Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

“ደሙን ሰጥቶ፣ አጥንቱን ከስክሶ ፣ የስኬት ማማ ላይ ያስቀመጣችሁ ጀግና ስርዓት ” ( ሄኖክ የሺጥላ )

$
0
0

Tensaye

በእውነት ወያኔ ምን በደለ ? እንደው ሀገር ባለማ ! ድልድይ በሰራ ፣ ግድብ በቆፈረ ! ውይ የሰው ነገር ! አሁን ማን ይሙት ወያኔ የደርግን ያህል ጨካኝ ሆኖ ነው እንዲህ የምትረባረቡበት ? እናንተ እኮ አታፍሩም ይሄኔ ፣ ከግድብ የመናገር ነጻነት ይቅደም ፣ ከውሃ ማቆር የሰው ልጆች እኩልነት ይቅደም ፣ ከልማታዊ አርሶ አደርነት የሰብአዊ ክብር ና የመንፈስ ልዕልና ይቅደም ፣ የተጻፈ ከማንበብ ( ዘላለማዊ ክብር ለክቡር ጥቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ የሚለውን አይነት ማለት ነው ) የመጻፍ መብት ይከበር ፣ በየመንገዱ ሥራ አጥቶ ከመደርደር ፣ የመሰለፍ መብታችን እውቅና ይሰጠው ፣ አስራ አራት ክልል በካርታ ላይ ከማስቀመጥ ፣ በፈለግነው ክልል ሄዶ የመስራት መብታችን ይጠበቅ ፣ የዜጎች እኩልነት በዜና እና በዝና ሳይሆን በነባራዊው ዓለም ፣ በለት ተለት ሕይወታችን ይተግበር እና ወዘተ ትሉ ይሆናል ።

በእውነት አታፍሩም ! አሁን እስኪ ማን ይሙት ፣ ድልድይ ይበልጣል ፣ የህዝቦች እኩልነት ? ለኛ የመጻፍ ነጻነት ይሻለናል ወይስ የማቃጠር መብት ? ዜጎች ደሞ እኩልነት ፣ እኩልነት ፣ እያላችሁ የምታላዝኑት ፣ እንኳንስ ይቅርና በዜግነት መብት በቁመት እኩል የሆኑ ሰዎች ማግኘት ዘንድሮ ቀላል ነገር ነው ወይ ? ደሞ በተወደደ ወረቀት መጻፍ ፣ መጻፍ ፣ መጻፍ ። አማራ ድሮም መጻፍ ይወዳል ! ክስ ይወዳል! ምናለ ባትጽፉ አትሞቱ ፣ እውነት ባትናገሩ አትሞቱ ፣ ስለ ሚኒሊክ ባትናገሩ አትሞቱ ፣ ስለ በላይ ዘለቀ ባታወሩ አትሞቱ ! አሁን የደደቢት ታሪክ አልበቃ ብሎ ነው አዳሜ የ አጼ ቴዎድሮስን ታሪክ የሙጥኝ ያለው ? አረ ምን እሱ ብቻ ፣ ሀገር ፣ ሀገር ፣ ሀገር ትላላችሁ ? ሀገር ምንድን ነው ? ባንዲራ ፣ ባንዲራ ፣ ባንዲራ ? ባንዲራ ድልድይ አይሆን ? ምንነት አይበላ ! ነጻነት አይሸጥ ። ይህ የአማራ ተረት ነው ። አሁን እስኪ ማን ይሙት ለኢትዮጵያ የሚጠቅማት ኮብል ስቶን ነው ወይስ አክትቪስት ? “እኛ ( ወያኔ-ትግሬዎች ) እኩል ሳትሆኑ እኩል አደረግናችሁ ፣ ከጨቋኝ ፊውዳል እጅ ታደግናችሁ ፣ ዛሬ በራሳችሁ ቋንቋ መናገር ስትችሉ ፣ የፈቀዳችሁትን ባንዲራ አወጣችሁ ፣ የብሔር ብሔረሰቦች መብት ያለገደብ ተከበረ ፣ ታዲያ ይሄም አልበቃም ብሏችሁ ፣ እኛ ታግለን ባመጣነው ፣ ስልጣን ላይ መቀመጥ አማራችሁ ? ” ።

ታዲያ ለምንድን ነው ይህን ” ደሙ ሰጥቶ፣ አጥንቱን ከስክሶ ፣ የስኬት ማማ ላይ ያስቀመጣችሁ ጀግና ስርዓት የምትፈታተኑት ? ” ተዉ ግን ፣ ተው ? እኔ ልሙት አሁን የወያኔ ጥፋቱ ምኑ ላይ ነው ? ይሄኔ እኮ << ምርጫ 100% አሸነፈ ፣ ነብዩን ገደለ ፣ የእስልምና ኮምቴዎችን አሰረ ፣ በስልጣን ላይ ያሉት አብዛኛው ካንድ ብሔር የተመረጡ ናቸው ፣ በዘር ተደራጅተው ሀገሪቷን ተቀራመቷት ፣ ወያኔ እጁ ላይ ደም አለ ፣ መንግስት ሳይሆን ቃሊቲ ( ዘብጥያ ) መውረድ ያለበት ስርዓት ነው ፣ ይህ ስርዓት ቢያንስ የቃልቻ ያህል እንኳ ለሀገር ሰላም አይጸልይም ፣ ይህ ስርዓት ሳይሆን የእባብ ስሪት ነው ” እና ወዘተ ትሉ ይሆናል ። ቆይ ቆይ << 17 ዓመት የታገለ ስርዓት አንድ ነብዩን ቢገል ምን አለበት ፣ ሀገር በማልማት ላይ ያለ መንግስት ፣ የህዝቡን ድምጽ ቢሰርቅ ምን አለበት ? ቆይ አሁን አባይን እየገነባ ያለ ኃይል ፣ መጅሊስን ቢያፈርስ ያን ያህል መጅሊስ ትልቅ ነገር ሆኖ ነው ፣ እንኳን መጅሊስ << ቲዊን-ታወር ፈርሶ የለም እንዴ ? >> ። ደሞ- መጅሊስ መጅሊስ አትበሉ ፣ በየሰፈሩ ህውሃት መጅሊስ አረቢ አስነጥፎ ሺሻ ያለገደብ እንዲገባ ያደረገውን ረስታችሁ ነው ስለሌላው መጅሊስ የምታወሩት ? ምን ታካብዳላችሁ ? ደሞ ተቃዋሚ የምትባሉት ሁሉ ትልቁ ችግራችሁ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ ? ትልቁ ችግራችሁ ንገረኝ ካላችሁ << ወሬኞች ናችሁ !>> እኛ ደሞ በወሬ አንፈታም ። አንድም ቆራጥ በመሃከላችሁ የለም ! <<ፈሳም ሁላ !! >> << ወያኔ እንዳንቺ አማሪካን ሀገር በርገር እየበላች መሰለሽ ስልጣን ላይ የወጣችው ? ታግላ ነው ፣ ከገባሽ >> ደሞ እኛ ልማት ላይ ነን ! አንቺን የሚያስጨንቅሽ ያንድ ጋዜጠኛ መሞት ነው አይደል ? እኛን የሚያስጨንቀን ግን ያርማታ ሙሌት ነው ? አንቺ እስክንድር ለምን ታሰረ የሚለው ነው አይደል እንቅልፍ የሚነሳሽ ? እኛን ወያኔዎችን እንቅልፍ የሚነሳን የሲሚንቶው መቡካት ወይም አለመቡካት ነው ፣ እኛን የሚያስጨንቀን የአበባ እርሻው ነው ፣ እኛን የሚያስጨንቀን የኦባማ በሰላም ወጥቶ መግባት ነው ፣ እኛ የልማት ኃይሎች ነን ። አሁን አንድ አቡበከር ተፈታ አልተፈታ ለኢትዮጵያ ምን ይጠቅማታል ? ከገባሽ እኛን የሚያስጨንቀን እንዴት ለቀጣዩ 100 ዓመት ያለ ተቀናቃኝ እንደምንገዛሽ ነው ።

አሁን እስኪ ማን ይሙት ወያኔን የመሰለ ስርዓት በኢትዮጵያ ምድር ተፈጥሮ ያውቃል? አንድ ዘር ፣ አንድ ዘር የምትሉት ደሞ ትግሬ ስለምትጠሉ ነው እንጂ ፣ ትግሬ ቢገዛ ምን አለበት ? ትግሬ ምን አረገ ? እኛ ከዘረኛ አማራ አድነናችሁ ፣ ትግሬ ፣ ትግሬ ትላላችሁ ? ደሞ ስልጣኑ አይ ማን ነው ያለው ? ሃይለማርያም ትግሬ ነው ? ነጋሶ ገዳዳ ትግሬ ነበር ? ግርማ ወልደጊዮርጊስ ትግሬ ነው ? ደመቀ መኮንን ትግሬ ነው ? አንድ ትግሬ ስልጣን ላይ የነበረ መለስ ብቻ ነበር ፣፣ እሱም በጭንቅላቱ ነው ፣ አሁን ደሞ እሱ ሞተላችሁ ( ሞቶም አልተዋችሁትም እንጂ !) ፣ ሃይለማርያም ጠቃላይ ሚኒስትር ሲሆን ደሞ ምን እንደምትሉ እናያለን ዘረኞች ! ስለ ጀነራሎች የምታወሩት ደሞ እኮ ፣ እነሱ ታግለው ነው ፣ ለ 17 ዓመት አፈር በልተው ፣ ታዲያ አንድ ባለ እስክርቢቶ አማራ መጥቶ ይውሰደው ? ደርግ ይምጣ እና ይግዛን ነው የምትሉት ? ይልቅ አንዳንድ ጥቃቅን ስህተቶች ይኖራሉ ፣ እነሱም በሂደት የሚስተካከሉ ናቸው ። እኛ በዲሞክራሲ ስርዓት ላይ መጏዝ ከጀመርን ገና 25 አመታችን ነው ። ዲሞክራሲ ምን እንደነበር ለማያውቅ ሕዝብ ፣ ሁሉንም ባንዴ ብንፈቅድለት ቀስ እያልን እናድርገው ብለን ነው ፣ ደሞ እናንተስ እንኳን የኛን ዲሞክራሲ ፣ የባቄላ ፈስ በቅጡ መቆጣጠር የሚችል መቀመጫ ሳይኖራችሁ ዘላችሁ ወንበር ላይ ቁብ ማለት ምን የሚሉት ችኮላ ነው ።

አንዳንድ ሽብርተኞች ፣ ህገ መንግስቱን ለመናድ ከውጭ ኃይሎች እና ሰርጎ ገቦች ጋ በማበር ፣ ድርጅታችን ኢህአዲግ ቀን ከሌት ፣ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል እየተጋበት ያለውን የወደ ልማት ጎዳና ባጭር ለመቅጨት ቢሞክሩም ፣ የድርጅታችንን አላማ በተረዱና ፣ በድርጅታችን ላይ ላለፉት ሃያ አመታት ትልቅ እምነት በጣሉ ግለሰቦች ( በግል ተነሳሽነት ) ይህ የወንጀል ተግባር በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል ። ከዚህም ውስጥ እንደምሳሌ የዚህ የሽብር ቡድኑ መሪ እና ዋነኛ ተዋናይ የነበረውን ሰው ( አንዳርጋቸው ጽጌ ) በቁጥጥር ስር አውለናል ። ያም ቢሆን ድርጅታችን ፣ አንዳርጋቸው ለመጽሐፍ ያለው ፍቅር ፣ የኛን የባለ ራዓዩን ጠቅላይ ሚንስትር ፍቅር ስላስታወሰን ፣ በራሳችን ተነሳሽነት ፣ ሙሉ ወጪውን ሸፍነን << አንዳርጋቸው ሆይ ኤርትራ ውስጥ ቦምብ ከምታፈነዳ ፣ እዚህ እኛ ጋ መጽሐፍ አሳትም >> ብለነው ፣ እሱም ምክራችንን ተቀብሎ መጽሐፍ እየጻፈ ነው ። ካላመናችሁ ጠይቁት ፣ እንደውም ዛሬ ገጽ 180ን ጽፎ ጨረሰ ! እንዴትም ብሎ ለጉምቦት ሃያ አለበለዚያ ለባዕለ የካቲት ወይም ፓርላማ ተመርቆ ከመከፈቱ አንድ ሳምንት በፊት ለአንባብያን እንደሚደርስ በዚህ አጋጣሚ መግልጽ እንፈልጋለን ።

እና አባካችሁ ፣ ይህን ” ደሙን ሰጥቶ፣ አጥንቱን ከስክሶ ፣ የስኬት ማማ ላይ ያስቀመጣችሁ ጀግና ስርዓት አትፈታተኑት ! አረ ተው ታማኝ ተመከር ! አሁን ወያኔን አሜን ብለህ ብትቀበል እኮ፣ እንደ ንዋይ ደበበ ጥሬ ስጋ ስትበላ ፎቶ ተነስተህ ትለጥፍ ነበር ፣ ደደቢት ታንክ ላይ ሆነህ ፎቶ ትነሳ ነበር ፣ ከፈለካት አይነት ሴት ጋ እንደፍለክ ትሆን ነበር ፣ አንተ ግን ዝም ብለህ ነጻነት ፣ እኩልነት ፣ የህዝቦች መብት እና ወዘተ ትላለህ ። ህዝቡ ራሱ ( በብላሽ !) ፣ በኪሳራ ነው ኑሮውን ለባርነት ፣ ህይወቱን ለጭቆኛ አሳልፎ የሰጠው ። ታዲያ አንተ ምን አገባህ ! ? ይልቅ እንደ ሰለሞን ተካልኝ ፣ ለጥሬ ስጋ ስትል ሀገርህ ላይ ፣ ለቀይ ወጥ ስትል ሕዝብህ ላይ ፣ ለሆድህ ስትል እውነትህ ላይ ተገልብጠህ ፣ የቀበሌ ስብሰባ መጥሪያ ” ሃሎ- ሃሎ ” ይዘህ ” ትናንት አንድ በሉ ፣ እሪ በል ቦሌ እሪ በል ፒያሳ ” ባልክበት ጉሮርሮህ ” ቅንድቡ ፣ እጁ ፣ አይኑ ፣ አፍንጫው” እያልክ ብትዘፍን አይሻልም ? አረ ተው ታማኝ ! አረ ተው !

አሁን አበበ ገላው ታላቁ መሪያችን ላይ ፣ ሊያውም በዓለም አደባባይ ፣ ትላልቅ ሰዎች በተገኙበት ፣ እንደዚያ መጮህ ነበረበት ? ማን ተዋረደ ? አበበብ ራሱ ! ያንን የሚያህል አስተዋይ መሪ ያዋረደ መስሎት ፣ ተሳስቷል !

አና አሁንም እኛ ልማት ላይ ነን
ከሰው ሕይወት የድንጋይ ቁመት የማረከን
እኛ አለታውያን
እኛ ኮንክርታውያን
እኛ ድልድያውያን
ከሀገር ውርደት የኛ ሆድ የበለጠብን
ከህዝብ ክብር ፣ ንዋይ እንደ ኩይሳ የደም ሲሳይ የጫነብን
ከነጻነት እና ፍቅር ፣ ጥላቻ መንገድ የሰራብን
የጥፋት ልማተኞች
የክፋት መንገደኞች
በሰው ደም የሰከርን
በአልኮል የሰከርን
በጥላቻ የሰከርን
ይህንንም በ 100 % ምርጫ ውጤት ያስመሰከርን
አስክሬኖች ነን
እና ታዲያ ምን አረግን ?

ተው ፣ አረ ተው ፣ ይህንን ” ደሙን ሰጥቶ፣ አጥንቱን ከስክሶ ፣ የስኬት ማማ ላይ ያስቀመጣችሁ ጀግና ስርዓት አትፈታተኑት !


የአስመራ ሰዎች በአዲስ አበባ – (ዜና ትንታኔ)

$
0
0

Eritreans in Addis Ababa protest against their government (Video)
ቻላቸው ታደሰ ለዋዜማ ራድዮ እንደዘገበው:

ኤርትራ በ1990 ዓ.ም ኢትዮጵያን በወረረች ማግስት መንግስት በረፊረንደሙ የተሳተፉና ለብሄራዊ ደህንነት አደገኛ ናቸው ያላቸውን በሽዎች የሚቆጠሩ ኤርትራዊያን በጅምላ ከሀገር ማባረሩ ይታወሳል፡፡ ሰዎቹ ሲባረሩ ያፈሩት ሃብትና ንብረት በአግባቡ ሳያደላድሉና በህጋዊ መንገድ ለተወካዮቻቸው ሳያስተላልፉ እንደነበርም አይዘነጋም፡፡ ይህ የግብር ይውጣ እርምጃ ብዙ ዓለም ዓቀፍ ወቀሳም አስከትሎ ነበር፡፡

የሁለቱ ሀገሮች የድንበር ጦርነት ምንጭ ሳይደርቅና ዕርቀ ሰላምም ሳይወርድ ኢህአዴግ-መራሹ መንግስት ከአምስት ዓመት በፊት ባወጣው ደንብ በወረራው ወቅት የተባረሩ ኤርትራዊያን እንደገና በኢትዮጵያ ቋሚ የመኖሪያ ፍቃድ እንዲያገኙ፣ የቀድሞ ንብረታቸው ከፈለጉም ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸው እንዲመለስላቸው ብሎም ከሀገሬው ሰው እኩል ንብረት ማፍራት እንዲችሉ ፈቅዷል፡፡ መታወቂያና የእርሻ ቦታም ሳይቀር ተስጥቷቸው ከሀገሬው ሰው ጋር ተቀላቅለው እንዲኖሩ ሁኔታዎችን አመቻችቷል፡፡ በባንክም ተቀማጭ የነበረ ገንዘባቸውም ተመልሶላቸው እንደማንኛውም የውጭ ዜጋ በኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዲሳተፉ፣ የማህበራዊ ግልጋሎቶችን ደግሞ ከዜጎች ጋር በእኩል እንዲያገኙ አድረጓል፡፡ ስለሆነም የዚህ ፖሊሲ መነሻና ግብ ምንድን ነው? ፖሊሲውስ በኢኮኖሚ በተዳከመችውና ወታደራዊና ፖለቲካዊ ጡንቻዋ በተመናመነባት ኤርትራ ላይ ምን ዓይነት የፖለቲካ፣ ፀጥታና ኢኮኖሚያዊ አንድምታዎች ይኖረው ይሆን? የሚሉትን ጥያቄዎች መመርመር ተገቢ ነው፡፡

በእርግጥ የኢትዮጵያ መንግስት በኤርትራዊያኑ ስደተኞች ላይ ፖሊሲውን ማስተካከል ያስፈለገው የሁለቱ ወንድማማች ህዝቦችን ለማቀራረብና ግንኙነታቸውንም ለማደስ አስቦ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ሆኖም ግን ይህ የኢትዮጵያ መንግስት ፖሊሲ ከሰብዓዊነትና ወንድማማችነት መርሆዎች ባሻገር ሌላ ዓላማ እንዳለው መታዘብ አይከብድም፡፡

መንግስት ለበርካታ ኤርትራዊያን ስደተኛ ወጣቶችም የከፍተኛ ትምህርት ስኮላርሽፕ በመስጠት በተለያዩ የሀገሪቱ ዩኒቨርስቲዎች ተመዝግበው በነፃ እንዲማሩ እያደረገ ነው፡፡ የተማሪዎቹን ጉዳይ ምፀታዊ የሚያደርገው ግን ከጦርነቱ መቀስቀስ በፊትም በርካታ ኤርትራዊያን በሀገራችን ነፃ ትምህርት ዕድል ተሰጥቷቸው ይማሩ የነበረ መሆኑ ነው፡፡ መንግስትም ከዜጎቹ በላይ ለኤርትራዊያኑ ተማሪዎቹ ደህንነትና ምቾት አብዝቶ ይጨነቅ እንደነበር የዚህ ሪፖርት አዘጋጅ ሳይቀር በኣካል ያየው ሃቅ ነበር፡፡ ሆኖም ተማሪዎቹ በወረራው ማግስት ትምህርታቸውን ሳይጨርሱ ከሀገር ከመባረር አልዳኑም፡፡

ኤርትራዊያን ወደ ኢትዮጵያ በጅምላ መሰደዳቸው የኢትዮጵያን መንግስት ያስደሰተ ይመስላል፡፡ መጠኑ ይለያያል እንጂ መንግስት የሚከተለው ፖሊሲ ቱርክ በሶሪያዊያን ስደተኞች ላይ ከምትከተለው ጋር ይመሳሰላል፡፡ የኤርትራው መንግስትም ጅምላ ስደቱ ሀገሪቱን በሰው ሃይሏ በተለይም በወጣቶች የማራቆት (emptying the nation) ፀረ-ኤርትራ ሴራ መሆኑን ይናገራል፡፡ በእርግጥም ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት በርካታ ኤርትራዊያን ከሀገር ተሰደዋል፡፡ መንግሰት የሚተገብረው ፖሊሲም ስደተኞችን በጣም ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ በየቀኑ ከ70 ያለነሱ ስደተኞች ድንበሩን እያቋረጡ ይገባሉ፡፡ ሀገራችንም በአሁኑ ጊዜ ከ93 ሽህ በላይ ኤርትራዊያን ስደተኞችን እያስተናገደች ትገኛለች፡፡ ከሶሪያዊያን ቀጥለው በአውሮፓ በብዛት ሁለተኛዎቹ ኤርትራዊያን ስደተኞች እንደሆኑም የዓለም ዓቀፍ ስደተኞች ድርጅት መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ መንግስት ፖሊሲ ግቦች የኤርትራን ወታደራዊ አቅም ማዳከም፣ ከውጭ የሚገባው የገንዘብ መጠን በዜጎች ስደት ሳቢያ እንዲመናመን ማድረግ፣ ኢኮኖሚዋም እንዲዳከምና ውስጣዊ ተቃውሞ እንዲቀሰቀስ ማድረግ እንደሆነ ይገመታል፡፡

ይህ የተናጥል ፖሊሲ ግን ምን ያህል ውጤታማና አዋጭ ነው? በኤርትራ ላይስ ምን ዓይነት ተጨባጭ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ የፀጥታና ማህበራዊ አንድምታዎች ይኖሩት ይሆን? የሚሉት ጥያቄዎች መነሳት ያለባቸው ናቸው፡፡ በንብረት ጉዳይ ላይ ተወሰነው ውሳኔ ሀገራችንን ብዙ ዋጋ ማስከፈላቸው አይቀርም፡፡

ለዚህም ተጠያቂ የሚሆነው የቀድሞው የመንግስት ዝርክርክና የተቻኮለ አሰራር ይሆናል፡፡ ፖሊሲው ወደፊት የሚያመጣው የደህንነት ስጋት ካለም ወደፊት የሚታይ ይሆናል፡፡ መንግስት ግን ወደ መሃል ሀገር የሚገቡት ኤርትራዊያንና የደንቡ ተጠቃሚ የሚሆኑት የደህንነት ስጋት የማይፈጥሩ መሆናቸው ተረጋግጦ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ሆኖም ግን በሚስጥራዊነቷና በመገለሏ “አፍሪካዊቷ ሰሜን ኮሪያ” በምትባለው ኤርትራ ውስጥ ሃቁን በምን መልኩ እያጣራው እንደሆነ ለማወቅ አዳጋች ነው፡፡

ስደቱ የኤርትራን መንግስት ፖለቲካዊ ዋጋ ቢያስከፍለውም የኢትዮጵያ መንግስት ፖሊሲ ግን ምን ያህል የኤርትራዊያንን ልብ ማሸፈት ይችላል የሚለው ወደፊት የሚታይ ቢሆንም ከድሮም እጁ አመድ አፋሽ የሆነው መንግስት ወጥነትና ግልፅነት ከጎደለው ፖሊሲው እምብዛም ትርፍ ያገኛል ብሎ ማሰብ አዳጋች ነው፡፡

ከኤርትራ በኩል ሲታይ ደግሞ በእርግጥ በርካታ ዜጎች በፈለሱ ቁጥር ከውጭ በሪሚታንስ (remittance) መልክ የሚገባው የገንዘብ መጠንም መቀነሱ አይቀርም፡፡ ይህ ደግሞ በውጭ ምንዛሬ ላይ ለሚተማመነው መንግስት የራስ ምታት ይሆንበታል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስትም ለዚህ ነው ባላንጣውን በቀጥተኛ ወታደራዊ ጥቃት ከመምታት ይልቅ በኢኮኖሚ ማዳከም የመረጠው፡፡ የኤርትራ መንግስት በገጠመው የምንዛሬ እጥረት ምክንያት ካናዳና እንግሊዝን ጨምሮ በተለያዩ ሀገሮች የሚገኙ ኤርትራዊያን የሁለት በመቶ አስገዳጅ ህገ ወጥ “ዲያስፖራ ታክስ” (diaspora tax) እንዲከፍሉ በማድረጉ ከመንግስታቶቹ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ውስጥ መግባቱ በተደጋጋሚ በሜዲያ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ስለሆነም አሁን በኢትዮጵያ የሚኖሩ ስደተኞችም በውድም በግድም የዚሁ ግዴታ ሰለባ ላለመሆናቸው ዋስትና የለም፡፡

ሀገሪቱ ከህዝብ ብዛቷ አንፃር ሲታይ በከፍተኛ ደረጃ ሕዝቧን ያስታጠቀችና ወታደራዊ ስልጠና የሰጠች (militarised state) እንደሆነች ይታወቃል፡፡ ሆኖም ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ቀደም ብሎ ስለ ግዙፍነቱ ይነገርለት ከነበረው የኤርትራ ጦር ሃይልም ባለፉት ጥቂት ዓመታት በርካታ ወታደሮች እየከዱ ወደ ኢትዮጵያና ሱዳን መሻገራቸው በእርግጥም የሀገሪቱን ወታደራዊ አቅም ከማዳከምም አልፎ ደህንነቷንም አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል፡፡

በዚህም ምክንያት ሳይሆን አይቀርም ከሶስት ዓመት በፊት ከኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ድንበር ዘለል ወታደራዊ ጥቃት ሲፈፀምበት ጦር ሰራዊቷ ምላሽ መስጠት ያልቻለው፡፡ አሁን ባለበት ሁኔታም ከኢትዮጵያ ጋር ፊት ለፊት ጦርነት የመግጠም እድሉ አናሳ ነው፡፡ የመንግስት ፖሊሲ ከሀገር የሚሸሹትን ባሉበት እንዲገደሉ የሚያዝ ቢሆንም የጦር ሰራዊቱ አመራሮች ግን በሰው በሽዎች የሚቆጠር ናቅፋ እየተቀበሉ ስደተኞችን ወደ ጎረቤት ሃገር በማሻገሩ ወንጀል እንደተዘፈቁ ዓለም ዓቀፉ የግጭት ጥናት ተቋም (International Crisis Group) ይገልፃል፡፡ በዚህ ሁኔታ ውሎ አድሮ ጦር ሰራዊቱም ሞራሉ እየላሸቀ ስለሚሄድ በጣሙን የመዳከም አደጋ አንዣቦበታል ማለት ይቻላል፡፡

አዲስ አበባ ያሉት የአቶ የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ መንግስት ተቃዋሚዎች ትጥቅ ትግል ስለማያደርጉ ኤርትራዊያን ስደተኞቹን የማደራጀትና የመመልመል ስራ አይሰሩም፡፡ በእርግጥ ኤርትራ የኢትዮጵያን መንግስት በነፍጥ የሚፋለሙ ሓይሎችን ብትደግፍም ኢህአዴግ-መራሹ መንግስት ግን ተመሳሳይ ፍላጎት ያለው አይመስልም፡፡ መንግስት ይህንን የማያደርገው ግን በኤርትራ ላይ ከሚከተለው ዋናው ፖሊሲ ጋር የሚጋጭበት ስለሆነ አይደለም፡፡ ምን ያህሎቹ ኤርትራዊያን ስደተኞች መንግስታቸው በሃይል እንዲወገድ ይፈልጋሉ? የሚለው ራሱ አጠያያቂ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የኤርትራ መንግስት በሃይል ቢገረሰስ ሀገሪቱን ሊረከብ የሚችል አስተማማኝ አማራጭ ሃይል እንደሌለም የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡

በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ኤርትራዊያን በመንግስታቸው ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ከማድረጋቸው ውጭ ኤርትራዊያን ስደተኞች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በተባበረ መንገድ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለማጋለጥ ሲጥሩ አይታዩም፡፡ ምናልባት ሀገር ውስጥ ላሉ ቤተሰቦቻቸው ደህንነት ስለሚሰጉ ይሆናል፡፡

በጦር ሰራዊቱ ውስጥም ቢሆን ከሶስት ዓመታት በፊት አስመራ ላይ ከታየው የጥቂት ወታደሮች የአጭር ጊዜ መጠነኛ አመፅጥ (mutiny) በስተቀር ምንም የአመፅ እንቅስቃሴ አይስተዋልም፡፡ በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ መንግስት በኤርትራ ላይ ያገኘው ፖለቲካዊ ድል የለም ማለት ይቻላል፡፡

ኤርትራዊያን በብዛት የሚገኙባቸው አፍሪካዊያን ስደተኞች ሜዲትራኒያን ባህርን እያቋረጡ በብዛት ወደ በአውሮፓ ከመግባታቸው ጋር በተያያዘ ኤርትራ በቅርቡ መልካም ዜና ሰምታለች፡፡ የአውሮፓ ህብረት የኤርትራ መንግስት ፍልሰቱን እንዲቀንስ 313 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ እርዳታ ሊለግስ ቃል ገብቷል፡፡

በእርግጥ የህብረቱ ውሳኔ ተግባራዊ ከሆነ በኢትዮጵያ መንግስት ፖሊሲ ላይ በረዶ የሚቸልስ ይሆናል፡፡ በአንፃሩ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ለሚሰቃየው የኤርትራ መንግስት ደግሞ ከሰማይ የወረደ መና እንደሚሆንለት አይካድም፡፡

የኤርትራ መንግስትና ሰራዊት ዋነኛ ኢኮኖሚያዊ ዋልታ የሆነውን የማዕድን ዘርፍ ሊያነቃቃው እንደሚችል ታዛቢዎች ይገምታሉ፡፡ ይህ ተግባራዊ ከሆነ በሂደትም በመንግስቱ ላይ የተጣሉ አንዳንድ ማዕቀቦች ሊነሱም ይችላሉ፡፡ ይህንን ሚስጢራዊ የተባለ ስምምነት ለመተግበርም የተለያዩ የህብረቱ ባለስልጣናት ኤርትራን ሲጎበኙ ሰንብተዋል፡፡

ይህ እንግዲህ አውሮፓ ህብረት የስደቱ ዋነኛ መንስዔ ኢኮኖሚያዊ ነው ብሎ ማመኑን ያሳያል፡፡ ውሳኔውን ተከትሎም እንግሊዝ ለኤርትራዊያን ስደተኞች ጥገኝነት መስጠት የቀነሰች ሲሆን ህገወጥ ኤርትራዊያን ስደተኞችንም ከሃገሯ ለማስወጣት በመዛት ላይ ስለመሆኗ የእንግሊዙ “ዘ ጋርዲያን” ጋዜጣ በቅርቡ ዘግቦ ነበር፡፡ የህብረቱ ውሳኔ ግን ከተባበሩት መንግስታትና ዓለም ዓቀፍ ሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ተቃውሞ እየገጠመው ይገኛል፡፡ በሀገሪቱ ያለውን ኢኮኖሚያዊ ችግር መካድ ባይቻልም ስደቱ በመብት ጥሰት ሳቢያ የመጣ መሆኑን ዓለም ዓቀፍ ሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ይገልፃሉ፡፡ በቅርቡም የተባበሩት መንግስታት ሰብዓዊ መብት አጣሪ ኮሚቴ የኤርትራን መንግስት በአስከፊ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ክፉኛ መከስሱ ይታወሳል፡፡

በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ነባራዊ ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው በጥቅሉ ሲታይ ግን የኢትዮጵያ መንግስት ፖሊሲ በኢሳያስ መንግስት ላይ ጠንካራ ፖለቲካዊ ንቃቃትን መፍጠር አልቻለም፡፡

ታዛቢዎችም በኤርትራ በኩል ተመሳሳይ አወንታዊ እርመጃ ሳይኖር የኢትዮጵያ መንግስት የተናጥል እርምጃ መውሰዱ የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም አያስጠብቅም በማለት ይተቻሉ፡፡ አሁንም ቢሆን ስደተኞችን መንከባከብ ተገቢ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የመንግስት አካሄድ በድምሩ ሲታይ ግን ከወረራው በፊት የነበረውን ሁኔታ በሙሉ ወደነበረበት ለመመለስ የሚፈልግ አስመስሎበታል፡፡ በእርግጥም የፖሊሲው ዓላማ በህዝቦች ወንድማማችነት ሽፋን በኤርትራው መንግስት ላይ የበቀል እርምጃ መውስድ ዋነኛ ታሳቢው ያደረገ ነው ማለት ይቻላል፡፡

«ፅናት እና እውነታው»

$
0
0

news ethiopia 2
ከአቡ ሙስአብ
ለኢንጅነር መሃመድ አባስ

ሰሞኑን በተለያዩ ማህበራዊ ድህረ ገፆች እዬተናፈሰ ያለውን ወሬ ለጎልጉል እንዲሁም ለዘ ሃበሻ ኔት የተሳሳተ መረጃ ያቀበሉት ኢንጅነሩ ቢሆኑም እንደ ሚዲያ መጀመሪያ ፅሁፉን ከመለጠፍ በፊት ይመለከተዋል የተባለውን አካል አነጋግሮ እውነታውን ማጣራት ተገቢ ነበር:: ሆኖም ያሳሆን በችኮላም ይሁን በግድዬለሽነት ፅሁፉ ተለጥፎ በአንዳንድ ሙስሊም ወገኖች ዘንድ ብዥታን የፈጠረ ሲሆን እውነታው ግን ከዚህ በፍፁም የተለዬ መሆኑ ለኢንጅነሩ ምናልባት ያልተረዱት እውነታ ወይም ግላዊ ጥላቻ ካላቸው ስለ «ፅናት» የማውቀውን እውነታ ለማቅረብ እሞክራለሁ።

ፅናት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ማህበር በሂጅራ አቆጣጠር 16/3/1435 የዛሬ አመት ከመንፈቅ አካባቢ የተመሰረተ ሲሆን

መስራቾቹም በሃገራችን ሙስሊሞችላይ መንግስት እዬወሰደ ካለው መራር ግፍና መከራ ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ የሆኑ በሃገራቸው በተለያዩ የዲን ዘርፍ አንቱታን ያተረፉ የብዙሃን ሂወቶችን ወደቀጥተኛው ጎዳና ወደ ኢስላም በአላህ ፈቃድ የለወጡ ታላላቅ ኡለማዎች ናቸው እንግዲህ እንደ ኢንጅነሩ ሃሳብ እነዚህ በችግሩ ምክንያት በሃገራቸው መብታቸው ተነፍጎ መኖር ስላልቻሉ ከሚወዱት ህዝብና ቤተሰቦቻቸው ተለይተው በተለያዩ ሃገራቶች በስደት የሚኖሩ ኡለማዎችን ከበሬ ወለደ ግላዊ ጥላቻቸው በመነሳት ቀጥታ ከህዋሃት ስውር ሴራ ጋር እነሱን ማያያዛቸውና መፈረጃቸው ምናልባት እንደሙስሊምነታችን እንድ ነገር ወደኛ በመጣ ጊዜ የነገሩን እውነታ ሳናጣራ በስሜት ተነሳስቶ መፈረጁ የታላቁን ቁርአን ህግ በመጣስ በሰዎቹ ላይ የውሸት ውንጀላ ማቅረቡ ከባድ ስህተት መሆኑን ቢረዱት መልካም ነው ።

እንግዲህ እነዚህ ብርቅዬ ኡለማዎቻችን ከሃገር ተሰደውም ቢሆን በሃገራቸው ሙስሊም ማህበረሰብ ላይ የሚደርሰውን ግፍና መከራ ስለሚያሳስባቸውና ስለሚያስጨንቃቸው «ፅናትን»ለመመስረት በቁ አላማቸውም እንደ ማለዳ ጮራ ፍንትው ያለ ምንም ብዥታ የሌለበት ነው ይኼውም በኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ላይ የሚደርሰውን ግፍና በደል በሁለንተናዊ መልኩ ችግሩን መካፈል ማለትም በዚህ ችግር ሳቢያ የተዘጉ መድረሳዎችን አገልግሎት እንዲሰጡ የተለያዩ ኡለማዎችን የወር ደመዛቸውን በመክፈል በተለይም ታዳጊ ህፃናት የቁርአንን ብርሃን አግኝተው እነሱም ያንፀባርቁ ዘንድ እስካሁን ድረስ በተለያዩ አካባቢዎች ይህ ነው የማይባል ያላሰለሰ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ

በተጨማሪም በትግሉ ምክንያት በተለያዬ ምክንያተ ችግር ላይ የወደቁ ወንድሞችን እና እህቶችን በተለይም የጠበቃ መክፈል ሳይችሉ ቀርተው በሃገራችን የነገሰው የፍርድ ድርቅ ምንም እንኳን ተስፋ አስቆራጭና «ከዝንብ ማር» የማይጠበቅ ቢሆንም ለነዚህ በተለያዩ ሃገራት እስርቤት ለሚሰቃዩ ታጋዮች የጠበቃ እና የቤተሰቦቻቸውን በመሸፈን የተለያዩ እገዛዎችን እያደረጉ ይገኛሉ ።

ሌላው ኢንጅነሩ የተሳሳቱት መረጃ ቢኖር እንዳሳቸው አባባል «በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ሴት እህቶቻችንን በማሳሳት ገቢያቸውን ያደልባሉ» ኢንጅነር ሆይ እንደርሰዎ ጭፍን ጥላቻ ሳይሆን የፅናት የገቢ ምንጭ ከመላው አለም የሚገኙትን ከማህበሩ አባላት ከወንዱም ከሴቶች እህቶቻችንንም በየወሩ ከሚሰበሰብ አነስተኛ የአባላት መዋጮና እንደዬ አባሉ በጎ ፍቃድ በሚነዬቱ (በሚለገሱ) ገቢዎች ከላይ የጠቀስኳቸወወን እና ሌሎች መሰል በጎ ተግባራቶችን በመስራት ትግሉን በሚችሉት መልኩ እዬደገፉ ይገኛሉ ።

ኢንጅነሩ ከመረጃ የራቁና ስለፅናት ያላቸውን ጥላቻ ያሳዩበት ሌላው ስህተት ደግሞ በውድና ጀግና ኮሚቴዎቻችን የተፃፉ መፅሃፎችን ማለትም የኡስታዝ ያሲን ኑሩን «ግብህን ቅረፅ »እና የታሪክ ሙሁሩን አህመዲን ጀበል«ፈርኦን የአምባገነኖች ተምሳሌት» የተሰኙትን መፅሃፍ በማሳተም ገቢውን ወደኪሳቸው አስገብተዋል ሲሉ ምንም መሰረት የሌለው ካባድ ስህተት ተስተው አሳስተዋል እውነታው ግን «ፅናት የሙስሊሞች ማህበር» ከ«ድምፃችን ይሰማ» ጋር በመተባበር «ድምፃችን ይሰማ በሳውዲ አረቢያ» ያሳተማቸውን መፅሃፎች የታሪክ ሙሁሩ አህመዲን ጀበል «ኒፋቅና የሙናፊቆች ማንነት ሲጋለጥ» እንዲሁም «በድምፃችን ይሰማ»የተዘጋጀውን «የተዘነበለ ፍትህ» የተሰኙትን መፅሃፍት ከምርቃቱ ጀምሮ መፅሃፍቶቹን ለአባላቱ በማስተዋወቅ እና በማሻሻጥ እንዲሁም «ድምፃችን ይሰማ በሳውዲ አረቢያ»በሚያወጣቸው የተለያዩ ፕሮግራሞች ላይ በመገኘት አጋርነቱን በተግባር ቢያረጋግጥም ኢንጅነሩ ግን መሰረት የሌለው የሐሰት ውንጀላቸውን ጭራሽ ይባስ ብለው «ድምፃችን ይሰማ በሳውዲ አረቢያን» ለመንግስት ለማጋለጥ ሲሰሩ ነበር ሲሉ ኮንነዋል። «ፅናት»በመነጋገር በመወያዬት ክፍተት ሊያመጡ የሚችሉ ጉዳዮችን በመተው በአንድነትና በወንድማማችነት በጋራ ወደምንጓጓለት የድል ምእራፍ ተሸጋግሮ ህዝበ ሙስሊሙ በሰላም በገዛ ሃገሩ በነፃነት እምነቱን ይተገብር ዘንድ ለሚተላለፉት የሰላማዊ ትግል ስልቶች ግንባ ቀደም ተሰላፊ በመሆን
«ከድምፃችን ይሰማ በሳውዲ አረቢያ»ጋር ያለውን ግንኙነት የበለጠ ማጠናከሩን ያሳያል።

እንግዲህ ኢንጅነሩ ከላይ የጠቀሱዋቸውን መፅሃፍት በፅናት ታትመል ሲሉ ነጭ ውሸትን ዋሽተዋል
ሌላውና ትልቁ ጉዳይ« ፅናት» «በድምፃችን ይሰማ » አመራር ላይ እንቅፋት ፈጥረዋል ብለው የወነጀሉት ሲሆን« ፅናት የሙስሊሞች ማህበር»እንደ ዋና ተግባር ከያዛቸው ስራዎቹ አንዱ ለድምፃችን ይሰማ ታዛዥ መሆኑን እና በሚወጡ የትግል መርሃዊ ግብሮችላይ በንቃት በመሳተፍ መተግበር መሆኑ እስካሁን ድረስ እያረጋገጠው ያለ እውነታ ነው ።

በመጨረሻም በተደጋጋሚ ብዙ የዋትሳፕ ግሩፖችን ከፍተው ሙስሊሙን ይበዘብዛሉ እያሉ ኢንጅነሩ ሲወቅሱ ነበር እውነታውግን በተለያዩ የዋትሳፕ ግሩፖች የተሰባሰቡ አባላቶችን በተለያዩ የማህበሩ መስራች ኡለማዎች አማካኝነት የአባላትን እውቀት ከፍ ሊያደርግ የሚችሉ የዲን ትምህርቶችን ማለትም
ተውሂድ
ፊቂህ
ተፍሲር
ሲራ
ብሉግ እና ሌሎችም መሰል የዲን ትምህርቶቹን በቀላሉ ለሙስሊሙ ኡማና ለአባላቶቹ በዋትስአፕ በማዳረስ ከማያልቀው የእውቀት ማእድ በማቋደስ ትውልድን በመነፅ ላይ ይገኛል ።
እንግዲህ ውድ አንባቢያን ስለፅናት የማውቀው ትክክለኛ እውነታ ይሄ ነው ምናልባት ኢንጅነሩ ደርሷቸው እውነታውን ሲረዱ የማስተካከያ ፅሁፍ እንደሚሰጡን ተስፋ አደርጋለሁ
ድል ፍትህ ለተጠማው ኡማ !!!

በወሎ በዝናብ እጥረት አዝመራ እየደረቀ ነው ተባለ * በአፋር በድርቁ የተነሳ በቀን ከ100 በላይ ከብቶች እየሞቱ ነው

$
0
0

Zehabesha News
afar
ዘ-ሐበሻ ከሰሞኑ ጀምሮ በአፋር ክልል ድርቅ እየተከሰተ መሆኑን; ዝናብም ከጣለ አንድ ዓመት እንደሞላው በተለይም ከብቶች እየሞቱ መሆኑን መዘገቧ አይዘነጋም:: ከወሎ አካባቢ ለዘ-ሐበሻ በድረሰው መረጃም እንዲሁ ዝናብ ባለመጣሉ የተነሳ የተዘራው እህል እየደረቀ የምግብ እጥረት እያስከተለ ነው::

ከወሎ አካባቢ የሚደርሱን መረጃዎች እንደሚያመለክተው መንግስት ይህን ለማስተባበል እየሞከረ ቢሆንም ችግሩ አግጦ እየታየ ነው::

በሌላ በኩል ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ የሚከተለውን ዘገባ አስተላልፏል:-

ባለፉት ሁለት ወራት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተከሰተው የዝናብ እጥረት የድርቅ አደጋ እንዳይከሰት ስጋት የፈጠረ ሲሆን ግብርና ሚኒስቴር በበኩሉ፤ የዝናብ እጥረት ቢኖርም የድርቅ አደጋና የምግብ እጥረት ስጋት የለም ብሏል፡፡
በአፋር ክልል ግን ሁኔታው ተባብሷል፡፡ በየቀኑ እስከ 100 የሚደርሱ ከብቶች በመኖና በውሃ እጥረት እየሞቱ መሆኑን ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡
የአፋር ክልልን አቋርጠው ወደ ጅቡቲ ወደብ ከሚጓዙ ሹፌሮች አንዱ ለአዲስ አድማስ እንደገለፀው፤ በመንገድ ዳርና ዳር በርካታ በጎችና ፍየሎች ሞተው ይታያሉ፡፡
በክልሉ ካለፈው ዓመት ሰኔ ወር ጀምሮ እስካሁን ድረስ ዝናብ የጣለባቸው ቀናት በጣት የሚቆጠሩ መሆናቸውን የጠቆሙት ምንጮች፤ የድርቁ ሁኔታ እየተባባሰ ቢሆንም በመንግስት በኩል ፈጣን እርምጃ አልተወሰደም ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል። የግብርና ሚኒስቴር ግን በዚህ አይስማማም። የዝናብ እጥረቱ የፈጠረው ድርቅ በእንሰሳቱ ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ከክልሉ መንግስት ጋር በመቀናጀት የመጠጥ ውሃና መኖ በማቅረብ ላይ መሆኑን ጠቁሞ ከብቶች እየሞቱ ነው ስለሚባለው ግን መረጃው እንደሌለው ገልጿል፡፡
በክልሉ የተከሰተው ድርቅ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመከላከል አስፈላጊው ሁሉ እየተደረገ ነው ያሉት የሚኒስትሩ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ም/ኃላፊ አቶ ወንድሙ ፍላቴ፤ “ሀገሪቱ በቂና አስተማማኝ የአደጋ መከላከል ዝግጁነት አላት” ብለዋል፡፡
ምንጮቻችን እንደሚሉት፤ በተለይ በአማራ ክልል በወሎ እንዲሁም በሐረር አካባቢ በተከሰተው የዝናብ እጥረት የድርቅ ስጋት አንዣቧል፡፡
ዘንድሮ በአገሪቱ የሰሜንና ምስራቅ እንዲሁም መካከለኛ ክፍሎች በአየር ፀባይ ለውጥ (ኤሊኖ) የተነሳ የዝናብ እጥረት መፈጠሩን የጠቆመው ግብርና ሚኒስቴር፤ በሰኔና በሐምሌ ይጠበቅ የነበረው ዝናብ መቆራረጥ ቀድሞ የተዘሩ ሰብሎች እንዳይበቅሉ ቢያደርግም ከነሐሴ ጀምሮ መዝነብ መጀመሩንና ቀጣይነት እንደሚኖረውም ገልጿል፡፡
“ገበሬዎች ዝናብ ሲዘንብ ጠብቀው ውሃውን በማቆር ለሰብሎቻቸው እንዲጠቀሙ እየተደረገ ነው፤ የግብርና ልማት ጣቢያ ሰራተኞችም የወትሮው የግብርና ስራ እንዳይስተጓጎል ያልተቋረጠ ድጋፍ እያደረጉ ነው” ብለዋል ም/ኃላፊው፡፡
በአሁኑ ወቅት ግብርና ሚኒስቴር የዝናብ እጥረቱን መቋቋም የሚችሉ የድንች፣ ስንዴ፣ ማሽላ፣ ጤፍና የመሳሰሉ ሰብሎችን ምርጥ ዘር በማቅረብ ችግሩን ለመከላከል ጥረት እያደረገ መሆኑንም ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡ በተለይ የሰብል አምራች በሆኑ አካባቢዎች የተከሰተው የዝናብ እጥረት በቀጣይ ዓመት የሃገሪቱ የምርት አቅም ይቀንሳል፣ ረሃብም ሊፈጠር ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ምንጮቻችን የገለፁ ሲሆን ግብርና ሚኒስቴር በበኩሉ፤ የተፈጥሮ ክስተቱ ፈታኝ ቢሆንም ሃገሪቱ በቂ የአደጋ መከላከል ዝግጁነት እንዳላት ጠቁሞ፣ በቂ ምርት ማግኘት እንደሚቻልና የምግብ እጥረት ስጋት እንደማይኖር አስታውቋል፡፡

ውድ ቴዲ አድሃኖም – ውሸትም ክብር አለው (ከስንሻው ተገኘ)

$
0
0

High-level Meeting on Disability and Development
ስንሻው ተገኘ

በምገኝበት አገር አብሮኝ የሚሰራ አፍሪካን-አሜሪካን ወዳጅ አፍርቻለሁ። ስለ ኢትዮጵያ አንዳንድ የታሪክ ግንዛቤዎች እንዲኖሩት ጉጉት ስላለው ደስ እያለኝ ከማውቃት አካፍለዋለሁ። አንዳንድ ጊዜ ግን የምደነግጠው እኔ ከማውቀው በላይ እየሄደ ስለ ኢትዮጵያ አዳዲስ ነገር፣ “ይቅርታ ምጥ ለእናቷ አስተማረች እንዳይሆንብኝ…” ይልና አዳዲስ ክስተቶችን ይነግረኛል። የትናንቱ ጥያቄው ደግሞ ልዩ ነበር። ይኸው ማይክል የምለው ጓደኛዬ “የኢትዮጵያ Gestapo ምን ስም አለው?” ብሎ አፋጠጠኝ። (በነገራችን ላይ ጌስታፖ ትልቁ የሂትለር የአፈናና የግድያ ተቋም ነበር። ይህ ከ 32,000 ሰራተኞች በላይ የነበሩት የስለላ ተቋምና ለአርያን ዝርያ ጠላት ናቸው የተባሉትን አይሁዶች፣ ኮሙኒስቶችና፣ የናዚ ፍልስፍና የሚቃወሙትን ሁሉ በስልት የሚያስወግድ ድርጅት በራሱ ጠንካራ ውስጣዊ መንግስት ነበር።)

በኢትዮጵያ የመለስን ራእይ ተከትሎ የተቋቋመ፣ ዳሩ ግን መቋቋሙ ብዙም ሳይወራ እንደ ጌስታፖ ያለ- ከቶም መብለጡን የማልጠራጠር- የስለላና የድምሰሳ ትልቅ ተቋም መፈጠሩን አልክድም። የአገራችንን የፖለቲካ ሁኔታ በቅርብና በጥልቅ የሚከታተለው አሜሪካዊ ግለሰብ ኢትዮጵያዊውን ጌስታፖ “አግአዚ ይባላል” አለኝ። ብዙ ንትርክ ለማንሳት አልፈለኩምና “አግአዚ” በአዲሱ ተቋም ውስጥ የሚገኝ ተወርዋሪ ሃይል- ጨካኝና ወደ አውሬነት የተጠጋ ስሜት ያላቸው ሰዎች ያሉት አካል መሆኑን ሳላወሳበት አልቀረሁም። የዚህ ታላቅ አካል ምርጥ የመሆኑ ምስጢር በጭካኔያቸውና በኢሰብአዊነታቸው ተመልምለው የገቡና ከጥቂት ስልጠና በኋላ ወደፍጹም “ባርባርነት” የተለወጡ ናቸው። ሂዱ ቀጥቅጡ። ከዛሬ ጀምሮ የምትጠቀሙበት ስልት በሞትና በህይወት መካከል የምታስቀሩበት፣ ጠላትን በሰውነቱ በሚያፍርበት ሁኔታ እንዲዋልል የምታደርጉበት ጥበብ ነው። …. ሌላም ሌላም ነው። ከወያኔ ገራፊዎች፣ መርማሪዎችና የህሊና ፖሊሶች እጅ ወጥተው ብዙ መናገር የሚያስጨንቃቸው ወገኖቻችን የሚነገር ብዙ ጉድ አለ።

በአንዳንድ የዚህ ሁሉ “ውርዴ” (መከራውን የጨለጡ) የሆኑ ግለሰቦች የሚዘከረው ሁሉ እስከወዲያኛው የሚቀፍፍና የሚዘገንን ነው።

በዚህ እድሜዬ ለእኔ ያንን በብዙ ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን የወል ሩካቤ ( በሴቶችም፣ በወንዶችም)፣ በኤሌክትሪክ የመጠበስ፣ የጥፍሮች መነቀል፣ አባለዘር ማምከን፣ ህሊናን የመበረዝና፣ ልብን የመስለብ ምርመራ ወዘተ… ማውሳት አይመቸኝም። የናዚዎችን ኮንሰንትሬሽን ካምፖች ያየሁ፣ በሰብአዊነት በመረበሽ ለቀናት ስረበሽ የነበርሁትን ሁኔታ ሁሉ የማስተውል እድሜ ጠገብ ሰው ያ ወደ አገሬ ይመጣል ብዬ አስቤ አላውቅም።

እንዲህ አይነት ሰው በሰው ላይ በሚያደርሰው ጭንቀትና ስቃይ ነፍሴን እያሰቃየሁ በንባብም ጭምር መከታተሌን ሳስብ እኔም እንደ አንዳርጋቸው ጽጌ “ሞትን የመሰለ ጸጋ የት ይገኛል?” እላለሁ፥ እሱ አራዊት በማይደርሱበት “ክርስቶሳዊ ስሜት” እኔ ደግሞ እንዲህ ያለውን ፍጹም በሆነ የአራዊት አለም የሚፈጽመውን ህሊናዬ ላይ በተፈጠረው ቁስል! በነገራችን ላይ የ21ኛው ክ/ዘመን አውራ ጀግናችን የሆነው አንዳርጋቸው ጽጌ ለእንግሊዙ አምባሳደር ሞትን ማግኘት አለመቻሉን የገለጠበት ቋንቋ ብዙ መጽሃፍ ይወጣዋል። የሚናገረው ብዙ ታሪክ አለው። የብዙ ፊልም ትረካ የሚገባው ነው። ሁላችንም እንደተከታተልነው ደግሞ “የፕሮፓጋንዳ ጊኒፒግ” ሊያደርጉት በመፈለግ በቴሌቪዥን ባቀረቡት ቁጥር ስቃይን የሚመሰክሩ በሲቃ ከአፉ የሚወጡ ቃላት እስከወዲያኛው የሚዘነጉ አይሆኑም። በዚያ ባለግርማ ሰውነቱ ላይ የደረሰው መከራ፣ በህሊናው ላይ የተካሄደው አስጨናቂ አገላለጥ፣ በሁላችንም መንፈስ ላይ የጣለው ጠባሳ በቀላሉ የሚይታይ አይደለም። በተኩሱና በሌላ ሌላው ምክንያት አራዊት ከአገራችን እንደናው ተሰደው የሰው አራዊት መተካታቸው የሚገርም አይደለም። እነሆ የአራዊት ስራ!

በሌላ በኩል ደግሞ የአንዳርጋቸው የአንድ ጊዜ ኢንተርቪው የተባለው አስራ አንድ ቅጥልጥል ፊልም ግጥምጥም ነው። በሁሉም ቅጥልጥል ፊልም የስቃይ ድምፅ ተከስቷል። አንዳርጋቸው በአማርኛም ሆነ በእንግሊዝኛ ሲናገር ማንንም የሚማርክና የሚያፈዝዝ ሲሆን ራሱን እንዲያወግዝ፣ ጓደኞቹንና ሌሎችን ፀረ-ወያኔ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን “ያለቦታውና ያለነገሩ” እንዲራገም ያስገደዱትን እንኳ በምን አይነት የመቃተት ስሜት እንደተናገረ አይተናል።

አይ ሰው የመሆን ጣጣ! እነዚህ ሁሉ ለፕሮፓጋንዳ የቀረቡ የአረመኔዎች ስራዎችና የኢትዮጵያ ህዝብ የወደቀበትን መከራ የሚመሰክሩ ናቸው። ለባረቀው ፕሮፓጋንዳ ደግሞ ለበረከት ስምዖን ልናጨበጭብ እንችላለን። (ሔኖክ የሺጥላ እንቅፋት አይምታውና “ሰሞኑን በፌስቡክ “በረከት ስምዖን ሞቶ አንዳርጋቸውን ሆኖ ተነሳ” የሚል ወደር የሌለው መጣጥፍ አቅርቦልናል። እንደእውነቱ ይበል የሚባልለት ቅኔ ነው። “ቅኔ” ሁሉ ቤት መምታት የለበትም!)

ለፕሮፓጋንዳ ብለው ባቀረቡት አንደኛው የአንዳርጋቸው መግለጫ በስተጀርባው የሚገረፍ ሰው ሃይለኛ ድምፅ ይሰማል። በቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት ከፓርቲው መስመር ውጭ የሆነ አመለካከት ያለው ሁሉ “የሕዝብ ጠላት” የመባል ጣጣ ነበረበት። ይልቁንም በግልጽ በስነጽሁፍ ረገድ የምእራቡ አለም ያወቃቸው እንደ ሶልቬትሲን፣ ቦሪስ ፓስተርናክ፣ ሶርኮብ ወደ “ጉላጎች” እየተላኩ ምድራዊ አበሳ እንዲቀበሉ ይደረጋሉ። በኋላ ጊዜ አመለካከቱ ከፓርቲው መስመር ውጭ የሆን ሁሉ የህዝብ ጠላትነት ካባ ይደርቡለትና አዳዲስ በተቋቋሙ የሩሲያ የፖለቲካ ሆስፒታሎች እየተባሉ በሚጠሩ “ሳይካትሪካል ሆስፒታሎች” ውስጥ ይገባሉ። ገሃነም፣ ሲዖል የሚባሉ ስፍራዎች መግለጫና ማስረጃ ያገኙት በእነዚህና እንደ ሻህ ኦፍ ኢራን፣ ራሳቸው አያቱላህ ኮሚኒ፣ ኢዲ አሚን የፍርሃት ሪፑብሊክ ሳዳም ሁሴን፣ የደቡብ አፍሪካ ቮርስተር ባቋቋሙአቸው የአፈና፣ የጭንቀትና የምድራዊ ስቃይ መቀበያ ስፍራዎች ደህና መገለጫ አግኝተዋል። የወያኔ አገዛዝ ደግሞ ከኮሎኔል ጎሹ ቀደም ብለው በትንቢት መልክ እንደገለጡት ከፖልፖት ያንሰያሪ አገዛዝ የከፋ ነው።

ማጋነን አይደለም። ማጋነን አልወድምም። በእኔ በኩል እንዲያውም እውነቱን በጠንካራ ቋንቋና በውል ማስረጃ (እያለኝ) ለማብራራት አቅም ማጣት የሚሰማኝ ነኝ። ወይም በወያኔ እስር ቤቶች የደረሰባቸውን ሁሉ ለመግለጥ በባህላዊ ሽብር ውስጥ መግባት ነው። የኢትዮጵያውያን ይሉኝታና ጠበቅ ያለው ባህል የወያኔ ምርመራና እስራት ምን ማለት እንደሆነ ባለ”ውርዴዎቹ” በአደባባይ ወጥተው እንዳይናገሩ የህሊናቸው ተቆጣጣሪ አድርጓቸዋል። የአሜሪካው ዲፓትርመንት አንድ መግለጫ በተወሰኑ እህቶቻችን ላይ ወያኔዎች ያደረሱትን ወራዳ ተግባር ሲገልጥ በሚችል መልኩ “ማስረጃ አለን” ይላል። የዚያን አይነት ስቃይ የደረሰባቸው እህቶቻችን አደባባይ ወጥተው ያንን ባይገልጡ የሚፈረድባቸው አይመስለኝም። ይህ ደግሞ ወያኔዎች በባህላችን ላይ የሚጫወቱት አንድ ታሪክ ነውር መደበቂያ ሆኖላቸዋል።

ካለኝና ካላችሁ መረጃ በመነሳት ይህን “የፖሊስ ስቴት” የሆነ መንግስት ጨምላቃ ገመና መዘክዘክ ይቻላል። ይኽ ደግሞ በስሜትና በአጫጭር ሃተታ የሚጻፍ ሳይሆን ለትውልድ በሚቀሩ መጻህፍትና ፊልሞች ቢሆን ይመረጣል። በአጭሩ ለመግለጥ ግን በዛሬው ቀን በዚህ ሰዓትና ዘመን እነደብረጽዮንና ጌታቸው አሰፋ ከሚመሩት “ፖሊስ ስቴት” የባሰ ገሃነም በአለም ላይ ያለ አይመስለኝም። ( ወያኔዎች ገና የመንግስትነትን ስም ከመቀዳጀታቸው በፊት በትግራይ ህዝብ ላይ ሲያደሩ የኖሩትን ስቃይ ከሚገልጸው “አሞራ” ከተሰኘው መጽሃፍ አንስቶ እስከ ካፕተን ተሾመ ተንኮሉና፣ የዱባይ ወንድማችን መግለጫ ቪዲዮ ድረስ ያለውን ሁሉ ተከታትያለሁ። ኢትዮጵያ ከፖልፖቱ ካምቦዲያ፣ ከሳዳም ሁሴን ኢራቅ፣ ከ… የባሰች የጭንቀት አገር ናት። ጓደኛ የላትም። እንደተከታተላችሁት ደግሞ ውዱ ጠቅላይ ሚኒስትራችን በፕሬዚዳንት ኦባማ ጉብኝት “ገለጣ”ው ላይ እስካሁን የተፈጸመው ሁሉ በ “ዲሞክራሲ ልምምድ” መልክ ነበር። በሩብ አመት አላለቅንም። ሁለተኛው ሩብ ምዕተ-አመት እየቀጠለ ነው።

ከገሃነም ያመለጡ እህቶቻችን፣ ወንድሞቻችንና ጓደኞቻችን የደረሰባቸውን ለመግለጥ ያፍራሉ፥ ይፈራሉ። በባህላዊው ይሉኝታና ሌሎች ሌሎች ምክንያቶች ተሸብበዋል። በዚህ መካከል ድፍረቱ በድፍረት ሳይቆጠር፣ የማስተዋል ችሎታችንን በሚደፍር አገላለጥ አደባባይ ወጥቶ የሚሰድብን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ተዎድሮስ አድሃኖም ሆኗል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ እንደሚነግረን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን እያንሸራሸረ በኢትዮጵያ የተሰራውን የልማት ስራ ሁሉ እያስጎበኘ ነው። በናዝሬት መንገድ ላይ ያለውን ግዙፍ የልማት ስራ አስጎብኝተውታል (የትግራይ አይሻልም ነበር?)። አንዳርጋቸው ደግሞ በዚህ ሁሉ ተመስጦ ኮምፒውተር እንዲሰጠው ጠይቆ መጽሃፍ ኣየጻፈ ነው። (ስላሴ ቅኔ አይሻልም ነበር?)

ቴዲ በአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ላይ እንዲህ ያለ አዛባ ጥሎ ደህና እንድንነጋገርበት አስችሎናል።

በብላቴን ጌታ ህሩይ፣ በሎሬንዞ ታእታዝ፣ በ አክሊሉ ሃብተወልድ፣ በዘውዴ ገብረ-ህይወትና ዘውዴ ገብረስላሴ፣ በይልማ ደሬሳ፣ በሃዲስ አለማየሁ ወንበር ላይ የተቀመጠው ቴዎድሮስ! የእኛንም ዘመን ጎሹ ወልዴን በኩራት እንጠቅሳለን!

ወያኔዎች መንግስት በያዙ ሰሞን፣ “ማዕከላዊ” ይባል በነበረው የምርመራ ማዕከል የታወቀ ገራፊ በቴሌቪዥን አቅርበው ለፕሮፓጋንዳቸው ተጠቅመዋል። “ውቃው” እየተባለ ይጠቀስ የነበረው “ገራፊ” ሲል የነበረውን ታስታወሳላችሁ? “ለምርመራ የሚቀርቡ ሰዎችን እንዲያውም ሻይና ቡና ኣየጋበዝሁ… በወንድማዊ ስሜት …” ይል ነበር። ቴዲ የረሳው “አንዳርጋቸውን ማታ ማታ ሸራተን ሆቴል ኣየጋበዝን … ራትና ሻምፓኝ እየ…” ስንቱን … ሲናገር ኣንዲህ ያለውን … ነገር ለምን ረሳ? በነገራችን ላይ እኔና ልጄ የምናውቀው አንድ ደራሲ በመጽሃፉ ውቃውን በማሰብ፣ “ደርግ በውሃ አጥምቆአል። ኣውነተኛው በእሳት የሚያጠምቀው በጊዜ ማህፀን ውስጥ ነበር። እነሆ ወያኔ ኢህአዴግ!” የሚል ቋንቋ ተጠቅሟል። (ከትዝታ በትዝታ የጠቀስኩት ነው።)

በዚህ ዘመን ከተገኙ ጀግኖች እናንተን በማስፈቀድ “አውራ ጀግናችን” የምለው አንዳርጋቸው እዉን መጽሃፍ ጻፈ? ይጽፋል? ወይስ አያ በረከት በሩን ዘግቶ ሁለተኛውን “ የሁለት ምርጫዎች ወግ” እየጻፈ ነው? የመጀመሪያ አልባረቀም ወይ? አለዚያ ሁላችንም እንደበረከት አድናቂና ብር ሰፋሪ አረብ ሳናነብና ሳይነበብልን እንድናደንቀው ልንገደድ ነው? (የበረከትን “ታላቅና ድንቅ” መጽሃፍ ባያነብበውም ኣንዳነበበው እንዲቆጠርለት የፈለገው ማን ነበር? የታላቁን ነቢይ ስም በመጠቀሙ ሆዴን ያመኛል።)

አንዳርጋቸው ጽጌ ያለበትን ሁኔታ የምናውቅ ይመስለኛል።

– ከአመት በላይ አካላዊና ሳይኮሎጂካል ግርፋትና እንደጥፍር መነቀል፣ መድፈቅና ሌላ ሌላው ስቃይ እንደደረሰበት ገጹና አነጋገሩ በግልጽ ይመሰክራሉ።

– የጄኔቫ ኮንቬንሽንና ሌሎች አለም አቀፍና ወያኔዎች ያወጡአቸው ህግጋትና ድንጋጌዎች ከሚያዝዙትና ከሚያራምዱት ውጭ ግለሰቡን ከጠበቃ፣ ከህጋዊ አማካሪዎች፣ ከቤተሰብ … አርቀው አስረዋል። አያያዙም ኢንተርናሽናል ውንብድና ነው።

– የፖለቲካ አክቲቢስቶች ከሆኑ ዳኞች ዘንድ እንኳን ያልቀረበ በመሰረቱ የጦር ምርኮና ነው፥ እነሱ እንዳቀረቡት።

– የእንግሊዝ አምባሳደር እንደምንም ብለውና ምን አልባትም የእንግሊዝ መንግስት አጠንክሮ በማስፈራራት አንዳርጋቸውን አነጋግረውታል። ለሰውየው በሰጠው ምላሽ ሞት ለእሱ በጣም እንደራቀና የሚፈልገውና የሚመኘው “ ሞትን” መሆኑን ገልጦላቸዋል። ይህንን ነው መጻሕፍት የሚወጡት የስቃይ ድምፅ ያልሁት። ወያኔዎች ከገባቸው ዛሬውኑ በወያኔዎችና በህዝባችን መካከል ወደመጨረሻው መተላለቅ የሚያመራ በሆነ ነበር። እግዚአብሄር ይመስገን ህዝባችን አልተጣደፈም።

– ከአምባሳደሩ ጉብኝት በኋላ የወጣው መግለጫ ይህ የእነ ቴዲ መንግስት በአስቸኳይ አንዳርጋቸውን አንዲፈታና ለደረሰበት የህሊናና የአካል ስቃይ ካሳ እንዲከፈል ነው።

እኔ ብሆን እነዚህንና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች በአደባባይ የምናውቃቸውን ጉዳዮች አነሳበት ነበር። ቴዎድሮስ አድሃኖምን በመሰረቱ ኣንዲያደግ የሚሻ የዋህ ማይም ይመስላል። ይሁንና አደባባይ ይዞ የሚወጣው ነገር ሁሉ እድገቱን የሚቀጭ ነው። ከቶዉንም ይኽ የሚጠቀስበትን ለሃኪሞች የሚገባ ስያሜ ከየት እንዳመጣ እጠይቃለሁ። አበበ ገላውን።

አንዲት ተናጋሪ ወፍ እንዲህ ያለ ወግ አላት። የእንግሊዙ ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና ፕሮፌሰር ለተማሪያቸው አንድ ጥያቄ አቅርበውለት መልሱን ይጠብቃሉ። ፕሮፌሰሩ ለፒኤችዲ ዲግሪው የመጨረሻ ፈተና ከተቀመጠው ወጣት ብዙ የምርምር ውጤቶችንና ረቂቅ የፍልስፍና ትንተና ይጠብቃሉ። እርግጥ መልስ ተሰጥቶአልና በየገጹ ቀያይ መስመሮች አጋድመዋል። እዚህም እዚያም። ተማሪው ይሞግታቸዋል። “ውሸት ነው፣ ትክክል መልስ አልሰጠህም ነው የሚሉኝ ሲል” ወዳጄ የጻፍኸውንም ሁሉ አንብቤአለሁ። ይሁን ኣንጂ “ውሸት ነው የጻፍከው። ዋሾ ነህ” የሚል ክብር ልሰጥህ አልችልም። አሉ የሚል አሳብ ከአንድ የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ መጽሄት አንብቤአለሁ። ታዲያ ይፈቀድልኝና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራችንን “ውሸት ተናግረዋል። ቀጣፊ ነዎ! አወናባጅና ዋጋ የማያወጣ ነገር ይዘው ገበያም ሆነወደ አደባባይ አይወጡ” ማለት ይቻላል። ደስ የሚለው የኦክስፎርዱ ፕሮፌሰር መግለጫ ነው “ዋሾ የሚል ክብር አልሰጥህም” ከዚያ በታች ምን አለ? ቢንጎ!

አለምነህ ዋሴ “ለመጀመሪያ ጊዜ”በይፋ ከሴት ጋር ስለተዳረችው ኢትዮጵያዊቷ ቤተልሄም ይርጋ ዘገበ

$
0
0

በሰሜን አሜሪካ በሁሉም ስቴቶች ተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ከተፈቀደ በኋላ አለምነህ ዋሴ ኢትዮጵያዊቷ ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ ከሴት አጋሯ ጋር ጋብቻ ፈጸመች ሲል ዘግቧል:: በድምጽ ያዳምጡት::

አለምነህ ዋሴ ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ ከሴት ጋር ስለተዳረችው ኢትዮጵያዊት ዘገበ

የአሳ ክትፎ አሰራር (Video)

$
0
0

መልክ በጉሮሮ ይገባል ይባላል:: ጤናማ ምግብ መመገብ ጤናማ ያደርጋል:: አሳ ለጤና ያለውን ጠቀሜታ ከዚህ ቀደም ብዙ ጊዜ አስተምረናል:: ዛሬ ደግሞ የአሳ ክትፎ አሰራርን አቅርበንላችኋል:: የ እህትቻንን ትምህርት በቭድዮ ተከታተሉት::

የአሳ ክትፎ አሰራር (Video)

የዘ-ሐበሻን የ2015 ዓመቱ ምርጥ ሰው ይምረጡ

$
0
0

zehabesha Person of The Year
ዘ-ሐበሻ በየዓመቱ እንደምታደርገው የአንባቢዎቿን ድምጽ በመሰብሰብ ለኢትዮጵያውያን ዘመን መለወጫ በዓል ዋዜማ የዓመቱን ምርጥ ኢትዮጵያዊ ትሸልማለች:: ወደ ኋላ መለስ ብለን እስካሁን በዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የዓመቱ ምርጥ ሰውን ክብር በተከታታይ ዓመታት ያገኙት መምህር የኔሰው ገብሬ;  ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ;  አንዱአለም አራጌ  እና  አብርሃ ደስታ  ነበሩ::

የዘንድሮውስ የዘ-ሐበሻ የዓመቱ ምርጥ ሰው ማን ይሁን? – ምርጫዎትን ከጥቂት ምክንያቶች ጋር አብረው በinfo@zehabesha.com ኢሜይል ወይም facebook.com/zehabesha ያሳውቁን:: በመደበኛ ስልክ ወይም በቫይበር በስልክ ቁጥር 612-226-8326 ወይም በስልክ ቁጥር 612-986-0557 ቴክስት ማድረግ ይቻላል::

ከሰሜን አሜሪካ ውጭ ያላችሁ ሰዎች በስልክ ቴክስት ለማድረግ ከፈለጉ ከፊት ለፊት የአሜሪካንን ማዞሪይ 01 ማስገባትዎን እንዳይረሱ:: የዘ-ሐበሻን የዓመቱ ምርጥ ሰው ይምረጡ::

ዘ-ሐበሻ ዕውነት ያሸንፋል!!


Sport: የፕሪምየር ሊጉ መክፈቻ –ቸልሲ ታሪክ አመለጠው

$
0
0

MAN UNITED 1-0 TOTTENHAM
ከጨዋታ በኋላ በኳስ ሜዳ
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መክፈቻ፡-

የጨዋታ ውጤት፡
ማንችስተር ዩናይትድ 1-0 ቶትንሃም
ቦርንማውዝ 0-1 አስቶን ቪላ
ኤቨርተን 2-2 ዋትፎርድ
ሌስተር 4-2 ሰንደርላንድ
ኖርዊች 1-3 ክሪስታል ፓላስ
ቼልሲ 2-2 ስዋንሲ

ቼልሲ ዛሬ በስታምፎርድ ብሪጅ ስዋንሲን ቢያሸንፍ ኖሮ 16 የመክፈቻ ጨዋታዎችን በማሸነፍ አዲስ ክብረ ወሰን ያስመዘግብ ነበር። አሁን 15 የመጀመሪያ ጨዋታዎችን በማሸነፍ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ክብሩን ይጋራል።

ቡድናቸው ማንችስተር ዩናይትድ ቶትንሃምን 1-0 የረታላቸው ሉዊ ቫንሃል ድሉ የልደት ስጦታ ሆኖላቸዋል። ከ1993 ወዲህ በልደታቸው ቀን ድል ሲቀናቸው ዛሬ የመጀመሪያው ነው። ጨዋታው ሲጠናቀቅ ከቢቲ ስፖርት ጋር በነበራቸው ቆይታ 64ኛ ዓመት ልደታቸውንም ድሉንም በሚወዱት ሬስቶራንት እንደሚያከብሩት ተናግረዋል።

የቼልሲው ግብ ጠባቂ ኩርቶዋ በአዲሱ የፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ቀይ ካርድ ያየ ተጫዋች ሆኖዋል። በቀዩ ካርድ ምክንያት በቀጣዩ ሳምንት ከማንችስተር ሲቲ ጋር አይሰለፍም።

ኦፊሴላዊ በሆነ ውድድር ላይ ለማንችስተር ዩናይትድ በመጫወት ባስትያን ሸዋንስታይገር የመጀመሪያው ጀርመናዊ ሆኖዋል።

ካይሊ ዎከር በራሱ ጎል ላይ ያስቆጠረው እና በአዲሱ የውድድር ዓመት የፕሪምየር ሊጉ የመጀመሪያ ጎል ሆኖ ለማንችስተር ዩናይትድ የተመዘገበው ጎል በፕሪምየር ሊግ ታሪክ በመክፈቻ ጨዋታ በራስ ላይ የተቆጠረ የመጀመሪያ ጎል ሆኖዋል።

አምስት ተጫዋቾች ከቶትንሃም ጋር በነበረው ጨዋታ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በውድድር ጨዋታዎች ለማንችስተር ዩናይትድ የመሰለፍ ዕድል አግኝተዋል። ፈረንሳዊው አማካይ ሞርጋን ሸንደርሊን፣ ሆላንዳዊው አጥቂ ሜምፊስ ዲፔ፣ አርጀንቲናዊው ግብ ጠባቂ ሰርጂዮ ሮሜሮ፣ ጣልያናዊው የመስመር ተከላካይ ማቲዮ ዳርሚያን እንዲሁም ተቀይሮ የገባው ሽዋንስታይገር። በጨዋታው ማንችስተር ዩናይትድ ያን ያክል ባይሆንም አሰልጣኝ ልዊ ቫንሃልን ጨምሮ ብዙዎች የ25 ዓመቱ የመስመር ተከላካይ ማቲዮ ዳርሚያን ባሳየው እንቅስቃሴ ተደስተዋል።

ከዋሽንግተን ዲሲ የጋራ ግብረሃይል የተሰጠ መግለጫ –“ያለነጻነት ፍትሕ የለም”

$
0
0

ሐምሌ ፴ ፳፻፯

በኢትዮጵያ አገራችን ፍትሕ ትንሽ ትልቁ ሙስሊም ክርስቲያን ሳይል ጥማቱን ከንግግር አልፎ በየአብያተ ክርስቲያናት ጸሎታቸውን ፣ በየመስጊዶች ሶላታቸውንና ጸሎታቸውን የሚያሳርጉት ስለ ፍትሕ በመጮህ ነው።የጥንቱን ታሪክ እንዳለ ብናቆየው እንኳ ባሳለፍነው ከሬት የመረረ ወያኔያዊ ስርዓት ፍትሕ በእውን ተከስታ ልትታይ ቀርቶ በዳሰሳና በሽታ እንኳ ደብዛዋ ጥፍቶ የ፺ ሚሊዮን ህዝብ የምኞት መዝሙር ሆና ፳፭ አመታትን አስቆጠረች። ዛሬም የፍትሕ ያለህ የሚለው የህዝባችን ጥያቄ ከዳር እስከ ዳር ቀጥሏል።

Ginbot 7

በርካቶች ህግ በማይከበርበት ፍርድ ቤት በወያኔ ተከሰው በወያኔ ተመስክሮባቸው በወያኔ ዳኛች፣ በወያኔ አቃቤ ህጎች፣ በወያኔ የግፍ ሰንሰለት አሳራቸውን የበሉ በዚያውም ያሸለቡ ደብዛቸው የጠፋ ቤቱ ይቁጠራቸው ለማለት ተገደናል። ለአሁኑ ግን በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ ሰሞኑን የተጠበቀ ምክንያቱም ወያኔ ከሚዘውረው ፍርድ ቤት ፍትህ ስለማይጠበቅ ነገር ግን የኮሚቴውን ንጹህነት የሚያውቅና ኮሚቴውን ነጻ ከማሰናበት ሌላ ላልጠበቀ ህዝብ በጣም አስደንጋጭ ነው። ስለሆነው በንጹሃን የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊዎች ላይ የተበየነውን ፍርደ ገምድል ብይን ለመቃወም እናም ለተበየነባቸው ጀግኖቻችን ሳይሆን ላንተ ይብላን ወያኔ ለማለት እንወዳለን። ከ፺፯ ዓመተ ምህረት ምርጫ ህዝባዊ እንቅስቃሴ በኋላ በሃይል ተጨፍልቆ ብልጭ ብልጭ ሲል የከረመው ህዝባዊና ኢትዮጵያዊ ወኔ ድንገት ሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ ከዓወሊያ ተቋም ገንፍሎ ምድሪቷን ያጥለቀለቀው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ትግል ስንቃኘው እንደዜጋ አድናቆት ስንቸረው በመብት ትግሉ ህይወት ያስከፈላቸውን አሳሳ፣ገርባ፣ኮፈሌዎችን፣እንዲሁም በፈሪ በትር የተቀጠቀጡትን አካል የጎደለባቸውን፣ ባኑዋር መስኪድ የጥቁር ሽብር ሰለባ የሆኑትን፣ለፍትሐዊ ትግሉ በህዝብ ተወክለው ህዝቡ ለጠየቀው ፫ ጥያቄዎች ከ፯ እስከ ፳፪ አመት ከመድረክ ጀርባ በተዘጋጀው የቀልድ ቲያትር መጋረጃ የሀሰት ፍርድ ለተወሰነባቸው ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ታላቅ ወገናዊ አክብሮት እንሰጣቸዋለን።

ትግሉ የጋራ ነው ድሉም እንደዚሁ፤ እኛ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የምንገኝ የጋራ ግብረ ሃይል በዚህ ሳምንት የሰማነው በባህሪው እውነት ከማያውቀው የወያኔ ፍርድ ቤት የጠበቅነው ነውና ባንደነቅም ሆኖም ግን እንዲህ አይነት በ፺ ሚሊዮን ህዝብ ላይ የተቀለደ ቀልድን በቀላሉ አንመለከተውም፤እንዲሁም ለጀግኖቹ ንጹሀኖች ፈጣሪ ያበርታቸው፣ቤተሰቦቻቸውን አምላክ ያጽናናቸው ስንል ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች ባጠቃላይ አብሽሩ የሚል መልዕክት እናስተላልፋለን።

ፍትሕ የተዘነበለችው ባጠቃላይ በኢትዮጵያውያኖች ላይ ነውና ለዚህ ሁሉ አብነቱ የፍትሕ ያለህ የሚል ጩኸታችን የሚቆመው ይህ ጸረ እስላም፣ጸረ ክርስቲያን፣ ጸረ አገር የሆነው ሰይጣናዊ ስርዓት በጸሎትም፣ በሁለገብ ትግልም፣ በተባበረ ህዝባዊ እምቢታም ተመንግሎ ነጻነታችንን ስንጎናጸፍ ብቻ ነው ብለን እናምናለን።ለዚህም በኛ በኩል ሰላም ላጣው ህዝባችን፣ፍትሕ ለጠፋበት ወገናችን፣በኩልነት ለምታኖረን ኢትዮጵያችን፣ ለሀይማኖት ክብራችን ባስገባን ቀዳዳ ሁሉ ገብተን የመጨረሻዋ እስትንፋሳችን እስክትቆም ድረስ አብረን ተባብረን ለመታገል በጋራ እንነሳ እንላለን።

ፈጣሪያችን አገራችንን ይጠብቅልን!!!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!
የዋሽንግተን ዲሲ የጋራ ግብረ ሃይል dcjointtaskforce@gmail.com

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ፍርድ ቤት ያልቀረቡበትን ምክንያት የማረሚያ ቤት ኃላፊ ቀርበው እንዲያስረዱ ታዘዘ

$
0
0

በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው እነ ዘመነ ካሴ በመከላከያ ምስክርነት የቆጠሯቸውና ለሦስት ጊዜያት የተጠሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ሐምሌ 29 ቀን 2007 ዓ.ም.ባለመቅረባቸው የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኃላፊ ያልቀረቡበትን ምክንያት ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲያስረዱና ምስክሩንም እንዲያቀርቡ ሌላ ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡

andargachew new picture

በሽብር ድርጊት ወንጀል ተጠርጥረው ዓቃቤ ሕግ ክስ የመሠረተባቸውን የእነ ዘመነ ካሴን ክስ እየመረመረ የሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት፣ ለሐምሌ 29 ቀን 2007 ዓ.ም. አቶ አንዳርጋቸውን መቅረብ አለመቅረባቸውን በችሎት ሲያረጋግጥ ግለሰቡ አልቀረቡም፡፡ ለምን እንዳልቀረቡ የማረሚያ ቤት ተወካይ ቀርቦ እንዲያስረዳ ፍርድ ቤቱ ቢጠይቅም ማንም ምላሽ ሊሰጠው አልቻለም፡፡

ፍርድ ቤቱ ሌላ ትዕዛዝ ሊሰጥ ሲል ከተከሳሾቹ አንዱ ተነስተው ማረሚያ ቤቱ የተለያዩ ምክንያቶች እየሰጠ መሆኑን ገልጸው፣ አቶ አንዳርጋቸውን የያዛቸው የፀረ ሽብር የጋራ ግብረ ኃይሉ በመሆኑ ማረሚያ ቤቱ የማያቀርብ ከሆነ ለእሱ ደብዳቤ እንዲጻፍላቸው ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ተከሳሹ በመቀጠልም፣ ‹‹ተከሳሹ ፍርደኛ ነው፡፡ ፍርደኛ ደግሞ የሚኖረው ማረሚያ ቤት ነው፡፡ ለምን ማረሚያ ቤቱ እንዲያቀርብ ጥብቅ ትዕዛዝ አይሰጠውም?›› በማለት ጠይቀዋል፡፡ ከታሰሩ ሦስት ዓመታት እንደሞላቸው በመግለጽ ቤተሰቦቻቸው ‹‹የአሸባሪ ቤተሰብ›› እየተባሉ የሚያከራያቸው በማጣታቸው፣ በየቦታው ተበትነው እየተሰቃዩ መሆኑን በመናገር ፍርድ ቤቱ አቶ አንዳርጋቸው በአጭር ቀጠሮ ቀርበው እንዲመሰክሩላቸው ጠይቀዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ እስከ ነሐሴ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ ብዛት ያላቸው ምስክሮችን እንደሚሰማና በአጭር ቀናት ማቅረብ እንደማይችል ገልጾ፣ ለጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በመኪና ሆነው አገሪቱ በልማት እያደረገች ያለውን ግስጋሴ እየጎበኙ መሆኑን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በቅርቡ መናገራቸውን የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

Source: Ethiopian Reporter Newspaper

ሰበር ዜና –ሪያድ ከተማ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ፀረ ወያኔ /ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ተቃውሞ ስትናጥ አደረች

$
0
0

sudi6(ዘ-ሐበሻ) ሰሞኑን የህወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ፍ/ቤት በሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የወሰደውን ኢፍተሃዊ ውስኔ በመቃወም ሪያድ ከተማ ውስጥ ትላንት አርብ ኦገስት 7 2015ምሸት ኢትዮጵያዊው ህዝበ ሙስሊም አንድነቱን ጠብቆ ተቃውሞውን አሰምቷል ። ቁጥሩ ከፍተኛ እንደሆነ ህዝብ የተገኘበት  ይህ ታላቅ ተቃውሞ የአካባቢውን ድባብ ለውጦት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። የተከሰተው ነገር በራሳችን እንደደረሰ ተሰምቶን በሶስት ቀን ውስጥ በተጠራ የተቃውሞ ጥሪ ይህን ያህል ህዝብ አንድነቱን ጥብቆ ለተቃውሞ በነቂስ መውጣቱየትግሉ አንዱነት ጥንካሬ መገለጫ መሆኑን የገለጹት ሼክ ሲዒድ አህመድ ህዝበ ሙስሊሙ በመንግስት ከባድ ፈተና እንደ ተጋረጠበት አውስተው ይህ ፈተና አዲስ ሆኖብን ሳንደናገጥትግሉን በበሰለና በስለጠነ መንገድ በማጠናከር እስከ ድል መቀጠል እንደሚገባ በቁጣ የወጣውን ህዝብ ሙስሊም በማረጋጋት በአባታዊ ምክራቸውን ገስጸዋል ።

ሼክ ሰዒድ በማስከተል አቡበከር በአንድ ወቅት በመንግስት ፀጥታ ሃይሎች ወህኒቤት ግፍ እይተፈፀመበት  « ፍ/ቤቱም የኛ ፤ ፖሊሱም የኛ ፤ አቅቤ ህጉም የኛ ፤ መርማሪውም የኛ ስለሆነየፈለከውን የመከላከያ ምስከር ብታመጣ ብትወጣ ብትወርድ ከፍርድ አታመልጥም እኛ ነን የምንፈርድብህ » ተብሎ በስረአቱ ካድሬዎች በምጸት ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በፊት ተነግሮትየነበረውን በተግባር ማየቱን ሼኩ ለተስብሳቢው በመጥቀስ በመሪዎቻችን ላይ የተፈፀመው ደባ ሊያስደንቀን እንደማይገባ ገልጸው የፍ/ቤቱን ኢፍታሀዊነት ለተሰብሳቢው በተጨባጭ አስረድተዋል። በውቅቱ በቁጣ ገንፍሎ የወጣውን ህዝብ ለማስተናገድ ተይዞ የነበረው ቦታ በመጨናንቁ የነበረውን የሪያድ የአየር ሙቀት በመቋቋም ከ ምሽቱ 1 ስዓት ጀምሮ እስከ ሊሊቱ9 ስዓት ድረስ በዘለቀው በዚህ  ፀረ ጭቆና ህዝባዊ ተቃውሞ ላይ አንዳንድ የስብሰባው ተሳታፊዎች  ህዝበ ሙስሊሙን በገዛ ሃገሩ መቆሚያ መቀመጫ ያሳጣውን የህወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግስረዓት እንዲያጠፋላቸው እያለቀሱ  ለፈጣሪያቸው  ፀሎት  «  ዱአ » አድርሰዋል ።  ሰሞኑን የህወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ፍ/ቤት በህዝበ ሙስሊም ተወካዮች ላይ ያሳለፈው ውሳኔሰረዓቱ በመላ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ላይ እየፈጸመ ያለው ሃይማኖታዊ ጭቆና ግፍና በድል አንዱ አካል መሆኑን የገለጹት እንዚህ የስብሰባው ተሳታፊዎች ከእንግዲህ ትዕግስታቸውመሞጠጡን ጠቅሰው  በዚህ አምባ ገነን ስረዓት ላይ የጀመሩትን ትግል እስከ መጨረሻ አጠናክረው ለመቀጠል በመወሰን የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።

በሳውዲ አረቢያ ድምጻችን ይሰማ ደጋፊዎች እያካሄዱ ባለው ሃይማኖታዊ ፀረ ጭቆና ትግል የህወሃትን/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግን ስረዓት የቦንድ ሽያጭና መስል የስረአቱን እንቅስቃሴበማሽመድመድ  የታወቁ  ግንባር ቀደምና ጠንካራ መሆናቸው  ይነገራል።  ኢንጂነር መሃመድ አባስ ከሪያድ ሳውዲ አረቢያ

የህወሓት‬ አገዛዝ በላይ አርማጭሆ የጀመረው የትጥቅ ማስፈታት ዘመቻ አሁንም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው

$
0
0

clash

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ እንደዘገበው አርበኞች ግንቦት 7 ጦርነት በከፈተባቸውና አሁንም እየተፋለመባቸው በሚገኙ አካባቢወች የሚኖሩ ደሀ ገበሬዎች ለንብረታቸው መጠበቂያ ጥረው ግረው ጥሪታቸውን በማሟጠጥ በገንዘባቸው ገዝተው በፈቃድ የታጠቁት የጦር መሳሪያ በህወሓት አገዛዝ እየተወሰደባቸው ይገኛል፡፡
ሰሞኑን በታች አርማጭሆ የተጀመረው ትጥቅ የማስፈታት የህወሓት መሰሪይ ተግባር ላይ አርማጭሆንም ጨምሮ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
በአጠቃላይ በአርማጭሆ እና በወልቃት ምድር ሰፍሮ የሚገኘው ህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት በህጋዊ መንገድ የታጠቀውን ገበሬ የጦር መሳሪያ መግፈፍ ዋነኛ ስራው ሁኗል፡፡

ላይ አርማጭሆ ከች ከንፈታ ቀበሌ ፈረስ ማጎሪያ ላይ ሰፍሮ የሚገኘው በህወሓት ቁጥጥር ስር የሚገኘው መከላከያ ሰራዊት ሰበብ አስባብ እየፈለገ የአካባቢውን ገበሬዎች ትጥቅ በመንጠቅ ስራ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል፡፡
የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ዘረኛ ቡድን ይቃወሙኛል ብሎ ከሚሰጋቸው ደሀ ገበሬዎች የሚነጥቀውን የጦር መሳሪያ ደጋፊዎቼ ናቸው ለሚላቸው ግለሰቦች እያስታጠቀ እንደሚገኝ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገልፀዋል፡፡
አርበኞች ግንቦ 7 በጎንደርና አካባቢው በህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት ላይ እየፈፀመው የሚገኘውን ጥቃት እና እያገኘ የሚገኘውን ሰፊ የህዝብ ድጋፍ ተከትሎ በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የህወሓት አገልጋይ በሆኑት ከፍተኛ ሹማምንቶችና የበታች ካድሬዎች መካከል ከፍተኛ ፍጥጫ ተፈጥሯል፡፡
የላይኞቹ የህወሓት አገልጋዮች ከከፍተኛ የህወሓት ባለስልጣናት የተሰነዘረባቸውን “የጎንደር ህዝብ እኛን ጠልቶ ለምን ከአርበኞች ግንቦት 7 ጎን ተሰለፈ?” የሚል ጥያቄ ለበታቾቻቸው በተለያዩ የግምገማ መድረኮች በማንሳታቸው ምክንያት ነው ፍጥጫው የተከሰተው፡፡

በባህር ዳር ቀበሌ 11 ወጣቶችና በፖሊሶች መካከል ግጭት ተፈጠረ * አባላቱ በገፍ እየከዱት በሚገኘው አየር ኀይል አለመተማመኑ ስር ሰዷል

$
0
0
Photo File

Photo File

አርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ እንደዘገበው የባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 11 አባይ ማዶ ወጣቶች አንድ አካባቢ ላይ ተሰባስበው በመጫወት ላይ እያሉ ፖሊሶች ድንገት መጥተው “ለምን አንድ ላይ ተሰብስባችሁ ቆማችሁ?” በማለት አምባጓሮ በመፍጠራቸው ነበር ግጭቱ የተነሳው፡፡
ፖሊሶቹ ወጣቶችን ከቆሙበት በኃይል አባረው ወደየቤታቸው ለማስገባት ሲሞክሩ ወጣቶቹ በፖሊስ ላይ የአጸፋ እርምጃ በመውሰዳቸው አንድ ፖሊስ ለከፋ ጉዳት እንደተዳረገ ታውቋል፡፡
የህወሓት አገዛዝ ለስልጣኑ የሚያሰጋውን የህብረተሰብ ክፍል እየመረጠ ትጥቅ ማስፈታቱን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ አምባገነናዊ ስርአት የግብአተ መሬት ጊዜውን በጥቂቱም ቢሆን ያራዝምልኛል ብሎ ከነደፋቸው እቅዶች መካከል አንዱ የሆነውን ህዝቡን ትጥቅ የማስፈታት ተግባር በታች አርማጭሆ ገበሬዎች ላይ በተለየ ሁኔታ በግፍ የሚያስታጥቀው የህብረተሰብ ክፍል ያለው ዘረኛው የህወሓት ቡድን በአማርኛ ተናጋሪው ገበሬ ላይ አሁን እየፈፀመ የሚገኘው የትጥቅ ገፈፋ ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ ሲያደርገው የቆየው መሆኑ ይታወቃል፡፡
አባላቱ በገፍ እየከዱት በሚገኘው አየር ኀይል ውስጥ ተፈጥሮ የቆየው አለመተማመን ስር ሰዶ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ታወቀ፡፡
ለሰላም ማስከበር ተልኮ ወደ ደቡብ ሱዳን ሊሄዱ የተመለመሉት የአየር ሀይል አባላት የደቡብ ሱዳን ጉዞ ተሰርዞ ወደ ሱማሊያ እንደሚሄዱ ስለተነገራቸውና በግምገማ በመወጠራቸው ምክንያት በርካታ አብራሪዎች፣ ቴክኒሻኖች እና ሌሎች የተለያዩ ክፍሎች ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች በመክዳት ላይ ናቸው፡፡
በመሆኑም በአየር ሀይል ውስጥ አለመተማመኑ ገደቡን አልፎ አብራሪዎች ለልምምድ በሚያበሩት አውሮፕላን ውስጥ የህወሓት አባላት ከጎን እንዲቀመጡ እየተደረገነው፡፡ በተጨማሪም አብራሪዎች ነዳጅ በሚሞሉበት ጊዜ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገባቸው ይገኛል፡፡

እየተቃወሙ ለመኖር…….!     ይገረም አለሙ

$
0
0

 

Arbegoch Ginbot 7የአርበኞች ግንቦት 7 ቃልን ወደ ተግባር የማሸጋገር እንቅስቅሴ ያሸበረው ወያኔን ብቻ አለመሆኑን ከተቃውሞው ጎራ ከሚሰማው የተቀዋሚ ተቀዋሚዎች ጩኸት እያየን ነው፡፡ ርጥቡ ሬሳ ደረቅ ያስነሳ አንዲሉ ይህ ሰሞነኛ ጩኸት የተረሳ እንዲታወስ የተተወ እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆኖ የአንዳንዶቹ ጯሂዎች የትናንት ማንነት ድብቅ ዓላማና ፍላጎት ጭምር  ጸሀይ እንዲሞቀው እየተደረገ ነው፡፡የማለባባስ አጉል ባህላችንን ተራምደው የይሉኝታ ገመዳችንን በጥሰው ስም እየጠቀሱ መረጃና ማስረጃ እያጠቀሱ አካፋን አካፋ ለማለት ለደፈሩ ወገኖቼ ያለኝን አክብሮት እገልጻለሁ፡፡ እያለባበስን አርባ አመት አልቅሰናልና በቃ ማለት ይኖርብናል፡፡

አደባባይ ወጥተው የሚጮኹትም ሆኑ ከኋላ ሆነው የሚገፉት የየግል ፍላጎታቸውም ሆነ  አንድ የሚያደርጋቸው ምክንያት ምንነትና አንዴትነት  በተለያዩ ሰዎች ተጽፋል፡፡ እውነት ናቸውና መስማማቴን እየገለጽሁ ያልተገለጸ የመሰለኝን ልጨምር፡

ስማቸው ብዙ ነው (ፖለቲከኛ ፣ጋዜጠኛ፣ነጻ ማህበር፣ወዘተ) መገኛቸው ሀገር ውስጥም ውጪም ነው፤ዓላማቸው ቢችሉ ምን-ይልክ ቤተ መንግሥት መታየት ካልሆነም በተቀዋሚነት ካባ አንድም ክብር ሁለትም ብር እያገኙ መኖር  ነው፡፡ ተባብሮ መስራት አይሆንላቸውም፡ እነርሱ የሚመሩት ወይንም በቀጥታም ሆነ በተዘዋወዋሪ የሚቆጣጠሩት ካልሆነ በስተቀር ማናቸውም ትግል (ሰላማዊውም የጠብ-መንጃውም) አንድ ርምጃ ሲራመድ ማየት አይፈልጉም፡፡

ሲያልሙት የኖሩትን ሥልጣን ለማግኘት የሚቻለው ደግሞ አንድም በምርጫ አንድም በጡንቻ ነው፡፡እነርሱ በሁለቱም መንገድ ለመሄድ አይችሉም፡፡(አንዳንዶቹ ሁሉን ሞክረው የከሸፈባቸው ናቸው፡፡) የምርጫው ነገር እንኳን ለእነርሱ ፓርቲ መስርተው በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው መቀመጫቸውን ሀገር ቤት አድርገው ለሚፍጨረጨሩትም አልተሳካም፡፡ ሀገር ቤት በሚገኙ ተቀዋሚዎች ተከልለው ያደረጉት ሙከራም አልተሳካም፡፡ ( የኢትዮጵያ ዴሞክራሲዊ ኃይሎች ህብረት ይጠቀሳል) የጡንቻውን መንገድ ቢያልሙትም አልሆነላቸውም፤አይሆንላቸውም፡፡ ከሌሎች ጋር ተባብረው በተቀዋሚነት ተከብረው ለመኖር፤ ከተቻለም  ተከልለውም ቢሆን ወደ ምኒልክ ቤተ መንግሥት ለመድረስ መከጀላቸው ባይቀርም መሪነቱን እነርሱ ካልያዙት ወይንም እንቅስቃሴው በቀዳሚነት የእነርሱን ዓላማና ፍላጎት የሚያሳካ ካልሆነ በጅ አይሉምና፡ በዚህም መንገድ ስንዝር መራመድ አልቻሉም፤አይችሉምም፡፡

ስለሆነም ያላቸው ምርጫ ላለፉት ሀያ አመታት ሲተገብሩትም ያየነው ተቀዋሚ እየተባሉ መኖር ነውና በሰላማዊ ትግል በተአምር፣ ወይንም በተቃራኒው መንገድ በጦር  የወያኔ ሥልጣን ቢቀየር ይህን ስለማያገኙ ጠንከር ያለ እንቅስቃሴ ሲጀመር ፈጥነው ይዘምቱበታል፡መገንባቱን ሳይሆን ማፍረሱን፣ ማቀራረቡን ሳይሆን ማለያየቱን፤ መደገፉን ሳይሆን ማደናቀፉን የተካኑበት ናቸውና እስካሁን በአብዛኛው ተሳክቶላቸዋል፡፡ ዛሬ ግን ተነቅቶባቸዋልና ድብቅ ማንነታቸውን ያጋልጡ፣ ቀሪ ህይወታቸውን ያበላሹ  ለልጆቻቸው መጥፎ ስም ያቆዩ እንደሁ አንጂ የሚሳካላቸው አይመስለኝም፡፡

ፊሺካው ተነፍቷል ጦርነቱ ተጀምሯል በተባለበት ማግስት በፍጥነት ተጠራርተው ከጀመሩት ጫጫታ ውስጥ አንዳችም መፍትሄ ጠቋሚ ሀሳብ አለመኖሩ ከመነሻው በተቃውሞው ሰፈር ይገኙ እንጂ ለውጥ ናፋቂ ሳይሆኑ ወሬ አሟሟቂ፤ የተግባር ሳይሆን የምላስና የብዕር ታጋዮች  መሆናቸውን የመሰከረ ነው፡፡ ትናትም ሆነ ዛሬ ሰላማዊውንም ሆነ የጠብ-መንጃውን ትግል የሚቃወሙት ተቀዋሚ እየተባሉ ሆነው ሳይሆን እያስመሰሉ፣  እየታገሉ ሳይሆን እያውደለደሉ ክብርም ብርም የሚያገኙበት ሜዳ እንዳያጡ በመስጋት ነው፡፡  ግን ለምን? እነርሱ በተቃዋሚነት እንዲኖሩ የወያኔ እድሜ  መርዘም አለበት?  የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንባ ገነን አገዛዝ ውስጥ መኖር አለበት ?ከእነርሱ ፍላጎትና ከሀገር ነጻነት የቱ ይበልጣል?፤የቱ ይቀድማል፡? በእውነቱ አሳፋሪም በታሪክና በትውልድ የሚያስጠይቅም እኩይ ተግባር ነው፡፡

ይህ አድራጎት ዛሬ የተጀመረ አይደለም፤ እንደውም ከአንዳንዶቹ ጋር አብሮ ያረጀ ነው፤ ትንሽ የቅርብ ግዜ ማሳያዎችን አንመልከት፡

ማሳያ አንድ፤  በ1992 ዓም ኢዴፓ የሚባል ፓርቲ ተመስርቶ በአጭር ግዜ ሰፊ እንቅስቃሴ አደረገና እውቅና አገኘ፤  በዚህ መልኩ እየገነነ ከቀጠለ በግልም ሆነ  በድርጅት እስከመኖራቸውም እንዳይረሱ የሰጉት እነዚህ የወያኔም የተቀዋሚውም  ተቀዋሚዎች የለመዱትንና የተካኑበትን የማደናቀፍ ዘመቻቸውን ከፈቱበት፤ የፓርቲው አመራሮች ቢቸግራቸው በእነዚህ ሰዎች በተወጠነውና በምድረ አሜሪካ በተዘጋጀ ጉባኤ ተካፋይ ሆነው የኢዴኃህ አባል ሆኑ፡፡ ሊቀመንበሩ ዶ/ር አድማሱ ገበየሁ የህብረቱ ዋና ጸኃፊ ለመሆን ቢበቁም  ከመነሻው የተገባው በእምነት ሳይሆን  የሰዎቹን አፍራሽ ዘመቻ በመፍራት ነበርና ብዙም ሳይቆይ ፓርቲው ከህብረቱ ወጣ፣ መኢአድ ለጉባኤ የላካቸው አባላቱ ሀገር ቤት ሳይመለሱ ነበር ጉባኤው በእነዚህ ሰዎች ሴራ መጠለፉን ገልጾ  የጉባኤውን ሂደት በመቃወም ጥያቄ አቅርቦ፤ጥያቄው ካልተመለሰ እንደማይቀጥል ያስታወቀው፡፡ ኢዴኃህም የቡና ውሀ ሆነ፡፡ (በምርጫ 97 የሰሩትም የሚረሳ አይደለም፡፡)

ማሳያ ሁለት ..ቅንጅት ሲመሰረት  መሪነቱን እንያዝ እንዳይሉ ከመስፈርቱ አንዱ በሀገር ቤት ያሉ የሚል በመሆኑ፣ እነርሱ ደግሞ አብዛኛዎቹ ከሀገር ውጪ ስለሚኖሩና  ሀገር ቤት ፓርቲ ስለሌላቸው አልተቻላቸውም፤ በእጅ አዙር አንዳይቆጣ ጠሩት ከቅንጅት የወቅቱ ጥንካሬ አንጻር ለዛ የሚያበቃ አቅም አልነበራቸውም፡፡ እናም በሚያውቁት በለመዱትና በተካኑበት ስልትና መንገድ ብዙ ዘመቱበት፤ ወዳጅ መስለው በመቅረብ መጥፎ እየመከሩ አቅጣጫ ለማሳት፣ በአመራሩ መካከል መጠራጠር ለመፍጠር ብሎም ቅንጅትን ከመረጠው ሕዝብ ለማጣላት ከውጪም በሀገር ውስጥም በመልእክተኞቻቸው በኩል ብዙ ሰርተዋል፡፡ የቅንጅት አመራሮች ለፓርላማ ሳይሆን ለወህኒ ሲዳረጉም ተደስተዋል፡፡

ማሳያ ሶስት፤የቅንጅት አመራሮች ከእስር ከወጡ በኋላ የፈጠሩት አለመግባባት እስከ መለያየት እንዲያደርሳቸው ከሁለቱም ወገን ደጋፊ መስለው በመሰለፍ የእብድ ገላጋይ ድንጋይ ያቀብላል አይነት የተጫወቱት አፍራሽ ሚና ቀላል አይደለም፡፡ ይህን ለማረጋገጥ በወቅቱ በዌብ ሳይቶች  በጋዜጦችና በማህበራዊ ድረ-ገጾች ወዘተ ላይ የተጻፉትን ማየት በየፓልቶኩ በያራዲዮው የተነገሩትን ማደመጥ በቂ  ነው፡፡

ማሳያ አራት፤  የቅንጅት ከፊሉ ወገን ተሰባስቦ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ሊቀመንበሩ አድርጎ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ የተሰኘ ፓርቲ መስርቶ በአጭር ግዜ በሀገር ውስጥም ሆነ አውሮፓና አሜሪካ ሰፊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የተበለጥን ሰይጣናዊ ስሜታቸው አገርሽቶ የከፈቱት ዘመቻም የሚረሳ አይመስለኝም፡፡(በአብዛኛው የሚዘምቱት ሀገራዊ ድርጅት ላይ ነው)

አንድነት የቅንጅት ወራሽ መሆኑና ( ቅንጅት የሚለው ስምና ሁለት ጣት ምልክት ወያኔዎችን ያባንናቸዋል)ከጅምሩ ያገኘው ተቀባይነት ያሰጋው ወያኔ ወ/ት ብርቱካንን ዳግም ሲያስር ለእነዚህ ሰዎች ፌሽታ ነበር፡፡አጋጣሚውን በመጠቀምም ቀሪዎቹን አመራሮች ከቅርብም ከሩቅም ወዳጅ መስለው በመቅረብ በምክርም በገንዘብም በሌላ ሌላውም ከወዲያ ወዲህ እያላጉ የት ይደርሳል የተባለውን አንድነት ሽባ አደረጉት፡፡ የእነርሱም የወያኔም ሴራ ተደማምሮ አንድነት አምስት አመት ሙሉ ታሞ በምርጫ 2007 ዋዜማ ግብአተ መሬቱ ተፈጸመ፡፡ እናቃብራችሁ አንኳን አላሉም፡፡

ማሳያ አምስት ሰማያዊ,- ይህኛውም ፓርቲ በ2004 ዓም ተመስርቶ በአጭር ግዜ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ  ለስድስት አመት የተዘጋን የሰላማዊ ሰልፍ ክልከላ በር አስከፈተ ተብሎ ስሙ ሲናኝ የሌላው መግነን የእኛን መኮስመን ያስከትላል የሚል ከይሲ አስተሳሰብ ያላቸው እነዚህ ወገኖች ዘመቻ የጀመሩት ከመቅጽበት ነው፡፡ ይሉት ቢያጡ  ሰበብ ቢቸግራቸው ከሌሎች ጋር ተባብሮ መስራት አለበት ብቻውን የትም አይደርስም አሉ፡፡ አልተሳካላቸውም እንጂ ይህን ሰበብ አድርገው በፓርቲው ውስጥ ክፍፍል እስከመፍጠር ደርሰውም እንደነበር ይታወቃል፡፡ሌላም ሌላም መጥቀስ ይቻላል፡፡አንድ ፓርቲ ጠንክሮ እንዳይወጣ ወይንም ፓርቲዎች ተባብረው በግንባርም ይሁን በውህደት ጠንክረው እንዳይታገሉ ካደረጉዋቸው ምክንያቶች አንዱ የእነዚህ ወገኖች ሴራ ነው፡፤

እነሆ አሁን ደግሞ የተለመደውንና መታወቂያቸው የሆነውን አፍራሽ ተግባር ጀመሩ፡፡  የኢሳይያስ ማንነትና የሻዕቢያ ምንነት የታያቸው ዛሬ ነው ? ጅብን ሲወጉ በአህያ ተከልሎ እንደሚባለው  ይህ ሰበብ ነው፡፡  ዋና አላማው ኢሳይያስንና ሻዕቢያን ከለላ አድርጎ በነጻነት ትግሉና ታጋዮቹ ላይ መዝመት ነው፡፡

ተቃውሞአቸው ምንድን ነው፡፡

የሚያነሱት ነገር ለክርክር እንዳይቀርብ ለመለስ ምትም አንዳይመች ተቃውሞአቸው ስልታዊ  መንገዳቸው የጎንዮሽ ነው፡፡የሚደግፉትም ሆነ የሚቃወሙት ነገር በግልጽ አይታወቅም፤ ዛሬ ያመሰገኑትን ነገ ይኮንኑታል፤ባከበሩ ማግስት ያዋርዳሉ፤ የእነርሱ የሆነ ሁሉ ቅዱስ በተቃራኒ የቆመ ወይም ለእነርሱ ያልተመቸ ሁሉ ርኩስ ነው፡፡ እነርሱ ሞክረውት አላስኬድ ባላቸው መንገድ ሌሎች መሄድ ከቻሉ በቅናት ያራሉ፡ እነርሱ ሊወዳጁት ያልቻሉትን ሰው ወይንም ድርጅት ሌሎች መወዳጀት ከቻሉ የውግዘት ናዳ ያወረዳሉ፤ እነርሱ ሞክረውት ያቃታቸውን ሌሎች ለማሳካት ከጀመሩ የማጥላላት ጥሩንባ ይነፋሉ፤ በታላቁ መጽኃፍ ትንቢተ ኢሳይያስ  ም፣48 ቁ.22 ላይ “ክፉዎች ሰላም የላቸውም” ተብሎ  እንደተጻፈው በክፋታቸው ለራሳቸው ሰላም አጥተው ሌላውንም ሰላም ያሳጣሉ፡፡

የሚሰሩትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ተብሎ አንዳይተው፣ ዓላማችን ላሉት ስኬት አስበው ወቅት ጠብቀው የሚሰሩ መሆናቸውን አይተናል እያየንም ነው ፡፡ የተለመደ ተግባራቸው ነው ተብሎ ተንቆ አንዳይተው ብእራቸውም ሆነ ምላሳቸው የሚረጨው መርዝ ለትግሉ ውጤታማነት ሆነ ከድል በኋላ ለሚፈለገው መረጋጋት ብሎም  ለኢትዮጵያውን አንድነት ጠንቅ ነው፡፡ መፍትሄው  አላማችሁ ገብቶናል በቃችሁ ማለት መቻል ነው፡፡ይሄ ካልበገራቸውም ማንነታቸውን


“በኢህአዴግ ስር ሁኖ እየተሰቃየ የሚገኘው የኢትዮጵያ ህዝብ ወደደም ጠላም ይህ ስርዓት እስከቀጠለ ድረስ መስዋእትነት መክፈሉ አይቀርም ”–ትህዴን

Next: Hiber Radio: የሕወሃት መሪዎች የስልጣን ሽኩቻ ወደ ሀይል ግጭት ሊያመራ ነው መባሉ ፣ መድረክ አገዛዙ በግብዣ ጋጋታ የህዝብ ንብረት ማባከን አቁሞ በድርቅ ለተጎዱት እንዲደርስ ጠየቀ ፣የአሜሪካና የአውሮፓ የህዝብ እንደራሴዎች አቶ አንዳርጋቸው በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቁ፣ ጀርመናዊው የፓርላማ አባል ሁለት ሐበሻ ስደተኞችን ስላስጠጉ የግድያ ዛቻ ደረሰባቸው፣ በእስራኤል ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ በልዩ የሆድ በሽታ መጠቃታቸው፣ ቃለ መጠይቅ ኦባማን በጉብኝታቸው ልትገል በሚል የፈጠራ ክስ ከተከሰሰው ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለ ፣ከአረና የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አምዶም ገ/ስላሴ ጋር ቃለ መጠይቅ እና ሎሎችም
$
0
0

arbegnoch ginbot 7
መስዋእትነት አይቀሬ ነው ታሪክ ሰርቶ ማለፍ ግን ክብር ነው!!

የትህዴን ርዕሠ አንቀጽ

በአሁኑ ግዜ በአገራችን ህዝብን የሚወክልና በህዝብ የተመረጠ መንግስት ሳይኖረን ይህንን እድል ለመፍጠር አጋጣሚውን ያገኙ ቡድኖች ሆኑ ግለሰቦች ከህዝብ ፍላጎት እና ከሃገር ጥቅም ይልቅ የግል ጥቅማቸውን‘ና የባእዳኖችን ፍላጎት በማስቀደም ያገኙትን የተለያዩ አጋጣሚዎች በመጠቀም የህዝብን ስልጣን እየነጠቁ ለህዝብ እና ለሃገር የቆሙትን እየገፉ እና እየገደሉ በጉልበት መንግስት ነን በማለት እስካሁን ስልጣን ላይ ይገኛሉ።

የኢህአዴግ አመራሮች ህዝብን የማገልገል ስራ ሳይሆን የየራሳቸውን ጥቅም በማስጠበቅ እና ስልጣን ላይ ወጥተው የህዝብን ሃብት ለግል ጥቅማቸው እያዋሉ፤ ህዝብን እንዳሻቸው እየጨቆኑ፤ እያንገላቱና እየጨፈጨፉ ባጠቃላይ ለትውልድ የሚተርፍ መጥፎ ታሪክና የማይረሳ የጥፋት አሻራ ጥለው እያለፉ መሆናቸው ግልፅ ነው።

የደርግ ስርዓት በህዝብ ልጆች መስዋእትነትና የአካል-መጉደል ከተደመሰሰ በኃላ ስልጣን የሙጥኝ ያለው ፀረ ህዝብ የኢህአዴግ ስርዓት ፋሺስታዊው የደርግ ስርዓት ለሃገር እና ለህዝብ የቆሙትን ንፁኃን ዜጎች በመጨፍጨፍ እንደሚታወቀው ሁሉ አሁን በአገዛዝ ላይ ያለው የኢህአዴግ ስርዓትም በፖለቲካ አመለካከታቸውና ደስ አላሰኙኝም በሚል ንጽሁሃን ዜጎች በድብቅና በግልፅ ብመጥፋት የራሱ የሆነ ጸረ ህዝብ እና ጸረ ሃገር የሆኑ መለያዎች አሉት።

የኢህአዴግ ስርዓት ካለፉት ጨቋኝ ስርዓቶች ለየት የሚያደርጉት በርካታ እኩይ ባህሪያቶች እዳሉት ግልጽ ነው። ስርአቱ የሚታወቅበት መቼም ሊለወጥ እና ሊሻሻል የማይችል አያሌ ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ ህዝብ አጀንዳዎች እንዳሉ ሆነው በተጨማሪም አለቆቹ በባእዳን የተነገረውን ትእዛዝ ለማስከበር ሲሉ ለባእዳኖች ባለመገዛቱ የሚታወቀውን የኢትዮጵያ ህዝብ ለመበቀል፤ኢትዮጵያን ለመበታተን’ና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የተዘጋጀውን የተሳሳተ ታሪክ ይዞ በተለይም ለስርዓቱ አልገዛም ባለው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ቂም ይዞ ለመበቀል ከፍተኛ በጀት እና የሰው ሃይል መድቦ ለጥፋት መነሳቱ የስርዓቱ ባህሪ ነው።

እንደሚታወቀው በመሳሪያ ጋጋታ እና በአፋኝ ህግ ብዛት ሃሳቡን እና ተቃውሞውን እንዳይገልጽ የተከለከለው የኢትዮጵያ ህዝብ ለስርዓቱ ያለውን እምቢተኝነት እና ተቃውሞ ባገኘው አጋጣሚ እየገለጸና ከዛም አልፎ የስርዓቱ አስመሳይ የምርጫ ሂደት ላይ ባለመሳተፍና ባለመምረጥ በስርዓቱ ላይ ያለውን ተቃውሞ ገልጿል። በመሆኑም የኢህአዴ ስርዓት በሚቀጥሉት 5 ዓመታት በስልጣን መቆየቱ የቂሙን ደረጃ የት ያደርሰዋል? ስልጣኑንስ የሚጠቀመው እውነት ሃገር እና ህዝብን ለመጥቀም ነው? ወይስ የተነሳለትን ኢትዮጵያን ህዝቧን የመበታተን ዘመቻውን አጠናክሮ ለማስቀጠል?

ለማኛውም! አጥፊ እና ጠፊ አብረው መኖር እንደማይችሉ ሁሉ መቼም ቢሆን ህዝብ ከኢህአዴግ ስርዓት ጎን ሊቆም አይችልምና ህዝቡ ለኢህአዴግ ባለመምረጡና ከህወሓት-ኢህአዴግ ጎን ባለመቆሙ ምክንያት የተለመደ የኢህአዴግ ቂም በቀል እርምጃ በእጥፍ መቀበሉ አይቀሬ ነው፤ ወያኔ በስልጣን እስካለ ድረስ በህዝቡ ላይ የሚደርሰው የጥፋት ዘመቻ፤ እስራት፤ ድብደባ፤ አፈና፤ በኑሮ ውድነት መሰቃየት፤ ከኖረበት መፈናቀሉ ሌላም ሌላም በከፋ ሁኔታ ይቀጥላል።

በኢህአዴግ ስር ሁኖ እየተሰቃየ የሚገኘው የኢትዮጵያ ህዝብ ወደደም ጠላም ይህ ስርዓት እስከቀጠለ ድረስ መስዋእትነት መክፈሉ አይቀርም ምክንያቱ የእኛ ከኢትዮጵያውያን ታሪክ አንጻር ሲታይ ለውጭ ወራሪውችም ሆነ ለውጥ ጸረ ህዝብ ስርአተወች አሜን ብሎ ተገዝቶ ኣይውቅም ስለዚህ መቼም ቢሆን አይቶ እንዳላየ መሞትን ይመርጣል ተብሎ አይገመትም።

ስለሆነም ማንኛው ኢትዮጵያዊ በሚከተለው ዓላማና በፖለቲካ አስተሳሰቡ ህይወት መክፈሉ ላይቀር እራሱን መስዋእት አድርጎ ብሄራዊ ክብሩን ለማስመለስና በሃገራችን ውስጥ እውነተኛና ያልተገደበ ዴሞክራሲ ለመገንባት፤ ለህዝብና ለሃገር ተቆርቋሪ የሆነ በህዝብ የተመረጠ መንግስት ለመመስረት በሚደረገው ትግል ላይ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ መሆን ይጠበቅበታል፣ ምክንያቱም ለማይቀረው መስዋእትነት ታሪክ ሰርቶ ማለፍ ክብርን ያጎናፅፋልና።

Hiber Radio: የሕወሃት መሪዎች የስልጣን ሽኩቻ ወደ ሀይል ግጭት ሊያመራ ነው መባሉ ፣ መድረክ አገዛዙ በግብዣ ጋጋታ የህዝብ ንብረት ማባከን አቁሞ በድርቅ ለተጎዱት እንዲደርስ ጠየቀ ፣የአሜሪካና የአውሮፓ የህዝብ እንደራሴዎች አቶ አንዳርጋቸው በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቁ፣ ጀርመናዊው የፓርላማ አባል ሁለት ሐበሻ ስደተኞችን ስላስጠጉ የግድያ ዛቻ ደረሰባቸው፣ በእስራኤል ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ በልዩ የሆድ በሽታ መጠቃታቸው፣ ቃለ መጠይቅ ኦባማን በጉብኝታቸው ልትገል በሚል የፈጠራ ክስ ከተከሰሰው ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለ ፣ከአረና የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አምዶም ገ/ስላሴ ጋር ቃለ መጠይቅ እና ሎሎችም

$
0
0

Habitamu

የህብር ሬዲዮ ነሐሴ 3 ቀን 2007 ፕሮግራም

<...መድረክ በዚህ አስቸኳይ ልዩ ጉባዔው በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል ።የገዢው ፓርቲ መጠቀሚያ ምርጫ ቦርድ ፈርሶ ገለልተኛ ቦርድ እንዲቋቋም፣ ሁሉንም የሰላማዊ የትግል ስልቶች ተግባራዊ የሚያደርግ የተጠናከረ ትግል ለማድረግ ይንቀሳቀሳል፣ እውነተኛ ተቃዋሚዎች ወደ ቅንጅት፣ግንባር ከተቻለ ወደ ውህደት እንዲመጡ ጥሪ አድርጓል፣ ለድርቁ ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቋል ... የህወሃት መሪዎች የስልጣን ሽኩቻ ወደ ውጥረት ተሸጋግሯል መቀሌ ላይ ልዩ ሀይል በጥበቃ ላይ ነው። የህወሃት አባላትና ደጋፊዎች የሁለቱ የአዲስ አበባና የመቀሌ ቡድኖች የስልጣን ሽኩቻ ወደ ሀይል ትቃት ይቀየራል የሚል ስጋት አላቸው። ህዝቡ ግን የሚያሳስበው ዝናብ ስለሌለ ድርቁ ነው…>

አምዶም ገ/ስላሴ የአረና የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ የመድረክን ልዩ አስቸኳይ ጉባኤ እና የህወሃት መሪዎችን የስልጣን ሽኩቻ አስመልክቶ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

<...አንዱ ወንድሜ ግንቦት ሰባትን ወደ በረሃ ሄዶ በመቀላቀሉ ከፖሊስ ጣቢያ ከመሸ በሁዋላ ወስደው ከፍተኛ ማሰቃየት ፈጽመውብኛል።በደረሰብኝ ድብደባ ስዳከም ከመሀከላቸው አንዱ ወጥቶ እየደከመ ስለሆነ ሆስፒታል ሲመጣ የሞተው ተደብድቦ ነው እንዳይሉ ብሎ ደውሎ ስሜን ሲሰጥ በሰመመን ውስጥ ሰማሁ …> ወጣት ባንተወሰን አበበ በአርባ ምንጭ ከተማ ወንድሙ ግንኦት ሰባትን ለትግል በመቀላቀሉ ሳቢያ በደህነቶች የደረሰበትን ስቃይ ለህብር ሬዲዮ ገልጿል ( ሙሉውን ያዳምጡት)
<…ፕሬዝዳንት ኦባማን ለመግደል የአልሸባብ ህዋስ ሆነህ ተንቀሳቅሰሃል ሲሉ ነው ሊከሱኝ የሞከሩት።በጨለማ ከሌሎቱ አምስት ሰዓት ከሀያ በላይ ፖሊሶች መጥተው ተይዤ ነው የተወሰድኩት ። በሌሊት ተወስጄ በሌሊት ተፈትቼያለሁ ። አሁንም አብረኸን ካልሰራህ የማትወጣው ችግር ውስጥ ትገባለህ ብለውኛል። …> ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለ አስገራሚ ስለሆነው የተለጠፈበት ወንጀል እና የእስር ቆይታው ከሰጠን ማብራሪያ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

የሚድትራኔያን ባህርን አቋረጠው ከፈረንሳዩ የካሌስ ወደብ የደረሱ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ዛሬም ያነባሉ(ልዩ እና ወቅታዊ ዘገባ)

ለኢትዮጵያውያን ቀን በቬጋስ የበዓል አከባበር ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ሪፖርት

ከሁበር መምጣት በፊት እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎች ቃለ መጠይቅ

ሌሎችም አሉን

ዜናዎቻችን

የሕውሃት ባለስልጣናት የስልጣን ሽኩቻ ወደ ሀይል ግጭት ሊሸጋገር ይችላል ተባለ

መድረክ በልዩ ጉባዔ አገዛዙ የግብዣ ጋጋታውን ትቶ በድርቅ እየተጎዳ ላለው ህዝብ እንዲደርስ ጠየቀ

የአሜሪካ እና የአውሮፓ ሴናተሮች አቶ አንዳርጋቸው ባሰቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቁ

ጀርመናዊው የፓርላማ አባል ሁለት ወጣት አበሻ ሰደተኞችን በማሰጠለላቸው የግደያ ዛቻ ገጠማቸው

ከ700 በላይ ሰደተኞችን ከሊቢያ ወደ ጣለያን የጫነች ጀልባ አስዛኝ የሆነ አደጋ ገጠማት

እስራኤል ውስጥ በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በልዪ የሆድ እቃ ህመም እየተስቃዩ ናቸው ተባለ

የመኢአድ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ በማዕካዊ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አለመታወቁ ተገለፀ

የኔቫዳ የትራንስፖርት ባለስልጣን ሁበርና ሊፍት ላይ ጫና ይፈጥራል የተባለ ረቂቅ ደንብ አቀረበ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

የፍርድ ቤት ውሎ

Previous: Hiber Radio: የሕወሃት መሪዎች የስልጣን ሽኩቻ ወደ ሀይል ግጭት ሊያመራ ነው መባሉ ፣ መድረክ አገዛዙ በግብዣ ጋጋታ የህዝብ ንብረት ማባከን አቁሞ በድርቅ ለተጎዱት እንዲደርስ ጠየቀ ፣የአሜሪካና የአውሮፓ የህዝብ እንደራሴዎች አቶ አንዳርጋቸው በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቁ፣ ጀርመናዊው የፓርላማ አባል ሁለት ሐበሻ ስደተኞችን ስላስጠጉ የግድያ ዛቻ ደረሰባቸው፣ በእስራኤል ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ በልዩ የሆድ በሽታ መጠቃታቸው፣ ቃለ መጠይቅ ኦባማን በጉብኝታቸው ልትገል በሚል የፈጠራ ክስ ከተከሰሰው ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለ ፣ከአረና የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አምዶም ገ/ስላሴ ጋር ቃለ መጠይቅ እና ሎሎችም
$
0
0

( ለገሰ ወ/ሃና )

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) አመራሮች ም/ል ፕሬዝደንቱ
1 ዘመነ ምህረት
2 ጌትነት ደርሶ አባል
3 መለሠ መንገሻ የወጣቶች ድርጅት ጉዳይ ሀላፊ
ዛሬ ነሐሴ 4/2007 ዓም 4:20 ሰአት አካባቢ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል ለዛሬ ተቀጥሮ የነበረው ተከሳሾች እና ከሳሽ ያቀረቡትን መቃወሚያ መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ነበር
በዚህ መሠረት
11214278_909515852449616_49166841129975178_n
1ኛ ተከሳሽ ዘመነ ምህረት ያቀረበው የክስ መቃወሚያ ሙሉበሉ ውድቅ ተደርጏል በተለይ የተከሰሰበት አንቀፅ እንዲሻሻል ያቀረበው መቃወሚያ ፍርድ ቤቱ አንቀፁ መሻሻል የለበትም ብሏል ዘመነ የተከሰሰበት አንቀጽ ከ15 አመት እስከሞት የሚያስቀጣ መሆኑ የታወቃል
3ኛ ተከሳሽ መለሠ መንገሻ ያቀረበው መቃወሚያ በከፊል ተቀባይነት አግኝቷል በዋናነት የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር (ኢህአግ ) አባል መሆን ከአመራሮቹ ጋር በስልክ ——-መገናኘት ወዘተ የሚለው የአቃቤ ህግ ክስ
መለሠ መንገሻ ያቀረበው መቃወሚያ የኢትዮጵያ ህዝብ አረበኞች ግንባር( ኢህአግ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት ያልተፈረጀ ስለሆነ አሸባሪ ተብየ ልከሰስ አይገባኝም ያለውን ፍርድ ቤቱ ተቀብሏል
11825567_909515825782952_515505813072519969_n
ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ላይ የቀረበው የሽብር ክስ ተሻሽሎ በህገመንግስቱ መሠረት በወንጀል ይከሰስ ሲል አቃቤ ህግ ተቃውሟል ተከሳሽ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበው መቃወሚያ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ( ኢህአግ ) በፓርላማ በአሸባሪነት አልተፈረጀም ያለው እውነት ቢሆንም
በአሸባሪነት ከተፈረጀው ከግንቦት 7 ጋር ተዋህዷል በአሸባሪነት ነው መከሰስ ያለበት ብሏል
ፍርድ ቤቱ ግን አልተቀበለውም የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ከተከበረ በህገመንግስቱ መሠረት ክሱ ተሻሽሎ ለነሐሴ 13/2007 ዓም በተመሳሳይ ሰአት እንዲቀርብ ታዟል
ሁለተኛ ተከሳሽ ጌትነት ደርሶ ምንም አይነት ሀሳብ አልሰጠም ምክንያቱ ደግሞ ቀደም ሲል ጠበቃ አልፈልግም ክርክር አላደርግም ከዚህ ፍርድ ቤት ፍትህ ስለማላገኝ ስላለ በዛው ቀጥሏል
11846672_909515829116285_2717405600234033280_n
ዛሬስ ተከሳሾች ምን አሉ ?
ቀድሞ የመናገር እድል ያገኘው መለሰ መንገሻ ነበር
፠ በአሸባሪነት በመከሰሴ ህክምና ተከልክያለሁ
፠ ዘርን መሠረት ያደረገ ጥቃት ደርሶብኛል( አማራ በመሆኔ)
፠ ለመከላከያ ምስክርነት ወደ አራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስወሰድ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞብኛል
፠ አጄኝ አጥብቀው በካቴና አስረው አመመኝ እጄ ሊቆረጥ ነው ስላቸው ለእጅህ ይገርምሃል እንዴ ገና አንገትህን እንቆርጠዋለን ተብያለሁ ብሎ ለችሎት አቤቱታ ቢያቀርብም ዳኞች ከተመካከሩ በኇላ ” እኛ የተቀመጥነው የቀረበልንን መዝገብ መርምሮ ውሳኔ መስጠት ብቻ ነው ” የሚል መልስ ሰጥተውታል::
ዘመነ ምህረት
፠ዘመነ ፊቱን ወደ ጏደኛው መለሰ ፊቱን አዙሮ ከዚህ ፍርድ ቤት ፍትህ አንጠብቅም ለምን ትደክማለህ
፠የህግ የበላይነት በሌለበት አቤቱታ ማቅረብ ተገቢ አይደለም
፠ ወደ ዳኛ ፊቱን አዙሮ ዛሬ ወደዚህ ስመጣ በእጁ ፓሊሱን እያመለከተ ደብድቦኛል ሲል አብረውት የመጡት ታሣሪዎች ሁሉም ባንድነት አዎ መቶታል አሉ ዘመነ መታኝ ያለው ፓሊስ ይሰቅ ነበር ለመለሠ እንዳደረጉት ዳኞቹ ተማከሩ የመለሱት መልስ በጣም ያስቃል የመለሱት የመጀመሪያውን ነው ” እኛ የቀረበልንን መዝገብ መርምረን ውሳኔ መስጠት ብቻ ነው የኛ ተግባር ” አሉ
፠ ከናንተ ፍትህ አንጠብቅም እኛ ፍርድ የምንጠብቀው ከእግዚአብሔር ነው ሁላችንም በእምነታችን ወደ ፈጣሪ መጮህ አለብን በተለይ የኦርቶዶክስ አማኞች አሁን ወቅቱ የጾም ነው በርትተን መፀለይ አለብን እውነተኛ ዳኝነት የሚገኘው ከፈጣሪ ብቻ ነው በማት ሀሳቡን አጠቃሏል::
ከነ ዘመነ ምህረት በመቀጠል ቁጥራቸው 10 አካባቢ እድሜያቸው 17 እስከ 20 የሚሆን ትንንሽ ልጆች ናቸው ለአቅመ እስራት ያልደረሱ ናቸው ችሎት የቀረቡት የመጡት ከጎንደር እና ከጎጃም አካባቢ ነው ስማቸው ሲጠራ አይሰማም ነበር በዚህ ምክንያት ስማቸውን አልያዝኩም
ስለተከሰሱበት የሸብር ክስ ምንም ያልገባቸው ናቸው ከአርበኞች ግንቦት ሰባት እና ከሌሎች አሸባሪ ድርጅቶች ጋር ሽብር ለመፍጠር ስትንቀሳቀሱ ነበር የሚለውን ክስ ሲሰሙ እኛ የምትሏቸውን ስሞች እየሠማን ያለነው ከናንተ ነው እኛ አናውቃቸውም እተደበደበን ያለነው አማራ በመሆናች ነው መርማሪዎች የጠሉት አማራነታችንን ነው ብለዋል ::

በምዕራብ ጎጃም የብአዴን አባላት አርበኞች ግንቦት 7 ውስጣችን ሰርጎ ገብቷል በሚል እርስበርስ እየተወነጃጀሉ መሆኑ ተሰማ * ክፍፍሉንም አባብሶታል

$
0
0

Zehabesha News
በምዕራብ ጎጃም የብአዴን አመራሮች መካከል መከፋፈል ተፈጠረ

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ እንደዘገበው የምዕራብ ጎጃም የብአዴን አመራርና አባላት ከሀምሌ 29 እስከ ነሀሴ 1 2007 ዓ.ም ባካሄዱት ስብሰባ ላይ ነው መከፋፈሉ ሊከስት የቻለው፡፡ የምዕራብ ጎጃም የብአዴን የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ሀብታሙ፣ የዞኑ ምክትል ከንቲባ አስፋው ገበየሁና የወረዳው የብአዴን ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አላምር ተሻለ የተባሉ የህወሓት አገልጋይ የመሩት በዱላ ቀረሽ ስድድብ፣ እርስበርስ መወነጃጀልና የተደበቀ ገመናን በመነስነስ ታጅቦ ለሦስት ቀናት የዘለቀው ስብሰባ ከመነሻው በዋናነት ለውይይት ያቀረባቸው አርበኞች ግንቦት 7 ባወጀው ጦርነት ላይ ተመስርቶ በሽበርተኝነት ላይ የሚያጠነጥን አንድ ሃሳብና የብአዴንን 35ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አከባበርን የሚመለከት ሌላ ተጨማሪ እርዕስ ያነገበ ሁለት አብይ አጀንዳዎች ነበሩ፡፡

ነገር ግን ስብሰባው የታቀደለትን አቅጣጫ ስቶ ፈር በመልቀቅ አባላትና የበታች የብአዴን አመራሮች ከአንድ ላይ በማበር በበላይ አመራሮቻቸው ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያነሱ የበላይ አመራሮች ደግሞ በፌደራል መንግስቱ በሚገኙ የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ላይ ጣታቸውን ቀስረዋል፡፡

በመሆኑም የህወሓት ጉዳይ አስፈፃሚ የሆነው ብአዴን ከሦስት ጎራ የመሰነጣጠቅ እጣ ገጥሞት ከፍተኛ አደጋ ተደቅኖበት ይገኛል፡፡

የብአዴን አባላትና የበታች አመራሮች የበላይ አመራሮቻቸውን “የህወሓት አሽከሮች በመሆናችሁ ለክልሉ ብሎም ለአገራችን ምንም አይነት አዎንታዊ ሚና አከናውናችሁ ለውጥ ልታመጡ አልቻላችሁም፡፡” በማለት ልክ ልካቸውን ነግረው እርቃናቸውን ሲያስቀሯቸው የበላይ አመራሮች ደግሞ በበኩላቸው “ችግሩ የኛ አይደለም የአሳ ግማቱ ከአናቱ እንዲሉ ብልሽቱ ያለው ከላይ ከአለቆቻችን ነው፤ የፌደራሉ የብአዴን አመራር በህወሓት አንገቱን ታንቆ ተይዟል፡፡” በማለት የብአዴንን ቁንጮዎች በአደባባይ አበሻቅጠዋቸዋል፡፡
የምዕራብ ጎጃም የብአዴን ዝቅተኛ አመራሮችና አባላት “በአገሪቱ ብሎም በክልሉ እስካሁን ምንም አይነት እድገት አልተመዘገበም፤ ዘወትር የምታቀርቡት ሪፖርት ነጭ ውሸት ነው፤ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተከናወነ የሚገኘው የልማት እንቅስቃሴ አንድ ክልል ላይ ብቻ ያተኮረ ነው፤ ልክ እንደ ትግራይ ሁሉ ዳያስፖራው ክልሉን እንዲያለማ እድል አልተሰጠውም በሩ ክርችም ብሎ ተዘግቷል…” የሚሉ ሃሳቦችን አጠናክረው አንስተዋል፡፡

አስፋው ገበየሁ፣ አማረ የተባሉና ሌሎች የምዕራብ ጎጃም የብአዴን አመራሮች በስርቆት ከፍተኛ ሀብት ማፍራታቸው በስብሰባው ላይ ተጋልጧል፡፡

በተጨማሪም የምዕራብ ጎጃም የብአዴን አመራሮችና አባላት በውስጣቸው የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት እንደተሰገሰጉ በማመን እርስበርስ ወደ መፈራረጅ በመሄዳቸው ሹጉጣቸውን ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠው በዓይነ ቁራኛ እየተያዩ ስብሰባውን ያጠናቀቁ መሆናቸውን ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡

በዳንሻ ከተማ ለህዝቡ ሊከፋፈል በመጋዘን የተከማቸ ከ30 ሺህ ሊትር በላይ የምግብ ዘይት የደረሰበት በመጥፋቱ በአካባቢው ከፍተኛ የሆነ እጥረት መከሰቱ ታወቀ፡፡
የምግብ ዘይቱን ለዳንሻና አካባቢው ህዝብ እንዲያከፋፍሉ የተረከቡት ክብሮምና ተክላይ የተባሉት ግለሰቦች ሲሆኑ ከ30 ሺህ ሊትር በላይ የሆነውን የምግብ ዘይት ተዘረፈብን ሲሉ ህብረተሰቡን ለከፋ ችግር ዳርገውት ይገኛሉ፡፡

“ሰላማዊ ትግል ለማይገባዉ አምባገነን በሚገባዉ ቋንቋ እናናግረዋለን!!”–ድምጻችን ይሰማ ደቡብ አፍሪካ (ደ.ይ.ድ.አ)

$
0
0

south africa

በትናንትናዉ እለት ሰኞ 10/08/2015 በደቡብ አፍሪካ የሚገኘዉ የሰላማዊ ትግል ተምሳሌት ድምጻችን ይሰማ ታላቅ ስብሰባ አደርገ። እንደሚታወቀዉ በቅርቡ አንባገነኑ ወያኔ ሚሊዮኖች በወከሏቸዉ የንጹሃን የህዝበ ሙስሊም ኮሚቴዎች ላይ ታሪክ ይቅር የማይለዉ ኢ_ፍትሐዊ ፍርድ በመፍረዱ ምክንያት የደቡብ አሪካዉ ድምጻችን ይሰማ ኮሚቴ በጠራዉ የዉይይት መድረክ ላይ የተገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያዊን ወገኖች ቁጣቸዉን ገለጹ።
በእለቱ የተከበሩ የህዝበ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ወገኖች ተወካዮችና የሐይማኖት ሊቆች፣ሼሆች፣ ኡስታዞች፣ የተገኙ ሲሆን ሼህ መሐመድ አሚን፣ ኡስታዝ ኡስማን አህመድ፣ የየእለቱ መክፈክቻ ንግግሩ ሹሞች ነበሩ።
” ሰላማዊ ትግል የሚነገርዉ ሰላም ለሚገባዉ እንጂ እንደ ወያኔ ላለ አምባገነን አይደለም ይህ አካሄዳችን ፈጽሞ በወያኔ ታጥቦ ተወስዷል በመሆኑም ሰላማዊ ትግል ማለት ነጭ ወረቀት ብቻ ማዉለብለብ አይደለም ” ኢስላም ሰላም ነዉ ” ነገር ግን ይህ ለሚገባዉ ብቻ ነዉ ለማይገባዉ ግን የምንሄደዉ መንገድ ሁሉ ለኛ ሰላም ነዉ! በሚል ታሪካዊ ንግግር የተከፈዉ ስብሰባ በቁጭትና በምሬት የተካሔደ ነበር።

በኦሮምኛ ቋንቋና በአማርኛ ቋንቋ በድንቅ ሁኔታ የተካሄደዉ የትናንቱን የድምጻችን ይሰማ ስብሰባ ላይ በኦሮምኛ ቋንቋ ስነ ግጥም የቀረበ ሲሆን በቅጽል ስሙ ( ፀረ ወያኔ ) በመባል የሚታወቀዉ ገጣሚ አብዱራህማን ቦንከሬ ሙስሊም ወንድሞቻችን በወህኒ ተከርችመዉ መሬት ለመቀራመት ወደ ሐገር ቤት የነጎዱ በሙስሊሙ ስም የሚንቀሳቀሱ የዲን ጠላቶች የወያኔ ዲያስፖራዎችን በቅንፍ ዉስጥ ያስገባ ስነ ግጥም ያቀረበ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ በተለያዩ የህዝበ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በደቡብ አፍሪካ በሚያደርጉት ዝግጅት ላይ የተለያዩ ጽሁፎችን ይዞ የሚቀርበዉ የጆሐንስበርጉ ጀማል ዲያስፖራ ላሜ ቦራ በሚል እርእስ ከበድ ያለ ምልእክት አስተላልፏል።

በእለቱ የተካሄደዉ ስብሰባ በፍቅር ያስተናገዱት ሼህ ይስሐቅ ሙስሊም ማለት ከግርግዳ ጀርባ ብርሐን የሚመለከት ህዝብ ነዉ ወደ ብርሐንኑም እኛዉ እራሳችን እንሄዳለን ሲሉ ሰምና ወርቅ ያዘለ ንግግር ሲያስቀምጡ ኡስታዝ ፈይሰልም አስተምሮት ያለዉ ድንቅ ንግግር ከማድረጋቸዉም ባሻገር ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ አይወክለንም ሙስሊም ካልሆኑ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ጋር ሊያጋጬን የማይጭረዉ የማይንደዉ ሐረካት እንዳለ እናዉቃለን እኛ የጋራ ጤላታችን ወያኔ ነዉ የሚሉ ታላላቅ ንግግሮችም የእለቱን ታሪካዊነት ሲያጎሉት ። በስተመጨረሻ አጠቃላይ ዉይይቱ ወደ መላዉ ሕዝብ የገባ ሲሆን የዉይይት መድረኩ በድምጻችን ይሰማ ደቡብ አፍሪካ አወያዮች የተመራ ነበር በመሆኑም፡…..

1. ኡስታዝ ሸምሱ
2. ጋዜጤኛ አብዱራህሚን
3. ከድምጻችን ይሰማ ኮሚቴዎች ጋር ታስሮ የነበረዉና በዋስ ከወጣ ወዲህ በስደት ደቡብ አፍሪካ የሚገኘዉ በሌለበት የ 15 አመት ፍርደኛዉ አሊ መኪ፡ ሲሆኑ ዉይይቱን የከፈተዉ ጋዜጠኛ አብዱራህሚን ለትዉስታ ያህል የፍርደኛ ንጹሐን ሙስሊም ወኪሎችን የፍርድ ቤ/ት ዉሎ ባስታወሰ መልኩ የማነቃቂያ ንግግሮች በማድረግ ሐሳብ የመስጤቱ እድል ወደ ህዝቡ ከሆነ ህዝቡ ከደቡብ አፍሪካ ከተለያዩ ስፍራዎች የተገኘዉ በቁጭት የተሞላዉ ህዝበ ሙስሊም እጥዮጵያዊያን ወገኖች ” ጉዞዉ ወደ ትግል ብቻ ነዉ ” የሚል ሐሳብ መሆኑን በጥቅል ያሳየ ሲሆን በሼህ ሸምሱም የተመራዉ የመፈክር ስእነ ስርአት (ለዲናችን እስከመጨረሻዉ ለመስራት ዝግጁ ነን ገንዘብም ሆነ ህይወት ለመስጠት ዝግጁ ነን በወያኔ አያሸብረንም!!! ) የሚል የህብረት መፈክር ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ጉድሽ ወያኔ

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>