Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

Health: ከትዳር አጋርዎ ጋር የሚፈጠር ግጭትን ለመቀነስ!

$
0
0

በትዳር ውስጥ ሁለት ከተለያየ ቦታ፣ ባህል እና እሳቤ ካላቸው ቤተሰብ ውስጥ የመጡ ጥንዶች በአንድ ጣራ ውስጥ ሲኖሩ በሀሳብ አለመግባባትና ግጭት መኖሩ የማይቀር ነው፡፡ እንኳንስ ከሁለት የተለያየ አመለካከትና ባህል ካላቸው ቤተሰብ የመጡት ይቅሩና በአንድቤት ውስጥ በአንድ አይነት አስተሳሰብና ባህል ለበርካታ ዘመናት የኖሩ ቤተሰባሞች መካከል እንኳን አለመግባባትና ግጭቶች ይፈጠራሉ ፤ዋነው ነገር ግጭቱ ለምን ተፈጠረ ሳይሆን፤ ሲፈጠር እንዴት እናስወግደው? ወይንም በቀላሉ ወደ መፍትሔው በመሄድ እንዴት እናብርደው? የሚለው ነው ፡፡
Black women fights
የሰዎች ሁሉ እተሳሰብና አመለካከት አንድ አይደለም፡፡ አንዱ ሌላውን ወደ ራሱ አስተሳሰብ ለማምጣት በሚያደርገው ጥረት ደግሞ አለመግባባትና ክርክር በመቀጠል ጭቅጭቅ መፈጠሩ የማይቀር ነው፡፡ የብዙ ባለትዳሮችም የጸብ መነሾም አንዳቸው የአንዳቸውን አስተሳሰብ ወደ ራሳቸው ለማምጣት በሚያደርጉት ጥረት የሚደረግ ክርክርና አለመግባባት የተነሳ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ንዴት አዘል የሆነን ክርክር ፤በተለይም በአንድ ወገን ሲያመዝን ሌላኛው ወገን ጥፋቴ ነው ቢልም ሆነ ሌላኛው ወገን የሚፈልገውን ለማድረግ ቢስማማ ጥሉንና ጭቅጭቁን ላያበርደው ይችላል፡፡ እንዲህ ያለ ችግር በትዳር ውስጥ ሲገጥመዎ ነገሩን ለማብረድ የተለያዩ አማራጮችን መጠቀም ያኖርቦታል፡፡ የትዳር አጋሮ ግልፍተኛ ሆኖ በሚከራከርዎ ጊዜ እርሶ በተረጋጋስሜት ሆነው በጥሞና ያድምጡት፡፡ የትዳር አጋሮ ንዴት በተሞላበትን ንግግሩን ከጨረሰ በኋላ ምን እየረበሸው ወይም እያስጨነቀው እንዳለ መልሶ እንዲያስረዳችሁ ጠይቁት፡፡ ጥያቄዋት ግን ቀላል ማብራሪያ የሚያስፈልገውና ወደሌላ ርዕስ ውስጥ የሚያስገባዎት አለመሆኑን ያረጋግጡ፡፡ የትዳር አጋሮ ለቀረበለት ጥያቄ አብራርቶ ሲያበቃ እርሶን በመወንጀል ላነሳቸው ነጥቦች ይቅርታ በመጠየቅና ያንን ድርጊት ደግመው እንደማያደርጉት ቃል በመግባት ክርክሩን ወደ ተሻለ የሐሳብ መግባባት ማምጣት ይቻላል፡፡

የትዳር አጋሮ ሙሉ በሙሉ ከተረጋጋ በኋላ ሌላ ነገር እየረበሸው እንዳለ ይጠይቁት፡፡ በአብዛኛው ሰዎች ንዴት ውስጥ እያሉ ትክክለኛውን ስሜት ማውጣት አይችሉም፡፡ በንዴት ውስጥምሆነው የሚናገሩት ትክክለኛውን የንዴታቸውን መንስኤ አያሳይም፡፡ ስለዚህ ከተረጋጉ በኋላ በድጋሚ በእርግጥ የንዴታቸው ትክክለኛው ምክንያት ለማወቅ መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡ ለትዳር አጋሮ ይህንን ጥያቄ በሚያቀርቡ ጊዜ ወዲያውኑ ትክክለኛውን መልስ ላያገኙ ይችላሉ፡፡ እርስዎ ግን ትክክለኛውን ምላሽ እስኪያገኙ ድረስ መጠየቆን አያቋርጡ፡፡ ይሄን የሚያደርጉት ግን የትዳር አጋሮ መረጋጋቱንና ከንዴት መውጣቱን እርግጠኛ ሲሆኑ ብቻነው፡፡ በዚህ በተረጋጋ ስሜት ውስጥ ሆኖ የሚነግርዎትን ምክንያት በጥሞና ከሰሙ በኋላ የሚያቀርብሎትን የመፍትሔ ሆነ የሐሳብ መጋራት የሚሰጠዋ ዋጋ ከፍተኛ ነው፡፡ ፀቡን አብርደው ፣የትዳር አጋሮን አረጋግተው ወደ ትክክለኛ ማንነቱ ከመለሱ በኋላ እንደገና ደግሞ የሱን ችግር ለመፍታት ዝግጁ በመሆንዎ ለትዳሮ ስምረት የሚያበረክተው ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፡፡ በዚህም ባለቤቶ ወይም የትዳር አጋሮ በዚች ምድር ላይ እንደሶዎ ያለ ታጋሽና የሚረዳው ሰው እንደሌለ ያስባል፡፡
በተረጋጋና ከስሜታዊነት በነፃ መንፈስ የምታደርጉት ክርክር ቀስ በቀስ ወደ ውይይት ይቀየራል፤ በዚህም ወቅት የሁለታችሁንም ስህተት በግልጽ ላማየት ይቻላል ፡፡

በዚህ ወቅት እርሶዎ ያቀረቡትን ሐሳቦች በምክንያታዊነት ቢፈርስብዎና ስህተት እንደሰሩ ቢያሳይብዎ ምንም ሳያመነቱ ለጥፋቶ ይቅርታ ይጠይቁ፡፡ በዚህ መንገድ በሚደረግ ውይይት የትዳር አጋሮም ቢሆኑ ጥፋተኛ ከሆኑ ይቅርታ የማይጠይቁበት ምንም ምክንያት አይኖራቸውም፡፡
ምንጭ፤- አዌክ መፅሔት

The post Health: ከትዳር አጋርዎ ጋር የሚፈጠር ግጭትን ለመቀነስ! appeared first on Zehabesha Amharic.


አድዋ መስክሪ –ጌታቸው ከኑርንበርግ ጀርመን

በሥራ ሂደት ባለቤቶች የተጥለቀለቀች ብቸኛዋ ሀገር! –ነፃነት ዘለቀ

$
0
0

ነፃነት  ዘለቀ (ከአዲስ አበባና ከፊንፊኔ)

ሰሞኑን አንድ ጉዳይ ገጥሞኝ የወያኔውን የዱርዬ መንግሥት በርካታ ቢሮዎች ማንኳኳት ነበረብኝ፡፡ ጉድ አየሁላችሁ፡፡ የጉድ ጉድ! ስንቱን ነግሬያችሁ እንደምዘልቀው ግን አላውቅም፡፡ በሀገራችን ተዝቆ የማያልቅ  ብዙ ጉድ እየፈላና እየተንተከተከ ነው፡፡ በአንዲት ሀገርና በአንዲት መናገሻ ከተማ ስንት መንግሥት እንዳለም ለማወቅ ሞክሬ አልተቻለኝም፡፡ አንዱ ጋ ስትሄድ አዲስ አበባ ይልሃል፤ ሌላው ጋ ስትሄድ ፊንፊኔ ይልሃል፤ ወደ አንዱ ኤፍ ኤም ብትሄድ ደግሞ ሸገር ይልሃል፡፡ አንዱ “ወደናዝሬት ልሄድ ነው” ሲልህ ሌላው “ወደአዳማ ልሄድ ነው” ይልሃል፡፡ ስሞችም ፖለቲካዊ ይዘት እየተላበሱ በአጠራር ልየነት መቀያየምና በነገር መጓነፍ ይታያል፡፡ “እህሉ አንድ ዓይነት ሴቱ አሥራ ሁለት” የሆነበት ዘመን ሆኗል፡፡ ዘመነ ግርምቲ! ቧይ!! አዲስ አበባ – ፊንፊኔ፣ ናዝሬት – አዳማ፣ ደብረ ዘይት – ቢሾቱ፣ አዋሳ – ሀዋሳ፣ ጅጅጋ -ጅግጅጋ፣ አለማያ- ሀሮማያ፣ ውጥንቅጡ የወጣባት ሀገር – ሰው በስያሜም ይለያያል? በስያሜና በተሰያሚ መካከል እኮ የባሕርይ ግንኙነት የለም፡፡ ስለዚህ ሰዎች ለምን በዚህ ቀላል ነገር ይሻኮታሉ? በተለመደው ቢጠራ ችግሩ ምን ይሆን? ባቢሎን በሣሎን፤ ባቢሎን በኢትዮጵያ፡፡

ወደ አንዱ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሂድ – ወግ ነውና ሲዳሩ ማልቀስ የወያኔ “መንግሥት”ም ያው መንግሥት መባሉ ነው እንግዲህ፡፡ እናም ስትሄድ ምን እንደሚገጥምህ ያየሁትን ልነግርህ ነው – ተዘጋጅ፡፡

በብዙ መሥሪያ ቤቶች ከዘበኛ ጀምሮ እስከላይኛው ሥራ አስኪያጅ ወይም ሥራ አስፈጣሚ ድረስ የምታገኘው ከትግሬው ብሔር የተገኙ ጥቂት የተማሩ ወይም ሞፈር ቀምበር ሰቅለው የመጡ – ግን እንደከተመኛ የለበሱ – ማይም ሰዎችን ነው – ከመደነቋቆር በስተቀር የማትግባባቸው ፍጹም ማይማን፡፡ አልፎ አልፎም የመሥሪያ ቤቶች የመግባቢያ ቋንቋ የሀገሪቱ ኦፊሴላዊ ቋንቋ አማርኛ መሆኑ ቀርቶ ትግርኛ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ – ይሄ ምንም ማለት አይደለም፡፡ ይህን ያነሳሁት ለወቀሣ ሣይሆን የትግሬው ጠባብ ቡድን ወደ ዘጠና ሚሊዮን የሚገመተውን መላዋን የሀገሪቱን ሕዝብ በምን ያህል ብልጫ ገለባብጦ አንድን የመንግሥት መሥሪያ ቤት በቁጥጥሩ ሥር እንዳደረገው ለማሳየት ነው፡፡ እንጂ ማንም ዜጋ በፈለገው ቋንቋ የመግባባት መብቱ ተፈጥሯዊ እንጂ ሰብኣዊ ስጦታ እንዳይደለ እረዳለሁ፡፡ በትግርኛችን የብሔራዊ አገልግሎት ድርሻን መውሰድ ቀንቼበት ወይም ተመቅኝቼ አይደለም፡፡ ሁሉም የኔው ነው፡፡

መሄድ የነበረብኝ መሥሪያ ቤቶች በውነቱ ጥቂቶች ነበሩ፡፡ ነገር ግን በነዚያ መሥሪያ ቤቶች በታዘብኩት የተወላገደ ሀገራዊ ምስል ምክንያት ሌሎች ብዙዎችንም ጨመርኩ – ለግንዛቤየ ስል ብቻ (just for curiosity purpose)፡፡ እናም መከላከያና ውጭ ጉዳይም አልቀሩኝም – ከሃይማኖቱም ፓትርያርክ ጽ/ቤትና ምግባረ ብልሹ ማለትም “ምግባረ ሠናይ” የሚባለውን የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስታን ሆስፒታልን ጭምር በሰበቡ ጎበኘሁ፡፡

አንድ ነገር ማስቀደም ፈለግሁ፡፡ በደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ ሥርዓት ከነጮቹ ውስጥ ያን ወንድምና እህቶቻቸው በጥቁሮችና በቅይጦች ላይ የዘረጉትን የአፓርታይድ አገዛዝ አጥብቀው የሚቃወሙና የሚታገሉም ነበሩ፡፡ እነዚያን ዓይነት ጤናማ አእምሮ የነበራቸውና ያላቸው ምርጥ የዓለማችን ዜጎች ከየቆሻሻ ክምሮች ውስጥ እያፈነገጡ የሚወጡበት ሁኔታ ብዙውን ጊዜ ይታያል፡፡ የእናት ሆድ ዥንጉርጉር መሆኑ አዲስ አይደለምና ከወያኔም አንጀተ ብቡ እንደማይጠፋ ሁሉ ከለዬለት ሰይጣንም ተስቶትም ቢሆን ምሕረትን የሚያደርግ አይጠፋም፡፡ የነዚህ የፀረ አፓርታይድ ነጭ ታጋዮች ጉዳይ ግን ለየት ይላል፡፡ እነሱን የመሰሉ ፀረ ጽዮናውያንም እንዳሉ ስንሰማ ለሰዎች አእምሯዊ ዕድገት ያለን አድናቆት ይጨምራል፡፡ የሚገርማችሁ ነገር የሚጓዙበትን ብርሃን መሰል ጨለማ የመጨረሻ ዕጣ ፋንታ ሲረዱ ከ32 እና ከ33 ዲግሪ የኢሉሚናቲ የዕድገት ደረጃ ሣይቀር እየወጡ የጓደኞቻቸውን የቀን ቅዠት የሚያጋልጡና መልካም ሕይወትን መኖር የሚጀምሩ ደጋግ የቀድሞ የሉሲፈር እምነት አራማጆች አሉ፡፡ በበኩሌ ምንም እንኳን ትልቅ አደጋ የሚጋረጥባቸው መሆናቸውን ብረዳም በነዚህ ወደኅሊናቸው የሚመለሱ ሰዎች በጣም እደሰታለሁ፡፡ በዚህ መልክ የዘርም ይሁን የእምነት ጓዶቻቸውን የዕውር ድንብር የጨለማ ጉዞ እየከዱ ወደ እውነት ጎዳና የሚገቡና በስህተታቸው የሚጸጸቱ አሉ፡፡ በሀገራችንም የነዚህን ዓይነት ከጠማማ መንገድ ተመለሾችን ቁጥር እንዲያበዛልንና የነፃነታችንን ቀን እንዲያቀርብልን ፈጣሪን በጸሎት ተግተን እንወትውተው፡፡

የሩዋንዳን ነገር ሣልጠቅስ ማለፍ አልወድም፡፡ አክራሪ ሁቱዎች ቱሲዎችን በሚጨፈጭፉበት ጊዜ ለዘብተኛ ሁቱዎች  ቱሲዎችን የመታደግ ብዙ ታሪካዊ ሥራ ሠርተዋል፡፡ በቤታቸው ሸሽገው አደጋውን እንዲያልፉ ያደረጉ የጤናማ አእምሮ ባለቤት ሁቱዎች ነበሩ፡፡ እንደጓደኞቻቸው ሣያብዱና ሣይወፍፉ በጭፍጨፋውም ሣይሣተፉ ለቱሲዎች መልካም ነገርን በማድረግ አሁን ላለው አንጻራዊ ሰላም የበቁ፣ በዚያም ምክንያት ኅሊናቸውን በደም ታሪክ ያላጨቀዩ ሁቱዎች አሉ፤ ለደግ አሳቢ አእምሮ ምሥጋና ይድረሰው፡፡ ሁሉም ያልፋል፤ የማያልፍ ነገር ቢኖር ኖሮ ቁጭት ንዴታችን ወሰን ባልተገኘለት፡፡

ከፍ ሲል ያልሁትን ያልሁት አለምክንያት አይደለም፡፡ ደጋግ ትግሬዎች አለን፡፡ ከነፈሰው ጋር የማንነፍስና በወገኖቻችን መገፋትና መሳደድ/መሰደድ የምንከፋ፣ የምንበሳጭና የምንቆጭ ጥሩ ጥሩ ትግሬዎች አለን፡፡ አላህ ጨርሶ አይበድልም፡፡ ከንፍሮም ጥሬ ይወጣል፡፡ እናም ጥቂቶችም ቢሆኑ በአሁኑ ሸውራራ የትግሬ አገዛዝ አንጀታቸው የሚያርር በዚህም ምክንያት የዘር ሐረጋቸው ያመጣውን ሀገራዊ መቅሰፍት ለመንቀል ከጭቁኖች ጋር ለመታገል የቆረጡ አሉ፡፡ ትግላቸው እስከሞት የሚያደርስ መሆኑን እያወቁ ለኅሊናቸው ሲሉ ከመከረኛው ሕዝብ ጎን ተሠልፈው የሚዋደቁ እነአብርሃ ደስታና አሥራት አብርሃም፣ አብርሃም በላይ – እንዴት ነገሩ ይሄ አብርሃ የሚሉት ስም … ብቻ ጥቂት የማይባሉ ትግሬዎች አሉን፡፡ ጌታ ጥሎ አይጥልም፡፡ ጥቂትም ቢሆኑ የመከራ ገፈታችንን የሚጋሩ ትግሬዎች መኖራቸው ሸክማችንን የሚጋራን ከመኖሩ አኳያ መጠነኛ እፎይታ ይሰማናል፡፡ በተረፈ ተከድኖ ይብሰል፡፡ ለዛሬ ግን ለምን ይከደናል? ያየሁትን እዘከዝከዋለሁ፡፡

በዬመሥሪያ ቤቱ ኃላፊውም ዘበኛውም ጽዳቱም ትግሬ ነው፡፡ ለይስሙላ ቢሮ ተቀምጦ የሚገኘውን ኃይለ ማርያም ደሳለኝን የመሰለ መናጆና “ሲጠሩት አቤት፣ ሲልኩት ወዴት” ባዩን ዜጋ ታዲያ ከቁም ነገር እንዳትቆጥሩት – አንድም ሥልጣን የሌለው በዓይን ጥቅሻና በቀጭኒቱ ሽቦ ከትግሬዎች መንደር የሚታዘዝ መጋጃ ነው፡፡ ይህ በጣም ግልጽ ነው፡፡  ወ/ሮ ትብለፅ ጎይታይ – የሰው ኃይል አስተዳደር የሥራ ሂደት ባለቤት፣ አቶ መሓሪ ሽኑን – የወጪና ገቢ ቁጥጥር የሥራ ሂደት ባለቤት፤ ዶክተር ሐጎስ ዕንቋይ – የአማራ ክልላዊ መንግሥት ዕንባ ጠባቂ የሥራ ሂደት ባለቤት፣ አቶ ዘርዑ መዓሾ – የደቡብ ሕዝቦች ክልል የመሬት ድልድል የሥራ ሂደት ባለቤት፤ ወ/ሮ ሐረጓ ግደይ – የአዲስ አበባ ሴቶች ሊግ ሰብሳቢ፤ ወጣት አረጋዊ አስገዶም – የአዲስ አበባ ወጣቶች ሊግ የዘርፍ ሰብሳቢ፤ እማሆይ አብረኸት ፍትዊ የኪዳነ ምሕረት ገዳም እመምኔት፤ አባ ናትናኤል ኪሮስ የአ.አ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ፤ አቡነ ናትናኤል የኦርቶደክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክና… አቶ ማለትም ዶክተር ኃይለሚካኤል ጎይቶም የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ የዕድሜ ልክ ፕሬዝደንትና በወያኔ ማዕከላዊ ጽ/ቤት የሙስና ማቀላጠፊያ ዘርፍ  የሥራ ሂደት ባለቤት … አይ! ያሣፍራል፡፡ አንዳርጋቸው ያቺን ስድ ሴት በተመለከተ ሲናገር የአማርኛውን “ያሸማቅቀኛል” የሚለውን ቃል በስሜታዊነት ዘንግቶት በእንግሊዝኛው “cringe” አደርጋለሁ ብሎ ነበር፡፡ እኔም በዚህ የትግሬው ገዢ መደብ ክሪንጅ አደረግሁ – ተሳቀቅሁለት – ተሸማቀቅሁላቸው፡፡ አንጎል ምን ያህል ቢጠፋ የዚህችን ቀመር የኋላ ጦስ እንዴት ያጧታል? እንዴ! ከታች እስከ ላይ በትግሬ አስይዘህ ስታበቃ፣ ሌላውን ዜጋ እንደባይተዋር ወርውረህ ስታበቃ፣ ሌላውን ዜጋ በተለይም አማርኛ ተናጋሪውን ጨፍጭፈህና አስጨፍጭፈህ ንቀህና አዋርደህ ከሀገሩ ጉዳይም አግልለህ የትሚናውን ጥለህ ስታበቃ፣ … በዚህ በተደናበረ አገዛዝ ስንት ዓመት ትኖራለህ? የአንዲን ቃል ልድገመው – ተሸማቀቅሁላቸው፡፡ እኔ ያፈርሁት በነሱ ነው፡፡ ማይምነት ለካንስ እስከዚህን ያጋልጣል? ሱቅ ውስጥ እንደገባ ሕጻን ሁሉ ነገር ዐይን ዐዋጅ ሆነባቸውና ተጨነቁ፡፡

ትግሬዎቹ የተማሩ ቢሆኑና ለቦታው ቢመጥኑ ለኔ ጉዳየ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ለቦታው የሚመጥን ሰው ከሆነ ትክክለኛ አገልግሎት ይሰጣልና የሚበሳጭና የሚናደድ ተስተናጋጅ አይኖርም፡፡ እነሱ ግን ምኑንም ስለማያውቁት በዘር ብቻ እየተጠራሩ ሀገሪቱን የጨረባ ተዝካር አድርገዋታል፡፡ የአምስተኛ ክፍል ጄኔራልና የአሥረኛ ክፍል ዶክተር ባለሥልጣን ባለባት ሀገር – የመካከለኛና ዝቅተኛ ቢሮዎች ባለሥልጣናት እስከምን ድረስ ሊማሩ እንደሚችሉ ይታያችሁ፡፡ ሀገሪቱን ከዳር እዳር እየተጫወቱባት እኮ ነው፡፡ ኧረ ጓዶች ፍጠኑና ይህችን ሀገር ከዚህ አረንቋ በቶሎ እናውጣት ማለትም አውጧት፡፡

በየቀበሌዎችና ወረዳዎችም ሄጃለሁ፡፡ ሁሉም ቦታ አዛዥ ናዛዡ ትግሬ ነው፤ ልብ አድርጉ – የሌላ ዘውግ ተሹዋሚ የለም እያልኩ አይደለም – ሞልቷል፡፡ ግን ራሱን ችሎ አይሠራም – ከጥቃቅን ነገሮች በስተቀር፡፡ ኦነግ ወይም ከወሮች አንድኛው እንዳይለጠፍበት በመስጋት ሁሉም የሌላ ብሔር “ሹም” ክፉኛ እየተሳቀቀ ነው ሥራ ውሎ የሚገባው፡፡ በተረፈ የትግሬው ባለሥልጠን ደረቱን ነፍቶ ሲነፈርርና በሥነ ልቦናዊ የበላይነት እርካታ ሲንጎማለል ታያዩታላችሁ፡፡

ባይገርማችሁ የዛሬ ሁለት ዓመት አሥረኛ ክፍልን ማለፍ ያቃተው አንድ ወጣት ትግሬ አሁን የአንድ ወረዳ ሥራ አስፈጻሚ ነው፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉም ተሹዋሚ ትግሬ በችሎታውና በትምህርቱ ሣይሆን በዘውጋዊ ቀረቤታው ነው፡፡ የቀረቤታው ልክ ደግሞ ከትግሬም ትግሬ እየተማረጠ ነው፡፡ ቅድሚያ አድዋ፣ ቀጥሎ ሽሬ፣ ቀጥሎ አክሱም … ዓይነት እጅግ የወረደ ጎጠኝነትና መንደርተኝነት፡፡ በትምህርትና በችሎታ መመደብማ ለይቶለት ገደል ከገባ ሃያ አራት ዓመታትን ሊያስቆጥር ጥቂት ወራት ብቻ ቀርተዋል፡፡ መለስ – ባለበት ሲያስመልሰው ውሎ ይደርና –  በሕይወት እያለ ለፖለቲካው እስከታመነ ድረስ ዘበኛንም ሚኒስትር ማድረግ እንደሚቻል በኩራት ተናግሮ ነበር፡፡ ለንግግርም ለከት የሌላቸው እንዴት ያሉ ባለጌዎች ናቸው እኮ! ፈጣሪን ምን ቢበድሉት ይሆን እንዲህ አበለሻሽቶ የፈጠራቸው? እኛስ ብንሆን ኃጢኣታችን ምን ያህል ከተራራ ቢገዝፍ ይሆን ካልጠፋ አምባገነን እነዚህን የመሰሉ የሲዖል ትሎች የሰጠን? እስኪ ቁጭ ብላችሁ አስቡት፡፡ ሀሁንና ኤቢሲዲን ባልቆጠሩ ማይማን እንዴት ሀገር ትተዳደር? ምን ዓይነት ውርጅብኝ ነው? በስማም!

ጭንቀቴን ልናገር፡፡ አሁን በትግሬ ወያኔ ከላይ እስከታች የተጥለቀለቀውን የሀገሪቱን ቢሮክራሲ ነገ ነፃ ስንወጣ እንዴት አድርገን ነው የምናስተካክለው? ማን ነው ወንዱ ይህን ሁሉ በትግሬ የተጨናነቀ መሥሪያ ቤት ሁሉ አስተካክሎ እውነተኛ የሁሉም ብሄሮች የተማሩ አባላት በውድድር አልፈው ሀገሪቷን እንዲመሩ የሚያደርግ? በጣም ከባድ የቤት ሥራ ተጎልቶላችኋል፡፡ መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት ካልታከለበት ከሆድና ከዘረኝነት የቤት ጣጣ በስተቀር አንድም ዕውቀት የሌለውን ይህን የወያኔ መንጋ በሠለጠነና በተማረ ኃይል ለመተካት ትልቅ ችግር ይገጥማችኋል – እናንት ኢትዮጵያውያን፡፡ እኔ ኢትዮጵያ ነፃ በወጣች ማግሥት ይህን ጉድ ላለማየት እግሬ ባወጣኝ  ከሀገሬ የምሰደድ ይመስለኛል፡፡ እፈራለሁ፡፡ አሁን ያለው ሁኔታ በጣም ያስፈራል፡፡ ሁሉም በአንድ ብሔር ይያዝ? አደገኛ መቅሰፍት ነው! የሚገርምህ ሌላ ነገር – ወያኔ ከሆንክ የፈለገውን ዓይነት የአካል ጉድለት ቢኖርብህ ከሥራህ የሚያነቃንቅህ የለም፡፡ ጣቶች የሌሉት ፖሊስ፣ እጅግ እግር የሌለው (በአርትፊሻል የሚንቀሳቀስ) የጥበቃ አባል ታገኛለህ፡፡ የትግሬነት ማንነት ብዙ ምናልባትም ሁሉንም ህጎች ይደፈጥጥልሃል፤ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ዘረኝነት በምንም ዓይነት ምድራዊ ህግ የሚገዛ አይመስለኝም፡፡ ህግ የሚሠራው ለሌሎች እንጂ ለወያኔ አይደለም፡፡ ይህም በጣም አሣፋሪ ነው፡፡ ከህግ ውጪ ይነግዳሉ፤ ከህግ ውጭ ያመርታሉ፤ ከህግ ውጪ ያከፋፍላሉ፤ ከህግ ውጪ የሀገርን ሀብት ይቀራመታሉ፤ ከህግ ውጪ ያስገባሉ፤ ከህግ ውጪ ያስወጣሉ፤ ከህግ ውጪ ይጠቃቀማሉ፤ ከህግ ውጪ ሌሎችን ያፈናቅላሉ፤ ከህግ ውጪ የፈለጉትን ቦታ አጥረው ይይዛሉ – ይሸጣሉ- ይለውጣሉ፤ ከህግ ውጪ – ከፈለጉ ላይመልሱ ጭምር –  ከባንክ ይበደራሉ፤ከህግ ውጪ ያሻቸውን ሁሉ አላንዳች ማመንታት ይፈጽማሉ፡፡ እነሱ ህግና እግዜር ሆነዋል – ኧረ ከማያውቁት እግዜሩም በላይ፡፡ እኛን ምሥኪኖቹን ምን ይዋጠን?

ሌሎች ዜጎችን ስታዩዋቸው አንጀታችሁን ይበሉታል፡፡ ሀገሪቱ በአንድ ብሄር ቁጥጥር ሥር እንደመዋሏ ሌሎች የቀላዋጭነት ጠባይ ይታይባቸዋል – ሀገሪቱ የነሱም እንዳልሆነችና ባይተዋር የመሆናቸውን ጉዳይ ሳይወዱ በግዳቸው እንዳመኑ ያህል ትረዳላችሁ – ከሁኔታቸው፡፡ ለበርካታ ዓመታት በቅልውጥናና በማጎብደድ መኖር የበታችነት ስብዕናን ሣያዳብር የሚቀር አይመስለኝም – ስለሆነም ኢትዮጵያውያንን ከዚህ አገዛዝ ነፃ አውጥቶ የራሳቸውን ሰብኣዊና ብሔራዊ ማንነት እንደገና ለማላበስ ከፍተኛ ትግል ሣያስፈልግ አይቀርም፡፡ በየመሥሪያ ቤቱ እንደልቡ ሲደነፋና ሌሎችን እያንጓጠጠና እያላገጠባቸው ሲያዝ የምታዩት ትግሬ ነው – ባለጌው የሕወሓት ጀሌ ማለቴ ነው፡፡ ሌላውማ እንደኔው አክስትና አጎት በልመና አዲስ አበባን እያጥለቀለቀ ነው፡፡ ግራ የተጋባ ነገር ነው የገጠመን፡፡ ማጣፊያው ያጠረን ግራ መጋባት፡፡ ቁጭ ብለን የሰቀልነውን ቆመን ማውረድ ያቃተን ትልቅ አደጋ፡፡

ትግሬ ያልሆነ የይስሙላው ባሥልጣን ለምሳሌ ጽዳቷ ቢሮውን ለማጽዳት ብትገባ ልታዘው የመጣች መስሎት የሚያሸረግድላት አይጠፋም – ትግሬ በመሆኗ ብቻ፤ በራስ የመተማመን ነገር ከብዙዎች ዜጎች ሙልጭ ብሎ ጠፍቷል፤ ፍርሀት ነግሦአል፡፡ በየቦታው የሚታየው የሌሎች ወገኖች መሳቀቅ በአንዲት ሀገር የተለያዬ ዜግነት መኖርን ያመላክታችኋል፡፡ “ለካንስ አእምሯዊ የዕድገት ደረጃውን ባልጨረሰ ሰው መገዛት እጅግ ከባድና አዋራጅም ነው” ብላችሁ ትተክዛላችሁ – ልክ እንደኔ፡፡ በየሄድኩበት ቦታ ሁሉ በሀፍረት እየተሸማቀቅሁ እመለሳለሁ፡፡ ደግሞም የሚከረፋኝ ነገር አለ፡፡ በቃ – ቢሮውም፣ ሕንፃውም፣ ምኑም ምናምኑም እንዳንዳች ነገር ይሸተኛል – እጅግ የሚቀረናና የሚከረፋ ሽታ፡፡ የሽታው መንስኤ እንደሚመስለኝ ማይምነቱ፣ ዘረኝነቱ፣ መድሎው፣ በየሥፍራው የሚታየው የማስመሰል፣ የመዋሸትና በግልጽ የማጭበርበር ወያኔዊ ባሕርይ በድምሩ የፈጠሩት ግማት ነው፡፡ የመሥሪያ ቤቱ ጋጋታ፣ የሥራ ሂደቶቹና ንዑስ የሥራ ሂደቶቹ ብዛት፣ የሥራ ፈት “ሠራተኛ”ው መርመስመስ፣ የቴሌቪዥኑና የጋዜጣው ዐይን ያወጣ ቅጥፈትና ዕብለት፣ የውሸቱ ምርጫ የማታለልና ሕዝብን የማነሁለል ሂደት፣ ዘገምተኛ ዜጎችን ሣይቀር ያጡ የነጡ ድሆችን በካድሬነት መልምሎ በማሠማራት በሕዝብ ላይ የሚደረገው ወከባ … ሲታይ ሀገር በነሲብ እየተነዳች እንደሆነ ግልጽ ይሆንላችኋል፡፡ ከምርጫ ውጪ ሌላ ዜማ የለም፤ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚያካሂዱ ይመስል በም..ር..ጫ(በትግርኛ ሥልት አንብቧት) ወሬ ናውዘዋል – የማያውቁትን ምርጫ፡፡ በየሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ ትርምስ ነው፡፡ እዚህም እዚያም ውክቢያ ነው፡፡ መርመስመስ ነው፡፡ ለቀልድ በተቋቋመ የሚንስትር መሥሪያ ቤት ውስጥ አንድ ሚኒስትር ሦስትና አራት ሚኒስትር ዴታ፣ ሃያና ሠላሣ ዋና የሥራ ሂደት ባለቤቶች … ቅብጥርስ ቅብጥርስ፡፡ ግን ሁሉም ከንቱ፡፡ ጠብ የሚል ነገር የለም፡፡ ሁሌ ቁልቁል፡፡ የመፈክሩ ዓይነት አበዛዙ… ሙስና የዕደገት ፀር ነው … እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን … ራዕይህን ከግብ እናደርሳለን … አንተ ብትለየንም ራዕይህና ውድ ባለቤትህ አዜቢና ከኛ ጋር ናቸው(ከራሴው ምርቃት ጋር)፤ ከሦስት ዓመታት በላይ የወሰደ በየትም ሀገር ያልታዬ ሀዘን – በዚህስ ሰሜን ኮሪያም ሳትበልጠን አትቀርም – ወዲያው ነው የረሱት የነኪምን ሞት፡፡ የባልና ሚስት ወይም የልጅ፣ የወንድምና የእህት ሞት እንኳን በስድስት ወርና በዓመት ይረሳል፡፡ ሕይወት በየፈርጁ ነው፤ የሞተ ይረሳል -ያልሞተ ኑሮውን ይቀጥላል፡፡ በሞተ ሰው ምክንያት ሕይወት ቀጥ አትልም – እንደኢትዮጵያ፤ እኛ ከመለስ ሞት በፊት እንደነበርነው ቀጥ ብለን አለን – እንዲያውም ብሶብን፡፡ በሞተ ማላዘን የጤናማነት ምልክት አይደለም፡፡ ደግሞም ብዙዎቹ መለስን ከልባው ወደውት አይመስለኝም – ለማስመሰል ነው፡፡ እንደታዘብኩት በርሱ ስም ልጁን የሚጠራ እንኳን አልገጠመኝም፡፡ ይህ በራሱ የሚያሳየው እርሱን የወደዱት ለጥቅማቸው እንጂ ማፈሪያቱን እንደማይክዱት ነው፡፡

ደግሞም… የዓላማና ግቡ ዝርዝር … የዚህ ሚኒስትር መ/ቤት ራዕይ …. ዓላማዎች …. ግብ …. የሥነ ምግባር መርሆዎች … ታማኝነት፣ ግልጽነት፣ ሃቀኝነት፣ ተጠያቂነት፣ ቅንነት፣ ለሕዝብ ታዛዥነት፣ … አቤት አቤት የሚነበበው ጉድ! በተግባር ግን ሁሉም ከዜሮ በታች፡፡ መጥኔ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን! ሶማሌና ጂቡቲ በስንት ጣማቸው! ምነው ጂቡቲያዊ ወይም ፊጂያዊ ወይንም ዶሞ ሃይቲያዊ ሆኜ በተፈጠርኩ ኖሮ፡፡

ለማንኛውም የቤቴን የሰሞኑን አዲስ ሹመት ልግለጽላችሁና ልሰናበት፡፡ መቼም ጊዜው የቀልድ ሆኗል፡፡ የቤተሰቤ አባላት ለጊዜውና ለአሁኑ ስድስት እንደሆኑ ይታወስልኝ – ቡችዬንና ውርየን ጨምሮ፡፡

 

በህገ መንግሥታችን አንቀጽ 39 መሠረት የነፃነት ዘለቀ ቤት አዲሱ የሥልጣን መዋቅር

 

ዶክተር ነፃነት ዘለቀ

የቤቱ የውጭ ጉዳዮች የሥራ ሂደት ባለቤት

ረዳት ፕሮፌሰር ሸዋርካብሽ እርገጤ

የቤቱ የቤት እመቤትነት ጉዳዮች የሥራ ሂደት ባለቤት

 

ወጣት ዘገየ ነፃነት (ወንድ ነው)

የቤቱ ፀረ-ኢሣት አባላትን የማብዛትና ፎክስሙቪስን የማዘውተር ንዑስ የሥራ ሂደት ባለቤት

 

ሕጻን ደምመላሽ ነፃነት

የቤቱ የሞሰብና ድስት ጉዳዮች ንዑስ የሥራ ሂደት ባለቤት

 

ችሎማደር (ቡቺ)

የግቢው ፀጥታና ደኅንነት ጉዳዮች የሥራ ሂደት ባለቤት

በድምጽሽ ይራዱ (ውርዬ)

የቤቱ ሞሰብ ገልብጥ ዐይጦችን አባራሪ ግብረ ኃይል የሥራ ሂደት ባለቤት

 

ማሳሰቢያ፡- ይሄ አበበ ገላው የተባለ ልጅ ነገር መፈልፈል ይዟልና ለርሱ ሸር ላለመመቸት ስል              የኔን የዶክትሬት ማዕረግ ያገኘሁት እንደወያኔዎቹ ከሴንቸሪ ዩንቨርስቲና ከመሳሰሉት           ዲግሪ ቸብቻቢዎች በዶላር ገዝቼ ሣይሆን በላቤና በጥረቴ በቤተሰብ ጉባኤ የተሰጠኝ            መሆኑን እንዲሁም ክብርት ባለቤቴ በሆም ኢኮኖሚክስ የረ/ፕሮፌሰርነትን ማዕረግ ከዚሁ       ቤተሰባችን ያገኘች መሆኗን ልገልጽ እፈልጋለሁ(አይ የምትጠምቀው ጠላ – የዶሮ ዐይን              ይመስላል፡፡)

ዘግይቶ የደረሰኝ አዝናኝ ወሬ!

የወያኔ የምርጫ ቡችሎች እንዲህ አደረጉ አሉ፡፡ በዚያን ሰሞን ደብረ ዘይት አካባቢ የምግብ ዘይትን ከየሱቁ ያጠፋሉ፡፡ ከዚያም ሕዝቡ ሲንጫጫ በየቀበሌው ያመጡና ሕዝቡ ወደነዚያ ቀበሌዎች በመሄድ ዘይት እንዲገዛ ያስነግራሉ፡፡ ነዋሪው ወደየቀበሌው ሲሄድ ግን “የምርጫ ካርድ የማይወስድ ዘይት አይሰሸጥለትም” ይሉና በግድ ካርድ ያስወስዳሉ፡፡ ይቺ ናት ምርጫ፡፡ ሕዝብን እያስራብክና በመሠረታዊ ፍላጎቱ እየመጣህ ምርጫ ካርድ እንዲወስድ ማስገደድ፡፡ ከዚያም በኮሮጆ ገልባጭ ልዩ ኃይል የሕዝብን ካርድ ለወያኔ ማዛወር፡፡ ከዚያም የግፍ አገዛዝህን መቀጠል፡፡ ቀልደኞቹ የወያኔ የምርጫ አስፈጻሚ ካድሬዎች ልክ ይሕዋ ምሥክሮች     ይቺን ጽሑፍ አይተዋታል?” እያሉ ሃይማታውን ለማስፋፋት እንደሚሞክሩት የወያኔ ጭፍሮችም በየመንገዱና በየጥጋጥጉ በየመውጫና መግቢያ በሮቸ እየጠበቁ “የምርጫ ካርድ ወስደሃል?” እያሉ ሲያሰለቹ ብታዩ ደግሞ አዲስ ሃይማኖት ተመሠረተ ወይ ትላላችሁ፡፡ የጉድ ሀገር፡፡ አፉን ከፍ በሚውል የምርጫ ካርድ መውሰጃ ጣቢያ ስንትና ስንት ሚሊዮን ሕዝብ መመዝገቡን ስንሰማ የወያኔውን ውሸት ለከት የለሽነት እንረዳለን፡፡ በ97 ያ ሁሉ ሕዝብ ተመዝግቦ 26 ሚሊዮን ነበር የተባለው – እርግጥ ነው ያ ቁጥር እውነትም ሊሆን ይችላል፡፡ በቀጣዩ የ2002 “ምርጫ” ግን ጥቂት መቶ ሺዎችን መዝግበው ሲያበቁ በሀገሪቱ 32 ሚሊዮን መራጭ እንደተመዘገበ ቅንጣት ሣያፍሩ በሚዲያቸው ለፈፉ፡፡ ቁጥር የሚያውቁ አይመስሉኝም እነዚህ ደነዝ ወያኔዎች፡፡ ከሁሉም የበደላቸው እርጉሞች፡፡

comment_stage_5

 

 

 

The post በሥራ ሂደት ባለቤቶች የተጥለቀለቀች ብቸኛዋ ሀገር! – ነፃነት ዘለቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

የ 119ኛው ዝክረ አድዋ ፤ 1888   –ከበደ አገኘሁ ቦጋለ

$
0
0

Battle of Adwaየተከበራችሁ አባቶች ፥ እናቶች፥ ወንድሞች፥ እህቶችና ልጆች ! ዛሬ በዚህ የተሰባሰብነው ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን የዛሬ 119 ዓመት እንደዛሬው በነገድ ወይምብ ብሔር እንዲሁም በሃይማኖት ሳይከፋፈሉ ፥ ለአንድ ብቸኛ ዓላማ በአንድነት ተሰልፈው ባህላቸውን ፤ ሃይማኖታቸውን፤ ታሪካቸውን፤ ሰብአዊና ብሔራዊ ነፃነታቸውን፤ ባጠቃላይ ኢትዮጵያዊ ማንነታቸውን አጥፍቶ የቅኝ ተገዥ ባርያ አድርጎ ለመግዛት ከአህጉረ አውሮፓ ተንቀሳቅሶ፥ ባህረ ኢያሪኮንና ቀይ ባሕርን ተሻግሮ፥ የእናት አገራችንን ክብረ ወሰን ጥሶ የገባውን የጣልያን ወራሪ የጠላት ጦር አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ጥቁር ሕዝቦች በአውሮፓውያን ቅኝ ገዥዎች ላይ ድል ተቀዳጅተው በዓለም ታሪክ ውስጥ ታላቅ ምዕራፍ ያስመዘገቡትን ታሪካዊ ዕለት እኛ የልጅ ልጆቻቸው በኩራት ለማስታወስ ነው ። ይህ ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን ደማቸውን ቀለም አጥንታቸውን ብዕር አድርገው ያስመዘገቡት ታላቁ የታሪክ መዝገብ የተመዘገበበት ዕለት፥ እሑድ ዕለተ ሰንበት ፥ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም ነበር።

ለመሆኑ የጦርነቱ መንስኤ ምን ነበር ?

አውሮፓንን ያጥለቀለቀው የ19ኛው ምእት ዓመት ዘመናዊ የእንዱስትሪ ለወጥ ወይም እንዳስትርያል ሪቮሉሺን ለእንዳስትሪያቸው ጥሬ ዕቃ፥ ማለት እንደማዕድን የመሳሰሉትን ሀብተ ከርሠ ምድሮች እንዲፈልጉ አውሮፓውያኑን አስገደዳቸው። ስለዚህ ዘመናዊ እንዳስትሪ ባስገኘላቸው ዘመናዊ የጦር መሳርያ አውሮፓዊ ያልሆነ ዘር የማይኖርባቸውን የአፍሪካንና የ እስያን ፤ ቀደም ብለውም የሰሜንና የደቡብ አሜሪካን ነባር ሕዝቦች እየጨፈጨፉ በቁጥጥራቸው ስር አደረጉ።የፈለጉትን ጥሬ እቃም በነፃ ማጋዝ ፤ ያመረቱትን ሸቀጥም በቅኝ በሚገዟቸው አገር ሕዝቦች ላይ በማጋረፍ ካፒታሊዝምን ገነቡ። በቅኝ የሚገዟቸውን ሕዝቦች ነባር ኃይማኖታቸውን፣ ቋንቋዋቸውንና ታሪካቸውን ለወጡት። የስነ መንግሥት፥ የምጣኔ ሀብት፥ የማኅበራዊ ኑሮ ነፃነታቸውንና ሰብአዊ ክብራቸውን ገፈፉት። ስነ ልቦናቸውን በመቀየር በራሳቸው እንደሰው  የመተማመን ባህርያቸውን እንዲያጡ በማድረግ የበታችነት ስሜት እንዲያድርባቸው አደረጉ። ባጠቃልይ በቃላት ለመግለጽ የሚያስቸግር ኢሰብአዊ ድርጊት የሚፈጽሙበት ዘመን ነበር። ይህን በመሰለው የዓለም ተጨባጭ ሁኔታ ፥ አውሮፓዊ ያልሆነ ሕዝብ ፥ በተለይም ጥቁር አፍሪካዊ ሕዝብ ሁኖ ለአውሮፓውያን ነጮች አልገዛም ፣ ክብረወሰኔንና ሰብአዊ ክብሬን አላስደፍርም ብሎ ለውጊያ መሰለፍ የማይሞከር እርምጃ ነበር። ዘመኑ ነጮች ነጭ ያልሆነውን ሕዝብ ነፃነት መግፈፍ ከላይ ከአዶናይ (ከአምላክ) የተሠጣቸው ሥልጣን አድርገው ይቆጥሩት ነበር።ለዚህ አላማቸውም ‘የሞራል የበላይነት አለን ‘ ይሉ የነበሩት ምስዮኖቻቸው በክርስትና ስም  “የቄሣርን ለቄሣር ፥ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር አድርግ ” የተባለውን መለኮታዊ ትእዛዝ ጥሰው የቄሣራውያን መሳርያ ሁነው ከክርስትና እምነት ጋር የተቃረነ የግፍ ተልእኮ ይፈጽሙና ያስፈጽሙ ነበር። በክርስትና ስም የተፈጸመውን ባርባራ ኪንግሶልበር የተባሉ አሜሪካዊት “ ዘ ፖይዝን ውድ ባይብል” በተባለው ታሪካዊ ልብ ወለድ መጽሐፋቸው በሰፊው ገልጸውታል። ፖፕ ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛም ይህን በሚመለከት የዛሬ 18 ዓመት አካባቢ በዘመኑ በክርስትና ስም ግፍ ለተፈጸመባቸው ሕዝቦች ይቅርታ ጠይቀውበታል።

አውሮፓውያን በዚህ መልክ በተለይም በአፍሪካ ሕዝቦች ላይ ይህን ግፍ ሲፈጽሙበት በነበረበት ዘመን አገራችን ኢትዮጵያ ለዚህ አይነት የነጮች ግፍ ሰለባ ባትሆንም በራሷ ልጆች በመሳፍንት አገዛዝ ተከፋፍላና በእርስ በርስ ጦርነት ተዳክማ ነበር። በዚህም ምክንያት ማዕከላዊ መንግሥቷ መኖሩና አለመኖሩ ለውጭ ኃይሎች አጠራታሪ ነበር። በዚህ ሁኔታ እንግሊዞች በ1797 ዓ.ም. ምጽዋ ላይ ሰፈሩ። ነገር ግን አካባቢው ያኔ በራስ ሚካኤል ስዑልና ማዕከላዊ መንግሥቱን ወክለው በነበሩት በጎንደር ነገሥታት ቁጥጥር ሥር እንደነብር በሚገባ የሚያረጋግጡ የታሪክ መረጃዎች ኣሉን። ይህ በዚህ እንዳለ ፥ በ1846 ዓ.ም ጀምረው ቆላማውን የባህረ ነጋሺ አካባቢ ግብጾች ሰፍረውበት ነበር። ከዚያም አንድ የግል ንብረት የነበረ የኢጣልያ የባህር ጭነት ማጓጓዥያ ኩባንያ አሰብን ከአካባቢው መስፍን (ሡልጣን) በ1874 ዓ.ም ገዛው። በመቀጠልም ከ3 ዓመት በኋላ በእንግሊዞች አበረታችነት በ1877 ዓ.ም የኢጣልያ ሠራዊት ምጽዋ ላይ ሠፈረ። በዚህም ወቅት ግብጽም በበኩሏ በዚህ አካባቢና በሃረር በኩል ክብረ ወሰናችን ደፍራብን ነበር።

ይህን በመሰለ ሁኔታ አገራችን ኢትዮጵያ ከአድዋ ጦርነት በፊት ለ20 ዓመታት ያለ እረፍት ከውጭ ጠላቶች ጋር ክብረ ወሰኗንና ብሔራዊ ነፃነቷን ለመጠበቅ ስትታገል መቆየቷ ይታወሳል። ለዚህ ታላቅ ብሔራዊ ነፃነትና ማንነት ጥበቃ ጀግኖች መሪዎቿም መስዋዕት ሁነዋል። ከተሰውት መሪዎች መካከል ሁለቱን እንጥቀስ። ዘመነ መሳፍንትን አጥፍተው ዘመናዊትና አሐዳዊት ኢትዮጵያን የመሠረቱት ጀግናው አፄ ቴዎድሮስ በጀኔራል ናፔር የተመራውን የእንግሊዝ ጦር በለስ ቀንቷቸው ድል ባያደርጉትም መቅደላ ላይ በ1860 ዓ.እ ‘’እምተቀንዮ በነገደ ያፊት ፥ ይሄሰኒ መዊት” ብለው ራሳቸውን ሰውተዋል። አዎ ‘የአቢሲንያው አምበሳ በአሮፓ ድመት ተዋርጀ እጅ ሰጥቸ ከምገዛስ የማይቀረውን ሞት ብመርጥ ይሻለኛል’ ብለው ፥ በፈረንጆች አቆጣጠር April 13, 1868 (በእኛ በ1860 ዓ.ም)፣ ሊረዳቸው የሚገባው የወገን ኃይልም ለጠላት አሳልፎ ስለሠጣቸው፣ የራሳቸውን ሺጉጥ ጥይት ጠጥተው፥ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ከ13 ዓመት የውስጥ ውጣ ውረድ በኋላ ይህን በሚመስል አሳዛኝ ሁኔታ ተሰውተዋል።

ከአፄ ቴዎድሮስ አሳዛኝ እረፍት በኋል ለሁለት ዓመት ያህል ንጉሥ ተክለ ጊዮርጊስ በሚል የዘውድ ስም የነገሡት ዋግሹም ጎበዜን ድል አድርገው የነገሡት አፄ ዮሐንስ 4ኛ እና የጦር መሪያቸው የነብሩት ጀግናው ራስ አሉላ አባ ነጋ የመሩት የኢትዮጵያ ጦር ፥ በ1867 ዓ.እ ጉንደት ላይ እና በ1868 ዓ.እ ጉራ ላይ የግብጽን ጦር ፣ በ1879 ዓ.እ  ዶጋሌ ላይ የኢጣልያንን ጦር ተዋግቶ ድል ተቃዳጅቶ ነበር። ከዚያም በመቀጠል አፄ ዮሐንስ ጎንደርን ወሮ የነበረውን የድርቡሽ/ሱዳን ጦር ለመዋጋት የሰሜኑን ግንባር ትተው ወደ ጎንደር ተመለሱ። ጎንደርን ነፃ ካወጡ በኋላ መተማ ከሀገራቸው ድንበር ላይ መጋቢት 1 ቀን 1881 ዓ.ም ፥ በፈረንጆች March 10, 1889 ለሀገራቸው ተሰውተዋል።

ስለዚህ እነዚህ ያለምንም ፋታ ከውጭ ወራሪ ኃይል ጋር ለ20 ዓመታት የተደረጉ ጦርነቶች ይህን ዛሬ የምናስበውን የአድዋን ድል በአፄ ምንይልክ ለተመራው ኅብረ-ብሔራዊ ጦር ትልቅ ልምድና ወታደራዊ ተመክሮ ሠጥተውት ነበር። በአንፃሩ ደግሞ ለ20 ዓመታት የተደረገው የማጥቃትና የመከላከል ጦርነት ብዙ ብሔራዊ የሀብት ምንጭ አስጨርሶ ነበር። የዘመነ መሳፍንት ስሜትም በአንድ አንድ አካባቢ ጨርሶ አልጠፋም ነበር። ከዚህም በተጨማሪ ከፍተኛ ድርቅ ሀገሪቷን ጎድቷት ስለነበር  ከአድዋ ድል በኋላ ጣልያንን ከኤርትራም ጭምር ጨርሶ ለማስወጣት የነበረውን ወታደራዊ እቅድ እንዲደናቀፍ አድርጎታል። ስለዚህ ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ ችግሮች ተባብረው የኢትዮጵያን ሕዝብ አጎሳቁለውት ስለነበር ነበራዊ ሁኔታው ለኢጣልያ ወራሪ ጦር ምቹ ሁኒታን የፈጠረ መስሎ ይታይ ነበር። ሆኖም ግን ይህን የተፈጥሮና ሰው ሠራሺ ችግር አፄ ምንይልክ በጣም አዋቂና አስተዋይ መሪ ስለነበሩ ሁሉንም በብልሀትና በትግስት ይዘውት ነበር። ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ብጡል ኃይለ ማርያምም ‘’መልካም ሚስት ለባልዋ ዘውድ ናት” እንደተባሉት ፥ እውነትም ዘውዳቸው ስለነበሩ የሚሠጧቸውን ምክር ሁሉ ንጉሠ ነገሥቱ በጥሞና ያዳምጡ ነበር። እቴጌ ጣይቱ በሀገራችን ሥርዓተ ትምህት መሠረት ከውዳሴ ማርያም ጥሬ ንባብም አልፈው ዜማውን ፤ እንዲሁም ጾመ ድጓና ቁም ጽፈት ጭምር ደበረ ታቦር ኢየሱስ እየተማሩ ያደጉ ሴት ነበሩ። ከዚህም ሌላ የስሜኑ መስፍን የደጃዝማች ዉቤ ኃይለ ማርያም ወንድም የደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም ልጅ ስለነበሩ የቤገምድርንና ስሜንን ፥ ከዚያም አልፈው ጠቅላላ የሰሜን ኢትዮጵያን ሕዝብ ስነልቦና በሚገባ ጠንቅቀው ያውቁ ስለነበር አፄ ምንይልክ “እቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዘኢትዮጵያ “ የሚል ማኅተመ ስም ሠጥተዋቸው ነበር። እቴጌ ጣይቱ ጎንደሬ ብቻም ሳይሆኑ ከወሎ ኦረሞወችና ሺሬ ከትግራይዮችም ተወላጅ ስለነብሩ ፥ ያኔ የጣልያን ጠቅላይ ምንስቴር የነበረው ፍራንሲስኮና መረብ ምላሺን “ኤርትራ” በሚል ስም በጣልያን ፓርላማ አሰይሞ ፥ ከአፄ ዮሐንስ ዘመነ ዕረፍት ጀምሮ ሲገዛ የነበረው ጀኔራል ባርትየሪ ውስጥ ውስቱን የሰሜን ኢትዮጵያን መሳፍንቶች በምንይልክ ላይ እንዲያምፁ ሲያደርጉት የነበረውን ማባበል እቴጌቱ በነበራቸው የሥጋ ዝምድና ትስስር አክሽፈውታል። ማለት የሰሜን ኢትዮጵያ መሳፍንቶች የጠላትን የማባበልና የመከፋፈል  ሴራ ሳይቀበሉት ቀርተዋል።

ጣልያን ኢትዮጵያን ጠቅልሎ የመግዛት ዓላማው የማይሳከለት መሆኑን ከተረዳ በኋላ የኤርትራ ግዛቱ ብቻ በኢትዮጵያ በኩል እውቅና እንዲያገኝለት ወሰነ። አፄ ምንይልክም ዙርያውን በአውሮፓ ቅኝ ገዥ ኃይሎች ተከበው ስለነብሩ ሁሉን ከማጣት ብለው፥ ከነበረው ተጨባጭ ሁኔታ ተነስተን ስናየው ሃሳቡን መቀበል ግድ እንደሆነባቸው መገመት አያዳግትም። ስለዚህ በሁኔታው አስገዳጅነት ሚያዝያ 25 ቀን 1881 ዓ.ም ኢጣልያ የኤርትራ ቅኝ ገዥ መሆኗን የሚያረጋግጥ 19 አንቀጽ ያለው ስምምነት ወሎ ውስጥ ልዩ ስሙ ውጫሌ ከተባለ ቀበሌ ላይ ተደረገ። በተለይ አንቀጽ 17 በጣልያንኛ የተጻፈው ከዐማርኛው ጋር የተቃረነና አሻሚ ትርጉም ይዞ ነበር ለአውሮፓ መንግሥታትና ሕዝቦች የተበተነው። ኢትዮጵያ የኢጣልያ ጥገኛ (protectorate)እንደሆነችና ከውጭ መንግሥታት ጋር የሚኖራት የዲፕሎማቲክ ግንኙነት በኢጣልያ በኩል ካልሆነ እንደ ነፃ ሀገር በራሷ ብቻ ማድረግ እንደማትችል ተደርጎ ነው ለአውሮፓ መንግሥታት የተበተነው ።

ይህ ውል የተጭበረበረ እንደነበር በኢትዮጵያ በኩል ሊታወቅ የቻለውም አለቃ አጽመ ጊዮርጊስ የተባሉ ኢትዮጵያዊ የቋንቋ ሊቅ በጣልያንኛ የተጻፈውን እንዲመረምሩት ተሠጥቷቸው ስለነብር ፣ አለቃ ይህን ነገር በሚገባ ለንጉሡ አደገኛነቱን አስረዷቸው። ይህን እንደተረዱ አፄ ምንይልክ ወደቤተ መንግሥታቸው እየተመላለሰ ፤ ‘’ጌታየና ግርማዊ’’ እያለ በለሰለሰ አንደበቱ በውዳሴ ከንቱ ሲደልላቸው የነበረውን ስኞር ኮንቲ አንቶሊኒ የተባለውን፥ ማለት ጣልያንን ወክሎ ውሉን የፈረመውን ዲፕሎማት አስጠርተው ፥ አንቀጽ 17 የተጭበረበረና ከዐማርኛው ቅጅ/ኮፒ በፍፁም የማይገናኝ መሆኑን እንደደረሱበት ነገሩት። እሱ ግን በተለመደው ለስላሳ አንደብቱ ‘’ይህን ያለወት ሰው በመንግሥትዎ ላይ ቅን አስተሳሰብ የሌለውና በጠላትነት ሊነሳብዎ ያሰበ ሰው መሆን አለበት አንጅ ነገሩ ምንም የተጭበረበረ ትርጉም የለውም” ብሎ ለጊዜው አሳመናቸው። ንጉሡም በአለቃ ላይ ተበሳጭተው አለቃን እንዲታሰሩ አደረጓቸው። ‘እውነትና ብርሃን እያደር ይጠራል ‘ ነውና ፥ ሳይውል ሳያድር ሙሴ ማሪ ዴሎሜኩል የተባለ ፈረንሳዊ ዲፕሎማት በጅቡቲ በኩል ወደ አንኮበር መጥቶ ልክ አለቃ አጽመ ጊዮርጊስ የተናገሩትን ነገር ሳይጨምርና ሳይቀንስ በማስረዳት አገራቸው ኢትዮጵያ የጣልያን ጥገኛ አገር እንደሆነች የአንቀጽ 17ቱ ውል እንደሚያስረዳ በአውሮፓ መንግሥታት ዘንድ ግንዛቤ እንደተጨበጠ ነገራቸው። ንጉሡም አለቃን ይቅርታ ጠይቀው ፈቷቸው።

አፄ ምንይልክ ይህን ከተረዱ በኋላ ለአውሮፓ መንግሥታት ማስተባበያቸውን ላኩ። ኢትዮጵያ ያቀረበችውን ማስተባበያ ያኔ ሦስተኛውን ዓለም በአብዛኛው በቅኝ ስትገዛ የነበረችው ታላቋ ብርታንያ  አልቀበለውም አለች። አፄ ምንይልክም እናንተ ባትቀበሉት ‘ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔርና ልጆቿ ትዘረጋለች’ ብለው በአምላካቸውና በሕዝባቸው ተማምነው አሻፈረኝ አሉ። አንቀጽ 17ን ብቻም ሳይሆን ጠቅላላ የውጫሌን ውል ኢትዮጵያ ማፍረሷን ወይም መሰረዟን ንጉሠ ነገሥቱ ጥር 4 ቀን 1885 ዓ.ም. ለዓለም አሳወቁ። ፈረንሣይና ሩሲያ የኢትዮጵያን ተቃውሞ በመቀበል የኢጣልያንን የኢትዮጵያ የበላይ ጠባቂነት እንደማይቀበሉት ተስማሙ። በተለይ የሩሲያው ንጉሥ ወይም ዛር ኒኮላስ ወታደራዊ እርዳታ ለማድረግ ወሰኑ። የጦር መሣርያም በመላክ ውሳንያቸውን በድርጊት ፈጸሙ።

በዚህ ምክንያት ከሁለት ዓመት ውዝግብ በኋላ የጣልያን ወራሪ ጦር መረብን ተሻግሮ ደብረ ሃይላ ላይ አደጋ ጥሎ አካባቢውን እንዲጠብቁ ተሹመው የነበሩትን የትግራይ ባላባቶች፣ ፊታውራሪ ንጉሤን፥ ቀኛዝማች ኃይለ ማርያምን፥ ቀኛዝማች አንድአርጋቸውንና ባላምባራስ በየነን ወግቶ በመስከረም 29 ቀን 1888 ወረራ መጀመሩን አፄ ምንይልክ ሰሙ። ከዚህ በኋላ አፄ ምንይልክ ጥቅምት 2 ቀን 1888 ዓ.ም የሚከተለውን የጦርነት አዋጅ አውጀው ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን ጦር ግምባር ከእቴጌ ጣይቱ ጋር ኅብረ ብሔር ሠራዊታቸውን መርተው ለመንቀሳቀስ ተዘጋጁ። የጦርነቱ አዋጅ በዛን ጊዜው ዐማርኛ ይህን ይመስል ነበር።

ቃለ አዋጅ !

“እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ፣ አገሬን ጠብቆ አኖረኝ። እኔም እስካሁን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ። እንግዲህ ብሞትም ሞት የሁሉም ነውና ስለኔ ሞት ኣላዝንም። ደግሞም እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም። እንግዲህም ያሳፍረኛል ብየ አልጠራጠርም።

አሁንም አገር የሚያጠፋ፥ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት እግዚአብሔር የወሰነልንን ባህር አልፎ መጥቷል። እኔም ያገሬን ከብት ማለቅ የሰውንም መድከም አይቸ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደ ፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር።

አሁን ግን በእግዚአብሔር ረዳትነት አገሬን አሳልፌ አልሰጠውም። ያገሬ ሰው ! ካሁን ቀደም የበደልኩህ አይመስለኝም። በድየህም ከሆነ ለሀገርህ ስትል ይቅር በለኝ። አንተም እስካሁን አላስቀየምከኝም። ስለዚህ ጉልበት ያለህ በጉልበትህ እርዳኝ። ጉልበት የሌለህ ለሚስትህ፥ ለሃይማኖትህ፥ ለሀገርህና ለታሪክህ ስትል በጸሎትህ እርዳኝ። ወስልተህ የቀረህ ግን ኋላ ትጠላኝ አለህ ፣ አልተውህም ! ማርያምን ! ለዚህ አማላጅ የለኝም ! “ የሚል ነበር የአዋጁ ቃል ።

አዋጁን አውጀው ወደ ሰሜን ጦር ግምባር ከመሄዳቸው በፊት የተቀረውንም የሀገሪቱን ክፍል ዙሪያውን አውሮፓውያን ከበውት ስለነበር ወሰን ጠባቂ ጦር መመደብ ነበረባቸው። በዚህ መሠረት የጅማው ሹም ጅማ አባ ጅፋር ፥ የሊቃው ሹም ደጃዝማች ገ/እግዚአብሔርና ደጃዝማች ጆቴ፥ የወላይታው ሹም ንጉሥ ጦና ካዎና ሌሎች፥ የምዕራቡንና ደቡቡን ድንበር እንዲጠብቁ። በምሥራቅና በሰሜን ምሥራቅ ደግሞ ከአፋር አርበኞች ጋር ተባብረው በአሰብ በኩል ጠላት እንዳይመጣ እንዲጠብቁ ራስ ወልደ ጊዮርጊስ፥ ደጃዝማች ተሰማ ናደውና የወሂን አዛዥ ወልደ ጻድቃን 15,000 ጦር ይዘው እንዲሰለፉ ሁኖ ነበር።የመናገሻ ከተማዋንና አካባቢውንም ራስ ዳርጌ ሣህለ ሥላሴ፥ ራስ ልዑል ሰገድና ደጃዝማች ኃይለ ማርያም 8000 ጦር ይዘው እንዲጠብቁ ተመድበው ነበር።

ይህን ካጠናቀቁ በኋላ የሰሜኑ ዘመቻ ቀጠለ። የመጀመሪያውን የጠላት ጦር አምባ ላጌ ላይ በፊታውራሪ ገበየሁና ፊታውራሪ ተክሌ የተመራው የግንባር አብሪ ጦር በሻለቃ ቶዘሊን ይመራ የነበረውን የጠላት ጦር  ኅዳር 28 ቀን 1888 ዓ.ም ደምስሰው ጠላት ሲጠቀምባቸው የነበሩትን መድፎችና ሌላ መሳርያ ከነብዙ ጥይቱ ማርከው፥ የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ ከአምባይቱ ላይ ሰቅለው እያውለበለቡ ቆዩ። (የአምባላጌ ከፍታ 11,279 ፊት ነው።) ቀጥለውም ግፋ ወደፊት በማለት ታህሣስ 29 የክርስቶስ የሥጋዌ ልደት መታሰቢያ ቀን መቀሌ ደርሰው መሺጎ ከነበረው ከጠላት ጦር ጋር ፍልሚያ ጀመሩ። ነገር ግን ምሺጉን ሰብሮ መግባት ከወገን በኩል ከፍተኛ መስዋዕትነት የሚጠይቅ መሆኑ ስለተረጋገጠ ፥ እቴጌ ጣይቱ ሲመሯቸው ከነበሩት መካከል 300 አርበኞችን ጠላት ባልጠበቀው መንገድ ልከው ፥ ጠላት ሲጠቀምበት የነበረውን የውሀ ምንጭ ኣስደፈኑት። ከ15 ቀን ቆይታ በኋላ የጠላትን ጦር በተለመደው ኢትዮጵያዊ ሰብአዊ ርህራሄ ምሺጉን ለቆ እንዲሸሺ ምህረት አደረጉለት። የዚህ ታሪክ ምንጭ አንዱ ከሆኑት ከአቶ ዮሐንስ መሸሻ ጽሑፍ ላይ የመቀሌውን ድል አስመልክቶ የገጠሙት ግጥም እንዲህ ይላል።

መቀሌ እንዳ ኢየሱስ ጦር ያሰፈረው ፥

አንድ ሺህ አንድ መቶው እውሀ እንዲጠማው፥

ምንጩን አዘግታ ጣይቱ አቃጥላው፥

ማጆር ጋሊያኖ ጉሮሮው ደርቆበት እንባ ሲወርደው፥

መኮነን አማልዶት እምየ ምንይልክ በምህረት ላከው ።

የኢትዮጵያ ጦር በዚህ ሁኔታ ጠላትን ከመቀሌ ካስለቀቀ በኋላ በቀጥታ ጠላት ሠፍሮበት ወደነበረው ሕዳጋ ሐሙስና አዲግራት መሄዱን ትቶ በምዕራብ በኩል ወደ አድዋ ሄደ። ምክንያቱም ሕዳጋ ሐሙስና አዲግራት ላይ የጠላትን ምሺግ በቀላሉ መስበር እንደማይቻል የወገን ጦር መረጃ ነበረው። የጠላት ጦርም የወገን ጦር ወደ አዲግራትና ሕዳጋ ሐሙስ እንደማይመጣ ከተረዳ በኋላ ፥ ወደ ምዕራብ ተንቀሳቅሶ ከአድዋ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ከምትገኘው ሳውርያ ላይ ምሺግ ቆፍሮ 20,170 የታጠቀ ጦር ይዞ የኢትዮጵያ ጦር ጥቃቱን እንዲጀምር ይጠባበቅ ነበር። ነገር ግን ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ወታደራዊ እቅድ እንጅ በጠላት ፕላን መሄድን ስላልፈለጉ ጥቃቱ ከጠላት በኩል የሚጀመርበትን ዘዴ ማቀነባበር ጀመሩ። ማን እንደሚጀምር ሲጠባብቁ ግን በሁሉም በኩል ስንቅ እያለቀ ነው። የባሰው ግን በጣላት በኩል ነበር። በዚህም ምክንያት ጠላት ጥቃቱን እንዲጀምር ሁኒታዎቹ እያስገደዱት መጡና የአድዋው ትያትር /ትርኢት እንደሚከተለው ሆነ።

የካቲት 20 ቀን 1888 ወደማታ አካባቢ የግፈኛውን የጣልያ ወራሪ ጦር ሲመሩ የነበሩት 5ቱ ጀኔራሎች እንትጮ ተራራ ላይ ድንኳናቸው ወስጥ ተሰብስበው የጥፋት ተልዕኳቸውን ማሳካት የሚችል ወታደራዊ ፕላናቸውን መቀየስ ጀመሩ። የጀኔራሎቹም ስም የሚከተለው ነበር። የኤርትራ ገዥ የነበረው ጀኔራል አረስቲ ባራትየሪና አራቱ የብርጌድ ኣዝዦች ፥ ጀኔራል አልበርቶን፥ ጀኔራል አርሞንዲ፥ ጀኔራል ዳቦርሚዳ፥ እና ጀኔራል ኢለና ነበሩ። በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ጣልያናዊና ጥቁር እራስ አስካሪ በዚያ ዘመን ደረጃ እጅግ ዘመናዊ ሥልጠና በተሠጣቸው የበታች የጦር መኮንንኖች ስር ተሰልፎ ትእዛዝ ከበላይ አዛዦቹ በመጠባበቅ በተጠንቀቅ ላይ ነበር። ያን የመሰለ ሠራዊት በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ለውጊያ ሲሰለፍ በታሪክ የመጀመሪያው እንደነበር ብዙ የታሪክ ጠበብቶች ይስማማሉ።

20 ኪሎ ሜትር ራቅ ብሎ አድዋ ላይ ደግሞ ፣ ቀደም ብሎ ጣልያኖችን በድንበር ሲከላከላቸው የነበረው የራስ መንገሻ ዮሐንስ ጦር ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ ከላይ ተደጋግሞ እንደተገለጠው የመላው ኢትዮጵያ ኅብረ ብሔር ጦር በታላቁ ንጉሠ ነግሥት ምንይልክ ኃይለ መለኮትና በጀግናዋ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ኃይለ ማርያም የበላይ አዛዥነት፣ በእግዚአብሔር የበላይ ጠባቂነትና በርሱም ፍፁም ታማኝነት፣ ሠራዊቱ ከዚህ እንደሚከተለው በሀገር ወዳድ አዛዦች ስር እየጣለ ለመውደቅ በቆራጥነት ተሰለፈ።

በሰሜን በኩል የትግራይ ጦር በራስ መንገሻ ዮሐንስ አዛዥነት፣ በስተደቡብ በሽሎዳ ተራራ በኩል ያኔ የማህል ሰፋሪ እየተባለ የሚታወቀውን ሠራዊት በመምራት ፊታውራሪ ገበየሁ፣ የሐረርን ጦር በመምራት የአፄ ኃይለ ሥላሴ አባት ራስ መኮነን ወ/ሚካኤል፣ የታች ወሎን ጦር በመምራት ንጉሥ ሚካኤል አሊ ፣ ዋግሹም ጓንጉል ፥ ደጃዝማች ኃይሉና (የራስ ካሣ አባት) ጃንጥራር አስፋው (የእቴጌ መነን አባት)የዋግን ፥ የላስታንና የአምባሰልን ጦር በመምራት በአድዋ ከተማ ደቡብ በኩል ፣ ራስ መንገሻ አትከም የኤፍራታን ፣ ራስ ወሌ ብጡል (የቴጌ ጣይቱ ወንድም) የቤገምድርንና ስሜንን ጦር በመምራት ፣ ደጃዝማች ባሻህና ሊቀ መኳስ አባተ የሽዋን ጦር በመምራት ፣ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት የጎጃምን ጦር በመምራት ፣ ደጃዝማች ባልቻ አባ ነብሶ ጀግናውን የኦሮሞና የጉራጌን ፈረሰኛ ጦር በማሰለፍ ‘’ኢትዮጵያ ወይም ሞት !” እያሉ ለእናት አገራቸው ነፃነት እየጣሉ ለመውደቅ ተሰለፉ።

የግብጹ ተወላጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፥ ታቦተ ጽዮንን በማስያዝ ፣ የአኩስሙ ንቡረ ዕድና የደብረ ሊባኖሱ እጬጌ አፍሮ አይገባውን መስቀል ተሸክመው፣ከአኩስም ቆይታቸው አድዋ ላይ ለውጊያ ወደተሰለፈው ብሔራዊ ጦር ሲጓዙ በተመለከታቸው ጊዜ ሠራዊቱ “የሙሴ ጽላት/ የአማላክ እናት መጣችልን” በማለት የበለጠ መንፈሳዊ ሞራልና ኢትዮጵያዊ ወኔ ተሰማው። በአምላኩ ኃይል ግፈኛውን ወራሪ የጣልያን ሠራዊት እንደሚያቸንፍ ያለምንም ጥርጥር እምነቱን በማረጋገጥ ‘ግፋ ወደፊት ማለት ጀመረ። ሊቀ ጳጳሱም “ ልጆቸ ሆይ ! በዛሬዋ ዕለት ፥ የካቲት 23 ፥ 1888፥ እግዚአብሔር አምላክ ከእኛ ከደካማዎቹ ጎን ተሰልፎ በግፈኛ ወራሪዎች ላይ እውነተኛ ፍርዱን የምናይበት ቀን ይሆናል። የቅዱሳን አባቶቻችሁ ፥ የነቅዱስ ያሬድ፥ የነቅዱስ ላሊበላ፥ የነቅዱስ ተክለ ሃይማኖት፥ የነአባ ኤዎስጣቴዎስ ከፋሌ ባህር፥ የነአባ ፊልጶስ ዘደብረ ቢዘን፥ የነአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ አምላክ ከእናንተ ከግፉአኑ ጋር ነው ! ሂዱ ወደፊት! ኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖታችሁን፥ መካነ ቅዱሳንና ሀገረ እግዚአብሔር የሆነችውን ቅድስት ኢትዮጵያንና ንጉሣችሁን ተከላከሉ ! ኃጢአታችሁ ይሰረይላችሁ።” በማለት ጸሎተ ንስሐ ለንጉሡና ለሠራዊቱ ሠጡ። ካህናቱም ከዚህ ድርጊት ጋር የሚዛመደውን፥ ንጉሠ እስራኤል ዳዊት ከ1,000 ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት የተነበየውን ትንቢት በዚህ ታሪካዊ አካባቢ የተወለደው ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ በ520 ዓ.ም አካባቢ በደረሰው የዜማ ስልት

  • ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ ፥ ከመ ያምስጡ እምገጸ ቀስት፥ ወይድኀኑ ፍቁራኒከ።
  • ጸርሁ ጻዳቃን ወእግዚአብሔር ሰምዖሙ ፥ ወእምኩሉ ምንዳቤሆሙ ያድኅኖሙ፥ ቅሩብ እግዚአብሔር ለየዋሃነ ልብ ።
  • ይገንዩ ቅድሜሁ ኢትዮጵያ ፥ ወጸላእቱሂ ሀመደ ይቀምሁ።
  • አንተ ቀጥቀጥኮ አርስቲሁ ለከይሲ ፥ ወወሐብኮሙ ሲሳዮሙ ለሕዝበ ኢትዮጵያ።
  • ኢትዮጵያ ታበጽህ እደዊሃ ሃበ እግዚአብሔር ፥ ነገሥተ ምድር ሰብህዎ ለአምላክነ ፥ ወዘምሩ ለስሙ እያሉ ይጸልዩ ነበር።

የእስልምና እምነት ተከታይ የነበሩ ኢትዮጵያውያንም ከክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ተሰልፈው እኩል መስዋእትነት ከፍለዋል። እንደ ካህናቱም ሁሉ መንፈሳውያን ሸኽወቹም ድዋ በመያዝ ወይም በመጸለይ አገራቸው ኢትዮጵያን ባህር አቋርጦ ከመጣው ግፈኛ ጠላት ከተቃጣባት ጥፋት እንዲታደጋት አምላካቸው አላህን በመማጸን ላይ ነበሩ። ክርስቲያኑም ሆነ ሞስሊሙ የክተት አዋጁ ከታወጀበት ከጥቅምት 2 ቀን 1888 ዓ.ም ጀምሮ ቀንና ሌሊት የጋራ አምላኩን ከመማጸን አላቋረጠም ነበር።

የጦርነቱ ዝግጅት ሰው ሰራሺ በሆነው ዘዴም ፥ ማለት በመረጃ አሰባሰብም በኩል የተጫወተው ወሳኝ ሚና ነበረው። ታሪኩ እንደዚህ ነበር። አውአሎም ሐረጎት የተባለ የአካባቢው ተወላጅ ወጣት ለኢጣልያ መንግሥት በመረጃ አቅራቢነት እንዲያገለግል ተቀጥሮ ይሠራ ነበር። ታድያ አውአሎም ምንም ቢሆን አፉ እንጅ ልቡ ወደወገኖቹ ያደላ ነበርና ፣ ጠላት በእናት አገሩና በወገኖቹ ላይ ሊፈጽመው ለተዘጋጀው ጥፋት ተባባሪ መሆንን አልመረጠም። ይህም ኢትዮጵያዊ ንቃተ ህሊናው ከጠላት የተማረውን የመረጃ አሰባሰብ ዘዴ አገሩንና ወገኑን እንዲጠቅምበት አስገደደው። ይህን የተቀደሰ ዓላማ ለጓደኛው ለብላታ ገ/እግዚአብሔር ያለምንም ፍርሀት ገለጸለት። ሁለቱ ጓደኞች ይህን ሲያሰላስሉ በነበረበት ወቅት ውዝግቡ በሰላም እንዲፈታ ድርድር ቀጥሎ ነበር። የነዚህ ሁለት ኢትዮጵያውያን አለቃ የነበረው ጣልያናዊው የመረጃ መኮንን ስለድርድሩ  “ ኃያሉ የጣልያን መንግሥት ሠራዊት ይህን የኢትዮጵያን የዝንብ መንጋ ባንድ ቀን አራግፎ ግዛቷን መቆጣጠር ያቅተዋል ተብሎ ነው ድርድር እየተባለ ጊዜያችን የምናጠፋው ?” እያለ ሲደነፋ ለሀገራቸው ሕዝብ ያለውን ንቀት ሲገልጽ፥ አውአሎም እየሰማ ውስጡ ይቃጠላል። ከዚያ ብላታ ገ/እግዚአብሔር አውአሎምን ከራስ መንገሻ ዮሐንስ ጋር የሚተዋወቅበትን መንገድ ይፈልግና ከራስ ጋር አገናኘው። ራስ መንገሻም የአውአሎምን ታማኝነት ካረጋገጡ በኋላ የሚከተለውን ዘዴ ይቀይሳሉ።

ዘዴውም ይህ ነበር። የካቲት 21 ቀን ማርያም ስለሆነች አብዛኛው መሳፍንት ከሚመራው ጦር ጋር ቤተ ክርስቲያን ለመሳለምና ለመጸለይ ወደ አኩስም ጽዮን እንደሚሄድ፣ የንግሥቲቱ ወንድም ራስ ወሌም ስለሞቱ ንጉሡና ንግሥቲቱ በኀዘን ላይ እንደሆኑ፣ አንዳንድ መሳፍንቶችም የሚመሩትን ጦር ይዘው ጣልያንን ድል ማድረግ እንደማይቻል ተስፋ ቆርጠው እየከዱ ወደየመጡበት እየተመለሱ እንደሆነ ፣ የተቀረው ሠራዊትም ስንቅ ጨርሶ ምግብ ፍለጋ ተከዜን ተሻግሮ ጠለምትና ወልቃይት ድረስ እንደሄደና ንጉሡና ንግሥቲቱ ከጥቂት የክብር ዘበኞቻቸው ጋር ድንኳናቸው ውስጥ ስለሚገኙ፥ ስንቅ ፍለጋ ወደ ጠለምትና ወልቃይት የሄደውና፥ ወደ ኣኩስም ጽዮን የሄደው ሠራዊት ከመመለሱ በፊት እሑድ የካቲት 23 ቀን አደጋ ቢጣል በቀላሉ ድል አድርጎ ንጉሡንና ንግሥቲቱን መማረክ እንድሚቻል አድርጎ፥ አዘናጊና የተሳሳተ መረጃ አውአሎም ለጀኔራል ባራትየሪ እንዲሠጠው ይሆናል። እቴጌ ጣይቱ እጅግ በጣም አርቆ አሳቢና ጥበበኛ ስለነበሩ ፥ የጠበቀ እምነት እግዚአብሔርም ስለነበራቸው፥  ከአውአሎም ጋር የተቀየሰውን ዘዴ በቃል ኪዳን ለማጠንከር አውአሎምን እንደልጃቸው እጁን ጨብጠው እየሳቡ ወደ ድንኳናቸው ይዘውት ገቡ። “ ይህን የማቀርብልህን ምግብ እንደ ክርስቶስ ሥጋ ወደሙ ቆጥረህ እናት አገርህንና ወገንህን ላትከዳ በመሃላ ቃል ገብተህ ይህን ያቀርበኩልህን ምግብ ተመገብልኝ “ አሉት። እርሱም “ አገሬንና ወገኔን ለጠላት አሳልፌ ብሠጥ ፥ ሰማይና ምድርን የፈጠር አምላክ ይፍረድብኝ” በማለት ይህን ጠንከር ያለ የተለመደውን አስተማማኝ ኢትዮጵያዊ ቃል ኪዳን ከገባ በኋላ ምግቡን ተመግቦ ፥ ኢትዮጵያ በድል አድራጊነት የተወጣችበትን ወሳኝ ብሔራዊ ግዳጁን ለመወጣት ወደጠላት ጦር ሠፈር ጉዞውን ቀጠለ።

ከጠላት ካምፕ እንደ ደረሰ ከላይ የተዘረዘረውን የተሳሳተ፥ ግን ለጠላት እጅግ አስደሳች የሚመስለውን መረጃ ለጀኔራል ባራትየሪ አቀረበ። ባራትየሪም በቀረበለት መረጃ ረክቶና ተደስቶ ከምሺጉ ወጥቶ ምንይልክን ለመማረክና አገሪቱንም በቅኝ ለመግዛት እየተዝናና መጣ። የተናቀው የኢትዮጵያ ጀግና ሠራዊት ግን ቀደም እንደተገለጸው በየምሺጉ ሁኖ ማህል እስከሚገባ ድረስ አድፍጦ ጠበቀው። ከዚያማ ያን ነጭ የሮማ ስንዴ በጋለ ጥቁር ምጣድ ይቆላው ጀመር !! (እልልልልል!!)። በዚሁ ዕለት ፥ እሑድ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. ወደ 11 ሰዓት አካባቢ እንደ አንድ አገር ሕዝብ በአንድ አመራር ሥር የተሰለፈው የኢትዮጵያ ጀግና ሕዝብ፥ በአምላኩ በእግዚአብሔር ረዳትነት ፥ በጀግና መሪዎቹ አርቆ አሳቢነትና አገር ወዳድነት ጠላቱን ደምስሶ ብሔራዊና ሰብአዊ ማንነቱን ጠብቆ አስጠበቀ። በዚህም ታሪካዊ ድል ከጠላት እብሪተኛ ጀኔራሎች መካከል ጀኔራል አርሞንዲና ጀኔራል ዳቦርሚዳ ሲገደሉ ፣ ጀኔራል ኢለና ወደኤርትራ እንደአጋጣሚ ከተወሰነ ጦር ጋር አመለጠ። 262 የኢጣልያን ተወላጅ መኮንኖችና 4,000 ተራ ወታደሮች ሲገደሉ ፥ 954 የደረሱበት ሳይታወቅ ቀርቷል (Missing in action)። 470 ነጭና 958 ጥቁር ራስ ባንዳዎች ቆስለዋል። ጀኔራል አልቨርቶን ጨምሮ 1,900 ነጭና ከ1,000 በላይ ወደውም ሆነ ተገደው ከጠላት ጋር ተሰልፈው ወገኖቻቸውን የወጉ የመረብ ምላሺ አበሾች ተማርከዋል። 56 መድፎችና 11,000 በዘመኑ የነበሩት ቀላልና ከባድ መሳሪያዎች ሊገመት ካልተቻለ ጥይት ጋር ተማርኳል። ክ100,000 በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሠራዊት ይዟቸው የተሰለፈው 40 መድፎችና 80,000 የሚሆኑ ቀላል የጦር መሣሪያዎች እንደነበሩ ሪቻርድ ፓንክረስትና ሌሎች የታሪክ ጸሓፊዎች ዘግበዋል። ከወገን በኩልም ለሀገራቸው ክብርና ነፃነት መስዋዕት የሆኑት ጥቂቶች አልነበሩም። ከ5,000 በላይ ተሰውተዋል። 8,000 ቆስለዋል። ከተሰውት ውስጥ የአፄ ምንይልክ የአከስት ልጅ፥ የወ/ሮ አያህሉሽ ሣኅለ ሥላሴ ልጅ ደጃዝማች ባሻህና ፊታውራሪ ገበየሁ ይገኙበታል።

ይህን በመሰለ ሁኔታ ለመጀመሪያ ጊዜ አውሮፓዊ የሆነ የነጭ ኃይል በጥቁር አፍሪካዊ ኃይል በመደምሰሱ ድሉ የኢትዮጵያውያን ብቻም ሳይሆን በዚያ ዘመን ተንቆና ተዋርዶ በቅኝ ግዛትና በባርነት ቀምበር ሥር ሲማቅቅ ለነበረው የመላው ጥቁር ዘር ሁሉ ነበር ተደርጎ የታየው። አዎ በአፍሪካ ፥ በካረብያንና በሰሜን አሜሪካ በዘረኛ ነጮች መንግሥትና ሕዝብ ሰብአዊነታቸው ተርሰቶ የነበሩት ጥቁሮች የደስታ ጭላንጭል የሰሙበት ዕለት ነበር። ከዚህም ዕለት ጀመሮ ነበር እነዚህ ህዝቦች ለነፃነታቸው ቆርጠው ለመታገል የበለጠ የተበራቱት። ወርሐ የካቲትንም ልዩ ትኩረት ሠጥተው ‘’Black History Month/ ታሪካዊ የጥቁሮች ወር “ እያሉ እስከዛሬ ድረስ በየዓመቱ እንዲያስቡት ካደረጋቸው አንደኛው ምክንያት ይህ የአድዋ ድል ነው።

እንግዲህ ከተለያዩ የታሪክ ምንጮች የቀዳዋቸው ፥ አባቶቻችንና እናቶቻችን የሠሩት እውነተኛው ትውልድ አኩሪ ታሪክ ከረጅሙ በአጭሩ ይህን ይመስላል። ጥያቄው ግን ዛሬስ ያች የታሪክና የብሔረሰቦች ቤተ መዘክር የሆነችው አገራችን ኢትዮጵያ የ 1888ቱ አይነት ጠንካራ የውጭ ወራሪ ክብረ ወሰኗን ጥሶ ቢገባ ለድል የሚያበቃት አስተዋይ መሪ አላት ወይ ? የጋራ ማንነቱ መገለጫ ከሆነው ከኢትዮጵያዊነቱ ይልቅ ለየግል ማንነቱ፥ ማለት ለዐምሐራነቱ፥ ለኦሮሞነቱ፥ ለትግሬነቱ፥ ለጉራጌነቱ፥ ለአፋርነቱ፥ ለወላይታነቱ፥ ለአገውነቱ ወዘተርፈ..ቅድሚያ እንዲሠጥ ተደርጎ እየተተካ ያለው አዲሱ ትውልድ ፣ ነገ ከነገ ወዲያ አንድነቱን ጠብቆ፥  የሚመጣበትን የውጭ ጥቃት ሊመክት  ይችላል ማለት እንዴት ይቻላል? ይህ የአሁኑ ትውልድ ለብሔር ማንነቱ ነው እንጅ ቅድመ ሁኔታ መሥጠት እንደማይችል እየተነገረው ያለው ኢትዮጵያዊነቱን እኮ በሕገ መንግሥቱ ኣንቀጽ 39 ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው እስከፈለገው ድረስ ነው። ማለት የብሔር ማንነት ግዴታ ሲሆን ኢትዮጵያዊ ማንነት ግን በአማራጭ ደረጃ ነው ትውልዱ እንዲቀበለው ተደርጎ እየተተካ ያለው። ለዚህ እኮ ነው ብሔራዊ ማንነት ከብሔር ማንነት ይቅደም የሚል አጀንዳ ያላቸው በግልም ሆነ በድርጅት ደረጃ እንዲዳከሙ ሁነው በግል ማንነት ላይ ያተኮረ አጀንዳ ያላቸው እየተጠናከሩ የመጡት።

ታድያ የዛሬ 119 ዓመት ‘’ አባት ያበጀው ለልጅ ይበጀው ‘’ ብለው ከአራቱም ማዕዘናት በአንድ ኢትዮጵያዊ ማንነት፥ በአንድ ሠንደቅ ዓላማ አርማ፥ በአንድ መንግሥታዊ አመራር ሥር፥ አንድ አገር አንድ ሕዝብ ብለው ተሰልፈው ደማቸውን ቀለም አጥንታቸውን ብዕር አድርገው ያስመዘገቡትን አኩሪ ታሪክ ጠብቀን ለተተኪው ትውልድ ማስተላለፍ አይጠበቅብንም? ለጥያቄው መልሱ አወንታዊ ነው መሆን ያለበት። አዎ እኛም ዛሬ ለነገው ትውልድ የሚያኮራና የነገው ትውልድ ዛሬ እኛ አባቶቻን የሠሩትን አኩሪ ታሪክ እያሰብነው እንዳለነው ሁሉ  ነገም እኛን እንድንታወስ የሚያደርግ ጥሩ ታሪክ እየሠራን እንለፍ። ይህ ነው የሰውን ልጅ ከእንስሳት ልዩ የሚያደርገው። እናም እንሰባሰብ እንጅ አንበታተን። አንድነት ኃይል መሆኑን ይህ አድዋ ላይ ከ 119 ዓመት በፊት የተሠራው ታሪክ ዘለዓለማዊ የሆነ ታላቅና ቋሚ ምሥክር ነውና በእኩልነት ላይ የተገነባ አንድነት እንገንባ እያልኩ ዝግጅቴን ከዚህ ላይ አጠናቃለሁ። በጥሞና ስላዳመጣችሁኝ አመሰግናለሁ፤ እግዚአብሔር ይሥጥልኝ።

 

ከበደ አገኘሁ ቦጋለ፣ የካቲት 23 ቀን 2007 ።

 

መወድስ ቅኔ ዘአለቃ ዘወልዴ ዘአንኮበር ለአፄ ምንይልክ የተሠጠ።

ትውልድ የኀልፍ ወሰነ አበው ወትውልድ ይተርፍ እምነ አቡሁ በግብር ፤

ምሳሌ ዝኒ ላዕሌከ ሣህለ ማርያም (ምንይልክ)ደብር፤

ሐሰውከሂ ኢትበለኒ እሙነ ዜናሁ ለሰሎሞን በኩር፤

ጠይቅ ወተዘከር ፥ እመ ነባቢሁ ተቀብረ አምጣነ ንባቡ ኢይትቀበር፤

በይነ ጽድቅሂ ወበይነ ርትዕ ወበይነ የዋሃት መንክር ፤

እስከነ ትግሬ ይመርሐከ ስብሐተ የማንከ ፍዳ ጸር፤

አርቲዐከሂ ፍኖተ ማዕከለ ወሎ ሀገር ፤

ተሠራሕ ለኮንኖ ወንገሥ በጎንደር።

The post የ 119ኛው ዝክረ አድዋ ፤ 1888   – ከበደ አገኘሁ ቦጋለ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአድዋ ድል በዓል በሚኒሶታ ተከበረ

$
0
0

ESM 2

ecm minnesota

(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ማህበረሰብ (ኮምዩኒቲ) በሚኒሶታ ያዘጋጀው 119ኛው የአድዋ ድል በዓል በሚኒሶታ ተከብሮ ዋለ::

በሚኒሶታ ከኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ ከወጣትም ሆነ ከአዛውንቶች የተውጣጡ የተለያዩ የማህበረሰቡ ክፍሎች በተገኙበት በዚሁ በዓል ላይ የአድዋ ድል በዓል በተለይ ለኢትዮጵያውያን እና ለጥቁር ሕዝቦች ያለው ትልቅ ም ዕራፍ ተዘክሯል::

ዛሬ በተከበረው በዓል ላይ በክብር እንግድነት የተገኙትና ስለአድዋ ድል ገለጻ የሰጡት ዶ/ር ዳንኤል ሲሆን የአድዋ ድል ከጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ጋር ያለውን ተያያዥነት አውስተው የተለያዩ ገለጻዎችን ሰጥጠዋል::

በዚሁ ዕለት በስፍራው የተገኙ የማህበረሰቡ አባላት እንዲሁ በበዓሉ ዙሪያ ትምህርታዊ አስተያየቶችን እንደሰጡም በስፍራው የተገኘው የዘሐበሻ ዘጋቢ አስታውቋል::

The post የአድዋ ድል በዓል በሚኒሶታ ተከበረ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሆሳህና ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤ/ክ በእሳት ነደደች (ቪድዮና ፎቶዎች ይዘናል)

$
0
0


ቤተክርስቲያኗ ከመቃጠሏ በፊት

ቤተክርስቲያኗ ከመቃጠሏ በፊት

ከተቃጠለች በኋላ

ከተቃጠለች በኋላ

ከተቃጠለች በኋላ

ከተቃጠለች በኋላ


(ዘ-ሐበሻ) እኔ የዘ-ሐበሻ ሪፖርተር ነኝ ያሉ በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች በፎቶግራፍ እና በቭዲዮ አስደግፈው በላኩት መረጃ የካቲት 21/2007 ዓ.ም በሀዲያና ስልጤ ሀ/ስብከት የሆሳዕና ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤ/ክ በእሳት መንደዷን አስታወቁ፡

የቃጠሎው መነሻ እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን ጉዳዩን ለማድበስበስ የሚደረገው ጥረት ም ዕመናኑን እያስቆጣ መሆኑንም ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል::

የካቲት 21 ቀን ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ህዝበ ክርስቲያኑን ለማጽናናት እንዲሁም የገቢ ማሰባሰብ መርሐግብር የሀ/ስብከቱ ሊቀጻጻስ ብጹዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በተገኙበት ከአ.አ በመጡ መምህራን እና ዘማሪያን መርሐ ግብር ተዘርግቶ የነበረ ሲሆን ማንኛውም ም እመን የሚቻለውን ስፍራው ድረስ በመገኘት ድጋፍ እንዲደርግ ያልቻለም በጸሎት እንዲያስቡ በእግዚአብሔር ስም ቅድስት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን አስተላልፋለች ሲሉ እኔ የዘ-ሐበሻ ሪፖርተር ነኝ ያሉ ከስፍራው ዘግበዋል::

ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው በዚሁ ቤተክርስቲያኒቱ በምትገኝበት ከተማ ከሳምንት በፊት በተመሳሳይ እሳት አደጋ አጠና ተራ ወድሟል::

The post የሆሳህና ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤ/ክ በእሳት ነደደች (ቪድዮና ፎቶዎች ይዘናል) appeared first on Zehabesha Amharic.

አድዋ! –ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

$
0
0

hqdefaultዋ! አድዋ ፤ ያ ሑዳዴ

መድፍን ፈንጅን ፤ በጎራዴ

ባሕር ተሻግሮ ፤ የሐበሻን ምድር

ቅኝ ሊገዛ ፤ ይሄ ደፋር!

አንች አድዋ ፤ የበኩር ልጅ

ላንቺ ውልደት ፤ ስንቱ ሲፈጅ

ተጸንሰሽ ፤ ከውጫሌ

ለደም መሬት ፤ ለአሞሌ

እርግዝናሽ ፤ ዘጠኝ ወሩ

ዓመታትን ፤ ማስቆጠሩ

ክፉውን ቀን ፤ ይዞ አሳሩ

ከብቱ እረግፎ ፤ ባገር ምድሩ

ሰው ሁሉ አልቆ ፤ በችጋሩ

በፋሽስት ሸር ፤ በእኩይ ግብሩ

ከብት የሚፈጅ ፤ ደዌ ረጭቶ

በምን ታርሶ ፣ በምን ለምቶ

የገበሬው ፤ ሀብት ጠፍቶ

አከርካሪው ፤ ተመትቶ

የሚቀመስ ፤ እህል ታጥቶ

ረሀቡ ፤ ሕዝቡን በልቶ

ምኑ ተብሎ ፤ ስንቱን ነግሮ

የግፍ ግፉ ፤ ተዘርዝሮ

ዝም ይሻላል ፤ ምን ተቆጥሮ

በክፉው ቀን ፤ ራብ ደክሞ

ያለቀ ሕዝብ ፤ በአዋጅ ተሞ

በዚያ ድቀት ፤ ተጎድቶ

አፈር ልሶ ፤ ግድ ተነሥቶ

አይቀር ነገር ፤ የሀገር ጥሪ

ነፍሱ የሷ ፤ እሱ አኗሪ

ጉልበት ሆኖት ፤ የሀገር ፍቅሩ

አስቆጥቶት ፤ መደፈሩ

ገሰገሰ ፤ ወደ አድዋ

ጠላት ሊግት ፤ የሞት ጽዋ

አድዋ ላይ ፤ ከግንባሩ

ሊሞሻለቅ ፤ ሲተም ጦሩ

እንደ ሙላት ፤ ደራሹ ጎርፍ

ሲያስገመግም ፤ ጠላት ሊቀስፍ

ከተፍ ሲል ፤ ፊት ለፊቱ

ጥሊያን ራደ ፤ ልብ አጥቶ

ባለ የሌለ ፤ መሣሪያ አጉል

እያስጓራ ፤ ሲከላከል

በመድፍ አረር ፤ በመትረየስ

ግማሽ ሲቀር ፤ ሲሠዋ ነፍስ

ጠጋ ሲባል ፤ ወደ ምሽግ

ሌላ አሳር ፤ ምን ይደረግ?

በስል ችንካር ፤ በውጋቱ

በጠርሙስ ጦር ፤ በስለቱ

ምሽግ ማዶ ፤ በተከለው

አርበኛውን ፤ እንዲያስቀረው

ጠርሙስ አልፎ ፤ የፈንጅ ንጣፍ

ፋኖ የሚፈጅ ፤ በነፍስ ወከፍ

ያ ባዶ እግር ፤ ቢቀረደድ

ቢሸረከት ፤ ቢጎራረድ

ማን ተሰምቶት ፤ ለማን ታውቆ?

በፈንጅውም  ፤ ረግፎ አልቆ

ሊነሣ ይሻል ፤ ሞቶም ወድቆ

በወደቀው ፤ ተረማምዶ

ምሽግ ሰብሮ ፤ ጥሶ ንዶ

በጠላት ላይ ፤ ማት አውርዶ

ቆርጦ ሲጥል ፤ አንገት ጎርዶ

በፉከራ ፤ ቀልቶ አጭዶ

ሲፈጅ ሲማርክ ፤ ቆልቶ አሳዶ

ብቻ በሀገር ፤ በሕዝብ ፍቅር

በሚፋጀው ፤ እንደ ገሞር፡፡

አንች የረፋድ ፤ የድል ፀሐይ

የወጣሽው ፤ አድዋ ላይ

ከአባትሽ ፤ ከምኒልክ

ድባቅ መትቶ ፤ ካገባው ልክ

ከጣይቱ ፤ ከእናት ኩሩ

ፋኖዎቹ ፤ እያጋፈሩ

አድዋ ላይ ፤ ከአፈሩ

በቅዱሱ ፤ ጊዮርጊስ ለት

ተራድቶሽ ፤ ተርፈሽ ከሞት

ሰዓቱ ሲደርስ ፤ መወለጃሽ

በጭንቅ ምጥ ፤ የተወለድሽ

በሰው አጥንት ፤ በሰው ልጅ ደም

የታረስሽው ፤ የዓለም ሰላም

የሐበሻ ዘውድ ፤ የድል ማማ

በአጥንት ዕዳ ፤ በደም ጉማ

ምታስከፍይ ፤ ቃል ሲሰማ

ያችን ገልቱ ፤ ከንቱ ሮማ፡፡

አድዋ ቅኔ ፤ አድዋ ዜማ

የምትማርክ ፤ ምትስማማ

ለሰው ልጅ ልብ ፤ ያላት ግርማ

የአውሬን ልብ ፤ ምታደማ

በአፍታ ፍልሚያ ፤ ፈጣን ሽኝት

ወዲያው ብልት ፤ እዚያው ጥጥት

በአርበኛ ወግ ፤ በፋኖ ደንብ

ሳይገመት ፤ ሳይታሰብ፡፡

ነጭ በጥቁር ፤ በግፍ ገኖ

በጨካኝ ክንድ ፤ ይዞ አፍኖ

ጥቁሩ ሲኖር ፤ ተኮንኖ

መገልገያ ፤ ዕቃ ሆኖ

አሜን ወዴት ፤ አለሁ ብሎ

አንገት ሰብሮ ፤ ተገልሎ

በምድሪቱ ፤ በመላ ዓለም

በግፍ ሲኖር ፤ አጥቶ ሰላም

ለነጭ ተድላ ፤ ጥሮ ማስኖ

እሱ እንደሚያንስ ፤ ከልቡ አምኖ

ቅስም ሐሞቱ ፤ ነኩቶ ፈሶ

መራር ሐዘን ፤ ልቡ ውስጥ ነግሦ

ሲኖር ዘወትር ፤ ቀንበር አዝሎ

አድዋ ላይ ፤ የድሉ አውሎ

አሽቀንጥሮ ፤ ሸክሙን ጥሎ

ነጩን እባብ ፤ ላይድን ገሎ

አነሣለት ፤ ከስር ነቅሎ

አስበርግጎ ፤ አስደንብሮ

ፈነቃቅሎ ፤ ጥልቅ ሰርስሮ፡፡

እናም ዓለም ፤ ተገደደ

ውዳቂ ሐሳብ ፤ በግድ ካደ

አዲስ ታሪክ ፤ ተሰነደ

የተጠላው ፤ ተወደደ

ሰው መሆኑን ፤ የአዳም ዘር

ከነጭ ቢጫ ፤ ከቀይ ፍጡር

እንደማያንስ ፤ ምን ቢጠቁር

አረጋግጦ ፤ ቆመ በክብር

እድሜ ለዚያች ፤ የድል ፀሐይ

ለበራችው ፤ አድዋ ላይ

የባርነት ፤ ሰንሰለቱን

በጣጠሰ ፤ እግር ብረቱን

ተቀዳጀ ፤ ነጻነቱን

ቀበረለት ፤ ባርነቱን

የሀገሩ ፤ የመብቱ

ራሱ ሆነ ፤ ባለቤቱ

ዕድሜ ለዚያች ፤ የድል ፀሐይ

ለበራችው ፤ አድዋ ላይ

የምዕት ዓመታት ፤ ጣር ጨለማ

ተወገደ ፤ ድል ተሰማ

ያች ፀሐይ ፤ የድል ጮራ

ደማቅ ጸዳል ፤ የገድል አውራ

የከበረች ፤ ስጦታ ናት

ምንም ነገር ፤ የማይተካት

ከሐበሻ ሕዝብ ፤ ለጥቁር ዘር

ለተገፋው ፤ ለበላ አሳር፡፡

የካቲት 19 2007ዓ.ም.

The post አድዋ! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው appeared first on Zehabesha Amharic.

በቤይሩት ኢትዮያዊቷ ራሷን አጠፋች በሚል ሰበብ….. ኤምባሲው ያለምንም ምርመራ ሬሳዋን አሳፍሩ ማለቱ ብዙዎችን አሳዘነ

$
0
0

በግሩም ተ/ሀይማኖት
ኢትዮጵያዊኖች በአረብ ሀገራት ስደታቸው ጥሩም መጥፎም ይገጥማቸዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ራሳቸውን አጠፉ በሚል ሰበብም አሰሪዎቻቸው ይገሏቸዋል፡፡ እንዴት ሞቱ የሚል ማጣሪያ ወይም ምርመራ አይደረግም፡፡ ከተቻለ ሬሳቸው ይላካል ካልሆነም ፍሪጅ ውስጥ ተቀምጦ ለተማሪዎች መለማመጃ ይደረጋል፡፡ የሚፈለግ አካልም ይወሰዳል፡፡ ሁሌም ይሄው ነው፡፡
ethiopian woman Arabባለፈው ሳምንት ሰኞ ዕለት ቤይሩት ውስጥ ሳይዳ ሀበፊ የተባለ አካባቢ አንዲት ኢትዮጵያዊት ሞተች፡፡ በአሰሪዎቿ በኩል ራሷን አጠፋች ነው የተባለው፡፡ በፎቶው ላይ እንደምታዩት ከልጅቷ ቁመት ያነሰ መስኮት ላይ ገመድ አስራ ነው ታንቃ የሞተችው ያሉት አሰሪዎቿ፡፡ ራሷን ለማጥፋት የሚያበቃ ምንም አይነት ችግር አልነበረባትም፡፡ ለሞት የዳረጋትን ነገር ቢያስቡ ቢያሰሉ የሚያገኙት ፍንጭ በማጣታቸው በርካታ ጓደኞቿ በሁኔታው ከፍተኛ የሆነ ጥርጣሬ አደረባቸው፡፡
እንዴት ከእሷ ቁመት ባጠረ ቦታ ላይ ታንቃ ሞተች? ሁኔታው አጠራጣሪ ነው ብለው ቤይሩት ላለው ኢትዮጵያ ኤምባሲ ደጋግመው ጥርጣሬያቸውን አመለከቱ፡፡ ኤምባሲው ከወትሮ አሰራሩ የተለየ ሁኔታ የለውም፡፡ በእነአለም ደቻሳ ጊዜ የታየው አለመቆርቆር መልኩንም ቅርፁንም አለወጠም፡፡ እንዲያውም ችላ ባይነቱን አሳድገውት የወሰዱት ርምጃ ብዙዎችን ያሳዘነ፣ እንባ ያራጨም ሆነ፡፡
መቼ ይሆን ለሞታችን መብታችን ለመረገጡ ሰሚ እና ተከራካሪ የምናገኘው የሚለው የዘውትር ጥያቄ ደጋግሞ ብልጭ እንዲል አደረገ፡፡ ኤምባሲው ለሉብናናዊቷ አሰሪ ስልክ በመደወል ያላትን እቃ ሰባስባችሁ አምጡ፡፡ በቃ!….
ለልጅቷ ቤተሰቦች ደውለን እንዲከሱ ለማድረግ ቢሞከርም ስልካቸው ሊነሳ አልቻለም፡፡ ያለው አማራጭ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማሳወቅ ነውና ይህን ተግባር አከናወንን፡፡ መፍትሄ ይገኝ ይሆን? ሬሳዋ ፍሪጅ ውስጥ ተቀመጦ ቀረ፡፡ መቼ አስታውሰው ይልኩት ወይም ይቀብሩት ይሆን? ኢንሹራንሷንስ ኤምባሲው ዝም ይል ይሆን? ያነጋግራል፡፡

The post በቤይሩት ኢትዮያዊቷ ራሷን አጠፋች በሚል ሰበብ….. ኤምባሲው ያለምንም ምርመራ ሬሳዋን አሳፍሩ ማለቱ ብዙዎችን አሳዘነ appeared first on Zehabesha Amharic.


“ዜና አትስሙ”ለሚለው ፓስተር ምላሽ –ክንፉ አሰፋ

$
0
0

በከፊል የተቀዳውን የፓስተሩን ንግግር የሰማሁት “ሰልማ”  የተሰኘውን ፊልም አይቼ እንደተመለስኩ ነበር። በዚህ አመት ለአራት የኦስካር ሽልማት የበቃው “ሰልማ” ፊልም ኦፕራ ዊንፍሬን ጨምሮ ምርጥ አክተሮች ይተውኑታል። ፊልሙ እ.ኤ.አ. በ1965 በዩናይትድ ስቴትስ የጥቁሮች የመምረጥ መብት ገፈፋን ተከትሎ፣  ዶክተር ማርቲን ሉተር ይህ መብት እንዲከበር የሚያደርገውን ትንቅንቅ ያሳየናል።  ፓስተር  ሉተር ለዜጎች የመምረጥ መብት እንዲከበር ያለማቋረት በመስበኩ ሲደበደብ፣ ሲንገላታና ሲታሰር እናያለን። በአላባማ ግዛት የሚኖሩ ጥቁሮች መብታቸውን ስለጠየቁ ብቻ የመርዝ ጭስ ቢረጭባቸው፣ ቢደበደቡ፣ ቢታሰሩ እና ቢገደሉም ሉተር ተስፋ አልቆረጠም።  ሰቆቃውን በብሄራዊ ቴሌቭዥን የሚያዩ ሁሉ በቁጭት ትግሉን ተቀላቀሉ።  ከግዜ  በኋላም የ”ሰልማ” እና የ”ሞንትጎመሪ” ጥቁሮች የመምረጥ መብታቸው ተጠበቀ።  በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተውን ይህንን ፊልም የሚያዩት ሁሉ በእንባ ይታጠቡ ነበር።

እዚህ ላይ ተስፋ ያለመቁረጥን ብቻ ሳይሆን የሜድያን ሚና፣ በተለይ ደግሞ የቴሌቪዥንን ሃይል እናይለን። ዘረኞች እና አንባገነኖች ሜዲያን የሚጠሉት ያለምክንያት አይደለም። በዩናይትድ ስቴትስ ዘረኝነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የመገናኛ ብዙሃኑ ነጻ በመሆኑ ህዝቡን ነጻ ሊያወጣው ችሏል።

የኛ ፓስተር ደግሞ ጭራሽ “ዜና አትስሙ” ሲል ይደመጣል። በዚያ በተነሳሽነት እና በቁጭት ስሜት ሆኖ የፓስተሩን ንግግር ለሚሰማው ደግሞ በጣም ያበሳጫል።  “አትስሙ” ሲል የመስማት መብትን መጋፋቱን አላስተዋለው ይሆናል። ፓስተሩ በዚህ አላበቃም የኢሳት ሰዎች ቅዥታሞች ናቸው ሲልም ይዘልፋል። ቀን ከለሊት ይቃዣሉ ሲል ፍርድ ሰጥቷል። ፍርድ ለመስጠት እርሱ ማን ሆኖ? መጽሃፍ የሚለን “አትፍረድ ይፈረድብሃል” ነው።

ክፉውን ነገር አትቃወሙ የሚል ነገር በመጽሃፍ ቅዱስ የለም። እንዲያውም በብሉይ ዘመን ነብያት የገዥዎችን ክፉ ስራ ያወግዙ ነበር። ይህ ሰው መንፈሳዊ ነኝ የሚለን ከሆነ ኢትዮጵያ በሚሰራውን ክፉ ነገር አንዲት ቀን ተቃውሞ ያውቃል?

ቄስ ወይንም ፓስተር ሲሆኑ ስራቸው ወንጌልን መስበክ ነበረበት። “ዜና አትስሙ” ማለት ወንጌል አይደለም። ፖለቲካ ነው። ለዚያውም ያንድ ወገን ፖለቲካ። እንዲህ አይነት መልእክት በቤተ-ክህነት ውስጥ ማስተላለፍ መንፈሳዊነት አይደለም። ንግግሩ  የጉባኤውን የግንዛቤ አቅም ዝቅ ከማድረግ የሚመጣ ንቀትም ይመስላል።

በኢትዮጵያ ያለው እውነታ ይህ ነው። ዜጎች በሽብር ስም ይታሰራሉ፣ ሰዎች ያለአግባብ ይሰቃያሉ፣ ወገኖቻችን ያለአግባብ ይገደላሉ፣…  መሬታቸው ለባእዳን እየተሰጠ ይፈናቀላሉ፣ ባለስልጣናቱ ያለ አግባብ ሃብት እያካበቱ ነው፣ ምርጫ ይጭበረበራል…. ዜናዎቹ እነኝህ ናቸው። ይህንን ሰምቶ የራሱን ግንዛቤ የመስጠት መብቱ የሰሚው ነው። ይህንን አትስሙ ማለት ምን ማለት ነው?
ESat

ዶክተር ማርቲን ሉተርም ፓስተር ነበር። ህልም ያለመ ፓስተር። ዜና ከመስማት ባሻገር ህዝብን ለመብቱ እንዲነሳ የሰበከ ፓስተር። በአመጽ-አልባ ትግል የጥቁሮችን መብት ያስጠበቀ ፓስተር። ፐሉተር ህልም የጥቁሮች የመምረጥ መብት  ብቻ ላይ አላበቃም።  አንድ ቀን ጥቁር ሰው ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካን  ይመራታል ብሎ ነበር። ይህ ህልሙ ከሞላ ጎደል በባራክ አኦባማ እውን ሆኗል።

እንዲህ አይነት አመለካከት ላላቸው የሃይማኖት መሪዎች፤ ዲታቆን፣ ቄስም ሆነ ፓስተሮች በሙሉ አንዲት መል እክት አለችኝ። ህልም ባይኖራችሁም፣ የዜጎች ህመም ባይሰማችሁም፣ ግፍን መቃወም ባትፈልጉም፤  ዝም ብላችሁ ወንጌልን ብቻ ስበኩ።  መንፈሳዊ ባልሆነ ንግግር የሌላው መብት አትጋፉት።

The post “ዜና አትስሙ” ለሚለው ፓስተር ምላሽ – ክንፉ አሰፋ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአድዋ ድልና እኛ –ዳንኤል አበራ

$
0
0

ይህ የአድዋ 119ኛ አመት መታሰቢያ እኛና አድዋ በተሰኘ ርእሰ ጉዳይ ላይ ያተኩራል። ድርሰቱ ስድስት ንኡሳን ክፍሎች አሉት። ሁላችንም በጦርነቱ በድሉም ወቅት ስላልነበርን የተጻፈ አንብበን ከምናውቀው አመሳክረን ነው ጽሁፉ የተዘጋጀው። የተጻፈ አንብበን ላልኩት የጳውሎስ ኞኞን ምክር ከልቤ አድርጌ ነው። ጳውሎስ ኞኞ ኢጣሊያና የኢትዮጵያ ጦርነት በሚለው መጽሃፉ እኛ ስለራሳችን ስንጽፍ እናጋንናለን ስለዚህ የውጭ አገር ምእራባውያን የመሰከሩልንን ተጠቅሜያለሁ ይላል። የጳውሎስ አንደኛውን ምክር ከልብ ማድረግ ነው። ሁለተኛ ቢያሳዝንም እውነት ስለሆነ የሰዎች ስም በክፉ ይነሳል፤ አያት ቅድመ አያት ለሰራው ባንጠየቅም የአያቶቻችን ስም ሲነሳ አለመቀየም ነው። ከተቀየማችሁም ምን ይደረጋል ከመጻፍ አይቀርም። ራስ ደስታ ዳምጠው በሁለተኛው የጣሊያን ጦርነት የደቡቡን ውጊያ የመሩ ለጣሊያን ባደረ ሀበሻ ጠቋሚነት ነው ተይዘው የተገደሉት። አባታቸው ፊታውራሪ ዳምጠው ከተማ በትግራዩ ጦርነት ነው የተገደሉት። አባትም ልጅም ተሰውተዋል ሲሆን እንዲህ ነው። ባንዳ በክፉ ይነሳል የባንዳ ልጅ ባንዳ ከሆነ ምን ይደረጋል? ባይሆን ልብ መግዛት ነው።

=—-[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

Adwavictory

Download (PDF, 482KB)

The post የአድዋ ድልና እኛ – ዳንኤል አበራ appeared first on Zehabesha Amharic.

የእሳት አደጋ በሆሳዕና ማርያም –ስለ ቃጠሎውና ከኛ ምን እንደሚጠበቅ (ከዘመድኩን በቀለ)

$
0
0

ከዘመድኩን በቀለ

በቅርቡ በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በኩል ጣና ሐይቅ ላይ በሚገኘው ጥንታዊው የዳጋ ቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳም ውስጥ ተነስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በእግዚአብሔር ቸርነት በመጥፋቱ ሁላችን እጅግ ደስስ ብሎን የነበረ ቢሆንም እሳቱ እጁን አርዝሞ አሁን ደግሞ ወደ ደቡብ ክልል ወርዷል ።

በትናንትናው እለት ደግሞ ከወደ ደቡብ በሃድያና ስልጤ ሃገረ ስብከት ከሆሳዕና ከተማ የተሰማው ዜና እጅግ የሚያሳዝንም የሚያስቆጭም ነው። ለጊዜው የእሳቱ መንስኤ ባይታወቅም ከተመሰረተች 106 ዓመት የሆናት የታሪካዊቷ የሆሳዕና ደብረ ገነት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት መውደሙን ከስፍራው የደረሰኝ በቪድዮ የተደገፈ መረጃ ያሳያል።

ጉዳዩን የበለጠ ለማጥራት እኔም የሀገረ ስብከቱን ዋና ስራ አስኪያጅ ክቡር ቆሞስ አባ ቢንያም ማንቾ እና የደብሯን አስተዳዳሪ መልአከ ምህረት ቀሲስ አስናቀን በስልክ አግኝቼ አነጋግሬያለሁ ። ሁለቱም አባቶች የእሳት አደጋው መንስኤ አሁን ላይ እንዲህ ነው ብለን መናገር ባንችልም የጥንቃቄ ጉድለት መሆኑ ግን ሚዛን እየደፋ በመሄዱ ግን ይስማማሉ ።

በተለይ የደብሯ አስተዳዳሪ እንደነገሩኝ ከሆነ ፤ ዕለቱ ቀዳሚት ሰንበት ፣ በዓሉም የእመቤታችን ወርሃዊ በዓል በመሆኑ ሥርዓተ ቅዳሴው በጠዋቱ 2 ሰዓት ላይ ተፈጽሞ እኛም ቤተክርስቲያኑን ዘግተን ቢሮ እንደተቀመጥን ፣ ምእመናንም ቤተክርቲያኗን ከብበው ጠበል ጻዲቁን እየቀመሱ ሳለ ነው ከቤተመቅደሱ ውስጥ እሳቱ ተነስቶ ሁሉም ተጯጩሆ ለማጥፋት ርብርብ የተደረገው ብለው አጫውተውኛል ።

የእሳቱን መነሳት ዐይተን የድረሱልን ጥሪ ደወል በመምታት እንዳሰማን ፣ ጭሱን እና ጥሪውን የሰሙ ሁሉ ዘር እና ሃይማኖት ሳይለዩ በሙሉ መጥተው በእሳት ማጥፋት እንቅስቃሴ ላይ ተሳትፏል ።
እሳቱ ከባድ ጉዳት በቤተክርስቲያኗ ላይ አያድርስ እንጂ በቤተመቅደሱ ውስጥ ጽላቱ ምንም እንዳልሆኑ የደብሩ አስተዳዳሪ አክለው ነግረውኛል ። እግዚአብሔር ይመስገን ።

በቤተክርስቲያኗ ቅፅር ግቢ ውስጥ በተደረገው ጊዜያዊ የገንዘብ ማሰባሰብ ሥራ ላይም የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያንና የእስልምና እምነት ተከታዮችና መሪዎች እንዲሁም የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ደገለ ኤርጌኖ ፣ የዞኑ የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አበራ አይደሞና የከተማዋ ከተማ ከንቲባም በግንባር በመቅረብ በግላቸው አስተዋፅኦ ከማድረጋቸውም በተጨማሪ እስከመጨረሻው በቤተክርስቲያኗ ሥራ ላይ በግላቸው ጭምር ተሳትፎ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል ብለውኛል እኒህ ሁለቱ የቤተክርስቲያን አባቶች አባ ቢንያም እና ቀሲስ አስናቀ ።

ቤተክርስቲያኗ ከመቃጠሏ በፊት

ቤተክርስቲያኗ ከመቃጠሏ በፊት

በሁኔታው ማዘን እና ማለቀሱ ብቻውን ዋጋ የለውም ። ይልቁንም ለተሻለ ሥራ እንድንነሳ ያስፈልጋል ።እናም በዚህ አጋጣሚ እኔ አንድ ኃሳብ በኢትዮጵያና በመላው ዓለም ለሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን በትህትና አቀርባለሁ ።

።።።። ባለሙያዎች ።።።።

፩ኛ ፣ የቤተክርስቲያን ልጆች የሆናችሁና የአርክቴክቸር ሙያ ያላችሁ የቤተክርስቲያን ልጆች ግሩምና ድንቅ ታሪካዊ የሆነ ዘመን ተሻጋሪ የቤተክርስቲያን ዲዛይን በነፃ ብታዘጋጁ ።

።።።። ምእመናን ።።።።

፪ኛ፣ ይህን ዜና የሰማን እኛ በመላው ዓለም ያለን የቤተክርስቲያን ልጆች ሀብታም ድሃ ሳንል ሁላችን በአንድነትና በአጭር ጊዜ ውስጥ እግዚአብሔር ከሰጠን ውስጥ ያለንን ገንዘብ ብናዋጣ ፣
።።።። የደብሩ አስተዳደር ።።።።

፫ኛ፣ የደብሩ አስተዳደር ቤተክርስቲኗን መልሶ ለመገንባት ይቻል ዘንድ አንድ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ቢያዘጋጅ ። በአስቸኳይም የህንፃ አሰሪ ኮሚቴ አቋቁሞ የባንክ ሒሳብ ቁጥር ይፋ ቢያደርግ ።
።።።። ማኅበራት ።።።።

በባለሙያዎች የተደራጀው የቤተክርስቲያናችን መመኪያ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን ፈጣን የሆነ ምላሹን እንጠብቃለን ። የጉዞ ማኅበራት ያላችሁ ወንድሞች ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት መንገዶችን ሁሉ ወደ ሆሳዕና ማድረግ ይጠበቅባችኋል የሚል ሓሳቤን አቀርባለሁ ።
በእኔ በኩል የሚጠበቅብኝን ሁሉ ለማድረግ ፈቃደኛም ዝግጁም መሆኔን እገልፃለሁ ። ለጉባኤው መሳካት ይረዳ ዘንድ ወዳጆቼን ፣ እኔን ራሴን ጨምሮ ጓደኞቼን በማካተት ስፖንሰር በማፈላለግ ለቅድስት ቤተክርስቲያን እንድረስላት ።
ሆሳዕናዎች አይዟችሁ አለን ከጎናችሁ ። አበው ” ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሃምሳ ሰው ግን ጌጡ ነው እንዲሉ ፣ እኛም እንረባረብ ።
አሁን በደረሰኝ ዜና መሰረት ኮሚቴ እስኪቋቋም ድረስ ደብሩ በጊዜያዊነት ዝግ የባንክ አካውንት በሆሳዕና ከተማ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባቴና ቅርንጫፍ የባንክ ሂሳብ ተከፍቷል ። ቁጥሩም 1000110719969 እንደሆነ ይፋ ሆኗል ።

እኔ ይህን ብያለሁ እናንተም የምትሉትን በሉ በዚህ ጽሑፍ ላይ Comment አና Share ይበረታታሉ ።
ዘመድኩን በቀለ ነኝ
የካቲት 22 /6/2007 ዓም
አዲስአበባ — ኢትዮጵያ

The post የእሳት አደጋ በሆሳዕና ማርያም – ስለ ቃጠሎውና ከኛ ምን እንደሚጠበቅ (ከዘመድኩን በቀለ) appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢሳያስ አፈወርቂን በጨረፍታ (ክንፉ አሰፋ)

$
0
0
isayas afewerki

ኢሳያስ አፈወርቂ

 

“አንድም ቀን ስቀን አናውቅም!” አሉ ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም። ይህን በሚሉ ጊዜ እፊታቸው ላይ ፈገግታ ይታይ ነበር – ምሬቱ እንዳለ ሆኖ። ኢሳያስ አፈወርቂ ሲስቁ አይተናቸው አናውቅም። ግን ኮስተር ብለው የሚናገሩት ነገር እኛኑ አያሳቀን ነው። “ካሳ ይገባናል! ካሳ ስጡን” ሲሉ አሳቁን። ቀጠል አድርገውም “ምጽዋና አሰብን ወያኔ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲጠቀምበት ፈልገው” እንደነበር ተናግረው አሳቁን። “…የሰራነው ጥፋት ስለሌለ የሚጸጥተን ነገር የለም።” አሉ እጃቸውን እንደ ጲላጦስ እያጠቡ። ከዚህ ቀደም ለስዊድኑ ጋዜጠኛ የአስመራው የፖለቲካ ስርዓት ስዊድን ካለው ስርዓት የተሻለ እንደሆነ አስረግጠው ነገሩት። ስለ ብሄራዊ ምርጫ ለጠየቀቻቸው የአልጃዚራዋ ጋዜጠኛም “ምርጫ ምንድነው?” ብለዋት ነበር። ከዚህ በላይ ምን የሚያስቅ ነገር አለ?

የፈለጉት ካሳ ግን ምን ይሆን? የገንዘብ ካሳ፣ የሞራል ወይንስ የሃገር? ….  ጾረና፣ ዛላምበሳ፣ ባድመ? ወይንስ ኢትዮጵያ!?

“በዋልድባም ባመት አንዴ ይዘፈናል።” ይባላል። ኢሳያስ አፈወርቂስ ባመት አንዴ ብቅ እያሉ ስለ ኢትዮጵያ የፈለጉትን ቢናገሩ ምን ይላቸዋል? በዚያ ላይ አሁን “የኢትዮጵያ ወዳጅ” ሆነዋል።

ናሳ የተባለው የአሜሪካ የጠፈር ምርምር ተቋም የአፍሪካ ቀንድን በሳተላይት ፎቶ አንስቶ ነበር። በፎቶው ላይ ሲታይ ኤርትራ ሙሉ በሙሉ አረንጓዴ ነበረች። ሳይንቲስቶቹ ይህችን ቆላማ ሃገር እንደሚወራው በረሃ ሳይሆን ይልቁንም ከጠበቁት በላይ ለም ሆና ተመለከቷት። ከሺዎች ኪሎሜትር የተነሳውን ይህንን ምስል እያቀረቡ ሲመለከቱት ግን ነገሩ ሌላ ሆኖ አገኙት። ከሩቅ የለመለመ ቅጠል መስሎ የሚታየው ነገር አረንጓዴው የወታደር ልብስ ኖሯል። ሳዋ፤ ትልቁ የኢሳያስ አፈወርቂ ዩኒቨርሲቲ ከህጻን እስከ አዛውንት እያስገባ ውትድርና ያሰለጥናል። በኤርትራ ዛሬ ሁሉም ዜጋ ወታደር እንዲሆን ተገዷል። የወያኔን ስርዓት በሃይል ለመጣል በአስመራ ጦር ያሰፈሩ የተቃዋሚ ሃይሎች ቁጥርም ቀላል አይደለም። አረንጓዴ የለበሱ እነዚህ ሃይሎች እድሜያቸውም ሁለቱን አስር ሊነካው ነው።

የኢሳት ጋዜጠኞች ኢሳያስን ለጠየቋቸው አንደኛው ጥያቄ ምላሹ ይኸው ነው። ሁሉም አረንጓዴ ለባሽ፣ ሁሉም ነጭ ለባሽ በሆነበት ሃገር ማን ማንን ሊጠብቅ ይችላል?  ”ባለስልጣናቱ ሁሉ ያለ አጃቢ የሚሄዱበት ምክንያት ምስጢሩ ምንድነው?” የሚል ነበር ጥያቄው። ጥያቄዋ አቅጣጫ ቀያሽ ጥያቄ ስለነበረች ለኢሳያስ አፈወርቂ እንደተመቻቸው ያስታውቅባቸዋል። መልስ ሲሰጡ ንፅፅር ውስጥ ገቡና እድሉን ባላንጣዎቸውን ለመምቻ ተጠቀሙበት። ባላንጣቸው ህወሃት ብቻ አይደለም። ምእራቡም፣ ምስራቁ ዓለም የእሳቸው ጠላት ነው።

በሁሉም ጉዳይ ላይ ባዕዳንን ይወቅሳሉ። እዚህ ላይ እውነት አላቸው። ታሪክ እንደሚነግረን ለሃያላን ሃገሮች አልንበረከክ ያለች ኢትዮጵያን ለማዳከም የባህር በር ማሳጣቱ ሴራ በባእዳን ነው የተጠነሰሰው። እሳቸውም ምስጢሩን በደንብ አድርገው ያውቁታል። ይህን ሴራ እውን ለማድረግ በቱርክና በግብፅ ከዚያም በጣሊያንና በእንግሊዝ ብዙ ተሞክሮ ነበር። የጉንደት፣ የጉራ፣ የኩፊት፤ የኮቲት እና የዶጋሊ ጦርነቶች ለዚህ ዋቢ ናቸው። ሁሉም አልተሳኩም። ይህንን የቤት ስራ በመጀመርያ ጀብሃ ከዚያ ቀጥሎ ሻእቢያ ከባእዳን ተቀብሎ መስራት ጀመረ። የነዚህ ባእዳን ህልም በመጨረሻ በኢሳያስ አፈወርቂ እውን ሆነ። 5 ሚሊዮን ህዝብ ላይጠቀምበት የሁለት ወደብ ባለቤት ሲሆን፣ 80 ሚሊዮን ህዝብ ግን ያለ ወደብ እንዲኖር ተደረገ።

እኝህ ሰው የርስበርስ ጦርነቱን አሸንፈው ኤርትራን ባስገነጠሉ ጊዜ ጀግና ነበሩ። የግዜ እንጂ የሰው ጀግና የለምና የጀግንነታቸው ጫጉላ እንዳሰቡት ረጅም አልዘለቀም። “ነጻነቱን” በቅጡ ሳያጣጥሙት ሌሎች ጦርነቶች ውስጥ ገቡ። ትልቁ እና ዋነኛው ጦርንርት ግን ከሕዝባቸው ጋር የገጠሙት ፍልሚያ ነው። ውጤቱም ስደት ሆነ። ዛሬ የኤርትራን ምድር ለቅቆ ለመጥፋት የማይጥር ዜጋ የለም። በኮንቬንሽናል ጦርነት ጊዜ ከሚሰደደው ህዝብ የበለጠ ቁጥር ያለው ህዝብ ይሰደዳል። ከኤርትራ ህዝብ ብዛት አንጻር ሲታይም ስደተኛው እጅግ ብዙ ነው። የተሳካለት የኤርትራ ተወላጅ በረሃ አቋርጦ ኢትዮጵያ፤ ሱዳን እና ሊቢያ ይዘልቃል። ያልተሳካለት ደግሞ በየጠረፉ የሻእቢያ ራት ይሆናል። የዜጎች ኩላሊት ሽያጭም እዚያው ይካሄዳል። በኤርትራ እንደቀልድ የሚነገር እውነታ አለ። ኢሳያስ አፈወርቂ ለኤርትራ ካበረከቱት ነገር ሁሉ የኢቦላ ወረርሽኝ በሃገራቸው እንዳይገባ ማድረጋቸው ነው። ከዚያ የሚወጣ እንጂ የሚገባ ሰው ስለሌለ።

በዚህ ዘመን ከሚከሰቱት እልቂቶች ሁሉ የላቀ እልቂት እና ሰቆቃ የምናየው በነዚህ ወገኖቻችን ላይ ነው። ስንት ኤርትራውያን እንደበላች የሲሲሊዋ ላምባዶዛ ትመስክር።

“ጽድቁ ቀርቶ፣ በቅጡ በኮነነኝ” ይላሉ አበው። የካሳውን ተረት ለጊዜው እንተወውና፣ ታሪክ ኢሳያስን የሚዘክራቸው በተያያዙት የግፍ አስተዳደራቸው ይሆናል። በለስ ቀንቷቸው የኤርትራን ምድር ነጻ ቢያደርጓትም ህዝቡ ግን ነጻነትን እንደናፈቀ እነሆ 23 ዓመታት አለፉ። ህዝበ ኤርትራ ነጻ አልወጣም። ኢኮኖሚውም እንደ ቤተ-ጸሎት በአስራት ላይ ነው መሰረቱ። ነጻነትን ሳያያት፤ የነጻነትን አየር ሳይተነፍስ ሁለት አስርተ አመታት እንደዋዛ አለፉ። ለኢሳያስ፣ ሀገርን መምራት አመጽን እንደመምራት ቀላል አልሆነላቸውም። ሰላምን ማሸነፍ፣ ጦርነትን እንደማሸነፍ አልሆነላቸም።…

ኢሳያስ አፈወርቂ ዳግም ከኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ጋር ተቀምጠው አየን። የቀረበላቸውን ጥያቄዎች ሁሉ ሰማን። መልሶቹንም አደመጥን። አደመጥን ማለቱን የመረጥኩት ያለ ምክንያት አይደለም። በአሁን ዘመን ብዙዎች ይሰማሉ እንጂ አያዳምጡም። ለወቀሳውም፣ ለትችቱም ሆነ ለክርክሩ አመቺ ሚሆነው ከመስማት ይልቅ ማዳመጥ ሲቻል ነው። የማይደመጥ ነገር በአብዛኛው የተዛባ ትርጉም ተሰጥቶት ነው የሚቀርበው።

ታዲያ አዲሱን ቃለ-ምልልስ እንዳደረጉ በማስታውቂያ ከተነገረ በኋላ ለመስማት ትንሽ  አስጠበቁን። በመጀመርያ የትግርኛው ምላሽ ተተርጉሞ እስኪቀርብ ተጠበቀ።  ከግዜ በኋላ ደግሞ የእንግሊዝኛውን ጠብቁ ተባልን። አዲስ ነገር እንዳለ ለመስማት እንደ ሰስፔንስ ፊልም ልብ እያንጠለጠሉ አከረሙን። ያም ሆኖ “ከጸሃይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም” ብለን አልደመደምንም። ቢያንስ አዲስ ቀልድ ይዘውልናል…. ከጸደቁ አይቀር ግን በአማርኛ ተናግረው ቢጸድቁብን መልካም ነበር። ስራውም ይቀል ነበር። ሁላችንም የምንግባባበት አማርኛ ጠፍቷቸው ነው እንዳንል፤ ደሴ ወይዘሮ ስህን ትምህርት ቤት ነው የተማሩት። ከዚያም በቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዩንቨርስቲ የነፃ ትምህርት ዕድል ተሰጥቷቸው ይማሩ ነበር። የፈረንጅኛው ቋንቋ ሊቀልላቸው ይችላል። የሚቀርባቸው ግን አማርኛ ነው።  ሃሜተኞች እንደሚሉት ኢሳያስ አፈወርቂ ለኢትዮጵያውያን የቤት ስራ መስጠት ስለሚወዱ ነው በአማርኛ ለመናገር ያልፈለጉት። ከዚህ በፊት የመቶ አመት፤ አሁን ደግሞ የመቶ ሰዓት የቤት ስራ።…

በአንድ ግዛት ውስጥ ሆነን ለሺዎች ዓመታት የኖርን፤ በቋንቋ፣ በታሪክ፣ በሃይማኖትና በሥነ ልቦናም አንድ የነበርን ህዝብ እንደሆንን ይሰማኝ ነበር። እንገንጠል አሉ። ገነጠሉዋት። ኤርትራ በጂኦግራፊም ሆነ በስትራቴጂ አቀማመጥዋ የኢትዮጵያ ራስ ነበረች ብለው የሚያምኑ ወገኖች በወቅቱ ሄዱብን ነበር ያሉት። ይህች ክፍለ-ሃገር ራስ ሳትሆን ራስ-ምታት ነበረች የሚሉት ወገኖች ደግሞ ሄዱልን ብለው ነበር።

ዛሬ ራስ ምታቱ ሲጸናባቸው እነሆ እየመጡ ነው። ዳግም ከኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ጋር ተቀምጠው አየን። ስለኢትዮጵያ ብቻ ይናገራሉ። ስለ ህዝቡ ይቆረቆራሉ። የኢትዮጵያ ችግር እንቅልፍ እንደነሳቸው ያወራሉ። ከዚህ ቀደምም ከኤልያስ እና ስለሺ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ። “… ያለፈውን እንርሳ። የታሪክ ባሮች አንሁን። ኑና እንወያይ።” ማለታቸውን እናስታውሳለን። መወያየት መልካም ነገር ነው። ለውይይት ግን ወቅትም ይወስነዋል። ያኔ በ99.9 በመቶ ውጤት ከተጠናቀቀው የሪፈረንደም ጫወታ በፊት “ኑና እንወያይ።” ቢሉን አሁን የገቡበት ችግር ውስጥ ላይገቡ ይችሉ ነበር።

በአንድ በኩል ከኢትዮጵያ የመለየቱ ቁጭት እንዳለ እናያለን። ደፍረው አልተናገሯትም እንጂ ስህተት እንደሰሩ ከሚሰጧቸው ቃለ-ምልልሶች መረዳት አያዳግትም። ለኢትዮጵያ ሕዝብ የመቆርቆሩ ጉዳይ ግን የአዞ እንባ ይመስላል። እዚያው እጉያቸው ላሉት ኢትዮጵያውያን ያልራሩ፣ መረብን ተሻግሮ ማሰቡ ግብዝነት ነው የሚሆነው።

በመጀመርያ አይናቸውን ጠረግ ጠረግ አድርገው የራሳቸውን ቤት ችግር ማየት ሲችሉ፣  የሌላውን ችግር አጥርተው ለመመልከት ይሳናቸዋል።

በቃለ-መጠይቁ ላይ ገጽታቸው እንደመሪ አይደለም። ሰውነታቸው ተጎሳቁሏል፣ ፈታቸውም ጠውልጓል። ከላይ ያጠለቁት ልብሳቸው የተጨማደደ ነበር። ከነበሩበት ደከም ያለ ጣራ ስር ሆነው፤ ግና ዘና ብለው በለሰለሰ አንደበት ይናገራሉ። የኢሳያስን ገጽታ የሚመለከቱ  ሰዎች በሌላ ሊተረጉሙት ይችላሉ። ራስ ወዳድ ያልሆኑ፤ ለግል ኢጎዋቸው የማይጨነቁ… ይባሉ ይሆናል። እንዲህ አይነቱ  ሁኔታቸውን ዋቢ በማድረግ ኢሳያስን እንደሞዴል የወሰዱም አሉ። ይህ ሰጥቶ ለመቀበል የሚደረግ ጨዋታና “የፖለቲካ ስህተት ላለመፈጸም” ካልሆነ በስተቀር መሬት ላይ ያለው እውነታ የሚያሳየው ሌላ ነው። በኢሳያስ አፈወርቂ ውስጥ የኤርትራን ህዝብ እናያለን። ተለይቶ ያለ፣ ከሌላው አለም የራቀ፣ የተቆሳቆለና ተስፋው የጨለመበት ሰው። እሳቸው የሚመሩት ህዝብ ነጸብራቅ ናቸው።

ኤርትራ አሁን ለደረሰችበት ደረጃና ለገባችበት ቀውስ ማንም ውጫዊ አካል ሊወቀስ አይችልም። ራሱ ስርዓቱ ያመጣው መከራ ነው። ከ99.9 በመቶው ተረት-ተረት ሪፈረንደም በኋላ ነጻ አውጪው ሻዕቢያ በአለም ላይ ታይቶ ያማይታወቅ አዲስ ስርዓት አሰተዋወቀ። ህግ አውጪ፣ ህግ አስፈጻሚና ህግ ተርጓሚው አንድ ነው። ህጉም አንድ ሰው ነው። የብዙሃን ፓርቲ ፓርላማ በህግ የተከለከለበት ሃገር።  ፕሬስ የሌለው መንግስት፣ ፍትህ እና ፍትሃዊ ስርዓት የሌለው ስርዓት። … ይህ አዲስ አይነት ስርዓት የህዝቡን ህይወት የለወጠ ቢሆን ኖሮ፤ እንደተባለውም ኤርትራን የአፍሪካ ሲንጋፖር ያደረገ ቢሆን ኖሮ፣ እንደ ሞዴል ሊወሰድ ይችል ነበር። እውነቱ ሌላ ነው። ህዝበ ኤርትራ ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ የቢቢሲን ያለፈው ሳምንት ዘገባ መመልከቱ ብቻ ይበቃል። የዊኪሊኩ ጁልያን አሳንጅ የለቀቀው አንድ ኬብል ላይ ህጻናት እንኳን በኤርትራ መንግስት ምን ያህል እየተሰቃዩ እንደሆነ ዘርዝሮታል።

እኝህ አንባገነን ሰው ዘንድ ሄዶ ጥያቄ የሚጠይቅና የሚጋፈጥ ጋዜጠኛ የሚደነቅ ነው። ህግ፣ ፍትህ፣ ዲፕሎማሲ ምናምን የሚባሉ ነገሮች የማይገባው ሰው ዘንድ ሄዶ ለመነጋገር መወሰን ቀላል አይሆንም። ይህን ስል ያለ ምክንያት አይደለም። ትውልደ ኤርትራዊው የስዊድን ዜጋ፣ ጋዜጠኛ ዳዊት ኢስኃቅ ድንገት ተይዞ ወዳልታወቀ ስፍራ ከተወረወረ 15 ዓመት ሞላው። ጋዜጠኛ ዳዊት የት እንዳለ እስካሁን አይታወቅም። በኤርትራ ዛሬ 20 ሺ የፖለቲካ እስረኞች በየእስር ቤቱ እንደታጎሩ የአምነስቲ ዘገባዎች ይጠቁማሉ። በኢሳያስ የግል እስር ቤት ውስጥ ከነበሩት 35 የቀድሞ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል 15ቱ በስቃይ ህይወታቸው አልፏል። በ“አደርሰር”፣ በ“አጂፕ”፣ በ“ኢራኢሮ” እና በ”ጋልዓሎ” እስር ቤቶችና በኮንቴይነሮች ታጉረው እየሞቱ ያሉት ቁጥር ጥቂት አይደለም። የምእራቡ አለም የዲሞክራሲ እሴቶች ከኤርትራ መዝገበ-ቃላት ተፍቀው እንዲወጡ ተደርጓል። በዚህ የፖለቲካ አየር እኝህ ሰው ፊት ቀርቦ የሚጎረብጡ ጥያቄዎችን ማንሳት በራስ መፍረድ ነው።…

ባየር ላይ የሚነገሩ በርካታ ጉዳዮች በቃለ-ምልልሱ ተነስተዋል። የመቶ አመት የቤት ስራው ጉዳይ ተነስቷል። ህገመንግስቱን ከሌንጮ እና ከመለስ ጋር የማርቀቁ ጉዳይ ተነስቷል። ከህብረብሄራዊ ድርጅቶች ይልቅ የዘር ድርጅቶችን ብቻ የመደገፋቸው ጉዳይም ተነስቷል።

ምላሻቸው ግን ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ሆነብን። አጠር ብለው ሲቀርቡ ይህን ይመስላሉ።

ጥያቄ፣ “ትውልድዎ እና እድገትዎን ይንገሩን?”

መልስ፣ “የትግሉ ውጤት ነኝ።”

ጥያቄ፣ “ስለጤናዎ ሁኔታ ይንገሩን “

መልስ፣ “እድለኛ ነኝ… ጠላት እንደሚያወራብኝ አይደለሁም።”

ጥያቄ፣ “በዘር የተደራጁ ሃይሎችን ነጥለው ለምን ይደግፋሉ?”

መልስ፣ “ሻእቢያ ድርጅት አቋቁሞ አያውቅም።”…..

እያለ ምላሻቸው ከጥያቄው ጋር አራምባና ቆቦ ሆነብን። የማይመቹ ጥያቄዎችን እንደቀልድ ያልፏቸውና ሌላ ታሪክ ሊነግሩን ይሞክራሉ። በመጨረሻ ግን ላሽ እያሉ ያለፏቸው ጥያቄዎች ላይ ጠቅለል አድርገው ምላሽ የሰጡ ይመስላል።

“..ያለፈውን እንተወው እና ወደፊት ምን ማድረግ ይገባናል የሚለው ላይ ማተኮር ነው ያለብን።” ሲሉ ምክር ሰጥተዋል። ይህች መልዕክት የቃለ-ምልልሱ ቁልፍ ትመስላለች። አስቀድመው “ባለፈው በሆነው በአንዳቸውም ነገር አንጸጸትም።” ብለውማል።

ከዚህ ቀደም ከኤልያስ እና ስለሺ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ያሉትንም እናስታውስ። “የራስን እድል በራስ መወሰን እስከመገንጠል የሚለው አንቀጽ በሕገ-መንግስቱ ውስጥ መጨመር ስህተት ነው።” ብለዋል። ራሳቸው ከቀድሞ ወዳጆቻቸው ጋር ሆነው ያረቀቁትን ሰነድ ነው ስህተት መሆኑን የነገሩን። ይህ ነገር ስህተት ከሆነ ታዲያ የሰራነው ስህተት የለም ብለው ለምን ይዋሻሉ? እንደሚባለው የአልዛይመር ችግር ይኖርባቸው ይሆን?

እርግጥ ነው። ስለ ኢሳያስም ሆነ ስለ ኤርትራ ጉዳይ እኛ አያገባንም። አምባገነንነታቸው የኛ ጉዳይ ላይሆን ይችላል። የዚያች ሃገር ጉዳይ “ኢትዮጵያዊ አይደለንም” ብሎ 99.9 በመቶ ድምጽ የሰጠው ህዝብ ጉዳይ ነው። ግና ባሰኛቸው ጊዜ እየተነሱ ቁስላችንን ሲነካኩብን ዝም የማለት ሞራል አይኖረንም። ከአሰብ በግፍ እና በአሰቃቂ ሁኔታ ተፈናቅለው ሲያበቁ መስቀል አደባባይ ለወራት የፈሰሱ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ከቶውንም ከአእምሯችን አይጠፋም። ኢሳያስ አፈወርቂ ዛሬ በሰራነው አንጸጸትም፣ እንዲያውም ካሳ ይገባኛል ሲሉ በድፍረት ተናገሩ። ምን እንላለን? በወገኖቻችን ላይ እየሰሩ ላሉት ግፍ ፈጣሪ ይከፍላቸዋል። ካሳቸውንም ከታሪክ መዝገብ ያገኙታል።

በፖለቲካ ቋሚ ጠላት ወይንም ቋሚ ወዳጅ የለም። የጋራ ጥቅም ግን አለ። ሰጥቶ መቀበል የሚሉት ነገር። ኢሳያስ አፈወርቂ ግን ለጋራ ጥቅም ሳይሆን ለጽድቅ እንደሚሰሩ አይነት ነው እየነገሩን ያሉት።  በኢትዮጵያ ችግሮች አሉ። አማራጭ የፖለቲካ በሮች በሙሉ ተዘግተዋል። አገዛዙ ፍጹም አንባገነን ሆኗል። ኤርትራን መጠጋት እንደ መፍትሄ የወሰዱ ወገኖች ሌላ የትግል አማራጭ ስላጡ ሊሆን ይችላል። የቸገረው እርጉዝ ያገባል እንደሚባለው። ያለፉት ተመክሮዎች ግን ሻእቢያን በጥርጣሬ እንድናይ ያደርገናል።  ከአስር አመት በፊት አስመራ የመሸጉ ሃይሎች አሁንም አስመራ ላይ ናቸው። አንዳንዶቹ እዚያው ሲያረጁ ሌሎቹ  ደግሞ አእምሯቸውን ስተው ሲለቅቁ  እያየን ነው። የእነ ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ  ደብዛ መጥፋት፣ 18 የአርበኞች ግንባር አባላት በድንገት መሰወር፣ አስመራን እንዳይለቅቁ እገዳ የተጣለባቸው የተቃዋሚ ሃይል አባላት… ወዘተ እጣ ፈንታ በኢሳያስ እጅ ላይ ነው ያለው። ስለ ኢትዮጵያ መቆርቆር ከዚህ ይጀምራል። እነዚህ ወገኖቻችንን ነጻ ካደረጓቸው በኋላ ኢትዮጵያውያንን ለውይይት ቢጠሩ አንድ ነገር ነው። በትንሹ ያልታመነ፣ በትልቁ አይታመንምና።

ቀድሞ “ከኤርትራ ውጭ ነጻነት ላሳር!” ብለው የነበሩ ሃይሎች አሁን ላይ ሆነው “ተሳስተናል!” እያሉን ነው። ለዚያውም በምሬትና በጥላቻ። ታዲያ ችግሩ የት ነው ያለው? ከተቃዋሚዎቹ ወይንስ ከሻዕቢያ? መልስ የሚሻው የብዙዎች ጥያቄ ነው።

The post ኢሳያስ አፈወርቂን በጨረፍታ (ክንፉ አሰፋ) appeared first on Zehabesha Amharic.

አድዋን ስንዘክር፡ –ማተቤ መለሰ ተሰማ

$
0
0

Battle of Adwaአስደናቂ ለሆነ የረጅም ዘመን አኩሪ ታሪክ ባለቤት የሆነችው፡ እናት ሃገራችን ኢትዮጵያ፡ ከ1762 እስከ 1845 ዓ.ም ድረስ በነበረው 70 አመት ጊዜ ውስጥ፡ በዘር ባይሆንም ልክ እንደዛሬው፡ ልጆቿ ተከፋፍለው፣ ልማትና ብልጽግናዋ ተገትቶ፣ ለሁለንተናዊ ውድቀት የተዳረገችበት ወቅት ነበር።

እጅግ በጣም የሚገርመው ደግሞ፡ ለዚያ ውድቀት የዳረጋት፡ የትግራዩ ተወላጅ እራስ ስዑለ ሚካኤል፡ አማቱንና በወቅቱ የነበሩትን ንጉስ አጼ ኢዩአሰን በቤት አሽከሮቻቸው አሳንቆ በማስገደሉ ነበር።

34

ማተቤ መለሰ ተሰማ

እንግሊዝ አጼ ቲዮድሮስ፡ ያሰሩባትን ዜጎቿን እነ ቆንሲል ካሜሮንን፡ በሃይል ለማስፈታት፡ ወደ ኢትዮጵያ ጦሯን በላከች ጊዜ፡ በሮቤርት ናፒር የሚመራው ወራሪው ጦር ከምጽዋ ዙላ፣ ከዙላ ሰናፈ፣ ከሰናፈ አሸንጌ፣ ከአሸንጌ ሙጃ፣ ከሙጃ መረዋ፡፡ በማረፍ እየተዝናና እና መንገድ እየሰራ ሚያዚያ 2 ቀን 1860 ዓ.ም. በሸሎ እሰኪደርስ ድረስ፡ መንገድ በመምራትና በመንከባከብ አምጥተው፡ የእኒያን ብሄራዊ ጀግና፡ የአጼ ቲዮድሮስን እልፈተ ህይወት ያፋጠኑት፡ አሁንም የትግራዩ ተወላጅ፡ ካሳ ምርጫ፡ ወይንም በንግስና ስማቸው አጼ ዩሃንስ እንደ ነበሩም ይነገራል። ምንም እንኳን በሗላ ከወራሬ ጋር ሲፋለሙ በክብር ቢወድቁም።

ዛሬ በምናሰበው በ1888 ዓ.ም አድዋ ላይ በተካሄደው፡ የኢትዮጵያና የኢጣልያን ጦርነት ጊዜ በእራስ መኮንን የሚመራው ቀዳሚ ጦር። አምባላጌ እንደደረሰ ገና መሬት ሳይዝ በወጊያ የጠመዱትም የትግራይ ተወላጅ ባንዳዎች ናቸው።

በ1928 ዓ.ም በሁለተኛው የኢጣልያ ወረራ ወቅት፡ አርበኛው ፊትለፊ ከጠላት ጋር ሲፋለም፡ በትግራይ በቀሉ ባንዳ በደጃዝማች ሃይለስላሴ ጉግሳ፡ የሚመራው የትግራይ ተወላጆች ስብስብ፡ ተመሳስሎ በጀርባ እየገባ ያልተጠበቀ አድጋ በማድረስ፡  ለሽንፈታችን ትልቅ አስተዋጽኦ ከማድረጉም በላይ፡ ሲሸሽ እየተከታተለ የደከመውንና ቁስለኛ ወንድሙን በመግደል፡ ከኢጣልያን የከፋ በርካታ የኢትዮጵያን አርበኛ ፈጅቷል።

ሀምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም. አቡነ ጴጥሮስ አዲስ አበባ ላይ ሲረሸኑ፡፡

ህዳር24ቀን 1929 ዓ.ም. አቡነ ሚካኤል ጎሬ ላይ ሲረሸኑ፡፡

የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. በግራዞያኒ ትእዛዝ አዲስ አበባ ላይ ከ30 ሺህ የማያንስ ህዝብ ሲጨፈጨፍ፡፡ ትዕዛዝ ፈጻሚዎቹ  አሁንም ትውልደ ሰሜን ወንድሞቻችን  ነበሩ።

1969ዓ.ም ሶማሌ ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅትም፡ ወያኔ መቃድሾ ከተማ ቢሮ ከፈቶ፡ በተለይ በሰራዊታችን ውስጥ የእሱን ሰው አሰርጎ በማስገባት፡ ለጠላት መረጃ ከማቀበል ጀምሮ፡ የሶማሌ የስለላ ማዕከል፡ የኢትዮጵያ ጦር ግንኙነት የሚያደርግበትን፡ ሬዲዮ እየጠለፈ ሲያቀርብለት በመተርጎም፡ ለሶማሌ ሰራዊት እየሰጠ በኢትዮጵያዊያን ላይ ጉዳት እንዲደርስ በማድረግ ትልቅ ክዕደት ሲፈጽም ነበር።

በአብዛኛው ማለት በሚያስደፍር ሁኔታ፡ በሃገራችን ላይ ወረራ በተሰነዘረ ቁጥር በርካታ የትግራይ ተወላጆች፡ ከጠላት ጎን በመሰለፍ የእናታቸውን ጡት ሲነክሱ ለመኖራቸው ድርሳናቶቹ ሁሉ ቁልጭ አድርገው ያመላክቱናል።

ዛሪም ታሪክ እራሱን ደገመና፡ ትግራይ የፈለቁ ጉዶች ናቸው፡ እኛን በዘርና በሃይማኖት ከፋፍለው፡ ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር እንደምስራቅ ጀረመንና እንደ ዩጎዘላቢያ ከዓለም ካርታ እንድትፋቅና እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ በማለት አፍ ሞልቶ ደረት ነፍቶ የሚናገር ዜጋ እንዳይኖር 24 አመት ሙሉ ሽንጣቸውን ገትረው በመስራት ላይ ያሉት።

ይህንን ስል ግን ትውልደ ትግራይ ሆነው፡ ለአገር አንድነትና ለወገን ነጻነት፡ የተጋደሉ አልነበሩም። አሁንም፡ የሉም እያልሁ አይደለም። ትናንት እነ አሉላ አባነጋን፣ እነ እራስ ስዩም መንገሻን፣ እነ ደጃዝማች አርያን እነ እራስ መነገሻ ስዩምን፣ ወ.ዘ.ተ. ዛሪም የትግራይ ዲሞክራሴያዊ ንቅናቄ ሰዎችን በተለይም የድርጅቱ መሬ የነበረውንና አሁን በህይወት የሌለውን ፍስሃ ሃይለማርያምን የመሰለ የሃገር

2.. ፍቅር ያንገበግበው የነበረውን። እነ ገብረመደህን አርያን፣ እነ አብርሃ በላይን፣ እነ አብረሃ ደስታን፣ እነ አስራት አብርሃምን ያፈራች ስለሆነ።

መነሻዬ የኢትዮጵያን ታሪክ፡ ወይንም የትግራይ በቀል የጥፋት መልክተኞችን ጉድና ሁላችንም ተደራሲዎች የሆንበትን፡ የወያኔን መግለጫ ቃላት መለኪያ መስፈርት የማይገኝለትን፡ የግፍ ክምር እየናድሁ የምታውቁትን በመድገም ጊዜያችሁን ለማባከን አስቤ አይደለም።

ይልቁንም በትግራዩ ተወላጅ፡ በእራስ ስዑለ ሚካኤል፡ መሰሬ ተንኮል ተበታትና የነበረችዋን ኢትዮጵያን፡ እምዬ ምኒልክ። እንዴት መልሰው እንደገነቧት በአይነ ህሌናችሁ ወደሗላ እንደትመለከቱ ለማነሳሳትና ለውይይት ሃሳብ ለማጫር  የተጠቀምሁበት ነው እንጅ።

ወደዛሬው ምልከታየ ስገባ።

አጼ ምኒልክ ነሃሴ 12 ቀን 1836 ዓ.ም በሽዋ ክፍለ ሃገር በተጉለትና ቡልጋ አውራጃ አንጎለላ ኪዳንምህረት ተወለዱ። ከ12 አመት እድሜያቸው ጀምሮ በግዞትም፣ በማደጎም፣ በአማችነትም ከአጼ ቲዮድሮስ ቤት አደጉ።

ከእድገታቸው እስከ ንግስናቸው ያለውን ታሪክ ለጊዜው ላቆየውና። ከነገሱ በሗላ በተለይም ከዛሬው መሰባሰቢያችን ጋር በቀጥታ የተያያዘውን ከፋሽትት ኢጣልያን ወራሬ ጦር ጋር ያደረጉትን ተጋደሎ ባጭሩ ልጥቀስ።

እምዬ ምኒልክ መላዋን ኢትዮጵያን ከማስረዳደራቸው በፊት። የሽዋ ንጉስ በነበሩበት ወቅት ከኢጣልያን መንግስ ጋር ወዳጅ በመሆናቸው እስከ መሳሬያ እርዳታ ድረስ ያገኙ ነበር። በሗላ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ሲሆኑ ግን። ኢጣልያን  ኢትዮጵያን ለመውረር በነበራት ፍላጎት መሰረት በአጼ ዩሃንስ ጊዜ የጀመረችውን ወረራ እያሰፋችና  እየገፋች ስትመጣ። በምኒልክና በኢጣልያን መንግስት መካከል የቆየው መልካም ግንጉነት እየሻከረ ሄደ።

አጼ ምኒልክ ከኢጣልያን ጋር የነበረው ወዳጅነታቸው እንዲቀጥል አጥብቀው  ቢጥሩም። በኢጣልያን በኩል ግን ተቀባይነት አላገኙም ነበር። በተለይም የውጫሌ ውል እየተባለ በሚጠቀሰው አንቀጽ 17 ላይ በኢጣልያነኛ የተጻፈው ሃገራቸውን እንደሚጎዳ ሲገነዘቡ ክተት ሰራዊት ምታነጋሬ በማለት የሚከተለውን ጥሬ ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ አስተላለፉ።

የአጼምኒልክ ጥሪ ሙሉ ቃል

እግዚያብሄር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ አገር አስፍቶ አኖረኝ። እኔም እስካሁን በእግዚያብሄር ቸርነት ገዛሁ። እንግዴህ ሞት ለሁሉ ነውና ብሞትም በእኔ ሞት አላዝንም። ደግሞ እግዚያብሄር አሳፍሮኝ አያውቅም። ከእንግዴህም ያሳፈረኛል በዬ አልጠራጠርም።

አገር የሚያጠፋ፣ ሃይማኖት የሚለውጥ፣ ጠላት እግዚያብሄር የወሰነልንን የባህር በር አልፎ መጧል። እኔም የሃገሬን ከብት ማለቅ የሰውንም መድከም አይቸ ዝም ብለው እያለፈ እንደፍልፈል መሬት ይቆፈር ጀመር። አሁን ግን በእግዚያብሄር እረዳትነት ሃገሬን አሳልፊ አልሰጥም።

የሃገሬ ሰው ከአሁን በፊት የበደልሁህ አይመስለኝም። አንተም እስካሁን አላስቀየምከኝም። ጉልበት ያለህ በጉልበትህ እርዳኝ። ጉልበት የሌለህ ለልጅህ፣ ለሚስተህ፣ ለሃይማኖትህ ስትል በሃዘን እርዳኝ። ወስልተህ የቀረህ ግን በሗላ ትጣላኛለህ። ማርያምን ለዚህ አማላጅ የለኝም። ዘመቻየ በጥቅምት ነውና የሽዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ወረኢሉ ከትተህ ላግኝህ።

የጥሬው መጨረሻ።

በማለት ካዘዙ በሗላ በእራስ መኮነን የሚመራውን ቃፊር ጦር አስቀድመው እሳቸው ህዳር 2 ቀን 1888 ዓ. ም ከአዲስ አበባ በመነሳት ወደ ሰሜን አመሩ።

ንጉሱ በመንገድ ላይ እንዳሉ በራስ መኮነን የሚመራው ቀዳሚ ጦር አምባላጌ ደረሰ። በዚህ ወቅት የኢጣልያን ጦር። የኢትዮጵያን ጦር ከመንግድ እንደመጣና እንደደከመ እንደገናም ቦታ ሳይዝ። ለመምታት ተዘጋጅቶ ቅድም እንዳልኩት በርካታ ትግራይ በቀል ባንዳዎችን በማሰለፍ ውጊያ ከፈተበት። ግን ከ6 ስአት በላይ በፈጀው ጦርነት። ኢጣልያን የመጀመሬያውን የሸንፈት ጽዋ። በእራስ መኮነን ጦር ተጎነጨና ከአምባላጌ ምሽጉ ተባበረ።

አጼምኒልክም ታህሳስ 29 ቀን 1888 ዓ.ም መቀሌ እንደደረሱ። አዚያ ሰፍሮ የነበረውን የጠላት ጦር ዙሬያውን በማስከበብ የሚጠጣው ወሃ ከማሳጣታቸውም በላይ። በውጊያም መድረሻ ስላሳጡት

3.

ያለቀው አልቆ የተረፈው የሃገር ሽማግሌዎችን አማላጅ በመላኩ መንገድ ተከፍቶለት ወደ አዲግራት ሸሸና ለሁለተኛ ጊዜ ሽንፈቱን አጣጣመ።

በዚህ ዘመቻ በኢትዮጵያ በኩል የተሰለፈው ሰራዊት። መቶሽህ እንደሚደርስ የሚገመት ሲሆን። ከዚህ መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆነው አርበኛ ጦርና ጎራዴ ብቻ የታጠቀ እንደነበርና ጠብመንጃ ያለውም ቢሆን ጠላት ከታጠቀው ዘመናዊ መሳሬያ ጋር ሲነጻጸር የሰማይና የመሬት ያህል የተራራቀ እንደነበር የታሪክ ጸሃፍት ያሰምሩበታል።

በዚህ ጦርነት በኢትዮጵያ በኩል የተሰለፉ ዋና ዋና የጦር አዝማቾች።

  1. እትጌ ጣይቱ ብጡል፡

2.ንጉስ ተክለ ሃይማኖት፡

3.ፍታውራሪ ገበየሁ፡

4.ደጃዝማች ጫጫ፡

5.እራስ መኮንን፡

6.እራስ መንገሻ ስዩም፡

7.እራስ መንገሻ አቲከም፡

8.እራስ ሚካሌል፡

9.እራስ ወሌ ብጡል፡

10.ደጃዝማች በሻህ አቡዬ፡

11.እራስ ጉግሳ፡

12.እራስ አሉላ አባነጋ፡

13.ዋግሹም ጓንጉል፡

14.እራስ ወርቄ  የተባሉት ነበሩ።

በኢጣልያን በኩል የጦር አዛዦች ደግሞ፡

  1. ጠቅላይ አዛዡ ሌትና ጀሪናል ባራቲይሪ፡
  2. ጀኔል ዦሴፔ ኦሪሞንዱ፡
  3. ጀኔራል አማኑኤል ደቦርሜዳ፡
  4. ጀኔራል ማቲዮስ አልቤርቶኒ፡
  5. ጀኔራል ዦሴፔ ኤሌና፡
  6. ኮሎኔል ቫሊንዞኖ፡ ነበሩ።

በዚህ የሃይል አሰላልፍ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም ልክ የዛሬ 119 አመት ከሌሊቱ በ11 ስአት በኢጣልያን ተንኳሽነት  አድዋ ላይ ወሳኙ ጦርነት ተከፈተ።

ሊነጋጋ ሲል ከሌሊቱ በ11 ስአት የተጀመረው ጦርነት። ቀኑን ሙሉ ውሎ ከሌሊቱ 5 ስአት በኢትዮጵያ አሸናፊነት ተጠናቀቀና ሃገራችን ኢትዮጵያ በጥቁር አንበሶች ልጆቿ አጥንት ክስካሽና ደም ፍሳሽ ሃያልነቷ በአም ሁሉ ተናኘ።

ውጤቱም የአለም ህዝብን  አስደነቀ። የጀግኖች አባቶቻችን አይበገሬነትም በማያጠራጥር ሁኔታ ታወቀ።  በኢጣልያን በኩል ከተሰለፉት የጦር አዛዦች መካከል ከጠቅላይ አዛዡ ከሌትና ጀኔራል ባራቲይሪ በቀር ሌላው የጦር አዛዥ ጀኔራልና ከፍተኛ መኮንን በሙሉ ተደመሰሱ።

በኢጣልያን በኩል ከተማረከውና ቆስሎ ከሸሸው ሌላ 9215 ተዋጊ ሲሞት። ከኢትዮጵያ 7000 ሰው ሞቷል። ከዚህ ውስጥ ከወገን የሞቱ አዋጊዎች።

  1. ደጃዝማች በሻህ አቡዬ፡
  2. ደጃዝማች ጫጫ፡
  3. ፍታውራሪ ገበየሁ፡
  4. ፍታውራሪ ተክሌ፡
  5. ቀኛዝማች ታፈሰ አባይነህ፡
  6. ፍታውራሪ ዳምጠው፡
  7. ደጃዝማች ማናዬ፡

4.

  1. ፍታውራሪ ወልደ ሚካሌል።
  2. ቀኛዝማች ተገኘወርቅ፡
  3. ፍታውራሪ አምባዬ።
  4. ቀኛዝማች ተሰማ ወልዴ፡
  5. ፍታውራሪ ሸንኮሩ፡
  6. ባላንበራስ በለው፡

14.ባላንበራስ አደራ ወ.ዘ.ተ. ይጠቀሳሉ።

ማጠቃለያ

በጣም የሚገርመው የአውሮፓ ሃያላን መንግስታት። አፍሪካን በቅኝ ለመግዛት። እንደ ቅርጫ ስጋ የተከፋፈሉበትና። እርስ በርስ ላለመነካካት የተፈራረሙት የካቲት 26 ቀን 1877 ዓ.ም ከአድዋ ጦርነት ከ3 አመት በፊት ሲሆን። በክፍፍሉም።

1ኛ. እንግሊዚ፡ ግብፅን፣ ሱዳንን፣ ናይጀርያንና ኬንያን።

2ኛ. ፈረንሳይ፡ ምህራብና ሰሜን አፍሪካን።

3ኛ. ፖርቱጋል፡ አንጎላንና ሞዛቢክን።

4ኛ. ጀርመን፡ ታንዛንያንና ቶጎን።

5ኛ. ቤልጅም፡ ኮንጎን።

6ኛ. ኢጣልያን፡ሶማልያንና ሊብያን ወ.ዘ.ተ በማድረግ ሲከፋፈሉ።

ኢትዮጵያን አልነኳትም ነበር። ምክናያታቸውም የረጅም ዘመን የተጠናከረ መንግስትና። አይበገሬ ህዝብ  እንዳላት ስለሚያውቁ።  እንደሆነ ይነገራል የተጨበጠ ማስረጃ ባይኖርም።

ዛሪስ በእኔና እናንተ ድርሻ። ሃገራችን ኢትዮጵያ በዓለም ህዝብ ዘንድ የነበራትን ክብር እንዳስጠበቀች ነች ወይ? የሚል ጥያቄ  ቢነሳ ሁላችንንም የሚያስማማን መልስ። አይደለም የሚለው እንደሚሆን አልጠራጠርም። ለምን? ከተባለ ልንሰጠው የምንችለው ምላሽ ግን የተለያየ እንደሚሆን እገምታለሁ።

በበኩሌ የእኔና የእናንተ ትውልድ ፈጹም እራስ ወዳድ ስለሆነ። ሌላው ሞቶለት እሱ ተጠቃሚ መሆንን ስለሚያሰላ ነው የሚል ነው ።

እናንተስ በእኔ ሃሳብ ትስማማላችሁ? አይደለም ሌላ ምክናያት ስላለ ነው ወኔ የከዳን የሚል ካለ ለመስማት ዝግጁ ነኝ። መልካም ውይይት እያልሁ እንደ እናንተው ቁጭ ብዬ የግል አስተያይቴን መሰንዘር እችል ዘንድ ዝግጅቴን በምትከተለዋ አጭር የግጥም ስንኝ ልቋጭ።

እርዕሷንም አድዋ ብያታለሁ!!

አድዋ

ከሰሜን ከደቡብ ከመግቢያና መውጫ፣

ከምስራቅ ከምእራብ ከሉም አቅጣጫ።

ቋንቋ ሳይለያቸው ዘር ማንዘር ሳይቆጥሩ፣

አማራ ኦሮሞ በማለት ሳይጠሩ፡

በዚያች የቁርጥ ቀን ቀድመው የደረሱ፣

ጥንት አባቶቻችን እነዝናር ልብሱ፡

ምሳሌ በመሆን በኩራት ሲጠሩ፣

ከመቃብር ጀርባ ዝንታለም ሊኖሩ፣

በአድዋ መልካ ላይ ታሪክን የሰሩ።

አባቶች ነበሩን የሃገር መከታ፣

ህይወት የሚሰጡ በመሆን አለኝታ።

እጅ ለእጅ ተሞሻልቀው በታጠቁት ካራ፣

ፈንጥቀው ያአለፉ እንደ ንጋት ጮራ።

ምኒልክ ለአድዋ ባቀረቡት ጥሪ፣

ያች ጣይቱ ብቱል ሆነች የጦር መሬ።

አዎ!! አድዋ!! አድዋ!! አድዋ!!

5.

የዛሬ ማፈሪያ የትናንት መኩሪያዋ፡

የዛሬ ማፈሪያ የትናንት መኩሪያዋ።

አመሰግናለሁ፡

ማተቤ መለሰ ተሰማ

በ2007 የ119ኛው የአድዋ የድል ባል በኖርዌይ የኢትዮጰያ ማህበር ሲያከብር የቀረበ የውይት መነሻ።

The post አድዋን ስንዘክር፡ – ማተቤ መለሰ ተሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከጨርቁና ከቋንቋው በስተጀርባ –ይሄይስ አእምሮ (ከኢትዮጵያ)

$
0
0

ዛሬ እሁድ የካቲት 22 ቀን 2007 ዓ.ም የወያኔ 40ኛ ዓመት ክብረ በዓል መዘምዘሚያ በወያኔው አባል በቱጃሩ አላሙዲን የሚሌኒየም አዳራሽ ውስጥ እየተከበረ ነው፡፡ ዘፈንና ደስታ አለቅጥ ሲበዛ የሚያስከትለውን ምልኪያዊ ሀዘን የተረዱ አይመስሉም፡፡

እኔ እንዳለመታደል ሆኖ የወያኔን ሚዲያ አልከታተልም – በሌላ ምክንያት ሣይሆን ለጤንነቴ ቅድሚያ ከመስጠት አኳያ ነው፡፡ ነገር ግን የሚከታተሉ ሰዎች ብዘውን ጊዜ  ምን እንደተላለፈ በመጠጥ ቤትና በሕዝብ መገናኛ ሥፍራዎች ይነግሩኛል፡፡ መስማት ባልፈልግም ጆሮየን መጠቅጠቅ አልችልምና እሰማለሁ፡፡ የዛሬውን አስደናቂ ወሬ የሰማሁት እንግዲህ ወድጄ ሳይሆን ተገድጄ መሆኑ ነው፡፡

የወያኔ በዓል በትግራይ ውስጥ ከሁለት ወራት ላላነሰ ጊዜ በትግርኛም እንዳስፈላጊነቱ በዐማርኛም ተከብሯል፡፡ በመሠረቱ ወደ ስድስት ሺህ ገደማ በሚገመቱት የዓለም ቋንቋዎች ቢከበርም ግድ አይሰጠኝም ብቻ ሣይሆን የምከፋ አይደለሁም፡፡

ሰዎች እየተዘባበቱና በወያኔ እየቀለዱ ሲናገሩ እንደሰማሁት ደብረጽዮን የሚባለው የወያኔ ባለሥልጣንና ቱባ ካድሬ በዚህ የሚሌኒየም አዳራሽ የበዓሉ መዝጊያ ሥነ ሥርዓት ላይ ያደረገው ንግግር ሙሉ በሙሉ በትግርኛ ነው አሉ፡፡ እርግጥ ነው – በሕወሓት በዓል ላይ ሌላ ቋንቋ እንዲነገር መጠበቅ አግባብነት ላይኖረው ይችላል፡፡ መሠረታዊ ችግሩ ግን የአንድ ፓርቲ ወይም የነፃነት ግምባር የመላ ሀገሪቱን ሕዝብ እንደነሱው አጠራር ‹ሕዝቦች› ንብረት የሆነውን ሚዲያ በጉልበት አስገድዶ – ፕሮግራሞቹንም ሁሉ አስቁሞ – ለግል ጉዳዩ ማዋሉ ነው፡፡ ይህ ማንአለብኝነት ነገና ከነገ ወዲያ በታሪክም በወንጀልም የሚያስጠይቅ ትልቅ ጥፋት ነው፡፡ እስካሁን ባለው ሁኔታ ሌሎች “አቻ” ፓርቲዎች ወይም የ“ነፃነት ንቅናቄዎች” – ለምሣሌ እንደ ኦህዲድና ብአዴን እንዲሁም ደኢሕዲን የመሳሰሉት –  ይህን የመሰለ በጣም የተራዘመ ደማቅ ሀገራዊ የመገናኛ ብዙኃን ሽፋን፣ የገንዘብ መዋጮና “መንግሥታዊ” የበጀት ድጋፍ አላገኙም – ከአሁን ወዲያም ቢሆን ፍትሃዊ የድርጅቶች እኩልነት በተግባር እንዲታይ ወያኔዎች የሚፈቅዱ ከሆነና ሕወሓት እስከመጋቢት ድረስ የሚቆይ ከሆነ የፊታችን መጋቢት 17/2007 እንደሚከበር የሚጠበቀው የኦህዴድ የምሥረታ ወይም ከደርግ ምርኮኛ ብሔራዊ ዘማቾች በወያኔ ተጠፍጥፎ ለመናጆነት የተሠለፈበት በዓል በምን አኳኋን እንደሚከበር ለማየት በጉጉት እንጠብቃለን፡፡ ከህዝብ ብዛት አንጻር ወያኔ ትንሽ የመቶኛ ሥሌት ይዞ ሳለ በዚህ መልክ በዓሉን ማክበሩ ሀገሪቱንና ሀብቷን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ሥር ማድረጉን ያመለክታል የሚል ግምት ያስጨብጣል፡፡ ይህ አካሄድ ሀብቷን ብቻ ሣይሆን ከወያኔ በእጅጉ እንዲያውም በፍጹም ሊወዳደር በማይችል ሁኔታ ኆልቁ መሣፍርት የሌለው የሕዝብ ቁጥር ይወክላሉ የሚባሉ “አቻ” ግምባሮችንና ንቅናቄዎችን እንዲሁም ውዝዋዜዎችን በእግሩ ሥር አውሎ እንደፈለገው እየተጫወተባቸው መሆኑን ይጠቁማል – እንደአካሄድ፡፡ ይህ ደግሞ በተለይ በጥገኛ ድርጅቶች ዘንድ ታላቅ የሀፍረት ምንጭ ሆኖ በታሪክ የሚመዘገብ ይመስለኛል፡፡

ባለራዕዩ መሪ ሙትቻው ሟች መለስ ዜናዊ አንድ ወቅት ስለ ሰንደቅ ዓላማ ሲጠየቅ – መጥቀስ ይቻላል –  “ባንዲራ ጨርቅ ነው፡፡ ምሥጢሩ ያለው ከባንዲራው በስተጀርባ ነው” ብሎ ነበር፡፡

መለስ በዚህ ንግግሩ ብዙ ተተችቷል፡፡ እንደኔ ግን ትክክል ነበር፡፡ ሰንደቅ ዓላማ ከጨርቅ ውጪ ከብረት ወይም ከእንጨት ተሠርቶ ሲውለበለብ አይቼ አላውቅም – እናም ከዚህ እሳቤ አንጻር መናገር ፈልጎ ከሆነ ስህተት አልነበረውም፡፡ ችግሩ የሚመስለኝ ከአመለካከትና ከንግግሩ በስተጀርባ ካለው ፍላጎት ነው – እንግሊዝኛ ተናጋሪዎቹ “intention” የሚሉት፡፡ እንደሚመስለኝ እርሱ ማለት የፈለገው “ሕወሓት ለ‹ሀገሪቱ› የፈጠረላት ባንዴራ ከጥንቱ ባንዴራ የተለዬ ነው፡፡ የጥንቱ ባንዴራ ብሔር ብሔረሰቦችንና ሕዝቦችን በኃይል ጨፍልቆ የግዛት አንድነት ለመመሥረት የሚጥርን ሥርዓት የሚወክል ሲሆን አዲሱና እኛ ሕወሓቶች የሠራነው ባንዴራ ግን የሀገሪቱ ዜጎች በፈቃደኝነት ላይ በተመሠረተ ሁኔታ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ፈጥረው የሚኖሩበትን ፍትሃዊ ሥርዓት የሚወክል ነው፡፡ ስለሆነም የጥንቱ ባንዴራ ከጨርቅነት ያለፈ ትርጉም ስለሌለው ከጨውና ስኳር መቋጠሪያነት ባለፈም ተቀዳዶ ቢጣልና ቢቃጠልም ሲያንሰው ነው” ነው፡፡ መለስ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እንደማይወድ እንዲያውም እንደአባቱ ገዳይ ያህል እንደሚጠላው የታወቀ ነው፤ የኢትዮጵያን ስም እንኳን በአግባቡ ለመጥራት ሲጠየፍ እንደነበርና ኢትዮጵያን መጥቀስ በሚኖርበት ዐረፍተ ነገር ሁሉ “ሀገሪቱ” እያለ በመጥራት ምድራዊውንና የሥልጣን ዘመኑን በአንድ ቅጽበት እስካጣበት ወቅት ድረስ በጥላቻ ናውዞ ይህችን ዓለም የተሰናበተ የመርገምት ፍሬ ነው፡፡ ስለዚህ ጨርቅ ቀርቶ ከዚያም ባለፈ ሊያስከፋ የሚችል ቃል ሊናገር ይችል ነበር፡፡ በንግግር ለማስቀየም ደግሞ እንደመለስ ዘርፋጭ ዓለማችን እስካሁን ያፈራች አትመስለኝም፡፡ እነሂትለርም የዚህን ቆሻሻ ሰውዬ ያህል እንደልባቸው ተናጋሪዎች አይመስሉኝም – መጠነኛም ቢሆን የተወሰኑ የሞራል ዕሤቶችን የሚያከብሩ ይመስሉኛል፡፡ ይሄ የኛው ጉድ  ግን ለይቶለት ከሁሉም ሃይማኖታዊና ሞራላዊ ማዕቀፎች ያፈነገጠ ነበር፡፡

የደብረጽዮን የትግርኛ ንግግርም ከመለስ የሰንደቅ ዓላማን ምንነት አገላለጽ ብዙም ለይቼ አላየውም፡፡ መለስ የኢትዮጵያን መለያ የሦስት ቀለማት ኅብር በሰም ለበስ ቅኔ “ጨርቅ” ሲል ለማዋረድ መሞከሩ ይህም ሰው – ደብረጽዮን – በሚሌኒየም አዳራሽ ለተሰበሰበው፣ ኢትዮጵያንም እንደሚወክል ለሚታመንና በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በሚተላለፍ የቀጥታ ሥርጭት በትግርኛ – ሊያውም ያለ አስተርጓሚ – መናገር የፈለገው  የተለዬ  “ኢንቴንሽን” በወያኔያዊ ልቡ ስላረገዘ እንጂ አንድምታውን አጥቶት አይደለም – የተወሰኑ ምናልባትም ብዙዎቹን የኢትዮጵያን ማኅበረሰብ አባላት በንዴት ለማንጨርጨር የታሰበ ድርጅታዊ ተልእኮን ለማሣካት ፈልጎ መሆን አለበት – በዚህ ጥርጥር የለኝም፡፡ ኦሮሞም በሉት ጉራጌ፣ ደራሳም በሉት ሽናሻ፣ ጠምባሮም በሉት ሃዲያ፣ ከምባታም በሉት ወላይታ፣ ጀምጀምም በሉት ኮንሶ፣ ጉሙዝም በሉት ኣሪ፣ በርታም በሉት አኝዋክ፣ፃማይም በሉት ሱርማ … ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ – በአዳራሹ ውስጥ ተገኘም በቲቪ ተከታተለም ከትግርኛ ይልቅ በአማርኛ እንደሚግባባ ትግሬ ብቻ ሣይሆን መላው ዓለም ያውቃል፡፡ By the way – በፈረንጅኛው ብራቀቅ ማን ይከለክለኛል –  አሁንም ልድገመውና  By the way የዋሽንግተን ዲሲ አምስተኛው የሥራ ቋንቋ አማርኛ መሆኑን እየመረራቸውም ቢሆን ወያኔዎች ሊያስታውሱት ይገባል – “የሚንቁሽ ዕግርሽ ሥር ወድቀው ይሰግዱልሻል” የተባለችው እምዬ ማርያም ብቻ እንዳልሆነች ልብ ይሏል – ዐማርኛም ገና ምን ዓይታችሁ – ጽላት እስኪቀረጽለት ድረስ በኢትዮጵያ ምድር ከፍ ያለ ሥፍራ ያገኛል – ዐማራ የሚባሉ የወያኔ የዕልቂት ሰለባዎች ከምድረ ገጽ ቢጠፉ እንኳን ዐማርኛ አይጠፋም – በዚህ ላይ ወረድ ብለን ተጨማሪ ነጥቦችን እንመለከታለን፡፡

ይህ ሰው – ደብረጥዮን – በዚህ ድርጊቱ ትግርኛ ተናጋሪውን ማስደሰት ይፈልጋል – ቢያንስ የዋሁን ክፍል፤ ትግርኛ ተናጋሪውን ማስደሰት የሚፈልገው ደግሞ በትግርኛ ፕሮግራም በሚሰራጭ የቴሌቪዥንም ሆነ የሬዲዮ ሥርጭት ሣይሆን ብሔራዊ ሥርጭት የሚካሄድበትን ዋና መስመር በማቋረጥ መሆኑን ያውቃል(ሉ)፤ ጀጋኑ ወዲታት ተጋሩ – ወየንቲ አዲ ትግራይ ኸምዚ’ኢና – ጋና ነርዕዮም ኢና… ይህች ትንሽዬ የዱባ ጥጋብ ከዚህ የምታልፍ መልእክት የላትም – እነዚህን ነፍጠኞች ገና እናሳያቸዋለን እያሉ ይመስላል – እነዚህ ከሙት መንፈስ ጋር ተፋላሚ ዶንኪሾቶች፡፡ በዚህ ሂደት ዐማርኛ ተናጋሪውንና ለጊዜው ማንኛውም ነገር ቢጠበስ ቢገነተር ምንም የማይመስለውን – የማይሞቀውን የማይበርደውን – ከርታታ ዜጋ ብቻ ሣይሆን መላዋን የሀገሪቱን ሕዝብ “ገዢህ እኔ ሕወሓት መሆኔን ሳትወድ በግድህ ዕወቅ፤ ምንም ብታስብ ምን ከኔ በላይ ጌታ ሊኖርህ አትችልም!” የሚል ውስጠ ወይራ መልእክት ለማስተላለፍ የፈለጉ ይመስላል – ቀላል ሰው ከዚህ የሚያልፍ አስተሳሰብ ሊኖረው አይችልምና፡፡ እንጂ ያ በሚሌኒየም ተሰበሰበ የተባለው ሰው ሁሉ ዐማርኛ ቋንቋን አጣርቶ አያውቅም ማለት ማሞ ቂሎን መሆን ነው፡፡ ዐማርኛን እንኳን አዲስ አበቤ ይቅርና እኔም አውቃለሁ ብዬ እንቀባረራለሁ – ከትግራይ ከመጣሁ ከ27 ዓመታት በኋላ፡፡ በአንድ ቋንቋ ውስጥ 50 ዓመትም ኖረህ እኮ ላታውቀውና ላትናገረው ትችላለህ፡፡ የበረከት ስምዖን ወላጆች ጎንደር ውስጥ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ኖረው በዐማርኛ ይቸገሩ እንደነበር በሕይወት ካሉም እንደሚቸገሩ ሰምቻለሁ፡፡

የጀመርኩትን ርዕሰ ጉዳይ በሚመለከት ንግግሩ ሣይሆን ከንግግሩ በስተኋላ ያለው ነገር ነው ለትርጉም ወሳኙ ብዬ ማመን እፈልጋለሁ፡፡ ወያኔ ዐማርኛን አሽቀንጥሮ መጣል ይፈልግ ነበር – ግን አልቻለም – አይችልምም፤ በምን አቅሙ? እየጠላውና እያንገሸገሸውም ቢሆን እስካሁን ለአገዛዙ ተጠቅሞበታል፤ እምትንጠራወዝ እስትንፋሱ ለይቶላት እስክትወጣና ወረደ መቃብር እስኪገባ ድረስም ይጠቀምበታል፡፡ ዐማርኛን ለማጥፋት – ልክ ዐማራ ተብለው የተፈረጁትን ሰዎች ለማጥፋት እንደሞከሩት  – ወያኔዎች ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም – ዐማርኛም ልክ እንደድመት ባለዘጠኝ ነፍስ ሆኖ ግና ክፉኛ ተገዳደራቸው – ሕይወት ያላቸው ተናጋሪዎቹ ሲሸነፉ ግዑዙ ቋንቋ አሸነፋቸውና ሥነ ልቦናዊ የበታችነት ህመማቸውን በየመድረኩ ያዝረከርክባቸውና ለሣቅ ለሥላቅም ይዳርጋቸው ገባ፡፡ ተጋሩ ወንድሞቼንና እህቶቼን የሌሎችን ብሔርና ብሄረሰቦች ስም እየሰጡ፣ ቋንቋቸውንም እንዲማሩ እያደረጉ ብዙ ሥውር ሥራዎችንና ሤራዎችን እንዲሠሩ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡ ነገር ግን እንደዐማርኛ የመሰለ የመግዣ መሣሪያ ሊያገኙ አልቻሉምና እስካሁን ከመድረክ ሊያገልሉት አልተቻላቸውም – ዐፄ ዮሐንስም በዚሁ መሣሪያ ነው አሉ ጎጃምን፣ ወሎንና ጎንደርን አንቀጥቅጥው የገዙት፡፡ በመሆኑም እየጠሉትም ቢሆን፣ ኦሪጂናል ተናጋሪዎችን እያጠፉም ቢሆን፣ ዐማርኛ መናገርን እንደነውር እንዲቆጠር በቀጥታም ሆነ በተዛዋሪ እየሠሩም ቢሆን፣ የቋንቋው ባለቤት እንደሆነ የሚነገርለትን ማኅበረሰብ እየናቁና እያንቋሸሹም ቢሆን፣ በትዕቢትና ዕብሪት ተወጥረው የነሱን ቋንቋና ባህል በሌሎች ላይ ለመጫን እየተንደፋደፉም ቢሆን …  የዐማርኛ ቋንቋን ግን እንደመሣሪያነቱ ሲጠቀሙበት ባጅተዋል፡፡ ምርጫ ስለሌላቸውም ነው፡፡

ቋንቋ የራሱ ህግ አለው፡፡ ማንም እንደፈለገ በዐዋጅ “ይህ ብሔራዊ ይሁን ፤ ያኛው ግን ከዛሬ ጀምሮ ብሔራዊ አይሁን”ማለት አይቻለውም፡፡ እንዲህ ቢቻል ኖሮ የዛሬዋ ዓለማችን የጋራ መግባቢያ ቋንቋ እንግሊዝኛ መሆኑ ቀርቶ የቻይናውያኑ መንደሪን ቋንቋ በሆነ ነበር፡፡ እንደገናም እንዲህ ቢቻል ኖሮ የኢትዮጵያ የጋራም በሉት የሥራ ቋንቋ ኦሮምኛ በሆነ ነበር – እነዚህ ቋንቋዎች በአፍ መፍቻነት እንደሚናገራቸው የሕዝብ ብዛት ቢሆን ኖሮ በየተገለጹበት አድራሻ ኦፊሴላዊ ቋንቋ ከመሆን የሚያግዳቸው አንድም ነገር ባልነበረ፡፡ የሚያግዳቸው ግን የታጠቀ ጉልበተኛ ወያኔን መሰል ውድብ ሣይሆን የማኅበረ-ኢኮኖሚውን መስተጋብራዊ ትስስር ተከትሎ በዘመን ማሕፀን የሚወለደውና የሚያድገው ሥነ ልሣናዊ ነባራዊ ሁኔታ ነው፡፡ እንጂ በቡድኖች ፍላጎት ቢሆንማ ኖሮ የኢትዮጵያ የጋራ ቋንቋ በአሁኑ ወቅት ትግርኛ ከሆነ ቢያንስ 24 ዓመታትን ባስቆጠረ ነበር፡፡ በዶክተር ተብዬዎች የወያኔ አቀንቃኞች የተጻፉ ብዙ ቅዠቶችን አንብቤያለሁ – ለምሣሌ ዐማሮች አናሳ(minority) ጎሣ እንደሆኑ፣ ትግሬው ብዙኃን(majority) እንደሆነ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋ ትግርኛ እንደሆነ ወዘተ.፡፡

ዐይናችንን እንጨፍንና በተመስጦ ጥቂት እናስብ፡፡ ዐማርኛ ባይኖር ኖሮ አገው ከአደሬው፣ ትግሬው ከቆቱው፣ ከፊቾው ከጉራጌው፣ ኑዌሩ ከሽናሻው፣ ሶማሌው ከኢሣው፣ አፋሩ ከከምባታው፣“ዐማራ”ው ከኦሮሞው፣… በምን ይግባቡ ነበር? ከ80 በላይ ቋንቋዎች በሚነገሩባት ድሃ ሀገር ስንት ብሄራዊ ቋንቋ ማበልጸግ ይቻላል? ከዚህ አኳያ የአፍ መፍቻን ቋንቋን ለአካባቢያዊ አገልግሎት እያዳበሩና እየተገለገሉ ለቅርስነትም እያቆዩ ሁለተኛ ቋንቋን (ተፈጥሯዊ ህግን እስከተከተለ ድረስ ማንኛውም ቢሆን ግዴለኝም) በጋራ ማዳበርና መጠቀም ማንን ይገድላል? በኢትዮዮጵያ ሁኔታና ለኔ እንደሚመስለኝ ይህን የዘመናት የታሪክ ሽመና ያወሳሰበውን ሥነ ልሣናዊ ቁርኝት በ40 ዓመት አይደለም በ400 ዓመትም ቢሆን መበጣጠስ አይቻልም – እርግጥ ነው እዚህና እዚያ በማቆሳሰል የተወሰነ ሰምበርና ጠባሳ ማኖር ይቻል ይሆናል፡፡ አለበለዚያ የኅልውና ጉዳይ ስለሆነ ምድረ ወያኔ ሁላ ጥላቻው እያንዘረዘራትም ቢሆን ዐማርኛዋን እየሰለቀች የአፓርታይድ ሥርዓቷን ትቀጥላለች – የቀብር ሥነ ሥርዓቷ እስኪፈጸም፤ ለነገሩ ዕድር የሌላት ሆና እንጂ ወያኔ እኮ ከሞተች ሰንብታለች – በሕይወት ያለች እየመሰለቻቸው ግን ሰዎች ይፈሯታል – የማይሞት አፏንና የውርድንበር አስደንጋጭ ተግባሯን እያዩ፡፡ ዐማርኛ ቋንቋን በሚመለከት ወያኔ ዕቅዱ ተሣክቶለት ዐማራ የሚላቸውን ወገኖች ከምድረ ገጽ ማጥፋት ቢቻለው እንኳን ዐማርኛን ከጋራ ቋንቋነት አንዲት ጋት እንዲያፈገፍግ ሊያደርገው አይችልም፡፡ ወደሽን ቆማጢት እንዲሉ ነው፡፡ በመሠረቱ ዐማርኛ ብሄራዊ ሆነ አልሆነ ለዐማርኛ ተናጋሪዎች የሚፈይደው ነገር ያለ አይመስለኝም፤ በመንግሥት ደረጃ ከታወጀባቸው የዕልቂት ዐዋጅና ተግባራዊ ማሳደድስ መቼ አስጣላቸው? ቋንቋቸው ብዙኃንን በድልድይነት በማገልገሉ ሳቢያ እንደውለታ ተቆጥሮ ከወያኔ ጭፍጨፋና እንግልት ሊታደጋቸው የሞከረ ማን ነው?

ወያኔዎች እውነተኛ ማንነታቸው ድንገት ብልጭ ሲልባቸው ልክ እንደዛሬው በዐማርኛ ተናጋሪ ኅብረተስበ መካከል – ሳይቸግር ጤፍ ብድር እንዲሉ –  በትግርኛ መቀናጣት ያምራቸዋል – እኔ እንደታዘብኩት ትርፉ ትዝብትና መሣቂያና መሣለቂያ መሆን ነው፡፡ በዚህ ድርጊት ትግርኛ አልከበረም – ዐማርኛም አልተዋረደም፤ የተከበረም ሆነ የተዋረደ ካለ ወያኔ መንደር ውስጥ የሚገኝ ሸውራራና ከፋፋይ አመለካከትና አስተሳሰብ ነው፡፡ በመሠረቱ ቋንቋ እስከዚህ ድረስ ለሥነ ልቦናዊ ቀውስ የሚዳርግ ነገር አይደለም፡፡ ቋንቋ የመግባቢያ መሣሪያ እንጂ የበታችነት ስሜት ጭቅቅትን በሰፊው ሕዝብ ላይ ለማራገፍ የሚዳክሩበት አቢይ ጉዳይ አይደለም፡፡ የማይምነት ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ብዙኃኑ የሚናገረውንና የሚግባባበትን ቋንቋ አስትቶ ወደጠበበ ዐውደ ልሣን የሚያወርድ ምንም ምክንያት የለም፡፡ እርግጥ ነው – በአሁኑ ወቅት ትግርኛ የገዢው መደብ ቋንቋ መሆኑ በስፋት ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ለምሣሌ የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ ነገ የዳዋሮ ማኅበረሰብ አባል ወደ ሥልጣን ቢመጣ ዳዋሮኛ የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ መግባቢያ ቋንቋ ይሆናል ማለት አይደለም – ሊሆን አይችልም ማለቴ ሣይሆን አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ግን እውነቱ እንደዚያ አለመሆኑን ለመጠቆም ብዬ ነው፡፡ ከፍ ሲል ለመግለጽ እንደተሞከረው ቋንቋ የራሱ ህግና ሥርዓት ያለው እንጂ ገዢዎች እንደፈለጉ የሚዘውሩት እንዳልሆነ መታወቅ ይኖርበታል፡፡ ስለሆነም ደብረጽዮንና በረከት እንዲሁም ሌሎቹ ወያኔዎች እየዳከሩበት የሚገኙት የኢትዮጵያን ሕዝብ የጋራ ቋንቋ የማጥፋትና ወደቀደመው የባቢሎን ዘመን የመመለስ ዕቅድ እንዲህ በቀላሉ ይሣካላቸዋል ብሎ ማመን የዋህነት ይመስለኛል፡፡ እንደኔ እንዲያውም የተቃጠለ አየር ከሰውነቷ እንዳይወጣ ጥረት አድርጋ ነገር ግን ያልተሣካላት ሴትዮ “ውይ! መንግጌ አባስኩሽ!” እንዳለችው እነዚህ ወያኔዎችም ዐማርኛን ለማጥፋት ባደረጉት ጥረት ይበልጥ ተፈላጊነቱን ሣይጨምሩት የቀሩ አይመስለኝም፡፡ እንዴ፣ ቋንቋ እኮ ከእስክርቢቶና ከወረቀት የማይበልጥ ወይም የማያንስ ተራ የመግባቢያ መሣሪያ ነው እንጂ እስከዚህ ድረስ አቅልን ስተው የሚራኮቱበት ነገር አይደለም – በቃ፣ ተራ ነገር ነው፤ ከዚያ አስበልጦ ማየት በሽታን መግዛት ነው – ልክ እንደወያኔ፡፡ ትግርኛ ተናገርክ ዐማርኛ፣ ጦጥኛ ተናገርክ ዝንጀሮኛ፣ አፋርኛ ተናገርክ ኦሮምኛ ዋናው በመግባቢያ መሣሪያነቱ መጠቀም እንጂ “የኔ”ና “ያንተ”ን ምን አመጣው? ያንተ የሆነ የነሱም ነው፤ የነሱ የሆነም ያንተ፡፡ Why should we really over-politicize languages? Personally, I do not see any difference between ‘my’ language and any of the tools I use in my daily life. Aha! I now vividly remember that Esperanto was a failure due to the selfish motive of humans! Hey, let’s get enlightened, please.

የኢትዮጵያ ሕዝብ የቋንቋም ሆነ የዘር ሐረግ ልዩነት እንደማይበግረው በቅርቡ ያዩታል ብዬ አምናለሁ፡፡ ለመሠሪ ተልዕኮና ለአፍራሽ ውጤት ሣይሆን ለእውነተኛው መግባቢያነት ትግርኛም ሆነ ሌላው ቋንቋ ሁሉ በመገናኛ ብዙኃናችን በተፈለገው ጊዜና በተፈለገው መጠን ሲነገር የሚያዳምጡበት ጊዜ ብዙም ሩቅ አይመስለኝም፡፡ ይህችኛዋ የደብርጽዮኒቷ የሚሌኒየም አዳራሽ ትግርኛ ግን “ኢንቴንሽኗ”(ድብቅ አጀንዳ) ትገባናለችና የ“ሲምፕል ሣይኮሎጂ” ሰለባዎች እንዳንሆንላቸው እንጠንቀቅ፤ ወያኔዎችና ሼሪክ አበጋዞቻቸው ሕዝብን ከሕዝብ ለማቃቃር ብቻ ሣይሆን በለዬለት የሁለትና ሦስት ጎራዎች ውጊያ አሠልፈው ለማጨራረስም የማያቅማሙ አረመኔዎችና ኃላፊነት የጎደላቸው ፍጡራን በመሆናቸው ጥንቃቄ ማድረግ ያለብን እኛ ሕዝቡ ነን፡፡ ቀላሎች ቀላል ሊያደርጉን አይገባቸውም፡፡ ሤራቸውን ለማክሸፍ ሕዝቡ በቶሎ መንቃት ይኖርበታል፤ በጥቃቅን መደለያዎች – ሆድን በማይሞሉ የወያኔ የማስመሰል ቅራቅንቦዎች መታለል የለብንም – በሚጨበጥ ነገር እንጂ መሬት ባልረገጠ የስሜት ዐውሎ ነፋስ እንዳንነዳ መጠንቀቅ አለብን፡፡ ከነዚህ አዛኝ ቅቤ አንጓቾች ተንኮል ራሳችንን እንጠብቅ፤ ትግሬውን ያስደሰቱ መስለው ለመታየትና በእግረ መንገድም ስንጥቃቱን ለማስፋት በሚያከናውኗቸው ከፋፋይ ተግባራት ሳንሞኝላቸውና ብዙም ፊት ሳንሰጣቸው በጋራ የጋራ ቤታችን የምትሠራበትን መንገድ እናመቻች፡፡  ትግሬው ወገን የወያኔን ጠባብ ዓላማ ይረዳና ከሰፊው ወገኑ ሊለያየው የሚችልን ይህን መሰል ላይ ላዩን ሲያዩት ምንም ነገር ያልሆነ የሚመስል በጥልቀትና በጥሞና ሲያዩት ግን ሥነ ልቦናዊ መደላድል የረገጠ የከፋፋይነት ሤራ ያለው ተንኮል ተገንዝቦ ተቃውሞውን በግልጽ ማሰማት አለበት፡፡ “የእስካሁኑ መሠሪ አካሄድ ይብቃ” ብሎ እነዚህን የእፉኝት ልጆች ሊታገላቸው ይገባል፡፡ ሌላውም ወገን በዚህ ዓይነት መሠሪ አካሄድ ብዙም ሳይከፋ ለመጨረሻው አርማጌዴዌዎናዊ ድል ይዘጋጅ፡፡ የመጨረሻው መጨረሻ ደወል ሊደወል የቀረው ጊዜ ብዙ ሩቅ አይመስለኝም፡፡ እስከዚያው በያለንበት ሰላም ያቆየን፤ የሀገራችንን ትንሣኤም በቅርብ ያሣየን፤ አሜን፡፡

yiheyisaemro@gmail.com

 

 

The post ከጨርቁና ከቋንቋው በስተጀርባ – ይሄይስ አእምሮ (ከኢትዮጵያ) appeared first on Zehabesha Amharic.

ባለ ራእዩ  መሪ ምን ይሆን ራእያቸው?። (ከ- ከተማዋ ቅጅራ)

$
0
0

ሕልሜን ፍቱልኝ።                                                                                        

KetemaTPLF በአገሩ ሁሉ ለሚኖሩት ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ታላቅ ግብዣ አድርጓል። በዚህ ቤት ሁሌ ደስታ ነው ሁሌ ፌሽታ ነው። ለድግሱ የተጠሩት ሁሉን ማድረግ የሚችሉ፣ ባለብዙ ህንጻ ባሌቤቶች፣ የፈለጉትን የሚወስኑ፣ ራእይ አስፈጻሚ ናቸው። በሚሰሩት ስተት ንጉሱ ከመረጧቸው ከድግሱ ተጠሪዎች ውጪ ማንም ሊጠይቃቸው የማይችል፣ የሚሰሩትን ግፍዊ ስራ  እንደ ጀብዱ  ደጋግመው የሚናገሩ፣ በአዳራሹ ውስጥ ለተሰበሰቡት መገለጫቸው  ነው። በዚህ መሃል ንጉሱ እንዲህ አሉ ለድግሱ ታዳሚዎች በአዳራሽ ውስጥ ላሉት። ህልም አልሜአለው ብለው ተናገሩ። ህልሜም ተፈጻሚነት እንዲኖረው ለድግሱ የተጠራችሁ ወዳጆቼ በሙሉ ሃላፊነት አለባችሁ ከአዳራሹ ውጪ ያልወጣ የንጉሱ ራእይ እንደፈለጉ ሊበሉ ሊጠጡ ለተመረጡት ተነገረ። ወዳጅ ዘመዶቻቸው  የተጠሩት ሁሉ ገብቶአቸው ይሁን ሳይገባቸው በጭብጨባቸው አጸደቁላቸው። ሳይገባቸው ነገሮች እንዲወሰን የሚያደርጉ ሁሉ ታሪክ በኃላ በአጨብጫቢነታቸው እንደሚዘክራቸው ሊያውቁት ይገባል። ህዝቡም የማያውቀው ራእይ ይነገረው ጀመረ። አዲሱ ንጉሳችን  የንግስናው ወንበር በጭንቀት ይሁን በኑዛዜ አልያም በራእይ  ታይቶላቸው ወይም ግራ  ገብቷአቸው ንግስናውን እንዴት  እንደተሰጣቸው ባይገባንም ቅሉ  ብቻ አዲሱ ንጉሳችን  ንግግራቸውን ሲጀምሩ እንዲ አሉ። የቀድሞ ንጉሳችንን ራእይ እናስፈጽማለን። ይሄንን ቃል ደግመው ደጋግመው ይነግሩናል። በመቀጠልም በመቀባበል በተለያዩ ሚዲያዎች እና አጋጣሚዎች የቀድሞ ንጉሳችንን ራእይ እናስፈጽማለን ይሉ ጀመር የአዳራሹ ታዳሚዎች። ራእዩን ያዩትም ሳይነግሩን ሄዱ ራእዩም የተነገራቸው የድግሱ ታዳሚዎችም ስለራእዩ ምንነት ሳይገልጹልን ራእዩን  ለማስፈጸም እሩጫ ሆነ። ለህዝባችን ይፋ ሆኖ ያልተነገረው ራእይ ምን ይሆን?

በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ብዙ ጥያቄዎች ተነሱ ጥያቄዎች በሙሉ በሚያለያይ እና ተቀባይነት በሌለው መልኩ በኃይል ተፈጻሚ ሆኑ። ገዳማዊያን ሳይቀሩ አለም በቃኝ ብለው አፈር ምሰው ጤዛ ልሰው ቅጠል በጥሰው ድንጋይ ተንተርሰው እግዚአብሔር በማመስገን የሚኖሩት ገዳማዊ አባቶች የግፍ በትር አረፈባቸው ታላቅ ተንኮል ተሰርቶባቸው በማያውቁት ነገር ባህታቸው ድረስ ሄደው ገፏቸው ደበደቧቸው። ይሄ ቦታ የናንተ አይደለም  ልቀቁ ተብለው ተዘባበቱባቸው እውን በቤተ ክርስቲያን እና አለም በቃኝ ባሉት አባቶች ላይ የግፍ በትር ማሳረፍ እና ቤተክርስትያንን ማፍረስ ይሆን ራእዩ?

በእስልምና እምነት ላይ ብዙ ሴራ ተሰራ የእምነት መሪያቸውን እንዳይመርጡ የመለያየት ስራ ተደረገ ይመሩናል ያሉትን ትተው ያላሰቡት መሪ ሆኖ በግዳጅ ተጫነባቸው። የለም መሪዎቻችንን እኛ እንምረጥ ባሉት ህዝብ ላይና ጥያቄ ያነሱትን በሙሉ የግፍ በትር ያርፍባቸው ጀመረ። ድምጻችንን ስሙን መሪዎቻችንን እኛው እንምረጥ ያሉትን ህዝብ ላይ ጥያቄውን ከመመለስ ይልቅ የሃይል ዱላ ያሳረፉና  ያሰቃዩ ቀጠሉ።  እስልምናን መከፋፈል  ይሆን እንዴ ራእዩ?

ነጻነት… ነጻነት… ነጻነት… ዲሞክራሲ… ዲሞክራሲ… ዲሞክራሲ…. ፍትህ… ፍትህ…. ፍትህ… ብለው በተናገሩት ነጻ ሰዎች ላይ ቤተሰባቸውን ማሰቃየት ከስራ ገበታቸው ማባረር የመሰብሰቢያ  ቢሮአቸውን በሃይል መዝጋት ስቃይና እንግልት መጫን። ምን አልባትስ   በነጻተት የሚናገር ህዝን እንዳይኖ ስለነጻነቱ የሚቆም ትውልድ እንዳይኖር  ይሆን ራእዩ?

ወንድም ከወንድሙ አጠላልፎ ገንዘብ አምላኪ አድርጎ ትውልዱን መቅረጽ ለምን ተፈለገ?። ስለ ጥቅሙ እንጂ ስለ አገር ክብር ስለ ወገን በደል እንዳያስብ ተደርጎ ያስተምሩታል እንጂ  ወደፊት  አገሩ ከዚህ ትውልድ ብዙ ነገር እንደምትጠብቅ እና ሃላፊነት እንዳለበት  እንዲነገረው ያልተፈለገበት ምን ይሆን ምስጢሩ? የወገን ፍቅር፣ ያገር ፍቅር፣ ከልቡ እንዲወጣ እና እንዳይሳልበት ተደርጎ ትውልድን ማስተማር የድግሱ ታዳሚዎች ምን ይሆን የሚያመጣላቸው ጥቅም? ። አንዱን ሃይማኖት ከሌላው ሃይማኖት ጋር የማጋጨት ስራን መስራት፣  በዘር፣ በጎሳ፣ በብሔር፣ እንዲጠላለፍ ሴራ ማሴር ትርፋቸው ምን ይሆን? ሲሻቸው ማሰር፣ ሲሻቸው ማሰቃየት፣ ሲሻቸው መግደል፣ ባጠቃላይ ህዝብ በሁሉም አቅጣጫ ሲበላላ፣ ሲጠጣላ፣ እና ሲሰቃይ ማየት   ድንገት ይሄ ይሆን እንዴ ራእዩ?

ጥቂቶች ተፈርተው ብዙሃኖቹ ተሸማቀው ማኖር ይሆን ሃሳባቸው። ጥቂቶች ባለስልጣን ሆነው ህዝቡ ለባለስልጣኑ ተገዢ ማድረግ ይሆን እቅዳቸው። ጥቂቶች ሃብታም አድርጎ ብዙኃኑን አደህይቶ የጥቂቶቹን እጅ ጠባቂ ማድረግ ይሆን ፍላጎታቸው። ጥቂቶች ፈላጭ ቆራጭ ህዝብ ግን ተፈላጭ ተቆራጭ እንዲሆን ማድረግ ይሆን ትግላቸው። አገር የቤተሰብ መምሪያ እስከሚመስል ድረስ በአንድ ጎጥ መያዝ ይሆን ራእያቸው?

እንዲህ እንዲህ እያልኩኝ ሃሳቤን የማወርደው ራእዩን ያዩት ባለራእዩ መሪ ራእያቸውን ሳያሳውቁን ስለሄዱ  ነው። ራእዩም የተነገራቸው የድግሱ ታዳሚዎች የአዳራሹ ስብስቦች ምን እንደሆነ ባልነገሩን እና ባላሳወቁን ራእዩን አስፈጻሚ እንደሆኑ  ደጋግመው ይነግሩን  ስለጀመሩ ነው። ታዲያ እየተፈጸሙ ያሉት እነዚህ እና እነዚህን  የመሳሰሉ ናቸው። ንጉሱ ያዩት ራእይ ለህዝቡ ሳይነግሩ ለምን ሄዱ?  ወይስ ጥሩ አማካሪ አልያም ጥሩ ወዳጅ አልነበራቸው ይሆን? ጥሩ አማካሪ አልያም ጥሩ ወዳጅ ቢኖራቸው ያዩትን ራእይ ሊፈቱት የሚችሉ በአገሩ እንዳሉ ይነግሯቸው ነበረ። ያሉት አማካሪ ጥሩ ስላልነበሩ እና የንጉሱን ህልም የሚፈቱትን የእግዚአብሔር መንፈስ ያደረባቸው የሚመጣውንም ያለፈውንም እግዚአብሔር የሚገልጥላቸው እንቆቅልሽን የሚፈቱ  በገዳም የሚኖሩትን መነኮሳት አባቶችን እንኳን አቅርቦአቸው ችግራቸውን ሊያስፈቱ ቀርቶ ገዳማቸው ድረስ ሄደው ማሰቃየትን ነው የመረጡት። ህልም ፈቺዎችን ኢማን ያላቸውን በአላህ መንገድ ያሉ ለአላህ የተገዙ ሼሆችን እያራቁ እና እያሰቃዩ መልካም ነገር መጠበቅ ከባድ ነው። ቅዱሳን አባቶችን ንጉሱ ካጠገባቸው ሊያቀርቧቸው ቀርቶ በገዳማቸው እና በመስኪዳቸው እንዳይኖሩ  ታላቅ በደል እያደረሱባቸው ራእዩ እንዴት ሊፈታ ይቻላል? ማንስ ይፍታው?።

ንጉሱ ያዩትን ራእይ አዳራሽ ውስጥ የተሰበሰቡ የኔ ናቸው ያሉአቸው እንዲበሉ የተፈቀደላቸው በሙሉ ሊፈቱት አይችሉም።  ታዲያ የንጉሱን ራእይ ማን ይፍታው? ግፍ ሲበዛ እግዚአብሔር እራሱ እንዲህ ይፈርዳል።

የእግዚአብሔር እጅ በግፈኖች እና በጨቋኞች ላይ ይወርዳል በእውነትም ፍርዱን እንዲህ ይፈርዳል።

ንጉስ ብልጣሶር ትልቅ ግብዛ አድርጎ ከመኳንቶችን ጋር ከሚስቶቹ ጋር ከእቁባቶቹ ጋር እየጠጣ እና እየጨፈረ ከእንጨት እና ከድንጋይ የተሰሩ አማልክትን ማመስገን ጀመረ። በዚህ ሰአት የሰው እጅ ጣት የንጉሱን አዳራሹን ጥሳ ገባች ግድግዳው ላይ ጽሁፍ ጻፈች። ንጉሱም የሰው ጣት በቤቱ ግድግዳ ላይ ስትጽፍ ተመለከተ። ያን ግዜ  የንጉሱ መልክ  ተለወጠ፣ ልቡ ታወከ፣ የወገቡ ጅማት ተፈታ፣ ጉልበቶቹም ተብረከረኩ።                                                                                                                     ንጉሱም አስማተኖች እና ጠቢባኖች ወደ ንጉሱ ይመጡ ዘንድ አዘዘ። ሁሉም ወደ ንጉሱ ቤት መጡ።ጽፈቱን  ያነቡና ፍችውን ይነግሩት ዘንድ ተናገረ። ይሄን ጽፈት እና ፍቺውን የነገረኝን ሐምራዊ ግምጃ  ይለብሳል በመንግስቴም ላይ ሶስተኛ ገዢ አድርጌ እሾመዋለው ብሎ ተናገረ። በግዛቱ ውስጥ ያሉት አስማተኞች፣ ጠቢባኖች ጽህፈቱን ሊያነቡት አልቻሉም ፍቺውንም ሊያውቁት አልቻሉም። የዚህን ግዜ ንጉሱ ደነገጠ ፊቱም ሲለዋወጥ ባዩት ግዜ መኳንቶቹም ደነገጡ።                                                                               በአገሩ ጥሩ መካሪ አይጥፋ ጥሩም ወዳጅ አያሳጣን ይባላል። ንግስቲቷ የንጉሱንና የመኳንቶቹን ጭንቀት አይታ እንዲህ አለች። አሳብህ  አያስቸግርህ ፊትህም አይለውጥ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ያለበት ሰው በመንግስትህ ውስጥ አለ። ማስተዋልና ጥበብ በፊቱ የሆነ እውቀቱ ከእግዚአብሔር የተሰጠው ህልምህን የመተርጎም እንቆቅልሽን የሚገልጥ የታተመውን የሚፈታ ዳንኤል የሚባል ቅዱስ አለና እርሱ ሁሉን ይነግርሃል አለችው። ንጉሱም ተጨንቆ  ስለነበረ በአስቸኳይ ይመጣ ዘንድ አዘዘ።

ዳንኤል ወደ ንጉሱ ቤት ገባ። ንጉሱም የጽህፈቱን ቃል ይፈታለት እና ይተረጉምለት ዘንድ ዳንኤልን ጠየቀው።  ንጉሱ ለዳንኤል ሲናገረው በግዛቴ ያሉትን ጠንቋዮች፣ ጠቢባኖች፣ ፈላስፎች፣ እና ሟርተኖች ጭምር የጽህፈቱት ፍቺ ሊነግሩኝ አልቻሉም። አንተ ግን ሁሉን እንደምታውቅ ተነግሮኛል ጽህፈቱን አንብበህ ከፈታህልኝ ቀይ ግምጃ አልብሼህ በግዛቴ ሶስተኛ ገዢ አድርጌ እሾምሃለው አለው።                                                 ዳንኤልም ያንተን ቀይ ግምጃ እና ሹመት አልፈልግም። ስጦታህም በሙሉ ላንተ ይሁን ነገር ግን ጽህፈቱን አንብቤ ትርጉሙን እነግርሃለው አለው።                                                                                                ጽህፈቱ እንዲህ ይላል ማኔ ቴቄል ፋሬስ የሚል ሲሆን የነገሩም ፍቺ እንዲህ ነው።

ማኔ ማለት እግዚአብሔር መንግስትህን ቆጠራት ፈጸማትም ማለት ሲሆን።

ቴቄል ማለት በሚዛን ተመዘነች ቀላም ተገኘች

ፋሬስ ማለት መንግስትህም ተከፈለች ለመዶንና ለፋርስ ሰዎች ተሰጠች ማለት ነው። ብሎ ቅዱስ ዳንኤል ቃል በቃል ፈታለት። ንጉስ ብልጣሶርም እጅግ ተደሰተ ቀይ ግምጃም አልብሶት በመንግስቱ ላይ ገዚ አድርጎ ሾመው።                                                                                                                        ትንቢተ ዳንኤል ፭(5)+፲፫-፴ (13-30)

ከ- ከተማዋቅጅራ

Email- waqjirak@yahoo.com

The post ባለ ራእዩ  መሪ ምን ይሆን ራእያቸው?። (ከ- ከተማዋ ቅጅራ) appeared first on Zehabesha Amharic.


Hiber Radio: ኢትዮጵያ ከሰሜ ኮሪያ መሳሪያ መግዛት አለመግዛቷን ምርመራ መጀመሩ; እንግሊዝ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የ4.9 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ማቋረጧ; 125 ኢትዮጵያውያን ወደሃገራቸው መላካቸው; የኢትዮጵያን የልብ ትርታ ለማድመጥ ግብፅ የአባይ ወንዝን ለመገደብ ለደቡብ ሱዳን 2 ቢሊዮን ዕርዳታ መመደቧ; ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ለመጠየቅ ቃሊቲ የሔዱ መከልከላቸውና ሌሎችም

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


ህብር ሬዲዮ የካቲት 22 ቀን 2007 ፕሮግራም
እንኳን ለ119ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሰዎ

አቶ ኦባንግ ሜቶ በህብር ሬዲዮ 5ኛ አመት እና 119ኛ የአድዋ ድል በዓል በተከበረበት ወቅት በቬጋስ ተገኝተው ያደረጉት ንግግር(ሙሉውን ያዳምጡ )

<...ኢትዮጵያውያን የአድዋን ድል ብቻ መዘከር ሳይሆን በአድዋ ሳቢያ የፋሺስቱ ጣሊያን አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ከ40 ዓመት በኋላ መቶ የጨፈጨፈበትን ንብረት የዘረፈበትንና ያወደመበትን የግፍ ድርጊት በአለም አቀፍ ደረጃ ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኝና የኢትዮጵያም ተገቢውን ካሳ እንድታገኝ የጀመርነውን ጥረት ማገዝ...የተቃውሞ ፊርማውን ...> አቶ ኪዳኔ አለማየሁ የአለም አቀፍ ፍትህ የኢትዮጵያ ጉዳይ ዋና ስራአስኪያጅ ከተናገሩት የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡ )

ስለ ፕሮስቴት ካንሰር ከዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ
አድዋ ግጥም በመርሻ አያሌው
ጣይቱ ግጥም በሐይማኖት ይመኑ

(ልዩ ዘገባ የሩሲያው የተቃውሞ መሪ መገደልና የቀሰቀሰው አለም አቀፍ ተቃውሞ)
ሌሎችም
ዜናዎቻችን:-
የእንግሊዝ መንግስት ለኢትዮጵያ አገዛዝ የሚያደርገውን የ4.9 ቢሊዮን ዶላር ዕርዳታ ማቋረጡን ገለፀ።

ኢትዮጵያ ማዕቀብ ከተጣለበት ሰሜን ኮሪያ የጦር መሳሪያ ትግዛ ወይም አትግዛ ለማጣራት የተባበሩት መንግስታት ምርመራ ጀመረ

አንድ ከፍተኛ የደቡብ አፍሪካን ዲፕሎማት ከሁለት ዓመት በፊት አዲስ አበባ ላይ ለመግደል በተጠነሰሰ ሴራ እጇ አለበት የተባለችው ሱዳን አቋሟን ገለፀች።

ግብፅ የአባይ ወንዝን ለመገደብ ለደቡብ ሱዳን 2 ቢሊዮን ዕርዳታ መደበች:: የኢትዮጵያን የልብ ትርታ ለማዳመጥ ነው ተብሏል።
የመኢአድ በተለያየ ደረጃ ያሉ ከመጭው የይስሙላ ምርጫ እራሳቸውን ማግለላቸውን ቀጥለዋል ፓርቲው በጉዳዩ ላይ የሰጠው መግለጫ የለም።

125 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከየመንና ከታንዛኒያ ወደአገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ።

የአገር ቤቱ አገዛዝ የፖለቲካ ጥገኝነት የሰጣቸው የቀድሞው የየመን ፕሬዝዳንት ቢሊየነር መሆናቸው ተጋለጠ።

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ለመጠየቅ ቃሊቲ የሔዱ ተከለከሉ። በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞችና ጦማሪያን ዛሬም የአገራቸው የነፃነት ጉዳይ እንደሚያሳስባቸው ገለፁ::

“የነፃነት ጥያቄዎች እስኪመለሱ ሙያዊ ነገሮችን ወደ ጎን ማድረግ ያስፈልጋል:
ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ።
በእስር ላይ የሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንና ጋዜጠኞች ዛሬም የአገራቸው የነፃነት ማጣት እንደሚያሳስባቸው ለጥየቃ ለሄዱ ጋዜጠኞች ገለፁ

The post Hiber Radio: ኢትዮጵያ ከሰሜ ኮሪያ መሳሪያ መግዛት አለመግዛቷን ምርመራ መጀመሩ; እንግሊዝ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የ4.9 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ማቋረጧ; 125 ኢትዮጵያውያን ወደሃገራቸው መላካቸው; የኢትዮጵያን የልብ ትርታ ለማድመጥ ግብፅ የአባይ ወንዝን ለመገደብ ለደቡብ ሱዳን 2 ቢሊዮን ዕርዳታ መመደቧ; ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ለመጠየቅ ቃሊቲ የሔዱ መከልከላቸውና ሌሎችም appeared first on Zehabesha Amharic.

ለአድዋ ድል በቀል ለኢትዮጵያ ስለሚያስፈልገው ፍትሕ -ኪዳኔ ዓለማየሁ

$
0
0

መግቢያ፤

ADWA4-600x310እ.አ.አ. በየካቲት 1896 ባልተጠበቀና እጅግ አስገራሚ በሆነ መንገድ፤ ኢትዮጵያ፤ እስከዚያ ድረስ በየትኛውም ኣሕጉር ተደርጎ የማይታወቀውን፤ አንድ በመልማት ላይ ያለች ሐገር፤ የአንድ ጠንካራ የሆነ የአውሮፓ መንግሥትን፤ የኢጣልያን የጦር ወረራ በድል የተወጣች መሆኑ ለምን ጊዜም ቢሆን በውጭ ጠላት የማትበገር፤ የነጻነት ጮራ ሐገር መሆኗን አረጋግጦላታል። ስለዚህ ታሪካዊ አኩሪ ድል፤ ብዙ ተጽፏል፤ የአድዋ ክብረ-በዓል በሚዘከርበት ጊዜም፤ ዝርዝር ታሪኩና አንድምታው በሰፊው ይነገራል፤ ይጻፋል። የዚህ ጽሑፍ ትኩረት ግን፤ በመጀመሪያ፤ የአድዋው ጦርነት ዋናው መንሰኤ ኢጣልያ ኢትዮጵያን የቅኝ ግዛቷ ለማድረግ የነበራት አጉል ምኞት ቢሆንም፤ የቀሰቀሰው አንደኛው ምክንያት የትርጉም ጠንቅ የነበረበት የውጫሌው ውል ስለ ነበር፤ ውሉ በአጼ ምኒልክና በኢጣልያኑ ተወካይ በአንቶኒሊ እንደ ተፈረመ፤ ወዲያውኑ በራስ መኮንን የተመራ አንድ የልዑካን ቡድን ወደ ኢጣልያ ተጉዞ ስለ ፈጸመው ጠቃሚ የዲፕሎማሲ ተግባር፤ ሁለተኛም አድዋ ላይ ለተከናነበችው እጅግ አሳፋሪ ሽንፈት፤ ኢጣልያ 40 ዓመት ሙሉ ጠብቃና ተዘጋጅታ፤ በቫቲካን ያልተቆጠበ ድጋፍ፤ በኢትዮጵያ ላይ ስለ ፈጸመችው አሰቃቂ የበቀል የጦር ወንጀል፤ ዳግመኛ ድል ብትነሳም፤ ለኢትዮጵያ ተገቢ የሆነ ፍትሕ ስለ አለመገኘቱና በመኪያሔድ ላይ ስላለው ትግል አጭር ዘገባ ይቀርባል።

[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

The post ለአድዋ ድል በቀል ለኢትዮጵያ ስለሚያስፈልገው ፍትሕ -ኪዳኔ ዓለማየሁ appeared first on Zehabesha Amharic.

አበበ ገላው የዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን የ20 ሚሊዮን ዶላር ቅጥፈት አጋለጠ

$
0
0

dr_tedros_adhanom
ቴድሮስ አድሃኖም ያራገቡት የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት የፈጠራ ወሬ መሆኑ ተረጋገጠ * የአውስትራሊያ መንግስት እና የሮተሪ ፋውንዴሽን በሪቱ ጃለታን አናውቃትም ገንዘብም አልሰጠንም አሉ

በአበበ ገላው

(አዲስ ቮይስ) ሰሞኑን የህወሃት መራሹ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በአንድ የአውስትራሊያ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ውድድር አሸናፊ በመሆን እና አስደናቂ ውጤት በማምስመዝገብ 20 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር በማሸነፍ ያገኘችውን ገንዘብ ለልማት ለማዋል ኢትዮጵያ ትገኛለች የተባለችን የ14 አመት ልጅ በመገናኛ ብዙሃን እና በማህበራዊ ድረ ገጾች ከማስተዋወቅ አልፈው በቢሯቸው ከልጅቷ ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል።

ሚኒስትሩ በሪቱ ጃለታ አህመድ ገና በለጋ እድሜዋ ይህን ያህል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለልማት በማዋሏ ለኢትዮጵያዊያን በተለይ ደግሞ ለዲያስፖራው አርአያ መሆኗን በይፋ አውጀው ነበር። ወጣቷ የሽልማት ገንዘቡን በሙሉ አባቷ አቶ ጃለታ አህመድ በተወለዱበት በምስራቅ ሀረርጌ፣ ጋራ ሙለታ፣ ትምህርት ቤት ልታሰራበት ማቀዷን ለጋዜጠኞች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተገኝታ ከሚኒስትሩ ጋር በጋራ በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋ ያደረገች ሲሆን ገንዘቡ የተገኘው ከፊሉ ከአውስትራሊያ መንግስት፣ ከፊሉ ደግሞ ከአውስትራሊያ የሮተሪ ክለብ መሆኑን ይፋ አድርጋ ነበር።
tewedros
ይሁንና ሸልማቱን አዘጋጀ የተባለው ባደን ፓወል ኮሌጅ በመባል የሚጠራው የመንግስት ትምህርት ቤት ስለጉዳዩ ምንም የሚያውቀው ነገር ባለመኖሩ ግራ በመጋባት ጉዳዩን ለምርመራ ወደ ፖሊስ መምራቱን ለማረጋገጥ የቻልን ሲሆን የአውስታራሊያ መንግስት እና ሮታሪ ፋውንዴሽን በበኩላቸው ለአዲስ ቮይስ በተናጠል በሰጡት መግለጫ እንዳረጋገጡት ለታዳጊዋ ምንም አይነት ገንዘብ አለመስጠታቸውን እንዲሁም ስለ እርሷም ሆነ ስለተባለው ውድድርና ሽልማት ሰምተው እንደማያውቁ አረጋግጠዋል።

የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይና ንግድ ሚኒስቴር በጹሁፍ በላከልን መግለጫ አንደገለጸው የአውስትራሊያ መንግስት በኢትዮጵያ ጋራ ሙለታ ትምህርት ቤት ለማሰራት 10 ሚሊዮን ዶላር ሰጠ መባሉን አስተባብሏል። ሚኒስቴሩ አክሎም በኢትዮጵያ ለትምርት በቀጥታ ድጋፍ ባይሰጥም ኢትዮጵያ ከሌሎች ሃገሮች ጋር ተጠቃሚ በሆነችበት አለም አቀፍ የትምህርት የጋራ ትብብር (Global Education Partnership) በኩል ድጋፍ እንደሚሰጥ ጠቁሞ ኢትዮጵያ በትብብሩ በኩል በሚሰጠው የገንዘብ እርዳታ ተጠቃሚ ነች በማለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጄና ሃንድ አክለው ገልጸዋል።
Bruce Allen
በአውስትራሊያ የሮታሪ ፋውንዴሽን ስራ አስኪያጅ የሆኑት ብሩስ አለን በበኩላቸው ስለ ተሸላሚዋም ልጅም ይሁን ስለሽልማቱ ከዚህ በፊት ሰምተው እንደማያውቁ አስገንዝበው ድርጅቱ የተባለውን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ እንኳን ለልጅ ሊሰጥ ለራሱም የበጎ አድራጎት ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ በቂ ገንዘብ እንደሌለው አስረግጠው ተናግረዋል። ስራ አስኪያጁ አክለው እንደገለጹትም ባለፈው አመት የበጀት አመት ሮተሪ በ አውስትራሊያ ያሰባሰበው ገንዘብ መጠን 5.6 ብቻ መ ሆኑን ጠቁመው 10 ሚሊዮን ዶላር ለልጅቷ በሽልማት መልክ ሰጠ መባሉ በጣም የሚያሳዝን ክስተት መሆኑን ገልጸዋል። ባለፈው አመት ሮታሪ ኢንተርናሽናል በአለም አቀፍ ለትምህርት ነክ እንቅስቃሰዎች የሰጠው ገንዘብ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በቻ የበረ ሲሆን ይህም ገንዘንብ ለ66 ፕሮጄክቶች መከፋፈሉን ለማወቅ ተችሏል።

ከዚህ በፊት በአለም ላይ ተሰምቶና ታይቶ የማይታወቀውን ይህን “ታልቅ ውድድር” እና የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት አዘጋጀ የተባለው የአውስትራሊያው የመንግስት ትምህርት ቤት1800 ተማሪዮችና 180 ሰራተኞች የሚሆኑ ያለከፍያ በበጎ አቃድ የሚሰሩ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን አመታዊ በጀቱ 12 ሚልዮን የአውስትራሊያ ዶላር ነው። ይህም ማለት የትምህርት ቤቱ አመታዊ በጀት ለ14 አመቷ ልጅ ሰጠ ከተባለው ሽልማት በ8 ሚሊዮን ዶላር የሚያንስ ሲሆን የሽልማት ገንዘቡን ትምህርት ቤቱ እንዴት እንዳሟላው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም ይሁኑ ተሸላሚዋ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ማብራሪያ አልሰጡም።

ሌላው አስገራሚ ጉዳይ በሪቱ ሽልማቱን አገኝ በተባለው ያለፈው የበጀት አመት የአውስትራሊያ መንግስት በገዘብ እጦት ምክንያት ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ አገሮች የሚሰጠውን እርዳታ መጠን ከ225 ሚሊዮን በ37በመቶ በመቀነስ ወደ 133 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር በመቀነሱ በአለም አቀፍ ደረጃ ሲተች የበነረ ሲሆን የበጀት ቅነሳ ያደረገው ለልጅቷ ለመስጠት አለመሆኑን ግን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መግለጫ ለመረዳት ተችሏል።
ይሁንና ይህ ጉዳይ በዙዎች ዘንድ ሆን ተብሎ ለስውር አልማ የዋለ የህወሃት ውስብስብ ተንኮል ጋር የተያያዘ ነው በማለት ጥራጣሪያቸውን በስፋት በመግለጽ ላይ ይገኛል ።

The post አበበ ገላው የዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን የ20 ሚሊዮን ዶላር ቅጥፈት አጋለጠ appeared first on Zehabesha Amharic.

ወሬ ሲነግሩህ ሃሳብ ጨምርበት –(በእውቀቱ ስዩም)

$
0
0

Bewketu Seyoum – Hagere Mariam (Maryland) USA [Must Listen)

ምኒልክ ጥቁረቱን ክዶ ነበር የሚል ቀደዳ በፌስቡክ ሲዞር ኣየሁ ልበል?
ትልልቅ ቅጥፈቶች ጀርባ ኣንድ ትንሽ መነሻ ይኖራል፡፡
መነሻውን እንመርምር እስቲ፡፡

ያድዋ ድል ማግስት የምኒልክ ዝና የጠራቸው የውጭ ኣገር ሰዎች ኢትዮጵያን መጎብኘት ጀምረው ነበር፡፡ ከኒህ እንግዶች ኣንዱ የሄቲው ታጋይ ጋዜጠኛ ቤኒቶ ሲልቪያን ነው፡፡
ሲልቪያንና ምኒልክ ያደረጉትን ጭውውት ስኪነር የተባለ ኣሜሪካዊ ዘግቦታል፡፡
በጭውውታቸው መሀል ምኒልክ ለሄቲው ሰውየi am not a Negro I am a Caucasian ማለቱን ስኪነር ዘግቧል፡፡

ምኒልክ ኔግሮ ኣይደለሁም ብለው ከሆነ ደግ ኣደረጉ ከማለት ውጭ የምለው የለኝም፡፡ ምኒልክ ጥቁር እንጂ ኔግሮ ኣይደለም።ኔግሮ የውርደት ስም ሲሆን ጥቁር የክብር ስም ነው፡፡
ኮኬሽያን የሚለው ቃል ግን ያስተርጓሚ ስተት መሆን ኣለበት፡፡በምኒልክ ዘመን ሰዎች ዘርን ለመግለጽ የሚጠቀሙባቸው ቃላት ከብሉይና ሃዲስ የተቀዱ ናቸው፡፡የሴም ዘር የካም ዘር የያፌት ዘር ወዘተ ይሰኛሉ፡፡ ኮኬሽያን የሚለው ቃል በወዘተ ውስጥ ኣይካተትም፡፡ኮኬሽያን በጊዜው በሊቃውንቱም ሆነ በመኳንንቱ ኣንደበት የሚዘወተር ቃል ኣልነበረም፡፡

ምኒልክ የሚገዛቸው ህዝቦች ጥቁር እንደሆኑ ያምን ነበር፡፡
እንደ ኤውሮፓ ኣቆጣጠር በ1878 ለንጉስ ሊዎፖልድ በጻፈው ደብዳቤ እንዲህ ይላል፡፡
“የኦሮሞ (ቃሉ ተተክቷል) የኣማራ የሱማል መልኩ ኣንድ ነው፡፡ ሁሉም ጥቁር ነው፡፡”

ምንጭ Acta Ethiopia vol 3 Edited by Sven Rubenson page302

ምኒልክ ጥቁረቱን ከመቀበል ኣልፎ ኣፍሪካዊ ጌቶች ጋር ጥቁረትን መሰረት ያደረገ ትብብር ጠይቆ ያውቃል፡፡ለምሳሌ ከሱዳኑ የማህዲስት መሪ ጋራ ሲደራደር የተናገረውን ታሪክ ጸሃፊዎች እንዲህ መዝግበውታል፡፡
Between us there has been no war. Now we have worse enemy who will make slaves of you and me.I am black :and you are black. Unite with me”
ትርጉም፤

”ባንተናኔ መሀል ጠብ ኖሮ ኣያውቅም፡፡ሁለታችንን በባርነት ሊገዛን የተሰናዳ የከፋ ጠላት ኣለብን፡፡ እኔ ጥቁር ነኝ፡፡ ኣንተም ጥቁር ነህ፡፡ እንተባበር“
ልብ በሉ ይህንን የሚለው ምኒልክ ነው፡፡
በካሊፋውና በምኒልክ መካከል የተደረገው ይህ ታሪካዊ ልውውጥ ተመዝግቦ የተገኘው ከጥልያኑ መኮንን ከባራቴሪ ማስታወሻ ውስጥ ሲሆን በእንግሊዝኛ ተርጉማ መጽሃፏ ውስጥ የዶለችውChris Prouty ናት፡፡Empress Taitu and Menilk በተባለው መጽሀፏ ገጽ 119 ላይ ታገኙታላችሁ፡፡
በተረፈ “ወሬ ሲነግሩህ ሀሳብ ጨምርበት”የሚለውን ያባቶቻችንን ምክር በመጋበዝ ልሰናበት፡፡

The post ወሬ ሲነግሩህ ሃሳብ ጨምርበት – (በእውቀቱ ስዩም) appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: ንዴት የሚያስከትላቸውን 4 የጤና ችግሮች ይወቁ

$
0
0

Anger 2
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

1. ለድንገተኛ የልብ ሕመም ያጋልጣል
በቶሎ የሚበሳጩ እና የሚናደዱ ከሆነ ራስዎን ለድንገተኛ የልብ ሕመም እያጋለጡ እንደሆነ ሊያውቁ ይገባል፡፡
2. አሉታዊ ስሜታዊነት ሰውነትዎን ለሕመም ያጋልጣሉ
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ከ85% በላይ የሚሆኑ የበሽታ ዓይነቶች ከሚኖረን ስሜት ጋር ተያያዥነት አላቸው፡፡
3. ንዴት በውስጥዎ ማመቅ ለድንገተኛ የልብ ሕመም ተጋላጭነትዎን በ3 ዕጥፍ ይጨምራል
በሚናደዱ ጊዜ ንዴትዎን ለማብረድና መፍትሔ ለመፈለግ ራስዎን የሚዝናና እና ንዴትዎን ሊቀንስ ሰለሚችል ነገርን ያድርጉ፡፡ ይህን የማያደርጉ ከሆነ እራስዎን ለልብ ሕመም በከፍተኛ ሁኔታ ያጋልጣሉ፡፡
4. የሰውነትዎን በሽታ የመከላከል አቅም ይቀንሳል
ንዴት በሰውነትዎ ውስጥ የሚገኙ በሽታ ተከላካይ የሆኑ ሴሎች እንዲዳከሙ እና በቀላሉ በበሽታ እንዲጠቁ መንገድ ይክፍታል፡፡
ንዴት ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች እና ሌሎችንም ስለሚያስከትል ቢቻል ባይናደዱ አልያም በዕለት ተዕለት የኑሮ ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሙ እክሎችን በተረጋጋ መንፈስና ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲፈቱና ጤንነትዎን አደጋ ላይ እንዳይጥሉ ስል አመክራለሁ፡፡
ጤና ይስጥልኝ

The post Health: ንዴት የሚያስከትላቸውን 4 የጤና ችግሮች ይወቁ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live