እንደ ባቡር ፉርጎ የተቀጣጠለዉ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት (ሳዲቅ አህመድ ከአንድ የህወሃት የጦር መኮንን ጋር ያደረገው ቆይታ)
[jwplayer mediaid=”47802″]
The post እንደ ባቡር ፉርጎ የተቀጣጠለዉ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት (ሳዲቅ አህመድ ከአንድ የህወሃት የጦር መኮንን ጋር ያደረገው ቆይታ) appeared first on Zehabesha Amharic.
እንደ ባቡር ፉርጎ የተቀጣጠለዉ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት (ሳዲቅ አህመድ ከአንድ የህወሃት የጦር መኮንን ጋር ያደረገው ቆይታ)
[jwplayer mediaid=”47802″]
The post እንደ ባቡር ፉርጎ የተቀጣጠለዉ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት (ሳዲቅ አህመድ ከአንድ የህወሃት የጦር መኮንን ጋር ያደረገው ቆይታ) appeared first on Zehabesha Amharic.
የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ራድዮ በሰበር ዜናው እንደዘገበው በላንድ ክሩዘር መኪና ተሳፍረው ወደ አርባ ምንጭ ከተማ በፍጥነት ያመሩ የነበሩ 10 የፌደራል ፖሊስ አባላት ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ከነመኪናቸው ሙሉ በሙሉ ተደመሰሱ፡፡
እንደ ራድዮው ዘገባ በትናንትናው ዕለት አመሻሽ ላይ አስሩ የፌደራል ፖሊሶች መጀመሪያ አንድ አይሱዙ የጭነት መኪና በኃይል በማስገደድ አስቁመው የተሳፈሩ ሲሆን መኪናው መንቀሳቀስ ሲጀምር “የጫንካቸውን ፖሊሶች አራግፍ አለያ ከነንብረትህ አብረህ ትጋያለህ!” የሚል የስልክ ማስጠንቀቂያ መልዕክት ለአሽከርካሪው በመድረሱ አሽከርካሪው መኪናውን አቁሞ ፖሊሶቹን “አልሄድም” ይላቸዋል፡፡ ቀጥሎም ፌደራል ፖሊሶቹ ሾፌሩን ለማንገራገር ሞክረው ትዕዛዛቸውን በቀላሉ ሊቀበል ባለመቻሉ ስልክ ተደዋውለው ሌላ ላንድ ክሩዘር መኪና እንዲመጣላቸው በማድረግ ተሳፍረው ጉዟቸውን ቀጥለው ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ሲደርሱ ቅፅበታዊ ጥቃት ተከፍቶባቸው ከነተሳፈሩበት መኪና ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል ብሏል የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ::
ራድዮው ዘገባውን በመቀጠል የአርባ ምንጭ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ባለው የልዩ ኃይል እና የፌደራል ፖሊስ ጦር ተወራ ጓዳ ጎድጓዳዋ ሳይቀር እየታሰሰ ነው ብሏል::
ራድዮው እንደሚልው እየተፋፋመ ያለው የፀረ-ወያኔ ትግል እየተካሄደባቸው ከሚገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ከተሞች አንዷ አርባ ምንጭ መሆኗ እና በህወሓት የደህንነት ተቋም ጥርስ ውስጥ ገብታ አገዛዙ በአዓይነ ቁራኛ እየተከታተላት የምትገኝ መሆኗ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ከሰሞኑ ደግሞ አርበኞች ግንቦት 7 አንድ አይሱዙ ሙሉ የጦር መሳሪያ ወደ ከተማዋ አስገብቷል በሚል የህወሓት ልዩ ኃይሎች፣ ፌደራል ፖሊሶችና ደህንነቶች በየመንደሩ ተሰራጭተው ከፍተኛ አሰሳ እያደረጉ የነዋሪዎችን የዕለት ተዕለት የህይወት እንቅስቃሴና ሰላም በማወክ ላይ ናቸው፡፡
በተያያዘ ዜና ሙሉጌታ አባ፣ ፀጋዬ ገብረ ፃድቅ እና በኃይሉ ሲሳይ የተባሉ የህወሓት ጆሮ ጠቢዎችና የአካባቢው ቆራጭ ፈላጮች ፎቶግራፋቸው በማህበራዊ ሚዲያው መሰራጨቱን ተከትሎ ከትናንት ምሽት ጀምሮ አርባ ምንጭ ከተማ ከከዚህ ቀደሙ በባሰ ሁኔታ በፌደራል ፖሊስ ተጥለቅልቃ እየታመሰች ትገኛለች ሲል ራድዮው ዘግቧል::
ይህን ዜና የሚያስተባብል መረጃ ከመንግስት በኩል እስካሁን የተሰጠ ነገር የለም:: ዘ-ሐበሻ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ያደረገችው ሙከራም አልተሳካም::
The post 10 የፌ. ፖሊስ አባላት ኮንሶና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ከነመኪናቸው ተደመሰሱ ሲል አርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ ዘገበ appeared first on Zehabesha Amharic.
ትናንት ዘ-ሐበሻ በሰበር ዜና መምህር ግርማ ወንድሙ መታሰራቸውን መዘገቧ አይዘነጋም:: ፖሊስ ዛሬ መምህር ግርማን ፍርድ ቤት አቁሞ ጠርጥሮ ያሰረበትን ምክንያት አስረድቷል:: የፌደራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የወንጀል ችሎት በመምህር ግርማ ላይ ፖሊስ የፈጸመውን ክስ ከሰማ በኋላ ፖሊስ አቶ ግርማ ቢፈቱብኝ መረጃና ሰነዶችን ሊያሸሹ ይችላሉና 14 ቀን ይፈቀድልኝ ሲል ጠይቋል:: የመምህር ግርማ ጠበቃ የተጠረጠሩበት ክስ ዋስትና የሚያስከለክል አይደለም ሲል ሲል በዋስ እንዲለቀቁ ጠይቆ ነበር:: ሆኖም ፍርድ ቤቱ ፖሊስ አብዛኛውን ምርመራ በማጠናቀቁ የጠየቀውን 14 የምርመራ ቀን ሰርዞ በ7 ቀን ውስጥ አሉኝ የሚላቸውን ማስረጃዎች አሰባስቦ እንዲጨርስ ፈቅዶ ውጤቱን ለመስማትም ጥቅምት 25 2008 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል። መምህር ግርማ ወደ ማረፊያ ቤት ሄደዋል::
በመምህር ግርማ ወንድሙ ላይ የቀረበው ክስ የሚከተለው ነው:- (ከመንግስት ሚዲያዎች እንደወረደ የተገኘ ነው)
የወንጀሉ ዝርዝር
ፖሊስ መምህር ግርማ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ምክንያት የሆነው ወንጀል የተፈፀመው መስከረም 2006 ዓ.ም ነው ብሏል።
በየካ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ወሰን ግሮሰሪ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖሩት አቶ በላይነህ ከበደ በመምህር ግርማ የማታለል ወንጀል የተፈጸመባቸው ግለሰብ ናቸው።
እንደ ፖሊስ የምርመራ መዝገብ እኚህ ግለሰብ ከትዳር አጋራቸው ጋር 400 ካሬ ሜትር ላይ ባረፈ መኖሪያ ቤታቸው ይኖሩ ነበር።
እንደ ምርመራ መዝገቡ መምህር ግርማ የግል ተበዳይን እምነት በመጠቀም የምትኖርበትን መኖሪያ ቤት እስከ ጥር 30 2006 ሽጠህ ካልወጣህ አስከሬንህ ይወጣል ይሏቸዋል።
የፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንደሚለው ልጅ ያልወለዱት ባልና ሚስት ከመሞት መሰንበት በማለት ይህንን ቤት በጣም በዝቅተኛ ዋጋ በ800 ሺህ ብር ይሸጡታል።
ቤቱ በዚህ ዋጋ እንዲሸጥ መምህር ግርማ በራሳቸው ሰዎች አማካኝነት ብዙ ያልተገባ ስራ ሰርተዋል ነው የሚለው የምርመራ መዝገቡ።
ከዚያም መምህር ግርማ በዚህ ብቻ ሳይመለሱ የግል ተበዳዩን ቦሌ አካባቢ በራዕይ ያየሁት ቦታ አለ እዚያ ነው ገዝተህ የምትኖረው ይሏቸውና ሌላ የማታለያ ዘዴ ቀየሱ ይላል ምርመራው።
ቤቱ የተሸጠበትን 800 ሺህ ብር አምጣና እንዲበረክትልህ ልፀልይበት ብለው በመውሰድ በዚያው ውለው አደሩ፤ የግል ተበዳዩም በእርሳቸው ላይ ያላቸው እምነት ባለመጥፋቱ በትዕግስት ስልክ ቢደውሉላቸውም ስልካቸው ዝግ ሆነባቸው፤ ይባስ ብሎ ከሀገር ወጡ ተባለ የሚለውም ተጠቅሷል።
የግል ተበዳይ ሁኔታው ማታለል መሆኑን ስለተረዱ 2007 መጋቢት ወር ገደማ ለፖሊስ ያመለከቱ ሲሆን፥ እርሳቸው ከሄዱበት እስኪመለሱ ፖሊስ የግል ተበዳዩን እና የምስክሮችን ቃል ተቀብሎ ቆይቶ ተጠርጣሪው መምህር ግርማ ወንድሙን ትናንት በቁጥጥር ስር አውሏቸው ነው ዛሬ ፍርድ ቤት ያቀረባቸው።
ተጠርጣሪው መምህር ግርማ እኔ የተባለውን ሰው ቀይ ይሁን ጥቁር አይቼው አላውቅም፤ ሆን ተብሎ ከጀርባ የተጠነሰሰብኝ ሴራ አለ በማለት ለችሎቱ አስረድተዋል።
The post መምህር ግርማ ዋስትና ተከለከሉ * የማታለል ክስ የቀረበባቸው መምህሩ “ሴራ ነው – ከሳሹን አይቼው አላውቅም” አሉ appeared first on Zehabesha Amharic.
የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ራድዮ በሰበር ዜናው እንደዘገበው በላንድ ክሩዘር መኪና ተሳፍረው ወደ አርባ ምንጭ ከተማ በፍጥነት ያመሩ የነበሩ 10 የፌደራል ፖሊስ አባላት ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ከነመኪናቸው ሙሉ በሙሉ ተደመሰሱ፡፡
እንደ ራድዮው ዘገባ በትናንትናው ዕለት አመሻሽ ላይ አስሩ የፌደራል ፖሊሶች መጀመሪያ አንድ አይሱዙ የጭነት መኪና በኃይል በማስገደድ አስቁመው የተሳፈሩ ሲሆን መኪናው መንቀሳቀስ ሲጀምር “የጫንካቸውን ፖሊሶች አራግፍ አለያ ከነንብረትህ አብረህ ትጋያለህ!” የሚል የስልክ ማስጠንቀቂያ መልዕክት ለአሽከርካሪው በመድረሱ አሽከርካሪው መኪናውን አቁሞ ፖሊሶቹን “አልሄድም” ይላቸዋል፡፡ ቀጥሎም ፌደራል ፖሊሶቹ ሾፌሩን ለማንገራገር ሞክረው ትዕዛዛቸውን በቀላሉ ሊቀበል ባለመቻሉ ስልክ ተደዋውለው ሌላ ላንድ ክሩዘር መኪና እንዲመጣላቸው በማድረግ ተሳፍረው ጉዟቸውን ቀጥለው ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ሲደርሱ ቅፅበታዊ ጥቃት ተከፍቶባቸው ከነተሳፈሩበት መኪና ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል ብሏል የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ::
ራድዮው ዘገባውን በመቀጠል የአርባ ምንጭ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ባለው የልዩ ኃይል እና የፌደራል ፖሊስ ጦር ተወራ ጓዳ ጎድጓዳዋ ሳይቀር እየታሰሰ ነው ብሏል::
ራድዮው እንደሚልው እየተፋፋመ ያለው የፀረ-ወያኔ ትግል እየተካሄደባቸው ከሚገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ከተሞች አንዷ አርባ ምንጭ መሆኗ እና በህወሓት የደህንነት ተቋም ጥርስ ውስጥ ገብታ አገዛዙ በአዓይነ ቁራኛ እየተከታተላት የምትገኝ መሆኗ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ከሰሞኑ ደግሞ አርበኞች ግንቦት 7 አንድ አይሱዙ ሙሉ የጦር መሳሪያ ወደ ከተማዋ አስገብቷል በሚል የህወሓት ልዩ ኃይሎች፣ ፌደራል ፖሊሶችና ደህንነቶች በየመንደሩ ተሰራጭተው ከፍተኛ አሰሳ እያደረጉ የነዋሪዎችን የዕለት ተዕለት የህይወት እንቅስቃሴና ሰላም በማወክ ላይ ናቸው፡፡
በተያያዘ ዜና ሙሉጌታ አባ፣ ፀጋዬ ገብረ ፃድቅ እና በኃይሉ ሲሳይ የተባሉ የህወሓት ጆሮ ጠቢዎችና የአካባቢው ቆራጭ ፈላጮች ፎቶግራፋቸው በማህበራዊ ሚዲያው መሰራጨቱን ተከትሎ ከትናንት ምሽት ጀምሮ አርባ ምንጭ ከተማ ከከዚህ ቀደሙ በባሰ ሁኔታ በፌደራል ፖሊስ ተጥለቅልቃ እየታመሰች ትገኛለች ሲል ራድዮው ዘግቧል::
ይህን ዜና የሚያስተባብል መረጃ ከመንግስት በኩል እስካሁን የተሰጠ ነገር የለም:: ዘ-ሐበሻ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ያደረገችው ሙከራም አልተሳካም::
The post 10 የፌ. ፖሊስ አባላት ኮንሶና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ከነመኪናቸው ተደመሰሱ ሲል አርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ ዘገበ appeared first on Zehabesha Amharic.
በትናንትናው እለት የብአዴን ምክትል ሊቀመንበርና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ቃለምልልስ ሲያደርጉ ተከታተልሁ:: ርእሰ መስተዳድሩ ባንድ ወቅት “አማራ የራሱን የጦር ጀኔራል መርጦ ህዝቡን እያስታጠቀ ነው” በሚል በትግራዩ ገዥ አቶ አባይ ወልዱ ለቀረበባቸው ክስ “አዎ ለክልሌ ጀኔራል ነኝ” ብለው መልስ ሰጡ የሚል ጽሁፍ አንብቤ ስለነበር ልቤ በኩራት እብጥ ብሎ ክብር ሰጥቻቸው ነበር:: በአማራው ላይ የሚደርሰው ዘርፈ ብዙ ጥቃት ያበቃ ዘንድ በብአዴን ውስጥ ያሉት አማሮች በቁጭት “በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ በቃ!”ብለው ተነስተዋል ማለት ነው ብየ ገምቸ ነበር:: ምንም ቢሆን ልጅ የወላጆቹን ባህሪ መውረሱ አይቀርም: ይኸው የብአዴን አማሮች ያባቶቻቸውን ወኔ ተላበሱ ብየ በደስታ የምሆነውን አጥቸ ነበር:: ይሁንና ሰውየው በሰሞኑ ያደረጉት ቃለመጠይቅ ላይ ብአዴን የአማራ ህዝብ የዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶቹ ተከብረው ከሌሎቹ ወገኖቹ ጋር በእኩልነት እንዲኖር ከትምክህተኞችና ከጠባቦች ጋር ብዙ ትግል እንዳደረገና ውጤት እንዳስገኘ ሲገልጹ ሰማሁና ከልብ አዘንሁ:: አቶ ገዱ እናንተ የምታወሩትን ወይስ ምድር ላይ የሚታየውን እንመን? እንደእኔ እምነት የአማራ ህዝብ መቸም ቢሆን ያላገጠመውን ፈተና በናንተ ጊዜ እየተፈተነ ነው:: አማራ ተኮር የሆነ ጭፍጨፋ የተፈጸመውና ህዝባችን አጎንብሶ እንዲኖር የተደረገው በናንተ ጊዜ ነው:: ይህ ሁሉ መከራ በአማራው ላይ ሲፈጸም “ለምን እንዲህ ይሆናል” ብላችሁ ለመሟገት የሚያስችል እንጥፍጣፊ ወኔ የላችሁም:: እንዲያውም ድርጅታችሁ በተላላኪነት ተግባር ተሰማርቶ ግፍ አንገፈገፈን ብለው ተቃውሞ ያሰሙትን ወገኖች አሳዶ በመምታት የወያኔ አፋኝ ስኳድ ሆኖ እየሰራ ያለ ድርጅት እንደሆነ ህዝባችን አሳምሮ ያውቃል:: “የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳ” ነውና እስቲ በኢህአዴግ ጊዜ በአማሮች ላይ የተፈጸመውን ግፍና የናንተን አቋም በጥቂቱ እናስታውሳችሁ:-
1. በደርግ የመጨረሻ ዘመን አሶሳ ላይ አማሮች ብቻ ተለይተው ሲታረዱና በእሳት ሲቃጠሉ ድርጅታችሁ አንድም ተቃውሞ አላሰማም::
2. የናንተን ድርጅት ያካተተው ኢህአዴግ መላ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ በኋላ አማሮች እየተለቀሙ ከነነፍሳቸው በገደል ሲጣሉ:በገጀራ ሲታረዱ: በእሳት ሲቃጠሉ ድርጅታችሁ የወገንተኝነት ስሜት ተሰምቶት “ለምን ምንም ያላጠፉ ሰዎች አማራ በመሆናቸው ብቻ እንዲህ አይነት ግፍ ይፈጸምባቸዋል?” ብሎ በመቆርቆር እወክለዋለሁ የሚለውን ህዝብ መብት ለማስከበር ሲንቀሳቀስ አልታየም:: እንዲያውም ያሁኑ ፓስተር የያኔው የድርጅታችሁ ሊቀመንበር ታምራት ላይኔ በጅጅጋ ተገኝቶ በሶማሊያ ክልል በሚኖሩት አማሮች ላይ የሶማሌ መንግስትና ህዝብ እርምጃ እንዲወስዱባቸው በመቀስቀስ ድርጅታችሁ ጸረ አማራ መሆኑን እናንተም የጠላት ሀይል አንድ ክንፍ መሆናችሁን አስመስክሯል::
4. አማራ ከየክልሉ ሀብት ንብረቱን ጥሎ የሞተው ሞቶ ማምለጥ የቻለው እግሩ ወዳመራው ሲሰደድ “አይደለም ኢትዮጵያ ውስጥ ሌላ ሀገር ውስጥ የሚኖር አማራ ካላግባብ ሀብት ንብረቱን ሊነጠቅ: ህይወቱን ሊያጣ አይገባም” ብላችሁ ስትከራከሩ አልተሰማችሁም:: ይባስ ብሎ የድርጅታችሁ የወቅቱ ሊቀመንበር አቶ አዲሱ ለገሰ ከኦሮሚያ የተባረሩትን አማሮች በተመለከተ ለተጠየቁት ጥያቄ ሲመልሱ የተባረሩት ሰዎች አጭበርባሪወችና ዘራፊወች ናቸው ነበር ያሉት:: የአማራ ሰዎች እንደዚያ በጅምላ ከየክልሎች አላግባብ እንዲፈናቀሉ ሲደረግ በአማራ ክልል ግን የሌሎች ክልሎች ተወላጆች በድርጅታችሁ ታቅፈውና ሹመኛ ሆነው በአማሮች ላይ እየፈረዱና ሀብቱን እየመዘበሩ በማናለብኝነት ቀጥለዋል:: ለዚህስ የምትሰጡት መልስ ምንድን ነው? የሚገርመው ደግሞ የአማራን ህዝብ ጥንብ እርኩሱን አውጥቶ ያዋረደው የክልሉ ተወላጅ አቶ አለምነው መኮንንን ህዝብን ያህል ነገር እንዴት እንዲህ ታረክሳለህ ተብሎ ሊጠየቅ ሲገባ እርስዎን ጨምሮ ሌሎች የድርጅቱ አባላት ባንድ ላይ ሰውየው የህዝብ ተቆርቋሪ እንደሆነና የተወራበት ሁሉ የጠላት ወሬ እንደሆነ ልታሳምኑን ስትደክሙ ሰምተን እጅግ አዝነናል:: በህዝብ ላይ ያን ያልተገረዘ የባለጌ መላሱን ያስረዘመውን ስድ አደግ ሰው ልትቀጡ ወይም ልትገስጹ ሲገባ ከህዝብ በላይ አድርጋችሁ በማየት የተገላቢጦሽ ለህዝብ የተቆረቆሩትን ሰዎች ወረፋችሁ::
5. በአማራ ክልል የሚኖሩ ብሄረሰቦች በዞን ተደራጅተው ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ ሲደረግ አማሮች በብዛት በሚገኙባቸው ሌሎች ክልሎች ግን ይህ እድል አልተሰጠም: ሌላው ቀርቶ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን እንኳ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ ዕድሉን አላገኙም:: ታዲያ እናንተ የታዘዛችሁትን ከመፈጸም አልፋችሁ እንዲህ የተዛነፈ አሰራር ሲታይ ምን ያደረጋችሁት ነገር አለ?
6. የአዊ ዞን ልጆቻቸው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአማረኛ እንዲማሩ ተስማምተው ያሳለፉትን ውሳኔ ከበላይ የመጣ ትእዛዝ ነው በሚል የብሄሩን መብት ገፍፋችሁ አዊወች በአዊኛ እንዲማሩ አደረጋችሁ: ይህን ውሳኔውን ያሳለፉትን ሰዎችም “የመንግስትን ፖሊሲ ተቃርነው የቆሙ” በማለት ፈርጃችሁ ከስራ እስከማባረር ድረስ የደረሰ ቅጣት ቀጣችኋቸው::
7. ለሱዳን ሊሰጥ በታሰበው መሬት ላይ የህዝብ ቁጣ ሲባባስ “የምንሰጠው መሬት የለም: ከሌላ የወሰድነውም የለም:: የራሳችን የሆነውን አንሰጥም የሌላውንም አንፈልግም” ብለው ነበር:: ይሁንና በተጨባጭ ከመተማና ካካባቢው በሱዳን ወታደሮች በሀይል እንደተፈናቀሉ ተፈናቃዮቹ አዲሳበባ ድረስ በአካል ተገኝተው ለፓርላማው አቤቱታ ማቅረባቸው በተጨማሪም ለአሜሪካው የአማረኛ ሬዲዮ ስርጭት (VOA) ቃለምልልስ መስጠታቸው አይዘነጋም:: አቶ መለስ ይህንን አስመልክቶ ከፓርላማው ለቀረባቸው ጥያቄ ሲመልሱ “አንድም ሰው አልተፈናቀለም” ብለው ሙልጭ አድርገው ዋሽተው ነበር:: እርስወም ድንበሩን በተመለከተ ለቀረበልወት ጥያቄ ከአቶ መለስ የተለየ መልስ አይደለም የሰጡት::
ተላላኪው ም/ል ጠቅላይ ሚ/ር እና የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ም/ል ደመቀ መኮንን; ሕወሓት የሚሳደበው አንሶ የአማራውን ሕዝብ ከተሳደቡት አቶ አለምነህ መኮንንና ከተላላኪ የአማራ የጦር መኮንኖች ጋር::
9. በአማራ ክልል ላይ ብቻ ያተኮረ በቤተሰብ ዕቅድ ስም እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል በወያኔ ተቀርጾ በናንተ የሚፈጸም አስነዋሪ ተግባር ነው:: የቤተሰብ ብዛትን መመጠን በሚል ምክንያት በአማራ ክልል ህዝብ ላይ ብቻ ያተኮረ የሴቶችን ማህጸን መቋጠር: የወንዶችን የዘር ፍሬ ማኮላሸት የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው:: አሁን ደግሞ ስልቱ ተቀይሮ የአማራ ሴቶችን የበሽታ መከላከያ ክትባት በማስመሰል መሀን የሚያደርግ መድሀኒት እንዲከተቡ ሲደረግ ብአዴን የወያኔን አላማ ለማስፈጸም ቀዳሚ ሆኖ የተሰለፈ ቡድን ነው::
10. አማሮችን ትጥቅ አስፈቱ የሚል መመሪያ በወረደላችሁ ጊዜ ምን ያህል ግፍ እንደፈጸማችሁ ትዝ ብሏችሁ ያውቃል? ወያኔ ይህን መመሪያ ሲያስተላልፍ ምክንያት እየፈጠረ አማሮችን ለመበቀል ካለው ፍላጎት በመነሳት ነበር:: ይህን ለማድረግ ደግሞ በራሱ ሰዎች ሳይሆን ህዝቡን እንወክለዋለን በምትሉት በናንተ ቢፈጸም ከተጠያቂነት ነጻ እንደሚሆን አሰበና “ህገወጥ መሳሪያ ታጣቂወችን መሳሪያቸውን እንዲያስገቡ አድርጉ” ሲል ትዕዛዝ ሰጣችሁ:: ይህን የበላይ ትእዛዝ ለማስፈጸም ነበር መሳሪያ ያልነበረውን ሳይቀር አስራችሁ የገረፋችሁት ብሎም የገደላችሁት:: የናንተ ህዝባዊነት መገለጫ የሰውን ክብር ገፋችሁ አባቶችን ሳይቀር ማሰቃየት ነው?
11. ለመሆኑ ቁልፍ በተባሉት የወታደራዊና የሲቭል ተቋማት ውስጥ የአማሮች ድርሻ ምን ያህል ነው? ይህስ አሳስቧችሁ ያውቃል? ወያኔ ገንዘብ የሚታፈስባቸውንና ስልጣንን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ተቋማትን ተቆጣጥሮ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ያገር ሀብት ዘርፎ ከሀገር ሲያስወጣ ምን ያደረጋችሁት ነገር አለ? የሀገር ሀብት ለሁሉም ክልሎች እንጅ ለአንድ ቡድን ብቻ አገልግሎት እንዳይሰጥ ለማድረግ የሰራችሁት ስራስ ምን አለ?
12. የብድርና የቁጠባ ወይም የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ አገልግሎት ለሁሉም አማራ ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ነው የምታከፋፍሉት? አገልግሎት ማግኘት የህዝብ መብት ነው:: እናንተ በአመራር ላይ የተቀመጣችሁ አገልግሎት ለማግኘት ሳይሆን ያለአድልዖ አገልግሎት ለመስጠት ነው:: ግን እናንተ በተግባር እያደረጋችሁ ያላችሁት ምንድን ነው? የአማራው ህዝብ በሙሉ እንደናንተ ፍጹም የወያኔ ሎሌ ሆኖ የታዘዘውን እንዲፈጽም: ሲገድሉት እንዲሞት ለማድረግ ስንት ግፍ ሰራችሁ? ጠላትና ወዳጅ በማለት ከፍላችሁ እንደናንተ ሊሆን ያልፈቀደውን ሰላማዊ ዜጋ በተለያየ መንገድ አላሰቃያችሁም?
13. ህዝቡ የፖለቲካ አማራጭ የማግኘት መብቱ በህገመንግስቱ የተጠበቀ ነው:: ይህንን የህዝብ መብት አክብራችሁ ህዝቡ በመረጠው እንዲተዳደር ምን አድርጋችኋል? በግድ ውጣ ተብሎ እንዲመርጥ የተደረገን ህዝብ ምርጫውን ነፍጋችሁ እጅ እጅ በሚል ውሸት እኛ ተመረጥን ስትሉ የብዙሀኑን መብት የነፈጋችሁና በህዝብ ላይ በጉልበት የነገሳችሁ አምባገነኖች እንደሆናችሁ አስተውላችሁት ታውቃላችሁ? መቸ ነው ወደህሊናችሁ የምትመለሱት?
14. ክልሎች ታሪክ እየጠቀሱ የመሬት ይገባኛል ጥያቄ ሲያነሱ የአማራ ክልል ግን በግላጭ በታሪክ የሚታወቀውን መሬቱን ማስከበር አልቻለም:: አንዳንድ የዋህ ሰዎች በአንድነት እስከኖርን ድረስ አንድ አካባቢ በዚህ ወይም በዚያ ክልል ቢካተት ችግር የለውም ሲሉ ይደመጣሉ:: እንደእኔ ከሆነ ይህ አባባል ፍጹም ስህተት ነው:: የመገንጠል መብት በተከበረበት ሀገር ትክክለኛ የራስን መሬት ሳይዙ ህገመንግስቱን ማጽደቅ አደጋው ቀላል አይደለም:: ዛሬ እየኖርን ያለነው አንድነቷ በተጠበቀ ሀገር ውስጥ አይደለም:: ህገመንግስቱም ቢሆን በአንድነት ለመቀጠላችን ዋስትና የሚሰጥ አይደለም:: የፈለገውን ማድረግ እየቻለ ያለው ወያኔ የተፈራረምንበትን ህገመንግስት መሰረት በማድረግ ነገ ብድግ ብሎ ለመገንጠል ወስኛለሁ ቢል በምን ነው ልንከላከል የምንችለው? የክልል መንግስታት ተፈራርመው ያጸደቁት ህገመንግስት በአለም አቀፍ መድረክ ተቀባይነት የማይኖረው ይመስላችኋል? በርግጥ በአሁኑ ጊዜ ከትግራይ ውጪ ያሉት ክልሎች መገንጠል እንፈልጋለን የማለት ድፍረቱ አይኖራቸውም: ድፍረቱ ቢኖራቸው እንኳ ወያኔ ጥያቄውን ለማዳፈንና ጥያቄ አቅራቢወችን ለመበቀል የሚሄድበት መንገድ አያጣም:: ነገር ግን የወያኔ ፈቃድ ሆኖ ክልሎች እንዲገነጣጠሉ ቢያደርግ ታሪካዊ መሬታችን ነው የምንለውን አካባቢ እንዴት ነው ማስመለስ የምንችለው? የአማራ ክልል ለመሆኑ ታሪካዊ መኖሪያ አካባቢው የቱ ነው? ይህ ጥያቄ ከተመለሰ በኋላ ነበር ህገመንግስቱ ቢፈረምም መፈረም የነበረበት:: ድርጅታችሁ አላግባብ የተወሰደበትን መሬት ለማስመለስ ያደረገው ምን ነገር አለ? “አማራ ነን:: ያላግባብ ወደትግራይ ክልል እንድንካተት ተደርገናል” እያሉ ለሚጮሁት የወልቃይት ወገኖቻችንስ ምን አደረጋችሁ? ታዲያ ለአማራው ህዝብ መብትና እኩልነት ያደረጋችሁት የሚያስፎክር ትግል የት አለ!
በርግጥ ማንም አሌ የማይለው ነገር ቢኖር አማራው ሀገሩ ኢትዮጵያ መሆኗን ነው: የኖረውም የሀገሪቱን ዳር ድንበር ለማስከበር: ሰላምና ጸጥታ ለማስፈን በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢወች ነው:: ይህችን ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አስከብሮ ለእኛ ያስረከበ ህዝብ እንደጠላት እየታደነ ሲገደል አባሪ ከመሆን ውጭ ለክልሉና ለህዝቡ ያበረከታችሁት አንድም አኩሪ ስራ የለም:: እናንተ የአማራውን ህዝብ የምታኮሩ ሳትሆኑ የምታሳፍሩ: የምታስከብሩ ሳትሆኑ የምታዋርዱ ሙሉ ትኩረታችሁን በሰፈር እየተደራጃችሁ ስልጣን ለመያዝ በርስ በርስ ሽኩቻ ጊዜአችሁን የምታባክኑ እንጥፍጣፊ ህዝባዊ ስሜት የሌላችሁ የምትገርሙ ሰዎች ናችሁ:: አይናችሁን ጨፍናችሁ በምትዋሹት ውሸት የአማራው ህዝብ አምኖ ይቀበለናል ብላችሁ አስባችሁ ከሆነ ተሳስታችኋል:: ብታምኑም ባታምኑም ህዝቡ እናንተን ህሊና የሚባል ነገር የሌላችሁ የወያኔ ጉዳይ አስፈጻሚ ሮቦቶች እንደሆናችሁ አድርጎ ነው የሚያያችሁ:: ወያኔም ቢሆን በፈለገው መንገድ ሊያሰልፋችሁ የሚችል ጅሎች አድርጎ እንደሚያያችሁና እንደሚታዘባችሁ አንጠራጠርም::
ሰሞኑን አቶ ኃይለማርያም ከፓርላማ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ የዶ/ር ደብረጽዮንን ስሜት ሳትገነዘቡ የቀራችሁ አይመስለኝም:: መቸም ኃይለማርያም ከራሳቸው የፈለቀች አንዲትም ቃል ሊናገሩ ድፍረት ይኖራቸዋል ተብሎ አይታሰብም:: ታዲያ ለሚቀርብላቸው ጥያቄ በወያኔ ተዘጋጅቶ የተሰጣቸውን መልስ ሸምድደው ገብተው “መንግሥታችን ርምጃ ይወስዳል…” ምናምን ሲሉ ዶክተሩ ስሜታቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው የፌዝ ፈገግታ ሲያሳዩ ነበር:: ዶ/ር ደብረጽዮን “ነገ ቃላችንን አጥፈን ተቃራኒውን ለማድረግ ብንወስንና ይህንን ባደባባይ ተናገር ብንለው ያው እንደለመደው መንግስታችን እንዲህ ያደርጋል እያለ መናገሩ አይቀርም:: የነዚህ ሰዎች ሰውነት ከምኑ ላይ ነው?” የሚል አይነት የግርምት ፈገግታ ነበር ሲያሳዩ የነበሩት:: ወያኔ እንዲህ የሚያሾፈው በሁላችሁም ላይ ነው::
አማራን የሚያህል ትልቅና ታሪካዊ ህዝብ እንወክላለን ብላችሁ ግን ለውርደትና ለእልቂት ስትዳርጉት: ለዚህ ውለታችሁ የሚሰጣችሁ ክፍያ በአናሳው ቡድን እንዲህ መሳቂያ መሳለቂያ መሆን ከሆነ ምን አይነት ህሊና ቢኖራችሁ ነው አሜን ብላችሁ ተሸክማችኋቸው የምትኖሩት:: “አማራ ሆዳም ነው” እንደሚሉን እናውቃለን:: የህዝብ ክብርና ነጻነት ከምንም በላይ አይደለም እንዴ! ባትበሉት ባትጠጡት ባፍንጫችሁ ቢወጣ ምን ነበረበት::
አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከመሃል የሶራ ዘፈን ተጫዋቹ አርቲስት ካሳሁን ታዬን ይዘው- በነ አለምነህ መኮንን ታጅበው በአማራው ሕዝብ ላይ ሲቀልዱበት ይታያል::
የጊዜ ጉዳይ ነው እንጅ እናንተም ሆናችሁ ጌቶቻችሁ ከፍርድ አታመልጡም: የውሻን ደም ከንቱ የማያስቀር ግፍን የሚቆጥር አምላክ አለ:: እስከዚያው ድረስ እናንተ ስልጣን ላይ ተቀምጣችሁ ለምታገኙት ፍርፋሪ አማራውን ረግጣችሁ እንድትይዙ የእድል በር የከፈተላችሁን የልደት ቀናችሁን በፌስታ ስታከብሩ እኛ ደግሞ ያችን የተረገመች ቀን በሀዘን እናስታውሳታለን:: መቸም ከአንጎል ክፍላችሁ የሆነ የጎደለ ነገር አለ መሰለኝ ጸጸትና ቁጭት ይሰማችኋል ብየ አላምንም:: የህዝብን አስተያየት በግብአትነት ተጠቅማችሁ ራሳችሁን ወደውስጥ አይታችሁ ስህተታችሁን ለማረም ከመሞከር ይልቅ የሚተቿችሁን ለማጥፋት የምትተጉ እንደሆናችሁ ግን እናውቃለን:: እስካሁን በሰራችሁት ስራ ክብር ያገኛችሁ መስሏችሁ ከሆነ ተሳስታችኋል:: እና ሞኝ ባያፍር የሞኝ ዘመድ ያፍር ነውና በስራችሁ ከማፈርና ከማዘን አልፈን ምነው ሳትወለዱ በናታችሁ ማህጸን ውስጥ ውሀ ሆናችሁ በቀራችሁ ነበር ብለን ድርጅታችሁ የተወለደበትን ቀን ብቻ ሳይሆን እናንተ የብአዴን ሰዎች እራሳችሁ የየተወለዳችሁበትን ቀን ሳይቀር እረግመናል::
The post በአማራው ስም የሕወሓት ተላላኪ የሆኑ ሆዳም የብአዴን አመራሮች በአማሮች ላይ የሠሯቸው 14 እርጉም ግፎች appeared first on Zehabesha Amharic.
ከጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ
ህወሃት መራሹ መንግስት በስልጤ ዞን ተማሪዎችን ከትምርት ቤት፤ የመንግስት ሰራተኞችን ከስራ ገበታ ለማፈናቀል የጀመረዉ ግልጽ ዘመቻ ትኩረት የተሰጠዉ በሚዲያ ብቻ ነዉ። እነዚህ የነገን የብሩህ ተስፋ እሸት የጨበጡ ወጣቶች የራሳችንን አሳተሳሰብና አመለካከት በምንሻዉ መልኩ እንተገብራለን በማለት አንባገነናዊዉን ስርዓት ፊት ለፊት እየተጋፈጡት እየደሙ እየቆሰሉ ነዉ።
አቅጣጫ የሚያሳይ፣ አይዞአቹ የሚል ወገንንም ይሻሉ። አንዳንድ ወንድሞችን ለማናገር ሞክሬ ነበር። ጉዳዩ አገራዊ ስለሆነ እንደ ስልጤ ጉዳይ ብቻ መታየት የለበትም በተናጠል የምናደርገዉ ነገር የለም ሲሉ ገልጸዉልኛል። አፋር ሲበደል፥ አፋር ያገር ያለህ ጩኸቴን ስሙኝ ብሎ ኢትዮጵያዊዉን በሙሉ ቢያሰልፍ፤ ሱማሌ፣አማራ፣ኦሮሞ ወዘተ በደልና ጭቆና ሲደርስበት የራሱን የመጀመሪያ የድረሱልኝ ጥሪ እያሰማ ወደ አገራዊ ጉዳይ የመቀየሩ ሒደት ያለና የነበረ ነዉ።
ስለዚህ ባገርም ይሁን ባህር ማዶ ያለዉ የስልጤ ማህበረሰብ አቅሙ በሚፈቅደዉና ማድረግ በሚችለዉ መጠን አስቸኳይ ስብሰባዎችን በማድረግ፣መግለጫዎችን በማዉጣት፣ ሰላማዊ ሰልፎችን በማድረግ ከቅበት እስከ ሁልባረግ፤ ከሁልባረግ እስከ ዳሎቻና ጦራ ያለዉን ወገን የመታደግ ሐላፊነት አለበት። ዝምታዉ በቅቶ የተቀናጀ ስራ የሚሰራበት ወሳኝ ወቅት ላይ ነን። ልብ ያለዉ ልብ ይበል። ጅግ ባሎቲ ይከታን!
ፎቶ ከሳንኩራ ወረዳ በአልም ገበያ ከተማ የተደረገ ተቃዉሞ ነው። ተማሪዎች እንደተጎዱ መረጃ ደርሶናል።
The post የስልጤ ዞን ወጣቶች የመንግስት ኃይሎችን እየተጋፈጡ ነው * የተጎዱ ተማሪዎች አሉ (አጭር ቪድዮም ይዘናል) appeared first on Zehabesha Amharic.
ሸንቁጥ አየለ
ልክ እንደ መምህር ግርማ ሁሉ ባህታዊ ገብረመስቀልን የዛሬ 20 አመት ህዝቡ ከኋላቸዉ እንደተከተላቸዉ ያስተዋለችዉ ወያኔ ባህታዊ ገብረመስቀልን በሀሰት ወንጅላ እስር ቤት ወርዉራ በርካታ ዉንጀላ አድርጋባቸዉ ነበር:: ማህበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ክርስቲያኖች መሃከል በእዉቀት መሰረት ላይ የቆመ ጽኑ እና ሀሰት የሌለበት እምነት የሚያራምድ እንደሆነ ሲያዉቁ አሸባሪ ብለዉ ድርጅቱን ለማፍረስ እየሰሩ ነበር:: አሁንም አጀንዳዉ የተንጠለጠለ ይመስላል::
እንግዲህ በርካታ ንጹሃንን ሀሰተኛ እና ወንጀለኛ ናቸዉ ለማለት በርካታ የሀሰት ፊልሞችን መስራት የለመደችዉ ወያኔ በመምህር ግርማ ላይ የተቀነባበረ የሀሰት ፊልማና ድራማ አዘጋጅታ ለህዝብ ታቀርባለች:: በህዝብ ለማስጠላት: ከህዝብ ለመነጠል::
ህዝቡ የሚያድነዉና የሚፈዉሰዉ እንዳይኖር ለማድረግ እንዲሁም ህዝቡ ተስፋ የሚያደርገዉ እንዳይኖር ለማድረግ ሁሉንም ደባዎችና ተንኮሎች
በመምሀር ግርማ ላይ ትሰራለች::ሀሰተኛ የሆኑ: የመፈወስ ጸጋ የሌላቸዉ: ጉበኞች: በክርስቶስ የማያምኑ: በቅናት የሚቃጠሉ : በርኩስ መንፈስ ሀይል የሚመሩ: ጉሰኞች የሆኑ ሰዎች ግን በእምነት ስም የሚነግዱ ሰዎችንም መልምላ በምስክርነት ታቀርባለች:: በቃ ይሄዉ ነዉ:: እዉነትን እፍን አድርጎ በገመድ መስቀል:: ከዚያም መምህር ግርማን ወንጀለኛ ናቸዉ እያሉ በሚዲያቸዉ ያናፋሉ::
እዉነተኞችን የሚፈራ : የሚያሳድድ: የሚወነጅል እና ከምድረ ገጽ እዉነትን የሚሰብኩ ወገኖች እንዲጠፋ የሚሰራ የማን ሀይል እንደሆነ የተገለጸ ነዉ:: እርኩሱ መንፈስ ነዉ:: ቢሆንም የኢየሱስ ክርስቶስን የጥበበ ስራ ማንም አያሸንፈዉም::
መምህር ግርማ ሁል ጊዜ ትምህርት ሲጀምሩ መዝሙር 68 ማለትም
1 እግዚአብሔር ይነሣ፥ ጠላቶቹም ይበተኑ፥ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ።
2 ጢስ እንደሚበንን እንዲሁ ይብነኑ ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ ኅጥኣን ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ።
3 ጻድቃንም ደስ ይበላቸው፥ በእግዚአብሔርም ፊት ሐሤት ያድርጉ፥ በደስታም ደስ ይበላቸው።
4 ለእግዚአብሔር ተቀኙ ለስሙም ዘምሩ ወደ ምድረ በዳ ለወጣም መንገድ አድርጉ ስሙ እግዚአብሔር ነው፥ በፊቱም ደስ ይበላችሁ በፊቱም ይደነግጣሉ።
የሚለዉን ሙሉዉን የመዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ አንብበዉ : አስከትለዉም የዮሐንስ ወንጌልን ቁጥር አንድን ሙሉዉን ማለትም 1 በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።
2 ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ።
3 ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።
4 በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።
5 ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም።
የሚለዉን የወንጌል ቃል ሙሉዉንም ዕራፍ አስተምረዉ እንዲሁም ልዩ ልዩ የኢየሱስ ክርስቶስን የማዳን ስራዎች ካስተማሩ ብኋላ የማዳን ስራቸዉን ይጀምራሉ:: በተጨማሪም እግዚአብሄር ለቅዱሳን እና ለመላዕክት እንዲሁም ለጻድቃን የሰጣቸዉን በርካታ ጸጋዎች እያጣቀሱ ካስተማሩ ብኋላ የሰዉን ልጅ እያጠቁ ያሉ ልዩ ልዩ አጋንንትና እርኩስ መንፈሶችን ከክቡሩ የሰዉ ልጅ ላይ ያባርራሉ::
በመላዉ አለም እዬሄዱ የአዳምን ልጆችም ጥቁር ነጭ ሳይሉ ይፈዉሳሉ:: ከአለም እስከ አለም ያለ እርኩስ መንፈስ ያለበት ሀይል እኝህ ሰዉ በሚሄዱበት ሁል ይርዳል:: ይርበተበታል:: በኢየሱስ ክርስቶስ ሀይልና ጥበብ ሁሉ ይከናወንላቸዋልና መምህር ግርማ ሲመጡ እርኩሳን መናፍስት ሁሉ ከክቡሩ የአዳም ልጅ ላይ ይወገዳል:: ልክ እንደ ቀደሙ ክርስቲያን ኢትዮጵያዊ አባቶች እንደ እነ አቡነ ዜናማርቆስ ያለ የማስተማርና የመፈወስ ጸጋ የተሰጣቸዉን መምህር ግርማን ግን ሰይጣን ማጥቃትና ማስጠቃት ከጀመረ ቆዬ:: የሰይጣን ሰራዊቱ ብዙ ነዉ:: ድምጹን ከፍ አድርጎ የሚጮህዉም በዛ:: በስማ በለዉ እኝህን ክርስቲያን አብረዉ የሚሳደቡ አንዳንድ የዋሃን በደራሽ ዉሃ ተወሳጅ የዋህ ሰዎችም ሞልተዋል::
ትምህርታቸዉን አንድ ቀን ሳይሰሙ: አስተምህሮታቸዉን ሳይመረምሩ: የማዳን ስራቸዉን ሳያስተዉሉ በኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን እና የመፈወስ ሚስጢር የሚሰሩትን የማዳን ስራ ሳይመረምሩ ዝም ብለዉ ከዲያቢሎስ ሀይል ጋር የሚጨፍሩ አንዳንድ የዋሃንም ያሳዝናሉ:: ሳይገባቸዉ እና በማያዉቁት ፈራጅ ሆነዉ የእርኩስ መንፈስ መጠቀሚያ ሆነዋልና እዉነትም ጸሎት ይገባቸዋል::
የቀደሙ ኢትዮጵያዉያንን ቅዱሳን አባቶችን ታሪክ እና ገድል በሙሉ ተረት ተረት እና ሀሰት ነዉ በማለት ወገቡን ገትሮ ስልጣን እና ጊዜ መከታ አድርጎ በሰዉ ስጋ ተመስሎ የመጣዉ እርኩስ መንፈስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ዉስጥ የሚደረጉ የክርስቶስን የማዳን ስራዎች ወንጀል ናቸዉ: አሸባሪነት ናቸዉ: ጽንፈኝነት ናቸዉ እንዲሁም ትምክህት ናቸዉ እያለ በመፈረጅ የክርስቶስን ቤት ለማፍረስ ከተጋ ይሄዉ እሩብ ምዕተ አመት ሆነዉ::የክርስቶስ ቤት ግን አስካሁን የኮሰመነ ቢመስልም አልፈረሰም:: ደግሞም አይፈርስም:: ሀይል እና ዘመን የክርስቶስ ኢየሱስ እንጅ የማንም አይደሉምና::
ኢየሱስ ክርስቶስን ወንጀለኛ ነዉ : ሀሰተኛ ነዉ ህዝቡን አታሏል ብለዉ እርኩስ መንፈስ ያለባቸዉ እና እግዚአብሄርን የማያዉቁ ሰዎች ስልጣንንና ዘመንን ተገን አድርገዉ እንደሰቀሉት ሁሉ በርካታ ንጽሁን የእግዚአብሄር ሰዎች አሁንም እየተሳደዱ ነዉ::
ጉልበትን እግዚአብሄር የሰጣቸዉ ዘመነኞች ሀሰት በመፈብረክ ነጹሃንን ያስወግዳሉ::
ሀሰት መሰረት ላይ የቆመ ዘመነኛ ባለ ጉልበት እዉነተኛ ክርስቲያኖችን : ሰዉን የሚፈዉሱትን የማንነት መሰረት ያላቸዉን : ኢትዮጵያዉያንን በእምነት አንድ የሚያደርጉትን መንፈሳዊ አባቶችን ፈጽሞ አይወዱም:: መምህር ግርማ ከአረብ እስከ ነጭ : ከነጭ እስከ ጥቁር እንዲሁም መላዉ ኢትዮጵያዊን ሁሉ እምነት ሳይለዩ በኢየሱስ ክርስቶስ ሀይል እየፈወሱ ሳለ በወንጀል ጠረጠርኳቸዉ ሲል ዘመነኛዉ ሀይል አስሯቸዋል::
የሆነ ሆኖ ግን በሀሰት የወንጀል ሰበብ ቢታሰሩም መምህር ግርማ ምንም የሚጎዱት ነገር የለም:: እሳቸዉ ቅዱስ ጳዉሎስ በሮሜ ሰዎች ምዕራፍ 8 እንዳለዉ እንዲህ የሚል ጽኑ እምነት አላቸዉና:-
35 ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? 36 ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።
37 በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
38 ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥
39 ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።
እናም በመምህር ግርማ መታሰር ማን ይጎዳል? እየተፈወሰ ያለዉ ህዝብ: በቀን በቀን የኢየሱስ ክርስቶስን የማዳን ስራ እያዬ የእምነት መሰረቱን እያጠበቀ ያለዉ ህዝብ ይጎዳል:: ማንስ ይጠቀማል? የሚጠቀመዉማ ያዉ እርኩስ መንፈስ ነዉ:: እንግዲህ ቢያንስ አንድ የማዳን እና የመፈወስ ጸጋ ያለዉን ሰዉ በሀሰት ወንጅሎ አሳስሯል እና ለጊዜዉ ደስታዉ ወደርም አይኖረዉም::
ቢሆንም ይሄ ሁሉ የሆነዉ እግዚአብሄር ቢፈቅድ እንጅ እርኩስ መንፈሥ በክርስቶስ አማኞች ላይ አንድም ስልጣን የለዉምና ሰይጣን ደስ እናዳይለዉ ጠላትም እንዳይኩራራ ቅዱስ ዳዊት እንዳለ እንዲህ እያል እንዘምራለን (መዝሙር 68):-
1 እግዚአብሔር ይነሣ፥ ጠላቶቹም ይበተኑ፥ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ።
2 ጢስ እንደሚበንን እንዲሁ ይብነኑ ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ ኅጥኣን ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ።
3 ጻድቃንም ደስ ይበላቸው፥ በእግዚአብሔርም ፊት ሐሤት ያድርጉ፥ በደስታም ደስ ይበላቸው።
4 ለእግዚአብሔር ተቀኙ ለስሙም ዘምሩ ወደ ምድረ በዳ ለወጣም መንገድ አድርጉ ስሙ እግዚአብሔር ነው፥ በፊቱም ደስ ይበላችሁ በፊቱም ይደነግጣሉ።
The post መምህር ግርማን ዘመነኞች ለምን ወንጀለኛ ብለዉ ወደ እስር ቤት ከተቷቸዉ? appeared first on Zehabesha Amharic.
ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው በማታለል ወንጀል ተጠርጥረው ጥቅምት 17 ቀን 2008 ዓ.ም. በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት መምህር (አጥማቂ) ግርማ ወንድሙ፣ አያት የሚገኘው መኖርያ ቤታቸው በፖሊስ መበርበሩ ታወቀ፡፡
ፖሊስ ቤታቸውን ሲበረብር ያገኘው ነገር ባይገለጽም፣ ለተጠረጠሩበት የወንጀል ድርጊት ማስረጃ የሚሆነውና ሌሎች ተጨማሪ ነገሮች ፍለጋ ሳይሆን እንዳልቀረ ምንጮች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
መምህር ግርማ ከሁለት ወራት በፊት የእስር ትዕዛዝ ተሰጥቶባቸው እንደነበር ተጠቁሞ፣ አንድ ቀን ፖሊስ ጣቢያ አድረው ጥቅምት 18 ቀን 2008 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል፡፡ በወቅቱም ፖሊስ የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጠይቆባቸው ነበር፡፡ የፖሊስን ጥያቄ በመቃወም የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ከእስር እንዲፈቱ በጠበቃቸውና በራሳቸው የጠየቁ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ አልተቀበላቸውም፡፡
መምህር ግርማ የተጠረጠሩበትን የማታለል ወንጀል የፈጸሙት፣ በመስከረም ወር 2006 ዓ.ም. እንደሆነና በየካ ክፍለ ከተማ ወሰን ግሮሰሪ አካባቢ ነዋሪ መሆናቸው ከተጠቆመው አቶ በላይነህ ከበደ መኖርያ ቤት ጋር የተገናኘ መሆኑ በምርመራው ተገልጿል፡፡
ፖሊስ በምርመራው እንዳረጋገጠው አቶ በላይነህ ከትዳር አጋራቸው ጋር የሚኖሩበት በ400 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ መኖርያ ቤት ነበራቸው፡፡ አቶ በላይነህ ቤታቸውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ካልሸጡ ሊሞቱ እንደሚችሉ መምህር ግርማ ሲነግሯቸው፣ ከፍተኛ ዋጋ ያወጣላቸው የነበረ ቤታቸውን በ800 ሺሕ ብር ለመሸጥ መገደዳቸውን የፖሊስ ምርመራ ይጠቁማል፡፡
መምህር ግርማ ቤቱን ማሸጥ ብቻ ሳይበቃቸው፣ ገንዘቡ እንዲበረክትላቸው እንዲፀለይበት እንዲሰጧቸው የተጠየቁት አቶ በላይነህ፣ ገንዘቡን መስጠታቸውን ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስረድቷል፡፡ ሊፀለይበት ወደ መምህር ግርማ ቤት ተወስዷል የተባለው ገንዘብ ውሎ በማደሩ፣ አቶ በላይነህ ወደ መምህር ግርማ ቤት ስልክ ሲደውሉ ስልኩ አልሠራ እንዳላቸውና ወደ ውጭ አገር መሄዳቸውን እንደሰሙ መግለጻቸው በፖሊስ ተጠቅሷል፡፡
ተጠርጣሪው መምህር ግርማ ለፍርድ ቤቱ ከሳሻቸውን ቀይ ይሁኑ ጥቁር እንደማያውቋቸውና ሆን ተብሎ የተሸረበባቸው ሴራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የተጠረጠሩበት ወንጀል ዋስትና የማያስከለክል መሆኑን በመግለጽ በዋስ እንዲለቀቁ ቢጠይቁም፣ ፍርድ ቤቱ አልተቀበላቸውም፡፡ ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ባለመቀበል ሰባት ቀናትን በመፍቀድ ለጥቅምት 25 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
The post ፖሊስ የመምህር ግርማን ቤት በረበረ appeared first on Zehabesha Amharic.
የዛሬ ሳምንት ገደማ በዝነኛው የቴሌቪዥን ሾው አቅራቢ ቢል ኮዝቢ የአስገድዶ መድፈር ድርጊትና ሙከራ ተፈጽሞብናል ከሚሉ ሴቶች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በአንድ ቦታ ተሰባስበው ነበር፡፡፡ ኤን ቢ ሲ በተሰኘው የቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው ታሪካቸውን የተናገሩት 29 ሴቶች በቢል ኮዝቢ ስለተፈጸመባቸው የአስገድዶ መድፈር ጥቃትና እሱን ተከትሎ ስለደረሰባቸው ማህበራዊ፣ ስነ ልቦናዊና ቤተሰባዊ
ቀውስ አውርተዋል፡፡
የቢል ኮዝቢ ከሳሾች
አብዛኞቹ አሁን እድሜያቸው ከ40 እና 50ዎቹ በላይ ሆኗቸዋል፡፡ በወጣትነታቸው የፊልም ተዋናይ፣ ሞዴልና ስራ ፈጣሪዎች ነበሩ፡፡ ሁሉም በሰውዬው የደረሠባቸውን ጥቃት ሲያወሩ ከፍተኛ ጭካኔ እንደተፈጸመባቸው ይገልጻሉ፡ ፡ የተለያየ የህይወት ታሪክና የስራ ዘመን የነበራቸው እነዚህ ሴቶች በቢል ኮዝቢ የወሲብ ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ሲገልጹ ከድርጊቱ አስቀድሞ ተመሳሳይ ሁኔታዎችን እንዳስተናገዱ
ተናግረዋል፡፡
ከከሳሾቹ መካከል አንዷ ሰኒ
ዌልስ ትባላለች፡፡ እሷ እንደምትገልጸው እ.ኤ.አ በ1965 ገና የ17 ዓመት ወጣት እያለች በቢል ኮዝቢ ሁለት ጊዜ የወሲብ ጥቃት ተፈጽሞባታል፡፡
‹‹ኮካ ጋብዞኝ እሱን ጠጣሁ፡ ፡ ከዚያ በኋላ ለ25 ደቂቃዎች ያህል ራሴን አላውቅም ነበር፡፡ ስነቃ እርቃኔን ነበርኩ፡፡ ክፍሉ ውስጥ ብቻዬን ነኝ፡፡ የተፈጠረው ነገር ሊገባኝ አልቻለም›› ትላለች፡፡
‹‹ወዲያው ልብሴን ለባብሼ በኮንትራት ታክሲ ወደ እናቴ ቤት ሄድኩ፤ሻወር ወስጄ ከተረጋጋሁ በኋላ ወደ እናቴ ቢሮ ሄጄ ጠራኋትና ‹እማዬ ቢል ኮዝቢ የደፈረኝ ይመስለኛል› አልኳት፡፡ እሷም በድንጋጤ ‹ወይኔ አምላኬ! አይሆንም! እየቀለድሽ መሆን አለበት፤ ሊሆን አይችልም› አለች፡ ፡ ቢል ኮዝቢ በህይወቴ እምነቴን ከሠጠኋቸውና ከከዱኝ ሰዎች መካከል አንደኛውና የመጀመሪያው ነው››
ሲንድራ ላድ ሌላኛዋ የቢል ኮዝቢ ከሳሽ ናት፡፡ እ.ኤ.አ በ1969 በሰውዬው ጥቃት ሲፈጸምባት ኒውዮርክ ከተማ ውስጥ በፕሮዲውሰርነት ትሰራ ነበር፡፡ እሷ እንደምትለው አንድ ቀን ቢል ኮዝቢ በስራ ጉዳይ ለመነጋገር በጓደኛው አፓርትመንት ውስጥ ቀጠራት፡፡፡ ‹‹በቀጠሮዬ ሠዓት በተባልኩበት ቦታ ተገኘሁ፤ ትንሽ የራስ ምታት እየተሰማኝ ስለነበር ነገርኩት፡፡ ‹ባንድ ጊዜ ሊያድንሽ የሚችል ተአምራዊ መድሃኒት አለኝ፡፡ ዶክተሬ የሠጠኝ ነው› አለኝና ወደ አንድ ክፍል ገብቶ ኪኒን ይዞ ወጣ፡፡ ስለምንነቱ አልነገረኝም፡፡ ስጠይቀው ‹አታምኝኝም እንዴ?› አለኝ፡፡ አምነዋል፡፡ ምክንያቱም እሱ ቢል ኮዝቢ ነው፡፡
መድሃኒቱን ከወሰድኩ በኋላ ሌሊቱን ሙሉ ምን እንደተፈጠረ አላውቅም ነበር፡፡ የማስታውሰው ጥዋት ከእንቅልፌ ስነቃ እርቃኔን እንደነበርኩ ነው፡ ፡ ወዲያው ራሴን ነው የወቀስኩ፡፡ ‹ ምንድነው ያደረኩት? በጣም ጠጥቼ ነበር ማለት ነው?› እያልኩ ነበር›› ትላለች ሲንድራ ላድ፡፡
በቴሌቪዥን ፕሮግራሙ ላይ ቀርበው በቢል ኮዝቢ የደረሰባቸውን የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ታሪክ ከተናገሩት ሴቶች መካከል ታዋቂ የፊልም ተዋናይትና ሞዴል የሆነችው ቤቨርሊ ጆንሰን አንዷ ናት፡፡ ቢል ኮዝቢ ከ40 በላይ በሚሆኑ ሴቶች ተመሳሳይ ክስ ቢቀርብበትም እስካሁን ድርጊቱን እንዳልፈጸመ እየገለጸ ነው፡፡
ቬቨርሊ ጆንሰን እንደምትለው ከሆነ የሴቶቹ አንድ ላይ ተሰባስበው ውይይት ማድረጋቸውና ድምጻቸውን ማሰማታቸው ለውጥ ሊያመጣ ይችላል፡፡ ‹‹ብዙ ባይሆንም ሴቶቹ ተሰባስበን እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምረናል፡፡ ሃይላችን ድምጻችን ማሰማታችን መሆኑ ገብቶናል›› ትላለች፡፡
አሁን የ62 አመት ሴት የሆነችው ጆንሰን በ1980ዎቹ አጋማሽ ለቢል ኮዝቢ ሾው በሰውዬው መኖሪያ ቤት ተገኝታ የሙከራ ቀረጻ ልታደርግ በነበረበት ወቅት ነው ጥቃት የተፈጸመባት – እሷ እንደምትለው፡፡ ስፕሪስ ሰጥቷት እንደጠጣችና ከዚያም በኋላ ወገቧን አቅፎ በመያዝ ሲታገላት እንደነበር በመጨረሻም የነበረችበትን ሁኔታ እንደማታስታውስ ገልጻለች፡፡
የኤንቢሲዋ ጋዜጠኛ ኬቲ ስኖው ካናገረቻቸው ሴቶች መካከል አንዷ የሆነችው ጀኒ ዳዝም በ2005 በቢል ኮዝቢ የወሲብ ጥቃት እንደተፈፀመባት ዘርዝራለች፡፡
ዝነኛው የቴሌቪዥን አቅራቢና የፊልም ሰው ቢል ኮዝቢ እ.ኤ.አ ከ1960ዎቹ ጀምሮ እስከ 2008 ድረስ ባለው ጊዜ የወሲብ ጥቃት ፈጽሞብና ያሉ በርካታ ሴቶች ‹አቤት› ማለት የጀመሩት በቅርቡ ነው፡፡ የተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች የሴቶቹን ክስ የሰውዬውን ስምና ዝና ለመናድ ተብሎ ታስቦበት የመጣ ነው ሲሉ ያጣጥሉታል፡፡ ሌሎች ደግሞ እውነታው መገለጥ አለበት የሚል አቋም ይዘው በመገናኛ ብዙሃን ፊት ቀርበው ይከራከራሉ፡፡
በ1989 የአስገድዶ መድፈር ሙከራ ተደርጎብኛል የምትለው ኤደን ቲርል ክሱን የሚያጣጥሉ ሰዎችን ትተቻለች፡፡ ‹‹የእኛን ተሰባስቦ ሰውዬውን መክሰሳችን ዝናውን ለመበከል ታስቦ የተደረገ አስመስለው የሚናገሩ ሰዎች ሞኝ ናቸው፡ ፡ ሰውዬው እኮ ዝናው እየደበዘዘ ከመጣ ሰነባብቷል፡ ፡ እኛ ድምጻችን ከፍ አድርገን እየጮህን ያለነው ልክ ያልሆነ ነገር አለ ለማለት ነው›› ትላለች፡፡
በኮዝቢ ሾው ፕሮግራም ላይ የፖሊስ ኦፊሰር ገፀባህርይ ወክላ የተወነችው ኤደን ቲርል ኮዝቢ ጥቃት ሊፈጽምባት የነበረው በመልበሻ ክፍል ውስጥ መሆኑን ታስታውሳለች፡፡ ‹‹ በሩን ቆልፎ ይታገለኝ ጀመር፤ ‹‹ቢል አንተ እኮ የልጅነት አርአያየ ነህ፤ አንተ እያየሁ ነው ያደኩት፡፡ እንዴት እንዲህ ታደርጋለህ?›› አልኩ፡፡ እሱም ‹እንደሱ አትበይ፤ ሁሉም ሴቶች የሚሉኝ እሱን ነው›› ሲል መለሰልኝና አቅፎ ‹‹ፍቅር እንስራ›› አለኝ›› በማለት ተናግራለች፡፡
ስራ ፈጣሪዋ ሊንዳ ኪርፓትሪክ ሌላኛዋ የቢል ኮዝቢ የወሲብ ጥቃት ሰለባ ነኝ ባይ ሴት ናት፡፡ አሁን 58 ዓመትዋ ላይ የምትገኘው ሊንዳ የ25 ዓመት ወጣት እያለች ኮዝቢ መጠጥ ካጠጣት በኋላ ጥቃት እንደፈጸመባትና በቀጣዩ ቀን ይቅርታ እንደጠየቃት ገልጻለች፡፡ የ78 ዓመቱ ዊሊያም ሄነሪ ኮዝቢ ፍርድ ቤት ባይቀርብም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የወሲብ ጥቃት ፈጽሞብናል በሚሉ ሴቶች ቅሬታ ተከቧል፡ ፡ ከእሱ ጋር ረዳት ሆኖ የሠራው ጆሴፍ ፊሊፕስ የተባለ ሰውም ክሱ እውነተኛ ሊሆን እንደሚችል በተለይ ከሲ ኤን ኤን ጋር ባደረገው ቆይታ መግለጹ ይታወሳል፡፡ ኮዝቢና በዙሪያው ያሉ ሰዎች ግን
ያስተባብላሉ፡፡
ከቁምነገር መጽሔት የተገኘ


The post የቢል ኮዝቢ ከሳሾች ተሰባስበዋል – ‘እማዬ ቢል ኮዝቢ የደፈረኝ ይመስለኛል’ appeared first on Zehabesha Amharic.
‹‹ጀማዬ ነይ ነይ
ጀማዬ…
የመውደድ ነገር ብትሰማ ዶሮ
ልጀቿን ይዛ ጓሮ ለጓሮ…››
የሚለው የአማርኛ ዘፈን በዚያን (ምናልባት ለህፃናት ካልሆነ በቀር) ተሻሽሎ ቀርቦ ባደመጥንበት ጊዜም ቢሆን ለማናችንም አዲስ አልነበረም፡ ፡ ይልቅስ አዲስ ሆኖ የተሰማን ኤፍሬም ታምሩ የዛሬ 34 ዓመት ግድም ማለትም በ1974 ዓ.ም ባስቀረፀው የካሴት ክር ውስጥ ‹‹መሪ›› ዜማ አድርጎ በተጫወተው ጊዜ ነበር፡፡
በወቅቱ ኤፍሬም ከዚህ ካሴቱ በፊት አንድ ክር ማሳተሙን የሚያውቁ (የዘፈን አድማጮች) ጥቂት ሰዎች ብቻ ነበሩ፡፡
‹‹ገና ልጅ ነኝ ጋሜ››፤ ‹‹እንዲያው ዘራፌዋ››፣ እና ‹‹መላዬ መላዬ›› የተባሉትን የህዝብ ዜማዎችን የዘፈነበት ይኸው የመጀመሪያ ስብሰቡ እምብዛም አልተደመጠም፡፡ ያለመደመጡ በዘፈኖቹ ኃይል ማጣት ወይንም በዘፋኙ ድምፀ ደካማነት አልበረም፡ ፡ የአሳታሚው ‹‹ሰንሻይን›› ሙዚቃ ቤት አቀራረፅ ድክመት ነበረበት፡፡ የቅጂ ጥራት ጉድለት፡፡
‹‹ጀማዬ ነይ ነይ›› የሚለውን የህዝብ ዜማ የተጫወተበት ሁለተኛው ክሩ በወጣ ግዜ ግን፣ ወደ የኢትዮጵያ የዘፈን መድረክ ተስፋ የሚጣልበት አንድ አዲስ ድምፃዊ እየመጣ መሆኑን የሚጠቁም ምልክት ታየ፡፡
ይህን ክር (በተለይም ጀማዬንና አካል ሸጋን) ባዳመጡ ሰዎች ዙሪያ የተካሄደው ክርክር ትዝ ይለኛል፡፡ ‹‹ድምፁ የሙሉ ቀንን ይመስላል፡፡ የለም የጌታቸው ካሣ.. ይመስላል የሚሉ ዓይነቶችን ማለት ነው፡፡ ‹‹ቅር-ቅር እያለኝ ሳጣሽ እየከፋኝ…›› የሚለውን ዜማ የሰሙትማ ጌታቸው ካሣ ራሱ ነው በማለት ለውርርድ የቃጣቸውም ነበሩ፡፡ ሆነም ቀረም ካሴቱ ሥሙንና ፎቶግራፉን ይዞ በመውጣቱ ኤፍሬም ታምሩ መሆኑን ሊቀበሉት ግድ ሆኗል፡፡
የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ባለፉት 50 ዓመታት ያፈራቸውን ድምፃውያን በሦስት ክፍሎች ማየት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያው ጥላሁን ገሠሠ በፊት ቀደምትነት የሚመራው ቡድን ሲሆን፣ የመካከለኛ ዘመን (ከ1970ወዲህ ያለው በሙሉ ቀን መለሰ የሚመራው ‹‹ወጣቱ›› ኤፍሬም ታምሩ የሚገኝበት የወንድ ዘፋኞች ቡድን ነው፡፡ ሦስተኛውና የመጨረሻው ደግሞ በ1980ዎቹ የሚገኘው በነአበበ ተካና መሰሎቹ የሚመራው ቡድን ነው፡፡ ይህ ምድብ አንስት ድምፃውያንን አይመለከትም፡፡
ኤፍሬም ለብቻው ያስቀረፃቸው ካሴቶች ቁጥር (ቅፅ) 12 ሲሆን፣ በተጨማሪም ከሌሎች ድምፃውያን ጋር በኅብረት አራት ዜማዎች የተጫወታቸው ሁለት ካሴቶች ታትመውለታል፡ ፡ ለማስታወስም ያህል ‹‹ብቅ በይ ሙና›› ያለበት አምባሰል ያሳተመውና ‹‹የብሩህ ተስፋ እሸት›› የሚለው ካሴት ላይ ‹‹ጎዳናው›› የሚለው ዜማ ነው፡
ኤፍሬም ‹‹ጀማዬ››ን ካሳተመ በኋላ በዓመቱ ‹‹እንደገና›› በሚለው ዜማ የሚመራ ሦስት ካሴት አቀረበ፡፡
‹‹ተሰናብታኝ ሄደች
ተሰናብታኝ…
ወጣ አለች ከደጅ
ልከተላት እንጅ…››
በጊዜው በሦስቱም ካሴቶች ውስጥ ከቀረቡት ዘፈኖች ሦስት እጅ ያህሉ ድርሰቶች የህዝብ ዜማና ግጥሞች ነበሩ፡፡ ‹‹እንዲያው ዘራፌዋ፣ መላዬ መላዬ፣ ጀማዬ ነይ ነይ፣ አንቺዬ ጎጃም እንዴት ነሽ፣ ሸግዬ፣ አካል ሸጋ፣ የሰማይ ላይ ኮከብ፣ ሸግዬ፣ ተከልከይ በዓዋጅ፣ ልኑር ካንቺ ጋር ወዘተ ሲሆኑ በኋላም ከኩኩ ሰብስቤ ጋር ‹‹ነይ ዛልነት››ን ተጫውቷል፡፡
የኤፍሬም ሦስተኛው ካሴት (ፍቅር እንደገና) ከታተመ በኋላ ግን ‹‹ድምፁ እገሌ የተባለውን ዘፋኝ ድምፅ ይመስላል›› መባሉ ቀረና ራሱ ኤፍሬም ታምሩ የራሱ የሆነ (Original) ወጥ አዘፋፈን ያለው መሆኑ ታወቀለት፡፡ ከፒያሳና መርካቶ አደባባዮች አልፎ በኢትዮጵያ የገጠር መንደሮችና ሠፈሮች ድረስ ዘልቆ በወጣቶች አካባቢ እንደሱ ለመዝፈን መሞከር ዘይቤ መሆን ጀመረ፡፡ ኤፍሬም የተወለደው በጎጃም ክፍለ አገር ደጀን ከተማ ውስጥ ነው፡፡ አራተኛውንና የኤፍሬምን ዝና ከፍ ያደረገው ‹‹ነይልኝ ነይልኝ!›› የሚለውን ዘፈን የያዘው ቅፅ ነበር፡፡ ግጥሙ የኢትዮጵያን ከተሞች እየዞረ ስንኞቹን የሚያስረው የትውልድ መንደሩን ደጀንን እያጣቀሰ ነበር፡፡
‹‹ካሥመራ ካርባ ምንጭ ከደሴም ሳትገኝ፣
ከሸዋ ካሩሲ ከባሌም
ሳትገኝ፣
ከጎጃም ከጎንደር
ሐረር ላይ ሳትገኝ፣
ባዋጅ በውደድ አዝላኝ
እያለች ወዳጄን፣
ማግኘት ቤቱን ይሥራ
ገባች አሉን ደጀን፡፡››››
ከዚህ በኋላ ኤፍሬም ሁሉምን ቦታ ይዞልን
ይመጣ ይሆን?የሚልለትና የሚናፈቅ ድምፃዊ ሆነ፡ ፡ በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የራሱን አድማጮች ፈጠረ፡፡
በአገራችን በሙዚቃው መስክ ከሱ በፊት ለጥቂት ሰዎች ብቻ እንደተሰጥዖ ሆኖ የቆየው (ለምሳሌ ካሣ ተሰማ፣ ጌታቸው ካሣ) ወንድ ወፍራም (Base) ድምፅ ይዞ ከሙዚቃ መንደር ገባ፡፡ በሚያሳዝንና በሚቁረጠረጥ ድምፅ ከፍታና ዝቅታ ‹‹ርክርክ›› እየሰራ በማንጎራጎር ዘመነኞች ከሆኑት ከሌሎች ወጣት ድምፃውያን የሚለይበትን የራሱን ያዘፋፈን (style) ባህርይ አሳየ፡፡ ይህ ችሎታው ካገራችን አድማጮች አልፎ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውንን መንፈስ ማረከና ተደማጭነቱ ድንበር የለሽ ሆነ፡፡
ነይልኝ ከወጣ ከዓመት ከመንፈቅ በኋላ ‹‹ልመደው››ን ይዞ ከተፍ አለ
‹‹ልመደው ልመደው ሆዴ
እንግዲህ እደር በዘዴ
አካል ሰው ቀረች ዘመዴ››
እንደ ብሔራዊ መዝሙር እዚያም እዚህም
የቻለ አንጎራጎረው፤ ያቃተው አፏጨው፡፡ ‹‹የድንገት እንግዳ፣ ብትውልም መልካም ውለታ፣ መሸ ደህና እደሩ፣ አጓጓዘን ጎዳና መንገዱ›› የሰማ የማይረሳቸው ተወዳጅ ዘፈኖቹ ሆኑና ይበልጥ አስወደዱት፡፡
በዚህም ወቅት ቢሆን በአዘፋፈን ችሎታው ላይ ሌላ ችሎታ እንዳለው ለማሳየት አልቦዘነም፤ የሚዘፍናቸውን ዜማዎች ራሱ ይመርጣል፡፡ ቅንብሩ በሚዘጋጅበት ጊዜ ሃሳብ እያዋጣ ዜማዎች የተሻለ የመደመጥ ጉልበት እንዲኖራቸው የሚጥር መሆኑን የሥራ ውጤቶቹ ብቻ ሳይሆኑ ሙያተኞችም የሚመሰክሩለት ድምፃዊ ሆነ፡፡
ኤፍሬም በብዙዎች ድምፃውያን ላይ ጎልተው የሚታዩ የአርቲስት እንከኖች የሉበትም ይሉታል፡፡ ለሁሉም ነገር መጠን አለው የሚል ስሜት ያጠላበታል ይላሉ፡፡ ትዳሩን ያከብራል፡፡ ሙያውን ያከብራል፡፡ በአልባሌ ቦታዎችና ድርጊቶች ሥሙ አይነሳም፡፡ ትዕቢት ሳይሆን ሙያውን አክብሮ የማስከበር ኩራቱ አያሌ ነው፡፡ የሚድያዎችን ድጋፍና ሽፋን ጠይቆ አያውቅም፡ ፡ ለሱ ድጋፍና ሽፋን እየሠራ የሚያቀርባቸው ሥራዎቹ ብቻ ናቸው፡፡ከነኩኩ ሰብስቤና ሂሩት በቀለ ጋር ‹‹ነይ ዛሌን፣ ብቅ በይ ሙናን፣ የፍቅርን ቅጣትን…›› የመሳሰሉ ዘፈኖችን በመጫወት ብቃቱን በኅብረት አሰራር ውስጥም አሳየ፡ ፡፡ ለሌሎች ድምፃውያን ከኤፍሬም ታምሩ ጋር አብሮ መዝፈን በስለት የሚገኝ አጋጣሚ እስኪመስል ተናፈቀ፡፡ በሙዚቃ ማኅበር በተዘጋጀው ‹‹የብሩህ ተስፋ እሸት›› ሰብስብ ውስጥ ከዘጠኝ ምርጥ ድምፃውያን ጋር ሲቀርብ በካሴቱ በሁለቱም በኩል ኤፍሬም ‹‹ጉዳናዬ››ና የህብረ መዝሙሩ መሪ ድምፃዊ ሆኖ መቅረቡን ያስታውሷል፡፡ ከዚህ በኋላ ኤፍሬም ማለት በሁሉም መስክ የተሳካለት ሆነ፡፡ ድምፃዊ ሆኖ መቅረቡን ያስታውሷል፡፡ ከዚህ በኋላ ኤፍሬም ማለት በሁሉም መስክ የተሳካለት ሆነ፡፡ የድምፃዊ ኤፍሬም ካሴት ወጣ ማለት ‹‹እስኪ አሰማኝ›› የማይባልበት ዝም ተብሎ የሚገዛበት ሆነ! አባት፣ እናትና ልጆች በነፍስ ወከፍ ወደ ቤታቸው ይዘውት የሚገቡት ዘፋኝ ሆነ፡፡ በርግጥ ‹‹እንደውም አልቃሻ ነው… ወዘተ›› እያሉ የሚያማርሩ ጥቂት አድማጮች የሉትም ማለት አይደለም፡፡ እንግዲህ ኤፍሬም ኢትዮጵያ አነሰችው፤ የውጭውን አለም ማየት የሕይወት ጥሪው ሆነ፡፡
በአገር ውስጥ እየኖረ ዘፈን ለማሳተም የመጨረሻ የሆነውን ካሴት አሳተመ፡፡
‹‹ወዳጄ በፍቅር ልቤ ነደደ
አንቺን እየለመደ፡፡
ሁሉም እንደ ቡና ቁርስ
ሲያማኝ ያመሻል
የሥም ስብራት በምን ወጌሻ
በምን ይታሻል
አሞራ ምን አገር አለው
ይሄዳል ሰማይ ለሰማይ…››
የሚለውን መሠል ዜማዎችን በጥሩ አስተጃጀብና በላቀ የአዘፋፈን ስልት ካቀረበልን በኋላ ወደ አሜሪካን ሄደ፡፡ ‹‹ወለባ ነይ፣ ፍቅር ትዝታ፣ የወደዱ ሰሞን፣ መውደድ አልፍሽ፣ ጉብል ሸጋ ማሬን…›› የመሳሰሉ ዜማዎችን ለሚወዱት አድማጮች ‹‹የመሰናበቻ›› የሚል አሳተሞ ተጓዘ ማለቱ ይሻል ይሆን?
ወደ አሜሪካን እስከሄደበት ጊዜ ድረስ፣ ስድስት ካሴቶችን በግል እና ሁለት ካሴቶችን በኅብረት በድምሩ ስምንት ካሴቶችን ያሳተመ ሲሆን፤ ከዚያ ወዲህ አራት ካሴቶችን (አልበም ይባላል በአሁኑ አጠራር) ልኳል፡፡
ኤፍሬም በአሜሪካ እየዘፈነም እየተማረም ሲኖር ቆይቶ ወደሀገር ቤት ጠቅልሎ ከገባ 4 ዓመት ሆኖታል፡ ፡ ኤፍሬም የሚወደድ ድምፅ ያለው ዘፋኝ ብቻ ሳይሆን መልከ መልካምና ረጅም ቁመና ያለው ጠባየ ትሁት አርቲስት መሆኑን የሚያውቁት ይናገራሉ፡፡
ይህን የዛሬ 18 ዓመት ግድም ማለትም ግንቦት 30 ቀን 1990 ዓ.ም በኤግዚቢሽን ማዕከል ለጥቆም በአዲስ አበባ ስታዲየም ከዚያም በሸራተን አዲስ ባቀረበው ዝግጅቱ አስመስክሯል፡፡ በወቅቱ ብዛት ያላቸውን ዜማዎች ባያቀርብም በተቻለው ዓቅም ለመታደም የቀረቡትን ተመልካቾች ለማስደሰት ሲጥር ታይቷል፡፡
ያንን የሚያክል ግዙፍ አካል ዞሮ ይወርድ የነበረው
እስክስታ እሱ ብቻም ሳይሆን ታዳሚ አብሮት እንዲዘፍን
ያደርግ የነበረው ጥረት የራሱን ምርጫ ብቻ ሳይሆን ‹‹ምን
ልዝፈንላችሁ›› እያለ በመጠየቅ የተመልካቹን ፍላጎት
ለማርካት የነበረው ጉጉት በየመሃሉ እረፍት ለመውሰድ ሳይቀር ፈቃድ በመጠየቅ ታዛዣችሁ ነኝ የማለት ትህትናው ዕለቱን የማይረሳ እሱንም የበለጠ የሚወደድ አድርጎት አልፏል ማለት ማጋነን አይደለም፡፡
ኤፍሬም የትውልድ አገሩን ኢትዮጵያንና ወገኖቹን አጥብቆ የሚወድ መሆኑን በሁለት መንገዶች አሳይቷል፡ አንዱ አሜሪካ ከሄደ በኋላ በሚልካቸው አልበሞቹ ውስጥ ‹‹ወይ አገር! አገሬ››ን እየሸጎጠ በመላክ ሲሆን… በሌላም በኩል በየዓመቱ እየመጣ ዕረፍቱን በወገኖቹ መካከል በማሳለፍ!… እንግዲህ አሜሪካን ከሄደ 25 ዓመት ያለፈው ሲሆን እዚያም ምናልባት አራት ኮምፓክት ዲስኮችን አሳትሟል፡፡ በተለይ የሩቅ ምሥራቅ፣ የሱዳንና የኢትዮጵያ እረኞች ውሁድ የአዘፋፈን ቃና ተመርኩዞ የተቀናበረው
‹‹ፍቅር ማገዶ አይደል አይደፋ እንዳመድ ተበጥሶ አይጣል መውደድ እንደ ገመድ ተመቸሽ ወይ ኑሮ
ለኔስ እጅ አጠረኝ እህል ውሃው
ሞልቶ
ሰው እየቸገረኝ…››
የሚለውና ‹‹ሰላሜ ነሽ›› የሚሉት ዘፈኖች አቻ የሌለውንና የመጠቀ የድምፃዊነት ችሎታውን ለመለካት ያስቻሉ ሥራዎቹ ነበሩ፡፡ ለጥቆም ‹‹ሽጉጥ ታጥቄና ወይ ልቤን›› ያሉበትን አልበም የላከ ቢሆንም በቅጂ ጥራቱ ፣በአስተጃጀብ ስልቱ፣ በህብር አወቃቀሩ ከሌሎቹ አልበሞች ጋር ሲነፃፀር ደረጃው ዝቅ ያለ ነበር የሚል ሐሜት አለ፡፡
‹‹ለኔ አዲስ
አይለደም፣ ቢልልኝ፣ ነገርሽ ሁሉ፤ ወዘተ…›› የሚሉት ዜማዎች የተሰሩበትን
አልበም አስቦበት ተጠንቶ ያለፈው ስህተት ታርሞ የቀረበ ሥራ መሆኑ በሚገባ ታይቶበታል፡፡
‹‹ደሞ ጀመረኝ››
ሃሳብ ለያዘው ለወዘወዘው…›› እና ‹‹ጠላ ጠላ አትበይ›› የሚሉት ዜማዎቹ ከኤፍሬም ገና ብዙ የማይረሱና አንጀት የሚበሉ ዜማዎችን ልናገኝ እንደምንችል የጠቆሙ ተስፋ ሰጪ ሥራዎች መሆናቸውን አሳይተዋል፡፡
በመጨረሻ ሲዲው በሁለት መንገድ እንግዳችን ሆኖ ተሞሽሯል፡፡ ‹‹ዘንድሮ›› በሚለው አልበሙና በ1994 የዘመን መለወጫ ዋዜማ የሸራተን ዝግጅቱ ማለት ነው፡፡ (ከዚህ በኋላ ለአድማጭ ያቀረበው ‹ኋላላ እንዳቆጭሽ› የተሠኘ አልበም መኖሩ አይዘነጋም)
ኤፍሬም ታምሩ ወደ መድረክ ብቅ ካለ ረጅም ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በመድረክ ላይ ወደ ግማሽ ምዕተ ዓመት የቆዩት እነ ጥላሁንና ማህሙድ ያላቸውን ዝናና ተደራሲ
ያህል ማፍራት የቻለ ድምፃዊ ነው፡፡
በአብዛኛው የአማርኛ ዘፈኖች አድማጭ
ኢትዮጵያዊ ራስጌ የኤፍሬም ምስልና ካሴት መገኘቱ ቀደም ሲል ሳነሳ የቆየሁትን መሠረተ ሃሳብ የሚያጠናክርልኝ ይመስለኛል፡፡
በመጨረሻም የወጣውን አልበሙን እንኳን ስናይ በየስርቻው ሳይቀር የምናደምጠው እሱኑ ነበር፡፡ ታክሲው፣ ሆቴሉ፣ መዝናኛው፣ ሱቆች… ወዘተ ምስክሮቻችን ናቸው፡፡
አሁን አሁንማ የኤፍሬም ዘፈን ሊወጣ ነው ሲል፣ በግራም በቀኝም ያቆበቆበው ድምፃዊ አፈግፍጎ እሳቸውን ባደረገን እያለና ‹‹የግርማዊነታቸውን›› ዘፈን እያዳመጠ ሲቆዛዝም ይሰነብታል፡፡ ግርማዊነታቸው ያልኩት ኤፍሬምን ነው፡፡ የዘፈን ንጉሥ የለም ያለው ማነው? ‹‹ግርማዊ ዳግማዊ ንጉሠ ዘፈን ዘ ኢትዮጵያ›› ብለው ማን ይከለክለኛል እሱን ‹‹ዳግማዊ ያልኩ ‹‹ቀዳማዊው›› ጥላሁን ገሠሠ መሆኑን ማንም ሰለማይስተው ብዬ ነው፡፡
‹‹…ወይ ዘንድሮ ዘንድሮ አያልቅም ተነግሮ
ጥንት ይጎርሳል እንጂ
እየተሰለፈ፣
ማን ይበላ ነበር
በር እየቆለፈ፡፡
ንብረት ወዳጅ ሆነ
ገንዘብ ዘመን ተካ
አልተመቸም ፍፁም
በሰው ለሚመካ
ከውሃው ብጠጋ ባህሩ ነጠፈ፤
ከዛፉም ብጠጋ ቅጠሉ ረገፈ፣ እንደምንም ብሎ ይኸስ ቀን ባለፈ ሆድም ተራራቀ አንዳንነፈጋገር
አንተ ላንተ ኑር ነው የዘንድሮ ነገር፡
፡…››
በአሥራ ሁለቱም ቅጾች (የኅብረቶቹን ጨምሮ) በያንዳንዱ ነጠላ ካሴት ውስጥ የዘፈን (Variety) ለመጠበቅ የሚያደርገው ጥንቃቄ ሪትሞችን ለማመጣጠን (Background) ለማሻሻል የአጃቢዎችን፣ የድምፃዊውን፣ የዜማ ግጥም ደራሲዎችን ተራክቦ የበለጠ ለማሰናሰል ያደረጋቸው ጥረቶች በቅድሚያ የራሱን ኤፍሬም ታምሩ አቻ የለሽ ተሰጥዖ የሚመሰክርለት ብቃቱ ሲሆን እንደሚታወቀው ሙዚቃ የቡድን ስራ በመሆኑ ለተዋጡት ሥራዎቹ አብረውት ሊወሱ የሚገባቸውንና ጉልህ ድርሻ ያላቸውን አርቲስቶች እዚህ ማንሳቱ ተገቢ ይሆናል፡፡
የምናደንቃቸው ሸጋ ዜማዎች ደራሲ ከሆኑት ጥቂቶቹ አበበ መለሰ፤ አበበ ብርሃኔ፣ ፀጋዬ ደቦጭ፣ አክሊሉ ሥዩም፣ ሞገስ ተካ፣ ዘላለም መኩሪያ…ወዘተ መሆናቸው መጠቀስ አለበት፡፡ ያለበለዚያ ግንዱን ትቶ አፀዱን ይሆናል፡፡
የብዙዎቹ ግጥሞቹን ደራሲ ይልማ ገብረዓብን ሳያነሱ ማለፍ ፍርደ ገምድል ያስብላል፡ ፡ በየካሴቱ ያጀቡት አቀናባሪዎችም ድርሻ ከ50 በመቶ የማይተናነስ ነው፡፡ እነሱን ሳያወሱ ማለፍም ወርቁን ትቶ ሚዛኑን ያሰኛል!… በተለይም የመጀመሪያ ሥራዎቹን እነ ዛምቤዚክና ቬነስ ባንድ ያጀቡት ሲሆን፣ አሜሪካን እስከሄደበት ጊዜ ድረስ የተቀረፁትን (የህብረት ዘፈኖቹን ጨምሮ) አምስት ያህል ካሴቶቹን ያጀበው ዝነኛው የሮሃ ባንድ ነው፡፡ ሁሉም የሙያ ቤተሰብ የሚያውቀውና የሚያደንቀው ኪቦርድ ተጨዋቹና አቀናባሪው ዳዊት ይፍሩ ከሁሉም በላይ ለኤፍሬም የሙያ እድገትና ዝነኝነት ብዙውን እጅ ድርሻ የሚይዝ መሆኑን ሙዚቃን ከማድመጥ አልፈው መተርጎምና መተንነተን የሚችሉ ጠቢቦች ሳይቀሩ የሚመሰክሩለት እውነታ ነው፡፡
ኤፍሬም ቀደም ሲል በኢቲቪ የምስል ላይብረሪ ሁለት ዘፈኖች ብቻ ነበሩት፡፡ በሸራተኑ ዝግጅት አንድ ሶስት ሳይጨምር አልቀረም፡፡ ‹‹ጀማዬ ነይ ነይ›› ና ‹‹እንዳልተመካብሽ›› ናቸው፡ ፡ ከመጨረሻ አልበሙ ደግሞ ‹ኋላ እንዳይቆጭሽ› ለሚለው ዘፈን ክሊፕ ሰርቶለታል፡፡ ጋዜጠኞች አነጋግረውት አያውቁም፡፡ ከሙዚቃ ውጪ ስለእሱ የህይወት ታሪክ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ በዚህም ምክንያት ስለ ኤፍሬም ሊነገር የሚገባውን ሁሉ ማቅረብ ያዳግታል፡፡ ግን ጨርሶ ካልተነገረ ይልቅ ጥቂት የተናገረ የሚሻል በመሆኑ ከኔ የተሻለ ፅሁፍ ወደፊት ይፃፋል ብዬ እጠብቃለሁ፡፡ (አብርሃምረታ አለሙ)
ይህ ዘገባ የተገላከልን ሃገር ቤት ከሚታተመው ቁምነገር መጽሔት ነው::
The post ኤፍሬም ታምሩ: ከትናንት እስከ ዛሬ የሙዚቃ ሕይወቱ ሲቃኝ appeared first on Zehabesha Amharic.
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው በፌደራል ክፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ከተበየነላቸው በኋላ አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆባቸው ጉዳያቸው በጠቅላይ ፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች ዛሬ ጥቅምት 22/2008 ዓ.ም በሌሉበት ለጥቅምት 29/2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ጥቅምት 17/2008 ዓ.ም እንዲሁም ዛሬ ጥቅምት 22/2008 ዓ.ም እንዲቀርቡ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸው ለሁለተኛ ጊዜ በሌሉበት ቀጠሮ የተሰጠባቸው አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ ሀምታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሽበሺና አብሯቸው ይገብኝ የተጠየቀበት አቶ አብርሃም ሰለሞን ናቸው፡፡
በዛሬው ችሎት ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግ ማስረጃ ዝርዝር ከብይን ጋር ተያይዞ ባለመቅረቡ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረበው የይግባኝ አቤቱታ ላይ መርምሮ ለመወሰን ስላልቻለ፤ ይግባኝ ያስቀርባል አያስቀርባል የሚለውን ለመወሰን በእስር ፍርድ ቤቱ ያሉ ዝርዝር የአቃቤ ህግ ማስረጃዎች ተያይዘው እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ የእስር ፍርድ ቤቱ ላይ የቀረቡ የአቃቤ ህግ ማስረጃዎች፤ በዋናነት የተከሳሾች ሞባይሎች፣ ከብሔራው ደህንነት ተገኙ የተባሉ ማስረጃዎች እንዲሁም በአብርሃም ሰለሞን ላይ የቀረበው የተከሳሽነት ማስረጃ ሲሆኑ አቃቤ ህግም ‹‹ማስረጃዎቼ በእስር ፍርድ ቤት ስለሚገኙ በቀጣይ ቀጠሮ አሟልቼ አቀርባለሁ›› ብሏል፡፡
በዛሬው ቀጠሮ ተከሰሾቹ ለምን እንዳልቀረቡ ምንም አይነት ምላሽና ትዕዛዝ አልተሰጠም፡፡ እነ የሽዋስ አሰፋ ጥቅምት 17/2008 ዓ.ም ባለመቅረባቸው ፍርድ ቤቱ ‹‹አቅርቧቸው ብለን አዘን ነበር፡፡ እኛ ነን የምናዛችሁ ወይስ ማን ነው? አሁንም ለቀጣይ ቀጠሮ አቅርቧቸው፡፡›› ብሎ ትዕዛዝ ሰጥቶ እንደነበር የሚታወስ ቢሆንም ለሁለተኛ ጊዜ ባልቀረቡበት ቀጠሮ ሰጥቶባቸዋል፡፡
The post አብርሃ ደስታ፣ ሃብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሽበሺ፣ የሺዋስ አሰፋና አብርሃም ሰለሞን ፍ/ቤት ሳይቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠባቸው appeared first on Zehabesha Amharic.
በሊሊ ሞገስ
ቆዳችን ያለንበትን የጤና ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ መግለፅ የሚችል የአካላችን ክፍል ነው፡፡ ጤናማ ቆዳ አስተውላችሁ ከሆነ በተፈጥሮ በጣም ለስላሳ፣ የሚያበራ(Glow)፣ ከሁሉም ቦታ እኩል የውጥረት(Tone) ደረጃ ያለው፣ ከምንም አይነት ሽፍታና የቆዳ እክሎች የጠራ ሆኖ እናያለን፡፡ ሁላችንም እንደምናውቀው የተቆጣ ቆዳ በተለይ ለሌላው በሚታየው ክፍላችን ላይ ማለትም እንደ ፊትና እጅ የመሳሰሉት ላይ ሲታይ በጣም ያስጨንቃል፤ ይረብሻልም፡፡
ግን ለምንድን ነው ቆዳ የሚታመመው? ባሉት መረጃዎች መሰረት ይህ ነው የሚባል አንድ መልስ የለም፡፡
ነገር ግን ለቆዳ መቆጣትና ለተለያየ የቆዳ ችግሮች እንደ መንስኤ ከሚጠቀሱት ውስጥ በዋነኛነት ዘመናዊ የአኗኗር ዘዴ የሚፈጥረው ጫና እና አካላዊ ውጥረት(Physical stress) ተፅዕኖዎች ቅድሚያ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል የአካባቢ ብክለት በስራችንና በኑሮአችን ምክንያት የሚፈጠር ውጥረት፣ በየምግቦቻችን፣ የመዋቢያና የመፀዳጃ ዕቃዎች ውስጥ የሚገቡ ከጤና አኳያ አላስፈላጊ የሆኑ ኬሚካሎች ወዘተ… ሲሆኑ ይህ ሁሉ ግብዓት እንደ ኮክቴል ሆኖ በአካላችን ስርዓት ላይ እንደ ውርጅብኝ ይወርዳል፤ የአካላችንን በሽታ የመከላከል አቅሙን ያዳክሙታል፡፡ በተለይ ደግሞ ስር የሰደዱ የጤና ችግሮች ካሉ ተደራርቦ የዚህ ሁሉ ጫና ውጤት በቆዳችን ላይ ይንፀባረቃል፡፡
ይህንን የቆዳ ችግር ለመፍታት ግን ይሄ ነው የሚባል አንድ የምግብ አይነት ብቻ እንዳለ ብነግራችሁ ምን ያህል ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ጉዳዩ ግን ሌላ ነው፡፡ እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ ግን አመጋገብና የአኗኗር ዘዴአችን በቆዳችን ጤንነት ማለትም እንደአንዱ የአካላችን ትልቁ ክፍል ስራውን በትክክል መስራት እንዲችል፣ የማርጀት ፍጥነቱ ላይ የቆዳ ችግሮችን መበርታትና የመዳን ፍጥነት ላይ ትልቅ ተፅዕኖ እንዳለው ነው፡፡
ስለዚህ ልክ እንደወትሮ ስለምግብ አይነቶችና ስለ አመጋገብ ከመግለፄ በፊት የቆዳችን ስራ ምን እንደሆነና እንዴት እንደሚሰራ በቅድሚያ መገንዘቡ ጠቃሚ ይመስለኛል፡፡
የቆዳችን አገልግሎት
ቆዳችን በሰውነታችን ውስጥ ከሚገኙ ክፍሎች ውስጥ እጅግ በጣም ትልቁ ሲሆን በአማካይ ወደ 2.7 ኪ.ግ ይመዝናል፡፡ ቆዳችን ከሚያከናውናቸው ስራዎች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. የመከላከል ሥራ (Protection)
የመጀመሪያው የቆዳችን ሥራ የተለያዩ የአካላችንን ክፍሎች ከውጫዊው ዓለም ጥቃት መከላከል ነው፡፡ ቆዳችን ሙሉ ለሙሉ የሰውነታችን በሽታ የመከላከል ስርዓት (immune sysetem) ዋና ክፍል ነው፡፡
በሚደንቅ ሁኔታ ቆዳችን በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ከዓይን በማይታዩ ባክቴሪያዎች የተሸፈነ ነው፡፡ እነዚህ ባክቴሪያዎች ምንም አይነት ጉዳት በቆዳችን ላይ ሳያስከትሉ በሰላምና በተድላ በቆዳችን ላይ ይኖራሉ፡፡
እነዚህ ባክቴሪያዎች ታዲያ ምንድን ነው የሚሰሩት አትሉም? ስራቸውማ በሚገርም ሁኔታ ጎጂ ባክቴሪያዎችን መዋጋትና ጥቃት መከላከል ነው፡፡
ሌላው የመከላከል ስራ አካል የሆኑት ደግሞ በቆዳ ህዋሶች መካከል ተቀብረው አካላችንን የሚጎዱ ጎጂ ህዋሳቶች ሲመጡ ለበሽታ መከላከል ስርዓት መረጃ የሚያቀብሉ ላንገር ሐንስ (Langerhans) የሚባሉ የህዋስ አይነቶች አሉ፡፡ በእነዚህ ህዋሶች በመታገዝ የሰውነታችን በሽታ መከላከል ስርዓት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፡፡
2. የሰውነትን ሙቀት መቆጣጠር
ሌላው የቆዳችን ስራ እና ችሎታ ደግሞ የሰውነትን ሙቀት መቆጣጠር ሲሆን የአካባቢያችን ሙቀት በጣም በትንሹ ቢቀየር እንኳን በቀላሉ መለየት ይችላል፡፡ ታዲያ የአካባቢያችንን የሙቀት መጠን መረጃ ለአዕምሮአችን በመላክ የሰውነት የሙቀት ደረጃ እንዲስተካከል ይረዳል፡፡
በቅዝቃዜ ወቅት አዕምሮአችን ለቆዳችን ትዕዛዝ በማስተላለፍ በቆዳችን ስር ያሉትን የደም ስሮች እንዲጠቡ በማድረግና ከቆዳ የላይኛው ክፍል ርቀው ወደታች ዝቅ በማለት ሙቀት ከሰውነታችን እንዳይባክን ከማድረግ በተጨማሪ ቅዝቃዜው ቢበረታ ደግሞ ጡንቻዎቻችን እንዲቀጠቀጡ በማድረግ ሰውነታችን ራሱ ሙቀት እንዲያመነጭ ያደርጋል፡፡
በሙቀት ጊዜ ደግሞ በተቃራኒው ለቆዳችን መልዕክት በመላክ ቀጫጭን የደም ስሮቻችን እንዲሰፉ በማድረግ ከልክ ያለፈ ሙቀት በቆዳችን አማካኝነት እንዲወገድ ከማድረግ በተጨማሪ የላብ አመንጭ ዕጢዎች ላብ እንዲያመነጩ በማድረግ ሰውነት እንዲቀዘቅዝ ያደርጋል፡፡
3. እንደ የስሜት ህዋስ ክፍል ያገለግላል
በቆዳችን ላይ ቁጥራቸው በርከት ያሉ ነርቮች ሲኖሩ በዋናነት አራት ነገሮችን እንድንለይ ያደርጋሉ፡፡ ሙቀት፣ ቅዝቃዜን፣ ንክኪን እና ህመምን፡፡ በንክኪ ላይ ብቻ ሻካራን፣ ለስላሳን፣ ግፊትን የመሳሰሉ የተለያዩ ንክኪዎችን የሚለዩ የነርቭ ህዋሶች አሉ፡፡
4. ቫይታሚን ዲ ማምረት
ሌላው የሚደንቀው የቆዳችን ስራ ደግሞ ፀሐይ ስንሞቅ ሙቀቱን ተጠቅሞ ቫይታሚን ዲ ማምረቱ ነው፡፡ ይህንን የሚሰራው ጠቃሚ ኮሌስትሮልን ወደ ቫይታሚን ዲ 3 በመቀየር ከዚያም በጉበትና ኩላሊት እገዛ አማካኝነት ዲ 3 ወደ አክቲቭ ወደሆነው ስሬቱ እንዲቀየር ያደርጋል፡፡
ዳችን አወቃቀር ምን ይመስላል?
ጤናማ ቆዳ እንዲኖረን ከፈለግን የቆዳችንን አፈጣጠር እና ስራ ማወቅ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ቆዳችን በሶስት ንብርብር ክፍሎች የተዋቀረ ነው፡፡ እነርሱም የላይኛው ክፍል(ኤፒደርሚስ)፣ የመካከለኛው ክፍል(ደርሚስ) እና የታችኛው ክፍል(ሐይፓደርሚስ ወይም ሰብኩታንዬስ) በመባል ይታወቃል፡፡
1. የላይኛው የቆዳ ክፍል(ኤፒደርሚስ)
ይህኛው የቆዳችን ክፍል ከላይ የምናየው ክፍል ሲሆን ውፍረቱ በቆዳችን ላይ ከቦታ ቦታ ይለያያል፡፡ ለምሳሌ ያህል የተረከዝና የመዳፍ ቆዳ ላይ ይህ ክፍል ከ1-5 ሚ.ሜ ውፍረት ሲኖረው በዓይናችን ቆብ ላይ ደግሞ 0.5 ሚ.ሜ ያህል ውፍረት ይኖረዋል፡፡
ይህ ክፍል ብቻውን እስት ንብርብር ክፍሎች ሲኖሩት በዚህ ንብርብር ውስጥ አንደኛ የሚባለው በውጭ የሚታየው ነው፡፡ አምስተኛው ደግ የንብርብሩ የታችኛው ክፍል ነው፡፡ በአንደኛው ክፍል ውስጥ የሚገኙት ህዋሶች ጠፍጣፋና ከሞቱ ህዋሶች የተሰሩ ሲሆን በየጊዜው እየተሸረሸሩ የሚራገፉ ናቸው፡፡ ይኸውም በአማካይ በየሁለት ሳምንቱ በመርገፍ በአዲስ ይተካል፡፡ የመጨረሻውና አምስተኛው ደግሞ አዳዲስ ህዋሶች የሚወለዱበት ክፍል ሲሆን አዳዲስ ህዋሶች ተወልደው እስኪያድጉ ድረስ በንብርብሩ ውስጥ ከአምስተኛው ወደ አንደኛው ክፍል ሽቅብ ይጓዛሉ፡፡ በመጨረሻም አርጅተው አንደኛ ክፍል ላይ ይወገዳሉ፡፡
የቆዳችንን ቀለም የሚያመርቱ ሜላኖሳይት፣ ጎጂ ህዋሳትን ለይተው የሚጠቀሙ ላንጋርሐንስ የተባሉት ህዋሶችና ሌሎች ምንነታቸው የማይታወቁ ህዋሶችም የዚሁ የኤፒዲርሚስ የተባለው ቆዳ ክፍል አካሎች ናቸው፡፡
2. የመካከለኛው የቆዳ ክፍል(ደርሚስ)
ይኸኛው የቆዳ ክፍል ከላይኛው (ኤፒደርሚስ) ከ10-40 ጊዜ እጥፍ ውፍረት ያለው ነው፡፡ ይህ የቆዳ ክፍል ሲታይ ወጣ ገባ የበዛበት ሲሆን በውስጡም የተለያዩ የደም ስሮች፣ ነርቮች ኮላዲንና ኢላስቲንን የሚያመነጭ ፋይብሮ ብላስት የሚባሉ ህዋሶች፣ የወዝ ማመንጫ ዕጢዎች፣ ፀጉርና የፀጉር ስሮች፣ የላብ ማመንጫ ዕጢዎችና ቱቦዎቻቸውን ይዞ እናገኘዋለን፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ የምናገኛቸውን ኮላጅንና አላስቲን በዋነኛነት የቆዳችንን ውጥረት፣ የመለጠጥ አቅም ወዘተ ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡
3. የታችኛው የቆዳ ክፍል(ሐይፓደርሚስ)
ይህ ክፍል ደግሞ ከሁሉም ክፍሎች ወፍራሙና ትልቅ የሆነ ሲሆን የተሰራውም በዋነኛነት ከኮላጅን ስሮችና ስብን ከሚያጠራቅሙ ህዋሶች ነው፡፡ በዚህ
ክፍል የሚጠራቀመው ላብ በተወሰነ ደረጃ ስንቀመጥ ስንጋደም ምቾት ከመፍጠር በተጨማሪ የኃይልና የሙቀት ምንጭም ሆኖ ያገለግላል፡፡ የሰውነታችን ክብደት ሲጨምር በእነዚህ ህዋሶች ውስጥ የሚጠራቀመው የስብ መጠን ይጨምራል፡፡ ስለዚህ አስፈላጊውን እንቅስቃሴ በማድረግና አመጋገብን በማስተካከል የላቡን መጠን መቀነስ ይቻላል፡፡
የቆዳ እርጅና ሒደት
የቆዳን እርጅና ማስቆም ባይቻልም የእርጅናውን ፍጥነት(Aging Speed) ግን ማዘግየት ይቻላል፡፡
ቆዳ እንዴት እንደሚያረጅ ለማወቅ ከላይ የተብራሩትን የቆዳ አፈጣጠርና ዋና ዋና ክፍሎቹን ማወቅ ግድ ይላል፡፡ በዚህ መሰረት እያንዳንዱ የቆዳ ንብርብር ክፍሎች የሚያረጁበት አካሄድም ይለያያል፡፡
የላይኛው የቆዳ ክፍል(Epidermis) እርጅና
የቆዳ የላይኛው ክፍል ሲያረጅ የቆዳን ቀለም የሚፈጥሩ ህዋሶች ቁጥር መቀነስን ያስከትላል፡፡ እነዚህ ህዋሶች ሜላኒን የተሰኘውን የቆዳ ቀለም የሚያመነጩ ሲሆን የእነርሱ ቁጥር አነሰ ማለት የሜላኒን መጠን ቀነሰ ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ቆዳችን የፀሐይ ጨረርን(Ultraviolet ray) መቋቋም እንዲያዳግተው ያደርጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ቆዳችን ላይ በሚገኙ ፍሪራዲካሎች መጠቃትና በቆዳ ካንሰር እስከ መያዝ ያደርሳል፡፡
ሌላው በዚህ ክፍል ውስጥ የሚገኙ ላንገርሐንስ የተባሉ የተህዋሲያን መምጣትን የሚያሳውቁ ህዋሶች ቁጥር መቀነስ ሲሆን ይህም ተህዋሲያን በቆዳ ላይ ሲያርፉ በፍጥነት በሽታን የመከላከል ስርዓትን(Immune sysetem) የማሳወቅ ሁኔታ ይቀንሳል፡፡
በተጨማሪ ይህ የላይኛው የቆዳ ክፍል ወዙን እና ውጥረቱን(tone) ያጣል፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት የላይኛው የቆዳ ክፍል ከመካከለኛው(Dermis) ከሚባለው የቆዳ ክፍል ተነስተው ጫፋቸው በላይኛው የቆዳ ክፍል(Epidermis) ብቅ ብቅ ከሚሉት የደም ስሮች ውጭ የራሱ የሆነ በውስጡ የተዘረጉ የደም ስሮች የሉትም፡፡ በመሆኑም ቆዳ ሲያረጅ በዚህ ክፍል እና በመካከለኛው ክፍል መካከል መለያየት(መራራቅ) ይፈጠራል፡፡ በዚህም ምክንያት በቂ አየርና ንጥረ ነገሮች ስለማይደርሱት ህይወት አልባ ቆዳ ይሆናል፡፡
የመካከለኛው የቆዳ ክፍል (Dermis) እርጅና
በዚህኛው የቆዳ ጤና ላይ እርጅና የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ስንመለከት በዋነኛነት የቆዳን የመጠንና ባህሪ (የልጅ ቆዳ) የምንለውን ባህሪ የሚያሳጡት የኮላጅን እና ኢላስቲን መጠን መቀነስ ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ኮላጅንን የሚያመርቱ ፋይብሮ ብላስት የተባሉ የህዋስ አይነቶች መኮማተር መጀመር ነው፡፡ ሌላው ኮላጅን ራሱ መቅጠን ይጀምራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሜታሎ ፕሮቲኔዝ የተባለ ኢንዛይም መጠን በቆዳ እርጅና ጊዜ መጠኑ ስለሚጨምር ኮላጅንን በመሰባበር የቆዳን የመለጠጥ ችሎታውን ይቀንሰዋል፡፡
ሌላው በዚህ ክፍል እርጅና ጊዜ የሚታየው ለውጥ ደግሞ የደም ዝውውር ስለሚቀንስ የአየርና የጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ማግኘትም ተያይዞ ይቀንሳል፡፡ ለዚህም ነው በእርጅና ጊዜ ቆዳ የመገርጣትና የመቀዝቀዝ ባህሪ የሚያሳየው፡፡
የታችኛው የቆዳ ክፍል እርጅና
ይህኛው የቆዳ ክፍል ደግሞ ላብ የሚከማችበት ክፍል ሲሆን በእርጅና ጊዜ የላብ ክምችቱ ይቀንሳል፡፡ ይህም የቆዳውን ሞላ የማለት ባህሪ ያዳጣዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ቅዝቃዜን የመቋቋም አቅሙ ይቀንሳል፡፡
የቆዳን እርጅና የሚያፋጥኑ ነገሮች ምንድን ናቸው?
የቆዳን እርጅና ከሚያፋጥኑ ነገሮች ውስጥ በዋነኛነት የሚጠቀሰው የቆዳ ህዋሶች በፍሪ ራዲካሎች መጠቃት ነው፡፡ ስለ ፍሪ ራዲካሎች ባለፈው ወር እትም ላይ በዝርዝር ያየን ስለሆነ ጠለቅ ብለን አንገባበትም፡፡ ለማስታወስ ያህል ግን ፍሪ ራዲካሎች ያልተረጋጉ፣ የኤክትሮን ጥማት ያለባቸው ባዕድ ኬሚካሎች ሲሆኑ የሚፈልጉትን ኤሌክትሮን ለመስረቅ ሲሉ ከህዋሶቻችን ጋር ይጋጫሉ፡፡ በዚህ ሂደትም ህዋሶቻችን ይጎዳሉ፡፡ ይህም ጉዳት ህዋሶች ዳግመኛ በትክክል ስራቸውን መስራት እስኪያቅታቸውና ይህም የህዋሶች የመራባት ሂደትን አውኮ ወደ የካንሰር በሽታ እስከማምጣት የሚያደርሱ ናቸው፡፡
ፍሪ ራዲካሎች በተወሰነ ደረጃ በተፈጥሮ ሰውነታችን ውስጥ የሚመረቱ ሲሆን በብዛትና በአደገኛ ሁኔታ ደግሞ የሚመረቱት ሰውነት ጎጂና መርዛማ የሆኑ ነገሮችን በምግብ፣ በመጠጥ፣ በሲጋራና ሌሎች ሱስ አስያዥ ነገሮች፣ በመድሃኒት፣ በተለያዩ ኬሚካሎች አጠቃቀም ምክንያት ወደ አካላችን ሲገቡ እነርሱን ለመሰባበር በሚያደርገው ጥረት ፍሪ ራዲካሎች በብዛት ይመረታሉ፡፡ ይህንን የፍሪ ራዲካሎች ምርት ለመቀነስ ግን በዋነኛነት ጤናማ የሆነ የአመጋገብ ስርዓትና የአኗኗር ዘዴ መከተሉ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው፡፡
ሌላው የቆዳን እርጅና የሚያፋጥኑ ነገር ግን ብዙም የማይወራለት ነገር ደግሞ ጣፋጭ ምግቦችና መጠጦችን በተለይ የታሸጉ ምርቶችን መጠቀም ሲሆን እነዚህ የምግብ አይነቶች የሚይዙት የተጣራ የካርቦሃይድሬት ምግቦችን ጨምሮ አዘውትሮ መመገብ የቆዳን እርጅና ያፋጥናል፡፡
የተጣራ የካርቦሐይድሬት ምግቦች የምንላቸው ስንል ደግሞ ገለባቸው የወጣላቸው እንደ የነጭ ዱቄት ምርቶች ማለትም ነጭ ዳቦ፣ ነጭ ፓስታ፣ በፈጣን ሁኔታ የሚዘጋጁ ምግቦችን ያካትታል፡፡
እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት የምግብ አይነቶች በውስጣቸው ከልክ በላይ የሆነ ስኳር የያዙ ሲሆን በኢንሱሊን አማካኝነት ስኳር በፍጥነት በሰውነታችን እንዲመጠጥ ያደርጋል፡፡ ይህ ሁኔታ ከጊዜ በኋላ ሰውነታችን ለተለያዩ የጤና ችግሮች እንዲጋለጥ ከማድረግ በተጨማሪ በቆዳችን ውስጥ ያሉትን የኮላጅንና ኢላስቲንን ስሮች በማስተሳሰርና በማጣበቅ የመለጠጥ ባህሪያቸውን ያሳጣል ብሎም የመሰባበር ባህሪ እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡ ይህ ደግሞ የቆዳ መሸብሸብን ያስከትላል፡፡ ስለዚህ ከተጣራ የካርቦሐይድሬቶችን ከመጠቀም ይልቅ እህሉን እንዳለ ፈጭቶ መጠቀም እንደዚሁ ጣፋጭ ምግብና መጠጦችን ቀንሶ በልክ ብቻ ማድረጉ ይመከራል፡፡
The post Health: የቆዳ እርጅናን ለመከላከል 4 ጠቃሚ መረጃዎች (በተለይ ለሴቶች) appeared first on Zehabesha Amharic.
ይሄንን “የስደት መንግሥት” የሚባልን ነገር እንደሰሞኑ ሁሉ ከሦስት ዓመታት በፊትም በጨረፍታ አሰምተውን ነበር፡፡ እኔ አሁን በዚህ ጽሑፍ የዚህን ጉዳይ ክወናውን (ቴክኒካል የሆኑ ነገሮችን) ለማተት ወይም ይሄንን ጉዳይ እያስኬዱት ስላሉ ሰዎች ብዙ የማውቀው ነገር ኖሮኝ ከእነሱ ሰብእና አኳያ ይሄንን ሐሳብ ለመፈተሽም አይደለም፡፡ ነገር ግን ከነባራዊ ሁኔናዎች ተነሥቸ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ መባል የሚገባው ብዙ ነገር አለና እሱን ማለት ነው የፈለኩት፡፡
መጀመሪያ “የስደት መንግሥት” የሚለውን ነገር እንደሰማሁ በተጨባጭ ያሉ ነባራዊ ሐቆችን ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ ሐሳብ ከመሆኑና በባዶ ምኞት ብቻ የተንጠለጠለ ከመሆኑ የተነሣ ግርምት የተሞላ ሳቅ ነበር ያጫረብኝ፡፡ ብልጣብልጥ የሆኑ የመሰላቸው ሰዎች ያሰቡት የትም የማያደርስ አስቂኝ ድራማ (ትውንተ ኩነት) ሆኖ ነበር የታየኝ፡፡
እንደሚመስለኝ እነዚህ ወገኖች ይሄንን ሐሳብ ለማሰብ ያበቃቸው ጉዳይ የኢትዮጵያ ሕዝብ የወያኔን አገዛዝ መጥላቱ፣ በቃኝ ማለቱ፣ ከዳር እስከዳር በወያኔ የተንገሸገሸና ወያኔን መገላገል የሚፈልግ መሆኑ ነው፡፡ ያለው ሁኔታ እንዲህ መሆኑም “በድንገት ሕዝባዊ ዐመፅ ተቀስቅሶ ወያኔ ይወገዳል፣ ይወድቃል፣ ይከላል” የሚል እምነት ማሳደራቸው ነው “ተዘጋጅተን እንጠብቅ” ብለው ለማሰብ ያበቃቸው፡፡ እኔ በግኔ ሰዎቹ ይህን በማሰባቸው ያላቸውን አስተዛዛቢ የብስለትና የማገናዘብ ጠልቆ የማሰብ ደረጃ፣ ለሀገራችን ፖለቲካ የቱን ያህል ሩቅ እንደሆኑ እንድገነዘብ አድርጎኛል፡፡
እነዚህ ወገኖቻችን ያልተዷቸው ነገሮች ምን ምን መሰሏቹህ?፡- እውነት ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔ በቅቶታል፣ በወያኔ ተንገሽግሿል፣ እጅግ ተማሯል እንዲህም ከሆነ ብዙ ቆይቷል አሁን አይደለም እንዲህ የሆነው፡፡ አሁን ጥያቄው “የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔ ከበቃው፣ በወያኔ ከተንገሸገሸና ፍጹም ተስፋ ከቆረጠ የቆየ ከሆነ በሕዝባዊ ዐመፅ ለመገላገል ያልሞከረው ለምንድን ነው ታዲያ?” የሚለው ነው፡፡
እነኝህ የስደት መንግሥት አቋቋምን የሚሉ ወገኖቻችን ይሄንን ጥያቄ ለማጤንና ለመመለስ ሙከራ ቢያደርጉ ኖሮ እኔ እርግጠኛ ነኝ በእንዲህ ዓይነቱ ቅዠት አያስቡትም ነበር፡፡
እነሱ ያሰቡት “በቃ! ሕዝቡ ተማሯል ከተማረረ ደግሞ ማመፁ አይቀርም፤ ዐምፆ ወያኔ በተወገደ ጊዜ ክፍተት ተፈጥሮ ሀገራችን ችግር ላይ እንዳትወድቅ” በሚል አጋጣሚውን ተጠቅመው ሥልጣን ለመያዝ ከመፈለግም ሊሆን ይችላል ብቻ ከሁለቱ በዘንዱ ምክንያት ተዘጋጅተን እንጠብቅ የሚለውን ብቻ ነው ያሰቡት፡፡ ሰዎቹ በሰጡት መግለጫ የገለጹት “ወያኔ በድንገተኛ ዐመፅ ሲወገድ ክፍተት ተፈጥሮ ሀገሪቱና ሕዝቧ ችግር ላይ እንዳይወድቁ ተዘጋጅቶ ለመጠበቅ!” የሚል ነው፡፡
ነገሮችን አገናዝቦ መመልከት ለሚችል ሰው ግን ይሄ ሽፋን እንጅ ሰዎቹ የሚሉትን ያህል ለሀገርና ለወገን ተቆርቋሪ ሆነው የሀገርና የወገን ጉዳይ እረፍት ነስቷቸው ይሄንን እንዳላሰቡ የእያንዳንዳቸውን የኋላ ፖለቲካዊ (እምነተ አሥተዳደራዊ) እንቅስቃሴ ታሪካቸውን በዳሰሳቹህ ጊዜ ትረዱታላቹህ፡፡ በቀላሉ እነዚህ ተጠራርተው የተሿሿሙት ወገኖቻችን “የሀገርና የወገን ጉዳይ አስጨንቋቸው፣ እረፍት ነስቷቸው ስለሀገርና ስለወገን ሲሉ ሳይፈሩና ሳያፍሩ ተጋፋጭ ሆነው በየመድረኩ ወያኔን ሲሞግቱ፣ ሲያወግዙ፣ ሲቃወሙ፣ ሲገዳደሩ፣ ሲከሱ፣ ሲወቅሱ፣ ሲፈታተኑ ያሳለፏቸውና እያሳለፏቸው ያሏቸው የትግል ተሞክሮዎች አሏቸው ወይ?” ብላቹህ ስትጠይቁ በምታገኙት መልስ ይሄንን ያልኳቹህን ጉዳይ ልትታዘቡ ትችላላቹህ፡፡
ዋናው ጥያቄ እንዳሉት ወያኔ ቢገረሰስ ተከትሎት ሊመጣ ከሚችለው ተገማች ነባራዊ ሁኔታ አኳያ ሀገራችን ችግር ላይ እንዳትወድቅ መረጋጋት እንዲፈጠር ማድረግ የሚችለው “የታጠቀ ኃይል ነው ወይስ የሆኑ ሰዎች ተቧድነው ሆነናል የሚሉት የስደት መንግሥት የተባለው?” የሚለው ነው፡፡
ለማንኛውም በየትኛው ምክንያት ተነሣሥተው እንዲህ ሊያስቡ እንደቻሉ ለጊዜና ለእግዚአብሔር እንተወውና ይህ ድርጊታቸው ግን የትም የማያደርስና ይልቁንም የሚጎዳ የማይጠቅም ስለ መሆኑ ዕንይ፡-
በነገራችን ላይ እጅግ በሚገርማቹህ ደረጃ ሲጀመር ጀምሮ “ዐመፅ ይነሣል፣ አይ! ዘንድሮማ ወያኔ ያበቃለታል!” ወዘተረፈ. ዓይነት ወሬዎችን ትንቢት እያስመሰለ ከየእምነት ቦታዎች እስከ የሥራ ቦታዎች ድረስ ሁሉም ቦታ ላይ የሚያስወራው ወያኔ እራሱ እንደሆነ ታውቃላቹህ? ለምንስ ይመስላቹሀል?
ይሄንን የሚያደርግበት ምክንያት ለምን መሰላቹህ! እኔ መቸም ለጥቅማቸው ሲሉ የወያኔን መኖር የሚፈልጉት መካሪዎቹ ነጫጭ ሰይጣኖች ምዕራባዊያኑ ይሆናሉ እንጅ ይሄንን መሰሪ አስተሳሰብ ወያኔ ጭንቅላት ኖሮት ያስበዋል ብየ ለማመን እጅግ እቸገራለሁ፡፡
ነገር ግን “ሰብአዊነት ስለሚገደን፣ ለሀገርና ወገን ማሰብና መቆርቆራችን፣ ግብረገብነታችን ስለሚይዘን፣ ክፋትና ሸር የዕኩያን ተግባር ነው ብለን ስለናቅነው ልናደርገው አንፈልግም እንጅ ሥራየ ብለን እናድርገው ብንል መልካም ነገር ማድረግ ነው እንጅ የሚያስቸግረው ክፋትና ሸር መሥራት ደሞ ምኑ ያቅታል? ለክፋትና ተንኮልማ ሰይጣኑን ራሱ አጋዥ አባሪ አይደለም ወይ?” ብላቹህ ካላጣጣላቹህት በስተቀር እኔ በጣም ይገርመኛል ይደንቀኛልም፡፡
ወያኔዎቹ እንደዚህ ዓይነት ወሬዎቹን ሥራዬ ብለው በሁሉም ቦታዎች የሚያስወሩበት ምክንያት “እንዲህ ሊደረግ ነው! እንዲህ ሊሆን ነው!” ተብሎ ለሕዝቡ ሲወራለት ሕዝቡ ይሆናል ይደረጋል ተብሎ የሚነገር ጉዳይ ባለቤት እራሱ መሆኑን ትቶ “ላምፅ፣ ተደራጅቸ ልታገል” ሳይል እጅና እግሩን አጣምሮ ይሄ “እንዲህ ሊሆን ነው! እንዲህ ሊደረግ ነው!” የተባለውን ነገር ብቻ በመጠባበቅ ዘመኑን የሚፈጅ ይሆናል፣ ሰው ሁሉ የሚሆነውን ለማየት ራሱን በተመልካች በታዛቢ ቦታ ላይ አስቀምጦ “ሊሆን ነው!፣ ሊደረግ ነው!” የተባለውን ለማየት ይጠባበቃል እንጂ “የራሴ ጉዳይ ባለቤቱ እኔው እራሴ ነኝ፣ ለእኔ ያለሁት እኔው እራሴ ነኝ፣ ለእኔ ብሎ ከሌላ ቦታ መጥቶ ስለእኔ ዋጋ ከፍሎ እኔን ነፃ ሊያወጣኝ የሚችል ኃይል የለም አይኖርምም ስለዚህ የራሴን ጉዳይ እኔው ራሴ ልጨርሰው ልከውነው” ብሎ ጉዳዩን የራሱ አድርጎ አይነሣም አይንቀሳቀስም፡፡
“ዐመፅ ይነሣል!፣ ዘንድሮ ወያኔ ያበቃለታል!” ተብሏል ማየት የሚፈልገው ያንን ዐመፅ እነማን አንሥተውት ወያኔ እንዴት ባለ ሁኔታ እንደሚወገድለት መመልከት ብቻ ነው፡፡ በዚህ ዘዴ ወያኔ ሕዝቡ የራሱን ጉዳይ የራሱ አድርጎ እንዳያስብ፣ መፍትሔም እንዳያፈላልግና እራሱ ዋጋ ከፍሎ ነጻ እንዳይወጣ ጉዳዩን የሚጨርስለት የምናብ ሌላ ሦስተኛ አካል ፈጥሮ ትወናውን በማድረግ እድሜውን እስከ አሁን ማራዘም ችሏል፡፡ ሕዝቡ እስኪነቃበት ድረስም ወደፊትም ሲጠቀምበት እንደሚቆይ እገምታለሁ፡፡
ይሄንን የምለው ፈጥሬ ወይም እንዲሁ በግምት እንዳይመስላቹህ! መረጃ አለኝ፡- ከበፊት ጀምሮ “በመጪው ዓመት፣ በቀጣዩ ጊዜ እንዲህ ይሆናል! እንዲህ ይደረጋል! ዐመፅ ይነሣል!” ወዘተረፈ. እያሉ እያስወሩ ሕዝቡን ከሚያጃጅሉ ከሚያዘናጉ የወያኔ ሰዎች አንዱን ተከታትየ አጥንቸው ነበር፡፡
ይህ ሰው “ቅዱስ ነኝ” ይላል ደመና ጠቅሶ ሳይቀር ወደ ፈለገበት እንደሚሔድ ሁሉ ይናገራል፡፡ ወያኔዎች የጨነቀው መላ ያጣ ሕዝብ ምንም ቢባል ላጣራ ልመርምር ሳይል እንደሚያምን እንደሚጃጃል ገብቷቸዋል፡፡ ከዚህም የተነሣ ደፍረው “ቅዱስ ነኝ በደመና ላይ ተጭኜ ወደፈለኩበት እጓዛለሁ” ምንትስ ሲሉ ጥቂትም እንኳን አይሸማቀቁም አይደነግጡም አይጨነቁም፡፡ ልክ እውነት እንደሚናገር ሰው በልበ ሙሉነት እንዲህ ዓይነቱን ቅጥፈት ማታለያ ማወናበጃ ቃል ይናገሩታል፡፡
እናም ይሄ “ቅዱስ ነኝ ድንግላዊ ነኝ” ምንትስ እያለ በየገዳሙ በየጸበሉ እየዞረ የሚያወናብድን ወያኔ ስከታተለው የእግዚአብሔርም ፈቃድ ሆኖ ተጋለጥ ሲለው ባልጠበኩት አጋጣሚ ባለትዳርና የልጆች አባት ሥራውም የወያኔ ደኅንነት (ሰላይ) መሆኑን ደረስኩበት፡፡ ወደ ኋላ መለስ ብየ “ትንቢት” እያለ ይናገራቸው የነበሩትን ነገሮችና ነገረ ሥራውን ሁሉ ሳስብ በቀጥጣም ይሁን በተዘዋዋሪ ሆን ተብሎ ታስቦባቸው ወያኔን ተጠቃሚ ሊያደርጉ በሚያስችሉ መልኩ ሕዝቡን በሥነልቡና መስለብ ማደንዘዝ የሚያስችሉ ሆነው አገኘኋቸው፡፡
እንደዚህ ሰው ያሉ በርካታ ካድሬዎች በየ እምነት ተቋማቱና እንደ አስፈላጊነቱ በሁሉም ቦታ አሉ፡፡ ይህንን ሥራም ሲሠሩ አገዛዙ በመንግሥት ስም ከሚሠራቸው የሥራ ክንውኖችና አቅዶች ጋር በሚገባ በመቀናጀት በማሰላሰል ነው፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔ ካንገሸገሸው ካቅለሸለሸው ከበቃው የቆየ ሆኖ እያለ ዐምፆ እንዳይገላገለው ካደረጉት ምክንያቶች አንደኛው ይህ ሲሆን ሌላኛውና ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ወያኔ እንደምታዩት የኢትዮጵያን ሕዝብ ቀደም ሲል ነጻነቱንና መብቶቹን በመንፈግና መፈናፈኛ በማሳጣት፣ መብታቸውን ለማስከበር በሚሞክሩት ላይ ኢሰብአዊ የመቀጣጫ የቅጣት እርምጃ በመውሰድ፣ ሩቅ ካልሆኑ ዓመታት ወዲህ ደግሞ ከመንግሥት ሠራተኛ እስከ ግል ሠራተኛ፣ ከገጠር እስከ ከተማ፣ ከተማሪ እስከ ሠራተኛ ፍጹም በቁጥጥሩ ስር አድርጎ ከእሱ አስተሳሰብ ውጭ ማድረግ አይደለም ማሰብም እንኳን እንዳይችል ለማድረግ ፍጹም ኢዲሞክራሲያዊ (ኢመስፍነ ሕዝባዊ) በሆነ አሠራር በግዳጅ በአንድ ለአምስት አደረጃጀት ጠርንፎ አማራጭ አስተሳሰቦችን እንዳያስተናግድ ተጠፍንጎ የተያዘበት የታሰረበት በር የተዘጋበት ሁኔታ ላይ ያለ በመሆኑ ሕዝቡ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ስር ሆኖ ዐመፅ አድርጎ ይሄንን የተንገሸገሸውን የተጸየፈውን አገዛዝ ለመገላገል በፍጹም እንዳይችል አድርጎታል፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔ ካንገሸገሸው፣ ካቅለሸለሸው፣ ከበቃው የቆየ ሆኖ እያለ ዐምፆ እንዳይገላገለው ካደረጉት ምክንያቶች ሦስተኛውና ዋነኛው ደግሞ የሚከተለውን ይመስላል፡-
በግልጽ እንደምታዩት ወያኔ የፋሽስት ጣሊያንን “ከፋፍለህ ግዛ” የአገዛዝ ዘዴን እንዳለች ወስዶ በመጠቀም ሕዝቡን በብሔረሰብ በሃይማኖት በጾታ ሳይቀር ከፋፍሎ እጅግ ኃላፊነት በጎደለውና ድንቁርና በተሞላበት መልኩ እርስ በእርሱ እንዲተላለቅ ሊያደርጉት የሚችሉ ሰይጣናዊ ሴራዎችን በመጠንሰስ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ እንዳይሆን፣ እንዳይተባበር፣ እንዲቂያቂያምና ተፈራርቶ በጎሪጥ እየተያየ እንዲኖር፣ ቀን እየተጠባበቀ እንዲኖር እንዳደረገው ይታወቃል፡፡
ወያኔ ይሄንንም ያደረገበት ምክንያት ሕዝቡ ሕዝባዊ ዐመፅን እንዳያስብ እንዳይሞክረው ለማድረግ ነው፡፡ ምክንያቱም እርስ በእርሱ የሚፈራራ በጎሪጥም እንዲተያይ የተደረገ ሕዝብ እየገዛው ያለው አንባገነናዊ አገዛዝ የቱንም ያህል አስከፊ፣ ፈላጭ ቆራጭ፣ አረመኔና ሊገላገለው የሚፈልግ ቢሆንም እንኳን እየመረረውም ቢሆን አርፎ ተሰብስቦ ይኖራል እንጅ ዐምፆ ለማስወገድ ሊሞክር አይደለም ሊያስብም አይፈልግም፡፡ በሆነ አጋጣሚ በአንድ አካባቢ ዐመፅ ቢቀሰቀስም እንኳ ሌላኛውም አካባቢ የዐመፁ ተካፋይ ተሳታፊ ተባባሪ አይሆንም፡፡ ይሄንንም ባለፈው ወያኔ ኦሮሚያ ብሎ በሚጠራው የሀገራችን ክፍል ከተሞች ዐመፅ በተቀሰቀሰ ጊዜ ተመልክታቹህታል፡፡
የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዐመፁን ያልተቀላቀለበት ምክንያት ደግሞ የዐመፁ ርእሰ ጉዳይ (አጀንዳ) የሆነው “የአዲስ አበባን ከተማ ለማስፋት የተያዘውን አቅድ መቃወም” የሚለው ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ ለጎጠኝነት የቀረበ ስለሆነ፣ ይህ ተቃውሞ እራስን ኢትዮጵያዊ አድርጎ ካለማሰብ የሚመነጭና የሀገሪቱ ዋና ከተማ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጅ የአንድ ብሔረሰብ ባለመሆኑ ከተማው የተፈለገውን ያህል ቢሰፋ ተቃውሞ ሊነሣበት የሚገባ ባለመሆኑ በአንዲት ሀገር ውስጥ ባለ ሕዝብ መሀል እንዲህ ያለ መከላከል ተገቢ እንዳልሆነ በመረዳቱ፣ ዐመፁን ያነሡ ሰዎች ከኢትዮጵያ ጥቅም ይልቅ ክልል ብለው የሚጠሩት ጥቅም ስለበለጠባቸውና ይህ አመለካከትም እጅግ ጠባብ አጥፊና የማይፈለግ በመሆኑ፣ አስፈላጊ አይደለም እንጅ እንተሳሰብማ ከተባለና በትክክለኛ መለኪያ የየብሔረሰቡ ቀየ፣ ርስት፣ ይዞታ፣ ሀገር ይከለል ቢባል “ክልላችን ነው አይነካብን!” ብለው ዐመፁን ያስነሡት የኦሮሞ ተወላጆች የኛ ነው የሚሉት ቦታ የእነሱ አለመሆኑ በሚገባ ስለሚታወቅ በእነኝህና በሌሎችም ምክንያቶች ብቻ ሳይሆን የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዐመፁን ያልተቀላቀለው ይልቁንም የተቀረው የሀገሪቱ ሕዝብም ዐመፁን ተቀላቅሎ ይሄንን አስከፊ አንባገነን አገዛዝ በዐመፅ ቢያስወግደው “አገዛዙ በጠነሰሰው ሰይጣናዊ ክፉ ሴራ የእርስ በእርስ መተላለቅ ሊከሰት ይችላል!” ብሎ እጅግ ስለሚፈራ ይህ እንዳይሆን ከመፈለጉ አንጻር አገዛዙ ክፉና አረመኔ የተጸየፈው ቢሆንም “በዐመፁ ወያኔን አስወግጀ ወደባሰ ችግር ውስጥ ከምገባ ቢመረኝም ሰጥ ለበጥ ብየ እየተገዛሁ በሰላም ብኖር ነው የሚሻለኝ!” ብሎ እንዲያስብ ስላደረገው ነው፡፡ እያየነው ያለው ይሄንኑ ነው፡፡ ነገም በሌላ ቦታ ተመሳሳይ ዐመፅ ቢቀሰቀስ ልናየው የምንችለው ተመሳሳዩን ነገር ነው፡፡
እናም የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔ ካንገሸገሸው ካቅለሸለሸው ከበቃው የቆየ ሆኖ እያለ ዐምፆ እንዳይገላገለው ካደረጉት ምክንያቶች ሌላኛውና ዋነኛው ምክንያት በዘር በሃይማኖት ተከፋፍሎ እንዲፈራራ፣ ቀን እንዲጠባበቅ፣ እንዲቂያቂያም በመደረጉ ነው፡፡ ለጊዜው እነዚህ ሦስት ምክንያቶች ይበቁናል፡፡
የብሔር ተኮር ፖለቲካን እያቀነቀኑ ያሉ የፖለቲካ (የእምነተ አሥተዳደር) ቡድኖች ደንበኛ የወያኔ ሰይጣናዊ ሴራ መጠቀሚያ ከመሆንና ለወያኔ ተጨማሪ ጉልበት አጋዥ ከመሆን ውጭ አእምሮ ልቡና ማስተዋል ኖሯቸው ይሄንን የወያኔን ሰይጣናዊ ሴራ በሚገባ ተረድተው ነቅተው ማርከሻውን ማክሸፊያውን መላ መንገድ ዘዴ ማመንጨት የሚችል ጭንቅላት የሌላቸው ሆኑ እንጅ መፍትሔው በጣም ቀላል ነበር፡፡
እሱም አንድነት ነው፡፡ አንድነት ቢፈጥሩ ወያኔ በሕዝቡ መሀል የዘራው የእርስ በእርስ ጥላቻ መፈራራትና መጠራጠር ሥጋት ይወገድና ሕዝቡ እንደ አንድ ልብ መካሪ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆኖ አንድ ሐሳብ አንድ ግንባር ፈጥሮ በዐመፅ ወያኔን የሚገላገልበትን ዕድል መጠቀም እንዲችል በማብቃት ወያኔ የቀበረውን ሰዓት ጠብቆ የሚፈነዳ ፈንጅ ማምከን ማክሸፍ ያቻል ነበር፡፡
ይህንን የአንድነት ስሜት በሕዝቡ ልብ መፍጠር እስካልተቻለ ጊዜ ድረስ በሕዝባዊ ዐመፅ ወያኔ ይወገዳል ብሎ ማሰብ እጅግ ጅልነትና አለማሰብ አለማስተዋል፣ ያሉ ነገሮችን መረዳት አለመቻል ነው፡፡ እንዴትስ ነው በመንገዱ ላይ ስንት ዓይነት ፈንጅ ተቀብሮበት እያለ በዚያ መንገድ የተቀበረውን ፈንጅ የሚያውቀውን ሕዝብ ሒድበትና ነጻ ውጣ ልንል የምንችለው? አስቀድሞ ፈንጅውን ማምከንና መንገዱን ነጻ ማድረግ ግድ አይልም ወይ? አንድነትን ፈጥረን ያለበትን የእርስ በእርስ መፈራራት ካስወገድንለት ሕዝቡ መንገዱ ከፈንጅ ነጻ መሆኑን ያውቅና የማንንም ትዕዛዝ ሳይጠብቅ መሬት አንቀጥቅጥ ዐመፅ በማድረግ ወያኔን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ቀብሮት ለመገላገል አንድ ቀንን እንኳን ማባከን የማይፈልግ ይሆናል፡፡
ይህ የወያኔ ፈንጅም ይመክንና መንገዱም ነጻ ይሆን ዘንድ የብሔር ተኮር የፖለቲካ (የእምነተ አሥተዳደር) ዘውግን በማቀንቀን የትጥቅ ትግልንም ሆነ ሰላማዊ ትግልን እያደረጉ ላሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች (የእምነተ አሥተዳደር ቡድኖች) ማስተላለፍ የምፈልገው ዐቢይ ጉዳይ ቢኖር፡- ኧረ እንዲያው እባካቹህ! ከዛሬ ነገ በስላቹህ ነገሮችን ትረዱና መፍትሔው ገብቷቹህ ወደ ትክክለኛውና ሁሉንም ተጠቃሚ ወደሚያደርገው አስተሳሰብ ትመጣላቹህ ብለን ስናስብ እናንተ ግን እጅግ በሚገርምና ግራ በሚያጋባ መልኩ አድሮ ጥሬ እየሆናቹህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻ የሚወጣበትን ብሩሕና መልካም ቀን የሚያይበትን ዘመን እጅግ እያራቃቹህት ትገኛላቹህ፡፡
ኧረ ተው! እባካቹህ! እያራመዳቹህት ያለው አስተሳሰብ ወያኔን ጠቅሞ እድሜውን እያራዘመው እንደሆነ እንዴት መገንዘብ ይሳናቹሀል? በዚህ የምትቀጥሉና ወያኔን በማገዝ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ ልብ እንዳይሆን የምታደርጉ ከሆነ ወያኔ ዘለዓለማዊ ሆነ ማለት አይደለም ወይ? ወያኔ እናንተንም በመጠቀም የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲህ አንድ እንዳይሆን፣ እርስ በእርሱ እንዲቂያቂያም፣ እንዲጠራጠር፣ ቀን እንዲጠባበቅ አድርጎት እንዳለ በሌላ በአንዳች አጋጣሚ ቢወድቅ ቢወገድ እንኳን እያራመዳቹህት ያላቹህት ዓላማ አቋም አስተሳሰብ ሕዝቡ እርስ በእርሱ ተላልቆ፣ ተጠፋፍቶ፣ ተፋጅቶ፣ እንዲያልቅ ያደርገዋል እንጅ እንዴት ሆኖ ነው ሰላምና መረጋጋት፣ ፍትሕና እኩልነት፣ ነጻነትና መብት ሊያገኝ ሊጎናጸፍ የሚያስችለው? ሰው እንዴት ዕድሜው እየገፋ ሲሔድ አይበስልም? እድሜ እኮ! ሰውን ይለውጣል ብዙ ያስተምራል አይደለም እንዴ? እንዴት ነው ታዲያ እናንተ ላይ ይሄ ሊሠራ ያልቻለው? እኔ እኮ ግራ ገባኝ!
ወደ ቀደመው ነገራችን ስንመለስ እነኝህን ሕዝባዊ ዐመፅ እንዳይነሣ እንዳይደረግና ወያኔ እንዳይወድቅ የሚገድቡ ነባራዊ ሁኔታዎችንና ተግዳሮቶችን “የስደት መንግሥት አቋቋምን” ያሉ ወገኖቻችን በፍጹም ግንዛቤ ውስጥ ሳያስገቡ በየእምነት ተቋማቱና በተለያየ ቦታ ሆነው የወያኔ ካድሬዎች የሚያስወሩትን ወሬ ብቻ በማድመጥና በመታለል “ዐመፅ ይነሣል!” በሚል ተስፋ የስደት መንግሥት ያሉትን እስከማቋቋም ድረስ ተታለዋልና ተጃጅለዋልና ነው ከላይ “የብስለት ደረጃቸውን ታዘብኩት፣ ለሀገራችን ፖለቲካ (እምነተ አሥተዳደር) ሩቅ እንደሆኑ እንድገነዘብ አደረገኝ” ማለቴ፡፡
ይህ እንቅስቃሴያቸውም ማድረግ የሚገባንን ነገሮች በጊዜውና በሰዓቱ ቶሎ በመቀናጀት አድርገን ሀገራችንን ነጻ እንዳናወጣ ሌላ የመዘናጊያ ጊዜ እንድናሳልፍ ጊዜ ገንዘብ እውቀት እንድናባክን አንድነት ኅብረት እንዳይኖረንና እንድንከፋፈል አድርጎ የሚያዳክመን በመሆኑ እንቅስቃሴው በቶሎ መገታት ይኖርበታል ብየ አምናለሁ፡፡
በዚህ እንቅስቃሴ ያላቹህ ወገኖቻችን እውነት ወያኔ በዚህች ሀገርና ሕዝቧ ላይ የሚያዘንበው ግፍና መከራ አሳስቧቹህ ነጻ መውጣታችንን ከሆነ የምትፈልጉት ለዚህም የጸና አቋም ካላቹህና ቁርጠኞች ከሆናቹህ ያለን አማራጭና መንገዱ አንድና አንድ ብቻ ነው፡፡ የአርበኞች ግንቦት አባትን የትጥቅ ትግል መቀላቀልና በጽናት በቁርጠኝነት መታገል፡፡
ይሄንን ስል ሁላቹህም በረሀ ግቡ ማለቴ አይደለም፡፡ ምናልባትም ብዙዎቻቹህ በዕድሜ የገፋቹህ ትሆኑ ይሆንና ይሄንን ማድረግ ያስቸግራቹህ ይሆናል፡፡ ሌላም ሌላም የትጥቅ ትግሉን በአካል ለመቀላቀል የማያስችሉ የጤናና የመሳሰሉ እክሎችም ይኖሩ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ባላቹህበት ቦታ ሆናቹህ እየሠራቹህ ትግሉን በገንዘብ ብትደግፉ፣ በየተሠማራቹህበት የሥራ ዘርፍና የሥራ የኃላፊነት ቦታ ወያኔ ተአማኒነት እንዲያጣና እንዲዳከም የሚያደርጉ የሚያስችሉ ሥራዎችን መሥራት ብትችሉ በግንባር ተሰልፎ ነፍሱን ለመስጠት ከቆረጠ ከተሰለፈ ከተዘጋጀ ታጋይ ያልተናነሰ ዋጋ አላቹህና በዚህ መልኩም መታገል ይቻላል፡፡
ብልጥ ሆነን ያሉ ዕድሎችን ለመጠቀም ፈተናን በብልጠት የማለፉ ብቃትና ብስለት ካለንና ዓላማችን የግል ጥቅምን ለማስጠበቅና ለሥልጣን ሽሚያ ካልሆነ ለዚህች ለምንወዳት ሀገርና ሕዝቧ ከሆነ ይሄንን ከማድረግ የሚገድበን አንዳችም እንቅፋት መሰናክል ይኖራል ብየ አላምንም፡፡ እውነት ነው ትግል ነውና ፈተናዎች ተግዳሮቶች መሰናክሎች ይኖራሉ፡፡ ይሁን እንጅ ነጻነት የሚያስፈልገው የነጻነት ጥመኛ ነን ካልን የሚጋረጡብንን ፈተና መሰናክሎች ለመሻገር ለመወጣት የሚያስችል ብልጠት ጽናት ንቃትና ዝግጅት ይዘን ያለው ዕድል ከጸጉር የቀጠነ እንኳን ቢሆን ከእግዚአብሔርን ጋር ትግሉን ለመወጣት ይቆርጣል እንጅ እጅ ሰጥቶ ለእርድ አይቀርብምና ያለ የሌለ ምክንያት መቀበጣጠር አይገባም፡፡
ገንዘብንም ነፍስንም ለመስጠት ሳንቆርጥ ወይም ከተጠቀሱት ድጋፎች አንዱንም ማድረግ ሳንችልና ሳንፈልግ ግን “ሀገሬን እወዳለሁ!” ምንትስ ብንል የምንቀልደው የምናፌዘው በራሳችን እንጅ በሌላ በማንም አይደለም፡፡ የመንግሥትንም ሥልጣን ለመያዝ ያሳሳቹህም የሚያሻማቹህም ከግል ጥቅም አሳዳጅነታቹህ፣ ዝናና ዕውቅናን ፈላጊነታቹህ እንጅ በእርግጥም የዚህች ሀገርና የሕዝቧ እጣ ፋንታ አሳስቧቹህ፣ እንቅልፍ እረፍት ነስቷቹህ አሳጥቷቹህ አይደለም፡፡
“አይ አይደለም! እኛ ለሀገራችንና ለሕዝባችን የማንከፍለው ዋጋ የለም!” ካላቹህ ደግሞ ነገ ዛሬ ሳትሉ የትጥቅ ትግሉን ተቀላቀሉ፡፡ የሥልጣን ክፍፍል አያሳስባቹህ የትግሉ ዓላማና ግብ እሱ አይደለምና፡፡ ለሥልጣን ክፍፍል ጊዜውና ቦታው ላይ ሲደረስም በፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ (መስፍነ ሕዝባዊ) ምርጫ ብቻ የሚፈታ በመሆኑ ይሄ ፈጽሞ ሊያስባቹህ የሚገባ ጉዳይ አይደለም፡፡ የሀገርንና የሕዝብን ጥቅም የሚያስቀድም የግል ጥቅሙ በፍጹም አያሳስበውም፡፡ ሀገር ትቅደም! ሕዝብ ይቅደም! ኢትዮጵያ ትቅደም!
ይሄ ከሆነ ምንም የሚረብሽ ነገር አይኖርም፡፡ ነገር ግን እንደደርግ ባለሥልጣናት ለሥልጣንና ለግል ጥቅም እየተሽቀዳደምን “ኢትዮጵያ ትቅደም!” ብንል መልሰን ወዳሳለፍነው ማጥ እንሰጥም እንደሆን ነው እንጅ ሀገርና ሕዝብን የሚጠቅም አንዳችም ሚና ልንጫወት የምንችልበት ዕድል አይኖርም፡፡
የትጥቅ ትግሉን የግድ አስፈላጊ ከሚያደርጉት ምክንያቶች አንድ ሁለቱን መጥቀስ ቢያስፈልግ፡-
አንደኛው ወያኔ “በእኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አንተሳሰቡ” ሆን ብሎ ከፈጠረው የእርስ በእርስ ግጭት ሥጋት አኳያ የታጠቀ ኃይል መኖሩ ሕዝቡን “ዐመፅ አድርጌ ወያኔን ባስወግድ ካለበት ደርሶ ሁኔታዎችን የሚቆጣጠር፣ ይህ ችግር እንዳይፈጠር የመከላከል የማረጋጋቱን ሚና ይጫወትልኛል ከዚህ ከሚፈራው ችግርም እድናለሁ” ብሎ እንዲያምንና እንዲደፋፈር የወያኔን ማስፈራሪያ እንዲንቅ ያደርገዋል፡፡
ሁለተኛ ምናልባት በተለያየ ምክንያት ሕዝቡ ዐመፅ አድርጎ ወያኔን የመገላገሉ ዕድል ቢጠብ ወያኔ ለዘለዓለም በጫንቃው ላይ ተጭኖ የሚኖርበትን ሁኔታ “ምን አማራጭ አለኝ? ይሁንለት!” ብሎ እንዳይቀበልና “በትጥቅ ትግል ገርስሸ ሀገሬን ነጻ አወጣለሁ! በትጥቅ ትግል መምጣቴም የወያኔ ሠራዊት ሲፈርስ ሲበተን ወያኔ በሀገርና በሕዝብ ላይ የጋረጠብንን ዘርንና ሃይማኖትን መሠረት አድርጎ ሊነሣ የሚችልን የእርስ በእርስ የግጭት አደጋና ሥጋትን በሚገባ ለመከላከል ለማክሸፍ ያስችለኛል” ብሎ እንዲያምንና እንዲያደርገውም ያስችለዋል፡፡
የታጠቀ የአንድነት ኃይል መኖሩ እስከ አሁን ተጠናክሮ የወጣ የኢትዮጵያን ሕልውና ማስጠበቅ ዓላማው ያደረገ የታጠቀ ኃይል አለመኖሩ ወያኔ እሱ ባይኖር ሊከተል የሚችለውን ቀውስ በማስፈራሪያነት እየተጠቀመ ሕዝቡን አሜን ብሎ እንዲገዛለት ለማድረግ ሲጠቀምበት እንደመኖሩ ሁሉ ይህ ኃይል መፈጠሩ ሕዝቡን ከዚህ ሥጋት ነጻ አድርጎት የሚተማመንበትን አማራጭ እንዲኖረው ያስችላል፡፡
እንዲህ ዓይነት መተማመን በሕዝቡ ልብ ሲፈጠር ብቻ ነው ሕዝብ ከታጠቀው ኃይል ጋር በመናበብ በልበ ሙሉነት ለማመፅና ወያኔን ለማስወገድ እንዲችል የሚያደርገው፡፡ የታጠቀ ኃይል መኖሩ ሕዝቡን ሁለት አማራጭ እንዲኖረው ያስችላል፡፡
የታጠቀ የአንድነት ኃይል መኖሩ ወያኔ በወደቀ ጊዜ ሠራዊቱ ሲፈርስ ከዚህ ሠራዊት የኢትዮጵያና የሕዝቧ ጉዳይ የሚገዳቸውን ወገኖች ወያኔ የጋረጠብንን ሥጋቶች ከመከላከል አኳያ በተደራጀና ባልተደራጀ በቡድንም በግልም የዜግነት ግዴታቸውን በመወጣት ጠቃሚ ሚና እንዲጫወቱ ያስችላቸዋል፡፡
ባጠቃላይ የታጠቀው ኃይልና ሕዝቡ በመናበብ በመደጋገፍ መንቀሳቀስ ሲችሉ ብቻ ነው ወያኔ ወደ መቃብሩ ሊወርድ የሚችለው፡፡ የታጠቀ የአንድነት ኃይል ሳይኖር ከላይ በገለጽኳቸው መሰሪ ችግሮች ተተብትቦ ባለው ሕዝብ ብቻ ለውጥ ሊመጣ ይችላል ብላቹህ የምታስቡ ወገኖች ካላቹህ የዘመነ ወያኔ ኢትዮጵያንና ወያኔ የፈጠራቸውን ያፈጠጡ ያገጠጡ ሥጋቶችን ጨርሶ ምንም የማታውቁ ምንም ነገር ማየትና መረዳት የማትችሉ ከንቱዎች መሆናቹህን በድፍረት ልነግራቹህ እወዳለሁ፡፡
ይህች ሀገር ሽግግር ማድረግ ካለባት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ተቆጣጥሮ ይህንን ሽግግር ለማድረግ ለራሱ ቃል የገባ የታጠቀ የአንድነት ኃይል የግድ የግድ የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ የታጠቀ ኃይል በሀገራችን ያለው ታሪክ መልካም ስላልሆነ የታጠቀ ኃይል ሲባል ደርግንና ወያኔን እያሰብን ሌላም ቢመጣ እንደዚያው የሚሆን እየመሰለን በመጭው እምነት መጣል የሚቸግረን ሰዎች በርካቶች አለን፡፡ ነገር ግን ዛሬ በዓለማችን መስፍነ ሕዝብ (ዲሞክራሲ) የሰፈነባቸው ሀገራት ይሄንን ሽግግር ለማድረግ የበቁት ሽግግሩን ለማምጣት ቆርጠው በታገሉና በተሳካላቸውም የታጠቁ ኃይሎቻቸው መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡
ሁለት ዕድል ከሸፈ ማለት ለዘለዓለሙ አይሳካም ማለት አይደለም፡፡ ዕድሉን አግኝቶ ያልታየን ያልተፈተሸን አካል መኮነን፣ ደምድሞ መፈረጅ፣ ማጠልሸት ከጀርባው ሌላ ዓላማ ከሌለው ጨለምተኝነትና ድንቁርና ነው፡፡ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ኃይል የታጠቀ ኃይል ስለሆነ ብቻ “ሥልጣን ቢይዝ ከደርግና ከወያኔ የተለየ አይሆንም!” የሚሉ ሰዎች ይሄንን የሚሉት ወያኔን ዘለዓለማዊ የማድረግ ድብቅ ዓላማ ከማንገብ ካልሆነ ይሄንን የሚሉት ሌላው ቢቀር አርፈን በመቀመጥ ለወያኔ ዕድሜ ብንሰጠው ወያኔ ጊዜ አግኝቶ ጡንቻውን እንዲያፈረጥም ዕድል ሰጥተነው ያለውን ሰይጣናዊ ዓላማ ሁሉ እንዲፈጽምብንና ለባሰ አደጋ የምንዳረግ በመሆኑ ምንም አማራጭ የለምና የተገኘውን አማራጭ ሁሉ በመጠቀም የትጥቅ ትግል መደረጉን በፍጹም ሊኮንኑ ሊቃወሙ እንደማይገባ ሊገነዘቡ ይገባል፡፡
ጠለቅ ብለን እንመርምር ካልን እውነት እንነጋገር ካልን ሲጀመርም ቢሆን ደርግም ሆነ ወያኔ በተለይ ወያኔ ግልጽ በሆነ መልኩ ፀረ ኢትዮጵያ የሆነ ጠባብና አደገኛ የዘር ጥላቻ የተሞላ የዘር ማጥፋት ዓላማና የጥፋት ተልእኮ አንግቦ የተነሣ የጥፋት ኃይል ስለነበር በፍጹም ለሥርዓት ሽግግር ብቁ ታማኝና የሚመጥን ተፈጥሮ ቁመና ብቃትና ሰብእና እንዳልነበረው ግልጽ ነበር፡፡ ደርግም ቢሆን “ካለኔ በስተቀር” የሚል ከፍተኛ የሥልጣን ጥማት የነበረበት ኃይል ስለነበር እሱም ምሳሌ ሊሆን አይችልም፡፡ እናም ሁለቱም የሥርዓት ሽግግር በዚህች ሀገር ለማምጣት የሚያስችል አቅም ብቃት ታማኝነት ችሎታ እንዳልነበራቸው በሚገባ ይታወቅ ስለነበር በምንም ሁኔታ ቢሆን ለምሳሌለት የሚበቁ አይደሉም፡፡
አርበኞች ግንቦት ሰባትን ያየን እንደሆነ ግን በምንም መልኩ ብናየው አምስት እጅ እንኳን ቢሆን ከደርግና ከወያኔ ጋር ተመሳሳይነት የለውም፡፡ ወያኔና ደርግ ያደረጉትን ላድርግ ቢልም እንኳን ጊዜውም ሌሎች ነባራዊ ሁኔታዎችም የሚፈቅዱለት አይደለም፡፡ ስለሆነም ይህ የታጠቀ የአንድነት ኃይል ያስፈልገናል፡፡
የትም ሀገር ቢሆን ለመስፍነ ሕዝባዊ (ለዲሞክራሲያዊ) ሥርዓት ታማኝ በሆኑ የታጠቁ ኃይሎች ሳይታገዝ ወደ መስፍነ ሕዝባዊ (ዲሞክራሲያዊ) ሥርዓት የተሸጋገረ አንድም ሀገር የለም፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
The post የስደት መንግሥት የችግራችን መፍትሔ ይሆናል ወይስ መንስኤ? appeared first on Zehabesha Amharic.
ፕሮፌሰር አየለ በክሪ፤ ስለንግሥተ ሳባ አፈ ታሪኮችና ታሪክ ይናገራሉ። ፕሮፌሰር አየለ “Ethiopic, An African Writing System: Its History and Principles.” መጽሐፍ ደራሲ ናቸው። (SBS Amharic Radio)
The post ፕሮፌሰር አየለ በክሪ፤ ስለንግሥተ ሳባ አፈ ታሪኮችና ታሪክ ይናገራሉ (AUDIO) appeared first on Zehabesha Amharic.
የህብር ሬዲዮ ጥቅምት 21 ቀን 2008 ፕሮግራም
<...ምርጫ 97ን ተከትሎ እኛ በኮሚሽኑ ያጣረነው እንኳን 193 ሲቪሎች፣ 6 ፖሊሶች ተገድለዋል። 763 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። 40 ሺህ በልዩ ልዩ እስር ቤቶች በአንድ ጀምበር ታስረዋል። ይሄ የሚረሳ አይደለም ነገር ግን እኛ አንድ ነገር ሲመጣ አንድ ሰሞን በዚያ እንገረማለን ወይ እናዝናለን መልሰን ደግሞ ወደ ሌላው እናልፋለን … እኔ በበኩሌ አቶ መለስ በምርጫ 97 የተገደሉት ሁኔታ እውነቱ እንዲወጣ የሚፈልጉ መስሎኝ ተሳስቼ ነበር። መንግስት ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃ ወስዷል ብለን ከወሰንን በሁዋላ ማስፈራራቱ ግርግሩ በዝቶ አቶ መለስ ጋር ስንገባ ለምንድነው እንዲህ የሚደረገው አጣሩ አላችሁን አጣራን እኔ ለምንድነው ይሄን ስላጣራሁ የምሞተው ትገደላላችሁ እየተባልን ነው ስንላቸው ...ይሄ ማስፈራራቱ ምናምኑ ቁንጥጫ ነው ጎራዴው ግን እኛጋር አለ አሉን።...> አቶ ምትኩ ተሾመ በምርጫ 97 የተፈጸመውን ግድያ ያጣራው የሕጋዊው አጣሪ ኮሚሽን አባል ጥቅምት 22 አስረኛ ዓመቱን በማስመልከት ካደረግንላቸው ሰፋ ያለ ቃለ ምልልስ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)
መምህር ግርማ ወንድም ማናቸው? ለምን ታሰሩ? ለመሆኑ ለቤተ ክርስቲያን ምን አድርገዋል? በእርግጥ እንደተባለው አጭበርባሪ ወይም ጠንቋይ ናቸው? አገዛዙ ከመምህር ግርማ የፈለገው ምንድነው? መምህር ግርማ ከኢትዮጵአ መንፈሳዊ አገልግሎት እስከ ሱዳን ስደት የኖሩበትን እና በአገር ቤት ያደረጓቸውን መንፈሳዊ አስተዋጽዎዎች ምንድናቸው? በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያሰናዳነውን ይዘናል( ልዩ ጥንቅር)
ሁበር በቬጋስ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች በተለይ አዲስ የጀመረው ተጨማሪ አገልግሎት ላይና የሁበር አሽከርካሪዎች የገጠማቸው ችግሮች (ውይይት )
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
እንግሊዝ ለኢትዮጵያ የሸጠችው ሊኩሌር ሰሜን ኮሪያ እጅ እንዳይገባ ስጋት ፈጠረ
በኢትዮጵያ ድርቁን ተከትሎ የማጅራት ገትር በሽታ ተከሰተ
በትግራይ ክልል ክትባት ተጀምሯል
የእንግሊዝና የኢትዮጵያው አገዛዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተገናኝተውም የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ መጨረሻው አልታወቀም
የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤተሰቦች ሕክምናና ጠያቂ መከልከሉን ተከትሎ ለአገዛዙ የሰብዓዊ መብትና ዕንባ ጠባቂ የአቤቱታ ደብዳቤ አስገቡ
ሳውዲ በየመን ላደረገችው ወረራ ኤርትራ ድጋፍ ማድረጉዋ ተገለጸ
የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ስርቆትን ለመከላከል በሚል ልምድ ሊወስዱ ናይጄሪያ እንደነበሩ የአገሪቱ ጋዜጣ ዘገበ
የቴሌ ባለስልጣናት አገልግሎቱን ለውጭ ኩባንያ መስጠት ገንዘብ ማሸሽ ነው ሲሉ ገለጹ
አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ በአበበ በቂላ ስም የተዘጋጀውን ሽልማት ተቀበለ
የባህር ዳር የባጃጅ ሹፌሮች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ
The post Hiber Radio : እንግሊዝ ለኢትዮጵያ የሸጠችው ሊኩሌር ሰሜን ኮሪያ እጅ እንዳይገባ ስጋት ፈጠረ፣ በኢትዮጵያ ድርቁን ተከትሎ የማጅራት ገትር በሽታ ተከሰተ፣በትግራይ ክልል ክትባት ተጀምሯል፣ የእንግሊዝና የኢትዮጵያው አገዛዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተገናኝተውም የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ መጨረሻው አልታወቀም፣የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤተሰቦች ሕክምናና ጠያቂ መከልከሉን ተከትሎ ለአገዛዙ የሰብዓዊ መብትና ዕንባ ጠባቂ የአቤቱታ ደብዳቤ አስገቡ ፣ሳውዲ በየመን ላደረገችው ወረራ ኤርትራ ድጋፍ ማድረጉዋ ተገለጸ ፣ የምርጫ 97ን ግድያ ካጣራው ሕጋዊው አጣሪ ኮሚሽን አባል ጋር ቃለ መጠይቅ የሰማዕታቱን አስረኛ ዓመት በመዘከር፣መምህር ግርማ ወንድሙን የተመለከተ ልዩ ዘገባና ሌሎችም appeared first on Zehabesha Amharic.
ከአንድ ዛፍ ፍሬ ለመልቀም የሚፈልግ ከመልቀሙ በፊት መጀመሪያ ፍሬውን መቅመስ ይኖርበታል። አንዳንድ ዛፍ ዠርገግ ብሎ ሲያዩት ልብ ይማርካል። አበባው በጭለማ ሳይቀር ይታያል፤ ያስደስታል። ለሕይወት የሚሆን ፍሬ ግን ላይኖረው ይችላል። እንደዚያ አምሮ ገምሮ ሳለ የሚጠቀሙበት ትሎች ብቻ ሊሆኑ ይችላሉ።
አንድ ሰው ስሙን ከአካዴሚክ ማዕረጉ (Ph.D) ጋር እየጻፈ ደብዳቤ ይልክልኝ ነበረ። ለማዕረግ ያበቃውን ድርሰት (dissertation) የጻፈው ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ነው። የኋላ ኋላ እንደተረዳሁት፣ አድራሻየን ፈልጎ የጻፈልኝ በችሎታው የሚያገለግልበትን ሥራ በማፈላለግ እንድረዳው ኖሯል። ዛፉ ዲፕሎማው ነው፤ ፍሬው ድርሰቱ ነው። የድርሰቱን ቅጂ በፈቃዱ ላከልኝ። ሳነበው አዘንኩ። እንዴት አንድ ዩኒቨርስቲ ይኸንን ድርሰት ለማዕርግ በቂ አድርዶ ይቀበለዋል? እኔ ብሆን ለPh.D ቀርቶ ለBAም እንኳን አልቀበለውም። እንዴት አንድ መርጦ በያዘው መስኩ የሚመራመር ሰው የአርዮስን ክሕደት ለንስጥሮስ ወይም የንስጥሮስን ክሕደት ለአርዮስ ይሰጣል? መምህሩስ (ምንም ሙስሊም ቢሆን) ይኸንን ስሕተት እንዴት ያሳልፈዋል? የአርዮስንና የንስጥሮስ ዳሕጽ ማማታቱን ለምሳሌ ያህል አነሣሁት እንጂ፥ ድርሰቱስ ስሕተት አልባ ገጾቹ በቍጥር ናቸው።
ይኸን ታሪክ ለምሳሌ እንዳነሣ ያሳሰበኝ አቶ ተክሌ የሻው ዶክተር ላጵሶ ዴሌቦ በኢሳት(ESAT) አማካይነት በሰጠው የኢትዮጵያ ታሪክ ትምህርት ላይ ስሕተት ስለታየው ያንን ለማረም በ10/30/ 2015 በቀረበ ጊዜ በሱና በጋዜጠኛው መካከል በተደረገው ውይይት ላይ የታዘብኩት ትዝብት ነው። ለዶክተር ላጵሶ አክብሮት አለኝ። መጻሕፍቱን ያነበብኩት እሱ ቸሮኝ ነው። የኢሳት ጋዜጠኞችና አቶ ተክሌ ወዳጆቼ ናቸው። ውገናየ ከታሪካችን ጋር ነው።
የጋዜጠኛውና የአቶ ተክሌ የሻው ውይይት አጀማመሩ ግራ የሚያገባ ነበር። ጋዜጠኛው፥ “ስሕተቱ ምንድነው፤ እስቲ ንገረን?” ብሎ በማስጀመር ፈንታ፥ የታሪክ ትምህርት ዲፕሎማ ሳይኖርህ፥ የታሪክ ባለሙያ (ባለ Ph.D) ለመሞገት ምን ችሎታ አለህ? የሚል መንፈስ ያዘሉ ጥያቄዎች አከታተለበት። እርግጥ ማንም ተነሥቶ ማንንም ቢተች አያምርበትም። አንድ ሰው እኩያው ያልሆነን ሰው ልተች ሲል መድረኩን መንሣት ይቻላል፤ የተለመደም ነው። መድረኩን ከሰጡ በኋላ ግን ሲያስፈልግ እንደጋዜጠኛ እየጠየቁ መልሱን በጥሞና ማዳመጥ እንጂ በፖሊስ ምርመራ ዓይነት በተሞጋቹ ስም መከራከር በጋዜጠኝነት ሙያ የተለመደ አይደለም። አዳማጮች የአቶ ተክሌን በመልሱ (በፍሬው) እንጂ በዛፉ (በዲፕሎማው) እንዳልፈረዱት እገምታለሁ። ደሞም እኮ መጽሐፉን ላነበበ አቶ ተክሌ ማንም አይደለም።
እርግጥ አንድ ሰው በአንድ ሞያ ላይ ለመዋል፥ ሞያውን ማስመስከር ይጠበቅበታል። Ph.D ሁሉ ተጠርጣሪ ነው አይባልም፤ እኔም አልልም። የፈለግሁት በሙያ ረገድ Ph.Dን ብቸኛ መተማመኛ ማድረግ ስሕተት ነው ለማለት ነው። ለምሳሌ የጋዜጠኝነት ዲግሪ የሌላቸው ታላላቅ ጋዜጠኞች እናውቃለን። ኢሳት ውስጥ አገራቸውን የሚያገለግሉ ሁሉ የጋዜጠኝነት ዲግሪ ያላቸው አይመስለኝም፤ ካላቸው አስተያየቴን በደስታ እለውጣለሁ።
የታሪክ ዕውቀት የሚገኘው የታሪክ ምንጮችን በማንበብ ነው። አቶ ተክሌ አንቱ የሚያስብል የታሪክ መጽሐፍ ደርሷ። በዚያ መጽሐፍ ውስጥ ዶክተር ላጵሶ ያለፋቸው ብዙ ቁም ነገሮችን አስተምሮናል። እኔም ብሆን ማንም የታሪክ አስተማሪ አላስተማረኝም። ታዲያ ከልጅነት ጀምሮ ውሎየ የኢትዮጵያን የታሪክ ሰነዶች ማንበብና መመራመር፣ ማመሳከርም ሆኖ ሳለ፥ ታሪክ አልተማርክምና ስለኢትዮጵያ ታሪክ ለመናገር ብቃት የለህም ብባል ማን እሺ ይላል?
ዶክተር ላጵሶ የመረመረው አቶ ተክሌ ያልመረመረው በሁለቱ ተራኪዎች ማህል ልዩነት የፈጠረው የታሪክ ምንጭ የትኛው ነው? እንዲያውም፥ ፕሮፌሰር ላጵሶ፥ “ዶክተር ስናይደር ነግሮኛል” ሲል ሰምቸዋለሁ። የታሪክ መምህራችን ዶክተር ላጵሶ ዶክተር ስናይደር ያነበበውን ደብተራዎች የጻፉትን አላየውም ማለት ነው። ትምህርት አስኪጨርሱ፥ ከመምህር በታች መሆን ሥርዓት ነው። መምህር ከሆኑ በኋላ ግን፣ ሲሆን መብለጥ አለዚያም እኩል ሆኖ መገኘት ያባት ነው። ለመስማት የፈለግሁት “ይኸንን ለዶክተር ስናይደር አስረድቸዋለሁ” ሲል ነበር።
በውይይቱ ላይ ለአቶ ተክሌ የቀረበለት ሌላው ጥያቄ፥ “ታሪክን መጻፍ የሚችል ማነው?” የሚል ነበር። ጥያቄው ያዘለው ምሥጢር ባይኖረው፥ መልሱ ቀላል ነበር፤ “ታሪክን መጻፍ የሚችል ታሪክ ዐዋቂ” ነው። ታሪክ ዐዋቂ የምለው፥ እንደ ዶክተር ላጵሶ ታሪክ የተማረውን፥ እንደ አቶ ተክሌ የታሪክ ምንጭ የመረመረውን፥ እንደ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት ገድላቱንና ታምራቱን የታሪክ ምንጭነታቸውን ያሳየውን፥ እንደ ደብተራዎቹ ድርጊቱ ሲፈጸም በጊዜው የነበረውን (ማን ይናገር? የነበረ፤ ማን ያርዳ? የቀበረ) ነው። ግን ጥያቄው ንጽሕና የጐደለውና ምሥጢር ያዘለ ለመሆኑ፥ በየቀኑ የምንሰማው ትችት ይመሰክራል። “የኢትዮጵያን ታሪክ የጻፉ ደብተራዎች ናቸው፤ አማሮች ናቸው” የሚለውን ዋጋ ቢስ ትችት ያቀፈ ነው።
ትችቱ በውይይቱ ላይም በግላጭ ተነሥቷል። ኢትዮጵያ ታሪካዊ አገር መሆኗን የነገሩንና ዓለምንም ያስረዱልን፣እኛንም ባባቶቻችን ታሪክ እንድንኮራ ያደረጉን “ደብተራዎችና አማሮች” ናቸው፤ ክብርና ምስጋና ይድረሳቸው።
ግን ታሪክ ጸሐፊነታቸው የተነቀፈው፥ደብተራዎችና አማሮች ስለሆኑ ነው ወይስ እንደሚታሙት “ተረት ተረት” ስለጻፉልን ነው? ታሪካችንን ማን እንዲጽፈው ነው የተፈለገው? ማንስ እንዳይጽፍ ማን ከለከለው? ምዕራባውያን ዘንድ ሄደን በታሪክ ዕውቀት የምንመረቀው ደብተራዎቹና አማሮቹ የጻፉትን ምዕራባውያን በየቋንቋቸው የተረጎሙትን አጥንተን አይደለም እንዴ? አውሮፓውያንና ኢትዮጵያውያን (አማሮችና ደብተራዎች) በጻፉት የኢትዮጵያ ታሪክ መካከል ያለው ልዩነት የት ላይ ነው? ምንም ልዩነት ሳይኖርባቸው አንዱ ዶክትሬት ያሰጣል፥ ሌላው ይነቀፋል። ስለ ግራኝ ዐመፅ ዐረብ ፋቂህ በዐረቢኛ የጻፈውንና ደብተራዎቹ የጻፉትን አስተያይታችሁታል? ከዝርዝሩና ከጸሐፊዎቹ የግል አስተያየት (ያላዩትን ከመጻፍ) በቀር እውነቱ ላይ በምንም አይለያይም። አንዱ “እገሌ ሞቶ ነፍሱ ገነት ገባች” ሲል፥ ሌላው ያቺኑ ነፍስ “ገሃነመ እሳት ገባች” ይላል።
አዲስ ማስረጃ ሲገኝ የተሳሳተ ታሪክ ማረም የተለመደ ነው። አሁን ዛሬ የትኛው አዲስ ሰነድ ተገኝቶ የትኛውን ተረት ሊያርም እንደቻለ ማስረጃ ይሰጠን። አብረን እንመረምረዋለን። ደብተራዎቹና አማሮቹ በዘመኑ ተገኝተው በዓይናቸው ያዩትንና በጆሯቸው የሰሙትን ጽፈዋል። ያላየና አዲስ ማስረጃ የሌለው ሰው የነሱን ድርሰት የመንቀፍ መብት እንዴት ይኖረዋል? ማስረጃ ተፈጥሮ እንደሆነ፥ ፍጡር ማስረጃ አንቀበልም።
ለአቶ ተክሌ የቀረበለት አስገራሚ ጥያቄ “አማራ ማነው?” የሚል ነበረ። ነገሩን የቆሰቆሰው ዶክተር ላጵሶ፥ ተጠያቂው አቶ ተክሌ! ሞረሽ ወገኔን ለምን መራህ ለማለት ይሆን? አለቦታው!
ሌላው የሚናፈሰው ነቀፋ “የኢትዮጵያ ታሪክ የሚባለው የነገሥታት ታሪክ እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ አይደለም” የሚል ነው። ይህ መሠረት የሌለው ነቀፋ በውይይቱ ላይ ሰፊ ቦታ ተሰጥቶታል። የዚህ ነቀፋ ምንጭ ሊቃውንቱ በግዕዝ ያቆዩልንን ታሪክ ምዕራባውያን ሲያሳትሙት “Royal Chronicles” የሚል ስም ስለሰጡት ይመስለኛል። ነቀፋውን አንድ ሰው ጫረው፤ ሆድ የባሰው ሁሉ እየተቀባበለ አለኳኰሰው። እኔ እንዳነበብኩት ከሆነ፥ የተነቀፈው ታሪክ የኢትዮጵያ መንግሥት ታሪክ ነው። መንግሥት ደግሞ ንጉሥና ሕዝብ ነው። የሌላው ሁሉ አገር ታሪክም ቢሆን፥ እንደኛው የመንግሥቱ ታሪክ ነው፤ ከዚህ የተለየ የሕዝብ ታሪክ የሚባል ብሔራዊ ታሪክ የትም የለም። ምናልባት “እገሌ እገሊትን አግብቶ እነ እገሌን ወለደ። በዘመነ ሕይወቱ ይህን ይህን ሠርቶ ከዚህ ዓለም በሞት ወይም በምንኵስና ተለየ” የሚል የቤተ ሰብ ታሪክና የጻድቃኑ ገድላትና ተአምራት ቢጠራቀሙ የሕዝብ ታሪክ የሚባል ነገር ይወጣቸው ይሆናል። ዶክተር ላጵሶ ከእነዚህ ገድላትና ተአምራት ውስጥ ብዙዎቹን እንዳላነበባቸው የመጽሐፉ ይዞትና የዘረዘራቸው ዋቢ መጻሕፍት ይመሰክራሉ። ማስረጃዎችን ፈልጎ ያላጣ አላገኘሁም ብሎ አያጕረመርምም።
ለምሳሌ፥ ታሪክ ጸሐፊዎች ኦሮሞዎች ዳዩ ዳባ የሚባል ንጉሥ እንደነበራቸው ያውቃሉ? ደብተራዎቹ የጻፉትን ተአምረ ማርያም ካላነበቡ ከየት አምጥተው ያውቁታል? ተአምሩ እንዲህ ይላል፤
አረሚዎች (= ኦሮሞዎች) የክርስቲያኑን ሀገር (ዋካትን፣ ጠጠራን፣ ምድረ በረሐን፣ መቅደላን) ሊያወድሙ ተመካክረው ከብዙ ቦታ ዋጃ ላይ ከተቱ። ምክንያቱም፣ አረሚዎች፣ (አዲስ ንጉሥ) ሲያንግሡ የነገሠው አገር የማውደም ልምድ አላቸው። በዚያን ጊዜም ዳዩ ዳባ የሚሉት ነግሦ ነበረ። አገር የሚያወድሙበትና ጦር የሚያውጁት በኅዳር ወር በሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል በዐል ዕለት ነበር። . . . እመቤታችን ማርያም አረመኔዎቹ አገሯን ለማጥፋት ጨክነው እንደተነሡ ስታይ፥ሳያስቡት፣ ወደምድረ አዳል መርታ ጠላቶቻቸው (ሙስሊሞቹ) እጅ ላይ ጣለቻቸው። ከ12 ነገሥታት (= የጎሳ መሪዎች) አንድ ንጉሥ ብቻ ተረፈ፤ ከሠራዊቱም አንዳንድ ለወሬ ነጋሪ ተርፎ ይሆናል።
ይህን እዚህ የጠቀስኩት “የአባ ባሕርይ ርድሰቶች” እሚባለው መጽሐፌ ውስጥ ስላልገባ ነው። ኢትዮጵያውያንም ሆኑ ምዕራባውያን፥ ደብተራዎቹና አማሮቹ የጻፉትን መሠረት ሳያደርግ ተአማኝነት ያለውን የኢትዮጵያን ታሪክ መጻፍ አይችልም። እነሱን (በእነሱነታቸው) የጠላ በምዕራባውያን እጅ አዙር ይጠቅሳቸዋል።
(አባ ባሕርይና አለቃ ታየ ስለ ኦሮሞዎች የጻፉትን የሚተቸውን “የአባ ባሕርይ ርድሰቶች” ለማንበብ የፈለገ ከኢንተርነት ስላለ (The Works of Abba Bahriy – by Dr. Getatchew Haile) በነፃ ቀድቶ ማንበብ ይችላል።)
The post (የላጲሶና የተክሌ ጉዳይ) ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ ፤ ወይ ጣፍጠው ወይ መረው ታገኟቸዋላችሁ (ጌታቸው ኃይሌ) appeared first on Zehabesha Amharic.
መብራት ሀይል ሰፊ ከመሆኑም በላይ ለአስተዳደርም ሆነ ለቁጥጥር አስቸጋሪ የሆነ ድርጅት ሲሆን ባለፉት ሦስት አመታት አንድ መለስተኛ ግድብ ሊሰራ በሚችል ወይም ህዝብ ላይ የተጫነሁን የአባይ ግድብ ወጭ በመጠኑም ሊሸፍን የሚችለዉን ገንዘብ በተሳሳተ ጥናት ምክንያት ለሕንዶች ሰጥተዉ ብዙ ሚሊዮን የዉጭ ገንዘብ ከዜጎች አፍንጫቸዉን ተይዘዉ በተሰበሰበዉ ገንዘብ ያለጥቅም በመበተን ምንም ዉጤት ሳይኖረዉ ስተታቸዉንም ለመሸፋፈንም ቢሞክሩም መልሶ ለማዋሀድም ባያፍሩም አልሸሹም ዞር አሉ እንደሚባለዉ የሁለቱንም ድርጅቶች የሚያስተዳድር ሊሾሙም እያሰቡ ነዉ ፡፡ከላይ እንደጠቀስኩት ድርጅቱ ሰፊ ሀገራዊ ተልኮ ያለዉ ለሀገርም እድገት ዋናዉ ቁልፍ ድርጅት ነዉ ፡፡
የመንግስት በመሆኑ ትርፉና ኪሳራዉ ባይታወቅም ብዙ ፕሮጀክቶችን ስለሚያንቀሳቅስ በመንግስት የካፒታል ወጭዎች እና በአበዳሪ ድርጅቶች(በመጭዉ ትዉልድ ላይ የሚጫን ዕዳ) እየተሸፈነ ሲገኝ እነዚህ ወጭዎች በድርጅቱ ዉስጥ የፕሮጀክቶች ጨረታና ግምገማ ሆን ተብሎ በጥቅማ ጥቅም ከጨረታ በፊትም ሆነ በቀጣይ መረጃ በማቀበልና በጥቅም በመደለል ህገ ወጥ ስራ ይሰራል ፡፡ሌላዉ የዉጭ ተጫራቾች እንደኛ ሀገር ሰዎች እና ድርጅቶች ለራስ የማደግ ሀሳብም ፍላጎትም የላቸዉም የስራ ሓላፊዎችን እና ባለስልጣኖችን ምን እንደሚፈልጉ ስለሚፈልጉ የፕሮጀክቱ ወጭ ዉስጥ በመጨመር በገንዘብም ሆነ በቁሳቁስ መልክ ማማልያ ያደርሳቸዋል እንደ ሀገር እንደ ጥሩ እሊና እንዳለዉ ሰዉ ፈረንጆች ጽፈዉ እነደተማርነዉ አንድ ፐሮጀክት በትንሽ ወጭ በተወሰነለት ጊዜ ዉስጥ የሚጠናቀቅ እና ሌሎች ሲሆኑ ሕጋዊ የሚመስሉ ግን ግልጽ ሌብነት እና ብክነት እየተፈጸመ ይገኛል ድርጅቱ በርካታ ፕሮጀክቶችን እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በርካታ በእቅድ ደረጃ የተቀመጡ ወደ ስራ ያልተገቡ በርካታ ፕሮጀክቶችም አሉ ፡፡
የዉጭ ድርጅቶች ወደ አለማቀፋዊ ስራ ዉስጥ ሲገቡ የሀገራቸዉንም ህህት ድርጅቶች እና ሌሎች ድርጅቶችን ያማከለ እድገት አቅደዉ ነዉ የሚገቡት ከላይ እንደጠቀስኩት እኛ ገቢያችን ታክስ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ብቻ ሳይሆን እንደ ህግና ድንብ ስንሄድ ፐሮጀክቶቻችን ወጭያቸዉ የቀነሰ እና ጥራት ያላቸዉ መሆን ሲገባቸዉ በሌላ በኩል ደገሞ የዉጭ ተቁራጮች ደግሞ ብዙ ትርፍ ማግኘትን አላማቸዉ አድርገዉ ነዉ የሚነሱት እንደ ምሳሌ ለመጠቃቀስ ድርጅቱ ዉስጥ በተለያየ ጊዜ በኃላፊነት ያሉ ሰዎች በዝምድናና በግሩፕ በብሔር የተደራጁ ሲሆን ሰራተኞች ኃላፊ ሆነዉ ሲሾሙ እንዲጠቀሙ እና እነዲዘርፉ ነዉ በድርጅቱ ዉስጥ አብዛኛዉ ሰራተኞች በስጋ ዝምድና እና በጋብቻ የተሳሰሩ በመሆናቸዉ ለሹመት የሚታጩት ሰዎችም በችሎታቸዉ ሳይሆን እነዲጠቀምና እነዲጠቅመኝ በማለት ነዉ ፡፡ለምሳሌ ያህል ኢትዮጵያ የመኪና ችግር የለባትም ስለዚህ አንድ ፕሮጀክት እንደ ክብደቱ በትንሹ 15 አና ከዚያ በላይ መኪናዎች በፕሮጀክት ወጭዎች ዉስጥ የተካተቱ ግን ለስራ ተብለዉ ግን ሳይሆን የዘመኑ ለቅንጦት የመጡ ቪ8 ቶዮታ ፒካፕ እና ኤክስኩዉቲቭ ቶዮታ መኪናዎች ምህረት ደበበ በሚያስተዳድርበት ጊዜ ከስሩ ባሉት የተወሰኑት እና በተዋረድ ባሉ የስራ ዓላፊዎች ዉሎአቸዉንና መዋያቸዉን ለመዝናኛ በደብረዘይት እና አዋሳ በድርጅቱ ነዳጅ ባጠቃላይ በአገር ሀብት ሲጫወቱ ኖረዋል ፡፡ያዉ ስራ በመቀጠል ምህረት ደበበ የራሱን ሰዉ ሲወክል በ ሰዉ ኃይል አስተዳደር የተመደበዉ ግለሰብ አሉ ያላቸዉን ያገሩ ሰዎች ቁለፍ ቁለፍ ቦታዎች ከደረደረ በኃላ ከ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ደብረ ጽዮን ጋር ባለዉ የጠበቀ ግንኙነት ወደ ልላ ቦታ ድርጅቱን ለቆ ሲሄድ ተመልሶ እንደሚመጣም ጭምር ነዉ ፡፡የአሁኖችም በምክትል ስራ አስኪያጅዎች የሚይዙት መኪና የአሁኑ ሀይዉንዳይ ዘመናዊ መኪና ነዉ ይህም ማለት በሕዳሴ መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት ለስራ የገባ ነዉ፡፡
ሌላዉ ድርጅቱ ካለዉ ስፋት አንጻር ያሉትን ሀብትና ንብረት በአግባቡ አያዉቅም በቅርቡ የሚሰራዉንም የሚሰራውን የድርጅቱን መኪና በጉልበት ሜቴክ ቢሆስድም አሁንም ቢሆን ካሉት የመኪና ብዛትና በየጊዜዉ በየ አዳዲስ ፕሮጀክቶች የሚገቡት መኪናዎች አንጻር ከሚወጡት በፕሮጀክቶች ወጭ ተደምረዉ ከወጫቸዉ በተጨማሪ ተጨማሪ አግባብ የሌላቸዉ የነዳጅና የጥገና ወጭዎችን ድርጅቱ ላይ ከመጫኑም በላይ ባሉኝ መረጃዎች ትዉልድ ሊከፍለዉ የማይችለዉ ዕዳ ተሸክሞ የሚገኝ መሆኑን መንግስት እራሱ አያዉቀዉም በየጊዜዉ ለፕሮጀክት ወጭዎች የሚዉል ቦንድ በመሸጥ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዘብ ቢያገኝም የወለዱም ክፍያም የተቆለለ ከመሆኑም በላይ መብራት ኃይል በህዳ ምክንያት ቢሸጥ የዉጭ እና የ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድርሻ ምን ያህል ይሆናል ብለዉም ዉስጥ አዋቂዎች ያስባሉ ፡፡ለሕዝባቸህን ግልጽ ለማድረግ ማንኛዉም ፕሮጀክቶች አገሪቱ ዉስጥ የሚሰሩት የመንገድ፡ የዉሃ፡የቴሌ፡የመብራት፡የጤና እና የሌሎች ፕሮጀክቶች በአበዳሪ አካላቶች ወጫቸዉ ሲሸፈን መቶ ፐርሰንት አይሸፍኑም ሀገሪቱ ከ10 እስከ 20 ፐርሰንት የሚሆነሁ ወጭዎች ለአስተዳደራዊ ወጭዎች እና ለአገር ዉስጥ እና በተጨማሪም በሀገር ዉስጥ ገንዘብም ሆነ ለአለም አቀፍ ክፍያ በዉጭ ሀገር ገንዘብ ለከፍያ ሲሁል በተጨማሪም ቀሪዉ 80 ፐርሰንት የሚሆነዉ ክፍያ ለ ኮንትራክተሮች ና ለአማካሪ ድርጅቶች ክፍያ ሙሉ በሙሉ በዉጭ ሀገር ገንዘብ የሚፈጸም ነዉ ፡፡ታዲያ 20 ፐርሰንት ጠቅላላ ድምሩ ቀላል አይደለም ቢሊየን እና ከዛ ብላይ ነዉ በአገር ዉስጥ ገንዘብ ብናሰላዉ ታዲያ እነዚህ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ከላይ እንደጠቀስኩት ተልኮቸዉ ብቻቸዉን ለማደግ ሳይሆን በሀገራቸዉ የሚገኙትንም ድርጅቶችንም ለማሳደገ ጭምር ሲሆን ልምሳሌ የመኪና፣የሆቴል እና የቱሪዝም ፤የቴክኖሎጂ አና የመሳሰሉትን ድርጅቶችንም ለማሳደግ ጭምር ነዉ፡፡
ይህንን አንድ በ አንድ ለማሳየት ልሞክር ከላይ ግልጽ ሌብነት ያልኩት በጨረታ ዉሰጥ በ ቴስቲንግ እና በሌሎች ሰም የተካተቱት መጠቃቀሚያ ሲሆን ከደሃዉ ጉሮሮ በታክስ ስም የተሰበሰበ ሲሆን ከ 15 ቀን እስከ 2 ወር በአዉሮፓ እና በቻይና እነዲሁም በሌሎች ሀገሮች ባለ ኮከብ ሆቴሎች ፣ቱሪስት መስህብ በመጎብኘት የሆነዉ ሆኖ በአንድ ፕሮጀክት በትንሹ ከ 50 ሰዉ በላይ ወደ ዉጭ የሚሄዱ ሲሆን በአማካይ የቀን አበል ድምር መቶ ሺ ብር፡ ለቴክኖሎጂ ዉጤቶች አርባ ሺ ብር ፡የአየር መንገድ ወጭ እና የአረፉበት ባለ ኮኮብ የሆቴል ወጭዎች ድምር ከሩብ ሚሊዮን በላይ ወጭ ሲሆን ባለዉ የሰዉ ብዛት ሲባዛ በብዙ ሚሊዮን ሲወጣ ፣በተጨማሪም ይህ ሁሉ ወጭ ከተሸፈነላቸዉ በተጨማሪ እዛ በቆዩበት ሁሉ በቀን ከ 100 አና 150 የዉጭ ሀገር ገንዘብ የቀን ሀበል የሚያገኙ ሲሆን በተጨማሪም ዉድ የቴክኖሎጂ ዉጤቶችን ዉድ ላፕቶፕ እና ሞባይሎች በጉብኝት ወቅትም ይበረከትላቸዋል ይህ ታዲያ በሀገር ላይ የሚደረግ ቀልድ በሙያተኛ ስም ምርትን ፋብሪካ ገብቶ አይቶ የመዉጣት ጉብኝት ሀገር ዉስጥ ሲገባ ወደብ ሲደርስ ካሉት የደረጃ መዳቢዎች ጋር በተቀናጀ ለሀገር ብልጽግና ከመስራት ይልቅ በተናጥል እና በግሩፕ ለዘረፋ መንቀሳቀስ ፡አገር ዉስጥ ሲገባ በኮሚቴ ለገቡት ዕቃዎች ትክክለኛነት መሰጠት ሲገባዉ ይህ ሁሉ ወጭ በኋላ በ ፕሮጀክት ማናጀር እና ሳይት ማናጀር ጥራት በሌላቸዉ እቃዎች እየተገነቡ ከምን ደረሰ ብሎ በየጊዜዉ ክትትል የሚያደርግ አካል ባለመኖሩ ፣በተጨማሪም ትርፍ እና አግባብ የሌላቸዉ የመኪናዎችን ወጭዎች ከጨረታዉና ከ ግምገማ ያለማስወጣት ድርጅቱ ላይ ወጭ ተጭኖበታል ፡፡
ድርጅቱ ብዙ ልምድ እዉቀት ባላቸዉ ድርጅቱን የሚያሳድጉ ማኔጅመንት ከዉስጥ ከሌለ ከዉጭ በመቅጠር ለህድገት እና ለለዉጥ የማይነሳሳ ቢሆንም ድርጅቱ ዉስጥ ያሉት የማኔጅመንት ሰዎች የድርጅቱን የሰዉ ኃይል ከመቅጠር በዘለለ ለድርጅቱ ህድገት በዉሳኔ ሰጭነት ሚና የላቸዉም ፡፡ ከኢንጅነሪንግ ሊያዉም ኤሌክትሪካል ኢንጅነሪነግ ናቸዉ ድርጅቱ ዉስጥ በኔትዎርክ እና በጥቅማጥቅም ዉስጥ በኃላፊነት ያሉት ሌሎች የኢንጅነሪንግ መስኮች ባጋጣሚም በድንገት አልፈዉ ለአላፊነት ይበቃሉ፣በተረፈ ሌሎች የትምህርት መስኮች በድርጅቱ ዉስጥ ከሙያ እና ለዉሳኔ ሰጭነት ለድርጅቱ እድገት የማይጠቅሙ ናቸዉ በፍርሃት እና በስጋት ነዉ የሚኖሩት ፡፡ለድርጅቱ ስራ የሚሰራዉ ሙያተኛ እና ድርጅቱን የሚመራ ሰዉ መለየት አልተቻለም ፡አሁን ድርጅቱን የሚመሩት ወ/ሮ ዉሎ እና አዳራቸዉ ዉጭ አገር እንዲሁም በመንግስት ስብሰባ ላይ ነዉ፡፡በድርጅቱ ዉስጥ ካለዉ ሙስና ስፋት በህገ ወጥ ያካበቱትን ሀብት ለማሸሽ በዘመድ ሀዝማድ ቢያስቀምጡም የተወሰኑትም ከደሞዛቸዉ ከምድር በላይ ቤቶችን በመስራት በማክራየት ምንጩም ለሽፋን በድርጅቱ ዉስጥ ባለዉ ብድር ማህበር ወስጄ ስራ ጀመርኩ ለማለትም ይሞካክራቸዋል፡፡በአገሪቱ ዉስጥ ያለዉ የጸረ-ሙስናም አብዛኛዉ ጥቆማ ወደስራ ከተገባ በኃላ በመርማሪዉና በኃላፊዎች በጥቅም በመደለል ጥቆማዎችን ወድቅ በማድረግ ከሙሰኞች ጋር ተካፍለዉ በመብላት ለጸረ- ሙስና ሰራተኞች የገቢ ምንጮች መሆናቸዉ የአደባባይ ሚስጥር ነዉ፡፡
ሌሎች ትንሽ የማይባል ባለዉ የሌብነት ኔትዎርክ ምክንያት ከተማ ክክፍሉም ሆነ ከስራ ክፍል ዉጭ ቁጭብለዉ የወሮች አበል እና ትርፍ ሰዓት መሙላት፡ ነዳጅ ያለ አግባብ መጠቀም ፡በፕሮጀክቶች የመስክ ነዳጅ ወጭዎች ፣የመንግስት መኪና ለአስጎብኚ ድርጅት ጋር በጥቅም መተሳሰር ፡የመኪና መለዋወጮችን በመስረቅ በፕሮጀክት ወጭዎች ሞኤንኮ ማስጠገን ፡ለሰፊዉ ህዝብ አገልገሎት ከመስጠት ይልቅ በጥቅም ለግል ባለ ሀብት ማስቀደም ፡የመስመር ህቃዎችን መሸጥ፡ሙስና ከመርቀቁ የተነሳ ለድርጅቱ በጨረታ የሚገዙት ዕቃዎችለይ ዋጋ በመቀነስ ጨረታዉን ካሸነፉ ብዋላ ጥራት የሌላቸዉን ማስገባት በየትኛዉም የመንግስት ኃላፊዎች እና ባለስልጣናት እንደሚደረገዉ በስራ ሰዓት ማሳጅ ቤት እና መቃሚያ ቤት መዋል እና ሌሎች ተዘርዝረዉ የማያልቁ ብዙ ችግሮች ናቸዉ፡፡
ሚኪ
The post መብራት ኃይል አንድ ወደፊት ሁለት ወደ ኃላ የሚራመድ ድርጅት | ከውስጥ አዋቂ የወጣ ትንታኔ appeared first on Zehabesha Amharic.
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ) ባጠቃላይ በአራቱም ማዕዘን የኢትዮጵያ ጠረፎች በቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ የሚኖረው በህወሓት ቁጥጥር ስር የሚገኘው መከላከያ ሰራዊት አባላት በየዕለቱ ያለማቋረጥ ስርዓቱን እየከዱ ሲሆን በተለይም ደግሞ ከሰሞኑ ቡሬ ግንባር በስልጠና ላይ ይገኙ የነበሩ እጅግ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች ያገኙትን ቀዳዳ ተጠቅመው በቡድን በቡድን እየሆኑ በመሽሎክ ከአካባቢው ተሰውረዋል፡፡ ወሎ ውስጥ ከአንድ ቀበሌ ብቻ 10 ወታደሮች ከጦር ግንባር ከድተው ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡
አሁንም ቢሆን አብዛኛው ሰራዊት መሽሎኪያ ቀዳዳ እያነፈነፈ ሊከዳ በቋፍ ላይ እንደሚገኝ የመከላከያ ምንጮቻችን የላኩት መረጃ ያረጋግጣል፡፡
The post በቡሬ ግንባር ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት አባላት ከዱ appeared first on Zehabesha Amharic.
የተከበሩ ፕ/ር ጌታቸው ሃይሌ ከአቶ ተክሌ የሻው ጋር ያደረኩትን ቃለምልልስ አስመልክቶ አንዳንድ ትችቶችን ልከውልን አንብቤዋለሁ። ትችት ላወቀበት በእውቀትና በስነምግባር ለማደግ ይረዳልና በአክብሮት እቀበለዋለሁ። ከእርሳቸው በፊትም አንዳንድ ሰዎች፣ ባለቤቴን ጨምሮ፣ በሁለቱም ቃለምልልሶቼ ደስተኞች እንዳልነበሩ ነግረውኛል። እንዲያውም ባለቤቴ የአቶ ተክሌን ቃለምልልስ ሰምታ ኖሮ ስትቃጠል አምሽታ ቤት ስገባ ገና እራቴን እንኳን ሳልበላ በሃይለቃል ነበር የተናገረችኝ። በጣም የገረመኝ ሙሉውን ቃለምልልስ ሰማሽው ስላት ፣” ከ20 ደቂቃ በሁዋላ ነው ያቆምኩት ” አለችኝ። ሙሉውን ስሜውንና እንወያያለን ብያት በሰላም እራቴን በላሁ።
እኔ ይህን መልስ ስሰጥ ራሴን ለመከላከል ወይም ራሴን እንከን የለሽ አድርጌ ለማቅረብ አይደለም። ሁሌም እራሴን እንደተማሪ እቆጥራለሁ። በቃለምልልሱና በተሰጡት አስተያየቶች ብዙ ትምህርቶችን መውሰዴን አልሸሽግም። እንግዲህ ተመልካች በቅን ልቦና አይቶ እንዲፈርድ አንዳንድ ነጥቦችን ማንሳትም ተገቢ ይመስለኛል። ፕ/ር ጌታቸው የአቶ ተክሌን ትምህርት በማስመልከት ያነሳሁት ጥያቄ ተገቢ እንዳልሆነ ገልጸዋል። በጋዜጠኝነት ትምህርት ” መጥፎ የሚባል ጥያቄ የለም” ይባላልና ጥያቄውን ማቅረቡ በጋዜጠኝነት መርህ ደረጃ ክፋት አልበረውም። ለዚህም እኮ ነው በአንድ ጉዳይ ላይ ምሁራን አስተያየት እንዲሰጡ ሲጋበዙ የሰዎች የትምህርት ደረጃ ተብራርቶ የሚቀርበው፣ ውይይቱ ክብደትና ትኩረት ያገኛልና። ፕ/ር ጌታቸው የጥያቄው አቀራረብ አቶ ተክሌን ለማሳነስ ተብሎ የተደረገ አድርገው ወስደውታል። ተመልካቾች እንደዛ ብለው ቢያስቡ አይፈረድባቸውም። ተመልካቾች ጋዜጠኛው የሚያስበውን ሃሳብ እንዲያስቡ ለማድረግ የአቀራረብ ስልቱን ማስተካከል የነበረበት ጋዜጠኛው ነውና ምናልባትም እንዲህ አይነት ትርጉም እንዲሰጠው አድርጌ አቅርቤ ከሆነ ስህተት ሰርቻለሁ እና እቀበለዋለሁ። ይሁን እንጅ ይህንና ሌሎችንም ጥያቄዎች እንድጠይቅ ምን አነሳሳኝ የሚለውን ማስረዳቱም ፣ በቅን ልቦና ለመፍረድ ይረዳልና የሚከተለውን ማብራሪያ አቀርባለሁ።
አቶ ተክሌ የዶ/ር ላፒሶን ቃለምልልስ ከሰሙ በሁዋላ ” ከዶ/ር ላፒሶ ጋር ያደረጋችሁትን ቃለምልልስ ሰማሁት አዳመጥኩት መልካም ነው፣ ሆኖም ፕሮፌሰሩ አውቀው ይሁን ሳያውቁ የሳቱዋቸው ጉዳዮች ስላሉ እነዚያ እንዲስተካከሉ ሃሳብ ልስጥ” የሚል ኢሜል ላኩ። እኔም በደስታ ልናስተናግዳቸው ዝግጁ መሆናችንን በመግለጽ ቀኑን እንዲያስታውቁኝ መለስኩላቸው። ሆኖም ከቃለምልልሱ ቀን በፊት አቶ ተክሌ ” ለዶ/ር ላፒሶ ያዘጋጀሁት መልስ ይህንን ይመስላልና በዚህ ቅደም ተከተል ቢሆንልኝ እምርጣለሁ” የሚል ረጅም ጽሁፍ አዘጋጅተው በድጋሜ ላኩልኝ። ጽሁፉን አነበብኩትና የተሰማኝን ጻፍኩላቸው። አንደኛውን አስተያየት ተቀበሉት፣ ሁለተኛውን ግን ” እርሱን ለኔ ተወው ” አሉኝ። በእኔ በኩል ከጽሁፋቸው መካከል አንደኛው በቀጥታ ቢተላለፍ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ አደጋ የሚያመጣ፣ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ አማሮችን ብቻ ሳይሆን መላውን ህዝብ ለእልቂት የሚዳርግ ከፍተኛ የታሪክ ጠባሳ ጥሎ የሚያልፍ ነገር መሆኑን አመንኩ። ይሄ ነገር አደገኛ መሆኑን ከኢዲቶሪያል ፖሊሲያችንም አንጻር ማስተላለፍ እንደማይቻል ጻፍኩላቸው። ይህንን አደገኛ የተባለውን ጽሁፍ እዚህ ላይ የማልጠቅሰው ለእርሳቸው ካለኝ አክብሮት አንጻርና እሳቸው ይፋ አድርገው ያላሉትን ማድረግ ስለሌብኝ ነው። ይህ አደገኛ መልዕክት በመላው አገሪቱ እየታዬ ባለው ኢሳት ቢተላለፍ ኖሮ ኢሳትም ሆነ እኔ ራሴ ዘላለም የምጸጸትበት፣ በወንጀልም የምጠየቅበት እሆን ነበር። በተለይ ሌት ተቀን ለአገራቸው የሚለፉትን ባልደረቦቼን መግደል ይሆንብኝ ነበር። ከዚህ በሁዋላ አቶ ተክሌ “ይህን መልዕክት እንደወረደ እንዳይናገሩት ምን ማድረግ አለብኝ?” የሚለውን አንስቼ ከራሴ ጋር ብዙ ተማገትኩ። ባልደረቦቼን አማከርኳቸው። “ቃለምልልሱን መሰረዝ” የሚለው አንድ አማራጭ ነበር፤ ይህ ደግሞ ፈጽሞ የማይሞከር ነው፤ ለሃሳብ ነጻነት የሚታገሉ ሰዎች ፣ የሰዎች ሃሳብ የሚያፍኑ ከሆነ ትግላቸው የውሸት ነው ማለት ነው ። ይህንን ንግግር ቆርጬ ባስቀረው ደግሞ “ኢሳት ሃሳባችንን አፈነ፣ ቆርጦ አስቀረ” የሚል የአፈና ዘመቻ ይከፈትበታል። ይህም ሌላ ፈተና ነው። ስለዚህ የነበረኝ አማራጭ በተቻለኝ መጠን ህዝብን ለግጭት የሚያነሳሳ ነገር እንዳይናገሩ መቆጣጠር ነበር። አውቀው ያደርጉታል ብዬ ባላምንም < ይህን ባይናገሩት ይሻላል” ስላቸው፣ እሱን በኔ ተወው ማለታቸው ፍርሃት ለቀቀብኝ። እውነት ለመናገር ወደ መጨረሻ አካባቢ ጣልቃ እገባ የነበረው በመጨረሻ ቅደም ተከተል ያስቀመጡትን እንዳይናገሩ እና በዋና ዋና ቅሬታዎች ላይ ብቻ አትኩረው ስሜታዊ ወይም አነሳሽ የሆኑት ቃላትን እንዳይጠቀሙ ለማድረግ እንጅ ለሌላ አይደለም። አቶ ተክሌ ያን ጽሁፍ አስቀድመው ባይልኩልኝ ኖሮ እኔም ስጨነቅ ባልሰነበትኩ፤ እሳቸውም ያሰቡትን ተናግረው፣ እዳውን ለእኔ ትተው፣ ይጨርሱ ነበር። ዞሮ ዞሮ አደገኛ ያልኩትን ሃሳብ ቆርጨ ማስቀረቴ ስለማይቀር፣ ኢሳትም “ሃሳባቸውን ቆረጠባቸው በሚል ከመተቼት አያመልጥም ነበር ። ለነገሩ፣ ጽሁፍ አዘጋጅቶ በዚህ ቅደም ተከተል ቢሆንልኝ እመርጣለሁ የሚል መልዕክት መላኩም ትክክል አልነበረም። እንዲያውም “አቶ ተክሌ ኢሳትን አጣብቂኝ ውስጥ ለመክተት ብለው ነው ይህን ያጻፉት ወይስ ሌላ ምክንያት ይኖራቸው ይሆን እያልኩ ብዙ አውጥቼ አውርጃለሁ።
ፕ/ር ጌታቸው ለምሳሌ በጽሁፋቸው ግርጌ ይህን ይላሉ
“አረሚዎች (= ኦሮሞዎች) የክርስቲያኑን ሀገር (ዋካትን፣ ጠጠራን፣ ምድረ በረሐን፣ መቅደላን) ሊያወድሙ ተመካክረው ከብዙ ቦታ ዋጃ ላይ ከተቱ። ምክንያቱም፣ አረሚዎች፣ (አዲስ ንጉሥ) ሲያንግሡ የነገሠው አገር የማውደም ልምድ አላቸው። በዚያን ጊዜም ዳዩ ዳባ የሚሉት ነግሦ ነበረ። አገር የሚያወድሙበትና ጦር የሚያውጁት በኅዳር ወር በሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል በዐል ዕለት ነበር። . . . እመቤታችን ማርያም አረመኔዎቹ አገሯን ለማጥፋት ጨክነው እንደተነሡ ስታይ፥ሳያስቡት፣ ወደምድረ አዳል መርታ ጠላቶቻቸው (ሙስሊሞቹ) እጅ ላይ ጣለቻቸው። ከ12 ነገሥታት (= የጎሳ መሪዎች) አንድ ንጉሥ ብቻ ተረፈ፤ ከሠራዊቱም አንዳንድ ለወሬ ነጋሪ ተርፎ ይሆናል።”
አሁን ይህን ጽሁፍ ፕሮፌሰሩ ኢሳት ላይ ልናገረው ቢሉ የሚፈጥረውን አደጋ ተመልከቱ። እንኳን ኢሳት ላይ ዌብሳይት ላይ እንኳን መቅረብ የሌለበት ጽሁፍ ነው፤ እዛው ትምህርት ቤት ውስጥ መቅረት ያለበት ነው። እንግዲህ ይህን አይወጣም ካልሁ፣ አቶ ተክሌ የማቀርበው መልስ ብለው የላኩት ደግሞ ከዚህም በእጅጉ ይብስ ነበር ። አባቶቻችን “እየዋሹም”፣ “አንተም ተው አንተም ተው ” እያሉ አንድነታችን እንዲቀጥል ካላደረጉን ያች አገር እንደ አገር መቀጠሏ አጠራጣሪ ነው። እንዴ የዛሬ አባቶች እኮ ነገ ያልፋሉ፣ እዳው እኮ ለኛና ለመጪው ትውልድ ነው የሚተርፈው። ኢትዮጵያን በስም ብቻ ሳይሆን በተግባር ልንወዳት ይገባል። ኢትዮጵያዊ ስንል ደግሞ ለሁሉም ስሜት መጠንቀቅ አለብን! አሁን በሁሉም ጎራ ዋሽቶ የሚያስታርቅ ሽማግሌ ያስፈልገናል።
ሌላው አቶ ተክሌን ስለትምህርታቸው የጠየኩበት ዋና ምክንያትም “ዶ/ር ላጲሶ የሳቱዋቸውን ጉዳዮች ለማስተካከል ” የሚል መልዕክት ስለሰደዱልን ብቻ ነው። የእኔ አላማ የነበረው አድማጩ አንድ የታሪክ ባለሙያ የሚያቀርበውን ትንተና ሌላ የታሪክ ባለሙያ እንዴት እንደሚያፈርሰው ማሳየት ነበር። ፈጣሪን ዋስ እጠራለሁ፣ እኔ እስከዚያ ሰዓት ድረስ አቶ ተክሌ የታሪክ ተማሪ እንጅ ሌላ ትምህርት ያላቸው አይመስለኝም ነበር ። ብዙ ታሪክ ያውቃለሁ፣ ብዙ ጊዜም ሰምቻቸዋለሁ። በፊት ቃለምልልሳቸውን ሳዳምጥ “ትንሽ ቶናቸውን ቢቀንሱት፣ ስንቱን ታሪክ ያስተምሩት ነበር” እል ነበር። የታሪክ ተማሪ መሆናቸውን እንዲናገሩ ስጠይቃቸው በሙሉ ልብ (confidence) ነበር። የፖለቲካል ሳይንስ ተማሪ ነኝ ሲሉኝ “ክው” አልኩ ። ታሪክን እንዴት አጠኑ ብዬ የጠየኳቸውም ተመልካቹ ቃለምልልሱን ክብደት እንዲሰጠው ለማድረግ እንጅ እሳቸውን አሳንሶ ለማቅረብ አልነበረም። የዶ/ር ላፒሶን ” ስህተት አስተካክላላሁ” ብለው ሲነሱ፣ ተመልካቹ “እኝህ ሰው ትምህርታቸው ምንድነው?” ብሎ መጠየቁ አይቀርም። አቶ ተክሌን ስለትምህርታቸው ባልጠይቃቸው ተመልካቹን ላሳስት እችል ነበር። አንዱ ተነስቶ “አቶ ተክሌ የታሪክ ተማሪ ሳይሆኑ እንዴት የዶ/ር ላጶሶን ስህተት ለማረም ይችላሉ? ብሎ ቢጠይቀኝ ኖሮ “እንዴ እሳቸው እኮ የታሪክ ተማሪ ናቸው” ብዬ መልስ ልሰጥ እችል ነበር። ያም ሰው ማስረጃ ቆጥሮ ቢከራከረኝ ልረታ እችል ነበር። “ለምን ታዲያ ስለትምህርታቸው ሳትጠይቃቸው ቀረህ ቢለኝና ተመልካቹን አሳሳትክ ብሎ ቢወነጅለኝ” መልስ የለኝም። እኔ ማንም ሰው ታሪክን መጻፍ ወይም ስለታሪክ መናገር የለበትም እያልኩ አይደለም። የቃለምልልሱ ዋና አላማ የአቶ ተክሌን ማንነት በማሳዬት ውይይቱ ትኩረት እንዲያገኝና አድማጭም እውነታውን እንዲረዳ ለማድረግ ነበር። በተለይ የታሪክ ተማሪዎች በታሪካችን ላይ የሚያቀርቡትን የተለያዬ የአረዳድና የአተናተን ስልት የማሳየት ፍላጎት ነበረኝ። ያም ሆነ ይህ አቶ ተክሌ ጥሩ መልስ ሰጥተዋልና በጣም አመሰግናቸዋለሁ። ላላቸው የታሪክ ግንዛቤም አድናቆቴ ከፍ ያለ ነው፤ ከዚህ በሁዋላ የምንገናኝባቸው ብዙ መድረኮች እንደሚኖሩም አምናለሁ።
በመጨረሻም አቶ ተክሌን “አማራ ማነው?” የሚለውን የጠየኩዋቸው፣ “ዶ/ር ላጲሶ የአማራውን ታሪክ አንቋሸዋል” ብለው ስለተናገሩ ብቻ ነው። ይህን መጠየቄ ስህተት ከሆነ እንግዲህ በድጋሜ ራሴን መመርመር ሊኖርብኝ ነው።
ፕ/ር ጌታቸው ስለጋዜጠኝነት ትምህርቴ ( ያው ስለኢሳት ጋዜጠኞች የጋዜጠኝነት ትምህርት) ያነሱት ነገር አለ። ለዚህ እንኳ መልስ ባልሰጥ ይሻላል። ምናልባት በግል ቢጠይቁኝ የተማርኩዋቸውን የትምህርት አይነቶች ሁሉ ዘርዝሬ ልጽፍላቸው እችላለሁ። እርሳቸው እንዳሉት የጋዜጠኝነት ትምህርት ሳይኖራቸው ጋዜጠኛ የሆኑ አሉ፣ ችግር የለውም፤ ከታሪክ ትምህርት ጋር ተነጻጽሮ መቅረቡ ግን ትክክል አይመስለኝም። ታሪክን መጻፍ በጣም ከባድ ነገር ነው፤ ፕ/ር ጌታቸው ከእኔ በላይ ያውቁታል። እንዲያውም አንድ ጊዜ ነፍሳቸውን ይማርና ፕ/ር መርዕድ ወልዳረጋይን ክፍል ውስጥ ስለሆነ ታሪክ ሲያስተምሩን “በዚህ ጉዳይ ለምን መጽሃፍ አይጽፉም” ስላቸው፣ “ታሪክ ጻሃፊው ደክሞ የጻፈውን መጽሃፍ አታነቡ፣ መጽሃፍ ቤት ገብታችሁ የምታነቡት ጋዜጣ ነው ያሉኝን አልረሳውም። ጋዜጣን ለማሳነስ ሳይሆን ታሪክን ለመጻፍ ድካሙንና ልፋቱን ለመግልጽ ነው። ፕ/ር መስፍንም ሆኑ ፕ/ር ጌታቸው ለዚህ አባባሌ ጥሩ መስረጃ ናቸው። ፕ/ር መስፍን የጂኦግራፊ ተማሪ ሆነው ” መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” ብለው የጻፉት ውብ መጽሃፍ ነው።
ሌላው ለደ/ር ላጲሶ ጥብቅና ቆምክ የሚለው አስተያየት ነው። እንዴ ጋዜጠኛ እኮ፣ ያው በእኛ አገር ባይለመድም፣ የሰይጣን ጠበቃ ( The devil’s advocate) ሆኖ ነው መቅረብ ያለበት። እንዴ ፈረንጅ ጋዜጠኞችም እኮ ያልተባለ ነገር ተብሎአል ብሎ ሲቀርብ ” አላላም” ብለው ይከራከራሉ። የአቶ ተክሌን መልስ ይዘህ ፕ/ር ላጲሶን መልሰህ መጠየቅ ነበረብህ የሚሉም ሰዎች አጋጥመውኛል። እንዴ ይህማ ትክክል አይደለም፣ ወሬ ማመላለስ ነው። መቼውንም የሚዘጋ አጀንዳ አይሆንም። ሁለቱ ቀርበው እንዲነጋገሩ የሚለው ሃሳብ ባይሆን ጥሩና የሚደገፍ ነው።
ለማንኛውም ፕ/ር ጌታቸውም ሆኑ ሌሎች ሰዎች ስለሰጡዋቸው አስተያየቶች አመስግኜ ልሰናበት። ተሳስቼም ከሆነ ከስህተቴ እየተማርኩ ፈጣሪ አገሬንና ህዝብን የምጠቅም ያድርገኝ፤ የማልጠቅም ከሆነም “በቃህ አርጅተሃል” ብሎ በጊዜ ያሰናብተኝ። ወይም ጋዜጠኝነት መክሊቴ ካልሆነ ሌላ መክሊት ይስጠኝ። አሜን ብለን እንሰነባበት። ( በነገራችን ላይ አቶ ተክሌ ቅሬታ የሚያቀረቡ ከሆነ የተጻጻፍነውን ኢሜልና ያዘጋጁትን መልስ ለማውጣት ዝግጁ ነኝ፤ አዳማጭም ያን ጊዜ የኔን ጭንቀት ይረዳዋል)
The post ይድረስ ለፕ/ር ጌታቸው ሃይሌና ለሌሎችም – ከፋሲል የኔያለም (ጋዜጠኛ) appeared first on Zehabesha Amharic.
[ Hiber Radio ] አቶ ምትኩ ተሾመ ምርቻ 97ን ተከትሎ ዛሬም ድረስ ስልጣን ላይ ባለው አገዛዝ የሀይል እርምጃ የተገደሉትን ፣የቆሰሉትን፣የታሰሩትን እና የደረሰውን ጉዳት ለማታራት የተቋቋመው ሕጋዊው አጣሪ ኮሚሽን አባል ናቸው። የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ዳና ፍሩህይወት ሳሙኤል፣ም/ሰብሳቢ ዳና ወልደሚካኤል መሸሻና የዛሬ እንግዳችን የኮሚሽኑ የመጨረሻ ውሳኔ አገዛዙን ባለማስደሰቱ ለመቀልበስ እጅ ጥምዘዛ ውስጥ ሲገቡ ታላቅ መስዋዕትነት ከፍለው የተፈጸመውን ግፍ አጋልጠዋል።ዛሬም ድረስ በዚህ ታላቅ የግፍ ድርጊት የተጠየቀ የለም።የሰማዕታቱን 10ኛ ዓመት መታሰቢአ አስመልክተን ከአቶ ምትኩ ተሾመ ጋር ቆይታ አድርገናል። ወደ ሁዋላ ከአስር ዓመት በፊት ቤተሰቦቻቸው፣ወገኖቻቸው በግፍ የተገደሉትን በጊዜው ለመገናኛ ብዙሃን ያቀረቡትን የዋይታ ጥሪ ሁኔታውን የበለጠ ያስታውሳልና በቃለ መጠይቁ መግቢያና በስተመጨረሻ አካተናል።
The post ከምርጫ 97 ግድያ ሕጋዊው አጣሪ ኮሚሽን አባል አቶ ምትኩ ተሾመ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ appeared first on Zehabesha Amharic.