Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

የተከበሩ አፍሪካዊ ኔልሰን ማንዴላ ስንብት! ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

$
0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ

ኔልሰን ሮሺስላሽላ ማንዴላ ለነጻነት የሚያደርጉትን ረዥሙን ጉዞ እ.ኤ.አ በ2013 መገባደጃ ወር ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ደመደሙ፡፡

Nelson Mandela

ኔልሰን ማንዴላ 1918-2013

ፀሐይ የደቡብ አፍሪካን ሕዝብ ከአፓርታይድ የጭቆና አገዛዝ ነጻ ባወጡት ኔልሰን ማንዴላ ላይ የመጨረሻ ማህለቋን ጣለች፡፡ ኔልሰን ማንዴላ ፈለግ አቸዉን ትተውልን አልፈዋል፡፡ በጥላቻ በተዘፈቀው ዓለም፣ በማያቋርጥ ሁኔታ በፍርሃት ተሸብቦ በሚገኘው ህዝብ፣ በአምባገነኖች በሃይል ተይዞ በሚሰቃየው ብዙሀን ህዝብ እና ስሜት አልባ ተደርጎ በተያዘው ህዘብ ላይ የፀሐይን ማህለቅ ለመጣል የኔልሰን ማንዴላን ፈለግ መከተል አለብን፡፡ በምንም ዓይነት መልኩ አንፈራም፣ የኔልሰን ማንዴላ መንፈስ ከአጠገባችን ናትና!

ኔልሰን ማንዴላን በፍጹም አግኝቻቸው አላውቅም፣ ባገኛቸው እንዴት ደስ ባለኝ! ለማግኘት የምፈልገው ደግሞ በዓለም ላይ እጅግ ከተከበሩት ሰው ጋር ተገናኝቸ ነበር በማለት ለስሜቴ ክብር ለመስጠት አይደለም፣ ነገር ግን ለአፍሪካውያን ክብርን፣ ኩራትን እና ሞገስን ላጎናጸፉት እኒያን ጀግና ኔልሰን ማንዴላን በዚህ አጋጣሚ አመሰግናለሁ የምትለዋን ቃል በትሕትና  ለማቅረብ እንጅ፡፡

ኔልሰን ማንዴላ ድልድይ ቀያሽ ነበሩ፡፡ ዘርን፣ ጎሳን እና የህብረተሰብ መደብን የሚያገናኙ ድልድዮችን ገንብተዋል፡፡ ኔልሰን ማንዴላ እሳት አጥፊ ነበሩ፡፡ በዘር እና በጎሳ ጥላቻ ተቀጣጥሎ የነበረውን ቤት እሳት በማጥፋት በደቡብ አፍሪካውያን ዘንድ እውነት እና ዕርቅ እንዲሰፍን አድርገዋል፡፡ ኔልሰን ማንዴላ መንገድ ቀያሽ ነበሩ፡፡ በረዥሙ ጉዞ ወደ ነጻነት የሚያደርሱ በስም “ደግነት“ እና  “ዕርቅ“ የሚባሉ ሁለት መንገዶችን በመገንባት የተናገሩትን በተግባር አሳይተዋል፡፡ ኔልሰን ማንዴላ የህንጻ ንድፍ ነዳፊ/architect ነበሩ፡፡ በአፓርታይድ አመድ ላይ በብዙሃን ዘር ዴሞክራሲ የተዋበውን ማማ ገንብተዋል፡፡ ኔልሰን ማንዴላ የልዩ ተሰጥኦ ባለቤት ነበሩ፡፡ ጥቁር እና ነጭ እርግቦችን በአንድ ጊዜ በመልቀቅ በነጻነታቸው ተንፈላስሰው እንዲበሩ አድርገዋል፡፡ ኔልሰን ማንዴላ ለዘላለም የሚኖር የለውጥ ሐዋርያ ነበሩ፡፡ ጥላቻን በፍቅር፣ ፍርሃትን በወኔ፣ ጥርጣሬን በእምነት፣ ታጋሽየለሽነትን በሩህሩህነት፣ ቁጣን በመግባባት፣ ጥላቻን በስምምነት፣ እና ቅሌትን በክብር የሚለውጡ ነበሩ፡፡

ኔልሰን ማንዴላ በዘመናዊው የህብረተሰብ ታሪክ ሂደት ውስጥ እንከን ባለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ እንከንየለሽ በመሆን እንከን ያላቸው ሰው ነበሩ፡፡ ሙሉ በሙሉ በዘር፣ በጎሳ እና በመደብ በተከፋፈሉ ወገኖቻቸው ላይ አንከንየለሽ ማህበርን ለማምጣት ጥረት አድርገዋል፡፡ ነጭ ደቡብ አፍሪካውያንን በልቦቻቸው ውስጥ ዘልቀው ከገቡት ከአፓርታይድ መጥፎ ገጽታ እና ከአስቀያሚ ዘረኝነት አድነዋቸዋል፡፡ በጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ልቦች እና ነፍሶች ውስጥ ይንከባለሉ የነበሩትን የበቀል ጥላቻዎች  ወደ ፍቅር እና ወንድማዊነት ስሜት ቀይረዋቸዋል፡፡ ኔልሰን ማንዴላ በእራሳቸው ልብ ውስጥ የፍቅር፣ የስምምነት እና የዕርቅ ጓሮን አልምተዋል፡፡ ኔልሰን ማንዴላ እጅግ በጣም እንከን ለበዛባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ምክራዊ መልዕክት እንዲህ በማለት አስተላልፈዋል፣ “ሰው ከጠላቱ ጋር ሰላም ለማውረድ ከጠላቱ ጋር አብሮ መስራት አለበት፣ እና ያ ጠላት የነበረው ወዳጅ ይሆናል“፡፡ ሌሎቻችን ግን ጠላትን በመግደል ሰላም እናመጣለን ብለን እናምናለን!

ማንዴላ መጥፎ ነገር ለማድረግ ጥሩ ጊዜ የለም በማለት ዓለምን አስተምረዋል፣ ሆኖም ግን “የሚመጣው ጊዜ ሁሉ ጥሩ ነገር ለማድረግ መሆኑን ማመን አለብን“፡፡  ለደቡብ አፍሪካውያን እና ለመላው አፍሪካውያን እንዲህ በማለት አስተምረዋል፣ “ለቆንጆዋ ደቡብ አፍሪካ እንዲሁም ለመላዋ አፍሪካ ህልሞች ካሉ እነዚህ ህልሞች ወደ ተግባር እንዲሸጋገሩ የሚያስችሉ መንገዶችም አሉ“፡፡ ከእነዚህ መንገዶች ሁለቱ “ደግነት” እና “ይቅርታ አድራጊነት” በመባል ሊሰየሙ ችለዋል፡፡ እነዚህን የማንዴላን ቃላት ለዘላለም ስናስታውሳቸው እንኖራለን፡፡ የሮበርት ፍሮስትን አባባል በመዋስ፣

እኛ …ይህንን በጥልቅ ተንፍሰን እንናገራለን፣
የትም በጊዜዎች እና በጊዜዎች ቢሆንም፣
ሁለት መንገዶች ሁለት መንታ መንገዶች በደን ጫካ ዉስጥ ነበሩ
ማንዴላ ጥቂትሰዎች የተጉአዙበትን መንገድ ወሰዱ፣
እና ሁሉንም ልዩነት ያመጣው ይኸ ነው፡፡

በደቡብ አፍሪካ ሁሉንም የመልካም ስራ ልዩነት ያመጡት ደግነት እና ይቅርታ አድራጊነት ናቸው፡፡

ሃያ ሰባት እና ከዚያም በላይ በትንሽ እስር ቤት አድሚያቸውን ያሳለፉ ሰው ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ትክክለኛ ትርጉም እንዲህ በማለት አስተምረውናል፣ “ነጻ መሆን እግረሙቅን ከእጅ ወይም ከእግር ማስወገድ አይደለም፣ ነገር ግን ሌሎችን በማክበር እና ነጻነታቸውን በማራመድ የመኖር መንገድ ነው“ ፕሬዚዳንት ክሊንተን “በተሻለው ቀን ሁሉ ሁላችንም ኔልሰን ማንዴላን መሆን አለብን“ ሲሉ እውነትም ልክ ናቸው፡፡ ነገር ግን ዛሬ መጥፎው ቀናችን ነው፣ ምክንያቱም ኔልሰን ሮሺስላሽላ ማንዴላ አብረውን የሉምና! ዛሬ ማንዴላን ለዘላለም ተነጥቀናል!

ኔልሰን ማንዴላን በፍጹም አላገኘኋቸውም፣ ነገር ግን ብዙ ንግግሮችን ከእርሳቸው ጋ አግኝቻለሁ፡፡ በእርግጥ ሁሉም ምዕናባዊ ነበሩ፡፡ ማንዴላ ግድየላቸውም፣ እንዲህ ብለዋል፣ “በእውኑ ዓለም በእርግጠኝነት ከማየው ይልቅ ራዕይዬ የበለጠ በመጓዝ ምዕናባዊ ኃይሌ ስሜትን/አዕምሮን የሚፈታተን ሀሳብን ይፈጥራል“፡፡ ነገር ግን የኔልሰን ማንዴላን ራዕይ በአዕምሯችን ዓይን ከተመለከትነው የሀሰት ምዕናባዊ ሀሳብ አይደለም፡፡ ከኮሎኒያሊዝም፣ ከኢምፔሪያሊዝም እና ከአፓራታይድ አመድ ነጻ የወጣችውን ጀግና፣ በእራስ የምትተማመን አዲሲቷን የፍቅር አፍሪካ ራዕያቸውን እናያለን፡፡ በኔልሰን ማንዴላ ራዕይ የምትመራዋን አዲሲቷን አፍሪካ ለመገንባት ምዕናባዊ ሀሳባችንን አሁኑኑ መጠቀም አለብን፡፡

አንዳንድ ሰዎች ትልቅ ሆነው ይወለዳሉ፣ ሌሎቹ ደግሞ የትልቅነት እምነትን ይላበሳሉ እየተባለ ይነገራል፡፡ ምንልባትም አንዳንዶቹ ታላቅነትን በአጋጣሚ ይጎናጸፋሉ፡፡ ኔልሰን ማንዴላ ታላቅ ነበሩ ምክንያቱም ይሞክሩ ነበር፣ ይሞክሩ ነበር እና ይሞክሩ ነበር፡፡ ማንዴላ እንዲህ በማለት አስተባብለዋል፣ “እኔ ነብይ አይደለሁም፣ ነብይን ሁልጊዜ እንደሚሞክር ሃጢያተኛ ካልቆጠራችሁት በስተቀር“፡፡ ሁላችንም ሃጢያተኞች ሁልጊዜ እስከሞከርን እና እጃችንን እስካልሰጠን ድረስ የሚሞክር ሃጢያተኛ ነብዮች ብንባል ኔልሰን ማንዴላ ሞተውም ቢሆን ህያው ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ፡፡

ለኔልሰን ማንዴላ ከፍተኛ የሆነ ሃዘን እና አድናቆት የሚደረግላቸው ናቸው፡፡ በከፍተኛ የስልጣን እርካብ ላይ ያሉ በዓለም ታላላቅ ከተሞች የሚገኙ መሪዎች ስለ ኔልሰን ማንዴላ የነጻነት ታጋይነት እና የሰብአዊ መብት ተሟጋችነት ያወሳሉ፡፡ የደቡብ አፍሪካ መሪዎች ስለኔልሰን ማንዴላ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ በአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ አመራር ሰጭነት እና የማያቋርጠውን እና ኢሰባዊ የነበረውን የአፓርታይድ ገዥ አካል በሰላማዊ እና በትጥቅ ትግል ለመጣል የተጫወቱትን ሚና በማድነቅ ይናገሩላቸዋል፡፡ ተራው የደቡብ አፍሪካ ህዝብ ኔልሰን ማንዴላን በኩራት የሀገራቸው አባት እንደሆኑ አድርገው ይናገራሉ፡፡ ስለኔልሰን ማንዴላ የኖቤል ተሸላሚነት፣ ስለዓለማቀፋዊ የሰብአዊ መብት እና ስልሰው ልጅ ሰብዕና ተከራካሪነት፣ ስለማህበራዊ ፍትህ እና ሰላም ለማስፈን በዓለም አቀፍ ደረጃ ስላደረጉት ያልተቋረጠ ትግል የዓለም ህዝብ አድናቆቱን ይገልጻል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የማንዴላ ተችዎች ጭቃ ጅራፍ ይዘው ይላሉ፡፡ ለዕርቅና ለሰላም ያላቸው የማይታጠፍ አቋም ለደቡብ አፍሪካ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ሃይል ሚዛን የሚያስፈልገውን አብዮት እንዳይመጣ ይከላከላሉ በማለት ይተቿቸዋል፡፡ ማንዴላ ለአፓርታይድ ጨቋኖች ብዙ ትኩረት በመስጠት ከእነርሱ ግን በመልሱ የወሰዱት ነገር አናሳ ነው በማለት ይታቻሉ፡፡ ከአፓርታይድ አለቆች ጋር በእርቀሰላሙ ጉዳይ ላይ ጥረት በማድረግ የመለሳለስ እና ሃይለኛ ሆነው ያለመውጣት ሁኔታ እንዳለባቸው ይተቻሉ፡፡ ተቺዎቻቸው በመቀጠልም አፓርታይድ አሁንም ቢሆን በኢኮኖሚው በኩል ሃያልነቱን እንደያዘ እና ሙስና በአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ የፖለቲካ ህይወት ውሰጥ እየተስፋፋ የመጣ ነቀርሳ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ የማንዴላን ውድቀት በተጨባጭ ሁኔታ ለመተቸት አልቻሉም፣ ነገር ግን እነርሱ በምዕናባቸው ሆኖ የሚታያቸውን በማቅረብ ይተቻሉ፡፡ እንዲህም ይላሉ፣ አፓርታይድ ከሞተ ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ በደቡብ አፍሪካ በከተሞች እና በገጠሮች የሚኖረው ህብረተሰብ ኑሮ ልዩነቱ በጣም ጠባብ ነው፡፡ ማንዴላ ስለዕርቅ ጉዳይ በትጋት የሰሩት ብዙም ለውጥ አላምጣም ይላሉ፣ እንዲያውም ደቡብ አፍሪካ ቀደም ሲል እንደነበረው በዘር ተከፋፍላ ትገኛለች ይላሉ፡፡ ሌሎቹ ተቺዎች ደግሞ ማንዴላ ስህተት ሰርተዋል፣ የገቧቸውን ቃልኪዳኖች አላከበሩም ይሏቸዋል፡፡ በከተሞች የሚገኙት ያጡት እና የነጡት በዕየለቱ የዕለት ዳቦ እየለመኑ የሚተዳደሩት ስለማንዴላ መልካም ነገር አይናገሩም፣ ምክንያቱም ማንዴላ አዲስ በፈጠሯት ደቡብ አፍሪካ እራሳቸውን እንደተቆለፈባቸው አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ በገጠሩ የሚኖሩት እና በመገለል ብዛት እየተሰቃዩ ያሉት ህዝቦች ህይወታቸው ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ለውጥ ያላመጣ መሆኑን ይከስሳሉ፡፡

የማንዴላን “የሃጢያት ነብይነት” የተጋነነ ትችት አንድ ነገር ልነግራቸው እፈልጋሉ፣ “እራሳችሁን እረገብ አድርጉ! በማንዴላ ላይ ከባድ ትችት ከመሰንዘራችሁ በፊት 27 ዓመታት ሙሉ በእግር ብረት ታስረው የቆዩትበን የጫማ ጉዞ በመከተል እስቲ አንድ ማይል እንኳ ለመጓዝ ሞክሩ፡፡ በከተማ እና በገጠር ለነጻነታችሁ ስትታገሉ ለቆያችሁት ልጠይቃችሁ የምፈልገው ነገር ማንዴላን ልዩ ኃይል እንዳለው መልዓክ አድርጋችሁ አትቁጠሩ ነገር ግን ማንዴላ እንደማኝኛችሁም ሁሉ ሰው ናቸው፡፡ ማንዴላ ነጻነትን ማጣት ምን ማለት እንደሆነ ብቻ ሳይሆን ክብርን እና ማንኛውንም ለህይወት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ በሚገባ የሚያውቁ ሰው ናቸው፡፡ ለማናቸውም ባዶ ተስፋዎች እና ተስፋቢስነቶች እንዲሁም ተፈጻሚነትን ላላገኙ ቃልኪዳኖች ኔልሰን ማንዴላን ይቅርታ እንዲያደርጉላቸው እጠይቃለሁ፡፡ ሰዎች ማንዴላን እንደ መላዕክ መቁጥር የለባቸውም፣ ነገር ግን ለሰው ልጅ ጥሩ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ለማድረግ የሚሞክሩ ሆኖም ግን ከፍተኛ ጥረትን ቢያደርጉም ሁሉም ነገር ያልተሳካላቸው ሃጢያተኛ ነብይ ነበሩ፡፡

ማንዴላ ተራ ሰው የነበሩ መሆናቸውን እናገራለሁ፣ ተራ ሰው አስገራሚ ከፍታ ላይ የወጡ፡፡ ማንዴላ የህግ ሰው የነበሩ መሆናቸውን እናገራለሁ፣ የሰብአዊ መብት የህግ ሊቅ፡፡ ማንዴላ ያልተከለሱ እና እውነተኛ አብዮታዊ የነበሩ መሆናቸውን እናገራለሁ፣ ደቡብ አፍሪካውያንን እና አፍሪካውያንን በሙሉ ነጻ ማውጣታቸው ብቻ ሳይሆን በጭቆና ቀንበር ስር ወድቆ የሚማቅቀውን የሰው ልጅ ዘር ሁሉ ነጻነት በማውጣታቸው ጭምር እንጅ፡፡ ማንዴላ ታላቁ የሰብአዊ መብት ተሟጋች የነበሩ ለመሆናቸው እናገራለሁ፣ ለኤች አይቪ በሽታ ሰለባ ለሀኑት፣ ለህጻናት ሰብአዊ መብት ጥበቃ፣ ጥራት ላለው ትምህርት መስፋፋት እና ለገጠር ልማት ስኬታማነት ግንባራቸውን ሳያጥፉ ይታገሉ ነበርና፡፡

የህግ ባለሙያ ለመሆን መረጥኩ ምክንያቱም ማንዴላ ለእኔ ተምሳሌት/ሞዴል አንዱ ነበሩና፡፡ እ.ኤ.አ በኤፕሪል 1964 የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪ በነበርኩበት ጊዜ ለመጀመሪያ ጊዜ ማንዴላ በሪቮኒያ የህግ ሂደት ያሰሙትን ንግግር ከሰማሁ ጀምሬ ንግግራቸው አእ ምሮዬ ዉስጥ ተቀርፅዋል፡፡ እንደ ማርቲን ሉተር ኪንግ “ደብዳቤ ከቢርሚንግሀም እስር ቤት“ ሁሉ የማንዴላ ንግግር በአዕምሮየ ተሰንቅሮ እያቃጨለ እንዲህ በማለት ያሳስበኝ ነበር፣ “በህይወት ዘመኔ ሁሉ ለዚህ ለአፍሪካ ህዝብ ትግል ነጻነት እራሴን መስዕዋት አደርጋለሁ፡፡ የነጮችን የበላይነት ለማስወገድ እታገላለሁ፣ እንዲሁም የጥቁሮችን የበላይነት ለማስወገድ እታገላለሁ፣ ሁሉም ህዝቦች በፍቅር እና በእኩልነት፣ ዴሞክሪያሴያዊ እና ነጻ ህዝቦች ሆነው በጋራ የሚኖሩባትን ዓለም እመኛለሁ፣ ለመኖር ቃልኪዳኔ እና እውን ሆኖ ማየት የምፈልገው ፍልስፍና ይኸ ነው፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ይህ ፍልስፍና እውን እንዲሆን ህይወቴን ለመስጠት ያለማመንታት የተዘጋጀሁበት ጉዳይ ትልቅ ጉዳይ ነው“፡፡ ኔልሰን ማንዴላ ይህንን ሲሉ በትክክል ምን ማለታቸው እንደሆነ ለመረዳት አስርት ዓመታትን ወስዶብኛል፡፡

ማንዴላ በሪቭኦኒያ የሕግ ሂደት ጥፋተኛ ተብለው የእድሜ ልክ እስራት ተበይኖባቸዋል፡፡ ማንዴላ በቁጥር 46664 የአፓርታይድ እስረኛ ተደርገዋል፡፡ የ27 ዓመታት ቁጥር 46664 እስረኛው ማንዴላ የዕለት ከዕለት ውርደት፣ ኢሰብአዊነት፣ ከባድ እና ጭካኔ የተሞላበት የጉልበት ስራ እንዲሰሩ በማስገደድ ግፍ ተፈጽሞባቸዋል፣ ከቤተሰቦቻቸው እና ከጓደኞቻቸው እንዲለያዩ ተደርጓል፡፡ የልጃቸውን የቀብር ስነስርዓት እንኳ ለመገኘት  አልተፈቀደላቸውም፣ የባለ 46664 ቁጥሩ እስረኛ በአፓርታይድ ጌቶች በሁሉም እይታ እና ተግባር እንዲሞቱ የተወሰነ ነበር፡፡ እስረኛ ቁጥር 46664 ግን አልሞቱም፣ በዚያች እግዚአብሄር በረገማት ደሴት እንዳይታዩ ሆነው ተወረወሩ፡፡ የኔልሰን ማንዴላ የ27 ዓመታት የግዞት እስራት ማንዴላን የሮብን ደሴት ተመላኪ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል፡፡ በጊዜ ሂደት በግለሰብ ደረጃ የማይታወቁት ቁጥር 46664 እስረኛ ተስፋ ለሌላቸው ህዝቦች የተስፋ፣ መጠጊያ እና ኃይል ለሌላቸው ለደቡብ አፍሪካ እና ለሌሎች ዓለም ህዝቦች ደግሞ የነጻነት ቀንዲል ለመሆን በቅተዋል፡፡

ቁጥር 46664 እስረኛ በአብዛኛው የ27 ዓመታት የእስር ሂደት በሚያቃጥለው ፀሐያማ ሀሩር የኖራ ድንጋይ ቁፋሮ እንዲቆፍሩ ይገደዱ ነበር፣ ማታ በእስር ቤታቸው ተቀምጠው ሰለወደፊቱ ዕቅዳቸው እና የአሰራር ስልታቸው ንድፍ ያወጡ ነበር፡፡ ሆኖም ግን በእራሳቸው፣ በቤተሰቦቻቸው እና በሌሎች ወገኖቻቸው ዘንድ ለመግለጽ በሚዘገንን መልኩ ስቃይ እና መከራ ሲያደርሱባቸው በነበሩት ጠላቶቻቸው ላይ በቀል እና ቅጣት ለመውሰድ አያስቡም ነበር፡፡ ቁጥር 46664 እስረኛ የአፓርታይድ ጨቋኞቻቸው መጥፎ አካሄዳቸውን እና ሰይጣናዊ ድርጊታቸውን እንዲተው ስትራቴጂ ይነድፉ ነበር፡፡ ቁጥር 46664 ህዝቦቻቸውን ከባስቱንታንስ የአፓርታይድ ደሴት ነጻ ለማውጣት ሌሊት ተጋድመው የወረቀት ላይ ንድፋቸውን በመስራት አርቺቴክት መሆን ጀመሩ፡፡ በደቡብ አፍሪካውያን የፖለቲካ ሰውነት ላይ ተንሰራፍቶ የቆየውን የዘረኝነት ቁስል ለማዳን እና ለመጠገን እዕምሯቸውን ክፍት በማድረግ ጥረት ማድረግ ጀመሩ፡፡ ቁጥር 46664 እስረኛ ከህዝቦች ነቢያትን እና ሃጢያተኞችን ለማውጣት ሌሊቱን በብቸኝነት በያዟት በጠባቧ እስር ቤታቸው ማስፈጸሚያ ዘዴዎችን ማውጠንጠን ጀመሩ፡፡

እ.ኤ.አ ጃንዋሪ 1 1990 እስረኛ ቁጥር 46664 ከሮበን ደሴት እስር ቤት ኔልሰን ማንዴላ ሲወጡ አየን፡፡ በክብር እና ተስፋን በሰነቀ አቀራረብ በጣም ፈገግ የሚሉ ሰው ተመለከትን፡፡ ለሶስት አስርት ተከታታይ ዓመታት ያህል በእስር ቤት ውስጥ የቆየ ሰው ከእራሱ ጋር በሰላም ለመኖር እና እንዲህ በክብር ለመቆየት እንዴት ይችላል? ወዲያውኑም ግልጽ ሆነ፣ የእስረኛ ቁጥር 46664ን እዚያው እስር ቤቱ ውስጥ በመራራው እና በተሰባበረው የእስር ቤት ጓደኝነት የሲኦል በር በሮበን ደሴት ላይ ተውት፡፡ እንዲህም ብለዋል፣ “የእስር ቤቷን በር አልፌ ወደ እስር ቤቱ አጥር ግቢ በር ስራመድ ወደ ነጻነት እየሄድኩ መሆኑን ተረዳሁ፡፡ ጥላቻየን እና ሰቆቃውን እዚያው እስር ቤት ትቸው ካልወጣሁ አሁንም እዚያው እስር ቤት እንዳለሁ አውቃለሁ“፡፡ ማንዴላ እስረኛ አልነበሩም!  እስር ቤቱ አፓርታይድ እራሱ ብቻ ነበር፣ እስረኞቹም የእስር ቤቱ ኃላፊዎች እና የአፓርታይድ ጌቶች ነበሩ፡፡ ኔልሰን ማንዴላ በአፓርታይድ የግንብ አጥር ተከልለው በእውን የሚገኙትን ጥላቻ፣ ፍርሀት እና በቀል በማስወገድ ነጻነትን ለማምጣት ሮቤን ደሴትን ለቀው ወጡ፡፡ ማንዴላ ዊኒ ማንዴላን ከጎናቸው በማድረግ በፊታቸው ታላቅ ፈገግታ እና ፍቅርን እንዲሁም ዕርቅ እና ልባዊ እውነትን  በማሳየት ከሮቤን ደሴት እስር ቤት ወጡ፡፡ “ኃጢያተኛውን ነብይን ተመለከትን! ሲራመዱ ሲናገሩ!  በዚያን ዕለት በአይኖቸ አልቅሻለሁ፡፡ ሌላ ያላለቀሰ ማን ነው?

ማንዴላ ሀሳባዊ አልነበሩም፣ ነገሮችን ሁሉ በአንክሮ የሚመለከቱ ጭምር እንጅ፡፡ የዕርቅን እና የዕውነትን መንገድ መረጡ፣ ምክንያቱም እነዚህ ወደ ፍትህ እና ሰላም ይመራሉና፡፡ ጥላቻ እና በቀል ወደ ሲኦል እንደሚወስዱ ማንዴላ ያውቃሉና፡፡ “ሰው የመሆናችን ተፈጥሯዊ ባህሪ አንዳችን ካአንዳችን እንድንተሳሰር ያደርገናል፣ በማዘን እና በጓደኝነት አይደለም፣ ነገር ግን ሰው እንደመሆናችን መጠን አሁን የሚያሰቃዩንን ነገሮች ለወደፊት ተስፋ ባለው ነገር መለወጥ የሚያስችል ችሎታም ስላለን ነው“፡፡ ማርቲን ሉተር ኪንግ ሲያደርጉት እንደነበረው ሁሉ ኔልሰን ማንዴላም በተመሳሳይ መልኩ ስልፍቅር… በተለይም ስለሰው ልጅ ያልተገደበ ፍቅር “አፋቸውን ከፈት” አድርገው በማስተማር ጥረት ያደርጉ ነበር፡፡ ከአፓርታይድ ጨቋኞች ጋር ዕርቅ ማድረግ የማይቻል ነው ሚሉትን ወገኖች ማንዴላ እንዲህ በማለት አስተምረዋል፣ “ተፈጽሞ አስከሚታይ ድረስ አንድ ነገር የሚሆን አይመስለንም“፣ እንዲህ ሲሉም መክረዋቸዋል፣ “በዚህች ዓለም ላይ ቅጣትን ከመፈጸም ይልቅ ምህረትን በማድረግ ብዙ ነገሮችን ማሳካት ትችላለህ“፡፡ ማንዴላ ትክክል ናቸው፡፡

ማንዴላ “በጎነት እና ይቅርታ አድራጊነት” በሚባሉ ሁለት አውራ ጎዳናዎች ረዥሙን የነጻነት ጉዞ ተጉዘዋል፡፡ ረዥም ጉዞ ነበር ምክንያቱም፣ ብዙ ተለዋጭ መንገዶችን መጓዝ ስለነበረባቸው፡፡ ሰፊውን የጓደኝነት ጎዳና እና ትልቁን የመቻቻል መንገድ መጓዝ ነበረባቸው፡፡ ትንሿን የፍርሀት እና ያለመግባባት መንገድ መጓዝ ነበረባቸው፡፡ በረዥሙ የጉዞ መንገድ ድፍረት፣ ታጋሽነት፣ ፍቅር፣ ጽናት እና ሩህሩህነት በማሳየት ብዙ ቆይታ ማድረግ ነበረባቸው፡፡

ማንዴላ በእስር ቤታቸው ክልል ተወስነው በጊዜ ብዛት ለመለካት በማይቻል መልኩ ታማኝነትን አዳብረዋል፡፡ “ሰዎች በውጭ በሚያከናውኑት መጠን እራሳቸውን ይለካሉ፣ ነገር ግን እስር ቤት ሰውን በውስጥ ጉዳዩች ማለትም ታማኝነት፣ ቅንነት፣ ግልጽነት፣ ሰብአዊነት፣ ለጋሽነት እና የማይለዋወጥ ባህሪ ላይ እንዲያተኩር ያደርገዋል“፡፡ ማንዴላ ወደ እስር ቤት ሲገቡም ሆነ ሲወጡ ቋሚ ጓደኞች ነበሯቸው፡፡ ሮናልድ ሬጋን እና ማጂ ታቸር የአፓርታይድን መንግስት መርዳት ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ማዕቀብም እንዲጣልበት አድርገዋል፡፡ በማንዴላ እና በኤኤንሲ ላይ “የአክራሪነት ባህሪ ዝርዝር ውስጥ“ በማስገባት እ.ኤ.አ እስከ 2008 ድረስ በዘለቀው ሁኔታ ማዕቀብ መጣል አልቸገራቸውም ነበር፡፡ እነዚህ የጊዜው ጥሩ ጓደኞች እና ተመሳሳዮቻቸው ማንዴላ ከፊደል ካስትሮ እና ከሙአማር ጋዳፊ ጋር ጓደኝነት መመስረታቸውን ለመተቸት ጊዜ አልወሰደባቸውም፡፡ ማንዴላ በፍጹም መንገዳቸውን የማይቀያይሩ እና ከአመኑበት ነገር ላይ በቀላሉ የሚያፈገፍጉ አልነበሩም፡፡ ማንዴላ እንዲህም ይሉ ነበር፣ “ጓደኛ ማለት የደስታ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በጭንቅ ጊዜም የሚገኝ ነው“፡፡ ወዲያው እንዳዩ ይጣሩ ነበር፡፡ በጊዜ ሂደት አሜሪካ “በዓለም ላይ በቃላት ሊገለጽ በማይችል መልኩ ትፈጽም በነበረው የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ“ ላይ ጠንከር ያለ ትችት ያቀርቡ ነበር፡፡ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ ወደ ኢራቅ ጦር ባዘመቱ ጊዜ ማንዴላ በዝምታ አልተመለከቱም ነበር፣ እንዲህ አሉ እንጅ፣”ኢራቅን ለነዳጅ ዘይቷ ሲል“ የወረረ እንዲሁም “በትክክል ማሰብ የተሳነው እና አርቆ ማየት የማይችል ፕሬዚዳንት“ በማለት በትችት ወርፈዋቸዋል፡፡

ማንዴላ የአስታራቂነት ጌታ እና የሰይጣን ነብይነት ከመሆናቸው በፊት አማጺ ነበሩ፣ ነገር ግን አማጺነታቸው በጸረ ዘር መድልኦነት ላይ ነበር፡፡ “አሸባሪ“ ነበሩ ነገር ግን የአፓርታይድን ስርዓት በመቃወም ላይ ብቻ፡፡ ለደቡብ አፍሪካውያን በሙሉ የነጻነት ታጋይ ነበሩ፡፡ ለህግ የበላይነት መከበር ቀናኢ ነበሩ፡፡ አሜሪካ ከህግ አግባብ ውጭ በኦሳማ ቢን ላደን ላይ የፈጸመችውን ግድያ ተችተዋል፡፡ ማንዴላ “የኮሙኒስት” ሽምቅ ተዋጊ እና የቀዝቃዛው ጦርነት አብዮታዊ ስለነበሩ አገራቸው የልዕለ ኃያላኑ የጦርነት መፎካከሪያ ሆና ነበር፡፡ ማንዴላ ለሰራተኛው መደብ መብት ተከራካሪ እና በዓላማቸው የጸኑ ታጋይ ነበሩ፡፡ ለዚህም እ.ኤ.አ በ1990 በዴትሮይት የሚገኙትን የአውቶ ሰራተኞች እንዲህ በማለት ነግረዋቸዋል፣ “እህቶች እና ወንድሞች፣ ጓደኞች እና የትግል አጋሮች፣ አሁን ከእናንተ ጋር ንግግር የሚያደርገው ሰው እንግዳ አይደለም፡፡ አሁን ነግግር እያደረገ ያለው ሰው የዩኤደብልዩ/UAW አባል ነው፡፡ እኔ ስጋችሁ እና ደማችሁ ነኝ፡፡“ በሮቤን ደሴት የኖራ ድንጋይ ቁፋሮ ተገደው ሲሰሩባቸው የነበሩትን ዓመታትን  አልረሱም፡፡ ማንዴላ ቡጢያቸውን የሚጠቀሙ ቦክሰኛ ብቻ አልነበሩም፣ ግን በብሩህ አዕምሯቸው በመመራት ጥብብ በተመላበት ዘዴ በመዋጋት ትጥቅ የሚያስፈቱ ጀግና ነበሩ፡፡  ማንዴላ በጣም ተጫዋች ሰው ነበሩ: በራሳቸዉም ላይ ይሰቁ ነበር፡፡ የመጀመሪያ የስልጣን ዘመናቸውን በቢሯቸው ካጠናቀቁ በኋላ የነጮች የንግድ ማህበረሰብ ስብሰባ ላይ በመገኘት እንዲህ ሲሉ ነግረዋቸዋል፣ “እኔ በአሁኑ ጊዜ ደኃ ጡረተኛ ነኝ፡፡ ስራ አጥ ነኝ፡፡ ልትቀጥሩኝ ትችላላችሁን?“

ማንዴላ እስከፈለጉበት ጊዜ በስልጣን መንበራቸው ላይ መቆየት ይችሉ ነበር፡፡ እንደሌላው የአፍሪካ አምባገነን ገዥ ሁሉ በስልጣን ላይ ተጣብቀው መቆየት ይችሉ ነበር፡፡ ከአራት ዓመታት በኋላ ስልጣናቸውን ማስረከብ ነው የመረጡት፡፡ በፍላጎታቸው ስልጣን በሚለቁበት ጊዜ ለደቡብ አፍሪካውያን እና ለአፍሪካውያን በሙሉ ሊተመን የማይችል ቅርስ ነው የሰጡት፣ የፖለቲካ ስልጣን የውልደት መብት እርስት አለመሆኑን ነገር ግን በህዝቦች ፍላጎት የሚሰጥ እና ሲያስፈልግም የሚቀማ ኃላፊነት መሆኑን በተግባር አሳይተዋል፡፡ በዚያ ድርጊት መሰረት ማንዴላ የህግ የበላይነትን በህገመንግስቱ እንዲካተት እና የደቡብ አፍሪካ ሉዓላዊነት እንዲጠበቅ በማድረግ ለሁሉም አፍሪካውያን አርአያ ለመሆን በቅተዋል፡፡

ማንዴላ ስልጣንን የህዝቦች ፈቃደኝነት፣ ፍላጎት ማስፈጸሚያ፣ የዓላማዎች ማሳኪያ ስልት እንጅ በእራሱ የመጨረሻ ግብ እንዳልሆነ አድርገው ነበር የሚመለከቱት፡፡ ጥሩ ነገር ለመስራት ስልጣንን መጠቀም አስፈላጊ እንደሆነ ያምናሉ፣ ኃይል የሌላቸውን ኃይል ካላቸው ለመጠበቅ፣ ስልጣንን አላግባብ መጠቀምን ለመከላከል፣ ስልጣንን በመጠቀም ኃይል የሌላቸውን ኃይለኞች ለማድረግ፣ ኃይልን በመጠቀም ወጣቶችን ኃይል እንዲኖራቸው ለማድረግ የኃይል መጠቀምን አስፈላጊነት ይናገሩ ነበር፡፡ ህዝብ ተስፋ እንዲኖረው የኃይል መጠቀምን አስፈላጊነት ያምኑ ነበር፡፡ ኃይልን መጠቀም ለመግደል ወይም ለመስረቅ ሳይሆን ህዘቦችን ለማዳን መሆን እንዳለበት ያምኑ ነበር፡፡ በሰላም ኃያልነት ያምኑ ነበር፡፡ ከባንቱስታንስ የዘረኝነት ደሴት በማላቀቅ ብሩህ የህዝቦችን ህይወት መመስረት እንዲቻል በደግ ስራ እና በዕርቅ ኃያልነት ያምኑ ነበር፡፡

ማንዴላ የዕርቅ ዋጋው እውነት ነው፡ ብለዋል፡፡  አንድ ሰው ለሰራው ስራ ወይም ላጠፋው ጥፋት በህዘብ ፊት ኃላፊነትን መውሰድ ዕርቅ የሚፈልገው ጉዳይ ነው፡፡ የአፓርታይድ ሰብአዊ መብት ደፍጣጮች አስከ አሁን ድረስ ለፈጸሙት ወንጀል ኃላፊነት በመውስድ ለፈጸሙት ለጥፋታቸው በህዝብ ፊት አምነው ይቅርታ መጠየቅ ይኖረባቸዋል፡፡ የጥፋት ሰለባዎቻቸው እና ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች የእነዚህን እኩይ ተግባር ፈጻሚዎች እውነተኛ ባህሪ ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ እውነት እና እውነት ብቻ እርምጃ ከመውሰድ እና የጥላቻ በቀል ከመውሰድ ያድናል፡፡ ማንዴላ አገራቸውን ከአፓርታይድ የሞራል ዝቅጠት ለማጽዳት እና ህዝቡን ከአፓርታይድ የጨለማ መንገድ ለማውጣት እንዲሁም የብዙሀን ፓርቲ ስርዓት እንዲጎለብት በማሰብ የእውነት እና የዕርቅ ኮሚሽን አቋቁመዋል፡፡

ለሶስት አስርት ሩብ ዓመታት ለነጻነት ረዥሙን ጉዞ የተጓዙት ሰው አሁን ማረፍ አለባቸው፡፡ ረዥሙን ጉዞ ተጉዘዋል፣ ምክንያቱም ነጻነትን የመጠበቅ ቃልኪዳን ነበራቸውና፡፡ አሁን አሸልበዋል፡፡ ለዘላለም በሰላም ይረፉ፡፡

ሆኖም ግን ወደ ነጻነት የሚደረገውን ረዥሙን ጉዞ ለማጠናቀቅ ገና ብዙ ማይሎች እና ብዙ ያልተሳኩ ቃልኪዳኖች ይቀራሉ፡፡ የማንዴላን ረዥሙን ጉዞ አሁን የሚጓዘው ማን ነው? የማንዴላን ቃልኪዳኖች የሚፈጽማቸው ማን ነው? ማንዴላ የአፍሪካ ወጣቶች ቀንዲል…

የማንዴላ ስንብት ለአፍሪካ ወጣቶች፡ “ትግላችሁን ቀጥሉ፣ በፍጹም እጅ እንዳትሰጡ…!”

ለአፍሪካ ወጣቶች ባስተላለፉት የስንብት መልዕክት ላይ እንድደነቅ እና በጉዳዩም ላይ የበለጠ እንዳስብ ያደርገኛል፡፡ ብልሁ የአፍሪካ አንበሳ እረፍት ስለሌላቸው ወጣት የአቦሸማኔ የአፍሪካ ነብሮች ምን ይላሉ?

ትልቅ ለመሆን ድፍረት ይኑራችሁ ፣ ማንዴላ የፍሪካን ወጣቶች ታሪካዊ መጻኢ ዕድል ያስታውሳሉ የሚል እምነት አለኝ፡፡ ታላቅ እንዲሆኑ መክረዋል፡፡ “አንዳንድ ጊዜ ታላቅነት በትውልድ ላይ ይወድቃል፡፡ ያንን ታላቅ ትውልድ ልትሆን ትችላላቸሁ፡፡ ታላቅነትህ ያብብ፡፡“

ማህበረሰቡን ከመለወጥህ በፊት መጀመሪያ እራሳችሁን ለዉጡ፣ አሮጌው የጥላቻ እና የፍርሃት መንገድ ለአዲሱ የመግባባት እና የዕርቅ መንገድ ቦታ መስጠት እንዳለበት ማንዴላ ለወጣቶቹ መክረዋል፡፡ መዘጋጀት አለባቸው፡፡ “ድርድር ሳደርግ ከተማርኳቸው ነገሮች አንዱ እራሴን እስክለውጥ ድረስ ሌሎችን መለወጥ አልችልም“፡፡ በፍጹም መጥላት የለባቸውም ምክንያቱም “ጥላቻ መርዝን እንደመጠጣት ያህል ነው፣ ጠላቴን ይገድልልኛል በሚል ተስፋ“፡፡ ጥላቻ ከውልደት በኋላ የሚመጣ ባህሪ ነው፡፡ “ባለው የቆዳ ቀለም ልዩነት፣ ባለው የአስተዳደግ ሁኔታ፣ ወይም ደግሞ በሚከተለው እምነት ምክንያት ማንም ማንንም ሊጠላ አልተወለደም፡፡ ሰዎች ጥላቻን መማር አለባቸው፣ እና ጥላቻን መማር ከቻሉ ፍቅር እንዲኖራቸው ሊማሩ ይገባል፣ ፍቅር በተፈጥሮ ወደ ሰው ልጅ ልብ ውስጥ ከተቃራኒው የበለጠ ለመግባት ስለሚችል::“

ሙከራቹህን ቀጥሉበት፣ ማንዴላ የአፍሪካ ወጣቶች ምንጊዜም እንዲሞክሩ እና በፍጹም በፍጹም እጅ እንዳይሰጡ በመምከር አዲሲቷን ጀግና አፍሪካ የመመስረት ቃልኪዳን ለመጠበቅ አንድ ሰው በቆዳው፣ በጎሳው እና በእምነቱ ጠቃሚነት ከጸጉሩ/ሯ ቀለም ልዩነት በስተቀር ጠቃሚነቱ  እርባና እንደሌለው አጽንኦ ሰጥተው አስተምረዋል፡፡ በአፍሪካ “ፍትህ እንደ ውኃ እንዲንቆረቆር እና እውነት እንደማያቋርጥ የጅረት ምንጭ እንዲፈስ” ወጣቱ መቀጠል እና ሙከራውን ማቆም እንደሌለበት ማንዴላ ምክር ለግሰዋል፡፡  በውድቀት ላይ ተመስርቶ የስኬት አዝመራ እንደሚታጨድ በመገንዘብ ወጣቶች ውድቀትን ሳይፈሩ ትግላቸውን መቀጠል እንዳለባቸው ማንዴላ ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡ “እኔን በማስገኘው ስኬት አትገምግሙኝ፣ ይልቅስ ምን ያህል ጊዜ እንደወደቅሁ እና ለስኬት ምን ያህል ጥረት በማድረግ እንደተነሳሁ እንጅ“ ውድቀት ኃጢአት አይደለም፡፡ ለመሞከር አለመቻል ነው ውድቀት ማለት፡፡ በህይወት ስንክሳር “ታላቁ ዝና ፍጹም አለመውደቅ አይደለም፣ ነገር ግን ትልቁ ነገር በወደቅን ቁጥር ለመነሳት የምናደርገው ጥረት ነው፡፡” ማንዴላ ለወጣቶቹ ሲመክሩ ወጣቶች በስኬት ማማ ላይ ፊጥ ለማለት ጥረት ማድረግ ብቻ ሳይሆን ትከሻቸውን በማጠንከር ሊመጡ የሚችሉትን ችግሮቸ ሁሉ በመጋፈጥ በድል አድራጊነት ለመውጣት ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው ምክንያቱም “ትላቁን ተራራ ከወጣህ በኋላ ሌሎች ብዙ ሊወጡ የሚችሉ ተራሮች እንዳሉ መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡“ በማለት አስተምረዋል፡፡

በአንድነት ሁኑ፣ የአፍሪካ ወጣቶች እንደወጣት ኃይል በአንድነት መምጣት እንዳለባቸው ማንዴላ ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡ እንዲህ ሲሉም መክረዋል፣ “አንድ ነጠላ ሰው ሀገሩን ነጻ ሊያወጣ አይችልም፡፡ አገራችሁን ነጻ ልታደርጉ የምትችሉት በአጠቃላይ በጋራ ስትንቀሳቀሱ ነው፡፡“

ጥሩ ሞራል ያለው/ላት ሰው ሁኑ፣ ደግነት የሞራል ቆንጆነት ነው፡፡ ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ ጥረት የማድረግ ጉዳይ ነው እና ማንም አዬ አላዬ ጥሩውን ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ አለማለት ነው፡፡ “ከዚህ ቀደም እንደተናገርኩት ሁሉ ለእራስ ታማኝ መሆን ነው፡፡ በቅድሚያ እራስህን ካልለወጥክ በህዝብ ላይ ውጤት ሊያመጣ የሚያስችል ተጽእኖ ልታመጣ አትችልም…ታላላቅ የሰላም መሪዎች በሙሉ ሀቀኞች ናቸው፣ ታማኞች ናቸው፣ ነገር ግን ከብር ፈላጊ አይደሉም::“

አገር ወዳድ አርበኛ ሁኑ፣ ማንዴላ በአገር ወዳድ አርበኝነት ላይ እምነት ነበራቸው፣ እናም የአፍሪካ ወጣቶች ለህዝቦቻቸው እና ለአህጉራቸው አርበኛ መሆን እንዳለባቸው መክረዋል፡፡ ማንዴላ እንዲህ አሉ፣ “በመጀመሪያ ደረጃ እኔ እራሴን ሁሌም የአፍሪካ አህጉር ወዳድ አርበኛ አድርጌ እቆጥራሉ፡፡“ የአፍሪካ አርበኞች የቅኝ ገዥ ጌቶቻቸውን ከአሁጉሩ አባረዋል፡፡ የአፍሪካ አርበኞች አፓርታይድን ያለደም መፋሰስ አስወግደዋል፡፡ የአፍሪካ ወጣቶች በአሁኑ ጊዜ በጋራ በመሆን ድህነትን፣ ድንቁርናን እና አምባገነንነትን ማስወገድ ይኖርባቸዋል፡፡

ደፋር ሁኑ፣ ወጣቶቹ ደፋር እንዲሆኑ ማንዴላ መክረዋል፡፡ “ድፍረት የፍርሃት አለመኖር ብቻ አለመሆኑን ተረድቻለሁ፣ ነገር ግን በፍርሃት ላይ ድል መቀዳጀት ማለት ነው፡፡ ጀግና ሰው ማለት ፍርሃት የማይሰማው ማለት አይደለም፣ ነግረ ግን ፍርሃትን የሚያሸንፍ እንጅ::“

ትልቅ ነገር አልሙ፣ ማንዴላ የአፍሪካ ወጣቶች ትልቅ ነገር እንዲያልሙ መክረዋል፡፡ ትልቅ እንዳይሆኑ እና ሀብታም ወንድ እና ሴት እንዳይሆኑ፣ ነገር ግን ሰላሟ የተጠበቀ እና የበለጸገች አፍሪካ እንድትሆን ማለም፡፡ “በእራሷ ሰላሟ የተረጋገጠ አፍሪካን አልማለሁ፡፡ ለቆንጆዋ ደቡብ አፍሪካ ህልሞች ካሉ ወደ ግቧ የሚያደርሱ መንገዶችም አሉ፡፡ እነዚህ ሁለቱ መንገዶች ደግነት እና ይቅርታ አድራጊነት በመባል ተሰይመዋል፡፡“

ከኋላ ሆናችሁ ምሩ፣ ማንዴላ በጅግናዋ አዲሲቱ አፍሪካ በአሮጌው የአስተዳደር ስልት አንዴ ስልጣን ከተቆናጠጡ በኋላ እስከሞት ድረስ ስልጣን አልለቅም ማለት ቦታ እንደሌለው ለአፍሪካ ወጣቶች ምክር ለግሰዋል፡፡ ማንዴላ ወጣቶቹን እንዲህ በማለት ተማጽነዋል፣ “ከመንጋዎቹ በኋላ እንደሚሆን እረኛ በጣም ፈጣኑን ከፊት እንዲሆን መፍቀድ፣ሌሎቹ ግን እንዲከተሉ ማድረግ፣ ሁሉም ከኋላ ባለ እንደሚታዘዙ እና እንደሚመሩ እንዲያውቁት ሳይደረግ ጉዞውን ማስኬድ“፡፡ ማንዴላ እንዲህ ይላሉ፣ “ከኋላ ምራ እና ሌሎችን ከፊት አድርግ፣ በተለይም ጥሩ ነገር በሚኖርበት ጊዜ እና ድልን በምታከብሩበት ጊዜ“፡፡ አደጋ በሚኖርበት ጊዜ የፊተኛውን ረድፍ ትይዛላቸሁ፡፡ ከዚያ በኋላ ህዝብ የናንተን አመራር ሰጭነት ያደንቃል… ከኋላ ሆነህ ምራ ሌሎቹ ከፊት ነኝ የሚል እምነት እንዲኖራቸው አድርጉ፡፡ “መሪነትን ማቆምም መምራት ነው“ በማለት ማንዴላ ወጣቶቹ በአንክሮ አንዲመለከቱት መክረዋል፡፡

ችግርና መከራ በትግል ላይ አንዳለ እወቁ ፣ ለነጻነት በሚደረገው ረዥሙ ጉዞ  ብዙ የህግ ሂደቶች እና ቅጣቶች እንደሚገጥሟቸው ማንዴላ ለአፍሪካ ወጣቶች ምክር ለግሰዋል፡፡ እንደሚሰቃዩ እንደ እንደሚፈረድባቸው፣ እንደሚዋረዱ፣ ኢሰብአዊነት ድርጊት እንደሚፈጸምባቸው ለአፍሪካውያን ወጣቶች ግልጽ አድርገውላቸዋል፡፡ በመጨረሻም ነጻነት እንደሚመጣ እርግጠኞች ሆነዋል፡፡ “ትናንት አክራሪ ተብየ ነበር፣ ከእስር ቤት ስወጣ ግን ብዙ ህዝቦች ጠላቶቸ ሳይቀሩ በእቅፋቸው አስገቡኝ፣ እናም ይኸንን ነው እንግዲህ  ለሌሎች ሰዎች መናገር ያለብኝ በሀገራቸው ለነጻነት የሚታገሉ ሰዎች አሸባሪዎች ናቸው“ የሚለውም መታወቅ አለበት፡፡

ከጠላቶቻችሁ ጋር ሰላም ሁኑ፣ ለሰላም ሲባል ከእነርሱ ጋር መገናኘት፣ እጅ መጨባበጥ እና ጠላቶቻቸውን እቅፍ አድርገው መሳም አንዳለባቸው ማንዴላ መክረዋል፡፡ “ከጠላትህ ጋር ሰላም እንዲመጣ ከፈለግህ ከእርሱ ጋር አብረህ መስራት አለብህ፣ ከዚያም ጓደኛ ታደርገዋለህ፡፡“

ድህነትን ተዋጉ፣ ማንዴላ የአፍሪካ ወጣቶች በአፍሪካ ቀንድ በጣም አንገብጋቢ የሆነ ችግር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡ ከመጨረሻው የድህነት ቋት ውስጥ ተዘፍቃ የምትገኘውን አፍሪካን የአፍሪካ ታላቁ ትውልድ እና የወደፊቱ ብሩህ ተስፋ መንጥቆ እንደሚያወጣት ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡ ድህነትን ማስወገድ የልገሳ ስራ አይደለም፣ የፍትህ ጉዳይ እንጅ፡፡ እንደ ባርነት እና አፓርታይድ ድህነት ተፈጥሯዊ አይደለም፡፡ ሰው ሰራሽ ነው፣ እናም በሰዎች ጥረት ሊጠፋ እና ድል ሊደረግ ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ትልቅ በሚሆነው ትውልድ ላይ ይወድቃል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የማንዴላ ታላቅነት በአፍሪካ ወጣቶች ላይ ወድቋል፡፡

በመርሆዎች ላይ በፍጹም አትደራደሩ፣ የአፍሪካ ወጣቶች በመርሆዎች መደራደር እንደሌለባቸው ማንዴላ አጽንኦ በመስጠት ለአፍሪካ ወጣቶች ምክር ለግሰዋል፡፡ ማንዴላ ለወጣቶቹ ሲያስተምሩ እድሜልካቸውን ከአፓርታይድ እና ከዘረኝነት ጋር ስዋጋ ስታግል ኖሪያለሁ ምክንያቱም እነዚህ ጭራቆች ለሰው ልጅ ሟች ጠላቶች ናቸው፡፡ “የዘር መድልዎን እና መገለጫዎቹን ሁሉ በጣም እጠላለሁ “ በህይወት ዘመኔ ሁሉ ስታገል ቆይቻለሁ፣ አሁንም እየታገልኩ ነው እና ቀኖቸ እስኪያልቁ ድረስ መታገሉን እቀጥላለሁ…፡፡”  ይህንን በሚገባ አድረገውታል፣ ፈጽመውታልም፡፡ የአፍሪካ ወጣቶች በጥላቻ እና በሁሉም መገለጫዎቹ ላይ ማለትም በጎሰኝነት፣ በፖለቲካ ማንነት፣ በማህበረሰባዊነት፣ በጎሳ ክፍፍል፣ በጾታ ጭቆና፣ በኢኮኖሚ ብዝበዛ እና በህብረተሰብ አድልኦ ላይ በመርህ ላይ የተመሰረተ እና ድርድር የማያስገባ አቋም መያዝ እንዳለባቸው ማንዴላ በአጽንኦ ጠይቀዋል፡፡

ብሩህ አላሚ እና ጽናት ይኑራችሁ፣ የአፍሪካ ወጣቶች ብሩህ አላሚዎች መሆን እንዳለባቸው ማንዴላ መክረዋል፣ ምክንያቱም የአፍሪካውያን ምርጥ ቀኖች ገና እየመጡ ነውና፡፡ “እኔ በመሰረቱ ብሩህ አላሚ ነኝ፡፡ ከተፈጥሮም መጣ ከእራስ ጥንካሬ የምለው ነገር የለም፡፡ በከፊል ብሩህ አላሚ መሆን ማለት የአንድን ሰው እራስ ወደ ጸሐይ ቀጥ ብሎ እንዲያመለክት እንዲሁም የአንድ ሰው እግሮች ወደፊት እንዲራመዱ የማድረግ ያህል ነው፡፡ በሰው ላይ ያለኝ እምነት በሚገባ በሚፈተሽበት ጊዜ ብዙ የጨለማ አጋጣሚዎች ነበሩ፡፡ ነግር ግን ተስፋ ቢስ ለመሆን አጅ አልሰጥም፣ አላደርገውምም አልሞክረውምም፡፡ ያ መንገድ የሽንፈት እና የሞት ነው፡፡“ የአፍሪካ ወጣቶች ያን ረዥሙን ጉዞ መጓዙን መቀጠል አለባቸው፡፡ የማንዴላ ጠንካሮች መሆን አለባቸው፡፡ “ጥንካሬው እና አስፈላጊው ጥበብ ቢኖርህም በዓለም ላይ ወደ ግለሰባዊ ድልነት ልትቀይራቸው የማትችላቸው ጥቂት መጥፎ አጋጣሚዎች አሉ፡፡“  

ተማሩ፣ ህዝብንም አስተምሩ፣ ማንዴላ ትምህርት ለአፍሪካ ወጣቶች ለእራሳቸው ስኬታማነት እና ለወደፊቷ አፍሪካ ቁልፍ ነገር እንደሆነ አስተምረዋል፡፡ “ዓለምን ለመለወጥ ትምህርት ትልቁ መሳሪያ ነው፡፡ ዜጎቹ ካልተማሩ በስተቀር ማንም ሀገር ቢሆን እድገት ሊያስመዘግብ አይችልም፡፡“

ዝምተኛ አትሁኑ፣ በጭራቅነት እና በፍትህ እጦት ጊዜ የምን አገባኝነት ባህሪ መኖር እንደሌለበት ማንዴላ ለአፍሪካ ወጣቶች አስተምረዋል፡፡ ጭራቃዊ ድርጊቶች ሲፈጸሙ እየተመለከቱ ዝም ከማለት የበለጠ ጭራቅነት የለም፡፡ ጭራቃዊ ድርጊት በየትኛውም መልኩ ሲፈጸም ስናይ ልንዋጋው ይገባል፣ ወጣቶች ጭንቅላታቸውን ክፍት ካደረጉ እውነት በእራሱ ይገለጽላቸዋል፡፡ “ምንም ዓይነት ድንገት ያገኘሁት ግንዛቤ የለኝም፣ ምንም ዓይነት መረጃም የለኝም፣ እውነት የተገለጸበት አጋጣሚም የለም፣ ነገር ግን በሺዎች የሚቆጠሩ ጨዋነት የጎደላቸው ድርጊቶች፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ውርደቶች፣ እና እንድናደድ፣ እንዳምጽ እና ህዝቤን አፍኖ የያዘውን ስርዓት እንድዋጋ በሺዎች የሚቀጠሩ ላስታውሳቸው የማልችላቸው አጋጣሚዎች ያሉ መሆኑን“ በማለት ማንዴላ ለአፍሪካ ወጣቶች አስተምረዋል፡፡ በተነገርኩት ላይ የተወሰነ ቀን የለም፣ ስለሆነም እራሴን ለህዝቤ ነጻነት መስዋዕት አደርጋለሁ፣ ይልቁንም በተግባር እያዋልኩት መሆኑን እራሴን አዚያው ውስጥ አገኘሁት፣ እንደዚያ ካልሆነ ወደ ተግባር መተርጎም የሚቻል አይሆንም፡፡”

ወደ ነጻነት፣ ዴሞክራሲ እና ሰብአዊ መብት ጥበቃ የሚደረገው ረዥሙ ጉዞ ቀላል አይደለም…፣ ማንዴላ ለነጻነት፣ ለክብር፣ ለዴሞክራሲ እና ለሰብአዊ መብት ጥበቃ የሚደረገው ትግል ረዥም፣ አስቸጋሪ እና አደገኛ መሆኑን ለአፍሪካ ወጣቶች መክረዋል፡፡ እንዲህም ብለዋል፣ “ወደ ነጻነት የሚያስኬድ ቀላል ጎዞ የትም ቦታ አይገኝም፣ እናም አብዛኞቻችን ከምንመኘው የተራራ ጫፍ ላይ ከመድረሳችን በፊት ደግመን እና ደጋግመን በሸለቆው የሞት ጥላ ስር ማለፍ አለብን፡፡“

ገና ብዙ የሚወጡ ተራሮች ይቀሩኛል፣ ወደ ነጻነት የሚደረገው ታላቁ ጉዞ በኮረብታዎች እና በተራሮች የሚያቋርጥ እና በሸለቆዎች የሚዘረጋ ነው፡፡ በጉዞው ላይ ያልተጠበቁ አደጋዎች ያጋጥማሉ፡፡ ለማረፍ ትንሽ ጊዜ ነው ያለው፡፡ ማንዴላ እንዲህ ብለዋል፣ “ለነጻነት የሚያስኬደውን ያንን እረዥሙን ጉዞ ተጉዠዋለሁ፡፡ በእራስ መተማመንን እንዳላጣ ጥረት አድርጊያለሁ፡፡ በጉዞው መንገድ ላይ የተሳሳቱ ቅደምተከተሎችን ፈጽሚያለሁ፡፡ ነገር ግን ከትልቁ ተራራ ጭፍ ላይ ለመውጣት ገና ብዙ ኮረብታዎችን መውጣት አንደሚኖርብኝ አረጋግጫለሁ፡፡ ለማረፍ ትንሽ ጊዜ ወስጃለሁ፣ ሰረቅ አድርጌም የከበበኝን አስደናቂውን አካባቢያዊ ሁኔታ ተመልክቻለሁ፣ የተጓዝኩትን ርቀት መለስ ብዬ ተመልክቻለሁ፣ ግን ለጥቂት ጊዜ ብቻ ነው ለማረፍ የቻልኩት፣ ነጻነትን ለማግኘት ኃላፊነት መምጣት አለበት፣ እና በምንም ዓይነት መልኩ ከወዲያ ወዲህ እያልኩ አልንገዋለልም፣ ረዥሙ ጉዞዬ አልተጠናቀቀምና፡፡“

ሁልጊዜ ደግ ለመስራት ሞክሩ ፣ ይቅርታ ለማድረግ፣ ዕርቅ ለማውረድ…. ጥሩ ነገር ለማድረግ፣ ይቅርታ ለማድረግ እና ዕርቀ ሰላም ለማውረድ ጥረት አድርጉ፡፡ የስኬት ቃልኪዳን ባይኖርም ሞክሩ፣ ውድቀት እንዳለ ብታውቁም ሞክር፣ ጥርጣሬ ያለ እና እርግጠኝነት የጎደለ መሆኑን ብታውቅም ሞክር፡፡ ደክመህ እና መቀጠል የማትችል መሆኑን ባታውቁም እንኳ ሞክሩ፡፡ ተስፋ በማይኖርበት ጊዜም ሞክሩ፡፡ ዓላማህን ካሳካህ በኋላም ቢሆን ሞክሩ፡፡ ለመሞከር አስቸጋሪ እና ትርጉምየለሽ በሆነበት ጊዜ እንኳ ቢሆን ሞክሩ፡፡ ምርጫ በሌለበት ግን ሙከራ ብቻ ባለበት ሁኔታም ቢሆን ሞክሩ፡፡ ጭራቅነት በመልካም ተግባር ላይ ድልን እንዳይቀዳጅ ሞክሩ፣ ማንዴላ እንደሞከሩት ሁሉ ሞክሩ፡፡

ስንብት፣ ለእኔ አፍሪካዊ ክቡር! ለእኛ አፍሪካዊ ክቡር!

ብዙ ምናባዊ ንግግሮችን ላደረግሁላቸው ለኔልሰን ሮሊህላህላ ማንዴላ የሚወዱትን እና የሚደሰቱበትን “የሸክስፒርን” ቃላትን በመዋስ የመጨረሻ ስንብቴን ላቅርብ፡፡ ማንዴላ በእስር ቤት ውሰጥ ሳሉ የሸክስፒር ጁሊየስ ቄሳር የቄሳር ቃላት ይስሟሟቸው ነበር፡፡

እስከአሁን ከሰማኋቸው አስደናቂ ነገሮች መካከል ለእኔ እንግዳ የሚሆነው ወንዶች ሞት የሚመጣ የመጨረሻ መሆኑን አይተው መፍራት አለባቸው የሚለው ነው፡፡ አለመፍራት አስደናቂ አይሆንምና፡፡ ለኔልሰን ሮሺስላሽላ ማንዴላ የሆራሽዎ የሀዘን ቃላትን በመጠቀም የመጨረሻ ስንበት አደርጋለሁ፡፡

አሁን የተከበረ ሰው ልብ ተሰብሯል፡፡
የተከበሩ ደህና ይደሩ፣
ነብስዎ በሰላም እንድታርፍ መላዕክት ይዘምራሉ፣

እና በዚህ አሳዛኝ ህልፈት የጆህን ዶኔን ቃላት በመጠቀም እጮሃለሁ፡፡

ሞት ኩራት አይደርብህ፣ አንዳንዶች ኃይለኛ እና አስፈሪ ብለው ቢጠሩህም፣ አትፈራም
ሞት ማዲባን አትገድልም አትችልም!

ዘላለማዊ ክብር ለማንዴላ፣ ዘላለማዊ ክብር ለኔልሰን ሮሊህላህላ ማንዴላ!

ታህሳስ 2 ቀን 2006 ዓ.ም


የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ፪ –ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

$
0
0

harar
ባለፈው ሳምንት የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካን ተጨባጭ እውነታዎችን ቃኝቼ ተከታዩን ክፍል በይደር አቆይቼው እንደነበረ ይታወሳል፤ እነሆም ዛሬ እንዲህ እቀጥላለሁ፡-

ሐረር እንደ ማሳያ

(መቼም ኢህአዴግ በብቸኝነት የሚኩራራበት የፖለቲካ ‹ስኬት›፣ ለዘመናት አንድ ሆኖ የኖረ ሕዝብን ‹ብሔር ብሔረሰቦች› በሚል ከፋፋይ የ‹ክርስትና ስም› እጥምቆ በአደባባይ ማስጨፈር ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ርግጥ ነው በአንድ ወቅት በፍትህ ጋዜጣ ላይ ‹‹የብሔር ብሔረሰቦች መብት እስከ መጨፈር›› በሚል ርዕስ የታተመ መጣጥፍን ተከትሎ ‹ፀረ-ብሔር ብሔረሰቦች› ተደርጌ በተመሰረተብኝ ክስ ፍርድ ቤት መመላለሴ ዛሬም ድረስ መቋጫ አላገኘም፤ ርግጥ ነው ኢትዮጵያውያን ወንድም እህቶቼ በስታዲዮሞች እየተሰባሰቡ የራስ ፀጉራቸው ላይ ላባ ሰክተው፣ ቆዳ አገልድመው እየዘለሉ ትርኢት ከማሳየት ባለፈ የመልካም አስተዳደር፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ መብቶቻቸው ተጠቃሚ መሆን አልቻሉም፡፡ …እውነታው ይህ ቢሆንም ወደ አጀንዳችን /የከሸፈው ፌደራሊዝምን/ ወደ መፈተሹ በአዲስ መስመር እንመለስ፡፡

ቋንቋን መሰረት ያደረገው ኢህአዴግ ሰራሹ ‹ፌደራሊዝም› አወቃቀር የሀገሪቱ መፃኢ ዕድል የተቋጠረበት ‹የሰዓት ቦንብ› መሆኑን ለመረዳት የምስራቅ ኢትዮጵያዋን ሐረር እንደ መሳያ መውሰዱን ግድ የሚያደርጉ በርካታ ገፊ ምክንያቶች አሉ፡፡ እንደሚታወቀው የሐረር ከተማ አመሰራረት ብዙሃኑ ህዝብ ከሚኖርበት ‹ጀጎል› ከተሰኘው በግንብ የተከለለ ቅፅር ጋር ይያያዛል፡፡ በ16ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ራሳቸውን ከብሔር ወረራ ለመከላከል በአካባቢው ነዋሪዎች እንደታነፀ በርካታ ድርሳናቶች የሚናገሩለት ጥንታዊውና ታሪካዊው የጀጎል ግንብ በአምስት (ሐረር፣ ኤረር፣ ሠንጋ፣ ቡዳ እና በርበሬ በር በሚባሉ) በሮች የተከፋፈለ ነው፡፡

ጀጎል ከ40ሺ ለማያንሱ የክልሉ ነዋሪዎች መጠለያ ሲሆን፣ ከነዚህ ውስጥ ከዘጠኝ ሺህ በላይ የሕዝብ ቁጥር ያላቸው የሐረሪ ተወላጆች እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይህም ሆኖ መስከረም 30 ቀን 1997 ዓ.ም. ‹‹የሐረሪ ሕዝብ ክልል መንግስት ሕገ-መንግስት›› በሚል ርዕስ ተሻሽሎ የፀደቀው አዋጅ፣ ስርዓቱ በአደባባይ ከሚመፃደቅበት ቋንቋን መሰረት ያደረገ ‹ፌደራሊዝም› የሚቃረኑ እና ከዴሞክራሲ ባህሪያት ጋር የሚጋጩ በርካታ አንቀፆች የታጨቁበት መሆኑ ለጠቀስኩት ሀገራዊ ስጋት መነሻ ነው፡፡ ለማሳያም ያህል የክልሉ ምክር ቤት ይቋቋምበታል ተብሎ በሕገ-መንግስቱ ውስጥ የተካተተውን የምርጫ ሕግ መመልከት የሚችል ይመስለኛል፡፡ ይህ ሕገ-መንግስት ተሻሽሎ ከመፅደቁ ሶስት ዓመት ቀደም ብሎ በስታስቲክ ባለሥልጣን ይፋ የተደረገው መረጃ የክልሉ ነዋሪ ህዝብ ብዛት በጥቅሉ 131,139 እንደሆነ ይገልፅና በየብሔሩ ሲከፋፈል ደግሞ ኦሮሞ 41%፣ አማራ 22.77%፣ ሐረሪ 8.65%፣ ጉራጌ 4.34% ሶማሌ 3.87%፣ ትግራይ 1.53%፣
አርጎባ 1.26% መሆኑን ይዘረዝራል፤ በስፋት የሚነገሩ ቋንቋዎችም ኦሮምኛ 56%፣ አማርኛ 27.53%፣ ሐረሪ 7.33%፣ ሶማሊኛ 3.70%፣ ጉራጌኛ 2.91%… ነው ይለናል፡፡

በመሬት ያለው እውነታ ይህ ቢሆንም የክልሉ ሕገ-መንግስት ደግሞ በአንቀፅ 49 ‹‹የሐረሪ ሕዝብ ክልል ምክር ቤት›› በሁለት ጉባዔዎች እንደሚመሰረት ከገለፀ በኋላ፣ እነርሱም ‹‹የህዝብ ተወካዮች ጉባኤ›› እና ‹‹የሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ›› እንደሆኑ ይነግረናል፤ ይኸው አንቀፅ በቁጥር 2 እና 3 ላይ ‹የሕዝብ ተወካዮች› ሃያ ሁለት፣ የሐረሪው በብሔሩ ተወላጆች ብቻ የሚወከሉ 14 አባላት ይኖሩታል ይላል፡፡ ይህ ሁኔታ በምርጫ ወቅት እንዴት እንደሚተገበር ደግሞ በአንቀፅ 50 ላይ ‹‹የጉባዔዎች አከፋፈል፣ አወካከልና አመራረጥ›› በሚል ርዕስ ስር እንደሚከተለው ተብራርቷል ‹የሕዝብ ተወካዮች› ለተሰኘው ጉባኤ ከጀጎል ነዋሪዎች አራት፣ ከጀጎል ውጪ ከሚገኙ የከተማና የገጠር ቀበሌ ገበሬ ማህበራት 18 አባላት ይመረጡበታል፡፡ ለሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ደግሞ በክልሉና ከክልሉ ውጪ በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች ከሚኖሩ የሐረሪ ብሔረሰብ ውስጥ 14 አባላት ይመረጡበታል፡፡ ይሁንና ሕጉ ብዙሃኑን የአካባቢው ነዋሪዎች የፖለቲካ ውክልና ከመንፈጉ በተጨማሪ ከክልሉ ተቋማትም ሆነ መብቶች እንዲገለሉ አድርጓቸዋል፡፡ በተለይም በራሱ በመንግስት መረጃ ሳይቀር በተወላጅነትም ሆነ ቋንቋውን በመናገር ከኦሮሞ ብሔር ቀጥሎ በሁለተኛነት የሚገኙት፣ እንዲሁም አብላጫውን የፖለቲካ ስልጣን ከያዘው ከሐረሪ ብሔረሰብ አባላት ከእጥፍ በላይ ቁጥር እንዳላቸው የተረጋገጠው አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በዞን ደረጃ እንኳ እንዲዋቀሩ አለመደረጉ ‹ፌደራሊዝሙ› ከአፋዊነት አለማለፉን ያመላክታል (በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች በዞን ደረጃ እንዲዋቀሩ የተደረጉ ጥቂት የማይባሉ ብሔሮች እንዳሉ ልብ ይሏል) እንዲህ አይነቱ አደረጃጀት ሌላው ቢቀር እንኳ በዚህ ዘመን ፋሽን ከሆነው ‹‹ውጡ፣ ክልላችሁ አይደለም!›› ከሚለው ነውረኛ
ፖለቲካ የመታደግ ጉልበት ሊኖረው የሚችልበት ዕድል ሰፊ ነው፡፡ በርግጥ ይህ ሁናቴ ዛሬም ድረስ መፅናቱ ‹ብሔረሰቡን እወክላለሁ› የሚለው የእነ አዲሱ ለገሰ ብአዴን ከተላላኪነት ያለፈ ሚና እንደሌለው የሚያመላክት ይመስለኛል፡፡

የሆነው ሆኖ የሙግቱ ዋነኛ መግፍኤ የጀጎል ነዋሪ ከሆኑት ውስጥ ከሶስት እጅ ለሚልቁት አራት፣ ለተቀሩት ጥቂት ሐረሪዎች ደግሞ አስራአራት የምክር ቤት ወንበር ከመስጠቱ ጋር ይያያዛል፡፡ በዚህ ሕግ መሰረት በጀጎል የምርጫ ክልል ከአራቱ ወንበሮች ውጪ ሐረሪ ያልሆነ የትኛውም ፓርቲም ሆነ ግለሰብ ለውድድር መቅረብ እንደማይችል በግልፅ ተደንግጓል፡፡ እንዲህ አይነቱ አናሳዎችን በብዙሃኑ ላይ የሚሾም ኢ-ፍትሃዊ የሥልጣን ክፍፍል አብዛኛውን የክልሉ ነዋሪ በገሃድ እየተንፀባረቀ ላለው ባይተዋር አገዛዝ ከማጋለጡም በላይ፣ ከመልካም አስተዳደር ጋር በአዋጅ የተፋታ እስኪመስል ድረስ በሙስናና በአድሎአዊነት ለተተበተበ ስርዓት ዳርጎታል፤ ይህ ሁኔታም በህዝቦች መካከል መከፋፈል እንዲፈጠርና በጥላቻ ምሽግ ውስጥ እንዲያደፍጡ ማስገደዱ አይቀርም፡፡
በጥቅሉ የብዙዎችን መብት ጨፍልቆና አንዱን ነጥሎ ተጠቃሚ የሚያደርግ ስርዓት ማንበር የማታ ማታ ጊዜውን ጠብቆ ከሚፈነዳ አደጋ ጋር ማላተሙና የብሔር ግጭት የመቀስቀስ መዘዝ ማስከተሉን አስቀድሞ ለማወቅ ነብይ መሆን አይጠበቅም፤ የኢህአዴግ ‹‹እኔ ከሌለሁ ኢትዮጵያ ትበታተናለች›› ፉከራም ይህን መሰል ተንኮል ከገመደው የክልል አወቃቀር ቀመር ጋር የተያያዘ ይመስለኛል፡፡ በርግጥ ወደ እንዲህ አይነቱ ድምዳሜ የሚገፋን የሃሳቡ አመንጪዎችም ሆኑ መበታተናችን አይቀሬ እንደሆነ የሚያረዱን ራሳቸው የኢህአዴግ መስራቾች መሆናቸው ነው፡፡ በተቀረ ‹የምንከተለው የፌደራል ስርዓት ቋንቋን መስፈርት ያደረገ ነው› እስከተባለ ድረስ በሐረሪ ያለው አስተዳደር በራሱ በኢህአዴግ አጋፋሪነት በፀደቀው ህገ-መንግስትም ጭምር ተቀባይነት እንደሌለው ከገዥዎቻችን የተሰወረ አለመሆኑ አከራካሪ አይደለም፡፡ በነገራችን ላይ የሐረሪ ብሔራዊ ሊግ ከፈለገ በክልሉ ምክር ቤት ሰላሳ ስድስቱም ወንበሮች ላይ የመወዳደር መብት ተሰጥቶታል፡፡ በግልባጩ ኦህዴድን ጨምሮ በሐረሪ ብሔረሰብ አባላት ያልተመሰረተ ማንኛውም የተቃዋሚ ፓርቲ ከሃያ ሁለቱ ወንበር ውጭ በአስራ አራቱ ላይ እጩ ማቅረብ እንደማይችል በሕግ ታውጇል፤ የስራ ቋንቋንም በተመለከተ በክልሉ ነዋሪዎች ከአማርኛ ቋንቋ በሁለት እጅ ያነሰ ተናጋሪ ያለው ሐረሪ እና በስፋት የሚነገረው ኦሮምኛ ብቻ እንዲሆኑ መደረጉም ራሱ አገዛዙ ከሚያቀነቅንለት የቋንቋ ‹ፌደራሊዝም› ጋር ይጣረሳል፡፡ በርግጥም የስርዓቱ ‹ኤጲስ ቆጶሳት› ደጋግመው ‹ለአስራ ሰባት ዓመታት የታገልነው ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአፍ መፍጫ ቋንቋው እንዲማር፣ እንዲዳኝ፣ እንዲተዳደር… ነው› የሚሉት ሀቲት ማደናገሪያ መሆኑን ለመረዳት ከዚህ የበለጠ ክስተት ሊኖር አይችልም፡፡

በአናቱም የክልሉ ፕሬዝዳንት እና ም/አፈ ጉባዔ ከሐረሪ ብቻ የሚመረጡ ሲሆን፣ ዋናውን አፈ-ጉባዔ ደግሞ በጋራ ሁለቱ ጉባኤዎች እንደሚመርጧቸው በአዋጅ ተደንግጓል፡፡ እንዲሁም በፌደራሉ ህገ-መንግስት ላይ የተካተተውና አጨቃጫቂው ‹‹የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት›› የተሰጠው በተናጠል ለሐረሪ ብሔረሰብ ብቻ ነው፡፡ ይህ አይነቱ ልዩ ችሎታም ሆነ ከላይ የተጠቀሰው ልጓም አልባ ሥልጣን በሌሎች ክልሎች በተመሳሳይ መልኩ ለሚገኙ ብሔሮች አልተሰጠም፤ ለምሳሌ በደቡብ ሲዳማ፣ ስልጤ፣ ጉራጌ…፤ በአማራ ክልልም የአገው ብሔረሰብ ከሐረሪ የበለጠ ቁጥር ቢኖራቸውም በዞን ደረጃ እንዲዋቀሩ ከመፍቀድ ያለፈ ያገኙት ልዩ መብት የለም፡፡
በነገራችን ላይ ሐረሪ እንዲህ ለሀገር አንድነት አስጊ በሆነ መልኩ እንዲደራጅ የተደረገው በተወላጆቹ ፍላጎት እና ጥያቄ ነው የሚል እምነት የለኝም፤ ምክንያቱም የብሔረሰቡ አባላት እንደማንኛውም ዜጋ በኢትዮጵያዊነታቸው የሚያምኑና የሚኮሩ መሆናቸውን ከታሪክ መረዳቱ አያዳግትም፡፡ እናም በግሌ የዚህ ሁሉ መግፍኤ ስልጣኑን ለማስጠበቅ ኤርትራን እና አሰብን የመሰለ የሀገር ጉሮሮ (ወደብ) ኃላፊነት በማይሰማው መልኩ አሳልፎ የሰጠው ኢህአዴግ እንደ መጠባበቂያ አስልቶ ያጠነጠነው የተንኮል ድር ይመስለኛል፡፡ የክልሉ ህገ-መንግስትም ሆን ተብሎ ወደ አንድ ወገን እንዲያጋድል መደረጉ (በአንዳች ክፉ ቀን ሊመዘዝ የሚችል አደገኛ የፖለቲካ አጀንዳ ማቀፉ) ከላይ የጠቀስኳቸውን ማሳያዎች ያስረግጥልናል፡፡

የኃይማኖት መቻቻል…
muslim and christian
የሐረሪ ክልል ሌላኛው ችግር የኃይማኖት ልዩነት ያነበረው ውጥረት ለነዋሪው ሕዝብ ተጨማሪ ስጋት መፍጠሩ ነው፡፡ ከዓመታት በፊት በእንግሊዝ ዋና ከተማ ለንደን አልቃይዳ እንዳቀነባበረው የታመነውን የቦንብ አደጋ አድርሷል ተብሎ ተጠርጥሮ ከተያዘ በኋላ ዘግይቶ በነፃ የተለቀቀው ሐምዲ ኢስሐቅ የሐረሪ ተወላጅና የጀጎል ልጅ መሆኑ ክልሉ በማዕከላዊ መንግስቱ በአይነ ቁራኛ እንዲታይ አድርጎት እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ሐምዲ በአደጋው ተጠርጥሮ ጣሊያን ሮም ውስጥ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ለዜናው ከፍተኛ ሽፋን መስጠታቸውን ተከትሎ፣ በወቅቱ አንድ ጊዜ ብቻ ታትማ የጠፋችው ‹‹መዝናኛ›› መፅሔት ባቀረበችው ሰፊ ዘገባ እንዲህ በማለት ማስነበቧ አይዘነጋም፡- ‹‹በሐረር ጥብቅ የእስልምና ሃይማኖት ትምህርት ስር እየሰደደ ነው፡፡ አንዳንድ ሃይማኖተኞች እስከ ፓኪስታንና አፍጋኒስታን በመዝለቅ የእስላማዊ ትምህርትና ትግል ስልጠናን በመቅሰም እንደሚመለሱ ተረድቻለሁ፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በቁጣና በቁጭት የሚመለከቱት ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ ‹እውነት ከእኛ መካከል የተፈጠረው ሐምዲ ይህንን ሰርቶ ከሆነ አደንቀዋለሁ› ብሎኛል አንድ ወጣት፡፡››

በ2004 ዓ.ም. አፈንዲ ሙተቂ በተባለ ፀሐፊ ተዘጋጅቶ፣ የቅጂ መብቱን በመጋራት የሐረሪ ባህል፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ወጪውን በመሸፈን ‹‹ሐረር ጌይ›› በሚል ርዕስ ባሳተመው መጽሐፍ ላይም ሐረር ‹‹እስላማዊ ከተማ ናት›› ተብሎ መገለፁ በራሱ የሚያመለክተው ጉዳይ አለ፤ መቼም ዓለማዊቷን ከተማ ‹እስላማዊት›› እያለ የሚጠራን መጽሐፍ መንግስታዊው ተቋም አሳትሞ ማሰራጨቱ፣ ሃይማኖትና መንግስት የተነጣጠሉ ናቸው ብሎ በአዋጅ ለሚለፍፈው ኢህአዴግ መራሹ ስርዓት ምፀት ይመስለኛል፡፡ በርግጥም ‹‹ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት›› የሚሉትንም ሆነ፣ ሐረርን እስላማዊ ለማድረግ የሚያሴሩትን እንዲህ አቅፎና ደግፎ ‹በኃይማኖታችን መንግስት ጣልቃ አይግባ› ያሉ መዕምናን ተወካዮችን (መንፈሳዊ መሪዎችን) ሰብስቦ ማሰሩ አገዛዙ የመጨረሻው አፈና ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያመላክት ነው፤ የፖለቲካ ተንታኞችም ‹መንግስታዊ ሽብርተኝነት› የሚሉት ይህ አይነቱን ተግባር ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
ድሬዳዋ
ሌላኛው የምስራቅ ኢትዮጵያ ውጥንቅጥ የፖለቲካ መገለጫ የድሬዳዋ አስተዳደር ነው፡፡ ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን በመጣባቸው የመጀመሪያዎቹ ዓመታትና በቀድሞዎቹ ስርዓታት ድሬ በሀገሪቱ ግንባር ቀደም የንግድ እንቅስቃሴ ከሚደረግባቸው ጥቂት ከተሞች አንዷ እንደነበረች ነዋሪዎቿ ዛሬም ድረስ በትዝታ ያስታውሳሉ፡፡ ለዚህም እንደምክንያት የሚጠቀሰው በዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ዘመነ መንግስት ከአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ እና ጁቡቲ ድረስ ተዘርግቶ የነበረው የባቡር መስመር ነው፡፡ ይሁንና ኢህአዴግ ትግል ላይ በነበረበት ወቅት ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞ ያሰሙበት ከነበሩ የሀገሪቷ ከተሞች ድሬዳዋ አንዷ መሆኗ ቂም እንዲይዝባት ከመግፋቱም በላይ ‹የነፍጠኛ መከማቻ› ተብላ በ‹ጥቁሩ› መዝገብ መስፈሯ ባለፉት ሃያ ሁለት የስልጣን ዓመታት ባለችበት ትረግጥ ዘንድ በማይታየው የስርዓቱ ‹ክፉ እጅ› ለመዳመጥ ዳርጓታል፡፡

የሆነው ሆኖ ድሬ በተጧጧፈ የንግድ ሂደት ደምቃ የምትታይበት ያ የመኸር ዘመኗ እንደ ጉም በንኖ፣ ለአስከፊ ድህነትና ሥራ እጥነት እጅ መስጠቷን ለማስተዋል ከተማዋን ለጥቂት ሰዓታት ብቻ ተዟዙሮ መቃኘቱ በቂ ይመስለኛል፡፡ ርግጥ ነው የኢኮኖሚዋ ዋልታ ከምድር ባቡርና ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪክ (ኮተን) በተጨማሪ ሕጋዊም ባይሆን የኮንትሮባንድ ንግድ እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ይሁንና ዛሬ ከሞላ ጎደል ሶስቱም የሥራ ዘርፎች በጥልቅ እንቅልፍ የተወሰዱ መስለዋል (ምንም እንኳ ከታማኝ ምንጭ ባላረጋግጥም ኮንትሮባንዱ ‹ፖለቲካዊ ቡራኬ› ማግኘት በቻሉ የስርዓቱ የጥቅም ተጋሪዎች በድብቅ እንደሚሰራ ይነገራል) ምድር ባቡርን በተመለከተ ግን በህይወት ለመኖሩ ደፍሮ የሚከራክር ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ በርግጥ ለድርጅቱ መፍዘዝ ብሎም መክሰም እንደምክንያት የሚቀርበው ‹ኪሳራ› ቢሆንም ስማቸውን መናገር ያልፈለጉ፣ የተቋሙ የሒሳብ ሠራተኛ የነበሩ አንድ የድሬዳዋ ነዋሪ በዚህ አይስማሙም፤ እንደእርሳቸው አገላለፅ መስሪያ ቤቱ ለኪሳራ የተዳረገው የህወሓት ሰዎች ከጀርባ ባሴሩበት ደባ ነው፤ ‹‹በኤፈርት ስር ከተቋቋሙ ድርጅቶች አንዱ የሆነው የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ላይ የተሰማራው ‹ትራንስ› ከጅቡቲ የሚጫኑ እንደ የዕርዳታ ስንዴና ማዳበሪያ መሰል ምርቶችን በጨረታ እንዲያሸንፍ ይደረግና በጣም እርካሽ በሆነ ዋጋ ለምደር ባቡር የኮንትራት-ኮንትራት ይሰጠዋል፤ ይህ ሁኔታም እየተደጋገመ ሲሄድ ድርጅቱን ለኪሳራ ዳረገው፤ በዚህ ላይ ማነጅመንቱ በተቋሙ ንብረትና ጥቅም ላይ ሙስና ሲፈፅም፣ የስርዓቱ መሪዎች አይተው እንዳላየ ያልፉ ነበር፤ ሠራተኛ ማህበሩ ሳይቀር በግልፅ ለፀረ-ሙስና ሪፖርት ያቀረበባቸው፣ ነገር ግን በሕግ ያልተጠየቁ የአስተዳደር ኃላፊዎች አሉ›› ሲሉ ገደል አፋፍ ስለቆመው የቀድሞ የድሬ ‹ደም-ስር› ምድር ባቡር በቁጭት ይናገራሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት የድርጅቱ ንብረት በሙሉ በመከላከያ ቴክኖሎጂ (መቴክ) ለሚመራው የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡ ከሰራተኞቹም አብላጫው ተባርረው አምስት መቶ ለሚሆኑት ኢንዱስትሪው ከጥቅምት 30 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ ደሞዝ እየከፋላቸው እንደሚገኝና ከነበሩት 19 ሞተሮች (ባቡር) መካከልም አገልግሎት የሚሰጡት አራት ብቻ እንደሆኑ የድርጅቱ ቅርብ ሰው አረጋግጠውልኛል፡፡ ከአዲስ አበባ-መተሀራ እና ከካሳራት-ኤረር በጠቅላላ 114 ኪ.ሜ. ለሚሸፍን የድልድይ (ሀዲድ) ዕድሳት ይውል ዘንድ የአውሮፓ ህብረት የለገሰውን 60 ሚሊዮን
ዩሮንም (ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ የወሰደው የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ የረባ ስራ ሳይሰራ ‹‹ቄሱም ዝም…›› መሆኑ ብዙዎችን ግራ ከማጋባቱም በላይ በሀገሪቷ ኃላፊነት የሚሰማው መንግስት ያለመኖሩ ማሳያ ነው፡፡

በአናቱም መንግስት ሕገ-ወጡን የኮንትሮባንድ ንግድ በኃይል ሲያስቀር፣ ካለበት ኃላፊነት አኳያ አማራጭ የስራ ዘርፎችን አለመፍጠሩ ለችግሩ መባባስ ዋነኛ ምክንያት ሆኖ ይቀርባል፡፡ በተለይም በከፍተኛ ባለስልጣናት አንደበት ሳይቀር የ‹ደረቅ ወደብ› አገልግሎት መስጫ በድሬዳዋ እንደሚመሰረትና ለአካባቢው ነዋሪ አማራጭ የሥራ ዕድል እንደሚሆን ተደጋግሞ ከተነገረ በኋላ፣ ሃሳብ ተቀይሮ ሞጆ ላይ እንዲመሰረት መደረጉ ከተማዋ ‹አልቦ ተቆርቋሪ› መሆኗን እንደሚያሳይ በአንድ ወቅት የመስተዳደሩ ምክር ቤት አባል የነበሩ ግለሰብ ይናገራሉ፡፡ የግለሰቡ መከራከሪያ ‹‹ድሬዳዋ ለጁቡቲ ካላት ቅርበት አኳያ የከባድ መኪናዎችን ምልልስ ያፈጥነዋል፤ ይህ ደግሞ በወደብ ላይ ለሚከማቹ ጭነቶች የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ ያስቀራል›› የሚል ነው፡፡ በርግጥም ከአዲስ አበባ እምብዛም ከማትርቀው ሞጆ ይልቅ፣ ለእንዲህ አይነቱ አገልግሎት ድሬዳዋ የተሻለች መሆኗን ለመረዳት ጥናትና ምርምር የሚጠይቅ አይመስለኝም፡፡

diredawa
የድሬ ፖለቲካ…

የድሬዳዋ ነዋሪዎችን በተመለከተ በ1998 ዓ.ም (በፈረንጆች 2007 ዓ.ም) በስታስቲክ ባለስልጣን የተደረገው ቆጠራ እንደሚያሳየው አጠቃላይ የሕዝብ ብዛቷ 341 ሺህ 834 ሲሆን፤ ኦሮሞ 45%፣ ሶማሌ 24.3%፣ አማራ 20.7%፣ ጉራጌ 4.5%፣ ትግራይ 1.2%፣ ሐረሪ 1.01% ቁጥር አላቸው፡፡ በስፋት የሚነገሩ ቋንቋዎች ደግሞ ኦሮምኛ 46.1%፣ አማርኛ 33.2%፣ ሶማሊኛ 13.4%… መሆናቸውን ይዘረዝራል፡፡ ይሁንና ድሬ በተፃፈው ሕግ እንደ ሀገሪቱ መዲና አዲስ አበባ በፌደራል መንግስት ስር መዋቀሯ ቢደነገግም፣ በገሃድ ያለው እውነታ የሚያሳየው (በተለይም ከምርጫ 97 በኋላ) ኦህዴድና ሶሕዴፓ (የሶማሌ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ) ባልተፃፈ ሕግ በሚፈራረቁበት አድሎአዊና ብልሹ መስተዳደር ውላ-ማደሯን ነው፤ በርግጥም ዛሬ በሥልጣን ላይ ካለው የኦህዴዱ አሳድ ዚያድ በፊት፣ የከንቲባነትና የምክትሉን ወንበር አንድ የምርጫ ዘመንን ዕኩል በመክፈል ሁለቱ ድርጅቶች በየሁለት ዓመት ተመንፈቁ ሲቀያየሩበት መቆየታቸው የሚያመላክተው ዓብይ ጉዳይ ፌደራሊዝሙ በሕይወት ለመኖሩ በ‹ሳይንስ›ም ቢሆን ሊረጋገጥ አለመቻሉን ነው፡፡
በድሬዳዋ የሚታየው ሌላኛው ‹ፌደራሊዝማዊ› ፌዝ፣ ከነዋሪው ሕዝብ ቁጥር ኦሮምኛ ተናጋሪው 46.1% ሆኖ ሳለ የሥራ ቋንቋ አማርኛ መሆኑ ነው፤ ማንነትን በ‹ቋንቋ› የሚወስነው ኢህአዴግ ድሬዳዋ ላይ ተመሳሳይ መንገድ አለመከተሉ (…መቀነቱ ማደናቀፉ) በኦሮሞ ተወላጆች ላይ የሚደረገውን ተቋማዊ ጫና የሚያመላክት ይመስለኛል፡፡ መቼም ሌላው ቢቀር እንኳ ቢያንስ ራሱ የቀረፀው ‹ፌደራሊዝም› ሁለቱንም የሥራ ቋንቋ ማድረግ የሚቻልበት በቂ መፍትሄ እንደማያጣ ግልፅ ነው፡፡ ይህ ኩነት ኦህዴድም ልክ እንደ ብአዴን ከተላላኪነትና ቱርጁማንነት ያለፈ የፖለቲካ ቁመና የለውም ወደሚል ጠርዝ ይገፋል (በነገራችን ላይ የአጀንዳው ተጠየቅ በዚህ መልኩ የቀረበው ከራሱ ከኢህአዴግ ርዕዮተ-ዓለም አንፃር እውነታውን ለመፈተሽ ሲባል ነው እንጂ በግሌ የብሔር ፖለቲካ ለኢትዮጵያችን ይበጃታል ብዬ ስለማምን አይደለም)

እንደ መውጫ

ቋንቋ ተኮር ፌደራሊዝሙ ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ እንደ አዲስ ሀገር ማዋቀሪያ አማርጭ ፖሊሲ ተደርጎ ሲጠነሰስ የፌደራሊዝሙ ቅርፅ አገሪቱን ይበታትናል ከሚለው ድምፅ ባላነሰ፣ ደርዝ ያለው ሙግት ሆኖ ቀርቦ የነበረው በሀገሪቱ የረዥም ጊዜ የሕዝብ ለሕዝብ ፖለቲካዊ ግንኙነት በአንድ ቋንቋ ብቻ የሚወሰን ማህበረሰባዊ ቡድን (ብሔር) ካለመገኘቱ ባለፈ፣ ያንን የተወሰነ ቋንቋ የሚናገረው ስብስብ በአንድ በተወሰነ መልክዐ-ምድራዊ ቅፅር ውስጥ አይገኝም የሚል ነበር፡፡ ይህንን ክርክር ከዚህ ፅሁፍ አውድ አንፃር ተጨባጭ የሚያደርገው የጠቀስኳቸው ሁለቱ የምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ናቸው፡፡ በሁለቱም ክልል ውስጥ ከኦሮሞ እስከ ትግሬ፣ ከአማራ እስከ ሶማሌ… ከጠንካራ ኢኮኖሚያዊ አደረጃጀትና የየራስ ወጥ መለዮ ጋር መገኘታቸው መልክዐ-ምድራዊውን የፌደራሊዝም ቅርፅ ትክክለኛ አማራጭነት ለማስረገጥ በቂ ማሳያዎች ይመስሉኛል፡፡

ከዚህ ባሻገር የኢህአዴግ ‹ፌደራሊዝም› እንኳን ድርጅቱ ሥልጣን ላይ ባለበት ወቅት ቀርቶ፣ በሕዝባዊ ማዕበል በሚወድቅበት ጊዜም ቢሆን በአንድ ጀንበር መቀየር እንደማይቻል ቢታወቅም ሂደታዊ የእርምት አካሄድ ብቸኛው ፖለቲካዊ ትክክለኝነት ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ይህ ፌደራሊዝም የብሔር ግጭትን ከመከላከል በላይ ተራምዶ፣ ሰሞኑን እንዲያ ‹አሸሼ-ገዳሜ› የሚባልለትን በሕዝቦች መካከል አንድነት ሊያጠብቅ ቀርቶ በአግባቡ ባለመተግበሩ (ለምሳሌ በሐረሪና ድሬዳዋ የሚገኙ፣ ነገር ግን በክልሎቹ ስልጣን ውስጥ ያልተወከሉ ብሄሮች) የተፈጠሩት ኩነቶች ወደሰዓት ቦንብነት እየተቀየሩ የመጡትን የተለያዩ ቋንቋ ተናገሪዎች የእርስ በእርስ ትንቅንቆች
መግራት ከማይችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው፡፡ ይህ ኩነት “ደግሞ የእዚህች አገር ህልውናን ለመፈታተን ጥቂት ጊዜያቶችን ብቻ መጠበቅ የማይቀር ዕጣ ፈንታ ያደረገው ይመስለኛል፡፡

በጅዳ ቆንስል በር ውላ የምታድረው እህት ክራሞት . (ነቢዩ ሲራክ)

$
0
0

ነቢዩ ሲራክ

      343ይህችን እህት በጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት በር ተቀምጣ ካየኋት ሳምንት አልፏል። አልፎ አልፎ ላነጋግራት ብሞክርም መልስ አትሰጥም። መጀመሪያ የየኋት ቀን አካባቢ ከስራ ለተፈናቀሉ እህቶች አነሰም በዛ መጠለያ እያለ ፣ ለምን በር ላይ ትሆናለች? ብየ የጠየቅኳቸው የቆንስሉ ጸጥታ አስከባሪ ” አንተየ የዚህች እህት ጉዳይ አስቸጋሪ ነው ። ከመጠለያው ብዙ ቆይታለች ፣ አሁን በር  ላይ የሆነችው ሃገር ቤት ለመሄድ ወረቀቷ አልቆ እያለ ” ሃገር ቤት አልሄድም!” በማለቷ እነረደሆነ ተነግሮኛል ። ” በመጠለያው የነበሩት ሰነዳቸው ባሳር በመከራ አልቆ ሲሸኙ ወደ ሃገር ቤት አልሸኝም ብላ ረብሻ ከማንሳት አልፎ ከተዘጋጀው መኪና ወርዳ ይህን የምታየው ሚኒባስ መስታውት ሰብራዋለች!  ከዚያን ቀን ወዲህ አትበላም አትጠጣም ፣ እኛንም የገረመን ይሄ ነው!  ሚን ታደርጋለህ! ” ነበር ያሉኝ …

       ይህ ከተነገረኝም “ወዲህ ሃገር ቤት አልገባም!” ያለችው እህት ለቀናት  በቆንስሉ በር አልጠፋችም። ከተቀመጠችበት ወንበር ጀርባ ባለው ግድግዳ ” ህጋዊ ሰነድ የሌላችሁ እና የወጣውን የሳውዲ ህግ መስፈርት የማታሟሉ ወደ ሃገር ግቡ !” የሚለው የቆንስል ማስታወቂያ ይታያል ። ከአጠገቧ በፕላስቲክ ኪስ የታጨቀ ጓዟን አስቀምጣ ፣  በሆዷ ቁርአን ታቅፋ አንገቷን ከመድፋት ባለፈ በአካባቢው አዛን ስትሰማ የዘወትር ጸሎቷን (ሰላቷን) ወንበሯን ፈቀቅ አድርጋ እንደምትሰግድ አንድ ዘወትር እንቅስቃሴዋን የሚከታተል ወዳጀ አጫውቶኛል… እንዲህ ሆና ኮርመት ብላ ውላ ታድራለች! ቀን ጸሃይ ሲወቃት ፣ ማታ ወበቁ ይፈራረቅባታል ! ካየኋት ቀን ጀምሮ ወደ መጠለያው እንድትገባ ብዙ ሁነን ብንማጸናትም አልተሳካልንም …

       ከሃገሯ በጤና የመጣችው እህት ችግር ውጋቷን እንድንጋራ ስንጠይቃት አትመልስም  !  ወደ ሃገር ቤት እንድትገባ በጅዳ ቆንስል ልትሸኝ ቢሞከርም አልተሳካም። የ”ሃገር ቤት ግቢ!” ” አልገባም!” አለ መግባባት  ፍርሻ ከመምጣቱ በፊት አንዳንዴ ኦሮምኛና ብዙ ጊዜ ግን የተሰባበረ  አረብኛ እየቀላቀለች መናገር ይቀናት እንደነበር አንድ ” በመጠለያው እያለች አውቃታለሁ!” ያሉ ወንድም አጫውተውኛል። ያን ሰሞን ወደ መጠለያው እንድትገባ ተለምና ብትገባም በመጠለያው ውስጥ ካሉ ግፉአን ጋር ግብ ግብ ፈጥራ መውጣቷን ሰምቻለሁ  !

     ይዚህች ግፉዕ እህት ሰላም የነሳና አዕሮዋን ያወከ የውስጥ ህመም ሚስጥር አይታወቅም! ትሰማለች ፣ ለመናገር አልፈቀደችም!  ባሳለፍናቸው የበር ላይ ውሎዋ ትንፍሽ ብላ ስትናገር ቢያን እኔ እስከ ዛሬ አልሰማኋትም ! ውስጧ እንጅ ውጭ አካሏ የተጎዳ አይመስልም! ከሁሉም የሚገርመው ይህች እህት ጤናዋ ታውኮ እንኳ ሃገር ቤት ከወገኖቿ ጋር መቀናቀል ሞት መስሏታል  ! ሌላው አስገራሚ ሂደት  የዚህችን መልከ መልካም እጣ ፈንታ የምንመለከትም ህጋዊ ሰነድ የሌለን ብዙዎች የሳውዲን መንግስት የምህረት ቀቢጸ-ተስፋ ሰንቀን ጤናችን ተጠብቆ እያለ” በሰላም ሃገር ቤት ግቡ !” የሚለውን የመንግስትና የወገን ምክር መቀበል አቅቶናል !  እንዴት ነው ነገሩ …?

አንድየ ይታረቀን ከማለት ባሻገር ምን ይባላል :) ብቻ እሱ ያቅልለው እንጅ የሚሰማ የሚታየው ይከብዳል ! … ያማል … ያማል  !

ነቢዩ ሲራክ

የተከለከለ ~~ ፍቅር –ሲፈቀር –ይገርም … እኮ! ምን ልበል ታዲያ -. ከሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 11.12.2013

ፍቅር የትውልድ ዋዜማ ነው።

የመንፈስ ማዕቀብ ሲነሳ የነፃነት ፈል ችግኝ ይበቅላል በዚህ ልጀምረው ….

4568ፍቅር ምንድን ነው? ማድመጥ። ፍቅር ዜማ – ጹዑም! ፍቅር የመንፈስ ጥንግ ሽብሻባ። ፍቅር የስሜት ቃናዊ መዝሙር። ፍቅር የአኃቲነት ብርቅ ወረብ። ፍቅር የመስጠት ለጋስ ፏፏቴ። ፍቅር የታሪክ ማውጫ ፍትኃ – ነገሥት። ፍቅር የውስጥነት ፍውሰት – ድህነት! ፍቅር ጣዕም ንጥር – መረቅ! ፍቅር ብጡል* ክብረት። ፍቅር ምህረት። ፍቅር ይቅርታ። ፍቅር ረቂቅ። ፍቅር ቀጥታ። ፍቅር መሆን። ፍቅር ኃብታም ነው ዲታ። ፍቅር ምህረት ነው ዘንባባ! ፍቅር ወድ ነው ስጦታ። ፍቅር ሩህሩህ ነው ርግብ። ፍቅር ፈውስ የራህብ። ፍቅር ጻድቅ የመስቀል ወተት። ፍቅር የመስዋዕትነት ጤና አዳም። ፍቅርን ሲሰጡ ሊፈቀሩ የሚችሉ ፍጡራን ፍቅርን ሲከለከሉ ደግሞ ማመጻቸው አይቀሬ ነው!  ይፈነዳል።

ዋ!

እናት ከሁሉም በላይ ትውደዳለች። እናት የመጀመሪያዋ የህይወት ትምህርት ቤት ናት። እናት መቅድመ የቤተሰብ አሰተዳዳሪ፤ የተፈጥሮ ሙሁራ ሊቀ-ሊቃውንት የርህርህና መግቢያም።  እናት ደግሞ ሴት ናት። እኔ በዓለም ደረጃ የፍቅር ምልክት ወይንም ዓርማ ሊሆን የሚጋባው ልብ ሳይሆን እናት ነው መሆን ያለበት። ስለምን? እናት ልልጇ የምትሰጠው ፍቅር የማያብል ነውና። እውነተኛ የፍቅር ተፈጥሮ የሚገኘው ከስፖርት ማልያና ከእናት ብቻ ነው። እናት የሥነ ፍጥረት ሙሉዑ አጀንዳ ናት! እናት የመንፈስ ቋንቋ ናት!  ዬዓለም ተወዳጁ ሥም እማማ!

 

እስኪ ወፍ ካወጣን አብረን … ወደ ተለምኩት ብያለሁ፤ ቀልቤን ወደ ገዛው፤ ሩኼን ወደ ዳኘው። ጉዞ በጋራ መልካም ነው። ኑሮም በወል ጣዕሜ ነው። … ሴት እህት ስትሆን ትፈቀራለች። ሴት አክት ስትሆን ትጠጋላች። ሴት ሚስት ስትሆን እንደ ነፍስ ትታያለች። ሴት ጓደኛ ስትሆን ትታመናለች። ሴት እናት ስትሆን የጸጋ ስግደት ይሰገድላታል። ሴት ይሁን ይሁን … አሜን አሜን … ስትል ….. ሰጥ ለበጥ ብላ ስትገዛና ስትረገጥ …. ስትመች ትመረቃለች ….

 

እኔ እንደማስበው በእምነቴ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት አምስቱ አዕማደ ሚስጢራት ላይ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልዑቅ ነገረ ሳይመር መቅረቱ በጣም ይጎረብጠኛል። እንደሚገባኝ ከሆነ ግን የተዋህዶ ልጆች ለቅድስት እናታችን ባለን ፍጹም ልዩ ፍቅርና ስስት ከጸጋ ስግደት ይልቅ የአምልኮ ስግደት ይገባታል ብለን እንዳንሟገት ብልሆቹ አቨው አስበውበት፤ ምንአልባትም መንፈስ ቅዱስም አቀብሏቸው ወይንም ሚስጢር ገልጦላቸው ሊሆን ይችላል። ለማንኛውም ከመንፈሳዊ ዓለም ወጥተን ወደ ገኃዱ ዓለም ስንመጣ … በፖለቲካ አስተሳሰብ ሴት ላቅ ስትል ግን „ጉልበታምንት“ ይለጠፍላታል። በጠራ ቋንቋ „ጉልበታም“ ትባላለች። ገና ሳትታወቅ እፍታ መስመር ላይ እኮ ነው …. ልደቷን ሳታከብር የምትገፋው – ገምድልንት* የተከለከለ ፍቅር ይሏችኋል ይህ ነው። ቁስለት!

 

ሴት ረድ ስትሆን ትወደዳላች። ሴት ሎሌ ስትሆን ትደነቃለች። ሴት የቤት ውስጥ ሰራተኛ ስትሆን ስንዱ ትባላለች። ሴት ጠቅልል ጠቅለል አድርጋ ስታጎርስ የራህብ ደራሽ ትባላለች። ሴት ጓዳ ጉድ … ጉድ ስትል ዓይን አብሮ ይዞራል። መንፈስም አብሮ ይንከራተታል። ልብም ዳንኪራውን ያስነካዋል ስሜትም አብሮ ይከትማል። ፍቅሬ ወ/ሮዬ ትባላለች። ዓለም የፈጠረው ቄንጠኛ የዘነጠ ሥያሜ ሁሉ ይሰጣታል። ሴት እንግዳ ስታስተናግድ ትመሰገናለች። ሴት ልጅ ስትሰጥ በዓይኔ ላይ ፍሰሺ ትባላላች። ሴት ስልጣን ልትጋራ ብቅ ስትል ግን „ኃይለኛ“ ተብላ ትኮረኮማለች ወይንም ትባረራለች። ሌላ ድልዝ ይፈልግላታል። ሌላ የሰብዕናዋ ድክምት ቁፋሮ ይጀመራል።  የተከለከለ ፍቅር … ጎባጣ

 

ሴት ገንዘብ ያዥ ስትሆን ትመረጣለች። ሴት ገንዘብ ስትሰበስብ ታማኝነቷ ይሰበክላታል። ሴት እልፍኝ ስታሰናዳ ትሞካሻለች። ሴት ስነጥፍ ወይንም ስነጠፍ እንደ ብርቅ ትታያለች። ሴት ቅራኔ ውስጥ ገብታ ስተቀረቀር ይጨበጨብላታል። ሴት መድረክ ላይ ወጥታ አቅም ባላው ብቃት በፍፁም ታማኝነትና ግልጽነት እኩል ስትመጥን አቅሟን ለአደባባይ ስታበቃ ግን በግሳፄ ትባረራለች ….. ድገም ሳትል ከቢጫው ቀዩ ካርድ ቀድሞ ያለ ማስጠንቀቂያ ከጨዋታ ውጪ ትሆናለች። ነዳላ ገጠመኝ። የአንተ ያለህ ….

 

ሴት ስትለብስ ትፈቀራለች። ሴት ስተሸቀረቀር እንጉርጉሮው ላቅ – መጠቅ ይላላታል። ሴት የተፈጥሮን ፍቅር ስትመግብ ንቢት ተብላ ትሞገሳለች – ትመገባለች – ትጎረሳለችም። ሴት ሽክ ብላ ከጎን ስትጓዝና ግብዣ ላይ እኩል ስትቀመጥ አጃችን* ይሞላል ልጎዝጎዝልሽ ነው። ሴት ገብያ ወጥታ ቀጨር መጨሬውን ስትሸማምት አበጀሽ ትባላለች። ሴት ኮስሜቲክስ ስትገዛዛ ውዳሴ ይነጠፍላታል።  ሴት ወንበርን ልትጋራ ጥንካሬዋን ስታስመከር ግን ትገፈተራለች …. ቆመጥ ይዘጋጅላታል ….. የተከለከለ ፍቅርነቀዝ!

 

ሴት ቤት ስትውል፤ እንደ እመቤት ትታያለች፤ ጨዋ የተረጋጋ መንፈስ የረበባት እዬተባለ ይሰበክላታል። – ደስታ ነዋ ስታፎከፉክ። ሴት አንገቷን ደፍታ መከራን ስትቀበል ቅኔ ይዘረፍላታል። ሴት የልጆች አሳዳጊ ብቻ ስትሆን ትበረታታለች – ትሸለማለች። ሴት በማይታዩ ሩትን /ጥቃቅን/ ተግባራት ስትሰማራ ማን እንደ አንቺ ትባላለች። ሴት አንደበቷ ታስሮ የሳሎን ጌጥ ብቻ ስትሆን ማለፊያ ይባልላታል። ሴት ግን ኃላፊነትን እኩል ለመጋራት ጠበቅ ጠንከር ብላ ብቅ ስትል ጦር ይሰበቅባታል።  ያደገ ወይንም ያልተነካ ድንግል ወጥ ሃሳብ ወይንም ግኝት ወይንም ላቅ ያለነ የቀደመ ግንዛቤ  ስታፈልቅማ እሷንማ በሽታሽቶሽ* መውቃት።የተከለከለ ፍቅር …. ምግለት!

 

ሴት ስትጋግር … ስትሰራ …. ስታጥብ … ልብስ ስትተኩስ፤ ስታረግዝ …. ስታጠባ …. ከሚፈለገው ቦታ ላይ ተገኝታለችና ይዘፈንላታል። ከዚህ አለፍ ብላ የመብትና የእኩልነት ጥያቄ ስታነሳ ግን ትወረወራለች …. እውነት ለመናገር በዘመናችን ያሉ ሴቶች እንኳን ጥቃ ሊቆምላቸው፤ እንክብካቤ ሊያገኙ ቀርቶ ገፍተው የሚወጡት በጣም ጥቂቶች ለምነው ለመታገል እንኳን ፈቃድ አያገኙም በወንድ ትምክህተኞች …. ዛሬም ከዛሬ 100 ዓመት በፊት ካላው ኮረብታ ላይ እንዳሉ አሉ እነ ተባዕት …. ከእነ- የወንድ የበላይነት ተጫኝ ስሜታቸው ጋር ተጋብተው። ስለ ሴቶች ብዕራቸው በተቆርቋሪነት የሚቃኙት ከአንድ ለእናቱ  ሙሁር ከፕ/ አለማዬሁ ገ/ማርያም በስተቀር …. ፕሮፌሰሩ ከክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ጋር በመገናኘታቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ሐሴትም አድምጠናል። ረስተውንም አያውቁም – ቅርባችን። ስለ ሴቶችን በሚያጠቃው የካንሰር በሽታ በተቆርቆሪነት የጻፉት ልብን የሚነካ ነበር። እውነት ልዩ አብነት ናቸው – ለእኔ። ድህነቴ እንጅ ለእሳቸው የምስጋና ቀን ባዘጋጅ ዕድለኛ በሆንኩ ነበር።

 

በፍጹም ሁኔታ የነፃነት ትግሉ ሆነ፤ ነገ የሚታሰበው የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መሰረቱና እርገቱ ከሴቶች ውጪ ሊታሰብም ሊሳካም እንደማይችል በጣም በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። የነፃነት ትግሉ የሴቶችን ሙሉዑ ተዋፆ በአጽህኖት፤ በተደሞና በአርምሞ ይጠይቃል። መደመጥ አለበት። አጥበቆ! አኔም የጥቃቱ ማዕደኛ በመሆኔ …. በልበ ሙለነት እጥፋለሁ … እንዲህና እንዲያ … ትርፉ ትራፊና ፍርፋሪ ካልሆነ ….

 

ይህቺ ለመላሾ እነ ተባዕት „ ቦታ አካፍለናል“ የሚሏት …. ልጥፍ ሽፋን ልግጫ ለማንም አይበጅም - ነገንም አያበጅ። የዶደመ …. መንገድ ነው። የነፃነት ትግሉ ሙሉዑነት ሊረጋገጥ የሚችለው የሴቶችን የመጠነ፤ ያስተዋለ፤ ያደመጠ፤ ያከበረ ተሳትፎ በቅንነት ተግባር ላይ ዛሬውኑ ሲያውል ብቻ ነው። ኢትዮጵያ ሀገራችን ካላት ያልተነካ ቅምጥ ዕምቅ ኃይል በላይ የሴቶች ሃብት እስከ ዛሬ ድረስ ሥራ ላይ አልዋለም። … ነገም ከፍቶት ይታዬኛል።

 

እርግጥ ማሳሳቻ አስፓልት አለ። „የሴቶች መምሪያ ከፍተናል … ጉዳያቸውን የሚከታተል መዋቅር ዘርግተናል“ … ይህ የሴቶችን ብቃት የሚያቀጭጭ አፋኝ የማስመሰያ ጅራፍ ነው። በአንድ ወቅት ፕ/ መራራ ጉዴናን አበክሬ እጠይቃቸው ስለ ነበር ንገሩልኝ የሴቶች መምሪያ በድርጅቴ መጀመሬን አሉ። የዛሬ 14 ዓመት መሆኑ ነው። አሁንም እሳቸው ከያዟት ቁልፍ ቦታ ግን ፈቀቅ አላሉም። ጨምድደው ጉብ ብለው ይለፉንም ዘግተው አሉ እንደ አገዱ። ይህ ትልቅ ግድፈት ነው። የእኔ ሙግት የነበረው በ2ኛው  የኢተፖድህ ጉባዔ ከዬትኛውም አባል ድርጅት አንድም የአንስት ውክል አካል ልትገኝ ደረጃዋ ባለመፍቀዱ ነበር – አበክሬ እናገር የነበረው።

 

ዘግይቶ የዛሬ ዓራት ዓመት ገደማ መደረክ ሲቋቋም አዬነው በመላጣ – ጎብጦ የሴቶችን እኩልነት በባዶ ቃላት ተለብጦ። ያው ቢገላበጡም ጃኬቱም ቢቀያዬር የተባዕት ክምር። የድርጀታቸውም አቅም … የወንዶች ብቻ – ቁልቁል። ይህ ለናሙና እንጂ በሽታው ሁሉንም ያካልላል። ከእከሌ ድርጀት እከሌ ይሻላል ብዬ ውዳሴ ባቀርብ የሴትነቴ ክብር ይዘቅጣል። ሴትነቴ ካለይግባኝ ዘቅዝቆ ይሰቅለኛል። ተፈጥሮም ፊቷን ታዞርብኛለች። አምላኬም ከልቡ ያዝንብኛል። ሃቁን ለከንቱ ውዳሴ ብሸብብ።*

 

በማናቸውም ዘርፈ እኔ ነኝ ባለ ወሳኝ ኃላፊነት ሁሉ ሴቶች ጉልበታም አቅም አላቸው። ለዛ የሚመጥን ቦታቸውን አትጋፉ ነው መሰረታዊ ትግሉ። አጽህኖታዊ መጠዬቁም። እድሉን ያገኙ ሴቶች ተዝርክርኮ ሳይሆን አምሮና ሰምሮ፤ በጥራትና በጥንቃቄ እንዲሁም በስልትና በብልኃት ሁለመናው ያምርበታል። ሴቶች ኃላፊነታቸውን ለመወጣት የሚተጉት …. በእናትነታቸው ፍጹም የማይታይ ሰማያዊ ጸጋ አስውበው ነው። ምቹ ሁኔታ  ካገኙ፤ በቂ እንክብካቤና ጥበቃ ለመክሊታቸው ከተደረገ …. ማን ችሏቸው። ያኮራሉ! ተወዳዳሪም የላቸውም። ሚስጢር ይመሰጠራል። ትርጉምም ይነበባል። ተፈጥሮም ይዘክራል። የሰብዕዊ መብት አከባበርም ጽኑ ባለሟል ሲገኝ በደስታ ይፍለቀለቃል። እኔ እላለሁ ሴቶች የተፈጥሮ ድንጋጌ ናቸውና።

 

አውሮፓ ያላችሁ ሁሉ እንደምትከታተሉት አውሮፓ በኢኮኖሚ ውጣ ውረድ ተሰቅዞ ሲባትልና ሲብተለተል የመፍትሄው ጭንቅላት የተገኘው አንፃራዊ በሆነ ሁኔታ ማለቴ ነው ከጀርመን ነበር። የጀርመኗ መሪ ጠ/ሚ ወ/ሮ አንጅላ ሜርክል ቀጥ አድርገው በማያዝ ማገር ሆነው አውሮፓን ከውርዴት ዘመኑንም ከጥፋት ታድገውታል። ጠ/ሚር ሜርክል ፓን አውሮፓኒስት ናቸው። በተግባር የከበሩ የመጀመሪያዋ የጀርመን ተወዳጅ ሴት መሪ ናቸው። እርግጥ ከዚህ ጋር ያሉ ከፈረንሳይ ጋር የተሳሰረ ትብትብ ቢሮክራሲን  ዘልዬ …

 

ለናሙና …. የእንግሊዟ ታችር፤ ንግስት ኤልሳቢጥም፤ ተፍርተው በአጭሩ ተቀጩ እንጂ ልዕልት ዲያናም አሳይተዋል አስመስክረዋል … ያን ጉልበታም ተዝቆ የማያልቅ ብቃት …. ከብልህነት ጋር። ይህ በኒውዘላንድ፤ በአውስትራልያ፤ በፊላንድና በብራዚልም ተመሳጥሯል። ሲዊዘርላንድ በሰባት ሰዎች ትመራለች። አራቱ ሴቶች ናቸው። ያውም ቁልፍ ቁልፍ ቦታ የያዙ … በጀርመን ካለፈው ወራት ሀገራዊ ምርጫ በኋላ ያለውን ሽግሽግ አልተከታተልኩትም እንጂ ቀደም ባለው ጊዜ በርካታ ሴት ሚ/ራት ነበሩ …. የእውነት አባዛኞቹ ሴቶች በማለት ብቻ የሰከሩ አይደሉም። እናታዊ ሥነ -ምግባራቸው አይፈቅድላቸውምና! ይልቁንም በመሆን የበለጸጉ እንጂ …..

 

በዓለም በፈጠራ፤ በሳይንስና ምርምር፤ በሰብዕዊ ተግባር፤ እንዲሁም በሥነ – ጥበብ የበርካታ ምርጥ ዕንቁ ሴቶችንመዋዕለ ተጋድሎ፤ የያዘው የኖቤል ተሸላሚ ሴቶችን አስኪ ገድሉን ጎብኘት አድርጉት ….  እኔ በመንፈሴ እማማ ዊኒን፤ ሜርክልን እያጨሁ ነው። ብቁ ናቸዋ። በዬዓመቱ ከሲኤንኤን ጀግኖች ሴቶችም እኩላዊ ብቃታቸውን ለአደባባይ አብቅተዋል። እርግጥ እዬታፈኑ፤ ሳይታዩ እንዲጠፉ እዬታደመባቸው፤ እንዲከስሙ የተዘመተባቸው፤ እንዲሁም አስታዋሽና ጠበቃ ያጡት ሚሊዮኖች የነጻነት ሴት አርበኛ፤ የሥነ ተፈጥሮ ሁነኛ፤ የሥነ ጥበብ እማ ወራ … የፈጣራ ቀንዲል ዕልፍ ናቸው። የዓለም ብቁ ዜጎች ሴቶች መሆናቸው ምንም ለድርድር የሚቀርብ አይደለም። በአግባቡ ተከታታይና ባለቤት ቢኖረውማ …. በቁጥር ይበልጡም ነበር – በሁሉም ዘርፍ።

 

ለሁላችንም የሚጠቅም ስለሆነ ደግሜ በመፃፌ እንደማላሰላችሁ በማሰብ በዘመነ ክሊንተን ያን የዓለም ስሜትን የሳበ የፕ/ ቢል ክሊንተን ተብዕታዊ ቅብጠት ብልኋ ባለቤታቸው እመቤት ሄነሪ ክሊንተን የሆነውን እንዳልሆነ አድርገው ትቢያ አልበሰውታል። በወቅቱ አንድ የፕሬስ ሰው እንዲህ ሲል ጠይቋቸው ነበር … „የሚባለውን አልሰማሽንም? … አላነበብሽውንም?“ ሲል ብልኋ እመቤት ግን መንፈሱ እንዲህ ነበር „ እናቴ ከልጅነቴ ጀምሮ ያስተማረችኝ ሰው የሚለኝን ከሰማሁ የምሰራው የሰወችን እንጂ የእኔን እንዳልሆን ነግራኛለች፤ አስተምራኛለች። መርሄ ይህ ነው። እኔ የኔን ሥራ እሰራለሁ ሌሎች ደግሞ የራሳቸውን ይሰሩ“ ነበር ያሉት። ሰማዬ ሰማዬት የዘለቅ ዕጹብ መልስ ነበር። በዚህም ትዳራቸውን ከነዙፋኑ ሀገራቸውን ከነአልማዙ እስከብረዋል። አንስትን የወከለ ማለፊያ ብቃት!

 

ከዚህም በኋላ በዘመነ ፕ/ባራክ ኦባማ የውጭ ጉዳይ ሚር/ ሆነው እጅግ ውስብሰብና ፈታኝ በሆኑ መሰናክሎች ሁሉ በማለፍ የሴቶችን የመወስን አቅም በተግባር አሳብበውታል አሁንም የፕ/ ባራክ ኦባማ ባለቤት ቀዳማይ እመቤት ሚሻዬል ኦባማ ሁለገብ ንብ በመሆን ባለቤታቸውን ለሁለተኛ ጊዜ የሥልጣን ባለቤትነት አብቅተዋል … ለዚህም ደረጃ ያበቋቸው ቀዳማይ እመቤት ወ/ሮ ሚሻዬል ናቸው። ነገም ለፕሪዚዳንትንት እራሳቸውን ችለው ሊወዳደሩ ይችላሉ። ተወዳጅም ናቸው – ወ/ሮ ሚሻዬል። ወንድሞቼ ሆይ! የነፃነት ትግሉ መሪ አባ ወራዎች ሆይ! ዓይን ካላችሁ ከዚህ ሀቅ ጋር የመንፈሳችሁ ብሌን ይታረቅ ዘንድ ብዕሬ በጽሞና ያሳስባችኋል … በአክብሮት – በትሁት መንፈስ።

 

በአፍሪካ ታሪክ ጉልበታሙ የፕ/ ማንዴላ ተገዳሎ የምዕተ ዓመቱ ታላቅ መዘክር ነው። ሚሊዮን ሰማዕት ሴቶች ታድመውበታል። በፆታዊ ችግር አፓርታይድ ያሴረውን መረብ ዝለሉትና ክብርት የነፃነት ብቁ አርበኛ እማማ ዊኒ ማንዴላ ባላቤቷ እስር ቤት በነበሩበት ጊዜ የነፃነት ትግሉን በግንባር በመምራት፤ ልጆቿን በማሳደግ፤ ለትዳር አጋራ አጥር ቅጥር በመሆን የጽናት ወተት ነበረች። ይህን ከባለቤቷ ጋር ትጻጻፍ ከነበረው የነፃነት ትግሉ ዋነኛ ትምህርት ቤት ዝክረ ደብዳቤዎች ማገናዘብ ይቻላል። ህያው ምስክር ነውና። ሁሉም ፍጡር እናቱን የሚወድበት ሚስጢር በሀገር ጉዳይ ላይ ቢውለው ምንያህል ፈውስ በነበረ – ለመለውዓለም። የ ዓለም ዝበርቅ አስፈሪ ውጣ ውረድ ፍቺ ያለው ከሴቶች ነበር … ባሊህ አጣ እንጂ …

 

በእኛዋ እናት ሀገርም … በቀደመው በዘመን ንግስት ዘውዲቱ የመቻልን ተፈጥሮ፤  ከእቴጌ ምንትዋብ የተግባር ሚስትነትና አርበኝነትን፤  ከከዕቴጌ ጣይቱ ብልህነት – ፖለቲካ መሪነትና አማካሪነት – ጠበብትነትና ጀግንነትን ጠብተን አድገናል። በዘመናችንም … ሳራ ግዛውና ሺብሬ በሰማዕትንተ፤  አያልነሽ – አለምዘውድ፤  ብርቱካን ሜዲቄሳ፤ ሰርካለም ፋሲል፤  ርዕዮት ዓለሙ፤ በላይነሽን ስንቶቹን የነፃነት አርበኞች እናት ሀገራችን አፍርታለች። መሬታች መሃን አይደለም። ተሳትፎውን በጉልበት ያነጠፈው* ያንጠፈጠፈውም የወንድ በላይነት ብቻ  ነው። አሁንም  በአንድነት ወ/ት ወይንሸት የምትሰጠውን ቃለ ምልልስ አኑትና አጣጥሙት …. ያው ታች ስለሆነች ቅጥቀጣው ያልፋታል ብዬም አስባለሁ … ቀና ካላች ግን ቅንጧን ነው … በለመደ እጅ … እህህህህህ!

 

እኔ … በአጽህኖት እናገራለሁ። የፖለቲካ መሪዎቻችን የውስጥ ለውጥ ያስፈልጋቸዋል። በፍጥነት። በንግግራቸው ውስጥ እንኳን ብጣቂ እርስት አልተሰጠነም። እንኳንስ በፍላጎታቸው ልብ። በራዕያቸው አንጎልም የለንም። አብሰንት ነን።  ምንአልባት ትዝ የምንላቸው የራባቸው ጊዜ ይሆናል። ለነገሩ ነጭ ሀገር ፋስት ፉድም አለ … ዘመኑ ተለውጦ እራስም ይጋገራል … ሀገር ቤትም ተለምዷል አሉ … የጓዳ ነገር። እንዲሁም በዬአጋጣሚው የሚሾሟቸው አብዛኞቹ የበታች ገዢዎቻችንም ለውጡ ገፍቶ እንዲያነጥራቸው እንሻለን። አቅም በመበተንም አንቱ ናቸውና! ይደግም። የበታቾቻቸው አቅም በመበተን አንቱ ናቸውና!

 

የበላዮች የበታቾቸውን የሚከታተሉበት መስመር ቢኖር መልካም ነው። የጉሮሮ አጥንቶች እነሱ ናቸው። የፓለቲካ አመራር ልም ነው። ጣጣውን የጨረሰ ለስምሪት የበቃ ንጥር ቅቤም፤ ለስምሪትም ስንዱ። እኔ የማዬው ዘመንተኛው ፖለቲካ ግን ሽርክትና ግርድፍ ሆኖ ነው። አብሶ አጋርን በመገፍተር እረገድ ከንፍሮ የወጣ አንድም መሪ አልገጠመኝም። ቆሞ ስለ አርበኛ አንስት የሚመሰክር ዓይናችን አላዬም …. እንደናፈቃቸው ይቅር ዓይነት ነው ነገሩ …

 

እርግጥ ነው ሥር ላይ ያለው ተግባርን የሚያደምጡት፤ ከበታቾቻቸው ለዛውም ስታስቲክሱን በሩቁ ነው። ያው ወያኔ ባላው የተዛነፈ ዳታ ይወነጀላል። የኛም እኮ ያው ነው። ከታች ወደ ላይ የሚተላለፈው ቁጥር ተብዬ። የበቃ ፍጽምና ያለው ተሳትፎ …  ለማዬት ወረድ ይበሉ። ሰፊ መድረክ ይክፈቱ። የትችት አንባ ይወጁ። እንዲያድጉ እንዲመነደጉ ከፈለጉ። … በራስ አነሳሽነት የሚደረገው የፈጠራ ተሳትፎም እምብዛም ነው። ሁልጊዜ ከላይ የተንጠለጠለ መና ይጠበቃል። የማኒፌስቶውን ጭብጥ ይዞ ጭብጥን በጭብጥ አፋጭቶና አታግሎ የነጠረውን የፓርቲያቸውን አቋም አሸናፊ ለማድረግ ፈጠራ ከአቅም ጋር ይጠይቃል። ማረር!

 

ያው ቁንጮቹ የሚሉትን በተገኘው አጋጣሚ የጎረሱትን እዬፈቱ ሲደግሙና ሲሰልሱ ዓመት ይዞ እስከ ዓመት ከዛው ለዛው ሲዳክሩ ነው የሚታዩት። ተመስገን ነው ዛሬ እድሜ ለኢሳት በተለያዬ መድረኮች መሰናዶ ከሊቃኖች አዳዲስ ነገር ስንቅ ስለሚገኝ ተሽሎ ሊሆን ይችላል። ግን የራስ ጌታ ለመሆን ማንበብ መልካም ነገር ነው። የዬትም ሀገር ነፃነት ትግሎች ለድል እርከን ያደረሱት አጋራቸውን በበሰለ ህሊና ባሊህ ብለው ነው።  … እርግጥ ላይኞቹ ሴቶች ማለት ሲጀመሩ የታችኞች ቅጂውን እንደ ገደል ማሚቶ ያስተጋቡታልና እባካችሁ ላይኖቹ ጀመሩት …. ግን በተለበጠ መልኩ ሳይሆን ቁምነገር ባለው ዕውነት – ከልብም። ዝም ብሎ ከሆነ ልጥፍ ይሆንና የተላመጠ አገዳ ይሆናል ምኖታችን።

እኛ እንላላን። እኔና ትዳሬ ብዕሬ …. ተከታታይ የሆነ አቅም ያለው የመንፈስ ጥሪት ለመገንባት ይሞክሩ ፖለቲከኞቻችን ….፤ ሙሁሮቻችን። የሴቶችንም ነገረ ሚስጢር አክለው …. የሃይማኖት አባቶቻችን ሲያሰተምሩን „ነገረ መለኮትን“ ነጥለው ሳይሆን „ከነገረ ማርያም“ ተነስተውአስቀድመው እነሱ በቅድሰት ድንግል ፍቅር ቅጥል እያሉ ነው። የእናታቸው ፍቅር ግብግብ እያደረጋቸው ነው። እኛም እንደ እነሱ ሆነን እናታችን የማናሰነካው – ተከተል አባትህን ሆኖ ነው። የድንግል ነገር የሁለመናችን ገዢ የሆነውም በዚህው ቅኝት ተቀረጽን ስለሆን። ማለት ለተዋህዶ አማንያን። አሳምረው ጠረቡን። መንፈሳችን በቅዱስ መንፈስ ገሩት ነው። ያኑርልን ሊቀ – ሊቃውንቱን። የቅድስትን የመንፈስ ድንግልና ፍቅር በማያልቅ ወተት አጥብተው አሳድገውናልና። በሥጋዊ ፍቅርም ቢሆን ፍቅር ድብን አድርጎት እያለቀሰ ከልቡ የሚያዜም ከልብ ጠብ ይላል … በስተቀር ድው የለ ትም  ….

 

ይህ ትግል የሚባለው ጀግና … አርበኛና ሰማዕት …. ድሆኖው* ጉድሎበታል፤ ጎታው* ተራቁቶበታል ታላቅ ነገር ቅናዊ ዕይታ፤ ሥልጣንን የማጋራት ግልጽነት፤ ኃላፊነትን በቅመም የመመጠን ሥልጡን ዕይታ። ትርጉም ያለው ተግባራዊ እርምጃ ከኢትዮጵያዊነት መሪዎች በአጽህኖት ይጠበቃል።  እኩላዊ መስመር ሳይፈጠር አሯል። አይታይም። የመከነ ጉድ ነው …. በዬትኛውም ሁኔታ በቦታው የሌለ ነገር ቢኖር ሴቶችን  በአክብሮት እኩል ለማሳተፍ ያለው ፈቃደኝነት ልሙጥ መሆኑ ነው ድርቅ የተጫወተበት፤ ዝናብ ሲሄድበት የከረመ አለት የመሰለ ለዛ የለሽ ጉድ። በጣም በረቂቅ ሁኔታ በሴቶች ላይ የተጣለው ማዕቀብ ዘመንና ጊዜ ይፈታዋል የሚል ግምት የለኝም። የተሳሳረ ድንቡልቡል ነገር ነው። በሩ ተቀርቀሯል። ጭላንጭል መተንፈሿ ቧንቧው የታነቀ ነው ….  ለዛውም እኮ ቆርጠው የሚወጡት ጥቂት ሆነው እነሱን እንኳን በአግባቡ ለመያዝ ምንም …. ታውቃላችሁ?! ምንም ነው 00000 በቅናሴ ያለ … ተቋም ቢኖር …. የሴቶች የእኩልነት የተሳትፎ መድረክ ድርሻ ምክነት።

 

ህይወት ካለሴቶች ኮረኮንች — አመዳም — ቡላ —- የፋደሰ —- ቀዝቃዛ — የነፈዘ —– ነው የተፈቀፈቀ። …. የትግሉም ዕጣ ፈንታው ይህ እንዲሆን ተገምድሎበታል። ይፍታህ በሉት! ነይልኝ — ነይልኝ — „የህይወቴ ህይወት“ ለዚህ ብቻ  … ። ትውልድን በአዲስ የተሳትፎ ፖለቲካዊ ባህል ለመገንባት ዳገት። ታሪካዊ ድርሻን ለመወጣት ክትከታ። የምንፈለገው ለአጃቢነት ወይንም ጥላ ለመያዝ ወይንም ለዘበኝነት ብቻ። ደንበር ሰበር ለሆነ ለሚመጥን የሥልጣን ክፍፍል ወይንም ተደማጭነት ማነቆ – እገዳ – ክልከላ … ሰባራ ጉድ፤ …. ጨምዳዳ ….. ዕጣ። የተሸበሸበ … ራዕይ። ሽራፊ …. ህልም። ያመለ … ነገ። የሻገተ … ተስፋ። ያልተጠረገው መንገድ ረቂቅ ሚስጢር ይህን ይመስላል። መፍትሄው ለዛሬ አዲስ መኃንዲሶች፤ እራሳቸውን የዘለሉ ሙሴዎች ያስፈልጉታል … ይመስለኛል።

 

እናሳርገው። ….. የምቀኝነት በሽታ ያለባቸው ድውያን በዬአጋጣሚው ያፈኑት ነገር መተንፈሻ ከሌለው አጉል ቦታ ይፈስና ብዙ መስመሮችን ይበርዛል። „ልብ ያለው ሸብ“ ብለናል … ከብሂሉ ጋር እርገት ይሁን። እኔ ምን እንደሚናፍቀኝ ታውቃላችሁ ዓይነታ የወጣለት መሪ … ደፈር ብሎ ስለ ሴቶች …. ጥብቅና አጋፋሪ የሚሆን ሊጋባ። የነፃነት እልፍኝ አስከልካይ ሀቀኛ ዓራት ዓይናማ። ሴቶች ብዙ አላቸዋ። ያጡት ያላቸውን የሚያቀኑበት ገብያ ብቻ ነው ….. ግጥም ታውቃላችሁ … ቅኔዊ። እንደ ግጥም የልብን ድርስ የሚያደርጉ ምርጥ ፉጡራን ናቸው አብዛኞቹ ሴቶች። እርዳታቸው – ፈጣን፤ ምክራቸው የልብ አድርስ፤ ጽናታቸው ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ፤ ፍቅራቸው የትውልድ ዋዜማ፤ ሥልታቸው ሥልጡን፤ ብልህነታቸው ተጨባጭን የዋጠ። ጉዟቸው ደፋር።

 

ሳልሄድበት የማልፈልገው ጥምዝ መንገድ ደግሞ ሌላው አጋር ለአጋር መገፋፋቱ ነው። ይህ ደግሞ ለአንስት የእኩልነት አንባ የከፋው ዕጣ ነውና ለአጋራችን እኛው አጋር በመሆን ጥጓ እንሁን። ብቃቷን ለመመስከር አንደበታችን እንፍታው፤ ለሴት እህታችን ብቃት ዋቢ እንሁንላት። ለሴት እህታችን ተጋድሎ ቀድመን እንገኝላት – ከጎኗ።  ለዘንካታ ትዕግስት ሞንሟና ምስጋና እንሆ!

 

ሴቶች የነፃነት ትግሉ ዓርማ ናቸው!

ሴቶች ለነጻነት ቅኔ ናቸው!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

መፍቻ

 

  • አጃ የልብ መደረስ፤ ከጠበቁት በላይ መርካት።
  • ቅንጧን … ቅንድቧን …
  • ብጡል የተለዬ … የተመረጥ …
  • መገምደል … ፍትህን የጣሰ ፍርድ።
  • ያነጠፈው …. ያደረቀው … ምደረበዳ ያደረገው …. ድርቅ ያስመታው … ለዘር ያላበቃው ….
  • ሽታሽቶ  …. እያረፉ፤ በፈረቃ በድርብ …. ማድቀቅ …. ማጥቃት ….
  • መሸበብ … መሸፈን … መጋረድ … እንዳይታይ ማገድ …
  • ድሆኖ … ከጭቃ የሚሰራ መሰል ግጣም ያለው የእንጀራ መያዣ … ሌማት፤ ወይንም ጥራር እንደማለት
  • ጎታ … ከጭቃ የሚሳራ ትልቅ የ እህል መያዣ … እንደ በርሚል ….

 

 

«ድምጽ አልባው አሳዛኝ የወገኖቻችን ለቅሶ በሳዑዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ!»

$
0
0

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ መዝናኛ ክበብ ሰራተኞች ሰንደቃላማችን በተሰቀለበት ግቢ ግፍ እና በደል እየተፈጸመባቸው መሆኑን ገለጹ

በኢትዮጵያን ሃገሬ ከጅዳ ዋዲ

በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ሁለት የጸጥታ ጥበቃዎችን ጨምሮ ከ13 በላይ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በስሩ እንደሚገኙ የሚነገርለት ይህ የመዝናኛ ማዕከል ከተቆርቆረ ሁለት አስርተ አመታትን ቢያስቆጥርም ከቅርብ ግዜ ወዲህ በተለያዩ ሰንካላ ምክንያቶች ከትርፋማነት ይልቅ ኪሳራ፤ ከእድገት ይልቅ ውደቀትን እያቀነቀነ አሁን ላለበት ደረጃ መድረሱን የሚናገሩ እማኞች በሰራተኞቹ ላይ እየተፈጸመ ያለው በደል ከመቸውም ግዜ በላይ እየከፋ መምጣቱን ገልጸዋል።
saudi 1
ይህ የኮሚኒቲ ማህበር ካፍቴሪያ ማዕከል ዛሬ ላለበት አሳፋሪ ደረጃ ምክንያት መሆኑ የሚነገረው በተለያዩ ወቅቶች በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ጀርባ ታዝለው ያለችሎታቸው አመራር የሚሆኑ ግለሰቦች ከኮሚኒቲው ካፍቴሪያ ሰራተኞች ጋር በቅርበት ተነጋግረው የካፍቴሪያውን መሰረታዊ ችግር ለመቅረፍ የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት ከመወጣት ይልቅ ከማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ እና ስርአት ውጭ በብሄር ተከፋፍለው እርስ በእርስ በመጋጨት በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ተላላኪ እና አፋሽ አጎንባሽ በመሆናቸው መሆኑንን ይጠቅሳሉ። የኮሚቲው አመራር አባላቶች ዲፕሎማቱ በሚሰጧቸው ትዕዛዝ እንደሚንቀሳቀሱ የሚናገሩ ምንጮች ከ10 አመት በላይ ያለ ደሞዝ ጭማሪ ደፋ ቀና የሚሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን መብት በመደፍጠጥ ፍሬ ፈርስኪ በሆኑ ጉዳዩች ተጠምደው «ሲሻም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል እንዲሉ» በተለያየ አቅጣጫ የወጪ ቀዳዳዎችን በማበጀት ወደ ማህበሩ ካዝና ዲፕሎማቱ እጃቸውን እንዲሰነዝሩ በመጋበዝ በሚፈጸም አስነዋሪ ተግባር ለኮሚኒቲው ውድቀት ግንባር ቀደም ምክንያት መሆናቸውን አክለው ይገልጻሉ። በዚህም ምክንያት የኮሚኒቲው ካፍቴሪያ በየአመቱ ኪሳራ አሳይቷል እየተባሉ አንገታቸውን እስከዛሬ አንገታቸውን ለመድፋት የተገደደዱት የኮምኒቲው ካፍቴሪያ ሰራተኞች በሳውዲ አረቢያ ውስጥ እየጨመረ የመጣውን የኑሮ ውድነት ተከትሎ ከዛሬ 10 አመት በፊት በተቀጠሩበት ደሞዝ የስደት አለሙን ህይወት መግፋት ተስኗቸው ለከፍተኛ ችግር በመዳረግ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በሳውዲ አረቢያ ምድር በባዕዳን የሚፈጸምብን ግፍ እና ስቃይ ሳያንሰን ባዲራችን ከፍ ብሎ በሚውለብለበት የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ በገዛ ወገኖቻችን መገፋታችን ያሳዝናል ያሉ አንድ የካፍቴሪያው ሰራተኛ ባለተዳር እና የሶስት ልጆች አባት መሆናቸውን ገልጸው ዛሬ በየአመቱ የመኖሪያ ፈቃዳቸውን ለማሳደስ እስከ 10 ሺህ ሪያል ለማውጣት እንደሚገደዱ አውስተው ለምኖርበት መኖሪያ ቤቴ በየስድስት ወሩ ከምከፍለው የቤት ኪራይ ጋር ተዳምሮ በ 2 ሺህ ሪያል ደሞዝ አይን ካልገለጹ ልጆቼ ጋር ኑሮን ማሸነፍ ተስኖኝ አቤት ለምለው አጥቼ በነዚህ ጨካኞች የሚፈጸምብኝን በደል ሳልወድ በግድ ለመቀበል ተገድጃለሁ ብለዋል። በተጠቅሰው ካፍቴሪያ ከ 8 ሰአት በላይ ያለ ተጨማሪ ክፍያ « ኦቨር ታይም» ሃይማኖታዊ በአላትን ጨምሮ ደስታ ምን እንደሆነ ሳያውቁ ከእጅ ወደ አፍ የሆነውን ኑሮቸውን ለማሸነፍ ደፋቀና እያሉ መሆናቸውን የሚናገሩ እነዚህ ወገኖች ተጨማሪ ስራ ሰርተው እራሳቸውን መደጎም የሚችሉበት ግዜ እንደሌላቸው እና አቅማቸው እንደማይችል ጠቁመው ጉዳዩ ያችን እልባት እስኪያገኝ ለወግን ተቆርቋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በጸሎት ከጎናቸው ይቆም ዘንድ ተማጽነዋል።
sudi
ይህ የኮሚኒቲ ማህበር እንደ ማህበር ህጋዊ ህልውና አጊቶ ስራ ከጀመረ ሁለት አስርት አመታትን ማስቋጠሩን የሚያወጉ አንዳንድ እድሜ ጠገብ አባላቱ በተጠቀሱት አመታት የአንባሳደሩን መኖሪያ ቤት ጨምሮ በሪያድ የኢትዮጵያን ኤንባሲን በ20 ሚልዮን ሪያል ወጪ አስገንብቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያስረከበ ታላቅ እና ስመጥር ማዕከል እንደ ነበር በማስታወስ ዛሬ ይህ የኮሚኒቲ ማህበር ግቢ ጥቂቶች እንዳሻቸው የሚያዙበት የአይንህ ቀለም አላማረኝም እያሉ የገዛ ወግናቸውን በቡጢ እይነረቱ ከግቢ የሚያባርሩበት ከሰሪዎቻቸው አምልጠው ህይወታቸውን ለማትረፍ ወደ ቅጥር ግቢው በሚመጡ እህቶቻችን ላይ ጾታዊ ጥቃት የሚፈጸምበት እና የወገኖቻችን ሬሳ የሚቆጠርበት የጥቂት ወሮበሎች መሸሸጊያ መሆኑ አሳዛኝ እና ሳፋሪ ነው ብለዋል። በአጠቃላይ ከቅርብ ግዜ ውዲህ ይህ በሪያድ የኢትዮጵያ የኮሚኒት መዝናኛ ማዕከል በወገኖቻችን ላይ ኢሰባአዊ ድርጊት የሚፈጸምበት መዕከል ለመሆኑ ምስክርነታቸውን የሚሰጡ ምንጮች የመዝናኛው መዕከል ሰራተኞች አብዛኛዎቹ የወጣትነት እድሜያቸውን እዛው የኮሚቲ ማእከል ውስጥ የጨረሱ እና በብስጨት ለስኳር በሽታ ለድም ግፊት እና መስል ተዛማጅ በሽታዎች ተዳርገው የተጎሳቆሉ በመሆናቸው ሌላ ስራ ፈልገው የማግኘት እድል እንደሌላቸው በማውሳት የሚመከተው አካል አሁን የሳውዲ አረቢያ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት ያወጣውን ህግ መስረት በማድረግ የደሞዝ ጭማሪ ሊደረግላቸው እንደሚገባ እና የሳውዲ አረቢያ መንግስት አሁን ባወጣው ህግ መስረት የተጠቀሱትን ወገኖቻችንን ከህገወጥነት ለመታደግ የመኖሪያ ፈቃዶቻቸው በኤንባሲው ስር ሊሆን የሚቻልበትን መፍትሄ ማፈላለግ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ሃላፊነት መሆኑንን ይገልጻሉ።

ይህን ተከትሎ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አክሳሪ ነው በሚል ለአያሌ አመታት ሲመዘበር መቆየቱን የሚናገሩ የሪያድ ነዋሪዎች በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አንባሳደር መሃመድ ሃሰን የቅርብ ዘምድ እንደሆኑ የሚነገርላቸው የኮሚኒትው ሊቀመንበር ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን አሊዬ ምንጩ የማይታወቅ 2 ሚልዮን ሪያል «25 ሚልዮን ብር » ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሶስተኛ ሃገር ሊያሻግሩ ሲሞክሩ በሳውዲ አረቢያ መንግስት ደህነት ሃይሎች ቁጥጥር ስር ውለው እስካሁንም እስር ቤት እንደሚገኙ ይገልጻሉ።

ሰበር ዜና: ኢትዪጲያዊ ሙስሊም የችሎት ውሎ (ቢቢኤን ልዩ ፕሮግራም)

$
0
0

ቢቢኤን ሰበር ዜና
ልዩ ፕሮግራም
ሁሉም ኢትዪጲያዊ ሙስሊም ሊሰማው የሚገባው የችሎት ውሎ
የኮሚቴዎቻችንን ጠበቆች ተማም አባቡልጉንና ጠበቃ  አዲስን አነጋገራናል፡፡ትግሉ በተጠናከረ መልኩ ለመቀጠል ህዝቡ የአሚሩን ትዛዝ በመጠበቅ ላይ ነው

[jwplayer mediaid="10799"]

መንግስት ከሰረየሰላም አምባሳደር በሆኑት የብርቅ ሰብእና ባሌበቶች ላይ መንግስት ፖለቲካዊ ፍረጃዉን ጭኖባቸዋል፤ ይህ ደግሞ መንግስት መክሰሩን ፍንትዉ አርጎ የሚያሳይ ነዉ።በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ዉድ ዜጎች የተወከሉትን ኢትዮጵያዉያንን ፍትህ-አልባ በሆነዉ ፍርድ-ቤት ለማሸማቀቅ መሞከሩ፤ አለም-አቀፋዊ የሆኑ የህግ መስመሮችን አልፎ ሰርዓት-አልበኝነትን ለማንገስ የሚደረግ አይን-አዉጣነት በመሆኑ በዛሬዉ ችሎት መንግስት ከስሯልና እናንተ የተስፋ ባለቤት የሆናችሁ ኢትዮጵያዉያን ድል አይቀርምና ተጽናኑ።መንግስት የኛዎቹን ማንዴላዎች መፍታት ሲገባዉ ወደ እስር ቤት ልኳቸዋል። የትላንቶቹ አፓርታይዶች ኩምሽሽ-ሽምቅቅ-ስዉር እንዳሉት የዛሬዎቹም የኢትዮጵያ አፓርታይዶች ኩምሽሽ-ሽምቅቅ-ስዉር ማለታቸዉ አይቀሬ ነዉ። ልክ እንደማንዴላ ሁሉ ኮሚቴዎቻችን ከተጎናጸፉት የሰብዓዊነት ማእረግ በላይ እፁብ-ድንቅ ምድራዊ ብሎም ሰማያዊ የሆነን የብርቅ ሰብእናን እርከንን ይሻገሩ ዘንድ የፍትህ ቀበኞች ወደ እስር ቤት መልሰዋቸዋል። ድል አይቀርምና ወደ ድል በሚያሽግረዉ ሰላማዊ ታንኳ “ድምጻችን ይሰማ!” እያልን በቃልኪዳናዊ ጥምረት እንጓዝ። ልብ ያለዉ ልብ ይበል!
BBN Your Voice

አጋጣሚዎችን ሁሉ ለራሳቸው ጥቅም የሚያውሉ ነውረኞች !

$
0
0

አበራ ሽፈራው
ከጀርመን

እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጥር ጥቅምት መጨረሽና  ህዳር ወር 2006 እጅግ አሳዛኝና በህይወት እስከአለን ድረስ የማንረሳው ክፉ አጋጣሚ በእህቶቻችንና በወንድሞቻችን ላይ ግድያን፣ መድፈርን፣ እስርን፣ መታረድንም፣ በመኪና እየተገጩም ጭምር መሞትንም መጀመሩን ያየንበትና የሰማንበት:: ክፉ ወር:: ብዙዎቻችን በውስጣችን ከራሳችን ጋር የተሟገትንበት፣ ምን እናድርግ? ብለን ከቅርብ ጓደኞቻችን ጋር የተነጋገርንበት:: ሌሎቻችንም ተሰባስበን በውስጣችን ያለውን ሃዘን በግልጽና በአደባባይ ዓለም ሁሉ እየሰማ የተነፈስንበት::  ሳውዲ አረቢያዎች ለዘመናት አብሮአቸው የነበረውን ጭካኔ በአይናችን የተመለከትንበት ምን አልባትም እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ከዚህ በላይ ሲጨቆኑና ሲረገጡ መኖራቸውንም ለማየት የቻልንበት ጊዜ ይህ ይፋ ወጣ እንጂ::

በእርግጥም ሳውዲዎች ጨካኞች ናቸው ስራቸውም እጅግ አሳፋሪ ነው:: ጊዜ ይለወጣል ሀብትም ይጠፋል  ነገር ግን ታሪካቸው በተለይም በወንድሞቻችን ላይ የተፈጸመው ግፍ ግን ለታሪክ ሲታወስ ይኖራል :: በሳውዲዎች ድርጊት ያላዘነ ኢትዮጵያዊ የለም እኔ እስካየሁትና እስከሰማሁት ድረስ:: ታሪክ የእኛን እንግዳ ተቀባይነትን እንደመዘገበ ሁሉ የእነሱንም ውለታ መላሽነት በእኛ ዘመን ለማየት ችለናል ይህንንም ታሪክ መዝግቦታል:: በክፉ ዘመናቸው በአገራችን ተሰደው እንደ እናት ቤት ኢትዮጵያ እንዳልተቀበለቻቸው ሁሉ ዘሬ ሰርተው ሳይሆን አምላክ በተፈጥሮ በሰጣቸው ተመክተው  የጥጋብ ዱላ በወገኞቻችን ላይ አዘነቡ የብዙ የኢትዮጵያውያን እንባ በአለም ሁሉ ፈሰሰ፣ የአምላክንም እጅ ተማጸነ፣ ብዙዎች የአምላክንም ምህረት በእንባ ለመኑ በእርግጥም አምላክ ሰምቷል መልሱም አንድ ቀን ለአገሬም ይሠጣል::

ላለፉት 50 ዓመታት አረቦች ለኢትዮጵያ ያላቸውን ጥላቻ በተለያየ መልኩ ለመፈጸም ሞክረዋል ዋናው መነሻቸውም በሁሉም መልኩ ለመስፋፋት ያደረጉትን እንቅስቃሴ ሁሉ እሽ ብሎ የተቀበላቸው ያለመኖሩና በአፍሪካ ቀንድ የአረቦች አስተሳሰብ ተግባራዊ ሊሆን ያለመቻሉ ሲሆን ይሁንና ሃሳቦቻቸውን ተግባራዊ ለማድረግ ግን አርፈው ተኝተዋል ማለት ግን አይደለም:: ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ ኢትዮጵያን ለመበታተን የተጠቀሙት አንደኛው መንገድ የዛሬዎችን ዘረኛ የህወሓት/ ወያኔ ቡድን እንደ ሌሎቹ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሁሉ አንደኛው መሳሪያ ሆኖ ያገለገላቸው እኩይ ቡድን መሆኑ ጭምር ነው::

በእርግጥም ኢትዮጵያና ልጆቿ ለአገራችው ሳይሆን የሌሎች ህዝቦችንና አገራትን ሰላም ለማስከበር ለመስወአት የቀረቡ የህወሃት ጀነራሎች የገቢ ምንጭ ሆነዋል፣ የአረቦችን ቆሻሻ ለመጥረግና በዚህ ዘመን የሌለን ባርነት ርካሽ ጉልበታቸውን ለመሸጥ ተገደዋል ይኸም ብሶ ለአስከፊ ችግር መጋለጣቸውም ቢሆን ከኢትዮጵያው የህወሓት ሥርዓት ማንነት ጋር የተያያዙ ችግሮች ውጤቶች ናቸውና መሰደድና የህወሃት ደላሎች መጠቀሚያ መሆንና ለመከራ መዳረግም ቢሆን የሥርዓቱ መዋቅሮች ለዚህ አስከፊ ችግር መፍትሄ መፈለግ አቅቷቸው ሳይሆን እራሳቸውን እስከጠቀማቸው ድረስ በዝምታ ቆይተው ችግሩ ተባብሶ  አስከፊ ደረጃ ሲደርስ ደግሞ “ ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል“ እንዲሉ አሳቢ መስለው  መነሳታቸው ደግሞ ያሳዝናል::

ለአሁኑ የአረቦችም ሆነ የሌሎች አገሮች ማጥቃት መነሻው በአገራችን ያለው የፖለቲካ ችግር ሲሆን የኢኮኖሚ ችግሩም ቢሆን የዚሁ የፖለቲካው ችግር ውጤት መሆኑ ማንም ይስማማበታል:: ለመነሻም እንዲሆነን የአገሪቷን ፖለቲካ ለ22 ዓመታት የተቆጣጠረው ህወሃት/ወያኔ  በግልጽና በአደባባይ የኢትዮጵያ ህዝብ አይኑ እያየ የአዋቀረው የንግድ ብዝበዛ፣ የአገሪቷ የንግድ እንቅስቃሴ ከፓርቲ ንግድ ወይም ከEFFORT በተጨማሪ ትልልቅ የንግድ ተቋማት በህወሃት ሰዎች መያዛቸው፣ ጠቅላላ የንግድ መድሎ መኖሩ፣ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቶች በሙሉ በሚያስብል መልኩና በተጠና መልኩ በህወሃት ሰዎች መያዛቸው፣ ለንግድ ስራ አስፈላጊ ናቸው የተባሉ ልዩልዩ የሚንስትር መስሪያ ቤቶች በነዚሁ ሰዎች መያዛቸውና ልዩ ልዩ የአገሪቷን ንግድ በሙሉ በማክሮ ኢኮኖሚ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ጭምር ለእነሱ የሚጥቅሟቸውን ሁኔታዎች እስከማመቻቸት ድረስ መድረሳቸውን ቀዳሚ እድሎችን የሚያገኙት እነሱ መሆናቸው ጭምር ናቸው::

ለአሁኑ ጥቃጣችን ምክንያት ከላይ የተጠቀሰው ጉዳይና ሌሎች ጉዳዮች ሲሆኑ በተጨማሪም አረቦች በተለይም ሳውዲ አረቢያ ለህወሃት ቅርበት ባለው ሼህ መሃመድ አላሙዲንና በሌሎች የንግድ ሸሪኮቻቸው አማካኝነት ባላቸው የቆየ ቅርርብ ማንነታቸውን በጥልቀት ያወቁ በመሆናቸው ወገኖቻችን ደራሽና ወገን ወይም የሚከላከልላቸው እንደሌላቸው ሰው ሆነው በአሳዛኝ መልኩ እንዲባረሩ መደረጉ ለህዝቡና ለተጎጂ ቤተሰቦች እንጅ ለህወሃት ሰዎች ቅንጣት ያህል እንደማይሰማቸው እርግጠኛ ነኝ:: ለዚህም ደግሞ የህወሃት የጭካኔ መጠንን ለመለካት የኢትዮጵያን ህዝብ ለህወሃት ያለውን አመለካከት በመለካት ማወቅ ቀላል ነው:: ይልቁንም በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ለህወሓት የማፍያ መዋቅር ሌላ የገቢ ምንጭ እንደፈጠረለት በቀላሉ መገመት ይቻላል:: ይህንን በቀላሉ ለመረዳት በተመላሽ ወገኞቻችን ንብረት ላይ የሚደርሰው የንብረት ንጥቂያ ብዙዎች በሳውዲ አረቢያ ከደረሰባቸው ስቃይ  ይልቅ በአገራችን በህወሃቶች የጉምሩክና በኤርፖርት አካባቢ የተደረጉት የፍተሻ ዝርፊያዎችና የንብረት ቅሚያ ቀላል ሊባሉ እንደማይችሉ እየተነገረ ይገኛል:: ይህም ችግር በአገር ውስጥ ተባብሶ ብዙዎችን ለተጨማሪ የስነልቦና ችግር ላይ መውደቅ ምክንያት እየደሆነ ይሰማል:: ታዲያ ይህንን የህወሃትን ሥርዓት ምን ልንለው እንችላለን?

ከላይ እንደገለጽኩት የህወሃት የማፍያ መዋቅር የትኛውንም አጋጣሚዎች እንደ አንድ ጥሩ አጋጣሚ የሚቆጥሩ መሆናቸውን ለማየት ከላይ ከጠቀስኩት ተግባራቸው በቀላሉ ለማየት ይቻላል:: አባይ ግድብ ብለው ይነሳሉ ከህዝቡ  ከልጆቹ ማሳደጊያ እየነጠቁ ሰብስበው ባልተጠና መልኩ የተጀመረን ፕሮጀክት ለማስፈጸም በሚል የተሰበሰበውን በጀትና ገንዘብ ለህወሃት የንግድ ተቋማት ትልቅ የብዝበዛ ምንጭነት እንዲያገለግል ሲደረግ እያየን እንገኛለን፣ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ከስደት በግድ ሲመለሱ በላብና በደማቸው የሰበሰቡትንና ከሳውዲዎች እጅ አምልጦ በእጃቸው ይዘው የመጡትንም በጥሬ ገንዘብና በአይነት መበዝበዛቸው፣ በዚሁ አስከፊ ጊዜ ለእነዚህ መከረኞች መድረስ ሲቻልና የተሰደዱት ከማቋቋም ይልቅና የኢትዮጵያ ህዝቦች ሆነው ሳሉ በመቶ ሚሊዮኖች ብር የሚቆጠርን ብር በብሔር ብሄረሰቦች ስም አውጥተው ሲደንሱበት ከማየት በላይና አሁንም የህወሃት የንግድ ተቋማት የኪስ ማደለቢያ ማድረጋቸውን ስናይ እጅግ የሚዘገንን ተግባር ነው ለማለት ያስችላል::

ትላንት ደርግ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1977 ዓ.ም የወሎና የትግራይ ወገኖቻችን በድርቅ ሲጠቁ የደርግ 10ኛ ዓመትና የኢሠፓን ምስረታን በከፍተኛ ወጭ አከበረ እያሉ ሲሳለቁበትና የትግላቸው መቀስቀሻ አድርገው ሲዘምሩበት እንዳልነበረ ዛሬ የትላንት ነጻ አውጭዎች ነን ባዮች የዛሬዎቹ በዝባዦች በአደባባይ ስራቸውን፣ምግባራቸውንና አላማቸውን ከመቼውም ጊዜ በላይ እንድናያቸው አድርጎናል:: ደግሞም የኢትዮጵያ ህዝብ ከመቼውም ግዜ በላይ ለራሱ እያሰበ መምጣቱና እየነቃ የትኛውንም የክፋት መዋቅራቸውንም ይዘርጉ ይህንን ሁሉ በጣጥሶ እነዚህን ጎጠኞች አይናችሁ ለአፈር ያለበት ግዜ ላይ ደርሰናል:: በአገር ውስጥ መቃወም ባይችልም ዝምታን መርጠው የነበሩ ሳይቀሩ ዛሬ በአደባባይ ህወሃትን ለመጋፈጥ ቆርጠው ታይተዋል:: ትግሉንም ለመደገፍ ግልጽና ስውር ትግሉን መቀላቀል ተያይዞታል፣ ለህወሃት አስደንጋጭ በሚሆን መልኩ ትግሉን ወደከፍተኛ ምዕራፍ ለማሸጋገር ግልጽና የህቡ የትግል መስመሮችን እየተቀላቀለ ይገኛል::

ከዚህ በላይ የእህቶቻችንንና የወንድሞቻችንን ደምና እንባ ሳይደርቅ ለእነዚህ የሳውዲአረቢያ ጨካኞች የአገራችንን መሬቶችንና ሌሎች የንግድ ፍቃዶችን ለመስጠት ከ300 በላይ የሚሆኑ ፕሮጀክቶችን መስማማታቸውን ስመለከት ምን ያህል አሳዛኝ እንደሆንንና እነሱን እስከጠቀመ ድረስ ኢትዮጵያዊነት በህወሃቶች ፊት ምንም እንዳልሆነ በቀላሉ መረዳት ይቻላል:: እንግዲህ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባይሆንም እና በሌላ ርዕስ የምመጣበት ቢሆንም ከኢትዮጵያ ድንበርን ወደሱዳን ለማካለል መነሳታቸውንም ስመለከት በጣም የሚያሳዝን መጥፎ አጋጣሚ ላይ መኖራችንንና የማንን መሬት ለሱዳን ለመስጠት እንደፈለጉም በደንብ አልገባኝም:: ስለሆነም ህወሃቶች ምን አይነት ትምህርት እንደተማሩ ምን አልባትም ብዙዎቹ ኢትዮጵያዊ ያልሆኑና በአጋጣሚዎች ኢትዮጵያ በሌሎች እኩይ ተግባርን በሰነቁ የኢትዮጵያ ጠላቶች እጅ መውደቋን ለመረዳት እንችላለን::

ዛሬ አስቸጋሪ እንዲያውም ለአገራችን ህልውና አስጊ የሆነ ጉዳይ ቢኖር ህወሃትን ለመጋፈጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ  መሆናችንን ማስብ ካልቻልን ነው :: ስለሆነም እነዚህ የታሪክ ጥቁር መዝገቦች፣የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት ጠላቶች፣ የህዝብና የትውልዱ ጠንቆችንና አጋጣሚዎችን ሁሉ ለራሳቸው የብዝባዛ መሳሪያነት የሚጠቀሙትን ጠላቶቻችንን ለመጋፈጥ አሁንም ያልቆረጥን እንቁረጥ::

ይህ አስከፊ የህወሃት ሥርዓት የሚፈልገውን ሳይሆን እውነተኛ ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያ የሚመኙትን ነጻነትና ፍትህ፣ ሁሉም ብሔረሰቦችና የኢትዮጵያ ህዝቦች በጋራ በእኩልነትና ያለመድሎ የምንኖርባት፣ ፍትህ የሰፈነባትን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን በሁሉም ኢትዮጵያውያን ፍቃድ የምንመሰርትበት፣ የህግ የበላይነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ከህወሃት የዘር ጭቆና መላቀቅ ያለብን ሰዓት ላይ ደርሰናል:: አጋጣሚዎችን ሁሉ እየተጠቀሙ ለብዝበዛና ለእልቂት ከሚዳርጉን ነውረኞች እራሳችንን እናድን::

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

aberashiferaw.wordpress.com

comment_stage_5

                                                              

በራሳሽን ላይ የምንሰለፍበት ቀን ናፈቀኝ? ራሳሽንን


ጠርዝ ላይ ያለ ስጋቴ –በመንትዮሽ። ከሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ
12.12.2013

ስጋት እንደሚፈቀድልኝ አስልቼ ሃሳቤን ንፉግ ሳልሆን ልገልጽ ወሰንኩ። መወሰንና መቁረጥ መልካም ናቸው። ካሰቡት

የሚያድርሱ ሰጋሮችና ገሮችም።

andu-family-45

በሌላ በኩልም ከመንፈስ መታከት ይታደጋሉ – ይመስለኛል። እመቤት ነፃነትና ፊታውራሪ ሂደት እውኃ በሚያደርግ ፋስ ለማን አዘነሉት?! የፊታውራሪ ሂደት የትርታ – ትብብር አማ ስንቱን ገበርዲን ስንቱን ሙሉወርድ ዋጠው? ስንት አቅም ባከነ – ስንት ፍቅርስ አለቀሰ? ስንት አብሮነትስ ተከፋ? ሰረዘው … ሰወረው? ፊታውራሪ ሂደት ብዙም ሳንርቀው ግራው – ቀኙ – ማዕከላዊነትን አግቶ ወይንም ነካክቶ። የቅርቡን ስናስበው ሁለት ምርጫ ይዞ ቀረቦ ነበር። ዘንባባ ወይንስ ሳንጃ በማለት አሳፈን። እኔ ከአጠው ቋጥኝ አፋፍ ላይ ሆኜ ናዳውን ለእህትና ወንድሜ፤ እህትና ወንድሜም አጸፋውን በመልቀቅ ተጠን። የባሰው ግን ሺዎች አለፉ፤ በእስር ማቀቁ … ስንት የፍቅር ቤት – ትዳር ተፈታ፤ ተናደ ~~~ አብሶ ህፃናት የወላጅ ናፍቆት አሰቃያቸው፤ ፍቅርና እንክብካቤ አጥተው ቀጨጩ። ኢዲህቅ፣ አማራጭ፤ ህብረት፤ ቅንጅት ….

ቅንጀት እራሱ ኢዲአፓ፤ አላይንስ፤ ግንቦት፤ አንድነት፤ መድረክ፤ ጥምረት፤ ዝም አንልም፤ ግንቦት ዲ፤                   የጥቃቱ ሰለባዎች በፋመ በቀል እዬተቀቀጡ ያሉ- የነገ ትውልድ ተስፋዎች ትብብር …. ያንተ ያለህ …. መከታከት ምዕራፋችን

ዬት ላይ ይናጠጥ ይሆን? …

ሎቢያችን በመደማመጥ የሚሰክነውስ መቼ? መንፈሳችን ከቋሳ ጸድቶ የጸዳ ማግሥት መቼ ይሆን ልደቱ? ክብሮቼ … በመኢህድ ዙሪያ ቢሆን በሥነ ደንብ ፊርማ ግብግብ የነበረውንም ታውቁታላችሁ። አንዲት ብሄራዊት ሀገር – በህብረ ቀለም ያጌጠች፤ አንድ የነጠረ ግን በብዙ የራቀን ፍላጎት የሰነቀ የነፃነት ራዕይ፤ አንድ መነሻ – አኃቲ መዳረሻ፤ ትርጉም ሰጥና አጉራሽ ጉዞ ተከትሎ ስንጥቅ ትርትር ገጠመኝ። ያደክማል። …. እህህህ …

ባለፉት ሳምንታት አንድነት ከመኢህድ ጋር አብሮ ለመስራት አንድ እርከን ላይ መድረሱን አነበብኩ።

ተከትሎም ብቸኛው የፓርላም አባልና የነፃነት ፈላጊ ቤተሰብ አባል የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ „ኡ ኡ የመደማጥ ያለህ“ በሚል እርእስ ከዘመንተኞች ጋር አብሮ ስለመሰራት አለልስ ምኞታቸውን ከማሳሰቢያ ጋር አካፈሉን። ለማጣፈጫ አንድነት የአደራ መክሊትን ተግባር ላይ በማዋል ላይ ስለሚገኘው አቶ አንዱዓለም አራጌ የመጸሐፍ ምርቃ ላይ ሥርዓት አዘጋጅቶ አደባባይ በስሙ እንዲሰዬም ፍላጎቱን ነገረን። እንደ መዳረሻ ደግሞ ከኢሳት አንድ ሰበር ዜና አዳምጠን … ያው ዘኃ ግራው በአንድነት ዙሪያ ነው …

እኔ ልዩ ስጋት አደረብኝና … ሁኔታውን እንዲያብራሩልኝ ለተከበሩ ለአቶ ግርማ ሰይፉ ኢሜል አድራሻቸውን ከጹሑፋቸው ሥር ስላገኘሁት ቁልጭ ያለቸውን ስጋቴ ቅልብጭ ባለች አጭር ሀተታ ቋጭቼ ላኩላቸው። ቀኑ ነበር። መልሱን እዬጠበቅኩ ነው። ከትቢያም ይሁን ከጭድ ከታችኛው ክፍል የሚመጡ ቀና ዕይታዎች የነገ የተስፋችን መሪ ከሆኑት ይገኛል በማለት እዬጠበኩ ነው። መቼም ነፃነት የራበው የነፃነት ንፉግ እንደማይሆን በመስላት።

ትናንት – ደግሞ የሞቀ – የሰከነ – ጥልቅ – ተቆርቃሪነትን ያቀለመ መልእክት ከአደራ ጽኑ ጠበቂያችን ከአቶ አንዱዓለም አራጌ ዘሃበሻ ላይ አነበብኩ። ስጋቴም በዚህ ጥግ ዙሪያ ነበር። ለተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ የፃፍኩትም ይኽንኑ የሙጥኝ ያለ ነበር። ልምዱ አለና። ክብረት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ እስር ቤት ላይ ሁና ነበር አንድነት በአዲስ መልክ የማጠናከሪያ ምርጫ ያደረገው። እንዲሁም መድረክ የተወለደው። ስጋቴ ቅርንጫፍ ሳይሆን ሥር ያለው ነው። ፊታውራሪ ሂደት በበለኃሰብ እጅ፤ ካቴና ላይ ሆና ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ያገለለ ድራማ ከወነ አንድ መጋረጃ። ያን ጊዜ  „ዝም አንልም“ የሚል አንጃ በአንድነት ውስጥ ተፈጠረ። ከዚህ ሁሉ በላይ ስደት ላይ የምንገኘው በክፉም በደገሙ የምንገናኝ የእትብት ልጆች የፊታውራሪ ሂደትን ሃዲድ ተከትሎ በመጣው ጦስ በኢትዮጵውያን የመወያያ የጋራ ቤታችን ስንፋጭ እስከ መለያዬት አደረሰን። ሙጃው ወያኔም አራት ኪሎ ተራራ ላይ ሆኖ ከበሮውን ደለቀ …. ሄሮድስ መለስም አፈር እንደቀራባቸው ሳይተነብዩ ፍልቅልቅ ብለው ሳቁብን – ፈነደቁ።

የተስፋችን ማህደር የነበረችው ክብረት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ለትውልዱ የመጀመሪያ ሴት በመሆን በአንድ ሀገራዊ የብሄራዊ ፓርቲ መሪ ስለነበረች የብቃቷን ጡት ወተት ለመቀለብ ቀን ስንቆጥር መክኖና ፈልሶ ቀረ። እኔ ረቂቅ ናፍቆት ነበረኝ። መድረክ ላይ በአካል ስላዬኋት እሳሳላትም ነበር። ህልሜ ግን ተኖ ቀረ። አንዲት የቆረጠች እርግጠኛ ሴት አዲስ ቡቃያ ወጣት፤ ከምንም ነገር ጋር ንክኪ የሌላት ሰንደቅን የታጠቀች ብቸኛ የነፃነት አርበኛ ያላስተናገደ የዴሞክራሲ ትግል ፍቺ የለሽ ቅልሞሽ ነበር ለእኔ። እሷ ከመፈታቷ በፊት ሁሉ ነገር ተከወነ። ስትፈታ መግቢያ ቤቷ ከውስጥ ተከርችሞ፤ አደራ ያስረከበቻቸው የአንድነት ቤተሰቦቿ ጉልቻቸውን በፋስ ፈረካክሰው፤ በጎሪጥ ዳርና ዳር ሆነው በእሳትና በቃጠሎ ታጥረው አገኘቻቸው … ምን ይሁን? መግቢያ ያጣቸው አብነት … እንደ ተዘጋባት … ጨርሱትን እኔ አቅም የለኝም። አቤቱ ድህነትህ መቼ ይሆን!

የእኔ ስጋት ምንጭ ይህ ነው። ትናት እነ – አቶ ሰዬ  ዘውድ ተድፍቶላቸው ብርቴን … ዛሬ ደግሞ እነ – አንባሳደር ስዩም አንዷለምን …. ይሆን – ይሆን? …. የፊታውራሪ ሂደት የማጥቃት ወቅቱ ተመሳሳይ ነው። ያው የምርጫ ዋዜማ። መደረክ ያን ጊዜ፤ ዛሬ መኢህድ፤ አቶ ሰዬ ትናት ዛሬ አንባሳደር ስዩም መስፍን። የሚኮረኩር ነገር አለው።  የሚመጠምጥ ነገር። ብርቴም እንደ ዛሬው እንደ አንዱዓለም ውዳሴ ይደረደርላት፤ ቅኔ ይዘርፍላት ነበር – በሁላችንም። አቡነዘሰማያት ተዘውትሮ ይደገምላትም ነበር። ስለሆነም የአደራ ዋቢው አቶ አንዱዓለም የዓመቱ ምርጥ ሰው ሆኖ መመረጡ የነገን የመታገያ ወርዱን ሊያጠበው ወይንስ ሊያሰፋው የትኛው ይሆን ቅዱ የቦዩ፤ ጥግ የሚያሳጣ ይሆንይሆን መዝሙሩ? ተንጠልጥሏል ስጋቴ …. ጭንቅን ታጥቆ – ትዝብትን ተሸክሞ – ተስፋ ማጣትን አርግዞ …. እግዚኦ ነው እግዚኦ!

በሌላ በኩል አያድርገው እንጂ አቶ አንዷለምን የሚያገል ሁኔታ ቢፈጠር እኛ እንደፈረደብን ጋ (ቡድን) ለይተን ደግሞ እንደ ትናንቱ መፋለጡን እንቀጥላለ? ይህም የመንትያው ስጋቴ ሥጋና ነፍስ ነው። የፊታውራሪን ሂደትን መርኃ ግብር ውስጥ ቼክ ማድረግ አለብን። እስከ መቼ በቆራጣና ቆልማማ አፍንጫው እዬዳነሰብን ይኑር?! ትርፍና ኪሳራውን እንመትረው። ጠቀሜታውን እንፈታትሽው። እንደ ኖርንበት ሁኔታ ይህ የታደለ የሽፍታ አስተዳደር ወያኔ በአገኘው የመተንፈሻ ጊዜ ተጠቅሞ የለበጣ ልጥፍ ድራማውን የሚከውንበት አዲስ ለም ማሳ እንዳናዘጋጅ ጠንቀቅ።

ስጋት ወጥሮኛል ~ መፈናፈኛ ነስቶ ያባትለኛል ~ ሰንጎ ይፈትለኛል። በዬጊዜው በሚከፋፈለው የኮርኒስ ግድግዳ እንኳን ሆኖ ደፋ ቀና የሚለው የነፃነት ፈላጊ ቤተኛ ዛሬም ሌላ ስንጠቃ ይጠብቀው ይሆን? ሌላ የመሬት ክፍፍል ዕጣ ፈንታ? እ! ከሁሉ የሚያሳዝኑኝ በተለይ ነጭ ሀገር ተወልደው የሚያድጉ ልጆች ደንበርና ወሰን በዬጊዜው እዬተሰራላቸው በፍልሰቱ መንደር ሰላም አጥተው ከአቻዎቻቸው ጋር አብረው እንዳያሳልፉ ተስፋቸውን ሲኦል መልቀቃችን ነው …. ተሳህለነ!

ውህደቱም ሆነ ጥምረቱ፤ አዲስ የማጠናከሪያ በሉት የማሟያ ሂደቱን እላይ ባሉት ተወስኖ ተግባራዊ ይሆናል። ታች ያለው አባል የሚሰማው አባል እንዳልሆነው ልክ እንደ እኛ በመግለጫ ነው። መግለጫውን ተከትሎ መለያዬት ሲመጣ ታች ያለው ወገን ነው በጠላትነት ተፈራርጆ ሲዋቃ ውሎ የሚያደረው።  እጅግ የማከብራችሁ መንፈሰቼ፤ የሀገሬ ልጆች ከእንግዲህስ ሞኝ አንሁን። የተስማሙት እነሱ ሲለያዩም እነሱ ብቻ ይሁኑ …። እኛ በምን እዳችን ነው በዬጊዜው እንዲህ እምንተረተረው። አለቅን – ሳሳን እኮ! ስደቱ የማይቻል ሸክም፤ በዛ ላይ ደግሞ በዬዕለቱ አጀንዳ ስንሰነጣጠቅ የምንገኘው …. ስለምን ነው? ረዳት ጠያቂ አልባ እኮ ፈለስን!

ክብሮቼ ልብ ልንለው – በማስተዋል ልንመረምረው የሚገባው ጉዳይን እንሰበው …. ከልብ ውስጣችን እባካችሁን በሞቴ እንምራው። ለምናምንበት አካል የምንችለውን እናድርግ። … ሃሳብን በሃሳብ እናታግል በመከባበር በሥልጡን ሁኔታ። ከዚህ በተረፈ እኛ ቢያንስ በስደት ተሳስብንና ተዛዝነን እንደ ተፈጥሯችን በአብሮነት እንኑር …. የሱባኤ ጊዚያችን በተመክሯችን ጥሪት እናበልጽገው። መሪዎቻችንም ቁርጣቸውን ሲያውቁ እነሱ መከባበርን አዝምረው፤ ፈርኃ ፈጣሪን ጥሪት አድርገው፤ መግባባትን አድምጥው፤ ለመቻቻል እጃቸውን ሰጥተው፤ ሁሉን ቻል በማድረግ ለኢትዮጵያዊነት ሊታገሉ ይችላሉ። አልበላም እያለ ለሚያስችግር ልጅ ብትባላ ብላ፤ ባትበላ ተዎው ሲባል፤ ራህብ ሲያኮራምቶ ለምኖ ይበላታል። እስኪ በዚህ መንገድ ደግሞ ይሞከሩ … መሪዎቻችን …

የፊታውራሪ ሂደት ከነቤተሰቡ ጥቃት ቀጥተኛ ሰለባ የሆነው የ አደራ ቤተኛ አቶ አንዱዓለም አራጌ ፤ – አምርሮ ህሊናው ያዘነው፤ ወጣት የነፃነት ደቀመዝሙር አቶ አንዱዓለም አዝመራውን ከአውድማው ማዬት ጓግቶ ግን …. ምች ሊያጠቃው ዳታ (ዝግመት)ሲፈታተነው መረረው ። መሆንን ያሰተማረን አቶ አንዷለም ይገባዋል። እውነቱንም ነው። ከትናንት ዛሬ እዬተጫነን ጉም እዬለበሰ ሲያዘግም፤ ተስፋው እዬራቀ ሲመጣ …. የፋመው ሲበርደው፤ የጋመው ሲቀዘቅዝ፤ ማግስት ከቅርበት ጋር ሲጣላ፤ ጉድጓድ ውስጥ በቋሳ የተነቀሰ በደል ተሸክሞ ፍዳ ሲከፍል፤ መተንፈሻ ቧንቧው ተጋርዶ አዬር ሲያጣ  - ሲቀረቀርበት፤ ድቅድቅ ባለ እስር ቤት – በተፈነ ጉረኖ ወይንም በረት ሁኖ ያን የመካራ ሌሊት ጋር ለሚያስልፍ የነፃነት ራህብተኛ አርበኛ ጨለማ ነው። ረግረግ ነው። ጨቀጨቅ ነው። ጥቁር ውስጥ ሆኖ ተስፋ አድርጎ እራሱን የሰጠበት ነገር ውሉ ሲላላ … ተስፋው ሲተረተር …. እሳትና ረመጥን ለመረጠ የመሆን ጀግና መርግ ነው ከባድ። ስለሆነም ከቋያው በተወሰነ ደረጃ ትንሽ ራቅ ያለው ቤተሰብ ቀለማሙን የአደራ ቡቃያ ከብክቦ ማሳደግ ግድ ይለዋል …. መልእክቱ ውስጥን ይመረምራል። መንፈሱ ውስጥን ያፋጥጣል። እያንዳንዱ ቃል ውስጥን ይፈታትሻል …. ከራስ ጋር ታርቆ „ሀ“ ብሎ „ሁ“ እንዲቀጥል መባታልን መታጠቅ … ገፋ አድርጎ መሄድን ይጠይቃል። ጫናው ከባድ ቢሆንም ….

እንደ – መሰብሰቢያ

አደራን ተቀብሎ ስለፍትህ የጸናው፤ የቀለጠበት ድርጅት ቢያንስ እውነተኛ ቦታውን እንዳይነሳው …. ስጋቴ ጠርዝ ላይ ነው ያለው … ወድቆ እንዳይፈጠፈጥ እዬሰጋሁ ነው …. እናንተስ ውዶቼ? ያቺ አጋሩም ብቻዋን በአንድ ክንድ አሳር ላይ ያለ ትዳርን ስንቅ በማቀበል፤ ሁሉን ችላ ጽናትን በመቀለብ፤ ታይተው የማይጠገቡ ጮርቃዎች የአባት ናፍቆት እዬቀጣቸው እንዲያድጉ በቀንበጥነታቸው በሄሮድስ መለስ ሰባራ ገል ሌጋሲ ተፈርዶባቸዋል። ደማሞቹ ሁለት ህጻናት ውስጣቸው ያለቅሳል – በናፍቆት ተርመጥምጧል፤ የደጁንም የቤቱንም ሙሉ ኃላፊነት …. የወሰደቸው የነፃነት ትግሉ ዓይነተኛ አካላዊ ክንፍ ባለቤቱም የሰው ህይወትን የመፈወስ የላቀ ሙያዊ ድርሻ፤ የወያኔው እውር ደህንነት አራዊቶች በዬምትንቀሳሰቀስበት ስንዝር የስለላ ጫና … ተሸክማ ያልበላቸውን ዕዳ ስትከፍል በመንፈሱ አንዱ … ያያታል። የማይገፉ ሌሊቶች ካለ መፍትሄ የተፈጥሮን ሂደት ተከትለው ይነጉዳሉ። …  ታዲያ በመራር – የብረት አጥር ኑሮው ከእንቡጦቹ ተለይቶ መኖሩ ላይበቃ የሚቀልጥለት አደራ ቡቃያው ሲጫጫ ውስጡ ተክኖ እንዳይታመም ጠርዝ ላይ ያለው ሌላው የተከደነና እምቅ ስጋቴ ነው …. ማህከነ! አብረን ቆዬን ሳትሰለቹኝ። ኑሩልኝ ታዳሚዎቼ።

 

 

እልፍነና እልፍነታችን በተግባር እልፍ እናድርገው።

 

 

Sport: ቀነኒሳ በቀለ በኤደንበርግ አገር አቋራጭ ውድድር ላይ እንደሚሮጥ ታወቀ

$
0
0

ከቦጋለ አበበ

ወደር የማይገኝለት የረጅም ርቀት አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በእዚህ ወር መጨረሻ በኤደንበርግ አገር አቋራጭ ውድድር እንደሚሮጥ ታውቋል፡፡ የዓለምአቀፉ አትሌቲክስ ማህበር ድረገፅ ሰሞኑን እንዳስነበበው ቀነኒሳ በኤደን በርግ ዘንድሮ ሲሳተፍ ለስድስተኛ ጊዜ ነው፡፡
የሠላሳ አንድ ዓመቱ የኦሊምፒክ የሦስት የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ቀነኒሳ እ.አ.አ ከ2006 ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ጊዜ በኤደንበርግ አገር አቋራጭ ውድድር ቢያሸንፍም 2010 ላይ ባልተጠበቀ ሁኔታ አራተኛ ሆኖ አጠናቅቋል፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላም አሥራ አንደኛ ሆኖ ውድድሩን ማጠናቀቁም ይታወሳል፡፡
kenenisa 1
ቀነኒሳ በዘንድሮው ውድድር ግን ሁለት ጊዜ የተሸነፈበትን ታሪክ ለመቀየር መዘጋጀቱ እየተነገረ ይገኛል፡፡
ቀነኒሳ በዓለም አገር አቋራጭ ውድድር በረጅምም ሆነ በመካከለኛ ርቀት አሥራ አንድ ያህል የወርቅ ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ የሚስተካከለው አትሌት የለም፡፡
በፈጣን የአጨራረስ ብቃቱ የተለየ ዝና ያለው ቀነኒሳ በቀለ እ.ኤ.አ ከ2010 ጀምሮ በጉልበቱ ላይ በአጋጠመው ተደጋጋሚ ጉዳት ምክንያት በተለያዩ ውድድሮች ድል ሳይቀናው ቀርቷል፡፡ በተለይም በለንደን ኦሊምፒክ በአምስትና አሥር ሺ ሜትር እንዲሁም በሞስኮው የዓለም ሻምፒዮና በተመሳሳይ ርቀቶች ያመለጡት የወርቅ ሜዳሊያዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ቀነኒሳ በሞስኮው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ባይካፈልም ከሻምፒዮናው በኋላ በተለያዩ የጎዳና ላይ ውድድሮች ወደ ድል መመለሱን አሳይቷል፡፡ አሁንም ቀነኒሳ የቀድሞ ክብሩን ለማስመለስ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝና ለ2016 የሪዮዲጄኔሮ ኦሊምፒክ እየተዘጋጀ እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ቀነኒሳ በመጪው ዓመት ከመም ውድድሮች ወጥቶ ወደ ማራቶን የመግባት እቅድ እንዳለው በመግለጽ አሁን ወደ ቀድሞ አቋሙ እንደተመለሰና በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ለዜናው ምንጭ ከሰጠው አስተያየት ማወቅ ተችሏል፡፡
ቀነኒሳ ባለፈው ክረምት በታላቁ የሰሜን በግሬት ኖርዝ ረን ኒውካስትል ውድድር ላይ በአሥር ኪሎ ሜትር የጎዳና ተወዳድሮ ላይ ውድድር የአገሩን ጀግና አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴና የወቅቱን የአምስትና አሥር ሺ ሜትር ንጉሥ ሞሐመድ ፋራን በማሸነፍ ወደ ቀደሞ ብቃቱ እየተመለሰ እንደሚገኝ አስመስክሯል፡፡
በኤደንበርግ ለማሸነፍ እንደተዘጋጀና በራስ መተማመኑም ከፍተኛ እንደሆነ የተናገረው ቀነኒሳ፤ኤደን በርግ ላይ ከተሸነፈባቸው ውድድሮች ይልቅ ባሸነፈባቸው ውድድሮች ጥሩ ትዝታ እንዳለውና ያንን ትዝታውን አሁን መድገም እንደሚፈልግ ገልጿል፡፡ ቀነኒሳ በተለይም በ2008 በዓለም ሻምፒዮና የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘቱ ይታወሳል፡፡
በስኮትላንድ ኤደንበርግ ከተማ በየዓመቱ የሚካሄደው የአገር አቋራጭ ውድድር በዓለማችን ታዋቂ አትሌቶችን ከሚያሳትፉ ውድድሮች አንዱ ነው፡፡ ዘንድሮም ውድድሩ ከአውሮፓና አሜሪካ እንዲሁም ከአፍሪካ የተውጣጡ ጠንካራ አትሌቶችን እንደሚያሳትፍ ታውቋል፡፡

በዛሬው ችሎት በነፃ የተሰናበቱትና ተከላከሉ የተባሉት የድምጻችን ይሰማ ዋና መሪዎች ስም ዝርዝር

$
0
0

ዘ-ሐበሻ በዛሬ ጠዋት ሰበር ዜናዋ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ውስጥ 10 በነፃ እንዲሰናበቱ፣ 14ቱ ዋና ዋና መሪዎች እንዲከላከሉ፣ ሌሎች 4ት ተጠርጣሪዎች የሽብርተኝነት ክስ ዝቅ ተደርጎ ሰውን በማነሳሳት ወንጀል እንዲከላከሉ መወሰኑን መዘገቧ ይታወሳል። ለአንባቢዎቻችን ግልጽ እንዲሆን በማሰብ ማን እነማን ተከላከሉ እንደተባለ፣ ማን እንዲፈታ እንደተወሰነ፣ ማን ክስ ዝቅ እንዲደረግለት እንደተደረገ ስም ዝርዝራቸውን ይዘናል። በነጻ የተሰናበቱት የእስር መፍቻ እንዲጻፍላቸው እና ይከላከሉ የተባሉት ደግሞ መከላከያ ማስረጃዎቻቸውን እንዲያሰሙ ከጥር 22 ጀምሮ ፍርድ ቤቱ ተከታታይ 5 ቀናት በተለዋጭ ቀጠሮ ለሕዝብ ክፍት በሚሆን ችሎት እንደሚያቀርቡ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ማንዴላ፣ ኦባማና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጉዳይ – ከሳዲቅ አህመድ (ያድምጡ)
ተከላከሉ የተባሉት፦ 

1. ኡስታዝ አቡበከር አህመድ
2. ኡስታዝ አህመዲን ጀበል
3. ኢንጅነር በድሩ ሁሴን
4. ኡስታዝ ያሲን ኑሩ
5. ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ
6. አሕመድ ሐጂ ሙስጠፋ
7. ኡስታዝ ሰኢድ አሊ
8. ጋዜጠኛ አቡበከር አለሙ
9. ሙኒር ሼኽ ሑሴን
9. ሙባረክ አደም ጌቱ
10. ሷቢር ይርጉ ማንደፍሮ
11. ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸው ዘውዴ
12. ካሊድ ኢብራሂም
13. አብዱረዛቅ አክመል
14. ሙሐመድ አባተ

 የቀረበባቸው የሽብርተኝነት ክስ ዝቅ ተደርጎ ሰውን በማነሳሳት ወንጀል እንዲከላከሉ የተወሰነባቸው

1. ሸኽ መከተ ሙሄ
2. ወንድም ኑሩ ቱርኪ
3. ኡስታዝ ባህሩ ዑመር
4. ወንድም ሙራድ ሽኩር

በነፃ እንዲሰናበቱ የተደረጉት፦
1. ዶ/ር ከማል ገለቱ፣
2. ሸኽ አብዱረህማን፣
3. ሸኽ ሃጂ ኢብራሂም፣
4. ሸኽ ጣሂር አብዱልቃድር፣
5. ሸኽ ሱልጣን አማን፣
6. ወንድም ሀሰን አሊ
7. ኡስታዝ ጀማል ያሲን፣
8. ወንድም አሊ መኪ፣
9. ወንድም ሀሰን አቢ እና
10. ወ/ሮ ሃቢባ መሃመድ

ጄነራል ሳሞራ የኑስ በውጭ ተቃዋሚዎች የመለስን የበላይነት መስክረዋል አሉ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ኢሕአዴግ ለይስሙላ ያከብረዋል እየተባለ በሚተቸውና ለ8ኛ ጊዜ የተከበረውን የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሕገ መንግሥት ቀን በዓል ምክንያት በማድረግ መንግስት ባሳተመው ‘ሕብረ ብሔር’ መጽሔት ላይ ቃለ ምልልስ የሰጡት የጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ጀነራል ሳሞራ የኑስ መለስ ከሞተ በኋላ በውጭ ያሉ ተቃዋሚዎች የሟቹን አቶ መለስ ዜናዊን የበላይነት መስክረዋልና እናመሰግናቸዋለን አሉ። በሰራዊቱ ውስጥ እኩልነት እንዳለ መናገራቸውም ብዙዎችን አስገርሟል።
Samora Yenus
በከፍተኛ ህመም እየተሰቃዩ ነው በሚል በተደጋጋሚ ተጽፎላቸው የነበሩትና አሁንም ህክምና ሁልጊዜ እንደሚከታተሉ የሚነገርላቸው ጄነራል ሳሞራ ከመንግስታዊው መጽሔት “የቀድሞው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ህልፈተ ሕይወታቸው በድንገት ከተሰማ በኋላ በውጭ የሚገኙ አንዳንድ ፀረሰላም ኃይሎች እና አንዳንድ ተቃዋሚዎች ኢትዮጵያ ለሽብርና ለሌሎች ፀረ-ሰላም ተግባር መጋለጧ አይቀርም ሠራዊቷም መዳከሙ አይቀርም በማለት ሲገልጹ ነበር። ይህ ሊሆን ያልቻለው ለምንድ ንነው ይላሉ? እነዚህ ወገኖች ይህን ተመኝተዋል ነገር ግን ያልሞከሩት ከምን አንፃር ነው?” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ “ከመለስ በኋላ ሠራዊቱ ይዳከማል ብለው ማሰባቸው የመለስ አስተዋፅኦ ጠንካራ ሠራዊት እንዲኖር፣ ጠንካራ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ኃይል እንዲኖር ያስቻለ ስለመሆኑ እውቅና መስጠት ስለሆነ እናመሰግናለን።” ካሉ በኋላ ቀጥለውም “ምክንያቱም መለስ ይህቺ አገር ጠንካራ የመከላከያ ኃይል እንዲኖራት ወሳኝ ድርሻ ነበረው ብለው ስላመኑ ነው ይህንን ማንሳት የጀመሩት፡፡ ይህን ማሰብ በመጀመራቸው ደግሞ መመስገን ይኖርባቸዋል፡፡” ብለዋል።

ሳሞራ በመንግስታዊው ጋዜጠኛ ለቀረበላቸው ለዚሁ ተመሳሳይ ጥያቄ በሌላ በኩል የአንድ ሰራዊት ጥንካሬ የሚለካው በሰራው አንድ ሥራ ብቻ አይደለም። ሠራዊቱ ይህቺ አገር እስካለች ድረስ አብሮ ይኖራል። ምክንያቱም ተቋሙ ቀጣይ ነው። ተቋሙ ለሁለት ነገር ብቁ መሆን አለበት። አንደኛ ለወቅታዊ ግዳጁ፣ ሁለተኛ ደግሞ ለወደፊት ለሚሰጥ ግዳጅ ብቁና ዝግጁ መሆን አለበት። የእያንዳንዱ አመራር ተልዕኮም ይሄ ነው። በተለይ የከፍተኛ አመራሩ ተልዕኮ ይህንን ማረጋገጥ ነው። ይሄን እንዴት እንፈፅመዋለን ለሚለው ደግሞ ሶስት መሰረታዊ ሥራዎችን በመሥራት ነው።
ዋናውና ወሳኙ የሰው ኃይሉን ማዕከል ያደረገ ሥራ መሥራት ነው። የሰው ኃይሉን ማብቃት። ቴክኒካዊና ሙያዊ እንዲሁም አካዳሚያዊ ብቃቱን ማሳደግ፣ ሳይንሳዊ ዕውቀቱን ማዳበር፡፡ እንግዲህ ሶስት የአቅም ግንባታ ሥራ መሥራት ዋነኛው ሆኖ የሰው ኃይል ማዕከል ያደረገ የአቅም ግንባታ ሥራ መስራት ያስፈልጋል። ሁለተኛው ሥራ በአደረጃጀቱና አሰራሩ ሕዝባዊ ባህሪውን እንደጠበቀ ከተልዕኮውና ከባህሪው የሚስማማ አደረጃጀትና አሰራር ያለው እንዲሆን ማድረግ ነው። አደረጃጀት አቅም ፈጣሪ ነው። አደረጃጀት ለዘለዓለም የሚኖር አይደለም። ከሁኔታው ጋር እየዳበረ አቅም እየፈጠረ የሚሄድ መሆን አለበት። አሰራሩም በተመሳሳይ ከሕዝባዊ ባህሪውና ከተልዕኮው የተጣጣመ አሰራር ዴሞክራሲ ያዊና ደስተኛ ሕይወቱን በአስተማማኝ የሚጠብቅ፣ የግዳጅ አስተሳሰቡንና ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰቦችን የሚያዳብሩ አሰራሮችን ማረጋገጥ ማለት ነው። አደረጃጀቱም፣ አሰራሩም፣ የሰው ኃይሉም ሦስቱን ሥራዎች በመሥራት ነው ለተጨባጭ ግዳጅም ሆነ ለወደፊት ለሚሰጠው ግዳጅም ዝግጁ የሚሆነው፡፡
“ስለዚህ ሠራዊቱ በዚህ እየተገነባ ስለቆየ ነው ውጤትም እየተገኘ የመጣው፡፡ ካብ አይደለም ሲሠራ የነበረው። ጠንካራ የመከላከያ ተቋም፣ ጠንካራ የመከላከያ ኃይል፣ ሕዝባዊ ባህሪውን የጠበቀ የመከላከያ ኃይል ነው ሲገነባ የነበረው። እና በዚህ ምክንያት ሊፈርስ አልቻለም፡፡ አይፈርስምም ይጠነክራል።
እነዚያ ወገኖች የተመኙትን አልሞከሩትም ማለት ግን አይደለም፡፡ የብተናና የተለያዩ ሥራዎችን አልሞከሩም ማለትም አይደለም። መከላከያ ሠራዊታችንን የሚያፈርሱት ሦስት ምክንያቶች ካጋጠሙ ብቻ ነው የሚል እምነት አለን። በንግግር አይፈርስም። በሦስት ነገር ግን ሊፈርስ ይችላል። አንደኛውና ዋናው ተልዕኮው ከተቀየረ ነው፡፡ እንግዲህ አሁን ተልዕኮው ሕዝባዊ ነው። የወረራ ተልዕኮ የለውም። የሠላም ተልዕኮ ነው ያለው፡፡ ምክንያቱም የኢትዮጵያ ህዝብ ተስፋው ከሰላም እንጂ ከጦርነት አይደለም፡፡ ስለዚህ ከዋናው ተልዕኮ አንደኛው ሠላም ማረጋገጥ ነው። ይህ ደግሞ በሕገ መንግሥቱ የተቀመጠለት ነው። ሁለተኛው ደግሞ የጦርነት አደጋ ካጋጠመ በአጭር ጊዜ እና በአስተማማኝ በመጨረስ ተመልሰን ወደ ልማታችን መግባት ነው።ሌላው ተልዕኮ ደግሞ የአፍሪካ ወንድሞቻችን ከእኛ ለሚፈልጉት ሁሉ አስፈላጊውን ድጋፍ ማበርከት ነው።
የእነርሱ ሰላም የእኛም ሰላም ስለሆነ በአቅማችን በሰላም ማስከበር ሥራ መሳተፍ ነው። አራተኛው ደግሞ በአገር ውስጥ ከፀጥታ ኃይሎች አቅም በላይ የሆነ ጉዳይ ካለ መሳተፍ። በህብረተሰቡ ላይ ሰብአዊና ተፈጥሮአዊ አደጋዎች ከአጋጠሙ የድርሻችንን መወጣት ነው። እነዚህ ተልዕኮዎች ሕዝባዊ ተልዕኮዎች ናቸው። ከሕገ መንግሥቱ የወጡ፣ የተቀዱ ተልዕኮዎች ናቸው።
“ሁለተኛው የሠራዊቱን ጥንካሬ ሊበረብር የሚችል ደግሞ የራሱ የሰራዊቱ የውስጥ ችግር ነው። ኢ-ዴሞክራሲያዊነት ከሰፈነ ሠራዊቱን ሊያፈርሰው ይችላል። ኢ-ዴሞክራሲያዊነት ከተፈጠረ በርካታ መዘዞች ይመጣሉ። ፀረ-ዴሞክራቲክ መሆን ከተጀመረ የህግ የበላይነት ይጣሳል ማለት ነው፡፡ በአንድ በኩል በህግና በአሰራር መሄድ ይቀራል። ሁለተኛ የሠራዊቱ ደስተኛና ዴሞክራሲያዊ ሕይወት ይበላሻል። ስለሆነም ጠንካራ አንድነት፣ አስተማማኝ አንድነት፣ የማይናወጥ አንድነት ያለውን ሠራዊት አንድነቱ እንዲናጋ ያደርገዋል። የጌታና የአሽከር አካሄድ ነው የሚኖረው፡፡ ይሄ ደግሞ ለአገሪቱም ለሁሉም አይጠቅምም።
“ሌላው ደግሞ ሙስና ነው። ሙስና ሠራዊቱን ሊያበላሸው ይችላል፡፡ ሙስና ፀረ ልማት ነው። ሠራዊቱን ሊበትነው እና ሕዝባዊ ባህሪውን እንዲያጠፋ ሊያደርገው ይችላል። አንድ ሠራዊት ሠራዊት ነው የሚባለው እንደ ወታደር እንደ አንድ አካል ሲያስብ እንጂ ለግሉ ሲያስብ አይደለም።
ለምሳሌ አንድ ወታደር በአንድ ሻለቃ ወይም በአንድ ቡድን ሊድን ከሆነ ሻለቃዋ መዳን አለባት፡፡ በሌላ በኩል አስሩ ከዳኑ ነው እርሱ መዳን የሚችለው። ቡድኑ ብቻውን ሊድን አይችልም። ስለዚህ ይሄ ሻለቃ አስሩን ማዳን አለበት።ወታደሩ መዳኑ የሚረጋገጠው አስሩ ከዳኑ ይሆናል። ብቻውን ሊድን ከፈለገ አይችልም። በተመሳሳይ አንድ የመቶ ካለችም ሶስት ቲም አሏት፡፡ የመቶዋ ልትድን ከሆነ ቲሟ መስዋዕትነት መክፈል አለባት፡፡ እንደዛ እያለ ነው የሚሄደው፡፡ ስለዚህ እንደ አንድ አካል የሚያስብ መሆን አለበት፡፡ ፀረ ዲሞክራሲ አካሄድ ካለ በውስጡ አንድነቱ ይላላል፤አስተሳሰቡም ይሸረሸራል ማለት ነው፡፡ ሙስናም በተመሳሳይ ለግል ማሰብን ይመጣል፤ ይህም ያፈርሰዋል። በአጠቃላይ በዚህ ነው የሚፈርሰው እንጂ በንግግርና በአሉባልታ አይደለም።” ብለዋል።

የአንድ ብሔር ተወላጆች በሰራዊቱ ውስጥ ቁልፍ ቦታ መያዛቸው፣ በትውልድ ብሔራቸው የተነሳም በሙስና ነቅዘው ሃብታም መሆናቸውን፣ መከላከያ ሰራዊቱም የሃገር ዘራፊዎች መሳሪያ መሆኑን በስፋት በሕዝብ ዘንድ የታወቀ ሆኖ ሳለ ኤታማዦር ሹሙ ይህንን ሽምጥጥ አድርገው በመካድ ለዚሁ መጽሄት “ወታደር ሲሆን ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን የመጠበቅ ተልዕኮ ነው ያለው። ሌላ ምንም ነገር የለውም። ከሌላው ዓለም የእኛ ደግሞ ትንሽ ይለያል። ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱ የሚጠበቀው በሕዝቡ፣ በሠራዊቱም በሁሉም እኩል ነው፡፡ የሁሉንም ሕዝቦች ተጠቃሚነት ስለሚያረጋግጥ በተወሰኑ ምሁራን ብቻ የሚጠበቅ አይደለም፡፡ስለዚህ የሁሉንም ህዝቦች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጠውን ህገመንግስት ሁሉም ህዝብ ማወቅ አለበት፡፡ ሁሉም ህዝብ ማወቅ አለበት ብቻ ሳይሆን እንዲያምንበትም መደረግ መቻል አለበት፡፡ካመነበት በኋላ ደግሞ እንደወታደር ለመጠበቅም ለመስዋዕት ራሱን ዝግጁ እንዲያደርግ ይገነባበታል።” ማለታቸው ትዝብት ውስጥ እንደጣላቸው ታዛቢዎች ይናገራሉ።

ይድረስ ለሚኒሶታ መድኃኔዓለም ምዕመናን፡ የተከፋፈሉት አባቶች 1 አስኪሆኑ ድረስ በአስተዳደር ገለልተኝነት ለመቆየት 7 ምክንያቶች

$
0
0

ቀን፡ 12-12-13
በሥላሴ ስም አንድ አምላክ አሜን።
ይድረስ ለሚኒሶታ መድኃኔዓለም ምዕመናን
ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን የተከፋፈሉት አባቶች አንድ አስኪሆኑ ድረስ በአስተዳደር ገለልተኝነት መቆየት ይገባታል!

deb
ምክንያቶች፦
1. የደብራችንን ሰላምና አንድነት ለመጠበቅ ያስችላል።
2. የተከፋፈሉትን አባቶቻችንን ለማቀራረብ በሚካሔደው ጥረት ውስጥ ተሳታፊ ለመሆንና የክርስቲያኖችን ድርሻን ለመወጣት ይጠቅማል።
3. የክርስትና ጠባይ ያልሆኑትን የፖለቲካና የዘረኝነትን ነገር በደብራችን እንዳይኖር ይረዳል።
(ስለአገርና ስለኅዝብ መበደል፣ ስለቤተክርስቲያን ጥቃትና መብት ገፈፋ መናገር ግን ፖለቲካ አይደለም።)
4. በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ በማንኛውም አካል በቤተክርስቲያን ላይ አንዲሁም በአገርና በህዝብ ላይ የሚደርሱ በደሎችን ተቃውሞ ድምጽን በነጻነት ለማሰማት ይረዳል።
5. ከሌሎች ቤተክርስቲያናት ጋር መልካም ግንኙነት እንዲኖርና በሕብረት ለማገልገል ያስችላል።
6. የምእመናንን ቁጥር ለማብዛትና የቤተክርስቲያናችንን ሁለንተናዊ እድገት ለማምጣት ያስችላል።
7. ወገናዊነት ሳይኖርና ያለህሊና ወቀሳ እምነትን በነጻነት ለመፈጸም ይጠቅማል።

ከዚህ አንፃር በአሁኑ ሰዓት ዘረኝነት፣ አድሎ፣ሙስና፣ወዘተ ወዳለበትና በቀጥታ በመንግስት በሚታዘዝ አስተዳደር ስር እንሁን የሚሉ ክፍሎች ተሳስተዋል። በደብረ ሰላም ዘረኝነት የለም! ለማንም የፖለቲካ ድጋፍ መስጠት የለም!
ስለሆነም ቤተክርስቲያንህን በመንግስት አመራር ስር ለማድረግ የሚሮጡትን ልትቀድማቸው ይገባል!
ለብዙ አመታት ገንዘብህን ፣ጉልበትህን ፣እውቀትህን ፣ጊዜህንና ላብህን አፍስሰህ እዚህ ያደረስከውን የአምልኮ ቤትህን እንዳትቀማ ተነስ።
የችግሩን መንሰኤና መፍትሄ ልቦናቸው እያወቀ አሳልፈው ሊሰጡህ ባሴሩትንም ‘ካህናት’ ላይ ርምጃ ልትወስድ ይገባል።

ለቤተክርስቲያን አንድነት እና ሰላም ከቆሙ ምዕመናን።

የራስን እድል በራስ መወሰን፣ እርስ በርስ እስከማጣላት…ሌላው ኢትዮጵያዊ የተዋረደበት፤ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን –በኦጋዴን!

$
0
0

የራስን እድል በራስ መወሰን፣ እርስ በርስ እስከማጣላት…

ሌላው ኢትዮጵያዊ የተዋረደበት፤ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን – በኦጋዴን!

ዘንድሮ በኢትዮጵያ ተከበረ የተባለውን የብሄሮች  ቀን ምን ያህሎቻችሁ እንደተከታተላቹህ አላቅም። ላላያችሁት ግንዛቤ ለመፍጠር ያህል… ዘንድሮ በአሉ የተከበረው ሱማሌ ክልል፣ በኦጋዴን ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን በመንገር ወጋችንን እንጀምራለን። ይህ ዝግጅት እስከዛሬ በትግራይም፣ በአማራውም ክልል ተደርጓል… ሆኖም በአሉ ላይ ሁሉም የየብሄሩን ባህል ለማሳየት ሲጥር እንጂ፤ አንደኛው ብሄር ሌላውን ሲሰድብ ያየንበት አጋጣሚ አልነበረም። የዚህ አመቱ የብሄር ብሄረሰቦች ወይም የብሄረተኞች ቀን ሌላውን ኢትዮጵያዊ በመውቀስ ላይ የተመሰረተ ነበር።

“አማራው፣ ደገኛው፣ የመሃል አገር ሰው…” እያሉ ቀጠሉ አስተያየት ሰጪዎቹ። በአሉን ምክንያት በማድረግ በኮንፈረንሱ ላይ የተገኙት ታዳሚዎች ወቀሳቸውን ቀጠሉ፤ “የመሃል አገር ሰዎች ‘ሽርጣም ሱማሌ’ እያሉ ይጠሩን ነበር” አለ። እኛንም በሃሳብ ወደኋላ መለሰን። የመሃል አገር ሰው ይህንን ቃል አይጠቀምበትም ለማለት አይደለም። ነገር ግን “ሽርጣም ሱማሌ” የሚለውን ቃል መስማት የጀመርነው፤ በኢትዮጵያ እና ሱማሌ ጦርነት ወቅት ነው። “ሽርጣም ሱማሌ” የሚለውን አባባል ሁሉም የመሃል አገር ሰው እንደማይጠቀምበት ሁሉ፤ በቴሌቭዥን መስኮት ላይ ብቅ ብለው ሌላውን ኢትዮጵያ የሰደቡት እና ያሰደቡትም መላውን የኢትዮጵያ ሱማሌ እንደማይወክሉ እናውቃልን። በመሆኑም ይህ ጽሁፍ በሁሉም የኢትዮጵያ ሱማሌዎች ላይ ያነጣጠረ ሳይሆን፤ የማያውቁትን ታሪክ ለማሳወቅ ያህል የተዘጋጀ መሆኑን ልብ ይበሉ።

 (በዳዊት ከበደ ወየሳ –  ጋዜጠኛ)

ethiopia somalia
በ1969 ዓ.ም. ሱማሌ ኢትዮጵያን ስትወር፤ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያንን አፈናቅለዋል፤ ገድለዋል፤ በሺህ የሚቆጠሩትን ማርከው ወስደው አገራቸው ውስጥ አስረዋል። ሱማሌዎች ይህንን በሚያደርጉበት ወቅት ታዲያ ሽርጥ እንጂ ሱሪ ታጥቀው አይደለም። በዚያን ወቅት ታዲያ የኢትዮጵያ ልጆች ዳር ከዳር “ሆ” ብለው ሲነሱ፤ በወገናቸው ላይ የደረሰው በደል ቢያንገበግባቸው፤ “ይሄ ሽርጣም ሱማሌ” ብለው ቢሳደቡ ሊገርመን አይገባም። ከዚያ በፊት በነበሩት ጦርነቶች ፈረንጆች ኢትዮጵያን ሲወሩ፤ “ይሄ ሶላቶ” ብለው እንደሚጠሯቸው ጠላት የነበረውን የሱማሌ ታጣቂ “ይሄ ሽርጣም” እያሉ በመፎከር፤ የገባበት ገብተው ደምሠውታል፤ ዳግመኛም የኢትዮጵያን ድንበር እንዳይሻገር አድርገውታል።

በ1970 የሱማሌ ጦር ሙሉ ለሙሉ በኢትዮጵያውያን ብርቱ ክንድ ተደመሰሰ። ከጅጅጋ እና አካባቢው ተፈናቅለው የነበሩት የኢትዮጵያ ሱማሌዎች ወደ ድሮ መንደራቸው ተመልሰው፤ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር ሰላማዊ ኑሯቸውን ቀጠሉ። “ሽርጣም ሱማሌ” የሚለውም አባባል እየቀረና እየተረሳ መጣ። ዘንድሮ በሱማሌ ክልል፣ በአሉ ሲከበር…  ሌላው ኢትዮጵያዊ ለሱማሌ ኢትዮጵያ የሰራው ውለታ ተረስቶ፤ የመሃል አገር ሰዎች “ሽርጣም ሱማሌ እያሉ ይሰድቡን ነበር” የሚል የጥላቻ መልዕክት ሲተላለፍ ሰማን።

ሌላው አስተያየት ሰጪ ደግሞ ቀጠለ።  “ድሮ ያስተማሩኝ ሰዎች ስማቸው ‘በቀለ፣ መኮንን፣ በየነ’ ነበር። አሁን ግን ጊዜው ተቀይሯል። አስተማሪዎቻችን ስማቸው መሃመድ እና አብዱል ሆኗል።” በማለት ለኢህአዴግን መንግስት ምስጋና ሲያቀርብ ስንሰማ፤ ጆሯችንን ማመን አቅቶን ተገረምነ። ኢትዮጵያ ውስጥ ትምህርት ሲጀመር፤ የዳግማዊ ምኒልክ ት/ቤት የመጀመሪያ መምህራን የመጡት ከግብጽ አገር ነበር። በኋላም ላይ ከህንድ ድረስ መምህራን እየመጡ አስተምረዋል፤ ወይም አስተምረውናል። በውጭ ሰው ስለተማርን… “ለምን የውጭ ሰው አስተማረን?” ብለን አንቆጭም፤ ይልቁንም ለእነዚህ መምህራን አክብሮት እና ምስጋናችንን እናቀርባለን እንጂ። በሱማሌ የተመለከትነው ግን ከዚህ የተለየ ነበር… እቺም እድሜ ሆና… እነበቀለ፣ መኮንን እና በየነ የሚባል ስም የነበራቸው ኢትዮጵያውያን ስላስተማሯቸው የሚናደዱ ሰዎችን ለማየት በቃን።

ደግሞም አንድ ሌላ እያሳቀ የሚያናድድ ነገር ሰማን። ሌላው አስተያየት ሰጪ እንዲህ አለ። “አካባቢያችን ልጅ ምግብ አልበላም ብሎ ሲያስቸግር፤ ‘አማራ መጥቶ እንዳይበላብህ’ በማለት ልጁ አማራ ሳይመጣበት ቶሎ እንዲበላ እናደርግ ነበር።” አለ።

“ጉድ እኮ ነው የሱማሌ ኢትዮጵያ ህዝብ አማራውን ይህን ያህል ይጠሉት ነበር? ማስፈራሪያስ አድርገውት ነበር?” እያልን ተገርመን ሳናበቃ ይኸው ሰውዬ ንግግሩን ቀጠለ።

“በሌላ በኩል ደግሞ የመሃል አገር ሰዎች (አዲሳባ ያለው ሌላው ኢትዮጵያዊ መሆኑ ነው) ልጆቻቸው ምግብ አልበላም ብለው ሲያስቸግሯቸው፤ “ሱማሌ እንዳልጠራብህ!” ብለው ሲያስፈሯቸው፤ ምግቡን ጥርግ አርገው ይበሉ ነበር።” ሲል ሰማን። አብረውኝ ኢቲቪን ይመለከቱ የነበሩ “የመሃል አገር” ሰዎችን በጣም አሳቃቸው። እርስ በርስ ተያየንና “ሱማሌ እንዳይመጣብህ!” ተብሎ ምግብ ሲበላ የነበረ ከመሃላችን ነበር?” ብሎ ጠየቀ አንዱ…

ሌላኛው “እኛ አያጅቦን ነው የምናውቀው” ሲል ትንሽ አሳቀን።

“ሱማሌ ሳይመጣብህ!” ተብሎ እያስፈራሩ ምግብ ያስበሉት ይፍረደን” በማለት በጉዳዩ ላይ ስቀን ልናልፍ እንችል ይሆናል። ነገር ግን … ለአማራው ድርጅት ‘ቆሜያለሁ’ የሚለው ብአዴን/ኢህአዴግ ነገሩን እንዴት አይቶት ይሆን?

የብሄር በሄረሰቦችን ቀን ምክንያት በማድረግ የሚተላለፈው የጥላቻ አስተያየት አሁንም እንደቀጠለ ነው። ኢቲቪን ከመዝጋታችን በፊት ሌላ አስተያየትም አደመጥን። ሰውየው እንባ እየተናነቃቸው፤ “መናገሻ ከተማችንን አዲሳባን ለማየት እንኳን አይፈቀድልንም ነበር።” ብለው ሲሉ፤ በራስ ተፈሪ መኮንን ዘመን የነበሩ የሱማሌ ፖሊሶች ታወሱን። በወቅቱ በአዲስ አበባ፤ በፖሊስነት ተቀጥረው ሰአት እላፊ እና ጸጥታ የሚያስከብሩት የመጀመሪያ ባለደሞዝ የአዲስ አበባ ፖሊሶች የሱማሌ ኢትዮጵያውያን ነበሩ። እናም “አዲስ አበባን ለማየት እንኳን አይፈቀድልንም ነበር” እያሉ የሚያለቅሱትን አዛውንት አይተን፤  “ወደ አዲስ አበባ መሳፈሪያ ካላጡ በቀር የባቡር መስመር ከተዘረጋ ራሱ፤ መቶ አመት አልፎታል”። በማለት ታዝበናቸው ዝም አልን።

ሌላዋ ሴት ደግሞ ቀጠለች። ሴትዮዋ መናገር ስላለባት ብቻ የምትናገር ነው የምትመስለው… “የድሮ እና የአሁኑን ሳስተያየው በጣም ብዙ ልዩነት አለው” ብላ ጀመረች። ልጅቷ እንኳንስ ስለቀዳማዊ ሃአይለስላሴ ዘመን ቀርቶ ስለደርግ ለማውራት እድሜዋ የሚፈቅድላት አይደለችም። ወሬዋን ግን በድፍረት ቀጠለች። “የድሮና የአሁኑ በጣም ልዩነት አለው… ዑውውውው።” በማለት የአሁኑን አዳነቀች። አድናቆቷን ሳታቋርጥ “የድሮ እና የአሁኑን ልዩነት ለመግለጽ ቃላቶች ያጥሩኛል” ብላ በቃላት እጥረት ምክንያት ልዩነቱን ሳትነግረን ቀረች።

ሌላው ደግሞ እንዲህ አለ። “ይሄ አካባቢ ለወታደራዊ ጦር ካምፕ ይጠቀሙበት ነበር እንጂ፤ ለህዝቡ ግድ አልነበራቸውም።” አለን። እውነት ነው። ፈረንሳይ ከጅቡቲ አልፋ ወደ ኢትዮጵያ የመስፋፋት ብዙም ህልም አልነበራትም። እንግሊዝ እና ጣልያን ግን… ሁለቱም ከሱማልያ ግዛቶቻቸው ተነስተው፤ ኦጋዴን እና አካባቢውን ጨምረው እስከ ሃረር ድረስ ለመግዛት፤ ግልጽ የሆነ እቅድ እና ሙከራ አድርገው ነበር። ሱማሊያ ነጻ ከወጣች በኋላ ደግሞ ከራሽያ ባገኘችው የጦር መሳርያ በመታገዝ እጅግ ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴ አድርጋለች። በዚህ ጊዜ ሁሉ ሰራዊቱ ከመሃል አገር እየተነሳ፤ ኦጋዴን እና አካባቢው በውጭ ሃይሎች ስር እንዳይወድቅ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ተደርገዋል። ይህ ሌላውን አገር በወታደራዊ ኃይል የመከላከል ስራ… ዛሬ ስሙ እና ውለታው ተረስቶ “አካባቢውን የወታደር ካምፕ አደርገውብን ነበር” በሚል ወቀሳ መቀየሩ ይገርማል።

አብረውን የነበሩት ጓደኞቼ በኢቲቪ ተናደዋል።  ቴሌቪዥኑን ከመስበራቸው በፊት በሰላም ዘጋነውና ሰላማዊ ጨዋታችንን ጀመርን። “ለመሆኑ ሌላው ኢትዮጵያዊ ደገኛ፣ የመሃል አገር፣ ክርስቲያን፣ አማራ…” እየተባለ ቅጽል እየወጣለት መሰደብ አለበት ወይ? ይህ ደገኛም ሆነ ነፍጠኛ ያሉት ኢትዮጵያዊ ለዚያ ህዝብ ውለታ አላደረገምን? ዝርዝር ውስጥ አንገባም። ሆኖም በታሪክ ቅኝት ወደኋላ መለስ ብለን የእውነትን ማህደር በማገላበጥ ታሪክን እስኪ እንመርምር። እንዲህ ነው።

ወደ አጼ ምኒልክ ዘመን እንሂድ… በፊት በቱርኮች፤ በኋላ ደግሞ በግብጾች ሲተዳደር የነበረው ህዝብ የጠመንጃውን አፈሙዝ በኢትዮጵያውያን ላይ አነጣጥሮ እንደነበር ይታወቃል። በ1524 ዓ.ም. ግራኝ አህመድ እና አሊ ኑር እንደገነኑት ሁሉ፤ በ1876 ዓ.ም. ደግሞ አሚር አብዱላሂን ጨምሮ ሌሎች የአካባቢው ገዢዎች ጉልበታቸው የደረጀበት ወቅት ነበር። በወቅቱ ነዋሪውን በቁጥጥራቸው ስር አውለው፤ “በክርስቲያን መንግስት አንገዛም” ማለታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ከዚያ እምነት ውጪ የነበሩትን የገደሉበትና ያጠፉበት ታሪክ ነው ያለን። (ይህም በአረብኛ ተጽፎ የሚገኝ ሰፊ ታሪክ ያለው ጉዳይ ነው) አሚር አብዱላሂም ቢሆን፤ ለአጼ ምኒልክ “አልገብርም” ማለት ብቻ ሳይሆን፤ “አንተም እንደኛ ካልሰለምክ በስተቀር፤ በክርስቲያን ንጉሥ አንገዛም” በማለት ለአጼ ምኒልክ፣ ሽርጥ፣ መቁጠርያ እና መስገጃ ምንጣፍ ነበር የላከላቸው።

አጼ ምኒልክ የተላከላቸውን ሽርጥ፣ መቁጠሪያ እና መስገጃ አብረዋቸው ለነበሩ ሙስሊሞች ሰጥተው፤ ፊታቸውን ወደምስራቅ ኢትዮጵያ አዙረው፤ በአሚር አብዱላሂ የሚመራውን ጦር፤ ጨለንቆ ላይ ገጠሙት። በዚያ የጨለንቆ ጦርነት በርካታ ኢትዮጵያውያን አለቁ። ከሚንልክ ጋር የነበሩ የአማራ ተኳሾች እና የኦሮሞ ፈረሰኞች፤ የአሚር አብዱላሂን ጦር አሸነፉት። ጥር 18 ቀን፣ 1879 አካባቢው በምኒልክ ጦር ነጻ ወጣ። አሚር አብዱላሂም በጅጅጋ አድርጎ አገር ጥሎ ጠፋ።

በኋላ ላይ የአሚር አብዱላሂ ዘመዶች ወደምኒልክ ዘንድ መጥተው፤ “እባክዎን አገሩን እንዳያጠፉት” ቢሏቸው፤ “እኔ አገር አቀናለሁ እንጂ አላጠፋም። እዚህ ድረስ የመጣሁትም ሃይማኖት ለማጥፋት አይደለም። ሁሉም ሰው እንደየ እምነቱ ያድራል።” ብለው ወደጀጎል በሰላም ሲሸኙዋቸው፤ ከነሱም ጋር እነበጅሮንድ አጥናፌ እና እነሻቃ ተክሌ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ይዘው ሀረር ገቡ። ከዚያ በኋላ አካባቢው በርግጠኝነት የኢትዮጵያ ግዛትነቱ ታውቆ፤ በአምስቱም የጀጎል በሮች ላይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እንዲሰቀል ሆነ። 3ሺህ ወታደሮችም ከራስ መኮንን እንዲቀሩ አድርገው፤ ክልሉ እንደገና በኢትዮጵያ መንግስት ስር ይተዳደር ጀመር።

አጼ ምኒልክ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ፤ የማረኩትን የግብጽ ወታደሮች አልገደሏቸውም። ይልቁንም ግብጾቹ የአሚር አብዱላሂን ጦር ለማበረታት ወታደራዊ ማርሽ ያሰሙ ነበር። አሁንም የምኒልክ ጦር በድል አድራጊነት ወደ አዲስ አበባ ሲገባ፤ አጼ ምኒልክ እነዚህኑ የጦር ሙዚቀኞች ታምቡር እያስመቱና ጥሩንባ እያስነፉ በወታደራዊ ስነ ስርአት አዲስ አበባ ሲገቡ ህዝቡ ግራና ቀኝ ተሰልፎ በታላቅ ደስታ እና እልልታ ተቀበላቸው። ያንጊዜ ታዲያ ማርከው ያመጡት ግብጾቹን ብቻ ሳይሆን፤ ለማዳ እርግቦች በሽቦ ቤት ያሉ እርግቦች እና ትላልቅ ሰሎግ ውሻዎች ጭምር ነበር። ያኔ ታዲያ እንዲህ ተባለ…

የምኒልክ ነገር፣ ይመስለኛል ተረት፤

አሞራው በቀፎ፣ ውሻው በሰንሰለት።

ይህ የሆነው የካቲት 28፣ 1879 ዓ.ም. ነው። እንግዲህ ሌላው ኢትዮጵያዊ የሚያውቀው እውነት ይህ ሆኖ ሳለ፤ የአካባቢው ሰዎች “ክልላችንን የጦር ካምፕ አደረጉብን” በማለት ምኒልክን እንደጨፍጫፊ እና ተስፋፊ ሲያዩ “እንቁላል ለመጥበስ መጀመሪያ ቅርፊቱን መስበር ያስፈልጋል” ከማለት ሌላ ብዙም የምንለው አይኖርም። ይልቁንስ ከአስር አመታት በፊት ይመስለናል… በዚሁ ኢቲቪ የተመከትነው አንድ ለቅሶ ነበር። ስለኢትዮጵያ አንድነት ሲባል፤ ምኒልክ እና አሚር አብዱላሂ ጦርነት ያካሄዱበት ጨለንቆ ድረስ ሄደው፤ መሬቱን ቆፍረው የሟቾችን አጽም ከመቶ አመት በኋላ በማውጣት፤ “ምኒልክ የጨፈጨፏቸው…” ብለው ደረት እየመቱ ሲያለቅሱና ሲያስለቅሱ አይተን፤ “ወይ ታሪክ!?” ብለን ያለፍንበት አጋጣሚ ተፈጥሮ ነበር።

በሱማሌ ክልል የተከበረው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን እና በሌላው ኢትዮጵያዊ ላይ የደረሰው ውርደት ምን ያህሉን ሰው እንዳበሳጨው ለማወቅ ያስቸግራል። እኛ ግን እንላለን… “የአካባቢው ሰዎች ታሪካቸውንና ማንነታቸውን ወይም ታሪካችንን እና ማንነታችንን አያውቁም ማለት ነው። ሰው ሱማሌ፣ ኦሮሞ ወይም አማራ ስለሆነ አዋቂ አይሆንም። አገር እና ብሄር ሰውን አይለውጥም፤ ትምህርት ግን ሰውን ይለውጣል” ስለዚህ አሁንም ትንሽ ወደኋላ መለስ ብለን የጋራ ታሪካችንን እንጨዋወት፤ በዚያው እንማማር፤ እንለወጥ።

እንደ እውነቱ ከሆነ፤ ይህ አካባቢ ከጥንት ጀምሮ በኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ተይዞ የነበረ ክፍለ ግዛት ነው። በ10ኛው ክፍለዘመን የሱማሌ ነገድ ከታጁራ ቤይ ተነስቶ መስፋፋት ሲጀምር የኦሮሞን ህዝብ እየተገፋ፤ በዋቢ ሸበሌ እና ጁባ ወንዝ መሃል በሚገኘው ቤናዲር በሚባለው ቦታ ላይ እንዲቆይ አድርጎት ነበር። በኋላም ኦሮሞዎቹን… ከታች የባንቱ ህዝብ ከላይ ሱማሌ ሲያስቸግራቸው ወደ ወላቡ፣ አበያ፣ ባሌ ድረስ ዘልቆ ራሱን በገዳ ስርአት እያደራጀ ቆይቶ፤ የግራኝ አህመድ ልጅ ወራሽ የሆነውን አሊ ኑርን ሐዘሎ ላይ ገጥሞ በ1551 ዓ.ም. እስከሚደመስሰው ድረስ በመሃል ብዙ ታሪኮች አልፈዋል። ከ10ኛው እስከ20ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ አካባቢው በዚህ አይነት ምስቅልቅል ውስጥ ነው የቆየው።

በኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የነበረው ምስቅልቅል እንዳለ ሆኖ፤ በተለያዩ ጊዜያት ከሱማልያ ግዛት የጦር መሳርያ ይዘው በመግባት፤ የኦሮሞውን ህዝብ በመግደል እና ከብቱን በመዝረፍ፤ ህዝቡን በማፈናቀል ብዙ ግፍ ተሰርቷል። እንደ እውነቱ ከሆነ ይህ ክልል፤ በሌሎች ላብ እና ደም የተገነባ ክልል ነው። ይህን በማለት ወደኋላ ተመልሰን የምንቀይረው ነገር የለም። ሆኖም የማያውቁትን ወይም እያወቁ ሊያውቁ የማይፈልጉትን አንዳንድ ነገሮች ብናስታውሳቸው ክፋት የለውም።

በምኒልክ ዘመን ከተፈጠሩት አኩሪ ገድሎች መካከል የአድዋ ጦርነት አንደኛው ነው። ይህ ጦርነት የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. በድል ከተጠናቀቀ በኋላ፤ በጦር ተማራኪዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ምኒልክ ዘንድ ምርኮኞችን አቀረቧቸው። ምኒልክ ምርኮኞች እንዲገደሉ አላደረጉም። ፈረንጅ ተማራኪዎችን ወደ አዲስ አበባ ይዘው ሲመለሱ፤ በኤርትራ እና በሱማሌ ተወላጆች ላይ ለየት ያለ ፍርድ ሰጡ። “ከአውሮፓ ወራሪ ጋር ሆነው የገዛ ወገናቸው ላይ ጥይት መተኮሳቸው ያሳዝናል። አሁንም ቀሪው ህዝብ እነሱን እያየ እንዲማር፤ ተንበርክከው የተኮሱበት ግራ እግራቸው እና ቃታ የሳቡበት ቀኝ እጃቸው ይቆረጥ።” ብለው ፈረዱ እንጂ አልገደሏቸውም።

ወደ አሁኑ የሱማሌ ክልል ልውሰዳቹህ። አካባቢው በ1879 ነጻ ከወጣ በኋላ ህዝቡ በሰላም መኖር ቢጀምርም፤ ኦሮሞዎቹ መሬት እና ከብታቸውን መነጠቃቸው ሊቆም አልቻለም። በወቅቱ የነበሩት የአካባቢው ኦሮሞዎች በተደጋጋሚ በሚደረግባቸው የድንበር ውጊያ ምክንያት ከብቶቻቸውን እየተዘረፉ፤ መሬታቸውን እየተነጠቁ፤ የሞቱት ሞተው፤ የቀሩት አካባቢውን እየለቀቁ ወጡ።  ባለንበት ዘመን ደግሞ ሰዎቹን ብቻ ሳይሆን የሰጡትን ስያሜ ጭምር ሊቀይሩት ሲጥሩ ተመለከትን። ለምሳሌ “ጅጅጋ” ማለት በኦሮምኛ “ዝቅ ዝቅ” እንደማለት ነው (የአካባቢው ከፍታ ዝቅ ያለ በመሆኑ የተሰጠ ስያሜ ነው)። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን “ጅጅጋ” ማለታችውን ትተው “ጅግጅጋ” በሚል መጤ ስያሜ ለመቀየር እና አዲስ ስም ለመስጠት የሚሯሯጡ ሰዎችን ታዝበናል።

የቅርቡን ታሪክ ትተን… እንደገና ወደኋላ እንመለስ። ይህ ሁሉ ግፍ በኦሮሞዎቹ ላይ ሲሰራባቸው፤ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ዝም አላሉም። ይልቁንም በራስ መኮንን አስተዳደር ወቅት… የሱማሌ እና የኦሮሞ ህዝቦችን በሚያጣሉት የድንበር ቦታዎች ላይ በሙሉ፤ ነፍጥ የያዙ ወታደሮች ተመደቡ። በኋላ ክልሉን ለቀው ሊሄዱ ሲሉ፤ ህዝቡ እንቢ ብሎ መሬት እየሰጠ፤ ልጆቻቸውን እየዳሩላቸው ኑሯቸውንም እዚያው አደረጉ። እነዚህ ነፍጥ አንጋቾች ወይም ነፍጠኞች…. አብዛኛዎቹ ከሰሜን ሸዋ የተውጣጡ ጎበዝ አልሞ ተኳሾች ነበሩ። ሱማሌው እንደለመደው የኦሮሞውን ከብት እና እርሻ ለመዝረፍ ድንበር እያለፈ ሲመጣ፤ በጥይት እየለቀሙ ስርአት አስያዙት። የ85 አመት አዛውንት የሆኑት  አቶ ሉልሰገድ ጎበና የሚነግሩን ቁም ነገር አለ… ቀደም ሲል በ1879 ምኒልክ ድል ሲያደርጉ እነሻቃ ተክሌን ሰንደቅ አላማ አስይዘው ወደሃረር መላካቸውን ተጨዋውተን ነበር። (የሻቃ ተክሌ ልጆች ደግሞ ፊታውራሪ ዝቅ አድርጌ እና ግራዝማች መኩሪያ ብዙ ታሪክ ያላቸው ጀግኖች ናቸው።) የሻቃ ተክሌ የልጅ፣ ልጅ፣ ልጅ ናቸው - አቶ ሉልሰገድ። በወቅቱ ልጅ ነበሩ። በአያታቸው ጊዜ የነበረውን ሁኔታ ያስታውሳሉ። የነገሩኝን ዝርዝር ታሪክ ሰብሰብ አድርጌ ላስነብባችሁ። እንዲህ አሉኝ… “በኋላ ላይ አያቴ ግራዝማች መኩርያ ተክሌ ወደ ጅቡቲ ድንበር አስተዳዳሪ ሆነው ተመደቡ። ከአፋሮች ጋር ጥሩ ወዳጅ ሆነው ነበር። ሱማሌዎቹ ተደራጅተው ወደ ኢትዮጵያ ሲዘልቁ፤ አፋሮቹ መጥተው ይነግሯቸዋል። ከዚያም ግራዝማች ሱማሌዎቹን እየተከታተሉ ይቀጧቸው ነበር…” እኚህ እና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ኑሯቸውን እዚሁ አድርገው፤ እስከ2ኛ የጣልያን ወረራ ድረስ ዘልቀዋል። ከጣልያን ጦርነት በኋላ ኤጄርሳ ጎሩን አስተዳድረዋል። በዚህ አይነት ወልደው እና ከብደው የኖሩትን ሰዎች ነው ታድያ… ዛሬ በብሄር ብሄረሰቦች ሽፋን የሚሰድቧቸው።

“ክልላችንን የጦር ካምፕ አደረጉት” አልነበር የተባለው? እንግዲያው ሌላም ታሪክ እንጨምር። በ1953 ዓ.ም. በዋርዴር እና በገላዲን አካባቢ የሱማሌ ጦር በወገናችን ላይ ጉዳት ሲያደርስ፤ በመልሶ ማጥቃት ዘመቻ የ3ኛ ክፍለ ጦር አንድ ሻምበል ተንቀሳቅሶ ድል ተጎናጽፎ ነበር። በዚያው አመት ጄነራል አማን አምዶም ቡርበርዴን እና ቡክሲን አልፎ ሲመጣ… በጥቂት እግረኛ፣ መድፈኛ እና ፓራ ኮማንዶ ወታደሮች ወሰን አልፈው የመጡ የሱማሌ ወራሪዎችን ደምስሠዋል። ኢትዮጵያውያን በዚህ የኦጋዴን በርሃ የተሰዉት አካባቢውን የጦር ካምፕ ለማድረግ ሳይሆን ህዝቡን ከወራሪ ለመጠበቅ መሆኑን ለማወቅ ዲግሪ መጫን አይኖርብንም። በዚህ የምስራቁን ድንበር በማስከበር ላይ ከተሰማሩት ጀግኖች መካከል፤ በኦጋዴን በርሃ የእድሜውን ማምሻ የጨረሰውን ጀግናው አብዲሳ አጋን መጥቀስ ያስፈልጋል። የሱማሌ ባህል እና ብሄራዊ ማንነቱ እንደተከበረ ሆኖ፤ የኢትዮጵያውያን የህይወት መስዋዕትነት ሊዘነጋ አይገባም።

ዘንድሮ በሱማሌ ክልል የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ሲከበር፤ ሌላውን ብሄር በመሳደብ ከሚከበር ይልቅ… ሌላው ብሄረሰብ ለዚህ ክልል ያደረገውን መልካም ነገር በማስታወስ፤ ታሪካቸውን በማወደስ… ሌላውን ኢትዮጵያዊ የሚያከብሩበትና የሚያመሰግኑበት ጥሩ አጋጣሚ ይሆን ነበር። ይህ ግን ሳይሆን ቀረና፤ የትላንቱ ታሪክ ተረስቶ… ጆሯችን የስድብ ውርጅብኝ ለማዳመጥ በቃ።

እሩቅ ባልሆነው በትላንት ታሪካችን… አካባቢው በሱማሌ ወራሪ ሃይል ሲያዝ የነበረውን ሁኔታ በማስታወስ ስንብት እናደርጋለን። በወቅቱ የሱማሌ ጦር ከራሽያ ያገኘው የጦር መሳሪያ ከኢትዮጵያ በአምስት እጥፍ የሚበልጥ ነበር። ይህን ሃይል በመያዝ በምስራቅ በኩል እስከ አዋሽ ያለውን የኢትዮጵያ መሬት ለመያዝ በቅተው ነበር። በገላዲን፣ በጅጅጋ፣ በደገሃቡር፣ በቀብሪደሃር፣ በጎዴ… እስከ ድሬዳዋ ድረስ የሱማሌ ጦር በምድር እና በአየር እየታገዘ ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ወርሯል። ይህ ሁሉ ወረራ ሲደረግ ታዲያ… የሱማልያ ጦር ዝም ብሎ… መንገዱ አልጋ ባልጋ ሆኖለት አይደለም የገባው። በያንዳንዱ ግንባር የኢትዮጵያ ወታደሮችን እየገደለ፤ ሰላማዊ የሆነውን የአካባቢውን ነዋሪ እየጨፈጨፈ ነበር – ድሬዳዋ ድረስ የዘለቀው።

እነዚህን ሁሉ አካባቢዎች መልሶ በማጥቃት ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ የተከፈለው መስዋዕትነት ቀላል አልነበረም። በአካባቢው የነበረው 3ኛ ክፍለ ጦር እና የኢትዮጵያ አየር ኃይል የፈጸሙት ታላቅ ጀብዱ ምንግዜም በታሪክ የሚወደስ ነው። F-5 ተዋጊ ጀቶች ከደብረዘይት እየተነሱ የሱማሌን እግረኛ በመትረየስ ሲረመርሙት፤ እግረኛው የኢትዮጵያ ጦር ደግሞ ሱማሌውን እግር በ’ግር እየተከተለ መግቢያ ያሳጣው ነበር። ከአየር ኃይል አብራሪዎች መካከል እነሜ/ጄነራል አምሃ ደስታ፣ ሜ/ጄነራል ፋንታ በላይ፣ ኮ/ል አስማረ ጌታሁን የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ደምሴ ቡልቶ እና ሌሎች… ከምንም በላይ ደግሞ በዚህ ጦርነት ላይ ህይወታቸውን እና አካላቸውን ያጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን፤ ለኢትዮጵያ ሲሉ ከየመን የመጡ መድፈኞች እና የኩባ ወታደሮች ጭምር፤ የከፈሉትን መስዋዕትነት ለአንድ አፍታም ቢሆን ልንዘነጋው አይገባም – ክብር ለነሱ ይሁን።

ኦጋዴን እና አካባቢው “ራሴን አስተዳድራለሁ” ብሎ ስራ መጀመሩ ደስ ያሰኛል እንጂ፤ ማንንም አያስቆጣም። ነገር ግን አሁን ያለው አይነት ጥላቻ፤ የአንድ መጥፎ ነገር አመላካች ነው። ሌላው ኢትዮጵያ ለዚያ አካባቢ ህዝብ የከፈለውን መስዋዕትነት ዋጋ የማንሰጠው ከሆነ፤ በርግጥም ችግር አለ ማለት ነው። አንዳንድ የሱማሌ ኢትዮጵያ ሰዎች ሌላውን ብሄር እንዲህ የሚጠሉት ከሆነ፤ “ምናለበት ታላቂቱ ሶማልያ በገዛችን ኖሮ?” የሚል አንደምታን ይፈጥራል።

በኦጋዴን ወይም በሱማሌ ኢትዮጵያ ውስጥ የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን ሲከበር፤ በአካባቢው ያሉትን የኦሮሞ ተወላጆች በማቀፍ በልዩነት ውስጥ አብረው መኖራቸው እንደጥሩ ምሳሌ ማሳየት ይቻል ነበር። በብሄር ብሄረሰቦች በአል ሰበብ… ሌላውን ህዝብ ከመሳደብ ይልቅ፤ ስለመስዋዕትነቱ ማመስግን ምንም ክፋት የለውም። ህዝብን ማመስገን ባንችል እንኳን፤ ምናል አምላካችንን ብናመሰግን? አምላክን በትንሹ ማመስገን ካልቻልን ያለንን ያሳጣናልና ተመስገን ማለትን እንወቅበት።

የማመስገን ነገር ከተነሳ አንድ የስንብት ታሪክ እናውጋ።

እኚህ ሰው… በኢትዮ-ሶማልያ ጦርነት ወቅት የኢትዮጵያ አየር ኃይል አብራሪ ነበሩ። በአየር ላይ ሆነው፤ የሱማሌ ተዋጊ ጀቶች ከፊት እና ከኋላ ሲመጡባቸው፤ በአየር ላይ እየተታኮሱ ቆይተው እሳቸው አቅጣጫቸውን ቀይረው ሲምዘገዘጉ፤ ሁለቱ የሱማሌ የጦር ጀቶች እርስ በርስ እንዲጋጩ አድርገው… ጸጥ አሰኝተዋቸዋል። እኚህ የአየር ኃይል አብራሪ በኋላ ላይ የሚያበሩት ጀት ተመትቶ እሳቸው በፓራሹት ወርደው ህይወታቸው ተረፈ። ሆኖም በሱማሌዎች መማረካቸው አልቀረም። ከሌሎች በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ጋር በሱማሊያ እስር ቤት ለአስራ አንድ ከታሰሩ በኋላ ተፈቱ። በእስር ህይወታቸው ያጋጠማቸውን ነገር ሲያጫውቱን እንዲህ አሉ።

“የታሰርኩት በአንድ ጉድጓድ ውስጥ ነው። እጅ እና እግሬ በካቴና ታስሯል። ከላይ ጣርያው ስለተሸፈነ የጸሃይ ሙቀትን እንጂ ብርሃኗን አይቼ አላውቅም። ወደውጭ የሚያወጡኝ ከጨለመ በኋላ በመሆኑ፤ ቀስ በቀስ የአይኔ ብርሃን ደከመ። እንዳልሞት ያህል ጥቂት ምግብ እና ውሃ ይሰጠኝ ነበር። በዚህ አይነት ለብዙ አመታት ስቆይ አምላኬን አማርሬው አላውቅም። አንድ ቀን ግን አምላኬን አማረርኩት። ‘ለምን እንዲህ ታሰቃየኛለህ?’ ብዬ በአምላኬ ላይ አዘንኩበት። የዚያኑ ቀን የነበርኩበትን እስር ቤት ለመጎብኘት አንድ የሱማሌ ወታደራዊ መኮንን መጣ። መኮንኑ እንደመጣ… እኔ ከጨለማው እስር ቤት እንድወጣ አዘዘ። ከዚያም እጅ እና እግሬ እንደታሰረ እሱ ፊት ቀረብኩ። የሱማሌው መኮንን እጅ እና እግሬ የታሰረበትን ሰንሰለት አይቶ ተቆጣ።”

“እንደዚህ አይነት ከፍተኛ እስረኛ እንዲህ ነው የሚታሰረው?” ብሎ አፈጠጠባቸው። አሳሪ ወታደሮች ግራ በመጋባት ዝም አሉ። እኔም አምላኬ ለቅሶዬን ሰማ። በእጆቼ እና በእግሬ ላይ የታሰረው ሰንሰለት ሊፈታልኝ ነው።” ብዬ ደስ አለኝ።

“የጦር መኮንኑ ቁጣውን ሳይቀንስ ሰንሰለቱን ፍቱ።” አላቸው። ከብዙ አመታት በኋላ ሰንሰለቱ ተፈታልኝ። የሱማሌው መኮንን አሁንም እየተቆጣ… “እንዲህ አይነት ከፍተኛ እስረኛ የሚታሰረው እንደዚህ ነው።” ብሎ… ቀኝ እጄን፣ ከቀኝ እግሬ ጋር፤ ግራ እጄን ደግሞ ከግራ እግሬ ጋር እንዲታሰር አዘዘ፤ እንደትእዛዙም ሆነ። በዚህ አይነቱ አዲስ አስተሳሰር… ቢያንስ ቆሜ እሄድ የነበርኩት ሰው አጎንብሼ ቀረሁ። በፊት እጅና እግር ለየብቻ በታሰሩበት ወቅት እንደልቤ እተኛ ነበር። አሁን ግን ለመተኛትም ተቸገርኩ። በፊት የነበረው አስተሳሰር ናፈቀኝ። ያንን ሁሉ አመት ስታሰር አንድም ቀን አምላኬን አማርሬው የማላውቀው ሰው፤ አሁን እርሜን አንድ ቀን ባማርር የባሰ ነገር መጣብኝ።” በማለት… ሰው ባለው ነገር ማመስገን እንዳለበት አስተምረውናል።

እኚህ በሱማሌ ጦርነት ወቅት ለአገራቸው ትልቅ ውለታ የሰሩ የኢትዮጵያ አየር ኃይል አብራሪ ታደለ ይባላሉ። (የአየር ኃይል ማዕረጋቸውን አላውቀውም) ከ11 አመታት እስር በኋላ ከሱማሊያ እስር ቤት ተፈትተው አገራቸው ከገቡት ኢትዮጵያዊ አንዱ ናቸው። ለ11 አመታት ብርሃን ባለማየታቸው የአይናቸውን ብርሃን ሊያጡ ተቃርበው፤ በህክምና ነገሮች ወደነበሩበት ተመልሰውላቸዋል።

እኚህ አብራሪ ከእስር ቤት ከወጡ በኋላ አንድ ልጅ ወለዱ፤ ስሙንም “በፀጋው” አሉት። ሃያ ምናምን አመታት ተቆጠረ። በፀጋው ታደለ ኢትዮጵያ አድጎ ለትምህርት ወደ አትላንታ መጥቶ፤ በታዋቂው ሞርሃውስ ዩኒቨርስቲ ሲመረቅ፤ ከትምህርት ቤቱ በሙሉ ከፍተኛ ነጥብ በማስመዝገቡ፤ ድንቅ ተማሪ ተብሎ… ሁሉንም ተማሪ በመወከል ንግግር ያደረገው እሱ ነበር። በእለቱ እንግዳ ሆነው የተገኙት የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ንግግራቸውን ከመጀመራቸው በፊት፤ መምህራኑን አመሰገኑ። ለዚህ ኢትዮጵያዊ ወጣት አድናቆታቸውን ለገሱት።

ስለሱማሌ እስር ቤት አስከፊነት እና ስለጭካኔያቸው አቶ ታደለ ከማንም የበለጠ አደባባይ ወጥተው መናገር ይችላሉ። እሳቸው ግን ያለፈውን እንዳለፈ ትተው፤ አዲስ ህይወት በመጀመራቸው ራሳቸው ተከብረው፤ ሌላውን ኢትዮጵያዊ የሚያስከብር ልጅ ለትውልድ አስረከቡ።

በሌላ በኩል ደግሞ ኦጋዴን ወይም የኢትዮጵያ ሱማሌ ከሽግግር መንግስቱ ግዜ ጀምሮ እስካሁን አስር የክልል ፕሬዘዳንቶች ተፈራርቀውባታል። ከነዚህ ፕሬዘዳንቶች መካከል አንዱ በኢትዮጵያ እና ሶማልያ ጦርነት ወቅት የሶማልያ አየር ኃይል ባልደረባ የነበረና ኢትዮጵያን በአየር ሲደበድብ የነበረ ሰው ነው። አንበሳው የኢትዮጵያ ጦር ተጠናክሮ በመጣበት ወቅት… በፋፈም ሸለቆ በኩል አድርገው ወደ ሃርጌሳ ይሮጡ የነበሩ ሰዎች ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው፤ በብሄር ብሄረሰቦች በአል ሽፋን ሌላውን እየሰደቡት ነው። እንዲህ አይነቱ አሳፋሪ ተግባር የማይደገም ስለመሆኑ ምንም ዋስትና የለንም። እነሱ ሌላውን ደገኛ፣ የመሃል እና የዳር አገር ሰዎች እያሉ የጥላቻ መርዝ ሲነሰንሱ፤ የኛ ጉልበታችን እውነትን መናገር ነው፤ ታሪክን ማስተማር ነው።

በመሆኑም በኦጋዴን ወይም በሱማሌኢትዮጵያ ክልል ውስጥ… ለአንደኛው ብሄር ወይም ለሌላው ሃይማኖት ሳይሉ… ለኢትዮጵያ ድንበር መከበር እና ለህዝቡ አንድነት ብለው የህይወት መስዋዕት ለከፈሉት ጀግኖች ሁሉ ኢትዮጵያዊ አክብሮት አለን። ስለነሱ ክብር… በጨዋ ኢትዮጵያዊነት ራሳችንን ዝቅ እናደርጋለን… እንደየእምነታችንም በህሊናችን እናስታውሳቸዋለን። እናም ክብር እና ማዕረግ ለነሱ ይሁን።

ዛሬም አንደ ጥንቱ ባርነትና የሰው ንግድ

$
0
0

Ethiopians in Saudi
(ተፈራ ድንበሩ)

በሰዎች መካከል በጥቅም ላይ በሚደረግ ግጭት ጦርነት ከተደረገበት ጊዜ አንሥቶ ተሸናፊዎች በባርነት እንደተገዙ የታወቀ ሲሆን ሰውን እንደ ዕቃ የመሸጥ-መለወጥ ሥራ የተጀመረው በአረብ ነጋዴዎች ነበር። “Hugh Thomas” የሚባል መጽሐፍ ፀሐፊ “The Slave Trade and Robin Blackburn’s The Making of the New slavery“ በሚል ርዕስ በጻፈው መጽሐፍ ላይ እንዳስቀመጠው ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ እሰከ 869 (ኢኤአ) አረቦች ሸቀጥ ይዘው ወደ አፍሪካ ሲወስዱ የአፍሪካ መሪዎች በገዛ ሕዝባቸው ሸቀጣቸውን ይለውጧቸው ነበር ብሏል። ከዚህ በታች ከመጽሐፉ በቀጥታ የተጠቀሰውን ይመለከቷል፦
“…it [slave trade] was pioneered by Arabs, its economic mechanism was invented by the Italian and Portuguese, it mostly run by Western Europeans, and it was conducted with the full cooperation of many African kings.” 1
ጎርዶን ሙሬይ ስለባሪያ ንግድ ከሬጂናልድ ኮፕላንድ ሥራ ጋር በማገናዘብ ያጠናቀረውን ጥናት እንደሚከተለው ገልጾታል፦

Read full Story in PDF/በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ስለምኒሊክና ስለኢትዮጵያ

$
0
0

ከዶ/ር ካሳሁን በጋሻው

Ato Bulcha

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

Emperor Menelik II s

እምዬ ምኒልክ፡ የጥቁር ሕዝብ ኩራት

የአጼ ምኒሊክን መቶኛ የሙት አመት መከበር ምክንያት በማድረግ በ DW ሬድዮ በተደረገው ጥያቄና መልስ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፣ ዶ/ር ሓይሌ ላሬቦና ዶ/ር ሹመት ሲሳይ (የታሪክ ተመራማሪዎች) ቃለ መጠይቅ ተደርጎ በሚሰጠው መልስ ላይ ስለ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በተናገሩት ላይ አስተያየቴን አቀርባለሁ። አንባቢያንን ቃለመጠይቁን ቢያዳምጡ ጥሩ ነው ባይ ነኝ፤ ሁለቱ የታሪክ ምሁራን ትምህርታዊ ትንተና ይሰጣሉና፡፡

ውሸት ሲደጋገም እውነት ሊመስል ይችላል፤ በተለይም የአገራችንን የኢትዮጵያን ታሪክ ለማያውቁ እውነታው ምን እንደሚመስል መረጃ ለማቅረብ እሞክራለሁ።

አቶ ቡልቻ ኦሮሞ ከባሌ እየተስፋፋ ሲመጣ ልብነ ድንግል እንዳይስፋፋ አቆሙት ይላሉ፡፡ ለምን ይህን ምሳሌ እንዳቀረቡም ግልጽ አይደለም ለሳቸው ትንታኔ የማይመች በመሆኑ፤ ለዛውም በአጼ ልብነ ድንግልና በኦሮሞች መሀከል ስለነበረው ግኑኝነት በከፊል ዶ/ር ሃይሌ ላሬቦ ሊያስረድዋቸው ሞክረዋል፤ ስለመስፋፋቱና እንዲያውም አማራውን እንደገፋው ለአቶ ቡልቻ መረጃ ላቅርብ፡፡

ጥንት ሌላ ስም የነበራቸው በኦሮሞ ከተያዙ ማግስት ስማቸው የተቀየረ፤ ደዋሮ-ጨርጨር፣ ጋፋት-ሆሮ፣ ገራሪያ-ሰላሌ፣ ዳሞት-ወለጋ፣ አበቤ-በቾ፣ ሽምብራ ኩሬ-ሞጆ … (የሃያኛው ክፍለዘመን ኢትዮጵያ ገጽ 50 በጥላሁን ገ/ስላሴ) በቅኝ ተገዛ የሚሉት ኦሮሞ ተጨማሪ ቦታ እንደያዘ እንጂ እንደተወሰደበት አይደለም ታሪኩ የሚመሰክረው፡፡

BULCHADEMEKSAአቶ ባልቻ የኦሮሞን ታሪክ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ሊያዛምዱት ይሞክራሉ፤ ኦሮሞም እንደ ደቡብ አፍሪካ ጥቁሮች ኢትዮጵያ ውስጥ ሲረገጥ የኖረ ሕዝብ አድርገው ያቀርቡታል። መፍትሄውንም ሲጠይቁ reconciliation እርቅ ኦሮሞ ይቅርታ ተጠያቂ የተቀረው ይቅርታ ጠያቂ በተለይም የፈረደበት አማራ ለዚህ ወንጀል ትልቁን ድርሻ ይወስዳል፡፡ ባለፉት አስተዳደሮች ስህተቶች አልተሰሩም ብሎ የሚከራከር የለም፤ ጥያቄው እንዴት አብረን ወደፊት መሄድ እንችላለን ነው?

እንደቅኝ ተገዛን የሚሉት ቡልቻ ደመቅሳ አገሪቱን በእርሻ ሚኒስቴርነትና በምክትል ገንዘብ ሚኒስቴርነት አስተዳድረዋል – ቸር ቅኝ ገዢ ነበር የነበራቸው፤ እኛ ቅኝ እየተገዛን ስለሆንን በሚኒስቴርነት ቅኝ ገዢዬን አላገለግልም ብለው አላንገራገሩም፡፡

ኦሮሞ በሲቪሉም ሆነ በወታደራዊው ክንፉ ታላቅ የሚባሉትን ስልጣኖች ይዞ የኖረና ያለ የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡ አገሪቱ ውስጥ ለነበሩትና ላሉትም ደግ ነገሮችም ሆነ ክፉ ነገሮች ተጠያቂነቱ እኩል ነው፡፡ አቶ ቡልቻ ቅኝ ገዢ የሚሉትን የአማራውን ክፍለሀገር ደጃዝማች ክፍሌ ዳዲ ያስተዳድሩት ነበር፡፡ (ምሳሌ የሚያቀርቡበት ደቡብ አፍሪካ የማስተዳደር ቅንጦት ይቅርና ነጭ በሚዝናናበት ቦታ ጥቁር መግባት አይፈቀድለትም ነበር)፡፡

ስለኦሮሞ ባለስልጣናት እስቲ እንመልከት

ምኒሊክ በሸዋ ሲነግሱ የረዷቸው አብሮ አደግ ባልንጀራቸው ጎበና ዳጬ ናቸው፡፡ የወለጋውም አስተዳዳሪ ኩምሳ ምኒሊክን በደጃዝማችነት አግልግለዋል፤ እነ ባልቻ አባ ነፍሶም የማይረሱ ታላቅ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡

የአጼ ሃይለስላሴ አባት ራስ መኮንን ወልደሚካኤል (ጉዲሳ) አባታቸው ኦሮሞ ነበሩ፤ እናታቸውም ወ/ሮ እመቤት እናታቸው ኦሮሞ ነበሩ፡፡

ራስ ዳርጌ የሸዋው ንጉስ ሳህለስላሴ ከወለዷቸው አራት ወንዶች መሃከል አንዱ ሲሆኑ ጥናታቸው አርሲ ውስጥ የአንድ አካባቢ ኦሮሞ ባላባት ልጅ ነበሩ (አባ ቦራ በታቦር ዋሚ፤ ገጽ 9)

ራስ አበበ አረጋይ መከላከያ ሚኒስትር

አቶ ይልማ ዴሬሳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ የገንዘብ ሚኒስትር

ደጃዝማች ክፍሌ ዳዲ የጎንደር አስተዳደር

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የእርሻ ሚኒስትርን ምክትል የገንዘብ ሚኒስትር

ሜጀር ጀኔራል ሙሉጌታ ቡሊ የክብር ዘበኛ አዛዥና የባህል ሚኒስትር

ደጀዝማች ገረሱ ዱኪ የኢሊባቡርና የጎሙገፋ አስተዳዳሪ

ሜጀር ጀኔራል ደምሴ ቡልቲ የሁለተኛው ክፍለ ጦር አዛዥ

ሌተና ጀኔራል ጃጌማ ኬሎ የአራተኛው ክፍለጦር አዛዥና የባሌ አስተዳደር

ፊታውራሪ ለማ ወልደጻድቅ የሲዳሞ ምክትል አስተዳደር

ሜ/ጀኔራል አበራ ወልደማርያም የአየር ኃይል ምክትል አዛዥ

ደጃዝማች በቀለ ወያ የጨቦና ጉራጌ አስተዳደር ከዚያም የጨርጨር አስተዳደር

ደጃዝማች ካሳ ወልደማርያም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትና የእርሻ ሚኒስትር

አንባቢያን መረዳት ያለብን ሁላችንም በመጀመሪያ ደረጃ ኢትዮጵያውያን መሆናችን ነው፡፡ ሕዝባችን በጋብቻ፣ በእምነት፣ በባሕል፣… የተሳሰረ በመሆኑ መሰረት የሌለው ታሪክ እያነበነቡ ሊበታትኑን የሚያስቡትን ታሪካዊ መረጃ እያቀረብን ወግዱ ልንላቸው ይገባል፡፡ ድር ቢያብር አንበሳ ያስር ነው፤ ምኒሊክም ያስተማሩን መቻቻልን አንድነትንና ፍቅርን ነው፡፡

 

 

በአዲስ አበባ ከ600 በላይ አባዎራዎች ቤታቸውን በ3 ቀናት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ ቀጭን ትዕዛዝ ተላለፈ

$
0
0
የአዲስ አበባ ከተማ ገጽታ (ፎቶ ከፋይል)

የአዲስ አበባ ከተማ ገጽታ (ፎቶ ከፋይል)

የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ደሃ ገበሬዎችን እያፈናቀሉ ቦታቸውን እየወሰዱ ነው

በአዲስ አበባ ከ600 በላይ አባዎራዎች ቤታቸውን በ3 ቀናት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ መታዘዛቸውን ኢሳት ቴሌቭዥን ዘገበ። እንደ ቲቪው ዘገባ ትእዛዙን የሰጠው የቦሌ ክፍለከተማ ሲሆን፣ ነዋሪዎቹ እስከ ማክሰኞ ቤታቸውን ለቀው ካልወጡ ፣ አፍራሽ ግብረሀይል በጉልበት እንደሚያፈርስባቸው አስታውቋል።
“በሶስት ቀናት ውስጥ የት እንሄዳለን?’ ሲሉ የሚጠይቁት ነዋሪዎች ፣በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ የሚታየው የቤት ኪራይ መጨመር አስግቶናል ብለዋል። ሜዳ ላይ እንዃ እንዳንወድቅ ሜዳውም እየታረሰ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ምሬታቸውን ገልጸዋል ሲል ዘግቧል።

በተያያዘ ዜናም ኢሳት በዜና ዘገባው በኦሮሚያ ልዩ ዞን የሚገኙ ባለስልጣናት በስልጣናቸው ደሀ ገበሬዎችን እያፈናቀሉ ቦታዎቻቸውን እየወሰዱባቸው ነው ሲል ዘገበ። ነዋሪዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው አርሶአደሮች በጉልበት መሬታቸውን እየተቀሙ ለበለጠ ድህነት እየተጋለጡ መሆኑን አስታውቋል። ከተቀሙት አርሶ አደሮች መካከል በሰበታ ነዋሪ ከሆኑት አንዱ ሲናገሩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሆኑት የአቶ ደምሴ ቡላ ባለቤት መሬታቸውን በጉልበት እንደነጠቁዋቸውና ክስ ሲመሰርቱም እንዳሳሰሩዋቸው ተናግረዋል ያለው ኢሳት በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ቤት ሰርተው ይኖሩ ነበሩ ሰዎች ቤቶቻቸው ከፈረሱባቸው በሁዋላ ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸው ይታወቃል ሲል የዜና ዘገባውን አጠቃሏል።

ኃያሉ አፄ ሚኒሊክ ለሴቶች እኩልነት ተግባራዊነት ዓለምን የቀደሙ ንጉሥ

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 

ስርጉተሥላሴ

ስርጉተሥላሴ

ያን ዘመን ሳስበው ዛሬን መስለችን ያስለቅሰኛል። ያን ፈርጣማ ዘመን ሳስታውሰው ዛሬ ውስጣችነን መሳሳቱ ያቃጥለኛል። ያን ገድላማ ብቁ፣ ሥልጡን፣ ልዑቅ የአመራር ጥብብ ሳናግረው ግን መጽናናትን፣ ሙላትን ያጎናጽፍልኛል። ክብራቻን፤ ማንነታችን፤ ተፈሪነታችን፤ መሪነታችን፤ ብልህነታችን፤ እርግጠኛ ያደረጋል፤ የቀደምቶቹ ብቃት የሰማይ ገደል ለዛሬ ፍንጣቂ ማስተዋል ቢልክልን አምላኬ ምን አለበትም እላለሁ። የባዕዳን ግራሞት ጭብጥ፤ የእርስ በርስ ችግራችውን ዋጥ አድርገው በጋራ ቆመው ትንግርትን ሰማዕታት ማዘከራቸው የህሊናችን ዳኛ ሆኖ እኛን ሊገራን ባለመቻሉ ግን የልቤ ክናድ ይላል። ነገ ሌላ ቀን ነውና ነገን እንዲመርቅልን ህይወቱ ያላቸው አበው ሱባዬ ቢይዙበት ምኞቴና ናፍቆቴ ነው … አንደ ዕምነታቸው።

ዓለም ስለ ሴቶች ብቃት ብጣቂ እውቀት ባልነበረበት ጊዜ የኛው አፄ ኃያሉ ንጉሥ ሚኒሊክ ደማቸው – መንፈሳቸው – ሙሉዕ ፈቃድ ሰጥቶ ተግባር ላይ የዋለ በኽረ ጉዳይ ነበር የሴቶች እኩልነት። ኢትዮጵያ ሚስጢር ናት። ኢትዮጵያ ገድል ናት። ኢትዮጵያ ዓለም – ዓቀፍ ህግ ናት።  ኢትዮጵያ የቀደመች ሥልጡን መምህርት ናት። በዘመኑ የጣሊያን ተጋነት፤  የኢትዮጵያ ጥበበኛው መሪ የአፄ ሚኒሊክ አመራር ደግሞ ዕርቅና ሰላም ፈላጊነት ዓለምን ያሰደመመ መረቅ ትውፊት ነበር። ምርኮኛን ተንከባክቦና መርቶ ወደ ሀገሩ መሸኘትም አብነታዊ የአፄ ሚኒልክ ልዑቅ በኽረ ተግባር ነበር። ዛሬ ያሉት ሰበነካዊ ዓለምዓቀፍ ድርጅቶች መሰረተ ጥንስስ ብቻ ሳይሆን ዓላማው ቀድሞ ኢትዮጵያ መሬት ላይ በድርጊታ ላይ የዋለው በድንቅነሽ አንባ ነበር – በብጡሎቹ።

ሀ. የእኩል ተሳትፎ ፈቃድ … ለሴቶች።

የጣሊያን ከመቀሌ አልፎ መስፋፋትን መመረጡ ያልተማቻቸው ንጉሥ ሚኒሊክ አልጋቸውን ለአጎታቸው ለራስ ዳርጌ አደራ ሰጥተው፤ ረዳትም ደጃዝማች ኃይለማርያምንና የወህኒ አዛዡን ወልደ ጻድቅን ጨምረው ሊነሱ ሲያስቡ ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ አልለይም ሲሉ ሙሉ እምነትና ፈቃድ ሰጡና እቴጌ ጣይቱ አብረው ዘመቱ። „ … ከጃንሆይ ጋር እቴጌ ጣይቱ አልለይም ብለው ጦራቸውን ይዘው ተጓዙ“ (ገጽ 100*)  „ „ወንድ ያለ ዕለት – በዕለት፤ ሴት ባለ በዓመት“ የሚለውን የሴቶችን መብት ደፍጣጭና ተጫኝ ኮስሳ ብሂል ቅስሙን እንኩት አድርገው የአካላቸውን ክፋይ የማይገሰስ ክብር ሰጥተው፤ ፈቃዳቸውንም ተንከባባክበውና አልምተው የታሪክ ዐይነታ ታዳሚ አደረጉት። ዘመናቸውንም ሙሉና ጌጣማ አደረጉት። የቀደመና የሰለጠነ መክሊት ባላጸጋው የንጉሦች ንጉሥ አፄ ሚኒሊክ የተግባር ምሰሶና ዋልታ ነበሩ ለሁለመናችን።

minilikለ. የጦር ጄኒራልነት፣ የአዋጊነት፣ የመሪነት፣ የአዝማችነት ጥንድ የእኩልነት ዕውቅና እና ዕሴቱ – ለሴቶች።

 ዓለምዓቀፉ የቅኝ ግዛትን ቅስም የሰበሩት ክቡር አፄ ሚኒሊክ „ሴትና አህያ በዱላ“ የሚለውንም ሥነ – ቃል ጨፍልቀው ከጠላት ጋር ለጦርነት ዐዲማህለያ ላይ በ10 ግንባር ካሰለፉት 30 ሺህ ጦር ውስጥ የልዕልታችን፤ የንግሥታችን  የእመቤት ጣይቱ ግንባር ከ3ሺህ ጦር ጋር አንዱ ግንባር ነበር። ይህ በዬትኛው የዓለም ታሪክና መዘክር የሚገኝ ጣዝማዊ ገቢር ነው። ማንም ሀገር እንዲህ በዚያ ዘመን የተግባር ዲታ የሆነ የሴቶች የእኩልነት ታሪክ የለውም። አባታችን፤ መሪያችን፤ መኩሪያችንና ንጉሣችን አፄ ሚኒሊክ ግን እኩልነትን የተቀበለ፤ እኩልነት በድርጊት ያዋለ፤ እኩልነትን ያከበረ – ያስከበረ – ያደመጠ፤ እኩልነትን በጥንግ ድርብ ካባ ያንቆጠቆጠ የመኖራችን ልዩ የታሪክ ጉልላት እንዲያብብ ፈቀዱ።

ስለዚህ አፄ ሚኒሊክ ለእኛ ለኢትዮጵያ ሴቶች ብቻም ሳይሆን ዓለምን በድርጊት ያስተማሩ ድንቅ የኢትዮጵያዊነት አንዱ ታላቅ ሚስጢር ናቸው። ንጉሥ ሚኒሊክ ለሴቶች እንደ አደራጅነተቻው የክብር አባላችን ሰንደቃችን ናቸው።

ኃያሉ የአፍሪካ ቀንዲል ንጉሥ ሚኒሊክ የሴቶችን የብቃት ሚስጢር መንፈስ ቅዱስ ስላቀበላቸው ውጤቱ አዲስ የጥቁር  የማይደፈር የድል ፕላኔት ሆነ። በውጊያውም ሳይደክሙ እቴጌ ጣይቱ ከአካላቸው ጎን ሆኑ በፋመው ውጊያ ላይ “ …  በዚህ ጊዜ ዐፄ ሚኒሊክ የጦር ወታደራቸውን በሚያበራታታ ቃል ሲያደፋፍሩ፤ እንዲሁም እቴጌ ጣይቱ እንደ ወንድ በጦርነቱ መካካል እዬተላላፉ የቆሰለውን ሲያነሱ፤ ለተጠማው መጠጥ፤ ለተራበው ምግብ ሲሰጡ ዋሉ“* ይሉናል ሊቁ ጸሐፊ (ገጽ 110 )የተደራጀ የቀይ መስቀል ተግባር በእናትነት ተፈጥሯዊ ክህሎት በቅሎ፤ በአጋርነት ጸድቆ፤ እንሆ … ሚስጢር ይቀዳል ከድንቅነሽ አንባ …. ከእግዚአብሄር በታች እኩልነታችን ያፀደቁ ብቸኛ መሪ፤ የእኩልነታችን መሸሸጊያ የልብ አድርስ እረኛ ፤ አስተዋሽ ጌታ ንጉሥ ሙሴ አፄ ሚኒሊክ።

ሐ. የእቴጌ ጣይቱ ብርሃነ ዘ ኢትዮጵያ በፖለቲካ እኩል የመወሰን አቀም ይለፍ በሀሴት ያረገበት ዕውነት፤

  “ሴት ቢያውቅ በወንድ ያልቅ“ ተረት ሆኖ ቀራንዮ የዋለበት ሌላው ትርጉም እቴጌ በባለቤታቸው የነበራቸው የላቀ ተደማጭነትና ተቀባይነት ነበር። ሴትነት ሰማይ ያረገበት ልበለው ከቶ? የአማካሪነት ልዩ ፈቃድ በገፍ ማግኘትና የመደመጥ እርግጠኝነት በልበ ሙሉነት መለገስ … አፄ ሚኒሊክ ለእቴጌ ጣይቱ ወደው ሰጡ። በጠባያቸው፣ በብልህነታቸው፣ በጣም ይወዷቸውና ያከብሯቸው ስለነበረ አብዛኛውን ጊዜ ውሳኔው የሚፀናው በእቴጌ ጣይቴ እንደ ነበረ ሊቁ ተክለጻድቅ መኩሪያ እንዲህ ይገልጡታል“ … አቴጌ የጠሉት ይነቀፋል ከሹመትም ይሻራል፤ የወደዱትም በንጉሰ ነገሠቱ ዘንድ ክብርና ሹመትም ያገኛል። ስለዚህ መሳፍንቱንና መኳንነቱ ንጉሡ ነገሥቱን እንደሚፈሩና ደጅ እንደሚጠኑ ሁሉ እንዲሁም እቴጌዪቱንም ደጅ ይጠኑ ነበር።  ዋው! ቅቤ የሚያጠጣ አንጀት የሚያረሰርስ ተመክሮ ነው። እንዴት ድንቅ ፈለፈል የሆነ ውብ ጥልፋማ ዘመን ነበር።

„ሴትና አይህያ … „ ቀርቶ … ውሳኔ የማመንጨት፤ የማሻሻል፤ የመሰረዝ የብቃት ልኬታን ይለፍ የሰጠው፤ እንዲሁም  የእቴጌ በራስ የመተማማን ስኬታማ ጉዞ  … ሲፈተሽ ደግሞ  „ይልቁንም የውጫሌ ውል የ17ኛው አንቀጽ ንግግር እንዲለወጥ በዐፄ ሚኒሊክና በኮንቱ አንቶኔሊ መካካል ክርክር ሲደረግ እቴጌይቱ በክርክሩ እዬገቡ ይነጋገሩበት ነበር። በኋለም በ 17ኘው አንቀጽ ንግግር ፈንታ የኢትዮጵያ ንጉሠ – ነገሥት ከመሬቱ አንድ ክፍል ወይንም በ17ኛው አንቀጽ የተባለውን ጥገኝነት ለሌላ ለውጭ አገር መንግሥት እንዳይሰጥ  ግዴታ ይግባና ይለወጥ ብሎ ሲያቀርብ …  ንጉሠ ነገሥቱ ይህንን ሃሳብ ከራስ መኮነን ጋር ሲመካካሩ እቴጌይቱ የፈቀድነውን ብናደርግ የኛ የግል ሥልጣናችን ነው እንጂ እሱን በፍጹም የሚያገባው ነገር የለም ብለው ውሉ እንዲቀር አደረጉ“ (ገጽ 131 እና 132)*

Emperor Menelik II sይህን ያህል ክብራችን ንጉሥ ሚኒሊክ ፍጹም የሆነ ሙሉ እምነት በሴቶች ብቃትና የመወሰን አቅም ነበራቸው። የሴቶችን ማንም ሊጋረው የማይችለውን የእናትነት ሰማያዊ ጸጋ ሥራ ላይ የዋሉ ብቸኛ ንጉሥ። ስለሆነም ሀገራቸውን፤ ሰንደቃቸውን ዳር ደንባራቸውን አስከበረው ተከበሩ። ምክር ስለ አዳመጡ ፍላጎታቸውን እውን አድርገው በሥልጣኔ ጎዳና እናት ኢትዮጵያን መሩ። ነፃነታችን በድል ስላቀለሙት አንገታችን ደፍተን ከመኖር ታደጉን። ተፈሪ፤ በራስ ቋንቋ የምትናገር፤ በቅኝ ያልተገዛች ብቸኛ አፍሪካዊት ሀገር፤ በራሷ ፊደል የምትጽፍ ሀገር፤ የጥቁር መመኪያና መጠጊያ፤ የእኔ የምትለው ህግ – ባህል – ወግ – እምነትና ልማድ ያላት ውብ ሀገር በደማቸው ሸለሙን። ቅይጥና የትውስት ነገር አልነበረንም። ሁለመናችን ጠረኑ እኛን ይመስል ነበር። የዛሬን አያድርገው አረሙ ወያኔ ለባዕድ እስከ ሸጠው እስከለወጠው ዱድማ ዘመን ድረስ ….። ክብራችን እናመሰግነዎታለን። ጌታችን እንወደወታለን ጸሐያችን፤  እመቤታችን ብርሃነ ዘ ኢትዮጵያ …. እቴጌ ጣይቱም የድርጊት ጀግንነተወት የተስፋችን ማህደር ነውና እናፈቅረወታለን። አላሰፈሩንም። ይልቁንም ድፈርትን አዋጡን እንጂ ….

ይቋጭ መሰል … ደግመን ያለገኘው እድል ነው ኃያሉ ሚኒሊክ በዛ ዘመን ሰጥተውን የነበረው። የእኩልነት ዕውቅና፤ የመኖር ነፃነት ኪናዊ ቃና። አፄ ሚኒሊክ ለሴቶች ተቀድቶ የማያልቅ ባለውለታ፣ ክንድና ደጅን ነበሩ።ይህ ዝቀሽ ታሪክ የሀገርን ዳር ደንበር በማስከበር ብቻ የተወሰነ አልነበረም። ለሰው ልጆች መብት ማስከበሪያ የዲሞክራሲ ሂደት ልዕል ጉልትም ነው ትምሀርት ቤት።

በዘመኑ በነበሩ ሌሎች መንግሥታዊ አስተዳደሮችና መዋቅሮች አመሰራረት ሆነ አመራር፤ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሥልጣኔ ጉዞ እርምጃ በተሰጣቸው የእኩልነት መብት እቴጌ ጣይቱ መጠነ ሰፊ ተግባራትን በመከወን የሴቶች ኮከብ፤ እመ ብዙኃን መሆን ችለዋል። ስለሆነም እቴጌ የናሙና የተግባር ተቋም ነበሩ። ያገኙትም ዕድል ባክኖ አልቀረም።  በአግባቡ በብልህነት ተጠቅመው ጸጋቸውን ዓለም እራሱ እንዲመሰክርበት አድርገዋል። የሰከነው ተሳትፏቸው በተግባር ከብሮ ሀገርን ያህል ዕንቁ ነገር አተረፈ። ትውልድን ገነባ። በነገራችን ላይ የቀደመው የእናት ሀገራችን ምስላዊ ካርታ እኮ እንደ ሌሎች ሀገሮች ቅኝ ለማደረግ ባሰበት ተሰመሮ የተሰጠን አልነበረም። በፍጹም! በደምና በአጥንት የጸደቀ አልማዝ እንጂ …. ። ይህ አዲሱ ዜማ „ጣይቱ የኛቱ“ ትንቢት ዕውን ከሆነ ኢትዮጵያዊነት እንደ ገና ያበራል። ተስፋ አያልቅ … ም። በመጨረሻ — አብሮነት ደስ ይላል – ያሳምራል … በመንፈስ ሃዲድ ለነበረን ቆይታ ትህትና ከአክበሮታዊ ምስጋና ጋር ሸለምኳችሁ።

ማሳሰቢያ  በትምህርተ ጥቅስ ባሉት ሥንኞች ውስጥ በጉልህ የተጻፉትና የተሰመረባቸው ኃይለ ቃላት፤ የበለጠ ለማሰረገጥ ብዬ እኔ እንጂ መጸሐፉ ላይ የለውም። በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ የሚገኙት ኮከብ ያለባቸው አገላለፆች ሁሉ ገፃቸው ከላይ ተጽፏል፤ የደራሲው ሥምና የመጸሐፉ እርእስ ሲደጋጋም እንዳትሰለቹ በማለት ከላይ አልጻፍኩትም።

( በ1936 ዓ.ም የኢትዮጵያ ታሪክ – ከዐፄ ቴወድሮስ እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከሊቀ ሊቃውነቱ ክቡር ተክለ ጻድቅ መኩሪያ መጸሐፍ የተወሰደ ነው) ከትህትና ጋር ..

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘለዓለም ያዘራሉ!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ::

ይቁረጥ –በዳዊት ዳባ

$
0
0

ዳዊት ዳባ
Friday, December 06, 2013
denfo.dd46.gmail.com

1998 በቅድስት ባይልልኝ ተደርሶና  ተዘጋጅቶ ለእይታ የቀረበው ህይወት እንደዋዛ ድራማ ላእይታ ከቀረበ ሀያ አንድ አመት ሆነው። ቅድስት በዚህ ስራዋ በየአረብ አገሩ ለስራ የሚላኩ ዜጎች በይበልጥም የሴት እህቶቻችን ሂወት ምን ያህል በመከራና ስቃይ የተሞላ እንደሆነ እንደወረደና መታየት በሚገባው መንግድ አሳይታናለች። ይህንን ፊልም በጊዜው ሁላችንም ተመልክተን ጉድ ብለናል። ለረጅም ጊዜ ዋና መወያያችንም ነበር።  መንግስት ነን ያሉት ለቀጣይ ሀያ ምናምን አመታት በየአረብ አገራቱ ወንድምና እህቶቻችንን በገፍ ሲልኩ በነዚህ አገራት የሚጠብቃቸውን ፍዳ አናውቅም ነበር ሊሉ አይችሉም። ይህ ፊልም የችግሩን መነሻ ጊዜ አመላካችም ነው።

በቀጠሉት አመታት በመከራ ብዛት አይምሯቸው ታውኮ ወይ ያካል ጉዳተኛ ሆነው ያለረፍት ከመስራትና በተለያዩ መንገዶች ክብር የሆነ ሂወታቸውን አጥተው   እሬሳቸው ወደ አገር  የተመለሱ ወገኖቻችን ከመብዛታቸው ብዛት አሁን አሁን በትናንሿ መንደር ደረጃ ብዙም ማሰብ ሳይፈልግ ሁሉም ዜጋ በስም እየጠራ በቁጥር የሚያስቀምጠው ሆኗል። እረ እንደውም በዘምድ አዝማድ መሀል። አንድ ወይ ከዛም በላይ ሉሁላችንም ተዳርሷል።  እንትና እኮ አረብ ሀገር ሄዳ ከዛ ያሳዝናል ብለን የምናወራው አንጀት የሚያኮማትር ሀዘናችን ከሆነ ውሎ አደረ ። ዛሬ የእንባሲ ሰዎቻችው አይምሯቸው ታውኮና ለዘላለሙ እንዳይድኑ በሽተኛ ሆነው የሚመለሱትን ሳይጨምሩ በሳምንት ከስድስት እስከአስር እሬሳ ወደ አገር እንልክ ነበር እያሉን ነው። በእርግጥ ይህን መነገርም አያሻንም እናውቅ ነበር።

ከአገር ቤት ወደ አደጉት አገራት የሚበሩ አይሮፕላኖች የኛዎቹን ጨምሮ በማደጎ ስም የሚቸበቸቡ ኢትዬጵያዊ ህጻናት ወና ደንበኞቻቸው ናቸው።  በተመሳሳይ ጦርነት ላይ ያለች አገር እስክትመስል ከየአረቡ አገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ በረራዎች እሬሳና ህሙማምን  በገፍ ማመላለስ ከጀመሩ ሀያዎቹን አመታት አስቆጥረዋል። በየአረብ አገራቱ ተጎጂ ስለሆኑ ዜጎቻችን ስናወራ የምናወራው ስለ አምስት ሞቶ ሺ ተጎጂዎች ወይ ስለ አንድ ሚሎዮን ተጎጂ ዜጎች አይደለም። ስለ ብዙ ሚሊዮን ተጎጂ ዜጎች ነው?። በተመሳሳይ  የምናወራው ዛሬ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ እየሆነ ስላለው ብቻ አይደለም ሀያ ሶስት አመት ስላስቆጠረ የዜጎቻችን መከራና አገራዊ ችግር ነው።

እነዚህ ብዙ ሚሊዮን ሰቆቃ የተፈፀመባቸው ዜጎች የበዙት ህጋዊ በሚባለው መንገድ ወደየ አረብ አገራቱ የተላኩ ናቸው። ህጋዊ የሚባለው መንገድ የትኞቹንም ተጎጂዎች እስከዛሬ አልታደገም። ህጋዊ መሆን አለመሆን  ምንም አይነት ልዩነትም አልነበረውም።  ልዩነቱ ፍዳውን ጉዞ ላይ መጀመር ወይ በሚመች አይሮፕላን ቶሎ ቦታው ደርሶ  የመከራውን ሂወት መጀመር ብቻ ነው። ወገኖቻችን እዛ ሲደርሱ ህጋዊ የሚያሰኛቸው ወረቀታቸው ባሰሪዎቻቸው እጅ ስለሚሆን ህገወጥ ብቻ ሳይሆን ያሰሪዎቻቸው ባርያ ነበር የሚሆኑት።  ላለመገደል፤ ላለመደፈር ሰቆቃ እንዳይፈፀምባቸው፤ ጉልበታቸው ያለአግባብ እንዳይበዘበዝ፤ የለፉበትን ሀቃቸውን እንዲይከለከሉ ህጋዊ ወረቀቱም ሆነ ወያኔዎች ተዋዋልን ወይ ስምምነት አደረግን ሲሉት የነበረው ቅራቅንቦ ምንም አልፈየደም።

ይህንን መካድም አይቻልም። አለም ሁሉ ያየውን ያለማቀፋ ሜድያዎችን ሽፋን ካገኙት ውስጥ የጋዳፊ ልጅ ሚስት ወ/ሮ ሀኒባል እህታችን ሸዋዬ ሞላ ላይ ያን ሁሉ ሰቆቃ የፈፀመችባት  ወረቀት ስለሌላት አይደለም። ወይስ ቤሩት ውስጥ ባደባባይ እየደበደቡና ኡ ኡ አድኑኝ፤ የወገን ያለህ እያለች አፍነው የወሰዷትና ጩህቷን አለም ስላየው ወስደው ከገደሏት በሗላ እሯሳን ገደለች ብለው የተፈፀማባትን ግፍ ያዳፈኑት አለም ደቻሳስ እሷም ህገወጥ ስደተኛ ስለነበረች ነበር ወይ?። በጭራሽ። እንዲሁ በየበረሀው የሰውነት ክፍሎቻቸውን የተሰረቁት ወገኖቻችን ህገ ወጥ ስለሆኑ ወይስ ተቆርቋሪ ስለሌላቸውና ውድ የሆነ የሰውነት ክፍላቸውን ስለተፈለገ።

አለም ባልሰለጠነበት ዘመን ሰዎች ያለፍላጎታቸው ባርያ ተደርገው ያድሩ ነበር። እጅግ ዘግናኝ ኢሰባዊ ድርጊት ይፈፀምባቸው እንደነበር አውቃለው። በጊዜው ባሮቹ ሲሸጡ ዋጋ ስላላቸውም ይሆናል  ዋና አላማው በሂወት እንዲኖሩና ስራ በነፃ እንዲሰሩ ነበር። ወያኔዎች  በየአረብ አገራቱ የምትልኳቸው ወገኖቼ ጉዳይ የሚመስለው “እስኪያብዱ ወይ እስኪሞቱ ባሰኛችሁ መንገድ አሟጣችሁ ተጠቀሙባቸው ነው።  ሰቆቃ ፈፅሙባቸው ነው። ሌላ ሙሉ ጉልበት ያለው ይላካል ትቀይሯቸዋላችሁ ነው።”   ይህን እንድል ያደረገኝ በየትኛውም ባርያ ማሳደር ህጋዊ በነበረበት ዘመን  ወይ በየትኛው የባርያ ስርአት የነበረበት አገር  ባርያ የተደረጉ የሰው ልጆች ሰቆቃና ስቃይ ስጋቸው መቋቋም እያቃተው በዚህ ብዛት(ሬሾ) ይሞቱ እንደነበር ወይ  ሰቆቃውን መሸከም እያቃተቸው ያብዱ እንደነበር ስለማላውቅ ነው። “ምን እያደረጓቸው ነው?” “ምን አይነት ማሰቃያ ነው የሚጠቀሙት?” የሚለው ጥያቄ ሁሌም የብዙ ተቆረቀቋሪ  ዜጎችና የኔም መልስ ያላገኘ እንቆቅልሽ ከሆነ ከረመ።

የሚያሳዝነው ግን የበዛው ኢትዮጵያዊ ሀዘኑና መጠቃቱ በየቤቱ እየገባ እያለም ባገር የመጣ(አገራዊ ችግር) አድርጎ በቶሎ አላየውም።  ችግር የሆነው በአገሪቷ ውስጥ ባለው አፈና ግዙፍነት  (አፈናውን በጭራሽ በጭራሽ አሳንሰን አንዳናየው)    ተጎጂዎቹ የሱ እህት፤ የነሱ ሰፈር ልጅ፤ ያአክስቷ ልጅ እንደሆነች እንጂ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በተመሳሳይ ስለባ እየሆኑ ያሉበት ስር የሰደደ አገራዊ ችግር አድርጎ አለማየቱ ነው።

ሁለተኛው ምክንያት ወደየአረብ አገራቱ የተገፉው ህዝብ በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ነው። ስለ አረብ አገራት ስናወራ የምናወራው ስለህዝብ ነው። ክፉ ሰዎች ያሉትን ያህል ደግና ጥሩ ሰዎች ደግሞ አሉበት። በአገሮቹ መሀከልም የሰማይና የምድር ያህል ልዩነትም አለ። እድለኛ ሆነው እነዚህ ደጋጎች ጋር ተቀጥረው መስራት የቻሉት ወይ ሰቆቃ የማይበዛበት  አገራት ውስጥ የሄዱት ጉዳተኛ የመሆን እድላቸው ያነሰ ስለሆነ የተወሰኑት አምሮባቸው ገንዘብም ይዘው ወደአገር ቤት ይመጣሉ። ጎጆ ይቀይሳሉ፤ ቆርቆሮም ይቀይራሉ። ህዝብ ይህንንም አይቷል ሰምቷልም ስለዚህም ይህንንም አዳምሮ ነው ችግሩን ሲያይ የነበረው።

ሶስተኛው ምክንያት ሰቆቃውን መሸከም አቅቷት እስከመጨረሻው ያንቀላፋችው  ወይ አይምሮውን የሳተውን ጨምር ሁሉም በሂወት እስከነበሩና እስከቻሉበት ጊዜ የገኟትን ወደቤተሰቦቻቸው መወርወራቸውን አላቆሙም። ብዙዎቹ በደም፤ በላባቸው፤ በሰውነታችውና በሂወታቸው ዋጋ ይከፍሉ ነበር እንጂ አኗኗራቸው የገንዘብ ወጪ አልነበረበትም። እጃቸው የገባችውን ሁሉ ነው ሲልኩ የነበሩት። መንግስትን ያፀናው የበዛው ከውጪ ይገባል የሚባለው ገንዘብ በዚህ መንገድ ወደ ወደ አገር ሲፈስ የነበረ ነው። በተጨማሪ መናገር ምንም ላይፈይዱ ቤተሰብ ማሳሰብ ነው ብሎ በደላቸውን መደበቅም አለበት። ድቅድቅ ባለ አፈና ውስጥ ለምንኖር ህዝቦች በነዚህና ይህን በመሰሉ ሊሎች ምክንያቶች ተጨማምረውበት ህዝብ የችግሩን ስፋት፤ የጉዳቱን ደረጃና አገራዊ ውርደት መሆኑን ለማወቅ ጊዜ ቢወስድበት አያስገርምም።

በአግባቡ ያልተረዳነው ግን የችግሩን ደረጃና ስፋት ብቻም አልነበረም ። ከዛሬ ሀያ ሁለት አመት በፊት የመጀመርያዋ አይምሮ ህመምተኛ፤ የመጀመርያው እሬሳ  ሲገባ ጀምሮ መንግስት ያውቅ  እንደነበረም ነው።  የምናወራው የውስጥ ሱሪያችንን ቀለም ለማወቅ ስለሚሰሩ ዘረኛ ውላጆች ነው። በአሀዝ ማስቀመጥ በሚችሉበት ደረጃ አንድ ብሎ ሲጀምር ጀምሮ ያውቁ ነበር ። እኛ ግን ችግሩን በየግሉ ወስደን የልጆቻችን እሬሳ ሲልኩልን ተቀብለን አልቅሰን እንቀብራለን። አብደው ሲመጡ ዜጋው ተቀብሎ በግሉ ለማዳን መከራውን ያያል።

ሌላው አይደለም የበዛው ህዝብ ስር የሰደደ ችግር መሆኑን የሚያውቀውና ተቆርቋሪነቱን ሲያሳይ የነበረውም ወገን ውስጥም ብዙ ቁጥር ያለው  ዋና መሆን ይገባው የነበረውን መንግስት ተብዬው እዚህ አገራዊ ውርደት ውስጥ ያለውን ድርሻና ሀላፊነት  አውጥቶ ነው ችግሩን ሲያይ የነበረው። ዛሬም ድረስ ይህ ዳተኛ አመለካከት አለ።  ዛሬም በሳውዲ በወገኖቹ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ሰቆቃ እያየም ይሄ ፖለቲካ  አይደለም  ወይ መንግስትን አታስገቡበት የሚሉ ተላላዎች ብዙ ናቸው። ይህንን አይነት አመለካከት ህዝብ ውስጥ እንዲቀጥል የስራ ድርሻቸው የሆኑ ጊንጦችም አሉ። ወዲያም አደረግነው ወዲህ ግን መሪዎቻችን ዘረኛ ውላጅ ወያኔዎች ባይሆኑ ኖሮ ዛሬ በሳውዲዎች ወገኖቻችን ላይ የተሰራው ወንጀል አይፈፀምም ነበር። ሲጀመር ተቆርቋሪ መንግስት ባለበት፤ ለዛውም ሀያ ሶስት አመት መግዛት የቻለና መንግስቱን ያፀና መንግስት ባለበት አገር ዜጎቹ እራሳቸውን እዚህ አይነት ችግር ውስጥ ማግኘት አልነበረባቸውም። አንዴ ከገቡም ዘረኛ ውላጅ ወያኔዎች ባይሆኑ ስልጣን ላይ ያሉት በጣም፤ በጣም፤ በጣም በቀላሉ ይህን ግፍና ውርደት ማስቀረት ይቻል ነበር። ሰውዲ አረቢያ ውስጥ የሆነው በቀላሉ በርግጠኛነት  መከላከል ይቻል የነበረ ችግር ነው። የሰማነው አይነት ዎይታ በሌለበትና በሰከነ ሁኔታ በቀላሉ ወደ አገራቸው መመለስ ሲቻል ነው እነዚህ ጉዶች ቁጭ ብለው ሲያዩ የከረሙት። ዛሬ  የህዝብ ጩህትና ውግዘቱ ሲበዛ ተንደፋድፈውና አተረማምሰውት ይባስ ብለው ችግሩን ፎቶ መነሻና መታያ አድርገው ከውነውታል።

“ይቁረጥ!። ማንሿከክ አላውቅ ወይ በተፈጥሮዬ ማሽንክነት የለብኝም። ይቁረጥ ብያለው። ያለበለዚያ እኔ እቆርጥልሀለው”። ከረጅም ጊዜ በፊት ካየሁት ድራማ ሁሌም የማስታውሰው ትወና ነው።

ዛሬ በአለም ያሉ የደሀ ይሁን የሀብታም፤ አንባገነናዊ ይሁኑ ዲሞክራሲያዊ፤ አፍሪካዊ ይሁኑ ኢሲያዊ፤ ትናንት ነፃ የወጡም ይሁን የኛ አይነት የጠገበ ታሪክ ያላቸው አገራት የየትኛዎቹም አይነት መንግስታት ህዝበቸው በሌላ አገር መንግስታትና ህዝብ በዚህ ደረጃ ሰቆቃ እንዲፈፀምበት አይፈቅዱም። ሲፈፅም ማየትም የሚያስደስታቸው አይደሉም። ለሀያ ሶስት አመት አይደለም ለአንድ ቀንም የዜጎቻቸውን ያለ አግባብ መበደል አይተው ዝም የሚሉም በጭራሽ አንዳቸውም አይደሉም። በአሁኑ ጊዜ በአለም ላይ ያሉ መንግስታት በሙሉ የሚመሩት ህዝብ እራሱን የዚህ አይነት ችግር ውስጥ እንዳይገባ ያቅማቸውን የሚቻላቸውን ሁሉ የሚያደርጉ  ናቸው። ለማድረግ ቁርጠኛነቱና ፍላጎቱም ያላቸው ናቸው። ስለዚህም ይቁረጥ ብያለው።

ዛሬ በኛ ላይ እየሆነ ያለው ወገንታዊ የሆነ መንግስት ስለሌን ብቻ ነው። የምንሰማውን የወገን መገደል፤ መደፈር፤ ይውጡልን መባል መንጓጠጥ፤ ማበድ በአጠቃላይ በየአረብ አገራቱ በወገናችን ላይ የደረሰውን ሰቆቃ ሁሉ  ማስቀረት የሚቻልበት አንድ ሚሊዮን ቀላል የሆኑ መንገዶች ባሉበት የሚፈፅም ነው። ምን ያደርጋል የኛዎቹ መሪዎች ጋር ፍላጎቱ የለማ። ወገንታዊነት ሸቀጥ አይደለም። እሱቅ የማይሸጥ ሆነ። ስለዚህም ለምን? እኛ ኢትዮጵያዊያን ላይ ብሎ ለሚጠይቅ በቂ ከበቂ በላይ አጥጋቢ የሆነ ምክንያት ያለው ችግር ነው። ወደፊትም የሚገዙን ወያኔዎች እስከሆኑ የዚህ አይነት አገራዊ ውርደትና የዜጎች መጎዳት የሚቀጥል ነው።

ችግሩ ላይ የዜጎች ግንዛቤና’ የመንግስት አያያዝ እላይ ባየንበት ጠቅለል ያለ ሁኔታ ላይ እያለ ነው ኢሳት አገልግሎቱን የጀመረው። ኢሳት በዋናነት ህዝብን ስለችግሩ በማሳወቅ ከፍ ያለ ሚና ተጫውቷል። ላለፉት ሶስት አመት ተኩል ህዝብ ማወቅ መብቱ የሆነውን እውነት ይነግረው ጀመረ። የመንግሰት ደርሻ፤ ግዴለሽነትና ዜጎቹን ለመታደግ አለመፈለግ ያጋለጥ ገባ።  ወያኔዎች አያሳደዱና እያዋከቡ እነዚህ የመከራ አገር የከተታቸው ጋዜጠኞች እቦታው ሆነው የመከራውን ብዛት እውነቱን የማጋለጥ የጀግና ስራቸውን ቀጠሉበት፤ ወገንታዊ ሜዲያዎች ይህ የዜጎች ሰቆቃና መከራ ዋና አምዳቸው ሆነ። ምሁራን ፀሀፍት እንዲሁ በውጪም በአገር ውስጥም ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶችና ወገንታዊ የሆኑ ዜጎች ባገኙት አጋጣሚ ይናገሩበት ይፅፉበት ጀመረ። ችግሩ ሊደበቅ ከሚችለው ደረጃ አልፎ የውጪ ሜዲያዎች ሽፋን ማግኘት ጀመረ። እንደምናያው ተንተክትኮ ተንተክትኮ መገንፈል ጀመራል። እዚህ ላይ ያለማቀፉ የሴቶች ማህበር ያደረገው ያላሰለሰ ጥረት  እጅጉኑ የሚያስመሰግናቸው ነው።

ወያኔዎች ይህን አገራዊ ውርደት የችግሩን መጠንና የተጎጂ ዜጎችን ሰቆቃ ግዝፈትና በነሱ ምክንያት ይህ መከራ አንደመጣብን ህዝቡ ማወቁ እየጨመረ መሄዱን ሲገነዘቡ ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ በሟቹ መለስ ዜናዊ የተደረሰ ‘ያዞ እንባ” የተሰኘ ድራማ መፍትሄ ነው ብለው መተወን ጀመሩ። ከሀያ ሁለት አመት በሗላ  መሆኑ ነው።ክንቅልፍ እንደባነነ ህፃን በገፍ ለመካራ ሂወት ስላጋዟችውና ስላሰደዷቸው ዜጎቻችን እንደማያውቁ ሆነው እንደ አዲስ ሊነግሩን ጀመሩ።  መፍትሄ ፈላጊዎች ችግሩ ላይ ተረቃቂዎች ሆነው ለመታየ እላይ እታች አሉ። ተሰብስበው አልቅሰው ሊያስምኑን ሁሉ ሞክረዋል። ይህ መራወጥ የገባው ድራማውን “ከአዞ እንባ” ወድ “ሀይሌ እንባ”  ቀይሮ ቁጭ ብሎ አየው።   መፍትሄ ብለው የሞከሩት ድራማ ያስገኘው ውጤት ህዝብ የበለጠ ስለችግሩ እንዲያውቅና መታየት በሚገባው መንገድ የገዘፈ ሀገራዊ ችግር አድርጎ እንዲያየው ማድረግ መቻሉ ብቻ ነው። አሁን ለረጅም ጊዜ ችላ ከመባሉ ብዛት ችግሩ ነቀርሳ ሆኗል። ለገዥዎቻችን መፍትሄውም ከጃቸው ወጥቷል። ህዝብ ብሄራዊ ውርደትና በያንዳንዱ ዜጋ ላይ የተሰነዘረ ጥቃት አድርጎ ወስዶታል። ለወያኔዎችና ደጋፊዎቻቸው የቀራቸውና ማምለጫው መንገድ በጊዜ ማቄን ጨርቄን ሳይሉ መሸሽ ብቻ ነው እላለው።

ይህ ፅሁፍ ለፕሮፌሰር ተኮላ ሀጎስ  ባደባባይ የተሰጠ መልስም  ተደርጎ ይወሰደልኝ። ጊዜው አንዳንድ መያዝን ይሻል።  የሚቀናቀን ካልመጠ ተመችተውኝ ቀድሜ ይዣቸዋለው።   ወደፊትም በፃፉ ቁጥር መልስ እሰጣለው። የበዛው አንባቢ ዘረኝነት ፃያፍ የሰውን ልጅ ፍረድና አመለካከት ምን ያህል እንደሚያዛባ ያውቃል። ዘረኝነትን ግን እስከ ቦርቃቃ አፉ፤ አስከ ስድስት እግሩ፤ አስከ ጥፍራም እጆቹና እስከ ተንጨባረረ ፀጉሩ አውሬውን ማየት ከፈለጋችሁ የኚህን እውቅ ፕሮፌሰር ፅሁፎች አንብቡ። በቅርቡ አቦጊዳ ላይ የወጣላቸው ፅሁፋቸው አውሬውን በደንብ ልታዩበት የምትችሉበት ነው።

 

Pen

 

ለባለስልጣናት እንጸልያለን፤ ግፍን ግን አንታገስም ! ግርማ ካሳ

$
0
0

Muziky68@yahoo.com

triad candles croppedበቅርቡ በአቶ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ላይ ጠንካራ ትችት ያዘለ ጽሁፍ ለአንባቢያን አቅርቤ ነበር። አዉራምባ ታይምስ ጽሁፌን «What’s the hell is wrong with Haile Mariam Desalegn”  በሚል ርዕስ  ነበር ለአንባቢያኑ ያቀረበዉ። ይህ  ርዕስ ፣  የአዉራምባ ታይምስ ኤዲተር ምርጫ እንጂ የኔ እንዳልሆነ በቅድሚያ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለሁ።

አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ብዙዎች እንደ «እግዚአብሄር ሰው» ይቆጥሯቸዋል። በየቀኑ ጸሎት እንደሚያደርጉ፣ መጽሃፍ ቅዱስን እንደሚያነቡም ይናገራሉ። እርግጥ ነዉ፣ ሰዎች ጸሎት ሲያደርጉና መጽሃፍ ቅዱስ ሲያነቡ፣  መልካም ነዉ። ነገር ግን ጸሎት ማድረግና መጽሃፍ ቅዱስ ማንበብ፣ በራሱ የእግዚአብሄር ሰው ያሰኛል ብዬ አላስብም። ቄስ፣ ወንጌላዊ፣ ፓስታር፣ ጳጳስ ..መሆን የእግዚአብሄር ሰው አያሰኝም። መስቀል ይዞ መዞር፣ በያሬዳዊ ዜማ ቅኔ መዝረፍ፣ በልሳን መጸለይ ….የእግዚአብሄር ሰዉነት መመዘኛ አይደለም።

አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ የተባረኩ ሴት ልጆች አሏቸው። ልጆቻቸው፣ የሚኒስቴር ልጆች ሆነዉ እያሉ፣ ሳይኮሩ፣ ከሌሎች በላይ ለመሆን ሳይሞክሩ፣  በሚሄዱበት ቤተ ክርስቲያን፣ እሁድ ከአምልኮ/ቅዳሴ  በኋላ፣  ሻሂ እያፈሉ ምእመናንን እንደሚያስተናግዱ አንብቢያለሁ። በአባታቸው ስልጣን፣ በሶሻል ስታተሳቸው ሳይመኩ፣ እራሳቸዉን አዋርደዉ፣  ሌላዉን ማገለገል መቻላቸዉ፣ በርግጥ የልጅ ትልቅ መሆናቸውን ያሳያል። የእግዚአብሄር ሰዉነት መመዘኛ እንግህ ይሄ አይነቱ ትህትና የተሞላበት ተግባር ነዉ። (የአቶ ኃይለማሪያም ባለቤት ወ/ሮ ሮማንም፣ ከአንድ አመት በፊት ቀዳማዊ እመቤት ከነበሩት የሰማይና ምድር ያህል የሚራራቁ፣   እንደ ቀድሞ ቀዳማዊት እመቤት ዉብአንቺ ቢሻዉ፣ ትሁትና ሰው አክባሪ እንደሆኑ ይነግራል )

አንድ ጊዜ እንዲህ ሆነ። አንድ ሰው ከኢያሪኮ ወደ ኢየሩሳሌም ሲጓዝ ወንበዴዎች አገኙትና በሕይወትና  በሞት መሃከል እስኪሆን ድረስ ደብድበዉት ሄዱ። ሃዘኔታና ርህራሄ የሌላቸው፣ ሌሎች ሲሰቃዩና ሲጎዱ ምንም የማይመስላቸው፣ የሰው ልጅ ስብእናና ክብር እንደ መጫወጫ ካርታ የሆነባቸው፣ ሰዉን በዉሸት ክስ የሚያስሩ፣ እየተኮሱ የሚገድሉና የሚደበድቡ፣ በሰላማዉያን ላይ ሽብር በመንዛት፣ ሰዎች  በሰላም ወጥተዉ በሰላም እንዳይገቡ፣ የፈለጉትን እንዳይጽፉና እንዳይናገሩ፣ በአገራቸው እንደ ስደተኖች እንዲሆኑ የሚያደርጉ፣ እያስፈራሩ ሌላዉን የሚያሸማቅቁ፣ የዘመናችን «ወንበዴዎች» በአገራችን ኢትዮጵያ ብዙ አሉ። እንደዉም በስፋት በየሬዲዮና ቴሌቭዥኑ የምንሰማዉ እነርሱን ነዉ።

በመንገድ ዳር የወደቀውና የተደበደበው፣ የሚረዳው ፈልጎ እያቃሰተ ሳለ፣  ድንገት አንድ ቄስ/ፓስተር በመንገድ ዳር አለፉ። ካባ ለብሰዋል። በታላላቅ መንፈሳዊ ጉባኤዎች የእግዚአብሄርን ቃል የሚያስተምሩ፣ መጽሃፍ ቅዱስ የሚያነቡና ፣ የ«እግዚአብሄር ሰው» የሚባሉ ናቸው።  ነገር ግን የቆሰለዉን ሰው ባዩ ጊዜ እንዳላየ ሆኑ። መንገድ ቀይረው ፣ ለተገፋዉና ለተጎዳው እጃቸውን ሳይዘረጉ ጉዟቸውን ቀጠሉ። ትንሽ ቆይቶም አንድ ሌዋዊ (ዲያቆን)፣ ትንሹ የ«እግዚአብሄር ሰው»  መጣ። እርሱም እንደ ቄሱ እንዳላየ ሆነ አልፎ ሄደ።

ሳምራዊያን የሚባሉ ነበሩ። እግዚአብሄርን እንደማያውቁ ሐጢያተኞችና የረከሱ  ተደርገዉ የሚቆጠሩ።  ታዲያ አንድ ሳምራዊ፣  በወንበዴዎች ተደብድቦ የወደቀዉ ሰው ባለበት መንገድ አለፈ። ቁስለኛዉን ሲያይ ቆመ። ከበቅሎው ወረደ። ተጎነበሰ። ከአንገቱ ሰዉዬን ደግፎ፣ የያዘዉን ወይን ጠጭና ዘይት በሰዉዬዉ ቁስል ላይ አፈሰሰ። ሽሚዙን ቀደደና የሰዉዬዉን ቁስል አሸገ። ሰዉዬን ተሸክሞ በበቅሎው ላይ ጭኖ፣  እርሱ ግን በእግሩ፣  አብረው መንገድ ጀመሩ።  ቁስለኛዉን ወደ አንድ ሆቴል ቤት ገንዘብ ከፍሎ አሳረፈ። አስገራሚ ፍቅር ! አስገራሚ ሰብዓዊነት ! አስገራሚ ርህራሄ ! ይህ ታሪክ፣  ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣  የእግዚአብሄር ሰዉ፣  ምን ማለት እንደሆነ ለማስተማር የተናገረው ግሩም ታሪክ ነዉ። ቄሱ፣ ወይንም ዲያቆኑ ሳይሆኑ፣  «የእግዚአብሄር ሰዉ አይደለም» ተብሎ ይቆጠር የነበረው ሳምራዊዉ ነበር፣  በአምላክ ሚዛን የእግዚአብሄር ሰው የተባለው።

በመጽሃፍ ቅዱስ ፣ ኢሳያስ 1፡ 16 እንደተጻፈው፣ እግዚአብሄር ምን ያህል የፍትህ አምላክ እንደሆነ፣ ሲናገር «መባዎቻችሁንና ሰንበታችሁን፣ በጉባኤ መሰብሰባችሁን አልወደዉም። በደልንም የተቀደሰዉንም ጉባኤ አልታገስም። መባዎቻችሁንና በዓላቶቻችሁን ነፍሴ ጠልታለች። ሸክም ሆነዉብኛል። ልታገሳችሁ ደክሜያለሁ።  እጆቻችሁን ወደ እኔ ብትዘረጉ፣ አይኔን ከእናንተ እሰዉራለሁ። ልመናንም ብታበዙ አልሰማችሁም …. ፍርድን ፈልጉ። የተገፋዉን አድኑ። ለድሃ አደጉ ፍረዱለት፤  ስለመበለቲቱም ተሟገቱ። » ነበር ያለው። ከሚደረጉ ዉጫዊና ሃይማኖታዊ ስርአቶች በላይ፣ እግዚአብሄርን የሚያስደስተው፣  የሰዉ ልጆች ደህንነትና ስብእና ነዉ።   አስር ሺህ ቅዳሴዎችና መንፈሳዊ ጉባኤዎች ይልቅ ፣ አንድን ሰው ከወደቀበት ማንሳት፣ አንድን በግፍና በዉሸት የታሰረን ሰው ማስፈታት፣ አንድ የተገፋና የተጮቆነን ሰው ቀንበር መስበር፣ አንድን ሰዉ ማዳን፣  በጌታ ፊት የበለጠ ክብር አለው። የእግዚአብሄር ሰው መሆን ማለት፣  ለፍትህ መቆም ማለት ነዉ። የእግዚአብሄር ሰው መሆን ማለት  ሙግት መፍጠር (መታገል) ማለት ነዉ። ምን አይነት ሙግት ?  የተቀደሰ ፣ ስድብና ጥላቻ የሌለበት፣  ሰላማዊ የሆነ፣  ለፍትህ የሚደረግ ሙግት!

በአገራችን ኢትዮጵያ ያሉ፣ ልንታገልላቸው ወይንም ልንሟገትላቸው የሚገባ  «መበለቶች» ብዙ ናቸው። ገዢዎች ከሚፈልጉት ዉጭ በመናገራቸው፣ እዉነትንና እኩልነትን በመስበካቸው ፣ በዉሸት ክስ፣  «ሽብርተኞች» ተብለው በወህኒ የተወረወሩ፣ ፍርድና ፍትህ የተነፈጉ ሁሉ «መበለቶች» ናቸው።  ሙስሊም ሊሆኑ ይችላሉ፣  ከርስቲያኖች ሊሆኑ ይችላሉ! ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ወላይታ ሊሆኑ ይችላሉ! ጉዳዩ የሰብአዊነት እንጂ የሃይማኖት ወይንም የዘር አይደለም።

ለምሳሌ እነ እስክንደርን እንዉሰድ። በግለሰብ ደረጃ እስክንድር ነጋን እና አንዱዋለም አራጌን አውቃቸዋለሁ። ብዙ ጊዜ በአገራችን ዙሪያ የተለያዩ ሃሳቦችን በግል ተለዋውጠናል። ስለ ትጥቅ ትግል፣ ስለ ግንቦት ሰባት ወዘተረፈ ያላቸውን አመለካከት በሚገባ አውቃለሁ። የጻፉትን እና በአደባባይ የተናገሩትን ተከታትያለሁ። የነርሱን አገር ወዳድነትና ሰላማዊነት፣ በየትኛዉም ፍርድ ቤት ሆነ አደባባይ፣  እጆቼን መጽህፍ ቅዱስ ላይ ጭኔ የምመሰክረው ነዉ።  እግዚአብሄርን  የሚወዱ፣ ቤተሰባቸዉን የሚወዱ፣ በአገራችን እርቅና ሰላም እንዲመጣ የሚናፍቁ፣ ማንም የማያነቃንቃቸው የሰላም አርበኞች ናቸው።  እስክንድርና አንድዋለም እንዲሁም ሌሎች የሕሊና እሥረኞች የአገራችን «መበለቶች» ናቸው። እስክንደርና አንዱዋለም እንዲሁም ሌሎች፣ በመንገድ ዳር ወንበዴዎች እንደደበደቡት ሰዉዬ ናቸው።

እንግዲህ «መጽሃፍ ቅዱስን እናነባለን፤ እግዚአብሄርን እናምናለን. ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንከተላለን» ካልን፣   እየመረጥን አይደለም እግዚአብሄርን የምንታዘዘው። ለተገፉ፣ ለወደቁ፣ በዉሸት ለታሰሩ፣ ፍትህ ለተነፈጉ፣  ወገኖቻችን መቆም መጀመር አለብን።  በጣም አሰምርበታለሁ። ለታሰሩ እስረኞች መቆም ክርስትና ነዉ !  ለፍትህ ለዜጎችን ነጻነት መቆም፣  መጽሃፍ ቅዱሳዊ ነዉ። የእግዚአብሄርን ቃል መታዘዝ ነዉ።

በአንጻሩ፣ ግፍ፣ ቀንበር፣ ጭቆና እያየን፣  ዝምታን ከመረጥን፣ የእግዚአብሄር ቃል እንደሚለዉ  መባዎቻችንና ሰንበታችሁን በጉባኤ መሰብሰባችንን እግዚአብሄር አይወደዉም። እጆቻችንን ወደ እርሱ ብንዘረጋ፣ አይኖቹን  ከእኛ ይሰዉራል።  ልመናንም ብናበዛ አይሰማንም።  ሌላዉ በግፍ ሲታሰር ዝም ማለት፣ ከራሳችን ጥቅምና ምቾት አልፈን አለመሄድ፣ የዘመኑ ጡንቸኞችን ቢያስደስትም፣ ጥቂት ፍርፋሬዎች ቢወረወርልንም፣  የዘላለም አምላክ እግዚአብሄርን  የማያስደስት  እርግማን ነዉ። ነዉር ነው።

አንዳንዶች የመንግስት ባለስልጣናት ላይ ተቃዉሞ ማንሳታችንን ተገቢ እንዳልሆነ ለማሳየት፣ ከመጽሃፍ ቅዱስ አንድ ጥቅስ ነጥለው በማውጣት ለማስተማር የሚሞክሩ፣ ቄስ/ፓስተር ተብዬ የአገዛዙ ካድሬዎች አሉ።  «ለባለስልጣን ጸልዩ፣ ታዘዙ» ተብሎ ስለተጻፈ «ፖለቲካ ዉስጥ ሳንገባ ፣ ታዘን መኖር ነው ያለብን» ይሉናል። አዎ ፣ በዚህ ምክንያት የአገሪቷን ሕግ እናከብራለን። ግብር በጊዜው እንከፍላለን። በትክክል የአገሪቷን ሕግ ከጣስን መቀጣታችን ተገቢ ነዉ እንላለን። ለአቶ ኃይለማሪያም ፣ ልቦና እንዲሰጣቸው፣ በልጆቻቸው ያለው የርህራሄና የፍቅር መንፈስ በርሳቸውም እንዲሰርጽ ፣ አብረዋቸው ያሉ የሰይጣን መልእክተኖችን ሳይሆን የእግዚአብሄርን መንፈስ ማዳመጥ እንዲጀምሩ፣ ሕዝብን ማስተዳደር የሚችሉበት ጥበብ  ጌታ እንዲሰጣቸው ሊጸለይላቸው ይገባል። እኛም እንጸልያለን።

ነገር ግን ባለስልጣናት ግፍ ሲፈጽሙ፣ ለነርሱ እንደምንጸልየዉ ሁሉ ፣ እነርሱን መሟገትንና መታገል  የግድ ነዉ። ነብዬ ናታን ንጉስ ዳዊት ስልጣኑን ተጠቅሞ የሰው ሚስት ደፍሮ፣ የደፈራትም ሴት ነፍሰ ጡር ስትሆን፣  ሐጢያቱን ለመደበቅ ባሏን ባስገደለ ጊዜ፣  ንጉሱን  ፊት ለፊት አወገዘ፣ ተቃወመ። «ለባለስልጣን ታዘዝ» ተብያለሁ ብሎ ዝም አላለም። ንጉስ ሄሮድስ አንቲጳስ፣ የወንድሙን ፊሊጵስ ሚስት ሄሮድያዳን ነጥቆ የራሱ በማድረግ ጸያፍ ተግባር በፈጸመ ጊዜ፣ መጥምቁ ዮሐንስ፣ በአደባባይ ነዉ «ንስሐ ግባ»  ብሎ ያወገዘዉ።  በዚህም ምክንያት ሄሮድስ የመጥምቁን አንገት ሁሉ አስቆርጧል።

የእምነት ሰው መሆን ማለት፣  ባርነትን መቀበል ማለት አይደለም። የእምነት ሰው መሆን ማለት አደርባይ መሆን አይደለም። የእምነት ሰው መሆን ማለት የፍትህ፣ የሰላምና  የነጻነት አርበኛ መሆን ማለት ነዉ። የእምነት ሰው መሆን ማለት እንደነ ነብዩ ናታን፣  ባለስልጣናት ስልጣናቸውን ተጠቅመዉ የሚፈጽሙትን ግፍ ማውገዝና መቃወም ማለት ነዉ። እነ ነብዩ ናታን እንዳደረጉት እኛም፣ ግፍን በምናወግዝበት ጊዜ፣ «እግዚአብሄርን እናምናለን»  የሚሉ ሊቀላቀሉን ይገባል እንጂ ዝም እንድንል ሊነግሩን አይገባም።

አቶ ኃይለማሪያምን  እንወዳቸዋለን፤ መልካም ሲሰሩ ፣ ደግፈናቸዋል፤ ወደፊትም እንደግፋቸዋለን። ነገር ግን ክፋታቸውን፣   አይተን ዝም አንልም። በሽብርተኝነት ስም ፍርድ ሲያዛቡ፣  በዜጎች ላይ ሲዝትኑ ዜጎችን ሲያስፈራሩ ዝም አንላቸዉም። «ባርነት ፣ ጭቆና፣ ግፍ፣ ዘረኝነት፣ የሰብአዊ መብት ረገጣ .. በቃ ! »  ብለናል።  ግፍን አንታገስም። ጥቂቶች የሕዝቡን መብት ረግጠው እንዲቀጥሉ አንፈቅድላቸዉም። ይሄን እንሟገታለን፤ ይሄን እንታገላለን። ጆሮ ያለው ይስማ። ልብ ያለው ያስተውል። እግዚአብሄር ልቦናችንን በፍቅሩ፣ አይምሯችንን በጥበቡ ይሙላልን ! አገራችን ኢትዮጵያ እንዲሁም ኤርትራን ይባርከልን !

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>