Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

ሐረርነት እና ጎንደርነት!

$
0
0

በሰሎሞን ተሰማ ጂ

አዳላህ እንዳልባል እንጂ፣ የዚህ መጣጥፍ ርዕስ “ጎንደርነት እና ሐረርነት”ም ቢባል አያወዛግብም፡፡ ነገር ግን፣ ሐረር ከጎንደር በምስረታዋም ሆነ በቀደምትነቷ የታወቀች ስለሆነ ነው ርዕሳችንን ሐረርነት እና ጎንደርነት ያልነው፡፡ እንደምታውቁት ስለሐረርነት እና ስለጎንደርነት ማውራት ማለት፣ ስለሐረሬዎች ወይም ስለሐረሪዎች ማውራት አይደለም፡፡ በተመሳሳይ መልኩም፣ ስለጎንደርነት ማውራት ማለት፣ ስለጎንደሬዎች ማውራት ማለት አይደለም፡፡ የዛሬዎቹ ሐረሬዎችም ሆኑ የዛሬዎቹ ጎንደሬዎች ከመፈጠራቸው ብዙ መቶ አመታት በፊትም ሐረርነት እና ጎንደርነት ነበሩ፡፡ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ልናወሳው የፈለግነው ስለሁለቱ ከተሞች ሳይሆን ስለታሪካቸው፣ ስለስነ-ሰብዓቸው፣ ስለሃይማኖታቸው፣ ስለፖለቲካቸው፣ ኤኮኖሚያቸውና ስለባሕላቸው ነው፡፡ በጥቅሉ ይህ፣ ጽሑፍ የሐረር እና የጎንደር (ወይም አዳላችሁ እንዳንባል የጎንደር እና የሐረር) ፖለቲካዊ ፍልስፍናን በደሕና መስኮት ወደውስጣቸው ለማሳየት የሚጥር ይሆናል፡፡ (በበሩ ገብቶ ሐረርነትን እና ጎንደርነትን በቅጡ ማወቅ የሚፈልግ ካለ፣ ጠቀም ያለ ገንዘብ ቆጥቦ/ቋጥሮ ለቀናት ወይም ለወራት ያህል ቢጎበኛቸውና ቢያጠናቸው ይበጃል፡፡) ሐረርነት እና ጎንደርነት ብዙ-ብዙ ምስጢራትን የተሸከሙ ጽንሰ-ሃሳቦች ናቸው፡፡
ይህንን ጽሑፍ ጽሁፍ ስጽፍ በማናነት ያነበብቸውንና ያዳመጥኳቸውን መጽሐፍትና የሬዲዮ ንግግሮች ለአንባቢያን ማውሳት አሻለሁ፡፡ በመጀመሪያ የሚመጣው በ1867 ወይም በ1868 እ.አ.አ. ተጽፏል ተብሎ የሚገመተው የእንግሊዛዊው ደራሲና ገጣሚ አርኖልድ ማቲው ሥራ ነው፤ “Hebraism and Hellenism” ይሰኛል፡፡ ይህ ደራሲ በሁለት ጽንሰ-ሃሳቦች መካከል ያለውን ልዩነት ለመተንተን ያደረገው ቁዘማ ተንተርሶ፣ በ20ኛው ክ/ዘመን የመንትዮች ተቃርኖ (Binary Opposition) የተባለ ኃይለ-ሃሳብ በቋንቋ፣ በስነ-ጽሑፍ፣ በፍልስፍና፣ በሂሳብና በኮምፒውተር ሳይንስ እንዲሁም በሌሎች የጥናት መስኮች ውስጥ ተሰራጭቷል፡፡ ማቲው ጥልቅ ቁዘማ ነበር የደረገው፡፡
harar
ከአርኖልድ ማቲው ለጥቆም በ1964 እ.አ.አ የተጻፈውን የሊዮ ስትራውስ (Leo Strauss) “Athens and Jerusalem” የተሰኘ ጥናታዊ ጽሑፍ ለማንበብ ጥረት አድረጌያለሁ፡፡ የሊዮ ስትራውስ ጽሑፍ፣ በተለይም በፖለቲካዊ ፍልስፍና አተያዮች በኩል ያለኝን ግንዛቤ እንዳሻሽል ጥሩ የአይን መግለጫ ሆኖኛል፡፡ በመጨረሻም፣ በሬዲዮ ንግግሮቹና አስተማሪ ጽሑፎቹ የሚታወቀው፣ የዶክተር ዳኛቸው አሰፋን “አክሱማዊነት እና ላሊበላዊነት” የተሰኘ ገለጻ ደጋግሜ ያዳመጥኩ መሆኔን ለአንባቢያን መግለጽ እወዳለሁ፡፡
የዶ/ር ዳኛቸውንና የአርኖልድ ማቲውን ፈለግ ተከትዬ፣ የጽሑፌን ርዕስ “ሐረርአዊነት እና ጎንደርአዊነት” ልለው አልፈለኩም፡፡ የመጀመሪያው ምክንያቴ፣ በሀገራችን ውስጥ ያለውን የዘርና የመንደርተኝነት/የጎጠኝነት ፖለቲካ የማልደግፍ በመሆኔ ሲሆን፤ ምናልባትም “-አዊነት” የሚለው ታካይ ምዕላድ ሌላ አይነት የፖለቲካ ትርጉም ሊሰጠው እንደሚችል ስለገመትኩ ነው፡፡ ሁለተኛውም ምክንያቴ ደግሞ፣ የአርኖልድ ማቲውንና የዶ/ር ዳኛቸውን ምዕላድ ከመጠቀም ይልቅ፣ የሊዮ ስትራውስ “Athens and Jerusalem” የሚለውን አካኼድ መከተሉ የሁለቱን አካባቢዎች ታሪክ፣ ባሕል፣ ፖለቲካ፣ ኤኮኖሚ፣ ሃይማኖትና ፍልስፍና ለመግለጽ የተመቸ ሆኖ ስላገኘሁት ነው፡፡ ስለሆነም፣ ርዕሴን “ሐረርአዊነት እና ጎንደርአዊነት” በማለት ፈንታ፣ “ሐረርነት እና ጎንደርነት” ብዬዋለሁ፡፡ አንባቢያንም፣ በዚህ “ትርጉሙ ብቻ” እንድትወስዱልኝ ስል በትህትና እጠይቃለሁ፡፡
ወደዋናው ርዕሰ ጉዳያችን እንመለስ፤ ሐረርና ጎንደር 1101 ኪሎ ሜትር ያህል ይራራቃሉ፡፡ አመሠራረታቸውም ቢሆን በጣም የተራራቀ ነው፡፡ ሐረር በ1248 ከአረብ ፔኑዜላ በመጡ 405 ሼኰች ተመሰረተች ተብሎ ይታመናል፡፡ በአቅሪያዋ (የዛሬን አያድርገውና) 18 ኪሎ ሜትር በስተሰሜን ምዕራብ በኩል የሐሮማያ (አለም ማያ) ሀይቅ ነበር፤ ምንም ደሴት አልነበረውም፡፡ ዛሬ ሙሉ ለሙሉ ደርቋል፡፡ ከዚህም ሌላ፣ ሐረር አምስት ሆስፒታሎችና አንድ ዩኒቨርሲቲ፣ አንድ የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ፣ አንድ የጤና ሳይንስ ት/ቤት (በተለምዶ Nursing School) አንድ የአውሮፕላን ማረፊያ (ድሬ-ጠያራ ይባላል፤ 12 ኪሎ ሜትር በስተሰሜን በኩል) ይገኝ ነበር፡፡ የአውሮፕላን ማረፊያው አገልግሎት መስጠት ካቆመ የአንድ አዛውንት ዕድሜ አስቆጥሯል፡፡ አንድ የሕዝብ ቤተ-መጽሐፍ አላት፡፡ ብቸኛው የከተማዋ ሲኒማ ቤት (ሐጂ ቦምባ-እየተባለ ይጠራል፣ በጣሊያን ጊዜ የተሰራ ነው፡፡ ከዚህም ሌላ፣ ሐረር የታወቀው የሦስተኛው ክፍለ ጦር መቀመጫ ነበረች፡፡ የዛሬን አያድርገውና፣ የታወቀው የሐረር ጦር አካዳሚም እስከ 1983 ዓ.ም ድረስ በርካታ የወታደራዊ ክሕሎት ያዳበሩ ወጣት መኮንኖችን አስተምሯል፡፡ ከሁሉም-ከሁሉም፣ የማይረሳኝ የሐረር ጀጎል (በግንብ አጥር የተከለሉት ሰባት ቀበሌዎችና ቤቶቹ ሲሆኑ)፣ ከተማዋ በ1998 ዓ.ም የዓለም ቅርስ ሆና ተመዝግባለች፡፡ ጀጎል ውስጥ የሐረር ገዢዎች (አሚሮችና ሕዝቡ በአንድ ግንብ አጥር ስር በጋራ ኖረዋል፡፡ ሐረር ከአዲስ አበባ 520 ኪሎ ሜትር በስተምስራቅ ትርቃለች፡፡

በተመሳሳይ መልኩም፣ ጎንደር ከአዲስ አበባ 748 ኪሎ ሜትር ያህል ስትርቅ፣ በ1626/7 ዓ.ም ገደማ በአፄ ፋሲል ተመስርታለች ተብሎ ይገመታል፡፡ መስራቿ አፄ ፋሲልም ሆኑ ወታደሮቻቸው፣ እንዲሁም ካህናቱና የእደ-ጥበብ ባለሙያዎቹ ከዚሁ፣ ከኢትዮጵያ ናቸው፡፡ ወይም የኢትዮጵያን አየርና እህል፣ ማርና ወተት እየተመገቡ ያደጉ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ (እያወራን ያለነው፣ ከተማዋ በምትቆረቆርበት ዘመን መሆኑን ልብ ይሏል፡፡) ከጎንደር 60 ኪሎ ሜትር በስተደቡብ በኩል የጣና ሐይቅ አለ፤ ከሠላሳ ሰባት (37) በላይ ደሴቶች አሉት፡፡ ልክ እንደ ሐረር ሁሉ፣ አምስት ሆስፒታሎች፣ እንድ ዩኒቨርሲቲ፣ አንድ የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ፣ አንድ የጤና ሳይንስ ት/ቤት፣ አንድ የአውሮፕላን ማረፊያ (አዘዞ አካባቢ ወይም 10 ኪሎ ሜትር በስተደቡብ በኩል) ይገኛል፡፡ አሁንም አገልግሎት ይሰጣል፡፡ እንደ ሐረር ሁሉ፣ አንድ የሕዝብ ቤተ-መጽሐፍ አላት፡፡ ብቸኛው የከተማዋ ሲኒማ ቤት በጣሊያን ጊዜ የተሰራ ነው፡፡ ከዚህም ሌላ፣ ጎንደር የምትታወቀው በወታደራዊ ከተማነቷ ነው፡፡ ጎንደርን የጎበኘ ሰው፣ ከሁሉም-ከሁሉም የማይረሳው የጎንደር አብያተ-ነገስታት ግንብ ነው፡፡ በርካታ ነገስታትም በዚህ ቅጥር ግቢ ውስጥ ኖረው አልፈዋል፡፡ ሕዝቡ ግን ከግንቡ አጥር ውጭ ነበር የሰፈረው፤ አሁንም ሰፍሮ ያለው፡፡ ይህም የነገስታት ቅጥር/ግንብ፣ እ.አ.አ በ1979 በዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል፡፡

የሐረርነት ጉዳይ ከእስልምና ጋር በቀጥታ ይያያዛል፡፡ በጀጎል ውስጥ ብቻ እንኳን 44 መስኪዶች ሲኖሩ፣ ከጀጎል ውጭ ደግሞ 38 መስኪዶች ይገኛሉ፡፡ ብዙዎቹ መሰኪዶችም የቅዱሳንን መቃብር በውስጣቸው ይዘዋል፡፡ መስኪዶቹ ውስጥ ለመቀበር ቅዱስ መሆን ወይም መሪ መሆን ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌም ያህል፣ የአው አባዲሪን፣ የአው ዜይንን፣ የአው ዶቢርን፣ የአው ሐኪምን፣ የአው ወሪቃን፣ አው ኡመርንና የሌሎችንም መቃብር ስፍራዎች ብንመለከታቸው መስኪዶችም ናቸው፡፡ (በነገራችን ላይ “አው” ማለት “ቅዱስ” ማለት ነው በአካባቢው ቋንቋ፡፡) ከመሪዎቹም ውስጥ አሚር ኑር ኢብን ሙጃህድ መቃብር መስጂድ ውስጥ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ሐረርነት አስክሬንን በማድረቂያ አማካይነት አድርቆ አያስቀምጥም፡፡ በሐረርነት እና በእስልምናም ሃይማኖት አስከሬን ማድረቅ “ሀራም” ነው፡፡ ሐረርን የሚጎበኝ ሰው፣ ከራስ መኮንን (ደርግ የምስራቅ አርበኞች) ሆስፒታል ብሎት ነበር፣ አጠገብ ያለውን የአሚር ኑር መቃብር ቢጎበኝ፣ እውነትነቱን ያረጋግጣል፡፡ ከዚህም ሌላ፣ በሐረር ከረመዳን ጾም አንድ ሳምንት በኋላ የሚከበረው የሸዋል ኢድ በዓል፣ ለሐረር ወጣቶች የመተጫጫና የፍቅር ቄጠማ የመቁረጫ ጊዜ ነው፡፡ ጎረምሶቹና ልጃገረዶቹ፣ ደማቅና ብርቅርቅ ልብሶችን ለብሰው ለክብረ በዓሉ ፈላና በር አጠገብ ድንኳን ተደኩኖ ለስድስት ቀናት ያህል ይታደማሉ፡፡ ያልቀናውም ለከርሞ እድሉን ይሞክራል፡፡
Gonder
በአንጻሩ፣ ጎንደርነት በእጅጉ ከክርስትና ጋር የተሳሰረ ነው፡፡ በጎንደር ከተማና በዙሪያዋ ብቻ እንኳን 44 አብያተ-ክርስቲያናት አሉ፡፡ አብዛኞቹ አብያተ-ክርስቲያነትም በዙሪያቸው የመቃብር ስፍራዎች አሏቸው፡፡ የተለየ ቅድስና ያለው ሰው ካልሆነ፣ ወይም ከነገስታቱ ወገን ካልሆነ በስተቀር ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ የሚቀበር ሰው የለም፡፡ ካለም አሰክሬኑ/አጽሙ በማድረቂያ እንዲደርቅ ተደርጎ ይቀመጣል፡፡ አስከሬንን ገንዞና አሽሞንሙኖ መሸኘት የጎንደርነት ክብር ነው፡፡ ከዚህም ሌላ፣ በጎንደር ለጥምቀት በዓል አምሮና ተውቦ ለመተጫጨት መውጣት አግባብ ነው፡፡ ባሕል ነው፤ ወግም ነው፡፡ ጎረምሶቹና ልጃገረዶቹ፣ አዲስና የክት ልብሳቸውን ለብሰው ለክብረ በዓሉ ፋሲል መዋኛ እየተባለ በሚጠራው፣ የጥምቀተ-ባሕር ተገኝተው ያከብሩታል፡፡ የቀናው ይተጫጫል፡፡ ያልቀናውም ለከርሞ እድሉን ይሞክራል፡፡

ስለባሕላዊ ጉዳዮች እናንሳ፡፡ ሐረርነት የሚመነጨው ፊት ለፊት ከመናገር ነው፡፡ ቂም መያዝም ሆነ ማኩረፍ የተለመደ አይደለም፡፡ በንግግሮቻቸው ጣልቃ “አቦ ተወኝ! አቦ ተይኝ!” ይላሉ፡፡ ከተገረሙ ደግሞ፣ “ወለበል!” ማለታቸው የተለመደ ነው፡፡ ያቺ የሚታወቁባትም ስድባቸው አለች፤ “እናትክ……!” ይላሉ፡፡ “አሚር” የሚለውን ስም ሐረርነት ለወንድ ልጁ በብዛት ይሰጣል፡፡ “(ገዢ! መስፍን!” እንደማለት ነው፡፡) ሐረርነት እነዚህ መሰል መገለጫዎች አሉት፡፡ በአንጻሩ ጎንደርነት ደግሞ፣ በፈሊጥ መናገርን ይወዳል፡፡ በቀጥታ ልጥፍ አድርጎ አይናገርም፡፡ በገደምዳሜ ወይም በምሳሌና በተረት መናገር ጨዋነት ነው፡፡ በጎንደርነት ውስጥ “ኧረ ባባጃሌው!” ማለት መገረም ነው፡፡ አልፎ አልፎም “ኦረ! ኦረ!” ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ የሚታወቁባት ስድብ የለቻቸውም፡፡ ፋሲል፣ ግዛቸው እና ቴዎድሮስ የጎንደርነት ተወዳጅ ስሞች ናቸው፡፡

ሐረርነት ውስጥ ኦሮምኛ ተናጋሪነት፣ የሐረሪ ቋንቋ ተናጋሪነት፣ የሶማሌኛ ተናጋሪነት፣ አርጎቢኛ ተናጋሪነት፣ አማርኛ ተናጋሪነት፣ ጉራጌኛ ተናጋሪነት፣ አረቢኛ ተናጋሪነት አሉ፡፡ የወደቀን ማንሳት፣ የሞተንም መቅበር የሐረርነት መለያ ባሕሪ ነው፡፡ ድንበር አሳብሮ ነግዶና ሸቅሎ ወደሀገር መግባት በሐረርነት ውስጥ የተለመደ ነው፡፡ በሐረርነት ውስጥ መሸፈት ወይም “ጥራኝ ዱሩ፣ ጥራኝ ደኑ” እየተባለ አይዜምም፡፡ አይፎከርምም፡፡ ጠዋት ተጣልቶ፣ ከሰዓት አብሮ “በርጫ” ላይ መጫወት የተለመደም ነው፡፡ ሽፍታ ወይም ወንበዴ ወይም ደግሞ ምቀኛ ፈጽሞ አይፈራም ነበር፡፡ እንኳን ሰውንና ጅቡንም “አባድር ጦም አያሳድረውም” ነበር፡፡ “አባድር! አባድር! ጦም አታሳድር!” ሲሉት የሚሰማ ቅዱስ ነበር-ሐረርነት ውስጥ!” (“ነበር!” ያልኩት ሆን ብዬ ነው፤ ዛሬ እነዚህ ሁሉ እሴቶች ላይኖሩ እንደሚችሉ ስለምገምት ነው፡፡ ያው እንግዲህ የግምት ጉዳይ ነው፡፡)

ጎንደርነትም ውስጥ አማርኛ ተናጋሪነት፣ ኦሮሚኛ ተናጋሪነት፣ ትግርኛ ተናጋሪነት፣ ግዕዝንም ተናጋሪነት አለ፡፡ ቅማንትኛ ተናጋሪነት፣ ጭልግኛ ተናጋሪነት፣ አገውኛና ወይጦኛ ተናጋሪነቶች ነበሩ፡፡ ዛሬ፣ እነዚህን ቋንቋዎች የሚናገሩ ሰዎች በብዛት ጎንደር ውስጥ የሉም፡፡ በጎንደርነት ውስጥ ለመረዳዳትና ለመተባበር አጥቢያና እድር መቋጠር ተዘውትሮ ይስተዋላል፡፡ የከፋው እና የከረፋው፣ “ኧረ ጥራኝ ዱሩ፣ ኧረ ጥራኝ ደኑ፤ ላንተም ይሻልኃል ብቻ ከማደሩ!” ብሎ ዱር ይገባል፡፡ ከቻለም፣ እንደመይሳው ካሳ፣ ሃምሳ ሰው ይዞ ወደ ቋራ ወይም ዘመዶቹ ዘንድ ይሸፍታል፡፡ አርባ አራቱ ታቦት ላጣና ለነጣ ነዳይ የእለት እንጀራውን አይነፍጉትም፡፡ የቆሎ ተማሪና የዜማ ተማሪ፣ ጎንደር መጥቶ፣ የመጣበትንም ትምሕርት አጠናቆ እስኪሔድ ድረስ ረሃብ አይለመጥጠውም፡፡

በሐረርነት እና በጎንደርነት ውስጥ ያሉት ትምህርቶች ከሃይማኖት ጋር የተጋቡ ነበሩ፡፡ ሐረርነት “ጌይ መድረሳ” ውስጥ የአረቢኛ ፊደላትን አስቆጥሮ ቁራን ሲያስቀራ፤ ጎንደርነት ውስጥ ያለው የሃይማኖት ትምህርት በበኩሉ፣ ከአቡጊዳ ጀምሮ መልዕክተንና ዳዊትን አስጠንቶ ወደ ዜማና ቅኔ ቤት ያስገባል፡፡ ሁለቱም ቢሆኑ፣ የሊቃውንትን ቋንቋ ከተራው ሕዝብ ቋንቋ ለይተው ይጠቀማሉ፡፡ ተራው ሕዝብ ወደ ሕዝባዊው ኪነጥበብና የምርት ስራ ተግባር ላይ ሲሰማራ፤ ልሒቃኑ ግን በቤተ-መንግስትና በቤተ-ሃይማኖት ተግባራት ላይ እንዲተጉ ተደርገው በሃይማኖት ትምህርት ቤቶቹ አማካኝነት ይዘጋጃሉ፡፡

በጎንደርነት ውስጥ ከሕፃንነት ጊዜ ጀምሮ የሚደረግ የወታደራዊ ስልትና ታክቲክ ልምምድ/ጨዋታ አለ፤ አካንዱራ ይባላል፡፡ ሕጻናቱ ወንዝ ዳር ሔደው በቡድን ተመራርጠው የለየለት የዱላ ምክቶሽና ድብድብ ያካሂዳሉ፡፡ ፈሪነትና ቦቅቧቃነት ክብረ-ቢስ ያደርጋል፡፡ ወንዝን በዋና ማቋረጥም ሆነ፣ ከፈረስኛና ደራሽ ወንዝ ጋር መገዳደር የተወደደ ጎንደርነት ነው፡፡ “የትም ፍጪው፣ ስልጣኑን አምጭው!” የሚል ተረት ከተተረተ፣ ያ ተረት ያለ ጥርጥር ለጎንደርነት የተተረተ ነው፡፡ በአንጻሩ፣ በያመቱ ከሚመጣውና ፈረስ መጋላ ላይ ከሚከናወነው የወንዶች ልጆች ቅል ሰበራ በዓል ውጭ ወታደራዊ ልምምድ የማድረጊያ ጨዋታ በሐረርነት ውስጥ እምባዛም አይስተዋልም፡፡ በሐረርነት ውስጥ መፍራት “የእናቱ ልጅ!” ያሰኛል፡፡ ሐረርነት የገንዘብና የወርቅ ባለቤትነት ስለሆነ እረኝነትም ሆነ እርሻ ማረስ ለዋቶዎች የተተወ ነው፡፡ “የትም ፍጪው፣ ገንዘቡን አምጭው!” የሚለው ተረት ካለ፣ የተተረተው እዚህ ነው፡፡ (ክፍል ሁለት ይቀጥላል፡፡ የሳምንት ሰዎች ይበለን!)


የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ሕንጻውን በተቃውሞ ከበው ዋሉ

$
0
0

ቋሚ ሲኖዶስ በመጪው ማክሰኞ የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚሰጥ ይጠበቃል
‹‹በኀይል ላይ ኀይል ጨምሬ እጠብቅሃለኹ›› /ዘላለም/
‹‹መናፍቅን ማውገዝ እንጂ ሥልጣን መስጠት አይገባም›› /ደቀ መዛሙርቱ/
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት የኮሌጁን አስተዳደር ሕንጻ በመክበብ የማስገደጃ ርምጃዎችን መውሰድ መጀመራቸው ተገለጸ፡፡

ሐራ ተዋሕዶ ብሎግ እንደዘገበው፦
ደቀ መዛሙርቱ ዛሬ፣ ሰኔ ፳ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ከማለዳው 12፡30 ጀምሮ የአስተዳደሩን ሕንጻ መግቢያና ዙሪያ መተላለፊያዎቹን በመክበብ መምህራኑና የቢሮው ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች እንዳይገቡ ሲከላከሉና ቀደም ብለው የገቡትንም በትእዛዝ ቃል ሲያስወጡ መታየታቸው ተዘግቧል፡፡

silase menfesawi collahe ‹‹ከማለዳው 12፡00 ላይ በመኝታ ክፍሎቻችን ኮሪዶሮች የፊሽካና የጭብጨባ ድምፅ ተሰማ፤ ከክፍላችን ስንወጣ ወደ አቡነ ጢሞቴዎስና ሌሎች መምህራን ቢሮ የሚያስገባው የሕንጻው ደረጃና መተላለፊያ በከፍታ ድምፅ በሚዘምሩ ተማሪዎች ተዘግቶ ነበር፤›› ያለ አንድ የተቃውሞው ተካፋይ የቢሯቸውን ቁልፍ ጥለው የሸሹ ሓላፊዎች እንደነበሩ ተናግሯል፡፡

የደቀ መዛሙርቱ ቁጣ የነደደባቸው የሹመት ተስፈኛው ዘላለም ረድኤትና የበላይ ሓላፊው ሊቀ ጳጳስ ከበባው እስኪያበቃ ድረስ በአካባቢው አልታዩም፡፡ የኮሌጁ ሪጅስትራር ሓላፊ ማልደው ገብተው ከተቀመጡበት ቢሮ በትእዛዝ ለመውጣት የተገደዱ ሲኾን ንጋት ላይ የመጡ ሦስት መምህራን ኹኔታው ተገልጾላቸው በክብር እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡ በበላይ ሓላፊው ቀጥተኛ ትእዛዝ ጠቅ/ቤተ ክህነቱ በስኬሉ የማያውቀው ደመወዝ እንደሚከፈላቸው ከሚነገርላቸው ሦስት ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች አንዷ የኾነችው ልዩ ጸሐፊያቸው ከተግሣጽ ጋራ ከስፍራው እንድትርቅ መደረጉ ተገልጧል፡፡

ከቀትር በኋላ 7፡30 ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የአጣሪ ኮሚቴው አባላት ከኾኑት የፓትርያሪኩ ልዩ ጸሐፊ አቶ ታምሩ አበራ፣ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊና የአጣሪ ኮሚቴው ጸሐፊ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ፣ የአስተዳደር መምሪያ ዋና ሓላፊ መዝገበ ጥበብ ቀሲስ ዮሐንስ ኤልያስ ጋራ በመኾን ወደ ግቢው ደርሰዋል፡፡

ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ የአዳራሽ ውይይት ከማካሄዳቸው በፊትና በኋላ ከኮሌጁ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ጋራ መገናኘታቸው ታውቋል፡፡ 180 ያህል ከሚኾኑ ደቀ መዛሙርት ጋራ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱና ሓላፊዎቹ ባካሄዱት ውይይት በአጣሪ ኮሚቴው ተጠንቶ የቀረበው ባለሦስት ነጥብ የመፍትሔ ሐሳብ ስለምን ተግባራዊ እንደማይኾን ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሓላፊዎች ከኮሌጁ አቅራቢያ ወደሚገኘው የአቡነ ጢሞቴዎስ መኖርያ ቤት ጎራ ብለው መውጣታቸውን የታዘቡት ደቀ መዛሙርቱ፣ ‹‹በአቡነ ጢሞቴዎስ ላይ ላለመወሰን የጓደኝነት ሥራ አትሥሩ፤ ከጓደኝነት ሃይማኖት ይበልጣል፤›› ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

ዘላለም ረድኤትን የኮሌጁ ዲን ለማድረግ በአቡነ ጢሞቴዎስ የሚደረገው ዝግጅት ፈጽሞ ተቀባይነት እንደማይኖረው ደቀ መዝሙሩ በግልጽ ተናግሯል፡፡ የአጣሪ ኮሚቴው ድካም ዋጋ ሊሰጠው እንደሚገባ የገለጹት ደቀ መዛሙርቱ፣ ‹‹መናፍቅን ማውገዝ እንጂ ሥልጣን መስጠት አይገባም፤›› በማለት ለዕረፍት በሚወጡበት በነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ ዘላለም ረድኤትን በዲንነት ለመሾም መታቀዱን በጥብቅ እንደሚቃወሙት አስታውቀዋል፡፡ የደቀ መዛሙርቱ ቁርጥ አቋም ‹‹በኀይል ላይ ኀይል ጨምሬ [ከኀይል ወደ ኀይል ተሸጋግሬ] እጠብቅሃለኹ›› እያለ ሲዝት የሚሰማውን የዘላለም ረድኤት ብርቱ የሥልጣን ምኞት በከንቱ የሚያስቀር ነው ተብሏል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ ‹‹ሳይጣራ ሰው አይታገድም›› ብለው እንደነበረ ሁሉ ከኮሌጁ እንዲባረርና ስለ ሃይማኖቱ ሕጸጽ ወደ ሊቃውንት ጉባኤ ቀርቦ እንዲጠየቅ የተወሰነበት ዘላለም ረድኤት ማንነቱ ተጣርቶ ከታወቀ በኋላ የሚታየው ዳተኝነት እንደሚያሳዝናቸው አልሸሸጉም፤ ኮሌጁን ከመናፍቅ የመጠበቅ ግዴታ ያለባቸው በመኾኑም የዓመቱ ተመራቂዎች ይኹኑ ሌሎች ደቀ መዛሙርት ጉዳዩን እስከ መጨረሻው በባለቤትነት እንደሚከታተሉት አስጠንቅቀዋል፡፡

ሰኔ ፲ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ የኮሌጁ ዲን እንዲኾኑ የተፈቀደላቸው መልአከ ብርሃን ፍሥሓ ጌታነህ ምድባቸው ወደ ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ የተቀየረው በዘላለም ረድኤት የተለመደ ክፉ ምክርና በአቡነ ጢሞቴዎስ እንቢታ ነው፡፡ የዘላለም ረድኤት ክፉ ምክር፣ ‹‹በማታ ተማሪ [የድጓ፣ ቅዳሴና ቅኔ ዐዋቂው መልአከ ብርሃን ፍሥሓ ጌታነህ በኮሌጁ ተከታታይ መርሐ ግብር ነው በዲግሪ የተመረቁት] እንዴት እንመራለን?›› የሚል እንደነበር ተጠቅሷል፡፡ ይህንንም ራሱ ዘላለም ሲያስረዳ፣ ‹‹በቀኑ መርሐ ግብር የሚገኘው የቴዎሎጂ ዲግሪ በማታው ተከታታይ መርሐ ግብር ከሚገኘው ዲግሪ ጋራ እኩል መታየት የለበትም፤›› በሚል መብራራቱ ተገልጧል፡፡

የኮሌጁን የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ በተለያዩ ማባበያዎችና ተንኮሎች በመቅረብ ጥቅሙንና ሥልጣኑን ለማስጠበቅ የሚጥረው ዘላለም ረድኤት፣ ያለደረጃው የኮሌጁን ሐላፊዎች (በተለይ ጥንተ ነውሩን የሚያውቁበትን)፣ መምህራንና ሠራተኞች በማሸማቀቅ ይታወቃል፡፡ ሐራዊ ምንጮች በተወለደበትና ባደገበት በሆለታ ኪዳነ ምሕረት አጥቢያ የሚያሰባስቧቸው መረጃዎች እንደሚያሳዩት ደግሞ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን ወደ ፕሮቴስታንት አዳራሽ እየሰበከና እየመለመለ በማስኮብለል በሚገባ ይታወቃል፡፡ ዘላለም ረድኤት ለሊቀ ጳጳሱ እንደነገራቸው፣ አሁን በኮሌጁ ያለው የደቀ መዛሙርቱ ተቃውሞና የሚዲያ ዘገባዎችም በእርሱ ብቃት ማነስና መናፍቅነት የተቀሰቀሰ ሳይኾን ‹‹የማኅበረ ቅዱሳን ሤራ ነው፡፡››

ብፁዕ ዋና ጸሐፊውና ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ለደቀ መዛሙርቱ የማረጋጊያ ትምህርትና ምክር ሰጥተዋል፤ በአጣሪ ኮሚቴው የቀረበው ሪፖርትና የመፍትሔ ሐሳብም የቋሚ ቅ/ሲኖዶስ አባላት ተሟልተው በሚገኙበት በመጪው ሳምንት ማክሰኞ በሚደረገው መደበኛ ስብሰባ ቀርቦ የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚሰጥበትና ውጤቱን በማግሥቱ ረቡዕ እንደሚያሳውቋቸው ቃል ገብተውላቸዋል፡፡

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱና የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሓላፊዎች ውይይቱ እንዳበቃ በደቀ መዛሙርቱ ተወካዮች መሪነት የኮሌጁን መማርያና ማደርያ ክፍሎች፣ ቤተ መጻሕፍቱንና የምግብ ቤት አዳራሽ እንዲሁም መጸዳጃ ክፍሎች ሳይቀር ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፤ በኹኔታውም በእጅጉ ማዘናቸው ተገልጧል፡፡ መዝገበ ጥበቡስ ምን ተሰምቷቸው ይኾን?!

Health: እባካችሁ ንጥሻ ገደለኝ፣ አስም እንዳይሆንብኝ ፈርቻለሁ

$
0
0

sneezin habesha አሁን ዕድሜዬ 37 ሲሆን ባለትዳርና የ2 ልጆች አባት ነኝ፡፡ ሀሳብ የሆነብኝ ነገር ሁሌ ጠዋት ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ ተከታታይና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ማስነጠስ ልቤን ውልቅ ሊያደርጋት ይደርሳል፡፡ ሲያስነጥሰኝ ታዲያ ሰውነቴ በሙሉ በላብ ይዘፈቅና መላ ሰውነቴን ያሳክከኛል፡፡ ብዙም ሳይቆይ ደግሞ ቀጭን ፈሳሽ ከአፍንጫዬ ይወጣል፡፡ አባቴ የአስም በሽተኛ ነበርና ይህ ነገርም ታዲያ በዘር የወረስኩት አስም እንዳይሆን እጅግ ፈርቻለሁና መፍትሄ ብትለግሱኝ እላለሁ፡፡
አበራ ነኝ

ውድ ጠያቂያችን አበራ ካለማቋረጥ እንደሚያስነጥስህ፣ ከዚህ ጋርም ተያይዞ ፊትህን እንደሚያሳክክህ፣ ከአፍንጫህም ቀጭን ፈሳሽ እንደሚወጣ እና አባትህም የአስም ህመም ተጠቂ መሆናቸውን ገልፀሀል፡፡ ካቀረብካቸው የህመም ምልክቶች ተነስተን ስንመለከተው ችግርህ ከአፍንጫ መቆጣት ጋር ተያያዥ ሆኖ ይታያል፡፡ ይህ መሰል ክስተትም ለብዙ ጊዜ እንደሚደጋገምብህ ገልፀሀል፡፡ ይህም መሆኑ የአፍንጫ መቆጣት ችግር ከአንዳች መንስኤ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ያሳያል፡፡ እንዲህ መሰሉ በየወቅቱ ከአንዳች መንስኤ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ችግር ከአለርጂ ህመም አንፃር የሚታይ ይሆናል፡፡ በዋናነት ደግሞ የጠቀስካቸው ምልክቶች ለአፍንጫ አለርጂ አይነተኛ ምልክቶች ናቸው፡፡ ይህን የመሰለ ህመም በህክምና መጠሪያው ‹‹የአፍንጫ አስም›› ወይም ‹‹አለርጂክ ሳይንሳይስቲስት›› ብለን ልንጠራው እንችላለን፡፡
የአፍንጫ አስም (አለርጂ) ልክ እንደሳንባ አለርጂ ትንፋሽ የማሳጠር፣ ሳል የማሳልና ሲተነፍሱ ‹‹ሲር ሲር›› የሚል ድምፅ የማያሰማ ይሁን እንጂ ዋና መንስኤው ከአለርጂ ጋር በመያያዙ ይመሳሰላሉ፡፡ እንዲሁም ህመሞቹ በየጊዜው እያሰለሱ የመምጣታቸውም ጉዳይ እንዲሁ ይመሳሰላል፡፡ የሚደረግላቸውም ህክምና ፀረ አለርጂ መድሃኒቶች በመሆናቸው ተያያዥ መሆናቸውን ያመለክታል፡፡ አንዳንዴ የአፍንጫ አለርጂ (አስም) ለሳንባ አስም (አለርጂ) ክስተት ጠቋሚ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ማለት ግን የአፍንጫ አስም ያለበት ሁሉ ወደ ፊት የሳንባ አስም ይከሰትበታል ማለት አይደለም፡፡ ከደብዳቤህ እንደተረዳነው አባትህ የአስም ህመም ያለባቸው እንደመሆናቸው መጠን አንተም የአፍንጫ አለርጂ ቢኖርብህ ብዙም አያስገርምም፡፡ ምክንያቱም አለርጂ በባህሪው በዘር የመተላለፍ ባህሪ ያለው በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን ወደ ፊት ልክ እንደ አባትህ የሳንባ አስም ተጠቂ ትሆናለህ እያልን አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ በአፍንጫ አለርጂ መልክ ግን መከሰቱ አልቀረም፡፡
ውድ አበራ አለርጂ ማለት ሰውነታችን ለአንድ ለሚያስቆጣው ነገር ሲጋለጥ የሚከሰት ችግር ነው፡፡ እንዲህ አይነት ባህሪው የሚኖራቸው ደግሞ አንዳንድ ሰዎች በተፈጥሯቸው አለርጂውን ለሚቀሰቅሰው ነገር ቁጠኛ ሲሆኑ ነው፡፡ ሰውነታችንም እንዲህ መሰሉን ቁጠኝነት የሚገልፀው በሰውነታችን የበሽታ መከላከያ ሃይል በኩል ሲሆን እነዚህም ሃይላት በሚያመርቷቸው ኬሚካሎች (በተለይ ‹‹ሂስታሚን›› የተባለው ኬሚካል) ቆዳን የማሳከክ፣ አፍንጫን የመለብለብ፣ ንፍጥ የማዝረክረክና ማስነጠስ መሰል ምልክቶችን እንዲያሳይ ያደርጋል፡፡ የተለያዩ ሰዎች ለተለያዩ ነገሮች ሰውነታቸው ተቆጭ ሊሆን ይችላል፡፡
በተለያዩ አበቦች ውስጥ የሚገኘው ፓለን፣ አንዳንድ ምግቦች፣ የተወሰኑ የመድሃኒት አይነቶች፣ የአቧራ ብናኞች፣ የእንስሳት ፀጉር (በተለይም ድመት)፣ የፋብሪካ ጭሶች (ወይም የሲጋራ ጭስ)፣ እንዲሁም መርዘኛ ነፍሳቶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የተለያዩ ሰዎች የተለያዩ የአለርጂ መነሻ ምክንያቶች ያሏቸው በመሆኑም ማን ሰውነቱ ለየትኛው የአለርጂ መነሻ ሊቆጣ እንደሚችል በውል ለይቶ ማወቅ ይኖርበታል፡፡ ለምሳሌ የድመት ፀጉር ሲሸታቸው አለርጂው የሚነሳባቸው ሰዎች ችግሩ እንዳይቀሰቀስባቸው መንስኤ የሆነችውን ድመት ማራቅ ይኖርባቸዋል፡፡ በመሆኑም አንተም ብትሆን አለርጂው በምን እንደሚነሳብህ ለይተህ በማወቅ እንዳይደጋገምብህ ከሚያስነሳብህ መንስኤ መራቅ አንዱ የመከላከያና የህክምና አማራጭ ነው ማለት ነው፡፡
ውድ ወንድማችን ከዚህ ውጭ ከላይ የጠቀስካቸው ምልክቶች ሲከሰቱብህ የሚከተሉትን መድሃኒቶች በማስታገሻነት መውሰድም ይመከራል፡፡ ባለ 4 ሚግ አንድ ኪኒን ክሎርፌኒራሚን (Chlorpheniramine) በቀን (Cetrizine) በየቀኑ ልትወስድ የምትችል ሲሆን ምልክቶቹም እንዳቆሙልህ መድሃኒቶችን መውሰድ ታቆማለህ፡፡ ወደ ፊትም ሲነሳብህ በዚህ መልኩ መቀጠል ይኖርብሃል፡፡ የአፍንጫን አለርጂ ከላይ ባለው መልኩ ለመከላከል እና ለማስታገስ መሞከር እንጂ ማዳን አይቻልም፡፡
ከዚህ በተጨማሪ አንዳንዴ ይህ የአፍንጫ አለርጂ ወደ ‹‹ሳይነሳይቲስ› ሊቀየር የሚችልበት እድሉ ስላለም ልታጤነው ይገባል፡፡ በተለይ የአፍንጫህ ፈሳሽ ወፍራምና ወደ ቢጫነት እየተቀየረ ከመጣ ስትናገር የአፍንጫህን መዘጋት በመነፋነፍ መልኩ ከታዘብክ እንደትኩሳትና ራስ ምታት አብረው ከታዩ በተጨማሪ ህክምናነት የአንቲባዮክ ህክምና ሊያስፈልግህ ይችላል፡፡ (ለምሳሌ ባለ 250 ሚሊ ግራም አንድ ክኒን አሞክሳስሊን በቀን ለሶስት ጊዜ ለ7 ቀናት ልትወስድ ትችላለህ) ይህ ህክምና የሚያስፈልገው ‹‹ሳይነሳይቲስ›› የተባለው የአፍንጫ መመርቀዝ ህመም በባክቴሪያዎች ሊመጣ ስለሚችል ነው፡፡ ውድ አበራ ከረጅሙ በአጭሩ ለጥያቄህ ያለው ምላሽ ይህን ይመስላል፤ መልካም ጤንነት፡፡

የቬጋሱ ኢትዮ ስታር ቡድን ለዘንድሮው 30ኛ ዓመት ውድድር አሸኛኘት ተደረገለት

$
0
0

esfna የቬጋሱ ኢትዮ ስታር ቡድን ለዘንድሮው 30ኛ ዓመት ውድድር አሸኛኘት ተደረገልት
የፌዴሬሽኑ ቦርድ ተጫዋቾቹ እንዲመጡ ቢወስንም ፕሬዝዳንቱ ውሳኔው ውድቅ ሆኗል ሲሉ ማስፈራሪያ ሰጥተዋል
ቅዳሜ በሚደረገው የቦርድ ስብሰባ የመጨረሻ ምልሽ ይጠበቃል

የቬጋሱ ኢትዮ ስታር ቦድን አባላት ዘንድሮ ዲሲ ላይ ለሚደረገው ጨዋታ ለመሳተፍ ከሄዳቸው በፊት ትላንት በከተማው በኮሚኒቲው አባላት በአንድ የሕዝብ መናፈሻ ውስጥ በተካሄደ ስነ ስርዓት አሸኛኘት ተደረገላቸው።
የቡድኑ አባላት ከዓመት በላይ ለፌዴሬሽኑ የቀድሞው የቡድኑበፌዴሬሽኑ ተወካይ በነጻ ምርጫ ስልጣኔን አለቅም በማለቱ ውክልናውን አንሱ አታንሱ ቡድኑ የሕዝብ እንጂ የግለሰብ አይደለም የሚል ተቃውሞ ያቀረቡ ሲሆን የፌዴሬሽኑ ቦርድ ለማስማማት የተለያዩ ጥረቶች ቢያደርግም ግለሰቡ የቦርዱን የማስማሚያ ሀሳብ ባለመቀበሉ ቦርዱ በአብላጫ (ሞሽን ) ተጫዋቾቹ ለዘንድሮው ውድድር እንዲገኙ ቢወስንም የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ የቦርዱን ውሳኔ ውድቅ ማድረጉን ተጫዋቾቹም አይወክለንም ባሉት ወኪል ስር ካልሆኑ በቀር በመጪው ቅዳሜ ያልጠበቁት እንደሚጠብቃቸው የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት በሬዲዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ መግለጻቸውን ተጫዋቾቹ ለህብር ሬዲዪ ገልጸዋል።
ህብር ሬዲዮ የፌዴሬሽኑን ፕሬዝዳንት ስለ ሰጡት ቃለ መጠይቅ ማብራሪያ እንዲሰጡ በተደጋጋሚ ቢሞክርም ስልካቸውን ባለማንሳታቸው አያነሱም።ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ ሙከራ አድርገናል።
በትላንቱ የቬጋሱ የኢትዮ ስታር ቡድን አባላት የሽኝት ፐሮግራም ላይ የቬጋስ የኢትዮጵያ ኪሚኒቲ የወቅቱና የቀድሞ አመራሮች መካከል ጥቂቶቹ ፣ በቡድኑ አባላት መካከልና ከስልጣን አልወርድም ባለው ግለሰብ መካከል በከተማው ከዚህ ቀደም ሽምግልና በማድረግ ግለሰቡ ምርጫ አይደረግም በማለቱ አባላቱ ምርጫ እንዲያደርጉ የወሰነው የሽማግሌዎች ቡድን አባላት፣ የቀድሞ የቡድኑ እኛ የሰሜን አሜሪካ የኢጥዮጵአውያን ስፖርት ፌዴሬሽን መስራች አንዱ አቶ ዘውዱ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የከተማው ነዋሪዎች በስፍራው ተገኝተው አሸኛኘት አድርገዋል።የቡድኑ አባላት ለድጋፍ ማሰባሰቢያ ያዘጋጁት ቶምቦላ ዕጣም ወጥቷል።
በቬጋስ የኢትዮጵያ ኮሞኒቲ ዋና ጸሐፊ አቶ ሽመልስ የፌሬሽኑ በቡድኑ አባላትና በተወካዩ መካከል የነበረውን ችግር ከዓመት በላይ ሳይፈታ በአሁኑ ወቅት ከከተማው መሰለፍ የሚገባው አንድ ቡድን ሆኖ ሳለ ውሳኔ ባለመሰጠቱ ግለሰቡም የራሱን ቡድን ይዞ ሁለት ቡድን እንዲኖር መደረጉ ያሳዝናል ብለዋል።
<<ይሄ የሕዝብ ቡድን ነው። ለዕውነት መብታችሁን ለማስከበር ባልመረጥነው ሰው አንተዳደርም ቡድኑ የሕዝብ እንጂ የግለሰብ አይደለም በማለታችሁ የፌዴሬሽኑ አመራር በተለይ ፕሬዝዳንቱ ከግለሰቡ ወግኖ እስከዛሬ መግፋቱና አሁንም ማስፈራራቱ ያሳዝናል።ይሄ ቡድን የቬጋስ ወኪል ነው >> ያሉትአቶ ገዛኘኝ ተፈራ ባለፈው ዓመት በቡድኑ አባላት እና ከስልጣን አልወርድም ባለው የቀድሞ የቡድኑ ዋና ጸሐፊ መካከል የተፈጠረውን ችግር ለመፍታትበኮሚኒቲው የተቋቋመው የሽማግሌዎች ቡድን ሊቀመንበር ሲሆኑ <<መልካም እድል ይግጠማችሁ >> ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የቬጋሱ ኢትዮ ስታር ቡንድ ችግር የወቅቱ የፌዴሬሽኑ ትልቅ ራስ ምታት መሆኑንና ከዚህ ቀደም የቡድኑ አባላትና ተወካዩን ለማስማማት ትልቅ ጥረት ቢደረግም አለመሳካቱን የፌዴሬሽኑ የውድድር ጉዳይ ሀላፊ አቶ ተካበ ዘውዴ ባለፈው ዕሁድ ለህብር ሬዲዮ የገለጹ ሲሆን ተአምር መጠበቅ ቢሆንም በቅዳሜው ወሳኝ የፌዴሬሽኑ የቦርድ ስብሰባ ላይ ከየአቅጣጫው ችግሩን በሽማግሌ ለመፍታት የሚያስቡ ስላሉ ውጤት ይገኝ ይሆናል የሚል ተስፋ እንዳለው ገልጿል።
የፌዴሬሽኑ ፕ/ት አቶ ጌታቸው በበኩላቸው ለአንድ ሬዲዮ ባለፈው ዕሁድ በሰጡት ቃለ መጠይቅ የቡድኑ አባላት አልመረጥነውም አይወክለንም ያሉትንና በስልታን ለመቆየት ድምጽ ለማግኘት ሲሉ ይደግፉታል፣ድምጻችንን አፍነዋል የሚለውን ወቀሳ እንደማይቀበሉት ገልጸዋል። ተጫዋቾቹ አይወክለንም ያሉትንና ለጊዜው በተወካይነት ዘንድሮ ከቡድኑ ጋር ሆኖ ተጫዋቾቹ በውድድሩ ይሳተፉ የሚለውን የቦርዱን የአብላጫ ውሳኔ ውድቅ መደረጉን ፕሬዝዳንቱ ጠቅመው በመጪው ቅዳሜ ተጫዋቾቹ ያልጠበቁት ይጠብቃቸዋል ሲሉ አስፈራርተዋል።
<<እንዴት ኢትዮጵያውያንን በሚያገኛኘው መድረግ ላይ ያለ አንድ የፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ያልወከልነውንንና የስልጣን ጊዜው ገደብ ይኑረው ቡድኑ የግለሰብ ሳይሆን እያንዳንዱ ተጫዋች ተሰሚነት ያለው የከተማው ቡድን ነው ባልን ያስፈራሩናል? ያሳዝናል>> ሲል የፕሬዝዳንቱን አስተያየት መሰረት አድርጎ አንድ የቡድኑ አባል ለህብር ሬዲዮ ገልጿል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የፌዴሬሽኑ ነባር አባልና ከመስራቾቹ አንዱና የቬጋሱ ኢትዮ ስታር ቡድን መስራች አቶ ዘውዱ ታከለ ለፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት በግልባጭ ለቦርድ አባላት የሚደርስ የቅሬታ ደብዳቤ ጻፈ።በዚህ በደብዳቤው ፕሬዝዳንቱ አቶ ጌታቸው በጻፈው ደብዳቤ ፌዴሬሽኑ በተጫዋቾች እንጂ በቦርድ አባላት አለመመስረቱን፣ በተለይ ፕሬዝዳንቱ አብዛኛው ተጫዋች አንቀበልም ብሎ በድምጹ ይውረድ ያለውን ግለሰብ በመቀበል የተጫዋቾችን ድምጽ ውድቅ ማድረጋቸውን ወቅሷል።የቬጋሱን ኢትዮ ስታር ቡድን ግለሰቡ ስም ቀይሬ እንደ ግል ንብረቱ በሱ ፈቃድ ማስመዝገቡን ጠቅሷል።ፕሬዝዳንቱ ከተጫዋቾቹ እውቅና ውጭ ግለሰቡን የሳቸው ደጋፊ ስለሆነ ብቻ ከህግ አግባብ ውጭ ይደግፉታል ብሏል።
የቬጋሱ ኢትዮ ስታር ክለብ የቀድሞ የቡድን ተወካይና ዛሬም በፌዴሬሽኑ በቦርድ አባልነት የሚገኘው አቶ ሙላት መለሰ በቅርቡ የፌዴሬሽኑ ቦርድ ጊዜያዊ የማስማሚያ ሀሳብ አቅርቦ እሱና ከቡድኑ አባላት መካከል አቶ ሲራክ ተወክሎ ቡድኑ በዘንድሮው ውድድር ተሳትፎ ቦርዱ በቀጣይ በሚያደርገው ውይይት ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ይሰጣል ቢልም ግለሰቡ አልቀበልም በማለቱ ቦርዱ ወደ ድምጽ መሄዱን አቶ ጥላሁን ፍስሐ የሳንዲያጎ ቴዎድሮስ ቡድን ተወካይና የቦርዱ አባል ለህብር ሬዲዮ ገልጸዋል።
አቶ ሙላት በሳቸው ተወካይነትና በሳቸው ቡድን መጫዋት የፈለገ መጥቶ ችሎታው ተገምግሞ መሳተፍ ይችላል በማለት የቡድኑ አባላት ማንንም አትጫወት አላልንም በራችን ክፍት ነው ብለዋል። ባለፈው ዓመት ከዳላስ ውድድር በፊት አቶ ሙላት ስልጣኔን አስረክባለሁ ቢሉም በከተማው በተያዘ ሽምግልና ስልጣንዎን ለማስረከብ ማረጋገጫ ይፈርሙ መባላቸውን ተቃውመው የራሳቸውን አዲስ ቡድን መስርተው ፌዼሬሽኑም ተቀብሎ ለዓመታት በቡድኒ ውስጥ የተጫወቱ ተጫዋቾች ድምጽ ሳይሰማ ቀርቷል። በዳላሱ ውድድር እንሳተፋለን ብላችሁ ከመጣችሁ በፖሊስ እናስወጣችሁዋለን ለችግሩ መፍትሄ የምንሰጠው በኦክቶበር በምናደርገው ውድድር ነው መባላቸውን የሚገልጹት ተጫዋቾች በወቅቱ ፌዴሬሽኔ ችግር ላይ ስለሆነ ዳላስ ሳይሄዴ የፌዴሬሽኑን ውሳኔ ሲጠብቁ ቢቆዩም ዛሬም ድረስ ውሳኔ አላገኘም። አቶ ሙላት ዘንድሮም በግላቸው ባዝመዘገቡት ኢትዮ ስታር ፋሲለደስ በሚል ፈቃድ የራሳቸውን ቡድን አባላት አሰባስበው ለመሳተፍ የሚሄዱ ሲሆን ፕሬዝዳንቱ ከቦርዱ ተለይተው የምንቀበለው ሙላትን ነው በማለት ዘንድሮም ተጫዎቾቹ እንዳይሳተፉ ማስፈራራታቸውን የቡድኑ አባላት በቅሬታ ገልጸዋል።
<<በኣለፈው ዓመትም ዓላማቸው ስንከለከል ተለጣፊው ፌዴሬሽን እንድንሄድና ይሄው ወያኔዎች ናቸው ለማለት ነበር።አሁንም ዲሲ ቦርዱ ይምጡ ሲል ፕሬዝዳንቱ የሚገፉን እሳቸው የሚደግፉትን ያልመረጥነውን ተወካይ ካልተቀበልን ተገፍተን የት እንድንሄድ ነው? ከእናት ፌዴሬሽናችን የትም አንሄድም።ቦርዱ የፌዴሬሽኑ በህግ የበላይ ባለስልጣን ነው ህግ ይከበር ሲሉ በትላንቱ የቬጋሱ ክለብ ዝግጅት ላይ ያነጋገርናቸው አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ቅሬታ አቅርበዋል።
<<ከዚህ ሁሉ ችግር ፌዴሬሽኑ ለምን በቬጋስ ሁለት ቡድን እንዲኖር አይፈቅድም? >> በሚል አቶ ተካበ ዘውዴን ቀደም ሲል ጠይቀናቸው <<የፌዴሬሽኑ ሕግ አይፈቅድም። በተወሰነ ቀን የሰላሳ ቡድን ውድድር ማድረግ በራሱ ከባድ ነው።ጠዋት የጀመርን በየቀኑ ማታ ነው የምንጨርሰው።እድል ላላገኙ ከተሞችም እድል መሰጠት አለበት>> ሲሉ ለህብር ሬዲዮ ገልጸዋል።
በ30ኛው ዓመት የፌዼሬሽኑ ዓመታዊ ውድድር ላይ ቦርዱ እንዳለው ተጫዋቾቹ ይሳተፋሉ ወይስ ፕሬዝዳንቱ እንዳሉት የሚቀበሉት የቡድኑን ተወካይ ብቻ ነው? ቀጣዩ ቅዳሜ ለመጨረሻ ጊዜ ጉዳዩ እልባት ያገኝለታል ብለው የሚጠብቁ አሉ ። ተከታትለን እንዘግባለን።

ይድረስ ለኢትዮጵያው ሥውር መንግሥት

$
0
0

ይነጋል በላቸው
ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ ኢትዮጵያን ማን እየገዛ እንደሆነ ከግምት ያለፈ ዕውቀት የለኝም፡፡ በመለስ ጊዜም ቢሆን ሀገሪቱ በዕውር ድንብርና በነሲብ ነበር የየሚገርም አጋጣሚ ነው፡፡ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንና በዚያ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያናችን ኃላፊዎች ጸሎት በቶሎ እንዲድኑ ሲጸልዩላቸው የሀገሪቱ የሃይማኖት ታዋቂ አባትና ተከታይ ምዕመኖቻቸው ግን በሰላም እንዲያርፉ ነው ጸሎት እየተደረገ ያለው – ለኔልሰን ማንዴላ፡፡ ይህ ነገር የሥልጣኔ ልዩነት ይሁን የባህል አልገባኝም፡፡ ይህን የዜና ሽፋን ከውጪ ወደ ሀገር ውስጥ በሚሰራጭ አንድ የተቃውሞው ጎራ ቴሌቪዥን አማካይነት እየተከታተልኩ ነኝ – ልክ አሁን፡፡ በመሠረቱ ከ94 ዓመታት ምድራዊ የሥጋ ለባሽ ሕይወት በኋላ አንድ ብዙ የሕይወት ውጣ ውረድ ያሳለፈና በእሥርም ብዙ የተሰቃዬ ሰው ዕድሜ እንዲረዝም መመኘት ከፍቅር ብዛት የሚመነጭ የዋህነት ይመስለኛል፡፡ በጀመርኩት ሃሳብ ትንሽ ልቆይና ወረድ ብዬ በዚህ ላይ እንደመጠቅለያነት እመለስበታለሁ፡፡
… በመለስ ጊዜም ቢሆን ሀገሪቱ በዕውር ድንበርና በነሲብ ነበር እስትንፋሷ ውሎ እሚያድረው፡፡ ሰውዬው የሚፈልገው ሁሉ እዛው ባለበት እየቀረበለትና እንደአንበሣ በብረት አጥር ውስጥ እየኖረ በስልክና በደብዳቤ ሲገዛንና ሲሸጠን ኖረ፤ ፈጣሪ በወደደው ሰዓት ያን የእፉኝት ልጅ ወሰደ፡፡ ጦስ ጥንቡሱ ግን አሁንም እንደገነነ አለ፤ መቃብር ውስጥ ሆኖ በመግዛት መለስ አንደኛ ሣይሆን አይቀርም፡፡ ይቺ ራዕይ የሚሏት ሀገርን የማጥፋት ተልእኮ በየወያኔው ጭንቅላት ውስጥ ሠርፃ ገብታ እነሱንም እኛንም ዕረፍት ነስታለች፡፡ አዳሜ እየተነሣ “ከመለስ ራዕይ ጋር ወደፊት!” ይላል፡፡ “ራዕያቸው ምን ነበር?”ተብሎ ሲጠየቅ በቅጡ የሚመልስ የለም፡፡ የፈረደበት የአባይ የሚሌኒየም ይሁን የሕዳሴ ግድብ አለ፡፡ እሱው መሰለኝ ትልቁ ራዕይ፡፡ በሌሎች ሀገሮች እዚህና እዚያ የተትረፈረፈ የወንዝና የኩሬ ግድብ እኛ ሀገር ሲደርስ ብርቅ ሆኖ ሰውን በመዋጮና በተስፋ ቁንጣን እየገደለ ነው፡፡ ራዕዩ ይሄው ነው፡፡ በተረፈ በሚሊዮኖች ላብና ደም ጥቂት ቅንጡ ሀብታሞችን የመፍጠር ራዕይ ካልሆነ በስተቀር፣ ለብዙ አሠርት ዓመታት ተከፍሎ በማያልቅ ብድር መንገድና ሕንጻ መሥራት ራዕይ ካልሆነ በስተቀር፣ ይበልጡን ለፖለቲካ ፍጆታ በሚመስል መልኩ የሀገርን ሀብት ለተወሰኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች በማዋል በአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞችና በኮብል ስቶን ሥራ አደራጅቶ ዜጎችን በጥቅም መከፋፈል ራዕይ ካልሆነ በስተቀር፣ ለዕይታ ሳይቀር የሚዘገንን የኔቢጤ (ለማኝ)፣ ወፈፌና ሰካራም፣ ብስጩና ግልፍተኛ፣ በረንዳ አዳሪና የዐዋቂና ሕጻናት ሴተኛ አዳሪዎችን በየዋና ዋና ከተሞች በብዛትና በስፋት ማምረት በልዩ ራዕይነት ካልተመዘገበ በስተቀር የመለስ ራዕይ ብሎ ነገር የሚጨበጥ ነገር አላየሁም – በዋና ራዕይነት እንዲመዘገብለት ከተፈለገ ዋናው የመለስ ራዕይ የተከፋፈለችና የደከመች፣ ለኤርትራ በምንም መንገድ የማታሰጋ ጥንጥዬ ኢትዮጵያን በሂደት መፍጠር ነው – ይሄ የሚታየው ብልጭልጭ ነገርና የዕድገት እመርታ የሚመስል የፎቅና የአስፋልት ወይም ሌላ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ሁሉ መለስ ሳይወድ በግዱ በሥሩ ባሉ ጥቂት ሀገር ወዳድ ወያኔዎች አማካይነት የተከሠተ – ‹ከሬዲቱ› ለርሱ ብቻ የሚሄድ ሳይሆን ለማለት ነው- በመለስ የጥፋት ራዕይና በአፈጻጸሙ መካከል እንደሳይድ ኢፌክ ሊቆጠር የሚችል አጋጣሚ ነው፡፡ ምን ማለቴ ነው – መለስ ኢትዮጵያን በማጥፋት ሂደት ተጠምዶ ሳለ ያን ሂደት ተዓማኒነት እንዲኖረው ለማድረግ ኢትዮጵያዊ መስሎ መታየት ወይም ማታለል ስላለበት ለዚያም ሲባል አንዳንድ የሚታዩና የሚጨበጡ ነገሮችን ማድረግ ስለነበረበት በኢትዮጵያዊ ስብዕና ዓለም አቀፍ አመኔታን ለማግኘት ሲል ባልጠበቀው ሁኔታ ከእጁ ሾልከው ክፉ ገጽታውን በጥሩ ቅባት ያዋዙለት አጋጣሚዎች ነበሩ ወይም ናቸው(ለዚህም ይመስላል ብዙ ኢትዮጵያውያን በዚህ ሰው ‹ምትሃት› ተወናብደው የወያኔን ትክክለኛ ተፈጥሮ እንዳያውቁ የተደረገውና ዐይናቸው በወያኔ ጥፋት ላይ እንዳያማትር እንዲያውም በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪም የርሱ ነገረ ፈጅ እስከመሆን እንዲደርሱ የተሞከረውና አሁን አሁን ደግሞ እየቆጫቸው መምጣቱን እየተገነዘብን ያለነው…) ፡- በሕክምና አነጋገር ለጉበት የወሰድከው መድሓኒት ኩላሊትህን ሊጎዳ ይችላል – ኔጌቲቭ ሳይድ ኢፌክት፡፡ ለራስ ምታት የወሰድከው መድሓኒት ከጨጓራ ህመምህ ሊፈውስህ ይችላል – ፖዚቲቭ ሳይድኢፌክት፡፡ የመለስም የአባይ ግድብና ሌላው ግርግር ሁሉ ከዚህ መሠረታዊ እውነት ያለፈ አይደለም፡፡ እውነተኛ የሕዝብ ፍቅርና የሀገር መውደድ ስሜት ቢኖረው ኖሮ… ታውቁት የለ – ምን ወደዚያ ውስጥ ከተተኝ … ፡፡ ይቅርታ – በዋናው የሃሳብ መስመሬ ላይ እንደአረብ ጣቢያ ጣልቃ እየገባ ኳርት የሚለዋውጥብኝና እንድዘባርቅ የሚያደርገኝ ዘርፈ ብዙው የሀገራችን ችግር በመሆኑ ታገሱኝ፡፡
ኢትዮጵያን በአሁኑ ወቅት እያስተዳደረ ያለው ማን ነው? የት ተቀምጦ? በስምና በአካል ይታወቃል ወይ? ብለን እንጠይቅ፡፡
bereket alamudi demekeእኔ በግል እንደምታዘበው ኢትዮጵያን በአሁኑ ወቅት እያስተዳደራት የሚገኘው ሰው አይመስለኝም፤ መንፈስ ነው፡፡ ይህ መንፈስ ግማሹ ቅዱስ ነው፤ ግማሹ ደግሞ እርኩስ ነው – አሁንም በኔ ዕይታ፤ ዕይታየ ትክክል ነው ትክክል አይደለም የኔ ጉዳይና የናንተ የኅሊና ፍርድ ነው፡፡
ቅዱስ ያልኩት በተከመሩብን ሁለንተናዊ የፖለቲካና ማኅረሰብአዊ ችግሮች የተነሣ እርስ በርስ ተበላልተን እንዳናልቅ እየረዳን ያለ አንዳች ኃይል መኖሩን ከመገመት ባለፈ ስለማምን ነው፡፡ ይህ ኃይል ባይኖር ኖሮ በሀገሪቱ እንደሚታየው ጭቆናና የኑሮ ውድነት አንድም ሰው በአንጻራዊ ሰላም ከቤት ወጥቶ ወደቤት በሰላም ባልገባ ነበር – እውነቴን ነው የምለው ይህን ዓይነት ደግ መንፈስ ባይጠብቀን ኖሮ ተበላልተን ለማለቅ የሚፈጅብን ጊዜ ሰዓታትን ብቻ በወሰደ ነበር(ሦርያንና ሊቢያን… ያዬ ይፍረድ – ሊያውም ከኛ በእጅጉ ያነሰ ጭቆናና እንግልት ደርሶባቸው!) ፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠረው በረንዳ አዳሪ፣ ሥራ አጥና ቤት አልባውም በ”ሰላም” ካደረበት ከየቱቦውና ከየላስቲክ ቤቱ ወጥቶ በቀጣዩ ቀን በየአደባባዩ ባላየነው ነበር፡፡ ካለአንዳች አለሁህ ባይ የመንግሥት መዋቅር በራሱ ኃይልና እንዲሁ በኪነ ጥበቡ ርሀብና ችግሩን ችሎ የሚኖር ሕዝብ ማየት የሚገርምም የሚሰቀጥጥም በድንቃ ድንቅ መዝገብ ሊመዘገብ የሚገባውም የሚሌኒየሙ ተዓምር ነው፡፡ አንድም ሥራና አንድም ደመወዝ የሌለው በሚሊየን የሚገመት ዜጋ ቀኑን አለበቂ ምክንያት እዚህና እዚያ ሲንከራተትና ሲንገላወድ ውሎ አሁንም ልድገመውና በየሥርቻውና በየሥርጓጉጡ በ”ሰላም” አድሮ የቀጣይዋን ዕለት ጀምበር ለማየት እባቡር መንገዱ ላይ ተሰጥቶ መታየቱ የትንግርትን እንጂ የመንግሥትን ኅልውና አያመላክትም፡፡ በዚህ ምክንያት የሀገራችንን በትረ ሥልጣን ከያዙ ሥውር ኃይሎች ውስጥ የተወሰነውን ‹የፓርላማ ወንበር› የተቆናጠጠው አንዳች የተቀደሰ ነገር መሆን አለበት ብዬ አምለሁ፡፡ እንዲያ ባይሆንማ ማን እየተዘባነነ ማንስ በችግር አለንጋ እየተገረፈ በርሀብና በጥም እየተሰቃዬ ይኖር ነበር? ሀሰት ነው?
deberestionበሌላ በኩል የሚታየውን መቋጫ የሌለው የግፍ አገዛዝና የዘረኝነት ቱማታ ስንቃኝ ከነዚህም ጋር የሚቆራኘውን አጠቃላይ የድቀት ሕይወት ስንታዘብ በተለይ በፖለቲካውና በሃይማኖቱ አመራር ረገድ የእርኩሱ መንፈስ ምን ያህል የበረታ እንደሆነ መረዳት አይቸግርም፡፡ ስለዚያም ምክንያት ይመስለኛል ይህ በመለስ የሙት መንፈስ የሚነዳ የአጋንንት መንጋ አንዳች ሥፍራ ተደብቆ ደህና ሰው ወደ አመራር ዝር እንዳይል እነአዜብንና በረከትን እየተመሰለ በላያችን ላይ የሚያንዣብብብን፡፡ እንደሚወራው አዜብ ወደ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ምክትል ሆና አይደለም ጽዳትና ዘበኛም ሆና ብትመጣ እንኳን ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስቡት፡፡ በሌላ ቦታ እያለች የማዘጋጃ ቤት ሹሞችን በስልክ እያስፈራራችና በአካል እያስጠራች ስንትና ስንት ግፍና በደል መፈጸሟ እየታወቀ አንድያውን በዚያ ቢሮ ስትገኝማ ከተማዋን ብቻ ሣይሆን እኛን ነዋሪዎቹን በጅምላና በችርቻሮ ባወጣንበት ዋጋ ቸብችባ በጥቂት ወራት ውስጥ ትጨርሰናለች፡፡ አዜብ – ዮዲት ጉዲት – እንኳንስ ማዘጋጃ ቤት ገብታ በሩቅ እያለችም – ለብልግናየ ይቅርታና – ለውሽማዋም ይሁን ለምትፈልገው ማንኛውም ሰው ቦታ ለማሰጠት፣ መብራት ለማሰጠት፣ የንግድ ፈቃድ ለማሰጠት፣ (እንዳስፈላጊነቱ ተመላሽ ሊደረግ ወይ ላይደረግ የሚችል) የባንክ ብድር ለማሰጠት፣ በመንግሥት ወጪ ረጃጅም የስልክና የውኃ መስመር ለማዘርጋት፣ የፈለገችውን ለማሾም ወይም ለማሻር፣ ንጹሕን ሰው ካለበደልና ጥፋቱ ዘብጥያ ለማስወረድ፣ በጥፋቱ የታሠረን በቅጽበታዊ ጣልቃ ገብነት ለማስለቀቅ፣ የዜጎችን ሀብትና ንብረት በሕግ ሽፋን ለማዘረፍና ለራሷ ካምፓኒዎች ወይም ለመሰላት ለማሰጠት፣ በነባርና አዳዲስ የአክሲዮን ካምፓኒዎች ራሷን በአባልነትና በቦርድ ሰብሳቢነት ለማስገባት፣ ወዘተ. ታደርገው የነበረውና አሁንም ከማድረግ የማትመለሰው አቅል ያጣ ሩጫ በሕዝብ ዘንድ የታወቀ ነው፡፡ ሴትዮዋ ለገንዘብና ለእንትን ሲሏት ገደል እንደምትገባ የሚያውቋት ይመሰክራሉ – አጉል ተፈጥሮ፤ ከምን ዓይነት ሥጋና ደም ተፈጥራ ይሆን ወገኖቼ? በዚህ ዓይነቱ ለከት የሌለው የገንዘብና የሀብት ፍቅሯ ነው እንግዲህ ሰውዬውን ቤተ መንግሥት ውስጥ እንደውሻ አሥራ በርሱ ስምና በርሷ ድፍረት ባጠራቀመችው ንዋይ ከዓለም መሪዎች መለስን በሀብት የሚበልጠው እንዳይገኝ ከፍተኛ ጥረት ላይ የነበረችው – በየባንኩ ብዙ ገንዘብ ታቁር የነበረችው፣ በየዓለም ማዕዘናት ብዙ ቤቶችንና የንግድ ተቋማትን ትመሠርት የነበረችው፣ በፍቅረ ንዋይ መታወሯ እንዳንዳች እያደረጋት እንዲያ ዐይን ባወጣ መንገድ ትዝብት ላይ ወድቃ የነበረችው፡፡ ይህች በገንዘብና በእንትን ፍቅር ያበደች የድብቁ ቢግ ብራዘር ተወዳዳሪ ሴት አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ብትገባ ምን ተዓምር ልትሠራ እንደምትችል ገምቱ – የምን መገመት ነው – ፍንትው ብሎ እየታዬ! የስንቱን ቤት እንደምታፈናቅልና ባወጣ እንደምትሸጥ፣ ስንቱን የኪስ ቦታ እንደምትቸበችብ፣ እንደ አንደኛው ባሏ ‹የዐይናችሁ ቀለም አስጠላኝ› እያለች ስንቱን ምሥኪን ሰው ከሥራና ከደመወዝ እንደምታግድ፣ እንደምታሳስርና ደብዛ እንደምታስጠፋ፣ ስንትና ስንት የሀገር ማፈሪያ ወንጀልና የቁጭ በሉ አሣፋሪ ድርጊቶችን እንደምትሠራ፣ ስንቱን ኮበሌ ካልተኛኸኝ እያለች ከትዳሩና ከጤናማ ኑሮው እንደምታፈናቅል (“አሮጊት ለምኔ! ገንዘብና ሥልጣን ባፍንጫየ ይውጣ!” ብሎ አሻፈረኝ የሚልን መቀመቅ እንደምታወርድ)፣ … በበኩሌ ቁልጭ ብሎ ይታየኛል – እባካችሁን ‹ህልም እልም› ብለን ሁላችን እናማትብበት፡፡ አዜብ ብሎ ከንቲባ? ወያኔ ይህን ካደረገ በርግጥም ራሱን ለማጥፋት ከምንጊዜውም በላይ ቁርጠኛ አቋም ላይ ደርሷል ማለት ነው፡፡ ይህችን የአጋንንት ውላጅ የባንዳ ልጅ ማሳረፍ ይገባል – በሰላም፡፡ በቃ – በመለስ ቀብር እንዳለችው ልጆቿን በማሳደግ ፈተና ላይ ብቻ ታተኩርና በዚያው ትታይ፡፡
አዜብ በሌብነቷ አይደለም ሹም አትሁን እያልኩ የምከራከረው፤ በሌብነቷ ከሆነ መብቷ ነው፡፡ ዓለማችን በሌቦችና አጭበርባሪዎች የተሞላች በመሆኗ የርሷ ሌባ መሆን እንግዳ ነገር አይደለም – በአመራርም ሆነ በተራ ዜጋነት ሌባና አጭበርባሪ ሀገር ምድሩን ሞልቶታል፡፡ አዜብ በተፈጥሯዊ ደመ ሞቃትነቷና ያንንም ተከትሎ በጉልህ ስለሚንጸባረቅባት የሴሰኝነት ጠባይዋ አይደለም ሹም እንዳትሆን የምመኘው፡፡ ያም መብቷ ነው – ካልሰለቻት እንኳንስ ነባር ታጋዮችን አዳዲሶቹንና እምቦቀቅላ ታጋዮችንም ታነባብራቸው፡፡ አዜብም ሆነች ቤቲ በተፈጥሮ የተሰጣቸውን መብት እስከፑንት (ላንድ) ቢጠቀሙበት የነሱ ጉዳይ እንጂ የማንም ራስ ምታት ሊሆን አይገባም፡፡ እኔን ክፉኛ የሚያሳስበኝ ድንበር የማያውቀው ውሸቷ ነው፡፡ በተራ ቃል ‹ውሸታም› መባል በፍጹም አይመጥናትም፡፡
በባህር ዳሩ የወያኔ ስብሰባ የተናገረችው ውሸት ስለሷ ባሰብኩ ቁጥር ስለእውነት በጣም ያመኛል፡፡ በዚያ ስብሰባ ‹መለስ ከዓለም መሪዎች በደመወዙ ብቻ ቤተሰቡን እያሰቃየ የኖረ ብቸኛው መሪ ነው፤ ከስድስት ሺ ብር ደመወዝ ለኢሕአዲግ ተቆርጣ በምትደርሰው አራት ሺህ ምናምን ብር ወርን ከወር እየጣጣፍን በመከራ ሲያኖረን የነበረና አእምሮውን ብቻ ይዞ የተወለደ… ይህ ሊሠመርበት ይገባል ፤ ሰው የሚለው አይደለም – እርሱ በዚያች ትንሽ ደመወዝ ብቻ ኖሮ ያለፈ የተለዬ መሪ ነው…› እያለች የቀላመደች ዕለት ስለርሷ ጨረስኩ፡፡ ስለርሷ ብቻም አይደለም፡- ስለወያኔ/ኢሕአዴግም ያኔውን ጨረስኩ፡፡ አንድ አንጋፋ ድርጅት ያን የመሰለ በሬ ወለደ ዓይነት ነጭ ውሸት ሰምቶ እርምጃ አለመውሰዱ ገርሞኛል – የዚያን ድርጅት የለዬለት ባዶነትም አረጋግጫለሁ፤ የሴትዮዋ ንግግር እውነትነት ቢኖረውም እንኳን የሀገርንና የድርጅትን ምስል በማጠየም ረገድ ቀልማዲት ያደረገችው ነገር እጅግ ሰቅጣጭ በመሆኑ በሕይወት የመኖርን መብት ሳይጨምር ከብዙ ነገር ልትታገድ በተገባት ነበር፡፡ ሕዝብ በሆነ ምክንያት በይሁንታ አፉን ቢለጉም እውነት እንዳይመስላቸው፡፡ ሕዝቡ በዕውቀት ከነሱ ስለሚበልጥ በዚያን ሰሞን ይህን የአዜብን የድህነት ወሬ የቡና ማጣጣሚያ ነው ያደረገው – ሳይጠማን እየጠጣን ብዙ ቡና ፈጅተንበታል – ጊዜው ሲደርስ ይህንን ኪሣራችንንም ታወራርዳለች፡፡ የዚህች ቀልማዳ ሴት ንግግር በአሣፋሪነቱና አጸያፊነቱ በሺዎች ዓመታት አንዴ እንደሚያጋጥም እጅግ ነውረኛ አነጋገር ሊወሰድ ይችላል፡፡ የርሷ ስህተት እንደግለሰባዊ ስህተት ተቆጥሮ በዝምታ ሊታለፍ ይችላል፡፡ የወያኔው ድርጅት በፍርሀት ይሁን በሌለው ይሉኝታ እርሷን በዝምታ ማለፉ ግን ይቅር የማይባል ታሪካዊ ህፀፅ ነው፡፡ ለነገሩ አሁንም ብዙም አልረፈደምና የሴትዮዋን ተፈጥሮ የምታውቁ ወያኔዎች እባካችሁን አንድ ነገር አድርጉ – ለናንተው ስትሉ፡፡ እኛ ሁሉንም ለምደነዋልና ስለኛ ብላችሁ እንደማትጨነቁ እናውቃለን፡፡ ሀፍረቱ ይበልጡን ለእናንተው ስለሆነ አዜብን ግዴላችሁም ተዋት፡፡
hailemariam and samoraቁጭ ብዬ በእርጋታ ሳስበው ሕዝብንና የታሪክ ፍርድን ንቆ ይህችን ሴት ባለሥልጣን ማድረግ የኋላ ኋላ ኢሕአዴግን ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍለው ይመስለኛል፡፡ እናም ኢሕአዴግ ለክብሩ ሲል – ክብር ካለው ነው ለዚያውም – አለበለዚያም ውርደቱን ቅጥየለሽ ላለማድረግ ሲል ይህችን ሴት ከማዘጋጃ ቤት ሹምነት የዕጩ መዝገብ ይፋቃት፡፡ እኔ ውርድ ከራስ ብያለሁ፡፡ ሰውን መናቅ ፈጣሪን መናቅ እንደሆነ ለሃይማኖት የለሹ ወያኔ መጠቆም እፈልጋለሁ፡፡ እርግጥ ነው – በአምባገነኖች ዘንድ ማይምንና እንደጤናማ ሰው ማሰብ የማይችልን አጋሰስ መሾም የተለመደ ነው፡፡ ሲበዛ ግን ያንገሸግሻል፡፡ ሕዝብ ስቆ ቢያልፈው የውሻን ደም መና የማያስቀረው ፈጣሪ፣ አይደለም ይህችን በሰው ቋንቋ ከመናገሯ ውጪ ከውሻ ብዙም የማትለየው ሴት ትቅርና ሂትለርንና ሙሶሊንን የመሰሉ ለሰማይ ለምድር የከበዱ አምባገነኖችን አይቀጡ ቅጣት አከናንቦ በጭቁኖች መሃል አዋርዷቸዋል፡፡ ይህች መናኛ ሴትም ከወያኔ ጋር የምትዋረድበት ዘመን እየመጣ ቢሆንም ማምሻም ዕድሜ ነውና ማሰብ ያልተሳናችሁ በጣት የምትቆጠሩ ወያኔዎች ካላችሁ የዛሬን ማሩን፤ ቀድሜ እንደገለጽኩት ውርደቱ የጋራችን ነው፡፡ ይበልጡን ግን – ልድገምላችሁ – የእናንተው ነው፡፡ ሴትዮዋን መሾማችሁ የግድ ከሆነ ብትፈልጉ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጓት፡፡ ያ ቦታ ከሕዝብ የራቀ በመሆኑ አንገናኝምና እንደፍጥርጥራችሁ፡፡ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ግን ሺዎችን በየቀኑ የሚያስተናግድ የሕዝብ መናኸሪያ በመሆኑ ባለሥልጣናቱ የሕዝብን ቀልብ እንደነገሩም ቢሆን የሚስቡ መሆን አለባቸው፡፡ ይህች ሴት እኮ አርከበ ዕቁባይ ለሕዝብ ጥሩ ሠራ በመባሉና ሕዝብም በተወሰነ ደረጃና በግል አበርክቶው ስለወደደው በዚያ ቀንታበት ኤች አይ ቪ ሲመረመር የሚያሳየውን ቢልቦርድ በተሰቀለ በጥቂት ቀናት ውስጥ እንዲወገድና ከዕይታ እንዲሠወር አድርጋለች፡፡ የባል ተብዬው የመለስና የሚስት ተብዬዋ የአዜብ የክፋት ደረጃ እንግዲህ እስከዚህ የወረደና ከአንድ ተራ ዜጋ እንኳን የማይጠበቅ ነው – ለቅጣት መምጣታቸውን በበኩሌ አምናለሁ፡፡ ተራ ዜጋ ምቀኛና ቀናተኛ ቢሆን ምንም አይደለም፡፡ የአንድን ሀገር በትረ ሥልጣን የጨበጠ ቁንጮ ያገር መሪና ሚስቱ ግን እንዲህ ያለ በራሱ በመለስ ወራዳ የቋንቋ አጠቃቀም ለመግለጽ እንዲህ ያለ ወራዳና ልክስክስ ጠባይ ሲያሳዩ የሀገርን አጠቃላይ ውድቀት ነው በጉልህ የሚያስረዳን፡፡ ያልዘሩት መቼም አይበቅልም፡፡ የዘራነውን እያጨድን ነን፡፡
ለማንኛውም አዜብን በከንቲባነት መሾም – ምክትልም ሆነች ዋና ለውጥ የለውም – የሚያስከትለው አደጋና ውርደት ታስቦበት በጊዜ አንድ ነገር እንዲደረግ የዜግነት ጥሪየን ማስተላለፍ እፈልጋለሁ፡፡
በሌላም በኩል ይሄ ለይምሰል ያህል በብሔረሰብ ተዋጽዖ አንጻር የሚደረገው ሹመት ይቁም፡፡ ምክንያቱም አንደኛ ማንም አያምንም – ይህን ያረጀ ያፈጀ ሥልት አንቀልባ ውስጥ ያለ ጡት ያልጣለ ሕጻንም ያውቀዋልና፡፡ እኔ ለምሳሌ በደመቀ መኮንን መሾም ምክንያት አልተደሰትኩም፡፡ አንደኛውና ትልቁ ነገር እንደውሻ አጥንትና ደም አላነፈንፍም፡፡ በብቃትና በችሎታ ከሆነ ሁሉም የሚኒስትር ካቢኔ ከኮንሶና ከሙርሲ ቢሆን ሃሳቡ አይበላኝም፤ ወያኔንም የጠላሁት በመጥፎ ድርጊቱ እንጂ በተሹዋሚዎች የዘር ሐረግ አይደለም – በጭራሽ፡፡ ሁለተኛ የደመቀ መሾም ስሜትን በማይነካ የቃላት አጠቃቀም ለየዋሃን አማሮች ካልሆነ በስተቀር መሬት ላይ የፈጠጠውን ኢትዮጵያዊ እውነት ለሚረዳ ሰው ‹አማራ ተሾመልኝ!› በሚል የሚያስፈነጥዝ አይደለም፡፡ ራሱን ከጥቃት የማያድን አማራ፣ የራሱ ናቸው የተባሉ ወገኖችን ጥቃትና እንግልት ለማስቆም አንዳችም ተሰሚነት የሌለው በድንና ገልቱ ሰውዬ ተሾመልኝ ብዬ ጮቤ የምረግጥ ሞኝና ተላላ መስዬ ከታየኋቸው – አዝናለሁ – ሞኞቹ እነሱ እንጂ እኔ አይደለሁም፡፡ ደመቀን መሣይ ከረፈፍ ሆዳሞች በሥርዓቱ ውስጥ ወይነው ገብተው ሀገሪቱን ምን ያህል እየጎዱ እንደሆነ ማስታወስም ተገቢ ነው፡፡ በጣም የምወደው ኦባንግ ሜቶ ቅድም ሲናገር እንደሰማሁት ሁልጊዜም እኔ ራሴ እንደምለው ወያኔ ማለት በዘርና በቋንቋ ተወስኖ ወይም ተቀንብቦ የተቀመጠ አለመሆኑንም መረዳት ይገባል፡፡ መነሻውና አስኳል አመራሩ ከትግራይ ይሁን እንጂ ለዚህ የወያኔ ሥርዓት ማበብና ማፍራት ዋና ተባባሪዎቹ ትግሬ ያልሆኑ የተጋቦት ወያኔዎች መሆናቸውን እናውቃለን፡፡ ግን ግን “የምታሸንፈውን ምታ ቢሉት ወደ ሚስቱ ዞረ” እንዲሉ ሆኖብን አንዴ የፈረደበትን የትግራይ ሕዝብ ብዙዎቻችን እንወርድበታለን፡፡ በበኩሌ አሁን እየሆነ ባለው ነገር ሁሉ የእያንዳንዳችን ልብ ሳይሰበር ነገ ይቅርታ እንደምንባባልና አብሮነታችን ካለሣንካ እንደሚቀጥል በሙሉ ልብ አምናለሁ፡፡ ንዴትና ብስጭት የማይፈጥረው አእምሮኣዊ ምስል ባለመኖሩ ደመናው ሲጠራና እውነት ስታሸንፍ አሁን ችግር የሚመስሉን ብዙ ነገሮች ከላያችን ላይ ተገፍፈው ይጠፋሉ፤ ያለ ነገር ነው – በዚህን መሰሉ ጊዜ የሚያጋጥም ብዙ ነገር አለ፡፡ መምሰልና መሆን ስለሚለያዩ የደፈረሰው ሲጠራና የሰላም አየር በሀገራችን ሰማይ ሲያረብብ የግጭትና የሁከት እርኩሳን መናፍስት ተጠራርገው ይወገዳሉና ስለነገው ከመጠን በላይ አንጨነቅ፡፡ የወቅት ንፋስ የሚፈጥራቸው ብዙ አላፊ ክስተቶች አሉ – በኛ ብቻ ሳይሆን በየሀገሩ፡፡ ሁሉም እንደሚያልፍ መረዳትና ለዚያ በርትቶ መታገል እንደሚገባ ተረድተን በወንድማማችነትና በእህትማማችነት ተባብረን ይህን የለያየንን ቆሻሻ ሥርዓት ለማስወገድ አብረን መታል ብቻ ነው የሚያዋታን፡፡ አለጥርጥር ሥርዓቱ ይወድቃል – ችግሩ በጣም ብዙ ምናልባትም ከእስካሁኑ የከፋ ቨስጠሊታ የታሪክ ጠባሳ ሳይተው የሚወድቀው እንዴት ነው? የሚለው ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የሁሉም ምክክር፣ ትብብርና ስምምነት ያስፈልጋል፡፡ እውነት ምን ጊዜም ከእውነት መንገድ ለማትወጣው ነገር በመለያየት አዲስ ግን በወያኔያዊ ትልምና ዐቅድ የተለወሰና በፀረ-ኢትዮጵያነት የተመረዘ ታሪክ ለማስመዝገብ የምንቻኮል ሰዎች ካለን ቆም ብለን እንድናስብ በእገረ መንገድ ጠቆም ባደርግ ደስ ይለኛል – ከወያኔ ብዙ ነገሮችን መማር እንችላለን፡፡ የሕዝቡ ችግረና ፍላጎት ይግባን፡፡ ‹ሕዝቡ ምን ይላል? ምንስ ይፈልጋል ?› ብለን እንራመድ እንጂ በየግል ፍላጎታችን የተጓዝን ተሳስተን አናሳስት፤ ታሪክም ይቅር አይለንም፡፡ መደማመጥ ለመልካም የጋራ ስኬት ጠቃሚ መሆኑን እየዘነጋን ለየህልማችን እውን መሆን በተናጠል ስንሮጥ የዓለም ፍጻሜ ተቃረበ፡፡
ማንዴላ እጅ ሆነዋል፡፡ ምናልባትም ይህች ጽሑፍ በአንዱ ድረ ገፅ ከመለጠፏ በፊት አንዳች ነገር ሊከሰት ይችላል፤ ወይም በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ዜና ዕረፍታቸውን እንሰማ ይሆናል – ለነገሩ ‹እግረ ቀጭን እያለ እግረ ወፍራም ይሞታል› እንዲሉ ከማንዴላ በፊት ለምሳሌ እኔ ራሴ ልቀድም እችላለሁ፡፡ የወደፊቱን ያለማወቃችን ምሥጢር ነው ሕይወትን ትርጉም ያላት እንድትሆን ያደረጋት፡፡ ተስፋ ባትኖር ሁሉም በቁም እንደሞተ ያህል ነው – ጧት ከቤቱ በሰላም የወጣ ሰው ማታ ሬሣው ወደቤቱ ሊመለስ እንደሚችል ቢያውቅ ማንም የመኖር ጉጉት አያድርበትም – የእግዜሩም እንበለው የተፈጥሮ ጥበብ መገለጫም ይሄው ነው – ስለወደፊቱ አለማወቅ፡፡ በዚህም አለ በዚያ በማንዴላ ሁኔታ ዓለም በጭንቀት ላይ የምትገኝ ትመስላለች፡፡ ጭንቀቷ ግን ለማንዴላ ለራሱ እንዳይመስላችሁ፡፡ ምሥጢሩ ወዲህ ነው፡፡(በነገራችን ላይ ‹ድኅረ ገፅ› የምንል ሰዎች ‹ድረ ገፅ› ማለትን ብንለምድ ደስ ይለኛል፡፡ ‹ድኅረ› ማለት ‹በኋላ›(post) ማለት እንደሆነና ‹ድረ› የሚለው ቃል ግን ‹ድር› ከሚለው የአማርኛ ቃል ተወስዶና ከ‹ገፅ› ጋር ተጋምዶ ‹website› የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል እንዲተካ መደረጉን ምሁራን ይገልጻሉ፡፡ ዕውቀት አይናቅምና በተለይ ድረ-ገፆች እባካችሁን ይቺን ነጥብ አትናቋት፡፡ መናደድ ሲያምረኝ ከምናደድባቸው ነገሮች አንደኛዋ ይህች ነች፡፡ )
የዓለም ሕዝብ አንድ አባሉ ከ94 ዓመታት በላይ በመሬት ላይ እየኖረ እንዲሰቃይ የሚፈልግ አይደለም፡፡ ይህ ዓይነቱ ሰዎች እስከዘላለሙ እንዲኖሩ የሚፈለግበት ምኞት – ከልብ ስለመሆኑ ማወቅ ቢያስቸግርም – በብዛት የሚታየው በኛይቷ ሀገር በኢትዮጵያ ነው፡፡ የመቶ ሃያ ዓመት ሽማግሌ ሲሞት ፊት የሚነጨው በሌላ ሀገር አይደለም – በኢትዮጵያ ነው – ሊያውም ይበልጡን በአማራው አካባቢ፡፡ ባህላችን ከኛ ወቅታዊ ግንዛቤ በልጦ የሚገኝበትን ሁኔታዎች አንዳንዴ እንታዘባለን፤ ከአንዳንዴም በላይ እንዲያውም፡፡ ለዚህም ነው በዛሬዋ ውሎየ እንኳ ሁለት ተቃራኒ ጸሎቶችን የታዘብኩት – አንድ ከኢትዮጵያውያን፣ አንድ ከደቡብ አፍሪካውያን፡፡ መቼም እኛ ከነሱ በልጠን እግዜሩ ለማንዴላ የማቱሳላን ዕድሜ እንዲሰጥልን ልንጸልይ እንደማንችል ቢያንስ ኅሊናችን ያውቃል – እውነቱን እንነጋገር ከተባለ፡፡ ይህ ምን ያሳያል? ፊት ለፊት የሚታየው ባህላችን ለሰው መጥፎ የማይመኝ መሆኑንና በብዙ ነገር ከሌሎች የምንለይ ሕዝብ መሆናችንን ነው ለዓለም እያስመሰከርን የምንገኘው – ምነው እውነተኛና በምንም ዓይነት ማዕበል የማይናወጥ አቋም ባደረገልን!
ማንዴላ እንዳይሞት የምንፈልግበት ምክንያት ግልጥ ነው፡፡ ዓለማችን በሰው እጦት ምች ስለተመታች ጥሩ ሰው ስናገኝ እንደብርቅ እናየዋለን፤ ሞት እንዳይነጥቀንም እንሳሳለታለን፤ እስከወዲያውም አብሮን እንዲኖር እንመኛለን – ትውልድ ቢያልፍም ከቀጣዩ ትውልድ ጋር፡፡ ብዙ ደጋግ ሰዎች ቢኖሩን ኖሮ የዓለም ሕዝቦች ትኩረት በአሁኑ ሰዓት ያለቪዛና የትራንስፖርት ወጪ ደቡብ አፍሪካ ሄዶ ፕሪቶሪያ ሆስፒታል ዙሪያ ባልከተመ ነበር፡፡ ጥሩ ሰው ብርቅ በሆነበት ዘመን መፈጠር እንዴት መታደል ነው! መለስም እንዲያ የተንጫጫንለት እኮ የርሱን አእምሮ ይዞ የሚወለድ – እንደአዜብ አነጋገር በዓለም የአንጎል ገበያ ተመራጭ ጭንቅላት ይዞ በሺዎች ዓመታት አንዴ የሚወለድ ዐዋቂና ታዋቂ በመሆኑ ነው፡፡ እኔ ለመለስ የነጨሁት ፊት እስካሁን አላገገመም፤ የምለብሰውም ማቅ ከላየ ላይ አልወረደም፡፡ እርግጥ ነው – ይበልጡን ለክፋት ቢጠቀምበትም መለስን በዕውቀቱ መቀጣጠብ አይቻልም፤ ሰይጣን ለዘዴው ከመጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅሳል እንደሚባል መለስም የነበረው ሁለገብ ዕውቀትና ብልጣብልጥ ተፈጥሮ ከብዙዎች መሪዎች ቢበልጥ እንጂ አያንስም፡፡ የኔነህ ሳይለኝ ቢሞትም የኔነው ማለት ወጪ የለውምና ሳልወድ በግዴ የኔነው ብዬ ብቀበለው ከሚኮሰኩሰው ኢትዮጵያዊነቱ አንጻር ብቻም ሳይሆን ከአጠቃላይ ስብዕናው የሚፈልቁ ብዙ የሚደነቁ ሰብኣዊ ተሰጥዖዎች እንደነበሩት አልክድም – አጭበርባሪው፣ አስመሳዩና መልቲው መለስ ዜናዊ፡፡ ግን ተሰጥዖዎቹን ለተንኮልና እንደሥራየ ቤት ነገርን በመጠምዘዝ ሕይወቱን ጨርሶ ዕውቀቱን ሳይጠቀምበት ሞተና ዐርፎ ዐሣረፈን፡፡ በሚስቱ ሲንገበገብ የነበረ አንድ ፈላስፋ መቃብሯ ላይ እንዲህ የሚል ጽሑፍ አስፍሯል አሉ፡- My wife lies here; let her rest in peace, so do I.
አትታዘቡኝ፡፡ በበኩሌ ማንዴላ እንዲያርፍ እጸልያለሁ – በሰላም ማረፍ ለኔ አይገባኝም – ሰው እየሞተ ምን ሰላም አለና፤ ማንዴላ በ‹ሰላም› እንዲያርፍም በ‹ሰላም› እንዲድንም ከጸሎት ጀምሮ ሁሉም ነገር ቢደረግም እስከዚች ሰዓት ድረስ አልዳነም ወይም አላረፈም፤ የዚህን ደብዳቤ የመጀመሪያ ረቂቅ ስጽፍ – አሁን ሰዓቱ ከሌሊቱ ስምንት ገደማ መሆኑን ልብ ይሏል – የማንዴላ የጤና ሁኔታ እንደሰሞኑ ሁሉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው የሚገኝ፤ ከአሳሳቢነቱም የተነሣ ፕሬዚደንት ጃኮብ ዙማ ሊያደርጉት የነበረውን የሀገር ውጪ ጉዞ እስከመሠረዝ ደርሰዋል፡፡ ዕንቁ ልጃችን – ብርቅዬ የአፍሪካ ብቻ ሣይሆን የዓለማችን ልጅ ማዲባ ሲያርፍ ደግሞ ነፍሱ በማኅተመ ጋንዲና በእማሆይ ተሬዛ፣ በአብርሃምና በያዕቆብ ነፍሳት አጠገብ እንድትቀመጥ የቸሩ እግዚአብሔር ፈቃድ ይሆን ዘንድ የሁላችንንም ጸሎት እኔም በበኩሌ እጸልያለሁ፡፡ ይቅርታችሁን – ቀደም ብዬ ማዲባን በአንቱታ የጠራሁት ብዙ ሰው ያለው እኔስ ለምን ይቅርብኝ ብዬ ከሰው ለመመሳሰል ነው፤ ስጨርስ በአንተ የጠራሁት የሕዝብ ሰው አንቱ እንደማይባል ስለምረዳ የአንጀቴን ነው – የሕዝብ ሰው ማለት ደግሞ የሚፈቀርና የሚወደድ ማለት ነው፡፡ አብንና ወልድን ማን አንቱ ይላል? ቅድስት ማርያምንስ? ኧረ መለስ ዜናዊንስ ማን በአንቱታ ጠርቶት ያውቃል? የሕዝብ ሰው ማለት እንዲህ ነው – ቺንዋ አቼቤ A man of the people የሚል ርዕስ ለአንድኛው መጽሐፉ የሰጠው እኮ ለነማንዴላ ዓይነቱ መላ ሕይወታቸውን ለራሳቸው ጥቅም መስዋዕት ላደረጉ ሣይሆን ለነመለስ ዜናዊ ዓይነቱ ለቤት ቀጋዎች ለውጭ አልጋዎች ነው፡፡ ዓለም ግን ምን ዓይነት የዕንቆቅልሽ ምድር ናት ጎበዝ?!
mandela ውድ ማንዴላ ሆይ! ሁልጊዜ ከኅሊናችን አትጠፋም – በአካል ብትለየን በመንፈስ ምንጊዜም አብረኸን አለህ – ከአሁኑም ከወደፊቱም ትውልዶች ጋር፤ ፈጣሪ አንተን እንደወሰደ በምትክህ ለዓለም ሰላም የሚተጉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቅን አሳቢ ዜጎችን እንዲልክልን ስትሄድ አሳስብልን፡፡ አፈሩን ገለባ ያድርግልህ፡፡ የሁለት ወር ሀገርህን ኢትዮጵያንም በፈጣሪ ፊት አስባት፡፡ ስቃይና ጣር ሳይበዛብህ በቶሎ ሂድልን፡፡ በዚህች አንተን ሳይቀር ለ27 ዓመታት በእሥር ባንላታች የእርጉማን ምድር ከአሁን በኋላ ለሴከንድም መቆየቱ መከራና ስቃይ መጨመር እንጂ ጤናውም ጤና አይሆንህም፡፡ ሰዎች ስንባል ራስ ወዳዶች ነን፤ ‹ቆይልን› የምንልህ በአንተ ስቃይ የኛን ‹ኢጎ› ለማስደሰት እንጂ አንተ አልጋ ላይ ውለህ የመከራ ቀናትንና ሌሊቶችን በእዬዬ ማሳለፍህ፣ በድጋፍ ሰጪ የሕክምና ቴክኖሎጂ እየታገዝክ ካለ እንቅልፍ መቆየትህ አንዳችም ነገር አይፈይድልንም – ለአንተም ለእኛም፡፡ በሀገሬ ሰው ይሙት ተብሎ እንደማይጸለይ አውቃለሁ ማዲባየ – ግን ‹ይህን አለ› ተብዬ ኩነኔ መግባቱን እመርጣለሁ እንጂ ስትሰቃይ ለማየት ከእንግዲህ ቆይልን አልልህም፡፡ በቃ፡፡ በሰላም ሂድልን፡፡ ስትመጣ እንደምትሄድ ይታወቅ ነበር፡፡ እኛም በሕይወት አለን የምንል ወገኖችህም ወረፋችንን ጠብቀን እንከተልሃለን፡፡ ዱሮም መንገደኛ ፊትና ኋላ ነው መባሉም ለዚህ ነው፡፡ ይብላኝ ለኛ ግና፡፡ በጅቦችና በእሪያዎች መካከል እንደተጣልን ተለይተኸን ለምትሄደው ለኛ ይብላኝ እንጂ አንተማ ከፋም ለማም 95 የሚጠጉ ክረምቶችን ለሕዝብህ ስትል ከአፓርታይድና ከመጥፎ ግላዊ ገጠመኞችህ ጋር ስትፋለም ኖረህ አሁን በመጨረሻው ሥጋዊ ሽንፈትህ ደረጃ ላይ ደርሰሃል፡፡ በዚያች በደቡብ አፍሪካዊቷ አዜብ እንኳን ያየኸውን አበሳ ማን ይረሳዋል? ብቻ ሆድ ይፍጀው ማዲባየ፡፡ እዚያው እስክንገናኝ ደህና ሰንብትልኝ፡፡
ሰላም ለኢትዮጵያና ሕዝቧ፤ በዚህ ዓለም አቀፍ ሀዘን መጽናናት ለሚያስፈልገው ሁሉ ፈጣሪ እንዲያጽናናው እመኝለታለሁ፡፡

የትኛው ነው ሊያስጨንቀን የሚገባው?

$
0
0

የትኛውከያሬድ ኤልያስ
ከሰሞኑ በአብዛኛው ሶሻልሚዲያ ላይ የምንመለከተው ወይም የምናነበው ቤቴልሄም አበራ(ቤቲ) የተባለች ወጣት ኢትዮጵያዊት በቢግ ብራዘር አፍሪካ ትእይንት (show) ላይ ከሴራሊዮኑ ቦልት ጋር ፈጸመችው ስለተባለው ወሲብ በተለየዩ ማህበራዊ ድረ-ገጾች እና መገናኛ ብዙሃን የሚሰጠው አስተያየት እንደቀጠለ ነው እሷም ከውድድሩ ከተባረረችም በኋላም የምታደርገው ቃለ ምልልስ እንደቀጠለ ነው የሷም መልሷም እንደዛው አገሬን ወክዬ ነው የሄድኩት ብዙም ነገር ስለአገሬ ተናግሬሃለሁ ከዛ በተረፈ ደግሞ የራሴ ህይወት አለኝ እንደፈለግኩ መሆን እችላለው ስዎም ደግሞ ይሄን ነገር ማስብ ያለበት እንደጌም ነው አለችን ።

አዉን እኔ ለማለት የፈለግኩት ነገር ቢኖር እንደሚከተለው ነው
እውን ከዚህ በላይ ስለዚች ልጅ የምንናገረው ሆነ የምንጽፈው ነገር ማብቃት አለበት ባይ ነኝ እንደማንኛውም ሰው ለመጀመሪያ ግዜ ይህንን ቪዲዮ እንዳየሁት እኔም ሌላው ሰው እንደሚሰማው መጥፎ ስሜት ተስምቶኛል እንደሌላውም ሰው አስተያየቴን ስጥቻለው በአውን ሰዓት ግን ይህንን ነገር ከሌላም ሰው ጋር ላለማውራትም ሆነ አስተያየት ላለመጻፍ መቆጠቤን እና ለዝችም ልጅ ምንም ማሰቢያ ግዜ እንደሌለኝ ይህንን የቪዲዮ ፊልም እስካየሁበት ቀን ዕለት የተባለችውን ልጅ በመልክም ሆነ በአካል እንደማላውቃት ሁሉ አሁንም ለራሴ ይችን ልጅ እንደ ኢትዮጵያዊነቷ እንደማላውቃት ማናችንም ብንሆን ደግሞ ስለሷ በምናስብበት ግዜ ሰለአገራችን ማስብ እንደሚበጅ እንድናውቅ።
በዚህ ወቅት ስንት ነገር ነው በህይወታችን ሆነ በአገራችን እያስጨንቀን ያለው በዚህ በኩል አገራችን ከደረሰባትና እየደረሰባት ካለው ነገር እንዴት ነው የምናላቅቃት ብለን በምናስብበት ሁኔታ ላይ እንደመሰናክል ሆኖ የዚች ልጅ ነገር እንደዚህ ሊያደናቅፈን የሚገባ አይመስለኝም ። እውን ነው ባአሁን ሰዓት ሊያስጨንቀን የሚገባው ነገር የዚች ልጅ ጉዳይ አይመስለኝም ይልቁንስ በነጻነት ናፍቆት አሳሩን ለሚበላው ህዝብ ያለ ፍትህ ያለምንም ጥፋት በእስር ለሚማቅቁት ለውድ ወንድሞቻችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በስደት ላይ ጉዳት እየደረሰበት ላለው ወገን በዓረብ አገራቱ ለሚሰቃዩት ሴት እህቶቻችን በየቀኑ እያየነው ባለው ነገር በዚህ ላይ ነው መጨንቅ ያለብን።
በኔ በኩል ለአንዴም ለመጨረሻም ይህን ነገር ብያለሁ ማነው ስሟ ቤቴልሄም ነው አይደል እኔ ለአንቺ ለዚህ ተርካሻ ስራሽ ግዜ የለኝም ላንቺ በማስብበት ግዜ ለሌላው በበረሃ ላይ ለሚንገላቱት ሴት እህቶቼ ማስቡ ይቀለኛል ለቤተሰቦችሽ ግን ብርታቱን ይስጣቸው ::

ስብሃት ነጋ “እውነት” ሲያዳልጣቸው – (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

$
0
0

sebehatሽማግሌው ስብሃት ነጋ ከጥቂት ቀናት በፊት በሰጡት ቃለ-ምልልስ አስበውት ይሁን ሳያስቡት “እውነት” አምልጧቸዋል። አጥብቀው ያነሷቸው የሙስና ጉዳዮች ራሱን የቻለ « አላማና ግብ » አላቸው። የመጀመሪያው በፓርቲያቸው ውስጥ ያለው ክፍፍል (የጥቅም) እንደተዳፈነ እሳት ውስጥ ለውስጥ እየተብላላ መሆኑን በግልፅ ያሳያል። ከተናገሩት የሚከተለውን እንመልከት፤ « .በጤናማ ሁኔታ የሚገኙ ሰዎችን እንቆርጣለን፣ እናስራለን ወዘተ እያሉ ሲያስፈራሩ የነበሩ የፖለቲካ፣ የመንግስት ሰዎች ነን የሚሉ የፀጥታና የስነ አእምሮ ሁከት ፈጥረዋል። መቶ ሚሊዮን የሰረቁና ያስዘረፉ፣ 10ሺህ ብር የሰረቀውን ሲያገላብጡት ያታያሉ። » ብለዋል። « እንቆርጣለን » ያሉት መለስ ዜናዊ ናቸው፤ መለስ በአደባባይ ይህን ከመናገር አልፈው ሲያስፈራሩም እንደነበር እናስታውሳለን። መለስ ያንን ያሉት በ10ሺዎች የሚገመት ቡና ከመጋዘን ጠፋ በተባለበት ወቅት ነው። ያንን ቡና የሰረቁትና ባህር ማዶ ሸጠው ገንዙቡን ኪሳቸው የከተቱት አዜብ መሆናቸውን ከዚህ ቀደም ምንጭ ተጠቅሶ ይፋ ተደርጓል። እናም ስብሃት “መቶ ሚሊዮን የሰረቁ..» ያሉት አዜብ መስፍንን ሲሆን፣ « ያስዘረፉ» ያሉት ደግሞ ባለቤታቸው አቶ መለስን ነው። « 10ሺህ የሰረቁ..» የተባሉት በቅርቡ የታሰሩት የጉምሩክ ሰዎችን ሲሆን..እነዚህን በንፅፅር ያስቀመጡት የአዜብ (ተላላኪዎች) ስርቆት መጠነሰፊ መሆኑን ለማመላከት ነው። ስብሃት እስካሁን አድፍጠው ቆይተው በዚህ ሰሞን ይህን መናገራቸው ..«አዜብ የከተማዋ ም/ል ከንቲባ ይሆናሉ» የሚባለውን በመስማታቸው ሆን ብለው ያደረጉት ነው፥ ይላሉ ታዛቢዎች። በተለይ ሽማግሌውን በቅርብ የሚያውቋቸው የፓርቲው ሰዎች « ስብሃት ከበረሃ ጀምሮ በቀለኛ ነው። ጥርሱ ውስጥ የገባን ሰው ካላስወገደ እንቅልፍ አይወስደውም፤ ብዙ ሰው አጥፍቶዋል። አሁንም አዜብን እግር በእግር የሚከታተለው ለዚሁ ነው» ይላሉ። በማስከተልም ፥ « ሙስና ከተነሳ ስብሃትም እስከአንገቱ ተነክሮበታል። በገርጂና ሳር ቤት የሚገኘው <ሉሲ አካዳሚ > በአሜሪካ በሚኖሩ ስጋ ዘመዶቹ ስም እንዲሁም በቀድሞ የአየር ሃይል ጄ/ል ሰሎሞን ስም የሚንቀሳቀስ ግን የስብሃት የግል ንብረት መሆኑን የማይታወቅ መስሎት ነው?….ጎንደር -ሑመራ ያለው የሰሊጥ እርሻ የስብሃት አይደለም?…በ10ሚሊዮን ብር በሚገመት በመቀሌ (አፓርታይድ መንደር) ስብሃት ዘመናዊ ቪላ እንደሚገነባ አይታወቅም ብሎ ይሆን?…» ሲሉ እነዚህ ወገኖች የስብሃትን ሙስና በከፊል ይጠቅሳሉ።
ስብሃት በዚህ አላበቁም፤ « ..እስካሁን ከፍተኛ ሙሰኞች ትንሹን ሙሰኛ ከሰው አሳስረው ያስፈርዱና ያሰቃዩ ነበር ይባላል። ከፍተኛ ሙሰኞች ከመርማሪው ጀምረው አቃቤ ሕጉም ዳኛው፣ ምስክሩም ይቆጣጠራሉ። ትንሽ የሰረቀም ምንም ያልሰረቀም ሲሰቃዩና ሲያደኸዩ የነበሩም፤ አሉም ይባላል። ስልክ እየደወሉም ይፈርዱ ነበር ይባላል።» ብለው አረፉት ስብሃት። ትክክል ናቸው!! ዳኛ ብርቱካን ሚዴቅሳ « ይህን ካልፈረድሽ በመኪና ገጭተን ነው የምንገድልሽ » ተብላለች። ያውም ከቤተ መንግስት ተደውሎ። አባተ ኪሾ ከደቡብ ባጀት ተመላሽ የሆነ ሰባ ሚሊዮን ብር (70.000.000) ለመንግስት ተመላሽ ሊያደርጉ ሲሉ …« ወዲህ በል..የምን መንግስት ነው?» በማለት ተቀብለው ኪሳቸው የከተቱት አዜብ መሆናቸውን አባተ ፍ/ቤት ጭምር ያጋለጡት ነው። ስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊ ደግሞ ታምራት ላይኔ በውሸት እንዲመሰክር አምስት ጊዜ አግባብተውት እንቢ ሲል ከማስደብደባቸው በተጨማሪ ሌላ ክስ እንዲመሰረትበት አድርገዋል። አቃቤ ሕግ የነበረው ዮሃንስ ወ/ገብርኤል የነስብሃትን የውሸት ክስ ተቀብዬ ተግባራዊ አላደርግም፤ ህሊናዬ አይቀበለውም .. በማለቱ ብቻ ለአምስት አመት እንዲታሰር አላደረጋችሁም?…ብዙ ማስረጃና መረጃ መደርደር ይቻላል።..
አሁን ስብሃት ተናገሩት እንጂ…ህዝቡ ብሎ-ብሎ የታከተው ነገር ነው!! እነ እስክንድር፣መሃመድ አቡበከር፣ አንዷለም አራጌ፣ ርእዮት አለሙ….ወዘተ በርሶ ጓደኞች በስልክ ትእዛዝ የተፈረደባቸው ናቸው!!… «ፍትሃዊ ስርአትና መንግስት አለ..» እያሉ ህዝብን የሚያደነቁሩት እነበረከትና የጋሪ ፈረስ የሆኑት ሃ/ማሪያም እርቃናቸውን የሚያስቀር ነገር ነው በስብሃት የተቀመጠው።

ጃዋር መሃመድ እና የአማራ ሊሂቃን –ከያሬድ አይቼህ

$
0
0

jawarከያሬድ አይቼህ – ጁን 28፥2013

የኦሮሞ-አማራ ምሰሶነት ንድፈ-ሃሳብ በቀረበበት በዚህ ሰሞን ፡ አቶ ጃዋር መሃመድ በአልጀዚራ ቲሌቪዥን ላይ “መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ … ኢትዮጵያዊነት ያለፈቃዳችን ተጭኖብን ነው” ማለቱ ለሁለቱ መሰሶዎች ሊሂቃን አብሮ መስራት ፍላጎት የመጀመሪያው የአደባባይ ፈተና ሆኗል። ሁለቱ ምሰሶዎች አብረው መስራት የሚችሉት ለሁሉም ብሄሮች የሚበቃ ምህዳር ያለው ‘ኢትዮጵያዊነት’ ሲቃኝ ብቻ ነው። ሌላ አቋራጭ መንገድ የለውም።

- ኢትዮጵያዊነት እና አማራነት -

አማራዎች አንድ መሰረታዊ ችግር አለብን። እኛ አማራዎች ኢትዮጵያዊነትን እና አማራነትን ለይተን ማየት ተስኖናል። በተለይ አሮጌው ትውልድ በፍጹም ኢትዮጵያዊነትን ከአማራነት ፡ አማራነትን ከኢትዮጵያዊነት ለያይቶ ማየት የማይችል የአስተሳሰብ መካኖችን በብዛት አሉበት።

እኛ አማራዎች ‘አንድነት’ ስንል ‘አንድ አይነትነት’ ማለታችን መሆኑ ተነቅቶብናል። አሃዳዊት ኢትዮጵያ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ያልጠቀመች ኢትዮጵያ ነበረች። አሁን ብዙአዊት ኢትዮጵያ ነግሳለች። ብዙአዊት ኢትዮጵያ የጃዋር መሃመድ ኢትዮጵያ ናት። ብዙአዊት ኢትዮጵያ የሌንጮ ባቲ ኢትዮጵያ ናት። ብዙአዊት ኢትዮጵያ የዋለልኝ መኮንን ኢትዮጵያ ናት።

አማራዎች ሆይ! የዱሮዋ ኢትዮጵያ ተመልሳ አትመጣም። አማርኛ ቋንቋ ሁሉም የሚናገርባት ፡ ኦርቶዶክስ ክርስትና የተንሰራፋባት ፡ አርንጓዴ-ቢጫ-ቀይ ብቻ የሚውለወለብባት ያች ኢትዮጵያ በታሪክ መጽሃፍት እና በቪዲዮ እንጂ ወደፊት ልትመለስ አትችልም። የአሃዳዊ ስርዓት ናፋቂዎች እርማችንን እናውጣ!

- አዲስ ኢትዮጵያዊነት -

ባለፉት 22 አመታት ኢትዮጵያዊነት እንደገና ተቀርጿል ፤ አዲስ መልክ ተላብሷል። ኢትዮጵያዊነት የአማራዎች ሶፋ መሆኑ ቀርቶ ለሁሉም የሚበቃ ሰፊ አግዳሚ ወንበር ሆኗል። “መጀመሪያ ብሄሬን ነኝ ፡ ቀጥሎ ኢትዮጵያዊ ነኝ” የሚለው አስተሳሰብ በትግሬዎች ሲነገር ሃሰት ቢሆንም ፤ በምስራቅ ፡ ምዕራብና ደቡብ ኢትዮጵያዊያን ቢነገር ግን ሃቅ ነው።

ትግራያን የሚዘነጉት እውነታ ቢሆር አማርኛን ቋንቋ የኢትዮጵያ መንግስት ቋንቋ ያደረጉት አጼ ዮሃንስ መሆናቸውን ነው። ይሄን እውነታ እያወቁ የትግራይ ሊሂቃን ክህደት ውስጥ የገቡት ህወሃት በኦሮሞዎች እና በአማራዎች ላይ የፓለቲካ የበላይነት ለመያዝ ብሎ ነው።

በአዲሱ ኢትዮጵያዊነት ፡ ኢትዮጵያውያን ብዙ አይነት ማንነት አላቸው። ዜጎች አንድ አይነትነትን እንደ ኢትዮጵያዊነት አይቀበሉም። አቶ ጃዋር እንደገለጸው ፡ አንድ አይነትነት በግዴታ የሚጫን ማንነት ነው። በሰፊው ኢትዮጵያዊነት ግን ብዙ አይነትነትን የሚያስተናግዱ ፡ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረቱ ማንነቶች ተንሰራፍተዋል።

- የጃዋር ቁንጥጫ -

ጃዋር የቀድሞው ስርዓት ናፋቂዎችን ትዝታና የፓለቲካ ቱሪስትነት በንግግሩ ቆንጥጦታል። የትዝታ ፓለቲካ ለምንወድ የጃዋር ንግግር ያበሳጫል ፤ ንግግሩ ግን ታሪካዊ ጭብጥ ነው። የአገራችን የፓለቲካ ውጥረት በትዝታና በፓለቲካ ቱሪስትነት የሚፈታ አይደለም።

ለሁለቱ ምሰሶዎች አብሮ መስራት የአማራ ሊሂቃን የጃዋር መሃመድን ንግግር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መቀበላቸው የመጀመሪያ ፈተና ነው። ይሄን ማድረግ ያቃታችሁ የአማራ ሊሂቃን ፡ በተለይ በቀድሞው የአሃዳዊ ስርዓቶች ነፍስ ያወቅን ፡ ከትግሉ ጡረታ ውጡ። እናንተ ለሁለቱ ምሰሶዎች አብሮ መስራት ዋና እንቅፋትና ፡ መርዝ ናችሁና ገለል በሉ። መርዛችሁ ለኢትዮጵያዊነት መስፋፋት ፡ መዳበር እና እመርታ እንቅፋት ነውና ዞር በሉ:: አዎ! ዞር በሉ!!

ክብር ለጃዋር መሃመድ!

ቪቫ ኦሮሚያ! ቪቫ ኢትዮጵያ!

- – - -
የጸሃፊው አድራሻ፦ yared_to_the_point@yahoo.com


Sport: የብሔራዊ ቡድናችን አጥቂ ጌታነህ ከበደ ዛሬ ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጓዘ

$
0
0

ከጥሩነህ ካሳ (የወርልድ ስፖርት ጋዜጣ አዘጋጅ)
2013 Orange African Cup of Nations: Zambia v Ethiopia
የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግን በኮከብ ግብ አግቢነት እየመራ የሚገኘው ጌታነህ ከበደን ከደቡብ አፍሪካ ክለቦች የቀረበለትን የዝውውር ጥያቄ ተቀብሎ ዛሬ ወደ ደ.አፍሪካ አቅንቷል፡፡ ጌታነህን ለመውሰድ የደቡብ አፍሪካው ሰልቲክ ክለብ ከፍተኛ ፍላጎት አሳይቷል፡፡ በርካታ ደጋፊዎች ያሉት ሰልቲክ ከሌሎች ክለቦች የተሻለ ክፍያ ማቅረቡም ታውቋል፡፡
ጌታነህም በዛሬው ዕለት የጤና ምርመራ ለማድረግ ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጉዟል፡፡ የጤና ምርመራውን ማለፍ ከቻለም አዲሱን የኮንትራት ውል ይፈራረማል፡፡ ጌታነህ ከደደቢት ክለብ ጋር ያለው ኮንትራት ውል የፊታችን ሰኔ 30 የሚጠናቀቅ በመሆኑ ዝውውሩን የተሳካ እንደሚሆንም ይጠበቃል፡፡

ከ110 በላይ ኢትዮጵያዊያን ባህር ላይ ቀሩ

$
0
0
ስለ ስደተኛው የቁራሌው ጩኸት እስከ ጠ/ሚኒስትር ቢሮ….
         በግሩም ተ/ሀይማኖት
yemen ‹‹…ብዙ ችግሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ ተቃዋሚ ሀይሎች ከጅቡቲ ወስደው መጠቀሚያ ሊያደርጓቸው ነበር፡፡ ብዙ እናውቀለን…›› ይህን በስደት ዙሪያ የአዞ እንባ ያነባው ኢቲቪ ለውይይት ከጋበዛቸው ውስጥ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ያዳለጣቸው ነው፡፡ ያዳለጣቸው ያልኩት መንግስት ያን ሁሉ ማስመሰያ ያደረገበት ምክንያት ምን እንደሆነ አባሳደሩ በግልጽ ሳያውቁ ስላስቀመጡት ነው፡፡ የስደተኛው ህይወት አሳዝኗቸው አይደለም፡፡ ተቃዋሚዎች ይዘው ሊጠቀሙባቸው ስለሚፈልጉ ወይም ስለሞከሩ ነገ ስልጣናቸውን ላለማጣት ነው፡፡ ያ-ካልሆነማ ስንት አመት በሙሉ በስደት ወገን ረገፈ ሲባል…ሲጮህ ዝም በዝምታ ብለው በስደተኛው የጣር ድምጽ ባላላገጡ ነበር፡፡ ግን የፈሩት ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች የትጥቅ ትግል ሊያደርጉ መሰናዶ ላይ ስለሆኑ ከሆነ አንድ ሰሞን አራግበው ዝም ማለት ጦሱ እንደሚብስ ለምን ልብ አላሉትም? የወጣውስ በአግባቡ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ካልተደረገ ወዴት እንደሚያቀና እንዴት አላገናዘቡም? ይገርማል፡፡ ሳዑዲ አረቢያ እየተሰቃየ ያለው ህዝብ ወዴት እያመራ ይመስላቸዋል? ለምንስ ያን አያስቡም? እንደ ዜግነቱ የሀገሩ ኤምባሲ ሊከራከርለት ሲገባ፣ ወደ ሀገሩ ሊመልሰው ሲገባ ኮሚኒቲ የሚባለው ውስጥ ተፋፍጎ ሶስት እና አራት አመት እንዲቀመጥ የአእምሮ መታወክ እንዲገጥመው ሲደረግ፣ በሽተኛውም ጤነኛውም በአንድ ቦታ እንዲቆይ ሲደረግ…ትኬት የሚቆርጥልህ ቤተሰብ ከሌለህ…ያመጣችሁ ሰው ትኬት ይቁረጥላችሁ..ተብሎ ከእሱ ዜግነት ይልቅ ለብር ክብር ሲሰጥ ሲያይ..ሀገሬ ባላት ኤምባሲ ሲበደል ለምንስ አይከፋው?ለምንስ አማራጭ አይወስድ? አንድ ሰሞን ሆይ ሆይ ብሎ ፖለቲካ ለማሳመሪያ ፕሮግራም ማድመቂያ ማራገብስ ውጤት ያመጣል? አያመጣም፡፡ መንግስት ህዝብን እያታለለ እስከመቼ የሚጓዝ ይመስለው ይሆን? ህዝቡ እኮ ያውቃል፡፡ ሳዑዲያ ፣ የመን.. እየተጨቆነ ያለው ወገኑ አይደለ እንዴ?ቤተሰቡ አይደለ እንዴ? ታዲያ የአንድ ሰሞን የሚሊኒየም አዳራሽ እና የኢቲቪ ለቅሶ የአዞ እንባ አልሆነም? ሆነ፡፡
   አስተዳዳሪዬ ባይላቸውም አስተዳዳሪህ ነን ብለው ላዩ የተጎበሩበት ሰዎች እስከ ጠ/ሚኒስትሩ ድረስ በውሸት ሲደልሉት፣ አፋቸው ሌላ ስራቸው ሌላ ሲሆንበት ቢጠላቸው ምን ሊደንቅ? ምንም፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለትጥቅ ትግል ስደተኞችን ሊጠቀሙባቸው ብቻ ሳይሆን ስደተኛው ሀገሩ መመለስ ካልቻለ እሱ ራሱ ተቃዋሚዎችን ፍለጋ በዳዴ መሄዱ አይቀርም፡፡ በተቃዋሚዎች ተጠቅሞ መታገሉም አይቀርም፡፡ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ካሉት ላይ ልበደርና ‹‹…ከጅቡቲ ወስደው ተቃዋሚዎች ለትግል ሊጠቀሙባቸው…›› ቀርቶ ስለ ስደተኞቹ መኖርስ ተቃዋሚዎች ያውቃሉ ወይ? እንደሚያውቁ አቃለሁ ግን እነሱ ‹‹..አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም..›› እንዲሉ ሆነዋል፡፡ ስደተኛው ኢትዮጵያዊ የሆነ እስከማይመስል ድረስ ተቃዋሚዎችም ረስተውታል፡፡ የተሻለ ሀገር ቢሆን የሚሰደደው እና ዶላር መቁጠር ቢጀምር ግን እኛ ያላንተ ይባል ነበር፡፡ ዛሬ ምን ሊያደርግ? መከራ እንጂ ዶላር ስለማይቆጥር አላስታወሱትም፡፡ መንግስት ግን መከራውን መስማቱን አይፈልግም እንጂ ከዚህ ችግር ተርፈው ከተማ ከገቡ ከኤምባሲው ምንም አይነት ግልጋሎት ቢፈልግ ጌሙ ፍራንካ ነው፡፡ ዜጋ ነህ ቅብርጥሴ…ምንትሴ አይሰራም፡፡ ገንዘብ ከያዘ የአማራ ልማት..የትግሬ ልማት..የእንትን ልማት…በቆዳ እስኪቀሩ መጋጡን እንደ ጅብ ይችሉበታል፡፡ እሰይ የወያኔ ኤምባሲ…ብራቮ ይህን ምስኪን ስደተኛ ተገፍቶም ተደፍቶም ያመጣውን በሰበብ አስባቡ ንጠቁ፡፡
     ደሀን የሚያስብ፣ ግፍ የሚፈጸምበት ስደተኛን የሚያይ የሚያስተውል መንግስትም ሆነ ተቃዋሚ አልገጠመንም፡፡ ያው ሁሌም ዞረሽ..ዞረሽ እንደሚሉት አይነት ነው የሚገጥመን፡፡ ትላንት ከሶማሊያ ጋር አብረው ሀገራቸውን የወጉ ተቃዋሚዎች አይነት አሁንም አሉን ከግብጽ ጋር ለመሰለፍ ያቆበቆቡ፡፡ ሀገራቸውን ከጠላት ጋር ወግተው ስልጣን ማግኘት እንጂ የህዝቡ ቁስል ያላቆሰላቸው ተቃዋሚዎች አሁንም አፍርተናል፡፡ ኢትዮጵያን እንወዳለን፣ ሀገሬ ክብሬ.. የ3000 ዘመን ታሪክ እያሉ ቀረርቶ የሚያሰሙ መንግስት እና ተቃወዋሚ አሁንም አሉን፡፡ ባይኖሩ በቀሩብን፡፡ ኢትዮጵያ ሀገሬ ጋራሽ ሸንተረሩ ሜዳማ…የሚል ቀረርቶ እያንቃረሩ መሬትና አፈሩን የሚወዱ ህዝቡን ያላማከሉ መንግስትና ተቃዋሚ አሉን፡፡ አሉ ከተባለ….
      በሰቀቀን ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ተሳቆ መውጫ ቀዳዳ ጠፍቶት፣ ሀገሩን መርገጫ መላ አጥቶ ያለውን ዜጋ ማን አስታወሰው? ማንም፡፡ የመን ውስጥ ሀረጥ የሚባለው የአለም አወቀፉ ስደተኞች ድርጅት ካምፕ ውስጥ ያለውን ስደተኛ ቁጥር ማን ይቀንሰው? የኢትዮጵያ መንግስት ከስደተኛ ቢሮው ጋር በመተባበር ዜጎቼን እየሰበአሰብኩ ነው ሲል ይቃዣል፡፡ ከዚህ ቅዠት ግን መቼ እንደሚነቃ እና እንደሚሰራ ነው ግራ የገባን፡፡ ስደተኛው አሁንም ስቃይ ውስጥ ነው ያለው፡፡ ስደተኛው አሁንም ባህር እየተሻገረ ነው ያለው፤ ስደተኛው አሁንም ባህር ላይ እየሰመጠ ነው የለው፡፡ ከሳምንት በፊት ከጅቡቲ ወደ የመን ድንበር እየገሰገሰ ያለ ጀልባ በመሳሪያ ተመቶ ሰጥሟል፡፡ የጫናቸው ዜጎቻችን በሙሉ ባህር በልቷቸዋል፡፡ ወደ 120 ሰው እንደሞተ ወዲያው ሰማሁ እና ለማጣራት አለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት ውስጥ እና ሜዲካል ሳን ፍሮንቴን (ድንበር የለሽ የህክምና ቡድን) ሰራተኞች ጋር ስልክ መታሁ፡፡ እነሱም ወሬውን አማቱት፡፡
    በመሳሪያ ነው የተመታው ስለተባለ ማን ነው የመታው የሚለውን ጨምሮ እንዲመልሱልኝ በመጠየቄ የውሾን ነገር ያነሳ ውሾ እንድንል ነገሩን አድበስብሰው እንዲያውም መረጃ ካገኘህ ስጠን አሉ፡፡ በሰዓቱ አስከሬን በመልቀም ስራ ላይ ተሰማርቶ የነበረ ሰው ነው ደውሎ መረጃውን የመረጀኝ፡፡ ከሌሎች አካላት ለማጣራት እንደሞከርኩት ደግሞ በመሳሪያ ተመቶ ሳይሆን በአሁኑ ወቅት ሀይለኛ ንፋስ(ማዕበል) ያለበት ወቅት በመሆኑ ያሰጠማቸው ማዕበል ነው በመሳሪያ አልተመታም ብለውኛል፡፡ ጀልባው ተመታም አልተመታም ለእኛ ወገኖቻችንን አጥተናል፡፡ ባንዴ 120 አካባቢ አርግፈናል፡፡ ይሄ መንግስት ፍካሬውን ሳይጨርስ የሆነ ሁነት ነው፡፡ ያሳፍራል፡፡ መንግስት የስልጣን ዘመኑን ማራዘሚያ የወቅቱን ፖለቲካ ማስከኛ ለፈፈው የሳምንት ሆይ ሆታ ሳይፈዝ ይሄ መሆኑ ያወራል እንጂ መቼ ይሰራል፡፡ ማውራት እና መስራት ለየቅል ናቸው ያሰኛል፡፡

በ “ቢግ ብራዘር አፍሪካ” የሚወዳደረው በአምላክ ለአገሩ ያለውን ፍቅር እየገለፀ ነው ተባለ

$
0
0

beamlak

ከግሩም ሠይፉ

ዘንድሮ የ “ቢግ ብራዘር አፍሪካ” አብሮ የመኖር ውድድር፣ በቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት ወሲብ በመፈፀም አነጋጋሪ ሆና የሰነበተችው ኢትዮጵያዊቷ ቤቲ ከውድድሩ ተሰናበተች፡፡ ውድድሩ ከተጀመረ አራተኛ ሳምንቱን የያዘ ሲሆን እስካሁን ቤቲን ጨምሮ ስድስት ተባርረው 20 ተፎካካሪዎች ቀርተዋል፡፡ ከእነሱም መካከል ሌላው ኢትዮጵያዊ በአምላክ ተስፋዬ (ቢምፕ) ይገኝበታል፡፡ ቢምፕ ለውድድሩ የሄደው አገሩን ስለሚወድና በተገኘው አጋጣሚ ስለ ኢትዮጵያዊነቱ ለመግለፅ ነው ያሉት እናቱ ወይዘሮ ደብሪቱ ሰለሞን፤ ባለፈው አንድ ወር በነበረው ቆይታ ይህንኑ ፍላጎቱን ሲያንፀባርቅ መቆየቱን ተከታትያለሁ ብለዋል፡፡ ‹‹ልጄ የአገር ፍቅር ስላለው በቢግ ብራዘር አፍሪካ ውድድር ፍቅሩን ለመግለፅ እድል አግኝቷል፡፡ ባንዲራው አብሮት ነው፡፡ ሁልጊዜም በሚለብሰው ካኒተራ ወይ ኮፍያ አሊያም በእጁ ላይ የአገሩ ባንዲራን ትቶ አያውቅም፡፡

የሚኖርበት መኝታ ቤቱ እንኳን በባንዲራ ያጌጠ ነው›› በማለት እናቱ ወይዘሮ ደብሪቱ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ ልጃቸው በአኗኗሩ እያሳየ ያለው ባህርይ ከልጅነቱ ጀምሮ ያደገበት ስብእናው እንደሆነ የገለፁት እናቱ፤ ባለፉት አራት የውድድር ሳምንታት እንዲባረር አንድ ድምፅ ብቻ እንደተሰጠበት ገልፀው፤ የውድድሩን ውጣውረድ በመቋቋም ሳይሰላችና ለሌሎች ተወዳዳሪዎች እንክብካቤ ሳይነፍግ እስከመጨረሻው ምእራፍ ሊዘልቅና ሊያሸንፍ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ በ “ቢግ ብራዘር አፍሪካ” ውድድር የኢትዮጵያውያን መሳተፍ ጠቀሜታ አለው የሚሉት ወይዘሮ ደብሪቱ፤ ውድድሩ የአገርን ባህል ለማስተዋወቅ እና ገፅታ ለመገንባት ሁነኛ መድረክ መሆኑን አስረድተው፤ ልጃቸው አብረውት ከሚኖሩት ተወዳዳሪዎች ስለ ኢትዮጵያ ብዙ ጥያቄዎች እንደሚቀርቡለት እሱም ስለ ባህሏ ፤ስለ ታሪኳ፤ የሰው ዘር መገኛ ስለመሆኗ፣ ስለ ቡና፤ ስለእንጀራውና ስለሽሮው ሳይሰለች ሲያስረዳ ተመልክተነዋል ብለዋል፡፡ ከውድድሩ በወጣች ማግስት አስተያየት የሰጠችው ቤቲ ስላሳለፈችው ጊዜ ስትናገር ቤቱን ለቅቆ መውጣት ከባድ ነው፡፡

ቦልት እና እኔ ጥሩ ወዳጆች ነበርን፡፡ ከውድድሩም በኋላ በወዳጅነት እንደምንቀጥል እርግጠኛ ነኝ” ብላለች፡፡ በውድድሩ ላይ እስከ መጨረሻው እዘልቃለሁ ብዬ አስብ ነበር ያለችው ቤቲ በውድድሩ፤ ምርጥ ተሳትፎ እንደነበራት፤ በዚህም መኩራቷን እንደተናገረች “ስዌታን” የተባለው የደቡብ አፍሪካ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ ቤቲ “ዘ ቼዝ” የሚል ልዩ ስም በተሰጠው የዘንድሮ “ቢግ ብራዘር አፍሪካ” አብሮ የመኖር ውድድር ገና በመጀመርያው ሳምንት ቦልት ከተባለው ሴራሊዮናዊ ተወዳዳሪ ጋር በፈፀመችው ወሲብ ትኩረት ስባ ስታወዛግብ ቆይታለች፡፡ በ “ቢግ ብራዘር አፍሪካ” የስምንት አመት ታሪክ በቀጥታ ስርጭት የታየ ወሲብ ሲፈፀም የቤቲ እና የቦልት የመጀመርያው ነበር፡፡ ቤቲ ለአገሯ ባህልና ወግ ክብር አልሰጠችም በሚል በማህራዊ ድረገፆች እና በብሎግ መድረኮች ላይ ስትብጠለጠል መሰንበቷም ይታወቃል፡፡ ቤቲ በ “ቢግ ብራዘር አፍሪካ” ኢትዮጵያን አትወክልም በሚል ለተቃውሞ በተከፈተ የፌስ ቡክ ድረገፅ ላይም በአገር ውስጥ እና በዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ትችት ተሰንዝሮባታል፡፡

የቤቲ ከውድድሩ ድንገት መባረር ፍቅረኛዋ ሆኖ ለሰነበተው ሴራሊዮናዊ ቦልት መርዶ እንደሆነበት ዘገባዎች ጠቁመዋል፡፡ ስንብቷን ባረጋገጠችበት ምሽት ሁለቱም በሃዘኔታ ተውጠው ሲተቃቀፉ እና ሲሳሳሙ መታየታቸውንም እነዚሁ ዘገባዎች አውስተዋል፡፡ ቦልት ምስጢረኛው፤ የልብ ወዳጁ እና ፍቅረኛውን ቤቲ በማጣቱ ብቸኝነት እንደሚያስቸግረውና እሱም ቢሆን በውድድሩ የማሸነፍ እድሉ የጠበበ እንደሆነ “ዘ ስታንዳርድ ዲጂታል ኒውስ” ጽፏል፡፡ ለሴራሊዮናዊው ቦልት ከዚህ በኋላ የሚኖረው የ “ቢግ ብራዘር አፍሪካ” ቆይታ ማራኪ እንደማይሆን እየተነገረ ሲሆን ፋቲማ ከተባለች ማሊያዊት ጋር የጀመረው ግንኙነት መፅናኛው ሊሆን እንደሚችልም ከወዲሁ ተተንብይዋል፡

 

(ምንጭ፡ አዲስ አድማስ ጋዜጣ የዛሬ ቅዳሜ ጁን 29 ዘገባ)

ጠቃሚ የትግል ግብአቶች

$
0
0
አበራ ሽፈራዉ /ከጀርመን/

አበራ ሽፈራዉ /ከጀርመን/

ክፍል አንድ
1 . መግቢያ
ህወሃት ኢህአዴግ ባለፉት ኢትዮጵያን በመራባቸዉ አመታት አገሪቷን እና ህዝቦቿን በግፍ ሲመራ ለመቆየቱ ምስክሮቹም ተጠቂዎቹም እኛዉ ነን። ለዚህ ጥቃታችን መፍትሔ ለመፈለግ የተደረጉ ትግሎችን ከግብ ለማድረስ የተደረገዉ እንቅስቃሴ ውጤታማ አልነበረም።ነገር ግን ምንም አስተዋጽኦ አላደረገም ብዮ አልደመድምም ። ምክንያቱም የህወሃት ኢህአዴግ ባህሪን ለማጋለጥ ያደረገዉ አስተዋጽኦ ቀላል አይደለምና ።
ለትግሉ ከግብ አለመድረስ ምክንያቶች ደግሞ የትግሎቹ መበታተን ፣ግቦቹ ግልጽነት የጎደላቸዉ መሆን፣በጋራ ሊያታግሉ የሚችሉና ግልጽ አላማ ያላቸዉ አለመሆናቸዉ ፣ አካባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን ከግንዛቤ ያላስገቡ መሆናቸዉ፣የህወሃት ኢህአዴግን የጭካኔ አቅም የሚመጥን ትግል አለመኖሩ፣በህወሃት የተሰጠንን የመለያየት የቤትስራ ሰርተን ባለመጨረሳችን፣ህወሃትን እንደ አገር ነጻ አውጭ ሃይል መቀበላችን ፣አንደኛዉ ሲጠቃ ነግ በኔ አለማለታችን፣የዉጭ ሃይሎች እንዲረዱን በአብዛኛዉ ጊዜ መጠበቅና ሌሎችም ።
በተለይም ህወሃት እንድንከፋፈል የሚያቀርብልንን ግብዣ በቸልተኝነት፣በአርቆ አስተዋይነት ማነስ ፣በራስ ወዳድነት፣ከሃገር ይልቅ ለግልና ለቡድን እንዲሁም ለፓርቲ እውቅና መሯሯጥ ፣ሰፊ ልዩነቶችን የሚፈጥሩ የፖለቲካና የማህበራዊ አስተሳሰቦችን ይዞ መቅረብና ሌሎችም ይገኙበታል። በእነዚህ ምክንያቶች ለአመታት ተከፋፍለን በመኖራችን ምክንያት ዛሬ ኢትዮጵያዉያን ለለየለት ጭቆና ተዳርገናል።
በተጨማሪም የውጭ ሃይሎች በህወሃት ኢህአዴግ ላይ ያላቸዉ ግንዛቤ የታሳሳተ መሆኑና አዉቀዉም እነሱ የሚያቀርቡትን ጊዜያዊና ዘለቀታዊ ጥቅሞቻቸዉን በሙሉ ፍላጎትና ተነሳሽነት የማስፈጸሙን ስራ ህወሃት በተገቢዉ መልኩ ማከናወኑ ሌላዉ ጉዳይ ነዉ። በተቃዋሚዉ በኩል የተቀነባበረ የዲፕሎማሲ ስራ አለመሰራቱና በቂና የተደራጀ ሃይል አለመገኘቱም ሌላዉ ችግር እንደሚሆን ግልጽ ነዉ።
የኢትዮጵያና የህዝቦቿ ችግር መፍትሔ ያለዉ በራሳችን በኢትዮጵያዉያን እጅ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለኝም ። ስለሆነም ግዜዉ አሁንም አረፈደም።አሁንም ግዜ ሳይረዝም ፤በፈጠነ ሁኔታ ፤ ግልጽ የሆኑ አቋሞችን ወስዶ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መግባት ከሁሉም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያን በሙሉ የሚጠበቅ ነዉ ።ለዚህም ይረዳ ዘንድ በየትኛዉም የትግል መስመር ያሉ ኢትዮጵያዉያን ልዩነቶችን ማጥበብ መቻልና በዉይይት ወደ መፍትሄ መምጣት ይጠበቅብናል፤ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መግባትም አብይ ጉዳይ ነዉ ብየ አምናለሁ።
2. ዋና ዋና የትግል ግብአቶች

ለመግቢያ ያህል ከላይ የተጠቀሱትን ካልኩኝ ይበቃል። አሁን ወደ ዋናዉ የርዕሴ ጉዳይ ልግባና ጥቂት የመነጋገሪያና የመፍትሄ ሃሳቦችን አቀርባለሁ።እንደኔ ከሆነ ወይም እንደኔ አስተሳሰብ ሁለት ትልልቅ ጉዳዮች የትግሉን አቅጣጫና ዉጤታማነት የያዙ ጉዳዮች ናቸዉ ብዮ አምናለሁ ።እነሱም የተቀዋሚዉ ሃይል መሰባሰብና ሁሉንም የህወሃት ኢህአዲግን መዋቅሮች በጠላትነት መፈረጅ ስህተት መሆኑ።
ሀ/ የተቀዋሚዉ ሃይል መሰባሰብ መቻል
berehanu merara hailu shawel beyene petrosየተቀዋሚዉ ሃይል መበታተን ከምንም በላይ የጎዳዉ እራሱን ተቃዋሚዉን ሲሆን በተቃራነዉ ህወሃትን በከፍተኛ ሁኔታ ጠቅሞታል ። በሚለያዩን ጉዳዮች ላይ ዉስጥ ውስጡ ከመተማማት ይልቅ፤ቡድናዊና ጎሳዊ ከሆኑ ጉዳዮች በዘለለ አገራዊ ይዘት ያላቸዉን ጉዳዮች በማንሳት ለትዉልድ ጭምር በማሰብ መነጋገር፣ መፍትሔ ማስቀመጥና መተግበር ይጠበቅብናል።ይህም የመለያየቱ የቤት ስራ አልቆና ጊዜዉ ያለፈበት መንገድ መሆኑንም ለጋራ ጠላታችን በማሳየት ወደ ስራ መግባት ፤የወደፊቱንም ችግሮች እየፈታናቸዉ እንድንሄድ ያስችሉናል።
ለ/ የህወሃት ኢህአዴግን መዋቅሮች በሙሉ በጠላትነት መፈረጅ ስህተት መሆኑ
አሁን ኢትዮጵያ ካለችበት ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ትግሉ ከብዙ ሃይሎች ጋር የሚደረግ ትግል ነዉ ብዬ አላምንም። ምክንያቱም አሁን ኢትዮጵያ የምትተዳደረዉ በጥቂት የህወሃት ሃይሎች እና በየክልሉ ካስቀመጣቸዉ ተወካዮቻቸዉ ጋር እና የጥቅም ተጋሪዎቻቸዉ ጋር ነዉ። ስለሆነም ትግሉን ዉጤታማ ለማድረግ ያስችል ዘንድ ነጻ ሊወጡ የሚገባቸዉን ሕዝቦች ፣ፓርቲዎች፣ የስልጣን ተዋርዶችን፣አደረጃጀቶችንና የገዥዉ የህወሃት የጭቆና ቀንበር የያዛቸዉን ተቋማት በሙሉ ለይቶ ከህወሃት ጭቆና ነጻ ማዉጣት ይጠበቅብናል።
በዚህም መሰረት ለዛሬ በዚህ በሁለተኛ ደረጃ የያዝኩትን ሃሳብ/ለ/ ወይም ጉዳይ ትኩረት እሰጠዋለሁ ። የጽሁፉም ዓላማ ህወሃትን እንዴት መነጠል ይቻላል በሚለዉ ላይ ያተኩራል።
2. 1. ነጻ ሊወጡ የሚገባቸዉ የህወሃት መዋቅሮች እና ሃይሎች
ሀ/ ነጻ የሚወጡ ህዝቦችን መለየትና የትግሉ አካል ማድረግ
ህወሃት በታሪክ አጋጣሚ እዚህ ለመድረሱ መነሻ ያደረገዉ ምክንያት የትግራይ ህዝብ ተጨቁኗል መባሉና ለትግላቸዉም ጭቆናዉን መነሻ አድርገዉት መታገላቸዉ ነበር።ነገር ግን በእዉነቱ ከሆነ የትግራይ ህዝብ በደርግ ዘመን ተፈጸመበት ከሚባለዉ ጭቆና በበለጠ ለአለፉት ሰላሳ ዘጠኝ አመታት ህዝቡ በህወሃት መገደሉን፣መታሰሩን፣መሰደዱን፣ በስቃይ ላይ መኖሩን እራሱ የትግራይ ህዝብ ምስክር ነዉ።ስለዚህ ይኸንን የሚያዉቅ ሁሉ ይህንን ህዝብ በየትኛዉም መንገድ ከህወሃት ጭቆና ማላቀቅ ችላ የሚባል ጉዳይ አይደለም ። የትግራይ ህዝብ የህወሃትን የጭካኔ በትር ከሌላዉ ኢትዮጵያዊ በላይ ለ39 ዓመታት ጠንቅቆ ያዉቀዋል።ስለዚህ ይኸንን ህዝብ በተለየ መልኩ ነጻ ማዉጣት ህወሃት መሸሸጊያ እንዳያገኝ ስለሚያደርገዉና ለህዝቡም እረፍት ስለሆነ ትኩረት ሊሰጠዉ ይገባል እላለሁ።ይህ ማለት የሌሎች ህዝቦች ጭቆና መጠን ለማሳነስ ሳይሆን ህወሃት ከለላ አድርጎና በስሙ የሚጠቀምበት ህዝብ ስለሆነም ጭምር ነዉ ። የሌሎች የአገራችን ህዝቦች ነጻ መዉጣት በህወሃት ዉክልና ተሰጥቶአቸዉ ህዝባቸዉን የሚጨቁኑ ጥቂት ሃይሎች ወይም የኢህአዴግ አካል ፓርቲዎችና ሌሎች ደጋፊ ተብለዉ ህወሃት የፈጠራቸቸዉ ፓርቲዎችን ከህወሃት ጭቆና ነጻ ለማዉጣት በሚደረገዉ ትግል ህዝቡን ነጻ ማዉጣት ያስችላል ብዮ አምናለሁ ።
ለ/ የኢህአዴግ አካል ፓርቲዎችንና ደጋፊ ፓርቲዎችን ነጻ ለማዉጣት መጣርና የትግሉ አካል ማድረግ
ሌሎች ከህወሃት ዉጭ ያሉ የኢህአዴግ አካል ፓርቲዎችንና ደጋፊ ፓርቲዎችን ከህወሃት ጭቆናና የበላይነት ነጻ ለማዉጣት ትልቅ እንቅስቃሴን የሚጠይቅ ቢሆንም የህወሃትን የበላይነት ለመሸርሸር ትልቅ ግብአት ሆኖ ስለሚያገለግል እዚህ ላይ ትልቅ ትኩረት ሊሰጠዉ ይገባል እላለሁ ። በእነዚህ ድርጅቶች ዉስጥ ያሉ አባላቶች ህወሃት በህዝቦቻቸዉ ላይ የሚፈጽመዉን ልክ ያጣ ግፍ እንዲያንገሸግሻቸዉ በማድረግ፤ ከዉስጥ ትግላቸዉን እንዲያቀጣጥሉ በማነሳሳት፤ ወደ ነጻነት የትግሉ ጎራ እንዲቀላቀሉ እድል በመስጠትና ድጋፍ በማድረግ፤ የትግሉን መፋጠን እንዲያግዙ በማድረግ ህወሃትን እርቃኑን እንዲቀር ማድረግ ይቻላል። ስለዚህ በጅምላ እነዚህን በጠላትነት ከመፈረጅ ይልቅ የነጻ መዉጣቱን ትግል እንዲቀላቀሉ ማድረግ ይጠበቅብናል።በዚህም ምክንያት በስራቸዉ ያሉ ህዝቦችን ነጻ ለማዉጣት ትልቅ መሰረት ይጥላል።
ሐ/ የመከላከያና የፖሊስ ሰራዊትን ነጻ ለማዉጣት መጣርና የትግሉ አካል ማድረግ
የኢትዮጵያ የመከላከያና የፖሊስ ሰራዊት የህወሃት የገዥ መደብ የብዝበዛና የጭቆና መሳሪያ ሆኖ እያገለገለ ስለመሆኑ ብዙዎቹ እያወቁ መሆኑና የተወሰኑ የሰራዊቱ አባላት ከግንዛቤ እጥረት የተነሳ ይህንን የጭቆና መሳሪያነታቸዉን የማያዉቁም እንዳሉ አንዳንድ ግንዛቤዎች አሉ ። ይሁንና በህወሃት የዘር ጭቆና እየተማረሩ በስቃይና በንዴት የነጻነቱን ትግል ጎራ ለመቀላቀል የሚፈልጉ ቁጥራቸዉ ቀላል እንደማይሆን ምንም ጥርጥር የለም። ይህንን ሰራዊት ነጻ ለማዉጣት ጥረት ማድረግ፣ ከለላ እንዲያገኝ መፍትሄ መፈለጉና በጠላትነት አለመፈረጁ ትልቅ የትግሉ ዉጤታማነት ግብአት ነዉና በዚህ ዙሪያ ትልቅ ስራ ሊሰራ ይገባል።
ይህ ጽሁፍ ተከታታይ በመሆኑ በሚቀጥሉት ጽሁፎች ላይ ሌሎች አስፈላጊ የትግል ግበአቶችንና የትግበራ ግብአቶችን እጠቁማለሁ።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

ጄ/ል ክንፈ ተመለሱ፤ መከላከያ ውጥረት ነግሷል – (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

$
0
0

kinfe dagnew

የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ብ/ጄነራል ክንፈ ዳኘው ላለፉት ሶስት ወራት ገደማ ከስልጣናቸው ታግደው ከቆዩ በኋላ በዚህ ሳምንት ወደ ሃላፊነት መመለሳቸውን የቅርብ ምንጮች ገለፁ። በጄ/ል ሳሞራ የኑስ ትእዛዝ ታግደው ከቆዩት ከፍተኛ ጄነራሎች መካከል አንዱ ጄ/ል ክንፈ እንደሚገኙበት የጠቆሙት ምንጮቹ ስልካቸውን በመጥለፍ በእንቅስቃሴያቸው ዙሪያ ክትትል ይደረግባቸው እንደነበር አስታውቀዋል። ጄ/ል ክንፈ በሳሞራ ታግደው የቆዩት የነአዜብ/በረከትን ቡድን በመቃወም ከነስብሃት ቡድን ጋር በመሰለፋቸው እንደሆነ ምንጮቹ አመልክተዋል። የጠ/ሚ/ር መለስን ሕልፈት ተከትሎ በመከላከያ ከፍተኛ ጄነራሎች መካከል የተፈጠረው ያለመግባባት ስር እየሰደደ መሄዱንና የልዩነቱ መንስኤም በሕወሐት የተፈጠረው ቀውስ – ጄነራሎቹ ጎራ እንዲለዩ ጫና ማሳደሩን ያመለከቱት ምንጮች፣ አክለውም ልዩነቱ በአገር ጉዳይ ዙሪያ ሳይሆን አንዱ ሌላኛውን በማስወገድ የራስን ጥቅም አስጠብቆ በስልጣን ለመቆየት የሚደረግ የሙስና መጠላለፍ ነው ብለዋል።
ጄ/ል ክንፈ የብረታ ብረት ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት በሟቹ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ እንደሆነ ያስታወሱት ምንጮቹ ከስልጣን ሊያግዳቸውም ሆነ ሊያወርዳቸው የሚችለው በህግ ስልጣን የተሰጠው ጠ/ሚኒስትሩ መሆኑን ያስረዳሉ። በዚሁ መሰረት ስልጣኑ በአዋጅ የተቀመጠው ለጠ/ሚ/ር ሃ/ማሪይም ቢሆንም – በግልፅ የሚታየው ግን ከህግ ውጭ የጄ/ል ሳሞራ ፈላጭ ቆራጭ ውሳኔ ከመሆኑ በተጨማሪ የታገደውን ጄ/ል ወደ ቦታው የሚመልሰው በተቃራኒው የቆመውና በሕወሐት ውስጥ ያለው የነስብሃት ቡድን መሆኑን ምንጮቹ ያመለክታሉ። አቶ መለስ ይዘውት የቆዩትና “በሕገ-መንግስቱ ተሰጠ” ከተባለው ስልጣን በአብዛኛው ለጠ/ሚ/ር ሃ/ማሪያም ሊሰጥና ሊተላለፍ አልቻለም ሲሉ የጠቆሙት ምንጮቹ ቁልፍ የሆነው የጦር ሃይሎች ጠ/አዛዥነትን ጨምሮ በርካታዎቹ ሕገ-ወጥ በሆነ ሁኔታ በሕወሐት ሰዎች ቁጥጥር ስር መውደቃቸውን አመልክተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ- ጄ/ል ሳሞራ የሚመሩት ስብሰባ በመከላከያ ከፍተኛ ጄነራሎች ተሳታፊነት በዚህ ሳምንት ሲካሄድ መሰንበቱን ምንጮች ጠቆሙ። ውጥረትና ያለመረጋጋት በተስተዋለበት የሳሞራ ንግግር በዋና አጀንዳነት የቀረበው የግንቦት ሰባት ጉዳይ ሲሆን በዚህም ፥ « ግንቦት ሰባት በመንግስትና በሕገ-መንግስቱ ዙሪያ መጠነሰፊ አደጋ ጋርጦብናል፤ በግንቦት ሰባት የሚደገፉ በአገር ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች ላይ አፋጣኝ እርምጃ ልንወስድ ይገባል፤» ማለታቸውን የገለፁት ምንጮቹ፣ ሳሞራ «ለምሳሌ.» ሲሉ ሰማያዊ ፓርቲን እንዲሁም « አንዳንድ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች» በማለት መፈረጃቸውን አስታውቀዋል። በተጨማሪ የሙስሊሙ ማህበረሰብ እያነሳ ያለውን ፍትሃዊ የመብት ጥያቄ፣ ሳሞራ ከግንቦት ሰባት ጋር ለማያያዝ መሞከራቸውን ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።
በሌላም በኩል የኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ሃላፊ ብ/ጄነራል ተክለብርሃን ወ/አረጋይ በበኩላቸው፥ ከእንግሊዝ አገር ረቀቅ ያለ መሳሪያ በማስመጣት በስካይፕ ተቃዋሚዎች የሚያደርጉትን ግንኙነቶች በመጥለፍና ተዛማች የስለላ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ከገለፁ በኋላ « ግንቦት ሰባት ከግብፅ ጋር ግንኙነት እንዳለው ለህዝቡ ከነገርነው ከጎናችን ይቆማል፣ ግንቦት ሰባትን በማውገዝ የእንቅስቃሴው ተባባሪ አይሆንም፣ በአገር ውስጥ ያሉትም ተቃዋሚዎች ላይ የሚወሰደውን እርምጃ ህዝቡ አይቃወምም፤ እንዳውም ለመንግስት ድጋፍ ይሰጣል፤» በማለት በተሰብሳቢ መኮንኖች ጭምር ገረሜታን የፈጠረ ንግግር ማድረጋቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል። በዚህም ለሕዝብ ያላቸውን ግምትና የግንዛቤ ደረጃ ያመላከተ ነው ያሉት ምንጮቹ የጄ/ል ተክለብርሃን የእውቀት ደረጃ ምን ድረስ እንደሆነ ያሳየ ነው ብለዋል። የኤንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በአቶ ደብረፂዮን ጭምር በበላይነት እንደሚመራና አቶ ሃ/ማሪያም የሚያውቁት እንደሌለ ምንጮቹ አያይዘው ጠቁመዋል። በሕገ – መንግስቱ መከላከያ ከየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ ገለልተኛ እንደሆነ ቢደነግግም፣ ከወረቀት በዘለለ ተግባር ላይ ሲውል እንደማይታይና የነሳሞራና ተከታዮቻቸው ተደጋጋሚ አቋምና ተግባር በቂ ማስረጃና ማሳያ መሆኑን ምንጮቹ በሰጡት አስተያየት አስረድተዋል።
በመጨረሻም፥ የታገዱ ሌሎች ጄኔራሎችን ጉዳይ እንዲሁም ባለፈው ወር በሳሞራ ትእዛዝ የተባረሩ የሕወሐት ጄነራሎች ወደ ከፍተኛ ንግድ መሰማራት በተመለከተ ዝርዝር መረጃውን ይዘን እንመለሳለን።

የአልሻባብ ተዋጊዎች ሁለት መሪዎቻቸውን ገደሉ

$
0
0

(ቪኦኤ) የአል-ሻባብ ተዋጊዎች ሁለት መሪዎቻቸውን ዛሬ መግደላቸውን የአማፂው ቡድን ቃል አቀባይ ዛሬ አስታወቀ፡፡ አንደኛው የአምስት ሚሊየን ዶላር ጉርሻ የታወጀበት ነው፡፡
አብዱልአዚዝ አቡ ሙስ’አብ ባሠራጨው የድምፅ መልዕክት የሙጃሕዲኑ ታጣቂዎች በመካከላቸው መከፋፈልን ለመፍጠር ይጥሩ በነበሩ በአባሎቻቸው ላይ ዘመቻ ካካሄዱ በኋላ የተወሰኑትን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውንና አንዳንዶቹ ደግሞ እጅ ለመስጠት አሻፈረኝ ማለታቸውን አመልክቷል፡፡

“ሁለቱ እጃቸውን እንዲሰጡ ሲጠየቁ አሻፈረን ብለው አንገራገሩ፣ በተኩስ መካከል ተገደሉ፤ አምላክ ነፍሳቸውን ይማርና በገነት ያስቀምጥ፡፡ ሃሣቡ እነርሱን ለመግደል አልነበረም፡፡ በቁጥጥር ሥር አውለን እሥልምና ችሎት ፊት ልናቀርባቸው ነበር፡፡” ነው የሚለው ከዚህ ጋር የተያያዘው አብዱልአዚዝ በሶማሊኛ ያሠራጨው መልዕክት፡፡

ሰዎቹ የተገደሉት ከሞቃዲሾ 350 ኪ.ሜ በስተደቡብ በምትገኝ ብራቫ የምትባል ከተማ ውስጥ እንደሆነ ታውቋል፡፡
al shebab
የተገደሉት ሰዎች እነማን እንደሆኑ የአል-ሻባብ ቃል አቀባይ አልተናገረም፡፡ ይሁን እንጁ የቪኦኤ ሶማሊኛ አገልግሎት የተለያዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮችን አነጋግሮ ኢብራሂም ሃጂ ጃማ ወይም ኢብራሂም አል-አፍጋን ወይም በተቀጥያ መጠሪያው አቡ ባካር አል-ዛይሊዪ እየተባለ ይጠራ የነበረውና ሼኽ አብዲሃሚድ ሃሺ ኦልሃዬ ወይም በቅፅል ሞዐሊም ቡርሃን መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡

መሪዎቹ የተገደሉት የዛሬ አሥር ቀን ሰኔ 12 መሆኑንም የቪኦኤ ምንጮችን የጠቀሰው የሶማሊኛ አገልግሎት ዘገባ አመልክቷል፡፡

የአል-ሻባብ ምንጮች እንደሚሉት አል-አፍጋን የተገደለው ከመስጂስ እየወጣ ሳለ በተተኮሰበት ተርታ ጥይት ሲሆን ሙዐሊም ቡርሃን የተገደለው ከቤቱ ተይዞ ከተወሰደ በኋላ ነው፡፡

ሌሎችም ተኩሶች የተሰሙ እንደነበረ ቢታወቅም የደረሰ ጉዳት ወይም ጥፋት ይኑር አይኑር ለጊዜው አልታወቀም፡፡

ይህ አጋጣሚ ከተፈጠረ ከሁለት ቀናት በኋላ ለተገደሉት ሁለት ሰዎች የቅርብ ወዳጅ እንደነበረ የሚነገረው ዋነኛው የአል-ሻባብ መሪ ሼኽ ሐሰን ዳሂር አዌይስ ከአካባቢው በጀልባ ካመለጠ በኋላ ማዕከላዊ ሶማሊያ ውስጥ ተይዞ እጁ ለመንግሥት መሰጠቱ ይታወቃል፡፡

ከተገደሉት አንዱ ኢብራሂም አል-አፍጋን በአል-ሻባብ ውስጥ በርካታ የሥልጣን ቦታዎች የነበሩት ሲሆን የቡድኑ ምክትል መሪ፣ የገንዘብ መምሪያው ኃላፊና የኪስማዮ ገዥ ሆኖ ሠርቷል፡፡

ተይዘው ለፍርድ እንዲቀርቡ ያሉበትን መረጃ ለሚሰጥ በእያንዳንዳቸው ራስ የአምስት ሚሊየን ዶላር ጉርሻ እንደምትሰጥ ዩናይትድ ስቴትስ ማስታወቂያ ካወጣችባቸው ሰባት የአል-ሻባብ መሪዎች አል-አፍጋን አንዱ ነው፡፡

አል-አፍጋን ዩናይትድ ስቴትስ፣ ቨርጂንያ ውስጥ ይኖር የነበረ ሲሆን እአአ በ1980ዎቹ ውስጥ ከሙጃሕዲን ጎን ተሰልፎ ለመዋጋት ወደ አፍጋኒስታን መሄዱንና በ1991 ዓ.ም የሶማሊያ ማዕከላዊ መንግሥት ሲወድቅና ሥርዓተ-መንግሥቱ ሲፈራርስ እጅግ የከፋ ዓይነት ጂሃድ ወደ ሶማሊያ ማስገባቱና ሶማሊያ ውስጥ የመጀመሪያውን የጂሃድ ማሠልጠኛ ሠፈር ማቋቋሙን ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡

አል-አፍጋን ከአል-ቃይዳው መሥራችና መሪ ኦሣማ ቢን ላደን ጋርም ብዙ ግንኙነቶች እና ንግግሮች እንደነበሩት ቢን ላደን በ2011 ዓ.ም ከተገደለ በኋላ ሲናገር ይሰማ እንደነበር ታውቋል፡፡

ሌላው ተገዳይ ሙአሊም ቡርሃን አል-ሻባብ ውስጥ ዋነኛ የሚባል የሃይማኖት ሊቅ እና የቡድኑ የመማክርት ምክር ቤት አባል እንደነበረ ተገልጿል፡፡

የአል-ሻባብ ተዋጊዎች ሁለት መሪዎቻቸውን ዛሬ መግደላቸውን የአማፂው ቡድን ቃል አቀባይ ዛሬ አስታወቀ፡፡ አንደኛው የአምስት ሚሊየን ዶላር ጉርሻ የታወጀበት ነው፡፡

አብዱልአዚዝ አቡ ሙስ’አብ ባሠራጨው የድምፅ መልዕክት የሙጃሕዲኑ ታጣቂዎች በመካከላቸው መከፋፈልን ለመፍጠር ይጥሩ በነበሩ በአባሎቻቸው ላይ ዘመቻ ካካሄዱ በኋላ የተወሰኑትን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውንና አንዳንዶቹ ደግሞ እጅ ለመስጠት አሻፈረኝ ማለታቸውን አመልክቷል፡፡

ትንሽ ስለ ጀዋር መሓመድ –በአብርሃ ደስታ

$
0
0

jawar አንድ ጓደኛየ አንድ የተቀናበረ ቪድዮ በፌስቡክ ገፄን ለጠፈልኝ፤ እንዳነበው እየጋበዘኝ መሆኑ ነው። ቪድዮው ስለ ጀዋር ነው። ግን የሌሎች ሰዎች ስሞችም (የኔን ጨምሮ) ተጠቅሷል። ልጁ ቪድዮውን ሲጋብዘኝ አንዳንድ ዲያስፖራ ተቃዋሚዎች ስለኔ ያላቸው አመለካከት እንዳውቅና ኢህአዴግ መቃወሜን እንዳቆም ‘በአሪፍ’ ተፅዕኖ ማሳደሩ ነው፤ ይህን ድምዳሜ የመጣልኝ ልጁ (ቪድዮው የላከልኝ) ከዚህ በፊት ይልክልኝ በነበሩ ተመሳሳይ መልእክቶች በመነሳት ነው። ይህን የፖለቲካ ስትራተጂ እንደማይሰራ በተደጋጋሚ ለማረጋገጥ ሞክርያለሁ።

ግን …

ሰዎች በኔ ሓሳብ ሊደሰቱ ወይ ሊናደዱ ይችላሉ፤ መደሰትም መናደድም መብታቸው ነው። እኔ ደግሞ የፈለኩትን የመፃፍ መብት አለኝ። ስለዚህ የኔ አቋም ሌሎች ሰዎች በሚሰጡኝ ምላሽ የተንጠለጠለ አይደለም።

ወደ ጀዋርና ቪድዮው ልመለስ። ቪድዮው ጀዋርና ሌሎች ሰዎች ስለተናገሩት ሓሳብ ቀነጫጭቦ ያቀርባል። በመጀመርያ ቪድዮው ትኩረት አልሰጠሁትም ነበር። በኋላ ስለ ቪድዮው የተፃፉ ነገሮች ሳነብ ግን ትኩረት እንደሚያስፈገው ገባኝ።

ባጠቃላይ ሲታይ የተቀናበረውን ቪድዮ አልወደድኩትም። አንደኛ የተቀመጠው የጀዋር ሓሳብ የተቆራረጠ ነው። ለድምዳሜው የሰጣቸው ማስረጃዎች በትክክል በቪድዮው አልተካተቱም። አንድ ጥሩ የነበረ ሓሳብ ቆራርጠን በማቅረብ ጥላሸት መቀባት ይቻላል። ስለዚህ ጠቅላላው የቀረበ አመክንዮ በተፈለገው መጠን ስላልቀረበ በቪድዮን በቀረቡ የተቀነጫጨቡ ሓሳቦች መገምገም አንችልም።

ሁለተኛ በቪድዮው የቀረበው የተቀነባበረ ሓሳብ ጀዋርን ለመገምገም ያስችለናል ብለን ከተነሳን የተናገረው ነገር የልጁን ስም ለማጥፋት በቂ ምክንያት ይሆናል ወይ? የሰጠው ሓሳብ የራሱ (የግሉ) አስተያየት ነው። ‘ኦሮሞዎች በደል ይደርሳቸው ነበር’ ብሎ ማለት ‘ኢትዮዽያን መጥላቱ’ ያሳያል ወይ? የብሄር ጭቆና መኖሩ ሓሳብ መሰንዘር ‘ኢትዮዽያዊ ስሜት’ እንደሌለው ምክንያት ወይ ማረጋገጫ ሊሆን ይችላል ወይ?

ስለ ኢትዮዽያ ስናወራ ስለኢትዮዽያውያን እየተናገርን ነን። ኢትዮዽያውያን ህዝቦች ናቸው። ህዝቦቹም ኦሮሞዎች፣ አማራዎች፣ ትግራዮች፣ ጉራጌዎች፣ ሶማሊዎች፣ ደቡቦች፣ ጋምቤላዎች፣ ቤኑሻንጉሎች … ወዘተ ናቸው። ‘ጉራጌ ተበደለ’ ሲባል ኢትዮዽያዊ እየተበደለ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ጀዋር ‘ኦሮሞች ተበድለዋል’ በማለቱ የተፈጠረ ችግር ምንድነው??? እንኳንም በድሮ ዘመን አሁንም እኮ ‘ጭቆና አለ’ ብለን እየተከራከርን ነን።

ሦስተኛ ጀዋር የሰጠው አስተያየት ጥሩ አይደለም ብለን እንነሳ፤ ታድያ ማድረግ ያለብን ጉዳይ ስም ለማጥፋት መሯሯጥ ሳይሆን አስተያየቱ ስህተት መሆኑ በሓሳብ ማሳመን መቻል ነው። በሰጠው አስተያየት ላይ የሓሳብ ክርክር መክፈት ይቻላል። አስተያየቱ ‘ስህተት’ ስለመሆኑ ማረጋገጥ የምንችል ከሆነ ጀዋርን ለማስተካከል እንዴት ያቅተናል?

አራተኛ አንድ ሰው የተለየ አስተያየት ስለሰጠ ‘የኢትዮዽያ ጠላት’ አድርጎ መፈረጅ መፍትሔ ይሆናል ወይ? ሁሉም ሰው ስለ አንድ ጉዳይ ተመሳሳይ አቋም ይኖረው ዘንድ ግድ አይደለም። የምንታገለው አንድ ዓይነት አስተሳሰብ እንዲኖረን ለማድረግ ሳይሆን እንደየምርጫችን በነፃነት መኖር እንድንችል ነው።

በመጨረሻም

ጀዋር በያዘው አቋም ልዩነት ቢኖረኝም በሰጠው አስተያየት ግን አልተከፋሁም፤ ጥፋቱም አልገባኝም። የብሄር ጭቆና እንደነበር (አሁንም ችግሩ በተገቢ መንገድ እንዳልተፈታ) ከጀዋር ጋር እስማማለሁ። በአሁኑ ሰዓት (ችግሩ ለመፍታት) ምን መደረግ አለበት በሚለው (ብሄርን ከሀገር ማስቀደሙ) ግን ከጀዋር ጋር የሓሳብ ልዩነት አለኝ።

እንደኔ ከሆነ የዘመናት የፖለቲካ ችግሮቻችን መፍታት የምንችለው ታሪክን እያስታወስንና ብሄርን እያስቀደምን የሀገራችን አንድነት በሚያዳክም መልኩ በመወያየት ሳይሆን የነበረው ጭቆና እንዲወገድ አብረን በመታገልና በእኩልነትና በአንድነት የምንኖርባት ኢትዮዽያ እውን በማድረግ ይመስለኛል።

ጀዋር መሓመድ በጣም ከማደንቃቸው ብርቅዬ ወጣት ኢትዮዽያውያን የፖለቲካ ተንታኞች አንዱ ነው። ጀዋር አድናቆቴን ይድረሰህ።

በሓሳብ መለያየት ጥፋት አይደለም። ስለዚህ የሰው ስም ለማጥፋት ዘመቻ መክፈት ተገቢ አይደለም።

ኢትዮዽያችንን ይባርክልን፤ አሜን።


የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌስቲቫል በሰሜን አሜሪካ ነገ በሜሪላንድ በድምቀት ይጀመራል

$
0
0

berhanu_woldemariam_large
(ዘ-ሐበሻ) ዓመታዊው የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌስቲቫል በሰሜን አሜሪካ ነገ እሁድ ጁን 30 ቀን 2013 ዓ/ም በደመቀ ሁኔታ እንደሚከፈት ታወቀ። ከተመሠረተ 30ኛ ዓመቱን የሚደፍነው የኢትዮጵያ ሰፖርትና የባሕል ፌደሬሽን በሰሜን አሜሪካ(ESNFA) ከሰሜን አሜሪካና ከተለያዩ የዓለም ክፍል የሚመጡ ወገኖች ዝግጅቱን ይታደሙታል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
ኢትዮጵያውያኑን በአንድነት እያሰባሰበ ላለፉት 30 ዓመታት የቆየው ይኸው ፌዴሬሽን በዚህ ዓመትም የተሳካ ዝግጅት ያከናውናል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። ይኸን ተከትሎ የቀድሞው ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃኑ ወ/ማርያም ባስተላለፉት መልዕክት “ፈደሬሽናችን ውስጣዊ ችግር በአጋጠመው ወቅት ያገባናል በማለት የተባበሩን የመገናኛ ብዙሃንን ምስጋና እናቀርባለን” ብለዋል። የቀድሞው ፕ/ት ሙሉ መልዕክት የሚከተለው ሲሆን ዘ-ሐበሻ ይህን የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ለአንባቢዎቿ ከመክፈቻው እስከ መዝጊያው በተከታታይ የምትዘግብ መሆኗን ትገልጻለች።

የ ኢትዮጵያ ሰፖርትና የ ባሕል ፌደሬሽን በሰሜን አሜሪካ(ESNFA) ከሃይማኖት ከጎሳ ከፖለቲካ ልዩነት የነፃና ለትርፍ ያልተቋቋመ ህዝባዊና ኢትዮጵያዊ ሰውነት ያለው ድርጅት ነው፡፡ ይህ ድርጅት ላለፉት 30 ዓመታት ኢትዮጵያውያንን በማሰባሰብና በማገ ናኘት ሕፃ ናትንና ወጣቶችን የ ኢትዮጵያን ወግ፤ ልማድና ባሕላቸውን እንዲያውቁ የረዳ፡፡ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ከወጡ ረዥም ጊዜ ላስቆጠሩ ኢትዮጵያውያኖች ከዘመድና ከወዳጆቻቸው ጋር መገናኛ መድረክ መሆን የቻለ አንጋፋ ድርጅት ነው፡፡ የበአሉ ሣምነት ጁላይ 4 የአሜሬካ የነፃነት በአል ማክበሪያ ሳምንት በመሆኑ (July 4th weekend Amercan Independence Day)ይህቺን ሁለተኛ ሀገ ራች፡ የ ሆነ ቺውን የአመሪካንን፡ የነፃነት፡ በዓል ከተቀረው አሜሪካውያን ጋር እንድናከብር አ ድር ጎ ና ል፡ ፡

ፈደሬሽናችን ESFNA ካሉት ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች አንኳሮቹ፡-

በየስቴቱ ያሉ ኢትዮጵያኖችን በያሉበት አካባቢ ሆነው የስፖርት ቡድን በማቋቋምና እነ ዚህም ቡድኖች በኢትዮጵያውያን አሰልጣኞችና ቡድን መሪዎች ተደራጅተው ለውድድር እራሳቸውን ማዘጋጀት ሲሆን የቡድኑም አባለት፤ አላማ ወጣቶቹ ሙሉ የኢትዮጵያዊነት መንፈስን የተላበሰ የቡድን ስሜት ኖሯቸው ዝግጅቱን ኢትዮጵያዊ ስሜት እንዲኖረው በማድረግ የወከሉትን ቡድን ወይንም ስቴት ለውጤት ማብቃት ሲሆን ይህም ለአንድ ሳምንት ተወዳዳሪ ቡድኖች በደረጃ የሚለያዩበት ነው፡-

ሌላው የኢትዮጵያ ቀን፡ሲሆን፤ በዚህ ዝግጅት፤ በጁላይ 4 ቀን የስቴቱንና የከተማይቱን ባለስልጣኖች በመጋበዝ የኢትዮጵያን ታሪክ የብሔር ብ ሔረ ሰ ቦ ች ን ባ ሕ ል ና ወ ግ የ ሚያ ስ ተ ዋ ውቅ ል ዩ ድ ራ ማዊ ት ዕ ይ ን ቶ ች የ ሚቀ ር ብ በ ት እንዲሁም ሕፃናት የተለያዩ በሕላዊ ትርዕቶችንና መዝሙሮችን የሚያሳዩበት ባጠቃላይ የሀገራችንን መልካም ገጽታ የሚያሳዩና የሚያስተምሩ ዝግጅቶችን በማቅረብ የታደሚውን የሀገር ስሜት መቀስቀሻ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያውያንን፤ በየትም ሀገር ቢሆን የሚያኮራና የሚያስከብር ጥሩ ቀለም ያለው የወግና ልማድ እንዲሁም የታሪክ ባለቤት መሆናችንን የምናሳይበት የዝግጅታችን ዋና አካል ነው››

ESFNA በሜዳው ውስጥ ከሚከናወነው ፕሮግራም በበለጠ ለበአሉ ድምቀት የሚሆኑ ከሜዳውውጭ የሚከናወኑትትእይንቶችሲሆኑ እነዚህምግለሰቦች በቡድንምሆነ በተናጥልሆነውከፌዴሬሸኑበሚከራዩትድንኳንውስጥለህዝቡ የሚያቀርቡት የተለያዩ አገልግሎቶች ሲሆኑ ከነዚህም በጥቂቱ የተለያዩ ኢትዮጵያ ስም ያላቸው የባህል የምግብ ቤቶች የባህላዊ የስጦታ እቃዎች፤የኢትዮጵያ ሙዚቃ መደብሮች የተለያዩ ኢትዮጵያዊ ዲዛይነሮች የሰሯቸው የሀገር ባህል አለባሳት መሸጫ ሱቆች የመፅሃፍት መደብር ወዘተ… እነዚህን የተለያዩ ፕሮግራሞች ለመሳተፍ የሚመጣው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የኢትዮጵያዊ ጨዋነት በተላበሰ ሁኔታ ምንም አይነት እረብሻና ብጠብጥ ሳይኖር ሳምንቱን ሙሉ ለጥበቃ የተቀጠሩትን በሊሶች ባስገረምና ባስደነቅ ሁኔታ በሰላም የሚያሳልፉበት ትንሺቷን ኢትዮጵያ የምናይበት የ ESFNA አካል ነው፡፡

ESFNA ከላይ ከተጠቀሱት የንግድ ድርጅቶች ጎን ለጎን ለሃይማኖት ተ ቐ ማት ና ለ እ ር ዳ ድ ጅ ቶ ች ያ ለ ክ ፍ ያ ቦ ታ በ መስ ጠት አ ላ ማቸ ውን እንዲያስተቃውቁ ያደርጋል ፡፡

ESFNA በዝግጅቱ ከሚያካትታቸው ፕሮግራሞች ሌላኛው በየ አመቱ በሚያደርገውዝግጅት ላይ የክብር እንግዶችን መጋበዝ ሲሆኑ እነዚህም በተለያዩ ስራ ዘርፍ ላይ ተሰማርተው ለኢትዮጵያ ባደረጉት አስተዋጽኦ ትልቅ ቦታ የምንሰጣቸው ገለሰቦች ናቸው፡፡ ከእነዚህም በጥቂቱ ቀደም ባሉት አመታት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ እድገት ትልቅ አስትዋፅኦ ያደረጉ፤ በኦሎምፒክና በዓለም አቀፍ የ ሰፖርት ውድድሮች ላይ የ ኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ ከሌሎች በልጦ እንዲውለበለብ የደረጉ ስፖርተኞች እንዲሁም ፌደሬሽናችን እያደገና እየተጠናከረ ሲመጣ ሃሳቡን ሰፋ በማድረግ ሌሎች ባለውለታ ባለሞያዎችን ማለትም በተለያዩ ሥራዎች በአለም አቀፍ ዝግጅት ላይ ተሳትፈው የኢትዮጵያን ስም ያስጠሩ፤ የታሪክ ተመራማሪወችና ደራሲዎች ሳይኒስቶችና በማሕበራዊና በበጎ አድራጎት ሥራ ከፍ ያለ ተሰትፎ ያደረጉ ግለሰቦች፤ አርቲስቶችና የሙዚቃ ባለሞያዎች የመሳሰሉትን ሲሆን የዚህ ፕሮግራም ዋናኛ አላማ እነዚህን ኢትዮጵያውያን ከህዝቡ ጋር ማስተዋወቅና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸ የገንዘብና የቁሳቁስ ስጦታዎችን መለገስ ሲሆን በተጨማሪ ለወጣት ኢትየጵያውያን የሃገራቸው ታላላቅ ሰዎች መልካም ተግባር አስተምሮ ለማለፍም ነው፡፡

በዚሁ 30 ዓመታት ውስጥ ቁጥራቸው ከሚሊዮን የሚበለጡ ኢትዮጵያውያንንና የኢትዮጵያን ወዳጆቻች፤ ከማስተናገዱም በላይ በሺዎቹ የሚቆጠሩ የንግድ ደርጅቶችን አሳትፏል፡ ፡ ቁጥራቸው በዛ ያሉ የ ኪነ ጥብብ አርቲስቶችን ሥራ ፈጥሯል፤ዝግጅቱ በሚደረግባቸውከተማዎችለሚገኙየኢትዮጵያውያንየንገድ ድርጅቶችና በከተማው ውስጥ ላሉ ሆቴሎችና የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በየዓመቱ አሰገብቷል፡ ዝግጅቱ በሚደረግባቸው ቦታዎች የስቴቱንና የከተማውን የመንግስ በለስልጣናት በመጋበዝ በስቴቱ ውስጥ የሚኖሩት የኢትዮጵያውያን ብዛት በማሳየት ለስቴቱም ሆነለከተማውተመራጭተወዳዳሪዎችቀልብየሚስብ ኢትዮጵያውያንንብዛት በ ማሳ የ ት በ ምር ጫው ላ ይ ኢት ዮ ጵ ያ ውያ ን ለ ውጥ ማምጣት እ ን ደ ሚች ሉ አሳይቷል፡ ፡

ESFNA እንደ ኢትዮጵያዊ በጎ አድራጎት ድርጅት ኢትዮጵያውያንን በአመት አንዴ ከማሰባሰብ ውጪሃገራችን በተለያየ ጊዜ ባጋጠማት ችግሮች እርዳታ ያደረገ ሲሆን ይኸውም ህዝባችን በርሃብ በጎርፍ አደጋ ሲጎዳ ፤ በኤች. አ ይ . ቪ . ወ ላ ጆ ቻ ቸ ውን ላ ጡና ወ ላ ጅ አ ል ባ ለ ሆ ኑ ህ ጻ ና ት መር ጃ የሚውል ገንዘብ ወደ ሃገር ቤት በመላክ እንዲሁም ወጣቶችን በውጤታቸው በማወዳደር የከፍተኛ ት/ቤት ክፍያ የገንነዘብ ድጎማ መስጠትና የመሳሰሉት ይገኙበታል …

ESNFA እንግዲህ በዚህ የ30 አመታት ጉዞ ውስጥ ለሰራቸው በጎ ተግባራት ሁሉ ወጣት ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ የአሜሪካን ስቴቶች ለስፖርት ውድድር ዝግጅቱ ላይ መገኘትና የህዝቡ ድጋፍና ተሳትፎ በዋናነት ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዝ ሲሆን በመቀጠልም በየአመቱ በገንዘብም ሆነ በነ ጻ አገ ልግሎት በመስጠት ለፌዴሬሽናችን እዚህ መድረስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉልንን ግለሰብና ድርጅቶችን ማመስግ ተገቢ ነው፡፡

የክብር እንግዶቻችን ሁሉ ጥሪያችንን አክብው በበአላችን ላይ በመገ ኘታቸው፤
የ ኢትዮጵ አየ ር መንገ ድ ለአለፉት 25 ዓመታት ለክብር እንግዶቻችንና በሎተር እጣለታዳሚውየሚሰጡነፃ የማጓጓዣየአየር ትኬቶች በመስጠት
በተለያዪ ጊዜያቶች ፈደሬሽናችንን ስፖንሰር በማድረግ ከአንድ ሚሊዮን ዶላር ያላነሰ ገንዘብ በመለገስና በክብር እንግዳነት ለጋበዝናቸውን ታሪክ ሰሪዎች ገንዘብና ሥራ በመስጠት የተባበሩንን 2002 ዓ.ም የክብር እንግዳችን ሼህ መሐመድ አሊ አላሙዲን፤
ላለፉት 15 አመታት ስፖነሰር ያደረገንን የዌስተርን ዩኒየንን
የሰንሻይን ሪል ስቴት፤ የጊፍት ሪል ሰቴትና ሮዜታ ሪል ሰቴትን
ስታድዮሙ ውስጥ ቦታ በመከራየት ከፍተኛ የገቢምንጭ ከመሆናቸውም በላይ ዝግጅቱ የ ተሟላ እንዲሆን የ ረዱንና የ ተባበሩንን የ ተለያዩ የ ንግድ ድርጅቶች
እንዲሁም የተለያዩ ባሕላዊና ዘመናዊ የሙዚቃ ባንዶችና ሙዚቀኞችና በግል የ ተባበሩንን አርቲስቶች
ፈደሬሽናችን ውስጣዊ ችግር በአጋጠመው ወቅት ያገባናል በማለት የተባበሩን የመገናኛ ብዙሃንን
ለአለፉት 30 ዓመታት ከየስቴቱ ክለባቸውን በመወከል ኮሚቴ አወቅረው የቦርድ አባል በመሆን ከማህላቸው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አደራጅተው ይህን ከፍያል ሀለፊነት ከየክለቦቻቸው በአደራ ቃል ኪዳን ተረክበው ዲሞክራሳዊ አሠራር በተሞላበት፤ ግልርጽነ ትና ተጠያቂነ ት አስፍነ ው ብዙዎች ለዓመታት ጊዛቸውንና ገንዘባቸውን ሰውተው አንዳንዴም ትዳራቸውንን ቤተሰቦቻቸውን አሰጨንቀውደከመኝ ሰለቸኝ ሳየሉ የሕዘብን እሮሮ ችለው ፈደሬሽኑ ይኸን ያህ ጊዜ እነዲ ቆይ በነፃ የደከሙትን የቦርድ አባላትንና የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴን ማመስገን ተገቢ ነው፡፡
ይህን ሁሉ ሕዝብ ለማሰባሰብ፡ መስዋዕት የተከፈለው በገንዘብና የጉልበት ሥራ ብቻ ሳይሆን በሺዎቹ የሚቀጠሩ ልጆቻችንና ወንድሞቻችን ለአንድ ሳምት ውድደር ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት ያላነሰ በየ አካቢያቸው ዝግጅት በማድረግ እንዲሁም ወደ ዘግጅቱ ለመምጣት ለጉዞአቸው ለስንቃቸው ገንዘብ በየመስራቤታቸው ትርፍ ሰዓት በመሥራት ገንዘብ አጠራቅመው፤በውድድሩም ጊዜም የጠዋት ብርድ የቀትር አሩር ፀሐይና ዝናብ ተፈራርቆባቸዋል፤በጨዋታው ላይም ብዙዎች በግጭት፡ ሲቆስሉ፤ ጭንቅላታቸው፡ እየ ተፈነ ከቱ፤ ትከሻቸው፤ ጉልበታቸው ክንዳቸውላይውልቃት የሚደረሰባቸውጥቂትአየደሉም፤በተለይምከሥራ ፈቃድ ሳየ ገ ኙ ውድድሩ አድምቀው ሲመለሱ ከሥራ የ ሚባረሩ ብዙዎች ናቸው፡፡እነዚህ ወጣቶች ለ30 ዓመት በመፈራረቅ ከፈተኝ መስዋዕት በመክፈላቸው ከፍያለ ምሰጋና አድናቆት ለቸራቸውይገባል፡፡
ማነኛውዝግጅት የሚያምረውና የዕድሜባለፃጋ የሚሆነውከሕዝብ ድጋፍ ሲያገኝ ብቻ ነው ለ30 ዓመታት በየስቴቱ ባደርግነው ዝግጅት ሁሉ ማለውሕብረተሰብ ድጋፍ በመስጠቱ ምስጋነችን ከፍያለ ነው፡፡
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ስፖርት ፈደሬሽን በሰሜን አሜሪካ ይኽን ያህል እድሜ ሲያስቆጥር ሁሉ ነገር ተመቻችቶለት እና መንገዶች ሁሉ አልጋ በአልጋ ሆነውለት ሳይሆን ከጥንሱ ጀምሮ የውስጥም ሆነ ከውጪየሚመጣበትን ችግር ሁሉ ሊቋቋም የቻለው የመነጋገርና የመቻቻል ልምድ ያዳበረ በመሆኑ ነው፡፡ ፌደሬሽናችን መቼም ቢሆን የ ግለሰቦችን ፍላጎ ት ከብዙኃኑ ፍላጎ ት አብልጦ ያስተናገደበት ጊዜ የለም ወደፊትም አየኖርም !! ዲሞክራሲያዊ ሂደቶችንም አይጥስም አይቀለብስም ስለዚህም ነ ው ጥቂት ግለሰቦች ፌደሬሽኑን በሚፈልጉት መንገድ ለመምራት ሲሞክሩ ትክክል ያለመሆናቸውን አስረድቶ የውይይት መድረክ ቢከፍትላቸው አንቀበልም ብለው ሌላ ፈደሬሽን አቋቁመው የ ፈደሬሽናችንን ስም እስከነ ምሕፃረ ቃሉ ሲጠቀሙየባለቤትነት መብታችን በመጠቀም በፍርድ ቤት ትእዛዝ ብናሳግድም ለሀያ ሥምንት ዓመታት የተጠቀምንበትን የጁላይ 4 ሣምንት (July 4 weekend) በመጠቀም ሕብረተሰቡን ለመከፋፈልና ፌደሬሽናችንን ለማዳከም ከኢትዮጵያዊነት ባሕል የወጣ ሥርዐት ለመከተል እየሞከሩ የ ሚገ ኙ ት ፡ ፡ የ ዚ ህ እ ኩ ይ ተ ግ ባ ር ውጤት ሕ ብ ረ ተ ሰ ባ ች ን ን መከ ፋ ፈ ል ብ ቻ ሳይሆን በሌሎች ሀገሮች የተከበርንበትንና የተደነቅንበትን ለብዙዎች አርአያ የሆንበትን ተግባር እያጠፉት ስለሆነ አጥብቀን እንቃወመው እናውግዘው፡፡

ለ ሚቀ ጥ ሉ ት 2 0 ዓ መታ ት ኢ ት ዮ ጵ ያ ውያ ን በ የ አ መቱ በ አ ን ድ መድ ረ ክ ላ ይ እየተገናኘን የፌደሬሽናችንን የወርቅ ኢዮ በልዩ 50ኛ ዓመት እንድናከብር ምኞታችን ነው፡፡

ከብርሃኑ ወ/ማርያም

የኢትዮጵያ ስፖርትና ባሕል ፈደሬሽን በሰሜን አሜሪካ መስራች: የቀዲሞ ፕሬዘዳንት ባሁኑጊዜ የክብር ፕሬዘዳንት

(ESFNA founder,former president,current honorary president)

የ ኢትዮጵያ፡ ስፖርትና፡ የ ባሕል፡ ፈደሬሽን፡ በሰሜን፡ አሜረካ

(ESFNA) ለዘልዓለም ይኑር፡ ፡
ESFNA_Banner2_large

የውጭጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም አሁንም በስብሰባ ላይ ሲዋረዱ የሚያሳይ ቪድዮ ይመልከቱ

አቶ ስዬ በተመድ ተቀጠሩ

$
0
0

አቶ ስዬ በተመድ ተቀጠሩ  (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

Siye_seattle

አቶ ስዬ አብርሃ በ

አቶ ስዬ አብርሃ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አሰከባሪ ተቋም ውስጥ በወታደራዊ አማካሪነት በጥሩ ደመወዝ መቀጠራቸውን ምንጮች ጠቆሙ። በሙስና ወንጀል ተከሰው ከወንድሞቻቸው ጋር ለስድስት አመት ታስረው የተፈቱት ስዬ በተፈቱ ማግስት የአሜሪካን ድምፅ ራዲዬን ጨምሮ ለተለያዩ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ « ፖለቲካ ከልጅነቴ ጥርሴን የነቀልኩበትና አብዛኛው እድሜዬን ያሳለፍኩበት በመሆኑ ከትግሉ መድረክ ልርቅ ጨርሶ አልችልም» በማለት አስረግጠው መናገራቸውን እነዚሁ ወገኖች ያስታውሳሉ። « መድረክ » የሚል የፖለቲካ ስብስብ ከፈጠሩና የአንድነት አባል መሆናቸውን በይፋ ካወጁ በኋላ «ለትምህርት» በሚል ወደ አሜሪካ የመጡት ስዬ ከአንድነት ፓርቲ ሪፖርት እንዲያደርጉ የቀረበላቸውን ተደጋጋሚ ጥያቄና ማስጠንቀቂያ ችላ በማለት መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውን አመልክተዋል። በመጨረሻ « በቅርቡ አገር ቤት ተመልሼ ትግሌን እቀጥላለሁ » ማለታቸውን ያልሸሸጉት ምንጮቹ ስዬ ይህን በተናገሩ ሰሞን በሲያትል በተደረገ ስብሰባ ላይ « ለ21 አመት የተጀመረውን ልማትና ዲሞክራሲ እናስቀጥላለን» በማለት ብዙዎችን አንገት ያስደፋና ያሳዘነ ንግግር ማሰማታቸውን አስታውሰዋል። በአቶ መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማቸውን ሃዘን ለመግለፅ አደባባይ መውጣታቸው ብሎም « ያሰራቸውን ስርአት ዲሞክራሲያዊ » አድርገው ለማቅረብ መሞከራቸው አስገራሚ ነበር ብለዋል።

ከሲያትሉ ስብሰባ በኋላ የኢትዮ ሚዲያ ኤዲተርን « አንተ አክራሪ ነህ» ሲሉ አቶ ስዬ ለመዝለፍ መሞከራቸውና በአንፃሩ ጋዜጠኛውም « ስዬ አንተ የተቃዋሚ ፓርቲ አትመስለኝም፤ የኢህአዴግ ባለስልጣን መሰልከኝ» በማለት እንደመለሰላቸው በስፍራው የነበሩ ታዛቢዎች ገልፀዋል። የተቃዋሚው ጎራ በተለይም «መድረክ»ን አዳክመው በመውጣት ለገዢው ፓርቲ አስተዋፅኦ አድርገዋል በማለት ብዙዎች ስዬን ይኮንናሉ። በቅርቡ ከስሚንቶ ጋር በተያያዘ በህገወጥ ንግድ ተሰማርተው ተገኝተዋል የተባሉትና የ«ምፍአም ትሬዲንግ» ባለቤት የሆኑት የስዬ ወንድም ምህረትአብ አብርሃ በድጋሚ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም በሙስና ወንጀል ተፈርዶባቸው የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው እንደወጡ ይታወቃል። ከዚሁ ክስ ጋር በተያያዘ አቶ ስዬን ጨምሮ የሁሉም ወንድሞቻቸው የባንክ አካውንት እንዲታገድ ተደርጓል። « ስዬ የባንክ አካውንት እንኳ የለኝም » ሲሉ እንደቆዩ ያስታወሱት ምንጮች « አሁንስ ስዬ ምን ይሉ ይሆን?…ምን ያክል ገንዘብ በባንክ አስቀምጠው ይሆን?» በማለት ይጠይቃሉ።

 

U.S. Double-talking Human Rights in Ethiopia, Again!

$
0
0

dt31372641427As my readers know, I enjoy watchin’ American diplomats chillin’ out and kickin’ it with African dictators. I like watchin’ ‘em kumbaya-ing, back-pattin’ and fist bumpin’. I have trained myself to decipher their cryptic diplomatese spoken with forked tongue. I have also learned to chew on their indigestible words with a whopping spoonful of salt and pepper.

Despite years of relentless effort, I have been unable to fathom their mendacity. I am mystified and spellbound by the depth of their duplicity and height of hypocrisy. Bewildered and frustrated, I was compelled to engage in a neologistic exercise and create a word that captured their culture of mendacity. I coined the term “diplocrisy” to refer to the deliberate and calculated use of double-talk, double-speak and double-dealing to misrepresent facts and mislead the inattentive public about what the U.S. is doing to actively promote human rights in Africa.

Diplocrisy is diplomatic hypocrisy in “lights, camera and action”. For instance, the diplocrites say, “We will work diligently with Ethiopia to ensure that strengthened democratic institutions and open political dialogue become a reality for the Ethiopian people…” Yet they turn a blind eye (or pretend to be legally blind) to the complete “closure of political space” in Ethiopia. (The euphemism “closure of political space” is what used to be called in the old days, oppression, repression and suppression.) The diplocrites promise to “work for the release of jailed scholars, activists, and opposition party leaders…”, but when Africa’s ruthless dictators tongue-lash them, the diplocrites become tongue-less (or tongue-tied) and their lips are sealed.

The diplocrites say, “When a free media is under attack anywhere, all human rights are under attack everywhere. That is why the United States joins its global partners in calling for the release of all imprisoned journalists in every country across the globe and for the end to intimidation.” The truth is they plug their ears to avoid hearing the pained whimpers of heroic journalists like Eskinder Nega, Reeyot Alemu, Woubshet Taye and so many other political prisoners chained deep in the bowels of Meles Zenawi Prison in Ethiopia. When they proclaim, “History is on the side of brave Africans…” and conveniently position themselves on the right side of the bed with Africa’s brutal dictators, I marvel at the height of their diplocrisy.

On June 20, 2013, I had another distressing opportunity to witness American diplocrisy in lights, camera, action when Donald Yamamoto, Acting Assistant Secretary, Bureau of African Affairs (and former ambassador to Ethiopia) testified before the House Subcommittee on Africa, Global Health, Global Human Rights, and International Organizations. Yamamoto presented testimony to answer a single question:  What is the U.S. prepared to do to improve the prospects for democracy and human rights in Ethiopia following the death of dictator Meles Zenawi?

Mr. Yamamoto’s answer, ungarnished with the sweet ambiguity of diplomatic argot, was “Not a damn thing!!!”

I find nothing surprising in U.S. inaction and aversion to action to help improve the human rights situation in Ethiopia or elsewhere in Africa. I have reluctantly come to the conclusion that the Obama Administration does not give a rat’s behind about Ethiopian or African human rights. That does not bother me anymore. I am cool with it! I also do not mind if the diplocrites think we are “fools and idiots”, as the former U.S. U.N. Ambassador (currently National Security Advisor) Susan Rice chose to vicariously describe those of us who opposed the regime of Meles Zenawi. But I do mind when we are treated as “fools and idiots.” What I find outrageous is the audacity of diplocrites who give testimony under oath which insults our intelligence (or what little scrap of gray matter they think we have).

On January 20, Mr. Yamamoto gave testimony which went beyond insulting our intelligence. He testimony gave new meaning to the phrase “speaking with forked tongue.” When Mr. Yamamoto was an ambassador in Ethiopia in 2009, his position on what could and should be done to improve human rights in that country was crystal clear and radically different than was revealed in his testimony in 2013.

In June 2009, Mr. Yamamoto was confident, forthright, frank, veracious and scrupulous as he advised Deputy Secretary of State Jacob Lew about what could and should be done to promote human rights and the rule of law in Ethiopia. In June 2013, Yamamoto’s testimony before the House Subcommittee on Africa  evasive, patronizing, platitudinous and clichéd and amounted to nothing more than an elaborate obfuscation of the truth about what the U.S. needs and has the capacity to do to help improve human rights in Ethiopia. In effect his entire testimony before the Subcommittee could be reduced to one simple proposition: The U.S. is not able, willing or ready to use its resources to help improve the human rights situation in Ethiopia!

Dateline: Addis Ababa, Ethiopia (6/23/2009):

In June 2009, Mr. Yamamoto, assessing the political and human rights situation, instructed Deputy Secretary Jacob Lew:

Your visit to Ethiopia comes at a time when the Ethiopian Government’s (GoE) growing authoritarianism, intolerance of dissent, and ideological dominance over the economy since 2005 poses a serious threat to domestic stability and U.S. interests.  The GoE has come to believe its own anxieties about a fundamental shift in U.S. policy against it.  This self-induced crisis of confidence has exacerbated the GoE’s natural tendency of government control over politics, the economy and personal freedoms.  To pre-empt retaliation, the GoE has increasingly purged ethnic Oromos, Amharas, and others perceived as not supporting the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) from the military, civil service, and security services…

 

… The May 2005 elections and their aftermath continue to weigh heavily on Ethiopia’s domestic political scene, and as a result, the government is systematically closing political space in Ethiopia.  The U.S. Embassy has taken the lead in advocating for transparent and open national elections in 2010, the next major milestone in Ethiopia’s democratization process… Since 2005, the government has enacted laws which limit and restrict party politics, the media, and civil society… The April 2008 local elections saw the ruling party take over all but three of over three million seats

Dateline: Washington, D.C. (6/20/2013):

In assessing the political and human rights situation in Ethiopia in 2013 for the Subcommittee on Africa, Mr. Yamamoto stated:

Ethiopia’s weak human rights record creates tension in our relationship and we continue to push for press freedom, appropriate application of anti-terrorism legislation, a loosening of restrictions on civil society, greater tolerance for opposition views, and religious dialogue. The ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) controls all aspects of government, including the legislative branch where the EPRDF and its allies hold 545 of 547 parliamentary seats. Political space in Ethiopia is limited and opposition viewpoints are generally not represented in government. In recent years, Ethiopia has passed legislation restricting press freedoms and NGO activities. 

Questions for Mr. Yamamoto:

Is the “Ethiopian government” less intolerant of dissent and less authoritarian and less ideologically dominant over the economy in 2013 than it was in 2009?

Does the “Ethiopian government” in 2013 have any “anxieties about a fundamental shift in U.S. policy against it”?

In the April 2008 local elections, the ruling party in Ethiopia took all but three of over three million seats. In 2010, the ruling party won 545 of 547 parliamentary seats (99.6 percent). What result does the U.S. expect in a “post-Meles” 2015 election?

In light of the “GoE’s natural tendency” to exercise total “control over politics, the economy and personal freedoms”,  when did the “GoE” stop its “preemptive retaliation of purging ethnic Oromos, Amharas, and others perceived as not supporting the ruling party from the military, civil service, and security services”?

In 2009, the “U.S. Embassy took a leading role in advocating for transparent and open national elections in 2010” which it described as “the next major milestone in Ethiopia’s democratization process”. The ruling party claimed victory in the 2010 election with a margin of  99.6 percent. Does the U.S. expect a 100 percent victory margin for the ruling party in the “next major milestone in Ethiopia’s democratization process” in 2015?

What specific measures or steps has the U.S. taken since 2009 in its “continued push for press freedom, appropriate application of anti-terrorism legislation, a loosening of restrictions on civil society, greater tolerance for opposition views, and religious dialogue” in Ethiopia?

Dateline: Addis Ababa, Ethiopia (6/23/2009)

In 2009, Mr. Yamamoto advising Deputy Secretary of State Jacob Lew argued for swift, decisive and forceful action and urged a no-nonsense approach to dealing with the “Ethiopian Government” on the issue of human rights:

…   Since 2005, the government has enacted laws which limit and restrict party politics, the media, and civil society… Laws have been passed regulating political financing, access to the press, and ability of civil society organizations (NGOs) to receive funding from foreign sources and participate in the political process… Without significant policy reform to liberalize the economy and allow mounting political dissent to be vented… [there could be] major civil unrest.  The United States can induce such a change, but we must act decisively, laying out explicitly our concerns and urging swift action.  Because the GoE has enjoyed only growing international assistance and recognition despite its recent record, it currently has no incentive to veer from the current trajectory to which the EPRDF is so committed.  If we are to move the GoE, we must be willing to use USG resources (diplomatic, development, and public recognition) to shift the EPRDF’s incentives away from the status quo trajectory….

 

If we are to move them, though, we need to deliver an explicit and direct (yet private) message that does not glad-hand them.  We must convey forcefully that we are not convinced by their rhetoric, but rather that we see their actions for what they are…  We should [assure them]… that we are not trying to promote regime change, and that we are delivering a similarly explicit message of the need for change to opposition groups.

Dateline: Washington, D.C. (6/20/13):

In June 2013, Mr. Yamamoto told the Subcommittee on Africa that the best the U.S. could do was to “encourage Ethiopia to improve its human rights record”:

Post-Meles Ethiopia presents the United States with a significant opportunity to encourage Ethiopia to improve its human rights record, liberalize its economy, and provide increased space for opposition parties and civil society organizations. Post-Meles Ethiopia also presents a significant challenge since Ethiopia plays an important role in advancing regional integration and mitigating regional conflict in Somalia and Sudan. Our partnership with Ethiopia balances these interests by focusing on democracy, governance, and human rights; economic growth and development; and regional peace and security.

Questions for Mr. Yamamoto:

What “significant policy reform” has been taken by the “GoE” since 2009 to liberalize the economy and allow mounting political dissent to be vented?

In what ways has the U.S. acted decisively to get the “GoE” to relax application of its draconian media, civil society and other repressive laws in Ethiopia?  Have any of the “laws enacted in Ethiopia after 2005 limiting and restricting party politics, the media, and civil society” been repealed, modified or in any way tempered or mitigated?

Since 2009, what “incentives” (or disincentives) (including “diplomatic, development, and public recognition”) has the U.S. used to “induce change” or redirect the “GoE from the status quo trajectory”? Alternatively, how has the U.S. “acted decisively, laying out explicitly our concerns and urging swift action” by the “Ethiopian Government”?

Could Ethiopia experience a “spark of major civil unrest” in 2013-14 if the “GoE does not undertake significant policy reform to liberalize the economy, allow mounting political dissent to be vented”, competently manage the economy and “control inflation”?

When and why did the U.S. stop trying to promote “regime change” in Ethiopia?

When did the U.S. stop “glad-handing” and start fist bumping with the leaders of the regime in Ethiopia?

Dateline: Addis Ababa, Ethiopia 6/23/2009

In June 2009, Mr. Yamamoto told Deputy Secretary Lew that the “Ethiopian government” maintained a chokehold on the economy and that its claims of double-digit growth are fabrications:

Foreign investment restrictions are widespread, including key sectors such as banking, insurance, and telecommunications.  The state-owned Ethiopian Telecommunications Corporation (ETC) is the only service provider in the sector, creating an environment of poor telecom service and access.  In a country of nearly 80 million people, there are only 920,000 fixed phone lines, 1.8 million cell phones, and 29,000 internet connections.  The GOE maintains a hard line stance on these key sectors…

The GOE publicly touts that Ethiopia has experienced double-digit real GDP growth of over 11 percent in recent years.  The GOE predicts real GDP growth of 10 percent this year.  Many institutions, including the World Bank and IMF, dispute the GOE’s growth statistics, stating that Ethiopia’s real GDP growth rate will most likely range between six and seven percent this year.

Dateline: Washington, D.C. (6/20/2013)

In June 2013, Mr. Yamamoto told the Subcommittee on Africa that

Ethiopia ranks among the ten fastest-growing economies in the world, averaging 10 percent GDP growth over the last five years. State-run infrastructure drives much of this growth. Our bilateral trade and investment relationship is limited by investment climate challenges and the lack of market liberalization… Currently about 100 U.S. companies are represented in Ethiopia. Total U.S. exports to Ethiopia in 2012 were $1.29 billion; imports from Ethiopia totaled $183 million.

Questions for Mr. Yamamoto:

Mr. Yamamoto: Which one of the following statements is false: 1) “Ethiopia ranks among the ten fastest-growing economies in the world, averaging 10 percent GDP growth over the last five years.” 2) Over the past five years, “Ethiopia’s real GDP growth rate  most likely ranged between six and seven percent.”

Why is “foreign investment” from China (instead of the U.S.) more widespread in Ethiopia in 2013?

Ethiopia has “invested some US$14 billion in infrastructure development between 1996 and 2006 and made “exceptionally heavy recent investment in its telecoms infrastructure” and made “exceptionally heavy recent investment in its telecoms infrastructure”? What accounts for the fact that Ethiopia has the worst “telecom service and access” in all of Africa and quite possibly the entire world?

Dateline: Addis Ababa, Ethiopia 6/23/2009

In June 2009, Mr. Yamamoto advised Deputy Secretary Lew how to leverage U.S. aid to bring about human rights improvements in Ethiopia:

Ethiopia is now the second largest recipient of U.S. foreign assistance in sub-Saharan Africa. However, the preponderance of this assistance is humanitarian, including food aid… of which a significant share supplements the Government of Ethiopia budget…. The increasingly difficult operating environment and growing transaction costs for non-budgetary foreign aid and, in particular, the proposed tight restrictions on non-governmental organization (NGO) implementing partners, call for a reassessment of the mix and effectiveness of U.S. assistance to Ethiopia in order to support U.S. foreign policy objectives…

Dateline: Washington, D.C. (6/20/2013)

In June 2013, Mr. Yamamoto told the Subcommittee on Africa one of the proudest achievements of U.S. human rights policy in Ethiopia:

On democracy and human rights, we recently secured agreements to do media development training and open two community radio stations.Mechanisms such as our bilateral Democracy, Governance, and Human Rights Working Group, bilateral Economic Growth and Development Working Group, and Bilateral Defense Committee are useful tools for advancing our policy objectives in our three focus pillars. At the same time, we are public in our support for an improved environment for civil society, those we believe to have been subjected to politically motivated arrests, inclusive democratic processes, and rule-of-law. Making progress on this area will continue to be challenging and will require a great deal of creativity…. Ethiopia is a significant recipient of U.S. foreign aid, having benefited from over $740 million in FY 2012 assistance…

Questions for Mr. Yamamoto:

In 2009, you stated that a significant amount of U.S. humanitarian aid “supplemented the Government of Ethiopia’s budget….” Doesn’t use of “humanitarian aid” to “supplement the Government of Ethiopia’s budget” flagrantly violate 22 USC § 2151n et seq. (Foreign Assistance Act of 1961, as amended) which provides in relevant part:

No assistance may be provided under subchapter I of this chapter to the government of any country which engages in a consistent pattern of gross violations of internationally recognized human rights, including torture or cruel, inhuman, or degrading treatment or punishment, prolonged detention without charges, causing the disappearance of persons by the abduction and clandestine detention of those persons, or other flagrant denial of the right to life, liberty, and the security of person, unless such assistance will directly benefit the needy people in such country.

Do you deny that the “Government of Ethiopia” has engaged and continues to “engage in a consistent pattern of gross violations of internationally recognized human rights”?

Is U.S. “humanitarian aid” still used in 2013 to “supplement the Government of Ethiopia’s budget”?

If the U.S. could use its aid leverage (through “a reassessment of the mix and effectiveness of U.S. assistance”) to bring about improvements in human rights in Ethiopia in 2009, why can’t it do the same in 2013?

You stated, “On democracy and human rights, we recently secured agreements to do media development training and open two community radio stations.” Is this the singularly proud outcome of “working diligently with Ethiopia to ensure that strengthened democratic institutions and open political dialogue become a reality for the Ethiopian people”?

Dateline: Addis Ababa, Ethiopia 6/23/2009

In June 2009, Yamamoto cautioned Deputy Secretary Lew to understand the “Ethiopian Leadership’s Guiding Philosophy”:

Understanding Ethiopia’s domestic political and economic actions, and developing a strategy for moving the ruling party forward democratically and developmentally, requires understanding the ruling Tigrean People’s Liberation Front’s (TPLF) prevailing political ideology: Revolutionary Democracy. Hard-line TPLF politburo ideologues explain the concept in antiquated Marxist terms reminiscent of the TPLF’s precursor Marxist-Leninist League of Tigray…. As an extension of this philosophy, to the ruling party, development is their gift to Ethiopia, and their first priority.  While they accept assistance from the international community, they resent attempts by donors to tell them how development should be done.  The leadership believes that only they can know what is best for Ethiopia, and if given enough time, Ethiopia will transform itself into a developed nation.

Questions for Mr. Yamamoto:

Has the “Ethiopian leadership’s guiding philosophy” changed since the passing of Meles Zenawi?

Is the “Tigrean People’s Liberation Front’s prevailing political ideology of Revolutionary Democracy” compatible with the values of the Founders of the American Republic?

You stated that “while the GoE accepts assistance from the international community, they resent attempts by donors to tell them how development should be done.  The leadership believes that only they can know what is best for Ethiopia.” Does the TPLF “leadership” in 2013 believe that “only they can know what is best for Ethiopia”?

Does the U.S. share the TPLF “leadership’s” belief that “only the TPLF can know what is best for Ethiopia?

Of Fools and Idiots

I don’t mind them double-talking us as though we are “fools and idiots”. If they must relate to us as such, we demand to be treated as “Shakespearean fools”. Our silence in the face of outrageous lies may give the misimpression that we are ignorant, witless, fainthearted and without much sense or sensibility. But we know the simple truth; and that truth is human rights in Ethiopia is an afterthought for the Obama Administration. There is no need to double-talk us on human rights anymore. Just tell us straight that human rights in a world in which the U.S. is at war with terrorism is for the birds, not Ethiopians! We’d understand. In the final analysis, in the struggle for human rights in Ethiopia and the rest of Africa, we must draw our inspiration from our tower of power Nelson Mandela and keep walking that long road.  We keep on walking, let them keep on talking, double-talking…!

Professor Alemayehu G. Mariam teaches political science at California State University, San Bernardino and is a practicing defense lawyer.

Previous commentaries by the author are available at:

http://open.salon.com/blog/almariam/

www.huffingtonpost.com/alemayehu-g-mariam/

Amharic translations of recent commentaries by the author may be found at:

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

http://ethioforum.org/?cat=24

ESFNA 2013: የመክፈቻ ስነ-ሥርዓት ዜና ፎቶ

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live