Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

Hiber Radio: በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ረሀቡን ዘንግቶ በተሃድሶ ድግስና ለፖለቲካ ስብሰባ በሚሰጠው የአበል ክፍያ የአገሪቱን ሀብት እያባከነ መሆኑ ተገለጸ፣በኢትዮጵያ እስር ቤት ውስጥ የአሜሪካ የደህንነት ሰራተኞች በደል ፈጸሙብኝ ያለ አሜሪካዊ ዜጋ ይግባኙ ውድቅ ሆነበት፣የ 19 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ወጣት ሚካኤል በሳውዝ ዳኮታ በጥይት ተገደለ ፣ግብጽ ህገ ወጥ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ማሰሯን ገለጸች፣እንግሊዝ በአየር ሀይላ ግቢ ለሰፈሩ ኢትዮጵያውያን ጥገኝነት መንፈጓ ቅሬታ አስነሳ፣ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ያለበት ሁኔታ አለመታወቅ አሳሳቢ መሆኑን ቤተሰቦቹ ገለጹ፣በቦትስዋና የፖለቲካ ጥገኝነት የጤቁት ኤርትራውያን ተጫዋቾች በወታደራዊ እስር ቤት እተሰቃዩ መሆኑ ተገለጸ፣ የአቶ አስማማው ሀይሉ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ እና ሌሎችም አሉን

$
0
0

hiber_radio_program_cover_102515_02

የህብር ሬዲዮ  ጥቅምት 14 ቀን 2008 ፕሮግራም

 <… የሀይማኖት አባቶች ፖለቲካ ውስጥ አንገባም በሚል ሽፋን በአገር ቤት የሚደረገውን በደል፣የዘር ማጥፋት ወንጀል አለመናገር አግባብ አይደለም የጥቅም ጉዳይ ካልሆነ በቀር አባቶቻችን እነ አቡነ ጴጥሮስ ለዕውነት ለአገራቸውሞተዋል ዛሬ ወጣቶች በገንዘብ የማይተመኑ ምሁራን መፍትሄ አጥተው ጫካ ገብተዋል። የሀይማኖት አባቶች ግንስርዓቱን ላለማስቀየም ፖለቲካ ውስጥ አንገባም የሚል አነጋገር ከየት የመጣ ነው? ከጥቅም አኳያ ነው…ማንም ሰው ስፍራ ይለቃል።የባቢሎን ግንብ እንኳን ተንዷል። መንግስት ይቀየራል።ቤተ ዕምነቶች ራሳቸውን ሊፈትሹ ይገባል። ፍርድና ፍትህ በሌለበት አገር ላይ የእምነት ተቋማት ፍርድ ሰጪ መሆን አለባቸው ።ለወገናቸው መጮህ አለባቸው። ይህ ካልሆነ ግን…>

ፓስተር ተፈራ ፈቃዱ  ከሰሞን አሜሪካ ኤልሻዳይ ዓለም አቀፍ የሳተላይት ቲቪ መንፈሳዊ አገልግሎት የሀይማኖት አባቶች ፖለቲካ ውስጥ አንገባም ማስፈራሪያ ማንን ለመጥቀም ሚለውን ጉዳይ አንስን ተወያይተናል (ሙሉውን አዳምጡት)

<…ጋዜጠኛ ተመስገን ዕውነትን ስለጻፈ ነው ወንጀለኛ ነው ብለን አናምንም።አሁን ሙሉ ለሙሉ ቤተሰብም እንዳይጠይቀው ተከልክሏል። በዝዋይ እስር ቤት የወገብና የጆሮ ህመሙ ሕክምና ተከልክሎ እስረኞች እንዳያናግሩት እንዳይጽፍ እንዳያነብ በስቃይ ታስሮ አሁን ሙሉ ለሙሉ አትጠይቁትም የበላይ ትዕዛዝ ነው ተብለናል።በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አናውቅም ደህነቱ ያሳስበናል…ተመስገን ለዕውነትና ለፍትሕ ቆሟል ሕዝቡ ዛሬም ከጎኑ ቆሞ ድምጹን እንዲያሰማለት …> ታሪኩ ደሳለኝ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም ስለወቅታዊው ክልከላ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ሰራዊት (ኢሕአሰ) አባልና የዚያ ታሪክ ጸሐፊው አስማማው ሀይሉ(አያ ሻረው አጭር የሕይወት ታሪክ)

በኢትዮጵያ የተከሰተው አስከፊው  የረሃብ አደጋ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ስጋት ፈጥሯል(ልዩ ጥንቅር)

ከአቶ ኦባንግ ሜቶ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ (ክፍል ሁለት)

 ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ረሀቡን ዘንግቶ በተሃድሶ ድግስና ለፖለቲካ ስብሰባ በሚሰጠው የአበል ክፍያ  የአገሪቱን ሀብት እያባከነ መሆኑ ተገለጸ

በኢትዮጵያ እስር ቤት ውስጥ የአሜሪካ የደህንነት ሰራተኞች በደል ፈጸሙብኝ ያለ አሜሪካዊ ዜጋ ይግባኙ ውድቅ ሆነበት

አምስት ብሔር ተኮር የኢትዮጵያ ተቋዋሚ ሐይሎች የኢሕአዲግ ስልጣንን ለማሳጠር  የጋራ ግንባር ፈጠርን አሉ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ያለበትን ሁኔታ አለማወቅ ቤተሰቡን እንደሚያሳስባቸው ገለጹ

ግብጽ ህገ ወጥ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ማሰሯን ገለጸች

እንግሊዝ በአየር ሀይሏ ግቢ የሰፈሩ ኢትዮጵያዊያኖችን ጥገኝነት መንፈጓ ቅሬታ  አስነሳን

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ሰራዊት አባልና ታሪኩን በሁለት ቅጽ የጻፉት አቶ አስማማው ሀይሉ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

ቦትስዋና ውስጥ የፖለቲካ ጥገኝነት  የጠየቁት 10ሩ ኤርትራዊያን ተጨዋቾች በወታደራዊ እስር ቤት ውስጥ እየማቀቁ ናቸው ተባለ

ኤርትራ የተመድ ላራዘመባት የመሳሪያ ማዕቀብ ዳግም  የኢትዮጵያውን አገዛዝ  ከሰሰች

የኔቫዳ ትራንስፖርት ባለስልጣን የሁበርና ሊፍት አሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር ሰባት ተጨማሪ ሰራተኞችን ቀጠረ

የኢትዮጵያው ዋልያ ብሔራዊ ቡድን የቡርንዲ ቡድንን በአስገራሚ ሁኔታ በማሸነፍ ለቻን 2016 ውድድር አለፈ

ሸንጎ ለመጪዎቹ ሁለት ዓመታት አዲስ አመራር መረጥኩ አለ  

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

The post Hiber Radio: በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ረሀቡን ዘንግቶ በተሃድሶ ድግስና ለፖለቲካ ስብሰባ በሚሰጠው የአበል ክፍያ የአገሪቱን ሀብት እያባከነ መሆኑ ተገለጸ፣በኢትዮጵያ እስር ቤት ውስጥ የአሜሪካ የደህንነት ሰራተኞች በደል ፈጸሙብኝ ያለ አሜሪካዊ ዜጋ ይግባኙ ውድቅ ሆነበት፣የ 19 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ወጣት ሚካኤል በሳውዝ ዳኮታ በጥይት ተገደለ ፣ግብጽ ህገ ወጥ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ማሰሯን ገለጸች፣እንግሊዝ በአየር ሀይላ ግቢ ለሰፈሩ ኢትዮጵያውያን ጥገኝነት መንፈጓ ቅሬታ አስነሳ፣ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ያለበት ሁኔታ አለመታወቅ አሳሳቢ መሆኑን ቤተሰቦቹ ገለጹ፣በቦትስዋና የፖለቲካ ጥገኝነት የጤቁት ኤርትራውያን ተጫዋቾች በወታደራዊ እስር ቤት እተሰቃዩ መሆኑ ተገለጸ፣ የአቶ አስማማው ሀይሉ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ እና ሌሎችም አሉን appeared first on Zehabesha Amharic.


እውን ፕ/ት ሳዳም ሁሴን እና መሀመድ ጋዳፊ በሰልጣን ላይ ቢኖሩ ለአለማችን ሰላም ይበጁ ነበር?

Previous: Hiber Radio: በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ረሀቡን ዘንግቶ በተሃድሶ ድግስና ለፖለቲካ ስብሰባ በሚሰጠው የአበል ክፍያ የአገሪቱን ሀብት እያባከነ መሆኑ ተገለጸ፣በኢትዮጵያ እስር ቤት ውስጥ የአሜሪካ የደህንነት ሰራተኞች በደል ፈጸሙብኝ ያለ አሜሪካዊ ዜጋ ይግባኙ ውድቅ ሆነበት፣የ 19 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ወጣት ሚካኤል በሳውዝ ዳኮታ በጥይት ተገደለ ፣ግብጽ ህገ ወጥ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ማሰሯን ገለጸች፣እንግሊዝ በአየር ሀይላ ግቢ ለሰፈሩ ኢትዮጵያውያን ጥገኝነት መንፈጓ ቅሬታ አስነሳ፣ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ያለበት ሁኔታ አለመታወቅ አሳሳቢ መሆኑን ቤተሰቦቹ ገለጹ፣በቦትስዋና የፖለቲካ ጥገኝነት የጤቁት ኤርትራውያን ተጫዋቾች በወታደራዊ እስር ቤት እተሰቃዩ መሆኑ ተገለጸ፣ የአቶ አስማማው ሀይሉ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ እና ሌሎችም አሉን
$
0
0

ከታምሩ ገዳ

በመጪው 2016 አኤ አ የአሜሪካን ፖለቲካ ውስጥ ትለቁን የሰልጣን አርከን የሆነት ፕሬዜዳንትነትን ለመያዝ በሩጫ ላይ ያሉት ቢሊነሩ ቱጃር ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ ጥቅምት 25 2015 አኤ አ በአየር ላይ በበቃው “ስቴት ኦፍ ዘ ዩኒኦን” በተባለው የ ሴኤን ኤን ቴለቭዥን ፕሮግራም ላይ “ ዛሬ እየጋየ ከምናየው የመካከለኘው ምስራቅ ችግሮች አኳያ የቀደሞዋቹ አምባገነኖቹ የኢራቁ ፕ/ት ሳዳም ሁሴን እና የሊቢያው ሙሃመድ ጋዳፊ በሕይወት ቢኖሩ ኖሮ አለማቸን 100% የተሻለ ሰላም ይኖራታል ብዮ አምናለሁ።”ሲሉ አምነታቸውን ገልጸዋል።
Saddam Hussein
በአሜሪካ መራሹ ጦር አኤአ በ 2003 ከሰልጣን ተወግደው በ2006 በሰቅላት የተገደሉት የ ኢራቁ ሳዳም ሁሴን እና ለ አራት አሰር አመታት ሊቢያን የገዙት ሙሃመድ ጋዳፊ (በጥቅምት 2011 ኤአ አ ተገደለዋል) አምባገነኖች እና በእጃቸው ብዙ ነፈሳት አንደጠፉ የሚያምኑት ሪፐብሊካኑ እጩ ፕሬዘዳናታዊ ተፎካካሪ ትራምፕ “ ሰዎች ዛሬ በሊቢም ሆነ በ ኢራቅ አንደ እንሰሳ አንገታቸወን ይቀላሉ ፣ የወረወራሉ። ሊቢያ ቀወስ ውስጥ ገብታለች፡ ኢራቅም ምስቀልቀሏ ወጥቷል ፣ሶሪያም እንዲሁ። በአጠቃላይ መካከለኛው ምስራቅ በእነ ኦባማ እና በእነ ሂለሪ ክሊንተን ፊት እየፈንዳ ነው። ታዲያ ይህ ሁኔታን ሰናነጻጽረው የእነ ጋዳፊ እና የ እነ ሳዳም ዘመን በጣም የተሻለ ነበር ማለት ይቻላል።” ሲሉ ገምታቸውን ሰንዘረዋል።

ኢራቅ የአሸባሪዎች “ሃርቫርድ ዮኒቨርሲቲ” ሆናለች የሚሉት ትራምፕ “የቱን ያህል ሳዳም መጥፎ መሪ ቢሆኑ ዘመነ ሳዳም አሁን ካለንበት ውጥንቅጥ የተሻለ ነበር ።” ብለዋል።በመቀጠልም ትራምፕ አሁን በአለም ላይ ከሚመለከቱት ሁናቴ አኳያ “ዘምናችን የመካከለኛው ዘመን ይመሰላል፣ ቸግራችንንም ለማመን ይከብዳል።” በማለት አለማችን ደህረ ሳዳም እና ድህረ ጋዳፊ ያለውን ችግርን አመላክተዋል።ትራምፕ በምረጡኝ ዘመቻቸው ላይ ቀጣይ ፕ/ት ከሆኑ አሜሪካንን ከሜኪሲኮ የሚያዋሰነው ድንበር ላይ ትልቅ የግንብ አጥር አጥራለሁ በማለት አወዛጋቢ ትችቶችን ተጋፍጠዋል።ሰሞኑንም አንዳንድ “የእክራሪዎች መነሃሪያዎች” ያሏቸው መሰጊዶችን አንደሚዘጉ ፎክረዋል ። ነገር ግን የአሜሪካ ሀገ መንግስት እርምጃቸወን ለማሳካት እንደማይፈቅደላቸው በቅጡ ኣንዳለተገነዘቡት ተናግረዋል። ምቼ ይሄ ብቻ በ ቅርቡ ለመጠይቅ ፈቃድ/እድል ያልሰጡት ጋዜጠኛን በጸጥታ ሰራተኞቻቸው ከ አዳራሽ አስባረወታል ።
dolandl trummp
የኢራቅ ነገር ከተነሳ ዘንዳ የቀደሞው የእንግሊዝ ጠ/ሚ/ር ቶኒ ብለዩር በ 2003 ጦራቸወን ከእሜሪካ ጎን አሰልፍው ኢራቅን መወረራቸው “ሰህተት ነበር” ሲሉ ነገ ሙሉው ቃለምለለሰ በሚቀረበው ሲ አኢን አኤን ፕሮግራም ላይ ቀረበው ይቀርታ የተጠየቁ ሲሆን የኢራቁ ወረራ ዛሬ በመካከለኛው ምስራቅ ለተከሰተው አክራሪ ቡድን (አይ ሲስ) መፈጠር ምንሰኢ ነው።” ብለዋል። ሳዳም ጅምላ ጨራሽ መሳሪያ አከማችተው ነበር የሚል ጥያቄ እና ትችቶች የቀረበባቸው ቶኔ ብልዩር መረጃው ሰህትት እንደ ነበር በማመን ይቅርታ ጠይቀዋል።ቶኒ ብለዪር 45,000 የሚደረሰ ጦር ወደ ኢራቅ በማዘመት ከ 100 በላይ ይ አንግሊዝ ወታደሮቻቸውን አጥተዋል። ሜል የተባለው ጋዜጣ “በመጨረሻ ላይ ቶኒ ብሌር ይቅርታ ጠየቁ ።ይህም ታሪካዊ ክስተት ነው “ብሎታል ።

ምንም ኣንኳን ከ 6ሚሊኦን በላይ ኢራቃዊ ሕይወቱን በከንቱ ቢገብርም፣ያቺ ታሪካዊ አገር እንደዋዛ በትበታተንም የቶኒ ብለዮር ወደ ይቅረታ እና ጸጸት መመጣት ሕዝባቸውን ሳያማክሩ ጦራቸውን የብስ እና ባህር አቋርጦ በሰው ግዛት ላይ ጣልቃ ገብነት/ወረራ ለሚያደረጉ አምባገነኖች /ጀብደኞች ትልቅ ትምህርት ሊሰጥ ይችላል።

The post እውን ፕ/ት ሳዳም ሁሴን እና መሀመድ ጋዳፊ በሰልጣን ላይ ቢኖሩ ለአለማችን ሰላም ይበጁ ነበር? appeared first on Zehabesha Amharic.

“ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር የምትኖርበት ጊዜ ሩቅ አይመስለኝም። ወደዱም፤ ጠሉም፤ ከኢትዮጵያ የተሻለ አማራጭ የሚያገኙ አይመስለኝም”–ፍስሐ ደስታ

$
0
0

ፍስሐ ደስታ፤ የቀድሞው የኢትዮጵያ ምክትል ፕሬዚደንት፤ ስለ አዲሱ መጽሃፋቸው “አብዮቱና ትዝታዬ” ይናገራሉ።
“ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር የምትኖርበት ጊዜ ሩቅ አይመስለኝም። ወደዱም፤ ጠሉም፤ ከኢትዮጵያ የተሻለ አማራጭ የሚያገኙ አይመስለኝም። ኢትዮጵያም፤ ኤርትራም አንድ ናቸው።”
– ፍስሐ ደስታ
Part 2
[jwplayer mediaid=”47726″]
“ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር የምትኖርበት ጊዜ ሩቅ አይመስለኝም። ወደዱም፤ ጠሉም፤ ከኢትዮጵያ የተሻለ አማራጭ የሚያገኙ አይመስለኝም” –  ፍስሐ ደስታ

The post “ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር የምትኖርበት ጊዜ ሩቅ አይመስለኝም። ወደዱም፤ ጠሉም፤ ከኢትዮጵያ የተሻለ አማራጭ የሚያገኙ አይመስለኝም” – ፍስሐ ደስታ appeared first on Zehabesha Amharic.

በጎንደር ከተማ 6 የፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት ተፈፀመ፡፡

$
0
0

ባለፈው አርብ ዕለት ጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጎንደር ከተማ ፖሊስ አባላት የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋይ የሆነውን አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክሩ አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ በታጠቀው ኮልት ሽጉጥ ተኩስ ከፍቶ 6 ፖሊሶችን መትቶ መሬት ላይ አጋድሟቸዋል፡፡

የጎንደር ከተማ (ፎቶ ፋይል)

የጎንደር ከተማ (ፎቶ ፋይል)

ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ ከጎንደር ከተማ እምብርት ፒያሳ ጀምሮ እጁን ሊይዙ የተከታተሉትን ፖሊሶች ቀበሌ 6 ቂርቆስ አካባቢ እስኪደርስ “አትቅረቡኝ! ብትመለሱ ይሻላችኋል…” እያለ የለመናቸው ሲሆን ነገር ግን ፖሊሶቹ ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ባለመቻላቸው ቆራጥ እና የማያዳግም እርምጃ ወስዷል፡፡

ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ በያዘው ኮልት ሽጉጥ አንዲት ጥይት ብቻ እስክትቀረው እጁን ሊይዙ ከተከታተሉት ፖሊሶች ስድስቱን እያለመ ከረፈረፋቸው በኋላ በመጨረሻዋ ጥይት ራሱን ገድሏል፡፡

እጁን ለጠላት አሳልፎ ላለመስጠት እሳት ጨልጦ የአርበኛ ሞት በሞተው ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ የኮልት ጥይት ሰለባ ከሆኑት 6 የፖሊስ አባላት ሦስቱ ወዲያውኑ ሲሞቱ ቀሪዎቹ ሦስቱ ደግሞ በጠና ቆስለው በሞትና በህይወት መካከል ሆነው ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ላይ ይገኛሉ፡፡ ቆስለው በህክምና ላይ የሚገኙት ፖሊሶች የደረሰባቸው ጉዳት እጅግ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ከሞት ሊተርፉ እደማይችሉ እየተገለፀ ነው፡፡
ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመን በህይወት ለመያዝ ሳይሳካላቸው የቀሩት የጎንደር ከተማ ጥቂት የህወሓት ተላላኪ ፖሊሶችና ደህንነቶች እንዲሁም የመስተዳደሩ አገልጋይ ባለስልጣናት አስከሬኑን በቁጥጥር ስር በማዋል “አንሰጥም” ብለው የነበረ ሲሆን በመጨረሻም በአካባቢው ህዝብ ግፊት የጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ አስከሬን ለቤተሰቡ ተሰጥቶ ስርዓተ ቀብሩ ተፈፅሟል፡፡

በተመሳሳይም ሳጅን ወለላው ዋናይሁን የተባለው የመተማ ወረዳ ፖሊስ የአመራር አባል እንደዚሁ አንድ በወወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክር ከነተከታዮቹ ተገድሏል፡፡

Source: (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)

The post በጎንደር ከተማ 6 የፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት ተፈፀመ፡፡ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ የቀረበ ጥሪ – [የጥሪ ማስታወቂያ]

$
0
0

በሚኒሶታ የሚገኘው ደብረሰላም መድሃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በነገው ዕለት (ማክሰኞ) ሚኒያፖሊስ ኤርፖርት የሚደርሱትን ብጹዕ አቡነ አትናቴዎስ እና መምህር ምህረተአብን ለመቀበል የሚከተለውን ጥሪ አቅርቧል::
debereselam

The post ከሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ የቀረበ ጥሪ – [የጥሪ ማስታወቂያ] appeared first on Zehabesha Amharic.

ቴድሮስ አድሃኖም የት ናቸው? –አንዳርጋቸው ጽጌ ‹‹በእንግሊዝ ቅበሩኝ ››

$
0
0

ከዳዊት ሰለሞን

የሶስት ልጆች አባት የሆኑት የግንቦት ሰባቱ ዋና ጸሐፊ አንዳርጋቸው ጽጌ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡና ያሉበት ሁኔታ ሳይታወቅ 16 ወራቶች ተቆጥረዋል፤ በወህኒ ቤት እንዳሉም ሊገደሉ እንደሚችሉ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡
andargachew new picture
አንዳርጋቸው ይበሩበት የነበረ አውሮፕላን የመን ሰንዓ ማረፉን ተከትሎ ታፍነው ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈው የተሰጡት በወርሃ ሰኔ 2014 መሆኑ አይዘነጋም፡፡ለአንድ ዓመት ያህል ድብቅ በሆነ እስር ቤት ውስጥ ለወራቶች ምርመራ ሲደረግባቸው የቆዩት አንዲ በቅርቡ ወደ መደበኛ ወህኒ ቤት መዘዋወራቸው ቢነገርም እስካሁን በውል ያሉበት ሁኔታ አይታወቅም፡፡ይገኙበታል የተባለው የቃሊቲ ወህኒ ቤት ኃላፊዎችም አንዳርጋቸውን ለምስክርነት ጠርቶ ለነበረ ፍርድ ቤት አንዳርጋቸው በወህኒ ቤቱ እንደማይገኙ አስታውቋል፡፡

አንዳርጋቸው በሌሉበት በቀረበባቸው ክስ በሁለት አጋጣሚዎች የእድሜ ልክና የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው መሆኑ አይዘነጋም፡፡እጃቸው ከተያዘበት ወቅት ጀምሮም የአንዳርጋቸው ቤተሰቦች ያቀረቡት የጉብኝት ጥያቄ አልተሳካም፣ጠበቃ ለማቆም የተደረገው ሙከራም እንዲሁ ፣በህግ ፊት እንዲቀርቡ ባለመደረጋቸውም ከዚህ ቀደም የተላለፈባቸውን ፍርድ በምን መንገድ ሊተገብሩት እንዳሰቡ አሳሪዎቻቸው ግልጽ አላደረጉም የእንግሊዙ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሪፕራይቭ ጠበቆቹ አንዳርጋቸውን እንዲጎበኙ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡

አሁን አንዳርጋቸው በቅርቡ ሊገደሉ እንደሚችሉ ስጋት የገባቸው በመሆኑ ለእንግሊዝ መንግስት ‹‹በእንግሊዝ ስርዓተ ቀብራቸው እንደሚፈጸም እንዲያረጋግጡላቸው ጠይቀዋል፡፡ለንደን ለሚገኙ ልጆቻቸው ባስተላለፉት መልእክትም ‹‹ጎበዞች››እንዲሆኑ መክረዋል፡፡

በቅርቡ በጣም ውስን ለሆኑ ደቂቃዎች በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደርን ያገኙት አንዳርጋቸው ለአምባሳደሩ
–የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ለወራት ከወህኒ ቤት ክፍላቸው እንዳይወጡ መከልከላቸውን
–የእስረኛ ቁጥር እንዳልተሰጣቸውን አሳሪዎቻቸው የእስር ምክንያታቸውን ወይም የተወነጀሉበትን ጉዳይ ያልነገሯቸው መሆኑን
–ጠበቃ ለማግኘት ጠይቀው መከልከላቸውን
— በህመም ላይ የሚገኙ ቢሆንም ህክምና እንዳያገኙ መደረጋቸውን

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአንዳርጋቸውን ኢሰብአዊ አያያዝ በመቃወም እንዲለቀቅ ጠይቋል፡፡የእንግሊዝ መንግስት ግን ምንም እንኳን የኢትዮጵያ መንግስት አጋርና አንዳርጋቸው ዜጋው ቢሆኑም በቤተሰቦቻቸው እንዲጎበኙና መደበኛ የሆነ ክስ እንዲመሰረትባቸው አልጠየቀም፡፡ባሳለፍነው ሳምንት የእንግሊዝ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ግራንት ሻፕስ የኢትዮጵያ መንግስት አቻቸውንና ሌሎች ባለስልጣናት ወደ ለንደን በመጋበዝ የንግድ ልውውጥ ስለሚደረግበት ሁኔታ መክረዋል፡፡

በሁለትዮሽ ግኑኝነቱ ወቅት ሻፕስ መንግስታቸው ከኢትዮጵያ ጋር በአጋርነቱ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዋና ጸሐፊ ፊሊፕ ሃሞንድ ከዝግጅቱ መጠናቀቅ በኋላ ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት የአንዳርጋቸውን ጉዳይ እንዳነሱባቸው ቢናገሩም ከእስር እንዲፈቷቸው ግን አልጠየቁም፡፡

በሪፕራይቭ የሞት ቅጣት ተከራካሪ ቡድን አባል የሆኑት ማያ ፎ ‹‹አንዳርጋቸው የሶስት ልጆች አባትና እንግሊዛዊ ነው፡፡ለ16 ወራት ያህል በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ለእስር ተዳርጎ ቶርቸር ተፈጽሞበታል፡፡በሌለበትም ሞት ተላልፎበታል፡፡ወደ እንግሊዝ የሚመለስበት ብቸኛው መንገድ ስርዓተ ቀብሩ ሲፈጸም እንደሆነ እንደሚሰማው መናገሩ በጣም አስደንጋጭ ነው፡፡አንዳርጋቸው ከህገ ወጥ እስሩ እንዲለቀቅ ከመጠየቅ ይልቅ የእንግሊዝ ሚኒስትሮች ልዩ የንግድ ትርኢት ባሳለፍነው ሳምንት ማዘጋጀታቸው አስገራሚ ነው፡፡ግዜው ሳይዘገይ የእንግሊዝ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንዳርጋቸው እንዲለቀቅና በለንደን የሚገኙትን ቤተሰቦቻቸውን እንዲቀላቀሉ በአስቸኳይ መጠየቅና መጫን ይኖርባቸዋል››ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

የኢህአዴጉ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም አንዳርጋቸው የአዳማውን አዲስ የፍጥነት መንገድ መጎብኘታቸውንና ላፕ ቶፕ ተሰጥቷቸው መጽሐፍ እየጻፉ እንደሚገኙ ለቪኦኤ በሰጡት አስገራሚ ቃለ ምልልስ መናገራቸው አይዘነጋም፡፡

The post ቴድሮስ አድሃኖም የት ናቸው? – አንዳርጋቸው ጽጌ ‹‹በእንግሊዝ ቅበሩኝ ›› appeared first on Zehabesha Amharic.

ይድረስ ለኢህአዴጋዉያን “ወገኖቼ” –ይገረም ዓለሙ

$
0
0

መቼም ፈጣሪ ለሰው ልጆች ሁሉ የቸረውን ለእናንተም አለነፋጋችሁምና ሰዎች ናችሁ፤ የተገኛችሁት ከምታሰቃዩት ወይንም ጌቶቻችሁ ሲያሰቃዩት  ከምትሳለቁበት ሕዝብ መካከል ፣የተፈጠራችሁትመ እየገደላችኋት ካለው ወይንም አገዳዳይና አስገዳይ ሆናችሁ ከቆማችሁባት ሀገር ነውና የእናት ሆድ ዝንጉርጉር ሆኖ ብንለያይም ኢትዮጵያዊ  ናችሁ፡፡ እናም ለዚህ ነው ወገኖቼ ማለቴ፡፡ ይህች መልእክቴ የምትመለከተው ራሳቸውን ለወያኔ አስገዝተው ወገናቸውን በጠላትነት ፈርጀው ለደደቢቱ ውጥን ስኬት በሚችሉት አቅም በሀገርና በሕዝብ ላይ የዘመቱትናና፤ህሊናቸው የሚያምንበትን ሳይሆን ሆዳቸው የጠገበበትን የሚሰሩትን ነው፡፡

eprdf

የቱንም ያህል ሥልጣን ወይንም ጥቅም ቢያውራችሁ  ከአይናችሁ እንዴት ጆሮአችሁን ታምናላችሁ? የቱንስ ያህል ጎመን በጤና ብሎ መኖርን ምርጫችሁ፣ አያያያዙን አይተህ ወደሚያደላው ማለትን የኑሮ መመሪያችሁ ብታደርጉ በኢትዮጵያውያን ላይ ባለፉት ሀያ አራት ዓመታት  የተፈጸሙና አሁንም በመፈጸም ላይ ያሉ በደሎች እንደምን አይታያችሁም?

ጌቶቻችሁ የሚመጻደቁበትንና እናንተም የሚሉዋችሁን እንደወረደ እየተቀበላችሁ የምታስተጋቡለትን ሕገ መንግሥት ታውቁታላችሁ? ጆሮአችሁ የሚሰማው ይቅርና አይናችሁ የሚያየው ነገር ሁሉ ሕገ መንግሥቱን ባከበረ መልክ የሚፈጸም ነው? ወይንስ እንደ ንጉሱ አጎንብሱ ለማለት ባልፈቀደ ዜጋ ላይ የሚፈጸም ኢ-ሰብአዊም ሆነ ሕገ ወጥ ተግባር  ተገቢና ትክክል ነው ብላችሁ ታምናላችሁ? የነገሮች  ሕገ ወጥነት፤ የድርጊቶች ኢ-ሰብዊነት በራሳችሁ ላይ ካልደረሰ በስተቀር አያማችሁም አይሰማችሁም ማለት ነው፡፡

በርግጥ እንኳን እናንተ ጠቅላይ ምኒስትር ተብለው የተቀመጡት አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ እንኳን ወያኔ የደደቢት ዓላማውን ተግባራዊ ለማድረግ ሲል የሚፈጽማቸውን ኢ-ሰብአዊ፣ ኢ-ዴሞክራሲያዊም ሆነ ኢ-ህጋዊ ተግባራት ለማስቆም አይደለም ለምን ብለው ለመጠየቅ አይችሉም፡፡ ከአቶ መለስ ወንበር ላይ ተቀምጠው ጠቅላይ ምኒስትር በተባሉ ሰሞን በአቶ መለስ ላይ ያዩት ሥልጣን በሳቸውም ላይ ያለ መስሎአቸው ይሁን  ወይንም እውነት ተፈታትናቸው በፍትህ ሥርዓቱ ላይ ጥያቄ እንዳላቸው ሲናገሩ ሰምተናቸው ነበር፡፡

በስም አንጂ በተግባር የሌሉት ሶስቱ የመንግስት ኃይሎች  ማለትም ሕግ አውጪው ሕግ አስፈጻሚውና ህግ ተርጓሚው  በጋራ ያካሄዱት በተባለ ስብሰባ ላይ  ከተሰብሳቢ ወንበር ላይ ተቀምጠው እይታቸውን ከበስተቀኛቸው ራቅ ብለው ወደሚታዩት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት በማድረግ «እንደ አስፈጻሚ አካል መሪ ከዳኝነት ሥርዓቱ ምላሽ የምፈልጋቸው ነገሮች አሉ፤ ሕዝቡ በጣም በከፍተኛ ደረጃ  የሚያነሳቸው ጉዳዮች አሉ፤በዚህ ላይ የዳኝነት ሥርዓቱ እንዴት እያየው እንደሆነ፣ እንዴትስ እየፈታው እንደሆነ ምክር ቤቱም አስፈጻሚውን አካል የሚከታተለውን ያክል የዳኝነት ሥርዓቱን ይከታተላል ወይ የሚል ጥያቄ አለኝ፡፡ በዚህ ላይ ማብራሪያ ቢሰጥ ጥሩ ይመስለኛል፡፡ የዳኝነት ሥርዓቱ አመራሮች እስከማውቀው ድረስ ጥሩ አመራሮች እንደሆኑ አውቃለሁ፣ ነገር ግን እሰከ ታች ድረስ በዚህ ደረጃ  ወርዶ የህዝቡን ፍላጎት፣ የሀዝቡን ጥያቄዎች፣ የህዝቡን አገልግሎት የማግኘት ጉዳይ፣ በተመለከተ እንዴት እያዩት እንዳለ  እንዴትስ ለህዝቡ መረጃ እየሰጡ እንዳለ ቢያብራሩና ብናውቀው የበለጠ ጥሩ ነው የሚል  ጥያቄ ላነሳ ፈልጌ ነው አመሰግናለሁ፡»ሲሉ በስም እንጂ በተግባር ኢትዮጵያዊ ካልሆነው ቴሌቪዢን ተመልክተናቸው ነበር፡፡

ጠየቁ እንጂ መልስ አላገኙም፣ ተናገሩ አንጂ ለተግባራዊነቱ አልተሰለፉም፤እንደውም የአቶ መለስን ራእይ ከማስፈጸም ውጪ የራሳቸው የሆነ ምንም እንደሌለ ነግረውን ለደደቢቱ የወያኔ ዓላማ መሳካት ከጳጳሱ ቄሱ እንዲሉ ሆነው እየሰሩ ነው፡፡ ቀድሞ አሳሪውም አሳሳሪውም ወንጃይ አስወንጃዩም ፈቺውም አስፈቺውም አንድ አቶ መለስ ነበሩ፣ በአቶ ኃይለማሪያም ሥልጣነ ዘመን ግን ብዙ መለሶች ተፈጥረው ሕዝቡን እያሰቃዩት ነው፡፡

አምናችሁም ይሁን  ሥልጣን ወይንም ጥቅም አሸንፎአችሁ አለያም ልኑር ብላችሁም ይሁን ዘር ከልጓም ይስባል ሆኖባችሁ ለወያኔ አርጋጅ አሸርጋጅ የሆናችሁ ከዚህችው ሀገር የተገኛችሁ ወገኖች በየግዜው የምናይ የምንሰማው ኢትዮጵያዊ ሆኖ መፈጠርን እስከመጥላት የሚያደርስ ከሰዋዊ ተግባር ያፈነገጠ ድርጊት እናንተን በማፈር ፋንታ የሚያኮራችሁ፤በማዘን ፋንታ የሚያስደስታችሁ፣ ለምን ብሎ ከመጠየቅ ካልሆነም ዝም ከማለት ይልቅ አበጀህ በለው ቀጥልበት በማለት ድጋፍ ለመለገስ የሚያበቃችሁ ምክንያቱ ምን ይሆን? እንዲህ የሆናችሁት ፈጣሪ ሳያዳላ የለገሳችሁን ሰዋዊ ተፈጥሮ ወደየት ጥላችሁት ነው?

በማእከላዊ ወንጀል ምርመራ ወንድ ሴት ሳይባል በፖለቲካ እስረኞች ላይ የሚፈጸመውን ዘግናኝ ድርጊት፣ ድርጊቱ የተፈጸመባቸው ዜጎች በተለያየ ግዜ ሲናገሩ ሰምተናል ተጽፎ አንብበናል፤በየወህኒ ቤቱ የሚፈጸሙ ኢ-ሰብአዊና ሕገ ወጥ ድርጊቶችን በየግዜው እየሰማን ነው፡ለመሆኑ ሰይጣናዊ ስሜታቸውን ለማርካትና የበቀል ጥማታቸውን ለመወጣት ካልሆነ በስተቀር ወህኒ ቤት ያሉ ፍርደኞችን በማሰቃየት ጌቶቻችሁ የሚያገኙት ጥቅም ምንድን ነው? እናንተስ በዚህ ከማዘን መደሰታችሁ ከማፈር መኩራታችሁ ምን ይባላል፡፡

በጠያቂ ክልከላ ይታወቀ የነበረው የወህኒ ቤት ሕገ ወጥነት ምግብ ወደ መከልል ተሸጋግሯል፤መጻህፍት ጋዜጣም ሆነ መጽሄት በመከልከል የሚታወቁት የወህኒ ቤት ንጉሶች መጽኃፍ ቅዱስ መንጠቅ ደረጃ መድረሳቸውን ሰምተናል፤ የሀሰት ወንጀል ፈብርኮ አባይ ምስክር አሰልጥኖ ንጹሀን ዜጎችን ወንጀለኛ ማድረግ ስራው የሆነው የዐቃቤ ህግ ተቋም ዛሬም ራሱን ከሕግ በላይ አድርጎ ፍርድ ቤት ነጻ የሚላቸውን ሰዎች አለቅም  በማለት ተግባሩ እንደቀጠለ ነው፡፡የደህንነት ኃይሉ ራሱን የቻለ አድራጊ ፈጣሪ መንግሥት ከመሆን የሚገታው ሕግ አልተገኘም፡፡ እህሳ ይህን ተግባር ስትደግፉ ምክንያታችሁ ምንድን ነው ወይንስ ሁሉም የተቃዋሚዎች የውሸት ወሬ ነው ትላላችሁ፡፡ሌላው ቢቀር ነግ በእኔ ማለት እንዴትና በምን  ከውስጣችሁ ታጥቦ ወጣ፡፡

ከሎሌነት ወደ ሰውነት መሸጋገር ያሰባችሁ እለት፤ ጌቶቻችሁ በእናንተ ላይ ያላቸው እምነት የተሸረሸረ እለት፤ አገልግሎታችሁ ያበቃ እለት፤ ሳት ብሎ ያዳጣችሁ እለት ወዘተ ከእነዚህ በአንዱ ዛሬ በሌሎች ላይ ሲፈጸም አይታችህ እንዳላየ፣ ሰምታችሁ እንዳልሰማ የምታልፉት ወይንም በቻላችሁት ሁሉ የምትደግፉት ሕገወጥና ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በእናተም ላይ ሊፈጸም እንደሚችል ነጋሪ ያስፈልጋችሁ ይሆን፡፡ ከብዙዎቹ ለምሳሌነት ሊጠቀሱ ከሚችሉት መካከል አቶ ታምራት ላይኔን ከሩቁ  ከቅርቡ ግዜ  ደግሞ አቶ መላኩ ፋንታን ማስታወስ በቂ ይመስለኛል፤አዙሮ የሚያይ አንገት ላለው፡፡

የሚገደሉት የሚታሰሩት የሚሰደዱት የሚሰቃዩት ዜጎች ጌቶቻችሁ የሚሉትን እየተከተላችሁ ጸረ ሰላም አሸባሪ  ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱ ስለሆኑ ነው ትሉ ይሆናል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ አይደለም መቃወም ሀሳብ የማቅረብ መብትም አቅምም የላችሁ ይሆናል፡፡በተቀዋሚነት ያስፈርጀናል ብላችሁ ትሰጉም ይሆናል፤

ጊቶቻችሁን አስተውላችሁ ተራመዱ እያሰባችሁም ተናገሩ እየዋሻችሁ አታሳፍሩን፤ እተደነባበራችሁ መሳቂያ አታድርጉን ለማለትስ አቅምም መብትም የላችሁ? ይህም ያስፈራችኋል? ክብዙው ትንሽ ላስታውሳችሁ አቶ መለስ ይህችን ዓለም በተሰናበቱበት ወቅት ሞታቸው ሲወራ እነ አቶ በረከት በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙን እየወጡ ሞታቸውን የሚመኙ ተቀዋሚዎች የሚያወሩት እንጂ ጠቅላይ ምኒስትሩ አልሞቱም አንደወም በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ ነው የሚገኙት አሉ፡፡ የራሳቸው መዋሸት አልበቃ ብሎ አዲስ አድማስ የሚባለው የቅዳሜ ሳምንታዊ ጋዜጣ አቶ መለስ በጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና በቤተ መንግሥት ከትላልቆቹ ባለሥልጣኖቻችው ጋር እንደሚመክሩ በመግለጽ የውሸቱ ተጋሪ አንዲሆን አደረጉት፡፡ ጎበዝ ሞት እንዴት ይደበቃል፡፡ ጌቶቻችሁ ውሸት የባህሪያቸው በመሆኑ ሀፍረት ይሉ ነገር አያውቃቸውም፤ ከለማበት የተጋባበት እንዲሉ ሆኖ እናንተም  በዚህ ውሸት አልፈራችሁም፡፡

አትዋሽ ክፉ አትስራ ወዘተ የሚለውን ቅዱስ መጽኃፍ ጥለው ለዓላማህ ስኬት እስከጠቀመህ ድረስ ሁሉንም ሥራ ሁሉንም ተናገር የሚለውን የወያኔ አብዮታዊ ዴሞክራሲ የተቀበሉት አቶ ኃይለማሪያም ዋንኛ ዋሾ ሆነዋል፡፡ የዞን 9 ጦማሪያንን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥቄ ሲመልሱ በጦማሪ ስም ተከልልው ከአሸባሪ ድርጅት ጋር በመገናኘት በሽብር ተግባር ላይ ተሰማርተው የተገኙ ለመሆናቸው በቂ መረጃ አለን በማለት በድፍረት ነበር የተናገሩት፡፡ ይህንንም የተቀዋሚዎች ወሬ ነው አንዳትሉ የታየ የተሰማው ከአልጀዚራ ቴሌቪዝን ነው( እናንት ምን ገዷችሁ እሱም የተቀዋሚዎች እጅ አለበት ትሉ ይሆናል) ታዲያ ጉዳያቸውን የያዘውና   በቀጠሮ ሲያንገላታቸው የቆየው ፍርድ ቤት  ከሳሽ ዐቃቤ ሕግ አንደ ክሱ አግባብ አሸባሪ ለመሆናቸው አላስረዳም  በማለት  ሁሉንም ነጻ ያላቸው የአቶ ኃይለማሪያም በቂ ማስረጃ የት ገብቶ ነው!!  እናንተ ግን ይህም አላሳፈራችሁ፤

ዲያስፖራ በሚል መጠሪያ የሚታወቁትንና ከሀገራቸው ውጪ በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ አዲስ አበባ ጠርተው  የውሸት አጋሮቻቸው የሆኑ አርቲስቶች ከእንግዲህ ሻማ ለልደት ብቻ ነው በማለት በዋሹበት አዳራሽ ሰብስበው በምግብ እህል ራሳችንን ችለናል በማለት በረሀብ ላይ ድል መቀዳጀታቸውን አወጁ፡፡ከእውነት ጋር ሲጣሉ መጋለጡ ውሎ አያድርማና ይህን ብለው ብዙም ሳይቆይ የረሀብ ነገር መሰማት ጀመረ፡፡ የመቋቋም አቅም አለን በማለት ደግመው ዋሹ፣ ነገር ግን  ረሀብን በጉራ ማባረር በውሸት መቋቋም አይቻልምና መንግሥታቸው ለጋሾችን እየለመነ ነው፡፡ ለምን ይዋሻል? መሪ ዋሸ ነገር ተበላሸ ነው፡፡እናንተ ወገኖቼ ግን በዚህም አታፍሩም ፡፡ እንደው ህሊናችሁን ያደነዘዘው ልባችሁን ያደነደነው ምን ይሆን፡፡የኢህአዴግ አባል ስትሆኑ በወያኔ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ስትጠመቁ የሚሰጣችሁ ሰዋዊ አስተሳሰብን የሚከላ ማደንዘዣ ይኖር ይሆን! ሁሉም አላፊ ነውና ዘለዓለማዊ ምድራዊ ኃይል የለም፤እናም ብትችሉ መልካም ነገር  ስሩ፤ ካልሆነም መጥፎ ስራ አትስሩ ለመጥፎ ሥራም አትተባበሩ፡፡

 

The post ይድረስ ለኢህአዴጋዉያን “ወገኖቼ” – ይገረም ዓለሙ appeared first on Zehabesha Amharic.

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አዲስ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎችን አስመረጠ

$
0
0

Zehabesha-News

በኖርዌይ የሚገኘው የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኦክቶበር 25፡ 2015 አጠቃላይ የአባላት የስድስት ወር ስብሰባና ለመጪው ሁለት አመታት ድርጅቱን የሚመሩ አዲስ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎችን አስመረጠ።

ዝግጅቱ በኖርዌጂያን የሰአት አቆጣጠር ከቀኑ 15፡00 የተጀመረ ሲሆን፣ በሀገራችን ባለው የአፈና አገዛዝ በግፍ ለተገደሉና በእስር እየተሰቃዩ ለሚገኙ እንዲሁም በተለያዩ የውጪ ሐገራት በስደት ህይወታቸውን ላጡ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ ፕሮግራሙ በይፋ ተጀምሯል።

በመቀጠል የድርጅቱ ሊቀመንበር የመግቢያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን እደዚሁም የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፓርት በድርጅቱ ጸሀፊ የቀረበ ሲሆን አባላቱም በሪፓርቱ ላይ ያላቸውን አስተያተት በመስጠት ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል። የስራ አስፈፃሚው ባለፉት ሁለት አመታት በድርጅቱ ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ ላበረከቱ የድርጅቱ አባላት የምስክር ወረቀት ሰጥቷል።

አባላቱ ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት ድርጅቱን የሚያስተዳድሩ ጠንካራ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎችን መርጠዋል። በመጨረሻም ምክትል ስብሳቢው አዲሱ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን በማስተዋወቅ የመዝግያ ንግግር አድርገው ዝጅግቱ በተያዘለት ሰአት በተሳካ ሁኔታ ከምሽቱ 19፡00 ተጠናቋል።

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ

አቢ አማረ የድርጅቱ ህዝብግንኙነት ሀላፊ

The post የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አዲስ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎችን አስመረጠ appeared first on Zehabesha Amharic.


የሀይማኖት አባቶች ሕዝብ ሲበደል ፖለቲካ ውስጥ አንገባም ዝምታ ማንን ለመጥቀም ? ሀይማኖቱ በደል ይደግፋል? ፓስተር ተፈራ ፈቃዱ ያብራሩታል

$
0
0

የሀይማኖት አባቶች በአገር ቤት ሕዝብ እየተበደለ፣እተራበ፣ግፍ እየተፈጸመበት በተቃራኒው በየቤተ እምነቱ ብዙዎቹ ይህን ግፍ አያወግዙም።ሌላው ቀርቶ ነገሩ እንዲስተካከል መጠየቅ እንኳን አይፈልጉም ። በተቃራኒው ይህን የሚያደርጉት በስልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ ዓላማ ለማራመድ ሲሆን ደግሞ የበለጠ ጉዳዩን መመርመር ሚናቸውን መጠየቅ ያስፈልጋል። ፓስተር ተፈራ ፈቃዱ ፖለቲካ በሚል የሚደረገውን ሽሽት ማንን ለመጥቀም መሆኑን ያብራሩታል።

የሀይማኖት አባቶች ሕዝብ ሲበደል ፖለቲካ ውስጥ አንገባም ዝምታ ማንን ለመጥቀም ? ሀይማኖቱ በደል ይደግፋል? ፓስተር ተፈራ ፈቃዱ ያብራሩታል

The post የሀይማኖት አባቶች ሕዝብ ሲበደል ፖለቲካ ውስጥ አንገባም ዝምታ ማንን ለመጥቀም ? ሀይማኖቱ በደል ይደግፋል? ፓስተር ተፈራ ፈቃዱ ያብራሩታል appeared first on Zehabesha Amharic.

[ፍኖተ ዴሞክራሲ አጫጭር ዜናዎች] –የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለተሰናባች የፓርላማ አባላት ተሰጡ * የወያኔ የግፍ መዋጮ ሕዝብን እያስመረረ ነው * ወያኔ በኮንሶ ሕዝብ ላይ የሀይል እርምጃ ወሰደ

$
0
0

parlamaፍካሬ ዜና
 ልዩ ልዩ አጫጭር ዜናዎች
 የወያኔ የግፍ መዋጮ ሕዝብን እያስመረረ ነው
 የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለተሰናባች የፓርላማ አባላት ተሰጡ
 የተራበው ህዝብ ቁጥር ጨመረ
 ወያኔ በኮንሶ ሕዝብ ላይ የሀይል እርምጃ ወሰደ
 የቻይና ኩባንያዎች ኢሰባዊነት ተጋለጠ
 የመኪና መገጣጠሚያ ኩባንያዎች ገበያ አልባ ሆንን አሉ
 በጅቡቲ ውጊያው ተፋፍሟል፤ ፈረንሳይም ሸርተት እያለች ነው
ወያኔ በአውሮጳና አሜሪካ የራሱን ቡችላ ማህበረሰቦች የማቁቋም ጥረቱን በመቀጠል በጣሊያን ሀገር ያለውን ነጻ
ማህበረሰብ የሚቃወም ከተማ አማረ በተባለ ቅጥረኛ የሚመራ ማህበረሰብ አቋቁሟል ። በርካታ አባሎቹ ከክልል
አንድ የመጡ መሆናቸውም ተዘግቧል ። ወያኔ በአውሮጳ ሀገሮች ያሉትን ቤተ ክርስቲያኖችንም ለመቆጣጠርና
ለማፍረስ የሚያደርገውንም ጥረት እጣጧጧፈ መሆኑ ተጋልጧል ።

የሻዕቢያ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን ለግጥሚያ ሄዶ ባለበት በቦትስዋና አስሩ ተጨዋጮች ለመመለስ እምቢ
በማለታቸውና በመኮብለላችው ብሔራው ቡድኑ ፈርሷል ሲሉ ዘጋቢዎች አቅርበዋል ። የሻዕቢያ ተጫዋጮች በገፍ
ሲከዱ ይህ የመጀምሪያቸው አይደሉም ። ይህ በዚህ እንዳለ ግን የአውሮጳ ማህበር ከኢርትራ የሚመጡትን
ስደተኞች ቁጥር ልንቀንስ እንችላለን በሚል አከራካሪ ስሌት ለሻእቢያ እርዳታ ሊሰጥ መወሰኑ ተረጋግጧል ።
በኢትዮጵያ በርካታ ግድቦችን የሰራው የጣሊያኑ የሳሊኒ (ሳልኮስት) ኩባንያ ፍቃድ ሳይሰጠው የግልገል ጊቤ
አራትን ቁፈራ ስራ በመጀመሩ ተወዳዳሪ/ተጫራጭ የነበሩ ኩባንያዎች ቅሬታ አሰሙ ። ግልገል ጊቤ ሶስት ስራው
አልቆ ለሙከራ 70 ሜጋ ዋት ሀይል ማንጨት ጀመሪ ቢባልም ስራውን ለመጨረስ የብድሩ ገንዘብ አነሰ ተብሎ
ክህገራችን ገንዘብ ለሳሊኒ መከፈሉም ይታወቃል ። ሳሊኒ ኩባንያ ለደርግም ለወያኔም ጉቦ እየሰጠ አለተገቢ
ጨረታ ኮንትራት ይይዛል መባሉም የሚረሳ አይደለም ። በተያያዘ ዜና ወያኔ ህዳሴ ግድብ የሚለው አስፈላጊው
ተርባይን መጥቶ ስራው ተጣደፈ የሚለው ተራ ፕሮፓጋንዳ ነው ያሉ ክፍሎች ይህ የአባይ ግድብ ገና ከችግሮቹና
ከገንዘብ እጥረቱ ያልተላቀቀ ነው ብለዋል ።

የደርግና የወያኔ ባለስልጣኖች ሁሉ ጸሃፊ ሆነናል ብለው መወራጨት ከጀመሩ ዓመታት ያለፈ ሲሆን በፋሺስቶቹ
ቁንጮዎች (መንግስቱና ፍቅረ ስላሴ )የተጻፉት ደግሞ ጭፍን ቅጥፈቶችና በበር ደረጃም ሀቅን ጨፋጫፊዎች
መሆናቸው የታየ ነው ። ከነዚህ በተሻል መልክ ይቀርባል የተባለው የፍስሃ ደስታ መጽሃፍም ምንም እንኳን
ጸሃፊው ህዝብን ለወንጀላቸው ይቅርታ ቢጠይቅም (በአብዛኞቹ የእርማ ውሰዱ ሰነዶች ላይ ያለው ፊርማ
የእሱነው ) በአያሌ ገጾች የደርግ ሀሰት (በተለይም በኢሕ አፓ ላይ) ደግሞ ማንሸራሸሩ አልቀረም ። በቅርቡ
ደግሞ የወያኔዋ ቅጥረኛ ገነት ዘውዴና ፋሺስቱና ፈርጣጩ መንግስቱ (ቅጽ 2) ቅጥፈታቸውን ያሳትማሉ ይባላል።
በእስር ቆይተው የነበሩት አራት ጦማሪያን ቢለቀቁም ወያኔ ጸረ ነጻ ፕሬስ የመሆኑ ባህሪ ቅንጣት አልቀነሰም ሲሉ
ኢፖእአኮና ሊሎችም የሰባአዊ መብት አስጠባቂ ድርጅቶች አሳሰቡ ። አሁንም ወያኔ በጋዜጠኖችና በነጻው ፕሬስ
ላይ አፈና እያከሄደ መሆኑ መረሳት የለበትም ያሉት እነዚህ ክፍሎች አፋኙ የፕሬስ ህግ ሳይሰረዝ፤ የታገቱ
ጋዜጠኞች ሁሉ ሳይፈቱ፤ ጸረ ነጻ ፕሬስ እርምጃዎች ሳይቆሙ የጦማሪያኑ መለቀቀ ብቻ ያለውን ሁኔታ ሊደብቅ
አይችልም ብለዋል ።

ወያኔ የኢኮኖሚ ጉዞአችን የደቡብ ኮሪያን ይመስላል ሲል ሳያፍር ለፈፈ ። በወያኔ ስር የኢትዮጵያ ለህዝብ የሚበጅ
ኢኮኖሚ አለማደግ ሳይሆን እየከሰረ መሆኑን ሕዝብ ስለሚያውቅ የሚታለል አይሆንም ። ወያኔ ከደቡብ ኮሪያ
የሚመሳሰልበት አንድ ጉዳይ ቢኖር ደቡብ ኮሪያን ከወያኔ ቢሻልም አምባገነን የነበረና ቹንግ ሂ ፓርክ የተባለ መሪ
ቀደም ብሎ ስለነበራት ብቻ ነው ። ፓርክና ወያኔ ግን አሁንም ቢሆን አይመሳሰሉም ።
የወያኔ የግፍ መዋጮ ሕዝቡን እያስመረረው ነው፡፡ ወያኔ ሥልጣን እርካብ በተቆናጠጠበት ወቅት ደርግ ለረሀቡ
ያስከፍል የነበረውን 10 በመቶ የሱር ታክስ ይኮንንና ያወግዝ እንደ ነበር አይዘነጋም፡፡ የወያኔ የታክስ ሥርዐት
ከሕዝብ አቅም ጋር ተዛምዶ የተተከለ ሳይሆን በማን አለብኝነት የተወሰነ በመሆኑ ግብር ከፋዩን ሕዝብ ለመረረ
ችግር ዳርጎታል፡፡ ለመለስ ሙት አመት፣ ለዓባይ ግድብ፣ ለመንገድ ግንባታ፣ ለግብዣ፣ ወዘተ. የተሰኙ መዋጮዎች
ሠራተኛችን በደሞዛቸው ላይ ያላቸውን መብት አሳጥቷቸዋል፡፡ በዚህ አስራ አምስት ቀናት ሕዝቡን ለብአዴን
35ኛ ዓመት ማዘጋጃ በሚል በግዴታ መዋጮ ጥለውበታል፡፡ ይህ ድርጊት የወያኔ እኩይ ባህሪ ይብሱን ያገጠጠበት
እንደሆኑ ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ በህንፃ ግንባታ ሥራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ዘጠና ከመቶው የሚሆነውን ሥራ
የሚወስዱት ከመንግስት በመሆኑ መዋጮ ሲጣልባቸው ላለመክፈል አሻፈረኝ ቢሉ ወደፊት ሥራ ለማግኘት
ይቅርና በአሁኑ ወቅት የያዙትንም ሥራ ሊነጠቁ ስለሚችሉ የተጣለባቸውን ውርጅብኝ ለመቀበል ተገደዋል፡፡
በተመሳሳይም ነጋዴዎች እንዲህ ዓይነቱን ዓይን ያወጣ ገፈፋ ከገፈተሩ ግብር ይጫንባቸዋል፡፡ በፈጠራ ከስም
ሊታሰሩ ይችላሉ፡፡ በዚህ ለብአዴን 35ኛ አመት የግዳጅ መዋጮ ማስተዋወቂያ ስብሰባ ላይ ከተገኙ ታዛቢዎች
መረዳት እንደተቻለው አብዛኛው ተሰብሳቢ በተደጋጋሚ ሲናገር የተደመጠው “ወገን በረሀብ እየረገፈ እናንተ
ለፈንጠዚያ መዋጮ መጠየቅ ተገቢ ያልሆነና በታሪክም ሊያስጠይቅ የሚችል ጉዳይ ነው፡፡” የሚለውን ንግግር
ነው፡፡ ለዚህ በአማራው ሕዝብ ስም የአማራውን ሕዝብ ቁም ስቅል እያሳየ ላለ ድርጅት ባለስልጣኖች መፈንጠዣ
ከአንድ ሚሊዮን እስከ አስር ሺ ብር የግዳጅ ክፍያ በልዩ ልዩ ሥራ ላይ በተሰማሩ ወገኖች ላይ እንደተጣለ
ለመረዳት ተችሏል፡፡

የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለተሰናባች የፓርላማ አባላት ተሰጡ በአዲስ አበባ ከወያኔ-ሰራሽ የሸቀጥ ዋጋ እየናረ ከመሄዱ በባሰ
የቤት ኪራይ ዋጋ ሰማይ ጥግ ደርሷል፡፡ ወያኔ ይህን የሕዘብ ችግር እቀርፋለሁ ብሎ ለማታለያነት እየተጠቀመበት ያለው
የጋራ መኖሪያ ቤቶችን መገንባት ነው፡፡ ይህ ግንባታ ሲጀመርም ለፖለታካ ተረፌታ ተብሎ እንደሆነ አይረሳም የሚሉ ወገኖች
እንደሚሉት ከግንባታው ለምሮ እስከ እደላው ድረስ ሆን ተብሎ ብልሹ እንዲሆን ተደርጓል ይላሉ፡፡ የቤቶቹ አሰራር እረጋ
ሰራሽ መሆኑ አንዱ ወነኛ ችግር ሲሆን የቤቶቹ እደላ የሚካሄደው በብሄረሰብ ማንነትና የወያኔ አባልነት ላይ ተሞርኩዞ
በመሆኑ ለአብዛኛው ተመዝጋቢ ላም አለኝ በሰማ ወተቷን አላይ ሆኖበታል፡፡ ለትግራይ ተወላጆች እስከ አራት ቤት በደም
ካሳ ስም ሲታደል ሌሎች ተመዝጋቢዎች አስራ አንድ አመት ሙሉ እንዲጠብቁ ተደርጓል፡፡ ዘንድሮ ከፓርላማ ለተሰናበቱት
የወያኔ አባላት ቦሌ ቡልቡላ ከተገነቡት የጋራ መኖሪያዎች ውስጡ የተመረጡ አራት ብሎኮች ተመድበውላቸዋል፡፡ ወያኔዎች
የመንግስት ቤቶች ውስጥ እየኖሩ የግላቸው የሆኑ አራትና አምስት ቤቶች ያከራያሉ፡፡ የወያኔ ከፍተኛ መኮንኖችም
በተመሳሳይ እነሱ በመንግስት ቤቶች ውስጥ እየኖሩ ቢያንስ ከሁለት ቤቶች በላይ ያከራያሉ፡፡ ሕዝቡ ግን የቤት ኪራይ
በየጊዜው እየናረ በመሄዱ በሀገሩ ላይ መኖር አልቻለም፡፡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በአብዛኛው ኪራይ ናቸው፡፡ የደረሳቸው
ሰዎች ወያኔዎችና ከወያኔዎች ጋር ንክኪ ያላቸው ይበዛሉ፡፡ ሌላ መኖሪያ ቤት ስላላቸው የደረሳቸውን የጋራ መኖሪያ ቤት
ያከራያሉ፡፡ ኪራዩንም እንዳሻቸው ይጨማራሉ፡፡ ወያኔ ይህን በየወሩ እየናረ በመሄድ ላይ ለውን የቤት ኪራይ ለማረጋጋት
ምንም ዓይነት ደንብ የማይደነግግበት ምክንያት አከራዮቹ በብዛት የወያኔ ካድሬዎች በመሆናቸው ነው በማለት ሕዝቡ
ምሬቱን በብስጭት ሲያወጣ ይደመጣል፡፡

ከድርቅ ጋር በተያያዘ የተራበው ሕዝብ ቁጥር እየጨመረ መሄዱ በይፋ ተነገረ፡፡ ወያኔን ሊሸፋፍን እየሚከረ ያለው ድርቅና
ረሀብ እየሰፋና እየመረረ በመሄዱ የዓለም የምግብ ድርጅት የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ በመንደርደሩ ሳቢያ በረሀብ
አለንጋ እየተንገላቱ ያሉት ሰዎች ቁጥር 8.5 ሚሊዮን አንደሆነ ቢገለጽም የተረጅው ቅጥር ከ16 ሚሊዮን በላይ ሊሆን
እንደሚችል ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኞች እየገለጹ ነው፡፡ ለእርዳታ ይፈለጋል ተብሎ የተሰላው ገንዘብ 12 ቢሊዮን ብር
ሲሆን ከዚህ ውስጥ ወያኔ አስቀድሞ ከካዝናው 4ቢሊዮን ብር እያወጣሁ ነው የሚለውን ልፈፋ ውሸት መሆኑን እየለፈፈ
ወያኔን በቅጡ የሚያውቁ የፖለቲካ ተንታኞች እያስረዱ ነው፡፡ ወያኔ ከረሀብተናው አፍ እየነጠቀ መብላት ልማዱ መሆኑ
ሊረሳ እንደማይገባው ያወሳሉ፡፡ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ወያኔ ዋሾ፣ ቀማኛና ቀጣፊ በመሆኑ በረሀብተናው ስም
አራት ቢሊዮን ብር ለወያኔ ቁንጮዎች ኪስ ማዳበሪያ ለማዋል ሲባል የተሰላ ሴራ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ በተመሳሳም የወያኔው
ጠቅላይ ሚንስትር ከረሀብተናው ጋር እንደተወያየ የመገናኛ ብዙሀኖቹ አስተጋብተዋል፡፡ ረሀብተኛ ምግብ ይቀርብለታል
እንጂ በስብሰባ አንዲደርቅ አይደረግም፡፡ ይህ ሁሉ ሽር ጉድ በማድረግ ወያኔዎች ከራሳቸው ውጪ የሚያታልሉት እንደሌለ
የሚረዱት አይመስሉም፡፡ በረሀብተኛ ሕዝብ ስም ገንዘብ ማካበት የተዳፈነውን የሕዝብ ቁጣ መጫር መሆኑን ለጊዜው
የሚያውቁት አይመስልም፡፡

ሰሞኑን ወያኔ በኮንሶ ሕዝብ ላይ የኃይል ርምጃ የወሰደ መሆኑ ታወቀ፡፡ የኮንሶ ሕዝብ ማንነቱን ለማስከበርና ባህሉን
ለማበልጸግ የእራሱ እስተዳዳር እንዲኖረው በመጠየቁ በፈጥኖ ደራሽ እና በፌደራል ፖሊስ በሚዘገንን ሁኔታ
ተጨፍጭፏል።የኮንሶ ሕዝብ በሰላማዊ ሁኔታ ላለፉት ዘጠኝ ተከታታይ ቅዳሜዎች እራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበት
መብቱን ለመጠየቅና ለማስከበር ሳያሰልስ እየተሰባሰበ ሲመክር ሰንብቶ ነበር፡፡ በየጊዜው የሚሰበሰብው ሕዝብ ቁጥር
እየጨመረ መሄዱ ጥያቄው የሕዝብ ጥያቄ ለመሆኑ ዓይነተኛ ማስረጃ ነው፡፡ የሕዝብ መነሳሳትን ክፉኛ የሚፈራው ወያኔ
ከበስተጀርባ ተቃዋሚዎች አሉ በሚል ሰልፈኛውን በጭካኔ ደብድቧል፡፡ ይህን የመሰለው አረመኔያዊ ድርጊት ትግልን
ያፋፍማል እንጂ አይገታውም የሚሉ የፖለቲካ ተንታኞች ቁጥር በርካታ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፌዴሬሽን የቻይና ኩባንያዎች ኢ-ሰብአዊነትን አጋለጠ፡፡ የቻይና ኩባንያዎች
የሠራተኞችን መብት የሚረግጡ፣ የሠራተኛ ማህበር ማቋቋምን የሚገድቡ፣ ሠራተኞችን የሚሰድቡ፣ የሚደበድቡ፣ ደሞዝ
ከልክለው ከሥራ የሚያባርሩና፣ ዝቅተኛ ደሞዝ የሚከፍሉ መሆናቸውን በመጥቀስ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታረሙ
የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፌዴሬሽን በተደጋጋሚ ደብዳቤ ቢጽፍም ምንም ምላሽ አለማግኘቱን ገልጿል፡፡ የቻይና
ኩባንያዎች በማንአለብኝነት ለሚጻፍላቸው ደብዳቤ እንኳ ምላሽ ባለመስጠተቸው ፌዴሬሽኑ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት
ክስ የመሰረት ቢሆንምና እስከወያኔው ጠቅላይ ሚኒስትር ድረስ ማመልከቻ ቢያቀርብም ያገኘው ውጤትና ምላሽ የሌለ
መሆኑን ገልጿል፡፡ የወቅቱን የኢትዮጵን የፖለቲካ ምህዳር በመተንተን የሚታወቁ ተንታኞች እንደሚያስረዱት የቻይና
ኩባንያዎች በወያኔ ውስጥ ያሉ መንግስቶች በመሆናቸው ማንም የሚነካቸው የለም ይላሉ፡፡ በተያያዘ ዜናም በአገር ውስጥ
ያሉ የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች ሊሠሯቸው የሚችሉ የግንባታ ሥራዎች ሁሉ ለቻይና ኩባንያዎች በገፍ እየተሰጡ
መሆናቸውን ብዙዎች በምሬት ይገልጻሉ፡፡ ቻይና ታበድራለች፤ ቻይና ትዘርፋለች፤ ቻይና የሥራ አጥ ዜጎቿ ማራገፊያ
አርጋናለች የሚሉ ወጣት ፖለቲኮች ቁጥር በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ በቅርቡ ኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን
አስተናጋጅ ከቻይና መቅጠሩ አገርን ብቻ ሳይሆን ዓለምንም ያስደመመ መሆኑ መስታወሱ ተገቢ ይሆናል፡፡
የመኪና መገጣጠሚያ ኩባንያዎች ገበያ በማጣታቸው እሮሮ እያሰሙ ናቸው፡፡ ወያኔ በጥናት ላይ ያልተመሰተረተ የገበያ
ሥርዐት እያካሄደ በመሆኑ የሚቋቋሙ በመፈራረስ ላይ መሆናቸው የታወቀ ነው፡፡ ባለሀብቶችን ለመሳብ ወያኔ ገበያ
እንደሚያመቻች ባዶ የተስፋ ቃል በመግባት ወደ ሥራ እንዲገቡ ቢያደርግም ችግሩ ሳውል ሳያድር በመከሰቱ በርካታ
ኩባንያዎች ለመዘጋት ተዳርገዋል፡፡ ከዚህ በፊት አንድ መቶ አራት የመኪና መገጣጠሚያ ኩባንያዎች የንግድ ፈቃድ የወሰዱ
መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ስድስቱ ብቻ በሥራ ላይ ሆነው ይታያሉ፡፡ በኪሳራ ከተዘጉት መካከል
አንደኛው ሆላንድ ካርስ የሚባለው ሲሆን በአሁኑ ወቅት እያመረቱ የሚገኙት ደግሞ ያንግ ፋን፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል
ኢንጂነሪንግ፣ ቤተሬት ኢንተርናሽናል የተወሰነ የግል ማህበር፣ በላይ አብሞተርስ፣ የብረታ ብረት ኢንጂነሪነግ ኮርፖሬሽን፣
ኒግማ ሞተርስ ናቸው፡፡ አገር ውስጥ የሚመረቱት መኪናዎች የፍሬን ላይ ችግር ያለባቸው ሲሆን የመለዋወጫ እቃቸው
በቀላሉ የሚገኝ ባለመሆኑና ቢገኘም እጅግ በጣም ውድ በመሆኑ ከእነሱ ይልቅ ከውጪ የሚገቡ ያገለገሉ መኪናዎች
ተመራጭነት እንደጸና መቀጠል ችሏል፡፡ ለመንግስት መሥሪያ ቤቶች በግዳጅ የተሸጡት መኪናዎች በአጭር ጊዜ ተሰናክለው
እንደቆሙ የታወቀ ነው፡፡ በመከላከያና በቻይና በጋራ የሚመረተው “ቢሾፍቱ” የሚል ስያሜ የተሰጠው መኪና ብዙም
ሳያገለግል እየቆመ ለመሆኑ አንበሳ አውቶብስ በግዳጅ እንዲገዛ ተደርጎ ከሁለት መቶ ስልሳ አውቶብስ በላይ እየተሳናከለ
ቆሟል፡፡ ይህን መጥፎ ስም ለማደስ የተለየ ስም በመስጠት ለመንግስት ሠራተኞች አገልግሎት የሚሰጡ አውቶብሶች
በአብዛኛው ጠዋትና ማት ሠራተኛ ወደ ሥራ ሲገባና ከሥራ ሰወጣ የሚነዱ በግብር ከፋዩ ሕዝብ ገንዘብ ተገዝተው ቀኑን
ሙሉ ተገትረው ይውላሉ፡፡ ገበያ ያላቸው መገጣጠሚያዎች የወያኔው መስፍን ኢንጂነሪግና የመከላከያው ብረታ ብረት
ኢንጂነሪንግ ሲሆኑ እነሱም በአንዳንድ የመንግስት መሥሪያ ቤቶች በግዳጅ ከሚሸጡት በስተቀር ሌላው ሰው አይገዛቸውም፡
፡ ወደ ጎረቤት አገር ለመላክ የታሰበ ቢሆንም ከቅዠት ሊሻገር የማይችልበት ምክንያት ኬንያ፣ ሱዳን፣ ኡጋንዳ እንደዚሁ
የቻይና የመኪና መገጣጠሚያ ኩባንያዎች ስላሉ ገበያ አይኖርም፡፡ ድርጅቶቹ ያመረቷቸው መኪናዎች በቆሙበት እየዛጉ
እንደሆነ በመግለጽ መንግስት ሊገዛቸው እንደሚገባ እየተወቱ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የግሉን የንግድ ዘርፍ የወያኔ
ኩባንያዎች በማጣበባቸው ገበያው በነፃነት እንዳይንቀሳቀስ እንቅፋት ሆነዋል፡፡ መከላከያም ከግዙፍ እስከ ትናንሽ
ሥራዎች በመግባቱ የግሉን የንግድ እንቅስቃሴ እያሽመደመዱት ይገኛሉ፡፡

በጅቡቲ ከመስከረም 30 ጀምሮ የተጧጧፈው የአገዛዙና የተቃዋሚው ፍሩድ ውጊያ አሁንም ተፋፍሞ እየተካሄደ ሲሆን
በቅርቡ በተልያዩ ከተሞች የፍሩድ ደጋፊዎች ናችሁ በማለት የገሌህ አገዛዝ በርካታ ዜጎችን አስሯል ። ከዚሁ ተያይዞ ፍሩድ
የተባለው ተቃዋሚ ሀይል ከታጁራህ ወደ ሰሜን የመኪና መንገድ ይሰራ የነበረውን የሲሺል ኩባንያ የጭነት መኪናዎች
ማቃጠሉ ተነግሯል ፡፤ ይህን እርምጃ ድርጅቱ የወሰደበት ምክንያት መኪናዎቹ የወታደር ማመላላእሻ ሆነው በማገለገላቸው
ነው ሲል የፍሩድ ፕሬዚዳንት መሃመድ ካዳሚ አብራርቷል ። ገሌህ ከቻይና በመቀራረቡ የተቆጡ አሜሪካና ፈረንሳይ ሲሆኑ
ፈረንሳይ የፍሩድ ፕሬዚዳንት በራዲዮኗ ቃል መጠይቅ እንዲደረግለት ፈቅዳ ለመናገር የቻለ መሆኑ ታውቋል ።
ታዬ አስቀስላሴ የሚባለው የወያኔ አሸርጋጅና ባለሟል ለአሽከርነቱ ካሳ በወያኔው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ደኤታ
ተብሎ መሾሙ ታውቋል። ታዬ አስቀስላሴ የብአዴን አባል ሆኖ ከማገልገሉ ባሻገር ፎረም 84 ን በማደረጀትና በውጭ
አገርም በዋሽንግተን ዲሲ የወያኔ ኢምባሲና በሎስ አንጀለስ የወያኔ ቆንስላ ውስጥ በመመደብ በአገርልጅነትና በትውውቅ
ግለሰቦችን ለወያኔ ባለሟልነት ሲመለምል የነበረ በተቃዋሚው ጎራ ውስጥ ሴራ በመጎንጎን ሆነ ስለላ በማካሄድ ለመከፋፈል
ጥረት ሲያደርግ የቆየ ዋና የወያኔ አገልጋይና አጫፋሪ ግለሰብ ነው።
በኢትዮጵያና በሱዳንና ወሰን አካባቢ በኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮችና በሱዳን ወታድሮች መካከል ሰሞኑን ግጭቶች
የተፈጥሩ መሆናቸው ከአካባቢው የተገኙ ዜናዎች ይገልጻሉ። የወያኔ አገዛዝ በወሰን አካባቢው የሚገኘውን ለም መሬት
ለሱዳን አሳልፎ ከሰጠ ጅመሮ የአካባቢው አርሶ አደር በየጊዜው በሱዳን ወታደሮች ላይ ጥቃት ሲፈጽም የቆየ መሆኑ
የሚታወቅ ሲሆን ሰሞኑን ኢትዮጵያውያኑ በሱዳን ወታደሮች ላይ የወሰዱት እርምጃ ጠንካራ በመሆኑ ሱዳን ተጨማሪ
ወታድሮች ለመላክ የተገደደ መሆኑ ተነግሯል። የወያኔ የሱዳን ባለስልጣኖች ስለጉዳዩ ምንም የሰጡት መግለጫ ባይኖርም
የሁለቱም ከፍተኛ የድህንነት ባለስልጣኖች ሰሞኑን ካርቱም ውስጥ የድብቅ ስብሰባ ማድረጋቸውን ከስብሰባው አካባቢ
ሾልኮ የወጣው መረጃ ይገልጻል። ሰሞኑን በድንበር አካባቢ የደረሰው ሁኔታ ከተነጋገሩባቸው ጉዳዮች መካከል አንደኛው
ሲሆን በቅርቡ በጋራ ለማኬሄድ ባቀዱት ፕሮጀክት ላይ እና እንዲሁም በሱዳን ስለሚገኙ ስደተኞች ጉዳይ የተነጋገሩበት
መሆኑ ታውቋል።

The post [ፍኖተ ዴሞክራሲ አጫጭር ዜናዎች] – የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለተሰናባች የፓርላማ አባላት ተሰጡ * የወያኔ የግፍ መዋጮ ሕዝብን እያስመረረ ነው * ወያኔ በኮንሶ ሕዝብ ላይ የሀይል እርምጃ ወሰደ appeared first on Zehabesha Amharic.

በኢትዮጵያ የተከሰተው የረሃብ አደጋ ወደ አስከፊ ሁኔታ እንዳይሸጋገር ለምን ዓለም አቀፉን ተቋም ብቻ ያሳስበዋል?

$
0
0

በአገር ቤት የድርቁ አደጋ ወደ አስከፊ የረሃብ አደጋ እንዳይቀየር ከፍተና ስጋት አለ። የአገዛዙ ሰዎች ድርቁን ከመካድ ጀምረው እንቆታጠረዋለን እያሉ ለጋሾችን ሲያዘናጉ አሁን ችግሩ አፍጥጦ መጥቷል። ዛሬም ግን ረሀቡ በአንዳንድ የአገራችን አካባቢዎች እያደረሰ ያለው ጥፋት ችግሩ ሳይከፋ ትኩረትም አፋጣኝ ምላሽም ይፈልጋል። የመንግስታቱ ድርጅት ችግሩ አሳሳቢ ነው እያለ ቢወተውትም የአገዛዙ ባለስልታኖች ዛሬም ትኩረታቸው ለፖለቲካ ስብሰባ በአበል እና በተሃድሶ ስም እየደገሱ የአገሪቱን ሀብት ማባከን ላይ ነው። የወቅቱን የረሀብ አደጋ ቃኝተነዋል።

በኢትዮጵያ የተከሰተው የረሃብ አደጋ ወደ አስከፊ ሁኔታ እንዳይሸጋገር  ለምን ዓለም አቀፉን ተቋም ብቻ ያሳስበዋል?

The post በኢትዮጵያ የተከሰተው የረሃብ አደጋ ወደ አስከፊ ሁኔታ እንዳይሸጋገር ለምን ዓለም አቀፉን ተቋም ብቻ ያሳስበዋል? appeared first on Zehabesha Amharic.

ኃይለማርያም ደሳለኝ በትጥቅ ትግል ያሉ ኃይሎች ወደ ሰላማዊ መሥመር እንዲመጡ ጠየቁ

$
0
0

hailemariam
ዛሬ በኢትዮጵያ ፓርላማ የቀረቡት የሕወሓቱ መንግስት ጠቅላይ ሚ/ር ኦብነግ የሚባል ድርጅት አልቋል; ኦነግ የሚባል ድርጅትም አልቋል ካሉ በኋላ ሌሎች ጠመንጃ ያነሱት ኃይሎች በሰላማዊ መንገድ ነፃነትን የጠየቁ የፖለቲካ መሪዎች በታሰሩበት ሃገር ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ ጠየቁ::

የአሜሪካ ድምጽ ራድዮን ዘገባ ያድምጡና አስተያየትዎን ይስጡ::
[jwplayer mediaid=”47760″]

The post ኃይለማርያም ደሳለኝ በትጥቅ ትግል ያሉ ኃይሎች ወደ ሰላማዊ መሥመር እንዲመጡ ጠየቁ appeared first on Zehabesha Amharic.

የመኢአድ ሕጋዊው ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት አማረ የአሜሪካ ቪዛ ተከለከሉ

$
0
0

ህብር ሬዲዮ ( ላስ ቬጋስ) የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) ሕጋዊው ፕሬዝዳንትና በአገዛዩ ምርጫ ቦርድ ህገ ወጥ ውሳኔ ከቢሮ የተባረሩትና በቅርቡ ከእስር በነጻ የተፈቱት አቶ ማሙሸት አማረ በውጭ ከሚገኙ የፓርቲው ደጋፊዎች ጋር ለመነጋገር ወደ አሜሪካ አቅደውት የነበረው ጉዞ በዛሬው ዕለት ቪዛ በመከልከላቸው ሳይሳካ መቅረቱን ለህብር ሬዲዮ የፓርቲው ምንጮች የላኩልን መረጃ ያስረዳል።
Mamushet_Amare_us_embassy_02
አቶ ማሙሰት አማራ ግብኖት 5 ቀን 2008 ከመንገድ ላይ በአገዛዙ ደህነቶች ታፍነው ከአራት ወራት በላኢ በተሌኤዩ እስር ቤቶች ሲንገላቱ የቆዩ ሲሆን በፓርቲው ውስጥ ከፕሮፌሰር አስራት ሊቀመንበርነት ጊዜ ጀምሮ ሲያገለግሉ የቆዩና በምርቻ 97 ከቅንጅት መሪዎች ጋር የታሰሩትን ጨምሮ በመረጡት ሰላማዊ ትግል ሳቢአያ ለስምንት ጊዜአት ታስረዋል።

አገዛዙ መቶ በመቶ አሸነፍኩ ካለበት ምርቻ ዋዜማ መኢአድና አንድነት ያካሄዱትን ሕጋዊ ጉባዔ በምርቻ ቦርዱ አማካይነት ድጋሚ እንዲደረግ ሲያስገድድ ከመላው አገሪቱ የተሰባሰቡ የመኢአድ የጠቅላላ ጉባዔን በቀናት ልዩነት በድጋሚ ጠሩ ሲሆን ለሁለተኛ ጊዜ ፓርቲውን በፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ መመረጣቸው ይታወሳል። የአገዛዙ ምርጫ ቦርድ የፓርቲውን ጉባዔ ውሳኔ በመሻር ቢሮውን በፖሊስ ቁጥጥር ስር በማድረግ አቶ ማሙሸትና ዛሬ በእስር ቤት የሚገኙትን የፓርቲውን የውጭ ግንኙነት ሀላፊና ሌሎች አመራሮችንና ውሳኔውን ያልተቀበሉትን አባላት አባሮ በምትካቸው ስልታኔን ለቅቄአለሁ ያሉትን ቀድሞ የፓርቲው ፕሬዝዳንት አቶ አበባው መሐሪን ከቤታቸው በማምታት ቦርዱ ስልታን ላይ በማስቀመጥ ግለሰቡ ከማን ጋር ሲሰሩ እንደቆዩ ችምር ያጋለጠ ውሳኔ ነው ሲሉ የፓርቲው ሰዎች መግለጻቸው አይዘነጋም።

አቶ ማሙሰት ቦርዱን ለፈጸመው ሕገ ወጥ ውሳኔ በፍርድ ቤት ክስ የመሰረቱት ቢሆንም ክሱ ዳር ሳይደርስ ግንቦት 5 ቀን 2008 ከቤታቸው አቅራቢያ በአገዛዙ ደህነቶች ታፍነው መጀመሪያ ቦሌ ምድብ ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸው እና በሊቢያ በኤይሲስ የተቀሉና የተገደሉ ኢትዮጵአውያን ሐዘናቸውን በገለጹበት ወቅት ተገኝተህ አመጽ ቀስቅሰሀል የሚል ክስ ቀርቦባቸው የደህነት አባላት ቀርበው በሀሰት ከመሰከሩ ድርጊቱን መስቀል አደባባይ ተገኝተው ፈጽመዋል በተባሉበት ሚአዚያ 14 ቀን 2008 በቦታው እንዳልነበሩ፣ በዕለቱ ምርቻ ቦርድን ከሰው ልደታ ፍርድ ቤት ክርክር ላይ እንደነበሩ ከፍርድ ቤት ማረጋገጫ አቅርበው፣በዕለቱ አብረዋቸው ፍርድ ቤት የነበሩ ጓዶቻቸውን አስመስክረው ፍርድ ቤቶ ክሱ ተቋርጦ በነጻ ይለቀቁ ቢላቸውም ሳይፈቱ ከእስር ቤት ወደ እስር ቤት መዛወራቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

አቶ ማሙሸት አማረ ከእስር ከተፈቱ በሁዋላ ለህብር ሬዲዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ ከዚህ በሁዋላ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ብታደርግ እንገድልሃለን መባላቸውንና የደህነቶች ክትትል ከወቱም በሁዋላ እንዳልተቋረጠ ነገር ግን እስኪገሉኝ ሰላማዊ ትግሉን እቀጥላለሁ ማለታቸው ይታወሳል።

አቶ ማሙሸት አማረ የመኢአድ ሕጋዊው አመራር እና ብዙሃኑ አባላት በምርቻ ቦርድ ሕገ ወጥ ውሳኔ ቢራችን ቢነጠቅም ተመልሰን ትግሉን እንቀጥላለን ሲሉ ከዚህ ቀደም በሰጡት ቃለ ምልልስ የገለጹ ሲሆን የሰሞኑ የአሜሪካ ጉዞዋቸው ከፓርቲው ደጋፊዎች ጋር ለመነጋገር የታቀደ ሲሆን በኤምባሲው ቪዛ ክልከላ ሳቢያ ጉዟቸው ተስተጓጉሏል።

The post የመኢአድ ሕጋዊው ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት አማረ የአሜሪካ ቪዛ ተከለከሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

የወታደሮቻችን ነገር –ከዲ/ን ዳንኤል ክብረት

$
0
0

የመቅደላው ጀግና ዐፄ ቴዎድሮስ በመጨረሻዋ ሰዓት ለጄኔራል ናፒየሪ በጻፉት ደብዳቤ አበክረው የጠየቁት ነገር ከሁለት ቀናት በፊት በተደረገው ውጊያ የወደቀውን የወዳጃቸውንና የጦር መሪያቸውን የፊታውራሪ ገብርዬን አስከሬን ለመቅበር እንዲፈቀድላቸው ነበር፡፡ ‹‹ፊታውራ ገብርዬን የኔን ወዳጅ ሳላነሣው ያደርኩ ከሞትኩኝ ሁሉንም አብረው ይቅበሩኝ ብየ ነበር፡፡ ቁሜ ከዋልኩ ግን ልቅበረው ይፍቀዱልኝ›› ይላል ደብዳቤው፡፡ ለሀገሩና ለወገኑ በክብር የተሠዋ አስከሬኑም የክብር ዕረፍት ይሻዋልና፡፡

last letter
አሜሪካኖችና አውሮፓውያን የተሰጣቸውን ግዳጅ ለመወጣት የዘመቱ ወታደሮቻቸው ሲሠው በክብር አስከሬናቸውን ወደ ሀገር በማምጣት በብሔራዊ ሥነ ሥርዓት የመቅበር ያልጠፋ ልማድ እንዳላቸው በየጊዜው ሚዲያው ያሳየናል፡፡ እነዚህ ወታደሮች ሀገራዊ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የዘመቱ በመሆኑ መሥዋዕትነታቸውም ሀገራዊ ሆኖ መታሰብ አለበት፡፡
በኢትዮጵያ የቅርብ ዘመን ታሪክ የተሠዉ ወታደሮችን በክብር የመዘከር፣ በክብር የመቀበልና በክብር የመቅበር ሥነ ሥርዓት አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ በኢትዮጵያና ኤርትራ ጦርነት የተሠዉ ስንት ወታደሮች ናቸው? የተሠዉትስ ወታደሮች መርዶ እንዴት ተነገረ? የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውስ እንዴት ተከናወነ? ሚዲያውስ ለዚያ ምን ዓይነት ሽፋን ሰጠው? የሁል ጊዜ ጥያቄዬ ነው፡፡ እኔ ሳልሰማና ሳላውቅ ተከናውኖ ካልሆነ በቀር፡፡ ለምንስ አስከሬናቸው በወታደራዊ ሥነ ሥርዓት ታጅቦ፣ ሰንደቅ ዓላማ ለብሶ፣ ብሔራዊ መዝሙር እየተዘመረ፣ ሕዝቡ ወደ አደባባይ በነቂስ ወጥቶ አላከበርናቸውም? እያልኩ እጠይቃለሁ፡፡

የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር በአፍሪካ ልዩ ልዩ ሥፍራዎች ዘምቷል፡፡ ሲዘምትም በክብር እንደተሸኘ በሚዲያዎቻችን አይተናል፡፡ እነዚህ ዘማቾች ሁሉም በሰላም ነው የተመለሱት? የተሠዋ ካለ ለምን ይፋዊ በሆነ ሀገራዊ ሥነ ሥርዓት አስከሬኑን ተቀብለን አልቀበርነውም? ፖለቲካው ተፈርቶ ከሆነ ለግዳጅ የተሠማራ ወታደር ወይ በድል መመለስ፣ ወይ መማረክ፣ ወይ መቁሰል አለያም መሠዋት እንደሚያጋጥመው እንኳን እኛ ታሪካችን በጦርነት የተሞላው ቀርቶ ሌሎችም ያውቁታል፡፡
የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ሶማልያ ሲዘምቱ ፓርላማው ወስኖ ነው የዘመቱት፡፡ የሄዱት በእር በርስ ጦርነት ሲታመስ ወደኖረውና እጅግ አስቸጋሪ ወደሆነው የጦርነት ሥፍራ ነው፡፡ ከሶማልያ መንግሥት ወታደሮችና ከአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ጦር ጋር በጋራ በመሆን በሶማልያ ከአልሸባብና ከሌሎችም ኃይሎች ጋር በመዋጋት ያገኙትን ድል ሚዲያዎቻችን ይዘግባሉ፡፡ መቼም የሄዱት ለጦርነት ነውና፣ በጦርነት ውስጥ መግደል፣ ድል ማድረግና መማረክ እንዳለ ሁሉ መሞት፣ መቁሰልና መማረክም አለ፡፡
ታድያ የሀገሬ ወታደሮች አልተሠዉም፣ አልቆሰሉም፣ አልተማረኩም? የሄዱት ሁሉ ሰላም ናቸው? ከሆኑ መልካም፡፡ ግን ቦታውም የነ አልሸባብ ቦታ፣ ሁኔታውም ጦርነት፣ ሰዎቹም ወታደሮች ናቸውና ቢያንስ መሞትና መቁሰል አይቀርም፡፡ የአሜሪካና የአውሮፓ ሚዲያዎች በአፍጋኒስታን፣ በኢራቅና በሶርያ ጦርነት የተሠዉትንና የቆሰሉትን ማንነት እንደሚናገሩት፣ በክብርም ሲቀበሩ እንደሚያሳዩት፣ የኛዎቹ የተሠዉት በክብር ሲቀበሩ፣ የቆሰሉት በክብር ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ለምን እንደ ሕዝብ አናያቸውም? ለመሆኑስ በክብር የተሠዉ የኢትዮጵያ ወታደሮች መቃብር የት ነው?
ወደኋላም ተመልሰን ከአድዋ ጦርነት በኋላ የሆነውን ስናስታውስ በእንዳ ኢየሱስ ያለው የአባቶቻችንን መቃብርና ከዚያ እልፍ ብሎ የሚገኘውን የጣልያኖች መቃብር መመልከቱ ብቻ በቂ ነው፡፡ በእንዳ ኢየሱስ የሚገኘው የአድዋ ዘማቾች አባቶቻችን መቃብር ለመሥዋዕትነታቸው የማይመጥን ነው፡፡ አልፎ አልፎም ፈርሶ እናየዋለን፡፡ የጣልያኖቹ መቃብር ግን በክብር ታጥሯል፡፡ ጠባቂም ተመድቦለታል፡፡ መቃብሩንም ለማየት የጣልያን ኢምባሲ ፈቃድ ይጠይቃል፡፡

grave of americane soldiers
በአሥራ ሰባቱ የደርግ ዓመታት የዘመቱት ወታደሮች ኢትዮጵያ የመለመለቻቸው፣ ያሠለጠነቻቸውና ያዘመተቻቸው ነበሩ፡፡ ምንም ጦርነቱ የእርስ በርስ ጦርነት ቢሆንም፡፡ የተሠዉት አብዛኞቹ ወታደሮች ለቤተሰብ መርዶ አልተነገረም፡፡ በተለይ ኤርትራ በረሃ የቀሩት መጨረሻቸው ምን እንደሆነ አልታወቀም፡፡ ጦሩ ሲበተን ወደ ቤተሰባቸው መምጣት የቻሉት ቁርጣቸው ታወቀ፤ ከዚያ ውጭ ያሉት ግን አሁንም ለቤተሰብና ለሀገር ጥያቄ እንደሆኑ ናቸው፡፡
የአንድ ወታደር ክብር የሀገራዊ ዓላማና የሀገራዊ ግዳጅ ክብር ማሳያ ነው፡፡ አሜሪካ ውስጥ በአውሮፕላን በተጓዝኩ ቁጥር ለአሜሪካ ወታደሮች የሚሰጠውን ክብር አደንቃለሁ፡፡ አውሮፕላኑ ምድር ደርሶ ተሣፋሪዎቹ እንደተቀመጥን ለወታደሮቹ ቅድሚያ ተሰጥቶ እያጨበጨብን ወደ በሩ እንሸኛቸዋለን፡፡ ወደ አውሮፕላን ውስጥ ስንገባም አስተናጋጆቹ ‹ዩኒፎርም የለበሱ ጀግኖቻችን አሉና እናክብራቸው›› ብለው ያውጃሉ፡፡ ሁላችንም እንጨበጭባለን፡፡ እኔ የሀገሬ ወታደር በአውሮፕላን እንኳን ባይሆን በታክሲና በአውቶቡስ፣ በመዝናኛ ቦታዎችና በአገልግሎት መስጫ ተቋማት እንዲህ ሲከብር ማየት እናፍቃለሁ፡፡
ወታደሮቻችንን ጉሮ ወሸባየ ብለን እንደሸኘናቸው ሁሉ የጀግና አቀባበል እንድናደርግላቸው፣ ሲሠዉ በክብር አደባባይ ወጥተንና የሞቱለትን ሰንደቅ ዓላማ አልብሰን እንድንሸኛቸው፣ የቆሰሉትን በክብር እንድንቀበላቸው፣ ያስገኙት ድል ብቻ ሳይሆን የገጠማቸው ፈተናና የከፈሉት መሥዋዕትነትም እንዲነገርላቸው እመኛለሁ፡፡ የክብር አቀባበልን ላሸነፈ ሯጭና እግር ኳስ ተጨዋች፤ የክብር አቀባበርንም ለአርቲስት ብቻ ማን ሰጠ?

The post የወታደሮቻችን ነገር – ከዲ/ን ዳንኤል ክብረት appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: ከሁለት ብልቶች ጋር የተፈጠረው ሰው አነጋጋሪ እየሆነ ነው!!

$
0
0

ምናልባት ከአሁን ቀደም ሁለት እጅ ወይም እግሮች ያሉትን ሰው ከማወቃችን አንፃር ይህን መሰል አፈጣጠር አስተውለን አናውቅም፡፡ እርግጥ ነው አንዳንዴ አንድ ሰው ከተለመደው አምስት ጣቶች ባሻገር ስድስትና ሰባት ጣቶችን ይዞ ሊወለድና በዚህ መልክም የተፈጠረ ሰው አይተን ይሆናል፡፡ አንድ ወንድ ልጅ ግን ሁለት ባህሪን ከያዘ የወንድ ብልቶች ጋር ይፈጠራል ብሎ ማሰቡም ሆነ ተፈጥሮ ማየቱ እጅግ የሚገርም ነው የሚሆነው፡፡ ይሁን እንጂ እንደዘርፉ የመራቢያ አካላት ተመራማሪዎች ከ5.5 ሚሊዮን ወንዶች ውስጥ አንዱ ይህን መሰል አፈጣጠር ይዞ ሊወለድ ይችላል ማለት ነው፡፡

Zehabesha News

ጉዳዩን በዓለም ላይ ስንመለከተው 1400 ወንዶች ከዚህ መሰል አፈጣጠር ጋር የሚኖሩ ሲሆን በአገራችን ደረጃ ደግሞ ሲታይ ከ10 ወንዶች በላይ ይሆናሉ፡፡ በእርግጥ አንድ ፍጡር ከሁለት የወንድ ብልቶች ጋር የመፈጠር ሂደት በአንዳንድ እንሰሳ ላይ የተለመደ ነው ይላል ሳይንስ፡፡ በተለይ እንደ እንሽላሊትና እባብ የመሳሰሉ እንስሳት ባለ ሁለት የወንድ ብልት ባለቤቶች ናቸው፡፡ በእነሱ ዘንድ ምናልባት አስገራሚ የሚሆነውም አንድ እባብ ወይም እንሽላሊት ነጠላ የወንድ ብልት ይዞ ሲፈጠር ሊሆን ይችላል፡፡

ይህ መሰል ለየት ያለ የወንድ ብልት አፈጣጠር በልዩ ስያሜው ‹‹Dipohallia›› በመባል የሚጠራ ሲሆን ስያሜውን ያገኘውም ከግሪክ ቃል ነው፡፡ ‹‹Di›› ማለት ‹‹ሁለት›› ሲሆን ‹‹Phallia›› ማለት ደግሞ ብልት ማለት ነው ይላሉ የህክምናው ዘርፍ ሰዎች፡፡ አንድ (ነጠላ) ብልት ይዞ መፈጠርን ደግሞ ‹‹Monophallia›› በማለት ይጠሩታል፡፡ ‹‹Mono›› ማለት ‹‹ነጠላ›› ማለት ተፈልጎ ነው፡፡ ስለዚህ ብዙ ወንዶች ሞኖፋሊክ ናቸው ማለት ነው፡፡ አስሩ የአገራችን ወንዶች ደግሞ ባለጥንድ ብልት መሆናቸው ነው፤  ‹‹ዳይፋሊክ››፡፡ ሁለት ጥንድ ብልቶችን ይዞ መፈጠር ራሱን የቻለ ሌላ ችግር እንዳለም ጠቋሚ ነው ይላሉ ምሁራን፡፡ ምክንያቱም ይህ መሰል የተዛነፈ አፈጣጠር መኖሩ ሌሎች የተዛነፉ አፈጣጠሮችም ስለመኖራቸው በተዘዋዋሪ ይጠቁማል ይላሉ፡፡ ብልቱ ብቻ ላይሆን ይችላል ጥንድ የሚሆነው፤ ሌሎች ከውስጥ አካሎቹም አንዱ ጥንድ ሊሆን ይችላል፡፡ እንዲሁም የሀብለ ሰረሰሩ ሽፋንም ክፍተት ኖሮት (Spina bifida) ለበሽታ ተጋላጭ ሆኖ ሊወሰድ ይችላል፡፡

ዳይፋሊያ በመባል የሚጠራው አፈጣጠር መነሻው በፅንስ ወቅት በሚከሰት የዝርያ ዝንፈት ሊሆን ይችላል፡፡ በፅንስ እድገት ውስጥ ፅንሱ የተለያዩ ክፍሎችን ሲሰራ ወደ ብልትነት የሚቀየረው የህዋስ ክፍል በውስጣዊ ወይም አካባቢያዊ ተፅዕኖ የተነሳ ወደ አንድ ብልት ማደግ ሲገባው ሁለት ብልቶችን ወደ መስራት አቅጣጫውን ይቀይራል፡፡ ይህ በተለይም በፅንሱ የአራተኛ ሳምንት ዕድሜ ላይ (በእርግዝና የመጀመሪያ ወር መጨረሻ) ላይ የሚፈጠር ክስተት ነው፡፡

በልዩ መጠሪያውም ‹‹Homeo Gene Expression›› በመባል ይጠራል ብሏል የዜናው ምንጭ፡፡ ቢሆንም ግን እጅግ ከስንት አንዴ የሚፈጠር ስህተታዊ አፈጣጠር እንጂ የተለመደም አይደለም፡፡

የብልቱ አሰራር በተመለከተም እንየግለሰቡ ይለያያል፡፡ አንዳንዶቹ ላይ ሙሉ የብልት መጠንና ሽንት ማፍሰሻ ቀዳዳ ላይኖረው ይችላል (ሁለተኛው ብልት)፡፡ አንዳንዶች ላይ ደግሞ ሁለቱም ብልቶች እንደየትኛውም ወንድ ሙሉ ባህሪ ያላቸው ይሆናሉ፡፡ ሁለቱም ከሽንት ፊኛ ሽንት የሚቀበል ቱቦና ቀዳዳ ይኖራቸዋል፡፡

በመሆኑም በሁለቱም ብልቶቹ እንደማንኛውም ወንድ ቆመው ሊሸኑ ይችላሉ፡፡ ሆኖም በሽንት ፊኛው ውስጥ ያለውን የሽንት መጠን በሁለቱም በኩል ስለሚያወርደው በአብዛኛው ከሌሎች ወንዶች በፊት ቀድሞ ሽንቱን ይጨርሳል ይላል ሪፖርቱ፡፡ ብልቶቹ ሲፈጠሩ አንዳንዴ ልክ እንደ ባላ በመሆን ከላይና ከታች ሆነው ወይም ደግሞ ጎን ለጎን (ግራና ቀኝ) ሆነው ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡ አንዳንዴ በቁመት ሊበላለጡ ወይም እኩል ሊሆኑም ይችላሉ፡፡ አንዳንዴ አንዱ የሚሸና ሌላው ድፍን ሊሆን ይችላል፡፡

ወሲብን በተመለከተ ሁለቱም ብልቶች በመነቃቃት ውስጥ ሙሉ መነሳሳትና መወጠር ይኖራቸዋል፡፡ እንደማንኛውም አይነት ነጠላ ብልት፡፡ ሲነቃቁም ሆነ ወደ ነበሩበት ሲመለሱ እንዲሁም ከግንኙነት በኋላ ከፍተኛ እርካታ (Orgasm) ላይ ሲደርሱ በእኩል ደረጃ ነው ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች፡፡ ይህ እንዴት ሊሆን እንደሚችልም ባለሙያዎቹ ሲናገሩ የወንድ ልጅ ብልትን ወሲባዊ ስሜት በዋናነት የሚቆጣጠረው አንጎላችን ውስጥ ያለው የብልት ስሜት ማዕከል በመሆኑ ነው፡፡ በመሆኑም ከዋናው የብልት ስሜት ማዘዣ ጣቢያ (Brain Command Psot) የሚመጣው የፍላጎት መነሳሳትና መርካት ለሁለቱም ተመሳሳይ ስለሆነ ነው፡፡ ሆኖም አንዳንዴ ሁለቱም ብልቶች በተመሳሳይ መልኩ የዘር ፈሳሽ ሊያፈሱ (Ejaculation) አንዳንዴ ደግሞ ሌላው ድፍን በመሆኑ ላያፈስ ይችላል፡፡

በቅርቡ አንድ ባለሁለት ብልቶች ባለቤት የሆነው ታዲያ ራሱን ከተደበቀበት አውጥቶ ስለራሱ መናገር የቻለ ወንድ ብቅ ብሏል፡፡ ይህ ልጅ አሜሪካዊ ሲሆን በ20ዎቹ ዕድሜ ውስጥም ይገኛል፡፡ ልዩ መጠሪያው ለጊዜው ‹‹DDD›› ይሁን ያለ ሲሆን (ራሱን ለመደበቅ ሲል) በኒውዮርክ አካባቢም ይገኛል፡፡ ስለራሱ ያለውን የብልቶች አይነትም በስዕል አስደግፎ በዌብሳይቱ ላይ ለቋል፡፡

በነገራችን ላይ አንባቢያን ‹‹Diphallia…›› በማለት በኢንተርኔት ውስጥ ምስሉን ማየት ትችላላችሁ፡፡ ይህ ሰው ስለራሱ በሰጠው ምላሽም በዛ ካሉ ተቃራኒ ፆታዎች ጋር ግንኙነት ማድረግ እንቻለ ነው፡፡ በቅርም ‹‹Double Header›› My life with two penises በሚል ስያሜ አንድ መጽሐፍ ለገበያ ያወጣ ሲሆን በዓለም ገበያ ላይም መሪነቱን በመያዝ እያነጋገረ የሚገኝም መፅሐፉ ለመሆን በቅቷል፡፡ በመፅሐፉም ውስጥ ከተቃራኒ ፆታ ጋር ያሳለፏቸውን የወሲብ ታሪኮች (በሌላ ቃለ መጠይቅ መናገር ያልፈለገውን ሁሉ) አካቶበታል፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ እንደ ሚናገረውም ይህ መሰሉ አፈጣጠሩ በህይወቱ ላይ በተለይ በወሲብ አፈፃፀም ህይወቱ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዳደረገበት ነው፤ የሚናገረው፡፡

‹‹BBC News Beat›› በተባለ የዜና አውታር ላይ ስለአስተዳደጉ ተጠይቆ ነበር፡፡ እንደተናገረው ከሆነ ቤተሰቦቹ ለወንድ ጓደኞቹ ብልቶቹን ማሳየት እንደሌለበት ሲመሰክሩት እንደነበር የተናገረ ሲሆን እሱ ይህን ምክር በወቅቱ የተረዳውም ምላብት እሱ ባለ ሁለት ብልቶች ባለቤት በመሆኑና ሌሎች ደግሞ ያላቸው አንድ ብቻ በመሆኑ በእሱ የተነሳ ጓደኞቹ በቅናት እንዳይሳቀቁ ይሆናል በሚል ነበር (ምስጢሩን መጠበቅ የፈለገው)፡፡ ይሁን እንጂ በአስራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ሲደርስ ነበር እሱ ራሱ ከሌሎቹ የተለየ አፈጣጠር እንደያዘ የተረዳውና ሀፍረት መሰማት የጀመረው፡፡ ትምህርቱን በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ እየተከታተለ ሳለ ታዲያ አንደኛውን ብልቱን ለማስቆረጥና እንደ ሌሎቹ ወንዶች ተመሳሳይ የመሆን ግፊት መጥቶበት ነበር (ከራሱ)፡፡ ይሁን እንጂ በተደጋጋ ካሰበበት በኋላ ቀዶ ጥገናው ሌላ ጣጣ ሊያመጣብኝ ይችላል በሚል ለመተው እንደወሰነና ከአሁን ቀደምም አብሮት ያደገና እስካሁንም አንዳችም ችግር ያልፈጠረበት በመሆኑ ሊጨነቅበት እንደማይገባ መወሰኑን ይናገራል፡፡ አይገርምም!!

The post Health: ከሁለት ብልቶች ጋር የተፈጠረው ሰው አነጋጋሪ እየሆነ ነው!! appeared first on Zehabesha Amharic.


Health: ‹‹የልጄን እናት ድንግል ሆና ባገባትም ከኤች.አይ.ቪ አልፀዳችም!! እኔ ግን አሁንም ኔጌቲቭ ነኝ››

$
0
0

እኔ የ26 ዓመት ወጣት ስሆን፣ ከዩኒቨርሲቲ አብራኝ የተማረች ጓደኛዬን ከተመረቅን በኋላ ተጋብተን ስንኖር ልጅ ፀነሰች፡፡ ሆኖም የእርግዝና ክትትል ታደርግ የነበረ በመሆኑ፤ ከእነዚህም ምርመራዎች ውስጥ አንዱ የኤች.አይ.ቪ ምርመራ ነበር፡፡ በዚህ መካከል ፖዘቲቭ መሆኗ ተረጋገጠና ቫይረሱ ወደ ልጁ እንዳይተላለፍ አስፈላጊው ጥንቃቄና ህክምና እንደሚያስፈልግ ተነገረን፡፡ እኔም መመርመር አለብህ ተባልኩ፡፡ ስፈራ ስቸር ተመረመርኩ፡፡ ሆኖም ውጤቱ ኔጌቲቭ ነበር፡፡ በጣም ተደሰትኩ፡፡ በአንድ በኩልም በጣም ተሰማኝ፡፡ በጣምም የገረመኝ ጉዳይ ግን ምን መሰላችሁ? ባለቤቴን ሳገባት ድንግል ሆና ሳለ እንዴት ኤች.አይ.ቪ ፖዘቲቭ ልትሆን እንደቻለች ነበር? ምክንያቱም ከእኔ እንዳልተያዘች እኔ ምስክር ነኝና፡፡ በዚህ የተነሳም በመካከላችን ችግር ተፈጥሯል፡፡ እባካችሁ ዘሐበሻዎች መፍትሄ አታጡምና ምክር ለግሱኝ፡፡
መዝገቡ ነኝ

HIV ETHIOPIA ADVICE

መልስ፡- ውድ ጠያቂያችን መዝገቡ ለጥያቄህ በቅድሚያ ልባዊ ምስጋናን ልናቀርብልህ እንወዳለን፡፡ በተፈጠረው ጉዳይም ስሜትህን ተጋርተናል፡፡ ሆኖም ጥያቄዎችህ በሁለት ግራ በሚያገቡ ጉዳዮ የተመላ ይመስላል፡፡ የመጀመሪያ ጉዳይ እንዴት ድንግል ሆና ኤች.አይ.ቪ ፖዝቲ ሆነች? የሚል ሲሆን ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ እንዴት እሷ ፖዘቲቭ ሆና እኔ ኔጌቲቭ ልሆን ቻልኩ? የሚልም ነው፡፡ በእውነቱ ሁለቱም ከበድ ባለ መልኩ ግራ የሚያጋቡ ይመስላሉ፡፡ ወደ ጥያቄህ ስንመለስ እንዳልከው ልጃገረድ ሆኖመገኘት ለወንዱ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ይመስላል፡፡ ባህሉም መሰረት የሚያደርገው ይህንኑ ስለሆነ፡፡

በእርግጥ ሳይንስም ልጃገረድ ሆኖ መቆየትን ጥሩና ገንቢ ባህሪ አድርጎም ያየዋል፡፡ በተለይ በዚህ ረገድ ከጋብቻ በፊት የሚደረግን ወሲብ አጥብቆ ይቃወማል፡፡ (አስገዳጅ ካልሆነ በቀር)፡፡ በተቻለ መጠንም ተጋቢዎች ከጋብቻ በፊት የኤች.አይ.ቪ ምርመራ አድርገው እንዲጋቡም ይመክራል፡፡ ልጃገረድነት ከኤች.አይ.ቪ ብቻ ሳይሆን ራሳቸውን ካልተፈለገ እርግዝና (ይህንንም ተከትሎ ከሚመጣው ውርጃ) እና ከሌሎች የአባላዘር በሽታዎች ራሳቸውን ለመጠበቅ ‹‹ንፁህ›› ሆኖ መቆየት ይጠቅማቸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅትም በሀገራችን የልጃገረዶች ማህበር ተቋቁሟል፡፡ አስተማሪነቱ ደግሞ የአስፈሪ ሁኔታ ስርጭቱን እያፋጠነ ለመጣው ኤች.አይ.ቪ እንደ አንድ የባህሪ ለውጥ የሚታይ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ልጃገረድነት የሴቷ እንጂ የወንዱ መስፈርት ሊሆን ባለመቻሉ እምብዛም አመርቂ ለውጥ ማምጣት ግን አልቻለም፡፡ በተለይም በአሁኑ ወቅት ሴቶችና ወንዶ እኩል ናቸው በሚባልበት ዘመን የሴቶችን ልጃገረድነት ብቻ እንደታማኝነት መለኪያ መቁጠርና በጋብቻም ወቅት ይህን መስፈርት መጠቀም አይመከርም፡፡ ወንዱስ ታማኝነቱ በምን ይረጋገጥ? የሚል ያስነሳልና፡፡

የሴት ልጅ ክብረ ንፅህና በግንኙነት ብቻ ሳይሆን በራሱ ጊዜም ሊጠፋ የሚችልበት አጋጣሚ አለ፡፡ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አስገድዶ መድፈር በዓለም ደረጃ እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ተገዳ በመደፈሯም ድንግልናዋን ልታጣ ትችላለች፡፡ በተለይም መደፈር በህጻንነት ወቅት የተደረገ ከሆነ ሴቷ ስለክብረንፅህናዋ መኖርና አለመኖር ሳታወቅ ልታድግ ትችላለች፡፡ እንዲህ አይነት አጋጣሚዎች ባለበት ማህበረሰብ ውስጥ ልጃገረድነትን ከታማኝነት ማረጋገጫ ጋር ማያያዙ ተገቢ አይደለም፡፡ በዚያ ላይ ልጃገረድ ስለሆነች በኤች.አይ.ቪ አትያዝም ብሎ መደምደም አይቻልም፡፡ ቫይረሱ ከግንኙነት ውጭ በሌሎች መንገዶች ሊተላለፍ ይችላልና፡፡ ድንግልና ስለሌላትም በቫይረሱ ተይዛለች ማለት አይቻልም፡፡ እስካልተመረመረች ድረስ፡፡

በዚያ ላይ የሴቷን ማንነት በዚህ መልኩ የሚፈትሸው ወንዱ ራሱ ማን ሆነና ነው፡፡ የእሱስ ታማኝነት በምን ይረጋገጥ? ይህ የድንግልና ፍተሻ ሂደት እንደዛምቢያ፣ ማላዊ፣ ስዊዘርላንድ፣ ዚምባብዌ እና መሰል የአፍሪካ ሃገርም የሚከናወን ባህል ነው፡፡ በተለይም በእነዚህ ሀገራት አንዲት ሴት ከጋብቻዋ በፊት ወደ ልጃገረድ ፈታሾች ትላካለች፡፡ እነዚህ ፈታሾች ሴቶች ሲሆኑ ፍተሻውንም የሚያካሂዱት በጣታቸው ነው፡፡ አንድን ጣት ወደ ብልታቸው ቀዳዳ በመክተት የጥበቱን ሁኔታ ይገመግማሉ፡፡ እናም በእነዚህ ሀገራት ወንዶ ከተለያዩ ሴቶች ጋር ቢቀብጡ ባህሉ የሚፈቅድላቸው ሲሆን ሴቶቹ ግን በጋብቻ ወቅት ሲፈተሹ ድንግል ሆነው ካልተገኙ ወንድ የሰርግ ጥሎሽ ሳይጥል ሊያገባት ወይም ሊያባርራት ይችላል፡፡

ወላጆቿም በእሷ የተነሳ የሚታፈርባቸው ይሆናል፡፡ በእዚህም የተነሳ በእነዚህ ሀገራት ሴቷ ከጋብቻው በፊት ወሲብ መፈፀም ከፈለገች በፊንጢጣ በኩል የሚደረግን ግንኙነት እንድትፈፅም ትገደዳለች፡፡ ይህ ደግሞ ከተለመደው አይነት ወሲብ በበለጠ ኤች.አይ.ቪን ከወንዱ ወደ ሴቷ የሚያስተላልፍ ነው፡፡

በተለይ በብዙዎች የአፍሪካ ሀገራት እየታመነ የመጣው ጉዳይ ከልጃገረዶች ጋር ወሲብ መፈፀም ከኤች.አይ.ቪ ይፈወሳል የሚል ኢ-ሳይንሳዊ አመለካከት ሲሆን በዚህም የተነሳ ልጃገረድነታቸው ተፈትሾ የተረጋገጠላቸው ሴቶች ለእነዚህ ወንዶች የሚዳሩበት አጋጣሚም እንዳለ ይታያል፡፡

በአጠቃላይ የድንግልና መኖርም ሆነ አለመኖር የአንድን ሴት ልጅ በኤች.አይ.ቪ መያዝና ያለመያዝ የሚያረጋግጥ አይደለም፡፡ ለባሏም የሚኖራት ታማኝነት እንዲሁ በልጃገረድነት መኖርና አለመኖር የሚወሰን አይደለም፡፡ በእርግጥ በድንግልና መቆየት በኤች.አይ.ቪ ላለመያዝ አንዱና ጥሩው አማራጭ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ግን እውን ሊሆን የሚችለው ይህቺ ልጅ ቫይረሱ ከሌለባት ወንድ ጋር ከተጋባች ብቻ ይሆናል፡፡

ይህ ደግሞ የሚረጋገጠው በምርመራ ብቻ ነውና ፍቅረኞች በድንግልና ሳይተማመኑ ተመርምረው ቢጋቡ ነው የሚመከረው፡፡ ታማኝነትም ቢሆን እንዲህ ነው፡፡ መተማመን ለራስም ሆነ ለጋራ ፍቅር ሲባል ታምኖበት የሚደረግ እንጂ በድንግልና ስለፀኑ ብቻ የሚመጣ ባህሪ አይደለም፡፡ እንደዛማ ከሆነ ሁሉም ወንድ ክብረ ንፅህና ስለሌለው ታማኝ አይደለም ሊባል ነው፡፡

በዚያ ላይ አንዲት ሴት ድንግልና የላትም ማለት በወሲብ የተነሳ አጥታዋለች ማለት አይደለም፡፡ በራሱ ጊዜም ሆነ በልጅነቷ በመደፈሯ ሳታውቅ ሊጠፋ ይችላልና፡፡ በተረፈ አንተም ሆንክ ሌሎች የድንግልና አፍቃሪያን ከዚህ አመለካከታችሁ እንድትፀዱ እምነቴ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚም ከጋብቻ በፊት ፀንቶ በመቆየትና በጋብቻም ወቅት ተመርምሮ መጋባት የሴቶችም የወንዶችም ባህል ይሁን እላለሁ፡፡ ይህም በመሆኑ እንግዲህ በአንድም በሌላ መልኩ ባለቤትህ በቫይረሱ ተያዘች፡፡ አንተ ደግሞ በአንጻሩ ኔጌቲቭ ሆንክ፡፡ ይህ መሰሉ ከባልና ሚስት ውስጥ አንዳቸው ኔጌቲቭ ሌላኛቸው ደግሞ ፖዘቲቭ የሚሆኑበት ክስተት ‹‹Discordance›› በመባል የሚጠራ ሲሆን አልፎ አልፎ የሚከሰት የተለመደ ጉዳይ ነው፡፡ ለእሷ መያዝ ምናልባት ከግንኙነት ውጭ ያሉ ምክንያቶች እንደ አንድ ምክንያትም ሊቆጠሩ ይችላሉ፡፡ ምናልባትም ድንግልና ሳይገረሰስ በተደረገም ግንኙነት ሊሆን ይችላል፡፡

ይህ መሰል በጥንዶች ላይ የሚስተዋልና አንዱ ኔጌቲቭ ሌላው ፖዘቲቭ የሚሆንበት ምክንያት በውል የሚታወቅ ምክንያት የሌለው ቢሆንም ወደ ፊት የኤች.አይ.ቪ መከላከያና ክትባት ለማግኘት ለሚደረገው ጥረት ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሎ ግን ይታመናል፡፡

ይህም ማለት ምናልባት ኤች.አይ.ቪ የተለያዩ ዝርያዎች ያሉት በመሆኑ የተያዝከው በአንዱ አይነት ሊሆን ይችላል እንጂ በሌላው አይነት ዝርያ አትያዝም ማለት ስላልሆነ ጥንቃቄ ማድረግን እንዳትዘነጋ እንላለን፡፡ ከዚህ በተረፈ የትዳር አጋርህ ለራስህና ለልጅህ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እያደረጋችሁ ስላለፈው ሳይሆን ስለወደፊቱ ትኩረት በማድረግ በፍቅር ትኖሩ ዘንድ እመኛለሁ፡፡ መልካም ፍቅር!

The post Health: ‹‹የልጄን እናት ድንግል ሆና ባገባትም ከኤች.አይ.ቪ አልፀዳችም!! እኔ ግን አሁንም ኔጌቲቭ ነኝ›› appeared first on Zehabesha Amharic.

ማረሚያ ቤት እነ አብርሃ ደስታና ሃብታሙ አያሌውን ፍርድ ቤት ባለማቅረቡ ዳኞች ውሳኔ ሳይሰጡ ቀሩ

$
0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ የተበየነላቸው የአንድነት፣ የሰማያዊ እና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች ላይ አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆ ጉዳያቸው በጠቅላይ ፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት አምስት ተከሳሾች ለጥቅምት 22/2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡
Habtamu abrhayeshiwas daniel
ዛሬ ጥቅምት 17/2008 ዓ.ም የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ቢጠበቅም ማረሚያ ቤት ሳያቀርባቸው በሌሉበት ቀጠሮ የተሰጣቸው የፓርቲዎች አመራሮቹ ሀብታሙ አያሌው፣ የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታ፣ ዳንኤል ሺበሽ እና አብሯቸው ይግባኝ የተጠየቀበት አብርሃም ሰለሞን ናቸው፡፡

የቂሊንጦ እና የቃሊቲ ማረሚያ ቤቶች እነ ሀብታሙን ፍርድ ቤት ያላቀረቡበትን ምክንያት ፍርድ ቤቱ ሲጠይቅ፣ ‹‹ቃሊቲ በፕላዝማ ይታያል ስለተባለ አላመጣናቸውም፤ ከአይ.ሲ.ቲ ጋር ተነጋግረው ነው ያስቀሯቸው›› የሚል መልስ ተሰጥቷል፡፡ ማረሚያ ቤቱ እነ ሀብታሙን ብቻ ሳይሆን በሌላ መዝገብ በተለያዩ ወንጀሎች ስር የተጠቀሱ ተከሳሾችንም አለማቅረቡ ታውቋል፡፡

ፍርድ ቤቱ በበኩሉ የቃሊቲ ማረሚያ ቤትን መልስ ካደመጠ በኋላ፣ ‹‹ይሄ ቪዲዮ ኮንፈረንስ የሚባል ነገር የሚሆን አይደለም፤ አቅርቧቸው ብለን አዝዘን ነበር፤ እኛ ነን የምናዝዛችሁ ወይስ ማን ነው? አሁንም ቀጣይ ቀጠሮ ላይ አቅርቧቸው›› ሲል በእነ ሀብታሙ መዝገብም በሌሎች መዝገቦችም ላይ ዛሬ ላልቀረቡ ተከሳሾች ተመሳሳይ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ በመሆኑም እነ ሀብታሙ አያሌው ሰኞ ጥቅምት 22/2008 ዓ.ም የተጠየቀባቸው ይግባኝ ያስቀርባል ወይስ አያስቀርብም የሚለውን ብይን ቀርበው ለመስማት ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡

The post ማረሚያ ቤት እነ አብርሃ ደስታና ሃብታሙ አያሌውን ፍርድ ቤት ባለማቅረቡ ዳኞች ውሳኔ ሳይሰጡ ቀሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ከውጭ ሚ/ር ደኤታነት ተነሱ

$
0
0

Birhane Gebrekirstos

(ዘ-ሐበሻ) የሟቹ አምባገን የኢትዮጵያ መሪ የቅርብ ሰው የነበረውና በውጭ ሃገር በተለይም በአሜሪካ እና በብራሰልስ በቆየባቸው ጊዜያቶች የአምባሳደርነት ስም ይዞ የገዢውን ፓርቲ አምባገነን መሪዎችን ገንዘብ በማሸሽ ሥራ ላይ ተሰማርቶ ቆይቷል እየተባለ በሰፊው የሚተቸው ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ደኤታነት ስልጣኑ ድንገት ተነሳ::

 

አንዳንድ የቅርብ ምንጮች ብርሃነ ስልጣኑን የለቀቀቀው በፈቃዱ ነው ይበሉ እንጂ ጉዳዩ በአዲስ አበባውና በመቀሌው የሕወሓት ቡድን ክፍፍል ጋር የተያያዘ ነው እየተባለ ነው::

በ2013 ዓ.ም ከደደቢት በረሃ ጀምሮ ለዓመታት ሕወሓት ውስጥ በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ያገለገሉት አምባሳደር ስዩም መስፍን፣ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ፣ አቶ አርከበ ዕቁባይና አቶ ዘርዓይ አስገዶም ባቀረቡት ጥያቄና ፓርቲው እየተገበረ ባለው የመተካካት ሂደት በሚል ሽፋን መሰረት ሥልጣናቸውን እንዲለቁ የተደረጉ ሲሆን አቶ መለስ ከሞቱ በኋላ እነዚሁ ባለስልጣናት ወደ ሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ለመግባት ጥረት አድርገው ነበር:: በተለይም ከአቶ አርከበ እቁባይ ጋር በጋብቻ ዝምድና እንዳላቸው የሚነገርላቸው አቶ ብርሃነ ገብረክርስቶስ አቶ አርከበን የሕወሓትና የኢትዮጵያ ጠ/ሚ/ር ለማድረግ ከሚሰራው ቡድን ጀርባ ሆነው ብዙ ሲንቀሳቀሱ ቆይተው በመቀሌው ቡድን በባለፈው የሕወሓት ጉባኤ ላይ መሸነፋቸው ይታወሳል::

አቶ ብርሃነ ከዚህ ቀደም በሕጋዊ ባለቤቱ ላይ ሲወሰልት በመያዙ የቀድሞ ሚስቱ ከዛሬ 12 ና 13 ዓመታት ገደማ በፊት ብርሃነን በዝሙት ጉዳይ ክስ መስርታበት በመረታቱ በርሱ ስም በኒውዮርክ ከተቀመጠው የሕወሃት ባለስልጣናት ገንዘብ ውስጥ ካሳ እንዲሆናት 5 ሚሊዮን ብር እንደተፈረደላት በተለያዩ ሚዲያዎች መዘገቡ አይዘነጋም::

በአቶ ብርሃነ ገብረክርስቶስ ቦታ ሌላ ሚ/ር ደኤታ መሾሙም ተሰምቷል:: ባለስልጣኑ ወደ ሌላ ቦታ ይዘዋወሩ/ አይዘዋወሩ ያገኘነው መረጃ የለም::

The post አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ከውጭ ሚ/ር ደኤታነት ተነሱ appeared first on Zehabesha Amharic.

የባራክ ኦባማና የወይዘሮ አዜብ መስፍን ታሪካዊ ግንኙነት

$
0
0

Azeb  Mesfin, wife of Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi

ይሄይስ አእምሮ

 

ጊዜው ትንሽ ራቅ ስለሚል ወሩንም ሆነ ዓመቱን አሁን በትክክል አላስታውስም፡፡ ያንን ጊዜ ዛሬ ጧት ያስታወሰኝ የዚያን ጊዜው አንዱ ልጄ የተናገረውን ነገር በጣም በተራራቀ ነገር ግን በጣም በሚመሳሰል አጋጣሚ ታናሽ ወንድሙ በሚያስደንቅና በሚያስገርም ሁኔታ በዚህች ዕለት ስለደገመው ነው፡፡ ታሪክ ለምን እንደማይሞት ዛሬ በሚገባ ተማርኩ – ከገዛ ልጄ፤ ታሪክ ራሱን እንደሚደግምም ጭምር፡፡ ለካንስ የሊቢያ እውነተኛ ባንዲራ ከ42 ዓመታት በኋላ የተነሣችው ለዚህ ኖሯል? እንግዲያውስ የኛም ብርቅዬና እየተገለባበጠች ለብዙ ሀገሮች ባንዲራነት የዋለች ሰንደቅ ዓላማችን እንደሞተች አትቀርም ማለት ነው፡፡

ሶሎሞን ተካልኝ ጎራ በቀየረና ወደ ወያኔ ገባ በተባለ ወቅት ዜናው በትኩስነት እየተስተጋባ ሳለ ያኔ ዕድሜው በአሥራዎቹ መጀመሪያ አካባቢ የነበረው ልጄ “ቴዲ አፍሮም እንዳይደገም” በማለት በፍሬ ሃሳቡ ብቻ ሣይሆን በፖለቲካ ግንዛቤው መዳጎስ በጣም አስገርሞኝ ነበር፡፡ አያችሁ – ታሪክ የሚጽፈው ቢጠፋ እንኳን አይሞትም – ከትውልድ ወደ ትውልድ በቃል ሣይቀር ይተላለፋል፡፡ አባትና እናት እናት እንዲሁም ሌሎች የቤተሰብ አባላት ሲገናኙ የሆድ የሆዳቸውን የሚጫወቱት በአብዛኛው ታሪክ ቀመስ ነው፡፡ ስሆነም ትናንሾቹ የቤተሰብ አባላት ከብበው እኛን ሳይታወቀን የሚኮመኩሙት የኛን ጨዋታ ነው – ያልሰሙና ያልተከታተሉ እየመሰሉ ጭምር፡፡ በዚያም ምክንያት ያለ ውድ በግዳቸው እኛ የምንጠላውን ይጠላሉ፤ እኛ የምንወደውን ይወዳሉ፡፡ በልጆች አስተዳደግ ላይ የቤተሰብ ተፅዕኖ ቀላል አይደለም፡፡ የዚያኔው ሕጻን ልጄ የዛሬው … ጎረምሣ ከቤተሰቡ ሲቀስም ያደገውን ወያኔን የመጥላትና ተቃዋሚን ያለመጥላት ጠባይ የገለጠው “ቴዲ አፍሮም እንዳይደገም” በሚል ነበር – አሳስቦት፡፡ ከንግግሩ ጀርባ የሶሎሞንን ወያኔነት እንዳልወደደለት በተለይ እኔ አባቱ አሳምሮ ይገባኛል፡፡ በወያኔው ሸፍጠኝነት በተጨናገፈው የ1997ዓ.ም ብሔራዊ የቴሌቪዥን የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት አንድ ዓመት አካባቢ ዕድሜ የነበረው አንዱ ሌላው ልጄ ደግሞ የቅንጅት ተራ ሲደርስ ፊቱ ፋሲካ እየመሰለና ሁለት ጣቶቹን ለማሳየት እየፈለገ ግና የቀለበት ጣቱ እያስቸገረችው ጭናችን ላይ ፊጥ ብሎ እንዴት በደስታ ይፍነከነክ እንደነበር ቤተሰቤ በሙሉ አሁን ድረስ ያስታውሰዋል፡፡ መንገድ ላይ ባለመውጣቱ ግን ጣቱ ሳይቆረጥና እንደታዳጊ ወጣት ነቢዩ ደረቱና ግንባሩ በአግዓዚ ቅልብ የወያኔ ጦር ሳይበሳሱ እስካሁን በሕይወት አለ፡፡ አሁን የማይታወሰኝ  የመግቢያ ሙዚቃ ገና ከመጀመሩ ምልክቱን እያሳዬ እንዲያ ይቅበጠበጥና ይደሰት የነበረው ምኑን ዐውቆትና ምንስ ገብቶት እንደነበር  ሲያስቡት በርግጥም ይገርማል፡፡ ምናልባት በደም ተላልፎበት? አዎ፣ ቤተሰብ እስካልጠፋ ሀገርም አትጠፋም!! ሃሌ ሉያ! ኢትዮጵያም ትነሣለች፡፡ አልሃምዱሊላህ – የሃይማኖትና የዘር ልዩነት የማይደረግባት ኢትዮጵያ ከወያኔ ከርሠ መቃብር ላይ ታብባለች – ብዙ ተምረናልና!

በነገራችን ላይ በየብሔር ብሔረሰቡ ቤተሰቦች ውስጥ በምናብ እየገባን ብንቃኝ አንዱ ላንዱ ያለውን ጥላቻና ውዴታ ልጆች ተሰባስበው በሚጫወቱበት ወቅት በሚወራወሯቸው የቀልድና የምር ቃላት በደንብ ልንረዳ እንችላለን፡፡ በአንፃራዊ ሁኔታ ይህ ዓይነቱ ክስተት የሁሉ እናትና ማረፊያ በሆነችው በእምዬ አዲስ አበባ ቀለል የሚል ቢመስልም ለወያኔው የዘር ከፋፋይ አገዛዝ ምሥጋን ይንሳውና በሌሎች አካባቢዎችና አነስተኛ ከተሞች ግን የጎላ እንደሚሆን መገመት አይከብድም፡፡

አንድ ወቅት እዚሁ አዲስ አበባ የሆነውን አሣዛኝ ነገር ልንገራችሁ፡፡ አንድ ልጅ አባቱ ይታሰርበታል፡፡ የሁለት ተኩል ወይ ግፋ ቢል የሦስት ዓመት ልጅ ቢሆን ነው ያኔ፡፡ ከቤተሰብ ጋር አባቱን ሊጠይቅ አሁን የአፍሪካ ኅብረት ወደተገነባበት የዱሮው ከርቸሌ ይሄዳል፡፡ አባቱ እስኪመጣ ታዲያ ሕጻኑ ከአንድ የእሥር ቤቱ ጠባቂ የፌዴራል ፖሊስ ጋር ጨዋታ ይይዛል – እነሱ በወያኔያዊ ተፈጥሯቸው ዐውሬ ቢሆኑም ደፍሮ የተጠጋቸውን ሕጻን መቼም ጨክነው ማባረር መጥፎ ግምት ያሰጣቸዋልና ያ ፌዴራል ፊት አልነሳውም፡፡ የሕጻን ነገር ሆነና ነገሩ ወታደሩን “እሹን ሽጠኝ” ይለዋል – ያነገበውን ክላሽንኮቭ፡፡ “ዋይ፣ ምን ይገበረልካ ማሙሼ ?”ብሎ ቢጠይቀው ሚስቶው ቋንቋ በደንብ የገባው የሚመስለው ሕጻን “ኢሃዲግን ልገልበት!” ይለዋል፡፡ አይ ሕጻንነት! ይሉኝታ የለ፤ ምሥጢር የለ፤ ሀፍረትና ፍርሀት የለ – ግልጽነት ብቻ፡፡ ወታደሩ በምንተፍረታዊ ሣቅ ቢሸፍነውም መደንገጡ ግን ያስታውቅ ነበር፡፡ እሥረኛ ሊጠይቅ የመጣው የሕጻኑ ቤተሰብም ክፉኛ ደነገጠ – በርግጥም ለጠርጣራና ጥላውን እንኳን ለማያምን የከሃዲዎችና የወሮበሎች መንግሥት አንድን ቤተሰብ በሽብርተኝነት ወንጀል ለመክሰስ ከዚህ በላይ ማስረጃ የሚያስፈልገው አይመስለኝም፤ ደግነቱ ጊዜው ረዘም ስለሚል እንደምንም “የሕጻን ነገር” ተብሎ ታለፈ እንጂ “በኢቴጲያ ሁዝቮች ፈªድ ለፀደቀ ህገ መንግሥቱን በኃይሊ ለመናድ” ያ ሕጻን ያደረገው ሙከራ ቀላል አልነበረም፡፡ አለበለዚያ “ይህ ልጅ ከቤቱ እንደዚህ የመሰለ ታሪክ ባይሰማ ኖሮ እንዲህ ያለ የከረረና የመረረ ጥላቻ በዴሞክራሲያዊ መንግሥታችን ላይ ሊኖረው አይችልም ነበር” በሚል ቤተሰቡ ለእሥራትና ከዚያም ለባሰ የከፋ ችግር መዳረጋቸው አይቀርም ነበር – ወያኔን እያወቅነው! “አስበሃል” በሚል የትም የሌለ የወንጀል ዓይነት ይቅርና “ልታስብ ማሰብህን የደረስንብህ መሆናችንን ገልጸን ብናስጠነቅቅህም እምቢ ብለሃልና ፀረ ኢህወደግ ዕላማህን ከማሰብህ በፊት ለማሰብ ማሰብህን ልናስቆምህ ተገደናል” ብሎ በዓለም ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ “ወንጀል” አስሮ የሚያሰቃይና ደብዛ የሚያጠፋ የማፊያ ቡድን ያለን መሆናችንን መቼም አንዘነጋም፡፡ እናም ይህ ሕጻን ለቤተሰቡ ጠንቅ ሊሆን ሲችል ፈጣሪ ታደጋቸው፡፡ ከፍላት የሚያወጣው አምላከ ኢትዮጵያ እኛንም ከነዚህ ጉግማንጉጎች በቶሎ ነፃ ያውጣን፡፡

ልጅ አስተዳደግ በማኅበረሰብ ቀረፃ ላይ ወሳኝ ሚና የሚጫወት መሆኑ የሚነገረው እንግዲህ ለዚህ ነው፡፡ የፍልስጥኤምና የእስራኤል ልጆች ሒሳብ ሲማሩ “በአንድ ጥይት 50 እስራኤላውያንን/ፍልስጥኤማውንን ብትገድል በአሥር ጥይት ስንት እስራኤላውያንን/ፍልስጥኤማውያንን ትገድላለህ?” እየተባሉ እንደሚያድጉና ንጹሓንና አፍቃሪያን ሊሆኑ የሚጠበቅባቸውን ታዳጊ እምቦቀቅላዎች እየመረዙ እንደሚያሳድጉ እንሰማለን፤ ይህ ዓይነቱ ፀያፍና ኢ-ሰብኣዊ ነገር በአንድ ወይ በሁለት ሥፍራዎች የተወሰነ ሣይሆን በብዙ ቦታዎች እንደሚተገበር መገመት አይቸግርም፡፡ ተጠያቂዎቹ እንግዲህ ክፉና ደግን ለይተዋል የተባሉት ግን ወደ ክፋት ዓለም ገብተው በግል ቂም በቀልና ጥላቻ በመታወር መላ ኃይላቸውንና መላ ዕድሜያቸውን ለጠብና ለአምበጓሮ የተሠለፉ ዐዋቂ ተብየዎች መሆናቸውን ልብ ይሏል፡፡ ዐዋቂ ማለት አስተዋይና ብልኅ ማለት ሊሆን ሲገባው በተቃራኒው መሆኑ ከማስገረም አልፎ ያሳዝናል፡፡ ክርስቶስ “ሕጻናት ወደኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው”፣ “ወደ ሕጻንነት ካልተመለሳችሁ መንግሥተ ሰማይን አትወርሱም” ወዘተ. የሚለን ትልቅ ስንሆን የሚቆራኘን ሰይጣናዊ መንፈስ በሕጻንነት ወቅት ይኖረብናል ተብሎ ስለማይጠበቅ ያኔ እውነተኛ የሰው ልጆች መሆናችንን ለማሳየት ይመስለኛል፡፡ እርግጥ ነው – ትርጉሙ እውናዊ ሣይሆን ፍካሬያዊ ነው፡፡ እናም ሁላችንም ሕጻናት እንሁንና የጋራ ኢትዮጵያችንን እንደገና እንገንባት፡፡ ሕጻናት ቂም የላቸውም፤ ሕጻናት ስላለፈ ነገር እያነሱ እንደትልቆች አይጨቃጨቁም፤ አይወራከቡም፡፡ ለሕጻናት ትናንትናና ነገ ብዙም ዋጋ የላቸውም፡፡ ለሕጻናት ትልቅ ዋጋ ያላት ዛሬ ናት፡፡ ሕጻናት እጃቸው የገባችን ማንኛዋንም ዕድል በከንቱ አያባክኑም፡፡ ጠቀማቸውም ጎዳቸውም በጃቸው ያለ ጊዜ ወርቃቸው ነው፡፡

ከተነሣሁበት ጉዳይ በተገናኘ መልኩ ለማኮብኮብ ያህል ስለሕጻናት አስተዳደግ ከፍ ሲል በገደምዳሜ ትንሽ ሃሳብ ከሰጠሁ ዘንዳ የ15 ዓመት ዕድሜ ያለው ሌላኛው ልጄ ሰሞኑን የተናገረውን አስደናቂ ነገር ልጠቁምና ጅምሬን ልቋጭ፡፡

የርሱን የቴሌቪዥን ቻናል በኔው ፍላጎት ደፍጥጬበት አለውድ በግዱ የኔን ጣቢያ አብረን እየተመለከትን ነው፡፡ በዚያ ጣቢያ – ጥቂት ቀናትን ቆይቼ ቀደም ሲል ጀምሬው ወደነበረው መጣጥፍ በመምጣቴ ጣቢያውን በትክክል ማስታወስ አልቻልኩም ግን ኢሣት ይመስለኛል – ስለ አሜሪካውያን ፕሬዝደንታዊ የምርጫ ቅስቀሳ በዜና ቀርቦ ሂደቱ እየተዘገበ ነበር፡፡ በዜናው ላይ “በአሜሪካ ህገ መንግሥት ድንጋጌ መሠረት ፕሬዝደንት ኦባማ ለሦስተኛ ዙር መወዳደር ስለማይችሉ ለተመራጩ አዲስ ፕሬዝደንት ሥልጣናቸውን አስረክበው በቀጣዩ ዓመት የፈረንጆቹ ጥር ወር ላይ ቤተ መንግሥቱን  ለቀው ከነቤተሰባቸው ይወጣሉ፡፡” የሚለውን ወሬ እንደሰማን ይህ ልጄ “እሱም እንደ አዜብ እንዳይሆን” አለና እንደዋዛ ወሬ ጣል አደረገ፡፡ እኔም አትኩሮቴ በአብዛኛው ቲቪው ላይ ስለነበር የልጁን አነጋገር ከቁብ አልጣፍኩትም ነበር፡፡ ቢያንስ ለሞራሉ ስል ዝም ብዬ ላልፈው ደግሞ አልወደድኩም፡፡ ለምን እንደዚያ እንዳለ ታዲያ ፊቴን ወደሱ ሳላዞር እንደዋዛ ጠየቅሁት፡፡ “የመለስ ሚስት አዜብ ለኃይለ ማርያም ቤተ መንግሥቱን አላስረክብም ብላ በግድ አይደል እንዴ የወጣችው?” ሲለኝ ታሪኩ ትዝ አለኝና በራሴ አፈር አልኩ፡፡ ስንትና ስንት የነገር ብልት የማወጣ ሰውዬ “እዚያ ድረስ ሄዶስ አያስበውም” ከሚል በኔ ዘንድ እምብዝም ያልተለመደ አስተሳሰብ የልጄን የፖለቲካ ንቃት መናቄን ስገነዘብ ለራሴውና በውስጤ በገዛ ልጄ ፊት የመቅለል ስሜት ተሰማኝ፡፡ በርግጥም ይህ ልጅ በ13 ዓመት ዕድሜው የተከናወነን ሀገራዊ ጉዳይ በደንብ ያውቅ ነበር ማለት ነው – ይህም ብቻ አይደለም፡፡ በ12 እና በ15 ዓመት ዕድሜው የተከሰቱ ሁለት የተለያዩ ፖለቲካዊ ኹነቶችን በማገናዘብ ከዴሞክራሲያውያን ቅቡልነት ያለው ልማድ ተነስቶ ኢ-ዴሞክራሲያውንን በምፀት ዱላ መምታት ይችላል ማለትም ነው፡፡ ሲገባኝና “ስባንን” ብዙም እንዳይታዘበኝ ብዬ ምክንያት ቢጤ ሰጠሁትና ጥቂት አዋራሁት፤ እርሱ ለቀልድ ያህል ቢናገረውም የአሜሪካ ህግ እንደኢትዮጵያ በአምባገነኖች መዳፍ ሥር የወደቀ ሳይሆን በህገ መንግሥት አስፈጻሚ መንግሥታዊ መዋቅሮች በአግባቡ የተያዘ በመሆኑ ማንም ከህጉ ውልፊት እንደማይል በእግረ መንገድ ነግሬው – እንደሚውቀው እየነገረኝም ጭምር – ወደሌላ ርዕስ ገባን፡፡

ኦ! ረስቼው፡፡ “ዐይን እንዳይገባብኝ” እንጂ ስለዚሁ ልጅ አንድ ሌላ ሰሞነኛ አጋጣሚም አለ፡፡ የወያኔ ሰንደቅ ዓላማ የሚከበርበት ዕለት ተማሪዎች ሁሉ በየት/ቤታቸው እንዲገኙ ታዘው ነበር፡፡ ይህ የኔው ልጅ እንደወትሮው ቁርሱን በጧት በልቶ እንዲሄድ ስቀሰቅሰው “አልሄድም” ይላል፡፡ ያስገረመኝ አለመሄዱ አይደለም፡፡ “ሰንደቅ ዓላማ ያለን ይመስል…” በማለት የሰጠው ከርሱ ያልጠበቅሁት መልስ ነው በጣም ያስገረመኝ፡፡ ወያኔዎች ጮርቃ ሕጻናትን አለርህራሄ የሚጨፈጭፉት ለካንስ “እባብ የወጣበትን ጉድጓድ አይረሳም” ከሚለው ነባር ብሂል በመነሣት “እነሱም ሲያድጉ የወላጆቻውን የኢትዮጵያዊነት ስሜትና ወኔ ይቀሰቅሳሉ፤ ትልልቅ ሲሆኑ የጥንቷን ትምክህተኛ ኢትዮጵያ አፍርሰን በምትኳ በአዲስ መልክ የሠራናትን አዲሲቷን የብሔር/ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ሀገር ኢትዮጵያን ገልብጠው የዱሮውን ሥርዓት ያመጡብናል”  ከሚል ፍራቻ መሆን አለበት፡፡ ሞኞች ናቸው፡፡ የኔ ልጅ እንዲህ ከሆነ – ስሙን ለጊዜው “አልፎአይቼው” ልበለውና –  ብዙ አልፎአይቼዎች በየቤቱ እንዳሉ እረዳለሁና የነገይቷ ኢትዮጵያ መፃዒ ሕይወት ለኔ እጅግ ብሩኅ ነው፡፡ አልደብቃችሁም – በፊት በፊት እፈራ ነበር፡፡ አሁን አሁን ግን ተስፋየ እየለመለመ መጥቷል፡፡ የአንዳርጋቸው ጽጌና መሰል ቆራጥ ኢትዮጵያውያን ደም የውሻ ደም ሆኖ አይቀርም፡፡ አንዲ ለእምዬ ኢትዮጵያ የተሰዋ በበግ ያልተተካ ይሥሃቅ ነው፤ አንዲ አቤል በቀናተኛ ወንደሙ ቃየል መለስ የተገደለ ሰማዕት ነው፤ ግዴለም አልሞተም ቢባልም ስቃዩ ከሞት በላይ ነውና ሰማዕት ነው፡፡

ይገርማችኋል የዛሬ ልጆች በጣም የረቀቁ ናቸው፡፡ ጥቂቶቹም ቢሆኑ ለቴክኖሎጂው ቅርበት ስላላቸው ይመስላል ከኛ ከነባር ገትጋታ ኢትዮጵያውያን በተለዬ በአንዳንድ መልካም ባሕርያት እየታነጹ መምጣታቸው ይሰማኛል፡- ለምሳሌ እንደኛ ዘረኞች አይደሉም፤ ስለዘር ሐረግ ሲነሣ ብዙዎቹ አይገባቸውም፤ ሰውን በሰውነቱ ነው ማየት የሚፈልጉት፡፡ ስግብግብነት ብዙም አላይባቸውም – እየተሻሙና እየተካፈሉ ሲበሉ እታዘባለሁ፤ ሲጋቡ ወያኔ በቀየሰላቸው የዘር መሥፈርት አጥንትና ደም እያነፈነፉ አይደለም፤ … ብቻ አለ አይደል … ብዙ ደስ የሚሉ ነገሮች አሏቸው – ወያኔያዊ ተፅዕኖዎች የሉም ማለቴ ግን አይደለም፡- ይሁንና እነዚህ ከ25 ለሚበልጡ ዓመታት የተዘሩ የወያኔ ተፅዕኖዎች በጊዜ ሂደት ተሸናፊ መሆናቸውን መመስከር አይቸግረኝም፡፡

ከፍ ሲል እንደጠቀስኩት በሕጻናት ተተኪዎቻችን ትልቅ ተስፋ አለን ማለት ነው – ከወያኔ የማያቋርጥ ጥቃት ግን እንታደጋቸው፤ የምንችል ከሆነና ራሳችንን መለወጥ የማይከብደን ከሆን በቤት ውስጥ በጥሩ ጠባይ እንቅረጻቸው፡፡ እንከታተላቸውና ከጥፋት እንታደጋቸው፡፡ ከወያኔ የትውልድ ማምከን ዕኩይ ተግባር የሚያመልጡ ልጆችን በወቅቱ እንድረስላቸውና ጭራሽ ጠፍተን እንዳንቀር ከዘንዶው አፍ እናድናቸው፡፡ በትምህርቱ ረገድም ቢሆን በቤት ውስጥ እናግዛቸው፡፡ ትምህርቱን ከቤት የማለፊያ ካርዱን ከትምህርት ቤት፡፡ “ኑሮ በዘዴ ጦም በኩዳዴ” ነው ወገኖቼ፡፡ አዎ፣ “ቀን እስኪያልፍ ያባትህ ባሪያ ይግዛህ”ስ እንል የለም? ምን እናርግ?

ከኛ ከድኩማኖቹ የተሻሉ ልጆችን ማፍራት አለመቻላችን ነበር የእስካሁኑ ችግራችን፡፡ እንደኛው አሲድና ቀናተኛ እየተካን ከድጥ ወደማጥ የመዘፈቅ ባህል ነበር ለብዙ ዘመናት ያዳከረን አባዜያችን፡፡ እንደኛው በሥልጣን አራራና ባልተገባ መንገድ ሀብት የማጋበስ ሱስ የተጠመዱ ልጆችን ማፍራት ነበር የዘመናት ዋና ተግባራችን፡፡ አባት ልጁን፣ ልጅ አባቱን በሥልጣን ሽሚያ ምክንያት የሚገድልና ቆንጥር ለቆንጥር የሚያሳድድ እርጉም ሽንት የመፈልፈል አባዜ ነበር ተጠናውቶን የቆየው፡፡ በመተትና በሟርት በመጠላለፍ አንዱ የሌላውን ውድቀት የሚያፋጥንበት ባህላዊ እሥር ቤት ውስጥ መዘፈቃችን ነበር ልንቀርፈው ያልተቻለን የዘላለም ራስ ምታታችን፡፡ ሀገርን የሚያቀጭጭና ከዕድገት ይልቅ ውድመትን የሚያስፋፋ የከንቱ ፉክክር እሥረኞች መሆናችን ነበር ትልቁ ወረርሽኛችን፡፡ አለመተሳሰብንና አለመተዛዘንን የተፈጥሮ ጠባያቸው ያደረጉ እርጉም ሽሎችን ወልዶ ማሳደግ ነበር ለከፋ ጉዳት እየዳረገን የመጣው የትውልድ መርገምታችን፡፡ … ከዚህ አዙሪት የወጡ በሀገራችንም ሆነ በሌላው ዓለም ከሚገኝ ነፃ አስተሳሰብና መልካም የሰው ልጅ አመለካከት በብዙው የሚማሩ ወጣቶችና ጎልማሦች፣ በዴሞክራሲያዊ መንግሥት ሥር ታንጸው የሚያድጉ ልጆችን ኢትዮጵያ ካገኘች እንደማንኛውም ሀገር በአጭር ጊዜ ውስጥ ያልፍላታል፡፡ ሁሉም በየቤቱ ከክፋትና ከምቀኝነት አባዜ የፀዱ ልጆችን ለማፍራት ቢጥር ቀስ በቀስ እኛ ስንሞትና ቦታ ስንለቅ ደህናው ትውልድ ሀገሪቱን ተረክቦ በጥፋትና በውድመት ወደኋላ ሣይሆን በዕድገትና በሥልጣኔ ወደፊት ያሽቀነጥራታል፡፡ (አንድ ሀብታም ሰው ቢቸግረው አሉ – የጨነቀው እርጉዝ ያገባል (ስትወልድበት ገደል ይገባል) እንደሚበላው መሆኑ ይመስለኛል – ምቀኝነት ከጤፍ እንደሚመጣ ጭንቅላቱ ውስጥ ማን እንደተከለበት አላውቅም አንድያ ልጁን እንጀራ ሳይበላ እንደጣሊያኖች በፓስታና በመኮረኒ፣ በላዛኛና በአኞሎ ዲቢቴሎ አቀማጥሎ ከሀበሻ ምግብ በማራቅ አሳደገው አሉ፡፡ ሰውዬው ያለፈለት ማይም ቢጤ ነውና ልጁን በገዛ ሀገሩ አዲስ አበባ ላይ ከእንግሊዝኛ በስተቀር ሌላ ቋንቋ እንዳይችል አድርጎም ነው ያሳደገው፡፡ አሃ! ለካንስ ኢትዮጵያን ለመምራት በፕሬዝዳንትነት ቦታ እወዳደራለሁ ያለው ኃይሌ ገ/ሥላሤም ልጁን ያስተማረው “አማርኛ መናገርና ድንጋይ መወርወር ያስቀጣል” ብለው ማስታወቂያ ከለጠፉ ዘመናዊ ት/ቤቶች በአንደኛው በመሆኑ ሞልቃቂት በ“ትውልድ ሀገሯ” እምብርት አዲስ አበባ ውስጥ ከቤተሰቧ ጋር እየኖረች አንድም ሀገርኛ ቋንቋ ጠፍቷት በእንግሊዝኛ ነበር ስትኮላተፍ አንዴ በቲቪ ያየኋት! አይ ኢትዮጵያ! ማለፉ አይቀርምና ሲያልፍ ስንቱን አውርተን እንጨርሰው ይሆን? ውጭ ያሉትስ በያሉበት ሀገር ቋንቋ ቢኮላተፉ አማራጭ አጥተው ነው፡፡ እዚህ ስንቱ ደንቆሮ ማይም መሰላችሁ ለልጆቹ አማራጭ እያሳጣ እንትን ላይ ተቀምጦ እንት ገማኝ የሚል! እንዲያው በውነት ከማይምነት የከፋ ለሰው ልጅ ጠላት ይኖር ይሆን? ከሰማችሁ አደራ እንዳትደብቁኝ፡፡  ለነገሩ ይህን ይህን አሁን እዚህ ማንሳት አይገባም፡፡) የኔው አውግቼውና አልፎአይቼው በስንት ጣማቸው! ይቺ ነገር የምቀኝነት ታስመስልብኝ ይሆን እንዴ? “ያጣ ወጉ ነው” ልባል፤ ግዴለኝም እችለዋለሁ፡፡ ለማንኛውም ደህና ሰንብቱልኝ እስኪ፡፡

 

yiheyisaemro@gmail.com

 

The post የባራክ ኦባማና የወይዘሮ አዜብ መስፍን ታሪካዊ ግንኙነት appeared first on Zehabesha Amharic.

(ሰበር ዜና) መምህር ግርማ ታሰሩ

$
0
0

Memeher Girma

(ዘ-ሐበሻ) በአውሮፓ የተለያዩ ሃገራት በማጥመቅ ላይ ቆይተው ወደ ሃገራቸው የተመለሱት መምህር ግርማ ወንድሙ በአዲስ አበባ ፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የመምህሩ ቅርብ ሰዎች የሆኑ ታማኝ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ::

እንደ ዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘገባ ከሆነ መምህር ግርማ ወንድሙ ፈቃድ ሳይኖራቸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም ተጠቅመው በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር በማስተማር እና በማጥመቅ ሥራ ላይ ተሰማርተዋል በሚል በቤተክህነት በቀረበባቸው ክስ ነው የታሰሩት::

በአገልግሎታቸው የተነሳ በወንጀል እንደሚጠየቁ በፖሊስ እንደተነገራቸው የተገለጸው መምህር ግርማ በአዲስ አበባ ፖሊስ ቁጥጥር ሥር ላይ ውለው ምርመራቸው እንደቀጠለ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል::

ምንጮቻችን የሚያደርሱንን መረጃዎች ይዘን እንቀርባለን::

The post (ሰበር ዜና) መምህር ግርማ ታሰሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>