(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል በሜሪላንድ ለ30ኛ ዓመት እያደረጉ ሲሆን በሌላ በኩል በአላሙዲ ስፖንሰር የተደረገው በRFK ስታዲየም ዲሲ በተመሳሳይ ቀን ተጀምሯል። በሜሪላንዱ የመክፈቻ ስነስርዓት ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የታደሙ ሲሆን አላሙዲ ስፖንሰር ባደረገው የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ደግሞ ጥቂት የወያኔ/ኢሕ አዴግን ሥርዓት የሚደግፉ ሰዎች ተገኝተዋል።
ይህን አላሙዲን ስፖንሰር ያደረገውን ዝግጅት በመቃወም በስታዲየሙ ደጃፍ የተቃውሞ ሰልፍ ሲያደርጉ የዋሉት ኢትዮጵያውያን “የአላሙዲ የደም ገንዘብ እይደልለንም” ሲሉ ተሰምተዋል።
አላሙዲ እጁን ከሰሜን አሜሪካው ስፖርት ፌስቲቫል ላይ እንዲያነሳ የጠየቁት ሰልፈኞቹ በተለይ አላሙዲ የስር ዓቱ ደጋፊ በመሆኑ እርሱን ብቻ የሚጠቅም የኢኮኖሚ ስርዓት በሃገሪቱ መዘርጋቱንም ሰልፈኞቹ በተቃውሟቸው አሰምተዋል።
ለ30 ዓመት የቆየውን ፌዴሬሽን ለመገንጠል አስበው ያልተሳካላቸውን አሁን በአላሙዲ ስፖንሰር የሚደረጉትን ግለሰቦች ሰልፈኞቹ “ተጠያቂ ናችሁ” ሲሉ የተሰማ ሲሆን፤ በተቃውሞ ሰልፉ ላይ በኢትዮጵያ እየደረገ ያለውን የሰብ አዊ መብት ጥሰት በማስታወስ ከወያኔ ጋር ተባብረዋል ያሏቸውን ሰዎች ስም በመጥራት አውግዘዋቸዋል። አላሙዲ በኢትዮጵያ የወሰደውን የመሬት ቅርሚትና በዚህም መሬት ላይ ያገኘውን ገንዘብ “የደም ገንዘብ” ሲሉ የገለጹት ሰልፈኞቹ በቀጣይም የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያደርጉ ታውቋል።
በዋሽንግተን በአላሙዲ ስፖንሰርነት የተዘጋጀው የስፖርት ፌስቲቫል በሰው እጥረት ድርቅ መመታቱን የታዘቡት አስተያየት ሰጪዎች “አላሙዲ ከፍሎ ከሌላ ስቴት ያመጣቸው ሰዎች ሳይቀሩ የርሱን ፌስቲቫል በመተው ወደ ኢትዮጵያውያኑ የሜሪላንድ ዝግጅት መምጣጣቸውን” ጠቁመዋል።
ከሲያትል በአላሙዲ ገንዘብ ሆቴልና የአየር ትኬት ተቆርጦልኝ ነው የመጣሁት ያለው አንድ አስተያየት ሰጪ “አላሙዲ ከኢትዮጵያ የወሰደውን ገንዘብ በዚህ በኩል ላካክሰው በሚል ነው በነፃ ሲቆርጡልኝ እሺ ብዬ እዚህ ከመጣሁ በኋላ በሜሪላንዱ የመክፈቻ ዝግጅት ላይ የተገኘሁት” ሲል ተናግሯል።
ኢትዮጵያውያኑ በአላሙዲ የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ተቃውሟቸውን አሰሙ
በሰዉ ድርቅ የተመታዉ የቦንድ ምንተፋ በተቃዋሚዎች የድምጽ ማእበል እየታመሰ ነበር
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራን የሚያዉለበልቡ ብቻ ሳይሆን የለበሱም ነበሩ።የኢትዮጽያ መንግስት አባይን ለመገደብ በሚል ስም ቦንድን ለመመንተፍ የሚያደርገዉን ሴራ እንቃወማለን አባይ ከመገደቡ በፊት ነጻነት፣ዲሞክራሲ፣ፍትህ ለመላዉ ኢትዮጵያን ያሻል በማለት በዘር በሃይማኖት ሳይለያዩም ድምጻቸዉን ያሰማሉ።
ቁጥራቸዉ የተመናመነ ግለሰቦች ሃፍረት በተሞላበት መልኩ ወደ አዳራሹ ቢያመሩም ከመካከላቸዉ አንዳንዶቹ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት የሟቹን መለስ ዜናዊ ቲሸርት በመልበስ ቢንጎማለሉም በፍርሃት እየነፈሩ መሆናቸዉ ግን ያስታዉቅ ነበር። “ተከብረሽ የኖርሽዉ ባባቶቻን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይዉደም” በማለት ኅብረ-ዜማን የሚያሰሙት ኢትዮጵያዉያን “ተመልከቱ ኢትዮጵያን አስመልክቶ ዝግጅት ቢያዘጋጁም የኢትዮጵያን ባንዲራን ለማዉለብለብ ግን ፍላጎቱ የላቸዉም! እኛ ግን በአባይ ስም አትነግዱ ስንላችዉ የኢትዮጵያን ባንዲራ እያዉለበለብን ነዉ” ይላሉ።
“እኛ ኢትዮጵያዉያን ነን ወደ አዳራሹ ለመግባት የዘር መለዮ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ማንነት ነዉ የሚያሻን” ብሉዉ ለመደራደር ቢሞክሩም አዘጋጆቹ የአባይ ጉዳይ በዘር የተደለደለ እንዲመስል አድርገዉታል። ያም ሆኖ ቁጥራቸው ከሰላሳ የሚያንሱ የቦንድ ተመንታፊዎች በሰአት 400 ዶላር በሚከፈልበት አዳራሽ ዉስጥ ሲገቡ ተስተዉሏል። በአዳራሹ ዉስጥም መዝጋቢ ሰዉ እንደሌለ ፣እንኳን ደህና መጣቹ ባይ እንዳልነበረ አንድ በተክለ-ሰዉነቱ የስብሰባዉን አዘጋጆች የዘር መስፍርት የሚያሟላ ልቦናዉ ግን ለኢትዮጵያዊነቱ የጸና ግለሰብ ዉስጥ ገብቶ የታዘበዉን ገልጿል።
በተገቢዉ መልኩ ጥናት ያልተደረገበት አባይን የመገደቡ ሙከራ የዲፕሎማሲና የደህንነንት አደጋ አለዉ፤ ስልጣንን ለማራዘምና አቅጣጫን ለማስቀየር በሚደረግ ደፋ ቀና ነዉ አባይን መገደብ በሚል ስም የኢትዮጵያ መንግስት የሚንቀሳቀሰዉ የሚሉ ተቺዎች ብዙ ናቸዉ። ባንጻሩ አባይ አሁን አይገደብ የሚሉት ፖለቲካውዊ ክፋት የተጠናወታችዉ ናቸዉ በማለት የኢትዮጵያ መንግስት ለማጣጣል ይሞክራል። አንድ የጋራ እዉነታ ግን አለ፤ በአባይ የመገደብ ጉዳይ ኢትዮጵያዉያን የተለያየ ሃሳብ የላችዉም! ህዝባዊ ዉክልና የሌዉ ህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት “ያላዋቂ ሳሚ ምን ይለቀልቃል” ግድቡን አያርገዉ ባዮች ቢኖሩ እንጂ…
ጁን 30 በሰዉ ድርቅ የተመታዉ የአትላንታ ጆርጂያ የቦንድ ምንተፋ ሂደት ክዉ ድንግጥም ያለ ነበር።
Hiber Radio: የቀደሞው የናይጄሪያ ፕ/ት “ኢትዮጵያ ውስጥ መሬት አልተቀራመትኩም”ይላሉ
<<…30ኛው ዓመት የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌስቲቫል መክፈቻ ኢትዮጵያዊነት የተንጸባረቀበት ነበር..>> ከስፍራው የተደረገ (ልዩ ዘገባ)
የፌዴሬሽኑ አመራር የአንድ ቡድን ችግር መፍታት አቅቶት ተራ በተራ እንዲጫወቱ አደረገ (ቃለ መጠይቅ)
ከአንድ ከተማ ሁለት ቡድን ተራ በተራ እየገባ እንደ አንድ ቡድን ይጫወት መባሉን ተጋጣሚዎች አልተቀበሉትም
መሐመድ ሞርሲ በግብጽ በሕዝባዊ አብዮት የተወለደው መንግስት ፕሬዝዳንት በሕዝባዊ ተቃውሞ ሊባረሩ ይሆን ? (ወቅታዊ ዘገባ)
ሶስት ወር በስራ ማቆም አድማ ላይ ያሉት አሽከርካሪዎች የመብት ጥያቄያችሁ ቀርቶ ስራ ግቡ ለተባለው የሰጡትን ምላሽ ተካቷል
ሌሎች ቃለ መጠይቆችም አሉን
ዜናዎቻችን
አሰሪዋን ገደለች የተባለች ኢትዮጵያዊት በስቅላት ተቀጣች
ዜጎች ለከፋ ችግር መጋለጣቸው ተነገረ
ተለጣፊው ፌዴሬሽን ዘንድሮም ተቃውሞ ገጠመው
የቀደሞው የናይጄሪያ ፕ/ት “ኢትዮጵያ ውስጥ መሬት አልተቀራመትኩም” ይላሉ
ካርቱም ከባእዳን ባለሃብት መሬት ነጥቃ ለዜጋዋ ሰጠች
በስራ ማቆም አድማ ላይ ያሉት ኢትዮጵአውያንና ኤርትራውያን የታክሲ አሽከርካሪዎች የመብት ጥያቄያቸውን ትተው እንደአዲስ እንዲቀጠሩ ጥያቄ ቀረበላቸው
የአገዛዙ የቤት ልማት የፖለቲካ ጨዋታ እንዳለበት ተገለጸ
ከዲያስፖራ በኮንዶሚኒየም ስም መጠነ ሰፊ የውጭ ምንዛሬ ለመሰብሰብ እንቅስቃሴ ተጀመረ
ውጤታማ መዝጋቢ ለተባሉ የኮሚሽን አሰራር ተዘርግቷል
ከኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ጋር የተፋለሙ የአልሽባብ መስራች እጃቸውን ሰጡ
ቡድኑ “ሁለት መሪዎቼን ገደልኩ” ይላል
ሌሎችም ዜናዎች አሉን
የድምጻዊ ሸዋንዳኝ ኃይሉ አዲስ አልበም እየተጠበቀ ነው
ድምፃዊ ሸዋንዳኝ ኃይሉ “ስጦታሽ’’ የተሰኘውን አዲሱን እና ሁለተኛውን አልበም ሊያወጣ ነው፡፡ በርካታ ኢትዮጵያውን የሙዚቃ ባለሞያዎች የተሳተፉበትና ዐሥራ አምስት ዘፈኖችን የያዘው “ስጦታሽ’’ የተሰኘው አዲስ የሙዚቃ አልበም በቅርብ ቀን ወደ ሕዝብ ጆሮ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በአልበሙ ውስጥ የተካተቱን ሰባት ዘፈኖች ያቀናበረው ታዋቂው የሙዚቃ ባለሞያ አበጋዙ ክብረወርቅ ሺወታ ሲኾን የአልበሙን ሙሉ ሚክሲንግ እና ማስተሪንግ የሠራውም እርሱ ነው፡፡ ወጣቱ የሙዚቃ አቀናባሪ ካሙዙ ካሳ ከአዲሱ የሸዋንዳኝ አልበም ውስጥ አምስት ዘፈኖችን አቀናብሯል፡፡ግሩም መዝሙር ሁለት ዘፈኖችን ሲያቀናብር ሚካኤል ኃይሉ አንድ ዘፈን በማቀናበር ተሳትፏል፡፡
ሸዋንዳኝን ጨምሮ ሞገስ ተካ፣ቴዎድሮስ ካሳሁን፣አማኑኤል ይልማ፣ጌቱ ኦማሂሬ፣አለማየሁ ደመቀ፣ጌትሽ ማሞና ብስራት ጋረደው በአጠቃላይ ስምንት አንጋፋ እና ወጣት የዜማ ደራሲያን በዚህ አልበም ላይ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡በግጥምም ይልማ ገ/አብ፣ቴዎድሮስ ካሳሁን ፣መሰለ ጌታሁን፣ጌትሽ ማሞ እና ታደሰ ገለታ ተሳትፈውበታል፡፡
የሙዚቃ አልበሙን በአገር ውስጥ አሳትሞ የሚያከፋፍለው በሙዚቃ ኢንደስትሪው የረጅም ጊዜ ልምድ ያለው ‹‹ኤሌክትራ›› ሙዚቃ ቤት ሲኾን ከኢትዮጵያ ውጭ ደግሞ ‹‹ናሆም ሪከርድስ›› መኾኑ ታውቋል፡፡
ሸዋንዳኝን በጨረፍታ
አዲስ አበባ ተወልዶ ያደገው ድምጻዊ ሸዋንዳኝ ኃይሉ የአንደኛ ደረጃ ትምሕርቱን በ‹‹ምስካየኅዙናን››፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምሕርቱን ደግሞ በሴንጆሴፍ ካጠናቀቀ በኋላ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመግባት ለሦስት ዓመታት የማኔጅመንት ትምሕርቱን ተከታትሏል፡፡ለማጠናቀቅ የአንድ ዓመት ጊዜ ሲቀረውም በልጅነት ዕድሜው ለጓጓለት ሙዚቃ በማድላቱ በሙዚቃ ፍቅር ተሸንፎ ትምሕርቱን አቋርጦ ወጥቷል፡፡
ሸዋንዳኝ ኃይሉ የልጅነት ዕድሜውን ባሳለፈበትና የትውልድ መንደሩ በኾነው፤ በአሁኑ ወቅት በተለምዶ ‹‹መስቀል ፍላወር›› እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በጊዜው አብረውት ላደጉ የዕድሜ አቻዎቹና ለትምህርት ቤት ጓደኞቹ የተያዘለትን ወይም ያጠናውን ዘፈን በማንጎራጎር ነበር መዝፈን የጀመረው፡፡በሴንጆሴፍ ትምህርት ቤት ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርቱን መከታተል ሲጀምርም የመዝፈን ፍላጎቱ በመጨመሩ ችሎታውን አሻሽሎ በትምሕርት ቤቱ የሙዚቃ ቡድን ውስጥ በድምፃዊነት መሳተፍ ጀመረ፡፡
በወቅቱ የነበረው የትምህርት ቤቱ አስተዳደር በተለየ መልኩ ለሙዚቃ ጥበብ ከፍ ያለ ግምት የሰጠ ነበር፡፡ ለሙዚቃ ዝንባሌ ያላቸው ተማሪዎች እንዲበረታቱ በማሰብ የሙዚቃ ቡድኑን በሙሉ በዘመናዊ የሙዚቃ መሣሪያ አደራጅቶት ነበር፡፡ በቂ የሙዚቃ ዕውቀት ያለው መምሕር በመቅጠርም ተማሪዎች ለኾኑት የቡድኑ አባላት ከፍተኛ እገዛ አድርጎላቸዋል፡፡ ሸዋንዳኝ በትምሕርት ቤቱ የሙዚቃ ቡድን ውስጥ እያለም የተለያዩ የእንግሊዘኛ ዘፈኖችን በመጫወት ቢታወቅም ለአርቲስት ጌታቸው ካሳ ዘፈኖች ልዩ ፍቅር ነበረው፡፡ በአጠቃላይ ሸዋንዳኝ በሴንጆሴፍ ዘመናዊ የሙዚቃ ቡድን ውስጥ የነበረው ቆይታ ከሁለት ዓመታት ዕድሜ የዘለለ ባይኾንም የትምሕርት ቤቱ እገዛና ድጋፍ ለዛሬው ሞያዊ ሕይወቱ የራሱ የኾነ ቦታና ዋጋ እንዳለው የድምፃዊው የሙዚቃ ዕውቀት፣ ክህሎት እና ጥንካሬው ማረጋገጫ ነው፡፡
ሸዋንዳኝ ዐሥራ ሁለተኛ ክፍልን ተሻግሮ ወደ ዩኒቨርስቲ በዘለቀ ጊዜም ከሙዚቃ ጋር አልተቆራረጠም፡፡ ይልቅስ ከኢትዮ ስታር ባንድ ጋር በመኾን በሳምንት ለሁለት ቀናት እየሠራ ለጥቂት ጊዜያት ያህል ቆየ፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሞያዊ ክህሎቱ እያደገ እና የምሉዕ ድምፃዊነቱ ቦታ እንደተረጋገጠ ዕውቅናው እየጨመረ፡፡ ይህኔ የተለያዩ ባንዶችን በመቀላቀል ተወዳጅነት ያተረፈለትን ሥራ ማቅረብ ጀመረ፡፡ ‹‹መዲና›› ፣ በአንጋፋው ድምጻዊ መሐሙድ አሕመድ ተመስርቶ የነበረው ‹‹ስሪ ኤም››፣ ‹‹ሩትስ ኤንድ ካልቸር››፣ ‹‹አዲስ››፣ ‹‹ሴቫንስ›› እና ‹‹ኤክስፕረስ›› የተሰኙት የሙዚቃ ባንዶች ሸዋንዳኝ በተለያዩ ጊዜያት ከእውቅ ድምጻውያን ጎን የሠራባቸው ናቸው፡፡ ድምጻዊ ሸዋንዳኝ ኃይሉ ‹‹በሴቫንስ እና ኤክስፕረስ›› የሙዚቃ ባንድ ውስጥ በነበረው ቆይታ ከእነ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ)፣ ትዕግስት በላቸው፣ አብዱ ኪያር፣ ሽመልስ አራርሶ፣ ጸደንያ ገብረማርቆስ እና ሌሎችም አርቲስቶች ጋር ሠርቷል፡፡
‹‹ጽጌረዳ›› የተሰኘው የግርማ በየነ ዘፈን የሸዋንዳኝ የመጀመሪያ ነጠላ ዜማ ሥራው ሲኾን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ስቱዲዮ የቪዲዮ ክሊፕም ሠርቶለት ነበር፡፡ አስከትሎም ‹‹ ስቅ አለኝ›› የተሰኘውን የመጀመሪያውን ተወዳጁን አልበም ለሕዝብ ጆሮ በማድረስ ከፍተኛ ተወዳጅነትን አትርፏል፡፡ ሸዋንዳኝ እ..ኤ.አ በ2004 ዓ.ም ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በተካሄደው ‹‹ኮራ›› ሙዚቃ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን በመወከል ከጸደንያ ገብረማርቆስና ኃዴ ኃይሌ ጋር በመኾንም በዕጩነት ለውድድር ቀርቦ ጥሩ ደረጃን አግኝቷል፡፡
ድምፃዊ ሸዋንዳኝ ኃይሉ ‹‹አፍሮ ሳውንድ›› የሙዚቃ ባንድን ከመሠረቱት ሦስት ባለሞያዎች አንዱ ነው፡፡ ከአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እና ከሙዚቃ ባለሞያው ግሩም መዝሙር ጋር በመኾን በጋራ ያቋቋሙትን ይህን ባንድ ለዘጠኝ ተከታታይ ዓመታት በፍቅር በመምራት እና ተናበው በመሥራት ውጤታማ ኾነውበታል፡፡ ‹‹ዛየን›› ሸዋንዳኝ ከሦስት ዓመት በላይ በፍቅር የሠራበት ሌላው ባንድ ነው፡፡
ድምፃዊ ሸዋንዳኝ በተለያየ ጊዜያት ከተጠቀሱት ባንዶች ጋር በመኾን፤ በቡፌ ደላጋር፣ በኢሉዥን፣ በሂልተን፣ በሸራተን ጋዝላይት፣ በኮፊ ሃውስና በሃርለም ጃዝ መድረኮች ላይ የሙዚቃ ሥራን በማቅረብ ወዳጅና አድናቂዎችን አፍርቷል፡፡ የመጀመሪያ አልበሙን ካወጣ በኋላም ከድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ጋር በአንድ ላይ በመኾን በቦሌ መንገድ ላይ ይገኝ የነበረውንና በወቅቱ በርካታ እንግዶችና ታዳሚዎችን በማስተናገድ በከተማው ተጠቃሽ የምሽት ክለብ የነበረውን ‹‹ላየን ክለብ›› በመከራየት ለስድስት ወራት ያህል በትጋት ሠርተውበታል፡፡ ሸዋንዳኝ ይህንኑ የምሽት ክለብ ሥራ ገፍቶበት ከሌሎች ሁለት ጓደኞቹ ጋራ በመኾን በቦሌ መድኃኒያለም የሚገኘውን ታዋቂው ‹‹ፋራናይት›› የምሽት ክለብን በመክፈት በዋና ሥራ አስኪያጅነት መምራት ከጀመረ ስድስት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡
ሸዋንዳኝ ከሰው ጋር ተግባብቶ እና ተከባብሮ መሥራት የሚያስችለው መልካም ባህሪ እና ብቃት ያለው አመራር መስጠት የሚችል በመኾኑ ድርጅቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ከባለድርሻዎቹ ጋር በፍቅር ተስማምቶ እየሠራ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም አገር ውስጥ ባለበት ጊዜ ኹሉ ዘወትር ሐሙስ እና ቅዳሜ ቀደም ሲል ከዛየን ባንድ ጋር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ከመሐሪ ብራዘርስ ጋር በመኾን እንግዶቹን በሙዚቃ ያዝናናል፡፡ከተለያዩ ባንዶች ጋር በመኾን ያለማቋረጥ የመድረክ ሥራን መሥራት በመቻሉ ችሎታውን ዕለት ከዕለት እንዲያዳብር እና በየትኛውም ቦታ ብቁ የኾነ ድምፃዊ መኾን አስችሎታል፡፡ በዚህ ብቃቱም በመላው ኢትዮጵያ በተዘጋጁ በርካት የሙዚቃ ዝግጅቶች፣ ለማኅበራዊ አገልግሎት በዋሉና በዕርዳታና መሰል የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች ላይ በመሳተፍ ሥራዎቹን ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡
ድምጻዊ ሸዋንዳኝ ኃይሉ የመጀመሪያውን አልበም ከማውጣቱ ቀደም ብሎ በነበረው ዕውቅና እና ተወዳጅነት ከአገር ውስጥ የመድረክ ሥራዎች በተጨማሪ ወደ ጣልያን፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ እና ዱባይ ተጉዞም የተለያዩ መድረኮች ላይ በመሥራት ችሎታውን አስመስክሯል፡፡ የመጀመሪያውን አልበም ካወጣ በኋላም ከኢትዮጵያ ውጪ፤ ግብጽ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ባህሬን፣ ዱባይ፣ አቡዳቢ፣ እስራኤል፣ ስዊድን፣ እንግሊዝ፣ ኖርዌይ፣ ሆላንድ፣ በአሜሪካ ከዐሥራ ሁለት ግዛቶች በላይ እና ሌሎች አገሮች በተደጋጋሚ ለኮንሰርት እየተጋበዘ ሥራዎቹን አቅርቧል፡፡ የሸዋንዳኝ የመጀመሪያ አልበም ከወጣ ጊዜ ጀምሮ ተወዳጅነቱ ለስምንት ዓመታት የዘለቀ በመኾኑ ለኮንሰርት ሥራ ወደተለያዩ አገራት መጋበዙ እስከአሁንም አልተቋረጠም፡፡
ሸዋንዳኝ ኃይሉ ምንም እንኳን አብዛኛው ሙዚቃዊ ሕይወቱ በውጭ ሀገር የሙዚቃ ስልቶች እና የአዘፋፋን ስታይሎች የተቃኘ ቢሆንም ተወዳጅ አገርኛ ቃና ያለው ድምጻዊ ነው፡፡ በአገራችን የሙዚቃ ኢንደስትሪ ውስጥ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ እየተደመጠና ተወዳጅነትንም እያገኘ ያለውን ዘመናዊ የአዘፋፈን ስታየልን በመፍጠር ረገድ ተጠቃሽ ከኾኑት አርቲስቶች መካከል ድምጻዊ ሸዋንዳኝ ኃይሉ አንዱ ነው፡
“አማራው ያሬድ አይቼህ” ደግሞ ምን ፍጠሩ እያለን ይሆን?
አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል፡፡ የወደቀም ግንድ ምሣር ይበዛበታል፡፡ ኢትዮጵያም ቀን ጣላትና፣ ቀን ጣላትናም በጠላቶቿ እጅ ወደቀችና፣ በጠላቶቿ እጅ ወደቀችናም የድፍን ስድና መረን ያደገ ዋልጌ ሁሉ የስድብና የዘለፋ አፍ ማሟሻ የመሆን ዕጣ ደረሳትና ይሄውላችሁ በየቀኑ ተነግሮ የማንሰማው ተጽፎም የማናነበው ነገር የሌለን ሆነን ዐረፍነው፡፡ የገዛ ልጆቿም እየከዷት አንዱ ወግጂልኝ ይላታል ሌላው ለርሷ ለመሞት ቆርጦ ተሰልፎላታል፡፡ ደርግ ጥሩ አማርኛ ነበረቺው፡- ‹የእናት ጡት ነካሽ› የምትል፡፡ ዛሬ ዛሬማ የእናት ጡት ነካሽ ብቻ ሳይሆን ባት ቆራጭም፣ ማጅራት ገትርም ማለቴ ማጅራት መቺም፤ አነጣጥሮ አናት በርቋሽም ልጅ ሞልቶናል – የልጅ በያይነቱና ማኅበራዊ በብፌ መልክ በሽበሽ ብሎ ፊታችን ላይ ተዘርግቶልናል (የምግብ ስሞች ናቸው)፡፡ የበዓሉ ግርማ የምናብ ፍጡር የሆነው የካድማስ ባሻገሩ አበራ፣ ገነት ሆቴል የፋሲካ ዋዜማ የጦፈ ዳንስ ላይ የአምቦዋ ሳዱላ ሉሊት ታደሰ ስሟን እንድትነግረው ሦስቴ ጨቅጭቆ ላለመንገር ደጅ ስታስጠናው ‹ከነስምሽ ገደል ልትገቢ ትችያለሽ› እንዳላት ዓይነት ጃዋር ሲራጅን ዓይነቱ ወያኔ ዘራሽ ጎረምሳ በ‹ጤፍ ብድር ሳይቸግር› እንዲያው ከሜዳ ይነሣና ‹ኦሮሞነቴን ካልተቀበላችሁ ከነኢትዮጵያችሁ ገድል ልትገቡ ትችላላችሁ› እያለ ይዝትብናል – ከነገር አባቶቹና አሰልጣኞቹ (አሰይጣኞቹ ብልም ያው ነው) ከነሌንጮ ለታ የቀሰመውን እንጂ እርሱማ በጥቂቶች ጥፋት የተነሣ ያን በክፉነት የሚታማውን ዘመን የት ደርሶበት፡፡ እኛ የኢትዮጵያዊነትን መቁነን የምንሰጥ ወይ የምንነሣ ይመስል በማናውቀው ነገር በትዝታና በታሪክ ዋሻ ውስጥ መሽገውና በአስተሳሰብ ላለማደግ ምለው ትናንትም ዛሬም እዚያው የሚኖሩ በሽተኞች ይነተርኩናል፡፡ ‹ጌታውን ቢፈሩ ገበር ገበሩን› ይባላል፡፡ አሁን ኢትዮጵያን ቀጥቅጦ እየገዛት ያለው አማራ ሳይሆን ወያኔ/ኢሕአዴግ መሆኑ እየታወቀ ‹ሞቶ መቃብር ውስጥ የገባ›ን አማራ መጨቅጨቅ ያስፈለገበት ምክንያት እንኳንስ ለሰው ዘር ለእግዜሩም ዕንቆቅልሽ ሣይሆንበት የሚቀር አይመስልም፤ ‹የሞተን› መውቀስ ደግሞ ከፈሪና ከባለጌ እንጂ ከጤናማ ሰው በጭራሽ አይጠበቅም፡፡ ጉደኛ ዘመን ውስጥ ነው ያለነው፡፡ ይሄ የበታችነትም በሉት የበላይነት የሚባል ምስቅልቅል ስሜት እንዴት ያለ መጥፎ በሽታ መሰላችሁ! Actually, psychologists say that there is no superiority complex as such; it is, they say, the extension or the byproduct of inferiority complex. Therefore, it is logically worthwhile to suggest that people who are busy of dismantling Ethiopia, in some instances, like the Woyanes’ seizure of political and economic power, along with voraciously plundering its resources and appallingly impoverishing the majority of its citizens, are people who are suffering from an overdose of inferiority complex. Otherwise, at normal conditions, you do not lay down your intrinsic identity to the negotiating table and bargain over it as if it is a commodity; identity is not an item to be given by someone nor should it be something to unreasonably bicker upon with somebody, that somebody being abstract or tangibly concrete. The Jawars and their likes of any ethnic group in Ethiopia are funnily engaged in this futile busy-ness and making us laugh. What is Ethiopianness after all? Who has the right to anoint Ethiopianness? What is the source of all this abracadabra and stupidity over Ethiopianness? Where the hell do people of other nations other than Ethiopians invest much attention and commotion on such unproductive and counter-productive matter? Who are more Ethiopians? The Amharas or the Oromos? The Tigrians or the ‘X and Y’s and others? How do some allegedly ‘erudite’ people become cunningly self-destructive to the extent of negotiating their inbuilt who-ness anew after leading an intermingled societal life for thousands of years presumably under one identity? What could be the nature of such an illness that makes people succumb to the traps of the astute who are there at the top of the tower of politics to merely exploit the idiocy of their prey? Anyways, whatever the present scenario might look like, believe me, these weeds of history will lament in the near future when Ethiopianness re-emerges with all its imaginable dignity and glamour. There are indications for the rise of the new sun and we surely will rejoice at the dawn of our freedom.
ይሄን ስም ዐውቀዋለሁ፡፡ ‹ጉረኛ!› እንዳትሉኝ እንጂ ያለ ብዙ ማጋነን ውሎና አዳሬ ከዚሁ ከድረ ገፆች ንባብ ጋር በመሆኑ ብዙ የብዕርና የእውነት ስሞችን መያዝና ማስታወስ አያቅተኝም፡፡ ይሄ ያሬድ የሚባለውን ስም ታዲያ የማውቀው በዚሁ ወያኔና አስመሳይ ቅጥረኞቹ ከተቃውሞው ጎራ ጋር በምናብ ጦርነት በሚተጋተጉበት የድረ ገፅ ዘመቻ ነው፡፡ በሌላ የያሁ ግሩፕም ሲበጠብጠን የነበረ ይመስለኛል፡፡ በጥባጭ መኖሩ ጥሩ ነው፤ ወያኔም በታሪካችን ብቅ ብሎ “ሰውና ሀገር ከኖሩ ለካንስ እንዲህም ያለ ጉድ አለ! ለካንስ በርግጥም ‹ሀገር ሲያረጅ ጃርት ያፈራል› እሚባለው ነገር እውነት ነው” እንድንልና ለወደፊቱ እንድንጠነቀቅ ማስታወሱ ለበጎ ነው፡፡ ሁሉም ክፉ ነገሮች ክፉ አይደሉም፤ በአንድ ወይ በሌላ መንገድ አስተማሪ ናቸው፡፡ ትምህርቱ በዝቶ እንዳሁኑ ናላን እንዳያናውዝና መፈጠርን እንዳያስረግም ግን ሁሉም ነገር መጠን ቢኖረው ደግ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የኛ ችግር መጠኑን አለፈና በየቀኑ የሚፈልቀው ጉድ አጃኢብ እያሰኘን ማስደመሙን ቀጥሏል፤ በተሎ ዕልባት ካላበጀንለት ከአሁኑ የባሰ መጥፎ ደረጃ ላይ መድረሱ ግን ይሰመርበት፡፡
በቅድሚያ የያሬድን የመሰለ በቅርበት ብቻም ሳይሆን በርቀትም ክፉኛ የሚከረፋና አንዳች አንዳች የሚል ሃሳብ ለማስተናገድ መድረክ መገኘቱ የሀገራችን ልጆች በርግጥም የምዕራቡ ዓለም ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ በጎ ልማድ እየማረካቸውና ተቃራኒ ሃሳቦችን በአንድ ማዕድ ማስኬድን እየለመዱ መምጣታቸውን በጉልህ ያሳያልና ይህን መነሻና መድረሻው የማያስታውቅና በአዛኝ ቅቤ አንጓችነት የሚቅመደመድ ጽሑፍ ያነበብኩበትን የዘሃበሻ ድረገፅ ማመስገን እፈልጋለሁ፤ በእግረ መንገድም ይህን ጽሑፌን እንዲቀበሉኝና በተመሳሳይ መድረክ እንዲያስተናግዱልኝ እማጠናለሁ፡፡
በቅድሚያ ያሬድ አይቼህ የተባለ ሰው ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ – የብዕር ስም እንዳይሆን በመስጋት፡፡ አለም ከተባለ ችግር የለብኝም፡፡ ችግሩ ሃሳቡ እንጂ ስሙ አይደለም፡፡ አማራ ነኝ የሚለውን ተረት ግን ይሂድና ሌላውን ይብላ(አፄ ኃ/ሥላሤ ኒክሰን የተባለ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ለጉብኝት መጥቶ ሳለ ከሽሮ ሜዳዎቹ ዶርዜ ሃይዞዎች የተሸለሟትን ባለጥበብ ድንቅ ነጠላቸውን ሊለካት እንደወሰደባቸው ላለመመለስ ሲያቅማማ ባዩት ጊዜና Nixon, go and eat another, answer my singular – ብለው በማሣፈር አስመልሰውታል አሉ – ለዚያውስ ፈረንጅ ማፈር ሲያውቅ አይደል፡፡) እናም ያሬድ ‹አማራ ነኝ›ነቱን እዚያችው ራሱ ይብላት ወይም ለማያውቀው ወስዶ ያብላት፡፡ ያሬድ አማራ ብቻም ሳይሆን ባይገርመውና ባይገርማችሁ ኢትዮጵያዊም አይደለም፤ በኢትዮጵያውያን መካከል ወይም ኢትዮጵያውያን ቢሆኑ ሊያሣፍራቸው በማይገባ ወገኖች መሀል ሽብልቅ የሚቀበቅብ ያሬድ፣ ‹የዱሮ አማሮች ለኢትዮጵያ መፈረካከስ መነሾዎች ናችሁና ገደል ግቡ፤ ሀገር እንደዳቦ የሚጠፈጠፈው በየመቶ ዓመቱ ስለሆነ ከዜሮ የጀመረች አዲስ ኢትዮጵያ ታንጻለችና በዚያች ኢትዮጵያ ካልተስማማችሁ ከነአሮጌ ኢትዮጵያዊ ማንነታችሁ እንጦርጦስ ውረዱ፣ ጃዋራዊ መሆን ካልቻላችሁ ዐርፋችሁ ተቀመጡ› የሚል ያሬድ አማራ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊም፣ እንዲያውም ከነአካቴው ሰውም አይደለም ቢባል ስህተቱ ለክፉ የሚሰጥ አይሆንም – ለዚህ አቋም ኃላፊነቱን እወስዳለሁ፡- በዚህ ልዩ የማንነት ጥያቄ ዙሪያ ቢያንስ እኔ አልሳሳትም ፡፡ ይህ ዓይነቱ ወንድምን ከወንድም ለማናከስ ቆርጦ የተነሣ በግብርና በአስተሳሰብ በሀገር ላይ የወየነ ግለሰብ በእናቱ ማኅፀን ሳለ ቢጨነግፍ ይሻለው ነበር፡፡ ይሄ ‹ሰው› በሰው አምሳል የተፈጠረ የሰይጣን ስሮት የትውልደ አጋንንት ውጤት ነው፤ ሰይጣን ደግሞ ይሉኝታና ሀፍረት ስለሌለው፣ ዜግነትና ሀገርም ስላልተበጀለት ድርጊቱም ሆነ ንግግሩ እንደልቡ ነው – ለዚህ ነው ይህ ያሬድ የሚባል ‹ሰው› በምግባሩ ሳቢያ አማራ ቀርቶ ሰው አይደለም በማለት ልከራከር የወደድኩት፡፡ የአንባቢ ሥጋት ይገባኛል – ‹የኢትዮጵያዊነትንና የአማራነትን መክሊት ለማበጀትና ማንነትን በመቁነን ለማደል አንተ ማነህ?› ቢለኝ ትክክል ነው፡፡ ያሬድ በብሔረሰብና በዜግነት የማንነት ችግር ውስጥ መዘፈቁን እንኳንስ እኔ ተሰዳቢው፣ አሰዳቢውና አሰዳዳቢው እንዲሁም አሳዳቢው ሁሉ ያውቃል፡፡ አማራ ነኝ እያልክ አማራን መሳደብ ማለት የውሸት ማንነትን መናጆ በማድረግ የስድብ ኳስህን ወደተፈለገው ግብ መለጋት ማለት ነው – ተዓማኒነትን ለማግኘት፡፡ አማራ ሳትሆን አማራ ነኝ እያልክ አማራነትንና በዚያም ተንጠላጥለህ ኢትዮጵያዊነትን መዝለፍ የጤና ሳይሆን ከኅልፈት መልስ ምድራዊ ፈውስ የማይገኝለት ትልቅ ደዌ ነው፡፡ ያሬድ አማራ ሊሆን አይችልም – በጭራሽ! ይህ የነቢባዊ ክርክሬ ማዕከላዊ ጭብጥ እንጂ አማራ ሆነው በዕብደት ምክንያት ከአማራነት ተራ የወጡ ብዙ ወፈፌዎች ስላሉና እያደረጉ የሚገኙትን በማድረግ ላይ ስለሚገኙ ይህ ሰው አማራ ሊሆን የሚችልበት በርና መስኮት ሁሉ ተከርችሟል የሚል ዝግ ውሳኔ እንደሌለኝ ልጠቁም እፈልጋለሁ – ግን ራስህን በራስህ ትቃረናለህ ብትሉ የለሁበትም፤ ከተግባራዊው የደምና የአጥንት አሌታዊ ፍልስፍና ባለፈ ዋናው እሳቤየ ግና ሰውዬውን በኢ-አማራነት ለመፈረጅ መነሻየ ተግባሩ እንጂ ደሙ አይደለም፤ አማራነትን መንጥሮ የሚያሳይ የደም ምርመራ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ገና አልገባም መሰለኝ፡- ያም አለ ይህ ያሬድ እንደወያኔ ሁሉ ለአማራ ጥፋት የቆመ እንጂ ለሌላ ገምቢ ነገር ያልቆመ በመሆኑ እሳት ካየው ምን ለየው ነውና ፀረ አማራ ፍጡር ነው – አማራ ሆነም አልሆነም፤ ትግሬው ገብረ መድኅን አርአያ የአሉላ አባነጋነትን የሀገር ወዳድነት ሽልማት የተጎናጸፈው ታሪክ ሲዘክረው በሚኖር መልካም ሀገራዊ ተጋድሎው እንጂ አማራን ወይም ሌላውን ዘውግ በሌላው እንዲጠላና እንዲጨፈጨፍ ለማድረግ በተበረከተ ሰይጣናዊ አስተዋፅዖ አይደለም – ከዚህ ጀግናና የኢትዮሰማይ ድረ ገፅ ዋና አዘጋጅ ባለቤት ከሆነው ጌታቸው ረዳን ከመሳሰሉ ፀረ ወያኔ ግለሰቦች ብዙ የምንማረው አለና ዕዝነ ልቦናችንንና ዐይነ ኅሊናችንን ፈጣሪ ለበጎ ነገር እንዲከፍትልን እንጸልይ ይልቁናስ፡፡ ሁሉንም ወያኔ ማለቱ ፋሽኑ ስላለፈበት እንጂ ይህ ሰይጣን ሰው ወያኔ ነው ማለትን በወደድኩ ነበር፤ ለወጣቱ ትውልድ መወናበድና ለኢትዮጵያዊነት መውደም የበኩሉን ተልእኮ በመወጣት ላይ የሚገኝ ከወያኔም በበለጠ እየሠራ ያለ መሠሪ ሰው ነው ቢባል ለማስረገጫው የዛሬ ጹሑፉን ዘሀበሻ ድረ ገፅ ላይ ማንበብ በቂ ነው ፡፡ ባለጌን ባለጌ ካላሉት በማያውቀው ጉዳይ ጥልቅ እያለ መፈትፈቱን ተውትና ዛሬና አሁን ወይም እየቆዬ ‹ጭንቅላታችሁን በደንብ እንዳገኘው ወረድ ብላችሁ ቁሙልኝ ማለቱ አይቀርም› – ሊሸናብን፤ የባለጌዎች መጨረሻ እንደዚህ ነው፡፡ መንግሥቱና መለስ በተፈጥሯቸው ያን ያህል ባለጌዎች ላይሆኑ እንደሚችሉ በበኩሌ ይሰማኛል – ሰው ነው እያጃገነና እያሽበለበለ እንደዚያ ጭምልቅ ያሉ ባለጌዎች ያደረጋቸው፡፡… ይህን የመሰለ ሰው ማኅበራችንን እንዲያውክ መፍቀድና በስሱ ገላችን እየገባ ሚጥሚጣና በርበሬ እንዲነሰንስብን፣ ምሣርም እንዲሰቀስቅብን ነጻ መልቀቅ ስህተት ነው፡፡ የዴሞክራሲን ዐይን እንደመደንቆል ስለሚቆጠርብኝ እንጂ የዚህን ከንቱ ዜጋ ጽሑፍ፣ የዚህን በዘጠኝ ወር ሳይሆን በአምስት ወሩ የተወለደ ሕይወት ያለው ጭንጋፍ ሰውዬ መጣጥፍ ለዳግመኛ አናንብ ብዬ በማይም ቃሌ ብገዝት ደስ ባለኝ፤ ምን ሊሠራልን? ለመናደድና ወርቃማ ጊዜያችንን በመንጨርጨር ልናሳልፍ? ወያኔዎች እኮ የኛን መትከንና መብገን በጣም ነው የሚፈልጉት፡፡ ስንናደድ አንጀታቸው ቅቤ ይጠጣል፡፡ ምክንያቱም ሀዘን አምላኪዎች ናቸውና፡፡ በዚህ ሰውዬ ጽሑፍ ግርጌ ከ100 የሚበልጡ – ብዙዎቹ ግን በተመሳሳይ ስሞች የተደጋገሙና በወያኔያውያን አፈ ቀላጤዎች የተጻፉ የሚመስሉ አስተያየቶችን ተመልክቼ ለነዚህ አስተያየቶች የባከነውን ጊዜ ሳስብ አዘንኩ፤ በስንቱ ወያኔያዊ ሥራ አስፈቺ ጊዜያችን እንደሚቃጠልም ታወሰኝ፤ ይሄው እኔም እንቅልፌን ትቼ በንዴት መብከንከኔን ተያያዝኩላችኋ! ምን ይደረግ? ጊዜው ማለቴ እኛው በሞኝነታችን ባመጣነው ጣጣ ተቸገርን፡፡ ማን ተከፋፍላችሁ ተነታረኩ አለን? ከዚህ በበለጠ ፍሬያማ ተግባር ላይ ጊዜያችንን ማዋል አንችልም ነበርን?
ያሬድም ሆነ ያሬዳውያን ጃዋርን ከወደዱት – በዓላማ ቁርኝት ማለቴ እንደሆነ ይሰመርልኝ – አዝለውት አገር ላገር ሊዞሩ ይችላሉ – ይህን መብት ማንም አይሰጣቸውም ወይም አይነፍጋቸውም፤ እኔም ሆንኩ እኛ በዚህ አንቀናም፡፡ አንድ ጥግ ላይ ተወትፎ የወያኔን አጀንዳ ማራመድ መጨረሻው እንደማያምር ግን የሚመለከተውን ሁሉ ማርዳት እፈልጋለሁ፡፡ በወሬ ሕዝብና ሀገርን ለማፍረስ መሞከር ቀላል ሊመስል ይችላል – ለጊዜው ብዙ ወጭ የለውም፤ የኢትዮጵያ አምላክ የፍጻሜውን ፍርድ ሲሰጥ ግን አሁን እንዲህ ቀን ሰጠኝ ብሎ በሀገር ሀብትና በሕዝብ ሥነ ልቦና ላይ ሲዘባነንና በወረት ፍቅር ተጠምዶ እየቀላመደ ሲዘባርቅ የነበረ ሁሉ ደብቁኝ ደብቁኝ እንደሚል መታወቅ አለበት፡፡ ከጠላት ወገን ቀለብ እየተሰፈረለትና ወርሃዊ ምንዳ እየተቀበለ የጠላትን አሉቧልታ በጮርቃውና ታዳጊው ትውልድ ላይ የሚያናፍስ ተባባሪ ሁሉ ዋጋውን የሚያገኝበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ይሁዳ ክርስቶስን የሸጠበትን 30 አላድ ሳይበላው በገዛ እጁ ዛፍ ላይ ተንጠልትሎ ሞቷል፤ የነ ያሬድና መሰል ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች የወደፊት ዕጣ ፋንታም ከዚህ የተለዬ አይሆንም፡፡ ሁለቱ ክህደቶች የጊዜ እንጂ የይዘት ልዩነት የላቸውም፡፡ ለነጃዋር ባላችሁ ቀረቤታ ወይም ለእኔ ባላችሁ ያልተገባና በቂ መደላድል የሌለው ሊባል በሚችል ግምት የተነሣ ይህን እውነት አዘል ደብዳቤ ልኬላችሁ የማታወጡ ድረ ገፆች እንደምትኖሩ ከልምድ አውቃለሁ፤ ለዚህም ፍርዱን የምጠብቀው ቢውል ቢያድርም ከእውነት ፈራጁ ከኢትዮጵያ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ደግሞም እውነት ትዘገያለች እንጂ ተደብቃ አትቀርም፤ ትቀጥናለች እንጂ አትበጠስም፡፡ ስለዚህ እውነትን እንዳለች ማስተናገድ ሲገባ በጠቆረ ነጣ፣ በወፈረ ከሣ ሚዛን የማያነሳ ቅድመ አእምሮ ፍርድ ተመሥርታችሁ ‹ባለጌና ውሻ በቤቱ ይኮራል› እንዲሉ በራችሁን ብትጠረቅሙብኝ የእውነት ዘገር ሌሊት እየመጣች ታስጨንቃችሁ፡፡ እውነትን እንዳመጣጧ እናስተናግድ እንጂ በምንም ዓይነት ቡልኮ ጀቡነን ጓዳችን ውስጥ ቀብረን ማስቀረት አይኖርብንም፤ ይህ ዓይነቱ ቸልታ ቆምንለት ከሚሉት ዓላማ የሚያስወጣ ከመሆኑም በላጥ ትልቅ ኩነኔ ነው – ሲያንስም ነውር፤ በዚያ ላይ የኅሊና ትዝብትም ቀላል አይደለም፡፡ ለማንኛውም ‹እኔ እያስመዘገብኩ ነው›፡፡ ይሄ ይታወቅልኝ፡፡ ፀረ ኢትዮጵያ መንጋ ሁሉ እንዲህ በአደባባይ እንደፏለለ ይቀራል ማለት ደግሞ ዘበት ነው ፡፡ ሰማይ ምድር ያልፋሉ፡- እግዚአብሔር በአመፀኞች ላይ የሚያሳልፈው ብያኔ ግን መቼም አይቀርም፡፡ ይህ ተብሎ ተብሎ ያለቀ አጠቃላይ እውነታ ነው፡፡
ባለፈው ሰሞንም ይሄው ያሬድ በአባ መላ ላይ የጻፈውን ተመልክቼዋለሁ – በዚያ ጽሑፉ አባ መላን እያበሻቀጠ ስሎታል፤ ሰው መለወጥ እንደማይችል፣ በአንድ አቋም የሚታወቅ ሰው በዚያው አርጅቶ መሞት እንደሚጠበቅበት… በተዛዋሪ የሚገልጸው ያ ጽሑፍ በአስቀያሚነቱና በምቀኝነት ልክፍቱ ወደር የማይገኝለት ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ሰው የሰውን ዕድገትና ለውጥ ለምን እንደሚመቀኝና ትኩር ጥምድ አድርጎ እንደሚይዝ አይገባኝም፡፡ የአንዳንድ ሰው ተፈጥሮ ይገርመኛል – የሰውን ዕድገትና መለወጥ እንደሥጋት ስለሚያይ ይመስለኛል – አንድ ነገር በሆነ ማግሥት ያን ሁኔታ ጥላሸት ለመቀባት እንቅልፍ አጥቶ ያድራል፤ ክፉኛ መረገም ነው፡፡ በሀገራችን ውድ ከሆኑ ቃላትና ሐረጋት ውስጥ ‹አመሰግናለሁ፤ ይቅርታ፣ ልክ ነህ/ሽ/ናችሁ፤ ኦ! ተሳስቼ ነበር› የሚሉት ጥቂቶቹ ናቸው፤ ምቀኝነትና ሰውን በተንኮል ለመጥለፍ ማሤር እንዲሁም ሰዎችን ለማደኽየትና ለማሳበድ በየጠንቋይ ቤቱ ማፋደስ ግን በብዛት ይስተዋላሉ – በዚህ ዓይነት ጉዞ ሀገር እንዴት ወደፊት ልትራመድ ትችላለች?
ይህ ያሬድ የሚባል ሰው በተለይ በረት እንደሚበጠብጥ ቀንዳም ፊጋ በሬ ዓይነት ነው፡፡ ያኔ ልጽፍ ፈለግሁና ረሳሁት ወይም ንዴቴ እንዳሁኑ በጣም አላስፎገላኝም ነበር ማለት ነው ተዘነጋኝና ተውኩት – ደግሞስ በስንቱ ላይ ተጸፎ ይዘለቃል፡፡ የአሁኑ ግን ወጥ ረገጠና አናደደኝ፡፡ እናም እውነቱን ‹እስከዶቃ ማሰሪያው› ልነግረው ፈለግሁ፡፡ ከባለጌ ሰው ብዙ አይጠበቅምና ከዚህ በላይ ስለዚህ ሰው መናገር አስፈላጊም ተገቢም አይደለምና በእግረ መንገድ ሌላ ጉዳይ አንስቼ ጽሑፌን ላብቃ፡፡ (በነገራችን ላይ በግለሰቦች ላይ እንዲህ ተናድጄ ጽፌ አላውቅም፤ በዚህም አንባቢን ከፍተኛ ይቅርታ እጠይቃለሁ – አይለመደኝም ጓዶች! ምን ላድርግ – የምንንጨረጨርበት ነገር በዛ እኮ፡፡)
ሌላኛው ስመ ጥር ወያኔ፣ አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት መሆን አማረኝ እያለ መሆኑን ዛሬም በድጋሚ ሰማሁ፡፡ በክበበው ገዳ አንደኛው የቀልድ ሲዲ ውስጥ እንደሚገኘው እንደሸምሱ ነፍሰ ጡር ሚስት እኔ መቶ ብር ያምረኛል – ኃይሌ ደግሞ ፕሬዚደንትነት ያምረዋል፡፡ ያምሮቶች መለያየት ግን አይገርምም ትላላችሁ? የኢትዮጵያ መሬት መረገም እጅጉን ይገርመኛል፡፡ እርግጥ ነው – በአንድ በኩል ይህ ሹመት ሲያንሰው እንጂ አይበዛበትም – ቤት ለመጠበቅና ተሹዋሚ አምባሳደሮችን ተቀብሎ ለመሸኘት እንኳንስ እርሱ ታዋቂው ሯጭ እኔም አያቅተኝም ባይ ነኝ፡፡ በዚያ ላይ ሌባ ግቢውን አይደፍርም – የተሰጣ እህልና ልብስም ፈጣንነቱን በተማመነ የመንደር ጩልሌ አይደፈርም ፤ ኃይሌ እንደአቦሸማኔ በሚፈተለኩ እግሮቹ ሩጦ ስሊውን ያንቀዋላ – ከዚህ ሌላ ምን የረባ ሥራ ሊኖረው እዚያ ቦታ፡፡ ግን ኃይሌ ይህን ቦታ ለምን ፈለገው?[Is he a real moron? I couldn’t get the point as to why he excessively wished to grab the scepter of Woyane’s fake presidential post.] ለካምፓኒዎቹ ዋስትና ለማሰጠት አስቦ ይሆን? ለተበደለው ጭቁን ኢትዮጵያዊ ፍትህና ርትዕ ሊያመጣ ፈልጎ ይሆን? ከአንጀት ለሕዝብ ሊሠራ ነው ወይንስ ለታይታና በሩጫው ሲያረጅ በአዲስ ጉልበት ወደፖለቲካው ገብቶ ስሙ አየር ላይ እንደተንጠለጠለ ሳይረሳ እንዲቆይ ሊያደርግ አስቦ ነው? ምን ዓይነቱ … ራስ ነው ወገኖቼ! በቅጥር የግል አስጠኚና በግል ጥረት ‘is’ን ከ’was’ ለየና ራሱን ምሁር ማድረጉ ይሆን? ኢትዮጵያ ሰው አጣች ብትባል ጊዜ ይህ ነው የሚባል የትምህርት ደረጃም ሆነ የአመራር ችሎታና ብቃት ሳይኖረው ከመሮጫ ትራክ በቀጥታ ወደቤተ መንግሥት ቢገባ ሀገር የሚያልፍላት መስሎት ይሆን? ወይንስ ለመለስ ሞት ያለቀሰ ሁሉ ለፕሬዚደንትነት ቢወዳደር የሚከለክለው የለም ያለው ይኖር ይሆን? ያኔ ናዝሬት ላይ – መለስ ሳይሞት – ‹የተሸለምኩትን ካናቴራና ፓንት ለውዱ ጠቅላይ ሚኒስትራችን በማስታወሻነት አበረክታለሁ› ብሎ እጅ መንሻ ያስገባው ለዚህ ይሆን እንዴ? የምን መጃጃል ነው? ደግሞስ በዕድሜስ ቢሆን ገና ትንሽ ነኝ ይላል አይደለም እንዴ? እንዲህ ምን አጣደፈው? ትንሽ ቆየት ቢል ይደርስበት ነበር እኮ! ኃይሌም ሆነ ሌላ ማንኛውም ዜጋ ለየትኛውም የሥልጣን ቦታ በገዛ ሀገሩ መወዳደርና ማቸነፍ መብቱ ነው – እኔ አሁን አምርሬ እየተቃወምኩ ያለሁት በዋናነት ጊዜውን ነው – the timing – ፡፡ ከጊዜው ጋር በተጓዳኘም የሰውዬውን ተፈጥሮ ገባ ብሎ ከመመርመር አኳያ የተገነዘብኩትን ነገር ስገመግመው የምለውን ነገር እንዳልል የሚገፋፋ በቂ ምክንያት አጣለሁ፤ እናም እላለሁ – ኃይሌ ይህ ህልሙ ይቅርበትና የሁላችንም አንጡራ ሀብት እንደሆነ ይቆይ፤ የሥልጣን ፍላጎቱ ትዝብት ውስጥ እንዳያስገባውና ነገ መሪያችን እንዲሆን ብንፈልገው ያን ዕድል እንዳናጣ አሁን ‹አይነጅሰን› ነው አንዱ መልእክቴ፡፡ እውነትን ብቻ እንነጋገር ካልን – በሀገር ውስጥ የሚኖሩ ልጆቹ ከኢትዮጵያዊ ቋንቋዎች ተለይተው በእንግሊዝኛ ቋንቋና በፈረንጅ ባህል ማደጋቸውን ባይናችን በብረቱ እያየን በምን ወደደንና ልምራችሁ ብሎ ይጫረት ያዘ? ምንስ ጎደለበት? መጀመሪያ ልጆቹን ኢትዮጵያዊ ማድረግ ይቀድማል ወይንስ ‹ስለኢትዮጵያና ህዝቧ ተጨንቆ› ለፕሬዝደንትነት ዕጩ ሆኖ መቅረብ ይቀድማል? ትንግርት እኮ ነው ወንድሞችና እህቶች እንዲሁም አባቶችና እናቶች!
ለነገሩ መለስ አባ ለጥፍ ደህና አድርግ በነገር አቅምሶታል አሉ – የመሌ ምላስ ባትታሠር ኖሮ ይሄኔ ስንቶቻችንን በስድብ ውርጅብኝ አሽሮን ነበር፡፡ የኃይሌን የሥልጣን ጥም ሰምቶ እንዲህ አለው አሉ፡ – ‹ሀገር እኮ በአእምሮ እንጂ በሩጫ ክሂሎት አትመራም፡፡› የልኬቱን መጠን ነግሮታል፡፡ ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት አንጻር ወደዚያ መግባቱ ነውር ነው እንጂ ለጫማ ጠራጊና ለመኪና ጠባቂ ከስሙኒ በላይ የማይወጣው ንፉግና ቆንቋና ለሰውም የማያዝን ዜጋ በየትኛው የሞራል ብቃቱና በየትኛውስ ማኅበረሰብኣዊ ዕውቀትና ችሎታው ነው ለፕሬዝደንትነት አብቁኝ የሚለው? አናውቀውም እንዴ? ‹እንደኔ ፈግታችሁ በላባችሁ አግኙ› የሚለው ፈሊጡ ለሥራ መትጋትን ከማበረታታት አንጻር መልካም አባባል መሆኑ የማይካድ ሆኖ ለተቸገረና ላጣ ለነጣ እንዲሁም ለታመመና ድንገተኛ አደጋ ለደረሰበት ዜጋ የሞራልም ሆነ የገንዘብና የማቴሪያል ድጋፍ ቢያደርግ ምኑ ይጎዳል? እስኪ ኃይሌ እገሌን አስታምሞ አዳነ፤ ለእገሌ መታከሚያ ‹ይህን ያህል ዕርዳታ ሰጠ› ሲባል ሰምተን እናውቃለን? ተው እንጂ – አታናግሩኝ እባካችሁ፡፡ መለስ ራሱ እኮ ስለኃይሌ የበጎ አድራጎት ሥራ ሲጠየቅ አሉ – ‹ይልቅስ ስለቻቺ ጠይቁኝ› ብሏል ይባላል፡፡ እናም ኃይሌ በዓለም የስፖርት አምባዎች ባንዲራችን ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ከማድረግ በተጓዳኝ በማኅበራዊ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ብዙ ይጠበቅበታልና በዚያ በኩል ይበርታልን – በነገራችን ላይ ስለ ኃይሌ ከምለው ውጪ የምታውቁት ነገር ካለ ንገሩኝና አስተካክሉኝ፡፡ በመሠረቱ ማንንም አለመርዳት መብቱ ነው – ግን በልባችን እንዲገባ ብዙ ይጠበቅበታል፡፡ የሕዝብን ልብ ማግኘት ቀላል አይደለም፡፡ ቸርነት ደግሞ አንዱ የቀልብ መግዣ መንገድ ነው፡፡ እያለህ የሌለህ መሆን ወይም መምሰል በባህላችን ነውረኛና ንፉግ ያስኛልና ይህችን ቀላል ነገር በመረዳት በሚያልፍ ዓለም የማያልፍ ትውፊት ትቶ ማለፍ ከብልሆች ይጠበቃል፡፡
ምንም እንኳን ለወያኔ ሹመት ታማኝነት እንጂ ዕውቀትና ችሎታ ባያስፈልግም በብዙ አሉታዊ ነገሮች የማውቀው ኃይሌ ምን ቢንቀን ነው ፕሬዝደንታችሁ ልሁን ብሎ ጠላታችን ወያኔ ጫማ ሥር እየተደፋ የሚጎናበሰው ብዬ ማሰቤ ደግሞ አልቀረም፡፡ ከገንዘብና ከዝና አጥሮች ውጪ መኖር የሚሣናቸው ኃይሌን መሰል በሽተኞች ያሳዝኑኛል፡፡ ያለውን ሳይበላ ለሀብት ብዙ የሚስገበገብና ስመጥርነቱ ሳያንሰው ለተጨማሪ ዝና አላግባብ የሚንሰፈሰፍ ሰው ስሜቴን ያጎፈንንብኛል፡፡ በእውነት እናንተስ አልተናደዳችሁበትም? እንደዘፈኑ ግጥም ‹የራስጌ ወለባ ያንገት ሀብል ናቸው› ብላችሁ እንዳትቀልዱብኝ እንጂ ለመሆኑ ሩጫና አመራር ምንና ምን ናቸው? ብንወደው ጊዜ ለምን ይቀልድብናል? የወደድነውስ በሩጫ እንጂ በማኅበራዊ ሣይንስ ዕውቀቱና በተመራማሪነቱ ነው እንዴ? ስንትና ስንት ሺህ ምሁራን በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪም ሞልተውን ሳለ ነገር ግን በሁኔታዎች አለመስተካከል ምክንያት አንገታቸውን ደፍተው ቀን እየጠበቁ ባሉበት ሁኔታ የትናንት ኃይሌ ገና ለገና በሩጫ እታወቃለሁና ቦታውን ይሰጡኛል ብሎ እንዲህ ያለ ጣጣ ውስጥ መግባቱ ማንን ለማስደሰትና ሳይታወቀውም ቢሆን ማንንስ ለማስከፋት አልሞ ይሆን? በውነቱ ከያሬድ ይልቅ በዚህኛው ጉዳይ በጣም ተናድጃለሁ፡፡ የያሬድ ለዓላማ ስለሆነ ነገር ከመጠረቅና የተዳፈነ ብሶትን ከማውጣት ባለፈ ያን ያህል ልናደድበት እንደማይገባኝ እረዳለሁ፡፡ በኃይሌ ግን አንጀቴ ነው የጨሰው – የማምነውን!
የብሶት አቅማዳየን ላስር ነው፡፡ ደህና ሁኑልኝ፡፡ ኃይሌንም ይቅናው፤ ውድ ፕሬዚደንታችን ኃይሌ ሣቅ በሣቅ ሆነው እንግዳ ሲቀበሉና ሲሸኙ እያየሁ ከአሁኑ መዝናናት ይዣለሁ፡፡ የምኒልክ ቤተ መንግሥት ለአርባ አራት ሰባት ካልተጠበለ ችግሩ የሚቀረፍ አይመስልም፡፡ ለማንኛውም ቸር እንሰንብት፡፡
የጃዋር ቃለምልልስ በፓልቷክ
ከያሬድ አይቼህ -
ጃዋር መሀመድ እንግዳ ሆኖ በፓልቷክ ዛሬ እሁድ ቀርቦ ነበር። ቃለ-ምልልሱን ከ1000 በላይ ሰዎች አዳምጠዉታል። ዋናዎቹ ጠያቂዎች የሲቪሊቲው አባ-መላ (አቶ ብርሃኑ እርገጤ) እና የቃሌው ማይጨው ነበሩ።
አባ-መላ ጃዋርን አጣብቂኝ ውስጥ ለማስገባት ሞከረ። አንዴ ኦህዴድ አባል ነበርክ አለው። ጃዋር “የማንም ድርጅት አባል ሆኜ አላቅም አለ”። አባ-መላ ጃዋርን የኦሮሞ አስገንጣይ አርጎ ለማቅረብ ሞከረ ፤ አልተሳካለትም። ጃዋር መጀመሪያ ኦሮሞ ፡ ቀጥሎ ኢትዮጵያዊ መሆኑን አስረግጦ አቀረበ።
ኦሮሞ እና አማራ ምሰሶዎች ናቸው የሚለው ንድፈ-ሃሳብ ሲቀርብ ጥሩ ንድፈ-ሀሳብ ሆኖ አግኝቼው ነበር። ሆኖም ግን ኦሮሞዎችን እንደ መሰላል ተጠቅሞ ፡ የኦሮሞዎችን ብሄራዊ ማንነት ሳይቀበል ፡ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመፍጠር እንደማይቻል ግልጽ ይመስለኛል። አሁንም የኦሮሞ-አመራ ምሰሶነት ለአገራችን ነጻ መውጣት ብሩህ ተስፋ ብዬ አምናለሁ።
- ጥንድ-ምሰሶ -
የኦሮሞ-አማራ ጥንድ-ምሰሶነት ሃቅ ነው። በህዝብ ብዛት አንጻር ፡ በኢትዮጵያ መንግስት የ2004 ዓ.ም. መረጃ መሰረት ፡ የኦሮሚያ ህዝብ የኢትዮጵያ 36% ሲሆን ፡ የአማራ ክልል ህዝብ ብዛት የኢትዮጵያ 22% ነው። በድምሩ 58% ነው ፤ የሁለቱ ህዝቦች ምሰሶነት ከዚህ ጭብጥ የተነሳ ነው።
ምሰሶዎቹ በኢትዮጵያ ፓለቲካ ተወዳዳሪ የሌለው የፓለቲካ ሃይል የመሆን እምቅ ችሎታቸው ግልጽ ነው። ነገር ግን እንዴት ነው ሁለቱ ሊሂቃን ጎን-ለጎን በመቆም የኢትዮጵያ ምሰሶ የሚሆኑት? አባ-መላ እና ማይጨው በሚሉት መንገድ ሊሆን አይችልም ፤ የኦሮሞ ሊሂቃን ፡ እኛ አማራዎች በቀረጽነው ኢትዮጵያዊነት ውስጥ እንዲካተቱ ማደርግ አይቻልም።
- ኦሮሚያ –
አንዱ በተደጋጋሚ ጠያቂዎቹ ጃዋርን ለማጥቃት የሞከሩበት መንገድ “ኦሮሚያ ሚባል አገር የለም” በማለት ነው። ለመሆኑ ወፍ ዘራሽ የሆነ አገር አለ እንዴ? ሁሉም አገር ሰው ሰራሽ እኮ ነው። አሜሪካ የዛሬ 400 አመት አልነበረም ፤ አሁን ግን አለ። ኤርትራ የዛሬ 20 ዓመት በፊት አልነበረችም ፤ አሁን ግን አለች።
ኦሮሚያም አለች። ባለፉት 22 ዓመታት የኦሮሞ ህዝብ ስነልቦና በኦሮሚያዊነት ተጠግኗል ፡ ተቀርጿል ፡ ተደራጅቷል። የቁቤ ትዉልድም ወደ ሃላፊነት ተረካቢነት እየገሰገሰ ነው። የቁቤ ትውልድ የሚያቀው ኦሮሚያን ብቻ ነው ፤ ‘እምዬ ኢትዮጵያን’ አያቅም።
ይሄንን ጭብጥ አባ-መላ እና መሰል ወገኖቻችን ይክዳሉ። ነገር ግን የኦሮሞ-አማራ ሊሂቃን በህብረት መስራት ሚችሉት የአማራ ሊሂቃን የኦሮሞን ኦሮሚያዊነት ሲቀበሉና ሲያከብሩ ብቻ ነው። “መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ ፡ ቀጥሎ ኢትዮጵያዊ” የሚለውን ማንነት የማይቀበሉ የአማራ ሊሂቃን የኢህአዴግ እድሜ አስረዛሚዎች ናቸው።
የኢህአዴግ አምባገነናዊ ስርዓት ህዝባችንን በሙስና ፡ በኑሮ ውድነት ቸነፈር ፡ በፍትህ መጥፋት ፡ በሰብአዊ መብት ጥሰት ፡ በፓለቲካ እስረኝነት እና በሃይማኖት መብት ጥሰት በሚያንገላታበት በአሁኑ ጊዜ ፡ የኦሮሞዎችን ኦሮሚያዊነት አልቀበልም ማለቱ አርቆ አለማሰብ ነው።
- አማራዎች ምን እናድርግ? -
አማራዎች ራሳችንን እናስቀድም። አማራዎች በቅድሚያ ለአማራ ህዝብ መብት እንቁም። ያንን ለማድረግ የምንችለው ከኦሮሞ ወገናችን ጋር ጥንድ-ምሰሶ በመሆን እንጂ የኦሮሞን ሊሂቃን ማንነት በመናቅ አይደለም።
የኦሮሞን ማንነት ካልተቀበልን ፡ የቀድሞ ገዢዎቻችን በኤርትራ ላይ የፈጸሙትን አይነት የስትራቴጂ ስህተት እንደግማለን። የአጼ ሃይለስላሴ መንግስት ኤርትራን በኮንፌደሬሽን ከኢትዮጵያ ጋር አዋህዶ ቢሆን ኖሮ የኤርትራ ህዝብ አሁን ባለበት ስቃይ ውስጥ አይገባም ነበር ፤ የብዙዎችም ህይወት በከንቱ አይጠፋም ነበር።
የአማራ ሊሂቃን እንንቃ!! ኤርትራ ጥቂት ሚሊዮን ህዝብ ብቻ የያዘ ነው ፤ ኦሮሚያ ግን ትልቅ ነው። አቅማችንን አውቀን ከኦሮሞ ሊሂቃን ጋር በመከባበር ፡ በመቀባበል እና በጋራ ጥቅም ላይ ባተኮረ ስትራቴጂ አሁን በላያችን ላይ የተንፈራጠጠውንና የበሰበሰውን የህወሃት መንግስት በቀላሉ ማንበርከክ እንችላለን።
አባ-መላ : ማይጨው እና እንዲሁም እነሱን መሳይ ወገኖቼ፦ የሻገተውን ፡ ያለፈበትን እና የነፈሰበትን ፤ እንዲሁም አማራዊነት የበላይ የሆነበትን ኢትዮጵያዊነት ለታሪክ እንተወው። ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን በቂ ምህዳር ባለው መድብለ-ብሄር ማንነት እንተካው።
ህወሃት በተንገዳገደበትና በበሰበሰበት በዚህ ወቅት አዲስ አስተሳሰብና አዲስ እይታ በመያዝ ለኢትዮጵያውያን ነጻነት እንታገል። የኦሮሞና-አማራ ሊሂቃን በዚህ መልክ በመስራት ወደ ድል እንገስግስ።
ከአክብሮት ጋር!
ቪቫ ኦሮሚያ! ቪቫ ኢትዮጵያ!
- – - – - – -
የጸሃፊው አድራሻ፦ yared_to_the_point@yahoo.com
በአዲስ አበባ የወተት እጥረት ተከሰተ; 1 ማኪያቶ 8 ብር ገባ
(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ የወተት እጥረት በከፍተኛ ደረጃ መከሰቱን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ:: ይህን ተከትሎ የአንድ ማኪያቶ መሸጫ ዋጋ 8 ብር መግባቱም በከተማዋ አነጋጋሪ እየሆነ መጥቷል::
በአዲስ አበባ የወተት እጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ነዋሪዎች በይፋ መናገር መጀመራቸውን ያስታወቁት መገናኛ ብዙሃኑ በወተት ላይ እጥረት ብቻ ሳይሆን የዋጋ መወደድም መስተዋሉ እያስቆጣቸው መሆኑ ታውቋል::
በካፌዎች የአንድ ስኒ ማኪያቶ ዋጋ እስከ 8 ብር መድረሱን የካፌ ተጠቃሚዎችም እየተናገገሩበት መሆኑን የሚዘግቡት መንግስታዊው ሚዲያዎች የካፌ ባለቤቶች የወተት መጥፋት ለእነሱም ስራ ማነቆ መሆኑን በመግለፅ ቀደም ሲል ከሚገዙበት ዋጋ በላይ ለመግዛትም አንዳንዴ ጨረታ እንደሚገቡም ብሶታቸውን ገልጸዋል::
ከዚህ በፊት ለጋዝና ለዳቦ እንደነበረው ወረፋ ሁሉ በአሁኑ ወቅት በስድስት ኪሎና በሌሎች አካባቢዎች በተለይ ጠዋት ጠዋት ወተት በማከፋፈያዎች ሱቅ በር ላይ ረጃጅም ሰልፎችን ማየት የተለመደ እየሆነ የመጣ ሲሆን በእነዚህ ማከፋፈያዎች ውስጥም አንድ ሊትር ወተት እስክ ከ16 እስከ 18 ብር ድረስ ዋጋ እየተሸጠ መሆኑ ተዘግቧል::
አንድነት አባሎቼን በማሰር የማደርገውን የሕዝብ ንቅናቄ ማደናቀፍ አይቻልም አለ
ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
አንድነት ፓርቲ የሶስት ወራት የህዝባዊ ንቅናቄ የትግል ስልቱ የመጀመሪያውን የአደባባይ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ሰኔ 30/10/2005 ዓ.ም በጎንደር ከተማ እንደሚያደርግ ማሳወቁ የሚታወስ ነው፡፡ ሁልጊዜም ህግ ጠብቆ በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሰው ፓርቲያችን የአገሪቱ ህገ መንግስት በሚደነግገው መሰረት የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ለሰሜን ጎንደር ዞን ማወቅ ለሚገባቸው የመንግስት አካልና ለከተማ መስተዳድሩ አሳውቆ ወደ ቅስቀሳ ከገባ ጥቂት ቀናት አልፈዋል፡፡
ምንም እንኳን ህግ አክብረን ሰላማዊ ትግላችንን ብንቀጥልም በሰሜን ጎንደር ዞን በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ አብርሃ ጅራ ከተማ የፓርቲያችን አባላት የሆኑት አቶ አለልኝ አባይ፣ አቶ እንግዳው ዋኘው፣ አቶ አብርሃም ልጃለምና አቶ አንጋው ተገኝ አንድነት ፓርቲ የሰጣቸውን ተልኮ ተቀብላችሁ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ለምን በተናችሁ ተብለው ከቅዳሜ ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ አቶ ማህሙድ ሸሪፍ፣ አቶ ጀማል ሰይድና አቶ አለሙ አባይነህ ፓርቲው የጀመረውን የሚሊዮኖች ድምፅ የሚያሰባስብ ፔቲሽን ለምን ታስፈርማላችሁ ተብለው ታስረዋል፡፡
ይህ ተግባር ህጉን ጠብቆ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ፓርቲያችን ላይ አሁንም በገዥው ፓርቲ ህግ ጥሶ ሰላማዊ ሰልፉን የማደናቀፍ ተግባር እየተፈፀመ ስለመሆኑ ግልጽ ማሳያ ነው፡፡ ይህና ሌሎች የገዢው ፓርቲ እኩይ ድርጊቶች አንድነትን በፍፁም ወደኋላ ሊመልሱት እንደማይችሉ ማሳወቅ እንወዳለን ፡፡ ይህን በድፍረት እንድንናገር ያስቻለን ከዓላማ ቁርጠኝነታችን በተጨማሪ ህግ አክባሪነታችን ነው፡፡ ስለዚህ በቅስቀሳ ቡድኑ ላይ ከሚካሄደው ዛቻና ማስፈራሪያ ውጭ በተለያዩ ወረዳዎች የፓርቲያቸውን ተልዕኮ ለማሳካት በፍፁም ሰላማዊነት እየሰሩ ያሉ አባላት ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ትግላችንን ሊቀለብሰው እንደማይችል ተገንዝቦ መንግስት ከህገ ወጥ ድርጊቱ እንዲቆጠብ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡
እነዚህ አባሎቻችንም በአስቸኳይ እንዲፈቱ እየጠየቅን ምንም አይነት ህገ ወጥ እርምጃ መብታችንን ከመጠየቅ እንደማይገድበን በድጋሚ ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡
በዚሁ አጋጣሚ ገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና የፀጥታ ሀይሎች በአንድነት አባላት ላይ እየወሰዱ የሚገኙትን እስርና ማስፈራሪያ ፊትለ ፊት በመቃወም ቁርጠኝነቱንና አጋርነቱን በማሳየቱ አንድነት ፓርቲ ለጎንደር ህዝብ የአክብሮት ምስጋናውን ያስተላልፋል፡፡
የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት!!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ሰኔ 24 ቀን 2005 ዓ.ም
አዲስ አበባ
አቶ ታምራት በንግድ ተሰማሩ፤ ቢተው ስልጣን ያዙ
( ከኢየሩሳሌም አርአያ)
በአሜሪካ ዴንቨር ከተማ ከቤተሰባቸው ጋር የሚኖሩት አቶ ታምራት ላይኔ የጋዝ እስቴሽን በመክፈት በንግድ ስራ መሰማራታቸውን ምንጮች ገለፁ። በሙስና ወንጀል ተከሰው ለአስራ ሁለት አመት ታስረው የወጡት አቶ ታምራት ከተፈቱ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ፥ አማኝ ሆነው እንደሚቀጥሉና ነገር ግን በማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከማንም ፖለቲካ ድርጅት ጋር ሳይወግኑ ለአገር ይጠቅማል የሚሉትን ሃሳብ እንደሚያካፍሉ፣ መፅሃፍ እንደሚያዘጋጁ…ገልፀው እንደነበር ያስታወሱት እነዚህ ወገኖች፣ ታምራት ያንን ቢናገሩም በቃላቸው ግን እንዳልተገኙ አስረድተዋል። « የኢየሱስ አገልጋይ ሆኜ እኖራለሁ» ያሉት ታምራት አሁን ወደ ንግድ አለም መግባታቸው እንዳስገረማቸው ምንጮቹ ጠቁመዋል። ሌላው ቢቀር በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ለሰሩት ጥፋት ህዝብን ይቅርታ ያለመጠየቃቸው አስገራሚ ነው ያሉት እነዚህ ወገኖች፣ በይፋ አደባባይ ወጥተው ህዝብን ይቅርታ የጠየቁት ዶ/ር ነጋሶና አቶ ገብሩ ብቻ እንደሆኑ አስታውቀዋል። አቶ ታምራትና አቶ ስዬ ግን ይህን ለማድረግ ጨርሶ እንደማይፈልጉ ከያዙት አቋም በቀላሉ መረዳት ይቻላል ብለዋል።
በሌላም በኩል የሕወሐት ማ/ኮሚቴ አባል የነበሩትና ደቡብን በበላይነት ሲያሽከረክሩ ቆይተው በ1993ዓ.ም በሙስና ወንጀል ተከሰው የታሰሩት አቶ ቢተው በላይ ለስድስት አመት ታስረው ከተፈቱ በኋላ በአቶ መለስ ዜናዊ የአፋር ክልል አማካሪ ተደርገው ተሹመው እንደነበረ ምንጮች አጋለጡ። ከአቶ አባተ ኪሾ ጋር ተከሰው የነበሩትና ከሕወሐት ተገንጥሎ ከወጣው <አንጃ> ቡድን አንዱ የነበሩት አቶ ቢተው ተመልሰው የመለስ አገልጋይ መሆናቸው ብዙዎችን ግራ ያጋባ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በአፋር ክልል አማካሪ ሆነው ለሶስት አመት የሰሩት ቢተው በአሁኑ ወቅት በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሎጅ ተዛውረው በመስራት ላይ እንደሚገኙ ምንጮቹ አረጋግጠዋል። የአቶ ቢተው ወንድም ኮ/ል ሲሳይ (በቅፅል ስሙ ሃመዴ) ጀግና ኢትዮጲያዊና አገሩን የሚወድ ታታሪ እንደነበርና በአሰብ ውጊያ ከነሂሊኮፕተሩ ጋይቶ ማለፉን ምንጮቹ አመልክተዋል። አንድም ቀን ስሙ በነመለስ ተነስቶ የማያውቀውና የጡረታ መብቱ እንኳ ሊከበርለት ያለቻለው ሟቹ ኮ/ል ሃመዴ ልጆቹ ያለአሳዳጊ ተበትነው መቅረታቸውን ምንጮቹ ሳይገልፁ አላለፉም።
ድምጻዊያን አምና በዳላስ ዘንድሮ በሜሪላንድ
ጥበቡ ተቀኘ
ባለፈው አመት የአሜሪካን እትዮጵያዊያን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሁለት በተከፈለበት ጊዜ ብዙ አርቲስቶቻችን ጥሩ ጥሩ ዳጎስ ያለ ብር በአላሙዲን ተከፍሏቸው ዲሲ ሲመጡ ያዩትን ውርደትና ቅሌት እነሱም ብሩን የሚያፈስላቸውም የማፍያ ግሩፕ የሚረሱት አይመስለኝም:: በተቃራኒው ደግሞ ዳላስ የነበረውን ዋናውን ፌዴሬሽን ለማገዝ ጥበብን ከህዝብ ጋር ካልሆነ በምንም አይነት ለብር አንገዛም በማለት የፈጣሪ ስጦታቸውን ተጠቅመው ህዝቡን ያዝናኑት እና ከጎኑ የቆሙት ያዩትን ደስታ እና አለም ታሪክ ሁልጊዜ በመልካም ሲያነሳው ይኖራል::
የጥበብ ባለሙያዎች ከህዝብ ውጭ ሌላ ምንም ሃብት እንደሌላቸው የታወቀ ነው:: ሲዲያቸውን የሚገዛው ኮንሰርታቸውን የሚታደመው በጭብጨባ የሚያበረታታቸው ህዝብ ብቻ ነው:: አላሙዲን የሚባለው ክፉ ጦስ ኪሳቸውን በጉርሻ ሲያሳብጠው ህዝብ ምን ያደርጋል? ብለው ለሃብታሞች ብቻ ለመዝፈን መወሰናቸው በጣም የሚያሳፍርና የሚያኮላሽ ተግባር ነው:: ዛሬ እንዲህ አይነት ተራ አስተሳሰብ ይዘው የሚጓዙትን እድሜ ይስጠንና እናያቸዋለን ነገ ስራዬን አድምጡልኝ ማለታቸው አይቀርምና::
ባለፈው አመት ዳላስ ከህዝባቸው ጎን በመቆም መከፋፈልን ሳይሆን አንድነትን ሲዘምሩና ሲዘፍኑ ከነበሩት ስመ ጥር ድምጻዊያን መካከል ማህሙድ አህመድ ጸሃይ ዮሃንስ አብዱ ኪያር እና ጎሳዬ ተስፋዬ ይጠቀሳሉ:: እነዚህ ታላላቅና ዝነኛ የኪነ ጥበብ ሰዎች የሚከፈላቸው ተራ የአላሙዲን ጉርሻ ሳያዝጎመዣቸው ህዝቡን ሲያዝናኑና አደራቸውን ሲወጡ ምን ያህል ክብርና ፍቅርን እንደሚያካብቱ ማሰብ የሚከብድ አይመስለኝም:: አንዳንዶቹ ድምጻዊያን ደግሞ ከሁለቱም ኳስ አንወግንም ብለው እንዳልሰሩ የማይካድ ሃቅ ነው ዛሬ ግን ድል ከህዝቡ ጋር እንደሆነ አውቀው ተቀላቅለውናል እናከብራቸዋለን:: ለክፉ ጊዜ ባይሆኑም ከመሰሪው አላሙዲን ጋር ባለመሆናቸው አስደስቶናል::
ዘንድሮ ያለፈውን ውርደት ለመድገም ወደ ዲሲ የመጡት ድምጻዊያኖችም ዲሲ አካባቢ በነጻነት የሚዟዟሩ አይመስለኝም ምክንያቱም ግልምጫውንና ስድቡን የሚችል አቅም ያላቸው ስለማይመስለኝ ነው:: ለነገሩ እንኳን እነሱ ዋና አዘጋጆቹም ቢሆን የአበሻውን ተቃውሞ እንደ ጦር እየፈሩ እንደሚጓዙ በአይናችን እያየነው ነው:: እንደውም እዚ ጋር አንድ ወዳጄ ያጫወተኝ ትዝ አለኝ:: ባለፈው መለስ ዜናዊ እዚህ አሜሪካ በአበበ ገላው ድምጽ እንደደነገጠ በዛው ሞቷል አሁን ደግሞ አላሙዲን ይሰደብና ደንግጦ አገር ቤት ሲመለስ ይሞታል ተብሎ እነደሚቀለድ ነግሮኛል:: ይህ መቼም የሚያሳየው ሰዎቹ ምን ያህል ህዝብን አንቀጥቅጠው እንደሚገዙ ነው አንድ ሰው እነሱን ክፉ መናገር አይፈቀድለትም:: ወይኔ ያገሬ ሰው!!
የኔ እምነት ማንም ሰው የፈለገውን የመደገፍና የመቃወም መብት እንዲሰጠው ነው ግን 30 አመት ያደረገን አንድ የኢትዮጵያውያን መገናኝ ኳሳችንን ለመበተን ለመከፋፈል እና ለወያኔ አላማ ለማዋል የሚደረገውን ጥረት እቃወማለሁ:: የሚደግፉትም አምነውበት ከሆነ ግድ የለኝም ውጤቱ እንዲህ 30 ሺ ለ ዜሮ መሆኑን ሲያውቁት ስህተት መሆኑን ሊረዱት ይገባል ባይ ነኝ::
የመደገፍና የመቃወም መብቴንም እያየሁት ያለሁት እዚህ አሜሪካ ነው እንጂ አገር ቤትማ ያለው ኢትዮጵያዊ በሙሉ ይህን እድል አላገኘውም የኢህአዴግ ደጋፊ ወይም አባል ካልሆነ አይማርም ቢማርም አይመረቅም ቢመረቅም ስራ አያገኝም ቢያገኝም አያድግም…. ኢህአዴግን መቃወም ሙሉ በሙሉ ወንጀል በመሰለበት በዚህ ጊዜ የአገር ውስጡ አልበቃ ብሏቸው ውጭ አገር ያውም አሜሪካ መጥተው ያልንህን ታደርጋለህ በሚል ማን አለብኝነት ሊበትኑን እና አፋችንን ሊያዘጉ ሲፈልጉ በጣም ይገርመኛል:: ታዲያ እነዚህን በመናቅና በብዙ ሚሊዮን ዶላር ያዘጋጁትን ድግስ ባለመሄድ ኢትዮጵያዊው ሁሉ ሲቀጣቸው ማየትና የታሪክ ምስክር መሆን እንዴት ደስ ይላል?
የተቆጣን እና በአላሙዲን የክፋት ተግባር የተናደድን ህዝቦች በመተባበር የምናደርገው ነገር ሁሉ ስሜት የሚነካ ነው ባለፈው አመት ዳላስ ላይ ስታዲየሙ በህዝብ ሞልቶ ሆ ሲል በአይኔ አይቻለው አሁን ደግሞ ሜሪላንድ የመክፈቻውን ስነስርአት የነበረው ዝናብና የተፈራው ስቶርም ሳይበግረው ይሄ ሁሉ ህዝብ ባንዲራውን ለብሶና ይዞ ሲከታተለው አይቻለው:: በጣም የሚይስደንቅና በቃላት ሊገለጽ የማይችል ከባድ የአገር ፍቅር ስሜትም ተሰምቶኛል::
መቼም ፈጣሪ ለኪነጥበብ ሰዎች የሰጣቸው የተፈጥሮ ስጦታ ይገርመኛል:: ያንን ሁሉ ሺ ህዝብ እያስደሰቱ መኖር ምን ያህል መታደልን እንደሚጠይቅ መቼም ለሁሉም ግልጽ ነው:: ባለፈው አመት ዳላስ ላይ ገጣሚ የዜማ ደራሲ እና ድምጻዊው አብዱ ኪያር እየዘፈነ የተሰማኝን ስሜት በምንም መልኩ ልገልጸው አልችልም:: መላ አካላቴን ውርር አድርጎኝ እንባ እንባ ይለኝም ነበር:: ህዝቡ በሙሉ ከዘፈኑ ጋር ያሳየው የነበረው እንቅስቃሴ ሁሉ አይኔ ላይ አለ::
ያልገቡበት የለም ያልገቡበት የለም
ሙቀትና ብርዱን ችለው በዚች አለም
ይቺ ቀን ታልፋለች እያሉ በማለም
ስትጣሪ ያልመጡት ጠልተውሽ አይደለም
እናቱን ሚጠላ ካንቺ አልተፈጠረም
የከዳማ እናቱን
እንጃ አበሻነቱን…..
ዘንድሮ ደግሞ በሜሪላንድ የመክፈቻው ስነ ስርአት ላይ እነዛን በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ አርንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ያላቸው አፉፋዎች የባህል ቡድኑ ወደ ሰማይ ሲለቋቸው ሳይ ይኸው ከባድ የአገር ፍቅር ስሜት መልሶ ነፍሴን ሲተናነቃት ይታወቀኝ ነበር:: ስሜቴን ደግሞ ይባስ ያወጣው የድምጻዊው ብርሃኑ ተዘራ(ያምቡሌ) የዘፈን ግጥም ነበር
ይሄ ሰው አማራ እረ ሚለው ማነው
ይሄ ሰው ኦሮሞ እረ ሚለው ማነው
ይሄ ሰው ከትግራይ እረ ሚለው ማነው
ይሄ ሰው ከደቡብ እረ ሚለው ማነው
ቢለያይም ቋንቛው ደማችን አንድ ነው
በናቴም አንድ ነኝ ባባቴም አንድ ነኝ
ከኢትዮጵያ አገሬ የለም የሚለየኝ….
የጥበብ ሰዎች ይህን ሁሉ የአምላክ ስጦታ ይዘው ከህዝባቸው ጎን ካልቆሙ በጣም የመሸማቀቅና የውርደት እድሜ እንደሚገፉ በታሪክ ያየነው ነው:: አላሙዲንም ወያኔም ያልፋሉ ያኔ ከህዝብ ፊት እንዴት ልትቆሙ ነው ምንስ ልትሉ ነው ማለት ይኖርብኛል ብዬ አምኛለሁ::
ይሄንን ጽሁፌን ከማጠቃለሌ በፊት ኳስና ዘፈን እንዲህ የህዝቡን ልብ ማማለል ከቻሉ ፖለቲከኞቻችንም ይህንን ጥበብ ሊካኑት ይገባል ባይ ነኝ:: መልካም የፍቅር እና የደስታ ኳስ ያርግላችሁ::
ጥበቡ ተቀኘ
July 01 2013
ዶ/ር መረራ ከአባይ ግድብ ይልቅ ለምግብ ዋስትና ቅድሚያ እንደሚሰጡ አስታወቁ
(ዘ-ሐበሻ) የመድረክ ከፍተኛ አመራር አባል ዶ/ር መረራ ጉዲና ከመንግስታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እርሳቸውና ድርጅታቸው ስልጣን ላይ ቢወጡ በቅድሚያ ለዜጎች የምግብ ዋስትና እንደሚሰጡ አስታወቁ። የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ዶ/ር መረራ በአባይ ጉዳይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሰጡት በዚሁ ቃለ ምልልሳቸው “በእኔ እይታ ጉዳዩን ስመለከተው ግብጾች ጦርነት ውስጥ ይገባሉ የሚል እምነት የለኝም፡፡ ሌሎች ብዙ አማራጮች አሏቸው፡፡ ግድቡ ተሰርቶ እንዳያልቅ ሊያደርጉ የሚያስችሉ የተሻሉ መንገዶች አሏቸው፡፡” ብለዋል። ቃለ ምልልሱ ለግንዛቤዎ ይጠቅማል ብለን ስላሰብን እንደወረደ አስተናግደነዋል።
አዲስ ዘመን፡- እንደ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲም ሊሆን ይችላል እንደ ተራ ኢትዮጵያዊ ወይንም ዜጋ ከግብጽ የምንማረው ነገር አለ፡፡ ግብጾች የቱንም ያህል መንግሥታቸውን አምርረው ቢጠሉ በሀገር ጉዳይ ግን ምንጊዜም አንድ ናቸው፡፡ በተለይ ደግሞ በዓባይ ላይ ያላቸው አቋም የተለየ ነው፡፡ ይሄንንም በቀጥታ ከተላለፈው የቴሌቪዥናቸው ስርጭት መረዳት እንችላለን፡፡ ወዲህ ወደ እኛ ሀገር ስንመለስ ግን በአባይ ላይ እንኳን አንድ መሆን አልቻልንም፡፡ በእዚህ ዙሪያ ምን አስተያየት አለዎት?
ዶክተር መረራ፡- እኔ ከምንም በላይ የምለው ኳሱ ያለው በኢህአዴግ ሜዳ ላይ ነው፡፡ በኢጣሊያ ዘመን ያየነው ነገር ነው፡፡ በእዚያ ዘመን የኢጣሊያን ባንዳ ሆነው ፔሮል ላይ ሳይቀር የሰፈሩና ያገለገሉ ኢትዮጵያውያን ነበሩ፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ኃይለሥላሴ ሌላ ኢትዮጵያ ሌላ ብለው ከእሥር ቤት ወጥተው የተዋጉ እንደ ባልቻ አባነፍሶ ያሉ ኢትዮጵያውያን ነበሩ፡፡ ከእዚህ የምንማረው ምንድን ነው፣ መንግሥት ስትሆን ቀዳዳ እንዳይከፈት ማድረግ አለብህ፡፡ በሀገር ፖለቲካ ላይ ብሔራዊ መግባባት ካልፈጠርክ ግብጾች ነገም ሆነ ከነገ ወዲያ የውጭን ኃይል ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡
ላለፉት 150 ዓመታት ያለውን የኢትዮጵያን ታሪክ ስናየው ደግሞ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከውጭ እጅ ነፃ የሆነ አይደለም፡፡ ከአጼ ቴዎድሮስ ጀምሮ አሁን እስካለው የኢህአዴግ መንግሥት ድረስ ያለው እውነታ የሚያስረዳው ይሄንን ነው፡፡
መንግሥት በሀገር ጉዳይ ላይ ተቃዋሚዎችን በሙሉ ልብ እንዲሳተፉ ካላደረገ ከእኔ ጋር አልተሳተፉም ብሎ ጧትና ማታ መጮሁ ዋጋ አይኖረውም፡፡ ተቃዋሚውም በማይሆን መንገድ በሀገር ጉዳይ ላይ መደራደር የለበትም፤ ይሄ ምንም ጥያቄ የለውም፡፡ መንግሥትም ቢሆን ሥልጣን ላይ ለመቆየት ሲል ብሔራዊ ጥቅም የሚጎዳ ነገር መፈጸም የለበትም፡፡ ስለዚህ በሁለቱም ወገን ጉዳዩ መታያት አለበት፡፡ ኢህአዴግ በሀገር ጉዳይ ላይ ከተቃዋሚዎች ጋር ብሔራዊ መግባባት መፍጠርና ወደ ውጪ እንዳያዩ ማድረግ ካልቻለ ዋናው ጥፋተኛ መንግሥት ነው የሚሆነው፡፡ ከዚያ ውጭ ያለው ክርክር የሚያስኬድ አይደለም፡፡
አዲስ ዘመን፡- በእዚህ ወሳኝ ወቅት ላይ መንግሥት በአባይ ዙሪያ ምን ማድረግ አለበት ነው የሚሉት?
ዶክተር መረራ፡- እኔ አሁን ኢህአዴግ በገባበት ደረጃ የተሻለውን የሚያውቀው እራሱ ኢህአዴግ ብቻ ነው።
አዲስ ዘመን፡- በዲፕሎማሲው ይቀጥል ማለትዎ ነው?
ዶክተር መረራ፡- ይሄ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ቅድሚያ የሚሰጠው ለዲፕሎማሲ ነው፡፡ በእኔ እይታ ጉዳዩን ስመለከተው ግብጾች ጦርነት ውስጥ ይገባሉ የሚል እምነት የለኝም፡፡ ሌሎች ብዙ አማራጮች አሏቸው፡፡ ግድቡ ተሰርቶ እንዳያልቅ ሊያደርጉ የሚያስችሉ የተሻሉ መንገዶች አሏቸው፡፡
አዲስ ዘመን፡- ለምሳሌ እንዴት ዓይነት?
ዶክተር መረራ፡- ቀዳዳዎችን በመጠቀም ሊሆን ይችላል፡፡ ሶማሊያ አለች፤ ለአልሸባብ የፈለጉትን ማቀበልም አለ፤ ጂቡቲንም ማባበል ይኖራል፤ እኔ እዚህ ጨዋታ ውስጥ አትገባም ብዬ የማስበው ኬንያን ብቻ ነው፡፡ እርሷም ብትሆን አንዳንድ ጊዜ አይታ እንዳላየች የምትሆነው ነገር አላት፡፡
ስለዚህ የዲፕሎማሲው መንገድ ካልሰራላት ግብፅ የምትከተለው መንገድ ይሄ ነው የሚሆነው፡፡ ግድቡ እዚያ አይደርስም እንጂ ተሰርቶ ካለቀ ግን የግድቡን ደህንነት የምትጠብቀው እራሷ ግብፅ ነው የምትሆነው፡፡ ምክንያቱም ግድቡ አንድ ነገር ከሆነ ውሃው ጠራርጎ ይዞ የሚሄደው ግብፅን እንጂ ኢትዮጵያን አይሆንም፡፡ ኢትዮጵያም በዲፕሎ ማሲው መግፋት እንዳለ ሆኖ እስከዚያው ራሷን ማደራጀት አለባት፡፡
ግብፅ ሠራዊቷን ልካ ኢትዮጵያን ትወራለች የሚል እምነት የለኝም፡፡ ከእዚያ ይልቅ መንግሥትን ሊያዳክሙ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭንም ብቻ ሳይሆን የውስጡንም የቤት ሥራ መስራት አለበት፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ እየተራበ ግብፅ የተሻለ እየተመገበች መቀጠል አይኖርብንም፡፡ በመሆኑም የራስህን ጥቅም አሳልፈህ በማይሰጥ መልኩ መደራደር ያስፈልጋል፡፡
አዲስ ዘመን፡- ለመጨረሻ ጊዜ ልጠይቅዎት፡፡ በእርስዎ ግምት የግድቡ ግንባታ ይሳካል ብለው ያምናሉ? እርስዎስ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊም ሆነ የመንግሥት ሠራተኛ ለግደቡ ቦንድ ገዝተዋል?
ዶክተር መረራ፡- ግድቡ ያልቃል የሚለው ላይ ጥርጣሬ አለኝ፡፡ ምክንያቱም በዜሮ ባጀት እየተሠራ ያለ ፕሮጀከት ነውና፡፡ እስካሁን የተሰበሰበው ብርም ከ10 በመቶ በላይ ሊሆን አልቻለም፡፡ ስለዚህ የሀገሪቷን ሀብትና ባጀት ሁሉ ወደ ፕሮጀከቱ ማዞር ነው ያለው አማራጭ፡፡ ይሄ ደግሞ የራሱ ችግር አለው፡፡ ስለዚህ በቀላሉ ያልቃል ብዬ አላምንም፡፡ የውጭ ጣጣ ሲጨመርበት ደግሞ ችግሩ በዚያው ልክ ይጨምራል፡፡ የቦንድ ግዥን በተመለከተ ወደድንም ጠላንም ዩኒቨርሲቲው የአንድ ወር ደመወዛችንን በዓመት ተከፍሎ የሚያልቅ ብሎ ወስዷል፡፡
አዲስ ዘመን፡- እርስዎ ተስማምተዋል?
ዶክተር መረራ፡- እኔ በእውነቱ አልተጠየኩም፤ በግድ ነው የተወሰደብኝ፡፡ ዩኒቨርሲቲው ሦስት አራት ሰው አነጋግሮ ሠራተኛው ወስኗል ማለቱ አግባብ አይደለም፡፡ ይሄንንም በግልጽ በደብዳቤ ጋዜጣ ላይ የጻፉ አሉ፡፡
አዲስ ዘመን፡- ወደ እርስዎ ልመለስና፣ እርስዎ ቢሮዎ ለግድቡ አስተዋፅኦ ያድርጉ የሚል ደብዳቤ ወይንም ቅጽ ቢመጣልዎት ይፈርማሉ?
ዶክተር መረራ፡- እርሱን እንኳ ያን ጊዜ ምን እንደማደርግ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ነገር ግን በፈቃደኝነት ፈርሙ ቢባል ብዙ ሰው አይፈርምም የሚል እምነት አለኝ፡፡
አዲስ ዘመን፡- ጥሩ መንግሥት ተከዜን በአራት ቢሊዮን ብር፣ ጣና በለስን በሰባት ቢሊዮን ብር በራሱ ወጪ ሰርቶ አሳይቷል፡፡ አሁንም ጊቤ ሦስተኛን በራሱ ወጪ እያሠራ ነው፡፡ እንደው እነዚህን ነገሮች ሲመለከቱ የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሰርቶ ይጨርሰዋል የሚል ጥርጣሬ አያጭርብዎትም?
ዶክተር መረራ፡- ሁለቱ ግድቦች የነበረባቸው ችግር የገንዘብ ብቻ ነው፡፡ ይሄ ግድብ ግን ችግሩ የገንዘብ ብቻ አይደለም፡፡ የውጭ አይኖች ሁሉ ኢትዮጵያ ላይ እንዲሆን ያደረገ ፕሮጀክት ነው፡፡ የአረቡ ዓለምንም በኢትዮጵያ ላይ ሊያስነሳ ይችላል፡፡ ከውስጥም ከውጭም በቂ ድጋፍ ሳይኖርህ ጠንከር ያለ የውጭ ዓለምም ተቃውሞ እየገጠመህ በቀላሉ የምታሳካው ፕሮጀክት አይደለም፡፡ ግድቡ እስኪያልቅ ድረስ ሌሎች ፕሮጀክቶችን ሁሉ ልታጥፍ፣ ግሽበት ውስጥ ሁሉ ልትገባ ትችላለህ፡፡
አዲስ ዘመን፡- እስኪ ወደ ሌላ ሃሳብ ልውሰድዎት፡፡ ግብጾች በተደጋጋሚ የሚያነሷ ቸው የ1929 እና የ1959 ስምምነቶችን ነው፡፡ አሁን ደግሞ የተፋሰሱ የላይኛው አገሮች የተፈራረሙት የኢንቴቤው ስምምነት አለ፡፡ እነዚህን ስምምነቶች እንዴት ያዩዋቸዋል?
ዶክተር መረራ፡- ይሄ ምንም የሚያነጋግር ነገር አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ላልፈረመችበት ሕግ የምትገደድበት ምክንያት የለም፡፡ ያ የቅኝ ግዛት ሕግ መቀየር አለበት፡፡ 86 በመቶ የሚያመነጭ አገር እንዴት አንድ ሊትር ውሃ እንኳን አይሰጠውም፡፡
አዲስ ዘመን፡- እርስዎ እንደ ግለሰብ ወይንም በፓርቲዎ ደረጃ መንግሥት ቢሆኑ ቅድሚያ የሚሰጧቸው ፕሮጀክቶች ምን ምን ይሆናሉ?
ዶክተር መረራ፡- እኔ ለምግብ ዋስትና ቅድሚያ እሰጣለሁ፡፡ በእዚህ ላይ መረባረብ ያስፈልጋል፡፡
አዲስ ዘመን፡- ይሄስ ቀላል የሚሆን ይመስልዎታል፣ ግብጾችስ ዝም የሚሉ ይመስልዎታል?
ዶክተር መረራ፡- አልኩህ እኮ ግብጾች ሊቃወሙ ይችላሉ፡፡ ትንንሽ ፕሮጀክቶችን እየተጠቀምክ ግን አቅምህን ታዳብራለህ፡፡ በመጨረሻ ይጠቅማል ከተባለ ከ30 ወይንም ከ40 ዓመት በኋላ ወደ አባይ ልትሄድ ትችላለህ፡፡ ያን ጊዜ ግብጾችም ሊያግዙህ ይችላሉ፡፡ ግብጾችም ብዙ ውሃ እንዲመነጭ የኢትዮጵያን ደን በማልማት በኩል እንዲገቡ አደርጋለሁ፡፡ እነርሱ ዛሬ የሚያስቡት ኢትዮጵያን ማልማት ሳይሆን ውሃውን ወደ ሲና በረሃ አሻግረው ለእስራኤል መስጠትን ነው፡፡
ሌላው ኢህአዴግ ለሚለው የገጠር ልማትና ኢንዱስትሪ ቅድሚያ እሰጣለሁ፡፡ ኢህአዴግ እኮ ዝም ብሎ ይጮሃል እንጂ በገጠር ልማት ላይ አልሠራም፡፡ ገና ብዙ ሥራዎች ገበሬው ላይ አልተሰሩም፡፡ አሁንም ድረስ ገበሬው የሚጠቀመው የ13ኛው ክፍለ ዘመን አስተራረስን ነው፡፡ ይሄንን ካልቀየርክ ለውጥ አታመጣም፡፡
አዲስ ዘመን፡- ግን እኮ ዶክተር ምርታማነት ጨምሯል?
ዶክተር መረራ፡- ይሄንን እኮ ኢህአዴግ በባህርዳሩ ጉባኤው አምኗል፡፡ ካድሬው ለምቷል፡፡ ገበሬው ግን ገና ነው፡፡ በሚፈለገው መጠን አልለማም፡፡ ስለዚህ ለመስኖ ትኩረት መስጠትና የግብርና አብዮት ማምጣት ያስፈልጋል፡፡ ከዚያ በኋላ ነው የኢንዱስትሪ ጥያቄ መምጣት ያለበት፡፡ የኢንዱስትሪ አብዮት ካላመጣህ ደግሞ ኢትዮጵያን የትም ማድረስ አትችልም፡፡
አዲስ ዘመን፡- ዶክተር ለሰጡኝ ማብራሪያ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ ምናልባት የግድቡ ግንባታ ሲጠናቀቅ ደግሞ መጥቼ አስተያየትዎን እወስድ ይሆናል…
ዶክተር መረራ፡- (ከረጅም ሳቅ በኋላ) ምንም ችግር የለውም፡፡ ለእዚያ ያብቃን፡፡ ያን ጊዜ መወቃቀስም መሞጋገስም ይቻላል፡፡
Sport: የባርሴሎናው ቴክኒሻን ኢኔሽታ ውለታውን እየመለሰ ነው
በውጤታማው የካታላኑ ክለብ በባርሴሎናና በስፔን ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ቴክንሽያንነቱ ይታወቃል የ29 ዓመቱ አንድሬስ ኢኔሽታ።
በአውሮፓውያኑ 1996 በአስራ ሁለት ዓመቱ ይስፔኑን ኃያል ባርሴሎናን ከመቀላቀሉ በፊት በአገሪቱ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ቢ በመወዳደር ላይ ለሚገኘው አልባሴቴ በተሰኘው እግር ኳስ ነው ከእግር ኳስ ስፖርት ጋር የተዋወቀው።
ተጫዋቹ ታዲያ የቀድሞ ክለቡ ወደ አራተኛው ዲቪዚዮን ከመውረድ በመታደግ ውለታ መላሽነቱን አስመስክሯል።
ለተጫዋቾቹ ደመወዝና ላለበት የተለያዩ ዕዳዎች የሚከፍለው ገንዘብ በማጣቱ ምክንያት ካለበው ዲቪዚዮን ወደ ታችኛው ዲቪዚዮን የመውረድ ከፍተኛ አደጋ ተጋርጦበት የነበረውን የልጅነት ክለቡን አልባሴቴን ሁለት መቶ ሺ ፓውንድ በመስጠት አለሁልህ ማለቱን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ተጫዋቹ የክለቡ ከፍተኛ የአክሲዮን ድርሻ ባለቤት ሲሆን ከሁለት ዓመታት በፊት በተመሳሳይ አራት መቶ ሺ ፓውንድ ድጋፍ ማድረጉን ዘገባዎቹ አስታውሰዋል።
በፊፋ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር የአውሮፓና የዓለም ዋንጫ ያነሳው የ29 ዓመቱ ኢኔሽታ በአልባሴቴ እግር ኳስ ክለብ ሁለት ዓመት ቆይቷል።
በተያያዘ ዜና የባርሴሎና የከተማ ተቀናቃኝ የሆነው የስፓኞል እግር ኳስ ክለብ ፐሬዚዳንት ዮአን ኮሌት ባርሴሎና ታዳጊ ተጫዋቾቻችንን ከአካዳሚያቸው አላግባብ ከመውሰድ ሊቆጠብ ይገባዋል ማለታቸውን ዴይሊሜል ዘግቧል።
የእስፓኞል የወጣቶች አካዳሚ አባላት የሆኑ አምስት ተጫዋቾች በቅርቡ አላግባብ በሆነ መንገድ ባርሴሎናን መቀላቀላቸውንም ዘገባው አመልክቷል።
Health: ስለ ወንዶችም ሆነ ሴቶች ስንፈተ ወሲብ ከባለሙያ ጋር የተደረገ ቃለምልልስ
በርካታ ባለትዳሮች በግልፅ ለመንገር ባይፈልጉም ከሁለቱ አንደኛው ከወሲብ የሚገኘውን ደስታ በመንፈጋቸው ሳቢያ ለዘመናት የገነቡትን ትዳር የጠዋት ጤዛ ሲያደርጉት አይተናል፡፡ ምንም እንኳን የስንፈተ ወሲብ ችግር ሳይንሳዊ ምክንያትና መፍትሄ ያለው ቢሆንም፤ ችግሩን በጋራ ለመፍታት የሚያስችል ግልፅነት ባለመኖሩ ትዳሮች ፈርሰዋል፡፡ ቤተሰብ ተበትኗል፡፡ ጥያቄው ያለው መፍትሄ ባለው ችግር ለምን ትዳሮች ይናጋሉ? ለምንስ ፍቅረኞች ወደ መለያየት ያመራሉ? የሚለው ላይ ነው፡፡
በቦስተን አካባቢ ባሉ ነጮች ላይ የተጠና ጥናት እንደሚያመላክተው 30 ሚሊየን የሚደርሱ ወንዶች የስንፈተ ወሲብ ችግር አለባቸው፡፡ ጥናቱ ጨምሮ እንዳረጋገጠው የወንዶች እድሜ በጨመረ ቁጥር ችግሩ የበለጠ እየሰፋ ይመጣል፡፡ ለምሳሌ በጥናቱ ከተካተቱት የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ 40 ዓመት ከሞላቸው ወንዶች 40 በመቶ የሚሆኑት እንደዚሁም 70 አመት ከሞላቸው ደግሞ በ70 በመቶዎቹ ላይ የስንፈተ ወሲብ ችግር ታይቶባቸዋል፡፡ የተለያዩ በሽታዎች ያሉባቸው ሰዎች ተለያይተው ሲጠኑ ደግሞ፤ ለምሳሌ የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች ከሌለባቸው በሶስት እጥፍ የስንፈተ ወሲብ ተጠቂዎች መሆናቸውን በቦስተን በተደረገው ጥናት ተረጋግጧል፡፡ ይህ ጥናት የስነ ልቦና ችግሮችና ውጥረቶች በሚበዛባቸው በአፍሪካና በኤዥያ ሀገሮች ቢሰራ የስንፈተ ወሲብ ችግር ምን ያህል የዓለም ችግር መሆኑን እንደሚያሳይ የአሜሪካዎቹ ተመራማሪዎች ጠቁመዋል፡፡
ዛሬ በዚህ አምዳችን በስንፈተ ወሲብ (Sexual Dysfunction) ምንነት፣ መንስኤ፣ ምልክቶችና አማራጭ የህክምና መፍትሄው ዙሪያ የሚያተኩር የባለሙያ ትንታኔን እናቀርባለን፡፡ ሙያተኛው አንድ የኩላሊት፣ የሽንት ቱቦ፣ የፊኛና የወንድ ብልት ዘር ፍሬዎች ስፔሻሊስት ቀዶ ሐኪም ናቸው፡፡
የስንፈተ ወሲብን ምንነትና በሁለቱም ፆታዎች በምን መልኩ እንደሚገለፅ በመጠኑ ብናየው?
ስንፈተ ወሲብ (Sexual Dysfunction) የምንለው በተለያዩ ምክንያቶች በሁለቱም ፆታዎች በኩል ወሲብ ለመፈፀም የሚያስችሉ ችግሮች ሲከሰቱ ማለት ነው፡፡ በሌላ አገላለፅ ደግሞ አግባባዊ (የሚያረካ) የወሲብ ግንኙነት አለመፈፀም አልያም በሚደረገው የወሲብ ግንኙነት አለመርካት (ጥሩ ውጤት አለማግኘት) ማለት ነው የስንፈተ ወሲብ ችግር የሚባለው፡፡
እንዴት ይገለፃል? ለሚለው ለግብረ ስጋ ግንኙነት ስሜት ማጣትና ከግንኙነቱ እርካታ አለማግኘት በሁለቱም ፆታዎች ላይ የሚታይ ችግር ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀሚያ አካላት አለመነሳሳትን በተመለከተ በአብዛኛው በወንዱ ላይ ይታያል፡፡ ፍላጎት ማጣት፣ ከግንኙነት በኋላ እርካታን አለማግኘት (የእርካታ መጨረሻ ላይ አለመድረስ) ብዙውን ጊዜ የሴቶች ችግር ነው ማለት ይቻላል፡፡
ለችግሩ መፈጠር መንስኤዎች ምንድናቸው?
የስንፈተ ወሲብን መንስኤ ስነ ልቦናዊና አካላዊ ብለን በሁለት ትላልቅ ጎራዎች ከፍለን መመልከት እንችላለን፡፡ አካላዊ ስንል ከግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀሚያ አካሎች ለውጥ፣ በደም ውስጥ ካሉ ንጥረ ነገሮች መዛባት፣ ከአዕምሮና ከህብለሰረሰር የሚነሱ ችግር ውስጥ ከመግባታቸው ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ እንደዚሁም ከልብ የሚነሱ ደም ስሮች በአግባቡ ወደ ብልት ሄደው የደም ዝውውሩን ውጤታማ ማድረግ ባለመቻላቸውና ብልትን እንዲቆም የሚያደርጉ ነርቮች ባለመስራታቸው የስንፈተ ወሲብ ችግር ይመጣል፡፡ ሌላውና ከአካላዊ ምክንያት ጋር የሚያያዘው ስሜት ቀስቃሽ ንጥረ ነገሮች (ሆርሞኖች) በሚፈለገው መጠን በሰውነት ውስጥ አለመኖር፣ ስሜት ቀስቃሽ ንጥረ ነገሮች በሚፈለገው መጠን እንዳይሰሩ የሚያደርጉ ሌሎች የሆርሞን አይነቶች በሰውነት ውስጥ በብዛት ሲከሰቱ፣ በብልት ላይ የተለያዩ አደጋዎች ሲደርሱ፣ በብልት አካባቢ በሚሰሩ ቀዶ ህክምናዎች ምክንያት በብልት አካባቢ ያሉ ነርቮችና ደም ስሮች ሲጎዱ ለስንፈተ ወሲብ ችግር መጋለጥን ያመጣሉ፡፡ በተጨማሪም ለሌሎች በሽታዎች መፈወሻ ተብለው የሚሰጡ ለምሳሌ ለደም ግፊት፣ ለጨጓራ፣ ለኮሌስትሮል፣ ለሽንት ማሸኛ፣ ለአዕምሮ ህመሞችና ለሌሎችም በሽታዎች የሚሰጡ መድኃኒቶች ችግሩን የማምጣት እድላቸው ሰፊ ነው፡፡ በአጠቃላይ 25 በመቶ የወንዶች ስንፈተ ወሲብ ለሌሎች በሽታዎች በሚሰጡ መድኃኒቶች የሚመጣ ነው፡፡ ከስነ ልቦና አንፃር ደግሞ ጭንቀት፣ ድብርት፣ ጫና፣ ውጥረትና ቀደም ሲል በነበረ የወሲብ ታሪክ ጥሩ ያልሆነ ክስተት ከነበረ ለምሳሌ በቅርብ ዘመዶችም ሆነ በሩቅ ሰዎች ተገዶ መደፈር ከነበረ ወሲብን መጥላት ይኖራል፡፡ በወሲብ መፈፀሚያ ቦታዎች አካባቢ ምቾት ማጣት፣ ከማይፈልጉት ሰው ጋር መኖር (ወሲብ መፈፀም) የወሲብ ስሜት አልባነትን ያመጣል፡፡ እንደዚሁም በአንድ ወቅት በሆነ ምክንያት ወሲብ ያለመፈፀም ችግር ገጥሞት ከነበረ ሁል ጊዜም ችግሩ አለብኝ ብሎ መጨነቅ ወደ ስንፈተ ወሲብ ችግር በቀጥታ የሚገፋ ሁኔታ ነው፡፡ ጠቅለል ባለ መልኩ መንስኤዎችን ስናየው አካላዊ ወይም ከበሽታ ጋር ተያይዞ የሚከሰተው ስንፈተ ወሲብ በአብዛኛው ከ40 ዓመት በላይ ባሉ ሰዎች ላይ የሚታይ ነው፡፡ በተለይም ከስነ ልቦና ጋር በተያያዘ ችግር ይበልጥ የሚጠቁት ወጣቶች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ከስነ ልቦናዊ ምክንያቶች ጋር የተያያዘው የስንፈተ ወሲብ ችግር ከ10 እስከ 20 በመቶ የሚደርስ ነው፡፡ በሌላ በኩል ግን ከ40-80 በመቶ የሚሆነው የስንፈተ ወሲብ ችግር በቂ የሆነ አካላዊ ምክንያት ያለው ነው፡፡ ከላይ በመንስኤነት ከተገለፁ ጉዳዮች በተጨማሪ የሚገልፀው አብዝቶ አልኮል መጠጣት፣ ሲጋራ ማጨስ፣ ሐሺሽ እና ለመዝናኛነት ተብለው የሚወሰዱ መድኃኒቶች ችግሩን በማምጣት ረገድ የጎላ ሚና አላቸው፡፡
ስንፈተ ወሲብን በማምጣት ወይም በማባባስ በኩል አስተዋፅኦ ያላቸው የጤና ችግሮች ካሉ ቢገለፁልኝ?
- ኢንፌክሽን
- የልብ ህመም
- የጉበት ህመም
- የኩላሊት ህመም
- የስኳር እና
- የደም ግፊት በሽታዎች እንደዚሁም
- የኮሌስትሮል ከፍ ማለት
- የጡንቻ መኮማተር (በተለይ በሴቷ)
- የደም ስር ችግሮች
- የነርቭ ህመም እና
- ሰውነትን የሚያንቀጠቅጥ ህመም (ፓርኪንሰንስ ዲዝዝ) ከላይ የገለፅኳቸው የጤና ችግሮች በአንድ በኩል ስንፈተ ወሲብን ያስከትላሉ፡፡ በሌላም በኩል ቀደም ሲል የተከሰተን ስንፈተ ወሲብ ያባብሳሉ፡፡
ስንፈተ ወሲብ መኖሩን ፍንጭ ከሚሰጡ ምልክቶች ዋና ዋና የሚባሉትን ብናያቸው?
- የወሲብ ፍላጎት ማጣት
- የወሲብ መፈፀሚያ አካላት ዝግጁ አለመሆን (አለመቆም)
- በተለይም ሴቶች ወንድንም ሆነ ወሲብን መጥላት
- ብልት ቶሎ ተልፈስፍሶ መውደቅ ወይም መርገብ
- ወሲብ በሚፈፀምበት ወቅት ህመም መኖር
- የሴት ብልት ጡንቻ መኮማተርና በሁለቱም ላይ ህመም መፍጠር
- ሴቶችን ለግንኙነት ዝግጁ የሚያደርግ ፈሳሽ በበቂ መጠን አለመኖር
- እርካታ ላይ አለመድረስ
ፈጥኖ እርካታ ላይ መድረስ በሳይንስ እንዴት ነው የሚታየው?
ፈጥኖ የዘር ፍሬን ማፍሰስ ችግር ያለባቸው በቁጥር ቀላል የማይባሉ ሰዎች ናቸው፡፡ ምክንያቱ ብዙ ነው፡፡ ዋናዋና የምንላቸው ምክንያቶች አንደኛው ለወሲብ ጉጉ ከመሆን የሚመነጭ ችኩልነት፣ ሁለተኛ ከአሁን አሁን የዘር ፍሬዬ ፈሰሰ ብሎ መጨነቅ፣ ሶስተኛ ራሴንም ሆነ ተቃራኒ ፆታዬን ማርካት አልችልም ብለው በተደጋጋሚ ስለሚያስቡ ስሜታቸውን ነፃ አድርገው ለመጋራት መቸገራቸው አራተኛው ከነርቭ ወይም ከብልት አፈጣጠር ጋር የተያያዘ ምክንያት ነው፡፡
የብልት ማነስ (መስፋት) ከስንፈተ ወሲብ ጋር ይገናኛል?
የብልት ጉዳይ ተፈጥሮአዊ ነው፡፡ ስንፈተ ወሲብ ደግሞ በቂ የሆነ አካላዊ አልያም ስነ ልቦናዊ ምክንያት ያለው የጤና ችግር ነው፡፡ ስለዚህ የብልት ማነስ ወይም መስፋት ከስንፈተ ወሲብ ጋር የሚያያዘው ነገር የለም፡፡
አንድ ወንድ የዘር ፍሬ በማፍሰስ ብቻ ትክክለኛውን የወሲብ ድርጊት ፈፅሟል ማለት ይቻላል?
የዘር ፍሬ እኮ ምንም አይነት ግንኙነት ሳይደረግ የሚፈስበት ሁኔታም አለ፡፡ ስለዚህ የዘር ፍሬ መፍሰስ በራሱ ለውጤታማ የወሲብ ግንኙነት ማረጋገጫ አይሆንም፡፡ የአንድ ሰው ወሲባዊ ግንኙነት ጥሩ (ውጤታማ) ነው የሚባለው ወሲብ ከመፈፀሙ በፊት ያለውን ስኬታማ የፍቅር ጨዋታን ሁሉ የሚያካትት ነው፡፡ በተጨማሪም ጥሩ የወሲብ ግንኙነት ተደርጓል ለማለት ሁለቱም ፆታዎች የመጨረሻው እርካታ ላይ መድረሳቸው መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
ለስንፈተ ወሲብ ችግር ተጠቂ የሆነው ግለሰብ በተጣማሪው ላይ የሚፈጥረው አሉታዊ ተፅዕኖ ምንድነው ይላሉ?
የሚያስከትለው ተፅዕኖ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ አንድ ግለሰብ ስንፈተ ወሲብ ውስጥ ማለት የእሱ ተጣማሪም የችግሩ ተጠቂ ናት ወይም ነው ማለት ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ወደ ምን ያመራል ብንል ትዳርን ወደ ማፍረስና ወደ ብጥብጥ ነው የሚያመራው፡፡ ብጥብጡም ሆነ ትዳር መፍረስ የቤተሰብ መፍረስን ያከስትላል፡፡ በትዳር ውስጥ የተገኙ ልጆች ካሉም ይበተናሉ፡፡ በአካልና በስነ ልቦና ጤና የሚጎዱም ይሆናሉ፡፡ በተለይ ደግሞ ህፃናቱን የሚረዳቸው ከሌለ የማህበረሰቡ ችግር ሆኑ ማለት ነው፡፡ እንዲህ ያለው ሁኔታ በብዙ ሺህ ሰዎች ሲከሰት ደግሞ ችግሩ የግለሰቦች መሆኑ ቀርቶ የሀገር ይሆናል፡፡ የአሉታዊው ተፅዕኖ አንዱ ገፅታ ይሄው ነው፡፡ ሌላኛው ገፅታ ደግሞ የችግሩ ተጋላጭ በሆነው ግለሰብ ላይ የሚደርሰው ነው፡፡ የስንፈተ ወሲብ ችግር ያለበት ሰው በስነ ልቦና ህመም የተጎዳ ነው፡፡ ራሱን ይጥላል፡፡ የዝቅተኝነት ስሜትን ያሳዳራል፤ ይህች ዓለም ለእኔ የተፈጠረች አይደለችም ወደሚል የተሳሳተ መደምደሚያ በመሄድ በራሱም ሆነ በአካባቢው ባሉ ሰዎች ላይ ጉዳት ለማድረስ እስከ መገፋፋት የሚሔድበት ሁኔታ ይኖራል፡፡ ሌላው ቢቀር ችግሩ እንዳለበት እንኳ አሜን ብሎ ለመቀበልና መፍትሄውን ባሉት አማራጮች ሁሉ ለመፍታት ፈቃደኝነትን ሊያጣ ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ ችግሩ አለብህ ብለው ሊነግሩት ከሚፈልጉት ሰዎች ጋር ሁሉ ፀብ የሚጭር ይሆናል፡፡ በአጠቃላይ ችግሩ ያለበት ሰው ከህይወት ጣእምን ያጣ ስለሚመስለው ሁልጊዜ ደስተኛ አይሆንም፡፡ በድብርትና በጭንቅት የተዋጠ የመሆን እድሉ ሰፊ ይሆናል፡፡
ችግሩ መኖር አለመኖሩን ለመለየት የሚያስችሉ ምርመራዎችስ?
ስነ ልቦናዊ ችግር ያለባቸውን ከዕድሜያቸውና ከሚሰጡን ታሪክ ተነስተን ማረጋገጥ እንችላለን፡፡ የችግሩ መንስኤ ከስነ ልቦና ውጪ አካላዊ ነው ብለን ካሰብን የተለያዩ ምርመራዎችን እናደርጋለን፡፡ ለምሳሌ ችግሩን ያመጣው በሽታ ነው ብለን ካሰብን በሚጠረጠሩ በሽታዎች ዙሪያ የላብራቶሪ ምርመራዎችን እናደርጋለን፡፡ የሆርሞን እጥረት (መዛባትን) ለማረጋገጥም የተለያዩ ምርመራዎች ይደረጋሉ፡፡ እንደዚሁም በአካላዊ ምርመራ ችግሩ መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ ጥረት እናደርጋለን፡፡ በአጠቃላይ የስነፈተ ወሲብ ችግር መኖር አለመኖሩን የሚያረጋግጡ ምርመራዎች በሀገራችን በበቂ ሁኔታ ይሰራሉ፡፡ ውጤታማም ናቸው፡፡
ህክምናውስ?
የችግሩ መንስኤ በእርግጠኝነት ስነ ልቦናዊ መሆኑ ከተረጋገጠ ስነ ልቦናዊ ችግሩን መፍታት ላይ እናተኩራለን፡፡ ለምሳሌ ፈጥኜ እርካታ ጥግ ላይ እደርሳለሁ የሚል ከሆነ የዘር ፍሬውን ማዘግየት የሚችልበትን ዘዴዎች በማማከርና በማሰልጠን የማረጋጋት ስራዎችን እንሰራለን፡፡ ስነ ልቦናው ችግሩ የገዘፈና ስር የሰደደ ከሆነ ለተጨማሪ የማማከር ስራ ወደ ስነ ልቦና ሙያተኞች እንልከዋለን፡፡ በሌላ በኩል በሌሎች በሽታዎች ተብለው ከሚወሰዱ መድኃኒቶች ጋር በተያያዘ ችግሩ የመጣና የሚወስዱትን መድኃኒቶች ማቆም የሚቻል ከሆነ መድኃኒቶችን ከመውሰድ እንዲታቀብ ይመከራል፡፡ ነገር ግን የሚወስዷቸው መድኃኒቶች ማቆም የማይቻላቸው ከሆነ ከተቻለ መድኃኒቶች የሚቀየሩበትን ሁኔታ እንፈልጋለን፡፡ ካልተቻለ ግን ከገጠመው ስንፈተ ወሲብ ጋር ተስማምቶ የሚኖርበትን ሁኔታ እንዲያመቻች ተገቢውን ምክር እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡ በተጨማሪም የስንፈተ ወሲብ ችግርን የሚያስተካክሉ በሀገራችንም ሆነ በዓለም አቀፍ የመድኃኒት ገበያ በርካታ መድኃኒቶች አሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህ መድኃኒቶችን መውሰድ ያለባቸው በዘፈቀደ ሳይሆን በሐኪሞም ትዕዛዝ መሆን ይኖርበታል፡፡ ከሌሎች አማራጭ ህክምናዎች ደግሞ የሚከተሉት በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡
- የሆርሞን እጥረት ላለባቸው ሰዎች የሆርሞን መተኪያ ህክምና መስጠት
- በብልት ላይ በመግጠም ብልት እንዲቆም በማድረግ ወዲያው የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም የሚያስችል (vaccum device)
- ግለሰቡ በግብረ ስጋ ግንኙነት በተዘጋጀበት ወቅት ብልት ላይ የሚወጉ መድኃኒቶች አሉ
- በሽንት ቧንቧ ወደ ውስጥ የሚከተቱ መድኃኒቶችን መስጠት
- በቀዶ ህክምና የተፈጠረውን ችግር ማሰተካከል
- ደም ስሮችን በቀዶ ህክምና ማስተካከል
ከአማራጭ ህክምናዎች የበለጠ ውጤታማው የትኛው ነው?
ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ በአፍ የሚወሰዱ መድኃኒቶች የስኳርና ሌሎች የጤና ችግር በሌለባቸው ሰዎች ላይ ከ70 እስከ 90 በመቶ ውጤታማ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ የስኳር በሽታ ባለባቸው ሰዎች ደግሞ መድኃኒቶቹ ከ50 እስከ 60 በመቶ ውጤት ይገኝባቸዋል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ከሙያው ጋር ቅርበት የሌላቸው ሰዎች ለስንፈተ ወሲብ ችግር መድኃኒት ሲያዝዙ ይታያል፡፡ አልፈው ተርፈውም የሆርሞን ህክምና ሲሰጡ ይስተዋላል፡፡ የሆርሞን ህክምናን ለመስጠት መታየት ያለባቸው ነገሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ ካንሰር ላለበት ሰው የሆርሞን ህክምና ቢሰጠው ካንሰሩን በከፍተኛ ሁኔታ ያባብሰዋል፡፡ ስለዚህ ለስንፈተ ወሲብ የሚሰጠው ህክምና ሌላ ችግር እንዳያስከትል በጥንቃቄና ታስቦበት ሊሰራ የሚገባው ህክምና ነው፡፡
ከስንፈተ ወሲብ ጋር በተያያዘ ሙያዊ ምክርዎትን ያክሉበትና ውይይታችን እንቋጨው?
በፍቅርም ሆነ በትዳር ውስጥ ያሉ ጥንዶች መገንዘብ በሚገባቸው ለግንኙነታቸው መነሻም ሆነ መድረሻ አልያም ብቸኛው ጣዕም ሰጭ ወሲብ መፈፀም ብቻ ነው ብለው ድምዳሜ ላይ መድረስ የለባቸውም፡፡ ከወሲብ ይልቅ በቅድመ ወሲብ ወቅት የሚፈፀመው የፍቅር ጨዋታዎች የበለጠ ጣዕም ሰጭና ጠቃሚ መሆኑን መገንዘብ ይገባል፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ስለ ፆታዊ ግንኙነት የሚኖራቸውን እውቀት በእየዕለቱ ማሳደግን መዘንጋት የለባቸውም፡፡ ምክንያቱም ይህ የፍቅር ጨዋታ ጭንቀትንም ሆነ ወሲብ በአግባቡ የመፈፀም ብቃት የለኝም የሚለውን የፍርሃት ስሜትን የማጥፋት እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡
በተፈጠረው ችግር ዙሪያ በግልፅ መነጋገርና አንዱ አንዱን ለመርዳት እንዲሁም በጋራ መፍትሄውን ለማፈላለግ ፈቃደኝነት ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡ ችግሩ በሴቷም ሆነ በወንዱ ይድረስ ብጥብጥ ከመፍጠር ይልቅ እንዲህ አይነት ችግር ይፈጠራል፣ ምንም ማለት አይደለም፣ ያለወሲብ መኖር እንችላለን ወዘተ… የሚሉ የማበረታቻ ቃሎችን ለተቃራኒ ፆታ መስጠት ያስፈልጋሉ፡፡ በሁለቱ መረዳዳት ችግሩ የማይፈታ ከሆነ ወደ ባለሙያ ሄደው በችግሩ ዙሪያ በግልፅ መነጋገርና መፍትሄ መፈለግ ይኖርባቸዋል፡፡
ጭንቀትን፣ ድብርትን፣ ውጥረትንና መሰል ስነ ልቦናዊ ችግሮችን ለማስወገድ ጥረት ማድረግ ተገቢ ይሆናል፡፡ አልኮል ከመጠጣት፣ ሲጋራና ሀሽሽን ከማጨስ መታቀብ እንደዚሁም የውስጥ ጤና ችግሮች ካሉ በወቅቱ መታከምም ተገቢ ሆናል፡፡ በአጠቃላይ የስንፈተ ወሲብ ችግሩ ከመድኃኒት ጀምሮ እስከ ቀዶ ህክምና የሚዘልቅ የህክምና መፍትሄ ያለው በመሆኑ ጥንዶች ትዳራቸውም ሆነ የፍቅር ግንኙነታቸውን ቀውስ ውስጥ ከመክተት በፊት ተረጋግተው ለመፍትሄው በጋራ መስራት ይኖርባቸዋል፡፡ በትዕግስት ጥረት ማድረግም አለባቸው፡፡
አውራምባ ታይምስ እንዯ ወንዳ ንብ አንዳ ተኩሶ ሞተ!
ከሁለ አስቀዴሜ ሰሊምና ጤና ሇዱሞክራሲ ናፋቂው ወገኔ እመኛሇሁ። ወዴ አንባቢያን ሆይ! የዛሬው መጣጥፌ ወይም
አስተያየቴ የሚያጠነጥነው፦ ጥቂት ከማይባለ ወራት ጀምሮ የተወሇጋገዯ አካሄደና የተንሸዋረረ አመሇካከቱ አነጋጋሪ
ሆኖ የቆየው፤ በቅርቡ ግን የመወሇጋገደም ሆነ የመንሸዋረሩ ምክንያት ምን እንዯሆነ ግሌጽ በሆነው በአውራምባ
ታይምሱ ባሇቤት በጋዜጠኛ ዲዊት ከበዯ ዙሪያ ነው።
ዲዊት ከበዯ በምርጫ 97 ማግስት የወያኔ መንግስት ሽንፈቱን አሌቀበሌ ብል በወሰዯው የኃይሌ እርምጃ ወዯ ዘብጥያ
ከተወረወሩት የአሸናፊው ፓርቲ አመራሮች ጋር አብረው ሇእስር ከተዲረጉት የነጻ ሚዱያው ባሌዯረቦች አንደ እንዯነበር
ይታወቃሌ።
ሇ20 ወራት በዘሇቀው እስር ቃሉቲ ቆይቶ ከተፈታ በኋሊ፦ አዱስ ፈቃዴ አውጥቶ አውራምባ ታይምስን ማሳተም
ጀመረ። ሇዲዊት ከበዯ የተሰጠው ፈቃዴ በግዜው እንዯሱው ከእስር ሇተፈቱት ሲሳይ አጌናና ዛሬም በእስር ሇሚገኘው
እስክንዴር ነጋ መከሌከለ ጥርጣሬ ያጫረ ቢሆንም ሇንባብ የበቃቺው የአውራምባ ታይምስ ይዘት ጥርጣሬውን
አዯበዘዘው። ዋና አዘጋጇ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ በሽብርተኝነት ተከሶ ሲታሰርና እሱንም ተከትል ማኔጂንግ ኤዱተሩ
ዲዊት ከበዯ እስከተሰዯዯበት ግዜ ዴረስ አውራምባም መንግስትን ስትፈትን ቆየች ….
በነገራችን ሊይ ዲዊት ከበዯ በቅርቡ ትታሰራሇህ የሚሌ መረጃ ስሇዯረሰኝ ሃገር ሇመሌቀቅ ተገዯዴኩ ብል ከኢትዮጵያ
በቀጥታ ወዯ አሜሪካ ከመብረሩ ጋር በተያያዘ፦ በግዜው የተሇያዩ አስተያየቶች ይሰነዘሩ እንዯነበር አስታውሳሇሁ።
ገሚሶቹ ዲዊት ሇሽሌማት ወዯ አሜሪካ በመጣበት ግዜ የተሰጠው የአንዴ አመት ቪዛ ከመቃጠለ በፊት አሜሪካ
ሇመግባት ፈሌጎ እንጂ ከመንግስት አካሊት ትታሰራሇህ የሚሌ ምንም ማስፈራሪያ አሌዯረሰውም የሚለ ሲሆኑ፤
አንዲድቹም ምንም ይሁን ምን የጋዜጣውን ባሌዯረቦች በትኖ ራሱን ሇማዲን መሮጡ ራስ ወዲዴነት ነው ሲለ ይወቅሱት
ነበር።
ይሁን እንጂ አውራምባ ታይምስ በሃገርቤት የህዝብን ብሶት በማስተጋባት ረገዴ ትጫወት ከነበረው ሚና አኳያ በዲዊት
ሊይ ይሰነዘሩ የነበሩት ወቀሳና ትችቶች ውኃ የሚቋጥሩ አሌሆኑም። በዛም ሊይ የውብሸት ታዬ መታሰር ዲዊትን
እንዲስበረገገውና ታስሮ ከሚማቅቅ በተገኘው አጋጣሚ ራሱን ከእስር አዴኖ ሇስዯት ያበቃውን ስርዓት ቢታገሌ ይሻሊሌ
የሚሇው አመሇካከት የብዙዎች ነበር።
በመሆኑም የዲዊት ከበዯን ወዯ ስዯት አሇም መቀሊቀሌና ብልም የወረቀቷ አውራምባ በዴህረ ገጽ ብቅ ማሇቷን ሁለም
የተቀበሇው በጸጋ ነበር።
በርግጥ የወረቀቷ አውራምባ የብዙ በሳሌ ጸሃፊያን ተዋጽኦ ያሇባት ከመሆኗ አንጻር የዴህረ ገጿ አውራምባ ስሟን እንጂ
ይዘቷን ሌትተካ እንዯማትችሌ የብዙዎቻችን ግምት ቢሆንም፦ የማኔጂንግ ኢዱተሩ አስተዋጾዎም ቀሊሌ እንዲሌሆነ
ከግምት በማስገባት የዴህረ ገጿ አውራምባም የማይናቅ ስራ ሌትሰራ እንዯምትችሌ ተስፋ ተጥልባት ነበር።
ይሁንና ብዙም ሳይቆይ የዴህረ ገጿ አውራምባ የተጣሇባትን ተስፋ የሚያሌፈሰፍስ ስራዎችን በገጿ ይዛ መታየት
ጀመረች። ከወረቀቷ አውራምባ በብስሇት ብቻም ሳይሆን በአቋምም የተሇየች መሆኗን የሚጠቁሙ አካሄድችን
አዘወተረች።አውራምባ ስሟ እንጂ ነፍሷ እንዲሌተሰዯዯ የሚያመሊክቱ ህጸጾች በገጾቿ ዯጋግመው ታዩ።
ይህን ያስተዋለም ጥርጣሬያቸውን ተናገሩ። ዲዊት ከበዯም ምሊሽ ሇመስጠት ሞከረ። ምሊሹ ግን ከራሱ ጋር የሚቃረን
ነበር። “እኔ እንዯላልቹ ዴህረ ገጾች ተቃዋሚውን ብቻ የምዯግፍ ወገንተኛ አይዯሇሁም” የሚሇው መሌሱ፦ ሁለንም
እረ እንዳት ነው ነገሩ? ያስባሇ ነበር።
ዲዊት በዚህ ምሊሹ፦ ሇሽሌማት ያበቁትን፤ ስዯት ሲቀሊቀሌም በብዙ መሌኩ የሚዱያ ሽፋን ሰጥተው የረደትን ፕሮ
ዱሞክራሲ ሚዱያዎች በሙለ የተቃዋሚ ሌሳን ናቸው ብል መፈረጁ ብዙዎችን አስከፍቷሌ።
በላሊ በኩሌ ዯግሞ በሃገር ቤት ያሇውን የሚዱያ አውታር መቶ በመቶ ተቆጣጥሮ እራሱንም ሇስዯት የዲረገውን የወያኔን
መንግስት ፕሮፓጋንዲ በመዘገብ ሚዛናዊ ወይም “ነጻ ጋዜጠኛ” ማሇት እኔ ብቻ ነኝ በሚሌ፤ ፍየሌ ከመዴረሷ አይነት
ሇራሱ በሰጠው ከፍተኛ ግምት መኮፈሱ ብዙዎቻችን ስሇ እሱ ያሇንን በጎ አመሇካከት አወረዯው፡፤ ይሁን እንጂአዴራጎቱ ከግብዝነት የመነጨ እንጂ “ወገን ከወገንህ ቢለት የመቶ አመት ቁርበት ከብት መሃሌ ቆመ” እንዱለ የዯም
ጥሪ ዯውሌ ነው ብሇን አሌጠረጠርንም።
በተሇይ የዲዊትን አካሄዴ መወሇጋገዴ ከመነሻው ያስተዋሇ አንዴ ጸሃፊ ሇንባብ ያቀረበው ጽሁፍ በግዜው መነጋገሪያ
ሆኖ መሰንበቱ ይታወሳሌ። ዲዊት የጽሁፉ አቅራቢ የኢትዮ ሚዱያ አዘጋጅ አብርሃ በሊይ እንዯሆነ ወፍ ነገረቺኝ በሚሌ
ጽሁፉ በአብርሃ ሇመጻፉ ማስረጃ ሳይዝ በዯፈናው አብርሃ በሊይ ሊይ ወረዯበት። እኔ ዯግሞ ዲዊት ሇአብርሃ የጻፈውን
ጽሁፍ ካነበብኩ በኋሊ ዲዊት ራሱ ወረዯብኝ።
ዲዊት ሇአብርሃ የጻፈውን ጽሁፉ ሳነብ ግሌጽ የሆነሌኝ ነገር፡ የአውራምባ ታይምስ ሞገስና ብስሇት አገር ቤት ያለት
ጸሃፍቶች መሆናቸው ነው። ያነበባችሁት እንዯምታስታውሱት ጽሁፉ ከአጻጻፍ ስሌት ጀምሮ ተራነት የተስተዋሇበት
በአለባሌታ የታጨቀ፤ ኢሳትን ከአብርሃ በሊይ ሇማቃረን የሞከረ ተራ መናኛና አጸያፊ ይዘት ነበረው፡፤
ከሁለ በሊይ የዲዊትን ግብዝነት ያስተዋሌኩት፤ አብርሃ በሊይን ከዘመኑ ቴክኖልጂ ጋር መዋሃዴ ያሌቻሇና ዴህረ ገጹ ኋሊ
ቀር እንዯሆነ የገሇጸበትን ክፍሌ ሳነብ ነበር። ይህን አስተያየት የሚሰጡት በዴህረ ገጽ ስራ ቆየትና በሰሌ ያሇ ሌምዴ
ያሊቸው ሰዎች ቢሆኑ ባሌገረመኝ ነበር። ነገር ግን ይህን አስተያየት የሰጠው ዲዊት ከበዯ ነው። ዲዊት ዯግሞ ይህን
አስተያየት በሰጠበት ግዜ፤ ጽፎ ሇማሳተም ወዯ ማተሚያ ቤት ከሚሮጥበት የፕሪንት ሚዱያ ወዯ ዴህረ ገጽ ከተሸጋገረ
አመትም አሌሞሊውም። እናም ይህ ሰው በርግጥም ራሱን የማያውቅ ግብዝ ነው አሌኩ….
የዴህረ ገጽ አሰራርን ቴክኒክ ብዙም ባሊውቅ በአሁኑ ወቅት ቴክኖልጂው ሁለንም ነገር አቅልት የዴህረ ገጽ አዘጋጅ
ሇመሆን ጠሇቅ ያሇ የአይ ቲ እውቀት የማይጠይቅና እንግሉዘኛ አንብቦ መረዲት የሚችሌ ሁለ ሉሰራው የሚችሌ
እንዯሆነ ሙያው ካሊቸው ወዲጆቼ ተረዴቻሇሁ። ዲዊትም አውራምባ ሊይ ሇመፈናጠጥ ግዜ ያሌፈጀበት በዚሁ
ቴክኖልጂው ባቀሇሇው መንገዴ መጠቀም መቻለ እንዯሆነም ተገንዝቤያሇሁ።
እንዱያውም ዲዊት የአብርሃ በሊይን ዴህረ ገጽ ኋሊ ቀር ማሇቱ ትክክሌ ነውን? ብዬ የጠየቅኩት አንዴ የአይቲ ባሇሙያ
ወዲጄ ሲያጫውተኝ፡ በርግጥ ኢትዮ ሚዱያ የዘመኑ ቴክኖልጂ ማንም በቀሊለ እንዱጠቀምባቸው ያዘጋጃቸውን
አፕሉኬሽኖች እንዯማይጠቀም ገሌጾሌኛሌ። ነገር ግን እንዯ ወዲጄ እምነት ኢትዮ ሚዱያ ባሇመፈሇጉ እንጂ ፤ የዘመኑን
ቴክኖልጂ በመጠቀም በሰአታት ውስጥ ዴህረ ገጽ ሇመክፈት ከሚጠይቀው የአይቲ እውቀት የበሇጠ ሌምዴና እውቀት
እንዯሚኖረው በርግጠኝነት ገሌጾሌኛሌ። ይህን ማወቄ ዯግሞ የዲዊትን ሳይሞቅ ፈሊ…ግብዝነት ያዯመቀብኝ።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዲዊት በአንዴ ፓሌቶክ ሩም ቀርቦ ተቃዋሚዎች እጄን ጠምዝዘው እነሱ የሚፈሌጉትን እንዴሰራ
ሉያስገዴደኝ ይፈሌጋለ ብል መናገሩንና በተሇይ አብርሃ በሊይ፤ ወይ የመንግስት ዯጋፊ አሌያም ተቃዋሚ መሆን እንጂ
“ግሬይ” የሚባሌ …የሇም እንዲሇው መናገሩን ሥሰማ ሇአብርሃ በሊይ ቁርጠኛ አቋም ከወገቤ ሰበር ብዬ እጅ ነስቻሇሁ።
የዲዊት አንዳ ነጭ አንዳ ጥቁር የሆነው አካሄደ ሇወራት ሲያነጋግር ቆየ፤ ሇአውራምባ ታይምስ (ሇጋዜጣዋ) ክብር
የሚሰጡ ወገኖችም የዲዊት እዚህም እዛም መራገጥ ከእሌህና ከኔ በሊይ ከሚሌ ባህሪ የመነጨ መስሎቸው በመሌካም
ስራው ያተረፈውን መሌካም ስም በውዥቀቱ እንዲያጠፋው በማሰብ ሇመምከር ሞከሩ። በኢሳት ሊይ የሚነዛውን የስም
ማጥፋት እንዱያቆምም መከሩ።
በቅርቡ ይፋ እንዯሆነው ዲዊትን በጥፋት ጎዲና የሚዘውረውና የሚያስጨፍረው ግን የባህሪ ችግር ሳይሆን የዘር ዛር
ነበር። አሁን የሁለም ጥያቄ ዲዊትን የዘር ዛሩ የሇከፈው መቼ ነው? የሚሌ ነው።
ሇዚህ ጥያቄ ዯግሞ የተሇያዩ ግምታዊ መሌሶች እየተሰጡ ይገኛለ።ገሚሶች ቃሉቲ እስር ሊይ እያሇም የስሇሊ ስራ እየሰራ
እንዯነበር ይናገራለ።ገሚሶቹ ዯግሞ ከእስር ከወጣ በኋሊ እንዯተሇከፈ ይገምታለ።የሇም ውብሸት ከታሰረ በኋሊ ነው
የሚለም አለ።ሁለም የሚስማሙበት ነገር ቢኖር፡ ዲዊት ወዯ ስዯት የመጣው አሁን እየፈጸመ ያሇውን ተሌዕኮ ቢቻሌ
ኢሳት ውስጥ ገብቶ እንዱያከናውን ሃሊፊነት ተቀብል መሆኑን ነው።
ኢሳት ውስጥ ገብቶ ቢሆን ኖሮ ሉያዯርስ የሚችሇውን ጥፋትና ሉያቀብሌ የሚችሇውን መረጃ ሳስበው ይዘገንነኛሌ።
ዲዊት ወዯ ኢሳት እንዲይገባ በር የዘጋበት መሌአክም ይሁን ሰው እሱ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊያን ወዲጅ ነው።
ዲዊት ሰሞኑን የፈጸመው ተግባር የጠቀመው ከወያኔ ይሌቅ ተቃዋሚውን ነው። የዲዊት የተሳሳተ አካሄዴ ሉታረም
የሚችሌ የባህሪ ችግር እንዯሆነ ሊመነው አብዛኛው ኢትዮጵያዊ እራሱን ግሌጽ አዴርጎ ያሳየበት መሌካም አጋጣሚ ሆኖ
አሌፏሌ።ላሊው ቢቀር ከወያኔ የመረጃ ቢሮ የተሊከሇትን የድ/ር ብርሃኑን ዴምጽ በዴህረ ገጹ ሲያወጣ ያሇምንም አጃቢ መግሇጫ
እንዲሇ ቢያቀርበው ኖሮ፤ ያገኘውን አቀረበ ታዱያ ጥፋቱ ምንዴነው? የሚለ 2+2=4 ነው ካሌተባለ ዞር ያሇ ሂሳብ
የማይታያቸውን ጥቂት የዋህ ተቆርቋሪዎችን ባሊጣ ነበር። ይሁንና ድ/ሩ ያሌተናገሩትን “ግብጽ” የሚሌ ቃሌ ጨምሮ
ግንቦት ሰባት ከግብጽ የገንዘብ እርዲታ እንዯተቀበሇ መጻፉ ፤ ነጻና ዯፋር ነኝ የሚሇውን ራሱ ሇራሱ የሰጠውን መገሇጫ
ጥሊሸት አሌብሶበታሌ። ከግዜጠኝነት ሥነ ምግባር ያፈነገጠ ዴርጅታዊ የፕሮፓጋንዲ ስራ እየሰራ መሆኑን
መስክሮበታሌ። እንቅስቃሴና ተግባሩን ከሙያዊ መርህ አኳያ ብቻ በሚመሇከቱ ወገኖችም ሳይቀር አስተፍቶታሌ።
የአውራምባ ታይምስ ሰሞነኛ ተግባር Drones በሚሌ መጠሪያ የሚታወቀውን የወንዳ ንብ ተፈጥሮ እንዲስታውስ
አዴርጎኛሌ። የነዚህ ወንዳ ንብ ተግባር ከንግስቲቷ ጋር ተገናኝቶ ዘር መፈጠር ብቻ ነው። እናም ሰራተኛው ንብ ወንዳ
ንቦቹን ሇአቅመ ንብ እስኪዯርሱ ይንከባከቧቸዋሌ። ከንግስቲቷ ጋር ግንኙነት የሚያዯርገው አንደ ብቻ ነው፡፤ ግንኙነቱን
እንዲዯረግም ወዱያውን ይሞታሌ። አንዳ ተኩሶ የህይወቱ ፍጻሜ ይሆናሌ። አውራምባም አንዳ ተኩሶ ከነጻ ሚዱያው
አሇም ተሇየ።
እንዯኔ እምነት ዲዊት ዴምጹን የተቀበሇው ከወያኔ መረጃ ክፍሌ ከሆነ፤ የወያኔ መረጃ ክፍሌ ትሌቅ ስህተት ሰርቷሌ።
ምክንያቱም የድክተሩ ዴምጽ በአውራምባም ወጣ በአይጋ ፎረም ምንም ሇውጥ ስሇማይኖረው፤ ዴምጹን በሇየሊቸው
የወያኔ ዴህረ ገጾች አውጥተው፤ አውራምባ በተቃዋሚው ጎራ ማሳሳት የሚችሇውን እያሳሳተ ቢቆይሊቸው የበሇጠ
ተጠቃሚ ይሆኑ ነበር ባይ ነኝ። እንዯ ወንዳ ንብ አንዳ ተኩሶ ከሚሞት ማሇቴ ነው።ነገር ግን ዲዊት ይህን ዴምጽ
ያገኘው ከወያኔ መረጃ ክፍሌ ሳይሆን ከላሊ አካሌ ከሆነ ግንቦት 7 ውስጡን ሉፈትሽ ይገባዋሌ ማሇት ነው።
ዛሬ አውራምባ ታይምስን ከፍተን የምናየው ሌክ እስከዛሬ አይጋ ፎረምንና ትግራይ ኦን ሊይንን ከፍተን በምናይበት “
ምን ዋሽተው ይሆን?” በሚሌ ስሜት መሆኑ ስራችንን አቅልሌናሌ። ከእንግዱህ በኋሊ በአውራምባ ሊይ የሚወጡ
ዘገባዎችን ሁለ የምንመሇከተው በአንዴና አንዴ መነጽር በመሆኑ ከስህተት አዴኖናሌ።እናም በኔ እይታ አውራምባ
ከወያኔ ይሌቅ የጠቀመው ተቃዋሚውን ነው።
ዲዊት ከበዯ በነጻ ጋዜጠኝነት ባርኔጣው ህዝብ የሚያከብራቸውን የፖሇቲካ ሰዎች ሇመቅረብና ሇመተዋወቅ ብልም
ሇመወዲጀት መቻለን በበርካታ አጋጣሚዎች ተረዴቻሇሁ። በተሇይ ብርትኳን ሚዯቅሳ ቃሌሽን ሇውጭ አሌያ ታሰሪ
የሚሌ ሌትቀበሇው የምትችሇው አማራጭ በቀረበሊት ወቅት የተሰማትን ስሜት ያማከረቺው ሇዲዊት እንዯነበር
በአውራምባ ሊይ እንዲስነበበን አስታውሳሇሁ።
ቃላን ከምሇውጥ እስርን በጸጋ እቀበሊሇሁ ያሇቺው ይህቺ ጀግና የመጨረሻ ቀን ጭንቋን ያዋየቺው ሰው የነጻ ጋዜጠኛን
ጭንብሌ ያጠሇቀ የአሳሪዎቿ አገሌጋይ እንዯነበር ስትረዲ ምን ይሰማት ይሆን?
እርግጠኛ ነኝ፡ብርትኳንም ሆነች ላልች ከዚህ ሰው ጋር የሌባቸውን ሃሳብ የተሇዋወጡ የፖሇቲካ ሰዎች ሁለ ወዯ ኋሊ
መሇስ ብሇው ውይይታቸውን በትውስታ እንዱመረምሩ ይገዯዲለ። ያም ሆነ ይህ ሲታመኑ መክዲት እንጂ አምኖ
መከዲት ጥፋትም፤ ሇጸጸት የሚዲርግም አይዯሇምና እዲው ገብስ ነው።
በሃገርቤት ያለ በአውራምባ ታይምስ ሊይ ይሳተፉ የነበሩ ጋዜጠኛና ጸሃፍቶችም ሇአውራምባ ቀብር ባይዯርሱም
በአውራምባ የውርዯት ሞት ግን ማዘናቸው የሚቀር አይመስሇኝም።
እናም በኔ እይታ አውራምባ ታይምስ ሇበርካታ ወራት በውስጧ ተዯብቆ በቆየው ፈውስ የሇሹ የዯም ካንሰር በሽታ
ስትሰቃይ ቆይታ በቅርቡ ከነጻው ሚዱያ ዓሇም በሞት ተሇይታሇች።
እንሆ በሃውሌቷ ሊይም ይህ አጭር ታሪኳ ተጻፈ።
አውራምባ ታይምስ በ1999 ከአባቷ ከ…. ከእስር መሌስ በዴንገት ተወሇዯች።
በጥሩ ምግባርም አዯገች! በህዝብም ተወዯዯች!
በኋሊም በዴንገት ተሰዯዯች!
በስዯት አሇምም ተዋርዲ ሞተች!
አዜብ ጌታቸው
azebgeta@gmail.co
ዘመቻ ቴዎድሮስ – የአንድነት ፓርቲ በጎንደር (ግርማ ካሳ)
(ግርማ ካሳ)
Muziky68@yahoo.com
ሰኔ 26 ቀን 2005 ዓ.ም
ያለ መታደል ጎንደርን በአካል አላውቃትም። ነገር ግን እንደ ማንም ኢትዮጵያዊ በልቤ ዉስጥ ልዩ ቦታ አላት። ያለ ጎንደር ኢትዮጵያ የምትባል አገር ትኖር ነበር ለማለት ያስቸግራል።
ግራኝ መሃመድ በቱርኮች እየተረዱ፣ አብዛኛዉ የኢትዮጵያን ክፍል ተቆጣጥረዉ በነበረ ጊዜ፣ ስመ ጥሩ ያልነበሩ፣ ብልሹዉ የሸዋ ንጉስ፣ አጼ ልብነህ ድንግል ይሞታሉ። አጼ ገላዉዲዮስ ይተኳቸዋል። የግራኝ ጦር በመጠንከሩ ሽሽት ወደ ሰሜን፣ ወደ ጎንደር ይጀመራል። አጼ ገላዉዲዮስ ያሸንፋሉ። ግራኝ መሃመድ ይሞታሉ። ጎንደር የኢትዮጵያ የፖለቲካ መዓከል ትሆናለች። ከአጼ ገላዉዲዮስ በመቀጠል ፣ አጼ ሱስኒዮስ፣ አጼ ፋሲል እያሉ በጎንደር፣ ገዢዎች መፈራረቅ ጀመሩ። የጎንደር ገዢዎች አገሪቷን በአንድ ላይ አድርገዉ ማስተዳደር ስላልቻሉ ዘመነ መሳፍንት የሚባለው ዘመን መጣ። ኢትዮጵያ ተበታተነች። በወሎ፣ በሸዋ፣ በትግራይ በጎጃም …የተለያዩ ገዚዎች መግዛት ጀመሩ።
ትዉልዳቸው ቋራ የሆነ፣ መይሳው ካሳ፣ የኢትዮጵያ አባት፣ ብቅ አሉ። መሳፍንቱን እያስገበሩ ንጉስ ነገስት ዘኢትዮጵያ ቴዎድሮስ ተባሉ። አጼ ቴዎድሮስ፣ ከጎንደር የጀመሩት ዘምቻ፣ ኢትዮጵያን አንድ አደረገ። አዎ ጎንደር በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ልዩ ቦታ አገኝች።
መሃዲስት ደርቡሾች ታሪካዊዋን የጎንደር ከተማ አጠቁ። ጀግናዉ አጼ ዮሐንስ ተንቀሳቀሱ። የደርቡሾችን ጦር እየመነጠሩ ከኢትዮጵያ ምድር አስወጡ። የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበር ላይ፣ በመተማ፣ ከጠላት በተተኮሰ ጥይት ወደቁ። ለኢትዮጵያ አንድነት ለግዛቷ መከበር፣ እኝህ ታላቅ ሰው በጎንደር ደማቸው ፈሰሰ። መስዋእት ሆኑ። ጎንደር ታሪክ የተሰራባትና ወደፊትም የሚሰራበት ሆነች።
ጎንደር በርግጥ ሕወሃት ከኢሕአፓ ካፈነገጠዉ፣ በአቶ ያረድ ጥበቡ (ከዚያም ታምራት ላይኔ) ይመራ ከነበረዉ አንጃ ፣ ኢሕዴን( የኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ) ጋር በመተባበር ኢሕአዴግን መሰረተ። «ሕወሃት ሚሊተሪዉን ይቆጣጠራል፤ ኢሕዴን ደግሞ ሕዝቡን ለማግባባት የፖለቲካ ሥራ ይሰራል» በሚል ስምምነት።
የሕወሃት ጦር በጎንደር በኩል ወደ ደቡብ ሲያልፍ «ዘመቻ ቴዎድሮስ» በሚል ነበር። አጼ ቴዎድሮስ እንዳደረጉት ፣ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ የተደረገ ዘምቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያን ባህር አልባ ለማድረግ፣ ሕዝቧን በዘር ለመከፋፈል የተደረገ ዘመቻ ነበር። «ቴዎድሮስን» መጥቀስ ያኔ የተፈለገዉ፣ የሕወሃቶችን እዉነተኛ ከፋፋይና ዘረኛ ገጽታቸውን ለመሸፈንና ሕዝቡን ለማታለል ነበር።
አጼ ቴዎድሮስ መሳፍንትን ያስገበሩት በጦርነት መሆኑ ይታወቃል። የመጀምሪያዉ ዘመቻ ቴዎድሮስ፣ የነፍጥ ዘመቻ ነበር። ሁለተኛው የሕወሃት «ዘመቻ ቴዎድሮስ» ግን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ሆን ተብሎ የተካሄደ፣ ቴዎድሮሳዊ ያልነበረ ዘመቻ እንደሆነ በሂደት ተረጋገጠ። አገሪቷ በዘር ተከፋፈለች። ኢትዮጵያዊነት እንደ ሐጢያት መቆጠር ተጀመረ። ዜጎች በኢትዮጵያዊነታቸዉ ሳይሆን በዘራቸው እንዲለዩ ተደረገ። አንዱ ግዛት ለአንዱ ዘር፣ አንዱ አካባቢ ለሌላው ዘር ተሰጠ። ኢትዮጵያ የሁሉም መሆኗ ቀረ። በማንም አገር ያልታየ፣ ግዛቶች ከፈለጉ እንዲገነጠሉ በሕግ ተደነገገ። አሉላ አባ ነጋ እንደራሴ ሆነው ያስተዳደሯትን፣ ባህር ምድሪ ተብላ ትታወቅ የነበረችዉን፣ ኤርትራን፣ ለተባበሩት መንግስታ ደብዳቤ ሁሉ በመላክ፣ እንድትገነጠል ግፊት ተደረገ። «ኢትዮጵያ የባህር በር አያስፈልጋትም» በሚል ወደብ እንዳይኖራት በማድረግ፣ ለጅቡቲ በመቶ ሚሊዮን ዶላሮች የሚሆን ገንዘብ በየጊዜው በገፍ መክፈሉ ግዴታ ሆነ። የጅቡቲን ወደብ በኮንትራት የሚያስተዳደሩት፣ የዱባይ ኩባንያዎች በመሆናቸው፣ በተዘዋዋሪ መንገድ አረቦች ኢትዮጵያን ማነቅ የሚችሉበት ሁኔታ ተፈጠረላቸው።
ከሃያ አመታት በፊት የጎንደር ሕዝብ ሕወሃትን ከትግራይ ወደ ደቡብ እንዲያልፍ ያደረገዉ፣ በአንድ በኩል የደርግ የግፍ አገዛዝ መሮት ስለነበረ ሲሆን በሌላ በኩል ፣ «ኢሕአዴግ ዲሞክራሲን፣ ፍትህን፣ እኩልነትን ያሰፍናል፤ የኢትዮጵያ አንድነትን ያስከብራል» በሚል፣ ኢሕዴኖች የሕወሃት አፍ ሆነው፣ አታለዉት ስለነበረ ነዉ።
ያኔ ለጎንደር ሕዝብ የተገባዉ ቃል ግን፣ እንኳን ተግባራዊ ሊሆን፣ ጭራሹን የግፍ አገዛዙ ብሷል። መሬቱ ለሱዳን እየተሰጠ ከፍተኛ ስቃይና መከራ እየደረሰበት ነዉ።
በኢትዮጵያ ያለዉን የግፍ አገዛዝ በመቃወም፣ ሕዝቡን በማደራጀትና በማንቀሳቀስ ላይ የሚገኘዉ፣ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ፣ ከጎንደር ሕዝብ ጋር ሆኖ፣ የኢትዮጵያ አንድነት እንዲከበር፣ ሕዝቧ በሰላም በእኩልነት እንዲኖር፣ የሕግ የበላይነትና የሰብአዊ መብቶች መከበር እንዲሰፍን የሚደረገዉን ትግል ለማገዝ፣ የሚሊዮች ድምጽ ለነጻነት በሚል መርህ፣ እዉነተኛ ዘመቻ ቴዎድሮስን አዉጇል። የጠመንጃ ዘመቻ ሳይሆን የሰላማዊ፣ የሰለጠነ፣ የሕዝባዊ ንቅናቄ ዘመቻ !
ሰኔ 30 ቀን በጎንደር ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል። በታሪክ እንዳነበብነው፣ አባቶቻችን እንደነገሩን፣ የጎንደር ሕዝብ እንደገና ታሪክ ይሰራል። «ዘረኝነት ይብቃ ! የግፍ አገዛዝ ይብቃ! ኢትዮጵያ ትቅደም! » እያለ ድምጹን ያሰማል። የነጻነት ደዉል ከፋሲለደስ አገር ይሰማል።
በጎንደር ወዳጆች፣ ዘምዶች ያሉን፣ በስልክ፣ በኢሜል፣ በፌስቡክና በትዊተር የሰልፉ ተካፋይ እንዲሆኑ እናበረታታ። በአካል የሰልፉ ተካፋዮች ባንሆንም፣ በመንፈስ ግን ከጎንደሬ ወገኖቻችን ጎን እንቁም ! ዘመቻ ቴዎድሮሶን እንቀላቀል ! ወገኖቻችን፣ ሊታሰሩ ፣ ሊገደሉ እንደሚችሉ እያወቁ ደፍረው ሰልፍ ለመውጣት ከተዘጋጁ፣ እኛ እንዴት ድምጻችንን ማሰማት እንፈራለን ? የአንድነት ፓርቲ ይፋ ያደረገዉ ፔትሽን እንፈርም። የትግሉ አካልና አጋር እንሁን ! አንፍራ ። አንደንግጥ። አንታለል። ከበስተጀርባ ሌላ አላማ ባላቸው የዉጭ ኃይሎች አንተማመን። እኛው እንበቃለን። የተባበረ የኢትዮጵያዉያን ኃይል ከተነሳ፣ አምባገነኖች ወደዱም፣ ጠሉም ለሕዝብ ፍቃድ ይገዛሉ።
ፔቲሽኑን ለመፈረም ወደ ሚከተለዉ የድህረ ገጽ አድራሹ ይሂዱ
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !
የብሮድካስት ይፍረስ ጥያቄና ፓርላማው!!! ዳንኤል ተፈራ
ዳንኤል ተፈራ
ዛሬ የነበረው የፓርላማ ውሎ ከቀደሙት በይዘት፣ በአጠያየቅ፣ በመልስ አሰጣጥና በማፅደቅ ከቀደሙ ስብሰባዎች ምንም የተለየ ነገር አልነበረውም፡፡ የሚንስትሮች ሹመትም ቢሆን የሚጠበቅ ነው፡፡ ግን እንዲህ በጨረፍታ ሳይሆን በደንብ የሚያነጋግረን ነው፡፡ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ አይነት፡፡ ወደ ፓርላማው ስመጣ እንደከዚህ በፊቱ የማሻሻያ ሞሽን ይቀርባል በአብላጫ ድምፅ ውድቅ ይደረጋል? የፓርላማው ጥርስ የማብቀል ጉዳይ ከምኞት ባሻገር ገቢራዊ እንዳልሆነ ለማየት የቻልን ይመስለኛል፡፡ እንግዲህ ፓርላማው ጥርስ ማብቀል ካልቻለ ያው ‹‹በገንፎ›› መኖር ነው፡፡
የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ ያቀረቧቸው ሁለት ሞሽኖች ተገቢነታቸው የሚያከራክር አይደለም፡፡ አንደኛው መንግስት ከሀገር ውስጥ ለመበደር ያሰበውን ገንዘብ ወደ ግሉ ሴክተር ቢዞር የግሉን ዘርፍ እንሚያበረታታ የሚጠይቅ ሞሽን ነበር፡፡ በአንድ ድጋፍ ብቻ ውድቅ ተደረገ፡፡ ታዲያ የበቀለው ጥርስ የታለ???
ሁለተኛው ብሮድባንድ የተባለውን ፕሬስ አፋኝ መስሪያ ቤት የሚመለከት ነው፡፡ አቶ ግርማ እንዳቀረቡት ባለስልጣኑ አንድ የግል ቴሌቪዥን ጣቢያ መክፈት ያልቻለ ነው፡፡ ይሄ ማለት የብሮድካት ባለስልጣን አብያ በሬ ነው እንደማለት ነው፡፡ አብያ በመባል የሚታወቀው በሬ ከፍተኛ መኖ የሚጠቀም ሲሆን ሰውነቱን ከማደንደን ባለፈ ለእርሻ ሲጠመድ መልገም ይጀምራል፡፡ ይተኛል፡፡ ሰነፍ ነው፡፡ በማሻሻያ ሞሽኑ ላይ እንደቀረበው ለብሮድካስት ባለስልጣንም የተመደበለት በጀት ከደመወዝ ውጭ ያለው መኖ መቀነስ አለበት፡፡ ማንኛውም መስሪያ ቤት የታለመለትን ዓላማ እያሳካ ካልሆነ መዘጋት ይገባዋል፡፡ ስለዚህ ብሮድካስትም መፍረስ አለበት ማለት ነው፡፡ ይሄ ተገቢ ሀሳብ ነው፡፡
ምክንያቱም ብሮድካስት የተባለው የባለስልጣን መ/ቤት እኛ የምናውቀው በህዝብ ዘንድ ተወዳጅ የነበሩትን ጋዜጣና መፅሄቶች ሲዘጋ ነው፡፡ እነ አዲስ ነገር፣ ፍትህ፣ ፍኖተ-ነፃነት፣ አዲስ ታይምስ፣ ልዕልናና ከ1997 ዓ.ም በፊት የነበሩ በርካታ ጋዜጦች ተዘግተዋል፡፡ በርካታ ወዳጆቼ የጋዜጣ ፈቃድ ለማውጣት ደጅ ጠንተው የገንዘብ ምንጫችሁ ይጠና በሚል ተልካሻ ሰበብ ፈቃድ ተከልክለዋል፡፡ እና ለዚህ መስሪያ ቤት በጀት ምን ይሰራለታል? የአቶ ግርማ የሞሽን ማሻሻያ ጥያቄ ትክክል ነበር፡፡ ብሮደካስት ብቻ ሳይሆን ህዝብን የማያገለግሉ ድርጅቶች ሁሉ መዘጋት አለባቸው፡፡
ምክር ቤቱ በግራ አጥቅቶ ግብ አስቆጠረ
አቶ ቡልቻ ከአንድነት ፓርቲና አባላት አናት ላይ መቼ ይወርዱ ይሆን ?
ከኢንጂነር ዘለቀ ረዲ
የተከበራችሁ አንባቢያን ባለፈው ሳምንት በተቃጠርነው መሠረት ዛሬም ስለወሎ ትንሽ ልበላችሁ። የደቡብ ወሎ ዋና ከተማ ደሴ ደርሰው ሐይቅን ፣መርሳን፣ ጉባ ላፍቶን፣ ኡርጌሳ፣ ሳንቃን፣ወልዲያን፣ጉብዬን፣ ሮቢትን ፤እያሉ ቆቦ ይገባሉ። ሁሉም የኦሮምኛ ትርጉም ያላቸው ስሞች ናቸው ቋንቋቸው ግን አማርኛ ኢትዮጵያውያንን በዘር መለየት አይቻልም። ተፈጥሮ ይገርምዎታል። ወሎዬዎች መልክና ቁምነገር ሲታደል ከፊት ተሰልፈው የወስዱ ይመስልዎታል። ህጻን አዋቂው ያምራል። የሰባ ዓመት ሽማግሌዎችና አሮጊቶች በሚገርም ሁኔታ አሁን በዚህ ዕድሜያቸው ላይ ሆነው በልጅንታችው የነብራቸውን ውበት ያሳብቅባቸዋል።ወጣቶቹን በሙሉ ዓይን ለማየት እንኳን ያሳሳሉ። ውበት ለመጨመር ምንም የሚቀባቡት ነገር የለም። ለነገሩ ተፈጥሮ ቀብታችው የለ? ለመዋቢያ ብለው ቢቀቡ ተፈጥሮ የለገሰቻቸውን ውበት ከማበላሽትና ወጪ ከማብዛት የዘለለ ጥቅም የለውም። የሚገርም ነው። ወሎዮቹ ቁመተ ለግላጋ ጸጉረ ረጂም፣ አፍንጫ ሰልካካ ፈጽሞ ክፋት የሚባል ነገር የሌለባቸው ገራገሮች ነቸው።
ወልዲያ እንደገቡ በውልዲያ ያሉ ወያላዎች የመኪና ተራ አስከባሪዎች መኪና ከሌለዎት የሚሔዱበትን አካባቢ ይጠይቁዎታል ልክ እንደነግሩዋቸው ተሩዋሩጠው ከፈለጉበት ቦታ ይሸኙዎታል። በመኪና ከሆነ የሄዱት ወደሚሄዱበት አከባቢ ሰው እንዲጭኑ ይጠይቅዎታል። ፈቃደኛ ካልሆኑ በደስታ ተቀብለው መኪናዎን እንጠብልዎት ይሉዎታል። ፈቃደኛ ከሆኑ በደንብ አድርገው ያጥቡልዎታል። ፈቃደኛ ካልሆኑም ምሳም ይሁን ቡና ብለው እስኪመለሱ ድረስ መኪናዎ ተቆለፈም አልተቆለፈም እንደነበረ ያገኙታል።በወልድያ መኪናዎትን ቆለፉ አልቆለፉ እንግዳ በመሆንዎ ብቻ እቃዎ እንዳይጠፋ ወያሎቹ ይጠብቅሉዎታል። ለነገሩ ማን ይሰርቃልና ወልድያ የሰው ንብረት መንካት ነውር ነው።
በቻይና ጉዋንዙ አፍሪካ ጎዳና ምሳ በልቼ መልሥ ሲሰጥኝ የተወሰነ ገንዘብ በመልስ መስጫው ውስጥ ትቼ እሄዳለሁ ቲፕ መሆኑ ነው። ነገር ግን ወይተሩ ገንዘብ መተዌን ሲያውቅ ተከታትሎ መጥቶ ገንዘብ ረስትሃል አለኝ። ላንተ ነው የተውኩት ስለው አይ ለኔ ደመወዜ ይበቃኛል። በመንገድ ለሚለምኑት ስጥ ያለኝ በወልዲያ አይቼዋለሁ። ልጆቹ ሁሉ ዋጋ መቀበል የሚፈልጉት ለሠሩበት ብቻ ነው። በሁሉም ወሎ ማለት ይቻላል። ወንዱን ጋሼዋ ሴቱን እቴዋ ብሎ መጥራት የተለመደ ነው። ጋሼዋ ብለው ሲጣሩ ልዩ መስህብ አለው። ካፋቸው ማር ጠብ ይላል።
በወልድያ አለፍ፣አለፍ ብሎ ጀበናቸውን ጥደው ቡና የሚያፈሉ ሴቶች አሉ። ሁሉም ሴቶች ማለትይቻላል። በአዲስ አበባ ቡና ስታፈላ የተሰቀልችውን ስዕል ይመስላሉ። ያምራሉ ለማለት ነው። ቡናዎን አዘው ሲጠጡ የመንደር ተርቲበኛ ወሬ ሁሉ ያጫውትዎታል። በዚህም ቡና በመንገድ ሱስ ይዞዎት የሚጠጡ ሳይሆን በቤትዎ ባለቤትዎ አፍልታ ከጎረቤትዎችዎ ጋር የሚጠጡ ይመስልዎታል። እርስዎ ቡና ሊጠጡ ገና እንደቀረቡ ቡናው በትንሽ ጀበና ተቀንሶ በገል እሳት ይቀርብልዎታል፡፡ እንዲያጨሱ የሚቀርብልዎት የወሎ ጢስ የሚባል የተቀመመ ሽታው እውድ የሚያደርግና አልባብ አልባብ የሚሸት ነው። ይህ የወሎ ጭስ ከተለያየ የእጽዋት አይነቶች ተቀምሞ የሚዘጋጅ መሆኑን ጠይቄ ተረድቻለሁ። ለእናንተም ትጠቀሙበት ዘንድ እነሆ፤ የሚዝጋጀውም፣ ውግርት፣አደስ፣ ቀጣዮ፣ ጠጄሳር፣ የባህርዛፍ ፍሬ፣የናና ቅጠል፣ እና ከሎሚ ልጣጭ ነው። እዚህ አዲስ አበባ ለራሱ አነዚህ እጽዋትና ፍራፍሬ ማግኘት ስለሚቻል የወሎን ጪስ አዘጋጅቶ ቤትን ማሽተት ይቻላል።
በዚህ በወልድያ እኔ እንደገባሁ ወያላው ወዴት እንደምሔድ ጠየቀኝ። ቆቦ አልኩት ወድዚያ የሚሔድ ሰው እንድጭንለት ጠየቅኝ። ቆቦን የሚያስጎበኙኝ ሰዎች ቀጥሬ እንደነበረና እነርሱ ስለሉ እንደማይመቸኝ ስነግረው ገብቼ መቆያ እስክበላ መኪናየን ልጠብልህ ብሎ እንዲያጥብ ፈቅጀለት መቆያ ወይም መክሰሴን በልቼ ስመጣ አጥቦ አልጨረሰም ነበርና አስመሸህብኝ ብዬ በጣም ተበሳጨሁ። እና ደጋግሜ በጣም ተቆጣሁት። ተራ አስከባሪው ወይም ወያላው ይቅርታ ጠይቆኝ ውሃ ስላልነበረ ከሩቅ ነው ያመጣሁት አንደሚችኩሉ ስለነገሩኝ መጀመር አልነበረብኝም። ነገ ግን መኪናዎ እንዲጽዳልዎት ካለኝ ጉጉት ተነስቼ አስቀይሜዎታለሁና ይቅርታ አለኝ። ከፍተኛ ይቅርታ ጠይቆ አጥቦ ጨረሰልኝ። ገንዘብ ልከፍለው ዋጋውን ስጠይቀው ምን ስላደረግሁ አቆይቼ ስላበሳጨሁዎት ሊከፍሉ አይግባም። ከልብዎት ይቅርታ ካዳርጉልኝ እርሱ ክፍያየ ነው አለኝ።
እኔ በእጅጉ ደነገጥሁ ያንን ሁሉ ስናገረው ያልተነገረ ልጅ እንደውም ክፍያው በይቅርታ ይለወጥልኝ ማለቱ በእጅጉ አስደመመኝ። ሌላው ልቤን የነካው የልጁ አነጋገር እንዲህ የሚለው ነው። ዛሬ እርስዎ ተበሳጭተው ከሄዱ ነገ ወልድያ አይቆሙም ሌሎች ጓደኞችዎትንም ከነሯቸው ወልዲያን ይጠሉዋታል። እኛ የምንጠቀምው በወልዲያ እርስዎ ከሚያገኙት ደስታ በተደጋጋሚ ሲመጡ ነው አለኝ። አያችሁዋት ቱሪዝም ምን እንደምትመስል? ይህ በወልዲያ ያለ ወጣት የሚያስበውን ህሳብ የኢህአዴግ የቱሪዝም ሚንስትር ሰራተኞቸ ያስቡታል የሚል ግምት የለኝም።ሌላው ይወልዲያ ሆስፒታል ሀኪሞችና ሰራትኞች ለህዝቡ የሚሰጡት አግልግሎት በእጅጉ ማራኪና አስደሳች ከመሆኑ የተነሳ ሆስፒታል የሄዱ ሳይሆን ምግብ ሊበሉ አንድ ትልቅ ሆቴል ገብተው የሚስተናገዱ ይመስልዎታል። ሰው አካበቢውን ይመስለል ይሉሀል እንዲህ ነው። በእርግጥ ይህ ሁሉ ቢሆንም የብዙ ትላልቅ ሰዎች ሀገር ወልዲያ ውሃ መጠማትዋ ግን አሳዛኙ ክፍል ነው። ያ ሁሉ መስተንግዶና ፍቅር እያለ የውሃ ችግር ስላለ ወልዲያን ለህዝቡ ፍቅር መሄድ ቢፈልጉም የውሃው ነገር ያሳስብዎታል። እንግዲህ ከልማታዊ ጋዜጠኞችና ልማታዊ ነኝ ከሚለው ብአዴን ብዙ ይጠበቃል። ብአዴን ሆይ ልማታዊነትህን በቴሌቪዥን ሳይሆን በመሬት ላይ እንየው።
ቆቦ ለጥ ባለ ሜዳ በሞቃታማው የሰሜን ወሎ ክፍል የተመሰረተች ውብ የውቦች ከተማ፤ በመስኖ ልማት በሀግራችን ካሉት ሁሉ በመጀመሪየው ተርታ ትቀመጣለች። በቆቦ ወንዶች ዘንድ ቅድሚያ ለሴት የሚለው አንጋገር የቃላት ሳይሆን በተግባር ነው። ወደገብያ የሚሄዱ ከሆነ የሚሸከሙት ነገር ካለ ወንዱ ያግዛታል። ባልና ሚስት ፊትና ሁዋላ ሳይሆን ጎን ለጎን ነው የሚሄዱት ለሴቶች ቅድሚያ መስጠትና የበለጠውን ከባዱን ሥራ ባል መስራትን ሌሎች አካበቢዎች ከንዚህ ከቆቦ ወንዶች ቢማሩ መልካም ነው። ምክንያቱም በአንድ አካባቢ ሴቶች ከባድ ሸክም ተሸክመው ሲሄዱ ወንዶች ባዶ እጃቸውን ጃንጥላ ይዘው የሚሄዱበት አንዳንድ ቦታ ስላለ ማለቴ ነው።
ባለፈው ሰምንት የጀመርኩትን ርዕስ ስለተጫዋቾቻችን እና ስለስፖርት ፌዴሬሽን በትንሹ ለመነካካት ሞክሬ ነበር። ከላይ በርዕሴ ካነሰሁዋችው ያልነካሁት የተመልከቾችን ጉዳይ ዛሬ ለመንካት እሞክራለሁ ብየ የነበረ ቢሆንም የመለያየት ፖለቲካ ከአባቶቻችን ልብ አልወጣ ስላለ ዛሬ አቶ ቡልቻ በተደጋጋሚ ስለሚናገሩት ነገር አንድ ለማለትት ፈለግሁ ተክታይ ጽሁፌን ሳምንት ስለምመለስበት አንባቢን ይቅርታ እጠይቃለሁ።
እንግዲህ የተከበራችሁ አንባቢያን ከላይ የጠቀስኩት ወጣት ትምህርቱ ከስምስንተኛ ክፍል ያልዘለለ የተሻለ የእውቀት ደረጀ የሌለው ነገር ግን የተሻለ አስተሳሰብ ያለውንና የዓለም ባንክ ድርጅት ውስጥ ይሰሩ የነበሩትን የአዋሽ ባንክ መስራችና የተሻለ የትምህርት ደረጀ ያላቸውን እቶ ቡልቻን ከዚህ የታክሲ ድንብ ተራ አስጠባቂ ጎን በጎን እንድታዩልኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ።
በመጀመሪያ ምንም የቋነቋ ተማሪ ባልሆንም ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ ላይ በነበርኩበት ጊዜ አስተማሪየ ስለቋነቋ ሲነግረኝ ቋነቋ እንደሚወለድ እንደሚያድግ፣ እንዲሁም እንደሚሞት የነገረኝ ሲሆን በእርግጠኝነት ያን ቀን አቶ ቡልቻ ይህ ትምህርት በሚሰጥበት ዕለት ፎርፈው ካልሆነ የእርሳቸውም አስተማሪ እንደሚያስተምር እርግጠኛ ሆኜ መናገር እችላልሁ። አቶ ቡልቻ ከምን አንጻር እንደሆነ ባይገባኝም በተደጋጋሚ ስለአመርኛ ቋነቋ ሲገዳቸው አያለሁ። መቼም ቋነቋ ብሎ ጨቁዋኝ የለም። የትኛውም ቋነቋ ከመግባቢያነት የዘለለ አንዳች ጥቅም የለውም። በእጅጉ የሚገርመው ነገር ሁሉም ቋነቋ ጎዶሎና መሆንሲሆን ቋነቋ ሁሉ ምሉዕ ስላልሆነ አንዱ ከአንዱ መዋዋሱ ነው። ቋነቋ ለራሳቸው ጎዶሎ መሆናቸውን አምነው እርስ በራሳቸው ተደጋግፈው አንዱ የሌለውን ካለው ተውሰው ተጠቃሚያቸውን እያገለገሉ ባሉበት ሰዓት እንደ አቶ ቡልቻ ዓይነቱ ቋነቋዎችን ብቻ ሳይሆን ተናጋሪዎቹንም ጭምር ለመልያየት በዚህ ባለቀ ዕድሜ መኩዋተን አስቸጋሪም አሳዛኝም ነው።
እኔ መቼም የአቶ ቡልቻንያህል ዕዉቀት የለኝም። ይህ የአቶ ቡልቻ የመከፋፈል አባዜ ከእኛ ሳይሆን ከአፍሪካ ቅኝ ገዢዎች የመጣ ሀሰብ ነው። ምዕራብያውያን አፍሪካን እንደ ቅርጫ ሥጋ በተከፋፈሉ ጊዜ ሰሜን ሶማሊያን የደረሰቻት እንግሊዝ ነበረች። ታዲያ እንግሊዝ የደረሰቻትን ሶማሊያን የከፋፍለህ ግዛ ዘዴዋን ተጠቅማ ሱማሌያውያንን በአመለካከት ከፋፍላ ከመግዛትዋም በላይ እንድ ቋነቋ፣ አንድ ሀማኖት ያላቸውን ሀዝብ ዳግመኛ እንዳይገናኙ አድርጋ እንድ ህዝብ የነበሩት በመብታትን እስከሁን ፈጽሞ አንድ ሀሳብ አንዳይሆኑ ስለ ሰራቻችው ሶማሊያውያን በአምስት ተከፍለው ተበታትነው ቀርተዋል።
በዚህ ወቅት ለቅኝ ገዥዎች ራስ ምታት የነበረው ጀግናው ሙላ ሙሐመድ አህመድ የነበረ ሲሆን ለዚህ ሰው እንግሊዛውያን ዘማድ ሙላ ሙሐመድ አህመድ ይሉት ነበር፡፡ እብዱ ማለት ነው። እነርሱ ሶማሊያን ሲበታትኑ ጤናማ እርሱ ስለሀገሩ አንድነት ሲታገል እብድ ይገርማል። አሁንም አቶ ቡልቻ የመበታትን ዓላማ ሲያራምዱ ትክክል እኛ ስለ አብሮነት ስንታገል ነፍጠኛ! እንግሊዞች እብድ የሚሉት ሙላ መሀምድ አህመድ አንገዛም ስላለ ነበር። ለመብቱ የሚታገል በገዥዎች አይወደድም። ኢህአዴግም እምቢ ለመብቴ የሚሉትን እንዴ ምንትሴ አንዴ ቅብርጥርሴ እያለ በየ እስር ቤቱ እንደ ሚያሰቃየው ማለት ነው።
አቶ ቡልቻ እያራመዱት ያለው አስተሰሰብ የማንን እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል። እኔ አቶ ቡልቻን ብሆን ኖሮ የማደርገው በተለያየ ምክንያት በፖለቲካ አመለከክታቸው ብቻ ታስረው በየእስር ቤቱ እየተሰቃዩ የሚገኙ የኦሮሞ ልጆች እንዲፈቱ እታገል ነበር። ዛሬ እነ ከበደ ገርባን የመሰለ ታጋይ ኦሮሞ በፖለቲካ አስተሰሰቡ ብቻ ታስሮ በሚስቃይባት ሀገር ተባብሮ የፖለቲከ እስረኞችን እንደማስፈታት የማይጠቅምና የማይደረስበት ዘር ቆጠራ ማንን ይጠቅመል?
ሌላው እቶ ቡልቻ በተደጋጋሚ ስለነፍጠኛው ስርዓት ለመንቀፍ መሞክራቸው ምን ያለበት ምን አይችልም። አይነት አይሆንምን? በመጀመሪያ በአጼው ዘመነ መንግስት ተምሮ ከፍተኛ ደረጃ ለመድረስ ነፍጠኛ ወይም የንፍጥኛው ስርዓት ደጋፊና አጫፋሪ ላባላዚያ ካላይ ካጣቀሰኳቸው ቤተሰብ አባለ መሆን ግድ ነበር። ከዚህም በላይ በአጼው ስርዓት የተሻለ ቦታ ለመያዝ የዚያ ሥርዓት ቀኝ እጅ መሆን ደግሞ ትልቁ ክራየቴሪያ ነበር። እርስዎ በአጼው ስርዓት እጅግ ታማኝ ባለሙዋሎች ከሚቀመጡበት የተሻለውን ቦታ ይዘው እንደነበር የታዋቃል፡፡ በዚህም የወቅቱ የሥርዓቱ ደጋፊ አሜሪካ ከሥርዓቱ ጋር ለነበረው ወዳጅነት ማጠናከሪያ ይሆን ዘንድ በዓለም ባንክ የመጀመሪያው ጥቁር ሆነው በቀጥታ እነዲገቡ ተደረጓል፡፡
በነፍጠኛው ሥርዓት ብዙ ጋሻ መሬት ኖሮአችሁ በርካታ ኦሮሞዎችን ጭሰኛ አድርጋችሁ ስታስገብሩ አልነበርን ጅብ እንኩዋን ቁርበት አንጥፉልኝ የሚለው በማያውቁት ሀግር ሄዶ ነው፡፡ እርስዎ ግን እዚሁ ይህን ሁሉ ባደረጉበት ቦታ ነዎት፤ ሌላው እርስዎ በአሜሪካን ሀገር ሄደው የተማሩት በወቅቱ የነፍጥኛው ስርዓት ማገር ስለነበሩ ነው። በተጨማሪ የእክሊሉ ሀብተወልድ ሥርዓት አልፎ አጭርና የሶስት ወር ቆይታ በነበረው የልጃችው የልጅ መኮንን ሥርዓት ውስጥ ባለሙሉ ስልጣን የግብርና ሚንስቴር ተደርገው የነብረው የውቅቱ የነፍጠኛው ሥርዓት ምሰሶና አቀንቃኝ ስለነብሩ እንጂ ለኦሮም ህዝብ ይታገሉ ስለነበረ አይደለም።
በወቅቱ እርስዎ የዓለም ባንክ ስራተኛ በነብሩበት ጊዜ ከእርስዎ ቀጥሎ ሁለተኛ ጥቁር በቦታው እንዲገባ ጠቁመውና ምሥክርነት ሰጥትው እንዲቀጠር ያደረጉት አክሎክ ቢራራን ነው። እርሳቸው ደግሞ አማራ እንጂ ኦሮሞ አይደሉም። ያን ጊዜ የተማረ ኦሮም ጠፍቶ አይደለም። እርስዎ አማራ ወዳጅዎን ያስቀጠሩት ገንዘብህ ባለበት በዚያ ደግሞ ልብህ አለ ያለውን የመጽሐፍ ቃል ለመፈጸም እንጂ፤ እኔ ማንም ኢትዮጵያዊ የተሻለ ቦታ ቢቀመጥ ግድ የለኝም። እርስዎ ደርሰው የኦሮሞ ተቆርቁዋሪ ነኝ ስላሉ ሲያደርጉ የነብሩት ነገር እንዳይሸፈን ገለጥ ለማድረግ ነው። በዚህ ጉዳይ ከኔ የተሻለ ዕውቀት ያለቸው ሰዎች አሉና ከዚህ በመነሳት ዘርዘር አድርገው እንደሚጽፉት እሙን ነው። ሌላው ለአስራ ሰባት ዓመት ደርግ ይህቺን ሀገር ሲገዛ በእርግጥ ከአሁኖቹ ተቃዋሚዎች አንደንዶች የኢሠፓ ከፍተኛ አምራር የነበሩ ሲሆን አንዳንዶች ግን ባሉበት ሆነው ስልብሔራቸው ሲጮሁ ነበር። እርስዎ ግን ኢህአዴግ ሀግሪቱን ሲቆጣጠር ነው ኦሮሞ ፌዴራሊስት የሚል መታውቂያ ይዘው የገቡት። ያም ሆኖ በፊትም ቢሆን የኖሩት ከፊውዳሎች ጋር ስለነበረ ቀጥሎም በአሜሪካ ሲቀማጠሉ በመኖርዎ የኦሮሞን ህዝብ ባህል ባለማወቅ የኦሮሞን ህዝብ ከሌላው ለመለየት ሲሰሩ የታያል፡፡ ዋናው የእርስዎ ዓላማ ግን በፊውዳሉ ሥርዓት በኦሮሞ ህዝብ ላይ ሲደርስ ለነበረው በደል ከበዳዮቹ ጎን ቆመው ስለነበረና አብረው ሲበደሉ ሰለነበረ ይህንን በደል የኦሮሞ ህዝብ እንዳይቆጥርብዎት ለማድረግ የሚደክሙ ይመስለኛል። ለነገሩ ከመላዕክት ቀጥሎ በይቅርባይነቱ ተወዳዳሪ የሌለው የኦሮሞ ህዝብ በደልዎን ስለማይቆጥር ተጨማሪ ጥፋት ከመስራት ቢቆጠቡ መልካም ነው።
ልክ አሁነ እርስዎ እንደሚደርጉት በተለያየ ጊዜ የሀገራችንን ህዝብ ለመከፋፈል የተሞከረ ሲሆን ብዙው የመከፋፈል ዓላማ በብልህ መሪዎች እና በጀግኖቹ የኢትዮጵያ አርበኞች ሳይሰካ ቀርቷል። በዋህነት በተደረገ እንግዳ ማክበር ግን አንዱ ተሳክቶለቸዋል። በአንድ ወቅት ሁለት አውሮፓውያን ወደ ንጉሱ ይመጡና ልናስተምር ከሀገራችን ተልከን መጥተን ነው ይሉአችዋል። ምንድን ነው የምተስተምሩት ክርስትና ይሉአቸዋል። ሁለታችሁም አንድ ዓይነት ዶግማና ቀኖና ነው ያላችሁ ሲሉአችው የለም የተለያየን ነን ይላሉ። ዓላማው ክርስትናን መስበክ ሳይሆን ኢትዮጵያውያንን በዓመለካከት መከፋፈል መሆኑ የገባቸው ንጉሱ። የማን ፊሎሶፊ ትክክል ነው ይሉአቸወል። በአጋጣሚ ሳይዘጋጁበት ስለተጠየቁ፤ አንዱ የኔ ነው አንዱም የኔ ነው ይለል። ንጉሱም ሂዱና ተስማምታችሁ ኑ ብለው ያበርሩአችዋል። አነደነትን የነፍጠኛ ፓረቲ ነው ከማለት በመጀመሪያ ካፋፋዮቻችን ከራሳችሁ ጋር ተስማሙ፡፡
በሌላ ጊዜም እንዲሁ አንዱ ሀይመኖት ለማስተመር መምጣቱን ሲነግራቸው ንጉሱ የእጅ ጥበብ የሚያስተምረን እንጂ ሀይመኖት የሚየስተምሩ መምህራን የምንማርበት መጽሐፍት አሉን ብለው አሰናብተው ወደ ሀግሩ የሚሸኙት መንገድ አሳይ አብረው ሰጡና ያሰናብቱታል። ያም ሰው ወደ ድንበር እንደደረስ አሞኛል በማለት ለተወሰነ ጊዜ ከአንድ ሰው ቤት ይተኛና ሁለቱን ሰዎች አንዱን ሳሎን አንዱን ጓዳ አድርጎ ለአንዱ ጸጋ አንዱን ቅባት ብሎ አንዱን ክርስትና አንድ ተንኮለኛ አውሮፓዊ ሰው ለሁለት ከፍሎ አንድ አሳብ የነበሩ ሁለት ኢትዮጵያውያንን ልባቸውን ለሁለት ከፈላቸው።እነርሱም የጎጃምን ህዝብ ለሁለት ከፍለው አፋጁት። ያም ፈረንጅ ንጉሱ እኔን ሳይቀበለኝ ቢቀርም እኔ ግን በሽተኛ መስዬ ተኝቼ ኢትዮጵያውያንን የተለያየ አመለከክት አስይዤ ጊዜ ጠብቆ የሚፈነዳ ቦንብና የማይነቀል እሾህ ለኢትዮጵያ ተክየባታለሁ፡፡ አለ ይባላል። ያ ችግር እስካሁን አለ የአቶ ቡልቻንም የመከፈፈል ሀሳብ ስር ሳይሰድ መመታት ስላለበት ነው።የእርሳቸው ሀሳብ ለትውልዱ ጊዜ ጠብቆ የሚፈነዳ ቦንብ መቅበር ነው፡፡ ዛሬ ትውልዱ ዘር ለመቁጠር ሥራም ኣላጣ ሚስት እንኩዋን ሲያገባ ፍቅር እንጂ ዘር አይቆጥርም። እርግጠኛ ሆኜ ስለትውልዱ መናገር የምችለው ጋብቻን በመግባባት እና በፈቃቀር እንጂ የማን ዘር ነሽ የሚለውን ጥያቄ ትቶታል። ስለዚህ የነ አቶ ቡልቻ ድካም ከንቱ ነው ባይነኝ።
ህዝብ በመከፋፈል የሚገኝ ትርፍ ሀገር መበታተን ብቻ ነው። ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ኖራ አቶ ቡልቻ አዋሽ የሚባል ባንክ ለመመሥረትና ሚኒሊክ ባካለሉት ክልል ያለከልካይ አንዱን በደቡብ ክልል በአዋሳ፣ አንዱን በሶማሊያ ክልል በጂጂጋ፣አንዱን በሐረሪ ክልል በሐረር ፣ በኣማራ ክልል በደሴና በመሳሰሉት ማቋቋም የቻሉት ሚኒሊክ ከአፍሪካ ቅኝ ገዢዎች ጋር እኩሌታውን በሀይል ቀሪውን በመደራደር ድንበር ስላካለሉ በሚኒሊክ ክልል ውስጥ እንደ ፈለጉ ማቆም ሲችሉ ነገር ግን ከድንበሩዋ አንድ ስንዝር አለፍ ብሎ ማቆም ያልተቻለው የሌላ ሀገር ስለሆነ ነው። እዚህች ቅርብ በኢትዮጵያና በሶማሌ ላንድ ድንበር ቶጎ ጫሌ ላይ የእኛን ሀገር ባንክ መክፈት የሚቻለው ከድልድዩ ወዲህ ብቻ ነው። ከድልድዩ ማዶ የሱማልያ ክልል ስለሆነ አይቻልም። ሚኒሊክ ያንን በማድረጋቸው ዛሬ ላይ ከማንም በላይ አቶ ቡልቻን ጠቅሟል። መቼም እርሳቸውን በየስርዓቱ እነዲጠቀሙ እግዜር ስለፈቀደ ብዙዎች በሚታሰሩባት ሀገር እርሳቸው እንደፈለጉ ይሆናሉ፡፡ ሀገሪቱ መቼም ለሚገለባበጡት ነው የምትሆነው፡፡ ንጡሐንማ ያልታደለ በር ቆዳው አታሞ የሆናል እንዲሉ ባየእስር ቤቱ ይማቅቃሉ፡፡
ሌላው በዚህ ሰዓት ሚኒሊክን የሚወቅስ ሰው ካለ የዓለምን ስቴት ፎርሜሽን ሂደት ያልተረዳ ሰው እንደሆነ ይገባኛል።ዕልጣንን ተረክቦ ሀገር ለመምራት የሚታገል አንድ ሰው ባማጃማሪያ ስለስቴት አመሠራረት ማወቅ ይጠበቅበታለ፡፡ ስቴት ሲመሰረት የራሱ ሂደት ዓለው ያ ሂደቱ ደግሞ በርካታ የነበሩ መንግስታትን ወደ አንድ የማምጣና ግዛትን የማስፋፋት ሂዳት ስለሆነ ግጭቶች ይፈጠሩና ጦርነቶች ይቀሰቀሱ ዘንድ ግድ ይላል። ዛሬ ላይ አቶ ቡልቻ ሊያስታውሱት ያልቻሉት ሚኒሊክ በዚያን ጊዜ በመላ ሀገሪቱ ዞረው ግዛቱን ባያስፋፉ ኖሮ የአሁኑዋ ኢትዮጵያ ትኖር ነበር ወይ የሚለውን ነው፡፡ደግሞስ እርሳቸው ላቆሙት ድርጅት በደቡብ ለማቆም የደቡብን መንግስትን መጠየቅ ግድ አይሆንም ነበር ወይ? ያስ ቢሆን ደግሞ እንዴት ይቻላል። የተለያየ ሀገር ስለሚሆን የመገበያያ ገንዘቡ አንድ ስለማይሆን ዛሬ በኬኒያ፣ በሱማሌና በሱዳን መክፈት እንዳልቻሉት እንዲሁም በሀዋሳና በደሴ መክፈት እንደማይችሉ እንዴት ሊግባቸው አልቻለም።ለነገሩ ዕወቅ ያለው በአርባ ቀን ሲያውቅ አትወቅ ያለው በአርባ ዓመቱ አያውቅም፡፡ እንደተባለው ነው። ጀርመን ስትመሠረት የነበረውን ከፍተኛ ፍጅት ቢያነቡ በቂ ይሆን ነበር።
አቶ ቡልቻ ይህንን ይሰማሉ ወይም አንብበው ይረዳሉ በሚል ግምት ሳይሆን ሌላው አንባቢ እንዲረዳና ተመዝግቦ ለታሪክ እንዲቀመጥ ብቻ ይህንን ማለት ወደድኩ እርሳቸው በተደጋጋሚ የአንድነት ፓርቲን የአዲሳባ ልሂቃንና የአማራ ፓርቲ ነው ይላሉ። ይህ አንጋገር እርሳቸው ሲናገሩት እንድነትን እየመረቁት ነው ማለት ነው። እኛ ትክክሉን ስንነግራቸው ስድብ ነው ይላሉ። ለማንኛውም ስለዚህ ነገር ሁለት ጥያቄ ልጥይቃቸውና አንዱን ብቻ በትክክል ከመለሱልኝ የእርሳቸው ሀሳብ ትክክል ነው ብየ ልከተላቸው ለነግሩ አንዱን አይደለም ግማሹን አይመልሱትም። የመጀመሪያው ጥያቄ እርስዎ ብሔርዎት ምንድን ነው ይሚለው ነው? እርስዎ ሲወለዱ የስንት ዓመት ልጅ ሆነው ተወለዱ? የተወለዱትስ እንዴት ነበር? እናትዎ እርስዎን ለመውለድ ምጥ በያዛቸው ጊዜ ከጎረቤቶቻችሁ ውስጥ እነማን ነበሩ? ይህንን ግን እናትዎት የነገሩዎትን እና በእምነት የተቀበሉትን ሳይሆን እርስዎ የሚያውቁትን ብቻ እንዲንግሩኝ እፈልጋለሁ። ይህንን በትክክል የሚያውቁትን የተወለዱበትን ቦታ የተወለዱበትን ሰዓት መናገር ከቻሉ እርስዎ የሚናገሩት ሁሉ ትክክል ነው ማለት ስለሆነ ልቀበልዎት።
ያለበለዚያ እርስዎም ሲወለዱ እንደኔና እንደሌላው ሰው ሁሉ ተወልደው ከሆነ እንኩዋን ብሔርዎትን ይቅርና እናትዎትንም በእምነት ነው የተቀበሉት እንጂ እርግጠኛ አይደሉም። ስለዚህ እኔ እንዲህ ነኝ ብሎ መናገር አይቻልም። ቋነቋም ከሆነ በአጋጣሚ እርስዎ ተወልጄበታልሁ ከሚሉት ቦታ በአሻጋሪ ካለው ቦታ ከሌላ ብሔር ተወልደው በምሥራቅ ወለጋ ስላደጉ ኦሮምኛ ችለው ይሆናል። ምክንያቱም ቋነቋ እንደሆን ያደጉበትን እንጂ የተወለዱበትን ዘር ማንጸባረቂያ አይደለም። ለዚህም ምስክር ከሁለት ኢትዮጵያውያን በእንግሊዝ ሀገር የተወልዱና ያደጉ ልጆች እንግሊዝኛ እንጂ የቤተሰቦቻቸውን ብሔር ቋነቋአለመቻል አንዱ ምሥክር ነው።የመለያየት ፖለቲካ የሠይጣንና የቅኝ ገዥዎች ነው።
አባቶቻችን እንደርስዎ ቢሆኑ ዛሬ ኢትዮጵያን ማግኘት እንዴት በከበደ ነበር። ምክንያቱም የተለያየ ቋነቋ ባህልና ሀይማኖት ስላለን ለማለት ነው። ግን ሚኒሊክ አትዮጵያን ከመሠረቱ በሁዋላ ጣሊያን ሀግራችንን ሊወር ሲመጣ የከምባታ፣የሶማሌ፣የአፋር፣የሀረሪ፣የቤንሻንጉል፣የ
አቶ ቡልቻ በተደጋጋሚ ስለመለያየትና መበታተን ሲናገሩ ነኝ የሚሉትን ብሔር አለማወቃቸው ያሳዝነኛል። አሁን ያለችው ኢትዮጵያ ስትመሰረት የአንበሳውን ድርሻ በወቅቱ የነበሩት የኦሮሞ ልጆች ይወስዱታል። ኦርሞ በባህሉ እንግዳ ተቀባይ አብሮት መኖር የሚፈልገውን ሰው በተለየ መልኩ በዘር ባይወለድ እንኩዋን እንደተወላጅ ኦሮሞ አድርጎ የመውሰድ ባህል ያለው ነው።በርካቶች ከአካባቢያቸው ለቀው ሥራ በሔዱበት ኦሮሞዎች ልጃቸውን ሚስት መሬታቸውን ርስት አድርገው ሰጥተው ኑዋሪ አድርገዋቸዋል። ለምሰሌ ጉዲፈቻ፣ሞጋፈቻና የመሳስሉት አንድን ኦሮሞ ያልሆነን ሰው ኦሮሞነትን የመስጫና የመቀበያ ስርዓቶች ናቸው። አንድ ሰው በትክክል ኦሮሞ ከሆነ እንደ አባቶቹ አንድ መሆንን ይሰብካል። አሁን እርስዎ እያራመዱት ካለው አመለካከትዎ ስነሳ በኦሮሞነትዎ ላይ ህሉ ጥያቄ እየፈጠረብኝ ነው።ልጅ አባቱን ካልመሰለ የአባቱ ልጅ አይደለም።
ሁለተኛው ጥያቄ አንድነት የአዲሳባ ልሂቃንና የአማራ ፓርቲ ስለመሆኑ እንዴት እርግጠኛ ሆኑ? ለምሳሌ ተወላጁ በእምነት ይቀበላል ቢባልም ያሰው ሲወለድ በቦታው የነበሩ ሰዎች ግን እርግጥኛ ናቸው። እስኪ አቶ ቡልቻ በእውነት እርስዎ እርግጥኛ ሆነው በተደጋገሚ ስለእንድነት ፓርቲ የአዲሳባ ልሂቃንና የአማራ ፓርቲ እንደሆነ ሲናገሩ እሰማለሁ። እኔን ጨምሮ ከአንድነት አባለት ሲወለዱ በቦታው ስለነበሩበት ሁለት ሰዎች ይጥቀሱ በእርግጥ ሊያደርጉት አይችሉም። ለምን በአንድነት ፓርቲ ላይ ያለዎትን ጥላቻ ከማንጽባረቅ የዘለለ በእውቀት ላይ የተመሠረተ ተቃውሞ አያቀርቡምና ነው።
በዚህ ላይ አንድ ነገር ማየት ከተቻለ አቶ ቡልቻ ማንም አማራ፣ትግሬ፣ደቡብ፣አፋር፣…ወይም ሱማሌ ሆኖ ለመወለድ አምልክቶ የተወለደ የለም። የሰው ልጅ ድግሞ ሰው ሆኖ መወለዱ ይበቃዋል። ምንም ሆኖ መወለድ ሀጢያት አይደለም። ግለሰቦች እንዲህ ነኝ ብለው ሊገዙ ይችላሉ። ግለሰቦች ሲገዙ ለሚሰሩት ስህተት ደግሞ ህዝብ አይጠየቅም። አቶ ቡልቻ በሚገርም ሁኔታ የኣማራ ህዝብ ያለበትን ሁኔታ ቢያውቁ ኖሮ እርስዎ ለራስዎ ይህን ህዝብ የሚረዳ ፓርቲ ያቋቁሙ ነበር።አንድነት ፓርቲን የአመራ ነው ከማለት በፊት የአንድነትን አደረጃጀት ማወቅ ተገቢ ነው። አንድነት የተሻለ አደረጃጀት ከአማራ ክልል ይልቅ በደቡብ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል፣ በአፋር፣ በቤኒሻንጉልና በትግራይ ክልሎች አሉት። ይህንን ፓርቲ የዚህ አካል ነው ብሎ መክሰስ እርስዎ አሁን የቆሙበት ቦታ በመጀመሪያ ኢህአዴግን ተከትለው መጥተው ቆሜበታለሁ ባሉበት ቦታ ናቸውን የሚል ጥያቄ ያስነሳብዎታልና ቆም ብለው አስበው ስለ አባባልዎ ማስተባብያ ቢሰጡ መልካም ነው።
ሌላው የተከበራችሁት የአንድነት ደጋፊዎች አሁን አንድነት ፓርቲ በመላው ሀገሪቱ የጀመርውን ሀዝበዊ እንቅስቃሴ ማሰናከያ አንዱ መንገድ የአቶ ቡልቻ ክስ ሊሆን ስለሚችል በተለያየ የግል አመለካክት ስለሚስጡ ሰንካላ ምክንያቶች ሳትዘናጉ ከአንድነት ጋር በመቆም በገዢው ፓርቲ ላይ ተጽዕኖ ማሳደር እንችል ዘንድ የአክብሮት ጥሪየን አስተላልፋለሁ። ለሳምንት ቸር ይግጠመን
13 ባለስልጣናት ተሾሙ
(ዘ-ሐበሻ) ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ አቶ በረከት ስም ዖንን እና የአዲስ አበባ ከንቲባ የነበሩትን አቶ ኩማ ደመቀሳን የጠቅላይ ሚንስትሩ የፖሊሲ ጥናት እና ምርምር አማካሪ ሚንስትር አድርገው ከሾሙ በኋላ በተጨማሪም ለ11 ተጨማሪ ባለስልጣናትን ሹመት ማስጸደቃቸው ከአዲስ አበባ የመጣው መረጃ አመለከተ። እንደመረጃው ከሆነ ም/ል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በጣምራ ይዘውት የነበረውን የትምህርት ሚ/ርነት ሥልጣን ተገፈው “የአማራው ሕዝብ ጠላት” በሚል ቅጽል ስም የወጣላቸው አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ስልጣኑን እንዲይዙት ተደርጓል።
በቅርቡ ከስልጣን በተባረሩት የፍትህ ሚ/ሩ ብርሃን ሃይሉ ምትክም አቶ ጌታቸው አምባዬ መሾማቸው ተገልጿል። አዳዲሶቹን ሹመኞች ዝርዝር እነሆ፦
1. አቶ ደመቀ መኮንን – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
2. አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ወላሳ – የትምህርት ሚኒስትር
3. አቶ ሬድዋን ሁሴን ራህመቶ- የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር
4. አቶ አህመድ አብተው አስፋው – የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
5. አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ነገዎ – የትራንስፖርት ሚኒስትር
6. ወይዘሮ ሮማን ገብረስላሴ መሸሻ – በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር
7. ወይዘሮ ደሚቱ ሃንቢሳ ቦንሳ – የሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ሚኒስትር
8. አቶ ጌታቸው አምባዬ በለው – የፍትህ ሚኒስትር
9. አቶ በከር ሻሌ ዱሌ – የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር
10. አቶ በለጠ ታፈረ ደስታ – የአካባቢ ጥበቃና የደን ሚኒስትር
11. አቶ መኮንን ማንያዘዋል እንደሻው – የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር
ያለፉት ሃያ አንድ ዓመታት ፖለቲካ –ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ
ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ የዕለቱን ንግግራቸውን የጀመሩት በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የታወቀውን የሩስያ ሥነ ጽሑፍ ሰው አሌክሳንደር ኸርት ሰርን አባባል በማስቀደም ነበር። ይህ ጸሐፊ ‹‹ታሪክ ከውርስ የሚገኝ ማብቂያ የሌለው እብደት ነው›› ይል እንደነበርና ይህ ብቻ ሳይበቃም “ታሪክ የእብዶች ግለ-ታሪክ ነው” ማለቱን አስታውሰዋል። ለዚህ አባባሉም ምሳሌዎች ያቀርብ ነበር ያሉት ዶ/ር ዳኛቸው፣ የፐርሺያ ጦር አቴንስን ሊይዝ ሲመጣ ካርቲዬስ የተባለው ጀግና ጦሩን ለማቆም ዘሎ ገደል ይገባል። ካርቲዬስ ገደል የሚገባው የዘመተበት ጦር ይቆማል በሚል እሳቤ ነበር። ኤፍጂኒያ ላይ ንጉሡ መርከቡ ከአቴንስ የባሕር ዳርቻ ለመልቀቅ ሲፈልግ ንፋስ ከሌለ ንፋስ እንዲመጣ በማሰብ የ13 ዓመት ሴት ልጁን ሰውቷል። ይህም እብደት ነው።
በሦስተኛ ደረጃ፡- የፕራሺያ ንጉሥ የተወሰነ ውቅያኖስ አስቀይሞኛል በማለት ወደ ሦስት መቶ ሺሕ ወታደር ሰብስቦ ውቅያኖሱን በጅራፍ ያስገርፈው ነበር። ይህም እብደት ነው። አራተኛ፡- አቴናውያን ከአእምሮ የፈለቀ ነገር ሲያስቸግራቸው የሶቅራጠስን አንጎል በሄሞሎክ አጥበው ገደሉት። አምስተኛ፡- ክርስትና ገና ብቅ ብቅ በሚልበት ጊዜ የሮማው ግዛተ ዐፄ ቄሣሮች የክርስትና አማኞችን ለአውሬ በመስጠት እምነቱን ይፈታተኑት ነበር። በመጨረሻም ክርስቲያኖቹ ደግሞ የበላይነትን ሲቆጣጠሩ ነገሥታቱ ካደረጉት አስከፊ ሥራ በላይ እርስ በርስ ጭከና በሞላበት አኳኋን ተበዳድለዋል። እንግዲህ አሌክሳንደር ኸርት ሰርን ‹‹ታሪክ የእብዶች ግለ-ታሪክ ነው›› ያለው ይህን ሁሉ ካለ በኋላ ነው።
ዶ/ር ዳኛቸው የአሌክሳንደር ኸርት ሰርን አባባል ወደ ሀገራችን ሲያመጡት አንድ ምሳሌ ጠቅሰዋል። “አንድ ሺሕ አራት መቶ ማይልስ የሚያህል የውኃ ጠረፍ ካስረከብን በኋላ አራት መቶ ኩንታል ድንች ለማያመርት ቦታ ከ50 እስከ 60 ሺሕ ወጣት በጦርነት ገብረናል። ይህ ደግሞ የእኛ ሀገር የታሪክ እብደት ነው” ሲሉ ከዐሥራ አራት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተደረገውን ጦርነት “የእብደት ታሪክ ነው” ብለዋል።
ዛሬ ከ21 ዓመታት በኋላ
ዶ/ር ዳኛቸው ከላይ የተጠቀሰውን የ“እብደት ታሪክ” ከተረኩ በኋላ አሁንስ ሲሉ ጠይቀዋል። በዚህ ንኡስ ሐሳብ ሥር “የት ነው ያለነው? ምን ዐይነት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው? ሥርዐቱ ምን ላይ ነው?” በማለት አንዳንድ ነጥቦችን አጋርተዋል።
ከሁሉም በላይ ኢሕአዴግ “አብዮታዊ ፓርቲ ነኝ” የሚለውን አገላለጽ በንግግራቸው ያስቀደሙት ዶ/ር ዳኛቸው፣ “አብዮት ብዙ ጊዜ ስለ ማኅበራዊ ፍትሕ የሚያወራ ነገር ነው። የፈረንሳይን፣ የአሜሪካን፣ የራሺያን እንዲሁም የእኛንም አብዮት ብናይ ሄዶ ሄዶ መሠረቱ ማኅበራዊ ፍትሕ ነው፤” ብለዋል።
“ማኅበራዊ ፍትሕ ደግሞ የሚገለጸው ፍትሐዊ የነዋይ ክፍፍል ላይ ነው” የሚሉት ዶ/ር ዳኛቸው በእኛም ሀገር “ገበሬው ደኃ ነው” በሚል “መሬት ለአራሹ” መባሉንም በማስታወስ የአብዮት ማዕከላዊ ማጠንጠኛ (focal point) ማኅበራዊ ፍትሕ እንደሆነ አስረድተዋል።
ኾኖም ግን አብዮት በተፈጥሯዊ ሂደቱ የሚሸጋገርባቸው ደረጃዎች እንዳሉት ዶ/ር ዳኛቸው ተናግረዋል። ይህም ከአንድ እስከ ሦስተኛ ደረጃ እየተባለ ሊከፋፈል ይችላል። ምሁሩ ደረጃዎቹን ከመግለጻቸው በፊት አብዮት በምን መልኩ ሊነሣ እንደሚችል ጠቁመዋል። አብዮት የሚነሣው በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ያለ የመንግሥት መዋቅር መቀጠል ሲያቅተው፣ ሕዝቡም ባለው ሥርዐት ርካታ ሲርቀው ጉሩምሩምታ ያሰማል። ከዚያም ወደ ቀውስ ይገባል። በአንፃሩ የተለያዩ ፓርቲዎች ብቅ ብቅ ማለት ይጀምራሉ፤ እናም ቀውሱ ለፍትሕና ለንዋይ አቅርቦት ያለው ተነሳሽነት ምንም የማይላወስ ይኾንና ሥርዐቱ ሲዳከም በተቃራኒው በትይዩ የሚቋቋሙ ኃይሎች ተጠናክረው “ይህን መንግሥት ብንሽረው ይሻላል” ብለው መንግሥትን ይለውጣሉ ብለዋል።
ዶ/ር ዳኛቸው መንግሥትን ለመለወጥ ሁለት ነገሮች ያስፈልጋሉ ይላሉ። አንደኛው “ብንለውጠው በጎ ነገር እናገኛለን” የሚል እምነት ሲኾን፣ ሁለተኛው ደግሞ መሥዋዕትነት ነው። እነዚህ ሁለቱ ነገሮች ሲቀናበሩ መንግሥት ይለወጣል። ይህ የአብዮታዊ ሂደት የመጀመሪያው ደረጃ ሲኾን ሁለተኛው ደረጃ የመንግሥት ለውጡ ከተሳካ በኋላ የሚያጋጥመው ከባድ ነገር ነው።
ሁለተኛው ደረጃ ከባድ ሊሆን የሚችልበትን ምክንያት ዶ/ር ዳኛቸው ሲያስረዱ፤ “አዲስ ሥርዐት ሲዘረጋ ጎበዝ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ ፈሪ ሰዎችም አሉ። አገር ወዳዶች እንዳሉ ሁሉ አጋጣሚውን መጠቀም የሚፈልጉ ሰዎች አሉ። ባለተስፋዎች እንዳሉ ሁሉ ኪሳቸውን መሙላት የሚፈልጉ አሉ። አንድ አብዮት እነዚህን ሁሉ አቅፎ ነው የሚመጣው። በኻያኛው መቶ ክፍለ ዘመን በድኅረ አብዮት መንግሥት ተብሎ ከተዘረጋ በኋላ የበላይነት የሚይዙት ሆዳሞቹ ናቸው። ክላሽ ሲተኩስ የነበረው ተወርውሮ አንድ ቦታ ቂብ ይላል። በዚህ ጊዜ በመካከላቸው ግጭት ይመጣል። ሕዝባዊነታችን ላላ፣ ርእያችን ግቡን አልመታም የሚሉ ይነሡና ከጥቅመኞቹ ጋራ ውዝግብ ይጀመራል” ብለዋል።
ሦስተኛው የአብዮት ደረጃ አብዮቱ ሕዝባዊ መኾኑ ያበቃና በ(Thermadorial) ወይም ራስን ማዳን ዋነኛው አጀንዳ ይኾናል ያሉት ዶ/ር ዳኛቸው፤ “አብዮቱ ተረስቶ ተመልሶ ራሱን ወደ መከላከል ያመራል። በዚህ ጊዜ ምንም ዐይነት የነፃነት ጥያቄዎችንና ንቅናቄዎችን አይታገሥም፣ የማዕቀብ ኃይሎቹ ይጠናከራሉ፣ ተቀናቃኝ ቡድኖች ጫና ይበዛባቸዋል፤” ብለዋል።
ሌላው ሦስተኛው የአብዮት ደረጃ (Thermadorial) ጊዜ ማዕቀብን ከማጠናከር ባለፈ አዲስ ነገር የለም። አዲስ አነጋገር የለም። ሁልጊዜ ወደኋላ ይኬድና ያለፈውን ስርዓት እንዴት መጥፎ እንደሆነ የሚነገርበት ጊዜ ነው ብለዋል። እንደምሳሌም ዶ/ር ዳኛው ስለሀገራችን ሁኔታ ሲጠቅሱ የአቦይ ስብሐትን ንግግር አስታውሰዋል። አቦይ ስብሃት “የድሮውን ስርዓት ማስታወስ አለብን” ማለታቸውን ጠቅሰዋል። አፄ ኃይለስላሴ ከነገሱ ግን 72 ዓመት ሆኗቸዋል። ያም ሆኖ የአብዮቱ ሕዝባዊነት ሲያበቃ (Thermadorial ደረጃ ሲደርስ) አንድ ክፍለ ዘመን ወደኋላ ሄደህ ታወራለህ፤ ምክንያቱም አሁን ባለህበት ሁኔታ የምታቀርበው አዲስ ነገር የለም። አዲስ ነገር አምጥቼ ላውራ ብትል “ያው የርግብ አሞራ” ብለህ ነው የምትዘፍነው፤ ያልቅብሃልና፤ አስደማሚ ፕሮጀክቶችን እየፈጠርህ እንዲህ አደርጋለሁ በማለት የሕዝባዊነት መሸርሸር (Thermadorial) ደረጃ መድረስ ነው። የራሺያ አብዮተኞች ይህን ሁኔታ ያውቁታል ሲሉ አስረድተዋል።
የአብዮቱ ሕዝባዊነት ሲያበቃ (Thermadorial ደረጃ ላይ ሲደርስ) ዐምባገነናዊ መሆን ይከተላል ያሉት ዶ/ር ዳኛቸው፣ “ይኸውም ፍጹማዊ ዐምባገነን አገዛዝ (Absolutism, Absolutist) መሆን ማለት ነው። በፍፁማዊ ዐምባገነንነት ከተቀናቃኞች ባለፈ አብዮቱን ታግለው ባመጡ ታጋዮች ላይ ሳይቀር የማይመለስ እንደኾነና ሕዝባዊነት የሚረሳበት ወቅት እንደኾነ አስረድተዋል። ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ደረጃም ከዚህ አንፃር በመመዘን ፍርዱን መስጠት እንደሚቻል አመላክተዋል።
ፉፁማዊነት (Absolutism) ምንድን ነው?
ዶ/ር ዳኛቸው የአብዮትን አመጣጥና ምንነት እንዲሁም የደረጃዎቹን ባሕርይ ከጠቀሱ በኋላ ‘ፍጹማዊነት’ (Absolutism) የሚለውን ጥቅል ሐሳብ አብራርተዋል። በዶ/ር ዳኛቸው እምነት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መንግሥታዊ ሥርዓት ‘Authoritarian’s’ ነው ወይስ ‘Dictatorial’ ከሚለው ሁሉ የሚስማማቸው “Absolutism” የሚለው ነው።
የዐፄ ኀይለ ሥላሴ የፈረስ ስም “ጠቅል” ነበር። ሥርዓታቸውና የፈረሳቸው ስም የተዋሃደ ነበር። ፈረሱን ተምሳሌታዊ ያደርጋሉ “ጠቅል” ሲሉ ፍፁማዊ ስርዓት (Absolute State) እየፈጠሩ ነበር። የሰሜኑን ባላባቶች ተራ በተራ በፖለቲካ ራቁት ካስቀሩ በኋላ “ጠቅል” ነው የሆኑት። እንደ ዐፄ ቴዎድሮስ “አገር በእጄ” ነው ያሉት። ዐፄ ኀይለ ሥላሴ ቢያንስ ግልፅ ነበሩ። አሁን ግን ለየት ያለ “ጠቅል” ነው የመጣብን ብለዋል።
በዶ/ር ዳኛቸው አነጋገር አሁን ያለው “ጠቅል” ስሙን የደበቀ ፈፁማዊነት (Absolutism) ነው። ስሙን የደበቀ ያሉትን (Absolutism) ሁለት መሠረታዊ ባሕርያት እንዳሉትም አስረድተዋል።
አንደኛው Absolutism የሚባለው “It is a power that is not oppose in fact by adequate countervailing powers” እንደሆነና ምንም ዐይነት ተቀናቃኝ ኀይል የሌለው ነው። የተደራጀውንም ሆነ ያልተደራጀውን የማይታገስ ፍፁማዊ ነው። ከተደራጀህ ትካተታለህ፣ ካልተደራጀህ አትችልም ያሉት ዶ/ር ዳኛቸው “አንዲት የፍልስፍና ማኅበር እንመሰርታለን ብለን ስንሯሯጥ አንድ ቅፅ ሰጡን። ቅፁ ከዘጠኙም ክልል አንድ አንድ ሰው ከሌላችሁ “ኢትዮጵያ” የሚባል ቃል አትጠቀሙም ተባልን እና ወሰዱንና በነርሱ ቅፅ አካተቱን። ወደፊት ደግሞ ምን አይነት የፍልስፍና ውይይት እንደምናደርግ ቅጂውን ትልኩልናላችሁ ይሉን ይሆናል” ብለዋል። እና በአሁኑ ወቅት አፀፋዊ ኃይል የለም (No countervailing Force) ሲሉ ገልፀውታል። በአሁኑ ወቅት ነጻና ራሱን ችሎ የቆመ ሲቪል ማኅበረሰብ አይፈቀድም። የሃይማኖት ተቋማት፣ እንደ ዕድር ያሉት ማኅበራዊ ተቋማት ሳይቀሩ ተገብቶባቸዋል። ምናልባት ዕቁብ አምልጦ ይሆናል በማለት የመጀመሪያውን የ‘Absolutism’ ምልክት አብራርተዋል።
አሁን ባለንበት ወቅት የብዙኃን መዋቅር (pluralistic structure) የለም፤ ሁሉም ነገር አሃዳዊ ነው ያሉት ዶ/ር ዳኛቸው ስልጣን ከአንድ ምንጭ ነው የሚመነጨው። ያ ስልጣን ደግሞ መጠን የለውም። “ከድንጋይ ጠረባ አንስቶ እስከፈለጓት ድረስ ተደራጅተህ ና” ነው የሚለው “የምትደራጀው በእኔ ስር ነው። አውቅሃለሁ እመዘግብሃለሁ፤ የምርጫ ቀን ደግሞ ተሰልፈህ ትወጣታለህ ነው የሚለው” ሲሉ አስረድተዋል።
ሌላው የAbsolutism ፀባይ የዴሞክራሲ ማዕከላዊነት (Centralized Democracy) መሆኑን ያብራሩት ዶ/ር ዳኛቸው በአሁኑ ወቅት ሊራቡና ሊበራከቱ የሚችሉ ቡድኖች (multiplied groups) እንዲኖሩ አይፈቀድላቸውም። በጥቅሉ “Uni-centric Power” ወይም ሁሉን ነገር ያካተተ ኃይል ነው ብለውታል።
በተጨማሪም የAbsolutism መንግስት ባሕርይ በሕግ የማይገሠጽ (a State that is not disciplined by law) የሚሉት ነው ያሉት ዶ/ር ዳኛቸው አገዛዙ ሕግ የማይገሥጸው ነው። አጥፊዎቹን እየቀጣ እራሱ ግን ሕጉ በማይደርስበት ቦታ ነው ያለው ብለዋል። በኢትዮጵያም ሕግ የማይገሰፀው ሹመኛ በየቀበሌው መኖሩን አስረድተዋል። ሀገሪቱም ቢሆን በስም ካልሆነ በስተቀር ሕገ-መንግስታዊ ሀገር አይደለችም። በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ ሕግ ያልገራው ፈረስ ነው ብለዋል።
የፍጹማዊ ዐምባገነን አገዛዝ የፖለቲካ ኃይል ምን ላይ ነው ያረፈው?
ዶ/ር ዳኛቸው የAbsolutism ስርዓትን ምንነትና ሁኔታ ካስረዱ በኋላ ስርዓቱ በምን አይነት የፖለቲካ ስልጣን ላይ እንዳረፈም አብራርተዋል።
“ስልጣን ዝም ብሎ አይኖርም። አንድ ቦታ ላይ ማረፍ አለበት። ምርኩዝ ያስፈልገዋል። በመጀመሪያ ማንኛውም የፖለቲካ ስልጣን ከኢኮኖሚ ኃይል ጋር የተቆራኘ ነው። በፊውዳል ሥርዓት ጊዜ አስገባሪዎቹ የፖለቲካ ሥልጣን ነበራቸው። ስለዚህ ሥልጣን በሁለት ነገር ላይ ያርፋል። አንደኛው ሥልጣን በተፈጥሮ ላይ ሲሆን ሁለተኛው ሥልጣን በሰው ላይ ያርፋል። ሥልጣን በተፈጥሮ ላይ የልሂቃን ሥልጣን ነው። ዛፉ አይፈራገጥም፣ ወንዙም አይፈራገጥም። ስልጣን በሰው ላይ ሲሆን ግን አስቸጋሪ ይሆናል።
አንድ መንግስት ሥልጣኑን ሲያፀና ሦስት ወሳኝ ነገሮችን ይተገብራል። አንደኛው በማጥመቅና በማሳመን (Persuasion) ሰዎች በእውቀተና በስሜት ያንን የበላይ ሥልጣን እንዲቀበሉ ማስገደድ። ለዚህ ነው ሬዲዮና ቴሌቪዥን ሃያ አራት ሰዓት ሲያወራ የሚውለው:: ሁለተኛው ቁሳዊ ጥቅማ ጥቅም (material Benefit) ነው። ለምሳሌ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ እናደርሳችኋለን፣ ግድቡ ሲጠናቀቅ ሁሉም ነገር አረንጓዴ ይሆናል … እንደዚህ ሲሆን እንደዚህ ይሆናል … ወዘተ እያሉ እኛ ከቆየን ትጠቀማለችሁ ይሉናል። ሦስተኛው ደግሞ አጅሬ ጉልበት (violence) ነው ብለዋል።
የሦስቱ ጣምራ ሂደት ሥልጣን በሰው ላይ (Power over men) እንደሚባል ያወሱት ዶ/ር ዳኛቸው ዴሞክራሲያዊ በሆኑና ባልሆኑ አገራት ከሦስቱ የሥልጣን ሂደቶች የትኛው የበላይ ይሆናል የሚል ነው። ርዕዮተ ዓለሙን እያሳመነ የሚሄድ ስርዓት ሊቆይ ይችላል። ቁሳዊ ጥቅም የሚሰጥ ሥርዓት የሚደራደርበት ነገር አለው። ጉልበቷ ግን ለአጭር ጊዜ “ቀጭ” ለማድረግ ትረዳለች። እና በፍፁማዊነት አገዛዝ ወቅት የማሳመንና ቁሳዊ ጥቅማ ጥቅም የመስጠት ሁኔታ እየቀነሰ ጉልበት እየጨመረ ይሄዳል” ብለዋል።
ሌላው በabsolute state ስርዓት በኢትዮጵያ ለየት የሚያደርገው power over other men derived from power over nature ነው ብለውታል። ይሄንንም ሲያብራሩ ፍፁማዊነቱ በተፈጥሮ በምጣኔ ሀብት ላይ የተመረኮዘ ነው። ነገር ግን ተፈጥሮን ምን አመጣው ብሎ መጠየቅ ይቻል ይሆናል። በኢትዮጵያ 60 ሚሊዮን ገበሬ ተፈጥሮ ላይ እየሰራ ነው። ተፈጥሮ ላይ የሚሰራን ሰው (ገበሬ) ተፈጥሮውን በመቆጣጠር የበላይ መሆን ነው። ይህ ደግሞ መሬት የመንግሰት ነው በማለት በ60 ሚሊዮን ገበሬ ላይ ስልጣንን ማፅናት ነው። ይህ ደግሞ (power over men derived from power over nature) የሚባለው እንደሆነ አስረድተዋል።
ይህ ደግሞ በዶ/ር ዳኛው አገላለፅ “የሚገርም መቆጣጠር” ነው ብለውታል። በሌላ አነጋገር ይህ የሚገርም ቁጥጥር 26 ሚሊዮን ገበሬ አውጥቶ ተራራ እና ወንዝ እያስቆፈረ መሆኑን አስረድተዋል። ዶ/ር ዳኛቸው “የቁጥጥር አባዜ” ያሉት ይህ አሰራር “ካድሬዎች በሚያወጡት ፕሮግራም መሠረት 26 ሚሊዮን ገበሬ ምንም ሳይከፈለው አርባ ቀን ማስቆፈር ማለት የሚገርም ነው። ፈውዳሎቹም እንደዚህ ያደረጉ አይመስለኝም። ሴት ልጇን አዝላ፣ ገበሬዎች ከቀሩ 60 እና 70 ብር እየተቀጡ፣ ከሁሉም ደግሞ የሚገርመው በቴሌቪዥን ሲቀርብ ባንዲራ ተይዞ አታሞ እየተመታ እልል እየተባለ… እንዴት ነው? የሰው ልጅ ሳይከፈለው፣ አርባ ቀን ለመስራት እየዘፈነ፣ እየዘለለ ጣራ እየመታ የሚሰራው? ምን አይነት የሰው ስነ-ልቦና ነው? የማይሆን አይነት የ‘ሕዳሴ ፕሮጀክት’ ይያዛል፤ ይፈርሳል …” ሲሉ አስረድተዋል።
ፍፁማዊነት እና ምስጢራዊነት
በዶ/ር ዳኛቸው አገላለፅ በ‘Absolutist State’ ትግል ስልታዊ ውሳኔዎች (tactical Decisions) አሉ። እነዚህ (tactical Decisions) ሁልጊዜ የሚሰሩት በምስጢር ነው። ይህ አሁን ያለው አገዛዝ absolutist ብቻ ሳይሆን Secretive (ምስጢራዊም) ነው። ለ‘Absolute’ ሥርዓት ምስጢር ጠቃሚና ወሳኝ ማሳሪያ ነው። ምስጢራዊ ሥርዓት ደግሞ ሄዶ ሄዶ የለየለት ‹ኦሊጋርኪ› ነው። ጥቂት አርስቶክራስት ናቸው ሀገር የሚመሩት። ቁጥራቸው ትንሽ ቢሆንም፤ ስፋታቸው ብዙ ነው። ሁለት ሚሊዮን አባል …. ሦስት ሚሊዮን አባል…. “አባል አባል … ይሄንን አባባል በጣም ያፈቅሩታል። ነገር ግን ከላይ የኦሊጋርኪ ማነቆ አለ። ምስጢር ጠብ አትልም። እያዞሩ ግን የሰው ምስጢር በቴፕሪከርደር ይሰበስባሉ። ይሄ ዝም ብሎ አባል ነኝ እያለ የሚሽከረከረውን ተውት ማነቆው እላይ ነው። ማነቆው ጠባብ ናት’’ ብለዋል።
ነፃነትና ሕግ
ፍፁማዊ ስርዓትን የተነተኑት ዶ/ር ዳኛቸው ይሄው ስርዓት ከነፃነትና ከሕግ ጋር ስላለው ግንኙነትም ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ነፃነትና ሕግ በጣም ወሳኝ ጉዳዮች መሆናቸውን በሰፊው አውስተዋል። ሕግና ነፃነት ወይም ነፃነትና ሕግ ያላቸው ዝምድና እንዲሁም ከህግ የበላይነት (Rule of law) ወደ Rule by law ‘‘ሕግ እያወጡ ማሸት’’ እያነፃፀሩ አሳይተዋል።
ሕግ እያወጡ መግዛት (Rule by law) የተወሰኑ ሰዎች እንደፈለጉ ሕግ እያወጡ ‘‘ተከተለኝ’’ ማለት ሲሆን የህግ የበላይነት (Rule of law) ግን በህግ መመራት መሆኑን አብራርተዋል።
ዶ/ር ዳኛቸው ነፃነትና ሕግ ያላቸውን ግንኙነት ሲያብራሩ ያለሕግ ነፃነት እንደሌለ ገልፀዋል። ሕግ በውስጡ ትእዛዝ ብቻ ሳይሆን መብትና ፍትህ ያዘለ መሆን አለበት ብለዋል። ትልቁ የእንግሊዝ ፈላስፋው ጆን ሎክ “ስልጣን በአንድ ቦታ ከተከማቸ በዚያው መጠን ነፃነት ይሞታል” ማለቱንም አስታውሰዋል።
የኢትዮጵያ የሕግ ታሪክ በአቶ አበራ ጀምበሬ መጠናቱን ያስታወሱት ዶ/ር ዳኛቸው፣ ሕግ ዝም ብሎ ትእዛዝ አይደለም። ሕግ ሰዎች በር ዘግተው የሚያወጡት ትእዛዝ አይደለም። ሕግ መብት የሚል ፅንሰ ሐሳብ አለው። ፍትሕ ከሚባለው ነገር ጋራ አብሮ ተጣምሮ የሚገለጽ ነገር ነው። በኢትዮጵያ በሕግ አምላክ ሲባል ሕግ ፍትሕን ማቀፉን ያመለክታል። ‘‘ሕጉ ይከለክላል’’ ሲባል ፓርላማ ያወጣው ሕግ ማለት ብቻ አይደለም።
አሁን ሕግ መብት ፍትህ የሚለው ቀርቶ ሰዎች አንድ ቦታ ተሰብስበው የሚያወጡት ትእዛዝ ሆነ፤ እነ እገሌ… አሸባሪ ናቸው እየተባለ ሕግ ይወጣል። የውጭውን መሬት ሸጬ ጨርሻለሁ አሁን ደግሞ የግቢህን እሸጣለሁ የሚል ሕግ ይወጣል፤ የኻያ አራት ወይም የኻያ አምስት ዓመት ወጣት ርእዮት የምትባል ትንሽ ልጅ አነበበች ነው ምናምን ተብሎ 14 አመት ሽብርተኛ ተብላ ይፈረድባታል። ታዲያ ይሄ ሕግ ፍትህ አለው?’’ ሲሉ በመጠየቅ በሀገራችን ላይ ሕግና ነፃነት የተራራቁ ሆነዋል። ሕጉ አለ ብለን እንቅልፍ እንዲወስደን ነበር ነገር ግን ሕጉ ጥበቃ ሊያደርግልን አልቻለም። ምክንያቱም ከሰዋዊ ሥልጣን አልተላቀቅንም (Power depersonalized) መሆን አልቻለም። የሕግ አመራር (Rule by law) ሳይሆን የሰው አመራር ነው ያለው ብለዋል።
ፍትህና ህግ እየተጋጩ መሆኑንም ዶ/ር ዳኛቸው አብራርተዋል። ፍትሃዊ ያልሆነ ሕግ፤ ሕግ አይደለም ብለዋል ‘Just Law’ እና ‘Unjust Law’ የሚባል ነገር እንዳለም አብራርተዋል። ማርቲን ሉተር ኪንግ ታስሮ አንድ ቄስ ‘‘አንተ ሰላማዊ ሰልፍ እያስወጣህ ሕግ እየሰበርክ ነው’’ አሉት እሱ በበኩሉ ‘‘እኔ ሕግ ሰባሪ አይደለሁም። እርስዎም ሆኑ እኔ ሴንት ኦገስቲንን አንብበናል። ‘Just Law’ የሚባል ነገር አለ Unjust Law የሚባል ነገር አለ። እኔ እየተቃወምኩ ያለሁት ዘረኛውን (Unjust Law)ን ነው። Unjust Law ደግሞ ሄዶ ሄዶ ህግ አይደለም አላቸው። እና ሕግ ዝምብለው ሰዎች የደነገጉት ትእዛዝ ማለት አይደለም። ቢያንስ ፍትሃዊ መሆን አለበት። ሂትለርም ሕግ እያወጣ ነበር የሚያሻው። እና አሁንም ሕገ መንግስቱን ተፃራችኋል፣ ሕጉ አይፈቅድም የሚባለው የሕግ Fetish (ልክፍት) ነውያለው’’ ብለዋል።
ሌላው የ‘Absolute State’ ባሕርይ የቃላት ቅየራ መሆኑን ዶ/ር ዳኛቸው አብራርተዋል። የድሮ ቃላቶች እንደ ወለቀ ሱሪ ይዘቀዝቁትና በውስጣቸው ያለው ሳንቲምና መሐረባቸው ይወጣና ሌላ ስያሜ ይሰጣቸዋል። ቃላቱ የሐሳብ ይዘታቸው ከወጣ በኋላ የራስህን ጫና ታሳርፍባቸዋለህ። በኢሕአዴግም ሁለት አይነት ቃል ነው ያለው። በኢህአዴግኛ ‘‘ኪራይ ሰብሳቢ’’ መጥፎ ቃል ‘‘ልማታዊ ባለሃብት’’ ጥሩ ቃል ነው። ይህ ማለት ከቃል ጋር ያለውን ሃሳብ እንዳንፈትሽ ቃሉን መጠቋቆሚያ ንቅሳት (ሲግናል) ያደርጉታል፤ ‘‘ኪራይ ሰብሳቢ’’ ሲሉህ ትደነግጣለህ፤ “Bad Boy” ነህ ማለት ነው።
‘‘እኔ የኮራሁ ኪራይ ሰብሳቢ ነኝ። እኔ የማውቀው ቤት ሲከራይ፣ ብስክሌት ሲከራይ፣ መኪና ሲከራይ ነው። እኔም ከደረግ የተረፈ ቤት እያከራየሁ እንጂ የዩኒቨርሲቲው ደመወዝ አይበቃኝም። ታክስ ግን እከፍላለሁ። እና ኪራይ ሰብሳቢ እያሉ ለምን ሞራሌን ይነኩታል። በአምስትና ስድስት ሺህ ዶላር ቤታቸውን የሚያከራዩ ጎበዞች እያሉ ዞረው እኔን ኪራይ ሰብሳቢ እንዴት ይሉኛል’’ ያሉት ዶ/ር ዳኛቸው የተሰጠንን ቃል ብቻ ይዘን እንድንቀጥል ነው የሚፈልጉት ሲሉ አስረድተዋል።
በመጨረሻ ኢህአዴግን የሚገልፅልኝ ከአንድ ጣሊያናዊ ፈላስፋ የወሰድኩት ሁለት ቃል አለኝ ያሉት ዶ/ር ዳኛቸው ሁለቱ ቃላትም Noviticsm and Beyond-ism የሚሉ ናቸው። Noviticsmየሚለው ቃል Novices ከሚለው ቃል የመጣ ነው። Novice ደግሞ አዲስ ጀማሪ ማለት ነው። Beyond-ism ያው Beyond መሄድ ማለት ነው።
Noviticsm ማለት ሁሉን ነገር እኛ እንደ አዲስ ጀመርነው ማለት ነው ያሉት ዶ/ር ዳኛቸው ገጣሚ በዕውቀቱ ስዩም አንድ ቀልድ አለው ‘‘ለቤተሰቤ አራተኛ ልጅ ለመሆን የመጀመሪያው ነኝ’’ ይላል። ይሄ Noviticsm ነው፤ Original ማለት ነው ብለዋል።
ወደ ጣሊያኑ ፈላስፋ (ሳርቱሪ) ሲመለሱ ሁሉም ትውልድ በዘመኑ Original ለመሆን ይሞክራል። ያልተባለና ያልተደረገ ነገር አደረኩ ለማለት ይሞክራል፤ “But it is not easy to be original”፤ ነገር ግን የታሪክ ቅጥያ የሚባል ነገር አለ። አልፌዋለሁ ስትል ይመጣል። ተሻግረነዋል ስትል የመጣል። አሁን ለምሳሌ በፊውዳል ጊዜ የነበሩት እንደ “ቀዳማዊ እመቤት” የሚባሉ አባባሎች እየመጡ ነው። ወደፊት ደግሞ ራስ፣ ደጃዝማች… እያለ ይቀጥላል’’ ብለዋል።
ይህን ካሉ በኋላ ዶ/ሩ ወደ ፈላስፋው ሲመለሱ “The easy way of being original” ማለት ብዙ አለማወቅ ነው። ብዙ አለማወቅ ደግሞ ታሪክን አለማንበብ ነው። ይሄ ደግሞ “Arrogance of Ignorance” ማለት ነው። ይህም ማለት አለማወቅ የራሱ የሆነ ‘Ignorance’ አለው። ስታውቅ ትሑት ትኾናለህ፤ ትሕትናን ታዳብራለኽ፤ ካላወቅኽ ግን ጣሊያናዊ ፈላስፋ በዚህ ዓለም ላይ አልፎ አልፎ ‘‘እኛ እስከመጣን ድረስ ዓለም ጨለማ ውስጥ ነበረች ዕድሜ ለእኛ ችቦ ብርሃን ታየ የሚሉ ጎበዞች ይመጣሉ’’ ብሏል። ጣሊያኑ ስለኢትዮጵያ የሚያውቀው ነገር ባይኖርም እስቲ ከኢትዮጵያ ጋ አዛምዱት ሲሉ ጠይቀዋል።
ባለሥልጣናት “በኢትዮጵያ ስንመጣ ብርሃን ሆነ” ማለት የተለመደ ነው። ስለህግ ሲወራ ኢትዮጵያ ከአሁን በፊት ምንም አይነት ሕግ ያልነበራት ትመስላለች። ጎበዞቹ ሲመጡ ሕግ እንዳመጡለት ነው የሚያወሩት። ጎበዞቹ [ኢህአዴጎቹ] ሁሌ ስንገዳደል አግኝተውን እነሱ ባመጡት ሕግ እንደ አዳኑን ይነግሩናል። ነገር ግን ይሄ አገር ስንት ሺህ አመት የኖረ ሕዝቡም ያልተፈራረመው ማኀበራዊ ውል (social contract) ያለው ሕዝብ ነው። ሕዝቡ ለዚህ ነው የማይፈርሰው። እንደአካፋው ብዛት ባለፉት 21 ዓመታት ይሄ አገር (ስቴት) መናድ ነበረበት። ከመንግስት ውል በላይ በማኀበራዊ ውሉ የጠነከረ ሕዝብ ነው። የሶማሌ ሕዝብ ማኀበራዊ ውሉ በጎሳ የላላ ስለሆነ ቢሉት ቢሉት አንድ መሆን አልቻለም ብለዋል።
ሁለተኛው የጣሊያናዊ ፈላስፋ አባባልና ከኢሕአዴግ ሁኔታ ጋራ ያዛመዱት ‹Beyond-ism› (ተሻግረዋል) የሚለውን ፅንሰ ሐሳብ ነው። ይህ ሐሳብ እብሪት ነው ብለዋል። በየቴሌቪዥኑ ‘‘በንጉሱ ጊዜ’’ የሚባለው አሁን አሁን ደግሞ ‘‘በሁለቱ ስርዓቶች’’ እየተባለ ነው። እና ‘‘ተሻግረነዋል’’ የሚለው አገላለፅ እብሪት ይወልዳል። ‘‘እኛ ነን የሁሉም ጀማሪ’’ ይባላል። ‘‘ድሮ እንዲህ ነበር አሁን እንዲህ ነው የማለት አባዜ ነው።’’ ብለዋል።
በመጨረሻም ዶክተር ዳኛቸው፣ አዲስ የመሆን ጥልቅ ፍላጎት ሁሉን ነገር አልፌአለሁ በሚል ሐሳብ ቢወጠርም ታሪክ ግን እንደ ሲሲፒየስ ሊመስል ይችላል በሚል ተዘምዶ ንግግራቸውን ቋጭተዋል። እንዲህ ሲሉ፡- “ሲሲፒየስ ማለት ትልቅ ቋጥኝ ይዞ ከገደል አፋፍ ላይ ይወጣና ልክ ገደሉን ወጣሁ ሲል ቋጥኙ መልሶ ይወርድበታል። የሀገር ታሪክ ማለት በከፊል እንደዚያው ነው። ይህም እነኾ 26 ሚሊዮን ገበሬ አሠማርቼ የኢትዮጵያን መልክአዊ ምድራዊ ገጽታ እለውጣለኹ የሚለው እብሪታዊ ፕሮጀክት መገለጫ ነው!!”