Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

መስከረም ሲጠባ አደይ ሲፈነዳ ……

$
0
0

 

ከይድነቃቸው ከበደ

(የሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ኋላፊ)

Yidnakachewየዘመን መለወጫ ክብረ በዓል በየትኛውም አገር እንደ አገሩ ወግና ልማድ በድቅመት የሚከበር በዓል ነው፤በእኛ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ደግሞ ልማድና ወጋቻን እጅግ ከመጠንከሩ የተነሳ ለአዲስ ዓመት ወይም ለዘመን መለወጫ ክብረ በዓል ዝግጅታችንም ሆነ አከባበራችን እጅግ በጣም ጠንካራና ደስ የሚል ነው፡፡

አዲስ ዓመት የሁሉ ነገር መጀመሪያ ነው ለዚህም ነው ብዙ እቅዶቻችን ከመስከረም ወር የሚጀምረው፤ያቀድነው ነገር በዓመቱ መጨረሻ ሊሳካ ወይም ላይሳካ ይችል ይሆናል ቁም ነገሩ ግን በዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ለማሳካት የታሰበ እቅድ መኖሩ ነው፤ለእቅዱ አለመሳካት ውጫዊና ውስጣዊ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ እነዚህን እንቃፋት የሆኑ ምክንያቶች ለይቶ ማወቅ በራሱ የእቀዱ አንድ አካል በማደረግ እንደገና ለመጪው አዲስ ዓመት ለተሸለ እቅድ ግባት ይሆናል፡፡

የዘንድሮ አዲስ ዓመት ከግለሰባዊ ፋይዳ በላይ አገራዊና ህዝባዊ የለውጥ ፋይዳ የበዛ እንደሚሆን ምልክቶቹ አብዝተው ይታያሉ፤እነዚህ ምልክቶች ከባለፈው ዓመት ለዘንድሮዎ የተሸጋገሩ የለውጥ ምልክቶች ናቸው፤በመሆኑም ለለውጥ የተነሳሳው ለወጥ ፈላጊ ለውጡኑ የሚያከሽፍበት አንዳችም ምክንያት ስለመኖሩ እጠራጠራለው ክሽፈት ቢያጋጥም እንኳን ወድቆ ለመነሳት ብዙ ጊዜ የሚባክን አይመስለኝም ፡፡

መውደቅ መነሳት ከሚንቀሳቀስ ነገር የሚጠበቅ ክስት ነው መንቀሳቀስ ደግሞ በሀገር ውስጥና በውጪ በሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን፣ ፖለቲከኞች፣ በአይማኖት ተቋመት፣በሲቪክ ማህበራት እና በመሳሰሉት እንቅስቃሴው መሰልቸትና ድካም የማይታይበት ጠንካራ እንቅስቃሴ ነው፤ይህ እንቅስቃሴ ከባለፉት ወድቆ መነሳት እንቅስቃሴ ት/ት የተቀሰመበት ስለመሆኑ ከምልክቶቹ መካከል አንዱ ነው፡፡

በአገራችን ለለውጥ የሚገፋፉ ብዙ ምክንያቶች መኖራቸው የሚታወቅ ቢሆንም ከብዙ ምክንያቶች በዋንኝነት ትኩረትን የሚስቡት የለውጡን አይቀሪነት አሳበቂ ምክንያቶች ከሆኑት ውስጥ፡-

1ኛ. በዓለም ላይ ካሉ ታላላቅ እምነቶች መካከል ክርስትና እና እስልምና ዋንኞቹ ናቸው፤እነዚህን እምነቶች በመቀበል እኛ ኢትዮጵያዊያን ከቀዳሚዎቹ መካከል እንገኛለን ክርስትናን እና እስልምና እምነትን መቀበላችን ብቻ ሣይሆን የተቀበልነው እምነት ህግና ሥርዓት አክብሮ በማስከበር ወደር አይገኝልንም፡፡ይሁን እንጂ መንግስት በልማት ስም  የአምልኩ ቦታዎችን በመጋፋት ቤተ ክርስቲያንን ተዳፍሯል፤ይህ ነገር ተገቢ አይደለም ያሉ የሃይማኖት አባቶች ተደብድበዋል፣ተገለዋል እንዲሁም ከአገር ተሰደዋል፡፡

መንግስት በሃይማኖት ሃይመኖት በመንግስት ጣልቃ አይገባም የሚለውን ህገ-መንግስታዊ ድንጋጌ መንግስት በመጣስ በሙስሊም እምነት ዘው ብሎ በመግባት የእመንቱን መሪዎች እስከመምረጥ ደረጃ ተደርሷል፤ ይህን አይቶ ዝም አለማለት እስላማዊ ግዴታ እንደመወጠት የቆጠሩ እንቢ ለእምነቴ ያሉ በእስር እና በስቃይ ላይ ይገኛሉ፡፡    በእነዚህ ታላላቅ እምነቶች መንግስት እጁን በማስገባት የፖለቲካ ዓላማ ማስፈፀሚያ ለማድረግ ያልፈነቀለው ድንጋይ ምን አለ? በተለይ በሙስሊሞች ላይ እተየፈፀመ ያለው በደል እና በእምነቱ ተከተዮች የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ ያለጥፋታቸው በሐሰት በመወንጀል አሸባሪ ብሎ በእስር ማሰቃየቱ እጅን ጨብጦ ጥርሱን ነክሶ ያልተቆጨ ማነው ?

2ኛ. ኢትዮጵያ አገራችን የብዙ ሺህ ዓመት አኩሪ ታሪክ ያላት እና የተለያዩ –ን–ዎች የሚነገርባት ህዝቧ የቋንቋ ልዩነት ሣይገድበው አንዱ ከሌላው የተዋለደባት እጅግ ውብ እና ማራኪ –ን–፣ብህል ፣ልምድ ፣ወግ ፣አለባበስ እና አመጋገብ ወዘተ….. የሚታይባት ድንቅ አገራችን ናት፡፡ ይሁን እንጂ የኢህአዴግ መንግስት ይህ ቦታ የናተ አይደለም በማለት ዜጎችን በማፈናቀል ሀብትና ንብረት በማውደም ጎጠኝነትና ዘረኝነት በማስፋፋት ላይ ይገኛል፤እንዲህ አይነቱ አሳፋሪ ተግባር በአገራችን በአራቱም አቅጣጫ በዘመቻና በእቅድ በመንግስት የተፈፀመ ህገወጥ ተግባር ነው፡፡በመሆኑም ከኢትዮጵያዊነት በላይ መንደረኝነት እንዲነግስ በመንግስት እየተደረገ ያለው ዘመቻ ያላስቆጨው፣ ያላንገበገበው ማነው ? ይህን ቁጭቱን እና በደሉን ለመግለፅ ጊዜና አጋጣሚውን እየጠበቀ ያለው ስንቱ ነው ?

እኛ ኢትዮጵያዊያን በእድሜና በውቀታቸው ከፍ ላሉ ሰዎች ያለን ከበሬታ እጅግ የላቀ ነው ፤ለዚህም ነው ለሽምግልና ጉዳይ ቶሎ እጅ የምንሰጠው በሽምግልና ካጣነው ነገር በላይ ያተረፍነው የበዛ ነው ፡፡ ይሁን እንጂ የቆየውና ጠቃሚ የሽምግልና ወገና ሥርዓት በመጠበቅ የአፋር ፣ የኦሮሚያ ፣ የጋምጎፋ (ቆጫ ወረዳ) እና የሲዳማ የአገር ሽማግሌዎች በአካባቢያቸው ለታየው አስተዳዳሪያዊ ችግር መፍትሔ ለመሻት ከታችኛው የአስተዳደር አካል እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያደረጉት ጥረት ውጤት አልባ ነበር፤ ከምንምንም በላይ የሽምግልና ክብር በመጋፋት መንግስት ጠቃሚ የሆነውን ወግና ሥርዓት ለመናድ የሄደበት መንገድ ሽማግሌዎችንና የተወከሉበትን ማህበረሰብ ምን ያህል ነው ያስከፋው ?

3ኛ. ‹‹ በኑሮ ውድነት የጎበጠው ትከሻችን እረፍት ይሻል ›› ኑራችን አላምር ሲል መፈክራችን ማማሩ የሚገርም ነው ! ይህ መፈክር ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ ባካሄደው የተቃውሞ ሠልፍ ከፍ ብሎ የተሰማ ጥያቄ ነወ፤ እውነትም አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የኑሮ ውድነት ትከሻውን ከማስጉበጥ አልፎ ህይወቱን እየነጠቀወ ነው፡፡ ባለ ሁለት ሃአዝ እድገት በመንግስት ተደጋግሞ የሚነገር አስማታዊ እድገት ምግብም መጠጥም አልሆን ብሎ በመንግስት የሚነገረው እድገትና የምንኖረው ሕይወት ሆድና ጀርባ ሆኖ አልገጥም እያለ ተቸግረናል፡፡

የስራ አጥነት ቁጥሩ በጣም የበዛ ነው፣ሰራተኛም ሰርቶ የሚከፈለው ወራዊ ደሞዝ ወሩን ሙሉ የሚያቆይ አይደልም፣ በኑሮ ውድነቱ ምክንያት 2.5 ሚሊዩን ዜጎች ለጎዳና ተዳዳሪነት መዳረጋቸው የመንግስት መስሪያ ቤት የሆነው የማህበራዊ ዋስትና ድርጅት ባስጠናው ጥናት መሰረት ይፋ አድረጎኃል፤ጎዳና ያልወጡ እቤታቸው ጎዳና የሆነባቸው ዜጎች ቤት ይቁጠራቸው፡፡

በመሆኑም እንዲህ አይነቱ ምስቅልቅል የበዛበት የኑሮ ውድነት ዋንኛው መንስሄ ብልሹ የመንግስት አስተዳደር ስለመሆኑ የእኛ መንገስትና ኑራችን ዋንኛ ማስረጃ ነው፤ስለሆነም እንዲህ አይነቱ ብልሹ የመንግስት አስተዳደር አቅፎና ደግፎ ይዞ የሚሄድ ጉልበትም ሆነ አንጀት ከወዴት ይምጣ ?

4ኛ. አሁን ያለው የአባገነን ሥርዓት የተረጋጋና ጉልበት አልባ መሆኑ ሌላኛው የለውጡን አይቀሪነት አሳበቂ ምክንያት ነው፡፡ ከእሳቸው ሞት በፊት ይታይ የነበረው የአንድ ሰው ፈላጭ ቆራጭነት ከእሳቸው ሞት በኃላ የስርዓቱ ፊት አውራሪዎች ከመብዛታቸውም በላይ በቡድን የተከፈሉና እኛ እናተ መባባላቸው ከጥጋባቸው በላይ የስልጣን ጥማታቸውን የሚያሳይ ነው፤ ግን በሁለት ሆዳሞች መሃል እህል ይደፋል እንጂ ማንም አይበላውም፡፡

ሌላው የስርዓቱ የፊት ሰዎች ከውስጣዊ ሹኩቻ ባለፍ በአደባባይ አንዱ ለሌላው በሙስና እና በስልጣን መባለግ ስም ማሰርና መክሰስ ሌላኛው አገር ጥሎ መሄድ መሳ ለመሳ እየተካሄደ ያለ ውስጣዊ ሹኩቻ ነው፤በእንዲ መልኩ በውስጥ የተወጠረው የአባገነን ስርዓት በተጠናከረ እና ሠላማዊ በሆነ ህዝባዊ ግፊት ፈንድቶ ውስጣዊ ሰንኮፉ የማይነቀልበት ምክንያት ምንድነው ?

5ኛ. ሐሳብን በነጻ የመያዝና የመግለጽ እንዲሁም የመደራጀት መብት ዓለም አቀፍ  እንዲሁም ሕገ መንግስታዊ መብት ነው፡፡በመሆኑም አንዱአለም አራጌ፣ ናትናሄል መኳንን፣ በቀለ ገራባ፣ ኦልባና ለሊሳ እና ሌሎችም የፖለቲካ እስረኞች እንደማንም ኢትዮጵያዊ የራሰቸው ኑሮ እና ህይወት ያላቸው ናቸው፤ ይሁን እንጂ ነፃነት እና ፍትህ ለነሱ ሁለተኛ ጉዳይ አይደለም የመጀመሪያ ጥያቄያቸው ነው ! ከራስ ወዳድነት አልፈው ይህ ጥያቄ የኛ ብቻ ሣይሆን የኢትዮጵያዊያን ጥያቄ ነው በማለት በአደባባይ ስለነፃነት እና ፍትህ የዘመሩ በዚህም አኩሪ ተግባራቸው በእኛ የኢትዮጵያዊያን ዘንድ ልዩ ቦታ የምንሰጣቸው ነን፡፡የታሰሩበት እና የሚሰቃዩበት ጉዳይ የኛም ጉዳይ ነው የሚሉ ቁጥራቸው መብዛቱ ሠላማዊ ትግሉ አባገነን ስርዓቱን የሚበላ እሳት መሆኑ ማሳያ ነው፡፡

ይህ በእንዲ እንዳለ  በአገር እና በህዝብ ላይ የሚፈፀም በደል ማቆም አለበት መንግስት እየወሰዳቸው ያለው እርምጃ የዜጎች ሰብአዊ እና ዲሞክራሳዊ መብቶችን የጣሱ ናቸው፤ በማለት ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብታቸውን ተጠቅመው ከምንም በላይ የጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር ጠብቀው ሚዛናዊ መረጃ ለእዝብ ያደረሱ ዓለም ዓቀፍ ተሸላሚ የሆኑ ጋዜጠኖች በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ እርዮት ዓለሙ እና ውብሸት ታዬ በስራቸው ዓለም ያደነቃቸው አድናቆቱም በሽልማት የታጀበ መሆኑ ለማናችንም ግልፅነው፡፡ይሁን እንጂ እነዚህ የዓለም ህዝብ ቆሞ ያጨበጨበላቸው ጋዜጠኞች አባገነኑ መንግስት በሽብርተኝነት ወንጅሎ በማሰር እያሰቃያቸው ይገኛል ፡፡ ይህ ስቃያቸው ያልተሰማው ማነው ? ከዚህ ስቃይ እንዲወጡ ምን ባደርግ ይሻላል እያልን እራሳችንን ያልጠየቅን ስንቶቻችን ነን ? በሆነውስ ነገር ያልተቆጨ ማነው ?

6ኛ. በውጪ የሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተፅኖ ሌላው ለአባገነኑ ሥርዓት የእግር እስታ መሆን ነው፤ በውጪ የሚገኙ ዜጎች በአገር ውስጥ ለታየው ብሉሹ አስተዳደር ፊት ከመንሳት ባለፈ በተደራጀና በሚያስደንቅ ሁኔታ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ነው፡፡ እንቅስቃሴውም ከሌላው ጊዜ በተሸለ በኢኮኖሚ እና በፖለቲካው ስኬታማ መሆኑ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ በተለያየ ወቅት በሰጡት ቃለ ምልልስ እና መንግስት በሰጠው መግለጫ በውጪ በሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን መንግስት መሸነፉን የሚያሳብቅ ነው፡፡

በመሆኑም ከላይ በማሳያነት የቀረቡ የለውጡ ግፊት ሃይል ከሆኑ ምክንያቶች ውስጥ የተጨለፈ ቢሆንም  በመንግስት የአስተዳደር ብሉሹነት ምክንያት ይህ አስተዳደር በቃኝ ለማለት ምክንያቱ ብዙ ነው፡፡ ስለሆነም መስከረም ሲጠባ አደይ ሲፈናድ ለውጥ ፈላጊ የፈለገውን ለውጥ ላለማጣት ከባለፈው ዓመታት ት/ት በመውሰድ በዘንድሩ አዲስ ዓመት ከግለሰባዊ ፋይዳ በላይ አገራዊና ህዝባዊ ለውጦች የምናይበት ዓመት ይሆናል፡፡

 


ሰማያዊ ፓርቲ የፊታችን እሁድ በአ.አ. የሚደረገው ሰልፍ በታቀደለት ጊዜ እንደሚካሄድ አስታወቀ

$
0
0

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ማብራሪያ

ሰማያዊ ፓርቲ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ሊያካሂደው የነበረው የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፍ በመንግስት ታጣቂዎች ህገ ወጥ እርምጃ ከተደናቀፈ በኋላ ነሐሴ 3ዐ ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ፓርቲው መስከረም 12 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ሰላማዊ ሠልፍ እንደሚያደርግ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የሰላማዊ ሠልፍና ስብሰባ ማሣወቂያ ክፍል እንዲያውቀዉ አድርጓል፡፡ ይህንን ተከትሎ የሰላማዊ ሠልፍና ስብሰባ ማሣወቂያ ክፍል ጳጉሜ 1 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ የሰለፉን ዓላማ፣ የሰልፉ ተሳታፊዎች የሚጓዙበትን መስመርና የሰልፉ መዳረሻ ከግንባታ ስራና ከፀጥታ ጥበቃ ጋር ያለውን ችግር አስመልክቶ ማብራሪያ እንደሚያስፈልግ በጠየቀዉ መሠረት፡-

blue party1ኛ. የሰልፉ ዓላማ፤
በህገ መንግሥቱ የተደነገጉት ሃሣብን በነፃነት የመግለፅ መብት እንዲከበር፣ዜጐች በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተዘዋውሮ የመሥራትና ሀብት የማፍራት መብታቸው እንዲከበር፣ በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 11፡3 በግልፅ የተደነገገው መንግሥት በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ኃይማኖትም በመንግሥት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም የሚለው ድንጋጌ እንዲከበር፣ መንግሥት የኑሮ ውድነትና ሥራ አጥነትን ለመቅረፍ የፖሊሲ ማሻሻያ እንዲያደርግ የሚሉትን ጥያቄዎች በሰላማዊ ሠልፍ መንግሥትን ለመጠየቅ መሆኑን፤

2ኛ. የሰልፉ ተሳታፊዎች የሚጓዙበትን መስመር
መነሻው ከፓርቲው ጽ/ቤት ግንፍሌ አካባቢ ተነስቶ በአራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል በኩል በአሮጌው ቄራ በአምባሳደር ቴአትር አልፎ መስቀል አደባባይ ሲሆን፣ በዚህ መንገድ ላይ ምንም ዓይነት የግንባታ ሥራ የሌለበትና ሠልፉ የሚደረገውም እሁድ ከጥዋቱ 3፡ዐዐ-7፡00 ሰዓት ባለው የእረፍት ቀን በመሆኑ በዕለቱ ምንም ዓይነት የመንግሥት ሥራና የትራፊክ መጨናነቅ የሌለበትና መድረሻ ቦታችንም መስቀል አደባባይ ከቅርብ ቀናት በፊት በኃይማኖት ተቋማት አስተባባሪነት ሠልፍ የተደረገበት መሆኑና ወደፊትም መስከረም 12 ቀን ከሚደረገው ሠልፍ አንድ ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከሁሉም ማዕዘናት በሚመጡ ምዕመናን የመስቀል በዓል የሚከበርበት ቦታ መሆኑን ጳጉሜ 04 ቀን 2005 ዓ.ም በፃፍነው ደብዳቤ አብራርተናል፡፡

የሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ሥነ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 3/1987 አንቀፅ 6 ቁጥር 2 “የከተማው አስተዳደር ጽ/ቤት በዚህ አዋጁ አንቀፅ 6 ንዑስ አንቀፅ 1 የተመለከቱትን በማገናዘብ ሰላማዊ ሰልፉ በሌላ ጊዜ ወይም በሌላ ስፍራ ቢደረግ ይሻላል የሚል አስተያት ካለው ምክንያቱን በመግለፅ ይህንኑ ጥያቄው በደረሰው በ12 ሰዓት ውስጥ በጽሑፍ ለአዘጋጁ የማሳወቅ ኃላፊነት አለበት፡፡ ሆኖም የከተማው አስተዳደር ጽ/ቤት ሰላማዊ ሰልፉ ምንጊዜም በየትኛውም ቦታ ሊካሔድ አይችልም ማለት አይችልም” በሚለው መሰረት የእዉቅና ጥያቄ የቀረበለት አካል በፅሁፍ በ12 ሰዓት ውስጥ መልስ የመስጠት ግዴታ ቢኖርበትም እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡

ፓርቲያችን በሕግ የሚጠበቅበትን ለሚመለከተዉ አካል የማሳወቅ ግዴታ በአግባቡ ስለተወጣና ለሰልፉም የሚያስፈልጉ ስራዎች እየተከናወኑ በመሆኑ መስከረም 12 ቀን 2006 ዓ.ም በታቀደው መሰረት ያካሂዳል፡፡ በመሆኑም በዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ የምናነሳቸው ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሲቪክ ማሕበራትና ዜጎች በአጠቃላይ በሰልፉ ላይ በመሳተፍ የዜግነት ድርሻቸውን እንዲወጡ ፓርቲያችን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

በመጨረሻም ሰላማዊ ሰልፉን በመቆጣጠርና የሕዝብን ሰላምና ፀጥታ የሚያውክን ሁኔታ በማስወገድ የሰላማዊ ሰልፈኞች መብቶችን ለመጠበቅ የፖሊስና የፀጥታ ኃይሎች በአዋጁ ቁጥር 3/1987 የተሰጣቸውን ኃላፊነትና ተግባር በአግባቡ እንዲያከናውኑ እናሳስባለን፡፡

መስከረም 6 ቀን 2006 ዓ.ም.

አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የግል ባንኮችን አካውንት አገደ

$
0
0

ዳዊት ታዬ /ሪፖርተር 

eth Bankየባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ በያዘው መንግሥታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ አካውንት ያላቸው የግል ባንኮች አካውንታቸውን እንዳያንቀሳቅሱ ታገዱ፡፡

ከአንዳንድ የግል ባንኮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ ያላቸውን አካውንት እንዳያንቀሳቅሱ የተገለጸላቸው፣ አካውንታቸው ባለበት ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ በኩል በተጻፈ ደብዳቤ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይህንን ዕርምጃ ለመውሰድ የተገደደበት ምክንያት ግልጽ ባይሆንም፣ ከሰኞ መስከረም 6 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ የነበራቸውን አካውንት ማንቀሳቀስ የማይችሉ መሆኑ እንደተገለጸላቸው ታውቋል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ ያነጋገርናቸው የግል ባንኮች ኃላፊዎች እንደጠቆሙት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዕርምጃ ያልተጠበቀ እንደሆነባቸው ነው፡፡ ‹‹ሆኖም የእኛን የተወዳዳሪዎቹን አካውንት እንዳይንቀሳቀስ ሲያደርግ ቢያንስ ምክንያቱን ሊገልጽ ይገባ ነበር፤›› ይላሉ፡፡ የግል ባንኮቹ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ አካውንት የከፈቱበት ዋነኛ ዓላማ አንዳንድ ክፍያዎችን በቀጥታ ከዚያ ለመክፈል እንዲያስችላቸው እንጂ ሌላ ዓላማ የሌለው መሆኑን የግል ባንኮች ኃላፊዎች ያስረዳሉ፡፡

አንድ ባንክ በሌላ ባንክ ውስጥ አካውንት ሊከፍት የሚችለው በሥራ ውስጥ የሚያጋጥሙ ክፍያዎችን በቀላሉ ለመፈጸምና የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ ነው በማለት የሚያስረዱት የግል ባንኮች ኃላፊዎች፣ ይህ በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ የተለመደ አሠራር ቢሆንም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደዚህ ዕርምጃ መግባቱ እንቆቅልሽ እንደሆነባቸው አስረድተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት 19 ባንኮች በሥራ ላይ ሲሆኑ፣ ሦስቱ የመንግሥት 16ቱ ደግሞ የግል ናቸው፡፡ የግሎቹም ሆነ የመንግሥት ባንኮች በጥምረት የሚያስተሳስራቸው የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር ሲሆን፣ አሁን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወሰደውን ዕርምጃ በማኅበራቸው በኩል ለመነጋገር ሐሳብ ያላቸው መሆኑንም የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንታቸው እንዳይንቀሳቀስ ወሰነ ማለት ግን በአካውንታቸው ውስጥ ያለውን ገንዘብ ያግዳል ማለት እንዳልሆነ ተጠቅሷል፡፡

አንዳንዶቹ የግል ባንኮች አካውንቱ ለምን እንዲታገድ እንደተደረገ ላቀረቡት ጥያቄ ማብራሪያ ባለማግኘታቸው በሁኔታው ማዘናቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንዳንድ ኃላፊዎችን ለማነጋገር የተደረገው ሙከራ ካለመሳካቱም በላይ፣ በሞባይል ስልካቸው በጽሑፍና በድምፅ የተላለፈላቸውን ጥያቄ ለመመለስ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡

“የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቅልኝ የምፈልገው ነገር አለ”ድምፃዊ ደሳለኝ ብርሃኑ (Video)

$
0
0

“የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቅልኝ የምፈልገው ነገር አለ” ድምፃዊ ደሳለኝ ብርሃኑ (Video)(ዘ-ሐበሻ) ነዋሪነቱን በሰሜን አሜሪካ ያደረገው ድምፃዊ ደሳለኝ ብርሃኑ አንድን ዘፈን እርሱ እና ሚካኤል ንጉሱ የተባለ ድምፃዊ መጫወታቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቅልኝ የምፈልገው አለ በሚል ዘፈኑ የርሱ መሆኑን አስታወቀ። ዜማና ግጥሙን ለሁለታችንም የሰጠን ኤፍሬም አበበ የተባለው ደራሲ ነው ያለው ድምፃዊ ደሳለኝ ደራሲው ዘፈኑን ለሌላ ድምፃዊ እንደሰጠው እያወቀ ሃገር ቤት ርቄ መኖሬን ከግምት በማስገባት ወንጀል ፈጽሞብኛል ብሏል። ቃለ ምልልሱን በቪዲዮ ይመልከቱት።

የቤተመንግስት ደህንነት ሃላፊ ተነሱ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

$
0
0

ከኢየሩሳሌም አርአያ

Azeb investment ethiopiaየቤተ-መንግስት የደህንነት ጥበቃ ዋና ሃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት የሕወሐት አባል አቶ ጌታቸው ተፈሪ ከስልጣናቸው መነሳታቸውን ምንጮች አስታወቁ። አቶ ጌታቸው ቀደም ሲል በክልል 14 ፖሊስ ኮሚሽን የደሕንነት ልዩ ተወርዋሪ ሃይል ሃላፊ ተደርገው ሲያገለግሉ መቆየታቸውን የጠቆሙት ምንጮች፣ ከዚያም ወደ ቤተ መንግስት ተዛውረው መመደባቸውንና በተጨማሪ የአገር ውስጥ ደህንነት ምክትል ሃላፊ በመሆን ከአቶ ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል ጋር ሲሰሩ መቆየታቸውን አስረድተዋል። የአቶ መለስና ወ/ሮ አዜብ የቅርብ ሰው የሆኑት አቶ ጌታቸው ተፈሪ በነበራቸው ታማኝነት የቤተመንግስት የደህንነት ሃላፊ ተደርገው በአቶ መለስ ተመርጠው እንደተሾሙ ያስታወሱት ምንጮች፣ በማያያዝም እስከ 1994ዓ.ም የቤተመንግስት የደህንነት ጥበቃ በሃላፊነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ዘርኡ መለስ በወቅቱ ከአቶ መለስ ጋር በፈጠሩት የፖለቲካ ልይነት ምክንያት ካዛንቺስ አካባቢ በሚገኘው የቀድሞ “ኮከብ ሬስቶራንት” የአሁኑ “ሚልክ ሃውስ” መኖሪያ ሕንፃ አንደኛ ፎቅ ቤታቸው ውስጥ አንገታቸው በስለት ታርዶና በድናቸው ተበላሽቶ መገኘቱን አመልክተዋል። ይህን አሰቃቂ ግድያ ያከናወነው አሁን በእስር ቤት የሚገኘው የቀድሞ አገር ውስጥ ደህንነት ሃላፊና የአቶ መለስ ቀኝ እጅ ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል መሆኑን ምንጮቹ አጋልጠዋል።

አቶ ጌታቸው ተፈሪ ከስልጣን እንዲነሱ የተደረገው በደህንነት ዋና ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ ትእዛዝ መሆኑን ያመለከቱት ምንጮች፣ በአሁኑ ወቅት በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ እንደማይታወቅ ጠቁመዋል። አቶ ጌታቸው ተፈሪ — የወ/ስላሴ መታሰር ቅር ሳያሰኛቸው እንዳልቀረና በተጨማሪም የነአዜብ ቡድን ደጋፊ መሆናቸውን ምንጮቹ አመልክተዋል።
በሌላ በኩል የኢ.ኤም.ኤፍ ምንጮች ቀደም ብለው እንደገለጹት፤ ባለፈው አመት የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ከሞቱ በኋላ “ቤተ መንግስቱን አንጠብቅም” ብለው ንዝህላልነት ካሳዩት መሃል እኚሁ የቤተ መንግስት ጥበቃ ሃላፊ ጌታቸው ተፈሪ አንዱ ነበሩ። በተለይም አዲሱ ጠ/ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከገቡ በኋላ የቤተ መንግስቱ ጥበቃ እንዲላላ ከማድረግ አልፈው፤ ለአዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር አክብሮት የማይሰጡ ሰው እንደነበሩ ይታወቃል።

(Breaking News) 4 የአየር ኃይል አብራሪዎችና አስተማሪዎች ግንቦት 7ን ተቀላቀሉ

$
0
0

የኢትዮጵያ  ሚግ-23 (ፎቶ ፋይል)

የኢትዮጵያ ሚግ-23 (ፎቶ ፋይል)

(ዘ-ሐበሻ) በቅርቡ በሱማሌያና በዳርፉር የሰላም ማስከበር ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ 4 የኢትዮጵያ ዓየር ኃይል አብራሪዎች እና የበረራ አስተማሪዎች የግንቦት 7 ንቅናቄን መቀላቀላቸውን ኢሳት በሰበር ዜናው ዘገበ።

የሕወሓት/ኢህ አዴግን አስተዳደር ከድተው ግንቦት 7ትን የተቀላቀሉት እነዚህ የአየር ኃይል ከፍተኛ የጦር መኮንኖች 2ቱ ሻለቃ እንዲሁም ካፒቴኖች እንደሆኑ ስማቸውም እንደሚከተለው ነው…

1፦ ካፒቴን አክሊሉ መዘነ፣
2፦ ካፒቴን ጥላሁን ቱፋ፣
3፦ ካፒቴን ጌቱ ወርቁና
4፦ ካፒቴን ቢንአም ግዛው

አና ጎመሽ –ርዕዮትና እስክንድር “የኅሊና እሥረኞች ናቸው” አሉ

$
0
0

 

hana

ለያዝነው የአውሮፓ 2013 ዓ.ም የአውሮፓ ፓርላማ የሳኻሮቭ ሽልማት ሁለት ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ ሰባት ዕጩዎች ቀርበዋል፡፡
ለያዝነው የአውሮፓ 2013 ዓ.ም የአውሮፓ ፓርላማ የሳኻሮቭ ሽልማት ሁለት ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ ሰባት ዕጩዎች ቀርበዋል፡፡

ሽልማቱ ለሃሣብ ነፃነት ለሚታገሉና ለታገሉ የሚሰጥ የአውሮፓ ፓርላማ ዓመታዊ ክንዋኔ ነው፡፡

ኢትዮጵያዊያኑን ዕጩዎች ርዕዮት ዓለሙንና እስክንድር ነጋን ለሽልማት ካቀረቡት አርባ የአውሮፓ ፓርላማ አባላት አንዷ የፓርላማው አባል፣ እንዲሁም የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴው እና የሰብዓዊ መብቶች ንዑስ ኮሚቴ አባል የሆኑት አና ጎመሽ ይገኙበታል፡፡

ርዕዮት ዓለሙርዕዮት ዓለሙ


በአሁኑ ምርጫ ርዕዮት እና እስክንድር ቁጥራቸው ወደ 12 ከሚደርስ ከመላው ዓለም ከተጠቆሙ ሰዎች መካከል ወደ ሰባቱ አጭር ዝርዝር የገቡ መሆኑን ሚስ ጎመሽ ጠቁመው ፓርላማው የፊታችን ጥቅምት ውስጥ በሚያደርገው የተሟላ ስብሰባው ላይ አንዱ ለሽልማቱ በድምፅ እንደሚወጣ አመልክተዋል፡፡

እስክንድርና ርዕዮት የተመረጡት ፓርላማው ባወጣው መስፈርት መሠረት የሚያደርጉት ትግል የሃገራቸው ዴሞክራሲ፣ ነፃነትና ፍትህ የለው አስተዋዖ ተመዝኖ መሆኑንም ሚስ ጎመሽ ገልፀዋል፡፡

እስክንድር ነጋእስክንድር ነጋ

“እነዚህ ሰዎች እውነተኛ የሰብዓዊ መብቶች ታጋዮች ናቸው – ያሉት አና ጎመሽ ሁለቱ የኅሊና እሥረኞች ብቻ ሣይሆኑ በኢትዮጵያና በመላ አፍሪካም ለነፃነት፣ ለዴሞክራሲ፣ ለሕግ የበላይነት ለሚታገሉ ሁሉም ደወል ወይም መታያ ናቸው” ብለዋል፡፡

የያዝነው የአውሮፓ ዓመት የሃሣብ ነፃነት የሳኻሮቭ ሽልማት ዕጩዎች ስሞች ለውጭ ጉዳዮች እና የልማት ኮሚቴዎቹ ጥምር ስብሰባ መቅረባቸውን የአውሮፓ ፓርላማ ያስታወቀው ከትናንት በስተያ ሰኞ ነበር፡፡

በፓርላማው መግለጫ መሠረት ፓኪስታናዊቷ ማላላ ዩሳፍዛይ፣ አሜሪካዊው ኤድዋርድ ስኖውደን፣ ኢትዮጵያዊያኑ ርዕዮት ዓለሙ እና እስክንድር ነጋ፣ ቤላሩሲያዊያኑ አሌስ ቢያላትስኪ፣ ኤድዋርድ ላባዉ እና ማኮላ ስታትኬቪች በመላ የሃገሪቱ የፖለቲካ እሥረኞች ስም፣ ሩሲያዊው ሚኻይል ኾርዶቭስኪ፣ የቱርኩ “የቆመ ሰው” በሚል መጠሪያ የተጀመረው በቱርክ መንግሥቱ ላይ አፍጣጭ የታክሲም አደባባይ ተቃዋሚዎች ንቅናቄ የመጀመሪያው ተሰላፊ ኤርዶም ግዩንድዩዝ፣ የሲኤንኤን ቴሌቪዥን አውታር “ፍሪደም ፕሮጀክት (የነፃነት ፕሮጀክት)፡- ዘመነኛውን ባርነት ማብቃት” የሚባለው ፕሮግራም ናቸው፡፡

Source VOA

አንድነት መስከረም 19 በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ግማሽ ሚሊዮን ሕዝብ ይወጣል አለ –መኢአድም በሰልፉ ላይ ንቁ ተሳትፎ አደርጋለሁ ብሏል

$
0
0

በዘሪሁን ሙሉጌታ – ሰንደቅ

sept 19አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር በጋራ በመሆን በመጪው መስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ግማሽ ሚሊዮን ሕዝብ እንደሚወጣ አስታወቀ። የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በበኩሉ ሰልፉ እንዲሳካ ከሰልፉ ዋና አስተባባሪ አንድነት ፓርቲ ባልተናነሰ ሁኔታ ንቁ ተሳታፊ እንደሚሆን ገልጿል።

የአንድነት ፓርቲ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስራት ጣሴ እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ሊቀመንበር አቶ አበባው መሐሪ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት ሰላማዊ ሰልፉ ዋና ዓላማ ህገ-መንግስታዊ ጥሰትን መቃወምና መንግስትን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ድርድር ለማምጣት ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።

ሰልፉን በዋናነት እያስተባበረ ያለው አንድነት ፓርቲ ለአዲስ አበባ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና የህዝባዊ ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ባቀረበው ቅጽ ላይ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በግምት ግማሽ ሚሊዮን (500ሺህ) ሰው እንደሚገኝ ይፋ አድርጓል። በሰልፉ ላይ መጠሪያቸውን 33 ያደረጉ ወደ 23 የሚሆኑ ፓርቲዎች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተገልጿል።
ቀደም ሲል የአንድነት ፓርቲ በሀገሪቱ ልዩ ልዩ ከተሞች ለሦስት ወራት ያህል ‘‘የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት’’ በሚል ርዕስ ሰላማዊ ሰልፎች ሲያካሂድ ቆይቷል። ከሕዝባዊ ንቅናቄው ዘመቻ መካከል የፀረ-ሽብር ህጉ ይሰረዝ የሚለው ይገኝበታል። ፓርቲው ይህንኑ ዘመቻ ማድረጉንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ፓርቲዎችን ማከራከሩ አይዘነጋም።

በመጪው መስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.ም በሚካሄደው ሰልፍ ላይ ሁሉም ፓርቲዎችን የጋራ መግባባት በደረሱበት ‘‘ህገ-መንግስታዊ ጥሰትን መቃወም’’ የሚል ጥቅል ሃሳብን በማንገብ፣ የፀረ-ሽብር ህጉና ሌሎች አፋኝ ሕጎች እንዲሰረዙ፣ የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ፣ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቄዬአቸው እንዲመለሱ፣ የሃይማኖት ነፃነት እንዲከበርና የኑሮ ውድነት እና የስራ አጥነት ጥያቄዎች በጎላ መንገድ በሰልፉ ላይ እንደሚንፀባረቁ ከአቶ አስራትና ከአቶ አበባው ገለፃ መረዳት ተችሏል።

‘‘የኢህአዴግ አባል መሆን ከኢትዮጵያዊ ዜግነት በላይ የሆነበት ጊዜ ላይ ደርሰናል’’ ያሉት አቶ አስራት፤ ኢህአዴግ አባል ያልሆነ ብዙሃኑ የሙሉ ዜግነት መብቱን እየተነፈገ ነው ብለዋል። ይህ ሁሉ የሚያሳየው በሀገሪቱ የሕግ የበላይነት ጠፍቶ ኢ-ህገመንግስታዊነት መስፈኑን የሚያረጋግጥ በመሆኑ፤ ለህግ የበላይነት ለህገ መንግስታዊነት ክብር የሚሰጥ የከተማዋና የአካባቢዋ ህብረተሰብ በሰልፉ ላይ በመውጣት ተቃውሞውን እንዲያሳይ ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የመኢአድ ፕሬዝዳንት ፓርቲያቸው ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር በመሆን ከዚህ ቀደም በመኢአድ ጽ/ቤት ሕዝባዊ ስብሰባ ማስተባበሩን በማስታወስ መስከረም 19 ቀን በተጠራው ሰልፍ ላይ መላ አባሎቹና መዋቅሩን በማንቀሳቀስ በሰልፉ ላይ በዝግጅት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

የሰልፉ አላማ ህብረተሰቡ ያለበትን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ሃይማኖታዊ ችግሮች ገደባቸው እያለፉ መሆኑን በገሃድ የሚያሳይበትና መንግስትም ከገባበት ኢ-ህገመንግስታዊ አካሄድ ቆም ብሎ ወደ ውይይት እንዲመጣ ለማስገደድ እንደሆነም ከፓርቲ አመራሮቹ ገለፃ መረዳት ተችሏል።

ሰልፉን ለማስተባበርና ስኬታማ ለማድረግ በአንድነት በኩል ልዩ ግብረሃይል መቋቋሙን የጠቀሱት አቶ አስራት፤ ሕዝቡም ያለአንዳች ማወላወል ወደ አደባባይ ወጥቶ ተቃውሞውን እንደሚያሳይም እምነታቸውን ገልፀዋል። ከሰልፉ በኋላ መንግስትና ተቃዋሚዎች በጋዜጣና በሬዲዮ የሚያደርጉትን የአሉባልታ ዘመቻ በማቆም ወደ ህጋዊና በሁሉም ወገኖች ተአማኒነት ወደአለው የውይይት መድረክ ይመጣሉ የሚል እምነት አለኝ ብለዋል።

“መንግስት አንድነት ሰላማዊ ሰልፍ በጠራበት ዕለት በተመሳሳይ በየቀበሌው ስብሰባ መጥራቱን እንዲሁም በቅርቡ ከሰማይ ወርዷል የተባለ መስቀል በአቃቂ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የገብርኤል ቤተክርስቲያን በዕለቱ ሄዶ እንዲያይ መደረጉ በሰልፉ ላይ ህብረተሰቡ እንዳይገኝ ከወዲሁ የሚደረግ ጥረት ቢሆንም በእኛ በኩል ህብረተሰቡ ያለበትን አንገብጋቢ ችግር ስለሚገነዘብ ሰልፉ ላይ ከመገኘት ወደኋላ አይልም። መንግስት ትንንሽ ምክንያቶችን ሰበብ በማድረግ መሰናክል ለመፍጠር ቢሞክርም የሰልፉ አላማ ይመታል” ሲሉ አቶ አስራት ገልፀዋል።


በሚ/ር ደኤታ ማዕረግ ከሚገኝ የልብ ወዳጄ ጋር በሃገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ያደረግኩት ሚስጢራዊ ውይይት

ከልቤ ሰው ጋ በአማኑኤል ሆስፒታል –ከወሰን ሰገድ ገ/ኪዳን (ጋዜጠኛ)

$
0
0

==== እንደ መግቢያ ====


ትናትና ያልጠበቅኩትንና ያልገመትኩትን “ዜና” ሰማሁ፡፡ የክፉ ቀን ጓደኛዬ ችግር ውስጥ መሆኑን እና አማኑኤል ሆስፒታል መግባቱን፡፡ ይህ ጓደኛዬ በእኔ ህይወት ውስጥ ልዩ ቦታ ያለው ነው፡፡ በጭንቅ ጊዜ፣ በመከራ ጊዜ፣ “የሰው ያለህ” በሚያሰኝ ጊዜ የሰውም ሰው መሆኑን በተግባር ገልፆ ያሳየኝ የልቤ ሰው ነው፡፡ የጭንቅ ጊዜ ወዳጄ፣ ጭንቅ ውስጥ ሆኖ እኔን ማግኘት ይፈልጋል፡፡ ግን ምን ያደርጋል!? መሽቷል፡፡ መንጋት አለበት፡፡
አይነጋ የለም ነጋ፡፡

ከዕንቅልፌ ስነሳ መንጋት ብቻ አይደለም፤ ረፋድ ሆኗል፡፡ ፊቴን ለመታጠብ ደጃፌን ከፍቼ ስወጣ በአጋጣሚ የተጎራበትኩት ጋዜጠኛ ብርሃኑ በላቸው “በለሊት አማኑኤል ሆስፒታል እሄዳለሁ ብልህ አልነበር እንዴ?” አለኝ፡፡
“ልሄድ ነው፤ ለሊቱን ሙሉ በሃሳብ ስናውዝ አድሬ ሲነጋጋ እንቅልፍ ጣለኝ” አልኩት ሰዓት እያየሁ፡፡ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ሆኗል፡፡
“ሲሳይ ምን ሆኖ ነው?… ለማንኛውም የምንተጋገዘው ነገር ካለ ንገረኝ” አለኝ ብርሃኑ ወደ ውጪ በር
እያመራ፡፡ ልክ ነው የዚህ ወዳጄ ስም ሲሳይ ነው፡፡ ከዚህ በፊት አስተዋውቄያቸዋለሁ፡፡ ሲሳይ በቀለ ይባላል፡፡ በ”የቃሊቲ ምስጢሮች” ትረካ ውስጥ ስሙን ያልገለፅኩት ለ”ጥንቃቄ” ብዬ ነው፡፡ አሁንም ስሙን መግለፄ ትክክለኛ ተግባር ይሁን አይሁን እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ግን ….
የሆነ ሆኖ የቁርጥ ቀን ወዳጄ ሲሳይ በቀለ ከእውቅ የዜማና ግጥም ደራሲዎች መሃል የሚመደብ ነው፡፡ በሕዝብ ልብ ውስጥ የቀሩ ምርጥ ምርጥ የግጥምና የዜማ ድርሰቶች አሉት፡፡ በአንጋፋና በወጣት ድምፃውያን አንደበት የናኙ፡፡ ይህ ሰው ነው አማኑኤል ሆስፒታል ለመግባት የተገደደው፡፡ ለምን!? ምን ገጥሞት ይሆን!?

==== በአማኑኤል ቅጥር ግቢ ====
ከቀኑ 5 ሰዓት የሆስፒታሉን ዋና በር አልፌ እየዘለቅኩ ሞባይሉን አወጣሁና ደወልኩለት፡፡ ስልኩ ይጠራል፤ አያነሳም፡፡ ሞባይሌ አምስት ጥሪ ያህል እንዳስተላለፈ አንድ የህሙማን ልብስ የለበሰ ሰው እጁን ከፍ አድርጎ ምልክት አሳየኝ፡፡ እሱ ነው፡፡ ሲሳይ በቀለ ነው፡፡
ገፅታዬ ላይ ምንም ለውጥ እንዳይታይ እየጣርኩ እጄን ዘረጋሁለት፡፡ ጨበጠኝ፡፡ ትከሻ ለትከሻ ተገጫጨን፤ ከዚያም ተቃቀፍን፡፡ ….ከሠላምታ በኋላ እጅ ለእጅ ተያይዘን ሳለ አጠገባችን ወደሚገኝ የሃኪም ቤቱ አንድ ጥጋት መራሁት፡፡
“ና! ወደ እኔ ክፍል እንሂድ፡፡” አለኝ ግቢው ውስጥ ወደሚገኝ የተከለለ ሌላ ግቢ እየመራኝ፡፡
ቀፈፈኝ፤ ቢቀፈኝም ምንም ማድረግ አልችልም፡፡የምንገባበት ግቢ ውስጥ ዱላ ይዘው ወዲያ ወዲህ የሚያወናጭፉ ታካሚዎች ይታዩኛል፡፡ ሞባይል ይዘው እየተጯጯሁ የሚነጋገሩ፤ ብቻቸውን የሚያወሩ፤ በዝምታ የሚንጎራደዱ…የሆነ ሰው ላይ የሚዝቱ፣ የሚሳደቡ ..ወዘተ ታካሚዎች ይታዩኛል፡፡
እነዚህን መሰል ታካሚዎች በሥጋት ዓይን እያየሁ ጓደኛዬን ተከተልኩት፡፡ ግቢው ውስጥ የሚገኝ ትልቅ ሕንፃ ሥር ወደ ታችኛው ክፍል ይዞኝ ወረደ፡፡
“አንተ ሻንጣ ስለያዝክ ሐኪም ነው የምትመስለው” አለኝ የያዝኩትን ላፕቶፕ እየጠቆመኝ – እናም የተኛበትን ክፍል በር አልፎ ገባ፡፡ አልጋው ላይ አረፍ ብሎ እኔም አረፍ እንድል ጋበዘኝ፡፡ ከጎኑ ተቀምጬ ክፍሉን ቃኘሁት፡፡ ፅዱ ክፍል ነው፡፡ 20 ያህል በሥነ ሥርዓት የተነጠፉ አልጋዎች ተዘርግተዋል፡፡ አልፎ አልፎ የተነጠፉት አልጋዎች ላይ ጋደም ያሉ ታካሚዎች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ ሞባይል ለብሰዋል፡፡ አንዳንዶቹ የሆስፒታሉን ሳይሆን የራሳቸውን ልብስ የለበሱ ናቸው፡፡
“አሪፍ ክፍል ነው፤” አልኩት ወሬ እንዴት እንደምጅምር ግራ ገብቶኝ፡፡
“ይኼኛው ክፍል የሳይኪክ ችግር የሌለባቸው ነው፡፡” አለኝ፡፡ ሌላም ሌላም ነገር ነገረኝ፡፡ አነጋገሩ ጤነኛ መሆኑን እንድረዳለት የሚያሳብቅ ነው፡፡እናም ዝም ብዬ ሰማሁት፤ ዓይን አይኑን እያየሁ ሰማሁት፡፡ ይህቺን የማዳመጥ አስፈላጊነት የተማርኩት አንድ የእርዳታ ድርጅት ለሳምንታት “ፒር ካውንስለር” የተባለ ኮርስ በሰጠን ጊዜ ነው፡፡ “እንዲህ ዓይነት ችግር ያለበት ሰው ችግሩን ሲነግርህ ከልብህ አድምጠው፤ ከልብህ ማዳመጥህን እንዲረዳልህ ዓይን ዓይኑን እየው፡፡ ዓይኑን ከማየት በተጨማሪ ማዳመጥህን እርግጠኛ ሆኖ ችግሩን በራሱ ፍቃድ ዘክዝኮ እንዲነግርህ ‹እህ! እህ!› እያልክ አበረታታው” የሚል ዓይነት ነው የኮርሱ ይዘት፡፡
እናም የሚነግረኝን “እህ!” ብዬ አዳመጥኩት፡፡ ልናገርስ ብል ምንድነው የምናገረው? ንግግሬንስ ከየትና እንዴት ነው የምጀምረው!?…ግራ ግብት የሚል ነገር ነው፡፡ ደግነቱ እሱ ራሱ ወደዋናው ጉዳይ ገባልኝ፡፡
“እዚህ ከገባሁ አንድ ወር አለፈኝ፡፡ ወዲያውኑ አንተን ማግኘት ነበር በጥብቅ የፈለግኩት፡፡ ትናንት እንደነገርኩህ ስልኬ ጠፍቶ ስለነበር ላገኝህ አልቻልኩም፡፡ የአንተን ቁጥር ለማግኘት የደወልኩላቸው ሁሉ የበፊቱን ስልክ ቁጥርህን ነው የሚሰጡኝ፡፡ ….አሁን እንዴት እንዳገኘሁህ ታውቃለህ!? በመዝሙር ዮሐንስ (ድምፃዊ) በኩል ነው፡፡”
“መዝሙር እንዴት ስልኬን አገኘ?”
“ሁለት ቀን ሙሉ ስልክህን ማግኘት ሞክሮ አልተሳካለትም ነበር፡፡ እንዳልተሳካለት ሲነግረኝ የድምፃዊ ትዕግስት ፋንታሁን ወይም የባለቤቷን ስልክ ካወቅህ እነሱን ጠይቃቸው አልኩት፡፡ በዚህ ሁኔታ ነው የአንተን ስልክ ትናንትና ያገኘሁት” አለኝ፡፡
የነገረኝ ነገር አልደነቀኝም፡፡ ድምፃዊ ትዕግስት ፋንታሁን በ2002 ዓ.ም “ና” በሚል ርዕስ ለአድማጭ ባቀረበችው አልበም ውስጥ የሁለቱን ግጥሞች የፃፍኩት እኔ ነኝ፡፡ (ሃሃሃሃ ይህቺ ነገር እንደማስታወቂያ እንዳትቆጠርብኝ) ያኔ ከትዕግስት ፋንታሁን ጋር ለሥራ እንገናኝ ነበር፡፡ (ከትዕግስትም ሆነ ከባለቤቷም ጋር አብሮ አደግ ነን) …እንዲያም ተባለ እንዲህ ያንን አስታውሶ እኔን ማግኘት መቻሉ አስደሰተኝ፡፡ ጤንነቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተረዳሁ፡፡ የልቤ ሰው የከፋ ሁኔታ ላይ ባለመሆኑ ተፅናናሁ፡፡ የሆነ ሆኖ ስለ ዘፈን ካነሳሁ ዘንዳ ዛሬ አማኑኤል ሆስፒታል ስለሚገኘው የልቤ ሰው ሲሳይ በቀለ የግጥምና የዜማ ደራሲነት ጥቂት በምልሰት ላውራ፡፡

====== ምልሰት =======
“እኔን ናፍቀሽኛል – አልናፈቅኩሽም ወይ
መራራቁ ቀርቶ – አንገናኝም ወይ
ፍ…ቅ …ር …..
ፍቅር አይገድሽም ወይ”

” አማላጅ ማን ይሁን፤ ማንን ልላክብሽ
ህመሜ ተሰምቶሽ – ፍቅር እንገድሽ….”
የዘፈኑን ግጥም በትክክል መከተቤን እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ የዜማው ለዛ እና ፍሰት ግን እስካሁን በጆሮዬ ይሰማኛል፡፡ ዘፈኑን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት በሬድዮ ነው፡፡ ከ20 እና ከ25 ዓመት በፊት፡፡ ድምፃዊው ማን እንደሆነ በስም አላስታውስም፡፡ የዜማና የግጥሙ ደራሲ ግን ሲሳይ በቀለ ነው፡፡
ሲሳይ በቀለ ከበርካታ ዕውቅና ድንቅ ድምፃውያን ያለ የጥበብ ሰው ነው፡፡ ከበርካታ የጥበብ ሰዎች ጀርባ ያለ ጥበበኛ ነን፡፡ ለጊዜው ለእነማን ለእነማን ሥራዎቹን እንደሰጠ ማውጋት አልፈልግም፡፡ ነገር ግን ሁለቱን ወንድማማቾች ታዋቂ ድምፃውያን ልጥቀስ፡፡ ፀሐይዬ ዮሐንስን እና መዝሙር ዮሐንስን፡፡
ለእነሱ ከሰጣቸው ሥራዎች ውስጥ አብዛኛው ሰው የሚወድለትን የመዝሙር ዮሐንስን “ልጅነቴ”ን ዘፈን ብቻ ላስታውስ፡፡ የ”ልጅነቴ” ዘፈን ዜማና ግጥም ደራሲ ይኸው የልቤ ጓደኛ ሲሳይ በቀለ ነው፡፡
“….ውሃ ሽቅብ ላይወጣ
ኑግ እንደሱፍ ላይነጣ
ልጅነቴ ናፈቀኝ ተመልሶ ላይመጣ….”

“ፊደል ይዤ በጉያዬ
ተቃቅፌ ከእኩያዬ….”
ይህንን የመዝሙር ዮሐንስን “ልጅነቴ” ሰምቶ በትዝታ የማይመሰጥ የለም፡፡ እነሆ የዚህ ዘፈን ግጥምና ዜማ ደራሲ ነው የልቤ ሰው፡፡ ዛሬ አማኑኤል ሆስፒታል የሚገኘው፡፡

===== ምን ሆኖ ነው!?====
የሆነው ብዙ ነው፡፡ ታሪኩም ረዥም ነው፡፡ 6 ዓመታት ያህል ወደ ኋላ የሚያስጉዝ ነው፡፡ ቤተሰቡ ተበትኗል፤ ልጆቹን አጥቷል፤ ቤቱም በእሱና በባለቤቱ ግጭት የተነሳ በሌላ ሰው እጅ ነው ያለው፡፡ ….ህይወት ፊቱን ካዞረችበት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ይኸው ነው፡፡ ከዚህ በላይ ማለት አልችልም፡፡ እንዲያም ሆኖ ፊቱን ሙሉ በሙሉ ወደ ጥበብ አዙሮ ቤት ተከራይቶ ራሱን እያስተዳደረ ህይወትን መቀጠል ችሎ ነበር፡፡
ከወራት በፊት ግን “ሰው ጠላሁ፤ ሰው ፈራሁ፤ መሸሽ ጀመርኩ” አለኝ፡፡
“ለምን?”
“የሚታመን ሰው ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ያሰብኩት ቀርቶ ያላሰብቡት ሲሆን ግራ ገባኝ፡፡ ጨነቀኝ፡፡ ሰው መሸሽ ጀመርኩኝ፡፡ ሰው ለመሸሽ ብዬ ትንሽ አልኮል አበዛሁ መሰለኝ ታመምኩኝ፡፡” አለኝ፡፡
“ሰው ይጠላል እንዴ?” ስል ጠየቅኩት እየፈራሁ እየተባሁ፡፡ “ትናንትና እንኳ አንተ ያለህበትን ከነገርከኝ በኋላ ይህንን ፃፍኩኝ” አልኩት ኮምፒውተሬን እየከፈትኩ፡፡ ፌስ ቡክ ላይ የፃፍኩትንና የተሰነዘረውን አስተያየት ጭምር አስነበብኩት፡፡ “ይህ ሁሉ ሰው አንተ እዚህ በመገኘትህ አዝኗል፡፡ የማያውቅህ ሰው ያንተን ጤንነት ተመኝቷል፡፡ እና እንዴት ሰው ይጠላል፤ ሰው ለሰው መድሃኒቱ ነው ይባል የለ እንዴ”
የፌስ ቡክን አስተያየት ካነበበ በኋላ ፊቱ ፈካ አለ፡፡ ወዲያው ደግሞ ተኮሳተረ፡፡
” ምን ላርግ? የሚታመን ሰው አጣሁ፤ በእምነት የሰጠኋቸውን ሥራ የእኔ ነው ብለው ያሳትሙታል፡፡ ገንዘቡ ይቅር ስሜን እንኳ ለመፃፍ (ለማንሳት) አይፈልጉም፡፡ …ሌላው ሌላውን ተወው፤ አሁን በቅርቡ የወጣው ዘፈን እንኳ የኔ ሥራ ነው፡፡ እኔ አልብላ፤ አልጠጣ ስሜን እንኳ መፃፍ ማንን ገደለ!?”
ዝም አልኩኝ፤ ዝም፡፡ ዝም ከማለት ሌላ ምን ማለት እችላለሁ፡፡ ሲሳይ በቀሌ “የኔ ፈጠራ ነው” እያለ የሚነግረኝ ዘፈን ሀገር ሁሉ ትከሻውን የሚሰብቅበት፣ የሚወዛወዝበት እጅግ ተወዳጅ የሆነ ዘፈን ነው፡፡ ይህ የእሱ ነው፤ የእሱ አይደለም ለማለትም ላለማለትም ድምፃዊውንና አሳታማውን ማነጋገር ያስፈልጋል፡፡
“መልካም፤ እንዲህ ዓይነት ነገር ያጋጥማል፤ ደግሞም ላንተ አዲስ አይደለም፡፡ አሁን እሱን እንተወውና እኔ እንድረዳህ የምትፈልገው ነገር ምንድነው? የምችለው ከሆነ ልረዳህ ዝግጁ ነኝ፡፡”
“አሁን በጣም ደህና ነኝ፡፡ በቅርቡ ከዚህ እወጣለሁ፡፡ ስወጣ የት እንደምኖር አላውቅም፡፡”
አመመኝ፡፡ የልብን ስር ጠቅ የሚያደርግ ህመም ተሰማኝ፡፡
“እዚህ እስካለሁ ድረስ መንግስት የሚያቀርብልኝን እንጀራ በልቼ ማደር እችላለሁ፡፡…”
ከዚህ በላይ መስማት አልቻልኩም፡፡ አቋረጥኩት፡፡
“ምን ችግር አለው!? አሁን እኔ ቤት ተከራይቻለሁ፤ ከእኔ ጋር ትኖራለህ፡፡ ከኔ ጋ ኖርክ ማለት የምትበላው አታጣም ማለት ነው፡፡ ይኼ ሊያስጨንቅህ አይገባም፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ የሚሆነው ይሆናል፡፡…” አልኩት፡፡
“አዎ ካንተ የምፈልገው ይኼን ነው፡፡ የልጄን ት/ቤት የከፈለልኝ ሰው ነው፡፡…”
“ግዴለም የምንችለውን እናደርጋለን፤ ዋናው ጤና ነው፡፡ ካንተ ጤንነት በኋላ ነው፤ አሁን አታስብ” አልኩት፡፡ “አታስብ” ይባላል እንዴ!!? አለማሰብስ ይቻላል እንዴ!!? እንጃ!!!!
እነሆ ለአንድ ሰዓት ያህል እንዲህ እና እንዲያ አብረን ቆየን፡፡ ልንሰነባበት ሆነ፡፡ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ከክፍሉ ለመውጣት በዝግታ ማዝገም ጀመርኩ፡፡ ተከተለኝ፤ ሊሸኘኝ፡፡ እየሸኘኝ
“ደግሞ በዚያው እንዳትጠፋ፡፡ እየመጣህ ጠይቀኝ፡፡ እስካሁን መዝሙር ዮሐንስ ብቻ ነው እየመጣ የሚጠይቀኝ!!”
“አልጠፋም፤ እመጣለሁ፡፡ በጣም የምትፈልገኝ ከሆነ ደውልልኝ፤ እመጣለሁ፡፡” አልኩት ዋናውን የግቢው መውጫ በርቀት እያየሁ፡፡
በመጨረሻም ተሰነባበትን፡- ነገን እያለምን፡፡ ነገም ሌላ ቀን ነው!!

Pen

 

“ከሰማይ ወረደ ለተባለው መስቀል የሳይንስ ምርመራ አይፈቀድም ተባለ”– (አዲስ አድማስ ጋዜጣ)

$
0
0

(ፎቶ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ)

(ፎቶ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ)


አለማየሁ አንበሴ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ለታተመው አዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደዘገበው፦

በአቃቂ ቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን ከሰማይ ወረደ የተባለው መስቀል ፓትርያርኩ በተገኙበት ለህዝብ እንዲታይ መግቢያ መንገድ እስኪሰራ ድረስ የተራዘመ ሲሆን፣ በመስቀሉ ላይ የሳይንስ ምርመራ እንደማይፈቀድ ተገለፀ፡፡ ከሶስት ሳምንት በፊት በፍንዳታ ድምፅና በብርሃናማ ቀስተደመና ከሰማይ ወረደ የተባለው መስቀል፣ በሚቀጥለው ሳምንት መስከረም 19 ቀን ለህዝብ ይታያል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፣ ፓትርያርኩ የሚገኙበት ስነስርዓት ለማዘጋጀት ጊዜው እንደተራዘመ የቤተክርስቲያኗ አስተዳዳሪዎች ተናግረዋል፡፡ መስቀሉ ለህዝብ የሚታየው ቅዱስ ፓትሪያርክ አቡነ ማቲያስ በተገኙበት ስነስርዓት መሆን አለበት መባሉን አስተዳዳሪዎች ጠቅሰው፤ መንገዱ ጭቃ ስለሆነ ጠፈፍ ብሎ ለመኪና እስኪስተካከል ድረስ ቀኑ መራዘሙን ገልፀዋል፡፡ ቀኑ ገና እንዳልተወሰነና ለፓትሪያርኩ ጋር ውይይት እየተደረገበት ነው ያሉት የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪዎች፤ ስነስርዓቱን ህዳር 11 ቀን ለማካሄድ እንደታሰበ ጠቁመዋል፡፡

ከአዲስ አበባና በአቅራቢያዋ ከሚገኙ አካባቢዎች በየእለቱ ከ3ሺ በላይ ሰዎች ቦታውን እየጎበኙ መሆናቸውን የገለፁት የቤተክርስቲያኗ መጋቢ ሃዲስ ፍሰሃ፤ እኛም በየእለቱ ከ15 ጊዜ በላይ ስለ ተከሰተው ተዓምር ገለፃ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ መስቀሉ ባረፈበት ሳር ላይ እንዲሁም ወደ ቤተ መቅደሱ ከገባ በኋላ የተነሱ ፎቶዎችን የያዘ ካርድ ታትሞ ለምዕመናን በ10 ብር እየተሸጠ ነው፡፡ በፎቶግራፍ ላይ የሚታየው መስቀል በሰው የተሰራ የዕደ ጥበብ ውጤት እንደሚመስል በመጥቀስ ከሰማይ ወረደ መባሉን የሚጠረጥሩ መኖራቸውን በተመለከተ መጋቢ ሃዲስ ፍስሃ፣ እውነቱን የሚያውቀው ፈጣሪ ነው ብለዋል፡፡

በምድራችን የተሰራ የሚመስል መስቀል ከሰማይ ሊወርድ አይችልም የምንል ከሆነ፣ በምድራችን የምናረባው አይነት በግ ለአብርሃም ከሰማይ ወርዶለታል የሚለውን የመፅሃፍ ቅዱስ ቃል መጠራጠር ይሆናል ብለዋል መጋቢ ሃዲስ ፍስሃ፡፡ የመስቀሉን ስሪት እንዲሁም መስቀሉ አረፈበት የተባለውን ሳርና አፈር ለመመርመር ሃሳብ ተነስቶ እንደሆነ ተጠይቀው መጋቢ ሃዲስ ሲመልሱ፤ “ይህ መስቀል የቤተክርስቲያኒቱ የክብር መገለጫ ነው” በማለት ተቃውመዋል፡፡

እስካሁን በስፍራው የተፈፀመውን ተአምር ሰምተው የሚያደንቁ እንጂ በመስቀሉና በቦታው ላይ እንመራመራለን የሚሉ ምሁራን አላጋጠሙኝም ያሉት መጋቢ ሃዲስ፤ “እንዲህ ያለ ጥያቄ ያላቸውም ካሉም፣ የማይሞከር ነው” ያሉት መጋቢ ሃዲስ፤ የሃይማኖት ጉዳይ ስለሆነ ቦታውን እንፈትሻለን፣ የወረደውን መስቀል እንመረምራለን ለሚሉ የሳይንስ ባለሙያዎች ፈፅሞ አይፈቀድም ብለዋል፡፡ መስቀሉ ከሰማይ ከመውረዱ አስቀድሞ ራዕይ ታይቶኛል የሚል ሰው እስካሁን አላጋጠመን ያሉት መጋቢ ሃዲስ፤ ቤተክርስቲያኒቱን ያቋቋሙት አባት ግን፣ ቦታው የእግዚአብሔር ክብር መገለጫ እንደሚሆን በራዕይ እንደታያቸው ተናግረው ነበር ብለዋል፡፡

የተወልደ በየነ (ተቦርነ) በዘፈን እናውራ ሲዲ የፊታችን ማክሰኞ ይመረቃል

$
0
0

Teborne CD Release Flayer (2)
(ዘ-ሐበሻ)፡ በተለያዩ የራድዮ ጣቢያዎች አዝናኝ የሙዚቃ ሥራዎችን በማቅረብ ተወዳጅነትን ያተረፈው ጋዜጠኛና የሙዚቃ አማካሪ ተወልደ በየነ በአይነቱ ልዩ የሆነው “በዘፈን እናውራ” የተሰኘ አስቂኝና ቁምነገር የያዘ ሲዲ ይዞ ቀረበ። ይህ በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኛል በሚል ከወዲሁ ግምት የተሰጠው ሲዲ የፊታችን እሁድ በቨርጂኒያ መዓዛ ሬስቶራንት እንደሚመረቅ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመልክቷል።

ከዚህ ቀደም ሽገር ሬዲዮ አሁን ደግሞ በኢሳት ራድዮና ቴኤቭዥን በሚያቀርባቸው የመዝናኛ ዝግጅቶች ተወዳጅነትን ያተረፈው ዜጠኛና የሙዚቃ አማካሪ ተወልደ በየነ በአይነቱና በአቀራረቡ ለየት በሚል መልኩ ይዞት የቀረበው የሲዲ ሥራ “በዘፈን እናውራ” ይሰኛል። በዚህ አዝናኝ ሲዲ ተወዳጁ ጋዜጠኛ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ከመሪ ጅምሮ እስከ ተቀዋሚ ያሉትን በዘፈን እያወራቸው ያስቃል፤ ያዝናናል ተብሏል።

ከመሪዎች በተጨማሪም ድምፃዊያኑንም በዘፈን እንደሚያወራቸው የተጠቀሰ ሲሆን በስራቸው ለተጠየቁት ምላሽ ከሰጡት ድምፃዊያን መካከልም ጥላሁን ገሠሠ፣ አስቴር አወቀ፣ ነዋይ ደበበ፣ ቴዎድሮስ ካሳሁን፣ ይገኙበታል ተብሏል:
የተቦርነ በየነው ይህ በአይነቱና በአቀረቡ የመጀመሪያ የሆነው ሲዲ ሴፕቴምበር 24 በመአዛ ሬስቶራንት ከ 8:30pm ጀምሮ ከተመረቀ በኋላ በመላው ዓለም ለአድማጭ እንደሚሰራጭ ይጠበቃል። በሲዲው ምረቃ ላይ መገኘት ለምትፈልጉ የመአዛ ሬስቶራንት አድራሻ 5700 Columbia Pike Falls Church, VA 22941 ነው። የሬስቶራንቱ ስልክ ቁጥርም (703) 820-2870 ነው።
መልዕክቱን በድምጽ ያድማጡ፦

ኦሮማይ ትግሉ በሚቻለውና በማንኛውም መንገድ!

$
0
0

ከቴዎድሮስ ሓይሌ (tadyha@gmail.com)

Oromayሠሞኑን የግንቦት ሰባት ዋና ፀሐፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ስለ ኤርትራ ቆይታቸውና ስለድርጅታቸው ቀጣይ የትግል እንቅስቃሴ ሠፊ ገለጻና ማብራሪያ በኢሣት ቴሌቪዠን ከሠጡ ወዲህ የዘረኛው የትግሬ ነጻ አውጪ ግንባር ደጋፊ የሆኑት መርገማዊ ልሳኖች( አይጋ ፎረም ፤ ትግራይ ኦላይንና አውራንባ ታይምስ) እና አንዳንድ ተንበርካኪ የመንደር ሬድዮኖች ሰፊ የውግዘትና የህዝብን መንፈስ ያሸብርልናል በተቃዋሚዎችም ላይ ጥርጣሬ ይዘራልናል በሚል ደካማ ግንዛቤ እያካሄዱ ካለው አሰልቺና ኋላቀር ፕሮፓጋንዳ እጅግ ተጋኖ እየቀረበ ያለው ከሻብያ ጋር አብሮ መስራት ታላቅ የሃገር ክህደት ስለመሆኑ እፍረት የለሽ ኡኡታ በማሰማት ላይ ይገኛሉ። ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

አፍሪካዊያን ከአይሲሲ በደቦ ወሙጣታቸውን ኢትዮጵያ ትደግፋለች

$
0
0

ቪኦኤ ዜና

የአፍሪካ ሃገሮች ከዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት – አይሲሲ አባልነት በደቦ እንዲወጡ ለማድረግ ኬንያ የጀመረችውን ጥረት እንደምትደግፍ የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር ኢትዮጵያ አስታውቃለች፡፡

578A83

በዓለምአቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ተከስሰው ጉዳያቸው እየታየ ያለው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታና ምክትል ፕሬዚዳንቱ ዊልያም ሩቶ /የተከሰሱባቸው ‘አቀናብረዋቸዋል’ ወይም ‘ተሣትፈውባቸዋል’ ተብለው የተጠረጠሩባቸው ‘በሰብዕና ላይ የተደረጉ ወንጀሎች’ የተፈፀሙት እንደስማቸው ቅደም ተከተል የኬንያ የገንዘብ ሚኒስትርና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር በነበሩበት እአአ በ2007 ዓ.ም ነው፡፡

አፍሪካዊያን ከአይሲሲ በደቦ ወሙጣታቸውን ኢትዮጵያ ትደግፋለች
የአፍሪካ ሃገሮች ከዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት – አይሲሲ አባልነት በደቦ እንዲወጡ ለማድረግ ኬንያ የጀመረችውን ጥረት እንደምትደግፍ የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር ኢትዮጵያ አስታውቃለች፡፡

ዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት በኬንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ላይ በሰብዕና ላይ በተፈፀሙ ወንጀሎች ክሥ መሥርቶ ጉዳያቸው ጄኔቫ ላይ እየታየ ሲሆን ፕሬዚዳንቱ ኡሁሩ ኬንያታ ደግሞ የፊታችን ኅዳር

የአፍሪካ ኅብረት በመጭው ወር ውስጥ በዚሁ የኬንያ ባለሥልጣናት ክሥና የፍርድ ሂደት ጉዳይ ላይ ልዩ ስብሰባ እንደሚያካሂድ የኅብረቱ ሥራ አስፈፃሚ አካል ምክትል ኃላፊ የሆኑት ኬንያዊው ኤራስቱስ ሞኤንቻ ለፈረንሣዩ የዜና ወኪል ገልፀዋል፡፡

ጉዳያቸው በዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት በተያዘው ከፍተኞቹ የኬንያ ባለሥልጣናት የፍርድ ሂደት ጉዳይ ላይ ኬንያዊያን የተለያየ አስተያየት አላቸው፡፡
በአይሲሲ እየታደኑ ያሉት ኦማር ሁሴን አል-በሽር – የሱዳን ፕሬዚዳንት
በአይሲሲ እየታደኑ ያሉት ኦማር ሁሴን አል-በሽር – የሱዳን ፕሬዚዳንት
በሌላ በኩል ደግሞ ዩናይትድ ስቴትስ የሱዳኑን ፕሬዚዳንት ኦማር ሁሴን አል በሽርን የመግቢያ ቪዛ ጥያቄ እያጠናች መሆኗን ገልፃለች፡፡

ለዝርዝር ዘገባው የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የቀይ ባሕር ሴራ፤ መጣ እያጓራ ! ከሎሚ ተራ

$
0
0

 

ምን አለ ብትተዉኝ መሬቴን ባለማ

ምን አለ ብታርፉ ወገኔ ቢሰማማ

             ……..

ወገን ደራሽ መሰሎ ሆዱን እየሞላ

ጎርፍ ሆኖ ሊወሰደው የቀይባሕር ሞላ

 

ምን አለባት የዚህ ግጥም መንደርደሪያ  አንባቢያንን ግራ ሊያጋባ ይችል ይሆናል ብዬ ሰግቼ ነበር፤ ሆኖም ኢትዮጲያዊያን ወገኖቼ በርካታዎቹ ““ድጓ ጾመዱጓ ፤ የደገሙ““በመሆናቸው መልዕክቱ በቀጥታ ምን ማለት እንደሆነ እንደሚረዱ አምናለሁና  ልቀጥል።

 

“”ይቺ፤ ምራቅ ሳትደርቅ፤”” ይባል ነበር አሉ ድሮ፤  ይግርማል” ሰለ ሻአቢያ ደባ አውርትን ሳንጨርሰ፡ እንደተመለከታችሁት የሻአቢያው መሪ በኤርትራው ቲቪ መሰኮት ብቅ ብለው በሁለት እጃቸው ወገባችውን ይዘው ጥርሳቸውን እያንቀጨቀጩ አንዳንዴም ጠያቂው (ጋዜጠኛው)  መግቢያ መውጫ እሰኪጠፋው፤ አይናችውን እያጉረጠረጡ  ለመሆኑ ኢትዮጲያ ማን ናት ? ?;;;;;;፤  ይቺ ከሁለተኛው አለም ጦርነት ማግሰት የተፈጠረች አገር  ? ? ;;;;;;;’  ኤርትራን ኮሎኒ ;;;;;;፤  አድርጋለች እየተባለ የሚወራው ? ? ;;;;፤  ይሄማ ለ ኢትዩጲያዊያን ትልቅ ክብር መሰጠት ነው። በሚል  ፌዛዊ አነጋገር ኢትዬጲያ ትላንት ወያኔ ሲገባ እንደተፈጠረች አይነት አድርገው ለማሰቀመጥ ሲሞክሩ መሰማት ምን ያኸል አሳዛኝና አሁንም ኢትዬጲያን የማጥፋት አባዚያችው እንዳልበረደላቸው አሰረግጠውልናል።

 

እንግዲህ ልብ በሉ ከእኚህ የ ኢትዬጲያ ሰም ሲጠራ ከሚያንገሸግሻችው ሰው ጋራ ነው ለኢትዮጲያ አሳቢ ናቸው፤  በሙሉ ልባቸው ወያኔ በኢትዬጲያ ሕዝብ ላይ የሚደረሰውን ግፍ ድጋፍ ለመሰጠት ቆርጠዋል። ድጋፋቸውም ወደር የሚገኝለት አይደለም ። እየተባለ ጠዋትና ማታ የሚለፈፈው። እኔ በበኩሌ እንዲገባኝ ለማድርግ ብዙ ጥረት አደረግኩ ። ብዙም ወደሖላ ተመልሼ ለመመልከት ሞከርኩ። አንዱም የሻአቢያ ተግባር ለ ኢትዬጲያ በጎ ነገር እንደሌለው እንጂ አንድም በጎ ተግባር እንደሌለው ነው መረጃው በሙሉ እሰካሁኗ ደቂቃ ድረሰ የሚያሳየኝ እና አንባቢያን ሆይ እባካችሁ እንደገና ቆም ብለን እንመርምር  በሻአቢያ እርዳታ አገር ነፃ አይወጣም። ሻአቢያ ከወያኔ ጋር ተባብርው ቀይባሕር እንዳይከቱን እንጠነቀቅ።

 

ይልቅ አገርውሰጥ ያለውን የሰላማዊ ትግል መደገፉ ጠቃሚና አሰፈላጊነቱን በሚከተሉት ሦሰት ነጥብ ለማሰቀመጥ ልሞክር እንሆ፦———

 

1ኛ)    የሰላም ትግል ማለት እኮ የሕብረተሰብን አሰተሳሰብና አመለካከት በጠመንጃ ሣይሆን በተሻለ አሰተሳሰብና አመለካከት የዲሞክራሲ ሰርአት እንዴት ማምጣት እንደሚቻል ማሰተማርና ማደራጀት ነው። ኢትዮጲያ በአለም ላይ ደሃ አገሮች ተብለው ከሚጠሩት አንዶና፤ ሕዝቦ በድህነትና ፍትሕ በማጣት፤ በጉሰቁልናና በሰደት፤ በበሽታ፤ በመፈናቀል፤ የምትታወቅ በመሆኗ፤ ይኸን አለማቀፍ ጉሰቁልና ለመቅረፍና የዲሞክራሲን ሂደት ለማምጣት በ አገር ውሰጥ የተጀመረው የሰላም ትግል ከጦርነት ትግል በላይ ዋጋ የሚያሰከፍል እንደሆነ የተረዱ ወጣት ታጋዬች ዋጋ እየከፈሉ እናዳለ በውል መረዳትና አንዳሰፈላጊነቱም ከያለንበት እንዳወጣጣችን ወደህገር በመመለሰ የሰላሙን ትግል በመቀላቀል በሐገር መሬት ላይ አሰፈላጊውን ዋጋ ለመክፈል የቆረጥን መሆን እንጂ በሻአቢያ ብብት ሰር ለመውደቅ መዘጋጀት መፍትሄ አይሆንም”። ከሁሉ በላይ የሰላሙ ትግል ሙሉ የሕዘብ ዽጋፍ ያለው ሲሆን ጦርነት ግን እንኳን እንደኛ ያለ ድሃ አገር ቀርቶ ዛሬ ባለማቀፍ ደረጃ ተደጋፊነት የለውም።

 

2ኛ)  ሻአቢያ ሲጀመርም፤ አሰካሁኖም ደቂቃ ደረሰ ለኢትዬጲያ መፈረሰ እንጂ፤ ግንባታ ሰርቶ አያውቅም ሊሰራም አይችልም።  ባገር ውሰጥ እየተካሄደ ያለውን የሰላም ትግል ባገር ውሰጥ ያሉት የመንግሰት አካላትም ሆኑ በሚሊቴሪው ክፍል፤ የሚገኙ አካላት ፖሊሱንም ጨምሮ በየቀኑ እየተከታተሉና፤ የወያኔ ግፍ አገዛዝ ምን ያኸል ሰርአተ አልበኛ እንደሆነ  እየተገነዘቡና ሊቆጣጠሩት ከሚችሉት በላይ እንደሆነና የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በሰተቀር ይኸንኑ የሰላም ትግል እንደሚቀላቀሉ በተለያየ ሁኔታ ምልክቶች እየታየ እንደሆነ በማሰተዋል መመልከት አሰፈላጊ ነው። ለምሳሌ በቅርቡ አገር ኮብልለው የወጡት ቱባ ቱባ የመንግሰት ባለሰልጣናትና የጦር ኦፊሻልሰ መመልከት አሰፈላጊ ነው።  ያኮበኮቡትን  አግዚአብሔር ይቁጠረው። ይኸ ሁሉ የሰላሙ ትግል ውጤት እንጂ ሻአቢያ በሰጠው ድጋፍ የተገኝ ውጤት እንዳልሆነ መረዳት በጣም አሰፈላጊ ነው።

 

3ኛ)  ወያኔ በሰላሙ ትግል በከፍተኛ ደረጃ ተዳክሟል። ለዚህ መረጃዎቹ መንግሰትነኝ ተብዬው አንዴ የሰላማዊ ሰልፍ ፍቃድ መሰጠትና ትርጉም በማይሰጥ ምክነያቶች መልሦ መከልከልና፤ ቀን ማራዘም ከብዙው በጥቂቱ ናቸው። ሌላውና ሊሰመርበት የሚያሰፈለገው ነጥብ ወጣቶቹ የሰላም መሪዎች በየጊዜው ከአንደበታቸው የሚሰማው የቆራጥነት አቆም አገራችን ምን አይነት ብርቅና ድንቅዬ ቆራጥ የሰላም ታጋዬች እንዳሏትና ምንም እንኳን የድሉ ጊዜ ቢረዝም ኢትዬጲያ  በቆራጥ የሰላም ታጋይ መሪዎቾ ተሰፋዋ የለመለመ እነደሆነ ያረጋግጣል። በ ሺ፤ የሚቆጠሩ ተከታዬችም እያፈሩ እንደሆነ በመረዳት ይኸንን የሰላም ትግል መደገፍና የሰላም መሪዎችን ማበረታታት እጅግ ጠቃሚና ወቅታዊ ነው እላለሁ።

 

ኢትዮጲያ’’’’’’’በሰላም ‘’’’’’’’’ታጋዮች’’’’’’’’ቆራጥ’’’’’’’አመራር’’’’’’’ድል’’’’’’ትቅዳጃለች ! !

 

በቸር ይግጠመን ፤   Saturday, September-21-13

 

Eriteria


የሰልፉ ዝግጅት ተጠናክሮ ቀጥሏል : Tomorrow at Meskel Square

የ ኢትዮጵያውያን ማህበረስብ በቤልጅግ በአምስተርዳም ከተማ ሕዝባዊ ስበስባ ጠራ

የአንድነት ፓርቲ ቀጣይ እጩ ሊቃነመናብርት ተለይተው ታወቁ

$
0
0

 ከግራ ወደ ቀኝ - ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣  አቶ ተክሌ በቀለ ፣ አቶ ግርማ ሰይፉ

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ፓርቲውን ለቀጣዮቹ 3አመታት በሊቀመንበርነት ለመምራት ከተወዳደሩት 5 ከፍተኛ አመራሮች ውስጥ 3ቱን ለመጨረሻው ዙር ውድድር እንዲያልፉ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መርጧል፡፡ ፓርቲውን በሊቀመንበርነት ለመምራት የተወዳደሩት አቶ ትግስቱ አወሉ፣ ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ አቶ ሽመልስ ሀብቴ እና አቶ ተክሌ በቀለ ናቸው፡፡

ዛሬ የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት በሚስጥር ድምፅ አሰጣጥ ስርአት ባደረጉት ምርጫ 1ኛ.ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው 2ኛ.አቶ ተክሌ በቀለ 3ኛ.አቶ ግርማ ሰይፉ ለመጨረሻው ዙር ውድድር አልፈዋል፡፡

ለመጨረሻው ዙር ሳያልፉ የቀሩት አቶ ትግስቱ አወሉ እና አቶ ሽመልስ ሀብቴ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ መሆኑን ተናግረው አንድነትን ለመምራት ከሚመረጠው ቀጣይ ሊቀመንበር ጋር ትግሉን ለማፋጠን እንደሚተጉ ለምክር ቤቱ ቃል ገብተዋል፡፡

1262887_516932691725003_368242465_o

የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት

- See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=5718#sthash.mnRx1QXg.dpuf

 

ሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ከተማን ከባድ ዝናብ መታት፤ መንገዶች በጎርፍ ተጥለቅልቀዋል

$
0
0

Heavy Rain
(ዘ-ሐበሻ) ኢትዮጵያውያን በስቃይ ላይ ያሉባት የሳዑዲ አረቢያዋ ሪያድ ከተማ ዛሬ ቅዳሜ ማታ በጣለ ከባድ ዝናብ የተነሳ ከተማዋ በጎርፍ ተጥለቀለቀች፣ መንገዶች በጎርፍ ተዘግተው በሥራ ላይ እና በ እለት ተለት ተግባር ላይ ችግር እንደፈጠረ አረብ ኒውስ የተባለው የዜና ወኪል አስታወቀ። የአረብ ኒውስን ጠቅሶ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢ እንደጠቆመው በነገው ዕለት እሁድ በሳዑዲ አረቢያ ትምህርት ቤቶች እና አንዳንድ የመንግስት መሥሪያ ቤቶች ዝግ ሆነው ይውላሉ።

በሪያድ ከተማ የጣለው ከባድ ዝናብ በመኪኖች ላይም ጉዳት ያደረሰ መሆኑን የዘገበው የአረብ ኒውስ በተለይ ሩዳህ፣ ናሲም እና ናጂም በተባሉ የሪያድ አካባቢዎች በጎርፍ ተመተው መንገዶች በውሃ ተጥለቅለቀዋል።

ይህ ከባድ ዝናብ በከተማዋ የመብራት አገልግሎት ላይም ችግር እንደፈጠረ የዘገበው አረብ ኒውስ መኪናዎች በጎርፍ እንደተወሰዱ በአንዳንድ ሰዎች ላይም ጉዳት መድረሱን ዘግቧል።

በሳዑዲ አረቢያ ከ35ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ በፖሊስ እጅ ያሉ ሲሆን እነዚህ ወገኖች በቤት ጥበት ሳቢያ በውጭ እንዲያድሩ በመደረጉ ዝናብ ሲደብደባቸው እንደነበር መግለጻቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያውያኑ አሁንም በሳዑዲ አረቢያ በከፍተኛ ችግር ላይ ናቸው።

ሳዑዲ አረቢያ በዝናብ እና በጎርፍ ከተመታች በኋላ ያሉ ፎቶዎች

$
0
0
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>