት ሊያስከትል የሚችል ችግር እንዳለ ይሸተኛል።ያ ከመሆኑ በፊት አደጋውን ተገንዝበው እውነት ለአማራው ማህበረሰብ ካሰቡና ከተጨነቁ በአንድ ነጠላ ድርጅት ስር ተሰልፈው የሚገኘውን እርዳታ በሚፈለገው ቦታ ለሚፈለገው ተግባር እንዲደርስ ቢያደርጉ የሚያስተማምንና ውጤት ያለው ጥረት ይሆናል። በየአቅጣጫው የሚገኘው የእርዳታ ገንዘብ ለምን ተግባር መዋል እንዳለበት በግልጽ መቀመጥ አለበት።ለትግል ማስኬጃ፣ለመደራጃ፣ለመጓጓዣ፣ለቆሰለው ህክምና፤ ለምግብ፣ ለሰላማዊ ሰልፍ ዝግጅት፣ለታሰሩት ስንቅና ጠበቃ፣ ለተሰዉት ቤተሰቦች እርዳታ፣ወላጅና እረዳት ላጡት መደጎሚያ፣ለተፈናቀሉት መቋቋሚያ …ወዘተ የሚውል መሆኑን ለይቶ አላፊነቱን የሚወስደው አካል ቢታወቅ እረጅው ለፈለገው ተግባር ለመርዳት ይቀለዋል።በጥቅሉ እርዳታው ተሰብስቦ ከምን ቦታ ላይ እንደሚውልና ተጠያቂው ማን እንደሆነ ካልታወቀ የረጁን እምነት ያሳጣል። በፖለቲካው ዙሪያ በሚደረገው የተለያየ ትግልና በሰብአዊው በንገድ የሚደረገው የእርዳታ እርብርቦሽ ተለይቶ ቢቀመጥ መልካም ይሆናል። በፖለቲካ ትግል ለተሰማሩት እርዳታ የሚሰበስብ አካል ለብቻው መንቀሳቀስ ይገባዋል እንጂ ከሕዝቡ ጉዳት ጋር በተያያዘው ሰብአዊ እርዳታ የማሰባሰብ እንቅስቃሴ ውስጥ ባይጣመር የተሻለ ነው።ለሰብአዊው እርዳታ የሚያሰባስበው ቡድን ከሁሉም የተውጣጣ ሕዝባዊ አካል ተጠያቂነቱም ለሕዝቡ ሲሆን ለፖለቲካ ድርጅቶች ግን የራሱ አባላት የሚመሩትና ተጠያቂነታቸውም ለፖለቲካ ድርጅቱ ይሆናል።
በጣም የሚገርመው ደግሞ በአሁኑ ጊዜ ይባስ ብሎ እርዳታ አሰባሰቡ እንደፖለቲካው አለሰላለፍ ጎጥ እየያዘ መምጣቱ ነው።የጎጃም፣የወሎ፣ የጎንደር፣የሸዋ…እያለ መሰባሰብ እንደተጀመረ ይፋ ይነገራል።ይህንን አይነት አደረጃጀት የምንታገለው ወያኔ በደስታ ይቀበለዋል፣ያበረታታዋልም።በዚህ በየአቅጣጫውና በየስሙ በሚገኘው እርዳታ ምክንያት አላስፈላጊ ግጭትና ክፍፍል እንዳያመራ በኢትዮጵያውያን ስም በተከፈተና የጋራ ቁጥጥር ወዳለበት አንድ የባንክ አካውንት ቢገባ የተሻለ ከመሆኑም በላይ እረጁን እምነት እንዲያድርበት ያደርጋል፤ለተረጁም የሞራል ብርታት ይሰጣል።ትግሉንም አገር አቀፍ ያደርገዋል።ተለያይቶ በየአቅጣጫው መባከን ሃይልን ማመንመን ሲሆን በከባቢ ስሜትና ጎጥ መሰለፍ ደግሞ ትልቁን የኢትዮጵያዊነትን መንፈስ ይሰብራል፣ሃይልን ይንዳል፣የአገርንም አንድነት ያናጋል፤አካሄዱም ከሚታገሉት የወያኔ አካሄድ አይለይም፤ የሱኑ ጉዞና መንገድ መከተል ይሆናል። በየቦታው በተለይም በአማራው ክልል ከተንጸባረቀውም ሕዝባዊ ትግል መልእክትና አቋም የተለየና ተጻራሪ ነው።አሁን በየቦታው የሚካሄደው ሕዝባዊ ትግልና አመጽ ኢትዮጵያዊነትን የሚያጎላ ነው።በአንድ ኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም ቦታ የሚካሄደውን ሕዝባዊ ትግል ለማገዝና የሚደርሰውን ጉዳት ለመታደግ በየጎጡ መደራጀት አስፈላጊ አይደለም። የሕዝቡንም ጉዳት ለመታደግ በፖለቲካ ድርጅታዊ ጥቃሞት አንጻር እየታዬ መደረግ አይገባውም። የህዝብ ጉዳት የፖለቲካ ድርጅቶች ሸቀጥ የሚሸጡበት ሱቅ አይደለም። በሃቅ ችግሩን ለመታደግና ለሕዝቡ ለመድረስ ከተፈለገ አንድ ወጥ የሆነ፣ከፖለቲካ ድርጅቶች፣ከእምነት ተቋማትና ከአካባቢ ጎጠኛ አስተሳሰብ ተጽእኖ ነጻ የሆነ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ የተዋቀረ ብሔራዊ እርዳታ አስተባባሪ አካል(National solidarity coordinating body) በዓለም አቀፍ ደረጃ አቋቁሞ መንቀሳቀሱ ይበልጥ አስተማማኝ ይሆናል። በመንቀሳቀስም ላይ ያለው ግሎባል አሊያንስ(Global alliance)የተባለው አሰራሩን ከፖለቲካ ድርጅት ትስስርና ዝንባሌ አጽድቶ ቢንቀሳቀስ የበለጠ ሊጠቅም ይችላል። እንደኔ ያለውን ለመርዳት የሚፈልግ ዜጋ ከመርዳት የሚያግደው ነገር የድርጅቶች ጋጋታ መኖር ነው።ይህ አይነቱ አሰራር ቢቀር መልካም ነው።
ወያኔ ያደረሰውና የሚያደርሰው ጥቃትና ጉዳት ጎሳና ቦታ የለዬ አይደለም።ይህን የጋራ ጥቃት በጋራ ሆኖ መቋቋምና ማሶገድ ተገቢና አስፈላጊ ነው።ከዚህ የተለዬ ሌላ አማራጭ የለም።ቢኖርም ውጤቱ የሚያረካ አይሆንም።እስካሁን የሚታገለውን ሕዝብ ለሚገጥመው ችግር ለመርዳት የተደረገውና ለመደረግም የታሰበውን ጥረት እያደነኩኝ ወደ መጥፎ አቅጣጫ እንዳያመራ በቅድሚያ እንዲታሰብበት ለማስገንዘብ ያቀረብኩት ይህ ሃሳብ በየፊናው በቀናነት የሚደረገውን የህዝቡን ተሳትፎና ጥረት ለመቃወም ሳይሆን ከአውሬዎች መንጋጋ ለመከላከል ወይም የእርስ በርስ ግጭትና ንትርክ ውስጥ ሳይገቡ አመርቂ ውጤት እንዲያመጣ ካለኝ ቅን ምኞት በመነሳት እንደሆነ እንዲታወቅልኝ አሳስባለሁ።ብዙ ስብስቦች በገንዘብና በቡድናዊ ስሜት ምክንያት ከመፈራረስ ደረጃ ላይ እንደደረሱና በደጋፊው ላይ ተስፋ መቁረጥን እንዳስከተሉ ያየሁ በመሆኑ ያ በድጋሚ እንዲከሰት አልሻም።
ማሳሰቢያ
አሁን አገራችንና ወገናችን ያለበት ወቅት ወሳኝ ደረጃ ላይ ደርሷል።ሕዝብ ከመንግሥት ጦር ጋር ተፋጧል፣እየተፋለመ ነው።ብዙ እልቂት ሊከሰት ይችላል፤ አሁንም እየተከሰተ ነው።የእርዳታ ያለህ ብሎ ይጣራል።የወገኑና የሃገሩ ጉዳይ የሚያሳስበው ሁሉ ለዚህ ጥሪ በያለበት መልስ ሊሰጠው ይገባል፣ከከባቢ እስከ ቤተሰብ ድረስ የገንዘብ እርዳታ ማሰባሰብ ይኖርበታል።የኮሚኒቲ ማህበራትም በአካባቢያቸው የሚኖረው ኢትዮጵያዊው ተገናኝቶ የሚችለውን ያህል እርዳታ እንዲያደርግ የአስቸኳይ ጊዜ ጥሪ(Emergency call) ማድረግ ይኖርባቸዋል። የሚሰበሰበውን ገንዘብ በተናጠልና በየጎጡ ለሚንቀሳቀሱትም ሆነ ለፖለቲካ ድርጅቶች ማስረከብ ሳይሆን በአገር አቀፍ ደረጃ ተቋቁሞ ለሚንቀሳቀሰው አካል ማስተላለፍ ይኖርበታል።ከተቻለም በሚመጣው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ወይም የመስቀል ዕለት በዓል ጋር የተያያዘ ዝግጅት በማድረግ ጎላ ያለ ገቢ ማሰባሰብ የሚቻልበት መንገድ ሊታሰብ ይገባል። በነዚሁ ቀናቶች በየአገሩ የሚኖሩት የኪነት ባለሙያዎች ተባብረው ለዚህ ህዝብና አገር አድን ዘመቻ ቅድሚያ በመስጠት ብሔራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪየን አቀርባለሁ።
በአንድነት ለአንድነት!
አገሬ አዲስ

የ‹‹አቶ››ና ‹‹ፕሮፍ›› ልዩነት—ከጫት ተራ እስከ ምርምር-ተቋም!  –በዮሴፍ ሙሉጌታ  ባባ (ዶ/ር)

$
0
0

 

kankokunmalimaali@gmail.com

ክፍል 15

(ማስታወሻ፡ይህ መጣጥፍ ‹‹የጫት ተራ ፍልስፍና›› ከተሰኘ ያልታተመ መጽሐፍ ተቀንጭቦ የተወሰደ ነው)

 

comment symbol icon

comment symbol icon

አበው ስፈላሰፉ ‹‹81 መጽሐፍ ከተማረ ሰው፣ መከራ የመከረው ይሻላል›› ይላሉ። አንድም፣ ‹‹እውቀት የሚንገበይበት ትልቁ ት/ቤት፣ የሕይወት ልምድ ነው›› ፤ ሁለትም ‹‹ልምዱ የሌለህን ነገር አታውቀውም››፤ ሦስትም ‹‹ ሆዳቸውን እንዴት እንደሚያማቸው የሚያውቁት የሚሰቃዩት ብቻ ናቸው›› የሚል አንደምታ አለው። ጃማይካዊያን ‹‹በመፃሐፍቶች ውስጥ የማናገኘውን ጥበብ የሚናገኘው ስናዝንና ስንሰቃይ ብቻ ነው—only through suffering and sorrow do we acquire the wisdom not found in books››—እንደሚሉ ማለት ነው። ለምሳሌ፡- ሕይወቱን ሙሉ ‹‹አንዷን ሳያቅ›› በሥነ-ወስብ (sexology) ዙሪያ 85 መጽሐፎችን ከደረሰ ‹‹ምሑር›› ይልቅ፣ ስለ ወስብ ምንነት የተሻለ ግንዛቤ ያለው፣ አንድ ሁለት ቀን በተግባር ወስብ የፈጸመ ግለሰብ ነው! እዝ ላይ፣ ‹‹የዕውቀት ምንጭ ልምድ ነው ወይስ ከልምድ ውጭ (ተፈጥሯዊ)?›› ለሚለው ፍልስፍናዊ ጥያቄ መልስ ለማፈላለግ አይደለም። እንድህ ዓይነቱን የቅንጦት ጥያቄ የተረጋጋ ማኅብረሰብ ውስጥ መኖር ስንጀምር አንድ ቀን እንፈላሰፍበታለን! ይልቅ፣ ‹‹የጥበብ መገኛ የምርምር-ተቋም ወይስ ጠጅ-ቤት?›› የሚለውን ጥያቄ ትንሽ ለመቃኘት ያህል ብቻ ነው።

‹‹ትምህርት የአመለካከት ለውጥ የማምጣት አቅም አለው ወይ?›› የሚል የብዙዎች ጥያቄ ነው። ለምሳሌ፡- ‹‹አቶፕሮፍመካከል የአመለካከት ልዩነት ከሌለ፣ የመማር ጥቅም ምኑ ላይ ነው?›› የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። በበኩሌ፣ በጫት-ተራ እና ቤተ-መጽሐፍት መካከል ያለውን ልዩነት ለማወቅ ያደረኩት ጥረት እስካዛሬ ድረስ አልተሳካልኝም። ምክንየቱም፣ በጥልቀት የተመራመረና ሕዝቡ ‹‹ፕሮፍ›› ወይም ‹‹ዶ/ር›› የሚለውን ግለሰብ 2 ለ 0 የሚሸኝ ነጋዴ ወይም ሾፌር  ጫት-ተራ አከባቢ እንደ አሸን በፈላበት ዘመን፣ በሁለቱ መካካል ያለውን ልዩነት ማወቅ አይቻልም የሚል አቋም አለኝ።። ቢሊ ሴንደይ፤ “ጋራዥ ውስጥ መቆም መኪና እንደማያሰኝህ ሁሉ፣ ቤተ-ክርስቲያን መሄድም ክርስቲያን አያሰኝህም” ያለው ነገር ትክክል ሳይሆን አይቀርም! በእርግጥ ድግሪ እንደ ሸቀጥ በገንዘብ በሚሸመትበት ዘመን ላይ ሆኜ፣ በምርምር-ተቋም እና ጠጅ-ቤት መካከል ያለውን ልዩነት መጠየቅ አልነበረብኝም!

ያም ሆነ ይህ፣  በትምህርት ዓለም አንድን ሰው ምሑር የሚያሰኘው ‹‹እራስህን እወቅ—know thyself›› የሚለው የግብጻዊያን መምህራን አባባል (የሶቅራጠስ አይደለም!) በሕይወቱ መተግበር ከቻለ ብቻ ነው።  ‹‹አቶዎችና ›› ‹‹ፕሮፍዎች›› መካከል ያለውን የአመለካከት ልዩነት በትክክል ለመረዳት ታድያ፣ ‹‹እራስህን እወቅ›› የሚለው የጥቁሮች/የግብጻዊያን አባባል ብቸኛው መለኪያ ይሆናል ማለት ነው። ለምሳሌ፡- የ‹‹እራስህን እወቅ›› ጥያቄን በተመለከተ ጠጅ-ቤት አካባቢ አራት ዓይነት ሰዎች አሉ፡- (1) ስለ ራሳቸውም ሆነ ስለ “ሌላ” ሰው ማንነት ግልብ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች፣ (2) ስለ “ሌላ” ሰው ማንነት ጠለቅ ያለ እውቀት ያላቸው፣ ግን ስለ ራሳቸው ማንነት በጣም ትንሽ ግንዛቤ ያላቸው ሰዎች፣ (3) ስለ ራሳቸውም ሆነ ስለ “ሌላ”ው ሰው ማንነት ጠለቅ ያለ እውቀትና ግንዛቤ ያላቸው ሰዎች፣ (4) ስለ ራሳቸው ማንነት ጠለቅ ያለ እውቀት ያላቸው፣ ግን ስለ “ሌላ” ሰው ማንነት ምንም ግንዛቤ የሌላቸው ሰዎች-ናቸው።

ከዝህ አንፃር ካየነው፣ ብዙ ‹‹ፕሮፍዎች›› ‹‹አቶዎች›› በተራ ቁጥር 1 እና 3 ሥር በየተራ (respectively) የሚደለደሉ ሲሆን፣ ጥቂት ‹‹ፕሮፍዎች›› ‹‹አቶዎች›› ደግሞ እንደየሁነታው በተራ ቁጥር 2 እና 4 ሥር በየተራ የሚደለደሉ ናቸው። የበለጠ ግልጽ ለማድረግ፣ በስም ‹‹አቶዎች›› ሆነው በአስተሳሰብ ግን ‹‹ፕሮፍዎች›› የሆኑ እንዳሉ ሁሉ፣ በስም ‹‹ፕሮፎች›› በአስተሳሰባቸው ግን ‹‹አቶዎች›› ያነሱ ግለሰቦች በእርግጠኝነት እንዳሉ በግልጽ ለማሳየት ነው። ለዝህ ምን ዓይነት ተጨባጭ ማስረጃ አለ? የጓደኛዬን የፕሮፍ ‹‹ጐንዳ››ን አመለካከት ለአብነት ማንሳት ይቻላል። (በነገራችን ላይ፣ በሀገራችን ባህል የሰዉን ስም መዘርነቅ ነውር በመሆኑ፣ በግለሰቡ ትክክለኛ ስም ምትክ “ጐንዳ” የሚለውን የአፋን-ኦሮሞ ቃል ተጠቀመያለሁ። ትርጉሙም “ጉንዳን” ማለት ሲሆን፣ የ‹‹ጐንዳ››ና መሰሎቹን አስተሳሰብ/ጸባይ አስቸጋርነት ለማመልከት ታስቦ የተሰጠ ስም ነው። ዝለዝህ፣ ይህ ምሳሌ ለሁሉም ‹‹ፕሮፍዎች›› የሚሰራ ነው)

ፕሮፍ ‹‹ጐንዳ›› ራሱንና ለሎችን የሚመለከትበት ‹‹መነጽር›› ከማስገረምም አልፎ ያሳብዳል! ‹‹እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን ብሎ በግትርነት የሚፀና ሰዉ ለድንቁርናዉ ምስክር ነዉ›› የሚለው የሚካኤል ሞንቴን አባባል ‹‹ጐንዳ››ን ማንነት ከ ሀ እስከ ፐ ይገለጸዋል የሚል እምነት አለኝ። ፕሮፉ ስበዛ ጥፋትጎምጅ (fault finder) ነው! የሌላ ሰው ሥራ (አመለካከት) ውስጥ ስሕተትን መፈለግ እንጅ፣ ጭብጥን በጭብጥ መመከት አይሆንለትም። ለላው ቀርቶ፣ የሌሎች ሰዎች ‹‹ኀጥያት” እንጅ፣ የራሱ የበሰበሰ አመለካከት አይታየውም። እንደ መዝሙረ-ዳዊት የሚደጋግማት አንድ ሐረግ አለችው፤  “እገሌን ታዘብኩት!” ግን “ወንፊት ለመርፌ ‹ጭራህ ላይ ቀዳዳ አለብህ› ትለዋለች” የሚለውን ነገር አንድም ቀን አስቦት አያውቅም። ሂስና ትዝብት ከራስ እንደምጀምር የተረዳ አይመስልም፤ ሰዎችን የሚያጃጅለው በአበባ ቃላቱ ነው፤ “የቃላቶች መጥለቅለቅ ባለበት ቦታ፣ የጥበብ እጥረት አለ” የሚለውን አባባል ጓደኞቹ በሚገባ የተረዱ አይመስልም። ስለዝህ፣ የራስን ሥራ አወዝፎ የሌላውን ሥራ መንቀፍ እንጅ፤ነባራዊ እውነት (objective truth) አንፃር ነገሮችን ማየት አይሆንለትም፤ በዝህ ምክንያት ሰውን የሚለካ በሰውነቱ ሳይሆን በትምህርት ደረጃ፣ በሀብት፣ በጾታ፣ በብሔር…ወዘተ ነው። እና ጐንዳ ዝነኛ ነኝ ብሎ የሚያስብ ዓይነት ሰው ነው!

የጐንዳ “ጽድቅ” እና  “ዝና” ከምን እንደመነጨ ግን አይታወቅም፤ ለትዳሩ ታማኝ ነው እንደይባል፣  “የብልት ፍልስፍናው” ያመዝናል! በዕውቀቱ ነው እንዳንል፣ የትምህርት ማስረጃዎቹ በአድርባይና ወሮ-በላ ምሁራን አማካኝነት ከዩንቬርስት እንደ ቻይና ዕቃ በርካሽ ዋጋ የተሸመተ ነው፤ ከድሃ ሕዝብ ክስ በወጣ ገንዘብ ዘርፎ ቤትና መኪና መግዛቱ፣ በሃብቱ እንደይኮራ እንቅፋት ሆኖበታል፤ ስልጣኑ በዝምድና የተገኘ እንጅ በብቃቱ አይደለም፤ የፍውዳል አስተሳሰብ ስላለው፣ በአመለካከቱ ካለፈው ትውልድ አንሶ እንጅ ተሽሎ የተገኘበት ጊዜ ፈጽሞ አልነበረም። ይህ ሁሉ ወራዳ ተግባር ስመለከት፣ “እገሌን ታዘብኩት!” የሚትለው መዝሙሩን በፍልስፍና መነጽር መመልከት ወደድኩ፤ እናም “ታዛቢውን ታዘብኩት!” የሚለው መደምደሚያ ላይ ደረስኩ!

ከአንድ የጫት ነጋዴ ወይም የካፌ አስተናጋጅ ያነሰ አመለካከት (አስተሳሰብ) ይዞ ለሎችን ለማስተማር ወይም ለመገጸጽ ወይም ለመምራት የሚቋምጥ ‹‹ፕሮፍ››ን ማዬትን የመሰለ አሳዛኝ ነገር የለም። እሱ የሚንቃቸው ‹‹አቶዎች›› ስለ እውነታ ከእርሱ በጣም የተሻለ ግንዛቤ እንዳለቸው ቢያውቅ ኖሮ፣ እንድህ ዓይነቱ የአስተሳሰብ ሽርሙጥና ይዞ በአደባባይ አይዘባርቅም ነበር።  ዝለዝህ ነው፣ ጫት-ተራ አካባቢ በስም ‹‹አቶዎች›› ሆነው በአስተሳሰብ ‹‹ፕሮፍዎች›› እንዳሉ ሁሉ፣ በምርምር ተቋም ወስጥም በስም ‹‹ፕሮፎች›› ሆነው በአስተሳሰባቸው ግን ‹‹አቶዎች›› ያነሱ ግለሰቦች አሉ የሚንለው አንድ የአሌክሳንደር ፑሽክን ግጥም የ‹‹ጐንዳን››ና መሰሎቹን የአስተሳሰብ ቅሬ አስታወሰኝ፡-

ግማሽ ክቡር―ግማሽ ነጋዴ፣

ግማሽ ታማኝ―ግማሽ ወንበዴ፣

ግማሽ ሩህሩህ―ግማሽ መደዴ፣

ከሆነ ቡድን ጋር፣

ይቻላል ወይ አብሮ መኖር?

(አያልነህ ሙላቱ እንደቶረጎመዉ!!)

 

‹‹እራስህን እወቅ›› የሚለው አባባል ራስን የሚያስኮፍስና ሌባ የሚያረግ ሳይሆን፣ ትሕትናና ሐቀኝነትን የሚያስተምር ነው። እንኳንስ በማጨበርበር የተገኘ ድግሪ፣ በትክክለኛ መንገድ የተገኘ የትምህርት ማዕረግ ዋና ዓላማ፣ ሕዝቡን በቅንነት እንድናገለግልበት እንጅ፣ ሌላው ላይ ለመዘነጥ/ለመሰልጠን አይደለም። ‹‹መዘነጥ እንዳለ ሁሉ መዘነጣጠልም አለ›› የሚለውን አባባል መርሳት የለብንም። የአንድ ግለሰብ ዕውቀት (ስልጠና) ብዙኅኑን ካለጠቀመ፣ የፕሮፈሰርነት ማዕረጉ ለሕዝቡ አንድ ኪሎ ሽንኩርት ወይም ድንች ሊሆን አይችልም። በተግባር ያልተገለጠ ዕውቀትና ከመልካም ሥራ የተለየ እምነት አንድ ነው። ሰው መከበር ያለበት በተግባሩና በአስተሳሰቡ እንጅ በማዕረጉ አይደለም፣ ከባለጌ ክቡር የድሃ ሥልጡን ይሻላልና!  ጥሩንባ የሚነፉ ሰዎች አላጣንም! ጋንዲ ‹‹ከአንድ ኩንታል ወሬ አንድ ኪሎ ተግባር›› ብሎ የለ! ስለዝህ፣ ስብከቱን ለሕሁድ እናቆየው!  በደበበ ሰይፉ ግጥም ልሰናበታችሁ፡

ከህይወትህ ወዲያ ላያልፍ—የጥናትህ መደቡ

ከህዝብ ጉያ ላይርቅ—የምርምርህ ክበቡ

ምንም ብትረቅ ምንም ብትርቅ—እምትደርስበት ግቡ

ወይ የመነሻህ ርካቡ………..

……የስንቱን አይነ ልቡና አታለልክ

አስተዋይነቱን አጭበረበርክ

በቋንቋ ግርዶሽ እየተጠለልክ

ተጠበብኩ ስትል ጠበብክ

አወቅኩ ስትል ደነቆርክ

በክፍል 16 ‹‹በመጀመሪያ ሙሲና ነበረ፣ ሙስናም በስልጣን ዘንድ ነበረ፣ ሙስናም ስልጣን ነበረ›› የሚለውን እንመለከታለን

ቸር-እንሰንብት!!!!

 

 

 

የወያኔ እኩይ የዘረኝነት ተግባር ማብቂያው ደረሰ!! –ከዲቦራ ለማ/ኖዌይ

$
0
0
Dibo

ዲቦራ ለማ

በመጀመሪያ እግዚአብሄር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ ለሰው ልጆች የሚያስፈልገውን ሁሉ ባህሩን የብሱን፣ ብቻ ምንአለፋችሁ ሁሉንም ሰርቶ፣ አበጃጅቶ ለመኖር ምቹ አድርጎ ከጨረሰ በኋላ አዳምን ፈጠረ፣ ለአዳምም ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም እልዳልሆነ አየና ረዳት እንድትሆነው ሄዋንን ከጎኑ አጥንት አበጀለት። ከዚያም ታሪኩ ብዙ ነው፣ እግዚአብሄር አዳምና ሄዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት ብሎ ባረካቸው። እንግዲህ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሰው በምድር ላይ እንደፈለገ እየተባዛ እንዲኖር ተፈቅዶለታል። መፅሀፍ ቅዱስ ላስተምራችሁ አይደለም! እንዲያው ለሰው ልጆች በሙሉ በነፃ የተሰጠውን ተፈጥሯዊ መብቶች በመፃረር በሀገራችን ያለው የወያኔ ስርአት እየፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለማውገዝ ያህል መንደርደሪያ እንዲሆነኝ ነው።
ዘረኝነት ከብዙ ዘመናት በፊት በተለያዩ አህጉራት እንደ አሜሪካና አውሮፓ በመሳሰሉት ሀገራት በጥቁሮችና በነጮች መካከል ጎልቶ ይታይ የነበረ ቢሆንም አሁን ባለንበት 21ኛ ክፍለ ዘመን ግን ዘረኝነት የኃላ ቀር አስተሳሰብ በመሆኑ አሁን ባለንበት ዘመን እንደቀድሞው ጎልቶ አይታይም። በዚያን ጊዜ የነበረው ዘረኝነት ነጮች በአፍሪካውያን ጥቁሮች ላይ ያሳዩት የነበረ የበላይነት እንጂ አሁን በሐገራችን ያለው አምባገነን ስርአት የራሱን ህዝብ በገዛ ሀገሩ ባሪያ አድርጎ እንደሚያሳየን አይነት ዘረኝነት አልነበረም። በርግጥ ወያኔ ከአመሰራረቱ ገና ከደደቢት በረሀ ይዞት የተነሳው አላማ ኢትዮጵያ የምትባልን ሀገር አፈራርሶ ታላቋ ትግራይ የምትባል የኢንዱስትሪ ከተማ መስርቶ ትግራይን ከኢትዮጵያ የመገንጠል አላማ ይዞ የተነሳ የማፍያ ቡድን ነው። ይህንንም እኩይ የዘረኝነት አላማ ለማስፈፀም ይዞ የተነሳው እስትራቴጂ ህዝቡን በዘር፣ በጎሳ፣ በሀይማኖት በመከፋፈል ከፋፍለህ ግዛው በተሰኘ አጋንንታዊ አስተሳሰብ ነው። በተለይ ያሰጉኛል ያስፈሩኛል ያላቸውን የአማራንና የኦሮሞን ህዝብ በጠላትነት በመፈረጅና ሁለቱን ብሄሮች በማጋጨት ከፍተኛ ወንጀል በኦሮሚያና በአማራ ክልል ተወላጆች ላይ ሲፈፅም ቆይቷል። አሁንም እየፈፀመ ነው።

ወያኔ የአማራ ህዝብ በኢትዮጵያ አንድነት ድርድር የማያውቅ መሆኑን አስቀድሞ ያውቅ ስለነበረ
ይህንን ህዝብ ለማጥፋትና ቁጥሩን ለማመናመን እጅግ በርካታ እኩይ ተግባራትን እየፈፀመ ይገኛል። የአማራውን ህዝብ ከተወለደበትና ካደገበት፣ የእድሜውን እኩሌታ ከኖረበት፣ ሀብት ንብረት ካፈራበት አካባቢ በማፈናቀልና ሜዳ ላይ ተበትኖ በገዛ ሀገሩ እንደስደተኛ መፃተኛ ሆኖ እንዲኖር አድርጎታል። የአማራው ህዝብ በተለያዩ አካባቢዎች የጅምላ ግድያ ተፈፅሞበታል። ይህ አልበቃ ብሏቸው እህቶቻችንን ተፈጥሮ የለገሳቸውን የመውለድና የመባዛት መብት በመገደብ መካን አድርጎ የሚያስቀር ክትባት እየሰጡ እንዳይዋለዱና ዘራቸው እንዳይቀጥል በማድረግ እህቶቻችን ልጅ ፍለጋ በየፀበሉ እንዲንከራተቱ አድርገዋል። ይህ ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል በአማራ ተወላጆች ላይ በዘረኛው ወያኔ ተፈፅሟል። ይህ ወንጀል እግዚአብሄር የሚፈርድባቸው እንዳለ ሆኖ በአለም አቀፍ የዘር ማፅዳት ወንጀል የሚያስጠቅይ አደገኛ ወንጀል ነው። ይህንን አይነት ወንጀል ወያኔ በገዛ ህዝቡ ላይ ሲፈፅም ምን ያህል ጥላቻ ለህዝቡ እንዳለውና በርግጥም ከደደቢት በረሃ ይዞ የመጣውን አማራን የማጥፋት ተልኮ በፍጥነት እየተገበረ መሆኑንም ያሳያል።

ከላይ እንደገለፅኩት በተፈጥሮ ከመባዛት በተጨማሪ በተፈጥሮ የተሰጠን ሌላ መብት አለን። ይህውም ማንም ሰው እዚህ ቦታ ከዚህ ብሄር መወለድ እፈልጋለሁ ብሎ የተወለደ የለም ሁላችንም ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልደናል በተወለድንበት ሀገር ውስጥ ደግሞ የትኛውንም አይነት ዘርና ቋንቋ ይዘን መወለዳችን በተፈጥሮ የተሰጠን መብታችን ነው። ማንም ሊከለክለን ወይም ሊሰጠን የማይችለው መብታች ነው። ሆኖም ግን ወያኔ ኢህአዴግ ይህንን ተፈጥሯዊ መብታችንን በመጋፋት በዘርና በቋንቋችን እያጥላላ ዘራችንን እየጠቀሰ አማራ፣ ኦሮሞ እያለ ሲሰድበን ኖሯል። ትግሬ ከመሆን ውጪ በተይ አማራ ሆኖ መገኘት ነፍጠኝነት ሆኗል። የፖለቱካ እስረኞች ሳይቀሩ አንተኮ አማራ ነህ ኦሮሞ ነህ እየተባሉ በዘራቸው እየተሰደቡ እንደሚደበደቡ ብዙዎች ተናግረዋል። ወያኔ ይህንን ጠባብ አስተሳሰቡን ወደሌላው ብሄር ለማጋባት ብዙ ቢሞክርም አልተሳካም ወደፊትም አይሳካም ህዝቡ አንድ ነው። ብሄር፣ ቋንቋ፣ ሀይማኖት ሳይለየው ለብዙ ዘመናት በመተሳሰብና በመከባበር አብሮ የኖረ ህዝብ ነው።

በአማራው ላይ የሚፈፀመው በደል ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም። ያስገረመኝ! በቅርቡ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ’’ህዝበ አማራው’’ አማራ እንደሆነ እየታወቀ፣ ወያኔ ትግራይን ሲገነጥል ግዛቱን ለማስፋት ሲል ህዝቡን እናንተ አማራ አይደላችሁም ትግሬዎች ናችሁ ተብለው በግድ ትግራዊነት የተቸራቸው የወልቃይት ጠገዴ ህዝቦች ኧረ እኛ ትግሬ አይደለንም አማራ ነን ድንበራችንም ተከዜ ድረስ ነው ትግሬ እንጂ ተከዜ ድንበር ተሻግሮ አያውቅም ብለው የማንነት ጥያቄ አቀረቡ። መንግስት ያለ መስሏቸው ኮሚቴ አቋቁመው ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው ጥያቄያቸውን እስከ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ቢያቀርቡም፣ ኮሚቴዎቹ የገጠማቸው እስርና እንግልት ነበር። ህዝቡም ይህንንኑ አስመልክቶ ሰላማዊ ሰልፍ ቢያደርግም አይምሬው ወያኔ ያሰረውን አስሮ የገደለውን ገድሎ የተሰጣችሁን ትግራዊነት ተቀብላችሁ ተቀመጡ ብሎት እርፍ አለው። ሰው የማንነት ጥያቄ ይዞ እንዴት ዝም ይላል ዝም አይልም ትግሉም እንደቀጠለ ነው።

ወያኔ ብሄር የሚሰጠን እሱ የሚነጥቀን እሱ ሆኖ ሳለ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት ለማስከበር ነው የትግራይ ተወላጆች አጥንታችንን ከስክሰን ደማችንን አፍስሰን የታገልነው ምናምን እያሉ ይደሰኩሩናል እነሱ እንደሚያስቡን ደንቆሮ መስለናቸው። መልክት ለወያኔዎችና ተላላኪዎቻቸው ለማንኛውም ዘረኝነት ለማንም አይበጅም፣ አሁን ጊዜው በጣም እረፍዶባችኋል ሀገር ማስተዳደር ካቃታችሁ ቆይቷል። በአራተኛ ክፍል ተማሪ ጀነራሎች ሀገር ቀርቶ ቀበሌ አይመራም፣ የአንድ ብሄር የበላይነትም ሆዳምነት ነው፣ እንደምታስቡትም ኢትዮጵያ አትፈርስም ህዝቡ ነቅቷል፣ ይበቃናል ትላላችሁ ብለን ታግሰን ነበር አሁን ግን እኛ በቃ ብለናል ጊዜው ቀርቧል የሁላችን ቁጣ በያለንበት ገንፍሏል፣ ፅዋው ሞልቷል ሀገራችንን ነፃ የምትወጣበት ጊዜው እውን ሆኖ በቅርብ ታዩታላችሁ። እንደምንፋረዳችሁም ማወቅ አለባችሁ ወንጀል ሰርቶ የትም መሰወር አይቻልም አለም አንድ ናት።

ዝምታ ወርቅ ነው ብሎ አንገቱን ደፍቶ ለ25 ዓመታት የተቀመጠውን ህዝብ ቆስቁሰው ቆስቁሰው የተዳፈነውን እሳት አነደዱት። የማያዳፍኑት እሳት በየአቅጣጫው ሲነሳ ወያኔ ማጣፊያው አጥሯት ግራ ገብቷታል። አንዴ መግለጫ አንዴ ምናምን ብታንጋጋም ግርግር ብትፈጥሩም ጊዜው እረፍዷል። ለ25 አመት ታፍኖ ሲናቅና ሲሰደብ፣ ሲገዛ፣ ስትረግጡት የነበረው ህዝብ አሁን ባንድነት በቃ ብለን ተነስተናል መመለሻ የለንም ጉድ ፈላብሽ ወያኔ የዘመናት ብሶት የወለደው ………….. ብላችሁ ነበር አይደል ያኔ ስትገቡ አሁን ደግሞ እኛ በተራችን ‘’የዘመናት ብሶት የወለደው የህዝብ ድምፅ የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት / ህወሀት/ ሲጠቀምበት የነበረውን የኢትዮጵያ ህዝብ ራዲዮ ተቆጣጥሮታል’’!!! ብለን ሀገራችንን ነፃ የምናወጣበት ቀኑ እሩቅ አይደለም።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

የኢትዮጵያ ነብሮች ሲበሳጩ ያጉረመርማሉ! –ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም 

$
0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም 

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ 

አሜሪካውያን የጀግንነት በላይነት የላቸውም፣  ማለትም  የኦሎምፒክ ጀግንነት ጠቅላይነት፡፡

Cheetah-14እ.ኤ.አ ነሐሴ 21/2016 የ26 ዓመቱ የኢትዮጵያ የረዥም ርቀት ማራቶን ሯጩ ፈይሳ ሌሊሳ በአንድ ወቅት በኦሎምፒክ ጨዋታዎች ታሪክ “የኦሎምፒክ ጨዋታዎች የፖለቲካ እንቅስቃሴ መግለጫ መድረኮች ሊሆኑ አይችሉም” በማለት ይገለጽ የነበረውን ሕግ ወደ ጎን አሽቀንጥሮ በመጣል በሪዮ ኦሎምፒክ ውድድር አስደናቂ የሆነ ታሪካዊ ድርጊትን ደግሟል፡፡

እ.ኤ.አ ጥቅምት 16/1968 በሜክሲኮ ኦሎምፒክ ተደርጎ በነበረው የ200 ሜትር የአጭር ርቀት የሩጫ ውድድር ቶሚ ስሚዝ እና ጆን ካርሎስ የወርቅ እና የብር ሜዳሊያ አሸናፊዎች ሆነው ነበር፡፡ በሜዳሊያ አሰጣጥ ስነስርዓት መድረኩ ላይ አድርገውት የነበረው ታሪካዊ ድርጊት በአሁኑ ጊዜ ትልቅ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ ይገኛል፡፡ የእጆቻቸውን ቡጢዎች ከፍ አድርገው ከራሳቸውበ በላይ ወደ ላይ በማንሳት የጥቁር ሕዝቦችን አይበገሬነት ምልክትነት በይፋ አሳይተዋል፡፡

ፈይሳ ከውድድሩ ማጠናቀቂያ መስመር ላይ ሲደርስ ሁለቱንም እጆቹን አጣምሮ ከእራሱ በላይ ከፍ አድርጎ በማንሳት የኢትዮጵያን ወጣቶች የአይበገሬነት የኃይል ምልክት እንቅስቃሴ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በይፋ አሳይቷል፡፡

ይህ ምልክት በዓለም ላይ የሚገኝ 3.5 ቢሊዮን ሕዝብ እንዲመለከተው የተደረገ ነበር፡፡

በዚያች ቅጽበታዊ ኩነት ፈይሳ ከያዘው እውነታ ጋር ተገናኘ፡፡ ያገኘውን የብር ሜዳሊያ ምርጫ ለዝና፣ ለዕድል እና ለታዋቂነት አውሎታል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ምንም ዓይነት የተለየ ችሎታ እንደሌለው እና እንደማንኛውም ተራ የዓለም ሕዝብ ሆኖ የመቀጠል ምርጫ ማድረግ ሲችል አርሱ ግን  የበለጠ ነገር ማድረግ ፈቀደ፡፡

ሆኖም ግን ፈይሳ የኩነቱን አጋጣሚ ለመያዝ መረጠ እና በዚህ መልኩ ተረጎመው፡፡

የኩነቱን አጋጣሚ ለመወሰን ጆሴፍ ካምፕቤል በመጽሐፋቸው እንደጻፉት እና ምዕናባዊ ገጽታን የሚላበሱ በሺዎች የሚቆጠሩ ጀግኖች እንዳሉ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ ፈይሳም ለህይወቱ ዘላለማዊ ጀግና ሆኗል፡፡

ፈይሳ የኢትዮጵያ የጀግንነት አንጸባራቂ ገጽታ ለመሆን በቅቷል፡፡

እጆቹን ከጭንቅላቱ በላይ ከፍ በማድረግ አጣምሮ በመያዝ የውድድር ማጠናቀቂያ መስመሩን እያቋረጠ በነበረበት ጊዜ ፈይሳ የዓለምን ጀግንነት ነው ያቋረጠው፡፡

ለመሆኑ ፈይሳን ከተራ የማራቶን ውድድር ሯጭነት እንደዚህ ያለውን የጀግንነት እርምጃ ለመውሰድ እና የጀግንነት ስብዕናን እንዲላበስ ያደረገው ምክንያት ምንድን ነው?

መልሱ አየር የመተንፈስን ያህል ቀላል ነው! ሌላ ምንም ሳይሆን የአስተሳሰብ አድማሱን አእምሮውን መለወጡ ብቻ ነው፡፡

ጆርጅ በርናንድ ሻው በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ያለለውጥ ምንም ዓይነት እድገት ሊኖር አይችልም፣ እናም አእምሯቸውን መለወጥ የማይችሉ ምንም ዓይነት ለውጥ ሊያመጡ አይችሉም“ ነበር ያሉት፡፡

ፈይሳ በአሁኑ ጊዜ በሀገሩ ውስጥ ስርነቀል ለውጥ አስፈላጊ እንደሆነ በሚገባ ግንዛቤ ወስዷል፡፡ በዚያች ውሱን በሆነች የኩነት አጋጣሚ ፈይሳ በእርሱ ጨቋኞች ጫማ ስር ወድቆ እና ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ እየተጨቆነ የእድሜ ልክ ክብር እና ሀብት እያገኘ ከመኖር ይልቅ የአንድ ሴኮንድ ነጻነት ይሻለኛል በማለት አእምሮውን ለውጧል፡፡

በሪዮ የማራቶን ውድድር ፈይሳ የውድድር ማጠናቀቂያ መስመሩን በሚያቋርጥበት ጊዜ የአትሌቲክሱን ድል አድራጊነት አይደለም ያቋረጠው፡፡ በምንም ዓይነት ይኸ አይደለም!

ሆኖም ግን ፈይሳ ፍርሀትን፣ ተስፋ የማጣት ጨለምተኝነትን፣ ሀዘንን፣ ብስጭትን፣ መጥፎ ዕድልን እና ጥርጣሬን አሽቀንጥሮ በመጣል የድፍረትን፣ የመስዋዕትነትን፣ የዓላማ ጽናት ቁርጠኝነትን፣ የአይበገሬንትን እና የተጨባጭ ተግባርን መስመር ነው በይፋ ያቋረጠው፡፡

በሩጫው የመጨረሻዎቹ ሰከንዶች ላይ ፈይሳ የጥሩምባ ጥሪ ድምጽ ሰማ፡፡

እንደ ጆሴፍ ካምፕቤል ባለ አንድ ሺ ፊት ምዕናባዊ ጀግንነት ፈይሳ ከተራው የዓለም ሕዝብ ለታላቅ ቁምነገር አድናቆትን እንዲፈጽም ጥሪ ቀረበለት፡፡

ፈይሳ ለጥሪው አውጥቶ እና አውርዶ በሚገባ አሰበበት፡፡ ለብዙ ጊዜ ሲያደርገው የነበረውን አሰበ፡፡ እንደ ካምፕቤል ጀግና ወሳኙ ጊዜ በሚመጣበት ጊዜ ፈይሳ ውሳኔ የማይሰጥ ልፍስፍስ  ወይም ደግሞ ወላዋይ አልሆነም፡፡ ቆራጥ ሆነ ።

ጥርት ባለ የእውነታ መንገድ እና በዓላማ ጽናት ላይ በመመስረት ከእራስ ወዳድነት፣ ከማን አህሎኝነት ስሜት እና ጥሩ የዓለም ህይወትን  ከመውደድ ይልቅ ማንኛውንም አደጋ በጽናት ተቋቁመው ለመልካም ነገር ለማህበረሰቡ መስዋዕትነትን ከፍለው ድልን የሚያቀዳጁ ጀግኖች መስመርን ነው ያቋረጠው፡፡

እንደ ካምፕቤል ምዕናባዊ ጀግና ማንኛውንም የጀግንነት አደጋዎች መጋፈጥ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ ፈይሳም ለሕዝቦቹ፣ ለሀገሩ፣ ለወጣት ወገኖቹ፣ ለባለቤቱ እና ለጥቅላላው ለዘመድ አዝማዶቹ የእራሱን ህይወት በመስዋዕትነት ሰጥቷል፡፡

ግን ለምንድን ነው ይህን ያረገው!?

Cheetah 8እ.ኤ.አ በ1968 በሰሜን ካሊፎርኒያ ከሳን ጆሴ ስቴት ዩኒቨርስቲ ሁለት የኮሌጅ ተማሪዎች የእጆቻቸውን ቡጢዎች ወደ አየር ከፍ አድርገው ከራሳቸው በላይ በመያዝ በአይበገሬነት የጀግንነት መስመሩን እንደዚሁ አቋርጠዋል፡፡

ካርሎስ እድሜው 23 እና ስሚዝ ድግሞ የ24 ዓመት ወጣቶች የነበሩ ሲሆኑ የስኬት፣ የዝና፣ የዕድል እና የታዋቂነትን የወጥመድ አደጋዎች ሁሉ ያለምንም ማወላወል ፊት ለፊት ተጋፍጠዋል፡፡ በአደባባይ ተንቀዋል፣ ተወግዘዋል፣ ተዋርደዋል፣ የማስፈራሪያ ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል፣ ተዘልፈዋል እናም የማጃጃል ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል፡፡ ከዚህም አልፎ እንዲያውም በውድድሩ አሸናፊ ሆነው ያገኟቸውን ሜዲሊያዎች ለዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴው እንዲመልሱ ተደርገዋል፡፡

ለመሆኑ እንደዚህ ያለ መስዋዕትነትን የከፈሉት ለምንድን ነው!?

የካርሎስ እና የስሚዝ ፎቶ ለጥቁር ኃያልነት ምልክት ሆኖ እንዲኖር ለመሆኑ ለዘላለም በአእምሮዬ ውስጥ ፍንትው ብሎ ይታየኛል፡፡

በአፍሪካ ቀንድ እምብርት እንደ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እኔ በግሌ በአሜሪካ የሲቪል መብቶችን እና የወጣቶችን የተቃውሞ ንቅናቄዎችን በተለይም ደግሞ በወጣት አማጺያን በ”ሕዝባዊ ሬፐብሊኮች” በካሊፎርኒያ በበርክለይ እና በኦክላንድ ይደረጉ የነበሩትን እንቅስቃሴዎች አስታውሳለሁ፡፡

ግን ለምን?

ሸክስፒር አስራሁለተኛው ሌሊት/Twelfth Night በሚለው መጽሐፋቸው እንዲህ በማለት ጽፈው ነበር፣“ጥቂቶች ታላቆች ሆነው ተፈጥረዋል፡፡ ጥቂቶች ደግሞ በሂደት ታላቅነትን ተጎናጽፈዋል፣ ሌሎች ጥቂቶች ደግሞ በእነዚህ ታላቆች ላይ እምነቶቻቸውን ጥለዋል፡፡

ሸክስፒር ከዚህም በተጨማሪ ጥቂት ሰዎች ደግም ሁልጊዜ ተጎጂ የሆኑ ሕዝቦችን መብቶች ለማስጠበቅ ሲሉ እውነትን በመናገር ሌሎችን ሰዎች በመጨቆን ጉዳት በሚያስከትሉ ሰዎች ላይ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እንዲያወግዙ እና እንዲጮኹ ሆነው ተፈጥረዋል የሚል ቢጨምሩበት ኖሮ እንዴት ደስ ባለኝ ነበር፡፡

በጣም የሚገርመኝ ጉዳይ ነው፡፡

የወርቅ እና የብር ሜዳሊያዎችን በእጅ ለማስገባት እንደ ነብር የሚወረወረውን የስሚዝን እና የካርሎስን የቪዲዮ ምስል እና በቀጣይነት ቀርቦላቸው የነበረውን ቃለ መጠይቅ ፈይሳ የውድድር ማጠናቀቂያ መስመሩን ቆርጦ ሲገባ እንደተደረገው ሁሉ ለብዙ ጊዜ ደጋግሜ ተመልክቸው እና አዳምጨው ነበር፡፡

ሁለቱ የኦሎምፒክ ጓደኛሞች በግዋንቲ የተሸፈኑ ሁለት ቡጢዎቻቸውን ወደ ላይ ወደ አየር ከጭንቅላታቸው በላይ ከፍ በማድረግ በሚያማምሩ ጌጣጌጦች ያሸበረቀውን ባለኮከብ የጽሑፍ ሰሌዳ ጨርቁን/ባነር በመበጠስ ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡

ግን አወዛጋቢ የሆነው የጥቁሮች ኃይለኝነት በነበረበት ወቅት እጆቻቸውን ወደ ላይ ወደ አየር ከፍ አድርገው ያንን ምልክት ያሳዩበት ምክንያት ለምን ነበር?

ፈይሳ የውድድር ማጠናቀቂያ መስመሩን በሚያቋርጥበት ጊዜ ሁለት እጆቹን በማጣመር ከራሱ በላይ ወደ አየር ከፍ በማድረግ ያንን ምልክት ያሳየበት ምክንያት ምንድን ነው?

ካርሎስ እና ስሚዝ የዓለምን የኦሎምፒክ መድረክ አጋጣሚን በመጠቀም በአፍሪካ አሜሪካውያን ላይ እየተፈጸመ እና እያሰቃያቸው የነበረውን ዘረኝነትን፣ ድህነትን እና የሁለተኛ ደረጃ ዜግነትን በመቃወም ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅ ነበር፡፡

ሆኖም ግን አይበገሬው ድርጊታቸው ወደላይ ከጭንቅላታቸው በላይ በተጣመሩት ቡጢዎቻቸው ብቻ ተወስኖ አልቀረም፡፡ ሆኖም ግን በርካታ በሆኑ አፍሪካ አሜሪካውያን ላይ ዕለት በዕለት በላያቸው ላይ የሚያናጥርባቸውን አውዳሚ የሆነ ድህነት የውድድሩን ፍጻሜ ተከትሎ ሲከናወን በነበረው የሜዳሊያ አሰጣጥ ስነስርዓት ላይ ጽኑ አቋማቸውን በግልጽ አሳይተዋል፡፡ በተለይም ደግሞ ካርሎስ ቀደም ሲል ላለቁት ወይም ደግሞ ለተገደሉት  እና ደመ ከልብ ሆነው ለቀሩት ሰዎች ማንም ምንም ዓይነት ጸሎት ያላደረገላቸው እና ያላሰባቸው በመሆኑ ጥቁር ነጠብጣብ ያለበትን ከረባት አስሮ ነበር፡፡ ይህም ማለት በጀልባ በመጓዝ ላይ የነበሩ ሰዎችን በጉዞው አማካይ ርቀት ላይ ሲደርሱ በውኃው አካላ ላይ እንዳሉ ከጀልባው ወደ ባህሩ ውስጥ እንዲወረወሩ እየተደረጉ እልቂት ስለተፈጸመባቸው ሰዎች ነበር፡፡

ፈይሳም እንደዚሁ በተመሳሳይ መልኩ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወይም ደግሞ በትክክለኛው እና ገላጭ በሆነው የባህሪ አጠራሩ መሰረት የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሀት) እየተባለ በሚጠራው ሕገወጥ የማፊያ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የግፍ አገዛዝ በወገኖቹ በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ እየደረሰ ያለውን ጭቆና እና የሁለተኛ ደረጃ ዜግነትን በመቃወም እጆቹን በማጣመር ወደ ላይ ከራሱ በላይ ከፍ አድርጎ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በይፋ አሳይቷል፡፡

በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ እንደዚህ ያለውን አስደናቂ የሆነውን እርምጃ ለምን እንደወሰደ ጥያቄ በቀረበለት ጊዜ ፈይሳ እንዲህ ነበር ያለው፣ “የኢትዮጵያ መንግስት የኦሮሞ ሕዝቦችን ይገድላል፡፡ እናም መሬቶቻቸውን እና ሀብታቸውን ሁሉ ይወስዳል፡፡ ስለዚህ የኦሮሞ ሕዝብ በአሁኑ ጊዜ ድርጊቱን በመቃወም ላይ ይገኛል፣ እኔም የኦሮሞ ማህበረሰብ ተወላጅ ስለሆንኩ ድርጊቱን በመቃወም ደጋፊነቴን ለማሳየት ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ወገኖቼን በየቦታው በመግደል ላይ ይገኛል፣ እናም እኔም የኦሮሞ ጎሳ አባል ስለሆንኩ ድርጊቱን በመቃወም ከወገኖቼ ጎን መቆሜን በግልጽ ለማሳየት ነው፡፡ የእኔ ዘመዶች በእስር ቤት ውስጥ በመማቀቅ ላይ ይገኛሉ፣ ስለዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸው ከጠየቁ ይገደላሉ፡፡ እጆቼን ከፍ በማድረግ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ያሳዬሁበት ምክንያት የኦሮሞን ተቃውሞ መደገፌን ለማሳየት ነው፡፡“

ፈይሳ የተናገረው ነገር ዋና ፍሬነገር/ ዳህራው እ.ኤ.አ በ1968 ስሚዝ እና ካርሎስ ተናግረውት ከነበረው እንዲህ ከሚለው ቃለመጠይቅ ብዙም የሚለይ አይደለም፡፡

ቃለመጠይቅ አድራጊ፡ እንደዚህ ዓይነቱን ድርጊት በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ በኦሎምፒክ ጨዋታዎች መድረክ ላይ ማሳየት ትክክለኛ ቦታው ነው ብላችሁ ታስባላችሁ?

ስሚዝ፡ እኛ አትሌቶች ነን፡፡ እኔ መምህር ነኝ ሆኖም ግን የፖለቲካ ሰው አይደለሁም፡፡ ይህንን ድርጊት የፈጸምነው የዓለም ሕዝብ በአሜሪካ በጥቁር ሕዝቦች ላይ የተንሰራፋውን ድህነት እንዲመከለተው እና ግንዛቤ እንዲወስድ በማሰብ ነው፡፡

ቃለመጠይቅ አድራጊ፡ ሜዳሊያ በማግኘት በሕዝብ ዘንድ ታዋቂነትን እና ዝናን ተጎናጽፊያለሁ ብለህ ታስባለህ ወይስ ደግሞ መስዋዕትነት ከፍያለሁ ነው የምትለው?

ካርሎስ፡ እኔ ሜዳሊያውን ምግብ ሆኖ አልበላውም፡፡ በእኔ የእድሜ የዕኩያነት ደረጃ ላይ ያሉት ታዳጊ ወጣቶችም ቢሆኑ ይህንን ሜዲሊያ አይበሉትም፡፡ ከእነዚህ ልጆች በኋላ የሚመጡት እና የሚያድጉት ልጆችም ቢሆኑ ሊበሉት አይችሉም፡፡ የወርቅ ሜዳሊያዎችን ሊበሏቸው አይችሉም፡፡ ሁላችንም የምናቀርበው ጥያቄ ቢኖር የሰው ለጆች ለመሆናችን ዕኩል እድል ይሰጠን የሚል ነው፡፡ እናም አሁን እንደማየው ከሆነ ከመሰላሉ በ5 ደረጃዎች ዝቅ ብለን እንገኛለን፡፡ እናም ሁልጊዜ መሰላሉን ለመንካት በምንሞክርበት ጊዜ እግሮቻቸውን በእጆቻችን ላይ ይጭናሉ፣ እናም በመሰላሉ ወደላይ እንድንወጣ አይፈልጉም፡፡

በእርግጥ ካርሎስ እና ስሚዝ በሜዳሊያ አሰጣጥ ስነስርዓቱ ወቅት እጆቻቸውን በአይበገሬነት መንፈስ ወደ ላይ ከፍ በማድረግ ቡጢዎቻቸውን ጠበቅ በማድረግ ዘረኝነትን እና የአፍሪካ አሜሪካውያንን የሁለተኛነት ደረጃ ዜግነትን ሲቃወሙ ብቻቸውን አልነበሩም፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት የአሜሪካ ወጣቶች እና በዓለም ላይ የሚገኙ ሕዝቦች ሁሉ ከጎናቸው ነበሩ፡፡

ፈይሳ ሁለት እጆቹን በማጣመር ከጭንቅላቱ በላይ ወደ ላይ ከፍ በማድረግ የውድድር ማጠናቀቂያ መስመሩን ሲያቋርጥ ብቻውን አልነበረም፡፡ የ100 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ መንፈሳዊ ድጋፎች፣ ፍቅር እና አድናቆት ነበረው፡፡

በአየር ላይ ከፍ ብለው በምስል ይታዩ የነበሩት በግዋንት የተጠቀለሉት የካርሎስ እና የስሚዝ እጆች የአንድ ሺ ቃላት ያህል ትርጉም ሊሰጡ ይችሉ ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን ለእኔ ይኸ ታሪካዊ ድርጊታቸው አንድ ቃል ብቻ ይወክላል፡ እምቢተኝነት!

የእነርሱ እምቢተኝነት ጨቋኝ ለሆነው እና ለዘረኛው ስርዓት ውድቀት ጽናት ያለው እና ሰላማዊ የሆነ መገዳደርን/አይበገሬነት ይወክላል፡፡

የእነርሱ እምቢተኝነት በአሜሪካ ውስጥ ለሚደረጉ የሲቪል መብቶች ንቅናቄ እና ለብዙሀን የማንነት ትግል እና ለሙሉ የዜግነት ጥያቄ እውቅና ውክልና ይሰጣል፡፡

ስሚዝ በዚያን ጊዜ የነበረውን የእንቆቅልሽ ሁኔታ አቅሎ ባለመመልከት እንዲህ ብሎ ነበር፡ “ውድድሩን የማሸነፍ ከሆነ አሜሪካዊ እንጅ ጥቁር አሜሪካዊ አይደለሁም፡፡ ሆኖም ግን አንድ የሆነ መጥፎ ነገር ሰርቼ ከሆነ እኔን ባሪያ/Negro ነው ይላሉ፡፡ እኛ ጥቁሮች ነን፣ እናም ጥቁሮች በመሆናችን እንኮራለን፡፡ ጥቁር አሜሪካውያን በዛሬው ምሽት ምን እንደሰራን በውል ይገነዘባሉ“ ነበር ያለው፡፡

በአሜሪካ ውስጥ ጥቁር አሜሪካዊ የመሆን እና ያለመሆን የሸክስፒር ዘላለማዊ ተቃርኖ እንዲህ የሚል ነው፡ መሆን ወይም አለመሆን… ወይም ደግሞ መሆን ይችላልን… ጥቁር እስከሆነ ድረስ?

ካርሎስ እና ስሚዝ በዚያ ገጻቸው ለዓለም ሕዝብ እንዲህ በማለት ነበር ያወጁት፣ “ላመንንበት ዓላማ በጽናት እንቆማለን፡፡ በምንም ዓይነት ሁኔታ ወደኋላ አናፈገፍግም፡፡“

የውድድሩ አሸናፊ የውድድር መስመሩን ሲያቋረጥ የሚበጥሰውን ባለነጠብጣብ የኮከብ ጨርቅ/ባነር በሚበጥሱበት ጊዜ የአፍሪካ አሜሪካውያንን መንፈስ በመላበስ እንዲህ በማለት ነበር የሚዘምሩት፣ “ከዚህ አቋሜ አንዲትም ጋት ንቅንቅ አልልም“ ነበር ያሉት፡፡

ፈይሳ ሌሊሳ በካርሎስ እና በስሚዝ አስደማሚ ድርጊት እጅግ ተመስጦ እንደነበር ምንም ዓይነት ጥርጣሬ የለኝም፡፡

እንደ ካርሎስ እና ስሚዝ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ የእርሱ ድፍረት ለሕዝቦቹ ይናገር ነበር፡፡ የእነርሱን የማጎሪያ እስር ቤቶች እና የማሰቃያ ክፍሎች እንደማይፈራቸው ፈይሳ ዘ-ህወሀት በሚገባ እንዲገነዘብ አድርጓል፡፡ ዘ-ህወሀት የእርሱን ቤተሰቦች ገሀነም እንደሚያስገባቸው በሚገባ ይገነዘባል፡፡ በእርግጥ ከገሀነም ጌቶች ከዚህ ያነሰ ሊጠበቅ አይችልም፡፡

ሆኖም ግን በዚያ ብቸኛ የእምቢተኝነት ቅርጹ ፈይሳ በኢትዮጵያ ውስጥ በዘ-ህወሀት የማፊያ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን እጅ እየተገደሉ እና እልቂት እየተፈጸመባቻው፣ በቁጥጥር ስር እየዋሉ፣ ወደ እስር ቤት የሚጋዙት እና ስይቃ እየተፈጸመባቸው ለሚገኙት ወጣት ወንድሞቹ እና እህቶቹ ፍጹም የሆነ አጋርነቱን አሳይቷል፡፡

ፈይስሳ ወደ ውድድር ማጠናቀቂያ መስመሩ እየተቃረበ በመጣ ጊዜ ለኦሎምፒክ ዝና እና የበላይነት ክብር እንዲሁም ከዚያ ጋር ተያያዞ ሊገኝ ስለሚችለው መልካም ዕድል ምንም ዓይነት ፍላጎት እንዳልነበረው ለዚያች ቅጽበት ምስክር ሊሆኑ ለሚችሉ ሰዎች ሁሉ ጉዳዩ ግልጽ ነበር፡፡

ፈይሳ የህይወቱን የማራቶንን የሩጫ ውድድር ለወገኖቹ ህይወት እና ክብር ሲል ሮጦታል፡፡

አሸንፎ ሜዳሊያ ለማግኘት ሳይሆን የእርሱን ወገኖች ከስቃይ እና ከውርደት ለማዳን ሲል የማራቶንን ሩጫ ሮጦታል፡፡

ለዚህች ለአንድ ጊዜ አልባ ለሆነች አጋጣሚ ለበርካታ ዓመታት በኮረብታዎች እና በሸለቆዎች እንደ ውኃ ቀጅ በመመላለስ ያለምንም መሰላቸት ሰልጥኗል፡፡

አፉ በዘ-ህወሀት ባይለጎም እና ባይሸበብ ኖሮ እንዲህ ብሎ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ለወገኖቹ አይናገርም ነበር፡፡

ሆኖም ግን የሚያምነበትን አቋሙን በእግሮቹ ተናግሯል፡፡ ከአፍ ይልቅ እግር እንዴት ድምጹን ከፍ አድርጎ ይናገራል እባካችሁ!

ካርሎስ እና ስሚዝም የሮጡት ለእራሳቸው ጥቅም ሲሉ ሳይሆን ለሰው ልጆች ዘር ሁሉ መብቶች መከበር ሲሉ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 በሳን ጆሴ ስቴት ዩኒቨርስቲ እ.ኤ.አ በ1968 ካርሎስ እና ስሚዝ ፈጽመውት በነበው ታሪካዊ ድርጊት ምክንያት ለመታሰቢያነት በተገነባው ሀውልት የምረቃ ስነስርዓት በሚደረግበት ጊዜ ዶ/ር ካርሎስ እንዲህ ብለው ነበር፡

“በሚክሲኮ ሲቴ ምንም እናድርግ ምን በጣም ውድ እና እንቁ, የተከበረ፣ ቆጥቋጭ፣ አስደንጋጭ እና ገላጭ  የሆነ ነገር፣  አድርገናል፡፡ አመልካች ጣታችንን በሰዎች ላይ አልቀሰርንም፡፡ ምንም ዓይነት ግፊት አላደረግንም፡፡ ሰንደቅ ዓላማችንን በራሳችን ላይ አልጠቀለልንም ወይም ደግሞ እንደ ህጻናት የሽንት መምጠጫ ጨርቅ/ዳይፐር አላሰርንም፡፡ ክብርን በሚያዋርድ መልኩ እዚያ አልቆምንም፡፡ እዚያ የቆምነው እንዲህ ለማለት ነው፣ ‘ሰዎች ጉድ እኮ ነው፡፡ እኔ አሜሪካዊ ነኝ፡፡ የአንተ ልጅ ነኝ፡፡ ቆስያለሁ፡፡ ለእራሴ ስል አልቆሰልኩም ምክንያቱም ከአንተ ጀግኖች መካከል እኔ አንዱ ነኝ፡፡ በአሎምፒክ ላይ ነኝ፡፡ ለውድድሩ ስል ቆስያለሁ፡፡ ስለ 200 ሜትር የርቀት ሩጫ ውድድር አይደለም እያወራሁ ያለሁት፡፡ እየተናገርኩ ያለሁት ስለሰው ልጆች  ሰባዊ መብት ነው፡፡ ለዚህም ነው ሜክሲኮ ሲቲ የሄድነው’”ነበር ያለው፡፡

እጆቹን ወደ ላይ ከፍ በማድረግ ፈይሳ ዘ-ህወሀት እየተባለ በሚጠራ ወንጀለኛ የማፊያ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የኢትዮጵያ የማስመሰያ መንግስት ተብዬ ድርጅት (አሁን በቅርቡ “ኢትዮጵያ ከጭፍን የጎሳ ጥላቻ ባሻገር“ በሚል ርዕስ ያዘጋጀሁትን ትችት ይመልከቱ፡፡) በሕዝቦች ላይ እያደረሰ ያለውን ስቃይ፣ መከራ፣ የመጥፎ ነገሮቸ ሁሉ መሞከሪያነት እና ከባድ ችግር ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የህሊና ዳኝነት ለአደባባይ እንዲደርስ አድርጓል፡፡

እንደ ስሚዝ እና እንደ ካርሎስ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ ፈይሳ የእርሱ ወገኖች፣ ልጆች፣ ቤተሰቦች እና ጎረቤቶች የብር ሜዳሊያ ሊበሉ አይችሉም በማለት ላይ ይገኛል፡፡ የብር ሜዳሊያው ክብር፣ ነጻነት እና የሰብአዊ መብቶችን አይገዛላቸውም፡፡

እንደ ስሚዝ እና ካርሎስ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ ፈይሳ ወገኖቹ በሙሉ ዕኩል በሆነ አንድ ዓይነት እድል መስተናገድ እንዲችሉ ፈልጓል፡፡ እንደ ሁለተኛ ደረጃ ዜግነት እንዲስተናገዱ አልፈለገም፡፡ እንደ ወንጀለኞች እና አሸባሪዎች ተደርገው እንዲፈረጁ አልፈለገም፡፡ ፈይሳ የፈለገው በአምላክ አምሳል እንደተፈጠረ እንደማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር፣ አምላክ ካጎናጸፋቸው የህይወት ሙሉ ዘላለማዊ መብት፣ ነጻነት እና ደስታን ከማግኘት መብት ጋር  በሰላም እና በድሎት እንዲኖሩ ነው የሚፈልገው፡፡

ፈይሳ የእርሱ ሕዝቦች በመሰላሉ ላይ እንደማንኛውም ሰው እንዲወጡ ይፈልጋል፣ እናም በምንም ዓይነት መልኩ መሰላሉ በዘ-ህወሀት፣ በአባሎቹ እና በግብረ አበሮቹ በክልከላ በመያዝ ከላይ ከቁንጮው ላይ እግራቸውን አንፈራጥጠው በመቀመጥ ሌላው ዜጋ ለመውጣት ሙከራ በሚያደርግበት ጊዜ እየኮረኮሙ በመከልከል የኢትዮጵያን ሕዝብ መሰላል የእነርሱ ብቻ መሰላል አድርገው እንዳይቀመጡ ይፈልጋል፡፡

እ.ኤ.አ ነሐሴ 21/2016 በሪዮ የማራቶን ውድድር የሜዳሊያ አሰጣጥ ስነስርዓት ላይ ፈይሳ ሌሊሳ የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ትውልድ (ወጣቱ ትውልድ) ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና የኩሩ ትወልድ ዝርያ ኩሩ እንደሆነ ኢትዮጵያውያንን በሙሉ እንደሚያኮራ ወይም ደግሞ እንደ ኩሩ አንበሶች የኮራ ጀግና የህብረተሰብ ክፍል መሆኑን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሚገባ አሳይቷል፡፡

ሆኖም ግን ፈይሳ ለአቻ ጓደኞቹ ያስተላለፈው እንደህ የሚል ግልጽ መልዕክት ነበር፣ “በዘ-ህወሀት የማፊያ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እየተፈጸመ ያለውን የእናንተን ስቃይ፣ የመሞከሪያ ዕቃ ስለመሆናችሁ እና ስለሚያደርስባችሁ መከራ እና ስቃይ ሁሉ 3.5 ቢሊዮን ለሚሆኑ የዓለም ሕዝቦች በሚገባ ተናግሪያለሁ“ የሚል ነው፡፡

ፈይሳ ለኢትዮጵያ በግዴታ ገዥዎች በምንም ዓይነት መንገድ፣ መለኪያ እና መስፈርት ሊመጥን የማይችለውን አሸባሪ እና የማፊያ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሆነውን እራሱን ዘ-ህወሀትን እንኳ “የኢትዮጵያ መንግስት” ብሎ ጠርቶታል፡፡

ፈይሳ እንደዚያ ዓይነቱን ደም የተጠማ የወሮበላ ዘራፊ እና የእራሱን ዜጎች ጨፍጫፊ ቡድን ስብስብ ታላቅ ቸርነትን በማሳየት በባህሪ እና በግብር ከማይገናኘው ጋር “መንግስት” ብሎ ጠርቶታል፡፡ ድንቄም መንግስት፣ መንግስት እንዳይባል የለ! የዱርዬ መንግስት እንጂ !

ዘ-ህወሀትን “መንግስት” ብሎ መጥራት ቦቅቧቃዎችን እና ፈሪ የሆኑትን ጥንብ ሲያዩ የሚያሽካኩትን ጅቦች“ኩሩ አንበሳ” ብሎ ከመመጥራት ጋር መሳ ለመሳ ነው፡፡

ማንም ቢሆን አካፋን አካፋ ብሎ መጥራት አለበት፡፡ እንደዚሁም ጅብን ጅብ ብሎ መጥራት አለበት፡፡

ዘ-ህወሀት ለዘራፊዎች በዘራፊዎች የተቋቋመ የዘራፊዎች መንግስት ነው (እ.ኤ.አ ግንቦት 2011 “ዘራፊነት፡ የአፍሪካ አምባገነኖች ከፍተኛ ደረጃ“ በሚል ርዕስ አቀርቤው የነበረውን ትችቴን ይመልከቱ፡፡)

ዘራፊዎች ምን ወርቅ ቢለብሱ ምንጊዜም ቢሆን ያው ዘራፊዎች ናቸው፡፡ ጅቦችም እንኳ ቢሆኑ ምንም እንኳን ነገር እንደገባው ሰብአዊ ፍጡር ቢሽከመከሙም (ጧ ብሎ መሳቅ) ያው ምንጊዜም ጅቦች ናቸው፡፡

አንበሶች ምንጊዜም ቢሆን ያው አንበሶች ናቸው፣ እናም ጅቦች የአንበሶቹን ማግሳት እና የአቦ ሸማኔዎችን ማጉረምረም በሚገባ ያውቃሉ፡፡

Cheetah 10ሆኖም ግን ፈይሳ በአንድ ላይ የተጠቃለለ አንበሳ እና አቦ ሸማኔ ነው፡፡

በዚያው ተመሳሳይ ቀን ፈይሳ የብር ሜዳሊያውን አሸናፊ በሆነበት ዕለት በሀገሪቱ ዋና መናገሻ በሆነችው በአዲስ አበባ ውስጥ ሊደረግ የነበረውን ሰላማዊ ተቃውሞ ለመከላከል ሲል ዘ-ህወሀት አፋኝ የደህንነት መንጋዎቹን፣ የፖሊስ ኃይሉን እና ወሮበላ ዘራፊ ወታደሮቹን በከተማይቱ አሰማርቷል፡፡

እንዴት ዓይነት በተቃርኖ የተሞላ ጊዜ ነው እባካችሁ! በሚሊዮን የሚቆጠሩትን ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በመከልከል እቤታቸው ውስጥ እንዲቀመጡ በማስገደድ ዘ-ህወሀት ሕዝቦች የእነርሱን ስራ ከመካከላቸው የእነርሱ በሆነ አንድ ሰው አማካይነት ቆንጆ በሆነ መልኩ 3.5 ቢሊዮን ሕዝብ እንዲመለከተው ሲደረግ ደስታ በተመላበት ሁኔታ ተቀምጠው ተመልክተዋል፡፡

ፈይሳ ወደ ውድድሩ ማጠናቀቀቂያ መስመር ላይ ሲያቃርብ የሚያሳየውን የቪዲዮ ምስል በምመለከትበት ጊዜ እ.ኤ.አ ሰኔ 1989 በቻይና ዋና ከተማ አንድ ግለሰብ በከተማይቱ እምብርት በታንኮቹ ፊት ተገትሮ በመቆም “በምንም ዓይነት ሁኔታ ከቆምኩባት ቦታ ንቅንቅ አልልም“ በሚል ሞገደኛ እና እልኸኛ ስሜት ዓላማውን የገለጸውን ወጣት አስታወሰኝ፡፡

ኃይለኛ በሆኑት በቻይናውያን ወታሮች እና የደህንነት ኃይሎች እብሪተኝነት በመቶዎች በሚቆጠሩ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ እልቂትን እየፈጸሙ ባሉበት በዚያ ቅጽበታዊ ጊዜ አንድ ትንሽ የሆነ አሞተ ቆራጥ ጀግና ሰው እምቢኝ አሻፈረኝ ካለሁባት ቦታ ጋት አልንቀሳቀስም በማለት ያሳየው ተጋድሎ የሚደነቅ እና የሚገርም ትይንት ነበር፡፡

ያ ተዋቂነትን ያልተጎናጸፈ ተራ ሰው የቻይና የጦር ማሽን/ፋብሪካ በእርሱ ላይ ምን ሊያደርስ እንደሚችል ምንም ዓይነት ፍርሀት አልነበረውም፡፡

ዘ-ህወሀት በእርሱ ላይ ሊያደርግ ስለሚችለው ሁኔታ ፈይሳ ይፈራልን?

ፈይሳ ቀጥተኛ በሆነ መልኩ በግልጽ እንዲህ በማለት ተናግሯል፣ “ባይገድሉኝ እንኳ በእስር ቤት ያማቅቁኛል፡፡ እስከ አሁን ድረስ ምንም የወሰንኩት ነገር የለም፡፡ ሆኖም ግን ምናልባትም ወደ ሌላ ሀገር የምንቀሳቀስ ይሆናል“ ነበር ያለው፡፡

የፈይሳ እናት ምንም ዓይነት ፍርሀት ሳያሳዩ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ እንዲህ ብለዋል፣ “መንግስት እየተናገረ ባለው ነገር ያምናሉን? እዚያው ባለበት ይቆይ፡፡ እዚያው እንዲቆይ ነው እኔ የምፈልገው፡፡ ደህና እንዲሆን ነው የምመኘው“ ነበር ያሉት ከመጣ ደህንነቱ እንደማይጠበቅ እርግጠኛ በመሆን መንፈስ፡፡

የፈይሳ ባለቤት የእርሷ ባለቤት ምን ዓይነት ጠንካራ እንደሆነ እንደምታውቅ እንዲህ ብላለች፣ “በወቅቱ ፈርቸ ነበር፣ ሆኖም ግን ይህ ሁኔታ የሚያስደንቀኝ አይሆንም ምክንያቱም እኔ እርሱን አውቀዋለሁና፡፡ በማህበራዊ ድረ ገጾች የሰዎችን ሬሳዎች በሚያይበት ጊዜ፣ ሰዎች በቁጥጥር ስር ሲዉሉ በሚመለከትብት ጊዜ እና ሰዎች ሲደበደቡ በሚመለከትበት ጊዜ በውስጡ ይቃጠል ነበር፡፡ ስለሆነም እኔ በዚህ ጉዳይ ላይ አልተደነቅሁም ነበር ምክንያቱም በውስጡ በርካታ ብስጭቶች በውስጡ ታምቀው ነበርና“  ነበር ያለችው፡፡

ፈይሳ የህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች እንደፈለጉ በጫማቸው ስር አድርገው የፈለጋቸውን ነገር እንዲፈጽሙበት እና በእነርሱ ስር ለመውደቅ የሚያስችል አቋም የለውም፡፡ ፈይሳ ባለው ፍጥነት ወደፊት በፍጥነት መገስገስ እንጅ በእነዚህ እርባናቢስ ቅጥር ነብሰገዳዮች እጅ ስር መውደቅን አልፈለገም፡፡

ፈይሳ በቀላል አገላለጽ ዘ-ህወሀትን ምንም ዓይነት ልብስ ሳይለብስ በሕዝብ አደባባይ ላይ ቆሞ የለበሰ መስሎት ያልለበሰ መሆኑን ሳያውቅ ራቁቱን ተገትሮ ይታይ የነበረውን የንጉስ አፈ ታሪክ በተጨባጭ አሳይቷል፡፡ ወይም ደግሞ ፈይሳ ይህንን በማድረጉ በእውኑ ዓለም በአሁኑ ጊዜ ሕዝብን እያሰቃዩ እና እየዘረፉ ያሉትን ደም መጣጮች በተጨባጭ ለዓለም ሕዝብ በሚገባ አሳይቷል፡፡

ፈይሳ በአሸናፊነቱ ስለሚያጣው የብር ሜዳሊያ እና የዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ስለሚጭንበት ቅጣት የሚያሳስበው ጉዳይ ነበርን?

ለዚህ ትንሽ ክብ ቁራጭ ብረት ምንም ዓይነት ደንታ ሊኖረው አይችልም ወይም ደግሞ ከዚህ ጋር በተያያዘ ስለሚያገኘው ዝና እና መልካም ዕድል ሁሉ ደንታው እና ጉዳዩ አይደለም፡፡ መቋጫ በሌለው መልኩ የእርሱ ጭንቀት እና በበለጠ መልኩ ያሳስበው የነበረው ስለወገኖቹ ደህንነት ነበር፡፡ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “ስለዚያ ነገር ምንም ማድረግ አልችልም [የዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ/ዓኦኮ ስለሚያደርገው ነገር]፡፡ የእኔ ስሜት ይህ ነበር፡፡ በሀገሬ ውስጥ ትልቅ ችግር አለ፡፡ በሀገሬ ውስጥ ተቃውሞ ማሰማት እና በተቃውሞ መንቀሳቀስ እጅግ አደገኛ የሆነ ነገር ነው:: ዓኦኮ እነዚያን ሁለት ቁራጭ ብረቶች መውሰድ እና  እኔን መገፍተር ይችላል…የእኔ ክብር እና የሕዝቦቼ ክብር በኦሎምፒክ ገበያ ወይም ደግሞ በሌላ በማናቸውም ገበያ ቢሆን ለሽያጭ ለድርድር የሚቀርብ አይደለም“ ነበር ያለው፡፡

ፈይሳን እና ቤተሰቡን እግዚአብሄር ይባርካቸው!

የኢትዮጵያ ወጣቶች ተባብረዋል በፍጹም ሊሸነፉ አይችሉም፣

እ.ኤ.አ ግንቦት 2011 “የአፍሪካ ወጣቶች ተባብረዋል በፍጹም ሊሸነፉ አይችሉም“ በሚል ርዕስ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡

ያ ትችት ያጠነጥን የነበረው ስለሙባረክ አገዛዝ ተፈረካክሶ መውደቅ ጉዳይ እና አምባገነኖች በስልጣናቸው ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ለመቆየት ስለሚወስዱት የኃይል እርምጃ ነበር፡፡ ያ ኃይልን የመጠቀሙ እርምጃ የደካሞች ዋና መሳሪያ እንደነበር ግልጽ አድርጌ ነበር፡፡ ምንም ዓይነት መሳሪያ ያልታጠቁትን ሰላማዊ ዜጎች በመንገዶች ላይ ተኩሶ መግደል እና አካለ ጎደሎ ማድረግ የጥንካሬ ምልክት አይደለም፣ ይልቁንም በተቃራኒው የፍርሀት፣ የደካማነት እና የቦቅቧቃ ፈሪዎች ዋና መለያ ምግባር ነው ነበር ያልኩት፡፡

እ.ኤ.አ ሰኔ 2010 “ስለኢትዮጵያ ወጣቶች እውነታውን መናገር“ በሚል ርዕስ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡ በዚያ ትችቴ በቁጣ ተሞልተው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ ወጣቶች በጊዜ የተሞላ የስነሕዝብ ቦምብ ነው የሚል የክርክር ጭብጥ ማስረጃዬን አቅርቤ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ወጣቶች ተስፋ እያጡ የመምጣት፣ የደስታ እጦት፣ የተሳሳተ እምነት መኖር እና ለብዙ ጊዜ በቆየ የኢኮኖሚ ቀውስ ሳቢያ ብርታትን ማጣት፣ የኢኮኖሚ ዕድሎች ያለመኖር እና የፖለቲካ ጭቆና ግልጽ ሆኖ እየገዘፈ መከሰቱ የማይካድ መሆኑን በማብራራት የክርክ ጭብጤን አቅርቤ ነበር፡፡ ወጣቶች ለነጻነት እና ለለውጥ ያላቸው ጥልቅ ፍላጎት በእራሱ ገላጭ ነው፡፡ ብቸኛ ሆኖ የሚቀርበው ጥያቄ ግን የሀገሪቱ ወጣቶች ለውጡን ሊያመጡት የሚችት እየጨመረ የመጣውን የኃይል እርምጃን በመጠቀም ነው ወይስ ደግሞ በሌላ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ነው የሚለው ነው፡፡

እ.ኤ.አ ጥር 2013 “ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2013፡ የአቦ ሸማኔው ትውልድ ዓመት“ በሚል ርዕስ ለኢትዮጵያ ወጣቶች መልዕክት በማስተላለፍ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡

በዚያ መልዕክቴ የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ትውልድ ይፋ ባልሆነ መልኩ የውይይት መድረክ በእራሳቸው በወጣቶቹ መካከል ማድረግ እና በብሄራዊ ዕርቅ የእነርሱ ሚናዎች ምን መሆን እንዳለባቸው አስቀድመው መወሰን እንዳለባቸው ጥሪ አቅርቤ ነበር፡፡ በዚያ መልዕክቴ ወጣቶች  ከምንጊዜውም በላይ እራሳቸውን ማጠናከር እና የእራሳቸውን የፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ምህዳር መፍጠር እና አንድ በአንድ ከጎሳ፣ ኃይማኖት፣ ቋንቋ፣ ጾታ፣ ክልል እና የመደብ መስመርን ሳይለይ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር መነጋገር እንደሚያስፈልግ የተማጽዕኖ ጥሪ አቅርቤ ነበር፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ለኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ወጣት ትውልድ ብዝሀነታቸውን እንደ ጥንካሬ መውሰድ እንዳለባቸው እና ብዝሀነታቸው እራሳቸውን ለመከፋፈል እና ለጥቃት ሊዳርጋቸው እንደማይገባ የተማጽኖ ጥሪ አቅርቤ ነበር፡፡

በዚያ ትችቴ ላይ የጾታ ልዩነት ክፍተትን ማስወገድ እና ሰላማዊ የእምቢተኝነት ጥረቶችን አጠናክሮ በመቀጠል የወጣት ሴቶችን ተሳትፎ ማስፋት እና ማጠናከር አስፈላጊ እንደሆነ አስምሬበት ነበር፡፡

እ.ኤ.አ ጥር 2014 “እ.ኤ.አ 2014፡ የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው እና የጉማሬው (የቀድሞው) ትውልድ ዓመት“ በሚል ርዕስ አቅርቤው በነበረው ትችት በኢትዮጵያ ውስጥ በወጣቶች ላይ ተጋርጠው ስለሚገኙት ተግዳሮቶች በዝርዝር ጽፌ ነበር፡፡ በዚህ ትችቴ የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ትውልድ ወጣቶች አደገኛ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ በማለት አውጀ ነበር፡፡

የ21ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ዋናው ችግር የወጣቱ ችግር ነው የሚል የክርክር ጭብጥ አቅርቤ ነበር፡፡ እንደ ዩኤስ የሕዝብ ቆጠራ ቢሮ ከ34 ዓመታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር በሶስት እጅ በመጨመር 278 ሚሊዮን እንደሚሆን እና ሀገሪቱ ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት በማስመዝገብ ላይ ከሚገኙት 10 የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ከሚገኙት ሀገሮች ምድብ ውስጥ ትመደባለች የሚል ትንበያ የሰጠ መሆኑን በመጥቀስ የክርክር ጭብጤን አቅርቤ ነበር፡፡

በአሁኑ ጊዜ ወደ አንድ መቶ እና ከዚያም በላይ ሊሆን ከሚገመተው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ውስጥ ወደ 70 በመቶ የሚገመተው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከ35 ዓመት በታች እድሜ (66 ሚሊዮን) ያለው የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡

ኔልሰን ማንዴል በአንድ ወቅት እንዲህ የሚል ምልከታ አድርገው ነበር፣ “የእኛ ልጆች የእኛ ታላቅ ሀብቶች ናቸው፡፡ ልጆቹ የእኛ የወደፊት ጸጋዎች ናቸው፡፡ በእነርሱ ላይ ከሕግ አግባብ ውጭ የሚፈጸም ማንኛውም ድርጊት ሁሉ የማህበረሰባችንን የአንድነት ክር ይበጥሳል፣ እናም ሀገራችንን ያዳክማል“ ነበር ያሉት፡፡

የኢትዮጵያ ወጣቶች የሀገሪቱ ታላቅ ሀብት የሆኑት እና የኢትዮጵያ የወደፊት ጸጋዎች  በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ አደጋ ላይ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ ሀብቶች የሆኑት ወጣቶች ፍጹም በሆነ መልኩ ተረስተዋል፣ ከሕግ አግባብ ውጭ ጭቆና ይፈጸምባቸዋል፣ ውድ የሆነው ጉልበታቸው በከንቱ እየጠፋ እና በከንቱ በመባከን ላይ ይገኛል፡፡

እንደ የአፍሪካ ሕዝቦች እና የጤና ምርምር ማዕከል/African Population and Health Research Center ዘገባ ከሆነ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ በጣም ዝቅተኛ የሆነ ጠቅላላ የትምህርት ሽፋን መጣኔ/Gross Enrollment Rate ካላቸው ሀገሮች መካከል አንዷ ናት…ዝቅተኛ የትምህርት ጥራት እና ከፍተኛ የሆነ የማቋረጥ መጣኔ እንደዚሁም ሁሉ በገጠር እና በከተማ መካከል ከፍተኛ የሆነ የጾታ ልዩነት መኖር ዋና የሀገሪቱ ችግሮች ሆነው ቀጥለዋል፡፡ እንደምንም ብለው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመግባት በጣም የጠበቡ ዕድሎች እንዳሏቸው ወይም ደግሞ የስራ ዕድል እንደማያገኙ ዘገባው ግልጽ አድርጓል፡፡

እ.ኤ.አ በ2012 በዩኤስኤአይዲ የወጣው ዘገባ እንዲህ ይላል፣ “ኢትዮጵያ የከተማ ወጣት የስራ አጥነት የተንሰራፋባት ሀገር ናት፡፡ ይህም የስራ አጥነት መጣኔ 50 በመቶ እንደሆነ እና ከፍተኛ የሆነ የስራ አጥነት ችግር ተንሰራፍቶ እንደሚገኝ እንዲሁም 85 በመቶ የሚሆነውን ሕዝብ በሚይዘው በገጠሪቱ ኢትዮጵያም የስራ አጥነቱ ችግር በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮ ይገኛል“ ነበር ያለው፡፡

ሌላው በዓለም አቀፍ የዕድገት ማዕከል/International Growth Center እ.ኤ.አ በ2012 በወጣት ስራ አጥነት ላይ የተደረገ ጥናት የግኝት ጭብጥ እንዲህ ይላል፣ “በአሁኑ ጊዜ ያለው (እ.ኤ.አ 2010/11 – 2014/15) የ5 ዓመት የኢትዮጵያ የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ገዥው አካል የወጣቶችን ስራ አጥነት ችግር ጉዳይ በቀጥታ አላካተተም…“ ነበር ያለው፡፡ ያ ጥናት እንዲህ የሚል የጥናት ውጤት አግኝቷል፣ “እ.ኤ.አ በ2011 38 በመቶ የሚሆኑት ወጣቶች አብዛኛውን ጊዜ ዝቅተኛ የጥራት ጉድለት በሚታይባቸው እና ዝቅተኛ ክፍያን በሚከፍሉ የግል ዘርፉ ውስጥ ተቀጥረው ይገኛሉ“ ነበር ያለው፡፡

በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉት ከፍተኛ ብዛት ያላቸው ወጣቶች ስራ አጥ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን መሰረታዊ የሆኑ ክህሎቶችን በተገቢው ስልጠና ያላገኙ በመሆናቸው ወደፊትም እንኳ የስራው ዕድል ቢፈጠር ተቀጥረው ለመስራት የማይችሉ ናቸው፡፡ በመንግስት ቁጥጥር ስር የሚገኙት የስራ ዘርፎች በብቃት ወይም ደግሞ በውድድር ላይ በተመሰረተ መስፈርት መሰረት ባለሞያዎችን የሚቀጥሩ ሳይሆን በፖለቲካ የመንግስት ወገንተኝነት እምነታቸው እና በማህበራዊ ግንኙነቶች እንደዚሁም ደግሞ  የገዥው ፓርቲ አባል ለሆኑት ስራ ፈላጊዎች ብቻ ተደራሽ የሆኑ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ማንኛውም ወጣት አባልነትን የሚገልጽ ካርድ ከገዥው ፓርቲ መያዝ ትክክለኛ በሆነ የግል ጥረት ከተያዘ የዩኒቨርስቲ ዲፕሎማ በላይ ጠቃሚነት አለው፡፡ ከዚህም በላይ የገጠር ወጣቶች መሬት አልባነት ለዚህ ለተፈጠረው ቀውስ እና ወደ ከተማ ለሚደረገው ከፍተኛ የሆነ የሰው ፍልሰት፣ ስራ አጥነት እና ተስፋየለሽነት እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

በኢትዮጵያ ወጣቶች ላይ ተጋርጠው የሚገኙ አደጋዎች ሙሉ በሙሉ በህብረተሰቡ ውስጥ ተንሰራፍተው የሚገኙ ማህበራዊ ቀውሶች ናቸው፡፡

እ.ኤ.አ በ2010 እንደወጣው የዘ-ህወሀት ዘገባ 150 ሺ ህጻናት የጎዳና ላይ ተዳዳሪዎች ሆነዋል፣ ከእነዚህም ውስጥ 60 ሺ የሚሆኑት በሀገሪቱ ዋና መናገሻ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡ ልጆቹ በመጀመሪያ ቤት አልባ የሚሆኑበት አማካይ እድሜ 10 እና 11 ዓመት እንደሆነ ተዘግቧል፡፡

ከኤች አይቪ ኤይድስ እና ከሌሎች በግብረ ስጋ ከሚተላለፉ በሽታዎች ጋር በተያያዘ መልኩ የወጣቶች የጤንነት አደጋዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመር ላይ ይገኛሉ፡፡ ምንም ዓይነት ዕድል የሌላቸው በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች አንደንዛዥ እጾችን በመውሰድ፣ አልኮልን በማዘውተር፣ በዝሙት አዳሪነት እና በሌሎች በወንጀል ድርጊቶች ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ በከተሞች አካባቢ ያለምንም ስራ እና የትምህርት ዕደል በርካታ የሆኑ ወጣቶች ስራ አጥ፣ ቤት የለሽ፣ ረዳት የለሽ እና ተስፋየለሽ ሆነው ይገኛሉ፡፡

እ.ኤ.አ በ2004 ዘ-ህወሀት ብሄራዊ የወጣቶች ፖሊሲን አወጀ፡፡ እናም ባደረገው የዳሰሳ ጥናት ዘገባ መሰረት እንዲህ የሚል ግኝት ተመዝግቦ ነበር፣ “44 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ከድህነት ወልል በታች ነው፡፡ በዚህ ዓይነት የድህነት ሁኔታ ወጣቱ በከፍተኛ ደረጃ ተጠቂ የሆነ የማህበረሰብ ከፍል ነው…አብዛኞቹ ስራ አጥ የሆኑት ሴት ወጣቶች የመሆናቸው ጉዳይ ደግሞ የዚህ ችግር ሰለባ የመሆናቸውን እውነታነት የበለጠ ተጨባጭ ያደርገዋል“የሚል ነበር፡፡ ሰነዱ የፖሊሲውን ተፈጻሚነት ሲያብራራ “መንግስት፣ የመምራት፣ የማስተባበር፣ የማቀናጀት እና የአቅም ግንባታ ስራዎችን የመስራት ኃላፊነትን ይወስዳል” የሚል ነበር፡፡

ሆኖም ግን እ.ኤ.አ በ2012 በዓለም አቀፍ የዕድገት ማዕከል/International Growth Center  በወጣት ስራ አጥነት ላይ የተደረገ ጥናት የግኝት ጭብጥ እንዲህ ይላል፣ “በአሁኑ ጊዜ ያለው (እ.ኤ.አ 2010/11 – 2014/15) የ5 ዓመት የኢትዮጵያ የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ገዥው አካል የወጣቶችን ስራ አጥነት ችግር ጉዳይ በቀጥታ አላካተተም…“ የሚል ነበር፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ ብሄራዊ የወጣቶች ፖሊሲ እየተባለ የሚጠራው ለዘ-ህወሀት ወጣቶችን ለይስሙላው ምርጫ መጠቀሚያነት ከመሆን ባለፈ ለወጣቱ አንዳችም የፈጠረው ፋይዳ የለም፡፡

እ.ኤ.አ በ2014 የወጣ ዘገባ አስከፊውን የገጠር ድህነት ለማምለጥ ወጣቶች እንዴት አድርገው የውስጥ ፍልሰትን እንደሚጠቀሙ ያመላክታል፡፡

ለበርካታ ዓመታት የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ትውልድ አንድ ቀን ሊነሳ እንደሚችል እና ያችንም ቀን እንሚጠብቃት ስናገር ቆይቻለሁ፡፡ ኢትዮጵያን ከዘ-ህወሀት ጅቦች ጠብቁ፡፡

ሳስተላልፈው በቆየሁት መልካም መልዕክት ሁሉ በጣም ኩራት ይሰማኛል!

እ.ኤ.አ የካቲት 2016 “ለኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ትውልድ የጥርሙስ ውስጥ መልዕክት፡ ነጻ ሆናችሁ ተወልዳችኋል፣ ነጻ ሆናችሁ ኑሩ!“ በሚል ርዕስ ስለሚመጣው ሁኔታ እንዲህ በማለት አስጠንቅቄ ነበር፡

“የኢትዮጵያ ወጣቶች ሙሉ በሙሉ ግንዛቤው አላቸው፡፡ ጥቂት የአቦ ሸማኔው ትውልድ አባላት በንዴት እና በከፍተኛ ቁጣ በመነሳሳት በእምቢተኝነት ከዘ-ህወሀት ፊት ለፊት ይቆማሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ድምጾቻቸውን ከፍ አድርገው ያንሾካሹኩ እና ያጉረመርማሉ፡፡ የኢትዮጵያ አቦ ሸማኔዎች ደስተኞች አይደሉም” በማለት አስጠንቅቄ ነበር፡፡ ለዚህም ነው በአሁኑ ጊዜ በመላ ሀገሪቱ ውስጥ ከጅቦች ጋር ፊት ለፊት በመጋፈጥ እና በማጉረምረም ላይ የሚገኙት፡፡

እ.ኤ.አ ጥር 2016 ዘ ኢኮኖሚስት የተባለው መጽሄት ለበርካታ ዓመታት በአእምሮዬ ውስጥ ሲመላለስ የቆዬ እንዲህ የሚል አንድ ጥያቄ አቅርቦ ነበር፡፡ ጥያቄውን በሰማሁበት ጊዜ መብረቅ እንደመታው ዛፍ ድርቅ ብዬ ነበር የቀረሁት፡፡ እንዲህ የሚል ጥያቄ ነበር፣ “አትዮጵያውያን ነጻ ቢሆኑ ኖሮ የት ይደርሱ ነበር?“ ዘ ኢኮኖሚስት ለእራሱ ጥያቄ መልስም እራሱ እንዲህ በማለት ነበር የሰጠው፣ “የኢትዮጵያ መንግስት ሕዝቦች በነጻነት እንዲተነፍሱ ቢፈቅድ ክንፍ አውጥተው ሊበሩ ይችላሉ፡፡“

“ብሪሪ፣ ኢትዮጵያ ብረሪ…“ በሚል ርዕስ አዘጋጅቸው በነበረው ትችቴ የምዕናባዊ በረራዬን አከናውኘ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ መብረር የምትችል ቢሆን ኖሮ ለመሞት በባህር ላይ አይጣሉም ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ሴቶች ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች በእርግጠኝነት ባሮች ለመሆን አይበሩም ነበር፡፡ በረሀዎችን በማቋረጥ ደም ለጠማቸው አሸባሪዎች የጥቃት ሰለባ አይሆኑም ነበር፡፡ ወደ ስደት አያመሩም ነበር፡፡ ለመብረር የሚችሉ ቢሆን ኖሮ እንደ አፍሪካ ዓሳ ይንሰፈፉ ነበር፡፡ ክንፎቻቸውን ወደ ሰማይ ከፍ በጣም ከፍ ያደርጉ ነበር፡፡ እንደ ድምጻዊዋ ወፍ ያዜሙም ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ወጣቶች እንዲበሩ እፈልጋለሁ፡፡

በምዕናባቸው በረራ እንዲያደርጉ እፈልጋለሁ፡፡

የእነርሱ የሆነች እና ከጎሳ ፖለቲካ፣ ከኃይማኖት ጽንፈኝነት እና ከጭፍን ጥላቻ ነጻ  የሆነች አዲስ ኢትዮጵያን እንዲያልሙ እፈልጋለሁ፡፡

በእራሷ ለእርሷ እና ለጎረቤቶቿ ሰላሟ የተጠበቀ፣ ከጭቆና እና ከወሮበላ ዘራፊዎች ነጻ የሆነች ኢትዮጵያን ለማየት እፈልጋለሁ፡፡

እያንዳንዱ የአቦ ሸማኔ ትውልድ የህንጻ ንድፍ ባለሞያ፣ ንድፍ ሰሪ፣ ፈጣሪ፣ ለኪ፣ ገንቢ እና ዜጎቿ እርስ በእርሳቸው ስለጎሳዎቻቸው ሳይሆን ስለሰብአዊ ፍጡርነታቸው፣ ስለእኩልነት ዕድሎቻቸው፣ ከሙስና፣ ከጭቆና እና ከወሮበላ ዘራፊዎች ነጻ ስለሆነች ኢትዮጵያ በአንክሮ የሚያስቡ የነጻ ኢትዮጵያ ስራ ፈጣሪ ዜጋ እንዲሆኑ አጥብቄ እጠይቃለሁ፡፡

ኢትዮጵያን በምዕናባቸው እንዲያንጿት እፈልጋለሁ፡፡

ማሸነፍ ልብን እና አእምሮን እንጂ ሜዳሊያዎችን አይደለም፣

እኔ ሁልጊዜ ከኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ትወልድ ጠርዝ ወይም ጫፍ ላይ እንደምቆም ግልጽ አድርጊያለሁ፡፡ (እ.ኤ.አ ጥር 2013 “የአቦ ሸማኔ – ጉማሬው ትውልድ መነሰሳሳት” በሚል ርዕስ አዘጋጅቸው የነበረውን ትችቴን ይመልከቱ፡፡)

በዚያ ትችቴ ላይ በኢትዮጵያ ለነጻነት፣ ለዴሞክራሲ እና ለሰብአዊ መብጥ ጥበቃ የሚደረገው ትግል ዋናው ምስሶ እንደሆነ እና የኢትዮጵያን ሕዝቦች ልብ እና አእምሮ ለመቆጣጠር በሚደረገው ጦርነት ላይ ትልቅ ጉዳይ እንደሆነ ለኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ትውልድ በዝርዝር ገልጨ ነበር፡፡ ልብን እና አእምሮን ለመቆጣጠር በሚደረግ የጦር ሜዳ ትግል ውስጥ ጠብመንጃዎች፣ ታንኮች እና የጦር አውሮፕላኖች ዋጋቢሶች ናቸው፡፡ ይህንን ጉዳይ ታሪክ በተጨባጭ አረጋግጧል፡፡ ዩኤስ አሜሪካ በቬትናም ጦርነት ድልን አጥታለች ምክንያቱም አውዳሚ የጦር መሳሪያዎች ኃይል፣ የአየር ኃይል፣ የኒኩሌር ኃይል፣ የገንዘብ ኃይል ሳይንሳዊ ወይም ደግሞ የቴክኒክ ኃይል ስላጡ አልነበረም፡፡ ዩኤስ አሜሪካ በጦርነቱ የተሸነፈችበት ዋናው ምክንያት የቬትናማውያንን እና የአሜሪካውያንን ሕዘቦች ልቦች እና አእምሮዎች ማሸነፍ ባለመቻላቸው ነበር፡፡

ህይወት ሜዳሊያ ስለማሸነፍ ጉዳይ አይደለም፡፡

ይልቁንም ህይወት ልብን እና አእምሮን ስለማሸነፍ ጉዳይ ነው፡፡

የዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የሚያብረቀርቁ ሜዳሊያዎችን ከስሚዝ እና ከካርሎስ ቀምቶ ወስዷል፡፡  እነዚህ ሁለት ጓደኛሞች ከአራት አስርት ዓመታት በላይ ይበገሬ የሰብአዊ መብት ተሟጋችነታቸውን በተግባር አረጋግጠዋል፡፡

ዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የፈይሳን ሜዳሊያ ይወስደው ወይም አይወስደው ለመሆኑ ገና ግልጽ አይደለም፡፡

እንደ ስሚዝ እና ካርሎስ በተመሳሳይ መልኩ ፈይሳ እ.ኤ.አ በ2016 የእርሱን ሕዝቦች ልቦች እና አእምሮዎችን የተቆጣጠረውን ሜዳሊያ ብቻ አይደለም የወሰደው ሆኖም ግን በእርገጠኝነት የወሰደው በዓለም ላይ የሚገኙትን በቢሊዮኖች የሚቆጠሩትን የሌሎችን የነጻነት አፍቃሪዎች ሕዝቦች ልቦች እና አእምሮዎች ጭምር እንጅ፡፡

ፈይሳ ልክ እንደ ስሚዝ እና ካርሎስ በተመሳሳይ መልኩ ለበርካታ ጊዚያት የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች በመሆን ሲወደስ እና ሲዘከር ይኖራል፡፡

ስሚዝ፣ ካርሎስ እና ፈይሳ የፈጸሙት ድርጊት እውነተኛ የአሜሪካ መስራች አርበኞች የፈጸሙት እውነተኛ የመንፈስ እና ቃላት ድርጊት እንደሆነ አምናለሁ፡፡

ወጣቱ አሌክሳንደር ሀሚልተን (አንዱ ያሜሪካ ቆርቅዋሪ) እንዲህ በማለት ጽፎ ነበር፣ “የሰውን ባህሪ ከእራሱ በላይ አድርጎ በቆራጥነት እና በጀግንነት እንዲወጣ ሊያደርግ የሚያስችል በነጻነት ውስጥ አንድ ልዩ የሆነ የማድረግ ጉጉት አለ“ ነበር ያለው፡፡ ሀሚልተን የእንግሊዝ በሙያ ክህሎት የተካነው የጦር ኃይል በአንድ የማድረግ ጉጉት በተጠናውተው ቆራጥ እና ጀግና አማጺ ሊሸነፍ እንደሚችል ያምናል፡፡ ካርሎስ እና ስሚዝ በዝቀተኛው የህብረተሰብ ክፍል የሚገኙት የሲቪል ማህበረሰቡን መብት የማስከበር ጉጉት ያደረባቸው ጀግኖች የመብት ተሟጋቾች በአሜሪካ ውስጥ ዘረኝነትን እና ድህነትን ሊያሸንፉ እንደሚችሉ ያምናሉ፡፡ ፈይሳ ለነጻነት ያለውን ጉጉት ቆራጥነት እና ጀግንነትን በተላበሰ መልኩ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቢሊዮኖች እንዲታይ በማድረግ ወደ ተጨባጭ ተግባር ተርጉሞታል፡፡

ወጣት ጀምስ ማዲሰን (የአሜሪካ ሕገ መንግስት መስራች አባት) አብዮታዊ በሆነ ብሄራዊ የአንድነት እና የዓላማ መንፈስን በመተግበር እንዲህ የሚል ዝናን ተጎናጽፏል፡ “የነጻነት መንፈስ እና አርበኝነት ሁሉንም የሰው ልጆችን የደስታ መጠን እና ዋጋዎች ግኡዝ ያደርጋሉ፡፡“  እንደዚሁም ሁሉ ካርሎስ እና ስሚዝ እ.ኤ.አ በ1968 እንዳደረጉት ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ የነጻነት መንፈስ እና አርበኝነት ፈይሳን እ.ኤ.አ በ2016 ግኡዝ አድርገውታል፡፡

የምክንያታዊነት ደጋፊና አምፅ አንቀሳቃሽ  የሆኑት ሳሙኤልሰን አዳምስ በአንድ ወቅት እንዲህ በማለት አስጠንቅቀው ነበር፣ “ለእውነተኛ አርበኞች ዝምታን መምረጥ አደገኛ ሁኔታ ነው“ ነበር ያሉት፡፡

እውነተኛ የአሜሪካ አርበኞች ስሚዝ እና ካርሎስ እና የኢትዮጵ አርበኛ ፈይሳ ሌሊሳ በኦሎምፒክ መድረክ ዝምታን መርጠው ነበር፣ ሆኖም ግን ወደ ላይ ከፍ ያሉት ቡጢዎቻቸው እና የተጣመሩ እጆቻቸው ስለዘርኝነት፣ ስለጎሳ ጥላቻ፣ ስለኢፍትሀዊነት እና ስለአድልኦ በርካታ ነገሮችን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵ የአቦ ሸማኔዎች ግድያ ለመጣል በማዛጋት ያጉረመርማሉ፣

“የአቦ ሸማኔ – ጉማሬ” መጽሐፍ ደራሲ የሆኑት የጋናው ኢኮኖሚስት ጆርጅ አይቴይ በአፍሪካ ውስጥ የሚታየውን የአመራር ቀውስ ለመግለጽ  የአቦ – ሸማኔን ተመሳስሎ በመውሰድ እንዲህ የሚል ምልከታ አድርገው ነበር፣ “የአፍረካ አቦ ሸማኔዎች በለውጥ የታጀቡ ጠንካሮች ናቸው፣ ምሁራዊ የአእምሮ የማድረግ ቅልጥፍና እና በተግባራዊ ውጤታማነት ላይ ልዩ የሆነ ትኩረት አላቸው፡፡ እረፍትየለሽ ትውልዶ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ሆኖም ግን የአፍሪካ አዲስ ተስፋዎቸ ናቸው፡፡ ስለሙስና፣ ስለውጤት አልባነት፣ ስለክህሎት የለሽነት እና ስለብቃትየለሽነት ወይም ደግሞ ስለእርባናቢስ ባህሪ ትዕግስቱ ፈጽሞ የላቸውም“ ነበር ያሉት፡፡

አቦ ሸማኔ ፈይሳ ሌሊሳን ተመልከቱት!

የኢትዮጵያ ተስፋዎች የሆኑትን የኢትዮጵያውን ወጣት አቦሸማኔዎችን ተመልከቱ፡፡

ኢትዮጵያውያን እንደ ሀገር እና እንደ ሕዝብ የመቀጠል የህልውና ዕድል ቢኖራቸው ያ የመኖር ህልውና ሁልጊዜ በእራሷ ወጣቶች የመፍጠር ችሎታ፣ የማይበገር የአካል፣ የአእምሮ ጥንካሬ የማሳየት ብቃት፣ ጽናት፣ መልካም ፈቃድ፣ የመፈጸም ብቃት፣ እና መስዋዕትነት በመክፈል ሁኔታ ላይ የሚወሰን ነው እላለሁ፡፡ ይኸ ሁኔታ በወጣቶች ላይ ታላቅ ሸክምን አስቀምጧል፡፡ ከባዱን ነገር ለማንሳት፣ ከባድ ስራዎችን ለመስራት እና መስዋዕትነትን በመቀበል የአንበሳውን ድርሻ (የአቦ ሸማኔውን ሳይሆን) ማድረግ አለባቸው፡፡

እንደዚሁም ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ የኢትዮጵያ ወጣቶች እንደ ወጣት መቀጠል ቢችሉ እና የመኖር ዕድል ቢኖራቸው በቀድሞው ትውልድ ለመጭው ትውልድ ንቁ እና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ በማድረግ ጥንካሬ ላይ የሚወሰን ነው፡፡

የኢትዮጵያ የጉማሬው (የቀድሞው ትውልድ) አቦ ሸማኔዎቻችን ተስፋ እንዳያጡ እና እንዳይወድቁ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ አለብን፡፡ ይህንን ማድረግ ከቻሉ በአንጸባራቂነት እንዲወጡ እና ደግመው እና ደጋግመው እንዲያደርጉት ማስቻል አለብን፡፡

እኛ የቀድሞው ትውልድ አባላት የቱንም ያህል ጊዜ ቢፈጅም፣ ገሀነም ወይም የቱንም ያሀል በከፍተኛ ደረጃ ላይ ደረሰ ቢሆንም በማንኛውም መንገድ ከአቦ ሸማኔዎቻችን ጎን በጽናት መቆም አለብን፡፡ ከእነርሱ ጋር የውይት መድረኮችን በመክፈት መወያየት እና እነርሱን እንደምንደግፋቸው እና እንደምንወዳቸው፣ በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ግንባታ ውስጥ ተሰማርተው እስካሉ ድረስ እኛ በደስታ የእነርሱ ውኃ አቀባይ እንደሆንን ልናረጋግጥላቸው ይገባል፡፡

አብዛኞቻችን እኛ የጉማሬው ትውልድ አባላት ታላላቅ ነገሮችን ለመስራት ሊያመልጡን የማይገቡ ዕድሎች በፍጹም ሊያመልጡን የማይገቡ ዕድሎች ናቸው፡፡ (ውይ እንዴት የሚያም ነገር ነው! እውነት እንዴት እንደሚጎዳ!)

ታላላቅ ነገሮችን ለእራሳችን መስራት ማለትም አይደለም፡፡ ለሌሎች ነው መስራት ያለብን፡፡ መስራት ያለብን ኃይል ለሌላቸው፣ መከላከያ ለሌላቸው፣ ለተስፋ የለሾች፣ ለመጠለያ የለሾች፣ ለሀገር አልባዎች እና ለምቾት የለሾች ነው፡፡

ከአቦ ሸማኔዎች ጎን በመቆም አቦ ሸማነኔዎቻችንን በመርዳት ይህንን ቅዱስ የሆነ አጋጣሚ እንዳናጣው ጥረት እናድርግ፡፡

የጀግና ጉዞ፣

ሺ ፊቶችን የሚጋፈጠው የጆሴፍ ካምፕቤል ጀግና በዓለም አቀፍ ደረጃ ጀግንነትን ለመስራት እና ድልን በወሳኝነት እስከመጨረሻው ለመቀዳጀት ሁሉንም ዓይነት ስቃዮች፣ መከራዎች መጋፈጥ አለበት፡፡ ማናቸውንም ፍርሀት ከሚያስከትሉ ነገሮች፣ ከሚያበሳጩ እና መከራ ከሚያስከትሉ ነገሮች ጋር ሁሉ ፊት ለፊት ይጋፈጣል፡፡ ሞትንም ሊጋፈጥ ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ጅግና በሁሉም ጉድለቶች ሳቢያ አይንበረከክም፡፡

ፈይሳም እንደዚሁ በተመሳሳይ መልኩ በእርሱ የዓለም ጀግንነት ከታላላቅ ተግዳሮቶች እና የህይወት አጋጣሚዎች ጋር መጋፈጥ አለበት፡፡

ያለምንም ጥርጥር ከእራስ መተማመን ጥርጣሬ፣ በእራስ ከማዘን፣ ከራስ ትችት፣ ከሀዘን፣ ከጥፋት፣ ከጸጸት፣ ከሀሜት፣ ከሀዘን እና ከብስጭት እራሱን ነጻ እንደሚያደረግ የሚያጠራጥር ጉዳይ አይለም፡፡

ቃላት ሊገልጹት ከሚችሉት በላይ ልጆቹን እና ባለቤቱን ሊያጣ እንደሚችል የሚያጠራጥር ጉዳይ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን እነዚህ ሁሉ ነገሮች ለእውነተኛ የሰው ልጆች ስጋ ለለበሱ ሰይጣኖች ሳይሆን ለሁሉም የሰው ልጆች መለያ ባህሪያት ናቸው፡፡

እነዚህ ነገሮች ለረዥም ርቀት ሯጩ ታላቅ ሸክም ናቸው፡፡

ሆኖም ግን ፈይሳ በማወቅ ሁሉንም የእርሱን ምቾት በመሰዋት ለልጆቹ፣ ለባለቤቱ፣ ለወላጆቹ፣ እና ለእርሱ ሕዝቦች እንደ ሰብአዊ ፍጡር ክብር እና ነጻነት አግኝተው እንዲኖሩ በማሰብ ያደረገው ጉዳይ ስለሆነ የሚጸጸትበት ነገር አይሆንም፡፡

ፈይሳ እና ሁላችንም ከእርሱ ጎን የቆምን እና በኢትዮጵያ ውስጥ ለዴሞክራሲ፣ ለነጻነት እና ለሰብአዊ መብት መከበር የማራቶን ሩጫ ለመሮጥ የተዘጋጀን ሰዎች ሁሉ በመጨረሻ የወርቅ ሜዳሊ አሸናፊዎች እንደምንሆን ምንም ዓይነት ጥርጣሬ የለኝም፡፡ ማራቶን መንፈስ አይደለም፣ ስለሆነም የፍጥነት ምህዋራችንን ጠብቀን መሮጣችንን መቀጠል አለብን፡፡

የጀግኖች ጉዞ በፍጹም ቀላል አይደለም፡፡ ለዚህም ነው በዓለም ላይ እንደዚህ ያለውን ከባድ ሸክም ለመቀበል ፈቃደኛ የሆኑ በጣም ጥቂት እውነተና ጀግኖች ብቻ ያሉን፡፡

አብዛኞቻችን ለውጥን እንፈራለን፣ እናም በይበልጥም ደግሞ የእራሳችንን አእምሮ ለመለወጥ እንፈራለን፡፡ ስለሆም በፍርሀት ብርድ ልብስ ውስጥ በመወሸቅ ፍጹም በሆነ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ወድቀን እንገኛለን፡፡

እንደ ጀግና ኢትዮጵያዊ የፈይሳ ገጽታ ለሁሉም ኢትዮጵያውን እንደ ነጻነት ጠባቂ፣ ዘብ፣  የዴሞክራሲ እና ሰብአዊ መብት ተሟጋችነት ሚና እውነታነት ተተርገሟል፡፡

እንደ ካምፔል ምዕናባዊ ጀግና በተመሳሳይ መልኩ ፈይሳም ሁሉንም ነገር መስዋዕት ያደረገለትን ጉዳይ አጥብቆ በመያዝ የሁሉም ፈዋሽ መድሃኒት እና ሀብት በመያዝ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገሩ ይመለሳል፡፡

ምናልባትም ፈይሳ ስለሰራው ቆራጥነት እና ጀግንነት ትልቅ አክብሮት ላንሰጥ እንችል ይሆናል፡፡

የእርሱ ቀደምት አባቶች ኢትዮጵያን ከውጭ ወራሪዎች፣ ከቅኝ ተገዥነት እና ከኢምፔሪያሊዝም ተጽዕኖ ለዘመናት የሀገራችንን ነጻነት ለመጠበቅ በደማቸው፣ በላባቸው እና በእንባዎቻቸው ክቡር ዋጋ የከፈሉ ሲሆን ፈይሳ ግን በእግሩ እና በእጆቹ ብቻ በመጠቀም ፈጽሞታል፡፡

ብቸኛው ልዩነት ግን ፈይሳ በሀገሩ በስልጣን ኮርቻ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው የሚገኙትን የማፊያ ወንጀለኛ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ የከፈለው መስዋዕትነት የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡

የፈይሳ እንደ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ አርበኛ ሆኖ እንደገና የመወለድ ሁኔታ የሚመጣው ሀገሩ ኢትዮጵያ  ከዘራፊዎች፣ ወሮበሎች እና ከወንጀለኞች አፈና ነጻ ከሆነችው ምድር ላይ ከቤተሰቡ ጋር እንደገና መገናኘት ሲችል ነው፡፡

ፈይሳ ወደ ሀገሩ በሚመለስበት ጊዜ እርሱን ሰላም ለማለት ሚሊዮኖች መንገዶችን ሁሉ በሰልፍ እንደሚያጣብቡ አልጠራጠርም…

አቤት ጉድ እኮ ነው፣ መላዕክቶች ወደ ሀገራቸው በሚመለሱበት ጊዜ…ሰይጣኖቹ በቀጥታ ወደ ገሀነም ይወርዳሉ፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 ያስተላለፍኩትን መልዕክት እንደገና በ2016 ለኢትዮጵያ ወጣቶች እናገራለሁ፣

እ.ኤ.አ በ2011 እንዲህ የሚል መልካም የሆነ መልዕክት ለኢትዮጵያ ወጣቶች አስተላልፌ ነበር፡

“የኢትዮጵያ ወጣቶች ተጋርጠውባቸው ስላሉት ማናቸውም ችግሮች መፍትሄ ሊሆን የሚችል ታምራዊ ቀመር በፍጹም የለኝም፡፡ ለሁሉም ወጣት ኢትዮጵያውያን ለማስተላለፍ የምፈልገው ዋና ጉዳይ እንዲህ የሚል ቀላል ነገር ነው፡፡ ‘በፍጹም እጅ እንዳትሰጡ፣ በፍጹም!’ አእምሮዎቻችሁን ከአእምሮ ባርነት ነጻ አውጡ፡፡ የመፍጠር ኃይላችሁን አሳድጉ፡፡ እርስ በእርሳችሁ ተማሩ፣ አስተምሩ፡፡ እንደ እናት ኢትዮጵያ ልጆችነታችሁ ተባበሩ፣ እናም በጎሳ፣ በቋንቋ፣ በአካባቢያዊነት ወይም በመደብ መሰረትነት የሚከፋፍላችሁን ማንኛውንም ርዕዮት ዓለም አስወግዱ፡፡ ስለሳይንስ እና ስለማህበረሰብ ትምህርታችሁ ብቻ ሳይሆን ከዚህም በተጨማሪ ስለ ሕጋችሁ፣ ስለሕገ መንግስት እና ስለሰብአዊ መብትም አጥኑ፡፡“ 

እ.ኤ.አ በ2016 እንደገና ይህንኑ መልዕክት በድጋሜ በአስቸኳይ እንዲህ በማለት ላክሁ፡

የኢትዮጵያ የወጣት ኃይል በምንም ዓይነት መንገድ የሚቆም እንዳልሆነ በእያንዳንዱ የሰውነታችን ክፍል ይታወቃል፡፡

በፍጹም እጅ እንዳትሰጡ! በፍጹም!

እንደ እናት ኢትዮጵያ ልጅነታችሁ ሁላችሁም ተባበሩ፡፡

ዘርን፣ ቋንቋን፣ ኃይማኖትን፣ አካባቢያዊነትን ወይም ደግሞ መደብን መሰረት በማድረግ የሚመጣን ርዕዮት ዓለም ወይም ጥረት አስወግዱ፡፡

እጆቻችሁን በማጣመር ወደ ቤተሰማያት አቅጣጫ በማድረግ ጉዟችሁን ቀጥሉ፡፡ በሰላማዊ መንገድ፡፡

መላዕክት ጉዟቸውን አጠናቅቀው በሚደርሱበት ጊዜ ሰይጣኖቹ ውር ብለው እንደሚበሩ እመኑ፡፡

የእናንተ ትግል ማተኮር ያለበት ከተራው ዓለም ሕዝብ ጋር ያለመሆኑን አስታውሱ፡፡

የእናንተ ትግል በገሀነም ውስጥ ካለው ከሰይጣናዊ ኃይል ጋር ነው፡፡

የእናንተ ትግል እንደገና ህይወት ዘርቶ የጭቆና ህልውናውን ለማስቀጠል የሞት ሽረት ትግል ከሚያደርገው ከጨለማው ልዑል ሠራዊት ጋር ነው፡፡

ሆኖም ግን እናንተ አሸናፊዎች እንደምትሆኑ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ምክንያቱም አምላክ ከእናንተ ጎን ተሰልፏልና፡፡

እመኑ!

የሀሰት ልዑሎች ይወድቃሉ፣ አፈር ትቢያም ይሆናሉ፣ እናም ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች ተብሎ በቅዱሱ መጽሐፍ ተጽፏልና፡፡

የሰላም እጆቻችሁን ለኢትዮጵያውያን ወገኖቻችሁ ዘርጉ!

እጆቻችሁን ወደ ላይ ወደ አየር ከፍ በማድረግ አጣምሩ፣ እናም ሰይጣኖች በምንም መንገድ ሊያቋርጧቸው አይችሉም፡፡

ለቅሶ ለዛሬ ማታ ብቻ ህልውና ሊኖረው ይችላል፣ ሆኖም ደስታ እና ሀሴት ከነገ ጠዋት ጀምሮ ይመጣል፡፡

አሁን የጧቱ ጊዜ ነው!

የኢትዮጵያ ወጣቶች በአንድነት ወደፊት! ጉዟችሁን በቆራጥነት እና በጽናት ቀጥሉ!

የኢትዮጵያ አቦ ሸማኔዎች ማጉረምረማችሁን የበለጠ አጠናክራችሁ ቀጥሉ!

ድል በእጆቻችሁ መዳፍ ውስጥ ነው! ድል በእጆቻችሁ መዳፍ ውስጥ ነው!

እመኑ!

የኢትዮጵያ ወጣቶች ተባብረዋል በፍጹም ሊሸነፉ አይችሉም!!!

ኃይል ለኢትዮጵያ ወጣቶች!  

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!  

ነሐሴ 25 ቀን 2008 ዓ.ም

 

ኢትዮጵያ፡ #ከተቃውሞ እና #ከተጋድሎ በኋላ!? [የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ]

$
0
0

Obangአሰላሙ አሌይኩም፣ እንደምን አላችሁ፣ አካም ጂርቱ፣ እንደምን አረፈዳችሁ (good afternoon everyone)፡፡ የኢትዮጵውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ኅብረት በዚህ ስብሰባ ላይ እንድናገር ስለ ጋበዘኝ ልባዊ ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ፡፡[1]

ከእናንተ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ጋር በመሆን ስለምትወዷት አገራችን የወደፊት ሁኔታ ለመወያየት መብቃት ታላቅ ዕድል ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት አገራችን በከባድ ቀውስ ውስጥ እንደምትገኝ ሁላችንም የምናውቀው ሃቅ ነው፤ ይህም ቀውስ በአንድ ጊዜ የተከሰተ ሳይሆን ለዓመታት ሲጠራቀምና ሲከማች የቆየ ነው፡፡ የአገራችን የወደፊት ሁኔታ ሁላችንንም የሚያሳስበን በመሆኑ እናንተም ይህንኑ ሃሳብ እንዳቀርብ በጠየቃችሁኝ መሠረት እኛ ኢትዮጵያውያን በኅብረት በመሥራት ለአገራችን የተሻለ የወደፊት ተስፋ ማምጣት እንዴት እንደምንችል ሃሳቤን ከዚህ እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡

በቅድሚያ ጥያቄዎችን እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ፤ ባለፉት ዓመታት ካገኘነው ውጤት በተሻለ ለወደፊቷ ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ የምናበረክተው አስተዋጽዖ ምንድነው? ባለፉት ዓመታት በተደጋጋሚ ስናካሂደው የነበረው ትግል ነጻነትና እኩልነት የሰፈነባትን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እንድንመሠርት ያላስቻለን ለምንድነው? ካለፉት የትግል ልምዶቻችን እንደገና እንድንቃኘው የሚያስፈልጉን የትኞቹን ነው? በለመድነውና በባህል በተቆራኘን ራሳችን ለሽንፈት በሚዳርግ መንገድ አሁንም መቀጠል ይገባናል? ወይስ የእኛ የረጅም ጊዜ ዕቅድ ውስጥ የተካተተ ባይሆንም ከሌሎች ቡድኖች በሚደርሱብን ምክንያት አጸፋ መመለሳችንን እንቀጥል? መፍትሄ ፍለጋ አውቀንም ይሁን ሳናውቅ ከመንገድ ወጥተናል? ከወጣንስ እንዴት መመለስ እንችላለን? ካልወጣን ያለምነውን ከግብ ማድረስ ለምን ተሳነን? ለችግራችን መፍትሄ እንዳናገኝ የሳትነው የት ላይ ነው?

በቅድሚያ ማወቅ የሚገባን ከዱሮ ዓመሎችንና ልምምዶችን መላቀቅ ቀላል እንደሆነ አቃልለን መመልከት የለብንም፡፡ ስለሆነም ኢትዮጵያ የእኛ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ዜጎች መብቶችና እሴቶች ክብርና እውቅና የምትሰጥ አገር እንድትሆን ካስፈለገ በመጀመሪያ ወደ ራሳችን መመልከት ይገባናል፡፡ አሁንም እየተከተልን ካለውና ካለፈው ታሪካችን ውስጥ መልካምና መጥፎ የምንላቸው የትኞቹ ናቸው? መልካም የምንላቸውን ለወደፊቱ እየጠበቅን በክፉ የተጠናወቱንን መጥፎ ባህሎችና አስተሳሰቦች እንዴት ነው የምናስወግደው? እነዚህ እያንዳንዳችን ራሳችንን ልንጠይቅ የሚገቡ ጥያቄዎች ናቸው፡፡

ዛሬና በቀጣይ ባሉት ሳምንታት፣ ወራትና ዓመታት የምናደርጋቸው ውሳኔዎች የአገራችንን የወደፊት ዕጣ ይወስናሉ፡፡ ነገር ግን አንዳንዶቻችን የምንታገለው ከመደናገጥ፣ ተስፋ ከመቁረጥ ወይም በሁኔታዎች ግፊት በመነሳሳት ነው፡፡ የዚያኑ ያህል ደግሞ በዚህ ባለንበት አገር ያለው የኑሮ ሁኔታ ወጥሮ ሲይዘን ከትግል ሃሳባችን እንደናቀፋለን፤ ሆኖም እናንተ ስለ ወደፊቱ የአገራችንና የልጆቻን ሁኔታ ያሳሰባችሁ በመሆናችሁ እዚህ ተገኝታችኋል፤ ግድ ባላችሁማ ኖሮ እዚህ ባልተገኛችሁ ነበር፡፡

ስለዚህ የወቅቱ አንገብጋቢና ቀዳሚ ጉዳይ የሚያለያዩን ነገሮች እንዳሉ ሆነው ሁላችንንም ለሚመለከተው ችግራችን መፍትሄ ለማምጣትና ነጻ፣ እኩልነት የሰፈነባት፣ ዴሞክራሲዊት ኢትዮጵያን ለመመሥረት የምንችለው እንዴት ነው? የሚለው ነው፡፡ ይህንን ማድረግ ስንችል ብቻ ነው ለሁላችንም የሚበጅ የወደፊት ማኅበራዊ መዋቅር መገንባት የምንችለው፡፡ ሆኖም አንዳንዶች ይህ አስተሳሰብ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ የተከፋፈሉ አገራት የወደፊቱን በማለም ተግባራዊ ማድረግ ይቻል ይሆን እያሉ በአግራሞት ይጠይቃሉ?

በአንድ አነስተኛ ምሳሌ ልጀምር – ከራሳችን ማለትም ከእኔ እና እናንተ ልጀምር! በኢትዮጵያ ውስጥ ሁላችንም በበርካታ መንገዶች ልዩ መሆናችን ይጎላል፡፡ ነገር ግን ዛሬ እዚህ ስብሰባ ላይ ከእናንተ ኢትዮጵውያን ሙስሊም ወገኖቼ ጋር ለመነጋገር ስመጣ በውስጤ ታላቅ ቅርበት፣ ወዳጅነትና አብሮነት እየተሰማኝ መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡ ግን ቆም ብለን ካሰብነው ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? እንደኔ ዓይነት የቆዳው ቀለም የጠቆረ፣ በእምነቱ ክርስቲያን የሆነ፣ በሞቃታማዋ ጋምቤላ በወንዞች መካከል የተወለደ፣ ከትንሽ መንደር የመጣ፣ አኙዋክ ከተባለ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት 0.01 በመቶ የሆነ፣ የተረሳ፣ ከእናንተ የቆዳ ቀለማችሁ ፈገግ ካለ፣ ከደጋና በረሃማው የኢትዮጵያ ክልል – ከኦሮሚያ፣ ከአፋር፣ ከሶማሊና ከሌሎች ሥፍራዎች ከመጣችሁ ሙስሊም ወገኖቼ ጋር እንዴት ለመገናኘት ቻልኩ?

የሁላችንም ባህል እና አኗኗር የተለያየ ቢሆንም ዛሬ ግን በዚህ ቦታ ለእያንዳንዳችን የሚጠቅምና ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚበጅ አንድ ዓላማ ተሰባስበናል፡፡ ማናችንም ብንሆን ግን ይህንን መሰሉ ትግል ስንጀምር በዚህ መልኩ አልነበረም፤ በጊዜ ብዛት ግን ሁላችንም እየተማርን አሁን ካለንበት ደረጃ ላይ ደርሰናል፤ ልክ ነኝ አይደል?

የኔን ብነግራችሁ፤ የኔ ህይወት ፍጹም የተቀየረው ታህሳስ 3፤ 1996ዓም (December 13, 2003) በአኙዋክ ሕዝብ ላይ በደረሰው ጭፍጨፋ ምክንያት ነበር፡፡ ለሶስት ቀናት በተካሄደው ግድያ 424 የአኙዋክ መሪዎች በግፍ ተገደሉ፡፡ ግድያውን የፈጸሙት ህወሃት/ኢህአዴግ ያሰማራቸው ወታደሮች ከታጠቁ የደጋው ክፍል ሚሊሻዎች ጋር በመተባበር ነበር፡፡ የጭፍጨፋው ዋና ተልዕኮም የራሱን ዕድል በራሱ ለመወሰን ለፈለገው “የአኙዋክ ሕዝብ ትምህርት ለመስጠት” እንደሆነ በወቅቱ ተነግሯል፡፡

ሕገመንግሥት በተባለው ሰነድ ላይ ይህ መብት በግልጽ የሰፈረ ቢሆንም አኙዋክና ሌሎች የላይኛው ናይል ሸለቆ ወገኖች መሬት ከነዋሪዎቹ ጋር ምክክር ሳይደረግ ለምን ሃብታቸውና መሬታቸው ይወሰዳል ብሎ መጠየቅ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ በዚያን ወቅት ዋንኛው ምክንያት ነዳጅ ነበር፤ ሲቀጥል ደግሞ ለም ምድር፣ የውሃ ሃብትና ማዕድናትን መዝረፍ ሆነ፡፡ ይህ መሰሉ ድርጊት በመፈጸሙ ለልማት መንገድ ለመጥረግ በሚል 16ሺህ አኙዋኮች የመኖር ኅልውናቸው ስለተጠረገ በጎረቤት ኬኒያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ዑጋንዳ ተሰድደዋል፡፡

ከ1996ዓም በፊትም በአገራችን ላይ ኢፍትሃዊነትና የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ ይካሄድ ነበር፤ ሆኖም እውነቱን ለመናገር በዚህ ዓይነቱ ትግል ሳይሆን ጋምቤላን ለማልማት በሚል ደፋ ቀና ስል ነበር፡፡ ነገር ግን የአኙዋክ ሕዝብ በአስከፊው የህይወት መስመር ውስጥ በገባበት ጊዜ በጣም ጥቂት የሆኑ ለመርዳት እጃቸውን የዘረጉ መሆናቸውን በወቅቱ መመልከት የሚያም ክስተት ነበር፡፡ ይህ የሆነው ከምክንያቶቹ እንደ ዓቢይ ምሳሌነት ሊጠቀስ የሚገባው እኛ ከሌሎቹ ኢትዮጵውያን የተለየን በመሆናችን ነበር፡፡ እውነቱን ለመናገር እኛ ከጋምቤላ የመጣን ወይም የደቡብ ኦሞ ሸለቆ ተወላጆች የሆኑ “እንደ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ” የምንታይ ባለመሆናችን ነው፡፡

ትግሉ በብዙ መልኩ እየተካሄደ ከቆየ በኋላ አካሄዳችንን መመርመር አለብን በሚል አንድ ጥያቄ ለራሴ ማቅረብ ጀመርኩ፡- ይኸውም “የአኙዋክ ሕዝብ ለራሱ ብቻ ፍትህና ነጻነትን መጎናጸፍ ይችላል? የሚል ነበር፡፡ በሌላ አነጋገር እንደ ኦሮሞ ባሉ በሌሎች ላይ የሚደርሰውን በምንመለከትበት ጊዜ የሚሰማን ነው፡፡

በ1997ዓም በተደረገው ምርጫ እና ከዚያ ጋር ተያይዞ በተካሄደው ማጭበርበር 197 ዜጎች በአዲስ አበባ ሲገደሉ ክስተቱ ሁላችንንም ሊያስተባብረን የሚችል ዕድል ነበር፤ ሆኖም ሳንጠቀምበት ቀረን፡፡ በዚያን ወቅት ግን እኔ ጭንቅላት ውስጥ ይደውል የነበረው በዘር ላይ፤ ያውም ደግሞ በአናሳ የዘር ድርጅት፤ የተመረኮዘ ድርጅት አቋቁሞ ፍትህን ማምጣት የሚቻለው እንዴት ነው? የሚለው ጥያቄ ነበር፡፡ በወቅቱ የቅንጅት ፓርቲ የተነሳበት ዓላማ በብዙዎች ዘንድ ታላቅ ተስፋ ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም ሁኔታው ከከሸፈ ከሁለት ዓመታት በኋላ የህወሃት/ኢህዴግ ሠራዊት ከጋምቤላ ወደ ሶማሌ ክልል ሲንቀሳቀስ ድምጻቸውን ያሰሙ አልነበሩም፡፡ የህወሃት ገፈት ቀማሽ የሆንነው እኛ አኙዋኮች ግን ሠራዊቱ ለምን ክልላችን ጥሎ እንደሄደ መገመት አላቃተንም ነበር፡፡ በዚህም በአንዳንድ ዓለምአቀፍ መያዶች ዘንድ “ያልተነገረው ዳርፉር” ተብሎ የሚጠቀሰውን የኦጋዴንን ዕልቂት አስከተለ፡፡

በወቅቱ በአኙዋክ የፍትሕ ምክርቤት የነበርን ከኦጋዴን ወገኖቻችን ጋር ብዙም ግንኙነት ባይኖረንም ስለ ሶማሊ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ዕልቂት፣ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ፣ የመንደሮች መፍረስ፣ የመሰረታዊ ልማቶች መፍረስ እና ስደት ድምጻችንን ማሰማት እንዳለብን ግድ አለን፡፡ በዚህም ምክንያት ያኔ ነበር ከእነርሱ ጋር ግንኙነት የጀመርነው፡፡ አንድ እንድንሆን የሚያመጣን ነገር ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነው ለነጻነት፣ ለፍትሕና ለአገራችን ሕዝብ ብልጽግና ለመሥራት እንደሚችሉ ተስፋ የሚሰጠን ነው፡፡ ይህ ሆኖ ሳለ እኛ ኢትዮጵያውያን ትርጉም ሊሰጥና ገቢራዊ ለውጥ ሊመጣ በሚችል መልኩ መተባበር ያልቻልነው ለምን ይሆን?

እኔ እንደማምነው ከሆነ የዚህ መልስ እኛ ኢትዮጵያውያን ተቀብለን በተግባር ላይ ያዋልናቸው ነገርግን ተዓማኒነት የሌላቸው፣ የማይጠቅሙ፣ የማይሰሩና እውነተኛ ያልሆኑ አመለካከቶቻችን ናቸው፡፡ እነዚህ አስተሳሰቦች በዚህ ዘመን የማይሰሩ ብቻ ሳይሆኑ ለጋራ ስኬታችን እንቅፋት በመሆን ክሽፈትን ያስከተሉብን ናቸው ብዬ አምናለሁ፡፡ እነዚህ እንደገና መመርመር፣ መታየትና መጠናት የሚያስፈልጋቸው ሲሆኑ ስህተት የሆኑትንና የማይጠቅሙትን ሁሉ ልናሸንፋቸው ወይም ልናስወግዳቸው የሚገቡ ናቸው፡፡

ለጋራ ስኬታችን ዕንቅፋት የሆኑብን ምክንያቶች

ለጋራ ጥቅማችንና ስኬታችን ዕንቅፋት የሆኑብን ምክንያቶች የመጡት ከየት ነው? ብለን መጠየቅ መጀመሪያው ሲሆን እንዴት ከእነዚህ ዕንቅፋቶች አልፈን በከፍታዎች ላይ በመብረር የችግራችን ዋንኛ ምክንያቶች እንዳይሆኑ ማድረግ እንችላለን የሚለው በተጓዳኝ ሊጠየቅ ይገባዋል፡፡ በቅድሚያ ሊጠቀስ የሚገባው ዕንቅፋት ክሽፈት የተሞላበት አካሄዳችን ነው፡፡ በዘር፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ አመለካከት ላይ የተመረኮዘ የተናጠል ወቅታዊ ትግል የመጀመሪያ ዕንቅፋት ነው ብዬ መጥቀስ እፈልጋለሁ፡፡

  1. የተናጠል ወቅታዊ ትግሎች፡- ይህ ማለት በአንድ ወቅት የሚነሳና የሚከስም በዘር፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካዊ አመለካከት ወይም ከአንድ ቡድን የተገነጠለ አንጃ ሃሳብ ላይ ትኩረት ያደረገ በነጠላ ሃሳብ ላይ የተመሠረተ ትግል ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያውያን ትልቁ ችግር፤ ነጻነት፣ ፍትህና ለህዝባችን ሙሉ ዴሞክራሲ እንዳያገኝ ዕንቅፋት ሆኖ ከፊታችን የተጋረጠው ነገር ሁሉን አሳታፊ ዘላቂ ትግል ከማድረግ ይልቅ የተናጠል ወቅታዊ ትግል ማድረግ ነው፡፡ ይህ በነጠላ እየተነሳን የምናደርገው ትግል በጣም የምንወደውና የተዋሃደን የትግል ስትራቴጂ ቢሆንም በታሪካችን በተደጋጋሚ የተረዳነው ግን ይህ አቀራረብና አካሄድ ፈጽሞ እንደማይሰራ ነው፡፡

የተናጠል ወቅታዊ ትግል በምናካሂድበት ጊዜ ዋንኛ ዓላማችን “የወቅቱን ፍላጎታችን” ማሳካት ነው፡፡ ይህንን እንድናደርግ የሚነሳሳን ደግሞ በወቅቱ የተከሰተ ግድያ፣ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ፣ ኢፍትሃዊነት፣ መሬት ነጠቃ፣ ወይም ተመሳሳይ በህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ወይም በፊት በነበሩት አገዛዞች ባደረሱት ጭቆና የሚጭረው ቅሬታ፣ ብስጭትና ንዴት ነው፡፡ ለእነዚህ ዓይነቶች ኢፍትሃዊ ተግባራት ምላሽ ስንሰጥ ሥራችንን የምናከናውነው ሌሎችን ሳንጋብዝ ወይም ሌሎች ከእኛ ጋር ሳይተባበሩ በተናጠል ነው፡፡ በመሆኑም የራሳችንን ሰልፎች፣ የራሳችንን የተቃውሞ ጥሪዎች፣ የራሳችንን ውይይቶች፣ የራሳችንን አቤቱታዎች (ፔቲሽን)፣ … በማቅረብ የራሳችንን ውሳኔዎች አሳልፈን ባላጋራችንን ለመታገል እንነሳና በራሳችን ችግር ላይ ራሳችን ጠላት ሆነን ክሽፈታችንን እንጋብዛለን፡፡

ከዚህ በፊት የተካሄዱና በዚህ ምድብ ውስጥ የሚገቡ፤ ህወሃት/ኢህአዴግ ከአነሳሱ ጀምሮ እየነጠለ ጥቃት ሲያደረገባቸው በመቆየቱ የተነሳ የራሳቸውን የተናጠል ትግል ያደረጉ እጅግ በርካታዎችን መጥቀስ ይችላል፡፡ እነዚህ በተናጠል ከተካሄዱ ወቅታዊ ትግሎች መካከል የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ፣ የሲዳማ፣ የአኙዋክ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ የአፋር፣ የሶማሊ፣ የሙስሊም፣ የክርስቲያን፣ አሁን ደግሞ የኦሮሞ ተቃውሞ፣ የአማራ ተጋድሎ፣ እያለ መዘርዝሩ ይቀጥላል፡፡ እኛ ስንጠቃ ሌሎች ከእኛ ጋር አለማበራቸውንና ድጋፍ አለማሳየታቸውን ስንመለከት እንናደዳለን፣ ተስፋ እንቆርጣለን፡፡ በመሆኑም እኛም ሆንን ሌሎች ለብቻችን ተጉዘን ስኬትን ማግኘት እጅግ አስቸጋሪ ወይም የማይቻል መሆኑ እንረዳለን፡፡ በሌላ በኩል ይህ ስሜት ሌሎች ከእኛ ጋር ለመተባበር አለመፈለጋቸው ንዴት፣ መራርነትና ጥርጣሬ ውስጥ ይከትተንና ሌሎች ስለ እኛ ግድ የላቸውም ወደሚል ድምዳሜ ላይ እንድንደርስ በማድረግ የበለጠ መራርነት፣ ቂም፣ ቅሬታ፣ ቅያሜ፣ ጥርጣሬ፣ ራስን ማግለል፣ ባይተዋርነት፣ ከዚያም አልፎ “አይፈልጉንም፤ አንፈልጋቸውም” ወደሚል ጥልቅና መራር ስሜት ውስጥ ያስገባናል፡፡

  1. ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ሊጠቅም የማይችል የትግል ስልት በተደጋጋሚ የምንከተለው ለምንድን ይሆን?

ሀ. ታሪካዊ ምክንያት፡- የተለያዩ እርስበርሳቸው የተቆራኙና ሥር የሰደዱ ሁሉን አቀፍ ከሆኑ መብቶች ጋር የሚጋጩ አመለካከቶች፡፡ እነዚህም፤

  • ጎጠኝነት – አንድን ጎሣ ወይም ጎጥ ከፍ በማድረግ “አንዱ ጎሣ/ጎጥ ሁሉንም ነገር ለራሱ ማድረግ አለበት” ወይም “የመብላት ተራው የእኛ ነው” በሚል ከፋፋይነት ላይ የተመሠረተ ነው። ይህ ላለፉት አርባ ዓመታት ስናየው የኖርነው ሃቅ ሲሆን ለራሴ ጎጥ፣ መንደር፣ እና/ወይም ቤተሰብ እኔ ካልቆምኩለት ማን ይቆምለታል? የሚል አስተሳሰብና ራስንና “የራሴ” ብለን የምንጠራቸውን ለማዳን የተመሠረተ አሠራር በዚህ ውስጥ ይካተታል፡፡
    • አጸፋ/ብድር መመለስ፡- አንዱ ጎጥ ወይም ጎሣ በሌላው ላይ ብድሩን መመለስ፤ የራሴ ለሚባሉ ወገኖች፣ ለቅርብ ወዳጆች፣ ለታማኞች፣ በማድላት ጥቅማጥቅሞችን በወገንተኝነት በመነሳሳት መፈጸም የጎጠኝነት አመለካከት ነው፡፡
  • ዘውዳዊ – በዘውዳዊ አገዛዝ ሥር የነበረው የኢትዮጵያ ታሪክ በዘር፣ በቤተሰብ ትስስር፣ በደም፣ “በእገሌ ልጅነት”፣ ወይም ለመሣፍንትና ለመኳንንት ታማኝ በመሆን የተመሠረተ ነበር፡፡ ይህ ስሜት አሁን ከሞላ ጎደል መልኩን እየቀያየረ ሲንጸባረቅ ይስተዋላል፡፡
  • ፊውዳላዊነት – አንድን ቡድን ወይም ጎሣ ወይም ወገን ከሌላው የተለየ፣ የተሻለ፣ የተመረጠ፣ የበቃ፣ ወይም “ስዩመ” ስለሆነ የመግዛት/የመምራት መብት አለው፤ “ወርቃማ ዘር” ስለሆነ ትርፉንም ለራሱ የማድረግ ሥልጣን ተሰጥቶታል፤ ሌሎች ዕድለቢሶች በሥሩ የመሆን ግዴታ አለባቸው የሚል ነው። ይህ ዓይነት አስተሳሰብ የለም ብሎ የሚከራከር ሊኖር ቢችልም እውነታው ግን የፖለቲካ ሥልጣን ወይም ከሕዝብ የሚነጭ ሥልጣን ምንነትን ባልተለማመደችው አገራችን አሁንም እየታየ ያለ አስተሳሰብ ነው፡፡
  • ማርክሲስት-ሌኒንስት ኮሙኒዝም – የሚቃወሙትን ሁሉ የመርገጥ ባህርይ ያለው ሲሆን ከፊውዳላዊነት በተለየ መልኩ ማርክሲስታዊ አስተሳሰብ “ሰፊውን ሕዝብ” እየጠቀምኩ ነው ቢልም በተግባር ግን “በጭቁኑ ሕዝብ” ስም የራሱን ሥልጣን ማመቻቸት ነው፡፡ ይህ በተለምዶ “የግራው አመለካከት” እየተባለ የሚጠራው በ1960ዎቹ የአገራችንን ወጣቶች የተጣባ ርዕዮት ነው፡፡ በዚህ አመለካከት ውስጥ ለአንዱ መኖር የሌላው መጥፋት የግድ ነው የሚል ጽንፈኛ አመለካከት እንደ ሃይማኖት የሚወሰድ ነው፡፡ ደርግ “በጠላቶቻችን መቃብር ላይ …” ይል እንደነበረው አሁንም ይህ አባባል በግልጽ ሲነገር ባይሰማም በድርጊት “ለእኔ መኖር ያንተ መጥፋት የግድ ነው” የሚለው የከረረ የግራ አስተሳሰብ በሁሉም መስክ ሲንጸባረቅ ይታል፡፡
  • ሥልጣን የማግኛው መንገድ ይኼው ነው – ከሌሎች በመንጠቅ ሥልጣንን የራስ የማድረግ አካሄድ ነው፡፡ በታሪክ እንደታየው ሥልጣን ለማግኘት በተናጠል በሚደረግ ትግል አንዱን የዘር/የጎሣ ቡድን በሌሎች ላይ እንዲነግሥ በማድረግ ሌሎችን የበዪ ተመልካች ማድረግ ነው፡፡ የህወሃት/ኢህአዴግ የሥልጣን አወጣጥ ይህንን ስልት ከሌሎቹ ስልቶች ጋር ያጣመረ ሲሆን በወቅቱ የሚካሄዱት የተናጠል ትግሎችም ወደዚሁ የሚመሩ ናቸው፡፡
  • ከእናንተ ይልቅ እኛ ጭቆናን ታግለን ለድል የበቃን ስለሆነ ሥልጣን የመያዝና በሥልጣን የመቆየት እንዲሁም ምርኮን በመበዝበዝ ተጠቃሚ የመሆን ተራው የእኛ ነው፤ ይገባናል የሚል አመለካከትና አሠራር፡፡ ህወሃት የዚህ ሁነኛ ተጠቃሽ ነው፡፡ ደርግን ለመጣል ምንም እንኳን ሌሎችም አብረዋቸው የተዋጉ ቢሆንም በራሳቸው ብቃትና በብረት ሥልጣን ላይ እንደመጡ አሁንም በብረት ኃይል ሥልጣን ላይ የመቀጠል ጥማት በግልጽ ይታባቸዋል፡፡ ሥልጣን ከፈለግህ እንደ እኛ ተዋግተህ የራስህ ማድረግ ነው የሚል አስተሳሰብ በዚህ ውስጥ የሚካተት ነው፡፡

ለ. አለመተማመን፡ የራስን ዓላማ በሚፈልጉት መንገድ እያስፋፉ ሌሎችን ግን በጥርጣሬ መመልከት፤

  • በዘር ላይ በመመርኮዝ ሥልጣንን የመያዝ አባዜ፣ ክህደት፣ ክፍፍል፣ ጥቃት፣ ጉዳት፣ ቁስል፣ ክሽፈት፣ የቆዩ ቅሬታዎች ኢትዮጵያውያንን ሲከፋፍላቸው የኖረ ከመሆን አልፎ ተገቢው ቅጣት ካልተበየነ ወይም ሃብትና የዕድሉ ተጠቃሚነት ወደ እኛ ካልዞረ እነዚህ ቁርሾዎች ዕልባት ሊያገኙ አይችሉም የሚል አስተሳሰብ፤
  • አንድን መሪ፣ ወይም አንድን ጎሣ፣ ዘር ወይም ቡድን ለመጥቀም የሚደረገው አሠራር አብሮ የመሥራትንና የመተባበርን ጥረቶች ሲያመክን መቆየቱ፤ ከህወሃት/ኢህአዴግ አሠራር ያልተለየ አዲስ መሪ የሚያመጣ ነገር ግን ለውጥ አልባ አካሄድ፤
  • በኢትዮጵያውያን ዘንድ ያለው የድብቅነት፣ ምሥጢራዊነት፣ ተንኮለኝነት፣ መጠላለፍ፣ የሚናገሩትና የሚያደርጉት የመለያየት፣ የአስመሳይነት፣ የማታለልና የግብዝነት ባህርያት ግልጽነትን፣ መተማመንና ተጠያቂነት ያሳጣን በመሆኑ፤
  • በአንዳንዶች ዘንድ በግል ወይም በቡድን በሚደረጉ ትግሎች ሥልጣን የመያዝ ድብቅ ምኞቶች መኖራቸው፤ ይህም ማለት “ምንም ችግር የለም አብረን እንሥራ” በሚል አብሮ ቆይቶ በኋላ ሥልጣን ላይ የመቆናጠጥ ድብቅ ዓላማ የማስፈጸም ሁኔታ፤
  • ሌሎችን የማሳተፍ እና ወደ እነርሱ የመድረስ ፍላጎት አለመኖር፤ የመከፋፈል፣ የመለያየት፣ የማግለል፣ የመገለል እና ከሌሎች ጋር ለመነጋገር አለመፈለግ፤
  • በተቀናጀ ዓላማ፣ መርህ፣ አመራርና አጀንዳ ለመመራት አለመፈለግ፤
  • ከማንም ጋር ቢሆን አብሮ ለመሥራት ያለመፈለግና ይህንንም በጠነከረ ሁኔታ መቃወም፤ ምክንያቱም አብሮ በመሆን ሰበብ ሌላውን ለሥልጣን የማብቃት ፍርሃቻ ውስጥ መግባት፤ ወይም እኔ በታገልኩት አንተ ሥልጣን ልትይዝ የሚል አስተሳሰብ፤
  • ተመቻችቶ ከተቀመጡበት የራስ ቡድን በመውጣት ከሌሎች ጋር መሥራት ከራስ ቡድን የመገለልና የመባረር አደጋ ውስጥ የሚያስገባ በመሆኑ፤
  • ሌሎች የሚፈልጉን ለራሳቸው ዓላማ ማሳኪያ “ሊጠቀሙብን ነው” የሚል አስተሳሰብ በመያዝ በቀጣይ በእነርሱ መዳፍ ሥር በመውደቅ ለችግር እንዳረጋለን የሚል ፍርሃቻ ከዝርዝሮቹ ውስጥ በዋንኝነት የሚጠቀሱት ናቸው፡፡

ሐ. በቅድሚያ ሰብዓዊ ፍጡር ተብሎ ከመጠራት ይልቅ “የዘር/የጎሣ” መለያን እንደማንነት መታወቂያ አድርጎ ላለመተው ማንገራገር፤ የዚህ ምክንያቶች፡-

  • ከተለያዩ በርካታ ቡድኖች ድጋፍ ከማሰባሰብ ይልቅ የራሴ ከምንለው ጎሣ ወይም ቡድን የምንፈልገውን ድጋፍ ለማግኘት ቀላል በመሆኑና በተለይም ለዚህ ቡድን ልዩ መብትና ሥልጣን ለማስገኘት የምንታገል መሆናችንን በመግለጽ ተስፋ የሰጠን ከሆነ፤
  • ከቡድኑ ወይም ከጎሣው ስብስብ ውጪ የሚሆኑትን ወይም የተለየ ሃሳብ የሚይዙትን እንደ ከሃዲ በመቁጠር ማግለልና ማዋረድ ስለሚቀል፤
  • ከታሪክ አኳያ በዘር ላይ የተመሠረተ ነፍጥ የማንሳት (የአርነት ንቅናቄ) ትግልን ለመቀላቀል/ለማድረግ ቀላል በመሆኑ፤
  • ከኅብረብሔራዊ ይልቅ በጎሣ ወይም በዘር ላይ በተመረኮዘ አጀንዳ ሥር ሰዎችን ማሰባሰብ የሚቀል በመሆኑ፤
  • ኅብረብሔራዊ ከሆነው ይልቅ የራሴ በሚሉት ቡድን ተቀባይነት ለማግኘት የማይከብድ በመሆኑ፤ ቡድኑን በሚፈልጉት አቅጣጫ ለመንዳት ስለሚቀልና የመርህ ጥያቄ ስለማያስነሳ፤
  • የቀድሞ ያልተፈወሱ ቁስሎች መገለልን በመፍጠራቸው የባይተዋርነት ወይም የብቸኝነትን ሠንሠለት ለመስበር አስቸጋሪ ማድረጋቸው ከብዙ በጥቂቱ የሚጠቀሱ ምክንያቶች ናቸው፡፡

መ. በቅሬታ ወይም በክስተቶች የሚመራ ትግል ጥልቅ መሠረት ከሌለው አይዘልቅም፤

  • በአንድ ወቅት የሚፈጸም ኢፍትሓዊነት፣ ግድያ ወይም አሠቃቂ ተግባር የአጸፋ ምላሽ እንድንሰጥ የሚያስተባብረን ቢሆንም ውሱን የተናጠል ወቅታዊ ትግል ከማካሄድ ሌላ ለዘላቂ ትግል ፋይዳ የሌለው መሆኑ፤ ይህ ዓይነቱ ቅሬታ ላይ ያተኮረ ትግል በአንድ ጎሣ፣ ዘር፣ ሃይማኖት፣ ክልል፣ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው የተሰባሰቡበት በመሆኑ ለዚህ ቡድን ጥቅም ብቻ የሚሆን ምላሽ ከመስጠት ያለፈ ተግባር ለመፈጸም አለመቻሉ፤
  • በስሜት የሚነዳ መሆኑ፤ ይህም ደግሞ በአንድ ወቅት የሚነሳሳውን ስሜት ለረጅም ጊዜ ብርታት ኖሮት ለማስቀጠል የሚቻል ባለመሆኑ፤
  • እነዚህ በስሜት የሚነሳሱ ትግሎች ሌሎችን ወይም አብዛኛዎችን የሚያነሳሱ ባለመሆናቸው ወይም ሌሎችን በማዕቀፉ የሚይዝ ባለመሆኑ “የኔ ትግል አይደለም” ወይም “ለኔ ምን ይረባኛል?” ወይም “ለኔ ምን ፋይዳ አለው?” የሚሉ አስተሳሰቦችንና አመለካከቶችን በሌሎች ላይ የሚያመጣ በመሆኑ፤ ይህም ደግሞ እነዚህ ትግሉን ያልደገፉ ጥቃት በሚደርስባቸው ጊዜ በተራው “እኛ ስንሰቃይ ስላልረዳችሁን እኛ ስለእናንተ አያገባንም የሚል” አጸፋዊ ምላሽ የሚያስከትል በመሆኑ በዚህ ሥር ከሚጠቀሱት በርካታ ምክንያቶች የተወሰኑት ናቸው፡፡

እነዚህን መሰናክሎች ማሸነፍ የምንችለው እንዴት ነው?

ከላይ ከተጠቀሱት መሰናክሎች አኳያ እነዚህ እንቅፋት የሆኑብንን የታሪክ፣ ያለፉ ቅሬታዎችን፣ የግልና የጎሣ ግጭቶችና ምኞቶች አሸንፈን ይህንን የሽንፈት ዑደት ሰብረን የምንወጣው እንዴት ነው? የሚለው መጠየቅ ያለበት ጥያቄ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ በአገራችን ከምንጊዜውም በላይ የከፋ አደጋ ተጋርጦብናል፤ ታዲያ ምን ማድረግ ነው የሚሻለን?

  1. የተለያዩ ሰዎችን የተካተቱበት ሁሉን አሳታፊ ዘላቂ ትግል መፍጠር፤

ሀ. ሁሉን አሳታፊ ዘላቂ ትግል እንደ ባህል በህዝብ ውስጥ እንዲሰርጽ ማደፋፈር፤

  • ትግሉ የሰው ልጆችን ሕይወት፣ መብቶች እና የሁሉንም ኢትዮጵያውያን ማንነት በሚያከብር መልኩ በመርህ ላይ መመሥረት፤
  • ትግል ማለት መቃወም ብቻ አይደለም፤ ትክክለኛው ትግል ሁሉንም ኢትዮጵውያንንም የሚጠቅም መሆን መቻል አለበት – ይህ ደግሞ ተሳስተዋል የምንላቸውንም የሚጨምር ነው፤
  • እንደ አገር ችግራችን የተጀመረው ህወሃት/ኢህአዴግ በ1983 ወደ ሥልጣን ሲመጣ አይደለም፤ ወደኋላ መለስ ብለን የቀደመውን ሥርዓታችንን፣ አንዳችን በሌላችን ላይ ያለንን አመለካከታችንን፣ ወዘተ ማጥናት ያስፈልገናል፤ ይህንን በማድረግ ሌሎችን በዘር፣ በጎሣ፣ በአመለካከት፣ በሃይማኖት፣ በቆዳ ቀለም፣ በፊት መልክ፣ በቋንቋ፣ በባህል፣ ወዘተ ሳንከፋፍል ለሁሉም የሚበጅ የፍትሕ ሥርዓት፣ እኩል መብቶችና የኢኮኖሚ ጥቅማጥቅሞች፣ ነጻነትና አክብሮት ለመሥጠት የሚያስችል ሥርዓት ለመመሥረት ያስችለናል፤
  • ለሥልጣን እና የራሳችንን ልዩ መብት ለማስከበር የምናደርገው የተናጠል ወቅታዊ ትግል ጊዜውን ጠብቆ የሚከሽፍ ነው፡፡ ከላይ ለማስረዳት እንደሞከርኩት እኔ ራሴ የነበርኩበት የአኙዋክ ትግል የተናጠል ወቅታዊ የነበረ በመሆኑ ከእኛ አካባቢ ያሉት ሌሎች ነጻነታቸውን ሳይጎናጸፉ በአኙዋክ ትግል መቼም ቢሆን ነጻነትን መጎናጸፍ እንደማይቻል ግልጽ ነበር፡፡ አሁንም ያለው ሁኔታ ይኸው ነው – በተናጠል የሚደረግ ወቅታዊ ትግል የታሰበበት ለመድረስ ራሱ ችግር ውስጥ የሚከት በመሆኑ፡፡
  • የምንፈልገውን ለውጥ ሆነን መገኘት ይገባናል፡፡ ይህ ከአሁኑ የሚጀምር እንጂ ሥልጣን ላይ ተኹኖ የሚታሰብ አይደለም፡፡ ስለሆነም ለምንሻው ለውጥ ከአሁኑ ኃላፊነት ልንወስድ ይገባናል፡፡
  • ከሌሎች አገራት መማር ያስፈልገናል፤ ከሶማሊያ፣ ከሊቢያ፣ ከሶሪያ፣ ወዘተ፤ የሚገባንን ትምህርት ልናገኝና ለአገራችን በተግባር ልናውለው ያስፈልጋል፤ የእነዚህ አገራት ዜጎች ተሰባስበው ለሕዝባቸው የሚጠቅምና ሁሉንም የሚሳትፍ የላቀ አጀንዳ ይዘው በመነሳት ተግባራዊ ማድረግ ተስኗቸው የራሳቸውን ከፋፋይ ሃሳቦችና ዓላማዎች ለመተግበር በመወጠን ለአገራቸው መፍረስ ከሆኑ ምክንያቶች አንዱ ሆነው ይጠቀሳሉ፤
  • “ሌሎችም” ይገባቸዋል የሚል አስተሳሰብ በግልጽ ልናስቀምጥ ይገባናል፤ ባለፉት ጊዜያት ባብዛኛው ያለው አመለካከት የአንድን ቡድን ዓላማ ወደፊት በማድረግ አገሬን እወዳለሁ በሚል ማስመሰያ የሌሎችን መብቶች በመርገጥ የራስን ቡድን ብቻ ማበልጸግና ከፍ ማድረግ በተደጋጋሚ የከሰረና የማይሰራ መሆኑን መገንዘብ በውል ያስፈልጋል፡፡

ለ. እነዚህን የላቁ መርኾዎች የሚያስተዋውቁ ፖለቲካዊ ያልሆኑ ተቋማት ሊፈጠሩ ይገባል፤

  • ፈጣሪ ለእኛም ሆነ በቅርብና በሩቅ ለሚገኙት ወገኖቻችን የሰብዓዊነትን ክብር ሰጥቶናል፤ ይህንን ተጠቅመን በተሻለ አመለካከት ለሕዝባችን የሚረባውን ልናደርግለት ያስፈልጋል፤
  • በፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በዘር፣ በአርነት ንቅናቄዎች፣ በሃይማኖት ድርጅቶች፣ በክልል፣ እና በሌሎች ቡድኖች የተደራጁ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚሠራ ዓላማ፣ ግብና መርኽ ሊኖራቸው ይገባል፤
  • እነዚህን መርኾዎች በሲቪክ ድርጅቶች አማካኝነት እንዴት መጠናከር እንዳለባቸው፤ ወደፊት ሊመጣ ስላለው ችግር ካሁኑ እንዴት እነዚህን መርኾዎች ማቀናበር እንደሚገባ እንዲሁም ይህንን በማድረግ በኢትዮጵያ ላይ ሊመጣ ካለው መከራ እንዴት መጠበቅ እንደሚቻል ሊመክሩበት ይገባል፤
  • እነዚህን ሁሉ በቅንብር በማካሄድ የአገራችንን የወደፊት ዕጣ እንዴት በሰላማዊ ሽግግር ለማምጣት እንደሚቻል እነዚህ ቡድኖች ሊመክሩበት የሚገባ ነው፤
  • ሁሉንም የምታስተናግድና ለሁሉም የምትሆን ኢትዮጵያ እንዴት መመሥረት እንደሚቻል በማጥናት በአገራችን ላይ ውድመትና ጥፋት እንዳይመጣ እንዴት መከላከል እንደሚቻል አስቀድሞ ሊሰራበት የሚገባ ተግባር ነው፤ ይህንንም ለመተግበር ሁሉን ዓቀፍ የሆነ ጠንካራ ተቋም – የኢትዮጵያ ጉዳዮች ተቋም (ኢጉተ) – የሚባል ካሁኑ ልንመሠርት እንችላለን (ወደፊት እንዳስፈላጊነቱ የሚቀየር ስም ነው፤ እኔ የራሴን ስም ነው የሰጠሁት)
  • ተቋም ማቋቋም እና በዚያ መስክ የተቀናጀ ሥራ መሥራት ከሚለው አኳያ የጋራ ንቅናቄያችን በቅርቡ የኢትዮጵያ የዕርቅና ርትዓዊ ፍትሕ ምክርቤት የሚባል ተቋም መሥርቷል፡፡

ሐ. በሽግግር ወቅት ተቋማት ሊኖራቸው ስለሚገባ ባህርያት፤

  • ለነጻነት፣ ለፍትሕ፣ ለደኅንነት፣ ለመብቶች መከበር እና ሁሉም ኢትዮጵያዊ – ትግሬዎችንም ጨምሮ – በሁሉም ክልል በሰላም በሚኖርበት ሁኔታ ላይ መሥራት፤
  • የአገር ውስጥ ልዕልና እንዲከበርና ይህም በመርህ ላይ የተመሠረተ እንዲሆን በማድረግ መበታተንና መከፋፈል እንዳይኖር ማድረግ፤
  • ለሁሉም ሰው ደኅንነት መሥጠት – የሁሉም ሰው ህይወት እንዲከበርና በማንም ሰው ላይ አንዳች አደጋ ወይም ጉዳት እንዲደርስ አለመፍቀድ፤ ይህ ደግሞ በተለይ በዘር ላይ የተመረኮዘ አደጋና ደም መፋሰስ እንዳይኖር ማድረግን ይጠቀልላል፤
  • በሽግግሩ ወቅት ለኢፍትሃዊነት ማብቂያ ማድረግ፤ የሕግ የበላይነትን ማክበር፤ ይህንንም በማድረግ ትርጉም ያለው ተሃድሶ እንዲመጣ ማድረግና ይህም ደግሞ አድልዖ በሌለበት መልኩ ርትዓዊ ፍትህ በዕርቅ እንዲመጣ መሥራት፤
  • ጠንካራ እና ገለልተኛ ድርጅቶች የሚኖሩ ከሆነ አገሪቱን ከመፈራረስ የሚታደጉ በመሆናቸው ብሶት ያለባቸው ወገኖች በግጭት፣ በዓመጽ ወይም በሌላ አገር ጠለላ በማግኘት መፍትሄ ከሚሹ ይልቅ በሰላማዊ መንገድ መፍትሔ የሚገኝበትን መንገድ መፈለግ፤ ማመቻቸት፤
  • በአገሪቷ ውስጥ በተንሰራፋው ሥር የሰደደ ጥላቻ ምክንያት ፍትሕ እንዳይጓደል ተቋማት መብቶች እንዲከበሩ እና የሕዝቡ ልዕልና እንዲከበር የማድረግ ሚና እንዲጫወቱ፤

በቅርባችን ያለችውን ሊቢያ ብንመለከት በተቃዋሚነት የተነሱት ኃይላት ለሕዝባቸው የሚጠቅም በመርህ ላይ የተመሠረተ ራዕይ ሊኖራቸው ባለመቻሉ፤ ለሁሉም የሚቆም ተቋም ባለመመሥረቱ አገራቸው ከሸፈች፡፡ በሶሪያም ዜጎች በትናንሽ ቡድኖች በመከፋፈላቸውና የጋራ ዓላማና ራዕይ ሳይኖራቸው በመቅረቱ በሚያሳዝን ሁኔታ አገራቸው ክፍቷን እየቀረች ነው፡፡

የኢትዮጵያ የዕርቅና ርትዓዊ ፍትህ ምክርቤትን ማቋቋም ለምን አስፈለገ?

በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲኖርና የወደፊቱ የአገራችን ሁኔታ ተስፋ ያለው እንዲሆን አንዱና ብቸኛ አማራጭ ዕርቅና ርትዓዊ ፍትሕ ማስፈን ስንችል ነው፡፡ ይህ ማለት ያለፉትን፣ አሁን ያሉትን እና ወደፊት ሊነሱ የሚችሉትን የበርካታ ዓመታት ጥርቅም ብሶቶች የምናመክንበትና ትርጉም ያለው ተሃድሶ ማድረግንም የሚጨምር ነው፡፡ ላለፉት መቶዎች ዓመታት እርስበርስ በተፈጠሩት ቁርቋሶዎች፣ ስህተቶች፣ በደሎች፣ … የተከሰተው የኅሊና ወቀሳ፣ ሃዘን፣ ቁስል፣ ህመም፣ መራርነት፣ … ይህንን ተከትሎ በማያቋርጥ አዙሪት ውስጥ እንድንገባ ያደረገንን ያለፈውን ህመማችን ሁሉ ወደ ዕርቅና ፈውስ መምጣት አለበት፡፡ እጅግ አሰቃቂ ነገሮች የደረሱብን ነን፤ በዚህም ምክንያት በአንድ ወቅት አሳዳጅ የነበረው ጊዜ ጠብቆ ተሳዳጅ ይሆናል፤ ይህ የማያቋርጥ የበዳይና የተበዳይ ዑደት አልለቅ ብሎን ዘመናትን አስቆጥረናል፡፡

ከዚህ ግን መውጣት የምንችልበት አማራጭ መንገድ አለ፡፡ በአገራችን የሕግ የበላይነትን ተለማምደን የምናውቅበት ዘመን ባለመኖሩ ብሶቶቻችን መፍትሔ ሳያገኙ እዚህ ደርሰናል፡፡ ባለፉት ዘመናት የተከሰቱትን እያንዳንዱን ስህተቶች ወደኋላ ሄዶ ለማስተካከል አይቻልም፤ ነገር ግን ለወደፊቱ ህይወታችን አዲስ ራዕይ ከፈጠርን ይህን ያለፈውን ታሪካችንን በአንድ ምዕራፍ ዘግተን የወደፊቱን በአንድነት መጓዝ እንችላለን፡፡ ይህንን እናደርጋለን የምንል ከሆነ ያለፈው ታሪካችን አስተማሪያችን ሊሆነን ይገባል እንጂ የወደፊቱን የሚወስንልን አድርገን በመውሰድ በመንገዳችን ላይ ዕንቅፋት አድርገን ፍትሕ፣ የሕግ የበላይነትና የበለጸገች ኢትዮጵያን እንዳናይ ሊጋርደን አይገባም፡፡ እንግዲህ እነዚህ መሠረታዊ እሳቤዎች ከላይ በተጠቀሰው በምክርቤቱ ተልዕኮ ውስጥ የተካተቱ ናቸው፡፡

የተናጠል ትግል የሚያደርጉ ግፍን በሚታገሉ ጊዜ የራሳቸውን የአርነት ንቅናቄ መፍጠር አማራጭ ያለው መፍትሄ አድርገው ይወስዳሉ፡፡ በ1960ዎቹ የተጀመረው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ የሁሉንም ኢትዮጵያውያን ጥያቄ መልስ ማስገኘት ቀዳሚ ዓላማው አድርጎ መቀጠል ነበረበት፡፡ ይህ ግን ሳይሆን ቀረ፡፡ ከዚያ ኪሣራ በኋላ ያየነው ነገር ቢኖር በየቦታው የራስን ወገን ነጻ ለማውጣትና ከኢትዮጵያ ለመገንጠል በየክልሉ የተነሱ የአርነት ንቅናቄዎችን ነው፡፡ ሁሉም ለነጻነት እታገላለሁ በማለት የራሱን የአርነት ንቅናቄ ዓላማ ማስተጋባት ጀመረየኦሮሞ ነጻነት ግምባር (ኦነግ)፤ የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግምባር (ኦብነግ)፤ የቤንሻንጉል ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ቤሕነግ)፤ የጋምቤላ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ጋሕነግ)፤ የሲዳማ ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግምባር (ሲብነግ)፤ የአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲዊ አንድነት ግምባር (አርዱፍ) ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

መብቶችን መጣስ የሚያስከትለውን ውጤት ለመረዳት ከዚህ በላይ የተጠቀሱትንና ሌሎች ድርጅቶች ባህርይ ማጥናት ምላሽ የሚሰጥ ነው፡፡ ይህ ግን በራሱ ለችግሮች ዘላቂ ምላሽ የሚሰጥ ሳይሆን ይበልጡኑ ችግሮችን እያሰፋ የሚሄድና ስህተትን እየደገምን እንድንሄድ የሚያደርገን አካሄድ ነው፡፡ በሥልጣን ላይ የሚቀመጠው ማንም ይሁን ሥርዓቱን የሚገዳደር ጠንካራ ተቋም መመሥረት ነው እንጂ የሚያሻው ሌላ አካሄድ የሚፈይደው አንዳች ነገር የለም፡፡ አለመታደል ሆኖ ይህ አመለካከት አሁንም ህወሃትን እንታገላለን በሚሉ አንዳንዶች ዘንድ ያልተለወጠ አመለካከት ነው፡፡

ከሁለት ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ህወሃት/ኢህአዴግን በሃይማኖታቸው ውስጥ ጣልቃ መግባቱን ተቃውመው በሰላማዊ መንገድ መታገል ጀመሩ፡፡ እናንተ እዚህ ስብሰባ ላይ ያላችሁ እንደምታውቁት እናንተም ሆነ አገር ቤት ያሉት የታገሉት ለአንድ ቀን፣ ለአንድ ሳምንት፣ ለአንድ ወር ወይም ለአንድ ዓመት ሳይሆን አገዛዙ አመራሮቻችሁን ሰንጥቆ በመግባት ዓላማውን ለማሳካት እስከቻለበት ጊዜ ድረስ ለሁለት ዓመታት ነው የታገላችሁት፡፡ ብዙዎች እስርቤት ገቡ ከእነርሱም መካከል እስካሁን ያልተፈቱ አሉ፡፡ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ትግል ስኬት ሊያገን ያልቻለው ሌሎች በደል በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ የደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን – ኦሮሞዎች፣ አማራዎች፣ ሶማሊዎች፣ ወዘተ ትግሉን ሊቀላቀሉ ባለመቻላቸው ነው፡፡ ነገርግን በእናንተው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ውስጥ ከሁሉም ኢትዮጵያ ዘር፣ ጾታ፣ ዕድሜ ክልል፣ የቆዳ ቀለም፣ ክልል፣ ቋንቋ፣ በአንድ ጥላ ሥር የተሰባሰቡ ነበሩ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ይኸው ዓይነት ስብጥር በኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክስም ይሁን ፕሮቴስታንቶች መካከል አለ፡፡ ውጤቱ ግን እንደምናየው ሆነ!

አሁን አንድ ዓመት ሊሞላው የተቃረበው የኦሮሞ ትግል እየተካሄደ ነው፤ የአማራው ተጋድሎም እንዲሁ እየተቀጣጠለ ነው፡፡ ኢትዮጵያውን ሙስሊሞችም ሆኑ ኦሮሞዎች፣ አማራዎች፣ … የሚጠይቁት አንድ ትልቅ ጥያቄ ለውድቀት ሳንዳረግ ተባብረን መቆም የምንችለው እንዴት ነው? የሚለው ነው፡፡ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንዳየነው የዚህች አገር ችግር በተናጠል ትግል የሚፈታ አይደለም፡፡ ሁላችንም አብረን ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ መሆን አይችልም!

ትልቁ ጥያቄ – አሁን የምንታገለውን ሥርዓት ማፍረስ የምንፈልገው ይህንኑ በሚመስል ሌላ ሥርዓት ለመለወጥ ነው? በተናጠል ወቅታዊ ትግል የምናደርግ ከሆነ ውጤቱ ከዚህ የተለየ ሊሆን አይችልም፡፡ የአገራችንም ሁኔታ ባክኖ ይቀራል፡፡ መባከን ማለት አንድ ታላቅ ዋጋ ያለው ነገር እንደሚገባው ባለመጠቀማችን ምክንያት ዋጋው ከንቱ ሲሆንና ጥቅሙ ባክኖ ሲገኝ ነው፡፡ ይህ የእኛ ሁኔታ ሲሆን በተደጋጋሚ ታይቷል፡፡ ዓቅማችንና ዕድሎቻችንን በተደጋጋሚ ስናባክን ኖረናል፡፡

በኢትዮጵያ ያለን የተፈጥሮ፣ የውሃ፣ የማዕድናት፣ ወዘተ ሃብት ብቻ ሳይሆን የሰውም ሃብት ነው ያለን፡፡ በጋምቤላ ስላለው የሺያ ዛፍ ሳስብ ብዙ ነገር ወደ አእምሮዬ ይመጣል፡፡ ይህ ዛፍ እጅግ በርካታ ለሆኑ ጥቅሞች በዓለም ዙሪያ መዋል ሲችል አለአግባብ እየተጨፈጨፈ ይገኛል፡፡ ይህንን ደግሞ ለመተካት በርካታ ዓስርተ ዓመታትን ይወሰዳል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ እስቲ ስለ ወጣቶቻችን እናስብ፡፡ ስንቶቹ በድህነት፣ በዓመጽ፣ በመብት ገፈፋ፣ በህክምና ዕጦት፣ … ገና በጨቅላ ዕድሜቸው እየተቀጡ ይሆን?! ስንቶቹስ የህይወታቸውን መስመር ለማስተካከል ብለው እንደወጡ ቀርተዋል? ስንቶቹስ የአልጋ ቁራኛ ሆነዋል? እጅግ በጣም ብዙ! ስለዚህ ፈጣሪ የሰጠንን መርኾዎችን በመከተል ይህንን መከራ ማስቆም፤ አሁን ያለን ዕድል እንዳያመልጠን፤ እንዳይባክንብን አጥብቀን ልንሰራ ይገባናል፡፡

በታሪክ እንደምንመለከተው ኢትዮጵያውያን እርስበርሳቸው አንዱ የሌላው መጥፊያ ምክንያት ሲሆኑ አይታይም፡፡ እናንተ ሙስሊም ሆናችሁ እዚህ እኔ አንድ ክርስቲያን ለእናንተ እንድናገር ማድረጋችሁ ሁላችንም ለአገራችን የምንመኘውና እርስበርሳችን የምንካፈለው እሴቶች በመኖራቸው ነው፡፡ በእናንተ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እምነት ውስጥ ህወሃት/ኢህአዴግ ጣልቃ በመግባት ሰላማችሁን በነሳችሁ ጊዜ የጋራ ንቅናቄያችን በጉዳዩ ላይ በተደጋጋሚ የተናገረው ብዙ የምንገናኝባቸውና የተሳሰርንባቸው ምክንያቶች ስላሉ ነበር፡፡ ይህ አንድ መሠረታዊ ተግባር በመሆኑ ነው እናንተ ሙስሊሞችም በሰሜኑ የአገራችን ክፍሎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ገዳማት በወደሙበት ጊዜ ድርጊቱን ያወገዛችሁት በነጻ ማኅበረሰብ ውስጥ የሚኖር ሰው የሚያደርገውን ትክክለኛ ተግባር በመከተል ነው፡፡

አቅጣጫችንን ለመቀየር ከየትና እንዴት እንጀምር?

  1. በምንስማማባቸው ጉዳዮች ላይ የጋራ ራዕይ መቅረጽ፤ ስኬትን የምንሻ ከሆነ ለማግኘት የምንፈልገው ዋናው ነገር ምን እንደሆነ በቅድሚያ ልናውቅ ይገባናል፡፡ ይህንን ካስቀመጥን በኋላ አንድ የጋራ ራዕይ መቅረጽ ወደሚያስችለን ደረጃ ላይ እንደርሳለን፡፡ ይህ ራዕይ ሁላችንንም የራሴ ብለን በምንወስዳቸው እሴቶች ዙሪያ እና የሁሉንም ጥቅም ሊያስከብር በሚችል መሠረት ላይ ሊገነባ ይገባዋል፡፡ ወደ ሌሎች የተለያዩ አጀንዳዎች ከመገባቱ በፊት ይህ ራዕይ በቅድሚያ ተቀምጦ የሁሉንም አዎንታ ማግኘት አለበት፡፡
  • የጋራ ራዕይ፡ ማንኛውንም ችግር፣ ለዘመናት የተጠራቀመ ቅሬታ፣ አለመግባባት፣ … ለመፍታት ከመጀመራችን በፊት የጋራ ራዕይ በቅድሚያ ያስፈልገናል፡፡ የጋራ ራዕይ በስምምነት ከነደፍን በዚያ ላይ ተመርኩዘን ሁሉንም ችግሮች ወደ ስምምነት በሚያመጣ መልኩ መፍትሔ ልንሰጣቸው እንችላለን፡፡
  • ራዕያችን በስሜት ሳይሆን በመርህ ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት፤ ለምሳሌ አንዱ መርህ “ከጎሣ በፊት ሰብዓዊነት ይቅደም” የሚለው ሊሆን ይችላል፤ ወይም “ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም” በሚል መርህ ለሌሎች ነጻነት ግድ ማለት፡፡
  • ይህንን የጋራ ራዕይ ለመንደፍ በሁሉም ባለጉዳዮች ዘንድ ውይይት እንዲኖር ማድረግ፤ ሁሉንም የሚያካትት ራዕይ ለመቅረጽ እንዲቻል፣ ሁሉንም የሚጠቅም የፍትሕ ሥርዓት ለመዘርጋትና ነጻነት ለማምጣት የአገራችን ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሁሉ ተገናኝተው መወያየት፣ መነጋገር ይገባቸዋል፡፡
  1. በኢትዮጵያ ደም መፋሰስ እንዳከሰትና አገሪቷ እንዳትከፋፈል በኅብረት መሥራት፤
  • በህወሃት/ኢህአዴግ ውስጥ ያሉትንም ጨምሮ የማንም ኢትዮጵያዊ ህይወት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ከለላ ማድረግ፤ ቃል መግባት፡፡
  • የጋራ ራዕይ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ጠቅሞ በሰው ህይወት፣ በንብረት ወይም በማንኛውም መዋዕለንዋይ ላይ ጥቃት እንዳይኖር በማድረግ ኢትዮጵያ ቀጣይ ሊቢያ ወይም ሶሪያ እንዳትሆን መታደግ፡፡
  1. የሽግግር መንግሥት ማቋቋም፤
  • ፓርቲዎች፣ የተለያዩ መሪዎች፣ ባለጉዳዮች፣ ለመርህ የሚገዙና የጋራ ራዕዩን የሚያከብሩ ኃላፊዎች የተካተቱበት የሽግግር መንግሥት ማቋቋም፤
  • ርትዓዊ ፍትሕና እውነተኛ ተሃድሶ በትብብር ማከናወን፤
  • ያለፉ ዘመናት ብሶቶችን፣ ምሬቶችን፣ የራስን ዕድል የመወሰን መብት፣ የመሬት ባለቤትነት፣ የሃብት አጠቃቀም፣ እና ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ሌሎች ክልሎችን፣ አካባቢዎችን በተመለከተ ተራ በተራ ውሳኔ ላይ መድረስ፤
  • ለሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖለቲካ ምህዳሩን ክፍት ማድረግ፤
  • የዕርቅ ሒደትን ማስጀመር፣ ማዳበርና ተግባራዊ ማድረግ፤

ይህንን ዓይነት የጋራ ራዕይ መንደፍ ከቻልንና ሁሉንም ሊያስተባብር ወደሚችል ተቀባይነት ያለው መርህ ላይ እኛ ኢትዮጵያውያን መድረስ ከቻልን የሌሎችን ክብር፣ ማንነትና እሴት የምታከብር የሁላችንም የምትሆን አዲስ ኢትዮጵያን መመሥረት እንችላለን፡፡ የጋራ ንቅናቄያችን ከዚህ በፊት ሲያደርግ እንደኖረው አሁንም ለዚህ መሳካት የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማድረግ እና ከሁሉም ወገኖች ጋር ለመሥራት፤ ሁሉንም ወገኖች ወደ ውይይት ለማምጣት ያለውን ፍላጎትና ፈቃደኛነት በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ ሁላችንም ለእያንዳንዳችን፤ እያንዳንዳችንም ለሁላችን መቆም አለብን፡፡

ስለዚህ “የወንድሜ ጠባቂ ማነው?” የሚለውን ዘመናት ያስቆጠረው ጥያቄ ሲጠየቅ እያንዳንዳችን ኢትዮጵያውያን በዘር፣ በጎሣ፣ በቆዳ ቀለም፣ በሃይማኖት፣ በቋንቋ፣ በፖለቲካ አመለካከት፣ በመልከዓምድር፣ በእውቀት፣ ወይም በማንኛውም መስፈርት ሳንከፋፈል “የወንድሜ ጠባቂ እኔ ነኝ፤ እኔን ያገባኛል” ማለት መቻል አለብን፡፡

ይህን ለማድረግና እያንዳንዳችን በትክክለኛው የአንድነት፣ የፍትህና የነጻነት መንገድ ለመጓዝ እንድንችል ፈጣሪ ይርዳን!

አክባሪያችሁና ወንድማችሁ

ኦባንግ ሜቶ

 

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር

[1] አቶ ኦባንግ ይህንን ጽሁፍ በንግግር ያቀረቡት ሐምሌ 9፤2008 (July 16, 2016) የኢትዮጵውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ኅብረት በተጠራው ስብሰባ ላይ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ በአገራችን ፖለቲካ ከተከሰተው ለውጥ አኳያ በጽሁፉ ላይ መጠነኛ ለውጦች ተደርገዋል፡፡

የደቡብ ጎንደር ዞን ፖሊስና ጸጥታ 92 የሥርዓቱ አገልጋዮችን ለይቶ ይፋ አደረገ

$
0
0

ከሙሉቀን ተስፋው
በደብረታቦርና አካባቢው የወያኔ አባልና ቅጥረኛ የሆኑ የዐማራውን ሕዝብ የሚያስፈጁ 92 ሰዎች የደበብ ጎንደር ዞን ፓሊስና ጸጥታ መዋቅር ከሕዝብ ጋር በመተባበር ለይቷል። ሕዝቡም ወረቀት አባዝቶ እያሰራጨ ነው። ሥም ዝርዝራቸው ቀጥሎ ቀርቧል።
ይህ በዚህ እንዳለ የማረሚያ ቤቱ በአራቱም አቅጣጫ እየተቃጠለ ሲሆን የከባድ መሣርያ በቃጠሎው ውስጥ ባሉ ታሳሪዎች ላይ እየዘነበ ነው።
የደብረታቦር ዩንቨርሲቲ የክረምት ተማሪዎች ወገኖቻችን እያለቁ አንማርም ብለው ዛሬ ጠዋት ግቢውን ለቀው ወጥተዋል።

 

14202584_1176086612463543_1909228206327054391_n

 

 

 

 


ህዝባዊዉን ተጋድሎ እንዴት እና መቼ መቀላቀል እችላለሁ? በተጋድሎዉ ሂደትስ ዉስጥ ምን ማበርከት እችላለሁ? –ሸንቁጥ አየለ

$
0
0

 

UNIty - satenaw 9ይሄ ጥያቄ የብዙ ሰዉ ጥያቄ ነዉ:: ህዝባዊዉን ተጋድሎ እንዴት እና መቼ መቀላቀል እችላለሁ? በተጋድሎዉ ሂደትስ ዉስጥ ምን ማበርከት እችላለሁ? የሚለዉ ጥያቄ የብዙ ኢትዮጵያዉያን ጥያቄ እየሆነ ነዉ::

ተጋድሎዉን ስለመቀላቀል ከማሰብ በፊት መጀመሪያ ተጋድሎዉ ለምን አስፈለገ የሚለዉን ጥያቄ መመለስ ይገባል::

እያንዳንዱ ህዝብ የተጋድሎ ዘመን አለዉ::ለኢትዮጵያዉያን ይህ የተጋድሎ ዘመን ነዉ::ተጋድሎዉ ከመንፈስ ልዕልና በላይ የህዝብን ህልዉና የማስጠበቅ ተልዕኮ አንግቧል::ተጋድሎዉ ህዝብን ነጻነቱን ከቀሙት: ዘረኛ ህሊና ቀፍዶ ከያዛቸዉ እና በባርነት አስተሳሰብ ከተቃኙ ዘረኞች እና እብሪተኞች ነጻ የማዉጣት ረዥም ጉዞን ሰንቋል:: ተጋድሎዉ የዲሞክራሲ: የሰባዊነት: የእኩልነት ብሎም የሁል አቀፍ ብልጽግና መሰረቱን የተነጠቀ ህዝብን ነጻ ስለማዉጣት ነዉ:: ተጋድሎዉ የአንድ ሰሞን እሩጫ አይደልም:: ህዝባዉያን አይደክሙም::ህዝብም እንደ ዉቃያኖስ ጥልቅና ሰፊ ነዉ::ተጋድሎዉ ትናንት አልተጀመረውም::ከሳምንት በፊት ወይም ካመት በፊት አልተጀመረም:: ተቃዉሞዉ ወያኔ መንበሩን ጨብጦ ዘረኝነትን: ኢፍትሃዉነትን: ኢ-ዲሞክራሲያዊነትን: ወገንተኝነትን ማስፈን ሲጀምር የተጀመረ ነዉ::ምናልባትም በብዙ መቶ ሽህ ሰዎች የተሰዉለት ተጋድሎ ነዉ:: ሌሎች በብዙ አስር ሽህዎች አሁንም በሰር ቤት የሚማቅቁለት ነዉ::ሌሎች ሽህ ዎች ደግሞ እየተሳደዱ መስዋ ዕተነት እየከፈሉት ያለ ታላቅ ሰበአዊ ተል ዕኮን ያነገበ ነዉ:: ተጋድሎዉ ዛሬ ኢትዮጵያዉያን አለም ከደረሰበት የሰበአዊነት: የዲሞክራሲ እና የሁል አቀፍ ብልጽግና ይቋደሱ ዘንድ ለማስቻል የማይታጠፍ የህዝብ ምኞትን የሰነቀ ይሄንንም እዉን ለማድረግ ያልተቆጠበ ህዝባዊ መስዋዕትነትን የተንተራሰ ነዉ::

እና አንተ የዚህ የተጋድሎ አካል ለመሆን ምን ቅድመ ሁኔታ ያስፈልግሃል? ድርጅት? ጓደኛ? ዘመድ? ገንዘብ? የተለዬ እዉቀት? የተለዬ ትምህረት? የተለዬ ወኔ?

ድርጅት ግድ አይደለም:: ምክንያቱም ያዉ እንደምታስተዉለዉ በኦሮሚያ የተጀመረዉ ተቃዉሞ ህዝቡ እራሱ ነዉ ያለ ድርጅት የመራዉ:: ህዉሀትንም አፍንጫዉን ይዞ የህዝብን ጥያቄ ተቀበልኩ እሲኪል ያስለፈለፈዉ:: ወያኔን ምጥ እና ጭንቅ ያስያዘዉ የአማራ ተጋድሎም ያለ ድርጅት እና ያለ መሪ በህዝብ ቀጥተኛ አመራር ነዉ እየቀጠለ ያለዉ:: ምናልባት ስለ ተጋድሎ ለመነጋገር የቅርብ የምትላቸዉን ሰዎች ስትጠይቅ አርፈህ ተቀመጥ ሊሉህ ይችላሉ:: ወገኖችህ እና ዘመዶችህ ገና ነገሩ አልገባቸዉ ሆኖ ያንተዉ ተቃዋሚ ሊሆኑም ይችላሉ::አንተንም እንደሞኝ ሊያዩህ ይችላሉ::ወይም ፈርተዉ ሊያስፈሩህ ይችላሉ::

እና ምን ያስፈልግሃል? እንዴትስ ተጋድሎዉን መቀላቀል ትችላለህ? እዉቀትና ገንዘብ የተጋድሎ ትራስም መሰረትም ሊሆኑ አይችሉም::የያዛቸዉ ሰዉ ሊጠቀምባቸዉ ፈቃደኛ እስካልሆነ ድረስ እንዴዉም የሰበብ እና የፍርሃት ምንጭ ናቸዉ:: ለህዝባዊ ተጋድሎ የተለዬ ወኔ እና ጀብደኝነት አያስፈልግም::ህዝባዊ መሆን በራሱ በቂ ነዉ::

እና ምንድን ነዉ ሚስጥሩ?

ተጋድሎዉ መንፈሳዊነት እና ልባዊነት ነዉ::ተጋድሎዉ ገንዘብ ያለዉ ሰዉ ገንዘቡን ለመስጠት እና ወገኑን ነጻ ለማዉጣት ሲወስን ነዉ::ተጋድሎ በሀሳብ ነዉ:: ተጋድሎዉ እዉቀት ያለዉ ሰዉ እዉቀቱን ስለወገኑ ነጻነት ወደ ስራ ላይ ሲተረጉመዉ ነዉ:: ተጋድሎዉ በአካልም ነዉ::ተጋድሎዉ ከሁሉም በፊት ያገባኛል ከሚለዉ አስተሳሰብ ጋር መጋባት ነዉ::

ተጋድሎዉ በጣም ቀላል ከሆነ ግን እጅግ ምጡቅ ከሆነ መሰረት ላይ ይጀምራል::ከመንፈሳዊነት:: አይሁዳዉያን በዘር ፍጅት ዘመናቸዉ አንድ ድንቅ እና ዉብ የተጋድሎ መርህ ነበራቸዉ::መንፈሳዊ ተጋድሎ::በጸሎት መጋደል ይቻላል::ስለህዝብህ ወደ አምላክህ ጠዋት ማታ በመጸለይ መጋደል ይቻላል;;ሚኒስቴሩ አጠገብ ሆነህ ስለሚያስተላልፈዉ የተሳሳተ ዉሳኔ በልብህ በመራገም እና በዉስጥህ እንቢተኝነትን በመኮትኮት ብሎም በማበልጸግ መጋደል ይቻላል::ቤተክርስቲያን ዉስጥ ስለ ህዝብህ ድምጽህን ከፍ አድርገህ ከወንድሞችህ ጋር በመጸለይ መጋደል ይቻላል::

አይሁዳዉያን ልጃገረዶች የናዚ ባለስልጣናት አለፈቃዳቸዉ ሊደፍሯቸዉ ሲሞክሩ የወንዶቹን ብልት መተዉ እራሳቸዉን የሚያጠፉ እንደነበሩ ታሪክ ይዘግባል:: ተጋድሎው ወሰን እና ልክ የለዉም::ህንዳዉያን የእንግሊዝን ቅኝ አገዛዝ በመቃወም ልዩ ልዩ የተጋድሎ ስልቶችን ሲከተሉ ነበር:; አንዱ እና የሚያስቅ ግን የሚያስገርም ተጋድሏቸዉ ታዲያ እንግሊዝ ባለስልጣናት ቢሮ ከገቡ ብኋላ እንግሊዛዉያን ባለስልጣናት ላይ ፈሳቸዉን ፈስተዉባቸዉ ይወጡ ነበር:: የእንግሊዝ ባለስልጣናት ናላቸዉ እስኪዞር: ወኔያቸዉ እስኪብረከረክ እና የሚያደርጉትን እሲያጡ ድረስ ይቅበጠበጡ ነበር::በህንዳዉያን የፈስ ተጋድሎ:: በ2002 የተመረጡት የህንድ ጠቅላይ ሚኒስቴር ይሄን እዉነታ እና የህንዶችን የነጻነት ተጋድሎ በዋዛ እያሳሳቁ ብዙ ተናግረዉበታል::

መስሪያ ቤት ዉስጥ የሚሰሩ አሻጥሮችን እና ኢፍትሃዊነቶችን ተደብቀህ በማጋለጥ መጋደል ይቻላል::ማህበራዊ ሚዲያዉ ላይ የተደበቁ ወንጀሎችን እና ግፎችን በብዕር ስም በማጋለጥ ተጋድሎዉን መቀላቀል ይቻላል:: ለአንድ ወገንህ ጥቂት የተጋድሎ ምክር በመለገስ እና መንፈሱን ከፍ በማድረግ መጋደል ይቻላል:: ከምትበላዉ ምግብ ላይ ቀንሰህ እና ገንዘብ አጠራቅመህ ለአንድ እስር ቤት ለተወረወረ የተጋድሎ ጀግና የተቃዋሚ መሪ/አባል/ ወይም ጋዜጠኛ አንድ ነገር ይዘህ በመሄድ ተጋድሎዉን በዉስጥህ ማቀጣጠል ትችላለህ::የመጀመሪያዉ ትግል ከራስህ ጋር ነዉ:: እራስህን ስታሸንፍ ታጋይ ሆነህ ትወጣለህ::

የት ነዉ የምትኖረዉ? ስራህ ምንድን ነዉ? ምሁር ነህ ወይስ ጨዋ? ፖለቲከኛ ነህ ወይስ መንፈሳዊ ? ሴት ነህ ወይስ ወንድ? ወጣት ነህ ወይስ ሽማግሌ ? ቆንጆ ነሽ ወይስ ፉንጋ? አርቲስት ነህ ወይስ አርሶ አደር? ጋዜጠኛ ነህ ወይስ ፖሊስ? የትም መሆን ይቻላል::ምንም መሆን ይቻላል::ስለ ነጻነት:ፍትህ: እኩልነት እና ዲሞክራሲ ለመዘመር እና ለመጋደል ግን ሰዉ መሆን በቂ ነዉ::

ወያኔዎች ለምሳሌ ዉጭ ያለዉ ኢትዮጵያን ከተቃዉሞ እና ከተጋድሎ ጉራዉ እንዳይገቡባቸዉ ብዙ ጥረት ያደርጋሉ:: ምንም እንኳን አሜሪካ እና አዉሮፓ ተቀምጦ ስንቱ ስለተቃዉሞ እና ተቃዋሚ ሲነሳበት እንደሚንቀጠቀጥ በደንብ ቢያዉቁም ዉጭ ሀገር ተቀምጦ ጸረ ወያኔ ተጋድሎዉን መቀላቀል እንደ ፈሪነት እንዲቆጠር በደላሎቻቸዉ እና የተጋድሎ ሚስጢር ባልገባቸዉ የዋሆች ያስወራሉ:: ሆዱን ተሞላ እና መኪና ከቀየረ ብሎም ዲግሪ ካንጠለጠለ ወገናዊነት እና ህዝባዊነትን የሚረሳዉ ዲያስፖራ እንደሚበዛ ወያኔዎች ያዉቃሉ:: ይሄን የብዙ ዲያስፖራዎች ፈሪ ልብ ወያኔዎች በደንብ ያዉቃሉ:: ሆኖም ለማደናገሪያነት ለትግሉ የሚያስፈልገዉን ቦታ እና ሁኔታ እነሱ ሊመርጡልህ ሲፈልጉ ዉጭ ቁጭ ብሎ መታገል ፈሪነት ነዉ እያሉ የመንፈስ ነጻነት የተጎናጸፉትን ኢትዮጵያዉያን ሊያጣጥሉ እየሞከሩ ፈሪዎቹን ዲያስፖራዎች ግን በፍርሃታቸዉ ተጀቡነዉ እንዲቀጥሉ ያበረታቷቸዋል::

ዛሬ በጎጃም እና በገንደር ኢትዮጵያዉያን የመኖር: የነጻነት እና የዲሞክራሲ መብታቸዉን ስለጠየቁ ያለ ርህራሄ በጥይት እየተደበደቡ ነዉ::እና አንተ አሁን ምን ማድረግ ትችላለህ? ተጋድሎዉን ለመቀላቀል ዛሬ ቁርስህን ሳትበላ ስለወገኖችህ በማዘን መጀመር ትችላለህ::ምሳህን በመተዉ ወገኖችንህን ማሰብ ትችላለህ::የሀዘን ልብስ በመልበስ የሞተ ወገን እና ዘመድ እንዳለ በማስነገር የአካባቢህ ሰዎች ለቅሶ እንዲደርሱህ ማድረግ ትችላለህ:: ወገኖቻቸዉ ለተገደሉባቸዉ ሰዎች ገንዘብ:ልብስ እና ልዩ ልዩ ቁሳቁስ አሰባስበህ ይዘህ መሄድ ትችላለህ:: ጮክ ብለህ ተራራ ላይ ወጥተህ ማልቀስ እና መጮህ ትችላለህ::ወይም ቤተክርስቲያን ከምታምናቸዉ ሰዎች ጋር ባዶ እሬሳ ሳጥን ተሸክማችሁ በመሄድ እዬዬ እያላችሁ ማልቀስ ትችላላችሁ::

ተጋድሎዉ ዘርፉ ብዙ ነዉ::ለተጋድሎ የተነሳዉን ወገን በቀጥታ መርዳት ትችላለህ::በገባህ እና በምትችለዉ መጠን ሁሉ እጅህን መዘርጋት ትችላለህ::አስተባባሪ የለም::መሪ የለም::ማህበረሰቡን ያለመሪ እና ያለ አስተባባሪ ያስቀረዉ ወያኔ ኢትዮጵያዉያንን ለዘላለም በጎሳ ፖለቲካ ባርነት ሲገዛ ለመኖር በማቀድ ነዉ::እናም እራስህ አስተባባሪ መሆን መቻል አለብህ::ብዙ ሰዉ ማስከተል የለብህም::ከምታምናቸዉ መጀመር ትችላለህ::ያም ባይሆንልህ ብቻህን መጀመር ትችላለህ::እንቢተኝነት እዉስጥህ መፈጠሩ ነዉ የተጋድሎ መጀመሪያ::

ስለ ህዝብህ በደል : መገደል : መገፋት : መሰደድ : የዘር መድሎ እና ኢፍትሃዊ አያያዝ ሁሉ መንፈስህ እንቢ ማለት አለበት::ሁሉም ነገር ቢያቅትህ መንግስት የሚባለዉን እና በጎሳ ፖለቲካ ላይ ተመስርቶ ኢትዮጵያዉያንን የነጣጠላቸዉን ሀይል ከጎሳ አባላትህ እና ከዘመዶችህ ጋር ሆነህ ማማት እና ማንቋሸሽ መጀመር አለብህ:: ይሄም የተጋድሎዉ መንገድ መጀመሪያ ነዉ::

ስለህዝብህ ስትል አንድ የተጋድሎ መሳሪያ እና ስልት እጅህ ላይ እንዳለ እንዳትረሳ::ለምሳሌ አንተ የአንድ ብሄር አባል ብትሆን እና ጎረቤትህ ደግሞ የሌላ ብሄር አባል ቢሆን አንተ ለጎረቤትህ ፍቅር በመለገስ እና ኢትዮጵያዉያኖች አንድ እንደሆኑ በማስተማር ኢትዮጵያዉያን ሁሉ በጸረ ወያኔነት በአንድ እንዲቆሙ መጋደል ትችላለህ::በዚህም የወያኔን የከፋፍለህ ግዛዉ ደባ ማፍረስ ትችላለህ::የኢትዮጵያዉያን የወደፊት ተስፋ በዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ዉስጥ በነጻነት እና በእኩልነት መሰረት ላይ ሊቆም የሚችለዉ ይሄን ዘረኛ እና ከፋፋይ ሀይል ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጋራ ሲቃወመዉ ብሎም ሲያወርደዉ እንደሆነ በማስረዳት በፍቅር ኢትዮጵያዉያን ወደ አንድ መንፈስ እንዲመጡ መታገል ትችላለህ::እስላም የለም::ክርስቲያን የለም::ይሄ ብሄር ወይም ያ ብሄር የለም::ኢትዮጵያዉያን ሁሉ በአንድ መስመር ሆነዉ ለተጋድሎ ወያኔን መግጠም አለባቸዉ::ወያኔ ሲወድቅ ብቻ ኢትዮጵያ ወደ ዲሞክራሲያዊነት እና ነጻ ማህበረሰብነት ትሸጋገራለች:: ይሄን ስታስብ ታላቅ የነጻነት መንፈስ ዉስጥህ ተጸንሶ ሲላወስ ይሰማሃል::

አላስተዋልከዉ እንደሆነ እንጅ በ1997 ዓም ወጥተህ ረዥሙን እና አታካቹን ሰልፍ ተቋቁመህ ቅንጅትን መርጠህ ወያኔን ዉድቅ ያደረግህ እለት ተጋድሎ ዉስጥ ነበርህ::አላስተዋልከዉ እንደሆነ እንጅ ያ የተሰረቀ ድምጽ እና የተጭበረበረ የምርጫ ዉጤት በተነሳ ቁጥር ልዩ ልዩ ሀሳብን የሚያጭርብህ ተቃዉሞ ዉስጥ ስለሆንህ ነዉ:: እያንዳንዱ ድርጊትህ የባህሪህ: የስሜትህ እና የእዉቀትህ መገለጫ ነዉ::የመምረጥ ነጻነት እና መብት ብታገኝ ወያኔን በካርድ ዉድቅ ለማድረግ መዘጋጀትህ በራሱ የነጻነት ተጋድሎ መንፈሱ እዉስጥህ በጉልህ እንዳለ ይነግርሃል::

ተጋድሎዉ ወደ ከፍታ በሚዘልቅበትም ጊዜ እንደ አንበሳዉ ህዝባችን ከኦሮሚያ እስከ አማራ እንደ ተቀጣጠለዉ ህዝባዊ መናወጥ ሊሆንም ይችላል::ግፋም ሲል እንደ ጎጃም እና ጎንደር አማሮች የወያኔን ተመራጮች አዉርዶ የራሳቸዉን የአስተዳደር ስርዓት በመምረጥ የጎበዝ አለቃቸዉን መሾም ድረስ ይሻገራል:: :ተጋድሎዉ እንዲህ እያለ ወደ ብዙ ከፍታ እና አንገት ላንገት ትግል ይዘልቃል::ስለ ትልልቅ ተጋድሎ ከማሰብህ በፊት ግን እጅህ ላይ ያለዉን መሳሪያ ተጠቀምበት::

ለምሳሌ ዛሬ እንዲህ ብለህ ጸሎት በማድረግ ጀምር:-

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርካት

ክፉዎችን እና ደም አፍሳሾች ወያኔዎችን እግዚአብሄር ስራቸዉን ይነቀለው

ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያዉያን የከፍታ የፍቅር ዘመን ይምጣላቸዉ

ህዝቤ ሆይ የመንፈስ ነጻነትህን የመንፈስ ነጻነታቸዉን ለሸጡ ዘረኞች አሳልፈህ እንዳትሰጥ እግዚአብሄር ካንተ ጋር ይቁም
እኔም ካንተ ጋር ነኝና

እግዚአብሄር ሆይ ኢትዮጵያን ከዘረኝነት አስተሳሰብ ፈዉሳት::በህዝቧም መሃከል ፍቅርን አምጣ !

ሆኖም ሁል ጊዜ ማወቅ ያለብህ ያንተን የተጋድሎ እና የብዙዎችን የተጋድሎ መንፈስ ለመግደል ወያኔ ተጋድሎዉን በሰላማዊ ተቃዋሚ ፓርቲነት መመዝገብ ብቻ አድርጋ ትቀሰቅሳለች:: በሰላማዊ ፓርቲነት የተመዘገቡትን ሀያላን የሰላማዊ ታጋይ ፓርቲዎችን ግን መሪዎቻቸዉ እና አባላቶቻቸዉን ታሳድዳለች: ታስራለች ብሎም ትገላቸዋለች::

ከዚያም ሲዘል ደግሞ የህዝብ ልጆችን ህዝባዊነት ለመግደል እና ህዝባዊዉን ተጋድሎ ለማኮስመን የወያኔ ተላላኪዎች አዉሮፓ ቁጭ ብላችሁ: አሜሪካ ተጎልታችሁ: ካናዳ መሽጋችሁ : አፍሪካ አገር ጥግ ይዛችሁ እያሉ ኢትዮጵያዉያን ዲያስፖራዎች በተጋድሎዉ ላይ እንዳይሳተፉ ይቀሰቅሳሉ::መንፈሰ ደካሞችን ያሸማቅቃሉ:: መታለል የሚፈልጉትን ያታልላሉ:: ከዚያም ሲዘል አንድ ሰዉ የህዝብን ጥያቄ እና ተጋድሎ ደግፎ አንድ ቃል ሲተነፍስ አንተ ደግሞ የማን ፓርቲ አባል ነህ? እያሉ የወያኔ ተላላኪ እና አድር ባዮቾ ሰዉን ያሸማቅቃሉ::

“ስለህዝባችን : ስለወገናችን እንዴት እንደምንጋደል የምንወስነዉ እያንዳንዳችን በተናጠል እና በጋራ ነዉ:: እና ዝም ብለህ ተጋደል::በቻልከዉ ሁሉ ተጋደል::ትግሉ ዘርፈ ብዙ ነዉ::ረዥምም ነዉ::ገና ወንድ ይፈተንበታል::ገና የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ይነጥርበታል::ገና የእግዚአብሄር ተልዕኮ ይስተዋልበታል::ይሄ የኢትዮጵያ ጉዳይ ብቻ የሚወሰንበት ሂደት አይሆንም::ብዙ ተሳሳቢ ጉዳዮች አብረዉ አሉበት:: የህዝባችን መራራ ትግል ዘርፉ ብዙ ነዉ::የትም ብትሆን ተጋደል::ህዝባዊነትህን እንዳትተዉ::ዛሬ ብራስልስ ወይም ኒዮርክ ልትሆን ትችላለህ:: ወይም በሚያምር ቤትህ ዉስጥ ቦሌ ልትሆን ትችላለህ::አለዚያም ጎንደር ከተማ:: ምናልባትም ባሌ ጥግ:: ወይም ሶማሌ ጫፍ ላይ:: ነገ ግን ጫካ ልትሆን ትችላለህ::ተነገወዲያ ደግሞ ህዝብህ ጉያ::ይሄ ሁሉ የሚሆነዉ ግን የህዝባዊነት መንፈስህን ከህዝብህ ጋር ካስተሳሰርህ ብቻ ነዉ:: ህዝብህ ጀግና ይፈልጋል::ህዝብህ ተቆርቋሪ ይፈልጋል::” ይሄን ጥቅስ ለማንኛዉም ልቡ ስለ ተጋድሎ የሚዋዥቅ ሰዉ ስታገኝ ልትነግረዉ የሚገባ ቁርጥ መልዕክት ነዉ::

እያንዳንዱ ህዝብ የተጋድሎ ዘመን አለዉ::ለኢትዮጵያዉያን ይህ የተጋድሎ ዘመን ነዉ::ተጋድሎዉ ከመንፈስ ልዕልና በላይ የህዝብን ህልዉና የማስጠበቅ ተልዕኮ አንግቧል::ተጋድሎዉ ህዝብን ነጻነቱን ከቀሙት: ዘረኛ ህሊና ቀፍዶ ከያዛቸዉ እና በባርነት አስተሳሰብ ከተቃኙ ዘረኞች እና እብሪተኞች ነጻ የማዉጣት ረዥም ጉዞን ሰንቋል:: ተጋድሎዉ የዲሞክራሲ: የሰባዊነት: የእኩልነት ብሎ የሁል አቀፍ ብልጽግና መሰረቱን የተነጠቀ ህዝብን ነጻ ስለማዉጣት ነዉ:: ተጋድሎዉ የአንድ ሰሞን እሩጫ አይደልም:: ህዝባዉያን አይደክሙም::ህዝብም እንደ ዉቃያኖስ ጥልቅና ሰፊ ነዉ::ተጋድሎዉ በተወሰኑ ግለሰቦች መሪነት ግብ አይደርስም:: ላንተ የተጋድሎ መጀመሪያ ቀንህ ግን ዛሬ ነዉ::ህዝብም ተጋድሎዉ እስከ ነጻነት ነዉ::ሀያ አምስት አመታት የታጋደለ ህዝብ ነጻነቱን ሳያስመልስ እና ነጻነቱን ሳይጨብጥ እረፍት የለዉም:: የኢትዮጵያዉያን ተጋድሎ እስከ ነጻነት የሚዘልቅ ነዉ:: ያንተ ቀንህ ዛሬ ነዉ::ስለህዝብህ መቆርቆር የምትጀምርበት አሁን ነዉ:: የመዳን ቀን አሁን ነዉ::የማሸነፍ ቀን አሁን ነዉ እንዳለ መጽሀፍ::ስለ ህዝብህ እዉነት የምትቆምበት ሰዓቱ አሁን ነዉ:: እናሳ ? ህዝባዊ ነህ? ወይስ ግላዊ?

https://www.facebook.com/S.Ayele.Eth/posts/11166156883874

የሕግ ባለሙያዎች ታሪክና ግዜ የጣሉባችሁን ኃላፊነት እንደምትወጡ ይጠበቃል! [በላይነህ አባተ]

$
0
0

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

justice
ታሪክና ግዜ በትውልድ ኃላፊነትን ይጥላል፡፡ ይህ ትውልድ በሮማውያን ዘመን ኃላፊነቱን በሚገባ እንደተወጣው ትውልድ ታሪክና ግዜ ኃላፊነት ጥለውበታል፡፡የሮማውያንን ተደጋጋሚ ጪፍጨፋ አያት ቅደመ-አያቶቻችን በሚያስደንቅ ጀብዱ መክተውታል፡፡ ከሮማውያን ቅኝ ገዥዎች ጪፍጨፋ በከፋ ሁኔታ በእጅ አዙር ቅኝ ገዥ አገልጋዮች ህጻናት ጭንቅላታቸውን በላውንቸር እንደሚበረቀሱ፣ እግራቸውን በባሩድ እንደሚቆረጡና ሆዳቸውን እንደሚዘረገፉ አምባ ጊዮርጊስ በዚች ቅጽበት አስገንዝቦናል፡፡ እነዚህን የእጅ አዙር ቅኝ ገዥ አገልጋይ ጨፍጫፊ ባንዳዎችም ሕዝብ ግብግብ ገጥሟቸው ይገኛል፡፡ ይህ የጪፍጨፋ ግዜ ከገዳዮች የወገነውን እርጉሞችና ድምጣችንን አጥፍተን እንጀራችንን የምናሳድደውን አድርባዮች በትዝብት ቴሌስኮፕ ይመለከተናል፡፡

በመላ አገሪቱ በአረመኔዎች እሚፈጸመው የሕዝብ ጪፍጨፋ በደመነፍስ የሚንቀሳቀሱ አውሬዎች እንኳ በሰው እማይፈጽሙት ጪፍጨፋ ነው፡፡ ይህንን ጪፍጨፋ የሚፈጽሙትን አረመኔዎች ከፍርድ ለማቅረብ እናንተ የሕግ ባለሙያዎች የመሪነቱን ሥፍራ እንድትይዙ ግዜና ታሪክ አደራ ጥለውባችኋል፡፡ ሕግ የተሰራው ህሊናውና እምነቱ ያላሰረውን መረን ለማሰር ይመስለኛል፡፡ ህሊናውና እምነቱ ያላሰረው መረኑ ኃይለ-ሰይጣን ደሳለኝ ዛሩን አውርሶ ከወንበር ጎልትቶት እንዳለፈው ሰይጣን በሕዝባችን የጪፍጨፋ አዋጅ አውጇል፡፡ ኃይለ-ሰይጣ ደሳለኝንና የጪፍጨፋ አዋጁን እንዲያውጅ ያዘዙትን አረመኔዎች ከፍርድ እንድታቀርቡ ታሪክ፣ ግዜና ሕዝብ በእናንተ በሕግ ባለሙያዎች ኃላፊነት ጥለዋል፡፡ ይህንን የሕዝብ፣ የታሪክና የግዜ ኃላፊነት ያልተወጣ ዜጋና የሕግ ባለሙያ በሞቱት አጽም፣ ከሞት በተረፉት ዜጎች፣ በመጪው ትውልድ፣ በታሪክና በእግዚአብሔር ሲጠየቅና ሲወቀስ ይኖራል፡፡

የሕግ ባለሙያዎች ሆይ! ጠበቃ፣ ዳኛ፣ አቃቤ ሕግ፣ ሚኒስቴር፣ ፕሮፌሰር፣ ወዘተርፈ ሆናችሁ የምታግበሰብሱት ገንዘብ፣ የምትነዱት መኪና፣ የምትኖሩበት ቪላ በማታውቁት ሰዓት ሞት ሲጠልፋችሁ ተከትሏችሁ አይሄድም፡፡ ታሪክ፣ ትውልድና እግዚአብሔር ግን እየተከተሉ እስከ ዓለም ፍፃሜ ሲወቅሷችሁ ይኖራሉ፡፡ ባልጠበቃችሁት መንገድ አፈር ለሚሆነው ገላችሁ ሳስታችሁ የሕዝብን ጪፍጨፋና የፍትህን መታረድ አግዛችሁ ወይም ችላ ብላችሁ እንደ በፊቱ ባንዳዎችና አድርባዮች የራሳችሁንና የልጅ-ልጆቻችሁን ቅልብ በታሪክና በትውልድ ወቀሳ ሲሸማቀቅ ከመኖር አድኑ፡፡ በህሊናውና በእምነቱ እሚገዛውን ሕዝባችንን የሚጨፈጭፉትን አረመኔዎች ለሕግ አቅርቡ፡፡ ህሊናና ሕግ ቀርቶ ደመነፍስም በማያስራቸው ጭራቆች እንደ ዓባይ እሚፈሰው የንጹሐን ደም የችሎት ያለህ፣ የፍትህ ያለህ፣ የጠበቃ ያለህ፣ የዳኛ ያለህ ሲል ይጮሃል፡፡

የሕግ ባለሙያዎች ሆይ! የንጹሐን ደም ጩኸት፣ ታሪክና ግዜ የጣሉባችሁን ሐላፊነት እንደምትወጡ ይጠበቃል፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

 

ነሐሴ ሁለት ሺ ስምንት ዓ.ም.

የማሪያም መንገድ ሲዘጋ የገብሬሉ ይከፈታል ብለን ነበር!!! –ግርማ ሠይፉ ማሩ

$
0
0

 

girmaseifu32@yahoo.com; girmaseifu.blogspot.com

girma seifu

ግርማ ሠይፉ ማሩ

አንድትን ፓርቲን ድንክ ለማድረግ ከመወሰናቸው በፊት አንድነት የሚከተለውን ሰላማዊ የትግል ስልታ፤ ሰላማዊ የሰለጠነ የስልጣን ሽግግር እንዲቀበሉ በተደጋጋሚ አሳሰብን ነበር፡፡ ከመሃከላችን እየመረጡ ማስር ትግሉን እንደማያዳክመው ይልቁንም እንደሚያጠነክረው ነግረናቸዋል፡፡ ከከፋም ትግሉ ወደ ሌላ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው በቅርብ ላገኘናቸው ሁሉ ነግረናል፡፡ መግለጫዎች አውጠተን አቋማችን ህዝብ እንዲረዳው አድርገናል፡፡ የመንግሰት ተቋማት ህዝብን እንዲያገለግሉ፣ ከተሰጣቸው ህዝብን የማገልገል ሃላፊነት ውጭ እንዳይንቀሳቀሱ የበኩላችን ለማድረግ ሞክረናል፡፡ ማነኛውም ያደረግናቸው እንቅስቃሴዎች ከፍርሃት ተቆጥሮብናል፡፡ ከሁሉም በላይ በምን ያመጣሉ ትዕቢት የፈለጉትን አድርገዋል፡፡ ይህ እንዲሆን በውስጣችን ታቅፈናቸው የነበሩትን ጭንጋፎች ተሳትፎ የሚያሳንሰው አይደለም፡፡ ይህም ቢሆን ግን ገዢው ፓርቲ በማይመለከተው የፓርቲ የውስጥ ጉዳይ ገብቶ ህገወጥ እርምጃ የፖሊስ ሰራዊት በማሰማራት ወስዶዋል፡፡ ዛሬ በሰላማዊ ትግል ጥላ ስር ለውጥ እናመጣለን ሲሉ የነበሩ ወጣቶች በማነኛውም መንግድ ለውጥ ለማምጣት ቆርጠው ተነስተዋል፡፡ ተገፍተው የገቡበት መሆኑን ስለምናውቅ ምርጫቸውን ማክበር ብቻ ሳይሆን በባርነት ከመኖር ሞትን መምረጥ የሰው ልጅ ትክክለኛ ምርጫ ነው ብለን እናከብራቸዋለን፡፡

የታፈነ ህዝብ ለመተንፈስ የሚያደርገው የዚህ ዓመት ህዝባዊ እንቅስቃሴ በምንም መመዘኛ ሰህተት ሊሆን አይችልም፡፡ ጥያቄዎቹን በየቦታው ያስነሱት ጉዳዮች የተለያዩ ቢመስሉም መንግሰት እንደሚለው የመልካም አስተዳደር ጉድለት አይደለም፡፡ የህዝብ ጥያቄ ያልገባው መንግሰት ደግሞ መልሱን ሊያገኘው እንደማይችል ደግመን ደጋግመን ተናግረናል፡፡ በየቦታው የተነሳውን ህዝባዊ ንቅናቄ ተከትሎ መንግሰት ህገወጥ እርምጃዎችን መውሰዱን ቀጥሎበታል፡፡

መንግሰት በቅርቡ እያደረገ ያለው ዜጎችን መቅጠፍ በምንም መመዘኛ ቀለም አልተሰጠውም እንጂ ከቀይ ሽብር- ነጭ ሸብር የሚለይ አይደለም፡፡ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን የፖለቲካ ልዮነቶች በውይይት እና ህዝብ በሚመርጠው መስመር መፈታት አለበት ተብሎ በሚታመንበት ጊዜ መንግሰት ገዳይ ጥይቶቸን በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየረጨ ይገኛል፡፡ ይህ መቼም ቢሆን ከተጠያቂነት የሚያድን አይደለም፡፡ የህዝብ መተንፈሻ የሚባሉትን መሰመሮች ሁሉ የዘጋ መንግሰት ህዝብ ለምን አደባባይ ወጣችሁ ብሎ ለመግደል የሚያስችል ስልጣን ማንም አልሰጠውም፡፡ ነገር ግን ጊዚያዊ ማዘዣውን ተጠቅሞ በተግባር ዜጎችን እየገደለ ይገኛል፡፡ ይባስ ብሎ ከነብስ ወከፍ መሳሪያ አልፎ የቡድን መሳሪያዎች፣ በእኔ ግምት ለውጭ ወራሪ ሀይል የተዘጋጀን መከላከያ አንቀሳቅሶ የህዝብን ድምፅ ለማፈን እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ለሚታዘብ ወቅቱ የመንግሰት የእብደት ደረጃ ልክ ያለፈበት እንደሆነ ለመረዳት አያስቸግርም፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እሰከ ምስራቅ የጠየቀው ለሰው ልጅ የሚገባውን ነፃነት እና ክብር ነው፡፡ መንግሰት ደግሞ ሆዳችሁን ከሞላቸሁ ፎቅ፣ ባቡር እና መኪና መንገድ ካያችሁ መች አነሳችሁ የሚል ይመስላል፡፡ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰብሰበው ለወጣቶች የሚነግሩት በሙሉ ሆድ ሰለሚሞላበት መንገድ ነው፡፡ ወጣቱ በአደረጃጀት ካልገባ ማግኘት እንደማይቻል ያስረዱት ደግሞ የስፖርትና ወጣቶች ሚኒሰትር መስሪያ ቤት የወጣት አደረጃጀት ሃላፊ ናቸው የተባሉ ሰው ናቸው፡፡ በሀገራችን ያለው የተፈቀደ አደረጃጀት መንግሰትን ለማወደስ የተቋቋሙት የወጣቶችና የሴቶች ሊጎች ናቸው፡፡ እነዚህ አደረጃጀቶች ገዢው ፓርቲ ሲየስነጥስ እንባቸው የሚመጣ ናቸው፡፡ እነዚህ ደግሞ የወጣቱን ችግር ሊናገሩ አይችሉም፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በወጣት ሰም ስብሰባ ተቀመጡ የተባሉ ሰዎች አብዛኞቹ በእውነት ይናገራሉ ተብለው የሚጠበቁ እንዳልሆነ ብዞዎች የተሰማሙበት ነው፡፡ እነዚህ ተሰብሳቢዎች ቢያንስ እድሜያቸው የወጣት አይደለም፡፡ ወጣት ያልሆነ የወጣት ችግር አያውቅም ማለት ሳይሆን በዚህ ስብሰባ ለመካፈል ለሚከፈል አበል ለማግኘት ሲሉ ወጣቶችን ትተው እራሳቸውን መርጠው የመጡ ሰዎች ናቸው፡፡ በዚህ በትንሹ ያልታመኑ በትልቁ ሊታመኑ አይችሉም፡፡

ጠቅላይ ሚኒሰትሩ የምር ውይይት ማድረግ ከፈለጉ የወጣቶችና ሰፖርቲ ሚኒስትሩ ሬዲዋን ሁሴን ስብሰባ ላይ የነገራቸውን የሚናግሩ ወጣቶችን መሰብሰብ ሳይሆን በአዲስ አበባ እና በየክልሉ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ሊወጡ ፈልገው የተከለከሉትን ወጣቶች ወይም ደግሞ የደህንነት ሰራተኞች በየጊዜው እያፈሱ በእስር ቤት የሚያጉሩዋቸውን ወጣቶች ማናገር አለባቸው፡፡ ለምሳሌ እነ አንጋው ተገኝ እና ጓደኖቹን ከጎንደር፣ እነ ስንታየሁ ቸኮል፣ ወይንሸት ሰለሺ  ከአዲስ አበባ፣ እነ ምርቱ ጉታ ከአዳማ፣ እነ ዘሪሁን ገሰሰ ከወሎ፣ ወዘተ ጠርተው ምን ጎደለባችሁ? ማለት ነበረባቸው፡፡ ለነገሩ እንጂ ጉዳዩ ከወጣቶቹ ጋር የሚያልቅ አይደለም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስተሩ እና ጓዶቻቸው የምር ለዚህች ሀገር መፍትሔ የመፈለግ ፍላጎት ካላቸው ከማን ጋር መነጋገር እንዳለባቸው ይጠፋቸዋል ብዬ አላምንም፡፡

ዛሬ በጫካ የሚገኙት የሰላማዊ ትግል መስመር ሲዘጋ ወደ ትጥቅ ትግል የገቡት ልጆች በምንም መመዛኛ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለወጣቶቹ እንደገለፁት በውይይት የሚገኘውን ውጤት ዘንግተው እና በድንጋይ ውርወራ መንግሰት ለመገልበጥ ፈልገው አይደለም፡፡ ይልቁንም መንግሰታቸው ውይይት ሰለሚፈራ እና በተወያየበት ሁሉ በጉልበት አንበርክኮ ለመውጣት ሰለሚፈልግ ነው፡፡ አሁንም በከተማ በድንጋይ ውርወራ መንግሰት ፋታ ለመከልከል የተዘጋጁ ወጣቶች መንግሰት ባዘጋጀው አደረጃጀቶች/ፎረሞች ብቻ እንዲሳተፉ በመምከር መፍትሔ አይገኝም፡፡ የተለያየ አስተሳሰብ ያላች ወጣቶች ሊደራጁበት የሚችሉበት መንገድ መከፈት አለበት፡፡ ትላንት ለእስር የተዳረገቸው የአንድነት አባል የነበረችው ወይንሸት ሰለሺ  በኢህአዴግ ወጣት አደረጃጀት የነበረች ቀጥሎም የባለ ራዕይ ወጣቶች አባል የነበረች ነች፡፡ በሲቪል ሶሳይቲነት ይንቀሳቀስ የነበረው ባለራዕይ ወጣቶች መንቀሳቀስ ሲከለከል አንድነት ተቀላቅላ ስርዓቱን ለመለወጥ ቆርጣ ተነሳች፡፡ ለዚህም ብላ አንድነትን ተቀላቀለች፡፡ አንድነት በህገወጥ መንገድ ሲፈርስ ደግሞ በፌስ ቡክ ትግል የምታደርግ ንቁ ወጣት ነች፡፡ በእኔ እምነት ወይነሸት ላይ የሚያቀርቡት አንድም ወንጀል የለም፡፡ ወንጀለኞች ቢወነጅሏት ለልጇ ዲሞክራሲያዊት ሀገር ለመመስረት ባደረገቸው ጥረት ነው፡፡ ለሆዴ አላድርም ነፃነት ይበልጥብኛል ሰለአለች ብቻ ነው፡፡

አሁንም ጥሪያችን መንግሰት የማሪያሙን መንገድ ክፍት ያድርግ በነፃነት መደራጃት የምንችልበትን መንገድ ክፍት ማድረጉን ማረጋገጫ ይስጠን፣ ከዚያ የኢትዮጵያ ህዝብ ምን እንደሚያደርግ ያውቃል፡፡ በአዲስ አበባ የተኮለኮሉ ኮብል እስቶኖችን መናፈቅ ትቶ በውይይት ወደ መፍትሔ ይገባል፡፡ ለመጀመር በአዲስ አበባ የወጣትና ሴቶች ፎረም አባል ያልሆኑ የአዲስ አበባ ልጆችን ለማነጋገር ከወሰኑ ትልቅ እርምጃ ነው፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒሰትር ስራ ላለማብዛት እኛ የዞን ዘጠኝ ወጣቶችን ወክለናል ያነጋግሩዋቸው፡፡

መልካም አዲስ ዓመት በተለመደው ሁኔታ ሳይሆን ለለውጥ የእውነትም አዲስ ዓመት ማድረግ የሁላችንም ሃላፊነት መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡ ክብር ህይወታቸውን ለሰጡ ጀግኖቻችን ….

ቸር ይግጠመን!!!!!

 

አሸባሪ ሕዝብና ለሽብር የተጋለጠ መንግሥት (ከይገርማል)

$
0
0
Peaceful #OromoProtests demonstrators arrested & beaten up. Police takes off shoes to prevent them from running.

Peaceful #OromoProtests demonstrators arrested & beaten up. Police takes off shoes to prevent them from running.

ብዙሀኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ የከፋፍለህ ግዛው ስርአት አብቅቶ የዴሞክራሲያዊ ስርአት እንዲመጣ በመጠየቁ ምክንያት ከትግሬ ወያኔ ጋር ግልጽ ጦርነት ውስጥ ገብቷል ማለት ከሚቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል::  ዛሬ ላይ የተጣለበትን የጭቆና ቀንበር መሸከም አቅቶት የማያማርር: በጥቃት ስሜት የማይብሰከሰክ ከትግራይ ወያኔና ከእድምተኞቹ ውጭ ያለ ሌላ ሰው ማግኘት ያስቸግራል:: በየአካባቢው የብሶት እንጉርጉሮ ይዜም: የለውጥ መፈክር ይስተጋባ ይዟል:: ከዚህም አልፎ ወያኔ በራሱ የፖለቲካ ፍልስፍና ከሞላቸው ጥቂት ካድሬወችና የጥቅም ተጋሪ የአመራር አባላት በስተቀር ሁሉም “የወያኔ የዘረኝነት አስተዳደር በቃን!” ብሎ አደባባይ ወጥቶ ድምጹን እያሰማ ነው:: የነገሩህን ሰምተህ: ያዘዙህን ፈጽመህ መኖር እንጅ መጠየቅ አትችልም የሚሉት ወያኔወች በተራቸው ድምጹን በሀይል ለማፈን እንቅልፍ አጥተው በመስራት ላይ ናቸው::

 

ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ኢትዮጵያ በልማት አድጋ ተመንድጋለች በሚል ሰበካ በገሀድ የምንኖረውን የድህነት ኑሮ አስረስተው በፕሮፓጋንዳ ሊያጠግቡን: የፈለገው አይነት መከራ ቢደርስብንም ልማት እንዳይደናቀፍ ሲባል ተቃውሞ ሳናሰማ ችለን እንድንኖር “እዚህ ብትጎሳቆሉም እዚያ ላይ ትካሳላችሁ” የሚል እንድምታ ባለው ውትወታ ሊያሳምኑን: የሚደክሙት ሀፍረት የለሽ የወያኔ ካድሬወችና አጫፋሪወቻቸው ማደናቆራቸውን ቀጥለዋል:: በርግጥ እዚህ ግባ በማይባል በዝቅተኛ ኑሮ ይኖሩ ለነበሩ ሁሉም በጃቸው ሁሉም በደጃቸው ለሆነ የዘመኑ ኢንቨስተሮችና ልማታዊ ባለሀብቶች ከልማትም በላይ ልማት ከዴሞክራሲም በላይ ዴሞክራሲ አለ:: ለእነርሱ ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ ነው:: ስለዚህ መቸም ያልታየ ልማት በወያኔ ጊዜ እየታየ ነው ብለው ደረታቸውን ነፍተው ይከራከራሉ:: በርሀብና በበሽታ የተጎሳቆለው ወገን ህመሙ ስለማይሰማቸው: ችግሩ ስለማይገባቸው በፈጠሩት ገነት ውስጥ ሁላችንም አብረን ተደስተን የምንኖርም ይመስላቸዋል:: ላባቸውን አንጠፍጥፈው በሚያገኟት አነስተኛ የወር ገቢ ገመናቸውን ሸፍነው ይኖሩ ለነበሩ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ከሙስና የጸዳ የወር ገቢ ለነበራቸው ዱሮ ደህና ኗሪ ይባሉ ለነበሩት ሰዎች ግን ያሁኑ ኑሮ ከሲዖልም የሲዖል ኑሮ ነው:: በምግብ እጦት እና በወያኔ ጥይት ለሚረግፉት ብዙሀን ጭቁኖች የወያኔ የአገዛዝ ዘመን በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማያውቅ የመከራ ዘመን ነው::

 

ሕንጻ ቢገነባ ለባለጊዜወች ድሎት: ውሀ የመሰለ አስፓልት ቢሰራ ለመኪናወቻቸው ምቾት ከመሆን አልፎ  አንጀቱ በርሀብ ለታጠፈ: በዴሞክራሲ እጦት ድምጹ ለታፈነ: ሰላምና ፍቅር ርቆት በፍርሀትና በሰቀቀን እንዲኖር ለተገደደ ሕዝብ ያስገኘው ጥቅም የለም:: በወያኔወች ቀጭን ትዕዛዝ ድሀና የድሀ ጎጆ የሀገር ገጽታንና የከተማን ውበት ያደበዝዛሉ ተብሎ ድሀ ከተገፋና ጎጆው ፈርሶ በቦታው የሀብታም ህንጻ ከተገነባ: የዴሞክራሲ መብት ለጥቂቶች ብቻ ተለክቶ ከተሰጠ: የፍትህ ሚዛን ከተዛባ: አድሎና መገለል ከነገሰ: ርሀብና ተስፋ መቁረጥ ስር ከሰደደ: ልማታዊነቱ ምኑ ላይ ነው? የልማትን ትርጉም የሚያውቅ ሰው የወያኔን መንግሥት ልማታዊ ብሎ ሊጠራው ቀርቶ ሊያስበው አይደፍርም::

 

ሁሉም እንደሚያውቀው ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አሸባሪ በተባለው ሕዝብ ላይ ርምጃ እንዲወስድ ለመከላከያ ሠራዊት ከጥቂት ቀናት በፊት ትዕዛዝ አስተላልፈዋል:: ይህን የርሳቸውን ትዕዛዝ ተከትሎ በተለይ በሰሜን ጎንደር ሕዝብ ላይ የምድር ጦርና የአየር ኃይል የተቀናጀ ጥቃት ተከፍቷል:: በዚህ ጥቃት ተወልደው በየአደጉበት ቀየ የአባ ጃሌው ልጆች በጥይት እየተበሳሱ እየወደቁ ነው:: እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት ጾታ ሳይለይ የዚችን ዐለም በጎና ክፉ ጎኗን ለማየት ያልታደሉ ሕጻናት: መካሪና ዘካሪ የዕድሜ ባለጸጎች: ሮጠው ያልጠገቡ ተስፋ ናፋቂ ወጣቶችና ቤተሰብና አካባቢያቸውን በሀላፊነት የሚመሩ ጎልማሶች በገፍ በግፍ ህይወታቸውን ተነጥቀዋል::

 

ፓስተር ያሬድ ጥላሁን የሚባሉ የወንጌል አገልጋይ አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ሕዝቡን ገድሎ ድምጹን እንዲያፍን ለመከላከያ ሰራዊት የሰጡትን ትዕዛዝ አስመልክተው በጻፉት ደብዳቤ “በአንደበትዎ የተነገረውና በታሪክ መዝገብ ተቀርጾ የሚኖረው ይህ ውሳኔዎ በእግዚአብሔር፣ በሰውና በኅሊናዎ ዘንድ ከፍተኛ ተጠያቂነት እንደሚያመጣብዎ ሳስብ ከልብ አዝናለሁ።” ሲሉ ያቀረቡትን ቅሬታና “ፖለቲካዊ መፍትሔዎች ላይ እንዲተኮር፣ የኃይል እርምጃው እንዲቆም፣ ተዓማኒ እርምጃዎች እንዲወሰዱና ሌሎችንም ያሳተፈ አገራዊ መግባባት ላይ እንዲደረስ አቅምዎ እሰከሚፈቅድ የበኩሎትን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ፤ ይህንንም ማድረግ ካልቻሉ ከሚፈሰው የንጹሐን ደም እጅዎን እንዲያነጹ ሰውን በመልኩና በምሳሌው በፈጠረ በሕያው እግዚአብሔር ስም እማጸኖታለሁ።” የሚለውን ተማጽኖና በሳል ምክር አንብቤ አቶ ኃ/ማሪያምም ጊዜ አግኝተው ሙሉ ጽሁፉን  ቢያነቡት ስል ከልብ ተመኘሁ:: ለነገሩ ሰውየው  ግራ የገባቸው እንደሆኑ ተግባራቸው ብቻ ሳይሆን ስማቸውም የሚሰጠን የሆነ ጥቆማ ሳይኖረው አይቀርም:: የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ሆነው ኃ/ማርያም ተብለው መጠራታቸው በራሱ የተምታታ ነገር እንዳለ የሚያሳይ አንድ ጭብጥ ነው:: አይደለም ታምር የመስራት የማማለድ ስልጣን እንኳ የላትም በሚል እምነት የተጠመቀ ሰው “ኃ/ማርያም” ተብሎ ሲጠራ ምን ማለት ነው?

 

የሆነው ሆኖ ትግሉ ተፋፍሟል:: ለመብትና ለነጻነቱ እየተዋደቀ ያለው ሕዝብ የወያኔን አልጋ ክፉኛ ይነቀንቅ: በመንግሥት ላይ ሽብር ይፈጥር ይዟል:: ከእንግዲህ በኋላ ሞትን ፈርቶ ራሱንና ወገኑን ለጭቆናና ለጥፋት አጋልጦ የሚሰጥ ወንድም ሆነ ሴት ይኖራል ተብሎ አይታሰብም:: ከእንግዲህ በኋላ ብዙ ሆኖ በጥቂቶች መሳደድና መዋረድ አይኖርም:: ከእንግዲህ በኋላ የሚያለቅስ ወንድ በሀገሬ ምድር አይታይም: ከእንግዲህ በኋላ ልጆቹን አስቀጥፎ ሀዘኑን ውጦ የሚቀመጥ ወላጅ: አባት እናቱን አስገድሎ አርፎ የሚቀመጥ ልጅ ይኖራል ተብሎ አይታሰብም:: ሕዝብ አምርሮ ሲነሳ መፈናቀል ሳይሆን ማፈናቀል ይችላል: መታሰር ሳይሆን ማሰር ይችላል: መሞት ሳይሆን መግደል ይችላል:: በዚህ መሀል ነገሩ ሁሉ ተገለባብጦ መንግስት መሸበሩ ሕዝብ ማሸበሩ አይቀሬ ይሆናል:: ማን አሸናፊ ማን ተሸናፊ እንደሚሆን ወደፊት ይታያል::

ትንሳኤ ለኢትዮጵያ!

የጀርመኗ ትልቋ ከተማ ሙኒክ  በወያኔ  የተገደሉትን ጀኖች ኢትዮጵያውያንን በደማቅ ሁኔታ አስባ ዋለች። በዘርይሁን ሹመቴ  / ከጀርመን

$
0
0

 

67ኢትዮጵያዊያንና  ትውልደ  ኢትዮጵያውያን  ዛሬ በ(28.12.2008ዓም) በ 03. 09. 2016 በጀርመን ሙኒክ  ከተማ በወያኔ  የጥይት  እሩምታ  ውድ  ህይወታቸውን  ላጡ    ንጹሃን  በማሰብ   ታላቅ የሻማ ማብራት  መርሃ  ግብር  አድርገዋል ። በተጨማሪም   የህዝብን የመብት  ጥያቄ  በተገቢውና በሰላማዊ  መንገድ  ከመመለስ  ይልቅ  መግደልና  ማሰርን አማራጭ  መፍትሄ  ያደረገውን   የወያኔንን  መንግስት በዚሁ  መርሃ  ግብር  ታዳሚው  በታላቅ  ድምጽ  አውግዘዋል። ይህንን  መርሃ ግብር  በሙሉ ሃላፊነት  ያዘጋጁት  በሙኒክና  አከባቢዎች  የሚገኙ ወደ 14 የሚደርሱ  ማህበራዊ  ተቋውማት እንዲህም  የሃህማኖት ድርጅቶች  በመተባበር  ነው ።

 

በሀገር ውስጥ የሚደረገው ህዝባዊ እንቢተኝነት እና ህዝባዊ አመጽ አድማሱን እያሰፋ አብዛኛውን የአማራ ክልሎች አዳርሷል።ኦሮሚያ ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ከ10 ወር በላይ በጽናት ህይወታቸውን እየገበሩ መራራ  ትግልን  ከወያኔ  ቅጥረኞች የአጋዚ  ወታደሮች  ጋር  እያካሄዱ  በሚገኝበት  መላው  የአማራ  ህዝብ እስከመጨረሻው የነጻነት ደጃፍ መስዋትን ለመክፈል ቆርጦ  ተነስቷል። ይህ የአንድነት ንቅናቄ  ጎጠኛውን  ወያኔን  ከማስደንገጡ  አልፎ  በንጹሃን  የኢትዮጵያ  ህዝብ  ላይ  የጦርነት አውጇል። በሙኒኩ  የሻማ  ማብራትና  የተቋውሞ  መርሃ  ግብር  ላይ  የተገኙት  ታዳሚያን ሀገር ቤት ያለው ወገን ህይወቱን ሳይሳሳ እየገበረ ባለበት በዚህ ወሳኝ ሰአት በጀርመን የሚኖሩ  ኢትዮጵያውያን ጊዜያቸውን እና ገንዘባቸውን መስዋእት በማድረግ ለትግሉያላቸውን አጋርነት እስከመጨረሻው  ድረስ  እንደሚያሳዩ አረጋግጠዋል። ከዚህም  በተጨማሪ  ይህ  የህዝባችን  በአረመናዊ  መንገድ  በወያኔ  ታጣቂዎች  እየደረሰበት  ያለው  ግድያ በመቃወም  ያላቸውን  አቅም ተጠቅመው  በሚኖሩበት በጀርመን ሀገር ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጫና እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ ግፊት በመፍጠር  ወያኔ  ስልጣንን  ለህዝብ እስከሚያስረክብበት  ጌዜ ይህን የዜግነት  ግዴታቸውን እንደማያቋርጡ  ገልጸዋል ።

 

በዚህ ወሳኝ ሰአት የወያኔ  ጎጠኛና  ከፋፋይ ስርአት  ለማስወገድ  የሚጠቅሙ  ማንኛውም  አይነት  እንቅስቃሴ  ከፍተኛ ተጽእኖ ሰጥተው  እንደሚሰሩ  ታዳሚዎቹ  በማረጋገጥ ፤ ለመላው  የኢትዮጵያ  ህዝብ  ያላቸውን የወገን አለኝታቸውን እና አንድነታቸውን እነደማያቋርጡ  አረጋግጠዋል ። በትእይንቱ  ወያኔ አገሪቱዋን  ማስተዳደር  ስላልቻለ  ስልጣኑን  በፍጥነት ለህዝብ  ያስረክብ ፤  በኢትዮጵያ  በአጋዚ  ወታደር  የሚፈሰው  ደም  የኛ  ደም  ነው ፤ ተላላኪው  ህውሃት  እንጂ  የኢትዮጵያ ህዝብ አይደለም ፤ ኢትዮጵያ  ውስጥ  የሚደረገውን  ትግል  እንደግፋለን ወዘተ የመሳሰሉት መፈክሮች  ታዳሚው  በታላቅ  ድምጽ  ሲያስተጋቡ  ታይተዋል።

 

በሙኒኩ  የሻማ  ማብራትና  ተቋውሞ  በሀይለማሪያም  በሚመራው  በወያኔ መራሹ ጦር  በአሰቃቂ  ሁኔታ የተገደሉትን ከ500 በላይ  ንጹሃን  ሰልፈኞችን በኦሮምያ እንዲሁም  ከ150 በላይ ስርአቱን  በመቃወም  በሰላማዊ  መንገድ  በአማራ  ክልል  በአደባባይ ወጥተው ሀይወታቸውን በጥይት ያጡትን ዜጎቻቸንን  በማሰብ  የህሊና  ጸሎት  በማድረግ  ሰማእተናታቸውን  ዘክረው  ውለዋል። በኢትዮጵያ ነጻነት እኩልነት አንድነት እንዲሁም  ፖለቲካ  ለውጥን  ለማምጣት  ውድ  ህይወታቸው  ለከፈሉት  ለእነዚህ  ጀግኖች የዚህ መርሃ ግብር ታዳሚዎች  የተሰማቸውን  ጥልቅ ሃዘን በመግለጽ  ለቤተሰቦቻቸው እና ለመላው  የኢትዮጵያ  ህዝብ  መጽናናትን ተመኝተዋል።

 

በውድ ልጆችዋ መስዋእትነት ኢትዮጵያ ነጻ ትወጣለች!

 

Zerihun Shumete / Germany

ከሰሜን ጎንደር የአማራ ሕዝብ ትግል አስተባባሪዎች ለምሊሻ ታጣቂዎችና ለመላው የአማራ ሕዝብና ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያዊ ወገናችን ሁሉ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ

$
0
0

north Gonderሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ሰሞኑን በተደጋጋሚ እንደዛተው የአማራን ክልል የጦርነት ቀጠና አደርጋለሁ ብሎ ተግባራዊ አድርጓል። ንጹሃን የአማራ ተወላጆችን ህጻናትን ጨምሮ ያለርህራሄ ባሰማራው አጋዚ ታጣቂዎች እያስገደለ ይገኛል።የሕዝባዊ ወያኔ መሪዎች የአጋዚ ጦር ብቻ ሳይሆን በሀሰት የገበሬ ታጣቂዎችን ጭምር <<አባይ እንዳይገደብ የሚፈልጉ የሻዕቢያና የኤርትራ ተላላኪዎች ናቸው>> በሚል ወገን ወገኑ ላይ እንዲተኩስ አበል እየከፈሉ መሳሪያ እያስታጠቁ ጭምር አሰማርተዋል። ይሄ ብዙ ርቀት አይወስዳቸውም።ሐቁን የአማራ ምሊሻ ይረዳል።ያውቃል።ሕወሓት በአማራ ሕዝብ ላይ ወልቃይት የአማራ ነው በማለቱ ለሰላማዊ ተቃውሞ የሰጠው የጥይት ምላሽ ሰጥቷል።

ብዙዎቹ የምሊሻ ታጣቂዎች በአገር ሽማግሌ ሐቁ ተነግሯቸው የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይን ጸረ አማራ የግፍ ግድያ ተቃውመው ሸሽተው ተመልሰዋል።አንዳንድ ይህን ዓላማ ያልተረዱትን የአካባቢ የአገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች፣መላው ሕዝባችን የወያኔ ሐርነት ትግራይ የራሳችንን ንጹሃን የገበሬ ምሊሻ ጭምር ለከፈተው ጸረ አማራ ጦርነት እንዳይጠቀም ማሳወቅ ማስጠንቀቅ አለብን።በደባርቅ የተስተዋለው የወያኔ ግልጽ ሴራ ማሳያ ነው:

ይሄ በአማራ ንጹሃን ላይ የተከፈተ ጦርነት መነሻው የወልቃይትን የአማራ ማንነት ክዶ ሕወሓት ወልቃይት የትግራይ ብሎ አስተዳደር ከልሎ ላለፉት ሃአ አምስት ኣመታት ስፍር ቁጥር የሌለው ዘር ፍጅት አድርጓል። ይሄ የወያኔ የጉልበት እርምጃና ሕገ ወጥ ውሳኔ የመተው ወልቃይት ጉዳይ በሕግ እልባት እንዲያገኝና እንዲስተካከል ህዝቡ ወኪል ኮምቴ መርጦ በሰላማዊ መንገድ ያቀረበውን ጥያቄ ወደ ሀይል ግጭት ሆን ብሎ ወያኔ ስለቀየረ ነው። ይሄ ጦርነት ስለ አባይ መገደብ አይደለም። የህዝቡ በዙሃኑ ምሊሻ  ወገናችን ዛሬ በአማራ ክልል የተሰማራው አጋዚ አልበቃ ያለው ወያኔ ጥቂቶችን  በሀሰት በመደለል የተከፈተው ጦርነት አማራን ለማጥፋት፣ወልቃይትን በጉልበት ወስዶ ለማስቀረትና የአማራን ሕዝብ ረግጦ ለመግዛት ነው።

ልጆችህ ተምረው የበይ ተመልካች እና ስራ አጥ ያደረገ፣ወገኖችህን ራሱ ባመጣው የዘር ፖለቲካ አማራ ስለሆኑ ብቻ ከተለያዩ ክልሎች ያሳደደ ነው።ለመሆኑ ወያኔ ያልሰራው ግፍ የቱ ነው? ይህን ላንተ መዘርዘር ለቀባሪው ማርዳት ነው።

ከወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪዎች መካከል ኮ/ል ደመቀ ዘውዱን ጨምሮ  ታጋዮች የነበሩ ደርግን ለመጣል የተዋደቁ እንጂ ወያኔ እንደሚለው የሻዕቢያም ሆነ የግብጽ ተላላኪዎች አይደሉም።አይሆኑምም።

ለዚህ የወያኔ ቅጥፈት ቦታ ሳትሰጥ ዛሬ በአማራ ሕዝብ ላይ ወያኔ ለከፈተው ግልጽ የዘር ማጥፋት ጦርነትን አውግዘህ በወገኖችህ ላይ አትተኩስ።መሳሪያህን ሕዝብ ግደል ብለው ባሰማሩህ ላይ አዙር። ከአጋዚ ጋር እንዳታብር:፡ ሲጠይቁህ የአማራን ሕዝብ እንደ ጠላት ወታደር ሊጨፈጭፉ ከመጡት ጋር አላብርም በል።

ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በዚህ አጋጣሚ የሕወሓት ዘረኛ አገዛዝ ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ተራ በተራ ያልረገጠው፣ያልገደለውና ያላስለቀሰው ብዙሃን ሕዘብ የለም።ላለፉት ዘጠኝ ወራት በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ እየተፈጸመ አለው ዘር ማጥፋት፣ ከሸኮ መዠንገር ጭፍጨፋ እስከ ኦጋዴን የዘር እልቂት፣ ከጋምቤላ የአኙዋ ንጹሃን የሁለት ዙር የዘር ፍጅት እስከ ሲዳማ ሕዝብ ላይ ተፈጸመ ግድያ እአሉ ብዙ መዘርዘር ይቻላል:፡ ዛሬም ወህኒ ቤቶች በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵአውያን አበሳቸውን ያያሉ። ከትላንት እስከ ዛሬ እየተፈጸመ ያለው የአማራ  ግድያ የተግባር ምስክር ነው። ዛሬ በአማራ ሕዝብ ላይ በይፋ ያወጀውን የዘር ማጥፋት እርምጃ አጠናቆ ነገ ወደ ሌላው ወገናችን መዞሩ አይቀርም። ባለፈው በጎንደር ተቃውሞ ወቅት በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ግፍ ስንቃወም ፍጹም ወገናዊ በሆነ ተቆርቋሪነት ነው።ዛሬ በአማራ ሕዝብ ላይ ወያኔ ዘምቶበታል። በየትኛውም አካባቢ ያለ ወገናችን ይህን የወያኔ ፋሺስት ስርዓት እርምጃ በአገኘው አጋጣሚ ሁሉ እንዲያወግዝ እንጠይቃለን።

በየአካባቢው የሚገኘው ሰላም እና ለውጥ ናፋቂ ሕዝብ ለመብቱ የሚነሳበት ወሳኝ ወቅት ነው። የሕዝብ ጠላት የሆነውን ወያኔን ማዳከም የሚቻለው በጋራ በተመሳሳይ ወቅት ፋታ የሚነሳ የጋራ ትግል በማድረግ ጭምር ነው።የሕዝቡ መሪዎች በአማራና በኦሮሚያ ክልል እንደተደረገው ይህ ወሳኝ ወቅት ሳያልፍ ተረባርበን ይህን ፋሺስታዊ የወያኔ ስርዓት ለመገርሰስ በበኩላችን የተጠናከረ ትግላችን ይቀጥል።

ሞት ለፋሺስቶች

የአማራ ሕዘብ ከተከፈተበት የዘር ማጥፋት ጦርነት ተባብሮ ያሸንፋል!

ለክቡር ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ [ዳንኤል ሺበሺ]

$
0
0

አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡፦ ሠይፎትን ወደ አፎቱ እንዲመልሱ የሚጠይቅ የግል ደብዳቤ፤
***********************************
ክቡር ሆይ፣ ሺህ ዓመት ይንገሱ፡፡
enqilf Hailemariamየዛሬ አያረገውና እርሶዎን ያነ በምንጠራዎት በቤተሰባዊ አጠራር <ጋሽ ኃይሌ> ብዬ ጉዳዬን ልጀምር፡፡
ጋሽ ኃይሌ፦ ሁሌም ቢሆን ስለ እርሶዎ የገዘፈው ግላዊ ስብዕናዎትን በተለያዩ ትላልቅ ሚድያዎችም ጭምር ከመመስከሬ ቦዝኜ አላውቅም፡፡ ነገር ግን የኅወሓትን ትብታብ ውስጥ የታመቀውን የሀገሪቱን ውስብስብና ጥልቀት ያላቸው ችግሮችን በጣጥሰው ይወጣሉ ብዬ  እያሰብኩ ጊዜ እንደማላጠፋም ግን አልሸሸገዎትም፡፡
ይህን ደብዳቤ ሳዘጋጅ ምን ሊፈይዱ? በምል ሀሳብ ከራሴ ጋር ሙግት የገጠምኩ ሲሆን፤ ምንም ይሁን ምን አሁን ፊለ ፊታችን የምናውቀው እርስዎን ስለሆነ በእርስዎ በኩል ለዋናዎቹ እንዲደርስ ማድረግ ተገቢ በመሆኑ ነው በቀጥታ ለእርስዎ የጻፍኩሎትና እባክዎትን በጽሞና እንዲያነቡና አንብበውም እንዲያሰላሰሉ በትህትና እጠይቅዎታለሁ፡፡

በአንድ በኩል ከጊዜ መንጎድ ጋር የፖለቲካ አቋማችን መራራቅ፤ በሌላ በኩል እርስዎ ያለ ሕዝብ ድጋፍ በፖለቲካ ሥልጣን ከፍከፍ ሲሉ እኔ ደግሞ በተቃራኒዮ በመንግስትዎ እየተደቆሰ ካለው ህዝብ ጋር መከራን በመምረጤ በሥልጣንም ሆነ በኢኮኖሚ ዝቅዝቅ ማለት እና እርስዎ በሥራ ጫና፤ እኔ ደግሞ በተቃራኒው ያለሁበት ሁኔታ ተዳምሮበት ምናልባትም መረሳሳትን አስከትሎ ሊሆን ይችላል፡፡ ቢሆንም ቅሉ አንዳንድ ትዝታዎችን ብጠቁም ለማስታወስ አይከብድዎትምና … ፡፡
ያነ በደጉ ዘመን ወደ ደርባባው ሱፎዎት ውስጠኛው ኪስዎ የገዛ እጄን በእምነት እየሰደድኩ ለኔ የምበቃኝን ያህል ገንዘብ በመውሰድ በእርስዎ ገንዘብ እርስዎን መጋበዘን፤ ሲቀላ (በአርባ ምንጭ ከተማ) በአሁኑ የኤርትራዉያኖቹ ዳህላክ ጫማ ቤት ለእግርዎ ተስማም ጫማ ስንመርጥ… ለኔም ሲገዙልኝ፤ ሼቻ አሻም ሬስቶራንት አስቀድሜ ምሣ አዝዤ ስጠብቅዎት፤ የወጋጎዳን መመስረትን ተከትሎ በአከባቢዬ የተቀሰቀሰውን ቀውስ ለማብረድ ስንመካከር አቤት የነበረን ፍቅርና መቀራረብ!

መውደድ ብቻም ሳይሆን ለምናከብራት ባለቤትዎ ለእተጌይቱ ሮማን ተስፋዬ’ም የምለው አለኝ፡፡ እርሳቸውም በትክክል የተሟላ የሴትነትና የእናትነት ፀጋ የተጎናፀፉ በዕውቀትና በጥበብ የተካኑና ለባልዋም ዘውድ ወይዘሮ መሆናቸውን በግሌ እመሰክርላታለሁ፡፡ ያኔ በዩኒቨርሲቲ መኖሪያ ቤታቸው እንጀራ ተቀራምተን ስንበላ በጆግ ውሃ እየቀዱ ስረጩብንና ሲያባረሩን፤ እኛም በውሃው ከመረስረስ ራሳችንን ለመከላከል ሲንል እርሶዎን ተሸክመን ወደ እልፍኞዎት አስገብተን በሩን በላይ ላይ እየዘጋን ስንጫወት፣ ስንስቅ፣ የተዘጋውን በር እንዲከፈትልዎት ሲማጸኑልን የነበረንበትን ጊዜ ዛሬ ላይ ሆኜ በህሊናዬ ሳስብ ያ! ዘመን ተመልሶ እንደማይመጣ አዕምሮዬ እየጠቆመም ቢሆንም ግን ገራገሩ ልቤ አሁንም በምኞቱ ቀጥሎበታል፡፡ ምን እያልክ ነው ያሉኝ እንደሆን እርሶዎን ባያገኙ ኖሮ ጋሼ እዚህ ላይ ስለመድረሳቸው እርግጠኛ አይደለሁም እያልኩ ነው፡፡
ዛሬም አንድ ነገር የማለት ግዴታ አለቦዎት፡፡
የአንድ መንግሥት ከሚጠበቅበት ትላልቅ ኃላፊነቶች ውስጥ ዋነኛው ሥርዓት አልበኝነትን መቆጣጠር፣ የህዝቦችን/የሰዎችን ፀጥታንና ሠላምንና የሀገሪቱን ግዛት አንድነትን ማስጠበቅ እንደሆነ እረዳለሁ፡፡ ምንም እንኳ ያልተሳካልን ቢሆንም፡፡ በአንፃሩ በአሁኑ ወቅት በሀገራችኝ እየተስተዋለ ያለው ግን ሥርዓት አልበኝነት፣ ለህግ ያለመገዛት . . . ነው የሚያሰኝ ምልክት አለ ለማለት ይቸግረኛል፡፡ የተበደለ፣ የተገፋ፣ የተሰደበ፣ ፍርድንና እውነትን ያጣ፣ በዚህም የተማረረና በሀገርቱ ከተንሰራፋው ሙስናና አድልዎ የተነሣ በድህነት እየደቀቀ ያለው ህዝብ የተሰማውንና በውስጡ የታመቀውን ስሜቱን ከመግለጽ ውጭ፡፡

ስለዚህ እርሶዎ በቀን ነሐሴ 24, 2008 ዓም የተናገሩት ለትልቁ ምክር ቤትዎ ባይሆንም “እኔ በበኩሌ ሁሉም የፀጥታ ኃይሎች ማንኛውንም እርምጃ እንዲወስዱ አዝዤያለሁ!” ብለው በድፍረት ተናግረዋል፡፡
ክቡር ሆይ፦ ለክብሮነትዎ ሁሌም ሠላምን እመኛለሁ፡፡ ሠላማችንን አያደፍርሱብን፡፡ ያወጁብን ነገር ታላቅ ጥፋት ነው፡፡ በህዝብዎ ላይ የተወጠነ አደገኛ ነገር ፡፡ ይህ ሕዝብኮ የጣሊያን ወራር ኃይል አይደለም፡፡ የአጥንትዎ ክፋይ ነው፡፡ በእርስዎ የሚተዳደር ሕዝብ፡፡ በገዛ ሀገርዎና  በሕዝብዎ ላይ በጠራራ ፀሐይ ጦርነት አውጀዋል፡፡ ተበድያለሁ ብሎ ደመ እንባ በሚያለቅስ ሕዝብ ላይ እንዴት የቡድንና የነፍስ-ወከፍ ጦር መሣሪያ የያዘ ጦር ኃይል በአንድ ጠቅላይ ጦር አዛዥ ይታዘዛል?? ወይስ አማራና ኦሮሞ ከመቼ ጀምሮ ነው የእርሶዎና የኢት/ያ ጠላት የሆኑት? በእውነት  በእርስዎና በአመራርዎ አፍርያለሁ፡፡ ስለዚህ በአስቸኳይ ሠይፍዎትን ወደ አፎቱ ይመልሱ!  የሕዝብዎት እንባ ምን እንደሆነ ለማዳመጥ ጆሮ ይስጡ እንጂ እደመስሳለሁ እያሉ የግዛትዎትን ነዋሪ ማሳደድዎትን ያቁሙ፡፡

ሌላውና እዚህ ጋ ጠቅሼ ማለፍ የሚፈልገው ነገር ቢኖር፦ እርስዎ ወደ ሥልጣን በመጡ ቁጥር ሁሌ እልቂትና መከራ በህዝብዎ ላይ ይበዛል፡፡ ግን ለምን  ይሆን??
ለምሣሌ፦ ➊ እርስዎ የወጋጎዳ ከፍ/አመራር በነበሩ ጊዜ የአርባምንጭ፣ የሳውላ የዳውሮና የአከባቢው እልቂትና ውድመት ይቅርና በገዛ በትውልድ ከተማዎ በሶዶ ብቻ መተኪያ የሌለው ሕይወታቸውን ያጡ  ምን ያህል እንደነበሩ ሁላችንም የምናውቀው ሲሆን፤ በዚህም እንደ ቅጠል የረገፈው የንጹኃንን ነፍስ፣ የወደመው ንብረትና የባከነው ጊዜ እንርሳው ብንል እንኳ የሚሆን አይደለም፡፡
➋ እርስዎ የደቡብ ክልል ከፍ/ባለሥልጣን በነበሩ ጊዜ በሀዋሳና በአከባቢዉ በከንቱ የፈሰሰው ንጹኃን የሲዳማና የሌላ አከባቢ ተወላጆችን ደም፤ የወደመው ንብረትና የባከነ ጊዜ እንዴት ምንም እንዳልተፈጠረ ልንቆጥር እንችላለን?
➌ አሁን ደግሞ በታሪክ አጋጣሚ የሀገሪቱን የፖለቲካ ሥልጣን ጠቅልለው መርሄ መንግሥት ከሆኑ ወዲህም እንደ ቀድሞ አለቃዎት ሁሉ ተመሳሳይ አንዳንዴም የከፋ ነገር መፈጸምን ሥራዬ ብለው ተያይዘዋል፡፡ እባክዎትን ጋሽ ኃይሌ!! ልማጽኖዎት፡፡

ስለዚህ መጽሐፉ <ቢሰሙም ባይሰሙም” እንደሚል፤ እኔም ለእርስዎ የሚከተሉትን ምክር ቢጤ ጠቆም ላደርግና እንሰነባበት፡፡
#1ኛ- ለጽሁፌ መነሻ የሆነውን የአሸባሪ ንግግሮዎትን በአስቸኳይ ይሳቡ፡፡ ህዝብን ይቅርታ መጠየቅ ክብር ነው እንጂ በፍጹም ውርደት ሊሆን አይችልም፡፡
#2ኛ፡ እኛ ተቃዋሚዎች ለሩብ ምዕተ ዓመታት ያህል ስናነባ የነበርነው ለዛሬው መመሰቃቀልና ለከፋ አደጋ ያዳረጉ አፋኝ ህጎች በሙሉ መሰረዝ/መሻሻል ብቻም ሳይሆን ቀደም ሲል በዚህ የተፈፀሙ ኢ-ፍትሐዊ የሆኑ ውሳኔዎች በድጋሚ እንዲታዩ፣ አሳታፊና ሁሉንም ባለድርሻዎችን ያቀፈ የሽግግር ሥርዓት እንዲቋቋም የሚጋበዝ ውጥንዎን ከወዲሁ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርጉ፤
#3ኛ፡  ይህ የማይሆን ከሆነ ሹልክ ብለው ወደ አንድ  ሀገር ተጉዘው ጥገኝነት ይጠይቁ ባልልም (ከሕዝቦዎ ጋር መከራ መጋራትን ትተው መሰደድ ለአንድ ሀገር መሪ ክብር ነው ብዬ ስለማላምን)፤ ሥልጣንዎትን በፍላጎትዎ መልቀቅዎትን ያውጁና እቤትዎ ቁጭ ይበሉና ታሪክ ይሥሩ፡፡  በርግጥ ይህንን በማድረግዎ ዘለግ ያለ ዋጋ ያስከፍሎዎት ይሆናል፡፡ ቢሆንም ከትውልድና ከታሪክ አንፃር ሲመዘን ብድራቱ ታላቅ በመሆኑ፡፡

ደፍረው ይህንን ካደረጉ የግድ ይቅርታ መጠየቅ  አይጠበቅብዎትም፡፡ በቂያችን ነውና፡፡ ይሄንን በማድረግ ለትውልድ የሚተላለፍና ዘመን የማይሽረውን ታሪክ ተክለው ከማለፍዎ ሌላ ሀገሪቷን ማነው የሚመራው? እየተባለ የሚነሣውን ውዥንብር በማጥራት በትክክልም መሪ መሆንዎትን ያረጋገጡልናል፡፡ ቸር ያሰማን!

ከሰላምታ ጋር
ዳንኤል ሺበሺ – አክባሪዎ
ነሐሴ 30ቀን, 2008 ዓ.ም ተፃፈ፡፡


በኢትዮጵያ ህዝብ የሚደረገው የእምቢተኝትና የአመጽ ትግሎችና  በህወአት አገዛዝ  ስር የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት

$
0
0

ነዓምን ዘለቀ

Neamin Zeleke

ነዓምን ዘለቀ

በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች እየተደረገ ያለው የእምቢተኘነትና የአመጽ ትግል ሳይቋረጥ ከመንፈቅ በላይ ባስቆጠረበት በአሁኑ ወቅት፣ ህወሃት እተማመንበታለሁ የሚለው የመከላከያ ሰራዊት ኣባላት፣ ህወሃት/ኢህአዴግ የሚከተለው የዘረኝነት፥ የኣድሎና የበደል ፖሊሲ ትክክል አለመሆኑን ተገንዝበው  ህዝባዊ ትግሉን በመቀላቀል ላይ ይገኛሉ። በዕለተ ዕሁድ ነሃሴ 29 ፥ 2008  ከ450 በላይ የሚሆኑ ወታደሮች በሰሜን ጎንደር የሚደረገውን ህዝባዊ ተቃውሞውን በመደገፍ ወያኔን በማስወገዱ ሂደት ተጋድሎ እንደሚያደርጉ ማሳወቃቸው፣ የወያኔ ስርዓት እያከተመለት መሆኑን አመላካች ነው። ከዚህ በፊትም፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የጀግንነት ስራ ሰርተዋል። የህዝባዊ እምቢተኝነቱን ትግል ሲቀላቀሉ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በምርጫ 97 ወገን ላይ ተኩሱ ሲባሉ አሻፈረኝ በማለት ሄሊኮፕተር ይዘው ወደጎረቤት አገራት አምልጠዋል።

 

መከላከያ ሰራዊት ኣባላት የህዝቡን ስቃይ ሰምቷዋል፣ አሁን ደግሞ የህዝቡን ድምፅ አስተጋብቷል፣ እንደወገኑ ሁሉ የወያኔ አገዛዝ “በቃኝ” አያለ ይገኛል። የኦሮሚያ ክልል ህዝብ ለወራት የታገለውን፣ የአማራ ክልል ህዝብ የሞተለትን አላማ አንግቦ በመነሳት ላይ ይገኛል ።  ህዝብና ሰራዊት የአንድ አገር ክፋዮች፣ የአንድ አገር ገጽታዎች ናቸው።  ከ90% በላይ የሆነዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እንደ ሲቪል ኢትዮጵያዊ ወገኖቹ ሁሉ ከአንድ ብሄር የበላይነት ተላቅቆ ሰላም፥ ፍትህና እኩልነት በሰፈነባት ኢትዮጵያ ዉስጥ መኖር ይፈልጋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጽኑ ፍላጎት ምንም አይነት ጭቆናና መድሎ በሌለበት ስርዓት ዉስጥ ከአባቶቹ የተረከባትን አገር የግዛት አንድነት አስከብሮ ለሚቀጥለዉ ትውልድ ማስረከብ ነዉ እንጂ ወያኔና ምዕራብያውያን እንደሚያስቡት ለ “ምግብ ለመኖር” ብቻ የሚዋጋ ሰራዊት አይደለም።

 

“ውትድርና ዲሞክራሲያዊ ሳይሆን አምባገነን ነው።” ሆኖም ትክክለኛ ውለታውን የሚያከብርለት ጠንካራ አመራር ይፈልጋል። የታችኛው ሰራዊት የበላይ አመራሩን ጀግና፣ ትክክለኛና በውትድርና ሳይንስና ዕውቀት የታነጸ ክህሎት ያለው አድርገው ለማመን ለመከተልም ይፈልጋሉ።

ወታደሩ በዘር በተመሰረተ አድሎ ሳይሆን፣ በተግባር፥ በልምድና በአገልግሎት ላይ የተመሰረተ ዕድገት፣ የደሞዝ ጭማሪና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች እንዲሰጠው ይፈልጋል።

ሰራዊቱ አገራዊ ግዳጁን በሚወጣበትና በአገልግሎት ላይ ባለበት ግዜ ሁሉ ለስራዉ የሚያስፈለገዉን ቁሳቁስ ሁሉ መንግስት የማቅረብ ግዴታ አለበት፥ ይህ ሎጂስቲክን፥ ወታደራዊ ዩኒፎርሙንና የምግብ አገልግሎትን ያጠቃልላል።

ሞራሉ የላሸቀና አቅምና ብቃት በሌላቸው የህዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይ ጄኔራሎች የሚመራ ሰራዊት፣ ሙሰኛና ኢፍትሃዊ የሆነን ስርዓት ማገልገል አለመፈለጉ ብቻ ሳይሆን አገሩን ከጠላት መከላከልም አይችልም። የህዝብ ትግል ሲጎመራ፣ ሰራዊቱ በዘራፊና ዘረኛ ኣዛዦቹ ላይ አመጽ ማቀጣጠልና አፈሙዙን ወደ አነዚህ ጨቋኞች መመለሱ አይቀሬ ይሆናል።

ህወሓት ዘረኛ አገዛዝ ነዉ።ኣምባገነናዊ ጸረ-ሕዝብ ስርዓት ነው።  ኢትዮጵያን የሚመራዉም በኣንድ ብሔር የበላይነት ላይ በተመሰረ ኣስተሳስብና ከዚሁ በሚመነጩ ፖሊሲዎች ነዉ። የወያኔ ስርዐት የመከላከያ ሰራዊት አባላትና ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠይቀዉን ጥያቄ በአግባቡ መመለስ የማይችል ስርዓት ነዉ። ህወሓት የኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠይቀዉን ጥያቄ መመለስ የማይፈልገዉ የጥያቄዎቹ መልስ የሱ መጨረሻ መሆኑን ስለሚያዉቅ ነዉ።

 

አሁን ያለው የህወሓት ፖለቲካዊና  ወታደራዊ አመራር ኢትዮጵያ ዉስጥ መሳሪያ አንስተዉ በተለያዩ ግንባሮች የሚንቀሳቀሱ አማጽያንን ለማጥፋት የሚያስችለዉ ምንም አይነት ህዝባዊ ድጋፍ የለውም። በመጠነ-ሰፊ ችግሮችና ቅራኔዎች የተዘፈቀ ሰራዊት  በሁሉም ኣቅጣጫ በሚጠመድ የህዝብ ትግል ኣካል ይሆናል አንጂ በህዝብ ላይ የማያባራ መከራና ግፍ ለሚፈጽም የዘረኛና የጨቋኙ የህወሃት አገዛዝ መሳሪያ ሆኖ በረጅሙ ሊቀጥል ኣይችልም።

 

በህወሃት አገዛዝ ስር የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ሞራል እጅግ የላሸቀ ነው። መንፈሱ የደከመ፣ አንድነቱ የላላ፣ በራሱ የማይተማመን እርስ በእስር በጎሪጥ ኣንዲተያይ የተደረገ፡ ዘረኛና ዘራፊ ጄኔራሎች የሚያዙት ነው። እንዲህ አይነቱ ሰራዊት ደግሞ በአንድነት በረጅሙ ለመዋጋት የሚያስችለው ሆኔታ ውስጥ የሚገኝ ኣይደለም።

ናፖሊዮንመንፈሰ ጠንካራ ሰራዊት የራሱን ሶስት እጥፍ ወታደር ያሸንፋል’” በማለት አንድ ሰራዊት ሊኖረዉ ስለሚገባ  የመንፈስ ጥንካሬና ሞራል ወሳኝነትና አስፈላጊነት ተናግሯል። ይህን ያለዉና ታላቅ የወታደራዊ ስትራቴጂና ታክቲክ ክህሎት አንደነበረው በሰፊው የተጻፈለት ናፖሊዮን፣ 300,000 አባላት የለዉን “ታላቁ ሰራዊት” ይዞ የተሸነፈዉ የሽምቅ ውግያ በገጠሙት ስፓኒሾችን በስፓንያ በሰራዊቱ ላይ ያደረሱበት ቡርቦራ አይነተኛ ምክንያትና  ለውድቀቱም ከትልልቆቹ መንስኤዎች ኣንዱ ነበር። ከናፖሊዮን በኋላ ሽምቅ ተዋጊዎች ኢትዮጵያን ጨምሮ በብዙ አገሮች ዉስጥ ትልልቅ መደበኛ ሰራዊቶችን ለሽንፈት ተደርገዋል። አልጄሪያ፥ ቻይና፥ ቬትናምና በቀዝቃዛዉ ጦርነት ወቅት የነበረችዉ አፍጋኒስታን የሽምቅ ዉግያ አይነተኛ ምሳሌዎች ናቸዉ። በሽምቅ ውጊያ የደርግን ስርዓት በማዳከም መቻላቸውም ከምክንያቶች አንዱ ሆኖ ስልጣን ላይ የወጡት የህወሃት መሪዎች ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ በአራቱም ማዕዘን የገጠማቸዉን የአማጽያን እንቅስቃሴ ማሸነፍ የሚችሉበት ምንም አይነት ህዝባዊ ድጋፍ ሰለሌላቸዉ እነሱ  በመጡበት መሸነፋቸዉ አይቀርም። ህወሃት ሽምቅ ተዋጊዎች ለማጥፋት የሚያደርገው “ቆሻሻ ጦርነት” ከጦር ወንጀለኝነት ጋር ስለሚያያዝ፣ በአለም አቀፍ ማህበረሰብም ይሁን በኢትዮጵያውያን መመርመሩ አይቀርም። ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ ህወሃት የሚደረግለት ድጋፍ መቀነሱ አይቀርም። አሁን እንደሚታየው በህወሃትን ስር የሚማቅቀው ሰራዊት ጠንካራ የተቀናበረ ሽምቅ ውጊያና የህዝብ ኣልገዛም ባይነት በሁሉም የኢትዮጵያ ኣካባቢዎች ከተጠመደና ከተቀጣጠለ  ኣገዛዙም “የስፓኝ ነቀርሳ” ይሆንበትና ወደ መፍረክረኩ ለጥቆም ኣብዛኛው የሰራዊቱ ኣባላት ወደ ህዝብ ትግል የሚቀላቀሉበት ሂደት ይፈጠራል።

ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለሚገኙ ስር የሰደዱና ዘርፈ ብዙ ችግሮች ተጠያቂዎቹ የሆኑት የህወሓት መሪዎችና የትግራይ ጄኔራሎች ናቸዉ። የእነዚህ መሪዎችና ጄኔራሎች ዘረኝነት፥ ጭካኔ፥ ስግብግብነትና ገንዘብ ማሸሽ አገራቸዉን ዋጋ እንደሚያስከፍል ሁሉ እነሱንም ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስከፍል ሊያዉቁ ይገባል። የኣምባገነናዊነትና የዘረኝነት ተግባሮች የሌላ ብሄር ዜጎችን እንደሁለተኛ ዜጋ፡ ከዚያም በታች  የመቁጠር አባዜያቸው፥ ለከት ያጣው ኢፍትሃዊ ተግባሮቻቸው፥ ዘረፋቸው፡ ኣፈናና ጭቆናቸው ሳቢያ  ከህዝቡም ሆነ ከኣብዛኛው  የመከላከያ ሰራዊት ኣባላት የተነጠሉ መሆናቸውን ሊያውቁ ይገባል። ይህንን ሁሉ በአይኑ የሚያየዉና የገፈትና የመከራ ህይወት ኣስከኣፍንጫው የተጋተው ሰፊው  የኢትዮጵያ ህዝብ ትዕግስቱ ተሟጥቶ አልቋል። በኦሮሞ ክልል ኣየታየ የሚገኘው ህዝባዊ የቁጣ ማዕበል ፡ ዛሬ በጎንደርና በጞጃም  ዉስጥ በከፍተኛ ሁኔታ በመደገም ላይ የሚገኘው በማያሻማ ሁኔታ ይህንኑ የሚያረጋግጡ ናቸው። ትግሉ በመላ የኢትዮጵያ ኣካባቢዎች የሚዛመትበትና የሚቀጣጠልበት፡  የወያኔ ኣርነት ትግራይ ኣገዛዝ  እውር ድንብሩ ወጥቶ የሚጨብጠውን የሚለቀውን የሚያጣበት፥ ብሎም ተፍረክሮኮና ተንኮታክቶ በህዝብ ትግል የሚንበረክክበት ጊዜ እሩቅ ኣይሆንም፤ የኢትዮጵያ  ህዝብ ለነጻነት ለፍትሃና ለአኩልነት የሚያደርገው  የአመጽ ትግልና የኣልገዛም ባይነት ትግል፥ የህዝባዊ አምቢተኝነት ትግሎች ሁሉ የህወሓት ኣገዛዝ  እስኪወገድ ድረስ በየኣካባቢው አንደ ሰደድ አሳት የሚቀጣጠል እንጂ የሚቆም ኣይሆንም።

 

(ቀደም ሲል  ለንባብ ከወጣው ሰፊ  መጣጥፍ የተወሰደ)

 

የህብር ሬዲዮ ነሐሴ 29 ቀን 2008 ፕሮግራም

$
0
0

habtamu05የህብር ሬዲዮ  ነሐሴ 29 ቀን 2008 ፕሮግራም

 <…በሕዝቡ ላይ የታወጀውን የዘር ማጥፋት ተቃውሞ በመሪዎቹ ላይ እርምጃ ወስዶየሕዝቡን ትግል የተቀላቀለውን ከሁለት ሻምበል በላይ ጦር ሰራዊት የዕምቢታ ጦርየሕዝቡ አጋር ነው ይሄ እርምጃ ማደግ አለበት ነገ ከነገ ወዲያ በክፍለ ጦር ደረጃተመሳሳይ እርምጃ ወስዶ  ከሕዝቡ ጎን መቆሙን እንዲቀጥል ሕዝቡ ተገቢውን መረጃመስጠት አለበትሰራዊቱ ራሱ በሕወሓት ዘረኛ የጦር አዛዦች የተንገፈገፈ ነው።አሁንም ለመላው የሰራዊት አባላት ጥሪ አለኝ…> / ደረሰ ተክሌ የቀድሞ የሰራዊቱየጥናትና ምርምር ሀላፊ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በመሪዎቹ ላይ እርምጃ ወስዶየሕዝቡት ትግል ስለተቀላቀለው ሁለት ሻምበል ጦር ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጡትማብራሪያ(ያድምጡት)

< …  አሁን በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው ግድያና አፈና ሌላው ቀርቶ እስረኞችበታሰሩበት እየደረሰባቸው ያለው ግፍ ይሄን ሕገ ወጥ ድርጊት ነው ተብሎ የሚታለፍአይደለም።ከኢትዮጵያ አልፎ ለአካባቢው አገሮች አደገኛ አለመረጋጋት የሚያመጣእርምጃ ስለሆነ ከዚህ ቀደም የተባበሩት መንግስታት የሳዳም መንግስት ኩርዶችንሲጨፈጭፍ የወሰደውን አይነት እርምጃ ሊወስድ ይችላልየኦሮሞም ሆነ የአማራሕዝብ ሌላውም ኢትዮጵያዊ ጭምር በጋራ በትግሉ ወቅት ያነሳቸውን አብይ ጉዳዮችያካተተ የሽግግር ሰነድ ማዘጋጀት ለውጡን በጋራ ማፋጠን በጋራ ጠላት ላይ ማተኮርያስፈልጋል ከዚህ በሁዋላ… >    ሔኖክ ጋቢሳ የህግ ባለሙያና መምህር ስለወቅታዊው ሁኔታ ለህብር ከሰጠን ቃለ መጠይቅ(ቀሪውን ያዳምጡ)

የአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት ስለወቅቱ የኢትዮጵያ ፓለቲካዊ ሁኔታ በተመለከተ የስጡትአስተያየት አዲሱ የእንግሊዝ መንግስት በአቶ  አንዳርጋቸው ፅጌ ከእስራት መለቀቅሙከራ  ዙሪያ የሰጠው ምላሽ እና የመብት ተሞጋቾች እና የአቶ እንዳርጋቸው ባለቤትምላሽ(ልዩ ዘገባ)

በቬጋስ በመጪው ረቡዕ 10 ጊዜ የኢትዮጵያውያን ቀን ይከበራል በአገር ቤት ባለውወቅታዊ ሁኔታ ሳቢያ በዕለቱ የሙዚቃ ዝግጅት አይቀርብም (የኮሚኒቲው /ሊቀመንበር የሰጡትን ማብራሪያ ይዘናል)

ወታደሩ ወገኔ ሕዝብ ላይ አተኩስ(ግጥም)

ዜናዎቻችን

የቅሊንጦ እስር ቤት እሳት ሆን ተብሎ በተቀነባበረ ሁኔታ በአገዛዙ እንዲነሳ መደረጉንአንድ የእስር ቤቱ ጠባቂ አጋለጠ

 እሳቱን ጭምር ለማጥፋት በሚሞክሩ እስረኞች ላይ በቀጥታ ሲተኮስ ነበር

የአቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ የእስረኞቹ መጨረሻ አልታወቀም የሟቾች ቁጥር ከአርባበላይ ደርሷል

በወሎ ከሁለት መቶ በላይ የመንግስት ሰራተኞች አገዛዙ በአማራ ላይ ለከፈተው ጦርነት ማብራሪያ የጠራውን ስብሰባ ተቃውመው ረግጠ ወጡ

ደሴ የቤት ውስጥ አድማ ቀጠለ

የቅሊንጦ የማጎሪያ ቤቱ ጠባቂዎች በልዪ የፖሊስ ሃይላት ተተኩ

የአትዮጵያዊው ጀግናው አትሌት ፈይሳ ለሊሳ ዘመድ በአገዛዙ ታጣቂዎች ጥርሱእንደረገፈ፣እግሩ በጥይት እንደ ተመታ ተናገረ

አትሌት ፈይሳ ወደ አገሩ ከተመለሰ ሞት ይጠብቀዋልየፈይሳ ዘመድ እማኝንነት

የካናዳ መንግስት እና ሽሪኮቹ በኢትዮጵያ እየደረስ ያለው የስብዓዊ መብት ረገጣን ችላማለታቸው ታላቅ ተቃውሞ ገጠማቸው

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ጉዳይን በቅርበት እየተከታተልነው ነውካናዳ

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞችበአስቸኳይ እንዲፈቱ ጥሪ ቀረበ

*አገዛዙ ግን ዛሬም በሩን ለውጭ ታዛቢዎች አልከፍትም እንዳለ ይገኛል

/ መረራ ጉዲና ተቃዋሚዎች በመንግስት ለውጥ ላይ ብቻ ሳይሆን  ከለውጡበሁዋላ ባለ ሁኔታ በፍጥነት በጋራ መስራት አለብን ብለዋል

ሌሎችም 

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብርሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድበአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነውበእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻእንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

 

አቶ ግርማ ሰይፉ ማሩ የቀድሞው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ታስረው ተፈቱ

$
0
0

ህገ ወጥ ጦር መሳሪያ ማዘዋወር ክስ ….. ከዚያስ?

ግርማ ሠይፉ ማሩ

Girma Seifu Maru

Girma Seifu Maru

ነሐሴ 30 2008 የዓመቱ ማለቂያ ብቻ ሳይሆን የመንግሰት ሹሞች በቴሌቪዝን የሚደሰኩሩትን መልካም አስተዳደር ብሎ ነገር ጫፍ ለማስያዝ እንኳን አቅም እንደሌላቸው አስመስክረዋል፡፡ ፈይሳ ለሊሳ ማራቶን ሮጦ ሁለተኛ ሲወጣ ከሀብታሙ አያሌው ጋር አብረን እያየን ነበር፡፡ ከወርቅ በላይ ያስደሰተኝ ግፋችንን ለዓለም ማሳየቱ ነበር፡፡ ቀደምኩሁ የሚለኝ ካልተገኘ በስተቀር ሰደስታዬን በመግለፅ አንደኛ ነበርኩ፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ እንደሌሎቹ ፎቶ መለጠፍ ሳያስፈልገኝ ወሬውን ብቻ ነበር የለጠፍኩት፡፡ ዛሬ ጠዋት ደግሞ በኢሳት እንዴት ልቡ እንደራሰ ፍስሃ ተገኝ ሲያስረዳ እየሰማው ደስታዬ እንደ አዲስ ሲሰማኝ ነበር፡፡ የዚህ ደስታ ዋናው ምንጭ ነሐሴ 29 ማታ እኔ ኤሊያስ እና ዳንኤል ሸበሺ ቀኑን ሙሉ በቂሊንጦ እሳት ጉዳይ ምንም መረጃ ባለመኖሩ ስንቃጠል ውለን ማታ ብሶታችንን ለመግለጽ በምሽት ፎቶ መነሳታቸን ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን በማድረጋችን ግን እንዲህ ወርደው ይዋረዳሉ ብዬ አላሰብኩም፡፡

ነሐሴ 30 እንደ ወትሮ ከቤቴ በጠዋት አልወጣሁም ምክንያቱም የቤተሰብ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ነበር የፍስሐ ተገኝን ትንተና ከመቲ ጋር መስማት የቻልኩት፡፡ አርፍጄ ቢሮ ብገባም ቢሮ መብራት የለም፡፡ ሰለዚህ የፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴን “ የሀብተጊዮርጊስ – አባ መላን” መፅሃፍ ሳነብ ቆየው፡፡ መኪናዬን ጋራዥ ለማሳየት በዘጠኝ ሰዓት ቀጠሮ ስለአለኝ ወደዚያው ቀረብ ብዬ ምሳ ለመብላት መስቀል ፍላወር አካባቢ መኪናዬን ለአጣቢ ሰጥቼ ከጓደኞቼ ጋር ምሳ እየበላሁ እያለ ስልኬ ጮኽች መኪና አጣቢዬ ነበር፡፡ “መኪናዋ በፖሊስ ትፈለጋለች” አለኝ፡፡ ለምን? ስለው “ወንጅል ተሰርቶበታል” እያሉ ነው አለኝ፡፡ ጉዳዬን ስጨርስ እንደምመጣ ነገሬው በፌስ ቡክ ጉዳዩን ፖስት አደረኩ፡፡ ነገር ሊፈልጉኝ ካልሆነ እኔ ካልሆንኩ መኪና ወንጀል አይሰራም፡፡ እኔ ደግሞ እንኳን ከእነርሱ ጋር እየተጋፈጥኩ ተፈጥሮየም ወንጀል ይጠየፋል፡፡ መኪና አጣቢው መልሶ ደውሎ “የተሰረቀ መኪና ነው” አለኝ አለ፡፡ አሁን ነገሩ ፍንትው ብሎ ገባኝ፡፡ ትላንት ምሽት በቂሊንጦ ስለተፈጠረው ግፍ የተነሳነው እና ለህዝብ ይፋ ያደረግነው ፎቶ እንደሆነ፡፡

ወደ መኪናዬ አመራው፣ ፖሊሶች ቆሻሻ እንዳገኘ ዝንብ ወረውታል፡፡ ከሩቅ ሲያዩኝ አንድ ግዳይ የጣሉ ይመስላሉ፡፡ ቀረብ ስል ፖሊሶቹ በዓይን ያውቁኛል “ለምን እንደሆነ አናውቅም ፖሊስ ጣቢያ መኪናው ከእነ አሽከርካሪው ይፈለጋሉ፡፡” አሉኝ፣ እንሂድ አልኳቸው መኪናዬ ውስጥ ሊገቡ ሲሉ እኔ መኪና ውስጥ አትገቡም አልኳቸው፡፡ በራሳቸው መኪና እንዲሄዱ እኔም መኪናዬን ይዤ እንደምሄድ ነገርኳቸው፣ መኪና ማምጣት አልቻሉም፡፡ በመጨረሻ መሄድ የሚፈልጉትን ፖሊሶች ስንት እንደሆኑ እና ምንም ያለመያዛቸውን አጣርቼ አስገባኋቸው፡፡ እግረ መንገዴንም ለምን እንደዚህ እንደአደረኩ፣ ወረቀት ይሁን የጦር መሳሪያ አስቀምጣችሁ መኪና ውስጥ አገኘሁ ብትሉስ አልኳቸው፡፡ ደነገጡ እንዴት እንዲህ ይደረጋል ብለው ምለው ተገዘቱ፡፡ ለማነኛውም ደህንነት ተብዬው የእነሱን ዩኒፎርም ለብሶ ይህን እንደሚሰራ አስረድቼ የቆምኩለት እና ማነኛውንም ዋጋ የምከፍልለትን ጉዳይ አጥብቄ አስረዳኋቸው፡፡ ላንቻ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ጥሩ እንክብካቤ ተደርጎልኝ እንደ አቅማቸው አስተናገዱኝ፡፡

ላንቻ ፖሊስ ጣቢያ ለአንድ ሰዓት ተኩል በቁጥጥር ስር ቆየው፡፡ በመጨረሻ በጠብ መንጃ ታጅቤ እኔ በሾፌርነት ልደታ ፖሊስ መምሪያ እንድሄድ ኮማነደር በጋሻው ለኮማንደር ወጋየሁ አስተላለፈኝ፡፡ ልደታ ፖሊስ መምሪያ ስደርስ ጉዳዬ ከትራፊክ አደጋ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተነግሮኝ እንድጠብቅ ተነገረኝ፡፡ ችግሩ ቀላል መሆኑን ይህች ቂሊንጦ መታሰቢያ ፎቶ ቢያንስ በትራፊክ ወንጀል ልታስከስሰኝ መሆኑን ገመትኩ፣ ፖሊሶች ከዚህ እዚያ ይሯሯጣሉ፣ ድንገት እኔ ያለሁበት ክፍል ውስጥ አንድ ሰው ተደውሎልኝ ነው ብሎ ገባ፡፡ ተከታትለው ሌሎችም ሰዎች መጡ፡፡ ነገሩ በደንብ ገባኝ፡፡ እነዚህ ሰዎች በእኔ ላይ ምስክር ሊሆኑ እንደመጡ ተረዳሁ፡፡ በዓይነ ቁራኛ ተከታተልኳቸው፡፡ ዓይኔን ማየት አፈሩ፡፡ ፖሊሶች በተለያየ ጊዜ ይመጡና ሙሉ ስሜን ይጠይቁኝና ሄደው ለአንድ ሲቪል ለለበሰ ደህንነት ሰራተኛ ይነገሩታል እርግጠኛ ነኝ ሰሜ ያስጠኗቸውል፡፡ በመጨረሻ ትራፊክ ጉዳይ መሆኑ ተቀየረ እና ሁከት መፍጠር የሚል መሆኑ ተነገረኝ እና ቃሌን እንድሰጥ ጥያቄ ሲቀርብ ፈቃደኛ እንዳልሆንኩ ገልጬ መርማሪዎቼ ፋይሌን ይዘው ወደ ኮማንደር ቢሮ ሄዱ፡፡

ከጥቂት ቆይታ በኃላ ተመልስው ጉዳያቸውን ከባድ ስለሆነ በሚል ለውይይት ወደ መመሪያው ሃለፊ ኮማንደር ወጋየሁ ጋር ቀረብኩ፡፡ አስገራሚው ነገር በፍፁም አግኝቼው የማላውቀው የእህቴ ባለቤት አብሮኝ ተከሳሸ ሆኖ አገኘሁት፡፡ የመጣው ግርማ ታሰረ ሲሉት ባለቤቱን ተከትሎ ነው፡፡ በቃ ተከሳሽ ሆነ፡፡ ክሱ ደግሞ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር/መያዝ ሆኖ ደረጃውን አሳደገ፡፡ እነ ዶክተር ታዬ፣ ፕሮፌሰር አስራት በዓይነ ህሊናዬ መጡ፡፡ በሄድኩበት መስመር የሞተ ወይም የተገጨ ስው ሳይገኝ ሲቀር፣ ሁከት ፈጠራ ሲያንስባቸው ለማስፈራሪያ ከፍ ያለ ነገር የተገኘው “ህግ ወጥ መሳሪያ ዝውውር ሆኖ” በደህንነት ትዕዛዝ ተሰጥቶዋል ማለት ነው፡፡ በነገራችን ላይ ክስ ሲመሰረትብኝ ምስክር ሆነው የቀረቡ ሶሰት አዳፍኔዎች መጥተዋል፡፡ ግምቴ ልክ ነበር አስተኳሽ የሚባሉት ቀርበው መስክረዋል፡፡ አንፀባራቂ የፓርኪን ልብስ ለብሰው ከእኛ ቲፕ እየተቀበሉ ሆዳቸውን ይሞላሉ፤ እኛ ላይ በሀስት ምስክር የሚሆኑት ደግሞ እነዚሁ ዜጎች ናቸው፡፡ እነዚህ ከመሆን መሞት በስንት ክብሩ እንደሚሻል ማን ይንገራቸው፡፡ አንደ እናቱን ያስቸገረ ልጅ እናቱን “እኔ መቼ ነው ሰው የምሆነው?” ቢላቸው “ሰትሞት” አሉት፡፡ ሲሞት ሰው ሞተ ተብሎ ዕድር ሰለሚቀብረው፡፡ እነዚህን ሰዎች ከመሆን ሞተው የሰፈራቸው ዕድር ሰው ሞተ ቢላቸው ይሻላቸው ነበር፡፡ እነዚሁ ሰዎች የእኔን መታሰረ ስምተው የመጡ ቤተሰቦቼን አዩኝ፣ ፎቶ አነሱኝ፣ ወዘተ እያሉ ለፖሊሶች ያቀርባሉ፡፡ ፖሊሶቹም እነርሱ የሚሉትን ያዳምጣሉ፡፡ መሞት ይሻላል፡፡

ለማነኛውም ከኮማንደር ወጋየሁ እና የስራ ባልደረቦቹ ጋር በነበረን ውይይት እኔ ነፃነቴን ከማንም የማልጠብቅ ዜጋ መሆኔን አስረዳኋቸው፣ በቂሊንጦ በተፈጠረው እሳት መንግሰት በእጁ ያሉትን እስረኞች ቆጥሮ አደጋ የደረሰባቸውን ሰዎች ለህዝብ አለማሳወቁ መንግሰት ተጠያቂ እንደሆነ እና ኃላፊነት የማይሰማው መንግሰት እንደሆነ ለማስረዳት እጄን አጣምሬ ይህን ግፍ ለመግለፅ እና በዚህ ጉዳት ለደረሰባቸው ጉዳት አጋርነቴን ለመግለፅ ይህን ማድረጌ እንደ ወንጀል እንደተቆጠረ ይህን ደግሞ መቼም የማደርገው እና ከማንም ለዚህ ፈቃድ እንደማልጠይቅ አስረድቻቸው ተለያይተናል፡፡ ለጥቂት ደቂቃዎች ለብቻቸው ካደረጉት ውይይት በኋላ በዋስ እንድለቀቅ ከምሸቱ 3፡00 ሠዓት መወሰኑን ተነግሮኝ በማግስቱ ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት እንድገኝ አብሮኝ መናጆ ከሆነው የእሀቴ ባለቤት ጋር ተለቀናል፡፡ ከጥናቱ ላይ ተነስቶ ተደናግጦ የመጣው መናጆዬ ነገ ፈተና አለበት፡፡ ፈተናው ላይ የሚፈጠርበት ጫና ምን እንደሚሆን አላውቅም፡፡ ለማነኛውም እኔ ወድጄ በማደርገው እርሱ ዳፋ መግባቱ አሳዝኖኛል፡፡

ኢትዮጵያችን እንዲህ ነች መሰዋዕትነት ልንከፍል መዘጋጀታችንን ዋጋ የማይሰጡ ህግ አስከባሪዎች፣ መብታችንን ወንጅል ለማድረግ ምስክር የሚሆኑ ሆድ አደሮች፣ ሶሰት ሺ አምስት መቶ የሚጠጉ እሰረኞች በምን ሁኔታ እንዳሉ የማያውቁ የእስረኛ ቤተሰቦች ሰሜት የማይረዱ የመንግሰት ሾሞች እና ለዚህ ምንም ግድ የማይሰጣቸው ሰዎች፣ ወዘተ … በተቃራኒው ደግሞ ኮሽ ሲል የትግል አጋርነታችውን የሚገልፁ ጥቂትም ቢሆኑ ምርጦች አቅፋ በአንባገነን ስርዓት መዳፍ ውስጥ የምትገኝ ሀገር፡፡ ሆ ኢትዮጵያ ሆይ ይህንን ግፍ መዝግቢው ……

 

 

የመጨረሻው ሰዓት –ዓይን ያወጣ ጭፍጨፋ የአምባገነኖች የውድቀት ምልክት ነው –አገሬ አዲስ

$
0
0

tplf-rotten-apple-245x300.pngበዓለም ታሪክ እንደታየው አምባገነኖች በመጀመሪያው ላይ ሕዝብን በፍርሃት ለማንበርከክ ሃይልን ይጠቀማሉ፤ተቃውሞና እምቢባይነት ሲበረታባቸውና ወደመውደቁ አቅጣጫ ሲያመሩ በቁጭትና በብስጭት በበቀል የሚዘገንን እርምጃ  ይወስዳሉ።በሁለተኛው ዓለም ጦርነት የሂትለርን ታሪክ ብንመለከት ሲነሳ የብዙ አገሮችን ድንበር እየጣሰ በጦር ሃይል ለማንበርከክ ሞክሮ ነበር፣አልሳካለት ሲል በመጨረሻው ሰዓት ያደረበት ብስጭት ወደ እብደት ተለውጦ አይሁዶችንና ተቃዋሚዎቹን ሰብስቦ እንደ እንጨት አቃጥሎና  በጋዝ አፍኖ ጨረሳቸው፤ከጥቂት ቀናትም በዃላ እራሱን አጠፋና ውድቀቱ ተረጋገጠ።

በኢትዮጵያ መሬት የዜጎች ደም በግፍ ሲፈስ በወያኔ ጊዜ መጀመሪያው አይደለም።በተለያዩ ጊዜያቶች በውጭና በውስጥ ጸረ ሕዝብ ጠላቶችና አምባገነኖች ሲፈጸም የነበረና ያለ፣የተለመደ ወንጀል ነው።ከጣልያን ወረራ ወዲህ አገር በቀሎቹ  አምባገነኖች ሁሉ እንደ ባህልና መብት አድርገው ወስደውታል። የዛሬ ሃምሳ አምስት ዓመት እነጄነራል መንግሥቱ ነዋይ መፈንቅለ መንግሥት አድርገው አለመሳካቱን ሲያረጋግጡና ከሞትን አይቀር በሚል ደም ፍላት በእጃቸው ስር አስረው ያስቀመጧቸውን  የመንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣኖች በረድፍ አሰልፈው እረሸኗቸው።በዚያ ጭፍጨፋ ለአገሪቱ ብዙ የደከሙ፣በጣሊያን ወረራ ጊዜ በርሃ ገብተው ለአገር ነጻነት የታገሉ አርበኞች ይገኙበታል። በዚህ ወቅት የወታደሩ ክፍል ተከፋፍሎ ደጋፊና ተቃዋሚ በመሆን ሚና ለይቶ ተጋደለ።ጥቂቶችም የአድማው መሪዎች በዚሁ የእርስበርስ ውጊያ ተመቱ፤አስከሬናቸው በየአደባባዩ ላይ ለቀናት ተዘርሮ ሰነበተ።ሌሎቹም በተለይም በዋና መሪነት ግልበጣውን ከወንድማቸው ከገርማሜ ነዋይ ጋር ያዘጋጁት የክብር ዘበኛው አዛዥ ጀነራል መንግሥቱ ነዋይ ቆስለው በሕይወት በመያዛቸው የንጉሱ መንግሥት ከተረጋጋ በዃላ በፍርድ ቤት ቀርበው የሞት ቅጣት ተበይኖባቸው ተክለሃይማኖት አደባባይ ላይ በስቅላት ተቀጡ።

የዛሬ አርባ ሁለት ዓመት የአቶ እንዳልካቸው መኮንን ካቢኔ ሥልጣኑን ለማደላደል በሚውተረተርበት ወቅት የሕዝብ ተቃውሞ አገርሽቶበት በከርቸሌ እስር ቤት ውስጥ የሚገኙ ሳይቀሩ ለመብታቸው በመነሳት ጥያቄ ሲያቀርቡና የእስር ቤቱን አስተዳደር ሲቃወሙ፣በእስርቤቱ ጠባቂ ፖሊሶች በግፍ ተረሸኑ፡፤የብዙ ሰው ሕይወት ጠፋ።ለዚያ የግፍ ጭፍጨፋ መንግሥት የሰጠው መልስ እስር ቤት ሰብረው ሊወጡ የሞከሩ ወንጀለኞች ላይ እርምጃ እንደተወሰደ የሚገልጽ ነበር።የአቶ እንዳልካቸውን ካቢኔም አልቆየም ከሥልጣኑ በወታደሮች ቡድን ተወግዶ አብዛኞቹ ባለሥልጣኖች ጋር ወደ እስር ቤት ተወረወሩ። በተፈጠረው ክፍተት ተጠቅሞ የሥልጣን እርካቡን  ከሕዝቡ ፍላጎት ውጭ በመንጠቅ ደርግ የተባለው ሰውበላ የወታደር መንጋ በቦታው ተተካ።ይኸው ቡድን ሲነሳ “ያለምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም” በሚል ቃለ ተስፋ ቢሆንም ውሎ ሳያድር አገሪቱን በደም አጨቀያት። በተነሳበት የሕዝብና የወታደር ተቃውሞ በአደባባይ በግፍ ብዙ ሰዎችን እረፈረፈ፤ተቃውሞው አገር አቀፍ እየሆነ ሲመጣ በውስጡ መረበሽና ተስፋ መቁረጥ ሰፈነ።ቡድኑ  ከሕዝቡ አልፎ እንዲመሩት ቀዳሚ ሊቀመንበርና እርእሰብሔር አድርጎ ከመረጣቸው ጄነራል አማን አምዶም ጋር ተፋጠጠ።በአንዳንድ የወታደር ክፍሎች በተለይም በአርሚ አቪየሽንና በመሃንዲስ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ከመፈታተን ደረጃ ላይ ሲደርስ ባልተጠበቀ ከቦ የማጥቃት እርምጃ ብዙዎችን ገሎ ሌሎቹን አስሮ በቁጥጥሩ ስር አደረጋቸው።

ተቃውሞው ግን አልበረደም ነበር።በተለይም ከጄነራሉ ጋር የተፈጠረው ፍጥጫ ከወሳኝ ደረጃ ላይ በመድረሱ በደርግ ዙሪያ ትልቅ ስጋትና ሽብር ተፈጠረ፡፤የጄነራሉ እምቢተኛነት በወታደሩ ውስጥ ካላቸው እውቅናና ክብር ከጀርባው ያሰለፈ ሃይል ሊኖር ይችላል የሚለው ስጋት እየጎላ መጣ።ጄነራሉን በማባበል ለማለሳለስ የተደረገው ጥረት ፍሬያማ ባለመሆኑ ከመቀደም መቅደም በሚል ስልት፣ጄነራሉን ከሚኖሩበት ቤት በመክበብ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ገደላቸው።ይህ እርምጃ ሊያስከትል የሚችለው ዋጋ ከፍተኛ ሆኖ ስለታያቸው፣ብሎም የተስፋ መቁረጥና የእብደት ስሜት ስላደረረባቸው ከነጄነራል መንግሥቱ ነዋይ ተመክሮ በመውሰድ ከሞትን አይቀር ሁሉንም በእጃችን ስር ያሉትን ገለን እንሙት ከሚለው ውሳኔ ላይ ደርሰው በገፍ ሰብስበው በአሰሯቸው ሃምሳ ሶስት የቀድሞ ባለሥልጣኖችና ሰባት ከወታደሩ የተውጣጡ ተቃዋሚዎቹ ላይ የሚዘገንን የግድያ እርምጃ ወስደው አገር አቀፍ ድንጋጤና ፍርሃት አሰፈኑበት።በወታደሩም ውስጥ ድፍረት ሳይሆን ሽብር ለቀቀበት።ይነሳብናል ብለው የጠበቁት የበቀል እጅ ሳይነሳ በመቅረቱ ለአስራሰባት ዓመት የአምባገነኖች የፍርሃት ድባብ መስፈንና  የሕዝቡን ስነልቦና የሰበረ አረመኔያዊና ኢሰብአዊ አድራጎት እንዲቀጥል ያበረታታ ነበር።ደርግ በሥልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ በአገሪቱና በሕዝቡ ላይ ያደረሰው በደል በአጭሩ ተነግሮ አያልቅም።በየወቅቱ በሕዝቡና በራሱ ውስጥ የተነሱትን ተቃዋሚዎች ፍጹም አረመኔያዊ በሆነ የግድያ እርምጃ አሶገደ።በነጄነራል ተፈሪ በንቲ፣በነኮሎኔል አጥናፉ አባተ ላይ የተወሰደው የግድያ እርምጃ የዚህ አካል ነው።ለተወሰነም ጊዜ ቢሆን የበረደ ቢመስልም በሕዝቡና በወታደሩ ውስጥ የነበረው ተቃውሞ ውስጥ ውስጡን ይብላላ ነበር እንጂ አልቆመም። በመጨረሻው ሰዓት ላይ በ1982 ዓ.ም. በከፍተኛ  የጦር መኮንኖች የተወጠነ አድማና የመገልበጥ ሙከራ ተደረገ።ምንም እንኳን ቢሳካ ኖሮ የተሻለ ለውጥ ይመጣ ነበር ብሎ መገመት ባይቻልም ሆኖም ግን ያም ከዝግጅት ድክመት የተነሳ ሳይሳካ ቀረና ከተሳተፉት መካከል ብዙዎቹ ተይዘው ካለፍርድ በመንግሥቱ ሃይለማርያም ውሳኔ በአንድ ሌሊት ከአስራአምስት የሚበልጡ ጄነራሎችና ከአርባ በላይ በጠቅላላው ከስልሳ የማያንሱ ከፍተኛ መኮንኖች ተረሸኑ። ይህ መውደቅን ያበሰረ የመጨረሻው ሰዓት አድራጎት ነበር።ዓመት ሳይሞላው ደርግ የተባለው በደም የበሰበሰው ስርዓት ፈራርሶ እንደጉም ተበተነ።

ከአስራ ሰባት ዓመት በዃላ በተቃዋሚ ስም፣ከጫካ ተንደርድሮ ቤተመንግሥት የገባው ቡድን  በደርግ የተፈጸመውን የግፍ ጭፍጨፋ በጊዜው ከሚቃወምባቸው ነጥቦች  ዋናውና አንዱ ነበር።ስልጣኑን ሲረከብ ግን በነጮቹ መንግሥታት በተለይም በእንግሊዝና በአሜሪካኖቹ ተሳትፎ  በተደረገው ድርድር በደርግ ዘመነመንግሥት በገፍ የሕዝብ ደም ያፈሰሱት ብዙዎቹ  ከዋናው ተጠያቂ ከአረመኔው መንግሥቱ ሃ/ማርያም ጭምር ወደ ፈለጉበት አገር እንዲወጡ አደረገ።ሕዝቡን ለማወናበድ ጥቂቶችን ይዞ  እስር ቤት አጉሮ ለይስሙላ ለፍርድ አቀረበ።በዛን ጊዜ ከዓለም ማህበረሰብ ተብየው ስብስብ ለቀረበበት ጥያቄ የሰጠው ምላሽ “ ሕዝብ የበቀል እርምጃ እንዳይወስድባቸው ለራሳቸው ደህንነት ሲባል የተደረገ እርምጃ ነው” የሚል ነበር።እንዳለውም ከጥቂት ዓመታት እስራት በዃላ ጥፋታቸውን አምነው ሕዝቡን ይቅርታ ሳይጠይቁ ሁሉንም በነጻ ለቀቀ። የተግባር አንድነቱን አሳዬ።የህዝቡ ደምም በከንቱ ፈሶ ቀረ።ተጠያቂዎቹም በየአገሩ ባሰደዱት ህብረተሰብ መሃል ገብተው፣ስደተኛ በመሆን  በስደተኛ ወንበር ላይ ተቀምጠው የተደላደለ ኑሯቸውን ቀጠሉ።በፈጸሙት ግፍ በመጸጸት ፈንታ እየተኩራሩ ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል እንዲሉ የፈጸሙት ወንጀል ተገቢና ሕጋዊ አድርገው በመከራከር መጽሃፍ ጽፈው የገበያ ሸቀጥ አደረጉት።በሥልጣን ዘመናቸው የኢትዮጵያውያኑን ሕይወት እንደበዘበዙት ሁሉ በስደት ዘመናቸውም ገንዘቡንም በዘበዙት።

የወያኔ ባለሥልጣኖች ከደርግ ባለሥልጣኖች የሚለዩበት ነገር ቢኖር ቢወገዱ በስደተኛ ሳይሆን በየአገሩ ኢንቬስተር በመሆን የሚኖሩበትን የገንዘብ አቅም ማካበታቸውና ማዘጋጀታቸው ነው።በሂደትም በመታየት ላይ ያለው ይኸው ነው።ልጆቻቸውንና ቤተሰባቸውን ቀድመው በማሶጣትና ቤትና ቋሚ ንብረት በመግዛት ፣በየኩባንያው የሽርክናና ባለቤትነት ድርሻ (share) በመያዝ የወደፊት ኑሯቸውን አደላድለዋል።በሚሊየን ከዛም በላይ የሚቆጠር ዶላር የሌለው ባለሥልጣን የለም።ማንኛውም አገር ባዶ እጁን የሚመጣ ስደተኛን እንጂ ብር ተሸክሞ የሚመጣን ወንጀለኛ አይጠላም፣ የወጡትን እጁን ዘርግቶ ተቀብሏቸዋል፣የቀሩትንም ሲወጡ በክብር ይቀበላቸዋል።ሰብአዊ መብት ጥሳችዃል፣ ሕዝብ ገላችዃል፣አገር ዘርፋችዃል፣ወንጀለኞች ናችሁ ብሎ አይጠያቃቸውም።

የወያኔ ዘረኛ ቡድን ከደርግ የሚለየው ነገር ቢኖር በዘር ደረጃ የተዋቀረ መሆኑ እንጂ በሥልጣን አያያዙና በሚከተለው  መመሪያው አይደለም።ሁለቱም ጸረ ሕዝብና አምባገነንነትን የሚከተሉ ቡድኖች ናቸው።ደርግ ተቃዋሚውን  አናርኪስት/ስርዓተ አልበኛ፣የአሮጌው ስርዓት ናፋቂ፣…በማለት ያሳድድ፣ይገል፣ያስር ነበር።በዚህ ስልት ሕዝቡ በፍርሃት ለአስራ ሰባት ዓመት የእሳት ሰንሰለት ተሸክሞ ኖረ።እሱንም ተክቶ አሁን በስልጣን ላይ ያለው ቡድን በተመሳሳይ ደረጃ ላለፉት ሃያ አምስት አመታት ተቃዋሚውንና ለመብቱ የቆመውን ማሳደድ ስራዬ ብሎ ያዘው።ብዙዎችን አሳደደ፣አሰረ፣ገደለ። ለሚወስደው ጨካኝ እርምጃው የሰጠው ምክንያት የአገርን አንድነት የሚያናጋ፣ሰላምና እድገትን የሚጻረር ተግባር ላይ የተሰማሩ፣የደርግና የቀድሞ ስርዓት ደጋፊዎች፣ አቀንቃኞች፣ነፍጠኞች፣አሸባሪዎች  የሚል ነው።በዚህ አረመኔያዊ አገዛዝ እጅ የብዙሃን ደም በሜዳ ላይ ፈሰሰ፣ገዳዮችም ተሾሙበት፣ተሸለሙበት።ፍትህና ሕግ ትርጉሙን አጣ።የአገራችን መሬት የደም ገንዳ/አሸንዳ ሆነ።

በተከታታይ ለፈጸመው ወንጀል ባለመጠየቁ በአጉል እብሪት አሁንም ግድያውን ሥራዬ ብሎ ቀጠለበት።ላለፉት አስር ወራት በኦሮሞው ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በአማራው ማህበረሰብ ላይ የግፍ መረቡን ዘርግቶ በጠራራ በየአውራ መንገዱ አያሌ ህይወት አጠፋ፣ብዙዎች ቆሰሉ፣ታፍሰው በየእስርቤቱ ተወረወሩ።በአደባባይ የፈጸመው ግፍ አልበቃ ብሎት  አሁን የሕዝብ ትግል በየቦታው ሲቀጣጠልና የመገርሰሱ አደጋ ገሃድ እየሆነ ሲመጣ፣ በደም ፍላትና ተስፋ መቁረጥ በአዘዞ፣በደብረ ታቦር፣ በጎንደር፣በአምቦ፣ በቂሊንጦ እስር ቤት ውስጥ በእጁ ላይ ያሉትን እስረኞች በእሳትና በመትረየስ ፈጃቸው።ይህን ግፍና አረመኔ ተግባር በስማቸው የሚነግድባቸው የትግራይ ተወላጆች አብዛኛዎቹ ከጥቂቶቹ በስተቀር በጸጋ የተቀበሉት በሚመስል መልኩ በዝምታ ተመለከቱት። በሌላው ላይ የሚደርሰው በደል፣የሌላው ቁስል እንደሰው ሳይሰማቸው ቀረ።በዚህም አላበቃም በየቦታው ድግስ እየደገሱ ወንጀለኛውን  መንግሥታቸውን እየጨፈሩ አሞገሱት፣ሕዝቡን ተሳለቁበት፣ ዛቱበት። ይበልጥም ጥላቻው እንዲበዛ የሚደግፉት መንግሥት በራሳቸው ላይ ወንጀል እየፈጸመ ሌላው በጥላቻ የፈጸመባቸው በማስመሰል የሚነዛውን ወሬ አሜን ብለው ተቀበሉት።ቀጣዩ የአረመኔው መንግሥት እርምጃ በየቦታው ቦምብ በመወርወር ጥቃቶችን በስውር እያከሄደ ሌላውን በመወንጀል ብዙ ሕዝብ ለመፍጀትና አገሪቱን የበለጠ ቀውስ ውስጥ ለመክተት እንደሆነ የታ ድርጊትና ሾልኮ የወጣው መረጃ ያረጋግጣሉ።

ለአለፉት ሃምሳ ዓመታት የተደረጉት የግፍ ጭፍጨፋዎች በተለይም በእስራት ላይ ባሉ አቅመቢስ በሆኑት ዜጎች ላይ የሚወሰደው የግድያ ውሳኔ የአምባገነኖች የእብደት ባህርይ፣ የተስፋ መቁረጥና የመጨረሻው ሰዓት ምልክት እንደሆነ እንረዳለን።

ለዴሞክራሲና ለሰብአዊ መብት ቆመናል የሚሉት የውጭ አገር መንግሥታትም አይተው እንዳላዩና ሰምተው እንዳልሰሙ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው አለፉት።የዜና ተቃማቱና ጋዜጠኞችም በከተማቸው አንድ ውሻ መኪና ገጭቶት ቢቆስል በየዜና መድረኩ የሚያስተጋቡትን ያህል ቀርቶ የግማሹን ያህል እንኳን በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተፈጸመውንና በመፈጸምም ላይ ያለውን ጭፍጨፋ ለደቂቃም ትኩረት አልሰጡትም።ዜጎቻቸው በሚያካሂዱት ንብረት ላይ አደጋ ሲደርስ ብቻ ያስተጋባሉ።መንግሥታቱ ተደጋግሞ ለቀረበላቸው አቤቱታም ደንታ አልሰጡትም፣እንደውም ምርጫቸው የንጹሃን ደም የሚያፈሰውን አረመኔ ስርዓት መርዳትና መንከባከብ  ነው።

ከጥቂት ጊዜ ወዲህ የሕዝቡ ትግል እየገፋ ሲመጣ   ሁለት ባላ ትከል አንዱ ቢሰበር ባንዱ ተንጠልጠል እንዲሉ ከወያኔ ያልተሻሉና ለጥቅማቸው የቆሙ ቡድኖችን በማሰባሰብ የጥገና ለውጥ እንዲደረግ ሙከራ በመደረግ ላይ ነው የሚለው ወሬ በስፋት ይነገራል።በአሜሪካና በአውሮፓ መሪዎች  የፖለቲካ  ማድቤት የሚፈተፈተው ድግስ  ይህን የሚመስል ነው።ምርጫቸው ያለው መንግሥት ተጠግኖ እንዲቀጥል ሲሆን የሕዝቡ ትግል ከቀጠለና የወያኔ ዕድሜ የሚያጥር መስሎ ከታያቸው በሌላ መሰል አገልጋይ ቡድን እንዲተካ ማድረግ ነው።በምንም መንገድ የአገሩን ጥቅም አሳልፎ የማይሰጥ አገር ወዳድ የሕዝብ መንግሥት እንዲመጣ አይፈልጉም።በኢትዮጵያ ውስጥ የሕዝብ መንግሥት መምጣት ማለት ሌላውን የአፍሪካ ሕዝብ ለዳግመኝ አልገዛም ባይነትና ጸረ ብዝበዛ ለውጥ የሚቀሰቅስ ስለሚሆን እንዳይሳካ የተቻላቸውን ሁሉ ያደርጋሉ።

በቅርቡ በአውሮፓ ማህበር/ፓርላማ/ ጣራ ስር አንድ ስብሰባ ተጠርቶ ነበር፡፤ስብሰባውን የጠሩት አና ጎመሽ የተባሉት የፖርቱጋል ሶሻሊስት ፓርቲ ተጠሪ ሲሆኑ በቢሮዋቸው ባደረጉት በዚህ ስብሰባ ላይ በቅርብ የሚያውቋቸው ሌሎች የአውሮፓ ፓርላማ አባላት ተገኝተው ነበር።በዚህ ስብሰባ ላይ ከኢትዮጵያውያኑ በኩል ከተጋበዙት አብዛኛዎቹ በጎሳ የተደራጁት ናቸው።ከነዚህም ውስጥ፣የኦሮሞ፣የአፋር፣የሲዳማ፣.የኦጋዴን፣ወዘተ ድርጅት ተወካዮች ሲሆኑ በአገር አቀፍ ትግልና በአንድነት ሃይሉ ጎራ የተሰለፉ  ግለሰቦችም ተካፍለው በአጠቃላይ በአገሪቱ ያለውን ሁኔታ ለማስረዳት ሞክረዋል። አገር አቀፍ አቋም ያላቸው አብዛኛዎቹ የፖለቲካ ድርጅቶችና ግለሰቦች ግን  አልተሳተፉበትም። የስብሰባ መካሄድ ለጥቂቶች  በምስጢር የተላለፈ ጥሪ ነበር ማለት ይቻላል።በስብሰባው ላይ የተሳተፉትአብዛኛዎቹ ችግሩ አገር አቀፍ እንደሆነ ቢገልጹም በተደጋጋሚ በተናጠልም ሆነ በጋራ የሚያቀርቡት  አቤቱታ መንግሥት በሕገመንግሥቱ የሰፈረውን የራስን ዕድል በራስ የመወሰንና የማስተዳደር መብት አላከበረም የሚል ነው፤ይህ ማለት በአንቀጽ ሰላሳ ዘጠኝ ስር የተቀመጠው መብት ሙሉ ለሙሉ አልተከበረልንም (የመገንጠልን መብት ጨምሮ) ማለት ነው።እንደሚታወቀው የከባቢ አስተዳደሩን የተረከቡና በሌላው ተወላጅ ነዋሪ ላይ የፈለጉትን እንዳደረጉና በማድረግም ላይ እንዳሉ አይካድም።ግን በዚያ ብቻ የረኩ አይመስልም።ከወያኔ ጋር ያላቸው ትንቅንቅ ሙሉ ለሙሉ አንቀጹ ተግባራዊ ይሁን በሚል ዙሪያ እንደሆነ የፖለቲካ አቅጣጫ የሚከታተል ሊገነዘበው ይችላል።ከወያኔ ጋር በብዙ ሲስማሙ የሚለያዩበት የአንቀጽ ሰላሳ ዘጠኝ አተረጓጎም ላይ ብቻ ነው። አሁን በዚህ ስብሰባ ላይ አቀራረባቸውን በመለወጥ የለዘበ አቋም የሚከተሉ መስለው በስብሰባውና ከስብሰባው በዃላ ለጀርመን ራዲዮ ዘጋቢ በሰጡት ማብራሪያ ለማሳየት ሞክረዋል።በቦታው በነበሩ ታዛቢዎች አስተያየት ግን የዓላማ ለውጥ  አድርገው ሳይሆን ያደረጉት የስልት ለውጥ ነው ሲሉ ተችተዋል።ቂጣም እንደሁ ይጠፋል ሽልም እንደሁ ይገፋል ነውና  የወደፊቱን የምናየው ይሆናል።

ይህ ስብሰባ በአውሮፓ ፓርላማ እውቅና ያገኘና የተዘጋጀ ሳይሆን በአንድ ግለሰብ በአና ጎመሽ አነሳሽነት የተደረገ እንደሆነ መገንዘብ ተገቢ ነው።በስብሰባው ላይ የተገኙት አንዳንዶቹ የፓርላማ አባላት  የአገራቸውን ጥቅም የሚያስጠብቅላቸው አማራጭ በማጣታቸው የተቸገሩ እንደነበረና አሁን ግን በዚህ ስብሰባ ምልክት እያዩ መምጣታቸውንና በየመንግሥታቸው በኩልም የተቻላቸውን ለማድረግ እንደሚሞክሩ ተናግረዋል። ወይዘሮ አና ጎመሽ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለረጅም ጊዜ ትኩረት የሰጡና በአውሮፓ ፓርላማ ውስጥ ሽንጣቸውን ገትረው የሚከራከሩ ግለሰብ ናቸው።የአሁኑም እርምጃቸው ሌሎቹ የፓርላማ አባላት ግንዛቤ አግኝተው ከጎናቸው እንዲቆሙ ለማድረግ ነው።ይህ ሂደት ግን በአንዳንዶቹ ኢትዮጵያውያን በኩል የአውሮፓ ፓርላማ ተሰብስቦ በኢትዮጵያ ላይ ውሳኔ እንዳስተላለፈ ተደርጎ ሲናፈስ ተስተውሏል፤ይህ እራሱ የአውሮፓን ገጽና አቋም በተሳሳተ መልኩ እንዲታይና ኢትዮጵያውያኑ ከትግላቸው ይልቅ በውጭ ሃይል እንዲተማመኑና ተስፋ እንዲጥሉ የሚያደርግና የሚያማልል ነው።እነሱ የሚፈልጉት ጥቅማቸው መጠበቁን እንጂ የኢትዮጵያ አንድነት መከበሩን፣የ ዴሞክራሲ ስርዓት መስፈኑን አይደለም። በማንኛውም ስርዓት ስር ቢሆን፣ በትልቋ ኢትዮጵያም ይሁን በተበጣጠሰች ኢትዮጵያ የሚፈልጉትን ካገኙ ዓይናቸውን አያሹም፤እንደውም በተዳከመ ደረጃ ላይ ባለ አገር ውስጥ የሚኖራቸው ቁጥጥር የባሰ ይሆናል።ስለሆነም በእነሱ ላይ ተስፋ መጣልና እንደአማራጭ ለሚያዋቅሩት ስብስብ በር መክፈት ወይም አሁን በሚካሄደው የወያኔ አረመኔ ተግባር ተደናግጦና ፈርቶ ከትግሉ ማገፈግፈግ ለቀጣይ ጥፋት እድል መስጠት ይሆናል። የተከፈለው መስዋእትነት ተከፍሎ የተጀመረው  ኢትዮጵያን አድኖ ለተሻለ ስርዓት የሚያበቃውን ትግል ከዳር እንዲደርስ ሁሉም ለውጥ ፈላጊ የቻለውን አስተዋጽኦ ማድረግ ይኖርበታል። በሽርፍራፊ የጥገና ለውጥ አረመኔው ቡድን እንዲቀጥል ወይም ከሕግ ተጠያቂነት እንዲሰወር ማድረግ ወይም በተመሳሳይ መንገድ የጎሳ ስብስብ የሆነ አዲስ መጥ አምባገነን ቡድን በተራው እንዲገዛ መፍቀድ ስህተት ብቻም ሳይሆን በራስ ላይ መፍረድ ነው።ለሁሉም የሚበጀው ሰብአዊነትና ዲሞክራሲ የሰፈነባት ኢትዮጵያ እንድትፈጠር ማድረግ ነው፤በዚያን ጊዜ የሁሉም ጥያቄና መብት መልስ ያገኛል፤ይከበራልም።የጎሳ መብት መከበር ማለት የሁሉም ሰው መብት የሚከበርበት ማለት አይደለም፤አለመሆኑንም በሽርፍራፊው የጎሳ መብትና አስተዳደር እያየነው ነው።

በሁሉም ኢትዮጵያውያን ምርጫ እንጂ በጥቂት ጎሰኞችና በውጭ ሃይሎች እርዳታ፣ፈቃድና ፍላጎት የምናድርበት ጊዜ ማክተም አለበት።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለው አማራጭ አንድ ነው።ተባብሮ መታገል! ለዚያም በየፊናው የሚታየው በክልልና ጎሳዊ ስሜት በተናጠል የራስን ጥቅም የማስከበሩ እሩጫ መቆም ይኖርበታል።ተቃዋሚ ነን የሚሉ የፖለቲካ ቡድኖች/ድርጅቶች ተባብረው ከሕዝቡ ጋር ተሰልፈው አመራር ሊሰጡ ይገባል።የሕዝቡን ትግል የነሱ ከውጭ አገር መንግሥታትና ከአረመኔው መንግሥት ጋር  ለሥልጣን የመደራደሪያ ዕድል አድርገው መጠቀም አይገባቸውም።ፊታቸውን ወደ ሕዝባቸው መመለስ ይኖርባቸዋል። ለውጭ መንግሥታት እኔ ከአለው መንግሥት የምሻል የጥቅማችሁ አስከባሪ እሆናለሁ ብሎ እራስን ማዋረድና ለባርነት የማጨት አዝማሚያ መቆም አለበት አለበት።በሥልጣን ላይ ያለውን ቡድን ለሥልጣን እንዳበቁትና ለቀውሱና ጥፋቱ ሁሉ ተጠያቂዎች እንደሆኑ እየታወቀ እነሱን መማጸን አያዋጣም፤የሚያዋጣው በራስ መተማመንና የተበታተነውን ሃይል ሰብስቦ ማታገሉ ነው።ለስልጣን ከሚደረገው ሽኩቻ ይበልጥ አገርና ሕዝብ የማዳኑ ጉዳይ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል።

1.በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር ለኢትዮጵያ አንድነትና ለተሻለ ስርዓት የሚደረገውን ሕዝባዊ ትግል በዲፕሎማሲና በቁስ መርዳት፣

2.ለቆሰለው ሕክምና ለተፈናቀለው መቋቋሚያ፣ለታሰረው ስንቅ፣ማቅረብ  የሚችል አንድ የክፉ ቀን ፈጥኖ ደራሽ የሆነ ብሔራዊ የእርዳታ አስተባባሪ አካል በአስቸኳይ ማቋቋም።በየቦታው በልዩልዩ ስም የሚደረገው ጥረት መልካም ቢሆንም የበለጠ ፍሬያማ ለማድረግ ወደ አንድ ብሔራዊ ተቋም ቢሰባሰብ የተሻለ ይሆናል።

3.በተጨማሪም ሰብአዊ መብት ሲረገጥና ሕግ ሲጣስ የሚከራከርና የሕዝቡን መብት የሚያስከብር የሕግ ባለሙያዎች ቡድን ማቋቋም ወይም የተቋቋመ ካለ ማጠናከር፣ከሰብአዊ መብት አስከባሪ ተቋማት ጋር ተባብሮ መስራት የሚቻልበትን ዘዴ መንደፍ፣

4.የተዛባ ዜና ከማቅረብ የራቀ ታማኝነት ያለው የሕዝብ ድምጽ የሆነ የሚዲያ አሰራር መሟላት፣ የሶሻል ሚዲያዎችን በስፋት መጠቀም፣

ከዚህ በላይ የተገለጹትንና ሌላውንም አስፈላጊ ተግባር ለማከናወን በውጭ አገር የሚገኙትንና በተናጠል የሚንቀሳቀሱትን ስብስቦችና ማህበራትን በማቀናጀት በተባባረ ጉዞ እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ የሚችል እነሱን ያካተተ ማእከል መፈጠር አስፈላጊና ወቅታዊ ነው። በየቦታው ያሉት ስብስቦች ይብዛም ይነስም ብዙ ተግባራትን እንዳከናወኑ መካድና መዘንጋት አይገባም።እነሱን ማጠናከር እንጂ ከነሱ የተለዬ ሌላ እንደ አዲስ ለመጀመር መነሳትም ጊዜ ከማባከኑም ባሻገር አላስፈላጊ አለመግባባት ሊፈጥር ይችላል።ጥረታቸው እንዲሰምርና እንዲሳካ በጋራ የሚመራና ከአገር ቤቱ ትግል ጋር የሚያቆራኝ አካል ለመፍጠር የሚረዳ በአስቸኳይ ሁሉንም የሚያሳትፍ ጉባኤ መጥራት አስፈላጊ ነው።ጉባኤው የቅርብና የሩቅ ተግባራትን መርምሮ የሚያስቀምጥና በተግባር ሊተረጉሙ የሚችሉትን መርጦ አላፊነቱን የሚሰጥ ይሆናል።

ለድል ወይም ለውድቀት ከወሳኝ ሰዓት ላይ ደርሰናል!ከተባበርን እናሸንፋለን፣ካልተባበርን እንሸነፋለን።

አገሬ አዲስ

ገደብ የሌለው ድንቁርና !  – nፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)

$
0
0

 

መስከረም 6፣ 2016

መግቢያ

TPLFካለፈው ህዳር ወር ጀምሮ እስከ ዛሬ ነሃሴ ወር ድረስ በአገራችን ምድር በህዝባችን ላይ አንድን አገር አስተዳድራለሁ ከሚል፣ ከዘጠና ሚሊዮን በላይ የሚቆጠርን ህዝብ ብቻ ሳይሆን፣ የሚቀጥለውንም ተከታታይ ትውልድ ህይወትና ዕድል የሚወስን አገዛዝ በጭፍን የሚያካሂደው ጭፍጨፋ፣ መደብደብና ማሰቃየት፣ እንዲሁም ካለምንም ማስረጃ እስርቤት ውስጥ መክተት አብዛኛዎቻችንን ያንገበግበናል፣ ያስለቅሰናልም። ማንኛውምን ከህዝብ ወገን የሚነሱ ቅሬታዎችን አዳምጦ በሰላም ማስተናገድና መፍታት እንደ መሞከር ይልቅ አገዛዙ ሆን ብሎ የያዘው ህዝብን ማስፈራራት፣ ማንገላታት፣ መግደልና፣ የተቀረውን ደግሞ እስርቤት ውስጥ መወርወር ሆኗል።

ባለፉት 25 ዓመታት ይህ አገዛዝ ጸባዩን እንዲያሳምር፣ ህብረተሰብአዊ ባህርይ እንዲኖረውና፣ የህዝብን ቅሬታዎችና የሚደርስበትን በደል ሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ እንዲያስተናግድ ያላደረግነው ጥረት ይህ ነው አይባልም። ከሌሎች ሁለት አገዛዞች ጋር ሲወዳደር ይልቅ ይህንን አገዛዝ በተቻለ መጠን እሹሩሩ በማለት ጸባዩን በማሳመርና ህዝባዊ ባህርይ ኖሮት የህዝብ ቅሬታዎችን በስነስርዓት እንዲያስተናግድ ሁላችንም በመሰለን መንገድ ድምጻችንን አሰምተናል። በአብዛኛዎቻንንም ዘንድ እንደዚህ ዐይነቱን ሰላማዊና የማስተማር መንገድ እንድንከተል ያስገደደን፣ አንድም ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ በታሪክ አጋጣሚ ሆኖ ከአንድ ብሄረሰብ የተውጣጣ በመሆኑ ትግላችን ወደ ማይሆን መንገድ እንዳይሄድ ለማድረግ ሲሆን፣ በሌላ ወገን ደግሞ ባለፈው 40 ዐመታት ህዝባችን ብዙ ስቃይንና ፈተናን የቀመሰ ስለሆነ ያለው አማራጭ መንገድ ሌላ ሳይሆን በማስተማርና በመቻቻል ላይ የተመሰረተ ሰላማዊ ትግል ከማካሄድ በስተቀር ሌላ አማራጭ ሊኖር አይችልም ብለን በመገንዘባችንም ጭምር ነው።  ይህ ብቻ ሳይሆን፣ ከብዙ አገሮችና ከአገራችንም ልምድ እንዳየነውና እንደተማርነው ከጦር ትግል ይልቅ በአርቆ አስተዋይነትና  በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ትግል ለአንድ ህብረተሰብ ዕድገት አማራጭ የሌለው ዘዴ መሆኑን በመረዳታችን ነው። ከተለያየ አካባቢና ብሄረሰብ የመጣንና የተለያየ ቋንቋ የምንነጋገርም ቢሆን፣ በሌላ ወገን ደግሞ ሁላችንንም የሚያስተሳስሩን ብዙ ነገሮች አሉ።  በታሪክ ሂደት  ውስጥ   እየተዋሃድንና አንድ  ሁላችንንም የሚያግባባ ቋንቋ፣ ኋላችንንም የሚያስተሳስረን ባህል፣ የምግብ ዐይነት፣ የአለባበስ ዘዴና ሌሎች ልዩ ልዩ ነገሮች የሁላችንም መግለጫ እየሆኑ የመጡበትን ሁኔታ እንመለከታለን። ስለሆነም የአንድን ህብረተሰብ ህግ ሂደት ካለመረዳት የተነሳ ባለፉት መቶ ዐመታት በተለያዩ አገዛዝ ጭቆናዎችና በደሎች ቢደርሱም ከህብረተሰብ ምስረታና ከሳይንስ አንጻር ልንክደው የማንችለው ሁኔታ ተፈጥሯል። ይኸውም ኢትዮጵያን እንደ አገራችንና እንደ አንድ ወጥ ህብረ-ብሄር፣  ይሁንና ግን ደግሞ የተለያዩ ብሄረሰቦችን ያቀፈች መሆኗን አምነን የተቀበልን ብዙዎቻችን ነን። ይሁንና ግን ይህ ያልተዋጠላቸውና ጊዜን የሚጠባበቁ ኃይሎች አጋጣሚን በመጠቀም እነሱ ከሌሎች ጋር ሲወዳደሩ በታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልክ ከፍተኛ ወንጀል እንደደረሰባቸው በማውራትና፣ በወጣቱና በተከታዩ ትውልድ ጭንቅላት ውስጥ በመትከል አንድ ህዝብ መስራት ያለበትን ታሪካዊ ስራ እንዳይሰራ አድርገውታል፤ እያደረጉትም ነው። ተጠራጣሪ በማድረግ በራሱ ላይ ዕምነት እንዳይኖረው እያደረጉ ነው። የህብረተሰብ ህግና ዕድገት አስቸጋሪ ሁኔታ ባለማጤን ወጣቱ የዝቅተኛ ስሜት እንዲኖረው የሚሆነውን የማይሆነውን በማውራት መተባበርና መከባበር እንዳይኖር  አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ፈጥረዋል።  በዚህም አካሄዳቸው በወንድማማች ህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ጥላቻንና አለመተማመንን ፈጥረዋል።  ለውጭ ኃይሎች የተገዙና ልዩ ተልዕኮዎች ያላቸው ይመስል ሆን ብለው የያዙት ስራ  አንዱን ጎሳ ከሌላው ማጋጨትና ደም እንዲፋሰስ ማድረግ ነው። በሃማኖትና በጎሳዎች መሀከል የባሰውኑ ክፍፍል እንዲኖር በማድረግ ህዝባችን በዘለዓለማዊ ፍጥጫ ውስጥ እንዲኖር  የማይሰሩት ሰይጣናዊ ስራ የለም።

ከዚህ ስንነሳ የወያኔ አገዛዝ ስልጣን ላይ ከወጣበት እስከዛሬ ድረስ ኢትዮጵያችንን እንደ አገሩ፣ ህዝባችንን እንደ አካሉና ስልጣን ላይ ያለ ኃይልም በመሆኑ የታሪክና የህዝብ ግዴታ እንዳለበት በፍጹም የተገነዘበ አይመስልም። ተጠሪነቱ እሱን አምነው ለሚከተሉት ጥቂት አጎብዳጆችና ለውጭ ኃይሎች ይመስል ባለፉት ሃያ አምስት ዐመታት በታሪካችንና በህዝባችን ላይ በቀላሉ ሊቀረፍ የማይችል በደል ሰርቷል፤ ዛሬም እየሰራ ነው። ህዝባችንና አገራችንን መሳቂያና መሳለቂያ አድርጓል። እንደ አንድ የገዢ መደብ የአገራችንን ብሄራዊ ነፃነታችንን ከማስከበርና በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ጠንካራ አገር ለመገንባት ማንኛውንም ጥረት  ከማድረግ ይልቅ ከውስጥ ተዳክማ በውጭ ኃይሎች በቀላሉ እንድትጠቃ ያላደረገው አገርን የማዳከም ስራ የለም።  ይህንን አካሄዱን እንዲያርም ያላደርግነው ጥረት ይህ ነው አይባልም። ይሁንና ግን አገዛዙ የባሰውኑ በማምረር አገርን በማዳከምና፣ ህዝብን በመበደልና በማሰቃየት ገፍቶበታል። እንዲያውም ተፋለሙኝ በማለት የራሱን የግል ጦር በመመስረት ከህዝብ ጋር ግብ ግብ ለማድረግ ተዘጋጅቷል። ባለፈው ህዳር ወርና አሁን ደግሞ በያዝነው ነሃሴ ወር የሚታየው የአገዛዙ  ድርጊት ይህ አገዛዝ በፍጹም ከስህተቱ ሊማር እንደማይችልና፣ የህዝባችንን ቅሬታ፣ በተለይም የወልቃይትን ጸገዴንና በኦሮሞ ክልል የተከሰተውን ተቃውሞ በአጠቃላይ ጦርነት ለማዳፈን ወይንም ለመደምሰስ የተዘጋጀ መሆኑን ነው። በተጨማሪም በነሃሴ 15 ፣  2008 አዲስ አበባ ላይ ሊደረግ የታቀደውን የእንቢ በይ የቀይ ካርድ የይዞ መውጣት ሰልፍ አስመልክቶ ጥሪውን ለማክሸፍ ያሰማራው እስከ 120 000  የሚጠጋ ወታደር የሚያረጋግጠው አገዛዙ የቱን ያህል አረመኔያዊ እንደሆነና  ወደ ፋሺስታዊ ድርጊት እያመራ መሆኑን ነው።  ይህ አካሄዱና ጠቅላላው ዝግጅቱ ያንን አካባቢ ብቻ የሚመለከት ሳይሆን ጠቅላላውን ህዝባችንንና የአገራችንን የወደፊት ዕድልና ዕድገት የሚመለከት ስለሆነ ዝምብለን ልናልፈው የምንችለው ነገር አይደለም። ስለሆነም አገዛዙንና የውጭ ኃይሎች አገራችንን የማዳከምና የመከፋፈል ህልምና ዕቅድ ማክሽፍ አለብን። ለዚህ ደግሞ የግዴታ ከመቼምውም የበለጠ በአንድ ርዕይ ስር በመሰባሰብና ኃይላችንን በማጠናከር የግዴታ የአገራችንን ክብር ማስመለስ አለብን። የአገር መቆራረስና መከፋፈል፣ እንዲያም ሲል በህዝባችን ላይ  የሚደርሰውን በደልና ግድያ ዝም ብለን ማየት የለብንም። አገራችንን ከጥፋት የማዳን ታሪካዊና የትውልድ ግዴታ አለብን።

 

ሰውን ከእንስሳ  የሚለየው ምንድነው ?

ለመሆኑ  ዝም ብለን ከመኖር በስተቀር በህይወታችን እኛን ከእንስሳ የሚለየን ምንድነው ብለን ጠይቀን እናውቃለን ወይ?  የኑሮአችንን ትርጉምና ዓላማ ለመረዳት እየደጋገምን ጥያቄዎች እናነሳለን ወይ? በተለይም ፖለቲካ የሚባለው ነገር ከሰው ህይወት፣ የኑሮው ፍልስፍናና የአኗኗር ዘዴ ተነጥሎ በሚታይበት ዓለም ውስጥና፣ ጥቂት ጉልበተኞች የብዙ ሚሊዮንን ሰዎች ዕድል በአሉታዊም ሆነ በአዎንታዊ መንገድ በሚወስኑበት ዓለም ውስጥ  የሰውን ልጅ ትርጉምና ያሉትን ባህርያቶች እያነሳ የሚጠይቅ በፍጹም ያለ አይመስለኝም። ከዚህም በላይ ከአርቆ-አስተዋይነት ይልቅ ስሜታዊነት ሁሉንም ነገር በሚወስንበት ዓለም ውስጥ የሰውን ልጅ ሚናና የህይወቱን ትርጉም እየመላለሱ የሚጠይቅ የለም። የሰው ልጅ ጭንቅላት ብዙ ውስጣዊ ባህርያት ቢኖሩትም፣ ሰው እንደመሆኑ መጠን እነዚህን ውስጣዊ ባህርያት የሚጠቀም በጣም ጥቂቱ ብቻ ነው። ስለሆነም አንዱ ሌላውን ሲንቀውና ሲያንቋሽሸው፣ ካለምንም ምክንያት እንደጠላት አድርጎ ሲቆጥረውና ሲያሳድደው፣ እንዲያም ሲል የሚኖርበት አካባቢ ለእሱ ብቻ የተፈጠረች ይመስል በጉልበቱ በመመካት ሁሉንም ነገር ቀምቶ ወደ ድህነት ዓለም ውስጥ ሲገፈትረው፣ እነዚህና አያሌ ነገሮች የአንዱ ደስታ የሌላው ስቃይ ሆነው እንደ ተፈጥሮአዊ ህግ በሚወሰዱበት ዓለም ውስጥ የሰውን የማሰብ ኃይል ጉዳይ እየመላለስን እንድንጠይቅ እንገደዳለን።  ሁሉም ሰው በእግዚአብሄር አምሳል ነው የተፈጠረው ተብሎ በሚሰበክበት ዓለም ውስጥና፣ ይህም ጉዳይ ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት ያለውና፣ በየአገሮች ህገ-መንግስት ተቀባይነት አግኝቶ የሰፈረ ቢሆንም፣ ጥቂቶች ጊዜው የኛ ነው ብለው የየአገራቸውን ህዝቦች ዕድል እነሱ በሚረዱበትና በሚፈልጉት መንገድ  በሚወስኑበት ዘመን የሰው ልጅ እግዚአብሄር የሰጠውን ልዩ ልዩ ባህርያት እንዳይጠቀም ተገዷል። ከዚህ ስንነሳ ባለፉት አስር ወራት በአገራችን ምድር የተከሰተውና በአገዛዙ ያላግባብና ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ በህዝባችን ላይ የሚፈጸመው የግድያ፣ የአፈና፣ የማሰርና የማሰቃየት ድርጊቶች የግዴታ እነዚህን መሰረታዊ ጥያቄዎች እንድናነሳ እንገደዳለን።

ዛሬ በአገራችን ምድር የተከሰተውን ሁኔታ አብዛኛዎቻችን ከስርዓት መበላሸትና ከዲሞክራሲ እጦት ጋር ነው የምናያይዘው። በመስረቱ ግን ሁኔታውን  ጠለቅ ብለን ማየት ያለብን ይመስለኛል። ባለፈው አርባ ዐመታት በአገራችን ምድር የተከሰተውን አስቀያሚ ሁኔታ በዲሞክራሲ እጦት ምክንያት ነው ብለን የምናሳብብ ከሆነ ለተወሳሰበው የአገራችን ችግር በፍጹም መፍትሄ የምናገኝ አይመስለኝም። በእርግጥ ዲሞክራሲያዊ መብቶችና ለህዝባችንም የሚስማማ ስርዓት መፈጠርና መዋቀር ያለባቸው ይመስለኛል። ይህ ጉዳይ እስከዚህም ድረስ የሚያጣላን አይመስለኝም። ጥያቄው ግን ለምንድነው ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዳንገነባ ያልቻልንበት ምክንያት? በተለይም ስልጣን ላይ የተቀመጡ ሰዎችም ሆነ ቡድኖች ለምድንነው ዲሞክራሲን አጥብቀው የሚጠሉት? ለምንድነው የሰው ልጅ ህይወት የቅንጣትም ያህል የማይሰማቸው? ብለን እየደጋገምን መጠየቅ ያለብን ይመስለኛል። በተለይም መንግስትና አገር የጥቂት ግለሰቦችም ሆነ ቡድኖች የግል ሀብት ሆነው በሚቆጠሩበት እንደኛውና በተቀሩት የአፍሪካ አገሮች ውስጥ ተራ ዲሞክራሲያዊ መብቶች በራሳቸው ትርጉም አይኖራቸውም። ስለሆነም የነገሩን ውስብስበነት ከዲሞክራሲ ባለመኖር ባሻገር ማየት ያለብን ይመስለኛል። ወደ ዋናውም መሰረተ-ሃሳቤ ልግባ።

ሰው ለመሆናችን በሚታየው አካላችን ብቻ የሚወሰን አይደለም። ሰው መሆናችን በአለን አካልና ሁሉንም ነገር አጠቃሎ በያዘው ጭንቅላታችን የሚወሰን ነው። ይህም ማለት የፈለግነውን ያህል ብናምር፣ ብንወፍርና ጉልበትም ቢኖረን፣ እንዲያም ሲል በሀብት የናጠጥንም ብንሆን የማሰብ ኃይላችንን መጠቀም እስካልቻልን ድረስ ከእንስሳም እምብዛም የምንለይ አይደለንም። በመሆኑም፣ ወደድንም ጠላንም፣ ተጠቀምንበትም አልተጠቀምንበትም የሰው ልጅ ልዩ ልዩ ባህርዮች አሉት። እነዚህም፣ አርቆ-ማሰብ፣ ሎጂካሊ  ማሰብና አዲስ ነገር መፍጠር፣ ወይም ለሚታዩ ችግሮች መፍትሄ መሰጠት፣ ኮመን ሴንስ፣ ንቃተ-ህሊና(Potentially)፣ ኢንቲዩሽን፣ መሰማት(feeling)፣ ርህሩህነት፣ ማመዛዘን፣ መፍጠር መቻል፣ ኢንተለጀንስ፣ ምህራዊነት(በማንበብና በትምህርት የሚገኝ፟)፣ በጥልቀትና በሰፊው ማሰብ፣ ስነ-ምግባርነትና ግብረ-ገብነት፣ ማህበራዊነትና ህብረተሰብአዊ ኃላፊነት መሰማት… ወዘተ፣ እነዚህ ሁሉ አብረወን የተፈጠሩና በጭንቅላታችን ውስጥ የሚገኙ ናቸው። ይሁንና ግን እነዚህ በጭንቅላታችን ውስጥ ያሉ ፖቴንሺያሎች ቢሆኑም ሊዳብሩና እያንዳንዱ ግለሰብ ራሱን ተገንዝቦ ህብረተሰብአብዊ ኃላፊነትን ሊቀበልና ህብረተሰቡን ሊለውጥ  የሚችለው ጭንቅላቱ በትክክለኛ ዕውቀት ሲኮተኮት ብቻ ነው። ጭንቅላት በመጥፎ ነገሮች ተበርዞ አካባቢውንም ሆነ ጠቅላላውን ህብረተሰብ እንዳይመርዘውና እንዳያናገው ከተፈለገ አገርንና ህብረተሰብን የሚያፈርሱ አዳዲስ ሁኔታዎች በሚፈጠሩበት ጊዜ የእነዚህን ምክንያቶችና አመጣጣቸውን አጥንቶ ለመዋጋት ይቻል ዘንድ አዕምሮ የግዴታ በትክክለኛ ዕውቀት መኮትኮት አለበት። አዕምሮ የረጋ ባለመሆኑና፣ በሚሆኑ በማይሆኑ ነገሮች በመታለል ከትክክለኛውን ፈር ስለሚወጣ በየጊዜው መታደስ አለበት።  ለዚህ ነው ሶክራተስ ሰውነታችን ለመንቀሳቀስና ለመስራት ጅምናስቲክ እንደሚያስፈልገው ሁሉ፣ ጭንቅላትም እንደዚሁ ጂምናስቲክ ያስፈልገዋል የሚለው። በተጨማሪም ሶክራተስ  እንደሚያስተምረን የሰው ልጅ ህይወት መፈተን አለባት። ራሱን እንዲገነዘብና ህብረተሰብአዊ ኃላፊነትን ለመሸከም እንዲችል የግዴታ ህይወቱ ከአስቸጋሪ ሁኔታ ጋር መለማምድ አለባት። በሌላ ወገን ደግሞ ጭንቅላታችን ብዙ ጥሩ ፖቴንሺያሎች ቢኖሩትም እዚያው በዚያው ጭንቅላታችን አረመኒያዊ ባህርይ፣ ስግብግብበት፣ መቸኮል፣ አርቆ-አለማሰብ፣ ሎጂካል በሆነ መልክ ማሰብ አለመቻል፣ ስሜታዊነት፣ ህብረተሰብአዊ ኃላፊነት አለመሰማት… ወዘተ. በጭንቅላታችን ውስጥ ያሉ እጅግ አደገኛ ባህሪያችንና በየቀኑ የሚፈታተኑን ናቸው። ይህም ማለት ጭንቅላታችን ወይም መንፈሳችን እዚያው በዚያው በቅራኔ የተወጠረና በዘለዓለማዊ ግጭት ውስጥ የሚኖር ነው። በተለይም ከተወሰኑ ሁኔታዎች ጋር እየተለማመድን ካደግን የኑሮአችን ፍልስፍና በሙሉ ጤናማውን የሰው ልጅ ባህርያት የሚቃረን ይሆናል።  ፍርደ-ገምድልነትን፣ መግደልን፣ ማሰቃየትን፣ መዋሸትን፣ አገርንና ህብረተሰብን ማዘበራረቅ  ወይም ማፍረስ ዋናው የኑሮአችን ፍልስፍና በማድረግ ለሚያድገው ትውልድም እንዲተላለፍ ማድረግ እንችላለን።

ከዚህ ስንነሳ ባለፉት አርባ ዓመታት፣ በተለይም ደግሞ ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት የተፈጠረውን ኢ-ፍትሃዊ አስተዳደር፣ አገር አፍራሽ ድርጊት፣ እንዲያም ሲል በአንድ ጥቁር ህዝብ መሀከል ስምምነት እንዳይኖር ጎሳን ከጎሳና፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት ጋር እያጋጩ ህዝቡ የኑሮው ፍልስፍና አድርጎ እንዲወስደው ማድረግ ከዚህ የጭንቅላት መከስከስ ወይም ደግሞ ጭንቅላት ውስጥ አሉ የሚባሉት ጥሮዎች ባህርያት ሙሉ በሙሉ መውደም ጋር የተያያዙ ናቸው ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል።  በዚህም ምክንያት የተነሳ ጭንቅላታችን አዳዲስ ነገሮች የመቀበል ኃይሉ ስለሚዳከም ከሌላ ሰው የመጣ አዲስና ገንቢ አስተሳሰብን ይቃወማል። ያገኘውን ዝና፣ የተጎናጸፈውን የኢኮኖሚና የማህበራዊ ስታተስ ይቀናቀነኛል በማለት ህብረተሰብአዊ ለውጥ እንዳይመጣና በዚያውም መሰረትም በሳይንስና በቴክኖሎጂ አማካይነት የሰፊው ህዝብ ኑሮ እንዳይሻሻል ያግዳል። በተለይም በአሁኑ ዘመን ውስጣዊ አገዛዞች ከውጭ ኃይሎች ጋር በሺህ ድሮች ተሳስረው በሚገኙበት ዓለም፣ የውስጥ ኃይሎች የውጭውን ኃይል ተገን በማድረግ ከውስጥ መስረታዊ ለውጥ እንዳይመጣ፣ እንዲያም ሲል በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ሰፋ ያለና የተወሳሰበ ኢኮኖሚ እንዳይገነባ እንቅፋት ይሆናሉ። በዚህ ዐይነቱ የተቆላለፈ ሁኔታና በጥቅም መተሳሰር የተነሳ ጭንቅላት የባሰውኑ እየዛገና ለዕድገት እንቅፋት እየሆነ ይመጣል። ስለሆነም ይህንን አካሄድ የሚቃውም ኃይል ከውስጥ ሲነሳ ህገ-መንግስቱን የሚጻረር የሽበረተኞች አካሄድ ነው በማለት በማስፈራራትና፣ ይባስ ብሎም አንዳንድ ግለሰቦችን ወይም ደግሞ በጅምላ በመግደል ነገሩን ለማብረድ ይሞከራል። ይሁንና ግን ይህ ዐይነቱ አካሄድ ችግሩን የሚፈታ ሳይሆን የሚያባብስና ህብረተሰብአዊ ፍጥጫውን ልዩ ዕምርታ የሚሰጠው ይሆናል። ይህ ዐይነቱ ችግርን ከመፍታት የባሰውኑ ማባባስ በብዙ ኋላ-ቀር በሚባሉ አገሮች የሚታይ አደገኛ አካሄድ ቢሆንም፣ እንደወያኔ ያለውን አገዛዝ ባህርይና ስልጣን ላይ ቁጥጥ ብሎ ህዝብን ማሰቃየት በተራ የፖለቲካና ከውጭው ኃይል ጋር በመተሳሰር ብቻ የሚገለጽ አይደለም። ሁኔታው በከፍተኛ ደረጃ ከህሊና-ሳይንስ አንፃር መታየት ያለበትና ከዝቅተኛ ስሜት ጋር በመያያዝ፣ በአንድ በኩል  በምንም ማስረጃ የማይደገፍ በአንድ ብሄረሰብ ላይ ያተኮረ የቂም በቀል „ፖለቲካ“ ሲሆን፣ በሌላ ወገን ደግሞ ይህንን ሁኔታ በመጠቀም የአንድን ጎሳ የበላይነት(Dominanz) አስፍኖ አንድን ብሄረሰብ ብቻ ሳይሆን ጠቅላላውን ህብረተሰብ ለማዳከምና ለመግዛት የሚካሄድ፣ ግን ደግሞ የመጨረሻ መጨረሻ የሚከሽፍ መጥፎ አካሄድ አድርጎ መረዳትም ያስፈልጋል። በሌላ አነጋገር፣ ባለፉት ሰላሳና አርባ ዐመታት በብዙ አገሮች አምባገነናዊ አገዛዞች የታዩ ቢሆንም አገሮቻችውን ለማዳከመና ለማፈራረስ የተነሱብት ጊዜ አልነበረም።  አብዛኛውን ጊዜ በብዙ የሶስተኛው ዓለም ተብለው በሚጠሩ አገሮች ውስጥ ያለው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውሶች የሚታዩት አገዛዞቹ ባለማወቅ በተሳሳተ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የሚሊታሪ ርዕዮተ-ዓለም ወይም ፖሊሲ ስለሚመሩ ነው። አብዛኛዎች አገዛዞች በዓለም አቀፍ ደረጃ በተዋቀረው የአገዛዝ ሂራርኪ ውስጥ ስለተካተቱና ወደ ታዛዥነት ስለተለወጡ ካለምንም ምሁራዊ ክርክር ሳያውቁ ተግባራዊ የሚያደርጓቸው ፖሊሲዎች ህብረተሰቦቻቸውን እንዲያናጉና ወደ አለመጋዝት እንዲያመሩ ያስገድዷቸዋል።   በሌላ ወገን ወያኔ የሚያካሄደው ማንኛውም ፖሊሲ ሆን ብሎና በውጭ ኃይሎች ታግዞ የሚካሄድ በመሆኑ ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት የተከላቸው መዘዞች፣ ያሰራጫቸው የጥላቻ መርዞች በቀላሉ የሚነቀሉና የተወሳሰበውን የአገራችንን ችግር በቀላል ፎርሙላ መፍታት የማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል።

ያም ሆነ ይህ፣ በተለይም ፊደል የቆጠረና ዩኒቨርሲቲም ገብቶ ትንሽም ዓመት ቢሆን ይህንንም ሆነ ያንን ትምህርት የተማረ ሰው ድርጊቱ በሙሉ ተንኮልና ጥፋት ከሆነ ይህንን ዐይነቱን ድርጊት ከአዕምሮ ባህርያት ሙሉ በሙሉ ተሟጠው ከመውደማቸው ጋር ማያያዝ ይቻላል። አንድ ሰው ተማረም አልተማረም የተወሰነ የሞራል ኮድ እንዲኖረው ያስፈልጋል። ወደ ትምህርት ቤት የሚኬደው እንዲያው ከተወሰነ ዐመት በኋላ ዲጊሪ አግኝቻለሁ ለማለትና ለመዘባነን ሳይሆን፣ የማሰብ ኃይሉን ለማዳበርና፣ አልተማረም ለሚባለው ዕውቀትን ለማስተላለፍና የኑሮን ትርጉም ተረድቶት ራሱን እንዲለውጥ ለማድረግ ነው።  የመማር ትርጉሙ የአንድን ህብረተሰብና የተፈጥሮን ህግ በመረዳት አንድ ህዝብ ታሪካዊ ስራዎችን ይሰራ ዘንድ መንገዱን ማሳየት ነው። በሌላ አነጋገር፣ የመማር ትርጉሙ፣ አገር ማፈራረስ፣ ተንኮል መስራት፣ ስግብግብነት፣ ከሌላው በልጦ ለመገኘት ሲባል አንዱን ማጥፋት፣ በተለይም ስልጣን  ጨብጬአለሁ ብሎ በጠብመንጃ ኃይል በመመካት ሰውን እያነጣጠሩ መግደልና የአንድን ቤተሰብ ህይወት እንዳለ እንዲፈራርስ ማድረግ አይደለም። የፈለገው ሰው ቢሆን፣ በተለይም ደግሞ የመንግስትንንም መኪና የጨበጠና አገርን አስተዳድራለሁ የሚል፣ አንድን ሰው ወይም ብዙ ሰዎችን እንደፈለገው የመግደል፣ የማሰቃየትና የማሰር መብት የለውም። እንደፈለግሁት አደርጋለሁ የሚል ሰው በመጀመሪያ ደረጃ ራሱ ሰው መሆኑን የማይረዳ፣ ወይም ደግሞ ራሱ ከማንኛውም ሰው በላይ ነኝ ብሎ የሚገምት ብቻ  ነው።

በመሰርቱ የወያኔን ሰዎችን ባህርይ መረዳት የምንችለው በዲሞክራሲ መኖርና አለመኖር አይደለም። ሰውን ማሰቃየታቸው፣ መግደላቸው፣ ጎሳን ከጎሳ ማጋጨታቸው፣ እነሱ እያበጡ እገር እንድትፈራርስ ማድረጋቸው፣ በተለይም ወጣቱን ትውልድ የዕጽ ሱሰኛ አድርጎ የኑሮን ትርጉም እንዳይረዳ ማድረግ፣ ይህ ሁሉ ርኩስ ድርጊት ሊገለጽ የሚችለው ውጥንቅጡ ከወጣው ወይም በስነስስርዓት ካልተዋቀረው ባህርያቸው ጋር የተየያያዘ ሲሆን ብቻ ነው። ወያኔ ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታትም ሆነ ከዚያ በፊት የፈጸማቸውን ወንጀሎችና በድሮ የትግል አጋሮቹ በየጊዜው የሚነገርንን ለማወቅ የግዴታ በኖይሮ ባዮሎጂስት ወይም በህሊና ሳይንስ መመረቅ ወይም መሰልጠን አያስፈልግም። ራሱ የምናየው ነገር፣ ህዝባችን የሚኖርበት ኑሮና የሚፈጸምባቸው ወንጀሎች ራሳቸው በቂ ትምህርት ስለሆኑና፣ ይህንንም ከኖርማል ሁኔታ ጋር በማመሳሰል የነዚህን ሰዎች የጭንቅላት ባህርይ ከሞላ ጎደል መረዳት ይቻላል። ብዙ መመራመር አይሰፈልገውም ማለት ነው። ባለፉት ሃያ ዓምስት ዓመታት ስለወያኔ አረመኔያዊነት ብዙ ተጽፏል፤ ብዙም ተነግሯል። ይሁንና ግን የሁላችንም ግምት ቀን እያለፈ በሄደ ቁጥር ማህበራዊ ባህርይ በመወሰድ ከዚህ አረመኔያዊ ባህርያቸው በመላቀቅ ከህብረተሰቡ ጋር ይቀላቀላሉ የሚል ግምት ነበረን። ስለሆነም አጻጻፋችን ከሞላም ጎደል በተቻለ መጠን ፈሩን እንዳይለቅና ትምህርታዊ በመሆን ግንዛቤ ሰጥቶአቸው ርህሩህ ባህርይ ያዳብራሉ የሚል ግምት ነበረን። እነሱ ግን ሆን ብለው የያዙት አንድም ሌላው ሞኝ ነው፣ በቀላሉ ልናታልለው እንችላለን በማለትና ለሆዱ ያደረውን በመግዛት፣በዚያም አማካይነት በህብረተሰብ ውስጥ ሚዛናዊነት ያለው ድርጊትና የሀብት ፈጠራ እንዳይካሄድ በማድረግ፣ በሌላ ወገን ደግሞ አልፎ የሄዳቸውን ይቀናቀነኛል ብለው በማሰብ እንዲጠፋ በማድረግ በፍጹም ሊማሩና ህብረተሰብአዊ ባህርይ ሊቀስሙ የማይችሉ ፍጡሮች እንደሆኑ ነው በየጊዜው ያረጋገጡልን።  በተለይም ከነሱ ኢ-ፍህታዊ አገዛዝ የሚመነጨውን ግፍ የሚቃወመውን ሁሉ ትግሬውን ወንድሞቻችንም ሆነ እህቶቻችን፣ እንዲሁም እናቶቻችንና አባቶቻችንን የተቃወመ በማስመሰል ወይንም በነሱ ላይ የተለየ ጥላቻ እንዳለ በማስወራት የዋሁን ህዝብ በማሳሳት እስካሁን ድረስ እያወናበዱ መግዛት ችለዋል። ይሁ ሁሉ የመጥፎ ባህሪያቸው መግለጫ ነው።

አንዳንድ የድሮ ታጋይ ነን የሚሉና ዛሬ ያገሪቱ ሁኔታ ያሳሰባቸው እንደነ ጄኔራል ጻድቃን እንደሚነግሩን ወይም ለማረጋገጥ እንደሚሞክሩት ሳይሆን፣  በተለይም የኋላ ኋላ ቀስ በቀስ የበላይነትን እየተቀዳጁ የመጡት እንደነ መለሰ ዜናውና ስብሃት ነጋ፣ ሌሎችም ዛሬ በስልጣን ላይ ያሉት በሙሉ እዚህ ደረጃ ላይ የደረሱት አረመኔያዊነታቸውን እያረጋገጡ ነው። በሌላ አነጋገር በዲሞክራሲያዊና በሰብአዊ መርሆች በመመራት ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመፍጠር አይደለም። ስለሆነም የጄኔራል ጻድቃን ድርጅቱን በአነሳሱ ዲሞክራሲያዊና አብዮታዊ አድርጎ ለማቅረብ መሞከሩ ቢያንስ ድርጅቱ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ ከሚያደርገው አረመኔያዊ ድርጊቱ ጋር በፍጹም የሚጣጣም አይደለም። በመጀመሪያ ደረጃ ድርጅቱ ዲሞክራሲያዊ ባህርይ ቢኖረው ኖሮ በትግሉ ዘመን በመሀከላቸው የነበረውን ቅራኔ ወይንም በሃሳብ አለመግባባት ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልክ መፍታት መቻል ነበረበት። በተጨማሪም በአንዳድ ግለሰቦች በሴቶች ላይ የሚደረገውን ግፍና ግድያ ወይም ወደ ገደል ውስጥ መውርወር ሲታይ ዝም ብሎ ማለፍ፣ ወይም እንደዚህ ዐይነቱ መጥፎ ድርጊት እንዳይደገም ወንጀሉን በፈጸመው ላይ ቁርጥ ያለ እርምጃ መውሰድ ሲገባ እነ ጄኔራል ጻድቃን ይህንን አጸያፊ ድርጊት ዝም ብለው የሚመለከቱ ነበሩ። ይህም የሚያሳየው የኋላ ኋላ ድርጅቱን በቁጥጥራቸው ውስጥ ያስገቡት እነመለስና ስብሃት ነጋ፣ እንዲሁም ሌሎችም አረመኔዎች እንደነበሩና የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ባህርይ እንዳልተዋሃዳቸው ነው የሚያረጋግጠው። ከዚህም ባሻገር ማንኛውም የዲሞክራሲን መፍክር ይዞ የሚነሳ ግለሰብም ሆነ ድርጅት ማሰብና ማቀድ ያለበት ስትራቴጂያዊ በሆነ መልክ ነው። በሌላ አነጋገር ማሰብ ያለበት ከስልጣን መያዝ ባሻገር ነው። የእነ መለስ ዜናዊና ስብሃት ነጋ እንዲሁም የተቀሩት የዛሬው ቱጃሮች ዕቅድ ማሰብ የሚችለውንና ትንሽም ቢሆን ከእነሱ የተሻለውን በማስወገድ ወደ ስልጣን የሚመጡበትን ሁኔታ ማመቻቸት ነበር። ይህንን ዐይነቱንና በብዙ መልክ የሚወራውንና ዕውነትም የሆነውን ወንጀላቸውን ሁሉ የተከታተለ፣ የወያኔ ሰዎች አንድ ሰው እንዲኖረው የሚገባውን ከላይ የዘረዘርኳቸውን ጤናማ ባህርዮች በሙሉ አንድ በአንድ እያጡና የምናየው አካላቸው ብቻ የሚንቀሳቀስ ሆኖ የባሰ ስግብግብነትንና አረመኒያዊነትን ከሰውነታቸው ጋር እያዋሃዱ የመጡበትን ሁኔታ እንመለከታለን። በመሆኑም ከነሱ አስተሳሰብና የአኗኗር ስልት ውጭ ያለ በሙሉ ሰው አይመስላቸውም። ማንኛውም ሰው ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንደሚያስፈልገው የተረዱና የሚረዱ አይደሉም። በተለያዩ መልኮች የሚገለጸው ፍቅር ጭንቅላታቸው ውስጥ የሌለ በመሆኑ ለሰው ልጅ ርህራሄ የላቸውም። ኮመን ሴንስና ኢንቲዩሽን ከጭንቅላታቸው በሙሉ ተሟጠው ያለቁ ስለሆነ ስሜት የላቸውም። የሚመስላቸው እነሱ ጠላቴ ነው ብለው የሚገምቱትን በሙሉ እያሰቃዩ የሚኖሩና፣ በዚህም የሚደሰቱ በመሆናቸው፣ ፍልስፍና ካልነው ይህንን የኑሮአቸው ፍልስፍና አድርገውታል።  ከዚህ ስንነሳ ዛሬ በአገራችን ምድር አፍጦ አግጦ የሚታየው የተበላሸ ሁኔታ፣ ህዝባችን ለድህነትና ለረሃብ መጋለጥ፣ ይባስ ብሎ በ21ኛው ክፍለ- ዘመን ተስቦና ኮሌራ ተስፋፍተው ብዙ ህዝብ ሲፈጁና ከተማው በሙሉ በቆሻሻ እቃ ሲሞላና፣ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ ከቆሻሻ መጣያ ቦታ እየፈለገ ሆዱን ለመሙላት ሲታገል ስናይ፣ ይህ ሁሉ ሊገለጽ የሚችለው እንዲያው በመልካም አስተዳደር እጦት ሳይሆን አገሪቱ ሰብአዊነትን ባጡና ሌላው ፍጡር በሙሉ ሰው በማይመስላቸው ሰዎች እንደምትተዳደር ነው። አስተሳሰባቸውና ድርጊታቸው በሙሉ የህብረተሰብንና የተፈጥሮን ህግ የሚፃረርና አንድ ህዝብ በረጋ መንፈስ ታሪክን እንዳይሰራ የሚያግድ እጅግ አደገኛ አካሄድ ነው።

ተፈጥሮአዊ ወይም ዩኒቨርሳል ህግ ምን ይለናል !

ታላቁ የሮማውያን የመንግስት ፈላስፋ ሴናካ የሚባለው ታላቅ መሪ እንደሚለን፣ ማንኛውም ህብረተሰብአዊ ችግሮችና ፖላቲካዊ ፍጥጫዎች የሚከሰቱት የተፈጥሮን ህግ ባለመረዳት ነው ። የተፈጥሮን ህግ ለመረዳት የማይችል ሰው ደግሞ የግዴታ የአንድን ህበረተሰብ ጤናማና ሚዛናዊ አካሄድን ያዘበራርቃል። የዕድገትና የሰላም ጠንቅ ይሆናል። አንድ ህብረተሰብ ዕውነተኛ ስልጣኔን እንዳይጎናጸፍ ልዩ ልዩ መሰናክሎችን በመፍጠር አንድ ህዝብ ፍዳውን እያየ እንዲኖር ያደርጋል።

ቀደመ ብዬ ለማሳየት እንደሞከርኩት የሰው ልጅ ከማሰብ ኃይል ጋር የተፈጠረ ነው። የማሰብ ኃይሉ በተለያየ መልክ የሚገለጽ ሲሆን፣ ይህንን በተለያየ መልክ የሚገለጸውን ግን ደግሞ በአንድ አጠቃላይ ውስጣዊ ኃይል የሚገዛውን ሎጂካዊ አስተሳሰብ በመጠቀም የማሰብ ኃይሉን በማዳበር ተፈጥሮን በመለወጥና በማሻሻል መኖሪያ ያደርጋታል።  የማሰብ ኃይሉን በመጠቀም የተዘበራረቀውን ሁኔታ በምሁራዊ ኃይል መልክና ስርዓት በመስጠት በአንድ በኩል በሰዎች መሀከል የሚኖረው ግኑኝነት ሚዛናዊነት እንዲኖረው ያደርጋል፣ በሌላ ወገን ደግሞ  የተፈጥሮን ህግ በመረዳት በተፈጥሮና በሱ መህከል ሊኖር የሚገባውን መደጋገፍ በመገንዘብ በተፈጥሮ ላይ ብዙም አደጋ ከማድረስ ይቆጠባል።  ተፈጥሮን የበለጠ ቅርጽ እየሰጠና እየተንከባከበ ወደ ምድራዊ ገነትነት ይለውጣታል። በዚህ ብቻ ሳይቆጠብ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠርና በማዳበር ስራውን ያቃልላል፤ እንዲያም ሲል በተወሰነ ሰዓት የበለጠ ምርትን ማምረት ይችላል። ይህ ዐይነቱ የማሰብ ኃይል ከዘርና ከቀለም ባሻገር ለሰው ልጅ ሁሉ የተሰጠ ጸጋና ከሰው ልጅ ጋር አብሮ የሚፈጠር ነው። ይሁንና ግን እያንዳንዱ ሰውና ህብረተሰብ ይህንን ተፈጥሮአዊ ጸጋ ለመጠቀም እንዳይችል የሚያግዱት የተወሳሰቡ ህብረተሰብአዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ግኑኝነቶች በየአገሮች ውስጥ አሉ። በአለንበት በ21ኛው ክፍለ-ዘመን ደግሞ የአንድ ህዝብ የማሰብና የመፍጠር፣ ወይም ደግሞ ያለማሰብና ያለመፍጠር ኃይል ከውጭው ዓለም ጋር ባለን ግኑኝነት የሚወሰን ነው።  የየአገሮች ባህሎች፣ ኢኮኖሚዊ ግኑኝነቶና ፖለቲካዊ አወቃቀሮች በጎሎባል ካፒታሊዝም ውስጣዊ ኃይል ስለሚወሰኑ፣ አንድን አገር በተስተካከለና በሳይንሳዊ ዘዴ ለመገንባት እጅግ አስቸጋረ እየሆነ የመጣንበትን ሁኔታ እንመለከታለን። በሌላ አነጋገር በብዙ መልክ የሚገለጸው ግሎባል ካፒታሊዝም የሃሳብ ጥራትን ከማምጣትና የማሰብ ኃይልን ከማዳበር ይልቅ እያዘበራረቀውና የሰውን ልጅ ወደ አልባሌ ተግባርና ወደ አረመኔያዊነት ድርጊት እየመራው እንደሆነ በምድር ላይ የሚታየውን ለተከታተለና ራሱን ለጠየቀ በቀላሉ መልስ ሊያገኝ ይችላል። በተለይም ደግሞ እንደኛ ባለው ምሁራዊ ኃይል እጅግ ደካማ በሆነበት አገርና፣ ሎጂካዊና የተወሳሰበ አስተሳሰብ ቦታ በሌላቸው አገሮች ውስጥ በተወሳሰበ መልክ ከውጭ የሚመጣውን አገርንና ህብረተሰብን አፍራሽ አስተሳሰብ ለመዋጋት እጅግ አስቸጋሪ ይሆናል። ከዚህም በላይ የዓለም ማህበረሰብ ሁሉ በአንድ ፎርሙላ መመራት አለባቸው እየተባለ በሚሰበክበት  ዓለም ውስጥ ውሸትን ከዕውነት፣ የሰይጣኑንመንገድ  ከመንፈሳዊው  ለመለየት በጣም ያዳግታል።

ከዚህ ስንነሳ የዩኒቨርሳል ህግ ወይም ተፈጥሮአዊ የማሰብ ኃይል ፈሩን ሊለቅ የሚችልበትን ሁኔታ ጠጋ ብለን እንመልከት። ለአንድ ሰው የማሰብ ኃይል መዳከም እንዲያም ሲል በአልባሌ ነገሮች መወጠርና ወደ ጨካኝነት ማምራት ብዙ ምክንያቶችን መስጠት ይቻላል። በተፈጥሮ ውስጥ ከአፈጣጠር ጋር የሚከሰተውን የማሰብ ኃይል ድክመትና በየአገሮች ውስጥ ያለውን የባህል ሁኔታ ወደ ጎን ትተን፣ ሌሎች የንቃተ-ህሊናችንን እንዲያም ሲል የማሰብ ኃይላችንን  መዳከም የሚወስኑ ነገሮች ላይ እናተኩር።  በመጀመሪያ ደረጃ በተለይም በዘመኑ በብዙ አገሮች የታዩትንና እንደትዝታ የሚወሩትን የጭካኔ እርምጃዎችና የግፍ አስተዳደሮች ለተመለከተ አረመኔያዊነት በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተስፋፋ የመጣውና መንግስታትም የበለጠ ጨቋኝ መሆን የቻሉት ከንቃተ-ህሊናቸው ጋር ሊስተካከል ከማይችል ቲክኖሎጂ፣ የጦር መሳሪያዎችና ቢሮክራሲያዊ አስተዳደሮች ጋር በመተዋወቃቸው ነው። በሌላ አነጋገር በካፒታሊዝም መስፋፋት በየአገሩ እየተንጠባጠበ የገባው ዘመናዊነት በተለይም በከፍተኛ የህብረተሰብ ሂራርኪ ውስጥ የሚገኘውን የሀብረተሰብ ክፍል አረመኔያዊ፣ ሀብት አውዳሚና አገር አፍራሽ እያደረገው እንደመጣ መገንዘብ እንችላለን። ይህም ማለት ዘመናዊነት ጭንቅላትን ብሩህ ከማድረግና ልብንም ርህሩህ አድርጎ ህብረተሰብአዊ ኃላፊነት እንዲሰማ ከማድረግ ይልቅ፣ አንዱ ሌላውን የሚንቅበትና፣ ራሱ ጥሩ ኑሮ እየኖረ ሌላው ደግሞ ተጨማደደና የተዝረከረከ ኑሮ እንዲኖር የሚያደርግበትን ሁኔታ እንመለከታለን። ይህ ዐይነቱ በብዙ አገሮች የሚታየው የጭቆናና ግፍ አስተዳደር በየአገሮች ውስጥ ያለው ህዝብ የማሰብ ኃይሉን እንዳያዳብር አፍኖ በመያዝ ለድህነት ዋናው ምክንያት ነው። በዚህም ምክንያት የተነሳ ፓለቲካዊ ንቃተ-ህሊና፣(Political Consciousness ) ህብረተሰብአዊ ንቃተ-ህሊና፣(Soical Consciousness) አካባቢን የመንከባከብ ንቃተ-ህሊና፣(Ecological Consciousness) ባህላዊ ንቃተ-ህሊና፣(Cultural Consciousness) ታሪካዊ ንቃተ-ህሊና፣(Historical Consciousness)… ወዘተ. እነዚህን የመሳሰሉት ለአንድ ህብረተሰb እንደ ማህበረሰብ ተስማምቶ እንዲኖር የሚያደርጉትና ታሪካዊ ነገሮችን እንዲሰራ የሚያስችሉት በብዙ መልክ የሚገለጹ ዕውቀቶች እንዳይዳብሩና የህብረተሰብ ኖርሞች ሆነው ማንኛውም ዜጋ እንዲከተላቸው ማድረግ አልተቻለም። በዚህም ምክንያት የተነሳ ውንብድና፣ ሸፍጠኝነት፣ በስነ-ስርዓት አለመስራት፣ ፕሪንሲፕል-አልባ መሆን፣ ለዚህም ለዚያም ነገር መስገብገብ፣ አለሁ አለሁ ማለት፣ ስንትና ስንት ወንጀል እየሰሩ አልሰራሁም ማለት፣ ወይም የሰራሁት አንድ ነገር አሳስቶኝ ነው ማለት ህብረተሰባዊ ኖርሞች በመሆን የአንድን ህብረተሰብ የተወላገደ ጉዞ ደንጋጊ መሆን በቁ። ይህ ዐይነቱ ባህርይ በብዙ ያለደጉ አገሮች፣ በተለይም ደግሞ በኛ አገር ጎልቶ የታያና የሚታይ በብዙ መቶ ሺህ ለሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት መጥፋትና ለተፈጥሮ ሀብት መውደም ምክንያት የሆነ ነው። ዛሬ በአገራን ውስጥ ያለውንም አረመኔያዊ አገዛዝ ከዚህ ዐይነቱ ሁኔታ ጋር ማያያዝ ይቻላል። ይህ ዐይነቱ ሁኔታ ባልተስተካከለ የኢኮኖሚ ዕድገትና ከታች ወደ ላይ በጥናት ባልተደራጀ መንግስታዊ አወቃቀር በመጠናከር አንድ ህብረተሰብ ፈሩን እንዲለቅ ሊደረግ ቻለ።

ከዚህ ስንነሳ በመሰረቱ በአንድ አገር ውስጥ የሚኖር ህዝብ ንቃተ-ህሊና መዳበር ሊወሰንና  ህዝቡም ያለውን ተፈጥሮአዊ ፖቴንሺያል ሊጠቀምና፣ ጤናማና የሚተሳሰብ ማህብረሰብ ሊገነባ የሚችለው መንግስታዊ አወቃቀርና የፖለቲካው ሁኔታ መልክ ሲይዙ ብቻ ነው።  የአሳ መግማት የሚጀምረው ከጭንቅላቱ ነው እንደሚሉት አነጋገር፣ ንቃታ-ህሊናው እጅግ ደካማ የሆነ ወይም ተሟጦ ያለቀ፣ ዓላማው አንድን ማህብረሰብ መገንባትና ህብረተሰብአዊ ስምምነት ሳይሆን ስግብግብነትን የሚያስቀድም፣ በውጭ  ኃይል ተማምኖ  ከውስጥ የሚነሱ ብሶቶችን ለማፈን እችላለሁ ብሎ የሚገምት ኃይል በታሪክ አጋጣሚ ስልጣንን በሚጨብጥበት ጊዜ አስተሳሰቡና ድርጊቱ ሁሉ ህብረተሰቡን መረበሽ ይሆናል። የአንድ ህዝብ አስተሳሰብ በመፍጠር ላይና የራስን ኑሮ በማሻሻል እንዳያተኩር የሆነ ያልሆነ ተንኮል በማውጠንጠን የሰፊው ህዝብ ጭንቅላት በአልባሌ ነገሮች እንዲጠመድ ያደርጋል። ኑሮው ጭንቀትና ሀዘን ብቻ እንዲህን በማድረግ የራሱን የግዛት ዘመን ለማርዘም የሆነ ያልሆነውን በህግ መልክ ተግባራዊ በማድረግ በአጠቀላይ ሲታይ አንድ ህብረተሰብ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሊዳረስ የሚችል ብሄራዊ ሀብት(National Wealth) እንዳይዳብር ያደርጋል። ይህንን ዐይነቱን አንድን ህብረተሰብ ማወላገድ በአገዛዙ ብቻ የሚወሰን ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ ኢንስቲቱሽኖችና ሽብርተኝነትን የሚፈለፍሉና በተለያየ መልክ የሚዶግሙ የካፒታሊስት አገር የስለላ ድርጅቶችም ዋና ተግባር ነው። በዚህ መልክ በተሰበጣጠረ ግኑኝነት የተነሳ አንድ ህዝብና አንድ አገር ልኡልናቸውን ያጣሉ። በዘለዓለማዊ ትርምስ ውስጥ እንዲኖሩ ይገደዳሉ።  ድህነት፣ ተደጋጋሚ ረሀብ፣ በአጠቃላይ ሲታይ አንድ ህዝብ ለህይወቱ የሚያስፈልጉት መሰረታዊ ነገሮች  እንዳይሟሉ ማድረግ የተፈጥሮ ህግ ሆነው ስለሚወሰዱ ጠቅላላው ህዝብ በልመናና በመጽዋት እንዲኖር ይገዳድል። በዚህ መልክ የአንድ ህዝብ የመፍጠር ኃይል ይዳፈናል። ንቃት-ህሊናውን ለማዳበር አቅም አይኖረውም። በተመጣጠኑ ምግቦች ዕጥረት በግልጽ የምናየው ሰውነቱ ብቻ ሳይሆን የማሰብ ኃይሉም ይዳከማል።

ለዚህ ዐይነቱ ለብዙዎቻቸን በግልጽ ከማይታየን የተሳሰረና ጭንቅላታችንን አፍኖ ከያዘን ሁኔታ መውጣት የሚቻለው  ጠቅላላው ህዝብ የመንፈስ ነፃነት ሲያገኝና፣ እንደልብም መንቀሳቀስ ሲችል ብቻ ነው። በሌላ አነጋገር የማሰብ ኃይሉን ማዳበር ሲችልና ራሱን ሲያገኝ ብቻ ነው። አንድ ህዝብ የማሰብ ኃይሉን ሲያዳብርና በሁሉም አቅጣጫ በተወሳሰበ መልክ ማሰብ ሲችል ለማንኛውም ጭግር መልስ ማግኘት ይችላል። አዳዲስ ችግር ፈቹ ቴክኖሎጂዎችን ያፈልቃል።  ይህ ማለት ምን ማለት ምን ማለት ነው ? ዛሬ በዓለም ላይ የምናያቸውና የምንጠቀምባቸው ቴክኖሎጂዎችና ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የምንሽከረከርባቸው መመላለሺያዎች  ከሰማይ ዱብ በለው የወረዱ ሳይሆን በሰው የማሰብ ኃይል የተፈጠሩ ናቸው። በተፈጥሮ ውስጥ ብዙ ተፈጥሮአዊ ነገሮች ቢገኙም እነዚህን አውጥተን በኃይል (Energy)አማካይነት ወደ መጠቀሚያነት መለወጥ የምንችለው በማሰብ ኃይላችን ብቻ ነው። ኃይል በተፈጥሮ ውስጥ ያለ ቢሆንም እሱን አባዝተን ለመሳሪያ መስሪያ መጠቀም የምንችለው እንደዚሁ በማሰብ ኃይላችን ነው። በሌላ ወገን ግን ይህንን የዩኒቨራሳል ህግ ያልተረዳና ለመጠቀም የማይችል አገዛዝም ሆነ ህዝብ እጣው ድህነትና ረሃብ፣ እንዲሁም ኑሮው መዘበራረቅ ይሆናል። እንደ አገራችን ባለ ሁኔታ የአገዛዙ የፖለቲካ ዘይቤ ተንኮል መጠንሰስ በሆነበትና፣ ስልጣን ላይ ለመቆየት ሲባል ብቻ አንዱን ጎሳ ከሌላው ጎሳ ጋር ማጣላት፣ ወይም አንዱን ሃማኖት ከሌላው ጋራ በማጋጨት በከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ አማካይነት ለዘለዓለም ስልጣን ላይ ለመቆየት መሞከር በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ያለን ውስጣዊ ኃይልና የተፈጥሮን ሀብት ያወድማል። በዚህም ምክንያት የተነሳ ጠቅላላው ህበረተሰብ በአልባሌ ነገሮች ስለሚጠመድና ምክንያቱን ሳያውቀው ርስ በርሱ ስለሚነታረክ ተፈጥሮ የሰጠውን ውስጣዊ የማሰብ ኃይሉን እንዳይጠቀምበት ይገደዳል። ይህ ዐይነቱ አካሄድ ኃይል ማወደሚያ ህግ (The Law of Energy Destruction) ይባላል። በሌላ አነጋገር ጠቅላላው የማሰብ ኃይል ህብረተሰብንና የተፈጥሮን ሀብት በማውደም ላይ የሚያተኩር ስለሚሆን ህብረተሰብአዊ ሀብት(National Wealth)እንዳይፈጠር መንገዱን ሁሉ ይዘጋል። አንድ ህዝብ የሰለጠነ ኑሮ እንዳይኖር ያግዳል። ይህ ዐይነቱ የኃይል ውድመት የሰውን የማሰብ ኃይል ድክመት የሚመለከት እንጂ በተፈጥሮ ውስጥ ያለን ኃይል አይደለም። በፊዚክስ ህግ ኃይል(Energy) ሊፈጠርና ሊወድም አይችልም። ተፈጥሮአዊ ኃይል ከአንድ ሁኔታ ወደ ሌላ ሁኔታ የሚለወጥ ብቻ ነው። ይሁንና ግን ኃይልን በስነ፟-ስርዓት ካለመጠቀም የተነሳ መባከን ይፈጠራል። በሌላ አነጋገር እንደዚሁ በተፈጥሮ ውስጥ ያለን ኃይልና ከአንድ ሁኔታ ወደሌላው የሚለወጠውን ኃይሉ ሳይቀንስ ለመጠቀም ከተፈለገ የግዴታ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች መፈጠር አለባቸው። ይህ ዞሮ ዞሮ የሰውን ልጅ የማሰብ ኃይል ሁኔታ ይጠይቃል። በአጠቃላይ ሲታይ ለሰው ልጅ ዕድገትና በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ስምምነትና ሰላም መኖር የዩኒቨርሳል ህግ ወሳኝ ሲሆን፣ የዩኒቨርሳል ህግን መረዳት ደግሞ በተለይም የማንኛውም ለፖለቲካ ስልጣን እታገላለሁ የሚል ግዴታ ነው። ይህንን ህግ ሳይረዳ ስልጣን ላይ የሚወጣ የግዴታ ህብረተሰቡን አንድገና ለአንድ ሺህ ዐመት በጨለማ ዓለም ውስጥ እንዲኖር ያደርገዋል።

ወደ ሁለተኛው፣ በሰውና በተፈጥሮ መሀከል ሊኖር የሚገባውን ግኑኝነትና መደጋገፍም መረዳት የምንችለው የማሰብ ኃይልን ከፍተኛ ቦታ ስንሰጠው ነው። የሰው ልጅ ተፈጥሮን ይፈልጋታል እንጂ ተፈጥሮ ሰውን አትፈልገውም። ብዙም ሳናስብ(Intutively) የሰው ፍጡርም ሆነ እንስሳ ሁሉንም ነገር ሊያገኙ የሚችሉት ከተፈጥሮ ነው። ለመተንፈስ አየር፣ ለመጠጣትና ለመታጠብም ሆነ ለመቀቀያ ውሃ፣ አፍርን ለማብቀያ ብቻ ሳይሆን ወደ ማሺንነት የምንለውጣቸው ጥሬ- ሀብቶች  በሙሉ ከተፈጥሮ ውስጥ የሚገኙ የሰው ልጅ ሳይፈጥራቸው በጸጋ የተሰጡ ናቸው። እነዚህን ግን በስነ-ስርዓት እያወጡና በተፈጥሮ ላይ ሚዛናዊንት እንዳይጓደል መጠቀም የሚቻለው የማሰብ ኃይላችንን ስንጠቀም ብቻ ነው። እንዲያው በጭፍንና በጉልበት እየተመካን በተፈጥሮ ላይ ዘመቻ ብናደርግ ተፈጥሮ ራሷ አንድ ቀን የቂም በቀሏን ትወጣለች። በሌላ አነጋገር ዝም ብለን ዛፍን የምናወድም ከሆነ የግዴታ ለዝናብ እጦት ወይም አለመዝነብ አመቺ ሁኔታ እንፈጥራለን። በተጨማሪም አንድ ቀን ኃይለኛ ዝናብ በሚዘንብበት ጊዜ መሬቱ በዛፍ መቆረጥ በመራቆቱ የተነሳ የመሬቱ ፍሬያማ አካል በጎርፍ በመጠራረግ እንደገና ዘር ዘርቶ ለማብቀል የማይቻልበት ሁኔታ ይፈጠራል። ከዚህም ባሻገር በየቦታው ለጊዜው ሀብት ለማካበትና በአንድ ጊዜ ቱጃር ሆኖ ለመገኘት ሲባል ከዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር በመስማማትና በመፈራረም  በሳይንስ ያልተጠና የማዕድን አወጣጥ በተፈጥሮና በሰው ህይወት ላይ ከፍተኛ አደጋ ያስከትላል። በዚህም ምክንያት የተነሳ አንድ አካባቢ ስለሚመረዝ ቦታዎች ከብት የማይረባባቸው፣ ሰው የማይኖርባቸውና ምንም ነገር የማይበቅልባቸው ይሆናሉ።

ይህ ብቻ ሳይሆን አንድ አገዛዝ በዓለም አቀፍ ኮሙኒቲው በሚባለው እየተመከረና እየታገዘ ከተፈጥሮና ከህብረተሰብ ህግ ጋር የማይጣጣም የኢኮኖሚ ፖሊሲ አውጥቶ ተግባራዊ የሚያደርግ ከሆነ የግዴታ የሰው የማሰብ ኃይል እንዲዘበራረቅ ያደርጋል። ውስጣዊ ኃይሉ ወደ አንድ አቅጣጫ እንዲያተኩር በማድረግ የመፍጠር ኃይሉ እንዲሟጠጥ ያደርጋል። በዚህም ምክንያት የተነሳ በተፈጥሮ ውስጥ ያለን ሀብት በማሰብ ኃይሉ እየታገዘ ህብረተሰብአዊ ሀብት እንዳይፈጠር ያደርጋል። በአገራችን ምድር ለሃያ አምስት ዐመታት ያህል ተግባራዊ መሆን የጀመረውና በገበያ ኢኮኖሚ ስም የሚካሄደው ፖሊሲ ዋና ዓላማው  ህብረተሰብን ማዘበራረቅ ብቻ ሳይሆን፣ እያንዳንዱ ዜጋ የተፈጥሮንና የህብረተሰብን ህግ ተረድቶ ቆንጆ ቆንጆ ነገሮች እንዳይሰራ የተወጠነ የኢምፔሪያሊስቶች ሴራ ነው። ሁሉ ነገር በገበያ ኢኮኖሚ ዙሪያ አካባቢ የሚሽከረከር ከሆነ የሰው ጭንቅላት ገንዘብ በማግኝት ይጠመዳል። ጠቅላላው የኑሮው ፍልስፍና ገንዘብ ወደ ማግኘት ስለሚለወጥ አብዛኛው ህዝብ ተፈጥሮ የሰጠውን በልዩ ልዩ መልክ የሚገለጽውን የማሰብ ኃይሉን እንዲያጣ ይገደዳል። በመሆነም ከሰብአዊነት ይልቅ አረመኔያዊነት በመስፋፋት አንድ ህዝብ ወደ መበላላት ያመራል። በተለይም ደግሞ እንደዚህ ዐይነት ናላው የዞረ አገዛዝ ስልጣን ላይ ሆኖ  የሱም መስገብገብና ድርጊቱ እንደምሳሌ በሚወሰድበት አገር አንድ ህዝብ አቅጣጫውን እንዲስት ይገደዳል። ግብረ-ገብነትና ስነ-ምግባር የህብረተሰቡ መለኪያዎች መሆናቸው ቀርቶ ሀብት ማካበትና በማቴሪያል መሸብረቅ መለኪያዎች ይሆናሉ።

ከዚህ ስንነሳ በወያኔ አገዛዝ በአገራችን ምድር ተግባራዊ የሆኑት የኢኮኖሚም ሆነ የጎሳ ፖለቲካዎች በሙሉ ከፍተኛ የሆነ የሀብት ውድመት እንዲፈጠር ነው ያደረጉት። እያንዳንዱ ዜጋ የማሰብ ኃይሉን በመጠቀም ርስ በርሱ የተሳሰረ  ግን ደግሞ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተደገፈ ህብረተሰብአዊ ሀብትና፣ ርስ በርሱ የሚደጋገፍና የሚከባበር ህብረተሰብ እንዳይፈጠርና እንዳይገነባ ነው ያደረገው። በተለይም የብሄረሰብ መብት የሚባለውና በክልል ደረጃ የተዋቀረው የከፋፍለህ ግዛ „ፖለቲካ“ ዋና ዓላማው ይህንን በተለያዩ ጎሳዎች መሀከል ሊኖር የሚችለውን የዕውቀትና የሃሳብ መለዋወጥ፣ እንዲያም ሲል የካፒታልና የሰው ኃይል እንቅስቃሴ እንዳይኖር ያገደ ነው። በመሆኑም ጠቅላላው ህዝብ አንድ ላይ ሆ ብሎ በመነሳት ብሄራዊ ምወይም አገር-አቀፍ  በሚባሉ ተግባሮች ላይ እንዳይሰማራ ያገደው እጅግ አደገኛ አካሄድ ነው። ከተማዎችን እንዳይገነባ፣ በየክልሉ የሰራ ክፍፍል በማዳበር ሰፋ ያለ ገበያ እንዳይገነባ፣ በአጠቃላይ ሲታይ ጠቅላላው ህዝብ እዚያው ቀጭጮ እንዲቀር የሚያደርግ ፖሊሲ ነው ባለፉት ሃያ አምስት ዐመታት ተግባራዊ የሆኑት። በዚህ ዐይነቱ የክልልና የማሰብ ኃይልን የማወደም ዕቅድና ተግባር የወዳጅ አገሮች የሚባሉት እንደ እንግሊዝና አሜሪካ እንዲሁም ሌሎች የምዕራብ አገሮች ተሳትፈውበታል። አገዛዙን በመሳሪያም ሆነ በገንዘብና በተለያዩ የተንኮል ዘዴዎች በማሰልጠንና በመደጎም ጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ በራሱ ተነሳሽነትና ዕውቀት አንድ ጤናማና ሚዛናዊ ያለው ህብረተሰብ እንዳይመሰረትና እንዳይገነባ አድርገውታል። በርዳታ ስም በመግባትና በመሰግሰግ አቅመ-ቢስ አድርገውታል። በዚያው መጠንም አገሪቱ ወደ አስረሽ ምቺው ተለውጣለች። ሰፊውን ህዝብ ቡና አምራች፣ አበባ ተካይ፣ የሸንኮራ አገዳ አብቃይና ስኳር አምራች በማድረግ ለምዕራቡ ዓለም የጥሬ-ሀብት አቀራቢ አድርገውታል። ባጭሩ የባሪያ ስራ እንዲሰራና ዘለዓለሙኑ እንደ ነፃና ኩሩ ዜጋ ሆኖ ራሱን አውቆ እንዳይኖር አግደውታል። ስለሆነም በአገራችን ምድር ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በከፍተኛ ደረጃ ሀብት ሊወድም የቻለውና ህዝባችንም የማሰብ ኃይሉን ተጠቅሞ ቆንጆ አገር እንዳይገነባ የተደረገው በዚህ ዐይነቱ የእከክልኝ ልከክልህ፣ በውስጥና በውጭ ኃይሎች መሀከል በተፈጠረው መተሳሰርና መተጋገዝ ነው። ከዚህም አንፃር ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ስልጣንን የተቆናጠጠው የወያኔው አገዛዝ የውጭ ቅምጥ ነው ማለት ይቻላል። ጠቅላላውን የኢትዮጵያን ህዝብም ሆነ የትግሬን ብሄረሰብ የሚወክል አይደለም። በከፍተኛ ደረጃ የተፈጥሮ ሀብትና የሰውን ልጅ የማሰብ ኃይል ያወደመና፣ አካሄዱና ተግባራዊ ያደረጋቸው ፖሊሲዎች በሙሉ ዩኒቨርሳል የሆነውን የሰውና የተፈጥሮ፣ እንዲሁም የህብረተሰብን ህግ የሚጻረሩ እጅግ አደገኛ ድርጊቶች ናቸው ማለት ይቻላል። በ1930ዎቹ ዓመታት የጀርመን ናዚዎች ተግባራዊ ካደረጉት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጋር እንኳን የቅንጣትም ያህል የሚወዳደር አይደለም። እጅግ በጠባብ ስሜት በመወጠር የሶስት ሺህ ዐመት ታሪካዊ ቅርስ እንዲወደም ያደረገና፣ በተለያዩ መልኮች የሚገለጹ አጸያፊ ድርጊቶች እንዲስፋፉና፣ የአብዛኛው ህዝብ የኑሮ ፍልስፍና እንዲሆን ያደረገ ተፈጥሮአዊ ህግን የሚጻረር ነው። በህብረተሰብአችን ውስጥ የጨአት መቃም መስፋፋት፣ የሴተኛ አዳሪዎች ቤት መስፋፋትና በዝሙት ዓለም ውስጥ መዋኘት፣ የአገሪቱ ሀብት ሊሸከም የማይችለውን ውድ ውድ መጠጦችና አሸብራቂ ዕቃዎች እያመጡ ሀብት ማውደምና ታዳጊውን ትውልድ እንዲባልግ ማድረግ… ወዘተ. እነዚህ ሁሉ የአንድን ህብረተሰብ ጤናማና ሚዛናዊ አገነባብ የሚጻረሩ ናቸው። አንድ ህብረተሰብ ተከታታይነት(Sustainable) እንዳይኖረው የሚያደርጉ ናቸው። የህብረተሰቡ ኑሮ የተዘበራረቀ እንዲሆን በማድረግ ለበሽታ የሚዳርጉት ናቸው። ኃይሉን የሚሟጥጡ ናቸው።

ይሁንና ግን ህዝባችን ብዙ ግፍ እየደረሰበት፣ በምድር ላይ የሚታየው እጅግ የሚዘገንና ህዝባችንም የባሰውኑ በድህነት ዓለም ውስጥ በተወረወረበትና በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ በረሀብ አለንጋ በሚገረፍበት አገር ውስጥ አገዛዙና ካድሬዎቹ፣ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ኩሙኒቲው የሚባሉት የአምባገነኖች የጀርባ አጥንት የሚነግሩን በአገራችን ምድር ተዓምር እየተሰራ መሆኑን ነው። ህዝባችንና አገራችን በታሪካችን  ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ የኢኮኖሚ ዕድገትና ብልጽግና እያዩ ናቸው ነው ብለው የሚነግሩን። ህዝባችን የሚኖረው በአሸበረቁ ቤቶች፣ በጋርተን በተከበቡ ከተማዎች፣ መንደሮችና ከተማዎች በልዩ ዐይነት የትራንስፖርቴሽን መገናኛዎች በመገናኝት ህዝባችን በምድር ላይ የገነት ኑሮን እየኖረ ነው እያሉ ለማሳመን የሚሞክሩት። ምንም ስለኢኮኖሚ ዕድገትና ስለ አገር ግንባታ ምንነት የማይረዱና፣ አንድስ ህብረተሰብ በምን መልክ መደራጀትና መገንባት እንዳለበት ለመገንዘብ የማይፈልጉ እዚህ አውሮፓና አሜሪካ የሚኖሩ የአገዛዙ አቀንቃኞች የሚሉንም ይህንን ነው። አገሪቱ ሌሎች አደጉ የሚባሉ አገሮች ደረጃ ለመድረስ የቀራት ትንሽ ጊዜ ነው እያሉን ነው።  ይህንን ዐይነቱን ነገሮችን እየገለበጡ ማየት ከድንቁርናና ከጭንቅላት መዛግ ጋር ማያያዝና ማገናኘት ይቻላል። የግሪክ ፈላስፎች የሚሉት አንድ ግሩም አባባል አለ። ይኸውም ጭንቅላት ከታወረ ዐይን ማየት አይችልም የሚለው ፍልስፍናዊ አባባል ነው። በሌላ አነጋገር ጭንቅላቱ ሰብአዊ በሆነ ትምህርት ያልተዋቀረ ስለሰው ልጅና ስለተፈጥሮ ምንነት ሊረዳ አይችልም። የኑሮ ፍልስፍና ስሌለውም  ኑሮው ሁሉ ገንዘብ ከማግኝት የሚያልፍ አይደለም። ስለዚህም ከእንደዚህ ዐይነቱ ጭንቅላታቸው ከታወሩ ሰዎችና ስለ ሰውልጅ ምንነት ከማይረዱ ኢትዮያውያን ምንም የምንጠብቀው ነገር በፍጹም ሊኖር አይችልም።  ይህንን ካልኩኝ በኋላ ወደ ተጨባጩ ሁኔታ ልምጣ።

ወያኔ ያልገባውና ሊገባው የማይችለው ነገር !

እስካሁን ድረስ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለብዙዎቻችን እንቆቅልሽ የሆነብን ነገር እንዴት አድርጎ የጠቅላላው ኢትዮጵያ የስልጣኔ ምንጭ ከሆነ አካባቢ ብቅ ያሉ ግለሰቦችም ሆነ ቡድኖች በተቀረው ህዝብ ላይ ሳይሆን በራሳቸውም ታሪክና ስልጣኔ ላይ እንደሚዘምቱ ነው። ሁላችንም አምነን የተቀበልነው ነገር ከአክሱም በፊትም ሆነ ከአክሱም ጀምሮ የነበሩት አገዛዞች ለዛሪዪቱ ኢትዮጵያ የስልጣኔ ምንጮች እንደሆኑ ነው። ወያኔዎች ግን ይህንን በመካድና የራሳቸውን ልዩ ዓለም በመፍጠር የተቀረይቱን ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን እያራቆቷትና ምስቅልቅሏን እያሳጧት ነው። ጠቅላላው ህዝብ የበደላቸው ይመስል ከውጭ ኃይሎች ጋር በማበር በህዝባችንና በአገራችን ላይ ሁለ-ገብ ጦርነት አውጀውብናል። ራሳቸው በልዩ ደሴት ይኖሩ ይመስልና፣ በራሳቸው ጥረት ብቻ ታላቋን ትግራይ ይገነቡ ይመስል ከፍተኛ ዝርፊያ እያደረጉ ነው።  የታሪክ ወንጀል እየሰሩ ነው።

ከዚህ ስንነሳ ወደ ሰሜኑ የውልቃይት ጽጌ ሁኔታ ስንመጣ እጅግ የሚያሳዝንም የሚያስቅም ሁኔታ እንመለከታለን። በመጀመሪያ ደረጃ ያ አካባቢ የወልቃይቶች እንደሆነ ራሳቸው አንዳንድ የትግሬ ምሁራንና የገዢው መደብ አባል የነበሩ አረጋግጠውታል። የትግሬ ክፍለ-ሀገር አካል ነው ብሎ ማውራት የተረት ተረት እንደማውራት ይቆጠራል። በሌላ ወገን ግን ወልቃይትና ጸገዴ ብቻ ሳይሆኑ፣ ጤናማ አስተሳሰብ ያለው ጠቅላላው አገራችን በዚያች ምድር የሚኖር ህዝብ ወይም የተለያዩ ብሄረሰቦች ሀብትና አገርም ነች። በተለይም ስለ ስልጣኔና ስለዕድገት፣ እንዲሁም ስለህብረተሰብና ስለ ህብረ-ብሄር ምስረታ፣ እንዲያም ሲል በአንድ ባንዲራ ስር ስለሚተዳደር ህዝብ የሚያወራ ይህ የኔ መሬት ነው፣ ያ ያንተ ነው ብሎ አንዱ ኢትዮጵያዊ በሌላው ላይ ሊዘምትበት አይችልም። በሌላ አነጋገር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በጠቅላላው ኢትዮጵያ ምድር በመንቀሳቀስ ህጋዊ በሆነ መልክ፣ የአካባቢውን ህዝብ ሳይጋፋ፣ ሊሰራ፣ መሬት ሊከራይና እዚያው በመቀመጥ ቤት ሰርቶ ሀብት ሊያፈራ ይችላል። ፋብሪካዎች በማቋቋምና የስራ መስኮችም በመክፈት ማህበራዊና ህብረተሰብአዊ ግዴታውን ሊወጣ ይችላል። ይህ ጤናማ አካሄድ ለማንኛውም በአንድ አገር ውስጥ ለሚኖር ህዝብ ለዕድገቱ እጅግ አስፈላጊ ነው። ይህ የኔ ክልል ነው አትድረሰብኝ ቢል በራሱ ላይ ነው የሚፈርደው። የዕውቀትና የሀብት መንሸራሸር እንዳይኖር ነው የሚያደርገው። አካባቢው እንዳይለማና ቀሰ በቀስም ህብረተሰብአዊ መተሳሰርና መደጋገፍ እንዳይኖር ነው የሚያደርገው። በአጭሩ የዕድገትና የስልጣኔ ዕንቅፋት በመሆን አንድ ህዝብ ለዝንተ-ዓለሙ በጨለማ ዓለም ውስጥ እንዲኖር ያደርጋል። ከዚህ ስንነሳ በወልቃይት-ጸገዴና በትግሬ ብሄረሰብ መሀከል የረጅም ዐመታት መተሳሰር ያለና፣ በተለይም ከትግሬ እየመጡ እዚያው እየሰሩና ሀብት እያፈሩ መኖር የተለመደ ነገር ነው። ነግሩ መበላሽት የጀመረው ወያኔዎች ትግል ሲጀምሩና ታላቋን ትግሬ እንመሰርታልን ብለው ወደ ድል ካመሩና አዲስ አበባ ላይ ቁጥጥ ማለት ከጀመሩ ወዲህ ነው።

ይህንን ህልማቸውን ዕውን ለማድረግ ስልጣን ከመያዛቸው በፊትም በኋላ ሆነ በወልቃይት ጸገዴ ኗሪ ሰዎች ላይ አሰቃቂ ድርጊቶችን ፈጽመውባቸዋል። የህዝቡ ቁጥር እንዲቀንስ እንደ ቢልጌት ከመሳሰሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ የጥቁር ህዝብ ቁጥር እንዲቀንስ እጅግ አደገኛ ስራ ከሚሰሩ ከናጠጡ ሀብታሞች ጋር በመመሰጣጠር የአማራው ህዝብ ቁጥር እንዲቀንስ የስትሬላይዜሽን ፕሮግራም ተግባራዊ አድርገዋል። ብዙ ጥናቶችም እንደሚያመለክቱት ወያኔ ስልጣን ከያዘ በኋላ የአማራ ብሄረሰብ ቁጥር ወደ አራት ሚሊዮን ያህል ቀንሷል። ብዙ ለአቅመ አዳም የደረሱ ሴቶች የወር አበባቸውን እንዳያዩና  እንዳያረግዙ ተደርገዋል። በተለይም በወንዶች ላይ አስቃቂ ግፍ ተፈጽሞባቸዋል። በጠራራ ጸሀይ የተገደሉት ዘመዶቻቸው ሬሳቸውን ለማንሳት ሲሯሯጡ የለም አሞራ ይብላው በመባል ተከልክለው የሰው ልጅ የአሞራና የጅብ እራት ተደርጓል። ይህ አጉል የጥላቻ ዘመቻ ሳይሆን በግልጽ የተካሄደ ነው። ይህ ድርጊት ፋሺስታዊ ድርጊት ነው። ሌላ ሊባል አይችልም።

ያም ሆነ ይህ፣ ይህ የወያኔ እጅግ አስቃቂ ድርጊትና ታላቋን ትግሬን የመገንባት ህልም ምንድነው የሚያረጋግጠው?  በአጭሩ ይህ ድርጊታቸው የሚያረጋግጠው ድንቁርናቸውን ነው። የተፈጥሮንና የህብረተሰብን ህግ ያልተረዱ መሆናቸውን ነው። በመጀመሪያ ደረጃ፣ አዲስ አበባ ተቀምጦ የኢትዮጵያን ህዝብ ወክላለሁ ብሎ ወደ ውጭ ዕውቂያን ያገኘ አገዛዝ አንድን አካባቢ በመሸንሸን ወይም ቆርጦ በመውሰድ የትግሬ አካል ለማድረግ መሞከር ከማሰብ ኃይል ጉድለት የሚመነጭ እጅግ አደገኛ አካሄድ ነው። በሁለተኛ ደረጃ፣ በታሪክ ውስጥ አንድ ወጥ የሆነ ብሄረሰብ ስልጣኔንና ዕድገትን ያመጣበትና የመነጠቀበት ሁኔታ በታሪክ ውስጥ ታይቶ አይታወቅም። የስልጣኔን ታሪክ በደንብ ለተከታተለ አገሮች ሊያድጉና የአንድ አገር ህዝብም የመፍጠር ችሎታው ሊዳብር የሚችለው፣ አንደኛው ከሌላው ህዝብ ወይም ብሄረሰብ ጋር ሲጋቡ፣ ሲቀላቀሉና የሃሳብና የባህል ልውውጥ ሲያደርጉ ብቻ ነው።  ከማዕከለኛው ምስራቅ አገሮች፣ ሶሪያ፣ ኢራክና ሌሎች የአካባቢው አገሮች ከሁለትና ከሶስት ሺህ ዘመናት በፊት ከተለያዩ አካባቢ የፈለሱ ህዝቦችን በማስተናገድ ነው በዘመኑ ስልጣኔያቸውን የተገናጸፉት። የግብጽ ስልጣኔ የኋላ ኋላ ዕምርታን ሊያገኝ የቻለው በታላቁ አሌክሳንደርና፣ ከሌላ አካባቢ በመጡ ፈላስፎችና ምሁራን አማካይነት ነው። በስድስተኛውና በአምስተኛው ክፍለ-ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት አዮን በምትባለው ደሴት የግሪኩ ስልጣኔ ሲያብብ ከግብጽና ከህንድ  በመጡ ዕውቀቶች፣ ነጋዴዎችና የዕደ-ጥበብ ሰዎች አማካይነት ነው። በአውሮፓ ምድር ውስጥም ከአስራአራተኛው ክፈለ-ዘመን ጀምሮ ቀስ በቀስ ስልጣኔ ዕምርታን ማግኘት የቻለው ከተለያዩ አካባቢዎች በመጡ ህዝቦች አማካይነት እዚያ ሲጋቡና ዕውቀታቸውን ሲያዳብሩ ነው። ጀርመንም ወደ ኋላ በቀረችበት በ18ኛውና በ19ኛው ክፍለ-ዘመን የፕረሽያ ነገስታት ወይም ሞናርኪዎች ከሆላንድና ከፈረንሳይ በሃይማኖት ሰበብ የተባረሩ አዋቂዎችን በማስተናገድና ቴክኖሎጂውን ውስጣዊ በማድረግ ነው ከሌሎች እርምጃዎች ጋር ተደምሮ ጀርመን በአንድና በሁለት ትውልድ ለማደግ፣ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ሰፋ ያለ ኢኮኖሚ መገንባት የቻለችው። ሆላንድ ራሷ በ17ኛው ክፍለ-ዘመን፣ እንግሊዝ ደግሞ እንደዚሁ በ18ኛው ክፍለ-ዘመን ከወጭ ዕውቀታቸውን ይዘው በመጡና እዚያው ኗሪ በሆኑ ይሁዲዎችና ሌላ ዘሮች አማካይነት ነው የኢንዱስትሪ አብዮት ባለቤት ለመሆን የበቁት።  ዛሬ አሜሪካን ኃያል መንግስት ሆኖ ብቅ ማለት የቻለው ከተለያዩ አገሮች የመጡ ህዝቦችን በማስተናገድ ነው። ይህ ዐይነቱ ህብብረተሰብአዊ ዕድገት በተፈጥሮ ውስጥ ይታያል። ሞኖ ካልቸርድ የሆኑ ሰብሎች በቀላሉ ለተባይ ይጋለጣሉ። ሌላ የሚከላካለቸው የሰብልና የአትክልት ዐይነት ከወደመ የማደግና የመዳበር ኃይላቸው የመነመነ ነው። ለጊዜው በማዳበሪያ ኃይል ምርታማ ቢሆኑም ከጊዜ ብዛት በኋላ ምርታማነታቸው በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ ነው የሚመጣው። በቀላሉ ለተባይም ይጋለጣሉ። በሌላ አነጋገር መቀላቀልና መደጋገፍ የተፈጥሮ ህግና ለዕድገትም በጣም አመቺ ነው። በዚያውም መጠን ውስጣዊ ጥንካሬን ያገኛሉ።

ከዚህ ስንነሳ የወያኔ የአማራን ዘር እያጠፉ የራስን ግዛት ለማስፋፋትና ለማበጥ መሞክር በፍጹም ወደ ዕድገት የሚያመራው አይደለም። ከላይ ለማሳየት እንደሞከርኩት የትግሬ ብሄረሰብ ከሌላው ህዝብ ጋር ሲጋባና ሲቀላቀል ብቻ ነው ጤናማ ዕድገትን ሊጎናጸፈ የሚችለው። የወያኔዎች ትልቁ ችግር ከውጭ ኢንዱስትሪ እያንጋጉ በመትከል ዕውነተኛ ዕድገትን የሚጎናጸፉ መስሏቸዋል። በታሪክ ውስጥ እንደተረጋገጠው የቴክኖሎጂ ምጥቀትና በኢንዱስትሪ ማደግ ኢቮሉሺናዊ አካሄዶች ናቸው። በምዕራብ አውሮፓ ውስጥ ከሞላ ጎደል ጤናማና የተስተካከለ ዕድገት ሊመጣ የቻለው የኢንዱስትሪ ዕድገት ከታች ወደ ላይ (Organic Grwoth) በመጓዙ ነው። በሌላ አነጋገር በመጀመሪያ የሚያማምሩ ከተማዎችን በመገንባት፣ ለህዝብ መኖሪያ ቦታዎችን በመስራት፣ የገበያ አዳራሾችንና ሌሎች ህዝቡን ሊሰበስቡና የፈጠራ ችሎታውን ሊያዳብሩ የሚችሉ ነገሮች በመስራት ነው።በመጀመሪያ ደረጃ በዕደ-ጥበብ አማካይነትና(Industrialiazation before Industrialization) በንግድ መዳበር የሀብት ክምችትን በማዳበር ነው ወደ ኢንዱስትሪ አብዮት መሸጋገር የቻሉት። በዚህም ምክንያት የተነሳና በከፍተኛ  ደረጃ የህዝብና፣(Social Mobility) የሀብት(Capital) እንቅስቃሴ  አማካይነት በቀላሉ ማደግና መበልጸግ ችለዋል።  ይኸኛው ነው ጤናማው የካፒታሊዝም ዕድገት። በአንፃሩ ይኸኛውን ጤናማውን የዕድገት ጉዞ ያልተከተሉ እንደ ብራዚል፣ ሜክሲኮና ብዞዎች የአፍሪካ አገሮች ውስጥ መዘበራረቅ የሚታየውና ስርዓት ማጣትና የሀብት መባከን ሊፈጠር የቻለው ተፈጥሮአዊ የሚመስለውን የህብረተሰብ አገነባብና የኢኮኖሚ ዕድገት አካሄድ ባለመከተላቸው ነው። በሌላ አነጋገር በአንድ ወጥ ብሄረሰብና ከላይ ወደ ታች በሚጫን የኢንዱስትሪ ተከላና ጋጋታ ሚዛናዊ ዕድገት ሊመጣ አይችልም። የህዝቡም የመፍጠር ኃይል ውስን ስለሚሆን ቲክኖሎጂያዊ ምጥቀት ሊታይ አይችልም።

ስለሆነም አንድን ህዝብ እየጨረሱና መሬትን እየቆረሱ በመውሰድ ታላቋን የትግሬን ሬፑብሊክ እንመሰርታለን፣ ጠንካራ ኢኮኖሚ እንገነባለን፣ በዚህም አማካይነት የተቀረውን የኢትዮጵያ ክፍል የጥሬ-ሀብት አምራችና ላኪ በማድረግ አቀጭጨን እናስቀረዋለን የሚለው ህልም በፍጹም የሚሰራ አይደለም። ከዚህ ባሻጋር የአንድ አገር ዕድገት በኢንዱስትሪ መንጋጋት ብቻ የሚገለጽ አይደለም። የአንድ ህዝብ ዕድገት ሁለንታዊ ነው። በሚያማምሩ ከተማዎችና መንደሮች የሚገለጽ ነው። በቲያትርና በሙዚቃ እንዲሁም በሙዚየሞች የሚታይ ነው። በጋርደኖችና በተለያዩ የመገናኛ ማመላለሻዎች የሚገለጽ ነው። እንደዚህ ዐይነቱ በልዩ ልዩ መልክ የሚገለጸው ስልጣኔ ከአንድ ብሄረ-ሰብ በተውጣጣና ከሌላው ጋር ባልተቀላቀለ በፍጹም ተግባራዊ ሊሆን የሚችል አይደለም። ከዚህ ይልቅ ወደድንም ጠላንም ብዙ ብሄረሰቦችን የሚያሰተናግደውና፣ በተለያዩ ነገሮች የሚገለጸው፣ ግን ደግሞ የተሳሰረው የተቀረው የኢትዮጵያ ክፍል ጥሩና አገር ወዳድ መንግስት ካገኘ ከሃያ እስከ ሃምሳ ዐመት ባለ ጊዜ ውስጥ የተስተካከለ ዕድገትን ሊያመጣ ይችላል። የኦሮሞው፣ የጉራጌው፣ የጎሙ-ጎፋው፣ የወላይታው፣ የከፍቼው፣ የአማራውና የሌሎችም ጤናማ አስተሳሰብ ወደ ዕድገት አቅጣጫ እንዲመጣ ከታቀደና ከተጠና ባጭር ጊዜ ውስጥ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ሁለ-ገብ ዕድገት ሊታይ ይችላል። ይሁንና እነዚህ የተቀሩት የኢትዮጵያ ግዛቶች ለማደግና በአጭር ጊዜ ውስጥ ዕምርታን ለማግኘት ከምዕራብ አውሮፓ የካፒታሊስት አገሮች ቴክኖሎጂን መስረቅና መኮረጅ አለባቸው። ብዙ ነገሮች የተፈጠሩ ስለሆነ ከእንግዲህ ወዲያ ብዙም አዲስ ነገር መፍጠር አንችልም። ጥያቄው ከውጭ የሚመጣውን ቴክኖሎጂ እንዴት አድርገን ከኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር ማገናኘትና ህዝቡ የራሱ በማድረግ ሊያሻሽላቸው ይችላል?  በሚለው ላይ ነው በየጊዜው ምርምር መደረግ ያለበት።

ያም ሆነ ይህ የወያኔዎች ሀብትን መዝረፍና ህዝብን እያፈናቀሉ ለማበጥና ለማደግ፣ እንዲያም ሲል  ሌላውን ለመዋጥና አቀጭጮ ለማስቀረጥ መሞክር ገደብ የሌለው ድንቁርና ነው። ሳይንሳዊ አካሄድ አይደለም።  የራሱን የትግሬ ህዝብ የሚያቀጭጨውና ዘለዓለሙኑ እየፈራና እየተባ እንዲኖር የሚያደርገው ነው። በራሱ ላይ እንዳይተማመን የሚያደርገው ነው። በሌላ ወገን ደግሞ ተሰርቶ ባልተገኘ ሀብት በመዘባነን ሌላውን የሚንቁበት ሁኔታ ይፈጠራል። ይሁንና ግን በዚህ አካሄዳቸው ወያኔዎች የተቀረውን የዋሁን የትግሬ ብሄረሰብ እየጠቀሙት እየመሰላቸው የመጨረሻ መጨረሻ እርቃኑን እንዲቀር እያደረጉት ነው። ይህ አስተሳሰባቸውና አካሄዳቸው እንዲሁም ኢ-ሰብአዊ ድርጊታቸው  በተገለጸላቸውና የበላይነት ስሜት በማይሰማቸው የትግሬ ምሁራን መቆም ያለበት ጉዳይ ነው። ይህ የወያኔዎች አካሄድ በተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ፣ በተለይም በአማራው ላይ ብቻ ያነጣጠረ ሳይሆን በጠቅላላው በጥቁር ህዝብና ስልጣኔው ላይ ያነጣጠረ እጅግ አደገኛ አካሄድ ነው። ስለሆነም እንደዚህ ዐይነቱ የአንድን ብሄረ-ሰብ የበላይነት ለማጎልመስ የታቀደ ህልም በእንጭጩ መቀጨት አለበት። የዕድገትና የስልጣኔ ፀር ነው። ጠቅላላው ህዝብ እየተሸማቀቀ እንዲኖር የሚያደረገው ነው። ስለሆነም ወያኔ የግዴታ ዲሞክራሲያዊ በሆነና በሰለጠነ አገዛዝ መተካት አለበት።

ኢ-ሳይንሳዊ የፖለቲካ አካሄድ !

በአገራችን የፖለቲካ ትዕይንት ታሪክ ውስጥ ቢያንስ አብዮቱ ከፈነዳበት ጊዜ ጀምሮ ስለ ፖለቲካ ስልት ያለን ግንዛቤ ሳይንሳዊ ያልሆነና ፍልስፍናዊ መሰረት የሌለው ነው። ፖለቲካ የሚባለው ህብረተሰብን የሚያረጋጋ፣ አርቆ-አሳቢ አድርጎን በማሰብ ኃይላችን እንድንፈጥር፣ አስተሳሰባችንን በማሾል የህብረተሰባችንን ሁኔታና በፖለቲካው መስክ የሚታየውን የተጣመመ አካሄድ በተወሳሰበ መልክ በመተንተን እንድንረዳውና መፍትሄም እንድንሻ የሚያደርገን ሳይሆን፣ የስልጣን መወጣጫና የራስን ጥቅም ማሳደጃ ሆኖ ነው የተገነዘብነውና ይህንንም  እንደስልት የተጠቅምንበት። ከዚህም በላይ ፖለቲካ ህብረተሰብአዊ ፕሮጀክትን ለማካሄድ የሚጠቅም መሳሪያና፣ በህብረተሰብ ውስጥ የሚከሰቱ ቅራኔዎችን በሳይንስ እየተነተኑ መፍቻ መስጫ መሳሪያ እንዳልሆነ ነው ሁላችንም እንድነረዳው የተደረገው። በዚህም ምክንያት የተነሳ ፖለቲካ የሚባለው በስሜታዊነት የታመቀ፣ የራሳቸው አጀንዳ ያላቸው ግለሰቦች እነሱን የሚመስል ስልጣንን ብቻ የሚመኝ አድርባይ እየፈለጉ በቡድን የሚደራጁበትና፣ አንዱን በማራቅ ሌላውን በማስጠጋት አንድን አገርና መንግስትን የግላቸው ሀብት አድርገው በመቁጠር በነሱ የተወላገደ አስተሳሰብ የማይስማማውን ሁሉ የሚወነጅሉበትና የሚያርቁበት መሳሪያ ሆኖ ነው የተወሰደው። ይህ ዐይነቱ የፖለቲካ አመለካከት ግንዛቤ ተግባራዊ በሚሆንበት ጊዜ በየካቲቱ አብዮት ዘመን እንደታየው የዲሞክራሲንና የማርክሲዝምን አርማ አንግቦ ዲሞክራሲ ያለገደብ እያለ የሚጮኸው ሁሉ ጠብመንጃ አንስቶ ወንድሙን የሚገድልበትና የሚያሳድድበት መሳሪያ ለመሆን በቃ። ፖለቲካ ሳይንስና ህይወት ያለው፣ ህዝብን የሚያቀራርብና ለስራ የሚያዘጋጅና ህብረተሰቡንም በየረድፉ አደራጅቶ ታሪክን ለመስራት የሚጠቅም መሳሪያና በየጊዜው እየተሻሻለ በየወቅቱ የሚከሰቱ ችግሮችን መፍቻ ዘዴ ከመሆን ይልቅ አንድን አገር ወደ ጦርነት አውድማነት መለወጫ መሳሪያ ሆነ። አብዮቱ ተቀለበሰ ከተባለና የብዙ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ህይወት ከጠፋ ከሰለሳ ዐመታት በኋላም አሁንም ቢሆን የፖለቲካ ግንዛቢያችን ይህንን ያህልም የተለወጠ አይመስለኝም። ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ምሁራዊነትን ያካተተ፣ የአንድን የህብረተሰብ ታሪክ በደንብ ያገናዘበና የዕድገቱንም ውጣ ወረድነት በደንብ ለመተርጎም የሚያስችል፣ ፍልስፋናዊና ሳይንሳዊ ዕውቀትን ምርኩዝ ያደረገ ለመሆኑ ብዙዎቻችን ጭንቅላት ውስጥ በፍጹም የለም። ከዚህም በላይ ለፖለቲካ እታገላለሁ የሚል ግለሰብም ሆነ ቡድን የግዴታ መንፈሳዊ ነፃነትን መቀዳጀትና፣ ከማንኛውም ለአንድ ህብረተሰብ ዕድገት ጠንቅ ከሆኑ ዕቡይ ተግባሮች መላቀቅን እንደሚጠይቅ እስከዚህም ድረስ ግልጽ አይደለም። በመሰረቱ ዕውነተኛ የፖለቲካ ሰው ስነ-ምግባራዊና ግብረ-ገባዊ ነው። ለአንድ ቡድን ወይም ብሄረሰብ ያደላ ሳይሆን ግዴታውና ኃላፊነቱን የአንድን ህዝብና የአገርን ደህንነት መጠበቅ ነው። ታሪክን ለመሰራት የሚችልና ለዚህም ለሰፊው ህዝብና ለተከታዮቹ ብቃት ያለው አመራር የሚሰጥ መሆን አለበት። ወደ አገራችን ስንመጣ እነዚህ መሰረተ-ሃስቦች በፍጹም የተጤኑና ከሰውነት ጋር የተዋሃዱ አይደሉም።

የዚህ ሁሉ ችግር ምንድነው ? በህብረተሰብአችን ታሪክ ውስጥ የህዝብን ችግር  ስልጣን በመያዝ አማካይነት እንፈታለን ተብሎ ትግል ሲጀመር ከመጀመሪያውኑ ከታች ወደ ላይ መጠናት ያለባቸውን ነገሮች፣ ማለትም ፍልስፍና፣ ሳይንስና የቲዎሪ ዘዴዎች ላይ ለመረባረብ ገቱና ዘዴው የለንም። እነዚህም ነገሮች  እንደ ቅድመ-ሁኔታዎች  መወሰድ ያለባቸውና በጭንቅላትም ውስጥ መቋጠር እንዳለባቸው ግንዛቤ የሚያደርግ የለም። ከዚህም በላይ ተነጻጻሪ ጥናት(Comparative studies) በሚባለው በህብረተሰብ ታሪክ ውስጥ የተለያዩ ህብረተሰቦችን ለማወዳደር የሚያስችል የቲዎሪና የኢምፔሪካል ጥናት ላይ ትኩረት ለመስጠት አለመፈላገችን ከመጀመሪያውኑ ለፖለቲካ የሚደረገውን ትግል የተኮላሸ አድርጎታል። እንዲዚህ ዐይነቱ የተቻኮለና መሰረት የሌለው የፖለቲካ ትግል ዘዴ የግዴታ የሸፍጠኝነትን ስልት ለሚያስቀድሙ በሩን ይከፍትላቸዋል። ከመጀመሪያውኑ ሰፋና ጠለቅ ያለ ዲሞክራሲያዊ ውይይት ስለሚዳፈን፣ የፖለቲካ ድርጅትን ለመመስረት የሚታገሉ ግለሰቦች የግዴታ ለማዳመጥና ለመደማመጥ ለማይፈልግ ካድሬያዊ ፖለቲካ መንገዱን ሁሉ ያመቻቻሉ። በዚህም ምክንያት የተነሳ ታሪክ መስሪያና የስልጣኔ መንገድ ቀዳጅ የሆነው በሳይንስ ላይ የተመሰረተው ፖለቲካ ወደ ቡድናዊነትና መፋጠጫ መድረክ በመለወጥ፣ በርዕዮተ-ዓለም ዙሪያ የሚደረግና የሚካሄድ ትግል ያስመስለዋል። በመሰረቱ ግን ያለፈውን ሃምሳ ዐመት ያህል የሚጠጋውን የፖለቲካ ትግል ታሪካችንን ለተመለከተ ፊዩዳላዊና ጠባብ አስተሳሰብን ያዘለ ነው። በርዕይ ደረጃ አንድን ህብረተሰብ ለመገንባትና መረጋጋት እንዲፈጠር የሚያስችለው ይኸኛው የፖለቲካ አመለካከት ነው በሚለው ላይ አይደለም ትግሉና ክርክሩ ያተኮረውና ይካሄድ የነበረው። እኔ እስከማውቀው ድረስ የግራ ፖለቲካንም ሆነ፣ ባለፉት ሃያ አምስት ዐመታት በሊበራል ርዕዮተ-ዓለምና በነጻ ገበያ ስም የተካሄደውን ትግል ስመለከት ትግሉ በቲዎሪ፣ በሳይንስና በፍልስፍና ላይ ያተኮረና የተመረኮዘ አይደለም። በመሆኑም ይሁ ሁኔታ የግዴታ አድማሳችንን በማጥበብ በድፍረትና በራስ በመተማመን በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ትግል ማካሄድ እንዳንችል አድርጎናል። ያለፈውን አስርና አስራአምስት ዐመት የፖለቲካ ትግላችንን ስንመለከት በዚህ ዐይነቱ አካሄዳችን ብዙም ስለ ስልጣኔም ሆነ ስለህብረተሰብ ግንባታ ለማይነግሩንና ለመተንተን ለማይችሉ ግለሰቦች በሩ ተከፍቷል። ከፖለቲካዊ ክርክርና ውይይት ይልቅ የራሳቸውን የበላይነት ለማስፈን ለሚፈልጉ ግለሰቦች አመቺ ሁኔታን ፈጥሮላቸዋል። በተለይም የግንቦት ሰባቱ ምርጫ ውጤት ሊከሽፍና ህዝባችንም አስራአንድ ዐመት ያህል የግፍ ጽዋን እንዲቀምስና እንዲሰቃይ የተደረገው ይኸኛውን በግለሰቦች ዙሪያ የሚካሄደውን የትግል ፈሊጥ በመከተላችን ነው።

ከዚህ መጠን ብሎ ስለቀረበው ስለፖለቲካ ያለን ግንዛቤ ስንነሳ የወያኔን የተጣመመ ፖለቲካ አካሄድና ህዝብን ማከረባበቻ መሳሪያ አድርጎ መቁጠር መገንዘቡ ከባድ አይሆንም። ወያኔ የትግሬዎች ድርጅት ስለሆነ ነው ይህንን ዐይነቱን የማከረባበት ፖለቲካ ሊያካሂድ የቻለው ከሚለው  ቀላል አስተሳሰብ መነሳቱና መደምደሚያ ላይ መድረሱ ለችግራችን መፍትሄ ሊሆን አይችልም።  ይህ ዐይነቱ አካሄድ የራሳችንን ድክመት ከመሸፈኑም ባሻገር የአገራችንና የህብረተሰብአችንን   አወቃቀርና፣ እንዲሁም የፖለቲካ ባህል እንዳንረዳው ያግደናል። በሌላ ወገን ደግሞ የድርጅቱን ታሪክ ለተመለከተና፣ የኋላ ኋላ ወደ ማፊያነት መለወጥ የግዴታ የመጣበትን ብሄረሰብ ተገን እንዲያደርገው አድርግታል። ይሁንና ግን እስከተወሰነ ደረጃ ድረሰም ቢሆን የህብረተሰብ መሰረቱን(Social Base) ለማስፋት እንደጣረና፣ በተለይም ተጨቆኑ የሚባሉትንና ለሆዳቸው ያደሩትን በመሰብሰብና በጥቅም በመግዛት የተወሰነ ሌጂቲሜሲ ለማግኘት እንደቻለ የማይታበል ሀቅ ነው። ይህ ባይሆን ኑሮ ሃያ አምስት ዓመት ያህል ስልጣን ላይ ለመቆየት ባልቻለ ነበር። ከዚህም በላይ ኢትዮጵያን ለማዳከምና አቅመ-ቢስ አድርጎ ለማቆየት የሚፈልጉ ኢምፔሪያሊስት ኃይሎችን ተገን በማድረግ ዓለምአቀፋዊ ዕውቅናን በማግኘት እነሱ የሚፈልጉትን ፕሮጀክት እንዲሰራላቸው ዕድል አገኙ። ወደ ሶሻል መሰረቱ ስንመጣ ወያኔ ሁለት አካሄድን የመረጠ ይመስላል። በአንድ በኩል ከዚህም ሆነ ከዚያኛው ብሄረሰብ የተውጣጡ ግለሰቦችንና፣ በአብዮቱ ዘመን የዚኸኛው ወይም ያዚያኛው የፖለቲካ ድርጅት አባል የነበሩ ግለሰቦችን ሲያቅፍ፣ በሌላ ወገን ደግሞ በማፊያ ስራ የተሰማራና በተለይም በራሳቸው ጥረት በማደግ ላይ የሚገኙ ግለሶቦችን በማስፈራራት፣ ውዝፍ ቀረጥ አልከፈላችሁም በማለት ወደ እስር ቤት ውስጥ መክተትና ሀብታቸውን መንጠቅ፣ አንዳንዶችን ደግሞ በመግደልና ይህንን የፖለቲካ ስልቱ በማድረግ እስካሁን ድረስ ቆይቷል። ይህንን ዐይነቱን ማፊያዊ ፖለቲካውን የሚከተለው ያልተማሩና ያለተገለጸላቸውን ትግሬዎችን በመጠቀም ነው።

የውጭውን ዓለም ድጋፍ ለማግኘት ሲል ደግሞ አውቆም ሆነ ሳያውቅ ድህነትን ፈልፋይ የሆነውን የኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲን በቀመበልና ተግባራዊ በማድረግ ዕውነተኛ የሊበራል የገበያ ኢኮኖሚ ፖሊሲ አራማጅ ሆኖ ቀረበ። በዚህም ምክንያት የተነሳ እስካሁን ድረሰ ቢያንስ ወደ 40 $ ቢሊዮን የሚቆጠር ዕርዳታ በማግኘትና ራሱን በማደለብ ስልጣኑን ለማጠናከር ቻለ። ከዚህ ስንነሳ በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ተንታኞች ወያኔ ብቻውን እንደቆመና  ካለውጭ ዕርዳታ እዚህ ለመድረስ እንደቻለ የሚሰጠው ትንታኔ ኢ-ሳይንሳዊ ብቻ ሳይሆን በጣም አደገኛም ነው። የውጭ ኃይሎች ለአንድ ደካማ አገር ዕርዳታ የሚሰጡት በእርግጥም የዚያ አገር መንግስት እነሱ የሚፈልጉትን ፖለቲካ፣ በተለይም ደግሞ የትርምስና የጦር ፖለቲካ እስካካሄደ ድረስ ብቻ ነው። የውጭ ኃይሎች በተለይም እንደ አሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም የመሳሰሉት የአገራችንን በሳይንስና በቴክኖሎጂ ዳብሮ የተረጋጋና የተከበረች አገር እንዲገነባ አይፈልጉም። በራሱ የሚተማመን አገር ወዳድ ዜጋና ባህሉን ዕምርታ እየሰጠ የሚጓዝ ትውልድ የነሱ ጠላት እንደመሆኑ መጠን  እንደዚህ ዐይነቱ ትውልድ ስልጣን ላይ እንዲመጣ በፍጹም አይፈልጉም። በመሆኑም አሁንም በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን የሚቀርበው „እሮሮ አሜሪካ ጊዜው ሳያመልጥህ ቶሎ ብለህ የህዝባችን ወዳጅ ሁን“ የሚለው አቤቱታ እጅግ አደገኛና ትጥቅ አስፈቺ ነው። ህዝባችን የዲሞክራሲንና የነጻነት እንዲያም ሲል የስልጣኔን ብርሃን እንዳያይ ከመጀመሪያውኑ በሩን እንደመዝጋት የሚያስቆጥር አደገና አካሄድና ትጥቅ አስፈቺ ነው። አደገኛ የሆነ በፖዘቲቭ ሳይንስ ላይ የተመሰረተ የድህነቱንና የጨለማውን ዘመን የሚያራዝም ነው። ከዚህም በላይ የአገራችን የሶስት ሺህ ዐመት ታሪክና በተደጋጋሚ ሊወሩ የመጡ የውጭ ኃይሎችን በጀግና ልጆቿ አማካይነት መክታ የመለሰችውን አገርና የጀግና ልጆቿን ታሪክ እንደማንቋሸሽ ይቆጠራል። ለኢትዮጵያ ህዝብ ያዘኑ ይመስል በየጊዜው እንደዚህ ዐይነት የእሮሮ ድምጽ ማሰማትና ደብዳቤ መጻፍ ከዓለም ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የሚጣጣም አይደለም። በመጀመሪያ ደረጃ የተለያዩ የአሜሪካ አገዛዞች በታሪካቸው ውስጥ ዕውነተኛ ሰብአዊነትን ያሳዩበትና እሴትም(Values) አላቸው የሚያስብላቸው ታሪክ የላቸውም። የዛሬይቱ አሜሪካ ታላቅ ሆኖ ብቅ ማለት የቻለው በመጀመሪያ ደረጃ 17 ሚሊዮን የሚጠጉ ኢንዲያኖችን ከጨፈጨፈ በኋላ ነው። ከዚያም በኋላ ጥቁር አሜሪካንን በፕላንቴሼን ኢኮኖሚ ላይ በማሰማራትና በመበዝበዝ ነው የካፒታል ክምችትን በማዳበር በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረት ዕድገትን ለመጎናጸፍ የቻለው። እስከ 1960ዎቹ አጋማሽ ድረስ ጥቁር አሜሪካውያን እንደ ነጩ በዕኩልነት የማይታዩ አልነበሩም። ይህ ሁኔታ በመሰረቱ አሁንም ቢሆን ስር ሰዶ ያለ ነው። ብዙ ጥቁር አሜሪካውያን ተነጥለው የሚኖሩና ከነጩ ጋር ሲወዳደር ኮሌጅና ዩኒቨርሲቲዎች ገብቶ የመማር ዕድላቸው በጣም የመነመነ ነው። በተጨማሪም ባልተመጣጠነ የምግብ ዐይነትና በድህነት የተነሳ በብዛት በተለያዩ የስልጣኔ በሽታዎች በሚባሉት የሚሰቃየው ጥቁር አሜሪካዊ ነው።  ከዚህ ስንነሳ የአሜሪካንን አገዛዝ እሴት(Values) ያለው አገዛዝ አድርጎ ማቅረብ የጥቁርን ህዝብ መስደብ ብቻ ሳይሆን በከፍተኛ ደረጃ ታሪክንም ማጣመም ነው።

ሌላው ቢቀር ቢያንስ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ ያለውን ዓለም አቀፋዊ የፖለቲካ ሁኔታ በምንመረምርበት ጊዜ የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም በምንም ዐይነት ዲሞክራሲና ብልጽግናን በሶሰተኛው ዓለም አገሮች፣ በተለይም በአፍሪቃ፣ በላቲንና እንዲሁም በማዕከለኛው አሜሪካ እንዲሰፍንና፣ እነዚህ አገሮች ራሳቸውን እንዲችሉ ያደረገበት ጊዜ የለም። በእነዚህ አገሮች ውስጥ ሁሉ የተካሄዱት የመንግስት ግልበጣዎችና በኮሙኒዝም ስም እየተሳበበ ለዲሞክራሲና ለዕድገት የታጋሉ ግለሰቦች እንዲታረዱ፣ ወደ እስርቤት እንዲወረወሩና እንዲሰቃዩ፣ የተረፈው ደግሞ ወደ ውጭ አገር እንዲሰደድ የተደረገው በአሜሪካን ኢምፔረያሊዝም ዕውቅ ፖሊሲና ድጋፍ ነው። እስካሁን ድረስም አብዛዎቹ የላቲንና የማዕከለኛው አሜሪካ አገሮች በብዙ ሺህ ድሮች በተሳሰሩ ችግሮች የሚሰቃዩት ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ በተዘረጋው አገሮችን ከማዳከም የሚሊታሪ፣ የኢኮኖሚና የፖለቲካ የአሜሪካን ስትራቴጂ ጋር በጥብቅ የተያያዘ ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን፣ አሜሪካና የተቀሩት የምዕራብ አውሮፓ አገሮች እነሱ ብቻ በተቀረው የዓለም ህዝብ ላይ የበላይነትን ይዘው ለመቆየት ሲሉ በሊበራሊዝምና በነጻ ገበያ ስም በአገሮች ላይ ጭነት በማድረግ፣ አልቀበለም ያሏቸውን ደግሞ ተቃዋሚ የሚሏቸውን ቡድኖችንና ግለሰቦችን በገንዘብ፣ በሃሳብና በጦር መሳሪያ በመደገፍ በአንድ አገር ውስጥ በወንድማማቾች መሀከል ጦርነት እንዲካሄድና ደም እንዲፈስ ያደርጋሉ። ዋናው ስትራቲጄያቸውም በተለይም ጥንታዊ የታሪክ አገሮችን፣ እንደ ኢራክ ሊቢያና ሶሪያ የመሳሰሉትን አዳክሞና አገሮችን በጎሳ ነጣጥሎ ትናንሽ አገሮች እንዲፈጠሩ ማድረግ ነው።  ከዚህም በላይ በዩጎዝላቢያ ላይ የተካሄደው ጣልቃ ገብነትና በኋላም የይጎዝላቢያ መበታተን፣ በቅርቡ ደግሞ ዩክሬይንና የተቀሩትን የባልቲክ አገሮችን አሳቦና ተገን አድርጎ ራሺያን መክበብና ወደ ጦርነት ውስጥ እንድትገባ ማድረግ ዋናው የአሜሪካን፣ የእንግሊዝና የተቀረው የምዕራብ አውሮፓ አደገኛ ፖለቲካ ነው። በመሆኑም አሜሪካን ለኢትዮጵያውያን የተለየ ሊሆን አይችልም። ብዙ ጥናቶች እንደሚያረጋግጡትና ካለብዙ ጭንቀትም መገንዘብ እንሚቻለው እስከየካቲቱ አብዮት ድረስና፣ በኋላም አሜሪካ ኢትዮጵያ እንድትዳከምና ቀጭጫ እንድትቀር ያላደረገው ሙከራ ይህ ነው አይባልም። ኢትዮጵያችንም በትናንሽ አገሮች እንድትሰነጣጠቅ የማያደርገው ጥረት ይህ ነው አይባልም።  በአሜሪካ አማካይነት ነው „ኢትዮጵያ ዘመናዊነትን ለመጎናጸፍ የቻለችው፣ እኛም የስኮላርሺፕ ዕድል ለማግኘት የቻልነው“ የሚለው አባባል ዘመናዊነት(modernization)ማለት ምን ማለት እንደሆነ ካለመገንዘብ የተነሳ የሚነፍስ አደገኛና አሳሳች አባባል ነው። ዘመናዊነት በሚለው ዙሪያ የተደረገውን ሰፊ የቲዎሪ ትንተናና ኢምፔሪካል ምርምር ለተመለከተ ከ1945 ዓመት በኋላ በአገራችንም ሆነ በብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮች የተካሄደው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ዝብርቅርቅነትን ያመጣና አዲስ ህብረተስብአዊ ግኑኝነትን የፈጠረ ነው። ይህንን ዐይነቱን ዘመናዊነት ለመረዳት ደግሞ፣ በቀላሉ የኛንና የብዙ የሶስተኛውን ዓለም አገሮች ከካፒታሊስት አገሮችና፣ በኋላ ደግሞ ከጃፓንና  ከደቡብ ኮሪያ ጋር በማወዳደር ውስጣዊ ድክመቱን መረዳት ይችላል። ይህንን በሚመለከት አሁን ለንባብ ባወጣሁት አዲስ መጽሐፌ ላይ በሰፊው ስላተትኩ  መጽሐፉን መመልከቱ ከሞላ ጎደል ጥሩ ግንዛቤ ሊሰጠን ይችላል። በዚያው መጠንም አገራችንና የተቀሩት የአፍሪቃ አገሮች መከተል ያለባቸውን የኢኮኖሚና የማህበራዊ ፖሊሲ መረዳት ይቻላል።

ያም ሆነ ይህ  ይህንን ትተን ወደ ውስጡ ፖለቲካ ስንመጣ አንድ አገዛዝ ለረጅም ጊዜ ስልጣን ላይ ለመቆየት ከፈለገ በህብረተሰቡ ውስጥ አሉ የሚባሉትን ቅራኔዎች በማባባስና አርቲፎሻል ነገሮችን በመፍጠር ለዘለዓለም ስልጣን ላይ ለመቆየት አይችልም። የግዴታ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ከተፈለገ በምድር ላይ የሚታዩትን ችግሮች፣ ማለትም ድህነትንና ረሃብን፣ በመሰረቱ መሰረታዊ ፍላጎቶች(Basic Needs) በመባል የሚታወቁትን ለመፍታት መቻል አለበት። በዚህ ብቻ ሳይረካ አገሩ የተረጋጋች እንድትሆንና፣ ዘላቂነት ያለው ስላም እንዲስፍን ከፈለገ ሰፋ ያለ የስልጣኔ ፕሮጀክት መዘርጋት አለበት። በዚህ መልክና በሚፈጠረው ህብረተሰብአዊ መተሳሰርና ጥንካሬ አንድ አገዛዝ ህዝባዊ ተቀባዊነትን በማግኘት እንደ አለኝታ ይታያል።  የብልጣ ብልጡ ወያኔ ተልዕኮውና ህልሙ ግን ይህ አይደለም። አገሪቱን በሁሉም አቅጣጫ ማዳከምና ከውስጥ ህብረተሰብአዊ ቅራኔዎች እንዲፋፋሙ በማድረግ እራሱን አጎልምሶ ታላቋን ትግሬ መገንባት ነው። ሞኙ ህዝባችን ይህንን እጅግ አደገኛና የጥቁር ህዝብ ጠላት የሆነውን ፕሮጀክቱን ዝም ብሎ መመልከት አለበት። ይህንን ዐይነቱን የህዝብ ጠላት የሆነውን አደገኛና በቀላሉ ሊቀረፍ የማይችለውን ተግባር ወያኔዎችና ግብረ አበሮቻቸው ፖለቲካ ይሉናል።

በመሰረቱ ይህ ዐይነቱ የፖለቲካ ግንዛቤና አካሄድ አንዳንድ የድሮ ድርጅቱ አባል ከሆኑት እንደሚሰማው ከሆነ፣ ድርጅቱ አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ በመሆኑ ነው ይህንን የፖለቲካ አካሄድ እንዲመርጥ የተገደገደው የሚለው አመለካከት ኢ-ሳይንሳዊ አቀራረብ ነው። ሁለቱንም መሰረተ- ሃሳቦች ነጣጥለን በምንተነትንበት ጊዜ ሁሉቱም ፅንሰ-ሃሳቦች የሚሰጡን የተለያየ ትርጉም አለ። በመጀመሪያ ደረጃ አብዮት የሚባለው ጽንሰ-ሃሳብ ጤናማ አስተሳሰብ ያለውና ስር-ነቀል እርምጃን የሚያካትት ነው። በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ በአንድ አገዛዝ የሚገለጽና ተግባራዊ የሚሆን ለዕድገት ጠንቅ የሆነ ህብረተሰብአዊና ፓለቲካዊ ግኑኝነት ባለበት ጊዜ የጥገና ለውጥ የማይቻል ከሆነ የግዴታ አብዮታዊ እርምጃ የሚያስፈልግበት ጊዜ አለ። ይህ ዐይነቱ አብዮት የግዴታ ከማርክሲዝም ጋር መያያዝ የለበትም። ማርክሲዝም እንደፍልስፍናና የፓለቲካ መመሪያ ሆኖ ከመፈጠሩ ወይንም ብቁ ከማለቱ በፊት ከሁለትና ከሶስት መቶ ዓመታት በፊት የከበርቴው አብዮት ተካሂዷል። በዚህም መሰረት ነው የፊዩዳሉ ስርዓት ሊገረሰስና ለከበርቴያዊ፣ እንዲያም ሲል ለኢንዱስትሪ አብዮት መሰረት መጣል የተጀመረው። በሌላ ወገን ደግሞ በኢንዱስትሪ አብዮት የተነሳ ህብረተሰብአዊ መመሰቃቀል ሲመጣና ድህነት ሲከሰት፣ እንዲሁም የአካባቢ መቆሸሽ ህዝቡን መኖሪያ ሲያሳጣው ማርክስና ተከታዮቹ ብቻ ሳይሆኑ ሮማንቲኮች የሚባሉ ምሁሮችም  ለህብረተሰብአዊ ለውጥ ታግለዋል። ትግላቸው ግን ደም መፋሰስን የሚጋብዝ ሳይሆን በሰብአዊነት መርሆች ላይ የተመረኮዘ እንደነበር በበቂው ተመዝግቧል። ዲሞክራሲ የሚባለው ጽንሰ-ሃሳብ ደግሞ የማያሻማ ትርጉም አለው። ሌላ ትርጉም ካልተሰጠው በሰተቀር ህዝብን የሚያካትትና የህዝብን ጥያቄ መመለሻ መሳሪያ ነው። በሌላ አነጋገር ለጥቂት ኤሊት ነን ባዮች የሚሰጥ ጽንሰ-ሃሳብና መሳሪያ አይደለም። በአገራችን ካልሆነ በስተቀር በታሪክ ውስጥ አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚባል ነገር የለም። ይሁንና ግን በብዙ የቀድሞ ሶሻሊስት አገሮች በማዕከል ደረጃ ያልተፍታታ ዲሞክራሲያዊ ሴንትራሊዝም የሚሉት አነጋገር ነበር። ይህ ዐይነቱ ዲሞክራሲያዊ ሴንትራሊዝም አገራችን ውስጥ አለ ከሚባለው አብዮታዊ ዲሞክራሲ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም።  በጊዜው የዲሞክራሲ ሴንትራሊዝም ሰፍኖባቸዋል በሚባሉት የቀድሞ የሶሻሊስት አገሮች ውስጥ የነበረውን የህዝቡን ኑሮ ስንመለከት አብዛኛው ህዝብ ስራ የነበረውና በህይወቱም እርግጠኝነት የሚሰማው ነበር። ድህነት የሚባል ነገር አይታወቅም ነበር። በውጭ ፖለቲካቸውም እንደኛው እንደ ዛሬው የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ተቀጢያዎች አልነበሩም። ከሞላ ጎደል ራሳቸውን የቻሉ ነበሩ። የተጨባጩ  ሶሻሊዝም(Real Socialism) ችግር ቀስ በቀስ እያለ ስርዓቱን ለማደስ ወይም ጥገናዊ ለውጥ ለመውሰድ አለመቻሉ ነው። ሁሉም ነገር በማዕከል ደረጃና ዕቅድ ይካሄድ ስለነበር ለግለሰብ ፈጠራ አመቺ ሁኔታን ሊያዘጋጅ አልቻለም። ከፖለቲካ ኢኮኖሚ ህግ አንጻር የማርክስን ዳስ ካፒታል ላነበበ፣ የኢኮኖሚ ዕድገቱ አካሄድ ቀስ በቀስ እያለ ከዝቅተኛ ወደ ከፈተኛ ደረጃ የሚሸጋገርን የኢኮኖሚ አካሄድ የተከተለ አይደለም። ሌላው የሶሻሊዝም ድክመት ልክ እንደካፒታሊስት አገሮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀብትን በመዝረፍ የተገነባና ሌሎች አገሮችን የጥሬ-ሀብት አምራቾች አድርጎ ለማስቀረት የቻለ ባለመሆኑ የመጨረሻ መጨረሻ ስርዓቱ ሊከሽፍ ችሏል። ይህ ማለት ግን አንዱ አገር ሌላውን ካልበዘበዘ ሊያድግ አይችልም ማለቴ አይደለም። ተጨባጩን የካፒታሊዝምን ዓለምአቀፋዊ የሀብት ክምችትና የብዝበዛ ዘዴ ለማሳየት ብቻ ነው።  ይሁንና ግን በጊዜው የሶሻሊዝም  ርዕዮተ-ዓለም መስፋፋትና ተግባራዊም መሆን ከካፒታሊዝም ውስጣዊ ቅራኔ ጋር የተያያዘና የአንደኛውና የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወጤት ነው ማለት ይቻላል። በጊዜው ግዴታዊ አካሄድ ነበር። በመሆኑም ሶሻሊዝም ወደ ናሺናሊዝምነት በመለወጥ ሶቭየትህብረት በአጭር ጊዜ ውስጥ ከእርሻ (Agrarian) ኢኮኖሚ በኢንዱስትሪ ላይ ወደ ተመሰረተ ኢኮኖሚ መሸጋገር ችላለች። ኃያል መንግስትም ለመሆን በቅታ ነበር። በጦርነት የፈራረሰውን ከተማዎቿን እንደገና መልሳ ለመገንባት ችላለች። ይህንን ሁሉ ያደረገችው በራሷ ጥረትና እንደ አሜሪካ ዕውቀትንና ሀብትን ከሌሎች አገሮች በመውሰድ አይደለም። ከዚህ ስንነሳ ስለ አብዮታዊ ዲሞክራሲና በቀድሞ የሶሻሊስት አገሮች የነበረውን ስርዓት መለያየት አለብን። እንዲያው በጥላቻ ላይ ተመርኩዘን የምናደርገው ዘመቻ በሰፊው እንዳናስብ ብቻ ሳይሆን፣ አማራጭ መንገዶችንንም እንዳንፈልግ ከመጀመሪያውኑ መንገዱን ይዘጋብናል።

ያም ሆነ ይህ ወደ ወያኔው አብዮታዊ ዲሞክራሲ ስንመጣ በምንም ዐይነት ለውጥን ሊያመጣ የቻለና የሚያስችል አይደለም። ለስርዓት ለውጥም የሚያመች አይደለም። የዚህ ዐይነቱ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ፍልስፍና፣ ሳይንስና ቲዎሪ ምን እንደሚመስል የሚታወቅ ነገር የለም። በመሰረቱ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ የፍልስፍና መሰረቱ ማርክሲዝምና የሶሻሊዝም ቲዎሪ መሆን ነበረባቸው። የወያኔ አገዛዝ ግን ከማርክሲዝም ጋር የተሰናበተው በመጀመሪያ ደረጃ ጫካ ውሰጥ ሆኖ ሰው መግደል ሲጀምር ሲሆን፣  በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ስልጣን ከጨበጠ በኋላ የኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲን ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረ ወዲህ ነው። ስለሆነም ይህ የተምታታ ፖሊሲው ለዘመናዊ ፊዩዳሊዝም መንገዱን የከፈተና፣ በዓለም አቀፍ ደራጃ ደግሞ የባሰውኑ ቀጭጨን እንድንቀር የሚያደርገን የስራ-ክፍፍል ውስጥ ነው የከተተን። አዲስ ዐይነት የሴንተር-ፔሪፌሪ(Center-Peripheri) ግኑኝነት ተግባራዊ ያደረገ „አብዮታዊ ዲሞክራሲ“ ነው ተግባራዊ የሆነው። ስለሆነም  የስትራክቸራል አድጀስትሜንትን ፕሮግራም ወይም የኒዎ-ሊበራል ኢኮኖሚ ፖሊሲን የተቀበለና ተግባራዊ የሚያደርግ አገዛዝ ለመሰረታዊ ወይም ለአብዮታዊ ለውጥ ዝግጁ አይደለም። እንደሚታወቀው የኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ዋና ዓላማው በየአገሮች ውስጥ አዲስ ዐይነት የሶሻልና የፖለቲካ ግኑኝነት(Social and Political Relationship) በመፍጠር አገዛዞችን በዓለም አቀፍ የአገዛዝ ሂራርኪ ውስጥ በማካተት ህዝቦችን ማሸትና ማድኸየት ነው።  ለዚህ ደግሞ ናኦሚ ክላይን(Naomi Klein) The Shock Doctrine በሚለው ግሩም መጽሀፏ ውስጥ እንዳሳየቸው የገበያ ኢኮኖሚ ብለው በሚጠሩት የሞኔተሪ ፖሊሲ የጠቅላላውን ህዝብ ጭንቅላት ሙሉ በሙሉ ማጠብ ነው። በሌላ አነጋገር፣ በዚህ ዐይነቱ የሾክ ዶክትሪን ቲዎሪ አማካይነት የአንድ አገር ህዝብ ጭንቅላት ከድሮ አስተሳሰቡ እንዲላቀቅ መደረግ አለበት። ጭንቅላቱ ተበጥብጦ ሲጣራ የዚያን ጊዜ የገበያ ኢኮኖሚን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ  ይጀምራል።  ሙያው ሁሉ ገንዘብን ማሳደድ ይሆናል። ናኦሚ ክላይን የብዙ አገሮችን የኢኮኖሚና የማህበራዊ ሁኔታ ኢምፔሪካል በሆነ ዘዴ ከመረመረች በኋላ የደረሰችበት ውጤት ይህ ዐይነቱ ሾክ ዶክትሪን በብዙ አገሮች ኢኮኖሚያዊ ብልጽግናንና የማህበራዊ ሁኔታን መሻሻል ሳይሆን ያመጣው፣ በከፍተኛ ደረጃ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድቀትን ነው ያስከተለው። ለዚህም ነው አጥፊው ካፒታሊዝም(Disaster Capitalism) ብላ የጠራችው።  ስለሆነም ይህ ዐይነቱ  የኢኮኖሚ ፖሊሲ አምባገነናዊ አገዛዝን በማጠናከር ሁኔታው እየተበላሸ ሲሄድ ደግሞ ወደ ፋሺስታዊ ስርዓት እንዲሸጋገር ማድረግ ነው። ለዚህ ደግሞ በአገዛዙና በህብረተሰቡ ውስጥ ያለው በጣም ዝቅተኛ የፖለቲካ ንቃተ-ህሊና በጣም አመቺ ነው። ስለሆነም ሴኪዩሪቲውን በአዲስ መልክ ማደራጀትና ማጠናከር፣ ልዩ አፋኛና አነጣጥሮ የሚተኩስ ቡድን ልክ ናዚዎች ያደራጁት ዐይነት ኤስ ኤስ(SS) የሚመስል ፋሺሽታዊ የጦር ኃይል በማደራጀት የተዘረጋውን ስርዓት ይቀናቀኑኛል የሚላቸውን ሁሉ እያነጣጠሩ መግደል ነው። ይህንን የመሰለውን አነጣጥሮ ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን የሚገድለውን ፋሺስታዊ አጋዚ የሚባለውን የጦር ኃይል ሲአይኤ(C.I.A) ሲያሰለጥነው፣ የፌዴራል ፖሊስ የሚባለውን አስፈሪ ኃይል ደግሞ እንግሊዝ ናት ያስታጠቅችውና ያሰለጠነችው። በተጨማሪም ኢትዮጵያ የሲአይኤ መመላለሻ ቤት ስትሆን፣ በውጭ ጉዳይ ምኒስቴርና በጸጥታ ኃይል ውስጥ እንግሊዞችና ሌሎች የምዕራብ አውሮፓ ሰዎች ተስግስገውበታል። ከዚህ በላይ የሃይማኖት ሰባኪዎችና የዕርዳታ ሰጪዎች በመምሰል በአገሪቱ ውስጥ በመሰማራት የአማራው ብሄረሰብ ዝቅ አድርጎህ ይመለከትሃል በማለት ህዝባችን ርስ በርሱ እንዲበላላና የማያልቅ ጦርነት ውስጥ እንዲገባ የጥላቻ መርዛቸውን እየረጩ ነው። እንግዲህ እነዚህ የወዳጅ አገሮች የሚባሉት ናቸው የወያኔ የጀርባ አጥንት በመሆን ህዝባችን ርስ በርሱ እንዲተላለቅና  አገራችንም በዘለዓለም ትርምስ ውስጥ እንድትኖር የሚያደርጉት። ይህ ዐይነቱ የፍርሃትና የጦርነት ፖለቲካ ደግሞ በአሜሪካን አገርም በግልጽ የሚታይ ነው። ፖሊሱን ወደ ወታደርነት በመቀየርና አነጣጥሮ የሚተኩስ ጠብመንጃ ይዞ እንዲዘዋወር በማድረግ፣ አደጋ ሊያደርሱብኝ ነው የሚላቸውን ለጋ ወጣቶች ሁሉ ሳይቀር ምክንያት እየፈለገ እያነጣጠረ እንዲተኩስ ፈቃድ ተስጥቶታል።  ስለሆነም ህዝቡ በፍርሃት ዓለም ውስጥ እንዲኖር ተገዷል። በዚህ መልክ በ1960ዎችና በ1970ዎቹ ዓ.ም በላቲን አሜሪካንና በሴንትራል አሜሪካ አገሮች ፋሺስታዊ አገዛዞች በመስፋፋት በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ምሁራንና የዋህ ህዝቦችን ገድለዋል፣ የተቀረውን ደግሞ በየስርቤቱ ጥለዋል።  ይህ ዐይነቱ የመንግስታት መኪናዎች አደረጃጀት ዘዴ ፣ በአንድ በኩል በየአገሮች ውስጥ የተፈጠረውን ልዩ ዐይነት ህብረተሰብአዊ ግኑኝነት መጠበቅ ሲሆን፣ በሌላ ወገን ደግሞ አገዛዞችን ፍጥጫ ውስጥ በመክተት በጎረቤት አገሮች መሀከል ጦርነት ለመቀስቀስና ህዝብን ለመጨረስ ነው። በዚህ መልክ የየአገሩ መንግስታት በመፈራራት የማያቋርጥ ወይም በቀላሉ መፍትሄ የማይገኝለት ጦርነት ውስጥ ይገባሉ። በዚያው መጠንም እነዚህ አገሮች በኢንዱስትሪ አገሮች የሚሰሩት የጦር መሳሪያዎች ማራገፊያ ወይም ገበያ ይሆናሉ። ይህ የካፒታሊዝም ውስጣዊ ህግ ነው። ካፒታሊዝምና ጦርነት የተያያዙ ናቸውና።

ከዚህ ዐይነቱ የእከክልኝ ልከክልህ ፖለቲካና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተዘረጋውን የአገዛዝ ሂራርኪ ስንረዳ ነው የወያኔንም የውስጥ ፖለቲካ መገንዘብ የምንችለው። ይህንን የተወሳሰበና በሺህ ድሮች ተሳስሮ ለስልጣኔና ለዕውነተኛ ዲሞክራሲ እንቅፋት የሆነውን ስርዓትና ከውጭ ኃይሎች ጋር ያለውን መተሳሰር ካልተረዳን  ስለ እኩልነትና ስለ ዲሞክራሲ ማውራት በፍጹም አንችልም። ስለዚህም የነገሮችን መተሳሰር መመልከት አለብን። ከዚህ ስንነሳ ካለፉት አስራአንድ ወራት ጀምሮ፣ በተለይም ካለፉት አራት ሳምንታት ጀምሮ ወያኔ በህዝባችን ላይ የሚያደርሰው ግድያና ማሰቃየት ከበስተጀርባው የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም አለበት። በተለይም ደግሞ የጎሳው ፖለቲካ ስላልሰራና በሃይማኖት መተላለቅም ስላልተከሰተ የምዕራቡ ዓለም በጣም ተደናግጧል። አገራችንን የመበታተኑና በዘለዓለማዊ ጦርነት ውስጥ ዘፍቃ እንድትቀር የታሰበውና የታቀደው ስትራቴጂ ስላልሰራ አገዛዙ አነጣጥሮ በመተኮስ እርምጃው እንዲገፋበት የአረንጓዴ መብራት ተስጥቶታል። ስለዚህም ነው እስከዛሬ ድረስ እንደዚያ በአገራችን ምድር ብዙ ደም እየፈሰሰ  የምዕራቡ ሚዲያ ምንም ነገር የማይጽፈውና የማያሰማው። ሁኔታው እንደሶሪያ እስኪሆን ድረስ ነው እነ አሜሪካና የተቀረው የምዕራቡ ዓለም የሚጠባበቁት።  በመሆኑም ከብዙ የዋህና ተማርን ከሚሉ ኢትዮጵያውያን የሚቀርበው እሮሮና የይድረሱልን ጩኸት ቦታና ትርጉም የለውም። ይህ ዐይነቱ የይድረሱልኝ እሮሮና ከአሜሪካን ሆኖ ተጠባባቂ መንግስት መመስረት አለብን እያሉ መጮህ ህይወቱን በተሰዋውና በየቀኑ በሚሰዋው ህዝባችን ላይ እንደማላገጥ ይቆጠራል።  ከዚህ ዐይነቱ ጭንቅት ለመውጣት የግዴታ በራሳችንና በህዝባችን ላይ መተማመን አለብን።  ራሳችንንም ነፃ ማውጣት የምንችለውና ጠንካራ አገር መገንባት የምንችለው በአሜሪካን በመታገዝ ሳይሆን በራሳችን ጥረት ብቻ ነው።

በሌላ ወገን ግን ወያኔ አሁንም የሚከተለው የግድያና የአፈና ፖለቲካው ውድቀቱን የሚያፋጥነው ነው። በተለይም በሰሜኑ የአገራችን ክፍል  የጎንደርና የጎጃም ህዝብ ቆርጦ መነሳቱ በጣም ያስደነገጠው ወያኔ በጠቅላይ ምኒስተርነቱ አማካይነት ይህ ዐይነቱን ከጭቆናና ከዘረፋ ለመውጣት የሚደረገውን የጦር እንቅስቃሴ ከውጭ ወረራ ጋር ለማያያዝ ነው የሞክረው። በአቶ ኃይለማርያም አባባል፣ የኢትዮጵያን ሀብት ለመዝረፍ ጠላት በየጊዜው ወረራ እንዳደረገባትና፣ አሁንም እንዳልተኛ ነግረውናል። አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ግን የሚነግሩን የተገላቢጦሹን ነው። በብዙ መቶ የሚቆጠር ጋሻ መሬት ለውጭ ከበርቴዎች በመሰረቱ ዘራፊዎች አከራይቶ የአገር ሀብት እንዲበዘበዝና ተራው ገበሬ ከመሬቱ እንዲፈናቀል፣ እምቢ ያለውን ደግሞ የሚገድለው ወያኔ ነው። የጎንደር፣ የጎጃም፣ የኦሮሞና የጋምቤላ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የሚታገሉት በመሬታችን ላይ ከአበባ ይልቅ ለምግብ የሚሆን እህል እንትከልበት፤ ከመሬታችን አታፈናቅሉን እያሉ ነው። በተጨማሪም አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ስለ ዕድገት ያላቸው አስተሳሰብ የተጣመመ ነው። አንድ ሰው መዋያው ያማረ ቤተ-መንግስትና ጋርተን ውስጥ የሚዘዋወርና የሚበላውም ምግብ የተለየ ከሆነ ስለሌላው ማሰብ አይችልም። ስለዚህም አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝና የካቢኔት ሹማምንቶቻቸውን የምንመክረው ሌላው የአገሪቱ ክፍሎች ጋ ሳይሄዱ እዚያው አዲስ አበባ ውስጥ ብቻ መርካቶ ቢዘዋወሩና አንድ ሁለት ቀን እዚያ ቢያድሩ ስለ ዕድገት ያላቸውን አስተሳሰብ ሊለውጡ ይችሉ ይሆናል። የምንመክራቸውም ሼራተን በመሄድና በመመገብ ሳይሆን፣ ወይም የተወሰነ አካባቢ በመዘዋወር ሳይሆን ስለ ዕድገት መናገር የሚቻለው በየቦታው በእግር በመዘዋወር የህዝባችንን አኗኗር ሁኔታ በመቃኘት ነው። እንደምናየው አብዛኛው  ህዝባችን እንደ አይጥ እየተሽሎከለከ በቆርቆርና በተሰባበረ የእንጨት ቤት ውስጥ የሚኖር ነው። ከዚህም በላይ አገሪቱ የቆሻሻ መጣያ የሆነችና ወደፊት በቀላሉ ይህንን ሪሳይክል ለማድረግ የማይቻልበት ሁነታ ተፈጥሯል። ይህ የሚያሳየን ምንድነው ፟? አንድ አገዛዝ የተፈጥሮን ህግ ሳይረዳ በራሱ ስሜትና በማፊያ መልክ በተደራጀው የዓለም-አቀፍ ኮሙኒቲ በሚባለው የወጣና የሚደገፍ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ ካደረገ የአንድን አገር የሰውና የተፈጥሮን ሀብት ያወድማል። አዳዲስ ቲክኖሎጂዎችን ሊፈጥር አይችልም። በዚህም የተነሳ ከህዝብ ቁጥር  ማደግ ጋር የሚያያዝ ምርታማነትን ሊታይ አይችልም፤ ዕውነተኛ ህብረተሰብአዊ ሀብትም አይፈጠርም። ዛሬ በአገራችን ምድር ያለውን የኢኮኖሚ ሁኔታ አስመልክቶ አንደ የገዢው መደብ አቀንቃኝ የሆነች ከአውስትራሊያ ለሚተላለፈው የአማርኛ ፕሮግራም አዘጋጅ ለቀረበላት ቃለ-መጠይቅ የሰጠችው መልስ የሚያስቅ ነው። የህዝቡ ጥያቄ(Demand) ስለአደገ ነው የኢኮኖሚ ችግር የሚታየው የሚለው ግራ የሚያጋባ ነው። በመሰረቱ በአለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በአገራችን ምድር አገሪቱን ሊያዳርስ የሚችል በመንግስትና በኢንስቲቱሽን የተደገፈ ብሄራዊ ሀብትን ሊፈጥር የሚችል የኢኮኖሚ ፖሊሲ አልተካሄደም። የስኳርና የኮካኮላ እንዲሁም የቢራ ፋብሪካ በየቦታው በመትከልና በማምረት የአንድን ህዝብ መሰረታዊ ፍላጎት ማሟላት አይቻልም። በሁለተኛ ደረጃ፣ አንደ ከአገዛዙ ጋር የተቆራኘ እንደ ኢፈርት የመሳሰለ ድርጅትና  አላሙዲ የሚባል ተልዕኮው ምን እንደሆነ የማይታወቅና ስለ ኢኪኖሚ ህግ መሰረታዊ ዕውቀት የሌለው ሰው ሁሉንም ነገር በሚቆጣጠሩበት አገር ውስጥ ስለ ዕውነተኛ ዕድገትና ሰለ ህዝብ ጥያቄ ማደግ ማውራት በፍጹም አይቻልም። በሶስተኛ ደረጃ፣ የግል ባለሀብቶች በየቦታው እየተንቀሳቀሱ ኢንቬስት እንዳያደርጉ መዓት እንቅፋቶች በተደቀነበት አገር ውስጥ የስራ መስክ መክፈትና የተለያዩ የምርት ዐይነቶችን ማምረት አይቻልም።  ይህም ማለት በአንድ አገር ውስጥ መንግስት ብቻውን የአንድን ህዝብ ፍላጎት ሊያሟላ አይችልም። ቴክኖሎጂያዊ ምጥቀትና ሰፋ ያለ የመዋዕለ-ነዋይ እንቅስቃሴ ሊታይ የሚችለው ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ ያለ የግለሰቦች ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ሲኖር ብቻ ነው።  በሌላ ወገን ግን መንግስትና ድርጅቱ ማፊያዊ በሆነ መልክ የሚንቀሳቀሱትን ግለሰቦች ምክንያት እየፈጠሩ ገበያውን ለቀው እንዲወጡ ያደርጓቸዋል።  አንዳንዶች ደግሞ በወያኔ የማፊያ ሰዎች ይገደላሉ። ታዲያ በዚህ ዐይነት ሁኔታ ውስጥ እንዲት አድርጎ ኢኮኖሚውን ማሳደግና በየጊዜው እያደገ የሚሄደውን የህዝብ ግላጎትና ጥያቄ ማሟላት ይቻላል ?

ያም ሆነ ይህ በየቦታው መፋፋም የጀመረውን ሰላማዊና ራስን ወደ መከላከል የተለወጠውን የህዝብ እንቅስቃሴ ወያኔ ለመፍታት የሚፈልገው የባሰዉኑ በጠብመንጃ ኃይል ብቻ ነው። በየጊዜው አረመኔያዊነቱን እያረጋገጠና ህፃናትንና እናቶችን ሳይቀር በጠራራ ፀሀይ በመግደል እንቅስቃሴዉን የሚገታ መስሎታል።  በዚህ መልክ የሚያካሄደው የጭፍን ፖለቲካው የባሰውኑ ኃይሉን እየበታተነበትና፣ ለትግሬዎች ወንድሞቻችንና እህቶቻችን፣ እንዲሁም እናቶቻችንና አባቶቻችን አደገኛ ሁኔታ ውስጥ እየከተታቸው መጥቷል። በተለይም ቶሎ ብለው አገዛዙን ማግለል የማይችሉና ሰፊው ወንድማቸው ጎን ቆመው ለዲሞክራሲና ለነፃነት ለመታገል የማይችሉ ከሆነ በተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ እንዲጠሉ ይደረጋሉ። ስለዚህም በአስቸኳይ ከሰፊው ህዝብ ጎን መቆማቸውን ማሳወቅ አለባቸው። የወያኔ አገርን የመበታተንና ኢትዮጵያን አዳክሞ ታላቋን ትግሬ የመገንባት ህልምና ፕሮጀክት ያከተመለት መሆኑን ማንኛውም ወጣት እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ትግሬዎች መረዳት አለባችው። አንድ ህዝብ ታሪክ ሊሰራ የሚችለው በመነጣጠልና በመናቆር ሳይሆን፣ በመሰባሰብና፣ ኃይሉን በማጠንከርና አንዱ ከሌላው በመማር የተረዳዳና ለጋራ ዓላማ የተነሳሳ እንደሆነ ብቻ ነው። በመሆኑም የፖለቲካን ሰፊና ገንቢ ትርጉም መረዳት የጊዜው አንገብጋቢ መሰረተ-ሃሳብ ይሆናል። ለአዲሲቱና ለዲምክራሲያዊቱ ኢትዮጵያ መገንባት የሁላችንንም ተሳትፎ ስለሚጠይቅ፣ ይህንን ከፋፋይና ህብረተሰቡን አዳክሞ የውጭ ኃይሎች ተገዢ የሚያደርገንን አገዛዝ በጋራ ትግል መጣል አለብን። ወያኔ የራሱ ጦር አልበቃ ብሎት ከውጭ ጦር በማስመጣት በህዝባችን ላይ መዝመቱ ማንኛውንም የፖለቲካ ውይይት መንገድ ዘግቶታል። ይህ አገዛዝ ስልጣን ወይም ሞት ብሎ ቆርጦ የተነሳ ስለሆነና፣ በዚህም የሚገፋበት በመሆኑ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ይህን አገዛዝ ይቅርታ እንዲጠይቅና ወደ ህዝብ እንዲመለስ የሚያደርገው ጥሪ እጅግ አሳሳችና አደገኛ ነው። ይህ ዐይነቱ አቀራረብ በአንደ በኩል በአገዛዙና በኢምፔሪያሊስት ኃይሎች የተቀነባበረብንን ልዩ ሴራ በቅጡ ካለመገንዘብ የሚሰነዘር ኢ-ፖለቲካዊ አባባል ሲሆን፣ በሌላ ወገን ደግሞ የህዝባችንን ዕውነተኛ የነፃነትና የስልጣኔ ጥም ለመረዳት ካለመቻል የሚቀርብ አስፈላጊ ያልሆነ ጩኸት ነው።

ከኛ የሚጠበቀው !

እኛ እዚህም ሆነ እዚያ ሆነን ጩኸታችንን የምናሰማ ኢትዮጵያውያን በአገራችን ምድር ሰላም፣ መረጋጋት፣ ዲሞክራሲና ነፃነት እንዲሁም በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ብልጽግና እንዲመጣ ከፈለግን ከሁለት ነገሮች አንዱን መምረጥ ያለብን ይመስለኛል። ለብዙዎቻቸን እስካሁን ግልጽ ያልሆነና ከጥንት ጀምሮ ፈላስፋዎችን ሲያከራከር የነበረው ሁለት የዕድገት ፈለገ አለ። አንደኛው እነሶክረተስና ፕላቶን የፈጠሩትና የመንፈስን የበላይነት ያስቀደመው መንገድ ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ በሚታዩና በሚጨበጡ ነገሮች ላይ ያተኮረው ዕውቀትን የመፍጠሩ ጉዳይ ነው። ይህ ዐይነቱ አካሄድ በተለይም ከአስራሰባተኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ በአንድ በኩል በነላይብኒዝ የሚወከለውና የእነ ፕላቶንን ፍልስፍና መሰረት ያደረገው የስልጣኔ መንገድ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በእንግሊዞች ኤምፕሪሲስቶች የሚሰተጋባው ከሶፊስቶች የተወሰደው ዕውቀትን የማፍለቅ ዘዴ ወይም ፖዚቲቭ ሳይንስ በመባል የሚታወቀውና፣ አንድን ተቀባይነት ያገኘን ስርዓትና አገዛዝ፣ እንዲሁም ከዚህ የፈለቁትን መመሪያዎች ሳይመረምሩ እንዳለ መቀበል ነው በሚለው መሀከል የተካሄደውን የጦፈ ክርክር ነው። በጊዜው እነላይብኒዝ ይከራከሩና ተከታዮቻቸውን ያስጠነቅቁ የነበረው ማንኛውም አገር የእንግሊዝ ፈላስፋዎችን መንገድ የምትከተልና፣ ፖሊሲዎች በሙሉ በዚህ መሰረት የሚወጡ ከሆነ መጪው የዓለም ህዝብ ዘለዓለሙኑ በጦርነትና በድህነት ውስጥ ዘፍቆ ፍዳውን እንደሚያይ ነው። ይህ አመለካከት በኋላ በመጡት በእነ ካንትና ሺለር፣ በኋላም በእነ ሄገል በመስፋፋት፣ የአንድ አገር ዕድገት የግዴታ በአርቆ አስተዋይነትና በከፍተኛ ንቃተ-ህሊና(Self-Consciousness) ላይ መመርኮዝ እንዳለበትና፣ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከሌሎች ህብረተሰብአዊና ማህበራዊ እንዲሁም ባህላዊ ዕድገት ተነጥሎ መታየት እንደሌለበት አስተምረዋል። በእነሱ አመለካከት አንድ ነገር ከሌላው ጋር የተያያዘ ስለሆነ፣ በአንድ አካባቢ የሚሰራ ስህተት የግዴታ በሌላው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል። በሌላ አነጋገር አንድ አገዛዝና አገር የተሳሰተ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የሚከተሉ ከሆነ የመጨረሻ መጨረሻ ጠቅላላዉን ሁኔታ ያዘበራርቃሉ። የአገራችንን ሁኔታ ለሚመለከተው ይህንን መረዳቱ ከባድ አይሆንም። ለዚህ ነው በአገራችን ብቻ ሳይሆን በዓለም-አቀፍ ደረጃ ሚዛናዊነት እየጠፋና ጥቂቶች እየደለቡና፣ ሲጠግቡ ደግሞ ወደ ጦርነት የሚያዘነብሉት። ይህንን ለማመልከት ሲል ነው ውድ ወንድማችን ዳዊት አለማየሁ „ሚዛንሽ ተዛባ አንቺ ዓለም“ እያለ ግሩም በሆነ መልክ የሚዘፍነው። ስለዚህ ይህ ሙዚቃና ታች ከዚህ ጽሁፍ ጋር የተያያዙት የድህረ-ገጽ አድራሻዎች ብዙ መልዕክቶችን ያስተላልፉልናል። የዓለምን የመዘበራረቅ ሂደት በትንሹም ቢሆን ጠጋ ብለን እንመልከት።

በተለይም ከአስራስምንተኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ የእንግሊዙ መንገድ ባሸናፊነት ከወጣ ጀምሮ ቀስ በቀስ ብዙ አገሮች ሳያውቁት ይህንን መንገድ በመከተል የየአገሮቻቸው፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የሚሊታሪ ፖሊሲ መመሪያ በማድረግ ህዝብን መቆጣጠሪያ ዘዴ አደረጉት። በጊዜው የእንግሊዝ ኤምፕሪሲስቶች የሰብአዊነት አመለካከት ያላቸውን አዋቂዎችን ካሸነፉ በኋላ ነፃ ገበያና ነፃ ንግድ የሚለውን በማወጅ፣ በዚያው መጠንም እንዴት አድርገው ዓለምን ለመቆጣጠር የሚችሉበትን ዘዴዎች ቀሰ በቀስ ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ። ይህ አካሄድ የመጀመሪያው የተጣመመው የግሎባላይዜሽን መሰረት ነው። ከዚህ በመነሳት ነው ቀሰ በቀስ የቅኝ-አገዛዝ ፖሊሲ አገሮችን የማዳከም ስትራቴጂ የተቀየሰውና ተግባራዊም የሆነው። በውጥኑ መሰረት አብዛኛዎች የአፍሪቃ አገሮች የጥሬ-ሀብት አምራችና አቅራቢ በመሆን እዚያው ቀጭጨው መቅረት አለባቸው። እንደ ህብረተሰብና እንደ አገር በሁሉም አቅጣጫ ማደግና መበልጸግ የለባቸውም። በተለይም የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም በአሸናፊነት ከወጣ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ ይህ መንገድ የበለጠውን በመርቀቅና እየተወሳሰበ በመምጣት የብዙ አገሮች መመሪያ ሆነ። ብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮች በዘመናዊነት ስም ዕውነተኛ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን ተግባራዊ ሳያደርጉ፣ በዚያው መጠንም የየመንግስት መኪናዎቻቸውን በአሜሪካ የጦር አደረጃጀት ስልት ማዘጋጀት ተገደዱ። ጠቅላላው የሲቪል ቢሮክራሲው በሙሉ በዚህ ዐይነቱ የፖዘቲቭ ሳይንስ መመሪያ በመሰልጠኑ በዓለምአቀፍ ደረጃ በተዘረጋው የሚሊታሪ-ኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስ ውስጥ በመዋሃድ በየአገሮች ውስጥ ሚዛናዊነት ያለውና ከተፈጥሮና ከህዝብ ፍላጎት ጋር እየተመጣጠነ የሚሄድ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ እንዳይሆን አገደው። በተለይም እ.አ በ1944 ዓ.ም እነ ዓለም የገንዘብ ድርጅትና(IMF) የዓለም ባንክ(World Bank) ከተቋቋሙ ጀምሮ ዋናው ተግባራቸው በተሳሳተ የኢኮኖሚ ፖሊሲ አማካይነት በየአገሮች ውስጥ የተዛባ ዕድገት የሚመስል ነገር  ማምጣትና፣ በዚያውም መጠንም ድህነትን መፈልፈል ነው። ይህ ዐይነቱ የፖሊሲ አወቃቀር በየጊዜው ስሙን በመለዋወጥና በየአገሮች ውስጥ ተግባራዊ በመሆን የብዙ አገሮች ኢኮኖሚዎችና ማህበረሰቦች እንዲዘበራረቁ ሆኑ። ቀስ በቀስም ማህበራዊ ቀውሱ ጥልቀት በማግኘት፣ እ.አ ከ1989 ዓ.ም በኋላ የተፈጠረውን አዲስ ክስተት ተገንና ሽፋን በማድረግ የየአገዛዞች ዋናው ተግባር አሸባሪዎችን መዋጋት ነው በሚል የአብዛኛዎቹ የሶስተኛው ዓለም አገሮች መንግስታት ዋናው ተግባር ወደ ጦርነት በማድላት የመንግስታቶቻቸውን መኪና የባሰውኑ ሚሊታራይዝ በማድረግና የየአገሮቻቸውን ሀብት በመምጠጥ በፍጥጫ ዓለም ውስጥ እንዲወድቁ ተገደዱ። በአስራሰባተኛው ክፍለ-ዘመን እነላይብኒዝና፣ የኋላ ኋላም ተከታዮቻቸው ሌሎች የጀርመን ፈላስፎች ያሰጠነቀቁት የነበረው ሁኔታ ዕውን በመሆን፣ ይህ ዐይነቱ መንግስታዊ አወቃቀርና ከዚህ የሚወጣው ፖሊሲ ለአንደኛውና ለሁለተኛው ዓለም ጦርነት ምክንያት ሆነ። የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ፍጻሜ ካገኘና አሜሪካንም የበላይነትን ከተቀዳጀ በኋላ ጦርነት ወደ ሶስተኛው ዓለም አገሮች በመሸጋገር ብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮች በጦርነት ዓለም ውስጥ እንዲዘፍቁ ተገደዱ። ከቬትናም እስከ አንጎላና ሞዛምቢክ ድረስ በ60ኛውና በሰባኛው ዓ.ም ይካሄዱ የነበሩት ጦርነቶችና ለብዙ መቶ ሺህ ህዝቦች ማለቅ ምክንያት የሆኑት  ዋናው ቀስቃሺዎች አሜሪካንና ተካታዮቻቸው ናቸው። እነዚህ በወንድማማቾች የተካሄዱት ጦርነቶች በሙሉ በመሰረቱ የውክልና ጦርነቶች(Proxy War) ናቸው። ዛሬ ወያኔ በአገራችን ምድር ላይ የሚያካሄደው ጦርነት የውክልና ጦርነት ነው። ካለበቂ ምክንያት በወንድማማቾች መሀከል የሚካሄድ ጦርነት ነው። እነ ሻቢያም ነፃ ወጣን እስካሉ ድረስ ጀምሮ ያካሂዱ የነበረው ጦርነት በውጭ ኃይሎች የታገዘና በማቴሪያልና በገንዘብ የሚደገፍ ለብዙ መቶ ሺህ ኢትዮጵያውያን-ኤርትራውያን እልቂት ምክንያት የሆነ ጦርነት ነው። የኦሮሞ ነፃ አውጭ ነኝ የሚባለው ድርጅትና ራሳቸውም የግራ ኃይሎች ነን ይሉ የነበሩት ሳያውቁት ያካሂዱ የነበረው ጦርነት በመሰረቱ የውክልና ጦርነት ነበር።  ኃይልን የሚበታትን፣ ሀብትን የሚጨርስና የድህነቱን ዘመን የሚያረዝመው ነው። በመሰረቱ በአንድ አገር ውስጥ በአንድ ህዝብ መሀከል በብሄረሰብና በርዕዮተ-ዓለም ስም አሳቦ ወይም ስልጣን ላይ ለመውጣት በማለት የማያስፈልግ ጦርነት ማካሄድ ይቅርታ የማይደረግለት  ነው።  የታሪክ ወንጀል እንደመስራት ይቆጠራል። ግሎባላይዜሽንና ነፃ ገበያ አማራጭ የሌላቸው የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ናቸው ተብለው መሰበክ ከተጀመሩበት ከ90ዎቹ ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በአንድ በኩል የዎል ስትሪት(Wall Street) ተዋንያንና በዓለም አቀፍ ኢንስቲቱሽኖች ውስጥ ሲሰሩ የነበሩና እንደሎሚ ልጣች ተመጥጠው ያለቁ ኤክስፐርቶችን እየላኩብን በቀጥታ የኢኮኖሚ ጦርነት አውጀውብናል። በተሳሳተ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ደሃ ሆነን እንድንቀር ለማንም የማይታይና ማንም ሊረዳው የማይችል የረቀቀ ጦርነት አውጀውብናል። ከዚህም በላይ  አሸባሪዎች የሚባሉትን በየቦታው እንድ አሸን እንዲፈልቁ በማድረግ ጦርነት አውጀውብናል፤ ለአለመረጋጋት ምክንያት ሆነዋል። ይሁንና የአሸባሪዎች ዋናው አማካሪ፣ መሳሪያ አቀባይና ገንዘብ አቅራቢዎች ደግሞ የአሜሪካን የስለላ ድርጅትና በዘይት ዶላር የናጠጡ የአረብ አገሮች ናቸው። አልሻባብ የሲአይኤና የወያኔ ውልድ ነው።  በዓለም አቀፍ ደረጃ በአሸባሪነት ስም የሚካሄዱት ግድያዎች በሙሉ ከዘጠና በመቶ በላይ በስለላ ድርጅቶች የሚካሄዱ ናቸው። ለዚህ ደግሞ እንደ ሃርፕ የመሳሰሉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀምና የወጣቱን ጭንቅላት በማዞር ነው።

ይህ ማለት ማለት ነው? እኛ  የዛሬውን አገዛዝ የምንታገልና ነፃነት እንዲመጣ የምንፈልግ ኃይሎች ሁሉ ከሁለት አንደኛውን መንገድ መምረጥ አለብን። ከመንፈሳዊውና ከሰይጣኑ መንገድ። በዝህቦች መሀከል ስምምነት እንዲመጣ፣ እያንዳንዱ ዜጋም የማሰብ ችሎታውን በማዳበር አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር የሰለጠነች አገር እንዲገነባ ከተፈለገ የግዴታ የመንፈሳዊዉን መንገድ መምረጥ አለብን። ወጣቱ ቄስ ዳነኤል እንደሚያስተምረን ወደ ገነት ለመግባት ከፈልግህ የሰይጣኑን መንገድ መምረጥ የለብህም። የግዴታ ቅዱሳዊውንና የገነቱን መንገድ ስትመርጥ ብቻ ነው ወደ ገነት መግባት የምትችለው።  በዩኒቨርሳል ህግ ወይም በተፈጥሮ ህግም መሰረት ዋናና ተቀዳሚው ተግባር የአስተሳሰብ አንድነት(Unity of Thought) ማዳበር ነው። የአስተሳሰብ አንድነትና ጥራት ሲኖር የስልጣኔው መንገድ ብሩህ ይሆናል። የአስተሳሰብ ጥራት ሲኖረን እርስ በራሳችን መናቆሩን እንተወዋለን። ሁለተኛው የዩኒቨርሳል ህግ መመሪያ በተናጠል አንድ ግብ መድረስ አይቻልም። በአንድ ጣት ምንም መስራት አይቻልም። በሁለት ጣቶች እርሳስ ማንሳት ይቻላል። በአምስት ጣቶችና በሁለት እጆች ብዙ ነገሮች መስራት ይቻላል። ብዙ ሰዎች ስንሆን ደግሞ ተራራንም ማንቀሳቀስ እንችላለን። ስለሆነም አንድ ጠንካራና ስላም እንዲሁም ብልጽግና የሚሰፍንባት አገር ለመገንባት ከፈለግን የግዴታ ኃይላችንን መስብሰብ አለብን። ሁሉም ታጋይ ነኝ እያለ በየቦታው ለመታየት የሚፈልግ ከሆነና፣ እዚህና እዚያ የፖለቲካ ፓርቲ የሚሉትን ፈሊጥ የሚመሰርት ከሆነ አንድ ጠንካራ አገር መገንባትና ሰላምን ማምጣት በፍጹም አይቻልም። ሶስተኛውና እጅግ አስፈልጊው የዩኒቭርሳል ህግ የግዴታ በራስና በራስ ህዝብ መተማመንን ይፈልጋል። ለዚህ ደግሞ የመንፈስ ነፃነት እንዲሰማ ያስፈልጋል። ከዚህ ስንነሳ የውጭ ተጠሪ የሆነና በውጭ ኃይል የሚተማመን ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል አገዛዝ በምንም ዐይነት ዕውነተኛ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ስልጣኔና ዕድገትን አያመጣም። በአራተኛ ደረጃ፣ ሌላው የዩኒቨርስ ህግ አንዱ ለሌላው ማሰብና ርስ ብርስ መረዳዳት አለበት። በተለይም መጦሪያ የሌላቸውንና በየቦታው የወደቁትን ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን፣ እንዲሁም እናቶቻችንና አባቶቻችንን መደገፍ ካልቻልንና መጠለያ ካልሰጠናቸው ስለ አገርና ዕድገት ማውራት በፍጹም አንችልም። በአምስተኛ ደረጃ፣ ሌላው የዩኒቨርስ ህግ የሚለን በአንድ አገር ውስጥ የተለያየ ብሄረሰብና አስተሳሰብ፣ እንዲሁም ልዩ ልዩ የምግብ ዐይነቶችና ባህሎች መኖራቸው ተፈጥሮአዊ ናቸው። ተፈጥሮ ራሷ በልዩ ልዩ ነገሮች የምትገለጽ ነች። ሰውነታችንም ራሱ እዚያው በዚያው አንድም ብዙም ነው።  ስለዚህም በአገራችን የተለያዩ ብሄረሰቦች መኖራቸው የውበታችን መግለጫዎች ናቸው እንጂ የመጠላላትና የመቀናናት ምክንያት ሊሆኑ አይገባቸውም። ጥያቄው እንዲዚህ ዐይነቱን ነገሮች በምን ዐይነት ፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ፖሊሲ ልንፈታቸው እንችላለን በሚለው ላይ ነው መነጋገር ያለብን።  ስለሆነም ሁሉም ህዝብ ከዘርና ከሃይማኖት ባሻገር መረዳዳት አለብን። በመረዳዳትና በመከባበር ብቻ ነው ጤናማና ተከታታይነት ያለው አገር መገንባት የምንችለው።

የለም እኛ በአሜሪካን ትምህርት ነው የሰለጠን ነው፣ የአሜሪካን እሴትም ትክክለኛው ነው ብለን ይህንን የሙጥኝ ብለን የምንይዝ ከሆነ ያለመረጋጋቱንና የፀረ-ስልጣኔውን መንገድ መረጥን ማለት ነው። የሰይጣኑንና የመበታተኑን መንገድ ፈለግን ማለት ነው።  ከዚህ ስንነሳ ወያኔን ለማስወገድ የሚደረገው ትግል ከዚህ ዐይነቱ የአስተሳሰብ ክልል ውጭ ሊታይ አይችልም። በሌላ አነጋገር በአገራችን ምድር ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የዚያች አገር ዜጋ መሆኑን እንዲረዳና ሙሉ ነፃነቱን እንዲቀዳጅ ከተፈለገ ነገሩ ወያኔን በማስወገድ ብቻ የሚያቆም መሆን የለበትም። በኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ በአጭሩ በአገር ግንባታና በሚሊታሪ ፍልስፍና ዙሪያ የምናካሄደው የጦፈለት ክርክር ወደ ፊት ይጠብቀናል። ዛሬ በሰሜንም ሆነ በደቡብ ከወያኔ ጋር የሚጋፈጠውና የነፃነት ያለህ እያለ የሚጮኸው ህዝባችን የሃሳብ ጥራትን ይጠብቃል። ከወያኔ ከተላቀቀ በኋላ በአስቸኳይ ጊዜያዊ ችግሩን እየቀረፍንለት ሰፊውን የአገር ግንባታ ተግባራዊ እንድናደርግ ከኛ ይጠብቃል።  የመጨረሻ መጨረሻ ዕውነተኛ ነፃነቱ በተጨባጭ ነገሮችም የሚመነዘር መሆን አለበት። አዳዲስ ከተማዎችንና መንደሮችን መገንባት፣ ሀብትንና የሰው ኃይልን ለማንቀሳቀስ በየቦታው ኢንስቲቱሽኖችን ማቋቋም፣ በህዝብ ዘንድ ያለን ገንዘብ ለማንቀሳቀስና ምርታማ በሆነ ነገር ላይ ለማዋል የባንኩን ስይስተም በአዲስ መልክ ማደራጀት፣ የምግብን ችግር  ለመቅረፍና በምግብ ራሳችንን ለመቻል የመሬትን ጉዳይ በአዲስ መልክ ለመፍታት መቻል፣ በተለይም ልዩ ልዩ የሰብልና የእህል ዐይነቶች ሊዘሩና ሊበቅሉ የሚችሉበትን ሁኔታ ማጥናትና በአስቸኳይ ተግባራዊ ማድረግ፣ በንጹህ ውሃ እጦት ለሚሰቃየው ህዝባችን በአካባቢውና ከረጅም ጊዜ አንጻር ደግሞ ቤት ውስጥ የመጠጥ፣ የመቀቀያና የማጠቢያ ውሃ የሚያገኝበትን ዘዴ ማጥናት፣ በተለይም የቤትን አሰራር በአዲስ መልክ በመቀየስ በማዕከለኛው ዘመን ይኖር ይመስል ለሚሰቃየው ህዝባችን አዲስ የአኗኗር ስልትን እንዲለምድ… ወዘተ. በነዚህና በአያሌ የአገር ግንባታ ነገሮች ላይ መረባረብ አለብን። ይህንን የህዝባችንን ህልምና ፍላጎት ዕውን ማድረግ የምንችለው ዓለምንና እያንዳንዱን አገር ከሚያጠፋው የሰይጣን ርዕዮተ-ዓለም የተላቀቅን እንደሆን ብቻ ነው። ለዚህ የተቀደሰ ተግባር ቀን ሌሊት መስራት አለብን። ብርታቱንና ጽናቱን ይሰጠን ዘንድ ራሳችንን በራሳችን ማግኘት አለብን። ሁሉም ነገር በጭንቅላታችን ውስጥ ስላለ ህዝባችን የተመኘውን ስለምና ዕድገት ተግባራዊ ለማድረግ ምንም የሚቸግረን ነገር የለም።ሁሉም ነገር አለን፣ ነገር ግን እንዳናስብና እንዳንሰራ ታግደናል !!

ፈቃዱ በቀለ

fekadubekele@gmx.de

 

http://www.ethiopia.org/index.php?lang=en

https://www.youtube.com/watch?v=fM2iZdooYFc

https://www.youtube.com/watch?v=Aca6RCE0CQg

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>