Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

የአጋርነት መግለጫ ለጎንደር ሕዝብ እንቅስቃሴ –አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ከሎስ አንጅለስ እና አካባቢው

$
0
0

በ7/24/2016
amharaበሎስ አንጅለስ እና አካባቢዋ የምንኖር አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ተገናኝተን በአሁኑ ሰዓት በጎንደር የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ማንነታቸውን በአግባቡ በመጠየቃቸው እየደረሰባቸው ስለአለው ስቃይ እና በሌሎችም አካባቢዎች እንዲሁ መሰረታዊ መብታቸው እንዲከበርላቸው ጥያቄ በማንሳታቸው እየደረሰባቸው ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት በሰፊው ተወያይተንበታል።

በተለይ በአሁኑ ሰዓት የወልቃይት ሕዝብ መሬቱን በግፍ ተቀምቶ የበይ ተመልካች መሆኑ ሳያንሰው የማንነቱ መግለጫ የሆነውን አማራነቱን በመካድ ያልሆነውን ነህ ተብሎ የተጫነበትን የማንነት ተፅእኖ በመቃወም በሚአደርገው የሞት የሽረት ትግል ይህ ጀግና ሕዝብ እያደረገልን ለአለው ጥሪ ዝምታን የሚመርጥ ህሊና ስለማይኖረን የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ ቆርጠን ተነስተናል።

ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ከምስራቅ እስከ ምእራብ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመሰረታዊ መብቱ በመታገሉ ምክንያት እየደረሰበት ያለውን ማንኛውንም ኢሰብአዊ ድርጊት በጥብቅ እናወግዛለን። እየሞተ፣ እየተደበደበ፣እየታሰረ፣ ከቦታው እየተሰደደ እና ተዘርዝረው የማያልቁ ግፎች እየተፈጸሙበት  በእነዚህ ድርጊቶች ሳይበገር እየአደረገ ያለውን ተጋድሎ  ማድነቅ ብቻ ሳይሆን ለሚአደርገው ተጋድሎ አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል ብለን የምናስባቸውን ሁሉ በየጊዜው እየተመካከርን ወደተግባራዊ እንቅስቃሴ ለመግባት ብሎም ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚአደርጉትን በማንኛውም መንገድ ለመርዳት ወስነናል።

በአገራችን ኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢ እየተፈፀመ ያለው ግፍ የሚካሄደው በጭካኔው፣ ከባእድ የሱዳን ወታደሮች ጋር ወግኖ ወገኖቹን በማጥቃት፣በመካከላችን ያለውን ትስስር ለማላላት በማከፋፈል ስራው እና ለግድያ በአሰለጠነው አግአዚ በመመፃደቅ ሽብር በመፍጠር ተወዳዳሪ በሌለው የወያኔ ስርዓት ስለሆነ መፍትሄው ይህን ስርዓት ከስሩ ገርስሶ መጣል ብቻ መሆኑን ተረድቶ ሕዝቡ ትግሉን በሁሉም አቅጣጫ አቀጣጥሏል፡፡ እኛም በየቦታው የተነሳው  የፃነት ጥያቄ መልስ የሚአገኘው እና የዜጎች ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ተጠብቆ በሰላም መኖር የሚቻለው የሰላምና የአንድነት ጠንቅ የሆነው ስርዓት ሲወገድ ነው ብለን እናምናለን። በአንድ አካባቢ የሚፈፀመው አስከፊ ክስተት ነገ በሌላ አካባቢ የሚፊፀም እኩይ ተግባር ስለሆነ ይህንን ኃይሉን አሰባስቦ በተናጠል በሕዝብ ላይ ጉዳት እያስከተለ ያለውን ስርዓት ለማስወገድ የትግሉን አድማስ በማስፋት በሁሉም አቅጣጫ በአንድነት ስሜት ኃይሉን አሰባስቦ በጋራ እንዲነሳ ጥሪ እናስተላልፋለን። የሁላችንም ጠላት የሆነውን ወያኔ አስወግደን ሁላችንም ተጠቃሚ የምንሆንበትን ነፃነት ማግኘት የምንችለው አንድነት ኃይል መሆኑን ተረድተን በመቀራረብ በጋራ ስንሰራ ብቻ በመሆኑ ይህንን በመረዳት እየተቀራረቡ  ለመስራት ወስነናል።

 

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

 

ሞት ለወያኔ

አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ከሎስ አንጅለስ እና አካባቢው


ለወያኔ ህልውና ጠባቂዎች የቀረበ ጥሪ?   (“”ድሪባ ገመቹ””)

$
0
0

Woyane
ህዋሀት ወያኔ ሀርነት ትግራይ በኖረበት በሃያ አምስት አመታት በትግራይ ህዝብ ስም ለስርአቱ ቅርብ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ቱጃር ሆነዋል በርካታ ህንጻዎች ገብተዋል በተለያየ የሀገሪቱ ቁልፍ የንግድ ወይም በስልጣ እርከኖች ላይ ቆራጭ ፈላጭ ሆነው ተሠማርተዋል፣

በተቃራኒው ምንም  የሌለው የእለት ጉርስና ልጆቹን ወደ ትምህርት የሚልክበት የሌለው የትግራይ ተወላጆችም እንዳለ አይካድም, ነገር ግን እነዚህን የስርዓቱ ተጠቃሚ ያልሆኑ የትግራይ ተወላጆችን ወያኔ በተጨነቀበት ሠአት እየሠበሠበ ሠላማዊ ሰልፍ እያሥወጣ ፕሮባጋንዳ ሲሰራባቸው እና ከሌላው ኢትዮጵያዊያን ጋር እያጋጨ የራሡ የስልጣን ፍጆታ ማሟያ አድርጎ ተጠቅሞባቸዋል,
ሌላው ማህበረሰብም የትግራይ ህዝብ የስራዓቱ ተጠቃሚ ነው ወደሚል ድምዳሜ  እንዲደርስ አድርጎታል፣

አብዛሀኛው የትግራይ ተወላጅ የስርዓቱ ተጠቃሚ ባዮሆንም እንኳ ህውሀት ወያኔ ሀርነት ትግራይን ከመጥፎ ድርጊቱ እንዲታቀብ ሲቃዎም አይታዬም, በጣም በጣት የሚቆጠሩ ነገ የሚመጣውን አደጋ የተገነዘቡ ናቸው ህውሀት ወያኔ ልክ እንዳልሆነ እየተናገገሩ ያሉት፣
አብዛሀኛው የትግራይ ተወላጅ ግን ህውሀትን እንደ ፈጣሪው እየተመለከተ ህውሃት ስለሚበድለው ሌላኛው ህዝብ ዴንታ የሌለው መስሎ የሚታየው፣
ለምን ብለን ብንጠይቅ ወያኔ በትግራ ህዝብ ስም በርካታ ነገር ለመዝረፍ ይመቸው ዘንድ የውሸት ፕሮባጋንዳ ሲሰራበትና ህዝቡ ህዋሀትን አምኖ እንዲቀበል ለረጅም አመታት በትግራይ ህዝብ ላይ ሰርቶበታል፣

በአሁን ሠአት ለትግራይ ተወላጆች ጥያቄ የምናቀርብ እትዮጵያኖች ለትግራይ ተወላጅ በተደጋጋሚ ጥሪ እያስተላለፍን እንገኛለን?

ጥሪአችንም”
ህውሀት ወያኔ ሀርነት ግራይ የኢትዮጵያን ህዝብ ሲገድል ሲያስር ያለምንም ርህራሄ ቶርቸር ሲያደርግ ለስርአቱ ታማኝ ናቸው ያላቸውን በሀብት ሲያበለጥግ ኢሉንታ የሌለው የሹመት አሰጣጥ ሀገሪቱን በእውር ድንብ እንመራለን በማለት በበርካታ ችግሮች የተተበተበች ሀገር እንድትሆን አድርገዋታል, ይህንን ደግሞ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሲመለከት ኖሯል,
ዛሬ ህዝቡ ትግስቱ ተሟጧል መብቱን ለማስከበር ቆርጦ ተነስቶአል።
የህዝብ ቁታ እንደማዕበል እየተጥለቀለቀ ለወያኔ አስደንጋጭ  ሆኖበታል፣ አንዳንድ የህውሀት የስርአት ታማኝ ተለላኪ በሆኑት ላይ ህዝብ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል, በአሁን ሠዓት ህዝብ ዝምብዬ አልሞትም እየገደልኩ እሞታለሁ በማለት ከወያኔ ጋር እየተታኮሰ ይገኛል, ይሄ አሁን እያየን የለነው ጅምር ነው, ነገ በመላ ሀገሪቱ የህውሀት ተልእኮ አስፈጻሚ የሆናችሁ ኢላማ ታርጌት እንደምትሆኑ ከሠሞኑ የህብ ቂጣ መረዳት ትችላላችሁ, ለወያኔ የሚወረወረው  ጦር ሁሉ እናን ጋር እንደሚያርፍ ጥርጥር የለውም, ምክንያቱም አሁንም የወያኔ ተላላኪነታችሁን እስካላቆማችሁ ድረስ ህዝብ አፈሙዙን ወደ እናንተ ማዞሩ አይቀርም,
የህዝብን ቁጣ በምንም ታምር ወያኔ አያስጥልም።
ይህ ከመፈጠሩ በፊት ከአሁኑ ከተበደለው ህዝብ ጎን እንድትቆሙ እና ይህንን የህዝብ ትግል እንድትቀላቀሉ እንጠይቃለን ይህ ትግል እናንተንም ከወያኔ ባርነት ነጻ ለማውጣትም ጭምር መሆኑን መረዳት ይኖርባችኃል????

ህውሀት ወያኔ ሀርነት ትግራይ በሀገራችን ላይ ለሚፈጠረው ችግር ዴንታ የለውም, የትግራይ ህዝብ ከሌላው ህዝብ ጋር ቢጋጭም ለህውሀት ጉዳዬ አይደለም, ወያኔ ሁሌ የሚተጋው ለራሡ ህልውና እና ከሀገር ለዘረፈው ንብረት ብቻ ነው። ለህዝብ ዴንታ የሌለው እንደሆነ ደግሞ የሚያሳየው በትግራይ ህዝብ ስም ይሄንን ሁሉ በደል እየፈጸመ ነው የሚገኘው፣ ለዚህም ነው የትግራይ ተወላጆች ወያኔን ዞር በል በስማችን አትነግድ ብላችሁ ከሌላው ህዝብ ጎን ተሰለፉ ብለን ጥሪ እያቀረብን ያለነው?

ይሄ ትግል የመረረ ነው  በወያኔ ተገፍቶ ቆርጦ ለነጻነቱ የተነሳን ህዝብ ከዚህ በኃላ ማስቆም የማይቻል መሆኑን መረዳት ይኖርብናል, ከአሁኑ እራስን ለማዳን ሠልፍን ማስተካከል አስፈላጊ መሆኑን በአጽኖት እንመክራለን,,,,,???

ሠልፍ የጀግና ነው” ድል የእግዛብሔር ነው!!!!
እትዮጵያ ለዘላለም ትኑር,,,,,,,,,,,,,

የጎንደር ብርሃኖች –ከተማ ዋቅጅራ

$
0
0

13681020_626757367488618_5689809962206469958_n
በአለም አቀፍ ምልክቶች ሶስት ቀለሞችን አብዝተው ይጠቀማሉ አረንጓዴ ቢጫና ቀይ። አረንጓደው የመፍቀድ የይለፍ ምልክቶች ቢጫው የማስጠንቀቂያ ቀዩ ደግሞ የማገድ የማቆም ምልክት ሆነው በአለማችን በምልክትነት ይጠቀምባቸዋል። ኢትዮጵያን እነዚህን ቀለማቶች የአገር መለያ ሰንደቅ አላማ አድርጋ መጠቀም ከጀመረች ከአለም አገራት በፊት  ዘመናቶችን አስቆጥራለች አረንጓዴው የልምላሜ ቢጫው የተስፋ ቀዩ የጀግንነት ምልክት እንደሆነ ያመለክታል። ዛሬ ጎንደር ላይ ካረንጓዴው አልፎ ቢጫው በርቷል ባንድራዋንም ከፍ አድርገው አውለብልበዋል። አስተዋይ መንግስት ካለ የምጥ ጣር መጀመሪያውን ምልክት አሳይተዋል ቀዩ መብራት መብሪያው ግዜው ደርሷል። የዛን ግዜ ምክንያት አያድንም።

ለ25 አመት አማራ ተብሎ ሲገደል ሲሰደብ ሰወቀስ በሌላው ህብረተሰብ የማጥላላት ስራ ሲሰራበት የነበረ  ህዝብ ችሎ እና  ታግሶ ዝም ብው ተቀምጠው ነበር።  ይህ ማለት ኃይል ኖሮት እንደሌለው ጀግንነት ውስጡ ሆኖ እንደሌለው አሸናፊነት ባህሉ ሆኖ እንደተሸናፊነት ለ25 አመት ዝምታን መምረጡ አማራውን እና ኦርቶዶክስን ሃይማኖት አከርካሪውን ሰብረነዋል ብለው ተዛበቱበት። በነገራችን ላይ ኦርቶዶክስም እንደ ኦርቶዶክስ እንዲደራጅ ከተለያየ አካላት የተለያዩ  ጥቃት እና ትችት እየደረሰበት ነው። የኦርቶዶክስን ሃይማቶት በመስደብ እና በማንቋሸሽ የተሰማራችሁ መንግስታዊም ሆናቹ መንግስታዊ ያልሆናችሁ አካሎች ከድርጊታችሁ እንድትታቀቡ ከወዲሁ አሳስባለው በኋላ ልትከፍሉት የማትችሉትን ዋጋ ሊያስከፍላችሁ ይችላልና ጫናውና እርግጫው ከበዛ እንደ ኦርቶዶክስ እንዲደራጅ ታስገድዱታላችሁ ያኔ መቀልበሻው ሲለሚያጥር ከወዲሁ  ከድርጊታችሁ ብትቆጠቡ የሚለውን ትዕዛዛዊ መልእክቴን በዚሁ አጋጣሚ ማስተላለፍ  እፈልጋለው።

ጎንደር እና ኦሮሚያ ያረንጓደውን ግዜ ጨርሰው ቢጫው ላይ ነው ያሉት። አሁን የቢጫው መብራት በወያኔ ላይ በመላው ኢትዮጵያ እንደበራ እወቁ። ይሄ ቢጫ መብራት ወደ ቀዩ መብራት መሄዱ ግድ ነው። ቀዩ ከመብራቱ በፊት እና ሁሉም ነገር ከመፈጸሙ በፊት ቢጫው መብራቱ ሊያሳስብ ያለው ነገር አለ 1 መከላከያ ሰራዊት ቀይ ከመብራቱ በፊት የስርአቱ አገልጋይ ወይንስ የህዝብ? 2ኛ፡ከፍተኛ ባለስልጣናት ለወንበራችሁ ወይንስ ለህዝባቹ? 3ኛ፡ጋዜጠኞች ለሆዳችሁ ወይንስ ለህዝባቹ? 4ኛ፡ለሰላዮች ለጢቂቶች መኖር ወይንስ ለህዝብ መኖር? 5ኛ፡ለሃይማኖት አባቶች ለጨቋኞችን ማገልገል  ወይንስ የተገፋውን ህዝብን ማጽናናት? እንግዲህ ምርጫው የናንተ ነው ቀዩ ከበራ በኋላ ማለፍ የሌለባቸውን በሙሉ ይዞ ያስቀራል። ድል የህዝብ ነውና።

በኢቲቪ በፋና እና  ፌስ ቡክ ላይ በተሰማሩት የወያኔ አቀንቃኞች  እንዲሁም ስድብን ፣ ጥላቻን እና መለያየትን በመፍጠር የፖለቲካ እውቅናን ማግኘት ለሚሹ የፌስ ቡክ የስድብ አባቶች እና እናቶች ወደ ትክክለኘው መንገድ መምጣ ያለባችሁ ግዜ አሁን ነው። ጎንደር ላይ የተለኮሰው ኢትዮጵያን ያጠቃለለ ብርሃናዊ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ቀድመው ለማዳከም  ቢሯሯጡም ቅሉ በያዙት ሚዲያም ወልቃይት የትግራይ ናት ለሚሉት ጠባቂ መከላከያ ተመድቦላቸው ሰልፍ እንዲወጡ ሲደረግ ወልቃይት የአማራ ናት ወገኖቻችንን በግፍ መግደል ይቁም ብለው ለሚወጡት ለጎንደር ህዝብ የተከለከለ ነው ተብሎ የማስፈራሪያ እና የዛቻ ቃሎችም ቢተላለፉበት ቅሉ የጎንደር ህዝብ ግን ቃሉን አክብሮ ዝምታውን ሰብሮ ቁጣውን ለመግለጽ እንደ 97ቱ  የአዲስ አበባ ሰልፍ መሬት አንቀጥቅጥ የህዝብ ሱናሚን በጎንደር ተደግሟል።

ከጎንደር ህዝብ በሰልፉ ግዜ የተላለፈው መልዕክት ኢትዮጵያዊ ወገኑን ሃይማኖት ከዘር ሳይለይ ያስተሳሰረ የወያኔን ጅማቶች የፈታ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በውስጥም በውጪም ያስደመመ ያወያየ  እና ለነጻነት በአንድነት ያነሳሳ ሰልፍ ነበረ።

ወያኔ ለ25 አመት ሲለፈልፍ ዝም ያለው ህዝብ ሞኝ እና ፈሪ የለፈለፈው ደግሞ ጀግና  እና ብልህ አድርጎ በያዘው ሚዲያ ቢያስነግርም በሰላም ዝም ብሎ የተቀመጠውን ህዝብ ነካክተው ነካክተው ጀግና  እና  ብልህ ማን እንደሆነ ይታያል ብሎ እሳት ሆነው ጎንደር ተነሳ ትግሉ ላይቀለበስ ወያኔዎች ኢትዮጵያን ለማነቅ ባዘጋጁት ሸምቀቆ እራሳቸውን ሊያንቃቸው የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ለመድረስ ወደ ቀዩ መብራት ጉዞ ተጀምሯል። በቅርብ ቀን በመላው ኢትዮጵያ ወያኔ ማለፍ ክልክል ነው የሚለው መብራት ፊታቸው ላይ ይበራል። ወያኔ  ስል ወያኔ ህውአትን ብቻ  ሳይሆን ወያኔአዊ ብአዴን ወያኔአዊ ኦፒዲኦ ወያኔአዊ ደህዴን ወያኔአዊ…. እያለ ይቀጥላል።

በጎንደር ህዝባዊ ሰልፍ ላይ የጀግኖች ሰልፍ ካሰኘው  በጥቂቱ ለመጥቀስ

  1. ህዝባዊ ሰልፉን ከማድረግ ምንም አያግደንም መትረየስ እንኳን ቢደገንብን ሰልፉን ከማድረግ የሚያስቆመን ምንም ሃይል አይኖርም
  2. መከላከያ ሰራዊት የአማራ ልዩ  ሃይል እንዲሁም የህውአት ሰራዊት ጎንደርን በመውረር ቀድመው ህዝቡን የማስፈራራት ስራ  በመስራት ሰልፍ የለም ማንም ወደ ሰልፉ እንዳይመጣ በሚወጡት ላይ እርምጃ  እንወስዳለን እያሉ መግቢያና መውጫውን አጋዚ አጥሮ ቢቆይም ሰአቱ ሲደርስ ግን ጀግናው የጎንደር ህዝብ የተደገነበትን መሳሪያ  ሳይፈራ ግልብጥ ብለው በመውጣት አጋዚን አስለቅቀውት ታላላቅ መልእክቶችን ሲያስተጋቡ ውለዋል።
  3. በጣም ያስደመመም እና ወያኔም አስደንግጦ አይኑን ያስፈጠጠ ልቦናቸውን በጭንቀት የሞላው የማስጣንቀቂያ መልዕክት ጎንደሬዎች አስተላልፈዋል። እንዲም በማለት <<መከላከያ  ሰራዊት እና  የአማራ ልዩ  ሃይል እንዲሁም አጋዚ ህዝቡን የምትደግፉ ከሆነ  ከህዝባችን ጎን ቁሙ አይ የምትሉ ከሆነ  ግን አንድ ጥይት ህዝባችን ላይ ቢተኮስ የገባው ሰራዊት ሳያልቅ በህይወት አይወጣም አጸፋችን እጅግ የከፋ  ነው።>> በማለት ጠንካራ እና ቆራጥ እንዲሁ ብስለት የተሞላበት መልዕክት ማስተላለፋቸው በጣም አስደምሞኛል።

ወያኔዎችም ብርክ ብርክ ያደረጋቸው እና ህዝቡም በአደባባይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ይዞ  በመውጣት ሳይወዱ በግዳቸው መስማት የማይፈልጉትን ከድንጋጤ ጋር መራራ  እውነት ህዝቡ ሲነግራቸው ዝምታን የመረጡት ለህዝቡ አስበው ሳይሆን ሊደርስባቸው የሚችለውን አጸፋዊ ምላሽ በመፍራት ተገደው እንጂ። የህዝቡም ጥያቄ ጥቂት አንባ  ገነኖች የሚነግሱባት እና  የፈለጋቸውን የሚያደርጉባት አገር ለአንዴ  እና ለመጨረሻ  ግዜ ጠፍቶ ህዝቡ የሚፈልገውን መርጦ   የፈለገው ቦታ ያለአድሎ መኖር የሚችልበትን እና ሁሉም ኢትዮጵያዊ መብቱ የተከበረባት ስርዓት ለማምጣት ለአንባ  ገነኖች   የመጨረሻውን ማስጠንቀቂያ  ቢጫው መብራት በኢትዮጵያ  በሙሉ በርቷል። ቀዩ  እና የመጨረሻው መብራት በቅርብ ቀን የሚበራበት ይጠብቁ። ብራቮ ጎንደር የነጻነት ፋና ያልበገርነት ተምሳሌት ።

ከተማ ዋቅጅራ

01.08.2016

Email- waqjirak@yahoo.com

 

 

የድጋፍ መልክት እና ይትግል ጥሪ –ከጥቁር አንበሳ ዘብ ለኢትዮጵያ የነጻነት ግንባር

$
0
0

tof
እንክዋን ኢትዮጵያን እና ሕዝብዋን ከዚህ ዘረኛ እና ፋሽስታዊ የወያኔ ቡድን ነፃ ለማውጣት ለሚደረገው የነጻነት ትግል ቀርቶ ፡ አንዲት የጽገሬዳ አበባ ለመቅጠፍም እጅ ይደማል።

የኢትዮጵያ ታሪክ በአብዛኛው ለነፃነት የተደረገ የጦርነት ታሪክ ነው። በርካታ ጦርንቶች ተደረገዋል። እነዚህ ሁሉ ጦርነቶች የተካሄዱት ደግሞ የሌላ አገር ድንበር ገፍተን ለመስፋፋት ባለን ዓላማ ሳይሆን የአገራችንን ሉአላዊነት እና አንድነት ያየር የባሕር እና የብስ ይድንበር ወሰናችንን ባጠቃላይ ኢትዮጵያን ከወጪ ወራሪ እና ሰርጎ ገብ ጠላት ለመከላከል የተደረጉ የመከላከል የተደረጉ ጦርነቶች ናቸው። ለዚህ የመከላከል እና የመልሶ ማጥቃት ውጊያ ከግብጾች ፡ ከቱሮክች ፡ ከደርቡሾች ፡ ከእንግሊዞች እና ከጣሊያኖች ጋር በተደጋጋሚ ተዋግተናል። በእነዚህ ሁሉ ውጊያዎች እና ፍልሚያዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ሕይወት የቀጠፉብቻ ሳይሆን በዘመናዊ ስንቅ እና ትጥቅ የደራጀውን እና የታጠቀውን ፡ የአውሮፓ ፋሽስታዊ ኃይል በማንበርከክ ሚሊዮን ጀግኖች ኢትዮጵያውያን የተፈጠሩበት እና የጥቁር ሕዝብ የነጻነት አርማ እና ክብር ነው። ይህ ጦርነት ፡ በተለያዩ ጊያዚያቶች እና አቅጣጫአዎች የመጡ ወራሪዎችን አሳፍረው  ፡ የመለሱ ጀግኖች ብቻ ሳይሆን እስከዛሬ በአገሪቱ ውስጥ  ሰላም እና መረጋጋት ጠፍቶ የደከመች እና የተበታተነች ኢትዮጵያን ማየት ለሚፈልጉ አረቦች እና አውሮፓውያን እንዲሁም መሰሎቻቸው የውክልና ጦርነት

የሚያደርጉ ባንዳዎችን እና የባንዳ ልጆችን ወያኔዎችን ፈጥርዋል። እናም ዛሬ እነዚህ የባንዳ ልጆች ናቸው አያት አባቶቻቸው ያልተሳካላቸውን የቅዠት ሕልም ለማሳካት ኢትዮጵያን በብሔር ፡ በሃይምት ፡ በቋንቋ ፡ ከፋፍለው አገርን በመሸጥ ሕዝብን እያተራመሱ ያጥፎት መጥፋት የሽብር ስራ በመስራት የበደኖ ፡ የአርባ ጉጉ፡ የአንኩ እና የጋምቤላው ፡ የአማራው እና የኦሮሞው ፡ ፍጅት የዚህ የባንዳ እና የባንዳው ልጅ ባንዳው ለገሰ(መልስ) ዜናዊ እና አረጋዊ በረሄ እና ግብረአበሮቻቸው ወዘተ የእርኩሰታቸው ራዕይ ውጤት ነው። ዛሬም በኦሮሙያ ክልል ፡ የተጀመረውን ትግል ለማኮላሸት የብዙ ኢትዮጵያውያንን ሕይወት በመቅጠፍ በአማራው ክልል የተነሳውን የማንነት ጥያቄ እና ኢትዮጵያዊ የነጻነት ትግል ለማዳፈን በጎንደር በተለይም በወጣቱ ሃይል የተጀመረው ስርነቀል የነጻነት እንቅስቃሴ ፡ ለማስቆም የተደረገው ትንቅንቅ የእነኚህ ባንዳዎች እና የባንዳ ልጆች የጥፋት እርኩስ መንፈስ ራእይ አስፈጻሚ ውጤት ነው። ወደድንም ጠላንም ፡ ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ ብሶት የወለደው የተዳፈነ እሳት በጎንደር ሕዝብ አልበገር ባይነት በጀግንነት እረመጡን ገላልጦ እንደሰደድ እሳት በመቀጣጠል ላይ ይገኛል። ይሂ የግፍ ዋንጫ ሞልቶ ፡ ፈሶ የተጀመረውን ኢትዮጵያዊነት የነጻነት ትግል ምንም ማስቆም የሚችል ምድራዊ ሃይል ከቶ አይኖርም። ይህ ሕዝባዊ አመጽ ፡ ሻጋታው ጸረ ኢትዮጵያ የወያኔ ቡድን ፈጻሜው የመጨረሻው መጀመርያ የመሆኑ አመላካች ነው። በዚህ ታሪካዊ አጋጣሚ የጥቁር አንበሳ ዘብ ለኢትዮጵያ የነጻነት ግንባር ፡ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም ለአማራ እና ለኦሮምያ ክልል ፡ ወያኔን በማስወገድ ለኢትዮጵያ ነጻነት የሚያደርገውን ትግል ያለውን አድናቆት እና ክብር እንዲሁም የትግል አጋርነቱን እየገለጸ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለቀድሞ የመከላከያ ሰራዊ እንዲሁም በውዴታም ሆነ በግዴታ የወያኔን የጥፋት እሜ ለማራዘም ከወንድም እህቶቻቸው ጋር አላስፈላጊ ደም ለተቃቡት የቡድኑ አገልጋይ ወታደሮች የትግል ጥሪያደርጋል።

 

አንደኛ ፡

ውድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወይ ፡ በታሪክህ አይተህው የማታውቀውን ውርደት ፡ ባለፉት የወያኔ የግፍ እና የመከራ አመታት ፡ አይተሃል ፡ ወልደህ ካደክበት ቀዬህ በግፍ ተፈናቅለህ ባይተዋር ሆነህ በሃገርህ እንደሁለተኛ ዜጋ ተቆጥረሃል። በአገርህ በየትኛውም ስፍራ ተዘዋውረህ በነጻነት ሰርቶ የመኖር መብትህን ፡ ተነፍገሃል። በሰላም አብረሃቸው ከምትኖረው ጎረቤቶችህ ጋር በብሔር እና በቋንቋ ሰበብ ተለያይተሃል። ኢትዮጵያዊ በመሆንህ ብቻ ፡ እረሃብ ፡ እስራት ፡ ሞት እና ስደት የአንታ እጣ ፈንታ ሆነዋል። ዝለዚህ ከዚህ የከፋ ውርደት ስለሌለ ሳትውል ሳታድር ለኢትዮጵያ ነጻነት እና ለሰባዊ ክብር ስትል ትግሉን አሁኑኑ ተቀላቀል። ጉልበት ያለህ በጉልበትህ ፡ እውቀት ያልህ በእውቀህ ፡ ገንዘብ ያለህ በገንዘብህ ፡ አረጋዊ እና አዛውንቱ በጸሎት እና ምሕላ ትግሉን አግዙ።

ሁለተኛ፡

ውድ የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ፡ ለአገር ሉአላዊነት እና አንድነት ፡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላም እና ደህንነት ፡ የክፈለከው የላብ ፡ የደም እና የአካል የሕይወት መስዋእትነት ፡ መና ቀርቶ በወያኔ የኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም እንደግል አሽከር ተቆጥረህ ፡ የደርግ ወታደር እየተባልክ ተዋርደህ እና ተንቀህ ለልመና እና ለእስራት ፡ ለሞት እና ለስደት ፡ የተዳረከው በዚህ ግፈኛ እና ዘረኛ የወያኔ ቡድን ነው። አሁን የወያኔ ግፍ ከልኩ ስላለፈ እብሬቱን ለማስተንፈስ እና ግባ ከመሬቱን ለማፋጠን ፡ ሕዝባዊ ትግሉ ተቀጣጥልዋል። እናም ውርደትን እና ንቀትን የተሸከምክበትን ተከሻ ማሳረፍ ከፈለክ ፡ ሞያዊ ብቃትህን ፡ አይበገሬ ኢትዮጵያዊነትህን የምታሳይበት ወቅት አሁን ስለሆነ በያለህበት አካባቢ ያለምንም ቅድመሁኔታ ፡ ለኢትዮጵያ ነጻነት ሕዝብዊ ትግሉን ተቀላቀል እና ሞያዊ እገዛ አድርግ።

ሶስተኛ፡

የወያኔ ቡድን ያረጀ እና የበሰበሰ ፡ በመሞት ላይ ያለ ቡድን ነው። ምንጊዜም ክፋቶች ያልፋሉ ፡ ሕዝብ ግን ቀጣይ ነው። ስለዚህ የዚህን በመሞት ላይ ያለ ቡድን እድሜ ለማራዘም ፡ ከወያኔ ከሚጣልላችሁ ፍርፋሪ ከርሳችሁን እየሞላችሁ የወገናችሁን ደም በከንቱ የምታፈሱ ፡ በጭቃኔ ሕይወት የምትቀጥፉ እና ወያኔን የምታገለግሉ የሰራዊቱ አባላት ፡ በታሪክ እና በኢትዮጵያ ሕዝብ ተጠያቂ እንደምትሆኑ ከወዲሁ ነገን እያሰባችሁ ፡ ሰልፋችሁን ከሕዝቡ ጋር አስተካክሉ ፡ ለኢትዮጵያ ነጻነት ሕዝባዊ ትግሉን ተቀላቀሉ።

አንደ አገር ፡ አንድ ሕዝብ ፡ አንድ ሰንደቅ ዓላማ እና አንድ የጋራ እድል ኢትዮጵያ።

ሰልፍ የጀግና ድል የእግዚአብሄር ነው።

ከጥቁር አንበሳ ዘብ ለኢትዮጵያ የነጻነት ግንባር።

 

 

ወገኖቻችንን ለዘመናተ የጨረሰው አደገኛው ዘንዶ፡-የኢትዮጵያ ሕገ-መንግስት –ሰርጸ ደስታ

$
0
0

13882704_10206976138181541_4933135800794013649_nየኢትዮጵያውያን ደም ሲገበርለት የኖረው የሕወሐት ኢህአዴግ ታላቅ ጣዖት ሕገ ምንግስት ከዚህ በኋላ ተነኮታኩቶ መሬት ወድቋል፡፡ ብዙዎች ሕገ መንግስቱን ለመናድ በሚል ለጣዖቱ ተገብረዋል፡፡ አምላኪዎቹ ቀን ከሌሊት ይዘምሩለታል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን ከምንም በላይ ጠላቱ ይሄ ጣዖት እንደሆነ የገባው ሰሞኑን ነው፡፡ እስከዛሬ እስኪ እናክብረው በሚል ጠጋ ሲሉት ዜጎችን እየጠለፈ ወደሞትና ጉሮኖ የሚያሰገባው ይህ አደገኛ የሕወሐት ኢሕአዴግ አምላክ ዘንዶ (ሕገ-መንግስት) ሰሞኑን ጎንደር ላይ ክፉኛ ቆሰለ፡፡ አምላኪዎቹ መጨረሻ እነሱኑ እንዳይውጣቸው ፈርተው አሁንም ሊላ ግብር ሊያቀርቡለት እጅግ እየተሯሯጡ ነው፡፡ ግን አይመስለኝም፡፡ ዘንዶው መጨረሻ የሚውጠው ሲያጣ ወደ አምላኪዎቹ መዞሩ እውን እየሆነ ይመስላል፡፡ ጎንድር ሁለተኛ እንደይመለስባት አድርጋ አድምታዋለች፡፡ ሌሎችም ብዙዎች አሁን ስልቱን የነቁበት ይመስላል፡፡ በኦሮምያ ብዙ ከዘንዶው ጋር ግብግቡ ቀጥሏል፡፡ ትንሽ የስትራቴጂ ለውጥ ማድረግ የሚያስፈልግ ይመስላል፡፡ ስልቱን ከጎነድሬዎቹ መማር ነው፡፡ ጎንደሬዎቹ ጠመንጃ ስላላቸው ብቻ አይደለም፡፡ በጣም የተቀናጀና ሰፋ ያለ ጉልበት እንዲኖራቸው በጥንቃቄ ነው ድል የተቀዳጁት፡፡ ጎደር ሁሉም አንድ ነው፡፡ ጎደሬዎቹ ኮሌኔል ደመቀን ለጎንደር ፖሊሶች አደራ ሲሰጡ ፖሊሶቹ ኮሌኔሉን ለዘንዶው አሳልፈው እንደማይሰጧቸው ለሕዝቡ ቃል ገብተውዋል፡፡ ሕዝቡም አልተጠራጠረም፡፡ የዘንዶው ሎሌዎች ብዙ ለፍተዋል፡፡ እንዲህ አይነቱ አንድነት በኦሮምያ እስካሁን ልናየው ልናየው አልቻልንም፡፡ አሁን ግን ለኦሮምያ ባለስልጣናትም ይሁን ፖሊሶች ኋላ ተመልሶ ይህ አደገኛ ዘንደዎ እንዳይውጠን ብለው ለራሳቸው ማሰብ ከቻሉ ራሳቸውን ሕዝቡን ይዘው ይከላከሉ፡፡

በአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ባለስልጣን ቀልድ ይሁን የምር አላውቅም ግን ጎንደር ላይ የአምላካችንን ፍላጎት የሚጻረሩ መልክቶች ተላለፈዋል ብለውናል፡፡ የሚያስቀው ይህ ዘንዶ ከሚጠላቸው መልዕክት ተብሎ ባለስልጣኑ ከተናገሩት አንዱ የኢትዮጵያ የነጻነት አርማ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማችን ነው፡፡ መቼም ጉድ ሳይሰሙ መስከረም አይጠባም አሉ፡፡ አንድ ከምን እንመጣ የማይታወቅ ለዘንዶው እንዲስማማው ተብሎ የኮከብ ቆጣሪዎች ደብተሮች የነገሯቸውን ትልቅ ኮከብ በሰነደቅ አላማችን ላይ ለጠፈው ለዘመናት የሕዝቦችን እኩልነት የሚገልጽ ነው ብለው አጃጃሉን፡፡ እስኪ ይህን ኮከብ አስተውሉት አንድነትን የሚያሳየው የቱ ጋር ነው፡፡ ይልቁንስ ሕዝብን ከሕዝብ በዘር በእምነት እየከፋፈሉ መሆኑን አሳምሮ ይናገራል፡፡ ጠነቋዮቻቸውንም አማክረው ይህን ምልክት ሲያቀርቡለት     ዘንዶው ከራማዬ ወዶት ተቀበሏቸዋል፡፡ እና አቶ ንጉሱ (የአማራው ኮሚኒኬሽን) ራስዎን ቢያድኑ ይሻልዎታል፡፡ ሌላው ዘንዶው እንዳይነኩበት የሚፈልጋቸው ልዩ አምላኪዎቹ (የጣዖቱ ካህናት) በጎንደሬዎቹ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ተላልፎላቸዋል፡፡ በእርግጥም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕዋት የሻቢያ ተላላኪ እንደሆነ አሳምሮ ያውቀዋል፡፡ ጎንደሬዎቹ ለዘመናት የተደበቀውን እውነት አደባባይ አወጡት፡፡ የተጠቀሱትም ግለሰቦች በትክክል ሕዝብ ማንነታቸውን አሳምሮ ያውቀዋል፡፡ እውነታው ይሄ ነው፡፡ አቶ ንጉሱ ሕዝብ አይሳሳትም፡፡ የተሳሳቱት እርሶ ነዎት፡፡ ወይም አዚም አርገውብዎት ነው፡፡ ይልቁንም አይፈሩበት ጎንደሬው ነጻነትዎን እያወጀልዎት ነው፡፡

ሌላው ብዙ የትግራይ ተወላጆች አካባቢ ከመቼውም በላይ በአሁኑ ወቅት ለዘንዶው ካሕናት ያላቸውን ወገንተኝነት እያሳዩ ይመስላል፡፡ ከአሁን በኋላ ምንም ሰበብ አይኖራችሁም፡፡ ጎንደሬዎቹ ሁሉንም ናቸው፡፡ ዘር፣ እምነት ምናምን አልያቸውም ሁሉም ጎንደሬዎች ናቸው እንጂ፡፡ ብዙ ጊዜ ብዙ ተመክራችኋል፡፡ አልሰማችሁም፡፡ አሁን ግን ጨው ለራስ ስትል ጣፍጥ አለዚያ የሚላችሁ ጊዜ እንዳይመጣ እፈራለሁ፡፡ ከዘንዶው ራቁ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ተቀላቀሉ ብዬ እመክራለሁ፡፡ አሁንም የዘንዶውን ካሕናት የሀሰት ትንቢት እየሰማችሁ ዘንዶው የመሰናበቻው ራት እንዳያደርጋችሁ፡፡ አባይ ጸሐዬ፣ ጀነራል ጻድቃን፣ ኮሌኔል አበበ በፎረሸ ስብከታችሁ ዳግም እናንተ ለምታመልኩት ዘንዶ ኢትዮጵያውያን ጭዳ አይሆኑም፡፡ ምን ይሻላል ብላችሁ ሌሎቹንም የዘንዶው ካሕናት ሰብሰብ አድርጋችሁ ምን አልባት የምትተርፉ ከሆነ ራሳችሁን አድኑ፡፡

ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት በዘንዶው ላይ ይነሳ! እስከዛሬ በተገበረለት ወገኖቻችን ይብቃ! የዘንዶው አምላኪዎችም እራሳችሁን ወደ ሕዝብ ማሸሽ የምትችሉበት ጥቂት ሰዓታቶች አሏችሁ፡፡ ከሕዝብ የዘረፋችሁት ሐብት ንብረት እያላችሁ እዛ ስትንደፋደፉ ዘንዶው የመጨረሻ እራቱ እንዳያደርጋችሁ!!!

 

እግዚአብሔር ለኢትዮጵያና ሕዝቦቿ የብርሀን ዘመን ያምጣ!

 

አሜን

 

ሰርጸ ደስታ

 

 

 

 

“ያበራሽን ጠባሳ ያዬ በእሳት አይጫወትም፡፡”- ነፃነት ዘለቀ

$
0
0

ነፃነት ዘለቀ (nzeleke35@gmail.com)

የሀገራceን ዕጣ ፋንታ በሕወሓት እጅ ሥር ከገባ  በትንሹ ሩብ ምዕተ ዓመት ደፍነን ወደ ግማሽ ምዕተ ዓመት እየገሠገስንነው፡፡ የዕዝ ጉዳይ ሆኖ የቀን ጎደሎ ገጠመንና እኛም ሀገራችንም በመጥፎ ስኬቶች እየተንበሸበሽን ዛሬ ላይ ደረስን፡፡ መስያሚያ ጆሮና መመልከቻ ዐይን በሌላቸው ወንድሞቻችን እየተረገጥንና በከፋፍለህ ግዛው እንግሊዛዊ የአገዛዝ ሥልት እየታመስን ብዙ ባጀን፡፡ ሆኖም ግና ሁሉ ነገር እንደሚጀመር ማለቁም አይቀርምና ይህ ከፋፋይ የወያኔ ሥርዓት-አልባ ሥርዓት ወደማይቀርለት ታሪካዊ ግብኣተ-መሬት ሊወርድ እያኮበኮበ መገኘቱ ለወዳጆቹ ቀርቶ ውድቀቱን ለሚመኙና ለውድቀቱም ለሚሠሩ የነፃነት ፋኖዎች ግልጽ የሆነ ይመስላል፡፡13882704_10206976138181541_4933135800794013649_n

ነገር ግን ሟች ይዞ ይሞታል ይባላልና ከዚህ እንደነቀርሣ ውስጣችንን በልቶ ከጨረሰን ፋሽስታዊ ሥርዓት በቀላሉ መገላገል የምንችለው ተበዳዮች ነን የምንል ወገኖች በተለይ ልዩ ዘዴ ቀይሰን ስንታገልና ንጹሓን ወገኖቻችን እንዳይጠቁ ስንከላከል ነው፡፡ በገበያ ግርግር ሌባ ይበራከታል፤ ሌባ ደግሞ የማመዛዘን ችሎታና የኅሊና ጤናማነት የለውም፡፡ ስለሆነም በግርግር ወቅት ለጉዳት የሚዳርግን ማናቸውንም ዓይነት የሥጋት ምንጭ አስቀድሞ ማድረቅ ተገቢ ነው፡፡ አለበለዚያ ጸጸቱ ለማይበርድ ከፍተኛ አደጋ መጋለጥ ይኖራል፡፡

ከሥጋት ምንጮች አንዱ ከዚህ ቀጥዬ የምነግራችሁ ነው፡፡ በደንብ ተረዱልኝ!

በሩዋንዳ ጭፍጭፋ ጊዜ ሕዝቡ አለውድ  ጎሣውን የሚገልጽ የመታወቂያ ወረቀት በግዴታ ይሰጠው ነበር፡፡ የዚያ ዓይነት ከሩዋንዳ ይልቅ ለጠባብ ዘር ቅድሚያ የሰጠ አሠራር ያስከተለውን መዘዝ በወቅቱ ታዝበናል፡፡ ሁቱዎች ቱትሲዎችን እንደዐይጥ እየጨፈጨፉ ሲጨርሷቸው በአብዛኛውና ለመለየት የሚቸገሩትን ሰው መታወቂያ እንዲያሳይ በማስገደድ መታወቂያው ላይ “ቱትሲ” የሚል የዘውግ ስም ካዩ በያዙት ገጀራ  ባልተለመደ ጭካኔ ቀረጣጥፈው ይገድሉት ነበር፡፡ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንዲህ ያለ መታወቂያ ላይ ከዜግነት ባለፈ ዘርን የሚጠቁም መንግሥታዊ ሥርዓት ሲያጋጥም መረገም እንጂ የሥልጣኔ ምልክት አይደለም፡፡ ከዚህ አንጻር እኛም ተረግመናል፡፡

የሀገራችን ጉግማንጉጎች በዚሁ የለዬለት አፓርታዳዊ አሠራር በየመታወቂያችን ላይ “ዐማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ ሀረሪ….” እያሉ ጽፈውበታል፤ “የተለዬ ዘር የለኝም፤ ‹ኢትዮጵያዊ› ብለህ/ሽ ጻፈው/ፊው” የሚልን ሰው በነፍጠኛነትና(የፈረደበት ዐማራነት) በቀድሞዋ ኢትዮጵያ ናፋቂነት እየፈረጁ ለስቃይና እንግልት ዳርገውታል – እንዲህ የሚልን ሰው ትግሬም ይሁን ኦሮሞ መታወቂያው ላይ “ዐማራ” ተብሎ እንዲጻፍበት ያደርጋሉ፡፡ በዚህ ጦስም ብዙዎች በተለይም በአገር አቋራጭ አውቶቡስ ተሣፍረው ሲሄዱ መንገድ ላይ በሚያጋጥሙ የተደራጁ ሽፍቶች አማካይነት አለርህራሄ ተጨፍጭፈዋል – መታወቂያን በዘርና በሃይማኖት መፈረጅ ጉዳቱ ከባድ ነው(የሃይማኖቱን ሰማዕትነት ነው ብንለውም እንኳን)፡፡ በግድያና በጭፍጨፋ ለሚያምን አይሲሳዊ ኃይል ዜጎችን በዚህ መልክ በጎሣ ፈርጆ በመታወቂያ ሞታቸውን ማወጁ ለጭራቆቹ ትልቅ እገዛ ማድረግ ነው፡፡ ዜጎችን በመታወቂያቸው ላይ በዘር መቦደን ለወፈፌ ጠላት ጭዳ ማድረግና የጥፋት ሥራቸውን በግማሽ እንደማቃለል ነው፤ ቋንቋቸውን የሚችል ሰው እንደምንም አሳምኖ ማምለጥ ሲችል በመታወቂያው ብቻ ይጠቃል ማለት ነው፡፡

ስለዚህ በኢትዮጵያ ያላችሁ የቀበሌ መስተዳድሮችና የወያኔው ባለሥልጣናት በምታምኑት ይሁንባችሁ ይህን መታወቂያ ነገ ዛሬ ሳትሉ አሁኑኑ ለውጡት፡፡መታወቂያ ላይ ከተፈለገ የደም ዓይነት እንጂ የዘር ማንነት አይጻፍም፤ ነውርና ወንጀልም ነው፡፡ አንደኛ አንድ ሰው የጠራ ማንነት ላይኖረው ይችላል – በአባቱ ኦሮሞ በእናቱ ትግሬ በአያቱ ዐማራ ቢሆን ይህ ዓይነቱ ሰው አንድ የዘር ሐረግ መዝዞ እንዲጠራበት ወይም እንዲታወቅበት ማድረግ አይቻልም፤ እርሱም አይፈልግ ይሆናል – ያለመፈለግ መብቱንም መጣስ ሰብኣዊ መብትን መጨፍለቅ ነው፡፡ ሁለተኛ ዘውጋዊ ማንነት በባለቤቱ ዘንድ መቅረት ይገባዋል እንጂ ከሀገራዊ ዜግነት በዘለለ መታወቂያ ወረቀት ላይ አስቀምጦ በኩራት ሊኮፈሱበት የሚገባ ጀብድ አይደለም፤ ማንም በፍቃዱ መርጦ ዐማራ ወይ ትግሬ – ይህን ወይም ያን አይሆንምና፡፡ ስንት ጅልነት አለ!

ስለዚህ ይህን ዓይነቱን ከድንቁርና ወይም ከተለዬ ድብቅ ፍላጎት የመነጨ አሠራር በአስቸኳይ መለወጥና ዜግነት በሚል ቦታ ላይ “ኢትዮጵያዊ” ብቻ ብሎ መጻፍ ከፊት ለፊት የተጋረጠን አደጋ በእጅጉ መቀነስ እንደሚቻል መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ነገረ ካለፈ በኋላ መቆጨት አይጠቅምም፡፡ ከአሁኑ መጠንቀቅ ተገቢ ነው፡፡ ሁሉም ዜጋ ይህን ወቅታዊ ማሳሰቢያየን በየሄደበት በማስተጋባት መንግሥት ተብዬው በዐይን የማይታይ ረቂቅ ተቋማችን መታወቂያ እንዲለውጥልን ጫና ይደረግበት፡፡ ደግሞም ይቻላል፡፡ አንዳንዴ ዜጎችን ማዳመጥ ተገቢ ነው፡፡ በጥላቻ ታውሮ ምንም አስተያየት ላለመቀበል ጆሮን መጠቅጠቅ ጉዳቱ ከፍተኛ ነውና ወያኔዎች እባካችሁን በዚህ ነገር አስቡበትና አፋጣኝ እርምጃ ውሰዱ፡፡ በውጭ ሀገራት ያላችሁ ወገኖቻችንም ይህ ጉዳይ በቀጥታ ባይመለከታችም ወገኖቻችሁና ዘመድ አዝማዶቻችሁ የዚህ ሸውራራ ወያዊ ሤራ ሰለባ ይሆናሉና ለዓለም አሰሙልን፤ በሩዋንዳ ለተከሰተው ዕልቂት አንደኛው መራጃ ይሄው በመታወቂያ ላይ ዘውግን የመጻፍ አላስፈላጊ ጣጣ ነበር፡፡ እርግጥ ነው – ወያዎች ይህን ያደረጉት የሥራ ዕድሎችን ከማከፋፈል አኳያ የማይፈልጉትን ዘውግ ከማዕዱ ለማራቅና እንዳስፈላነቱም ከዚያ ለከፋ አደጋ በቀላሉ ለመዳረግ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ሆኖም ይህ ነገር በእንግሊዝኛው የቃል አጠቃቀም backfire  ሊያደርግና ካሰቡት ውጪ የጎንዮሸ ጉዳት እንደሚኖረው አልተረዱትም፡፡ ወያኔዎች በጥቅምና በሥልጣን ጥማት ያበዱ፣ በቂም በቀልና በጥላቻ የሰከሩ ደምባራዎች ስለሆኑ የፊት የፊቱን እንጂ የአህያን ያህል አንድ አሥር ሜትር ያህል እንኳን ወደፊት ራቅ አድርገው መመልከት የማይችሉ፣ ዕውቀትና ጥበብ በራቸውን የጠረቀሙባቸው የአስተሳሰብ ድሆች ናቸው፡፡ ለማንኛውም “ያበራሽን ጠባሳ ያዬ በእሳት አይጫወትም፡፡”ና ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ የእሳትን አስከፊ ጉዳት ለማየት በግድ እጅን ወደነበልባላዊ እቶን መክተት አይጠበቅብንም – ቀድሞ ከተቃጠለ ሰው መማር አስተዋይነት ነው – ሊያውም በነፃና እንደክፍያም ከታሰበ ከከንፈር መጠጣ ባልዘለለ የሀዘን ስሜት ብቻ፡፡

ኢትዮጵያዊነት የብሄር/ብሄረሰብ ጥያቄና ፌዴራሊዝም ! –ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር

$
0
0

የኢትዮጵያውያን ፎረም በአውሮፓ ባዘጋጀው በዴን ሀግ ከተማ  ከ28.07-30.07.2016 በሚደረገው     የኢትዮጵያውያን  የስፖርትና የባህል መድረክ ላይ ለውይይት የቀረበ ጥናት ! መልካም ንባብ!!     

  ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)

መግቢያ !
13882497_10206705956951835_2221566154745392193_nአብዮቱ ከፈነዳ ከ1966 ዓ.ም ጀምሮ ህዝባችን ሰላምና እረፍት ማግኘት አልቻለም። አብዮቱ ሲፈነዳ፣ የንጉሳዊ አገዛዝ ሲፈርስ፣ የሱ መሰረት የሆነው የፊዩዳሉ ስርዓት ሲደመሰስ ሰፊው ህዝብ የነፃነት ብርሃንን የማየት ዕድል አጋጥሞት ነበር። እስከተወሰነ ደረጃም ድረስ ነፃነትን በመጎናጸፍ እንደቆመበት የህብረተሰብ ክፍል የየራሱን ማህበራዊ ተቋም መመስረት ችሎ ነበር። ይሁንና ግን ይህ የተጎናጸፈው ድልና የተስፋ ብርሃንን ማየት ከውስጥ ከዚህና ከዚያ ብቅ ባሉ ድርጅቶች፣ ግን ደግሞ ዕውነተኛ ዓላማቸው በማይታወቅ ኃይሎች በመወጠርና ጦርነት ውስጥ እንዲገባ በመገደዱ አገሪቱ እስካሁን ድረስ ጋብ ሊል ያልቻለ ትርምስ ውስጥ እንድትወድቅ ተገደደች።

በመሰረቱ አብዮቱ ሲፈነዳ የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎችና፣ እንዲሁም ደግሞ በብሄረሰብ ነፃነት ስም የሚታገሉ  ድርጅቶችን ጥያቄዎች መመለስና ማስተናገድ የሚችል ነበር። እንደሚታወቀው በአገራችን ምድር የዲሞክራሲ መብትና የመሬት ለአራሹ ጥያቄዎች ሲነሱና እስከተወሰነ ደረጃም ድረስ መልስ ሊሰጣቸው ሙከራ ሲደረግ፣ የጥያቄዎቹ አነሳሰም ሆነ ተግባራዊ የማድረጉ ጉዳይ ከዘጠና በመቶ በላይ የሚሆነውን ህዝባችንና ልዩ ልዩ ድርጅቶችንም የሚያካትትና በጋራ እጅ ለእጅ ተያይዞ ለመተርጎምና ቀስ በቀስ ነፃነትን ለመቀዳጀት የሚያስችል ሂደት ነበር። ይሁንና ግን የአብዮቱ መፈንዳት፣ የንጉሳዊው አገዛዝና የሱ መሰረት የሆነው የፊዩዳል ስርዓት መገርሰስና ልዩ ልዩ የጥገና ለውጦች ቀስ በቀስ ተግባራዊ መሆን ከረጅም ጊዜ አንፃር ሲታይ ዕድገትንና ነፃነትን ሊያመጣ የሚችለውን አካሄድ ያልተገነዝቡ ኃይሎች በመሰረቱ በወታደራዊ አገዛዙ ላይ ሳይሆን በህዝባችን ላይ በመዝመት አገራችንን ትርምስ ውስጥ ለመክተት ችለዋል። ከሰላሳ ዓመታት በላይ በየቦታው የተካሄደው ጦርነት አገሪቱን ውጥረት ውስጥ መክተቱ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ የሰውና የሀብት ውድመት እንዲፈስ አድርጓል። ካለማወቅና በሰፊው ካለማሰብ የተነሳ ከዚህ ብሄረሰብ ነው የመጣሁት፣ ስጨቆን ነበር ፣ ስለዚህም የምፈለገው ሌላ ነገር ሳይሆን „ነፃነቴን“ ብቻ ነው በማለት የተካሄደው እልክ አሰጨራሽና የወንድማማቾች ርስ በርስ መተላለቅ አገራችን ዛሬ ላለችበት አስከፊና እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ከፍተኛውን አስተዋፅዖ አድርጓል ማለት ይቻላል።

በአገራችን ምድር ከሃያ አምስት ዓመታት ጀምሮ ስልጣን ላይ ቁጥጥ ያለውና፣ የአገራችንና የህዝባችንን የመኖርና ያለመኖር ዕድል የሚወሰነው የወያኔ አገዛዝ በቡሃ ላይ ጆሮ ደግፍ ተጨምሮበት እንደሚባለው አነጋገር አገራችንን በብሄረሰብ በመከለልና የክልል ፖለቲካ ተግባራዊ በማድረግ ህዝባችን በአንድነት ተነሳስቶ በጋራ አገሩን እንዳይገነባ አድርጎታል። የሚሆነውን የማይሆነውና፣ ከታሪክ ጋር ግኑኘት የሌላቸውን ነገሮች በማውራትና የጥላቻ መርዙን በመርጨት ምስኪኑ ህዝብ ርስ በርሱ እንዳይተማመን አድርጓል። በተለይም ወያኔ ስልጣን ከያዘ ጀምሮና ይህን ዐይነቱን የከፋፍለህ ግዛና የጥላቻ ፖሊሲ ሲያዳምጥ ያደገ ወጣት የኢትዮጵያዊነት ስሜት ላይሰማው ይችል ይሆናል። ስለሆነም ከዚህኛው ወይም ከዚያኛው ብሄረሰብ ነው የመጣሁት በማለት ርስ በርሱ እንዳይግባባና በጎሪጥ እንዲተያይ ለማድረግ ተችሏል። በመሆኑም አብዛኛው ወጣት የመለያ ቀውስ(Identity Crisi)እንዳለበት ግልጽ እየሆነ መጥቷል።  በእርግጥም ወያኔ ስልጣን ከጨበጠ ጀምሮ ለተወለደ ልጅና በወያኔ የትርምስ ፖለቲካ ውስጥ ላለፈና ጭንቅላቱ ውስጥ ካካተተ ወጣት የኢትዮጵያዊነት ጉዳይ ሊምታታበት ይችላል። በተለይም ደግሞ በምድር ላይ የሚታየው የኢኮኖሚና የማህበረዊ ጉዳይና የተወሰነውም የህብረተሰብ ክፍል በገንዘብ መናርና መባለግ አዲስ ታዳጊ ወጣት ስለህብረተሰብና ስለኢትዮጵያዊነት ምንነት ሊምታታበት ይችላል። በዚህም የተነሳ በብዙዎቻን ዘንድ የሚነሳው ጥያቄ የአገራችንና የህዝባችን የወደፊት እጣ ምን ይሆናል? ኢትዮጵያስ ባለችበት መልኳ ልትቀጥል ትችላለች ወይ? ወይስ ሌሎች የአፍሪካ አገሮች ውስጥ እንደሚታየው በአገራችንም ምድር የእርስ በርስ መተላለቅ በመከሰት አገራችን አሁን ባለችበት መልኳ ልትቀጥል ትችላለች ወይ? የሚለው ነገር እያሳሰበን መጥቷል። የነገሩን አሳሳቢነት ለመረዳት አንዳንድ የተሳሳቱና ከታሪክና ከህብረተሰብ ግንባታ ጋር ሊያያዙ የማይችሉ ነገሮችን በማንሳት ዛሬ አገራችን ለምን ይህ ዐይነቱ ሁኔታ ላይ ለመድረስ እንደቻለች ለመወያየት እንሞክር።

 

የህብረ-ብሄር ምስረታ አስፈላጊነትና የብሔረሰብ ጥያቄ ጉዳይ በአጠቃላይ !

እንደሚታወቀው በህብረተሰብ ታሪክ ውስጥ ብሄረሰቦች የሌሉበት አገርና የተለያዩ ብሄረሰቦች ሳይጋቡና ሳይዋሃዱ እያንዳንዱ ብሄረሰብ በራሱ ክልል ብቻ ተወስኖ የኖረበት ማህበረሰብ በፍጹም የለም። የሰው ልጅ ውስጣዊ ኃይል(Dynamism) ስላለው በአንድ ቦታ ረግቶ ሊኖር በፍጹም አይችልም። በተለይም በአንድ አካባቢ የስራ-ክፍፍልና ገበያ የሚባሉት ነገሮች ሲዳብሩ፣ የዚህ ወይም የዚያ ጎሳ ተወላጆች ከሌላ አካባቢ በመምጣት የተቀረው እዚያ በመጋባትና በመዋለድ፣ እንዲሁም አዲስ የስራ ባህል ሲለምድና ገቢ ሲያገኝ ድሮ ከነበረበት የጎሳ ወይም የብሄረሰብ ስንሰለት በመላቀቅ የአስተሳሰብ አድማሱ ይሰፋል። እንደዚህ ዐይነቱ የህዝብና ወይም የግለሰቦች እንቅስቃሴ የማይታየው ወይም በጥቂት ብቻ የሚካሄደው በከብት አርቢነት ሙያ በሚተዳደሩና፣ ዘላን እየተባሉ በሚጠሩ ጎሳዎች ዘንድ ነው። የእንደነዚህ ዐይነት ጎሳዎች እጣ ደግሞ እግዚአብሄር የሰጣቸውን የመፍጠር ኃይል ለመጠቀም አለመቻል ብቻ ሳይሆን፣  በተለያየ ጊዜ ከተፈጥሮ በኩል የሚመጣባቸውን አደጋ መቋቋም አይችሉም። ህይወታቸውም ተደጋጋሚና አሰልቺ ሰለሚሆን የመፍጠር ኃይላቸው ውስን በመሆን አዳዲስ መሳሪያዎችን በመስራት ኑሮአቸውን መልክ ሊሰጡትና ወደ ተሻለ የአኗናር ስልትና ዕድገት ደረጃ ላይ ሊሸጋገሩ በፍጹም አይችሉም።

በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች ሆኖ በአንድ ክልል ውስጥ ከሚኖሩት ውስጥ፣ እስከዚህም ድረስ በአንድ ቋንቋም ሆነ በባህል ካልተሳሰሩት ውስጥ አንደኛው የህብረተሰብ ክፍል ወይም ጎሳ በባህል፣ ቋንቋን በማዳበርና የአገዛዝ መዋቅርን በመዘርጋትና፣ በመጀመሪያ ደረጃ በአካባቢው ያለውን የጥሬ-ሀብትንና መሬትንም ጭምር በመቆጣጠር ከራሱ የተውጣጡ ብሄረሰቦችንም ወደ መበዝበዝ ያመራል። ግብር(tribute) እንዲከፍሉ ያስገድዳል። የተወሰነውንም ለጦር በመመልመል ከውጭ የሚመጣበትን ወራሪ ኃይል መክቶ በመመለስ የበላይነትን ይቀዳጃል። በአካባቢው ሌላ አገዛዘ እንደዚህ ካለ በጉልበት ለማስገበር ይሞክራል፤ ወይም በመጋባትና ርስ በርስ በመተሳሰር አገዛዙን ያስፋፋል። በህብረተሰብ ውስጥ በሚደረግ ማህበራዊ እንቅስቃሴ(Social Mobility) በተለይም በንጉስ መልክ በተዋቀረ አገዛዝ ከአንድ ጎሳ ብቻ በመውጣጣት የበላይነቱን ይዞ ሊቆይ አይችልም። ከአንድ ጎሳ የተውጣጣ አገዛዝ ወይንም ኤሊት በጎሳው ላይ የበላይነቱን ይዞ ሊቆይ የሚችለው በክላን በሚተዳደርና ገና ባልተሰበጣጠረና(Undifferenciated or non-segmented) በስራ-ክፍፍል ባልዳበረ ማህበረሰብ ውስጥ ብቻ ነው። ስለሆነም በንጉስ መልክና በፊዩዳላዊ ስርዓት ስር በተዋቀረ አገዛዝ ውስጥ ባለው ቅራኔና ሬሶርስን ለመቆጣጠር በመፈለግ የተነሳ በተለያየ አካባቢ የሚገኙ ከተለያዩ ንዑስ-ጎሳዎች የተውጣጡ የገዢ መደቦች ርስ በርስ በመጋባት የጎሳ ውስንነት ቀስ በቀስ ይደመሰሳል።

ይህ ዐይነቱ ከተለያየ አካባቢ የተውጣጡ የገዢ መደቦች ርስ በርስ መጋባትና የአገዛዝ መዋቅርን ማስፋፋት በአውሮፓ ምድር የተሰፋፋና የተለመደ ነበር። በተለይም በእንግሊዞችና በፈረንሳዮች የገዢ መደቦች መሀከል መተሳሰርና መጋባት ነበር። በሌላ ወገን ደግሞ በዕድገትና በአስተዳደር ቀድመው የሄዱ ግን ደግሞ ገና ወደ ህብረ-ብሄር(Nation-State) ደረጃ ላይ ያልደረሱ አገሮች፣ ሌሎች በዕድገት እስከዚህም ያልገፉ አገሮችን በመውረር ህልውናቸውን ለመደንገግ በቅተዋል። ጀርመን እ.አ በ1871 ዓ.ም በአንድ ግዛት ውስጥ ከመጠቃለሏ በፊት በስዊደን፣ በዴንማርክ፣ በአውስትሪያና በፈረንሳይ ተደጋጋሚ ጦርነት ተከፍቶባትና እስከተወሰነ ጊዜያትም ድረስ በተለይም የተወሰነው የጀርመን ክፍል በፈረንሳይ አገዛዝ ቁጥጥር ስር ነበር። እንደዚሁም እንግሊዝ  የካቶሊክ ሃይማኖት ተከታይ የሆነውን የሰሜኑን አየርላንድ ህዝብ በማስገደድ የተወሰነው አልቀበልም ሲል ደግሞ ከመሬቱ በማፈናቀልና ተከታይ የሆናቸውን የስኮቲሽንና እንግሊዛዊያንን በማስፈር የኋላ ኋላ አየርላንድ የካቶሊክንና የፕርቴስታንት ሃይማኖት ዕምነትን በሚከተሉ በመከፋፈል አንድ ጎሳ በሃይማኖት የተነሳ ሊለያይ በቅቷል። በጊዜው የእንግሊዝ ዋና ዓላማ የስራ ኃይል ለመፈለግና የአየርላንድንም ሪሶርስን ለመቆጣጠር ስለነበር የተከተለው ዘዴ  አንድን ህዝብ በሃማኖት መከፋፈልና እንዲጠላሉ ማድረግ ነበር።  የኋላ ኋላ ልዩነቱ እየከፋ በመሄድ አንድ ወንድማማች ህዝብ ርስበርሱ ለረጅም ዓመታት እንዲጨራረስ ተደረገ።  የአውስትሪያው የሀብስበርግ ሞናርክያዊ አገዛዝም የተለያዩ ጎሳዎችን በጉልበት በማጠቃለል ነበር በአንድ በኩል አገዛዙን ለማሰፈን የቻለው። በሌላው ወገን ደግሞ ከረጅም ጊዜ አንፃር ሲታዩ ለህብረ-ብሄር ምስረታ ሊሆን የሚችል መስረት በወረረባቸው አገሮች ውስጥ በመጣል እንደ ሀንጋሪ የመሳሰሉ አገሮች ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ የበቃው። የሀብስበርግ ሞናርኪያዊ አገዛዝ ከተደመሰሰ በኋላ አውስትሪያ ወደ ሪፑብሊክነት በመሸጋገርና አገዛዟን ውስን በማድረግ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት የሰፈነባት አገር ለመሆን በቃች። ዛሬ የምናየውንም የዕድገት ደረጃ ላይም ለመድረስ በቃች። በዚህ ዐይነቱ ተሻልን የሚሉ አገዛዞች ባደረጉት ጦርነትና መስፋፋት የግዴታ በህዝቦች ዘንድ መቀላቀልንና መዋለድን አስከትሏል።

በአውሮፓ የህብረተሰብ ታሪክ ውስጥ የህብረ-ብሄርን ወይም በአንድ አገዛዝ መጠቃለልንና የሪፑብሊክን መመስረት ልዩ የሚያደርገው፣ የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ በተለያዩ ኤፖኮች ጭንቅላትን የሚያድስ ምሁራዊ እንቅስቃሴዎች መካሄዳቸው ነው። በተለይም በጣሊያን ምድር ሬናሳንስ የሚባለው ምሁራዊ እንቅስቃሴ ከመከሰቱ በፊት የኢጣሊያን ህዝብ አንድ የሚግባባበት  ቋንቋ ስላልነበረውና፣ ለዕድገት አስቸጋሪም ስለነበር ዳንቴ የሚባለው ፈላስፋ ህዝቡ የሚግባባበትን አንድ ቋንቋ በመፍጠርና ተግባራዊ በማድረግ ለሬናሳንስ እንቅስቃሴ ተቀዳሚ ስራ በማዳበር እምርታ ሊሰጠው ችሏል። ሬናስንስ የሚባለው እንቅስቃሴ ሲጀምር፣ ሲስፋፋና ሲዳብር የዕደ-ጥበብ ስራ፣ ንግድና የከተማ ግንባታዎች በመስፋፋት ህዝባዊ እንቅስቃሴ በመዳበር  ተሰበጣጥሮና በተለያየ ጎሳ ተከፋፍሎ ይኖር የነበረው የኢጣሊያን ህዝብ በመሰባሰብ የስልጣኔ ባለቤት ሊሆን ችሏል። ይሁንና ግን ከካቶሊክ እምነት ለመላቀቅ ያልቻለው የኢጣሊያን ህዝብ በካቶሊክ የገዢ መደቦችና በቀሳውስት በመሰቃየት እንደ እንግሊዝና፣ ሆላንድ፣ የኋላ ኋላ ደግሞ እንደ ፈረንሳይና ጀርመን ሙሉ በሙሉ ሪፑብሊክን በመመስረት አንድ ህዝብ ሊሆን አልቻለም። ከውስጥ በነበረው የገዢ መደቦች ሽኩቻ የተነሳ ጣሊያን በወጭ ኃይሎች ልትወረርና በሪናሳንስ አማካይነት የተቀዳጀችውን ስልጣኔ በጠቅላላው በጣሊያን ምድር ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ አልቻለችም። ይህ ዐይነቱ ልዩነት እስከዛሬም ድረስ በተለይም በሰሜኑና በደቡቡ ኢጣሊያን  ክፍል መሀከል ጎልቶ የሚታይ ሀቅ ነው።

ወደ ሌሎች አገሮች ስንመጣ የህብረ-ብሄር ምስረታ የተለያየ መልክ የያዘ መሆኑ እንረዳለን። የእንግሊዚን የህብረ-ብሄረሰብ አመሰረራት ለየት የሚያደርገው፣  የህብረ-ብሄረሰብ ምስረታው ሳይንስና ቴክኖሎጂን የዕድገት መሰረት ለማድረግ በሚፈልጉት የፕሮቴስታንት መሪዎችና፣ ሳይንስንና ቴክኖሎጂ፣ እንዲሁም አጠቃላይ ዕድገት እንዳይኖር በሚቃወሙት በካቶሊክ እምነት ተከታዮች መሀከል የተካሄደ የጦፈ ትግል ሲሆን፣ በተጨማሪም በመሬት ከበርቴው፣ በአሪስቶክራሲውና በሌላ ወገን ደግሞ እያደገ በመጣው የኢንዱስትሪና የንግድ ከበርቴ መሀከል ነበር። የካቶሊክ ሃይማኖት ተከታዮችና ቄሶች፣ የመሬት ከበርቴዎችና አሪስቶክራሲው የነበራቸውን ስታተስ ላለማጣት ሲሉ ለውጥ እንዳይመጣ አግደው ይዘው ነበር። ይህ ሁኔታ ደግሞ እንግሊዝን አንድ ወጥና ጠንካራ መንግስት ሆና እንዳትወጣ አግዶ ሲይዛት፣ እንግሊዝ ሀብቷን ወደ ሮም ላለው የካቶሊክ አገዛዝና ስፔይን የምታስተላልፍ ነበርች። ይህ ሁኔታ በዚህ መቀጠል እንደሌለበት የተረዱት የቱዶር ሞናርኪዎች ሃይንሪሽ ሰባተኛውና ስምንተኛው፣ በተለይም በሬናሳንስ ዕውቀት የሰለጠነው ሃይንሪሽ ስምንተኛው የእንግሊዝ ንጉስ በሮሙ የካቶሊክ ሃይማኖት ህግ የሚገዛ ሳይሆን በራሱ እንደሚገዛና ነፃም እንደሆነ በማወጅ የመጀመሪያውን የካቶሊክን ሃይማኖት የበላይነት ዕምነት ይሰብራል።  ይሁንና ግን አብዮቱ እስከፈነዳበት እስከ 1642-1651 ዓመት ድረስ የፊዩዳሉና የአሪስቶክራሲው መደብ የበላይነት ያያለበትና ለዕድገትም እንቅፋት በመሆኑ የጥገና ለውጥ በሚፈልጉት ፓርሊያሜንታሪያንና በንጉሳዊ አገዛዝ ተከታዮች ዘንድ የጦፈ ጦርነት በመካሄድ ለመጨረሻ ጊዜ የካቶሊክ ሃይማኖት የበላይነት በመሰበር የከበርቴውን መደበ የበላይነት ይረጋገጣል። ለማኑፋክቱር አብዮት እንዲያም ሲል ለካፒታሊዝም ዕድገት የሚያመች ሁኔታ ይፈጠራል። ይህ የጥገና ለውጥና ከዚያ በኋላ የማኑፋክቱር አብዮት መካሄድና የገበሬው መደብ ከመሬት እየተፈናቀለ መምጣትና ወዝአደር መሆን የእንግሊዝ ህዝብ እንዲሰበጣጠርና በአንድ አገዛዝ መዋቅር ስር እንዲጠቃለል አድርጎታል።  በሌላ አነጋገር ለአንድ ህብረ-ብሄር ምስረታና ለካፒታሊም ዕድገት እንቅፋት የነበረው የካቶሊክ ሃይማኖትና የመሬት ከበርቴውና አሪስቶክራሲው፣ እንዲሁም የበላይ ጠባቂያቸው የሆነው ንጉሳዊ አገዛዝ ከተደመሰሰ በኋላ ነው እንግሊዝ ቀስ በቀስ ወደ ኢንዱስትሪ አብዮትና ወደ ካፒታሊዝም ዕድገት ለመሸጋገር የቻለቸው። በዚህም አማካይነት ነው ወደ ህብረተሰብ ምስረታ ልታመራ የቻለችው።

ወደ ጀርመን ስንመጣ ጀርመንም እስክ 1871 ዓ.ም ደረስ ከሶስመቶ በላይ በሚቆጠሩ መሳፍንት የምትተዳደርና በውጭ ወራሪ ኃይሎች የምትሰቃይ ነበረች። ይህ በዚህ መቀጠል እንደሌለበት የተረዳው የፕረሺያ የንጉሳዊያን አገዛዝ አልገዛ ያሉትን በኃይል በመውረር፣ ሌሎችን ደግሞ በጥቅም በመግዛት የመጨረሻ መጨረሻ ወደ አንድ ግዛትነት ልታመራ ችላለች። ማርቲን ሉተር መጽሀፍ ቅዱስን እስካተመበትና የፕሮቴስታንትን ሃይማኖት እስካወጀና የህዝቡ የማሰብ ኃይል በትምህርት አማከይነት መዳበር አለበት ብሎ መስበክ እስከጀመረበት ድረስ ጀርመንም በጎሳና በሃይማኖት የተከፋፈለች ነበረች። መጽሀፍ ቅዱስ ወደ ጀርመንኛ ቋንቋ ሲተረጎምና አድባራት የሃይማኖት መማሪያ ተቋሟት መሆናቸው ቀርቶ ወደ ህዝብ መማሪያነት ሲለወጡ የህዝቡ ኃይል መሰብሰብና የማሰብ ኃይሉም መዳበር ይጀምራል። የመፍጠር ችሎታውም ያድጋል። በዚህ አማካይነት የፕሮቴስታንት ሃይማኖት በተስፋፋባቸው አካባቢዎች  የንግድ እንቅስቃሴና የዕደ-ጥበብ  ሙያዎች ይዳብራሉ፤ ይስፋፋሉም። በተለያዩ ጊዜያት የወጡ ጥናቶች እንደሚያረጋግጡት ከሆነ ቀደም ብሎ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት የተስፋፋባቸው አካባቢዎች የካቶሊክ ሃይማኖት ተከታይ ከሆኑት አካባቢዎች ጋር ሲወዳደሩ በዕውቀትም ሆነ በቴክኖሎጂ፣ እንዲሁም በንግድ እንቅስቃሴና ከተማዎችን በመገንባት በብዙ እጅ ቀድመው እንደሄዱ ነው። ይሁንና ግን አገሮች በአንድ ግዛት ውስጥ ሲጠቃለሉ ሁሉም አካባቢዎች ወይንም ክፍላተ-ግዛቶች የግዴታ አንድ ወጥ ትምህርትንና ተመሳሳይ የሆኑ ለቴክኖሎጂ ዕድገት የሚያመቹ ሙያዎች ዕውቀቶችን በመቀበል ዕድገታቸው ተመጣጣኝ እየሆነ ሊመጣ ችሏል።

በአጠቃላይ ሲታይ በአውሮፓ ምድር ውስጥ የህብረ-ብሄረስ ምስረታ፣ በአንድ በኩል በተለያየ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ሲደደገፍና፣ የኋላ ኋላ ደግሞ በኢንዱስትሪ አብዮትና በንግድ አማካይነት መልክ ሲይዝ፣ አስቸጋሪ በሆነባቸው ቦታዎች ኃይል ወሳኝ ሚናን መጫወት ችሏል። በተለይም ከሰላሳኛው ዓ.ም ጦርነት የካቶሊክና የፕሮቴስታንቶች ሃይማኖት ጦርነት በኋላ እ.አ በ1648 ዓ.ም የህብረ-ብሄር ምስረታ ተቀባይነት በማግኘት አብዛኛዎቹ የአውሮፓ አገሮች ብሄራዊ ነፃነታቸውን ለማስከበርና ወደውስጥ ደግሞ መረጋጋትን ለማስፈንና ህዝቡን በአንድ ባንዲራ ስር ለማጠቃለልና የዜጋዊ ስሜትነት እንዲሰማው ለማድረግ ወደ ውስጥ ያተኮረ የተቀነባበረ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ግንባታ ማካሄድ ጀመሩ። በየአገሮች ውስጥ የናሺናሊዝም ስሜት በመዳበር ሁሉም አገዛዝ መጀመሪያ አገሬን ታላቅ አገር ማድረግ አለብኝ ብሎ በመነሳት ጥገናዊ ለውጥ ማካሄድ ጀመረ። በዚህም መሰረት ለነጋዴውና በማደግ ላይ ላለው የኢንዱስትሪ ከበርቴ እንክብካቤ በማድረግ የውስጥ ገበያ(Home Market) እንዲስፋፋ ለማድረግ በቃ። ከእንግዲህ ወዲያ ካፒታሊዝምና የህብረ-ብሄረሰብ ግንባታ የማይነጣጠሉ መሰረተ-ሃሳቦች ሆኑ።  ከዚህ ዐይነቱ አጠር መጠን ያለ ትንተና በመነሳት ነው ዛሬ በአገራችን ምድር የተንሰራፋውን አገዛዝና የብሄረሰብ ጥያቄ ጉዳይ መረዳት የምንችለው።

የህብረ-ብሄር ምስረታ ሙከራና የብሔረሰብ ጥያቄ በኢትዮጵያ !

የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ግዛት መሰረት የተጣለው ከአክሱም አገዛዝ በፊትና ከአክሱም አገዛዝ ጀምሮ ነው ማለት ይቻላል። ሁላችንም እንድምናውቀው የህብረተሰብ ታሪክ ተከታታይነት ያለውና፣(Evolutionary Process) ከአንድ ቦታ ጀምሮ ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች የሚስፋፋ ነው። የአክሱም ስልጣኔን ልዩ የሚያደርገው ከውጭ በመጣ ባህልና አስተሳሰብ ውስጠ-ኃይል ማግኘት መቻሉ ነው። በመጀመሪያ ግን የግዕዝ ቋንቋን አመሰራረት ስንመለከት፣ ቋንቋው እንደ ፊደል ከመቀረጹና ከማደጉ በፊት የገበሬው የመነጋገሪያ ቋንቋ ነበር። በጊዜው በነበረው ምናልባትም ዳማት በሚባለው ንጉሳዊ አገዛዝ ፊደል ሲቀረጽለት፣ የመጀመሪያዎቹ ፊደሎች ኮንሶናንት ነበሩ። እንደዛሬው የተራቡና በሁለት መቶዎች የሚቆጠሩ አልነበሩም። በአራተኛው ክፍለ-ዘመን የክርስትና ኃይማኖት ሲገባና በንጉስ ኢዛና የሚመራው ንጉሳዊ ቤተሰብ የክርስትናን ሃይማኖት ሲቀበል፣ በዚያው መጠንም የመጀመሪያው የግዕዝ ፊደል ቫውል ተጨምሮለትና ተስፋፍቶ በመነበብ ለቋንቋውና ለባህል ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ማበርከት ቻለ። ከዚያ በኋላ የያሬድ ሙዚቃና የቤተክርስቲያን የሙዚቃ መሳሪያዎች በመፈጠርና በመዳበር ለባህላዊ ዕድገት ዕምርታ ሊሰጡት ችለዋል። ይሁንና ግን የአክሱም ስልጣኔ በዘጠነኛ ዓ.ም ንግስት ዮዲት ተብላ በምትጠራው የአገው ተወላጅ ሴት ሲደመሰስ የተቀረው ወደ ደቡቡ ክፍል በመሸጋገር እንደገና በአስራሁለተኛው ክፍለ-ዘመን በዛግዌ ዲናስቲ አማካይነት እምርታን በማግኘት ሊያብብ ችሏል። የሰሎሞናዊ ዲናስቲ በመባል የሚታወቀው እስከ አስራአራተኛው ከፍለ-ዘመን ድረስ ስልጣን ከመያዙና ከያዘም በኋላ ግዕዝ የአገዛዞችና የቤተክርስቲያን ቋንቋ ነበር። በሌላ በኩል አማራ እየተባለ የሚጠራው አብዛኛው ህዝብ ደግሞ የሚግባባበት ወይም የመነጋገሪያው ቋንቋው አማርኛ ስለነበር ግራ የተጋባው የንጉሳዊው አገዛዝ የግዕዝን ፊደል በመውሰድና በማሻሻል የአማርኛ ቋንቋ መጻፊያም በማድረግ፣ የንጉሱም ሆነ የተቀረው ህዝብ የመነጋገሪያ ቋንቋ እንዲሆን ያደርጋል። ጨ፣ ሸ፣ ኘ የሚባሉት ፊደሎች በመፈጠርና ከነበረው ፊደል ጋር በመዋሃድ ለአማርኛ ቋንቋ ማደግ እምርታን ይሰጡታል።

ይህ በእደዚህ እንዳለ የሰለሞናዊት አገዛዝ ፊዩዳላዊ የመሬት ስሪትን በማስፋፋት በገባርና በአስገባሪዎች መሀከል ያለውን ግኑኝነት ያጠነክራል። የክርስቲያኑ ገበሬ ርስት የሚባል የመሬት ይዞታ ቢያገኝም ለፊዩዳሉ መደብ፣ ለንጉሳዊ ቤተሰቦችና ለቤተክርስቲያን ግብር በመክፈል የሚበዘበዝ ነበር። ከዚህም በላይ የአብዛኛው ህዝብ ሙያ ግብርና ስለነበርና፣  በዕደ-ጥበብ ሙያ ከተሰማራው ጥቂቱ የህብረተሰብ ክፍል ጋር የመገናኘትና የመገበያየት ዕድል ስላልነበረው ምርታማነትን በማሻሻልና የተወሰነውን ምርቱን ገበያ አውጥቶ በመሸጥ ኑሮውን ማሻሻል አልቻለም። ከሰለሞናዊ አገዛዝ በኩል የአስተዳደር ጥገናዊ ለውጥና ከውጭ የመጣ ሃይማኖትን ለመቀበል የተደረገው ሙከራ በመክሸፉ የፊዩዳሉ ስርዓት ለብዙ መቶ ዓመታ እንዲቆይ አድርጎታል። ይሁንና ግን ንጉሳዊው አገዛዝ ሌሎች ከሱ ክልል ውጭ ያሉትን በማስገበር ተገዢ ለማድረግ ችሏል። በአንድ ግዛት ስር ባልተጠቃለሉ፣ ይሁንና ግን ግብር እንዲከፍሉ በተደረጉ የደቡብ ግዛትም ዘንድ የሰራ-ክፍፍልና የንግድ እንቅስቃሴ ለመዳበር ባለመቻላቸው እነሱም በዕድገት ወደ ኋላ የቀሩና የኋላ ኋላ በመጀመሪያ በክርስትና ሃይማኖት መስፋፋት ወደ አንድ ግዛት ለመጠቃለል ያመሩ ክፍሎች ነበሩ ማለት ይቻላል። የማዕከላዊ ግዛት መሰረት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች በጣም በውስን ደረጃ የተጣሉት በአፄ ቴዎድሮስ አማካይነት ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያን ዘመናዊና የኢንዱስትሪ አብዮት ዕድል እንዲያጋጥማት ለማድረግ ያላቸው ህልም፣ ከውስጥ በፊዩዳሉ የገዢ መደቦችና መሳፍንቶች፣ እንዲሁም የሃይማኖት መሪዎች፣ ከውጭ ደግሞ በተለይም በእንግሊዞች ተንኮል ይጨናገፋል። አፄ ቴዎድሮስ እንግሊዞችን ኢንጂነሮችንና በተለያዩ ሙያዎች የሰለጠኑ ሰዎችን እንዲልኩላቸው ደብዳቤ ሲጽፉ፣ እንግሊዞች የላኩላቸው ግን የሃይማኖት ሰባኪ ቄሶችን ነው። የዚህ ውጤት ምን እንደሆነ ይታወቃል። ያም ሆነ ይህ  አፄ ቴዎድሮስ ካለጥገናዊ ለውጥና ካለ ኢንዱስትሪ ወይም ቴክኖሎጂያዊ ምጥቀት ህብረ-ብሄር እንደማይመሰረት ገብቷቸው ነበር ማለት ይቻላል። ይህ ህልማቸው ግን የኋላ ኋላ በአፄ ምኒልክ እስከተወሰነ ደረጃ ድረስ ተግባራዊ ሊሆን በቅቷል።

አንዳንድ የአሮሞ ምሁራን የአፄ ምኒልክን ወደ ደቡቡ ክፍል መስፋፋትንና ሌሎችን አካባቢዎች በአንድ አገዛዝ ስር ማጠቃለል ልዩ አድርገው ይመለከቱታል። በሌላ አነጋገር በነሱ ግምት እንደዚህ ዐይነቱ የተቀረውን አካባቢ በአንድ አገዛዝ ስር በኃይል ማጠቃለል በኢትዮጵያ ምድር ብቻ እንደተካሄደ አድረገው ነው የሚያቀርቡት፤ ወይም ሰውን ለማሳመን የሚሞክሩት። ይህ ግምታቸው ወይም ታሪክን በዚህ መልክ መተርጎማቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ህብረ-ብሔረን ለመመስረት ከተደረገው ሙከራና ከተሳካው ጋር በፍጹም የሚጣጥም አይደለም። በመጀመሪያ ደረጃ በአፄ ምኒልክ የአገዛዝ መዋቅር ውስጥ አማራዎች ብቻ ሳይሆኑ፣ ራሳቸው የኦሮሞ የገዢ መደቦችም ተሳትፈውበታል። በሌላ አነጋገር የተገለጸላቸው የኦሮሞ የገዢ መደቦች የህብረ-ብሄርን ምሰረታ የደገፉና የጦር አዝማቾችም ነበሩ። በእርግጥ የአፄ ምኒልክ ወታደሮች አልገበር ያሏቸውን ባላባቶች አንዳንድ አላስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎች ወስደውባቸዋል። እንደዚሁም የኦርሞ ተዋጊዎች በአፄ ምኒልክ ወታደሮች ላይ ከፍተኛ እልቂት አስከትለዋል። የታሪክ ማስረጃዎች እንደሚያረጋግጡት ከሆነ በሁለቱም በኩል ብዙ ሰው ህይወቱን አጥቷል።፡

በአብዛኛዎቹ የኦሮሞ ኤሊቶች የታሪክ አተረጋጎምና ግንዛቤ መሰረት ኦሮሞዎች በአንድ አገዛዝ ስር የሚታደደር ማህበረሰብ እንደነበራቸው ሆኖ ነው የሚቀርበው። እንደሚታወቀው ኦሮሞዎች ዛሬ ኦሮሚያ የሚባለውን ግዛት ከመቆጣጠራቸው በፊት ግዛቶቹ በአምስት የተለያዩ ብሄረሰቦች ቁጥጥር ስር የነበሩና ነገስታትም የሚተዳደሩ ነበሩ። እነዚህ ነገስታትና ብሄረሶቦቻቸው በእርሻ ሙያና በሌሎች ነገሮች የሚተዳደሩ ነበሩ። ከአስራስድሰተኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ ኦሮሞዎች ወደ ተለያየው የኢትዮጵያ ክፍላተ-ግዛት ሲስፋፉ እነዚህን ነገስታት በመደምሰስ ነው ብዙ ቦታዎችን መቆጣጠር የቻሉት። ወደ አማራው ክፍላተ-ግዛትም በመስፋፋትና ከህዝቡ ጋር በመጋባትና በመዋለድ በዚያ አካባቢ በልዩ ልዩ መልክ ለሚገለጸው የባህል ዕድገት አስተዋፅዖ አበርክተዋል። የኦሮሞ ኤሊቶችን ታሪክ ለመቀበል የሚያስቸግረው ሌላው ምክንያት አቀራረባበቸው ከህብረተሰብና ከህብር-ብሄር አገነባብ ታሪክና ሂደት ጋር በፍጹም ስለማይጣጣም ነው። በሌላ አነጋገር፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ እንደ አንድ ህብረ-ብሄር በአንድ ማዕከላዊ አገዛዝ ጥላ ስር ተደራጅቶ የነበረ አይደለም። ለአንድ ማዕከላዊ አገዛዝና ህብረ-ብሄር የሚያስፈልጉ ቅድመ-ሁኔታዎች የኦሮሞ ኤሊቶች ኦሮሚያ ብለው በሚጠሩት አካባቢና ማህበረሰብ ውስጥ አልነበረም። በቋሚ ወታደር፣ ፖሊስና በሲቪል ቢሮክራሲ የተደገፈ የአስተዳደር መዋቅር በየቦታው አልነበራቸውም። እንደዚሁም ህዝቡን ለማስተዳደር የሚያስችል በየቦታው የተዘረጋ ኢንስቲቱሽን አልነበራቸውም። ከዚህም በላይ ለአንድ ህብረ-ብሄር እንደ መሰረታዊ ቅድመ-ሁኔታ የሚያስፈልግ በማኑፋክቱር ላይ የተገነባ ኢንዱስትሪና ሰፋ ያለና የዳበረ የስራ ክፍፍል አልነበራቸውም። በተጨማሪም ሰፋ ያለ የገበያ ኢኮኖሚ አልነበራቸውም። ከዚህና ከሌሎች ለአንድ ህብረ-ብሄር ከሚያስፈለጉ መሰረታዊ ጉዳዮች ስንነሳ ኦሮሞን እንደ ብሄር ወይንም እንደ ህብረ-ብሄር የሚያስጠራው ምንም ዐይነት ሳይንሳዊ ማስረጃ የለም። ስለሆነም በሌለ ነገር ላይ መነታረኩ ጊዜ ማጥፋት ነው የሚሆነው። የጋራ ችግርንም በአንድነት ተሰማምቶና ተባብሮ እንዳንሰራ እንቅፋት ይሆናል። ለሁለመንታዊ ዕድገት በሆኑ የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂና የፍልስፍና ጉዳዮች ላይ እንዳንረባረቡ መንገዱን ይዘጋብናል።

ያም ሆነ ይህ የአፄ ምኒልክ አገዛዝ ወደ ደቡቡ ክፍል መስፋፋትና፣ እዚያ አዳዲስ የአስተዳደር መዋቅሮችን መዘርጋት አዲስ የህብረተሰብ ግኑኝነት(Social and political relationship) እንደፈጠረ መገንዘብ ይቻላል። በማዋቅም ሆነ ባለማወቅ በባላባትና በጭሰኞች መሀከል የሚገለጽ ግኑኝነት ሊፈጠር ተችሏል። በዚህ ዐይነቱ አዲስ የህብረተሰብ ግኑኝነት የአፄ ምኒልክን አገዛዝ የተቀበሉ የየአካባቢው ባላባቶችም ተጠቃሚ ሆነዋል። ይህም ማለት የባላባትና የጭሰኝነት ግኑኝነት በመጤው አማራና በኗሪው ህዝብ ብቻ የሚገለጽ አልነበረም። የዚህ ዐይነቱን አጠቃላይ የፊዩዳል ስልተ-ምርት ግኑኝነት መረዳት የሚቻለው በዘመኑ የነበረውን የፖለቲካ፣ የህብረተሰብ፣ የባህልና የኢኮኖሚ ንቃታ-ህሊና መዳበርና አለመዳበር ጋር ያገናኘን እንደሆን ብቻ ነው። እንደሚታወቀው አፄ ምኒልክ የተገለጸለት አዲስ ቢሮክራሲያዊና ምሁራዊ መሰረት አልነበራቸውም። የአስተዳደራቸው መሰረት የፊዩዳል ኢንስቲቱሽንና ቤተክርስቲያን ነበሩ። እሳቸው በአስተሳሰብ በብዙ እጅ ቀድመው የሄዱ ቢሆንም የሳቸውን የዘመናዊነት ፍላጎትና ህልም በምሁራዊ ዘዴ እየተነተነ ተግባራዊ የሚያደርግ ኃይል ባለመኖሩ የዘመናዊነቱ ሂደት ውስንና ውስጠ-ኃይሉም በጣም ደካማ ነበር። ይሁንና ግን አንድ ኢትዮጵያን ለመመስረት የሚያስችልና፣ ዛሬ ኢትዮጵያ ብለን ለምንጠራትና የራሳችንም መለያ ለመሆን የበቃች እገር መሰረት ጥለው አልፈዋል ማለት ይቻላላል።

በአጠቃላይ ሲታይ የኢትዮጵያን ወደ ህብረ-ብሄር መሽጋገርና በጠንካራ መሰረት ላይ እንድተገነባ አስቸጋሪ የሚያደርገው ነገር የተለያዩ የአገሪቱ ግዛቶችች፣ ከተማዎችና መንደሮች በስነ-ስርዓት አለመገንባታቸው፣ የዕደጥበብ ሙያና የንግድ እንቅስቃሴ አለማደጋቸው፣ በዚህም አማካይነት ከክልላዊ አስተሳሰብ ተላቆ በሰፊ ሜዳ ላይ ለመዋኘት የሚፈልግ የከበርቴ መደብ መፍለቅ አለመቻሉ ነው። ይህ ዐይነቱ የተጨናገፈ አካሄድ የኋላ ኋላ በብሄረሰብ ደረጃ ለሚንቀሳቀሱ፣ የታሪክን ሂደትና የህብረተሰብ ግንባታን ለመረዳት ለማይፈልጉ ኃይሎች መንገዱን አመቻችቷል ማለት ይቻላል።

ያልተስተካከለ ዕድገት፣(Unequal Development)የብሔረሰብ ጥያቄ አነሳስና

ጎልቶ መታየት !

አፄ ምኒልክ ከሞቱ በኋላ አፄ ኃይለስላሴ ከስደት እስኪመለሱ ድረስ ያለውን ጊዜ በመተው፣ ንጉሱ እንደገና የስልጣን ወንበራቸው ላይ ከተቀመጡ በኋላ የተከተሉትን ፖለቲካና የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጠጋን ብለን እንመልከት። በአፄ ኃይለስላሴ ዘመን የማዕከላዊ አገዛዝ ሂደት እንደተጠናቀቀ ይታወቃል። ይሁንና ግን አፄ ኃይለስላሴ እንደገና ስልጣናቸውን ከተረከቡ በኋላ የሰሩት ትልቅ ስህተት የጣሊያን ወራሪ ኃይል የደመሰሰውን የፊዩዳል ስርዓት እንደገና መመለሳቸውና ማጠናከራቸው ነው። በተጨማሪም ጣሊያን ያቋቋማቸውን አዳዲስ ኢንስቲቱሽኖችና የገነባቸውን ከተማዎች በዚያው በመቀጠል ከማስፋፋትና ከማዳበር ይልቅ እንዲፈራርሱ ማድረጋቸው ነው። በእሳቸው ዘመን አዲስ አበባ ውስጥ አዲስ ቢሮክራሲያዊ ኃይል ቢቋቋምም ወደ ክፍለ-ሀገር ከተማዎችና ወረዳዎች፣ እንዲሁም ምክትል ወረዳዎች ስንሄድ አፄ ኃይለስላሴ የዘረጉት የተገለጸለት ዘመናዊ ኢንስቲቱሽን አልነበረም። በመሆኑም የአገሪቱን የሰውና የማቴሪያል ሀብት ሊያንቀሳቅስና ህዝባዊ ሀብት ሊያዳብር የሚችል ዘመናዊ እንስቲቱሽን አልነበረም። ስለሆነም ግራ የተጋባውና ያልተማረው ህዝብ የተሰማራው እስከዚህም ድረስ ሀብረተሰብአዊና ብሄራዊ ሀብት(National and Social Wealth) ሊፈጥሩ በማይችሉ ጥቃቅን የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ ነው። በመሰረቱ እነዚህ ከእጅ ወደ አፍ የማያልፉ የገቢ ምንጮች በመሆናቸው በየሎካሉ ላሉ ኋላ-ቀር አስተደዳሮች የገቢ ቀረጥ ምንጮች ሊሆኑ የቻሉ አልነበሩም። በዚህም ምክንያት የተነሳ የየሎካሉ አስተዳደሮች በቂ የገቢ ምንጭ ስላለነበራቸው ለህዝቡ የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶችንና የስራ መስኮችን ሊያቋቋሙም ሆነ ሊከፍቱ አልቻሉም። በጊዜው የነበሩትም የሎካል የአስተዳደር መዋቅሮች እጅግ ወደ ኋላ የቀሩ በመሆናቸው እንዴት አድርገው አካባቢያቸውን ማልማት እንደነበረባቸው እስከዚህም ድረስ የሚያውቁት ነገር የለም። አብዛኛው ስራ የሚሰራው በዘፈቀደ ነበር ማለት ይቻላል።

ወደ አጠቃላዩ የኢኮኖሚ ፖሊሲያቸው ስንመጣ ደግሞ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ አፄ ኃይለስላሴ የተከተሉት የኢኮኖሚ ፖሊሲ በዘመኑ በሌሎችም የሶስተኛው ዓለም አገሮች የተካሄደውን ዐይነት የምትክ የኢንዱስትሪ ተከላ( Import Substitution  Industrialization) እየተባለ የሚጠራውን ነው። እንደሚታወቀው ጣሊያን ጠቅላላ አገሪቱን ሲገዛ ለራሱ ፍጆታ የሚጠቅም ኢንዱስትሪዎች አስፋፍቶ ነበር። እንዲሁም የሬዲዮ ጣቢያ ዘርግት ነበር። አፄ ኃይለስላሴ እንደገና ስልጣናቸውን ሲረከቡ በሞግዚትነት ተከትላቸው የመጣችው እንግሊዝ ጣሊያን ያቋቋመውን ኢንዱስትሪና የሬድዮ ጣቢያ ነቃቅላ በመወሰድ አገዛዙ ሀ ብሎ እንዲጀምርና ሁኔታውን እንዲያዘበራርቅ አድርጋለች። ያም ሆነ ይህ አፄ ኃይለስላሴ ስልጣን ከተረከቡ በኋላ በአዲስ አበባና በአካባቢው፣ እንዲሁም በአንዳንድ የክፍለ-ሀገር ከተማዎች ያቋቋሟቸው ኢንዱስትሪዎች ለአጠቃላይ የሀብት ክምችት( Capital Accumulation)  የሚያገለግሉና በየአቅጣጫው ሊስፋፉ የሚችሉ አልነበሩም። ሰፋ ያለ በሁሉም መልክ ሊገለጽ የሚችል ለስራ-ክፍፍል መዳበር የሚያመች የኢንዱስትሪ ፖሊሲ አይደለም አፄውና አገዛዛቸው የተከተሉት። እነዚህም የስኳር፣ የብስኩት፣ የመጠጥ፣ የጨርቃ ጨርቅ፣ የሲጋራና፣ እነዚህን የመሳሰሉትን የኢንዱስትሪ ተከላዎችን ነው የአፄው አገዛዝ ተግባራዊ ያደረገው። እነዚህ ኢንዱስትሪዎች በአዲስ አበባና በአካባቢው በመቋቋመቸው፣ 1ኛ) የሰው ኃይል ፍልሰት ከገጠር ወደ አዲስ አበባ እንዲያመራና ከተማዋን እንዲያጣብብ አድርጎታል። 2ኛ) የአዲስ አበባ ከተማ ራሱ በእቅድ የተሰራ ስላልነበር አዳዲስ የሰው ኃይል ከገጠር ሲመጣ ይህን አዲስ የህብረተሰብ ክፍል ሊያስተናግድና መጠለያ ሊሰጥ የሚችል ኢንስቲቱሽን አልነበረም። በመሆኑም ህዝቡ ራሱ በዘፈቀደ እዚህና እዚያ አልባሌ መኖሪያቤቶችን  በመስራትም ሆነ በመከራየት አዲስ አበባ በዕቅድና ስርዓት ባለው መልክ እንዳትገነባ ለመሆን በቃች። 3ኛ) ከገጠር ወደ አዲስ አበባ የዘመተው አዲስ የሰው ኃይል ዘመናዊ በሚባሉ የኢኮኖሚ መስኮች ውስጥ የስራ ዕድል ለማግኘት ባለመቻሉ ባልባሌና ሀብትን ሊፈጥሩ በማይችሉ የስራ መስኮች እንዲሰማራ ተገደደ። ሴቱ፣ ሴተኛ አዳሪ፣ እንጀራ ጋጋሪና በችርቻሮ የሚተዳደር ሲሆን፣ ወንዱ ደግሞ በሊስትሮነት፣ በሱቅ ነጋዴነትና፣ በአናጢነትና በልብስ ስፌትነትና እነዚህን በመሳሰሉት፣ ኢንፎርማል ሴክተር በመባል በሚታወቁት እንዲተዳደር ተገደደ። 4ኛ) ይህ ዐይነቱ ኢንፎርማል ሴክትር ዘመናዊ ከሚባለው የኢኮኖሚ መስክ ጋር ግኑኝነት ስላልነበረው፣(Linkages) ህብረተሰብአዊና ብሄራዊ ሀብት ለመፍጠር የሚያስችል አልነበረም። በዚህ መስክ ተሰማርቶ የሚተዳደረው የህብረተሰብ ክፍል ገቢው በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ ከዘመናዊ መስክ የሚመረቱትን ምርቶች ገዝቶ ለመጠቀም አይችልም ነበር። 5ኛ) ይህ ዐይነቱ ግኑኝነት አለመኖርና የሰፊውም ህዝብ የመግዛት ኃይል መዳከም፣ በአንድ በኩል የገንዘብን በፍጥነት መሽከርከር ሲያግደው፣ በሌላው ወገን ደግሞ ለአገዛዙ ሰፊ የገቢ ቀረጥ መሰረት ሊጥልለት አልቻለም። በዚህም ምክንያትና አገዛዙ በተከተለው የተበላሽና የህብረተሰቡን ፍላጎት ያላካተተና ቀስ በቀስ ከታች ወደ ላይ ሊያድግ የሚችል የኢንዱስትሪ ተከላና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት( Systematic Industrialization and Organic Growth) ባለመከተሉ በአገሪቱ ውስጥ ያልተስተካከለ ዕድገት(Unequal Development) ሊስፋፋ ችሏላ። ይህ ዐይነቱ የተበላሸ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ትንሽ ገንዘብ ያለውን ባለሀብት ወደ ነጋዴነት እንዲያመራና እንዲያተኩር በማድረግ በአገሪቱ ምድር በኢንዱስትሪ ተከላ ላይ ሊያተኩርና ቀስ በቀስ እያለ ሊያድግ የሚችል የኢንዱስትሪ ከበርቴ እንዳያድግ አደረገ። በተጨማሪም ይህ ዐይነቱ የተዘበራረቀና ዓላማው ምን እንደሆን የማይታወቅ የኢኮኖሚ ፖሊሲ አስተሳሰቡ የተዘበራረቀበት የህብረተሰብ ክፍል እንደአሸን እንዲፈልቅ አደረገ። ከኢትጵያዊነት ይልቅ አሜሪካንን የሚናፍቅ ኃይልና፣ ከዘጠና በመቶ በላይ ከሚሆነው ህዝብ የተገለለና በራሱ ዓለም ውስጥ የሚኖር የህብረተሰብ ክፍል ብቅ በማለት ባህላዊና ማህበራዊ ቀውስ እንዲፈጠር ተደረገ። በዚህም መሰረት የኢኮኖሚው ፖሊሲ በአገሪቱ ውስጥ ሰፋ ያለና ዘመናዊ ገበያ እንዲዳብርና እንዲስፋፋ የማያመች በመሆኑ ህብረተሰቡን ሊያስተሳስር፣ የማሰብ ኃይሉን ሊያዳባር የሚያስችለው፣ የፈጠራ ችሎታውን ሊያሳድግና አዳዲስ መሳሪያዎችንና ምርቶችን  በማምረት ማንነቱን ሊገልጽ የሚችል የህብረተሰብ ክፍል ብቅ ሊል አልቻለም። በአፄው ዘመን ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ነፃ ዜጋ የሚታይና መብትና ክብር ያለው መሆኑ የሚቆጠርና የሚከበር አልነበረም። ዘመናዊ የሚባለው አዲስ አበባ የተዘረጋው ቢሮክራሲ ይህንን ክፍተትና ኋላ-ቀርነት ለማረም የሚችል ባለመሆኑ፣ በአገሪቱ ውስጥ እዚያው በዚያው ዘመናዊና ፊዩዳላዊ የአስተዳደር መዋቅሮች በመዘርጋት ለአጠቃላይ ዕድገት ጠንቅ መሆን ችለዋል ማለት ይቻላል። በመሆኑም የአፄው አገዛዝ ፖለቲካዊ፣ ህብረተሰብአዊ፣ ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ንቃተ-ህሊና የጎደለው ብቻ ሳይሆን፣ ስትራቴጂካሊ ለማሰብ የሚችል አልነበረም። በአገሪቱ ውስጥ ሰላም እንዲስፈንና አገሪቱም በውጭ ኃይሎች እንዳትጠቃ በኢኮኖሚ መስክ መካሄድና መወሰድ ያለበትን ሁለ-ገብ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ ባለመቻሉ ለሰላም ጠንቅ የሆኑ ነገሮችን ዘርግቶ አለፈ።

ወደ መንግስት መኪናው አውቃቀር ስንመጣ፣ መንግስታዊው አወቃቀር ከታች ወደላይ ከህብረተሰቡ የማቴሪያል ዕድገት ጋር እየተቀናጀ ያደገ መንግስታዊ አወቃቀር አይደለም የተዘረጋው። የወታደሩ፣ የፀጥታው ኃይል፣ ፖሊስና ሌሎች አውታሮችም በውጭ ኃይሎች የሰለጠኑ በመሆናቸው ለውጭ የስለላ ኃይል ሰርጎ መግባት የሚያመቹ ነበሩ። ይህ ዐይነቱ ስርጎ መግባት በተለይም አብዮቱ ከፈነዳ በኋላ ተግባራዊ የሆነና፣ በወታደሩና በፀጥታው ኃይል መተማመን እንዳይፈጠር ያደረገ ነው። አሜሪካንን በሚደግፍና መረጃዎችን የሚያቀብል፣ በሌላ ወገን ደግሞ ቀስ በቀስ እያለ ለሶቭየቶች ታማኝ ሊሆን የሚችል ኃይል የሚመለመልበት ነው። ይሁንና ግን የኢትዮጵያ መንግስት መኪና አወቃቀር  ለብዙ ዐመታት ከአሜሪካኖች ጋር የተያያዘ ስለነበርና፣ የአሜሪካን የኑሮ ፍልስፍና ከደሙ ጋር የተዋሃደ ስለነበር፣ በተለይም ኮሙኒዝምን ወይም ሶሻሊዝምን የሚጠላው ኃይል ለአሜሪካ ያደላና በአብዮቱ ዘመን ህብረተሰብአዊ ለውጥ እንዳይኖር ያገደ ነው። ይህ ኃይል ደርግ ሊወድቅ ሲልና በኋላ የአሜሪካን ፓስፖርት እየተሰጠው አሜሪካን ገብቶ ኑሮውን እንዲመሰርትና ተደላድሎ እንዲኖር የተደረገ ነው።

ያም ሆነ በታሪክ ውስጥ የመንግስትን አመሰራረትና ለዕድገት አመቺ መሆን አለመሆን ስንመለከት በራሳቸው ጥረት የመንግስታቸውን መኪና ያላዋቀሩ አገሮችና የራሳቸው ፍልስፍናዊ መመሪያ የሌላቸው አገሮች ለዕድገት ጠንቅ እንደሚሆኑ ነው።  የሶቭየቱና የቻይናው አብዮት ከሞላ ጎደል ሊሳካና እነዚህ አገሮች ኃያልና የሚፈሩ መንግስታት ሆነው ብቅ ማለት የቻሉት የራሳቸውን የመንግስት መኪና በራሳቸው ጥረት በመገንባታቸው ብቻ ነው። ይህ ዐይነቱ በራስ ጥረት የመንግስት መኪናን ማዋቀርና አገርን መገንባት አገር ወዳድነትንና ብሄራዊ ስሜትን ያዳብራል።ለዕድገት ያመቻል። መተማመንን ይፈጥራል። በህዝብና በአገዛዝ መሀከል ሊኖር የሚገባውን መደጋገፍና መተሳሰብ ያጠናክራል። ዛሬ በብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮች፣ በተለይም በአፍሪካ አገሮች ውስጥ ያለውን ጭቆና፣ የሀብት ዘረፋና ሙስና ስንመለከት ዋናው ምክንያት መንግስታትና አገዛዞች ከታች ወደ ላይ በአንዳች ፍልስፍናና ሳይንስ ያልተገነቡ መሆናቸውን ናቸው። አብዛኛዎቹ መንግስታት በውጭ ኃይሎች በተለይም በአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም የሚጠመዘዙና የእሱንም ጥቅም የሚያስጠብቁ ናቸው። ስለሆነም በአንዳች ፍልስፋና የማይመሩና የህዝቦቻቸው ተጠሪ ያልሆኑ አገዛዞችና መንግስታት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ ላይ ስቃይን ያደርሳሉ፤ አንድ አገር በዘለዓለማዊ ትርምስ ውስጥ እንዲኖር ያደርጋሉ። ችግሩ ከአንድ ትውልድ ወደ ሌላ እንዲሸጋገር በማድረግ ህዝቦች በዘለዓለማዊ ድህነት ውስጥ እንዲኖሩ ያደርጋሉ።  ህዝባቸው በራሱ ላይ እንዳይተማመንና ቢያንስ እንኳ መሰረታዊ ነገሮችን እንዳያሟላ እንቅፋቶችን ይፈጥራሉ። ስለዚህም ለአገር ወዳድነትና ብሄራዊ ስሜት መዳበር በአዲስ ፍልስፍና ላይ የተመሰረተ የመንግስት መኪና አወቃቀር እጅግ አስፈላጊ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። አዲሱ የመንግስት መኪናና ልዩ ልዩ ኢንስቲቱሽኖችም ከማኝኛውም የውጭ ኃይል ተፅዕኖ የተላቀቁ መሆን አለባቸው። ከላይ እስከታች ያሉ ባለስልጣናትም ሆነ አዳዲስ የሚቀጠሩ ወይም የሚሾሙ የህይወት ታሪካቸው መጠናት አለበት። ቀደም ብሎ ሆነ አሁንም ከማንኛውም የውጭ ኃይል ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግኑኝነት የነበረውና የውጭ ኃይሎችን የሚያመልክ ግለሰበም ሆን ቡድን ለስልጣን እንዲበቃ መደረግ የለበትም፤ ወይም በአማካሪነትም ቢሆን እንኳ በስልጣን አካባቢ መድረስ የለበትም። ይህ ሲሆን ብቻ ነው አንድ አገር በሁሉም አቅጣጫ ለማደግና ህዝቦቿም ዕውነተኛ ነፃነትን ሊቀዳጁ የሚችሉት። ይህንን የተቀደሰ ዓላማ በሆነው ባልሆነው ለማሰናከል መሞከርና የማይሆን ዘመቻ እያካሄዱ እንቅፋት መፍጠር የኢዮጵያዊነትን ስሜት ማኮላሸቱ ብቻ ሳይሆን ህዝባችን ዘለዓለሙን ደሀ ሆኖ እንዲቆይ ሁኔታውን ማመቻቸት ነው። በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ጠንካራ አገር እንዳይገነባ እንደማሰናከል ይቆጠራል። ዛሬ በአብዛኛው ተማርኩ በሚለውና ውጭ አገር በሚኖረው ምሁር ዘንድ ያለው ትልቁ ችግርና የአስተሳሰብ ክፍተት ይህንን ሁኔታ በቅጡ ለመረዳት አለመቻል ነው። በተጨማሪም ለውይይትና ለክርክር ዝግጁ ባለመሆን ሽምጥጥ በማለት ወደ ስልጣን ለማምራት ከፍተኛ ሩጫ ማድረግ የትኛው አገር ወዳድ እንድሆነ የትኛው ደግሞ የአገር ጠላት እንደሆነ ለማወቅ የማይቻልበት ሁኔታ ተፈጥሯል።

የብሄረሰቦች እንቅስቃሴ መጠንሰስና መስፋፋት፣ እንዲሁም ብሄራዊ ስሜት ያለመዳበር ጉዳይ !

የኤርትራን የነፃ አውጭ ድርጅቶች መጠንሰስ ስንመለከት በመሰረቱ የኢጣሊያን የቅኝ አገዛዝ ያሰፈነው ልዩ ዐይነት ስርዓት በተወሰነው የኤርትራ የህብረተሰብ ክፍል ላይ የህሊና ጫና ወይንም ደግሞ የኢትዮጵያዊነት ስሜት እንዳይዳብር አድርጎታል። በተጨማሪም የአረቦች ተፅዕኖ ቀስ በቀስ ነፃ አውጭ ነኝ የሚሉትን በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ ዘመቻ እንዲያካሂዱ አግዞአቸዋል። በተለይም አፄው ኤርትራን ለጊዜው በፌዴሬሽን መተዳደርና፣ ጊዜው ከማለቁ በፊት በኃይል ማጠቃለል ኤርትራው ውስጥ የነበረውን ሁኔታ የባሰውን አባብሶታል። አፄው ስትራቴጂካል በሆነ መልክ ማሰብ የማይችሉ በመሆናቸውና የሪፐብሊክ አሰተሳሰብ የተዋሃዳቸው ስላልነበሩ በኤርትራም ሆነ በጠቅላላው የአገሪቱ ግዛት ፓርሊሜንተሪ ዲሞክራሲ እንዲዳብር ለመፍቀድና ሁኔታውን ለተረጋጋና ለዕድገት ለማመቻቸት ዝግጁ አልነበሩም። የመሰላቸው በሽወዳና በተንኮል እንዲሁም በኃይል ሁኔታውን መቆጣጠር የሚችሉ ሆኖ ነው የተሰማቸው። የዲስፖቲክ አገዛዝ ዋናው ችግር  ኃይል አለኝ ብሎ ስለሚገምትና ሁሉንም ለመቆጣጠር የሚችል ስለሚመስለው አንድን የፖለቲካ ክስተት ከሁሉም አቅጣጫ ለማየት አለመቻሉ ብቻ ሳይሆን፣ አማካሪው የሚለውን ባለመስማትና በጥርጣሬ ዐይን በመመልከት ያለውን ሁኔታ የባሰውን ማባባስ ነው። ስለሆነም አፄ ኃይለስላሴ የተከተሉት ስታሬቴጂክና ፖለቲካ አልባ አካሄድ የኤርትራን ነፃ አውጭ ድርጅቶች እልክ ውስጥ ከተታቸው። አብዮቱ ከፈነዳም በኋላና እስከመጨረሻው ድረስ የተካሄደው በእልክ ላይ የተመሰረተ የጭፍጨፋ ፖለቲካ ሁኔታው የባሰውን አበላሸው እንጂ ለችግሩ መፍትሄ ሊሆን በፍጹም ሊሆን አልቻለም። በሰፊው ሳይታሰብበትና ከሁሉም አቅጣጫ ውይይት ሳይካሄድበት ዝም ብሎ በፊዩዳል ግብዝነት „ሁሉንም ነገር ወደ ጦር ግንባር“ በሚለው መፈክር የተደረገው ዘመቻና ጦርነት የሰውና የማቴሪያል ኃይል የፈሰሰበት፣ የአገሪቱን ሁለ-ገብ ዕደገትና የኢትዮጵያዊነትን ስሜት እንዲቦረቦር ያደረገ ነው። ማንም ኃይል አንድን የህብረተሰብ ክፍልም ሆነ የብሄረሰብ እንቅስቃሴን በጉልበት ሊያሸንፈው አይችልም። ውስጥ ካለው የተዛባ የፖለቲካ፣ የማህበራዊና የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጋር ተያይዞ የሚያድግ እንቅስቃሴ በመሆኑ፣ እንደዚህ ዐይነቱን የውስጥ ችግር በፖለቲካ ሪፎርምና ሁለ-ገብ በሆነ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ግንባታ ፖሊሲ ብቻ ነው ማረምና ብሄራዊ ወይም የአገር ወዳድ ስሜትነት ማዳበር የሚቻለው።

በሌላ ወግን ግን የኤርትራው የነፃ መውጣት እንቅስቃሴ ብሶት የወለደውና የቅኝ አገዛዝ የህሊና ተጽዕኖ ውጤት ቢሆንም፣ እንቅስቃሴው የተጀመረውና የተካሄደው በተገለጸላቸውና የዲሞክራሲን ትርጉም በተረዱና ከጭንቅላታቸው ወይም ከሰውነታቸው ጋር ባዋሃዱ ኃይሎች አይደለም። እንቅስቃሴው እየጎለመሰ ሲሄድ ወደ ዘረኝነትና ወደ ማንአለኝበት ያመራና፣ በእንቅስቃሴው ውስጥም የትግሉን ዓላማ ለመወያየት ለዲሞክራሲያዊ ውይይት የሚያመች ሁኔታ የሌለበት ወደ አምባገነንነት ያመራ ነው። ስለሆነም ወጣቱ ክፉውን ከደጉ እንዳይለይ በጥላቻና በንቀት መንፈስ እንደሚረዝ በማድረግ፣ ከምሁራዊ እንቅስቃሴ ይልቅ ይበልጥ ወደ ጦርነት ስልትና ትግል በማምራት ጭካኔነትን ከደሙ ጋር እንዲያዋህድ ለማድረግ በቃ። በጦርነቱ ውስጥ የተሳተፉትና ከሞት የተረፉት የኢትዮጵያ ወታደሮች እንደመዘገቡት ከሆነ በተማረኩት የኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ይደርስ የነበረው ስቃይ እጅግ ዘግናኝ እንደነበር ነው። ይህ ብቻ አይደለም። አቶ ኢሳያስና ግብረ አበሮቹ ኤርትራን ከኢትዮጵያ ለመገንጠልና ነፃ ለመውጣት ሲሉ አዲስ አበባና አንዳንድ የአገሪቱ የክፍለሀገር ከተማዎች በንግድና በስራ ዓለም ተሰማርተውና ተደላድለው፣ እንዲሁም ሀብት አፍርተው የሚኖሩ ኤርትራውያንን ሁሉ በጥላቻ መንፈስ በመመረዝና ማፊያዊ በሆነ መልክ በማደራጀት አገራችንን ውስጥ ለውስጥ ሲቦረቡሩና ሀብቷን ሲዘርፉ ነበር። አብዮቱ ከፈነዳም በኋላ ነፃ እንወጣለን በማለት ትግል የጀመሩ እንደወያኔ የመሳሰሉ ቡድኖችን በማስታጠቅና በማደራጀት አገራችን ዛሬ ላለችበት አስከፊ ሁኔታ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርጓል። አገሪቱ በሁሉም አቅጣጭ በጦርነት እንድትወጠርና ማዕከላዊው መንግስት እንዲዳከም ያላደረገው ጥረት ይህ ነው አይባልም። ከዚህ ስንነሳ በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ነን በሚሉና ዛሬ በአሜሪካን ምድር ተደላድለው በሚኖሩ አንዳንድ የድሮ ባለስልጣኖች የሚነገረው አባባል፣  የእነ ኢሳያስ ቡድን „ኢትዮጵያ እንድትገነጣጠል አይፈልግም“ የሚለው አባባል ከተጨባጩ የኢትዮጵያ ሁኔታና ከኮመን ሴንስም ሆነ ከሎጂካዊ አቀራረብ ጋር በፍጹም የሚጣጣም አይደለም። ይህ ብቻ ሳይሆን፣ እነዚህ „የኢትዮጵያ ተቆርቋሪዎች“ በእዚህ ዐይነት አቀራረባቸው የሚያረጋግጥሉን ስለዲሞክራሲና ስለ ነፃነት ያላቸውን እጅግ የተዛባ አመለካከት ነው። ለመሆኑ የእነ አቶ ኢሳያስ ቡድን ኢትዮጵያ እንዳትበታተን የሚፈልግ ከሆነ ለምን ወያኔንና የኦሮሞ ነፃ አውጭ ድርጅቶችን አስታጠቀ ?  እነዚህ ትላልቅ ስዎች ያልገባቸው ነገር የእነ ኢሳያስ ዋናው ዓላማ ኢትዮጵያን ከውስጥ መቦርቦርና ማዳከም ብቻ ሳይሆን፣ የወታደሩ አገዛዝ አትክሮው ሁሉ ወደ ጦር ሲያመራና ኃይሉንና ሀብቱን በጦርነት ላይ ሲያውል መዳከም ይጀምራል፤ እኛም በቀላሉ ልናሸንፈው እንችላለን ከሚለው ስሌት በመነሳት ደርግን የሚቃወሙ ኃይሎችን ሁሉ ማስታጠቅና ማደራጀት እንደነበር በፍጹም የተረዱ አይመስልም። ስለሆነም የእነ ኢሳያስ ድርጊት በቀጥታ ኢትዮጵያ እንድትበታተን ከመደገፍ ውጭ ሊታሰብ አይችልም።   እነ አቶ ኢሳያስ በሁሉም አቅጣጫ ጦርነት እንዲከፈት ሁኔታውን ሲያመቻቹና እንገነጠላለን ያሉ ኃይሎችን ሁሉ ሲደግፉ ማዕከላዊው አገዛዝ የግዴታ ለኢኮኖሚ ግንባታና ለሌሎች ስራዎች ሊጠቅምበት ወይም ሊያውል የሚችለውን ሀብት ጦርነት ላይ እንዲያውል ተገደደ።  ከውስጥ የሰው ኃይልም ሆነ ሀብት እንዲወድም ተደረገ። በሌላ ወገን ግን በዚህ ዐይነቱ እርኩስ ተግባርና ተንኮል የኤርትራ ተገንጣይ ቡድኖችና ሰፊው የኤርትራ ህዝብም በምንም ዐይነት ተጠቃሚ ሊሆኑ አልቻሉም። በከፍተኛ ምሁራዊና በሳይንሳዊ አስተሳሰብ ላይ ተደግፎ የተካሄደ እንቅስቃሴና ጦርነት ባለመሆኑ የመጨረሻ መጨረሻ የጨለማ ኑሮ ውስጥ ሊወድቁ ቻሉ።  እንደገና ሊያገግሙ የማይችሉበት ሁነታ ውስጥ ወደቁ። አገዛዙ ብቻ ሳይሆን ሰፊው የኤርትራ ህዝብና በተለይም ወጣቱ በቀላሉ መፍትሄ የማይገኝለት የሳይኮሎጂካል ቀውስ ውስጥ ነው የወደቁት። በቀላሉ ራሳቸውን በራሳቸውን ማግኘት እንዳይችሉና እየባነኑ እንዲኖሩ ነው የተደረጉት። ከዚህ ስንነሳ ኤርትራ ያለቀላት አገር ነች። በምንም ዐይነት እንድገና በራሷ ጥረት አገግማ ካለበት ሁለመንታዊ በሽታ ድና ልትነሳ አትችልም። ህዝቡ፣ በተለይም ወጣቱ ከፍተኛ የሆነ የህሊና ጥገና ድጋፍ የሚያስፈክልገው ነው። ራሱን በራሱ ለማወቅ የብዙ መቶ ዐመታት ጉዞና ህክምና ያስፈልገዋል። አገዛዙም በዲሞክራሲያዊ ብቻ ሳይሆን በከፍተኛ ደረጃ በሚያስብ ኃይል እስካልተለወጠ ድረስ ለአገራችንና ለአካባቢው አገሮች የሰላም ጠንቅ ነው የሚሆነው። በሌላ ወገን ደግሞ በኢርትራ ውስጥ ዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ  ስርዓት ለማምጣት በፍጹም አይቻልም። የተገለጸለት ኃይል ባለመኖሩ የኤርትራ ህዝብ እጣ የጨለማና የመሰደደ ኑሮ ብቻ ነው የሚሆነው።

ይህ ሁኔታ ምንን ነው የሚያረጋግጥልን ? ዛሬም ሆነ ወደፊት፣ በዚህ አገዛዝም ሆነ በሌላ አገዛዝ ኤርትራ ውስጥ ያለው አገዛዝና ወደፊትም ቢሆን ኢሳያስን የሚተካው ግለሰብም ሆን ቡድን ከደሙ ጋር የተዋሃደ ጭንቅላቱን አንቆ የያዘው የጨለመ አስተሳሰብ ስላለ ከበጥባጭነትና ከጦርነት ቀስቃሽነት በፍጹም ሊላለቀቅ አይችልም። ወጣቱና ሰፊው ህዝብም የዚህ የጨለማ አስተሳሰብ ሰለባ ስለሆነና በቀላሉ ሶሻላይዝድ ሊሆን ስለማይችል በኢትዮጵያና በኤርትራ መሀከል ሊፈጠር የሚችለው ግኑኝነት ምናልባት  ከመቶና ከሁለት መቶ ዐመታት በኋላ የሚሆን ይሆናል። ዛሬ በአንዳንድ የዋህ ኢትዮጵያውያን የእነ ኢሳያስን አገዛዝ ለኢትዮጵያ አሳቢ አድርጎ ለማቅረብ መሞከርና፣ ውስጥ ያለንን ችግር ለመፍታት የሚያስችል አቅም ሳይኖረን በኤርትራና በኢትዮጵያ መሀከል ስለሚኖረው የወደፊቱ ግኑኝነት ደፋ ቀና ማለትና ሰሚናሮች ሲዘጋጁ ስናይ ይህ ደፋ ቀና የሚለው ኢትዮጵያዊ ኃይል ሁኔታው የቱን ያህል ያለተገለጸለት መሆኑን ነው የምንገነዘበው። አንዳንድ ድርጅቶችና ግለሰቦች የሚሰሩት የማያስፈልግ ስራና ቅስቀሳ ብዙውን የዋህ ኢትዮጵያዊ እያሳሳተው ነው። በሌላው ወገን ግን በኤርትራና በኢትዮጵያ መሀከል ወደፊት ጥሩ ግኑኝነት እንዲመሰረት ከተፈለገ ቀናና ተራማጅ አስተሳሰብ ያላቸውን ኤርትራውያንንን መደገፍና ከእነሱ ጋር አብሮ መስራት አስፈላጊ ይመስለኛል። በግልጽ ለመወያየት ከፈለጉ ድረስ በሩን ክፍት ማድረግ ያስፈልጋል። በአካባቢው ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ ተራማጅና በሰብአዊነት መርሆች ላይ የተመሰረተ ሰፋ ያለ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ያስፈልጋል። ስለሆነም የኢትዮጵያ ተራማጆችና የስብአዊነት አስተሳሰብ አራማጆች ከኤርትራውያን ተራማጆችና የሰብአዊነት  ጠበቃዎች ጋር ቢሰሩና ሃሳብ ለሃሳብ ቢለዋወጡ ሁለቱም ህዝቦች ዕውነተኛ ወዳጅነትን ሊፈጥሩና፣ ቀጥሎም ወደ ኮንፌዴሬሽንና ከዚያ በኋላ ዳግሞ ሁኔታው ሲበስል ወደ ውህደት ሊያመሩ የሚችሉበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል። ይህ ጉዳይ ሊታሰብ የሚችለው ከእነ ኢሳያስ ስሌትና አገዛዝ  ባሻገር ነው።

ያም ተባለ ይህ፣ በአጠቃላይ ሲታይ በኢትዮጵያ ውስጥ የብሔረሰብ እንቅስቃሴ መዳበርና ነፃ እንውጣ እያሉ እዚህና እዚያ የጦር ትግል ማካሄድ ከአጠቃላዩ የተበላሸ ፊዩዳላዊ አመለካከትና የሪፑብሊክ መንፈስ እጦትና ከተበላሸ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ፖሊሲ ጋር የተያያዘ ነው። ያልተስተካከለ ዕድገት ወይም የተዛባ የኢኮኖሚ ፖሊስ የግዴታ ተጨቆን ለሚሉ ኃይሎች መፈናፈኛ መንገድ በመስጠት ያለውን ክፍተት ተጠቅመው በመሰረቱ በአገሪቱ ላይ ዘመቻ እንዲያካሂዱ ረድቶአቸዋል። ስለሆነም የብሄረሰብ እንቅስቃሴ በጊዜው የነበረው እጅግ የተዳከመ ኢኮኖሚና የህብረተሰብአዊ አወቃቀር ውጤትና በአገሪቱ ምድር ዲሞክራሲያዊ መብቶችና በነፃ መደራጀት ካለመቻል ጋር የተያያዙ ናቸው ማለት ይቻላል። የዚህኛው ወይም የዚያኛው ብሄረሰብ ተወካይ ነኝ የሚለው ኤሊት የስልጣን ተካፋይ አይደለሁም ብሎ  የሚያራግበው ወሬ እንጂ በመሰረቱ ጥያቄውም ሆነ እንቅስቃሴዎቹ በምንም ዐይነት ሰፊውን የኦሮሞ ብሄረሰብም ሆነ የኤርትራ ህዝብ የሚመለከቱና የሚወክሉ አልነበረም።  የእንቅስቃሴያቸው አጀማመርና ጎልቶ መታየት ተራማጅ የሚያስመስላቸው ቢመስልም፣ ከዛሬው ሁኔታ ተነሰተን  እንቅስቃሴያቸውን ስንመረምር በብሄረሰብ አካባቢ ብቻ መሰባሰቡና ትግል መቀጠሉ ዕውነተኛ የነፃነት ትግል እንዳያራምዱ አድርጎአቸዋል። እንቅስቃሴያቸው  እየጎለመሰ ሲመጣ ሳይንሳዊ መልክ እያጣና ነፃነት ተቀናቃኛች በመሆን የባሰውኑ የጥቁርን ህዝብ ነፃነትና ዕድገት በሚጠሉ የውጭ ኃሎች ጉያ ስር እንዲወድቁ አስገድዷቸዋል። እራሳቸው ነፃ እንወጣለን ብለው መንቀሳቀስ የጀመሩት ድርጅቶች ከዚህም ከዚያም ዕርዳታ በማግኝት በታሪካቸው ላይ ብቻ ሳይሆን የዘመቱት፣ ያለሙትንም ነፃነት መጎናጸፍ እንዳይችሉ ተደርገዋል። በዚህም መልክ እንቅስቃሴያቸውን ከብሔራዊ ባህርይው በማውጣትና ዓለም አቀፋዊ መልክ እንዲኖረው በማድረግ  ኢትዮጵያንና ዕድገቷን ለሚጠሉ አገሮችና በሃይማኖት ስም ተጥቀመው አገራችንን ለመበታተን ለሚፈልጉ ኃይሎች ሁኔታው እንዲመቻች ለማድረግ በቅተዋል። ስለሆነም የጦር ትግላቸው በአገዛዙ ላይ ብቻ ያተኮረ ሳይሆን የገዢው መደብ ተጠቃሚ ነው በሚለው የህብረተሰብ ክፍል ላይ፣ በተለይም በአማራው ላይ ጦርነት በመክፈት የብዙ ሰዎች ህይወት ተቀጠፈ፤ ብዙ ንብረትም አወደሙ። በሌላ ወገን ግን ይህ ዐይነቱ በየብሄረሰብ አካባቢ የተደረገ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያዊነት ስሜት እንዲደመሰስ አደረገ። በተለይም ወጣቱ እየተመለመለ በመግባትና በጥላቻ ስሜት እንዲመረዝ በመደረጉ ብሄራዊ ወይም አገራዊ ስሜቱ ሙሽሽ ብሎ እንዲወድም ተደረገ። ይህ ዐይነቱ በኢትዮጵያ ላይ መዝመትና የኢትዮጵያዊነት ስሜት ደብዛው እየጠፋ መምጣት በአንድ ወቅት ብሄራዊ አጀንዳ ይዘው ይታገሉ የነበሩ ግለሰቦችንም የብሄረሰብ አርማ ይዘው እንዲያራግቡ አስገደዳቸው። በተለይም የወያኔ አገዛዝ ስልጣን ከያዘና ከኦሮሞ ህዝብ የነፃነት ድርጅት(OLF) ጋር አገር በሚያስተዳድሩበት ጊዜ፣ አንድ ወቅት ማርክሲስት ወይም ሶሻሊስት ነኝ እያለ ያዙኝ ልቀቁኝ ይል የነበረው ሁሉ የቤተሰቡን ግንድ በመቁጠር እኔም ኦሮሞ ነኝ ማለት ጀመረ። ይህ የሚያሳየው የቱን ያህል የመንፈስ መረጋጋት አለመኖርና አርቆ አለማሰብን ነው፤ ለስልጣን መስገብገብንና በፕሪንሲፕል አለመመራትን ነው። እነዚህ ኃይሎች ወይም ግለሰቦች ዛሬ ደግሞ 180 ዲግሪ በመዞር እንደገና የኢትዮጵያ ጠበቃ በመሆን ወጣቱ ከድሮ አባቶቻችን መማር ያለበት ነገር አለ በማለት ሲናገሩ ይሰማል።

     የወያኔ የክልል ፖሊሲና ጠንቁ !

በመጀመሪያ ደረጃ በተለይም አብዮቱ ከፈነዳም ሆነ ከመፈንዳቱ በፊት ብቅ ያሉትንና ወደ ጦር ትግል ያመሩትን የብሄረሰብ እንቅስቃሴዎች የፖለቲካ ንቃተ-ህሊና ሁኔታ ስንመለከት፣ አብዛኛዎቹ በጊዜው የግራ ስም ቢይዙም ወይም በማርክሲዝም ሌኒንዝም ስም ቢምሉም ርዕያቸውም ሆነ ትግላቸው በምንም ዐይነት ከሶሻሊዝም ጋር ወይንም ከማርክሲዝም ጋር የተያያዘ አልነበረም። ትግላቸውን ለመጀመር ሲነሳሱ፣ በጊዜው የነበረው ጭቆና በብሄር ላይ የተመሰረተ ሳይሆን ፊዩዳላዊ ባህርይ ያለውና፣ ይህ ጭቆና ጠቅላላውን የአገሪቱን ህዝብ የሚመለከት እንደነበር በፍጹም አልተገነዘቡም። የተወሰነው የገዢ መደበ ከአማራው ብሄረሰብ በመውጣቱ የአማራውን ብሄረሰብ ብቻ የሚጠቅም፣ የኑሮውን ደረጃ የሚያሳድግለትና ከሌሎች ብሄረሰቦች የበለጠና የተለየ መሆኑን የሚያሳይ ልዩ ዐይነት ፖለቲካና የኢኮኖሚ ፖሊሲ የተከተለ አድርገው ነበር የቆጠሩት።

የሞናርኪውን አገዛዝ ጠቅላላውን የፖለቲካ አወቃቀርና ፍልስፍናውን ስንመለከት ግን፣ አገዛዙ የፊዩዳሉን፣ የአሪስቶክራሲውንና የንጉሳውያን ቤተሰብን ጥቅም የሚያስጠብቅ ነበር። ርዕዮተ-ዓለሙንም ስንመለከት ፊዩዳላዊና የንጉሱን ፍጹማዊነትና አገራችንን ለመግዛት ከእግዚአብሔርር የተላኩ ናቸው በማለት ሰፊው ህዝብ አምኖ እንዲቀበል የሚያደርግ እንጂ በመሰረቱ አማራ ብሔረሰብ የሚባለውን ርዕይ የሚያንፀባርቅ አልነበረም። በተለያዩ የህብረተሰብ ታሪኮችም ውስጥ እንደታየው ስልጣን ላይ ያሉ የገዢ መደቦች የሚከተሉት ፖሊሲና ርዕዮተ-ዓለም ሁልጊዜ ከራሳቸው ጥቅምና ከሚደግፋቸው የህብረተሰብ ክፍል በመነሳት እንጂ የአንድን ህዝብ ወይም ብሔረሰብ ጥቅም አጉልቶ በማሳየት አይደለም።  ከዚህ ስንነሳ የኦርቶዶክስ ሃይማኖትና በዘፈንም ሆነ በምግብና በአለባበስ የሚገለጸው የአማራ ባህል ነው የሚባለው በመሰረቱ የአማራዉ ብቻ አልነበረም። አይደለምም። እነዚህ ዐይነት በልዩ ልዩ መልክ የሚገለጹ ባህሎች ከህብረተሰቡ ዕድገት ጋር  በህበረተሰብአዊ ሂደት ታሪክ ውስጥ ሰዎች አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ያዳበሩት ነው። በተጨማሪም በአንድ አካባቢ የሚዳብር ባህል ከተለያዩ አካባቢዎች ከመጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመዋሃድ ልዩ ዐይነት ዕምርታን የሚያገኝ ነው። በመሰረቱ በአንድ አካባቢም ሆነ ህብረተሰብ ውስጥ የሚፈልቅና የሚዳብር ባህል የተለያዩ ባህሎች ጥምር ውጤት(Synthetic) ነው። ስለሆነም ይህ የአማራው ባህል ነው፣ ያኛው የኦሮሞ ነው ብሎ መጥራት በጣም ያስቸግራል።   አንድን ባህል ወይም ባህሎች ከላይ ወደ ታች የምትጭናቸው ነገሮች አይደሉም። የሰው ጭንቅላት ውጤቶች በመሆናቸው እንደየህብረተሰቡ የዕድገት ደረጃ እየተሻሻሉና ልዩ መልክ እየያዙ የሚሄዱ ናቸው፤ ወይም ቀጭጨው በመቅረት ለዕድገት፣ ለሰፊና ለተገለፀለት አስተሳሰብ እንቅፋት ይሆናሉ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ርዕዮተ-ዓለም የአገዛዝ መሳሪያ ሆኖ ከመታወቁ በፊት በአጋጣሚና ሰዎች በአንድ አካባቢ ሲሰባሰቡና ልዩ ህብረተሰብአዊ ግኑኝነት ሲፈጠሩ የሚያዳብሩት ነው። በሌላው ወገን የሃይማኖትን ጥያቄ ስንመለከት ከደብቡ ይልቅ በመጀመሪያ ደረጃ በኃይል ተግባር የሆነው በአክሱም ግዛትና አካባቢው ብቻ ነው። የኋላ ኋላ ተቀባይነትን በማግኘት የተስፋፋ ነው ማለት ይቻላል። የአማርኛን ቋንቋና የግዕዝን ፊደል አመሰራረት ስንመለከት የህዝብ ቋንቋ የነበሩና በገዢውም መደቦች ቅርጽ በማግኝት የተስፋፉ ናቸው። ስለሆነም የአማርኛ ቋንቋ ልዩ የሆነና የጠቅላላው ህዝብ መግለጫ እየሆነ የመጣ ነው። እንደሚባለው ከሆነ ወደ 50% የሚሆኑ ቃላቶች ከኦሮምኛ ተወሰደዋል። በመሰረቱም ቋንቋ ሊዳብር የሚችለው ከሌሎች ቋንቋዎች ጋር ሲገናኝና ሲዋሃድ ብቻ ነው። ለምሳሌ በጀርመንኛ ቋንቋ ውስጥ የእንግሊዘኛም ሆነ የፈረንሳይኛ ቃላቶች ተካትተዋል። በመሆኑም የአማርኛን ቋንቋ እንደ አገዛዝ መሳሪያና የአንድ ብሄረሰብ ቋንቋ አድርጎ መውሰዱ ስሀተት ብቻ ሳይሆን እጅግ አደገኛም ነው። ጠቅላላው ህዝብ ደንቁሮ እንዲቀር የሚደረግ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ዘመቻ የሚካሄድበትና፣ በተለይም የውጭ ኃይሎች እንግሊዝና አንዳንድ የምዕራብ አውሮፓ አገሮች ከ1920ዎቹ ዓመታት ጀመሮ የሚያካሂዱት የማዳከምና፣ ህዝባችንን በጦርነት ዓለም ውስጥ በመንከር ርስ በርሱ እንዲጨፋጨፋ ለማድረግ የታቀደ የኢምፔሪያሊስቶች ሴራ ነው። በዚህ ዐይነቱ ሴራ ውስጥ ነው ወያኔም ሆነ በዚህም ሆነ በዚያኛው የስለላ ድርጀቶች የሰለጠኑ ኢትዮጵያውያን ዘመቻ የሚያካሂዱትና ለመጨራሻ ጊዜ የኢትዮጵያን ውድቀት የሚያፋጥኑት።

ያም ሆነ ይህ በአገራችን ምድር በብሄረሰብ ስም የተካሄደውና የሚካሄደው እንቅስቃሴና ጦርነት ፍልስፋና አልባና የዕውነተኛ ነፃነት መሰረት የሌለው ነው። በመጀመሪያ ደረጃ በማርክስዝምና በሶሻሊዝም ስም የሚምልና መመሪያው ያደረገ ትግልንና እንቅስቃሴውን በብሄረሰብ ደረጃ ሊገድበው አይገባም። ይህ ዐይነቱ አካሄድ ዓለም አቀፋዊ ባህርይ ያለውንና „ሁሉም ጭቁን ህዝቦች በአንድነት ተባብራቸሁ ተነሱ“  የሚለውን መፈክርና መመሪያ የሚቃውም ነው። እነ ሮዛ ሉክሰምበርግ የብሄረሰቦችን „የራስን ዕድል በራስ መወሰ“ን የሚለውን መፈክር ሲቃወሙ በመሰረቱ እንደዚህ ዐይነቱ አካሄድ ዓለም አቀፋዊነትንና ዕውነተኛ ነፃነትን የሚቃወምና፣ የነፃነትንንም ትግል የሚያደናቅፍ መሆኑን በመገንዘባቸው ነው። ከፕላቶን ፍልስፍና አንፃር ስንነሳ ደግሞ የሰውን ልጅ የማሰብ ኃይልና በዕውቀት አማካይነት በማዳበር ለሁሉም ዜጋ የሚስማማ ህብረተሰብን ለመመስረት የሚያስችለውን አካሄድ የሚያደናቅፍ ነው። የሰውን የማሰብ ሃይል የሚገታና ተጨናግፎ እንዲቀር የሚያደርግ ነው። አንድ ግለሰብም ሆነ ብሄረሰቦች እግዚአብሔር የሰጣቸውን በልዩ ልዩ መልክ የሚገለጸውን የማሰብ ኃይላቸውንና የፈጠራ ችሎታቸውን እንዳያዳብሩ የሚያግድ ነው። በዚህም ተባለ በዚያ የብሄረሰብ ጥያቄ በአንድ አገር ውስጥ ከሰፈነ አጠቃላይ የጭቆናና የፀረ-ዕድገት ፖሊሲ ጋር የተያያዘ ሲሆን ሊፈታም የሚችለው ጥቂት የብሄረሰብ ተወካይ ነን በሚሉትና በሚያካሄዱት የጦር እንቅስቃሴ አማካይነት አይደለም። ዕውነተኛ የነፃነትና የዕድገት እጦት በዚህ ዐይነቱ የፍልስፍና አልባ አካሄድ ተግባራዊ እንደማይሆን ከኤርትራው ትግልና  ውጤቱ መማር ይቻላል። እንደምናየው ውጤቱ ፋሽሽታዊ አገዛዝና የጨለማ ኑሮ ነው። ውጤቱ ድህነትና መሰደድ ነው። ውጤቱ የህሊና ድቀትና ጠባብ አስተሳሰብን መጎናፀፍ ነው። በአጭሩ ውጤቱ ነፃነት ሳይሆን፣ በልዩ ልዩ መልክ የሚገለጽ የነፃነት እጦት ነው። አንድ ዲስፖቲያዊ አገዛዝ በመመስረትና ጦርነትን ፍልስፍናው በማድረግ አንድ ህዝብ ዘለዓለሙኑ እየተሰቃየ እንዲኖር የሚያደርግ ነው።

ከዚህ ሁኔታ ስንነሳ የወያኔ የክልል ፖሊሲ እንደምናየው ለየብሄረሰቦች ዕውነተኛ ነፃነትን ያጎናፀፈ አይደለም። ለከፋፍለህ ግዛ የሚያመች ፖሊሲ በመሆኑ፣ በየክልሉ አዲስ የዋር ሎርዶች(War Lords) እንዲፈልቁና ህዝቡን አድኸይተውና አደንቁረው ራሳቸው ተመቻቸውና ደልቶአቸው እንዲኖሩ አዲስ ሁኔታ ተፈጥሮላቸዋል። በየአካባቢው ያለውን ሁኔታ ስንመለክት በዕቅድ የሚስራ ስራ የለም። ከተማዎችና መንደሮች በዕቅድ የተገነቡ ሳይሆኑ የድሮውን ሁኔታ በማባባስ ህዝባችን ከእንስሳ በታች እንዲኖር የተደረገበትን ሁኔታ እንመለከታለን። በየአካባቢው በልማት ስም የሚካሄዱት እንቅስቃሴዎች የአበባ ተከላዎችና የስኳር አገዳ ተከላዎች ናቸው። ጨአትና ቡና በመትከል ህዝቡን ማደንዘዝና የውጭ ከረንሲ ለመቃረም የሚደረግ ሩጫ ነው። ያለፉትን የ25 ዓመታት የክልል ፖሊሲ ስንመለክት በህዝባችንና በታሪካችን ላይ ውድቀትን ያስከተለ ነው። እያንዳንዱ ግለሰብ እንደሰው የማሰብ ኃይሉን እየተጠቀመ እንዳይኖር የተደረገበት ሁኔታ በአገሪቱ ውስጥ ሰፍኗል። ይህ ዐይነቱ በብሔረሰብ ነፃነትና የራስን ዕድል በራስ መወሰን በሚለው ስም የሚካሄድ ፖለቲካ ለህብረተሰብአዊና ለሀብት እንቅስቃሴ(Social and Capital mobility) እንቅፋት የሆነ ነው። በአገሪቱ ውስጥ አጠቃላይ ህብረተሰብአዊ ሀብት(Soical Wealth)እንዳይዳብር ያገደ ነው። ይህ ዐይነቱ አካሄድ በተለይም የአረብ አገሮችና ዕድገታችንን የሚቃወሙትንና፣ በተለያዩ ድሮች ያሰሩንን ኢምፔሪያሊስት ኃይሎችን ጥቅም የሚያስጠብቅ ነው። ሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የባህል ዕድገትና ምጥቀት እንዳይኖር የሚያግድና ድህነትን ያስፋፋና የሚያስፋፋ ነው። በመሰረቱ እንደዚህ ዐይነቱ ፖሊሲ የተፈጥሮንና የህብረተሰብ ህግን የሚፃረር እጅግ አደገኛ አካሄድ ነው። የሰውን ልጅ ወይም የእያንዳንዱን ዜጋ  የማደግ ፍላጎት የሚያግድ ነው። በአንድ አገር ውስጥ ያለን ሀብት በስነ-ስርዓት እያወጡ በኃይልና(Energy) በማሽን አማካይነት እየተደገፉ በማምረት የሰውን ፍላጎት ለሟሟላት እንዳይቻል እንቅፋት የሚሆን ነው። በተፈጥሮና በሰው ልጅ መሀከል የሚኖረውን መደጋገፍና፣ እንዲሁም ደግሞ በሰዎች መሀከል በልዩ ልዩ መልከ መዳበር ያለበትንና ሊገለጽ የሚችለውን ግኑኝነት የሚጻረር ነው። የሰውን ልጅ ተፈጥሮአዊ የማሰብ ኃይል የሚያፍን  የነፃነትና የዕድገት እንቅፋት ነው።

በመሰረቱ ከትግሬ ብሔረሰብ ወጣሁ የሚለውና ሃያአምስት ዐመታት ያህል አገራችንን የሚቆጣጠረውና የሚያተራምሰው አገርን የሚያዳከም እንጂ የብሔረሰቦችን መብት ተግባራዊ የሚያደርግና ነፃነታቸውን እንዲቀዳጁ የሚያደርግ አይደለም። እንደዚሁም የራሱን የትግሬን ብሄረሰብ ወይም ሰፊውን ትግሬን የሚጠቅም አይደለም። በዚያው ደንቁረው የሚያሰቃራቸው ነው። በሌላ ወገን ደግሞ ለብሄረሰቤ ነፃነት የተጋልኩ ነኝ፣ ለዚህም ጠበቃ የቆምኩ ነኝ ካለና ድልን ከተቀዳጀ በኋላ መቀሌ ጠቅልሎ መግባት ነበረበት። መሀከል ከተማ ውስጥ ሆኖ በብሄረሰብ ስም ነፃነትና የራስን ዕድል በራስ መወሰን ስም እየተመጻደቀ በታሪክና በህዝብ ላይ መቀለድ አልነበረበትም፤ የለበትም። ታስቦም ሆነ ሳይታሰብ ወያኔ እዚህ ደረጃ መድረሱና በአገሪቱ ውስጥ ለሚገኙ ልዩ ልዩ ብሄረሰቦች አርቲፊሻል መለያ መስጠቱ ለጊዜው የጠቀመው ቢመስልም፣ አንድ ቀን ህዝቡ ሆ ብሎ በአንድ ላይ ሲነሳ በወያኔ ላይ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላው በትግሬ ብሄረሰብና በዚህም በዚያም ብሎ ጥቅም አግኝቻለሁ ብሎ በሚሯሯጠው ላይ እንደሚነሳና መግቢያ እንደሚያሳጣው የታወቀ ነው። ስለሆነም የመጨረሻ መጨረሻ የትግሬ ብሄረሰብ እንዳለ ነው የሚጎዳው ማለት ይቻላል። በመሰረቱ ግን ወያኔ የተከተለው ፖለቲካ የትግሬን ብሄረሰብ እንዳለ የሚጠቅም ሳይሆን በቤተሰብ የተሳሰረ በአዲስ የገዢ መደብ የሚደገፍና፣ ከኤርትራ በመጡ በማፊያ መልክ በተደራጁ ኃይሎች የተከበበና በኢምፔሪያሊስት ኃይሎች የሚጠመዘዝና ማንኛውንም ድጋፍ የሚያገኝ ነው። ስለሆነም ህብረተሰብአዊ ትርምስና ድህነት እዚያው በዚያው እንዲቀጥሉ በማድረግ ህዝባችን የዕውነተኛ ስልጣኔ ባለቤት እንዳይሆን የሚያደርግ እጅግ አደገኛ አካሄድ ነው። ዛሬ በአዲስ አበባ ውስጥ በየቦታው የሚታየው እጅግ አፀያፊ ተግባርና ሰፊው የአዲስ አበባ ህዝብ በቆሻሻ ቦታዎች እንዲኖር መገደዱ ከስግብግብነትና ከማን አለብኝነት ጋር የተያያዘ ነው። ጥቂት ግለሰቦችና ቡድኖች ከውጭ ኃይሎች ጋር በጥቅም በመተሳሰርና ተላላኪ በመሆን የታሪክን ሂደት በማጣመም በቀላሉ ልንወጣው የማንችለው የተወሳሰበ ችግር ውስጥ ጥለውናል ማለት ይቻላል።

ይህ ዐይነቱ አካሄድ በአንድ አገር ውስጥ የሚኖርና ከዚህም ሆነ ከዚያኛው ብሄረሰብ የተውጣጣ ግለሰብ እንደሰውና እንደዜጋ እንዳይታይ የሚያደርግ ብቻ ሳይሆን የአገሩን ስም በስሙ እንዳይጠራ የሚያስገድደው ነው። በአንድ አገር ውስጥ ተወልዶ የአገሩን ስም እንዲጠራ ሳይሆን፣ ከአንድ ክልል ተወለድኩ ብሎ እንዲጠራ የሚያስገድደው ነው። „ከእናቴ ሳይሆን ከማህፀኗ ነው የተወለድኩት“ ብሎ እንደመናገር ዐይነት አስተሳሰብ ተስፋፍቷል፤ የጊዜው ፈሊጥም ሆኗል። ይህ ዐይነቱ ዘመቻና ጥላቻ በመሰረቱ አንድነትንና ሁለንታዊነትን፣ ወይም ደግሞ በአንድ ነገር የተጠቃለለን ግን ደግሞ ልዩ ልዩ ነገሮችን የያዘውን የተፈጠሮን ህግ የሚቃወም ነው። ተፈጥሮም ሆነ ሰው በአንድነትና በልዩ ልዩ ነገሮች ብቻ ነው የሚገለጹት። በአንድ በኩል እንደ ግለሰብአዊ፣ በሌላ ወገን ደግሞ እንደ ህብረተሰብአዊ አካል። ሰውነታችንም እንደዚህ አንድም ሁለንታዊም ነው። ማንኛውም ሰው እንደሰው የሚገለጸውና እንደሰውም የሚኖረውና የሚያስበው የተለያዩ ኦርጋኖችና የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ሲኖሩት ብቻ ነው። እንደሚታወቀው የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች በስራ-ክፍፍል የተደራጁና፣ በሌላ ወገን ደግሞ ስራቸውን በማቀነባበር እንደሰው እንድንቀሳቀስ፣ እንድናሰብና እንዲሁም እንድንፈጥርና እንድንሰራ የሚያደርጉን ናቸው። ከዚህ ስንነሳ በብሄረሰብ ስም ተሳቦ በወያኔ ተግባራዊ የሆነው የክልል ፖለቲካ  ይህንን ተፈጥሮአዊ ህግ ወይም ዩኒቨርሳል ህግ የሚቃወም ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ብቻ ሳይሆን የጠቅላላው ህዝብም  ጠላት ነው ማለት ይቻላል።

የኢትዮጵያ ጠንቆችና ኢትዮጵያዊነትን የሚቀናቀኑ አካሄዶች !

ኢትዮጵያዊነትን አጉልቶ የሚጠራ ወይም ሞትኩልሽ እያለ ባንዲራ የሚያውለበልብና፣ ለስልጣን ብሎ እዚህና እዚያ የሚሯሯጥ ሁሉ ዕውነተኛ ኢትዮጵያዊ ወይም ሰው ነው ሊያሰኘው የሚያስችል አይደለም። ላይ ለማሳየት እንደሞከርኩት አፄ ኃይለስላሴና ደርግም ኢትዮጵያውያን ቢሆኑም በመሰረቱ የኢትዮጵያን አንድነትና የህዝቦቿን ፍላጎት አናግተው ነው የሄዱት። በመሰረቱ አንድ የገዢ መደብ ስልጣን ላይ በሚቆይበት ጊዜ የገዢ መደብ ነኝ ብሎ ለመመፃደቅ ሳይሆን መስራት ያለባቸው ታሪካዊና ህብረተሰብአዊ ግዴታዎች አሉ። አንድ መንግስትና በአንድ አገር ውስጥ ያለ ሀብት  የገዢ መደቦች የግል ሀብት አይደሉም። በአንድ አገር ውስጥ ያለ ሀብት የጠቅላላው ህዝብ ሀብት ነው። መንግስትም ሆነ የመንግስት መኪና የህዝብ ተወካዮች እንደመሆናቸው መጠን አባትና እናት ልጆቻቸውን መንከባከብና በስነስርዓት ማሳደግ እንዳለባቸው ሁሉ አንድ የገዢ መደብና መንግስታዊ መዋቀሮች የአንድን ህዝብ መሰረታዊ ፍላጎት በማሟላት ወደ ሚቀጥለው የዕድገት ደረጃ ለመሸጋገር አስፈላጊዊን ቅድመ-ሁኔታዎች ማዘጋጀት አለባቸው። ለዕድገት የሚሆኑ አመቺ ሁኔታዎችን መፍጠር አለባቸው። ከዚህ ስንነሳ በተለይም የአፄው አገዛዝ የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም ያሰጠበቀና አገሪቱ በፀና መሰረት ላይ እንድተገነባ ማድረግ የቻለ አልነበረም።

በመሆኑም በአንድ በኩል ኢትዮጵያ አገሬ እያሉና ባንዲራ እያውለበለቡ፣ በሌላ ወገን ደግሞ  የኢትዮጵያን ህዝብ ደህንነትና ብልጽግና እንዲሁም አገራችን የሳይንስና የቴክኖሎጂ ባለቤት እንዳትሆን አጥብቀው የሚታገሉና ከተለያዩ የኢምፔሪያሊስት ኃይሎች ጋር የሚሰሩ ትላልቅ ሰዎች የሚመስሉ አሉ። በአብዛኛዎቻችን ዘንድ የተደረሰበት መደምደሚያ እዚህና እዚያ የሚንቀሳቀሱ የብሔረሰብ እንቅስቃሴዎች ብቻ ለአገሪቱ ደህንነት አደገኛ እንደሆኑ ነው። ከነዚህ ይልቅ እስከዛሬ ውስጥ ለውስጥ እንደነቀርሳ የሚሰረስረን በመሰረቱ ከፊዩዳላዊ አስተሳሰብ ያልተላቀቀና፣ ጥቅሙንና ህልሙን በተለይም ከአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ጋር ያገናኘ የድሮው ቢሮክራሲና የአሪስቶክራሲ ልጅ፣ እንዲሁም ደግሞ አዲስ ብቅ ብቅ ያሉ የዓለምን ፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ አወቃቀር በደንብ ያላገናዘቡ ኤሊት ነን ባዮች ናቸው ለአገራችን አንድነትና መበልጸግ ጠንቆች የሆኑትና የሚሆኑት። የተሰጣችውን መድረክ በመጠቀም ወጣቱን የሚያሳስቱና፣ የሾለና ሳይንሳዊ አስተሳሰብ ኖሮት አገሩን በፀና መሰረት ላይ እንዳይገነባ የሚያደርጉ ናቸው። በተለይም የአገራችን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ሳይንሳዊ ፈሩን ለቆ ከወጣ ከዛሬ አርባ ዐመታት ጀምሮ የሁሉም ትግል ስልጣንን በመጨበጥ ላይ ያተኮረ ስለሆነ በፖለቲካ ስም የተካሄደው ውዝግብ ሰፋ ላለ ምሁራዊ እንቅስቃሴና ሳይንሳዊ ክርክር አመቺ አልነበረም። ቡድናዊ ስሜትም ስላየለና ፖለቲካውም ይበልጥ በዘለፋና በጥላቻ ላይ የተመረኮዘ ስለነበር ስነ-ስርዓት ባለው መልክ ለመታገልና ወጣቱን ለማስተማር በፍጹም አልታቻለም። አብዮቱ ለአንዴም ለመጨረሻም ጊዜ ድምጥማጡ ጠፋ ከተባለ በኋላም አዲስ ምሁራዊ ኃይል ብቅ በማለት ወጣቱን ማስተማርና የበሰለ አስተሳሰብ እንዲኖረው ማድረግ አልተቻለም።  በመሆኑም ዕውነተኛ በሳይንስና በጥበብ ላይ የተመረኮዘ ኢትዮጵያዊ ስሜትን ማዳበር አልተቻለም። ዛሬም እንደትላንትናው ፊዩዳላዊ አሰትሳሰብ ከጥራዝ ነጠቅ የዘመናዊነት አስተሳሰብ ጋር በመዋሃድ ዕውነተኛ ኢትዮጵያዊ ስሜትን የሚያኮላሽ የመሳፍንት አገዛዝ ለማምጣት ደፋ ቀና እየተባለ እንደሆን እንመለከታልን።

ስለሆነም በአለፉት ሃያ አምስት ዓመታት እዚህና እዚያ የተደረገውን መጯጯህና ጠላት ነው በሚባለው ላይ ያነጣጠረውን ተቃዎሞ ስንመለከት፣ ሁላችንንም አንድ የሚያደርገን አንድ ነገር ብቻ ነው። ሁላችንም በወያኔ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ አለብን። ይሁንና ግን ወደ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ስንመጣ የሚያለያዩንና የማንስማማባቸው አያሌ ጉዳዮች አሉ። አንደኛ ፣ ወያኔ እንዴት ስልጣን ላይ እንደወጣና በዚህ ዐይነቱ አገር አፍራሽ ፖለቲካው ማን ከበስተጀርባው እንዳለና፣ የሃሳብና የማቴሪያል ድጋፍም እንደሚሰጠው በመሀከላችን ስምምነት የለም። ቢታወቅም እንኳ በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ስሙ እንዲነሳ አይፈለግም። እንዲያውም በአንዳንድ ተቃዋሚ ነን፣ የዚህ ወይም የዚያ ድርጅት የውጭ ፖለቲካ ተጠሪ ነን በሚባሉት ቃለ-መጠይቅ ሲጠየቁ የሚሰጡት መልስ ለወዳጅ አገሮች አስታውቀናል እያሉ ነው። ይህ ዐይነቱ አባባል በመሰረቱ የትግልን ዲያሌክቲክንና ሎጂክን በፍጹም አይመለከትም። አንድ የውጭ ኃይል ስልጣን ላይ ካለ አገዛዝ ጋር እጅና ጓንቲ ሆኖ የሚሰራ ከሆነና፣ አገዛዙ አገራችንን በማፍረስ ፖለቲካው እንዲገፋበት ማንኛውንም ዐይነት ድጋፍ የሚሰጠው ከሆነ ሎጂካሊ ሲታሰብ አንደኛው ወዳጅ፣ ሌላው ደግሞ ጠላት ሊሆን አይችልም። ስለሆነም ይህ ዐይነቱ እጅግ የተምታታና ከሳይንስና ከሎጂክ ጋር የማይጣጣም ትግል የሚባለው ፈሊጥ ለህዝባችንና ለአንድነታችን የሚደረገውን ትግል ዓላማ-ቢስ ያደርገዋል። በሁለተኛ ደረጃ፣ አገዛዙ እስካሁን ድረስ በተከተለውና በሚከተለው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ላይና፣ ህዝባችንን ወደ ድህነት በገፈተረው የኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ላይ አንዳችም ስምምነት የለም። እንዲያውም በአብዛኛዎች አነጋገርና ግንዛቤ አሁንም ቢሆን በአገራችን ምድር በመንግስት የተደገፈ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ነው የሚካሄደው እየተባለ ነው  የሚነገረን። ሀቁ ግን እነ አቶ መለስ ስልጣን ሲይዙ ከቀረበላቸው ቅድመ-ሁኔታዎች አንዱ የኒዎ-ሊበራል የነፃ ገበያ ኢኮኖሚን ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው ነው። በመሆኑም በእነ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅትና(IMF) የዓለም ባንክ አማካይነት የዓለም አቀፍ ኮሚኒቲው ባዘዘው መሰረት የነፃ ገበያ ቅድመ-ሁኔታዎች ናቸው አንድ በአንድ የዋሉት። እነዚህ ደግሞ በተግባር ሲተረጎሙ ስትራቴጂክ የሆኑ የአገሪቱ ሀብቶች በአገዛዙና በእሱ ስር በተደራጀው ኤፈርት በሚባለው ድርጅት ቁጥጥር ስር ነው እንዲወድቁ የተደረገው። ይህ  ዐይነቱ በውጭ ኃይሎች ተዘጋጅቶ የመጣውና ተግባራዊ የሆነው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ነው አገራችንን መቀመቅ ውስጥ የከታት።

በመሀከላቻን ያለው ትልቁ ችግር ትግል በሚባለው መድረከ ውስጥ ከዚህም ከዚያም የተሰባሰበ፣ የዚህ ወይም የዚያኛው ድርጅት አባል ወይም ደጋፊ የነበረ፣ ክፉም ሆነ ደግ ስራ የሰራ በአንድ የትግል መድረክ ውስጥ መካተታቸው ነው። ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታትም የጭንቅላት ተሃድሶ ስራ ስላልተሰራ ትግል የሚባለው ፈሊጥ በመግበስበስ የሚካሄድ እንጂ በጠራ ርዕይ ዙሪያ ጥናት እየተጠና አይደለም። ስለሆነም አንዳንዱ በሚጠይቅበት ጊዜ የሚሰጠው መልስ ወያኔን ከመጥላት የሚያልፍ አይደለም። አብዛኛው ታጋይ  ወይም የአገር ተቆርቋሪ ነኝ ባይ፣ ትግሉ ይህንን ወይንም ያንን ድርጅት፣ ይህንን ወይንም ያንን ግለሰብ ከመደገፍና ከማምለክ የሚያልፍ አይደለም። ይህም ማለት እስከዛሬ ድረስ የሚካሄደው ትግል ህዝባችንን የስልጣኔ ባለቤት ለማድረግና አገራችንም በአካባቢው አገሮች ደግሞ ምሳሌ እንድትሆንና እንድትከበር ሳይሆን  ስልጣን ላይ ለመቀመጥና ለመታወቅ ብቻ የሚደረግ ትግል ነው ። ከዚህ ስንነሳ ትግሉ የአገር ወዳድነት ስሜት ይኑረው አይኑረው ለማወቅ በጣም የሚያስቸግር  ነው። መግበስበስ የበዛበት ትግል በመሆኑ ትግሉን መልክ ለማሲያዝና፣ ወዳጅና ጠላትን ለመለየት የማይቻልበት ሁኔታ ከተፈጠረ ረዘም ያለ ጊዜ ሆኗል ማለት ይቻላል።አንዳንዱ ግራ ይሁን ቀኝ፣ ፋሺስት ይሁን ሌላ፣ በአጭሩ  ምን ዐይነት ርዕዮተ-ዓለም እንደሚከተል የሚታወቅ ነገር የለም። ስለዚህም ሰፋ ወዳ አለና ወደ ተወሳሰበው የዓለም ሁኔታ ስንመጣ አብዛኛዎቻችን፣ በተለይም ደግሞ በተከታታይ ለድህረ-ገጾች የሚጽፉም ሆነ ተጋብዘው ንግግር የሚያደርጉ ኢትዮጵያውያን ስለዓለም ሁኔታና የዓለም ፖለቲካ፣ የሚሊታሪና የኢኮኖሚ አወቃቀር፣ እንዲሁም  በአገራችን ላይ ስለሚኖራቸው ተፅዕኖ የሚያስተምሩንና የሚነግሩን ምንም ነገር የለም። መሰረታዊ በሆኑ ጥያቄዎች ላይ ግልጽነት ከሌለ ደግሞ ለኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነትና፣ እንዲሁም በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ ለተመሰረተ ሰፋ ላለ ኢኮኖሚ መታገል በጣም አስቸጋሪ ይሆናል ማለት ነው።

እንደሚታወቀው እ.አ ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ የዓለም የፖለቲካ፣ የሚሊታሪና የኢኮኖሚ ሁኔታ እጅግ እየተመሰቃቀለና፣ በተለይም አብዛኛዎቹ የሶስተኛው ዓለም አገሮችና ህዝቦቻቸው ከአቅማቸው በላይ እየሆነ መጥቷል። ኮሙኒዝም ከፈራረሰ በኋላ ብቸኛው ኃያል መንግስት እኔ ብቻ ነኝ የሚለው የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም በሱ ቁጥጥር ስር ያሉ፣ የዓለም አቀፍን ስም የያዙ ኢንስቲቱሽኖችን መሳሪያ በማድረግ፣ በተለይም በአፍሪካ አገሮች ላይ ጫና በማድረግ ኢኮኖሚያቸውን ለማዘበራረቅ ችሏል። በነፃ ገበያ ስም አማካይነት ተግባራዊ የሆኑት የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች በሙሉ፣ የተወሰነውን የህብረተሰብ ክፍል ሲያደልቡ፣ በሌላ ወገን ደግሞ ሰፊው ህዝብ ወደ ድህነት እንዲገፈተር ተገደደ። የውጭው ገበያ ክፍት በመሆኑ ከውጭ የሚገባው አዳዲስና በጠቀሜታ ላይ(Second hand goods)የዋሉ ዕቃዎች ከውስጥ የማመረት ኃይላቸውን አዳከሙ። በዚህም ምክንያት የተነሳ አዳዲስ የስራ መስክ መከፈት ቀርቶ፣ ራሱ ሰራተኛው ሲሰራ ከነበረበት በመባረር የስራ አጥ ለመሆን ተገደደ። ይህ በራሱ በትላልቅ ከተማዎች ውስጥ አዲስ ዐይነት የህብረተሰብ ቀውስ በመፍጠር፣ ተከታታይና ጥሩ ገቢ የሌለው ሰፊ ህዝብ በቆሻሻ  ቦታዎች(Slums) እንዲኖር ተገደደ። በሌላ ወገን ደግሞ አዳዲስ የሚሰሩት ህንፃዎችና የመኖሪያ ቤቶች ከተማዎቹ ውስጥ ካሉት የመብራትና የንጹህ ውሃ አቅርቦት ጋር እየተመጣጠኑ ባለመሰራታቸው በከፍተኛ ደረጃ ንጹህ ውሃንና ኃይልን በመጋራት ሰፊው ህዝብ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዲወድቅ ተገደደ። ይህ ዐይነቱ ሁኔታ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ አፍጦ አግጦ ይታያል።፡በግሎባላይዜሽንና በነፃ ንግድ ስም ተግባራዊ የሆነው የኢኮኖሚ ፖሊሲ እንደምናየው አገራችን ከጥገኝነት ያላቀቀ ሳይሆን የባሰውኑ ዕዳ ውስጥ የከተተንና፣ ኢኮኖሚያችንን ያዘበራረቀ ነው። በዚህም ምክንያት የተነሳ አገራችን እንደ አገርና ህዝባችንም እንደ ህብረተሰብ እንዳይታይና ህልሙንና ፍላጎቱን ተግባራዊ ሊያደርግ የሚችልበት ሁኔታ እንዳይፈጠር ተደርጓል። የኢትዮጵያዊነት ትርጉሙም እየጠፋና ሰፊው ህዝብ እየተናቀና ተመጽዋች እየሆነ ለመኖር ተገዷል።

ይህ በቻ አይደለም፤ የአሜሪካን ኃያል መንግስት በቻይናና በአንዳንድ በኢኮኖሚ እያደጉ በመጡ አገሮች የበላይነቱን ላለመነጠቅ ሲል በአንዳድን አፍሪካ አገሮች ውስጥ የጦር ሰፈሩን በመዘርጋት፣ ብዙ የአፍሪካ አገሮች በጦርነት እንዲታመሱ እያደረገ ነው። በዚህም ምክንያት የተነሳ አገዛዞች ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ቅድሚያ መስጠት አለባቸው በማለትና መኮንኖችን በማሰልጠን የብዙ አፍሪካ መንግስታትን አትኩሮ ወደ ጦርነት እንዲያዘነብሉ ማድረግ ችሏል። ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለማህበራዊ ፕሮጀክቶች ሊውሉ የሚችሉ ሀብቶች በዚህ ዐይነቱ አሳሳቸ ፖሊሲ አገሮች እየወደሙ ናቸው። የወያኔ አገዛዝም በዚህ ዐይነቱ የፀረ-ሽበርተኝነት ፖሊሲ በመካተት ይኸው እንደምናየው ራሱን ማጎልመሱ ብቻ ሳይሆን የሰው አገር ድንበር ጥሶ በመሄድ አገራችን ተወዛግባ እንድትኖር አላስፈላጊ ሁኔታዎች ፈጥሯል።

በመሰረቱ እነዚህ ከላይ አጠር መጠን ባለ መልክ የዘረዘርኳቸው ጉዳዮች የፖለቲካ ፓርቲዎችና በየጊዜው በየተሌቪዠኑ እየቀረቡ ገለጻ የሚሰጡ፣ ወይም ስለ ዓለም ፖለቲካ የጥያቄና መልስ ምልልስ የሚያደርጉ ግለሰቦችና ድርጅቶች ተግባሮችና ግዴታዎች ነበሩ። እንደማየውና እንደምከታተለው ከሆነ ጋዜጠኞችም ሆነ ራሳቸው ተጠያቂዎቹ በዓለም ላይ ምን እንደሚካሄድ የማያውቁ ይመስል የሚጠይቁትና የሚሰጡትም መልሶች ከተጨባጩ የዓለም ሁኔታ ጋር በፍጹም የሚጣጣም አይደለም። ሁኔታው በዚህ መልክ የሚቀጥል ከሆነ ጋዜጠኞችም ሆነ ራሳቸው ተጠያቂዎች በብዙ ሺህ የሚቆጠር ወጣትን በማሳሳት የኢትዮጵያዊነት ስሜት ደብዛው እንዲጠፋ ለማድረግ ይችላሉ። ዕውነተኛ የአገር ወዳድ ስሜትነት እንዳይዳብር በማድረግ ይህንን ወይንም ያኛውን ኃያል መንግስት እየተለማመጠ የሚኖር ትውልድ እንዲኮተኮትና የስልጣኔውም መንግድ እጅግ አስቸጋሪ እንዲሆን መንገዱን ሁሉ ያመቻቻሉ።

ስለሆነም የኢትዮጵያ ጠንቆችና ኢትዮጵያዊነትን የሚቀናቀኑ አስተሳሰቦችና የትግል ዘዴዎች ናቸው የምላቸው ነገሮች አብዛኛውን ጊዜ ዋና ምክንያታቸው በሰፊውና በሎጂካዊ መንገድ ካለማሰብ የመነጩ ናቸው። አብዛኛዎቻችን አንድ ወጥ አመለካከት አዳብረናል። አገርን በመገንባትና በማፍረስ መሀከል የተደረገውን በውስጥና በውጭ ኃይሎች መሀከል ያለውን የተወሳሰበ ትስስር ለማየትና ለመተንተን የምንችልበት መሳሪያ ያለን አይመስለኝም። በተለይም የተለያዩ ምሁሮች በአንድ ነገር ላይ ለምን የተለያየ አመለካከት ሊኖራቸው ይችላል ብለን ጥያቄ ስለማናቀርብ ነገሩን በመናቅና በመናናቅ መሀከል ያለ፣ ወይም ያለመስማማት ችግር አድርገን እንወስደዋለን። በመሰረቱ በሁለት ሰዎች ወይም በተለያዩ ድርጅቶች መሀከል ስምምነት ሊኖር የማይችለው አንድን የህብረተሰብ ሁኔታ በተለያየ መልክ ስለሚተረጉሙትና የተለያየ መልስ ለመስጠት ስለሚፈልጉ ነው። ወደ አገራችን ስንመጣ ያለው ችግር ግን በመሰረቱ አንድን የህብረተሰብ ታሪክ ለማንበብ የሚያስችለን አስተሳሰብ ወይም ስልት(School of Thought) ለማዳበር ያለመቻላችን ነው። አብዛኛዎቻችን በምን ዐይነት ቲዎሪ እንደምንደገፍና አንድን ተጨባጭ ሁኔታ እንዴት አድርገን ማንበብ እንዳለብን የተገነዘብን አይመስለኝም። ካለቲዎሪ ተግባር ስለማይኖር፣ በጭፍኑ የሚደረግ ትግል ወደ አጉል ግብግብና ጥፋት ያመራናል።

ስለዚህም ለኢትዮጵያ ጠንቅ የሆኑ ነገሮች፣ 1ኛ) የሃሳብ ጥራት አለመኖር፣ 2ኛ) በአንዳች ዐይነት ርዕይ አለመመራት፣ 3ኛ፟) የሃሳብ ጥራትና ርዕይ ሳይኖር ይህንን ሆነ ያንን ድርጅት በመከተል ወደ ጠብ ማምራት፣ 3ኛ) ለመደማመጥ ያለመቻል፣ 4ኛ) በፕሪንሲፕል አለመመራትና ለህሊና ለመገዛት አለመቻል፣ 5ኛ) ለአገር ዕድገትና ስልጣኔ የሚደረገው ትግል ከፍተኛ ዕውቀትን እንዲመጠይቅ ለመገንዘብ አለመሞከር፣ 6ኛ) ስለሆነም በዕድገት ስም የሚምል ወይም ተማርኩ የሚል ሁሉ ስለ ዕድገት አንድ አንድ ዐይነት አመለካከት ሊኖረው እንደማይችል ለመረዳት አለመሞከር፣ 7ኛ፟) ይህንን በሚመለከት በምሁራን ዘንድ የተደረገውን ሰፋ ያለ ትግልና ክርክር ለማወቅ አለመጣር፣ 8ኛ) የፖለቲካን ትርጉም ለመረዳት ያለመቻል፣ 9ኛ) የዓለምን የፖለቲካ፣ የሚሊታሪና የኢኮኖሚ አወቃቀር በየዋህነት መነጽር መመልከት 10ኛ፟) አሳሳች ኃይሎችን ለማወቅ ጥረት አለማድረግና ዝም ብሎ እነዚህ ወዳጃችን ናቸው፣ ይረዱናል ብሎ ዝም ብሎ በጭፍን ዕምነት መጓዝ… ወዘተ. እነዚህና ሌሎች አያሌ ነገሮች ለአገራችን ዕድገትና ሰላም ለሚደረገው ሰፊው ህዝባችን  እንቅፋት በመሆን ተብትበውን ይዘዋል።   ጤናማ የሆነ በሰብአዊነትና በዲሞክራሲያዊ መሮሆች ላይ የተመረኮዘ የኢትዮጵያዊነት ስሜት እንዳይዳብር ያግዱናል። ከድህነት እንዳንላቀቅና ዘለዓለማችንን ተመጽዋች ተቀባይ እንድንሆን ያደርጉናል። ባጭሩ የሳይንስና የቴክኖሎጂውን መንገድና ለሁለ-ገብ የሚደረገውን በራስ ላይ የመተማመንን ትግል ያግዱብናል፤ ዘለዓለማችንን በጨለማ ዓለም ውስጥ እንድንኖር ያደርጉናል።

 

የብሄረሰብ ጥያቄ አፈታትና የፌዴራሊዝም ጉዳይ !

ለሁላችንም ግልጽ መሆን ያለበት ጉዳይ የብሄረሰብን ጥያቄ በክልል እየከለሉ ችግሩን መፍታት በፍጹም አይቻልም። ከላይ ደረጃ በደረጃ ለማሳየት እንደሞከርኩት መስረታዊ ጥያቄ የተገለጸለት ዲሞክራሲያዊ ኢንስቲቱሽንና የፖለቲካ ጥበብን የተካነ መደብ አለመኖሩ ነው ያለውን መጠነኛ አለመግባባት ሊያባብሰው የቻለውና የሚችለው። በተለይም ያልተገለጸለትና ዲሞክራሲያዊ ያልሆነ ኢንስቲቱሽንና የገዢ መደብ ከውጭ ኃይሎች ጋር በመቆላለፍ ማንኛውንም አገር አፍራሽ ፖሊሲ የሚያካሄድ ከሆነና የጦር ሰፈርም በመስጠት በአካባቢው ሰላም እንዳይኖር የሚያደርግ ከሆነ  ለብሄረሰብ ነፃነት እንታገላለን የሚሉ ኃይሎች ነገሩን ሊያባብሱት ይችላሉ። ከእንደዚህ ዐይነቱ አስቸጋሪ ሁኔታ መውጣት የሚቻለው በሁሉም ነገሮች ላይ ግልጽ የሆነ ውይይትና ጥናት ሲካሄድ ብቻ ነው። በፍልስፍናና በሳይንስ ዙሪያ ግልጽ አቋም መያዝ የተቻለ እንደሆነና፣ የነፃነት ጉዳይ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል የሚመለከት መሆኑን ግንዛቤ ከተደረሰበት በቀላሉ መፍትሄ መስጠት ይቻላል።

በመሰረቱ የአንድ ብሄረሰብም ሆነ ህዝብ ጥያቄ በመጀመሪያ ደረጃ መሰረታዊ ነገሮችን፣(Basic Needs) ማለትም፣  የተስተካከለ ምግብ፣ ንጹህ ውሃ፣ መጠለያ ማግኘት፣ ህክምናና ትምህርት ቤት ማግኘት ናቸው። እነዚህ ነገሮች የማንኛውም ህዝብ ጥያቄዎችና ከመብትም ጋር በጥብቅ የሚተሳሰሩ ናቸው። ማንኛውም ብሔረሰብ ሰው እንደመሆኑ መጠን፣ ለመኖር፣ ለማሰብና ለመስራት ይችል ዘንድ በየጊዜው ተመጣጣኝ ምግብ ማግኘት አለበት። እንዲዚሁም ንጹህ ውሃ ማግኘት አለበት። የለም መጀመሪያ መብትህን ማግኘት አለብህ፤ ለዚህም የራስህን ዕድል በራስህ ለመቀዳጀት ከፈልግህ ታጋል የሚባል ከሆነ አንድ ህዝብ ዕውነተኛ ነፃነቱን እንዳይቀዳጅ እንደማድረግ ይቆጠራል። በተለይም በአውሮፓ የህብረተሰብ ታሪክ ውስጥ የብሔረሰብ ጥያቄ እንደመታገያ መሳሪያ ሆኖ ተወስዶ አይታወቅም። በአውሮፓ የትግል ታሪክ ውስጥ ቅድሚያ የተሰጣቸው ጭንቅላትን የሚያዳብሩ የፍልስፍናና የተፈጥሮ ሳይንስ እንዲሁም ቋንቋን ማበልጸግና በማዳበር ላይ ያተኮረ ነበር። በሁሉም አገሮች የተለያዩ ቋንቋዎች ይነገሩ ነበር። ይህ አካሄድ አለመግባባትን በመፍጠሩና፣ ለዕድገትም እንቅፋት በመሆኑ የግዴታ አንድ ቋንቋ መፍጠርና ማዳበር ተቻለ። በዚህ አማካይነት  በአጭር ጊዜ ውስጥ ስልጣኔ መቀዳጀት ተቻለ። ወደእኛ አገር ስንመጣ ግን የተያዘው የዳበረውን የግዕዝና የአማርኛ ቋንቋ በማጥፋት ሁሉም አዲስ በተፈጠረለት አዲስ ፊደልና በቋንቋው እንዲነጋገር በማድረግ ህዝቡ ጭንቅላቱን እንዳይከፍትና እንዳይፈጥር ማድረግ ነው። በተለይም የቋንቋ ምሁራን ነን የሚሉ የእንግሊዝ ሰላዮች በአገራችንና በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች በመሰግሰግ አደገኛ ስራ እየሰሩ ነው። በውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ውስጥ የተሰገስጉ የእንግሊዝ ሰላዮችና ትላልቅ ህንፃዎች በመገንባት በዕርዳታ ስም የሚዘባነኑት ዋና ተልዕኮአቸው  ብሄረሰብን ከብሄረሰብ ማጋጨትና በተለያዩ የሃይማኖት ተከታዮች መሀከል መፋጠጥ እንዲኖርና የርስ በርስ ጦርነትም እንዲከካሄድ ማድረግ ነው። ለሁሉም ህዝብ ደህንነትና ለአገራችን ዕድገት እታገላለሁ የሚል ሁሉ ይህንን የተመሰጣጠረ ሁኔታ ጠጋ ብሎ መመልከትና መመርመር አለበት። በየዋህነት እዚህና እዚያ የሚደረገው መሯሯጥ የመጨረሻ መጨረሻ ገደል ውስጥ ነው የሚከተን።

ሰለዚህም የችግሩ አፈታት ከዲሞክራሲያዊ ሁኔታዎችና ቀስ በቀስ ብቃትነት ያላቸው አገር አቀፋዊ እንስቲቱሽኖች ከመቋቋማቸው ጋር የተያያዘ ነው። ብሄረሰብን በክልል አካልሎ ፌዴራላዊ አገዛዝ ነው ያለው ማለት ቀልድ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ፌደራላዊ አወቃቀር ከሪፑብሊካዊ አስተሳሰብና አገዛዝ ጋር የተያያዘ ነው። በሌላ አነጋገር የአንድን ግለሰብም ሆነ የአንድን ደርጅት ዲስፖታዊ አገዛዝና ሬሶርስን መቆጣጠር የሚቃወም ነው። ሪፑብሊካዊ አገዛዝ የግለሰብ ነፃነቶችንና ከዚህ ጋር የተያያዙ ማንኛውም መብቶችን፣ ማለትም የፕሬስ ነፃነትና በነፃ መደራጀትንና ሃሳብን መግልጽ የሚያከብር ነው። ሪፑብሊካዊ አወቃቀር በገዢው መደብና በመንግስት መኪና መሀከል ያለውን ልዩነት ቁልጭ አድርጎ የሚያስቀምጥና፣ የመንግስት ኢንስቲቱሽኖች የአንድ የገዢ መደብ የግል ሀብት እንዳልሆኑ የሚያረጋግጥ ነው። በመሆኑም በህግ አውጭው፣ አጽዳቂውና አስፈጻሚው መሀከል የስራ ክፍፍል መኖር አለበት። አንድ የገዢ መደብ በህግ አስከባሪ ፍርድ ቤት ውሳኔ ውስጥ መግባት የለበትም። ይህ ሲሆን ብቻ ወደ ፊዴራሊዝም ስርዓት ለማምራት ይቀላል።

በመሰረቱ የፌዴራላዊ ስርዓት አወቃቀር ሀብትን ለማንቀሳቀስና ለዕድገት የሚያመች ነው። በማዕከላዊ አገዛዝ አማካይነት ተግባራዊ ሊሆን የማይችለው ዕድገትና ከዚህ ጋር የተያያዙ እንስቲቱሽናዊ ለውጦችና መሻሻሎች ተግባራዊ ሊሁኑ የሚችሉት አንድ አገር በፌዴራል ደረጃ ስትዋቀር ነው።  ይህ ብቻ ሳይሆን፣ በክፍለ-ሀገሮች መሀከል ውድድር እንዲኖር በማድረግ ዕድገትን ያፋጥናል። ይሁንና ግን አንድን አገር በፌደራል ደረጃ ማዋቀር የግዴታ በየቦታው የተገለጸለትና የማሰብ ኃይሉ ከፍተኛ የሆነን አገዛዝንና የተማረ የሰው ኃይልን ይጠይቃል። እንደ አገራችን ባለ ሁኔታ ውስጥ በክልል ደረጃ የሚዋቀር ፌዴራልዝም የግዴታ ወደ ዋር ሎርድነት የሚያመራና ዕድገትን የሚቀናቀን አካሄድ ይሆናል ማለት ነው። በየክልሉ ተዋቀሩ የተባሉት የፌዴራሊዝም አስተዳደሮች በሙሉ በምንም ዐይነት ፊዴራሊያዊ የሚያሰኛቸው አይደሉም። በአጠቃላይ ሲታይ በአንድ ዲስፖቲያዊ አገዛዝ ቁጥጥር ስር ያሉና ባስፈለገበት ጊዜ ጣልቃ በመግባት በኗሪው ላይ ጦርነት የሚያውጅ ነው። በየቦታው የሚካሄዱትም  የልማት ክንውኖች በሙሉ አገራችንን ወደ ማዕከለኛው ዘመን በፍጥነት እንድትጓዝ  ያደረጉ እንጂ ሰፊውን ህዝብ ከድህነት ያላቀቁና ስርዓት ያለው ኑሮ እንዲኖር ያደረጉ አይደሉም።

ክዚህ ሁሉ አስቸጋሪ ሁኔታ ለመውጣት ቀደም ብዬ ባለፈው ጽሁፌ ላይ ለማሳየት እንደሞከርኩት በመጀመሪያ ደረጃ ከሁሉም ብሄረሰቦች የተውጣጡ ግለሰቦች የሚሰለጥኑበት ኢንስቲቱሽን ማዋቀርና እዚያው ውስጥ ገብተው እንዲማሩ ማድረግ ችግሩን ሊፈታው ይችላል ብዬ አምናለሁ። በመሰረቱ በአገራችን ያለው ችግር የብሄረሰብ ጥያቄ አለመፈታት ጉዳይ አሁንም አገራችን ፊዩዳላዊ ወይም ያልተገለጸለት አስተሳሰብ ባላቸውና ኋላ-ቀር በሆኑ እንስቲቱሽኖች መተዳደሯ ነው። በዚህም ምክንያት የተነሳ ህዝባችን እንዳይማርና እንዳያውቅ ተደርጓል። ርስ በርሱ እንዲጠራጠር ሆኗል። ይህንን ችግር ለመፍታት የሚቻለው ከኤሊት ትምህርት ባሻገር አጠቃላይ የሆነ የማስተማር ዘመቻ ሲካሄድ ነው። በቅርቡ በሁለት የዲሞግራፊ ፕሮፌሰሮች አማካይነት ተጽፎ ለንባብ ከቀረበ መጽሀፍ መገንዘብ የሚቻለውና ብዙ ጥናቶችም የሚያረጋግጡት ለአንድ አገር ችግር ዋው መፍትሄ ሰፊውን ህዝብ ያካተተ ትምህርትና ሰፋና ጠለቅ ያለ ዕውቀት አስፈላጊ እንደሆኑ ነው። ከዚህ ስንነሳ የብሄረሰቦች ችግር እየተባለ የሚጠራውንና እንደ ጊዜ ቦንብ ሆኖ የሚፈራውን ችግር መፍታት የሚቻለው በዕውቀትና በተስተካከለ ዕድገት አማካይነት ብቻ ነው። በሌላ ወግን ግን ከዛሬ የክልል ፌደራሊዝም ይልቅ በክፍለ-ሀገር ደረጃ የዋቀረ ለስራና ሀብትን ማንቀሳቀስ የሚያመች ፊዴራላዊ አወቃቀር ቢዘረጋ ለዕድገት በጣም ያበጃል። በየክፍለ-ሀገራት የሚዋቀረውም አስተዳደር በዕውቀትና በችሎታ ሲሆን እንደ ቋንቋ የመሳሰሉትን ነገሮች በቀላሉ መፍታት ይቻላል። ያም ሆኖ የአማርኛ ቋንቋና ወደፊት ደግሞ ግዕዝ ብሄራዊ ቋንቋ ብቻ ሳይሆኑ የሳይንስና የፍልስፍና መማሪያዎች ሆነው መዳበር አለባቸው። እነዚህን በማዳከምም ሆነ በመከልከል ዕድገትን መቀዳጀት አይቻልም። እነዚህ ሁለቱ ቋንቋዎች በሁሉም ነገር የዳበሩና ለሳይንስና ለቴክኖሎጂ የሚያመቹ ናቸው። አሁን በቅርቡ በፊዚክስና በማቲማቲክስ በሰለጠኑ ኢትዮፕያውያን ፕሮፌሰሮች ከአማርኛ፣ ከግዕዝ፣ ከኦሮሞኛና አንዳንድ የእንግሊዘኛ ቃላት ታኮሎበት ለመማሪያ የቀረበው መጽሀፍ የሚያረጋግጠው በአገራችን ሁሉም የትምህርት ዐይነት በዚህ መልክ ቢቀርብ ለዕድገት ማምችቱ ብቻ ሳይሆን ለመግባባትና ሃሳብ ለሃሳብ ለመለዋወጥ በጣም ያመቻል።

ያም ሆነ ይህ ማካሄድ ያለብን ፖለቲካ ጥበብ የተሞላበት መሆን አለበት። የችግሩን መንስኤ በሚገባ መመርመር አለብን። ለመብታችን እንታገላለን የሚሉትን የዚህም ሆነ የዚያኛውን ታጋዮች ሁሉ እንደተገንጣይና እንደ አገር በታታኝ አድርገን መመልከት የለብንም። ያለውን ችግር ከሳይንስ አንፃር እንዴት እንደምንፈታው ቁጭ ብሎ ማጥናትና መወያየት ያስፈልጋል። በሌላ ወገን ደግሞ ሌሎች አንድነትን ይቀናቀናሉ ብለን ከመጻፉችንና ከማውራታችን  በፊት የአገር አንድነት እንዲጠበቅና በህዝብ መሀከል መተማመን እንዲኖር ምን ምን ነገሮችን ሰራን ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን። እንደሚታወቀው ለዛሪይቱ ኢትዮጵያ በዚህ ዐይነቱ እጅግ አስቀያሚ ሁኔታ ላይ መገኘት ሁሉም የየበኩሉን አስተዋፅዖ አድርጓል። ግራ ነኝ ከሚለው ጀምሮና ከቢሮክራሲውና ከአሪስቶክራሲው ወገን የተወለደው ሁሉ፣ ሁሉም በየፊናው ለዛሬይቱ ኢትዮጵያ በዚህ ሁኔታ ላይ መገኘት  የየበኩሉን በየፊናው አስተዋፅዖ አበርክቷል። አብዛኛው ባለማወቅ ሲሆን፣ ጥቂቱ ደግሞ የራሱን የኢኮኖሚና የሶሻል ስታተስ ለመጠበቅ ሲል አሻጥር መስራቱና ከኢምፔሪያሊስት ኃይሎች ጋር ማበሩና ለመበታተን የሚያመች ኢንፎርሜሽን ማቀበሉ ኢትዮጵያን አዳክሟታል፤ ለዚህ ዐይነቱ ግራ የገባው አገዛዝ ሁኔታውን አመቻችቶ ሰጥቷል።

ለመቋጠር ያህል፣ የኢትዮጵያ አንድነት ሊጠበቅ የሚችለው የህዝቡ ኑሮ ሲሻሻል ብቻ ነው። ከድህነትና ከስንዴ ልመና ሲላቀቅ ብቻ ነው። በአዲስ የዕድገት ጎዳና በአንድነት ተነሳስቶ አገሩን ለመገንባት ሲንቀሳቀስ በቻ ነው። የኢትዮጵያ አንድነትና ህዝባችንም የሚከበረው የሳይንስና የቴክኖሎጂ ባለቤት መሆን ሲቻል ብቻ ነው። ሰፋ ያለ የስራ ክፍፍል፣ ቆንጆ ቆንጆ ከተማዎችና መንደሮች፣ እንዲሁም ጠቅላላውን አገሪቱን የሚያዳርስና አንዱን ክፍለ-ሀገር ከሌላው የሚያገናኝ፣ ከተማን ከገጠሩና ከመንደሩ ጋር የሚያይዝ የመገናኛና የመመላለሻ የባቡር ሃዲድ ሲዘረጋ የዚያን ጊዜ ሁሉም ጠብመንጃ ማንሳቱን ያቆማል። ሁሉም በየፊናው ሆዱን ለመሙላትና ቤት ለመስራትና ልጆችም ለመውለድና ለማሳድገ ደፋ ቀና ማለት ይጀምራል። አሁንም ለአንድነትና ለኢትዮጵያዊነት በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ሁለ-ገብ(Holistic) የኢኮኖሚ ግንባታ እጅግ አስፈላጊ ነው። ከዚህ ውጭ ማሰብና በየፊናውና በቡድን ቡድን መደራጀቱና አሳሳቾችን እየጋበዙ የሆነ ያልሆነውንና፣ ከሳይንስ ውጭ የሆነ ነገር ንግግር እንዲያደርጉ ማድረግ የድህነቱና ያለመረጋጋት ዘመኑን ያራዝማል። ስለሆነም የውስጥ ለውስጥ ጨወታዎች መቅረት አለባቸው። ሁሉም ነገር ለሳይንስ፣ ለፍልስፍናና ለቴክኖሎጂ የሚለው አስተሳሰብ በሁላችንም ጭንቅላት ውስጥ መቀረጽና ተግባራዊ መሆን አለባቸው። በሌላ ወገን ግን ለብሄረሰቤ ነፃነት እታገላለሁ የሚለው ግለሰብም ሆነ ድርጅት ቆም ብሎ ራሱን መጠየቅ አለበት። እጅግ በተሳሰረና በብዙ ችግሮች በተወጠረ ህብረተሰብ ውስጥ እንዴት አድርጎ እሱ የሚለውን የብሄረሰብ ነፃነት ተግባራዊ እንደሚያደርግና ይህም ምን እንደሚምስል በዝርዝር ማስረዳት አለበት። ካለበለዚያ የብሄረሰቦች ጭቆና ሰፍኗል እያሉ ማራገቡ ብቻ የትም ሊያደርሰን አይችልም። ችግሩ የአንድ ወይም የሁለት ብሄረሰብ ችግር ብቻ አይደለም በአገራችን ምድር የሰፈነው። በአገራችን ምድር የሰፈነው ፀረ-ዲሞክራሲያዊ ስርዓትና ጭቆና እንዲሁም ድህነትና ኋላ-ቀርነት ከዘጠና በመቶ በላይ የሚሆነውን ኢትዮጵያዊ ሁሉ የሚመለከት ነው። ችግሩ የአማራም የኦሮሞም ሆነ የጠቅላላው ብሄረሰብ ችግር ነው። ችግሩ የቋንቋ ሳይሆን የነፃነት እጦት ነው። መሰረታዊው8 ጥያቄ ሁሉንም ነገር ሊያካትት የሚችል ሰፊ የዕድገት እጦት ጥያቄ ነው።             

       ፈቃዱ በቀለ                 fekadubekele@gmx.de

ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ፡ አሁን ውሳኔው ከሰው ሳይሆን ከእግዚአብሔር ነው!- ሰርጸ ደስታ

$
0
0

Woyane

ኢትዮጵያ እንደ ሕወሐት/ኢሕአዴግ ያለ የአገር ጠላት የሆነ አገዛዝ ገጠሟት አያውቅም፡፡ ሕወሐት መጀመሪያውንም ዓላማው ኢትዮጵያ የምትባለውን አገር ለማጥፋት እና ትግራይን ከኤርትራ ጋር በመገንጠል መንግስት መሆን ነበር፡፡ ቀስ ብሎ የመጣ የሐሳብ ለውጥ ነው ትግራይን ከመገንጠል ለምን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን  ለማጥፋት ሰፋ ያለ ዕቅድ አናቅድም በሚል ወደ ኢትዮጵያ ሥልጣን የመጣው፡፡ ዛሬ በሕዝቡ ዘንደ በይፋ እንደተባለው ዋናው የሻቢያ ቅጥረኛ ሕወሐት እንደሆነ ለሁላችንም ግልጽ ነው፡፡ ሕዝቡን በዘር መከፋፈልና አንድነት እንዳይኖረው ማድረግ ሕወሐት  ከሻቢያ ከተሰጠው ትዕዛዝ አንዱ ነው፡፡ ኋላም ይሄው ስልት አገርን በመከፋፈል በሕዝብ ላይ እንደፈለገው መሆን ስላስቻለው የራሱ አድርጎ ወሰደው፡፡ ሕወሐት/ኢሕአዴግ በመጀመሪየዎቹ የስልጣን ዘመኖቹ በሻቢያ መሪዎች ቀጥተኛ አዛዥነት ነበር ኢትዮጵያን ሲመራ የነበረው፡፡ ሆኖም ሕወሐት ውስጥ ይህን የማይቀበሉ በኢትዮጵያዊነታቸውም የሚኮሩ ሰዎች እንዳነበሩ አንዘነጋም፡፡ እንደምሳሌ በጀግንነቱ የሚታወቀውን ኃያሎም አረዓያን ማንሳት ጥሩ ግንዛቤ ይሰጣል፡፡ የሕወሐት መሪዎች ሻቢያ በሐኒሽ ደሴቶች ምክነያት ከየመን ጋር ጦርነት በገባ ጊዜ ወታደር ለሻቢያ ሊልኩ አስበው ቀድሞውንም የሻቢያን ነገር የማይወደው ኃያሎም ይህ ሊሆን አይችልም በማለት መቃወሙ አይዘነጋም፡፡ በዛን ወቅት ኃያሎም ከሠራዊቱ ጋር የደቡብ እዝ ኃላፊ ነበር፡፡ ያችን ሻቢያን የተቃወመበትን ቂም ይዘው የሕወሐት ባለስልጣናት ከሻቢያ ጋር በመሆን ኃያሎምን የሚያጠፉበት ተንኮል መሸረብ ያዙ፡፡ ከዛም የሎጂስቲክ መምሪያ በሚል ከሠራዊቱ ነጥለው አዲስ አበባ አመጡት፡፡ በመጨረሻም በአንድ ሻቢያ እንዲገደል ሆነ፡፡ ሻቢያም እስከ ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ ቆራጭ ፈላጭ ሆኖ አገልጋዩ ሕወሐትን በሞግዚትነት አሳደገው፡፡ እግዚአብሔር ጊዜው ሲደርስ ሻቢያና ሕወሐት ተጣሉ፡፡ ሆነ፡፡  ማንም ያ ይሆናል ብሎ አልገመተም፡፡ ቀድሞውንም ሻቢያ አስቦት የነበርው የኢትዮጵያ ሕዝብ በዘር ስለተከፋፈለ ትግራይን ወርሬ ሕዝቡን አንድፈለኩ አደርገዋለሁ ብሎ አስቦ ነበር፡፡ ጦርነቱንም ከትግራይ እንጂ ከሌው ኢትዮጵያ ጋር እንዳልሆነ በስፋት ነገረ፡፡ የትኛውም ያህል ከትግራይ በወጡ የሻቢያ ቅጥረኞች የሕወሐት ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ሕዝብ ልቡ ቢደማም የትግራይ ወገኖቹን ለመታደግና የአገርን ዳር ድንብር ለመጠበቅ አንድ ሆኖ ተነሳ፡፡ ሻቢያና ወያኔ በታትነንዋል አንድ አይሆንም ብለው ያሰቡተ ሕዝብ ይህ አጋጣሚው ለኢትዮጵያውያን አንድ መሆን ትልቅ ክስተት   ሆኖም የኢትዮጵያውያን አንደ መሆን ሕወሐትን ትልቅ ሥጋት ፈጠረበት፡፡ ለዛም በዘር የመከፋፈሉን ሥራ አጠናክሮ ቀጠለበት፡፡ ሕዝቡንም በማይፈልጋቸው ራሱ በቀጠራቸው ቅጥረኞች መሰቃየቱን ቀጠለ፡፡

በ1993 የዩኒቭረሲቲ ተማሪዎች ዓመፅ ምክነያት የአዲስ አበባ ሕዝብ ባሳየው ተቃውሞ ምክነያት አሁንም ሕዝቡ ለፖሊስ ሳይቀር የማይበገር አንድነት እንዳለው ተራዳ፡፡ ለወደፊት እንዲህ ያለ ተቃዎሞን የሚያፍንበትን ሕዝብን የሚገድልበትን ልዩ ኃይል እንደሰው የማያስቡ መደብደብና መግደል ብቻ የተማሩ ፌደራል ፖሊስ በሚል አንደ ቡድን አቋቋመ፡፡

በ1997 ምርጫ ተከትሎ በነበረው የሕዝብ ተቃውሞ ላይ በይፋ በጦር ሰራዊቱ ሕዝብ ፈጀ፡፡ ከዛ በኋላ አንድም እድል እንዳይኖር ጭራሽ ሁሉንም ነገር ዘግቶ ሕዝቡን በዘር በሐይማኖት እየከፋፈል አፋኝነቱን አጠናከረ፡፡ ሕወሐትን የሚናገር ሁሉ አሸባሪ፣ ሕገመንግስቱን በኃይል ለመናድ የሚል ታበፔላ እየተለጠፈበት ለእስርና ለሞት ሆነ፡፡ በመጨረሻም አንድም የተደራጀ የፖለቲካ ቡድን ሳይዝ ፓርላማውን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠርኩት፣ ሕዝብ መረጠኝ እያለ ያለመረጠውን ሕዝብ ጭራሽ ማበሳጨቱን ቀጠለ፡፡ አሁን ሕዝብ የሚያደራጀው አካል የለም፡፡ የግፉና ጫናው ብዛት ሞልቶ ሲፈስ ሕዝቡ ያለምንም ቀስቃሽ በራሱ ጊዜ ተነሳ፡፡ በኦሮምያ ይሄው ዛሬ 9 ወር ሆነ፡፡

ከላይ ያነሳሁት ትንሽ መንደርደሪያ እንዲሆነኝ ነው፡፡ በጥልቀት ላየው በደሉ ብዙ ነው፡፡ ዛሬ በኢሕአዴግ መዋቅሮች ሁሉ የሕወሐት ተወካይ የሌለበት የለም፡፡ ብዙ ገቢ የሚያስገኙ የአገሪቱ ድርጅቶች የኢትዮጵያ አየር መንግድን፣ ጉምሩክን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ የሕወሐት ተከታዮች ናቸው የሚመሯቸው፡፡ የመከላከያን የሥልጣን እርከን  እርሱት፡፡ የመከላከያ አምራች ድርጅቶችም እደዛው በተለያየ አገራት ያሉ የአገሪቱ ቆንሲላዎችን ለማሰብ እንኳን ይከብዳል፡፡ እንዚህ ሁሉ በትግራይ ተወላጆች መወረራቸው ሳያንስ እንዚሁ የትግራይ ተወላጆች በሕዝቡ ላይ ይደነፉበታል፣ ይገድሉታል፣ ያስሩታል፡፡ ይህ ትግራይ ላለው ሕዝብም የተለየ አይደለም፡፡ ከትግራይ የወጣው የትግራይ ተወላጅ በብዛት በአንድም ይሁን በሌላ የዚሁ የሕዝብና አገር ጠላት የሆነው ሕወሐት ደጋፊዎችና የሥረዓቱም ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡

አሁን ያለውን ሕወሐትን ለማስወገድ የሚደረገውን ፍልሚያ እየመራው ያለ አንድም የተደራጀ ኃይል የለም፡፡ የፍልሚያው ባለቤት ሕዝብ ነው፡፡ ሕዝቡ ለድርጅቶችም ያለው መተማመን ጎድሏል፡፡ አሁን ችግሩን በራሱ ሊወጣው የቆረጠ ይመስላል፡፡ ሕዝብ እንደ ሕዝብነቱ በየትኛውም የአገሪቱ አካባቢ በሕወሐት አፋኞች እየሞተ፣ እየተሰቃየ ነው፡፡ በትግራይ በሕዝብ ላይ ያለው አፈና ከሌላው ቢብስ እንጂ የተሻለ አይደለም፡፡ ግን እሰከ አሁን ባለው ሁኔታ ምንም እድል አልነበረውም፡፡ አሁን አገሪቱ ውስጥ እየሆነ ያለው አገሪቱ የኢትዮጵያውያን ሳትሆን የሕወሐት ባለስልጣናትና፣ የሐወሐት ደጋፊዎች በሕዝቡ ስቃይ ላይ እንደልባቸው የሚኖሩባት አገር ሆናለች፡፡ ለዚህ ከትግራይ የወጡ የትግራይ ተወላጆች ግንባር ቀደም ናቸው፡፡ የሌሎች ብሔረሰብ ተወላጆችም በአነስተኛ ዳረጎት በሎሌነት ለሕወሐት ሕልውና እያገለገሉ ናቸው፡፡

ሕወሐት አስደግሞ ያሳተመው ሕገ መንግስት የሚባዙ ሰነዱ ለብዞዎች ሞትና ሥቃይ ምክነያት እንደሆነ አንድም ምሁር ይሁን የፖለቲካ መሪ ደፍሮ ሊናገረው አልወደደም፡፡ እንደውም ሕገ ምነግስቱ ወድር የማይገኝለት እየተደረገ ይሞገሳል፡፡ ሲጀምር ይሄ ሕገ መንግስት የሚባው የሕወሐት የጥንቆላ ሰነድ የኢትዮጵያ ሕዝብ በግድ እንዲቀበለው የተደረገ እንጂ ሕዝብ ወዶና ፈቅዶ የተዘጋጀ አይደለም፡፡ ሕወሐትና ሌሎች የታሪክ ነቀርሳዎች በሕዝብ ላይ እንደልባቸው ለመሆን ያዘጋጁት ሰነድ ነው፡፡ ወደር የሌለው እየተባለ የሚወደሰው ሕገ መንግስት ከተለያዩ ዓለም ዓቀፍና አገሮች የተቀዱ (በቀጥታ የተኮረጁ) ደንቦችንና ሕጎችን ማካተቱ አንድ ነገር ሆኖ ሳለ ልክ በሳል ሰዎች ያወጡት እንደሆነ መወደሱ አሳዛኝ ነው፡፡ ልብ በሉ እነዚህ ሕገ መንግስተ በሚባለው ሰነድ የተካተቱ ነጠቦች አንድ መንግስት ጻፈውም አልጻፈውም ማድረግ የሚገባው መሠረታዊ የሰዎች የህልውና መብታት እንጂ ጽፌልሀለሁ እያለ የሚደነፋበት አይደለም፡፡ እነዚህን መሠረታዊ የሆኑ መብቶችን በአጃቢነት ተጠቅሞ ሕወሐት ለሕዝብና አገር አደገኛ ጠንቅ የሆኑ አንቀጾችን በዚህ የጥንቆላ ሰነዱ አካቶታል፡፡ አንቀጽ 39 ወደድንም ጠላንም ሆን ተብሎ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እንደገባ ብዙዎች እናውቃለን፡፡ ከዚህ ውጭ የሰንደቅ ዓላማን መልክ ዛሬ የሕገ መንግስት አካል እያስመሰለ ሕዝብን ሊከስበት ሊገድልበት የሚመክረው ሕወሐት በታሪክ የማይታወቅና የራሱና የራሱ ብቻ የሆነ የፓረቲውን ማንነት እንጂ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሊወክል አይችልም፡፡ ሕዝብ ከመሠረታዊ የሰንደቃላማዎቹ ቀለማት ውጭ ማንም ጠንቋ እየነገረው ድሪቶ ምልክት የመቀበል ግዴታ የለበትም፡፡ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ያለውን ባንዲራ መያዝ ወንጀል የሆነበት የታሪክ ምዕራፍ ላይ መድረሳችን ራሱ አሳዛኝ ነው፡፡ ለዘመናት አባቶቻችን የአገር ማንነት ምልክት አድርገውት የሞቱለት አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ እንጂ ሕወሐት አስጠንቁሉ ድሪቶ የደረተበትን ጨርቅ አይደለም፡፡ ደግሞስ ሕወሐት ስለ ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ለማውራት የትኛው ሙራልስ ሲኖረው ነው፡፡ የጨው መቋጠሪያ ጨርቅ ነው ብሎ የአገርን ክብር ምልክት የሆነውን ሰንደቅ ዓላማ ያጣጣለው ሕወሐት ለኢትዮጵያውያን የራሱ በደብተራ አስመትቶ ያመጣውን ድሪቶ እንድንቀበል አስገድዶ ዛሬም አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማውን የሽበረቶኞች ምልክት ይለናል፡፡ ጉድ ነው ዘንድሮ፡፡ ለዚህም ሰዎች ሕገመንግስቱን በመጻረር ተብለው ዜጎች ይከሰሳሉ ይገደላሉ፡፡ ሌላው ይሄው የሕወሐት የጥንቆላ ሰነድ ሕገ መንግስት ምንም ሚና የሌለውን የአገር ርዕሰ ብሔር ተብዬውን (ፕሬሲደንት) የስልጣን ገደብ ያስቀምጣል፡፡ 6 ዓመት ቢበዛ ደግሞ 12 ዓመት ይላል፡፡ አገርን ለመምራት ትልቁን ስልጣን የተሸከመውን ጠቅላይ ሚኒስቴር ተብዬውን ግን ምንም ገደብ ሳያበጅለት ያልፈዋል፡፡ እዚህ ጋር ስታነቡት ሟቹ ጠ/ሚኒስቴር ለራሳቸው እንዲመቻቸው ጠንቋዮቻቸውን አማክረው የደረሱት ሰነድ እንደሆን በደንብ ታስተውላላችሁ፡፡ ዛሬ ላይ ሁሉም ሕገ መንግስቱ በሚያዘው መሠረት እያለ ሲቀርብ ይገርመኛል፡፡ አዚም የዞረበት ሁሉ ሕገመንግስቱ ሕገመንግስቱ እያለ ያልቃል፡፡ እንግዲህ ይህ ሰነድ ነው ድንቅ እየተባለ ዛሬ ድረስ ለሕዝብና አገር ጥፋት ምክነያት እየሆነ እየታየ ሁሉም ፈዞ የሚያሞግሰው፡፡ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ያለ መጀመሪያ መቃወም ያለበት ይህን የሕወሐት መርዘኛ ሰነድ ነው፡፡ ጨው ለራስሕ ስትል ጣፍጥ ነው፡፡

ሌላው ሕወሐት ባለፉት 25 ዓመታት በሕዝቦች መካከል መቀራረብ እንዳይኖር በደንብ ለያይቷል፡፡ ከሁሉም በላይ ግን ሕወሐትና ሌሎች ኦሮሞን እንወክላለን የሚሉ ድርጅቶች የኦሮሞን ሕዝብ ከኢትዮጵያዊነቱ እንዲመክን በማድረግ ፍጹም አቅም የሌለውና እንደልባቸው የሚፈነጩበት አድርገውታል፡፡ ይህን ማድረግ የግድ ነበረባቸው፡፡ ኦሮሞ በሙሉ በማያወላዳ ኢትዮጵያዊነቱ ካለ የእነሱ ሕልውና እንማይኖር አሳምረው ያውቁታል፡፡ አስገራሚው ነገር በኢትዮጵያ ታሪክ የኦሮሞ ከፍተኛ ተሳትፎ የነበረበትን የታላቁን የሚኒሊክን ዘመን ከምንም በላይ አክፍተው እእምሮውን በርዘውታል፡፡ የኢትዮጵያም ሆነ የኦሮሞ ሕዝብ ጉልበት እዛ ታሪክ ላይ እንዳለ አሳምረው ያውቁታል፡፡ ያ ታሪክ ለሕወሐትና ለደጋፊዎቻቸው ምን ያሕል እንደሚያስፈራቸው ለማወቅ በቅረቡ አንድ የሕወሐት ደጋፊ የሆኑ ግለሰብ የተናገሩትን ማዳመጥ በቂ ነው፡፡ አኖሌና ጨለንቆ ለኦሮሞ የዚህ ዘመን ትውልድ በደንብ ተጋነውን ከፍተው አእምሮው ውስጥ ተቀረጾለታል፡፡ የዛ ዘመን ጀግኖች አባቶቹ ታሪክ ውርደት ሆኖበታል፡፡ አሳዛኝ ነው፡፡ ከኦሮሞ ወገን የሆነው የልጅ ልጃቸው ኢያሱ ንጉስ እንዲሆን ሚኒሊክ አልጋ ወራሽ ማድረጋቸው  ለምንድነው ብሎ እንዳያስብ ሕወሐቶችና አጋሮቻቸው በኦሮሞ ሕዝብ ላይ አዚም አድረገውበታል፡፡ የትኛውም ዘመን በደል ለኦሮሞ ሕዝብ ከአሁኑ በከፋ እንዳልነበረ መረዳት እንኳን እንዳይችል ተጋረዶበታል፡፡ ምኒሊክ ነበሩ እኩ ኦሮሞን ስልጣን እንዲይዝ ዙፋናቸውን ያስረከቡት፡፡ በሚኒሊክ ዘመንም ነበረ እኮ ታላላቅ የሚባሉ የአገሪቱ ስልጣኖች በኦሮሞ ልጆች እጅ የነበረው፡፡ ያ ታሪክ ለኦሮሞ ሕዝብ ብሎም ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ታላቅ ጉልበት እንደሆነ የሚያውቀው ሕወሐትና አጋሮቹ እናገረዋለሁ የቀድሞ የኦነግ አመራሮች ፍጹም ከኦሮሞ ሕዝብ አእምሮ እንዲመከን ከመደረግም አልፎ እጅግ የከፋ ሆኖ እንደያየው አደረጉት፡፡ ያ የጀግኖች ታሪክ ለሕወሐትና አጋሮች ቢያስፈራቸው አይገርምም፡፡ የዛ ዘመን ጀግኖች ዛሬም መንፈሳቸው አስፈሪ ነውና፡፡ የአባቶቹን ደም ያረከሰው የዛሬው የኦሮሞ ተወላጅ የቱ ጋር ጉልበቱ እንመከነ ዛሬም ሊረዳው አልቻለም፡፡ የቀድሞው ዘመን ናፋቂዎች የሉታል፡፡ ያስፈራሩታል፡፡ የቀድሞውን ዘመን የመሩት አባቶቹ እንደሆኑ ሳያውቅ የቀድሞውን ዘመን ይፈራዋል፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ከሥልጣን እየወጣ የሄደበት የአጼ ኃይለስላሴ ዘመን አይነገርም፡፡ ከፍቶ የሚነገረው ኦሮሞ ትልቁን ስልጣን የያዘበት የታላቁ ሚኒሊክ ዘመን ታሪክ ነው፡፡ በአኖሌና ጨለንቆ አእምሮውን ደፍነው ዛሬ እንሱ የፈነጩበታል፡፡ አሳዛኝ ነው፡፡ ከመቼውም ዘመን ለኦሮሞም ሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደዚህ ዘመን ያለ ውርደት አልገጠመውም፡፡ አንድ ሰው በጣም የሚወደው ልጁ ይሞትበትና እየመሰለ የልጁን አባት ከሐዘን እንዳይወጣ ለብዙ ወራት አንድ ተንኮለኛ የሆነ ጎረቤቱ ጠዋት ጠዋት እየመጣ የልጁን ነገር እያስታወሰ እንዴት ያለ ልጅ አጣሕ እያለ ብሶቱን እያነሳ ሲያስለቅሰው የውላል፡፡ የልጁ አባት ከልጁም ከኑሮውም ሳይሆን ጭራሽ ብዙ ችግር ይደርስበታል፡፡ መስራት ባለመቻሉም ይደኸያል፡፡ በዚህ ያ ተንኮለኛ ጎረቤቱ ደስ ይለው ነበር፡፡ ከእለታት አንድ ቀን አንድ ቅን ሌላው ጎረቤቱ ወደ ልጁ አባት ይሄድና የሄ ጎረቤትህ ሆን ብሎ አንትም በሀዘንና በድህነት እንድትሞት እያደረገህ ነውና ወዳጄ ራስህን ጠብቅ ይለዋል፡፡ ያም የልጁ አባት ነገሩ እውንም ገባውና ወደራሱ ተመልሶ ኑሮውን መኖር ቻለ ይባላል፡፡ ዛሬ አኖሌና ጨለንቆ የሚዘከሩለት የኦሮሞ ሕዝብ ለኦሮሞ የሚያዝኑ መስለው ኦሮሞ ፍፁም አቅም ያጣ ሊያደርጉት የሚያሴሩ ጠላቶቹ እንደሆኑ ዛሬም አልተረዳም፡፡

የኦሮሞ ሕዝብ የኢትዮጵያን ሕዝቦች ሁሉ መሪ በመሆን ሊንቀሳቀስ ይገባው ነበር እንጂ እንደዛሬው በትንንሽ ጉዳዮች ታስሮ ባልኖረም ነበር፡፡ ከኢትዮጵያዊነቱ እጅግ ስለራቅ በገዛ አገሩ ባይተዋር ነው፡፡ ሰልፍ ሲወጣ አባቶቹ የሞቱለት አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ትቶ ለዛሬው ሞት እንግልትና ባርነት ያበቁትን ድርጅቶች አርማ ይዞ ይወጣል፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ከከሕወሐት ሚስጢረኛ አጋር ከሆነው ኦነግና መሰሎቹ የአእምሮ ባርነት ራሱን ነጻ አድርጎ በኢትዮጵያዊነቱ የነጻነቱ መሪ ተዋናይ እስካልሆነ ድረስ እሱም በባርነት ይቀጥላል ሌሎችም ኢትዮጵያውያን ያለዚህ ሕዝብ ነጻ ሊወጡ እይችሉም፡፡

ዛሬ የተደረገውን ሠላማዊ ሰልፍ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ፍፁም ኢትዮጵያዊነት አጅቦት ቢሆን መላው የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚያነቃንቅ ክስተት ሊያደርገው በቻለ ነበር፡፡ ሞትም ቢኖር አብረውት ብዞዎች በሞቱም ነበር፡፡ ያ አልሆነም፡፡ የጎንደርን ሰልፍ ስኬታማ ያደረገው ቁርጠኛ ኢትዮጵያዊነቱ እንጂ መሣሪያ ስለያዘ ብቻም አደለም፡፡ መሣሪያ መያዝ በራሱ ሌላ ችግር በፈጠረም ነበር፡፡ አሁንም እላለሁ የኦሮሞ ሕዝብ ወደ ሙሉ ኢትዮጵያዊነቱ ተመልሱ ተግሎን ሊመራው ካልቻለ ነጻነት የለም፡፡ ጉልበት የለም፡፡ ዛሬ ማም ማን መለማመጥ አያስፈልገውም ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ነው የምለው፡፡ እስከዛሬ ብዙ ማባበሎችና ማደባበሶች ነበሩበት አሁን ጥርት ያለ አቋም ላይ መቆም ይገባል፡፡

በየ ቦታው ያሉ የትግራይ ተወላጆች ሕወሐትን እንጂ የትግራይ ሕዝብን እንደማይወክሉ በአጽዕኖት ሊታሰብበት ከሚገባቸው ጉዳዮች አንዱ ነው፡፡ የትግራይ ሕዝብ ከሌላው ኢትዮጵያ ሕዝብ የተለየ ጥቅምም ሆነ የአስተዳደር ፍትሕነት የለውም፡፡ ምን ዓልባትም ከሌሎች በከፋ ሁኔታ ዛሬ ባርነት ይኖራል፡፡ በሌሎች አካባቢዎች የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ግን በአብዛኛው በሚያሰኝ የሕወሐት ደጋፊዎች እንደሆኑ በተግባርም በቃልም እያሳዩን ነው፡፡ ሌላውንም በግፍ ለማኖር የበኩላቸውን እያደረጉ ነው፡፡ እነዚህ ወገኖች ዛሬ በሌላ ሕዝብ አደጋ ላይ ቢወድቁ ተጠያቂ የሚሆኑት ራሳቸው እንጂ አደጋውን የሚያደርሱባቸው አይደሉም፡፡ በግልጽ እንደምናየው እነሱ ሌላውን ለሞትና ለእንግልት ለሕወሐት እየሰለሉ እያስገደሉ በሠላም እንኖራለን ብለው ካሰቡ ጭንቀላታቸው በጥቅም መታወሩን ከማስተዋል ሌላ ምንም አይባልም፡፡ በግልጽም እንዳየንው ሕወሐት ከምንም በላይ እነዚህን ደጋፊዎቹን ይጠብቃል፡፡ የሌላው ሕዝብ ሕይወት ለሕወሐት እንደ ድል ነው የእነዚህ ደጋፊዎች ቁሳዊ ንብረት ግን ትልቅ ጥፋት ተደርጎ የሕወሐትን ሚዲያዎች ያጨናንቁታል፡፡ ከዚህ በኋላ ለእነዚህም ወገኖች እላለሁ ጨው ለራስሕ ስትል ጣፍጥ….. ዛሬ ንብረቴን ነኩብኝ የምትል ነገ ራስህም ለመኖርህ እርግጠኛ አይደለህም፡፡ ከምንም በላይ አደገኛ የሆነውን ምርጫ አለህና፡፡ በየትኛውም እይታ ግን እነዚህ የሕወሐት የግፍ አገዛዝ ተጠቃሚዎች መከራውን እየበላ ላለው የትግራይ ሕዝብ ምሳሌ ሊሆኑ አይችሉም፡፡

በየሥልጣኑ እርከን ላይ ያላችሁ ባለስልጣኖችም የሕወሐት ባርነታችሁ ይበቃ ዘንድ እስከዛሬ የበደላችሁትም ቢሆን ዛሬም ሕዝቡ ይቅር ይላችኋልና ራሳችሁን ከሕዝቡ ቀላቅሉ፡፡ የታጠቃችሁ ኃይላትም እንዲሁ፡፡ እየተለመናችሁ ሳይሆን ከሚመጣው ማዕበል ትድኑ ዘንድ ለሕዝብ ያላችሁን ወገንተኝነት ዛሬ በድፍረት ለመግለጽ ወስኑ፡፡ ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ …. በመጨረሻም ከሕዝቡ ጎን ቆማችሁም አልቆማችሁምም መውደቃችሁ እውነት ነው፡፡ ይህ ከላይ ከኃያሉ እግዚአብሔር የመጣ እንጂ የሰው አድርጋችሁ አትዩት!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ! ይጠብቅ!

 

አሜን

 

ሰርጸ ደስታ

 

 


 ነፃነት ለኢትዮጵያ——— በጋዜጠኛ ቶማሰ ሰብሰቤ

$
0
0

Freedomነፃነት የሌለው ህዝብ ሁሌም አይተኛም።በየትኛውም መንገድ ይተነፍሳል።ነፃነት የፈለገ ያክል አንፀራዊ ቢሆንም ሰው ሰለ ማንነቱ አና ሰለ ሀገሩ በነፃነት የማውራ መብት አለው።ህዝብ ያልተመቸውን አልተመቸኝም ብሎም መናገር ይችላል።በሀገር ጉዳይ ሁሌም ያገባዋል።ከህዝብ የበለጠ መንግስት ስለ ሀገር ነፃነት አይጨነቀም።ኢህአዴግ የፈለገ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠቅም ነገር ቢመጣ እሱ የማይጠቀም ካልሆን አይወደውም።ለምን?መንግሰት ለራሱ ነው የሚኖረው።ህዝብ ለሀገሩ። ጃ ፣ደርግም እና ኢህአዴግም የሚሰቁት ስለ ራሳቸው መልካም ነገር ስነግራቸው ነው።ይህ ሀገር ይጎዳል ብለን በኢትዮ ያዊነታችን ከጠየቅን እኔ አውቅላችዋለው ብለው ንፁሃን ይጨፈጭፋሉ።

 

አሁን ያለው ነፃነት እንዴት ይገለፃል?

 

ባለፉት 25 አመታት  ኢህአዴግ ነፃነት ሰፍሮ ሰቶናል።ሰለዚህም የሰፈራ ነፃነት ነው ።በነፃነት ብዙ ቦታዎች መሄድ እንድትችል ያደረገው ኢህአዴግ በወሳኝ ቦታዎች ነፃነት የለህም።ኢትዮጵያን ከኢህአዴግ ውጪ ለውጥ ያሰፈልጋታል ካልን ይህ የትኛውን ህዝብ አይመለከተውም ኢህአዴግ በስናይፐር ቋፐ ያደርግሃል። በነፃነት ችግራችን ለአለም እናሰማ ካልክ ሀገር ከሀዲ ነህ ተብለ ዘብጥተያ።የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ መወዳደር እንጂ ማሸነፍ አልተፈቀደላቸውም።፣ነፃ ሀገር ፣ ነፃ ፕሬስ ፣ነፃ ፖለቲካ ፣ ነፃ አመለካከት በኢህአዴግ ሰፈር ክልክል ነው።በየትኛውም የኑሮ ደረጃ ፖለቲካ አለ።በዚህ ፖለቲካ ደግሞ ካድሬ አለ።ኢህአዴግ ሰካራም ከጠጣ በሃላ እንኳን ሰለ እሱ ፖለቲካ ብቻ እንዲያወራ ሰርቷል።የኢህአዴግ የነፃነት አናት ላይ ቷ« የትኛውም ነፃነት ወያኔን የማይነካ መሆን አለበት » የሚል ነው።

 

ሚሰት ከባሏ ከጋር ምሳ እየበላች «አየህ ውዴ ቆይ መንግስት ምን ያደርግ እሺ ።ህዝቡ ቤት ያቃጥላሉ።ንብረት ያወድማሉ።እነዚህ እማ አሸባሪዊች ናቸው ኢህአዴግ እውነቱን ነው» ስትለው ለባሏ።ባል «እረ ልክ ብለሻል» አላት እና የ25 አመት ሚሰቱን እያየ በሆዴ« ያለኩትን ሰንምተሽ ልታሳፍሽኝ ነው »አላት ይባላል።የኢህአዴግ ነፃነት እንኳን ኦሮሞን ከአማራ ሊያግባባ ይቅር እና  ባል እና ሚስትን እርስ በእርስ በቁራኛ አስቀምተጣል።

 

ነፃነት ለምን ተፈለገ?

 

ዲሞክራሲ ያለ ነፃነት ቀለሀ እንደ ሌለው ጥይት ነው።ዲሞክራሲን ሰጠው ካሉ ደግሞ ከእነምናምኑ ነው እንጂ መርጦ አይደለም።ነፃ ትውልድ ካለ ሌብነት ፣ሀገር ክህደት ፣አንባገነንነት ፣ አድርባይነት ፣ ግፍ እና ጭፍጨፋ ያለም።ነፃ ትውልድ ለማምጣት ነፃነት ቆጥሮ አይሰጥን።ለዚህም ነው ትላንትም ዛሬም ነፃነት ኢህአዴግ ቆልፎ ያሰቀመጣት።ግን ህዝብ ነፃነት ይወልዳል እና ዛሬም እያየን ነው።ወያኔ የመልካም አሰተዳደር ችግር አለብኝ ፣ብዙ ባለ ስልጣኖቼ እውነት ነው ዘራፊዎች ናቸው ቢልም ፤ እኛ በቤተ መንግስር እናተ በቤተ ድህነት ውስጥ ናቹ ብለው ብነግሩንም እኛ ደግሞ በነፃነታችን ሰርዓቱ በቃን ፤ አዲስ ሰርዓት ያሰፍልገናል ማለት እንቀጥላል።

 

ኢህአዴግ ምን ያሰፈራዋል?

 

ብሶቴን ፣ችግሬን ፣ማንነቴን ፣ ሰቃዬን በአደባባይ ላይ ልናገር ለኢህአዴግ ሁሌም ራሰ ምታቱ ነው።አደባባይ እና ጎዳናዎች የመንግስት ውዳሴ ማሰነገሪያ እንጂ የህዝብ ጥያቂ ማቅረቢያ እንዳይሆኑ ሰርቷል።በየትኛው ቦታ በነፃነት የሚያወራ ሲጨልምቷ ወደ ቤቱ ሲገባ የሰራውን ይህ በው ብሎ ግድያ።ሁሉም ህዝቦች ለነፃነት ዘብ ከቆሙም ያመዋል።ኢህአዴግ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ያመዋል።የአማራ አመፅ ያሰኮርፈዋል።አንዱም እንዳይሳካ እየሰራ ነው።

 

 

 

ነፃነት ጠያቂው ማነው?

 

በኢህአዴግ ሁሉም  ህብረተሰብ ብዙ ጥያቄ አለው ።ከሁሉም ከባዱ ወያኔ ከስልጣን ውረድልን ሲባል ነገሮች አለቁ።የትኛውም ህዝብ ወያኔን በቃኝ ካለ አሸባሪ ነው።ተልዕኮ አለው።ብዙ ድራማ ይሰራል ።ሰው ይጨፈጨፋል ከዚያን እድሜ ማራዘም።ከዚያ ለሀገሬው ህዝብ ውሸት መንገር።ይህ የተነሳው ህዝብ አሸባሪ ነው ለእናተ አይበጅም ይሉናል።ልንግራቹ የምወደው የተነሳው ህዝብ ከኢህአዴግ እንጂ ለኢትዮጵያ መልካም አሳቢ ነው።ኢህአዴግ የሚኖረው ኢህአዴግ እሰካከ ነው።ኢትዮጵያ ግን ህዝቦቾ ናቸው ሀብቶቾ።

 

የጎንደር ነፃ ሰላማዊ ሰልፍ ምን አሰተማረን?

 

የጎንደር ህዝባዊ ኢህአዴግ ትክክል አለመሆኑን አሳይቷል።በቃኝም እንዴት እንደሆነ አይተናል።ከጎንደር ሶስት ነገሮችን በትንሹ ወስደናል።

አንደኛው ህዝብ የትኛውን ጥያቄ ለማንሳት ከመንግስት ፍቃድ እንደማያስፈልገው ያሳየ ነው።መቶ በመቶ ሰላማዊ ሰልፍ በተከለከለበት ሀገር ወደ በአዴን ቢሮ ሄዶ አንተብ ልቃወምህ ነውና ሰልፍ ፍቀድልኝ እንኳን ጎንደሬ ሌላውም አይቀልድም።ሁለተኛው ኢህአዴግ የሚከለክለው ባንዲራ ይዞ መውጣት።ሶስተኛ ጎንደሬዎች አማራነትን ሳይሆን ኢትዮጵያዊነትን አሳይተዋል።ስለ ኦሮሚያ ጠይቀዋል።ስለ ሙስሊም አሰምተዋል።የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱልን ብለዋል።በአንድ ቀን ህዝብ ሲቆጣ አሳዪን።

 

ኦሮሞ ለኦሮሞ ሳይሆን ከዛም በላይ ነው

 

የኦሮሞ አመፅ ኦሮሚያን መገንጠል ነው ብለው ለሚያወራ ሰው ምላሽ የሰጠ ሰልፍ ኦሮሞ አካሂዳል።አማራ ወንድሜ ነው።ሁላችንም ጠላት ገዥው ፓርቲ ነው ብለዋል።ይህ ነው እውነቱ በቃን ፣ሰለቸህን ፣ለውጥ በአዲስ መንግስት ነው ህዝብ ያለው።

 

ህዝቡ ምን ይላል?

 

ከኢህአዴግ ነፃ መውጣት የህዝቡ ጥያቄ ነው።ህዝቡ ያለው በቃኝ ኢህአዴግ ነው።በምዕራቡ አለም የአንድ ሰው መፈንከት የሚያሰደነግጠው ፣ የሶሪያ ነውጥ በእየሰዓቱ የሚያወራው ሚዲያ ስለ ወንድሙ መሞት እና መከፋት ስለምን አያወራም።The nearest is the best የሚለው የጋዜጠኝነት መሰታዊ መርህ ማን ወሰደው ?ወይስ ለሚዲያዎቹ ከኦሮሚያ እና አማራ ሶሪያ ይቀርባል? በዚህ ነው ህዝቡ ያፈረባቹ ።የኢህአዴግ ድግስ አጃቢ ሚዲያ ፤ በህዝብ ድግስ  ያለመገኘት አለ ነገር አሰባለ።

 

 

 

 

የሰማያዊ ፓርቲ ነገር መደገፍ፣ ወይንስ ማደናቀፍ ? –ይገረም አለሙ

$
0
0

blue-party.jpgአንደ መነሻ፤ አሁን በሥራ ያለውና ወያኔዎች በማጥቂያ መሳሪያነት የሚጠቀሙበት ነገር ግን እነርሱ የማያከብሩትና የማይገዙበት ህገ መንግስት ሰላማዊ ሰልፍን በተመለከተ እንዲህ ይላል፡፡
አንቀጽ 30 ንኡስ አንቀጽ 1 “ ማኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሳሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ ፣ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፡፡ ከቤት ውጪ የሚደረጉ ሰብሰባዎችና ሰለማዊ ሰልፎች በሚንሳቀሱባቸው አካባቢዎች በህዝብ አንቅስቃሴ ላይ ችግር እንዳይጥሩለማድረግ ወይም በመካሄድ ላ ያለ ስብሰባ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ ሰላምን ዴሞክራሲያዊ መብቶችን የህዝብን የሞራል ሁኔታ አንዳይጥሱ ለማስጠበቅ አግባብ ያላቸው ሥርዓቶች ሊደነገጉ ይችላሉ፡ ”
ነገር ግን አግባብ የላቸው ሥርዓቶች የተባሉት እስከ ዛሬም አልወጡም፡፡ በመሆኑም ጉዳዩ የሚስተናገደው ከህገ መንግስቱ አስቀድሞ በ1983 ዓም በወጣው የሰላማዊ ሰልፍና የፖለቲካ ስብሰባ ሥነ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 31/1983 ድንጋጌ ነው፡፡ የዚህ አዋጅ አንቀጽ 6/2 ስብሰባ ወይንም ሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርገው አካል ከ 48 ሰዐት በፊት አስቀድ ለአካባቢው የመስተዳደር አካል አንዲያሳውቅ ነው ግዴታ የሚጥለው፡፡ ለአካባቢው መስተዳድር ደግሞ የጸጥታ ጥበቃ የመመደብን ኃላፊነት ይሰጥና ስብሰባውም ይሁን ሰላማዊ ሰልፉ አዘጋጆቹ ባሰቡት ቀን አንዳይካሄድ የሚያደረግ በቂ ምክንያት ሲኖር ይህንኑ ገልጾ ለሌላ ቀን እንዲተላለፍ ከመንገር ያለፈ ሥልጣን አይሰጠውም፡፡
በተግባር ስናይ እንደኖርነው ግን በጠያቂም በተጠያቂም ዘንድ ይህ የሚታወቅ አይመስልም፡፡ በመሆኑም ፖለቲከኞች አይደለም ሰላማዊ ሰልፍና ህዝባዊ ስብሰባ የምክር ቤት ስብሰባቸውን በሆቴል ለማድረግ የፈቃድ ደብዳቤ ሲያስገቡ ተጠያቂውም ሲከለክል ነው ስንሰማም ስናይም የኖርነው፡፡ ነገሩ ያልተጻፈ ነገር ግን በሁሉም ዘንድ ተግባራዊ የሚሆን ልማዳዊ ህግ ሆነና ጋዜጠኞችም ፈቃድ ጠይቃችኋል፣ ተፈቅዶላችኋል ወዘተ እያሉ ሲጠይቁ መስማት የተለመደ ሆኗል፡፡ይህም በመሆኑ በወያኔ ፈቃድ ያልተሰጠው ሰልፍም ሆነ ስብሰባ በፖለቲከኞች ተካሂዶ አያውቅም፡፡ ወያኔ ደግሞ አይፈቅድም፡፡
አሁን ግን ይህ ህገ መንግስታዊ መብት ጎንደር ላይ ተግባራዊ ሆነ፡፡ ጎንደሬዎች ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ማሳወቅ አንጂ ማስፈቀድ አይጠበቅብንም ፣ህግ አክብረን የምናደርገውን ሰልፍ በህገ ወጥ መንገድ ለመግታት ከተሞከረ እኛም ህገ ወጥ አንሆናለን ( ብትተኩሱ አንተኩሳለን) በማለት መብታቸውን ብቻ ሳይሆን ህገ መንግስቱንም አስከብረው ዋሉ፡፡ ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ ስብሰባን በተመለከተ የፖለቲካ ፓርዎች ታሪክ ይህ መሆኑ እየታወቀ ሰማያዊ ለእሁድ ነሀሴ 1/2008 በባህር ዳር ሰላማዊ ሰልፍ ጠራሁ ማለቱ ወቅታዊውን የህዝብ ተቃውሞ ለመደገፍ ወይንስ ለማደናቀፍ ብሎ መጠየቅ ግድ ይሆናል፡፡ አንዲህ አይነት ነገሮች በይሉኝታ ለፓርቲዎች ባለ ስስት ወይንም ለአመራሮቹ ባለ ቅርበት ወዘተ በዝምታ እየታለፉ ብዙ ጉዳት ደርሷል፡፡ የሀገራችንን ፖለቲካና ፖለቲከኞች በቅርብ ሲከታተል ለኖረ የሰማያዊ የሰልፍ ጥሪ ከፕሮፓጋንዳ ፍጆታ አልፎ ተግባራዊ እንደማይሆን መረዳት አይገደውም፡፡ አስቀድሞ ለምን ብሎ መጠየቅ ለሚያወሩት ግን ተግባራዊ አንደማያደርጉት ራሳቸውም ለሚያውቁት ነገር አደናቃፊ ተደርጎ መታየት ስለሆነ ነው አስተያየቴን ከውጤት በኋላ ማድረጉን የመረጥኩት፡፡
የአዳራሽ ስብሰባ ያልተሳካላት የአደባባይ ሰልፍ መጥራት ለምን?
ሰማያዊ ፓርቲ ከወር በፊት በባህር ዳር የአዳራሽ ሕዝባዊ ሰብሰባ መጥራቱን ነገሮን ብዙም ሳይቆይ የአካባቢው መስተዳደር ለሌላ ግዜ አስተላልፉት ስላለን የቀረበውን ምክንያት ተቀብለን አስተላፈናል ተብሎ ቀን ተቆርጦ ተነገረን፡፡ አስተዳደሩም በሁለተኛው ቀን ተስማቶ እውቅና መስጠቱን ነግረውን ውጤቱን ሰንጠብቅ ለቅስቀሳ የተሰማሩ አባሎቻችን ታሰሩ ተብሎ ነገሩ የውኃ ሽታ ሆነ፡፡ በአካባቢው አስተዳደር እውቅና ያገኘ ስብሰባ በማን ነው የተከለከለው? አባላቱን ያሰረው ማነው?ለምንና በምን ምክንያት ነው የታሰሩት? ወዘተ ሰማያዊዎች ይህን እንኳን መከታተል መጠየቅ ቀርቶ ያንኑ የቢሮ መግለጫ እንኳን አለወጡም፡፡ አባላቱ የተፈቱት አሳሪው ሲበቃው ነው፡፡ ታዲያ የአዳራሽ ስብሰባ አዘጋጀሁ ብሎ ያልተሳካላትና ይህንንም በዝምታ ያለፈው ሰማያዊ ፓርቲ ድንገት ተነስቶ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱ መደገፍ ወይንስ ማደናቀፍ የሚል ጥያቄ አያስነሳም ትላላችሁ?
የሰላማዊ ሰልፉ ጥሪ ግብታዊ መሆን፤
ሰማያዊ ባህር ዳር ላይ ሰላማዊ ሰልፋ መጥራቱን የነገረን የጎንደሩ ሰልፍ በስኬት በተጠናቀቀ ማግስት ነው፤፡፡ሰላማዊ ሰልፍ የሚደረገው ዓላማው ታውቆ የሰልፉ ግብ ተለይቶ ሊገጥም ይችላል የሚባል ችግር ተተንብዮና መፍትሄ ተተልሞ በሰፊው ታቅዶና በቂ ዝግጅት ተደርጎ ነው፡፡ በተለይ በፖለቲካ ፓርቲዎች የሚጠራ ሰላማዊ ሰልፍ ታስቦ ታቅዶ በቂ ዝግጅት ተደርጎ የሚከናወን እንጂ ኮሽ ባለ ቁጥር አለን ለማለት፣ የህዝቡ ትግል ሲቀጣጠል የድል አጥቢያ አርበኛ ሆኖ ለመታየት፣ በህዘብ መስዋዕትነት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ወዘተ ለፕሮፓጋንዳ የሚጠራ መሆን የለበትም፡፡
ተግባራዊ እንደማያደርጉት እያወቁ ጣልቃ መግባት ለምን ?
ከላይ በመግቢያው የተገለጸውን የህገ መንግስቱንና በ1993 ዓም የወጣውን አዋጅ ድንጋጌዎች ተግባራዊ በማድረግ ለአደባባይ የበቁት ሰልፎች ( በኦሮምያም በአማራም) በፖለቲካ ድርጅቶች ያልተዘጋጁ ናቸው፡፡ፓርቲዎቹ አይደለም የአደባባይ ሰልፍ የሆቴል ስብሰባም ተፈቅዶላችኋል ካልተባሉ የማያደርጉ ለመሆናቸው እነርሱም አይክዱም የወያኔን አንባገነንነት በመከራከሪያነት ያቀርባሉ እንጂ፡፡ ታዲያ አሁን ምን ተገኝቶ ምን ታስቦ ምን የተለወጠ ነገር ኖሮ ነው ሰማያዊ ባህር ዳር ላይ ሰልፍ ጠራሁ ማለቱ ?
እዛው ባህር ዳር ላይ አይደለም የአደባባይ ሰልፍ የአዳራሽ ሰብሰባ ማድረግ ያልቻሉት የሰማያዊ አመራሮች ሰላማዊ ሰልፍ ሲጠሩ በአካባቢው መስተዳድር በኩል ምን የተለወጠ ነገር አይተው ነው? ወይንስ እኛም እንደ ጎንደሮች ማሳወቅ አንጂ ማስፈቀድ አይጠበቅብንም ብለን መብታችንን ተግባራዊ እንደርጋለን የሚል ወኔ በአንድ ጀንበር ተላብሰው? ብለን ጠይቀን ምላሽ ለማግኘት እንዳንሞክር ውጤቱ ከሁለት አንዱንም አላሳየም፡ እንደውም ከከንቲባው ጽ/ቤት ምላሽ እንዳገኙና መቼ የተጀመረና በየትኛው ህግ የተደነገገ አንደሆነ የማይታወቅ የስምምነት ሰነድ ለመፈራረም እንደተቀጠሩ ነበር የተናገሩት፡፡ መጨረሻ በምክትል ሊቀመንበሩ በኩል የተነገረውም ከወትሮው ለየት ለ ነው፡፡ እስከ ዛሬ የምንሰማው ፈቃድ ተከለከልን የሚል ነበር፤ የአሁን ግን ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ሰልፉን ሰርዘናል የሚል ነው፡፡ ሳይመክሩ ሳይዘክሩ ሳያቅዱና ሳይዘጋጁ ጠሩ፣ በዛው መልኩ ሰርዘናል አሉ፤ ታዲያ ይህን ምን ይሉታል፡፡ ሰማያዊዎች ምላሽ ቢሰጡበት መልካም ነው፡፡አባላትና ደጋፊዎችም ለምን ብላችሁ ጠይቁ፡፡ያለፈው ይበቃል፡፡

በኦሮምያ ዉስጥ ተቃዉሞ ተደርጓል፥ህወሃት ተንገዳግዷል –ጻዲቅ አህመድ

$
0
0
ከሁለት መቶ በላይ በሚሆኑ ከተሞች የተደረገዉ የኦሮምያ ተቃዉሞ የተሳካ ነበር። ህዝቡ ሰልፉን በሰላማዊ ምንገድ ቢያደርግም የህወሃቱ የሽብር ጦር አጋዚ 67 ሰዎችን ገድሏል። ከ 500 በላይ የሚሆኑን አቁስሏል። ሰልፉ በተለያኡ ከተሞች ባንድ ግዜ በመደረጉ ታሪካዊ ነበር። ይህ ሰልፍ ህወሃትን ያንገዳገደ ቢሆንም አምባገነናዊዉ ስርዓት በኦሮሞ ህዝብ ላይ ያለዉ ጭካኔ የተስተዋለበት ነዉ።


በኦሮምያ ዉስጥ ተቃዉሞ ተደርጓል፥ህወሃት ተንገዳግዷል – ጻዲቅ አህመድ

ዐማራው፣ ዐማራዊ ማንነቱን አረጋግጦ፤ ጀግንነቱንና ኢትዮጵያዊነቱን በደሙ እያስከበረ ነው! –ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት      

$
0
0

ሐምሌ  ቀን ፪ሺህ፰  ..             ቅፅ ቁጥር ፲፱

Moresh-901.jpgዐማራው የኢትዮጵያዊነት ዋልታና ማገር፣ ወራጅና ጭምጭም፣ ስሚንቶና አሸዋ መሆኑ ይታወቃል። ይህን ማንነቱን ጠንቅቀው የሚያውቁ፤ የአገርና የትውልድ ከኻዲዎች፣ ዐማራውን የሌሎች ነገድና ጎሣዎች ጠላት አድርገው በመሳል፣ ላለፉት ፳፭(ሃያ አምሥት) ዓመታት የዘረኛው የትግሬ ወያኔ አገዛዝ፣ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል እንዲፈጸምበት አድርገዋል። በመሆኑም በቁጥር ከአምስት ሚሊዮን የማያንሱ ዐማሮችን በልዩ ልዩ መንገዶች ከምድረ-ገጽ እንዲጠፉ አድርገዋል። አንዳንድ አወቅን የሚሉ፣ የማንነት ቀውስ ውስጥ የገቡ ሰዎችም «ዐማራ የሚባል ነገድ የለም» እስከ ማለት የደረሱ መኖራቸውን፣ ዐማራው በትዕግሥትና በትዝብት ሲያያቸው እንደኖረ ይታወቃል። ወያኔም በትዕቢት ተወጥሮ፣ ዐማራን «ፈሪ፣ ሽንታም፣ ወራሪ፣ ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛ»፣ ወዘተርፈ እያለ የዐማራን ዘር ከመግደልና ከማንገላታት አልፎ፣ መልካም ስምና ታሪኩን ጥላሸት ሊቀባ መሞከሩ በግልጽ ይታወቃል። ሆኖም፣ ሁሉም ነገር ገደብና ወሰን አለውና፣ የዐማራው ድምፅ ከፍ ብሎ እንዲሰማ በቆራጥነት የቆሙት ልጆቹ ባሰሙት ጩኸት፣ ይኸውና የጉዳዩ ባለቤት የሆነው የዐማራው ሕዝብ ከሐምሌ 5ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ፣ በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ፋና ወጊነት የተቀጣጠለው ሕዝባዊ አመጽ ጎንደር ከተማን፣ አዘዞን እና ደንቢያን አካቶ፣ በዛሬው ዕለት ማለትም ሐምሌ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. ሕዝባዊ አመጹና እምቢተኝነቱ ወደ ገብርየ አገር፣ «ራስ ጋይንት» ተሸጋግሮ ውሏል። የራስ ጋይንት ሕዝብ የወያኔን የስለላና የአፈና መዋቅር በጣጥሶ፣ «ወልቃይት ጠገዴ ዐማራ ነው!»፣ «ደንበራችን ተከዜ ነው!»፣ «አላማጣ፣ ሰቆጣ የዐማራ ነው!»፣ « የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች፣ ኮሎኔል ደመቀ፣ አንዱዓለም አራጌ፣ እስክንድር ነጋ ይፈቱ! በኦሮሞ ወንድሞቻችን ላይ የተከፈተው ጥቃት ይቁም!» እያሉ፣ ዐማራዊ ማንነታቸውን አስረግጠው፣ ጀግንነታቸው በኢትዮጵያነት የተለወሰ ኅብር መሆኑን አሳይተዋል።

የዐማራዊነት ጀግንነትን እንኳን ወዳጅ ጠላቶች፣ ማለትም፦ ደርሽቦች፣ ግብፆች፣ ጣሊያኖችና እንግሊዞች የመሰከሩት ገሐድ ዕውነት ለመሆኑ ለአፍታ መጠራጠር አይቻልም። ይህ ጀግንነትና ኅብረ-ብሔራዊነት የዐማራው ማንነት መገለጫው በመሆኑ፣ ሌሎቹ አግልለውትና የሞት ፍርድ ፈርደውብት እያለ እንኳን፣ ይህንም እያወቀ፣ በእነርሱ ላይ ቂምም ሆነ ጥላቻ በልቡ አልቋጠረም። ጎንደር፣ ጋይንት፣ ደብረታቦር፣ ባሕርዳር፣ አዘዞ እና ቆላድባ በተካሄዱ የሕዝባዊ እምቢተኝነት የተቃውሞ ሰልፎች፣ «በኦሮሞ ወንድሞቻችን ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋት እንቃወማለን!»፣ «በቀለ ገርባ ይፈታ!» የሚሉ መፈክሮችን ከራሱ ኅልውና በፊት አስቀድሞ አስተጋብቷል። ይህ የዐማራው የማንነቱ መለያ፣ የሆደ ሠፊነቱ መገለጫ፣ የትዕግሥቱ ስፋት መታወቂያ በመሆኑ፣ ሕዝባችን ላሳየው ጀግንነት፣ ቆራጥነት፣ ከሁሉም በላይ ዐማራዊ ማንነቱን ከኢትዮጵያዊነት ጋር ለንቅጦ፣ ለአገራችን ዳግም ትንሣኤ የለኮሰው የለውጥ ችቦ እኛ  በውጭ በስደት የምንኖረውን ልጆቹን አኩርቶናል።

ጎንደር፣ የኢትዮጵያ አንድነት ሲቋጠርበት እና ሲፈታበት የኖረ ታሪካዊ ምድር ነው። ዘመነ መሣፍንት የተጀመረው የትግሬው ራስ ሥዑል ሚካኤል በጎነጎነው ሤራ አማካኝነት በአገራችን በተከለው የእርስ በእርስ ጦርነት ከዚሁ ጎንደር ላይ ነው። ይህ ሤራ አገራችንን ለ70 ዓመታት ያህል ማዕከላዊ አመራር አሳጥቶ፣ ሕዝባችን እርስ በርሱ እንዳጫረሰ ይታወቃል። ይህ የብላ ተባላና፣ የፍዳ ዘመን የተቋጨውና የኢትዮጵያ አንድነት የተቋጠረው፣ ከዚሁ ጎንደር ውስጥ ከቋራ በበቀሉት፣ በአባ ታጠቅ ካሣ (ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ) በተመራው ፀረ-ዘመነ መሣፍንት እንቅስቃሴ ነው።

ከ1520 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 1535 ዓ.ም. ድረስ በክርስትና ሃይማኖትና በፍትሐ ነገሥት ላይ የተመሠረቱን ዕሴቶችን አጥፍቶ አረባዊ ማንነት ለማለበስ የተነሳው ግራኝ አሕመድ፣ ለ15 ዓመታት ያህል አገሪቱና  ሕዝቡን ለማጥፋት ያደረገው ጥረት፣ የተገታው ጎንደር ላይ፣ ዘንተራ፣ ደጎማ ሥር በተደረገ ጦርነት ላይ ነው። ይህ በጎንደር ምድር በግራኝ ላይ የተገኘው ድል ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት ማንሰራራትና መቀጠል ዋስትና ሆኖ ማገልገሉ ግልጽ ነው።

ልክ እንደዛሬው የትግሬ-ወያኔ ኢትዮያንና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት እንደሚያደርገው ሙከራ፣ ከ1928 ዓ.ም. እስከ 1936 ዓ.ም. የጣሊያን ፋሽስት ኢትዮጵያውያንን በነገድ ከፋፍሎ ለመግዛት ሞክሮ ነበር። ሆኖም የፋሽስት ጣሊያኖች ቅዠት ለመጨረሻ ጊዜ ላይመለስ ያከተመው፣ ጀግኖቹ የጎንደር አርበኞች፣ ጎንደር ላይ መሽጎ በነበረው የጄኔራል ናዚ ጦር ላይ፣ በሣንቃ በር፣ በቁልቋል በር፣ በሊማሊሞ፣ እና በጭልጋ ሰራባ ላይ በተጎናጸፉት ድል ነው። ይህም የኢትዮጵያን ነፃ አገርነት እንዲረጋገጥ ወሣኝ ሚና የተጫወተ እንደሆነ ይታወቃል።

በሌላ በኩል ወያኔ ለ17 ዓመት በትጥቅ ትግል የቆየው ትግራይና ጎንደር ክፍለ-ሀገሮች ውስጥ መሆኑ ይታወቃል። በ17 ዓመቱ ግብግብ ጎንደር አያሌ ጀግኖቹን አጥቷል። የደርግ አገዛዝ በሕዝቡ አመኔታ ሲያጣ፣ ወያኔ ዲሞክራት መስሎ በአስተጋባው ፕሮፓጋንዳው፣ «ከደርግ የከፋ አይመጣም» በሚል የሞኝና አርቆ ካለመሳብ በመጣ ችግር፤ ወያኔ ባገኘው ድጋፍ ተበራቶ፣ ጎንደር ከተማን እንደያዘ፤ ማዕከላዊ መንግሥቱ በሥልጣን ላይ ለመቆየት የቻለው ሁለት ወራት አይሞላም። የጎንደር በወያኔ እጅ መውደቅ፣ ለኢትዮጵያ መበታተን ፈር ቀደደ። ስለዚህ ሰሞኑን፣ ጎንደር ላይ የተጀመረው ሕዝባዊ አመጽ፣ ያለፉት ታሪኮቻችን ፈለግ ተከታይ በመሆኑ፣ የአገራችን የአንድነት ትንሣኤ ብሥራት እንደሆነ በልበ ሙሉነት ታሪክን ነቃሽ በማድረግ መመስከር ይቻላል። በመሆኑም ዛሬም ዘረኛውን የትግሬ-ወያኔ ቡድን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ አሽንቀንጥሮ ለመጣል፣ ጎንደር ላይ የተለኮሰው የለውጥ እሣት፣ ወያኔን ለብልቦ፣ የአገራችን አንድነትና የሕዝባችን ዕውነተኛ በግለሰብ ነፃነት ላይ የተመሠረተ ነፃነትና ዕኩልነት እንደሚያጎናጽፈን ጥርጥር የለንም።

ጥሪ ለኢትዮጵያ ሕዝብ፦ በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ በግፍ የተገደሉ ወገኖቻችን ደም ደመ-ከልብ ሆኖ የማይቀረው የሕይዎት መስዋዕትነት ከፍለው ያቀጣጠሉትን የነፃነት ትግል ወደፊት ስንገፋ ብቻ ነው። የትግሉም የመጀመሪያ ግብ እያንዳንዷ የኢትዮጵያ ግዛት ከግፈኛው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ነፃ እስክትወጣ ድረስ መሆን ይኖርበታል። በትግሉ ወቅት ለወደቁ ኢትዮጵያዊ ሰማዕታት፣ በስማቸው መንገዶች፣ ትምሕርት ቤቶች፣ እና የመታሰቢያ ሐውልቶች ልናቆምላቸው ይገባል።

በዚህ አጋጣሚ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት፣ ላለፉት አራት ዓመታት፣ የዐማራው ድምፅ እንዲሰማ ያደረገው ጥረት፣ ሰሚ ጆሮ እና አዳማጭ ኅሊና ያገኘ መሆኑን፣ ከጎንደር ሕዝባዊ አመጽ ለማረጋገጥ በመቻላችን፣ ልፋታችን የበለል አለመቅረቱን እንድንገነዘብ አድርጎናል። ይህም የተያያዝነውን የዐማራን ኅልውና እና ማንነት የማስጠበቅ ትግላችን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እያረጋገጥን፣  እስካሁን በቀጥታ የትግሉ አካል ያልሆኑ አካባቢዎች ትግሉን በፍጥነት እንዲቀላቀሉ ጥሪያችን እናቀርባለን።

 

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

ዐማራነታችን የማንነት መገለጫ መታወቂያችን፣ ኢትዮጵያዊነት ኃይማኖት ማተባችን ነው!

ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን  በንጹሃን  ሰልፈኞች ላይ መንግስት እየፈጸመውን የሚገኘውን  ግፍ ለማውገዝ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በበርሊን ለማድረግ ወሰኑ።

$
0
0
Peaceful #OromoProtests demonstrators arrested & beaten up. Police takes off shoes to prevent them from running.

Peaceful #OromoProtests demonstrators arrested & beaten up. Police takes off shoes to prevent them from running.

ዘርይሁን ሹመቴ ከጀርመን

ኢትዮጵያውያን  በጀርመን ኑረምበርግ በምትባል ከተማ ነሃሴ 1 2008 ዓም ባደረጉት ታላቅ ስብሰባ በመላው  የኢትዮጵያ ክፍል እየተቀጣጠለ ባለው የሀዝብ ለአምባገነናዊ  ስርአት አልገዛ ባይነት ምክንያት በመንግስት ታጣቂዎች  እየተፈጸመ  ያለውን ግድያ እስራት እንዲሁም ድብደባ አውግዘዋል። በተጨማሪም  በጀርመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ  ኢትዮጵያውያን በአሰቃቂ  ሁኔታ  በንጹሃን  ኦሮሞ እና አማራ ህዝብ የመንግስት ታጣቂዎች እየፈጸሙ ላሉት የነፍስ መገደል እና እስራት በመቃወም  በጀርመን በርሊን ከተማ  ድምጻቸውን ለአለም ለማሰማት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ለማዘጋጀት ፕሮግራም  አዘጋጅተዋል።

 

በስብሰባውም  የአርበኞች ግንቦት ሰባት የኮምኒኬሽን  ሀላፊ አርበኛ ኑር ጀባ ከኤርትራ ቀጥታ  በስልክ መስመር በመግባት ለታዳሚው  ከእያንዳዱ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚነሱት ህዝባዊ አመጽ ጀርባ  የአርበኞች ግንቦት ሰባት ከፍተኛ እንቅስቃሴ አለበት በማለት ማረጋገጫ  ሰጥቶል። የኮምኒኬሽን  ሀላፊው አርበኛ ኑር ጀባ በማከልም አምባገነናዊነትን ዘረኝነትን እንዲሁም ኢፍትሃዊነትን በመቃወም  በአደባባይ በመንግስት ሀይሎች በጥይት ለረገፉት ንጹሃን የኦሮሞ እና የአማራ ተወላጆች የወያኔ መንግስት ሃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ መውሰድ እንዳለበት አሳስቧል። እንደ አርበኛ  ኑር ጀባ  ገለጻ መሰረት አርበኞች ግንቦት ሰባት የወያኔን መንግስት በ3 ዓይነት መንገድ እየታገለ መሆኑን ለታዳሚው  ገልጸዏል። 1ኛው ህዝባዊ አመጽ በአገር ውስጥ በማነሳሳትና በመደገፍ 2ኛው ከኢትዮጵያ ውጭ  ወያኔንና የወያኔ ድርጅቶችን የማዳከም እንቅስቃሴ 3ኛው የትጥቅ ትግል ናቸው።  በተለያዩ  ጊዜያት የወያኔን ስርዓት በሀይል ለመጣል በሚደረገው  የትጥቅ ትግል በውጭ  የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እያደረጉት የሚገኘውን  የሞራል የቁሳቁስ የገንዘብ እርዳታ አርበኛ ኑር ጀባ  በሰራዊቱ ስም  ታላቅ ምስጋናውን በማስተላለፍ ፤ ይሀ ዓይነቱ  ድጋፍ  በሰፊው  እንዲቀጥል ጥሪ አስተላልፉዋል። ታዳሚውም በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች

የሚገኘው  የኢትዮጵያ ህዝብ በጨቋኞች አምባገነኖችና ከፋፋዮች መገዛት በቃኝ ብሎ  በአደባባይ ጸረ ወያኔ ትግሉን ለወራት አፏፉሞ በመቀጠሉ እና እጅግ አስገራሚ መስዋቶችን እየከፈለ በመሆኑ ለዚህ  ትግልን የተፈለገውን ግብ እንዲመታ  ለመደገፍ ወስነዋል። በዚህ የአቁዋም መግለጫ በውጭ አገር የሚኖሩ መላው ኢትዮጵያውያን በንጹሀን ህዝቦች ላይ ከፍተኛ ጭካኔ የተሞላበት ጭፍጨፋ እና ግድያ ሲፈጸም ቸል ማለት እንደሌለበት ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

 

ይህንን ተከትሎም  ታዳሚው ለኢትዮጳያ ህዝብ  ያለውን አጋርነት ከዚሀ በታች በተዘረዘሩት እንቅስቃሲዎች ገልጸዋል።

1ኛ የወያኔ ኢህአዲግ በህዝባችን ላይ እየፈጸመ ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት ለአለም አቀፍ ህብረተሰብ በማጋለጥ

2ኛ በበርሊን ከተማ  ከፍተኛ የተቁዋሞ ሰልፍ በማዘጋጀት የአለም  አቀፍ ማህበረሰብ በወያኔ ላይ ተጽእኖ እንዲያደርግ በመታገል

3ኛ አለአግባብ  የታሰሩ የህዝብ ተወካዮች ጋዜጠኞች የፖለቲካና የሀይማኖት መሪዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ከፍተኛ ግፊት በማድረግ

4ኛ ወያኔ ኢህአዲግ ሃገሩንና ህዝቡን ማስተዳደር ስላልቻለ በአስቸኩዋይ  ከስልጣን የሚወርድበትን እንዲሁም ስልጣኑን ለህዝብ አስረክቦ የሽግግር መንግስት ለመመስረት  የሚያስችል ነጻና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ  እንዲካሄድ መንገዶች በመፍጠርና በማመቻቸት ናቸው።

 

ዘርይሁን ሹመቴ ከጀርመን

 

 

 

የኦሮሚያ እና የአማራ የህዝቦች እምቢተኝነት እውን ኢህአዴግ እንዳለው ባለቤት የለውም? –በጋዜጠኛ ቶማስ ሰብሰቤ

$
0
0

ባለቤት አለው።

እንዴት?

እንማን?

Unity-1-741x437

የትኛውም መንግስት ከስልጣን ለማውረድ ሁለት መንገዶች አሉ።አንደኛው በታጠቀ ሀይል እየተመራ የራሱ ወታደር ፣የጦርነት ስልት ያለው ፣አለቃ እና ምንዝር የሚጨንር ያልው ትግል ነው።ሁለተኛው መሪ የሌው ባለቤት ህዝባው ትግል ነው።ሁለቱም የተለያዩ ባህሪያት አላቸው።በመጀመሪያው ማለትም ታጥቀው እና ተደራጅተው ስልጣን የያዙት እንደ ደርግ እና ኢህአዴግ ያሉት ናቸው።በሁለተኛው ስልት በኢትዮጵያ ታሪክ ተሞክሮ ያልተሳካው ህዝባዊ ነው።ህዝባው ትግል ባለቤቶ እንደ ህውሃት ፣እንደ ደርግ ያሉ መሪዎች እና ድርጅቶች አይፈልግም።ትግሉ የተጨቆኑ ፣ፍትህ ያጡ ፣እኩልነት እና ዲሞክራሲ የጠማች  ህዝቦች የሚያካሂዱት ነው።

 

ዛሬም ኦሮሚያ እና አማራ ያነሳው ትግል ህዝባው ነው።ከሁለቱ ህዝቦች ጀርባ ማንም አይንቀሳቀስም።ከጀርባቸው ግን አንድ ትልቅ ሃይል አለ ህዝብ።ማንንም የማይፈራ ፣ለሀገሩ የሚሞት እና እሳት ትውልድ።ለዚህም ነው የዛሬው ትግል ባለቤቱ ማን የሚለው ለመለየት ያወዛገበን።ኢህአዴግ ባለቤት የሌለው ትግል ነው ይላል።አንዳንዴም አንዳንድ ሃይሎች የሚሉ ምክንያቶች ይሰማል።ለኢህአዴግ ግልፅ ሊሆንለት የሚገባው ይሄ ትግል በግንቦት ሃያ ወይም በኦነግ የሚመራ ቢሆን ኖሮ ለምን ህዝቡን አያግዙትም ነበር።ሄደው ሄደው ካሸነፉ ስልጣኑ የእነሱ ሰለሆነ ለምን ዝም አሉ።ግንቦት ሰባትም ሆነ ኦነግ ይህን ያህል መጠነ ሰፊ የህዝብ እንቢተኝነት አግኝተው ለምን ሊጠቀሙበት አልፈለጉም?ከኢህአዴግ ጋር የሚመጣጠን መሳሪያ እና ተዋጊ ባይኖራቸው ከሚሊየን መሳሪያ ፣ከሚሊየን ወታደር የሚበልጥ ህዝብ በቀላሉ አግኝተው እነዚያ በሳል ታጋዮች እንዴት ሊያሳልፍት ወደዱ?።መልስ አንድ ብቻ ሰለሆነ ነው በኦሮሚያ የኦነግ ፋላጎት ሳይሆን ፍትህ ነው ።በአማራ ግንቦት ሰባት ሳይሆን ብሄራዊ ጭቆና ነው።እዚህ ታጋዩ ህዝብ፤ባለቤቱ ህዝብ፤የሚሰማው ህዝብ ፤ አሸናፊው ህዝብ ይሆናል።የማይካደው በኦሮሚያ ከኦፒዲዮ የበለጠ ሌላ ባንድራ ያየነው የመገንጠል ሳትሆን የኦፒዲዮ ግፍ ሰለሂነ ሲሆን በአማራ ያየነው ባንድራ ሀገራዊ ሰሜት እንጂ ሌላ ትርጉም የለው።ለዚህ የሚመሰለው ደግሞ ህዝብ ያውቃል።

 

ህዝብ ላይ ጥይት ተኩሶ ያሸነፈ የለም።ይህ የቅርቡ የሰሜን አፍሪካን አመፅ እና ማዕበል አሳይቶናል።በቱኒዚያ ለ23 አመታት ሀገሪቱን ሲበዘብዙ የነበረው ፕሬዘዳን የጣለው ህዝብ ሲሆን አብዮቱን ያቀጣጠለው አንድ ወጣት ነው።ቱኒዚያዊው መሀመድ ቦአዚዝ ድግሪ ይዞ ስራ አጥ ሆነ።እንደ ምንም ብሎ ተበዳድሮ የፍራፍሬ ነገዴ ሆኖ ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል ብሎ ኑሮን ጀመረ።ከእለታት በአንዱ ቀን ግን የአብባገነኑ መንግስት የሆነ ወታደር ቦአዚዝን ከሚሰራበት ጎዳና አስነስቶት ፍራፍሬው በተነበት።አሁን ተሰፋ አለቀ።ቢአዚዝ እራሱን የከተማው መስተዳድር ፊት ለፊት ቆሞ ፍትህ በሌለበት ሀገር አልኖርም ብሎ እራሱን በጋዜዝ አቃጥሎ ተሰዋ።ቱኑዚያዎች ያለአንዳች የታጠቀ አይል ብሶታች  ገለፁ።አንባገነኑ መንግስት ገለበጡት።ይህ ህዝባው ትግል ነው።አንዱ ቦአዚዝ ሚሊዮኖች ተከተሉት።

 

በሊቢያ ፣ግብፅ ፣ ሱዳን እና አልጄሪያም ብዙ ቦአዚዞች መጡ።መንግስት በህዝብ ተረታ።ህዝብ ማለት እንዲ ነው።የመጨረሻው ቀን እስኪመጣ ይታገሳል።ትግስቱ ካለቀ ይጋረፋል።ህዝባው አመፅ ሲነሳ ብዙ ብሶቶች ሰላሉ ቀደም በህዝቡ ልብ ሰላለ ትንሽ ጋዝ በቂ ነው ለመቀጣጠል።ቱኒዚያ አንባገነኑን መሪ የደመሰሰችው ቦአዚዝ ብቻ ሰለሆነ አይደል በህዝቡ ዘንድ የሚታይ እውነታ ፣ጭቆናው ፣ግፍ ሰላለም ጭምር ነው።ዛሬም ለኦሮሚያ እና የአማራ ህዝብ ሲነሳ የትላንት ሰቃዮች ከጀርባው አለ።ቱኒዚያ ለቦአዚዝ ሲነሳ አማራ በወልቃይት መነሳቱ አይቀርም ጊዜ ይጠይቃል እንጂ።በኢኮኖሚ እና በስልጣን ክፍፍል የተጎዳው ኦሮሞ ይባስ ብሎ መሬቱን ሲቀማ ልክ እንድ ቦአዚዝ ያለ አብዮት ይፈጥራል።የቱኒዚያ ሆነ ግብፅ አብዮት ባለቤቱ ህዝብ ነው።ጀማሪውም ህዝብ ነበር።ዛሬም የተወሰኑ የታጠቁ ድርጅቶች ፍላጎት ሊኖራችው ይችላል ኢህአዴግን ለመጣል ያ ጊዜ ግን ዛሬ የእነሱ አይደለም ።

ዛሬ አማራ አና ኦሮሚያ የምናያቸው ህዝባዊ እንቢተኝነት  በባዶ እጅ ስርዓቱ በቃኝ ነው።የታጠቀ ሳይሆን የህዝብ ጊዜ።ዛሬም ለኢህአደግ አልረፈደም እና ይህን አሰብበት።አንድ ሰው ስትገድል እናት እና አባቱ ፣የማቱ ቤተሰቦች ፣ጓደኞቹ እና የሰፈሩ ሰዎች ልብ ውስጥ ጥላቻ እና ቁጭት ትፈጥራለህ።ህዝብ ላይ በተኮስከው እጅህ ህዝብ ይበላሀል።ዛሬ የአንተ ቢመስል መንግሰት ይነግሳል ይወርዳል ህዝብ ይኖራል።የሰሞኑን የንፁሃን እልቂት ያዊእና ጭፍጨፋ መላው ኢትዮጵያዊ ከተማሪዎች ሞት ፣ ከ77 ድርቅ ፣ከደርግ ጭፍጨፋ ፣ከ97  ጭፍጫፋ ካጣናቸው የበለጠ ቂም እና ክፋት አለው።ለምን ካልከኝ ይሄ የዘር ጭፍጨፋ ጋር ተመሳሳይ ነውና።ግን ግን ኢህአዴግ ሆይ ትግራይ  ይህን አመፅ ትግራይ ቢሆን እንዲ ትጨፈጭፍ ነበር?

 

በቅርብ የኢትዮጵያ ታሪክ፡ትግራይ እሚባል ክፍለ-ሃገር፡ አልነበረም። –ዘርኡ መሃሪ

$
0
0

Tigray_Map~0ትግራይ ሳይሆን፡ ትግሬ ጠቅላይ-ግዛት የሚባለው ግን በአጼ ምንሊክ የተካለለ ነው። “ትግራይ” እሚለው ታድያ እንዴት መጣ? የየትኛው አካባቢ መጠርያነበር? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ፡ ብዙ ሰው (ወጣት የትግሬ ክፍለሃገር ተወላጅ ጭምር)የማያቀውን ሃቅ እንደሚከተለው እጠቅሳለሁኝ።

ኤርትራ እሚባል እንዳልነበረ ሁሉ፡ ትግሬ ጠቅላይ ግዛት እሚባልም አልነበረም። ከፍ ብሎ እንደተጠቀሰው፡ በአጼ ምንሊክ ግዜ ነው በጠቅላይ ግዛትነትየተዋቀረው።  ልብ በሉ፡ ትግሬ እንጂ ትግራይ አላልኩም። ትግሬ ጠቅላይ ግዛት የሚለው አጠራር እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ(በአጼ ኅይለሥላሴም በደርግም ጊዜ)የነበረ አጠራር ነው::

 

ትግራይ የሚለው አጠራር ታድያ መⶬ ነው የታወቀው? መልሱ በ1928 ወረራ አካባቢ፡በጣልያንና በእንግሊዝ የሚል ይሆናል፡ ከዛ በፊትና በሃላ ትግራይየሚለው ቃል የየትኛው አካባቢ መጠርያ ነበር?

 

ትግራይ ማለት ብዙ ባላባቶⶭ ያልነበሩበት አካባቢ፡ ከተለያዩ አካባቢዎች(ከኤርትራ፡ ከተቀረው የትግሬ አውራጃዎⶭ) ለከብቶቻቸው ሳር ፍለጋ፡ ወይምበሽፍትነት ሄደው እዛው የቀሩ ሰዎች የሰፈሩበት፡አሁን በትግሬ ክፍለ-ሃገር ሽሬ እና አካባቢው የሚገኘው፤ በሰሜን እስከ ኤርትራ ድንበር፡ በምአራብ እስከ ተከዜወንዝ ያለው ቦታ ነው። አንዳንዴ ሰዎⶭ ዓድዋንም ይጨምራል ይላሉ።  በአሁኑ አጠራር፡ ሰሜናዊ ምአራብ እየተባለ እሚጠራው አካባቢ ብⶫ ነበር ትግራይተብሎ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሲጠራ የነበረው። ለምሳሌ ያክል ለመጥቀስ፡ አንድ የተንቤን ተወላጅ፡ያኔ፡ ከተንቤን ወደ ሰሜን አቅጣጫ ለመሄድ ሲነሳ፡ የት ነውእምትሄድው ተብሎ ቢጠየቅ፡ መልሱ (ናብ ትግራይ ኢየ) ወደ ትግራይ ነው እምሄደው የሚል ይሆናል። ተንቤኖⶭ ትግራይ ሲሉ፡ ቀደም ብዬ የጠከስኩትንአከባቢን ነበር እሚያቁት። በዓጋሜ በኩል ቢሆንም ተመሳሳይ ነው። የዓጋሜ ነዋሪዎⶭ ትግራይ ሲሉ፡ ከዓጋሜ በስተ መእራብ ሲሄዱ የሚገኙትን፡ ቀደም ብዬየጠከስኩውⶨውን ቦታዎⶭ ማለታⶨው ነበር። ይሄ እንግዲህ ጸህፊው በሚያቀው፡ በኢትዮጵያ አቆጣጠር እስከ 70ⶩ ድረስ የነበረ ነው። ምሳሌ ልጥቀስ፡ የደርግእድገት በህብረት ዘመⶫ በተጀመረበት ወቅት ነው። በትግሬ ጠቅላይ ግዛት ተመድበው ሲሰሩ የነበሩ የዘማⶮⶭ ሃላፊዎⶭ፡ ከዓዲ ግራት ተነስተው፡ በላንድሮቨራቸው ፡ወደ ሽሬ በሚያመሩበት ጊዜ ብዘት እምትባል ትንሽ ከተማ ይደርሳሉ። ብዘት እንደደረሱ፡ አንድ መንገደኛ ወደ እነሱ ጠጋ ይልና፡ አፈናጥጡኝሲል ይጠይቃቸዋል። እነሱም፡ ወድየት ነው እምትሄደው ብለው ቢጠይኩት ወደ ትግራይ ሲል መለሰላቸው። ትግራይ ያለው ሽሬ አካባቢ ማለቱ ነበር።

 

እንግዲህ የህዝቡ ስሜትና ኩራት በአውራጃ የተመሰረተ  ሲሆን፡ ከፍ ሲል ደግሞ በኢትዮጽያዊነቱ የሚኮራ ነበር። አሁንም ቢሆን፡ አውራጃዊ ስሜት ትግራይከሚለው ስሜት ያይላል። በኤርትራም እንደዚያው ነው። የትግራይ እና የኤርትራ ዘመናዮⶭ ከፈረንጆⶭ የሰነቁትን የጥላⶭ ፍሬ፡ ከበረሃ ምሽጋⶨው ሆነው እየዘሩኤርትራንና ትግራይ አሚለውን ማንነት ለመፍጠር ብዙ ተጉዘዋል። በዚ አንጻር ሲታይ፡ የመሃል አገር ሰው አውራጃነትን ከተወ ዘመናት አልፈዋል። አነሰ ቢባልበጎንደር፡ጎጃም፡ወሎ እና ሽዋ ነው እሚያስበው፡ ያም ቢሆን በጣም የደበዘዘ ነው። አብዛኛው የነዚህ ጠቅላይ ግዛቶⶭ ህዝብ በኢትዮጽያዊነቱ ይቆረቆራል። ይሄከፍተኛ የእድገት ልዩነት ነው። ለዚህም ነበር፡ ወራሪዎⶭ፡ ይህንን የኢትዮጽያ ክፍልንና የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ለይተው ሲዘምቱባⶨው የነበረውና፡ አሁንምበተወካዮⶫⶨው በኩል ያንን የሚያደርጉት።  ትምክህተኛ እያሉ የሚጠሩት፡ ከነሱ ልቆ ስለሄደ ነው። እነሱ በአውራጃ በሚያስቡበት ጊዜ፡ የጠቀስኩዋⶨው የመሃልአገር ሰዎⶭ ኢትዮጽያዊነትን ያራምዱ ነበር። ትምክህቱ እንግዲህ ላቅ ብለው ማሰባⶨው ነው።በህብረተሰብ እድገት ደረጃ -ቤተሰብ፡ዘመድ፡ መንደር፡ወረዳ…ወዘተ…- እያልን በምንመዝንበት ጊዜ፡ ላቅ ብሎ እምናገኘው ኢትዮጽያዊ የመሃል አገሩ ነው። ለዛም ነው፡ በኢትዮጽያዊነቱ እማያመነታው።

 

ጣልያን፡ ኤርትራን ሲለቅ፡ ኤርትራዊነት የሚለውን ስሜት ለመፍጠር ቢሞክርም፡ ቢዙም ሳይሳካለት ነው አገሩን ለቆ የሄደው። የኤርትራን የማንነት ስሜትመፍጠር ያልቻለው ጣልያን፡ ትግራይ የሚለውንም መፍጠር አልቻለም፡ አንዳንድ የሰሜን ባላባቶⶭን ከማማለሉ በስተቀር። ጣልያንን ተከትሎ የመጣውእንግሊዝ ግን የዋዛ አልነበረምና፡ በደንብ ነው የሰራበት። ከዓድዋ በፕሮተስታንት እምነታⶨው ምክንያት በድንጋይ ተወግረው የተባረሩት አቶ ወልደማርያም፡ ወደኤርትራ ሄዱና ከአንድ የሰራየ ሴት ወልደአብ የሚባል ልጅ ወለዱ፡ ብሁዋላ አቶ ወለደአብ ወልደማርያም የተባሉት፡ፕሮቶስታንቱ፡ የኤርትራው ብሄረተኛመሆናⶨው ነው። ያኔ ነው፡ በእንግሊዝ መንግስት የትግራይ ትግርኚ የሚለውን ሃገር የመከፋፈል ደባ፡ ከኦጋዴን ፕሮጀክቱ ጋር አዳብሎ የገፋበት። ይሄ እንግዲህበ1930ዎⶩ (በአውሮጻውያኑ 1940ዎⶩ)መሆኑ ነው። በዛን ጊዜ በኤርትራ የተወለዱ ሰዎⶭ አሁን የ80 ዓመት እድሜ ባለጸጎⶭ ናⶨው። እነዚህ ናⶨውእንግዲህ፡ ያ በልጅነታⶭው የተለከፉበት መርዝ አለቅ ብሎአⶨው ለሺዎⶭ አመታት አንድ ሆኖ የኖረውን ህዝብ በዘረኝነት ሲያተራምሱት እሚታዩት። ለነገሩ፡ክአድዋ የሚወለዱት የስብሃት ነጋ ዘመዶⶭ ትውልዳⶨው ከእንግሊዝ ይመዘዛል። 5 ትውልድም አይደርስም፡ ዋአሮ የወለደⶫⶨው ፡የአገር ጎብኚው ማንስፊልድልጆⶭ ናⶨው። ለገሰ ዜናዊ የአበባው የልጅ ልጅ ነው፡ ጎጃሜ። አበባው-ነጋድራስ ተሰማ – አስረስ- ዜናዊ:፤ ይገርማል! መለስ ዘሩ ጠፋበትና፡ ወንድም ከወንድምሲያጋድል ሴኦል ገባ። ወይ ጉድ።

 

 

 

 

 


የኦሮሞ  እና የአማራ የህዝብ እንቢተኝነት እስከ ነጻነት።- ከተማ  ዋቅጅራ

$
0
0

Unity-1-741x437

የኢህአዲግ ሲሪቷ የከፋፍለህ ግዛ  መርከብ እየሰጠመች ነው። መርከቧ ላይ የተሳፈራችሁ በሙሉ በአስቸኳይ መውረጃው  ግዜው አሁን ነው። ልብ ለሚያደርግ ላስተዋለ ሰው ይህ የመጨረሻ የህዝብ ማስጠንቀቂያ  ነው።

ትላንትና ቴዎድሮስ የሚባል ጀግና  የተፈጠረው እንግሊዞች በግድ ህዝባችንን ለመግዛት ስለመጡ ነው።

ትላንትና ምኒልክ፣ አብዲስ አጋ፣ በላይ ዘለቀ፣ ባልቻ አባነፍሶ፣ የተባሉ ጀግኖች የተፈጠሩት ጣልያን በግድ ህዝባችንን ለመግዛት ስለፈለጉ ነው።

ታዲያ ዛሬ  አንባ ገነኖች ህዝባችንን ረግጠን መግዛት አለብን ሲሉን  እንደ አያት ቅድመ አያቶቻችን ጀግኖች የማይነሳ መስሎአቸው ይሆንን?  ድሮም ጃግና የነበሩት የኢትዮጵያ  አባቶች ዛሬም ጀግና የሚሆኑት የኢትዮጵያ ልጆች። ድሮም በግድ የማይገዙ አባቶች ዛሬም በግድ የማይገዙ ልጆች፣ ድሮም ጠላትን ለመምታት እስከሚጠፋም ያልተኙ አባቶች ዛሬም  ለለውጥ የተነሱ የኢትዮጵያ  ልጆች፣ ድሮም እየተዋደቀ ጠላትን ጥለው ነጻነትን ያበሰሩ አባቶች ዛሬም እየተዋደቁ አንባ ገነን ስርአትን አጥፍቶ ነጻነቱን የሚያመጣ ቆራጥ የኢትዮጵያ  ልጆች እንዳሏት ማወቅ ተስኗቸው ይሆንን?

ኩርንችት የዘራ ኩርንችት ይሰበስባል መልካም ዘርን የዘራ ያማረ ፍሬ ይሰብስባል ይባላል። ወያኔም የዘራውን የጥፋት ዘር መሰብሰቢያውአቸው  ደርሶአል። ዋይ ዋይ ለናንተ!

በሰላም ይኖር የነበረውን ህዝብ ነካክተው ነካክተው ቀፎው እንደ ተነካካበት ንብ ገልብጦ ወጥቷል። የወጣው ህዝብ ነጻነቱን ጫፍ ሳያደርስ በዳዬችንም ሳይደመስስ  አይመለስም። ይህ እውነት ነው ህዝብን ተዋግቶ የሚያሸንፍ ምንም ኃይል የለም። መፈራገጥ ለመመላለጥ ካልሆነ  በቀር።

ከዚህ በታች ማሳሰቢያዎችን ማስቀመጥ እፈልጋለው ይህ የሚሊዮኖች ህዝብ ማሳሰቢያ  ነው። በማሳሰቢያ መልክ የቀረበ  ትእዛዝ እንጂ ልመና  አይደለም።

ማሳሰቢያ 1 በኢህአዴግ ወንበር ላይ ቁጭ ብላችሁ የስልጣኑን በትር የያዛችሁ ኢትዮጵያኖች በሙሉ የሚሊዮኖችን ህዝብ ለማፈን መሞከር ሞኝነት ነው ይልቁንም ልትሰጥም ካለችው ከኢህአዴግ መርከብ ወርዳችሁ ወደ ህዝባችሁ ኑ። አሁን የመጨረሻ እድላችሁን የምታሳዩበት አጋጣሚ ላይ ስለሆናችሁ ከህዝብ ጋር በመሆን ወርቃማ ግዜአችሁን ትጠቀሙበት ዘንድ ህዝቡ ትዕዛዝ ያስተላልፋል።

ማሳሰቢያ 2 ለሃይማኖት አባቶች የሃይማኖቱ ስርአት በሚይፈቅደው መልኩ የህዝብን እንባን ማበስ ሲገባችሁ መከራውን ቢቻላችሁስ እንኳን ከፊት በመቅደም መካፈል ሲገባችሁ በተገላቢጦሽ ጥቂቶችን ለማገልገል ትዕዛዝ በመቀበል በኢትዮጵያ  ህዝብ ላይ የምትፈጽሙትን ክደት በፈጣሪም ቅጣትን በህዝብ ዘንድ ደግሞ ፍርድን የሚሰጥበት ግዜ ስለደረሰ እንደ ሃይማኖት አባትነታችሁን ለእውነት ብቻ  በመቆም በህዝባችን ላይ የሚደርሰውን ግፍና ግድያ ልታወግዙ ይገባል ይህንን ማድረግ ስትችሉ የህዝቡን በደልና ቁጣ ላይ ውሃ ለመቸለስ የምታስቡ በሙሉ ከድርጊታችሁ ትቆጠቡ ዘንድ ህዝባችን ያሳስባል።ፍርዱ ከምድርም ከሰማይም ነውና ያኔ መሸሽ አይቻልም።

ማሳሰቢያ 3 ለEBC TV እና ለFBC እንዲሁም ሌሌሎች ጋዜጠኞች የኢትዮጵያ  ህዝብ ከዳር እስከዳር በሚሊዮን ለተቃውሞ  እየወጣ ጥቂት ለምትሉ የስርአቱ ባሪያዎች ስለነጻነት እና  ስለእኩልነት ለመናገር በሚወጣው ሰላማዊ ህዝባችን ላይ አጋዚ እየተኮሰ ሲገድል አንድ አንድ ጸረ ሰላም ሃይሎች በፈጠሩት ሁከት ጥቂት ሰዎች ተገድለዋል በማለት ከሰው ህይወት ይልቅ ስለጠፋው  ንብረት አብዝታችሁ ስለምትጮሁ  ሆድ አደሮች፣ እነዚ ጸረ ልማት እና  ጸረ ዲሞክራሲ ናቸው እያላችሁ በኢትዮጵያ  ህዝብ ላይ የምትሳለቁ ጋዜጠኞች፣ በአፋጣኝ ከዚህ ድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ አሳስባለው  በመስጠም ላይ ካለችው ከኢህአዴግ መርከብ ላይ በመውረድ የህዝብ አጋርነታችሁን የምታሳዩበት ሰአት አሁን ነው።ይህ ሳይሆን ቀርቶ በውሸት ወሪያችሁ ጥቂት ጥቂት ስትሉ ግዜ እንዳያልፍባችሁ ይታሰብበት። ነገሮቹ ወደከፋ ደረጃ ከደረሱ በኋላ ተገድጄ ነበረ የሚለውን ተልካሻ  ምክንያት የኢትዮጵያ  ህዝብ ይቅርታን ያደርግልናል ብላችሁ አትጠብቁ። ህዝብ ላይ እየተሳለቃችሁ የስርአቱ አገልጋይ ሆናችኋልና የምትከፍሉት ዋጋ ከባድ ነው። የመጨረሻው ሰአት ላይ ስለሆነ እንደ ከዚ ቀደሙ ህዝብ ላይ ተሳልቆ መኖር አይቻልም።

ማሳሰቢያ 4 የኢትዮጵያን ህዝብ በመሰለል የምታገለግሉ ጆሮ ጠቢዎች እንዲሁም በቴሌቪዢን(እያዩ  መስሚያ) መስኮት ብቅ እያላችሁ ህዝብ ላይ መንግስት እርምጃ መውሰድ አለብት እያላችሁ የምትዘባርቁ ግለሰቦች  ህዝባችንን እየጠቆማችሁ አሳልፋችሁ የምትሰጡ የስርአቱ ጥቅመኞች በሙሉ ከአሁን በኋላ ሰልየም ሆነ በEBC TV በመቅረብ የምትዘላብዱ ግለሰቦች ግዜው ሳይረፍድባችሁ ከድርጊታችሁ ትቆጠቡ ዘንድ እናሳስባለን ይህንን ሳታደርጉ ቀርታችሁ በቀደመው ስራዬ ሆነን እቀጥላለው የምትሉ ከሆነ ከህዝባችን ዘንድ የከፋ ነገር እንደሚያጋጥማችሁ ለመናገር እፈልጋለው።

ማሳሰቢያ 5 ለመከላከያ ሰራዊት ከህዝብ ወጥታችሁ ህዝብን የምትገድሉ ከድርጊታችሁ ትቆጠቡ ዘንድ ቆም ብላችሁ ታስቡ ዘንድ የመጨረሻው ሰአት ላይ ናችሁ።ኢህአዴግ የተሳፈረባት መርከብ እየሰጠመች ባለችበት ሰአት የዚህ ስርአት አገልጋይ መሆን አብሬ ልስጠም ማለት በጣም ሞኝነት ነው። የመጨረሻውን ጥሪ ህዝባችን ያቀርብላችኋል ኑ ከሰፍው ህዝብ ከወገናችሁ ጋር ተደባለቁ እናንተ የህዝብ ህዝቡም የናንተ ወዳጅ ነውና። የህዝቡን ጥሪ ወደ ጎን በመተው እየገደልን እንቀጥላለን ማለት ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍላችኋል ገድሎና  አሰቃይቶ በየትኛውም አለም ላይ በሰላም መኖር አይቻልምና።

ማሳሰቢያ 6 ለፖለቲካ  ሰዎች እና ለሙህራን ህዝብ ጭቆናው በቃኝ ብሎ ገፍቶ በወጣበት ሰአት ትግሉን ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማስተሳሰር ይገባችኋል ወያኔ ባለው ስልጣን እና መሳሪያ ተጠቅሞ የህዝቡን እንቢተኝነት በሃይል ዝም ሊያስብል እና የመከፋፈል ስራን በመስራት ህዝብ ከህዝብ እንዲጣላ ሲተጋ እናንተ በሁሉም ነገር ከወያኔ በልጣችሁ በመገኘት የተንኮል ሴራውን የማክሸፉ ስራ  ወደፊት መጥታችሁ መናገር መቻል አለባችሁ። ወያኔ አላማ  አድርጎ እየሰራበት ያለው በተለይ አማራ  እና  ኦሮሞን በማጣላት እንደጠላትነት እንዲተያዩ  በማድረግ የስልጣን ግዜውን ማራዘም እንደሆነ የታወቀ  ነው ፖለቲከኞቹ ይሄንን የወያኔ አላማ በመስበር ህዝቡን በማስተሳሰር የድርሻችሁን ትወጡ ዘንድ ግድ ይላችኋል ይሄንን ሳታደርጉ ቀርታችሁ ህዝባችን ላይ የሚደርሰው ስቃይና  መከራ በችለተኛነት አልያም በዝምታ  ማለፍ ተጠያቂነት እንዲሁም  የታሪክም ተወቃሽም  ያደርጋል እና  ቢታሰብበት እላለው።

ሳጠቃልለው ህዝቡ በቁጣ ገንፍሎ ጭቆና በቃኝ ብሎ ከዳር እስከ  ዳር ወጥቷል የስርአት ለውጥ እንደሚፈልግም በግልጽ እየተናገረ  ነው። ለውጥ እስከሚመጣ ወደ ኋላ የማይልበት ሰአት ላይ ነው። ቀፎውን ገልብጦ  የወጣ  ንብ አውራዋ ስትገባ  ብቻ  ነው ወደ ቀፎው ተመልሰው የሚገቡት  የኢትዮጵያ  ህዝብ ከዳር እስከ  ዳር ግልብጥ ብሎ ስርአቱ በቃን ብለው ወጥተዋል ነጻነቱን አግኝቶ  እውነተኛ  መሪውን እስከሚያገኝ ወደ ቤቱ አይገባም። አበቃው።

ከተማ  ዋቅጅራ

09.08. 2016

Email- waqjirak@yahoo.com

 

 

ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በጀርመን ፍራንክፈርት

$
0
0

ዘርይሁን ሹመቴ ከጀርመን

unnamedበጀርመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ  ኢትዮጵያውያን በአሰቃቂ  ሁኔታ  በንጹሃን  ኦሮሞ እና አማራ ህዝብ የመንግስት ታጣቂዎች እየፈጸሙ ላሉት የነፍስ መገደል እና እስራት በመቃወም  በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ  ድምጻቸውን ለአለም ለማሰማት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራት በጋራ ለአርብ ነሃሴ 06 2008ዓም 12 08 2016 ጥሪ አስተላልፉዋል።  ይህ የተቋሞ ሰልፍ በበርሊን  ለማድረግ ታቅዶ የነበረ ሲሆን ፤ለአመቺነቱ በፍራንክፈርት ከተማ እንዲሆን ተወስኗል። በዚህም  ሰልፍ ጥቁር በመልበስ  በመላው  ኢትዮጵያ በወያኔ ጦር በግፍ ህይወታቸውን  ላጡት ለንጹሃን  ዜጎቻችን የተሰማንን  ጥልቅ  ሃዘን እንግለጽ።

የሰልፉ አላማዎች

1ኛ የወያኔ ኢህአዲግ በህዝባችን ላይ እየፈጸመ ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት ለአለም አቀፍ ህብረተሰብ በማጋለጥ

 

2ኛ የአለም  አቀፍ ማህበረሰብ በወያኔ ላይ ተጽእኖ እንዲያደርግ በመታገል

 

3ኛ አለአግባብ  የታሰሩ የህዝብ ተወካዮች ጋዜጠኞች የፖለቲካና የሀይማኖት መሪዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ከፍተኛ ግፊት በማድረግ

 

4ኛ ወያኔ ኢህአዲግ ሃገሩንና ህዝቡን ማስተዳደር ስላልቻለ በአስቸኩዋይ  ከስልጣን የሚወርድበትን እንዲሁም ስልጣኑን ለህዝብ አስረክቦ የሽግግር መንግስት ለመመስረት  የሚያስችል ነጻና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ  እንዲካሄድ መጠየቅ ናቸው።

ሰልፉ የሚጀምርበት ሰዐት: -12:00

ሰልፉ የሚጠናቀቅበት ሰአት:-17:30

የሰልፉ መነሻ ቦታ:- ፍራንክፈርት ሀብት ቫኸ (Frankfurt Hauptwache)

ሰልፉ የሚጠናቀቀው:-ኢትዮጵያ ኢምባሲ በር ላይ

አስቸኳይ መልዕክት! ይድረስ ለብአዴ‬ን አመራር -ያሬድ ጥበቡ

$
0
0

‎ያሬድ ጥበቡYared Tibebu

የትግራይ ማህበረሰብ ውስጥ ለወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ ምላሽ ተደርጎ የሚታየው ብአዴን በነፍጠኞች ተይዟል፣ መሪዎች መመንጠር አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን የድርጅቱ ልሳኖች ከሰሞኑ ዘግበዋል። በመሆኑም ‪እነ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው‬ አልሰሙ እንደሆነ በመቐለ ቤተመንግስት እየ‬ተደገሰላቸው ያለውን ፍጅት ከወዲሁ አውቀው በጀመሩት ከህዝብ ጋር የመወገን ትክክለኛ ፖሊሲ ከዚህ ከተደገሰላቸው እርድ እንዴት መዳን ይቻላቸዋል? ባለፉት 40 አመታት ህወሐትን ከቅርብም ሆነ ከሩቅ እንዳጠናት ሰው የሚከተሉትን ምክሮች መሰንዘር ይጠበቅብኝ ይመስለኛል። ከተሰነዘረባቸው አደጋ ለመዳን የብአዴን መሪዎች የሚከተሉትን እርምጃዎች በአፋጣኝ መውሰድ ይኖርባቸው ይመስለኛል።

  1. የክልል ምክርቤቱን ስብሰባ ጠርተው፣ ‎ያለምክርቤቱ ጥሪ ወደክል‬ል የገቡትን የአግአዚና ፌዴራል ፖሊስ ሀይሎች ክልሉን በአፋጣኝ ለቀው እንዲወጡ ውሳኔ ማሳለፍና፣ ይህንንም ለህዝቡ በመገናኛ ብዙሀን ማስተላለፍ
  2. በዚሁ የክልል ምክርቤት ስብሰባ ወቅት ‎የመከላከያ ሰራዊቱ‬ በሃገር ውስጥ ፓለቲካ እጁን እንዳያስገባና፣ ብቸኛ ተግባሩ ሃገሪቱን ከውጪ ጠላት መከላከል መሆኑን ግልፅ ማድረግ፣ እግረ መንገዱንም የመከላከያና ደህንነት አመራሩ የሃገሪቱን ብሄራዊ ተዋፅኦ የተከተለ እንዲሆን ጥያቄ ማቅረብ፣
  3. በብአዴን ውስጥ ተሰግስገው ‎ለህወሐት የሚሰልሉ‬ እንደ ካሳ ተክለብርሀን፣ ታደሰ ካሳ፣ አለምነው መኮንን ወዘተ የመሳሰሉትን የአመራር አባላት ከአባልነታቸው ማገድና ካስፈለገም ወደ እናት ድርጅታቸው ህወሐት እንዲመለሱ ፈቅዶ ‎ማሰናበት
  4.  የኢህአዴግ አመራርና አደረጃጀት የብሄረሰቦችን ተዋፅኦ የጠበቀ እንዲሆን ማድረግና፣ የህዝብ ቆጠራውን ተከትሎ፣ የኢህአዴግ አመራር 34% ኦሮሞ፣ 28% አማራ፣ 6% ትግራዋይ ወዘተ እንዲሆን ውሳኔ ማስተላለፍና ለተግባራዊነቱ መታገል
  5. ከአማራ ክልል የተወሰዱትን ‎የድንበር መሬቶች‬ ለማስመለስ መወሰንና፣ ይህንኑ ውሳኔ የሚከታተል ከተቀሙት ቀበሌዎች ነዋሪዎች፣ ምሁራንና፣ የፖለቲካ ልሂቃን የተውጣጣ ግብረሃይል ማቋቋም
  6. የክልሉን ፕሬዚዳንትና ሌሎች ‎በህዛባዊ ወገንተኝነታቸው የሚታወቁ‬ የብአዴን አመራር ‎አባላትን‬ ካልታሰበ የህወሐት አፈናና እገታ ሊታደግ የሚችል ጥበቃ‬ እንዲደረግላቸው አስፈላጊው የሰው ሃይልና የፋይናንስ ምደባ እንዲረግ መወሰን። ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ፣ የክልሉን ልዩ ሃይል የጥበቃ አቅም ማጎልበት፣ አስፈላጊውን ሥልጠናና ትጥቅ እንዲያገኙ መወሰን፣
  7. የክልሉ ‎ህዝብ ነቅቶ ለመብቱ‬ ቀናኢ ሆኖ ዘብ ‎እንዲቆምና‬ በእለት ተእለት ህይወቱ አዛዣና ናዛዥ መሆኑ እንዲሰማው፣ ባለፉት 25 አመታት ተግባራዊ ሲደረጉ የቆዩትን ከህወሐት የተወረሱ የአፈና አሰራሮች ለማጥፋት በክልሉ ሸንጎ ላይ ለህዝቡ ቃል መግባት
  8. ብአዴን የሚመራው ክልል ተነጥሎ እንዳይቆምና፣ ህወሐት ሌሎቹን ክልሎች ይዞ እንዳያጠቃው፣ ሌሎቹን ክልሎችም የሚመሩት አባላት የቀድሞ የኢህዴን አባላት እንደነበሩ በማስታወስ፣ በተለይ የኦሮሚያ ክልል አስተዳዳሪዎች ለተመሳሳይ አላማ እንዲቆሙ የወንድማማችነት ግንኙነት መፍጠር፣ የትግል ህብረትን ማጠናከር
  9. በአንዳንድ ቦዘኔዎች ወይም በራሱ በህወሐት ሰርጎ ገቦች ‎በትግራዋዮች‬ ላይ የተናጠል ዘር ተኮር ‎እርምጃ እንዳይኖር‬ ነቅቶ መጠበቅ፣ አዝማሚያው በታየበት ሁኔታ ሁሉ እርምጃ መውሰድ፣

እነዚህንና መሰል እርምጃዎችን በመውሰድ የብአዴን አመራር የራሱን አንገት ከተሳለለት ቢላዋ ከማዳን አልፎ፣ ያለምንም ድርጅትና አመራር ጭቆና ስላስመረረው ብቻ እምቢ ለመብቴ ብሎ ለመስዋእትነት የተሰለፈውን የክልሉን ህዝብ ከእልቂት ከማዳንም አልፎ፣ ኢህአዴግ ራሱ የመፍትሄው አካል የሚሆንበትን እድል ሊከፍት ይችል ይመስለኛል።

ይህን ማድረግ አቅቶት ግን የብአዴን አመራር ካመነታ፣ ሳያታሰብ እንደ መብረቅ ብልጭ የሚለው የወያኔ ሰይፍ አናቱን ሊጨፈልቀው ይችላል። ‎ለብአዴን መሪዎች ግልፅ ሊሆንላቸው የሚገባው ነገር፣ ‎ወያኔ ከውልደቱ እስከዛሬ‬ም ድረስ የብዙ ድርጅቶችን አመራርን ደም እየጠጣ ያደገ የተመነደገ ድርጅት ነው።

በጥቅምት 1968 ዘገብላ በተባለ ቦታ ቲ ኤል ኤፍ የተሰኘውን የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት አመራር አባላት “ኑ ድርጅታዊ ውህደት እንፈፅም” ብሎ ከተሰበሰቡ በኋላ እዚያው አፍኖ በመግደል ደም ከጠጣ ጀምሮ በደም አበላ እንደተዘፈቀ የኖረ ሀይል ነው። የብአዴን አመራርም ደም የመጨረሻው አይሆንም። እንግዲህ ‎ግማሽ እርግዝና የለም‬። የክልላችሁ ህዝብ ሁኔታ ኣሳዝኗችሁ መጠነኛ ወገንተኝነት በማሳየታችሁ፣ በወያኔ የተዘጋጀላችሁ መልስ እርድ መሆኑ ይፋ ተደርጓል። ባለፉት 25 አመታት እንደታዘብኩት ‎ወያኔ አንድ እርምጃ ከመውሰዱ በፊት ትግራይ ኦንላይንና አይጋ ፎረም በተባሉ አፈቀላጤዎቹ መድረክ ለፈረንጆቹ የሚሆን መረጃ መሰል ትንተና በእንግሊዘኛ ይፅፋል፣ ከዚያ በቀናት ውስጥ የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል።

አይጋ ላይ የወጣውን የመቐለ ፅሁፍ አንብቤ ይህን ምላሽ ስፅፍ ማምሸቴ የብአዴን ወገኖቼ እጣ ስላሳሰበኝ ነው። ከህዝብ ጎን ስለቆሙ ለምን ይታረዳሉ በማለት። የብአዴን መሪዎች ዛሬ ለሚገኙበት ህዝባዊ ወገንተኝነትና በመቐለ ቤተመንግስት ለተሳለላቸው የእርድ ካራ፣ ባለፉት 25 አመታት ተስፋ ባለመቁረጥ አንድ ቀን ከህዝባችሁ ጎን እንደምትቆሙ የተመሰረታችሁበትን ህዝባዊ መሰረት እንደ ተስፋ መልህቅ በመያዝ፣ “እኔ የማውቃቸው የኢህዴን ልጆች ለጠባብ ብሄርተኝነት እጃቸውን አይሰጡም” በማለት በስደት ስመሰክርና ስከራከር ቆይቻለሁ። የጎንደር ህዝባዊ እምቢተኝነት ላይ ከወያኔ ጋር ተዳብላችሁ ሳትወገዙ፣ የናንተም ልዩ ሀይል በህዝቡ ላይ ሳይተኩስ አብራችሁ ቆማችሁ ሳይ የተሰማኝን እርካታ በቃላት የምገልፀው አይደለም። ሞትን አሸንፋችሁ እንደተነሳችሁ ያህል ነው የተሰማኝ። አሁንም የተጣለባችሁን ጋሬጣ አልፋችሁ በዓይነ ስጋ ለመተያየት ያብቃን። ከህዝቡ ጎን ቆማችሁ ሰማእት ብትሆኑም፣ ስማችሁ ከመቃብር በላይ ይውላል። ተጭበርብራችሁ ግን የወያኔ እርድ ካራ ስር እንዳትወድቁ አደራዬ ጥልቅ ነው። ከክፉ ይሰውራችሁ።

ከስርዓት በአድሎዊነት የሚጠቀሙ አድርባዮች እንጂ ህዝብ አይደለም –በላይ ዘለቀ

$
0
0

guzu

የኢትዮጵያን የጦርነት ታሪክ  ወደ ኋላ ስንመረመር የእርስ በእርስ ጦርነቶችን ጨምሮ በወራሪዎች የተሰነዘሩብን ጭምር ተደምረው በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ላይ ያሳረፉት ጫና ቀላል አይደለም፡፡ ራስ አሉላ አባ ነጋ አንዴ ከግብጽ አንዴ ከጣሊያን ወራሪ ሃይል ጋር የኢትዮጵያን የቀይባህር ድንበር በአልሞት ባይ ተጋዳይነት እየታገሉ እስተ እርጅና እድሜአቸው ድረስ ታግልዎል፡፡ በአድዎ ጦርነት ጊዜ የአውዳሚ መሳሪያዎች ጫና ቀላል ቢሆንም ደካማ ኢኮኖሚ ላላት አገራችን በሰውና በንብረት ላይ የደርሰው ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ምንም እንኳን አንዳን የትግራይ ወንድሞቻችን በባንዳነት ቢሰለፉም እዉነተኛ የትግራይ ልጆችም የተዎደቁለት ድል ነው፡፡  በማይጨው ሽንፈት በተጠናቀቀው የጣሊያን ወረራም ጊዜ ፋሺሰት ጣሊያን የመርዝ ገዝ የሚረጭ ቦምብ በኢትዮጵያዊያን ላይ ሲያዘንብ የትግራይ ህዝብም  ተጠቂ ነበር፡፡ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለማስከበር እና ንጉሳዊ አስተዳደሮ እንዳይገረሰስ እና ሃይማኖት እንዳይረክስ በትግሬ አባቶቻችን የተከፈለው መስዎእትነት ግን ዛሬ በዘመናችን ከትግራይ በመጡ ገዣዎቻችን ተዛብቶ እየተተረጎመ ነው፡፡

አጼ ሚኒሊክ  የሳህለ ስስሴን ንግስና ቆጥረው አንድ ቀን በአያቶቻቸው ዙፋን እንደሚቀመጡ እያሰቡ ቀደም ብሎ ላልቶ የነበረውንና ፤ንጉስ ሳህለስላሴ ያጠነናከሩትን ግዛት የበለጠ እያስፋፉ ንግስናቸው ይጠባበቁ ነበር፡፡ በኋላም የሸዎው ንጉስ የሚለው በአጼ ዮሃንሰ ፀደቀላቸው ፡፡ ኢትዮጵያዊያን መሳፍንት የአገኙትን የሃይል ሚዛን ተጠቅመው ፤ በአብዛኛው ጊዜም ከውጭ ሃይል የሚደረግን ድጋፍ ተገን አድርገው ተቀናቀኞቻቸዉን በማስወገድ የነገሱበት የታሪክ ሂደት አለ፡፡ አፄ ዮሃንስ የእንግሊዘን ጦር መቅደላ በመምራት በአጼ ቴዎድሮስ ሞት እና በመቅደላ በተዘረፉ ቅርሶች ዋጋ በታጠቀዉ መሳሪ  ዋግ ሹም ጎበዜን (እራሳቸውን አጼ ተክለጊዮርጊስ ብለው አንግሰው ነበር) ድለ በማድረግ መንገስ ችለዋል፡፡ ዋግ ሹም ጎበዜ በጊዜው ያላቸውን የሰራዊት ብዛት ለመግለጽ እና አናሳ ሰራዊት ያለው ደጃች ካሳ ምርጫ ጦርነት እንዳሞክር ለማስፈራራት በቁና ሙሉ ጤፍ  አስይዘው ለመልክተኛቸው ቢልኩም ደጃች ካሳ ምርጫ  ቁና ሙሉ ጤፉን አስፈጭተው መልሰው ላኩላቸው፡፡ ዋግ ሹም ጎበዜ ማስፈራራት ቢሞክሩም በምላሹ ግን ሰረዊትህ ቢበዛ እንደ ጤፉ እቆላዎለሁ የሚል መልስ መጣላቸው፡፡ ይህን ታሪክ ተክለፃዲቅ መኩሪያ የኢትዮያ ታሪክ ከአጼ ቴዎደሮስ እስከ አጼ ሃይለስላሴ በሚለው መጽሃፋቸው መዝግበውታል፡፡

ደጃች ካሳ  በኋላ አጼ ዮሃንስ አጼ ተክለጊዮርጊስን፤ የእህታቸውን ባል ድል አርገው ይዘው በወረንጦ አይናቸውን ያወጦቸው በዘመኑ የነበረውን ጭካኔ መገለጫ እንጂ በሙሉ በዎግ ህዝብ ላይ የተካሄደ የዘር ማጥፋት ሊሆን አይችልም፡፡ አፄ ሚኒሊክ ከአድዎ ድል ማግስት በባንዳነት ተሰማርተው የነበሩት የትግራይ ተወላጆች ላይ እርምጃ ወስደዎል፡፡ ምንም እንኳን የአፄ ሚኒሊክ ቸርነተት በአደባባይ የሚታዎቅ እና በታሪክ ደርሳናትም የተመዘገበ ቢሆንም ፤ ንጉሱ በተሰየሙበት የአደባባይ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የትግራይ ባንዶች እጃቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡ የአፄ ሚኒሊክ ዘመን በወታደራዊ ፍርድ ቤት የተወሰደ እርምጃ በመላው የትግራይ ህዝብ ላይ የተወሰደ አድርጓ መውሰድ አንድም በጊዜው የነበረውን ዘመን አለመረዳት ወይም የባንድነትን ታሪክ ለመሸፈን የሚደረግ ሙከራ ነው፡፡
ወታደራዊ ደርግ በተማሪዎች ትግል እና በሰራተኛ ማህበራት አመፃ ኣና ውክቢያ ይላጋ ከነበረውን ንጉሳዊ መንግስተ ስልጣን በመመንተፍ ወደ ስልጣን ሲመጣ፤ በተማሪዎች ትግል ውስጥ አብረው ይሳተፉ የነበሩት ከፊል የትግራይ ልጆች ኢትዮጵያ ብሄርተኝነትን በማቀንቀን ከኢትዮጵያ ወንድሞቻቸው ጋር አንድ በመሆን የጋራ ትግል ለማካሄድ ቃል በመግባት ሕዝባዊ መንግስት ለመመስረት ብዙ ደክመዎል፡፡ ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ቁማር ፤ ቀዝቃዛው ጦርነት እና እርስ በርሰ የመጠላለፍ ፖለቲካ ኢህአፓንና እና መኢሶንን የመሰሉ ኢትጵያዊ ድርጅቶችን ከመስመር አስወጥቶ ሕወሃት ለተባለ ጠባብ ዘረኛ ቡድን መንገድ ጠርጎለታል፡፡

ተኃሕት ቆይቶም ሕወሃት የተባለው ፤ ማገብት፤ ሻብያ እና ጀብሃ በሚባሉት ድርጅቶች ጥላ ስር የተሰበሰቡት የሰሜን ኢትዮጵያ ልጆች የሄዱበት መንገድ ግን ከመጀሪያዉ የኢትዮጵያን መሰረት የናደ ነበር፡፡ ለረዥም ዘመን ሉዓላዊነቶን ጠብቃ ፤ እንደ ሃገር በንጉሶቾ በማእከላዊ አስተዳደር እየተመራች የቋየችን ሃገር ታሪክ ወደጎን በማደረግ የኢትየጵያ ታሪክ የ100 ዓመት ታሪክ ነው ፤ ህዳሴዎ ዛሬ እራሱን ኢህአዴግ ብሎ የሚጠራው እንዳበሰረላት ገዢው ቡድን ይናገራል፡፡

በተለያዩ ሃገራት ታሪክ የህዝቦች የጭቋና ታሪክ የባርነት ፍንገላን ጨምሮ የታሪካችን አካል ቢሆንም ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ያለፈ ታሪክ እስረኛ እንድንሆን ከጥዎት ጀምረው በዘር ላይ የተመሰረተ ፖሊሳቸውን እየተገበሩ ይገኛሉ፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት የሚደክም ማንኛዉም ግለሰብ እንደሚረዳው በገዢዎቸ ጭቋና ምክንያት ታፍነው የነበሩ ሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ዛሬ ባለንበት በ21 ኛው ክፍለ ዘመን በዲሞክራሲ መንግስት ምስረታ ፤ የግለሰቦችን ነፃነት የሚያከብር እና የህዝብን እኩልነት የሚገነዘብ መንግስት ሲኖር መልስ የሚያገኙ እንጂ አንድ ጠባብ ቡድን የሚያሽከረክራቸውን የየአካባቢውን ቋንቋ ተናጋሪ ልሂቃን ብቻ ወንበር ላይ በማስቀመጥ በማስቀመጥ በፌዴራሊዝም በመቀለድ (ፌዝራሊዝም በመመስረት) የሚሆን ነገር አይደለም፡፡

ወያኔ ለ25 ዓመታት ያለፉት ስርዓት በትግራይ ህዝብ ላይ የጭቋና ቀንበር ዘርግተው ነበር ሲል፤ አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ የነበረው ስርዓት የአማራ ህዝብ ወኪል አድርጎ ያቀርባል፡፡ ይህንንም ስብከቱን በየክልሎቹ ባቋቃማቸው ወኪሎቹ አማካኝነት ባለፉት የጭቋና ስርዓት እኩል ተጎጂ በነበረው የአማራ ህዝብ ላይ ጥፋት እንዲታወጅበት አድርጓል፡፡ የአማራ አርሶ አደር እና ጭቁን ማህበረሰብ ጉልበቱ እስኪዝል እና ላቡን አንጠፍጥፎ በኢትዮዮጵያዊነት ከሚኖርበት ቀየ እንዲፈናቀል እየተደረገ ይገኛል፡፡ ቡንዝልፎ

ወያኔ የተባለው ትግርኛ ተናጋሪ ገዢ መደብ ግን እራሱን ብቸኛ የትግራይ ህዝብ ወኪል አድርጎ በማቅረብ የትግራይ ገበሬ ለእኩይ አላማው በማሰለፍ፡ በደረግ ግፋዊ አመራር የተማረረን የአማራ ህዝብ የእርካብ መወጣጫ አድርገገጓ ለስልጣን በቅቶል፡፡ ወያኔ ደርግን በማሸነፍ እና 25 ዓመት እኩይ አላማውን እንዲያስፈፅም የተከፋፈሉት ኢትዮጵያዊያን ምቹ ሁኔታ የፈፈጠረለትን አጋጣሚ ወያኔ በመታበይ የህዝብ ድጋፍ ያለው አስመሰለው፡፡ የኦሮሞን ህዝብ ከአማራው ጋር ለማጋጨት እና የኢትዮጵያ ህዝብ አንጡራ ሃብት እየዘረፈ በመቶ አመት በስልጣን ለመቆየት እና ለመፈንጨት የቆመጠው የዘረኛው ወያኔ ቡድን የወያኔ ተላላኪና ቡችላዎችን እንደነ አባዱላ ፤ ሙክታር  ከኦሮሚያ በማስቀደም ከአማራዉም ድንበር የሚሸጠው ደመቀ፤ ካሳ ተክለብርሃን የመሳሰሉትን በማሰለፍ የቆመጠለት አላማ መክሸፍ አለበት፡፡የወያኔ አኖሌ የማን ውጤት እንደሆነ ታሪክ በቅርቡ ፍረርድ ይሰጣል፡፡ በህዘባዊ የተቃዉሞ እንቅስቃሴዎች  የፈሰሰው የወንድሞቻችን ደም በቅርቡ  የወያኔዎች መጨረሻ እንደጋዳፊ ስለሚሆን ፈሶ አይቀርም፡፡ ኦሮሞ እና አማራ ወንድማማች እና አንድ ህዝብ እንጂ  የወያኔ 25 ዓመት የደገሰላቸው እርስ በእርስ እልቂት ተቀልብሶ አሁን የደረሱበት የትብብር መንፈስ መቀጠል አለበት፡፡

 

ወያኔ በአንድ በኩል አገሪቱን ተቋጣጥሮ ኢኮኖሚዉን እንዳሻው እየመዘበረ በሌላ በኩል ደግሞ የትግራይ ሪፐፕሊክን የወደፊት ግዛት ማስፋፋት አቅድ እየተገበረ ይገኛል፡፡ የወልቃይት ጠገዴን እና ራያ እና አዘቦን ግዛት በጠመንጃ ወደራሱ ግዛት ካደረገ በኋላ ተከዜ ማዶ ያለ ግዛቱን ለማስፋፋት ተጨማሪ ወረዳዎችን በቅርብ ጊዜ በህዝባዊ ሪፈረንደም ለመጠቅለል እየቃዠ ያለ ገዢ መደብ ነው፡፡ የወልቃት የማንነት ጥያቄ ለ25 ዓመታት መስዎዕትነት የተከፈለበት ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ሁነኛ ምዕራፍ ላይ ደርሶል፡፡

ወያኔ ኢትዮጵያዊ አስተሳሰብ ስለሌለው በትግራይ ድርቅ ማግስት የደርግ መንግስተ በድርቅ የተጓዱ የትግራይ ገበሬን  ወደ ሌላ የኢትዮጵያ ግዛት ሲያሰፈር  በወቅቱ አማፂው የወያኔ ቡድን የትግራይን ህዝብ ከቀየው ተፈናቀለ ቢልም በድርቅ ለተጓዱት የተላከለትን እርዳታ ግን እታገለለታለሁ ለሚለው ህዝብ አንድም ሳያሸት መሳሪያ ታጥቋበታል፡፡ የጭቁን ገበሬዎች  ጥያቄን አንግቦ የተነሳው ወያኔ ዛሬም ከገባሬው ጋር እንደተቃቃረ ይገኛል፡፡
በትግራይ ህዝብ ስም እየማለ በተግባር ግን የትግራይን ህዝብ እንደህዝብ ከሚጎራበታቸው ወንድም ህዝብ ጋር ለማቃቃር እየሰራ ያለው ወያኔ/የትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን ነው፡፡ ጦር ሰራዊቱን ፤ የሃገር ደህንነት መስሪየ ቤቱን፤ ቢሮክራሲዉን እና ኢንቨስትመንቱን አንድ አናሳ ቁጥር ካለው የኢትዮጵየያ ህዝብ አካል ከሆነው ከትግራይ የመጡ ፤ ክህሎቱ እና እዉቀቱ የሌላቸው እንደተቋጠጠሩት የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡ ይህን ሀቅ የትግራይ ምሁራንም ሆነ ወጣትም በዝምታ ማለፋቸው ምን ይሆን፡፡

 

የትግራይ ምሁራን እና ወጣቶች ዛሬ ትግሬ እንደ አንድ ታታሪ ህዝብ በላቡ እና በጥረቱ የተሻለ ደረጃ ሊደርስ እና የተሸለ ህይወት ሊኖር የሚችለው በኢትዮጵያ አገራችን በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት ስንችል ነው፡፡ ይህ ስርዓት እውን ሲሆን ነው የትግራይ ህዝብ እውነተኛ ልጆች የሚፈጠሩት ፤ ትግሬም እንደ ህዝብ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ታሪክ በሌሎች ወገኖቹ የሚወደሰው፡፡  የትግራይ ነፃ አውጭ የቀድሞውን የደርግ መንግስት ስለ ወጋ እና ስላጣን ስለያዘ የትግራይ ህዝብ ብቻ መስዎዕትነት የከፈለ የሚመስላቸው የዎሆች፡ አለፍ ሲልም የትግራይ ህዝብ ብቻ ጀግና የሚመስላቸው የወያኔ ጠባብ ፖለቲካ ሰላባ የሆኑ የትግራይ ወጣቶች ማወቅ ያለባቸው  ሰው ሁሉ እኩል ነው የሚለው ሃቅ ብቻ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያዊያን እያካሄዱት ያሉት ህዝባዊ አመፃ የጋራ ቤታችንን ኢትዮጵያ ሁላችንንም በእኩልነት እንድታስተናግደን ያለመ፤ የኢትዮጵያ አንጡራ ሃብት ከስግብግብነት ወጥተን የጋራ ማድረግ ከቻል በቂ ነው፡፡ ህዝባዊi አመፃዉን የትግራይ ወንድሞቻችን እንዲደግፉት እና ደፍረው እንዲወጡ ጥሪየን አቀርባለሁ፡፡ኢትዮጵያ በመስዎዕት ልጆቾ በክብር ለዘላለም ትኖራለች፡፡

ህዝብን ከዕልቂት ማዳን የሁሉም ዜጎች ግዴታ ነው! –የጎጃም ህብረት በካናዳ

$
0
0

13900394_1172695232752529_754692305_nየኢትዮጵያን ህዝብ ለአለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በዘር ከፋፍሎ በመግዛትና አንጡራ ሃብቱዋን በመዝረፍ ላይ ያለው ህወሃት፤ ህዝቡ በሰላማዊ መንገድ ፍትህ፣ ዴሞክራሲና እኩልነትን ሲጠይቅ ከማሰርና ከማንገላታት አልፎ በጠራራ ፀሃይ የሺህ ኢትዮጵያውያንን ደም በማፍሰስ ላይ ይገኛል።  በማን አለብኝነት እና በፍጹም ፈላጭ ቆራጭነት አገራችንን ለመበታተን በእኩይ ተግባሩ ገፍቶበታል:: በመሆኑም: እኛ የጎጃም ህብረት በካናዳ አባላትና ደጋፊዎች፡

  1. በመላ ኢትዮጵያ በተለይም በኦሮምያ፣በጎንደርና በጎጃም የወያኔ አገዛዝ የሚያካሂደውን የሰላማዊ ሰዎች ጭፍጨፋ አጥብቀን የምናወግዝ ከመሆኑም በላይ ይህንን ጭፍጨፋና ዘረኛ አገዛዝ በመቃወም በመታገል ላይ ካለው ወገናችን ጎን ለመቆም ዝግጁ መሆናችንን እናስታውቃለን።
  2. በሁሉም ወገናችን ላይ ህወሃት እያደረሰ ያለውን እልቂት ተቀምጦ ማየት ከጥፋቱ ተባባሪነት ጋር የማይተናነስ በመሆኑ በየትኛውም የዓለም ክፍል የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ባመቸው መንገድ ሁሉ ተደራጅተን ህዝባችንን እንድንታደግ ጥሪ እናቀርባለን።
  3. የትግራይ ህዝብና ቀና ልቦና ያላችሁ ልሂቃንም ህወሃት በስማችሁ ቀሪውን የኢትዮጵያ ህዝብ ሲዘርፍ፣ የንፁሃንን ደም እንደጎርፍ ሲያፈስስ፣ አገሪቱን ሲያጠፋ በዝምታ ከተመለከታችሁና እናንተን እንደሰባዊ ጋሻ ሲጠቀም ከፈቀዳችሁ የሚከተለው እልቂት የከፋ እንደሚሆን እሙን ነው። አገሪቱ ላይ የሚደርሰው ጥፋት ሁላችንንም የሚጎዳን በመሆኑ ፈጥናችሁ ከኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ጎን እንድትቆሙ እናሳስባለን።
  4. የኢትዮጵያውያን የጋራ ጠላት የሆነው ህወሃት አገራችንን ከምንጊዜውም በከፋ ሁኔታ ውስጥ የከተታት በመሆኑ፤ ኢትዮጵያን ለማዳን በጋራ መቆም ከአሁን የተሻለ ጊዜና አማራጭ ስለሌለ ለዴሞክራሲ መስፈን እንታገላለን የምትሉ የፖለቲካ ድርጅቶችና ንቅናቄዎች ሁሉ በአንድነት ተነሱ።

ኢትዮጵያ በልጆቿ መስዋዕትነት ነፃ ትሆናለች!!

 

ነሃሴ 2 ቀን 2008 ዓ ም

 

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>