Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 8745

ቋንቋ መግባቢያ ነው ፤ ከዚያ ዉጭ ማየት ዘረኝነት ነው –ግርማ ካሳ

$
0
0

Language - Satenawአንድ የማደንቃቸው የአማርኛ አስተማሪ ነበሩኝ። ከሰባት ቤት ጉራጌ ስለነበሩ ጉራጌኛ ይናገራሉ። ብዙ አመት ሰሜን ስለኖሩም ትግሪኛ ለምደዋል። እንግሊዘኛን ስትጨምሩበት አራት ቋንቋዎች መሆናቸው ነው። አንድ የማውቃት ነርስ አለች። ከወላይታ ብሄረሰብ ናት። ይርጋለም አድጋ ሲዳምኛ ትናገራለች። ባል አግብታ ወደ አርሲ አካባቢ ለብዙ አመት ኖራለች፡ ከዚያም የተነሳ አካም ቡልቴም ትላለች። (እንግዳ የሆነውን ቁቤ ማንበብ አትችልም እንጂ) ለአንድ ስምንት አመት አስመራ መካነ ሕይወት ሆስፒታል ሰርታለች። ትግሪኛን እዚያ ለመደች። እንግሊዘኛን ስትጨምር ስድስት ቋንቋዎች መሆናቸው ነው።

ቋንቋ መግባቢያ ነው። ቋንቋ ማወቅ መቼም ቢሆን የሚጠቅም እንጂ የሚጎዳ አይደለም። ታዲያ በአገራችን ቋንቋንን የጠብና የመከፋፈያ መጠቀሚይ ብዙዎች ሲያደርጉት እየታዘብን ነው። በተለይም በአክራሪ ኦሮሞ ብሄረተኞች ዘንድ። አንዳንዶች ሌሎች አፋን ኦሮም እንዲማሩ ከማበረታታት ይልቅ፣ ለምን አማርኛ ይነገራል ይላሉ። ለኦሮምኛ አለማደግ አማርኛን ተጠያቂ ያደርጋሉ። ከዚህም የተነሳ አማርኛን ይጸየፋሉ። አማርኛን ማየት አይፈልጉም። ትግላቸው ኦሮሞ የሚሉትን ማኅበረሰብ ለመጥቀም ሳይሆን፣ ጸረ-አማርኛ ትግል ነው።

በኦሮሚያ ለምሳሌ በብዙ ቦታዎች( ከአዳማ አካባቢ በስተቀር ፣ (እርሱም ሕዝቡ ተቃዉሞ ስላሰማ) የአማርኛ ትምህርት አይሰጥም። ለምን አማርኛ እንደ ጠላት ቋንቋ ስለሚታይ። ከዚህም የተነሳ ብዙ የኦሮሞ ልጆች በተቀረው የኢትዮጵያ ክልሎች ሥራ የማግኘት እድል የላቸውም። ይሄ ትልቅ በደልና የኢኮኖሚክ ግፍ ነው። ኦሮሞው ከሌላው ማህበረሰብ ሥራ የምግኘት፣ በኢኮኖሚ የመሽሻል እንድል በጣም ያነሰ ነው የሆነበት።

በጣም የሚያሳዝነውና የሚያሳፍረው ደግሞ ኦሮሞው አማርኛ መማር እንደሌለበትና በኦሮሚያ አማርኛ የሥራ ቋውንቋ መሆን እንዳለበት የሚነገሩን፣ የኦሮሞ ልሂቃን፣ እነርሱ ግን ልጆቻቸውን በአዲስ አበባ፣ በአዳማ ምርጥ ትምህርት ቤቶች ነው አማርኛ በደንብ አውቀው እንዲማሩ የሚያደርጉት። አንድ የኦሮሚያ ዳኛ የነበረ ሰው አሉ፣ የኦሮሞ ድህረ ገፆች ላይ የሚጽፉ። አዳማ ነበር የሚኖሩት። “ልጆችዎት አማርኛ መጻፍና ማንበብ ይችላሉ ወይ ?” ብዬ ጠየቅኳቸው። “”አማርኛ ብቻ ሳይሆን አፋን ኦሮሞ በደንብ መጻፍና ማንበበ ይችላሉ” አሉኝ። “ታዲያ የርስዎ ልጆች ያገኙትን እድል ለምን ሌላው ከአዳማ ውጭ ያለው ኦሮሞ ይነፈጋል ? ምን ችገ አለው አማርኛም ኦሮሞኛ ሁለቱም ትምህርት ቢሰጥ ? ” ብዬ ጠየኩ። እኝህ ዳኛ መልስ አልመለሱልኝም። ለብዙ አመታት የኦህደድ መሪ የነበሩት አባ ዱላ፣ ልጆቻቸዉን ያስተማሩት በዝነኛው የቅድሱ ዮሴፍ ትምህርት ቤት ነው እንደሆን ነው የሚነገረው። ሌሎች የኦህዴድና ተቃዋሚ ነን የሚሉ የኦፌኮ አመራሮች ልጆችን ብትመለከቱ አብዛኞቹ የሚማሩት በቅዱስ ዩሴፍ፣ በሳንፈርድ፣ በባይብል አካዳሚ፣ በሊሴ ገበረማሪይም በመሳሰሉት ት/ቤቶች ነው። ይሄን ምን ትሉታላላችሁ?

በኦሮሚያ የሥራ ቋንቋ አፋን ኦሮሞ ብቻ ነው። ለምሳሌ በአዳማ ሰማኒያ በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ኦሮሞ ያልሆነ ቢሆንም፣ የናዝሬት ማዘጋጃ ቤት ግን የሥራ ቋንቋ አፋን ኦሮሞ ነው። ይሄ ኢፍትሃዊና ጸረ-ዲሞክራሲያዊነት አይደለምምን ? ያው አዳማ፣ ከመንግስት መስሪያ ቤት ዉጭ ሌሎች መስሪያ ቤቶች በሙሉ የሚሰሩት በአማርኛ ስለሆነ ፣ አዳምም ከአዲስ አበባ ጋር ከመቼዉም ጊዜ በላይ እየተገጣጠመች በመገጣጠሟ ችግሩ ከፍቶ በጣም አልታየም። በሌሎች የኦሮሞያ ቦታዎች ግን ያለው ሁኔታ በጣም ይሳዝናል። ኦሮሞኛ የማይነገረው ማህበረሰብ ፣ ንብረቱን፣ ገንዘቡን ይዞ ከአብዛኛዎ ኦሮሚያ እየሸሸ ፣ አዲስ አበባ አካባቢ እንደ አዋሳ ባሉ ቦታዎች እየተከማቸ ነው። ግድ የለም ብሎ የቆየውምም በሃይል መሬትህ አይደለም ተብሎ ይፈናቀላል። (እስቲ እግዜር ያሳያችሁ ፣ ለመኖር ወይንም ለመዝናናት አይደለም ፣ እየነዱ እንኳን ለማለፍ የተቆረጠ ጡት የሚመስለው የጥላቻ ሐዉልት የቆመበት፣ የአርሲ አካባቢ ማን ነው የሚሄደው?) በኦሮሚይአ ኢንቨስት ለማድረግ፣ ለመኖር፣ ለመዝናናት ፣ ለመጎብኘት የሚፈልግ ሰው የለም። ያ ደግሞ ሕዝቡን የበለጠ አይዞሌት ከማድረጉ የተነሳ፣ የበለጠ ወደ ኋላ እንዲቀር ነው ያደረገው። ከሌሎች ጋር ንግድ፣ ትስስር ከሌለ፣ የኦሮሞው ማህበረሰብ ራሱን አግሎ ከተቀመጠ, ከምንም በላይ የሚጎዳው ራሱን ነው። ለዚህ ደግሞ ተጠያቂዎችቹ የኦሮሞ ልሂቃን ናቸው። ይሄ መስረታዊ የሕዝብን የኢኮኖሚ ችግር አለማየታቸው በአፍ እንጂ በተግባር ለኦሮሞው እንዳልቆሙ የሚያሳይ ነው።

እስቲ አዋስን እና መቱን ወይንም ነቅምቴን አወዳድሮ። በደርግ ጊዜ ነቀምቴ የወርቅ አገር የወለጋ ዋና ከተማ፣ እንደመቀሌ ካሉ የትናየት የምትበልጥ ነበረች። አሁን ነቀምቴ አቧራ ብቻ ናት። ወድቃለች። ሞታለች። በኢሊባቡር ብዙ ለቱሩስት የሚሆኑ፣ ፏፏቴዎች፣ ወንዞች አሉ። በዚያ ሆቴል ቤቶችን ሪዞርቶች ቢገነቡ ብዙ ሰው ሊስቡ ይችሉ ነበር። ግን ማንም ወደዚያ አይሄድም። ፖለቲካው፣ ዘረኝነቱ፣ አፋን ኦሮሞ ብቻ ወይም ሞት የሚለው አመለካከት፣ ብዙዎችን አፋን ኦሮሞ የማይናገሩት እያራቀ ነው።

ታዲያ የኦሮሞ ልሂቃን ለምን የኦሮሞ ማህበሰብ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆን፣ ኑሮዉን እንዲቀይር የሚረዱትን ፖሊሲዎች አያስቀምጡም? ለምንድን ነው ሁልጊዜ የነርሱ አጀንዳ ቋንቋ ብቻ የሚሆንው ? ለምንድን ነው አሁንም አይምሯቸው በጥላቻ የሚበረዘውው ? ምን ችግር ነበረው፣ ኦሮሞ፣ አማራ፣ አፋን ኦሮሞ፣ አማርኛ ከምንባባል፣ አማርኛም የኔ ነው፣ አፋን ኦሮሞም የኔ ነው። ብለን ሁለቱንም ቋንቋ ብንማር፣ በሁለቱም ቋንቋ ብንሰራ ? እንዴት ቋንቋን በመካከላችን ልዩነት እንዲኖር ምክንያት አድርገን እንጠቀምበታለን ?

አፋን ኦሮሞ የኢትዮጵያ ቅርስ ነው። ዜጎች፣ ከኦሮሚያም ዉጭ ያሉም ሳይቀር፣ ሊማሩትና ሊናገሩት ይገባል። ያንን የሚያበረታታ ሐሳቦችና ፖሊሲዎች መቀመጥ አለባቸው። እንዴት አፋን ኦሮሞን እናስፋፋለን ብለን ከጥላቻ በጸዳ መልኩ መነጋገር እንችላለን። ግን አፋን ኦሮሞ እንዲያድግ አማርኛ ይጥፋ፣ አማርኛ አይነገር፣ የሚለው ግን ዘረኝነት ነው። ጠባብነት ነው። በሽታ ነው። ይህ አይነቱ አስትተሳሰብን መታገሥ ሳይሆን እንዲሸነፍ ማድረግ ነው ያለብን።

(በሚቀጥለው ጽሁፍ አክራሪ የኦሮሞ ልሂቃን፣ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ለምን እንደሚቃወሙ አንዳንድ ሐሳብ እሰጣለሁ ለኦሮሞው ጥቅም ብለው ሳይሆን ፣ አሁን ያለው ኦነግ የቀረጸውና ሕወሃት ኦነጎችን ለማስደሰትት ያስቀመጠው ኦሮሚያ የሚለው ክልል ሊከፈል ነው፣ ወደፊት ደግሞ ኦሮሚያ ሪፑብሊክ የማየት እድል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊጠፋ ነው ብለው ነው። ነገር ግን በሜዳ ያለው ዴሞግራፊክ እዉነታ የሚያሳየው ኦሮሚያ የሚባለው ሊቀጥል እንደማይችል ነው። ዘጠኝ ሚሊዮን የሚሆነው የአዲስ አበባ ህዝብን ጬምሮ፣እስከ አምቦ፣ ወሊሦ፣ ቡታጅራ፣ አዳማ፣ ፍቼና ደብረ ብርሃን ድረስ ያለው ግዛት ፣ ከአዲስ አበባ ጋር ባለው ትስስር፣ ሕብረ ብሄራዊ (ኮስሞፖሊታን) ይዘት ያለው እየሆነ ነው። በመንግስት ባይታወጅም በተግባር ግን የራሱ ክልል እየሆን ነው። ያንን ደግሞ ጊምቢናና ደምቢደሎ ውይንም ሜኔሶታ ያሉ አክራሪ ኦሮሞዎች ሊለዉጡት አይችሉም። ጥያቄዎች ቀርበው ሕዝቡ እንዲመርጥ ከተደረገ፣ ህዝቡ በኦሮሚያ ሥር ሳይሆን የራሱ ክልል እንዲኖር እንደሚፈልግ፣ ራሳቸውው የኦሮሞ ልሂቃን የሚያውቁት ነገር ነው)


Viewing all articles
Browse latest Browse all 8745

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>