Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

የዘ-ሐበሻ 5ኛ ዓመት፡ ዘ-ሐበሻን ይርዱ፤ የዘ-ሐበሻ ክንድ ይሁኑ

$
0
0

zehabesha 5th year
የተከበራችሁ የዘ-ሐበሻ ጋዜጣና ድረገጽ አንባቢዎች፦

እነሆ “ዕውነት ያሸንፋል የሚለውን መርህ እንደያዘ ዘ-ሐበሻ ጋዜጣና ድረ ገጽ ዴሴምበር 28 ቀን 2013 የተመሰረተበት 5ኛ ዓመት ይሞላል። ባለፈው የኖቬምበር ወርን “የአንባቢዎች አስተያየት መቀበያ ወር” በሚል ሰይመን ከእናንተ አንባቢዎቻችን ገንቢ አስተያየቶችን አንድ ወር ሙሉ ተቀብለናል። ድረገጻችንን በየእለቱ በመጎብኘት አስተያየትም በመስጠት ለምታስተካክሉን አንባቢዎቻችን ምስጋናችንን በዚህ አጋጣሚ እየገለጽን፤ ይህን የዲሴምበር 2013 ወርን ደግሞ እስካሁን ዘ-ሐበሻን በምን መልክ እንርዳ ስትሉ ለነበራችሁ እና ለመርዳት ለምትፈልጉ “ዘ-ሐበሻን የመርጃ ወር ስንል” ሰይመነዋል። እስከ ዲሴምበር 31 ቀን 2013 ድረስም ዘ-ሐበሻን ለመርዳት ለምትፈልጉ በፔይፓል የመክፈያ ዘዴ አዘጋጅተናል።

እንደሚታወቀው ዘ-ሐበሻ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ጉዳይ ለሕዝብ መረጃ ከሚያደርሱና ከሚመረጡ የተለያዩ የዜና ምንጮች መካከል አንዷ ሆና መቀመጧ እናንተን አንባቢዎቻችንን ብቻ ሳይሆን እኛ አዘጋጆቹንም አስደስቶናል። ቀን ከሌሊት ደከመን ሰለቸን ሳንል ላለፉት 5 ዓመታት በሃገራችን ጉዳይ በቂ ነው ባይባልም ብዙ መረጃዎችን አቀብለናል የምናቀብለውም ይህን ውጤት ለመቀበልና በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ አብቦ ለማየት ነው። ። ወደ ፊትም ይህ አገልግሎታችን በቪድዮና በድምጽ ተጠናክሮ እንዲቀጥል፣ በቂ የሰው ሃይል ጨምረን አሁን ከምንሰራው የተሻለ አገልግሎት እንድንሰጥ፣ በአሁኑ ወቅት በራሳችን ሰርቨር ስለምንጠቀምና አንድ ሰርቨር ብቻ በየሰዓቱ የሚጎበኙንን ወገኖቻችንን ማስተናገድ ስለማይችል ሌላ 2ኛ ሰርቨር ለመጨመር እኛ አሁን ያለን የገንዘብ አቅም በቂ አይደለም። በፖለቲካው፣ በማህበራዊ ጉዳይ፣ በጤናው፣ በስፖርት፣ በመዝናኛ ጉዳዮች የተሻለ ሥራ ለመስራት አቅሙ አለን ብለን እናስባለን። ይህን የምናሳካው ግን አሁን የዘ-ሐበሻን 5ኛ ዓመት በማስመልከት በምታበረክቱልን የገንዘብ ድጋፍና፣ የቁሳቁስ እርዳታ ነው።

በአጭሩ ይህ መልዕክት ዘ-ሐበሻን ያግዙ ይርዱ ለማለት ነው።

ዘ-ሐበሻ በሕጋዊነት ተመዝግባ በምትገኝበት ሚኒሶታ ውስጥ በጃንዋሪ ወር ላይ የ5ኛ ዓመት እና የገቢ ማሰባሰቢያ የራት ምሽት የምታዘጋጅ ሲሆን ለዚህም ታዋቂው አክቲቪስት እና አርቲስት ታማኝ በየነ ለመገኘት ቃል ስለገባልን በዚህ አጋጣሚ ልናመሰግን እንወዳለን። በሚኒሶታ የማትኖሩና በዓለም ዙሪያ የምትገኙ የዘ-ሐበሻ ደጋፊዎች ግን ዛሬ ነገ ሳትሉ የዘ-ሐበሻ ክንድ ትሆኑ ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃችኋለን።

ዘ-ሐበሻን ለመርዳት እዚህ ጋር ይክፈሉ

እናመሰግናለን።





በሰላማዊ ትግልና ባህሪያቱ -ክፍል አራት (በአቶ ግርማ ሞገስ)

$
0
0

 

Girma Moges

አቶ ግርማ ሞገስ

በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርት (አንድነት) በሰላማዊ ትግልና ባህሪያቱ ክፍል አራት በአቶ ግርማ ሞገስ በስካይፕ የሚሰጠው ስልጠና ተጠናቋል። ዝርዝሩ ዝቅ ብሎ ቀርቧል።]

አምባገነኖች ስልጣን ላይ ለመቆየት ህጋዊነት፣ የህዝብ ድጋፍ እና ትብብር፣ የአገር ተፈጥሮ እና የኢኮኖሚ ሃብት ባለቤትነት የተባሉትን የፖለቲካ ኃይል ምንጮች መቆጣጠር አለባቸው። የፖለቲካ ኃይል ምንጮች የሚኖሩት ሰማይ ውስጥ ወይንም አምባገነኖች ደም ውስጥ ሳይሆን ባለቤታቸው ከሆነው ህዝብ ጋር እንደሆነ በስልጣና ክፍል ሶስት አጥንተናል። እርግጥ አምባገነኖች በእነዚህ የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ላይ ያላቸውን ቁጥጥር የሚያገኙት ህዝብ ፈቅዶላቸው ወይንም ፈርቶዋቸው ወይንም የተወሰነው ህዝብ ፈቅዶላቸው የቀረው ህዝብ ደግሞ ፈርቷቸው ሊሆን ይችላል። ያም ሆነ ይኽ የእነዚህ የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ባለቤት እራሱ ህዝብ እንደሆነ ግልጽ ነው። ለዚህም ነው የፖለቲካ ኃይል ምንጭ ማለትም የመንግስት ስልጣን ምንጭ ወይንም ባለቤት ህዝብ ነው የሚባለው። ህዝብ የፖለቲካ ነፃነቱን የሚነጠቀውም ይኽን የፖለቲካ (የመንግስት) ስልጣን ባለቤትነቱን በኃይል በአምባገነኖች ሲነጠቅ ነው። ነፃ ሆኖ የተወለደ የሰው ዘር ለምን ነፃነቱን ለጥቂት አምባገነን ገዢዎች አስረክቦ ካለነፃነት መገዛትን ይቀበላል? የሚለውን ጥንታዊ የፖለቲካ ፈላስፎች እና ተመራማሪዎች ጥያቄ አንስተን በክፍል ሶስት ማጥናታችን ይታወሳል።

 ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Download (PDF, 213KB)

 

በማንዴላ ሞት መንግሥቱን ከግፍ ለማንፃት? በልጅግ ዓሊ

$
0
0

በልጅግ ዓሊ

madiba2የማንዴላን ሕልፈተ ሕይወት ተመልክቶ በዓለም ደረጃ የሚያስደንቅ ሁኔታ ስናይ ሰነበትን። ማንዴላ የሠራውን መስራት ሳይሆን እሱ የታሰረበትን ዓላማ በተጻራሪ የሚተገብሩ ሁሉ በቀብሩ ላይ ለመገኘት ከተደበቁበት ብቅ ብቅ ማለታቸው የሚስደምም ነው።

በተለይ አንዳንዶቹ በተለያየ የመገናኛ ዘዴዎች ስለ ማንዴላ ጥሩ ምግባር ቃለ መጠይቅ የሰጡትን  ስናጤናቸው ብዙ የሚያስተዛዝብ ሁኔታዎችን እንገነዘባለን።  በሺህ መጽሐፍ፣ በሽህ ሬዲዩ ቢታገዙም በደም የወየበ ታሪካቸውን  የማይሰርዝላቸው ፋሽሽቶች ይህችን ወቅት ተጠቅመው ለሕዝብ ሃሳቢ ሆነው ለመታየት መራወጣቸው የሚገረም ነው። ይህንን ወቅት ለመጠቀም “እኔም ነበርኩበት“ የሚለው ፋሽሽቱ መንግሥቱ ኃይለማርያምም ሳይቀር ከዚምባዌ ድምጹን አስምቷል።

ታሪክ  እንደ ማንዴላ ያለውን ጀግናን ሲያከብር ቡከን ፋሽስትንም ሲኮንን ይኖራል። ይህንን መቀየር የሚችል ማንም አይኖርም። ማንዴላ እንዲህ የተወደደውን ያህል እነ ሒትለር፣ እነ ሙሶሎኒ ፣ እነ እስታሊን ደግሞ ሲኮነኑና ሲወገዙ ኖረዋል። ለወደፊቱም እንዲሁ። ታሪክ በሠሩት ግፍ ብዛት ከትውልድ ትውልድ እየተሸጋገረ ሲያወግዛቸው ይኖራል።

የማንዴላ ሞት ዜና በጎላበት ጀምበር በጀርመንም የናዚ ፋሽሽቶች መሪ ሒትለር ሲነሳ መሰንበቱ አንድ ሌላ አስገራሚ ክስተት ሆኗል። ትግሌ (ማይን ካንፍ ፣Mein Kampf )  ሒትለር እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1923 በመንግሥት ግልበጣ ሙከራ ምክንያት ታስሮ በነበረበት ወቅት የጻፈው መጽሐፍ ነው። ይህ መጽሐፍ እንደ ናዚዎች ማኒፌሰቶ ሆኖ ይታያል። መጽሐፉ በአይሁዳውያን ላይ ጥላቻን የሚያስፋፋና ጀርመኖች ምስራቅ አውሮፓንን መውረር እንዳለባቸው የሚቀሰቅስ ነው። በጀርመን ሕግ በተደነገገው መሠረት ይህን መጽሐፍ መልሶ የማሳተም መብት እገዳ (copy right) በ2015 ዓ.ም ያልቃል። ስለሆነም ማንም የፈለገ አካል የማሳተም መብት ይኖረዋል።

ይህንን ድንጋጌ በሚመለከት ጀርመን ውስጥ የጦፈ ክርክር ሲከናወን ሰንብቷል። እንደተለመደው የናዚ ደጋፊዎች ሒትለር ሃገሩን ይወድ ነበር፣ ለሃገሩ ጥሩ ሰርቷል . . .  ወዘተ.  የሚል ለሒትለር በታሪክ ጥሩ ቦታ ለመስጠት እንቅልፍ አጥተው ሰንብተዋል። ደጋፊዎቹ መጽሐፉን እንደገና ለማሳተም ሲታገሉ በተቃራኒው የቆሙት ደግሞ በሒትለር የተፈጸመውን ግፍ እያነሱ እንደ ሒትለር ዓይነት በዓለም ውስጥ ዳግም እንዳይነሳ መጽሐፉ መልሶ መታተም እንዳይችል ሲታገሉ ተስተውሏል።

በጀርመን ሃገር ባይረን ተብሎ በሚጠራው ክፍለ ሃገር ግን በ2015 የሚልቀውን የማሳተም መብት በመጠቀም የሒትለር መጽሐፍ  እንደገና ለማሳተም የተደረገው ጥረት ከሽፏል። የባየር አስተዳዳሪዎች በሒትለር የተጨፈጨፉትን በማክበር መጽሐፉን እንደገና ማሳተም ኢ-ሰባዓዊነት ነው ሲሉ ወስነዋል።

http://www.bbc.co.uk/news/world-europe-25346140

የክፍለ ሃገሩ መንግሥት ብዙ በሒትለር የተጎዱ ቤተሰቦችን አነጋርግሮ ይህንን መጽሐፍ ማሳተም በቤተሰቦቹ ላይ ሕመምን መቀስቀስ እንደሚሆን አሳምኖ ማሳተምም ሆነ ማባዛትን እንደገና ከልክሏል። ይህ ውሳኔ ፋሽሽቶችን ለሚቃወሙ ጀርመኖች ትልቅ ድል ነው።

ይህ ዓይነት ትግል የሚደረገው በጀርመን ብቻ መሆን የለበትም። በእኛም ሃገር ይህ ዐይነቱ አመለካከት ሊዳብር ይገባል። ወያኔ ስልጣን ከወጣ በኋላ የተጀመረውን የጎጠኝነት ፖለቲካ ለመቃወም የተጀመረው ትግል የመንግሥቱ ኃይለማርያምን ወንጀል ለጊዜው ወደ ጎን አድርጎ ትግሉ በወያኔ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ቀጥሏል። ግን ይህ ሃገርን የማስቀደም ክቡር ዓላማ በመንግሥቱ ደጋፊዎች ሲጣስና የመንግሥቱን አረመኔነት ለማድበስብስ የሚደረገው ጥረት ብልጭ ድርግም ማለት ከጀመረ ሰነባብቷል።

የፋሽሽቱ ደጋፊዎች መሪያቸው ከወደቀ በኋላ ስለ መሪያቸው ትልቅነት ማውራት የተለመደ ባህሪያቸው መሆኑንም ታዝበናል። እዚሁ ጀርመን ውስጥ ሒትለር ሃገሩን ይወድ ነበር እንደሚሉት የፋሽሽት ደጋፎዎች ማለት ነው። የሒትለር ደጋፊዎች ለዚህም ድጋፋቸው የሚያቀርቡት ምክንያት ባንድ ወቅት ከየሃገሩ በሰበሰባቸው እስረኞች ያሰራው አውራ መንገድ (Autobahn) ሁል ጊዜ ይጠቀሳል። “ሒትለር ቢኖር ኖሮ ጀርመን የትና የት በደረስች ነበር“ በማለት  ዓመኔታ ለመሸመት ይጥራሉ።

እነዚህ የአስተሳሰብ-ደሃ ጀርመኖች በዴሞክራሲ ካገኙት የዓለም የኤኮኖሚ ትልቅነት ይልቅ የእነርሱ ዘር ትልቅነት ላይ የተመረኮዘው የሒትለር ዓላማ ታላቅነትን የሚያጎናጽፋቸው ይመስላቸዋል። ለዚህም የሒትለርን መሪ መፈክር አንግበው ሲጓዙ ይታያሉ። በአሁኑ ሰዓት ያለውን የዓለም ሥርዓትና ይህም ሥርዓት ለጀርመን ሕዝብ የሰጠውን ጥቅም የሚያውቀው የጀርመን ሕዝብ ሥርዓቱን በማናጋት ይህንን የተንደላቀቀ ኑሮውን ለማበላሸት የሚጥሩትን ወገኖች ዕድሉ እንዲሰጣቸው ብዙሃኑ የጀርመን ህዝብ ፍላጎት የለውም።

ፋሽሽቶችን ከፍ አድርጎ ለማሳየት የሚደረገው ጥረት በጀርመን ብቻ ሳይሆን በኢጣሊያም ይታያል። በቅርብ ጊዜ ግራዚያኒ ሐውልት ተሰርቶለታል። ሞሶሎኒንም እንደ ጀግና የሚቆጥሩ አልታጡም። በተለይ በፋሽሽቱ ሥርዓት ጥቅም ያገኙ የነበሩ ወገኖች የሌላው ሕብረተሰብ ቁስል አይሰማቸውም። ይልቁንም እንጨት ሊሰዱበት ይፈልጋሉ።

በእኛም ሃገር የሚስተዋለው ከዚህ የተለየ አይደለም። “መንግሥቱ ሃገር ወዳድ ነው “፣ “መንግሥቱ ቢኖር እንዲህ አይደረግም“፣ “መንግሥቱ ቆራጥ ነበር“. . . .  ሌላም ሌላም ብዙ ከሥርዓቱ ጥቅመኞች የምንሰማው ባዶ ጩኽት አለ። ቆራጥነቱንም በፍርጠጣው፤ ሃገር ወዳድነቱም የተማረ የሰው ኃይል እንዳይኖር በቀይ ሽብርና በሌሎቹ የግድያ ዘዴዎቹ አስመስክሯል። ወንጀሉ የመንገድ ላይ ስጦ ሆኖ የተመለከትነው ነው።  ለሃገራቸው አንድነትና ልዋላዊነት አጽማቸውን ሲከሰክሱ የነበሩ ጀግኖች በመንግሥቱ ነፍስ ገዳዮች ከሃዲ እየተባሉ ሲገደሉ፣ ፈሪ  ፈርጣጩ ቡከን ጀግና ተብሎ ሲወደስ መስማት ውርደትም ሃፍረትም ይሆናል። እነዚህ ጀግኖችን እየሰደቡ ይጽፉ የነበሩ አሁን ደግሞ በውጭ ሃገር የዚህ ፋሽሽት ቆዳ ለማዋደድ የሚደርጉት ጥረት የሚያሳፍር ነው። ለመሆኑ በዚህ ዓይነት ክህደት ይች ሃገር ከወያኔ ነጻ ትወጣለች ብለው ያስቡ ይሆን?

የመንግሥቱ ደጋፊዎች ሰሞኑን የኔልሰን ማንዴላን ሕልፈተ ሕይወት ምክንያት በማድረግ የሃገራችንን ፋሽሽት አረመኔው መንግሥቱን   ቃለ መጠይቅ በማድረግ ፋሽሽታዊ የሆነውን ገጽታውን እንደገና ለማደስ ጥረት አድርገዋል። ደጋፊዎቹ  ይህንን ቡከን ፋሽሽት ከሃገሩ አልፎ ለዓለም አቀፍ ጭቆና እንደታገለ ሊነግሩን ይፈልጋሉ። እነዚህ የመገናኛ ዘዴዎች መንግሥቱን ቃለ መጠይቅ በማድረግ በመንግሥቱ በግፍ የተገደሉትን ወገኖች መልሰው ለመግደል ይጥራሉ። በሕይዎት በተረፉትና የወላድ መኻን በሆኑት ወላጆች ቁስል ላይ ጨው እየነሰነሱ መሆናቸን እንዲገነዘቡ አስታዋሽ የሚሹ ይመስላሉ። እንደ ባየር ክፍለ ሀገር ጀርመኖች የሌሎች ሃዘን ሳይሰማቸው የዚህን አረመኔ ፋሽሽታዊ ገጽታ ለማሳመር ጥረት አድርገዋል። ይህ ደግሞ የሚያሳፍር እንጂ የሚያኮራ ድርጊት አይሆንም። ከማሳፈርም አልፎ  በመንግስቱ ኃይለማርያም የተገደሉትን ሰማዕታት መልሶ  እንደመግደል መግደል ይቆጠራል። በሃገር ላይ የተሰራ ወንጀልም ነው።

በቃለ መጠይቃቸው ላይ ማንዴላን የጦር ሥልት በማስተማር ትልቅ ጥረት ያደረጉትን እነ ጀኔራል ታደሰ ብሩን ለምን መንግሥቱ ራሱ እንደገደላቸው እንኳን ማንሳት አልፈለጉም። ሳያውቁት ቀርተው አይደለም ነገሩን ሳያነሱት የቀሩት። እንደተለመደው መጠየቅ የሚገባቸውን ሃቆች በመሸፈን የፋሽሽቱን ቆዳ የሌለውን መልክ እንዲኖረው ለማድረግ እንጂ።

http://www.bbc.co.uk/news/world-africa-23515879

እነዚህ የሬዲዮ ጣቢያ ሃላፊዎች የመንግሥቱ ጉዳይ መነሳት ለጸረ ወያኔው ትግል ከፋፋይ መሆኑ አይታያቸውም። ከፋፋይ መሆኑም ቢያውቁም ከመንግሥቱ ይበልጥ ሃገር በወያኔ ብትፈርስ ድንታ እንደሌላቸው ነው ድርጊታቸው የሚያሳየን። የብዙሃኑ ጸረ ወያኔ ትግል  መንግሥቱን ሥልጣን ላይ ወይም ደጋፊዎቹን ስልጣን ላይ ለመመለስ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ትግላችን ዘረኝነትን አጥፍተን ዴሞክራሲን መገንባት መሆኑ  ያልገባቸው ካሉ ትልቅ ስህተት ላይ ወድቀዋል። በኢሠፓ አባልነታቸው እንደገና ወደ ስልጣን ተመልሰን እንወጣለን ብለው አስበው ከሆነ ተስፋ ሊቆርጡ ይገባል። ምንም ይሁን ምን ወደ ኋላ አንመለስም።

መንግሥቱ በሃገር መክዳት ለፍርድ መቅረብ እንጂ እንደ ጀግና በየቦታው ቃለ መጠይቅ እየተደረገለት የእሱ ቆዳ ተገልብጦ እንዲለበስ ጥረት መደረግ የለበትም። ከሃገር ሰርቆና ዘርፎ በፈረጠጠው ገንዘብ የሚገዛው የዕውቅና የሃገር ወዳድነት ጃኖም ሊኖር አይገባም። የወንጀለኛ ቆዳ እንጂ። ንፁህ ነን የሚሉ ካሉ በዚህ ጉዳይ ላይ ራሳቸውን ከፋሽሽቱ በመነጠል ግልጽ የሆነ አቋማቸውን ሊያሰሙ ይገባል።

በተለይ በሕዝብ ገንዘብ የተቋቋመ እንደ ኢሳት ዓይነት የዜና ማሰራጫ በመንግሥቱ ግፍ የተሰራባቸው ሁሉ እርዳታቸውን የለገሱት መሆኑን አስተዳዳሪዎቹ ልብ ሊሉት ይገባል። እርዳታቸውን ለጠላታቸው ማስተዋወቂያ ሲያደርጉት ሊያጡት የሚችሉትን ድጋፍ መመዘን ብልዕነት ነው። ለምን ቢባል ጥያቄው የሞራል ጥያቄ ነውና!!  አሊያ ግን የኢሳትን ዓላማ ጥርጣሬ ውስጥ ይከተዋል።

http://ethsat.com/ESAT-Radio-player/archive/ESAT_Radio_Wed_11_Dec_2013.mp3

ለኢሳት ገንዘብ በማሰባሰብ ጥረት ያደረጉ “የሰበዓዊ መብት ታጋይ ነን” የሚሉ ደግሞ ይህ ድርጊታቸው ለሁሉም የሰው ዘር ሰብዓዊ መብት መከበር እንዳልቆሙ ያጋልጣቸዋል። ያገኙት ተሰሚነትም ፀሐይ እንደነካው በረዶ ሊቀልጥ ይችላል።

ይህንን አረመኔ ለፍርድ ይቅረብ ብለው ሲናገሩ ያልተሰሙ፣ በመንግሥቱ ስለተጨፈጨፉት ሲናገሩ ያልተደመጡ፣ ለፍትህ ያልቆሙ፤ ዛሬ ለዚህ አረመኔ መድረክ መስጠታቸው የሃገሪቱ ዜጎች ሁሉ በእኩል አይን እንደማያዩ ድርጊታቸው አጉልቶ ያሳየናል። ሌላው ቢቀር ማንዴላን በሚመለከት ባለውለታዎች ሲነሱ ጀኔራል ታደሰ ብሩም ሆነ ማንዴላን በብዙ የደገፉ የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መንግስት ባለስልጣናት የአሟሟት ሁኔታም መጠቀስ ነበረበት። ታሪክ ግማሽ የለውምና ሙሉው የኢትዮጵያውያን አስተዋጽኦ በዘገባው መካተት ነበረበት።

http://www.bbc.co.uk/news/world-africa-23515879

ወያኔን አስወግደን ሃገራችንን ዴሞክራሲያዊት እናደርጋታለን ብለን የምናስብ ሁሉ ከደርግና ከመንግስቱ ኃይለማርያም ፋሽሽታዊ ወንጀል ራሳችንን ነጥለን መንግሥቱም ይሁን ወያኔን የህዝብ ጠላትነታቸውን አውቀን ካልሄድን ሃገራችንን ከወያኔ ጭቆና ነጻ የምናወጣበትን ቀን እናራዝመዋለን። ትግሉ ጥርት ብሎ ለዴሞክራሲ ካልሆነ በስተቀር ከሃገር በተሰረቀ ገንዘብ መልሰን ስልጣን እንወጣለን በሚል እቅድ መጓዝ በሃገሪቱ ውስጥ ሊነሳ የሚችለውን ችግር አለማጤን ይሆናል። ማንም ከድጡ ወደ ማጡ መሄድ የሚፈልግ አይኖርም።

መንግሥቱን ለቃለ መጠይቅ የጠሩ የሬዲዮ ጣቢያዎች ይህንን በማድረጋቸው ምን ያህል ከወያኔ ጋር የሚደረገውን ትግል እንደከፋፈሉ ካልተረዱ የሚያሳዝን ነው። በዚሁ አጋጣሚም የሕዝብ ድጋፍ እንደሚያጡ ሊረዱት ይገባል። ነጻ ፕረስ ሃላፊነት የጎደለው ፋሽሽቶችን ማመጻደቂያ ሊሆን አይገባምና ከዚህ መጥፎ ምግባር መቆጠብ አስተዋይነት ይመስለኛል።

ሂትለር፤ ጀኔራል ፍራንኮ፤ ሞሶሎኒ፤ መለስ ዜናዊ፤ መንግስቱ ኃይለማርያም፤ (በቁም የሞተ) ሁሉም ፋሽሽቶች ሞተዋል። ስማቸው ግን ከታሪክ ጠባሳ ገጾች አይፋቅም። ባንጻሩ ጋንዲ፤ ማንዴላ፤ ማርቲን ሉተር ኪንግና ሌሎቹም ጀግኖች ሞተዋል። ግን ሰማዕታት ናቸው። ታሪካቸውም በጀግንነት የወርቅ ቀለም ተጽፎ ትውልድ ሲወራረሰው ይኖራል። የሁለቱም ወገኖች ስም ከመቅበር በላይ ውሏል። ሆኖም የፋሽሽቶቹ የነ ሂትለር በፀረ-ህዝብነት፤ የነማንዴላ ግን በህዝባዊነት!!

በፋሽሽቶች ለተጨፈጨፉ ሁሉ የሚያስብ በሰላም ይክረም !

ታህሳስ 2006

Beljig.ali@gmail.com

 

 

Sport: ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለባለን ደ ኦር አሸናፊነት የበለጠ ዕድል እንዳለው ተገመተ

$
0
0

ከይርጋ አበበ

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከሦስት ዓመት በፊት የዓለምን ስፖርት አፍቃሪዎች ያነጋገረ የዝውውር ገንዘብ ተመድቦለት ወደ ሪያል ማድሪድ ከተዘዋወረ አንስቶ ስሙ እየገነነ መጥቷል። ክለቡ ማድሪድም ተጫዋቹን የገዛው የልጁን መልከ ቀናነት ተጠቅሞ የማሊያና የምስል ሽያጭ ለመጠቀም አስቦ ነው እስከመባል ደርሶ ነበር። በተጨማሪም ራሱ ሮናልዶ በማንቸስተር ዩናይትድ እንደነበረ ቆይታው ስኬታማ ሊሆን አይችልም የሚል አስተያየትም ተሰንዝሮበት ነበር።

ነገር ግን የ28ዓመቱ ፖርቹጋላዊ ሮናልዶ በስፔኑ ግዙፍ ክለብ ታሪክ መሥራቱን ተያይዞታል። በሪያል ማድሪድ ቆይታው 28ጊዜ ሦስታ (ሃትሪክ) ሲሰራ፣ በድምሩ 218 ጨዋታዎችን ተጫውቶ 227 ኳሶችን ደግሞ ከግብ ማሳረፍ የቻለ ምርጥ ተጫዋችነቱን አስመስከሯል።
የዓለምአቀፉ እግር ኳስ ማህበር ከፈረንሳዩ ፍራንስ ፉትቦል መጽሔት ጋር በመተባበር በየዓመቱ በሚያዘጋጀው የዓለም ኮከብ ተጫዋቾች ክብር ባለን ደ ኦር ሽልማት ሮናልዶ ለዘንድሮው ሽልማት ከታጩት የመጨረሻዎቹ ሦስት እጩዎች መካከል አንዱ ሆኗል። የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ፊታውራሪ የሆነው ሮናልዶ በብዙ የስፖርት ቤተሰቦች ዘንድ የኮከብነት ክብሩ ይገባዋል እየተባለ ይገኛል። ለእዚህ ንግግራቸው ማጠናከሪያ አድርገው ያቀረቡት ደግሞ ተጫዋቹ ከ2013 መባቻ ጀምሮ ባለፉት 11 ወራት ተጫውቶ ያገኛቸውን ድሎች ነው።
የአውሮፓውያን አዲሱ ዓመት ከ20ቀናት በኋላ የሚጀምር ሲሆን አዲሱ ዓመት ከመግባቱ በፊት የክርስቲያኖ ዶ ሳንቶስ አቬሮ ሮናልዶ ገድል ሊጠቀስ ይገባዋል ብለው የሚከራከሩ የልጁ አድናቂዎች እየተናገሩ ናቸው። «ተጫዋቹ በአንድ የውድድር ዓመት በአምስት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ዘጠኝ ግቦችን መረብ ላይ ማሳረፍ የቻለ ተጫዋች ነው። በአንድ የጨዋታ ዘመን (2013ሙሉ ዓመቱን ለማለት ነው) ከሃምሳ በላይ ግቦችን በማስቆጠር ብቸኛው ተጫዋች ነው። በስፔን ላሊጋ ከምንጊዜም ሦስታ (ሃትሪክ) አስቆጣሪዎች መስመር ሁለተኛው ተጫዋች ነው» የሚሉትን ነጥቦች አንስተው ይከራከራሉ።
Ronaldo Christiano
በሪያል ማድሪድ እግር ኳስ ክለብ ታሪክ ከምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ የክለቡ ባለውለታዎች ጎራ የተቀላቀለው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ባለፈው ማክሰኞ ምሽት ክለቡ ሪያል ማድሪድ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታ ወደ ቤልጄም ተጉዞ የቤልጀሙን ኮፐን ሀገንን ሁለት ለባዶ ሲረታ ያስቆጠራት ግብ ሌላ ታሪክ እንዲሠራ ምክንያት ሆናለታለች። ይህች ግብ ተጫዋቹን በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ጨዋታዎች ዘጠኝ ግቦችን በማስቆጠር ብቸኛው ተጫዋች እንዲሆን አስችላዋለች።
ከዚህ ቀደም ከሮናልዶ ጋር ተስተካካይ ክብረወሰን የነበራቸው ዝላታን ኢብራሞቪች፣ ፍሊፖ ኢንዛጊ፣ ሩድ ቫን ኒስትሮይ እና ሄርናን ክሪስፖ ሲሆኑ፣ ሮናልዶ ከእነዚህ ተጫዋቾች በአንድ ግብ በመላቅ ብቸኛው ተጫዋች ሊሆን ችሏል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ13 የስፔን ፕሪሜራ ሊጋ ጨዋታዎች 17 ግቦችን በማስቆጠር የፒቺቺውን ውድድር እየመራ ይገኛል።

A full list of the Ballon d’Or winners and runners-up since 1956.

1956

1st Stanley Matthews (English, Blackpool)
2nd Alfredo Di Stefano (Argentinean, Real Madrid)
3rd Raymond Kopa (French, Real Madrid)

1957
1st Alfredo Di Stefano (Argentinean, Real Madrid)
2nd Billy Wright (English, Wolverhampton Wanderers)
3rd= Duncan Edwards (English, Manchester United)
3rd= Raymond Kopa (French, Real Madrid)

1958
1st Raymond Kopa (French, Real Madrid)
2nd Helmut Rahn (West German, Rot-Weiss Essen)
3rd Just Fontaine (French, Stade Reims)

1959
1st Alfredo Di Stefano (Argentinean, Real Madrid)
2nd Raymond Kopa (French, Real Madrid)
3rd John Charles (Welsh, Juventus)

1960
1st Luis Suarez (Spanish, Barcelona)
2nd Ferenc Puskas (Hungarian, Real Madrid)
3rd Uwe Seeler (West German, Hamburg)

1961
1st Omar Sivori (Argentinean, Juventus)
2nd Luis Suarez (Spanish, Inter Milan)
3rd Johnny Haynes (English, Fulham)

1962
1st Josef Masopust (Czechoslovakian, Dukla Prague)
2nd Eusebio (Portuguese, Benfica)
3rd Karl-Heinz Schnellinger (West German, Koln)

1963
1st Lev Yashin (Soviet Union, Dynamo Moscow)
2nd Gianni Rivera (Italian, AC Milan)
3rd Jimmy Greaves (English, Tottenham Hotspur)

1964
1st Denis Law (Scottish, Manchester United)
2nd Luis Suarez (Spanish, Inter Milan)
3rd Amancio (Spanish, Real Madrid)

1965
1st Eusebio (Portuguese, Benfica)
2nd Giacinto Facchetti (Italian, Inter Milan)
3rd Luis Suarez (Spanish, Real Madrid)

1966
1st Bobby Charlton (English, Manchester United)
2nd Eusebio (Portuguese, Benfica)
3rd Franz Beckenbauer (West German, Bayern Munich)

1967
1st Florian Albert (Hungarian, Ferencváros)
2nd Bobby Charlton (English, Manchester United)
3rd Jimmy Johnstone (Scottish, Celtic)

1968
1st George Best (Irish, Manchester United)
2nd Bobby Charlton (English, Manchester United)
3rd Dragan Džajić (Yugoslavian, Red Star Belgrade)

1969
1st Gianni Rivera (Italian, AC Milan)
2nd Luigi Riva (Italian, Cagliari)
3rd Gerd Muller (West German, Bayern Munich)

1970
1st Gerd Muller (West German, Bayern Munich)
2nd Bobby Moore (English, West Ham United)
3rd Luigi Riva (Italian, Cagliari)

1971
1st Johan Cruyff (Dutch, Ajax)
2nd Sandro Mazzola (Italian, Inter Milan)
3rd George Best (Irish, Manchester United)

1972
1st Franz Beckenbauer (West German, Bayern Munich)
2nd Gerd Muller (West German, Bayern Munich)
3rd Gunter Netzer (West German, Borussia Monchengladbach)

1973
1st Johan Cruyff (Dutch, Barcelona)
2nd Dino Zoff (Italian, Juventus)
3rd Gerd Muller (West German, Bayern Munic)

1974
1st Johan Cruyff (Dutch, Barcelona)
2nd Franz Beckenbauer (West German, Bayern Munich)
3rd Kazimierz Deyna (Polish, Legia Warsaw)

1975
1st Oleg Blokhin (Soviet Union, Dynamo Kiev)
2nd Franz Beckenbauer (West German, Bayern Munich)
3rd Johan Cruyff (Dutch, Barcelona)

1976
1st Franz Beckenbauer (West German, Bayern Munich)
2nd Rob Rensenbrink (Dutch, Anderlecht)
3rd Ivo Viktor (Czechoslovakian, Dukla Prague)

1977
1st Allan Simonsen (Danish, Borussia Monchengladbach)
2nd Kevin Keegan (English, Hamburg)
3rd Michel Platini (French, Nancy)

1978
1st Kevin Keegan (English, Hamburg)
2nd Hans Krankl (Austrian, Barcelona)
3rd Rob Rensenbrink (Dutch, Anderlecht)

1979
1st Kevin Keegan (English, Hamburg)
2nd Karl-Heinz Rummenigge (West German, Bayern Munich)
3rd Ruud Krol (Dutch, Ajax)

1980
1st Karl-Heinz Rummenigge (West German, Bayern Munich)
2nd Bernd Schuster (West German, Real Madrid)
3rd Michel Platini (French, Saint-Etienne)

1981
1st Karl-Heinz Rummenigge (West German, Bayern Munich)
2nd Paul Breitner (West German, Bayern Munich)
3rd Bernd Schuster (West German, Barcelona)

1982
1st Paolo Rossi (Italian, Juventus)
2nd Alain Giresse (French, Bordeaux)
3rd Zbigniew Boniek (Polish, Juventus)

1983
1st Michel Platini (French, Juventus)
2nd Kenny Dalglish (Scottish, Liverpool)
3rd Allan Simonsen (Danish, Vejle)

1984
1st Michel Platini (French, Juventus)
2nd Jean Tigana (French, Bordeaux)
3rd Preben Elkjær (Danish, Verona)

1985
1st Michel Platini (French, Juventus)
2nd Preben Elkjær (Danish, Verona)
3rd Bernd Schuster (West German, Barcelona)

1986
1st Igor Belanov (Soviet Union, Dynamo Kyiv)
2nd Gary Lineker (English, Barcelona)
3rd Emilio Butragueño (Spanish, Real Madrid)

1987
1st Ruud Gullit (Dutch, AC Milan)
2nd Paulo Futre (Portuguese, Atletico Madrid)
3rd Emilio Butragueño (Spanish, Real Madrid)

1988
1st Marco van Basten (Dutch, AC Milan)
2nd Ruud Gullit (Dutch, AC Milan)
3rd Frank Rijkaard (Dutch, AC Milan)

1989
1st Marco van Basten (Dutch, AC Milan)
2nd Franco Baresi (Italian, Milan)
3rd Frank Rijkaard (Dutch, Milan)

1990
1st Lothar Matthaus (German, Inter Milan)
2nd Salvatore Schillaci (Italian, Juventus)
3rd Andreas Brehme (German, Inter Milan)

1991
1st Jean-Pierre Papin (French, Marseille)
2nd= Dejan Savicevic (Yugoslavian, Red Star Belgrade)
2nd= Darko Pancev (Yugoslavian, Red Star Belgrade)
2nd= Lothar Matthaus (German, Bayern Munich)

1992
1st Marco van Basten (Dutch, AC Milan)
2nd Hristo Stoichkov (Bulgarian, Barcelona)
3rd Dennis Bergkamp (Dutch, Ajax)

1993
1st Roberto Baggio (Italian, Juventus)
2nd Dennis Bergkamp (Dutch, Inter Milan)
3rd Eric Cantona (French, Manchester United)

1994
1st Hristo Stoichkov (Bulgarian, Barcelona)
2nd Roberto Baggio (Italian, Juventus)
3rd Paolo Maldini (Italian, AC Milan)

1995
1st George Weah (Liberian, AC Milan)
2nd Jurgen Klinsmann (German, Bayern Munich)
3rd Jari Litmanen (Finnish, Ajax)

1996
1st Matthias Sammer (German, Borussia Dortmund)
2nd Ronaldo (Brazilian, Barcelona)
3rd Alan Shearer (English, Newcastle United)

1997
1st Ronaldo (Brazilian, Inter Milan)
2nd Predrag Mijatović (Yugoslavian, Real Madrid)
3rd Zinedine Zidane (French, Juventus)

1998
1st Zinedine Zidane (French, Juventus)
2nd Davor Suker (Croatian, Real Madrid)
3rd Ronaldo (Brazilian, Inter Milan)

1999
1st Rivaldo (Brazilian, Barcelona)
2nd David Beckham (English, Manchester United)
3rd Andriy Shevchenko (Ukrainian, AC Milan)

2000
1st Luis Figo (Portuguese, Real Madrid)
2nd Zinedine Zidane (French, Real Madrid)
3rd Andriy Shevchenko (Ukrainian, AC Milan)

2001
1st Michael Owen (English, Liverpool)
2nd Raul (Spanish, Real Madrid)
3rd Oliver Kahn (German, Bayern Munich)

2002
1st Ronaldo (Brazilian, Real Madrid)
2nd Roberto Carlos (Brazilian, Real Madrid)
3rd Oliver Kahn (German, Bayern Munich)

2003
1st Pavel Nedved (Czech, Juventus)
2nd Thierry Henry (French, Arsenal)
3rd Paolo Maldini (Italian, AC Milan)

2004
1st Andriy Shevchenko (Ukrainian, AC Milan)
2nd Deco (Portuguese, Barcelona)
3rd Ronaldinho (Brazilian, Barcelona)

2005
1st Ronaldinho (Brazilian, Barcelona)
2nd Frank Lampard (English, Chelsea)
3rd Steven Gerrard (English, Liverpool)

2006
1st Fabio Cannavaro (Italian, Real Madrid)
2nd Gianluigi Buffon (Italian, Juventus)
3rd Thierry Henry (French, Arsenal)

2007
1st Kaka (Brazilian, AC Milan)
2nd Cristiano Ronaldo (Portuguese, Manchester United)
3rd Lionel Messi (Argentinean, Barcelona)

2008
1st Cristiano Ronaldo (Portuguese, Manchester United)
2nd Lionel Messi (Argentinean, Barcelona)
3rd Fernando Torres (Spanish, Liverpool)

2009
1st Lionel Messi (Argentinean, Barcelona)
2nd Cristiano Ronaldo (Portuguese, Real Madrid)
3rd Xavi Hernandez (Spanish, Barcelona)

FIFA Ballon d’Or

2010
1st Lionel Messi (Argentinean, Barcelona)
2nd Andres Iniesta (Spanish, Barcelona)
3rd Xavi Hernandez (Spanish, Barcelona)

2011
1st Lionel Messi (Argentinean, Barcelona)
2nd Cristiano Ronaldo (Portuguese, Real Madrid)
3rd Xavi Hernandez (Spanish, Barcelona)

2012
1st Lionel Messi (Argentinean, Barcelona)
2nd Cristiano Ronaldo (Portuguese, Real Madrid)
3rd Andres Iniesta (Spanish, Barcelona)

አርሰናል በማን. ሲቲ ግማሽ ደርዘን ጎል ገባበት (All Goals & Highlights)

$
0
0

የአርሰናል እና የማን.ሲቲ ጨዋታ ጎሎች እና የጨዋታውን ሃይላይት እነሆ፦

Manchester City vs Arsenal (6-3) All Goals & Highlights 914.12.2013] by Mojogoals
99cab68bfe5d90795d3b37d36741c4d8_M
በ16ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜርሊግ የሊጉ መሪ አርሰናል ወደ ኢትሃድ አቅንቶ ማንቸስተር ሲቲን ቢያስተናግድም የ6ለ3 ሽንፈት ገጥሞታል፡፡ ሲቲ የሊጉን መሪ አርሰናልን ማሸነፍ በመቻሉ በሊጉ በ3 ነጥብ ልዩነት በ3ኛ ደረጃ መቀመጥ ችሏል፡፡
የአርሰናል አስደናቂ አጀማምር በተከታታይ ባደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች ደብዝዞ ታይቷል፡፡ ፈርናንዲኒሆ ሁለት፣ አጉየሮ፣ ኔግሬዶ፣ ሲልቫና ያያ ቱሬ አንዳንድ ጎሎችን በስማቸው ከመረብ አገናኝተዋል፡፡

አርሰናል ኳስን ይዞ በመጫወት በኩል ብላጫ ስለተወሰደበት ለሲቲ አጥቂዎች ምቹ ሆኖ አምሽቷል፡፡ ዋልኮት ሁለት ጎሎችን ከመረብ በማገናኘት ሁለት ጊዜ አርሰናልን አቻ ቢያደርግም ሲቲ በመልሶ ማጥቃት የአርሰናልን መረብ በተደጋጋሚ መፈተሽ ችሏል፡፡መርቲ ሳከር ለአርሰናል ቀሪዋን ጎል ከመረብ አሳርፏል፡፡ አርሰናል በሳምንቱ በሻምፒዮንስ ሊግ በጣሊያኑ ናፖሊ 2ለ0 ተሸንፎ መመለሱ ይታወሳል፡፡ ማንችስትር ሲቲ በተመሳሳይ ባለፈው ሳምንት በግማሽ ደርዘን ጎል ቶተናምን አሸንፏል፡፡ ቸልሲ ክሪስታል ፓላስን 2ለ1 በማሸነፍ 2ኛ ደረጃ ይዟል፡፡

“ወደ ፖለቲካው ተመልሻለሁ”–አቶ ልደቱ አያሌው

$
0
0

በምርጫ 97 በፊት ኢትዮጵያዊው ማንዴላ ተብለው እንዳልተሞካሹ ሁሉ ከምርጫ 97 በኋላ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አይንህ ለአፈር ከተባሉት ፖለቲከኞች መካከል አንዱ እንደሆኑ የሚነገርላቸው የቀድሞው የኢዴፓ ሊቀመንበር አቶ ልደቱ አያሌው ወደ ፖለቲካው መመለሳቸውን አስታወቁ። “ለትምህርት ከ2 ዓመታት በላይ በውጭ ሃገር በመቆየቴ እንዲሁም ከኢዴፓ ሃያ አምስቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አንዱ ብሆንም፣ በጠቅላላ ጉባኤ ከሊቀመንበርነት ስለወረድኩ የፓርቲው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ስለማልመራ” ከሚድያው ጠፍቻለሁ ያሉት አቶ ልደቱ ወደ ፖለቲካው መመለሳቸውን ያስታወቁት በአዲስ አበባ ከሚታተመው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።
lidetu
“በኢትዮጵያ ውስጥ የኢኮኖሚ እድገቱን መካድ ስህተት ነው፤ እድገቱ ዘላቂነት እንደሌለው አለመገንዘብም ስህተት ነው” የሚሉት አቶ ልደቱ “ሦስተኛ አማራጭ” የተሰኘ የኢዴፓ አቋምን በቃለ ምልላቸው ላይ ገልጸዋል።

በቃለምልልሳቸው ላይ ኢሕአዴግ አመጣሁት ስለሚለው ዕድገት አቶ ልደቱ “”የእድገቱ መጠን መንግስት እንደሚለው ሳይሆን፣ ስምንትና ሰባት ፐርሰንት ይሆኖል ብዬ አምናለሁ፡፡ ይሄም ቢሆን መጥፎ እድገት አይደለም፤ ጥሩ እድገት ነው፡፡ በእርግጥ በኢትዮጵያ ደረጃ ላለ ድሃ አገር ከስድስት ፐርሰንት በታች የወረደ እድገት፤ ኢኮኖሚው እንደተኛ (ሪሴሽን ውስጥ እንደገባ ነው የሚቆጠረው፡፡ በጣም በከፍተኛ ደረጃ ማደግ ነው የሚጠበቅብን፡፡ የሌሎችም አገራትም ታሪክ ያንን ነው የሚያሳየው፡፡ እንደ አሜሪካና እንደ እንግሊዝ አገር አይነት ትልቅ ኢኮኖሚ ውስጥ ሶስትም አራትም ፐርሰንት ማደግ ከባድ ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ዓይነት ኢኮኖሚ ተይዞ ግን፤ ደብል ዲጂት ማደግ ይቻላል፡፡ መጣ የሚባለው እድገት በህብረተሰቡ ህይወት ውስጥ መታየት አልነበረበትም ወይ? ሊታይም ላይታይም ይችላል፡፡ አንድ ኢኮኖሚ ማደግ ሲጀምር ሁሉንም ህብረተሰብ ይጠቅማል ማለት አይቻልም፡፡ ይሄ በየትም አገር ሆኖ አያውቅም፡፡ እንኳን ዘጠና ሚሊዬን ህዝብ ያለበት አገር ይቅርና፣ 3ሚሊዮን ህዝብ ባለበት አገርም ኢኮኖሚው ማደግ ሲጀምር ሁሉም ህብረተሰብ ተጠቃሚ ይሆናል ማለት አይደለም፡፡ ቀስ በቀስ ነው ተጠቃሚው እየበረከተና እያደገ የሚመጣው፡፡ ስለዚህ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ድህነት ይታያል። ድህነት ብቻ አይደለም በርሃብም የሚሰቃዩ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች መኖራቸው ግን እድገት የለም ወደሚለው ድምዳሜ አይወስደንም፡፡ እድገትም ባለበት አገር ሰው ይራባል፤ ሰው በድህነት ይማቅቃል፡፡ እንኳን በእኛ በጀማሪ አገር ቀርቶ፣ የዳበረ እድገት አላቸው የሚባሉ አገሮችም የሚቸገሩ ሰዎች አሉ፡፡” ብለዋል።

“መንግስት የሚፈጥረው ጫና ለተቃዋሚዎች መዳከም አንድ ምክንያት ነው እንጂ ብቸኛ ምክንያት አይደለም፡፡” ሲሉ በቃለ ምልልሳቸው ላይ የተናገሩት አቶ ልደቱ “አንድ ተቃዋሚ ፓርቲ እኮ ጠንካራ ነው የሚባለው፤ መንግስት የሚያደርግበትን ተጽዕኖ ተቋቁሞ ማሸነፍ ሲችል ነው፡፡ መንግስት ተጽእኖ የማያደርግ ከሆነማ ሁሉን ነገር የተመቻቸ ከሆነማ ትግልም አያስፈልግም። አገራችን እንደ አሜሪካ ሆናለች ማለት ነው። መንግስት ተፅዕኖ የማያደርግ ከሆነ፣ በጣም የምንመኘው ደረጃ ላይ በቀላሉ ደርሰናል ማለት ነው፡፡ ተዝናንተን በምዕራቡ ዓለም እንደምናየው በምርጫ እየተወዳደርን አሸናፊና ተሸናፊ ልንሆን እንችላለን ማለት ነው፡፡ ግን እዚያ ደረጃ ላይ ለመድረስ ቀርቶ ጨርሶ አልተጠጋንም፡፡ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ ጫና የሚያደርግ መንግስት ነው ያለን፡፡ ይህን ለመለወጥም ነው የፖለቲካ ትግል እያካሄድን ያለነው፡፡ ህዝቡን አስተባብረንና አታግለን፤ የመንግስት ጫና እንዲቆምና ለውጥ እንዲመጣ ማድረግ እንችላለን፡፡ ይልቅስ ትልቅ እንቅፋት የሆነብን ውስጣዊ ችግር እንዳለብን መገንዘብ አለማቻላችን ነው፡፡ ውስጣዊ ድክመቶችን ለመፈተሸ አለማድረጋችን ነው ካንሠር ሆኖ የሚበላን፡፡ በ1997 ዓ.ም ምርጫ ተቃዋሚዎች ጥምረት እየፈጠሩ የህዝቡን ትኩረት በመሳብ በምርጫ ውጤት አምጥተዋል፡፡ የፓርቲዎችን ብርቱ ፉክክር የሚያካሂዱበት ነፃነት ተፈጥሮ ነበር፡፡ ለ2007 ዓ.ም ምርጫ ግን ጥምረት የመፍጠር ህዝቡን የማንቀሳቀስና ብርቱ ፉክክር የማካሄድ ሁኔታ ጎልቶ አይታይም፡፡” ብለዋል።

በቀጣይ 2007 በሚደረገው የኢትዮጵያ ምርጫ ላይ “መሰረታዊ ለውጥ ይመጣል ብዬ አላስብም፡፡” የሚሉት አቶ ልደቱ ለዚህም ምክንያታቸው “አንደኛ ነገር ገዢው ፓርቲ ከስህተቱ እየተማረ አይደለም፡፡ አሁንም በየቀኑ የሚነግረን፤ ዲሞክራሲ ኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲ ሞልቶ እንደተትረፈረፈና ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ለማድረግ ምንም ችግር እንደሌላቸው ነው፡፡ ይህቺ አገር በልማት ብቻ ሳይሆን በዲሞክራሲም እያደረገች እንደሆነ ነው ኢህአዴግ የሚነግረን። ይሄ ቀልድ ነው፡፡ በተጨባጭ ያለው ሁኔታ ኢህአዴግ እንደሚለው አይደለም፡፡ የዲሞክራሲ ስርዓት በአግባቡ በዚች አገር እንዲያብብ እያደረገ አይደለም። ገዢው ፓርቲ ላይ ቁርጠኝነት እየታየ አይደለም፡፡ በተቃዋሚ ፓርቲዎች በኩልም አብዛኛው ውስጣዊ ድክመታቸውን ሳይፈትሹ ነባሩን አስተሳሰብና አቀራረብ እንደያዙ ናቸው፡፡ ስለዚህ በ2007 ዓ.ም ምርጫ፣ መሠረታዊ ለውጥ ያመጣል የሚል እምነት የለኝም፡፡ መሠረታዊ ለውጥ ቢመጣ የሚችለው እነዚህ ሁለት ጐራዎች ከስህተታቸውና ከችግራቸው ተምረው የተግባር ማሻሻያዎችን ሲያደርጉ ነው። ይሄን ሲያደርጉ አይታይም፡፡ አሁን የቀረው አንድ ዓመት ነው፡፡ በዚህ አንድ ዓመት ውስጥ መንገዳቸውን ካላስተካከሉ፣ ምርጫው ከአለፉት ምርጫዎች የተሻለ ይሆናል ብዬ አላምንም፡፡” የሚል ነው።
lidetu-ayalew-and-muse-semu
ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ኦፍ ለንደን ፤ ስኩል ኦፍ ኦሬንታል ኤንድ አፍሪካን ስቴዲስ የሚባል ውስጥ “ዲቨሎፕመንት ስተዲስ አጥንቼ ወደ ሃገሬ ገብቼ መኖር ጀምሬያለሁ ሲሉ ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ የተናገሩት አቶ ልደቱ “ከ1997 ዓ.ም. ምርጫ በኋላ ኢዴፓ ‹‹ሶስተኛ አማራጭ›› የሚል ሃሳብ ይዟል፡፡ ይሄ ሃሳባችሁ ከምን አደረሳችሁ?” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ “ሶስተኛ አማራጭ ሲባል፣ ልዩ የርዕዮተ አለም መስመርን ለመግለጽ ሳይሆን፣ የአቀራረብና የስልት ጉዳይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ፓለቲካ፣ እስከ አሁን ድረስ ሁለት ፅንፍ የያዘ ነው። ሁለትም ነገር መደገፍ ወይም ሁሉንም ነገር መቃወም፡፡ የገዥው ፓርቲ አባል ከተሆነ፤ ተቃዋሚ የሚሰራውን ነገር ሙሉ በሙሉ ማጥላላት፤ የተቃዋሚ አባል ከተሆነ ደግሞ መንግስት የሚሠራውን ነገር ሁሉ መቃወም፡፡ እንዲህ ሁለት ጫፍ የያዘ አሰላለፍ፤ ለአገራችን ፖለቲካ አልጠቀመም፡፡ ከመቻቻል ከመደማመጥ አርቆናል፡፡ ለዚህም ነው፤ ከሁለቱ ጽንፎች የተለየ አማራጭና የተለያየ አቀራረብ ያስፈልጋል የሚል አስተሳሰብ ይዘን የመጣነው፡፡ በመንግስትም ሆነ በተቃዋሚ የተሠራ ነገር ለአገርና ለህዝብ የሚጠቅም ከሆነ ልንደግፈው ይገባል፡፡ የማይጠቅምና የሚጐዳ ከሆነ ደግሞ በተጨባጭ መረጃ መቃወምና እንዲቀየር መታገል ያስፈልጋል፡፡ በስሜታዊ ጽንፍ ሳይሆን በምክንያታዊ አስተሳሰብ ነው ፖለቲካው ሊመራ የሚገባው፡፡ አለበለዚያ፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወደ ዲሞክራሲያዊ የመቻቻል ባህል ሊቀየር አይችልም። ሁለት ስሜታዊ ፅንፎችን ይዞ፣ ብሔራዊ መግባባት ለማምጣት በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ፣ ምክንያታዊ አስተሳሰብ ነው የሚያዋጣን ብለን ሶስተኛ አማራጭ ይዘናል፡፡ ይሄንን አቀራረብ ይዘን ስንመጣ ፈተናዎች ገጥመውናል፡፡ ሁለቱ ጽንፎች ለረዥም ጊዜ ስር የሰደዱና የከረሩ ስለነበሩ፣ ብዙ ሰዎች የእኛን አስተሳሰብ ለመቀበል በጣም አስቸግራቸዋል፡፡ ደግሞም አያስገርምም፡፡ ሰዎች በቀላሉ ይሄን አስተሳሰብ የሚቀበሉ ከሆነ፤ ከመነሻው የአገራችን ፖለቲካ ከባድ ችግር የለበትም ማለት ነው፡፡ የአገራችን ፖለቲካ ግን ለረዥም ጊዜ የዘለቀ ትልቅ ችግር አለበት፡፡ ስለሆነም፤ ሦስተኛ አማራጭ ብለን ያቀረብነው የምክንያታዊ አስተሳሰብ አቅጣጫችንን ብዙ ሰዎች በቀላሉ ሊቀበሉት አልቻሉም። “ተቃዋሚ ከሆንክ በቃ ማንኛውንም ነገር ትቃወማለህ፡፡ ኢህአዴግም ከሆንክ ማንኛውንም ነገር ትደግፋለህ፤ ሌላ ሦስተኛ አማራጭ የለም” የሚል የተዛባ አመለካከት ይሰነዘርብን ነበር፡፡ “እንዲያውም ሦስተኛው አማራጭ የምትሉት ነገር ወላዋይነት ነው” በማለት ውዥንብር የመፍጠር ነገርም ነበር። በሂደት ግን፣ ብዙ ሰው ጉዳዩን እያብላላው፣ እያጤነውና እየተገነዘበው እንደሆነ አይተናል፡፡ እኛ በምንፈልገው ፍጥነት ህብረተሰቡ ተረድቶታል የሚል እምነት የለንም፡፡ ገና ብዙ ይቀራል፡፡ የኢትዮጵያ ፖለቲካ እስከአሁን በመጣበት የጽንፈኝነት መንገድ የትም ሊያደርሰን እንደማይችል ብዙዎች እየገባቸው ነው፡፡ ሁለቱ ጽንፎች የሚፈጥሩት ቅራኔና ውጥረት፣ ከዴሞክራሲ እያራቀን እንጂ ወደ መቻቻል እያመጣን እንዳልሆነ ሰው እየተገነዘበው ነው፡፡
“ሁለቱ የፅንፍ ሃይሎችና ጐራዎች አይጠቅሙም ትክክል አይደሉም” የሚለው አስተሳሰብ እየጐላ መጥቷል፡፡ “ሁለቱም ፅንፎች አይጠቅሙም፤ ችግር አለባቸው” ከተባለ ክፍተት መኖሩን ነው የሚያሳየው፡፡ ያንን ክፍተት የመሙላት ጉዳይ ነው የሶስተኛው አማራጭ ፋይዳ፡፡ ይሄንን አስተሳሰብ ይዘን እንደነበር በተለይ በፓርላማ በነበረን ተሳትፎ በደንብ ማሳየት ችለን ነበር፡፡ ፓርላማ ውስጥ ሌሎች ተቃዋሚዎች ከሚያራምዱት አስተሳሰብ በተለየ ሁኔታ፣ መንግስት ከሚሠራቸው ነገሮችና ከሚያራምዳቸው አቋሞች ውስጥ ለህዝብና ለሀገር የሚጠቅም ነገር ስናገኛቸው በድፍረት ስንደግፍ ታይቷል፡፡ ሰው ለዛ የሚሠጠው ትርጉም ምንም ይሁን እኛ ለሀገርና ለህዝብ ይጠቅማል ብለን እስካመንበት ድረስ በድፍረት ወጥተን፤ ይሄ አቋም ከገዢው ፓርቲም ይምጣ ከተቃዋሚ ፓርቲም ይምጣ ለአገርና ለህዝብ የሚጠቅም እስከሆነ ድረስ እንደግፋለን ብለን ማሳየት ችለናል፡፡ ገዢው ፓርቲ ጥሩ ያልሆኑ ነገሮችን ሲሰራ ደግሞ ከሌሎች ተቃዋሚዎች በበለጠ በመረጃ በተደገፈ ከመተቸትና በጠነከረ መልኩ በመታገል ምክንያታዊነታችንን ማሳየት ችለናል፡፡ ከተቃዋሚ ፓርቲ ውስጥም ጥፋት ወይም ድክመት ሲኖር፣ ተቃዋሚ ነውና እሱን አንነካውም አንልም፡፡ እንዲስተካከል እንተቻለን፡፡ ለሰላማዊ ትግልና ለአገር የማይበጅ፣ ለመቻቻል ፖለቲካ ማይጠቅም ሆኖ ካገኘነው፣ ተቃዋሚውንም ቢሆን በድፍረት የመተቸት አዲስ ባህል ይዘን መጥተን አሳይተናል፡፡ ያን የማይወዱ ሰዎች ብዙ ነበሩ፡፡
“በሂደት እየተረዱ ሲመጡ፣ ግን እኛ የያዝነው አቋም ትክክል እንደሆነ መገንዘብ የቻሉ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡ ይሄ አቋማችን በአገራችን ያልተለመደ አዲስ አቋምና አካሄድ ስለሆነ፤ አንዳንድ ሰዎች በእኛ ላይ የሚያወሩትን አሉባልታ ማራገብ ተጠቅመውበታል። በእኛ ላይ ከንቱ ጥርጣሬና ጥላቻ እንዲስፋፋ በማድረግ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳርፈዋል። በሌላ በኩል ግን ከነባሩ የጽንፈኝነት ፖለቲካ የተለየ ምክንያታዊ ፖለቲካ ማራመድ ለዚህ አገር እንደሚያስፈልግ በደንብ ለማሳየት ችለናል፡፡ ስለዚህ ሦስተኛ አማራጭ ይዘን መምጣታችን፣ ጥቅምም ጉዳትም ነበረው፡፡ ከአጭር ጊዜ አንፃር፣ ሊያስወድድ የሚችል የፖለቲካ አቋም አልነበረም፡፡ ለአሉባልታ አጋልጦናል፡፡ ከረጅም ጊዜ አንፃር ግን ይሄ ምክንያታዊ የፖለቲካ መስመራችን እየሰፋና እያደገ፣ በተለይ በአዲሱ ትውልድ ዘንድ ተቀባይነት እያገኘ የሚመጣ አቋም ነው፡፡ ስለዚህ ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው ብዬ ነው የማስበው፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ የበለጠ እየተጠናከረ ነው፡፡ ግን ሂደቱን እኛ ስለተናገርነውና ስላራመድነው ብቻ ውጤት ያመጣል ማለት አይደል፡፡ ከአጠቃላይ ከአገራቱ ሶሽዬ ኢኮኖሚክ የእድገት ደረጃ ጋር ተያይዞ ነው ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችለው፡፡ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ወጥቶ ስለተናገረ ብቻ፣ የበቃ የፖለቲካ አመለካከት ያለው ህብረተሰብ ይፈጠራል ማለት አይደለም፡፡ እንደዛ አይነት ህብረተሰብ የሚመጣው ኢኮኖሚያችን ሲያድግና ሲዳብር፤ ትምህርት ሲስፋፋና ከሌላው አለም ጋር መስተጋብራችን የበለጠ ሲጠናከር ነው፡፡ በአጭር ጊዜ የሚቀየር ነገር አይደለም፡፡ የአስተሳሰብ ለውጥ እውን የሚሆንበት ሂደት በጣም የተራዘመ እንዳይሆንና እንዲፋጠን በማድረግ ረገድ ግን የኢዴፓ ሚና ከፍተኛ ነው፡፡” ሲሉ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በአቶ ልደቱ ወደ ፖለቲካው መመለስ ዙሪያ የዘ-ሐበሻ ተከታዮች ምን ትላላችሁ?

(ሰበር ዜና) የሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ባለበት በገለልተኛነቱ እንዲቀጥል ተወሰነ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ ታላላቅ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ አንዱ የሆነው የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ለረጅዥም ጊዜ ምዕመናኑን በሁለት ሃሳብ ከፍሎ ሲያወዛግብ የቆየው በሃገር ቤት ያሉት አባቶች እና በውጭ የሚገኙ አባቶች አንድነት እስኪያመጡ ድረስ በገለልተኝነት እንቆይ እና፤ ወደ ሃገር ቤቱ ሲኖዶስ እንጠቃለል የሚለው ሃሳብ ዛሬ ውሳኔ አግኝቷል።
deb
ከግማሽ ቀን በላይ በወሰደው የደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ አስተዳደር ቦርድ የጠራው ጉባኤ ዛሬ ዲሴምበር 15 ቀን 2013 ዓ.ም የተደረገ ሲሆኑ፤ የቤተክርስቲያኑ አባላት በዚህ ጉዳይ ውሳኔ እንዲሰጡ ተደርጎ በጉባኤው ላይ ከተገኙት ውስጥ በአብዛኛው ድምጽ የሰጡ ምዕመናን በገለልተኛነት እንዲቆይ በመምረጣቸው ቤተክርስቲያኑ እስካሁን እንደነበረው በገለልተኛንቱ እንዲቀጥል ተወስኗል።

በዚህ ጉባኤ ላይ የቤተክርስቲያኒቱ ካህናት ዛሬ ምርጫ እንዳይደረግ ሆኖም ግን የአንድነት ትምህርት እየተሰጠ እንዲቆይ ጥያቄ ማቅረባቸውን ጉባኤው ውስጥ የነበሩ ወገኖች ለዘ-ሐበሻ ገልጸው አብዛኛው ምእመናን ግን የካህናቱን ሃሳብ ውድቅ እንዳደረገው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በሚኒሶታ የሚገኙ ከ30 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ይህን የውሳኔ ቀን በጉጉት ሲጠብቁት የቆየ ሲሆን ውሳኔውን ለማወቅ ዛሬ ሙሉ ቀን የዘ-ሐበሻ ስልክ ሲጨናነቅ ነበር የዋለው።

በዛሬው ጉባኤ ዙሪያ ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎች መረጃ እንዲሰጡልን ለቤተክርስቲያኒቱ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ መኳንንት ታዬ ከምሽቱ 6:30 ጀምሮ ስልካቸውን ስንደውል የነበረ ሲሆን ስልካቸው ዝግ በመሆኑ ሃሳባቸውን ማካተት አልቻልንም። ሆኖም ግን እንዳገኘናቸው የነበረውን ሁኔታ ጠይቀን ለአንባቢዎቻችን እንደምናካፍል ቃል እንገባለን።

ያ’ገሬና የኔ –አትክልት አሰፋ (ጋዜጠኛ) –ከቫንኩቨር

$
0
0

እናቴና አገሬ ሙግት ገጠሙና፣
ሚስቴና እናት አለም ተወዳደሩና፣
ልጄ እና እማምዬ ፉክክር ገቡና፣
አንዱን ምረጥ ብለው ድርቅ ሲሉብኝ፤
እናቴም ውዴ ናት፣
ሚስቴም የኔ ፍቅር፤
ልጄም ንጉሴ ነው፤
የሚጣፍጥ ከማር፤
የግሌ የራሴ የማ’ለውጣቸው፣
በሰላሳ ዲናር የማልቀይራቸው፤
እናት፣ ሚስት፣ ልጄ፤ ሁሉም የኔ ናቸው።
እኔ ግን ያገሬ፤
እኔስ የ ‘ማምዬ…
የግል ንብረት ነኝ ብዬ መለስኳቸው።
ዲሴምበር 15/2013- ቫንኩቨር (በርናቢ)


በሕወሓት አፈና ቢፈተንም ዓረና መድረክ በማይጨው ሕዝባዊ ስብሰባ አደረገ

$
0
0

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

ባለፈው ቅዳሜ ዓረና መድረክ በጠራው ህዝባዊ ስብሰባ ለመሳተፍ ወደ ማይጨው ከተማ ተጉዤ ነበር። ከመቀሌ -ማይጨው በመኪና የሦስት ሰዓት ጉዞ ነው። ከሰባት ዓመት በፊት የማውቃት ማይጨው ምንም አልተቀየረችም። ብዙ የህወሓት ባለስልጣናት እዛው ማይጨው ነበሩ። ስብሰባዎችና ስልጠናዎች ነበሯቸው።

Arena-Tigray-logoቅዳሜ ከማይጨው ወጣቶች ጋር ተገናኝቼ ነበር። ወጣቶቹ ለውጥ ይፈልጋሉ። ግን ይፈራሉ። የሰለማዊ ትግል ዉጤታማነት ይጠራጠራሉ። ህወሓት በምርጫ ስልጣን ሊያስረክብ ይችላል ብለው አያምኑም። በሰለማዊ መንገድ ከሚቃወሙ በትጥቅ ትግል ቢሳተፉ ይመርጣሉ። ምክንያቱም በትጥቅ ትግል ህወሓት ከስልጣን የሚባረርበት ዕድል ሊኖር ይችላል ብለው ያስባሉ።

በማይጨው የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችም (በተለይ መምህራንና የግብርና ሰራተኞች) በስርዓቱ ቅሬታ አላቸው። የራያ አከባቢ ተወላጆች የሆኑ የህወሓት ካድሬዎችም በስርዓቱ ደስተኞች አይደሉም። ሁሉም ለውጥ ይፈልጋሉ። ግን ዓረና ህወሓትን ታግሎ ሊያሽንፈው ይችላል የሚል እምነት የላቸውም። በራያ ቦታ የሚገኙ የህወሓት አባላት (የራያ ተወላጆች) ህወሓትን ማሸነፍ የሚችል ተቃዋሚ ፓርቲ ካገኙ ህወሓትን እንደሚቃወሙ ይገልፃሉ።

የህወሓት መሪዎችም ይህንን ያውቃሉ። እንደዉጤቱም ህወሓት ከሌላ አከባቢ ታማኝ ካድሬዎች እየላከ የራሱ አባላት ይሰልላል፣ ይቀጣል፣ ያባርራል። በዚህ መንገድ የራያ ህዝብ በራሱ ሰዎች እንዲበደል ይደረጋል። የራያ ተወላጆች የሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ለእንጀራቸው ሲሉ ህዝብ ይበድላሉ። ህዝብ ካልበደሉ ይቀጣሉ፣ ይባረራሉ፣ ሌላ የሚተዳደሩብት የስራ መስክ የላቸውም።

Abrham Destaየራያ ቦታ በህወሓት ከተረሱ አከባቢዎች አንዱ ነው። የራያ ህዝብ የክረምት ምግብ የነበረ ‘በለስ’ ለምርምር ተብሎ በገባ የሀር ትል ምክንያት ከጥቅም ዉጭ ሁነዋል። መንግስት የበለስ ጉዳቱ ለማካካስ የወሰደው እርምጃ የለም። በብዙ የራያ ቦታዎች የዉኃ ችግር አለ። የዉኃ ችግሩ ለመቅረፍ ብዙ ጉድጓዶች የተቆፈሩ ቢሆንም የዉኃ ቦይ ማስገባት ባለመቻሉ እስካሁን የዉኃ አገልግሎት የማያገኙ የራያ ቦታዎች አሉ።

ከዓመታት በፊት ለመስኖ እርሻ እንዲዉል በጥናት መሰረት የተመረጠ ‘የጎልጎል ራያ’ ሜዳም እስካሁን አልተተገበረም። የህወሓት መሪዎች ጎልጎል ራያን በመስኖ የማልማት ዕቅድ ሰርዘውታል። ፕሮጀክቱ ለመሰረዝ የሰጡት ምክንያት በራያ የሚገኝ ዉኃ ‘ጨዋማ’ ስለሆነ ለመስኖ ጥቅም አይውልም የሚል ነበር። የሚገርመው ነገር ደግሞ አሁን ጎልጎል ራያ በኢንቨስትመንት ስም ለባለ ሃብቶች እየተሸጠ ነው የሚገኘው። ስለዚህ የህወሓት ሰዎች የጎልጎል ራያን በመስኖ የማልማት ፕሮጀክት የሰረዙበት ምክንያት ሰፊ ለም መሬቱ ለባለሃብቶች ለመሸጥ ስለፈለጉ ሊሆን ይችላል።

የራያ ህዝብ ጀግናው ጥላሁን ይግዛውን ለመዘከር ሐውልት ለመገንባት ተብሎ ከራያ ተወላጆች ወደ 700,000 ብር የሚጠጋ ገንዘብ ከሰባት ዓመት በፊት የተሰበሰበ ሲሆን እስካሁን ድረስ ምንም ነገር አልተሰራም። የራያ ህዝብ ለጥላሁን ይግዛው ሐውልት ለመስራት የተሰበሰበ ገንዘብ የት እንዳለ ማወቅ ይፈልጋል፣ ይጠይቃል። አስተዳዳሪዎቹ የሰጡት መልስ ገንዘቡ ለኮብልስቶን አውለነዋል የሚል ነበር። ህዝቡም ኮብልስቶን የራሱ በጀት እንዳለው ሲከራከር ደግሞ አስተዳዳሪዎቹ ገንዘቡ የት እንዳለ እንደማያውቁ ይናገራሉ።

በማይጨው አከባቢ በሚገኙ ተቋማትም የሙስና አሰራሮች መኖራቸው ኗሪዎች ይናገራሉ። በዚሁ ምክንያት የችፑድ ፋብሪካ፣ ማይጨው ግብርና ኮሌጅና ማይጨው ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተመሳሳይ ሁኔታና ወቅት የዳታ ኮምፒተሮች እንዲጠፉ ተደርገዋል። የዳታ ኮምፒተሮች እንዲጠፉ ሲደረግ ተቋማቱ ኦዲት እንዳይደረጉ ይረዳል። ኦዲት ካልተደረጉ ሙስና መሰራቱና አለመሰራቱ ለማወቅ ይከብዳል። የሙስና ጉዳይ ይፈተሽ።

ቅዳሜ ማይጨው በነበርኩበት ሰዓት በከተማው የኢንተርኔት አገልግሎት አልነበረም። ለዚህም ነበር ስለ ማይጨው ሁኔታ በወቅቱ መፃፍ ያልቻልኩ (ኢንተርኔት መጠቀም የሚቻለው በሞባይል ብቻ ነበር)። በወቅቱ የዓረና የማይጨው ከተማ አባላት የማይጨው ህዝብ ዓረና ፓርቲ በጠራው የእሁድ ህዝባዊ ስብሰባ እንዲሳተፍ ይቀሰቅሱ ነበር። ህዝቡም ለዓረና ጥሩ አመለካከት ነበረው። የዓረና አባላት ‘ዓረና’ የሚል ፅሑፍ ያለው ነጭ ቲ-ሸርት ለብሰው ነበር የሚቀሰቅሱ።

የህወሓት ሰዎችም ህዝብ በዓረና ስብሰባ እንዳይሳተፍ ለማድረግ የራሳቸው ቅስቀሳ ጀመሩ። ህወሓቶች ትልቅ ስፒከር ተጠቅመው በዕለተ እሁድ (በዓረና ስብሰባ) በማይጨው ከተማ የእግር ኳስ ውድድር ስላለ መላው ወጣት ተጫዋቾችን እንዲደግፍና እንዲያበራታታ ያውጁ ነበር።

የራያ ተወላጆች ያልሆኑ ካድሬዎች ለራያዎቹ በእሁድ ቀን በሚደረገው የዓረና ስብሰባ ሰው እንዳይሳተፍ እንዲመክሩና እንዲያስፈራሩ ተነገራቸው (ይህ መረጃ የተገኘው ከካድሬዎቹ ከራሳቸው ነው)። በስብሰባው የተሳተፈም እንዲመዘግቡ ትእዛዝ ተሰጣቸው። በተጨማሪም ሰው ለመያዝ ሲባል የተለያዩ ያልታሰቡ የህዝብ ስብሰባዎች ተጠሩ። አብዛኛው የማይጨው ወጣት በራሳቸው ስብሰባ እንዲገኝ አዘዙት። የችኮማዮና የመኾኒ ‘ስራ አጥ’ ወጣቶች ‘ስራ እንዲሰጣቸው’ ለእሁድ ስብሰባ ተጠሩ። እሁድ በስብሰባው የተገኘ ስራ እንደሚሰጠው፣ ያልተገኘ ግን ስራ እንደማያገኝ ተነገረው።

የማይጨው ህዝብም ለህወሓት ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ የሙዚቃ ባንድ እንደሚመጣለት ሲነገረው ነበር። ህወሓት በማይጨው ከተማ የሙዚቃ ኮንሰርት ሲያዘጋጅ (ወይ አዘጋጃለሁ ሲል) ለመጀመርያ ግዜ ነው። ይህም ዓረና ህዝባዊ ስብሰባ በጠራበት ቀን ነው። እሁድ ቀን በስብሰባው ተሳታፊ ስለነበርን ህወሓቶች የራሳቸው ስብሰባ ስለማካሄዳቸው ሙሉ መረጃ አልነበረኝም። የሙዚቃ ኮንሰርቱ ስለ መሳካቱም እርግጠኛ አይደለሁም። የሙዚቃ ኮንሰርቱ ያልታቀደና ያልታሰበበት ስለነበረ ያልተሳካ ሙከራ ሊሆን ይችላል (ከተጋበዙት ሙዚቀኞች ቅሬታ ያሰሙ ነበሩ፤ በቂ ግዜ ስላልተሰጣቸው)።

እሁድ ጠዋት ሰው ዓረና ወደ ጠራው ስብሰባ መግባት ከመጀመሩ በፊት የተወሰኑ የፀጥታና የፕሮፓጋንዳ ሐላፊዎች አደራሹ አከባቢ ተሰብስበው ነበር። ወደነሱ አከባቢ ስንሄድ ተበትነው ጠፉ። አብዛኞቹ የማይጨው ካድሬዎችና ፖሊሶች ግን ተባብረውናል። ተሳታፊ እንዲሰልሉና እንዲያስፈራሩ የተላኩ ካድሬዎች ከጎናችን ነበሩ። ‘እንደምንም ብላቹ ህወሓትን ማባረር የምትችሉ ከሆነ ከጎናቹ ነን’ ይሉን ነበር። ላደረጉልን ትብብር እናመሰግናለን። ህወሓትን ከስልጣን ማባረር የምንችል ግን ሁላችን ስንተባበር ነው።

ህዝብ ወደ አደራሹ ገባ። ስብሰባውም ተጀመረ። እኛ ስለ ህወሓት መጥፎነትና የለውጥ አስፈላጊነት አወራን። ህዝቡም አስተያየት ሰጠ። ከህዝቡ የተረዳነው ነገር ቢኖር የራያ ህዝብ የህወሓትን መጥፎነት ከኛ በላይ ያውቃል። የህዝቡ ጥያቄ ህወሓትን እንዴት ከስልጣን ማውረድ ይቻላል? ዓረናስ አንዴ እየመጣ፣ ብዙ ግዜ እየጠፋ ህወሓትን ማሸነፍ ይችላል ወይ? ዓረናን ብንደግፍና ህወሓትን ከስልጣን ማባረር ባንችል ዋስትናችን ምንድነው? ህወሓት ሽፍታ ነው፤ ሊያጠፋን ይችላል ወዘተ የሚሉ ሐሳቦች ተነስተዋል።

ህዝቡ በሰጠው አስተያየትና ትንተና ተገርምያለሁ። ህዝቡ ለውጥ ይፈልጋል። በህወሓት መሪነት እምነት የለውም። ህዝቡ ያጣው ነገር ህወሓትን ሊያባርር የሚችል ዓቅም ያለው የተቃዋሚ ፓርቲን ነው። ህዝቡ የሚመራው ፓርቲ ካገኘ ለመታገል ዝግጁ ነው። ዓረና ቆራጥነት ካለው ህዝቡ ከዓረና ጎን ተሰልፎ እንደሚታገል ቃል ገብተዋል።

የማይጨው ስብሰባ ለየት የሚያደርገው ተሰብሳቢው በሙሉ የህወሓት ተቃዋሚ መሆኑ ነው። የህወሓት ካድሬዎች አልነበሩም። ሁላችን በአንድነት ለመታገል ቃል ስንገባ በአደራሹ የነበረ ሁሉ ቃሉ ሰጠ። አብረን ለመታገል ቃል ገባን። (ኩልና ብሓባር ንምቅላስ ንዓሪ ኢልና ዓረና)። ሦስት ሰዓት ተኩል የጀመረ ስብሰባችን ዘጠኝ ሰዓት ተኩል ተጠናቀቀ።

እኔ የተረዳሁት ነገር አለ። የህወሓት ስጋት ዓረና አይደለም። የህወሓት ስጋት የህዝብ ማወቅ ነው። ህወሓት የትግራይ ህዝብ የፖለቲካ እውቀት እንዲኖረው አይፈልግም። ምክንያቱም የትግራይ ህዝብ የፖለቲካ ንቃተ ህሊናው ከፍ ካደረገ ለህወሓት ካድሬዎች አሜን ብሎ አይገዛም። ካልተገዛ ደግሞ የህወሓቶች ህልውና ያበቃል። የህወሓቶች ጥረት ህዝብ በስብሰባው እንዳይሳተፍና አማራጭ ሐሳብ እንዳይሰማ መከልከል ነበር። ህወሓት የሚሰጋው ዓረና እንዳይቃወመው ሳይሆን ህዝቡ ፖለቲካ አውቆ እንዳይቃወመው ነው።

ይሄ ተንኮል ግን የህወሓት ዕድሜ ያራዝማል የሚል ግምት የለኝም።

በ“ኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ” መስራች ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

$
0
0

መስራች ጊዜያዊ ኮሚቴ  
ታህሳስ 3 ቀን 2006 ዓ.ም

newspaper_for_rentበሀገራችን ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ተረጋግጧል ከተባለበት ከ1985ዓ.ም. ጀምሮ የመገናኛ ብዙሃን ሙያ ከመጎልበት ይልቅ እያደር በመጫጨት ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘ  የሙያው ባለቤቶች የሆኑት ጋዜጠኞች ለተለያዩ ጥቃቶች ሲጋለጡ ቆይተዋል፡፡ ለምሳሌ ጋዜጠኞች በስራቸው ምክንያት አለአግባብ ይታሰራሉ፤ ማስፈራሪያና ዛቻ ይደርስባቸዋል፣ ይደበደባሉ፣ ማግኘት የሚገባቸውን ጥቅማ ጥቅሞች እና መብቶቻቸውን ይነፈጋሉ፣ ሲልም ከዚህ የከፉ በደሎች ይደርሱባቸዋል፡፡ የሚያሳዝነው ደግሞ ከመንግሥት ከሚደርስባቸው መሰል የመብት ጥሰትና እንግልት በተጨማሪ፣ ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ መገናኛ ብዙሃንን መመዝበር የሚፈልጉ የተለያዩ አካላትም ጥቃት ሰለባ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ከዚህም ባሻገር በተለያየ መንገድ ጥቅሞቻቸው አይከበሩም፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ጋዜጠኞች ለሌሎች መብት መከበር የሚጮሁትን ያህል በራሳቸውና በሙያው ላይ የተጋረጡ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታትም ሆነ እንዳይፈጠሩ ለመስራት አልታደሉም፡፡ ይህንን ሊያከናውን የሚችል ተቋምም ሆነ ማህበር የላቸውም ለማለት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ በቅርቡ በኢትዮ-ምኅዳር ከፍተኛ አዘጋጅ ኤፍሬም በየነ ላይ የደረሰውን ሁሉ መመልከት ይቻላል፡፡ ጋዜጠኛው የሥራ ባልደረቦቹ የቀረበባቸውን ክስ ለመከላከል እና እግር መንገዱን የሙያ ግዴታውን ለመወጣት በሄደበት ወቅት የደረሰበትን አወዛጋቢ የትራፊክ አደጋ ተከትሎ በተግባር ለጋዜጠኝነትና ለጋዜጠኞች የሚቆረቆሩ ተቋማት አለመኖራቸው በተጨባጭ የታየ ጉዳይ ነው፡፡ ስለሆነም እነዚህና መሰል ችግሮች በእርግጥም ነፃና ገለልተኛ የሆነና ለጋዜጠኝነት ሙያ እንዲሁም ለጋዜጠኞች መብት የቆመ ማኅበር ማቋቋም ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ አድርጎታል፡፡

ከዚህ እውነት በመነሳት ከጥቅምት ወር 2006 ዓም ጀምሮ “የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ” በሚል ስያሜ በጋዜጠኝት መርህ ላይ የተመሰረተ እና ለጋዜጠኞች መብት የቆመ የሙያ ማኅበር ለመመስረት ሰፊ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የሙያው ባለቤቶችም በጋራ ተባብረው ማኅበሩን በቅርቡ እውን ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህንንም ጋዜጣዊ መግለጫ ማዘጋጀት ያስፈለገው ይህንን የተግባር እንቅስቃሴ ይፋ ለማድረግ ነው፡፡

“የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ” የሚመሰረተው በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 30 በተፈቀደው የመደራጀት መብት መሠረት ሲሆን፣ በአጠቃላይ ጋዜጠኞችን በመደገፍ፣ የሙያ ብቃታቸውን በማሻሻል እንዲሁም በማበረታታት በሀገሪቱ ያለውን የጋዜጠኝነት ሙያ ለማበልፀግ የሚሰራ ነፃ የሙያ ማኅበር ይሆናል፡፡ ምንም እንኳን ማኅበሩ በርካታ ዝርዝር ዓላማዎችን ያነገበ ቢሆንም፣ በዋናነት ተጠቃሾቹ የሚከተሉት ናቸዉ፡-

1. በኢፌድሪ ሕገ- መንግሥት አንቀፅ 29 መሠረት የተፈቀደውን ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ለማስከበር

2. የጋዜጠኞችን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ

3. በተከታታይ ትምህርትና ሥልጠና የጋዜጠኞችን ሙያዊ ብቃት ለማጎልበት

4. በጋዜጠኞች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር

5. አስፈላጊ ሆኖ በተገኘ ጊዜ የገንዘብ፣ የቁሳቁስና የሕግ አገልግሎት ድጋፍ ለማደረግ

6. በዘርፉ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ጋዜጠኞች እውቅና ለመስጠት የሚሉ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ በዋናነት በአባልነት የሚያቅፋቸው አባላት በጋዜጠኝነት ሙያ በማንኛውም የመገናኛ ብዙሃን መስክ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙትን ሲሆን፤ ከዚህም በተጨማሪ በሙያው ለመሰማራት በሂደት ላይ የሚገኙትንና ከሙያው ጋር ከፍተኛ ቁርኝት ያላቸውን ግለሰቦች ተባባሪ በሚል የአባልነት ዘርፍ ያቅፋል፡፡

ስለሆነም በሙያው አገልግሎት በመስጠት ላይ የምትገኙ ጋዜጠኞች ሁሉ፣ በዚህ በምስረታ ላይ ባለው የእናንተው ማኅበር ላይ፣ የበኩላችሁን ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የማኅበሩን ህላዌ እውን ታደርጉ ዘንድ ተጋብዛችኋል፡፡ በቅርቡም በሚጠራው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ፣ የማኅበሩን የአመራር አባላት በመምረጥ ሂደት እንድትሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

 

እናመሰግናለን!!!

መስራች ጊዜያዊ ኮሚቴ  

 

ታህሳስ 3 ቀን 2006 ዓ.ም

 

 

 

 

 

Hiber Radio: ከሳዑዲ የመጡ ኢትዮጵያውያን ባለባቸው ችግር የተነሳ ተመልሰው ለመሰደድ ማሰባቸውን ገለጹ

$
0
0

የህብር ሬዲዮ ታህሳስ 6 ቀን 2006 ፕሮግራም

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

<<... አጼ ምኒሊክ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለዓለም አቀፍ የነጻነት ምልክት ናቸው። መታሰቢያቸውም በዓለም አቀፍ ደረጃ ጭምር ሊከበር ይገባል ...>>

አቶ ኪዳኔ አለማየሁ የዓለም አቀፍ ህብረት ለፍትሕ የኢትዮጵያ ጉዳይ ዋና ስራ አስኪያጅ ለህብር ከሰጡት ቃለ መጠይቅ

<<...በእስራኤል ያለው ሁኔታም ለኢትዮጵያውያን አስቸጋሪ ነው። ...መቶ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን እስረኞች በእስራኤል በእስር ቤት አሉ...>> አቶ ሳሙኤል አለባቸው በእስራኤል የኢትዮጵያን እናድን ማህበር ሊቀ መንበር በዚያ ስላለው የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይ ከደረግነው ወቅታዊ ቃለ መጠይቅ የተወሰደ

ማንዴላ ማንዴላ(ግጥም)

ታይም መጽሔት የዓለማችን ሰው ስላላቸው የካቶሊኩ ጳጳስ የተጠናከረ ዘገባ

ሻምበል ጉታ ዲንቃ(የማንዴላን ህይወት ከተቀነባበረው የግድያ ሙከራ የታደጉት ሰው በማንዴላ ቀብር ላይ እንዲገኙ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንዲሄዱ የተደረገበትን ሁኔታ በተመለከተ ቃለ መጠይቅ

ኩላሊት ምን ሲሆን ስራውን ያቆማል ? አስቀድሞ መከላከል ይቻላል? (የህክምና ባለሙያ ማብራሪያ)

ሌሎችም ዝግጅቶች

ዜናዎቻችን

- የማንዴላ ስርዓተ ቀብር በታላቅ ስርዓት ተከናወነ

- ከሳውዲ የመጡ ኢትዮጵያውያን ባለባቸው ችግር ተመልሰው ለመሰደድ ማሰባቸውን ገለጹ

- የአጼ ምንሊክ መቶኛ ዓመት መታሰቢያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊከበር እንደሚገባ ተገለጸ

- በኢትዮጵያ ከአስር ዓመት በፊት የተደረገው ጭፍጨፋ ታሰበ

- በቬጋስ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ለህንጻ ማሰሪያ በአንድ ምሽት 322 ሺህ ዶላር ተሰበሰበ

ሌሎችም ዜናዎች አሉን

10ሩ የማንዴላ ድንቅ አባባሎች (ፍኖተ ነፃነት ቁጥር 82)

$
0
0

Fnote910ሩ የማንዴላ ድንቅ አባባሎች
ያልተመለሰው የመሬት ጥያቄ
ቀናዋ የማንዴላ መንገድ
የማይበቅል ዘር በመሰራጨቱ
በገበሬዎችና በባለስልጣናት
ማሀከል ውጥረት ተፈጠረ
በጉጂ ዞን መንግስታዊ
ስርዓት አልበኝነት ተባብሷል
ፍኖተ ነፃነት ቁጥር 82 ሰኞ ታህሳስ 7 ቀን 2006 ዓ.ም

–ፍኖተ ነፃነት ቁጥር  - 82 _PDF_

 

አይ አበሻ! አበሻና ልመና፦ አንድ (መስፍን ወልደ-ማርያም)

$
0
0

መስፍን ወልደ ማርያም

ኅዳር 2006

Pro Mesfinበዓለም ሕዝቦች መሀከል ውድድር ቢደረግ ያለጥርጥር አበሻ አንደኛ ከሚወጣባቸው ነገሮች አንዱ ልመና ሳይሆን አይቀርም፤ ለአበሻ፣ ልመና የኑሮ ዘዴ ነው፤ እንዲያውም ከልመና ውጭ የሆነ ኢትዮጵያዊ ኑሮ የለም ለማለት የሚቻል ይመስለኛል፤ ስለዚህም ልመና ባህላዊ ጥበብ ሆኖአል፤ አንዳንድ አላዋቂዎች፣ አንዳንድ አዋቂዎችም አንዳንዴ እየተሳሳቱ ልመናን እንደነውር ይገልጹታል፤ ልመና ነውር አይደለም፤ ለጨዋ ልጆችማ አንዳንድ አጥንትን የሚያበላሽ ሥራ ከመሥራት ለምኖ መብላት ክብር ነው፤ ይህ ባህላዊ ጥበብ ያልገባቸው የድሬ ዳዋ ለማኞች ብቻ ናቸው፤ እጃቸውን እየዘረጉ ‹‹እስቲ አሥር ብር ስጠኝ!›› ይላሉ! በጫት ሞቅ ሲላቸው መቶ ብር ይጠይቃሉ፤ የድሬ ዳዋ ልመና መሆኑ ነው!

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ቄሶቹ ምንም ይስበኩ በተግባር እንደሚታየው ጽድቅ የሚገኘው በልመና ነው እንጂ በሥራ አይደለም፤ ሥራኮ ለአበሻ ከእርግማን የመጣ ነው፤ አበሻ አልተረገመ፤ ታዲያ ለምን ብሎ ይሥራ! አሁን እንደሚሰማውና እንደሚመስለኝ አገዛዙም እንደተቀበለው የቻይና ሰዎችም እንደመሰከሩለት ከሥራ ጋር ጠብ አለው፤ ደግሞስ ለምን ይሥራ! ለአንድ እንጀራ? ለተራበ አብልተው ለመጽደቅ የሚፈልጉ ስንትና ስንት ሰዎች አሉ፤ ስለዚህም ደግ ሰዎች መጽውተው እንዲጸድቁ በግድ ለማኞች ያስፈልጋሉ፤ ለመጽደቅም መለመን ያስፈልጋል፤ ጸሎት ልመና መሆኑን አትርሱ፤ ስለዚህም ዋናውና ከፍተኛው ልመና ወደእግዚአብሔር ነው፤ ብልጦቹ እግዚአብሔርን የሚለምኑት ሥልጣን፣ ሀብትና ጉልበት ነው፤ አንድ ቀን ተነሥተው እግዚአብሔር ሥልጣን፣ ሀብትና ጉልበት እንደሰጣቸው ያውጃሉ፤ አውጀውም በሕዝብ ራስ ላይ ይወጣሉ፤ በራሱ ላይ ወጥተውም ይጨፍራሉ፤ ሰውን ከመሬቱ፣ መሬቱን ከሰው መለየት ይሳናቸዋል፤ ሰውን ከመሬቱ፣ መሬቱን ከሰው ያጣላሉ፤ እግዚአብሔር ለእናንተ ብቻ እንዴት ሰጣችሁ? እግዚአብሔር እኛን ለምን ነፈገን? ብሎ የሚጠይቃቸውን እየደበደቡና እያቃጠሉ፣ እየገረፉና እያራቆቱ በዝምታ እንዲገዛ ያደርጉታል፤ አልበቃው ካለም አካሉን ለውሻ ሰጥተው ነፍሱን ወደእግዚአብሔር ይወረውራሉ፤ እግዚአብሔር እየቆጠረ የማይመዘግብ ይመስላቸዋል፤ የጠጠረ ጉልበታቸው ዓይኖቻቸውን አውሮ፣ ኅሊናቸውን አፍኖ እግዚአብሔር በዕዳ እንደሚይዛቸውና በጥጋባቸው ያደሉትን መከራና ስቃይ፣ የወረደውን እንባና ደም ከነወለዱ እንደሚያስከፍላቸው መገንዘብ ያቅታቸዋል።

እግዚአብሔር ፍርዱን እስቲሰጥ ድረስ ሥልጣን፣ ሀብትና ጉልበት ተረክበናል የሚሉት የተለያዩ ስሞችን እየለጠፉ በተዋረድ የለማኞችን ሠራዊት ያደራጃሉ፤ ሕዝብ ሁሉ ከነዚህ የለማኞች ሠራዊት በአንዱ ውስጥ ለመግባት በፉክክር ይተላለቃል፤ ሠራዊቱ ውስጥ በመግባት የሚገኘው ጉርሻ ልጆቻቸውን እንኳን ከረሀብ የማያድን መሆኑን ሳይገነዘቡ መብታቸውን እያስረገጡ የሌሎችን መብት ለመርገጥ መሣሪያ ይሆናሉ፤ እነዚህ እንግዲህ ልመናን በማኅበረሰቡ ውስጥ ተክለው እየኮተኮቱ የሚያስፋፉት ናቸው፤ ልመናን ባህል የሚያደርጉት እነዚህ ናቸው፤ ልመናን ታሪካችን ያደረጉት እነዚህና ከነሱ የቀደሙት ገዢዎቻችን ናቸው።

በእኛ ባህል የራበውን በማብላት ጽድቅ ይገኛል፤ ስለዚህም ለምኖ መብላት ይቻላል፤ ስለዚህም ሰዎች መጽውተው እንዲጸድቁ በግድ ለማኞች ያስፈልጋሉ፤ እንግዲህ ለምነው እየበሉ መኖር ከተቻለና እግዚአብሔርን በመለመን ጽድቅ ከተገኘ፣ የመሬቱንና የሰማዩን ጣጣ በልመና መገላገል ከተቻለ ታዲያ ሥራ ለምን ያስፈልጋል! ለነገሩስ ሥራ በእርግማን የመጣ ነው፤ ስለዚህ የተረገሙት ሲሠሩ ያልተረገሙ የሚመስላቸው ይለምኑ፤ ለሌላው ዓለም ልመና የችግር ምልክት ነው፤ ለአበሻ ግን ልመና የጽድቅ ምልክት ነው፤ የጨዋ ልጅ፣ ማለት በልመና በሰዎች ላይ ሥልጣንን ከአግዚአብሔር አግኝቻለሁ ብሎ የሚያምን፣ አይሠራም፤ ቀን ቢጥለውም የጨዋ ልጅ በእጁ ሠርቶ ከሚበላ ለምኖ ቢበላ ይሻለዋል፤ ሆድ የተፈጥሮ ነው፤ ረሀብም የዕለት ከዕለት የተፈጥሮ ግዳጅ ነው፤ ስለዚህም ለአበሻ የተፈጥሮን ሆድና የተፈጥሮን ረሀብ በልመና መወጣት የተፈጥሮን ሥርዓት መከተል መስሎ ይታየዋል።

ሌላ ቀርቶ ተማሪ ለምኖ ካልበላ ትምህርት አይገባውም፤ ለተማሪ ሲሆን ልመና አይባልም፤ ቀፈፋ ነው፤ አበሻ በልመና ምን ይህል እንደተራቀቀ የሚያመለክተው ለተለያዩ ልመናዎች የተለያዩ ስሞች ማውጣቱ ነው፤ እንደተባለው ተማሪ ሲለምን ቀፈፋ ነው፤ በዘመናዊ ቋንቋ የትምህርት ታክስ ነው፤ ምግብ የሚቀርብበትን ሰዓት እየጠበቀ ከተፍ የሚለው ቀላዋጭ ነው፤ አብዛኛውን ጊዜ ለቀላዋጭ ቀላል ሰበብ የሚሆነው ቀላውጦ የሚያገኘው ወሬ ነው፤ ሌላም የልመና ዓይነት አለ፤ እርጥባን ይባላል፤ — ደርቄአለሁና አርጥቡኝ ማለት ነው! ‹ላሊበላዎች› የሚባሉት ለምነን ካልበላን እንቆመጣለን በማለት ልመናን የኑሮ መሠረት አድርገውታል፤ ሌላም የልመና ዘር አለ፤ ደጅ መጥናት ይባላል፤ ደጅ መጥናት ማለት ብርዱን ችሎና እንቅልፉን አቋርጦ በሌሊት እየተነሡ በመኳንንቱና በመሳፍንቱ፣ በንጉሡ፣ በንጉሠ ነገሥቱ ደጃፍ ላይ አጥር ወይም ዛፍ እየተደገፉ የተፈለገውም ሰው ብቅ ሲል በመሬት ላይ በመነጠፍ እጅ በመንሣት ፊት ለማስወጋት ለመታወቅና ለሹመት ለመታጨት የሚጠቅም የልመና ዘዴ ነው፡፡ በአበሻ አገር ሁሉም ነገር በልመና ነው፤ ምግብ በልመና፣ ትምህርት በልመና፣ መሬት በልመና፣ … በልመና፣ ግብር የሚከፈለው በልመና ነው፤ ሥልጣን የሚገኘው በልመና ነው፤ ንጉሥነትም የሚገኘው በልመና ነው፤ ባጭሩ ኑሮ ማለት ልመና ነው፤ ልመና ማለት ኑሮ ነው ።

 

 

የማለዳ ወግ …ስደተኛው ዘፋኝ በሳውዲ በርሃ …(ነቢዩ ሲራክ)

$
0
0

ነቢዩ ሲራክ

Bekah

   የእንጀራ ነገር ሆኖብኝ እጓዛለሁ ፣ እጓዛለሁ ፣ እጓዛለሁ … እንደጨው ተበትነናልና ስፍር ቁጥር የሌላቸው ወገኖቸን በየሔድኩበት ከተማ ፣ እግር በጣለኝ የሳውዲ የቀለጡ በርሃዎች ወንድም እህቶቸን አገኛለሁ ። ላፍታም ቢሆን ጊዜ ሰጥቸ እየኑሩት ስላለው ኑሮ ፣ እየገፉት ስላለው ክፉም ደግ ተሞክሮ እጠይቃቸዋለሁ አንድም ሳይደብቁ የሆድ የሆዳቸውን ያጫውቱኛል …
እለተ ቅዳሜ በማለዳው ያቀናሁት በያንቦና በጅዳ መካከል በምትገኝ የዋዲ በርሃ ዙሪያ ነበር ። አየሩ ተቀያይሯል ፣ ከዚህ ቀደም ወደዚህ ቦታ ሳመራ እንደ እሳት ነበልባል የሚጋረፈው ሙቀት ዛሬ የለም ። ለስራ ወዳቀናሁበት በድቅድቁ በርሃ ላይ በተሰራው የድንጋይ መከስከሻ ፋብሪካ እንደደረስኩ አንድ መልከ መልካም ወንድም የግቢውን በር ከፍቶልኝ ለመግባት ወዴት መሄድ እንደምፈልግ ጠየቀኝ  ፣ ወጣቱ \ሃበሻ ለመሆኑ ቅንጣት ያህል አልተጠራጠርኩምና የሚጠይቀኝን ትቸ እኔው ጠየቅኩት “ሃበሻ ነህ! ” ነበር ያልኩ ። ይህን ስጠይቀው እንደ መሽኮርመም እና እንደመሳቅ እያለ “አዎ ሃበሻ ነኝ ፣ ኢትዮጵያዊ ! ” ሲል መለሰልኝ !  ብዙ ሃበሾች አላችሁ?  ስል ጥያቄየን ቀጠልኩ “አዎ አምስት ሃበሾች አለን! ” አለኝ ፈገግ እያለ … በአሻጋሪ መምጣቴን የሚጠብቀው የፋብሪካው ሃላፊ “አስገባው ፣ አስገባው! ” ሲል ፍልቅልቁ ወደ የት እንደምሄድ የጠየቀኝ ወንድም ተደናግጦ በወራጅ ብረት እንደነገሩ የተዘጋውን የግቢ ብረት አጥር ከፍቶልን እኔና የስራ ባልደረባ ረዳቴ የፊሊፒን ዜጋው ግላዲ ወደ ግቢው ገባን ፣ ወጣቱን ወንድም በመስኮት በኩል አንገቴን ወጣ አድርጌ ስራየን ከዋውኘ እንደማገኘው ቃል ገብቸለት ወደ ውስጥ ገባሁ  …

  unn2343     ሱዳኑ የፋብሪካ ሃላፊ ከድንጋዩ መፍጫ የቅርብ ርቀት ካለው ጋራጅ አጠገብ ከተሰራች ባለሁለትና ሶስት ዛኒጋባ ቆርቆሮ ቤት ወጥቶ ሞቅ ያለ ሰላምታ ሰጥቶ ተቀበለን ። ድንጋዩን እየከሰከሰ ጠጠር የሚያደርገው ፋብሪካ ነጭ አመድ ወደ ሰማይ እየተፋ የጓራል …ዲንጋው እየተፈጨ ጠጠር እየተሰራ መሆኑ ነው! የመንገድ መደልደያ ፣ የምንገድ መጥረጊያ እና የመንገድ ማለስለሻ ዳምጤ ከባባድ የኮንስትራክሽን መኪኖችን ጨምሮ ጥገና የሚያስፈልጋቸው መኪኖች ጋራጁን አጨናንቀውታል  … ከጋራጁ ጀርባ ደግሞ እኛ መመርመር ያከብን የተሽከርካሪ ጎማ መአት ተከምሯል። …አምስት የተባሉትን ሃበሾች አግኝቸ እስካዎጋቸው ቋምጫለሁ …የፊት የፊቱን እያስቀረብኩ ፊሊፒኑ አጋሬ ምን መስራት እንዳለበት አሳወቅኩት ፣ ስራውን አጣድፊ ግን በአግባቡ መርምሬ እንደጨረስኩት ሌሎች ሁለት ሃበሾች ሃበሻ ወንድማቸው መምጣቴን ሰምተው ኖሮ በፈገግታ እየተፍለቀለቁ መጥተው ሰላምታ ተለዋዎጥን …

  ሃበሻ ዝር በማይልበት በርሃ ያገኙኝን ወንድም እነርሱም ሊያስተናግዱ ሊያጫውቱኝ እንደቋመጡ አልጠፋኝም … በተንቀሳቃሽ ኮንቴነር በፋይዚት ግሩም ሆና የተሰራቸው ማረፊያ ቤት  ከጋራጁ የቅርብ ርቀር ትገኛለች ። አቧራ የጎረሰውን እጀን ሳልተጠብ በበርሃው ወዳገኘኋቸው ወንድሞች ማረፊያ ቤት አመራሁ … ረመድ ረመድ እያልኩ ከመድረሴ ወንድሞቸ በደስታ እየተፍለቀለቁ ግማሽ መንገድ ላይ ተቀበሉኝ ! ጠባቧ ቤት ማረፊያ ቤት ብቻ እንዳልሆነች ከበር የተደረደሩትን ጫማዎች ስመለከት ገባኝና ጫማየን አውልቄ “ቤት ለእንቦሳ! ” ብየ ዘው ብየ ገባሁ…  ቤቷ ጽድት ያለች ናት … ሶስት አልጋዎች ሶስቱን ማዕዘኖች ጥግ ይዘው ተዘርግተዋል ። የተቀበሉኝ ወንድሞቸ ሶስት ሲሆኑ ዘግየት ብሎ ሌላ ወንድም ገባ … አምስተኛው ወንድም የት እንዳለ ስጠይቅ እሱ ስራ ላይ እንደሆነ ገለጹልኝ። ሁላችንም የምናወራው ከአልጋዎች ላይ ተቀምጠን ነው ።  እንደገባኝ ከሆነ አልጋዎች ይተኛባቸዋል ብቻ ሳይሆን በመቀመጫነት ያገለግላሉ!  … ጫዎታችን ከመጀመራችን በፊት እጀን ለመታጠብ ውሃ ቢጤ ስጠይቅ ድምጹ ጎርነን ያለው “ሸዋንግዛው እባላለሁ!” ብሎ የተዋወቀኝ ወንድም በእጅ ከምትያዝ ማቀዝቀዣ ውሃ ይዞ ወደ ” በር ላይ ላስታጥብህ! ” ብሎ ግማሽ ጎኔን ከበሩ ወጣ አድርጌ እንደነገሩ ጣቶቸን ውሃ አስነካሁ ብል ይሻላል ፣ ብቻ ታጠብኩ !

  unnajgj6    ወጋችን  የጀመርነው በድፍኑ አበሻ ሁኘ እንጅ ማንነቴን የተረዳ ሰው የለም! ብዙ የህይወት ልምዳቸውንና ስለስራቸው ስለተመለከቱት የቴክኒክ ስራየ ፣ ሱዳኑ ሲጠራኝ ስለሰሙት የእንጀራ ስሜና ስለ አጠቃላይ የሳውዲ ህይወት እንዳንፈራራ ፣ እንዳንደባበቅ ፣ እንደ መተዋወቂያ አወራን … ጋዜጠኛ መሆኔን ትንፍሽ ሳልል “ራዲዮ ትሰማላችሁ ፣ ኢንተርኔት ፊስ ቡክ ትከታተላላችሁ? ” በማለት ደጋግሜ ጠየቅኳቸው!  አዎንታቸውን ገለጹልኝ ። ስሜን የእኔ ነው ሳልል ታውቁታላችሁ?  ስላቸው አዎንታቸውን በዝርዝር ገለጹልኝ!  ስገባ በር የከፈተልኝ እያሱና የቀሩት ሁለት ያህሉ በአካል የማያውቁት  ግን ማንቴስ ተብሎ የተዋወቃቸው “የነቢዩ “  የፊስ ቡክ ጓኞች እንደሆኑ በኩራት ገለጹልኝ :) አክለውም በቅርቡ የለቀቃቸውን የራዲዮ መጠይቆች እያነሱ የሚያውቁትን ሰው ስም ስላነሳሁላቸው በደስታ ብዙ አወሩኝ !  … እንዲህ ጥቂት ከቀጠልን በኋላ ግን እነርሱ እዚህ ስላደረሳቸው መንገድ መጠየቅ ጀመርኩ !  ሁሉም የሆነውን ሁሉ ሲያጫውቱኝ  ” አበባ ተሸልሜ በጭብጨባ የተሸኘሁ ዘፋኝ ነበርኩ !” ያለኝ  ድምጸ ጎርናናው የሸዋንግዛው ታሪክ ልቤን ነካው …  ብዙም ሳልቆይ ግን የእውነተኛው አለም  ማንነቴን ገላልጨ ለወንድሞቸ ሳጫውታቸው ነገሮች ተቀያየሩ!  … በጣም ተገረሙ !  ብዙ ተጫወትን … ለዛሬ እንዳላደክማችሁ በሚል በሳውዲ በርሃ ስላገኘሁት ዘፋኙ ወንድም ትኩረቴን ላድርግ  …

     ሸዋንግዛው እና ከቀሩት ጓደኞቹ ሃገር ቤት አይተዋወቁም ። ዳሩ ግን ድህነት ፣ የኑሮ ውድነት ፣ የማደግ የመመንደግ ፍላጎት በቁንጮዋ ነዳጅ አምራች ሀገር በሳውዲ በርሃ ላይ አገናኝቷቸዋል ! … ከሁሉም ወንድሞች ይልቅ ዘፋኙን ስደተኛ  ሸዋንግዛውን እዚህ ያደረሰ መንገድ ለማወቅ ጓጉቻለሁ !  እናም ላፍታ ከዘፋኙ ወንድም ጋር የሆድ የሆዳችን ላፍታ አወጋን … ሸዋንግዛው ንጉሱ ይባላል ፣ እድሜው በአርባወቹ  ውስጥ እንጅ ከዚያ አይዘልም! ዘፋኝ መሆኑን ካጫወተኝ ታሪክ አልፎ በበርሃው ሲያንጎራጉር ከተቀረጻቸው ድምጾች እና የተለቀቀውን ነጠላ ዜማ ሰምቸ ለመረዳት ጊዜ አልወሰደብኝም … “ዘመኑ የዘፋኝ ነው” በሚባልበት ዘመን ድምጸ መረዋውን  ዘፋኝ ወደ ሳውዲ ምን አመጣው ?  በሚል ባለጉዳዩ ስደተኛ ዘፋኝ ጠየቅኩት  … መልሶልኛል ….

    ሸዋንግዛው ንጉሴ በቀድሞው የአርሲ ክፍለ ከሃገር ሎዴ ኤዶሳ በሚባል አከቀባቢ በአንድ መንደር ተወለደ። የሙዚቃ ጥበብ ገና በብላቴና እድሜው የለከፈችው ሸዋንግዛው በሎዴ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርቱን ሲከታተል ጥበብ አብራው አደገች ። ገና ከጅምሩ የጥበቡ ምሳሌ ከልብ የሚወደውን ክቡር ዶር ጥላሁን ገሰሰን ጥሩ ምሳሌ አድርጎ ገሰገሰ።  ሎዴ የትምህርይ ቤት ኪነት ለመመረጠረም ተሰጥኦ ያደለው ተርገብጋቢ ድምጽ ተሰጥኦና ፍላጎቱን ደገፈው ፣  የቀደሙትን ዜማ እያነሳሳ ሲለው የራሱን እየገጠመና እያንጎራጎረ ህይወት በፈለገችው መንገድ ትጓዝ ዘንድ ሸዋ ብርታት አገኘ። ብዙም ሳይቆይ ታዳጊው ሽዋንግዛው ከትምህት ቤት ወደ ወረዳ ኪነት ከፍ እያለ ሄደ … ከወርቁ ቢቂላ ( በኋላ ከሃይሌ ገ/ስላሴ ጋር አለም አቀፍ ሩጫን ይሮጥ ነበር) ታዳጊ እያለ የሙዚቃ ዝንባሌ ስለነበረው በአርሲ ሎዴ የወረዳ ኪነት አብረው እንደሰሩ ሸዋ ሩቅ ተጉዞ ዘርዘር ያለ ትዝታውን አዎጋኝ ። ሸዋ ብዙ ትዝታ አለው ። በአስደሳቹ ፈገግ ፣ በአሳዛኙ ትክዝ  እያለ አጫውቶኛል …

ታዳጊው ሸዋንግዛው በወረዳው ኪነት ቡድን  ተግቶ እየሰራ ባለበት ወቅትም ወደ ክፍለ ሃገር ኪነት ቡድን ለመምረጥ በተደረገ ውድድር ከወረዳ ወደ አርሲ ክፍለ ሃገር ቢመረጥም የወረዳው ሃላፊዎች በቅንነት “ልጃችን አሰልጥለን አንሰጥም !” በማለታቸው ወጣቱ በሙያው ርቆ የመሄድ ስሜቱ ተጎዳ !  እናም በብስጭት ወደ ውትድርና አለም ገባ ። ሸዋንግዛው ማንጎራጎሩን ባንድ በኩል በሌላ በኩል ሳይወድ በተጎዳ ስሜት ገፋፊነት የገባበትን የውትድርና ስልጠና ወሰደ። ቀን ቀንን ሲወልድ ግን ውትድርናው ወደ ጦር ሜዳ ሳይሆን ወደ አሳደገው የሙዚቃ ጥበብ ዶለው !  ሸዋ በብስጭት የተጎዳኘው የውትድርና ስልጠና እንደጨረሰ የባሌ ሸዌ የጦር እዝ ማዕከል የኪነት ቡድን አባል ለመሆን ጊዜ አልፈጀበትም ።

     በጦሩ የኪነት ቡድን በመስራት ላይ እንዳለ የደርግን ስርአት የሚታገለው የኢህአዴግ ጦር ወደ ከተማዎች እየገፋ ሲመጣ የኪነት ቡድኑ ወደ ሲዳሞ በመሄድ ሌላ ተጨማሪ የመከላከል ስልጠና እንዲያደርግ ሲታዘዝ ሸዋንግዛው  ከጓዶቹ ጋር ስልጠናውን ወሰደ። ከዚያም ድልድሉ ወደ ሞያሌ ሆነና ወደ ዚያው አመራ። በጭንቁ ቀን ያልተለየው የጥበብ አውሌ ተጭኖት ማንጎራጎሩን ስላላስቆመው እንቅስቃሴውን ያዩ የሰራዊቱ አባላት ሸዋንግዛው የደቡብ እዝ ኦርኬስትራ ቡድን እንዲቀላቀል ግፊት አድርገው እንዲመረጥ ቢያደርጉም አሁንም የጦር አዛዡ ” ሸዋግዛውን ወደ ደቡብ እዝ አልለቀውም! ” በማለታቸው እድሉ ተጨናገፈ። ይህም ሲሆን ዳግም እክል የገጠመው ዘፋኙ ወጣት ተስፋ አልቆረጠም። ሙዚቃው እንቢ ቢለው በልጅነት ወደ ሚወደው ሌላ ሙያ አጋደለ። ባለበት ብርጌድ የእግር ኳስ ብቃቱን አስመስክሮ እግር ኳስ መጫወቱን በደስታ ተቀላቀለ  ! በወቅቱ ኳሱም ተሳክቶለት ኮከብ ኳስ አግቢ በመሆን ተመርጦ እንደነበረ ሲያጫውተኝ ህይወት በትግል እንደምትፈተን አሸንፎም መውጣት ግዴታ እንደሆነ ሸዋንግዛው በፈገግታ እየገለጸልኝ ነበር ። ኢህአዴግ መላ ሃገሯን ሲቆጣጠር ጦሩ ፈረሰና ከሞያሌ ወደ ኬንያ የገባው ሸዋንግዛው እና የቀረው ስደተኛው በቀይ መስቀል ትብብር ወደ ሃገር ቤት ሲገባ ቤተሰቦቹን ከጠየቀ በኋላ ወደ  አዲስ አበባ ገባ…

  232 አዲስ አበባ ለአርሲው ተወላጁ ለሸዋንግዛው የተመቸች ነበረች። በተለይም በልጅነት የተለከፈባት የሙዚቃ ጥበብ ተሰጥኦውን  የሚያጎለብትበት ብቸኛ እድል አገኘ ። እናም በየምሺት ቤቶች “ከተፋ ቤቶች” ተሰማርቶ ምሽቱን እያደመቀ እና ራሱንና ቤተሰቦቹን በመርዳት መስራት ጀመረ ። ባለትዳር የሆነው ሸዋንግዛው በምሽት ስራው በአሁኑ ሰአት ታዋቂ ከሆኑ ዘፋኞች ጋር እኩል ድምጽ ማጉያን ተጋርቶ በጥበብ ተናኝቷል !

  ይህም ሁሉ ሆኖ ፣ ይህንን የከበደ መንገድ ተጉዶ ሸዋንግዛው ከልጅነት እስከ እውቀት ሙጥኝ ያላትን ጥበብ አዳብሮ የራሱን ወጥ ዘፈን ለማውጣት አቅሙ አልገደደውም። ያም ሆኖ ግን  በማይቆጣጠረው እክል ስራውን ለሃገር መናኘቱ አልሆንልህ እያለው መቸገሩ አልቀረም። ሸዋንግዛው እንዲህ እየሆነ ህይወትን ሲገፋ ለማደግ የሚያደርገው ግብግብ ባያሸበርከውም ሩጫው አልፎ አልፎ  እንዳደከመው ሳይደብቅ አጫውቶኛል።  የጥበብ አውሌ ብቻዋን ከተዘፈቀበት ድህነት ራሱን ቀና አላደረገችውም!  ይህ እንዳይሆን ፣ በሰው ሰራሽ ምክንያት በጥበብ ላይ የሚሰራ ደባ እየደሰቀው መፈናፈኛ እንዳሳጣው ሸዋንግዛው ይናገራል ! በተለይም “ከከተፋው” ዘፋኝነት ጎን ለጎን ብዙዎችን ዘፋኞች ያሳወቀውን ነጠላ ዜማ ግጥምና ዜማውን ራሱ ደርሶ ቢያወጣም ሃገር ስራውን እንዳያውቅለት ጫና ፈጣሪዎች አላገዙትምና ድንቅ የባህል ዘፈኑ ሳይደመጥለት እንደቀረ ዜማዋን እንድሰማት በመጋበዝ ሸዋ ብዙ አጫወተኝ።  በሙዚቀኞች መካከል ውስጥ ለውስጥ የሚሰራውን “የቲፎዞ ” ድጋፍ ፣ አንዳንድ የሃገር ቤት ጋዜጠኞች በተለይም  የኤፍ ኤም ራዲዮ ጋዜጠኞችን ድጋፍ ማጣቱ አውኮተ አሰናክሎታል። ሸዋ ባለሙያዎች ሙያቸውን በሙስ አርክሰው የሚሰሩትን በገደምዳሜም ቢሆን አጫውቶኛል። እኔም በሙስናው ዙሪያ ያለውን አበሳ ወገንተኛ ዘመም የቲፎዞ አካሄድ ግልጥልጥ አድርገው ካወሩት ጉዳዩ ብዙ እንደሆነ ከዚህ በፊት የማውቀውን ታሪክ ሸዋንግዛው አስታወሰኝ …

ሸዋን ሳውዲ አረቢያ ስላደረሰው መንገድ እና የወደፊት ህልሙ እንዲያጫውተኝ ጠይቄው እንዲህ አለኝ ” ነጠላ ዜማው አልሳካ ሲለኝ ድህነቱንና የኑሮ ውድነቱን ለማሸነፍ እንዳልቻልኩ የገባት ጅዳ የምትኖረው እህቴ በኮንትራት ስራ እንድመጣ አመቻቸችልኝ። ተሳክቶም ልክ የዛሬ 11 ወር ወደ ሳውዲ አረቢያ በኮንትራት ስራ መጣሁ ።  በዘፈን ብዙዎች ይሳላካላቸዋል ። እኔ የእድል ጉዳይ ሆኖ አልተሳካልኝም ። ይህ ደግሞ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ። የመጣውን መቀበል እንጅ አላማርረውም። አሁን የምሰራው “ሮለር ” በሚባል የኮንስትራክሽን ተሽከርካሪ ላይ ነው። በሃገራችን ዳምጤ ይባላል። ዳምጤን እየነዳሁ በርሃውን ማቅናት ነው የአሁን ስራየ ። በቃ ! ህይዎት እዚህ አድርሶኛል! እንደኔ ሃሳብና ህልም ከሆነ እንደ ምንም የሁለት አመት ኮንትራቴን ጨርሸና ገንዘቤን ሰብስቤ እግዚአብሄር ብሎ የሙዚቃዋ አድባር ከጠራችኝ ወደ ሙዚቃው መመለስ ነው ሃሳቤ፣ ካልሆነ የማገኛትን ይዠ ቤተሰቤንና ራሴን እየረዳሁ በሃገሬ መኖር ነው የምፈልገው!  ለእስካሁኑ  እግዚአብሔር ይመስገን! ወደፊትም እሱ ያውቃል! ” በማለት ሸዋንግዛው መልሶልኛል…

    ሸዋንግዛው “ይሻላል እንደሁ! ” ብሎ በኮንትራት ከመጣ ቀን ጀምሮ ስራውን የበርሃውን ቃጠሎ ተቋቁሞ ከጓደኞቹ ጋር እየሰራ ቢሆንም በደመወዝ አከፋፈሉ ላይ ቅሬታ እንዳለውና ይህም ፈተና እንደሆነበት ገልጾልኛል።  ከሸዋንግዛው ጋር በነበረን ቆይታ በበርሃው ውሎ አዳር ስለሚለከታቸው በእረኝነት ተቀጥረው ስለሚገፉ ኢትዮጵያውያን ይዞታ ሲያጫውተኝ እንዲህ ነበር ያለኝ ” የእኛን ተወው ደህና ነው ፣ የእረኛ ወንድሞቻችን ህይወት ብታየው ያሳዝናል፣ ሃበሾችን ከሩቅ ታውቃቸዋለህ። ስናናግራቸው ደስተኛ እንዳልሆኑ ይገልጹልናል። ወደ ሃገር ቤት እንዳይመለሱ ከድህነትና ኑሮ ውድነቱ በተጨማሪ ያላቸውን ቅሪት አንጠፍጥፈው ተሰደዋልና ምን ይዘን እንግባ ?  ይሉሃል ! ምን ትላቸዋለህ? ያ ያ ስላለ እንጅ ከኢትዮጵያ መጥተህ በበርሃው ውሃ እየተጠማህ የመንጋ በግ ፣ ፍየልና ግመል እረኛ ሆነህ ኑሮን መግፋት ይከብዳል። ታለቅሳለህ! ” ሲል ፊቱን በሃዘን ክችም አድርጎ ዘፋኙ አዝኖ አሳዘነኝ …

    አዎ እኔም በአካል ተገኘቸ ያየሁትና ዛሬ በርሃ ላይ ባገኘሁት ዘፋኝ የተገለጸልኝ ህይወት በእርግጥም ያሳዝናል!  ያማል!  ማለቱ ብቻ ስሜትን የሚገልጸው አይሆንም …ብቻ በባለጸጋ አረቦች ሃገር ከአረቦቹ ጓዳ ፣ እስከ ደራው ከተማና በርሃው የእኛ ህይዎት ሲሰሙት ውለው ቢያድሩ ተነግሮ አያልቅምና በዚሁ ልግታው እና ወደ በርሃው ውሎ የመጨረሻ ምዕራፍ ላቅና…

    ከሸዋንግዛውና ከጓደኞቹ የነበረኝ አጭር ቆይታ ታላቅ የጽናትን እና ዥጉርጉሩን ህይዎት የተረዳሁበት መልካም አጋጣሚ ሆኗልና እዚያው ውየ ባድር ደስታየ በሆነ ነበር … ያ እንዳይሆን የእንጀራ እና የህይወት ጉዳይ አልፈቀደልኝም!  እናም መለያየት ግድ ሆነ  ! በሳውዲ ራብቅ በርሃ ላይ ያገኘሁትን ዘፋኙን ሸዋንግዛውንና  ጓኞቹን ስለያቸው በፍቅር ተሳስቀን እና ተቃቅፈን ተሳስመን ነበር …ደግሜ ልጎበኛቸው ቃል በመግባት …

     ሸዋንዳኝን ስለየው ያቀበለኝን ባንድ ወቅት ሰርቷት በህዝብ ጀሮ ያልደረሰችውን “ሸዋ ጥበብ ያውቃል! ” ነጠላ ዜማው እየኮመኮምኩ በርሃውን ለቅቄ ወደ ጅዳ መገስገስ ጀመርኩ  …

” ከወዲያ ከወዲህ ስታንገላታኝ
ይህች የመንዝ ልጅ አስራ ልትፈታኝ
ቃሌ አይታጠፍም የመጣው ቢመጣ
እንዳሻት ታድርገኝ አላበዛም ጣጣ ” ይለዋል  ሸዋ… በጥበቡ የሸዋን ጉብል የከበደ ፍቅር ሲገልጸው ….
የሙዚቃው የደመቅኩት ምንጃርኛውን ሞቅ ደመቅ ባለው ቅንብርና ዜማ የታጀበ ብቻ በመሆኑ አይደለም!  የሸዋ ግጥሞች መልዕክት አላቸው …

     የእንጀራ ነገር ሆኖብኝ እጓዛለሁ ፣ እጓዛለሁ ፣ እጓዛለሁ … እንደ ጨው ተበትነናልና ስፍር ቁጥር የሌላቸው ወገኖቸን በየሔድኩበት ከተማ  ፣ በቀለጡ በርሃዎች እና መንደሮችም ወንድም እህቶቸን አገኛለሁ ! እንዲህ በማለዳ ወጌ ወጋወጉን ለተሞክሮ ሳካፍላችሁ ደግሞ ደስታ ይሰማኛል ! ህይዎት እንዲህ ይኖራል …

ሰላም

ነቢዩ ሲራክ

YeMaleda Weg

ኮሜዲያን ዶክሌ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ታወቀ

$
0
0

comedian temesgen battery
(ዘ-ሐበሻ) በቅርቡ ወደ ሰሜን አሜሪካ የመጣው እና ከስራ ባልደረባው ከኮሜዲያን ተመስገን ባትሪ ጋር በመሆን የኮሜዲ ሥራውን እየተዟዟረ በማቅረብ ላይ የሚገኘው ኮሜዲያን ዶክሌ (ወንደሰን ብርሃኑ) በቨርጂኒያ አሌክዛንደሪያ ሆስፒታል ኢመርጀንሲ ሩም ገባ በሚል የተሰራጨው መረጃን ተከትሎ ዘ-ሐበሻ ባደረገችው ማጣራት ኮሜዲያኑ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ አረጋግጣለች።

ይህ ወሬ እንደተሰማ ዘ-ሐበሻ ኮሜዲያኑን ወደ አሜሪካ ወዳስመጣው ያቆብ ፕሮሞተር ደውላ የፕሮሞተሩ ስልክ ባይነሳም ከአዲስ አበባ አብሮት ወደመጣውና በቨርጂኒያ አንድ ቤት ውስጥ አብሮት ወደሚኖረው የሥራ ባልደረባው ኮሜዲያን ተመስገን ባትሪ ጋር በመደወል እንዳረጋገጠችው ኮሜዲያን ዶክሌ ትናንት ምሽት ከገባበት የኢመርጀንሲ ሩም በመውጣት አሁን እቤቱ ይገኛል። እንደ ኮሜዲያን ተመስገን ባትሪ ገለጻ በዶክሌ ላይ በ እግሩ ላይ በወጣች እባጭ የተነሳ አላራምድ ብላው ወደ ኢመርጀንሲ ሩም ሄዷል። ሆኖም ግን በተደረገለት ህክምና አርቲስቱ በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛል።

ለኮሜዲያን ተመስገን ዘ-ሐበሻ ‘እንደሚታወቀው በሰሜን አሜሪካ እየተዟዟራችሁ ከዶክሌ ጋር ሥራችሁን እያቀረባችሁ ነው፤ ይህ አደጋ ከሥራችሁ ያቆማችሁ ይሆን?” በሚል ላቀረበችው ጥያቄ “አሁን ዶክሌ በመልካም ሁኔታ ላይ ስለሚገኝከሥራችን የሚያግደን ነገር የለም” ብሏል።

ከኮሜዲያን ተመስገን ጋር በስልክ ያደረግነው ምልልስ የሚከተለው ነው፦
[jwplayer mediaid="10960"]


“ሕወሓት ከመለስ ሞት በኋላ እየተዳከመ ያለ ድርጅት ነው፤ ኢህአዴግ ለዘለዓለም መግዛት አለብኝ የሚል ድርጅት ነው”ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ

$
0
0

ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ ከህወሓት ጋር 17 ዓመታት በትግል ያሣለፉ እና ከፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዷ ነበሩ፡፡ በ1993 ዓ.ም ከፓርቲው ከተሰናበቱ አባላት አንደ ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት የ“አረና” ፓርቲ አባል የሆኑት ወ/ሮ አረጋሽ በአጠቃላይ ጉዳዮች ዙሪያ ከ“ሎሚ” አዘጋጅ ቶማስ አያሌው ጋር ያደረጉት ቆይታ የመጀመሪያ ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
ሎሚ፡- የኢህአዴግ ጭቆናና፣ አፈና፣ የተንሰራፈው በመላው ሀገሪቱ ነው የሚል አቋም ካላችሁ፣ ብሔር ተኮር ፓርቲ የመሰረታችሁበት ምክንያት ምንድነው;
አረጋሽ፡- ፓርቲ የሚመሰረተው በአካባቢ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ መሰረት አድርጐ ነው፡፡ ተጨባጭ ሁኔታ ስል የማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ሰብዓዊ መብት፣ የኢኮኖሚ ችግሮችን ለመጥቀስ ፈልጌ ነው፡፡ ማንኛውም ድርጅት በዚህ መልኩ ነው የሚመሰረተው፡፡ አረናም በዚሁ መሠረት የተመሠረተ ፓርቲ ነው፡፡
aregash adane 2
ከሕወሐት ክፍፍል በኋላ አረና ሲደራጅ፣ ለአገራችን የታገልንለት ዓላማ ሙሉ በሙሉ ስላልተሣካ፣ ያልተሣካው እንዲስተካከል አለያም የተሻለ ለማድረግ የራሣችንን ጫና ማሣደር አለብን ብለን ነው አቋም የያዝነው፡፡ ስንደራጅ ሀገራዊ ፓርቲ የመመስረት ዓላማም ፍላጐትም ነበረን፡፡ ነገር ግን በነበርንበት ሁኔታ አገራዊ ድርጅት መመስረት ቀላል አልነበረም፡፡ ጠንካራ ርዕዮተ ዓለም፣ በጣም ወሣኝ አባላት ያሉት አገራዊ ድርጅት መመስረት አሁንም ቢሆን አስቸጋሪ ነው፡፡ ሀገራዊ ድርጅት የመመስረት ፍላጐት ቢኖረንም የነበርንበት ተጨባጭ ሁኔታ አልፈቀደልንም፡፡ በተግባር ስንመለከተው የብሔረሰቦች መብት ሙሉ ለሙሉ ባይከበሩም፣ ሀገራዊ ፓርቲ ለመመስረት ሁኔታዎች እስኪፈቅዱልን ድረስ ብለን አረናን መሰረትን፡፡
ይህን ካደረግን በኋላ አረናን ይዘን ቁጭ አላልንም፡፡ ሀገራዊ ፓርቲ ካልተመሠረተ የትግራይም ይሁን የሌላው ብሔር ብሔረሰቦች ችግር ይፈታል ብለን አናምንም፡፡ ሀገራዊ ፓርቲ የሚመሠረትበትን ሁኔታ መፍጠር አለብን ብለን ከሌሎቹ ኢትዮጵያ ውስጥ ህጋዊ እውቅና ካላቸውና በሰላማዊ መንገድ ከሚታገሉ ፓርቲዎች ጋር በአጭር ጊዜ ውይይት ጀመርን፡፡ መድረክ በሚባለው ድርጅትም የገባነው በዚሁ ምክንያት ነው፡፡
ሎሚ፡- ከክፍፍሉ በኋላ ተዘጋጅቶ የነበረው “ሕዝባዊ” የተባለ ጋዜጣ በምርጫ 97 በጋዜጣው ርዕሰ አንቀፅ ከገዢው ፓርቲ ይልቅ ቅንጅት ላይ ጠንካራ ትችት ታቀርቡ ነበር ይባላል፤ እንዲያ ተደርጎ ከሆነ ትኩረታችሁን ወደ ተቃዋሚ ፓርቲ ያነጣጠራችሁበት ምክንያቱ ምንነበር;
አረጋሽ፡- ከኢህአዴግ ይልቅ ወደ ቅንጅት ያተኮረ ነበር የሚለው አስተያየት ለኔ ትክክል አይመስለኝም፡፡ ጋዜጣውን በትክክል አንብቦ ተረድቶ የተሰጠ አስተያየት አይመስለኝም፡፡ ያኔ ኢህአዴግን ነበር የምንታገለው፡፡ ከዴሞክራሲ አንፃር፣ ከህግ ልዕልና አንፃር፣ ከመናገርና መደራጀት አንፃር፣ ከፕሬስ ነፃነት አንፃር… እነዚህን እና ሌሎች ተጨባጭ ሁኔታዎችን መነሻ እያደረግን በጋዜጣችን ጠንከር ጠንከር ያሉ አስተያየቶችን እንሰጥ ነበር፡፡ የ97 እንቅስቃሴ ሲመጣም ኢህአዴግ “ዴሞክራሲያዊ፣ ግልፅ እና ነፃ ምርጫ ይመጣል” ብሎ ከጀመረ በኋላ ኃይሉ ሲዛባበት፣ ስልጣኑ እየተንገዳገደ መሆኑን ሲረዳ ቀድሞ የገባውን ቃል ማጠፍ ጀመረ፡፡ እንዲያውም የመሸነፍ አዝማሚያ ሲያይ ባልተጠበቀ ሁኔታ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በቴሌቪዥን በመቅረብ “ኢህአዴግ አሸንፏል” ነበር ያለው፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፤ ፀረ-ዴሞክራሲ የሆኑ አዋጆችን አውጇል፡፡
ከዚህ በመነሣት ተገቢ አለመሆኑን በሚመለከት በርካታ ነገሮች ፅፈናል፡፡ “ይሄ የዴሞክራሲውን አካሄድ ማጥበብ እንደሆነ፣ ገና ቆጠራው ሣይጠናቀቅ እኛ አሸንፈናል ብሎ መናገር ኢ-ዴሞክራሲያዊ እና አምባገነናዊነት እንደሆነ፣ ተቃዋሚዎቹም ቢሆኑ በህጉና በአግባቡ መያዝ እንዳለባቸው፣ የሕዝብ ድምፅ በአግባቡ ሊቆጠርና ተግባራዊ ሊሆን እንደሚገባው፣ መሸነፉን አምኖ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መቀበል እንዳለበት በሚመለከት ደጋግመን ፅፈናል፡፡ ከዚህ አንፃር ካየነው ቅንጅትን የሚያጠቃ አቋም ነበራችሁ የሚለው አስተያየት አሳማኝ አይደለም፡፡ ቅንጅት ላይ ጫና ወይም ትኩረት ማድረግ ሳይሆን፣ ቅንጅቶች ምን ማድረግ እንዳለባቸው የጠቆምንበት ሁኔታ ነበር፡፡
ሎሚ፡- ፓርቲያችሁ አረና በ2006 ዓ.ም. ምን ዓይነት እንቅስቃሴ እያደረገ ነው;
aregash adane 1አረጋሽ፡- አረና ጳጉሜ ውስጥ ሦስተኛ ጉባዔውን አካሂዷል፡፡ አንዳንድ ሕገ ደንቦቹን አስተካክሏል፤ የሚሻሻሉ ነገሮችን አሻሽሏል፡፡ አዳዲስ አመራሮችን መርጧል፤ ለምሣሌ የቀድሞው የፓርቲው ሊቀ-መንበር በአዲስ እንዲተኩ አድርገናል፡፡ ወጣቶችን ወደ አመራር አምጥተናል፡፡ ለውጥና የማሸጋሸግ ስራ ተሰርቷል፡፡ ወጣቱ ወደ ፖለቲካው መድረክ ቢመጣ የትግል ሂደቱን እየተላመደና እየተማረበት ይሔዳል በሚል ነው፡፡ እኛ የወደፊት መሪዎች አይደለንም፤ የወደፊት መሪዎቹ ወጣቶቹ ናቸው፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፤ የዕቅድ አቅጣጫዎችም ተቀምጠዋል፡፡ በተቻለ መጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሀገራዊ ፓርቲ እንዲፈጠር የማድረግ ስራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል እያደረግንም ነው፡፡ በእውነቱ ይህ በእኛ ፍላጐት ብቻ የሚወሰን አይደለም፡፡ የሌሎቹም ፍላጐት ያስፈልጋል፡፡
እንዲሁም ሀገሪቱ የወጣት ምሁራን የተሻለ አመራር እንድታገኝ የማድረግ ኃላፊነት አለብን የሚሉ ግለሰቦችን የማሰባሰብ አቅም ያስፈልጋል፡፡ እኛ ይህ ሁኔታ እንዲፈጠርና እንዲመቻች ካሉት ፓርቲዎች ጋር በፕሮግራሞቻችን ተስማምተን ሀገራዊ ፓርቲ እንዲመሠረት እንቅስቃሴ እያደረግን ነው፡፡ ለዚህ ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ ንዑስ ኮሚቴ ከኛም ከሌሎችም ድርጅቶች ተውጣጥቶ እየተንቀሣቀሰ ነው፡፡ የአረና ጉባኤ አንደኛው ማጠንጠኛም ይሔ ነው፡፡ ሌላው የጉባኤው አጀንዳ ፓርቲው በተጠናከረ መልኩ ከሕዝቡ ጋር መገናኘት፣ እስከ ገጠር የዘለቀ እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳለብን የሚያሳስብ ነው፡፡ ይሁንና እነዚህን ነገሮች እንዳናደርግ የሚያግዱን ችግሮች አሉ፡፡ አንዱ የገንዘብ አቅም ነው፡፡ ህዝቡ ከስጋትና ከፍራቻ አልወጣም፡፡ ቢሆንም ባለን አቅምና ችሎታ በትናንሽ ከተማዎች ስብሰባ በማድረግ እንቅስቃሴያችንን ጀምረናል፡፡ እንዲሁም ከመድረክ ጋር በመሆን በናዝሬት፣ ሀዋሳ፣ መቀሌ ከተማዎች ሕዝባዊ ስብሰባ ለመጥራት በመንቀሳቀስ ላይ እንገኛለን፡፡
ሎሚ- ፓርቲያችሁ ባደረገው ጉባኤ ማጠናቀቂያ ላይ ባወጣው መግለጫ “ውህድ ፓርቲ” እንደሚያስፈልግ ደጋግሞ ገልጿል፡፡ ወደዚህ አቋም የመጣችሁበትን አቋም ቢያብራሩልን;
አረጋሽ፡- ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት ሀገራዊ ድርጅት ቁልፍ ሚና አለው፡፡ በተበታተነ መንገድ በክልሎች ብቻ ተደራጅቶ ለውጥ ማምጣት ከባድ ነው፡፡ ስለዚህ ያሉት ችግሮች ሀገራዊ መፍትሔ ካልተቀመጠላቸው በስተቀር በክልል ደረጃ ብቻ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የምንፈልገውን ለውጥ አናመጣም፡፡ ጠንካራ አመራር ያስፈልጋል፡፡ ሀገር የሚቀይር ኃይል ያስፈልጋል፡፡ ሀገር እንዲቀየር ከተፈለገ ሀገራዊ ፓርቲ መኖር አለበት፡፡ ይሕም ማለት ውህደት መፍጠር ማለቴ ነው፡፡ ውህደት ሲኖር ነው በሀገርም ሆነ በክልል ደረጃ ያለውን ችግር አብሮ መፍታት የሚቻለው፡፡ በግንባር ደረጃ ብቻ አብሮ መታገል መንግስትን ላይፈትነው ይችላል፡፡ ተገቢውን ጫና አሳድሮ መንግስት ነፃና ግልፅ የሆነ ምርጫ እንዲያደርግ ሊያስገድደው አይችልም፡፡ ስለዚህ ሀገራዊ ፓርቲ ተፈጥሮ፣ ሀገራዊ አመራር ካልተመሠረተ ለየብቻ በሚደረግ ትግል የሚመጣ ለውጥ የትም አያደርስም በሚል ነው ለውህደት የተነሳነው፡፡
ሎሚ፡- የህወሓት መመስረቻና መቀመጫ በሆነው ትግራይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በርካታ ወጣቶች በማህበራዊ ድረ ገፆችና በሌሎች ሚዲያዎችም በገዢው ፓርቲ ላይ ተቃውሟቸውን እየገለፁ ነው፡፡ ይሔ ምንን ተከትሎ የመጣ ይመስልዎታል;… በአንፃሩ የሴቶች እንቅስቃሴ የማይንፀባረቀውስ ለምንድን ነው;
አረጋሽ፡- የዚህ ዓይነቱ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ እየሄደ ነው፡፡ መሠረታዊ መነሻውም ትግራይ ውስጥ ያለው ኢ-ፍትሃዊ ስርዓት አካሄድ ነው ብዬ ነው የማምነው፡፡ ያ ሁኔታ በወጣቱ ላይ ተንፀባርቋል፡፡ ሕዝቡ ደጋግሞ የታገለ ሕዝብ ነው፡፡ ብዙ መስዋዕትነት የከፈለ ሕዝብ ነው፡፡ መስዋዕትነት የከፈለው ደግሞ የዲሞክራሲ፣ የኑሮ፣ የኢኮኖሚ ለውጥ እንዲመጣ ነው፡፡ ሕዝቡ ከዚህ በኋላ የምንበደልበት ስርዓት አይኖርም ብሎ ነው ሦስትና አራት ልጆቹን ከአንድ ቤት ልኮ ያታገለው፡፡ ያንን እምነት ይዞ የታገለ ሕዝብ፣ መልሶ ለዚህ ዓላማ ነው የታገልኩት የሚለው ድርጅት (ህወሓት) ሲጨቁነው ምሬት ሊሰማው የማይችልበት ምክንያት የለም፡፡
አስተዳደሩ ሕዝቡን ከሌሎች ክልሎች በበለጠ ተቆጣጥሮና ወጥሮ ይዞታል፡፡ በትግራይ ውስጥ ሁሉንም ሕዝብ በወጣት፣ በሴቶች፣ በተለያዩ ማህበሮች አደራጅቶ ከህወሓት ትዕዛዝ ውጭ እንዳይመራ እየተደረገ ነው፡፡ የወገንተኝነት፣ የዝምድና ሥራ፣ የሙስናም ጉዳይ አለ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ችግሬ እየተሰማ አይደለም የሚል ስሜትም አለ፡፡ ይህንን መሠል እሮሮዎች እየወጡ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ የተማረው ክፍል በተወሰነ መልኩም ቢሆን የነፃነት ስሜት ስላለው ያንን ማስተጋባት ጀምሯል፡፡ ተቃውሞው ከዚህ የመነጨ ይመስለኛል፡፡ ሌላኛው የሕወሓት ሥጋት ተጨማሪ ኃይል እየፈጠረ ያለው የአረና እንቅስቃሴ ነው፡፡ የአረና እንቅስቃሴ ወጣቶችን እያደራጀ ነው፤ ወጣቶችን ወደ አመራርነት እያመጣ ነው፡፡ ዓላማውን እየገለፁ ነው፤ ትግራይ ውስጥ ያለውን ችግር አብሮ እየተወያየበትና እየመከረበት ነው፡፡ ይሔ ደግሞ የበለጠ እንዲነቃቃ አድርጐታል፡፡ በተለይ እኛ የቀድሞ የህወሓት አባላት ለሕዝብ ችግር መታገል አለብን ብለን መንቀሳቀሳችን ትልቅ ራስ ምታት ሆኖባቸዋል፡፡ የዚህ ሁሉ ድምር፣ የሕዝቡ ምሬት፣ የእኛ እንቅስቃሴ ተዳምሮ ወጣቱን እንዲነሳሳ እያደረገው ነው፡፡
የሴቶች ተሳትፎን በሚመለከት… አረና ከተመሰረተ ገና አምስት ዓመቱ ነው፡፡ እንቅስቃሴያችን ደግሞ ውሱን ነበር፡፡ ሴቶችን ማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡ በማህበር ተደራጅተዋል፤ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ሳይቀር በሊግ (በአንድ ለአምስት) ተጠርንፈዋል፡፡ ይሕም ሆኖ የአረና አባላት የሆኑ ሴቶች አሉ፡፡ በአመራር ደረጃም የተወሰኑ አሉ፡፡ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴያችን እየጠነከረ ሲሄድ ሴቶቹ የመምጣታቸው ነገር ይጨምራል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ኢህአዴግ ዋነኛ ኃይሎቹ ሴቶች ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ በልማት፣ በማህበር አደራጅቶ እንዲንቀሣቀሱ ያደረገው ሴቶችን ነው፡፡ ይህም ጥቅም ፈጥሮለታል፡፡ እኛ ይህን አዝማሚያ መስበር አለብን፡፡ ግን በሂደት ለውጦች ተፈጥረው የሴቶች እንቅስቃሴም እየጐላ መምጣቱ አይቀርም፡፡
ሎሚ፡- በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሴቶች እንቅስቃሴ በማይታይበት ሁኔታ እንደ ብርቱካን ሚደቅሳና፣ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ያሉ ሴቶች እስከ መታሰር የሚከፍሉትን መስዕዋትነት እንዴት ይመለከቱታል;
አረጋሽ፡- የእነሱ ወደ እስር ቤት መሄድ በተናጠል የሚታይ ነገር አይደለም፡፡ የኢህአዴግ መንግስት ስልጣኑን በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ መልቀቅ የማይፈልግ ድርጅት ስለሆነ፣ ለይስሙላ ዴሞክራሲ አለ፣ ነጻ ምርጫ እናደርጋለን እያለ በሚዲያ ቢያስተጋባም በተግባር ግን ዜሮ ነው፡፡ በሕዝብ ድምፅ ተሸንፎ ሥልጣኑን ለማስረከብ የተዘጋጀ ድርጅት አይደለም፡፡ ከስልጣን የመውረድ ስጋትና ፍራቻ ስላለው፣ ዴሞክራቲክ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን አይፈልግም፡፡ ኃይል ያለው ሀሳብን፣ ኃይል ያለው ፅሁፍን ይፈራል፡፡
የሕዝብ ተቀባይነት ያላቸው ድርጅቶች… እንዲጠናከሩ፣ እንዲያብቡ ወደ መድረክ እንዲመጡ አይፈልግም፡፡ ብዙኃኑን ሕዝብ ያንቀሳቅሳሉ ያላቸውን ሰዎች በአጭር ጊዜም ይሁን በረጅም ጊዜ ለይቶ ያዳክማቸዋል፡፡ ምክንያቱም ሀሣባቸው ወይም የሚያነሱት ጥያቄ የራሣቸው “የግል” አይደለም ብሎ ስለሚያስብና ሕዝብ ጋ ከደረሰ ችግር ይፈጥራል ብሎ ስለሚሰጋ በአጭሩ የመቅጨት ስራ ይሰራል፡፡
የብርቱካንም ይሁን የርዕዮት እንዲሁም የሌሎች የፖለቲካ ታሳሪዎች ሁኔታ ከኢህአዴግ ስጋት የመነጨ ነው፡፡ ምንም ዓይነት ሀሣብ እንዲስተጋባና እንዲሰማ አይፈልግም፡፡ አዲስ ሀሣብ ሕዝቡ ጋር ደርሶ ኃይል እንዲፈጥር አይፈልግም፡፡ በሽብር እና በሌሎች ምክንያቶች በማሳበብ ሊወጡበት የማይችሉበት ቦታ ውስጥ ያስገባቸዋል፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፤ ከማሰር ጐን ለጐን የማሳቀቅና ከመንገዳቸው የማስወጣት ሥራዎችም ይሰራል፡፡ በአጠቃላይ በብዙ መንገድ ይኮረኩማል፡፡ ኢህአዴግ ነፃና ግልፅ የሆነ ምርጫ አካሂዶ ሲሸነፍ ሊወርድ፣ ካልተሸነፈ ሊቆይ የተዘጋጀ ፓርቲ አይደለም፡፡ ለዘላለም እኔ ነኝ መግዛት ያለብኝ ብሎ የሚያምን ድርጅት ነው፡፡ ይሔንን አስተሳሰቡን የሚፃረረውን ድርጅትም ይሁን ግለሰብ ማጥፋት የለመደ ፓርቲ ስለሆነ የሚወስዳቸው እርምጃዎች ከዚህ ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡
ሎሚ፡- ህወሓት “የአዲስ አበባ እና የመቀሌ” በሚል ቡድን ለሁለት መከፈሉ ይነገራል፤ የኢህአዴግ “አስኳል” ነው የሚባለው ህወሓት ውስጥ መከፋፈል መከሰቱ የሚፈጥረው አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ውጤት ይኖራል;
አረጋሽ፡- በህወሓት ውስጥ ክፍፍል አለ፤ ለሁለት ተከፍሏል የሚባለውን ነገር ላውቀው አልቻልኩም፡፡ ክፍፍል አለ ብዬ ለመውሰድ ትክክለኛ መረጃ የለኝም፡፡ “ተከፋፍለዋል” የሚል እምነት የለኝም፤ አንድ ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ እንኳን ተከፋፍለው አንድ ሆነውም ለመዝለቅ የማይችሉበት ሁኔታ ላይ ናቸው የሚለው ጥያቄ ቢነሣ ነው የሚሻለው፡፡
aregash adane 3በአጠቃላይ ሕወሓት ከመለስ ሞት በኋላ እየተዳከመ ያለ ድርጅት ነው፡፡ ሁልጊዜም ደጋግመው “የጠ/ሚ መለስን ራዕይ እናስተገብራለን” ነው የሚሉት፡፡ ራዕይ ለተወሰነ ጊዜ ትቶላቸው ሊሆን ይችላል፡፡ ሁኔታዎች ግን በየጊዜው ነው የሚቀያየሩት፡፡ ከሁኔታውና ከጊዜው ጋር የሚሄድ “ራዕይ” ካልያዙ የያዙት እምነት የሚገድላቸው ይመስለኛል፡፡ አዳዲስ ሀሣቦችን፣ አዳዲስ አቅጣጫዎችን ከነባራዊው ሁኔታ ጋር እያስተሳሰሩ መሔድ ካልቻሉ ለውጥ ሊመጣ አይችልም፡፡ ሕዝብ የሚጠይቃቸውን ጥያቄዎች ግምት ውስጥ የሚያስገባ ራዕይ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ሕዝቡ ተበደልን ሲል፣ ዴሞክራሲ የለም ሲል የህግ ልዕልና የለም ሲል፣ ፍትህ የለም ሲል፣ ጉቦና ወገንተኝነት እየተስፋፋ ነው ሲል፣ መፍትሄ አምጡልን ሲል፣ “ሀገሪቱ በእድገት ላይ ነች፤ አንዳንድ ችግሮች ብቻ ነው፤ እነሱንም በሂደት እንፈታቸዋለን” የሚል ምላሽ እየሰጡ መዝለቅ አይችሉም፡፡ ተከፋፍለዋል የሚለው ግን እኔ የተከፋፈሉበትን ሁኔታ ስላላየሁ ስለሱ አስተያየት ለመስጠት ይከብደኛል፡፡
ሎሚ፡- የትግራይ ሕዝብና የህወሓት ግንኙነትስ ምን ይመስላል;
አረጋሽ፡- ህወሓት ከትግራይ ሕዝብ ጋር የተሳሰረ ታሪክ አለው፡፡ 17 ዓመት ሙሉ ሕዝቡ ታግሏል፡፡ አመራሩ ተለወጠ እንጂ አሁንም ሕዝቡ የችግሩ ገፈት ቀማሽ ነው፡፡ ያንን ሁሉ ትግል ያደረገው ደግሞ ደህና ስርዓት ይመጣል ብሎ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር አብሮ በመኖር ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊ የሆነ ስርአት ይመጣል ብሎ ነው መስዕዋትነት የከፈለው፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ደግሞ ህወሓት ይሔንን እንዳይቀጥል እያጠፋ፣ ኢ-ዴሞክራሲያዊ፣ ኢ-ፍትሃዊ እየሆነ፣ አፋኝ እየሆነ ነው ያለው፡፡ ከዚህ አንፃር የትግራይ ሕዝብ በህወሓት ላይ እየተማረረ ነው፡፡ መፍትሄ ስጡን እያለ ነው፡፡ ስብሰባ በተደረገ ቁጥር ችግሩን በስፋት ይገልፃል፡፡ እንዲሰሙትም እየጠየቀ ነው፡፡ ይሁንና ተደጋግሞ ጥያቄ ቢያቀርብም መፍትሄ ግን አላገኘም፡፡ በዚህ ምክንያት ቅሬታ እየተፈጠረ ነው፡፡ ጠንካራ የሆነ ድርጅት ከተፈጠረ የትግራይ ሕዝብ አብሮ ከመታገል ወደኋላ አይልም፡፡ አሁን ግን የእኛ አቅም ነው የሚወስነው፡፡ ሀገራዊ በምንለውና ይፈጠራል በምንለው ፓርቲ ዙሪያ የሚወሰን ነው፡፡ ለትግልም ሆነ ለመብቱ በሰላማዊ መንገድ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመታገል የትግራይ ሕዝብ ዝግጁ ነው፡፡ እኛ ጋ ድረሱ፤ ከተማ ብቻ ቁጭ አትበሉ እያለ ነው፡፡ አንድ ጊዜ አለን ትላላችሁ፤ ሌላ ጊዜ ትጠፋላችሁ የሚለው ጥያቄ ተደጋግሞ እየተነሳ ነው፡፡ የህወሓትና የትግራይ ሕዝብ ሁኔታም እየሻከረ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ የትግራይ ሕዝብ ለውጥ ፈላጊ ነው፡፡

የኢትዮጲያ ሰላም በአንድነታችን ላይ ነው (ገብሬሉ ተስፋዬ)

$
0
0

   ገብሬሉ ተስፋዬ ኖርዌ

The shadow of a supporter of Ethiopia's Unity for Democracy and Justice party (UDJ) is seen through an Ethiopian flag during a demonstration in the capital Addis Ababa

               የሚያኮራ የሚያስደስት ኢትዮጲያዊ አንድነት ሰሞኑን በተደረጉት የተለያዩ ሰላማዊ ሰልፎች ላይ አይተናል:: በሳውዲ አረቢያ እየተሰቃዩ ላሉት እህትና ወንድምቻችን ሀይማኖትና ዘርን ሳንለይ ያሳየነው የአንድነትና የቁጣ መንፈስ በጣም የሚያስደስት ነው:: ይሄ ያሳየነው አንድነት እና ቆራጥነት መቀጠል ሊኖርበት ይገባል:: ካልሆነ ግን የችግራችንን ሥር መንቀል አስችጋሪ ነው:: ሳውዲ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጲያዊያን ሲገደሉ፣ሲደበደቡ እና ሲደፈሩ በኢትዮጲያዊነታችው መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል:: ይሄ አይነቱ ኢሰብሐዊ ጥቃቶች በሰፊው እየደረሰ ያለ ሲሆን አንድነታችንን አጠናክረን ወደ ፊት ካልተጓዝን በተለያየ ቦታና ሀገር ኢትዮጲያዊነት ሊደፈር ይችላል::

       በመጀመሪያ መግለፅ የምፈልገው የኢትዮጲያን ክብር እና ማንነት ያጠፋው ወያኔና አመራሩ ናችው:: ስለዚህ ሁል ጊዜ ለሚፈጠሩት ችግሮች ሆይ ብለን መነሳት ብቻ በቂ መፍቴ አይሆንም ዋናው የችግሩን መንሴ ወያኔን ማስወገድ ነው:: ወያኔ ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ እህትና ወንድሞቻችን ተሰደዋል፣ተገድለዋል፣ተደፍረዋል ይሄ አዲስ ነገር አይደለም ሁላችንም ቢሆን እየሰማን እያየን የቆየነው ነገር ነው:: በአሁኑ ሰሀት በሳውዲ አረቢያ እየተደረገ ያለው ግፍ በዛ እንጂ በፊትም የነበረ ነው::የወያኔ አገዛዝ በሀገር ፍቅር ወይም በአንድነት ላይ የተመሰረተ አይደለም:: ይሄን በደንብ አድርጎ ለብዙ  አመታት አሳይቶናል:: የእናትና የአባቶቻችንን መሬት ለበአድ ሀገር ተወላጆች በመሸጥ፣መሀበረሰቡን በዘር እና በሀይማኖት በመከፋፈል፣እህትና ወንድሞቻችንን ለበአድ ሀገር አሳልፎ በመስጠት እና በመሳሰሉት ማየት ይቻላል::

 የአንድነታችን  መላላት መንሴወች እና መፍቴያችው ያልኩዋችውን ላብራራ

         አንደኛው እንደ ሰው እናም እንደ ኢትዮጲያዊ ለሚደርሱብን ኢሰብሀዊ ድርጊቶች አይሆንም፣አይደረግም የሚል ቆራጥ መንፈስ በውስጣችን መመንመኑ :: ይሄ ወደ ምን ያመራል ብንል ለገንዘብ እና ላአንዳንድ ጥቅማ  ጥቅሞች አገርን አሳልፎ ወደ መሸጥ:: ሰው እንደመሆናችን መጠን ቆም ብለን ልናስብ ይገባል  የወያኔ መንግስት የህዝብ  ጥርቅም መሆኑን:: ህዝብ ደግሞ የእያንዳንዱ ሰው ስብስብ ነው :: ስለዚህ እንደ ሰው ወያኔ ለሚያደርስብን ጥቃቶች አይሆንም ካልን ወያኔ የሚቀጥልበት ምንም ምክንያት አይኖርም:: ህዝብ የመረጠው መንግስት ደግሞ ለህዝቡ አንድነት የቆመ ነው::

   ሁለተኛው የወያኔ የአገዛዝ ስልት ነው:: በህዝብ ያልተመረጠ መንግስት(ወያኔ) ስልጣን ላይ ለመቆየት የተለያዩ  ጫናዊ የአገዛዝ ስልቶችን ይጠቀማል:: ከሁሉም የሚከፋው ዘርን ከዘር  እና ሀይምኖትን ከሀይማኖት  በማጣላት የህዝቡን አንድነት የሚበታትኑት ነው:: ለዚህም ምስክሩ ኢትዮጲያን ለቀው የሚሰደዱ ሰዎች የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ችግር ያላችው ብቻ አይደሉም ጥሩ የትምህርት ደረጃ እና ክፍያ ያላችውም ናችው::ይህ የሚያሳየው የደንነት እና የአንድነት ስሜታ በመሀበረሰቡ መመንመኑን ነው::መፍቴው ህዝብ የመረጠውን መንግስት ለማምጣት የበኩላችንን  አስተዋፆ ማድረግ:: ለምናደርጋችው ማንኛውም እንቅስቃሴወች ከማስተዋል ጋር ሊሆን ይገባዋል:: ሌላው እንደ አሜሪካ ካሉ ያደጉት ሀገራት በዘርም በቀለምም በሀይማኖት የማይገናኙ ህዝቦች እንዴት ለአንድ አላማ እንደቆሙ ትምህርት ከነርሱ በመውሰድ::

ሦስተኛው የኛ የሆኑ ችግሮችን ሌላ ሀገሮች መተው ችግራችንን ይፈቱልናል ብሎ መጠበቅ:: ይሄ እምነታችን ያመጣብን የራሱ የሆኑ ችግሮች አሉት፥ ከችግሮቹም አንዱ ያሀገራችንን ታሪክና ሚስጥራት አሳልፈን መስጥት:: ይሄ ደግሞ የተለያዩ የምእራብአዊ ሀገሮች በኢትዮጲያ ፖለቲካ እንደፈለጉት እጃችውን እንዲያስገቡና እንዲያሶጡ መንገድ ከፍቶላችዋል:: ይሄም ለአንድነታችን መላላት ትልቅ አስተዋጾ አለው::ለምሳሌ የጫካ ውስጥ ጎሾችን ብንወስድ በተናጠል ሳር በሚግጡበት ጊዜ በቀላሉ አውሬ ያጠቃችዋል ግን ሶስትም አራትም ሆነው ሲግጡ እራሳችውን በሁሉም አቅጣጫ ከአውሬ መከላከል ይችላሉ:: ስለዚህ መፍቴው ምንልያይበትን ነገር ከማየት አንድ የሚያደርገንን ነገር በማየት ችግራችን እርስ በእራስ በመወያየት መፍታት ነው::

አራተኛው ከታሪክ አለመማራችን ነው:: ኢትዮጲያ ባለ ብዙ ታሪክ ሀገር ስትሆን  የሚያስደስት ታሪክ እንዳላት ሁሉ የሚያስከፋም ታሪክ አላት:: ታሪካችንን በአግባቡ መርምረን አጥንተን ምንጓዝ ብንሆን ኖሮ አንዳይነት ችግሮች በተደጋጋሚ ባልመጡብን ነበር::መፍቴው የሰው አገርን ታሪክ ቀድሞ ከማወቅ ይልቅ የሀገራችንን ታሪክ አምብበን ተረድተን ተገንዝበን ለችግራችን ቀድመን መፍቴ ፈልገን መገኘት ይኖርብናል::

በኔ እምነት ከላይ የጠቀስኩዋችው አራት ነጥቦች ለአንድነታችን መላላት ቁልፍ ከሆኑ መሰረታዊ ችግሮች አንዳንዶቹ ናችው:: በአሁኑ ሰሀት ኢትዮጲያ እየሄደች ያለችበት ጎዳና አስከፊ እንደሆነ ለማንም ግልፅ ነው:: ስለዚህ እኛ ኢትዮጲያውያን ከምን ጊዜ በበለጠ ለአንድነታችን እናም ለሀገራችን  ሰላም የበኩላችንን አስተዋጾ ማድረግ ያለብን ሰሀት አሁን ነው::

ፍቅር ለኢትዮጲያ እዝብ!

“አና ጐሜዝ አሁንም ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ይቆረቆራሉ” –አቶ አስራት ጣሴ (የአንድነት ፓርቲ ዋና ፀሐፊ)

$
0
0

ከአቶ አስራት ጣሴ (የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ)

ከአና ጐሜዝ ጋር ከአንድ ሠዓት ተኩል ለማያንስ ጊዜ ነው የቆየነው፡፡ የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባላት ከእኛ ጋ የተገናኙት ገለፃ ለማድረግ አስበው ሣይሆን የእኛን አስተያየት ለመስማት ነበር፡፡ ውይይቱ፣ ኢትዮጵያ ያለችበትን ተጨባጭ ሁኔታ፣ የፖለቲካ ምህዳሩን እና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችን የሚዳስስ ነበር፡፡ በወቅቱ ከሞላ ጐደል ተደጋጋፊ እንጂ የሚቃረኑ ሀሣቦች አልተነሱም፡፡ በእኔ በኩል፣ በኢትዮጵያ ሰላማዊ ትግል በከፍተኛ ችግርና አደጋ ላይ እንደሚገኝ፣ ኢትዮጵያም መስቀለኛ መንገድ ላይ እንደሆነች፣ ከፊታችን አሳዛኝና አስጊ ሁኔታዎች እንዳሉ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት ሕዝቡ ሰላማዊ ትግሉን አስመልክቶ ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታዎች እያሣየ መሆኑን ገልጫለሁ፡፡
Ana Gomez
“ሰላማዊ ትግል” የሚለው “ሰላማዊ እንቅልፍ” የሚል ደረጃ ላይ ለመድረሱ ዋነኛ ምክንያቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትከሻቸውን ታስረው ለመንቀሣቀስ ያለመቻላቸው ነው፡፡ የህዝባዊ ስብሰባዎች እና የሰላማዊ ሰልፎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ መታገድ፣ የአዳራሽ መከልከል፣ ልሳናችንን እንዳናሳትም መታገድን ጨምሮ በርካታ ሕገ መንግስታዊ ጥሰቶች እየተፈጸሙብን ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ሕገ መንግስቱን እየጣሱ ነው እየገዙን ያሉት፡፡ ሕገ መንግስቱ እየተተገበረ ነው የሚያስብል ሁኔታ የለም፡፡ ከድጡ ወደ ማጡ እየገባ ነው ያለው፡፡ ነገሮች ተባብሰዋል፡፡
የስልጣን ኃይል ሚዛኑ በማን እጅ ላይ ይገኛል ብሎ መጠየቅ እስኪያስፈልግ ድረስ ሁሉም ነገር ተወሳስቧል፡፡ በሚኒስትር ደረጃ የተቀመጡት ሲቪሎቹ ናቸው ወይስ ከጀርባ የሚያስተዳድሩን አሉ? ሂደቱ ሀገሪቱን ወዳልተፈለገ ቀውስ ሊወስዳት የሚችል ትልቅ አደጋ ነው፡፡
ከአና ጎሜዝ ጋ በተተወያየንበት ወቅት የተቃዋሚ ፓርቲ አንድ ተወካይ ብቻ በፓርላማ እንደሚገኝን ተናግሬያለሁ፡፡ አስቀድመውም ያውቁታል፡፡ በ1997 ዓ.ም. የተቀማውን ድምጽ ትተን 180 የሚሆኑ ተቃዋሚዎች በፓርላማው መቀመጫ ነበራቸው፡፡ አሁን ግን ወደ አንድ ወርዷል፡፡
ኤልሳቤት ሃይኒ የተባለች የቢቢሲ ጋዜጠኛ ያነሣችውን ጥናት ለአና ጎሜዝ አሳይቻቸው ነበር፡፡ አንድ ፓርቲ በምርጫ ከ51-59 ፐርሰንት አግኝቶ ካሸነፈ ታላቅ ድል ነው፡፡ ከ60-69 አምጥቶ ካሸነፈ “ዝረራ” የሚባል ውጤት ነው፡፡ ከ70-79 አምጥቶ ካሸነፈ ደግሞ የሕዝቡን ጥያቄዎች የመለሰ ፓርቲ ነው፡፡ ከ80-89 የሚያገኝ ፓርቲ ግን የሚፈራ፣ አምባገነን፣ ጉልበተኛ ፓርቲ ነው፡፡ ከ90-99 ፐርሰንት ከተገኘ ደግሞ ምርጫ አልተካሄደም ማለት ነው ይላል፡- ጥናቱ፡፡ በኛ ሀገር ይኸው “99” አልፎ ዜኀር ነጥብ ስድስት ሁሉ ተጨምሮበታል፡፡ ስለዚህ ይሄ በግልፅ የሚያሣየው ፍፁም የዴሞክራሲ ስርዓት መጣሱን ነው፡፡ ምህዳሩ ተዘግቷል፡፡ ተደፍኗል፡፡

አስራት ጣሴ

አስራት ጣሴ

የተቃዋሚ ፓርቲዎች በየጊዜው የምናቀርባቸው የውይይት እና የእንደራደር ጥያቄዎች ከስልጣን ጋር ግንኙነት የላቸውም፡፡ ሀገራዊ አጀንዳዎች ናቸው፡፡ ብሔራዊ ውይይት፣ ብሔራዊ ንግግር ይከፈት ብለን ደጋግመን ብንጠይቃቸው ባለሥልጣናቱ አሁንም ያሾፋሉ፡፡ “የምርጫ ስነምግባር ደንብ” ፈርሙ እንባላለን፡፡ እንኳን “የምርጫ ስነምግባር ደንብ” ይቅርና የማንወደውን፣ እየተጐዳንበት ያለውን “የፀረ ሽብር አዋጅ” ተቀብለን ነው የምንተዳደረው፡፡ ምክንያቱም በሕግ የተደነገገ ነው፡፡ እንዴት ተደርጐ ነው “የምርጫና ስነምግባር ህግ” በምክር ቤት ጸድቆ በነጋሪት ጋዜጣ በወጣ ህግ ለይ ዳግም ፈርሙ የምንባለው? የሚል ሀሳብም አንስቻለሁ፡፡
መንግስት “ፀረ ሽብር” አዋጁን የማጥቂያ መሣሪያ አድርጎታል፡፡ ሽብርተኝነት የአውሮፓም፣ የአሜሪካም ከፍተኛ ስጋት በመሆኑ የፀረ ሽብር ህግ አውጥተዋል፡፡ ወደ እኛ ሃገር መለስ ስንል የፀረ ሽብር ሕጉ የወጣው ሽብርተኞችን ለመቅጣት ብቻ ሳይሆን፣ ሰላማዊና ሕጋዊ ፓርቲዎችን ጭምር ለማጥቃት ነው፡፡
ሽብርተኝነትን በማንኛውም መልኩ፣ በየትኛውም ገፅታው እንቃወመዋለን፡፡ ሽብርተኝነት ምን እንደሆነ እናውቃለን፡፡ በአፍጋኒስታን፣ በፓኪስታን፣ በኢራቅ፣ በናይጄሪያ /ቦኮ ሀራም/ እናውቀዋለን፡፡ እዚህም በሕዝብ፣ በህፃናት፣ በእርጉዝ ሴቶች፣ በሽማግሌዎች፣ በወጣቶች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት እናውቀዋለን፤ እንቃወማለንም፡፡ ኢትዮጵያውያን በባህላችን፣ በአስተዳደጋችን፣ በኃይማኖታችን፣ በእምነታችን… ለሽብርተኞች የተጋለጠ ስነ ልቦና የለንም፡፡ “ሽብርተኝነት” ይምጣብን የሚል ልመና ካልተያዘ በቀር ኢትዮጵያዊ ሽብርተኝነት የለብንም፡፡ የ“ጸረ ሽብር” አዋጁ በሽብርተኝነት ከፈረጃቸው ፓርቲዎች መካከል… ለአብነት ግንቦት 7፣ ዋና መቀመጫው በአሜሪካና አውሮፓ ከተማዎች ነው፡፡ ይሄ እንቆቅልሽ ይሆናል፡፡ አወሮፓውያን ከተማዎቻቸውን ለአሸባሪዎች ምሽግነት መርጠዋል ማለት ይሆን?
ሌላ እንቆቅልሽም አለ፡፡ ስርዓቱ “ሽብርተኛ” ብሎ ያሰራቸው ሰዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ሽልማቶችን እና ክብሮችን እያገኙ ነው፡፡ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት አለሙ፣ አንዱአለም አራጌ… ወዘተ በፀረ ሽብር አዋጁ ነው የታሰሩት፡፡ በ”ሽብርተኝነት” የተፈረጁት ግን በአሜሪካና፣ አውሮፓ ከተማዎች እንደፈለጋቸው እየተዘዋወሩ ነው፡፡ አውሮፓና አሜሪካ ሽብርተኞችን እየደገፉ ነው ማለት ነው?
የፖለቲካ ምህዳሩ ከድጡ ወደ ማጡ እየገባ ነው፡፡ የሕዝብን ችግር፣ እሮሮ በሳዑዲ አረቢያ በዜጐቻችን ላይ የሚደርሰው እልቂት፣ የስራ አጥነት፣ በስታቲስቲክስ ማሣየት ይቻላል፡፡ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ የኑሮ ውድነት፣ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ የሙስና መንገስ፣ የስርዓቱ መገለጫ ሆኗል፡፡ እነዚህ ጉዳዮች የአውሮፓ ህብረትን ትኩረትና ዕይታ ሊስቡ ይገባል፡፡ ይሄን የምንለው ግን ትግሉን ታገሉልን ለማለት አይደለም፡፡ ትግሉ የራሣችን ነው፡፡ ትግሉ የኢትዮጵያውያን ትግል ነው፡፡ ነገር ግን እናንተም ደግሞ ባላችሁ ደረጃ፣ ባላችሁ የግንኙነት መስመር፣ የሚደረገውን ነገር ለማድረግ ጥረታችሁን ቀጥሉ ብለናቸዋል፡፡ የተወሰነ ድጋፍ ካልተደረገ ወደፊት ሊመጣ የሚችለው ችግር ሁላችንንም ጉዳት ላይ የሚጥል ነው፡፡ ጉዳቱ ስርዓቱን የሚመሩት ሰዎችንም ጭምር የሚምር አይደለም፡፡
አና ጐሜዝ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ያላቸው ግንዛቤና የመቆርቆር አቅም አሁንም ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተረድቻለሁ፡፡ በውይይቱ ወቅት እንኳ ከሌላ የአውሮፓ ፓርላም አባል ጋር ያለመስማማት ሁኔታን አይቼባታለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብና፣ ኢትዮጵያ ልታከብራቸው ከሚገቡ በዓለም ላይ ከፍተኛ የፖለቲካ ስብዕና ካላቸው ሰዎች መካከል አንዷና ትልቋ አና ጐሜዝ ናቸው ብዬ አምናለሁ፡፡ ጐሜዝ የኢትዮጵያን ሁኔታ በቅርብ ይከታተላሉ፡፡ ለኢትዮጵያ ያላቸው ተቆርቋሪነት ከ1997 ዓ.ም. ከነበረው የበለጠ ነው፡፡ የሰጧቸው ቃለ ምልልሶች ዛሬም ለኢትዮጵያ ሽንጣቸውን ገትረው እንደሚከታተሉ ያመላክታሉ፡፡
በውይይቱ ወቅት “እኔ እኮ ዛሬ ኢትዮጵያ ለመግባት የቻልኩት አቶ መለስ በሕይወት ባለመኖራቸው ነው፡፡ በሕይወት ቢኖሩ እዚህ ሀገር አልገባም” ነበር ያሉን፡፡ ከፍተኛ ጥንካሬና ተቆርቋሪነት ነው ያየሁባቸው፤ ውይይታችን የታሰሩት የፖለቲካ እስረኞችን ጭምር የሚመለከት ነበር፡፡
የአውሮፓ ፓርላማ ልዑካን ቡድን ኃላፊ በስብሰባው ላይ አልተገኘችም፡፡ እና ምክትሏ ሆና ነው ስብሰባውን የመራችው፡፡ “ኃላፊዋ በአሁኑ ሰዓት እዚህ ስብሰባ ላይ ያልተገኘችው ቃሊቲ እስረኞችን ለመጠየቅ ሄዳ ነው” ብላን ነበር፡፡ ከዚህ ቀደም የአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ተወካዮች መጥተው፣ ጠ/ሚኒስትሩ ከፈቀዱ በኋላ “ቃሊቲ” ሄደው ተከልክለው ሣይገቡ ነው የተመለሱት፡፡ እርሷም በዛው እለት በዚህ ጉዳይ ተበሣጭታ ወደ ሃገሯ ተመልሣ ለምክትሏ ስለሁኔታው ገልጻላት ነበር፡፡ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የእስረኞቹን ጉዳይ በበቂ ለማስረዳት ሞክሯል፡፡
የአውሮፓ ፓርላማ በኢትዮጵያ ጉዳይ ያላቸው እውቀት አናሳ ነው፡፡ የሚያውቁት ጥቂቱን ነው፡፡ ግንዛቤ አላቸው ከተባለ ደግሞ ብዙ ትክክል ያልሆነ መረጃዎችን የያዘ ነው፡፡ ለምሣሌ ሀገሪቱ በልማት እየተራመደች መሆኗን፣ ኢትዮጵያ የአውሮፓ የፀረ ሽብር ከፍተኛ አጋር መሆኗን፣ የአፍሪካ መዲና መሆኗን… ይሄም የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ እንሚያሣይ የሚገልፁ አሉ፡፡ የአና ጐሜዝን ሩብ ያህሉን የማያውቁ አሉ፡፡ አብዛኛዎቹ ከኛ ለመስማት ስለነበር ፍላጐታቸው የሚያውቁትን ለኛ ለመናገር አስፈላጊ አድርገው ላይመለከቱት ይችላሉ፡፡ በውይይቱ ወቅት ሁሉም ጊዜ ሰጥተው በጥሩ ሁኔታ ነው ያዳመጡን፡፡ በትኩረት ያነሱት ግን በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን መብዛት ነው፡፡

ቴዲ Vs ምኒልክ፡ ስለ ጥቁር ሰው ወይንስ ስለ ጥቁር ገበያ? –ከታምራት ነገራ (ጋዜጠኛ)

$
0
0

ቴዲ አፍሮ ዳግማዊ ምኒልክን አስመልክቶ ለዕንቁ መጽሄት የሰጠውን ቃለ መጠይቅ ተከትሎ ሱናሚ ሊባል የሚቻል ንትርክ ስለ ቴዲ እና ስለ ዳግማዊ ምኒሊክ በሶሻል ሚዲያ ተናፍአል፡፡ ሰሞኑ ደግሞ የዳግመዊ ምኒልክ ያረፉበት መቶኛ ዓመት የሚታሰብበት መሆኑ ለሱናሚው ትልቅ ድምቀት ሰጥቶታል፡፡
ቴዲ አፍሮ ጥቁር ሰው ከሚለው አልበሙ ወዲህ ስለዳግማዊ ምኒልክ በተለያዩ ቦታዎች ተናግሯል፡፡ እኔን ግን ከቴዲ አፍሮም ፣ ከዳግማዊ ምኒሊክም፣ ከጥቁር ሰው አልበምም በእጅጉ የሳበኝ የዳግማዊ ምኒልክ ተዋስዖ (Discourse) ነው፡፡ በተለይም ተዋስዖው እየተካሄደ ያለበት ገበያ በእጅጉ ስቦኛል፡፡ አንድን ተዋስዖ ስናስተውል የተዋስዖውን በርካታ ክፍሎች ለያይተን ልናይ እንችላለን፡፡ ለምሳሌ የአንድን ተዋስዖ ይዘት የሚያጠና ሰው በተዋስዖው ውስጥ ጎልተው በተደጋጋሚ የሚታዩ ሐሳቦች፣ ቃላት፣ እና ዝንባሌዎች ያጠናል፡፡ በተያያዥነትም በተዋስዖው ዙሪያ ወሳኝ የሚባሉትን መልዕክት አስተላላፊ ምርቶች ለምሳሌ ዘፈኖች፣ ፊልሞች፣ አልበሞች፣ መጽሐፍትን፣ መፈክሮች፣ እና ፖስተሮች ሊያጠና ይችላል፡፡ በተዋስዖው ዙሪያ ያሉ ተዋናዮች ላይ ማተኮር የሚፈልግ ሰው ደግሞ ተዋስዖውን የሚያንቀሳቅሱትን የሐሳብ አመንጭ እና አከፋፋይ ጋዜጠኞች፤መጽሄቶች፤ ፀሐፍት፤ ምሁራን ፤አርቲስቶች ዙሪያ ጥናቱን ያተኩረል፡፡ ልክ እንደዚሁ አንድ ሰው አንድ ተዋስዖ የሚካሄድበትን ገበያ አተኩሮ ማየት ይችላል፡፡
Teddy afro minilik
ገበያ የሚለውን ቃል የምጠቀመው በተዋስዖው ውስጥ ያለውን ትርፍ ወይንም ኪሳራ ብቻ ለማሳየት ሳይሆን ተዋዖውን በሚያካሂዱት ግለሰቦች፣ ተቋማት፣ ቡድኖች እና ሐሳቦች መካከል የሚደረገውን ግብይት የሚካሄድበትን ሥርዓት (System) ለማመላከት ነው፡፡ እንደ እኔ እንደ እኔ ወቅታዊው፣ ትልቁ፣ እና እውነተኛው ጥያቄ ቴዲ፣ ጃዋር፣ በቀለ፣ ጫልቱ፣ እና አብደላ ስለ ዳግማዊ ምኒልክ ምን አለ? ምን አለች? ምን አሉ? አይደለም፡፡ ስለ ዳግማዊ ምኒልክ በክፉም ኾነ በደጉ መናገር እስከ ዛሬ ድረስ በኢትዮጵያ እንዴት ሱናሚ ማስነሳሳት ቻለ ? ስለ ዳግማዊ ምኒልክ እገሌ ገለመሌ ቢል ስለለምን ይኼን ያህል ያወዛግበናል? ይኼ ለእኔ ትልቁ እና ዋነኛው ጥያቄ ነው፡፡ ሱቅ በደረቴዎች የዳግማዊ ምኒልክ አድናቂዎችም ኾኑ ተቺዎች ስለ ዳግማዊ ምኒልክ የሚያስደስታቸውን፣ የሚያምኑበትን፣ እንደውም ሕይወታቸውን እስከሚሰጡለት ድረስ የሚያምኑትን ነገር እየተናገሩ፣ እያደረጉ እንደኾነ ሊወተውቱን ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በዳግማዊ ምኒሊክ አድናቂዎችም ሆነ አውጋዦች መካከል በሚደረገው ምልልስ ከመሳተፍ በመጠኑም ራቅ እና ከፍ ብለን ለማየት ከሞከርን ግን የዳግማዊ ምኒልክን አድናቂዎችም ኾነ ተቺዎችን የሚያስተዳድረውን ገበያ ለማየት እንችላለን፡፡ የዳግማዊ ምኒልክ ደጋፊዎችም ኾነ ተቺዎች በዳግማዊ ምኒልክ ተዋስዖ ዙሪያ ያላቸውን ሐሳብ በተገኘው አጋጣሚ እና ሥፍራ ከማስተላለፋቸው አልፈው በዳግማዊ ምኒልክ ዙሪያ አለኝ የሚሉትን ዕውቀት እና ግንዛቤ እንዴት እንደ ጨበጡት፣ ማን እንደሰጣቸው፣ ከየት እንዳገኙት፣ እና እንዴት እንደ ቀረበላቸው የሚኖራቸው ግንዛቤ እጅግ ውሱን ነው፡፡ አንድ ባለሱቅ በሱቁ ውስጥ ስላለው እቃ እና ዋጋ መጠነኛ ግንዛቤ ይኖረዋል ሊኖረውም ይገባል፡፡
ከዛ ባለፈ ግን አገሪቷን ወይንም ዓለምን ስለሚያንቀሳቅሰው የገበያ ሥርዓት፣ የገበያ መርህ፣ የገበያ ተቋማት፣ እና የገበያ ሕግጋት ኃይል ያለው ግንዛቤ እጅግ አነስተኛ ነው፡፡ ጩኸት፣ ትርምስ፣ምሥጢር፣ ግርግር፣ ፍርሀት… ዳግማዊ ምኒልክ እና ሥርወ መንግሥታቸው በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ካላቸው ሰፊ ተጽዕኖ ተነስተን ከተወያየን እስከ ዛሬ አይደለም ገና ለሚቀጥሉት ብዙ መቶ ዓመታት የማንግባባቸው በርካታ ነጥቦች ይኖራሉ፡፡ ለእኔ አሳሳቢው ጉዳይ ስለዳግማዊ ምኒልክ በሁሉም ጉዳዮች ላይ ሙሉ ስምምነት ላይ መድረስ አይደለም፡፡ አሳሳቢው ጉዳይ ለምን በውይይቱ መካከል ስክነት፣ እርጋታ፣ ዕውቀት፣ እና እውነት ጠፍተው በሥፍራቸው ጩኸት፣ ትርምስ፣ እና ድንቁር እንደ ምን ነገሡ ነው፡፡ እንደ እኔ እምነት በዳግማዊ ምኒልክ ዙሪያ የሚደረገው ተዋስዖ ከስክነት ትርምስ እንዲበዛው፣ በምክንያት ከሚናገሩ ሰዎች ጯኂዎች መድረክ እንዲያገኙ፣ አዋቂዎች ከአላዋቂዎች እንዳይለዩ፣ እውነት የያዙ ፈርተው ሐሰተኞች እንዲዳፈሩ ነገር ዓለሙ በአጠቃላይ ትርምስ እንዲበዛበት ሆን ተብሎ እተደረገ ነው፡፡
minilikበዚህ አጋጣሚ ርዕሰ ጉዳዩ የምኒልክ ተዋስዖ ስለኾነ እንደ ምሳሌ ልጠቀመው ብዬ እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ ብሔራዊ እና ፖለቲካዊ ተጽዕኖ ስላለው ማንኛውም ተዋስዖ በእርጋታ፣ በአመክንዮ እና በዕውቀት መናገር አይቻልም፡፡ ይህ ትርምስ የተፈጠረው ደግሞ በአብዛኛው ኾን ተብሎ በተገነባ የተዋስዖ ገበያ ሥርዓት እንጂ ዝም ብሎ በአጋጣሚ ከሰማይ ዱብ ያለ ክስተት አይደለም፡፡ የዳግማዊ ምኒልክን ተዋስዖ በምናየው እጅግ አጨቃጫቂ በኾነ መልኩ በመላው አገሪቷ እንዲተዋወቅ የተማሪዎች ንቅናቄ እና የሕወሃት መንግሥት ዋነኛውን ሚና ተጫውቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት በዳግማዊ ምኒልክ ዙሪያም ኾነ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ብሔርተኝነት ዙሪያ የምንሰማቸውን በርካታ ሀሳቦች ጥንስሳቸው በ1966ቱ የተማሪዎች ንቅናቄ ነው፡፡ በተማሪዎች የተነሱትን አንዳንድ ሐሳቦች ለምሳሌ መሬት ላራሹ የደርግ መንግሥት በከፊል ተግባራዊ ተደጓል፡፡ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት እስከ መገንጠል እና ሌሎች መሰል ሐሳቦችን ግን እንኳን ሊተገብር መኖራቸውንም እንኳ በአግባቡ ሳይናገር ዘመኑን ጨረሰ፡፡ በ1983ዓ.ም ሕወሃት ሥልጣን እንደያዘም ሻዕቢያን እና ኦነግን በግራ እና በቀኝ አስከትሎ በተማሪዎች ንቅናቄ የተጠነሰሱ በርካታ ሐሳቦችን በመላው አገሪቷ አወጃቸው፡፡ የፈለገውን ሕግ አደረገ ያልፈለገውን ችላ አለ፡፡ ሌዋታን፤ የገበያው ጌታ ማንኛውም መንግሥት በሚያስተዳድረው አገር ላይ በሚካሄደው ተዋስዖ ላይ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡ ኢትዮጵያን ለማስተዳደር የታደለ ማንም ግለሰብ እና ቡድን ደግሞ በኢትዮጵያ ተዋስዖ ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ በእጅጉ ኃያል ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል ኋይት ኃውስን ለመቆናጠጥ እድል የቀናው ፓርቲ በአሜሪካ ላይ በተለያዩ ጉዳዮች ተዋስዖውን ሊያነቃንቅ ይችላል፡፡ ነገር ግን አሜሪካንን የሚገዛው ፓርቲ በአሜሪካ ተዋስዖ ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ ኢትዮጵያን የሚያስተዳድረው ፓርቲ በኢትዮጵያ ተዋስዖ ላይ ከሚኖረው ተጽዕኖ ጋር ሲነጻፀር አቅሙ እጅጉን ውሱን ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ፓርቲ ዋይት ኃውስን ያዘ ማለት ኮንግረስ በእጁ ነው ማለት አይደለም፡፡ ስለዚህ በፖሊሲ እና በጀት መሰል ጉዳዮች ላይ ያለው ተጽዕኖ ይወሰናል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ተዋስዖን በመቅረጽ፣ በማዳበር፣ እና በማከፋፈል ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ሚዲያ፣ የሕትመት ቤቶች፣ እና መሰል ተቋማት በዋይት ኃውስ እጅ ውስጥ አይደሉም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አንድ ቡድን በድንገት ተነስቶ ወዲያውኑ የአገሪቷን ተዋስዖ ወደ ፈቀደው ርዕዮተ ዓለም (Ideological) ዝንባሌ መንዳት እንዳይችል የሚያደርጉት ዘልማዶች እና ሕግጋቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ የአሜሪካን ዶላር እና ሳንቲሞች ላይ የሕያው ፕሬዝዳንት ምሥል እንዳይቀረጽ ህግ አለ፡፡ ይህ ሕግ እንደ አሁኑ በይፋ ሕግ ሆኖ ከመጽደቁ በፊት የሕያው ፕሬዝዳንት ምሥል በዶላር ላይ እንዳይቀረጽ ያልተጻፈ ስምምነት ነበር፡፡ የኛ ብር መልኩ ስንቴ ተለዋወጠ? እንደ ኢትዮጵያ ዓይነት ማንበብ እና መፃፍን የመሰለ ዝቅተኛው የተዋስዖ መሳተፊያ ክህሎት ጭራሹኑ በሌለበት ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ገደብ የሌለው ሥልጣን በእጁ ላይ የወደቀ ቡድን በአገሪቷ ተዋስዖ ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ ልክ የለውም፡፡
በዚህ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የሚኖረው ጉልበትም የተዋስዖውን ይዘት ከመቆጣጠርም አልፎ ተዋስዖው የሚካሄድበትን ገበያ ሕግጋት እንደ ፈለገው መቆጣጠር እንዲችል አቅም ይሰጠዋል፡፡ ሕወሃት ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ በዳግማዊ ምኒልክ ዙሪያ የለኮሰውን ተዋስዖ ለአጃንዳ አጠር ሎሌዎች በሊዝ አኮናትሮ ገበያውን በጌታነት ከላይ ሆኖ እየዘወረው ነው፡፡ በአንድ አገር የተዋስዖ ገበያ ላይ እጅግ ተፈላጊው ግብ እውነትን ማግኘት ነው፡፡ እውነት በአንድ ጉዳይ ላይ የሚኖረንን የመረጃ ትክክለኝነት እና ሐሰትነት ላይ ብቻ የተገደበ ግንዛቤ አለመኾንኑ፤ በተዋስዖ ትንታኔ ውስጥ በአብዛኛው እውነት ስንል ከመረጃው ትክክለኝነት እና ስህተትነት ባሻገር ያሉ ሐሳቦችንም ይዳስሳል፡፡ በተዋስዖ ትንታኔ ውስጥ እውነት የተዋስዖው ተሳታፊዎች በመረጃው ላይ የሚኖረቸውን ትርጓሜ፤ በትርጓሜው ላይ ያላቸውንም ስምነት ሊያካትት ይችላል፡፡ ዳግማዊ ምኒልክ ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ዘመቱ የሚለውን አረፍተ ነገር እንውሰድ፡፡ ይህኑ አረፍተ ነገር አንድ የዳግማዊ ምኒልክ ነገር ሲነሳ ሆዱን ባር ባር የሚለው ወዳጃችን ብድግ ብሎ ዘመቻው ከእግዚአብሄር ለኢትዮጵያ የተሰጠ ቅዱስ ስጦታ ነው ብሎ ይህንኑ አረፍተ ነገር ሊተረጉመው ይችላል፡፡ የዳግማዊ ምኒልክ ነገር ሲነሳ የሚያንገሸግሸው ሌላኛው ወዳጃችን ደግሞ ብድግ ይልና ዘመቻው የተካሄደው ዳግማዊ ምኒልክ አያቶቼን እንዲያጠፏቸው በሰይጣን ስለታዘዙ ነው ብሎ ትርጓሜውን ይሰጠናል፡፡ እነዚህም ሆኑ ሌሎች በርካታ ትርጓሜዎች በዳግማዊ ምኒልክ ተዋስዖ ዙሪያ ይኖራሉ፡፡ እያንዳንዱ ቡድን የራሱን ትርጓሜ ይዞ ወደ ገበያው ይመጣል፡፡ ትርጓሜ ሊሸጥ፣ ትርጓሜ ሊገዛ፡፡ ሕወሃት ግን ገበያው ውስጥ ትርጓሜ ይዞ ከመቅረብ የተዋስዖ ቸርቻሪነት ከወጣ ሰነበተ፡፡
tedy afro new
እጅግ የሚያዋጣው የገበያውን ሥርዐት እና መዋቅር መቆጣጠር እንደ ሆነ ስለገባው ችርቻሮውን ለጉልቶች ሰጥቶ ኪራይ ይሰበስባል፡፡ ሕወሃት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የተዋስዖ ገበያ በነጻ ገበያ መርህ እንዲመራ ፈጽሞ አይፈልግም፡፡ ይልቁኑ የተዋስዖው ገበያ የሚያስተዳደረው ሻጭንም ሆነ ሸማችን በሚያደናብረው የጥቁር ገበያ መርህ ነው፡፡ በነጻ ገበያ መርኾዎች የሚንቀሳቀስ የተዋስዖ ገበያማ እውነትን ያገኛታል፡፡ እውነትን ያገኛት እርሱ ደግሞ አርነት ይወጣል፡፡ ለምሳሌ በአሁኑ ወቅት በገበያው ካሉን እልፍ አዕላፍ የምኒሊክ ትርጓሜዎች በተደጋጋሚ ጮክ ብለው የሚሰሙት ሁለቱ ጽንፈኞች ብቻ ናቸው፡፡ ምክንያቱም የኢትዮጵያ የተዋስዖ ገበያ የሚመራበት ሥርዐት የገበያው ተሳታፊዎች ወደግራም ሄዱ ወደቀኝ ወደ አንድ ትርጓሜ እንዲሰባሰቡ፤ በዚያ ትርጓሜ ዙሪያም አዲስ እውነት ቀርጸው የጋራ አገር እንዲገነቡ የሚፈልግ የገበያ ሥርዓት አይደለም፡፡ ሕወሀት ምን ዐይነት ሚዲያ፤ በምን ያህል መጠን እንደሚኖር ይወስናል፡፡ ያለማንም ሀይ ባይነት የትምህርት ሥርዐቱን ወደ ፈለገው የትርጓሜ አቅጣጫ ያሳልጣል፡፡ የአደባባዮች፣ የመንገዶች፣ የሀውልቶች፣ አስፈላጊ ከኾነ ደግሞ የከተሞችን ስም እርሱ ወደፈለገው የተዋስዖ ትርክት እንዲያፈገፍጉ በማድረግ ገበያውን እንዳፈተተው ያቆማል፣ ይበትንማል፡፡ የብሔራዊ መዝሙር፣ የባንዲራ፣ የብሔር ብሔረሰብ ክብረበዓላት ይቀርጻል፣ ያውጃል፣ ይበጅታል፣ ያስፈጽማል፡፡ የአየር በአየር ነጋዴዎች ለጥቂት ደቂቃ አገሪቷ ውስጥ ያሉት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከፓርቲው ገለልተኛ ቢሆኑ፤ ነፃ ሚዲያ በብዛት እና በጥራት ቢስፋፋ፤ የትምህርት ሥርዓቱ የሚቀረጸው አሁን ከሚታየው ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት በተለየ መልኩ ቢኾን ኖሮ ምን አይነት የተዋስዖ ገበያ በኢትዮጵያ እንደሚኖር ለመገመት አያዳግትም ፡፡ በምናባዊቷ ኢትዮጵያም እንኳን ስለዳግማዊ ምኒልክም ኾነ ስለጨለንቆ ሙሉ በሙሉ አንስማማም፡፡ ነገር ግን ውይይቱን የሚያስተናብሩት የጥቁሩ ገበያ የአየር በአየር ነጋዴዎች ፤ ውይይቱንም የሚመሩት ለጥቁር ገበያው የተመረቱ አልበሞች፣ መጽሐፎች፣ ድግሶች እና ሰልፎች አይሆኑም፤ የውይይቱ ይዘትም ልክ 1983 ዓ.ም እንደ ነበረው እጅ እጅ አይልም ነበር፡፡ ያልጨረቱ ሀልዮቶች፣ ያልነፈሰባቸው ትችቶች፣ አዳዲስ ዘርፎች በየጊዜው እየበቀሉ እያደጉ ስለዳግማዊ ምኒሊክም ሆነ ስለ ኢትዮጵያ የሚደመጡት ትንታኔዎች እና ትርጓሜዎች ለተዋስዖው ሞገስ ይሆኑት ነበር፡፡ የገበያው የበላይ ጠባቂ ሕወሃት እጅጉን የሚጠነቀቀው ስምምነት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በየትኛውም ተዋስዖ ላይ የሰከኑ አስታራቂዎችን ሳይሆን ስምምነት ላይ ለመድረስ ይቅር እና ለመደማመጥ የማይችሉትን ያበረታታል፡፡
በዚህ ድቅድቅ ጭለማ ውስጥም ሁሉም በእውር ድንብር ይተራመሳል፡፡ ጥቂት ትንሽ ሻል ያሉ አራዶች በየጥጋጥጋቸው ርዕስ እና ትርጓሜ እየመረጡ ቢጫ ሰው ፣ ሰማያዊ ዶሮ፣ ሲያዴ ፈረስት፣ እና ሚያዚያ 9 ምናምን የሚል የአየር በአየር ቡቲክ ይከፍታሉ፡፡ ከዚህም ከዚያም የለቃቀሙትን የትርጓሜ ሰልባጅ አዲስ ልብስ አስመስለው ይሸጣሉ፡፡ እነዚህ የአየር በአየር ነጋዴዎችም የገበያውን ሕግ አይቀይሩም፡፡ አንዳንዶቹ እንደውም የገበያው መሰረታዊ ሕግ ከተቀየረ ሕልውናቸው አደጋ ላይ እንደሚኾን ስለሚገነዘቡ ከጥቁር ገበያነት ወደ ነጻ ገበያነት እንዲለወጥም አይፈልጉም፡፡ ገበያውን እንዴት አድርጌ ነው የምጠቀልለው ብለው ሁሉ የሚገዛው ትርጓሜ ለማምጣትም አፈልጉም፡፡ የአየር በአየር ነጋዴዎች ናቸው እና ቶሎ ቶሎ ከግርግሩ አትርፈው ሽል እና ሽብልል ከማለት ውጪ ገበያውን ሙሉ ለሙሉ ለመማረክ ወገቡም የላቸውም፡፡ To be fair ለሕወሀት ሳይሆን ለእውነት ‘ፌር’ ለመሆን የኢትዮጵያ ተዋስዖ ገበያ የጥቁር ገበያን መርህ መከተል የጀመረው ግንቦት 20/1983 አይደለም፡፡ ከሕወሀትም በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ የትርጓሜ ገበያው በገዢው ቡድን ተፅዕኖ መሆኑ አይካድም፡፡ የወቅቱ ትክክለኛ መረዳት ተዋስዖው የጥቁር ገበያ ሥርዐት መኾኑን ማስተዋል ይገባል፡፡ እንዴት ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ትርጓሜዎች በሰላም ሊንሸራሸሩ የሚችሉት ? በእርጋታ እና በስክነት የሚንቀሳቀስ የተዋስዖ ገበያ ሥርዐት መመስረቻ ቁልፎቹ ምንድን ናቸው ? በባህሎቻችን እና በቋንቋችን ውስጥ ምን ያህል ሀብት ምን ያህል ድህነትስ አለ ? አሁንም ስለጥቁር ሰው ማሰብ ይፈልጋሉ ? I don’t .

Health: በወር አበባ ሰሞን ህመም እና ምቾት ማጣትን የምትቀንሺባቸው 6 ስልቶች

$
0
0

ከቅድስት አባተ

(በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 57 ላይ ታትሞ የወጣ)

የሴቶች ጉዳይ ብንላቸው የምንግባባቸው ጥቂት ነገሮች አሉ፡፡ አንዱ ወር ጠብቆ ፅንስ ለመፍጠር ዝግጁ መሆናቸውን ለመናገር የሚመጣው የወር አበባ ነው፡፡ እጅግ በርካታ የሆኑ እና ሴቶች የወር አበባቸው በሚመጣ ወቅት ከቀላል መነጫነጭ አንስቶ ሁሉን ነገር እስከመጥላት የሚያደርስ የህመም እና ምቾት የማጣት ስሜት ይገጥማቸዋል፡፡ ሁነቱ ተፈጥሯዊ የሆነና ለክፉ የሚሰጥ አይደለም፡፡ ይሁንና የዚያን ሰሞን ስሜት እና ህመም ማቅለል እና ንጭንጩንም ጭምር ማቃለል እንደሚቻል ባለሞያዎች ያስረዳሉ፡፡ የዛሬው ትኩረታችንም ይህ ነው፡፡ ቀላል የሚባሉ እና የህክምና ጥበብን እጅግም በማይጠይቁ ስልቶች የወር አበባ ሰሞንን ማቅለል የምትችይባቸውን ስልቶች እነሆ ብለንሻል፡፡

women health

የወር አበባ ለምን?

ተፈጥሮ የወር አበባን ስትፈጥር መራባትን አስባ ነው፡፡ ሴቶች አዲስ ነፍስ የመፍጠር ስልጣን በየወሩ ይሰጣቸዋል፡፡ አብሮ ለመፍጠር የተዘጋጀ ጥንድ እስካለ ድረስ ይህ ይሰራል፡፡ በየወሩ የሚዘጋጁት እንቁላሎች የሚዳብርና ፅንስ የሚያደርጋቸው የወንድ ዘር ሲያገኙ እዚያው ሆነው ጽንሱ ሲፈጠር ያ ካልሆነና ሴቲቱም በመፀነስ እቅድ ውስጥ ካልሆነች ደግሞ እንቁላሎቹ ወደ ውጪ መውጣት ይኖርባቸዋል፡፡ እንግዲህ በየወሩ ከደም ጋር ተቀላቅለው የሚወጡት እነዚህ እንቁላሎች ናቸው፡፡ ታዲያ ይህ ክስተት በብዙ ሆርሞኖችና የሰውነት ውስጥ ውስብስብ ተግባራት የሚከወን እንደመሆኑ ብዙ ለውጦችን ሴቶች ማስተናገዳቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቢያንስ 80 ከመቶ የሚሆኑ የዓለማችን ሴቶች ከቀላል ህመም አንስቶ እስከ ከበዱት ድረስ በወር አበባ ሰሞን ይገጥማቸዋል፡፡ እጅግ አሳማሚ የሆድ ቁርጠት፣ የስሜት መቀያየር፣ መነጫነጭ ራስ ምታት እና ሌሎቹም የሚጠቀሱ ማሳያዎች ናቸው፡፡ እነዚህን የወር አበባ ሰሞን ችግሮች ማቅለያ ዘዴዎችን ታዲያ የህክምና ሰዎች ለሴቶች ሁሉ ያጋራሉ፡፡ የዲስከቨሪ መፅሔት እና ውሜን ሄልዝ ኤክስፐርቶች ካነሷቸው መካከል ዮጋ ማዘውተር ጨው መቀነስ፣ አመጋገብ ማስተካከልና አንዳንድ ቀለል ያሉ መድሃኒቶችን መውሰድን ያነሳሉ፡፡

የወር አበባ ሰሞን ጨው ቀንሺ

በወር አበባ ሰሞን እንቁላሎች ዝግጁ ሆነው የሚጠብቁት ልጅ እንደሚፈጠር በማሰብ ነው፡፡ ስለሆነም ጽንሱ ቢፈጠር የሚያስፈልገውን የጨው ፈሳሽ እና ኤሌክትሮላይት ለመሙላት ሰውነትሽ ብዙ ጨው የዚያን ሰሞን ይኖረዋል፡፡ ብዙ ጨው መኖሩ ደግሞ ውሃን የመሳብና በሰውነት ውስጥ መጠራቀምን ይፈጥራል፡፡ ይህ በራሱ የሚፈጥረው ሰውነትን የማስጨነቅ ተፅዕኖ ስለሚኖር ከውጪ የምትወስጂውን ጨው የወር አበባ ከሚመጣባቸው ቀናት አስቀድመሽ ቀንሽ፡፡ በተለይ የተጠባበሱ ምግቦች ውስጥ ከፍተኛ የጨው ክምችት ስለሚኖር ከእነዚህ ምግቦች በዚያ ሰሞን መቆጠብ ጥሩ እንደሆነ ባለሞያዎቹ ያሰምሩበታል፡፡

ዮጋ እንደ መዝናኛም እንደ መድሃኒትም

የወር አበባ ወቅትን ህመም ለማስታገስ መዝናናት፣ ውጥረትን መቀነስ እና የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ በእጅጉ የሚመከሩ መላዎች ናቸው፡፡ ዮጋ ደግሞ ሁሉንም በአንድ አዋህዶ የያዘ የተመስጦ ስፖርት ከመሆኑ አንፃር ቁጥር አንድ ተመራጭ ስፖርት ያሰኘዋል፡፡ ‹‹ዮጋ ስፖርት ብቻ አይደለም፣ አዕምሮና አካልን በአንድነት ከውጥረት መንጥቆ የሚያወጣ መድሃኒትም ነው›› ይላሉ የዲስክቨሪ መፅሔት የህክምና አማካሪ፡፡ በኢንዲያን አካዳሚ ኦፍ አፕላይድ ሳይኮሎጂ የጥናት መፅሔት ላይ የሰፈረ የጥናት ውጤትም ተመሳሳይ ጥቅሞችን ያነሳል፡፡ ጥናቱ ዮጋ የስነ ልቦና እና የአካላዊ መዝናናትን በማጎናፀፍ ከወር አበባ ወቅት ህመምና ምቾት ማጣት በመገላገል በኩል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ይናገራል፡፡

ካልሲየምና ቫይታሚን ዲ ውጤት አላቸው

በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ አሜሪካ ውስጥ በዚህ ላይ ምርምር ያደረጉ ባለሞያዎች ቫይታሚን ዲ እና ካልሲየም ማዕድን የወር አበባ ጊዜዎትን በእጅጉ ቀላል የማድረግ ሚና እንዳላቸው አሳይተዋል፡፡ በጥናቱ በየዕለቱ እስከ ስድስት መቶ ሚሊግራም ካልሲየም የወሰዱ ሴቶች ዘንድ የወር አበባ ወቅት ህመሞች የሚባሉት እንደ ሆድ ቁርጠት፣ ራስ ምታት፣ የምግብ አምሮት እና የስነ ልቦና ጫናው በግማሽ ቀንሶ መገኘቱን በጥናታቸው ፅፈዋል፡፡ ይህ የካልሲየም መጠን አንድ ብርጭቆ ወተትና አንድ ብርጭቆ እርጎ በጋራ ቢጠጡ የሚያገኙት ምጣኔ ነው፡፡ ባለሞያዎቹ ካልሲየምን በክኒን መልክ መውሰድ ቢቻልም ተመራጩ ግን ከወተት ተዋፅኦ ውጤቶች ማግኘቱ እንደሆነ አበክረው ያሳስባሉ፡፡ ቫይታሚን ዲ ተመሳሳይ ተፅዕኖ እንዳለው ባለሞያዎቹ አስረድተዋል፡፡ እንደ ካሮት እና መሰል አትክልቶች ቫይታሚኑን ማግኘት ወር አበባን ቀለል ያደርጋል፡፡

ለማይግሬይንና ራስ ምታቱስ?

በወር አበባ ወቅት የሚከሰተው ራስ ምታት ከወትሮው በተለየ አናትን የሚነቁርና ሁሉን ነገር የሚያስጠላ ሊሆን ይችላል፡፡ ቀደም ሲል ያነሳናቸው የመዝናኛ እና ችግሩን የመቅረፊያ ስልቶች እየሰሩ ካልሆነ በባለሞያ የሚታዘዝ ህመም ማስታገሻን መውሰድ ይመክራል፡፡ ምናልባት ሌላ ጊዜ ከሐኪም ትዕዛዝ ውጪ የምንወስዳቸው ማስታገሻዎች በዚህ በኩል ውጤታቸው አርኪ ስለማይሆን ነው፡፡ ሌላ ማስታገሻ ለመጠየቅ ባለሞያን እንዲያዩ የሚመክረው በውጪ ሀገራት ለዚህ ተብለው የሚሰሩ ልዩ ማስታገሻዎች አሉ፡፡ በእኛ ሀገር ፋርማሲዎች በስፋት የሚገኙ ባለመሆናቸው ባለሞያ መገናኛቸውን ሊያመላክትዎት ይችላል፡፡

ፋይበር ያላቸውን ጠጠር ያሉ ምግቦች ጥቅም

ባለሞያዎቹ እንደሚሉት በወር አበባ መምጫ ሰሞን ህመሙን እና ሆድ ቁርጠቱን የሚያመጡት የሆርሞን ለውጦች የሆድ ህመም እና ተቅማጥ ከሚያመጡት ጋር ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ ስለሆነም ሆድን ያዝ የሚያደርጉ እንደ ጎመን አጃ፣ ሙዝና የመሳሰሉትን ምግቦች ብትወስጂ ሆድሽን ያዝ አድርገው የምግብ አምሮቶሽን ይገቱታል፡፡ አንዳንድ ሴቶች ዘንድ የሚታየውንም የዚያን ሰሞን የሆድ መለስለስና መለስተኛ ተቅማጥ ለመቆጣጠር ያግዛሉ፡፡

በዚያ ሰሞን ዋና መዋኘት?

ብዙ ሴቶች በወር አበባ መምጫ ሰሞን ከሰው ራቅ ብለው ቤት አካባቢ ሆነው ቢቆዩ ይመርጣሉ፡፡ የባለሞያዎች ሀሳብ ግን ይለያል፡፡ ከሰው መቀላቀሉ እና ዘና ማለቱ ይመከራል፡፡ በተጨማሪም ዋና መዋኘት ከፍተኛ ጠቀሜታም እንዳለው ጨምረው ያስረዳሉ፡፡ በዋና ወቅት በሰውነት እና በውሃው መካከል በሚደረገው ፍትጊያ የሚፈጠረው ግፊት የሆድ ቁርጠትና የዚያን አካባቢ ቁስለት የሚመስል ስሜት አዝናንቶ የማፍታትና ህመምንም የመቀነስ አቅም አለው፡፡ በቀን ቢያንስ ለ20 ደቂቃ ብትዋኚ ጥሩ ነው ተብሎ ተመክሯል፡፡ ነገር ግን የግድ ወደ ዋና ገንዳ እንድትገቢ አትገደጂም፡፡ የዋናው ነገር ካልተመቸሽ በቤት ውስጥ መታጠቢያ ቤት ለብ ያለ ውሃ በገንዳው ሞልተሽ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሰውነትሽን ብታሳርፊው የዋናውን ያህል ባይሆንም ጥሩ ውጤት ታገኚያለሽ፡፡

 

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>