Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

የውስጥ እንደራሴ –እንደ ህዝብ … –ሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

ሥርጉተ ሥላሴ 25.02.2015 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

676

የትውልድ ፍካቱ ሲታይ በምህረቱ – ህይወቱ።

እስትንፋስ ቅምረቱ፤ ሲሳይ ሃብትነቱ – ነብያቱ።

ዕሴት ነፍስነቱ፤ ሊቀ ሊቃውንቱ – ህዝብነቱ።

አብነት መክሊቱ – ብሩክ ቀናነቱ፤ ብላቴ – ወተቱ።

ነበር ለናቱ ድር ማገር – ቀንና ህብስቱ።

ከውስጡ ዕውነቱ። ዓናቱ –  በአንቱ።

ጥበብ ቤቷን ሳርታ – ማዱንም ሰጥታ፣

እልል ብላ ኩላ – ማጫ አማትታ፣

አፍሪካን አቅልማ – ቅኔውን አጉልታ፤

ዘሃውን – በድጓ፤ ንባቡን – በዕድማታ

ዜማውን – በዜማ፤ ጣዕሙነን – አሰርፃ – አቅንታ

ትርጉም – በሥም ሠርታ

ተክሊል – አቀዳጅታ

ከሁሉ አቃ – – አልቃ – አልቃ — በሜሮን ቀብታ!

ቃን – ሰጠችን፤ መርቃ – አድምቃ!

የኔታን ሸለመች – ሸማ አጎናጽፋ!

ምን አለ በሥጋ – ሞት ባይኖር – ሞት ባይኖር

በመኖር – በመኖር።       12.02.2015 / ቪንተርቱር/

ሳያሾልክ – ጊዜውን፤ ሳያስተጓጉል – ጸጋውን፤ ሥጦታን አብርቶ የመራ እንደ አንድ ዜጋ ወይንም ቀንጣ ፍጥረት ሳይሆን እንደ አንድ የሰከነ፣ ልበ ሙሉ ጨዋ ህዝብ ሊታይ የሚገባው የአህጉራችን ቀንድ ነበር ብላቴ ጌታ ሎሬዬት ጸጋዬ ገበረመድህን። የቅኔው ዐፄ መንፈሱ ቀናይ ነበር ለአፈሩና – ለባዕቱ። የሥነ ጥበቡ አባወራ ህሊናው ብሩህ ነበር ለሰንደቅዓላማው ለአረንጓዴ ቢጫ ቀዩ። ለተውኔት ዕድገት ዓምዱ ነበረ – ርስቱ፤ ብሄራዊ ነፃነቱ ክብረ ዘውዱ ነበር – ጉልቱ። ለቋንቋ ሥልጣኔ አንጎል ነበር ጌታዬ – የኔታ።

በጥምረት ብቃቶቹ ለአፍሪካ ጠሐይነቱ፤ ለዓለም ሙቀት ነበር የሥነ ጥበብ እጬጌው ብላቴ ጌታ ሎሬዬት ጸጋዬ ገ/መድህን። የብላቴ ጌታ ዬትንፋሾቹ ዘር ቆሞስ ነበሩ። ዘሮቹ ደግሞ የኢትዮጵያዊነት ማህተመ – ህሊና። ጠብታው ተስፋ ነበር – የማግሥት ገቨር። ተስፋውም ሀገሩ ኢትዮጵያ በነፃነት ጸንታ – ደምቃ  – በቅታ – ልቃ መታዬት ነበር የባተለበት – የውስጠ – ህትምቱ። ከቅንጣቷ ነገር እስከ ግዙፉ የሀገሩ ጠረን ድረስ ለብላቴው ትርጉማቸው፣ ንባባቸው፤ ሚስጢራቸው የድህንት ቁርባኖች ነበሩ – አልፋና ኦሜጋ። የማይገሰሱ – የማይደፈሩ – የሚያበሩ የማይሰበሩ መንፈሰ ዕሴቶች። ቀንዲል።

ባለቅኔው – ገጣሚው – ጸሐፊው፣ ሐያሲው፤ መምህሩ፤ የሰብዕዊ መብት ተሟጋቹ ብላቴ  የሚያውቀው ኢትዮጵያዊነቱንና ሰው መሆኑን ብቻ ነበር። ብላቴ የሚያወቀው የጥቁር አፈር የእማማ አፍሪካ ጥሪኝ ንጥር ውጤት መሆኑን ብቻ ነበር። ብላቴ  በኢዮጵያዊነቱ ሳያፍር፣ አንገቱን ሳይደፋ ቀና ብሎ ነበር የኖረው፤ የሐገር ሃበትነትነቱን ለአደባባይ ያበቃውም በዚህ ማህሌት ውስጥ ነበር፤ የታሪክ ማማ ነበር ለእማማ። ሥነ – ጥበብን በሁለንታናዊ ሁለመናነት ብድግ አድርጎ ያሳደገ – በትረ፤ ኢትዮጵያዊነትን ልቡ ያደረገ ህብረ ሙሴ! ኑሮው ከውስጡ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ጠረን የተቃኘ፤ ፀዳሉ ፍሉቅ – ፍሬውም ዘለቅ ነበር የአብነት ትምህርት ቤትነቱ። ዬማንነቱ ጽናጽለ ድምጸ – ደም ግባቱ ሆነ ብሄራዊ ግርማ ሞገሱ ሚዛን የማይወጣለት ዘለግ ያለ ዕድሜ ጠገብ ነበር ጎልቶ የሚታይ፣ ሁለመናው መጠነ ሰፊ፣ ባለ ብዙ ዘርፍ ትውፊተ ውርስ ነው። በብላቴ መንፈስ ውስጥ የልዩነት ጸላዬ ሰናይ ሊቀርብ አይችልም ነበር። ስለምን? የብላቴ መስቀል ኢትዮጵያ ነበረችና። ጋኔሉን ሁሉ የሚያባርርበት – የሚከካበት ጽናቱ፣ ኃይሉ፣ መድህኑ ኢትዮጵያዊነተ – መስቀሉ ነበር የሁለመናው መናገሻ – መዲናው፤ መተንፈሻ ቧንቧውም። የብላቴ ዕምነተ – ሃይማኖት ኢትዮጵያዊነት ነበርና። የብላቴ ቀለመ ጥልፉ ኢትዮጵያዊነት ብቻ። የብላቴ ባህል መሪ ኢትዮጵያዊነት ብቻ። የብላቴ ወግ ኢትዮጵያዊነት ብቻ። የብላቴ ዘር ግንድ ኢትዮጵያዊነት ብቻ። ትውፊቱም – እሱ። ምግባሩም ትውፊት፤ እሱ – በእሱ እንቁላሌ በእንቁላሌ የተሠራ የልዕልት ኢትዮጵያ የማህጸኗ ርትሃዊ ጠሐይ ብቻ ሳይሆን የማንንት – የእኛነት የብርሃን ሃዲድ መሃንዲስ ነበር።

ጋሼ ጸጋዬ እንደ አባትነቱ – አባት። እንደ መሪነቱ ቆፍጣና – መሪ። እንደ ሥጦታው የሥነ ጥበብን ህግጋትን ያከበረ – የተገበረ፤ ለህግጋቱ የተገዛ፤ ለሰው ልጆች እኩልነትና ነፃነት ታግሎ ያስተማረ – ዕውነት፤ በሰውነቱ እንደ ሰው የኖረ ብቻ ሳይሆን ሰው መሆንን ሆኖ በቁሙ የሰበከ፤ ሲያልፍም መንፈሱን በመምህርነት – በሐዋርያነት ተክሎ አፅድቆ በሥጋ የካቲት 25.2006 እ.አ.አ ልክ ዛሬን ቀን የተለዬ ታላቅ አህጉራችን ነው። ክፍለ ዘመናችን ነው።

እያንዳንዷ እርምጃው፤ የስንኞቹ ጉዞ የአኃቲነት ተዘውታሪነት ( the unit of frequency) ንድፋቸው ሆነ ንቃሳታቸ አይራገጡ – አይፈነጩ – አያዘግሙ – አይቆራርጡ – አይታበዩ – አያፈርሱ – አይጫድሩ – አይቦጫጭሩ – አያዘግሙ፤ አይለግሙ – አይድኹ፤ አይዋጉ፤ ብጥብጥ አይፈጥሩ፣ አያሯሩጡ – አያደፍጡ – አይቆጡ – አያዳሉ፤ አያሳክኩ – ትናጋ አያስደርቁ፤ ትንፋሽ ነስተው – አይነዶለደሎ፤ በዘፈቀደ አይራማዱ፤ ጠብ ጠማኝ ብለው አንባጎሮ አያስነሱ፤ አያንዘላልጡም ነበር፤ ከማዕዳችን ውስጥ እንጂ በዝንፈት ውጪውን ሳያውቁ የሰበሉ ነበሩ። ፍሬዎቹ አይጎረብጡ – አይፈልጡ – አይቆርጡ፤ – አይቀዱ – አይቦጫጭቁ፤ አያስሩ – አይቀፈድዱ፤ አያስሉም ወይንም አይሰለቹም። ይልቁንም በቅኑ ለግላጋ ጽዑም ለዛ ሰተት ብለው በትህትና ከውስጥ ለውስጥ አጋብተው ከነጩ ደም እንደ ነጩ፣ ከቀዩ ደም እንደ ቀዩ፣ ከፕላዝማው ደግሞ እንደ ፕላዝማ አብረው እንደ ተፈጠሩ ቀዶ ጥገና ሳያስፈልጋቸው ልክክ ብለው በማያዳግም ሁኔታ የራስ አካል መሆን የሚችሉ ማህተሞች ናቸው። የመንፈሱ ጭማቂዎች – ፈውስ መድህኖችና ለማዳ ሲሆኑ ለጥበቡ እራሱ የፊደል ገበታዎች ናቸው – ለዚህም ነው ጸጋዬ ቤት የሚባለው። እርግጥ ረቂቅና ጥልቅ ከመሆናቸውም በላይ አጥኑኝ የሚሉ ናቸው። በግርድፍ ወይንም በድምስስ መሄድ አይቻልባቸውም ወይንም አይጋልብባቸውም። ፍልስፍና ብቻ ሳይሆኑ ሥራዎቹ የምርምር ተግባር የመሆንን አቅም ያላቸው፤ ለወደፊቱ ትውልድ እንደ አንድ ሥርዓተ ትምህርት ተቀርፆላቸው ዜጎች የሚመረቁባቸው አቅም ናቸው። ለዚህ በህይወት እስካለን ድረስ ለቋንቋ እድገትና ብልጽግና ተስፋ ያለን፤ ለቋንቋችን ቀናይ ሰዎች ተግተን እንሠረበታለን። ለነገሩ የአማርኛ ቋንቋ ዕለተ ተንሥኤ እኮ ዘወትራዊ ሁኗል። ፋሽስትን ድል አድርጎ እራሱን ነፃ ያወጣ ቋንቋ ቢኖር አማርኛ ቋንቋ ነው። እኛን ቀደምን አንባሳደራችን – የፊደል ገበታችን። ካቴናውን ሁሉ አመድ አድርጎ በጣጥሶ እንሆ ጉብ አለ ከአናት። ጉልላት ሆነ ተናፋቂው!

የጌታ ብላቴ የመንፈስ ጭማቂዎች ልዩ፣ ከልዩ የፈለቁ በመሆናቸው ሥጋን በስተው ነዳለ ወይንም ቀዳዳ አይፈጥሩም። ወይንም አሽገው አይለጉሙም። ነፃነት የሸለሙ የፍትህ ሚዛኖች ናቸው። ምህረትን የሚያውጁ ፍትኃተ – አንባ ናቸው። ራሳቸው ነፃ የወጡ እንዲሁም ሌላውንም ከአርነት የሚታደጉ ትጉኽ አርበኞችም። ስለምን? መነሻቸው ከላቀውና ዓለምን ከፈጠረው ፈተናን አሸንፎ ከተፈጠረው ሚስጢር የተቀዱ ማንነትን የነገሡ ናቸውና። ተፈጥሯዊ ናቸው። ማስዋቢያ ደባልነት አይሻቸውም። ሲፈጠሩ ተኩለው ነው። ስክነታቸው የተንጠባጠቡ ወይንም የሚፈራገጡ ወይንም ጥገና የሚያስፈልጋቸው ጋድም ልስኖች አይደሉም። ተቀብተው የተፈጠሩ ቅብዕ – ቅዱሶች እንጂ። አንዱ እርእሥ እራሱ ብቻውን ሲሰላ ዓዋጅ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ሥነ ጹሑፍ ህገ = መንግሥት ሆኖ እናገኘዋለን።

የዬኔታው የፊደላት ምት ፍሰት፣ እንዲሁም ሐረጋማ ወጥነት ሆነ የቃላቱና የፍቺው ሂደት ትንፋሽና መንፈስ የገነት ብር አንባር ነው። በቃላቶች ደም ውስጥ ያሉ ሴሎች ሁሉ ንቁና ትጉኃንም መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ዝቅ ብለው ለማገልግል የወሰኑና የሆኑም ናቸው። የፍላጎቶቹ አቅጣጫ ሁሉ የሀገርን መኖርን፤ የነፃነትን ተፈጥሮ፤ የዜግንትን ፍሬ ነገር፤ የአብሮነትን ቃናዊ ጣዕም፤ የቀለምን ቀለማማነት ጌጣማ ትርፍ በጥንቃቄና በማስተዋል፤ እንዲሁም በአርምሞና በተደሞ የተረጎሙ ቋሚ የዝባድ ሐውልቶቻችን ናቸው። በጋሼ ጸጋዬ ቤት በሰው ልጆች ተፈጥሮ ውስጥ ደንበር፤ ወሰን፤ ክልል፤ አልተከተረም። በፍጹም። ሰው እንደ ሰው ቁሞ የሚሄደው 24 አካላቱ ተሽንሽኖ ሳይሆን እንደ ተፈጥሯቸው በሰመረ አኃቲነት መኖር ሲችሉ ስለመሆናቸው ሊቀ ሊቃውንቱ ሆኖበት – ኖሮበታል። ህይወቱ እራሱ ብቁ ሰባኪ ነበር ማለት እችላለሁ። ሥራዎቹ ማህደራቸው „ሰው መሆንን“ ብቻ ያወድሳሉ – ያነግሣሉ። ያቀስሳሉ – ይዳኛሉ። በዬኔታ ብላቴ ዕዝነ ህሊና ውስጥ „ሰው“ በባህል፤ በጎሳ፤ በኑሮ ደረጃ፤ በኃይማኖት አልተሸነሸነም። ለጋሼ ጸጋዬ እንደ ቃሉ „ሰው ማለት ፈጣሪ በአምሳሉ ባርኮና ቀድሶ፤ እንደ እራሱ አድርጎ እንዲያመሰግነው የፈጠረው የተፈጥሮ የላቀው ቅዱስ ፍጡር ነው“ ብሎ ነበር የሚያምነው።

ስለዚህ ጋሼ ጸጋዬ ዕምነቱና ፍላጎቱ፤ ስሜቱና ራዕዩ፤ አስትምህሮቱና አቅጣጫው፤ ዶግማውና ቅኖናው፤ ህልሙና ግብዕቱ መነሻቸው ሆነ መድረሻቸው „እንደ ሰው ተፈጥሮ እንደ ሰው ዬመኖርን ህግጋት የደነገጉ፤ በተመክሮ የበሰሉ ለዬዘመኑ ብሩህ ቋሚ ህገ – አምዶች ናቸው። ተቋማት። የዬኔታ ጌታ ብላቴ ወርቆች ከጓሮ ቀጭጨው የቀሩ ሳይሆኑ ይልቁንም  ዓለምን ያስደመሙ በድምቀትም ቦግ ብለው ያበሩ ጨረራማ ዘመናዊ ሞገዶች ናቸው። ሥራዎቹ በራሳቸው የተማመኑ፤ የትውልድን ኃላፊንት በብቃት የተወጡ ዕጹቦች ናቸው። „የወንድ ልጅ ዕንባውን … „_ እርእሱን ብቻ ቁጭ አድርጋችሁ እዩት። ተፈጥሮን በፆታ የመረመረ፣ አዳምን ያመሳጠረ፣ የተረጎመ የዘለቀ ተግባር ነው። የሊቁ የሊወናርዱ ዳቬንቺን የአዳምና የመንፈስ ጉዞ በፈጣሪ ርቁቅ ዶግማ ያሳዬውን ሥዕል አባታችን አናገረው ሚስጢሩን። ሳይንስ – ፍለስፍና – የተፈጥሮ ሚስጢር የተገለጠለት – ኑሮን በአግባቡ ለማድመጥ የጠራ ጆሮ ያለው አድርጎ መፍጠሩን እርእሱ ብቻውን ይነግራችኋል። ከዚህ በተጨማሪ … የሊቀ ሊቃውንቱ ብላቴ ሎሬዬት ጸጋዬ ገ/መድህን ተግባራት ንዝረቱ ይሰበስባል ወደ ቤት እዩ፤ በውስጡም ኑሩ ይላል። ይጣራል፣ ውበታችሁን መርምሩና አጊጡበት፤ አላችሁ ተዝቆ የማያልቅ፤ ያልደረሳችሁበትም ከከርሰ ምድር በላይና በታች በደምና በሥጋችሁ ቅንብርና ቅምረት ዕንቁ አለና ገስግሱ ወደ ውስጥነታችሁ በጋራ ይላል፤ አታባክኑ ጸጋችሁንም በማለት አብዝተው ይመክራሉ። ውበታችሁን አቆሽሻችሁ መልከ ጥፉ አትሁኑ ይላሉ – ትንቢትም ይናገራሉ። አዎና! –  ያናግራሉ በርትሁ አንደበት ….. ልሳን አላቸውና።

…. ጋሼ ፀጋዬ የጸደቀው ሲፈጠር ነው። ስለምን „ሰውን“ መተርጎም ስለ ቻለ። አባቴ – ህገ ወንጌልን አልተላለፈም፤ ወይንም ቁራዕንን ወይንም ባህላዊ የዕምነት ሌሎች አንባዎችን። ስለዚህ እራሱ ጋሼ ፀጋዬ ህግ ነበር ማለት ይቻላል። የመኖርን ህግጋት ሠርቶልናል – በጋራ ቤታችን በኢትዮጵያ። ለዛውም እያባበለ – እያቆላመጠ –  እያስማማ – እንደ ነፋሻማ ጅረት አስክኖ እዬመራ። ሰውነት እዬደባበሱ እያከሙ በውስጥ ለውስጥ በሚጓዙት ቅኔዎቹ፤ በስንኝ – ጧፎቹ፤ በጥበብ ሐረጋማ ሥነ – ህሊናው፤ ትብስ ትብሺ ተባብለን፣ ቤት ያፈራውን በፍቅር ተካፍለን፣ ክብራችን ጠብቀን፣ በእኩልነት በአፈራችን እንኖር ዘንድ ሐዋርያነት። ተመክሮው ለብሄራዊ ነፃነታችን አደራ በይ ሳንሆን ዘብ እንቆም ዘንድ እንጂ ለጎጥ ጨረታ ቀርበን ሰብዕናችን ቀረመት እንዲውል አልነበረም ያስተማረን። የአፍሪካ አቅም እንሆን ዘንድ፤ የአለም ጉልበት እንሆን ዘንድ ነበር ዝቅ ብሎ የመከረን። የሥነ ጥበብን ሥነ – ተፈጥሮ ብርንዶ በአፋ አፋችን ሲያጎርሰን – ኢትዮጵያዊነት ዜግነታችነን ውጠን ኃይል እንሆን ዘንድ ብቻ ነው እንጂ …. መጠጊያ ጥርኝ  አፈር በባዕታችን ተነፍገን አፈር ለማኝ ወይንም በክትና በዘወትር ልጅነት ሰብዕናችን ተድጦ በግርድና በባርነት እንኖር ዘንድ አላሰተማረንም። ለህትምት የበቃውን „እሳት ወይ አባባ መድብሉን“ በማስተዋል እንደ ጸሎት መጸሐፋችን ማለት እንደ ውዳሴ ማርያም ወይንም እንደ ድርሳነ ሚኬኤል ብንመላለስበት የዬኔታ ጌታ ብላቴን ሎሬት ጸጋዬን ገ/መድህን ተፈጥሮ ሚስጢር የፍጽምናን ተፈጥሮ ማዬት እንችላለን። ሚስጢሩን ስናገኘው ዘመን ባመጣው የጥፋት ውሃ መረከብ ገብትን በመጠመድ ጊዜም አናጠፋም። በጎጥ ሱሰኝነት በሽታም ሆነ ጉንፋን አንጠቃም። ዘርም ከሥሩ አፍልሰን የእርግማን ምርተኛ ሆነ ሞርተኞች አንሆንም። ይልቁንም ወደ አትራፊ የወል ጉዳያችን በመረዳዳት – እናተኩራለን። አቅምም – አናባክንም። ልዕልት ኢትዮጵያን አብርተን በጸጋዎቿ እናሳድጋታለን። ፍቅርን – እናውቃለን። ፍቅር ማወቅ ብቻ ነው ዬአዋቂነት መለኪያው – ዬዕድሜም እንዲሁ። ፍቅር መኖርን ብቻ ሳይሆን ዘመንን ሆነ ወቅትን እንደ ባህሬው ያኖራል። ፍቅር ለሀገር ልዑላዊነት ኤዶሙ ነው።

እንደ እኔ መጠመድ ከሌላ ሥራ ይሠራል – መኖርም ይኖራል። ተጽዕኖን በግል የሚጫኑ ወይንም በሌላው የሚጥሉ ቢታቀቡ የነፃነት ፊደል በመንፈስ ተቆጠረ ማለት ነው። ነገር ግን እንደሚታዬው ከሆነ በብዙ ሁኔታ ሰው እራሱን አስሮታል። ገድቦታል። ሌላውንም ለማሰርም ይንደፋደፋል። ስለምን? ከሰው ምክንያታዊ ተፈጥሮ ዝንፍ ስለሚል። አልፎ ተርፎም ዬእያንዳንዱ የሰው ልጆች እንቅስቃሴ እዬጎረጎረ ሰላምንና ነፃነትን ይነስታል። ይህ ድርጊት ተነሳቹን ወይንም ተጠቂውን ብቻ ሳይሆን የነሳቹን ወይንም የአጥቂውን ኩርማ መንፈስም ያውካል። ስለምን? እኩይ ተግባር መንፈሱ እራሱ እውክና ተራጋጭ ነውና። ስለሆነም በግራ ቀኙ በኩል ዬነፃነት ጥርኝ ለማኝ ይሆናል ማለት ነው። ውቅያኖሶች ሲቀዝፉ በነፃነት ነው። ነፋስም ሲዳንስ እንዲሁ። ወፎችም በባንዳቸው ሲዘምሩ በመሰሉ። ብርሃን ሲጨፍርም – በነፃነት። ሰውም እንዲህ እንዲሆን ነበር የተፈጠረው፤ ቢያንስ በእጁ ባለው ነገር ላይ እንዲወስን – አንዲሆነውም። በሌላውም ላይ እራፊ ግፊያ እንዳያደርግም። ግን የሚታዬው በተቃራኒው ነው። መቅዘፊውን መንፈስ በመስበር በጠባቡ ጉሮኖ ውስጥ ገብቶ አዬር ማጣት፣ ማሳጣትም – በፈቃድ። ስለምን? – አላውቅም። ሰው ወዶ እንዴት ያለተገደበውን ነፃነት እራሱ ግድብ ይሠራለታል? በሌላው ላይስ ለምን? አንድ ጥብቆ ክፍል ከስድስት ወይንም ከሰባት ቢከፈል መግቢያ ሊኖረው ይችላል ይሆናል። ማኖር ግን አይችልም። ቢያንስ የጋሼ ጸጋዬ አድናቂዎች፤ አክባሪዎች፤ ወዳጆች፤ ፈለጉን የተከተሉ፤ ሥሙን የሚያነሱ፣ አብነቱን ለመከተል የቆረጡ፤ የሚዘምሩለት ሆነ የሚያዜሙለት በእሱ መንፈስ – እሱ ባለፈበት ህይወት ውስጥ እራሳቸውን መለካት ያለባቸው ይመስለኛል። እኔንም ጨምሮ። ትክክል በልኩ ወይንስ ዝቅ …. ?

ክወና። የቅኔውን ልዑል የኔታ ብላቴ ጌታ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህንን በሥጋ መለዬቱን ስናስበው – ውስጣችን የሚሰማነን የከሰለ ሃዘን የሚክስልን መፍቻው አንድ ነው። ብቸኛው ፈውስ እሱ በቀዬሰው የፓን አፍሪካዊነት – ኢትዮጵያዊነት መንፈስ ለመኖር ቆርጦ መወስን ስንችል ብቻ ነው። እሱ በኖረበት እርግጠኛ ማንነት ውስጥ መኖር ስንችል ነው። ከህይወቱ ሆነ ከምግባሩ ለመማር ልቧችንና ህሊናችን ስንከፍት ነው። በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ብሩህ ሰንደቅ ዓላማችን ሥር ስንሰባሰብ። በመንፈሰም በአካልም።

ስለሆነም የአባትን አቋምን መቀበሉ ሳይሆን ፍሬ ነገሩ በውስጡ አለሁ የለሁም? ብሎ መፈታተን ያስፈልግ ይመስለኛል። የኔ ክብር፣ የእኔ ሃይማኖት አባትዓለም ነፍስህን አርያም ገነት ያኑርልን አምላካችን። አሜን! በተረፈ የፊታችን ሃሙስ በ26.02.2015 እ.ኤ.አ የመንፈሱ ውደሳ – በሥሙ በተሰዬመው የማስታወሻ ድምጸ ራዲዮ Radio Tsegaye  or www.lora.ch.tsegaye or www.tsegaye.ethio.info Aktuell Radio Sendung ላይ ልዩ ዝግጅት ይኖራል – በሁለት ጉዳይ። በምንና ምን? አዬር ላይ ከ15 – 16 ሰዓት ስንገናኝ ወይንም አርኬቡ ላይ በማግሥቱ ጊዜው ከኖረዎት ገብተው ሲያደምጡት ያገኙታል። አክብሮቱንም – ፍቅሩንም – ስስቱም – ናፍቆቱንም ሁሉንም በዘንካታ ትህትና ሰጥቼ ልሰናበት ወደድኩኝ። ነገ ሌላ ቀን ነውና በቀጣዩ በአዲስ ጉዳይ እስክንገናኝ ድረስ መኖሩ ከተገኘ ማለቴ ነው የእኔ ክብሮችና ማዕረጎቼ ደህና ሰንብቱልኝ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ ዘሃበሻ ማህበራዊ ድህረ ገፅ – እጅግ አመሰግናለሁ።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/13104

http://ethio.info/tsegaye/February2009/TESFA-ELEGY-FOR-TSEGAYE-GEBRE-MEDHINE.pdf

ጋሼ ጸጋዬ ለእኔ እንደ ህዝብ ሊታይ የሚገባው የወስጥም እንደራሴ! ስለምን? የመንፈሱ ሥነ – ፍላጎት ማህጸን ህዋስ ህዝብ ነውና! ሴሉ ደግሞ ዜግነተ – ኢትዮጵያዊነት! ክብር!

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ

The post የውስጥ እንደራሴ – እንደ ህዝብ … – ሥርጉተ ሥላሴ appeared first on Zehabesha Amharic.


ሕወሃትና ሕግ ጠበኞች ናቸው –ግርማ ካሳ

$
0
0

የሚከተሉት በቀጥታ ከኢትዮጵያ ሕገ መንግስት የተወሰዱ ናቸው።

አንቀጽ 20፣ ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2

«ማንኛውም ሰው ያለምንም ጣልቃ ገብነት የመሰለዉን አመለካከት ለመያዝ ይችላል።

tplf-rotten-apple-245x300ማንኛውም ሰው ያለምንም ጣልቃ ገብነት ሐሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው። ይህ ነጻነት በሀገር ዉስጥም ሆነ ከሀገር ዉጭ  ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሁፍ ወይም በሕትመት፣ በሥነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማናኝዉም የማሰራጫ ዘዴ፣ ማንኛዉንም ዓይነት መረጃና ሐሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነጻነቶችን ያካትታል»

አንቀጽ 38 ንዑስ አንቀጽ ሐ

«ማንኛዉም ኢትዮጵያዉ ዜጋ፣ በቀለም፣ በዘር፣ በብሄር. በብሄረሰብ፣ በጾታ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ ወይም በሌላ አመለካከት ወይም በሌላ አቋም ላይ የተመሰረተ ልዩነት ሳይደረግበት በማናቸዉም የመንግስት ደረጃ በየጊዜው በሚካሄድ ምርጫ የመምረጥና የመመረጥ»

በርካታ የህወሃት ባለስልጣናትና ካድሬዎች ስለ ሕግ እየደጋገሙ ያወራሉ። ስለ ሕግ፣ ስለ ሕግ መንግስቱ የሚደረገዉን ዉይይት አንፈራም። በአንቀጽ 20 መሰረት፣ «ስለሚያገባን እንጦምራለን»  በድብቅ ሳይሆን በሶሻል ሜዲያው፣ ድብቅ ስም ይዘው ሳይሆን እናት አባቶቻቸው የሰጧቸውን ስም ይዘው፣ ፎቶዋቸውን ለጥፈው በይፋ አስተያየቶችን የሰጡ፣ የጦመሩ፣ ዞን ዘጠኞች ለምን ታሰሩ ? ብእር አንስተው በይፋ የጻፉ እነ ርዮት አለሙ፣ እስክንድር ነጋ፣ ዉብሸት ታዬ፣ ተመስገን ደሳለኝ የመሳሰሉት ለምን ታሰሩ ? አንቀጽ 20 «ማናቸውንም» የሚል ቃላት አካቶ የለም ወይ ? እስቲ ይመለስልን !!!

አንቀጽ 38 ማንኛውም ዜጋ የመምረጥና የመመረጥ መብት አለው። ታዲያ ከ200 በላይ የሰማያዊ ፓርቲ ተወካዮች ተመራጭ እጩ እንዳይሆኑ ለምን ተሰረዙ ? ኦሮምኛ አትናገሩም ፣ የዚያ ደርጅት አባል ነበራችሁ ፣ እጣ አልወጣላችሁም .፣ ወዘተረፈ እየተባለ ዜጎች እንዳይመረጡ መሰረዝ ሕግ መንግስቱን በአፍጢሙ መድፋት አይደለም ወይ ?

ታዲያ ህወሃት፣  ራሱ የማያከብረዉን ሕግ፣  ሌሎች እንዲያከብሩለት ለምን ይጠበቃል ? ሕግ መንግስቱን በአፍጢሙ ደፍቶት ስለ ሕግ መንግስቱ የማዉራት ምን ሞራል ኦቶሪቲ አለው ?

አገር ዉስጥ ላሉ ድርጅቶች አንዳንድ ሐሳቦች – ናኦሚን በጋሻ

ህወሃት ሕግን የማያከበር አራዊተ ስርዓት ነው።ሕግን ከማያከበር ቡድን ጋር ሕጋዊ ትግል የራሱ ጠቃሚ አስተዋጾ ቢኖረዉም ዘልቆ አይሄድም። ታዲያ አገር ቤት ያሉ ሰላማዊና ሕጋዊ የፖለቲካ ድርጅቶች ምንድን ነው ማድረግ ያለባቸው ? አንዳንድ ሐሳቦችን ላስቀምጥ፡

  1. በአቶ በላይ የሚመራው የአንድነት ፓርቲ ፣ እውቅናውን ለተለጣፊው ቡድን ቢሰጥበትም፣ በብሄራዊ ምክር ቤት አመራር አባላት አዝማችነት፣ አብዛኞቹ የአንድነት አባላት ከሰማያዊ ወንድሞቻቸው ጋር ትግሉን ቀጥለዋል። ይሄ በስፋት ቢቀጥል ጥሩ ነው።
  2. የአንድነት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የተወሰኑቱ፣ ንብረት ( እንደ ማተሚያ ማሽን የመሳሰሉት) ለማስመለስና በፓርቲው ላይ የተወሰደውን እርምጃ ሕገ ወጥ መሆኑን በመከራከር ወደ ፍርድ ቤት ሄደዋል። ፍርድ ቤቱ ምን ሊወስን እንደሚችል ቢታወቅም፣ እስከ መጨረሻ ተቋማትን በመፈተሽ የበለጣ ማጋለጡ ጠቃሚ ነው።
  3. የማታ ማታ የአንድነት ሕጋዊ እውቃና በፍርድ ቤት ዉሳኔ ተመለሰም አልተመለስም ሰማያዊና አንድነት እሣት በተነሳ ጊዜ በተግባር እንደተዋሃዱት፣ ቀጣዩ ትግላቸውንም ፣ መኢአድና የትብብሩ ሌሎች ድርጅቶችን በማሰባሰብ መቀጠሉ ትልቅ ትኩረት ሊሰጥበት ይገባል። አንድ ጠንካራ ኃይል ይዘው መዉጣት አለባቸው።
  4. ከመድረክ ጋር በጋራ ጉዳዮች አብሮ የሚሰራበት መንገድ መመቻቸት አለበት።
  5. ከጥቂት ወራት በኋላ የሚደረገውን ምርጫ ሰማያዊና መድረክ ቦይኮት እንደሚያደረጉት በመገልጽ ምርጫው እንዲራዘም በጋራ ቢጠየቁ ጥሩ ነው። መኢአድ ምርጫዉን ቦይኮት ሊያደርግ እንደሚችል ይጠበቃል። በነ አቶ በላይ የሚመራው አንድነት፣ መኢአድ ፣ ሰማያዊና መድረክ በምርጫ ቦርድ ሕገ ወጥ የሆኑ እርምጃዎች እንደተወሰዱ የሚያሳዩ ሰነዶችን በማቅረብ ( በጣም ብዙ አሉ) ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ቢወስዱ ጥሩ ነው። ፍርድ ቤቱ ምርጫዉን ማራዘም ይችላል።  ምርጫው እንዲራዘምም የዲፕሎማሲ ግፊት ማድረግ ይኖርባቸዋል።

ከዚህ ዉጭ አገር ቤት ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያደርጉት ነገር አይኖርም። ወደ ምርጫው ገብተው ጥቂት የፓርላማ ወንበር ሊያገኙ ይችላሉ። ሆኖም ከዚያ ምንም ሊገኝ እንደማይችል መቼም እነ ዶር መራራ፣ ዶር በየነ በሚገባ ያወቁታል። ምርጫው ካልተራዘመና አዲስ ምርጫ ቦርድ ካልመጣ የሚያመጣው ዉጤት አይኖርም። ምርጫውን ይርሱት !!!! ከዚህ በኋላ ምርጫ ፣ ምርጫ ቢሉ የበለጠ ህዝብ ይታዘባቸዋል። በዚህ ምርጫም ተጨባጭ ነገር ካላስገኙ ይቅርታ አይደረግላቸውም። ያስቡበት እላለሁ።

በመጨረሻ አንድ በጣም ትልቅ ነገር ልናገር። ሕዝቡ በሚያደርጋቸው ሕገ ወጥ ግን ሰላማዊ የእምቢተኝነት ትግል፣ ወይንም አገዛዙ በዉስጡ ባለው ችግር መፈረካከስ ካጋጠመው፣ አገሪቷ ወደ ቀዉስ ልትሄድ ትችላለች።  ጠንካራ አማራጭ የሚሆኑ ድርጅቶች በአገር ቤት ሁልጊዜ መኖር አለባቸው። በመሆኑም ተደራጅቶ መጠበቁ ጥሩ ነው።

 

The post ሕወሃትና ሕግ ጠበኞች ናቸው – ግርማ ካሳ appeared first on Zehabesha Amharic.

በአዲስ አበባ አንበሳ አውቶቡሱ መንገድ ስቶ የቤት መኪናውን ገጨ

$
0
0

anbesa bus
(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ በየቀኑ እየደረሱ ያሉ የመኪና አደጋዎች ቁጥር ከ እለት ወደ እለት እየጨመረ መሄዱ ነዋሪዎችን በከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደከተተ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ይናገራሉ:: በዚህ በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ እንኳ በጊዜው ስለመኪና አደጋዎችና ስለሚወድመው የሰው ሕይወትና ንብረት በተደጋጋሚ ጽፈናል:: አሁን ደግሞ ከአዲስ አበባ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው አራት ኪሎ የድል ሐውልት አደባባይ አካባቢ ከስድስት ኪሎ መስመር ወደ ለገሀር ይጓዝ የነበረ የአንበሳ ከተማ አውቶቡስ ባገጠመው የፍሬን ችግር ከአንድ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ የሁለቱም ተሽከርካሪ ሹፌሮች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል::

በዚህ የመኪና አደጋ በተሳፋሪዎች ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም አደጋው በፎቶ ግራፍ ላይ እንደምትመለከትት በጣም አሰቃቂ ነበር:: ከስድስት ኪሎ ከሚገኘው ቤታቸው ሃገር አማን ብለው ወደ ሥራቸው በማሽከርከር ላይ የነበሩትና ጉዳት የደረሰባቸው አቶ ግርም ጎርፉ የተባሉ ግለሰብ የአንበሳ አውቶቡሱ ድንገት መስመሩን ስቶ በመምጣት እንደገጫቸው ገልጸዋል::

The post በአዲስ አበባ አንበሳ አውቶቡሱ መንገድ ስቶ የቤት መኪናውን ገጨ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከድምፃችን ይሰማ የተላለፈ ጥሪ –“የፊታችን አርብ ታላቅ አገር አቀፍ ተቃውሞ ይኖረናል!”

$
0
0

muslim addis 3

‹‹እስር ከትግላችን አያስቆመንም!›› —– ረቡእ የካቲት 18/2007 – ድምፃችን ይሰማ

መንግስት ህገ መንግስታዊ መብቶቻችንን በመጣስ ላለፉት ሶስት ዓመታት ከፍተኛ በደል ሲፈጽምብን ቆይቷል፡፡ እኛም እንደህዝብ ድምጻችንን አዋሕደን እና በአንድነት ቆመን ሰላማዊ ትግል ስናካሂድ ቆይተናል፡፡ ትግላችን እስካሁን አንድም ከሰላማዊነት መርህ ዝንፍ ሳይል የቆጠለ ሲሆን መንግስት ትግሉን ለማስቆም የሚወስዳቸው ግልብ እና አገር አጥፊ እርምጃዎችም ከመርሃችን ሊያዛንፉን እንደማይችሉ በተደጋጋሚ በተግባር ለማረጋገጥ ችለናል፡፡

ሰሞኑን መንግስት በተለመደው ግፍ መር እርምጃው በርካታ ሙስሊም ወንድምና እህቶችን በማሰር ዘመቻ ላይ ተጠምዷል፡፡ አንዳችም ጥፋት ያልፈጸሙ ወጣቶችንም የ28 ቀን የፍርድ ቤት ቀጠሮ በመጠየቅ ወደማጎሪያ ካምፖቹ አስገብቷል፡፡ ይህ ‹‹ሙስሊሞችን በማሰር ከትግላቸው አስቆማለሁ!›› ከሚል መናኛ ቀቢጸ ተስፋ እና ባዶ ምኞት የመነጨ ለመሆኑ እማኝ መጥራት አያሻም – ካሁን ቀደምም መንግስት ሲፈጽመው የቆየው፣ ግና ሊያሳካቸው ያልቻለው ህልሙ ነውና!

አዎን! ደጋግመን ስናሳይ እንደቆየነው ሁሉ ህዝብን ማንገላታት አንጂ ማሸነፍ ፈጽሞ የሚቻል አይደለም! ህዝብ ምንጊዜም አሸናፊ ነው! በአላህ ፈቃድ ያሸንፋልም! ይህን ህገወጥ እና ሊሳካ የማይችል እኩይ የመንግስት ምኞት በተለያዩ ስልቶች መታገል የነፍስ ወከፍ ሐላፊነታችን የሚሆነውም ለዚሁ እንጂ ለሌላ አይደለም፡፡ በመሆኑም ከነገ ወዲያ አርብ የካቲት 20/2007 መላው አገሪቱን ያሳተፈ ታላቅ አገር አቀፍ ተቃውሞ ይኖረናል፡፡ የተቃውሞውን መርሃ ግብር አስመልክቶ በነገው እለት የምናሳውቅ በመሆኑ እስከዚያው መረጃውን ላልደረሳቸው ሁሉ በማዳረስ ተዘጋጅተን እንጠብቅ፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና!

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ! አላሁ አክበር!

The post ከድምፃችን ይሰማ የተላለፈ ጥሪ – “የፊታችን አርብ ታላቅ አገር አቀፍ ተቃውሞ ይኖረናል!” appeared first on Zehabesha Amharic.

“የህወሓት 40ኛ ዓመት በዓል የጨረሻው በዓል እንዲሆን ተባብረን ሕወሓትን እንቅበር”–የአርበኞች ግንቦት 7

$
0
0

የአርበኞች ግንቦት 7 ወቅታዊ ጽሑፍ:

ድግሶችን፣ ወታደራዊ ሰልፎችንና ሀውልቶችን ማብዛት የአባገነኖች ሁሉ የጋራ ባህርይ ነው። ዘረኛውና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝም በሕዝብ እየተጠላ፣ እያረጀና እየወላለቀ በሄደ መጠን በየተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ደግሶ መብላት፤ ወታደራዊ ሰልፍና የመሣሪያ ጋጋታ ማሳየት እና በየመንደሩ ሀውልት መመረቅ ሙያው አድርጎት ቆይቷል።
arbegnoch ginbot 7
የህወሓት ድግሶችና ፌሽታዎች የአገራችን ሀብት ከማሟጠጣቸውም በላይ የመንግሥት ሠራተኞችን፣ የአርሶ አደሮችንና የአነስተኛ ነጋዴዎችን ኪስ እያራቆቱ ናቸው። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች በእስር ቤቶች እየማቀቁ በሚገኙበት ሁኔታ፤ በመቶ ሺዎች የሚገመቱ የአማራ አርሶአደሮች ተፈናቅለው እያለ፤ በጋምቤላና በኦጋዴን ወገኖቻችን ላይ ዘግናኝ የጅምላ ጭፍጨፋዎች እየተደረጉ፤ በአፋር፣ በሲዳማ፣ በቦረና፣ በወልቃይት እና በመላው ኢትዮጵያ ግጭቶች በበዙበት፤ ሕዝብ እያለቀሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት “የብሔር፣ ብሔረሰቦች መብት ተከበረ” እያሉ እነዚህኑ በደል እየደረሰባቸው ያሉ ዜጎችን ማስጨፈር እና ለእነዚህ ጭፈራዎች በርካታ ሚሊዮኖች ብር ማውጣት በእጅጉ ያስቆጫል። እነዚህ ጭፈራዎች ለህወሓት ሰዎች የገቢ ምንጮች መሆናቸው ጥርጥር የለውም፤ ለድሀው ኢትዮጵያዊ ግን መራቆቻዎች ናቸው። ከዚህም አልፎ በዘረኝነት እየተበደለ ያለ ሕዝብ ስለእኩልነት ዝፈን ማለት ክብረ ነክ ተግባር ነው። ዘንድሮ በአሶሳ የተደረገው አገር አቀፍ ድግስ ካለቀ ጥቂት ወራት በኋላ አገራችን በሌላ ዙር የህወሓቶች ድግስ ተወጥራለች።

ሰሞኑን በባህር ዳር በተደረገው የጦር ሠራዊት ሰልፍ እና ሰልፉን ተከትሎ በነበረው የድግሶች ግርግር ከሁሉም በላይ የተሰደበውና የተዋረደው የሠራዊቱ አባል ነው። አዛዦቹ መቶ በመቶ የህወሓት አባላት የሆኑበትን ሠራዊት “የኢትዮጵያ መከላከያ” ተብሎ መጠራቱ ራሱ የሚያሳፍረው ኢትዮጵያዊ ወኔ በልባቸው ውስጥ እየተንቀለቀለና እልህ እየተናነቃቸው ያሉ የሠራዊቱን አባላት ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እንዴት የኢትዮጵያ ጠላቶች በሆኑ የህወሓት ካድሬዎች ይመራል? እንዴት የአስር አለቃ እንኳን ሊሆን የማይገባው የህወሓት ካድሬ “ጄኔራል” ተብሎ ኢትዮጵያዊያን ወታደሮችን እንደ ሎሌው ያዛል? እንዴት አንድ የህወሓት ሎሌ ሹመት ተሰጥቶት እየፏለለ በልምድ፣ በትምህርትና በእውቀት የሚበልጠውን ኢትዮጵያዊ ተንቆ ይዋረዳል? ይህ ቁጭትና እልህ ሠራዊቱ የዘረኛውን ህወሓት ሰልፍ አድማቂ መሆኑ የሚያከትምበት ጊዜ ይበልጥ እንዲናፍቅ የሚደረገው ነው። አልያማ ሰልፍ ያሳመረ ሠራዊት ሁሉ አሸናፊ እንዳልሆነ የታወቀ ነው። በሰልፍ ብዛትና በመሣሪያ ትዕይንት ማሸነፍ ቢቻል ኖሮ የትም አገር አምባገነኖች ባልወደቁም፤ ህወሓት ራሱን ስልጣን ላይ ባልወጣም ነበር።

የህወሓት ምሥረታ 40ኛ ዓመት ድግስም ሌላው የታሪክና የሀብት ውድመት የሚያስከትል ክስተት ነው። የካቲት 11 ቀን 1967፣ ጥቂት ኢትዮጵያዊያን እናታቸውን ኢትዮጵያን ለመግደል ያሴሩበት እና ልጆች በእናታቸው ላይ ቢላዋ የሳሉበት ዕለት በመሆኑ በሀዘንና በሱባኤ እንጂ በድግስና በጭፈራ የሚታሰብ ዕለት አይደለም። ሲነሳ ምንም ይሁን ምን ዛሬ በደረስንበት ሁኔታ ሲገመገም፣ ኢትዮጵያ በታሪኳ ውስጥ ህወሓትን የመሰለ መሠሪና አድርባይ ድርጅት ገጥሟት አያውቅም። እነሆ ዘንድሮም ይኸው አድርባይ ድርጅት የመሪዎቹን የሀብትና ዝና ረሀብ ለማስታገስ ሲል ያልነበረ ታሪክ እየፈጠረ በድግስ ስም ከድሀው ገንዘብ እየሰበሰበ ለሀብታም የህወሓት አባላትና ደጋፊዎች ያሸጋግራል። የድግሶቹ ሁሉ አዘጋጆች፣ እቃ አቅራቢዎችና ተጠቃሚዎች ራሳቸው የህወሓት መሪዎችና አሽቃባጮቻቸው ሲሆኑ ከፋዩ ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። በህወሓት ድግስ የሚባክነው የሕዝብ ሀብት ስንት ሆስፒታል ይገነባ እንደነበር ስናስብ እና ይህ ሀብት በተገቢው ቦታ ውሎ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ስም ብቻ የያዙ ዩንቨርስቲዎቻችንን ትምህርት መቅሰሚያ ማድረግ እንችል እንደነበር ስናሰላ ሀዘናችን ጥልቅ ነው። ህወሓት ለልጅ ልጆቻችን የሚተርፍ ዕዳ እየቆለለ ዳንኪራ ሲረግጥና ሲያስረግጥ ማየትና መስማት ህሊና ሊሸከመው ከሚችል በላይ ነው።

አርበኞች ግንቦት 7፡ የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በህወሓት ወታደራዊ ሰልፍ እና የመሣሪያዎች ትዕይንት የሚረበሽ ድርጅት አይደለም። ይልቁንም በሰልፉ ጨኸት የታፈነው የኢትዮጵያዊ ወታደር ጩኸት ይሰማዋል። ኢትዮጵያዊ ወታደር በአዛዦቹ ላይ ጥርሱን ነክሶ፣ ቂም አርግዞ ሰልፋቸውን እንደሚሰለፍ አርበኞች ግንቦት 7 ያውቃል። አርበኞች ግንቦት 7፣ የሠራዊቱ አባላት ውስጥ ውስጡን እየተሰቃዩ የታዘዙትን መፈፀማቸው መብቃት አለበት ይላል፤ ወይ ተቀላቀሉን፣ አሊያም እውስጡ ሆናችሁ ሥርዓቱን የማዳከም ሥራዎችን ሥሩ። በእናንተ ውርደት የዘራፊዎች፣ ሙሰኖች፣ ጎጠኞችና ዘረኞች ደረት አብጦ መታየት የለበትም።

አርበኞች ግንቦት 7፣ የዘንድሮው የህወሓት 40ኛ ዓመት በዓል የጨረሻው በዓል እንዲሆን፤ ከርሞም ተመሳሳይ አዋራጅ በዓል እንዳናከብር፤ ሠራዊቱ በዘራፊዎች ታዞ የሚሰለፍበት ውርደት እንዲያበቃ ተባብረን ህወሓትን እንቅበር ይላል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

The post “የህወሓት 40ኛ ዓመት በዓል የጨረሻው በዓል እንዲሆን ተባብረን ሕወሓትን እንቅበር” – የአርበኞች ግንቦት 7 appeared first on Zehabesha Amharic.

ብርሃኑ ተዘራ ከጃኪ ጎሲ ጋር የሠራው አነጋጋሪ ዘፈን የ1 ደቂቃ ማስታወቂያ ተለቀቀ (ይዘነዋል)

$
0
0

ባለፈው ሳምንት ዘ-ሐበሻ የላፎንቴኑ ብርሃኑ ተዘራ ከጃኪ ጎሲ ጋር በመሆን ሃገራዊ ስሜት ያለው ዘፈን መስራታቸውንና በቅርብ ቀን እንደሚለቀቅ መዘገቧ ይታወሳል:: በዚህም መሠረት ዛሬ የዚህ አነጋጋሪ ዘፈን የአንድ ደቂቃ ተቆርጦ በሶሻል ሚድያዎች ተለቋል::

ሙሉው ዘፈንን በሚቀጥለው ሳምንት በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ይጠብቁ:-

Birhanu Tezera and Jacky Gosee

The post ብርሃኑ ተዘራ ከጃኪ ጎሲ ጋር የሠራው አነጋጋሪ ዘፈን የ1 ደቂቃ ማስታወቂያ ተለቀቀ (ይዘነዋል) appeared first on Zehabesha Amharic.

ሀይለማርያም ደሳለኝ የወልቃይትን ህዝብ ለማነጋገር ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ

$
0
0

ኢሳት ዜና :-የህወሀትን 40ኛ ዓመት አክብረው ሲመለሱ እግረ መንገዳቸውን በ አማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎችን እየጎበኙ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ፤የካቲተ 16 ቀን በወልቃይት ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት የህዝቡን ተቃውሞ በመፍራት መሰረዛቸው ነዋሪውን ክፉኛ አስቆጥቷል።
H Desalegn
የወልቃይት ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የካቲት 16 ቀን ወልቃይትን እንዲጎበኙ በአካባቢው ሹመኞች መነገሩን ተከትሎ በየገጠር የሚኖረው ህዝብ ሳይቀር በመሰባሰብ እና ምሳ በማሰናዳት ሲጠባበቃቸው ቢውልም የውሀ ሽታ ሆነው ቀርተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩን በአካል አግኝቶ የአስተዳደራዊ በደል ጥያቄውን ለማቅረብ ከ8 ሺህ በላይ ህዝብ ተሰባስቦ እንደነበር የገለጹት የነዋሪዎቹ አስተባባሪዎች፤ ህዝቡ ተቃውሞውን ለመግለጽና ጥያቄ ለማቅረብ እንደተዘጋጀ የተረዱት የአካባቢው ሹመኞች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ወልቃይት እንዳይገቡ አድርገው ቅጠታ ወደ ደጀና እንደወሰዷቸው ተናግረዋል።

ይህ በመሆኑም ተሰባስቦ ሲጠባበቅ የነበረው ህዝብ በቁጣና በብስጭት ወደ ቤቱ መመለሱን የገለጹት አስተባባሪዎቹ፤ ንዴታቸውን መቆጣጠር የተሳናቸው የአካባቢው ወጣቶችም በአደባባይ የህወሀትን ባንዲራ በማቃጠል የዚያኑ እለት ለትግል ወደ በረሀ መውጣታቸውን ተናግረዋል።
ቀርቦ በማናገር እንጂ ከህዝብ በመደበቅ ወይም በመሸሽ ከችግር መሸሽ እንደማይቻል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሊረዱት ይገባል ያሉት ነዋሪዎቹ፤ አንድ የሀገር መሪ- ከህዝብ ጋር የዚህ ዓይነት ድብብቆሽ ጨዋታ ውስጥ መግባቱ እጅግ እንዳሳፈራቸውም ገልጸዋል።

<<አማራዎች ሆነን ሳለን ያለፍላጎታችን ወደ ትግራይ ክልል እንድንጠቃለል ተገደናል፣ የማንነት ጥያቄያቸን ምላሽ እንዲያገኝ ጥያቄ በማቅረባችን ለበርካታ ዓመታት ተነግረው የማያለቁ በደሎችና ግፎች እየተፈጸሙብን ነው>> የሚሉት ወልቃይቶች፤ << በቅርቡ በተደራጀ ሁኔታ በደብዳቤ ላቀረብነው አቤቱታም እስካሁን ከመንግስት ምላሽ አላገኘንም፤ መንግስት መልስ የማይሰጠን ከሆነ፤ ራሳችን መልስ ለመስጠት እንገደዳለን>፡>በማለት አስጠንቅቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የወልቃይት ህዝብ ላለማየት ተራምደውት ያለፉት አቶ ሀይለማርያም ትናንት ምሽት ከ አቶ አርከበ እቁባይና ከአማራ ክልል ርእሰ-መስተዳድር ከ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር በመሆን ኮምቦልቻ ከተማ መግባታቸው ታውቋል።

ዛሬ ጧት የኮምቦልቻ ከተማ ተማሪዎች – ለአቶ ሀይለማርያም አቀባበል ለማድረግ በሚል ከትምህርት ገበታቸው በግዳጅ መወሰዳቸውን የገለጹት ምንጮችን የከተማውም ነዋሪ በተመሳሳይ መንገድ ለ አቀባበል ተብሎ በግዳጅ እንዲወጣ መደረጉን ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማለዳ ላይ የዛሬ ዓመት የተመረቀውን የ ኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ እንደ አዲስ እንዲመርቁ ከተደረገ በሁዋላ ለአዋሽ-ኮምቦልቻ የባቡር ሀዲድ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጣቸውን የገለጹት ምንጮቹ፤ የመሰረት ድንጋይ የማኖር ፕሮግራሙ የተካሄደውም የሽህ መሀመድ ሁሴን አል አሙዲ የቆርቆሮ ፋብሪካ አጠገብ በተጣለ ዳስ ውስጥ እንደነበር አመልክተዋል።

ወደ ዳሱ እንዲገቡ የታደሙት << አዋሽ -ኮምቦልቻ ሀራ ገበያ>> የሚል መግቢያ ባጅ የተሰጣቸው የኢህአዴግ ካድሬዎች ብቻ መሆናቸውን የጠቀሱት ምንጮቹ፤ ይሁንና ከነበረው እጅግ ጥብቅ ፍተሻ አኳያ፤ ተጋባዦቹ የኢህአዴግ አባላት ሳይሆን አደገኛ ጠላት ነበር የሚመስሉት ብለዋል።

አቶ ሀይለማርያም የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጣቸውን ተከትሎ “ኢህአዴግን ምረጡ” የሚል ቅስቀሳ መደረጉን የጠቀሱት ምንጮች፤ የመሰረት ድንጋይ ሊጥሉ መጡ የተባለውም ሆነ ከአመት በፊት የተመረቀን አውሮፕላን ማረፊያ እንደ አዲስ እንዲመርቁ የተደረገውም ለምርጫው ህዝቡን ለማታለል እንደሆነ በደንብ ገብቶናል”ብለዋል።

የምንልሰውና የምንቀምሰው ባጣንበት ወቅት በባቡር ፕሮፓጋንዳ ሊያታልሉን አይችሉም ያሉት ነዋሪዎቹ፤ በትራንስፖርትም ረገድ ቀደም ሲል 1 ብር የነበረው የታክሲ ታሪፍ እስከ 3 ብር፣ 2 ብር የነበረው እስከ 6 ብር ደርሶ ህዝቡ እየተማረረ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

The post ሀይለማርያም ደሳለኝ የወልቃይትን ህዝብ ለማነጋገር ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከአንድነት ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበርና ከሰማያዊ ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበር የተሰጠ የጋራ መግለጫ

$
0
0

ANAASO Blueእንደሚታወቀው የኢህአዴግ አገዛዝ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጸረ ዲሞክራሲ አካሄዱ እየባሰበት የመጣና መሠረታዊ መብቶችን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ማፈኑን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡ በቅርቡ በአንድነትና በመኢአድ ፓርቲ ላይ አገዛዙ በሚያዝዛቸው የተቋማት ኃላፊዎች ቀጭን ትዕዛዝ የፓርቲዎቹ ሕልውና ለጥቂት ግለሰቦች ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡ ይህ ዓይነቱ ህገ-ወጥ ድርጊት መቼዉም ቢሆን ተቀባይነት አይኖረውም! ለአገራችን የሠላማዊ የስልጣን ሽግግር ከባድ መሠናክል ሊሆን እንደሚችል ሁሉም ይገነዘባል ብለን እናምናለን፡፡ የኢህአዴግ የምርጫ ቦርድ እንዲህ ዓይነቱን ክፉ ስራ ሲወስን የአገራችንን የረጅም ሠላም አይተው ሣይሆን በአገዛዙ ቁንጮ ሰዎች በመታዘዝ በተቋም ስም የሚሠሩት የማደናገር የድንቁርና ተግባራቸዉ አንድ አካል ነው ብለን እናምናለን፡፡ ማህበራችን ይህን ድርጊት እጅጉን ያወግዛል። በመሆኑም ድርጊቱን በጋራ እንቃወማለን።

በምርጫ ቦርድ ስም የተወሰነው ህገ-ወጥ ውሣኔ ምክንያት መላ የአንድነትና የመኢአድ አባላት የፖለቲካ እንቅስቃሴአቸው ተገድቧል፡፡ ይሁን እንጂ ለአገራቸው ካላቸው ፅኑ ፍቅር አኳያ ትግሉን ለማስቀጠል ከሠማያዊ ፓርቲ ጋር አብሮ ለመሥራት የአባልነት ፎርም በመሙላት ትግሉን ቀጥለዋል፡፡ ይህ ዓይነቱ የአባላት ቆራጥ ውሣኔ ሊበረታታና ሞራል ሊሰጠው የሚገባ ነው ብለን እናምናለን! እኛም በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የሁለቱ የድጋፍ ማህበራት ሙሉ በሙሉ ድጋፋችንን እንደምንሰጥ እናረጋግጣለን፡፡

ስለሆነም በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የአንድነትና የሠማያዊ የድጋፍ ማህበራት በጋራ በኮሜቴ ደረጃ ተዋቅረን በዋና ዋና ጉዳዬች ላይ ማለትም በፋይናንስ፤ በእስረኞች ጉዳይ እና በዲኘሎማሲው ዙሪያ ሙሉ በሙሉ በትብብር አብረን እየሠራን የሰማያዊ ፓርቲንና ሌሎች በሃገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን በጋራ ድጋፍ ለመስጠት ውሣኔ አሣልፈናል፡፡ በቀጣይም በጋራ የኮሚቴ ውይይቶችን እያደረግን ለሰማያዊ ፓርቲ የሚያስፈልጉ የሞራልና የማቴሪያል ርዳታ እንደምንሰጥ እናረጋግጣለን፡፡
የሰማያዊና የአንድነት ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበራት
የካቲት 19 2007 ዓ/ም

The post ከአንድነት ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበርና ከሰማያዊ ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበር የተሰጠ የጋራ መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.


ለአንድ ቀን የሚቆይ የቦይኮት ዘመቻ በድምፃችን ይሰማ ጥሪ ቀረበ

$
0
0
10920943_352316331618819_5078649879608517565_n‹‹እስር ከትግላችን አያስቆመንም!›› – ለአንድ ቀን የሚቆይ የቦይኮት ዘመቻ
ነገ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከምሽቱ 12 ሰዓት ስልካችንን እናጠፋለን!
መንግስት ሙስሊሞችን ከያሉበት በማሰር ህገ ወጥ ዘመቻ ላይ መሰማራቱን እና በህዝበ ሙስሊሙ ላይ ግፍ መፈጸሙን በመቃወም ነገ ጁሙዓ ታላቅ አገር አቀፍ ተቃውሞ እንደሚኖረን እና በዛሬው እለትም የተቃውሞው መርሃ ግብር ይፋ እንደሚሆን መገለጹ ይታወሳል፡፡በዚሁ መሰረት እነሆ የነገው አገር አቀፍ ተቃውሟችን በመጠነኛ የቦይኮት ዘመቻ (የራስን መብት በራስ ላይ የመንፈግ ተቃውሞ) የሚጀመር ይሆናል፡፡ኢትዮ ቴሌኮም ለመንግስት ከፍተኛ ትርፍ ከሚያስገኙ ካምፓኒዎች አንዱ ሲሆን
በቀን ከተጠቃሚዎች በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ገቢ ያገኛል፡፡ ሙስሊሙ
ማህበረሰብ ደግሞ የአገሪቱ ግማሽ እንደመሆኑ መጠን በአንድ ቀን ለቴሌ
የሚያስገኘው ገቢ እንዲሁ በሚሊዮን የሚቆጠር ነው፡፡ በመሆኑም የማይናቅ
ቁጥር ካለው ማህበረሰብ የሚያጣው የአንድ ቀን ገቢ ለኢትዮ ቴሌኮም
በሚሊዮን የሚቆጠር ብር አክሳሪ መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ የነገው
ቦይኮት በኢቲዮ ቴሌኮም ካምፓኒ ላይ የሚያተኩረውም ለዚህ ነው፡፡
ነገ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ ሁላችንም ስልካችንን
በመዝጋት ተቃውሟችንን እናሰማለን፡፡ አስቸኳይ ጉዳይ ካላጋጠመን በስተቀርም
ስልካችንን አንከፍትም፤ አንጠቀምምም፡፡

አስቸኳይ ጉዳይ ሲያጋጥመን ለአፍታ ስልካችንን በመክፈት ቶሎ ጉዳያችንን ፈጽመን ወዲያው እንዘጋለን፡፡
ይህንን አገር አቀፍ እና መላ አገሪቱን ያካለለ ዘመቻ ላልሰሙት ሁሉ በማሰማት ለስኬቱ የቻልነውን ሁሉ መጣር ታላቅ ተግባር ሲሆን ለዲናችን ስንል ለምንከፍለው
መስዋእትነትም ከጌታችን አላህ ዘንድ ምንዳችንን እንተሳሰባለን፡፡ አላህ ፈተናውን
እንዲያነሳልንም አጥብቀን ዱዓ እናደርጋለን፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ
አይደለምና!!!

አዎን! አንድነት ያለው ህዝብ ያሸንፋል!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!

ድምጻችን ይሰማ!

The post ለአንድ ቀን የሚቆይ የቦይኮት ዘመቻ በድምፃችን ይሰማ ጥሪ ቀረበ appeared first on Zehabesha Amharic.

የመለስ ትሩፋቶች ደራሲ ኤርሚያስ ለገሰ ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት የጻፈው ግልጽ ደብዳቤ

$
0
0

ከአንድ ሰአት በላይ የፈጀውን ጥናታዊ ጵሁፍህን ሰማሁት። ሰምቼ ስጨርስ ደነገጥኩ። ከራሴም ጋር ለሰአታት ሙግት ገጠምኩ ። ኢህአዴግን ለቅቄ የወጣሁት ልቤ የፈቀደውን በነጳነት ለመናገር ነውና የማውቀውን እና የሚሰማኝን መናገር እንዳለብኝ ተሰማኝ ። ርግጥ በሐይማኖት ጉዳዬች ላይ መናገር ከባድ እንደሆነና ዋጋ እንደሚያስከፍል ጠንቅቄ አውቃለሁ ። በሌላ በኩል የሚያውቁትን አለመግለጵም የፀፀት ዋጋ አለው። በመሆኑም ባለመናገሬ ከሚሰማኝ ሙግት መናገሩን ስለመረጥኩ የሚከተለውን አጭር አስተያየት ለመስጠት ተገደድኩ።
1• ያቀረብከውን መረጃዎች እንዴት እንዳሰባሰብካቸው የተገለፀ ነገር የለም። በተለይም በድህረና ቅድመ ምርጫ 97 ባሉት ሶስት አመታት( ከኃላም ከፊትም) ያቀረብካቸውን መረጃዎች ምንጭ ማወቅ እፈልጋለሁ ። ይህን ጥያቄ የማነሳበት መሰረታዊ ምክንያቶች ስላሉኝ ነው።
daniel kibret
1•1• በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2001 አ• ም• ኢሕአዴግ ለሕዝቡ ይዞለት የመጣው እቅድ ” በአክራሪነት ” ስም ሀይማኖቶችን ማዳከም ነበር። ይህንንም ለማቀጣጠል እንዲረዳው በኢህአዴግ ቢሮ፣ በኮሙዩኒኬሽን ጵ/ ቤት፣ ፌደራል ጉዳዬች እና ፌደራል ፓሊስ መረጃ እንዲሰባሰቡ ተደረገ። የእስልምና ጉዳዬች ላይ ዝርዝር ጥናቱን እንዲሰራ የቤትስራ የተሰጠው ሽመልስ ከማል ነበር። ዛሬ አንተ ካቀረብክልን ውስጥ ግማሹ የቃላት ለውጥ እንኳን ሳይደረግለት በሽመልስ ከማል ጥናታዊ ፅሁፍ የቀረበ ነበር። በወቅቱ እጅግ ከመደንገጤ የተነሳ ሽመልስ እንዴት እንዲህ አይነት ጥናት እንደሰራ ለማወቅ ከጀርባው መጓዝ ነበረብኝ ። መጓዜ ያልጠበኩትን ውጤት አመጣ። ሽመልስ በእስልምና ላይ ከፍተኛ ጥላቻ የያዘው በቤተሰቡ ውስጥ በተፈጠረው ምስቅልቅል እድገት መሆኑን ተገነዘብኩ። አባቱ በአንድ ወቅት የመስኪድ አስተዳደር ነበሩ። በኃላ የሳውዲ ጉዞ አድርገው ሲመለሱ አስተዳደሩን በመነጠቃቸው ከሀይማኖቱ በተቃራኒ ተሰለፋ ። ” ከመካ መዲና ደርሶ መልስ” የሚል መጵሀፍ አሳትመው ክርስትና ተነሱ። ስማቸውም ወደ ሀይለየሱስ ተቀየረ። ባስታወቀው እርምጃ ቤታቸው ተመሰቃቀለ።ወንድማማች እና እህታማቾች የሚጠሩበት የአባት ስም እስከ መለያየት ደረሰ። ባጭሩ የሽመልስ ፀረ -እስላም የመሆን ምንጩ ይሄ ነው። በመሆኑም በሽመልስ ሲቀርቡ የነበሩ ዳታዎችና ትንታኔዎች እንደወረዱ ከአንተ ሲቀርቡ ስሰማ የመረጃ ምንጭህን ተጠራጠርኩ። በተለይ ቴኳንዶ ፣አክሱም፣ መያዶች …ወዘተ ብለህ የገለጵከው የካርቦን ግልባጭ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።

1•2• ሌላኛው ዳታ የሰበሰበው የፌደራል ጉዳዬች ሚኒስተር የነበረው ዶክተር ሽፈራው ከፓሊስ ጋር በመሆን ነበር። ዶክተሩ ያጠናቀረው መረጃ ተመሳሳይ ሲሆን በማጠቃለያው ” የኦርቶዶክስ አክራሪነት አለ” የሚል ነበር። የአክራሪነቱ አስኳል ማህበረ ቅዱሳን እንደሆነ አፅንኦት ሰጥቶበት ነበር። ይህ የዶክተሩ መረጃ በአንተ ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ አልቀረበም ።
( ግምቴን አስቀምጬ ለማለፍ ይህን የዶክተር ሽፈራው ዳታና ትንታኔ ለሌላ የእስልምና መምህር እንዲደርሰው ይደረግና እንደአንተ እንዲያቀርብ ይደረጋል ። ርዕሱንም ” የኦርቶዶክስ አክራሪነት ” ብሎ እንዲጠራው ይደረጋል ።)

2• የመረጃዎቹ ምንጭ እንደተጠበቀ ሆኖ ኩነቶቹ ሲፈጠሩ ሀገሪቷ የነበረችበትን ፓለቲካዊ ሁኔታ ከግምት አላስገባህም። ለምሳሌ ከምርጫ 97 በኃላ በኦሮሚያ የተከሰቱት የሐይማኖት ግጭቶች የተጠነሰሱት በአቶ መለስና ደህንነት ጵ/ ቤት ሲሆን ዋነኛ አሰፈጳሚዎቹ እነ አባዱላና የኦህዴድ ካድሬዎች ነበሩ። ” ቅንጅት የክርስቲያን ጠበቃ ነው” የሚለው መልእክት የተቀረፀው አንተ በጥናታዊ ጵሁፍህ ላይ ” ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል” የሚለው መርሆ አቀንቃኝ የሆነው አቶ በረከት ነው። በየጉራንጉሩ መልእክቱን ያሰራጩት ደግሞ ” እኔ ከሞትኩ… ” በሚለው ብሂል እነ አባዱላና ጁነዲን ናቸው። በተለይ በድሬደዋ የጠነሰሱት ሴራ ባይከሽፍ ኖሮ ዘግናኝ እልቂት ይከሰት ነበር። በመሆኑም ከምርጫ 97 በኃላ የተከሰቱት ግጭቶች ( በተለይ በኦሮሚያ) ጠንሳሾቹ አሁን እየመሩን ያሉት ፓለቲከኞች ሲሆኑ መንስኤውም ፓለቲካው የፈጠረው ነበር። አንተ ግን በየትኛው ቦታ ላይ የፓለቲከኞቹን ሚና ማንሳት አልፈለክም ። ይልቁንስ መንግስት አበረደው፣ መከላከያ አረገበው ማለትን መርጠሀል። ጥናትህን ሰፋ ብታደርገው ኢትየጵያ ውስጥ አክራሪነት በዋነኛነት እየሰፋ የሄደው በፓለቲካው መበላሸት ምክንያት የተፈጠረ መሆኑን ትደርስበት ነበር። አሁንማ በድጋሚ ለማየት ጊዜው አልረፈደም።
ermias copy
3• በጥናታዊ ጵሁፍህ ላይ በአሁን ሰአት ያለውን የኢትየጵያ ሙስሊሞች ” ኢትዬጲያዊነት የተላበሰ፣ ሰላማዊና ፍትሐዊ ጥያቄ” ማንሳት አልፈለክም ። እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተቃወሙት የመንግስት ጣልቃ ገብነት ነው።ኢህአዴግ ከሀይማኖቱ ላይ እጁን እንዲያነሳ ነው በሰላማዊ መንገድ እየጠየቁ ያሉት። አመራራችን በእኛ ይመረጡ፣ ተቋማችንን ራሳችን እናስተዳድር የሚል ነው። ለዚህ ደግሞ እኔ በየትኛውም ቦታና ሰአት ምስክር መሆን እችላለሁ። ታዲያ አክራሪን፣ አክራሪ ካልሆነው ለይቶ የማስረዳት አላማ ካነገብክ ለምን ፍትሐዊ የሆነውን ይህን ጥያቄ ሳታነሳ ቀረህ? እንደ ገዥዎቻችን ” የሙስሊሙ ጥያቄ አክራሪነት የወለደው ነው” የምትለን ከሆነም ወደ መድረክ አውጣውና እንነጋገርበት ።

4• አጀንዳህ ስለ ” ሙስሊም አክራሪነት ” ሆኖ ወደ ማጠቃለያህ ላይ በውጭ ሀገር ያለውን ሲኖዶስ ወደ መዝለፍ ለምን ተሸጋገርክ። ከአንደበትህ የወጣው ቃል ” የሐሰት ሲኖዶስ ተቋቁሞ መንጋ የማይጠብቅ ጳጳሳት ይሾማል ” የሚል ነው። ይህ ንግግር በራሱ አንድነት የሚያመጣ ነው? ውጭ ያለው ሲኖዶስ የሐሰት ነው / አይደለም ከሚለው ትርክት በፊት ይህ እንዲፈጠር ያደረገው ምክንያት ምንድነው የሚለውን ብታነሳ የተሻለ መልስ ታገኝ እንደነበር እገምታለሁ። ሐገር ቤት ያለውን ሲኖዶስ ማን ከጀርባ ሆኖ እንደሚያሽከረክረው ካላወክ በኢትዮጵያ ምህዳር ላይ መኖርህን እንድጠራጠር ያደርገኛል።

4• ሌላኛው ” ለምን አሁን?፣ ምን አዲስ ነገር አለ?” የሚል ጥያቄ እንዳነሳ አድርጐኛል ። የሙስሊሞች ሰላማዊ ትግል በተጠናከረበት፣ መንግስት በጅምላ ማሰር በጀመረበት ፣ ማህበረ ቅዱሳን ላይ በተዛተበት ወቅት ለምን የሚከፋፍል አጀንዳ ይዞ ብቅ ማለት ተፈለገ? የማን አጀንዳ ነው እየተራመደ ያለው የሚለውን ማየት ተገቢ ይሆናል
Ermias Legess / የ መለስ ትሩፋቶች/

The post የመለስ ትሩፋቶች ደራሲ ኤርሚያስ ለገሰ ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት የጻፈው ግልጽ ደብዳቤ appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: የማይግሬን ራስምታትን ለማስታገስ የሚጠቅሙ 6 ሁኔታዎች

$
0
0

Migrin
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር )

የማይግሬን ራስምታት በሚነሳበት ጊዜ ህመሙን ለማስታገስ የሚጠቅሙ ሁኔታዎችን እገልጽላችኋለሁ፡፡
1. የተረጋጋ እና ፀጥ ያለ ቦታ ይምረጡ
✔ በአካባቢዎ የሚገኝ መብራት ማጥፋት እና ከተቻለ እንቅልፍ መተኛት፣
✔ የሞቀ ወይንም የቀዘቀዘ ውኃን በላስቲክ በማድረግ በእራስዎ እና በአንገትዎ ላይ ማስቀመጥ፣ ይህ ማለት ደግሞ
• ቅዝቃዜው በማደንዘዝ ሕመም እንዳይሰማዎ ሲያደርግ ሙቀቱ ደግሞ የራስና የአንገት ጡንቻዎችን እንዲፈታቱ ያደርጋል
• ሕመም የሚሰማዎ ቦታ ላይ በቀላሉ ማሸት አንገትዎን እና ትከሻዎን ማሸት
✔ ገላዎን በሙቅ ውሀ መታጠብ
2. በቂ እረፍት ማድረግ
✔ መደበኛ የእንቅልፍ ሰዓት ይኑርዎ
✔ ሁሌም በተመሳሳይ ሰዓት የመተኛት ልምድ ያዳብሩ
✔ በቀን እንቅልፍ መተኛት ያስለመዱ ከሆነ ከ20-30 ደቂቃ ብቻ ቢሆን ይመከራል። ከዛ በላይ እንቅልፍ ከወሰዱ የለሊት እንቅልፍዎን ሊያዛባ ይችላል
✔ እንቅልፍዎ ያልመጣ ከሆነ እራስዎን አያስገድዱ መጽሐፍ በማንበብ ራስዎን ያድክሙ
3. አመጋገብዎን ያስተካክሉ
✔ መደበኛ የሆነ የምግብ ሰዓት ይኑርዎ
✔ ቁርስዎን መመገብ አይዘንጉ
✔ ማይግሬን ቀስቃሽ የሆኑ ምግቦችን ያስወግዱ (እንደ ቼኮሌት፣አይብ፣ቡና እና የአልኮል መጠጦች)
4. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የማይግሬን ራስ ምታትን ይቀሰቅሳል ነገር ግን ሐኪምዎን በማማከር ቀለል ያሉ እንቅስቃሴዎችን ያድርጉ
(ለምሳሌ እንደ ውሃ ዋና፤የእግር ጉዞ የመሳሰሉትን ማድረግ ይችላሉ)
5.ጭንቀትዎን ይቆጣጠሩ
ጭንቀት የማይግሬን ራስ ምታትን ይቀሰቅሳል፡፡ በዕለት ተዕለት የኑሮ ሁኔታዎች የሚያጋጥሙንን አስጨናቂ ነገሮች መከላከል ባይቻልም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በመፈፀም መቀነስ ይችላሉ።
✔ ቀለል ያለ የኑሮ ዘይቤ ይኑርዎ
✔ ጊዜዎን በአግባቡ ይጠቀሙ
✔ የዕረፍት ጊዜ ይኑርዎ
✔ ለነገሮች በጎ አመለካከት ይኑርዎ
✔ ራስዎን ዘና ያድርጉ
6. የራስ ምታትዎን በተመለከተ የግል ማኅደር ይኑርዎ
✔ በግል ማኅደር መመዝገብ ራስምታትዎን የሚያስነሳውን ሁኔታ ለማወቅ እና ምን እንደሚያስታግስልዎም ለማጤን ይረዳል፡፡
ጤና ይስጥልኝ

The post Health: የማይግሬን ራስምታትን ለማስታገስ የሚጠቅሙ 6 ሁኔታዎች appeared first on Zehabesha Amharic.

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ISIS በአራት ኪሎ ቤተ መንግስት የተቀመጠው ህወሃት/ኢህአዴግ ነው

$
0
0

Muslim in ethiopia
ከዳዊት ሰለሞን (ጋዜጠኛ)

ኢትዮጵያዊያኑ የእስልምና እምነት ተከታዬች ፍጹም ጨዋዎች መሆናቸውን ለመመልከት ላለፉት ሶስት ዓመታት በአገሪቱ ያደረጓቸውን ሰላማዊ ተቃውሞዎች መታዘብ ይበቃል፡፡ሺህዎች በታደሙባቸው ተቃውሞዎች አማንያኑ የሚጤስ ጧፍን ሳያጠፉ ቅጥቅጥ ሸንበቆ ሳይሰብሩ ወደየቤታቸው ተመልሰዋል፡፡

እነዚሁ ሙስሊሞች ፓርቲዎች በጠሯቸው ሰላማዊ ሰልፎች (አንድነትና ሰማያዊ) በመገኘት አቡበከር እንዲፈታ የጠየቁትን ያህል እስክንድር ነጋ፣ርዕዮት ዓለሙ፣አንዷለም አራጌና ሌሎችም ነጻነታቸውን እንዲያገኙ ጠይቀዋል፡፡
በአንጻሩ ስርዓቱ ISISዊ ተግባሩን በወታደሮቹ በኩል በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡እነ ጋዜጠኛ የሱፍና ሰለሞን በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ የተፈጸመባቸው ማሰቃየት ፣በኮፈሌ፣ደሴ፣በአዲስ አበባና በሌሎች ስፍራዎች አይ ኤስ አይ ኤስ (ፌደራል ፖሊስ) በወሰደው ጭፍን እርምጃ ብዙዎች ደማቸው ፈሶ ይህችን ዓለም ተለይተዋል፡፡ይህ ድርጊት መንግስታዊው ISIS የፈጸመው ከማለት ውጪ ምን ሊሰኝ ይችላል ?

ሽብርተኛው ቡድን ያርዳል፣ያሰቃያል፣ሰብዓዊ ክብርን ያዋርዳል ፡፡ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ይሀንን አጥብቀው ይቃወማሉ፡፡ነገር ግን በመንግስታዊው ሽብርተኛ ቡድን ይታሰራሉ፣ባልዋሉበት በኢትዮጵያ እስላማዊ መንግስት ለመመሰረት አሲረናል በሉ ተብለው እንዲፈርሙ ይደረጋሉ፣ውሃ የተሞሉ ላስቲኮች ብልታቸው ላይ ተንጠልጥሎ፣እግራቸው ተገልብጦ ይገረፋሉ፣በአፍጋኒስታን፣በኢራቅ ፣በሶማሊያ ስልጠና ወስደናል እንዲሉ ይገደዳሉ፣መንግስት የለም ወይ በማለታቸው ብቻ በአደባባይ ይረገጣሉ፣በጥይት ይመታሉ፣መንግስት በሚቆጣጠረው ሚዲያ ሹማምንት ቀርበው ‹‹ሽብርተኞች ፣ክርስቲያኖችን ለማጥፋት የተላኩ የጥፋት መልእክተኞች ይባላሉ፣ጥናት አቀረብን የሚሉ የሌላ ሐይማኖት መምህራን ኢትዮጵያዊያኑ ሙስሊሞች እየደረሰባቸው የሚገኘውን የመብት ጥሰት ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ‹‹አክራሪዎች ››ይሏቸዋል፡፡

እውነት ብትቀጥንም ፈጽማ የማትጠፋ መሆኗ ግን የትግል ተስፋ ነው የሚለው ማን ነበር?

The post የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ISIS በአራት ኪሎ ቤተ መንግስት የተቀመጠው ህወሃት/ኢህአዴግ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው! –ከኣባ ሚካኤል

$
0
0

የካቲት ፳፫ ቀን ፪ሺህ፯ ዓም

ተፃፈ ከኣባ ሚካኤል።

loveቸሩ መድኃኔ ዓለም ይመስገንና እርሱ በመጀመሪያ የሰውን ዘር ከዘለዓለማዊ ሞት ሊታደግ ሲመጣ ዓለሙ በሙሉ እርሱን ደስ የማያሰኝ የጌታ ጠላት ነበር። ጌታ መድኃኔ ዓለም ግን ለሰው ልጅ ያለው ፍቅር እርሱን ከዙፋኑ ስለሳበው ዕውነተኛ የፍቅር መሥዋትን ይህቺውም ሕይወቱን ኣሳልፎ እስኪሰጥ ድረስ ወድዶናል፥ በደሙም ነፃ ኣውጥቶናል።  ሕግ ሁሉ በፍቅር ስለሚፈጸም ጌታ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ ካለን በኋላ ጌታችን ያለው፦ እኔንስ ብትወዱ ትዕዛዜን ጠብቁ ነው፥ በዕውን ትዕዛዙን ጠብቃችኋል?

ዛሬ በኢትዮጵያ ሃገራችሁ ውስጥ ፖለቲካው ባመጣባችሁ በደል ምክንያት በተከበራችሁበት ሃገራችሁ ላይ ለመኖር ስላልቻላችሁ በዐራቱም ማዕዘናት ተሰድዳችሁ ባላችሁበት ክፍለ ዓለማቶች ሁሉ ኃይማኖታችሁን ጠብቃችሁ ቤተ ክርስቲያኖችንና መስጊዶችን ከፍታችሁ እየተገለገላችሁ ትገኛላችሁ። ይህንንም በማድረጋችሁ እራሳችሁን ታድጋችኋል፤ ይህም ለጊዜው መልካም ነው፥ ምንም ቢሆን እንደ ዕራስ ሃገር ኣይሆንምና።

ባላችሁበት ሥፍራ ሁናችሁ ደግሞ የሃገራችሁን ውሎና ኣዳር በትጋት ትከታተላላችሁ። ሁላችሁም “በዚያች ሃገር” ላይ ሳይሆን በኢትዮጵያ ሃገራችሁ ላይ ሠላም ወርዶና እርቅ ተደርጎ መቻቻልን የተዋሃደ ሕዝባዊና ፍህታዊ የሆነ መንግሥት ፈጥራችሁ እንዲሁም የመከላከያ ኃይሏ ለሕዝቧ እንዲያገለግል እንጂ ሥልጣን ላይ የሚወጣውን ጥቅም ኣስከባሪ እንዳይሆን ቀርጻችሁ ወደ ሃገራችሁ ተመልሳችሁ ተከብራችሁና ኣክብራችሁ መኖርን ትሻላችሁ።

በውድ ሃገራችን ላይ እንጂ በባዕድ ሃገር ላይ ኣንኖርም ያሉና በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩትን የእህቶቻችሁንና የወንድሞቻችሁን ሕይወት ስናይ ደግሞ ነፃነታችውን ለማግኘትና እናንተም በየሃገሩ ተበትናችሁ የምትገኙትን ወደ ሃገራችሁ እንድትመለሱ በሚያደርጉት ትግል ላይ እናንተ የፈራችሁትንና ከሃገር ያሳደዳችሁን ህዋሓት፦ እነርሱ በጠራራ ፀሐይ እየተጋፈጡት ድብደባ፣ እስራት፣ መሸማቀቅ፣ ረሃብ ወዘተ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛውን የፍቅርን ዋጋ ሞትን እየሞቱላችሁ ይገኛሉ።

የሚገርመኝ ቢኖር ክርስቲያኖች ወይም ሙስሊም ሆናችሁ ሳለ ጠላትህ ቢራብ ኣብላው፣ ቢጠማም ኣጠጣው፣ ቢራዝ ኣልብስው /ሮሜ ፲፪ ቁ ፳/ የሚለው የኣምላክ ቃል በየጊዜው እየተሰበከላችሁ ጠላቶቻችሁ ሳይሆኑ የገዛ ወንድሞቻችሁ እንኳን ቢራቡም፣ ቢጠሙም፣ ቢራቆቱም፣ በግፍ ቢገደሉም ወዘተ ፓትርያርኩም፣ ጳጳሱም፣ ቄሱም፣ ፓስተሩም፣ ሼሁም፣ ኢማሙም እንዲሁም ምዕመኑ ዝም። እግዚዖታን እንኳን ነፈጋችሗችው።  በሃገር ቤቱስ ላሉት ውስጡን ለቄስ ነው፥ ህዋሓት ናት የሓይማኖቱን ሥራ የምትሠራው። ከሃገራችሁ ዕርቃችሁ በነፃነት የምትኖሩ ክርስቲያኖች እስቲ ቆም በሉ። በእውን የሞተላችሁን ክርስቶስን ትወዱታላችሁ? ትዕዛዙንስ ትፈጽማላችሁ? ኣምላካችሁ ክርስቶስ ለሞተላት ክብርት ቤተ ክርስቲያን ፍቅር ኣላችሁ? ወይስ ከኢትዮጵያ ጠላት ጋር ኣብሮ የወገኑ ሞት ለእርሱ ሕይወት እንደ ሆነለት ሆድኣደር ሆናችሁ? ሙስሊሞችስ?

ህዋሓት ዛሬ ሳይሆን ከ፳፬ ዓመት በፊት ጀምራ የኦርቶዶክስ ክርስቲያንና የእስልምናን ዕምነት ለማጥፋት በሚገባ የቤት ሥራዋን ሠርታ ዛሬ በተግባር እየተረጎመችው ነው። ንዋየ ቅዱሳኖችን ኣውጥታ ሽጣለች፣ ቤተ ክርስቲያንን ኣቃጥላለች፣ መነኮሳትን ከገዳም ድረስ በመሄድ ደብድባለች፣ በቅርቡም ኢትዮጵያ ካለው ሲኖዶስ ይልቅ ለኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በሃገር ቤት ግልጋሎት የሚሰጠውን ማኅበረ ቅዱስንን ልትመታ ቃጥቷታል፥ ምንም እንኳን ማኅበረ ቅዱሳን ከሃገር ቤት ውጪ የተከፈቱትን ኣብያተ ክርስቲያናት ህዋሓት በሚቆጣጠረው በሃገር ቤቱ ሲናዶስ ሥር እንዲተዳድሩ በማድረግ ከፍ ያለ ሚና ቢጫወትም ለህዋሓት ማኅበረ ቅዱሳን ከኣብዮታዊ ዲሞክራሲው ኣይበልጥበትምና ከ፪ሺህ፯ ምርጫ በውኋላ ተመልሳ የቃጣችውን በተግባር ልታውል ትችላለች ብዬ እገምታለሁ፤ እስልምና ኃይማኖትን የሚመሩትን ትመርጣለች፤ ፕሮቴስታንቶቹን ደግሞ ኣንድ ቀን መንካቷ ኣይቀርም።

እስቲ እዩ፥ በኣካባቢያችሁ ስለ ኢትዮጵያ የሚያስቡትንና ኢትዮጵያን ነፃ በማድረግ ኃይማኖት እና ፖለቲካ ተከባብረው በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲኖሩ ደማቸውን ከሚያፈሱት ጋር ኣጋር በመሆን ጊዜያቸውንና ገንዘባችውን ለትግሉ መሳካት የሚሰጡትን፣ ስለ ወገናቸው ግድ የሚላቸው፣ ስለ ኃይማኖታችውም ስለ ሃገራቸው ፖለቲካም ቢናገሩ ዕውነተኞችና ታሪክ ሠሪዎችን፣ ህዋሓት እስካለች ሃገሬን ባላይስ መጀመሪያ ነፃነቴን ያሉትን። በኣንፃሩ ደግሞ እናንተ ዛሬ ገንዘብ ኣግኝታችሁ ቤት በሃገር ቤት ስትሠሩና ንብረት ስትመሠርቱ ወደ ሃገር ቤት የምትልኩት የውጪ ምንዛሪ የህዋሓትን የጭቆና ሥርዓት እንደሚረዳ እያወቃችሁ ስለራሳችሁ ብቻ ትጨነቃላችሁ። ገንዘባችሁ ባለበት ምናችሁ ኣብሮ ይኖራል ኣለ? ህዋሓት እንዲህ እያረገች ነው የምትቆጣጠራችሁ።

ከሃገራችን ተከትሏችሁ የመጣው የፖለቲካ ችግር ደግሞ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናችሁን በሦስት ቦታ ከፍሏታል። ኣሁን ባላችሁበት ሃገር የኣቡነ ማቲያስ ሥም የሚጠራባቸውን ቤተ ክርስቲያኖችን ብትመለክቱ፥ ወይ በበላይነት ወይም በኃላፊነት ላይ ያሉት ካህናቶችና ግለሰቦች የህዋሓት ደጋፊዎች ናችው። በመሆናቸውም፥ ምዕመኑን በተቻላቸው መጠን ኢትዮጵያን ከህዋሓት እንዳያላቅቅና ወደ ተቃዋሚ የትግሉ ጎራ እንዳይሄድ ኣድርገውታል። ኣይ ሃገራችን መልካም ኣስተዳደር ኣላት ትግሉ ኣያስፈልግም የምትሉ ካላችሁ ግን ለምን በሃገራችሁ እንደማትኖሩ ይገርመኛል፥ ሌላ ተልዕኮ ከሌላችሁ በስተቀር።

በምን ሰሌት እያሰላችሁ ነው ህዋሓት ከምትመራው ሲኖዶስ ጋር ተሰልፋችሁ ቤተ ከርሰቲያኒቷን  እያጠፋችኋት ያላችሁት። ባለፈው ሣምንት ውስጥ ከእንጦጦ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ዕድሜ ጠገብ ወርቆች ወዘተ ለኣባይ ግድብ መዋጮ ተወሰዱ የሚል ዜና ሰማሁ ግን ኣቡነ ማቲያስ  ከጽህፈት ቤታቸው ስለዚህ ጉዳይ ያወጡት መግለጫ የለም። እናንተ የእርሳቸውን ሥም በማንሳት የምትተባበሩትስ ምን ኣላችሁ? ምንም። ቤተ ክርስቲያኗስ ኣትጠፋም፥ ኣንዴ በክርስቶስ ደም ላይ ተመሥርታለችና፥ ውዮ ግን ለእናንተ የኣምልኮ መልክን ብቻ ለያዛችሁ፥ ለወገናችሁ ስቃይ ሳይሆን ስለራሳችሁ ብቻ ለምትጨነቁ።

በውጭ ሃገር ሲኖዶስ መቋቋሙን  ባንደግፈውም የኣቡነ መርቆርዮስን ፓትርያርክነት የሚክዱት ህዋሓት የሰለበቻችው የዋሆች ካልሆኑ በስተቀር ኣሁንም ቢሆን ሕጋዊው ፓትርያርክ እንደሆኑ ሌሎቻችን እንረዳዋለን። ይህንንም የውጪውን “ሲኖዶስ” ደግሞ ጠጋ ብሎ ላየው ሰው፥ የጎንደር ሃገር ስብክት እንጂ የኢትዮጵያ ሲኖዶስ ለመባል የሚችል ስብስብ ኣይደለም፤ እንዲሁም ለወደፊቱ ፓትርያርክ ለመተካት እንኳን ሥልጣን የለውም።  እዛ ጊዜ ላይ ቢደረስ፥ የገለልተኛው ቁጥር ከሌሎቹ እንደሚበልጥ እገምታልሁ።

ለዚህ ሁሉ ችግር መንስኤ የሆነችውን ህዋሓትን በማስወገድ ነፃነታችሁን ማወጅ ኣማራጭ የሌለው መንገድ ነው። ኣቋማችሁን ኣስተካክላችሁ ስለ ኢትዮጵያ ጉዳይ ስብሰባ ስትጠሩ በስበሰባው ላይ ተገኙና ስለ ኃይማኖታችሁና ስለ ሃገራችሁ ያገባናል በሉ። በፀሎትና በሃሳብ እንዲሁም በገንዘባችሁ ወገኖቻችሁን ታደጉ። ካህናቶቻችሁ በሃገር ቤት የሚደረገውን ግፍ ኃይማኖትን በጠበቀ መልኩ እንዲያወግዙ ግዴታ ኣለባቸውና ይህንን እንዲያደርጉ ጫና መፍጠር ኣለባችሁ። ካህናቶቹ ይህንን ባያደርጉ ግን፥ ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ ግድ ከሚላቸው ካህናቶች ከሚያገለግሉበት በመሄድ የሕብረት ጸሎት በማድረግና በተግባር ደግሞ ሰለ ኢትዮጵያ ነፃነት ከሚታገሉት ጎን በመቆም ዕውነተኛ ፍቅርን በማሳይት ትዕዛዝ ማክብራችሁን ኣረጋግጡ።

ተፃፈ ከኣባ ሚካኤል።

 

 

The post ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው! – ከኣባ ሚካኤል appeared first on Zehabesha Amharic.

ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች የተሳተፉበት የስልክ ጥሪ ማቆም አድማ ተካሄደ

$
0
0

10920943_352316331618819_5078649879608517565_nየካቲት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን እንዳዲስ ተጠናክሮ በቀጠለው ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን የማሰር ዘመቻውን በመቃወም ድምጻችን ይሰማ የጠራው ስልክን ለ12 ሰአታት የማጥፋት ዘመቻ በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን ዘጋቢያችን ገልጿል፡፡

በርካታ ሙስሊሞች ስልኮቻቸውን አጥፍተው የዋሉ ሲሆን፣ በማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃን የሚያደርጉትን እንቅስቃሴም አቁመው ውለዋል። በርካታ ክርስቲያኖችም ጥሪውን ደግፈው ስልካቸውን ዘግተው ውለዋል።

እርምጃ የመንግስት ዋነኛ የገቢ ምንጭ በሆነው ቴሌ ላይ የኢኮኖሚ ጉዳት ለማድረስ ታቅዶ የተተገበረ ነው።

Source:: Ethsat

The post ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች የተሳተፉበት የስልክ ጥሪ ማቆም አድማ ተካሄደ appeared first on Zehabesha Amharic.

በአማራ ክልል ነዋሪዎች በአገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች መማረራቸውን ተናገሩ

$
0
0

Amharamapየካቲት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በክልሉ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ እና የተለያዩ ቢሮዎች በየእለቱ ጉዳያቸውን ለማስፈጸም የሚመላለሱ ባለጉዳዮች በተለያየ ሰበብ ፈጻሚ በማጣት መቸገራቸውን ድርጅቱ ባዘጋጀው የአስተያየት መስጫ መዝገብ ላይ ማስፈራቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያሳያል።

ከተለያዩ አካባቢዎች ጉዳይ ለማስፈጸም እንደመጡ የገለጹት ቅሬታ አቅራቢዎች በተለይ በስብሰባ ሰበብ ለረዢም ጊዜ መጉላላታቸውን ባሰፈሩት የሃሳብ መስጫ ደብተር ላይ ለማንበብ ይቻላል። አስተያየት ሰጪዎች በዋነኝነት ያነሱት ችግር ባለስልጣኖች በስብሰባ ሰበብ ባለጉዳይ ለማስተናገድ አለመቻላቸውን ሲሆን፣ የብቃት ማነስም ችግርም ተጠቅሷል።

“ለማን ብሶታችንን እንናገር ፣ ጠዋት ስንመጣ ከሰአት ከሰዓት ስንመጣ ጠዋት፣ ቢሮ ኃላፊው የለም፣ ሂደት አስተባባሪው የለም፣ የድርጅቱና የመንግስት ሚዲያ በየመድረኮች ሚናገሩት ሌላ ፣

…የከተማው ህዝብ በመሬት እጦት፣ የመንግስት ሰራተኛው በደመዎዝ ማነስና ፣ተመርቆ ከቤተሰቡ ጋር ቁጭ ብሎ በመቅረቱ የገጠሩ ህብረተሰብ በማዳበሪያ ውድነት ተወጥሮ ፣ በሌትና በቀን የቁም ቅዠት አያሰቃየው አሁን ለማን ነግሮ መፍትሄ ያገኛል? ለመንግስት ቢነግሩ ከወረቀት የዘለለ የተግባር ፍሬ የለውም ኧረ ለማን እንንገረው?አምላክ አይፈጥን እንደሰው!እባክህ ጌታዬ የኢትዮጵያ አምላክ በ2007 ምርጫ ገላግለን ፣ በቸርነትህ መንግስት በዘር በዘመድ አዝማድ በገንዘብ እየተሸበበ በቁማችን እየተጓዝን ተቀበርን፡፡

…..ለአመራሮች በጣም ከፍተኛ የሆነ ስልጠና ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ባለስልጣኖቹ ድሃውን ህዝብ በማንገላታት የታወቁ መሆናቸው በአለም ታውቋል የነሱን ምቾት ካገኙ ለሌላው ምንም ደንታ የላቸውም……

…..ባሁኑ ሰዓት አቤት ባይ ሲበዛ ፍትህ ሰጪ ግን የለም፡፡ለምን ይሆን ህብረተሰቡን የተጣላው?እግዛብሄር ይሆን መንግስት ነው አልገባኝም…….

የሚሉት አስተያቶችን የያዙ ማስታሻዎች ለስሙ በተቀመጡ ያአስተያየት መቀበያ ደብተሮች ላይ ሰፍረው ይነበባሉ፡፡

የገዢው መንግስት ባለስልጣናት ከህዝቡ አስተያየት በመሰብሰብ አገልግሎት አሰጣጣችንን እናስተካክላለን እያሉ ቢናገሩም የአስተያየት ደብተሮችን እንደማይመለከቱ አስተያየት ሰጪዎች ገልጸዋል፡፡

Source:: Ethsat

The post በአማራ ክልል ነዋሪዎች በአገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች መማረራቸውን ተናገሩ appeared first on Zehabesha Amharic.


ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሰቆጣ አርሶደአሮች በረሃብ ምክንያት ተሰደዱ

$
0
0

esat

esat 2

ESAT 3
የኢሳት ወኪል እንደዘገበው በሰቆጣ አካባቢ የተከሰተውን ከፍተኛ ድርቅ ተከትሎ አርሶደአሮቹ ወደ ምእራብ ጎጃምና ሌሎች የአማራ ክልል አካባቢዎች በመሰደድ ላይ ናቸው።

ተፈናቃዮቹ ከክልሉ ባለስልጣናትም ይሁን ከፌደራል መንግስቱ ምንም አይነት እርዳታ አለማግኘታቸውን ገልጸዋል።

ብዙዎቹ ተፋናቃዮች ወጣት ወንዶችና ሴቶች ሲሆኑ፣ በሰፈሩባቸው አካባቢዎች ስራ ሰርተው ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ እየጠየቁ ነው።

ተፈናቃዮቹ በዝናብ እጥረት ምክንያት ሰብላቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙን ገልጸዋል።
መንግስት በአካባቢው ስለተከሰተው ድርቅ እስካሁን የሰጠው ምንም አይነት መልስ የለም።

The post ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሰቆጣ አርሶደአሮች በረሃብ ምክንያት ተሰደዱ appeared first on Zehabesha Amharic.

የጉራጌ ካድሬዎች አንገታቸውን ያስደፋ ክስተት

$
0
0

‹‹ያለ ኢኮኖሚ የበላይነት የፖለቲካ የበላይነት አይመጣም››

የሚለው የህውሃት ኢህአዲግ ፖለቲካ ኢኮኖሚውን ከመቆጣጠር ባለፈ ደጋፊዎቹን በኢኮኖሚ በማብቃትና በተጠቃሚነታቸውም ፖለቲካውን በመጠበቅ የበረኛነት ሚና እንዲጫወቱ በ97 ምርጫ ማግስት ከተወሰዱትርካሽ እርምጃዎች አንዱ በግምታዊ አቀማመጥ መሃከለኛ ገቢ ያላቸውን የመርካቶ ጉራጌዎች በማዳከም የህውሃትን ተጠቃሚዎች ማጠናከር ነበር::
Ethiopia
የወቅቱ የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዲኤታ ኤርሚያስ ለገሰ ይህንን ይላል በምርጫ 97 ማግስት አቶ መለስና በረከትን ጨምሮ ከፍተኛ የኢህአዴግ ካድሬዎች ‹‹ጉራጌ አብዮት አካሄደብን›› በማለት ይናገሩ ነበር፡፡ በኢህአዴግ ማእከል በተዘጋጀው ሰነድ ላይ የጉራጌ ብሄረሰብ ከትምክህት ጎራ ጋር በተቀላቀሉ ልጆቹ ምክንያት የሀይል አሰላለፍ ቀውስ ውስጥ በመግባት ከጥገኛ ኃሎች ጋር ተሰልፎ ወደ ዝቅጠት ገብቶ እንደነበር ይገልጻል፡፡ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የብሄረሰቡ ተወላጆች(በጉራጌ ዞን ያለውን መዋቅራችንን ጨምሮ) የዜጎችን በነጻነት የማሰብና የመምረጥ መብት በመጋፋት እስከ ጎጣቸው በመሄድ ‹‹ኢህአዴግን የመረጠ ውሻ ይውለድ!›› የሚሉ ቃል ኪዳኖችን እስከ ማጥለቅና መማማል ዘልቀው ነበር በማለት ይከሳቸዋል፡፡ የጉራጌ ብሄረሰብ እንደ ሌሎች የሀገራች ጭቁን ብሄረሰቦች ህገ-መንግስታዊ መብቱ በተከበረበት፣ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት በተጎናጸፈበት ሁኔታ ወደ ትምክህት ሀይል ሽግሽግ ማድረጉ ያልተጠበቀ እንደነበር ሰነዱ አመላከተ፡፡( ቅንፍ የራሴ በምርጫ ኢህአዴግን አለመምረጥ መብት ሳይሆን ትምክህተኝነት የሚባል ሃጥያት ነበር ዛሬም ነው)

በቀረበው ዶክመንት ላይ በመመስረት በየወረዳው የተካሄዱት መድረኮች አስደንጋጮች ነበሩ፡፡ የምርጫ 97 ውጤት የኢትዮጵያ ህዝቦች የትግ ውጤት መሆኑን በመካድ ‹‹ጉራጌ መራሽ አብዮት›› የሚል ስያሜ እስከ መስጠት ተደረሰ፡፡ ጣቶች በሙ ወደ ጉራጌ ብሄረሰብ በተለይም የብሄሩ ተወላጅ የኢህአዴግ ካድሬዎች ላይ ተቀሰሩ፡፡ ነጋዴው ጸረ-ኢህአዴግ እንዲሆን ከአመታት በፊት የተጠነሰሰ ሴራ እደሆነ በሰፊው ተነገረ፡፡ የጉራጌ ካድሬዎች አንገታቸውን ደፉ፡፡

ኢኮኖሚውን የሚቆጣጠር ኃይል በሂደት ፖለቲካ ኢኮኖሚው ላይ የበላይነት ማሳረፉ ስለማይቀር ጉራጌን ከንግዱ ዓለም ማስወጣት ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም፡፡ ሮማን (የህወሃት ባለሃብቶችን መፍጠር አላማ አስቀጣይ የሆነች) የጉራጌ ነጋዴዎችን እንዳያሰራሩ የምትቀጣበት ምክንያት ይህ ነበር፡፡
እነ ሮማ በፈጠሩት ልዩነት ጉራማሌዋ መርካቶ ይበልጥ ተዘበራረቀች፡፡ ተመሳሳይ እቃዎች በነባሮቹና አዲሶቹ ነጋዴዎች መካከል የዋጋ ልዩነት አሳየ፡፡ የግብርና የሊዝ እፎይታ ያገኙት አዲሶቹ ነጋዴዎች ዋጋቸውን አወረዱ ሸማቹሚስጥሩ ሳይገባው ቅናሽ ወዳገኘበት አዲሶቹ ነጋዴዎች ፊቱን አዞረ፡፡ ቀስ በቀስ ነጋዴው ከገበያ ወጣ፡፡
የማፊያ ባህሪ ያላቸው አዲሶቹ ነጋዴዎች ሰው ሰራሽ እጥረት በመስከሰትም ተወዳዳሪ አልነበራቸውም፡፡ በሰአታት ውስጥ አንድ ኪሎ ጨው ዋጋ ከአንድ ብር 50 ብር የተሸጠበት አጋጣሚ ልብ ይሏል፡፡

ነባሩ ነጋዴ ከገበያ መውጣቱ እልህ የተጋቡት የጉራጌ ካድሬዎቹ እነ ሺሰማ ክትትል ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ ከብዙ ጥረት በኋላ ሸፍጥ የሚሰራበትን ቦታ ይደርሱበታል፡፡ ሮማንና ወዳጆቿ ፋይል የሚሰርዙና የሚደልዙት፣ ግብር የሚጨምሩትና የሚቀንሱት፣ ሱቅ የሚሰጡትና የሚቀሙት አምባሳደር ፊልም ቤት የሚገኘው ካፍቴሪያ የሕገወጥነቱ ማዕከል ነበር፡፡….

ከምርጫ 97 በኋላ የጉራጌ አብዮትን ለመቀልበስ በስብሰባ ማዕከል በተጠራ የመጀመሪያው ዙር ማጠቃለያ ኮንፍረንስ ላይ ተገኝቼ ነበር፡፡ በጉባኤው የተሳተፉት ከአንድ ሺህ በላይ የጉራጌ ነጋዴዎችና ባለሃብቶች ነበሩ፡፡ ይህን ለአንድ ሳምንት የዘለቀ ጉባዔ የመራው ዶ/ር ካሱ ኢላላና ሚኒስትር መኩሪ ነበሩ፡፡ ነጋዴዎች በሲቃ ስለ ሮማንና ሉሌ የሚነሱት ወንጀል ጨጓራ የሚልጥ ነበር፡፡ በተለይ የክፍለ ከተማው የገቢዎች ኤጀንሲ ሙያተኛ የሆነ የጉራጌ ተወላጅ ስራየን ለመልቀቅ ብዙ ተሟግቻለሁ በማለት የገለጸው ታሪክ ዶ/ር ካሱ አንገቱን አቀርቅሮ አንዲቀር አድርጎታል፡፡ ከመቀመጫው ተነስቶ የኮንፈረንሱን ተሳታፊ አንባ እየተናነቀው ይቅርታ ጠይቋል፡፡

እንዲህ ነበር ያደረጉት፣
ሎሌና ሮማን ከቢሮአቸው ሳይወጡ ከአስር እጥፍ በላይ ግብር እንዲጥሉ ሙያተኞችን አስገደዱ፡፡ ከስረው ለመዘጋት አፋፍ ላይ ያሉ ነጋዴዎችን ከግብር ሕጉ በተቃራኒ ታክስ አስከፈሉ፡፡ በድርጊቱ የተበሳጨ አንድ ነጋዴ ራሱን በገመድ አንጠለጠለ፡፡ ተመሳሳይ ሱቅና የንግድ ዓይነት ያላቸውን ጎረቤት ነጋዴዎች አንዱን በዜሮ ፣ሌላውን በአስር ሺዎች ታክስ እንዲከፍል አድርገዋል፡፡ ይህ በዘር ላይ የተመሰረተ እርምጃ ቀድሞ በነጋዴዎች ዘንድ የነበረን በደጋገፍ እንዲቀር በማድረግ እርስ በራስ በጥላቻ እንዲተያዩ አድርጓል፡፡ በዚህ ምክንያት መሳሪያ የተማዘዙ፣ በገጀራ ተፈነካክተው ወህኒ የወረዱ ነጋዴዎች ይገኙበታል፡፡

(ለግምገማ ቀርባ የነበረችው ሮማን እንዳትጠየቅ አርከበ ተከላክሎ አትርፏታል)

The post የጉራጌ ካድሬዎች አንገታቸውን ያስደፋ ክስተት appeared first on Zehabesha Amharic.

ከሃረር እስከ ጎዴ እንዲሁም ሃርጌሳ አፈሳው እና አፈናው ተጥውጡፏል

$
0
0

(ምንሊክ ሳልሳዊ) ባለፉት ቀናቶች ውስጥ ወያኔ እና የኦጋዴን አማጺ ሃይሎች ያደረጉትን ጦርነት ተከትሎ ከግድያው በተጨማሪ ከሃረር እስከ ጎዴ ያካልለ የመንገድ ላይ አፈሳ እና የቤት ለቤት አፈና እየተካሄደ እንደሆነ ከሰራዊቱ እስጥ የሚገኙት ወታደራዊ ደህንነቶች ተናግረዋል::
news
በልዩ ሃይል መሪነት እና በሕወሓት ጦር ተባባሪነት እየተፈጸመ ያለው አፈሳ እና አፈና የወያኔ ጦር ባልውፉት ቀናት የደረሰበትን ሽንፈት እና ኪሳራ ለማካካስ የጀመረው ሲሆን እስካሁን የቤት እመቤቶችን ጨምሮ ከ400 ሰዎች በላይ ተይዘው መታሰራቸው ሲነገር ዋና ዋና ናቸው የተባሉ የኦጋዴን አማጺ ሃይሎች አባላት ወደ መሃል አገር መላካቸው ታውቋል::በዚህም መሰረት የስለላ ስራ ያካሂዳሉ የተባሉት አጋስ መሃመድ አብደላ እና አብዱላዚዝ አብዶ ቀሽር የተባሉ የአማጺ አባላት ይገኙበታል::አፈሳው እና አፈናው በሃረር በጎዴ በቀብሪበያህ በቀብሪ ደሃር በጅጅጋ በሃርሸክ እና በሰሜን ሱማሊያ ሃርጌሳ እየተካሄደ እንደሆነ ምንጮቹ ገልጸዋል::

በአንድ በኩል እንደራደር እያለ በአንድ በኩል በውጊያ የሚጠዛጠዘው ሰው በላው ወያኔ ምን ያህል የፖለቲካ ኪሳራ እና መበስበስ እንደሚጠቁም እና የኦጋዴንን ነዋሪዎች እያፈነ እና እያሰቃየ በየትኛው የሞላር ሚዛን ድርድር ላይ እንደሚቀመጥ እና ከነማንስ ነው የሚደራደረው የሚለው ጉዳይ ጥያቄ አስነስቷል::

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በኦጋዴን አማጺ ሃይሎች እና በወየኔ ጦር መካከል በኦጋዴን ደገሃቡር አከባቢ ከፍተኛ ውጊያ መካሄዱ ሲታወቅ በሰጋጋ አከባቢ የኦጋዴን አማጺ ሃይሎች ኮማንደር ተገለዋል:: የአማጺ ሃይሎች ተዋጊዎች በአከባቢው ከሚገኘው ልዩ ሃይል ተብሎ ከሚጠራው እና በወያኔ ጦር ጋር የአከባቢው ነዋሪዎች መታፈናቸውን ተከትሎ ከሃረር ከተማ 160 ኪሎሜትር ደቡብ ምስራቅ በምትገኝ በአኪርሚሽ ላስጋሎል በተባለ ቦታ መዋጋታቸውም ይታወሳል::

The post ከሃረር እስከ ጎዴ እንዲሁም ሃርጌሳ አፈሳው እና አፈናው ተጥውጡፏል appeared first on Zehabesha Amharic.

የአገርዎ፣ የግልዎ እና የሕዝብዎ ስቃይ እና ሕመም ያሳሰብዎታል? -የአዲስ ቃል ኪዳን ታቦት የፈውስ አገልግሎት

$
0
0

የአዲስ ቃል ኪዳን ታቦት የፈውስ አገልግሎት

የአገርዎ፣ የግልዎ እና የሕዝብዎ ስቃይ እና ሕመም ያሳሰብዎታል?

arkofthecovenantዛሬ በዓለማችን ዙሪያ የሰው ልጅ መከራም ዕውቀትም እየበዛ፣ ሁኔታዎች ሁሉ ለሰው ልጅ ስጋት ሆነው ባለበት ወቅት ፣ ኢትዮጵያ ተብላ በምትታወቅ ምድር እና ሕዝብም ላይ በአገር ውስጥም በውጭም ያለው የመከራ ስጋት፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ቁርኝት ያለው ኢትጵያዊውን ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊውን ብቻ ሳይሆን፣ ከአገሪቱዋ ጋር በአንድም በሌላም የጥቅም ግኑኝነት ያላችውን ባዕዳን አገራትን፣ አለያም የመሳሪያ ሸቀጦቻቸውን ለማራገፍ የእርስ በእርስ ጦርነት ቀጥሎ ሊነሳባት የሚችል አገር የትኛዋ ናት? ብለው የገበያ ጥናት የሚያደርጉትን መሳሪያ አምራች ድርጅቶችን ሁሉ ሳያነጋገር የሚቅር አይመስልም ፡፡

የምድሪቱዋ እና የሕዝቡ ዕጣ ፈንታም  በምሑራን፣ በታዋቂ  ሰዎች፣ በጀግኖች እና በስመጥሮች አለያም በምዕራቡ፣ በምስራቁ ወይም በዓረቡ ዓለም እርዳታ ለጋሾች ወይም ብድር አበዳሪ አገሮች፣ በተባበሩት መንግሥታት፣ በአውሮፓ ሕብረት፣ በአፍሪካ አንድነት ድርጅት፣ በፖለቲካ ድርጅቶች ወይም ንቅናቄዎች፣ ብቻ ሊፈታ ይገባዋል ብሎ ማሰብ የዋህነት ሲሆን፣ ባለፉት ዘመናትም የነዚህን ድርጅቶችም ሆን ግለሰቦችን በር በማንኩዋኩዋት ምን ያህል አመርቂ ውጤት እንደተገኘ፣ የተጨበጠ መረጃ ለጊዜው ባይኖረንም፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያምነውም፣ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ብሎ የሚለውንም ከዛች ምድር የወጣ ሰው ሁሉ፣ ለሐገሪቱዋና ለሕዝቡ ቀጣይ መፍትሔ ለማምጣት እና ሁሉም ተዋዶ እና ተከባበሮ የሚኖርባትን አዲሲቱን ኢትዮጵያ ለመገንባት ያገባኛል የሚል ሰሜት ሊኖረው ግድ የሚልበት ወቅት ላይ የተደረሰ ይመስላል፡፡

ቅጥሩዋ እየፈራረሰ፣ ሕዝቡዋም ግራ በመጋባት በተበታተነበት ሁኔታ፣ ቅጥሩዋን ከሚሰሩ ጋር ሁሉ እጅ ለእጅ በመያያዝ፣ የሕዝቡ መከራ መከራዬ፣ የሕዝቡ ደስታ ደስታዬ ስለሆነ ላበረክት የምችለው ጉዳይ አለኝ፣ ስለዚህም ያገባኛል የሚለው ግን ምን ያህሉ እንደሆነ ቤት ይቁረጠው?

በሌላ በኩልም በአገሪቱ ላይ ከልማት እና ከዕድገት በስተቀር፣ ሰው አልተበደለም፣ ሕዝብ፣ አልታሰረም፣ አልተሰደደም፣ አልሞተም፣ ነጻነቱንም አልተነፈገም፣ ሕዝቡዋ፣ ሳይራብ፣ ሳይታረዝ፣ ሳይሰደድ፣ ሳይታምም በነፃነት ደልቶት እየኖረ ስለሆነ፣ ችግርም ቢኖር በአይን የሚታየው ልማት እና ያገሪቱዋ መሻሻል ስለሚበልጥ፣ የሚሰቃየው ሕዝብ ላገሪቱዋ ማደግ የሚከፈለው ዋጋ ነው ብሎ በማሰብ፣ የሰውን ልጅ ክቡር ሕይወት ከቁሳዊ ነገር ባነሰ መልኩ በመመልከት እና ተቃዋሚዎች የሌለውን ችግር እየጋነኑ ሕዝቡን ያሸብሩታል ብሎ በማመን፣ በሥልጣን ላይ ካለው  መንግሥት ጋር በመተባበር ለመንግሥት ዓላማ ለመታገልና በሥልጣን ላይ መቆየትም እንዳለበት የሚያምኑም የአገሪቱ ልጆችም ሆኑ ፣ ባዕዳንም እንደማይታጡ ልብ ማለት ይገባል፡፡

በአገሪቱና በሕዝቡ ላይ በደል እና መከራ እንዳለ ቢያወቁም፣ ወደ አገር ቤት እንደፈለጉ መመላለስ የሚፈለጉ፣ ያላቸውን ሐብት እና ንብረት ማጣት የማይፈለጉ፣ ዘመዶችን መጠየቅ፣ ትዳር መመስረት…ወዘተ የሚፈለጉ፣ ከመንግሥት ጋር ላለመቀያየም ካላቸው ፍርሐት የተነሳ ባገሪቱም ሆነ በሕዝቡ ላይ የሚደርሰው መከራ አያገባኝም በማለት መሰማትም ማየትም አልፈልግም ማለትን የመረጡ፣ ካለባቸው የግል ችግርም የተነሳም የአገርን ችግር ለመስማት አቅም ያጡ፣ በዘር እና በጎሳ ማንነት ምክንያት ኢትዮጵያዊነት የሚለው ሰሜት ከውሰጣቸው እንዲጠፋ በመደረጉ ምክንያትም ከተደራጁበት ብሔረሰብ፣ ቤተ እምነት ወይም የፖለቲካ ድርጀት አመለካከት በስተቀር የሌላው ጉዳይ አያገባኝም ብለው እንዲገደቡ የተደረጉት ባንድ በኩል፣ በሌላው በኩል ደግሞ የማንኛውም ዘር፣ ጎሳ፣ ፖለቲካ፣ ሐይማኖት ወይም  እምነት ጉዳይ አጥር ሳይሆንባቸው፣ የሰው ልጅ መከራና ስቃይ  እንደሰው ብቻ ተሰምቶአቸው፣ የትውልዱ ሕመም ያመኛል እና ፈውስ ያስፈልገናል፣ እኔንም ያገባኛል ከሚለው ጋር ፣ የየራሱን ጎራ ለይቶ ተፋጦ ያለበት የቀዝቃዛ ጦርነት ካምፕ በስውርም በገሐድም በአገር ውስጥም በውጭም ከትሞ በደፈጣ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡

በኢትዮጵያ በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት፣ በኢትዮጵያ ሕዝብ ያልተመረጠ፣ ከጫካ መጥቶ ሥልጣንን በጉልበት የያዘ፣ በጉልበት እና በግድ ሕዝቡን እያስጨነቀ፣ እየገደለ፣ እያሰረ፣ እያሰደደ፣ በሕዝቡ ላይ፣ አካላዊ፣ ማሕበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ  እና ሥነልቡና ላይ ከፍተኛ በደል እና ስቃይ ያደረሰ፣ ሀገርን የበታተነ፣ ዳር ድንበርን የቆረሰ እና ያስቆረሰ፣ ዘረኛው የወያኔ መንግሥት፣ ስለሆነ፣ በምንም መልኩ ይሁን ከሥልጣን መወገድ አለበት፣ ሰለዚህ ለዚህ ዓላማ ከቆሙ በሰላማዊም ሆነ በትጥቅ ትግል ከሚያምኑ ድርጅቶችም ሆነ ግለሰቦች ጎን በመቆም የምችለውን ሁሉ ላበረክት ይገባኛል ብለው የሚያመኑት እና ወደ አደባባይም እየወጡ ያሉት ጥቂት የሚባሉ አይደሉም፡፡

በሐይማኖታዊ አመለካከት ምክንያት ለመንግሥት ባለሥልጣናትም ሆነ ለሕዝቡ መጸለይ እንጂ፣ ማመጽም መቃወመም አያገባኝም፣ ስለዚህ ራሱ ፈጣሪ፣ ወይም በሌሎች በኩል መላ እስከሚያመጣ ድረስ አኔ እርፌ  መቀመጥ አለብኝ ከሚሉት ሌላ፣ ሐይማኖታዊ አመለካከቴ ለወገን መከራ፣ ረሐብ፣ መሰደድ፣ መታሰር፣ መታመም፣ መታረዝ ግድ እንዲለኝ ያዘኛልና፣ ለዚህ በጎ ተግባር ከተሰማሩት ሁሉ ጎን በመቆም ማደረግ የሚገባኝን ሁሉ ማበርከት ይገባኛል ብለው በሚያምኑት መሐል፣ አንደኛው ራሱን ጻድቅ ሌላውን ሐጢያተኛ አድርጎ እንዲመለከት እና፣ ቤተ እምነቶችም በመንግሥት ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ስውር እና ገልጽ ሽኩቻ፣ በአገር ውስጥም በውጭም ምዕመናኑን ባለተቁዋረጠ ግራ መጋባት ውሰጥ እንዲዋከቡና፣  ማን ከማን ጋር መነጋገር ወይም አለመነጋገር፣ ማን ከማን ጋር ማህበራዊ ግንኙነት ሊኖረው እነደሚገባ፣ ወይም እንደማየገባ ፈርተው እና ተገድበው፣ የተቃዋሚ ወይም የደጋፊ መሪዎችን፣ ወይም የቤተ እምነቱን መሪዎች ባረኮት ካላገኙ እንዳይንቀሳቅሱ፣ ያገር ቤት ፖለቲካው መዘዝ በውጭም ያለውን ሕዝብ  የመኖር ነጻነቱን ገፍፎ የሕሊና እስረኛ እያደረገው ይገኛል፡፡

ከኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያውያን ጋር የተያያዘ ጉዳይ ላይ መካፈል፣ መስማት፣ መናገር ወይም በስብሰባ ላይ መገኘት ፖለቲከኛ ያስብለኝ ይሆናል በሚል ፍራቻ ፣ የሐይማኖት መሪዎች፣ ወይም የፖለቲካ ሰዎች ባሳደሩባቸው ተጽዕኖ፣ በፍርሐት ታስረው እንዲቀመጡ በወሰኑላችው አጥር ውስጥ ተደበቀው በመኖርየራሳቸውን ነጻነት በገዛ ፈቃዳቸው አስነጥቀው መኖር የሚፈለጉ እና  ፖለቲካ እና ፖለቲከኛነትን እንደ ወንጀል የሚመለከቱትም ደግሞ በሐገር ውስጠም በውጭም በፍርሕት እስር ቤት ውስጥ ወዶ ገባዎች ሆነዋል፡፡

ሕዝቡ በአንዱ ወይ በሌላው ምክንያት፣ ባገሩም ሆነ በተሰደደበትም ምድር በነጻነት እንዳይኖር፣ እንዳያስብ፣ እንዳይናገር፣ ሐሳቡን በነፃነት እንዳይገለጽ፣ በየስፍራው ራሳቸውን መለስተኛ ነገሥታት አድርገው በሾሙ ሰዎች ወይም ቡድኖች ባሳደሩበት ተጽዕኖ፣ በግልጽ እና በስውር የሥነ ልቦና ጫና ውስጥ እንዲቀመጥ መደረጉ ፈውስ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው፡፡

ስለዚህ ወዶም ሆነ ተገዶ ለዚህ ባርነት የተጋለጠ ሁሉ ፈውስ ያስፈልገዋል፡፡ ሁላችን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የዚህ ጥቃት ሰለባ ሆነናል፡፡ ራሳችንን ነጻ ሳናወጣ ሌላውን ነጻ ማውጣት እንደማንችል ማመን አለብን፡፡ በኢትዮጵያ ምድር ያለውን ችግር ለማቃለል፣ አገርን እየመሩ ያሉትም ሆነ ወደፊትም ለመምራት የሚፈለጉት ሁሉ ራሳችውን ከዚህ ባርነት ነጻ ማውጣት እና፣ በሌላውም ላይ የጫኑበትን ቀንበር ማውረድ ይኖርባቸዋል፣ በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት መሪዎች ምንም አይነት ስም ቢሰጣችው በአለም አቀፉ መድረክ ለጊዜውም ቢሆን አገሪቱዋን ወክለው የተቀመጡ ስለሆኑ፣ በአገር ውስጥም ሆን በውጭ በስደት ለሚኖረው ሕዝብ መከራ እና ስቃይ ግንባር ቀደም ተጠያቂ የሚያደረጋቸው መሆኑን አውቀው ማሰተካከል እንዲያደርጉ ምክር እንደተለገሳቸው፣ በአገር ውስም በውጪም ያሉ አማካሪዎቻቸው በአደባባይ እያጋለጡት ያለ ሚሰጥር ነው፡፡

እነእርሱም የሚከተላቸውን የበቀል ጅራፍ ከመፍራት ይመስላል፣ «ሥልጣን ወይም ሞት!» ብለው እንዲገፉበት እና ሰላማዊ የፖለቲካ ድርጀቶች እንኩዋን በሰላማዊ መንገድ የሚያደርጉትን አማራጭ እንቅስቃሴ በማፈን የሕዝብን ቁጣ እያባባሱና፣ የነገሮች አዝማሚያ ወደ ከፋ ሁኔታ እንዲቀጥል ጥርጊያ መንገዱን እያፋጠኑት ስለሚመስል፣ ላደረጉት መልካምም ሆነ ክፉ ነገር፣ ተጠያቂነታችውን በማመን፣ እነእርሱ ራሳቸው በየጊዜው ያጠፋውንም ሆነ ያላጠፋውን ሕዝብ ወይም ግለሰብ «ይቅርታ ጠይቁ! «እያሉ እንደሚያዙት ሁሉ ፣ እነርሱም ያጠፉ እና ሊያጠፉም የሚችሉ ሰዎች መሆናችውን በመገንዘብ፣ ሕዝብን ይቅርታ በመጠየቅ፣ በጨዋነት፣ ያገር መሪዎች ያባትነት ባሕሪን ተላበሰው፣ ወገንን በማስታረቅ ማገልገል ሲገባችው፣ የማሰተዳር አቅማቸውም ተሙዋጦ ካለቀባቸው፣ እና በሠላም ከሥልጣን መውረድ እንኩዋን ቢኖርባቸው፣ ትውልዱን መታደግ ተቀዳሚ ተግባር በማደርግ ለሠላም እጃቸውን ቢዘረጉ እና፣ ምድሪቱዋ ላለፉት አርባ ዐመታት በርካታ  ትውልድን ስትገበር የቆየችው ሳያንስ፣ ዛሬም የአንድ አገር ሕዝብ የሆነውና ወንድማማች ሕዝብ፣ እንደገና ሊጠፋፋ ሲያደባ እያዩ እና እየሰሙ በቸልታ ማለፍ የሕዝቡ ደም በእጃቸው መሆኑን ሊገነዘቡት ይገባል፡፡

ስለዚህ፣

ይህ ከላይ የጠቀስናቸው ልዩነቶች ሁሉ እንዳሉ ሆኖ፣ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ደረጃ በቅርቡ መላ የማይደረግለት ካልሆነ፣ እጅግ አሳሳቢና፣ የአደጋ ደመናም ያንዣበበባት በሚመስል፣ ወደ እርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ሊያስገቡ የሚችሉ ሁኔታዎች እየተመቻቹ እንደሆነ በርካታ ስጋቶች የሚጠቁሙ ሲሆን፣   ከችግሩም በመሸሽ ወገን አገር እየለቀቀ እና እየተሰደደ፣ በበረሐ እና በባሕር የሚያልቀው ሕዝብ እየተበራከተ፣ በአገር እና በውጭ እስር ቤት እየማቀቀ፣ ያለውን ሕዝብ ለመታደግ፣ ምንም አይነት የፖለቲካ፣ የሐይማኖት፣ የዘር አመለካካት ልዩነት ሳያግደን ፣ እያንዳንዱ በነፃነት እንዲያስብ፣ በነጻነት እንዲናገር፣ በነጻነት የፈለገውን ሊሰማ፣ በነጻነት፣ ሊንቀሳቀስ፣  ፈጣሪ አስቀድሞ የሰጥዎትን፣ በመቀጠልም በስደት ባሉበትም አገር የዲሞክራሲ መብት በሰጠዎ መብት ተጠቅመው፣ ሐሳብን በነፃነት በመለዋወጥ፣ መኖር መብትዎ  በመሆኑ፣ ያገባናል የሚሉ የፖለቲካ፣ የሲቪክ ድርጅቶች፣ የሐይማኖት ተቁዋማትም ሆኑ ግለስቦች የሚያደረጉት እንቅስቃሴ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ቢቅጥልም አለያም በውድም ሆነ በግድ ቢውርድም፣

  1. የምድሪቱን እና የሕዝቡን እጣ ፈንታ ጉዳይ ላይ በመመካከር፣ እንደ ሰው ልጅ በመከባበር እና በመደማመጥ፣ ወገን ከደረሰበት መከራና ስቃይ ለመፈውስ፣ ተቀራረቦ መነጋገር እና እርቅ ያስፈልጋል ብለን ስለምናምን፣ እርቁ ደግሞ ከራስ ጋር ከመታረቅ ጀምሮ፣ ከወገን ጋር ሕብረት እስከመፍጠር ድረስ የሚዘልቅ ስለሆነ፣ ሰው ሁሉ አንዱ ሌላውን በመፍራት፣ አንዱ ሌላውን ወገኑን በመሰለል፣ ሕጋዊ ባለሆነ የፍርሕት እስር ቤት ውስጥ ያለ ወገን ሁሉ ከዚህ የባርነት ሕመም መፈወስ አለበት ብለን ስለምናምን፣

 

  1. እርቅ ሲባል የተበዳይ ቁስል እና ሕመምን ከመፈወስ ይጀምራል እና፣ እስካሁን በሕዝቡ ላይ ለደረሰው መከራና በደል፣ ተጠያቂ ሊሆኑ የሚገባችው እና ወንጀል በመፈጸም በትውልዱ ላይ ለደረሰው መከራ ተጠያቂነት ያለባችው ሁሉ፣ ሕግ በሚፈቅድው መሰረት ወደ ፍርድ አደባባይ ሊያቀረቡዋችው በሚችሉ አካላት በኩል ሊወሰድ የሚገባውን እርምጃ፣ ለሕግ ባለሙያዎች፣ የፖለቲካውን እና የኢኮኖሚውን፣ጉዳይ እንዲሁ ለሚመለከታችው ባለሙያዎች በመተው፣ የተቀረው ሕዝብ ግን ወደ ሠላም፣ ወደ መፈቃቀር እና ወደ እርቅ የሚደረስበትን መንገድ ለማዘጋጀት ጥርጊያ መንገድ ማበጀት ያስፈለጋል ብለን ስለምናምን፣

በትውልድ በሐይማኖቶችና በዘሮች መካከል ያለው የመራራቅ እና የጥላቻ ሕመም ሊፈወስ ይገባዋል በሚል መርሆ፣ ማንኛውንም ዘር፣ የሐይማኖት፣ ወይም የፖለቲካ ድርጅትን የማይወክለው እና ዓለም አቀፋዊ አገልግሎት ያለው The Ark of the New Covenant Healing ministry  (የአዲስ ቃልኪዳን ታቦት የፈውስ አገልግሎት) www.adonairapha.org ከላይ በተጠቀሱት ሁለት ነገሮች ያምናል፡፡ እነዚህንም በተግባር ለመፈጸም የሚቻለውን ሁሉ እያደረገ ሲሆን በሌላ በኩልም ደግሞ «ከጎሳ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ እንስጥ» በሚል መርህ አቶ ኦባንግ ሜቶ የሚመሩት የአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ Solidarity Movement for a New Ethiopia www.solidaritymovement.org ለእርቅ፣ ለሰላምና ለፍትህ ካለው ዓላማ ጋር በመተባበር፣ «ለመተማመን እንነጋገር»  በሚል መሪ ሐሳብ ኢትዮጵያውያንን የሚያገናኝ መድረክ ከከፈተ ጥቂት ወራቶች ተቆጥረዋል፡፡እስካሁን በዋሽንግተን ዲሲ እና በሜኒሶታ ሁለት መድረኮችን ያዘጋጀ ሲሆን፣ ሶስተኛውን መድረክ ከፈውስ አገልግሎታችን ጋር በመተባበር በቅርቡ በኖርዌይ፣ ለማድረግ አስበናል ይህን መሳይ ጉባዔ ሲደረግ በምድረ አውሮፓ የመጀመሪያው ሲሆን፣ የውይይት መድረኩ በኖርዌይ ተጀምሮ በሌሎች ሀገራትም የሚቀጥል ሲሆን፣ ውይይታችን ሁሉ ከጥላቻ፣ ከበቀል፣ ከመናናቅ እና ከምሬት ነጻ የሆኑ ጉባዔዎችን በማድረግ ለወገኖቻችን ፈውስን ለማመጣት ቅድሚያ ሰጥተን እየሰራንበት ያለው ጉዳይ ነው፡፡

ስለዚህ በቅርቡ የተለያ አመለካከት ያላቸው ሰዎችን በመጋበዝ፣ በመፈራረስ ላይ ያለች ኢትዮጵያን ለማዳን እና በአገር ውስጥም ሆነ በውጭም ያለውን ሕዝብ ከደረሰበት የአካል እና የሥነልቦና፣ ጉዳት እንዲያገግም የሚያደረግ  ፈውስ ለትውልዱ ለማምጣት፣ ሌሎች ድርጅቶች እና ግለሰቦችን ከመውቀስ  ይልቅ፣ እኛስ ምን ማበርከት እንችላለን? ብለን ትውልዱን የመታደግ ምክር ለመመካከር፣ በዚህ አገር እና ትውልድን  የማዳን ጉበዔ ላይ እንዲገኙ በማክበር እየጋበዝንዎ! የስበሰባውን ስፈራ እና ተጋባዥ እንግዶችን  ስም ዝርዝር በተከታታይ እናስታውቃለን፡፡ ስለ ጉባኤው ያለዎትን አስተያየት በሚከተሉት ኢሜይል አድራሻዎች  ሊልኩልን ይችላሉ፡፡

የዚህን ደበዳቤ መልዕከት ሊያገኙዋቸው ለሚችሉዋቸው የመንግሥት መሪዎች እና ደጋፊዎቻቸው፣ ለመንግሥት ተቃዋሚዎች እና ደጋፊዎቻቸው፣ ለአያገባኝም ባዮች ሁሉ እንዲያደርሱልን በታላቅ ትሕትና እንጠይቃልን?

ከማክበር ሠላምታ ጋር

ሰዋሰው ስለሺ ዮሐነሰን

የአዲሰ ቃልኪዳን ታቦት የፈውስ አገልገሎት መስራችና መሪ

The Ark of the New Covenant Healing Ministry

www.adonairapha.org

mail@adoniarapha.org

ወይም

Obang Metho,
Executive Director of the SMNE
Phone 202 725-1616
Email:Obang@solidaritymovement.org
Website: www.solidaritymovement.org

 

ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውምማቴ. 9፣12

ከላይ የተጠቀሰው ቃል የሰውን ልጅ ክቡርነት በመረዳት፣ ለሰው ልጅ ሲል ሕይወቱን ሊሰዋ ወደ ዓለም የመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የሰዎች ችግር እና መከራ እየተሰማው ዘር፣ ጎሳ፣ ማሕበራዊ ማንነትን ሳይለይ፣ በአካልም፣ በአዕምሮም በሥነልቦናም ሕመም የደረሰባቸውን ሰዎች፣ ለመታደግ፣ ለማጽናናት እና ለመፈወስ በሚጉዋጉዋዝበት ጊዜ፣ የሌላውን ድካም እና ሐጢያት በማጉላት ራሳቸውን ጻድቅ አድርገው የሚመጻደቁ ፈሪሳውያውያን እና ቀሳውስት (የቤተ ዕምነት መሪዎች)፣ ከሐጢያተኛ እና ከቀራጮች ጋር ለምን ግንኙነት ያደርጋል? ብለው ሲከስሱት፣ “ፈሪሳውያንም አይተው ደቀ መዛሙርቱን። መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር አብሮ ስለ ምን ይበላል? አሉ ኢየሱስም ሰምቶ፣ “ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም” ነገር ግን ሄዳችሁ። ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ያለው ምን እንደ ሆነ ተማሩ፤ ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና አላቸው።»

የሕዝብዎ እና የአገርዎ ሕመም የሚሰማዎት ከሆነ ራስዎን አያግልሉ!

The post የአገርዎ፣ የግልዎ እና የሕዝብዎ ስቃይ እና ሕመም ያሳሰብዎታል? -የአዲስ ቃል ኪዳን ታቦት የፈውስ አገልግሎት appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢህአዴግ 98 ቢሊዮን ብር ነጠፈበት!! –“ታላቅ ሥራ ተሰርቷል! እናመሰግናለን!” ኦባንግ

$
0
0

birr4123111

ይህ ዘገባ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ዘገባ ነው

ኢህአዴግ በዓለም ባንክ በኩል ከእንግሊዝ የዓለምአቀፍ ልማት ተራድዖ መ/ቤት ሊለግስለት ታቅዶ የነበረው 4.9 ቢሊዮን ዶላር (98ቢሊዮን ብር) የገንዘብ ድጋፍ ነጠፈበት፡፡ አቶ ሬድዋን አልነጠፈብንም ይላሉ፡፡ ኦባንግ ሜቶ በበኩላቸው “የታላቅ ሥራ ውጤት ነው፤ እናመሰግናለን” ብለዋል፡፡

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ጥቅምት 2፤2005 (October 12, 2012) “ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!! ብያኔው ከጸና ኪሣራው በቢሊዮን ዶላር ሊደርስም ይችላል!” በሚል ርዕስ የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ያካሂድ ስለነበረው ፕሮግራም በዘገበበት ወቅት የሚከተለውን ዜና አትሞ ነበር፡- “ከ1998ዓም ጀምሮ የመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) በሚል በአራት ተከታታይና ሁለት ተጨማሪ የገንዘብ ድጎማ የሚደረግባቸውን ፕሮግራሞች የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ ይህ መሠረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን ለማሟላት ተወጥኖ የሚካሄድ ፕሮጀክት በትምህርት፣ በጤና፣ በእርሻ፣ በንጹህ ውሃ አቅርቦት፣ በገጠር መንገድ ሥራ፣ ወዘተ መስኮች ላይ እንዲውል (PBS I, PBS I-AF (Additional Financing), PBS II, PBS 11-AF, PBS-Social Accountability Program and PBS III) በማለት በተለያዩ ደረጃዎች ለተከፋፈለው ኦፐሬሽን ማስፈጸሚያ የሚውለው ገንዘብ ከ13ቢሊዮን ዶላር የሚበልጥ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛው የዓለም ባንክ ድርሻ 2ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የተቀረው በሌሎች ለጋሽ መንግሥታት እና ድርጅቶች የሚሸፈን ነው፡፡ PBS III የተሰኘውን በሦስት ንዑሳን ፕሮግራሞች የተከፋፈለውን ፕሮጀክት ለማስፈጸም በአጠቃላይ የሚፈጀው 6.3ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው፡፡”

ይህ ለመሠረታዊ ልማት እንዲውል በዓለም ባንክ በኩል የሚሰጠውን ገንዘብ የሚደጉሙት ምዕራባውያን አገራት ሲሆኑ አንዷ ተጠቃሽ አገር እንግሊዝ ናት፡፡ ሆኖም ኢህአዴግ ከምዕራባውያን በዓለም ባንክ በኩል የሚያገኘውን ገንዘብ ለራሱ የፖለቲካ መጠቀሚያነት እያዋለው መሆኑ ለዓለም ባንክ ተደጋጋሚ መረጃዎች ሲቀርቡ ቆይተዋል፡፡ በተለይ ሟቹ መለስ በቀጥታ በሰጡት ትዕዛዝ 424 የአኙዋክ ተወላጆች ከተገደሉ በኋላ ኢህአዴግ በቦታው ያሰማራው የመከላከያ ሠራዊት በሥፍራው የሚኖሩትን ከመኖሪያ ቀያቸው በማፈናቀል እምቢ ያሉትን በግድ በማስነሳት፣ በመግደል፣ አስገድዶ በመድፈር፣ በማሰቃየት፣ ወዘተ ግፍ ሲፈጽም መቆየቱ በተለያዩ ዓለምአቀፋዊ ዕውቅና ባገኙ ዘገባዎች ሲነገር ቆይቷል፡፡ የዓለም ባንክ ለመሠረታዊ ልማት በማለት የሚሰጠው ገንዘብ ኢህአዴግ ወታደሮቹን የግፍ ሥራ ላይ በማሰማራት ደመወዝ የሚከፍልበት መሆኑን በመጥቀስ ወደ ኬኒያ የተሰደዱ የክልሉ ነዋሪዎች አቤቱታ አቅርበው እንደነበር ጎልጉል በወቅቱ የዘገበው ዜና ነበር፡፡ ““ኢህአዴግ አንገቱን ታንቋል”፤ዓለም ባንክ ርምጃ ለመውሰድ ጫፍ ደርሷል” በሚል ርዕስ የተጻፈውን ዜና ለማንበት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡

money lostከዚሁ ጋር በተያያዘ “ሚስተር ኦ” በመባል የሚጠሩት አኙዋክ ተወላጅ ኢህአዴግ የዕርዳታ ገንዘብ ለሰብዓዊ መብት ረገጣና ለራሱ የፖለቲካ መጠቀሚያነት እንዳዋለው በመጥቀስ የእንግሊዝ መንግሥት ከግብር ከፋይ ዜጎቹ የሚያገኘውን ገንዘብ አምባገነንነት እየደገፈበት መሆኑን በተለይም የዓለምአቀፍ ልማት ተራድዖ መ/ቤቱ ተጠያቂ ስለሆነ ከዚህ እንዲታቀብ ክስ መመሥረታቸው ይታወቃል፡፡ የክሱ ሒደት እየተካሄደ ባለበት ባሁኑ ወቅት ሚስተር ኦ በተደጋሚ እንደመሰከሩት ኢህአዴግ ነዋሪዎችን በግዳጅ ከቀያቸው በማፈናቀል የሚያካሂደው የግዳጅ ሰፈራና የመንደር ምሥረታ ሕገወጥ መሆኑ በመቃወማቸው በተደጋጋሚ ከፍተኛ ድብደባ እንደረሰባቸው ተናግረዋል፡፡ ብዙዎች ለአካላዊ ሥቃይ ደርሶባቸዋል፣ ሴቶች ክብረንጽህናቸው ተደፍሯል፣ አዛውንትና ህጻናት ለአሰቃቂ መከራ ተዳርገዋል፤ ይህንንም እርሳቸው እንዳዩ ሚስተር ኦ ይመሰክራሉ፡፡

የሚስተር ኦ የፍርድቤት ጉዳይ ወደ ውሳኔ ሊደርስ ባለበት ወቅት የልማት መ/ቤቱ ይህንን ዓይነት ውሳኔ መውሰዱ ከፍርድ ቤቱ ጉዳይ ጋር የሚያያዝ እንደሆነ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ይናገራሉ፡፡ የልማት ተራድዖ መ/ቤቱ ቃል አቀባይ ግን የመ/ቤታቸው ውሳኔ ከሚስተር ኦ የፍርድቤት ጉዳይ ጋር ያልተያያዘ እንደሆነ መናገራቸውን የእንግሊዙ ዘጋርዲያን ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ መ/ቤቱ ለዚህ ውሳኔ የደረሰው ኢትዮጵያ “የዕድገት ስኬት” እያስመዘገበች በመምጣቷ የመሠረታዊ ልማት አገልግሎት የገንዘብ ዕርዳታ የማያስፈልጋት በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

ይህ መጠኑ እጅግ ከፍተኛ የተባለውና ለኢህአዴግ ንጹህ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ የሚያስገኝ ገንዘብ እንደነጠፈበት መሰማቱን አስመልክቶ ጋዜጣው የኢህአዴግ ፅ/ቤት ሃላፊ የሆኑትን ሬድዋን ሁሴን በጠየቃቸው ወቅት የመለሱት አልነጠፈብንም የሚል እንድምታ ያለው ነው፡፡ “እነርሱ ያሉት ዕርዳታውን አንሰጥም ወይም እናቆማለን ሳይሆን ዕርዳታ አሰጣጡ እንደገና ይዋቀራል ነው” በማለት ሬድዋን ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ ሆኖም 4.9 ቢሊዮን ዶላር (98ቢሊዮን ብር) ዕርዳታ ለመስጠት ከዓለምባንክ ጋር ስምምነት የነበረው የእንግሊዝ የልማት ተራድዖ መ/ቤት “ኢትዮጵያ አድጋለች” በማለት በ2015/2016 በፓውንድ 256ሚሊዮን ብቻ (5በመቶ) ዕርዳታ ለመስጠት መወሰኑን የኢህአዴግ ጽ/ቤት ሃላፊው ሬድዋን ሁሴን አላብራሩም፡፡

ኢህአዴግ ለዕርዳታ የሚሰጠውን ገንዘብ ዜጎችን ለማሰቃየት፣ ወታደር ለመቀለብ፣ ወዘተ እንደሚጠቀምበት በተደጋጋሚ ዘገባዎች እና ማስረጃዎች ሲወጡበት የከረመ ቢሆንም ማስረጃዎቹን ተከትሎ የዓለም ባንክ በዕርዳታ አሠጣጡ ላይ አንዳች ውሳኔ እንዳያደርግ ብዙ ሲደክም ቆይቷል፡፡ በዚህም ምክንያት ጉዳዩ ውሳኔ ሳይሰጥበት እንዲስተጓጎል በማድረግ ለሁለት ዓመታት ያህል እንዲጓተት ማድረጉን ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸው ወገኖች ይመሰክራሉ፡፡

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ኦባንግ ሜቶ ጉዳዩን ገና ከጅምሩ የሚያውቁትና ድርጅታቸው ለዓመታት ሲሰራበት የነበረ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ በመሆኑንም ይህንን የእንግሊዝ የልማት ተራድዖ መ/ቤት ውሳኔ የጋራ ንቅናቄያቸው ከደጋፊዎቹ ጋር በመሆን ያገኘው ድል እንደሆነ በፌስቡክ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል፡፡ “ገና ከጅምሩ ከጋራ ንቅናቄያችን ጋር በመሆን ይህንን ሥራ በመደገፍ የተባበራችሁንን ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ፤ ታላቅ ሥራ ተሰርቷል፤ እናመሰግናለን” ብለዋል “ጥቁሩ ሰው” ኦባንግ ሜቶ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ አቶ ኦባንግ በተለይ ከጎልጉል ለቀረበላቸው አጭር ጥያቄ በሰጡት አስተያየት የጋራ ንቅናቄያቸው ደስታውን የገለጸው የልማት ገንዘብ በመቋረጡ ሳይሆን በልማት ስም የሚሰጠው ዕርዳታ ለሰብዓዊ መብት ረገጣ በመዋሉና ለዚህም ደግሞ ከበቂ በላይ ማስረጃ ድርጅታቸው ያለው በመሆኑ ነው፡፡ “አገር ብትለማ የሁሉም ደስታ ነው” ያሉት ኦባንግ አገርን በማልማት ሽፋን ደጋፊና ተቆርቋሪ የሌላቸውን ንጹሃን መበደልና የመኖር መብታቸውን መንፈግ ግን በየትኛውም መልኩ እርሳቸውም ሆነ አኢጋን የሚቀበለው እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

ኢህአዴግ በቅርቡ አካሂዳለው ለሚለው ምርጫ እንደ ዕቁብ ዕጣ በማውጣትና በማስወጣት “አልደረሳችሁም” እያለ የተቀናቃኝ ፓርቲ አመራሮችን ከምርጫ እያስወገደ ባለበት፤ ሌሎችንም ሕጋዊ አይደላችሁም እያለ በተለጣፊ ድርጅት በማስበት ኅልውናቸውን እያሳጣ ባለበት ባሁኑ ወቅት በዜጎቹ ላይ የሚያካሂደውን መረን የለቀቀ የመብት ገፈፋ ለሥልጣን ያበቁትን ምዕራባውያንን ያስደሰተ እንዳልሆነ ይነገራል፡፡ የአውሮጳ ኅብረት ምርጫውን አልታዘብም ከማለቱ በተጨማሪ በሚዲያ ላይ የተጫነው አፈና በዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ይፋ ከሆነ ወዲህ ማነቆው በኢህአዴግ ላይ እየከረረ መምጣቱን ያሳያል፡፡ ኢህአዴግን ለሥልጣን ከማብቃት አልፋ ነፍጥ አንጋቢዎቹን የህወሃት መሪዎች ጸጉርና ጺም ከርክማ፤ ልብስ አልብሳ፤ ቋንቋ አስተምራ፤ የከተማ አኗኗር እንዴት እንደሆነ አሠልጥና፣ ቶሎ ባይገባቸውም ፕሮቶኮል አስተምራ፣ እስካሁንም ተንከባክባ እዚህ ድረስ ያቆየቻቸው እንግሊዝ እንዲህ ያለውን የውጭ ምንዛሪ ምንጭ ስታደርቅ “ቀጣዩስ ምን ይሆን?” የሚል ጥያቄ እንዲነሳ አድርጓል፡፡ “ምዕራባውያን መግደልም ማንሳትም ያውቁበታል” በማለት አስተያየት የሚሰጡ ወገኖች እንደሚሉት ቀጣዩ የኢህአዴግ ጉዞ በከፍተኛ ሁኔታ ለህወሃት ሲቀጥል ለኢህአዴግ አስጊ ከመሆን ባሻገር በውጭ ምንዛሪ እጥረት በየጊዜው የሚፈጠረውን ግሽበት በዕርዳታ ገንዘብ የሚያስተካክለው ኢህአዴግ እንዲህ ያለው የገንዘብ ማዕቀብ ክፉኛ ያነጥፈዋል ሲሉ ግምታቸውን ይሰጣሉ፡፡ ሙስናው መረን በለቀቀባት አገር ከሕዝብ እየተዘረፈ በተለያዩ አገራት ባንኮች በውጭ ምንዛሪ የሚከማቸውን ገንዘብ በሚካፈሉትም ላይ የድርሻ ቅነሳ የማስከተሉ ጉዳይ አብሮ የሚታይ እንደሆነ ይነገራል፡፡

ከዚህ ዜና ጋር ተያያዥነት ያለውን ጥቅምት 2፤2005 (October 12, 2012) ያተምነውን ዜና ከዚህ በታች እንደሚከተለው እንደገና አትመነዋል፡፡

ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!!

ብያኔው ከጸና ኪሣራው በቢሊዮን ዶላር ሊደርስም ይችላል!

ኢህአዴግ ከዓለም ባንክ ያገኘውን 600 ሚሊዮን ዶላርና በተመሳሳይ ፕሮጀክት ወደፊት ሊያገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ገንዘብ በተመለከተ አደጋ ውስጥ መውደቁ ተሰማ። ኢንስፔክሽን ፓናል (Inspection Panel – IP) የተሰኘ ተቋም ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው ኢህአዴግ የቀረበበት ውንጀላ ከተረጋገጠ የሚያጣው ገንዘብ በቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ታውቋል። ይፋ የሆነውን መረጃ አስመልክቶ ከኢህአዴግ ወገን እስካሁን በይፋ የተሰጠ ምላሽ የለም።

ግፍ የሚፈጽሙ መንግስታትን፣ በልማት ስም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጽሙ ወንጀሎችን መረጃዎችን በስፍራው በመገኘትና ከመሠረቱ ዘልቆ በመግባት አደራጅቶ ተጠያቂ የሚያደርገው ኢንክሉሲቭ ዴቨሎፕመንት ኢንተርናሽናል Inclusive Development International (IDI) ከሰለባዎቹ ውክልና ተሰጥቶታል። ተቋሙም በውክልናው መሰረት ለኢንስፔክሽን ፓናል በዝርዝር የሰለባዎቹን በደል በማተት አሳውቋል።

የኢህአዴግ መከላከያ ሠራዊት የሚያደርሰውን እስራት፣ ግርፋት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ከመኖሪያ ቦታ ማፈናቀል፣ የግዳጅ ሰፈራ ወዘተ በማምለጥ ወደ ኬንያ የተሰደዱ የጋምቤላ ነዋሪዎች ይህ ሁሉ ግፍ የሚፈጽምባቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በልማት ስም ከዓለም ባንክ በሚያገኘው የዕርዳታ ገንዘብ በመሆኑ ለባንኩ በላኩት የአቤቱታ ደብዳቤ አመልክተዋል።

አቤቱታውን መሠረት በማድረግ የሚደረገው ምርመራ ውጤት ይፋ ሲሆን፣ በሌሎች አገሮች እንደተደረገው በዕርዳታ ስም የሚገኝን ገንዘብ ኢህአዴግ ለፖለቲካ ተግባር መጠቀሙ ሲረጋገጥ፣ በመስከረም ወር መጀመሪያ አካባቢ ከዓለም ባንክ ተፈቅዶ የነበረው 600ሚሊዮን ዶላር ሊከለከል ይችላል፡፡

የዛሬ ዘጠኝ ዓመት አካባቢ በሟቹ ጠ/ሚ/ርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ መለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትዕዛዝ በጋምቤላ ክልል በተለይ የተማሩ ወንዶች ላይ በማተኮር 424 ንጹሐን የአኙዋክ ተወላጆች በተገደሉበት ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩት ወደ ጎረቤት አገር ኬንያ መሰደዳቸው ይታወሳል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ክልሉ ሰላም የለም፡፡ በየጊዜውም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሲካሄዱበት ቆይቷል፡፡ በተለይም ለም የሆነውን እጅግ ሰፋፊ መሬት ለውጪ ባለሃብቶች በሳንቲም በመሸጥ ላይ የሚገኘው የኢህአዴግ አገዛዝ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቀድሞው የደርግ ዘመን ሲካሄድ ከነበረው ባለፈ መልኩ እጅግ በሚያሰቅቅ ሁኔታ በመንደር ምስረታና አስገድዶ የማስፈር ፖሊሲ ከመኖሪያ ቀዬ የማፈናቀል ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን የኦክላንድ ተቋም፣ ሂውማን ራይትስ ዎች፣ … የመሳሰሉ ድርጅቶች ያወጧቸው ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡

ከ1998ዓም ጀምሮ የመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) በሚል በአራት ተከታታይና ሁለት ተጨማሪ የገንዘብ ድጎማ የሚደረግባቸውን ፕሮግራሞች የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ ይህ መሠረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን ለማሟላት ተወጥኖ የሚካሄድ ፕሮጀክት በትምህርት፣ በጤና፣ በእርሻ፣ በንጹህ ውሃ አቅርቦት፣ በገጠር መንገድ ሥራ፣ ወዘተ መስኮች ላይ እንዲውል (PBS I, PBS I-AF (Additional Financing), PBS II, PBS 11-AF, PBS-Social Accountability Program and PBS III) በማለት በተለያዩ ደረጃዎች ለተከፋፈለው ኦፐሬሽን ማስፈጸሚያ የሚውለው ገንዘብ ከ13ቢሊዮን ዶላር የሚበልጥ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛው የዓለም ባንክ ድርሻ 2ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የተቀረው በሌሎች ለጋሽ መንግሥታት እና ድርጅቶች የሚሸፈን ነው፡፡ PBS III የተሰኘውን በሦስት ንዑሳን ፕሮግራሞች የተከፋፈለውን ፕሮጀክት ለማስፈጸም በአጠቃላይ የሚፈጀው 6.3ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ የባንኩ ድርሻ የሆነውን 600ሚሊዮን ዶላር ቦርዱ መስከረም 5ቀን 2005ዓም አጽድቋል፡፡

በአስገድዶ ማስፈር፣ መንደር ምስረታና ሌሎች በርካታ የሰብዓዊ መብቶቻቸው የተጣሱባቸው በኬንያ የሚገኙ ሦስት የአኙዋክ ስደተኞች ተወካይ ድርጅቶች በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ ሌሎች የሰብዓዊ ድርጅቶች ጋር በመሆን ባንኩ ሊሰጥ የወሰነውን ገንዘብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም ከመዋል ይልቅ ለኢህአዴግ የፖለቲካ ዓላማ ማስፈጸሚያ እየዋለ መሆኑን በመጥቀስ ለባንኩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጂም ዮንግ ኪም መስከረም 6፤ 2005ዓም ደብዳቤ ልከዋል፡፡ በጥያቄያቸውም መሠረት በዓለም ባንክ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የሚፈሰው ገንዘብ “በልማት ስም የኢትዮጵያ መንግሥት በጋምቤላ ክልል ለሚያካሂደው የመንደር ምስረታ እየዋለ ነው” በማለት ይከሳል፡፡ ሲቀጥልም የአኙዋክ ሕዝብ ለዘመናት ከኖረበት መንደር በማፈናቀል “የተሻለ አገልግሎት ይሰጣችኋል” በማለት በግድ የማስፈር ተግባር እየተፈጸመ ሲሆን “የተባለው አገልግሎትም ሆነ ለእርሻ የሚሆን በቂ ቦታ እንዲሁም ለከብቶች የሚበቃ የግጦሽና የውሃ ቦታ የላቸውም” በማለት ሰፈራውን የተቃወሙ ሁሉ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ረገጣ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡ ይህንን ግፍ የሚፈጽሙት ደግሞ የዓለም ባንክ ለመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) ስም ለልማት እንዲውል ከሚሰጠው የዕርዳታ ገንዘብ በመንግሥት ተቀጥረው ደመወዝ የሚከፈላቸው ሠራተኞች መሆናቸውን ገልጾዋል፡፡ ይህንን ጉዳይ ከዓለም ባንክ ጋር እንዲነጋገሩላቸው Inclusive Development International (IDI) የተባለውን ድርጅት መወከላቸውን አስታውቀዋል፡፡ (የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)

ተመሳሳይ ጉዳዮችን በዓለምአቀፍ ደረጃ በመከታተልና በማስፈጸም የታወቀው IDI በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከተው የመልሶ ማቋቋምና ልማት ዓለምአቀፍ ባንክና (International Bank for Reconstruction and Development (IBRD)) የዓለምአቀፍ ልማት ማኅበር (International Development Association (IDA)) ሥር ለሚገኘው የኢንስፔክተር ፓናል ባለ 18ገጽ ደብዳቤ ጽፏል፡፡ (የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል) ይህ የኢንስፔክተር ቡድን ከፍተኛ ሥልጣን ያለው መ/ቤት ሲሆን የዓለም ባንክ የሚሰጠውን ገንዘብ በትክክለኛ ቦታ ላይ አለመዋሉን በመጥቀስ ክስ የሚያቀርቡ ወገኖችን ጉዳይ በመከታተልና ቦታው ድረስ የራሱን ምርመራ በማካሄድ ውጤቱ ተግባራዊ እንዲሆን የባንኩን እጅ የማስጠምዘዝ ዓቅም ያለው እንደሆነ ከዚህ በፊት ያካሄዳቸው የምርመራ ውጤቶች ይጠቁማሉ፡፡

ይህ የመርማሪ ቡድን የቀረበለትን አቤቱታ መቀበሉንና በጉዳዩ ላይ የማንም ተጽዕኖ የማይደረግበትን የራሱን ምርመራ እንደሚያደርግ ከትላንት በስቲያ ባወጣው ባለ 8ገጽ መግለጫ ላይ አሳውቋል፡፡ ይህ የአቤቱታ ፋይል ቁጥር የተሰጠው ጉዳይ በግልባጭ ለባንኩ ፕሬዚዳንትና ለከሳሽ ተወካይ ድርጅት (IDI) እንዲደርስ ተደርጓል፡፡(የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)

ጎልጉል የሰሜን አሜሪካ ዘጋቢ ባጠናከረው መረጃ መሠረት ቡድኑ ከያዝነው ዓመት የጥቅምት አጋማሽ በኋላ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ያቀናል። ቡድኑ ስደተኞቹ የሚገኙባቸውን፣ እንዲሁም ጉዳዩን በሚመለከት አስፈላጊ የሚላቸውን ቦታዎችና ግለሰቦች ሙሉ በሙሉ ያነጋግራል። ለስራው መሳካት የሚሆነውን ሁሉ በሚፈለግበት ቦታ በመገኘት በግንባር እንደሚያከናውን ለማወቅ ተችሏል።

በተለያየ ጊዜ ኢህአዴግ የሚፈጽመውን ግፍና በደል በማደራጀት ሥርዓቱ ላይ ከትጥቅ የጠነከረ ትግል ማካሄድ እንደሚቻል አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል:: አያይዘውም በመላው አገሪቱ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣና የመብት ጥሰት በማሰባሰብ የኢህአዴግን የገንዘብ ምንጭ የማድረቅ፣ ብሎም በእርዳታ ገንዘብ የሚገነባቸውን የአፈና ተቋማት ማስለል እንደሚቻል አስታውቀዋል። ይህንን ታላቅ ስራ የሰሩትን አካላት ልምዳቸውን ለሌሎች በማካፈል አስፈላጊውን ስራ ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል። (የመግቢያው ፎቶ የተወሰደው: ዘጋርዲያን)

 

Source: ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

The post ኢህአዴግ 98 ቢሊዮን ብር ነጠፈበት!! – “ታላቅ ሥራ ተሰርቷል! እናመሰግናለን!” ኦባንግ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>