Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

እንጦጦ አካባቢ አንድ የከተማ አውቶብስ በሰባት ሰዎች ላይ የሞት አደጋ አደረሰ

$
0
0

ከእንጦጦ ኪዳነ ምህረት ወደ ሺሮ ሜዳ ሲጓዝ የነበረ የከተማ አውቶብስ በሰባት ሰዎች ላይ የሞት አደጋ አደረሰ።
entoto
እንጦጦ ኪዳነ ምህረት አካባቢ ትናንት ምሽት 2 ስአት ከ25 ላይ ነው አደጋው የደረሰው።

በአደጋው ሶስት ሶስት ሰዎች ወዲያውኑ ህይዎታቸው ሲያልፍ ሶስቱ ደግም ወደ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ ሊደረግላቸው ሲል መንገድ ላይ አርፈዋል። አንደኛው ደግሞ ዛሬ ጠዋት ላይ ህይወቱ አልፏል።

በአደጋው ህይዎታቸው ያለፈው ሁሉም መንገደኞች ሲሆኑ፥ የአደጋው መንስኤም በመጣራት ላይ ይገኛል ተብሏል።

በርካታ ሰዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑም ተገልጿል።

አውቶብሱ ከኤሌክትሪክ ምሰሶ ጋር ተጋጭቶ ስለነበር የድንገተኛ አደጋ ቁጥጥሩን አስቸጋሪ አድርጎት እንደነበርም ተነግሯል።

ምንጭ፦ ፋና ኤቢሲ


የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እንዲያዋጡ መጠየቃቸውን ተቃወሙ

$
0
0

7928383556_e809223ebdነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጹት የሰራዊቱ አባላት ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እንዲያዋጡ በተጠየቁበት ወቅት ተቃውሞ
አሰምተዋል። በባድሜ አካባቢ የሰፈሩት የመከላከያ አባላት በደሞዝ ክፍያ ሳምንት መነሻው 200 ብር ሆኖ በየደረጃው ያሉ ወታደሮች እንደ ማእረጋቸውና ደሞዝ መጠናቸው
እንዲከፍሉ ሲጠየቁ፣ የሰራዊቱ አባላት ደሞዛችን አይቆረጥም በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል።

ደሞዝ ከፋዮቹ ከላይ የመጣ መመሪያ ነው በሚል ሊያግባቡዋቸው ቢሞክሩም የሰራዊቱ አባላት ፈቃደኞች ሳይሆኑ ቀርተዋል። አንድ የ3ኛ ሻለቃ አንደኛ ጋንታ አባል የሆነ ወታደር
አመጹን መርተሃል ተብሎ ሊታሰር ሲል አምልጦ እስከነመሳሪያው ተከዜ ውስጥ ገብቶ መሞቱ ታውቋል። ይህንን ተከትሎ መጠናኛ ብጥብጥ መነሳቱን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።
በአሁኑ ሰአት ውጥረቱ እንዳለ ሲሆን፣ ከመከላከያ እየጠፉ የሚሄዱትም ቁጥራቸው እየጨመረ ነው።

ባለፉት 3 ቀናት መከላከያን ጥሎ የጠፋ አንድ ወታደር እንደገለጸው፣ ሰራዊቱ በከፍተኛ ምሬት ውስጥ እንደሚገኝና የሚከዳው ሰራዊት ቁጥርም ከፍተኛ መሆኑን ተናግሯል። በተከዜ
አካባቢ በሚካሄደው የኮንትሮባንድ ንግድ የአንድ አካባቢ ሰዎች የሆኑ የመከላከያ አዛዦች እየተጠቀሙ ነው የሚለው አባሉ፣ ከእነሱ ውጭ ያለው የመከላከያ አባል በችጋር እየተጠበሰ
ባለበት ወቅት ለመለስ ፋውንዴሽን በሚል እንደገና መዋጮ መጠየቁ ብዙዎችን ስሜት የረበሸ ሆኗል ብሎአል።

እነሱ ተጨማሪ ገቢ አላቸው፣ እኛ ግን የምትሰጠንን ደሞዝ እንኳ ቆጥበን ለቤተሰቦቻችን እንዳንረዳ በመዋጮ እና በሰበብ አስባብ ይወስዱብናል ሲል ተናግሯል።
በኢትዮጵያ በወታደራዊ አዛዦችና በተራው ሰራዊት መካከል ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ልዩነት አለ። አብዛኞቹ የመከላከያ መኮንኖች የህወሃት አባላት ሲሆኑ፣ በአዲስ አበባ እና በኢትዮጵያ
ዋና ዋና ከተሞች ዘመናዊ ቪላዎችንና ፎቆችን ሰርተው በወር በመቶሺዎች የሚቆጠር የኪራይ ገቢ ያገኛሉ። በአገሪቱ ውስጥ የሚካሄደውን የኮንትሮባንድ ንግድ የሚያስፈጽሙት፣
በመከላከያ ስም ያለቀረጥ የሚያስገቡዋቸውን እቃዎች በርካሽ በመሸጥ ህጋዊዎቹን ነጋዴዎች እያከሰሩ ከስራ ውጭ እያደረጉዋቸው መሆኑን በርካታ ነጋዴዎች ለኢሳት ይናገራሉ።

  1. Source: Ethsat

ዓባይ እንደዋዛ፤ የግብፆች “ተፈጥሯዊና ታሪካዊ መብት” ክስተቶች ክፍል አምስት (አክሎግ ቢራራ)

$
0
0
Dr. Aklog Birara

Dr. Aklog Birara

አክሎግ ቢራራ (ዶር) የዛሬዋ ኢትዮጵያ ባለቤት አላት ለማለት አያስደፍርም። የህወሓት/ኢህአዴግ ሕገ-መንግሥት ኢትዮጵያ የምትባለ ረጂም ታሪክ ያላላት እንዳትሆን ከስሯ አናግቷታል። ሉዓላዊነት ከኢትዮጵያ ተዘዋውሮ በቋንቋ ለተደራጁ አዲስ መሳፍንት ለሆኑ የክልል አለቃዎች ተሰጥቷል። ህወሓት/ኢህ አዴግ ይኼን ያደረገበት ስትራተጂካዊ ምክንያት የታወቀ ነው፤ ከፋፍሎ ለመገዛት እንዲያመች። አስቸጋሪ ሆነ የምናየው ተቃዋሚው ክፍል ባለቤትነት ለመያዝና አገሪቱን ለመታደግ ብቁነት አለማሳየቱ ነው። ሻቢያ፤ ህወሕትና ሌሎች የጎሳ ስብስቦች አገሪቱን ለድርድር አቅርበው እንደ ሸቀጥ ቸርችረው የባህር በሯን ከዘጉ በኋላ አሁንም ልዩ ልዩ ክፍሎች ካለፈው አልተማሩም ለማለት ይቻላል። ዛሬም እንደ ዱሮው፤ ኢትዮጵያ በገዢው ፓርቲና በአንዳንድ ስብስቦች ለድርድር ታጭታ ትገኛለች። በ60ዎቹና በ70ዎቹ መጀመሪያ ለሃገራቸው ልማትና ለዲሞክራሲ—   [ሙሉውንለማንበብእዚህላይይጫኑ]—-

የህብረቱ ሂደትና የውህደት ጥያቄ (ኢትዮ ለጋ)

በባህር ዳር ከተማ ተደርጎ በነበረው ስብሰባ ላይ የኢህአዴግ ተወካዮች ምሬታቸውን ገለጹ (ከአስግድ ታመነ)

$
0
0

f0c3a021df8a28f4e3936660c10f3aba_L

በባህርዳር ከተማ ተደርጎ በነበረው ስብሰባ ላይ የምክር ቤት አባላት ፣” የህዝብ ወኪሎች ብንሆንም ስራ አስፈጻሚው አካል የምናቀርበውን ሪፖርት አይቀበልም” ብለዋል። አንድ ኢንቨስተር ከአንድ የህዝብ ተመራጭ የተሻለ ተሰሚነት አለው ያሉት ተማራጮች መፍትሄ ለማምጣት ካልቻልን የእኛ ተመራጭነት ምንድነው ሲሉ የምክር ቤት አባላት ጥያቄ አቅርበዋል audio ( 00-01፡54)
የህዝብ ተወካዮቹ እንደገለጹት በአሁኑ ጊዜ በፍድር ቤቶች አካባቢ ከፍተኛ ችግር እንዳለም ገልጸዋል። አንድ ተወካይ የመንግስት ሆስፒታሎች እየተዳከሙና መድሃኒቶች እየተሸጡ፣ ህዝቡም ከመንግስት የጤና ተቋማት ይልቅ ወደ ግል እየሄዱ መሆኑን ገልጸዋል።
ህብረተሰባችን ምን ላይ ነው ያለውን የማጥናት ችግር አለ ያሉት ሌላው ተወካይ፣ በምዞርባቸው ቦታዎች ሁሉ ህዝቡ መውደቂያ አጣን ብሎ እንደሚጮህ ተናግረዋል። 
ኢህአዴግ ለመጪው ምርጫ ዝግጅት በሚመስል መልኩ በተለያዩ ደረጃ የሚገኙ የህዝብ ተወካይ የሚላቸውን ሰዎች እየጠራ በማወያየት ላይ ነው።እስካሁን ድረስ በተደረጉት ውይይቶች አብዛኛው ተወያይ በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ሆነ የኢኮኖሚ ና የአስተዳደር ችግሮች እንዳሉ በድፍረት መግለጹን ኢሳት ሲዘግብ መቆየቱ ይተወቃል።

የኢትዮጵያውያን የስፓርትና ባህል ፌዴሬሽን 12ኛው ዓመታዊ በዓል በምዩኒክ ከተማ ጀርመን ተጠናቀቀ

$
0
0
MUNICH 2014 ESCFE Festival  Photo courtesy of escfe.net

MUNICH 2014 ESCFE Festival
Photo courtesy of escfe.net

የኢትዮጵያውያን የስፓርትና ባህል ፌዴሬሽን 12ኛው ዓመታዊ በዓል በምዩኒክ ከተማ ጀርመን ክጁላይ 30 ቀን 2014 ዓ..ም. እስከ ኦገሰት 2 ቀን 2014 ዓ.ም በፕሮግራሙ መሰረት ተካሂዶ ተጠናቁኣል፡፡የተለያዩ ስፖርታዊ ዝግጅቶች የአዋቂዎች 25 ቡደኖች ሲዘጋጁ 18ቱ በ1ኛ ዲቪዚዮንና ሰባቱ ደግሞ በ2ኛ ድቪዚዮን ሲመደቡ፤ በ1ኛው ድቪዚዮን 25ቱ ቡደኖች በአራት ግሩፕ እንዲከፈሉ ተደርገዋል፡፡ በሁለተኛው ድቪዚዮን ሰባቱ ቡድኖች በሁለት ግሩፕ ሆነው ተዘጋጅተዋል፡፡ሁለት ቡድኖች እንዳልመጡና እነርሱም ስዊድንና ኢትዮ ፍራንስ መሆናችው ተነግሯል፡፡ የማጣሪያውን ወድድር ከ1ኛው ድቪዚዮን 8 ቡድኖች ሲያልፉ፤ ክ2ኛው ድቪዚዮን 4 ቡድኖች አልፈዋል፡፡ በጥሎ ማለፉ ጨዋታ ከስምንቱ ቡድኖቸ ለመጨረሻው የዋንጫ ጨዋታ ኢትዮ ኖርዌይና ኢትዮ ለንደን ተቃዋሚዎቻቸውን በማሽነፍ አልፈዋል፡፡ከሁለተኛው ደቪዚዮን ኢትዮ ምዩኒክ 96 ና ኢትዮ ሸቱትጋርት ተቃዋሚቻችውን አሸንፈው ለመጨረሻው የዋንጫ ጨዋታ አልፈዋል፡፡በመጨረሻም ኢትዮ ለንደን ከኢትዮ ኖርዌይ ጋር ተጫውተው ኢትዮ ለንደን 2 ለ 1 ውጤት የ12ኛውን ዓመት የኢትዮጵያውያን የአውሮፓ የስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን  አሽናፊ ሆኗል፡፡ ከሁለተኛው ድቪዚዮን በኢትዮ ሽቱትጋርትና ኢትዮ ምዩኒክ 96 በተደረገው የዋንጫ ጨዋታ ኢትዮ ሽቱትጋርት አሸንፎ የ2014 ዓመት  የሁለተኛው ድቭዚዮን ውድድር አሽናፊ ሆኗል፡፡ የታዳጊ ወጣቶች የእግር ኩኣስ ውድድር በቂ ግዜ ተስጥቶት ከዚህ በፊት ከነበረው በተሻለ መንገድ ተከናውኗል፡፡ኢትዮ ስዊዘርላንድና ኢትዮ ኢሚሊያ ታዳጋዎች ብዙ ተስፋ የሚጣልባቸው እንደሆኑ በሜዳው ላይ በተግባር አስመስክረዋል፡፡ይህንን በጣም ከባድና አስቸጋሪ ዝግጅት በማቀናበር ለተሳተፉት አስልጣኞች ዝቅ ብለን ከልብ የሆነ ምስጋናችን ይድረሳችሁ እንላለን፡፡ለታዳጊ ወጣቶች አሽናፊዎችም የዋንጫና የሜዳልያን የኩኣስ ሽልማቶች በተገቢው መንገድ ከፌዴሬሽኑ ባልስልጣናት ተስጥቷቸዋል፡፡ሌሎችም አካባቢዎች በዚህ ደረጃ ተዘጋጅተው ለሚቀጥለው ዓመት ውድድር የታዳጊ ወጣቶችን ቡድኖች አዘጋጅተው እንዲቅርቡ ጥሪ እናደርጋለን፡፡ በስፖርቱ መስክ የሴቶች እህቶቻችንና እናቶቻችን ተሳትፎ እንዲጨምር ሴቶች እራሳቸው ጥረት በማድረግ ካሁኑ ዓመት የተሻለ ሁኔታ ቢፈጥሩ የተሻለ ይሆናል፡፡ባሁኑ ዓመት የኢትዮ ምዩኒክ የቮሊቮል ቡድን በብቸኝነት ቀርቦ ተወዳዳሪ በማጣት ብቸኛው ተወዳዳሪና አሸናፊ በመሆን የሜዳሊያ ሽልማት ተደርጎላቸዋል፡፡ ለሚቀጥለው ዓመት ውድድር በተወዳዳሪነት እንደሚቀርቡ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ 5 ኢትዮጵያውያን የእግር ኩአስ ዳኞች ጠቅላላ የእግር ኩኣስ ውድድሮችን በታዛቢነት በሶስቱም ሜዳዎች በመሆን ፌዴሬሽኑ እየመደባቸው እስከ መጨረሻው ድረስ ተግባራዊ ሆኗል፡፡ እነዚህ 5 ኢትዮጵያውያን ዳኞች የነበራቸው ሃላፊነት አንድ ጨዋታ ሲደረግ የሚጫወቱበት ሜዳ ላይ በመገኘት የሁለቱንም ቡድኖች የተጨዋቾች መታወቂያ እያንዳንዱን ተጨዋች እሱ መሆን አለመሆኑን ማረጋግጥ ሲሆን ይህን ያላሟላ ተጨዋች አይጫወትም፡፡ ተጨዋች ሲለወጥ የሚለወጠውን ተጨዋች ማንንት ማረጋገጥና ለረዳት ዳኛው በሚቀጥለው የጨዋታ መቁኣረጥ ልውውጥ እንዳለ ማሳወቅና እንዲቀየር ማድረግ፤ በጨዋታው ወቅት ያለውን ሁኔታ መዘግብ ለምሳሌ ጎሎችን፥ ቢጫ፥ ቢጫና ቀይና ቀይ ካርድ መጻፍ፥ ሌሎች ሁኔታዎች ከተከሰቱም ጽፎ በመጨረሻ ለፌዴሬሽኑ ሃላፊ ማቅረብ ናቸው።የታዳጊ ወጣቶችን፥ የሸማግሌዎች ቡድንና የሁለተኛ ዲቪዝዮን የመጨረሻ የዋንጫ ጨዋታ በኢትዮጵያውያን ዳኞች ተመርቷል፡፡ የኢትዮጵያውያን ዳኞች እንዳይገኙ አዘጋጁ የኢትዮ ምዩኒክ ቡድን ፍላጎት ሰለነበረ፥ ፌዴሪሽኑ ከኢትዮጵያውያን ዳኞች ጋር ብዙ የስልከ ግነኙነቶች በማድረግ፥ በተለይም በቴክኒክ ኮሚቴ ሃላፊው ጥረት እንዲገኙ እንደተደረገ ነው ፡፡

የዝግጅቱቦታ

የዝግጅቱ ቦታ በጣም አመቺ ሲሆን በተለይ ለህፃናት ብዙ የሚመች ነው፡፡የእግር ኩኣስ ሜዳዎቹ ሶስት ሲሆኑ ሶስቱም መብራት ዬላቸውም፡፡ አንዱ ሜዳ ቢያንስ መብራት ቢኖረው ችግር ቢያጋጥምና ቢመሽ በመብራት መጫወት የሚቻልበትን ሁኒታ አመቺ ያደርጋል፡፡ወደፊት የሚያዘጋጀው ቡድን ይህንን  ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ነጥብ ነው፡፡ለነጋዴዎች ብዙ ትናንሽና ትላልቅ ድንኩኣኖች  በመትከል የተለያዩ አገራዊ ምግቦች በ€10 ለተመጋቢዎች ቀርበዋል፡፡ለስላሳ መጠጥ €3 ነበር፡፡ እኔን የምዩኒክ ባህል የሚለው ድንኩኣን ውስጥ የሚሽጠው ደረቅ ጥብስ በእንጀራ ከአዋዜ ጋር ቁኣሚ ምርኮኛ አድርጎኛል፡፡የኢሳት ድንኩኣን ውስጥም „ኢሳት የኢትዮጵያውያን ጆሮ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር“ የሚል ማሰታወቂያ በተደጋጋሚ ያስማ እንደነበር ነው፡፡የተለያዩ አረንጉኣዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ያላቸው ጌጣጌጦች፥ሹራቦች፥ ቀሚሶች፥…ወዘተ ለሽያጭ በየድንኩኣኖቹ ቀርበዋል፡፡ የኢትዮጵያን ባንዲራ ቀለም ጫማ ላይ መደረጉን ያዩና ያስቆጣቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ይሄ ለወደፊቱ ቢታስብበት መልካም ነው፡፡ ከድንኩኣኖቹ መሃከል የተለያዩ ዝግጅቶች የቀረቡብት ዋናው መድረክ ላይ የወያኔው ቀኝ እጅ የሆነው  አቶ እስጢፋኖስ ወይም በሌላ ስሙ ጂሚ የሚባለው የኮሎኝ ከተማ ነዋሪ የሆነው የወያኔን ፖለቲካ የእሱን ግሩፖች ጀርመኖችና ሌሎችንም በማቅረብ ፕሮፓጋንዳውን በብቸኝነት እንዲያካሂድ መደረጉ የአዘጋጁን የፖለቲካ ወገንተኝነቱን ያሳያል፡፡የተሻለ የሚሆነው ለሁለቱም ወገኖች ማለትም ለወያኔ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች እኩል ግዜና መድረክ ለየብቻቸው መስጠት ወይም ሁለቱንም ወገኖች መድረክ አለመስጠት ነው፡፡ በተለያዩ ድንኩአኖች ቡና፥ ኤስፐሬሶ፥ አሳምቡሳና ለልጆች የተጠበሰ ድንችና ሌሎች ለስፖርቱ እንግዶች በአማራጭነት ቀርበዋል፡፡ወደ ሁዋላ ለየት ብለው የሚገኙ ድንኩአኖችን ጠጋ ብሎ ለተመለክተ በጣም አሳዛኝና አደገኛ የሆኑ ሸቀጦች የሚሸጡብት ሰፍራ ነበር፡፡ ጫት የሚታኘከበትና የሚሽጥበት፥ ሺሻ የሚሳብበትና ሌሎች አድንዛዥ እፆች ሰፈር ነበር፡፡ይህ ሁኔታ የአዘጋጁ የኢትዮ ምዩኒክ ስምምነት ተግባራዊ ሊሆን ስለማይችል፤ በዚህ ነጥብ ያለ ምንም ይቅርታ መወገዝ ያለበት ነው፡፡ ለታዳጊ ወጣቶች ስለጫት ሽያጭና መቃም፥ሺሻ እንዴት መሳብ እንዳለብትና ከሌሎች አደንዛዥ እፆች ጋር ለማስተዋወቅ ካልሆነ በስተቀር፤ ይህ ዓይነቱ ድርጊት አስመልክቶ ኢትዮ ምዩኒክ በሰራው ጥሩ ስራ እንደተመሰገነው በዚህ ፀረ ስፖርት ድርጊት መወገዝ ያለበት ነው፡፡ፌዴሬሽኑም የዚህ ዓይነት ፀረ ስፖርት ድርጊቶች አዘጋጁ አገር አስተማማኘ በሆነ መልኩ ተግባራዊ እንዳያረግና ከልከል መሆኑን ማሳወቅና ይህንን የማያሙኣላ ቡድን ከፌዴሬሽኑ ሊወገድ የሚችልበትን ሁኔታ ተግባራዊ ማድረግ ይኖርበታል፡፡አዘጋጁ ቡድን ላለበት አገር ፖሊሶች ዝግጀት እንዲያደርጉ በቅድሚያ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡

 የኢትዮምዪኒክናኢትዮሆላንድጨዋታ

በኢትዮ ምዪኒክና ኢትዮ ሆላንድ መሃከል የእርስ በርስ መማታት ሁኔታ ተፈጥሮ ሶስቱ ጀርመናዊ ዳኞች ጨዋውን አቁኣርጠው ሄደዋል፡፡ከዚያም በፊት አንድ የኢትዮ ምዩኒክ ተቀይሮ ከወጣ በሁላ አጨዋቹን ዳኛ በመስደቡ ቀይ ካርድ ሲሰጥወ፥ ዳኛውን „ሰምህ ማነው? ከጨዋታ በሁኣላ እገኘሃለሁ“ በማለት ካሰፈራራው በሁኣላ አጨዋቹ ዳኛ „ኣራት ደቂቃ እሰጠሃለሁ፡፡ ከሜዳው ከልል ውጭ ካልሄድክ ጨዋታወን አቁኣረጣለሁ“ ካለው በሁኣላ በመሪዎቹ ገፋፋኒት ሜዳውን ጥሎ እንድሄድ ተደርጉኣል፡፡ከዚያ ጨዋታው በኢትዮጵያዊው ዳኛ የቀረው የጨዋታ ሰዓት እንዲያልቅ ተደርጉኣል፡፡ይሀ ዓይነቱ አስራር ትክክል ሰላልሆነ ለወደፊቱ ሊሻሻል ይገባል፡፡ምከንያቱም  ጀርመንያዊ ዳኛ ጨዋታውን ያቁኣረጠበትን ምክንያት ለፌዲዲሪሽኑ ማሳወቅና ለጨዋታው መቁኣረጥ ምክንያት አንድ ቡድን በቻ መሆኑን ወይም ሁለቱም ቡድኖች መሆናቸውን በግልጽ ሊያስቀምጥ ይገባል፡፡ፌዴሬሽኑ ውሳኒውን ዳኛው በሰጠው መረጃ መሰረት አድርጎ ለጨዋታው መቁኣረጥ ምከንያት አንድ ቡድን ከሆነ፤ ይህንን ቡድን 3 ለ 0 ተሽናፊ እንዲሆን ማድረግ፤ ሁለቱም ቡድኖች ለጨዋታው መቁኣረጥ ምክንያት ከሆኑ ደግሞ ሁለቱም ቡድኖች 0 0 ነጥብ እንዲኖራቸው ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ጨዋታው በምንም መልኩ ሊቀጥል አይገባውም፡፡ይሄ ጥፋተኛውን  ውይም ጥፋተኞችን በተዘዋዋሪ የተስራውን መጥፎ ድርጊት ማበረታታት ይሆናል፡፡ባይገርማችሁ አንድ ወጣት ልጅ አጠገቤ ቆሞ ሲደባድቡ እያየ „እንዴ ትላልቅ ስዎችም ይደባደባሉ ?“ በማለት ሲገረም አድምጫለሁ፡፡የዛሬው አልፏል፡፡ ለወደፊቱ ፌዴሬሽኑ ሊያሰብበት ይገባል፡፡

የታዳጊወጣቶችየቅጣትምትሁኔታ

ዋታው የጥሎ ማለፍ ውድድር ስለሆነና እኩል ለእኩል ስለወጡ፤ አሽናፊውን በቅጣት ምት ለመለየት ተራ በተራ የኢትዮ ፓርሚሊ ከኢጣሊያና የኢትዮ ስዊዝ ቡድኖች ተጨዋቾች ቅጣት ምት ይመቱ ነበር፡፡ በጣም የሚገርመው ከሁለቱም በኩል ያሉት በእድሜ አንጋፋ ከሆኑት ተጨዋቾች የተሻለ የአመታት ችሎታ የነበራቸው ታዳጊ ወጣቶች ነበሩ፡፡ምሰጋናው በማያሻማ መልኩ ለአስልጣኞቻቸው የሚስጥ ነው፡፡በርቱ በርቱ ያስኛል፡፡ ታዲያ ጥሩ ጥሩ የሚባሉት ሁልግዜ በቅድሚያ የሚመቱት ሲሆኑ፥ ቅጣት ምቱ እኩል ለእኩል በመሆን ለረጅም ደቂቃዎች ስለቀጠለ ጎበዝ የሚባሉት መትተው ሌሎቹም ተራ በተራ መምታት ነበረባቸው፡፡አንድ እናትና አባት አካባብዬ ነበሩ፡፡“ውይ እሱ እንዳይመጣ ብቻ እኔ አላይም፡፡ቅጣት ምቱን የሳተ እንደሆነ በጣም ስለሚናደድ እሱም አይተኛም፡፡ እኛንም አያስተኛንም፡፡“ ስትል አያገባም ያለችው ልጃቸው ተራው ደረስና ሮጣ ላለማየት ሄደች፡፡ አባትዬወም ዓይኑን ወደሌላ እቅጣጫ አዞረ፡፡ እኔ ልጃቸው የፍጹም ቅጣት ሲመታ አየሁና ማግባቱን ነገርኩኣቸው፡፡እንዲያውም የጣሊያኑ ቡድን ልጃችው ያለበት በአሽናፊነት ለሚቀጥለው ውድድር አለፈ፡፡በማግስቱ ባልና ሚስቶቹን እግኝቼአቸው ስለነበር፤ ደህና መተኛታቸውን ጠይኩኣቸው፡፡ ሁለቱም ከት ብለው በመሳቅ በሰላም መተኛታችውን አረጋገጡልኘ፡፡ይሀም የሚያሳየው ወላጆቹም ምን ያህል አብረው እንደሚጨነቁ አንዱን ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል ነው፡፡

መብረቅናጨዋታማቁኣረጥ

አንድ መሰረታዊ የሆነ ስህተት በሕፃናት የመጨረሻው የዋንጫ ውድድር ወቅት ተፈጽሟል፡፡ይኸውም ዝናብና የመብረቅ አደጋ በነበረበት አጨዋቹ ዳኛ ጨዋታውን ማቁኣረጥ ሲገባው መቀጠሉና ዳኛው እንኩኣ ቢሳሳት የፌዴሬሽኑ መናገሪያው ውስጥ የነበሩት አባላት ለዳኛ ጨዋታውን እንዲያቆም መንገሩ አስፈላጊ ነበር፡፡ አሁን ሁኔታው ምንም ዓይነት አደጋ ስላልደረስ እስየው በማለት ለወደፊቱ ፌዴሬሽኑ ለሁሉም ዳኞች የዚህ የመብረቅ አደጋ ሁኒታ ሲከሰት ጨዋታውን እንዲያቁኣርጡ በመመሪያ መልክ ተዘጋጅቶ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡እዚህ ላይ ወሳኙ ዳኛው በቻ ሊሆን ይገባል፡፡ የተለያዩችግሮች  

ለቡድኖችየሚጠጣውሃእቅርቦት

አዘጋጁ አገር ለቡድኖች የሚጠጣ ውሃ በየቀኑ ተመጣጣኝ የሆነ የውሃ እቅርቦት  ከዚሀ በፊት በቀጣይነት ይደረግ እንደነበርና በምዩኒክ በዓል ላይ ግን በተገቢው መንገድ እንዳልተሟላ ነው፡፡አያንዳንዱ ቡድን ጨዋታውን እስከጨረሰ ድረስ የሚጠጣ ውሃ አቅርቦት የአዘጋጁ የኢትዮ ምዩኒክ ሃላፊነት ሆኖ ሳለ በተገቢው ተግባራዊ ባለመደረጉ ቅሬታዎች ተስንዝረዋል፡፡ይህ በጣም ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ስለሆነ ፌዴሬሽኑም ይሀ ጉዳይ መሙኣላቱን ማረጋግጥ ይኖርበታል፡፡

የቁልፍበዛትማነስ

የተጨዋቾች መልበሻ ቤት ቁልፍ አለመኖር፤ የፌዴሬሽኑ ቢሮ ራሱን የቻለ ቁልፍ አለመኖር ችግር እንደፈጠረ ታይቷል፡፡

ኖራለመቀባት

የቁጥር ሜዳ 1 ኖራ ለማስቀባት ብዙም ትኩረት እንዳልተስጠውና ዳኞች መጥተው ሜዳውን ካዩ በሁኣላ በዚያ ሁኔታ የስምንት ቡድኖችን የማጣሪያ ውድድር ለማጫወት እንደማይችሉ ካሰታወቁ በሁኣላ የሚቀባውን ሰው ፍለጋ መራወጥ ተጀመረ፡፡ ከተባለው ሰዓት በጣም ዘግይቶ ቀቢው ሰውየው መጥቶ ሜዳውን ከቀባ በሁኣላ ጨዋታዎቹ ተካሂደዋል፡፡ከዚህ የምንማረው ትምሀርት ሜዳውን ለመቀባት የሚያሰችል ሁኔታ ዝግጅት አስፈላጊ እንደሆነና ወዲያው መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ማዘጋጀት ተገቢ እንደሆነ ነው፡፡ሁለተኛው አማራጭ ኖራው በድንብ ባልተቀባባት ሜዳ ላይ ለማጫወት 14 የሚተከሉ ባንዲራዎች ወይም በፕላስቲክ የሚስሩ ምልክቶች ማዘጋጀት ነው፡፡ ይህ የመጨረሻው አማራጭ ነው፡፡

የጀርመኖችዳኞች

የጀርመኖች ዳኞች በመጀመሪያው የማጣሪያ ውድድር ላይ ከነበሩት ብዙዎች ጥሩ አልነበሩም፡፡በተለይ ረዳት ዳኞቹ ለስም የነበሩ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ መሃል ዳኞቹ ሜዳ 1ና 2 የነበሩት በአብዛኛው ጥሩ ዳኞች ነበሩ፡፡ በሜዳ 3 ላይ በማጣሪያው ውድድር ላይ የነበሩት ዋና ዳኞችም ሆኑ ረዳቶቹም በአብዛኛው ጥሩ አልነበሩም፡፡ክጥሎ ማለፍ ውደድሩ ጀምሮ አስከ ፍፃሜው ጨዋታ ድረስ የዳኙት ዳኞችም ሆኑ ረዳቶቹ ጥሩ ነበሩ፡፡ አንድ ጨዋታ ላይ ግን በማጣሪያ ውድድር ወቅት የመጀመሪያውን ግማሽ ግዜ ጨዋታ በሶስት ዳኞች ተመርቶ እረፍት ከተደረገ በሁኣላ  ሁለቱ ዳኞች ወዴት እንደሄዱ ሳይታወቅ ተሰወሩ፡፡ በጣም ብዙ ደቂቃዎች ከቆዩ በሁኣላ ተመለሱ፡፡ዋናው ዳኛ ግን ያለሁለቱ ዳኞች ጨዋታውን ቀጥሏል፡፡ይሀ እነዚህን ዳኞች በጣም የሚያስተች ሲሆን፥ ዋናው ዳኛም እነርሱን ይዞ የመቅረብ ሃላፊነቱን ባለመወጣቱ ሶስቱም ጀርመናዊ ዳኞች የስሩት ሰራ ትክክል አይደለም፡፡

ኩኣሶች

ኩኣሶች በብዛት ስለሚወስዱ ዳኞችና ታዛቢዎቹ ሁለት ሁለት ኩኣስ ለአንድ ሜዳ ይዘው ቢቀርቡና ጨዋታው ሲያልቅ ለፌዴሬሽኑ ተዋካዮች ኩኣሶቹን ቢያስረክቡ ብዙ ኩኣሶች ሊወስዱ አይችሉም፡፡በተጨማሪ ፌዴሬሽኑ የራሱ የሆን አንድ መንፊያ ቢኖረው መልካም ነው፡፡

ግርማሳህሌናማይክራፎን

የፌዴሪሽኑ ሰራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባል የሆነው የኢትዮ ፓሪስ መሪ የነበረው አቶ ግርማ ሳህሌ ማይኩን መቼ ነው የሚለቀው ፥ ለሌላ ሰውስ የሚያቀብለው በማለት ፓልቶክ ቢሆን ቢያንስ ቀይ ከባሰም ባውንስ ሊደረግ እንደሚችል ሲዘባበቱበት ተደምጧል፡፡በዚህም አስታከው ማይኩን ና ሃላፊነቱንም ለሌሎች ቢያስረክብ ሸጋ መሆኑንም እነዚህ ወጣት ጠቅ ጠቅ አድራጊዎች  አልሸሸጉም፡፡ይሀንን ሲሉ ሌሎችንም ለረጅም ግዜ በተለያየ ሃላፊነት ላይ ያሉትንም ስም ሳይጠቅሱ ጎንተል አድርገዋል፡፡

ተጋባዥእንግዶች

ተጋባዥ እንግዶች በምን መልክ እንድሚጋበዙ ግልጽ በሆነ መልክ እንዳልተቀመጠና በጉኣደኝነት እንደሆነ ተደርጎ ሲተች ተደምጧል፡፡ይሀ ትችት ባሁኑ በዓል ላይ የተጋብዙትን ፈጽሞ የሚቃወም አይደለም፡፡ሰለዚህ ሁኔታ ፌዴሬሽኑ እንዴት አንድ ሰው በእንግዳነት እንደሚምረጥ ለማንም ሰው ግልጽ በሆነ መልኩ በጽሁፍ ማብራሪያ ቢሰጥበት ጥርጣሬዎችና አሉባልታዎች ብዙ ቦታ አያገኙም፡፡

የፌዴሬሽኑገቢናወጪምርመራሪፖርትጉዳይ

የኢትዮጵያውያን የስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን ነኝ ብሎ የሚንቀሳቀስ ከሆነ፥ የፌዴሬሽኑ የሂሳብ ገቢና ወጪ ከመጀመሪያው ገንዝብ ያዥ ወቅት ጀምሮ እስካሁኑ እስከ 2014 ድረስ ነፃ በሆኑ ኦዲተሮች ተመርምሮ ለህዝብ እንዳልቀረበ ነው፡፡አይ ተደርጉኣል ከተባለም በተጨባጭ ፌዴሬሽኑ ሪፖርቱን ለህዝብ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡አቶ ብርሃኑ ገንዘቡ ባንክ ተከፍቶ እንዲቀመጥ ተጠይቆ ገንዝብ ያዥ በነበረበት ወቅት አሻፈረኝ እንዳለ እንደሚታወቅ ነው፡፡ባሁኑ ወቅትስ የፌዴሬሽኑ የባንክ አካውንት ተከፍቶ ገንዘቡ በባንክ ደረጃ የሚንቀሳቀስ ለመሆኑ ምንም ፍንጭ አይታይም፡፡በዚህ ላይ ፌዴሬሽኑ ማብራሪያ ሊሰጥ ይገበዋል፡፡

መኪናየማቆሚያቦታ

መኪናዎችን ከተፈቀደው ቦታ ሳይሆን ባልተፈቀደ ቦታዎች ሃላፊው እየነገራቸው በትእቢት በማቆማቸው ፖሊሶች መጥተው መኪናዎቹን በማስነሳታችው እያንዳንዱ ባለመኪን በትንሹ €300 ያህል እንደሚከፍል ነው፡፡ የፌዴሬሽኑ ተወካይ በማይክራፎን ደጋግም ቢናገርም ብዙ ስዎች በራሳችው ጥፋት ተቀጥተዋል፡፡ አንዳንዶቹም ሽጋ ኮረዳዎችን ለማንሆልል ትላልቅ ሽንጣም  መኪናዎች ተከራይተው ለማሳየት የመጡም  ከተቀጢዎቹ መሃከል እንደነበሩ ነው፡፡ 

ስለዓርብየመዝናኛምሽት

ዓርብ እለት ማታ የስፖርቱ ዝግጅት አካባቢ ባለው ከተማ ለምዩኒክ ቡድን እርዳታ የሚሆን የሙዚቃ ምሸት፤ በሲዲ ሙዚቃ  አጨዋቾች ውድድርና በታወቁት በይሁኔና በናቲ ዘፋኝነት ተዘጋጅቶ ለተሳታፊዎቹ በቂ በሆነ አዳራሽ ውስጥ የሙዚቃ አፍቃሪዎች በጣም በዝግጅቱ እንደረኩና ለአዘጋጆቹ ምስጋናውን እንዳቀረበ ነው፡፡ ለዚህ ምሽት መግቢያው €20 ነበር፡፡ይህ ዓይነቱ አዘጋጁና የሙዚቃ አፍቃሪዎች ረክተው የሚጠናቀቅ ዝግጅት ይደግም የሚያስኝ ነው፡፡

የቅዳሜው የሜዳ ላይዝግጅት

ቅዳሜ እስክ ቀኑ 6 ሰዓት ወይም ግማሽ ቀን ድረስ በጣም ሙቀት ነበር በሜዳ 1 ላይ ትሪቡን ላይ ከፌዴሬሽኑ ኢንፎርሜሽንስ ከሚተላለፍለት አጠገብ በግራ በኩል ትልቅ ዣንጥላ ተተክሎ ከተሪቩኑ ከፍተኛ ቦታ ላይ አንድ አግዳሚ ወንበር ላይ ከተለያዩ ከተሞች የመጡ አናቶች መቀመጫውንና ጥላው ሰር በመጠለል ፀሃይን ለመሽሽ አመቺ ቦታይዘው ተቀምጠዋል፡፡ልጆቻቸው ደግሞ በሜዳ ቁጥር 1 ላይ የኩኣስ መጫወት ፍላጎታቸውን ሲያረኩ በመመልከት ይወያያሉ፡፡በመጨረሻም አግዳሚ ወንበሩ በአንድ ክፉ ጀርመን ተነስቶባቸው የትሪቡኑ ስሚንቶ ላይ ጋዜጣ አንጥፈው መቀመጥ ተገደዱ፡፡የመጀመሪያውን የታዳጊ ወጣቶች የዋንጫ ጨዋታ እንደ ስፖንጅ ባይደላቸውም ከፀሃዩ ንዳድ ግን ራሳችውን በማዳን በጥላው ሰር ሆነው ለማየት ችለዋል፡፡ ልክ የሁለተኛው የህፃናት ጨዋታ ከተጀመረ በሁኣላ ሃይለኛ ዝናብ ከመብረቅ ነጎድጉኣድ ጋር ቢያንስ ለሁለት ሰዓት በመጣሉ፤ መጠለያ ፍለጋ ዱብዱብ ወደ አቅጣጫው ሆኖ ነበር፡፡ነጎድጉኣድ ያስከተለው ሃይለኛ ዝናብ ረገብ ብሎ በመጠኑ እየዘነበ በነበረበት ወቀት ሶስት ጨዋታዎች በቁጥር 1 ሜዳ ላይ ተካሂደዋል፡፡በመጨረሻም የሽልማት ሰነ ስርዓት ተካሂዶ በሜዳ ላይ የተዘጋጀው በዓል ፍፃሜ ሆኗል፡፡

የፌዴሬሽኑተወካዮችናየክለቦችተወካዮችስብሰባ

የፌዴሬሽኑ ተወካዮችና የክለቦች ተወካዮች ስብሰባም ተደርጉኣል፡፡የሚቀጥለው አዛጋጅም በዚሁ ስብሰባ ላይ ይወሰናል፡፡ በወሬ ደረጃ ሽኩሹክታ የሰማነው ኢትዮ  አዲስ ፍራንክፈርት እንደሆነ ነው፡፡ይህን ወሬ ሹክ ያለን ሰው በዚያው ቀጥሎ እንዴት ነው ፍራንክፈርት ብዙ ግዜ የማዘጋጅት እድል የሚሰጠው? ሲል አጉረምርሟል፡፡

የቅዳሜማታየሙዚቃምሽት

በቅዳሜው ምሽት ታዋቂው ድምፃዊ መሃሙድ አህመድ ከጃኖ ባንድ ጋርና በዓርብ ምሸት በሲዲ ሙዚቃ በማጫወት ውድድር አሸናፊ ከሆነው ጋር የሙዚቃ አፍቃሪውን ለማስደሰት እንደተዘጋጁ ነው፡፡መግቢያው €40 ሲሆን ዋጋው ቅዳሜ ከቀኑ 6 ስዓት ድረስ ትኬቱ በሜዳው አካባቢ መሽጥ እስከተጀመረበት ድረስ አይታወቅም ነበር፡፡ይህም እጅ ላይ የሚታስረው እልቁኣል ስለተባለ ውጭ ያሉ ሰዎች ሰብረው እንደገቡና በሁኣላም ሶስት መኪና ሙሉ ፖሊሶች መጥተው በስነ ስርዓት ተሰልፈው ከፍለው እንደገቡና ሙዚቃው እንደቀጠለ ነው፡፡ በመጨረሻም ጥሩና አዎንታዊ የሆኑትን አዳብሮ እንዲቀጥልና ጎጂና አሉታዊ የሆኑትን ደግሞ እንዲያስወግድ ለሚቀጥለው አዘጋጅ አገር ለማስተላልፍና በሚቀጥለው ዓመት የተሻለ ዝግጅት እንዲሆን በማስብ እስከዚያው በሰላም ሁላችንንም ያድረሰን፡፡   ከተንሳይት በቃና ኦገስት 4 ቀን 2014 ዓ.ም   Email:  tsedal2009@gmx.de

የአማራ ክልል አመራሮች ከግንቦት7 የኦህዴድ ደግሞ ከኦነግ ጋር እያበሩ ነው ሲል አቶ አዲሱ ለገሰ ያዘጋጁትና ለጠ/ሚ አማካሪዎች የተላከው ሰነድ አመለከተ

$
0
0

ነሃሴ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰነዱ ላይ ኢህአዴግ የአመራር ችግር እንዳጋጠመው፣ የትራንስፎርሜሽኑ እቅድ አለመሳካቱ እንዲሁም በጋምቤላ ተማኝ መሪ መጥፋቱ ተዝርዝሯል።
በሃምሌ ወር መጨረሻ የተዘጋጀው ሰነድ ግልባጭ ለጠ/ሚኒስትሩ አማካሪዎች ለአቶ በረከት ስምኦን፣ ለአቶ ደስታውና ለአቶ ኩማ ደመቅሳ ተደርጓል።

የቀድሞው ም/ል ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢህአዴግ የፖሊሲ ስልጠና ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ አዲሱ ለገሰ ” የኢህአዴግን ተቃዋሚ ሃይላት ማንኮላሻ አቅም ግንባታ እና የአመራር ግንባታና የትራንስፎርሜሽን ጉዞ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የፖሊሲ አማካሪዎች የቀረበ የሚለው ባለ 39 ገጽ ጽሁፍ፣ ኢህአዴግ ከላይ እስከታች የአመራር ችግር እንደገጠመው በዝርዝር ያቀርባል።

ጽሁፉ በመግቢያው “አገራችንን በፈጣን ቀጣይነት ያለውና ህዝቡ በየደረጃው ተጠቃሚ የሚሆንበት የእድገት ጉዞ ከድህነት አላቆ በተራዘመ ሂደት ከበለጸጉት አገሮች ጎራ ለማሰለፍ ይህንን ለማድረግ
የሚያስችል አላማ፣ ስትራቴጂ ስልቶችና ፖሊሲዎችን መቀየስ ይጠይቃል። በሌላ አነጋገር አቅጣጫውን በትክክል የሚያመላክት መስመር መቀየስ የትራንሰፎርሜሽን ስኬት የመጀመሪያ ቅድመ ሁኔታ ነው።
መስመሩን ለመቀየስ ይህንኑ ማድረግ የሚችል ብቃት ያለው አመራር ይጠይቃል። ኢህአዴግ በዚህ ፈተና ውስጥ ነው።” ብሎአል።

ሰነዱ ” ለአብነትም እነ አቶ መላኩ ፈንታን ማንሳት ይበቃል” ይልና ” ይህን ተከትሎ በአገሪቱ ያሉ አመራሮች ለመቀበል አለመቻላቸው እና የኡመድ ኡቦንግ ሃገር መክዳት፣ በጋምቤላ ክልል ያለው አመራር ታማኝና አስተማማኝ አለመሆኑ፣ የአማራ ክልል አመራሮች ከግንቦት ሰባት ጋር የተያያዘ አመራር መገኘት፣ የኦህዴድ አመራር ከኦነግ ጋር በማበር እና በአማራ ላይ የደረሰውን በደል በቸልታ መመልከት” በማለት ይጠቅስና “በአሁኑ ሰአት በትግራይ ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ( የአመራሩ ቸልተኝነት እንደተጠበቀ ሆኖ)፣ በአፋር፣ በሶማሌ እና በሃረሬ ምርጫውን ማሸነፍ የሚችል አመራር ድምጽ የማግኘት እድል አለው” ብአሎል።

ሰነዱ “የትራንስፎርሜሽን ትግል በውል ይጀመራል እንጅ አይጠናቀቅም ቢባልም በስጋት በተቀመጡት ክልሎች አሁንም አፋጣኝ ስራ ካልተሰራ ኪሳራ ሊያመጡ ይችላሉ” ብሎአል። የአመራሩ ደካማነት የትራንስፎርሜሽን ጉዞ ሳይሳካ እንዲቀር አድርጎታል የሚለው ሰነዱ፣ ድርጅቱ ሰዎችን የሚመለምልበትና የሚያሰለጥንበት መንገድም ብዙ ችግሮች ያሉበት በመሆኑ፣ የምልመላ ዘዴውንና የስልጠና መንገዱን
እንዲቀይር ይመክራል።

ኢህአዴግን በመሰረቱ አራቱ ድርጅቶች መካከል ያለው ትውውቅ ደካማ በመሆኑ ከከፍተኛ እስከ መካከለኛ አመራር ያሉት በአንድ ማእከል ስልጠና እንዲሰጣቸው እየተደረገ መሆኑንም ተጠቅሷል። ኢህአዴግ እጅግ በጣም የሚበዛው አባሉ አርሶ አደር በመሆኑ ፣ የፖለቲካ መሪዎችን በብዛት ለመፍጠር አለመቻሉን የሚጠቅሰው ሰነዱ፣ ከእንግዲህ በዩኒቨርስቲዎችና በከተሞች ላይ ትኩረት ተደርጎ ሰዎችንየመፈለጉ ስራ እንዲጀመር ያሳስባል።

news

Health: የማህፀን በር ካንሰር

$
0
0

በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 65 ላይ ታትሞ የወጣ

የሴት ማህፀን ከስነ ተዋልዶ አካሎች ውስጥ አንዱ ሲሆን የተለያዩ ክፍሎችን የያዘና በፊት ለፊት በኩል ከሽንት ፊኛ በስተኋላ በኩል ደግሞ በትልቁ አንጀት የመጨረሻው ክፍል የሚወሰን አካል ነው፡፡ የሴት ማህፀንን ስንመለከት በመሰረቱ በሁለት ተከፍሎ እናየዋለን፡፡
- ዋናው የማህፀን አካል (Body of The Uterus)
- የማህፀን በር (Cervix)
Cervical Cancer
ይህ ዋናው የማህፀን አካል ሴት ልጅ ወላድ በሆነችበት የዕድሜ ክልል ውስጥ ከማህፀን በር ጋር ሲነፃጸር ሁለት እጥፍ ርዝመት አለው፡፡ የማህፀን በርም ዋናው የማህፀንን ክፍል ከውጪኛው ስነ ተዋልዶ ክፍል ጋር የሚያገናኝ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ መሰረታዊ ተግባራት አሉት፡፡
- በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ የወንድ ዘር ወደ ማህፀን እንዲገባ መንገድ ይከፍታል
- የወር አበባ የሚወጣበት መስመር ነው
- በእርግዝና ጊዜ ልጅ ከማህጸን አካል የሚወጣበት መንገድ ነው

በመሰረቱ ይህ የማህፀን በር ከነ አካቴው የተዘጋ ሲሆን በእነዚህ በሶስቱ ሁኔታዎች ክፍት ሆኖ ይገኛል፡፡ ይሄንንም ተንትነን ስንመለከተው፤

- በእንቁላል መመረት(Ovulation)ወቅት፡- የሴት ዕንቁላል ከእንቁላል ማቀፊያው ወጥቶ ወደ ማህፀን ቱቦ በሚጓዝበት ወቅት፣ ይህም የሚሆነው በየ28 ቀን ዑደት ባላት ሴት በ14ኛው ቀን ሲሆን ይህም የግብረ ስጋ ግንኙነት ይኖር እንደሆነ ለእርግዝና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ነው፡፡
- በወር አበባ ወቅት፡- የወር አበባ ከማህፀን በሚወጣበት ጊዜ እንደየአስፈላጊነቱ ከ3-7 ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- ምጥ በሚጀምርበት ወቅት፡- የማህፀን አካል እየተኮማተረ ቀስ በቀስ የማህፀን በር ይከፈታል፣ ይህም የፅንሱን ጭንቅላትና አንዳንድ ጊዜም የፅንሱን መቀመጫ ሊያሳልፍ በሚችል መልኩ አጠቃላይ ክፍት ይሆንና ከወሊድ በኋላ ተመልሶ ቀስ በቀስ ወደ ቀድሞው ቦታ ይመለሳል፡፡
ስለ ማህፀን በር ጠቅላላ ግንዛቤ ይሄንን ያህል ከተመለከትን በብዛት ሴቶች የሚጠቁበትንና ከሴቶች የስነ ተዋልዶ አካላት ውስጥ በሁለተኛ ደረጃ በብዛት የሚይዘውን የማህፀን በር ካንሰር እንዳስሳለን፡፡ ይህ የማህፀን በር ካንሰር በብዛት የሚታየው ከ35-55 የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች ላይ ቢሆንም ማንኛውም የግብረ ስጋ ግንኙነት የጀመረችን ሴት ሊያጠቃ የሚችል ህመም ነው፡፡ ከግብረ ስጋ ግንኙነትም ጋር በብዛት ሊዛመድ የቻለበት ዋናው ምክንያት ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ የተባለው በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ የሚተላለፈው የቫይረስ አይነት ለዚህ ችግር ዋናው መንስኤ በመሆኑ ነው፡፡ በማህፀን በር ካንሰር የመጠቃት ሁኔታ ከላይ እንደተጠቀሰው በብዛት የሚታይ ሁኔታ ቢሆንም ለዚህ ሁኔታ ያጋልጣሉ ተብለው የሚታመኑ በርካታ ሁኔታዎች አሉ፡፡
- በአነስተኛ ዕድሜ የግብረ ስጋ ግንኙነት መጀመር ዕድሜ ባነሰ ቁጥር የማህፀን በር በካንሰር የመጠቃት እድሉም አብሮ እየጨመረ ይሄዳል፡፡
- የግብረ ስጋ ግንኙነት አጋሮች ቁጥር በጨመረ ቁጥር
- የሰውነትን የመከላከያ ብቃት የሚቀንሱ የተለያዩ ሁኔታዎች በሚኖሩበት ወቅት
- በአባላዘር በሽታ መጠቃት እንዲሁም የኤች.አይ፣ቪ ቫይረስ በሰውነት ውስጥ መኖር
- የእርግዝና ቁጥር በጨመረ ቁጥር
- የወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒት ለረጅም ጊዜ መውሰድ
- እንዲሁም ሲጋራ ማጨስ በጥቂቱ ይጠቀሳሉ፡፡
ይህ የማህፀን በር ካንሰርን እንደማንኛውም የካንሰር አይነት አደገኛ የሚያሰኘው አጀማመሩ ከዛው ከቦታው ይሁን እንጂ ጊዜ እያገኘ በመጣ ቁትር ወደ አካባቢው ወዳለ የማህፀን፣ የፊኛና፣ የአንጀት ክፍሎች ብሎም ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች በመሰራጨት አንደኛ ደረጃ ሊያደርስ በመቻሉ ነው፡፡

የማህፀን በር ካንሰር በሚኖርበት ወቅት ሊታዩ የሚችሉ ስሜቶች

የማህፀን በር ካንሰር በሚኖርበት ወቅት በተለይ በሽታው በጀመረበት ጊዜያት ውስጥ ምንም አይነት ምልክት ላይታይ እንዲሁም የህመም ስሜት ላይሰማ ቢችልም ሁኔታዎች በቀጠሉ ቁጥር የሚታዩ ስሜቶች፤
- የወር አበባ በማይጠበቅበት ወቅት ከማህፀን ደም የመፍሰስ ሁኔታ በብዛት የሚታይ ስሜት ነው፡፡ ይህንንም ስንል ወትሮ ከሚታየው የማህፀን ፈሳሽ ጋር ደም የተቀላቀለ ፈሳሽ ማየት በውስጥ ሱሪ ላይ ትንሽ/ብዛት ያለው ደም ማየት፣ ማህፀንን በሚታጠቡበት ጊዜ ደም ማስተዋል፣ ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ ደም የመፍሰስ ሁኔታ ሊታይ ይችላል፡፡
- ወትሮው የሚታየው የማህፀን ፈሳሽ ብዛት መጨመር፣ ቀለሙን መቀየር እንዲሁም መጥፎ ሽታ መከተል ሊታይ ይችላል፡፡
- ሁኔታዎች እየተባባሱ በሄዱ ቁጥር በማህፀን አካባቢ ህመም መሰማት፡፡ ይህም በአብዛኛው በአንድ ወገን ብቻ የሆነ የህመም ስሜት ሆንና ወደ ወገብና ወደ እግር የመሰራጨት ባህሪ ይኖረዋል፡፡
- እንዲሁም ውሃ ሽንትና አይነ ምድርን መቆጣጠር የማይቻልበት ሁኔታ እንዲሁም በማህፀን በኩል አይነ ምድር ማየት ፊስቱላ መፈጠሩንና ሁኔታው መባባሱን ሊያመላክት ይችላል፡፡
- አጠቃላይ የሰውነት ድካም ስሜት፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ የሰውነት ክብደት እጅግ በጣም መቀነስ እንዲሁም ደም ማነስ በብዛት የሚታዩ ሁኔታዎች ናቸው፡፡

የማህፀን በር ካንሰርን ለመከላከል አልያም በጊዜ ለማወቅ የሚረዱን መፍትሄዎች

የማህፀን በር ካንሰር ቀስ እያለና ጊዜውን እየወሰደ የሚባባስ ችግር እንደመሆኑ መጠን አንድ ሰው ምንም አይነት ስሜት የለውም ማለት ጨርሶ ምንም አይነት አደጋ ላይ አይደለም ማለት አይደለም፡፡ ለዚህም ከዚህ በታች ሁኔታውን ለመከላከል ወይም በጊዜ ለማወቅ የሚረዱንን መንገዶች እንመለከታለን፡፡

- ከላይ የተጠቀሱትን ለማህፀን በር ካንሰር ያጋልጣሉ የተባሉትን ነጥቦች ከግንዛቤ በማስገባት አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ
- በአሁኑ ወቅት ባደጉ ሀገሮች ውስጥ የማህፀን በር ካንሰር መንስኤ የሆነውን ቫይረስ የሚከላከል ክትባት በዓለማችን ዝግጁ ሆኖ ቢገኝም ይህ ክትባት ባደጉ ሀገሮች ውስጥ ብቻ በመገኘቱና እንዲሁም ዋጋው ከፍተኛ እንደመሆኑ ሀገራችን ላለው ሁኔታ እንደ መከላከያ ዘዴ ልንጠቅሰው አንችልም፡፡
- ማንኛውም ዕድሜው ከ18-40 ዓመት የሆናት ሴት ቢያንስ በየ3 ዓመቱ የማህፀን ሐኪም ጋር በመሄድ አጠቃላይ የማህፀን ምርመራ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
- ማንኛውም ከ18-65 የዕድሜ ክልል ውስጥ ያለች ሴት ወይም የግብረ ስጋ ግንኙነት ከ18 ዓመቷ በፊት የጀመረች ሴት ለመጀመሪያው 3 ዓመታት በየዓመቱ የሚደረግ የፖፕ ስሚር ምርመራ ማድረግ፣ ለሶስት ተከታታይ ዓመታትም ምንም አይነት ምልክት ያልታየ እንደሆነ ከዛ በኋላ በየ3 ዓመቱ ይህንን ምርመራ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ አብዛኛው ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች ላይ ይህ ምርመራ ወሳኝነቱ እየቀነሰ ይሄዳል፡፡
ከላይ እንደተጠቀሰው ይህ የማህፀን በር ካንሰር ምንም አይነት ስሜት ላይኖረው እንደመቻሉ መጠን በየ1-3 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ የፓናስሚር የተባለው ምርመራ ከመጣ በኋላ የማህፀን በር ካንሰር ሳቢያ የሚከተለውን የሞት ቁጥር 50 በመቶ ቀንሶ እናየዋለን፡፡
ይህ ምርመራ በመሰረቱ ትንሽ እንጨትና እንዲሁም አነስተኛ ብሩሽ በመተቀም ከማህፀን በር ላይ ናሙና የሚወስድበት የምርመራ አይነት ሲሆን በምርመራው ወቅት ህመም አለ እንኳን ብንል በጣም አነስተኛ የህመም ስሜት የሚያስከትል የምርመራ አይነት ነው፡፡ ይህ ከማህፀን በር የተወሰደው ናሙና በማይክሮስኮፕ ከተመረመረ በኋላ አንዳች አይነት ጥርጣሬን የሚያስከትል ሁኔታ የተፈጠረ እንደሆነ በትንሽ መሳሪያ ተጠቅሞ እንደየአስፈላጊነቱ የታየ ናሙና ወስዶ በደንብ ማጤን ተገቢ ነው፡፡
በአብዛኛው ሴቶች ፓፕስሚር ምርመራ ከማድረጋቸው በፊት ለ24 ሰዓታት ማህፀናቸው ባይታጠቡ እንዲሁም በማህፀን የሚገባ ምንም አይነት መድሃኒት ባይጠቀሙ ይመረጣል፡፡

ይህ ችግር በሚከሰትበት ወቅት ምን ማድረግ ተገቢ ነው?
አንድ ሴት የማህፀን በር ካንሰር አላት ካልን የሚቀጥለው እርምጃ የሚሆነው የካንሰሩ ደረጃ ምን ላይ ነው የሚለውን ማወቅ ይሆናል፡፡ ይሄም የተለያዩ ምርመራዎችን በማድረግ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ በመቀጠል ሐኪምዎን አማክረው እንደየአስፈላጊነቱና እንደየደረጃው ተገቢውን መፍትሄ ማግኘት ያስፈልጋል፡፡
ለዚህም ከላይ እንደተጠቀሰው በየጊዜውና እንደየአስፈላጊነቱ ምርመራ ማድረግ ከዚህም በተጨማሪ ደግሞ ማንኛውም አይነት ከላይ የተጠቀሱት ሁኔታዎችና ስሜቶች በሚከሰትበት ወቅት በቶሎ የህክምና ባለሙያ ማማከር ግድ ይላል፡፡ ለዚህም ሴቶች ሁሌ ለጤናችን ትኩረት እናድርግ እላለሁ፡፡


መኢአድና አንድነት ውህደታቸውን ለማራዘም መገደዳቸውን ገለፁ

$
0
0

ለውህደቱ መራዘም  ምርጫ ቦርድን ተጠያቂ አድርገዋል 
መንግስት በግል ሚዲያዎች ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ አውግዘዋል

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ነገ ሊያካሂዱት የነበረውን ውህደት ለማራዘም መገደዳቸውን አስታወቁ፡፡ ለውህደቱ መራዘም ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡ 

udJ&AEUPበሌላ በኩል  መንግስት በግል ሚዲያዎች ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ፣ የህዝብን መረጃ የማግኘት መብት የሚገድብና የመናገር ነፃነትን የሚያሳጣ በመሆኑ እንደሚያወግዙት ፓርቲዎቹ ገልፀዋል፡፡ 
“መኢአድና አንድነት ወደ ሰላማዊ የትግል ጦርነት ውስጥ መግባታቸውን ለህዝብ ማሳወቅ ይወዳሉ” በሚል ርዕስ ከትላንት በስቲያ ፓርቲዎቹ  በሰጡት መግለጫ፤ “መኢአድ በ2005 ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ምዕላተ ጉባኤ ያልተሟላ በመሆኑ መዋሀድ አትችሉም የሚል ተልካሻ ምክንያት በማቅረብ ምርጫ ቦርድ  ውህደቱን እንድናራዝም አስገድዶናል  ብለዋል፡፡ 
በ2005 በተካሄደው ጉባኤ ከ600 የጠቅላላ ጉባኤ አባላት 390 ያህሉ ተገኝተው ህጉ በሚፈቅደው መልኩ ጉባኤው መካሄዱን ራሱ ምርጫ ቦርድም ያውቃል ያሉት የመኢአድ ሃላፊዎች፤ጉባኤው ሲካሄድ የምርጫ ቦርድ ተወካዮች መጥተው ምዕላተ ጉባኤው መሙላቱን ቢያረጋግጡም ቦርዱ ግን ምዕላተ ጉባኤው አልተሟላም በሚል ለአንድ ዓመት ያህል አዎንታዊ ምላሽ ሳይሰጥ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡ 

“በህወሓት /ኢህአዴግ የሚመራው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ፣ በሰላማዊ ትግሉ ላይ ከፍተኛ መሰናክሎችን በመፍጠር ከዚህ ቀደም የተደረጉ አገር አቀፍ ምርጫዎችን በማዘረፍ ህዝብ የድል ባለቤት እንዳይሆን አድርጓል” ያሉት ፓርቲዎቹ፤ አሁን ደግሞ ጠንካራ ፓርቲዎች ተዋህደው በተደራጀ ሃይል በሰላማዊ ትግሉ እንዳይገፉ አሳማኝ ያልሆነ ምክንያት በመደርደር ውህደታችንን እንዳንፈጽም የሚያደርገውን ጫና እንቃወማለን ብለዋል።

“ምርጫ ቦርድ እንቅፋት ቢፈጥርም ፓርቲዎቹ ግን በሃሳብና በቁርጠኝነት ተዋህደዋል” ያሉት የአንድነትና መኢአድ አመራሮች፤በተጠናከረ ሃይል በሰላማዊ ትግሉ በመግፋት አላማቸውን እንደሚያሳኩ ገልፀዋል፡፡ 

የምርጫ ቦርድን ውሳኔ አስመልክቶ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው የአንድነት ፕሬዚዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፤ በዚህ ጉዳይ ምርጫ ቦርድ ሄደው እንደነበር አስታውሰው መኢአድ በወቅቱ ለምርጫ ቦርድ የላከው የምዕላተ ጉባኤ ዝርዝር 285 እንደነበርና ኮረሙ ተሟላ የሚባለው ከ300 አባላት በላይ በስብሰባው ሲሳተፉ እንደሆነ  ከምርጫ ቦርድ እንደተገለፀላቸው ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ 

መኢአድም የስም ዝርዝር ወረቀቶች ተረስተው መቅረታቸውን በመጠቆም  ለምርጫ ቦርድ 118 ተጨማሪ የተሳታፊ አባላትን ዝርዝር ቢያቀርብም  በወቅቱ ያልተላከ የአባላት ስም ተቀባይነትና ተአማኒነት የለውም በሚል የቦርዱ የህግ ክፍል አለመቀበሉን የገለፁት ኢ/ር ግዛቸው፤“መኢአድ ህጋዊና አገር አቀፍ ፓርቲ ሆኖ ሳለ በማህተምና በፊርማ የተረጋገጠ ማስረጃ ሲያቀርብ እንዴት አይታመንም ትላላችሁ፤አይታመንም የምትሉበትን ምክንያት በማስረጃና በመረጃ አቅርቡ” በማለት ቢከራከሩም ከቦርዱ ምላሽ  አለማግኘታቸውን ጠቁመዋል፡፡  
“ኮረም ሞላ አልሞላ የሚለው ለውህደቱ እንቅፋትነቱ አላሳመነኝም” ያሉት የአንድነት ፕሬዚዳንት፤ ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ጉባኤ ሲካሄድ የራሱን ታዛቢዎች በማስቀመጥ ታዛቢዎቹ ለቦርዱ ሪፖርት እንደሚያቀርቡ ጠቁመው፣ቦርዱ ታዛቢዎች ያቀረቡለትን ሪፖርት ከፓርቲው ሪፖርት ጋር በማመሳከር ችግሩን መፍታት ይችል ነበር ብለዋል፡፡ “መኢአድ ጉዳዩን በአፋጣኝ ወደ ፍ/ቤት መውሰድና መብቱን በህግ ማስከበር አለበት” ሲሉም ኢንጂነር ግዛቸው አሳስበዋል፡፡ 

በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የጽ/ቤቱ ምክትል ዋና ሃላፊ አቶ ወንድሙ ጐላ ስለጉዳዩ ጠይቀናቸው ሲመልሱ፤ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎች የመሃድ መብት እንዳላቸውና መዋሃዳቸው የተሻለ እንደሚሆን እንደሚያምን ጠቁመው ነገር ግን ፓርቲዎቹ በምርጫ ቦርድ እንዲያሟሉ የሚጠየቁትን መስፈርት ማሟላት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡ “በአሁኑ ወቅት እንዲያሟሉ የጠየቅናቸውን መስፈርቶች በደብዳቤ ገልፀናል” ያሉት ሃላፊው፤እነዚህን ነገሮች እስካሟሉ ድረስ መዋሃድ የማይችሉበት ምክንያት እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ ፓርቲዎቹ እንዲያሟሉ የተጠየቁትን መስፈርቶች አስመልክቶ የጠየቅናቸው ሃላፊው፤ “አሁን ሩቅ ቦታ ነኝ፣ በእጄ ላይ ዝርዝሮቹ የሉም፣ ሆኖም ያላሟሉት ነገር እንዳለ ግን ግልጽ ነው” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ 
በሌላ በኩል መኢአድና አንድነት፤መንግስት በግል ሚዲያዎች ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ የህዝብን መረጃ የማግኘት መብት የሚገድብና የመናገር ነፃነትን የሚያሳጣ በመሆኑ እንደሚያወግዙት አስታውቀዋል፡፡ ሰሞኑን የፍትህ ሚኒስቴር በአቴቪ ባሰራጨው መግለጫ፤ ህገመንግስቱን በሃይል ለመናድና የሃይማኖት አክራሪነትን በመስበክ አመፅ ቀስቅሰዋል ባላቸው አምስት ተጠርጣሪ የግል ፕሬሶች  ላይ  ክስ መመስረቱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ 

ምንጭ፥ –  አዲስ አድማስ

ታጋይ ሞላ አስገዶም ከውጭ ጋዜጠኞች ጋር ያደረገው ቃለምልልስ (ቪድዮ)

$
0
0

የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) ሊቀመንበር የሆነው ታጋይ ሞላ አስገዶም ከውጭ ጋዜጠኞች ጋር ያደረገው ቃለ-ምልልስ።
“አደረጃቻችን በብሄራችን ብንደራጅም ትግራይ ከሌሎች የኢትዮጵያ ህዝብ ለመለየት አይደለም፣ እንደ ስትራተጂ አንድነትዋ የተጠበቀ፤ የተጠናከረችና የብሄርብሄረሰቦች እኩልነት የተጠበቀባት፤ ፍትህ የነገሰባት አገር እንድትሆን ነው አለማችን። ስለዚህ በብሄራችን የመደራጀትና የትግራይ ህዝብ መባሉ እንደ ታክቲክ ነው እንጂ እንደ ስትራተጂ አይደለም። በዚ በመነሳት ትግላችን ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄርብሄረሰቦች ያቀፈ በመሆኑ፤ በምናካሂደው ትግል ልዩነት የሚባል ነገር የለም። ከኛ ጋር አብረው መስዋእት እየከፈሉ ነው ያሉት።” ከቃለምልልሱ የተቀነጨበ። ሙሉውን ከቪድዮው፦


ታጋይ ሞላ አስገዶም ከውጭ ጋዜጠኞች ጋር ያደረገው ቃለምልልስ (ቪድዮ)

ዐይነ ስውር ድንጋይ ወርውሮ፣ ጠላቱን ስቶ ወዳጁን መታ!

$
0
0

“ምነው ወዳጅህ እኮ ነኝ፤ ቢለው”
“ዝም በል! ዋናው አለመሳታችን ነው!” አለው

ከዕለታት አንድ ቀን ሁለት ጓደኛሞች ጫካ ሄደው እንጨት ቆርጠው ለመምጣት ይፈልጋሉ፡፡ አንደኛው በመጥረቢያ ቅርንጫፍ እየቆረጠ ሳለ እጁና ሳያስበው ቆርጦ ጣለው፡፡ 
ጓደኝየው የተቆረጠውን ክንድ በፌስታል ውስጥ ከትቶ፤ እጁ የተቆረጠ ጓደኛውን ይዞ ወደ ቀዶ – ጥገና ሐኪም ወሰደው፡፡ 
ዶክተሩም – “በጣም ዕድለኛ ነህ እኔ የተቆረጡ አካላትን መልሶ የማጣበቅ ክሂል ባለሙያ ነኝ፡፡ በአራት ሰዓት ውስጥ ተመልሰህ ና” አለው፡፡ 
ጓደኝየው – “እሺ ዶክተር ባሉኝ ሰዓት እመጣለሁ” ይልና ይሄዳል፡፡ 
ከተባለው ሰዓት በኋላ ሲመለስ፤ ዶክተሩ፤ 
“እጨርሳለሁ ካልኩበት ሰዓት ቀድሜ ጨረስኩ፡፡ ገዋደኛህ ጤንነቱ ተመልሶ እዚህ ታች ወዳለው ግሮሠሪ ሄዷል፡፡”
ጓደኝየው በደስታ ጮቤ እየረገጠ ወደተባለው መጠጥ ቤት ሄደ፡፡ ጓደኝየው ጭራሽ የዳርት ውርወራ ግጥሚያ ይዟል፡፡ 
ከጥቂት ሣምንታት በኋላ ጓደኛሞቹ አሁንም ወደጫካ ሄደው እንጨት ቆረጣ ላይ ተሰማሩ፡፡ ባለፈው እጁን የቆረጠው ሰው አሁን ደግሞ እግሩን ቆርጦ ጣለው፡፡ ጓደኝየው እንዳለፈው ጊዜ የተቆረጠውን እግር ፌስታል ውስጥ ከትቶ ጓደኛውን ይዞ ወደዚያው የአካል ቀዶ ጥገና ሐኪም ዘንድ ይዞት ሄደ፡፡ 
ሐኪሙም፤ 
“አየህ፤ የእግር ቀዶ – ጥገና ትንሽ ከበድ ያለ ነው፡፡ ከስድስት ሰዓት በኋላ ተመለስ” አለው፡፡ 
ጓደኝየውም፤ 
“እንዳልከው አደርጋለሁ ዶክተር” ብሎ ሄደ፡፡ 
ከስድስት ሰዓታት በኋላ ተመልሶ ውጤቱን ለማወቅ ወደ ሐኪም ሲመጣ፤ 
ሐኪሙ “ይገርምሃል ከነገርኩህ ሰዓት አስቀድሜ ሥራ አገባደድኩ፡፡ ጓደኛህ እዚያ ታች ወዳለው እግር ኳስ ሜዳ ሄዶልሃል” አለው፡፡ 
ጓደኝየው ሐኪሙ አመስግኖ ወደ ኳስ ሜዳው ወርዶ ሲያየው፡፡ ያ እግረ የተገጠመለት ጓደኛው ምን የመሳሰሉ ጎሎች እያገባ ነው፡፡ 
ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ግን፣ ያ ጓደኝየው እጅግ ከባድ የመኪና አደጋ ይገጥመውና አንገቱ ሙሉ ለሙሉ ተቆረጠ፡፡ ጭንቅላቱ ብቻውን ወደቀ፡፡ 
እንደተለመደው የፈረደበት ጓደኛ ጭንቅላቱን በፌስታል ከትቶ ቀሪውን የጓደኝየውን አካል ጭኖ ወደ ሐኪሙ በረረ፡፡ 
ሐኪሙም፤ 
“ጭንቅላት መግጠም እጅግ ከባድ ነው፡፡ ለማንኛውን ከአሥራ ሁለት ሰዓት በኋላ ተመለስ” አለው፡፡ 
ተመልሶ ሲመጣ፤ ሐኪሙ፡- 
“ይቅርታ አድርግልኝ፡፡ ጓደኛህ ሞቷል” አለው፡፡ 
ጓደኛውም፤ 
“ዕውነትክን ነው፡፡ የጭንቅላት ነገር ከባድ መሆኑን እገምታለሁ” አለ፡፡
ሐኪሙም፤
“ቀዶ ጥገናውን እንኳ ደህና አድርጌ ነበር የሰራሁት፡፡ ግን አየህ፤ አንተ ስታመጣው እዛ ፌስታል ውስጥ ታፍኖ ትንፋሽ አጥሮት ነው የሞተው!” 
*   *   *
እጅ እግሩን ከቆረጠበት አደጋ ያልተማረ፣ አንገቱን የሚቆረጥበት ሰዓት ይመጣል! ከስህተት አለመማር መዘዙ ራስን እስከማጣት ያደርሳል፡፡ 
የአካላችን ሁሉ አናት የሆነው ጭንቅላት የሁሉ ነገራችን መሪ ነው፡፡ አንዴ ካመለጠ የማይገጣጠም መሆኑም ይሄንኑ የሚያመላክተን ነው፡፡ ሁሉን ተግባራችንን በአቅል በአቅል የሚያስቀምጥልን፣ የሚያደራጁልን፣ መንገድ የሚያገባልን የህይወት መሪያችን እሱ ነው፡፡ በሀገር ደረጃ ሲታይም፤ ተቋሞቻችንን፣ ድርጅቶቻችንን፣ ት/ቤቶቻችንን፣ ኮሚሽኖቻችንን፣ ሚኒስቴሮቻችንን፣ ኢንዱስትሪዎቻችንን ወዘተ የሚመሩ ርዕሰ – አመራሮች እንደጭንቅላት ናቸው፡፡ የእነዚህ ጭንቅላቶች ልክ መሆን፣ ቅጥ መያዝና የድርና ማግ መቀናጀት ነው የሀገርን ጤና ልክነት የሚረጋግጠው፡፡ ይህ የጭንቅላት ክህሎት ከሌለ፣ ካልተባ፣ ከቀልብ ካልተዋሃደ ወጥነት ያለው አመራር ማግኘት አይቻልም፡፡ ጨርሶ ባዶ የሆነ ዕለት ደሞ መሄድ ቀርቶ መቆም ያቅታል፡፡ 
ገጣሚና ፀሐፌ ተውኔት ፀጋዬ ገ/መድህን፣ በ “በልግ” መጽሐፉ፤
“በዚህ በያዝኩት ጎራዴ፣ አንተግክን ቀንጥሼ ብጥለውም” 
ከባርኔጣህ በስተቀር፣ ዋጋ ያለው ነገር አይወድቅም”
የሚለን ለዚህ ነው 
“የዕውቀት ማነስ ፓለቲከኛ አደረገኝ” ከሚል ሰው ይሰውረን፡፡ አንዳንድ ፖለቲካ እጅግ አስመሳይ ከመሆኑ የተነሳ “የፆም መኪያቶ” “መኪያቶ” የሚባለውን ዓይነት ይሆናል፡፡ ወይ ሙሉውን መፆም ነው፣ አሊያ የሚለውን ሃሳብ ጨርሶ መርሳት ነው፡፡ “ፀብ ክርክር ካለበት ጮማ – ፍሪዳ፤ ፍቅር ያለበት ጎመን ይሻላል” ይላሉ አበው፡፡ በላሸቀ ኢኮኖሚ ውስጥ የፖለቲካ ጀግና መሆን እያደር ሽባ እንደሚያደርገን መገንዘብ ጭንቅላት ይዞ ማሰብን አይጠይቅም፡፡ ስለዚህ አስቀድሞ ኢኮኖሚውን ማዳን ነው፡፡ የዝሆን ጥርስ አናት ያለው ጉልላት ላይ ያለ የታችኛው ህዝብ መከራ አይታየውም፡፡ ያም ሆኖ የማይለወጥ ነገር የለም ሁሉም የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡ ወይም እንደ ቪክተር ፍራንክል፤ 
“ሁኔታዎችን መለወጥ ካልቻልክ ራስህን ለመለወጥ ትገደዳለህ” እንላለን፡፡ ቪክተር ከ2ኛው ዓለም ጦርነት ሆሎኮስት ቃጠሎ እልቂት የተረፈ ሳይካትሪስትና ፀሐፊ ነው፡፡ ከእልቂት ከተረፈ በኋላ በሰው ልጅ ላይ ምን ለውጥ እንደሚመጣ አስተውሏል፡፡ ለእያንዳንዱ ለውጥ ያ ሁሉ መስዋዕትነት መደገም አለበት ማለት አይደለም፡፡ ከማዕበሉ በኋላ የረጋ አየር፣ አየርም ቢሉ ለውጥ የሰፈነበት፤ ይመጣል ማለት እንጂ! 
የበላይም ይናገር የበታች ለሀገራችን የሚጠቅመው መደማመጥ ነው፡፡ በአንድ አቅጣጫ ብቻ እንደሚኬድበት መንገድ (One way road) አንሁን፡፡ የሚነገረንን እንስማ፡፡ ሌላው ሰው ድንገት ከእኔ የተሻለ ሀሳብ ቢያቀርብስ? እንበል፡፡ 
ደራሲ ከበደ ሚካኤል 
“አሁን የት ይገኛል ቢፈልጉ ዞሮ
መስማት ከማይፈልግ የባሰ ደንቆሮ”
ያሉትን አለመዘንጋት ከብዙ አባዜ ያድናል፡፡ እርግጥ ይህንንም የሚሰማ ካለ ነው፡፡ 
አበሻ በኢኮኖሚው መዘበትና ምፀት ማውራት ይችልበታል፡፡ ኢኮኖሚው አላፈናፍን ሲለው መውጫው በግጥም መተንፈስ ነው፡- 
“በቆሎ፤ በዝናብ፣ ሲጠብስ እያያችሁ
ሰዉ ሥራ አይሰራም፣ ለምን ትላላችሁ!”
የፖለቲካ ምፀት ሲያምረው ደግሞ፤ 
ዐይነ ስውር ድንጋይ ወርውሮ፣ ጠላቱን ስቶ ወዳጁን መታ፡፡
“ምነው? ወዳጅህን? ወዳጅህ ነኝ እኮ!” ቢለው፤
“ዝምበል፡፡ ዋናው አለመሳታችን ነው!” አለ ይባላል፤ ይላል፡፡ 

ምንጭ፥ –  አዲስ አድማስ

Comment

የኢህአዴግ ዲሞክራሲና የቴሌ ኔትዎርክ ተመሳሰሉብኝ

$
0
0

phone-towerእኔ የምለው … አንዳንድ የመንግስት ተቋማት በእነሱ ብሶ ለምንድነው ቁጣ ቁጣ የሚላቸው? (“የማይመቱት ልጅ ሲቆጡት ያለቅሳል” አሉ!) ከምሬ እኮ ነው… እኛ የተበደልነው አርፈን ተቀምጠን እነሱ እየተመላለሱ ይቆጡናል፡፡ (ኧረ “ፌር” አይደለም!) ያውም እኮ ሳንደርስባቸው ነው፤ ቤታችን ድረስ እየመጡ – በኢቴቪ መስኮት፡፡ ከሁሉም አንጀት የሚያበግነው ደግሞ ትላንት እኛው በድምፃችን ይመሩናል ብለን የመረጥናቸው ተወካዮቻችን፣ ማታ ማታ በቲቪ እየመጡ መቆጣታቸው ነው፡፡ (ለ90 ሚ. ህዝብ ማስጠንቀቂያ አይፃፍማ!) ይሄን ሁሉ ያስቀባጠረኝ የሰሞኑ የኢትዮ- ቴሌኮም ቁጣ የተቀላቀለበት መግለጫ ነው፡፡ (እኛ ሳንቆጣ እሱ ይቆጣን?!)
በእርግጥ መጀመሪያ የምስራቹን ነበር ያስቀደመው፡፡ ግዙፍ የማስፋፊያ ፕሮጀክቶቹን በስኬት ማጠናቀቁን በድል አድራጊነት ስሜት አበሰረን፡፡ (የቴሌ ድል የእኛም ድል ነው!) እንደመሰለኝ… የቁጣው መንስኤ የኢቴቪ ጋዜጠኛ ጥያቄ ነው፡፡ “ደንበኞች አሁንም የአገልግሎት ጥራት ችግሮች አሉ እያሉ ነው” የሚል ጥያቄ ሳያነሳ አልቀረም – ጋዜጠኛው፡፡ (ግን እኮ አልዋሸም!) ይሄኔ ነው ቁጣ ቁጣ ያለው – “አገልጋያችን” ኢትዮ-ቴሌኮም፡፡
አያችሁ… እዚህ አገር ሁሉ ነገር የተገላቢጦሽ ነው፡፡ በሌላው ዓለም ቢሆን እኮ የሚቆጣው ደንበኛ እንጂ አገልግሎት ሰጪው አይደለም፡፡ የሚቆጣው ህዝብ እንጂ መንግስት አይደለም፡፡ (መንግስትማ አገልጋይ ነው!) እኔ የምላችሁ… “ደንበኛ ንጉስ ነው” የሚለው አባባል እኛ አገር “ደንበኛ እርኩስ ነው” በሚል ተቀይሯል እንዴ? …በእርግጥ የኛ አገር ነጋዴዎች ወይም አገልግሎት ሰጪዎች “The Customer is always right” (ደንበኛ ሁሌም ትክክል ነው)  የምትለዋን አባባል ሲሰሙ “መስሎሃል!” እንደሚሉ ነገረ ስራቸው ያስታውቃል፡፡ እናም …ቢቆጡን፣ ቢያንገላቱን፣ መብራት ቢከለክሉን፣ ኔትዎርክ ቢነጥቁን፣ ውሃ ቢወስዱብን፣ ታክሲ የለም ቢሉን፣ ዘይት ቢያጠፉብን፣ ስኳር ቢያስወድዱብን፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ቢፈጥሩብን ወዘተ… ዝም ብለን መቀበል ብቻ ነው፡፡ ለምን “ደንበኛ ንጉስ”  ሳይሆን “እርኩስ ነው”
እናላችሁ… የኢትዮ ቴሌኮሙ ኃላፊ በኢቴቪ መስኮት ገጭ ብለው የመንግስት “የገቢ ኩራት” ስለሆነው መ/ቤታቸው ሽንጣቸውን ገትረው ተከራከሩ፡፡ የኔትዎርክ ማሻሻያው “ነዳጅ እንደሚበላ አሮጌ መኪና ሆነ” (አባባሉ የእኔ ነው!) ሲባሉ… አልካዱም፡፡ “በአንዳንድ አካባቢዎች አሁንም ኔትዎርክ ይጠፋል” የሚለውን ቅሬታም ተቀብለዋል፡፡ በመጨረሻ ግን “እናስ ምን ይጠበስ?!” ዓይነት ምላሽ ነው የሰጡት፡፡ “ይሄን ያህል ግዙፍ ፕሮጀክት ሲሰራ እኮ እንዲህ ዓይነት ችግሮች ያጋጥማሉ” አሉን፡፡ (ኔትዎርክ በዓመት አንዴ ጠፋ ብለን የምንሞላቀቅ “ቅንጡዎች”  አደረጉን እኮ!) በመካያውም… “የኔትዎርክም ሆነ ሌሎች ችግሮች በሂደት ይፈታሉ” … ብለው ገላገሉን፡፡ ይሄኔ ነው ኢህአዴግ ነፍሴ ትዝ ያለኝ፡፡ ኢህአዴግ ሁሌም ዲሞክራሲው ተንገራገጨ ወይም መልካም አስተዳደሩ ተሰናከለ አሊያም የሰብዓዊ መብት አያያዙ እያሳጣን ነው…በተባለ ቁጥር “በሂደት ይፈታል” ይለናል፡፡ የእሱ አይደለም የገረመኝ፡፡ የቴሌኮም መድገም ነው፡፡ (አወያይ መመሳሰል አሉ!)
ለዚህም ነው የኢህአዴግ ዲሞክራሲና የቴሌ ኔትዎርክ የተመሳሰለብኝ፡፡ (ሁለቱም የኋሊት ነው የሚጓዙት ልበል!) ለማንኛውም በሂደት ይፈታል ተብላችኋል – ኔትዎርኩ!!

ምንጭ፥ –  አዲስ አድማስ

‹‹አያ ጅቦ ሳታመኻኝ ብላኝ›› በበፍቃዱ ሃይሉ

$
0
0

‹‹ታዲያ ጥፋቴ ምንድን ነው ትላለህ?!››፣ ብሎኛል አንዱ መርማሪዬ ስለዞን ዘጠኝ እና እኔም እራሴ እንደጦማሪም እንደአራማጅ ተራማጅም ሠራሁ የምላቸውን ነገሮች ዝርዝር ነግሬው ሳበቃ፡፡ በኋላ ላይ በእስር ቤት ቋንቋ ከ‹‹አባሪዎቼ›› ጋር መገናኘት ከተፈቀደልን በኋላ ስንጠያየቅ ለካስ ሁላችንም ይቺኑ ጥያቄ ተጠይቀናል፡፡ ይኼ ነው እንግዲህ የምርመራችንን ሒደት የሚገልፀው ጥያቄ፡፡ ‹‹ተጠርጥረን›› የተያዝንበትን ጉዳይ የሚያረጋግጥ ሥራ ሠርተን ባለመገኘታችን (ወይም ‹‹ባለመናገራችን››) ታዲያ ጥፋትህ ምንድን ነው? ተባልን፡፡ ምርመራው የኛን ነፃ መሆን አለመሆን ለማጣራት ሳይሆን ጥፋት ለማግኘት ነበር፡፡ ብዙዎች ‹መንግሥት ዞን ዘጠኝን ለምን ሁለት ዓመት እንደታገሠው› ግራ በመጋባት ይጠይቃሉ፤ ባሕሪው አይደለምና፡፡ የኢትዮጵያ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት ምኅዳር በቀላሉ እንደገመቱት ተይዘን፣ ተመርምረንና ‹‹ተገኘባችሁ›› የተባልነው ‹‹ የግንቦት 7 [እና ኦነግም ጭምር] አባልነት [ብሎም ግብ አስፈጻሚነት] ›› በሽታ ለተከሳሽነት አብቅቶናል፡፡ ቀጣዩ የክርክር ሂደት ነው፡፡
ከዚያ በፊት ግን ዞን ዘጠኝን በሩቅም በቅርብም የሚያውቁ በግራ መጋባት መልስ እንደሚሹ በማሰብ ይቺን አጭር ማስታወሻ ለመጻፍ ተገድጃለሁ፡፡ የእስራችን ሂደት ምን ይመስላል? የምርመራችንስ? እውን የግንቦት ሰባት አባል ነን? [ታዲያ] ለምን ታሰርን? በቅርቡ እንፈታ ይሆን?

ደቂቅም ይሁን ሊቅ ስለኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እውነታ የሚጽፍ ማንኛውም ሰው [ኢትዮጵያ ውስጥ ሳለ] አንድ ቀን እታሰር ይሆን እያለ መስጋቱ አይቀርም ፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም በአንድ መጽሐፋቸው ላይ ሰው ነገረኝ ብለው የኢትዮጵያ ሕዝብን በሦስት የመደቡት፡- የታሰረ፣ ታስሮ የተፈታ እና ወደፊት የሚታሰር በማለት፡፡ እርግጥ ዞን ዘጠኝ ‹‹ሐሳቡን መግለጽ ፈርቶ ዝም ያለ ሁሉ እስረኛ ነው›› ብሎ መደምደም ሦስቱም ምድብ አንደኛው ውስጥ ያጠቃልለዋል ‹‹የታሰረ›› በሚል፡፡ ዞን ዘጠኞች ጦማራችንን በከፈተን በሁለት ሳምንት ሲታገድብን እና ሌላ ስንከፍት ግና መጨረሻ ላይ ታጋቾቹ እኛ እንደምንሆን እናውቅ ነበር፡፡ ያንን የሚያረጋግጥ ተደጋጋሚ የደህንነቶች ክትትል እና ምልክቶች ስለደረሱን መታሰራችን ማስደንገጡ ባይቀርም ያልተጠበቀ ግን አልነበረም፡፡
እስሩ በክትትሉ የተገኘነውን ስድስት የዞን ዘጠኝ አባላት እና ሦስት ጋዜጠኛ ጓደኞቻችንን መሆኑን በተለይ የጋዜጠኞቹ [ቢያንስ ለእኛ] ያልተጠበቀ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ የኋላ ኋላ ስንመለከተው ግን በእኛ አስታኮ እነሱንም ማሰሩ የታሰበበት ዘመቻ እንደሆነ መገመት አይከብድም፡፡ እኛን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ሒደትም ቢሆን በቅጡ የታሰበበት ነበር ሁላችንም (ከአስማማው በቀር) ከቀኑ በ11፡00 ገደማ በያለንበት ስንያዝ አስማማው በማግሥቱ ታስሯል፡፡ ሌሎቻችን ቤታችን በሚፈተሸበት ሰዓት ሕጉ የሚፈቅድበት ሰዓት(12፡00) አልፎ ነበር፡፡ በቁጥጥር ስር ካዋሉን በኋላ የሕገ-ወጥ አያያዝ ሰለባ የመሆናችን ሂደት የሚጀምረው ከዚህ ነው፡፡

ማዕከላዊን በክፉ ስሙ ቀድሞ ለሚያውቀው ሰው ግቢውን መርገጥ በራሱ ልብን ያርዳል፡፡ ሆኖም በልቤ /ጓደኞቼም እንደእኔ ሳይሰማቸው አይቀርም/ አንደኛ እኛ ጸሐፊ እንጂ ወታደር ወይም ሰላይ ባለመሆናች፣ ሁለተኛ መቼም ከበፊቱ የተሻለ ሰብዓዊ አያያዝ ሳይኖርም አይቀርም የሚል የዋህ ተስፋ በማሳደሬ ብዙም አልተሸበርኩም ነበር፡፡ የገባሁ እለት ከታሳሪዎች በተሰጠኝ ማብራሪያ ‹‹ሳይቤሪያ›› መግባቴን አወቅኩ፡፡ ከዚያ የ HRW-They want confession የተሰኘ ሪፖርት ላይ የተፃፉ ነገሮች ሁሉ ትክክል መሆናቸውን ለመረዳት የፈጀብኝ ከአንድ ሳምንት ያነሰ ጊዜ ነበር፡፡

ምርመራ ማዕከላዊ ስታይል
ምርመራ በማዕከላዊ ከብልጠት ይልቅ ጉልበት ይበዛበታል፡፡ መርማሪዎቹ የምርመራ ችሎታቸው ተጠርጣሪውን የተጠረጠረበትን ጉዳይ ከማውጣጣት ይልቅ የምርመራ ችሎታ እንዳላቸው ለማሳመን የሚጥሩበት ጊዜ ይበዛል፡፡ ይህም አልሰራ ሲል ጥፊ፣ ካልቾ፣ ከአቅም በላይ ስፖርት ማሰራት እና ግርፋት ድረስ ይዘልቃሉ፡፡ ይህ እንግዲህ እኔ ላይ ከተፈራረቁብኝ አምስት መርማሪዎች እና ሌሎችም አብሮ ታሳሪዎቼ ከነገሩኝ የተረዳሁት ነው፡፡ እርግጥ ሌሎች ‹‹እርቃንን ቁጭ ብድግ›› የሰሩ ተጠርጣሪዎችም ገጥመውኛል፡፡ ከባባድ ቅጣት (ወፌ ላላ ግርፋት፣ ጥፍር መንቀል) የደረሰባቸው ሌሎች ታሳሪዎች አብረውኝ የታሰሩ ቢሆንም ይህ የተፈፀመባቸው ግን ወደማዕከላዊ ከመምጣታቸው በፊት ነው፡፡ ከነዚህ መካከል የሀሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ይገኙበታል፡፡ የሚገርመው በዚህ ዓይነቱ ምርመራ የሰጡት ቃል ለማመሳከርያ ማዕከላዊ መምጣቱ ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ወደማዕከላዊ ከመዛወራቸው በፊት ከባድ ቅጣት የተቀጡበትን ቦታ የት እንደሆነ እንዳያውቁ አይናቸው ተሸፍኖ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እሥረኞችም መኖራቸው ነው – የደርግን ‹‹ቤርሙዳ›› ያስታውሳል!

እናም በሚያዋርድ እና ክብርን በሚነካ ስድብ በሚያስፈራ የቤቱ (የማዕከላዊ) ጥላ እና ኃይል በተቀላቀለበት የምርመራ ሂደት የተከሳሽ ቃላችንን ሰጠን፡፡ ቃላችን መቶ በመቶ እውነት አልነበረም፡፡ ጫናው በበረታ ቁጥር መስማት የሚፈልጉትን ‹‹ዓመፅ ለመቀስቀስ ፈልገን›› የመሳሰሉ በራስ ላይ ፈራጅ (Self-incriminating) ሐረጎችን እየተናገርን ነበር፡፡ ያም ግን ለመርማሪዎቻችን በቂ አልነበረም፡፡ ስለዚህ በሚጽፉበት ሰዓት እያንዳንዷን ‹‹ሠራን›› ያልነውን ሁሉ ሊያስከስሰን በሚችልበት ሁኔታ እየገለበጡ እና እየበጠበጡ ፃፉት፡፡ አንዳንዶቻችን እየተከራከርን ሲያቅተን ፍርድ ቤት ይፍታው ብለን ፈረምን፣ቀሪዎቻችን የቻልነውን ያህል ተደብድበንበት ፈረምን፡፡ ‹‹ከተናገርኩት ቃል ውጪ አንድም ቃል አልፈርምም›› በሚል እስከመጨረሻው ታግሎ የተሳካለት አቤል ብቻ ነበር፡፡

በምርመራው ሂደት የተረዳነው ነገር ቢኖር የማዕከላዊ መርማሪዎች ብቃት (Intelligence) አርጩሜ ብቻ መሆኑን ነው፡፡ እኔ ምርመራ ሲባል ይመስለኝ የነበረው ፖሊሶች ተጠርጣሪዎችን ፈፀሙ ስለሚባለው ነገር በቂ መረጃ ይዘው ግፋ ቢል ለምንና እንዴት እንደፈፀሙት ማውጣጣት ነበር፡፡ ‹‹ዕድሜ ለማዕከላዊ›› የተረዳሁት ነገር ቢኖር ምርመራ ማለት ለካስ ‹‹የሠራኸው ወንጀል ምንድን ነው?አውጣት!›› ማለት ኖሯል- ማዕከላዊ ስታይል፡፡ ‹‹ነጻ ነኝ›› ቢሉ ሰሚ የለም፡፡ አንዴ ታስረሃል ወንጀል ሊገኝብህ የግድ ነው፤ ካልሆነ ይጋገርብሃል፡፡
አሁን ሳስበው ማዕከላዊ ፈርሶ በሥር-ነቀል ለውጥ እንደገና መቋቋም ያለበት ተቋም ነው፤ ቢያንስ በሁለት ምክንያት፡፡ አንደኛ የምርመራው ሂደት (በራሳችን ጉዳይ እንደተረዳሁት) ትዕዛዝ አስፈፃሚነት ይስተዋልበታል፡፡ ማለትም በመርህ የሚመራ አይደለም፡፡ ሁለተኛ ምርመራው እውቀት መር አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ የአገሪቱን ደህንት አደጋ ውስጥ የሚጥል ጉዳይ በምርመራው ድክመት ሳይታወቅ ሊታለፍ ይችላል፡፡ ይህ ችግር የተከሰተው ደግሞ መርማሪ ፖሊሶቹ ከብቃት ይልቅ ለታዛዥነት የተመቹ ታማኞች ሆነው በመመልመላቸው ነው፡፡

‹‹ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ››
በምርመራው ሂደት የተጨቀጨቅነውም ሆነ ተገድደን የፈረምነው ጽሑፎቻችንን የበይነ መረብ ዘመቻዎቻችንን፣ የወሰድናቸው ስልጠናዎችም ሆኑ አንዳንዶቻችን የሰጠናቸው ስልጠናዎች አመፅ ለማስነሳት መሆኑን ‹‹እመኑ›› በሚል ስለነበር የጠበቅነው ግፋ ቢል በወንጀለኛ መቅጫው አንቀጽ 238 ወይም 257 ሊከሱን አስበው ነው ብለን ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የክስ መዝገቡ ሲመጣ ‹‹ሽብር›› ያውም ከአስራ አምሰት ዓመት እስከ እድሜ ልክ የሚያስቀጣ አንቀጽ 4 መሆኑን ሳውቅ በበኩሌ ሳቄ ነበር የመጣው፡፡

ማስረጃ ተብለው ከክስ መዝገቡ ጋር የተያያዙት በአብዛኛው ጽሑፎቻችን፣ የዘመቻዎቻችን፣ የጋዜጣ መግለጫዎች እና በተለያዩ ሥልጠናዎች ወቅት የተዘጋጁ የሥልጠና መመሪያዎች (Manuals) ናቸው፡፡ ከዚህ በተረፈ ከግንቦት 7 እና ከኦነግ ጋር ያገናኛችኋል የተባልነው በሦስት ‹‹ሰነዶች›› ነው፡፡ አንደኛው ናትናኤል ኢሜይል ውስጥ በጥቅምት 2001 ተልኮለት የተገኘ የግንቦት 7 የዜና መጽሔት ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ገና የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ አዋጁ ሳይወጣ፤ ግንቦት ሰባትም አሸባሪ ከመባሉ በፊት መሆኑ ነው፡፡ ሁለተኛ ሶልያና ቤት ተገኘ ተብሎ እናቷ ‹‹ቤቴ ውስጥ አልተገኘም፣አልፈርምበትም›› ያሉት እና ለግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ሰራዊት ምልመላ መመዘኛ ሰነድ ነው፡፡ ይህ የሶሊ የዘለቀ አቋም ለሚያውቅ ሙግት አያስፈልገውም፡፡ እኔ እንደውም ትዝ ያለኝ ከመታሰሬ በፊት የትዊተር ፕሮፋይሏ ውስጥ የነበረው ‹‹no for war›› የሚል መፈክር ነው፡፡ ሦስትኛው ደግሞ ማሕሌት ኮምፒውተር ውስጥ የተገኘው የኦነግ ፕሮግራም ነው፡፡ በርግጥ አብረው የተገኙት የሌሎች የኦሮሞ ፓርቲዎች ፕሮግራሞች ማስረጃ ተብለው አለመቅረባቸው መረዳት ብቻ – እሷም ለምን ፕሮግራሙን እንደያዘችው፤ እነሱም ለምን የኦነግን እንደመረጡ ያጋልጣልና የእመኑኝ ሙግት አያስፈልገንም፡፡ በመሰረቱ ሦስቱንም ‹‹ሰነዶች›› መያዝ ከቡድኞቹ ጋር ግንኙነት መመሥረት የሚሰሩትንም መውደድ ማለት አየደለም፡፡ ይህም ለመሪዎቻችን ባይታያቸውም እንኳ ለወገኖቻችን የጠፋቸዋል ብዬ አላስብም፡፡

ሌላውና በአስቂኝለቱ ተወዳዳሪነት የሌለው ውንጀላ ‹‹48 ሺሕ ብር በናትናኤል በኩል ተቀብለው ተከፋፍለዋል›› የሚለው ነው፡፡ ይህ ብር ፤‹‹አሸባሪ›› ከተባሉት ቡድኖች የተወሰደ እንዲመስል በሚያደናግር አገላለጽ የተጻፈ ቢሆንም የክስ መዝገቡ ውስጥ የተያያዘውና ገንዘቡ የመጣበት ደረሰኝ እንደሚያረጋግጠው የተላከው ከARTICLE 19 ነው፡፡ ይህንን ጨምሮ በእስር ላይ ለምትገኝ ጋዜጠኛ ቤተሰቦች መደገፊያ /ለእስረኛይቱም ማበረታቻ/ የተላከ መሆኑን ለመርማሪዎቹ በዝርዝር አስረድተናቸዋል፡፡ ይህንን እያወቁ ውንጀላውን ማኖራቸው እውነትም እኒህ ሰዎች ወንጀለኞች ናቸው ብለው አምነው ሳይሆን ‹‹ከቻልን አደናግረን እናስቀጣቸዋለን (የማይችሉበት ሁኔታ አይታየኝም)፣ካልቻልን ደግሞ በቀጠሮ ጊዜ እንገዛበታለን፣ ነጻ እስኪወጡም ቢሆን በእስር እናቆያቸዋለን›› የሚል ክፉ ምኞት ነው፡፡
befekadu
… ሳታመኻኝ ብላኝ!
አህዩት ከታች አያ ጅቦ ከላይ ሆነው ወራጅ ውሀ እየጠጡ ነበር አሉ፡፡ ነገር ያማረው አህዩትን ‹‹አታደፍርሽብኝ›› ሲላት ነገሩ የገባት አህይትም ‹‹ሳታመኸኝ ብላኝ›› አለችው ይባላል፡፡ የኛም ነገር እንደዚያው ነው፡፡
ፖሊስ ሲይዘን እኛ ላይ ይህ ነው የሚባል የመክሰሻ መረጃ አልነበረውም፤ እንዲያውም ከስማችን በቀር የሚያውቁት ነገር አልነበረም፡፡ ሌላው ቀርቶ ከደህንነቶታቸው በአንዱ ልከንላቸው የነበረውን የጽሑፋችንን ስብስብ እንኳን ሳያነቡት ነበር የያዙን፡፡
አሁንም ማስረጃ ብለው ከክስ መዝገባችን ጋር ያያያዙት ቢያንስ በእኔ ግምት ዘጠና በመቶ የሚሆነው ‹‹ሰነድ›› እኛው ነፃ ያወጣናል ብለን የሰጠናቸው ጽሑፎቻችን ናቸው፡፡ በመርማሪዎቻችን ንግግር ውስጥ እኛ ላይ ወንጀል የማግኘት Desperate ፍላጎት አይተናል፡፡ ምናልባትም እንደገመትነው ቢያንስ እስከ 2007ቱ ምርጫ ድረስ ከማኅበራዊ ሚዲያ ገለል እንድንልላቸው ፈልገዋል፡፡ ከዚህ የተሻለም አማራጭ አልታያቸውም ይሆናል፡፡
በእስካሁኑ ሂደት የማዕከላዊን ለገዢው ፓርቲ ወገንተኝነት በዓይናችን አይተን አረጋግጠናል፡፡ ቀጣዩ ደግሞ የፍትሕ ሥርዓቱን በአደባባይ መፈተሽ ይቀረናል፡፡ ለአሁኑ ግን በቅርቡ እንፈታ ይሆን… የሚል ጥያቄ ‹ሕጋዊ› ሳይሆን መላ ምታዊ አማራጮችን እገምታለሁ፡፡
ኢህአዴግ ወይም የኢህአዴግ መንግሥት የሚያዘው ፖሊስ እኛን በቁጥጥር ሥር ሲያውለን ስለወንጀላችን ማረጋገጫ (ጠበቆች Beyond reasonable doubt) እንደሚሉት ዓይነት ባይኖረውም መቼም የሆነች ስህተት ሳላገኝባቸው አልቀርም በሚል ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ወትሮም የተንቦረቀቀ የሚባለው የፀረ-ሸብርተኝነቱ አዋጅ ውስጥ የሚጥለን ነገር በቀላሉ ማግኘት አልቻሉም፡፡ አለመቻላቸው ግን የተነሱበትን እኛን የመክሰስ ዓላማ አላጠፋውም፡፡ የክስ መዝገቡን ሲያዘጋጁ አንድም የረባ ዐረፍተ ነገር ሳይጽፉ ይዘውን ፍርድ ቤት መቅረባቸው በራሱ አንድም የረባ ጥርጣሬና ማረጋገጫ እንደሌላቸው አመላካች ነው፡፡ ቢሆንም በቅርቡ ይለቁናል የሚል ግምት የለኝም፡፡ ለምን;

1ኛ. ኢህአዴግ በጣም የሚናደድባቸው እና ታሳሪውን በሚያዋርድ መልኩ ካልሆነ በቀር ከማያደርጋቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ- አንዴ ያሰረውን ተቺውን ፤ ያውም ብዙ ደጋፊ ያለውን መፍታት ነው፡፡ ኢህአዴግ እንደልጅ እልህ ይጋባል ማለቴ ነው፡፡ (ይህንን ስል የእስራችንን ኢፍትሀዊነት የተመለከቱትን ጩኸቶች መጥላቴ አይደለም፤ ያለ እነርሱ መንፈሳችን አይጠገንም ነበር፡በአደባባይ የምናመሰግንበት ቀን ይመጣል)
2ኛ. መጀመሪያ የተጠራጠሩበት እና ኋላ የዋጧት ጥርጣሬያቸው፤ ማለትም (ምርጫውን ተከትሎ) አመፅ ማስነሳት በሚሉት ጉዳይ ላይ እቅድ እንደሌለን ቢያምኑም እንኳን ምናልባት እምነታቸው ከተሳሳተ Risk መውሰድ አይፈልጉም፡፡ ( መጀመሪያም የቀለም አብዩት ዶክመንተሪ አዝማሚያ ያስታውሷል)
3ኛ. ምንም እንኳን ዓመፅም፤ሽብርም የማስነሳት ፍላጎትም አቅምም፤ እንደሌለን ቢያምኑም የገዥው ፓርቲ ጠንካራ ተቺዎች መሆናችንን ስለሚያውቁ እና ስላልወደዱልን ፍርድ ቤት በምንመላለስበት ረዘም ያለ ጊዜ ባለው እስር ወቅት ቢያንስ የእስርን ምሬት እንድንቀምሳት ይፈልጋሉ፡፡ ቅጣትን ጨርሶ በነፃ መለቀቅ እንደማለት፡፡
4ኛ. ኢህአዴግ መፍረድ አይፈራም፡፡

የሁለት ሀገር ስደተኛው –ጋዜጠኛ። (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 10.08.2014 (ሲዊዘርላንድ -ዙሪክ)

እንሆ – በዚህ ዘመን ታሪክን እንደ ከሰል አመድ ባደረገ ጽልመታዊ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ዘመን – የአንድነቱ ልዑል የአሉላ ማሾ ከወደ ስሜን የብራና ኮከብ መሪን አሰቀድሞ ብቅ አለ። ይህ ደፋርና ንቁ፤ በራስ የመተማመን መንፈሱ ሙሉዑ የሆነ ዕንቡጥ ስሜቱን ለመግለጽ ያለውን ብቃቱን ብራና ቆሞ የሚመስከርለት ድንቅ ወጣት ጋዜጠኛ አብርሃማ ደስታ ነው። አብርሽ የሥርዬት መንገድ ነው።

የወያኔ ሃርነት ትግራይ በጎሳ የሚዘረዝራቸው በደሎችን ሁሉ እዬመነዘር በግልጽ፤ በተብራሩ፤ ስሜትን በሚፈትሹ፤ አጫጭር ዘገባዎቹ ዘመኑ የፈቀደለትን ታሪክ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ሲያኮመኩመን የቆዬ ትንታግ ነው። ጋዜጠኛና መምህር አብርሃም ደስታ „ ትግራይ የኢትዮጵያዊነት ባለ ጉልትነቷን እዬፈገፈገ እንድታጣ ከዘመተባት ጠላቷ ከአረሙ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ጋር ትፋታ ዘንድ ቆሞ ያሰተማረ – የሰበከ – የመከረ ትጉህ ወጣት ነው።

ታናሼ አብርሽ በፎሎቄማ የአጻጻፍ ለዛው የብዕር ፍቅረኞችን ሰጥ ብሎ እንደሚወርደው ኢትዮጵያዊ ወንዝ መንፈሳቸውን የገዛ፤ ማህል ላይ ወለል እያለ የሚያስቸግረውን ግራጫማ የዞግ ወረርሽኝ በሽታንም ሳይቀር በመግራት ህሊናን ሚዛን ላይ ያሰቀመጠ –  ዬእርቅም ድልድይም ነው። በቀልና እኛ - በበደል ዓይን፤ በቀልና እኛ በፍትህ ጆሮ፤ በቀልና እኛ በመገፋት የዕንባ ምጥ እያቆላመጠ በሥነ – ጥበብ ማራኪያዊ ውበት እንድንፈታተሽ ከህሊና መንበር ጋር ፊት ለፊት ያገናኘ ብቁ የጥበብ ሰው ነው። እንደ እኔ ብዙ ነፍሳትን ከጥፋት ውሃ በሁሉም አቅጣጫ ታድጓል ባይም ነኝ።

አብርሽ በራሱ ውስጥ ስሜቱን – ፍላጎቱን – ራዕዩን አቅርቦ እያባበለ – እያሟገተ ቀልብን ይዞ መልእክቱን በማስተዋል እንከታተለው ዘንድ በብቃቱ ፍቅርና ሰፊ ተደማጭነት ያገኘ ትጉህ የብዕር ገበሬ ነው። አብርሽ ጨርሶ ሚዲያ ዳስሷቸው ያማያውቀውን የገበሬ መንደሮችን ሳይቀር ከትግራይ ወጣ ብሎም የዳሰሰ ወርቅ ወጣት ነው። ለምሳሌ በዘመነ ታሪካቸው ብዕርና ብራና ጎብኝቷቸው የማያውቁትን በጎንደር እንደ „ጮንጮቅ“ ያሉትን እጅግ ትንሽ የገበሬ መንደር ሳይቀር የደረሰውን ህዝባዊ በደል በማጋለጥ ሃቅን አደባባይ አቅርቦ ዬወያኔ ሃርነት ትግራይ የነፃነት ጠላትንትነት፤ የርትህ ዘረፋን፤ የሰላማዊ ሰዎችን ሰላም ቀማኛነትን ቁልጭ ባለ ንጹህ አግባቢ ቋንቋና በውባውብ የቃላት ቅንብሮቹ ዘዬ ዕውነትን ለባለታሪኩ ለፍተሻ ያቀረበ ባተሌ የሰከነ ጋዜጠኛ ነው።

አብርሽ መምህር እንደመሆኑ መሰሉን ለመተካትም በትምህርቱ ዘርፍም አባታዊ ሃላፊነቱን የሚወጣው ወያኔ ሃርነት ትግራይ „ ከትግራይ ውጪ ያሉ ኢትዮጵውያን በጥቅሉ አማራ በሚል ሥያሜ ሰው ያልሆኑ፤ ሁለት ትላልቅ ጆሮ ያላቸው። አንዱን ጆሮውን ለብሰው፤ ሌላውን አንጥፈው የሚተኙ“ እያለ ትግራይን ከኢትዮጵያ ገንጥሎ፤ ጥላቻን ኮልኩሎ በበቀል ብቅል አብቅሎ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የነበረውን መሬት ያያዘ የቁርሾ ብክል ደም በማምከን በኢትትዮጵያዊነት መንፈስ የኔ ፍሬዎችን ያጠበ፤ ያጸዳ፤ የወያኔ ቆሻሻውን ሁሉ የጠረገ ብልህ ወጣት ነው። መምህር አብርሃ ደስታ በተማሪዎች የኢትዮጵያዊነትን አቅም በመገንበት፤ ኢትዮጵያዊነትን ብድግ ያደረገ ለጋ ወጣት ነው። እንደ ሌሎቹ የጎሳ ጥመኞች አዛውንት መምህራን የመረጥከውን መውሰድ ትችላልህ በማለት ታሪክን ለባንዳ በረድ ያለጋለጠ ንቁ ወጣትም ነበር። ታሪክን ማህል ላይ ገትሮ ያለጠቆረ የሙያውን ሥነ – ምግባር ክብር ያስጠበቀ ታታሪ ወጣት ነው። ስለሆነም ይህ ጋዜጠኛ፤ ጸሐፊና መምህር ወጣት ድርብ ሃላፊነቱን የተወጣ – የቆረጠ የቀለም – ቀለማም አባትም ነው።

እጅግ የምትናፍቁኝ የሀገሬ ልጆች። „የሥላሴ አንድነትና ልዩነት“ ለተዋህዶ ልጆች የተሰጣቸው አባቶች ብቻ ነው የሚተረጉሙት – የሚያመሳጥሩት። „ካህን“ በመሆን ብቻ ይህ ታላቅ የዕምነት ዶግማ ሊደፈር ከቶውንም አይችልም፤ ስለ „ነገረ ማርያምም“ ቢሆን በተመሳሳይ ሁኔታ የተፈቀደላቸው ብቻ አንደበታው ተከፈቶ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ በአማንያን ሥረ ህሊና ማብቀል ይችላሉ። ታናሼ ጋዜጠኛ አብረሃም ደስታም „ማንነትን“ የተነተነበት መንገዱም ሆነ የሂደቱ ረቂቅነት ፍጹም ልዩ ስለነበር „እኔ ማን ነኝ? ከዬት ተገኘሁ? እንዴትስ መጣሁ? ከማንስ ተፈጠረኩ? ግንደ – ዘሬ እንዴት ተፈጠረ? ቅርንጫፉና ግንዱ እንዴት ሀረግን ፈጠሩ?“ በማለት ልክ የተቋም ያህል ነበር ያስተማረው። ዬአብርሽ ጸጋ ከሩቅ፤ ወይንም ከወንዝ ወዲያ ማዶ ወይንም ህዋው ላይ አይደለም የሚነሳው – ከተጨባጩ ከጠረኑ ከራሱ ውስጥ ተነስቶ አካባቢውን ቃኝቶ ደረጃውን እዬጠበቀ ወደ ብሄራዊ፣ አህጉራዊና፣ ዓለማቀፋዊ ትንፋሹን ያመጠዋል – ያጣጥመዋል። መሬት ይዞ ስለሚነሳ ዘርቶ ሊያበቅል የሚፈልገው ነገር  እጥፍ ድርብ እንደ ተፈጥሮው ማብቀል ዬቻለ ትምህርተ – ገቢራን ነው። አብርሽ ለትግራይ ህዝብ የታሪኩ አባወራ እንደ ሥሙ የአብራሃሙ ቤት ነው። „መድህን“ ቢሉትም ይገባል። ታዳሚዎችም ሆነ አድናቂዎቹ ዕልፍ ነን።

እኔ አብርሽን እጅግ አውደዋለሁ። እሱ በሚጽፋቸው ጹሑፎች ሥር የአስተያዬት ግድፈቶች ከሥር ተጽፈው ሳይ እጅግ ልቤ ይቆስል ነበረ። ይህ ልጅ – ይህ ወጣት – ይህ ቀንበጥ – ይህ ጀግና በወያኔ ሃርነት ትግራይ ሆነ በሰሉ የወያኔ ደጋፊዎቹ  የከረፋ የበደል ክምር ተጠያቂ ሊሆን ከቶውንም ፈጽሞ አይቻልም።

ወገኖቼ ይህን ቢፈቅድ እኮ ጋዜጠኛ አብርሃም ደስታ ለዶተሬትነቱ ሰፊ ዕድል ማግኘት ይችል ነበር። ተነጥፎ ተጎዝጉዞለት። ሀገር ውስጥ እኖራላሁ ቢልም እስከ ሚ/ር ደረጃ የሚያደርስ ዕድሉ ሰፊ ነበር። የመጀመሪያውን የወያኔ ሃርነት ትግራይ መስፈርት የሚያሟላ ጉልህ ወጣት ነበር። ግን አላስፈለገውም። መኖር የፈለገው በእውነተኛው ዓለም በጋህዱ ዓለም ነበር። ገሃዱ ዓለም የሚፈልገው ደግሞ እንደ ተፈጥሮው የሆነ ነፃነትን ነው።

የመኖር – የመተንፈስ፤  የመናገር፤ የመጻፍ፤ የመደራጀት፤ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ፤ የህግ የበላይነት፤ በድምጽ የሚመራ ሀገር፤ በደል – አድሎ – ስጋት – ረሃብ የሌለበት የእኩልነት ዜግነት ዓለም ነው። ይህን ከወያኔ ሃርነት ትግራይ የ40 አመት ትግል ጠብቆ ማዬት አልቻለም። ስለዚህ ከበደሉ ማሳ እራሱን አውጥቶ እሱ ስለሚያልማት ኢትዮጵያ መናገር ጀመረ …. ማስተማር ጀመረ …. መስዋዕትነቱን ተርጉሙት በነፃነት ህገ – ህግጋት መገዛት ቻሉ! በማለት ወቀሳውን ካለይሉኝታ  ለአራዊቱ ወያኔ  ገለጸ …. ሰሚ አጣ … እንዲያውም ተጠቂም ሆነ።

እኔ በጣም ለረጅም ጊዜ አስተውለው የነበረው አብይ ጉዳይ „ጋዜጠኛ አብርሃ ደስታ“ ለማለት እንኳን ጋዳ ነበር። ሙያው የሚጠይቀውን ያሟላ ሆኖ እያለ። ዘገባዎቹ ትኩስ – ግልጽ – የተብራሩ – ከማህበረሰቡ የተነሱ – ፈጽሞ በግነት ያልተወረሩ – ብዙኃኑን ያደመጡ –  አጭር – ደፍረው ጦርነት ውስጥ የሚያገቡ – ቅራኔ የተጋሩ፤  ዬእውነትን ጅረትን ተከትው ዬሚጓዙ – የዘመኑን ባህሪ ያደመጡ ነበሩ። ይህ ሙያው የሚጠይቀው በጋዜጠኛ አብርሃም ደስታ በቀጥታ በተፈጥሮው ያገኘው ልዩ ብቃቱ ነበር። ለነገሩ በሥልጠና የሚገኝ ክህሎት ነበር — ግን እሱ ከላይኛው ተፈቀደለት።

ወደ ሥነ -ጹሑፍ ሥልጡነነቱ ስትሄዱ ደግሞ  የነጠረ አቅም ነበረው፤ ጹሑፎቹ  የወያኔን ሆድዕቃ አሳምረው ጎርጉረው ግን ሳይጠገቡ እንዳጓጉ ላጥ ይሉ ነበር። ልብን እንደ ቅል አንጠልጥለው። ዝንፈት ያልጎበኛቸውም ነበሩ።

በሰብዕዊ መብት ተቆርቋሪነቱም ቢሆን ቁስሉ የተሰማው መንፈስ ነበር የሚታይበት። በሴቶች የእኩልነት ተሳትፎ ላይም አንጋፋ – ጎልማሳ – ወጣት – ጋዜጠኞች የሚዘሉትን ሥነ – ምግባር ያሟላ ነበር ማለት እችላለሁ። እጅግ አብዝቼ እምከታተለው ዘርፍ ነውና። በአብርሽ የዜና ትንተና የመረጃ አቅጣጫ ደግሞ ድንቅ ትርጉም ይታፈሳል። ዘገባዎቹ ሁሉ – ከቆዳ መልስ ነክቷቸው አያውቅም።  ወይንም ተቆርጦ እንደ አደረ ዝንጣፊ ጥንዙል አልነበሩም። ትኩስ ትኩሱን ለመንፈሳችን ይቀልብን ነበር። እንሆ አሁን ትግራይ አንደበቱ ተዘጋ …. ስለ አሉላ መንፈስ፣ ስለ አሉላ ጸሐይ – ትግራይ ምን ይል ይሆን? ጸጥ – ረጭ – ዝም —-  ያቺ የእኔ ጀግና ወ/ሮ አልጋነሽ ገብሩና መንገድ እንደወጡ ያዳመጥነው ዬፍሬዎቻስ – የነገ ተስፋዎቻችን ጉዳይ ማን ይንገርን – ዝግት ድርግም ያለ ጉድ …. ዳፍንት!

እኔ አንጀቴን የሚበላኝ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ጎጣዊ ማንፌስቶ ትሸታላቸሁ ብሎ የሚመጣን ኢትዮጵያዊ ዜጋን ለመቀበል ያለን አቅም ስስ መሆኑ ነው። ሁልጊዜ ጥርጣሬ። ሁልጊዜ ወቀሳ። ሁልጊዜ ዱላ። አብሶ ወጣቶች ባልበሉት ዕዳ ስለምን እንደሚወቀሱ ፈጽሞ አይገባኝም። እንዲገባኝም አልፈቅድለትም።

ማያያያዣ ነገር – አሁን የአንድነቱ አንደበቱን – ብቃቱን – አቅሙን ሳልጠግበው ለካቴና የበቃው አቶ ሃብታሙ አያሌው „ዬወያኔ ደጋፊ ዬነበር“ በሚል ከልብ ለመቀበል የነበረን ፈቃደኝነት ያረረ ነበር። አሁን ሲታሰር ጀግና እንለዋለን? ወያኔ አሁን ከሚያደርስባቸው ማናቸውም ስቃይ የኛውም የመንፈስ ረገጣ ሆነ ጥቅጠቃ ዘመን ይቅር የሚለው አይመስለኝም። አንድ ሰው በነፃነት ትግሉ እሰለፋለሁ ሲል በጣም ብዙ ነገሩን ነው የሚያጣው። የሚተርፈው የመንፈስ ጥሪት ለህሊና ማደሩ ብቻ እንጂ በግራ በቀኝ በሚወርደው ወጀብ ያለው ወጨፎ መመዘን ከቶ አይቻልም።

ለነፃነት ታጋዮቻችን ለመንፈሳቸው ጥበቃ ጥንቃቄ በሚመለከት ምድረበዳ ነው። ወያኔ እዬከፈለ። ውጭ ሀገር ላሉ ቱቦዎቹ ሳይቀር እንኳን ቀለብ እዬሰፈረ የእኛ ደግሞ በብላሽ ለማገልግልም ቆመጥ —- እም!

እርግጥ ተሰውረው – ተቀላቅለው አንድ ደረጃ ላይ የሚሾልኩ ይኖራሉ። ከዚህ ስጋት አንጻር ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አራሳቸው ከፈለጉ ወደ ውርዴታቸው ያዝግሙ። በእኛ በኩል ያለውን መልካም አቀባባልና ፍቅር ከመሰጠት መቆጠቡ ግን የማይጠቅም ነው። ባይሆን ደረጃውን ይጠብቅ ያግባባል — እንጂ ገና በሩ ሳይደርሱ …

አንጀቴን እዬበለኝ የምጽፈው አብርሽ የሁለት ሀገር ስደተኛ የነበረ መሆኑ ነው። እኛ የነጻነት ፈላጊ ቤተሰቦች በይደር ዬያዝናቸው ጉዳዮች ነበሩን። ወያኔ ከጎጥ ዶክተሬኑ በማምለጡ እርምጃውን እዬተከታተለ መተንፈሻውን መዝጋቱ በሁለት ወጀብ ሲንገላታ እነሆ በእጅ ወድቆ እንደፈለጉት ይዘለዘላል። የበለጠ – የቀደመ – የተሸላ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን „የኢትዮጵያዊነት ፋና“ በመሆኑም ጭምር ሁለመናውን ይደምስሱታል።

ፎቶዎቹን ስብስብ አድርጌ ስመለከታች መልሼ በዚህ መንፈስ እንደማለገኘው ሳስበው መንፈሴ ይመረቅዛል – በመግል። ፈዞ በድኑን ብቻ ይሆናል ዬሚሰጡን። ቀጣዩ የእሱ የወደፊት ተስፋ ሁለት ያጣ ጎመን እንዳይሆን እንደማንንኛውም የብዕር አርበኛ ለዓለም ዓቀፉ የብዕር ሽልማት ይበቃ ዘንድ ተግቶ መሥራት ያስፈልጋል። የታሪኩ ጠበቂና ዘብ አደር ልሆንለት ይገባል። አብሶ ወጣት ኢትዮጵውያን አብርሽን እንደ ወጣት አብነታቸው፤ እንደ ወጣት ሙሴያቸው ሊያዩት እንደሚገባ በእናትነቴ ዝቅ ብዬ እጠይቃለሁ።

የተግባር ዲታው እውነተኛውና አንጋፋው የኢትዮጵያ መምህራን ማህበርም በክህሎት የተቀመመውን ተመክሮውን አበልጽጎ ለሙያ አጋሩ ያለውን አክብሮትና አድናቆት ሊገልጽ ዬሚችልበትን ስልት መፍጠር እንዳለበት አሳስባለሁ – በትህትና። በአንድ ወቅት የክፍለሃገር አዳራጃችሁ ነበርኩና – ህገ ደንባችሁ እንዲህ ለሙያው አርበኛ አክብሮቱን እንደማይነፍገውም አስባለሁ። በተጨማሪም ጋዜጠኛና መምህር ርዕዮት ዓለሙም ታሪካችሁ ናት። እሷንም አዘውትራችሁ ልታስቧት እንደሚገባ በትህትና እጠቁማለሁ።

በሌላ በኩል ደግሞ እንደ ሥነ ጥበብ ቤተሰብ አባልንቴ ወጣት ከያንያን አብርሽን – ክታባቸው እንዲያደርጉት በትህትና አሳስባለሁ። እንደ ጋዜጠኝነቴም ደግሞ የሙያ አጋራቹ ከፊተኛው ረድፍ ላይ በመገኘት ለሙያው አህጉርና ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ወቅታዊ መረጃዎችን በመላክ – ተግባሩን በማስተዋወቅ እረገድ ተጓዳኝ ተግባራትን አቅሙ ያላችሁ ወገኖቼ ትከውኑ ዘንድ በአጽህኖት አሳስባለሁ።

ምን ቀረኝ? ለሰብዕዊ መብት አስከባሪ ድርጅቶችም መረጃዎችን በአጫጭር በእንግሊዘኛ ከተሰሩ ባለው መስመርና ግንኙነት የሎቢውን ተግባር በቀላሉ መከወን ይቻላል። አብሶ የፍርዱን ሂደት የቀጠሮ ቀናቱን ውሎዎች ሁሉንም በእንግሊዘኛ መሠራታቸው እጅግ ጠቃሚው መንገድ በመሆኑ አትኩሮት ቢሰጠው መልካም ነው።

ማህበራዊ ድህረ ገጾች፤ የመወያያ መድረኮች፤ ሚዲያዎች ለአጋራቸው – ለጀግናቸው የነበራቸው አቅርቦትና አክብሮት አብነት ነበር ማለት እችላለሁ። የአብርሽ ጹሑፎች ሆኑ ዘገባዎችን በሽሚያ ነበር የሚያወጡትና አዬር ላይ የተገባውን አክብሮት ይሰጡት የነበረው። ተመስገን። በዚህ ልጽናና።

በቀጣይም በአብርሽ የነጻነት ራህብተኛ ጹሑፎቹ ዙሪያ ውይይቶች – ትናንሽ ወርክ ሾፖችን በዬአካባቢው ፈጥሮ አጀንዳ ማደረግ የተገባ ይመስለኛል። አሁን ለምሳሌ „እኔና ሚኒሊክ“ የሚደንቅ ጹሑፍ እኮ ነው።  ስለሆነም የቆዩትንም  ከአርኬቡ እያወጡ ድጋሚ እንዲነበቡ ቤተኛ ማደረጉ መንፈሱ ከመንፈሳችን ጋር እንዲቆራኝ ይረዳል። አብሶ አሁን ፆም ስለሆነ በጸሎት መተጋጋዙም መልካም ነው። ፎቶውን በፌስ ቡኮች – በቲተር አካውንቶች ሁሉ መጠቀም ሌላው መንፈስ አራሽ መንገዶቻችን ሊሆኑ ይገባል። ጹሑፎቹ የማሰባሰብና ታሪካዊ ቋት ማበጀትም – ነገን ያሳድራል።

በማናቸውም ብሄራዊ ህዝባዊ ስበሰባዎች ሰላማዊ ሰልፎች፤  ጀግናችን አጀንዳችን፤ ጀግናችን ኮከባችን መሆኑን ከውስጣችን ሆነንበት እንታይበት ዘንድ ዝቅ ብዬ አሳስባለሁ። ለእኔ አብርሽ የአንድነቱ ልዑል ዬአሉላ አባነጋ የአደራ ማሾዬ ነው። በብዙ ጹሑፎቼ እሱን እንደ ማመሳካሪ እያደረኩኝ ሰርቼበታለሁ። አሁንም ከልቤ ውስጥ ትንሽ ሙዳያ አለች። በእሱ ውስጥ ታናሼ የሙያ አጋሬ፤ የሥነ ጥበብ ቤተኛዬ፤ እንዲሁም የነፃነት ፈላጊ ቤተሰቤ አበርሽ በክብር ለዘለአለም ይኖራል፡“ አራዊቶች የፈለገውን ነገር አስገድደው ያሰፈርሙት። የእሱ ነው ብለው ይጻፉ። ለእኛ የባንዳ መረጃ ምናችንም ነው። ይልቁንስ አብርሽን የሚገልጸው የሚያብራራው ዬሚያነበው “ የኢትዮጵያዊነት ህግ – አመክንዮ“ መሆኑ ብቻ ነው መስተውታችን ሆነ ሰነዳችን።

ማንም ሰው የአብርሽን ፍቅር ሊቀማን አይችልም። አይፈቀድም። የተከለከለ መንገድ ነው። የእሱ የተስፋ ማሳዎች ዕሸቶች ናቸው – ነገን ያበልጋሉ። እኔ አብዝቼ  እወደዋለሁ። የእሱ መፈጠረ ከብዙ ነገር ታድጎናል። ኢትዮጵያን ከበቀል ያዳና ትንሽዬ ወጣት የድህነት መንገድ ነው …..  አብርሃ ደስታ። አጋጣሚና ሁነኛ ጊዜ አግኝቶ ቢሆን ኖሮ ሰፊ ማሳን ማልማት በቻለ ነበር። ታዲያ ወ ያኔ አቅል ብሎ አልሰራለት። ፈሪ – ብዕርን መድፈር የተሳነው ልፍስፍስ።

የትግራይ ህዝብ ቢያውቀው አብርሽ እንደ መጥምቁ የኋንስ „መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስኃ ግብ“ እያለ እንደ መራው ሐዋራያዊ ተግባር ነው የፈጸመው እሱ እራሱ መልእክተ የኋንስ ነው። በሁሉም ዘርፍ ሲመዘን የአብርሽ ተልዕኮ የብዙኃኑ ፍቅርና ሰላም የተራቆተው ወያኔ ሃርነት ትግራይ እርቃነ – መንፈስ ጎጂ ጉዞ ስለመሆኑ፤ ነገን የማያሳድር ዛሬንም ያማያበርክት ስለመሆኑ ነበር እንደ ተሰጠው መክሊት ሲፈጽም የቆዬው።

ክወና – አብርሽ ሞገድ ነው – ሃቅን የታጠቀ፤ አብርሽ ነበልባል ነው – በራስ መተማመንን የዋጠ፤ አብርሽ ፍቅር ነው  የነፃነት መርህን ከልቡ የተቀበለ። አብርሽ አብነት ነው መከራን ለመቀበል የፈቀደ። ስለሆነም ስቃዩ ስቃያችን፤ መከራው መካራችን፤ ሰቆቃው ሰቆቃችን ነው። የኔ አባት ላደርክልን መልካም ነገር ሁሉ አመስግንሃለሁ። ውድድድ /////

 

የኔዎቹ እንሰነባበት – ፍቅርም – ናፍቆትም – ውስጥም ተሸለማችሁ። ቸር አገኛችሁ ዘንድም አምላኬን ጠዬኩኝ። ደህና ሰንብቱልኝ። ውድድድ

 

ጀግኖቻችን የመንፈስ ሀብሎቻችን ናቸው!

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጥር!

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

Comment

የከዱ የግንቦት 7 አባላት አቶ አንዳርጋቸውን እያሰቃዩ ነው ተባለ፤ * 2 መምህራንና 1 ዳኛ በአንዳርጋቸው ጉዳይ ታፍነዋል

$
0
0

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን መያዝ ተከትሎ ለወያኔዎች ከአዲስ አበባ እስከ ደብረዘይት ትልቁን የምርመራ ስራ እየሸፈኑ ያሉት ከግንቦት ሰባት ሕዝባዊ ሃይል ጋር በኤርትራ የነበሩ እና ከአቶ አንዳርጋቸው ጋር የፖለቲካ ስራ ሲሰሩ የነበሩ በኋላም ከድተው የገቡ ቅጥረኞች መሆናቸው ታውቋል። እነዚህ ቅጥረኞች ከመጀመሪያው ሰርጎ ገቦች እንደሆኑ ሳይጠረጠር ወደ ግንቦት ሰባት ከገቡ በኋላ ከአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ቀደም ብሎ በመክዳት ወደ ወያኔ የተቀላቀሉ ናቸው ሲል ጦማሪ ምኒልክ ሳልሳዊ ዘገበ።

Andargachew Tsigeእንደ ምኒልክ ዘገባ ከሆነ በአዲስ አበባ እና በደብረዘይት ትልልቅ ሆቴሎች ተይዞላቸው በምርጥ መኪኖች እየተንሸራሸሩ አቶ አንዳርጋቸውን በማሰቃያ ክፍል ውስጥ በማምጣት እውነቱን አውጣ አንተ እንደዚህ ብለኸን አልነበረም በማለት በተለያየ ጊዜ በስብሰባ እና በውይይት ወቅት የተነጋገሩትን የፖለቲካ ኦፕሬሽኖችን እና የትግል ስትራቴጂዎችን በመጥቀስ ከፍተኛ ስቃይ እና ድብደባ እያደረሱብት ነው።

ከሕወሃት ከአንድ ብሄር ከተመለመሉ መርማሪዎች ጋር በጋራ በምርመራ ላይ የተሰማሩት ሶስቱ የግንቦት ሰባት ከሃዲ አባላት አንዳርጋቸውን በማሰቃየት ላይ ያሉት -
1) ሽታው ሽፈራው ኤርትራ የነበረ የጎጃም ሰው
2) ቴዎድሮስ ስዩም ኤርትራ የነበረ ከአዲስ አበባ የሄደ
3) ኢልያስ ጥረት ጎንደር ውስጥ የነበረ እና ከአንዳርጋቸው ጋር ሲሰራ የነበረ ናቸው ሲል በዝርዝር የጠቆመው ጦማሪ ምኒልክ ሳልሳዊ በወያኔ ተንኮል ተተብትበው ግንቦት ሰባትን በመክዳት ለምቾታቸው የሕዝብን ትግል በጥቅም በመለወጥ በዘመናዊ መኪና እየተንፈላሰሱ በአዲስ አበባ እና ደብረዘይት ምርጥ ሆቴሎች ውስጥ እየተዝናኑ የነጻነት ታጋይ የሆነውን አንዳርጋቸውን በቶርች በማሰቃየት ላይ መሆናቸውን ዘግቧል።

ምርመርውን በመሪነት የሚያንቀሳቅሱት የሕወሓት ደህንነቶች የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ በአከባቤው አንዳርጋቸውን በተመለከተ ለብአዴን ይሁን ለ ኦሕዴድ ሰዎች ምንም አይነት መረጃ እንዳይሰጣቸውና ወደ ማሰቃያ ክፍሉ ምንም እንዳይቀርቡ ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገ እንደሆነ ለማረጋገጥ መቻሉን የገለጸው ጦማሪው ከአንዳርጋቸው ጋር የተያያዘውን የሃገር ውስጥ ኔትወርክ በማፈራረስ ረገድ ከላይ ስማቸው የተጠቀሰው ከሃዲዎች እስከ ክፍለሃገር ድረስ በስፋት እየሰሩ ሲሆን እስካሁን በማፈራረስ ሙከራው ምንም አይነት ውጤት እንዳልገኙ ታውቋል ብሏል።

ጦማሪው ዘገባውን ሲቋጭም “ከአንዳርጋቸው ጋር በተያያዘ ከየክልሉ የግንቦት ሰባት መዋቅር ውስጥ አሉ የተባሉ እየተለቀሙ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ከጎንደር ክፍለሃገር መምህር ተስፋዬ ተፈሪ እና መምህር ጌታቸው የተባሉ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን እንዲሁም የጎንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ እንደሆነ የሚነግረው አቶ አበራ በከሃዲዎች ጥቆማ ከሃምሌ አጋማሽ ጀምሮ ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ የት እንደታሰሩ እንኳን እንደማይታወቅ ተገልጿል።” ብሏል።


ለዲያስፖራ ኗሪ ኢትዮጵያውያን በሙሉ።

$
0
0

endaleየትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር (ወያኔ)ለስድብና ለማዋረድ ሥራ በክፍያ ያሰማራቸው ቅጥረኛ ባንዳዎችን እንዋጋ!! ለሃገርና ለሕዝብ የቆሙ ግለሰብ ኢትዮጵያውያንን፤ ድርጅትና፤ ተቋማትን እያሳደዱ እንዲሰድቡና እንዲያዋርዱ ወያኔ አሰልጥኖ ያሰማራቸው ቅጥረኞች ሕዝብን ስይፈሩና ሳያፍሩ የባንዳነት ተግባራቸውን ቀጥለውበት ይገኛሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት የሚል ስያሜን የያዘው የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር (ወያኔ) እነዚህን ተሳዳቢ ቅጥረኞች ያሰማራው የቻይና መንግሥት የኮሚንስት ፓርቲውን አመራር የሚቃወሙና የሚተቹ ግለሰብና ተቋማትን ለማሸማቀቅ ሲል አቋቁሞት የነበረውን የ50 ሳንቲም ፓርቲ (50 Pence Party ) ዘዴን በመውረስ ሲሆን ዓላማውም ለወያኔ የማይመችን ኢትዮጵያዊ ግለሰብ፤ ማህበረሰብንና ተቋምን ሁሉ በመስደብ በማዋረድና በሃሰት ክስ በማሸማቀቅ ቅስሙን ሰብሮ ተገዢ ለማድረግ ነው። —- [ሙሉውንለማንበብእዚህላይይጫኑ]—-

Hiber Radio: የአንድነትና መኢአድን ውህደት ያገዱት የወ/ሮ አዜብ ወንድም መሆናቸው ተገለጸ፤ ከደ/ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ስደተኞች የጉበት በሽታ እያስተላለፉ ነው

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ነሐሴ 4 ቀን 2006 ፕሮግራም

<< ...መኢአድና አንድነትን እንይዋሃዱ ምርጫ ቦርድ የሰጠው ሕገ ወጥ ውሳኔን በቀጥታ የወሰነው የቦርዱ ጽ/ቤት ም/ ሀላፊ የወይዘሮ አዜብ መስፍን ወንድም ነው...መኢአድ የቦርዱን ውሳኔ በመቃወም ልዩ ልዩ ጠንካራ ተቃውሞዎችን ይጠራል። ስራ ማቆም አድማ እና ሌሎችንም ያካትታል ሕዝቡ ጥሪያችንን ይጠባበቅ ...>>

አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ የመኢአድ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ለህብር ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<...ፕሬዝዳንት ኦባማ ጋና ላይ ከዓመታት በፊት ለአፍሪካ ጠንካራ መሪ ሳይሆን ጠንካራ ተቋማት ያስፈልጋል ያሉበትን ዛሬ ዘንግተዋል...ኢትዮጵያውያን ጠንካራ ተቃውሞ ማቅረባችን ጠቃሚ ነበር ይህ ባይሆን አሜሪካውያን አፍሪካውያን ደገፉት ይሉን ነበር... >

አቶ ኦባንግ ሜቶ አሜሪካ የኢትዮጵያን አምባገነኖችን በመጋበዙዋ የቀረበው ጠንካራ ተቃውሞ ውጤታማ መሆኑን ለህብር በሰጡት ቃለ መጠይቅ ገለጹ (ሙሉውን ያዳምጡት)

የአሜሪካና የቻይና የኢኮኖሚና የዲፕሎማሲ ግብ ግብ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተንሰራፋባት አፍሪካ ሜዳ ላይ (ልዩ ዘገባ)

ኢራቅ የተወለዱት አዲሶቹ አሸባሪዎችና በክርስትና ሀይማኖት ተከታይ ላይ ጭምር የፈጸሙት ጅምላ ግድያ እና የመስፋፋታቸው ስጋት (ልዩ ጥንቅር)

የኢትዮጵያዊነት ቀን ክብረ በዓል ዝግጅት በቬጋስ(ቃለ መጠይቅ)

ሌሎችም አሉ

ዜናዎቻችን

* የአንድነትና መኢአድን ውህደት በህገወጥ ውሳኔ ያገዱት የምርጫ ቦርድ ባለስልጣን የወ/ሮ አዜብ መስፍን ወንድም መሆናቸው ተገለጸ

* መኢአድ የቦርዱን ውሳኔ ሳይቀበል የስራ ማቆም አድማን ጨምሮ ጠንካራ ተቃውሞ እጠራለሁ አለ

* የእንግሊዝ መንግስት በአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ የኢትዮጵያውን አገዛዝ ባለስልጣናት ጠርቶ አነጋገረ

* ኢ/ር ግዛቸው ገዢው ፓርቲ በምርጫ ቦርድ በኩል የተቃወመውን የአንድነትና መኢአድ ውህደት የሚያቋርጥ ውሳኔ በችኮላ ማስወሰናቸው ግራ መጋባት ፈጠረ

* 24 ኢትዮጵአውያን ስደተኞች ሰሞኑን ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ ገባችሁ ተብለው ተያዙ

* ከደ/ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ስደተኞች የጉበት በሽታ ለኢትዮጵያውያን እያስተላለፉ መሆኑ ተገለጸ

* ኢትዮጵያዊው የድህረ ገጽ ባለቤት በሕወሓት አገዛዝ ላይ የ120 ሚሊዮን ዶላር ክስ ከፈተ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

ታሪክ ሲደገም! –ከኢየሩሳሌም አረአያ

$
0
0

Interview with the former Ethiopian PM Fikre Selassie Wegderes – Pt 1
የደርግ ዋና ሞተር የነበረው ፍቅረስላሴ ወግደርስን ጨምሮ በርካታ ነፍሰ በላዎች ከእስር ተፈተው መፅሐፍ በነፃነት ሲፅፉ እያየን ነው። ለምን ፃፉ የሚል ተቃውሞ የለኝም። ነገር ግን ፍቅረስላሴ ደራሲ በአሉ ግርማን ቀርጥፈው ከበሉ ቁልፍ የደርግ ባለስልጣናት ዋናው ሆኖ ሳለ አንድም ነገር ስለበዓሉ ግድያም ሆነ ስለጨፈጨፏቸው በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ምንም ያለው ነገር የለም።

እንዳውም ደርግ ትክክለኛ እንደነበረ ሊሰብክ ሞክሮዋል። የጥቃቱ ሰለባዎች ምን እንደሚሰማቸው ለማወቅ የግድ እነሱን መሆን አይጠበቅም። እነፍቅረስላሴ ወንጀላቸውን ሸፍነው ውሸት እየፃፉ በሚኖሩባት አገር እውነት የፃፉ ሰላማዊ የአገር ልጆች ዞን 9ኝና ጋዜጠኞች፣ የተቃዋሚ አባላት እነሃብታሙና አብርሃ የመሳሰሉት በሚያሳዝን ሁኔታ በነፍቅረስላሴ ቦታ ወንጀል ተፈብርኮባቸው እስር ቤት መግባታቸው ያቃጥላል።

እነፍቅረስላሴ በበአሉ ግርማ ላይ ያነሱትን የጭካኔ በትር የአሁኑ ገዢዎች ከላይ በጠቀስኳቸውና በነእስክንድርና ርእዮት ወዘተ..ንፁሃን ላይ በተመሳሳይ የጥፋት ሰይፋቸውን መዘዋል። የደርግ ጨካኞች እነገስግስ ገ/መስቀልና እርገጤ መድበው በተባሉ ይፈፅሙ የነበረውን ዘግናኝ ስቃዮች “እቃወማለሁ፣ ታግየዋለሁ” ይል የነበረ ድርጅት ወይም ስርዓት ዛሬ እነ ታደሰ መሰረትን የመሰሉ ገራፊዎች አሰማርቶ ንፁሃን የኢትዮጵያ ልጆችን እየገረፈ ማሰቃየቱ ታሪክ እራሱን እየደገመ እንዳለ በቂ ማሳያ ነው! ገዢዎቹ ግን ማወቅ ያለባቸው ነገር እስር፣ ግርፋትና ስቃይ በጭራሽ መፍትሄ ሊሆኑ አይችሉም። ደግሞም በግዜ ሒደት እናንተና የደርግ ነፍሰ በላዎቹ እነፍቅረስላሴና ተከታዮቹ በፍርድ አደባባይ መገተራችሁ አይቀሬ ነው። .
« እናንተም እረሱ እኛም እናርሳለን
መኸር ሰብሳቢውን አብረን እናያለን» ….ወዳጄ ኮሜዲያን አብርሃም አስመላሽ (አፈሩን ገለባ ያድርግለት) ለገዢው ተላላኪዎች በምሬት የተናገረው።

አቶ በረከት ከአንድ ወር በኋላ ለምርመራ ወደ ሳዑዲ አረቢያ እንደሚመለሱ ተገለጸ፤ ግማሽ ሚሊዮን ብር ለህክምናቸው ወጪ ሆኗል

$
0
0

bereket simon
ከኢትዮጵያ ሃገሬ ጅዳ በዋዲ

የልብ ህክምናቸውን ጨርሰው ሰሞኑን ወደ ኢትዮጵያ ያቀኑት አቶ በረከት ስሞዖን የጤንነታቸው ሁኔታ ከበፊቱ በተሻለ ሁኔታ ላይ መሆኑን የሚያመለክቱት በሳውዲ አረቢያ «የቡግሻን» ሆስፒታል ምንጮች ባለስልጣኑ በአፋጣኝ ህክምና ተደርጎላቸው ባይሆን ኖሮ በሽታው ሙሉ ለሙሉ ሽባ « ፓራላይዘድ » ሊያደርጋቸው ይችል እንደ ነበር ይገልጻሉ።

ሳውዲ አረቢያ ጅዳ ከተማ የሚገኝ በተለምዶ «ቡግሻን ተብሎ የሚጠራ ሪፈራል hospital » ውስጥ የኚህን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን የልብ ችግር ለመፍታት ከ 6 ሰዓታት በላይ ህክምና መውሰዱን የሚናገሩ የሆስፒታሉ ምንጮች የልብ ቦንቦውን የምሳፋት ስራ የተሳካ እና ጥንቃቄ የተሞላበት ቢሆንም አቶ በረከት የጤንነት ሁኔታቸው በማህበራዊ ገጾች መነጋገሪያ መሆኑ ተከትሎ በውስጣቸው የፈጠረው ጭንቀት ከህክምናው በኃላ የልብ ምታቸው ለውጥ ባለማሳየቱ በህክምና ባለሙያዎቹ ላይ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጥሮ እንደነበር አክለው ገልጸዋል ። በልብ ዙሪያ የሚከሰቱ ችግሮች ዋስትና እንደሌላቸው የሚናገሩ አንዳንድ የሙያው ጠበብቶች የልብ ቦንቦ ቸገር አብዛኛውን ግዜ የሚከስተው ከውፍረት እና ከደም መርጋታ ጋር ተያይዞ መሆኑን በመጥቀስ በሽታው « በግራ በኩል የሚገኘውን የሰውነት ክፍል ባልታሰበ ግዜ ሙሉ ለሙሉ ሽባ « ፓራላይዝድ በማድረግ እስከሞት ሊያደርስ የሚቸል አደገኛ በሽታ መሆኑን በመጥቀስ።

በተመሳሳይ መልኩ የኚህን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን የጤንነት ሁኔታ በቀጣይነት ለማረጋገጥ፡በየወሩ ምርመራ ማድረግ እንደሚገባቸው ይናገራሉ ። ሰሞኑንን ባህርዳር የብሄር አማራ ዴሞክራሲ ንቅናቄ « ብ.አ.ዴ.ን » ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ሊትዮጵያ ህዝብ በመንግስት መገኛኛ ብዙሃን የታዩት አቶ በረከት የፊታቸው ገጽታ መልካም ጤንነት ላይ መሆኑን ቢገልጽም በአጋጣሚ ህይወታቸውን ሊያሳጣቸው ከሚችለው የልብ በሽታ እራሳቸውን ለመታደግ የጤና ምርመራ «ቼክ አፕ» ለማድረግ ከወር በሃላ ወደ ሳውዲ አረቢያ እንደሚመለሱ ለማወቅ ተችሎል።

የአቶ በርከት ስሞዖን ቀጣዩ የሳውዲ አረቢያ የጤና ምርመራ ጉዛ ጅዳን አልፎ ሪያድ ሊዘልቅ እንደሚቸል የሚገልጹ ውስጥ አውቂ ምንጮች እኚህን የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ሼክ አላሙዲን በሳውዲ መንግስት በኩል በፕሮትኮል ለማስገባት እቅድ እንዳላቸው አክለው ተናግረዋል። በሼኽ አላሙዲን የግል አይሮፕላን በድብቅ ሳውዲ አረቢያ ገብተው ህክምናቸውን ሲከታተሉ ለቆዩት አቶ በረከት ስሞዖን እስካሁን 60 ሺሕ የሳውዲ ሪያል (60 ሺህ ሪያል በአሁኑ የኢትዮጵያ ምንዛሪ « ግማሽ ሚልዮን ብር » ነው) መውጣቱን እና ጠቅላላ የህክምን ወጪውም በሼኩ ሙሉ ለሙሉ መሸፈኑን ለማረጋገጥ ተችሏል።

ፕሬስ የሌለው መንግስት ከሚኖረን መንግስት የሌለው ፕሬስ ቢኖረን እንመርጣለን

$
0
0

ዳዊት ሰሎሞን

10570542_10204024912521089_4618968976545930065_nእርግጥ ነው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የአዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጆች ለስደት ሲዳረጉ ‹‹አዲስ ዘመንንም አዲስ ነገርንም አላነብም››በማለት ነግረውን ነበር፡፡ሌጋሲያቸውን ለማስቀጠል ቤተ መንስግስት የገቡት ሃይለማርያም በበኩላቸው በአንድ ጋዜጣዊ መግለጫ የፎርቹንን ኮሪደር እንደሚያነቡ ሲናገሩ አድምጫለሁ፡፡

የቅንጅት አመራሮች በድርድሩ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ እንደገቡ ብዛት ያለው የኢትዮ ቻናል ጋዜጣ ተጠርዞ መመልከታቸውን መናገራቸውም አይዘነጋም፡፡ገዢዎቻችን ከቀድሞዎቹ ነገስታት ባነሰ መልኩ ‹‹አዝማሪ ምን አለ?››በማለት ለመጠየቅ አለመፍቀዳቸው ትርጉሙ ንቀት ብቻ ነው፡፡ህዝቡን የሚፈልጉት እነርሱ

ሲናገሩ እንዲያደምጥ ብቻ እንጂ ሲናገር ሊሰሙት አይደለም፡፡ስለዚህ ጋዜጦችን አያነቡም፡፡የማያነቧቸውን ጋዜጦች አዘጋጆች ለስደት ሲዳረጉ ደግሞ ቅንጣት ታህል አትሰማቸውም፡፡
በጥቂት ወራት ውስጥ የተደረጉ ፕሬስን ከአገሪቱ ገጽ ለማጥፋት የተወሰዱና እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን ተመልከቱ፡፡ጋዜጠኞች ተሰባስበው ለመመስረት ቀና ደፋ ያሉለት አዲስ ማህበር እውቅና ተነፈገው፣የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንና ሶስት ጋዜጠኞች ለእስር ተዳረጉ፣ትግራይን ህዝብ ፍዳ በሶሻል ሚዲያ ሲያጋልጥ የቆየው አብርሃ ደስታ ጨለማ ቤት ተወረወረ፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አስጠናሁ ያለውን ወረቀት አቅርቦ ጋዜጦችን በኒዮ ሊበራሊስትነት ከሰሰ፣ከጫካ ጀምራ የህወሃት አፍ የነበረችው ፋና የጋዜጣ አከፋፋዮች ላይ ዘመቻ ከፈተች፣ዘመቻውን ተከትሎ በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ አከፋፋዮችና ጋዜጣ አዟሪዎች ስቅይት ደረሰባቸው፣ፍትህ ሚኒስትር የህትመት ውጤቶች አሳታሚዎች ላይ ከፍተኛ የወንጀል ክስ መመስረቱን ነገረን፣ክሱ መነገሩን ተከትሎ ማተሚያ ቤቶች ጋዜጦችን የማስተናገድ ፍርሃት ወረራቸው አንዳንዶቹም በግልጽ ይህን ጋዜጣ እንዳናትም ቀጭን ትዕዛዝ ደርሶናል አሉ፣ካፌዎች በግድግዳቸው ላይ ‹‹ጋዜጣ ባለማንበብዎ እናመስግናለን እና ጋዜጣ ማንበብ አይቻልም››የሚሉ ማስታወቂያዎችን መለጠፍን ስራቸው አደረጉት ፡፡

ስደት ብርቃችን አይደለምና ይህው የተወዳጇን አዲስ ጉዳይ መጽሔት ባለቤትና አዘጋጆች ስደት ሰማን ፡፡ይህ ለኢህአዴግ ምኑ ነው?ፕሬስ የሌለው መንግስት እንዲኖረን የሚፈልግ በመሆኑ ደስታውን የሚችለውም አይመስለኝም፡፡ኮካዎች ምን ትላላችሁ?

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live