Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

አቶ አርከበ ዑቕባይና ወንድሙ አቶ ጌታቸው ዑቕባይ ከነቤተሰቦቻቸው አሜሪካ ገብተዋል

$
0
0

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

አቶ አርከበ ዑቕባይና ወንድሙ አቶ ጌታቸው ዑቕባይ ከነቤተሰቦቻቸው አሜሪካ ገብተዋል። አቶ ጌታቸው በትእምት (በመስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጂነሪንግ በኋም በሴመንት ፋብሪካ) ሓላፊ የነበረና ከወይዘሮ አዜብ መስፍን ተጣልቶ ስራው የለቀቀ ነው።
arkabe equbay
ወደ ሰሜን አሜሪካ ተጉዘው ከነበሩ የህወሓት አባላት ግማሾቹ ፈርተው አሜሪካ መቅረታቸው ታውቋል። ከነዚህ የጠፉ ባለስልጣናት መካከል የማረት ሐላፊው አቶ ተኽለወይኒ አሰፋ አንዱ መሆኑ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው (የተኽለወይኒ ራሴ አኣላረጋገጥኩም)።

ዓረና ትግራይ ፓርቲ ጉባኤው በደማቅ ሁኔታ እያካሄደ ነው።


የሸህ ኑሩ ልጅ ለምን ታሰረ ? BBN

ስለእግራቸው ውጤት (የስንኝ ቋጠሮ ለብሔራዊ ቡድናችን ተጫዋቾች) –ከፋሲል ተካልኝ አደሬ

$
0
0

waliyaa2
ያልከውን አላልኩም..ሰማህ ወይ ወዳጄ?
እንዴት እበላለሁ?..እጄን በገዛ እጄ::

ክብሬን አላቀልም..እንደምን አድርጌ?
እንደሌለ አውቃለሁ..
የቁሳቁስ እንጂ..የጀግና አሮጌ::

መቼም..መቼም..መቼም አልዘነጋ
የናቤን..የማሞን..ክብርና ዋጋ::
እንዳልከው በእግራቸው..በዓለም የነገሱ
ሁሌም የሚኖሩ..በታሪክ ሲወሱ
ሕያው ጀግኖቻችን..መቼም አይረሱ!!!

ሰማህ ወይ ወዳጄ?
ፈለግ ተከትለው..ዛሬ በእግር ኩዋሱ
በፈጸሙት ገድል..ቢንቆለዻዸሱ
በእግራቸው በሠሩት..
ባስመዘገቡት ድል..አገር ስላኮሩ
በክብር ቢነሱ..በክብር ቢጠሩ
ፈጽሞ አልገባኝም..ምንድ ነው ነውሩ?!?

ሰማህ ወይ ወዳጄ?
ስቼ ያሳሳትኩት..
…አልታይህ አለኝ
ስለእግራቸው ውጤት..
እንኩዋንም ደስ አለህ!..
…እንኩዋንም ደስ አለኝ!
* * *

___ ፋሲል ተካልኝ አደሬ ___ —

አንድነት በአዳማ የጠራው ሰልፍ በሰላም ተጠናቀቀ

$
0
0

udJ Adma


(ዘ-ሐበሻ) የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት በሚል በጎንደር፣ ደሴ፣ ባህር ዳር፣ ጂንካ፣ ወላይታ ፣ባሌ ሮቢ፣ ፍቼና አርባ ምንጭ ተካሂዶ የነበረው የአንድነት ፓርቲ ሰላማዊ
UDJ Dr hailu Areayaሰልፍ ዛሬ ደግሞ በአዳማ ከተማ ተደርጎ በሰላም መጠናቀቁን የፍኖተ ነፃነት ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን ከስፍራው ዘገበ። እንደ ጋዜጠኛው ዘገባ በዛሬው የአዳማ ሰላማዊ ሰልፍ መንግስት ፌደራል ፖሊሶችን በማሰማራት፣ የሰልፉን መንገድ በማስቀየርና በኢቲቪ በኩል ድራማ ለማሠራት ቢሞርክም እንዳልተሳካለትና ከምንም በላይ ሰልፉ በሰላም ተጠናቆ ሕዝቡ ድምጹን ከፍ አድርጎ ያሰማበት ነው።

በአዳማ ከተማ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የአንድነት የምዕራብ ቀጠና ሃላፊ አቶ አስናቀ ሸንገማ በኦሮምኛ ቋንቋ፣ የአንድነት የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ስዮም መንገሻ እንዲሁም ዶክተር ሃይሉ አርአያ ንግግር ማድረጋቸውን የገለጸው ጋዜጠኛው ስልፈኛው በመፍክሩ መንግስትን የተለያዩ ጥያቄዎችን ጠየቋል፡
ከነዚህም መካከል፦
- ውሸት ሰልችቶናል
- የኢቴቪ የሃሰት ዶክመንተሪ ፊልም ከአሸባሪነት አይለይም
- ድህነት በፕሮፓጋንዳ ብዛት አይጠፋም
- ሰብዓዊ ልማት ለሁሉም
- ስራ ማግኘት የዜግነት መብት ነው
- አምባገነኖች ባሉበት የአንዷለም ቤት እስር ቤት ነው
- ርዕዮት አለሙ ጋዜጠኛ እንጂ አሸባሪ አይደለችም
- ድሌ ዛሬ ነው! ድሌ ዛሬ ነው ድሌ ድሌ ድሌ
የሚሉ መፍክሮችን እነዚሁ ከፍርሃት የተላቀቁ ኢትዮጵያውያን አሰምተዋል።

አንድነትየሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት በሚል ላለፉት 3 ወራት በመላው ኢትዮጵያ በመዘዋወር ሕዝቡን በሰላማዊ ሰልፍ በማደራጀትና ፊርማ በማሰባሰብ ሲያደርገው የቆየውን ሰላማዊ ትግል በመቀጠል የፊታችን እሁድ ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር በመሆን በመስቀል አደባባይ ት ዕይንተ ሕዝብ መጥራቱን ዘ-ሐበሻ ከቀናት በፊት መዘገቧ ይታወሳል።

 

 

የመከላከያ ሠራዊቱ-ድምበር አስከባሪ ወይስ አሳሪና አስተዳዳሪ ?

$
0
0

  ( እምብኝ በል-ጎፍንን )         

ethiopian-troopsየደርግ ወታደራዊ መንግሥት የፖለቲካ ሥልጣኑን በለስ ቀንቶት  ሥልጣን ለመያዝ  ለበቃው ህወሃት ከለቀቀ በኋላ ህወሃት ትኩረት ሰጥቶ ያጠናክር የነበረው የካድሬውንና የመከላከያ ሠራዊቱን መዋቅር ነበር። በመከላከያ ሠራዊቱ ሥር  የአጋዚ ሠራዊት (የፌደራል ፖሊስ እያሉ የሚጠሩት) ቅጥረኛ የከተማ  ነዋርዎች ነብሰ ገዳይ ቤት ለቤት እያውደለደለ ንብረት በመዝረፍ የተሰማራ በቤተ-መንግስት በጅት ይተዳደር የነበረውን የደርግ ልዩ ጥበቃ ኃይልን ቦታ የተካውና በህወሃት የሚመራው፤ የፖሊስ ኃይል ፤ የደህንነትና ፈጥኖ ደራሽ ኃይል እንዳሉበት ግምት ውስጥ አስገብተን ማለት ነው። በመሆኑም እነዚህ መዋቅሮች እስከ ዛሬ ድረስ የሥርዓቱን እድሜ በማራዘም ረገድ የተጫወቱት ጨዋታ ቀላል አይደለም ወይም የህወሃት የጀርባ አጥንት ናቸው ቢባል ነገሩን ክብደት ሊሰጠው እንደሚችል በመግለጽ ለዛሬ ያለኝን ትኩረት በዚህ ላይ ላድርግና በመጠኑም ቢሆን  በዚህ ተቋም ላይ ያለኝን ሃሳብ ማካፈሉ ጉዳዩን በቅርበት ለሚከታትሉ ምንጭ ወይም የመነሻ ሀሳብ የሚሆን መስሎ ስለታየኝ ከዚህ የሚከተለውን የግል  አስተያየቴን ለአንባቢዎቼ አቀርባለሁ።

በሽግግሩ ወቅት የመከላከያ ሚንስትር የነበረው ስየ አብርሃ ሲሆን ከፀደቀ 18 ዓምታትን ያስቆጠረውና በሥራ ላይ ሳይውል የቀረው በህወሃት ተረግጦ የሚገኘው ሕገ-መንግስት ከመታውጁ በፊት ስየ አብርሃ -የቀጣይቷ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራስያዊት ሪፐብሊክ ሠራዊትን በሚመለከት፦ እንዲህ ብሎ ነበር ፦የመከላከያ ሠራዊቱ ከዋና መንገድ 20 ኪ/ሜትር  ከዋና ከተማ 40 ኪ/ሜትር ርቆ እንዲሰፈር እንደሚደረግ ፤ የሠራዊቱ ብሔራዊ አስተዋጾም እንደየ መጣበት ብሔር ወይም ብሔረሰብ ሕዝብ ብዛት እየታየ እንደሚመደብና ወታደራዊ ብቃቱም ፕሮፌሽናል ስታንዳርድ  (ዓለም አቀፋዊ ደረጃውን የጠበቀ) ወይም እንዲኖረው ተደርጎ እንደሚሰለጥን መሪ አቅጣጭ ተቀምጦለት ነበር። ይሁን እንጅ ስየ አብርሃ ይሁን ሌላው በመከላከያ ሠራዊቱ ውስጥ በከፍተኛ አመራር ደረጃ ላይ የነበረው አካል ይሁን አሁን ያለውም ቢሆን ይህን መርሕ እንዲተገበር ሲያደርጉት አልታዩም። በርግጥ ስየ አብርሃ በመከላከያ ሚንስትርነቱ ብዙ አልቆየበትም። ቢቆይም እዚህ ግባ የሚባል  መሠረታዊ ለውጥ ያመጣል ብየ አልጠብቅበትም ነበር። ምክንያቱም እሱም ቢሆን በህወሃት ውስጥ ለረጅም ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ በአመራር ላይ የቆየና ወደኋላ አካባቢ በጥቅምና በሥልጣን ክፍፍል ተገቢውን ድርሻ ባለማግኘታቸው በህወሃት ውስጥ ክፍፍል ሲፈጠር በሟቹ መለስ ዜናዊና በአዲሱ ለገሰ ውሳኔ ተገፍተው ከጎድና ከወጡት አንዱ ቢሆንም አሁን ህወሃት የሚያራምደውን የአንድ ጎሣ (የትግሬ) የበላይነትን ዓላማ ወደ ፊት ይገፉ ከነበሩት ጽንፈኞች ስፊ ድርሻ የነበረው በመሆኑ ለተወሰኑ ወራቶች የህወሃት ተቃዋሚ መስሎ ብቅ ቢልና ኢትዮጵያዊነቱን ለማስመስከር ቢሞክርም  እምነት እንዳንጥልበት የሚያደርጉ ብዙ ሊገልፃቸው የሚገቡ ነገሮችን አፍኖ መያዙና ለግል ሕይወቱ ቅድሚያ መስጠቱ ከትግሉ ጎራ መራቁን አመልካች ነው። ይህን ስል ግን የስየን ጠንካራ ጎኖቹን ማለትም ራሳቸውን ደብቀው (አድፍጠው) ዝም ካሉት አረጋሽ ፤ተወልደና ዓለምሰገድ እንዲሁም አብረው ብዙ ሳይራመዱ ተመልሰው የሥልጣን ጥማታቸውን ለማስታገስ ከወሰኑት ሐሰን ሽፋና አባይ ፀሀየን ከመሰሉት በእጅጉ የተሻለ መሆኑን ፤ ለሥርዓቱ አለመገዛትና ድርጅቱን ጥሎ በመውጣት ህውሃትን በውጭ ሆኖ መመልክቱ ብዙ አስተማሪ ነገር እንዳገኘበት፤ እንድሁም ይመራውና ይታገልለት የነበረው ድርጅት ቅጥረኛና ፀረ-ኢትዮጵያ ድርጅት መሆኑን፤ ከሱ በፊት የተገደሉ የታሰሩ ፤ የተባርሩ ነባር ታጋዮችን እጣም በሱ ላይ በመድረሱ አዛኝ ልቦና ሊያድርበት ይችልላ የሚለውን በታሳቢነት በማሳደር አሁንም ስየ ከሕዝብ ጎን በመሆን ትግሉን ቢቀጥል የተሻለ እንደሚሆን እግረ መንገዴን መጠቆም እወዳለሁ ምክንያቱም ኢትዮጵያ አሁን ከደረሰችበት አደገኛ ሁኔታ እንድትደርስ ካደረጉት አንዱ ስለሆነ  ከደሙ ንጹሕ ለመሆን የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚክስ ተግባር መፈጸም ይጠበቅበታልና ህወሃትን  አለበት።

የመከላከያ ሠራዊቱ ከላይ በተቀመጠለት መርህ መስረት ስፍሮ የሀገር ሉዓላዊነትን ማስከበር ሲግባው  የሚፈጽመው ተግባር ግን በግልባጩ በየመሸታ ቤቱና ስራ አጥተው ሰውታቸውን ሸጠው በሚያድሩ ምስኪን እህቶቻችን መኖሪያ መንደር ለመንደር ትጥቁን ተጀብሎ መዋያና ማደሪያ ማድረጉን ፤ በገጠርና በየከተማው በአስዳደር ሥራ ጣልቃ ሲገባ ፤ መሬት ሲመራና ሲያካፍል ፤ በየተሰማራበት አካባቢ ሴቶችን አስገድዶ ሲደፍር ፤ በኃይል አስገድዶ የጠለፋ ተግባር ሲፈጽምና አለቆቹ  እንደ አንድ የገቢ ምንጭ ቆጥረውት ሩዋንዳ ፤ ሱዳንና ሶማሌ ድረስ እየሰደዱ ከዩኤን ወፍራም ደመወዝ በዶላር እንዲከፈለው በማስደረግ ለአለቆቹ የሀብት ምንጭ ከመሆንና መጠቀሚያ ከመሆኑ ባሻገር በሕዝቡ ዘንድ የሚያስመሰግን ተግባር ሳይሆን የሚፈጽመው አሳፋሪና የጠመንጃውን አፈሙዝ በሕዝብ ላይ በማዞር በአደባባይ ንጹሃን ዜጎችን ከመግደል ከመደብደብና ከማፈን ውጭ ኢትዮጵያዊ የአገር መከላከያ ሠራዊት መሆኑን የሚያስመሰክር ተግባር አልፈጸመም ። እዚህ ላይ እንደሰለጠነው አገር ሰራዊት የተፈጥሮ አደጋ ሲደርስ ሄዶ አላገዘም ፤አቅም ለተሳናቸው ድጋፍ አላደረገም በማለት መክሰሴ አይደለም የጠመንጃውን አፈሙዝ በምን ሂሳብ ነው ወደ ሕዝብ እንዲያነጣጥርና አልሞ እንዲተኩስ የሚደረገውና ሕዝብ የሚጨርሰነው ነው? ?

የመከላከያ ሠራዊቱ ውስጡ በሰፊ ቅራኔ ውስጥ የተሞላ ቢሆንም ከአማራው ብሔር የመጣው የመከላከያ ሠራዊት አማራውን ሲያጠቃና ሲጨፈጨፍ ተባባሪ ሆኖ ከማገልገልና ነገሩን ከማባባስ አልፎ የአማራውን ብሔር ሕዝብ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ መብት ተነካ ብሎ የአማራውን ሕዝብ ጥቃት ሲመክት አልታየም። ከኦሮሞው ብሔር የመጣው የኦሮም ተወላጅ የሆነው የመከላከያ ሠራዊት አባልም ኦሮሞው ሲንገላታ ከመተባበር የዘለለ ተግባር ሲፈጽም አልታየም። በርራ ላይም  በየግዳጁ ሲግባ በፊቱና በኋላው የሁለት ወገን እሣት የህወሃት አለቆቹና ሥርዓቱን ለመጣል በመታል ላይ ያሉት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ጥይት እንደሚገድለው ይታወቃል።ይህ ሁሉ እየሆነ ግን የሥርዓቱን እድሜ ለማራዘምና በአለቆቹ ዘንድ ምስጉን ለመባልና በበጎ እንዲታይ ምዝብሩን ሕዝብ በማንገላታት በመግደል  ስቃዩን በማባባስ ለሰሞንም ቢሆን የህወሃት ታማኝ መስሎ እያደረ ይገኛል። የደርግ የጦር ሠራዊት በጅምላ ጨፍጫፊነት የሚታወቅ ቢሆንም የሥርዓቱ  ከአናቱ  ወይም ከላይ የተበላሸ መሆን እንጅ በጦር ሠራዊቱ ውስጥ አንድ የሚያደርግ ባህሪ ኢትዮጵያዊነትን ስንቅ የሰነቀ ነበር።  ያም ሆኖ ይህ ዛሬ የሚታየው የአገር ሉዓላዊነት መደፈር አስከፊ ጥቃትና ገጽታ በኢትዮጵያችን እንዳይመጣ ግን ሕይወቱን አሳልፎ የሰጠ፤ ደሙን ያፈሰሰ፤ አጥንቱን የከሰከሰ ነበር። ይሁን እንጅ የደርግ ሥርዓት ሲናድ በሠራዊቱ ላይ የደረሰበትን የሞራል ፤ የአካል ፤ የህይወት ዋስትና ማጣትና የጎዳና ተዳዳሪ እንዲሆን መዳረጉ በዜግነቱ ሊከበር አለመቻሉ መቼም ቢሆን የማይረሳ የህወሃት በቀልተኛነት ታሪክ በታሪክ ማህደር ተዘግቦ የሚጠብቅ ይሆናል። የአሁኖቹ ሰሞነኞችና አዲስ ናፋቂዎችም ነገ መሀሉ ዳር -ዳሩ መሀል የሚሆንበት ሁኔታ ሲፈጠር በማን ላይ ሊያሳብቡ ማንን ምክንያት ሊያደርጉ እንደሚችሉ እግዚአብሔር ብቻ የሚያውቀው ጉዳይ ይሆናል። እንደኔ የግል አስተያየት ግን ህወሃትን መከታ በማድረግ በማንኛውም አይነት መዋቅር የተፈጸመች እያንዳንዷ ግፍ ጊዜዋን ጠብቃ  ብህዝብ ፊት ለፍርድ እንደምትቀርብ ትንበያ  ወይም ጥንቆላ ሳይሆን በግልጽ እንደሚሆን በድፍረት መናገር ከእውነቱ መራቅ አይደለም።

  በሽግግሩ ወቅት በተቋቋመው ሕገ-ምንግሥት አንቀጽ 87 ላይ የመከላከያ መርሆዎች ይልና፦ከዚህ የሚቀጥለውን ደንብ ያትታል።ደንቡ ግልጽነት የጎደለውና አሻሚ ትርጓሜ እንዲሰጥ የተደረገ ውይም የያዘ ሲሆን ሆነ ተብሎ ለማጭበርበር የተዘጋጀ መሆኑን ያመለክታል። ራሱን እንደመንግሥት አደርጎ የሚቆጥረውና በማርክስዊ ሌኒናዊ ሊግ ትግራይ የሚመራው የታጠቀው የደደቢት ፖለቲካዊ ኃይል በክህደት ተወልዶ በክህደት ያደገና የፀረ-ሕዝብ ተቋም ቢሆንም በየጊዜው የሚቀያየረውን የማጭበርበሪያ ስልት ደግሞ ለይቶ ማወቅ የግድ ይሆናል ብየ አስባለሁ።

1/ የሀገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት የብሔር ብሔረሰቦችን ፤የሕዝቦችን ሚዛናዊ አስተዋፅኦ ያካተተ ይሆናል።

 እንደሚታወቀው በደርግ መውድቂያ አካባቢ ህወሃት አገር ለማጥፋት ብዙ ቁጥር ያለው ሠራዊት አስታጥቆ ነበር ። ወደ መሀል አገር ሲገባም በአምሳሉ የፈጠራቸውን ጨምሮ ይህ ኃይል የማይናቅ ቁጥር ነበረው። ከተራ ውንብድና ወደ ሕጋዊ ውንብድና ሲሸጋገርና አገር መግዛት በእጅ የተያዘና የሚቻል መሆኑ ሲረጋገጥ በቅጥፈት ያደገው ህወሃት ያሰለፈውን ኃይል የሥርዓቱ አገልገጋይና ታማኝ በማድረግ ማስቀጠል ስለነበረበት የሚጠቀምበት መንገድ መፈለግ የግድ በመሆኑ የተወሰነውን የህወሃት ኃይል የአካባቢውን ህዝብ በማስለቀቅ ዳንሻ በተባለ ቦታ ውስጥ በአንድ ማዕከል የመተዳደሪያ በጀት ስጥቶ ሲደራጅ የቀረውን ለማሸጋሸግ ደግሞ ድርጅቱ መላ መምታት ነበረበት። ይኸውም በሕጉ መሠረት የሰፈረው የሠራዊት ምደባ ሕግ እንደ ብሔሩ ወይም ብሔርሰቡ ብዛት ሚዛናዊ መሆን አለበት ስለሚል ይህን ሕግ ለመከላከል አብዝኛው የህወሃት ሠራዊት በአማራው ክፍለ ሀገራት ብዙ ጊዜ ስለቆየ አማርኛ መናገር የሚችለውን በቀጥታ የአማራ ብሔር ተወላጅ እንደሆነ አድርጎ መመደብ ነበረበት ተመደበ  ኦሮምኛ ተናጋሪ ህዝብ ባለበት ተወልደው ያደጉ ትግሬዎችም የኦሮሞውን ሠራዊት ኮታ እንዲቀላቀሉ ተደረገ ( አባዱላ ፤ዘገየ የማነብርሃን…ወዘተ የመሳስሉ)  እዚህ ላይ ለኢህአፓና ለደርግ አንምበረከክም ያሉትና ለህውሃት የተንበረከኩት ኢህዴኖች በዚህ የተግባር አፈፃፀም ወቅት ብአዴኖች የሆኑት በድጋሚ ለህውሃት ተንበረከኩ። ለህወሃት መረጃ በማቀበል፤ መንገድ በመምራት፤ በስለላና በአጠቃላይ የህወሃትን ዓላማ ስኬታማ ለማድረግ ታጥቀው ያገለገሉ ባለሟል የሆኑት እስላሙን ከእስላሙ፤ ክርስቲያኑን ከክርስቲያኑ ፤ደገኛውን ከቆለኛው፤ ሽናሻውን ከአገው ጋር፤የደቡቡን ከሰሜኑ፤ የምሥራቁን ከምዕራቡ ጋር በማጋጨት አገር ያጠፉት (አዲሱ ገለሰ ፤ ታምራት ላይኔ ፤ ተፈራ ዋልዋ ፤ ብረከት ስምኦን ፤ታደሰ ካሳ ፤ህላዊ ዮሴፍ) በዚህ መጥፎ ምግባራቸውና በአማራው ሕዝብ ላይ በፈፀሙት ሁሉም አይነት ግፍ  ሰፊው የአማራ ሕዝብ ለሁሉም ጊዜ አለውና አንድ ቀን ይፋረዳቸዋል።እዚህ ላይ ልብ ብላችሁ እንድታነቡልኝ የምጠይቀው ቢኖር ህወሃት ሕዝብና አገርን መግደል ዓላማው አድርጎ የተነሳ ሲሆን ዓላማውን ለማሳካት ለ40 ዓመታት ያህል ሥራውን እየሰራ ይገኛል ተግብሩ ወይም ዓላማው ጥፋት ነው ነገር ግን ለዓላማው አሁንም ወደፊት የሥርዓቱ እድሜ እንዲረዝም ለማድረግ ተስፋ ባለ መቁረጥ እየታገለን ይገኛል። እኛም የሕዝብና የአገር ጠላት መሆኑን ተገንዝበን በቻልነው መንገድ ሁሉ ድንጋያችን እየወረወርንበት እንገኛለን ነገር ግን ትግሉ አንድ የዘነጋው መሠረታዊ ጉዳይ አለ ይኸውም ቀደምት የኢህዴን አመራር የነበሩና ዛሬም ህወሃት በተለያዩ ከፍተኛ የኃላፊነት ደረጃ ላይ አስቀምጧቸው የሚገኙትን በዋናነት ከፍ ሲል ስማቸውን የዘረዘርኩት አደገኛ የኢትዮጵያ ጠላቶች መሆናቸውን ቅድሚያ ሰጥቶ አለመንቀሳቀሱና አሁንም ትኩረት እንዲደረግበት ለምሳሰብ ነው። ዛሬ በተለያዩ መዋቅሮች ቁልፉን ቦታ ይዞ የአማራውን ክልል በቅኝ -ገዥነት እየገዛ የሚገኘው ኃይል ምንጭ በእነዚህ በተጠቀሱ ግለሰቦችና በዙሪያቸው በተሰማሩ አሾክሿኪዎች አማክኝነት ነው። ህግ መጣስ የተጀመረው በዚህ ጊዜ ባይሆንም ኢህዴን ያሰለፈው ምስኪኑ የአማራ ብሔር ሠራዊት ግን በብር ከ3ሽህ በታች ድጎማ እየተሰጠው ወደ የመጣህበት ከብትና  ፍየል ጥበቃህ ተመለስ እየተባለ መሳለቂያ ሆኖ እንዲሄድ ተገዶ ከሠራዊቱ አባልነቱ ተወገደ። የቀረውም በህወሃት ካድሬና የሠራዊት አለቆች በየጊዜው እየተገመገመ እንዲባረር ሲደርግ ድምጣቸውን አጥፍተው ሰጥ ለጥ ብለው የተግዙት የሠራዊት አባላትም ህወሃትን የሚያስጭንቅ ውጫዊ ሁኔታ በተፈጠረ ቁጥር ወደ እሥር መወርወር ፤በድብቅ በመግድል፤ ጤና በሚነሳ መድኃኒት ተወግተው እንዲሞቱ ማድረግ የድርጅቱ መደበኛ ባህሪ እየሆነ መጣ። 1/ለምሳሌ ኮሎኔል ታደለ ገብረሥላሤ ሩውንዳ አዝማች ሆኖ ሄዶ የነበረ ህወሃትን ከደደቢት እስከ ደቡብ፤ ምእራብና ምሥራቅ ግንባር ከፋች በመሆን የሚታወቅ እንደነበር የማይካድ ነው። 2/ኮሎኔል ናቃቸው ጫቅሉ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርንት በመጨረሻ የወጣው ዝነኛ ተዋጊና አዋጊ ታመው በህክምና ላይ በነበሩበት ወቅት ህወሃት ሆነ ብሎ በመርዝ ተወግተው እንዲሞቱ ያደረጋቸው ሰለባዎች ናቸው። ይህ አድሎ እስከመቼ ይቀጥላል በሚል በመከላከያ ሠራዊቱ ውስጥ ተነስቶ የነበረው የመከለከያ ሠራዊቱ ጥያቄና አመጽ በተለይም በአማራው የመከላከያ ሠራዊት አባላት እድገቱን ጨምሮ ክልሉ በልማት ወደ ኋላ መቅረቱና በብአዴን አመራር ቦታ የተቀመጡት አማራ ያልሆኑና ለአማራው ብሔር ሕዝብ የማይጠቅሙ ጠላቶች ናቸው በማለት 1/በረከት ስምኦንና 2/ተፈራ ዋልዋን  እንዲሁም ሌሎችንም ምሳሌ አድርጎ የተነሳው እንቅስቃሴ እየተገመገመ እያለ ድንገት የኢትዮ-ኤርትራው ጦርነት ተጭሮ ሠራዊቱን ለመምታት ምቹ ሁኔታ ተፈጠረ እነሆ  ከዚያ በኋላ ገዥው ኃይል አመጹን አዳፍኖ ሠራዊቱን የሥርዓቱ አሽከር በማድረግ ሕዝብ እንዲጨርስ አሰማርቶት ይገኛል ። አሁን ይህችን መጣጥፌ እያዘጋጀሁ እያለሁ በፖሊስ ስም የሚሸቅጠው የአጋዚ ሠራዊት በመባል የሚታወቀው የሠራዊት ኃይል በሰላማዊ ፓርቲ አመራር ኃይልና አባላት ላይ ያደረሰውን ጥቃት እየተመለከትኩ በድርጊቱ እጅግ አዝኘ እስከ መቼ? በሚል ጥያቔ ስሜት ውስጥ ገብቼ ነው።

2/ የመከላከያ ሚንስትር  ሆኖ የሚሾመው ከስቪል ይሆናል።

የሕግ ባለ ሙያ ባልሆንም እስከ አሁን በመከላከያ ሚንስትር ሚንስትር ሆነው የነበሩትን ወስደን ስንመለከት በትግል ላይ የነበሩ ለፓርቲያቸው የሚያደሉ ሠራዊትን በበላይነት ሲመሩና ሲያዋጉ  ሲያዋጉ የነበሩ ሲሆን ምንጫቸውም ያው ከህወሃት እንደሆነ ይታወቃል። ከአገር አጥፊው መለስ ሞት በኋላ የመጣው ካቢኔም ለማጭበርበሪያ ይሆን ዘንድ አንዳንድ የሹመት መስጠትና የመለዋወጥ ሁኔታዎችን ያደረገ ቢሆንም ከኋላ ያሉት አስተኳሾችን እነማን እንደሆኑ ስለምናውቃቸው የተጃጃሉት እራሳቸው እንጅ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዳልሆነ ሊገነዘቡ ይገባል። ነገር ግን ቀልዱን አበዙት። እነሳሞራም ራሳቸውን አንቱ ያሉ በፀረ_ህዝብነት ታሪካቸው የታወቁ ስለሆነ ማንም የሚያዛቸው እንዳልሆኑ መግደል የሚፈልጉትን ከመግደል እንደማይታቀቡ ግልጽ  ሆኖ እያለና ነፍጥ አምላኪ ኃይልን በጎ ነገር ሊያመጣ ይችላል ብሎ ማሰብ አይቻልም። ማንም ይሾም ማንም ይህ ሥርዓት ፀረ-ሕዝብ ፤ ፀረ- ኢትዮጵያ እስከሆነ ድረስ መውወድ ብቻ ነው ያለበት።

3/ የመከላከያ ሠራዊት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ከመጠበቅ በተጨማሪ በዚህ ሕገ-መንግሥት መሰረት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚሰጡትን ተግባሮች ያከናውናል።

ይላል። ይህን ነጥብ በሁለት ከፍለን ብንመለከተው መሰሪነቱን ለመረዳት ይቀላል፦

ሀ/ የመከላከያ ሠራዊት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ይጠብቃል፦ አዎ!! የአንድ አገር የመከልከያ ኃይል(ሠራዊት) ተቀዳሚ ተግባሩ የአገርን ዳር ድንበር (ሉዓላዊነት) ከማንኛውም ጥቃት መጠበቅ ማስከበር ነው። በዚህ ዙሪያ ይህ የህወሃት የመከላከያ ኃይል በአገር ሉዓላዊነት ጉዳይ የተፈተነበት ወቅት ነበረ ወይ ? ካልነበረ በምን መለኪያ ሊታመን ይችላል ? ለዚህ የሚያበቃ መንፈሳዊና ብሔራዊ ሞራል አለው ወይ? በከፍተኛ ደረጃ አመራር ላይ ያሉት ከዚህ ጨዋታ ውጭ ከሆኑ እታች ያለው ኃይል አገራዊና ሕዝባዊ ፍቅር አለው ብሎ ለመናገር ዋስትና የሚሆኑት ከየት ሊገኙ ይችላሉ ? ትንሽ በኢትዮ-ኤርትራው ጦርንት ዙሪያ ልቆይና የመጨራሻ መደምደሚያየን አስቀምጣለሁ።

በ1958 የተቋመው ኤ.ኤል.ኤፍ ( የኤርትራ ነፃ አውጭ ግንባር) ቀደም ሲል ከዘውዳዊው ሥርዓት ጋር በኋላ ከወታደራዊ መንግሥት ጋር ውጊያዎችን ያካሂድ እንደነበር ይታወቃል ። ወደኋላ አካባቢ ግራ ዘመም የሚመስል ነገር ግን ያልነበረ ኢ.ኤል.ኤፍን ከሁለት እንዲከፈል አደረግ። አዲስ በተቋቋመው ኤ.ሕ.ኤል.ኤፍ (የኤርትራ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር **ሻቢያ**) እና በኤ.ኤል.ኤፍ መካከል ቅራኔዎች እያደጉ በመሄዳቸው አንዱ ሌላውን መብላት ጀመረ። በመሆኑም ሻቢያ ጉልበት እያገኘ ጀብሃ እየተዳከም መጣ ። ሻቢያ ጀብሃን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ትጥቅ የያዙ በኤርትራ ውስጥ ይንቀሳቀሱ የነበሩትን የማዳከም አቅም አገኘ። በ1967 ዓ/ም የተቋቋመው ተጋድሎ ሀርነት ትግራይ በኋላ ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ በኤርትራ ከተከሰተው ሁናቴ ጋር የሚያገናኘው ብዙ መሠረታዊ ምክንያት ሊኖር እንደሚችል ነገር ግን ይህን ጉዳይ ቀንጭቦ ማለፍ ስለማይገባ ራሱን አስችሎ ማቅረቡን በማመን ወደ ተነሳሁበት ነጥብ ልመለስና ጀብሃም ሆነ ሻቢያ ህወሃትን በቀጥታም ይሁን በተዛዋሪ የማደራጀትና የማስታጠቁን ጉዳይ በበላይነት ይዘውት እንደነበር ይታወቃል። ደርግ በሚያደርጋቸው ዘመቻዎችም በጋራ ማለትም ሻቢያና ህወሃት በከፍትኛ ደረጃ ይተባበሩ ነበር። ይህ ግን ቀጠለ ወይስ አልቀጠለም ? ወደሚለው ስንገባ ሻቢያ የአዛዥነቱን ህወሃት የታዛዥነቱን ጉዳይ በአግባቡ ሊያደርጉ ባለመቻላቸው በመሃከላቸው የነበረው ጥብቅ ግንኙነት በህወሃት አልታዘዝም ባይነት ምክንያት ሊቀጥል አልቻለም። ለይቶላቸው የከፋ ግጭት ባይፈጥሩም ደርግ እስኪወድቅ ድረስ ይረዳዱ ነበር።ይህ በዚህ እንዳለ ግን ሻቢያ ህወሃትን ማጥመዱ አልቀረም ህወሃትም ሻቢያን የማደናቀፍ ተግብሮችን ማራመድ ጀመረ። ለምሳሌ ዴሞክራሲያዊ ምንቅስቃስ ህዝብ ኤርትራ የሚባለው ድርጅት ፀረ-ሻቢያ ሆኖ እንዲቆም የማደራጀቱን ሥራ ይመራው የነበረው ህወሃት ነበር።ሻቢያ ይህን ተግባር ቢያውቅም የተነሳበትን የመገንጠል ዓላማ ላለማደናቀፍ ህወሃትን ይጠቀምበት እንደነበርና ወደፊት ግን ወጥመድ ውስጥ ለማስገባት አለመቦዘኑን የሚያመላክቱ አንዳንድ ጉዳዮች ነበሩ። ከላይ እንደገለጽኩት ይህን ጉዳይ ባጭሩ ማሳየት ስለማይቻል ገረፍ ገረፍ አድርጌው ልለፍና ደርግ ከወደቀ በኋላ በአዲሲቷ አፍሪቃዊት አገር ኤርትራና ኢትዮጵያ ምን አይነት አንድነትና ልዩነት ነበር የሚለውን በመነካካት በጉዳዩ ሰፊ እውቀት ያላቸውን አባንኘ በሰፊው እንዲያብራሩት በመተው በበኩሌ የማውቀውን እንዲህ ለመግለጽ እሞክራልሁ።

  ወዶም ይሁን ተገዶ ኤርትራን በአማራ ገዥ መደብ በቅኝ አገዛዝ የነበረች አገር ናት በማለት አስቀድሞ እውቅና የሰጠው ህወሃት እንደሆነ ይታወቃል። ሻቢያ አስመራን ህወሃት አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ በኋላ ከበሮ መደለቁ ብቻ ሳይሆን ሁለቱ አገሮች በመሠረታዊ ጉዳዮች በጥቅም የሚያስተሳስራቸው ውሎችን መፈራረማቸው ይታወቃል። ከብዙ በጥቂቱ ማንኛውም ኤርትራዊ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ፓስፖርት ወይም የመታወቂያ ደብተር እንደማያስፈልገው፤ኢትዮጵያ የጦር ካሳ ለኤርትራ መክፈል እንዳለባት፤ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ኤርትራዊ ጡረተኞች የጡረታ ደመወዛቸው በኢትዮጵያ እንደሚከፈል፤የአስብ ወደብ ኢንሹራንስ በኢትዮጵያ እንደሚሸፍንና የመንገድ ሥራ ጥገናው በኢትዮጵያ ወጭ እንደሚከናወን፤ኤርትራዊያን ማንኛውንም ምርት ከኢትዮጵያ ሲገዙ ታክስ እንደማይከፍሉ …ወዘተ ተብለው 25 ወሎችን ዛሬ የመናፍቃን መሪ ነኝ በሚለውና የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ሲኖዶስ ከሁለት የከፈለው ታምራት ላይኔ በኩል ተፈራርመዋል።

ያ ሁሉ እከከኝ ልከክህ ከንቱ ውዳሴው ሳይውል ሳያድር ወደ ግጭት አመራ አንዴ አንዱ ሲገፋ ሌላ ጊዜ ደግሞ ተገፍቶ የነበረው ሲገፋ መቆየቱ ይታወቃል። ሸራሮ የነበረው የህወሃት ጦር ሻቢያ በኢትዮጵያ ድንበር ምሽግ እየሰራና እየተጠጋ መሆኑን ተመልክቶ የሻቢያን ምሽግ ሰብሮ በመግባት የሻቢያን ጦር በማባረር ባረንቱ ድረስ መሸኜቱንና በዚህ ጉዳይ የሠራዊቱ አመራሮች ማን አዟችሁ ነው ተብለው አዲስ አበባ ተጠርተው መገምገማቸውን አንድ የሠራዊቱ አመራር የነበረ አጭውቶኝ ነበር። ተገምጋሚዎቹ ከአዲስ አበባ ሳይለቁ የሻቢያ ጦር ተደራጅቶ በመመለስ ጥቃት መሰንዘሩና ከዚያ በኋላ የሻቢያ ጠብ አጫሪነት ግልጽ ሆኖ የሁለቱ የኢትዮ-ኤርትራው ጦርነት በሁሉም ወገን ታወጀ የህወሃት ጦር አስመራ ሲጠጋ ተመለስ ተብሎ ድርድሩ ተጀመረ ።ብዙ የአገር ኢኮኖሚ ወደመ ከሰማኒያ ሽህ የማያንሱ ውድ ኢትዮጵያውያን የጦርነት ሰለባ ሆኑ ሻቢያ በአሽናፊነት ደመደመ። እንግዲህ የመከላከያ ሠራዊቱ አገር ወዳድነት ወይም በሌላ አነጋገር ለአገሩ ለሉዓላዊነት የነበረው ወኔና ወታደራዊ ብቃቱ የታየው በዚህ ጊዜ ብቻ ነበር።

ለ/ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚስጡትን ተግባሮች ያከናውናል፦በኢትዮጵያችን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀው ህወሃት በምርጫ 97 ሲሸነፍ የምርጫ ሳጥን ለመዝረፍ ፤ በአሸባሪነት ስም የተቃዋሚ ኃይሎችን አንገት ለማስደፋት የታወጀ አዋጅ ካልሆነ በስተቀር የሕዝብን ሰላም የሚያደፈርስና ፀጥታን ሊያናጋ የሚችል ክስተት አለመፈጠሩን ብርቅም ዜና ስለማዳምጥ ስለማነብ የታየ ነገር እንደሌለ እርግጠኛ ነኝ። በነዚህ ተግባሮች የመከላከያ ሠራዊቱ እጁን አስገብቷል። ሀቁ ይህ ከሆነ የመከላከያ ሠራዊቱ የአገርን ሉዓላዊነት ያስከብራል ሲባል የማንን አገር የዚየትኛውን ሕዝብ አገር? ለህወሃት እሰየው የሚያስብል በሕዝብ ዘንድ ግን ከፍተኛ አደጋ ያደረሰ የተፈጥሮ አደጋ ደርሶ በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ቀውስ መፈጠሩን በዜና ሰምቸዋለሁ ምስሉንም አይቻለሁ። አንድ የመከላከያ ሠራዊት አባል የሆነ ግን ድጋፍ ሲሰጥ አልተመለከትኩም ወይንስ ይህ በሕግ አልተደነገገም? ይቅርታ የዚህን አገር የጦር ኃይል ተልዕኮ ስለማይ ነው።የኛዎቹ ከሕዝብ አብራክ የመጡ ቢሆኑም እንዲያልቅ በተፈረደበት ሕዝብ ጉዳይ መግባት እንደሌለበት የታዘዘ ይመስላል። እንግዲህ ከዚህ የባስ የሚመጣ ስለማይኖር ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ያለዚያ ድንጋይ ነው ብለው ይወረውሩሃል እንደተባለው የሰላማዊ ትግሉን ወይም የትጥቅ ትግሉን መቀላቀል የተሻለ አማራጭ እንደሚሆን ያለኝን ኃላፊነትና የዜግነት ግዴታየን በዚህች ጦማሬ እንካችሁ ብያለሁ።

4/ የመከላከያ ሠራዊት በማናቸውም ጊዜ ለሕገ-ምንግሥቱ ተገዥ ይሆናል።

ሕገ መንግሥቱን አስመልክቶ ሕግ አውጭው፤ ሕግ ተርጓሚውና ሕግ አስፈፃሚው ተግባራዊ ሳያደርጉት ፤ ሳያምኑበትና ለሕገ-መንግሥቱ ተገዥ ሳይሆኑ በውል ያልተብራራን ሕግ በህዝብ ላይ መጫንና ሕዝብ ስለ ህገ መንግሥት ያለውን ግንዛቤ እንዲዛባ ማድረግ ሥርዓት አልብኝነትን በንቃት ማስፋፋት ብቻ ሳይሆን ሕዝብን በነገር እየተነኮሱ በሕገ-መንግሥት ሽፋን እያጭበረበሩ ሰጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛና ስለ ዴሞክራሲ፤ ፍትሕና ነፃነት ስለ ዜግነት መብቱ እንዳያስብ በታጠቀ ኃይል እያስፈራሩ የሥልጣን እድሜን ለማራዘም የሚያገለግል የመከላከያ ሠራዊት እንደትስ አድርጎ ነው ለሕገ መንግሥቱ ተገዥ ይሆናል የሚባለው? ይህን ጉዳይ በሚቀጥለው  ንኡስ ማጠቃለል ስለሚቻል የመከላከያ ሠራዊቱ በማናቸውም ጊዜ ለሕገ-መንግሥቱ ተገዥ ይሆናል የሚለው መቼ በሚል? አልፈዋለሁ።

5/ የመከላከያ ሠራዊት ተግባሩን ከፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ በሆነ አኳኋን ያከናውናል። በሰለጠነውና ዴሞክራሲ በሰፈነበት አገር የአገር መከላከያ ሠራዊት ከድርጅታዊ ፖለቲካ ወይም ለመንግሥት ከመቆም አልፎ ህግን በማስከበር እንዴት እንደሚንቀሳቀስ እየተመለከትን ወደ አገራችን ስንመለስ በተለይም በዘመነ ህወሃት የአገር መከላከያ ሠራዊቱ ለገዥው ህወሃት በመቆም ገና ትእዛዝ ሳይወርድለት አድራጊ ፈጣሪነቱን በምን አይነት ሂደት እንደሚተረጉመው በስፋት ተመልክተነዋል። የተቃዋሚ ድርጅቶችን በማዋከብ አንድ ቦታ ላይ ብቻ ተወስነው እንዲቀመጡና፡ህዝቡን እንዳያገኙት በማድረግ ቀዳሚውን ሚና የሚጫወተውም ይኸው የመከላከያ ሠራዊት ነው። የሕዝብን እምብኝ ባይነትና የውስጥ ብሶት በመሣሪያ ኃይል አፍኖ ይዞ መኖር እንደማይቻል ከዚህ በፊት በዘውዳዊው ሥርዓት፤ በወታደራዊ አገዛዝ ሕዝቡ አስመስክሯል ይህ ከሆነ የሚጠበቀው «ማየት መልካም ሁሉን እይው ግን በትዳር ቀልዱን ተይው»የሚለውን የሙሉቀን መለሰን የግጥም ስንኝ እያስታወስኩ ለህወሃት የመከላከያ ሠራዊት የመጨረሻውን ምክሬን በዚህ መጣጥፌ እደመድማለሁ። ወደፊት ሕግ ተርጓሚ የሚባለውን የኢትዮጵያ የፍትሕ ሚንስቴርና በህወሃት ጊዜ ተወልደው በህወሃት ጊዜ ተምረው ዳኛ ስለሆኑትና ዳኝነትና ዳኛ በኢትዮጵያችን በሚል ርእስ አንድ ጹሑፍ ይዥ ለመምጣት እሞክራለሁ ። እስከዚያው ደህና እንሰንብት!

አዲሱ 2006 ዓ/ም የሰላም ፤ የጤና ፤ የመተሳሰቢያ ፤ የእድገትና የድል ዘመን ይሁንልን!!

ቅዳሜ ከሰዓትን ከአቶ ግርማ ሰይፉ ጋር በቶሮንቶና ኦታዋ ቆይታ ያድርጉ (Toronto City Hall)

አውስትራሊያን ከኢትዮጵያ ጋር የማመሳሰል ሕልም

$
0
0

 መስከረም 8 2013

ከታክሎ ተሾመ

 

አውስትራሊያ ቀለመ ብዙ አገር  ናት። ከ200 በላይ  ቋንቋ  የሚናገሩባት በዝንቅ ማኅበረሰብ የተመሰረተች፤በጥሬ ማዕደኗ፤ ወንድ ሴት ሳይል የሰዎች የተፈጥሮ ሰብአዊ መብት የተከበረባት አገር ማን ትባላለች ብሎ ለሚጠይቅ  መልሱ አውስትራሊያ  ናት ብሎ በድፍረት መናገር ይቻላል።

 

አዎ እርግጥ ነው አውስትራሊያ በስደት የምኖርባት አገር ናት፤ ከዚህ በፊት ዴሞክራሲ የሚባል ነገር ስላላየሁ  ከዚህች አገር ውጭ ዴሞክራሲ ያለ መስሎ ስላልታየኝ  ወደድኳት፤ ተመችታኛለች። መፋቀርና መቻላል  ስላለ ብዙ እድሎችና ሕይወትን የሚለውጡ አጋጣሚዎች  የተመቻቹ  ናቸው።

 

አውስትራሊያን  ጥሩ  አገርና  መልካም ሕዝብ ያሰኛት የተለያዩ ምክንያቶች  አሏት። አውስትራሊያ ራሷን  የቻለች አገር  ከመሆኗ  በፊት  እርግጥ ነው ብዙ ጦርነቶች  ተካሂደውባታል።  ይሁን እንጂ ራዕይ ባላቸው ሰዎች አማካኝነት ከችግር  ተላቃ  ዴሞክራሲ የሰፈነባት አገር ለመሆን የቻለቸው  ሌበርና ሊበራል  የተሰኙ ሁለት አንጋፋ ፓሪቲዎች  በመፈጠራቸው  ነው። ሁለቱ  ፓርቲዎች  የየራሳቸውን  የፖለቲካ ፕሮግራም ይዘው  ሲከራከሩ ከዚህ ቀደም የሰሩት ሥራ እየተገመገመ  ሕዝቡ የሚበጀውን  ይመርጣል።

 

በአውስትራሊያ የፌደራሊ ምርጫ ሲደረገ  ጦርሰራዊት፤ ፖሊስ ወይም ደህንነት የሚባሉ በየምርጫ ጣቢያው  አካባቢ ድርሽ አይሉም። የአውስትራሊያ ዜጋ ሁሉም የሚበጀውን ፓርቲ የመምረጥ ኃላፊትም ሆነ ግዴታ አለበት። መስከረም 7 ቀን 2013 ቅዳሜ  ከጧቱን 8 ሰዓት  ጀምሮ እስከ ምሽቱ 6 ሰዓት ድረስ  ምርጫ ተካሂዷል።  በዚህ ወቅት ለውድድር  የቀረቡ፤ የአውስትራሊያ ሌበር ፓርቲና የአውስትራሊያ ሊበራል ፓርቲ በዋናነት ሲወዳደሩ እንዲሁ አናሳ የሚባሉ 1 ናሽናል ፓርቲ 2  ግሪን ፓርቲ  3 የግል ተወዳዳሪዎች 4  ዩናይትድ ፓርቲ  የመሳሰሉት ለውድድር  ቀርበው  ነበር። ከ2007  እስከ  2013 ዓ.ም ድረስ  የአውስትራሊያ  የሠራተኞች ፓርቲ ሌበር ሥልጣን ላይ  ነበር። ነገር ግን መስከረም 7 ቀን 2013 ዓ.ም በተደረገው ምርጫ ከምሸቱ 8.45 ሰዓት ላይ ተቃዋሚ  የነበረው  የአውስትራሊያ ሊበራል ፓርቲ 88 ድምጽ ሲያገኝ ሌበር ፓርቲ 54  ድምጽ አግኝቶ የሥልጣን ባለቤት ለመሆን በቅቷል።

 

ከላይ እንዳልኩት በምርጫ ወቅት የሳጥን ስርቆት አልነበረም፤ ሥልጣን ላይ የነበረው ሥልጣን አለቅም ብሎ ጦር አላዘመተም። እንዲያውም አሸናፊውን እንኳን ደስ ያለህ በማለት ወደፊት እየተመካከሩ አገርና ሕዝብ ለመምራት ቃል ኪዳን በመግባት የእለቱ ምርጫ  ተጠናቋል።

 

ይህንች አጭር ጽሁፍ ላቀርብ የተገደድኩበት ምክንያት የአውስትራሊያው ምርጫ በኢትዮጵያ መቼ ይሆን የሚደገም የሚለው ጥያቄ  ስላስገደደኝ  ነው። እርግጥ ነው፤ አንድ አገር  እንደ አገር ሲቆረቆር ብዙ ውጣ ውረዶችን  ማለፍ ግድ  እንደሚለው  ይታወቃል። ከታሪክ  መረዳት  እንደሚቻለው አገራችን ኢትዮጵያ ከዓለም ቀደምት መሆኗን ነው የሚነግረን። ነገር ግን ረጅም  እድሜ  ብታስቆጥርም ከአብራኳ በሚፈጠሩ መንግሥታት ሕዝቦቿ  በነፃነት እንደ ዜጋ እየኖሩ አይደለም።

 

ኢትዮጵያ ከዓለም የሚወዳደሩ ምሁራን ልጆች እንዳሏት አይካድም። ነገር ግን አገርና ሕዝብን ለመታደግ የታደለች አገር  አይደለችም። በመሆኑም  በየጊዜው  እስር፤ ስደትና ሞት የዘወትር እጣ ፈንታችን  ሆኗል። ይሁን እንጂ ችግሮችን አስወግዶ ዴሞክራሲያዊ የሆነ በሕዝብ የሚመረጥ መንግሥት ለማምጣት ረጅም  ዓመታት የተለያዩ ትግሎች ተካሂደዋል። ለትግሉ ስኬት አለመበቃት የተለያዩ ምክንያቶች እንዳሉ አይካድም።  ከፓለቲካ ድርጅት  መሪዎች  እስከ ግለሰቦች ድረስ ያለውን ብሎም ከሕይወታችን ጋር በንፅፅር ማስቀመጡ ተገቢ  ይመስለኛል።

በመጀመሪያ ደረጃ ዓላማን  በትክክል በመረዳት ወደየትኛው መስመር ነው የምንጓዝ፤ የምንታገለው ለጐጂ ወይስ ለጥሩ ዓላማ የሚለው ተለይቶ ከታወቀ  ትግሉ ትርጉም ያለውና የተሟላ  ይሆናል። ይህ ማለት የትግሉ ዓላማና የጉዟችን አቅጣጫ ከታወቀ ሕዝቡ ሊከተል ይችላል። ከተለያዩ ዓለም ትግሎች ተሞክሮ መረዳት እንደሚቻለው  ትግላቸው ውጤት ከማምጣቱ በፊት  ብዙ እልህ አስጨራሽ ትግልን ማለፍ ይጠበቅባቸው ነበር።  በመሆኑም  በደቡብ  አፍሪካ፤ በሰሜን  አሜሪካና በሌሎች አገራት ለነፃነት የታገሉ ድርጅቶች ለአሸናፊነት የበቁት  ሽንፈትንና  ተስፋ  መቁረጥን በፀጋ  መቀበልን  ባለመፈለጋቸው  ነው።

 

ከዚህ በፊት የተደረጉ ትግሎች በድርጅቶችም ሆነ በግለሰቦች ላይ አስደሳችና አሳዛኝ ገጠመኞችን ተመልሰን ስንቃኝ ብዙ ትምህርቶችን መቅሰም  ይቻላል። ለአገራችውና ለሕዝባቸው ሲሉ ከዚህ በፊት የተሸነፉ ፓርቲዎች በችግሮች ተስፋ  ሲቆርጡ  አንዳንዶች  ዛሬም ድረስ  የሚችሉትን  ያህል  እየተፈረጋገጡ  ይገኛሉ።

 

 

በአገራችን የተፈጠሩ በርካታ ተቃዋሚ ድርጅቶች በውስጥና በውጭ  እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ ስንቶች ናቸው መሰናክሎችን ማለፍ የሚችሉ ብለን ስንጠይቅ በጣት የሚቆጠሩ ሆነው እናገኛቸዋለን። በመጀመሪያ ደረጃ  ይጠንክሩም  ይኩሰሱ  አገር ቤት ውስጥ  የሚንቀሳቀሱ  ድርጅቶች የለውጥ ተስፋ እንደሚሆኑ እገምታለሁ።

 

ከላይ ከተጠቀሱት  የተስፋ ፓርቲዎች በተጨማሪ በውጭ የተሰባሰቡ ጅርጅቶችም እንዲሁ የአጋዥነት ግዴታ  እንዳለባቸው ብዙዎች ሲናገሩ እየተደመጠ ነው። እርግጥ ነው በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ከጉልበት እስከ ገንዘብ ድረስ የሚችለውን ያህል ለአገሩ እያበረከተ መሆኑን ማንም አይክድም። ነገር ግን  አንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች እርስ በርሳቸው በሚያደርጉት ፍክቻ  ትግሉ ወጥነት ኑሮት ስኬታማ እንዳይሆን መሰናክል መፍጠሩ አልቀረም።

 

ዋናው ነገር ግን ትግሉ ስኬታማ ሊሆን የሚችለው አገር ቤት በሚደረገው ትግል ስለመሆኑ አምንበታለሁ፤ ብዙዎችም አባባሌን  የሚስማሙበት ይመስለኛል። እነዚህ የአገር ቤት ተቃዋሚ ድርጅቶች ለአገራቸውና ለሕዝባቸው  መብት  መከበር  ሲሉ ብዙዎች የእሳት ረመጥ እስከ መሆን ደርሰዋል። እስር፤ ግርፋት ቢደርስባቸው የጀመሩትን ሰላማዊ ሕዝባዊ ተቃውሞ ትግል ከግብ ለማድረስ ቆርጠው መነሳታቸውን  በአንደበታቸው  እየሰማንና  ተግባራቸውን  እያየን  ነው።

 

እርግጥ ነው የአገር ቤት ድርጅቶች ለመስዋዕትነት መዘጋጀታቸው ቢያስደስትም የጀመሩት ትግል ውጤት እንዲያመጣ ከተፈለገ  ማበረታቻ  ያስፈልጋቸዋል። ይህ ሲባል  በስደት የተበተነው ትውልደ ኢትዮጵያዊና የፖለቲካ ድርጅቶች በሞራል፤ በገንዘብ፤ በዲፕሎማሲ፤ አገር ቤት ገብቶ አብሮ  መታገልን ግድ ይላል። እያንዳንዱ ለአገሩና ለሕዝቡ ሲል የራስ ተነሳሽነት ስሜት  ካለውና ከልብ የሚታገል ከሆነ ውጤታማ  ይሆናል። ብሎም የድርጅት መሪዎች ተነሳሽነታቸውም ቢሆን ዘላቂነት ይኖረዋል። ለዚህ ደግሞ ኃይል ሊሆን የሚችለው እምነት መሆኑ  አያጠያይቅም።  ስለሆነም እያንዳንዱ ኃላፊነትን መቀበል ሲጀምርና ወደ አንድ መመጣት ሲችል የትግሉ አቅጣጫ  ይስተካከላል ብሎ  በድፍረት  መናገር ቢያስ  ነው።

 

ከመግቢያየ ላይ  እንዳልኩት አውስትራሊያ  ዛሬ ከደረሰችበት የእድገት ደረጃ ከመድረሷ በፊት ብዙ ፈተናዎችን እንዳለፈች ከአውስትራሊያ ቤተ መጽሃፍት ውስጥ ገብቶ የታሪክ መጽሕፍቶችን ለሚያገላብጥ አስቀያሚና አስደሳች ታሪካቸው በሚገባ ተቀምጧል።  መስከረም 7 2013  በአውስትራሊ የተካሄደውን  የመንግሥት  ምርጫ በቅርበት ማየት ብቻ ሳይሆ  ተሳትፊ  እንዳየሁት ከሆነ  ተሽናፊው ለአሸናፊው ሥልጣኑን በሰላም አስረከቧል።

 

ከላይ ይህን ካልኩ ዘንዳ  ከምርጫ በኋላ   ቤቴ ቁጭ ብየ ቴሌቭዝኝ እየተመለከትኩ እግሬን ሳይሆን አእምሮየን  ኢትዮጵያ አድርጌ ጉደኛዋ አገራችንስ በምን ላይ  እንደምትገኝና የ1997 ቱ  ምርጫ ተመልሸ ስቃኝ አዘንኩ፤ ተከዝኩ እርር ትክን አልኩ። እርግጥ ነው ሃዘኔ ግን ተስፋን  ያዘለ ነው። ምክንያቱም ከዚህ ቀደም በተናጥል ይደረግ የነበረው ትግል አሁን፤አሁን በተቀናጀ መልክ  ሰላማዊ ሕዝባዊ ትግል ለማካሄድ  መስማማታቸውን እየሰማን ነው። ስለሆነም  ተስፋ ጥሩ ነው “ቸር  ተመኝ በጐ “እንድታገኝ ይሉየል በአውስትራሊያ ያየሁት  የሰላም የሥልጣን ዝውውር በኢትዮጵያም ይደገማል የሚል የተፍሳ  ስንቅ ተሸክሜአለሁ።

 

ሁሉም ፊቱን ወደ ሰላም እንዲያዞር ኃያሉ ልዑል እግዜአብዜ ይርዳን።

“በስልጣን ምክንያት ህወሓት ለሁለት የተከፈለ ይመስለኛል”–አቶ ገብሩ አስራት (ቃለ ምልልስ)

$
0
0

ሐገር ቤት የሚታተመው ሎሚ መጽሔት አቶ ገብሩ አስራትን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አነጋግሯቸዋል። ዘ-ሐበሻ ለአንባቢዎቿ ይጠቅማል በሚል እንደወረደ አቅርባዋለች።

ገብሩ አስራት 1

ሎሚ፡- ባለፈው መቀሌ ላይ “አረና” ሕዝባዊ ስብሰባ አከናውኖ ነበር፡፡ የነበረው ሁኔታ በአጠቃላይ ምን ይመስል ነበር;

አቶ ገብሩ፡- እንግዲህ የመቀሌውን ስብሰባ ከሁለት ጉዳዮች አንፃር ልንመለከተው እንችላለን፡፡ አንዱ ሕዝቡ እንዴት እንደተቀበለው ስብሰባውን … ሁለተኛው መንግስት ወይም በክልሉ ያለው ፓርቲ ስብሰባው እንዳይካሄድ ያደረጉትን ጫና በተመለከተ መመልከት ይቻላል፡፡ እንግዲህ አስቀድሜም መንግስት ስብሰባው እንዳይካሄድ የፈጠረውን ጫና ነው የማየው፡፡ እንግዲህ ትግራይ ውስጥ ገዢው ፓርቲ ህወሓት ነው፡፡ ህወሓት ከእሱ ውጭ ሌላ ፓርቲ እዛ ቦታ ላይ እንዲንቀሳቀስ ፍላጐት የለውም፡፡ ይህም ባፈለው 2002 ዓ.ም. በተካሄው ምርጫ ጠ/ሚ መለስ ትግራይ ውስጥ ምንም አይነት ክፍተት መኖር የለበትም፣ ምንም አይነት የሀሣብ ልዩነት መኖር የለበትም ብለው የተናገሩበትና በርካታ ስድቦች የተሰነዘረበት በተለይም በ”አረና” ላይ በርካታ ስድቦችን ያወረዱበት ጊዜ ነበር፡፡ እንግዲህ አሁን ያለው አመራርም የእሣቸውን “ሌጋሲ” ፈለግ እከተላለሁ የሚል ስለሆነ አካሄዱ ተመሳሳይ ነው፡፡ በትግራይ ውስጥ ምንም አይነት የፖለቲካ አስተሳሰብ እንዲኖር አይፈልግም፡፡ በህገ መንግስትም ፣ በቃልም ተቃዋሚ ቢኖር አንጠላም ሊሉ ይችላሉ፡፡ ዋናው ስጋታቸው በአካባቢው የተለየ ሀሣብ ፣የተለየ አመለካከት ፣ የተለየ አደረጃጀት እንዳይኖር ስጋትና ጭንቀት ያለባቸው ስለሆነ አጠቃላይ ድርጅቱን በእነሱ ስር የተደራጀ ሲቪክ ማህበረሰብ፣ የመንግስት ድርጅቶችን አደራጅተው ነው አንድ ፓርቲ በዛ አካባቢ ስብሰባ እንዳያካሂድ የሚያደርጉት፡፡ ባለፈው ጊዜም ስብሰባ ስናካሂድ እንደውም እነሱ በሚመሯቸው ድርጅቶች ፣ ኩባንያዎች /ኢፈርት/ ሠራተኞችን ሰብስበው በዚህ ስብሰባ ላይ መገኘት ከጠላት ጋር እንደማበር ይታሰባል ብለዋቸዋል፡፡ እና ስለዚህ ስራ ለማግኘት አትችሉም፣ ስጋት ላይ ትወድቃላችሁ ፣ ከጠላት ጋር የመተባበር ያህል አድርገን ነው የምናየው ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡

ይህንን ካሉ በኋላም በዚህም አላበቃም በኢትዮጵያ የምርጫ ሕግ መሠረት እንደተፈቀደው ማንም ፓርቲ ሊቀሰቅስ ይችላል፡፡ መቀስቀስ የማይችለው በትምህርት ቤትና በቤተ እምነት ቦታ ውስጥ እንጂ በሌላ ቦታ ድምፅ ማጉያ ተጠቅሞ መቀስቀስ ይችላል የሚል ነገር አለ፡፡ መቀሌ ላይ ግን ሌላ ህግ አውጥተዋል ወይም አውጥተናል ነው የሚሉት፡፡ እኛ ግን አላየነውም፣ ህጉ ምንድነው የሚለው ማንኛውም እንቅስቃሴን ማጉያ ተጠቅሞ መቀስቀስ አይቻልም ነው የሚሉት፡፡ ይሄ እንግዲህ ከሀገሪቱ ህግ ፣ ከፌዴራል ህግ ጋር የሚጣረዝ ህግ ነው፡፡ ህግም ቢሆን ማለቴ ነው፡፡ ማውጣትም አይችሉም፡፡ እንደዚህ ያለ የምርጫ ቦርድ ሕግ እያለ መንግስት ወይም አስተዳደር ይሄንን ህግ ሊያወጣ አይችል፡፡ እኛ ህግ አውጥተናልና መንቀሣቀስ አትችሉም እያሉ ነው የሚናገሩት፡፡ ለምን ስንላቸው ደግሞ ድምፅ ማጉያው ማለት ነፍሰ ጡሮችንና በሽተኞችን ሊያውክ ስለሚችል መናገር አይቻልም ፡፡ በዛ ምክንያት ነው የከለከል ነው ይላሉ፡፡ ያም ሆኖ ግን መስኪዶች፣ ቤተክርስቲያኖች በድምፅ ማጉያ መልእክት ያስተላልፋሉ፡፡ ራሣቸው ህውሓቶችም በድምፅ ማጉያ ዳንኪራ እየመቱ የሚያጥለቀልቁበት ሁኔታ አለ፡፡ ለተቃዋሚዎች ነው ያልተፈቀደው እንጂ ራሣቸው በማይክራፎን ከተማውን የሚያውክ ነገር ይጠቀማሉ፡፡ ስለዚህ በዚህ ምክንያት ያንን ከለከሉን፡፡ እና ይሄ ህግ ይፈቅድልናል ብለው የኛ አባላትም ተንቀሣቀሱ፡፡ ግን አሰሯቸው፡፡ ሁለት ሦስት ጊዜም ነው ይህንን ያደረጉት፡፡ ሹፌሮችንና የተከራየነውንም መኪና አገቱ፡፡ ስለዚህ በዚህ መልኩ ስብሰባ እንዳይካሄድ አግተዋል፡፡ በንጋታው ደግሞ ስብሰባ ስናካሂድ እያንዳንዱ የቀበሌ አስተዳደር ማን እንደሚገባ እንዲመለከት እዛ አሰልፈዋቸው ነበር፡፡ አብዛኞቹም ሴቶች ናቸው፡፡ /የቀበሌ ሴቶች/ እነዚህን አሠልፈው ማነው ወደዚህ ስብሰባ የሚገባው የሚል ሊስት ይዘው አስቀመጡ፡፡

ጭራሽ ስብሰባ እንዳይካሄድ ነው የሞከሩት፡፡ በሌላም እያንደንዱ ቀበሌ ለሕዝቡ ስብስባ እንዲመጣ በፅሁፍ ጭምር ደርሰው እንድትገኙ የሚል አስተላለፉ ….የምንናገረው ስለመልካም አስተዳደር ፣ ስለ ንግድ ምናምን ነው ብለው መቅረታ የለባችሁም ወሣኝ ስብሰባ ነው ብለው ፣ እኛ ስብሰባ በምናደርግበት ቀን እነሱም ስብሰባ ጠሩ፡፡ ይሄ አካሄድ ደግሞ ምንም አይነት ሰው ወደኛ እንዳይመጣ የማድረግ አላማ ያለው ነው፡፡ ያም ሆኖ ግን ሕዝቡ ፍላጐት ነበረው እንዲያውም ስብሰባውን እንድናካሂድ ግፊቱ የመጣው ከሕዝቡ ነበር፡፡ ያም ሆኖ እነሱ ባይከለክሉት ኖሮ አዳራሹም አይችልም ቦታም አይበቃም ነበር፡፡ ይሄም ሆኖ ወጣቱ ይሄን ሰብሮና ጥሶ አድራሹን ሞልቶታል፡፡ እና እዚህ ላይ ለማለት የምፈልገው በተለይ በሁለት ጉዳዮች ላይ እኛ ያቀረብነው በከተማ የሊዝ አዋጆች ላይ ፣ በነጋዴዎች የግብር ጫና፣ በዜጐች ሰብአዊ መብት እጦት እንደዚህ እንደዚህ ያሉ በርካታ ጉዳዮች ላይ ነው፡፡ ሕዝቡ ግን ትኩረት አድርጐ ያቀረበው ነፃነቱን እንደተነፈገ ነው፡፡ ትግራይም ውስጥ እንደተነፈጉ ተናጋሪዎች ናቸው፡፡ እኛ ንግግሩን ጀመርነው እንጂ የጨረሰው እዛ የተሰበሰበው ሕዝብ ነው፡፡

ገብሩ አስራት ሌላው ደግሞ ይሄ የሊዝ መሬት ዜጐችን ጭሰኛ ለማድረግ እየሞከረ እንዳለ በአፅንኦት ተናግረዋል፡፡ መሬታችንን ቀሙን፣ በወላጆቻቸው /ውርስ/ ያገኙት መሬት ላይ ዋስትና እንዳጡ ፣ ይህንንም ተናገሩ፡፡ እንግዲህ የሚገርመው ስብሰባውን በፀሎት ለመጀመር ነው ፕሮግራም የያዝነው፡፡ ሁሉም የስብሰባው ታዳሚ ተነስቶ ለሰማእታት ፀሎት ሲያደርግ አንድ ወጣት ግን ከመቀመጫው ሣይነሳ ቁጭ ብሏል፡፡ ኋላ ላይ ግን ለምን በፀሎቱ ወቅት እንደተቀመጠ ምክንያቱን ተናገረ፡፡ ይሄ ወጣት ሲናገር “እኔ እናንተ ለምን ተነስታችሁ እንደምትፀልዩ አልገባኝም፡፡ ምክንያቱም እኔ አባቴ በትግሉ ተሰውቷል፣ ወንድሜና እህቴ ተሰውተዋል፡፡ ግን ያመጡልን ምንም ነገር የለም፡፡ ለምንድነው የምፀልየው; እኔ የምፀልየው ኢትዮጵያው ውስጥ ነፃነት ሲረጋገጥ፣ መብት ሲረጋገጥ ነው እንጂ አሁን ቆሜ አልፀልይም፡፡ ቤተሰቦቼ የተሰዉበት ሁሉ ተግባራዊ እየሆነ አይደለም፡፡ አፈና ፣ ሙስና ይህንን ለማምጣት ከሆነ የተሰዉት አልፀልይም፡፡ የምፀልየው ኢትዮጵያ ውስጥ ነፃነት ሲረጋገጥ ብቻ ነው” ብሏል፡፡ ይህ ንግግር ተሰብሳቢውን በጣም ያስገረመ ንግግር ነው የነበረው፡፡በአጠቃላይ መንግስትና የክልል ፓርቲ ስብሰባ እንዳይካሄድ ሕዝቡ ሌላ አማራጭ እንዳይሰማ ቢያደርጉም ሕዝቡ ግን ከፍተኛ ፍላጐት ነበረው፡፡ እንዲያውም እኛ ካሰብነው ጊዜ በላይ ተወያይቶ በጥሩ ሁኔታ ስብሰባውን አጠናቀናል፡፡

ሎሚ፡- አንዳንድን ዘገባዎች አሉ ይህ በሕዝብ ውስጥ የሚባለው ነው መረጃውን በእርስዎ አንደበት የማስተላለፉ መልእክት ደግሞ የእርስዎ ይሆናል፡፡ አረና ጥሩ እየተንቀሣቀሰ ቢሆንም የአባላቶቹ ወደ አሜሪካ መጓዝ በፓርቲው ላይ ችግር አይኖረውም ወይ የአቶ ስዬ እና የአቶ አሰግድን የሚያነሱ ሰዎች አሉ;

አቶ ገብሩ፡- ይሄ ምናልባትም የመረጃ ጉዳይ እንዳይሆን ለመናገር እሞክራለሁ፡፡ አቶ ስዬ የአረና አባል አይደሉም፡፡ የአንድነት አባል ናቸው፡፡ አቶ አስግድም ተመልሰዋል፡፡ አሁን ትግራይ ውስጥ ነው ያሉት፡፡ ስለዚህ የእኛ አባል ሆኖ ከሀገር ውጭ የሚገኝ የለም፡፡ ስለዚህ ይህን መረጃ ሕዝብ እንዲያውቀው ይገባል፡፡

ሎሚ፡- በህወሓት ውስጥ እውነት ልዩነት አለ; ህወሓት ለሁት ተከፍሏል የሚባል ነገር አለ ይሄን እንዴት ይገልፁታል;

አቶ ገብሩ፡- እኔ እንግዲህ በፖለቲካ ምክንያት ፣ በፖለቲካ ልዩነት ምክንያት ህወሓት ውስጥ መከፋፈል አልተመለከትኩም፡፡ ያም ሆኖ በስልጣን ምክንያት ህወሓት የተከፈለ ይመስላል፡፡ ይህም የታየው መቼ ነው ባለፈው የፓርቲው ጉባኤ በተካሄደበት ጊዜ ነባሮቹን ሙሉበሙሉ ጠራርጐ አስወጥቷል፡፡ ካድሬዎቹ ይሄ የሆነው ምንድነው ህወሓት ውስጥ የተጠናከረው በካድሬ ደረጃ አባል ነው ስልጣኑን የተቆጣጠረው እንጂ ራሱ ሀሣብ ሊያመነጭ የሚችል ፣ ሀሣብን ሊቀምር የሚችል፣ ንድፈ ሀሣብን በደንብ ተገንዝቦ ሊያስረዳ የሚችል ኃይል ህወሓት ውስጥ አሁን የለም፡፡ ከፋም በጀም የተሻለ አቅም ያላቸው ሰዎች ከዚህ ተገለዋል ብሎ መናገር ይቻላል፡፡ ስለዚህ የስልጣን ሽግሽግ ነው ለዚህ ያነሱት፡፡ ይህንን መሠረት አድርገው ነባር የተባሉትን ጠራርገው አስወጡ፡፡ እዚህ ላይ ግን ነባር የተባሉትንና ተጠርገው ከወጡት እኩል በፓርቲው ረጅም እድሜ ያላቸው ደግሞ እዛው ቀርተዋል፡፡ ስለዚህ ነገሩ የስልጣን ሽኩቻ ይመስላል ብሎ መናገር ይቻላል፡፡

ሎሚ፡- አሁን የኃይል ሚዛኑ የትኛው ክፍል ጋር ነው;

አቶ ገብሩ፡- ይሄ ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም አስቸጋሪ ነገር ነው፡፡ እንግዲህ የኢትዮጵያ ፖለቲካና ስልጣን የተመሠረተው በማን ላይ ነው የሚለውን መመልከቱ ጥሩ ነው፡፡ ሦስት አካሎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ አንዱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማየት ይቻላል፡፡ ሁለት የመንግስት አካላት፣ ሦስተኛው መከላከያና የደህንነት አካላትን ነው ማየት የሚቻለው፡፡ አቶ መለስ በነበሩበት ጊዜ እነዚህ ሦስት አካላትን ተቆጣጥረው የሄዱበት ጊዜ ነበር፡፡ እንግዲህ የአቶ መለስ መንግስት አምባገነን መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ እንደ አምባገነንነቱም ሁሉንም የስልጣን አካላት ተቆጣጥረው በእጃቸው ውስጥ አስገብተው ቆይተዋል፡፡ እንደውም አሁን ኢህአዴግ ተዳክሟል የሚያሰኘው ምንድን ነው በአንድ ሰው ተሰባስቦ ፣ የአንድ ሰው ፈላጭ ቆራጭ፣ ስልጣን የነበረው አሁን ተበታትኗል፡፡ ከስልት አንፃር ይሄ መዳከምን ያሣያል፡፡ ይህ ከሆነ በኋላ ስልጣኑ የት ላይ ነው የሚለው ነገር በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ እንደ አቶ መለስ ተጠናክሮ የወጣ ሰው የለም፡፡ የአቶ መለስ ፍላጐት ቀድሞም ምንድነው የፑቲን አይነት አስተዳደር ነው በዚህች ሀገር ላይ ፍላጐታቸው የነበረው፡፡ ደካማውን ፊት ላይ አስቀምጠው እሣቸው ከኋላ ሊነዱት ነበር አቶ ኃ/ማርያምንና ሌሎችንም ወደ ስልጣን ያመጡት፡፡ ያም ሆኖ ግን እሣቸው አልቆዩም፡፡ አቶ ኃ/ማርያም በዚህ አጋጣሚ ስልጣን ያዙ፡፡ አሁን አቶ ኃ/ማርያም መከላከያውንና ደህንነቱን በእጃቸው ለመቆጣጠር ይችላሉ 1111 የሞራል ብቃትስ አላቸወይ; የፖለቲካው ብቃትስ አላቸወይ; የሚለው ጥያቄ የሚያስነሳ ነገር ነው፡፡ ፓርቲውንስ ቢሆን እንግዲህ ነባሮች ዳግም ተመልሰዋል ብአዴን ውስጥ አቶ መለስ እያሉ ውጡ ተብለው ታዘው ወጥተው የነበሩትም እንደገና ተመልሰው መጥተዋል፡፡ እነዚህንስ ለማዘዝ ይችላሉ ወይ;ከፍተኛ ውሣኔዎች ላይ የማዘዝ አቅም ይኖራቸዋል ወይ; የሚለው አንድ ጥያቄ ነው፡፡ እንግዲህ በመንግስት የሚባሉት ፣ በፓርላማ፣ በካቤኔ ውስጥ የዚህ ነፀብራቅ ነው፡፡በደህንነቱ፣ በመከላከያው የማዘዝ ስልጣን ከሌለህ በመንግስት ውስጥም የማዘዝ ችሎታህ አነስተኛ ነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ አሁን ችግሩ የስልጣን ክምችት በአንድ አካል ላይ አለ፡፡ ይሄ ነው የሚወሰነው፡፡ ደህንነቱም ሆነ መከላከያው ትልቅ ተፅእኖ አለው በኢትዮጵያ፡፡ እንደውም ወሳኙ እሱ ነው፡፡ እሱን ማዘዝ፣ ማሰማራት ፣ እሱን መቆጣጠር የማይችል ኃይል በኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይል ይዣለሁ ማለት አይችልም፡፡ ይህንንስ ማድረግ ይችላል ወይ; አሁን ያለው አመራር ለሚለው ነገር ጥያቄ ውስጥ ያስገባል፡፡ ፓርቲዎችም ቢሆን ከአቶ መለስ ሞት በኋላ የየራሣቸው ነፃነትና መብት ለማስከበር አዝማሚያም እየታየባቸው ነው፡፡ የብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ህወሓት በአጠቃላይ የፖለቲካ ሂደት ላይ ተፅእኖ ለማሣደር እየሞከሩ ነው ያሉት፡፡ በይፋ ያልወጣ ሽኩቻ እየታየ ነው፡፡ ውስጥ ለውስጥ፡፡ ድሮ የነበረው የአንድ ግለሰብ ተፅእኖ አሁን የመሰበር ሁኔታዎች ነው ያሉት፡፡ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉንም ለመወሰን ኃይሉም አቅሙም ያለው የለም፡፡ የሚፈለገው እሱ ነው ወይ ሌላ ጥያቄ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሄ የአቶ መለስ ሌጋሲ የሚባለው ግን እንደዛ ያለ ሰው ካልፈጠረ በስተቀር ጥንካሬ አለው ብሎ ለማለት አይቻልም፡፡

ሎሚ፡- አሁን እንግዲህ በስርአቱ ውስጥ ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ መንሰራፋቱ ይነገራል፣ የሚታይም ነገር ነው፡፡ከሀገር ውጭም ገንዘብ የማሸሽ ሁኔታ አለ ይሄን እንዴት ይመለከቱታል;

አቶ ገብሩ፡- እንግዲህ ሁልጊዜም እንደምለው ራሱ የሙስና ምንጭ በኢትዮጵያ ያለው የሙስና ምንጭ የለሚው ነገር ካልታወቀ መፍትሄም አይገኝለትም፡፡ ኢህአዴግ ሙስናን እየታገልኩ ብሎ ለማስመሰል የተወሰኑ ባለስልጣኖችንና ነጋዴዎችን ያስራል፡፡ ይፈታል፡፡ ግን ይሄ መፍትሄ ነው ወይ; በኢትዮጵያ የሙስና ምንጭ መሠረት የሆነው እነዚህ ነጋዴዎች ናቸው ወይ; የተወሰኑ ባለስልጣናት ናቸው ወይ; የሚለውን ነገር ማንሣቱ የሚጠቅም ይመስለኛል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ሙስና ሊቀንስ፣ ሊቃለል የሚችለው ከስርአቱ ጋር በቀጥታ ተያያዥነት አለው፡፡ የአንድ ስርአት ፓርቲ አገዛዝ ከሆነ ዞሮ ዞሮ ሙስናን ነው የሚያነግሰው፡፡ደጋፊዎቹን ያጠናክራል፣ በሀብት ያጠናክራል፣ በገንዘብ ያጠናክራል፣ ፖሊሲው ነው፡፡ አባሎቼ የሚላቸውን ቢሰርቅ ፣ ቢዘርፍ ምንም ሊላቸው አይችልም፡፡ ፖለቲካውን የሚቃወሙ ሊነካኩ የሚችሉ ሰዎች አንዳንድ ጊዜም በሰውም ምንም ለውጥ አያመጣም ብሎ የሚያስባቸውን ሰዎች በሙስና ይቀጣል እንጂ ከመሠረቱ ስርአቱ ነው፡፡

እንደሚታወቀው ይሄ በውጭ ሀገር ገንዘብ አላቸው ወይ; አስቀምጠዋል ወይ; የሚለው ነገር በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን የአለም ተቋማት እንደሚነገረው የሸሸው ገንዘብ በርካታ ነው፡፡ ይሄ ገንዘብ የማነው የኔ ነው የሚል ባይታወቅም በኢትዮጵያ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እየሸሸ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ግን ወደዛ መሄድ አያስፈልግም፡፡ እዚህ ሀገር ያለው ሀብት ከየት መጣ የሚለው ነገር ቢጠየቅ እኮ መልስ የለም፡፡ሰርቶ ነው ወይ; ከደሞዙ ነው; በተለይ አንድ የመንግስት ባለስልጣን ትላልቅ ቤቶችን የሚያሰራ ደሞዝ አለው ወይ; ህንፃዎችን የሚያሰራ ደሞዝ አለው ወይ; ብዙ ሀብት ቤተሰቦቹን በከፍተኛ ደረጃ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውጭ ድረስ ልኮ የሚያስተምር ደሞዝ አለው ወይ ተብለው ቢጠየቁ የኢህአዴግ አመራሮች መልስ የላቸውም፡፡ ስለዚህ ሙስናው የራሱ የስርአቱ ባህሪ ነው፡፡ ምክንያቱም ሙስናን እንታገል ቢባል፣ ኢህአዴግ በሚከተለው አግባብ እንዴት ሙስናን መታገል ይቻላል; ነፃ ማህበረሰብ ፣ ሲቪል ማህበረሰብ በሌለበት እኮ ይሄ ሙሳኝ አለ ብሎ መቃወም አይቻልም፡፡ ጠንካራ ነፃ ጋዜጦች “Invest get journalism”መስራት በማይቻልበት ሁኔታ እንዴት ነው ሙስናን መዋጋት የሚቻለው; የመንግስት ተጠያቂነት ግልፅነት በሌለበት እንዴትነው ሙስናን መታገል የሚቻለው; ሕዝብ ሰልፍ ወጥቶ መቃወም በማይችልበት፣ ተሰብስቦ መነጋገር በማይችልበት እንዴት ነው ሙስናን መታገል የሚቻለው; ስርአቱ በባህሪው አምባገነናዊ ስርአት ነው፡፡ “አብዮታዊ ዴሞክራሲ” ብሎ የአንድ ፓርቲ ፈላጭ ቆራጭነት አረጋግጣለሁ የሚል መንግስት ከሙስና አይነፃም፡፡ ነፃ ሊሆን አይችልም፡፡ በአለምም ያየነው፣ በአፍሪካም የሚታየው ፓርቲዎች የህብረተሰቡን እንቅስቃስቃሴ በሙሉ “ገዢ ፓርቲዎች” ሕዝቡ ትንፍሽ እንዳይል ፣ እንዳያጋልጥ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ ኢህአዴግም ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ መታየት ያለበት የአንድና ሁለት ባለስልጣን የማሰርና የማጋለጥ ጉዳይ አይደለም፡፡ ዋናው ነገር ስርአቱ በቁርጠኝነት መታገል የሚችል እስከሆነ ብቻ ነው፡፡ ይሄንን ደግሞ ኢህአዴግ አይችልም ያውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ መሬት እንደተዘረፈ ያውቃል፡፡ እሱ ነው የሚያዘርፈው፡፡ የመንግስት በጀት እንደተዘረፍ ያወቃል ግን እራሱ ነው የሚያዘርፈው፣ የመንግስት ልማት ተቋማት በሚሊዮኖች ይዘረፋሉ ያውቃል መንግስት ግን መፍትሄ የለውም፡፡ መፍትሄም ከኢህአዴግ ይመጣል ብሎ ማሰብ የዋህነት ይሆናል፡፡ ምንም ሊመጣ አይችልም፡፡

ለዚህም ነው ከአመት አመት እየተባባሰ እንደውም አሁን የስርአቱ ዋና መገለጫ እየሆነ ያለው ከዚህ በመነሣት ነውና፡፡ አንድ እንደ አቅጣጫ መታየት ያለበት፣ መረሳት የሌለበት ሙስና ከስርአቱ የሚመነጭ ስለሆነ ፣ በፀረ ሙስና በኩል የተወሰኑትን በማሰር የሚቋጭ አይደለም፡፡ሰፊ ነፃነት፣ሰፊ መብት፣ ጠንካራ የህግ የበላይነት፣ ነፃ ባለስልጣኖችን ሊጠይቅ ሊያስር የሚችል አቃቢ ህግ “ነፃነት ያለው” ፍርድ ቤት ሊወስንባቸው የሚችል ያለምንም ተፅእኖ ከሌለ ሙስናን መታገል እንዴት ይቻላል፡፡ ስለዚህ ታዩታላችሁ ሙስና ኢህአዴግ እስካለ ድረስ እየባሰበት የሚሄድ ይሆናል፡፡ አሁን ተራ ሙስና አይደለም የማፍያ አይነት የተደራጀ ሙስና ነው እየተካሄድ ያለው፡፡

ሎሚ፡- እንደታዘቡት ከሆነ ፣የሙስሊሙ ጥያቄ አለ ይሄን እንዴት ይመለከቱታል; ሌላው ከቅርብ ቀናት ወዲህ በመንግስት በኩል አክራሪነት ፣ ሽብርተኝነት፣ አሸባሪነት የሚሉ ቃላት ይሰማል ይሄስ በእርስዎ እይታ እንዴት ታዘቡት;

አቶ ገብሩ፡- እንግዲህ በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ጊዜ ተናግረናል፡፡ እኔ እንግዲህ ኢህአዴግ አንዳንድ ችግሮች ሲነሱ የሚሄድበት አግባብ ችግሮች አሉበት፡፡ የሙስሊሙ ጥያቄ ፣ የአባይ ጥያቄ፣ የብሔር ብሔረሰቦች ጥያቄ እነዚህ በዚህ አገር ከባድ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ በተለይ በሙስሊሞች ጉዳይ መታየት ያለበት ካለው ማህበረሰባዊ እድገት፣ አለም አቀፋዊ ሁኔታ መንገድ ነው መታየት ያለበት፡፡እንግዲህ የሙስሊሞች ጥያቄ መታየት የጀመረው እኮ መለስ በነበረበት ጊዜ ነው፡፡ እንደማስታውሰው እኔ ከተለያዩ የአለም ክፍሎች የተውጣጡ ፣ የሙስሊም አባላት መጥተው ከአቶ መለስ ጋር ተገናኝተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሙስሊሞች አያያዝ የሚያሳስባቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ጥያቄዎችም ያኔ አንስተዋል፡፡ ካነሷቸው ጥያቄዎች መሀል፣ የበአላት ማክበር፣ ወለድ የሌለው ባንክ የመክፈት ጉዳይ እንዲህ እንዲህ ያሉ ወደ አስር የሚጠጉ ጥያቄዎች አንስተው ነበር፡፡ በወቅቱ እናየዋለን የሚል መልስ ነው የተሰጣቸው፡፡ ከዛ በኋላ የታየም ነገር የለም፡፡ ውስጥ ለውስጥ የሚነሱ ጉዳዮች አሉ፡፡ ብዙ የመብት ጥያቄዎች፡፡ ይሄ እያለ ግን ኢህአዴግ ይሄን የሚያባብስ እርምጃ ወስዷል፡፡ ምንድነው እንደምታስታውሰው በተለይ “ፌድራል ጉዳዮች” የሚባል የመንግስት አካል የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን በሌላ ሙስሊም ለማስጠመቅ ሙከራ አደረገ፡፡ “አልሀበሽ” የሚባል ገንዘብ አውጥቶ ይሄን ተማሩት አለ፡፡ እያንዳንዱ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሙስሊም በዚህ ውስጥ እንዲጠመቅ ሙከራ አደረገ፡፡ ሙስሊሞች ተቃወሙት ፣ ሃረር ላይ ….. ሚኒስትሩ ሣይቀር ስብሰባ አደረገ፡፡ ይሄ ጣልቃ ገብነት ነው፡፡ …. አንድን ኃይማኖት በሌላ ኃይማኖት በዚህ እመን ማለት ጣልቃ ገብነት ነው፡፡ ያለጥርጥር ነገሩ ከዚህ ተነሣ ከዛ የአወሊያ ትምህርት ቤትም ተነሣ ይሄ የቆየ ነው፡፡ ድሮ የነበረ ትምህርት ቤት ነው፡፡ ያንን ለመቆጣጠር ሞከረ፣ ያም አይሆንም የሚል ምላሽ ቀረበ፡፡

እንደገና የምርጫ ጉዳይ ተነሣ፡፡ ቀላል ጥያቄ በጣም ቀላል …. ምርጫው በመስኪዶች ይሁን የሚል፡፡ ይሄ ሁሉ ኢህአዴግ የማያዝበት መንገድ ግን ሽንፈት ነው የሚመስለው፡፡ አንዳንዶቹን ጥያቄዎች መመለስ ሽንፈት ስለሚመስለው ነገሩን ያጦዘዋል፡፡ ወደ አስቸጋሪ ሁኔታ ይገፋዋል፡፡ የኢትዮጵያን ሙስሊሞች እንደማውቃቸው በመሠረቱ በጣም ተቻችለው በመኖር ተግባብተው በመኖር የሚታወቁ ሙስሊሞች ናቸው፡፡ የሱፊ እምነት ፣ ካተሚያ እምነት በኢትዮጵያ ያለው ተቻችሎ የኖረና የሚኖር ሙስሊም ነው፡፡ ያም ሆኖ ግን ልክ በክርስቲያኑ ውስጥ እንደሚታየው ድሮ የሚታወቁት ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ አልፎ አልፎ የድሮ ፕሮቴስታንቶች ይታወቁ ነበር፡፡ በኋላ ላይ ግን ጴንጤዎች መጡ፣ ሌሎችም መጡ፣ ጆባ መጣ ይሄ በነበረው አይን ሲታይ ፅንፈኛ ነው እና ክርስቲያኑ ሁሉ ያኔ ተደናገጠ ግን ሊያቆመው አይችልም፡፡ ከአለም ጋር ይገናኛል፡፡ ሕዝቡ ብዙ ብዙ እምነቶች አሉ ተቀብሎ ያምናል፡፡ በሙስሊምም የሚሆነው ይሄ ነው፡፡ ዋህቢያ መጣ፣ ሳላፊ መጣ ሌሎችም ሌሎችም ሺሀ ሊነሳ ይችላል፡፡ ይሄ እንግዲህ መንግስትም ይሁን ማንም ሊያቆመው አይችልም ይሄንን ዝንባሌ፡፡ መንግስት ማድረግ ያለበት እነዚህ አስተያየቶች፣ እነዚህ መስመሮች፣ ከህገ መንግስቱ ወጥተው፣ ሰላም እንዲኖር፣ መረጋጋት እንዳይጠፋ መቆጣጠር እንጂ ከዛ ባለፈ ይሄ እምነት ነው ትክክለኛ ይሄ ደግሞ ትክክለኛ አይደለም ብሎ መናገር መብቱ አይደለም፡፡

ማስተማርም የለበትም፡፡ ግን ኢህአዴግ ትንሹን ነገር አግዝፎ ስለሚያየው ነው፡፡ ኢህአዴግ መንግስት ሆኖ ከግለሰብ ጋር እየተጣላ የሚውል መንግስት ነው፡፡ በጣም ነው የሚያሣዝነው፡፡ አይንቀውም ትንሽ ነገር ነው እቆጣጠረዋለሁ ብሎ አያምንም፡፡ ሰራዊትይዞ ፣ ስፍር ቁጥር የሌለው ፌድራል ፖሊስ ፣ የክልል ፖሊስ፣ የፀጥታ ኃይሎች ይዞ እያለ በሁለት ሦስት ሰዎች እየተሸበረ ነው ያለው፡፡ ኢህአዴግ ሽብር ነው ውስጡ ያለው፡፡ ስለዚህ በሙስሊሙ ይሄ ነገር ሲነሳ ይሸበራል፡፡ ሲሸበር ደግሞ ለዚህ ምላሽ የሚሰጠው በማተራመስ ነው እንጂ ነገሮችን ከስትራጄክ አንፃር አያያቸውም፡፡ ሰልፍ ያስወጣል፣ አገሪቱን በሙሉ በስብሰባ ያስወግዛል፣ በየቀበሌው ፣በየከተማው …. አውግዙ ይሄ መፍትሄ አይሆንም ፣ ሰልፍ ውጡ ይሄ ፕሮፖጋንዳ ነው፡፡ከፕሮፖጋንዳ በዘለለ ነው መታየት ያለበት፡፡ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ሲነሱ በስትራ ቴጂክ እንጂ በፕሮፖጋንዳ ሊፈቱ አይችሉም፡፡ ምን ማለቴ ነው የአባይ ጉዳይ ሲነሳ ያነሣነው ነገር ነበር፡፡ አባይን ስንነካ አንድ ስትራቴጂክ ጉዳይ ነው ለኛ …. ስትራቴጂክ ጉዳይ ስለሆነ በአንድ ፓርቲ ፣ በአንድ ክፍል ብቻ መፍትሄ የሚያመጣ አይደለም፡፡ መግባባት ያስፈልጋል፡፡ ተቃዋሚዎች ሁሉ ለዚህች ሀገር ኃላፊነት አለብን የሚሉ ተግባብተው መሄድ አለባቸው፡፡ ምክንያቱም ይሄንን ትልቅ ነገር ከነኩ በኋላ ተባብረው መስራት እንጂ የሚያስፈልገው እንዲሁ “አካኪ ዘራፍ” ብሎ ማሰናበት አይቻልም፡፡ የሙስሊም ጥያቄ ሲነሳ እኔ ኢህአዴግ እንደሚያየው አያስደነግጠኝም፡፡ ያን ያህል የሚያስደነግጥ ፣ የሚያስፈራ፣ የሚያሸብር ነገር የለም፡፡ መቆጣጠር የሚቻል ነው፡፡ ያም እሱ በሚያስበው ችግር ቢኖራም፣ እሱ ባወጣው የፕሮፖጋንዳ አቅጣጫ መመራት ሣይሆን ፣ እስቲ እንነጋገርበት ሙስሊሞችን ሲያነጋገር አንዱን ክፍል ብቻ ማነጋገር የለበትም፣ ሁሉንም አነጋግሮ መፍታት ይችላል፡፡ ከተቃዋሚዎችም ጋር ቢሆን መቶ በመቶ የሚቃወሙትንም ማነጋገር እንጂ የራሱን ደጋፊዎች ብቻ አንድ የዩንቨርስቲ ምሁር ማናገር ተገቢ አይደለም፡፡ ስለኔ ምን ይላል ብሎ የተለየ ሀሣብ ሊያገኝ ይችላል፡፡ ስለዚህ የሙስሊሙም ጥያቄ ከአጠቃላይ የዴሞክራሲና የሰብአዊ መብት ጋር ተያይዞ መታየት ያለበት ነው የሚመስለኝ፡፡


Hiber Radio: በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ የዓመት በዓል ገበያው ቀዝቅዟል

$
0
0

የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ጳጉሜ 3 ቀን 2005 ፕሮግራም

እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሰዎ

በዓሉ የሰላምና የጤና እንዲሆን መልካም ምኞታችን ነው !

<... ሎስ አንጀለስ ሊትል ኢትዮጵያ ተብሎ በስሙ በውጭ አገር መንገድ የተሰየመለት ብቸኛ ቦታ ነው። በዚህ ተሰባስበን ኢትዮጵያውያን የአዲስ ዓመት በዓልን እናከብራለን።ይሄ በሎስ አንጀለስ ብቻ ሳይሆን በርካታ ኢትዮጵያውያን ባሉባቸው ቦታዎች መጠሪያችንን ማኖር ይቻላል...>

በሎስ አንጀለስ ዕንቁጣጣሽን አስመልክቶ የተከበረውን ዓመታዊ ፌስቲቫል አስመልክቶ ሊትል ኢትዮጵያ እንዲሰየም ጥረት ካደረጉት አምስት ሴቶች አንዱዋ ሜሮን አሀዱ ለህብር ከሰጠችው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ

<<...በናዝሬት/አዳማ ሰልፉ ከመደረጉ በፊትና በሰልፉም ወቅት የተለያዩ ተጽኖዎች ነበሩ። እነዛን ተቋቁመን ከ15 ሺህ በላይ የከተማዋ ነዋሪ አደባባይ ወጥቶ ሶስት ኪሎ ሜትር ያህል በከተማዋ መንገዶች ተዘዋውሮ ተቃውሞውን አሰምቷል።...ሕዝቡ የራሱን መፈክር ያሰማና ብሶቱን ይገልጽ ነበር...ይህ እንቅስቃሴ ነጻነት እስኪገኝ ድረስ የሚቀጥል ነው...>>

አቶ ዳንኤል ተፈራ የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሃዝሬት/አዳማውን ሰልፍ አስመልክቶ ለህብር ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ።ለዲያስፖራው የአዲስ ዓመት መልክታቸውም ተካቷል።

ልዩ የበዓል መሰናዶ አካተናል

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

<<...ይሄ መንግስት እኮ በህክምና ቋንቋ ሞቷል። የቀረው ቀብሩ እንዴት ነው የሚፈጸመው የሚለው ነው...>> አባ መላ በቬጋስ የአዲስ ድምጽ አገራዊ ጉባዔ ላይ ተገኝቶ ከሰጠው ማብራሪያ (የተወሰነውን አካተነዋል)

<<...የበዓል አመጋገባችን በተለይ ቅባት የበዛበት ነገር ማብዛቱ ለጤና ጉዳት አለው። በእነዚህ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል...በተለይ ለአዲሱ ዓመት አምስት ምክሮች አሉኝ እነዚህም...>>

ዶ/ር ኤፍሬም መኮንን ከአትላንታ የበዓል አመጋገባችን መሰረት አድርገን አነጋግረናቸው ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

(ሌሎችም ቃለ መጠይቆች አሉን)

ዜናዎቻችን

በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ የበዓል ገበያው ቀዝቅዟል

ዶሮ 180 ብር፣በግ መካከለኛ 1500 ብር፣ በሬ ከ10 ሺህ እስከ 15 ሺህ ብር አንድ ዕንቁላል 2 ብር ከ70ሳንቲም ተሽጧል

አሜሪካ ሶሪያን ማጥቃቱዋ በኢትዮጵያ ንግድ ላይ ተጽዕኖ ይፈጥራል ተባለ

የኢንጂነር ሀይሉ ሻውል <<ሕይወቴና የፖለቲካ እርምጃዬ>> የተሰኘው መጽሐፍ ነገ ለንባብ ይበቃል

የኢራን ዲፕሎማት ኦባማ ሲሪያን ካጠቁ አንዱዋን ልጃቸው ትታፈናለች ሲሉ አስጠነቀቁ

የኢትዮጵአው ዋልያ በሰሞኑ ድል የብራዚል ጉዞውን እያመቻቸ ነው

ሌሎችም ዜናዎች አሉን

ሸንጎ በአዲስ አበባ የተጠራውን ሰላማዊ ሠልፍ እንደሚደግፍ አስታወቀ

$
0
0

የሸንጎ መግለጫ፦

ሸንጎ በአዲስ አበባ የተጠራውን ሰላማዊ ሠልፍ ይደግፋል
ጳጉሜ ፪፣ ፪፼፭
September 7, 2013

shengoህገመንግስታዊና ተፈጥሮአዊ መብታቸውን ተጠቅመው ሰላማዊ የፖለቲካ ተሳትፎ ለማድረግ የሚጥሩ የፖለቲካ ድርጅቶችን ህወሓት/ኢህአዴግ ቀንተቀን እያጠበበው ከመጣው የፖለቲካ ምህዳር ሊያስወጣቸው የሚያደርገውን ጥረት ሸንጎ እያወገዘ፣ የተቃዋሚ ድርጅቶች የሚደርስባቸውን አስከፊ እንግልትና በደል ተቋቁመው ህዝባዊ እንቅስቃሴውን ማስቀጠላቸውን ያደንቃል።
ያለውን አምባገነን አገዛዝ ታግሎ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመፍጠር የታጋይ ድርጅቶችን አንድ ላይ መቆም ግድ የሚል በመሆኑ በነጠላ የሚደረጉ ትግሎችን በማስተባበር ትግሉን ውጤታማ ማድረግ ወደሚቻልበት ደረጃ ማድረስ አስፈላጊ ነው። አንድነት መስከረም አምስት በአዲስ አበባ የጠራውን ሰላማዊ ሠልፍ 33ቱ ፓርቲዎች በጋራ ለማዘጋጀት መወሰናቸው እሰየው የሚያሰኝና ትግሉ ጥሩ አቅጣጫ ይዞ መጓዝ እንደጀመረ የሚያመላክት ነው። ይህም ትብብር ከፍወዳለ ደረጃ እንደሚደርስ ትስፋችን ነው።
የፖለቲካ ድርጅቶች እንዲህ ተባብረው በሚቆሙበት ወቅት ህዝቡም በነቂስ በመውጣት የተባበረ ጠንካራ ጉልበት እንዲፈጥር ሸንጎው ያሳስባል።
በተባበረ ትግል ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እንገነባለን!

አዲስ ዓመት –በነተበ ሥርዓት

$
0
0

(ሩት ዳግም)

COEEFMesganaDancersCA4

Enqutatash -Happy New Year

      ጊዚያቶች  ክንፍ  አውጥተው የሚበሩ ይመስላሉ። 2005 አምና ለመሆን በቅቷል። የተፈጥሮን ህግጋት ጠብቆ በዳመና የጠቆረው ዳመና  እየገለጠ፣   አበቦች እየፈኩ መድሪቷ የመስከረም ወር መጥባቱን ብታበስርም፤ በክፉ የወያኔ አገዛዝ ቀንበር ስር ለሚማቅቀው የአገሪትዋ ህዝብ ዛሬም እንጉርጉሮው የሀዘን ነው። የኑሮ ውድነቱ፣ የሰብአዊ መብት ጥስቱ፣ ፍትህ ማጣት እና በመሳሰሉ ስር በሰደዱ ችግሮች እግር ተወርች ተቀፍድዶ ነገን በተስፋ ተሞልቶ አዲስ ዓመት ይጠብቃል ማለት ዘበት ነው። ይልቁንም አዲስ ዓመት ይዞት በሚመጣው የኑሮ ጣጣ የሚቆዝመው ህዝብ ቁጥር እልፍ ነው።

     ‹‹ትራንስፎርሜሽን›› የሚባል የወያኔ ዕድሜ ማራዘሚያ የተዘጋጀው እቅድ እንደተወራለት በአምስት ዓመት ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ  ህዝብን የሚያሰልፍ አለመሆኑን ሁሉም ተገንዝቦታል። ይልቁንም የህውሃት ግዙፉ ድርጅት ኤፈርት በያዛቸው ትላልቅ ፕሮጀክቶች አመቻቺነት ጥቂት የወያኔ ባለስልጣናትን በሙስና ፈጣን ባቡር ወደ ሚልኒየር፣ ቢልየነር ተርታ  መላውን ህዝብ ደግሞ በድህነት ቀፍድዶ ወደአዘቅት የሚያደርስ ሆኗል። በዚህ አሳዛኝ ህይወት ላይ  ለሚገኝ ህዝብ አዲስ ዓመትን በአዲስ ተስፋ መጠበቅ የቀን ቅዠት ነው። ወትሮስ በዘረኝነት፣ በሙስና በሀገር ክህደት ብል እንደበላው ነጠላ የነተበ መንግስት የአገርን ገበና በምን አቅሙ ይሸፍናል??

     በአይነ ህሊና የዘመን አሮጌ ልብስ የደረበውን የዘንድሮ ዓመት መለስ ብላችሁ ብትቃኙት ቅንጣት ያህል አስደሳች ነገር ለማግኘት ይከብዳል። በ2005 ዓ.ም. በወያኔ መንግስት የስልጣን ሽኩቻና ሹም- ሽር ያየለበት፤ እስርና ግድያ በአደባባይ የተፈጸመበት፣ ፍትህ ማጣት ያየለበት፤ በኑሮ ወድነት፣ በመብራት መጥፋትና መምጣት፣ በውሃ መቋረጥ፣ በታክሲ፣ ዘይት፣ የስኳርና የስንዴ በመሳሰሉ ሰልፎች መሽቶ እስኪነጋ ህዝብ የሚደክምበት ተስፋ አስቆራጭ የቀን ጨላማ ነበር። በመንግስት ሚድያ ደግሞ “የታላቁ መሪ” አቶ መለስ ውዳሴ “ውርሳቸውን/ሌጋሲያቸውን” እናስቀጥላለን በሚል የማያባራ የቆሸሸ ፖለቲካ ህዝብን ማሰላቸት ሥራዬ ብለው ከርመውበታል። ይሁንና ይህ ወቅት አልፎ የመለስ እኩይ ተግባር፣ ክህደትና ተዘርዝሮ የማያልቅ ክፉ ተግባር ትውልድ ሁሉ በሚማርበት መልኩ በዚያው በሀገራችን፤ በዚያው ሚድያ የሚነገርበት ዕለት ይመጣል።

አሁን ባለው የጨለመ ድባብ አዲስ አመት ሲመጣ ህዝቡ እንደ ወግ ልማዱ

“ከብረው ይቆዩ ከብረው

በዓመት ወንድ ልጅ ወልደው

ሠላሳ ጥጆች አስረው

ከብረው ይቆዩ ከብረው” የሚል የልጆቹን ዜማ ተቀብሎ እያዜመ ነገን በተስፋ ያልማል ማለት የአብዛኛውን ህዝብ ኑሮና የተጫናበትን መከራ ያለማወቅ ነው።

 

ይሁንና ይቺን መከራኛ አገር ላይ ተፈናጠው እንዳሻቸው ደንገላሳ ለሚጋልቡዋት የህውሀት ባለስልጣናትና ጋሻ ጃግሬዎቻቸው  ግን ሁሌም አዲስ ዓመት፤ ሁሌም በዓል ነው ያቺ ቀን እስክትመጣ . . . በሙስና በዘር ፖለቲካ ውርስ በተባለ አስማታዊ ብልሃት ከባዶ ኪስ ተነስተው በአንድ ሌሊት ከሚልኒየር ተርታ የሚሰለፉ የዘመናችንን ጉዶች ማየት የተለመደ ሆኗል።

ግና በመዲናችን በየመንገዱ ዳር ተገጥግጠው ከሚታዩት በመስተዋት ካሸበረቁት ህንጻዎች ጀርባና በየመንገዱ ዳርና በየጎዳናው ድህነት ጠልፎ እንደ ጉድፍ የጣለውን በርካታ ህዝብ ማየት ያማል። እናም የሀገሪቱን የሁለት ዲጂት ዕድገት ቱልቱላና የሆነውን በማመዛዘን የአዲስ ዓመት ፌሽታ ባይገባው ይደንቃል? እፍረት አልባው መንግስት ሀገራችን ኢትዮጵያ በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በዓለም ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ካሉ ሀገራት ተርታ ተመድባለች እያለ እውን ያልሆነውን ህልም ሊያሳይ ቢሞክርም ዩናትድ ኔሽን ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት በ Multidimensional Poverty Index መሰረት ኢትዮጵያ ከመንግስት አልባዋ ሱማሌ ጭምር ተበልጣ ከመጨረሻው የድሀ አገር ተሰልፋለች። የበለጠችው አገር ኒጀርን ብቻ መሆኑ ነው። “ጉድ ሳይሰሙ መስከረም አይጠባም !” እንዲሉ።

በሥራ አጥነት፣ በየተልካሻ ምክንያት ከሥራ በተባረሩ፣ በዘራቸው ሳቢያ በተሰደዱ፣ በሃይማኖታቸውና በፖለቲካ አመላካከታቸው ሳቢያ ለእንግልትና ስቃይ በተዳረጉ በርካታ ቤተሰቦች ባሉበት አገር ደስታን ለማጣጣም እንዴት ህሊና ይቀበላል? ለእውነትና ለህሊናቸው ብቻ ስለቆሙ በአሰቃቂ እስር ቤት ታጉረው ከሚወዱት ቤተሰብ በግፍ የተነጠሉ ወገኖቻችንን አስበልተን ምን አይነት የበዓል ድግስ ይኖረናል??

ሀገራችን ኑሮ፣ የመልካም አስተዳደር ችግር፣ የፍትህ ማጣት እንደ ጎርፍ ጠራርጎ ጎዳና ላይ ካወጣቸው እጅግ በላቀ ሁኔታ ለልመና መውጣት አፍረው በየቤታቸው በችግር አለንጋ የሚገረፉት እጅግ እጅግ በርካታ ናቸው፤ ዛሬ ልጆቻውን በቀን አንዴ እንኩዋን ለመመገብ የማይችሉ ቤተሰቦች የተበራከቱበት ሃገር ሆናለች። ታዲያ ዓለምን ያነጋገረው በስደት በየበረሃውና በአረብ ሀገራት  የሚያልቀው ወጣት የሁለት ዲጅት ዕድገት ውጤት ይሆን?

በየቤታቸው በችግር የሚጠበሱትን ወገኖች ካነሳሁ ከጥቂት ወራት በፊት ያጋጠመኝን ልጥቀስ አዲስ አበባ ኡራየል አካባቢ አንዲት አነስተኛ ሱቅ የምፈልገውን ዕቃ በመሸማመት ላይ ነበርኩ፤ እናም ከሁዋላዬ አንዲት በእድሜና በኑሮ ጉስቁልና ወገባቸው የጎበጠ ጠይም እናት ብዙ ደቂቃ መቆማቸው ስለሰቀቀኝ “እናቴ እርሶ ግዙና እኔ እቀጥላለሁ” አልኩዋቸው። ሽቁጥቁጥ በሆነ ትህትና መርቀውኝ ባለሱቁን “ቡና ይኖርሃል?” አሉት

“ቡና አለ! ኪሎ ባለመቶ ሃምሳ፣ ባለምቶ ሃያ ወይም ባለመቶውም ጥሩ ነው . . .” በእጁ እየዘጋገነ ሊያሳየቸው ሞከረ

ዓይናቸው ዓይኖቻችንን የሚሸሹ መሰለኝ፣ ጥቂት አሰቡና “ የአስር ብር አድርግልኝ”

“እማማ አያዋጣኝም…’’

“እንግዲያውስ የሩብ ሩብ ስጠኝ’’ ሀዘን፣ ሸንፈት የኑሮ ድካም በደማቁ ጠይም ፊታቸው ላይ ይነበባል።

“በዚህስ ዘይት ትሸጥልኝ?’’ በፌስታል የያዙትን ትንሽ የዘይት ጠርሙስ አውጥተው እያሳዩት

“እኔ ጋር በችርቻሮ የለኝም። እታች ካለው ሱቅ ይሞክሩ” አላቸው

ተስፋ በቆረጠ መንፈስ “ዘይቱ ቢቀርም ግድ የለም። ብቻ ይቺ ቡና ሱስ  ነው ያስቸገረች . . .’’ አሉና ወገባቸው ላይ ክታሰረችውን መቀነት ፈትተው ብሩን ቆጥረው ከፍለው ሄዱ።

በዓይኔ ተከተልኳቸው ይህ የበርካታ የሀገራችን እናቶች ኑሮ መሆኑን ባውቅም፤ ያለፉትን የኑሮ ውጣውረድ ወለል አድርጎ የሚያሳይ ገጽታቸው፤ ሽቁጥቁጥነታቸው ለልመና እጃቸውን ለመዘርጋት ያልተረታ መንፈሳቸው፤ ነገር ግን ድህነት አንገዝግዞ ሊጥላቸው ያቃረበው የተጎዳ አካላቸው ከፊቴ ላይ እየተጋረጠ ፋታ ነሳኝ .  . . ለምን አንድ ኪሎ ቡና እንኩዋን ሳልገዛላቸው. . . ቁጭት ያዘኝ፤  ደጋግሜ ራሴን ወቀስኩ፤ አሮጊትዋ  ግን ከዓይኔ ርቀዋል።  ባለሱቁን መኖሪያ ቤታቸውን ጠየኩት። አልፎ አልፎ ወደ ሱቁ እንደሚመጡ ቤታቸውን ግን እንደማያውቀው ነገረኝ። በሌሎቹ ቀናት ደጋግሜ ባለሱቁን ብጠይቀውም አይቶአቸው እንደማያውቅ ነገረኝ። ለባለሱቁ ይህ ደጋግሞ የሚያየው የህይወት ትዕይንት ስለሆን ቁብ አልሰጠውም።

እንግዲህ “ሁለት ዲጂት…” ይህን መሰል የበርካቶችን ህይወት ያለመዳሰሱ ቀልድ ህሊናን ይኮሰኩሳል? በየመንገዱ በጠኔ በህመም ወድቆ በአደባባይ ያለምንም ረጂ ሊሞት የሚያጣጥር ወገን እንደ ዋዛ ማየት በተለመደበት አገር፤ ከየመንገዱ የበቀሉ ደሃውን በግፍ አፈናቅለው በበቀሉ ህንጻዎች መመዘኛ ዕድገትን መለካት ፌዝ ነው። የለየለት ቧልት ነው። በየመንግስት ትምህርት ቤቱ ደጃፍ ብትቆሙ ርሃብ ጉስቁልና እንደለበሱት ልብስ አመድ ያስመሰላቸው ልጆችን በመቶ ሳይሆን በሺዎች የሚቆጠር ታያላችሁ። ከዚህ ሁሉ የኑሮ ቀዳዳ ጥቂቱን አለመድፈን ደግሞ ሌላ ስቃይ ነው። በአንዲት ትንሽ ብልቃጥ ለምትለካ መጠጥ ብቻ 2 እና 3 ሺህ ብር በመክፈል በየዕለቱ ሸራተን በመሳሰሉ ትላልቅ ሆቴሎች በዘረፉት ገንዘብ የሚምነሸነሹ የሞሉበት አገር መሆኑ ደግሞ የአገሪቷ ሥርአት ለመኮላሸቱ ሌላው ማሳያ ነው። በየኮንፌሽየስ  እንደተገለጸው በመጥፎ አስተዳደር ስር በሚገኝ አገር የጥቂቶች ብልጽግና የሚያሳፍር ነው። ሰሞኑን የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ኑሮ ጠንቆች ሲል ባስጠናውና ይፋ ባደርገው መረጃ መሰረት ከሚልዮን የሚልቁ በልመና የሚተዳደሩ አሉ። እውነታው ከዚህም ይከፋል።

ይባስ ብሎ የመጨረሻ በሌለው ድህነት ተውጠን  አንድ  ቁጥር ዘረኛና አምባገነን ስርአት የተጫነብን ምን ፍርጃ ነው ያሰኛል። ኢትዮጵያን በዘር ፣ በቋንቋ እና በሃይማኖት ከፋፍሎ የህዝቡን አንድነት ለማጥፋት የሚጥረውን አገዛዝ መቃወም ደግሞ “አሸባሪ’’ የሚል ታርጋ አስለጥፎ ዘብጥያ ያስወረውራል። በወያኔ እኩየ ስራዓት የህግ የበላይነት የለም፤ ዲሞክራሲ ተደፍጥጡዋል፤ የደህንነት ዋስትና የለም፤ ነፃ ፕሬስ ተረት ሆኗል፣ የብዙሃን ፓርቲ ያልምንም እፍረት ተገፍትሮል። የሲቪክና ሙያ ማህበራት የማሽመድመዱ ተግባር ተከናውኗል።

ይለቁንም ዘረኞች ግፈኞች፣ ወንጀልኞች፣ አምባገነኖች፣ ሙሰኞች እንዳሻቸው ዛሬም እየፈነጩ፤  በተቃራኒው ፍትህና እኩልነት ለህሊናቸው፣ የሚታገሉና የሚዋረዱበት፣ የሚሰደዱበት የሚታስሩበት አገር መሆኑ ያስቆጫል።

በርግጥ የታፈኑ ብሶት ገንፍሎ የነጻነት ደማቅ ፀሐይ የምናይበት ጊዜ እንደሚመጣ ቅንጣት አልጠራጠርም። ያኔ በርግጥም ክረምቱ ያልፋል፣ ምድሪቱም በነጻነት ጸበል ይለመልማል፤ ሰማያችን ከክፉ የዘረኝነት ዳመና ይጠራል። ከተራራ ተራራ “አበባ አየሆሽ” ዜማ ይናኛል።

“የእማምዬን ቤት

ወርቅ ይዝነብበት

የአባብዬን ቤት

ወርቅ ይዝነብበት” በርግጥም ትርጉም ይኖረዋል። መልካም ዘመን ያምጣልን። አሜን!!

የሐምሌ ጨረቃ! (ክፍል አንድ) –ከአንዱዓለም አራጌ ዋለ (አንድነት ም/ሊቀመንበር ከቃሊቲ ማጎሪያ)

$
0
0

የሐምሌ ጨረቃ!

ከአንዱዓለም አራጌ ዋለ (አንድነት ም/ሊቀመንበር ከቃሊቲ ማጎሪያ)

ክፍል አንድ

(ሊያነቡት የሚገባ)

andu_udj

ከጉልበተኞች ጠመንጃ የሚወጣ ጥይት ስጋን እንጂ እምነትን ሊገድል እንደማይችለው ሁሉ፣ ከቤተሰብና ወዳጅ ዘመድ ተነጥሎ ቅዝቃዜ በዋጠው ጠባብ ክፍል ውስጥ መታሰርም አካልን እንጂ ምናብን (ህልምን) ሊያስር የሚችልበት ጉልበት የለውም፡፡ ከቶስ እንደምናብ ሜዳውን፣ ተራራውን፣ ቁልቁለቱን፣ ዳገቱን፣ ሸለቆውን፣ ኮረብታውን በሰከንድ ክፍልፋዮች ከብርሃን ፈጥኖ በመምዘግዘግ ያለመዛነፍ ያሰበበት የሚደርስ ምን ኃይል አለ? ከጠባቧ ክፍል ውስጥ ‹‹ድርሻህ›› ተብላ በተሰጠችኝ 90 ሴንቲ ሜትር ላይ ቀሪ ህይወቴን አሳልፍ ዘንድ በግፍ ፍርድ ብታሰርም ዕረፍት ለማያውቀው ምናቤ ገለታ ይድረሰውና ይዞኝ ይከንፋል፤ ወደ ምፈልገው አድርሶ ይመልሰኛል፡፡

አንዳንዴ ከጁፒተር ማዶ ያሉ ተንሳፋፊ ዓለማቶችን ቢያስቃኘኝም፣ አብዛኛውን ጊዜ ግን በሀገሬ ሰማይ ስር በጥቅጥቅ ደመና ላይ አንሳፎ ታላላቅ ወንዞቿን፣ ሃይቆቿን፣ የተንጣለሉ መስኮቿንና ሰማይ ጥግ የሚደርሱ ተራሮቿን በመንፈስ ያስጐበኘኛል፡፡ በተራሮቿ ግርጌና በመስኮቿ እምብርት ላይ ችምችም ብለው የተሰሩ ጐጆ ቤቶችንና በውስጣቸው ለሺ ዓመታት በፍቅር የኖሩ ደሃ ኢትዮጵያውያንን እንደጓደኞቻቸው ከሚመለከቷቸው የቤት እንስሳቶቻቸው ጋ ይታዩኛል፡፡ በየከተሞቹ ከድህነትና ከአፈና ጋር ግብግብ የገጠሙ፣ ከድህነትና ከፖለቲካ አፈና ነፃ ለማውጣት በዓለም ዙሪያ የተበተኑ ወገኖቼን ሳይቀር በአይነ- ህሊና ያስጎበኘኛል፡፡ አንዳንዴ ውሸትን እንደብልህነት፣ አፈናን እንደ አገዛዝ ስልት የወሰዱ አሳሪ ወንድሞቼና እህቶቼ የህሊና ጓዳ ውስጥ ይዞኝ ዘው ይልና ያረበበውን እብሪት፣ ፍርሃት፣ ጭንቀት፣ እርስ በእርስ የሚላተሙ ሃሳቦቻቸውን ፍልሚያ… ያሳየኛል፡፡

እነዚህ ምን አይነት ኢትዮጵያውያን? ምን አይነትስ ወላጆች ናቸው? ብዬ ራሴን እጠይቃለሁ፡፡ የምናብ ፈረስ ጋልቤ የምጐበኘው የዚህን ዘመን ክንዋኔ ብቻ ሳይሆን የተደራረበውን የዘመን ጉም እየጠራረጉ ያለፉ አያሌ ዘመናትን ወደ ኋላ አስጉዞ ያሳየኛል፡፡ የኢትዮጵያን የከፍታ ዘመናት፡- አክሱምን፣ ላሊበላን፣ ጐንደርን፣ ያልዘመርንለትን የገዳ ዴሞክራሲ ስርዓትንና ሌሎች የጥንት ስልጣኔዎችን በብላሽ ያስኮመኩመኛል፡፡ የኢትዮጵያን የዳር ድንበር ነፃነት ለማስከበር አባቶቻችን ያደረጓቸውን የጀግንነት ውሎዎች በተለይም የጀግንነታችን ማማና የጥቁር ህዝብ ሁሉ ኩራት የሆነውን የአድዋን ጦርነት ደጋግሜ አየዋለሁ፡፡ አድዋና መሰል የጀግንነት ማማዎች ላይ ቆሜ ኢትዮጵያውያን በየቀያቸውና በየዘመኑ ሰብዓዊ ክብራቸው ተረግጦ፣ በጭቆና አዘቅት ውስጥ ወድቀው ሲዘቅጡ ይታዩኛል፡፡ አንዳንዴ ኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ ልዕልናቸውንና ነፃነታቸውን ለመጐናፀፍ ያደረጉትን ትግል ያሳየኝና መንፈሴን ያበረታዋል፡፡

ታሪክ እንደሚዘክረው ከኋላ ቀሩ የፊውዳል አገዛዝ ነፃ ለመውጣት (በትክክል ወዴት ያመራ እንደነበር መናገር ባይቻልም) የመጀመሪያ አብሪ ጥይት የተተኮሰችው የ1953ቱ የእነ ጄኔራል መንግስቱና ገርማሜ ንዋይን የመፈንቅለ-መንግስት ሙከራ በተደረገበት ዕለት ነው፤ አቤት! እርሱን ተከትሎ የተሻለ ንቃት ያለው ኢትዮጵያዊ በሙሉ ‹‹ሕዝባዊ መንግስት›› ለመመስረት ያሳየው እንቅስቃሴ! የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለዓመታት የሞቱለት፣ የተጋዙለት፣ የተደበደቡለት፣ የተሰደዱለት… ሰላማዊ ትግል እና ያነሷቸው ጥያቄዎች ጆሮዬ ላይ ደጋግመው አስተጋብተዋል፡፡ በወቅቱ የዘውዳዊ ስርዓት ገበሬዎች፣ ተማሪዎች፣ ሰራተኞችና ልዩ ልዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተቃውሞአቸውን በሰላማዊ መንገድ አሰምተው፣ በሰላም ወደ ቤታቸው እንዲገቡ የነበረውን ትዕግስት አሁን ካለው ሁኔታ ጋር ባነፃፀርኩት ቁጥር እንደ አዲስ እደመምበታለሁ፡፡ ንጉሳዊውን ስርዓት በመቃወም ተደጋጋሚ ሰልፎች ላይ ይሳተፉ የነበሩት እና ዛሬ ለድል የበቁት የቀድሞዎቹ ተማሪዎች፣ የአሁኖቹ ገዥዎች የትምህርት ነፃነትን ከመርገጣቸውም በላይ ቅሬታ በተነሳ ቁጥር የተማሪዎች መኝታ ቤት ድረስ በመዝለቅ ደም ማፍሰሳቸውን ሳስብ፤ ለተቃውሞ አደባባይ የሚወጡ ንፁሃን ላይ ከውሃ ይልቅ ጥይት ማዝነብ የሚቀናቸውና ተቃዋሚዎቻቸውን በውሸት ድሪቶ ዘብጥያ የሚያወርዱ አምባገነኖች መሆናቸውን ሳስብ የማይፈታ እንቆቅልሽ ይሆንብኛል፡፡

ዘውዳዊ ስርዓቱን የተቃወሙ ሰዎች ከነገስታቱ በላይ ከዘመን ጋር የማይዘምኑ፣ ከአፈሙዝ ጋር የተጋቡ እንዴት ሊሆኑ ቻሉ? የሚል ጥያቄ አነሳለሁ፡፡ የምናብ ፈረሴ ኢትዮጵያውያን ወደዚህ ዓለም በመጣሁበት ሰሞን ከነበረው የጭቆና አገዛዝ ነፃ ለመውጣት አልመው ወደ ከፋ የአምባገነንነት ገደል የወደቁበትን የእልቂትና የዋይታ አብዮት እየደጋገመ ያስቃኘኛል፡፡ በተፋላሚዎች መካከል የርዕዮተ-ዓለም ልዩነት ባይኖርም አፈ-ሙዝን በአፈ-ሙዝ ለማሸነፍ የተደረገው ደም መፋሰስና ወንድም በወንድሙ አስከሬን ላይ ቆሞ የፎከረበት የእርስ በርስ ጦርነትም ሌላኛው እረፍት የሚነሳው ጉዳይ ነው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ የግፍ ቋት የነበረውን ደርግ በኢትዮጵያ ሕዝብ ድጋፍ አሸንፎ በድል አድራጊነት ወደ ምኒሊክ ቤተ-መንግስት ሲገባ ሌላ የግፍ ቋት ይሆናል ብለው ያልጠበቁ አያሌዎች ነበሩ፡፡ ረጅሙ የመከራ ሌሊት መልሶ ላይጨልም ነግቷል ብለው ለተሻለ ነገር የተዘጋጁ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ትንሽ የሚባል አልነበረም፡፡ በአሁኑ አገዛዝ ከቀደሙት ህገ-መንግስታት የተሻለ ህገ-መንግስት ቢፀድቅም ቃልና ተግባር ሳይገናኙ ይኸው 22 ዓመታት አልፈዋል፡፡

እነሆም የሌላ ዙር የአፈና ሰለባ ሆኜ ወደምማቅቅበት እስር ቤት የምናቤ ፈረስ መልሶ አደረሰኝ፡፡ ሌላ ዙር እስር፣ ሌላ ዙር አፈና፣ ሌላ ዙር የህፃናት ለቅሶ፣ ሌላ ዙር የወላጆች ሰቆቃ፣ ሌላ ዙር ውርደት፣ ሌላ ዙር የአጤዎች ቀረርቶ፣ ሌላ ዙር የህዝብ እንባ፣ ሌላ ዙር… ባለንበት መርገጥ ቀጥለናል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ የከበረና ከፍ ያለ መስዋዕትነት በመክፈል የዳር ድንበር ነፃነቱን ማስከበር ቢችልም በአገሩ ሰብዓዊ ክብሩንና ነፃነቱን ከራሱ ገዢዎች አስከብሮ መኖር የቻለበት ዘመን የለም፡፡ አንዴ ሞቅ ሌላ ጊዜ ቀዝቀዝ እያለ የቀጠለው የኢትዮጵያ ህዝብ የነፃነት ትግል በድቅድቁና ዝናባማው የሐምሌ ጨለማ የምትወጣውን ‹‹ጨረቃ›› ይመስላል፡፡ በተለይ የኤሌክትሪክ ብርሃን በሌለበት የገጠሩ የሀገራችን ክፍል የልጅነቱን የመጀመሪያ ዓመታት እንደእኔ ላሳለፈና የኢትዮጵያን የፖለቲካ ትግል በአንክሮ ለተከታተለ ሁሉ ስርዓቱና ጨረቃዋ የአንድ አባት ልጆች ይሆኑበታል፡፡ የሐምሌ ወር ጨለማ ጥቁር ነው፡፡ እንደግድግዳ ፊት ለፊት ቆሞ ነፍስን ያስጨንቃል፡፡ ጫፉ የማይታይ የጥላሸት ቁልል ይመስላል፡፡ ከጨለማው መደቅደቅ የተነሳ በቅርብ እርቀት ያለ ቁስን እንኳን ለመለየት የሚያስችል ብርሃን የለም፡፡ ወደሰማይ ለሚያንጋጥጥም በጥቁር የደመና ከል የተጋረደ ነው፡፡ በዚህ መሃል ግን ህልቆ መሳፍርት ለሌላቸው ዘመናት የሐምሌ ወርን እየጠበቀች እየደጋገመች የምትወጣው ጨረቃም ወቅቷን ጠብቃ መውጣቷን አላቋረጠችም፡፡ ከአንድ ጥቁር የደመና ኮረብታ ወደሌላው ስትወረወር ለቅፅበት ትንሽ ብርሃን ብትፈነጥቅም ምድሩን እንደቡልኮ የሸፈነውን ድቅድቁን ጨለማ ሰንጥቆ ለማለፍ የሚችል የብርሃን ፍንጣቂ በመልቀቅ የጨለማውን ሀይል መግፈፍ የሚችል አቅም የላትም፡፡ እንዲያውም በብርሃን ጅረት የተሞላው መላ አካሏ በጨለማው ፅልመት ጠልሽቶና ከጨለማው ጋር ተመሳስሎ ይታያል፡፡ የሐምሌ ጨረቃ ወይ ድቅድቁን አትገፋ፣ ወይም የሐምሌን ወር አትዘል በየዘመኑ፣ በየአመቱ ፍሬ አልባ ዑደቷን ቀጥላለች፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግልም እንዲሁ፡፡ እንደ ሐምሌ ጨረቃ ሁሉ የኢትዮጵያ ሕዝብም የሀገሩን የህላዌ እድሜ ያህል ከጭቆናው ሌሊት ጋር በየወቅቱ ግብግብ ይገጥማል፡፡ በተለይም ከ1953 ዓ.ም ወዲህ ያሉት 50 ዓመታት ህዝባችን ከአብራኩ ከወጡ አምባገነን ገዥዎች መዳፍ ነፃ ለመውጣት ተደጋጋሚ ትግል አድርጓል፡ ፡ አሁንም እያደረገ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የሰብዓዊ ልዕልናው ባለቤት ለመሆን የሚያስችለውን የተጠና፣ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት የሚመራና ህዝብ የራሱ ያደረገው የፀና ሰላማዊ ትግል በማድረግ ለውጤት አልበቃም፡፡

ለምን? በረጅሙ የሀገራችን ታሪክ የሀገርን ዳር ድንበር ማስከበርን የመሳሰሉ ገንቢ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ፍልስፍናዎች ማዳበር የመቻላችንን ያህል፤ በሌላ መልኩም አሉታዊ የሆኑ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ፍልስፍናዎች እንዳዳበርን መረዳት ይቻላል፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ፖለቲካዊ መስተጋብራችን የተፋለሰ እንዲሆን አስተዋፆ አድርገዋል፡፡ በተለይም ከዘመነ-መሳፍንት በኋላ ያለውና በዚያ ዘመን የፖለቲካ ብሒል የተቃኘው ፖለቲካዊ ፍልስፍናችን ከምህዋሩ የወጣ ነው፡፡ በአመዛኙ በፍርሃት፣ በአድርባይነትና በጊዜያዊ ጥቅም የተለወሰ ፍርሃት፣ የማያምኑበትን መናገር፣ በአርምሞ ማሳለፍ፣ ያልሆነውን ሁነን መታየት፣ ነገሮችን በሚስጥር መያዝ፣ ተጠራጣሪነትና በውል ባልታሸ ሁኔታ እራስን ማዕከል ያደረገ አስተሳሰብ ማራመድ የመሳሰሉትን ለአብነት ያህል ማንሳት ይቻላል፡፡ በየዘመኑ የሚነሱ አምባገነኖችና የጎበዝ አለቆች ጥላ ስር ለመጠለል መሞከር እነርሱን አይነኬ አድርጐ መቁጠር እራስን ፍፁም አቅመ-ቢስ አድርጐ መረዳት ለገዥዎች ማሸርገድና ቅዳሴ-ማህሌት መቆም አያሌ ኢትዮጵያውያን በየዘመኑ እንደ ፖለቲካ-ጥበብ የሚቆጥሩት አካሄድ ነው፡፡ ይህም ሁሉ በጥልቅ አስተሳሰብና ከዚያም በሚመነጭ እምነት ላይ ቢመሰረት ችግር አልነበረውም፡፡ የተሳሳተ እምነት በማንገብ የጨለማ አገዛዞችን የነፃነት ንጋት ናቸው ብለው የሚዘምሩ፤ በረሃብ ስንሞት በቁንጣን ነው ብለው ሊያሳምኑን የሚዳዳቸው፤ የአገዛዞች ዋልታና ማገር የሆኑ ኢትዮጵያውያንን በየዘመኑ አይተናል፡፡ እያየንም ነው፡፡

ከዘመናት የአፈና አገዛዝ ነፃ ልንወጣ ይገባናል ብለን የምንታገል ወገኖች እንደመኖራችን ሁሉ፤ አገዛዙ የፀሐይ መውጫ ምኩራብ ነው ብለው የሚያምኑ ወገኖች እምነታቸውን ያራምዱ ዘንድ መብታቸው ነው፡፡ ከስሜታዊነት በፀዳ መልኩ ጨለማው በእርግጥም ጨለማ መሆኑን አይኖቻቸውን ገልጠው እንዲያዩና እንዲመለሱ ማድረግ ይገባል፡፡ ሞታችን ከጨለማው ጋር ነው ብለው በጨለማው አካልነታቸው መቀጠል የሚፈልጉ ከሆነ ደግሞ ታግሎ ማሸነፍና እነርሱም ከጨለማ ነፃ እንዲወጡ ማድረግ ነው፡፡ ከባዱ የቤት ስራና እስከአሁንም ነፃነት ከእኛ እንዲርቅ ትልቁን አስተዋፆ እያበረከተ ያለው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ‹‹መሃል ሰፋሪው›‹› ኢትዮጵያዊ ይመስለኛል፡፡ እውነቱን ለመናገር በፖለቲካ ትግል ባሳለፍኳቸው ጥቂት ዓመታት ከባዱ ፈተና የገጠመኝ ከቤተሰቤ፣ ከወዳጆቼና ከቅርብ ጓደኞቼ ነው ብል ማጋነን አይሆንም፡፡ እነዚህ ወገኖች ፖለቲካ ውስጥ ገብቼ ከአገዛዙ ጋር ግብግብ ከመግጠም ይልቅ አንገቴን ደፍቼ ልጆቼን እንዳሳድግ ምክራቸውን በተደጋጋሚ ለግሰውኛል፡ ፡ ለነገሩ ትዳር ባልያዝኩበት፣ ልጆች ባልነበሩኝ ወቅትም ‹‹አርፈህ ተቀመጥ!›› የሚለው ምክራቸው አልተለየኝም ነበር፡፡ ትግል ውስጥ እንዳልገባ የሚሰጡኝ ምክንያቶች ሁለት ናቸው፡፡ የሀገራችን ፖለቲካ በደም መፋሰስና በሸፍጥ የተሞላ መሆኑ አንደኛው ሲሆን በተጨማሪም ከኢኮኖሚ አዋጭነት አንፃር ፖለቲካ ፈፅሞ የማይመከር መሆኑን ያስረዱኛል፡፡ በመሆኑም አንገቴን ደፍቼ፣ ገዥዎች ወደአጋዙኝ ተግዤ እንድኖር፤ ልጆቼንም እንዳሳድግ ምክራቸውን ለግሰውኝ ነበር፡፡ አሁን እንኳን በእስር ላይ እያለሁ እንደሳይቤሪያ ብርድ አጥንትን ሰብሮ የሚገባና ነፍስን የሚወጋ ምክራቸውን ይልኩልኛል፡፡ ‹‹ነግረነው አልሰማንም››፣ ‹‹ህፃናት ልጆቹን ያለአባት ትቶ እንዴት ይታሰራል?›› ይላሉ፡፡ አንዳንዶቹ ከመበሳጨታቸው የተነሳ የመጐብኘት መብቴ ቢከበር እንኳን ሊጐበኙኝ እንደማይፈልጉ ይናገራሉ፡፡ ወንጀልሰርቼ እንዳልታሰርኩ፣ ለመስራትም እንደማላስብና ሰላማዊ የትግል ስልትን የሃይማኖት ያህል እንደማምንበት ወዳጆቼም ሆኑ አሳሪዎቼ እኔ የማውቀውን ያህል ያውቃሉ ብል ያጋነንኩ አይመስለኝም፡፡

ያም ሆኖ ግን ወዳጆቼ ስርየት እንደሌለው ሃጢያት፣ የአገዛዙ ዋናዎችም የሰማይስባሪ እንደሚያክል ወንጀል የቆጠሩት የተቃውሞ ፖለቲካ ጐራ መቀላቀሌን፣ በሀገሬ አንገቴን ቀና አድርጌ በመራመዴና የማምንበትን በቀጥታ በመናገሬ ነው፡፡ አገዛዙም ይኽን አይነት በፍርሃት የተሸበበ ማህበረሰብ እንዲፈጠር ይፈልጋል፤ ወዳጆቼም አገዛዙ በግፍ ስላሰረኝ የነቢይነት ደረጃቸውን በመደመምያስባሉ፤ እርስ በእርሳቸው ይመጋገባሉ፡፡ የትችት ጦራቸውን እስር ቤት ድረስ የሚወረውሩት አብዛኞቹ ጓደኞቼ በታላላቅ ዩኒቨርስቲዎች የተማሩና የሚያስተምሩ፣ በመደበኛ ትምህርት ልህቀታቸው በሊቀ- ጠበብትነት ጐራ የሚሰለፉና ይህች ደሀ አገር ከውስን ጥሪቷ ቆንጥራ ያስተማረቻቸው ናቸው፡፡ የሆነ ሆኖ ዛሬ ወዳጆቼ ያሉት ደርሶብኛል፤ ትንቢታቸው ሰምሯል፡፡ አዎ! ልጆቼ በድንገት ከቤት ወጥቶ እስከአሁን ወደቤት ስላልተመለሰው አባታቸው በህፃንነት የአእምሮ ጓዳቸው ውስጥ እያንሰላሰሉና እየተጐዱ መሆኑን በሚገባ እረዳለሁ፡፡ በተለይ ልክ የታሰርኩ እለት የትምህርት ቤትን ደጃፍ የረገጠው የልጄ የሩህ ጥያቄዎች ከዕለት ወደ ዕለት እየበረከቱ መጥተዋል፡፡ ‹‹ማሚ፣ እኔ አባት የለኝም እንዴ?››፣ ‹‹አባባ መቼ ነው ቤት የሚመጣው?››፣ ‹‹የአንተ ስራ መቼ ነው የሚያልቀው?›› የሚሉ ናፍቆት ያንገበገባቸውን ጥያቄዎች ያነሳል፡፡

እኔ የምከፍለው ዋጋ ይቅርና ልጆቼም በውል በማይረዱት ነገር ትልቅ ዋጋ እየከፈሉ መሆኑን በጥሞና እገነዘባለሁ፡፡ ቀድሞውንም ያልጠበኩትም አልነበረም የሆነው፡፡ ግና! በልጆቼ ሰብዕና ላይ የከፋ ስብራት እንዳይደርስ እውነተኛ ፈራጅ ወደሆነው ፈጣሪ ከመፀለይ በቀር ምን ማድረግ ይቻለኛል? ይህችን ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀላቀለው በእስር ቤት ነው፤ ይኸው አሁን ደግሞ ባልጠኑ እግሮቹ፣ ክፉ ደግ ባለየ ህሊናው ከሚያፈቅረው አባቱ ተለይቶ በባዕድ ምድር የፖለቲካ ስደተኛ ሆኖ የሚንከራተተው የናፍቆት እስክንድር ነጋ ህይወት ለዚህ የበቃው አባቱ እንደኔ የወዳጆቹን የአርምሞ ጥያቄ ባለመቀበሉ ጭምር ነው፡፡ አባታቸውን ተመላልሰው መጠየቅ በማይችሉበት እርቀት ላይ የታሰረባቸው የናትናኤል መኮንን ልጆች እንባም ሰብዓዊ ፍጡርን በተለይም የወላጆችን ልብ ምንኛ እንደሚሰብር ግልፅ ነው፡፡ ከሚያስተምርበት አዲሰ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ ከግቢ ውጭ እንደሚፈለግ በስልክ ሲነገረው የጠመኔውን ብናኝ ከእጁ ላይ አራግፎ የወጣው የኦሮሞ ፌዴራሊስ ኮንግረስ /ኦፌኮ/ ም/ሊቀመንበር በቀለ ገርባ ‹‹የኦነግ አባልና የፌደራላዊ አገዛዙን በኃይል ማስገንጠል አሲረሀል›› በሚል ክስ ተፈርዶበት ከህፃናት ልጆቹ ተለይቶ በዝዋይ እስር ቤት የግፉን ፅዋ እየተጎነጨ ነው፡፡ በእርግጥ አቶ በቀለም እንደ እኛ አርፎ ልጆቹን እንዲያሳድግ ተነግሮት ነበር፡፡ ሌሎች አያሌ ኢትዮጵያውያንና ልጆቻቸውም ተመሳሳይ የመከራ ህይወት እየገፋ ይገኛሉ፡፡ ልጆቻችንና የትዳር አጋሮቻችን እየከፈሉ ያሉት ዋጋ እኛ በእስር ቤት ከምንከፍለው የከፋ ይመስለኛል፡፡

ለጓደኞቼና ለወዳጆቼ የማነሳላቸው ጥያቄዎች ይኖሩኛል፡፡ ነፃነት አልቦ ህይወት ምን ምን ይላል? ለመሆኑ ነፃነትን በገዥዎች ችሮታ የተጐናፀፈው የየትኛው ሀገር ህዝብ ነው? በየትኛው ክ/ዘመን ይሆን? …አባቶቻችን ዳር ድንበራቸውን ለማስከበር ልጆቻቸውን፣ ሚስቶቻቸውንና ዘመድ አዝማዶቻቸውን ከኋላቸው ጥለው ወደ አድዋ መዝመታቸው ስህተት ነበር እያላችሁን ይሆን? ቴዎድሮስ በመቅደላ፣ ዮሐንስ በመተማ ለሀገር ክብር መውደቃቸው ትርጉም የለሽ ነበር ማለት ነው? ሌሎች አባቶቻችንስ በጉራ፣ በጉንደት፣ በማይጨው እና በአያሌ የጦር አውድማዎች ለሀገር ክብር እንደወጡ ሲቀሩ የሚናፍቋቸው ሚስቶችና የሚሳሱላቸው ህፃናት ልጆች ያልነበሯቸው ይመስሏችኋል? አሉላ አባ ነጋ እስከ እርጅና ዘመኑ ድረስ ለሀገሩ ዳር ድንበር አጥር ሆኖ ጣሊያንና ግብፅን በማስጨነቅ ዛሬ የምንኮፈስበትን ታሪክ ማጐናፀፉ ስህተት ነበር እያላችሁ ይሆን? የእነ በላይ ዘለቀ፣ የእነ አብዲሳ አጋ፣ የእነዘርአይ ደረሰ፣ የእነ ራስ ደስታ ዳምጠው፣ የእነ አቡነ ጴጥሮስና የሌሎችም ስመ-ጥር ጀግኖቻችን ውሎ በከንቱ ጀብደኝነትና ግብታዊነት የተሞላ ነበር ማለት ነው? እነዚህ ጀግኖች የሀገራቸውን ዳር ድንበር ክብር ለማስጠበቅ ከቀያቸው ርቀው ሲጓዙ ሞትን ከፊት ለፊታቸው እያዩት የቆሙለት እውነት አመዝኖባቸው እንደነበር ዘንግታችሁት ይሆን? አባቶቻችን በየተራራውና ኮረብታው ስለሀገር ክብር ባይቀበሩ ኖሮ የዛሬዋን ኢትዮጵያ ማግኘት የምንችል ይመስላችኋል? ወይስ የዳር ድንበር ነፃነት ከተከበረ፣ ዜጐች በጭቆና ቀንበር ቢማቅቁ ምንም ክፋት የለውም እያላችሁ ነው? ወይስ ጭቆና ከአብራካችን በወጡ ሰዎች እስከሆነ ድረስ እንደክብር ይቆጠራል እያላችሁ ነው? የሀገርን ዳር ድንበር ለማስከበር የተከፈለው ዋጋ ጠጋ ብለን ስናየው የህዝብን መሰረታዊ የሉዓላዊነት ጥያቄ እንደሚያነሳ ሳታችሁት? አባቶቻችን ለሀገር ነፃነት የከፈሉት ዋጋ ተገቢ አልነበረም ካላላችሁ በስተቀር ለዜጐች ሉዓላዊነትና ለዕውነተኛ ዴሞክራሲያዊ መንግስት መታገል ስህተት ሆኖ የሚገኘው በምን ቀመር ነው? በዩኒቨርስቲዎች ስለ- ሰብዓዊ ፍጡር ልዕልና የምትማሯቸውና የምታስተምሯቸው ትምህርቶች ‹ነፃነት›ን በተመለከተ ምን ነበር ያሏችሁ? ወይስ ዲሞክራሲና ነፃነት ለእኛ ሀገር አይሰራም እያላችሁ ነው? የጥቁር ህዝብ ኩራት የሆነውን የአድዋን ድል ያስመዘገቡ አባቶች ልጆች ሉዓላዊነታችን ከገዥዎቻችን መዳፍ ነጥቀን ማስከበር ካልቻልን ‹የእሳት ልጅ አመድ› መሆን አይመስላችሁም? ሌላው ቢቀር ኢትዮጵያ የቅኝ ግዛትን ቀንበር እንዲሰብሩ የረዳቻቸው የአፍሪካ አገሮች በዴሞክራሲ ጐዳና በርቀት ጥለውን ሲተሙ፤ የእኛ በጭቆና አረንቋ ውስጥ መዳከር እንዴት ቁጭት አይፈጥርባችሁም? ወይስ የእናንተ ድርሻ ትችትና ታዛቢነት ብቻ ነው? እነዚህ ከፍ ብዬ ያነሳኋቸው ጥያቄዎች ለምወዳቸው ጓደኞቼ ብቻ ሳይሆን ‹‹የመሃል-ሰፋሪነት›› ሚና ለመረጡ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ሁሉ የተሰነዘሩ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያውያን በፖለቲካ ባህላችን ውስጥ ያሉ ሸንኮፎችን አስቀድመን መግረዝ ካልቻልን፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል እንደ ሐምሌዋ ጨረቃ አሁንም በከንቱ ብቅ ጥልቅ ከማለት የዘለለ ፋይዳ አይኖረውም፡ ፡ ምናልባት የሀሳባችሁ ማጠንጠኛ ባለፈው ግማሽ ምዕተ-ዓመት ማሳካት ያልተቻለው እንዴት አሁን ይቻላል? የሚል ከሆነ ይኸንን ጥያቄ ማንሳት፣ ለጥያቄውም መልስ መስጠትና በመልሱም ላይ ተመስርቶ በእውነተኛ ነፃነትና ህዝባዊ ልዕልና ላይ የተመሰረተች ኢትዮጵያን ለመፍጠር መታገል እንደሚያስፈልግ መተማመን ላይ መድረስ ይጠበቅብናል፡፡ የተወሰኑ ጥያቄዎችን አክዬ ላንሣ፡ ፡ ሁሉም የግል ጥቅሙንና የአብራኩን ክፋዮች ብቻ በሚያስቡባት ሀገር እንዴት ህዝብ ከአገዛዝ ነፃ ሊሆን ይችላል? በየማጀቱ አገዛዙን በመርገም ነፃ መውጣት ቢቻል ኑሮ ከረጅም ዘመናት በፊት ነፃ አንወጣም ነበር ትላላችሁ? አባቶቻችን ለነፃነት መስዋዕት መሆናቸው ትክክል ነበር የምትሉ ከሆነ የስብዕና መሰረትና የነፃነቶች ሁሉ የበላይ ለሆነው የሰብዓዊ መብት መታገል ትክክል የማይሆንበት አሳማኝ ምክንያት ምንድን ነው? ከገዥዎች መዳፍ ለመውጣት አሳማኝ ምክንያት ምን ሊሆን ይችላል? ይኽን ከገዥዎች መዳፍ ለመውጣት የሚደረግን ትግል እንዳላየን አይተን ብናልፍ ለሁላችንም የማይቀረው ሞትን ተጋፍጠን ወደመቃብር ስንወርድ በምን አይነት ክብርና የህሊና እረፍት ማሸለብ እንችል ይሆን? የዘወትር ህልማችን ሰብዓዊ ልዕልናችን ተጠብቆ የምንኖርበትንና ልጆቻችን የማያፍሩበትን ሀገር ማውረስ ሆኖ ሳለ የአገዛዙን የጭቆና አርጩሜ በመፍራት ከእምነታችን ውጭ የሆኑ ተግባሮችን ስንፈፅም የምንበጀው እስከመቼ ነው? ለዘመናት እላያችን ላይ ቤት የሰራብንን የጭቆና ቀንበር መስበር በረጅሙ የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ያልተከወነ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲንከባለል የመጣ የቤት ስራ ነው፡፡ በውዝፍ ያደረ ቁምነገር ከቅርሶቻችን ሁሉ የገዘፈና የታሪካችን ፈርጥና የማንነታችንም መደምደሚያ ነው፡፡ በዚህ የሰብዓዊ ልዕልና ጉዳይ ላይ መታገል ሰው የመሆንና ያለመሆንን ጥያቄ መመለስ ነው፡፡ በነፃነት አለመታገል የቤት ስራውን ለልጆቻችን ወዝፎ ማሳደር በጭቆና ቀንበር ለመገዛት ህዝበ ውሳኔ የመስጠት ያህል ይቆጠራል፡፡ በሌላ በኩል ነፃ ለመውጣት እንደቀድሞ ነፃ አውጭ አበጋዞችን መጠበቅ አይገባንም፡፡ ይኽን የምናደርግ ከሆነ ሰማያችን በጭቆና ደመና እንደተሸፈነ ይቀጥላል፡፡ ጥቂቶችን አንጋጠን ስንጠብቅ በውስጣችን ያለውን ትልቅ የነፃነት ሃይል እንዳናይ ግርዶሽ ይሆንብናል፡፡

ይኽን በመሰለው የነፃነት ትግል የሚጀምረው የራስን የከረመና የተሳሳተ ፖለቲካዊና ማህበራዊ አስተሳሰብ ከመሞገት ነው፡፡ ከዚያም ከፍ ሲል እንደ ፖለቲካ ባህልና የብልህነት ቁንጮ በመውሰድ ለህፃናት ልጆቻችን ሳይቀር በምክር መልክ የምንለግሳቸው ልዩ ልዩ ያልተሰለቀቁ አሉታዊ አስተሳሰቦችን በቅድሚያ ታግሎ መጣል ያስፈልጋል፡፡ እያንዳንዱ ስለሁሉም ፤ሁሉም ስለእያንዳንዱ ግድ በማይሰጠው ሀገር ውስጥ አምባገነኖች የሚዘውሯቸው አገዛዞች መኖራቸው የግድ ነው፡፡ በዚህ ዘመን ስለነፃነት ክብርነት ለማንም ማስረዳት እምብዛም አይጠበቅብንም፡፡ ነፃነት እንደ እንጉዳይ በየዛፉ ስር ያለትልቅ መስዋዕትነት በቅሎ የሚገኝ አይደለም፡፡ ይኸንን የነፃነትን ውድነት ስንረዳ የሀገርን ዳር ድንበር ለማስከበር እንደዘመቱት አባቶቻችን ሁሉ ያለነፃነት ከመኖር ይልቅ ህፃናት ልጆቻችን ጥለን፣ ከሞቀ ቤታችን ወጥተን በእስር ቤት የሲሚንቶ ወለል ላይ መጣልን እንመርጣለን፡፡ በነገራችን ላይ ደጋግሜ ከምጠቅሳቸው ጀግኖች ጋር እራሴን እያወዳደርኩ አለመሆኑን አንባቢዎች ልብ እንድትሉልኝ እወዳለሁ፡፡ በታሪክ ኮረብቶች ላይ ከድንቅ የጀግንነት ውሎዎቻቸው ጋር ከፍ ብለው የሚታዩ ጀግኖች ጫፍ የሚደርስ አንዳች ስራ እንዳልሰራሁ ጥሩ አድርጌ እገነዘባለሁ፡፡ አላማዬ የዳር ድንበርን ሉዓላዊነት ከሰብዓዊ ሉዓላዊነት ጋር ማነፃፀር ነው፡፡

ሌላው የአገር ውስጥ ገዥዎችንን እንዴት ከውጭ ሀገር ወራዎች ጋር ያነፃፅራል? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ ሁለቱም የዘመቱት በነፃነታችንና ሰብዓዊ ክብራችን ላይ ነው፡፡ የነፃነት ትርጉም ከሀገር ልጅነትም በላይ ነው፡፡ በሰላማዊ ትግል መንገድ ስንጓዝ ትግላችን ጨቋኝ ወንድሞቻችን ወደልባቸው እንዲመለሱና ሁላችንም በነፃነት የምንኖርባትን የጋራ ሀገር እውን እንድትሆን ከማድረግ ጋር ነው፡፡ ከዚህ በዘለለ እንዲታመሙና እንዲሞቱ አይደለም ፡፡ በእኛና በልጆቻችን ላይ እያደረሱት ያለው በደል በእነርሱም ላይ እንዲደርስ ፈፅሞ የምንመኘው ነገር አይደለም፡፡ ነ ፃነትን ከውጭ ሀገር ወራሪም ሆነ ከሀገር ውስጥ ጨቋኝ መጠበቅ መቼም በይደር የሚያዝ ተግባር አይደለም፡፡ ስለሁላችን ነፃነትና ሉዓላዊነት የተዘረጋ የተማፅኖ ቃል እንጂ፡፡ በሀሰት ‹‹አሸባሪ›› ተብለን ዘብጥያ ብንወርድም ትግሉን ከመቀጠል ውጭ ሌላ አማራጭ የለም፡፡ ነፃነትን መጠየቅና መታገል ነፃነቱን የተጠማ የነፃነት ታጋይ ሁሉ ድርሻ መሆን ይኖርበታል፤ ይሁንና የናፈቃችኋትን ነፃነት አታገኟትም ብለው ወህኒ መወርወር የአፋኞች የአፈና ተግባር ቢሆንም መንበርከክ ለከፋ መከራ፣ ለበረታ ጭቆና ከማገለጥ ውጪ ትርፍ አልባ ነው፡፡ የአሁኖቹ ገዥዎች እንደ ቀድሞዎቹ ሁሉ የተሳሳተ የፖለቲካ ባህላችን ያበቀላቸው መሆኑን መረዳት ይገባል፡፡ የፖለቲካ ባህላችንና አስተሳሰባችን ካልተቀየረ እንደ እስከ አሁኑ ሁሉ ሌሎች አምባገነኖችንም ማብቀሉን ይቀጥላል፡፡

በአምስት አመት ውስጥ ማዕከላዊ እስር ቤት ሁለት ጊዜ ስታሰር፤ ሃላፊዎች ተለዋውጠው ባገኛቸውም የሁለቱም ዋና ኃላፊዎች ቃልና ተግባር ግን ትንሽ እንኳ ልዩነት አልነበረውም፡፡ በሚገርም ሁኔታ ሁለቱም እንዳገኙኝ የጠየቁኝ አንድ አይነት ጥያቄ ነበር፡፡ ‹‹ወንድ ከሆንክ ለምን ጫካ አትገባም?›› የሚል፡፡ ወንድነት ማለት አፈ-ሙዝን፤ በማይናወጥ የፍቅርና የወንድማማችነት መንገድ መጋፈጥ፤ ተጋፍጦም ሳይገሉ መሞት ነው ወይንስ በራሳችን ጥላ ሳይቀር እየደነበርን ንፁሃንን መግደል? የሚገርመው እኮ ለአፈ-ሙዝ ፍልሚያ የጥሪ ካርድ የሚበትኑት ወገኖች የደሃ ኢትዮጵያውያን ወንድማማቾችን ደም ለማፍሰስ እንጂ እነርሱማ ከመኪና ተደግፈው ለመውረድ ምንም የማይቀራቸው ናቸው፡፡ አንዳንድ በተለይም የአገዛዙ ዋነኛ ሰዎች ይችን ሀገር ለሁላችን ወደሚበጅ ንጋት ይዘዋት ለመውጣት እድሉን ለዓመታት ቢያገኙም ሊጠቀሙበት አልቻሉም፡፡ ይልቅስ እብሪት የሁለንተናቸው ማጠንጠኛ ምህዋር ሆኖአል፡፡ አንዳንዶቹን በጨረፍታ በማየት ለወንድማማችነትና የኢትዮጵያን የባጁ ችግሮች ለመፍታት በጐ አስተዋፆ ሊያደርጉ ይችሉ ይሆናል፣ ሕዝብን እንኳን ባይፈሩ ፈጣሪን ይፈሩ ይሆናል ብለን ተስፋ ብናደርግም ሁለቱንም እንደማይፈሩና የኢህአዴግ ዋና ሰዎች መለያ የሆነውን እብሪትና ሃኬት የሙጥኝ ብለው መንጐድ ቀጥለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ታሪክ አገዛዞች ከዚህ የተለየ ሲያደርጉ አልታዩም፡፡ ይኸኛው አገዛዝ ከቀድሞዎቹ ለመለየት የሚሞክረው በእውነት ላይ ያልተመሰረተ የፕሮፓጋንዳ ደመራ በማቀጣጠል ነው፡፡ የፕሮፓጋንዳ ደመራው ህዝቡንም ሆነ አገዛዙን በብርሃን እንዲመላለስ አላደረገውም፡፡ ሊያደርገውም አይችልም፡፡ አገዛዙም ሆነ ህዝቡ ከፍርሃትና ከጨለማ ጉዞ ነፃ ሊወጣ የሚችለው የእውነት ችቦ ለኩሶ ከዚያም በሚገኘው ብርሃን ዙሪያ ተሰባስቦ መወያየት ሲቻል ነው፡፡ ለዜጐች ሉዓላዊነት ክብር የሚሰጥ አገዛዝ ቢኖር የፕሮፓጋንዳ ደመራ አቀጣጥሎ በዙሪያው መጨፈር ባላስፈለገ ነበር፡፡ ምክንያቱም ተግባር ከቃላት በላይ ይናገራልና፡፡ የአገዛዙን አምባገነናዊ ባህሪዎችና ተግባሮች በመተንተን ከዚህ በላይ ጊዜ ልናጠፋ አይገባንም፡፡ ምንስ የማይታወቅ ነገር አለ? እንኳን የአፈናው ሰለባዎች ኢትዮጵያውያን ቀርቶ ዓለምም በቅጡ ተረድቶታል፡፡ አገዛዙ ለህዝብ ፈቃድ የሚገዛ ቢሆን ለመቃወም ከቤታችን መውጣት ባላስፈለገን ነበር፡፡

ትልቁ መፈተሽ ያለበት ጉዳይ ከ50 ዓመታት በላይ የአገዛዝ ስርዓትን ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዋር ለማስወገድ የተደረገው ጥረት፣ የተከፈለው የህይወትና የአካል መስዋዕትነት እንዴት እስካሁን ለፍሬ ሊበቃ አልቻለም? የሚለው ነው፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎች እስከ አሁን ቢያንስ ወደተሻለ ምዕራፍ ትግሉን ለማሸጋገር አልቻሉም? እስከ አሁን በተደራጁ የፖለቲካ ትግል ውስጥ ገብቶ ከመታገል ይልቅ በተለየና የራሳችን በሆነ መንገድ አስተዋፆ እናበረክታለን ብለን በተለያየ መስክ ተሰልፈን የምንገኝ ሰዎችም ምን ያህል አስተዋፆ አበረከትን? ብለን ራሳችንን መፈተሽ ይገባናል፡፡ ጊዜው በተግባር የማይደገፍና የተጠጋገኑ ምክንያቶችን በመደርደር ብቻ ከተጠያቂነት የምናመልጥበት አይደለም፡፡ ኢትዮጵያውያን የአፈናው ሰለባዎች መሆናችንን አለም በቅጡ ተረድቶታል፡፡ አገዛዙ ለህዝብ ፈቃድ የሚገዛ፣ የህግ የበላይነትን የሚያከበር ቢሆን ኖሮ ለመቃወም ከቤታችን መውጣት ባላስፈለገን ነበር፡፡ ትልቁ መፈተሽ ያለበት ጉዳይ ከ50 ዓመታት በላይ የአገዛዝ ስርዓትን ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዋር ለማስወገድ የተደረገው ጥረት፣ የተከፈለው የህይወትና የአካል መስዋዕትነት ዛሬም ለፍሬ ሊበቃ ያልቻለበትን ምክንያት ነው፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎችስ ስለምን ትግሉን ወደተሻለ ምዕራፍ ማሸገር ተሳናቸው? ዛሬም ድረስ የተደራጀ የፖለቲካ ትግልን ተቀላቅሎ ከመታገል ይልቅ በተለየና የራሳችን በሆነ መንገድ አስተዋፆ እናበረክታለን ብለን በተለያየ መስክ ተሰልፈን የምንገኝ ሰዎችም አበርክቶአችን ምን ያህል እንደሆነ ራሳችንን መፈተሽ ይገባናል፡፡ ጊዜው በተግባር የማይደገፍና የተጠጋገኑ ምክንያቶችን በመደርደር ብቻ ከተጠያቂነት የምናመልጥበት አይደለም፡፡ የነፃነት ጉዳይ ‹ለነገ…› ተብሎ በይደር የሚቆይ አይደለም፡፡

 

- See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=5640#sthash.q1MeZSR5.dpuf

ሀሳብን አወላግዶ ትርጉም መስጠት ከሀሳብ ነጻነት ሊመደብ አይገባም (ሰመረ አለሙ)

$
0
0

ሰመረ አለሙ

ቀደም ሲል ዳግማዊ ጉዱ ካሳ በሚል ስም ለልጂ ተክሌ የጻፈዉን ከግምት በማስገባት እሱ በጠቃቀሳቸዉ ጉዳዮች ላይ መጠነኛ ግንዛቤ ለመስጠት ብእር መምዘዝ ግድ ብሏል።

Freedom of Speechበመጀመሪያ ደረጃ ጸሀፊዉ ቋንቋዉ ላይ ያለዉን የበላይነት ለመግለጽ እወዳለሁ (ሃሳቡን አላልኩም ልብ በሉልኝ)  ወረድ ብዬ ደግሞ ጽሁፉን በስሱ ሳጠናዉ ጽሁፉ በቀጥታ የተነጣጠረዉ ልጅ  ተክሌ ላይ  ሁኖ ዶ/ር ብርሀኑን አስመልክቶ ልጂ ተክሌ የዘገበዉ በእጅጉ እንዳበሳጨዉ ከጽሁፉ ለመረዳት ከመቻሉም በላይ የጉዱ ካሳ ጽሁፍ ሀሳብን በነጻነት መግለጽ ላይ የተመዘዘ ሰይፍ ነዉ ተብሎ ቢነገር ለክርክር አይዳርግም የሚልም አመለካከት አለ። ጉዱ ካሳ ዲማቶ ከመዉደቃቸዉ በፊት ዘሎ መሀል ገብቶ የቁርጥ ቀን ወዳጂ መሆኑንም አሳይቷል ለዚህም አድናቆት ይቸረዋል።

ብቻ ሲያመጣዉ አንዴ ነዉ የጉዱ ካሳንና፡የልጂ ተክሌን ጽሁፍ  ካነበብን በሗላ ደግሞ በጥሩ ኢትዮጵያዊ አቀራረብ ስለ ዶ/ር ብርሀኑ ሌላዉ እንደ ልጂ ተክሌ አንጀቱ የበገነ አንድ ጽሁፍ አስነበበን። አዎ ዶ/ር ብርሀኑ እና አቶ አንዳርጋቸዉ ሊሸፈኑ የሚችሉ ካለመሆናቸዉም በላይ ሊሸፈቱም ግድ ይላል ሁኔታዉን እስከዛሬ በቅርብም በሩቅም ስንከታተለዉ ነበር። መለሰ ዘራዊ በህይወት ቢኖር እና ቢፈልግ እነዚህን ሰዎች የሚፈልጉትን  ሰጥቶ ይመልሳቸዉ ነበር ይጠቅማሉ ብሎ ከገመታቸዉ ይህም ግለሰቦቹ ላይ ካለን ጥላቻ ሳይሆን የህይወት ታሪካቸዉን በሚገባ ከመበርበር የተወረወረ አስተሳስብ ነዉ።

ወደ ጉዱ ካሳ ሌላዉ ክፍል ስንሸጋገር ዶ/ር ብርሀኑ ስለ ዋሂቢሰቶቹ ያላቸዉን አመለካከት አስመለክቶ በመደገፍ “ኢትዮጵያዉስጥ የሸሪያ ህግ ተቋቁሞ ኢትዮጵያ የእስላም አገር ትሆናለች የሚል እብድ ነዉ” የሚለዉን የሀጂ ነጂብን ማረጋገጫ ሰጥቶናል። እዚህ ላይ ጉዱ ካሳ  እስላም ይሁን ሌላ  እርግጠኛ ባንሆንም  ይህን ማረጋገጫ አምነን  ዶ/ር ብርሀኑን እንድናምን የተፈለገበት ምክንያት ግን ግልጽ አይደለም። እዉነታዉ ግን ሓጂ ነጂብ በጣም ጥበበኛ እንደኛዉ አገላለጽ ደግሞ ጩሉሌ ብለዉ ሊጠሩ የሚገቡ ሰዉ ናቸዉ። ብዙ ንግግራቸዉን ባለፈዉ አምስት አመት ተከታትለነዋል አንዳንድ ስብሰባቸዉንም ተሳትፈናል። ሐጂ ነጂብ እስላሞች ስብሰባና ሌሎች ስብሰባዎች ላይ የሚያወሩት የተለያየ ሃሳብም ነዉ። የህዋትንም መንግስት እንደዛሬዉ ከመጣላታቸዉ በፊት መንግስታችን ነዉ በማለት ሙሉ ድጋፋቸዉን ሲሰጡ የነበሩም ሰዉ ነበሩ። የሀጂ ነጂብ ሚስት ወ/ሮ ዘይነብ ይባላሉ እሳቸዉ የተናገሩትን ሙሉዉን ቃልም ቀድተነዋል “ኢትዮጵያ የእስላም አገር ትሆናለች ማሺ አላህ; አቶ መለሰ ወደ እስልምና ቢመለሱ ይሻሎታል ኢትዮጵያ በሸሪያ ትተዳደራለች” ይላል ቅንጫቢዉ ከዚህም የባሰ አባባል ታክሎበታል። ወ/ሮ ዘይነብ እና ሀጂ ነጂብ አንድ ሀይማኖት አንድ እምነት አንድ የኢስላም አይዲዮሎጂ የሚጋሩ ባልና ሚስት ናቸዉ በየስብሰባዉም ተከታትለዉ የሚሄዱ ናቸዉ።የሚለያዩት ሐጂ ነጂብ እንዲህ ያለ ቋንቋ የሚናገሩት በእስላሞች ዝግ ስብሰባ ነዉ እነ ጁሀርን የመሳሰሉ ጸረ ኢትዮጵያ ሀይሎችን በክብር ሲጋብዙ።

በጉዱ ካሳ ጽሁፍ አቶ አንዳርጋቸዉ ተደጋግመዉ ተነስተዋል እዉነታዉ ግን አቶ አንዳርጋቸዉ ህወአት ሲደናብር እጅ እና እግር ቀጥለዉለት ነብስ ዘርተዉበት ተሸልመዉ ተሸኝተዉ የሚኖሩ ሌላዉ ጩሉሌ ሰዉ ናቸዉ። አቶ አንዳርጋቸዉ ሕወአት ኢትዮጵያን ሲወርር የፕሮፓጋንዳ ሀላፊ ሁነዉ የሰሩ የህወአት የቁርጥ ቀን ልጅ ናቸዉ እንዲህ ያለዉ ስልጣን ለትግሬዎችም ቢሆን ለመስጠት ደጋግሞ ማሰብን የሚጠይቅ ነበር ለትግሬዉ ድርጂት። ዶ/ር ብርሀኑን በተመለከተ የህወአት ልዩ አድናቂ ከመሆናቸዉም በላይ ለመለስ፤ ለበረከት ስምኦን ለሰየ አብረሀ ልዩ አመለካከት የነበራቸዉ ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵየ በነበሩበት ጊዜ ከፕራይቬታይዜሺን ፕሮግራም ምን ያህል ሊያተርፉ እንደሚችሉ ሲያሰሉ የነበሩ  ግለሰብ ናቸዉ። ታዲያ ሁኔታዉ ይህ ሁኖ ሳለ እነ ጉዱ ካሳ  በ ኢቫንጀሊካን ሰበካ መንገድ ተጉዘዉ ኢሳትን፤ ከረንት አፌይርስን እና ሌሎች ደካማ የሚዲያ ተቋማትን በመጠቀም ግንቦት 7ን ከምንም በላይ አገዝፎ ለኢትዮጵያ አሳቢ አስመስሎ መሪዎቹ አንዳርጋቸዉ ጽጌና ብርሀኑ ኢትዮጵያን ካለችበት የሚያድኑ አድርገዉ አቅርበዉልናል። ይህ እንዴት ይተገበራል? ቀላል ነዉ ጸረ ኢትዮጵያን ሀይሎችን አስተባብሮ ኢትዮጵያ ላይ መዘመት (ኦነግ፤ኦብነግ፤ሻቢያ፤ግብጽ………………) እንግዲህ እነዚህ ሀይሎች ናቸዉ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ሊያደርጉ የሚችሉት ጎበዝ ተደፍረናል ትዉልዱን እያዩም መቀለጃ አድርገዉናል ቀደም ያለ ጊዜማ ቢሆን እንዲህ ያለ ቀልድ ለ አሳቢዉም ያስፈራ ነበር።

እንደእዉነቱ ከሆነ አንድን የሚዲያ ተቋም ተቆጣጥሮ እንደ ሂትለር ፕሮፓጋንዳ ህዘብን አደንዝዞ አማራጭ አሳጥቶ ህዘብን ዉዥምብር ዉስጥ መጨመር ለአንድ ህዝብ አማራጭ አይሆንም አለፍ ሲልም ወንጀል ይሆናል። ዛሬ ሁኔታዎች ተለዉጠዋል በኢትዮጵያ ስም ተቋቁመዉ ከላይ የተመለከትነዉን አይነት የተወላገደ አስተሳሰብ እኛ ዉሰጥ ፈጥረዉ የራሳቸዉን እቅድ ለሚያሳኩ ዜጎች ወገን ዞር በሉ ብሏል። ይህን ክስረት የተረዱ የዜና ድርጅቶችም ከሉበት ከፖለቲካ አቅዋም እና ትርፍ ሊያመጣልኝ ይችላል ከሚለዉ አመለካከት ተላቀዉ በመጠኑ በራቸዉን ከፍተዋል መሆንም ያለበት ይኸዉ ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ በሚደረገዉ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ጥቃት የሚመለከትን ዜጎች ሁሉ ያገባናል። አለም አቀፍ የፖለቲካ ተልእኮ ያለዉ የዋሃቢስቶች  እንቅስቃሴ በማጭበርበር ፖለቲካ ኢትዮጵያዉያንን ሲያምስ ይህ ነገር ሊታሰብበት ይገባል እያልን በጽሁፍም በቃልም ሀሳብ ስናቀርብ ከወያኔ በላይ ወያኔ ተብለን ዉርጅብኝ ቀርቦብናል። ይህ ማንንም አይረዳም እዉነት ከአጀማመሯ ብትቀጥንም በሗላ ግን እየገዘፈች እንደምትሄድ የተፈጥሮ ህግ ያሳያል። ኢትዮጵያ ዉስጥ ይህ የአዲሱ እስላም እንቅስቃሴ ያደረገዉን የቤተ ክርስቲያን ቃጠሎ፤ የንብረት ዉድመት፤አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ዜጎችን መግደል ነጻ የሆኑ የሚዲያ ተቋማት ዘግበዉታል ታድያ እነሱን ኪሳራ ዉስጥ የሚከት ሁኔታ ሲፈጠር ወያኔ ነዉ ያደረገዉ የሚለዉ የፌዝ አነጋገር እየተለመደ መጥቷል።  እነዚህ ማስረጃዎች ህዝቡ ዘንድ እንዳይደርሱ ቢደረግም፤የኢትዮጵያ ሚዲያዎችን በማጭበርበር እና ግፊት በማድረግ ህዝቡ ዘንድ እንዳይደርስ ጫና ቢደረገም  ለሀገራቸዉ በጎ የሚያስቡ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ለእይታ አቅርበዉታል አንባቢ በጉግል ከተመለከቱት ከብዙ በጥቂቱ ተመልካቹን የማያሳቅቀዉን ብቻ መርጠን አዉጥተነዋል ቀሪዉን ብርታት እና ጥናቱ ያላችሁ ዜጎች የዚህን ኢሰብአዊ ስራ መመልከት ትችላላችሁ።1.

እዚህ ላይ እነዚህን ሰዎች ኮትኩቶ እዚህ ያደረሳቸዉ የህወአት መንግስት መሆኑን አንባቢ እንዲረዳዉ ያስፈልጋል ሆኖም የህወአት ትግራይ ቢኮተኩታቸዉም አድራጊዎቹ እነሱ በመሆናቸዉ ለዚህ ወንጀል በህብረት ተጠያቂ መሆናቸዉም ሊሰመርበት ይገባል። እዚህ ላይ ታማኝ በየነም ምንም እንኳን ቀደም ባለዉ ጊዜ ለሀገሩ ብዙ ዉለታ የዋለ ዜጋ ቢሆንም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በነ ዶክተር ብርሀኑ ተጋልቦ የኦነግ ወዳጂ ሁኖ ወደ ኢትዮጵያን መንደር የተኮሰዉን ሳናነሳ ልናለፍ አንፍለግም።ይህንን ነገር አስመልከተዉ ታማኝ በየነን አንዳንድ ጥንቃቄና ትምህርት የሚያስፈለገዉን ጉዳይ  የዘገቡ ወገኖች  (ዲ/ን ሙሉጌታ) በመኖራቸዉ ታማኝ በየነም ከዚህ ይማራል ብለን እንገምታልን ሌሎች ታማኝ በየኖችም ጥንቃቄን ያደርጋሉ ብለን እናምናለን።

ዛሬ ነገሮች ተለዉጠዋል ኢትዮጵያን የሚጎዳ ማንኛዉም አይዲዮሎጅ፤እምነት፤እይታ የሚዲያ ተቋማትን በሞኖፖሊ ይዞ ኢትዮጵያዊነትን የማፈን እንቅስቃሴ ጊዜዉ አልፎበታል ተጎጂዎቹም ከማንም በላይ የሚዲያ ተቋማት እና ይህን የሚያራምዱ ድርጂቶች እና ቡድኖች ይሆናሉ። በጊዚያዊ ጥቅም ተገፋፍተዉ ታላቁን ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያን ማጣት ከጥቅም ጉዳቱ ስለሚያመዝን ቆም ብለዉ ማሰብ ይጠበቅባቸዋል።  ይህንን ኪሳራ በብዙ የኢንተርኔት  የዉይይት መድረክም ጭምር ተመልክተናል በብዙ መቶዎች ያስተናግዱ የነበሩ በወረደና በጸረ ኢትዮጵያ አቋማቸዉና ተልእኮዋቸዉ ዛሬ ክፍላቸዉን ሬሳ የወጣበት  ቤት አስመስሎታል። ህዝቡ የሚፈልገዉን ስለሚያዉቅ ዛሬም ተቋማት በጊዜያዊ የቴርሞ ሜትር መለኪያ ብቻ ሳይወሰኑ የረጅም ጊዜ እይታችሁን መዝኑ እንላለን።

እንግዲህ መባል ያለበት ተብሏል ካጠፋሁም በዚህ ተቆጡኝ  semere.alemu@yahoo.com

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

የሼኽ ኑሩ ወንድ ልጅ በእስር ላይ እንደሚገኝ ተነገረ! (ድምፃችን ይሰማ)

$
0
0

ድምፃችን ይሰማ

ከሁለት ወራት በፊት በሰው እጅ ሕይወታቸው የጠፋው ሼኽ ኑሩ ወንድ ልጅ በመንግስት ደህንነቶች ታፍኖ ተውስዶ መታሰሩ ተሰማ፡፡ በደሴ አረብ ገንዳ አካባቢ ነዋሪ የነበሩትና መንግስት ለፖለቲካ ጥቅም ሲል ገድሏቸዋል ተብሎ በስፋት የሚታመነው ሼኽ ኑሩ ወንድ ልጅ በመንግስት ደህንነቶች ታፍኖ ከተወሰደ በኋላ አሁን ያለበት ቦታ በውል መታወቅ አልቻለም፡፡ እንደ አከባቢው ምንጮች ከሆነ የሼኽ ኑሩ ልጅ የታሰረው ከአባቱ ግድያ ጋር በተያያዘ ‹‹አባቴን ያስገደለው መንግስት ነው!›› በሚል በዙሪያው ላሉ ሰዎች በመናገሩ ነው ተብሏል፡፡ ይህ ወጣት ተመሳሳይ እስር ሲያስተናግድ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ከጥቂት ሳምንታት በፊትም ተመሳሳይ ንግግር በመናገሩ በደህንነቶች ለቀናት ታፍኖ ከተወሰደ በኋላ ማስፈራሪያና ምክር ተለግሶት ተፈቷል፡፡ ሆኖም ከተፈታ በኋላም የመንግስት ደህንነቶች ያስጠነቀቁትን ‹‹ከአሁን በኋላ አባቴን መንግስት አስገድሎታል እንዳትል!›› የሚል ምክር ጥሶ በመገኘቱ ለድጋሚ እስር ተጋልጧል፡፡

 

Ethiopian Musilms

መንግስት ከሼኽ ኑሩ ግድ ጋር በተያያዘ ለሳምንታት የዘለቀ ከፍተኛ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ሲያካሄድ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ ዘመቻ ኢሕአዴግ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎችን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ተቋማት መግለጫ በማውጣት ከፍተኛ የሚዲያ ሽፋን ለመስጠት ተሞክሯል፡፡ በተጨማሪም በበርካታ የገጠር ከተሞች በተሌም በአማራ ክልልና ደቡብ ወሎ ‹‹ሕዝቡ የሼኽ ኑሩን ግድያ እንዲቃወም›› በሚል የግዳጅ ሰልፍ እንዲወጣ ከመደረጉም በላይ ‹‹ግድያውን የፈጸሙት ሙስሊሞች ናቸው›› በሚል ‹‹መንግስት እርምጃ ይውሰድ!›› የሚል መልእክቶች በተከታታይ በመንግስት ሚዲያዎች ሲያሰራጭ ነበር፡፡ ሆኖም ከሼኽ ኑሩ ግድያ ጋር በተያያዘ ሙስሊሙ ኅብረተሰብ ምንም ንክኪ እንደሌለውና ሙስሊሙ ኅብረተሰብ የሚያደርገው ተቃውሞ ፈጽሞ ይህን መሰል ጸየፍ ድርጊቶችን የሚስተናግድበት መርህ እንደሌለው በማስረገጥ፤ በዋነኝነትም የእንቅስቃሴው መርህ የሆነው ‹‹የምንሞትለት እንጂ የምንገድልበት አላማ የለንም›› መፈክር ተደጋግሞ ተጠቅሷል፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብም በሃይል እርምጃዎች የማያምንና የሚሰነዘርበትን ዱላ በጸጋ ከመቀበል ውጪም አጸፋ የሰጠበት አጋጣሚ እንደሌለ በአስረጂነት ቀርቧል፡፡

አሁን የት እንደታሰር በውል የማይታወቀውና ከቤተሰብ ጋር እንዳይገኛኝ የታቀበው የሼኽ ኑሩ ወንድ ልጅ የገለጸው ሀሳብ አብዛኛው ህብረተሰብ የሚያምንበትና በተለይም በደሴ ከተማ ሕዝብ ዘንድ ግድያውን መንግስት እንደፈጸመው በስፋት የሚታወቅ እውነት ነው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም በተለያዩ ወቅቶች ከሼኅ ኑሩ ግድያ ጋር በተገናኘ የመንግስት ረጅም እጆች መኖራቸው የሚያመላክቱ መረጃዎች ወጥተዋል፡፡ ሼኅ ኑሩ ከመንግስት ሀላፊዎች ጋር በቅርበት ሲሰሩ የቆዩ ቢሆንም በሞታቸው የመጨረሻ ወቅቶች ግን ከአካባቢው አስተዳደር ሀላፊዎችና የጸጥታ ሹሞች ጋር በአካሄድና መርህ ላይ ባለመስማማታቸው ስብሰባ ረግጦ እስከውጣትና ዳግም አብሮ የመስራት ፍላጎት እንደሌላቸውም ሲገልጹ ነበር፡፡ መንግስት ሞታቸውን ተከትሎም የአስከሬን ምርመራ እንዳይደረግና የቀብር ስነ ስርአቱ በአፋጣኝ እንዲፈጸም በማስደረግ የግድያው ሁኔታ ተሸፋፍኖ እንዲቀር ለማድረግ ጥረት አድርጓል፡፡ የሼህ ኑሩ ግድያ ‹‹በመንግስት የተፈጸመ ድራማ ነው›› ሲል ሕብረተሰቡ ደጋግሞ መግለጹ ይወሳል፡፡

አላሁ አክበር!

አያ ተክሌ ምነዉ አህያዉን ትተዉ ፈረሱን ቢጋልቡ

$
0
0

 በደርብ ከፈለኝ

አዋቂ መስሎኝ ሰምቼዉ
ትልቅ ሰዉ መስሎኝ ተጠግቼዉ
በቃኝ . . . በቃኝ  አወቅኩትና  ናቅኩት
ለካስ ወዳጄ ኖሯል ፈረስ እየናቀ አህያ የሚጋልብ
በሬ እያቀጨጨ ጅብና ድብ የሚያደልብ

comment picከላይ አያ ተክሌ ብዬ የጀመርኩህ ተሳስቼ ነዉ። ከአሁን በኋላ ግን አቦይ ተክሌ ብዬ ነዉ የምጠራህ። አይዞህ “አቦይ” ያልኩህ እንደ አቦይ ስብሐት አርጅተህብኝ አይደለም። አወቃለሁ አንድ ፍሬ ልጅ ነህ . . .  አዎ ልጅ ነህ . . .  አሁንም ልጅ!  “አቦይ” ብዬ ሹመት የሰጠሁህ  አነጋገርህ፤ አስተሳሰብህና እንዳዉ አኳኋንህ ሁሉ ከአቦይ ስብሐት ጋር ስለተመሳሰለብኝ ነዉ፤ ወይም እንደ አቦይ ስብሐት ቀላማጅ ነህ ትቀለማድለህ ማለቴ ነዉ። አቦይ ተክሌ ምንም ቢሆን የቅርብ ጓደኛዬ ነህና የጓደኝነቴን ምክር ቢጤ ልሰጥህ እስኪ ስማኝ። አቦይ ስብሐት ሃያ ሁለት አመት ሙሉ ቀላምደዋል፤ ከአሁን በኋላ ልቀላምድ ቢሉም አንድ ሐሙስ ነዉ የቀራቸዉ። አንተ ግን አንድ ፍሬ ልጅ ነህ፤ እንግዲህ ይታይህ 35 አመት፤ 40 አመት፤ 50 አመት፤ ስልሳ አመት እያልክ ወዳጅና ጠላት፤ዘመድና ባዳ ፤ ጎረቤትና የማዶ ሰዉ ሳትለይ ይህንን ሁሉ አመት እየቀላመድክ ልትኖር ነዉ . . .  ያዉም በዚህ እንደ አሞራ በሚበርረዉ የዳያስፖራ ኑሮ። ምነዉ ተክሌ ቢቀርብህ!  መዶሻ የያዘ ሰዉ ሁሌም የሚመለከተዉ ሚስማር ብቻ ነዉ ሲባል ሰማሁና መዶሻ የያዘ ሰዉም መሰልከኝ፤ አሁን ግን በደንብ አድርጌ ሳይህ መዶሻ የያዘ ሰዉ ሳይሆን ጭራሽ መዶሻዉን እራሱን መሰልከኝ።

 

“ዬት ይደርሳል የተባለ ጥጃ ሉካንዳ ታየ” . . .  አያ ተክሌ . . .  ይቅርታ አቦይ ተክሌ ማለቴ ነዉ . . . ይህ ስንኝ የተቋጠረዉ ለሌላ ለማንም ሳይሆን ላንተ ብቻ ይመስለኛል። እስኪ ንገረኝ ተክሌ ምነዉ የነካሄዉ ነገር ሁሉ አይበረክት ወይ አንተ አትበረክት። እስኪ መለስ ብለህ አስበዉ ECADF፤ EHSNA፤ ESAT TV ፤ ESAT Radio ሁሉንም ነካ ነካ ግን አንዱንም ሳታረካ አንተም ሳትረካ እንዳዉ ዉኃ ላይ እንደተንሳፈፈ ኩበት ባክነህ ቀረህ። ምነዉ ወንድሜ ተክሌ እንዲህ ነበር እንዴ እኔና አንተ የምንተዋቀዉ? ምን ላድርግ እንደዛ ማታ ማታ እንደምንጫወትበት ካርታ ተበዉዝክብኝኮ። ምነዉ ተክሌ የተደበቀዉ ጸባይህ እየወጣ ነዉ ወይስ ድሮ ሳዉቅህም እንዲህ ወናፍ ነበርክ? ተክሌ ከሁሉም ከሁሉም የምታናድደኝ ደርሶ አዋቂ ለመመሰል  ቱግ ቱግ ስትል ነዉ፡፡ ዉድ ጓደኛዬ ተክሌ እባክህ ተረዳኝ እኔ አዋቂ አትሁን ማለቴ አይደለም፤ ግን አዋቂ ለመሆን አዋቂ ሁን እንጂ አዋቂ አትምሰል። ደግሞም ቱግ ቱግ እንኳን ባንተ በእንደኔ አይነቱ አንድ ክንድ ከስንዝር በማትሞላዉ ባንተ በሸበላዎቹም አያምርም። ስለዚሀ ተክሌ እባክህ እንዳቅምህ . . .  አዎ እንዳቅምህ!

 

በያ ሰሞን በየድረ ገጹ እየገባሁ  ያገኘሁትን ሁሉ ሳነብ አንተም የሞነጫጨርከዉን አገኘሁና አንብቤዉ በጽሁፍህ ሳይሆን በጓደኝነትህ አፈርኩ። እስኪ ንገረኝ ተክሌ ምን ይሁን ብለህ ነዉ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዉን ፖለቲካ አትተንትን ያልከዉ፤ እናስ ምን ይተንትንልህ? እኮ ንገረኝ ተክሌ የፖለቲካ ፓርቲ መሪ ፖለቲካ ካልተነተነ ሌላ ምን ይተንትን?  ለመሆኑ ያልተተነተነ ፖለቲካ ምን አይነት እስትራቴጂ ነዉ የሚወጣለት? ምነዉ ተክሌ “አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት” የምንላትን ሴትዮ ሆንክብኝ! የፖለቲካ ፓርቲ መሪ ሆኖ የአገሩን የፖለቲካ ሁኔታ የማይተነትንና መጻኢዉን እዉነት በስዕል ቀርጾ የማያሳየን ከሆነ ምኑን የፖለቲካ ፓርቲ መሪ ሆነ . . .  እንደሱ አይነት የፖለቲካ ፓርቲ መሪማ ካንተ ጋር የዋለ ሰዉ ማለት ነዉ። አይዞህ ተረት ጎበዝ ነህ ብዬ ነዉ (ከአህያ ጋር የዋለች . . . )  አቦይ ተክሌ ችኩልነትህን ድሮም አዉቀዋለሁ፤ ከተናገርክ በኋላ የምታስብ ሰዉ መሆንህም ለእኔ አዲስ አይደለም፤  ግን ምነዉ ተክሌ . . .  ያንተ እዉነት የሰዉ ሁሉ እዉነት ይመስልሃል እንዴ? እንደዚህማ ከሆነ እዉነት የሚባል ነገር ምድር ላይ የለም ማለት ነዉኮ!  ተክሌ እባክህ በዚህ “ካፍ ከወጣ አፋፍ” በሆነበት አለም ከመናገርህና ከመጻፍህ በፊት አስብ። ፈረንጆቹ (Think twice before you speak once) ይላሉ። ተክሌ አንተ ግን የሚጽፈዉ እጀህ ደራሽ የሚናገረዉ አፍህ ነካሽ ነዉና እባክህ እንዳዉ በዚያች በምታከብራት በወላዲት አምላክ ይዤሃለሁ ከመናገርህ  በፊት አምስቴ አስብ (Think five times before you speak once).

 

መቼም የኛ ነገር “አፍ ያለዉ ጤፍ ይቆላል” ነዉና አንድ ሰሞን ይችኑ የምትንጣጣዉን አፍህን አይተዉ  ኢሳቶች ወያኔ ላይ ብትንጣጣላቸዉ ብለዉ አስጠጉህ አንተ ግን ጠላትና ወዳጅ ሳትለይ ሁሉም ላይ የምትተኩስ ጉድ ነህና ኢሳቶች ላይ እሳት ሆንክባቸዉና እሳት አደጋ ጠርተዉ በግዜ ተገላገሉህ። ተክሌ ልክ እንደ ቁመትህ ምን ያህል ትንሽ ሰዉ እንደሆንክ ያየሁት በስራ አጋጣሚ የምታዉቀዉን ነገር ሁሉ ድረ ገጽ ላይ እንዳላዋቂ ሳሚ መለቅለቅህ ነዉ። አሁን ይህ ምን ይባላል? አዋቂነት ወይስ ጅልነት? መልሱ ቀላል ነዉ፤ ተክሌ አንተ አዋቂነት የሚባል ነገር በአጠገብህ ያለፈም አይመስለኝም። ጅልን ለማወቅ ደሞ ጅል መሆን የግድ ይላልና እስኪ እዚያ የሞነጫጨርከዉ መጣጥፍ ላይ የከተብከዉን ዝባዝንኬ እንዳለ ላሳይህ

 

“ይሁን እንጂ፤ የኢሳት አስተዳዳር የሆነው ወዳጄ ነአምን ዘለቀ የዛሬ አመት አካባቢ እንዲህ ያለው ተመሳሳይ ስብሰባ ሲዘጋጅ፤እባክህን መሪዎቹ ንግግር ያሳጥሩና ለሰዉ እንዲተነፍስ ግዜ ይስጡት ብዬ አሳስቤው ነበር። ነአምን አንዳንዴ አይሰማም። ወይም ቢሰማም አያደምጥም” አቦይ ተክሌ

 

“ነአምን አንዳንዴ አይሰማም። ወይም ቢሰማም አያደምጥም” . . . ወይ ጉድ! አንተንስ ምን እንበል? . . .  ተክሌ የሚባል ስም ከተሸከምክ ጀምሮ ሰምተህም አዳምጠህም የማታዉቀዉን ጆሮም አፍም የሌለህ እንግዳ ፍጥረት! ለካስ አለምክንያት መዶሻ አልተባልክም!  ነአምንማ እንተም እንደመሰከርክለት አንዳንዴ ነዉ እንጂ አብዛኛዉን ግዜ ይሰማልኮ፤ እንደዚህ ብዙ ግዜ የሚሰሙ ኢትዮጵያዉያን ደግሞ ብርቅዬ ናቸዉ . . . የሉማ! እስኪ ንገረኝ ተክሌ ምንድነዉ እየነገርከን ያለኸዉ፤ አንተ ሁሉን ነገር  አዋቂዉ ተናግረህ ነአምን አላዋቂዉ አለመስማቱን ነዉ ወይስ ከዚህ ሌላ የምትለን ነገር አለ? ደሞኮ ከብዙ ጉድ ያዳነን የነአምን አንዳንዴ አለመስማት ነዉ እንጂ ሰምቶህማ ቢሆን ኖሮ የዛሬዉ ትግላችን ከወያኔ ጋር መሆኑ ቀርቶ አንተ የቀደድከዉን ቀዳዳ መቋጠር ላይ ይሆን ነበር። ችግሩ ዲሲ ላይ አትቅደድ ብለዉ ሲያባርሩህ ቶሮንቶ ሄደህ ደሞ እንደገና ትቀድዳለህ . . .እስኪ ንገረን የሚቀደድ የሌለበት ዬት አገር እንስደድህ?

 

አቦይ ተክሌ  . . . ዶ/ር ብርሐኑ በሐይማኖት ጉዳዮች ላይ የጻፉት ሰፋ ያለ ጽሁፍ አልገባህ እንደሆነ መጠየቅ አንድ ነገር ነዉ፤ አለዚያ ስምም፤ሀሳብም ጸባይም  እንደምትጋራቸዉ እንደ አቦይ ስብሐት ህዝብ አንዳለ ባኮረፈበት አገር “ያኮረፉ ሰዎች እንጂ ያኮረፈ ህዝብ የለም” ብትል አባባሉ ለግዜዉ ሊያምርልህ ይችል ይሆናል፤ እመነኝ የሚሰማህ ግን አታገኝም። የዶ/ር ብርሀኑ ጽሁፍ ላይ ገጽ 16 መጨረሻና ገጽ 17 መጀመሪያ ላይ የቀረበዉ ሃሳብ ጥልቅ ወይም ሐቀኛ አይደለም ብለሃል። እስኪ ንገረኝ ተክሌ ምንድነዉ መለኪያህ? ጥልቀቱን ባንተ ስንዝር ሐቀኝነቱን ባንተ ሚዛን ነዉ የለካኸዉ? ከሆነ… አብረን ስለኖርን ዝንዝርህንም ሐቅህንም በሚገባ አዉቃለሁና አልፈርድብህም። አቦይ ተክሌ እንዳዉ ያንተ ነገር “አህያ ማር አይጥማት” ሆኖብህ ነዉ እንጂ እስኪ አሁን ምኑ ላይ ነዉ ያ ጽሁፍ ጥልቀት ያጣዉ ምኑስ ላይ ነዉ ሀቅ የጎደለዉ? አንድን ሰዉ ደደብ ነዉ ብሎ አንድ ሙሉ መጽሐፍ መጻፍ ይቻላልኮ፤ ለዚህ ደግሞ የሚያስፈልገዉ ብዙ ጥረትም አይደለም አንድ ያንተ አይነት ጭንቅላት ይበቃል። ችግሩ የሚመጠዉ የሰዉየዉን ደደብነት ዋቢ ጠቅሶና መረጃ አስይዞ ማቅረቡ ላይ ነዉ፤ እንደዚህ አይነቱ መረጃ ደግሞ እንኳን አንተ አያገባዉ ይገባል ያልከዉ ሰዉ ላይ ቀርቶ የእርጎ ዝንብ የሆንከዉ አንተ ላይም ማቅረብ አስቸጋሪ ነዉ። አይህ ወንድሜ ተክሌ አንተም እንደዚሁ ነህ። ሰዉን “ደደብ” ለማለት አፍህ ይቀድማል መረጃ ተብለህ ስትጠየቅ የምታሳየን ግን ያንኑ የምናዉቀዉን ባዶነትህን ነዉ . . .እሱ ደግሞ ሰለቸን . . .  አዎ ሰለቸን! ሰማህ ተክሌ ሰለቸን።

 

አቦይ ተክሌ ደሞ ብለህ ብለህ አንተም እንደ ወያኔ ምሁራን ተቃዋሚዉን ሁሉ “ሊብራል” ልትለዉ ነዉ እንዴ! መቼም አንዳንዴ ነካ ሲያደርግህ እንደ ዕብድም መሆንም ያምርሃል እንጂ በወያኔነት እንኳን በፍጹም የምትታማ ሰዉ አይደለህም፤  ግን . . . ግን ጠንቀቅ በል ልጄ ዉኃኮ ሲወስድ እያሳሳቀ ነዉ . ..  እንግዲህ ይታይህ ተክሌ ባንተ መንቀዥቀዥኮ መወሰድህ ነዉ!  ብሉይን በመቀበል ከዚያ ክርስትናን፤ ከዚያ እስልምናን፤ ከዚያ ካቶሊክን፤ ከዚያ ፕሮቴስታነንስዝምን፤ በመቀበልና በማቻቻል የኖረች አገር ናት ብለሀል አገራችን ኢትዮጵያን። እርግጥ ነዉ፤ ግን ለመሆኑ ብሉይ የሚባል ሐይማኖት አለ አንዴ ወይስ አንተዉ ወደኋላ ሄደህ ልትጀምር ነዉ? ደግሞስ ክርስትና፤ ካቶሊክና  ፕሮቴስታነንስዝም ስትል ካቶሊክና ፕሮቴስታንት ምን መሆናቸዉ ነዉ? ክርስትና አይደሉም እንዴ? ወይስ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከምንም ተቋም ጋር የማይገናኝ “ክርስትና” የሚባል ሐይማኖት አለ? አየህ ተክሌ ምን አይነት የተበላሸ ጭንቅላት እንዳለህ የሚያሳየዉ እንደዚህ አይነት ቆሻሻና ወደ አንድ ወገን ያጋደለ ትንተናህ ነዉ። ይልቅ ምነዉ እንዲህ አይነቱን ጭንቅላት የሚፈልገዉን ትንተና ለዚያ አትችልም ላልከዉ ሰዉ ብትተዉለት! ማቻቻል የሚል ቃልም ተናግረሃል፤ ምን ማለትህ ነዉ? ኢትዮጵያ ዉስጥኮ ማን ማንን ችሎ እንደኖረ ግልጽ ነዉ . . .  እና አሁንም በዚያዉ እንቀጥል ነዉ እንዴ የምትለን? ዶ/ር ብርሀኑኮ በዚያ ጸሁፉ ዉስጥ ያስነበበን የተለያየ ሐይማኖት ቢኖረንም እንዴት ሁላችንም ያሰኘንን ሐይማኖት ባሰኘን መንገድ እያመለክን (ይግባህ መቻቻል አይደለም) በእኩልነት ተከባብረን መኖር እንደምንችል ነዉ። ይህንን ደግሞ ሊብራል ዲሞክራሲ በሚገባ ተንትኖ አስቀምጦታል። አየህ ተክሌ  ፖለቲካ ተንትን ተብሎ ስራ ሲሰጥህ አንደጋይኮ ኮሜርሻል ነገር ትደባልቃለህ፤ አዋቂ ሲተነትን ደሞ አትተንትን ብለህ ትወርድበታለህ፤ ምነዉ ተክሌ . . .  “ያግቡብሽ እምቢ ያዉጡብሽ እምቢ” ሆንክሳ!

 

ኦባማ ሲመረጥ ምሁር ነበር ብለሃል. . . . አይደለም ብዬ ብከራከርህስ?  ምነዉ ተክሌ የማታዉቀዉ ዉስጥ ገብተህ ትፈተፍታለህ! አባማ ፕሬዚዳንት ሆኖ ሲመረጥ የፖለቲካ ሰዉ (ሴኔት) ነበር፤ ዛሬም የፖለቲካ ሰዉ ነዉ። በእርግጥ ኦባማ የምሁር ችሎታዉም ተሰጥኦዉም አለዉ፤ ግን በምሁርነት የሚበልጡት ሺዎች አሉ፤ ኦባማን አባማ ያሰኘዉ በምሁርነት ችሎታዉ ላይ አዳብሎ የያዘዉ ከፍተኛ የፖለቲካ ችሎታዉ ነዉ (ይህ ችሎታ የፖለቲካ ትንተናዉንም ያጠቃልላል)። አለዚያ ለምሁርነቱማ ሀርቨርድና ፕሪንስተን ዉስጥ አባማን የሚያስከነዱ ብዙ ምሁራን አሉኮ። ተክሌ አንተኮ አንዳንዴ የምትናገረዉንም የምታዉቅ አይመስለኝም፤ ለዚህ ይመስለኛል ‘ተክሌ’ ከተናገረ በኋላ ነዉ የሚያስበዉ እየተባልክ የምትታማዉ። ምሁር ምሁርነቱ ሲቀንስ ወደ “ቡሽነት” ይለወጣል ነዉኮ ያልከዉ? የፈጣሪ ያለህ!  . . .  ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም አሉ፤ ዕድሜ ላንተ ዘንድሮ ሊጣባ ነዉ። አየህ ተክሌ በዚህ አንተ ባልከዉ ስሌት ከሄድንኮ ኢሳት ዉስጥ ዜና ያነበበ ሰዉ ሁሉ ወናፍነቱ ሲጨምር ‘ተክሌ’ ይሆናል ማለት ነዉኮ . . .  እንዴ! እኛ አነተ አንዱም አላስቀምጥ ብለኸናል ደሞ ስንት ተክሌ ሊኖረን ነዉ?  ከዚህስ ቸሩ ፈጣሪ ይጠብቀን!!

 

“የፖለቲካ ተንታኝ የምለው፤ በፖለቲካ ውስጥ በቀጥታ በአድራጊ-ፈጣሪነት ሳይሳተፍ ወይም መሳተፍ ሳይጠበቅበት፤ የአንድን ፖለቲካዊ ስብስብ/ማህበረሰብ ፖለቲካዊ ሁኔታ እየቃኝ፤ ከአካባቢያዊና አለማቀፋዊ ሁነቶች ጋር እያጣቀሰ የሚናገር ነዉ” ብለሀል። ለመሆኑ ይህ የተናገርከዉ ነገር ያንተ ህግ ነዉ ወይስ የሁላችንም?  ያንተ ከሆነ ያንተ ነገር ሁሉም ግራ የተጋባ ነዉና አልፌሃለሁ። ግን ምነዉ ተክሌ ሰሜን አሜሪካ ዉስጥ እየኖርክ ፖለቲካ በምሁርና በፖለቲከኛዉ ሲተነተን ልዩነቱ አልገባህ አለ? እስኪ የሚገባህ ከሆነ ምሳሌ ልስጥህ . . .  ፕሮፌሰር ላሪ ሰባቶ (ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቨርጂኒያ) አንተ ያልከዉ አይነት የታወቀ ምሁርና ፖለቲካ ተንታኝ ነዉ፤ ግን ፖለቲካ አድራጊም፤ፈጣሪም አይደለም ። ተሳትፊ ግን ነዉ። አንተ ከዬት እንዳመጣኸዉ አላዉቅም አንጂ  ሰዉ ሆኖ ፖለቲካ  ላይ የማይሳተፍ የለም፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ  ፖለቲካ አድራጊም፤ፈጣሪም  ተሳታፊም ናቸዉ፤ ዋናዉ ስራቸዉ  ፖለቲካ መተንተን ላይሆን ይችላል፤ ግን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የአሜሪካንን ፖለቲካ ተንትነዉ ለህዝብ ማቅረብ ግዴታቸዉ ነዉ።  ህዝቡም ጆሮዉን በአብዛኛዉ የሚሰጠዉ ለፖለቲካ ኤክስፐርቱ ለላሪ ሰባቶ ሳይሆን ለፖለቲከኛዉ ለኦባማ ነዉ። አየህ ተክሌ ባንተ አባባል ፕሬዚዳንት ኦባማ ፖለቲካ ትንተናዉን ለላሪ ሰባቶ መተዉ አለባቸዉ ማለት ነዉ፤ ወይም የኦባማ ፖለቲካ ትንታኔ ያልጠራ የላሪ ሰባቶ ትንታኔ ግን የጠራ ነዉ ማለት ነዉ . . . እንዴት ሆኖ!  እርገጠኛ ነኝ ይህንን ጽሁፍ አንብበህ ስትጨርስ በራስህ ቅዠት ይምትስቅ ይመስለኛል። በነገራችን ላይ የኢትዮጵያም ፖለቲካ እንደዚሁ ነዉ፤ ጋዜጠኛዉም፤ የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሩም፤ ሌላ ሌላዉም ሊተነትነዉ ይችላል፤ ግን ህብረተሰቡ (አንተን ላይጨምር ይችላል- አዋቂ ነሃ!) በብዛት ጆሮዉን የሚሰጠዉ ፖለቲካዉን የፖለቲካ መሪዎች ሲተነትኑት ነዉ። ደሞ ማነዉ ምሁር ሁሉ ፖለቲካ መተንተን ይችላል ብሎ የነገረህ?  አቦይ ተክሌ ሌላዉ ትልቁ ችግርህ ሰዉ ያለማክበር ነቀርሳ አለብህ፤ ለምሳሌ ዶ/ር ብርሀኑን አንዴ ዲባቶ ብርሀኑ ፤ አንዴ ብርሀኑ ነጋ፤ ሌላ ግዜ ደግሞ ልክ እንደ ቆሎ ጓደኛህ “ብሬ” ብለህ ጠርተዋኸል። ዶ/ር ብርሀኑ በዕድሜ ይበልጥሃል ደግሞም አስተማሪህ ነዉ፤ ስለዚህ አጠገቡ ስትሆን ዶ/ር ብርሀኑን እንዳሰኘህ መጥራት ትችላህ እሱ ያንተና የሱ ጉዳይ ነዉ፤ ለኛ ስትጽፍልን ግን ኢትዮጵያዊ ባህላችን ነዉና ማክበር ግዴታህ ነዉ። ይህንን ታላቆችህን የመዘርጠጥ ነቀርሳ በግዜ ካልታከምከዉ ብዙ ታዳጊ ልጆቻችንን ታበላሻለህና አንተዉ  ጽሁፍህ ላይ በጠቀስካት በእመ ብርሀን የዤሃለሁ እባከህ ታላቆችህን አክብር።

 

ኢትዮጵያ ዉስጥ ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ያነሱትን የመብትና የነፃነት ጥያቄ ሙሉ በሙሉ የምንደግፍ ኢትዮጵያዉያን፤ የምንደግፍ ግን ንቅናቀዉን በጥርጣሬ አይን የምንመለከት ኢትዮጵያዉያንና ጭራሽ ንቅንናቄዉን የምንቃወም ኢትዮጵያዉያን አለን። አቦይ ተክሌ አንተም የሙስሊሙን ህብረተሰብ እንቅስቃሴ መጠራጠር መብትህ ነዉ፤ ያ እዚያ ሙንጭርጭርህ ላይ የወረድክበት የፖለቲካ ተንታኝም አትጠራጠሩ አላለምኮ! መቼም ያንተ ዱላ ልክ እንደ ወያኔ ፌዴራል ፖሊስ ዱላ ያገኘዉ ሁሉ ላይ ይመዘዛል እንጂ ዶ/ር ብርሀኑማ እንድያዉም የሙስሊሙን እንቅስቃሴ የሚጠራጠሩ ሰዎችን በመንግስት ፕሮፓጋንዳ የተደለሉና የሐይማኖት አክራሪነትን የሚፈሩ ብሎ በሁለት ከፍሎ ነዉ ያስቀመጣቸዉኮ። አንተ ግን በዚያ በተከፈተ ቁጥር አንደ “ታድፋለች ቅጥ” በሚሰፋዉ አፍህ “ብሬ አድበሰበሰው” ብለህ አረፍከዉ። መቼም በባህላችንም ቢሆን ነዉር ነዉና አደባባይ ላይ “ባለጌ” ብዬስ አልሰድብህም!

 

ምንም ቢሆን ተሰድደህ ዳያስፖራዉን የተቀላቀልከዉ ለትግል ነዉና አስኪ አንድ ነገር ልጠይቅህ . . . . ክርስቲያኑ የሙስሊሙን የመብትና የነፃነት ጥያቄ በጥርጣሬ የጎሪጥ ከተመለከተዉ፤ ሙስሊሙ ደግሞ ይህንን እሱን በጥርጣሬ የሚለከተዉን ክርስቲያን በትግል አጋርነቱ ካላመነዉና ካልተቀበለዉ እንዴት ሆኖ ነዉ የኛ ትግል ግቡን መትቶ አገራችን የምንገባዉ? ይሄዉልህ ተክሌ በዚያ አስቀያሚ የፖሊስ ዱላህ ደጋግመህ የጨረገድከዉ ሰዉ እንዲህ አይነቱን አንተ አይቶ ለመረዳት አመትና ሁለት አመት የሚፈጅብህን ነገር እሱ በግዜ አይቶና ተንትኖ ለህዝብ ያቀረበ ሰዉ ነዉኮ! ምነዉ የልጅነት ገደኛዬ እንዲህ ገብስ ሆንክብኝ ከገብስም የነፈዘዉ! ለመሆኑ ጽሁፉን በደምብ አንብበኸዋል ወይስ ለትችት የሚመችህን ቦታ ብቻ ነዉ እየመረጥክ ያነበብከዉ፤ ለዚያዉምኮ አንተኑ ለትችት የሚያጋልጠዉን ቦታ ነዉ የመረጥከዉ። ለነገሩ አንተ መምረጥ መች ታዉቅበታለህ? ብታዉቅ ኖሮ አንዳቅምህ ትኖር ነበር። ዶ/ር ብርሀኑኮ እንደ ማንም ሰዉ የሚተች ሰዉ ነዉ፤ እንዳዉም እንደሱ ለትችት የተጋለጡ የፖለቲካ መሪዎች በጣት የተቆጠሩ ናቸዉ፤ በየቀኑ እንደሰሩ ነዋ! አንተ ግን ወይ አትሰራ፤ ወይ አታሰራ እንዳዉ “ዝናር በቅፌን” ይመስል መናኛ መናኛዉን ኮተት ተሸክመህ ከሚሰሩ ሰዎች ጋር ትቀላቀላለህ። አሁን እስኪ ተክሌ በሞቴ ንገረኝማ . . .  ተክሌ እንዴት ጎበዝ ነዉ፤ ዶ/ር ብርሀኑን እኮ አገኘዉ፤ ልክ ልኩን ነገረዉ ብለዉ ያንተ ብጤ ጥቅት ወናፎች ቢያናፍሱልህ እዝያ ቁመትህ ላይ ስንዝር ይሚጨምሩልህ ይመስልሃል? ቢጨምሩስ?

 

አየህ አቦይ ተክሌ ጽሁፍኮ ፊደልና ፊደል ማገናኘት ስለምንችል ብቻ የምንገባበት የጨረባ ተዝካር አይደለም። መጻፍ ማሰብ፤ ማሰላሰል፤ ማንበብና ነገሮችን የማመዛዘን ችሎታን የሚጠይቅ ትልቅ ስራ ነዉ፤ አንተ ደሞ ነገሮችን መቀላቀል ነዉ እንጂ ከእነዚህ እሴቶች ጋር በተለይ ከማሰብና ከማመዛዘን ጋር ጭራሽ የምትተዋወቅም አይመስለኝም። እዩኝ እዩኝ ትላለህ፤ አወቅኩ አወቅኩ ታበዛለህ። አንዳንዴማ ጭራሽ ካንተ በላይ የሚያዉቅ ሰዉ ያለም አይመስልህም። የሰዉ ልጅ የማዉቁ ትልቁ ምልክት አለማወቁን ማወቁ ነዉ። ኦይ ተክሌ ላንተ ግን ይህ የጠቢባን አባባል ተረት ነዉ የሚመስልህ። እባክህ የማታዉቀዉን ነገር አላዉቅም በል። በተለይ በተለይ የማተዉቀዉ ነገር ላይና በደምብ ያልገባህ ነገር ላይ አትጻፍ፤ አትተች አስተያየትም አትስጥ። ዉድ ጓደኛዬ ተክሌ አንግዲህ አንድም ገና የምታድግ ሰዉ ነህና ደሞም ሰዉ እፈር ተብሎ የሚነገረዉ ዉድቀቱን ሲረዳ ስለሆነ “እፈር “ ብዬህ አፌን አላበላሽም። እስከዛሬ እንዳየሁህ አንተም እንጣጥ እንጣጥ ማለት ነዉ እንጂ እፍረት የሚሰማህ ሰዉ አይደለህም። እንጣጥ የሚያበዛ ሰዉ ደግሞ ያመለጠዉ ለታ ዕድሜ ልኩን ያፍራል። እንግዲህ ይህ መጥፎ ቀን ሳይመጣብህ ከአቅምህ በላይ መዝለሉን አቁም። እርግጠኛ ነኝ ተክሌ ይህንን ጽሁፍ አንብበህ “ዲሞክራሲ” የማይገባቸዉ ሰዎች ሀሳቤን የመግለጽ መብቴን ሊቀሙኝ ነዉ እንደምትል፤ ሆኖም የዚህ ጽሁፍ ጥረት የዲሞክራሲ ጽንሰ ሀሳብ አንዲገባህና ከሰዎች ጋር በቡድን ስትሰራ ሌሎችን ሳትጋፋና ሳታስቀይም ሀላፊነት ተሰምቶህ ግዴታህን እንድትወጣ ነዉ እንጂ የሁላችንም ትግል ለመብት መከበር ነዉና መብትህን የነካም የደፈረም የለም። የፖለቲካ መሪዎቻችንን መተችትና ስህተት ሲሰሩ ተከታትሎ ማጋለጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነገር ነዉ፤ ነገር ግን የሌለ ስህተት እየፈጠርክ፤ ያልተጻፈ  እያነበብክና ሰዎች ደፋር ተቺ ነዉ እንዲሉህ ብቻ የሚሰሩ ሰዎችን ባትቦጫጭቅ ጥሩ ይመስለኛል። አንድ ሰዉ ባጠፋዉ ጥፋት የሚያዝነዉ ለሌሎች ካለዉ ክብርና ፍቅር ነዉና . . .  ተክሌ እስኪ እባክህ ለህዝብ ክብር ስትል ጥፋትህን ተረዳና ከራስህም ከወገንም ጋር ታረቅ። የምትመኘዉን ትልቅ ሰዉ ለመሆን ከፈለግክ የትልቅነት መንገዱ ይህ ነዉ። እግዜር ይርዳህ!


የማለዳ ወግ …አምላክ ሆይ ! የአዲሱ አመት ተስፋና ምኞታችን አሳካው !

$
0
0

YeMaleda Weg
ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ

አንድየ ሆይ! ያላንተ እዚህ መድረስ አይታሰብምና ከሁሉ አስቀድሜ ለከበረው ስምህ ፣ ለማይደፈር ለማይገሰሰው ሰማያዊ ክብርህ ፣ ለቸርነት ፣ ምህረት ይቅርታህ ምስጋና ይድረሰው ! አባታችን አዳም ትዕዛዝክህ ተላልፎ ታላቁን ስህተት ፈጸመ ፣ ከገነትም ተባረረ ! አባት ሆይ ! አዳም አጠፋ ብለህ አልተውከንም ! የምህረት አምላክ ነህና መንግስትህን እንወርስ ዘንድ በህግ ትዕዛዛትህ እንድንመራ አዘዝከን! ዳሩ ግን ትዕዛዛት ህግ ቀኖናህን ስንጥስ ኖርን … ይህ ሆነ ብለህም አልተውከንም …
ያለባላ በዘረጋህው ሰማይ ፣ ያለመሰረት ባነጠፍከው ምድር ፣ በእጹብ ስራህ የምድር መቀነት አድርገህ ባንሰራፋህው ውቅያኖስ እና ወንዝ ደምቀን ስታኖረን የምንበላው የምንጠጣውን የምንለብስ የምንጠለልበት በመለኮታዊ ስልጣን ከቸርነት እና ከምህረትህ ጋር ያልተውከን አንተው ብቻ ነህ ! እናም እናመሰግንሃለን ! ዘመን በዘመን ሲተካ ፣ ትውልድ በትውልድ ሲታደስ የዛሬ ባለተሮች ሆነናልና ለቀኖና ህግ የምንገዛ ለሰማያዊ ትዕዛዝህ የምናከብር አድርገን ! በይቅርታ ቸርነትህ ተጠብቀን አዲሱን አመት ስንቀበል የአዲሱ አመት ምኞታችን ብዙ ነው …ከሁሉም በላይ የሰው ልጅን ኢትዮጵያን እና ህዝቧን አንድነታችን ከሚያናጋ ፣ ህብረታችን ከሚንድ እኩይ ስራ ሁሉ ትጠብቃት ዘንድ ምኞቴ ነው ! በአዲሱ አመት መባቻ አሮጌው አመት ለመሸኘት ስንሰናዳ የሃገር የወገናችን ጉዳይ የሚያሳስበን የሚያስጨንቀን ተጠራርተን እንዲህ ብልን የህብረት ምኞት ተመኘን … አዲሱ ዓመት ሲጠባ፣ በአዲስ መንፈስ አዲስ ሕልም ለአገራችን ብሩህ እድገት ለወገኖቸቻችን ሰላም ጤና ህብረት ጥንካሬ የማለሙንቀዳሚ የምኞት ህልም ለማጠናከር ቃል ገባን። ኢትዮጵያ የብሔር፣ የሃይማኖት፣ የሃብት፣ የትምህርት፣ የፖለቲካ አመለካከት እና ሌሎችም ልዩነቶች አብሮነታችንን የማያደናቅፉባት፤ ከነልዩነታችን በጋራ እድገት የምንጠቀምባት፤ ለሁላችንም እኩል ዕድል እና ተጠቃሚነት የሚቀርብባት፤ ሁላችንም እንደ የችሎታችን ለጋራ ነጻነታችን፣ ደኅንነታችን እና ብልፅግናችን የምንሠራባት ሃገር ትሆን ዘንድ ተመኘን . …ለሃገራችን ብሩህ መጻኤ ህይዎት በጋራ ስኬታማ የምንሆንባት፤ እንዲሁም ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያፈቅራት፣ በዜግነቱ የሚደሰትባትና የሚኮራባት ኢትዮጵያ እንድትሆን በጋራ የአዲስ አመቱን አዲስ ምኞት ተመኘን ! አቤቱ የጭንቀት ምልጃ ልመናችን ተቀበለው ! ተስፋ ምኞታችን አሳካው !
ስደት ክፉ ነገር ነው … በስደት ረክሰናል ፣ በስደት ተዋርደናል ፣ በስደት መልካሙ ገጽታችን ከፍቷል ! ለስደቱ የከፋ መከራ አማኝ ለመሆኔ የአረብ አለም የገፋሁት ህይዎት አማኝ ምስክር መሆኔን በፊትህ ስመሰክር አንተ አታውቀውም ብየም አይደለም ! እናም ለቀሩው ትምህርት ቢሆን ደግሜ ደጋግሜ እናገረዋለሁ !

ለአመታት በከተምኩበት የአረቡ አለም የስደተኛ የከፋ መከራ የከፋ ነው ! የተሻለ ኑሮን ለመግፋት ከሚለው የተሻለ ኑሮ ፈላጊ ይልቅ የኑሮ ውድነት እና ድህነቱ አፈናቀሏቸው ወደ አረብ ሃገራት የሚሰደዱት ወገኖች ስቃይ በቃላት ሊገልጹት የሚቻል ያለመሆኑ ምስጥር ስደቱ ከሞት ጋር ተፋጦ የሚከወን ነው! ይህ በመኖርና አለመኖር መካከል በሚደረገው አሰቃቂ ስደት በሶማሌና በጅቡቲ እና በሳውዲ በቀይ ባህር ማዕበል እና ጭልጥ ባሉ በርሃዎች እልፍ አእላፍ ዜጎች ውሃውና በርሃው እየበላቸው በሃዘን ተለይተውናለል ! በራሳችን አዘዋዋሪ ዜጎች በንዋው ፍቅር ተለክፈው ጨክነው ጎድተውናል! ዜጎች በዘላን ሴሰኛ አረቦች እየተደፈሩ ሊናገሩት የሚሰቀጥጥ ግፍ እየተፈጸመባቸው እስከ ወዲያኛው አሸልበዋል ! ነፍሳቸውን ይማረው ! በባህር እና በበርሃዎች የቀሩትን ዜጎችስቃይ ህልፈት እያመመን ሲቀጥል በውል በማይታይ የማይጨበጥ የሃገራት የህግን ማዕቀፍ ወደ አረብ ሃገራት በኮንትራት ስራ ስም የሚሰደዱ ዜጎች ሰቆቃም ከህገወጡ ስደት ባልተለ የከፋ ሆኗል! ያሳለፍነው አሮጌ አመት ዜጎች ያለ ጠባቂ መብት አስከባሪ እንደጨው ሲበተኑ የሚሰደርስባቸው ፈተና ቀላል አልሆነም! ድህነትንና የኑሮ ውድነትን ሸሽተው የመጡ እድሜ ያልጠገቡ እህቶች እና ወንድሞች መሪር የመከራ ጩኸት ከፍ ብሎ ተሰምቷል ! ብዙዎች ድምጻቸው ሳይሰማ በግፍ ጠፍተዋል ፣ ከሞት የተረፉት በአካልና በመንፈስ ሁከት ደዌ ተሸብበው አብደውና ጨርቃቸውን በአደባባይ ጥለው ያየንበት አሰቃቂ ሰቆቃ ተስተናግዷል ! ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈጸም ለመብት ማስጠበቁ የተሰየሙ ምስለኔዎቻችን የፈየዱልንን የመብት ጥበቃ ከማውሳት የበደሉንን በቁጭት ማዘከሩ ይቀላል ! ይህ ሆነ ብለን ግን አንተን ከማመስገን እና በጎ በጎውን ከመመኘት አንቦዝንም !
አቤቱ አምላክ ሆይ ! የምህረት የቸር አምላክ ነህና በአዲሱ አመት በስደት የተሰበረ ልባችን አጽናው ! ለሃገሩ ለወገኑ ቀናኢ መንግስት ስጠን ! ከተሰየሙለትና ከቆሙለት ሃገር ወገናዊ በጎ አላማ ይልቅ በቡድናዊ ስሜት ኑሯችን ያጨለሙትን ልብ አቅናው ! በመዋዕለ ንዋይ ታውረው በወገን ደም የሚበለጽጉትን አዘዋዋሪ ደላሎች በጭካኔ የታበለ ልብ አራራው !
ከህብረት ይልቅ መለያየትን ፣ ከሰላም ይልቅ ብጥብጥን ከመመኘት ሰውረን ! ክፉ ክፉ ከሚያሳስበን እኩይ ሰይጣናዊ ምግባር እቅበን ! ልዩነታችን ከፍቷልና በህብረት አንድነት ትስስር አሽረው ! አንድ አድርገን ! አዲሱን አመት በአዲስ ተስፋ እጀምረው ዘንድ በማወቅና ባለማዎቅ ያስቀየምኩ ፣ ያስከፋኋቸው ይቅርታየን ይቀበሉ ዘንድ ልባቸውን አራራው ! አቤቱ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ ! አንተም በይቅርታህ ጎብኘን ! ዘመኑን የምህረትና የይቅርታ ዘመን አድርግልን !
አቤቱ ሁሉንም ማድረግ የማይሳንህ አምላክ ሆይ ! የአዲሱ አመት ተስፋና ምኞታችን አሳካው !
አሜን ! ! !
ነቢዩ ሲራክ
መስከረም 1ቀን 2006 ዓ.ም
ከሳውዲ አረቢያ

ርዕዮት ዓለሙ በ እስር ቤት የረሃብ አድማ ጀመረች፤ በሙስና የታሰሩት ኮ/ል ሃይማኖት እያስፈራሯት መሆኑን ተናገረች

$
0
0

 ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ

ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ

የ2005 ዓ.ም በዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የዓማቱ ምርጥ የሴት ጋዜጠኛ በሚል የተመረጠችውና በእስር ቤት እየማቀቀች የምትገኘው ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ከትላንት ጀምሮ ከእናት ከአባት እና ከነፍስ አባት ውጪ እንዳትጠየቅ በመከልከሏ የረሃብ አድማ ላይ መሆኑና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉ በፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው መረጃ ገለጸ።

በቅርቡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ከተመሰረተባቸው ውስጥ አንዷ የሆኑት ኮ/ል ሃይማኖት (በተመሳሳይ ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው እና የጉምሩክ አመራር የነበሩት አቶ ገ/ዋህድ ባለቤት)፤ ርዕዮት ያለችበት ክፍል እንዳሉና፤ ከኮ/ል ሃይማኖት በተደጋጋሚ ዛቻ ፣ ስድብ እና ማስፈራሪያ እየደረሰባት እንደሆነ በዛሬው እለት ሊጠይቋት ለተፈቀደላቸው ለእናቷ ገልፃለች፡፡ እንዲሁም ከማረሚያ ቤቱ የሴት ፖሊሶችና እና ደህንነቶችም ተመሳሳይ ማስፈራሪያ፣ ስድብ እና ዛቻ እየበረታባት እንደሆነ ተናግራለች፡፡

ዛሬ ለበዓል ሊጠይቋት ከሄዱ ቤተሰቦቿ እና ጓደኞቿ መሃል እናቷ ብቻ እንዲያዩአት የተፈቀደላቸው ሲሆን፤ እየደረሰባት ያለውን የሰብአዊ ጥሰትም በመቃወም ከትላንት ጀምሮ የምግብ አድማ ላይ መሆኗን በመግለጿ፤ ይዘውላት የሄዱትን ምግብ መልሰውታል ያለው ጋዜጠኛው “በዚህ ስሜት ውስጥ ያሉትን የርዕዮት ቤተሰቦች ለማፅናናትም የሚከብድ ነገር ነው፡፡” ሲል ስሜቱን ገልጿል።

የዓመቱ የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ምርጥ ሰው –የአንዷለም አራጌ የሕይወት ገድል

$
0
0

በ1997 ዓ.ም ኢዴፓ /ቅንጅትን ወክሎ በተወለደበት ክ/ሀገር ፋርጣ ወረዳ ለተወካዮች ም/ቤት ተወዳድሯል:፡ በምርጫው ውጤት ቅንጅት ቢያሽንፍም ከፍተኛ አመራሩና አባላቱ በተለያዩ እስርቤቶች ሲታሰሩ እሱም አብሮ ቃሊቲ እስር ቤት ለሁለት ዓመታት ቆይቷል፡: በሁለት ዓመት ቆይታውም የብረት ግድግዳ በመሆን ፅናቱን አስመስክሯል:፡ ከእስር ቢለቀቅም ከፖለቲካው ወደ ኋላ አላፈገፈገም፡ አንድነት ፓርቲን በመቀላቀል የብሔራዊ ም/ቤትና የሥራ አሥፈፃሚ አባል በመሆን ለዋና ጸሐፊነት ተመርጦ ላንድ ዓመት በቆራጥነት አገልግሏል፡: ብቃቱን በማስመስከሩም በም/ሊቀመንበርነት የሕዝብ ግንኙነት ሐላፊ ሆኖ ተመርጦ በማገልገል ላይ እንዳለ፤ በተጨማሪም የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር እንዲሆን ብዙዎች እየቀሰቀሱ ባለበት ወቅት ነው ርምጃው ያልጣመው ገዥው ፓርቲ ከግንቦት 7 ጋር በማገናኘት የሽብርተኝነት ጥላሸት በመቀባት መስከረም 3 ቀን10 ሰዓት ላይ ከመንገድ የታጠቁ ኃይሎች ከመኪና አስወርደው ይዘውት በመሄድ አሁን እድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ይገኛል።
Andualem Arage
አንዱዓለም አራጌ ማነው? ለሚለው ጥያቄ ለአንባቢያንና ለውጥ ለማምጣት ለሚታገልለት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሕይወት ታሪኩ ትንሽ ጨለፍ አድርገን ለመፈንጠቅ እንሞክራለን።

የትውልድ አካባቢና የልጅነት ጊዜ አቶ አንዱዓለም አራጌ በጎንደር ክ/ሀገር በደብረታቦር አውራጃ በፋርጣ ወረዳ ጉና ተራራ ሥር ወይንም ግርጌ ክምር ድንጋይ ከተባለ ቦታ በ65 ዓ.ም ጥቅምት25 ቀን ተወለደ፡፡ የኢትዮጵያ አብዮት ሊፈነዳ ሁለት ዓመት ሲቀረው በምጥ ዋዜማ ማለት ነው፡፡ “ሰው አካባቢውን ይመስላል” እንደሚባለው አንዱዓለም አራጌ በክ/ሀገሩ ከራስ ዳሽን ተራራ ቀጥሎ በሁለተኛደረጃነት ከሚጠቀሰው ጉና ተራራ ስር በመወለዱ ለኢሕአዴግ እንደ ጉና ተራራ ኮርቶና ከብዶ ታይቶታል፡፡ እናም አስሮ በሽብርተኝነት በመወንጀል አሞቱን ያፈሰሰ መስሎታል፡፡ አንዱዓለም አራጌ ግን እንዲህ በቀላሉ የሚፈታ አይደለም፡፡ ለምንም ነገር የማይበገር፣ ችግር የማይፈታው፣ ለቆመለት ዓላማ ወደ ኋላ የማይል፣ ከሁሉም በላይ ቅጥፈትንና እብለትን አጥብቆ ይጠየፋል፡፡ባጭሩ ትክለ ሰውነቱ ወይንም nስብእናው በቁም ነገር የታነፀ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ለቆመለት ዓላማና ላመነበት ነገር ያላንዳች ይሉኝታና ፍርሃት ሽንጡን ገትሮ ይከራከራል፡፡
በዚህ አቋሙና ፅናቱም ነው ገና በለጋ እድሜው ሩጦ ሳይጠግብ፣ ሠርቶ ሣይደክም በተደጋጋሚ የእሥር ሰለባ ለመሆን የበቃው፡፡

አ ን ዱ ዓ ለ ም አራጌ አሥራ አንድ ዓመት እስከሚሞላው ድረስ ክምር ድንጋይ ከወላጆቹ ጋር ቆይቷል፡፡ አባቱ የቤተ ክህነት ሰው በመሆናቸው ልጃቸው በፅኑ የግብረገብ ሥነ ምግባርኮትኩተውና ገርተው ከማሣደጋቸውም በላይ የቤተክህነት ትምህርት እንዲማርላቸው በመሻት ካንድ ከታወቁ መርጌታ ልከውት በተመላላሽነት እየተማረ እንዳለ አዲስ አበባ የሚኖሩ አያቱ ክምርድንጋይ ይሄዳሉ፡፡ እሳቸውም የቤተክህነት ሰው ነበሩና ንቃቱን፣ ጨዋነቱን፣ ትህትናውንና አርቆ አስተዋይነቱን በዚያች አጭር ጊዜ ቆይታቸውአስተዋሉና “ይኸ ልጅ ዘመናዊ ትምህርት መማርአለበት” ብለው ወደ አዲስ አበባ ይዘውትይመጣሉ፡፡ሕይወት በአዲስ አበባአንዱዓለም አራጌ ካያቱ ጋር አዲስ አበባ ከመጣ በኋላ መስከረም መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በመግባት ከ1-8ኛክፍል ድረስ ሁለት ጊዜ ደብል ወይንም አጥፎ በማለፍ በ6 ዓመት ውስጥ ስምንተኛ ክፍልን አጠናቀቀ፡፡

Andualem Arage kids
ዘጠንኛና አሥርኛ ክፍልን የተማረው ኮከበ ጽባህ ሲሆን የደረጃ ተማሪ ስለነበር 11ኛና 12ኛ ክፍልን የተማረውና ከፍተኛ ውጤት አምጥቶ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለመግባት የበቃው በሳንጅዮሴፍ ት/ቤት በመማር ነበር፡፡ አንዱዓለም አራጌ በከፍተኛ ውጤት አ.አ.ዩ በመግባት በታሪክ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል፡፡በዩኒቨርስቲ ቆይታውም በተለያዩ ክበባት በመግባት በኃላፊነትም ሆነ በአባልነት ካንድ ንቁ ተማሪየሚጠበቅበትን ግዴታ ተወጥቷል፡፡ በዩኒቨርስቲው ውስጥ በአራት ዓመት ቆይታው የት/ቤት ጓደኞቹ በሚያደርጋቸው ክርክሮችና በአቋሙ ፅናት እጅግ አድርገው ያደንቁት እንደነበር ዛሬ በቅርብየሚያውቁት ይናገራሉ፡፡

አንዱዓለም አራጌ ከሚታወቅባቸው ቁም ነገሮች መሀከል ባገራችን ገና የሰላማዊ ትግል ፅንስ ሐሳብ በቅጡ ባልታወቀበት ወቅት እሱ ሰለሰላማዊ ትግል ይሰብክ ነበር፡፡ ይህንንም ሲያደርግ የአንጋፋሰላማዊ ታጋዮችን አርማ በማንሳትና መርሃቸውን እንደ ምርኩዝ በመጠቀም ነው፡፡ ማርቲን ኪንግ፣ ማንዴላ፣ ማኅተመ ጋንዲን ታሪካቸውን በማጥናትና የሄዱበትን መንገድ በመከተል በዩኒቨርስቲቆይታው መርሃቸውን መርሁ በማድረግ የትግል ብቃቱን እንዳዳበረ በቅርብ የሚያውቁት በአጽንኦት ይናገራሉ፡፡ የአንዱዓለም አራጌ ልዩ ባህሪውና ተሰጥኦው ወይንም ትክለ ሰውነት ከላይ ለመጥቀስእንደሞከርነው በሰላማዊ ትግል ገና ከወጣትነቱ ዕድሜው ጀምሮ ቆርቦ እያለ ገዥው ፓርቲ “ሽብር አራማጅ” ብሎ በመወንጀል ጥላሸት ሲቀባው ማየትና መስማት ያለንበትን ዘመንና ሥርዓት ምንያህል አስጨናቂና አስከፊ እንደሆነ መገመቱ ከባድ አይሆንም፡፡ እያንዳንዳችንም ውለን ስለመግባታችን ዋስትና የለንም፡፡ ሁላችንም የሱ እጣ እንደሚጠብቀንና ጥላሸት እንደምንቀባም በርግጠኝነትመናገር እንችላለን፡፡

የሥራ ዓለምአንዱዓለም አራጌ ከአ.አ.ዩ ትምህርቱን ጨርሶ ከወጣ በኋላ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ እየተቀጠረ ሠርቷል፡፡ ከነዚህ ውስጥ የዓለም ባንክና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች መኅበርበግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

የፖለቲካ ሕይወቱ

አቶ አንዱዓለም አራጌ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቆይታው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የፖለቲካ ሀሁን ከመቁጠር ጀምሮ በማዳበር ብስለቱን ያስመስከረ ቢሆንም በድርጅትውስጥ ታቅፎ መታገል የጀመረው ግን በ1992 ዓ.ም የኢዴፓ መሥራች አባል በመሆን ነበር፡፡ በኢዴፓ ውስጥ በቆየባቸው ዓመታትም ከቋሚ ኮሚቴ አባልነት ጀምሮ ደረጃ በደረጃ አድጎ ም/ዋናጸሐፊ በመሆን በከፍተኛ ኃላፊነት ሠርቷል፡፡ በመሆኑም በ1997 ዓ.ም ኢዴፓ /ቅንጅትን ወክሎ በተወለደበት ክ/ሀገር ፋርጣ ወረዳለተወካዮች ም/ቤት ተወዳድሯል። በምርጫው ውጤት ቅንጅት ቢያሽንፍም ከፍተኛ አመራሩና አባላቱ በተለያዩ እስር ቤቶች ሲታሰሩ እሱም አብሮ ቃልቲ እስር ቤት ለሁለት ዓመታት ቆይቷል፡፡ በሁለት ዓመት ቆይታውም የብረትግድግዳ በመሆን ፅናቱን አስመስክሯል፡፡ ከእስር ቢለቀቅም ከፖለቲካው ወደ ኋላ አላፈገፈገም፡፡ አንድነት ፓርቲን በመቀላቀል የብሔራዊ ም/ቤትና የሥራ አሥፈፃሚ አባል በመሆን ለዋና ጸሐፊነት ተመርጦ ላንድ ዓመት በቆራጥነት አገልግሏል፡፡

ብቃቱን በማስመስከሩም በም/ሊቀመንበርነት የሕዝብ ግንኙነት ሐላፊ ሆኖ ተመርጦ በማገልገል ላይ እንዳለ ነው ርምጃው ያልጣመው ገዥው ፓርቲ ከግንቦት 7 ጋር በማገናኘት የሽብርተኝነት ጥላሸት በመቀባት መስከረም 3 ቀን 10 ሰዓት ላይ ከመንገድ የታጠቁ ኃይሎች ከመኪና አስወርደው ይዘውት የሄዱት፡፡
Andualem 2-10-2 (2)
የቤተሰብ ሁኔታ
ወጣቱ ፖለቲካኛ አንዱዓለም አራጌ ባለትዳርና የሁለት ህፃናት አባት ነው፡፡ አንዱዓለም አራጌ ትዳር የመሠረተው ከእስር ከተፈታ በኋላ በ2000ዓ.ም ከዶ/ር ሰላም አስቻለው ጋር በሥርዓተ ተክሊልነው፡፡

አንዱ ዓለም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ባደረገው የነፃነት ትግል ወህኒ ተወርውሮ ጠባብ ክፍል ውስጥ ቢቀመጥም በፍርድ ቤት የሚከተለውን ተናግሮ ነበር፦
“መንግሥት ለኢትዮጵያ ሕዝብ የአፋና ሥራ እየሠራ ነው፡፡ እኔም አንዱ የዚህ ሰለባ ነኝ፡፡ ፍ/ቤት ነፃ ሆኖ የራሱን ሂደት ያያል የሚል እምነት ስለሌለኝ እስከመጨረሻው የሞት ፍርድ ድረስ ቢደርስብኝም ከመቀበል ሌላ የምከራከረውም ሆነ የምናገረው ነገር የለኝም”
አንዱዓለም አራጌ መስከረም 4 ቀን2004ዓ.ም፡፡

የሕሊና እስረኛው አንዷለም አራጌ የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የ2005 ዓ.ም ምርጡ ሰው ተብሎ ተመርጧል።

2005 እንዴት አለፈ? –የአመቱ አበይት ክንውኖች –በማህሌት ፋንታሁን Zone 9

$
0
0

ዶ/ር መሠረት ቸኮል

ዶ/ር መሠረት ቸኮል

በማሕሌት ፋንታሁን

ክቡራት የዞን 9 ነዋሪዎች ዓመቱ ከማለቁ በፊት እንዴት እንዳለፈ ለማስታወስ እንዲረዳን በማሰብ በ2005 የተከናወኑ አበይት ተግባራትን በዓመቱ የጊዜ መሥመር ላይ እንደሚከተለው ለማሳየት ሞክረናል፡፡ መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ፡፡
መስከረም
•  መስከረም 11/2005 የተከበሩ ኃ/ማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ሆነው፣ የተከበሩ ደመቀ መኮንን ደግሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ቃለ መሐላ ፈፀሙ፣
•  መስከረም 17 ቀን 2005 ድምፃዊ ቴድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በሒልተን ሆቴል አንድ ሺሕ ያህል ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ጋብቻውን ፈፀመ፣
ጥቅምት
•  ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ አሜሪካን ሃገር ከሚገኘው የዓለም አቀፉ የሴቶች ሚዲያ ፋውንዴሽን የ2012 ‹ፅናት በጋዜጠኝነት ሥራ› የተሰኘ ሽልማት አገኘች፣
•  የ2005 የእስልምና ምክር ቤት /መጅሊስ/ ምርጫ በየቀበሌው ተካሄደ፣
ሕዳር
•  የጋዜጠኝነት እና የኮሚውኒኬሽን ባለሙያ ዶ/ር መሠረት ቸኮል ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፣
•  ጠ/ሚኒስቴር ኃ/ማርያም ደሳለኝ አቶ ቴድሮስ አድሃኖምን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤አቶ ሙክታር ከድር እና ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በጠ/ሚኒስቴርነት ማዕረግ የሲቪል ሰርቪስ፣ የትራንስፖርት እና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር፤ አቶ ከበደ ጫኔን የንግድ ሚኒስቴር እንዲሁም ዶ/ር ከሰተብርሃን አድማሱን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አድርገው ሾሙ፣
tewedrosታኅሳስ
•  በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ የወንጀል ችሎት በቀረበባት የሽብርተኝነት ወንጀል 14 ዓመታት እስርና 33 ሺሕ ብር ቅጣት የተጣለባት ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮተ ዓለሙ፣ በይግባኝ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የእስር ጊዜዋን ወደ አምስት ዓመታት በመቀነሱ ምክንያት ለሰበር ችሎት “በሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል” ስትል አቤቱታ አሰምታ፤ ሠበር ሰሚ ችሎቱ በሰጠው የመጨረሻ የቅጣት ውሳኔ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያስተላለፉትን የቅጣት ውሳኔ አፀና፣
•  የአውሮፓ ፓርላማ አባላት ለጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ፤ ከሽብርተኝነት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ክስ ተመስርቶበት የ18 ዓመት እስር የተፈረደበት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በአፋጣኝ ከወህኒ ቤት እንዲለቀቅ ጥያቄ አቀረቡ፣
•  አራት በፍ/ቤት እስር የተፈረደባቸው የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች የ2012 የሄልማን/ሃሜት ሽልማት መሸለማቸውን፤ ተሸላሚዎቹ በእስር ላይ የሚገኙት እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታዬ እንዲሁም በሌለበት የተፈረደበት የቀድሞዋ የ“አዲስ ነገር” ጋዜጣ አዘጋጅ መስፍን ነጋሽ ሲሆኑ ጋዜጠኞቹ ሽልማቱን ያገኙት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ለማስጠበቅ ላደረጉት ጥረት መሆኑም ተጠቅሷል፣
ጥር
•  የ33ቱ ፓርቲዎች ኅብረት በሚያዚያ ወር የተካሄደውን የአዲስ አበባ መስተዳደር እና በመላው ሃገሪቱ በሚካሄደው የወረዳና የክልል ምክርቤቶች ምርጫዎች ላይ ላለመሳተፍ ውሳኔ አሳለፉ፣
•  በአሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው የሚመራው ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ31 ዓመታት ቆይታ በኋላ በደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ በቃ፤ በዚሁ የአፍሪካ ዋንጫ ላይ አዳነ ግርማ ከ37ዓመት በኋላ የመጀመሪያ የሆነችውን ብቸኛ ጎል ለኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ አስቆጠረ፣
•  ኢትዮጵያ የራሷን ሳተላይት ለማምጠቅና የሰው ኃይሏን ከቴክኖሎጂው ጋር ለማስተዋወቅ የሚያስችል የሙከራ ሥራ መጀመሯን፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚ ዘርፍ አስተባባሪና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል አስታወቁ፣
•  በ2004 ከሃያ ዓመት እስር በኋላ የተፈቱት ከፍተኛ የደርግ አመራር የነበሩት ኮሎኔል ደበላ ዴንሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፣

አቡነ ማቲያስ

አቡነ ማቲያስ

የካቲት
•  ድምፃዊ ታምራት ሞላ ለረጅም ዓመታት ሕክምና ሲከታተል በነበረበት የደም ካንሰር ሕመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፣
•  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክርስቲያን 6ኛውን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስን አድርጋ መረጠች፣
•  የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ተባባሪ ፕሮፌሰር የነበሩት ዶክተር ዮናስ አድማሱ በ69 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፣
•  በአዲስ አበባ በባሕል ሕክምና ታዋቂ የነበሩት ሐኪም ማሞ ኃይሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፣
•  ከሁለት ዓመት በፊት በአምባሳደርነትና በምክትል አምባሳደርነት ማዕረጐች ተሹመው በተለያዩ አገሮች ከተመደቡ የቀድሞ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል ዐሥራ ስምንት የሚሆኑት ወደ አገር እንዲመለሱ ተደረገ፤ ሁለቱ በድጋሚ ሹመት ወደሌሎች አገሮች ሲመደቡ የተቀሩት ግን በአገር እንዲቀሩ ውሳኔ ተላለፈ፣
መጋቢት
blue party•  በኢትዮጵያ ሕዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ፣ በሰማያዊ ፓርቲ እና በባለራዕይ ወጣቶች ማኅበር አስተባባሪነት፤ በጣሊያን አፊሌ በተባለ ቦታ የተገነባውን የግራዚያኒ ኀውልት እና መታሰቢያ ቦታ በመቃወም፤ ከሰማእታት ኀውልት (6 ኪሎ) አንስቶ እስከ ጣሊያን ኤምባሲ የሚዘልቅ የእግር ጉዞ መጋቢት 8/2005 ጥሪ ተላለፈ፤ ሰልፉን ለማካሄድ የተገኙ አባላት እና የሰልፉ ዓላማ ደጋፊዎች ሰማእታት ኀውልት መሰባሰብ እንደ ጀመሩ ፖሊስ ሰልፉን ሕጋዊ አይደለም ብሎ በኃይል በመበተን እና 40 የሚሆኑ በሰልፉ የተገኙ ሰዎች ለአንድ ቀን ታስረው ተፈቱ፣
•  የኢሕአዴግ ዘጠነኛ ጉባዔ በባሕር ዳር ከተማ ለአራት ቀናት ተካሄደ፣
•  ‹ኢትዮትዩብ› በአሜሪካ አምስተኛ ዓመቱን አከበረ፣ በዕለቱም ‹ለፕሬስ ነፃነት የተጋ› በሚል ዓመታዊ ሽልማት ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተሸላሚ በወኪል ተበረከተለት፣
•  የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መታሰቢያ “መለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን” መሥራች ጉባኤ በአፍሪካ ኅብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄደ፣
ሚያዚያ
abune_petros•  ላለፉት አምስት ዓመታት በተደረገ ኮንትራት አማካኝነት በአሜሪካ ስትጎበኝ የነበረችው ሉሲ (ድንቅነሽ) ጉዞዋን ጨርሳ ወደ ሃገሯ ተመልሳ ለሕዝብ ዕይታ ክፍት ሆነች፣
•  ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ጀርባ የሚገኘው የአቡነ ጴጥሮስ ኀውልት፤ በአዲስ አበባ በመሠራት ላይ በሚገኘው የቀላል ባቡር ግንባታ ምክንያት ከነበረበት ቦታ ተነስቶ ብሔራዊ ሙዚየም እንዲገባ ተደረገ፣
•  በጋምቤላ ክልል አኙዋክ ዞን አቦቦ ወረዳ ልዩ ቦታው ቁርጫ በሚባል አካባቢ 17 ተማሪዎችንና በኢንቨስትመንት ሥራ ላይ የተሠማራው ሳዑዲ ስታር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሠራተኞች የሆኑ ስድስት ሰዎችን፣ በድምሩ 23 ሰዎችን በጥይት ደብድበው በመግደልና በሽብር ወንጀል ተከሰው ከነበሩት 14 ግለሰቦች መካከል፣ ዘጠኙ በሞት እንዲቀጡ ተወሰነባቸው፣
•  ጋምቤላን ለሰባት ዓመታት በፕሬዚዳንትነት የመሩት አቶ ኡሞድ ኡቦንግ የጋምቤላ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) እና የክልሉ ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ከፓርቲው ምክትል ሊቀመንበርነትና ከክልሉ ፕሬዚዳንትነት እንዲነሱ በመወሰኑ፣ ምክትል ፕሬዚዳንቱ አቶ ጋትሉዋክ ቱት በምትካቸው የክልሉ ፕሬዚዳንትነት ሆነው ተሾሙ፣
•  የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰኔ 20 ቀን 2004 ዓ.ም. የሰጠውን የጥፋተኝነት ብይንና ብይኑን ተከትሎ የተጣለባቸውን የቅጣት ውሳኔ በመቃወም፣ ከነሐሴ ወር 2004 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ አቤቱታ አቅርበው በነበሩት፣ እነ እስክንድር ነጋ ላይ ሚያዝያ 24 ቀን 2005 ዓ.ም. የመጨረሻ ውሳኔ ተሰጥቶ ይግባኝ ካሉት ፍርደኞች ውስጥ ከክንፈሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ) በስተቀር የሁሉም የሥር ፍርድ ቤት ቅጣት ውሳኔ እንዲፀና ተደረገ፤ በመሆኑም ክንፈሚካኤል በሥር ፍርድ ቤት ተጥሎበት የነበረው የ25 ዓመት ፅኑ የእስራት ቅጣት ማቅለያው ሲያዝለት ወደ 16 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀነሰ፣
•  የፌዴራሉ ዋና ኦዲተር በ124 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች የ2004 ዓ.ም. ሒሳብን ኦዲት በማድረግ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርብ፣ መንግሥት ሊያገኘው የሚገባ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አለመታወቁንና በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ደግሞ መንግሥት ማጣቱን አሳወቀ፤ ከዚህ ውስጥ ትምህርት ሚኒስቴር 401.757 ሚሊዮን ብር የሚሆነውን ከፍተኛ ድርሻ የያዘ ሲሆን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 173.756 ሚሊዮን ብር፣ የግብርና ቴክኒክ ሙያና ትምህርት ሥልጠና ፕሮጀክት ማስተባበሪያ 155.597 ሚሊዮን ብር የታየባቸው መሥሪያ ቤቶች መሆናቸው ተገለፀ፣
ግንቦት
Melaku-Fenta-and-Gebrewahid-Woldegiorgis•  የፌደራል ፀረ ሙስና እና የሥነ ምግባር ኮሚሽን የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መላኩ ፋንታን ጨምሮ ሌሎች የባለሥልጣኑ ኃላፊዎችና ባለሀብቶች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በመዋላቸው የክስ የፍርድ ሒደቱ ተጀመረ፣
•  በባሕርዳር ከተማ የፌደራል ፖሊስ አባል የሆነ ግለሰብ በከፈተው ተኩስ 10 የሚሆኑ ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ ወንጀለኛው ፖሊስም ራሱን አባይ ወንዝ ውስጥ ወርውሮ ሕይወቱን አጠፋ፣
•  በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ዣቪየር ማርሻል በ61 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፣
•  በከፍተኛ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር በዋሉት በሚኒስትር ማዕረግ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ ምትክ፣ የአዳማ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አቶ በከር ሻሌ ተሾሙ፣
•  በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በመምህርነት፣ በተመራማሪነት እና በልዩ ልዩ የኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉት እና “ቤተ ክሕነትና መንግሥት በኢትዮጵያ ከ1262-1527” (Church and state in Ethiopia 1262-1527) በተሰኘው መጽሐፋቸው የሚታወቁት ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፣
•  አዲስ አበባ የሚከበረውን የአፍሪካ ሕብረት 50ኛ ዓመት የወርቅ እዮቤልዩ በዓል ላይ ሰማያዊ ፓርቲ ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ቢያደርግም የአ.አ መስተዳድር ሰልፉን ጥበያ የሚያደርግ የፖሊስ ኃይል እጥረት አለብን በማለት ለሌላ ጊዜ እንዲያዘዋውሩት ጠየቀ፣
•  የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/የአፍሪካ ኅብረት የተመሰረተበትን 50ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች ዋናው ጽ/ቤት በሚገኝበት በኢትዮጵያ አከበረ፣
•  የሕዳሴው ግድብ ቀጣይ የግንባታ ምዕራፍ የሆነው ወንዙን አቅጣጫ የማስቀየስ ሽራ ተከናወነ፣ ይህን ተከትሎም ከሃገሪቷ ፖለቲከኞች ጋር በቀድሞው የግብፅ ፕሬዝዳንት ሙርሲ የተመራ ውይይት ሲካሄድ የግድቡ ሥራ እውን እንዳይሆን የሚያደርጉ ሐሳቦች መሰንዘራቸው፤ ይህ ውይይትም በስህተት በሃገሪቱ የብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣቢያ በቀጥታ ተላለፈ፣
•  ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ ከተማ መነሻውን የፓርቲው ፅ/ቤት፤ መድረሻ ቦታውን ኢትዮ-ኩባ አደባባይ ያደረገ፣ በርካቶችን ያሳተፈ እና ከ97 ምርጫ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄደ፣
UDJ Candlelight vigilሰኔ
•  አንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ‹‹ሚሊዮን ድምፆች ለነፃነት›› የተሰኘ፣ ለሦስት ወራት የሚቆይ ሕዝባዊ ንቅናቄ ጀመረ፤ በንቅናቄው ሕዝባዊ ስብሰባዎች፣ ሠላማዊ ሰልፎችና በፀረ-ሽብር ሕጉ ላይ የተቃውሞ ፊርማ እንደሚሰበሰብ ተነግሯል፣
•  ለቀደሙት 20 ወራት በሽብር ወንጀል ተፈርዶበት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኘው ጋዜጠኛ፣ ጦማሪ እና አራማጅ እስክንድር ነጋ፤ ከባለቤቱ እና ልጁ ውጪ በሆኑ ቤተሰቦቹ፣ ወዳጆቹ እና አድናቂዎቹ እንዲጎበኝ ሲፈቀድለት የሚጎበኝበት ሰዓትም እንደማንኛውም በማረሚያ ቤቱ የሚገኙ ታራሚዎች እንደሆን ተደረገ፣
•  በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የ2013ቱ የቢግ ብራዘር አፍሪካ ውድድር ከኢትዮጵያ የሄደችው ቤቲ የወሲብ ትእይንና አነጋጋሪ መሆን፣
•  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሦስተኛውን ጨዋታ በሃገሩ አድርጎ ተጋጣሚውን ደ/አፍሪካን 2-1 በመርታት የቀሪውን ጨዋታ ነጥብ ሳያሳስበው ምድቡን በአንደኝነት መምራቱን ቢያረጋግጥም በማግስቱ በፌዴሬሽኑ ስህተት ብሔራዊ ቡድናችን ሦስት ነጥቦችንና ሦስት ጎሎች የሚያስቀጣውን ጥፋት ማጥፋቱን ተነገረ፣
•  ፓርላማው በ2005ዓ.ም የሥራ ዘመን ማጠናቀቂያ ላይ የሥልጣን ሹም ሽር በማድረግ አስር አዳዲስ ሚኒስተሮች ሾመ፣
betty-bba-chase-ethiopia•  የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ወደ ኮንፌደሬሽን ካፕ የምድብ ማጣሪያ ያለፈ የመጀመርያ ክለብ መሆኑ፣
ሐምሌ
•  ወጣት የፖለቲካ ተንታኙ ጃዋር መሐመድ አልጀዚራ የቴሌቪዥን ጣቢያ በሚያዘጋጀው ‹ዘ ስትሪም› በተሰኘ ፕሮግራም ላይ ስለ ኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ እና ተያያዥ ጉዳዮች የብዙዎችን (በተለይም ማኅበራዊ አውታር ተጠቃሚዎችን) ትኩረት የሳበ እና ያነጋገረ ንግግር አደረገ፤
•  አንድነት ፓርቲ በጎንደርና ደሴ ከተሞች በተመሳሳይ ቀን (ሐምሌ 7/2005) ‹‹ሚሊዮን ድምፆች ለነፃነት›› በተሰኘው ሕዝባዊ ንቅናቄው ሠላማዊ ሰልፎችን አካሄደ፣
•  አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገ/ሥላሴ ከሁለት ዓመት በኋላ በሚካሄደው በ2007ቱ ጠቅላላ ምርጫ አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ በመወዳደር ወደ ፓርላማ ለመግባት ማቀዱን በቃለ ምልልሶች አረጋገጠ፣
ነሐሴ
merara gudina•  የአምስት ፓርቲዎች ጥምረት የሆነው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት መድረክ ዶ/ር መረራ ጉዲናን ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ፣
•  1434ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች በተለይ በአዲስ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም ሲከበር፣ ፌደራል ፖሊስ በዓሉን ለማክበር የተገኙትን በርካታ ሰዎች ላይ እስር እና አካላዊ ጥቃት ፈፀመ፣
•  ሞስኮ በተዘጋጀው የ14ኛው የዓለም አትሌትክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 3ት የወርቅ፣ 3ት የብር እና 4ት የነሃስ ሜዳሊያ በማግኘት ከዓለም 6ኛ ከአፍሪካ 2ኛ ሆና አጠናቀቀች፤ ወርቁን ያስገኙት ዝነኞቹ የረጅም ርቀት ተወዳዳሪዎች ጥሩነሽ ዲባባ እና መሰረት ደፋር እንዲሁም በታሪካችን ለመጀመሪያ ጊዜ የሆነውን የ800ሜ ርቀት አሸናፊ መሐመድ አማን ናቸው፣
•  የአቡነ ጳውሎስ እና የቀድሞ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ሙት ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበሩ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሙት ዓመት ለማክበር መንግሥት አረንጓዴ ዘመቻ አደረገ፣ በርካታ ፓርኮችንም በስማቸው ተሰየመላቸው፣
•  ወጣቱ ድምፃዊ ኢዮብ መኮንን ባደረበት ድንገተኛ ሕመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፣
•  የ33ቱ ፓርቲዎች ዐቢይ ኮሚቴ ባደረገው የጋራ ስብሰባ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት በየጋዜጣው ላይ የሚሰጡት መግለጫ የፓርቲው አቋም መሆኑ በመረጋገጡና በጋራ ለመሥራት ከተስማሙበት የጋራ ሰነድ ውጪ ሆነው መርሖችን በመጣላቸው ምክንያት ፓርቲው ከኅብረቱ መታገዱን አሳወቁ፣
•  ሰማያዊ ፓርቲ ነሐሴ 26/2005ዓ.ም በአዲስ አበባ ሊያካሂድ ያቀደውን እና ከሦስት ወር በፊት ሲያስተዋቅ እንዲሁም ዝግጅት ሲያካሂድ የከረመበትን ሠላማዊ ሰልፍ፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ ሰልፉ እንዳይካሄድ ከለከለ፣
•  በተለያዩ የእምነት ተቋማት ኅብረት ጠሪነት፤ በመንግሥት ወኪሎችና የኢሕአዴግ አባላት ቀስቃሽነት የሃይማኖት አክራሪነትና ፅንፈኝነትን ለመቃወም በሚል ነሐሴ 26/2005ዓ.ም በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሠልፍ ተካሄደ፣
Ethiopia national teamጳጉሜ
• የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ የምድብ ማጣርያ ከሴንትራል አፍሪካ ሪፐብሊክ ጋር ኮንጎ ብራዛቪል ላይ ገጥሞ ተጋጣሚውን 2 ለ 1 በመርታት፤ ምድቡን በመሪነት በማጠናቀቅ አፍሪካን የሚወክሉ 5 ቡድኖች ተለይተው ለሚወጡበት 10 ብሔራዊ ቡድኖች ለሚያደርጉት የደርሶ መልስ ጥሎ ማለፍ ከገቡት ውስጥ መካተት ቻለ፡፡

Health: ኮሌስትሮልዎ ከፍ ያለ ከሆነ ዓመት በዓሉን የግድ በሥጋ ብቻ ማክበር የለብዎትም

$
0
0

ከዶ/ር ዓብይ ዓይናለም
ኮሌስትሮል ከተለያዩ ምግቦች ወደ ሰውነት ዘልቆ እና ከመጠን አልፎ ሲጠራቀም የደም ባንቧዎች ግድግዳና መንገዳቸው ላይ በመለጠፍና መንገዱን በማጥበብ ደም እንደልቡ ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች እንዳይደርስ ያግዳል፡፡ ይህም ለህዋሳቶች በህይወት መቆየት ወሳኝ የሆኑት ንጥረ ነገሮችና ኦክስጅንም አይሄዱም ማለት ነው፡፡ በጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስና ኦክስጅን ማጠርን ተከትሎ የሚመጣው እንደኩላሊት ድክመት አይነት ክፉ ህመሞችም ከሚከሰቱባቸው መንስኤዎች ዋነኛውም ይኸው የኮሌስትሮል ጠንቅ ነው፡፡ ኮሌስትሮል በተፈጥሮው ክፋት ያለው ቅባት አይደለም፡፡ የተለያዩ የፆታ ሆርሞኖችን ጨምሮ የሚዘጋጁበት ንጥረ ነገር በመሆኑ ለሰውነታችን እጅግ በጥቂት መጠኑ ያስፈልገዋል፡፡ ነገር ግን በተለያዩ ምግቦች ስንወስደው ይጠራቀምና መዘዝ ያመጣል፡፡ እሾህን በእሾህ ነውና ባለሞያዎች ዋነኛዎቹ ኮሌስትሮልን ከደም ውስጥ በከፍተኛ ምጣኔ ለማውረድና ከመዘዞቹ ለመጠበቅ ከሚመክሩዋቸው ማርከሻዎች ውስጥ ዋናኛዎቹ ምግቦች ሆነው ተቀምጠዋል፡፡ በተለያዩ በሳይንስ በተረጋገጡ መንገዶች ከመድኃኒት ይልቅ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው የኮሌስትሮል ምጣኔያቸው ከፍተኛ ለሆኑ ሰዎችና ለሌሎች ወደዚያው እየተንደረደሩ ላሉትም እንዲያዘወትሩዋቸው የተመከሩ ምግቦች ላይ በዛሬው ሜዲካል ፊቸራችን ትኩረት አድርገናል፡፡ እነዚህ ከመድኃኒት ይልቅ የተመረጡት የኮሌስትሮል መቀነሻ ምግቦች የትኞቹ ይሆኑ? በምን አይነት አሰራር? – አዲሱ ዓመት ኮሌስትሮላችንን የምንቀንስበት ይሁን!
aokado
1. አፕል
አፕል በተለይ መጥፎ የሚባለውን አይነት የኮሌስትሮል አይነት ከሚቀንሱ ፍራፍሬዎች ይመደባል፡፡ አፕል ሟሚ የሆነ ፔክቲን የተባለ ቅመም ያለው ሲሆን ኮሌስትሮልን ከደም የመምጠጥ ባህሪ ስላለው ደም ውስጥ ያለውን ኮሌስትሮል ይቀንሳል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም አፕል ውስጥ ያሉት ፍላቪኖይድስ የሚሰኙ ፀረ መርዛማ ኬሚካሎች ኮሌስትሮል ቅባት በደም ውስጥ እንደልቡ እንዳይንቀሳቀስ መንገዱን በመቁረጥም ይሳተፋል፡፡ አንድ አፕል ዶክተርን ያስጥል የሚባለው ብሒል እውነት ከሚሆንባቸው የአፕል የጤና ጥቅሞች አንዱ ይኸው የኮሌስትሮልን መጠን የመቀነስ ተግባሩ እንደሆነ በጥናት መረጋገጡን ሃርቫርድ ኒውስሌተር የሐምሌ ወር እትም በዝርዝር ያትታል፡፡
2. ቡናማ ሩዝ
ቡናማው የሩዝ አይነት በውስጡ ልዩ ዘይት አለው፡፡ ይህ ዘይት ነው ኮሌስትሮልን የመቀነስ ብቃት ያአለው፡፡ በተለይ ቡናማ ሩዝን እንደ አተር እና መሰል ጥራጥሬዎች ጋር ቀላቅሎ መመገብ ምርጥ የፕሮቲን ቅልቅል እንደሆነ እና ኮሌስትሮልንም መዋጊያ መሆኑን ባለሞያዎቹ ይጠቁማሉ፡፡ ቡናማ ሩዝ ማግኒዥየም፣ ቫይታሚን ቢ እና ፋብየርን የያዘ በመሆኑም ከልብ ጋር ተስማምቶ የሚዋሃድ ለልብ ጤና የሚጠቅም እንደሆነ በስፋት ይገለፃል፡፡
3. ቀረፋ
ስለቀረፋ ጠቀሜታ የቀደሙት ሰዎችም በስፋት ሲያወጉ እና ከበረከቱም ሲካፈሉ ቆይተዋል፡፡ የህክምናው ሳይንስ ሰዎችም ያደረጉት ጥናት ይህንን ያረጋግጣል፡፡ ጆርናል ዲያቤትስ ኬር የተሰኘ የምርምር ውጤቶች ማስፈሪያ መጽሔት ላይ የወጣ ጥናት እንደሚለው በቀን ግማሽ ማንኪያ ቀረፋ መጠቀም በስኳር ህሙማን ዘንድ አብዝቶ የሚታየውን የደም ግፊት ህመም በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ይቻላል፡፡ መጥፎ የሚባለውን አይነት ኤልዲኤል ኮሌስትሮልም ከደም ውስጥ ማውረድ መቻሉን ማረጋገጣቸውን አጥኚዎቹ በመጽሔቱ አስፍረዋል፡፡ ስለሆነም በሻይም ይሁን በሌላ የአመጋገብ መልክ ቀረፋን ማዘውተር ኮሌስትሮልን ይዋጋል፣ ከምግብ ዝርዝርዎት ይጨምሩት ይላሉ ባለሞያዎች፡፡
4. ነጭ ሽንኩርት
ስለነጭ ሽንኩረት ጥቅሞች ዘርዝሮ መጨረስ ይከብዳል፡፡ በነጭ ሽንኩርት ውስጥ ታምቀው ከሚገኙ ንጥረ ነገሮች አንዱ የሆነው አሊሲን ባክቴሪያ እና ፈንገሶችን ከመግደሉ በተጨማሪ ለአንዳንድ የጨጓራ ችግሮችም ሁነኛ መፍትሄን ይሰጣል፡፡ የደም መርጋትን ማስቀረቱም ልዩ ጥቅሙ ነው፡፡ ከእነዚህ ቀደም ብለው ከሚታወቁ ጥቅሞች በተጨማሪ በምን አይነት ስርዓት እንደሆነ ባይታወቅም ለጤና ጎጂ የሆነውን ኮሌስትሮልን መጠን የመቀነስ ጥቅም እንዳለው ሳይንቲስቶች በቅርቡ በጥናት ጽሑፎቻቸው አሳይተዋል፡፡ ግምቶች እንደሚያሳዩት ግን ነጭ ሽንኩርት ኮሌስትሮልን የሚቀንሰው የጉበትን ኮሌስትሮል የማምረት አቅም በማዳከም ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ነጭ ሽንኩርትን የማይደፍሩ ከነበረና የውፍረትና የኮሌስትሮል ጉዳይ የሚያሳስበዎት ከሆነ ወደ ነጭ ሽንኩርት ቢያዘነብሉ ከጠቀሜታውን ይቋደሳሉ፡፡
5. አጃ
አጃን በተለያየ መልክ ለሚጠቀሙት ኢትዮጵያውያን ጠቀሜታዎቹ ብዙም እንግዳ ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ ከኮሌስትሮል ቅነሳ ጋር ስለመያያዛቸው ግን ብዙም የሚታወቅ አልነበረም፡፡ እንደ ጥናቶች ጥቆማ ግን አጃ ውስጥ ያሉ ፋይበሮች የኮሌስትሮልን ምጣኔ በከፍተኛ መጠን ይቀንሳሉ፡፡ አጃ ውስጥ ያሉት ግሉካጎን የሚሰኙ ንጥረ ነገሮች ይህን ቁልፍ ስራ ይሰራሉ፡፡ ቀን ከ5 እስከ 10 ግራም አጃ መውሰድ የኮሌስትሮልን መጠን በቀን ቢያንስ በ5 በመቶ እንደሚቀንሰው ባለሞያዎቹ ይገልፃሉ፡፡ በየትኛውም መልክ ቢወስዱት በጣም እሳት ሳያጠቃው ሲወሰድ አጃ ውጤቱ ከፍተኛ ነው ይባላል፡፡ አሜሪካን ጆርናል ኦፍ ክሊኒካል ኒውትሪሽን ላይ የሰፈረው ጥናት ይህን ያረጋግጣል፡፡
6. ኦሜጋ ፋቲ አሲድ ከነጭ ዓሣ
ቅባት ያላቸው ዓሣዎች በተለይ ኦሜጋ ፋቲ አሲድ በብዛት ያላቸው ሲሆን ይህም ለልብ በሽታ፣ ለመዘንጋት ችግር እና ለሌሎችም ጭምር በመዋጋት በኩል ከፍተኛ ጠቀሜታዎችን ስለመስጠቱ ከዚህ ቀደም ብዙ የተባለለት ነው፡፡ ሳይንቲስቶች ጥቅሞቹ በዚህ ብቻ እንደማይቆም ጠቁመው ለኮሌስትሮል ቁጥጥርም ሚናው የላቀ እንደሆነ እየገለፁ ይገኛሉ፡፡ በአሜሪካው የሎማ ሊንዳ ዩኒቨርሲቲ የተሰራ ጥናት እንደጠቆመው መጥፎ ቅባቶችን ከዓሣ በሚገኙ ጤናማ ቅባቶች መተካት የጥሩውን አይነት ኮሌስትሮል ምጣኔ በ6 በመቶ ጨምሮ ተገኝቷል፡፡ ይህም በተዘዋዋሪ መጥፎው አይነት ኮሌስትሮል ምጣኔ እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡
7. ሻይ
ሻይ ካንሰርን በመከላከል በኩል ያለው አስተዋፅኦ ከታወቀ ረዘም ያሉ ጊዜያትን አስቆጥሯል፡፡ በቅርቡ የተደረጉ ተጨማሪ ጥናቶች ደግሞ በደም ውስጥ የሚገኝ ኮሌስትሮል መጠንን በመቀነስ የደም ፍሰትን የማቀላጠፍ ሚናውም አቻ የማይገኝለት መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ በተለይም ጥቁር ሻይ ላይ በተደረገው ጥናት በሶስት ሳምንታት በተከታታይ ጥቁር ሻይን የጠጡ ባለከፈተኛ ኮሌስትሮል ሰዎች ደም ኮሌስትሮል ቅባት መጠናቸው በ10 በመቶ ሊቀንስ መቻሉ በዩኤስዲኤ የምርመራ ውጤቶች ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡
8. ጎመን
ጎመንና ሌሎቹም አረንጓዴ ቅጠል ያላቸው ምግቦች ዘንድ የሚገኘው ሊውቲን የተባለው ንጥረ ነገር ከማርጀት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ የአይን ጡንቻዎች መድከም ሁነኛ መፍትሄ ሆኖ ያገለግላል፡፡ በዚህም በርካቶችን ከአይነ ሰውርነት ሲጠብቅ መኖሩን ባለሞያዎች በጽሑፎቻቸው አስፍረውታል፡፡ ተጨማሪ ጥቅሞቹ ደግሞ የልብ በሽታን ከመዋጋት ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ ይህንንም የሚያደርገው የደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ ተለጥፈው የሚገኙ የኮሌስትሮል ቅባት ክምችቶችን እያጠበ በማውጣት ብቃቱ ነው፡፡ በሚቀጥለው ጊዜ ወደ ገበያ የሚወጡበት ምክንያት ካለ ከፌስታልዎ ውስጥ ጎመን አብሮ ተገዝቶ መምጣቱን ያረጋግጡ፡፡ ለልብዎ ጤና ወሳኝ ቅመሞች አሉትና፡፡ በዚህ መልክ ከኮሌስትሮል ጥርቅምና ተያይዘው ከሚመጡት በሽታዎች ራስዎን ይጠብቃሉ፡፡ የቤተሰብ ኃላፊ ከሆኑም ለቤተሰብዎ አባላት ይህን በረከት እንዲያካፍሉ ባለሞያዎች ይመክራሉ፡፡ ታዲያ ጎመኑ ለዛው እስኪሟጠጥና ጠቃሚው ቁልፍ ንጥረ ነገር ተጠቃሎ እስኪሄድ አያብስሉት፡፡
9. አቮካዶ
አጎካዶ ሞኖሳቹሬትድ የሚሰኙት ጤናማ ቅባቶችን በብዛት የያዘ ፍሬ ሲሆን ይህ ተፈጥሮውም ጤናማ የሚባለውን የኮሌስትሮል አይነት ከደም ውስጥ ለመጨመርና መርዛማውን ባለዝቅተኛ ግዝፈት ኮሌስትሮል ለመቀነስ ይረዳዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሲቶስትሮል የተባለ ከምግብ የምንወስደውን ከፍተኛ ኮሌስትሮል መጥጦ የማስቀረት ከፍተኛ ብቃት ያለው ንጥረ ነገር ስለሚይዝ ጠቀሜታውን ከፍ ያደርገዋል፡፡ ይሁንና አቮካዶ ከፍተኛ የቅባትና ካሎሪ ይዘት ያለው ፍሬ ስለሆነ ማዘውተሩ ለውፍረት ሊዳርግ ስለሚችል አለፍ አለፍ እያሉ ቢጠቀሙበት የበለጠ እንደሚመከር የሐምሌው ወር 2011 የሃርቫርድ ህክምና ትምህርት ቤት ኒውስ ሌተር ያሳስባል፡፡
10. ቸኮሌት
ቸኮሌት ቅባት እንዳለው በብዛት ቢነገርም በውስጡ ያለው የፀረ መርዛማ ኬሚካሎች (አንቲኦክሲዳንትስ) ምጣኔ የሚበልጥ በመሆኑ ጠቀሜታው የበለጠ ይጎላል፡፡ በተለይ ጥቁር ቸኮሌት ይህን በብዛት ስለሚይዝ የኮሌስትሮል ቁጥጥር ውስጥ የራሱን ጠቃሚና ጣፋጭ ሚና ይወጣል፡፡ የአሜሪካ ክሊኒካል ጆርናል መጽሔት ይህን በማስረጃ አስደግፎ ጽፎታል፡፡ ጥቁር ቸኮሌት በ12 ሳምንታት ጊዜ ውስጥ 24 ከመቶ የሚሆነውን የኮሌስትሮል መጠን ሊቀንስ መቻሉ በጥናቱ ታውቋል፡፡ የደም መርጋትንና የህዋሳት መጣበቅን የመግታት ተጨማሪ ጥቅሞቹንም የሚያስታውሱት ባለሞያዎች ከወተት የተደባለቀው ቸኮሌት ጠቀሜታው ያን ያህልም ስለሆነ ጥቁሩን ቸኮሌት የሙጥኝ ይበሉ ብለዋል፡፡ ቸኮሌት ለፍቅረኛ ብቻ ያለው ማነው? ለራስዎም ጤንነት ሁነኛ መፍትሄ ነው፡፡ መጥፎ ሙድን በመለወጥ ዘና የማድረግ ብቃቱን ታዲያ እንዳይዘነጉ፡፡ ትንሽ ድብርት ቢጤ ከሞካከረዎት ቸኮሌት ጥሩ መፍትሄ ነው፡፡µ

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live