Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

“ሲመረው የማይነሳ ህዝብ የለም ባለም፣” አለ አቦይ ስብሐት ነጋ! –ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

$
0
0

Al 898ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም 

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

የኢትዮጵያውያን የጸደይ አብዮት በ2016 የክረምት ወቅት መጀመሩ ነውን? 

አንድ ህዝብ ታምቆ ፣ ታምቆ ማለት ተጨቁኖ  በዘመንታ አይቆይም ። ዩኒቨርሳል universal  ማለት ነው ።  አንድ ህዝብ እንደ ህዝብ መጠን  በዓለም ታሪክ  አንዳስቀመጡት አንደፈለጉት  የሚቀመጥ አይደለም። ሲመረው ይፈነዳል።  ይሄ ዓለም አቀፋዊ  እውነታ /universal  truth  ነው። ሲመረው የማይነሳ ህዝብ የለም ባለም።  በታሪክም /historically።  አሁንም።  ለወደፊትም ። (አዛውንቱ የእንጨት ሽበት ባለቤቱ አቦይ ስብሀት ነጋ፣ የዘ-ህወሀት ጭንቅላት፣ ንጉስ፣ የክርስትና አባት፣ ተጽእኖ ፈጣሪ እና የአለቆች ሁሉ አለቃ (ካቦ) እ.ኤ.አ በ2015 ከተናገረው የተወሰደ።)  (ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ ።)

በዘ-ህወሀት ላይ የፍርዱ ቀን ደረሰ ማለት ነውን?

Eth Demos2

እ.ኤ.አ ታህሳስ 2015 “የኢትዮጵያውያን የጸደይ አብዮት በበጋው ወቅት መጀመሩ ነውን?  በሚል ርዕስ በኢትዮጵያ በመምጣት ላይ ስላለው የጸደይ አብዮት ትችት አቅርቤ ነበር፡፡“

በዚያ ትችቴ ላይ እንዲህ የሚል ምልከታ አድርጌ ነበር፡ “በኢትዮጵያ እንደመዥገር በስልጣን ኮርቻ ላይ ተጣብቆ የሚገኘው የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሀት) በምን ሰዓት እና መቼ ቀን እንደሚወድቅ በእርግጠኝነት መተንበይ አልችልም፡፡ ሆኖም ግን የመውደቂያው የእጅ ጽሁፍ በግድግዳው ላይ በጉልህ ተጽፎ ይታያል“ ነበር ያልኩት፡፡

ያንን ትችት ካቀረብኩ ከአንድ ወር በኋላ እ.ኤ.አ ጥር 2016 “ለኢትዮጵያውያን ምንም የሚቀር ሀገር የላቸውምን?” በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችቴ ደግሞ ዘ-ህወሀት የፍርድ ቀኑ በደረቅ ሌሊት እየተሳበ እንደሚደርስ ሌባ ቀስ ብሎ ሳይታሰብ በድንገት ከተፍ ይላል በማለት ተናግሬ ነበር፡፡

በአሁኑ ጊዜ በዘ-ህወሀት ላይ የፍርዱ ቀን ደረሰ ማለት ነውን?

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለፍትህ እና ለፍትሀዊነት መስፈን ሲል ለ25 ዓመታት ያህል ድምጹን ከፍ አድርጎ ሲጮህ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ግን እንደበቀቀን የሚለፈልፍበት ሰፊ አፍ እንጅ የሚሰማበት ጆሮ እና ህሊና የሌለው የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሀት) ሲቀርብለት ለቆየው ህዝባዊ የተማዕጽኖ ጥያቄ ሁሉ አላየሁም አልሰማሁም በማለት ጆሮዳባ ልበስ ሲል ቆይቷል፡፡

ዘ-ህወሀት በተደጋጋሚ ከሕዝብ ሲቀርብለት ለቆየው የተማጽዕኖ ጥያቄ ሁሉ በኤኬ-47 ካላሽንኮቭ እና በሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎች አማካይነት የእሩምታ ተኩስ በመክፈት የሕዝብ እልቂትን በመፈጸም የአጻፋ ምላሽ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

ሰዎች እንዲህ የሚል አባባልን ይናገራሉ፣ “ፍትህ ልክ አንደምዘገይ ባቡር ነው፣ ምን ቢዘገይ መድረሱ አይቀርም፡፡“   የፍትህ ባቡር በኢትዮጵያ ዘግይቷል፣ ሆኖም ግን የዚያን ባቡር በሐዲዱ የሚተላለፈው መድረሱን የሚገልጥ ድምፅ መስማቴን ሳላቆአርጥ ለበርካታ ዓመታት ተናግሬአለሁ፡፡ የፍትህ ባቡር ቀስ አያሌ አየመጣ ነው! የፍትህ ባቡር አያዘገመ ነው ነው! የፍትህ ባቡር አየገሰገሰ ነው! የፍትህ ባቡር አየደረሰ ነው!  የፍትህ ባቡር ደርሰ አንዴ!?

እ.ኤ.አ በ2016 የኢትዮጵያ የፍትህ የምጽአት ባቡር ጣቢያው ገባ!?

ከባቡር ጣቢያው ሲገባ እየተመለከትኩት ነው፡፡ ሆኖም ግን የባቡሩ ተሳፋሪዎቹ ማን አንደሆኑ በእርግጠኝነት የማውቀው ነገር የለም፡፡

የኢትዮጵያ የፍትህ ባቡር የሰላም ወይም ደግሞ የእርስ በእርስ ጦርነትን የሚያውጁ ተሳፋሪዎች ናቸው ያሉት?

የሰላም ፈጣሪዎች አንዲሆኑ አመኛለሁ እጸልያለሁ።

“ሰላም ፈጣሪዎች የተባረኩ ናቸው” በሚለው መለኮታዊ ትእዛዝ አምናለሁ።

ሆኖም ግን የሰላም ፈጣሪዎችን ጥሪ እየሰማሁ አይደለም፡፡

እንዲህ የሚለውን የጦረኞችን የጦርነት አዋጅ የጥሪ ቀን እየሰማሁ ነው፡ “ማረሻዎቻችሁን ወደ ጎራዴነት ቀይሩ እንደዚሁም ሁሉ የአበባ ማስተካከያ መሳሪያዎቻችሁን ወደ ጦር ቀይሩ፡፡ ደካሞች እንዲህ በሉ፣ ’እኔ ጠንካራ ነኝ!‘“ አንደተባለው ።

ለሩብ ክፍለ ዘመን ያህል በዘ-ህወሀት ጉልበት ስር ወድቆ ደካማ በመሆን ሲያገለግል የቆየው ሕዝብ በአሁኑ ጊዜ በአይበገሬነት፣ በፍርሀትየለሽነት ዓይኑን አፍጥጦ በመቆም እንዲህ እያለ ይዘምራል፡ “እኛ ጠንካሮች ነን! ኢትዮጵያ ትጠንከር! አንዲት ጠንካራ ኢትዮጵያ ለሁላችንም !“

ጋንዲ እንዳስተማሩን ሁሉ ጥንካሬ ከአካላዊ ብቃት፣ ከጦር መሳሪያዎች ወይም ደግሞ ከሚፈነዱ ቦምቦች፣ ሮኬቶች እና ሚሳይሎች አይመጣም የሚለውን እንደማምን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡

ጥንካሬ የሚመጣው ከማይበገረው የመንፈስ ጽናት ነው፡፡ የጥንካሬ ምንጭ የልብ ወርቅ እና የአረብ ብረት መሆን ነው፡፡

ከሩብ ክፍለ ዘመን የዘ-ህወሀት አምባገነናዊ አገዛዝ በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የማይበገረውን ኃይላቸውን እንዲህ በማለት በማሳየት ላይ ይገኛሉ፡ “ዘ-ህወሀት! በቃ በቃ ነው! ከዚህ በኋላ አብረን መቀጠል አንችልም! ሽንጣችንን ገትረን እንዋጋለን! ከእንግዲህ በኋላ አንተን አንፈራህም! አፈር ድሜ በልተህ ገሀነም ግባ፣ ገሀነም፣ ገሀነም!“ እያሉ ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ2010 በቱኒሲያ ሕዝባዊ ለውጥ በመጣ ጊዜ በውድቅት ሌሌት ቀስ እያለ እየተሳበ እንደሚመጣ ሌባ ነበር፡፡

የቱኒሲያ ሕዝባዊ የአመጽ ብልጭታ በመካከለኛው ምስራቅ እና በሰሜን አፍሪካ ባሉ ሀገሮች ሕዝቦች ላይ እሳት ጫረ፡፡ ገሀነም ፈነዳ እናም የህዝብ ቁጣ የአፍሪካን አምባገነኖች አይገቡበት እየገባ ማርበድበድ ጀመረ፡፡ እንደ አይጥ በየቆሻሻ ቱቦው እየተያዙ አፈር ድሜ እየበሉ ወደማይቀረው ዓለም ተሰናበቱ፡፡

ያ በጨለማ በውድቅት ሌሊት ቀስ እያለ ሲሳብ የነበረው ሌባ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የፍትህ ባቡር ውስጥ ተሳፍሮ እየመጣ ነውን?

እኔ ስለዚህ ጉዳይ የማውቀው ነገር የለም ምክንያቱም ከዚህ በታች ለሚቀርቡት ጥያቄዎች ምላሽ የማውቀው ነገር የለምና፣

ዘ-ህወሀት በ100 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ነግሶ ከሰብአዊነት አውርዶ እና ባሪያ እድርጎ በአምባገነንነት እና በጭቆና እንደ ብረት ቀጥቅጦ እንደ ሰም አቅልጦ እየገዛ ሊቆይ የሚችለው ለምን ያህል ጊዜ ነው?

ዘ-ህወሀት ሀገሪቱን የባሪያ የእርሻ ቦታ በማድረግ እነርሱ ጌቶች ሆነው እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ዜጋ ደግሞ ገባር ሆኖ እየተገዛ እና እየተሰቃየ ሊቆይ የሚችለው ለምን ያህል ጊዜ ነው?

ዘ-ህወሀት አርሶአደሮችን ከመሬት ይዞታቸው በኃይል እያፈናቀለ እርሱ የዜጎችን አንጡራ ሀብት እያጋበሰ ለአስከፊ ድህነት እየዳረጋቸው ሊቆይ የሚችለው ለምን ያህል ጊዜ ነው?

ዘ-ህወሀት የቤት ባለቤቶችን ከመኖሪያ ቤታቸው በኃይል እያፈናቀለ፣ የንግድ ድርጅት ባለቤቶችን ከንግዳቸው እያባረረ እና ቤተክስቲያኖችን እና መስጊዶችን እየደፈረ እና ቅዱስ ቦታዎችን እያረከሰ ያገኘውን ሁሉ እያግበሰበሰ የማይሞላውን ኪሱን በማሳበጥ ሊቆይ የሚችለው ለምን ያህል ጊዜ ነው?

ዘ-ህወሀት የኢትዮጵያ ሕዝቦች ከቀደምቶቻቸው ጀምረው ሲኖሩበት የነበረውን መጠነ ሰፊ የእርሻ መሬቶቻቸውን በኃይል እያፈናቀለ በመቀማት እና በመዝረፍ በርካሽ ዋጋ ለቻይናዎች፣ ለህንዶች፣ ለሳውዲዎች፣ ለቱርኮች እና ለሌሎች በሳንቲም ደረጃ እየቸበቸበ ኪሱን ሲሞላ የሚቆየው ለምን ያህል ጊዜ ነው?

ዘ-ሀወሀት ሕገ መንግስታዊ መብቶቻቸውን በመጠቀም በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞቻቸውን የሚገልጹትን የኢትዮጵያ ወጣቶች እንደ በሬ እያረደ እልቂትን በመፈጸም ሊቆይ የሚችለው ለምን ያህል ጊዜ ነው?

ዘ-ህወሀት የ100 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ድምጾች እያፈነ ሊቆይ የሚችለው ለምን ያህል ጊዜ ነው?

ዘ-ህወሀት በእግር ጫማው የ100 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን አንገት በመርገጥ ሊቆይ የሚችለው ለምን ያህል ጊዜ ነው?

ንገሩኛ እኮ ለምን ያህል ጊዜ?

እኔ ግን ጊዜው ሩቅ አይሆንም እላለሁ!

ሩቅ አይሆንም! በምንም ዓይነት ሁኔታ ሩቅ አይሆንም!

ነሐሴ ለዘ-ህወሀት የቀውጥ ወር ነው፡፡

አሁን በህይወት የሌለው እና ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ትንሹ አምላክ እንዲሁም ለሁለት አስርት ዓመታት በዘ-ህወሀት ኮርቻ ላይ ተፈናጥጦ የቆየው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ህይወቱ አለፈ እየተባለ የሚነገርለት በነሀሴ ወር ነው፡፡ አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በእርግጠኝነት የሞተበት ቀን ግን በዘ-ህወሀት ሚስጥር ሆኖ ተቀምጧል፡፡

ከአራት ዓመታት በኋላ እ.ኤ.አ ነሀሴ 2016 እንዲህ የሚል ጥያቄ እጠይቃለሁ፣ “የዘ-ህወሀት ኮርቻ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለዘላለሙ ተንኮትኩቶ የሚወድቀው መቼ ነው?“

የኢትዮጵያ ጀግኖች ሕዝቦች ከዘ-ህወሀት የስቃይ እና የመከራ አገዛዝ ነጻ ለመውጣት ረዥሙን የጨለማ ጉዞ በመጋፈጥ ያንን አስቸጋሪ እና አንገብጋቢ የሆነውን ጥያቄ በመመለስ ህልሞቻቸውን ማሳካት የሚችሉት መቼ ነው? (መቀመጫ ኮርቻውን በዛፉ ጫፍ ላይ አስቀምጠው፣ ነፋስ በሚነፍስበት ጊዜ ኮርቻው ወድቆ ይንኮታኮታል፣ ቅርንጫፉ ሲዘነጠል ኮርቻው ይወድቃል እናም ድልዳሉ ኮርቻ እና ሁሉም ኮተቱ አንዴ ወድቆ ይንኮታኮታል፡፡)

በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ ዘ-ህወሀትን ዶግ አመድ የሚያደረግ አደገኛ የሆነ ሕዝባዊ ማዕበል፣ ቁጣ እና የበቀል ጥላቻ የሰደድ እሳት በመቀጣጠል ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ በየቦታው በመነሳት ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ አቦ ሸማኔው (ወጣቱ ትውልድ) አካባቢውን ሁሉ በመውረር ላይ ይገኛል፡፡ በየቦታው የቁጣ ድምጹን ከፍ አድርጎ በማሰማት ላይ ይገኛል፡፡

በዘ-ህወሀት የዛፍ ጫፍ ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘው የወንጀለኝነት እና የሙስና ቅርንጫፍ በህዝባዊ የቁጣ እና የበቀል ማዕበል ተዘንጥሎ አፈር ድሜ ሊበላ የሚችለው መቼ ነው?

ቅርንጫፉ ተሰብሯል ማለት እችላለሁ! በእርግጠኝነት! ብቸኛ ጥያቄ ሆኖ ሊቀርብ የሚችለው የዘ-ህወሀት የወንጀለኝነት፣ የሙስና እና የሰብአዊ መብት ረገጣ ወንጀሎች ኮርቻ ሊወድቅ ይችላል ወይ የሚለው ሳይሆን ይልቁንም ወድቆ ሊንኮታኮት የሚችለው በእርግጠኝነት መቼ ነው የሚለው ነው፡፡

ስለሆነም ነገሩ አሮፓውኖች አንደሚሉት አባባል ብናየው እንዲህ የሚል ነው፡

ዝትቱ እና ግብስብሱ ዘ-ህወሀት በግድግዳ ላይ ተቀምጧል፡፡ 

ዝትቱ እና ግብስብሱ ዘ-ህወሀት ታላቅ ውድቀት ደርሶበታል፡፡ 

ሁሉም የንጉሱ ፈረሶች እና የንጉሱ ሰዎች የተፈረካከሰውን ዝትቱን እና ግብስብሱን ዘ-ህወሀት እንደገና መልሰው አንድ ሊያደርጉት ከቶውንም አይችሉም፡፡ 

ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በለው ወይም ደግሞ ሳሞራ የኑስ፣ ስብሀት ነጋ፣ በለው ወይም ቴዎድሮስ አድሀኖም፣ ስዩም መስፍን፣ አርከበ እቁባይ፣ አባይ ጸሀዬ፣ በለው አባዲ ዘሞ፣ ጸጋይ በርኸ፣ አዜብ መስፍን፣ ሀፍቶም አብርሃ፣ ሬድዋን ሁሴን፣ በለው ወይም ምስኪኑ ናሙና ኃይለማርያም ሰሳለኝ ወይም ደግሞ ሌላ የዘ-ህወሀት ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አባል የዘ-ህወሀትን ዝትት እና ግብስብስ ውዳቂ እንደገና ጠጋግኖ አንድ ሊያደርገው ከቶውንም አይችልም፡፡ አይችልም በምንም አይነት !

ዘ-ህወሀት የፖለቲካ ቀውስን በመምራት ላይ ይገኛል፣

በአሁኑ ጊዜ በዘ-ህወሀት ቁጥጥር ስር ያለችው ኢትዮጵያ የዕለት ከዕለት ስራዋን በመስራት በስርዓት የምትመራ ሀገር መሆኗ በፍጹም ውድቅ ሆኗል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በዘ-ህወሀት የጎሳ ፌዴራሊዝም ሸፍጥ ቁጥጥር ስር እጅ ከወርች ተጠፍንጋ በምትገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ አንድም ደስተኛ የሆነ ቡድን የለም፡፡

ዘ-ህወሀት እራሱን በስልጣን ኮርቻ ላይ እንደ መዥገር አጣብቆ ለመቆየት ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ የጎሳ ፌዴራሊዝምን እና ከፋፋይ የጎሳ ፖለቲካ ስልቱን ሲያራምድ ቆይቷል፡፡ ዘ-ህወሀት የአንዱን ጎሳ ቡድን ከሌላው የጎሳ ቡድን ጋር በማጋጨት በከፍተኛ ደረጃ የፍርሀት፣ የጥልቅ ጥላቻ እና የጥላቻ ስልቶችን በህዝቦች ላይ በመጫን ሲተገብር ቆይቷል፡፡ ዘ-ህወሀት የራሳቸው ስብዕና የሌላቸውን አሰስ ገሰስ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመሰብሰብ ለማታላያነት እራሱን ኢህአዴግ ብሎ በመጥራት እና እውነተኛ የህዝብ ወካይ ፓርቲዎች አስመስሎ በማቅረብ በሸፍጥ እያጭበረበረ ከሩብ ከፍለ ዘመን በላይ በአምባገነንነት ሲገዛ ቆይቷል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ያፈጠጠው እና ያገጠጠው እውነታ ዘ-ህወሀት (ኢህአዴግ ወይም እራሱን በማንኛውም ስያሜ ቢጠራም) በኢትዮጵያ ውስጥ ባለ በእያንዳንዱ ጎሳ ከፍተኛ በሆነ መልኩ ተቀባይነትን በማጣት እንደ አሮጌ ቁና ተወርውሯል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ዘ-ህወሀት እያራመደው ያለው የጎሳ እና የፓርቲ የድብበቆሽ ጨዋታ ያበቃበት መሆኑን በሚገባ ተገንዝቧል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ዘ-ህወሀት በኃይል ሳይገፈተር፣ ያለውጊያ እና ከኋላው ጥቃት ሳይፈጸምበት በኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ የእራሱን ፍላጎት ለመጫን ፍጹም ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሶ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝቦች የአንድነት መሰረታቸውን በማጠናከር ቀጥ አድርገው ይዘዋል፡፡ ዘ-ህወሀት እነርሱን እንዲደበድብ እና እንዲያሰቃይ የሚፈቅዱበት ሁኔታ በፍጹም የለም፡፡

ጦርነቱን ወጣቱ ትውልድ በግንባር ቀደምነት በመምራት ላይ ይገኛል፡፡ የሚመራው ግን የኃይል ድርጊትን በመጠቀም ሳይሆን ሰላማዊ በሆነ መልኩ የህዝባዊ እምቢተኝነት ስልቶችን በመተግበር ነው፡፡ ድፍረት የተመላበት ህዝባዊ እምቢተኝነትን በማራመድ ነው፡፡ ጽናትን በተላበሰ የኃይል አልባን ተቃውሞ ተግባራዊ በማድረግ ነው፡፡ ያለምንም ፍርሀት፣ ያለምንም ማቅማማት፣ ያለምንም ጥርጣሬ እንደ አረብ ብረት በጽናት ጠንክሮ የሞት ሽረት ትግል በማድረግ ላይ  ነው፡፡

በዘ-ህወሀት ግድብ ላይ ወጣቶች ታላቅ የቦይ መቀልበሻ ናቸው፡፡

ለበርካታ ጊዚያት ዘ-ህወሀት ወጣቶችን በመደለል በብርቅርቅ ነገሮች ለመግዛት ሙከራ አድርጎ ነበር፡፡ ዘ-ህወሀት ወጣቶችን የማስፈራራት፣ በቁጥጥር ስር የማዋል እና ወደ እስር ቤት ዘብጥያ የመጣል ሙከራ አድርጓል፡፡ ዘ-ህወሀት በአሁኑ ጊዜ በየቦታው ወጣቶችን እንደ ፋሲካ ዶሮ በማረድ እልቂትን በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን ወጣቶች በየአውራ መንገዶች በመውጣት እንዲህ በማለት ድምጻቸውን ከፍ አድርገው በመጮህ ላይ ይገኛሉ፡ “በአሮሚያ ወንድሞቻችንን መግደሉን አቁሙ፡፡ የአማራን ሕዝብ የጅምላ ግድያ አቁሙ፡፡ የዘ-ህወሀት የበላይነት ይቁም፡፡ የፖለቲካ እስረኞች ያለምን ቅድመ ሁኔታ አሁኑኑ ይፈቱ!“ በማለት ድምጻቸውን በማስተጋባት ላይ ይገኛሉ፡፡

አሁን በህይወት የሌለው የዘ-ህወት ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አድራጊ ፈጣሪ መሪ የነበረው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ አንደተምሳለት የሚከተለው የናዚ መሪ በአንድ ወቅት “ወጣቱን የያዘ አካል የወደፊቱን ድልአድራጊ ይሆናል” ብሎ ነበር፡፡

ዘ-ህወሀት በምንም ዓይነት መንገድ የኢትዮጵያን ወጣቶች ሊሸጥ ሊለዉጥ ሊያሸንፍ አይችልም፡፡ ሆኖም ግን የኢትዮጵያ ወጣቶች ኢትዮጵያን የእራሳቸው ያደርጋሉ፡፡ ዘ-ህወሀትን ያሸነፋሉ ።

ዘ-ህወሀት በህዝባዊ አመጹ የተቀጣጠለውን ቁጣና እና የበቀል እርምጃ ጣቶቹን በመቀሰር እና በሰላማዊ መንገድ በሚያምጹ ተማሪዎች ላይ እልቂትን በመፈጸም ከገደቡ ወጥቶ በማፍሰስ ላይ ያለውን የቦይ መቀልበሻ እንደሚቆጣጠር አድርጎ ያስባል፡፡

ዘ-ህወሀት መገንዘብ የተሳነው ነገር ቢኖር (ወይም ደግሞ ሆን ብሎ ሊገነዘበው የማይፈልገው ነገር) ከተማሪዎች ቁጣ እና የበቀል እርምጃ ከሚቀጣጠልበት ጀርባ መጠነ ሰፊ የሆነ በህዝባዊ ተስፋ መቁረጥ፣ በጥላቻ እና በምሬት የተሞላ ህዝባዊ ባህረ አሳት እንዳለ አለመገንዘቡ ነው፡፡

ዘ-ህወሀት አስተማማኝ ወታደራዊ ብቃት እንዳለው፣ በቅጥፈት የተፈበረከ የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገበ ስኬታማ እንደሆነ እና በሀገሪቱ አስተማማኝ የፖለቲካ መረጋጋት፣ ወዘተ እንዳለ አድርጎ ሌት ከቀን እንደ በቀቀን በመለፍለፍ ተግባራት ላይ በመጠመድ እራሱን ህጋዊ እና እውነተኛ እንደሆነ አድርጎ የማቅረብ ቅዠቱን ያሳያል፡፡

ዘ-ህወሀቶች እራሳቸውን ብቻ ጀግናዎች እና ጠንካራዎች፣ እነርሱ ብቻ ብልሆች እና አዋቂዎች፣ እነርሱ ብቻ ምርጦች ሌሎች ህዝቦች ግን ባዶዎች፣ እነርሱ ብቻ ወርቆች፣ ሌሎች ሕዝቦች ግን ጨርቆች እንደሆኑ አድርገው ያቀርባሉ፡፡

የዘ-ህወሀት አፈቀላጤ ከጥቂት ጊዜ በፊት እያንዳንዱ ሰው ፈሪ፣ ቦቅቧቃ እና የአዕምሮ ዘገምተኛ እንደሆነ አድርጎ እየተንተባተበ እና እየተጎላደፈ ተናግሯል፡፡

ዘ-ህወሀት የሚፈልገውን ነገር ማሰብ ይችላል፣ የመረጠውን ማመን ይችላል፡፡

ሆኖም ግን እነዚህ ማናቸውም ነገሮች ቢሆኑ ከዚህ በኋላ ምንም የሚያመጡት ነገር የለም፡፡

የተባበሩ ህዝቦች በፍጹም አይሸነፉም የሚለው አባባል ዓለም አቀፋዊ እውነታ ነው፡፡

ዘ-ህወሀት ጠብመንጃዎችን፣ ታንኮችን እና የጦር አውሮፕላኖችን መጠቀም ይችላል፣ ሆኖም ግን ዘ-ህወሀት ሰላማዊ ኢትዮጵያውያንን በገደለ ቁጥር ሕዝቦች ለነጻነታቸው ሲሉ ችግሮችን ለመፍታት ጠንካራ እና አይበገሬ እየሆኑ ይሄዳሉ፡፡

ምንም የሚመጣ ነገር የለም፡፡

በቅርቡ በተለቀቀ በአንድ የቪዲዮ ምስል አንድ ሰው እንዲህ ሲል ተደምጧል፣ “በዘ-ህወሀት አገዛዝ ሁላችንም ሞተናል፡፡ የቁም ሞት ሞተናል፡፡ ወደፊት አሁን ካለንበት የበለጠ ሞት አይጠብቀንም“። 

በመንገድ በመሄድ ላይ ያለ አንድ ሰው እንደዚህ ያለ ለማመን የሚያስቸግር መግለጫ ሲናገር መስማት ማለት በስርዓቱ ላይ ያለውን አጠቃላይ የሆነ የህብረተሰቡን ጥልቅ የሆነ ስሜት የሚያመላክት መሆኑን ያስገነዝባል፡፡ 

ህዝቦች ከነጻነት ማጣት እና ከባርነት፣ ከሁለተኛ ዜጋነት እና ከሰብአዊነት ከወረደ አያያዝ መካከል መወሰን እንዲችሉ ምርጫ እንዲመርጡ ሲገደዱ ለመዋጋት ይመርጣሉ እንጅ ሾልከው በመሸሽ ለመብረር አይሞክሩም፡፡

ይህ መርህ ዘ-ህወሀት የአእምሮ ዘገምተኛ እና ዝቅተኛ እያለ ለሚዘልፈው ለእያንዳንዱ ሰውም ቢሆን ይሰራል፡፡

ናዚዎች በጀርመን ውስጥ የነበሩት አረያኖች ከሌሎች ሕዝቦች የበለጡ ዜጎች መሆናቸውን እና ሌሎች ሕዝቦች ግን አሰስ ገሰስ እና የማይረቡ መሆናቸውን ለማመላከት ሲሉ እንዲህ በሚል ትንሽ ለየት ባለ ሁኔታ ገልጸው ነበር፡ “ከሰብአዊነት የወረዱ”ነበር ያሉት፡፡ 

የዘ-ህወሀት ኃያሎች ከኢትዮጵያ ብዙሀን ህዝብ ጋር ሲነጻጸሩ፣

ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘ-ህወሀትን እንደሚያሸነፍ ምንም ዓይነት ጥያቄ የለውም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ በእርግጠኝነት ድልን ይቀዳጃል፡፡

በዘ-ህወሀት ላይ የፍርድ ቀን ደርሷል፣

ከልባቸው እና ከህሊናቸው በማውጣት አስከፊው የዘ-ህወሀት አገዛዝ በቃ! አንገሸገሸን! ቋቅ አለን! ከዚህ በላይ ልንቀጥል አንችልም! የሚልን የህዝብ አመጽ ለማቆም የሚያስችል ምድራዊ ኃይል በዚህች ሀገር ላይ ከቶውንም ሊኖር አይችልም፡፡

በዓለም ላይ ያለ የትኛውም ሕዝብ ቢሆን በአምባገነኖች ታፍኖ ለዘላለም መኖር አይችልም። ማንኛውም ሕዝብ ለዓመታት በጭቆና እጅ ከወርች ተጠፍንጎ ሲገዛ መኖር አይችልም ፡፡  ታሪክ ይመሰክ ራል ፡፡

ሰብአዊ ፍጡር የሆነ ሕዝብ  እንደ ቁሳቁስ እንደ ግኡዝ ነገር  ወይም ድጋይ ቁጭ ብሎ  አይቀርም ።  ዘህዋሃት  የኢትዮጵያን  ህዝብ እንደ ቁሳቁስ እንደ  ግኡዝ ነገር   እንደ  ድጋይ  አድርጎ  ነው  የሚ ያየው ።  ሕዝቦች በከፍተኛ ሁኔታ ባመረሩ ጊዜ ያምጻሉ ይዋጋሉ  ለሀገራቸው ለነታፃ ቸው  ይሞታሉ ፡፡

የእኔን ቃላት ለዚህ እውነታ መውሰድ የለባችሁም፡፡

የዘ-ህወሀትን የክርስትና አባት አዛውንቱን እና የእንጨት ሽበት የተላበሰውን ስብሀት ነጋን ጠይቁ፡፡ እንዲህ በማለት እንደወረደ ያለውን ሁኔታ ይነግራችኋል፣ ጥሬውን እንዳለ!

አንድ ህዝብ ታምቆ ፣ ታምቆ ማለት ተጨቁኖ  በዘመንታ አይቆይም ። ዩኒቨርሳል universal  ማለት ነው ።  አንድ ህዝብ እንደ ህዝብ መጠን  በዓለም ታሪክ  አንዳስቀመጡት አንደፈለጉት  የሚቀመጥ አይደለም። ሲመረው ይፈነዳል።  ይሄ ዓለም አቀፋዊ  እውነታ /universal  truth  ነው። ሲመረው የማይነሳ ህዝብ የለም ባለም።  በታሪክም /historically።  አሁንም።  ለወደፊትም ። (አዛውንቱ እና የእንጨት ሽበት ባለቤቱ አቦይ ስብሀት ነጋ፣ የዘ-ህወሀት ጭንቅላት፣ ንጉስ፣ የክርስትና አባት፣ ተጽእኖ ፈጣሪ እና የአለቆች ሁሉ አለቃ (ካቦ) እ.ኤ.አ በ2015 ከተናገረው የተወሰደ።) 

በቆራጥነት ወደፊት! 

ጠንካራ ነን! ኢትዮጵያ ጠንካራ ናት! በአንድነት ለጠንካራ ኢትዮጵያ! 

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!  

ነሐሴ 3 ቀን 2008 ዓ.ም


ማልቀስ ለሆዳም ነው! በላይነህ አባተ

$
0
0


eth cryበላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

በባህርዳር አንድ አያት “በካራና በበርበሬ እዋጋለሁ ሲሉ ሌላዋ ልጃቸው ሰይጣንን ተናንቆ የሞተባቸው እናት ደሞ “አታልቅሱ፤ ልጄ ለተቀደሰ አላማ ተሰውቷል” አሉ፡፡ እኒህ የተቀደሰው ልጅ እናት እንዳሉት ከወልቃይት እሰከ ጎንደር፣ ከጎንደር እስከ ባህርዳር፣ ከባህርዳር እስከ ሞያሌ ሰይጣንን ተናንቀው ለወደቁት የተቀደሱ ሰዎች አይለቀስም፡፡ ከተለቀሰ መለቀስ ያለበት ለእኛ ለሆዳሞች ነው፡፡

መለቀስ ያለበት ለሰይጣን አገልጋዮችና ተላላኪዎች ነው፡፡

ደረት መመታት ያለበት ከሰይጣን እየተሞዳሞደን ልማታዊ ጠበቃ፣ ልማታዊ ሐኪም፣ ልማታዊ የምጣኔ ሐብት በለሙያ፣ ልማታዊ መሐንዲስ፣ ልማታዊ ዘፋኝ፣ ልማታዊ ተዋናይ! ልማታዊ ነርስ፣ ልማታዊ ፋርማሲስት፣ ልማታዊ ጠራጊ፣ ልማታዊ ጋዜጠኛ፣ ልማታዊ ታክሲ ነጅ ወዘተርፈ ለሆን ሆዳም ዲያስፖራዎች ነው፡፡

እንባ መፍሰስ ያለበት ለአጋሰስ ቦንደኛ ዲያስፖራ ነው፡፡

መለቀስ ያለበት ጀግኖች ባሩድ እንደ መብረቅ እየወረደባቸው በየጎዳናው እየተመሙ እምቢኝ በሚሉብት ሰዓት እንኳን ባደባባይ በቤታችንም ልሳናችንን ለምንለጉመው ቦቅቧቃዎች ነው፡፡

ፊት መነጨት ያለበት ከሳይጣን እየተሞዳሞደን የደም ገንዘብ ለምናግበሰብስ ሆዳም ቱጃሮች ነው፡፡

መለቀስ ያለበት በደም የተበረዘውን ዳሽን ቢራ ለምንሰረብቅ ሆዳሞች ነው፡፡

ሚሾ መወረድ ያለበት ከሳይጣን ሆቴል ገብተን በደም የተቦካ እንጀራ ለምንመገበውና  ከሰው ሥጋ በተሰራ ፍራሽ ለምንተኛው ህሊና ቢሶች ነው፡፡

መለቀስ ያለበት ከሰይጣን ጋር ለምንጸልይ፣ እቁብ ለምንበላና ቡና ለምንጠጣው ነው፡፡

ደረት መመታት ያለበት ከሰይጣን መደብሮች እቃ ለምንገዛው ነው፡፡

ፊት መነጨት ያለበት በጥቅም ጉረሮው ታንቆ ወገኑ ሲረግፍ ድምፁን ለማይሰማ ዳያስፖራ ነው፡፡

ልክ ነዎት የጎበዝ እናት! የእርስዎ ልጅ የተቀደሰ ነው! ሽለላና ቀረርቶ እንጅ ልቅሶም አያስፈልገው!

ደረት መደቃት ያለበት ደም እንደ ጅረት ሲፈስ እንኳን መገዘት ጸሎትም ለሚከለክሉ አቡንና ጳጳሳት ነው!

መለቀስ ያለበት በላይ ስናስገባና በታች ስናስወጣ ኖረን እንደ ቅንቡርስ ለምንሞተው ነው!

ጀግናዋ እናት እውነትዎን ነው!  ልጅዎ ለተቀደሰ አላማ ተሰውቷል! ልቅሶ አያስፈልገውም!

ልቅሶ እሚያስፈልገን በልማት ስም ፍርፋሪ ፍለጋ ከሰይጣን ጉያ እንደ እባብ ለምንሽሎከለከው ሆዳሞች ነው!

ልክ ነዎት እማማ!

መለቀስ ያለበት እንደ አሳማ ስንውጥ ኖረን በድንገት ለምንደፋው ሆዳሞች ነው!

የእርስዎ ልጅማ እሚገባው ቀረርቶና ፉከራ ነው!

መለቀስ ያለበት ከክብሩ ከርሱን ለሚመርጥ ሆዳም ነው!

የልጅዎን ነፍስ በገነት፤ ሥጋውን በሐውልት፤ ስሙን ደሞ በታሪክ ብራና ያስቀምጠው፡፡

ነሐሴ ሁለት ሺ ስምንት ዓ.ም.

ወልቃይት በምእራብ ኣንዳመጸው ሁሉ ራያም በምስራቅ ያምፃል። ህወሃት ወያኔ ሆይ! እብጠትሽ መተንፈስ ኣለበት! -ቦሩ በራቃ

$
0
0

 

raya

እነሆ የወያኔዎቹ የ25 ኣመት መሰሪ ሴራ በኣስተማማኝ ሁኔታ መበጣጠስ ጀምሯል። በኦሮምያና በኣማራ ክልል የተነሳው ጸረ ወያኔ እምቢተኝነት የተናጠል ትግል መሆኑ ቀርቶ ስልታዊ ኣጋርነትን ሲፈጥር እያየን ነው። በዚህም ሁለት ኣበይት ድሎች እየተመዘገቡ ናቸው። የመጀመሪያው ድል ከዚህ በፊት ያልታየና የኣንዱ ወገን ክንድ ብቻውን መድከሙ ኣብቅቶ ሁለት ፈርጣማ ክንዶች ወያኔን በተመሳሳይ ወቅት በህብረት መደቆስ መጀመራቸው ነው። ሁለተኛውና ዋነኛው ድል ደግሞ ወያኔ 25 ኣመት የገዛበት ኦሮሞና ኣማራውን የማናቆሪያ ካርዱ ኣርጅቶ በስብሶበት መበጣጠስ መጀመሩ ነው። ሁለቱ ድሎች እንክብካቤ እየተደረገላቸው ወደፊት መቀጠል ከቻሉ ለህወሃት ወያኔ መንግስት የመጨረሻው መጀመሪያ ይሆናል።

ሁላችንም ኣንዳየነው ጎንደርና ባህር ዳር ላይ በተካሄዱ ሰልፎች የኣማራ ህዝብ ለኦሮሞ ህዝብ ያለውን ወገንተኝነት በግልጽ ቁዋንቁዋ ለወያኔ ነግሮታል። ኦሮምያ ወስጥም ቢያንስ መቶ በሚሆኑ የዞንና የወረዳ ከተሞች የኣማራን ህዝብ ጥያቄ የኦሮሞ ህዝብ እንደሚደግፈውና በሁለቱ ወንድም ህዝቦች መሃል ፍቅር የሚዘራ መንፈስ በግልፅ ተስተዉሏል። በርግጥ ሁለቱም ኣንድ ኣይነት ጠላትና ተመሳሳይ የጭቆና ቀንበር ስር የወደቁ ነጻ ህዝቦች ናቸው። ሁለቱም ብዙሃን ሆነው በኣንድ ኣናሳ ቡድን የጠመንጃ የበላይነት ነጻነታቸውን የተቀሙ ናቸው። ሁለቱም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳይ እጅጉን የሚመለከታቸው ቢሆንም በባለጊዜው ኣናሳ ቡድን ከኣገሪቷ ከፍተኛ የስልጣን ደረጃዎች የተገለሉ ወገኖች ናቸው።

በኦሮሞና ኣማራ ህዝቦች መካከል ሊገነባ ሰለሚገባው ጠንካራ የወዳጅነት ድልድይ በሌላ ኣርእስት እመለስበት ይሆናል። ኣሁን ወደተነሳሁለት ጉዳይ ልዝለቅ። ዛሬ የምናየው የትግራይ ካርታ ድሮ በደርግ ዘመን ከምናውቀው ካርታ በእጅጉ የገዘፈ መሆኑ ግልፅ ነው። በምእራብ እነ ወልቃይት ጠገደ በምስራቅ ደግሞ እነ ራያና ኣዘቦ በማናለብኝነት ተቆርጠው ወደ ትግራይ ተካልለዋል። ህወሃት ስልጣን ሲይዝ ትግራያዊ ያልሆኑ መሬቶችን በግድ ወደ ትግራይ በማካለል ዘላለም በሰላም ተደላድሎ የሚኖር መስሎት ነበር። ለነገሩ ይህ ኣይነቱ ኢፍትሃዊ ኣከላለል ከዚያም በፊት መደረጉን ለመካድ ኣይደለም። ነገር ግን እንደ ወያኔው ዘመን ኣይን ያወጣ ኣልነበረም። ወልቃይት ላይ ያለው ህዝብ ከትግራይ መጥቶ እዚያ ቦታ ላይ እንዲሰፍር ሰለተደረገ ብቻ ያ መሬት ጎንደርነቱ ተክዶ ትግራይ ሊሆን ኣይችልም ኣልቻለምም። ወልቃይቴውና ድፍን የጎንደር ህዝብም ይህን እውነታ በሚገባው መልኩ ለህወሃቶች እየነገረ ይገኛል።

የወልቃይት ጉዳይ በቂ ሽፋን ያገኘና ወደ ትግልም የተገባ በመሆኑ ብዙም የምናገረው ነገር ኣይኖርም። የፅሁፉ ኣርእስት ወደሆነው የራያና ኣዘቦ ጉዳይ ላምራ። ራያ ማለት ትግራይ ውስጥ በተፈጥሮ ለምና ለእርሻ ተስማሚ የሆነ መሬትና ኣየር ንብረት የታደለ ኣካባቢ ነው። በደቡብ ኣላውሃ ከሚባለው ኣካባቢ ተነስቶ በሰሜን ኣላጄ እስከሚባለው ቦታ የሚደርስ ሲሆን በቆዳ ስፋቱ ከቀድሞው የኣክሱምና የኣድዋ ኣውራጃዎች ይበልጣል። ራያና ኣዘቦ የሚባሉት ጎሳዎች ትግሬዎች ኣለመሆናቸውን ታሪክ ኣበጥሮ ያስረዳል። በርግጥ ለዘመናት በትግራይ ፊውዳሎች ኣገዛዝ ስር ሲጨቆኑ በመኖራቸው ዛሬ ትግርኛ ተናጋሪ ተደርገዋል። እንደዛም ሆኖ ኣፋን ኦሮሞ የሚናገሩ ራያዎች ዛሬም ድረስ ኣሉ። ለምሳሌ በቅርቡ ሳሊሃ ሳሚ የተባለች ዝነኛ የኦሮሞ ኣርቲስት ለሙዚቃ ስራዋ ቪዲዮ ልትሰራ ወደ ኣካባቢው በተጉዋዘችበት ለራያ ኣረጋዊያን ባደረገቻቸው ቃለመጠይቆች ኣረጋዊያኑ ጥርት ባለ ኣፋን ኦሮሞ ታሪካቸውን ሲናገሩ ሰምተናቸዋል። ከኣፋን ኦሮሞ ተናጋሪ ራያዎች ኣንዳንዶቹ እንዲያውም ጎልማሶች ናቸው። በዚህ ቃለመጠይቅ ላይ ሲናገሩም ልጆቻቸውን በብሄር ማንነታቸው ቁዋንቁዋ ማስተማር እንደማይችሉና ትምህርት ለመከታተልም ሆነ ህይወታቸውን ለማሸነፍ የግድ የትግርኛ ቁዋንቁዋ ኣቀላጥፈው መናገር እንደሚጠበቅባቸው ገልጠዋል።

ለመሆኑ ራያ በወያኔ ትግል ውስጥ የነበረው ሚና እስከምን ድረስ ነበር?

በቀዳማዊ ሃይለስላሴ መንግስት ላይ በተለያዩ ጊዜያት ካመፁት የኢትዮጵያ ኣካባቢዎች መካከል ራያ የመጀመሪያው ነበር። ገና በ1928 ነበር ያመጸው። ዛሬ ሁሉም ለምዶት ‘ወያኔ’ የሚለው ቃልም የመጣው የወቅቱ የራያ ኣመፀኞች ይጠሩበት የነበረ የትግርኛ ስማቸው ነበር። ጥሬ ትርጉሙም ‘ኣመፀኛ’ እንደማለት ነው። እናም ራያዎች ‘ቀዳማይ ወያኔ’ በመባል ይታወቃሉ። የዛሬው ህወሃት ቃሉን ከራያዎች ኮርጆ መጠቀም የጀመረውም በወቅቱ በኣድዋ ትግሬዎች በደል ደርሶባቸው ልባቸው የራቀውን ራያዎች ለማማለል መሆኑን ለታሪኩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ይናገራሉ። የራያ ወያኔዎች ትግል የጀመሩት በዛሬዋ የቆቦ ወረዳ ነበር። ከዚያም ኣመጹ በኣጭር ጊዜ ውስጥ መላውን ራያና ዋጅራት ኣውራጃዎችን ኣዳረሰ። ቀጥሎም የእንደርታ ትግሬዎች የራያ ወያኔዎችን ኣመጽ ተቀላቀሉ። በራያዎችና በትግሬዎቹ መካከል የትግል ህብረት ሊመሰረት የቻለው ከኣስር ኣመት በላይ ራያዎች ብቻቸውን ሆነው ካመጹ በሁዋላ ነበር። የህብረት ትግሉም ራያ፣ ዋጅራትና እንደርታን ነጻ ማውጣት ችሎ ነበር።

ሁዋላ ላይ ግን በ1943 ተመታ። የኣጼ ሃይለስላሴ መንግስት በእንግሊዞች የታገዘውን የኣየር ድብደባ ራያ ላይ ቢፈፅምም ኣመፁ እንደተፈለገው ሊደመሰስ ኣልቻለም። እናም የኣጼው መንግስት ሌላ ስልት ነበር የተጠቀመው። ልክ ሁዋላ ላይ የባሌውን ኣመፅ መሪ ዋቆ ጉቱንና የሸገሩን የመጫና ቱለማ ኣመራር ኣባል ጀነራል ታደሰ ብሩን ለመማረክ እንደተጠቀመው ሁሉ የራያ ኣመፅ መሪዎችንም ለማስገበር በኣድዋው ባላባት ደጃዝማች ገብረሂወት መሸሻ የሚመሩ ወደ ስምንት የሚገመቱ የትግሬ መኩዋንንትን ልኮባቸው በሽንገላ ካስገበራቸው በሁዋላ እንደፈጃቸው ይነገራል። የወቅቱ የራያና ዋጅራት ኣመፅ (ቀዳማይ ወያኔ) በዚህ መልኩ ነበር በትግሬ ከሃዲዎች የተመታው። መሸሻና ግብረ ኣበሮቹ ለዋሉት ውለታ የማእረግ እድገትና ንጉሳዊ ስጦታ የተበረከተላቸው ሲሆን ኣመፀኛው ራያ ግን ሲቆረቆስ መኖር እጣ ፈንታው ሆነ። ከዚሁ ጋር በተይያዘም የራያን የኣንድነት ክንድ ሸራርፎ ለማዛል ሲባል ለሁለት ተከፍሎ ገሚሱ ትግራይ ገሚሱ ደግሞ ወሎ ጠቅላይ ግዛቶች ስር እንዲተዳደር ተደረገ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የራያዎች ልብ ቂም እንደቁዋጠረ ነው።

ህወሃት በ1970ቹ መጀመሪያ በደርግ መንግስት ላይ የትጥቅ ትግል ሲጀምር የራያዎቹን የጀግንነት ልብ ለመጠቀም በእጅጉ ነበር የቁዋመጠው። ራያዎች የንጉሱ መንግስት ወድቆ ድርጉ ስልጣን ቢይዝም ልዩነት ኣልመጣላቸውምና ደርግንም በደስታ ኣልተቀበሉም። ከፊውዳሉ ስርኣት ለይተው ኣልተመለከቱትም። ሰለሆነም የትግልን ኣስፈላጊነት ኣሁንም ያምኑበት ነበር። ይህን ልባቸውን የተረዳው ህወሃት ወያኔ ይሸንግላቸው ጀመር። ራያዎች የትግሬዎችን ሽንገላ ከልባቸው ባይቀበሉትም ከትልቁ ሰይጣን ትንሹ ይሻላል በሚል ስሜት ብቻ የህወሃትን የትግል ጥሪ በኣስር ሺዎች ተቀላቀሉት። ኣቶ ጥኡማይ የተባሉት ጸሃፊ በፈብሯሪ 2013 Raya Under Destruction በሚል ርእስ ባስነበቡት ፅሁፍ እንዳስቀመጡት ከሆነ ዋናው የወያኔ ወታደራዊ ኣቅም መገለጫ የሆነውን የሃዱሽ ወይም ሃይሎም ኣርእያ ጦር የጀርባ ኣጥንት የሆኑት የራያ ልጆች ነበሩ። ሃየሎምን ስመ-ገናና ያደረጉት በስሩ የተሰለፉት በሺዎች የሚቆጠሩት ትንታግ የራያ ታጋዮች ናቸው በማለት ያስረዳሉ ፀሃፊው። በጦርነቱ ወቅትም ሆነ በሁዋላ ግን ብዙዎቹ የራያ ልጆች የጥይት ማብረጃ (canon fodder) ሆነው ኣንደቀሩና ከዛም የተረፉት የመለስ-ስብሃት ገዳይ ቡድን ሰለባ ሆነው መቅረታቸውን ውስጥ ኣዋቂው ጸሃፊ ኣቶ ጥኡማይ በምሬት ይገልጻሉ።

በኣይበገሬነታቸው የሚታወቁት ራያዎች ትግሉን ከድሉ ኣድረስው የመንግስት ለውጥ ቢመጣም በህወሃት የስልጣን ክፍፍል ውስጥ የነበራቸው ወይም ዛሬም ድረስ ያላቸው ቦታ ግን ኣዚህ ግባ የሚባል ኣይደለም። እንደጀግንነት ገድላቸውና እንደከፈሉት መራራ መስዋእትነት ቢሆን ኖሮ ህወሃት ራያ ራያ መሽተት ነበረባት። ዛሬ የራያ ልጆች በተራ ወታደርነት ኣልያም ግፋ ቢል ጥቂት ወታደራዊ ማእረጎች ቢኖራቸው እንጂ የህወሃት መንግስትን የፖለቲካና ወታደራዊ ሃይል የመቆጣጠር ኣቅም እንደተነፈጉ ነው። ምናልባት ከፍተኛ የማእረግ ደረጃ ላይ ደርሷል የሚባለውም ቢኖር የራያነት ስሜቱ ሞቶበት ትግሬነቱን ተቀብሎ መኖርን ኣሜን ብሎ የተቀበለ መሆን ኣለበት። ህወሃት በፌዴራሉ መንግስት ደረጃ ለማስመሰል ያህል ብላ ትግራዋይ ላልሆኑት የኣገሪቷ ብሄሮች ኣከፋፈልኩ የምትለውን መናኛ የስልጣን ኣይነቶችን በትግራይ ክልል ደረጃ እንኩዋን ለራያዎች ኣላጋራችም።

ራያ ቀደም ሲል ሲታገላቸው ከኖረው ጨቁዋኝ ስርኣቶች ሁሉ በከፋ መልኩ ኣሁን ባለው የትግሬ መንግስት ኣደገኛ ጥቃት እየተፈፀመበት ይገኛል። የሚያሳዝነው ህወሃት የራያዎችን የጀግንነት ጀብድና መስዋእትነት ተጠቅሞ ስልጣን ከያዘ በሁዋላ ራያን እንደተቀሩት የትግራይ ኣካባቢዎች ኣንዳይበለፅግ ኣንቆ ይዞታል። በማህበራዊ ኣገልግሎቶች ሲታይ የራያው ኣካባቢ እጅግ ሁዋላ ቀር መሆኑን እናያለን። ረሃብና ድርቅ መልሶ መላልሶ የሚጎበኘው የትግራይ ኣካባቢ ቢኖር ደቡባዊ ዞባ የሚባለውና ራያዎች የሚኖሩበት ኣካባቢ ነው። በዚህ በዘንድሮው ድርቅ እንኩዋን ቢቢሲ ሽፋን ሰጥቶ የዘገበበት ኣሳዛኙ የሰሜኑ ክፍል ረሃብ ዛሬም መስረቱን ጥሎ የሚገኘው እዛው የፈረደበት ራያ ነው። ራያና ወሎ በኣጼ ሃይለ ስላሴም ዝመን ዋነኛው የኣገሪቱ የረሃብ ተጠቂ ነበረ። በደርግም ዘመን በረሃብ እጅግ ተጎድቶ በሰፈራ ስም ከቀዬው ተነቅሎ የተበተነ ህዝብ ነው። ዛሬም ለም መሬትና እርጥበታማ ኣየር እያለው የረሃብ ተምሳሌት ሆኖ ቀጥሏል። ህወህት ወያኔ ቀደም ሲል ድንጋይና ኣለታማ የነበሩትን እነ ኣድዋ፣ ኣክሱምና ኣድግራት የመሳሰሉት ኣካባቢዎች ላይ ከፍተኛ መዋእለ ንዋይ በማፍሰስና በእስራኤል መንግስት ድጋፍ በመታገዝ የመልሶ ማልማት ስራ በመስራት የኣየር ንብረቱን መቀየር ሲችል በተቃራኒው በተፈጥሮ ለም ኣፈርና እርጥበታማ ኣየር የነበረውን የራያ ኣካባቢ ግን ወደ ምድረበዳነት ቀየረው።

ቀደም ሲል የጠቀስኩዋቸው በራያ ጉዳይ ላይ ጥናት ያካሄዱት ፀሃፊ ማስረጃ እያስደገፉ ባቀረቡት ጽሁፍ ራያ በህወሃት መንግስት ስር እድገቷ የሁዋልዮሽ ማሽቆልቆሉን ያስረዳሉ። በ1994ቱና በ2007ቱ የህዝብና ቤት ቆጠራ ወቅት ከራያ የተሰበሰቡትን ዳታዎችን በማወዳደር የሚተነትኑት ጸሃፊው በ1994 ወቅት ከነበሩት 11 የራያ ከተሞች መካከል ሰባቱ (64%) ማለትም ሮቢት፣ ጎብዬ፣ ዋጃ፣ መርሳ፣ ኮረም፣ ወዲሰምሮ እና ጫለና ወድመዋል ወይም እየወደሙ ናቸው። በኣንጻሩ ግን ኣድዋ ኣውራጃ ስር የሚገኙ የገጠር መንደር የነበሩ ከተሞች ለማመን በሚያስቸግር ፍጥነት እያደጉ ናቸው። ለምሳሌም ገርሁሰናይ በ1033%፣  እዳጋ ኣርቢ በ377%ና ነበለት በ266% እስከ 2007 ኣም ያደጉ ሲሆን ቀደም ሲል በ1994 ወቅት ያልነበረ ዲዎዲቦ የተባለ ኣዲስ ከተማ መቆርቆሩንም ያትታሉ።

ህወሃት ኣንደዚህ ያሉት የኣድሎኣዊነት ባህሪይው ሲነሳበት ሽንጡን ገትሮ የሚከራከረው በጦርነት የደቀቀውን ኣካባቢ ቅድሚያ ሰጥተን ማልማት ስለነበረብን ነው ይላል። ይሁን እንጂ እነ ኣድዋና ኣክሱም ከራያ ከተሞች ጋር ሲወዳደሩ በደርጉ ዘመን ሰላማዊ ቀጣና ነበሩ ማለት ይቻላል። ለምሳሌ የራያዋ ኮረም ከተማ ብቻዋን መላው ኣድዋ ኣውራጃ ላይ ከተጣሉት ቦምቦች የላቀ ቁጥር ያለው የቦምብ ድብደባ ነበር የተፈፀመባት። እናም ህወሃት የምትሰጠው ምክንያት ኣይሰራም። በጦርነት የደቀቁ ኣካባቢዎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው ቢሆን ኖሮ ኮረም ከኣድዋ በላይ መልማት ነበረባት። ህወሃት እንደተመኘው በፍጥነት ሳትፈርስ ከዛሬ የደረሰችው ብቸኛዋ የራያ ከተማ ኣላማጣ ናት። እስዋም ብትሆን ነዋሪዎችዋ ራሳቸውን ከተቀረው የትግራይ ክልል ጋር ኣወዳድረው የከተማቸው ውድቀት ሲያሳስባቸው ተወካዮችን መርጠው ወደ መቀሌ ልከው ኣቤት ብለው ነበር። ነገር ግን ኣውራዎቹ የህወሃት ባለስልጣናት እነሱን የሚሰሙበት ጆሮ ኣልነበራቸውም። እንዲያውም የትግራዩ ክልል ፕሬዚዳንት ኣባይ ወልዱ የኣላማጣ ህዝብ ተወካዮችን ብሶት እንደመስማት ቡልዶዘሮች በፍጥነት ወደ ከተማዋ ተልከው የማውደም ዘመቻውን እንዲያቀላጥፉ ነበር ያደረገው። ይህን ሰይጣናዊ ድርጊት የተቃወሙ የኣላማጣ ነዋሪ ራያዎች በኣድዋ ተወላጆች በሚመሩ የትግራይ እስር ቤቶች ውስጥ እየማቀቁ እንደሚገኙ የኣቶ ጥኡማይ ጥናታዊ ጽሁፍ ያስረዳል።

ኣዎን! ራያ በትግራይ ክልል ስር ኣልተመቸውም። እድገቱ እንደ ካሮት ቁልቁለት ሆኖበታል። ማንነቱን ከማጣቱ በተጨማሪ በማህበራዊ ኣገልግሎቶችም ሆን ተብሎ ወደ ዳር የተገፋ ህዝብ ነው። ህወሃት ወያኔ በመቀሌ፣ በኣክሱም፣ በኣድዋ፣ በኣድግራት ወዘተ እንዳደረገው ሁሉ የራያን ኣካባቢ ማልማት ያልፈለገው የራሱ ምክንያት ስላለው ነው። ራያዎች ኣንድ ቀን ትግራይን እንደሚሰናበቱ ልቡ ያውቀዋል። ራያዎች ራያ እንጂ ትግሬ እንዳልሆኑና ቀኑ ሲደርስ ወደ መሰረታዊ ማንነታቸው እንደሚመለሱ ስለሚያውቅ ነው። ታድያ ወያኔ ህወሃት ይህን ኣውቆ ራያን ለስሙ ትግራይ ክልል ውስጥ ኣግቶ እንደ እንጀራ ልጅ ሲጎዳው ራያስ የእንጀራ ልጅነቱን መገንዘብ ይሳነዋል እንዴ? በተለይም ወንድም የወልቃይት ኣማራ ህዝብ “ኣማራ ነኝ እንጂ ትግሬ ኣይደለሁም፣ የወልቃይት መሬትም የጎንደር እንጂ የትግራይ ኣይደለም” ብሎ ሲያምፅ ራያስ ምን ይሰማዋል? ራያዎች የኣመጽን ምንነትና ኣሰፈላጊነት ገና ከማለዳው ሞክረው ለኢትዮጵያ ህዝቦችም ያስተማሩ ኣይበገሬ ነብሮች ናቸው። ዛሬ ላይ ኣፋቸውን ተሎጉመው ትግራይ ስር ተረግጠው መገዛት በፍፁም ኣይገባቸውም። በምእራብ ወልቃይት ኣንዳመጸው ሁሉ በምስራቅም ራያ ያምፃል። የ1928ቱንና የደርጉን ዘመን የጀግንነት ገድሉን በመድገም ባክኖ የቀረውን የውድ ሰማእታቱን ኣላማ ከግቡ ያደርሳል!

 

ዝም ያለ ከተስማማ እኩል ይቆጠራል።በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖረውን የትግራይን ሕዝብ ይመለከታል (የጉዳያችን ማስታወሻ)

$
0
0

23ህወሓት ከመነሻው ጀምሮ ግድያ የጀመረው በትግራይ ሕዝብ ላይ ነበር።የትግራይ ሽማግሌዎች ”የፊውዳል እና የነፍጠኛ አምላኪ” እየተባሉ በህውሃት ግልፅ እና ስውር የግድያ መንገድ ተፈጅተዋል።የህወሓትን እንቅስቃሴ በቀዳሚነት የተቃወመ የትግራይ ሕዝብ ነበር።የአክሱም እና ተንቤን ሕዝብ ህወሓትን ደግፎ ቆሞ አያውቅም ነበር።ህወሓት በማኔፌስቶው ላይ ” የትግራይ ሕዝብ ትግል ፀረ-አማራ፣ ፀረ-እምፔራሊዝም እና ፀረ ንዑስ ከበርቴ” መሆኑን ከገለፀ በኃላ አላማውም ”የትግራይ ሪፑብሊክ መመስረት ነው” ይላል። ይህንን አባባል በመጀመርያ ላይ የተቃወሙት እና ለሰማዕትነት የደረሱት የትግራይ ወጣቶች እና አረጋውያን ነበሩ።ይህ ሁኔታ እስከ 1983 ዓም ሲቀጥል የአክሱም እና ተንቤን ሕዝብ በተለይ በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ጉዳይ ህወሓትን በእየቦታው ሲሞግቱ የነበሩ አሁንም የትግራይ አዛውንት ነበሩ።በ1990 ዓም የተቀሰቀሰው የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሰንደቅ አላማው እና ለኢትዮጵያዊነቱ ያሳየው ፅናት (ህወሓት ኢትዮጵያውያንን በአደባባይ ሲዋሹ ቢታዩም) ለትግራይ ሕዝብ ሰንደቅ አላማ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ዳግም ያረጋገጠ ታሪካዊ አጋጣሚ ነው።

በ1968 የወጣው የህወሓት ማኔፈስቶ –
ኢትዮጵያውያን የህወሓት የጎጥ ፖለቲካ አይን ያወጣ ቢሆንም ሁሉን ችለው ኢትዮጵያዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ ሲያተኩር ቆይቷል።አቶ መለስ ሕይወት ሲያልፍ የአዲስ አበባ ሕዝብ ትግራይ ተወለዱ ኤርትራ ሳይል ከአየር መንገድ አስከሬን አጅቦ የወጣው ሕዝብ በኢትዮጵያ ላይ የተፈፀመውን ድርጅታዊ ወንጀልን ማንም እረስቶት አይደለም።በመላው ኢትዮጵያ ለቀናት የዘለቀ ሃዘን ሲታወጅ የኢትዮጵያ ሕዝብ በጨዋነት ቀናቱን በዝምታ አሳልፏል።
ይህ ሁሉ የሚያሳየን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሚገባው በላይ ጨዋ ሕዝብ መሆኑን ነው።ህወሓት ከጎንደር እና ዓለም ከተማ የመብራት ትራንስፎርመር በምሽት ሊሰርቅ እጅ ከፍንጅ የያዘው ሕዝብ የዘር አድልዎ እንደተደረገበት እያየ በአርምሞ አሳልፏል።በያዝነው ዓመትም በአርማጮ እና ወልቃይት ሕዝብ ላይ ህወሓት ከአድዋ እና ሽሬ እናቶችን በመኪና አመላልሶ ጠብመንዣ እያስያዘ በአማራው ሕዝብ ላይ ሁለት ጊዜ በሰልፍ ሲዝቱ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በዜና እወጃው ሲያሳይ የትግራይ ሕዝብ ይቃወማል ተብሎ ይጠበቅ ነበር።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻም ጎንደር እና ጎጃም ላይ በህወሓት ሰራዊት ግልፅ የሆነ ወረራ ተፈፅሟል።እስከ አሁን ድረስ እንደ ሁማን ራይት ዘገባ ከአንድ መቶ በላይ ሕዝብ ተገድሏል።በሆስፒታል የሚገኙ በከባድ ሁኔታ የቆሰሉ ደግሞ ከ500 በላይ እንደሆኑ እና ከእነኝህ ከቆሰሉት ውስጥ አሁንም የሞቱት አስከሬን እየወጣ መሆኑ ይታወቃል።አሁንም ከትግራይ ሕዝብ በህወሓት ላይ የተሰማ ተቃውሞ የለም።
ይህ ብቻ አይደለም ዛሬ ሮብ ነሐሴ 4/2008 ዓም ከባህር ዳር እና ጎንደር የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከመቀሌ በአንቶኖቭ አይሮፕላን የመጡ የአጋዚ ወታደሮች ወደ ጎንደር እና ባህርዳር ገብተዋል።ይህም ግልፅ የሆነ የጅምላ ፍጅት ህወሓት ልትፈፅም መሆኑን አመላካች ነው።ይህንንም የሚቃወም የትግራይ ሕዝብ ሰልፍ አልታየም።

ስለሆነም የትግራይ ተወላጅ እስካሁን እየሆነ ላለው ሁሉ ግልፅ ተቃውሞ በህወሓት ላይ ሲያሳይ አይታይም።ይልቁንም በማህበራዊ ድረ-ገፆች ላይ የትግራይ ተወላጅ መሆናቸውን የሚናገሩት ”ትግራይ ኦንላይን” እና ”አይጋፎረም” በገፃቸው ላይ የሚፅፉት አማራውን እና ኦሮሞውን የሚያጣጥሉ እና ንቀት የሚያሳዩ ፅሁፎችን ነው።እነኝህ ድረ-ገፆች አላስፈላጊ ፅሁፎችን ሲለጠፉ አሁንም ከትግራይ በኩል ተቃውሞ የሚያሳይ አንድም የጎላ ድምፅ አልተሰማም።

ባጠቃላይ የትግራይ ሕዝብ ህወሓት ለሚሰራው ግፍ እና አገራዊ ወንጀል ሁሉ ዝም ማለት የለበትም።በእራሱ በትግራይ ህወሓትን የሚቃወም ሕዝብ ለማየት የኢትዮጵያ ሕዝብ እየናፈቀ ነው። አሁን ባለንበት ሰዓት የኢትዮጵያ ሰራዊት ውስጥም ግልፅ የሆነ መለያየት እየታየ ነው።ሰራዊቱ ውስጥ የትግርኛ ተናጋሪ እና ሌላ አካባቢ የመጡ በጥይት እርስ በርስ እንደተጋደሉ ተሰምቷል።ሰራዊቱ ከቀናት ምናልባትም ከሰዓታት በኃላ ሰራዊቱ አፈሙዙን በአቶ አባይ ወልዱ ቅልብ ሰራዊት ላይ እንደሚያዞር ምንም ጥርጥር የለውም።የትግራይ ሕዝብ ግን የወገኖቹ መጨፍጨፍ እንዳልሰማ ዝም ሊል አይገባም። ይህ ሁኔታ ሁላችንም አላስፈላጊ ወደ ሆነ መሰረታዊ የአስተሳሰብ ለውጥ ውስጥ እንዳያስገባን እና በግለሰቦች የተፈፀመብን የዘር አድልዎ ወደ ከፋ ድምዳሜ እንዳያደርሰን ያሰጋናል። ነገን አርቆ ማሰብ ለእራስ ነው።የትግራይ ሕዝብ ከእዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ ውስጥ ሊወጣ የሚችልበት ቀላሉ መንገድ ህወሓትን መቃወም እና ፋሽሽታዊ አስተሳሰብ ከተፀናወታቸው አባይ ወልዱን እና ግብረ አበሮቻቸውን በቁጥጥር ስር በማዋል እና መሰረታዊ አገራዊ ፖለቲካዊ፣ምጣኔ ሃብታዊ ለውጦች ላይ እና እኩል ተጠቃሚነት ላይ ሲስማማ ብቻ ነው።ከእዚህ ውጭ ግን ”ዝም ያለ ከተስማማ እኩል ይቆጠራል” እንዲሉ በድርጊቱ ከመስማማት እንዳያስቆጥር ከፍተኛ ስጋት አለ።እጅ አጣጥፎ ሁኔታውን እንደ ሲኒማ ከመመልከት ህወሓትን አደብ አስገዝቶ ለዘላለም ከምንኖርበት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር አንድ መሆን ብቸኛው አማራጭ ነው።
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com

«ከተራበ ለጠገበ እዘኑ!» –ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት   

$
0
0

ማክሰኞ ነሐሴ ፫ ቀን ፪ሺህ፰  ዓ.ም.             ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፳

moresh.jpg

ከአባቶቻችን ወርቃወርቅ አባባሎች አንዱ፣ «ከተራበ ለጠገበ እዘኑ» የሚለው ነው። ለዚህ አባባል መሠረታዊ ምክንያቱ የተራበ ሰው፣ አንጄቱን አጥፎ፣ አንገቱን ቀልሶ፣ ይቀመጣል። ካንደበቱ ክፉ ነገርአይወጣም። አረማመዱ በአግባቡና በማስተዋል ነው። ንግግሩ የታረመና ትሕትና የተላበሰ ነው። በዚህም ምክንያት ከማናቸውም አደጋ የተጠበቀ ነው። ስለሆነም ለእርሱ ሕይዎትና ጤንነት ሌላ ውጫዊአካል አዛኝ አይሻም።

በሌላ በኩል፣ የጠገበ ሰው፣ ሲራመድ ይወናጨፋል፣ መሬቱን ይነርታል፤ ሲናገር በማን አለብኝነትና በትዕቢት፣ ሰዎችን ያስቀይማል። ያዋርዳል። ይህም በራሱ ላይ ጠላት እንዲገዛ ያደርገዋል። በዚህምየተነሳ፣ ወይ ሲዘል ወድቆ ይሰበራል፤ ወይም ሰዎችን ከፍ ዝቅ አድርጎ ሲናገር፣ አንዱ ትዕግሥቱ ያለቀበት ካቲውን ይለውና የሰው ዕዳ ሆኖ ያልፋል። ይህ በሰው ልጆች ሕይዎት ተደጋግሞ የታየ ክስተትበመሆኑ፣ አስተዋይ አባቶቻችን፣ «ከተራበ ለጠገበ እዘኑ» ይላሉ። ዕውነት ነው! የጠገበ ያሳዝናል። አወዳደቁ አሳዛኝ፣ ከመሆኑ በላይ ዳፋው ለሌሎችም ሰዎች ስለሚተርፍ በጥብቅ ሊታዘንለት ይገባል።

ዛሬ በአገራችን በኢትዮጵያ እጅግ ካለመጠን የጠገቡ ሰዎች አሉ። ጥጋባቸው መረን ለቆ፣ አንድን ሠፊ ቁጥር ያለውን የዐማራ ነገድ፣ «ዐማራን እንደሲጋራ አጭሰን ረግጠነዋል» (ስየ አብርሃ)፤ «ገድለንየቀበርነውን ዐማራ አንታንሱብን» (ሣሞራ የኑስ)፣ «ዐማራውንና ኦርቶዶክስን ሰባብረን ጥለነዋል»(ስብሃት ነጋ)፣ «ዐማራ ትምክህተኛ ነው!» (ገብረኪዳን ደስታ)፣ «ዐማራ የትግሬ ጠላት ነው» (የሕወሓትፕሮግራም)፣ «ዐማራ መንገድ ላይ ቁጭ ብሎ ሲለምን ማየት እሻለሁ» (መለስ ዜናዊ)፣ በአጠቃላይ ዐማራውን «ሽንታም፣ ፈሪ፣ ቀሚስ እናለብሰዋለን፣ ገድለን ቀብረነዋል፣ ነፍጠኛ፣ ትምክህተኛ፤ የትግሬጠላት» ወዘተርፈ በማለት ላለፉት 40 ዓመታት በኢትዮጵያ ተፈጠሩ ለተባሉ ችግሮች ሁሉ፣ ዐማራውን ተጠያቂ በማድረግ፣ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ፈጽመውበታል። ይህ ሁሉ አባባልናድርጊት፣ ጥጋብና እብሪት የፈጠረው፣ ነገን አሻግሮ ማየት ከማይችሉ ትናናሽ ቅንጭላቶች የሚወጣ ቃልና ድርጊት መሆኑን ማንም አይስተውም። ምን ይመጣብናል፣ ምንስ ያደርጉናል ከሚል እብሪትየመነጨ የጥጋበኞች መለያ ለመሆኑ መጠራጠር አይቻልም።

ይህ በወያኔ ሠፈር የሚታየው ጥጋብና እብሪት፣ ለእውነተኛ ኢትዮጵያውያን፣ ከተራበው ዐማራ፣ ጉራጌ፣ ሱማሌ፣ አፋር ወዘተርፈ ይልቅ፣ የጠገበው የወያኔ ቡድንና ተባባሪዎቹ ከልብ የሚታዘንላቸውእንዲሆኑ እያደረገ ነው። በጥጋብና በእብሪት እየሠሩት ያለው ሥራ፣ ለትውልዳቸው እየገዙለት ያለው የዘር ጠላትና አሁን አሁን ደግሞ፣ በወያኔ ጀኔራል ተብየዎች የሰረጸው ፍርሃትና እያስተጋቡት ያለፍርሃት፣ ለጥጋበኞች እንድናዝን ጥሪ የሚያቀርብ ነው። ምክንያቱም ጥጋባቸው፣ እጅግ አደገኛ ወደሆነ የጥፋት ጎዳና እየገፋቸው በመሆኑ፣ የሚከተለው ሕዝባዊ እልቂትና አገራዊ ጉዳት፣ እንርሱን በማጥፋትብቻ የማይገደብ፣ ለትውልድና ለሀገር መጥፎ ጠባሳ ጥሎ የሚያልፍ በመሆኑ፣ በግልጽ ሊታዘንላቸው ይገባል። በንፁሐን ዜጎች ላይ የሚያወርዱት የጥይት ናዳ፣ የሚፈስ የወጣት፣ አዛውንት፣ ሽምግሌ፣ወንድና ሴት ደም ወደ ፈጣሪው አቤት እያለ ነው። እግዚአብሔርም የፍጡሮቹን እንባና ደም በከንቱ ፈሶ እንዲቀር የሚፈልግ አምላክ አይደለምና፣ ጥጋበኞቹን በቃችሁ ከሚልበት ዘመን ላይ የደረሰ ስለሆነ፣«ለኃጥአን የወረደ ለጻድቃን እንዳይሆን» ለጥጋበኞች ልናዝን ይገባል። በሕዝቡ ላይ የሚፈጽሙት በደልና ግፍ ከልክ በላይ ሞልቶ በመፍሰስ ላይ በመሆኑ፣ በአገሪቱ በአራቱም ማዕዘኖች ያለው የሕዝባዊተቃውሞና የትግሬ-ወያኔ ሰላማዊ ተቃውሞውን ለማፈን በግፍ የሚገድላቸው ሰዎች አስከሬን ብዛት አፍ አውጥቶ እየተናገረ ነው።

ይህ ዛሬ የትግሬ-ወያኔ በጎንደር ከተማ፣ ቆላድባ፣ ዳንሻ፣ ሙሤ ባንብ፣ ደባርቅ፣ ዳባት፣ አዲስ ዘመን፣ ወረታ፣ ደብረታቦር፣ ጋይነት፣ ባሕር ዳር፣ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ምድር እያፈሰሰው ያለው የንፁሀንዐማሮች ደም «ምነው እናቴ ትግሬ ባልሆንሽ፣ የሚባልበት ቀን ክፉ ቀን ይመጣል» እያሉ አባቶቻችን የሚፈሩትን የትንቢት ቃል እንዲፈጸም ለፈጣሪ ጥሪ እያቀረቡ መሆኑን የሚያሳይ ድርጊት በመሆኑ፣ለትግሬ-ወያኔ ትውልድ ልናዝን ይገባል። ይህ ወያኔ በፍርሃትና በመርበትበት እየወሰደ ያለው የጥፋት እርምጃ፣ የኋላ ኋላ ጦሱ ለትግራይ ትውልድ ስለሚሆን፣ የሚፈራው ክፉ ቀን ከዚህ በባሰ መልኩእንዳከሰት፣ የትግራይ ሕዝብ ከወያኔ ራሱን በፍጥነት ለይቶ ከዐማራ ወገኑ ጎን እንዲቆም ጥሪያችን እናቀርባለን። «ከተራበ ለጠገበ እዘኑ!» ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ሰኞ ነሐሴ ፪ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ.ም. ቅፅ፬ ፣ ቁጥር ፲፱ ለዚህ ጥሪ አዎንታዎ ምላሽ ለማይሰጡ የወያኔ ባለሥልጣኖች፣ የስለላና የአፈና ቡድን አባሎችና ተቋሞች፣ የወያኔ ተባባሪዎችና ደጋፊዎች ላይ የማያዳግም ርምጃ በመወሰድ፣ ሕዝባዊ አመፁወደታለመለት የወያኔን ሥርዓት የመጣል ግቡን ባጭር ጊዜ ውስጥ ዕውን እንዲሆን እያንዳንዱ የዐማራ ነገድ ሕዝባዊ አመጹን በንቃት፣ በቁርጠኝነት እና በጀግንነት እንዲሳተፍ ጥሪያችን እናቀርባለን።

ይህ ሕዝባዊ አመጽ፣ የዐማራውን በኢትዮጵያ ውስጥ የመኖርና የመሥራት፣ የኅልውና ጥያቄ አረጋግጦ፣ የኢትዮጵያን ትንሣኤ የሚያበስር እንዲሆን፣ የእንቅስቃሴው አቅጥጫ ወያኔ-ጠቀም እንዳይሆን፣የአመጹ በትር ወያኔና መሰሎቹ ላይ እንጂ፣ ሕዝብ ላይ እንዳያነጣጥር ብርቱ ጥረት እንደሚደረግ ተስፋ አለን።

ኢትዮጵያ ስንል በውስጧ ያሉትን ነገድና ጎሣዎቿን አንዱም ሳይቀነስ ነውና፣ የወያኔ ባለሥልጣኖች «ወያኔ ትግሬ፣ ትግሬም ወያኔ ነው» ቢሉንም፣ በዚህም የተደለሉ ትግሬዎች እንዳሉ ብናውቅም፣ እኛከነሱ ተሽለን መገናችን ዋና መገለጫው፣ ጠላታችን ወያኔና ወያኔ የዘረጋው ሥርዓት እንጂ፣ የትግራይ ሕዝብ በነቂስ አለመሆኑን የመለየት ብቃታችን ስለሆነ፣ በዚህ ረገድ ርምጃዎቻችን የተጠኑና ኋላ ፀፀትላይ የማይጥሉን እንዲሆኑ ከፍተኛ ጥረት ማደረግ የግድ ይላል።

በዚህ አጋጣሚ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ባለፉት 25 ዓመታትም ሆነ፤ ሰሞኑን በጎንደርና በጎጃም ክፍለሀገሮች፣ የወልቃይት የማንነት ሕጋዊና ሰላማዊ ጥያቄ፣ ወያኔ በኃይል ለማፈን በወሰደውየተለመደው የሞኝና የፈሪ በትር ተመትተው ለወደቁ ወገኖቻችን ላሳዩት ጀግንነት አርአያዎቻችን፤ ለከፈሉት መስዋዕትነት ባለዕዳዎች መሆናቸውን እየገጽን፣ ደማቸው ደመ-ከልብ ሆኖ እንዳይቀርየምንችለውን ሁሉ ለማድረግ ወደኋላ የማንል መሆኑን በድጋሚ እናረጋግጣለን። በጀግኖቻችን መስዋዕትነት የዐማራው ኅልውና እና የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ እንደሚረጋገጥ ላፍታምአንጠራጠርም።

በዚህ አጋጣሚ የሕዝባዊ እንቅስቃሴው ባጭር ጊዜ ውስጥ ግቡን እንዲመታ ሕዝቡ የሚከተሉትን በያካባቢው እንዲያከናውን ያሉንን ሀሳቦች ለመግለጽ እንወዳለን።

  1. ሕዝቡ በያካባቢው የጎበዝ አለቃውን በመምረጥ ለሕዝባዊ እንቅስቃሴው ዓላማ መሳካት የሚያግዙ ሕዝቡን የማስተባበርና የመምራት ሥራ ቢሠራ፣
  2. የሕዝባዊ እንቢተኝነት አመራር ከራሱ ከሕዝቡ መሀል ባሉት እንጂ፣ ውጭ ሆነው አለን በሚሉት እንዳይጠለፍ፣ የመሪዎቹን ማንነትና ከራሱ ውስጥ እንዳሉ ሕዝቡ እንዲያውቅ ቢደረግ፤
  3. የወያኔ የስለላና የአፈና መዋቅሩ ሠራተኞች የሆኑትን ለይቶ በማውጣት በምክር ከተመለሱ መልካም፣ ካልሆነ በማናቸውም መልኩ ከሕዝቡ የሚነጠሉበትን መንገድ መቀየስ፣
  4. ዋና ዋና የመገናኛ በሮችን በተጠናከረ ቡድን ማስጠበቅ፣
  5. ለተቀላጠፈ ግንኙነትና የመረጃ ልውውጥ ከወያኔ የተሰወሩ ግልፅና አጭር የሆኑ ኮዶችን መጠቀም፣ የመገናኛ ስልቱን መለዋወጥና ቀልጣፋ ማድረግ፤
  6. ለወያኔ ደጋፊዎች ግልጽ ማስጠንቀያ መስጠት፣
  7. የወያኔን የንግድ ድርጅቶች፣ ፋብሪካዎች፣ ተሽከርካሪዎች፣ ወዘተርፈ ለይቶ መመዝገብ፣ በነርሱ አለመገልገል፣ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም ከጥቅም ውጭ ማድረግ፣
  8. ወያኔና ደጋፊዎቹን ከማናቸውም ማኅበራዊ ግንኑነቶች ማግለል፣
  9. በትግሉ የተሰው ሰዎችን ማንነት መረጃ ማሰባሰብና መያዝ፣
  10. በትግሉ ወቅት የሕይዎት መስዋዕትነት የከፈሉ እና የተጎዱ ወገኖቻችንን ቤተሰቦች በሁሉም ረገድ ድጋፍ ማድረግ፣

 

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

የዐማራው ኅልውና በጀግኖች ልጆቹ ይከበራል!

ሞት ለወያኔ!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

በመጪው ቅዳሜ –በመላ ኦሮሚያ ሰላማዊ ሰልፍ ይካሄዳል (ከጀዋር መሐመድ)

$
0
0

Debrebrhanባለፈው ሰንበት በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ በአስርታት ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ ወያኔን ተቃውሞ በሰላም ወደ ቤቱ ተመለሰ። በጣም ጥሩና ታሪካዊ ሰልፍ ነበር። በእለቱ ከጥቂት ሰዓታት በኋል ግን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ አወዳይ ከተማ ወጣቶች ሰልፍ ወጥተው በአጋዚ አልሞ ተኳሾች 26ቱ ቆስለው እስከ አሁን 6 ሞተዋል። ይሄንን እንደምሳሌ ጠቀስኩ እንጂ ኦሮሚያ ውስጥ ወያኔ ሰላማዊ ሰልፈኞችን በጥይት እሩምታ ሲፈጅ አዲስ አይደላም።

ባለፉት 9 ወራት ካ600 በላይ ዜጎች ተገድለዋል፣ 5000 የሚሆኑ የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸውል። ይሄንን ቁጥር ወስደን ብናሰላው፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ በየእለቱ ባማካይ ከሁለት እስከ ሶስት ሰዎች ኦሮሚያ ውስጥ በመንግስት ታጣቂ ሃይሎች ሲገደሉ እንደነበረ ማየት ይቻላል። ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈጸም የአምባገኖች ጸባይ ነው ተብሎ ሲታለፍ ነበር። ነገር ግን ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጣ የሚገደልው የኦሮሚያ ህዝብ ብቻ መሆኑ ግልጽ እየሆነ ሲመጣ ነገሮችን መለሰን እንድናጤን አድርጎናል። ለመሆኑ በተለያዩ ክልሎች ለወጡ ሰላማዊ ሰልፈኞች የተለያየ ምላሽ ምክንያቱ ምንድ ነው?

1) የኦሮሚያ ሰልፈኞች የጦር መሳሪያ ይዘው አለምውጣታቸው። ምክንያቱም እንደሚታወቀው ባለፉት 25 አመታት ተደጋጋሚ ትጥቅ የማስፈታት ዘመቻ በኦሮሚያ ሲካሄድ ነበር። እናም በግልጽ የታጠቀው ህዝብ አናሳ ነው። በተጨማሪም የኦሮሞ አመራሮች ህዝቡ መሳሪያ ይዞ እንዳይወጣ ሲማጸኑ ነበር። ይሄም የተደረገበት ምክንያት ያቺ ሀገር እና ህዝብ ወደ ዳግም ጦርነት ሳይገቡ በነፍጥ-አልባ ትግል ለውጥ ለማምጣት ካለ ምኞት የተነሳ ነው። ነገር ግን ይህን የኦሮሞን ሰላም ወዳድነት ህወሀቶች እንደ ፈሪነት መቁጠራቸው ገሃድ ወጥቷል።
2) ባለፉት 9 ወራት በኦሮሚያ ውስጥ በተካሄደው ትግል ብዙ ከተሞች ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ሲወጡ እንኳን የትግሬዎች ንብረት እና ህይወት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጓል። ይህ አቋም ግን ሀወሀቶች እንደ ጅልነት (naivity and harmlessness) የተቆጠረ ይመስላል።

ባጠቃልይ የህወሀት መሪዎች እንድን ህዝብ የሚሰሙት በጠመንጃ ሲጋፈጣቸው እና ዘመዶቻቸው ሲነካ ብቻ መሆኑን ደጋግመው አረጋግጠዋል። ለኦሮሞ ህዝባ ያላቸውን መጠን ያለፈ ንቀት እና ጥላቻ በተደጋጋሚ አሳይተዋል። እናም አንድ እጅ ብቻውን ማጨብጨ ስልማይችል የኦሮሞ ህዝብ እራሱን ከተከፈተበት የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለመታገድ የስትራቴጂ ለውጥ ሊያደርግ እየተገደደ ነው። ሆኖም ግን ወደዚህ ዓይነቱ መመለሻ የሌለው መንገድ ከመግባታችን በፊት የመጨረሻ እንድል መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። በዚሁም መሰረት የሚቀጥሉት እርምጃዎች ይወሰዳሉ:

1. በመጪው ቅዳሜ በኦሮሚያ ከተሞች የተቀናጁ ሰልፎች ይካሄዳሉ። እነዚህ ሰልፎች ልክ እንደ ከዚህ በፊቶቹ ሁሉ ፍጹም ሰላማዊ ይሆናሉ። በሰላማዊ ሰልፎቹ ላይ መንግስት ኦሮሞ ላይ እያካሄደ ያለውን ግድያ ባስቸኳይ እንዲያቆም፣ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ካላንዳች ቅድመ ሁናቴ እንዲፈቱ፣ ኦሮሚያን በኣጋዚ ጦር ማስተዳደር እንዲቆም፣ ህዝቡ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብቱ እንዲጠበቅ የሚሉና የመሳሰሉ ሌሎች መሰረታዊ መብቶችን መከበር የሚጠይቁ ጥያቄዎችና መፈክሮች እንዲንጸባረቁ ይደረጋል።

2. ለዚህ ሰልፍ ፍቃድ አይጠየቅም። በህጉ መሰረት ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የሚያስፈልገው መንግስትን ማሳወቅ ብቻ በቂ ነው። ይህ ጽሁፍ እንደማስታወቂ እንዲረዳ ለኦሮሚያ እና ለፌደራሉ መግስት መሰራቤቶች ገቢ አድርገናል። የኦሮሚያም ሆነ የፌደራል የታጠቁ ሀይሎች ሰላማዊ ሰልፎቹን ለማስተጓጎልም ሆነ በእለቱ በህዝቡ ላይ ጥቃት የሚፈጽሙ ከሆነ ቀጥሎ ለሚመጣው አደጋ ተጠያቂ እንደሚሆኑ በዚሁ ማስጠንቀቅ እንወዳለን። የተቀረው የኢትዮጲያ ህዝብም ለምስክረነት ይህን ግልጽ ማስታወቂያ በጥሞና እንዲያነብልንና ከጎናችንም እንዲሰለፍ ባክብሮት እንጠይቃለን።

ከዳላስና ፎርትወርዝ  የውይይት ፎረም በሀገራችን ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ     ዳላስ/  ቲክሳስ

$
0
0

  dallas1
ላለፍት ሩብ ምዕተ ዓመታት የህዋት ወያኔ ኢህአዴግ አገዛዝ  የኢትዮጵያን ህዝብን በዘር፣በቋንቋና በሃይማኖት  በመከፋፈል አምባገነናዊ ፣ፋሽስታዊና ዘረኛ የሆነ ሥርዓቱን  በሕዝቡ ጫንቃ ላይ በመጫን እንደ መንግሥት በሚመራው ህዝብ ይፈፀማል ተብሎ የማይታሰብ የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ ዜጎችን በጅምላ በመጨፍጨፉ፣ለእስር፣ለግዞትና አሰቃቂ ለሆነ ስደት በመዳረግ ታሪክና ትውልድ ይቅር የማይለው በደልና ወንጀል የፈፀመ ወንጀለኛ ድርጅት ነው። ህዋት ወያኔ ከጅምሩ የአማራን ዘር ለማጥፋት ደከመኝ፣ ደምና ግድያ ሰለቸኝ ሳይል ከፍተኛ የሆነ ኢ ሰብዓዊ ወንጀሎችን ፈጽሟል ። የመብትና የዲሞክራሲ ጥያቄ ያነሱትን የጋምቤላ ፣የአኝዋክ፣የአፋርና ሌሎች ሕዝቦች ላይ እንዲሁም በታላቁ የኦሮሞ ሕዝብ ላይ የፈፀመው ግድያና የጅምላ እስር አጅግ አሳዛኝ ነው።
በኦገስት 8/2016 በዳላስና ፎርት ወርዝ የውይይት ፎረም አባላት ወቅታዊ በሆነ የሀገራችን ጉዳይ በጥናትና በመረጃ ላይ የተመሰረተ ሰፊ የሆነ ውይይትና ግምገማ ካደረግን በኃላ ከዚህ በታች ያለውን የአቋም መግለጫ  አውጥተናል።
1/ ኛ የወልቃይት፣ማይፀብሪና የጠለምት ህዝብ የአማራ የማንነት የመብት ጥያቄን ፎረሙ ትክክለኛ የመብትና የነፃነት ጥያቄ ነው ብሎ ያምናል። ህዋት ወያኔ ይህን አካባቤ በትግራይ ግዛት ስር ለማድረግ ያለምንም ታሪካዊ መረጃ በድፍረትና በማንአልበኝነት ገና በርሀ እያለ የታወቁ ባላባቶችን በሰውር በመግደል ኢ ሰብአዊ ፍጅት አድርገዋል። ህዋት በዘመናችንና በሀገራችን በደል ያልፈፀመበት የሀገሪቱ ክፍል የለም እንደ ወልቃይት፣ጠገዴ ና የማይፀብሪ ህዝብ ላይ ለአርባ ዓመታት በተከታታይ የዘር ማጥፋት ያደረገበት ቦታ የለም። ስለዚህ የዳላስ ፎርት ወርዝ የውይይት ፎረም ይህን የማንነት የአማራነትና የኢትዮጲያዊነት የመብትና የነፃነት ትግል በሙሉ ልብ በመደገፍ ለንቅናቂው ተገቢ የሆነ የሞራልና የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ በሙሉ ልብ ተስማምተናል።
2/ ኛ በእራሱ  በህዋት ወያኔ ” ህገ መንግሥት ” ተደራጅተው ህገ መንግሥታዊ  መብታቸውን በመጠቀም የወልቃይት፣ ጠለምት ና የማይጸብሪ  የአማራ የማንነት መብት ለማስከበር በሕዝብ የተቋቋመው ና ተጠሪነቱ ለሕዝቡ የሆነውን የኮምቴ አባላት በህዋት ወያኔ የትግራይ ባለሥልጣኖች አነዴ በማባባል በሌላ ጊዜ በማስፈራራት ዝም ለማሳየት ሞክረው በመጨረሻ በትግራይ በተላከ አፋኝ የትግሪ ጦር  የኮምቴ አባላትን ለማፈን በተደረገው ጥረት ላይ የኮምቴውን አባላት በተለይም ኮረኔል ደመቀ ዘውዴን በጨካኟች እጅ እንዳይወድቅ  የጎንደር ሕዝብና ሠራዊት ያደረገው ተጋድሎና ከሳምንት በሆላ ኮረኔሉንና የኮምቴ አባላት ማስለቀቅ ብቻ ሳይሆን የህዋት ወያኔ ሥርዓት እንዲወገድ መሪት እንቅጥቅጥ የሆነው በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ የተሳተፈበት ሰላማዊ ሕዝብ የህዋት ወያኔ ሥርዓት ወደ ማይቀረው የመቃብር ሞት መሄድን አመልካች መሆኑን የሚመለክትና በህዝቡ የተላለፍት መፈክሮችና መልዕክቶች ኢትዮጵያዊነትን ያሰየ በዚህ ሥርዓት በግፍ የታሰሩ ፣የተገደሉ፣የተፈነቃሉ  የአማራ፣የኦሮሞ፣የአኝዋክ ፣የጋምቤላ ወዘተ ብሶት ያስተናገደ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችን፣የሲቤክ ማህበር አክቲቢስቶችንና ጋዜጠኟችን ከእስር እንዲፈቱ  የጠየቀ እንቅስቃሴ መሆኑን ፎረሙ ገምግሞ የጎንደሩ ተቃውሞ የኢትዮጵያ ህዝብ የነፃነት ፋና ቀዳጅ መሆኑን ፎረሙ በማመን እውነተኛ የተጋድሎ ፊሽካ መነፋቱን አረጋግጠናል ።
3ኛ/ በድቦታቦር፣በኦሮማይ ፣በባህርዳር፣ በደብረ ማርቆስ ና በአዲስ አበባ የተደረጉ ሰልፎች የአምባገነኑ ሥርዓት ማክተሚያ መሆናቸውን ፎረሙ አረጋግጦ ይህን ህዝባዊ አመፅና ትንንቅ ህዋት ወያኔና የውጭ ጠላቶች ጠልፈው አቅጣጫውን እንዳያስቱትና እነዳያከሽፍት ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ድርጅቶች፣አገር ወዳድ ሙሁራን፣ የሲቢክና የሙያ ማህበር መሪዎችና አክትቢስቶች ትግሉ አቅጣጫ ይዞ ለግብና ለድል እንዲበቃ አንድ ወጥ አመራር እንዲፈጠር  ፎረሙ ጥሪ ያደርጋል።
4ኛ/ ህዋት ወያኔን ለማስወገድ ሊገባው የሚገባ ቋንቋ የመሳርያ ትግል ብቻ መሆኑን ፎረሙ ያምናል። ለዚህም በሰፊወ በጎንደር በወልቃይት ጠገዴ በላይና ታች አርማጭሆ በጋይንትና በድርርቦታቦር በሊቦና በደንቢያ  በጎጃምና በወሎ የተጀመረው የትጥቅ ትግል ሊደገፍ የሚገባው ነው። ከህዝባዊ እንቢተኝነት ወደ ህዝባዊ አመፅ የተቀየረውን ትግል መነሻው ህዋትን በየክልሉ ማስወገድ ሁኗ መዳረሻው ኢትዮጵያን ነፃ በማውጣት ለሁሉም ዜጎች እኩል የሆነች የግልና የጋራ መብትና ነፃነት የተጠበቀባት ኢትዮጵያን ለመመስረት በሚስችለው ጠመዝማዛ የትግል ጎዳና ፎረሙ የዜግነት ግዳጅን ለመወጣት ወስኖል።
6/ ፎረሙ በሀገራችን በሚካሄደወ የመብትና የነፃነት ትግል አሸራቸውን ለማስቀመጥ ከሚፈልጉ ከማናቸውም ኢትዮጵያዊ ስብስብ በጋራ ለመሰራት ዝግጅ መሆኑን እየገለፀ የህዝብን ትግል በእብጠትና በብልጣብልጥነት ለመጥለፍና አቅጣጫ ለማስቀየር ከሚሞክሩ የህዋት ወያኔና መሰል የኢትዮጵያ ህዝብ መሰረታዊ ጠላቶች ሰርገው የሚገቡት እንታገላለን እናጋልጣለን በመጨረሻ  ፎረሙ የደረሰበት ውሳኔ ኢትዮጵያንና ኢትዬጵያዊነትን የሚስተምሩ ፣ታሪካችንና የትውልድ ሃላፊነትን  የሚስገነዝቡ ሙሁራንን በመጋበዝ ትመህርት እንደሚሰጥ ወስነናል። በመጨረሻ የተቀጣጠለወ ህዝባዊ አመፅ ለድል ይበቃ ዘንድ ለትግሉ እገዛ ለማድረግ  የሚስችል የገንዘብ ማሰባሰብ በማድረግ  ሰብሰባው ተፈጽሟል ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር  ትኑር።
ሞት ለህዋት ወያኔ!
የዳላስና ፎርት ወርዝ የውይይት
ፎረም
ዳላስ/  ቲክሳስ

ኢሕአዴግ የሚወገድ እንጂ የሚጠገን ስርዓት አይደለም! –አገሬ አዲስ

$
0
0

Woyane

ሰሞኑን የአሜሪካ ዋና ከተማ ዋሽንግተን የኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ሆና ከርማለች።አገሪቱን ለሃያ አምስት ዓመት ቀስፎ ፣ሲበዘብዝ፣ሲገልና ያገሪቱን ድንበርና አንጡራ ሃብት ከውጭ ሃይሎች ጋር ሲቀራመት የቆየው ወያኔ መራሹ ኢሕአዴግ በሕዝብ ተቃውሞ ማእበል ከተጥለቀለቀ ወራቶች አልፈዋል፡በኦሮሞው፣በጋምቤላው፣በኦጋዴው፣በቤኒሻንጉል፣በጋምቤላ ተወላጅ ብቅ እልም እያለ ሲካሄድ የቆየው ትግል ከሳምንታት በፊት ለዓመታት ሲብላላ የቆየው የአማራው ኢትዮጵያዊነትን የተላበሰ የሕዝብ ቁጣና የለውጥ ፍለጋ አመጽ ከዳር እከዳር እየተቀጣጠለ በመሄድ ላይ በመሆኑ ወያኔንና ደጋፊዎቹን ሽብር ላይ ጥሏቸዋል።ይህን ሕዝባዊ አመጽ ልዩ የሚያደርገው ነገር ቢኖር ማንም የፖለቲካም ሆነ የታጠቀ ድርጅት ሳይገባበትና ሳይመራው ሕዝቡ እራሱ በወሰደው ቆራጥነት የተካሄደ የነጻነት ትግል መሆኑ ነው። ሳይከፋፈል በአንድ ዓላማ ቆሞ ሊቀጥል የቻለውም ለሥልጣን ሳይሆን ለነጻነት የሚደረግ ሕዝባዊ ትግል በመሆኑ ነው።

የወያኔ መሪዎች  አባይ ጸሃየ፣ሳሞራ የኑስና የመሳሰሉት ወንጀለኞች ስጋት ሲወጥራቸው ከቀናት በፊት ሥልጣን ላይ ያወጣቸውን የአሜሪካንን መንግሥት ለመማጸን ዋሽንግተን ገብተው እንደተማከሩና፣እኛ ከሌለን አገሪቱ ብጥብጥ ውስጥ ትገባለች፣ከባቢውም በኢሲስ አሸባሪ ሃይል  ይጥለቀለቃል የሚል ተረትተረት ይዘው መቅረባቸው ታውቋል።በጣም የሚገርመው አልሸባብን እንዳይጠፋ ስውር ድጋፍ እያደረገ ጸረ ሽብር ነኝ ብሎ ዓለምን በማሞኘት እርዳታ በመሰብሰብ  የተካነው ወያኔ መራሹ ቡድን ፣አልሸባብና ሽብር የገቢ ምንጩ አድርጎ ስለሚጠቀምባቸው እንዲጠፉ አይፈልግም።እነሱ ጠፉ ማለት የገቢ ምንጬ ደረቀ ማለት ነው።ከምዕራቡ ከሚያገኘው ድጋፍና እርዳታ በተጨማሪ መሣሪያ የሚሸጥለት ደንበኛው በመሆኑ አልሸባብን ደፍሮ ከልቡ አይዋጋውም።እንደማስፈራሪያ ይጠቀምበታል። አሜሪካኖቹም ቢሆኑ ከልባቸው የሽብር ሰንሰለቱ እንዲበጠስ አይፈልጉም፤ምክንያቱም በዚያ ሰበብ የመከላከያ ተቋማቸውን ለመገንባትና መሣሪያም ለመሸጥ ስለሚረዳቸው ነው። የሚተማመኑበት ወያኔ መራሹ ኢሕአዴግ ሥልጣኑን እንዲያጣ አይፈልጉም።ወያኔ ተወገደ ማለት በአፍሪካ ደረጃ ለዘረጉት የዘረፋ መረብ ተባባሪና አጋር ማጣት ማለት ነው።የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል መሳካት በተመሳሳይ ሁኔታ የሚገኙት የአፍሪካና የሌላ አገር  ሕዝቦች ለሚያደርጉት የለውጥ ትግል ምሳሌ ስለሚሆን በተፈለገው መንገድ ማዳፈኑን ይመርጣሉ።ግፋ ቢል በጥቃቅን ጥገና የሚፈልጉት ስርዓት እንዲቀጥል ለማድረግ ይሞክራሉ።በኢትዮጵያም የሕዝቡን ትግል ለመቀልበስና  ከነጭራሹም ለማጥፋት ጥቃቅን ጥገና እንዲደረግ ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸው ታውቋል።በሌላም በኩል በአገር ቤት ከሚገኙት የተቃዋሚ ድርጅቶች መካከል በህይወት የቆዩት(ለምን እንደቆዩም የሚታወቅ ባይኖርም ለስርዓቱ ካላቸው የተለሳለሰ አቋም ሊሆን ይችላል የሚል አስተሳሰብ በሰፊው ይወራል)የመድረክ ም/ሊቀመንበር ዶር.መረራ ጉዲናና የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር እንጂነር ይልቃል ጌትነት ሰሞኑን፣እስከአሁንም ድረስ በዚችው የአሜሪካ ዋና ከተማ ሲንቀሳቀሱ የከረሙ ሲሆን በአሜሪካም መንግሥት አስተዳርና የውጭ ጉዳይ ቢሮ በተደረገላቸው ጥሪና ግብዣ በአገሪቱ አሳሳቢ ጉዳይ ላይ እንደተወያዩ የሚገልጽ ሾልኮ የወጣው መረጃ ሲያረጋግጥ ሁለቱም ሳይክዱ ይፋ አድርገዋል።መረጃውና የየድርጅቱ መሪዎች እንዳስረዱት የአሜሪካ መንግሥት የጥገና ለውጥ ተደርጎ ያለው ስርዓት እንዲቀጥልለትና እነሱም እንዲተባበሩ የተጠየቁ መሆናቸውን የሚጠቁም ነው።

በአገርቤትም ይኸው ጉደኛ  የአገዛዙ ቡድን አከርካሪቱን ሰብሬዋለሁ ብሎ የፎከረበትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን መሪ አድርጎ በሾመው ጳጳስ በኩል ሕዝቡ በተለይም ወጣቱ ትግሉን እንዲያቆም ወላጆች ተጽእኖ እንዲያደርጉ ና ቀሳውስትም ታቦት ተሸክመው ሕዝቡ እንደታቦቱ ወያኔን ተሸክሞ እንዲኖር ለማድረግ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።ሕዝብ በገፍ ሲገደል፣ ሲታሰር፣ሲሰደድ፣ሲቆስል ድምጹን ያላሰማና የፈጣሪን ትዕዛዝ ጥሰሃል ብሎ መንግሥትን ያልጠየቀ ጳጳስ አሁን ከወንጀለኞቹ ጎን ቆሞ ለነጻነት የሚደረገውን ትግል ለማኮላሸት መሞከሩ  የውጭ ወራሪዎችን የተከላከለችውን አገር ወዳድና አርበኛ የሆነችውን ቤተክርስቲያኗን ማርከስ ይሆናል።ቤተክርስቲያኗ ሊያጠፋት ለተነሳው አገር በቀል ጠላት መሳሪያ ሆና እጇን በእጇ እንዳታጠፋ ቀሳውስቱ የተዘረጋውን ሴራ ተገንዝበው ማውገዝና ከሕዝቡ ጎን መሰለፍ አለባቸው።መማጸን ያለባቸው የተበታተነው ሕዝባዊ ሃይልና የተቃዋሚው ጎራ እንዲሰባሰብና በአንድነት እንዲቆም በማድረጉ ተግባር ላይ መሆን ይኖርበታል።

በሌላው ዙሪያ ባለፈው ሰኞ ኦገስት 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በዋሽንግተን ከተማ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከመቸውም ጊዜ በበለጠና በደመቀ ሁኔታ ብዙ  ሰው የተሳተፈበት ሰላማዊ ሰልፍ  አድርገው የአሜሪካ መንግሥት ለወያኔ መራሹ አስተዳደር የሚያደርገውን እርዳታ እንዲያቆም፣ በተጨማሪም በሰላማዊ ሕዝብ ላይ የግድያና  ወንጀል የሚፈጽመው ቡድን በሕግ እንዲጠየቅ፣ሕዝቡ የመረጠው አስተዳደር እንዲመሰረት ጠይቀዋል።ይህም ቢሆን ለአሜሪካን መንግሥት ሌላ እራስ ምታት ነው።ተቃውሞውን ባይወዱትም  በገዛ ቤታቸው ደጃፍ ሲመጣ በዝምታ ሊያልፉት አይችሉም።ግን ስር ነቀል መፍትሔ እንዲመጣ ይፈልጋሉ ማለት አይደለም።

አሜሪካኖች የሚያካሂዱት ሙከራ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ ሙሉ መልስ የሚሰጥ ሳይሆን የአገዛዙን ሕገመንግሥት ተቀብሎ እንዲያድር የሚያስገድድ ሁኔታ ለመፍጠር እንደታሰበ የሚያረጋግጥ ነው።የኢትዮጵያ ሕዝብ ከበስተጀርባው ለሚጎነጎን ሴራ ትኩረት ሳይሰጥ በጀመረው የነጻነት ትግል እንዲቀጥልበት ማሳሰብ ይገባል።ሰላምና ድርድር አስፈላጊ መሆኑ ቢታመንም የብዙ ወጣቶችና ዜጎች ሕይወት የጠፋበት ትግል ተቀልብሶ ወንጀለኞች በሕግ ሳይጠየቁ በመንበራቸው ላይ እንዲቆዩ የሚደረገውን የውጭ አገርና የአገር ውስጥ ጥረት በውስጥና በውጭ የሚታገለው ኢትዮጵያዊ ማውገዝና መከላከል ይኖርበታል።ያ ካልሆነ ግን ውጤቱ እንዳለፉት ጊዜያቶች ወጣቱን አሳልፎ በመስጠት መስዋእት አድርጎ ባዶ እጅ መመለስ ይሆናል።የትግሉ ዓላማ የጥገና ለውጥ ማድረግና ወንጀለኛው ቡድን በስልጣን ላይ እንዲቆይ ማድረግ ሳይሆን አማራጩ መንገድ በስልጣን ላይ ያለው ቡድን ተወግዶ በምትኩ ሁሉንም ያሳተፈ የሽግግር መንግሥት መመሥረት ብቻ ነው።ያ እስኪሆን ድረስ ሕዝቡ ትግሉን  መቀጠል ይኖርበታል፤በተስፋ ተደልሎ ለዳግማዊ የበቀል እርምጃና ጥፋት በር መክፈት አይኖርበትም ።የ97ቱን ተመክሮ ሊያስታውሰው ይገባል።

የተቃዋሚ ሃይሎች የሕዝቡን ፍላጎትና ጥያቄ ከግቡ ለማድረስ ተባብረው ከጎኑ መሰለፍ እንደሚገባቸው ሊያውቁት ይገባል፤ከሕዝብ ጀርባ በማንኛውም ሃይልና አገር ግፊትና ሽንገላ የጥገና ለውጥ እንዲመጣ መተባበርና ሃሳቡን መቀበል የወንጀለኞች ስርዓት እንዲቀጥልም መፍቀድ  ከጥፋት ሃይሎች ጎን እንደሚያሰልፋቸው በቅድሚያ ሊገነዘቡት ይገባል።የሕዝቡን ጥያቄ በማክበር ከጎኑ ሲቆሙ ብቻ ነው ሕዝባዊና አገር ወዳድነታቸው የሚረጋገጠው።በውጭ ሃይል ከመተማመን በራስ ሕዝብ መተማመኑ ማዋጣት ብቻ ሳይሆን ያኮራል።ወያኔንና አሜሪካኖችን አሳብ ላይ የጣላቸውና ለጥገና ለውጥ የገፋፋቸው የሕዝቡ ትግል መፋፋም ነው፤ይበልጥ ሲፋፋም ደግሞ ለከፍተኛ የሕዝብ ጥያቄ ማለትም ለሽግግር መንግሥት መመስረት ጥያቄ ማጎብደዳቸው አይቀርም።

በሕዝቡ ትግል ላይ ውሃ ለማፍሰስ የሚሞክሩ እንዳሉ ሁሉ ትግሉንም ለማቀናጀትና ከግቡ ለማድረስ የሚጥሩ ሕዝባዊ ሃይሎች በየአቅጣጫው በመፈጠር ላይ ናቸው።እነዚህ የለውጥ ሕዝባዊ ሃይሎች ተጠናክረውና ተቀናጅተው ለድል እንዲበቁ ማድረግ የአገር ወዳዱ ድርሻ ነው።በየወረዳው ሕዝባዊ ሃይሉ አስተዳደሩን ከጨቋኞች መዳፍ ነጻ ቢያወጣ ለዘለቄታው የሽግግር መንግሥት ምስረታ ሂደት የመጀመሪያው እርምጃ ይሆናል።ይህ ድል እንዳይከስም የሚያስፈልገው ድጋፍ መቅረብ ይኖርበታል።አገዛዙ ለመኖር ሲል የማያደርገው ሙከራ አይኖርም።ሁሉም ሙከራ ካልሰራለት በመጨረሻው አስተዳደሩን ወታደራዊው ሃይሉ እንዲቈጣጠረውና የማምለጫ በር እንዲከፈትለት እንደሚያደርግ በኦሮሞና በደቡብ ክልሎች የታየው ሂደት ማስረጃ ነው።አሜሪካኖቹም ቢሆኑ ወያኔ ተዳክሞ ሕዝባዊው ትግል የበላይነቱን ከያዘ እንደ ግብጽ የወታደር መንግሥት በሾኬ ሥልጣኑን ይዞ ጥቅማቸውን ቢያስከብርላቸው ይመርጣሉ።

በውጭ አገር ያለው ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያዊ ክልል፣ቋንቋ፣ እምነትና ድርጅታዊ አቋም ሳያግደው እጅ ለእጅ ተያይዞ  ለአገር አድኑ ትግል የሚያስፈልገውን ድጋፍ ማበርከት ይጠበቅበታል።የሚከተሉትን ተግባራት ለማሟላት ከቻለ የውስጡ ትግል ተጠናክሮ ለድል እንደሚበቃ አያጠራጥርም።ምንም ጊዜ ቢሆን የሕዝቡን ትግል አሳልፎ ለሚሰጥ ውልና ድርድር ሳያጎበድድ ብዙ ወጣቶችና አገር ወዳዶች መስዋእት የሆኑበት ትግል ከዳር እስኪደርስ መፋለም አለበት።የተጀመረው  ሕዝባዊ ትግል እንዲጠናከርና ግብ እንዲመታ የሚከተሉትን እርምጃዎች መወሰድ ይኖርበታል።

  1. ኢትዮጵያዊ በያለበት አገር ለመንግሥትና ለሰብአዊ መብት ድርጅቶች ሁኔታውን በማስረዳት በገዢው ቡድን ላይ የኤኮኖሚና የዲፕሎማቲክ ተጽእኖ እንዲያደርጉ፣ለሕዝቡ መብት ጥያቄ እንዲተባበሩ መጠየቅ።ቢቻል በአንድ ቀን በተመሳሳይ መፈክር ዙሪያ ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ዝግጅት ማድረግ።ለበቂ ዝግጅትና እንዲሁም ከሚኖረው ስነልቦናዊ እድምታ መጭው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት መስከረም  1 ቀን 2009 ዓ.ም.(September 11) ለዚህ የጋራ ትግል ዕለት ቢሆንና ዝግጅቱ ከአሁኑ ቢጀመር።ይህ ማለት ግን እስከዚያ ድረስ ዝምታ ይስፈን ማለት አይደለም።ትግሉን ማንጸባረቅና ማስተጋባት ይቁም ማለት አይደለም።በተገኘው አጋጣሚና ቀዳዳ መቀጠል አለበት።የተከፈተውን የነጻነት መስኮት ሳይዘጋ በር እንዲሆን ማድረግ ይገባል።
  2. ለሚታገለው ሕዝብ የአቅም ግንባታ ማለትም፣ለተፈናቀለው መቋቋሚያ ፣ለሚታገለው ለስንቅና መጓጓዣ፣የግንኙነቱን መስመር ለማዳበርና ትግሉን ለማያያዝ በሚረዳው ተግባር ላይ የሚውል የገንዘብ እርዳታ ማሰባሰብ፣በየቤተክርሰቲያኑ፣በየሬስቶራንቱና በሱቅና የንግድ ተቋም የገንዘብ መሰብሰቢያ ሳጥን በማስቀመጥ እርዳታ መሰብሰብ።ይህን ተግባራዊ የሚያደርግ በየአገሩ ከሁሉም የተውጣጣና ታማኝነት ያለው ግብረሃይል ማቋቋም።በየአቅጣጫው የሚሰበሰበው ገንዘብ በአንድ የባንክ ቁጥር እንዲገባ ማድረግ።ወደተፈለገው ቦታና ተግባር እንዲደርስ የሚቻልበትን መንገድ ማጥናትና ተግባራዊ ማድረግ።
  3. ለቆሰለው የሕክምና እርዳታና መድሃኒት በአስቸኳይ ለማሟላት ጥናትና ዝግጅት፣አገር ውስጥ ያሉት የሕክምና ባለሙያዎችም ከሕዝቡ ጎን ቆመው በሙያቸው እንዲተባበሩ ማድረግ።
  4. በወያኔ/ኢሕአዴግ የተፈጸመውን ወንጀል፣ግድያና ማቁሰል፣አስመልክቶ መረጃ ማሰባሰብ፣ በሕግ የሚጠይቅ አካል ለመፍጠር በሙያው የተሰለፉ ኢትዮጵያውያን ተገናኝተው በአገር ውስጥና ለዓለም ፍርድ ቤት የሚቀርብ ክስ ለመመስረት ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥሪ ማድረግ።ይህ አንዱ የትግል አካል እንደሆነም ማሳሰብ።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ያቸንፋል!!

አገሬ አዲስ

 


ነፃነት ትግሉ ዓለም አቀፍ ትኩረት ስቧል።ትግሉን እስከ ነፃነት በመግፋት ዕድሉን እንጠቀምበት –ጉዳያችን

$
0
0

ኢትዮጵያ የሃያ አንደኛ ክፍለ ዘመን አዲስ ትውልዷ በፀረ ወያኔ የትግል መንፈስ በአዲስ መልክ ነፃነት ወይንም ሞት! ብሎ ተነስቷል።የህወሓት ወያኔ ቡድን በጎጥ ተጠራርቶ ኢትዮጵያን ዳግም በባርነት ቀንበር ለመተብተብ በንፁሃን ኢትዮጵያውያን ገላ ላይ አዲስ ሳንጃ ወድሯል።በሺህ የሚቆጠሩትን ደም በከንቱ አፍስሷል።ብዙዎችን አካለ ስንኩላን አድርጎ የቤተሰብ ሸክም ሆነዋል።ሌሎች ሚልዮኖችን ከሀገር አሰድዷል፣በገዛ አገራቸው የበይ ተመልካች ሆነዋል።

world newsበአንፃሩ ግን ህወሓት ለአድር ባይ እና ለመንደሩ ሰዎች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ሻንጣ ተሸካሚ እስከ ከፍተኛ የንግድ ሥራ ድረስ በአንድ ጎጥ ሰዎች አስይዞ ኢትዮጵያን የቅምጥል ህወሐታውያን እና የበይ ተመልካች ዜጎች በሚል ከፋፍሏታል።
ከወራት በፊት በኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን የተነሳው ሕዝባዊ አመፅ እና ባለፉት ሳምንታት በጎንደር እና ጎጃም የተነሱት ፀረ ወያኔ ንቅናቄዎች የመላው ዓለምን ትኩረት ስቧል።ይህ ለነፃነት ትግሉ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው።ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ የትኛውም ክፍል የተደረጉ ፀረ ወያኔ እንቅስቃሴዎች ከአለፈው 1997 ዓም ወዲህ የአሁኑን ያህል የዓለምን ትኩረት ስቦ አያውቅም።በኢትዮጵያ የሥርዓት ለውጥ እንደሚመጣ እና ሁኔታዎች እንዳሉ ሊቀጥሉ እንደማይችሉ ዓለም አቀፍ ሚድያዎች ብቻ ሳይሆን ከወያኔ ጋር የጥቅም ሽርክና ያላቸው መንግሥታትም ተረድተውታል። ይህ ማለት ግን የወያኔ ስርዓት አብቅቶለታል ማለት አይደለም።እያንዳንዱ ግለሰብ የእኔ አስተዋፅኦ ምንድነው? ብሎ መጠየቅ እና ለተግባራዊ ሥራ መነሳት አለበት። በምንም አይነት ሁኔታ ግን ወያኔ በመግደል ብዛት እድሜውን ለጥቂት ጊዜ እየተንገታገተ ያቆይ ይሆናል እንጂ በስልጣን እርከን የመቆየቱ ሁኔታ ግን አብቅቶለታል።

ዓለም ስለኢትዮጵያውያን የነፃነት ትግል ምን አሉ?

           ”የኢትዮጵያ መንግስት በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን እየገደለ የምዕራቡ ዓለም ለምንድነው እርዳታ የሚሰጠው?” ዋሽንግተን ፖስት ጁላይ 9/2016 
Ethiopia’s regime has killed hundreds. Why is the West still giving it aid?” Washington post July 9,2016.
/////////////////////////////
”ሰኞ እለት ተቃዋሚ መሪዎች እና አምነስቲ ኢንተርናሽናል እንዳሳወቁት በሳምንቱ መጨረሻ በመላ አገሪቱ በተደረገ ተቃውሞ  የኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች አያሌ ሰዎችን ገደሉ።በመንግስት በኩል መደነባበሩ እየጨመረ ነው።” 
ኒዎርክ ታይምስ፣ኦገስት 8/2016
”Ethiopian security forces shot dead several dozen people in weekend protests across the country as frustration with the government grows, an opposition leader and Amnesty International said Monday” New York times, August 9,016.
//////////////////////////////////////////////////////
”ኦባማ ከጎበኙአት አንድ ዓመት የሆናት ኢትዮጵያ በተቃውሞ እየተናጠች ነው”ዋሽንግተን ፖስት፣ኦገስት 9፣2016
‘A year after Obama’s visit, Ethiopia is in turmoil” Washington Post, Augest 9,2016
///////////////////////////
”የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በኦሮምያ እና አማራ መንግስት ለተጠቀመውን ከመጠን ያለፈ ኃይል በገለልተኛ አካል መመርመር አለበት”  ሮይተርስ ኦገስት 10፣2016 
”U.N. High Commissioner for Human Rights, said that allegations of excessive use of force across the Oromiya and Amhara regions must be investigated”
//////////////////////////////////////////////////
የአውሮፓ ህብረት  ኦገስት 10/2016 ጉዳት ለደረሰባቸው ሁሉ ማዘኑን ገልጦ ባፋጣኝ ሰላም የሚመጣበት መንገድ እንዲፈለግ ይጠይቃል።
//////////////////////////////////////////////////
የአሜሪካ ኢምባሲ ሰኞ ኦገስት 8/2016 ባወጣው መግለጫ በአመፁ ለደረሰው ጉዳት ማዘኑን ገልፆ ጉዳዩ እንዳሳሰበው ይገልጣል።
/////////////////////////////////////////////////
ከእዚህ በተጨማሪ ቢቢሲ በተደጋጋሚ፣አልጀዝራ፣ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ፣ ሮይተርስ ተቃውሞውን አስመልክቶ ህወሓት ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ እንደገባ ኢትዮጵያም በብዙ ውጥረት ውስጥ እንዳለች ፅፈዋል።
////////////////////////////////////////////////
በሌላ በኩል የእንግሊዝ መንግስት ዶ/ር አርከበ ዕቁባይን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናትን አስጠርቶ እንግሊዝ የኢትዮጵያ ሁኔታ በእዚሁ ከቀጠለ አዲስ አበባ የሚገኝ ኤምባሲዋን እንደምትዘጋ መግለጧን ኢሳት በነሐሴ 3/2008 ዓም  ዜናው ገልጧል።
ባጠቃላይ ከላይ የተጠቀሱት ለናሙናነት የቀረቡት ዘገባዎች በሙሉ በሶስት ቀናት ውስጥ ብቻ የወጡ ዘገባዎች ናቸው።ይህ የሚያሳየው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዲሞክራሲ፣ፍትህ እና ነፃነት የሚያደርገው ትግል ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ ሕጋዊ እውቅና እያገኘ መምጣቱን ነው። ይህ ለትግሉ ትልቅ ዕድል ነው። የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ በአገር ቤት እና በውጭ የሚኖር እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ትግሉን በሁሉም አቅጣጫ ማስፋፋት እና ወደ ግብ የማድረስ ኃላፊነት አለበት።
ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

ህወሃት ኢህአዴግ በኦሮሚያ ክልልና በአማራ ክልል በገጠመው ውጥረት በአፋር ክልል በሎጊያ የግዳጅ ሰልፍ እንዲካሄድ አደረገ –አካደር ኢብራሂም ( አኩ አፋር )

$
0
0
740px-Afar_in_Ethiopia.svgህወሀት መራሹ የኢህአዴግ መንግስት በህዝብ ተመርጫለሁ ባለበት በ2008ዓ.ም ክፍተኛ የህዝብ እንቢተኝነት እየገጠመው ይገኛል።
ባለፉት 9 ወራት በመላው ኦሮሚያ በመካሄድ ላይ ያለው ህዝባዊ ትግል የወያኔ መንግስት ካሁን በኋላ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው፣ ሰው ገዳይ አሸባሪ ድሪጅት መሆኑን ያየንበት ትግል ነበር።
በቅርብም በጎንደር ጅግኖች የተነሳበት ቁጣ የወያኔ ጥላት ጥቂቶች እንዳልሆኑ ያሳዩበት ኢትዮጲያ ውስጥ በእኔና በወያኔ ዕድሜ ታየቶ የማይታወቅ፣ ጥቂት የሻዓቢያ ተላላኪዎች ከሚለው የኢብኮ ቋንቋ የሻዓቢያ ተላላኪ ወያኔ እንጂ እኛ ኣይደለንም ወደሚለው የሚሊዮኖች ድምጽ የተሸጋገረበት ታላቅ ትዕይንተ ህዝብ ነበረ።
በአሁኑ ግዜ የወያኔ አገዛዝ ሊያበቃ የመጨረሻ ጫፍ ላይ ደርሰናል።
በመሆኑም ካሁን በፊት ብዙ የፖለቲካ ሰዎች እንደ አስጠነቀቁት የወያኔ ሰርዓት ማብቅያ ህዝቦችን እርስበርስ በማጋጨት ኢትዮጲያን መበተን እንደሚሆን የብዙዎች እምነት ነው።
ይህም አሁኑኑ ወያኔ አንዱ ብሔር የአንዱን ብሔር የመብት ትግል የሚቃወም አድሪጎ የማቅረብ፣ አስገድዶ ሰልፍ ማስድረግ ጀምሯል።
እኔ እንደ ሚመስለኝ ወያኔ ከትግራይ ባሻገር ደጋፊ እንዳለው የማስመሰል የከሸፈ አካሄድ ነው።
የአፋር ህዝብ በፉጹም ወያኔ ሊሆን አይችልም።
የሚገርመው አፋርን በመወከል ስልፍን የሚያስተባብሩት ትግረዎች መሆናቸው ነው።
የሎግያ ከተማ ውስጥ ስንት አፋር ይኖራል ?
ሎግያ የአፋር ከተማ ብትሆንም የአፋር ነዋሪዎችን በማፈናቀል ከጫፍ እስከ ጫፍ የትግራይ ቡና ቤት፣ አክሱም ቡቲክ፣ ምናምን በማለት ከተወረረች ቆይተናል።
ታዲያ እንዴት ነው የራሱን ከተማ የተነጠቀውን ህዝብ ነጣቂውን አንባገነን ዘረኛን በመደገፍ ሰልፍ የሚወጣው ?
ይህን አይነት የወያኔ የክሸፈ ፕሮፓጋንዳ ኢትዮጲያዊያን ይጋጫሉ የሚል ስጋት ባይኖረኝም ምናልባት አፋር ወያኔ ነው እንዴ ? ብሎ የሚጠይቅ ካለ የአፋር ህዝብ የጭቁኑ ኢትዮጲያ ህዝብ አካል እንጂ የማነኛውም ኢትዮጲያዊ የመብት ትግልን አይቃወምም።
ወያኔ ከፊት ለፊት የሚታየንን ነጻነት ላይ እንዳንደርስ ቀስቱን ወደ ሌላ አቅጣጫ እያዞልን መሆኑን ተርድተን ወደ ፊት ወደ ፊት እንግፋ
ወደ ፊት ከሄድን አፋሩም ሶማሌም፣ ጋምቤላም፣ ሓረረም፣ ሌላ ሌላም ማንም ነጻነት ያልጠማው ኢትዮጲያዊ የለም።
ብቻ ወደ ፊት ነጻነት እስከገኝ የለም ወደ ኋላ!!!!
 
አካደር ኢብራሂም ( አኩ አፋር )

የእድገቱ ጉዳይ -እድገት ከነጻነት አይለይም–አክሎግ ቢራራ (ዶር)

$
0
0

Dr Aklog Biraraየቀለም ቀንድ ጥያቄ ባለሁለት አሃዝ እድገት አለ ሲባል ዋናዎቹ መስፈርቶች ምንድን ናቸው እና እንዲት? ለምሳሌ፤ አሁንም አገራችን የአንድ ወቅት ዝናብ ሲቋረጥ ከፍተኛ ችግር መድረሱንና ለጋሾችን መለመናችንን አላቆምንም፡፡ ለመሆኑ ይህ ለብዙዎቻችን ግልጽ ሊሆን ያልቻለ ተቃርኖ እንዴት ነው የሚገለጸው? ሌሎች አገሮች ከተፈጥሮ የሚከሰት ረሃብን እንዴት ተወጡት፤ እኛስ እንዴት ልንወጣው እንችላለን? ምሳሌዎች አሉ፤ እነማን? –[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ] —–

በቃለት መንግስት? –ሰለሞን ለታ

$
0
0

Woyanes shoud face justice አንድ የኦርቶዶክስ የእምነት አባት የነገሩኘን ሰለኢሀዲግ መንግስት አወዳደቅ ምን እንደሚመስል ላካፍላችሁ። እርሳቸው በሊቀ ትጉሃን ማእረግ  የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ናቸው::  የተገናኘንበት አጋጣሚ  1996 EC ክረምት ወር ላይ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ በባህርዳር ከተማ በኦርቶዶክስና ወንጌላዊያን ከርስቲያናት መካከል የነበረውን ግንኙነት ለማጥናት ሂጀ በነበረበት ወቅት ነወ:: ረጅም ዘመን ያስቆጠረ በግምት 500 ገጽ አካባቢ የሚሆን ትልቅ መጽሃፍችውን  ይዘው ወደኔ ቀረቡና ልጀ ይህ መንግስት ሊውድቅ የሚችልበት ሚስጥር እዚህ መጽሃፍ ውስጥ ይገኛል አሉኝ። እኔም በመገረም  የሚሉኝን ለመስማት ጓጓሁ። ከዛም ትረካቸውን እንዲህ ጀመሩ።

“አንበሳው  በ ጂቡ ይበላል።ጂቡ ደግሞ በተኩላዎች ይበላል። ተኩላዎች በጉንዳኖች ይበላሉ”  የሚለውን ክፍል አነበቡልኝ። ታዲያ ይሔ ምንድን ነው አልኳችው።ሚስጥሩ ወዲህ ነው ።አንበሳው ሞአንበሳ ዘእመነገደ ይሁዳ ተብሎ ለርጂም ዘመናት በሀገራችን የሰፈነው ዘውዳዊው አገዛዝ ነው። እርሱ በጂቡ በደረግ በ1974 EC  ተበላ። ቀጥሎ እነዚህ የምታያችው ገዥዎች እንድተኩላ በየገደላገደሉ  ተሺሎክልከው ለነጻነት ታግለው  ጂቡን በሉት። ነገር ግን አላማቸውን የዘነጉ መርዛማ ፍሬ ያላቸው ቡድንተኞች ስለሆኑ  በጉንዳን በተመሰለው በሰፊው ህዝብ የብረት ክንድ ይደመሰሳሉ አሉኚ። በዎቅቱ እንደተረት መጽሃፍ ቆጥሬው የነበረ ሲሆን ባመቱ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ መንግስት ሲገጥመው ርሳቸው የንገሩኚን አስታውሸ ኢሃዴግ ኣበቃለት ብየ ነበር፥፥

ነገር ግን ዛሬ መንግስት ፩፪ ኣመት ሁኖታል፥፥ርሳቸው መጽሀፉ ውስጥ ሌሎች ማብራሪያዎችን ዕያነበቡ ስለመንግስቱ ባሀሪ ነገሩኝ፥፥ ህዝቡ ላይ እንደመዥገር ተጣብቆ ደም የሚመጥ ስርኣት ስለሚሆን ሲነቀልም ያደማል ብለውኚ ነበር ::አዎዳደቁ ድንገተኛ ነው:: ልክ ከባህር የዎጣ አውሎ ንፋስ ቤት ና ዛፍ  ዕንደሚገነጣጥለው ህዝብ የስርአቱን መሰረት ያፈራርሰዋል  ይጥለዋል አሉኝ:: መቼ እንደሚሆን አብረን እናያለን::

ቅኝ ተገዥነቱን ያወቀ ሕዝብ  በከፊል ነፃ ነው! –ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት            

$
0
0

 ሐሙስ ነሐሴ ፭ ቀን ፪ሺህ፰  ዓ.ም.              ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፳፩

Moresh-901.jpgየኢትዮጵያ ሕዝብ በትግሬ ወያኔ ቅኝ ተገዥ ከሆነ ድፍን 25 ዓመት ሆነው። በእነዚህ ረጅም ዓመታት፣ የተማሩትም ሆነ ያልተማሩት ዜጎች፣ በቅኝ ተገዥነት መያዛቸውን ያወቁትም ሆነ ለማወቅ የጣሩት በጣም ጥቂቶች ናቸው። እነዚህ በቅኝ ተገዥነት ተይዘናል ያሉት የጥቂቶቹ ድምፅ፣ በብዙኃኑ፣ ከሁሉም በላይ በጎሣ ፖለቲከኞቹ ድምፅ ተውጦ፣ ወያኔ፣ ያላንዳች ሀግ ባይ፣ ሩብ ምዕተ ዓመታት  የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅምና ሉዓላዊነት በእጅጉ የጎዱ ሥራዎችን እንዲሠራ ሠፊ ዕድል ሰጠው። በመሆኑም የኢትዮጵያዊነት አያያዥ ማገርና ወራጅ፣ መሠረትና ጭምጭም የነበሩትን፣ የኢትዮጵያዊነት ዕሴቶቻችን ከሥራቸው ነቀላቸው። ሕዝቡን በነገድ ከፋፍሎ እሣትና ጭድ አደረጋቸው። የኢትዮጵያ ነገዶች ሙጫ በመሆን ከሌሎች ነገዶችና ጎሣዎች ጋር ሰምና ፈትል ሆኖ፣ ኢትዮጵያዊነትን ሲገነባ የኖረውን የዐማራ ነገድ፣ በዘር ጠላትነት ፈርጆ፣ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ፈጸመበት። አምስት ሚሊዮን ዐማራ ከምድረ ኢትዮጵያ እንዲጠፋ ተደረገ። በወለጋ፣ በኢሉባቡር፣ በከፋ፣ በሐረርጌ፣ በጎጃምና በጎንደር ይኖሩ የነበሩትን ዐማሮች በግፍ ሀብት ንብረታቸውን ነጥቀው ለርሃብ፣ ለድህነትና ለአገር አልባነት አሳልፎ ሰጣቸው። ይህ ዓለም በዝምታ እየተመለከተው ያለው የዘር ጥቃት፣ ዛሬ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት ዐማሮች የቅኝ አገዛዙን ሰንሰለት በጣጥሰው፣ ፍፁም ነፃ የሆነ ዐማራዊ ማንነታቸውን አረጋግጠው፣ የኢትዮጵያን ትንሣዔ ለማብሰር ከአፋኙ የወያኔ የስለላና የአፈና መዋቅር ኃይል ጋር የሞት ሽረት ትግል እያደረጉ ይገኛሉ።

የዐማራው ነገድ ዛሬ በትግሬ ወያኔ ቅኝ ተገዥ መሆኑን ከማወቅ አልፎ፣ ለነፃነቱ ቆርጦ የሕይዎት መስዋዕትነት እየከፈለ ነው። በዚህ የሞት ሽረት ትግል ውስጥ፣ እስካሁን በጎንደር ከተማ፣ አዘዞ፣ ቆላድባ፣ አርማጭሆ፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣ ወልቃይት፣ ጋይንት፣ ደብረታቦር፣ ባሕር ዳር ወዘተርፈ ቁጥራቸው ገና በውል ያላወቅናቸው አያሌ ወንድምና እህቶቻችን ባልሞ ተኳሾች የጥይት አረር ወድቀዋል። በርካቶቹ በወያኔ እስር ቤቶች የመከራን ጽዋ እየተቀበሉ ነው። ዐማራውን ለዚህ ግፍ ያበቁት በወያኔ የመከላከያ፣ የፖሊስና የፀጥታ ሠራቶች የተቀጠሩ ብቻ ሳይሆኑ፣ ከሕዝቡ ጋር የሚኖሩት በየኮንዶሚኒየሙ በሰፈራነት የተሰገሰጉት ትግሬዎች መሆናቸውን ስንገነዘብ፣ «ለካ እስከ ዛሬ በጉርብትናም ሆነ በጋብቻ ከእነዚህ ሰዎች ጋር የፈጠርነው ግንኙነት፣ እኛን ለማጥቂያ ውስጣችንን ገልጠው እንዲያዩን ሁኔታዎችን ያመቻቸ ነው፤» ብለን እንድናስብ አስገድደውናል።

ባሕር ዳር እና ጎንደር በጥይት ለተቀጠፉት ሰዎች ገዳዮቹና አስገዳዮቹ በከተሞቹ ነዋሪ የሆኑት የወያኔ የውስጥ አርበኛ ትግሬዎች መሆናቸውን በተጨባጭ አረጋግጠናል። ይህም «ወያኔን እና ትግሬን ለዩ» ለሚሉ የዋሕ ፖለቲከኞችና የሰብአዊ መብት ጠበቆች ነን ለሚሉ ሁሉ የሚያራምዱት ሀሳብ መሠረት የሌለው መሆኑን አሳይቷል። ሕዝብን በሙሉ የክፋት ሥራ ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ አይደለም የሚባለው፣ ሕዝቡ የጥፋት ተባባሪ አይደለም ከሚል መነሻ ሳይሆን፣ ሕዝብን በሕዝብነቱ መወንጀልም ሆነ ለጥፋቱ ተጠያቂ ማድረግ ለችግሮቹ ዘላቂ መፍትሔ አያስገኝም ከሚል መነሻ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። ዛሬ የትግራይ ሕዝብ በወያኔ አገዛዝ ተጠቃሚ መሆኑ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም። ሌላውን ቁሣዊና ለወዲፊቷ ትግራይ ልማትና ዕድገት የተሠሩትን መጠነ ሠፊ ሥራዎች ትተን፣ በአገዛዙ ባለሥልጣኖች እንደ ዐማራውና ኦሮሞው አይጠረጠሩም፣ አይፈተሹም፣ በሥራቸው የመረጃ ታኮ አይለጠፍባቸውም፣ የመሥራትና የመንቀሳቀስ መብታቸው የተገደበ አይደለም፤ የፈለጉትን  ሠርተውና ተናግረው በሰላም ተኝተው ያድራሉ። ይህ ጥቅም አይደለም የሚል ካለ፣ ይህን መብት ያጡት የዐማራ ልጆች ጥቅሙ ከቁሣዊ አልፎ የኅልውና እና የነፃነት ዋጋ ያለው መሆኑን እየከፈሉት ባለው የደምና የሕይዎት ዋጋ ሊማር ይገባዋል።

ከሁሉም በላይ፣ የትግራይ ሕዝብ፣ ልጆቹ የሁሉም ነገር አድራጊና ፈጣሪዎች መሆናቸውን ስለሚያውቅ፣ በልጆቹ ድርጊት ይመካል። ከመመካትም አልፎ እየኮራ ሌሎችን ሲያዋርድ እያየን ነው። ይህም ለአጉል ትዕቢት ዳርጎት ሌሎችን «ሽንታም፣ ፈሪ» በማለት  በየምርመራ ጣቢያውና በየፓልቶክ ክፍሉ የምንሰማው የዕለት ተዕለት ስድባቸው ነው። ይህ ድርጊት የሌሎችን ነገድ ልጆች አዕምሮ አያነቁርም፣ ደም አያፈላም፣ አያስቆጭም የሚል ካለ «ግሞ ሲሉህ፣ ጥንቦ በለው» ተብሎ ያላደገ የማንነት መገለጫ ዕሴት የሌለው፣ የተዋራጅ ሕዝብ ባህል ብቻ ነው። በመሆኑ፣ ከ25 ዓመታት ትዕግሥትና የአብሮነት ፍላጎት በመነጨ፣ ዐማራው ወያኔ የጣለበትን ዕዳ፣ ያሸከመውን የመከራ ቀንበር ተሸክሞ መቆየቱ ግልጽ ነው።

የዐማራው ሕዝብ ዛሬ ግን ከመከራ አልፎ፣ ማንነቱን በመነጠቁ «አሻፈረኝ፣ መከራው በዛብኝ፣ ሸክሙ ከምችለው በላይ ሆነብኝ፣ ግፉ ከአናት በላይ ወጣ፣» ብሎ ማንነቱን ለማስከበርና ነፃነቱን ሙሉ በሙሉ ለማስመለስ ከአፋኙ የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ሠራዊት ፊት ለፊት በባዶ እጁ እየተጋፈጠ ይገኛል። ይህም ዐማራው በቅኝ ቅዛት መያዙን ከማወቅ አልፎ፣ ለነፃነቱ ቁርጠኛ ውሣኔ ላይ የደረሰ መሆኑን ያሳያል። ካልቆረጡ ከግብ አይደረስምና! በዚህ ረገድ የቁርጠኝነቱን ጉዞ፤ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በከፈተው የጀግንነት ድርጊት፣ ለዐማራው ወጣት አርአያነቱን አሳይቷል። ዐማራው ማንነቱን አስጠብቆ የኢትዮጵያ ትንሣዔ አብሳሪ የሚሆነውም በዚህ መንገድ ብቻ መሆኑን የትግሬ-ወያኔ ባሕሪ አስተምሮናል። ስለዚህ ትግሉ፣ መስዋዕትነትን ቀንሶ፣ ባጭር ጊዜ ውስጥ የድሉ ባለቤት የሚሆንበትን መንገድ መከተል ብልኅነት ብቻ ሳይሆን፣ አዋቂነትም ነው።

ለዚህም የሚረዳው፣ በየቀበሌውና ወረዳው የጎበዝ አለቆችን በመምረጥ የተደራጁ ቡድኖችን መፍጠር ሲቻለው ነው። በየደረጃው የተመረጡ የጎበዝ አለቆች በተመሳሳይ መልክ ከሚደራጁ አቻዎቻቸው ጋር ተያያዥና ተጋጋዥ የሆኑ ሥራዎችን ለመሥራት ሁኔታዎች በፈቀዱት መጠን የግንኙነት ሰንሰለት መፍጠር እጅግ አስፈላጊና ጠቃሚም ነው። ይህ ግንኙነት በአስተማማኝ ሁኔታ ከተመሠረተ በኋላ፣ የወያኔን የስለላና የአፈና መዋቅር ኃይል ለማሳሳት፣ የገንዘብ አቅሙን ለማዳከም፣ በተለያዩ ቦታዎች የሕዝባዊ እንቢተኝነቱ እንቅስቃሴን፥ ሰልፍና የመሳሰሉን፣ ማካሄድ። ለትግሬ-ወያኔ አፋኝ ኃይል፣ የኃይል ምንጭ፣ የሥንቅና የትጥቅ አቅርቦት ክምችት ያለባቸውን ቦታዎች በማጥናት ድንገተኛ ወረራ በማድረግ የሕዝብ ማድረግ የግድ ይላል። ይህ ሁሉ ሲሆን፣ አመራሩ ከውስጥ ከሕዝቡ መሀል ያሉ፣ የንቅናቄው ተሳታፊዎች አምነው የመረጧቸውን እንጂ፣ ከርቀት «መንፈስ ነን» የሚሉ የአየር በአየር የፖለቲካ ሰዎች ነን ከሚሉት ጋር እንቅስቃሴው እንዳይያያዝ ጥንቃቄ መደረግ አለበት። «የአህያ ባል ከጅብ አያድንም» እና በዚህ ረገድ ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው። ወያኔ እንኳን ሰበብ አገኝቶ፣ ራሱ ወንጀል ፈብርኮ፣ ሰዎችን ማሰር መግደሉ ይታወቃልና፣ ከውጭ ሆነው የሚፎክሩ ድርጅቶች፣ ለሕዝቡ መመቻ፣ መረጃ እየሰጡ ናቸውና በወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ባለቤቱ ዐማራው ራሱ እንጂ፣ ሌሎች አለመሆናቸውን በግልጽ ሊያውቁት ይገባል።

በመሆኑም የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ የመላው ዐማራ ጥያቄ በመሆኑ፣ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የወሎ፣ የሸዋ፣ የሐረርጌ፣ የአዲስ አበባ፣ የወለጋ፣ የአርሲ፣ የከፋ፣ የጋሞጎፋ፣ የሲዳሞ፣ የባሌ እንዲሁም በዓለም ላይ በስደት የሚኖረው ዐማራ የትግሉ አካል እንዲሆን፣ የንቅናቄው አስኳል የሆነው የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ የመሪነቱን ቦታ በመያዝ፣ ሕዝቡን መድረስ ይጠበቅበታል። ከሁሉም በላይ የእንቅስቃሴው ባለቤቶች «እኛ ነን፣ እኔ ነኝ» ለሚሉ ወገኖች አቅማቸውንና ቁርጣቸውን እንዲያውቁ፣ የንቅናቄውን ዕለታዊና ሳምንታዊ ዘገባዎች ለዓለም ማኅበረሰብ የሚሰማ፣ ሕዝቡ የሚፈልገውን ርዳታ ተቀብሎ በትግሉ ውስጥ ላሉት አመራሮች ማስረክብ የሚችል ታማኝ ግለሰብ ወይም ቡድን ካለ እርሱን፣ ከሌለ በፍጥነት ተሰይሞ፣ ሕዝቡ እንዲያውቀው ቢደረግ ውንዥንብሩን ያጠራዋል፤ የሰከነ ሥራም ለመሥራት ያስችላል ብለን እናምናለን።

ሌለው፣ ንቅናቄው ሊመራባቸው የሚገቡ ቋሚ መፈክሮች ያሹታል። መፍክሮቹን ማንም እንደፈለገ እንዳይለጥጣቸው ከወልቃይት ጠገዴና ከዐማራ ማንነት ጋር የተያያዙ፣ ይህንም ባጭሩ መልዕክት የሚያስተላልፉ ሊዘጋጁ ይገባል እንላለን። ይህ ሲሆን ጎንደር ላይ የተቀጣጠለው የዐማራ የማንነት ጥያቄ፣ ቅኝ ገዥውን ቡድን ድባቅ መትቶ፣ ዐማራው ማንነቱናና ኅልውናውን አስጠብቆ፣ የኢትዮጵያን ነፃነት ዕውን ለማድረግ የበኩሉን አስተዋፅዖ ያደርጋል ብለን እናምናለን። በዛሬዪቱ ኢትዮጵያ የዕውቀትም ሆነ የሀብት ባለቤቶች እነርሱ መሆናቸው ስለሚታወቅ፣ በዚህ ነፃነት ከማንም ይልቅ ተጠቃሚዎቹ ትግሬዎች ይሆናሉ። ስለዚህ በነገይቱ ኢትዮጵያ ትግሬዎች ያላቸውን ዕውቀትና ሀብት በሥራ ላይ አውለው በነፃነት ለመጠቀም፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ ነፃ መውጣቱ ፍቱን አብነት ነው። ለዚህም ከጠፊው የወያኔ ቡድን ጋር ሳይሆን፣ ከዘላለማዊው የኢትዮጵያ ሕዝብ እና ከታሪክ ጋር መቆም ይጠበቅባችኋል።

ወያኔ ለትግሬም ሆነ ለኢትዮጵያ አጥፊ እንጂ፣ አልሚ አይደለም። የትግራይ ተወላጆች፣ በጊዜአዊ ሥልጣንና ጥቅም ተገብዛችሁ ሊሆን ይችላል፤ ይህ ግን ዘላቂ አይደለም። ከዘላቂ ጥቅም፣ ክብር፣ ማንነትና ከሠፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እንድትቆሙ ጥሪያችን እናቀርባለን።

 

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

የዐማራነት ማንነት በትግላችን ያብባል!

ዐማራነት ነፃነትና ዕኩልነት ነው!                                        

ዐማራነት ፍትሕና ኢትዮጵያያዊነት፣ ጀግንነትና መስዋዕትነት ነው!

ጤና ካልሰጠ አይደለም ጣት እጅም ሆነ እግር ከመባቀያው ላይ ተቆርጦ ሊጣል ይችላል:: (ከይገርማል)

$
0
0

Oromo amhara unityከወያኔ በፊት በነበሩት ጊዜያት ፖሊስ በሰወች መሀከል ምንም ልዩነት ሳያደርግ የመንግስትን ትእዛዝ ለማስፈጸም ይንቀሳቀስ ስለነበር “የፖሊስ ዘመድ የቤንዚን አመድ የለውም” ይባል ነበር:: ይህ የሚያሳየን ፖሊስ “እናት; አባት: እህት: ወንድም: ልጅ: – – -ሳይል በህግ የሚፈለጉትን ለህግ በማቅረብ ለየትኛውም ወገን ህገወጥ ከለላ ሳይሰጥ ሁሉንም ህዝብ በእኩል አይን አይቶ ግዳጁን ይፈጽም ስለነበረ ነው:: በዚህም ምክንያት ፖሊሱ ልጀ: ወንድሜ: አጎቴ – – – ያድነኛል የማይባልበት ጊዜ ስለነበር “የፖሊስ ዘመድ የቤንዚን አመድ የለውም” ይባል ነበር::

 

የዛሬው አባባል ግን ተቀይሯል:: አሁን ላይ እያየነው ያለነው የፖሊስ ዘመድ: የፖሊስ ወዳጅ መኖሩን ነው:: ለዚህም ዋናው ምክንያት የወያኔው መንግስት ዘረኛ አስተዳደር የፈጠረው የገዥ ብሄርና የተገዥ ብሄሮች መከሰት ነው:: በአሁኑ ወቅት ያለው ተጨባጭ እውነታ የሚያሳየው ተጠቃሚ የትግሬ ብሄርና ተጎጅ የአማራ: የኦሮሞ: የጋንቤላ: የደቡብ: – – – ብሄር ብሄረሰቦች መኖራቸውን ነው:: በዚህም የተነሳ ትግሬ የተባለ ሁሉ ጥቅሜን እያስከበረልኝ ነው የሚለውን ዘረኛ መንግስት በብቸኝነት ደግፎ በጽናት ቆሟል:: ይህን አጉራ-ዘለል የትግሬ ወያኔ ተግባር ያየ የአማራ ፖሊስና ታጣቂ ሀይል በበኩሉ ወገኑን ከጥቃት ለመከላከል ጠበንጃውን ወደወያኔ አዙሮ ወድሯል::

 

አማራው ወገኖቸ ናቸው ብሎ ባጎረሳቸው: ባለበሳቸው: መኖሪያውን አጣቦ መጠጊያ በሆናቸው: ቁስላቸውን ባከማቸውና እንባቸውን በጠረገላቸው ትግሬወች ያጎረሰበት እጁ ተነክሶ: መሬቱን ተነጥቆ: ከለበሳት ጨርቅ ውጭ አንድም ነገር ሳያንጠለጥል ተሳዶ: በየአካባቢው ታርዶ በደምና በእንባ እንዲታጠብ ተደርጓል:: የአማራን ህዝብ አፍነው መሬቱን እንደያዙ ለማስቀረት “በወልቃይት የመጣ በአይናችን የመጣ ነው:: አማሮች አርፋችሁ ተቀመጡ: አለዚያ ዋ!” ብለው አሮጊቶች ሳይቀሩ ጠበንጃ ይዘው በሰልፍ ሲያስፈራሩ ታይተዋል:: በየክልሎች የሚኖሩ ትግሬወች በወያኔ አስተዳደር ላይ ልቡ የሸፈተውን ብቻ ሳይሆን ቀልባቸው ያልወደደውን ጭምር እየጠቆሙ ለሞትና ለእስር ዳርገውታል: በውጭ ሀገር የሚኖሩት ትግሬወች ተሰባስበው ወያኔ በኢትዮጵያውያን ላይ በፈጸመው ግድያና እስር ተደስተው እያሞገሱ ጨፍረዋል – በስለላ: በሀሳብ: በገንዘብና በቁሳቁስ ደግፈው ቆመዋል:: ታዲያ ይህንን ጉደኛ አስተዳደር ለመደገፍ የወያነን ትእዛዝ ተቀብሎ በወገኖቹ ላይ የሚተኩስ ፖሊስ ይኖራል? ለዚህም ነው “የፖሊስ ዘመድ የቤንዚን አመድ የለውም” የሚለው “የትግሬ ዘመድ ትግሬ: የወያኔ ገረድ …ዴንና …”ዴድ”” መባል ያለበት::

 

በብአዴን ውስጥ ያላችሁ ወያኔ ጠል: አማራ ወዳድ የሆናችሁ ሰዎች የህዝብን ትግል አኮላሽተው የወያኔን ግፈኛ ስርአት ለማስቀጠል እየሰሩ ያሉትን አባላት በቁጥጥር ስር አውላችሁ ለዞንና ለወረዳወች የተጠንቀቅ መመሪያ አስተላልፉ:: ይህን ለማድረግ ስልጣናችሁን ተጠቅማችሁ የራሳችሁ ታማኝ ፖሊስ ወይም ታጣቂ ሀይል በማሰማራት የወያኔ ሰላዮችንና እምነት የማይጣልባቸውን ሰዎች ትጥቅ አስፈትቶ በቁጥጥር ስር በማዋል መሆን አለበት:: ይህ እርምጃ በያንዳንዱ ዞንና ወረዳ እንዲተገበር መመሪያ ማስተላለፍ ይኖርባችኋል::

 

በአማራ ክልል የሚኖሩትን ትግሬወች አሰባስባችሁ በየካምፖች እንዲጠበቁ አድርጉ:: ይህን ማድረጋችሁ ሁለት ጥቅም ይኖረዋል:: አንደኛው ወያኔ በየአካባቢው የሚደረገውን እንቅስቃሴ እንዳያውቅ የመረጃ ምንጩን ማድረቅ ማስቻሉ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በጥቃት ስሜት እየተብከነከነ ያለው አማራ በትግሬወች ላይ እርምጃ እንዳይወስድ ለመከላከል ስለሚበጅ ነው::

ሲፈጥረኝ አሳቢ ለምን አልጨነቅ ማስተዋል ላቃተው የኔቢጤ ገልቱ:

እንዳያር እንዳይከስል ባላዋቂ ቆስቋሽ ማሰብ በተሳነው-

እንደገና ዳቦ በታች በላይ እሳት በመሀል ግለቱ::

 

በአማራ ክልል የሚገኙትን የወያኔ ሰራዊትና ፖሊስ አባላት ትጥቅ ማስፈታት የሚከብድ አይሆንም: በውቅያኖስ ውስጥ ያረፈ ጠብታ መርዝ አንድም አሳ ሊገድል አቅሙ አይኖረውም:: እንዲያውም ወያኔን እያጫወቱ ወደመሀል አማራ በመሳብ ትጥቅ ማስፈታቱን መልመድ ይጠቅማችኋል:: በትግራይ – ሽሬ መሽጎ የነበረው የደርግ ሰራዊት የተመታው በወያኔ ሀይል ብቻ ሳይሆን በህዝቡም ርብርብ ነበር:: እናንተ “በአማራው ላይ እየደረሰ ያለው ዘርፈ-ብዙ ግፍ ያብቃ!” ብላችሁ ስትፈክሩ የሰማ አማራ ብቻ ሳይሆን ዋልያና ቀይ ቀበሮም በደስታ ይቦርቃሉ:: ልብ በሉ! በታሪክ ከትግራይ ያገኘነው አንድም ጥሩ ነገር የለም:: ያገኘነው ነገር ቢኖር ዘረኝነትንና ክፍፍልን: ተንኮልንና ውሸትን: ረሀብንና ኤድስን: አድርባይነትንና መሸማቀቅን ነው:: አዎ በሽታውም የመጣው በወያኔ ግዜ: ረሀቡ የጸናብን በወያኔ ጊዜ: ባህልና ታሪካችን የረከሰ በወያኔ ጊዜ: ለዘር ተኮር ግድያና ስደት የተዳረግነው በወያኔ ጊዜ ነው::

 

ፍልፈሉ ሳሞራ የኑስ እንደነገሩን “ወያኔ ማለት ትግሬ: ትግሬ ማለት ደግሞ ወያኔ ማለት ነው”::  መጀመሪያ ስልጣን ሳይዙ ከበረሀ ሆነው የሚያስተላልፉትን ቅስቀሳ ሰምተን ቢሆን ኖሮ ለዚህ ሁሉ ብሄራዊ ኪሳራ ባልተዳረግን ነበር:: ያኔ በረሀ እያሉ አማራ ብሄራዊ ጠላታቸው እንደሆነ: መሬት የመንግስት እንደሚሆን: ኢትዮጵያ በብሔረሰቦች እንደምትከፋፈልና መገንጠል የሚፈልግ ብሄር መብቱ በህገመንግስት እንደሚከበርለት ነግረውን ነበር:: አሁንም እየነገሩን ነው “ትግሬ ማለት ወያኔ ነው: ወያኔ ማለትም ትግሬ ነው::  ብለው:: ይህን መስማት አቅቶን “ወያኔንና ትግሬን እንለይ” እያልን የምናዜም ከሆነ ችግሩ የማንም ሳይሆን የራሳችን ይሆናል::

 

ጎጃሞች የተፈጥሮ ምሽጋችሁ የሆነውን አባይ ተጠቀሙበት:: ከጎጃም ወደሌሎች አካባቢወች የሚያስወጡና የሚያስገቡ መተላለፊያወችን ከዘጋችሁ ወያኔ መግቢያ ቀዳዳ አይኖረውም:: በመተከል የምትኖሩ አማሮች ተደራጅታችሁ ራሳችሁን መከላከል ብቻ ሳይሆን ህዝቡን አስተባብራችሁ ከራሳችሁ አልፋችሁ በወያኔ ላይ የሚደረገውን ትግል ለመደገፍ ተንቀሳቀሱ:: ፓዊን ብሎም መተከልን በቁጥጥር ስር ለማዋል ለሆድ ህመም ተብሎ የሚጠጣ የግራዋ ጭማቂን ያህል የሚመር-የሚከብድ አይሆንም::

 

አንድ ማመን ያለብን ነገር አለ: ካለመስዋእትነት ድል እንደማይኖር:: ስለዚህ አካላዊ ብቻ ሳይሆን ዐዕምሯዊ ዝግጅት ሊደረግ ግድ ነው:: አንድ ሰው በሞተ ቁጥር ትግሉ የበለጠ እየከረረና እየሰፋ መሄድ ይኖርበታል:: ከፊት የቆሙትን ወገኖቻችንን አስቀጥፈን የምናፈገፍግ የአንድ ሰሞን የአጓት ጥጋበኞች ልንሆን አይገባም:: ደም የሚከፈለው ለስር-ነቀል ለውጥ እንጅ ለጥገናዊ-ለውጥ መሆን የለበትም:: ይህን ትግል ለማክሸፍ የሚሞክር ዘመድ ቢኖር ከጠላት ጋር ተደርቦ ሊመታ ይገባል:: “ጣት ገማ ተብሎ ተቆርጦ አይጣልም” የሚባለው ብሂል ጊዜ ያለፈበት ኋላ-ቀር አመለካከት ነው:: ጤና ካልሰጠ አይደለም ጣት እጅም ሆነ እግር ከመባቀያው ላይ ተቆርጦ ሊጣል ይችላል::

 

ትንሳኤ ለኢትዮጵያ!

ከታሪክ መዝገብ- ለመሆኑ አማራ ማነው –ኀይሌ ላሬቦ

$
0
0

ከጎራ ፈርዳ የተባረሩ አማሮች


ዛሬ በሥልጣን ላይ ያለው የወያኔ መንግሥት ዐማራ በተባለው ኅብረተ-ሰብ ላይ ብዙ ግፍና ዐመፅ እንደፈጸመና እንዳስፈጸመ በገፍ ይነገራል። በኅብረተሰቡ ላይ ተፈጸሙ ከተባሉት ድርጊቶች አብዛኞቹ በሥዕል የተቀረጹ፣ ለሰው መብት በቆሙ ባስተማማኝ ብሔራዊና ዓለም-ዐቀፍ ድርጅቶች ከነማስረጃቸው የተጠናቀሩ፣ እሙን በሆኑ ያይን ምስክሮች የተደገፉ ስለሆኑ ማስተባበሉ ከመደናቈርና የአትኳራ ግብግብ ከመግጠም ውጭ ሌላ ፋይዳ ያለው አይመስለኝም። የግፎቹ ኢሰብኣዊነትና የፈጻሚዎቻቸውም አውሬነት ለሚሰማ ሁሉ ከመዘግነን አልፎ፣ ሰው ሁኖ መፈጠሩን ራሱን የሚያስጠላ ከመሆኑ የተነሣ፣ ልቦና ያለው ተመልካቺም ሆነ ሰሚ፣ መንግሥት ነን ባዮቹ የወያኔ ገዢዎች በጀርመንና በኢጣሊያን ምድር ከታዩት ከናዚና ከፋሽስት መንግሥታት መሪዎች በምን ይለያሉ ብሎ ለመጠየቅ ይገደዳል።

 

በበኩሌ ጥላቻው ከየት መጣ ብዬ አውጥቼ አውርጄ ማሰላሰል ከጀመርሁ ዓመታት ቈጥራለሁ። ዕድል ቀንቶኝ ከብዙ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጋር ኑሬአለሁ፤ አድጌአለሁም። ስለዚህ ፍንጭ ይሰጠኝ ይሆናል ስል ወደልጅነት ሕይወቴ ወደኋላ ተመልሼ በዐይነ-መነጽሬ ሳይና ሳሰላስል፡ ሁሌዬ ተመላልሰው እፊቴ የሚደቀኑብኝ ሁለት ገጠመኞች ናቸው። አንደኛው በሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን ከሚትባል ከተማ በሠላሳ ኪሎሜትር ያህል ርቀት የሚገኝ መንዲዳ የተባለ መንደር አለ። ባንድ የኢጣሊያን መሐንዲስ ለሕንፃ ሥራ ተቀጥረው ከሰሜን የመጡ ሠራተኞች ባካባቢው ዘመናዊ ምግብ ቤት ስለሌለ፣ ሁሌዬ የሚበሉት ከተማሪዎቹ ጋር አብረው ነበር። የቀረውን ምግብ ሁሉ በልተው፣ ጠላዉን ብቻ መተው ለማዳቸው ሁኖ ስለነበር፣ አስተናጋጁ ገርሞት አንድ ቀን ምክንያቱን ሲጠይቃቸው አላንዳች ማፈር “ዐማሮች ናችሁ አሉን፤ ዐማራ ቅጥኝ አለውና እንዳይተላለፍባችሁ ምንም ዐይነት መጠጥ ቢሰጣችሁ እንዳትጠጡ ተብለን ስለተመከርን ፈርተን ነን” ብለው በጨዋነት መልስ ሰጡ። ሌላው በአሥመራ ከተማ በአንዳንድ አስተማሪዎች አነሣሽነት፣ ተማሪዎቹ እነዚህን ዐማሮች አታናግሯቸው ተብለው ስለተመከሩ፣ ከደቡብ የመጣነው በመጀመርያው ዓመት ምንም ብንጥር ጓደኛ  ማፍራት ከባድ ነበር። እምብዛም ባይሆን ጥቂት ከምንቀርባቸው ጋር ችግሩ ምን እንደሆነ ለማወቅ ተሰባሰብን። መልሱ እውነትም ‘ዐማሮች’ ስለሆነን እንደነበር ለማወው ብዙም አልፈጀንም። ከሁሉም የከፋብን ግን ዐማሮች አይደለንም ስንል፣ ቀጥሎ የመጣው ልውውጥ ነበር። “ዐማሮች ካልሆናችሁ፣ ታዲያ ጋላ ናችሁ እንዴ!” ተባልን። ለዚህም በአሉታ ስንመልስ፣ “ታዲያ ከጋላ በታች ሰው አለ እንዴ!” ሲሉን ክው አልን። እንግዴህ እነዚህ የልባቸውን የሚናገሩ ላቅመ አዳም እንኳን ያልደረሱ ልጆች ናቸው፤ በጭንቅላታቸው ውስጥ የሚያንሸራሽሩት አሳቦች ግን የአካባቢውን ስሜት የሚያንፀባርቁ ሊሆኑ አይችሉም ብዬ መከራከሩ የሚያዋጣ  ስለማይመስለኝ አልፈዋለሁ። ሁኖም የገጠመኙ ወቅት የወያኔ መሪዎች ልክ ወደጫካ ያመሩበት ጊዜ ስለነበር፣ የዛሬውን ሥራቸውን እያየሁ የለም እነሱ በዚህ ዐይነት አስተሳሰብ የተበረዙ ሰዎች አልነበሩም ብዬ ማሰቡ ያዳግተኛል። በአፍሪቃ ቅኝ ገዢዎችና በፋሽስቶች እጅ ባካባቢዎቻቸው ይካሄድ የነበረው ኀይለኛ ስብከት፣ በዐማራ ላይ ጥላቻ፣ በተቀረው የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ላይ ደግሞ ከፍተኛ ንቀት እንዳሳደረባቸው አይጠረጠርም ብል በሐሰት የምወነጀል መስሎ አይታየኝም።

 

በሁለተኛ ደረጃ መታወቅ ያለበት ወያኔዎች የቀዝቃዛ ጦርነት ፍጻሜው ውጤት መሆናቸው ነው። በዚህ ጦርነት ሕይወት ወቅት እንደመዥገርት የሕዝባቸውን ደም እየመጠጡ የደነደሱ መንግሥታት እምብዛም ሳይቈዩ ወዲያው ፈረጡ:: የሁለተኛው ዓለም መሪዎች ተራ በተራ ከሥልጣናቸው ሲወድቁ፣ ያልታደሉት ታረዱ፤ በለስ የቀናቸው ደግሞ ለፍርድ ቀርበው ሰለባቸው ከነበሩት ጋር ተፋጠጡ። በሦስተኛው ዓለም የሁለቱ ኀያላን ባላንጣዎች መንግሥታት ማለትም የአሜሪቃና የሶቭየት ኅብረት ቱኪዎቻቸው የነበሩት ገዚዎች ግን፣ እንደሁለተኛው ዓለሙ መሪዎች በያመዳቸው አልቀሩም። እንደኢትዮጵያው መንግሥቱ ኀይለማርያም፣ የሱማሌው ሲያድ ባሬና፣ የድሮዋ ዛይር የዛሬዋ ኮንጎ ሞቡቶ ሴሴኮ የመሳሰሉት፣ ያን ሁሉ የድሎታቸውና ያምባገነንታቸው ወቅት ድንፋታና ጉራ ረስተው ይሰብኩ ለነበሩት ለናት አገር ፍቅር እንደመቆም፣ ሁላቸውም ነፍሴ አውጭኝ እያሉ  በደንገለላ ሳይሆን በሽምጥ አፈረጠጡ። በጦርነቱ ድልና የበላይነት ያገኘችው አሜሪቃም በኢትዮጵያ ውስጥ መንግሥቱ ኀይለማርያምና ጀሌዎቹ እጣር ላይ መሆናቸውን ሲታይ፣ ዕድሉ ሳያመልጣት በራሷ ተላላኪዎች ሊትተካቸው እንደተሟሟተች፣ ከደርግ መንግሥት ፍጻሜ ዋዜማ በተደረገው በአስችኳይ ስብሰባ ላይ ጥርት ብሎ ይታያል። በስብሰባው፣ አሜሪቃ ሥልጣን ቋማጩቹን ገለልተኛ አገላጋይ መስላ ቢታደራደራቸውም፣ ኳሱንም ሜዳውንም ሙሉ በሙሉ በወያኔ እጅ እንደተወች ለመረዳት አብዛኛውን ተመልካች አያዳግትም ነበር ቢባል ሐቅ ይመስለኛል። ባሜሪቃና በዐረቦች ትብብር፣ የኅበረተሰባዊነትና የመደብ ጦርነት አንጋቢው ደርግ በመስኮት ሲሸመጥጥ፣ የጐጥና የጐሣ አንጋቾቹ ወያኔዎች በበር አድርገው ብቅ አሉ። በአንድ አስተዋይ ጓደኛዬ  አባባል፣ ጅሎቹ የሩሲያን አምባገነን ቡችሎች፣ ባሜሪቃ አፋኝ አደንዝዝ ማጅራት መቺዎች ተበሉ።

 

በጫካ ኑሮ ዘመናቸው ወያኔዎች የተራማጅነት ጨንበል እንዳጠለቀ ወረተኛ ሁሉ፣ በኅብረተሰብአዊነት የተኰተኰቱ፣ የቻይናው ማኦ ቲሰቱንግ ታማኝ ደቀመዛሙርት፣ የአልባኒያው ሆችሚኒ አድናቂዎችና አጨብጫቢዎች ሲሆኑ፣ አሜሪቃ ግን የበዝባዦች ቊንጮና ደመኛቸው ነበረች። ሁኖም በደማስቆ መንገድ ክርስቲያኖችን ድምጥማቸውን ሊያጠፋ ሲጓዝ እንደነበረው ሐዋርያዊው ጳውሎስ፣ እነሱም ባንዴ ከአሜሪቃን ጥልቅ ጥላቻ  ወደጥብቅ ፍቅር ተለወጡ። ሥልጣን ላይ እንደወጡ የተገበሩትም ልክ የአሜሪቃ መንግሥት ዋና ጸሓፊ የነበረው ክሲንጀር ጥቂት ቀደም ሲል ስለኢትዮጵያ አረቀቀ የተባለውን ነው ማለት ይቻላል። በቀዝቃዛ ጦርነትና በዐረብ-እስራኤል ግጭት ሰበብ ከ፲፱፻፷ዎቹ መጨረሻ ላይ ጀምሮ፣ አሜሪቃ ስለኢትዮጵያ የነበራት መምርያ ከድሮው ከቅኝ ገዢዎቹ ከአውሮጳውያን መርህ ብዙም የማይለይና የማይራራቅ ነበር ማለት ይቻላል። የአውሮጳ ቅኝ ገዢዎች ኢትዮጵያ ካልተበታተነች የአፍሪቃን ክፍለ አገር በዘለቄታ ከሥልጣናቸው ሥር ለመያዝ አስተማማኝ ዋስትና አይኖረንም ይሉ እንደነበር ሁሉ፣ አሜሪቃም በቀይ ባሕር አካባቢ ያላትን ጥቅሟን እስከሚቻል ጊዜ ድረስ ለማስከበር፣ ኢትዮጵያ እንደ ዐረብ አገሮች ተከፋፍላና ተነጣጥላ ካልጠፋች በስተቀር አይሳካም ወደሚል አቋም የደረሰች ይመስላል። ቅኝ ገዢዋ ኢጣልያ ኢትዮጵያን ለመቈጣጠር “የዐማራን አከርካሪ በማያዳግም ሁናቴ መስበር አለብን” ትል የነበረውን አባባል፣ የወያኔም ባለሥልጣኖች በየጊዜው አስተጋብተውታል። ስለዚህም የወያኔና የአውሮጳውያን ቅኝ ገዢዎች ሕልም አንድ ነው ማለት ይቻላል። እንግዴህ አሜሪቃ የ“ትግራይን ረፓብሊክ” መፍጠር ዋና ግቡ ያደረገውን ወያኔን ለሥውር ዓላማዋ ቢትመርጥ ምንም የሚገርም አይመስለኝም። አሜሪቃም እንደአውሮጳውያኖች ቅኝ ገዢዎች ዐማራ ቢጠፋ ደንታቢስ ቢትሆን ምን ይገርማል።

 

እንደተለመደው የወያኔ መንግሥት ሥራ ከዚህ በፊት በተለያዩ ጽሑፎቼ እንዳነሣሁ፣ በጥላቻና በድንቁርና ላይ የተመሠረተ ሁኖ ነው እንጂ እነሱና እነሱን የመሳሰሉ የጐጥና የጐሣ ምሁራንና ልሂቃን የሚነበንቡት ዐማራ በሕይወት ኑሮም አያውቅም ማለት ይቻላል[1]። ዐማራ [በግእዝ ቋንቋ አምሐራ] ለመጀመርያ ጊዜ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ስሙ የሚነሣው፣ በተለያየ ስም “ድግናጃን፣” “ደጋዛን”ና “ግዳዣን” በመባል በሚታወቀው በአክሱም ንጉሥ የሓዋርያነት ሥራ በተያያዘ ጉዳይ ነው። ንጉሡ ከመናገሻ ከተማው ወደመቶ ዐምሳ ሰባኪዎችን “ደብተራ” ብሎ ከሠየማቸው በኋላ፣ ሕዝቡን እንዲያከረስትኑ ወደ “ዐማራ” ምድር እንደላካቸው ሰነዱ ይገልጣል። እንግዴህ በዚህ ሰነድ መሠረት “ዐማራ” የሚያመለክተው፣ የተወሰነ የመሬት ክልል መሆኑ አይካድም። የተለያዩና በየጊዜው የመጡት የውጭ አገርና ያገር ቤት ጸሓፊዎች አላንዳች ማዛባት እንደሚናገሩ፣ ክልሉ በምዕራብ በኩል በአባይና እሱን በሚመግበው የበሽሎ ወንዝ፣ በሰሜን በአንጎትና ላስታ፣ በደቡብ በወንጭት ወንዝ፣ በምሥራቅ ደግሞ ወደደንከል በረሃ በሚደርሰው ሰፋፊ ገደላንገደል የተከበበውን ምድር ይዋሰናል። ይኸ ዝርዝር እንደማስረጃ ካገለገለን እንግዴህ፣ ዛሬ የወያኔ መንግሥት ዐማራ ብሎ የሚጠራቸውን እንደነጐጃም፣ በጌምድር፣ ሸዋ እንዲሁም የወሎን ከፊሉን አያካትትም።

 

የዚህ ክልል ነዋሪዎች አፈታሪክ የሚነግረን፣ “ዐማሮች” ምንጫቸው በቀጥታ ከአክሱም ሲሆን፣ “ዐማራ” የሚለው ቃል ትርጒሙ “ነፃ ሕዝብ[2]” ማለት እንደሆነ ነው። ሁኖም ዐማራ በሰፊውና በገነነ መልኩ በመቈራኘት የሚታየው ከገዢው መደብ ጋር በመያያዙ ይመስለኛል። የአክሱማውያን መንግሥት ከብዙ የጨለማና የድብልቅልቅ ዘመን በኋላ የተተካው፣ በታሪክ ዟጐ በመባል በሚታወቀው ሥርወመንግሥት ሲሆን፣ ከሱም ቀጥሎ የመጣው “ሰለሞናዊ’” እያልን የምንጠራው ነው። የዛጐ መንግሥት በአገዎች እንደተቋቋመ ሁሉ፣ በታሪክ መሠረት የሰለሞኖች ሥርወ መንግሥት ቈርቋሪ ደግሞ ግእዙ “ንጉሠ አምሐራ[3]” በሚለው በአፄ ይኩኖአምላክ እንደሆነ ይታወቃል።  እዚህ በጣም መጠንቀቅ የሚገባን ነገር አለ። “ንጉሠ አምሐራ” የሚል ስያሜ ይኑራቸው እንጂ፣ ጐንደር የነገሥታቱ ቋሚ መናገሻ ከተማ ሁና እስከተቈረቈረችበት ማለትም እንደአውሮጳ አቈጣጠር [አ.አ.] እስከ ፲፮፻፴፪ ዓ. ም. ጊዜ ድረስ፣ ምናልባትም ከመጀመርያው “ንጉሠ አምሐራ” ውጭ፣ በዐማራ ምድር ውስጥ የነገሠ ሌላ ንጉሥ ነበር ማለት ያዳግታል። ግዛታቸው ሰፊ፣ ተራራማና ገደላገደል የሞላበት ስለነበር፣ ለቊጥጥር እንዲያመቻቸው ሲሉ፣ ነገሥታቱ የሚኖሩት በየጊዜው ሰፈር እየቀያየሩ “በዟሪ” ወይንም “በተሽከርካሪ ከተማ፡” ነበር። ሥልጣናቸውን በየጊዜው በመፈታተን እከፍተኛ አደጋ ላይ የሚጥሉት ሁናቴዎች አብዛኛውን ጊዜ የሚፈጠሩት በአገራቸው ደቡብና ምሥራቅ ባሉት የእስላሞች ባላባቶች በኩል ስለነበር፣ ይኸንን በመገንዘብ የዟሪ ከተማቸው ዋና ዋናዎቹ ግዛቶች በደቡብ እንደነይፋትና ሸዋ፣ ደዋሮና ፈጠጋር የመሳሰሉት አገሮች ነበሩ። ከዘመነ-መሳፍንት በኋላም ቢሆን፣ በዐማራ ምድር ውስጥ የነገሠ ንጉሥ እንደሌለ ስለምናውቅ ወደዝርዝሩ መሄድ አስፈላጊ ሁኖ አይታየኝም።

ዐማራ የተባለው ክልል የ”ዐማራ” የነገሥታት መቀመጫ ሁኖ እንደማያውቅ ግልጽ ከሆነ፣ አገሩን የሚገዙት ነገሥታቱስ ከዐማራ ቤተሰብ ወይንም ክልል የተወለዱ ነበሩ ወይ ብሎ መጠየቁ ተገቢ መስሎ ይታየኛል። አፄ ይኩኖ አምላክ “ንጉሠ አምሐራ” ቢባሉም፣ በመከታተል አልጋቸውን የወረሱት ነገሥታት ግን፣ ምናልባትም ከመጀመርያዎቹ ጥቂቶቹ በስተቀር፣ የአብዛኞቹን የቅርብ ወላጆቻቸውን [ማለትም አባትና እናት] ብንመለከት፣ ሙሉ በሙሉም ሆኑ፣ በከፊል ከዐማራ ዘር ወይንም ምድር መሆናቸው እጅግ በጣም አጠያያቂ ነው ማለት ይቻላል። ለማንኛዉም እስኪ ወደጥልቅ ሳንገባ ለማስረጃ ያህል የሚከተሉትን እንያቸው። በ፲፮ኛ ዘመን የነገሡት ነገሥታት፣ ካፄ ልብነድንግል ባለቤት ከጐጃሜዋ[4] ከእቴጌ ሰብለወንጌል በስተቀር፣ የሁሉም ሚስቶቻቸው የትግራይ ወይንም የሐዲያ ተወላጆች ነበሩ ማለት ይቻላል። የቄንጠኛዋ የጐንደር ከተማ መንግሥት ነገሥታት፣ የአፄ ሱስንዮስ ዝርያ ናቸው። እርሳቸው ደግሞ በእናታቸው ከቤተእስራኤል ሲሆኑ፣ ወልድ ሠዓላ ይባሉ የነበሩት ሚስታቸው እቴጌ ሥልጣን ሞገሳ በበኩላቸው ከኦሮሞ ብሔረሰብ መሆናቸው ይነገራል። እናታቸውም እስላም ነበሩ ይባላል። ከዚህ የምንማረው ነገር ቢኖር፣ ጐንደርን ከቈረቈረው ከልጇ ፋሲለደስ ጀምሮ እስከ ዘመነ-መሳፍንት ድረስ በኢትዮጵያ ዙፋን ይቀመጡ የነበሩት የኦሮሞ፣ የቤተእስራኤል ደም ካላቸው ብሔረሰብሶች የተወላለዱ ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሩ ማለት ነው።

 

የዘመነመሳፍንቱ ነገሥታት በደምገንቧቸው የነበረው ደም በግልጥ የቋራና የኦሮሞ ድብልቅ ነው። የገዛራሳቸውን “ርእስ መስፍን ዘኢትዮጲያ[5]” በሚል የማዕርግ ስም ሠይመው፣ ነገሥታቱን በዘፈቀደ እንደጉልቻ እየቀያየሯቸው በበላይነት የሚመሩት ፈላጭቈራጮቹ መሪዎች ደግሞ ከመላ ጐደል የየጁ ኦሮሞች[6] ነበሩ። ዘመኑም የሚታወቀው በሥርወመንግሥታቸው የ“ወረሼኮች[7]” በመባል ነው። ዘመነ መሳፍንት ማለት እንግዴህ የኦሮሞ ዝርያ ናቸው የተባሉት የየጁ መኳንንት ላንድ መቶ ዓመት ያህል የጐንደርን መንግሥት ሙሉ በሙሉ የተቈጣጠሩበት የኢትዮጵያ ታሪክ ዘመን ነው ማለቱ እውነትትን ያንፀባርቃል ብዬ አምናለሁ።

 

ከዘመነመሳፍንት ባሻገር፣ ወደዛሬዋ ወደዘመናዊት ኢትዮጵያ ብንመጣ ሁናቴው ብዙም አይቀየርም። ሦስቱ አጼዎች (ቴዎድሮስ፣ ዮሐንስ[8]ና ምኒልክ) ከገዛ ራሳቸውም ሆኑ ከሚስቶቻቸው መካከል አንድም ጭንጩ ዐማራ በርግጥ የለም ማለት ይቻላል። አፄ ቴዎድሮስ[9] ከቋራ፣ አፄ ዮሐንስ ከትግራይ፣ አፄ ምኒልክ ከተለያየ ብሔረሰብ ናቸው። ልጅ ኢያሱና አፄ ኀይለሥላሴ[10]  ደግሞ ያማራ ደም አለባቸው ቢባልና ቢለካ በርግጥ ካሥር የአንድ ግማሽ እጅ እንኳን ላይሞላ ይችላል ብል ሐሰት አይደለም።

ከነገሥታቱ ወረድ ብለን በሁለተኛ ደረጃ የሚገኙትን ባለሥልጣናት ብናይ፣ ደረጃው ሁሉንም አካባቢና ብሔረሰብ ያካተተ ሁኖ እናገኘዋለን። ሁኖም በገዢዎች ትውልድ አካባቢ ለሚመራመር ግለሰብ ታላቁ ችግር፣ ታሪክ ጸሓፊው በግልጥ ካልተናገረ በስተቀር በስም ብቻ ተመሥርቶ ባለሥልጣኑ ከየትኛው ብሔረሰብ ወይንም አካባቢ እንደመጣ መንገር በጣም ያዳግታል። ምክንያቱም በኢትዮጵያ መንግሥት ታሪክ ውስጥ አንድ ግልጥ ሁኖ የሚታይ ጉዳይ ቢኖር፣ ሥልጣንና ሹመት የግለ-ሰቡ የአገልግሎት ብቃትና ትጋት ፍሬ ውጤት እንጂ በትውልዱ ዘርና አካባቢ የተገደበ አይደለም ማለት ይቻላል። ሿሚው በመጀመርያ ደረጃ እንደመስፈርት የሚጠቀማቸው የተሿሚውን ችሎታና ታማኝነት እንጂ ከየትኛው ቤተሰብና ብሔረሰብ ወይንም ቀዬ መምጣቱን አይደለም። ከዚህ ጋር በተያያዘ፣ አንድ በጥብቅ መታወቅ ያለበት ነገር ቢኖር፣ ብዙ ጊዜ በተሳሳተ የአውሮጳውያን ታሪክ በመመሥረት ስለኢትዮጵያ የጉልተኛ ባላባት[11] ሥርዐት የሚናገሩ በርካታ ጸሓፊዎች ቢኖሩም፣ ሐቁ ግን እውነትን ለማዛባትና ለማወናበድ ካልሆነ በስተቀር ሥርዐቱ ባገራችን በግልጥ የታየበት ጊዜ የለም። መደብ፣ ወገንና አካባቢ ጠቃሚነታቸው በሁለተኛ ደረጃ ሊሆን ይችላል። ግን እንደችሎታና  ታማኝነት ወሳኝ መስፈርቶች አይደሉም። ስለዚህም ነው እንግዴህ ከላይ እንደተባለው ስለባለሥልጣኖቹ ማንነትና አካባቢ ብዙም የማናውቀው። ሁኖም አንዳንዴ ካንድ ጉዳይ ጋር በማማያያዝ፣ የጥቂቶች ማንነታቸው ሲጠቀስ ይታያል። እስኪ ከነዚህ መካከል ለወጉ ያህል ጥቂቶቹን እንመልከት። በአፄ ሱስንዮስ ዘመን ከሁሉም ታላቅ ሹመት ሁኖ የሚገመተውን የጐጃምን ግዛት፣ “ጐጃም ነጋሽ” የሚለውን ያገሩን ገዢ ማዕርግ ተከናንቦ ለብዙ ዓመታት ያስተዳደረው የጉራጌው ተወላጅ “ጐጃም ነጋሽ ክፍሎ” ነበር። ያፄ ሠርፀድንግልን ሁለት ልጆች አግብቶ፣ መላ ኢትዮጵያን በበላይነት ያስተዳድር የነበረው በጊዜው የመንግሥት ፈላጭ-ቈራጩ መኰንን፣ የወለጋው ተወላጅ ራስ ዘሥላሴ[12] ነበር። በ “ዳሞት ጸሓፊላምነት” ማዕርግ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብም ሆነ፣ ወሰንና ድንበር ለማስጠበቅ ሲል ብዙ ጦርነት በጀግንነት በመዋጋት፣ ንጉሠነገሥቱን እንደአ.አ. ከ፲፮፻፲፯ እስከ ፲፮፻፳፯ ዓ.ም. በታማኝነት አገልግሎ፣ በመጨረሻም የዳሞት ግዛቱን ከኦሮሞ ወረራ ሊከላከል ሲል በጦር ሜዳ ላይ ሕይወቱን የሠዋው ደጃዝማች ቡኮ፣ ከመጀመርያዎቹ የኦሮሞች ታላላቅ ገዢዎች አንዱ ነበር። እንዲሁም ንጉሠነገሥቱ “እንደልቤ ታማኝ” ይሉት የነበሩት፣ ዋናው አማካሪያቸውና፣ ከቁመታቸው ዕጥረት የተነሣ በኦሮሞኛ ቃል “ጢኖ” በመባል የሚታወቁት፣ ጸሓፈ ትእዛዙ አዛዥ ተክለሥላሴ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ነበሩ። ጽሑፋቸው እንደሚያመለክተው፣ አዛዥ ጢኖ ከኦሮሞ ቋንቋና ባህል በተጨማሪ፣ ዐማርኛና ግእዝ አሳምረው የሚያውቁ፣ ቅኔ የሚቀኙ፣ አንደበታቸው የተባ፣ ብዕራቸው የሰላ ጸሓፊ ናቸው። እነዚህ ለእንደዚህ ዐይነት ወግና ማዕርግ ሊበቁ፣ ዕውቀትንም ሊገበዩ የቻሉት፣  “ጋላ” በኢትዮጵያ ፈጸመ የተባለው ወረራ ግማሽ ዘመን ማለት ዐምሳ ዓመት እንኳን በማይሞላው ጊዜ ውስጥ ሲሆን፣ እስከኛ ጊዜ ድረስ ባሉት ዐራት መቶ ዓመታት ውስጥማ ምን ያኽል መቀራረብና መዋሐድ እንደተካሄደ መገንዘብ የሚያዳግት አይሆንም።

ከላይ ስለልጅ ኢያሱና አፄ ኀይለሥላሴ አንሥቻለሁ። ከነዚህ ሁለቱ ጋር በተያያዘ፣ በቅርብ ጊዜ ባነበብሁት ባንድ ሊቅ ሕዝቅኤል ኢብሳ በተባሉ ያንድ ዩኒቬርሲቲ መምህር ተደርሶ በበርካታ የኢትዮጵያ ድረ-ገጾች በወጣ ጽሑፍ ላይ አንዳንድ ኂሶች መሰንዘሩ ተገቢ መስሎ ይታየኛል። ሊቁ ኢትዮጵያ፤ የኦሮሞ እውከት፤ ስለብሔራዊ ጥያቄና ወደሕዝበ መንግሥት ሽግግር[13]” በሚል ድርሰታቸው፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር [ኢ.ሕ.ዴ.ግ] በመባል የሚታወቀው የወያኔ መንግሥት በዐዋጅ ኦሮሞ ብሎ በሠየመው ሕዝብ ላይ የጐሣው አቀንቃኞች ደርሶበታል የሚሉትን ግፍና ሰቈቃ ይተርካሉ። ታሪክን በገለልተኛነት ለሚመራመርና የኦሮሞን ሕዝብ ታሪክ ለሚያውቅ ምሁር፣ የሊቁ ንግግር የተለመደውን ደጋግሞ ከመወሸከት ውጭ ምንም አዲስ ነገር ስለማያፈነጭ ጊዜ ላለመፍጀትና የጽሑፌን አቅጣጫ ላለመለወጥ ስል አልፈዋአለሁ። ሁኖም ላነሣ የፈለግኋቸው ሁለት አውራ ነገሮች አሉ።

 

አንደኛ፣ እንዴት ሁለቱ የሴማውያን ዘሮች ማለትም ትግሬዎችና ዐማሮች፣ ኦሮሞችን አገልለውና ካስፈለገም የሥልጣን ፍርፋሪ ብቻ በመወርወር ያስተዳደሩን ሥልጣን የግላቸው ሀብት እንዳደረጉ፣ ምሁሩ አበክረው ይናገራሉ። እንዲህም ሲሉ፣ ሊቁ በጽሑፋቸው የሚጠቅሱትን የእንደነጆን ማርካኪስ [John Markakis[14]] ዐይነቶቹን የግራዘመም ጸሓፊዎችን አሳብ ከማንሸራሸር በስተቀር፣ ከማንም ታሪክ ጸሓፊ የሚጠበቁትን አመዛዛኝ ልቡናና የማያዳላ አእምሮ በመጠቀም የኢትዮጵያን ታሪክ ያገናዘቡት አይመስሉም። በመጀመርያ ደረጃ ከላይ ያየነው በዘመነ መሳፍንት አገሩን ይገዛ የነበረው የወረሼኮቹ ሥርወ መንግሥትም ሆነ፣ ነጋሾቹ መሳፍንት እንደፍላጎታቸው የሚለዋዉጣቸው ነገሥታት በስም ሰለሞናውያን ይሁኑ እንጂ፣ ከመላ ጐደል የኦሮሞ ዝርያ መሆናቸውን አይተናል። ስለዚህም በኢትዮጵያ እየተፈራረቁ ከፍተኛ ሥልጣን ይዘው የነበሩት ትግሬዎችና ዐማሮች እንጂ ኦሮሞች ለዚህ አልበቁም ማለት በጠራራ ቀን ፀሐይ የለችም ብሎ እንደመሟገት የሚቈጠር መስሎ ይታየኛል።

 

በሁለተኛ ደረጃ የገረመኝ ነገር ቢኖር፣ ምሁሩ በምዕራባውያን ኀይሎች አነሣሽነትና በሥልጣን ሽኩቻ፣ ባንድ በኩል በልጅ ኢያሱና በአባታቸው ንጉሥ ሚካኤል፣ በሌላው ደግሞ በልጅ ተፈሪና (ኋላ አፄ ኀይለሥላሴ) በደጋፊዎቻቸው መካከል፣ እንደኢትዮጵያ አቈጣጠር [ኢ.አ.] በመስከረም ፲፯ ቀን ፲፱፻፱ ዓ.ም. የተካሄደውን የሰገሌን ጦርነት በሚያስደንቅ ሁናቴ በመተርጐም፣ በወሎ ኦሮሞችና በሸዋ ዐማሮች እንደሆነ አድርጎ ማቅረባቸው ነው። በሁለቱም በኩል የሚዋጉትም ሆነ፣ ጦሩን በበላይነት የሚመሩት፣ አብዛኞቹ ኦሮሞች ወይንም የኦሮሞ ደም ያላቸው ሲሆኑ፣ ምሁሩ እንዴት አድርገው እንደዚህ ለመደምደም እንደበቁ አይናገሩም። ምናልባት ኦሮሞ ሲሉ፣ እንደነፃ አውጪ ነን ባዮቹ የፓለቲካ ድርጅቶች፣ የተወሰነ መስፈርት ካላቸው ደግሞ ምሁሩ በጽሑፋቸው ውስጥ ይኸንን ግልጥ አያደርጉም። አባባላቸው ደግሞ ኦሮሞች እርስበርሳቸው አይዋጉም የሚል ከሆነ፣ በጣም ሩቅም ሳይሄዱ የእረኝነትን ሥርዐት ትተው፣ በኦሞ ወንዝ አካባቢ በመንግሥትነት ተቋቁመው የነበሩትን፣ የጅማ አባጅፋርን፣ የጉማንና የጐማን ከዚያም ባሻግር የለቃ-ነቀምትንና የለቃ-እናርያን ንጉሦች፣ እንዲሁም በወሎ ውስጥ የየጁዎች ባላንጦች የነበሩትን የማመዶችን ሥርወ መንግሥት  ማየት ይበቃል። በአገዛዛቸው ጨካኝነት፣ በኦሮሞም ሆነ መሬታቸውን ከነጠቁ በኋላ “ባዕዳን” ብለው በፈረጁባቸው ባገሩ ተወላጆች ላይ ያደርሱባቸው የነበረው ግፍና ሰቈቃ፣ የጐሣው ልሂቃን ’የአበሻ” ነገሥታት በሕዝባችን ላይ ፈጸሙበት ከሚሉት እጅግ ይከፋል እንጂ በምንም ረገድ አያንስም ብዬ እገምታለሁ።  ሊቅ ሕዝቅኤል በዚህ ድርሰትና በሌሎችም ጽሑፎቻቸው ይልቁንም በጀርመን አገር ታትሞ በወጣው በEncyclopedia Aethiopiaca ኦሮሞ-ነክ ዐምዶች [vol. 4 O-X] ላይ ከፖለቲከኞች እንጂ ካንድ ገለልተኛ የታሪክ ምሁር የማይጠበቁ አያሌ የተዛቡ አስተያየቶች አስቀምጠዋል። እንደዚህ ዐይነቱ የታሪክ አተረጓጐም ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየው የኢትዮጵያ ምሁራን ታሪክን የፖለቲካ ደንገጡር እንዳደረጓት ነው ብል ሐሰት አይመስለኝም። በዚህ ረገድ ሊቅ ሕዝቅኤል ብቸኛ አይደሉም[15]፤ እንደጊዜው ፖለቲካ የሚቀያየሩ የወረት-በላ ምሁራን የበዙበት ዘመን ስለሆነ፣ ነገሩ የሚገርም መስሎ አይታየኝም በማለት አሳቤን ልቋጭና ወደዛሬው ጥያቄዬ ልመለስ።

 

ዐማራን በተመለከተ በቂ ያልሁ ስለሚመስለኝ፣ ልቀጥልና ወደዐማርኛ ልሻገር። የዐማርኛ ቋንቋ ምንጩና መነሻው ዐማራ ከተባለው ክልል እንደሆነ አይካድም። ልክ እንደዐማራ እሱም በዘተለምዶ ተቈራኝቶ የሚገኘው ከገዢው መደብ ጋር ቢሆንም፣ ሐቁ ግን ቋንቋው በደምቡ ያደገውና የዳበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ባደረገው ያልተቈጠበና ሰፊ አስተዋፅኦ ነው ማለት ይቻላል። ስሙ ከተወለደበት ምድር ጋር ተያይዞ ቢቀርም፣ እውነቱ ግን በየአካባቢው የሚገኙትን የተለያዩ ቋንቋዎች ቃላትንም ሆነ አገባብ በመከለስ፣ በማዳበልና በማቀያየጥ አዋህዷቸውና አመሳስሏቸው ይገኛል። የቋንቋ ጥናት ምሁራን ሴማዊ ብለው ፈርጀውታል። በኔ አመለካከት ይኸ ዐይነቱ አከፋፈል በርካታ ታሪካዊ ጥላሸት የለበሰ በመሆኑ እንደአስተያየት እንጂ እንደዐምደ ሃይማኖት ሁኖ መወሰድ የለበትም። ያም ሁኖ ግን፣ ሐቁ ዐማርኛ በኩሳውያንና በሌሎችም ባካባቢው ካሉት ቋንቋዎች ቃላትና አገባብ በሰፊው ከመደባለቁ የተነሣ ሴማዊ ብሎ መጥራቱ ፋይዳ ያለው አይመስለኝም። የራሱን ስያሜ ሰጥቶ፣ “ኢትዮጵያዊ” ወይንም “አፍሪቃዊ” ማለቱ የሚቀል ይመስለኛል። በፊደልም ሆነ በአነባብ ከማንኛውም ያለም ቋንቋ የተሻለ ነው ብዬ አምናለሁ። ብዙዎች ቋንቋዎች ንባባቸው በጽሑፍ ተቀርጾ ካለው ፊደል ጋር በፍጹም አይጣጣምም። ለምሳሌ በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ሰበብ ባለም እየተሰራጨ በመጣው የእንግሊዝኛ፣ አንድ ቊጥር ወይንም “One” ሲነበብ “ዋን” ብሎ እንጂ እንደጽሑፉ “ዖንእ” አይደለም። እንዲሁም ከአውሮጳዉያን ቋንቋዎች መካከል ጽሑፉና አነባቡ አገባቡን ተከትሎ ይሄዳል ከሚባሉት ቋንቋዎች መካከል ኢጣሊያንኛ አንዱ መሆኑ ይታወቃል። አባባሉ እውነትነት ቢኖረውም፣ ሐቁ ግን እሱም ቢሆን መጠነኛ ሕገወጥነት ያጠቀዋል። ለምሳሌ ያህል ኢጣሊያንኛ የዐማርኛ “ሸ” የሚል ፊደል ስለሌለው፣ የሚጻፈው ቢያንስ ሦስት ፊደላትን በማቈራኘት ነው። “ሻ-ካሎ[16]” ለማለት “scia-callo” መጻፍ ይኖርበታል። በዚህ መልክ ስናየው ያማርኛ ፊደል የተራቀቀና ዘመናዊነትን ያሟላ ነው ማለት ይቻላል። ፊደሎቹ በዛ በማለታቸው፣ ለጥናት መጠነኛ ጊዜ ቢፈጁም፣ አንዴ ጠንቅቋቸው ላወቀ ግን በቅልጥፈት፣ በቀላልነትና በይዘት ደረጃ ወደር የሚገኝለት ቋንቋ አይደለም ሊባል ይችላል። በኮምፑቴር አገላለጽ “የሚነበበው እንደተጻፈው ነው[17]” የሚለው አባባል የሚገባው ከማንኛዉም ቋንቋ ይልቅ ለዐማርኛ ነው ቢባል እውነትነት አለው::

 

ዐማርኛ ባገሪቷ ውስጥ ያሉትን የልዩ ልዩ ብሔረ-ሰቦችን ድምፅ ሊያስተናግድ ሲል ጥንት ከአባቱ ግእዝ በወረሳቸው ፊደላት ላይ እንዳስፈላጊነቱ አዳዲስ ፊደል ሊፈጥርና ሊጨምር በቅቷል። አብዛኛውም የቋንቋው  ተናጋሪ የሚገኘው ከጥንት ትውልዱ ክልል ውጭ ነው። የተለያዩ ማስረጃዎች እንደሚገልጹ ከሆነ፣ በሁሉም ዘንድ ባይሆን እንኳን በተወሰኑት በዛሬዎቹ ሱማሌዎችም አካባቢ ተስፋፍቶ እንደነበር አል-ፋቂህ በመባል የሚታወቀው የግራኝ ታሪክ ጸሓፊ እስላሙ ዐረብ በ“የአበሻ ወረራ” በሚል መጽሐፉ ከመዘገበው ፍንጭ እናገኛለን። አፄ ልብነድንግልን በድንገት በሰፈሩበት ዐምባ ላይ ለመያዝ ዐቅዶ፣ ግራኝ ለወታደሮቹ በዐማርኛ ብቻ እንዲናገሩ ጥብቅ ትእዛዝ ሰጠ።  ወታደሩም እንደታዘዘው አድርጎ፣ ሳይጠረጠር የደኅንነቱን ጠባቂዎች ዐልፎ ንጉሥ ነገሥቱን ለመያዝ ምንም አልቀረውም ነበር። አፄውን ሊያስመልጣቸው ያበቃው ምናልባት ግራኝ ራሱ ሳይታወቀው በራሱ [አደርኛ?] ቋንቋ መናገሩ ይመስላል።

 

ዐማርኛ ለተለያየ ብሔረሰብና አካባቢ የኢትዮጵያዊነቱ መግለጫ መሆኑ አይካድም። ከላይ የጠቀስናቸው እንደነጐጃም ነጋሽ ክፍሎ፣ ጸሓፈላም ቡኮና ራስ ዘሥላሴ የዐማራ ተወላጆች እንዳልሆኑ ይታወቃል። አጭር በመሆኔ “ጢኖ” የሚል የኦሮሞኛ ስም ተስጥቶኛል ባዩ ጸሓፌ ትእዛዝ አዛዥ ተክለሥላሴም በጽሑፋቸው ስለቋንቋው ሲገልጡ፣ “ዐማርኛ ቋንቋችን” እያሉ ኩራት በተሞላበት ስሜት ሲናገሩ ይታያሉ። በላስታና በሸዋ፣ በበጌምድርና በወሎ፣ እንዲህም በጐጃም ግዛቶች አማርኛ የኩሳውያንን ቋንቋዎች ተክቶ ይገኛል። በአርጐባና ጋፋት በመሳሰሉት አገሮች ደግሞ የሴማውያንን ቋንቋዎች ቦታ ወስዷል።

 

አማርኛ ያፋቸው መክፈቻ ቋንቋቸው ቢሆንም፣ እነዚህ እላይ የተጠቀሱ አገሮች እንደአ.አ. በ፲፱፻፺ዎቹ ዓ.ም. ላይ፣ ዐማሮች ናችሁ የሚል ስያሜ በሥልጣን ላይ ባለው መንግሥት በግድ በላያቸው ላይ እስከተለጠፈባቸው ጊዜ ድረስ “ዐማራ” በመባል አይታወቁም።  ራሳቸውን ይጠሩ የነበሩት በሚኖሩበት አገርና ቦታ ስም ጐንደሬ፣ ጐጃሜ፣ መንዜ በመባል እንጂ በፈጠራ በተሰጣቸው ዐማራ በሚል ብሔረሰብነታቸው አልነበረም። ታሪክም ራሱ የሚያመለክተው ይኸንኑ ሐቅ ነው። ከ፲፬ኛ እስከ፲፰ኛ አዝማን ድረስ በተከትታይ ድረስ የተጻፉት የነገሥታቱ የታሪክ ሰነዶች ዐማራ የሚለውን ቃል ከቦታ እንጂ ከብሔረሰብ ጋር አያቈራኙም። እንዲሁም እስከ፲፱ኛ ዘመን ድረስ በተጻፉት የክርስቲያኖቹም ሆኑ የእስላሞቹ ዜና መዋዕል ውስጥ “ዐማራ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው በአሁን ጊዜ በወሎ ግዛት ውስጥ የሚገኘውን የቦታ ስም እንጂ ብሔረሰብን አይደለም[18]

ጽሑፌ የሚያስረዳው አንድ መሠረታዊ ነገር ቢኖር፣ ኢትዮጵያውያን ከገዢው መደብ ጀምሮ እስከ ተራው ሕዝብ በጋብቻና በአምቻ የተሳሰሩ መሆናቸውን ነው። ያገሩ አስተዳደሩም ሆነ ቋንቋው በተለምዶ ዐማራና ዐማርኛ ቢባልም ሁሉም ኅብረተሰብ በባለቤትነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጎባቸው ያስመዘገባቸውና የገነባቸው መሆኑን የታሪክ ሰነዶች ይመሰክራሉ። ዐማራ የሚያመለክተው የዚህ አስደናቂ ግንብ አሳቡንና መሠረቱን የጣለው ሕዝብ የሚኖርበትን በጣም የተወሰነ ክልል እንጂ አሁን በሥልጣን ያለው መንግሥት ለጥቅሙ ሲል አብዛኛውን የኢትዮጵያን ሕዝብ በገፍ በማግለል ጭብጥ የማይሞሉና ማንንም የማይወክሉ መሰሎቹን ብቻ አሰባስቦ የፈጠረውን ኅብረተሰብ አይደለም።

 

[1] . መጥሌነትና ድንቁርና ብዙውን ጊዜ ተያይዘው ናቸው የሚሄዱት። ኢጣሊያን አገር ተማሪ ሳለሁ፣ አንድ ከደቡቡ [በሥልጣኔ ወደኋላ ከመቅረቱ የተነሣ “mezzo-giorno” ወይንም “መንፈቀ-ዕለት” ይሉታል] በኩል የመጣ የደስደስ ከፊቱ ያለው ጓደኛችን ካገር ቤት የተላኩልንን የውብ ቤቶች ሥዕል (ፎቶግራፍ) እያየን ሲንጯጯህ ሰምቶ መጣና፣ ሥዕሎቹን ሲያይ ገርሞት፣ “እናንተ ጥቁርች፣ሥዕሎቹ ከየት ናቸው” ሲል ጠየቀን። “ካገራችን” ስንለው፣ ደጋግሞ ያየው የታርዛን ፊልም ትዝ ብሎት ነው መሰለኝ፣ “አፍሪቃ ውስጥ ሁሉም እዛፍ ላይ የሚኖር መስሎኝ! ታዲያ ቤትም አለ እንዴ” ሲለን ከኛ አንዱ፣ “እውነትህን ነው ሁላችንም የምንኖረው በዛፍ ላይ ነው። የኢጣሊያን አምባሳደር ደግሞ የሚኖረው ከሁሉም በረዘመው ዛፍ ላይ ነው” ብሎ ባሽሙር ሲያሽማጥጥበት ነገሩ ያነውኑ ገባው።

[2] . ቃሉ መሻዘር  “ዐም (ዕብራይስጥ)= ሕዝብ”፣ “ሐራ = ነፃ”

[3] . ትርጒሙ “የዐማራ ንጉሥ” ማለት ነው።

[4] . የጐጃም ነዋሪ አማራ እንዳልነበረ ዝቅ ብሎ ይታያል።

[5] . ትርጉሙ “የኢትዮጵያ የበላይ ገዢ”።

[6] . ትንሹ ራስ አሊ በመባል የሚታወቀው ከእንግሊዝ መንግሥት ጋር በተፈራረመው የንግድ ውል የንጉሡንና የራሱን ማኅተም በሰነዱ ላይ ቢያኖርም፣ ራሱንየኢትዮጵያ ንጉሥ ብሎ ነው የፈረመው።

[7] ቃሉ ሙሻዘር ሲሆን ከኦሮሞኛ “ወረ = ቤተሰብ”፣ ከዐረብኛ “ሼኽ/ሸይኽ = ሼኽ”፣ ከአማርኛ “ኦች = የብዙ ምልክት” የተወጣጣ ነው። ባንድጋ ሲጋጠም “የሼይኽ/ሼኽ ቤት/ቤተሰብ” ሲሆን፣ ስሙ የሚያመለክተው ሥርወመንግሥታቸው የኦሮሞ፣ የአማራ ወይንም የአርጐባና የእስላም ቅልቅል መሆኑን ነው።

[8] . የአፄ ዮሐንስ ባለቤት እቴጌ ምሥጢረ ሥላሴ የአፋር ተወላጅ ነበሩ። አፄ ዮሐንስን ያገቡት ከከረስተኑ በኋላ ነው።

[9] . አፄ ቴዎድሮስ የቋራ ብሔረሰብ ሲሆኑ፣ ባለቤታቸው እቴጌ ተዋበች የታናሹ ራስ አሊ ልጅ ናቸው።

[10] ልጅ ኢያሱ የወሎው ገዢ የንጉሥ ሚካኤልና የወይዜሮ ሸዋረጋ ምኒልክ ልጅ ናቸው። አፄ ኀይለሥላሴ ባያታቸው ኦሮሞ ሲሆኑ እናታቸው ጉራጌ ናቸው ይባላል፣ ባለቤታቸው እቴጌ መነን አስፋው የልጅ ኢያሱ የእኅት ልጅ ናቸው።

[11] . በ እንግሊዝኛ ፊውዳሊዝም [feudalism] በመባል የሚታወቀው ሥርዐት ነው።

[12] . ጸሓፊው የራስ ዘሥላሴ አባቱ ከወረብ እናቱ ከጐናን ምድር ሲሆኑ የተወለደው በመጤነት በደርኀ ምድር ነው ይላል። አንዳንድ ጸሓፊዎች ቦታዎቹ በወለጋ ውስጥ ይገኛሉ ቢሉም የተረጋገጠ ነገር የለም።

[13] . Ethiopia: An Oromo Dilemma. The National Question and Democratic Transition”

[14] . ጆን ማርካኪስም ሆኑ ብዙዎች እሳቸውን የመሰሉ የውጭ አገር ጸሓፊዎች እንደሊቅ ሕዝቅኤል በኢትዮጵያ ምድር አልተወለዱም ብቻ ሳይሆን ቋንቋውንም አይናገሩም፤ ላገሩና ለባህሉ ባዳ ናቸው፤ ግንኙነታቸው ደግሞ ከተማሪዎቻቸውና እንደነሱ በአውሮጳውያን ተቋማት ከተማሩት ኢትዮጵያውያን የማያልፍ ስለሆነ ሕዝቡንም በቅርብ አያውቁትም። ስለዚህም ለኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ታሪክና ባህል ያላቸው ግንዛቤ የሚያንፀባርቀው በትርጒም ካነበቡትና በአካባቢያቸው ካሉት የቀሰሙት መሆኑ መካድ ያለበት አይመስለኝም።

[15] . በጣም የሚገርመው አብዛኞቹ የኦሮሞ ምሁራን ነን ባዮች እንደፖለቲካ ልሂቃኖቻቸው በታሪክና ተረት መካከል ያለውን ልዩነት የተገነዘቡ አይመስሉም። በኦሮሞ ታሪክ ውስጥ ብዙ ምናቦች አሉ። ለምሳሌ ያህል፣ የቦረንና የበርይቱማ ዝምድና እንደሐቅ አድርጎ መውሰድ ሮማውያን ገናናዋን የሮም ከተማ የቈረቈሩት ሮሙሉስና ረሙስ በጤግሮስ ወንዝ ከተጣሉ በኋላ ተኲላ እያጠባቻቸው አሳደገቻቸው የሚለውን ምናብ ሐቅ አድርጎ እንደመቀበል ነው። በሌላው ደግሞ በኦሮሞ ላይ የተፈጸመውን ግፍና ሰቈቃ ሲወሽክቱ፣ ኦሮሞች በሌሎቹ ላይ የፈጸሙትን አያነሡም። አፄ ምኒልክ የገባር ሥርዐት በሕዝባችን ላይ ጣሉብን እያሉ ንጉሠነገሥቱን በግፍ ሲወቅሱ፣ “ሕዝባቸው” በየወረረበት ሰፋሪውን ያገሩን ተወላጅ በአረመኔ መልክ እንደጨፈጨፈ፣ ለባርነት እንደዳረገ፣ የባላይነቱን በተቀበለው ደግሞ የሃበታ፣ ጠለታ፣ ሞጋሳ/ⶁአሳ፣ ገበሮ እያለ የተለያዩ የጭቆና ሥርዐቶች እንደጫነባቸው ሊናገሩ አይፈልጉም።

[16] .  ‘Sciacallo = ቀበሮ”

[17] . የእንግሊዝኛው፣ “What you read is what you see.”

[18] . እንዲሁም ከዚሁ ጋር በማያያዝ የምጨምር ነገር ቢኖር፣ ባሁኑ አጠራር ኦሮሞ፣ ድሮ ደግሞ ጋላ በመባል የሚታወቀው ሕዝብ ሁናቴም ልክ ይኸንኑ የዐማራን ይመስላል። ጥንት ቦረን፣ ሜጫ፣ ቱለማ፣ ኢቱና ጉጂ በመሳሰሉት ስሞች ራሳቸውን ይጠሩ የነበሩትን ብሔረ-ሰቦች ፣ ኦሮሞ በሚባል በጋራ መጠርያ ስም ሥር እንዲካተቱ አስገድዷቸዋል[18]። ጉዳዩ ራሱን የቻለ ሰፋ ያለ ጽሑፍ ስለሚፈልግ ቦታው ስላልሆነ፣ አሁን ልለፈው። ሁኖም አንድ መሰመር የሚገባ  የማይካድ ሐቅ አለ።

 


  ይድረስ ለትግራይ ተወላጆች: በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምን ዜጋ በዘር ድንኳን ውስጥ አይሰገሰግም –አገሬ አዲስ

$
0
0

tigrayኢትዮጵያ የልዩ ልዩ ቋንቋ ተናጋሪና ልዩልዩ ባህልና ልማድ ያለው ሕዝብ የሚኖርባት አገር ነች።ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ያሰኛት ሕዝቧ የእምነትና የጎሳ ልዩነት ሳይለያየው በአንድ አገር ልጅነት ደሙን አፍስሶ የመጣበትን የውጭ ወራሪ ሃይል መልሶ የአንድ ነጻ  አገር ዜጋ ለመሆን በመብቃቱ ነው።ይህ በታሪክ የተረጋገጠለት ክብሩና መታወቂያው ከጥቂት ዓመታት ወዲህ እንዲበረዝና አቅመቢስ ሆኖ ለውጭ ወራሪ ሃይሎች የተመቸ እንዲሆን በገዛ ዜጎቹ የተቀመረው የጥፋት መንገድ አሁን አንድነቱን እየቦረቦረው መጥቷል።ያ በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ ቋንቋና ክልሉን መውደድ እንጂ ማፍቀር የማያውቀው ዜጋ አሁን የሚያፈቃቅረውንና የክብር ካባውን ኢትዮጵያዊነቱን ጥሎ በሰፈር ጉድጓድ ውስጥ ለመጠለል ሲራኮት ማየት ትውልዱን የሚያሳብድ መርዝ የጠጣ አስመስሎታል።አሁን ትግሬነት፣አማራነት፣ኦሮሞነት፣ጋምቤላነት፣ጉራጌነት፣አፋርነት፣ሶማሌነት….የበላይነቱን እየያዘ ኢትዮጵያዊነት እየቀጨጨ መጥቷል።

የውጭ ወራሪዎች አንድ አገር ሲወሩ በመጀመሪያ የሚያደርጉት ሕዝቡን የሚያስተሳስረውን ነገር ማጥፋት ነው፤ሰንደቅ ዓላማውን ቀዶ ጥሎ በሌላ መተካት፣የሚግባባበትን አንድ ቋንቋ ሽሮ በራሳቸው ወይም በተለያዩ ቋንቋዎች እንዲንጫጫ ማድረግ፤አገራዊ ድንበሩን አፍርሶ በክልልና በሰፈር መተካትና ሕዝቡን የእዚያና የዚህ በማለት መበታተን ነበር።ጣሊያንም ኢትዮጵያን ሲወር ያደረገው ይህንን ነበር፤አሁን በስልጣን ላይ ያለው ቡድንስ ከዚህ የተለዬ ምን አደረገ?

በቀስተደመና ህብራዊ ቀለም ውስጥ ጎልቶና ደምቆ የወጣውን አረንጓዴ፣ቢጫና ቀይ ቀለም የመጀመሪያ ነጻ አገር የኢትዮጵያ መሪዎች የነበሩት አስተዋዮች ለመምረጥ ዕድሉን በማግኘታቸው ይህንን ማራኪ ቀለም አዋህደው ምልክታቸው አደረጉት። ለዘመናት ሳባውያን፣አጼ ካሌብ፣አጼ ልብነድንግል፣አጼ ዩሃንስ እንዲሁም ሌሎቹ የኢትዮጵያ መሪዎች እየተቀባበሉ አክብረው ያቆዩትን ፣የብዙ አፍሪካውያን የነጻነት አርማ ሆኖ የታዬና የተወሰደ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በመጀመሪያ ጣሊያን በራሱ ባንዲራ አሁን ደግሞ የጣሊያኖችና የሌሎች ቅኝ ገዢዎች ወኪል የሆነው ወያኔ በነጻነትና በእኩልነት ስም የተለያዩ ክልሎች በሚያውለበልቡት ዝብርቅርቁ በወጣ ባንዲራ ለውጦ አንድነቱን አናጋው።አንድ ቋንቋ ተናግሮ እንዳይግባባ በእኩልነትና በነጻነት ስም አደንቁሮ አራራቀው።የባቢሎንን ግንብ ታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ምድር ደገመው።

ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚጋራው እየጠፋ የሚለያይበት እየጎላ በመሄዱ ለጋራ ችግሩ አብሮ ለመቆም አልቻለም።በየአቅጣጫው የጎሳ ነጋሪት እየተጎሰመ የገዛ አገሩን ለማፈራረስ ግብ ግብ የገጠመ ይመስላል።እኛ የሚለው ስሜት በእኔ ነት ተተክቷል።እኛ የሚለው በእነሱ ተቀይሯል።እጅ ለእጅ ተያይዞ የገጠመውን ችግር አብሮ ከማሶገድ ይልቅ  አንዱ በሌላው ላይ ጣቱን ከመቀሰር አልፎ ቃታ ለመሳብ ተዘጋጅቷል። በዚህ ሁሉ ግርግርና የእርስ በርስ ግጭትና እልቂት የሚጠቀመው የሕዝቡን አንድነትና የአገሪቱን መኖር የማይሻው ወገን ነው።ለዚያ ደግሞ ከውጭ በሩቁ የተቀመጠው ጠላት  ሳይሆን ጉዳይ ፈጻሚው በሕዝቡ ቋንቋ እየተናገረ ስሜቱን እየቀሰቀሰ እጁን እንዲሰጥ የሚገፋፋው  አገር በቀሉ የጠላት መሳሪያ የሆነው ሃይል ነው።ያ ሃይል ላለፉት 25 ዓመታት ስልጣኑን በጉልበት ወስዶ የሚያተራምሰው ቡድን ህወሃት የተባለውና በስሩ ያሰለፈው ኢሕአዴግ የተባለ ጭፍራው ነው።

ህወሃት በኢትዮጵያዊነቱ ኮርቶና ለኢትዮጵያም ነጻነትና ህልውና ከፍተኛ ድርሻ ያበረከተውን የትግራይ ተወላጅ እንደባህሉ ይዞት የኖረውን የኢትዮጵያዊነት ስነልቦና አሶልቆ በጠባብ ክልል እስር ቤት ውስጥ አጭቆ ከሌላው ነጥሎና ከሌላው ቀምቶ በመስጠት፣ በርካሽ ድለላዎች እያታለለ ተከታዩ አድርጎታል።ኢትዮጵያ ብትፈራርስ የማንም መብትና ሰላም እንደማይከበር እየታወቀ ዘላቂነት በማይኖረው የሃብት ዘረፋ፣የመሬት ንጥቂያ ወንጀል ውስጥ እያስገባ ከሌላው ወገኑ ጋር  እንዲቃቃር ብሎም ደም እንዲቃባ አድርጎታል።ይህንን መሰሪ ተግባር ከጥቂቱ በስተቀር ብዙሃኑ የትግራይ ተወላጅ የተገነዘበው አይመስልም። አደገኛነቱ ቢገለጽላቸውም ሰምተው ወደ ልቦናቸው አልተመለሱም።በነሱ ስም ስልጣን ላይ የተቀመጡት ከሃዲዎች በአገር ውስጥና በውጭ አገር እየዘረፉ የብዙ ሚሊየን ዶላር ንብረት ሲያካብቱ፣በውጭ አገር ባንክ ሲያስቀምጡ፣ልጆቻቸውን ለመተካት ሲያስተምሩና ሲያዘጋጁ፣እነሱ ሲበሉ በሩቁ እያገሳ መቀመጡን የመረጠ ይመስላል። ጥፋት እያዩ፣በነሱ ስም የተቋቋመው ድርጅት ህወሓት አገር ሲያፈርስ፣ወገን ሲገድል፣ ሲያቆስል፣ሲያስር፣ሲያሳድድ፣ቤት ሲያፈርስና ህዝብ ሲያፈናቅል፣አጼ ዩሃንስና እራስ አሉላ አባነጋ እንዲሁም ሌሎቹ የትግራይ ተወላጆች ከወራሪዎች ጋር ተፋልመውና በህይወታቸው ዋጋ አስከብረው ያቆዩትን ያገሩን መሬት ለሱዳን(ለደርቡሾች)ቆርሶ ሲሰጥ ለምን አላሉም።ያም በመሆኑ የጥፋት መልእክተኞቹ የልብ ልብ ተሰምቷቸዋል፤ይበልጥ የጥፋቱ አድማስ እንዲሰፋ ሌት ተቀን እየሰሩ ነው።

በሌላም በኩል በውጭ አገር በተለይም በአሜሪካና በአውሮፓ የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ ለመከፋፈል ከፍተኛ በጀት በመመደብና የስለላ መዋቅሩን በመዘርጋት ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፤አሁንም እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።ከሚጠቀምበት አንዱ በኢትዮጵያዊነት አብሮ ሲያከብር የነበረውን የእስፖርትና የባህል በዓላት በጎሳ መልክ እንዲዘጋጁ ማድረግ ነው፡፤የኦሮሞ በሚለው ስር ለዓመታት ሲካሄድ እንደቆየው ሁሉ አሁን ደግሞ የትግራይ በሚል ስያሜ ተመሳሳይ ዝግጅት ለመጀመሪያ ጊዜ በሆላንድ ለማካሄድ እየተሯሯጠ ነው።ይህ ከኦገስት 18-21  “ቬስቲቫል ተጋሩ በአውሮፓ” በሚል ሽፋን የተዘጋጀ የወያኔን ደጋፊዎች የሚያዝናናና የሚያሰባስብ ዝግጅት ልዩልዩ ፕሮግራሞችን ያቀፈ ሲሆን የአባይ ቦንድ ሽያጭም የሚጧጧፍበት የገበያ አዳራሽ እንደሚሆን የወጣው መረጃ ያረጋግጣል።በጎሳ ዙሪያ በሚዘጋጀው በኳሱም ሜዳ ሆነ በባህላዊ ዝግጅቱ ላይ የሚገኘው ሕዝብ በኢትዮጵያዊነት ከሚዘጋጀው ማንኛውም በዓል ዝግጅት ያነሰ ለመሆኑና የብዙሃኑን ቀልብ ለመሳብ እንዳልቻለ በኦሮሞ ወንድሞቻችን በተደጋጋሚ ታይቷል። የሆላንዱም የወያኔ ካምፕ የሚያዘጋጀው እንዲሁ የተመናመነ ቁጥር ያለው አዘጥዛጭ ብቻ የሚሳተፍበት እንደሚሆን ከወዲሁ ምልክት እየታዬ ነው።በየዋህነት ወያኔን ሲደግፉ የነበሩት አሁን በአገራችን ውስጥ በተፈጠረው ሁኔታ በመንግሥት ላይ ጥያቄ እያነሱ እራሳቸውን በማራቅ ላይ ናቸው።

ዓይን ያወጡ ደረቆችና የጠባብነት በሽታ የለከፋቸው ጥቂት የትግራይ ተወላጆች የሞት የሽረት ትግል በማድረግ ላይ ቢሆኑም የማታ ማታ የሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም።

ህወሃትን እንቃወማለን በማለት በአረና ትግራይ፣በትግራይ ብሄራዊ ትብብር(ታንድ)በትግራይ ዴሞክራቲክ ንቅናቄ ስር የተደራጁት የትግራይ ልጆችም ከነዋሪው ፈቃድና ጥያቄ ውጭ በማስገደድ በትግራይ ክልል ስም  የተፈጸመውን የመሬት ነጠቃውንና መስፋፋቱን ሲቃወሙ አይሰማም፣እንደውም ለታላቋ ትግራይ ስሜት ያደሩ ይመስላል።አንዳንዶቹም አብረው የፈጸሙትን ጥፋትና እቅዱን ለማመን አልደፈሩም። ይህም በመሆኑ በመካከላቸው ያለው ልዩነትና ጠብ  የዓላማ ሳይሆን የስልጣን እንደሆነ፣ወደፊትም ታርቀው ያንኑ የተነሱበትን ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዓላማ ሳይቀጥሉበት አይቀሩም የሚል ጥርጣሬ እየጎላ መጥቷል።ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ ትግሬነታቸው እንደሚያሳስባቸው ምልክቶች እየታዩ ነው።ይህ ትክክል አይደለም ካሉ በግልጽ ማብራሪያ ሊሰጡ በተፈጸሙት  ወንጀሎችም ላይ ያላቸውን አቋም ሊያሰሙ ይገባቸዋል።እነሱም በስህተት ወንጀል ፈጽመው ከሆነ ይቅርታ መጠየቅ ጨዋነት ነው።በተጨማሪም የትግራይ ተወላጅ ከሌላው ጋር ተባብሮ ይህን የጋራ ጠላት እንዲሻሻልና እንዲጠገን ሳይሆን እንዲያሶግድ ቅስቀሳ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።ዝምታ የድጋፍ ያህል እንደሚቆጠር ሊያውቁት ይገባል።

መላው የትግራይ ተወላጅ ሆይ

በስምህ የሚፈጸመውን ወንጀል አውግዝ፣ህወሓት/ኢሕአዴግ በስምህ የሚነግድ፣ካልሆነለት ለአደጋና ለችግር አጋልጦህ የሚሸሽ፣ለዓለም አቀፍ ዘራፊዎች ተጠሪ የሆነ የሌቦች ስብስብ መሆኑን ተረዳ።እንኳንስ ያገሪቱን የተፈጥሮ ሃብትና መሬት ያገሪቱንም የመከላከያ ሰራዊት ዘራፊዎች በየአገሩ በሚቀሰቅሱት  የእርስ በርስ ግጭት እየማገደ የጦር ሜዳ ሸቀጥ አድርጎ የሚነግድበት መሆኑን ተገንዘብ።ሃይማኖትህን አርክሶ የፖለቲካ መሣሪያ አድርጎ መጠቀሙን ተቃወም። የፈጣሪን ቃል ጥሰው ለጥቅም ያደሩ ጳጳሳትንና ቀሳውስትን፣የእስልምና ሃይማኖት መሪ ኢማሞችን አትስማ፣አትከተል።ቤተመቅደስህንና መስጊድህን አታስደፍር።

ህወሃት ለወራሪዎች ጥቅም ሲል አንተንና ሌላውን በቋንቋ እረገድ ከልሎ ሊያጫርስህ የተዘጋጀ፣በደምህ ያቆየሃትን አገርህን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እንጂ ለእድገትህና ለሰላምህ የሚጨነቅ አለመሆኑን ተረዳ።የጠቀመህ መስሎ ከሌሎቹ ነጥሎ ለሚያቀርብልህ ጊዜያዊ ጥቅም አትደር።ውጤቱ የከፋ ሊሆን ይችላልና ለምን ለእኔ ብቻ ብለህ ጠይቅ።እድገት የሚቻለው የትልቅና የሰፊ አገር ባለቤት ሲሆኑ እንጂ የጠባብ ቀበሌ ኑዋሪ እስረኛ በመሆን እንዳይደለ እወቅ።አንተና ሌላው ኢትዮጵያዊ ደሙን አፍሶ ያስከበረውን የትግራይ የድንበር መሬት(ባድመን)አሳልፎ ለመስጠት የተፈራረመ ወንጀለኛ ቡድን ነገ ከእኔ ጋር ይቆማል ብለህ አታስብ።ሕዝባዊ ትግሉ ከጠነከረ ጣጥሎህ፣አንተን ለመከራ አጋልጦህ ይፈረጥጣል።አዘጋጅቶ ባስቀመጠው አገር የድሎት ኑሮውን ሊገፋ እንደሚችል አስብ።በፍርሃት ከኖርክበት ያገርህ መሬት አትኮብልል።ኢትዮጵያዊ  በተለይም አማራውና ኦሮሞው እንዲሁም የቀረው ሕዝብ ጨዋና አስተዋይ እንጂ አብሮ የኖረ ወገኑን የሚያሳድድ አውሬ ፍጡር አለመሆኑን እወቅ።ጥቃቱ በዝቶባቸው፣ ከሚችሉት በላይ ሆኖባቸው ጥቂቶች አላስፈላጊ ጉዳት ለማድረስ ቢነሱ ሁሉንም በአንድ ዓይን ተመልክተህ አትጥላ፣አትፍራ።የሕግ የበላይነት በሌለበት አገር ይህን መሳይ አደጋ ሊከሰት ስለሚችል ለዚህ ክስተት ምክንያት የሆነውን ስርዓት ለማሶገድ ከሌሎቹ ጋር ለመታገል ተሰለፍ።ለብዙሃኑ ጥቃትህ ጥቃታቸው፣ጉዳትህ ጉዳታቸው ስለሆነ አጋልጠው አይሰጡህም። አንተም የነሱ ጉዳትና ጥቃት ያንተ እንደሆነ አረጋግጥ።

ሌላው ለመብቱ ሲነሳ አንተን ለማጥፋት የተነሳ ነው የሚለውን አስበርጋጊና አስፈሪ ሰበካ(ፕሮፓጋንዳ) አትቀበል፤ሌላው የሚያደርገው በተለይም አማራው የሚታገለው እሱን ብቻ ሳይሆን አንተንና ሌላውን ኢትዮጵያዊ ከበዝባዦችና ከጨቋኞች መዳፍ ነጻ ለማውጣት መሆኑን አውቀህ ተባበር።

ተጋብተህና ተዋልደህ ለዘመናት ከኖርክበት ያገርህ መሬት በይሆናል ፍራቻ ለቀህ አትውጣ።ከሌላው ማህበረሰብ ጋር ተጋብተህና ተጋብተሽ ለተወለዱት ልጆች አስቡ።በዚህ አይነቱ ሂደት ቤተሰብ ፈራርሶ ልጆችም ካለእናት ወይም ካለአባት የሚደርስባቸው የህሊናና ስነልቦናዊ ስብራት ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ በተመሳሳይ ደረጃ ከተከሰተው ከኤርትራውያኑ ታሪክ ተማር።ወንጀለኛ እንጂ በደል ያልፈጸመ አይሸሽም፤በሥራው ስለሚተማመን ባለበት ይቆያል።በደል የፈጸሙትን፣ሕዝብ የጎዱትን፣አገርህን ለመበታተን የሚጥሩትን ወገኖቼ ብለህ አትጠጋ፣አጋልጣቸው፤አሶግዳቸው።

ጨለማ አልፎ ብሩህ ቀን መምጣቱ አይቀርምና በዚህ የጨለማ አገዛዝ የሚፈጸመው ወንጀል የድል ጎህ ሲቀድ መታየቱ ስለማይቀር ከአገዛዙ ጋር ተባብረህ የሚፈጸመውን በደልና የምትሰጠውን ድጋፍ መርምር፤ሊያጋጥምህ ከሚችለው ታሪካዊ ቁስል ነጻ ለመሆን ዛሬውኑ ምርጫህን አስተካክል።ኢትዮጵያዊነት ወይም ትግራዊነት!ትልቅነት ወይም ትንሽነት! ለዲሞክራሲ መታገልና የነጻነት ባለቤት መሆን ወይም በጠባብ የጎሳ በረት ውስጥ ገብቶ የዘላለም መከራ ሲገፉ መኖር።ሌላ ምርጫ የለም!!

የሌላው ማህበረሰብ ተወላጅ የሆንከው ኢትዮጵያዊም ጎሰኛ በሆነው አስተዳደር በደረሰብህ በደልና ኢሰብአዊ ጥቃት ተነሳስተህ እንዳንተ በስርዓቱ ተበድሎ የኖረውን ወገንህን በቋንቋው ወይም በጎሳ ግንዱ ከጨቋኞቹ ጋር አዳብለህ አታጥቃው፡ሊያጠቁትም የሚነሱም ካሉ አይሆንም በላቸው።እስከአሁን ድረስ ያሳየኸው ጨዋነት አይለይህ።እልህ አስጨራሽ ሁኔታዎች ሊፈጠሩና ሊገፋፉህ ይችሉ ይሆናል፣ግን እጅ አትስጥ።ፈተናውን በለመደው ትእግስትህና ጨዋነት ተወጣው።ተቃውሞና ሃይልህ በገዢው ቡድንና የዚያ ተከላካይ በሆነው ተቋም ላይ ያነጣጠረ ይሁን።ሰላዮችንና የስርዓቱን አገልጋዮች ከሌላው ሰላማዊ ሕዝብ ነጥለህ ተመልከት።

ለተጨማሪ ግንዛቤ ከዚህ በታች በዩቱብ የተላለፈውን ጥሪና መልእክት ታዳምጡ ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁ።

https፡//youtu.be/7WQcSmVdTQ8

በአንድነት ለአንድነትና ለነጻነት!!

አገሬ አዲስ

ከወያኔ ለመገላገልም  ሆነ ለመደራደር- መተባበርና መጠናከር –ይገረም አለሙ

$
0
0

Unity-1-741x437የዶ/ር መረራ ጉዲናን አባባል ልዋስና “በቅድሚያ ሁለት ነገር ልበል”፡፡ የወልቃይት ጠገዴ ኮሚቴ አባላትን ኮሽታ ሳያሰማ ከጎንደር አፍኖ ለመውሰድ ያደረገው ሙከራ ያልተሳካላት ወያኔ  የህዝብ ጥያቄ በወኪል አይቀርብም፣ ጥያቄ ካለው ራሱ ህዝቡ ያቀርባል አለን፣ ሰማን፡፡ አረ አንዴት ሆኖ ? ብለን ታዝበን፣ ወይነው ደደቢት ሲገቡ ትግራውያንን እንወክላለን ማለታቸውንስ አንደምን ዘነጉት ብለን ጠይቀን ውለን ሳናድር በጎንደርና በጎጃም   ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ   ጥያቄውን ሲያቀርብና በቃችሁን ብሎ ሲነግራቸው ደግሞ  ባለቤት የሌለው ሰልፍ አሉ፡፡  ሀራምባና ቆቦ፡፡

ሁለተኛው  ዶር መረራ አሜሪካ በተደረገ ሰብሰባ ላይ የተናገሩት ነው፡፡ ድርጅታቸው በምርጫ 2002  ለመሳተፍ ከበቃባቸው ምክንያች አንዱ  ወያኔ ለተቀዋሚዎች  የተወሰነ ወንበር ሊሰጥ ይችላል ይባል ስለነበር ትንሽ ፍርፋሪ ብናገኝ በማለት አንደነበር  እውነቱን አፈረጡት፡፡ ሌሎቹ አንደርሳቸው ደፍረው አይናገሩት አንጂ አምስት አመት እየጠበቁ በምርጫ የሚሳተፉት ፖለቲከኞች ዋንኛው ዓላማቸው ፍርፋሪ ወንበር አግኝተው በተለይ ራሳቸውን ፓርላማ ማስገባት መሆኑ እሙን ነው፡፡ ምርጫ 97ትን ያየ በምርጫ አይቀልድም ያለው ወያኔ ፍርፋሪ የሚያቀምስ አልሆነም አንጂ፡፡

ሰሞነኛው የድርድር ወሬ፤

ድርድር የሚባለው ነገር ሰሞኑን በየቦታው እየተነሳ ነው፡፡ ጉዳዩ በዚህ ወቅት እንዲነሳ ያስቻለው ሁለት ምክንያት ይመስለኛል፣ አንደኛው የገዢዎችን ገዳይ ሰራዊት እያሰለጠኑ፣ ገንዘብ እየረዱ የባለሥልጣኖችን ጡንቻ እያፈረጥሙ ህዝብ የሚያስገድሉ የሚያስገዙ ሀያላን የሚባሉት መንግሥታት የሚተማመኑበት ኃይል መንገዳገዱ ሲታያቸው ሁሉንም ወገን በማግባባትም በማስገደድም እናደራድር ማለታቸው፤ ሁለተኛው ደግሞ ወያኔ በጨነቀው ግዜ ድርድርን ለውጥረት ማስተንፈሻና  ለወንዝ መሻጋሪያ የሚጠቀምበት መሆኑ፤ ከቀደመ ታሪካቸው መታወቁ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ በምርጫ 97 ማግስት ቅንጅትና ህብረት በጋራ የጠሩትን የቤት መዋል አድማ ለማስቀረት በዲፕሎማቶች አደራዳሪነት (በአሜሪካ ኤንባሲ ጉዳይ አስፈጻሚ ዋና ተዋናይነት) ከጸሀይ በታች በማናቸውም ጉዳይ እንደራደራለን ብሎ አድማውን ያሰረዘው ወያኔ የፈጸመው ክህደት የቅርብ ግዜ ማስረጃ ሆኖ ይጠቀሳል፡፡ በመሆኑም  አይሆንም ብሎ ከመዘናጋት ሊሆን የችላል ብሎ መዘጋጀት ተገቢ ነውና ነው የጉዳዩ መነሳት ወቅታዊም ተገቢም ይመስለኛል፡፡

ሕዝብ በደሙ ባቀለመው ትግል ማነው የሚደራደረው?

ኢትዮጵያውያን የወያኔን አገዛዝ  ለሀያ አምስት ኣመት ቻሉ፡፡ ጩኸታቸው የቁራ ሆኖ፣ ትእግስታቸው በፍርሀት ተቆጥሮ ወያኔዎች ከመታረም ይልቅ በንቀታቸው ገፉበት፤ ሁሉን ነገር በጠመንጃችው መከወን አንደሚችሉ በመተማመን ማሰሩን፣ መግደሉን፣ ማሰቃየቱን  ዋና ስራቸው አደረጉት፡፡ ለህዝብ ጥያቄ ምላሻቸው አሸባሪ ሆነ፡፡ የእነርሱ ጣት የሚስበውን ቃታ የሌላው ኢትዮጵያዊ ጣት መሳብ የማይችል እስኪመስላቸው ድረስ በጠብ-መንጃቸው ተማመኑ፡፡

በተቃራኒው ተቀዋሚ ብለው ለራሳቸው ስም ሰጥተው፣ እዛና እዚህ የየራሳቸውን ጎጆ ቀልሰው፣ አለን የሚሉ ፖለቲከኞች በህዝብ ስም ለራሳቸው ስልጣን፣ በዴሞክራሲ ስም ለየግል ጥቅማቸው የሚጥሩ ሆኑ፡፡ ይህም ሆኖ ህዝቡ ከዛሬ ነገ ይማራሉ በሚል  ምረጠን ሲሉት መርጦ፤ ሰልፍ ሲጠሩት አደባባይ ወጥቶ፣ በገንዘቡም በቁሳቁሰም በሚችለው እየደገፈ ለውጤት አንዲያበቁት ጣረ፡፡ የግል ጉዳያችሁን በየጓዳችሁ አስቀምጡና በጋራ ጉዳይ ተነጋገሩ፣ እማማ ኢትዮጵያን ከአገዛዝ ለማላቀቅና ህዝቡን የሥልጣኑ ባለቤት ለመድረግ ተባበሩ እያለም ጠየቀ፡፡ ፖለቲከኞቹ ግን “አድሮ ቃሪያ”  ከመሆን አላላፉም፡፡ እናም  አበው ማርም ሲበዛ ይመራል አንደሚሉት በቅዱስ መጽኃፍም ለሁሉም ግዜ አለው ተብሉ እንደተጻፈው ህዝቡ ተቀዋሚዎቹን ማስታመሙ የወያኔንም አገዛዝ መሸከሙ  በቃኝ አለና ጠሪም መሪም ሳይሻ ርስ በርስ ተጠራርቶ፣ እያንዳንዱ ራሱን በራሱ መርቶ  አደባባይ ወጥቶ ከመትረየስ ጋር ተፋጠጠ፡፡ እኛም ቤት ጠመንጃ እኛም ልብ ውስጥ ወኔ አለ ብሎም መግደል ለለመዱት ሞትም እንዳለ አሳያቸው፡፡

ከዚህ በኋላ የድርድር ነገር ቢነሳ ለጥያቄው መነሳት ምክንያቱ የህዝቡ ትግል ነውና በህዝብ ደም ላይ ቆሞ የሚደራደረው ማነው? ሊታሰብበት ብቻ ሳይሆን በቶሎ መልስ ሊፈለግለት የሚገባ ጥያቄ ይመስለኛል፡፡ወያኔ አንድም ለምርጫ አጃቢነት ሁለትም ለመድብለ ፓርቲ ማሳያነት ሶስትም ለትኩሳት ማብረጃነት የሚጠቀምባቸው  በምርጫ ቦርድ መዝገብ ላይ ብቻ የሚታወቁ ብዙ ፓርቲ ተብየዎች አሉ፡፡ ዶ/ር መረራ ፍርጥ አድርገው እንደነገሩን የፓርላማ ወንበር ፍርፋሪ ለማግኘት የተቀመጡ ፓርቲዎችም አሉ፡፡ በውጪ ደግሞ  የህዝብ እንቅስቃሴ ሲታይ ብቅ እያሉ መግለጫ ከመስጠት ያለፈ ተግባር የማናይባቸው ፓርቲም ህዝባዊ ድርጅትም የሚባሉ አሉ፡፡ ከእነዚህ  አንዳንዶቹ ህዝቡ ራሱን በራሱ አነሳስቶ ባካሄደው ትግልና በደም ባቀለመው ተጋድሎ  የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ደፋ ቀና ሲሉ አይተንና ሰምተን ታዝበናል፡፡ወያኔ የሚገባው በሚያውቀው ቋንቋ ሲያነጋግሩት ነው ብለው ይህንኑም በተግባር እያሳዩ ያሉ ድርጅቶም አሉ፡፡

ታዲያ! ሀያላኑ በወያኔ ላይ ያላቸው መተማመን ተሸርሽሮ፣ ወያኔም ብተኩሱ እንተኩሳለን ከሚለው መልእክትና ለግድያ የላካቸው  ከሞቱበት ዘመቻ በጠመንጃ የትም እንደማይደርስ “ተምሮ” ሁለቱም ለጥገናዊ ለውጥ ተስማምተው ድርድር ቢሉ ለዚህ ውጤት መገኘት መስዋዕትነት የከፈለውንና አሁንም እየከፈለ ያለውን ህዝብ ወክሎ የመደራደር ብቃትም፣ ሞራልም፣ ተአማኒነትም ወዘተ የሚኖረው ማነው? ወይም የትኞቹ ናቸው? ወይንስ “የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሁሉ ” በሚባለው የአፍ ፈሊጥ ሁሉም? ይህ እየሞተ እየደማ እየታሰረና እየተሰቃየ ያለ ህዝብ መቼም እነ እገሌ ይወክሉኝ ይደራደሩልኝ ሊል አይችልም፣ እንዴት ሆኖ፡፡  እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ማሰብና ራስን ለቤተ መንግስት ለማብቃት ሳይሆን ሀገሪቱን ዴሞክራሲያዊት ለማድረግ ከምር የሚታገሉ ኃይሎች መሰባሰብ መነጋገር ማቀድ ቀድሞ መዘጋጀት የሚገባቸው፡፡

ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ፣. ለመሆኑ  ፖለቲከኞቻችን ፣ምሁራኖቻችን ከምር ለለውጥ እንዲነሱ  የስንት ሰው ህይወት መጥፋት አለበት? በአንድ ጀንበር ከመቶ ያለነሱ ዜጎች መገደል የግል አጀንዳውን በየኪሱ አስቀምጦ ከገዳዩ አገዛዝ ሕዝብን ለመገላገልም ሆነ ለድርድር ለማንበርከክ  በቁርጠኝነት አንዲነሳ ያላደረገው ፖለቲከኛም ሆነ ምሁር ስለ ወያኔ ገዳይነት ለመደስኮር ምን የሞራል ብቃት ይኖረዋል?  በዚህ ውቅት አርበኞች ግንቦት 7 እና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ጥምረት የመፍጠራቸው ዜና አስደሳችና ወቅታዊ ነው፡፡ አለመታደል ሆኖ አርአያነቱን ከመከተልና ከሚመስሉትና ከሚመስላቸው ጋር ከመተባበር ለተቃውሞ የሚጣደፉና እንከን ለማውጣት የሚሯሯጡ አንደማያጠፉ ይገመታል፡፡

ሀያላኑ በሚያውቁበት ጥቅማቸውን የማስጠበቅ ስልት፣ ወያኔም በተካነበት  እንደ ሰንቤሌጡ አጎንብሶ  ወጀቡን የማሳለፍ ብልጠት ተስማምተው የድርድር ነገር ቢነሳ ቀድሞ የሚጠሩትና ተሸቀዳድመው የሚገኙት የወያኔ መጠባበቂያዎቹ ናቸው፤ከዛ የወንበር ፍርፋሪ ለማግኘት የሚታገሉት፡፡ እነዚህ የወያኔን ህልውና ለመታደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ለመስማማት የሚገዳቸው አይደሉም፡፡መሰረታዊ የለውጥ ጥያቄ የሚያነሱ ወገኖች ከእነዚህ ጋር ተዳብለው ለድርድር ቢቀርቡ ተግዳሮት የሚገጥማቸው ከወያኔ በላይ ከእነዚህ ፓርቲዎች ይሆናል፡፡ ይህ ሲሆን ደግሞ ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን አክብረው  የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች በምርጫ የሚያዘውን ሥልጣን በድርድር ስም በአቋራጭ ለማግኘት አልመው ተቀባይነት የማያገኙ ጥያቄዎችን በማንሳት ድርድሩ ለውጤት አንዳይበቃ  እያደረጉ ኃይሎችን  በመቃወም ከዚህ አድራጎታቸው እንዲቆጠቡና ለድርድሩ መሳካት አንዲሰሩ  ጠየቁ የሚል ፕሮፓጋንዳ ልንሰማ አንችላለን፡፡

ለመታገልም ለመደራደርም መጠንከር፣መተባበር፤

በቃኝ ብሎ የመጨረሻው መጀመሪያ የሆነውን ትግል የጀመረው ህዝብ  የሚያካሂደው ትግል  በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ እንዲቀጥል የሚያስችሉ እገዛዎችን ከማድረግ ባሻገር  በግል በመጠናከርና በጋራ ተባብሮ በመስራት በሕዝብ ተቀባይነት ያለው፣ በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ   ከወያኔ አንጻር  አማራጭ ተደርጎ የሚታይና ከእርሱ ውጪ ድርድር ውጤት አያመጣም ሊባልለት የሚበቃ ሀይል ሆኖ መውጣት ያስፈልጋል፡፡ ይህ ሀይል በአንድ በኩል ከህዝቡ ትግል በተጨማሪ ወያኔን ለድርድር ለማንበርከክም ሆነ እምቢ ካለ ለማስወገድ የሚያስችል የተጠናከረ ትግል ማካሄድ፣ ከዚህ ጋር አብሮ በምንም ይሁን በምን ወያኔ ወደ ድርድር ከመጣ በሚል የመደራደሪያ አጀንዳዎችን አስቀድሞ ማዘጋጀትና አይነኬ ቀይ መስመሩን በግልጽ ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡

ይህ ሲሆን ወያኔ ለመጠባበቂያነት ያስቀመጣቸው የግለስብ ፓርቲዎች ቢያንስ በሀያላኑ መንግስታት ዘንድ ለድርድር አይታሰቡም፡፡ ለወንበር ፍርፋሪ የሚታገሉት ደግሞ  ብቻቸውን ለድርድር ለመቅረብም ሆነ  መሰረታዊ የለውጥ አጀንዳ ያላቸውን ለመሞገት የሞራል ብቃት አይኖራቸውም፡፡ የእኛን አድል ፈንታ ሲወስኑልን የኖሩትና አሁንም በዚሁ ለመቀጠል የሚዳዳቸው ሀያላንም አንዳንድ ፕሮፓጋንዳቸው እንጂ ተግባራቸው ጎልቶ የማይታይ ፖለቲከኞችን በጓዳ በር እየጠሩ የሚያካሂዱት ስራም ይሁን ሴራ ውጤት አንደማያመጣላቸው ይገነዘባሉ፡፡

እናም በሀገራችን በአብዛኛው አይሆንም የተባለው  ሲሆን፣  ይሆናል የተባለው ሳይሆን ሲቀር እያየን የመጣን አንደመሆኑ አይሆንም ብሎ ተዘናግቶ አጋጣሚ ቢሆን ሱሪ በአንገት ከመንደፋደፍ በሁሉም ዘርፍ ተዘጋጅቶ መገኘት ጠቃሚ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ በየግል መጠናከርና በጋራ  ተባብሮ መቆም በጣም በጣም አስፈላጊና ወሳኝ ነው፡፡ ትግሉ  ለሥልጣኑ መቀጠል  ሀያ አራት ሰአት ከሚሰራ ሀይል ጋር በመሆኑም ግዜ የለም፡፡አዎ ሕዝቡ ቀድሟል ግዜ የለም ፡፡

እንደው ለመሆኑ ይህ የግፍና የገፍ ግድያ በቁጭት ያላነቃው፣ በምሬት ያላነሳሳውና ያላስተባበረው፣ ከራስ በላይ አንዲያስብም ያላደረገው ወዘተ ፖለቲከኛና ምሁር መቼና ምን ሲሆን ይሆን የሚነሳው ! !

ኢትዮጵያ ሆይ! ከሰይጣን ተላላኪ ካህን እንዲገላግልሽ እጆችሽን ወደ ሰማይ ትዘረጊያለሽ! -በላይነህ አባተ

$
0
0

1-eregna-newyorkበላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

መጽሐፉ እስተንፋስ ያለው ሁሉ እንዲተነፍስ ያዝዛል፡፡ ዳሩ ግን ካህናት ይህንን የመጽሐፍ ቃል በመሻር የሕዝቡን እስተንፋስ ለመዝጋት የሰይጣን ተላላኪ ሆነው ተሰልፈዋል፡፡ ሰይጣን  እንደ እግዚአብሔር በአካል ባይታይም በጭራቅነቱ፣ በውሸታምነቱ፣ በከሐዲነቱ፣ በአታላይነቱ፣ በሌባነቱ፣ በስግብግብነቱ፣ በከፋፋይነቱና በክብርየለሽነቱ ይታወቃል፡፡ እነዚህ የሰይጣን ባህሪያት በባዕዳን ከወንበር የተጎለቱትን ባንዳ ገዥዎች ይገልጧቸዋል፡፡ ካህናት በተለይም አቡኖችና አቡኖችን እንደ መጋዣ የተሸከሙት ጳጳሳት ለገንዘብና ለስልጣን ሲሉ አምላካቸውንና አገራቸውን ክደው የባንዳዎች ተላላኪ ሆነው የኢትዮጵያን ሕዝብ ልሳን ሊዘጉ ሲሯሯጡ ይታያል፡፡

ኢትዮጵያ ሆይ! እነዚህ ካህናት ልጆችሽ ሲታረዱ፣ ሲገረፉ፣ ሲታሰሩ፣ ሲሰደዱና ሲራቡ አብረዋቸው ቆመው አያውቁም፡፡ ዛሬ ይባስ ብለው እነዚህ ቆብ ደፊ፣ ሸማ ጠምጣሚ፣ ዘንግ ሰባቂ፣ ጸናጽል አፋጪና ከበሮ ደላቂ ካህናት ከፎቃቸውና ከሉመዚናቸው እየወጡ የቁርጥ መቁረጫ መስቀላቸውን አንጠልጥለው ከጭንቅ የገቡትን ነፍሰ-ገዳዮች ለመታደግ ልፋጭ እንደለመደ ውሻ ከልጆችሽ ደጆች ሲልከሰከሱ ይታያሉ፡፡ አንቺም ይህን በሰይጣንና በሰይጣን ተላላኪዎች የሚፈጸም ከራስ ዳሽን የረዘመ ግፍ ችለሽ ተቀምጠሻል፡፡ እባክሽ እማማ እነዚህን የሰይጣን ተላላኪ ካህናት “ልጆቼ ሲገደሉ አትግደል አላላችሁም፤ ሲገረፉ አትግረፍ አላላችሁም፤ ሲራቡ አላበላችሁም! ሲሸጡኝ አልከለከላችሁም” ብለሽ ደጀ ሰላም እንደ ገባ ውሻ አብከንክነሽ አባሪያቸው፡፡

ኢትዮጵያ ሆይ! እግዚአብሔር ለልጆችሽ ክፉና ደጉን እንዲለዩበት አእምሮ፣ ሃይማኖትና ጥበብ ከዓለም በፊት ሰጥቷቸው ነበር፡፡ ቅዱሱ መጽሐፍም ነጣቂዎችንና ተኩላዎችን ከፍሪያቸው ታውቃላችሁ ሲልም አስተምሯቸው ነበር፡፡ ምነዋ ዛሬ የተማሩት ልጆችሽ የተማሩትን ረስተው ካህናትን በስራቸው ከፍሪያቸው መለየት አቃታቸው? በየትኛው የቅድስና ሥራቸው የነፍሰ-ገዳይ ተላላኪ አቡንና ጳጳሳትን ብፁዓንና ቅዱሳን እያሉ ጠሯቸው? እባክሽ እናት ዓለም ልጆችሽ ቆብ የደፋውን ተላላኪ ካድሬ አባ እያሉ እንዳይጠሩ፤ መስቀል የጨበጠውን የሰይጣን ተከታይ ይፍቱኝ እንዳይሉ፤ ካባ የደረበውን ከርሳም አቡንና ጳጳስ ብፁዕና ቅዱስ እያሉ ከመለኮት እንዳይጣሉ ምከሪያቸው!

ኢትዮጵያ ሆይ! እንደ ዛሬው በባዕዳን ሴራ የደም አበላ ስትሆኝ ልጅሽ አቡነ ጴጥሮስ እንደ እንደተሰዋልሽ ታስታውሻለሽ! ምነዋ ዛሬ በስንት ለጋ ልጆች ሰማእታት ተንበሽብሸሽ የካህን ሰማእት መካን ሆንሽ? ምነዋ እናትዬ ጅብ ሲበላ ጅብ ተከትለው የፍታትና የተዝካር ልፋጭ በሚጎትቱ የካህን ውሾች ተሞላሽ?

ኢትዮጵያ ሆይ! ከጠላቶችሽ እንጅ ከአንቺ ጋር የሚሰለፍ እንደማይኖር ታውቂያለሽ፡፡ ዙምባቤ ሌባ ሲታሰር ባዙቃ እሚነፉት ምዕራባውያን ባሳደጓቸው ውሾች የልጆችሽ ደም እንደ ጎርፍ ሲፈስ ውሾቹን መቀለቡን እንደቀጠሉም ትረጃለሽ፡፡ ይህንን ሴራ የተገነዘቡት ልጆችሽም ክብርሽን ለመመለስ ደማቸውን እያፈሰሱ እንደሆነም ታውቂያለሽ! ምነዋ ታዲያ እናት ዓለም የሰማእት ልጆችሽን ተዝካር እሚዝቅ እንጅ ነፍሳቸውን የሚታደግ ካህን አጣሽ? ምን ብታስቀይሚው ለሰይጣን እሚላላክ ሲኖዶስ ከእምብርትሽ እንደ ጦር ተከለብሽ?

ኢትዮጵያ ሆይ! ከሰይጣን ተላላኪ ካህን እንዲገላግልሽ እጆችሽን ዛሬም ወደ ሰማይ ትዘረጊያለሽ!

 

ነሐሴ ሁለት ሺ ስምንት ዓ.ም.

ተይ አንቺ ውሻ!!!   በዮሴፍ ሙሉጌታ  ባባ (ዶ/ር)

$
0
0

 

kankokunmalimaali@gmail.com

ክፍል 12

Woyane Generals -- satenaw  ጭብጥን በጭብጥ መመከት የማይፈልጉ አንድ አንድ ሰዎች፣ ብዕርን እንደ ጦር ይፈራሉ። በእርግጥ ሰውዬው እንዳለ ‹‹ብዕር የወጋዉን ቁስለኛ ዶክተር አያድነዉም!›› ከማንኛውም የጦር መሣሪያ በላይ እሳት የሚተፋ ብዕር የሚፈራ ለዝህ ይመስለኛል። በሀገራችን ኢትዮጵያ ‹‹ፍደል ቆጠርኩ›› የሚል ጥሩንባ ነፊ፣ ለተነሳው ሐሳብ/‹‹ክርክር›› ምክንያት ማቅረብ ስያቅተው፣ ተቃራኒውን/ሌላውን ወገን ለማሸማቀቅ፣ የስድብ ውርጅብኝ ማጦዝ ይጀምራል። እንድህ ዓይነቱ ሕፀፅ ‹‹አህያውን ፈርቶ ዳውላውን›› (Argumentum ad Hominem) ይባላል!! በሥነ-አመክንዮ፣ ሐሳብን በሐሳብ መመከት ማለት፣ ‹‹አንድ በቂ ምክንያት ከሃምሳ ሰበቦች የተሻለ ነዉ!›› የሚለውን አባባል በትክክል መረዳት ማለት ነው።

በሕዝብ ስም የራሳቸውን ኑሮ አደላድሎ መኖር የሚፈልጉ ሰዎች፣ ማንኛውንም ‹‹ነገር›› ከነባራዊ እውነት (Objective Truth) አንፃር ለመረዳትና ለማብራራት አይፈልጉም። ያላቸው ብቸኛ አማራጭ፣ በተለያዩ ድኅረ-ገጾች ላይ ቅዱሱን ነገር ፍጹም እርኩስ፣ እርከሱን ደግሞ ፍጹም ቅዱስ አድርጎ ማቅረብ ነው። ይህንን ስያደርጉ ትክክለኛ ስማቸውን ይቀይራሉ። በዝህ የተነሳ፣ አብዛኛው ሰው የሚደርስበትን ትችትና ስድብ በመፍራት፣ እውኔታውን ለመጻፍ አይደፍርም። በተለይ፣ አድናቆትንና ክብርን አብዝቶ የሚሹ ምሁራንና ጻሐፍዎች፣ ከሌላ ወገን የሚሰነዘርባቸውን ሂስ/ማስፈራሪያ/ስድብ መቋቋም ይሳናቸዋል።

አንድ ጸሐፍ/ተመራማር አንዱን ወገን ላመስደሰት፣ ሌላውን ደግሞ ለማስከፋት እስከጻፈ ድረስ፣ መቼም ቢሆን ቡከን መሆኑ የማይቀር ነገር ነው። የምርምር ዓለም እስከገባኝ ድረስ፣ የአንድ ጸሐፍ/ተመራማር ዋና ተልዕኮ መሆን ያለበት አንድን ወገን በጅምላ ማዋረድ (ማስከፋት)፣ ሌላውን ወገን ደግሞ ማወደስ (ማስደሰት) ሳይሆን፣ በሰከነ መንፈስ እውነቱን ጽፎ ማኅበረሰቡን/ግለሰቡን ማስተማር፣ መገጸጽና ማስረዳት ብቻ ነው።

ይሁን እንጂ፣ ሌላውን ወገን ላለማስቀየም በሚል ሰበብ፣ የማያምኑበትን ነገር እንደ ወረደ ተቀብለው ጽፈው የሚያስተምሩ ሰዎች አሉ። ይህ ደግሞ ቡከንነትና በጣም አሳፋር ድርጊት ነው። ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ስብሃት ገብረ-እግዚብሄር ለተስፋዬ ገ/አብ የለገሰውን ምክር መቼም ቢሆን መርሳት የለብንም፤ “ሰዎች ሲያደንቁህ አትኩራራ! ሲያጥለሉህ ደግሞ አትደንግጥ። የምረግሙህም የሚያደንቁህም በብዛት ይፈጠራሉ። መልስ እንዳትሰጥ። ይህን እርሳዉና ሌላ መፅሐፍ ጀምር።”

‹‹የሰው ልጅ ህሊና ትንሹ እግዚአብሔር ነው!›› ከተባለ፣ አንድ ግለሰብ ትክክለኛውን ነገር ጽፎ ማስተማር እንጅ፣ የለሎችን ዛቻ/ስድብ ፈርቶ እውነቱን መደበቅ የለበትም። በዓሉ ግርማ እንድህ ይላል፤ ‹‹ድፍረት የሌላት ብዕር ወረቀት ባታበላሽ ይመረጣል፣ ከአድርባይ ብዕር ባዶ ወረቀት ብዙ ይናገራል።›› እንድህ ዓይነቱ ድፍረት ግን ንብረትና ልጆች ላፈሩት ግለሰቦችም ሆነ ‹‹ከአስር ድግሪ አንድ ግሮሰሪ›› ቢሎ ለሚፈላሰፉ አድርባዮች ላይዋጥላቸው ይችላል። ይሁን እንጅ፣ ገንዘብና ህሊና የተሰማሙበት ጊዜ አልነበረም፤ አይኖርምም። ስለዝህ፣ የሰው ልጅ ለእውነት የመኖርና የመሞት ግዴታ አለበት።

ፍልስፍና በተፈጥሮው የአዞ-ቆዳ አለው! ‹‹ዳንሰኛውን ከዳንሱ ነጥሎ ማዬት የማይችሉ ሰዎች›› የሚሰነዝሩትን ማንኛውም ዓይነት አፍራሽ ትችት (ስድብ፣ ማስፈራሪያ፣ ዛቻ…ወዘተ) የማስተናገድ አቅም አለው።  በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ፣ ስፍር-ቁጥር የሌላቸው ጥያቄዎች ይከሰታሉ። ለእነኝህ ጥያቄዎች እንዳስፈላግነቱ ጊዜያዊና ዘላቂ መፍትሔዎችን ማፈላለግ፣ የፍልስፍና ተፈጥሯዊ (ሳይንሳዊ አላልኩም!) ግዴታ ነው። ይህንን ተልዕኮ በማሳካት ሂዴት ውስጥ፣ ከሌላ ወገን ለሚሰነዘርበት ማንኛውም ዓይነት አፍራሽ ትችቶች እጅ መስጠት የፍልስፍና ተፈጥሮአዊ ባህርይ አይደለም። በሰው ልጅ ታሪክ ውሰጥ፣ ፍልስፍና ፈላስፎችን እየቀበረ፣ ራሱ ግን ሕያው ሆኖ የሚኖርበት ዋና ምክንያት ይሄው ነው። ለምሳሌ፣ በሀገራችን ኢትዮጵያ፣ የሰውሻዊያንን ፈተና ማለፍ የሚቻለው፣ በእውቀት ደረጃ ሳይሆን፣ በጥበብ (በፍልስፍና) ብቻ ስንመራ መሆኑን ለአንድ አፍታም ቢሆን መዘንጋት የለብንም።  ለመሆኑ ሰውሻዊያን ማን ናቸው?

ሰውሻዊያን ሰው ያላሰበውን የሚያሳስቡ ሰዎች ናቸው!! ሰውሻውያን የተባሉበት ዋና ምክንያት ደግሞ፣ ድርጊታቸውና አካሄዳቸው ሉሉ ከሚትባል የአፄ ኃይሌ ሥላሴ ውሻ ጋር በጣም ስለምመሳሰል ነው። ዶ/ር መረራ ጉዲና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅ ጉዞና የሕይወቴ ትዝታዎች በተሰኘ መጻፉ ውስጥ ሰለዝች ጉደኛ ውሻ እንድ ሲል አስፍሮ ነበር፡-

‹‹በአፄ ኃይለ ሥላሴ ላይ ተንኮል የሚያስብባቸዉን ሰው ፊቱን አይታ የምትናገር ውሻ አንደነበራቸው፣የውሻዋ ፊት በጣም ከተቆጣ እጅ ሊነሳ የሄደው ባለስልጣን እንዲገደል ወይም እንዲታሰር፣ መጠነኛ ቁጣ ከሆነ ደግሞ፣ ስልጣኑ እንደምቀነስበት፣ አንድ ቀን በጣም ቀልደኛ ነው የሚባለዉ የአፄ ኃይለ ሥላሴ በለስልጣን፣ አቶ ይልማ ዴሬሳ የሚባለው (ይህ ሰው አነጄነራል መንግስቱ ኖዋይ የአፄ ኃይለ ሥላሴን በለሥልጣን ሰብስቦ የጨረሱ ግዜ፣ አቴጌ ታማለች ብለው ሲጠሩት እኔ ኢኮኖምስት ነኝ እንጅ ሀኪም አይደለሁም ብሎ ዲኖዋል ይባላል) አፄውን እጅ ሊነሱ ሲሄዱ፤ ውሻው ያዙኝ ልቀቁኝ ትላለች አሉ። የውሻዋን ጨወታ በትክክል የሚያውቁ አቶ ይልማም ‹ተይ አንቺ ውሻ ሰዉ ያላሰበውን፣ አተሳስቢ› አሉዋት ይባላል።››

   በሀገራችን ኢትዮጵያ፣ አንድ ተመራማሪ/ጸሐፍ ትምክህተኝነትንና ጠባቢነትን አስወግዶ፣ በንፁህ ህሊና ከሱ የሚጠበቀውን ተልዕኮ በሚወጣበት ጊዜ፣ የሉሉን መንቃራ አመል የተላበሱ ሰዎች ሆን ብሎ ችግር ይፈጥራሉ።  ሰውሻዊያንና ሉሉ የአንድ ሣንትም ሁለት ገጽታ ናቸው ያልኩበት ምክንያት ለዝህ ነው። ‹‹ተው ወንድም-አለም ሰው ያላሰበዉን፣ አታሳስብ!›› ማለት ግን ጠቢብነት ነው። ፈጣሪ ከሰውሻዊያን ፍልስፍናዊ ወጥመድ ይሰውረን እያለኩኝ፣ በማረፊያ በቀለ ግጥም የዛሬ መጣጥፌን ላሳርግ!

 

እንደ ተንጣለለ―አንደ ውብ ከተማ

ባንድ ጎንህ ብርሃን―በሌላው ጨለማ

ግማሽን ገልጠህ―ግማሽህን ግጠም

ልክ እንደ ጨረቃ―ተደበቅ ግድየለም

ይበቃኛል በርግጥ―ግማሽህን ማየት

ግማሽ በመሆኑ―ሰው የመሆን እዉነት

 

በክፍል 13 ‹‹የዶ/ር መረራና በእውቀቱ መንገድ!›› እንመለከታለን

ቸር እንሰንብት!!!  

 

የማንቂያ ደውል።- ዳዊት ዳባ

$
0
0

Bell-123909540w1በሀገራችን እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ እንቢተኝነት የነፃነት የእኩልነት የፍትህና የኢኮኖሚ ጥያቄ መሆኑን ሁሉም የሚገነዘበው መሆኑ ቢታወቅም፤ ትግሉ የህዝባችንን ጥያቄ በመለሰ መልኩ እንዲጠናቀቅ ምን  ይጠበቃል የሚሉትን ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን ለመዳሰስ እንሞክራለን።

የፖለቲካ ድርጅቶች፤- የህዝባችንን ጥያቄ በሀይልና በማሸበር ለማፈን የተለመደውን ተግባሩን ወያኔ ተያይዟል። ህዝብ እንደተፋው አሁንም ለመቀበል ዝግጁ አይደልም።  ድርጅቶች ወቅቱ የሚጠይቀውን ሀላፊነት ተገንዝባችሁ የህዝቡን ጥያቄ ግምት ውስጥ ያስገባና ለውጡን ሊሺከምና ሊያሻግረን የሚችል ብሎም ባለድርሻዎችን ሁሉ ያሳተፈ መፍትሄ እንደምትሰሩ ይጠበቃል።

ትግሉን የሚያንቀሳቅሱ ሀይላት፤- እስካሁን የሰራችሁት ስራ  የሚያመለክተው አንድ ታላቅ ነገር በዜጎች ዘንድ ለውጥ የሚታለም ብቻ ሳይሆን የሚታይ አልፎም የሚጨበጥ ማድረግ ችላችሗል።  አድካሚ የሆነው ስራና የበዛ ሀላፊነትን ለመሸከም መድፈራችሁ የአጥፊውን ወገን ያለፈበትና ያለቀለት ታክቲክ በማክሸፍ ደረጃ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። አበው እንደሚሉት ለአንበሳ አይመትሩም ለብልህ አይመክሩም ቢሆንም ለለውጥ ፈላጊውም ሆነ ላገዛዙ አልፎም ለውጪ አገራት  ጥርት እንዲልና ዞሮ ዞሮ መዳረሻው ይህ ስለሆነም “የስርአት ለውጥ” የሚለውን የሚሰማ አድርጉት። አጨራረሱ በቅጡ ታስቦበታል ነው  ግምቱ።

ያሉን ጥቂት የመገናኛ ብዙሀን ትግሉን ያለወገንታዊነት በእኩልነት ሽፋን እየሰጣችሁ መሆኑን እርግጠኛ ሁኑ። የሚተላለፉ መልእክቶች ሆኑ ወቅታዊ ትንታኔዎች የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ የሚያደርሱን  እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ቢደረግም ጥሩ ነው። ሁላችንም እንደምንገነዘበው የተሳሳተ ድምዳሜ ፖለቲካዊ መፍትሄ የመስራቱን ሂደት አስቸጋሪ ያደርገዋል። በንኪያ ሰላምታ የህዝብ ትግል ይጎዳል። ጊዜው የሚሻው የሜዲያ ሽፋን አይነት ትግሉ እራሱ ነው። በመሬት ላይ የሚቀናጅበትን፤ ቀጣይ የሚሆንበትንና አዳዲስ የትግል ፈጠራዎች የሚያጭር ቢሆን ጠቃሚ ነው። መሳርያ የያዘውን የለውጡ አካል የሚሆንበትን ሂደት ማፍጠን ይቻላል። የሚሞተውንና የሚታሰረውን ሰው መቀነስ ይቻላል። ትግሉ ያልተጀመረባቸው ቦታዎች ማስጀመር ይቻላል…..ብዙ ብዙ።

ህዝባዊ ሀርነት ትግራይ፤- ህዝብ የችግሩን ምንጭ በትክክል ተገንዝቧል። “የወያኔ የበላይነት ይብቃ” ነው እያለ ያለው። አስተዳዳራዊ መዋቅሮች እየፈራረሱ ነው። አጋር ድርጅቶች በድርጅታዊ ነፃነትና እኩልነት ጥያቄ ማንቁረት ይዘዋል።  መሳርያ የያዘው እያጉረመረመ ነው። ቅሬታውን ተኩሶ እስኪገልፀው መጠበቅ ይቻላል። የሲቪል አስተዳደሩን አፍረሶ በወታደር አገዛዝ መተካት ለችግሩ መፍትሄ ተደርጓል። ኦሮሚያ ላይ ይህ ሆኗል። አማራ ክልልም በቀጣይ የሚጠበቅ ነው። ግን አልሰራም አይሰራምም። ይህ በአለማቀፍ ደረጃ የሚፈጥረው ተፅኖ እያያችሁ ነው። ትላልቆቹ ብሄረሰቦች የሚለውን እውነት የወለደው ይህው ነው።  በአጠቃላይ ቀላል የሆነ ማንቂያ ደውል ለናንተ መስቀመጥ የሚቻልበት ሁኔታ ያለ አይመስልም። ያም ሆኖ ጊዜው የሚሻውን ለየት ያለ የመፍትሄ ሀሳብን ይዞ መምጣትና መሞከር ይቻላል። መንግስታዊ ሽብር እየፈፀማችሁና ዜጎችን እየጨፈጨፋችሁ ለመዝለቅ መሞከሩ ግን የትም አያደርስም።

የወያኔ ሀርነት ትግራይ ደጋፊዎች፤- ከተለመደው ፋይዳ የሌለውን ደረቅ ክርክራችሁን አቁሙ። የህዘብ አሸናፊነት አይቀሬ ነውና አገዛዙ ያዋጣኛል ብሎ የገፋበትን  ሽብርና ጭፍጨፋ ላይ በማንኛውም መንገድ የሚገለፅ ድርሻ እያደረጋችሁ እንዳልሆነ ለራሳችሁ እርግጠኛ ሁኑ።  ሊሰሟችሁ የሚችሉ አይመስለንም።  ከቻሉ ከመንግስታዊ ሽብር እንዲታቀቡ መምከሩ ይጠቅማችሗል።  ይህ ባይሆን ግን ህዘብ በየትኛውም መሰዋትነት ድሉን ይጨብጣል። ኪሳርው በህዋዋትና በናንተ ኪሳራ ይወራረዳል።

ድል የህዝብ ነው።

ዳኮታ የጥናት ማእከል።

8/13/2016

dakotareserech2@yahoo.com

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>