Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

ሪክ ለመስራት እንዘጋጅ –አቶ ተክሌ በቀለ የአንድነት ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር

$
0
0
ተክሌ በቀለ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት

ተክሌ በቀለ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት

አንድነት ፓርቲ የኢህኣዴግን ምንነት ላላመኑ ወገኖች ለማጋለጥ በትጋትና በስሌት ሲሰራ ቆይቷል፡፡እየሰራም ነዉ፤እዚህ ደርሷል፡፡ “የሆደ ሰፊዉን ምርጫ ቦርድ” ሆድ በገሃድ አጋልጧል፡፡በነአሞራዉና ወዲ ቐሺ(በተጋሩ ሁሉ) ትግልና ሞት የሚቀልዱትን በህዝብ ፊት ወጥተዉ ዛሬም እንዲዋሹና ለኢትዮጵያችን የፖለቲካ ታሪክ እነማን ምን እንደሆኑ አንድነት ፓርቲ የበኩሉን ሚና ተጫዉቷል፡፡ ለኔ ከባድመ ዉሳኔና ልህዝቡ በወቅቱ ከተነገረዉ ጋር ይመሳሰላል፤ይጠጋጋል፡፡ኢህኣዴግ ምርጫዉን እንደማይፈልገዉ፤ከፈለገዉም ለተለመደዉ ቀልዱ ከነማን ጋርና በምን ሁኔታ እንደሚፈልገዉ ፓርቲያችን ሶስተኛዉን (የአዉሮፓና አሜሪካ ታዛቢዎች የሌሉበት ምርጫ መሆኑን፤የህዝብ ታዛቢዎች የተበላሸ የምርጫ ሂደትና ፓርቲዎችን የማፈራረስ/የማዳከም ስራዎች) ነጥብ አስመዝግቧል፡፡

በዚህ ሂደት ላይ ሰፊ እዉነታ ለህዝብ ይቀርባል የሚል እምነት አለኝ፡፡ከምርጫዉ ቦርድ መጋረጃ ካሉት ወገኖች ጋር በሃሳብ እየተሸነፈ ግን ተሳትፎዉ ያለተቋረጠ አንድ ከፍተኛ አመራር እንዳለ እናዉቃለን፡፡ሁሉን ነገር በደንብና በመርህ የምንሰራዉ ለኢህኣዲግ/ምርጫ ቦርድ ካለን ፍርሃት ሳይሆን ለወደፊቱ ለምናስተዳድረዉ ህዝባችንና ለኢትዮጵያችን ፖለቲካ ክብር ስንል ነዉ፡፡እናም ከደንብ ወጥተን የሰራነዉ ክዋኔም በግፍ የገፋነዉ አመራርም፤አባልም የለም፡፡በመቻቻል መንፈስ ዲሰፒሊን ተጥሶም እንዲጓተት ተደርጓል፡፡ይህንንም የኢህኣዴግ ተባባሪነት ለታሪክ አስቀምጠነዋል፡፡

ምርጫ ቅንጦት ሆኖብን፤የተከበሩ እየተባሉ ለመጠራት ሳይሆን እፊታችን ላይ ያለ እድልና ስልትም ስለሆነ አንድነት ፓርቲ መጪዉን ምርጫ የምር እንዲሆን ወስኗል፡፡ ኢህኣዴግ ደግሞ ማበላሸቱን ተያያይዞትል፡፡ምርጫ በአምባገነን ቡድኖች ለሚገዙ አገራት ለለዉጥ እንዱ ስልት እንጂ ብቸኛዉ አለመሆኑ ይታመናል፡፡ፓርቲያችን ለለዉጥ ተደራጅም ይላል፡፡እዉነተኛ ፓርቲዎች ከምርጫዉ ባሻገር ላለዉ ግብ እንዲዋሃዱና እንዲተባበሩም ጥሪ አቅርቧል፤ስልቶችን ለማቀራረብም እየጣረም ነዉ፡፡የአንድነት ኣባላት በያለንበት ድርብ ሃላፊነት አለብን፡፡ለአንድነት ሃይሎች ስልቶቻችን ሁሉ በማቀራረብ የተጀመረዉ የስልጣን ሃይሎችን እያራገፉ ትግሉን በሰለጠነና አንድነቱን በጠበቀ መልኩ የማስቀጠልና ልዩነቶችን በማቻቻል ሰፊ መሰረት የማንበር ሃለፊነት አለብን፡፡ ታሪክ ለመስራት እንዘጋጅ፤ፊታችንን ወደ ዋናዉ ግብ እናድርግ፤ከሃዲዱ አንወርድም!


የውድ ኮሚቴዎቻችን የሰው ምስክር የማሰማት ሂደት በዛሬው ዕለት ተጠናቋል!

$
0
0

ፈኢዝ መሀመድ ለታሪክ ምሁሩ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል፣ ለኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋ፣ እንዲሁም ለኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ምስክርነቱን ሰጥቷል!

ማክሰኞ ታህሳስ 28/2007

የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎቻችን ችሎት ከግንቦት 5/2006 ጀምሮ አቃቂ ክፍለ ከተማ በሚገኘውና በተለምዶ ‹‹08 አዳራሽ›› ተብሎ በሚጠራው ቦታ የመከላከያ ምስክራቸውን ማስደመጥ ከጀመሩ በኋላ የፍርድ ሂደቱ ሰሚት አካባቢ በሚገኘው በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት እንዲከታተሉ ሲደረግ የቆየ መሆኑ ይታወሳል፡፡ በዚሁም መሰረት ከግንቦት 5/2006 ጀምሮ የመከላከያ ምስክራቸውን ሲያስደምጡ የቆዩ ሲሆን የዛሬውን ጨምሮ በአጠቃላይ 153 ምስክሮችን አስደምጠው የሰው የመከላከያ ምስክሮቻቸውን በዛሬው ዕለት አጠናቅቀዋል።

10923644_887061558011868_2343527696380665851_n
በዛሬው ችሎት ምስክርነቱን ለሶስት የኮሚቴው አባላት የሰጠው ፈኢዝ ሙሀመድ ሲሆን የመጀመሪያውን ምስክርነቱን ለታሪክ ምሁሩ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል አሰምቷል፡፡ አቃቤ ህግ በኡስታዝ አህመዲን ጀበል ‹‹ኢሜል ውስጥ አገኘሁት›› ብሎ ያቀረበው መረጃ እርሱ የጻፈው እንዳልሆነ ያስረዳው ፋኢዝ ሙሃመድ የተባለውን ኢሜል ለኡስታዝ አህመዲን የላከለት ራሱ መሆኑን እና ኢሜል ያደረገውም ከሰለፊያ ጋዜጣ፣ ከኢቲቪ፣ እንዲሁም ከተለያዩ ጋዜጦችና መፅሄቶች ያገኘውን መረጃ መሆኑን ገልጿል፡፡ ከላካቸው ጽሁፎች ውስጥም በወቅቱ የመጅሊስ አካላት ሲናገሩ የነበሯቸውን ንግግሮች እና መጅሊስ የአህባሽ ስልጠና መስጠቱን የሚያመለክቱ መረጃዎች መኖራቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።
ፋኢዝ ቀጣይ ምስክርነቱን የሰጠው ለኡስታዝ ካሚል ሸምሱ እና ለኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋ ሲሆን ኡስታዞቹ ለስሜት አለመገዛትን፣ እውቀት በኢስላም ያለውን ቦታ እና ሃይማኖታዊ መቻቻልን እና እኩልነትን አስመልክቶ ከሰጧቸው ትምህርቶችና ስለጠናዎች ጋር በተያያዘ የቀረበባቸውን ክስ በማስመልከት ክሱን አስተባብሎ ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡ ከአቃቤ ህግ ለቀረበለት መስቀለኛ ጥያቄም በአግባቡ መልስ ሰጥቷል።

644398_887061511345206_3213473828817844196_n

በዛሬው ዕለት ለውድ ኮሚቴዎቻችን ሊመሰክር የነበረው ሁለተኛ ምስክር ላፕቶፕ ኮምፒዩተሩ ከማዕከላዊ ስላልመጣ የቪዲዮ ማስረጃ በሚያቀርቡበት ወቅት አብሮ ምስክርነቱን እንዲሰጥ ትዕዛዝ የተሰጠ ሲሆን የሰው ምስክርነት የማሰማት ሂደቱም ዛሬ ማብቃቱ ታውቋል፡፡ ውድ ኮሚቴዎቻችን ቅሬታዎች እንዳሉባቸው በማሳወቅ አቤቱታ ለማቅረብ ያደረጉት ሙከራም ‹‹በቢሮ በኩል ቀርባችሁ አስረዱ›› በሚል ተቀባይነት አለማግኘቱ ታውቋል፡፡

ቀጣዩ ቀጠሮ የፊታችን ሰኞ ጥር 4/2007 ነው።
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!

ድምፃችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

ለመላው የክርስትና ኃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፥ –ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

$
0
0

እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፪ሺህ፯ኛ የልደት በዓል አደረሳችሁ!

moreshነገ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድራችን በአካል የተገለጸበትን ፪ሺህ፯ኛ ዓመት እናከብራለን። እግዚአብሔር ወልድ በምድር በአካል ከእኛ ጋራ በታየበት ዘመን ያስተማረን ትልቁ ቁምነገር ፍቅርን ነው። በተቃራኒው እኛ የዘመኑ ኢትዮጵያውያን በመካከላችን ፍቅር ጠፍቶ እንበጣበጣለን። በስደት የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ሌላው ቀርቶ በእምነቱ ሥፍራ እንኳን ሰላም ካጣ ቆይቷል። የዚህ ሁሉ ብጥብጥ እና ፍቅር መጥፋት ምንጩ የትግሬ-ወያኔ እና እሱን መሰል ፀረ-ኢትዮጵያ ዓላማ ያላቸው ድርጅቶች እና ልሂቃን ናቸው። ስለዚህ እኒህን የጥፋት ኃይሎች በጋራ ትግላችን ግስጋሴያቸውን ልናቆመው ይገባል። ክርስቲያኖች ከኢየሱስ ክርስቶስ ምሣሌ መማር ካልቻልን እና ካልተፋቀርን መከራችን ይረዝማል፣ ሥቃያችንም አያባራም። የትግሬ-ወያኔ እና መሰል አጋሮቹም እንደሠለጠኑብን ዘመናት ይቆጠራሉ።

ለዚህ መፍትሔው ፈጣሪያችን በፍርድ ቀን ሲመጣ የሚጠይቀንን ጥያቄዎች፥ ማለትም፦ “ስታመም ጠይቃችሁኛል? ስራብ አብልታችሁኛል? ስታረዝ አልብሳችሁኛል? ስታሠር አስፈትታችሁኛል? ስጠማ አጠጥታችሁኛል?” የተባሉትን ሠርክ እናስታውስ፣ በተቻለንም መጠን የሕይዎት መመሪያዎቻችን ለማድረግ እንጣር።

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የክርስትና ኃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያንን እንኳን ለበዓለ-ልደቱ አደረሣችሁ፣ አደረሰን፣ ይላል። በዚህ አጋጣሚ ድርጅታችን ማስተላለፍ የሚፈልገው ጥሪ፦ ባለፉት ፳፬(ሃያ አራት) ዓመታት በትግሬ-ወያኔ ግፈኛ እና ናዚያዊ አገዛዝ ከምድረ-ገፅ የጠፉትን በቁጥር ከ፭(አምሥት) ሚሊዮን የማያንሱ ዐማሮች እናስታውስ። በገዛ አገራቸው ከቅኝ ተገዢዎች በከፋ መልክ ሰብዓዊ መብቶቻቸውን የተነጠቁትን ኢትዮጵያዊ ዐማሮች እንታደግ።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን ይባርክ!

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

ኮማንደር ቢኒያም ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን በድቅድቅ ጨለማ ብርድ ላይ እያስተኛው በማሰቃየት ላይ ነው

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በካንጋሮው ፍርድ ፍትሃዊ ባልሆነ ፍርድ እስር ቤት የተወረወረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ ፍርድ ቤት በማያውቀው ሁኔታ በአንድ የህወሓት ኮማንደር በእስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰበት እንደሚገኝ ከስፍራው ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ።

Temesgen Desalegn behindbarኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ማን እንደሚመራት በማይታወቅባት ሁኔታ አንድ ደህንነት ወይም ወታደር የፈለገውን የማዘዝ ስልጣን ያለው ሲሆን እንገዛለታለን የሚሉትን ህገመንግስት ወደ ጎን በመተው የፈለጋቸውን እርምጃ እየወሰዱ በመሆኑ በስር ዓቱ ውስጥ ያለውን አለመደማመጥ ያሳያል የሚሉ የፖለቲካ ተንታኞች በቅርቡ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን በአንድ ደህንነት ት ዕዛዝ ብቻ ለ3 ሳምንታት ከሃገር እንዳይወጣ ፓስፖርቱን መቀማቱን ያስታውሳሉ።

በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ በዝዋይ እስር ቤት እየደረሰ ያለው ስቃይ ኮማንደር ቢኒያም በሚባል አዛዥ ሲሆን ተመስገንን በአንድ ምሽት ከ5 ጊዜ በላይ በድቅድቅ ለሊት በማስወጣት ብርድ ላይ እንደሚያስተኙት ከስፍራው የደረሰው መርጃ ያጋልጣል።

በተለይ ተመስገን ደሳለኝ “የመንግስት ገመና” በሚል ከእስር ቤት ከፃፈ በኋላ ደህነነቶች እና ይኸው ኮማንደር ቢኒያም የሚባል አዛዥ የእንግልሃለን ሬሳህን እዚህ ብንጠለው ዞር ብሎ የሚያይህ የለም በሚል እንደሚያስፈራሩት የጠቆሙት የዜና ምንጮቻችን ድብደባ እንደተፈጸመበትም ታውቋል።

ኢትዮጵያ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ግለሰቦች የሚያዙባት፤ በአንድ ግለሰብ ትዕዛዝም ሕይወት የሚጠፋባትና የሚበላሽባት ሃገር እየሆነች መምጣቱ የስርዓቱን ደጋፊዎች ሳይቀር እያስቆጣ እንደሚገኝ ከተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ግንቦት 7 የሕወሓት አስተዳደር በለቀቀው ‘አዲሱ’የአንዳርጋቸው ምስል ዙሪያ ምላሽ ሰጠ * “ሁላችንም አንዳርጋቸው እንሁን”

$
0
0

ግንቦት 7 ወቅታዊ አቋሙን በሚገልጽበት ርዕሰ አንቀጽ ባለፈው እሁድ የሕወሓት አስተዳደር ስለአንዳርጋቸው ጽጌ ስላስተላለፈው ዘገባ ምላሽ ሰጠ:: ሙሉ ር ዕሰ አንቀጹን ዘ-ሐበሻ እንደወረደ አስተናግዳዋለች::
Ginbot-7-Top-logo_4
ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌን እንሁን!!!

በህወሓት ሙሉ ቁጥጥር ስር የሚገኘው የፌደራል ፓሊስ በእሁድ ታህሣሥ 28 ቀን 2007 ዓ.ም. የቴሌቪዥን ፕሮግራሙ በግፍ እስር ላይ የሚገኘውን የግንቦት 7 ዋና ፀሐፊን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አቅርቦት ነበር። ይህ የ10 ደቂቃዎች ምስል ለቁጥር በሚያታክት ብዛት ተቆራርጦ የተቀጣጠለ በመሆኑ አቶ አንዳርጋቸው ምን ተጠይቆ ምን እንደመለሰ ማወቅ አይቻልም። ስለሆነም በንግግሩ ይዘት ላይ አስተያየት መስጠት ይናገረው አይናገረው በአልታወቀ ጉዳይ ማብራሪያ መስጠት ይሆናል። ስለዚህም፣ በንግግሩ ይዘት ላይ ጊዜ ከማጥፋት ህወሓት አንዳርጋቸው ጽጌን አሁን ማቅረብ ለምን እንደፈለገ መተንተን ይበልጥ ጠቀሜታ አለው ብሎ ግንቦት 7 ያምናል።

አሁን ህወሓት በውስጥም በውጭም ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የገባበት ጊዜ ነው፤ በራሱ በድርጅቱ ውስጥም ሰላም የለም። ህወሓት የትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ስር እንደሆነ አድርጎ በመቁጠር መላዋን ኢትዮጵያን ለመዝረፍና ለማጥቃት እንደ መንደርደሪያ፤ በሌላኛው የኢትዮጵያ ክፍል ተቃውሞ ሲበዛበት ደግሞ እንደ መደበቂያ ዋሻ ሲጠቀምበት የነበረው ጊዜ አብቅቶ የትግራይ ሕዝብ በህወሓት ላይ ማመጹ በግልጽ በተግባር እየታየ ነው። በርካታ የትግራይ ልጆች በህወሓት ላይ ነፍጥ አንስተዋል፤ ከፊሎቹ ደግሞ በሰላማዊ ትግል ህወሓትን ማስወገድ ይቻላል ብለው በክልላቸውም ከክልላቸውም ውጭ ከህወሓት ጋር ፍልሚያ ገጥመዋል። ህወሓት መሠረቴ ነው ከሚለው የትግራይ ክልል ፈጽሞ ሊነቀል የሚችል መሆኑ ግልጽ ምልክቶች እየታዩ ነው። የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) ከትግራይና ከተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያገናኘው የአማርኛና የትግርኛ የቴሌቪዥን ፕሮግራም መጀመሩ የህወሓት ሹማምንትን ናላ ያዞረ እርምጃ ሆኗል።

የህወሓት ሌላው መተማመኛው የጦር ሠራዊቱ ነበር። ህወሓት፣ የኢትዮጵያን መከላከያ ጦር ሠራዊት ዘረኛ በሆነ መንገድ አደራጅቶ፤ ከፍተኛ አመራሩን በታማኝ አባላቱ ሞልቶ ተደላድሎ የተቀመጠ መስሎ ታይቶ ነበር። አሁን ግን ይህም ምስል አሳሳች እንደሆነ ግልጽ እየሆነ መጥቷል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት የኢትዮጵያ ጠላት የሆነውን ህወሓትን የማገልገል ፍላጎት የሌላቸው መሆኑን፤ እንዲያውም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን በመቆም የህወሓትን ውድቀት ለማፋጠን ያላቸውን ጉጉት በግልጽ እያሳዩ ነው። አየር ኃይል ውስጥ ያለው ተቃውሞ ገሀድ የወጣ ዜና ሆኗል። እንደ አየር ኃይል ገሀድ የወጣ ዜና አይሁን እንጂ በሌሎችም የሠራዊቱ ክንፎች ያለው አመጽ ተመሳሳይ የጡዘት ደረጃ ላይ ደርሷል።

andargacew Tsige ብአዴን እና ኦህዴድ ውስጥ ለአገራቸው ለኢትዮጵያ፣ እንወክለዋለን ለሚሉት ሕዝብ እና ለራሳቸው ክብር ያላቸው አባላት ብቅ ብቅ እያሉ ነው። ብአዴንንና ኦህዴድ እንደ ድሮ ፍጽም ታማኝ አገልጋዮች የመሆናቸው ጊዜ እያበቃ ነው። ደኢህዴንም ቢሆን ሙሉ በሙሉ የሚታመን አይደለም። ጊዜው ለህወሓት እጅግ የመክፋቱ ምልክት ደግሞ እራሱ ህወሓት ውስጥም ስምምነት የሌለ መሆኑ ነው። ህወሓት ይይዘው ይጨብጠው ጠፍቶታል።

ለዓመታት የዘለቀው የሙስሊም ወገኖቻችን ተቃውሞ እረፍት ነስቶት እያለ በባህርዳር የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ተቃውሞ ተጨመረበት። የአምቦውን ተቃውሞ አዳፈንኩ ሲል የጎንደር ተቀሰቀሰበት። ለጉራና ለሀብት ዘረፋ ሲል ያስጀመረው የአባይ ግድብ፣ ጥበቃው ብቻ እንኳን ፋታ የሚነሳ ሥራ ሆነበት። ጋምቤላ፣ አፋርና፣ ሶማሊ የግጭት ቀጠናዎች ከሆኑ ዓመታት አስቆጠሩ።

ከላይ የተዘረዘሩት ጉምጉምታዎች፣ ተቃውሞዎችና አመጾች ተቀናጅተው የመጡ ዕለት መድረሻ እንደሚያጣ የተገነዘበው ህወሓት ትኩረት ማስቀየሻ መፈለጉ ግድ ነበር። በግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እምነት በአሁኑ ሰዓት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ወደ ሚዲያ መቅረብ ምክንያቱ ይህ ነው። አንዳርጋቸውን ወደሚዲያ በማቅረብ ትኩረትን የማስቀየስ ስትራቴጂ!

ginbot 7የፊልሙ ማጀቢያዎች የነበሩት የሂውማን ራይትስ ዎች ሪፓርት፣ ስለእንግሊዝ ጋዜጣ የተነገረው፣ አሜሪካ ስለምትፈጽመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተዘከረው፣ ወዘተ … ወዘተ የሚያመላክቱት አንድ አቢይ ሀቅ አለ። ይህም ኢትዮጵያዊያን ፀሐይና ብርድ ሳይበግራቸው “እኔ አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ” እያሉ በእንግሊዝ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት፣ በእንግሊዝ ኤምባሲዎች እና በአውሮፓ ኅብረት ሲያደርጓቸው የቆዩ ተቃውሞዎች ውጤታማ መሆናቸው ነው። በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የፈጠሩት ጫና ወያኔን ወደ ተከላካይነት አውርዶት “እኔ ንፁህ፣ አሜሪካ ርኩስ” እንዲል አድርጎታል። ወያኔ፣ ስለንፅህና ምስክርነትት ይሰጥልኛል ብሎ ተስፋ ያደረገው ደግሞ ራሱ ነፃነቱን ገፎ እስረኛው ያደረገው ሰው መሆኑ ጥረቱ እንደምን ውል አልባ እንደሆነበት ያሳያል። ንፅህናን ነፃ ባልሆነ ሰው ማስመስከር ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው? ይህ ክስተት፣ የኢትዮጵያዊያን ዘርፈ ብዙ ተቃውሞ የወያኔን የመከላከል አቅም ማዳከሙን በግልጽ ያሳያል። ይህ ለኢትዮጵያዊያን ትልቅ ብሥራት ነው።

ከላይ የተዘረዘሩት ምክንያቶች ህወሓት አንዳርጋቸውን ወደሚዲያ ለማቅረብ ምክንያት ይሁኑ እንጂ የአንዳርጋቸው ለሶስተኛ ጊዜ በወያኔ ቴሌቬዥን መታየት በኢትዮጵያዊያን ላይ የፈጠረው ስሜት ህወሓት ከጠበቀው ፈጽሞ የተለየ ነው።

ኢትዮጵያዊያን አንዳርጋቸውን ሲያዩ የሚታያቸው ጽናት፣ አርበኝነትና አልበገር ባይነት ነው። የአንዳርጋቸው ምስል በታየ ቁጥር ኢትዮጵያዊያን ፀጉራቸው ይቆማል፤ ደማቸው ይፈላል። ወያኔዎች አንዳርጋቸውን የፈለጉትን ቢያናግሩት ችግር የለም። ለጊዜው በእጃቸው ውስጥ ስለሆነ ያላለውን ያለ ሊያስመስሉ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያውቃል። ወደፊት ደግሞ ሊናገር ያልፈለገውን ያናግሩት ይሆናል። ይህ ሁሉ የሚያመጣው ለውጥ የለም። አንዳርጋቸው ስለወያኔ ምንነትና ማንነት ማንም ሳያስገድደዉ በነፃነት አገር ዉስጥ በግልጽ ተናግሯል፣ አሁንም ወያኔዎች እራሳቸዉ በሰሩት ፊልም ዉስጥ እነሱ በማይገባቸው መንገድ ለኢትዮጵያን ሕዝብ ተናግሯል። እንኳንስ እነሱ እሱም ራሱ በማይገባው መንገድ አንዳርጋቸው ኢትዮጵያዊያን ልብ ውስጥ ገብቷል። አንዳርጋቸውን ስናይ በህወሓት ፋሽስታዊ መዳፍ ውስጥ የወደቁብንን ጀግኖቻችንን ሁሉ ያስታውሰናል። በአስር ሺዎች ይቆጠራሉ። የአንዳርጋቸው ምስል ለግላጋ ወጣቶች፣ በሳል አዛውንት፣ ምርጥ ወንድሞችና እህቶች በወያኔ እስር ቤቶች ፍዳቸውን እያዩ መሆኑን ያስታውሰናል። ምስሉ ብቻውን ያናግረናል፣ ያነቃናል፣ ያነሳሳናል!!!

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አንዳርጋቸው ጽጌን፣ በርካታ ጀግኖቻችንን፣እራሳችንንና አገራችንን ከወያኔ እስር ነፃ ለማውጣት ክንዳችንን እናበርታ፤ ሁላችንም “እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነን” እንበል፤ ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌን እንሁን ይላል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

የኢሳት ጋዜጠኞች መሳይ መኮንን እና ፋሲል የኔዓለም አስመራ ገቡ

$
0
0

የኢሳት ጋዜጠኞች መሳይ መኮንን እና ፋሲል የኔዓለም አስመራ ገቡ

(ዘ-ሐበሻ) ኢሳት በሰበር ዜና እንዳቀረበው ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ከዋሽንግተን ዲሲ እንዲሁም ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ከሆላንድ ኤርትራ ገቡ::

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም


ከኢሳት እንደተገኘው መረጃ ከሆነ ጋዜጠኞቹ አስመራ የገቡት ትናንት ሲሆን በኤርትራ ቆይታቸውም እዚያ ያለውን ሃይል እንደሚጎበኙና ዘገባም እንደሚያቀርቡ በተጨማሪም የኤርትራ ባለስልጣናትን እንደሚያነጋግሩ ይጠቁማል::

የቀድሞው የጀርመን ድምጽ ጋዜጠኛና የአሁኑ የኢሳት ራድዮ ከፍተኛ አዘጋጅ መሳይ መኮንን; እንዲሁም የቀድሞው የአዲስ ዜና ጋዜጣ ዋና አዘጋጅና የአሁኑ የኢሳት ቲቭ ኤዲተር ፋሲል የኔዓለም በአስመራ ለስንት ጊዜያት እንደሚቆዩ እስካሁን የተገኘ መረጃ የለም::

ከእናቷ ጋር አስፓልት እየተሻገረች መኪና የበላት የ19 ዓመቷ የነፋስ ላይ ሻማ የሜሪላንዷ ቤዛ አማረ

$
0
0

beza amare
ትናንት በዘ-ሐበሻ የዜና እወጃ ላይ ኢትዮጵያዊቷ በሜሪላንድ ከአውቶቡስ ወርዳ ወደ ቤቷ ስታመራ በመኪና ተገጭታ መሞቷን ዘግበን የሟቿን እህታችን ፎቶ ባለመለጠፋችን በርከት ያሉ አንባቢዎቻችን ፎቶዋን እንድናቀርብ ጠይቀውን ነበር::

የ19ኝ ዓመቷ ቤዛ ፎቶ ግራፍን አቅርበናል:: ቤዛ አማረ የተባለችው የ 19 ዓመት ወጣት የተገጨችው ሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላንድ ሲሆን፣ ከአውቶቡስ ወርዳ ከ እናቷ ጋር ወደ ቤት ለመሄድ መንገድ እየተሻገሩ ሳለ ነበር። ፖሊስ እንደሚለው ሲሻገሩ የነበረው “ተሻገሩ” የሚለው የ እግረኞች ምልክት ሳይበራ ነበር። ገጪው የ 68 ዓመት ሰው ፣ ጥቂት ጉዳት ደርሶበት ታክሞ ከሃኪም ቤት ወጥቷል።

ለቤዛ የቀብር ስነ ስርዓት ማስፈጸሚያ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ በሜሪላንድ እየተደረገ ሲሆን ሁላችሁም እንድትሳተፉ ጥሪ ቀርቧል:: ነብስ ይማር::

ገንዘብ ለማዋጣት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ

ኢትዮጵያዊያን አንዳርጋቸውን ሲያዩ የሚታያቸው ጽናት፣ አርበኝነትና አልበገር ባይነት ነው። ሲል ግንቦት 7 ለፍትህ፣ ለዲሞክራሲና ለነፃነት ንቅናቄ ገለጸ።

$
0
0

g7-logoግንቦት 7 <<ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌን እንሁን!!!>> በሚል ርእስ ዛሬ ታህሳስ 29 ቀን ባስነበበው ርእሰ-አንቀጽ፤በህወሓት ሙሉ ቁጥጥር ስር የሚገኘው የፌደራል ፖሊስ እሁድ እለት በቴሌቪዥን ፕሮግራሙ በግፍ እስር ላይ የሚገኘውን የግንቦት 7 ዋና ፀሐፊን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለ 10 ደቂቃ አቅርቦት እንደነበር በማውሳት፤ይህ የ10 ደቂቃዎች ምስል ለቁጥር በሚያታክት ሁኔታ ተቆራርጦ የተቀጣጠለ በመሆኑና አቶ አንዳርጋቸው በትክክል ምን እንዳለ የሚያስረዳ ባለመሆኑ፤ በይዘቱ ላይ አስተያዬት መስጠት አስፈላጊ እንዳልሆነ ገልጿል።
ከዚያ ይልቅ ህወሀት አንዳርጋቸውን ለምን አሁን ሊያቀርበው ፈለገ?የሚለውን ነጠብ ማዬት እንደሚያስፈልግ የጠቆመው ግንቦት 7፤ ህወሀት በውስጥም፣በውጪም በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የገባበት ወቅት በመሆኑ በተለይ ውስጣዊ ውጥረቱን ለማስተንፈስና አቅጣጫ ለማስቀየር አንዳርጋቸውን በተቆተራረጠ ምስልና ድምጽ አጅቦ ማቅረቡን ጠቅሷል። <<የህወሓት ሌላው መተማመኛው የጦር ሠራዊቱ ነበር።>>ያለው ግንቦት 7፤ ህወሓት፣ የኢትዮጵያን መከላከያ ጦር ሠራዊት ዘረኛ በሆነ መንገድ አደራጅና ከፍተኛ አመራሩን በታማኝ አባላቱ ሞልቶ ተደላድሎ የተቀመጠ መስሎ ቢቆይም አሁን ግን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት የኢትዮጵያ ጠላት የሆነውን ህወሓትን የማገልገል ፍላጎት እንደሌላቸውና ይልቁንም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን በመቆም የህወሓትን ውድቀት ለማፋጠን ያላቸውን ጉጉት በግልጽ እያሳዩ መሆናቸውን መረጃዎችን ዋቢ አድርጎ አብራርቷል።
እንደ አየር ኃይል ተቃውሞ ገሀድ የወጣ ዜና አይሁን እንጂ በሌሎችም የሠራዊቱ ክንፎች ያለው አመጽ ተመሳሳይ የጡዘት ደረጃ ላይ መድረሱን የገለጸው ግንቦት 7፤ብአዴን እና ኦህዴድ ውስጥም ለአገራቸው ለኢትዮጵያ እና እንወክለዋለን ለሚሉት ሕዝብ እና ለራሳቸው ክብር ያላቸው አባላት ብቅ ብቅ እያሉ ነው ብሏል። እነኚህንና ሌሎችንም በመላ ሀገሪቱ የተቀጣጠሉትን የመብት ጥያቄዎችና አመጾች የተነተነው ግንቦት 7፤ <<ተቃውሞዎችና አመጾች ተቀናጅተው የመጡ ዕለት መድረሻ እንደሚያጣ የተገነዘበው ህወሓት ትኩረት ለማስቀየስ ሲል አቶ አንዳርጋቸውን እንዳቀረበው ገልጿል።
የፊልሙ ማጀቢያዎች የነበሩት የሂውማን ራይትስ ዎች ሪፓርት፣ ስለእንግሊዝ ጋዜጣ የተነገረው፣ አሜሪካ ስለምትፈጽመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተዘከረው ሁሉ የሚያመላክቱት አንድ አቢይ ሀቅ አለ።>>ያለው ንቅናቄው፤ ይህም ኢትዮጵያዊያን ፀሐይና ብርድ ሳይበግራቸው “እኔ አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ” እያሉ በእንግሊዝ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት፣ በእንግሊዝ ኤምባሲዎች እና በአውሮፓ ኅብረት ሲያደርጓቸው የቆዩ ተቃውሞዎች ውጤታማ መሆናቸውን ነው ብሏል። <<ኢትዮጵያዊያን አንዳርጋቸውን ሲያዩ የሚታያቸው ጽናት፣ አርበኝነትና አልበገር ባይነት ነው። የአንዳርጋቸው ምስል በታየ ቁጥር ኢትዮጵያዊያን ፀጉራቸው ይቆማል፤ ደማቸው ይፈላል።>> ያለው ግንቦት 7፤ ወያኔዎች አንዳርጋቸውን ወደፊትም እንዲሁ ሊናገር ያልፈለገውን ቢያናግሩት የሚፈጠር ምንም ለውጥ እንደሌለ አስምሮበታል።
<< እንኳንስ እነሱ አሳሪዎቹ እሱም ራሱ በማይገባው መንገድ አንዳርጋቸው ኢትዮጵያዊያን ልብ ውስጥ ገብቷል።>> ያለው ግንቦት 7፤<< አንዳርጋቸውን ስናይ በህወሓት ፋሽስታዊ መዳፍ ውስጥ የወደቁብንን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ጀግኖቻችንን ሁሉ ያስታውሰናል። ያነቃናል፣ ያነሳሳናል!!!”ብሏል። ንቅናቄው በመጨረሻም _<<አንዳርጋቸው ጽጌን፣ በርካታ ጀግኖቻችንን፣እራሳችንንና አገራችንን ከወያኔ እስር ነፃ ለማውጣት ክንዳችንን እናበርታ፤ ሁላችንም “እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነን” እንበል፤ ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌን እንሁን >>ሲል ለ ኢት ጰያ ህዝብ ጥሪ አቅርቧል።


መታረም የሚገባዉ ማነዉ? ርዕዮት አለሙ ከቃሊቲ እስር ቤት

$
0
0

በግል የህትመት ዉጤቶች አማካኝነት በሀገሬ ዉስጥ የምመለከታቸዉን ችግሮች ለህዝብ ማቅረብና እንደዜጋም መፍትሔ ይሆናሉ ብዬ የማስባቸዉን ሀሳቦች መጠቆም ከጀመርኩ አምስት አመታት አለፉ፡፡ የመጀመሪያ ፅሑፌን ያዘጋጀሁት ” “ስህተቶችን” ለማረም የተፈፀሙ ስህተቶችና የስህተት ማረሚያ እርምጃዎች” በሚል ርዕስ እንደነበረ አስታዉሳለሁ፡፡ በዚህም ፅሑፍ የፕሬስ፣የፖለቲካፓርቲዎች ምዝገባና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የተመለከቱ አዋጆች የወጡበት ምክንያትና እንደሀገር የሚያሳድሩትን ተፅእኖ ለመዳሰስ ብሎም ኢህአዴግ ከስህተቶቹ እንዲታረም ለመምከር ሞክሬያለሁ፡፡
Ryotየኢህአዴግ ሰዎች በአንድ የገዢዉ ፓርቲ ልሳን በሆነ ድረገፅ አማካኝነት የማስጠንቀቂያ ይዘት ያለዉ ምላሽ መስጠት የጀመሩት ከላይ ከጠቀስኩት የመጀመሪያ ፅሁፌ ጀምሮ የነበረ ቢሆንም በአዲስፕሬስ ጋዜጣ ላይ በአዘጋጅነት ተቀጥሬ መስራት ስጀምር ግን ሁኔታዉ እየባሰ መጣ፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም አዳማ ላይ ከተለያዩ ሚዲያዎች ለተዉጣጣን ጋዜጠኞች የሰጠዉን ስልጠና ከተካፈልኩ በኋል ከስልጠናዉ ጋር በተያያዘ ለህትመት ያበቃሁት ፅሁፍ ኢህአዴጎችን በእጅጉ አስቆጣቸዉ፡፡ በመሆኑም ወደቢሮአችን ተደዉሎ ከኢህአዴግ ፅህፈት ቤት የተደወለ መሆኑ ከተገለፀ በኋላ ለጽሑፌ ምላሽ የላኩ በመሆኑ በፍጥነነት እንድናወጣዉ ቀጭን ትዕዛዝ ተሰጠን፡፡ ምላሻቸዉን ለማዉጣት የእነሱ መደወልም ሆነ ትዕዛዝ አስፈላጊ አልነበረም፡፡ የዝግጅት ክፍላችን አንድ ጽሑፍ የቀረበበት አካል ምላሹን በዚያዉ በተፃፈበት የህትመት ዉጤት ላይ ማስነበብ እንደሚችል በህግ የተደነገገ መሆኑን ከማወቁም በላይ የትኛዉንም አይነት ሀሳብ ለማስተናገድ ክፍት ነበርና ምላሻቸዉን በጋዜጣችን ላይ ታተመ፡፡ በዚህ ብቻ ግን አልተገቱም፤ በወቅቱ የገዢዉ ፓርቲን ሀሳብ በማቀንቀን ይታወቁ የነበሩት እንደ ዳጉ ኢትዮጵያና ሰነድ ያሉ ጋዜጦች ሀሳቦቼን በሃሳብ መምታት ባለመቻላቸዉ ይሁን ባለመፈለጋቸዉ ተራ ዘለፋዎችን ያወርዱብኝ ጀመር፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የገዢዉ ፓርቲ ደህንነቶች ስልክ በመደወል፣ በዝግጅት ክፍላችን አድራሻ በስሜ ደብዳቤ በመላክና በአካልም በማግኘት ጭምር መንግስትን የሚተቹ ፅሑፎችን እንዳልፅፍ ሊያስፈራሩኝ ሞከሩ፡፡ “ማስፈራራት የሚቻለዉ የሚፈራ ሲኖር ነዉ” እንዲሉ ሙከራቸዉ ዋጋ አልነበረዉም፡፡ ምክንያቱም የመጀመሪያ ፅሑፌን ለህትመት ከማብቃቴ በፊት ልከፍለዉ ስለምችለዉ መስዋዕትነት በሚገባ አስቤበታለሁ፡፡ የሀገሬን ጉዳይ በንቃት የምከታተል ዜጋ እንደመሆኔም ከገዢዉ ፓርቲ የተለየ ሀሳብ ያቀነቀኑ ሰዎች የደረሰባቸዉን በሚገባ አዉቃለሁ፡፡ በመሆኑም ከሁለት መጥፎ ምርጫዎች አንዱን ማለትም እነሱ የደረሰባቸዉን ግፍ እንዳይደርስብኝ የሀገሬን ጉዳይ በተመለከተ ፍዝ ተመልካች መሆንን ወይም በሙያዬ የምችለዉን አስተዋፅኦ አበርክቼ የሚመጣዉን መቀበል መምረጥ ነበረብኝ፡፡ ሁለተኛዉን የተሻለ መጥፎ ምርጫ ከመረጥኩ የሰነበትኩ በመሆኑም እየበረከቱ የመጡትን ማስፈራሪያዎች ከቁብ ሳልቆጥር የጋዜጠኝነት ስራዬን መቀጠል ቻልኩ፡፡ በዚሁ መሰረት ስራ ለመያዝ፣ የደረጃ እድገት ለማግኘትም ሆነ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከደህንነት ስጋት የፀዳ ኑሮ ለመኖር የኢህአዴግ አባል ካልሆነም ደጋፊ መሆን ከጊዜ ጊዜ ግድ እየሆነ መምጣቱን የሚያሳዩ፣ ገዢዉ ፓርቲ እንዳጎናፀፈን የሚገልፅልን ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በተጨባጭ አለመኖሩን የሚሞግቱ፣ የኢህአዴግን እንደሀገር የማሰብ ችሎታ ወይም ፍቃደኝነት አናሳ መሆን የሚተቹና ሌሎችም መንግስት ቀናነት ቢኖረዉ ኖሮ ሊታረምበት የሚያስችሉትን በርካታ ፅሑፎች አቀረብኩ፡፡ አንድ ቀን ጧት ግን አምባገነኑ መንግስታችን ከጀመርኩት ጉዞ ገታኝ፡፡ ሰኔ10/2003 በወቅቱ እሰራባት በነበረችዉ ተወዳጇ ፍትህ ጋዜጣ ላይ የቀድሞዉን ጠቅላይ ሚኒስትር በተመለከተ ፅሑፍ ለህዝብ ማቅረቤን ተከትሎ ሰኔ14/2003 ዓ.ም ለእስር ተዳረግሁ፡፡
ማዕከላዊና ቃሊቲ ምንና ምን ናቸዉ?

ዉድ አንባብያን፤ ፊዘኛዉ መንግስታችን በሽብርተኝነት እንደሚጠረጥረኝ ገልፆ በእጆቼ ካቴና በማጥለቅ በቁጥጥር ስር አዋለኝ ካዋለኝ ከዚያ ቀን ጀምሮ እስካሁን ድረስ ለቁጥር የሚያታክቱ የመብት ጥሰቶችን እየፈፀመብኝ ይገኛል፡፡ ለአብነት ያህል እጅግ በጣም ጥቂቶቹን እነሆ!
ከህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ነዉ የሚባልለት ህገመንግስት በጥበቃ ስር ያሉ ሰዎች በጠበቆቻቸዉ የመጎብኘት መብት እንዳላቸዉ ቢገልፅም እኔና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ግን ይሄ መብታችን በማዕከላዊ አለቆች ተጥሷል፡፡ ጠበቃዬን ለማግኘት የተፈቀደልኝ ምርመራዉ ከተጠናቀቀና ቃል ከሰጠሁ በኋላ ወደቃሊቲ ለመዉረድ የአስርቀናት ዕድሜ ያህል ሲቀረኝ ነበር፡፡ በቤተሰብና በጓደኞቼ ለመጎብኘት የተፈቀደልኝም ሁለት ወር ከ3 ሳምንታት ክልከላ በኋላ ነበር፡፡ ከጠበቃዬ ጋር እንዳልገናኝ ተደርጎ የሚካሄደዉ ምርመራ የፃፍኳቸዉን ፅሑፎች ለምን እንደፃፍኩ፣ ከበስተኋላዬ ሆኖ የሚገፋኝ አካል ስለመኖር አለመኖሩና የመሳሰሉት ጥያቄዎች ላይ ያተኮረ ቢሆንም አልፎ አልፎ ደግሞ መልኩን ይቀይራል፡፡ አንዳንድ ቀን መርማሪዎቹ በማስተምርበት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በተካሄዱ ስብሰባዎች ላይ ያቀረብኳቸዉን ሀሳቦች እያነሱ ከመንግስት የደህንነት ሀይሎች የሚያመልጥ ምንም ነገር እንደሌለ በመግለፅ ቢጤ ያሰሙኝ እንደነበር ሳልጠቅስ ማለፍ አልፈልግም፡፡፡ እንዲህ አይነቱ ንግግራቸዉ አሰልቺዉን ምርመራ ዘና እልበት ዘንድ የሚረዳኝ የእፎይታ ጊዜ ሰጥቶኛል፡፡ በአደባባይ ስብሰባዎች ላይ የተናገርኩትንና ደህንነት ሊሰልለዉ የማያስፈልገዉን ግልፅ ነገር እንደ ትልቅ የደህንነቶች የስራ ዉጤት ተደርጎ ሲገለፅ ከመስማት በላይ ምን የሚያዝናና ነገር ይገኛል? የት/ቤት ርዕሰ መምህራኖች በሙሉ የኢህአዴግ አባል እንዲሆኑ የተደረገበት ምክንያት መንግስት እንደሚለዉ የትምህርት ፖሊሲዉን ለማስፈፀም ሳይሆን የመምህራንንና የተማሪዎችን የፖለቲካ አቋም ለማወቅና ይህንኑ ሪፖርት ለማድረግ መሆኑን የማይረዳ መምህር ይኖራል? ይህንን ለማድረግ ፍቃደኛ ያልሆኑ ርዕሰ መምህራኖች ሰበብ እየተፈለገላቸዉ ከቦታቸዉ እንዲነሱ ሲደረግስ ስንታዘብ አልኖርንም? “ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል” አለ ያገሬ ሰዉ! ሆዴ ባዶ እንዳይቀር ሁሉን መተንፈሴን ትቼ የጀመርኩትን የማዕከላዊ ምርመራ ጉዳይ ልቀጥል፡፡
የምርመራዉ ይዘት ከጥቂት ሳምንታት በኋላ መልኩን እየቀየረ መጣ፡፡ በሪፖርተርነት እሰራበት የነበረዉ የኢትዮጵያ ሪቪዉ ድረገፅ አዘጋጅ ኤልያስ ክፍሌ የሽብር ተልዕኮ እንደሰጠኝ በሀሰት እንድናገርና ተከሳሽነቴ ቀርቶ ምስክር ሆኜ እንድፈታ ለማድረግ የተለያዩ ጫናዎቸው ይደርሱብኝ ጀመር፡፡ ለአምስት ደቂቃ ያህል ጧትና ማታ ወደመፀዳጃ ቤት ለመሄድ ከሚከፍቱልኝ በስተቀር ለአስራሶስት ቀናት ያህል ብቻዬን አንድ መጥፎ ሽታ ያለዉ ክፍል ዉስጥ ተዘግቶብኝ ከረምኩ፡፡ በዚህ ወቅት ጉዳዬን የያዘዉ ዐቃቤህግ ማዕከላዊ በመምጣት እያስጠራኝ ሀሳቤን የማልለዉጥ ከሆነ እድሜ ልክ ወይም ሞት እንደሚያስፈርድብኝ ይዝትብኝ ነበር፡፡ ሀሰን ሽፋ በበኩሉ በሀሳባቸዉ የማልስማማ ከሆነ የያዘኝን የወጣት ጀብደኝነት ማስተንፈስ ለነሱ ከባድ ስራ አለመሆኑን ነግሮኛል፡፡ በኔ በኩል ደግሞ ከተጠረጠርኩበት ወንጀል ንፁህ መሆኔ እንጂ ኤልያስ ላይ በሀሰት መመስከሬ ሊያስፈታኝ እንደማይገባ ስለማምን ይህንኑ በተደጋጋሚ አስታዉቄ ተከሳሽ መሆንን መረጥኩ፡፡ ኢህአዴግ እስካለ ድረስ የተሻለዉን መጥፎ እየመረጡ መኖር ዕጣፋንታችን ከሆነ ቆየ አይደል?
ማዕከላዊ እያለሁ ከተፈፀሙብኝ የመብት ረገጣዎች ዉስጥ አንዱ የሆነዉ በአንድ ፖሊስ የተሰጠኝ ጥፊና ከግድግዳ ጋር ማጋጨት በተለይ ወንድ የፖለቲካ እስረኞች ከሚፈፀምባቸዉ ለዘላቂ የአካል ጉዳት የሚዳርግ ከባድ ድብደባ አንፃር ሳስተያየዉ የማዕከላዊ መርማሪዎች እንደሚሉት “ቁንጥጫ” ተብሎ ከመግለፅ የሚያልፍ ባለመሆኑ ብዙ ልልበት አልፈልግም፡፡ በወቅቱ የነበርነዉ ሴት እስረኞች ላይ ያን ያህል የከፋ አካላዊ ድብደባ አልተፈፀመም ማለት ግን የማዕከላዊ መርማሪዎች ለሴቶች ይሳሳሉ ማለት አይደለም፡፡ ለማሳያነት እስካሁን ድረስ ማዕከላዊ በተፈፀመባት ከባድ ድብደባ የተነሳ በህመም የምትሰቃየዋን የፖለቲካ እስረኛ እማዋይሽ አለሙን መጥቀስ ይቻላል፡፡ አይ ማዕከላዊ! ማዕከላዊ ዘና ብለዉ የሚራመዱ ኩሩ የኢትዮጵያ ልጆች በገቡ ሳምንት በማይሞላ ጊዜ ዉስጥ በቃሬዛና በሰዎች ድጋፍ በሸክም ሲያሳልፉና የድረሱልኝ ዋይታ ሲያቀርቡ የሰማሁበት አሰቃቂ ቦታ ነዉ፡፡ ምስላቸዉ ከአይኔ ላይ፣ ጩኸታቸዉ ከጆሮዬ ተጣብቆ የሚኖረዉ እነዚህ ወገኖቼን እያሰብኩ መናደድ መቆጨት የዕለት ተዕለት የኑሮዬ አካል ሆኗል፡፡
የማዕከላዊዉን የመብት ረገጣ እዚህጋ ገታ ላድርገዉና በተለይ የፖለቲካ እስረኞችን ሰብአዊ መብት ከመጨፍለቅ አንፃር አምሳያዉ ወደ ሆነዉ የቃሊቲ እስር ቤት ልለፍ፡፡ ጳጉሜ3/2003 ዓ.ም ቃሊቲ እንደገባሁ በኋላ ላይ የጥበቃ ክፍል ሀላፊ እንደሆነች በተገነዘብኩት ሀላፊ አማካኝነት ጋዜጠኝነቴ ከታሰርኩ በኋላ የቀረ በመሆኑ ግቢዉ ዉስጥ በሚኖረኝ ቆይታ አርፌ መቀመጥ እንደሚኖርብኝ ተነገረኝ፡፡ አልጋ እስከሚለቀቅ ተብሎም እኔና በአንድ መዝገብ የተከሰስነዉ ወ/ሮ ሂሩት ክፍሌ ምንም እንኳን ሁለታችንም የሳይነስ በሽታ ያለብን ቢሆንም ሽንት ቤት አጠገብ መሬት ላይ ፍራሽ አንጥፈን እንድንተኛ ተደረገ፡፡ ዉድ አንባቢያን ስለቃሊቲ ስታስቡ ወደ አዕምሮአችሁ የሚመጡት ያማሩ ግንብ ቤቶችና የተዋቡ አልጋዎች ከሆኑ ኢቲቪ እንደሸወዳችሁ ልነግራችሁ እወዳለሁ፡፡ የፓስተር ዳንኤል ገ/ስላሴ ፕሪዝን ፌሎሽፕ የተባለ ድርጅት እንዳሰራቸዉ የሚናገሩት እነዚህ ያማሩ ግንብ ቤቶች ሁለት ክፍሎችና መፀዳጃ ቤት ብቻ ያሏቸዉ ሲሆኑ የተቀሩት በሴቶች ዞን ዉስጥ ያሉ ክፍሎች ከሁለት ያረጁ ግንብ ቤቶች በስተቀር በቆርቆሮ የተሰሩና እስረኞች በተጨናነቀ ሁኔታ የሚኖሩባቸዉ ናቸዉ፡፡ የቃሊቲ ምቾት አልባነት የሚሰማዉ አካልን ብቻ አይደለም፡፡ ቃሊቲ ከአካል በከፋ ሁኔታ ለነፍስና ለመንፈስ ይጎረብጣል፡፡ እንዴት ቢሉ እንዲህ እልዎታለሁ፡፡ የቃሊቲ የሴቶች ዞን ቤተመፃሕፍት ከጥቂት ወራት ጀምሮ በመፅሐፍቱ አይነትም ሆነ ቁጥር መሻሻልን ቢያሳይም እኔ ቃሊቲ ከገባሁ ጀምሮ እስከቅርብ ጊዜያት ድረስ ግን ከመኖር በማይቆጠር ደረጃ የሚገኝ ነበር፡፡ ይህንን ክፍተት ቤተሰብና ጓደኞቼ በሚያስገቡልኝ መፀሐፍት ለመሙላት ባስብም ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የሚመጡልኝ መፅሐፍት የቃሊቲን ሳንሱር እንደወደቁ ተገልፆ እኔጋ ሳይደርሱ ይመለሳሉ፡፡ ከነዚህ መፅሐፍት ዉስጥ አዲስአበባ ዩኒቨርስቲ የሚሳትማቸዉ የታሪክ መፅሐፍት ሳይቀር ይገኙበታል፡፡ ቃሊቲ ለመንፈስም አይመችም ያልኳችሁ በዚህ ብቻ አይደለም፡፡ በራሴ ወጪ ኢንድራ ጋኒዲ ናሽናል ኦፕን ዩኒቨርስቲ በርቀት ፖለቲካል ሳይንስ ለማጥናት ከብዙ ዉጣዉረድ በኋላ ተፈቅዶልኝ የተበዘገብኩ ቢሆንም የመማሪያ ሞጁሎቹን ለማስገባት ግን የቃሊቲ አለቆች ፍቃደኛ አልነበሩም፡፡ ከብዙ ደጅጥናት በኋላ ሞጁሎቹ ሲገቡ ደግሞ በትምህርቱ ዙሪያ ላነባቸዉ የሚገቡኝ አጋዥ መፅሐፍት ስለፖለቲካ የሚያወሩ በመሆናቸዉ በፍጹም ሊገቡ እንደማይችሉ የመፅሐፍት ገምጋሚዎቹ አረዱኝ፡፡ ይባስ ብሎ በዚያን ወቅት ከሌላዉ ጊዜ በተለየ ሁኔታ ምንም አይነት መፅሐፍት እንዳይገቡልኝ በመደረጉ ለጠቅላላ ዕዉቀት ያህል ሞጁሎቹን ማንበቤን ብቀጥልም ትምህርቱ ግን በዚህና በሌሎች ምክንያት ለማቋረጥ ተገደድኩ፡፡
በቃሊቲ የኔ ብቻ ሳይሆን ከእኔ ጋር የተቀራረቡ ወይም ደግሞ ሰላምታ ያቀረቡልኝ ሰዎች ሳይቀር መብታቸዉ ተጥሷል፡፡ ከሁለት አመታት በላይ የሚሆነዉን ጊዜ በርካታ እስረኞች በነበሩበት ክፍል ያሳለፍኩ ቢሆንም እኔን እንደሌላዉ እስረኛ ለመቅረብ የሞከሩ በሙሉ ስሜትን የሚጎዳ ወከባ፣ዘለፋና ለየት ያሉ ፍተሻዎችን አስተናግደዋል፡፡

በህክምና ጉዳይ የነበሩብኝን ችግሮች በተመለከተ ቤተሰቦቼ ደጋግመዉ የገለፁት መሠረታዊ ችግር በመሆኑ በዚህ ፅሑፍ ነካ አድርጌዉ ብቻ አልፋለሁ፡፡ ጡቴ ዉስጥ በበቀለዉ እጢ ምክንያት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህክምና ክትትል በማደርግበት ወቅት በቀጠሮዬ ቀን ወደ ሆስፒታሉ ከምወሰድባቸዉ ይልቅ የማልወሰድባቸዉ ጊዜያት ይበዙ ነበር፡፡ የግራ ጡቴ ቀዶጥገና ከተደረገለት በኋላ በወቅቱ ክትትል ታደርግልኝ የነበረችዉ ዶክተር በሶስተኛ ቀን የቁስሉ ፕላስትር መቀየር እንዳለበትና በሳምንቱ ደግሞ ክሩ መዉጣት እንዳለበት ገለፀችልኝ፡፡ አብረዉኝ የሚሄዱት አጃቢ ፖሊሶች ከዶክተሬም ጋር ስነጋገር እዛዉ ነዉና የሚቆሙት እንዲህ አይነቱን ነገር ለማድረግ የሚችል ጤናጣቢያ ማረሚያቤቱ እንዳለዉ ተናገሩ፡፡ እኔም ቀጠሮ ቢሰጠኝ እንኳ በዚህ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ወደሆስፒታሉ ተመልሼ መሄድ አዳጋች መሆኑን ስለማዉቅ የተባሉት ነገሮች ቃሊቲ መፈፀማቸዉን አልጠላሁትም፡፡ በመሆኑም ለህክምና ክትትል የሶስት ወራት ቀጠሮ ተሰጠኝ፡፡ ክሩ መዉጣት ባለበት ቀን ስለጉዳዩ ለጥበቃ ክፍሉ አስታወቅኩ፡፡ እነሱም አሁን ደቡብ ሱዳን ከሚገኝዉ ጦር ጋር አብራ ከተጓዘች አንዲት የህወሐት ታጋይ የነበረች ነርስ ጋር አገናኙኝ፡፡ እሷም እዛዉ ጨርሼ መምጣት እንደነበረብኝና እዚህ ክሩን ማዉጣት እንደማይችሉ ነገረችኝ፡፡ የምታሳየኝ ጥላቻ በሷ እጅ የህክምና አገልግሎት ከማግኘት ቢቀር የሚሻል መሆኑን የሚጠቁም በመሆኑ ብዙም ልከራከራት አልፈለኩም፡፡ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉ ሌሎች ሀላፊዎች ወደጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንዲወስዱኝ ብጠይቅም “ቀጠሮ የለሽም” በሚል ሰበብ ሳይወስዱብኝ ቀሩ፡፡ በአሁኑ ወቅት የቀኝ ጡቴም ተመሳሳይ እጢ ያለበት በመሆኑ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ወደ ምኒሊክ ሆስፒታል ቀዶጥገና አደርግ ዘንድ የላከኝ ቢሆንም (ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በእድሳት ላይ በመሆኑ)እጅግ የከፋ ህመም ካልታመምኩ በቀር ቃሊቲ ሆኜ ቀዶጥገና ማድረጉን አልፈለኩም፡፡ በመሆኑም አልፎ አልፎ የሚሰማኝን ህመም በህመም ማስታገሻ መድሀኒቶች በማቃለል የቃሊቲን አስቀያሚ ቀኖች በመግፋት ላይ እገኛለሁ፡፡

ሌላዉ የቃሊቲ ቆይታዬን በተመለከተ ልጠቅሰዉ የምፈልገዉ ጉዳይ ከመንግስት አካላትና ከተለጣፊዎቻቸዉ ጋር ካለፍላጎቴ እንድንገናኝ እየተደረገ የሚፈፀምብኝ የሰብአዊ መብት ረገጣ ነዉ፡፡ ለምሳሌ ያህልአንዱን ብቻ ልጥቀስ፡፡ አምና መጋቢት ወር ዉስጥ አምባሳደር ጥሩነህ ዜናን ጨምሮ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መምጣታቸዉን የገለፁ ሌሎች አስር ሰዎች ከአመት በፊት ወደገባሁበትና ከሌሎች ከአራት ሰዎች ጋር ብቻ ወደምኖርበት ክፍል መጡ፡፡ እኔም ኮሚሽኑ በተለይም ደግሞ አምባሳደሩ የሰብአዊ መብት አከባበርን አስመልክቶ የሚሰጧቸዉ ከእዉነት የራቁ መግለጫዎች የሚያሳዝኑኝ በመሆኑ ለመነጋገር ፍቃደኛ አለመሆኔን በማስታወቅ ከክፍሉ ወጥቼ በሩ ላይ ቆምኩ፡፡ ከሰዎች አንዱ የምኖርበትን ክፍልና አልጋዎቻችንን ፎቶ ሲያነሳ ተመለከትኩ፡፡ ገረመኝ፤ መሬት አንጥፌ ስተኛ፣በተደራራቢ አልጋ የላኛዉ ክፍል ላይ ከጡት ህመም ጋር እየታገልኩ ስተኛና በተፋፈገ ክፍል ዉስጥ ስኖር ለምን የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ፎቶ አላነሳም? ማረሚያ ቤቱ በጥሩ ሁኔታ እስረኞቹን የያዘ መሆኑን ማሳያ ለማድረግ እንደተፈለገ ገመትኩ፡፡ እዉነታዉ ግን ይቺ ያለሁባት በቆርቆሮ የተሰራች ክፍልና ጠባቧ ግቢ አምና መስከረም ላይ በጠያቂዎች የመጎብኘት መብቴ መጣሱን ተከትሎ በጥድፊያ የተዘጋጀች ማግለያ ቦታ መሆኗ ነዉ፡፡ ክፍሉን ብቻ ፎቶ አንስተዉ መሄዳቸዉ ያላረካቸዉ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰዎች በማግስቱ አራት ሆነዉ መጡ፡፡ ሁለቱ ወደግቢዉ ዉስጥ ሲገቡ ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ በሩጋ ቆሙ፡፡ ግቢዉ ዉስጥ ከገቡት አንዱ ትላንት ለምን ላናግራቸዉ እንዳልፈለኩ ጠይቆኝ በድጋሚ ከነሱ ጋር መነጋገር ያልፈለኩበትን ምክንያት እያስረዳኋቸዉ እያለ የግቢዉ በር ክፍት ስለነበር ግቢዉ በርጋ ከቆሙት አንዱ ፎቶ ሊያነሳኝ ሲሞክር ለመመልከት ቻልኩ፡፡ ምስሌን አንስቶ ቢሆንና ስለኔ አንዳች አይነት ዉሽት ሲናገሩ ብሰማ ጉዳዩን በዝምታ እነደማላልፈዉ ነገርኩትና ወደቤት ዉስጥ ገብቼ በሩን ዘጋሁት፡፡

ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ከክፍሉ ወጥቼ ኢህአዴግ ማሰሩ ሳይበቃዉ ሰብአዊ መብትን ለማስከበር እንዳቋቋማቸዉ በሚናገረዉ ተለጣፊ ድርጅቶቹ ሳይቀር ሰብአዊ መብቴን ለምን እንደሚጥስ ከሀላፊዎቹ አንዷን በማስጠራት ጥያቄ አቀረብኩላት እሷም ሰዎቹ ካሜራ መያዛቸዉን እንደማታዉቅ ነገረችኝ፡፡ በ2005ዓ.ም ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች የህዝብ ግኑኝነት ክፍል እኔን ለማናገር እንደመጣ የገለፀልኝ ሰዉ ኮቱ ዉስጥ ደብቆ በያዘዉ ሪከርደር ድምፄን ለመቅረፅ ሲሞክር ደርሼበት ይህንን ማድረግ የሚችለዉ የግል ፕሬስም ተገኝቶ ንግግራችንን የሚቀርፅ ከሆነ ብቻ መሆኑን ነግሬዉ ነበር፡፡ ይሄንን ያልኩበት ምክንያት የግል ፕሬሱ ባልተገኘበት ለመንግስት ሚዲያዎች ብቻ አስተያየታቸዉን የሰጡ ግለሰቦች ሀሳባቸዉ ተቆርጦና ተቀጥሎ ለማለት ያልፈለጉት ይዘት ይዞ እንደሚቀርብ አዉቅ ስለነበር ነዉ፡፡ የተናገርኩትን ሙሉዉን ነገር ቀርፀዉ ሊያወጡልኝ የሚችሉ አካላት በሌሉበት ለሰዉዬዉ አስተያየቴን መስጠት ያለፈለኩትም ይኸዉ እንዳይደርስብኝ በመስጋት ነበር፡፡ አስገራሚዉ ነገር ይቺ የኮሚሽኑ ሰዎች ካሜራ መያዛቸዉን እንደማይታወቅ የገለፀችልኝ ሀላፊ ያኔም የሰዉየዉን የድምፅ ሪከርደር መያዝ በተመለከተ ላቀረብኩላት ጥያቄ የሰጠችኝ ተመሳሳይ መልስ ነበር፡፡
የቃሊቲ ጉድ ማብቂያ ስለሌለዉ አንድ የመጨረሻ ጉዳይ ላንሳና የፅሁፌ መነሻ ወደሆነዉ የአመክሮ ጉዳይ አልፋለሁ፡፡ ዉድ አንባቢያን በሀገሪቱ ዉስጥ ያሉ የትኞቹንም እስረኞች አያያዝ የተመለከቱ ህጎችን፣ አዋጆችን፣ ደንቦችንም ሆኑ መመሪያዎችን በጣሰ ሁኔታ ከወላጆቼ በቀር ጠበቃን ጨምሮ በሌላ በማንም ሰዉ የመጎብኘት መብቴን ከተነጠቅኩ አመት ከኣራት ወራት አልፎኛል፡፡ አዛዉንት እናትና አባቴም ከእርጅና፣ ህመምና ድካም ጋር እየታገሉ የቃሊቲን ፈታኝ መንገድ መዉጣትና መዉረዳቸዉን ቀጥለዋል፡፡
ነገረ አመክሮ

ያለፈዉ አመት ነሐሴ ስምንት ቀን ከሰአት በኋላ ወደ ጠበቃ ክፍል ሃላፊዋ ቢሮ በአንዲት ፖሊስ ተጠርቼ ተወሰድኩ፡፡ እዚያም ከፌደራል ማረሚያ ቤቶች ዋናዉ መስሪያ ቤት የይቅርታና የአመክሮ ጉዳይ ክፍል እንደመጣና ኮማንደር አስቻላዉ እንደሚባል ከነገረኝ ሰዉ ጋር ተገናኘሁ፡፡ ኮማንደሩ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ያቀረበልኝ የመጀመሪያዉ ጥቃቄ “ይቅርታ ለምን አልጠየቅሽም? ይቅርታ በመጠየቅ ላይ ያለሽ ሀሳብስ አልተቀየረም ወይ?” የሚል ነበር፡፡ ይቅርታ ያልጠየኩት ስላላጠፋሁና የተፀፀትኩበት ጉዳይ ስለሌለ በመሆኑና አሁንም ምንም የተቀየረ አቋም እንደሌለኝ አስረዳሁተ፡፡ “ይሄ የፍርድቤት ጉዳይ ነዉ፡፡ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ እስካለሽ ድረስ ወደዚያ መመለስ አይኖርብንም” አለኝ፡፡ እኔም አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት እንዳሻዉ የሚያሽከረክረዉ ፍርድቤት በንፁሃን ላይ የጥፋተኝነት ዉሳኔና ፍርድ ማስተላለፉን አሜን ብዬ ይቅርታ የምጠይቅበት ምንም አይነት ምክንያት እንደሌለ ገለፅኩለት፡፡ ጥቂት ደቂቃዎች ያህል ስለጤንነቴና በጊቢዉ ዉስጥ ስለሚያጋጥሙኝ ችግሮች በተመለከተ ጥያዎችን ስያቀርብልኝ ቆየና ወደ መጣበት ሌላዉ ዋና ጉዳይ ተመለሰ፡፡
“ቅድም ይቅርታ የማልጠይቀዉ ስላልተፀፀትኩ ነዉ ብለሻል፡፡ አመክሮ እኮ የሚሰጠዉ ለተፀፀተ ሰዉ ነዉና እንዴት ልታደርጊ ነዉ?” በማለት ስለ በአመክሮ የመፈታት አካሄድ አንዳንድ የሚኒስተሮች ምክር ቤት ደንቦችን ጭምር በመጥቀስ ሊያብራራልኝ ሞከረ፡፡ “ታዲያ እንዲህ ከሆነ በይቅርታና በአመክሮ መሀል ምንም አይነት መሰረታዊ ልዩነት የለም ማለት ነዋ?” ለሚለዉ ጥያቄ ቀጥታ መልስ ሊሰጠኝ አልፈለገም ይልቁኑ ሁሉም ታራሚ 2/3ኛዉን የእስር ቅጣቱን ለመፈፀም ሁለት ወራት ገደማ ሲቀሩት እንደታረመና እንደተፀፀተ የሚገልፅ ፎርም መሙላት ስለሚኖርበት እኔም ለመፈታት ከፈለኩ ይህንኑ ማድረግ እንደሚጠበቅብኝ አስረግጦ ነገረኝ፡፡ የፃፍኩት የማምንበትንና መቼም ልቆምለት የምችለዉ እዉነት መሆኑን፣ በዚህ የተነሳ አሸባሪ መባሌ ደግሞ የበለጠ ኢህአዴግን እንድታገለዉ የሚየደርገኝ እንጂ የሚያፀፅተኝ ባለመሆኑ እንዲህ አይነቱን ከማንነቴ ጋር የሚቃረን ፎርም እንደማልሞላ አስረግጬ ነገርኩት፡፡ ኮማንደሩም ላልታረመና ለልተፀፀተ ሰዉ አመክሮ መስጠት ለእነሱም እንደሚከብዳቸዉ ከገለጸልኝ በኋላ “እኛ ፎርሙን ብንሞላልሽስ?” የሚል አስገራሚ ጥያቄ አቀረበልኝ፡፡ እኔ “ታርሜያለሁ” እንዳልኩ ተደርጎ ምንም አይነት ነገር ቢደረግ ሀሰት መሆኑን ከማጋለጥ ወደኋላ እንደማልል አስታወቅኩት፡፡ በዚህ አይነት ተመሳሳይ ሀሳቦች ላይ እየተሸከረከርን ጥቂት ጊዜ ከፈጀን በኋላ እንዳሰብበት አሳስቦኝ ተለያየን፡፡
ይህ ከሆነ ሀሁለት ወራት በኋላ የመፈቻዬ ቀን የነበረዉ ጥቅምት 14/2007 ማለፊን ተከትሎ “የአመክሮ ፎርሙን ለምን አትሞይም?” የሚል ጥያቄ ከተለያዩ ሀላፊዎች ይቀርብልኝ ጀመረ፡፡ ከህዳር አጋማሽ ጀምሮ ደግሞ ጥያቄዉ እየጨመረ መጣ፡፡ በተለይ በመጨረሻዎቹ የህዳር ወር ቀናት በአንዱ አራት ሆነዉ ክፍሌ ድረስ በመምጣት አነጋገሩኝ፡፡ ለኮማንደሩ የሰጠሁትን ምላሽ ሰጠኋቸዉ፡፡ የሃለፊዎቹ ሁኔታ ከሁለት አመት በፊት የሆነዉን አስታወሰኝ፡፡ ያኔም የይቅርታ ፎርም ለመሙላት ፍቃደኛ ሳልሆን በመቅረቴ እንዳሁኑ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ፎርሙን እሞላ ዘንድ ይጠይቁኝ ነበር፡፡ በእንቢታዬ ስፀና ግን የተለያዩና አብዛኛዎቹም እስከዛሬ የዘለቁ የመብት ጥሰቶችን ይፈፅመብኝ ጀመር፡፡ ያሁኑስ እምቢታዬ ምን ያስከትል ይሆን? አላዉቅም፡፡ አንድ ነገር ግን አዉቃለሁ፡፡ መታረምና መፀፀት ያለብን ኢህአዴግ በሀገር ላይ የሚያደርሰዉን ጥፋት በመቃወማችን ምክንያት የታሰርን እኛ ሳንሆን አምባገነኑ መንግስት መሆኑን!

ዉድ አንባቢያን በመጨረሻ ሰብአዊ መብቶች የተከበሩባት ኢትዮጰያን ለማየት እንዲያበቃን እየተመኘሁ፣ ለተግባራዊነቱም የምችለዉን ሁሉ እንደማደርግና እንደምከፍል ቃል እየገባሁ እሰናበታችኋለሁ፡፡ “ምን ልታደርጊ ትችያለሽ?” የምትሉኝ ካላችሁ መልሴ የሚሆነዉ ማን እንደተናገረዉ ባላስታዉስም “የፍቅር አብዮት” የተሰኘ መጸሀፍ ሳነብ ያገኘሁት አንድ አባባል ነዉ ፡፡
” ሁሉን ማድረግ አልችልም ሁሉን ማድረግ አለመቻሌ ግን የምችለዉን ከማድረግ ወደ ኋላ አያስቀረኝም”

ርዕዮት አለሙ
ከቃሊቲ እስር ቤት

ባለቤት የሌለው መሬት –ቤጌምድር! (የመከላከያ ሰራዊት በትግራይ እና አማራ ተዋጊዎች መካከል ሰፈረ (ከዚያስ?))

$
0
0

begemedeir

(ዳዊት ከበደ ወየሳ)

ሉም ኢትዮጵያዊ ስለዚህ አካባቢ እኩል ግንዛቤ ላይኖረው ይችላል:: በመሆኑም ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ስለዚህ አካባቢ ታሪካዊ ዳራ ማሳየት አስፈላጊ ሆኗል:: እናም በታሪክ መንኮራኩር ትንሽ ወደኋላ መሄድ ሊኖርብን ነው::
 ይህ የሰሜን አውራጃ ከጥንት ጀምሮ ቤጌምድር ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን በራሱ መሪዎች ይተዳደር የነበረ ስፍራ ነው:: በደርግ ዘመን ስሙ ተቀይሮ ስሜን ጎንደር ሲባል በወቅቱ ከፍተኛ ክርክር የተደረገ ቢሆንም; ቀስ በቀስ ቤጌምድር መባሉ ቀርቶ ስሜን ጎንደር የሚለውን ስያሜ ይዞ ዘልቋል:: ይህ የቤጌ ምድር ክልል በሰሜን ከኤርትራ ጋር በመረብ ወንዝ, ከትግራይ ጋር ደግሞ በተከዜ ወንዝ ተፈጥሮአዊ ድንበር ሰርቶ ይተዳደር ነበር:: 

የኢትዮጵያ አፈር የጠራው ጠቢብ፣ የድሆች አባት ዶ/ር በርናርድ ተለየን ! -ነቢዩ ሲራክ

$
0
0
የማለዳ ወግ …የድሆች አባት ዶ/ር በርናርድ ተለየን !
* የኢትዮጵያ አፈር የጠራው ጠቢብ
*” ክብር ሞቱ ለሰማዕት ”
(ጸሐፊው ነብዩ ሲራክ)

(ጸሐፊው ነብዩ ሲራክ)

ዛሬ የምናዘክረው ሰው የኢትዮጵያ አፈር ፍቅር ጠርቶት ለጉስቁል ተገፊው ደሃ የሀገሬ ሰው ህይዎት ትንሳኤ ተግቶ ለውጥ ስላመጣ  ጠቢብ ነው። ዝካሬ ታሪኩ ቢያስተምረን ፣ አርአያ ሰብዕናው ግብአት፣ ተሞክሮ ቢሆነን ፣ ህይዎት ንብረቱን በእኛው ቀዬ ስላፈሱሰ ትጉት ሀኪም ነው ! ነፍሳቸውን ይማር ብለን ለሰሩት ስራ ክብር በመስጠት እናዘክራቸዋለን!  ዶክተር በርናርድ አንደርሰን ይባላሉ ! በርናርድ ዛሬ አይሰሙም ፣ አያዩንም …

የዶር በርናርድን እረፍት ያረዳችኝ መነኩሴዋ እናቴ ሀዘኑ ጎድቷት ” ልጀዋ ዋርካችን ተገረሰሰ እኮ ፣ የድሆች አባትና ጠዋሪ መድሃኒታችን አጣንኮ … ” ነበር ያለችኝ … ያልጠበቅኩት ነበርና ድንጋጤው መላ አካሌን ወረረው  ። የእንባ ሳግ እየተናነቃት ሃዘኗን ያጋራችን እናቴን ከማጽናናት ባለፈ ምንም ማለት አልተቻለኝም! እናም ስለ ጠቢቡን የድሆች አባት ዶር በርናርድ አንደርሰን ላዘክር በተጎዳ ስሜት ብዕሬን ሳነሳ ጠቢቡ በሰጡት የኑዛዜ ቃል መሰረት ቀብራቸው በሚወዷት ሀገረ ኢትዮጵያ ምድር ይሆን ዘንድ በተናዘዙት መሰረት ሊፈጸም ተቃርቧል ። ውድ ባለቤታቸው የአርበኛው ደራሲ ገሪማ ታፈረ ልጅ ከሲስተር እማዋይሽ ገሪማም  ከምድረ አሜሪካ የዶር በርናርድን ቃል ለመፈጸም ዛሬ እኩለ ቀን አ.አ ይገባሉ  !  ጥቂት ስለድሆች አባት በርናርድ አንደርሰን ላጫውታችሁ …

ዶር በርናርድን ሳውቃቸው  !

ከአራት አመት በፊት ጠቢቡ ወንድም አግኝቻቸዋለሁ  ።  ስለሚሰሩት በጎ አድታጎት  በቅርብ የሚያውቋቸው ስለደግነት ቸርነታቸው አውርተው የማይጠግቡ ወገኖችን አግኝቸ ብዙ ተነግሮኛል። ከዚህም ተነስቸ ጠቡቡን ወንድም በአንድ የራዲዮ ዝግጅት ከአንጋፋው የረጅም ጊዜ የጀርመን ራዲዮ ጋዜጠኛ ከተክሌ የኋላ ጋር በመሆን በአንድ ዝግጅት ለማቅረብ ጠይቄያቸው ነበር ። ዶር በርናርድ ግን ” ምኑን ሰርቸ ታሪኬ ይነገራል ! ” በማለት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ፋና ወጊና አርአያ ተግባራቸውን ለማስተዋወቅ አልተሳካልኝም ! ያም ሆኖ ጠቢቡ በርናርድ እና ባለቤታቸው ሲስተር እማዋይሽ ገሪማን  በኢትዮጵያ ባህል በተሽቆጠቆጠው ቪላቸውን ሲያስጎበኙኝ እዚህ  ስላደረሳቸው መንገድ አውግተናል ።   “አጴ ቴዊድሮስ በተወለዱበት እና ባቀኑት ሃገር የአህያ ግንባር የምታክል ማስታወሻና መዘከሪያ ቦታ እንዴት አይኖራቸውም?  ” በሚል ለቴዎድሮስ መታሰቢያ ሙዝየም ለማስፈቀድ ሲከላተሙ ያገኘኋቸው ከእውቋ ሀገር ወዳድ  ከወ/ሮ እማዋይሽ ገሪማ ጋር በመሆን የምድረ አሜሪካ የተደላደለ ኑሮ ስላፈናቀላቸው የእናት ኢትዮጵያ ፍቅር ፣ በታሪካዊዋ የጎንደር ከተማ  ስላሰሩት የአዛውኖቶች መጠለያ  ፣ ለህሙማን መርጃ ባቋቋመው የህክምና እርዳታ መስጫ ቦታና ያኔ ጅምር ስለነበረው የሆስፒታል ግንባታ መሰረት በሚጣልበት ማሳ ላይ ቆሜ ህልማቸውን አውገተውኛል ፣ ሃሳባቸውን ተጋርቻለሁ!

ለመሆኑ ዶር በርናርድ አንደርሰን ማናቸው?

በሃገረ ጃማይካ ካትሪን ደብር ተብላ በምትታዎቅ አንዲት መንደር እ.ጎ.አ መስከረም 21 ቀን 1944 ዓም ህጻን በርናንድ አንደርሰን  ከአርሶ አደር ወላጆቹ ተወለደ።  የበርናንድ ህይዎት በጃማይካዋ የካትሪን ትንሽ የገጠር መንደር መጀመሩ እንጅ ከዘር ማንዘሩ ርቆ በሌላ የአለም ጫፍ ካለችው ኢትዮጵያ ጋር በፍቅር ተቆላልፎ ህይወቱን ያሳልፋል ብሎ የሚገምት አልነበረም ። ገና ከልጅነት ህይዎቱ ጀምሮ ብሩህ አዕምሮ የታደለው በርናንድ በካሪቪያን ውስጥ አንጋፋ በሆነው የዎልማር የወንዶች ት/ቤት ተግቶ በመመማር ወደ ተሻለ ደረጃ መሸጋገር ጀመረ ፣ ከዚያም ጉዞውን ቀጠለ … የተሻለ እውቀት ጥም እያንገበገበው ወደ አደገችው ምድረ አሜሪካ አቀና ፣ በትምህርቱ በመግፋት እ.ጎ. አ 1960 ዎቹ መጀመሪያ በዋንሽን ግተን ዲሲ የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በህክምና ሳይንስ የመጀመሪያውን የባችለር ዲግሪ ሲቀዳጅ በከፍተኛ ማዕረግ ነበር ።  ለጎልማሳው በርናንድ በከፍተኛ የህክምና ተቋማት የላቀ ውጤት ማምጣት ተራ ትምክህት ሆኖ ሳይገታው የተሻለና የላቀ ፣ ከፍ ያለ ትምህርት የመቅሰም ህልምን ሰንቆ የማታ ትምህትቱን በመከታተሉን ገፋበት ። ይህንንም ህልም በአጭር ጊዜ ታጥቆ ለስኬት አደረሰው ። እ.ጎ. አ በ1970 ዎቹ በርናንድ በከፍተኛ ማዕረግ የዶክትሬት ማዕረግ ተመረቀ !

የዚያ ደርባባ ጎልማሳ ዶር ማንነት የተገነባው ከመደበ ኛው እውቀት ባለፈ አብሮት ከተቆራኘ ሰብዕና እንደነበር የሚያውቁት ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ ። ዶር በርናርድ አንደርሰን በሙያው ያጡ የነጡ፣ ጉስቁል ፣ምንዱባንን ለመርዳትና ለመደገፍ ቆርጦ ተነሳ ፣ ከምንም በላይ ደግሞ እንደ ቃል ኪዳን አድርጎ የያዘውን ተተኪ ፍለጋና ተተኪን ማፍራት ነበርና ድሎት ሳያታልለው ያደገ የተመነደገችውን ምድረ አሜሪካ ለቆ ወደሚያውቀው የድሆች ምድር አቀና  !  ወደ ጃማይካ ኪንግስተን …

ጃማይካ ኪንግስተን …

ህልሙን ለማሳካት ወደ ትውልድ ሃገሩ ጃማይካ ተመልሶ በወቅቱ ታዋቂ ከነበረው የኪንግስተን የህዝብ ሆስፒታል ስራውን ጀመረ ። የቀዶ ጥገና ጥበብ ባለሙያው ጎልማሳ ሃኪም ቅድሚያ የሰጠው በድህነት የሚማቅቁ ወገኖቹን መታደግ ነበር ፣ በህክምና ድጋፉ ፣ በተጓዳኝ ጥናትና ምርምሩ አንቱ በሚያሰኘውን ተመክሮ ራሱን እያጎለበተ ጉዞ የጀመረው ሃኪም በህክምና ድጋፍ ከመስጠት ርቆ ሔዶ በመምህርነት ሙያው ተተኪ ትውልድን የማነጽ ህልሙን አሳካ ። በዚህም ጉዞው ዶር በርናርድ አንደርሰን ለሃገሩና ለወገኑ ይህ ነው የማይባል አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ቻለ  !

ከጃማይካ መልስ በዋሽንግተን …

የጃማይካ ኪንግስተን ተልዕኮውን በሚገባ ከውኖ አቅፋ ደግፋ እውቀት ወደ መገበችው ሀገረ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ተመለሰ ። ዶር በርናርድ ለዚህ ላበቃው ዩኒቨርሲቲ ከእለትጉርሱ ያጠራቀመውን ከ100 ሽህ የአሜሪካ ዶላር የለገሰ ፣ ለሚሰረሰው በጎ ስረሰ ከመደሰተረ ውጭ ፣ መወደስ የማይሻ ሰብአዊም ነበር ።
ዶር በርናርድ ከጃማይካ መልስ እንደ አቻ የሙያው ባልደረቦቹ  ሃብት ንብረት የሚያካብትባቸው ሆስፒታሎ ች በከፍተ ኛ ገንዘብ ሊቀጥሩት ሲሻሙ አሻፈረኝ አለ።   ጥቅም ፍለጋ መማሰኑን ” ወዲያልኝ ” ብሎ ፣  የጤና ከለላና ሽፋን የሌላቸው ፣ በድንገተኛ አደጋ ተጎድተው ህይዎታቸው አጣብቂኝ የገቡትን የስልጡኑ ሀገር ተገፊ ምንዱባን መታደግ ወደ ሚችልበት በዲሲ ጄኔራል ሆስፒታል በአነስተኛ ደመወዝ ተቀጥሮ መስራት ጀመረ ።  በሙያው ተግቶ ፣ በሰብዕናው ጸንቶ ፣ ባሳየው ስኬትም በአጭር ጊዜ አንቱታን በማግኘቱ የሆስፒታሉ ሊቀመንበርና የቀዶ ጥገናው ክፍል ዋና ዳይሬክተር ለመሆን በቃ !  በአስተዳደር እና በሙያው ክህሎት የዲሲ ጀኔራል ሆስፒታል ከፍ ወዳለ ደረጃ ያደገው በዶር በርናርድ አንድሰን አመራር እንደነበር ዝክረ ታሪኩ ያስረዳል። ዶር በርናንድ ሆስፒታሉን ከማስተዳደር ጎን ለጎን የግል ክሊኒክ በድሆቹ መኖሪያ አቅራቢያ በዲሲ ሮድ አይላንድ መንገድ በመክፈት ፣ ለቻሉት በአነስተኛ ክፍያ ፣ ያልቻሉትን በነጻ በማከም ግልጋሎት ይሰጥም ነበር ።

የዶር በርናርድ አፍሪካና ኢትዮጵያ ትስስር …

በቀጣይ ዝካሬ ዶር በርናርድ ስነሳ እንደ አባት አቅርቤ ፣ እንደ ታላቅ ትጉህ ጠቢብ አንቱ እያልኩ መተረኬ ይገባኛል ፣ መልዕክቴ ከገባችሁ ለእኔ ያ በቂ ነው!  ብቻ ያገሬ ሰው ዶር በርናርድን  “የድሆች አባት ” ስላለበት አንድምታ ዘልቀን እናወጋለን …

ታህሳስ 24, 2007  ዓም ይህችን አለም የተለዩን ያልተጨበጨበላቸው ፣ ያልተነገረላቸው የኢትዮጵያ ወዳጅ ጃማይካዊ አሜሪካዊ ዶር በርናርድ የምናዘክረው በታላቅ  ክብር ነው  !  “ዶር በርናርድ ጉስቁል ምንዱባን ን ስትደግፍ ኖረሃልና ሞትህ የክብር ሞት ነው  ! ” ክብር ሞቱ ለሰማዕት ”  በሚል ታህሳስ 29 ቀን 2007 ዓም እኩለ ሌሊት በዋሽንግተን ዲሲ በተደረገ ሰፊ የጸሎትና የዝክር ስነ ስርአት ቤተሰብ ፣ ወዳጅ ዘመድና አድናቂዎቻቸው በተገኙበት የክብር ስንብት አድርገው በርናንድ በድናቸው እንዲያ ርፍ ወደ ፈቀዱባት ቅድስት ሀገረ ኢትዮጵያ በክብር ተሸኝተዋል ! በዚሁ ፕሮግራም ከተሰራጨው ዝክረ ህይዎት ያገኘሁትን መረጃ በቀጣይ እንደሚሆን አድርጌ የምናየው ይሆናል !

ለመላ ቤተሰብ ለወዳጆቻቸውና ለአድናቂዎቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ  !  ለሩቅ አሳቢ ቅርብ አዳሪው የድሆችን አባት ፈጣሪ በቀኙ ያሰረቀምጣቸው ዘንድ የዘወትር ጸሎቴ ነው  ! ነፍስ ይማር  !

ነቢዩ ሲራክ
ታህሳስ 30 ቀን 2007 ዓ.ም

በጎንደር አርማጭሆ የተቀሰቀሰው ግጭት ሊበርድ አልቻለም

$
0
0

10923573_1560615314186107_7573440129440943485_nኢሳት ዜና :-ባለፈው ሳምንት ታጣቂዎች በከባድ መሳሪያዎች በመታጀብ በጎንደር አርማጭሆ ውስጥ <<ሶረቃ>> የሚባለውን አካባቢ ወደ ትግራይ ለማካለል በወሰዱት እርምጃ የተነሳው ግጭት እስካሁን ሊበርድ እንዳልቻለ በስፍራው የሚገኘው የኢሳት ወኪል ያጠናቀረው ሪፖርት ያመለክታል።
ወኪላችን እንዳለው ታጣቂዎቹ፤ አርሶ አደሮችን በኃይልና በማን አለብኝነት አስነስተው ቦታውን ለማካለል ያደረጉትን ጥረት የአካባቢው ህዝብ ከዳር እስከዳር በመንቀሳቀስና ውጊያ ጭምር በመግጠም ነበር ያከሸፈው።በወቅቱ የታጣቂዎቹን እርምጃ ተከትሎ በተቀሰቀሰው ግጭት ከሁለቱም በኩል ጉዳት መድረሱ ታውቋል።
ውጥረቱ እስካሁን ያልበረደ ከመሆኑም ባሻገር የ አካባቢው ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር እየተጠራራ ንብረቱን ለማስጠበቅ በአንድ ተሰባስቦ መዘጋጀቱ፤ ሌላ ዙር የከፋ ግጭት ይቀሰቀሳል የሚል ስጋት አሳደሯል።

የበደል ድርድር –የቅጥፈት ውድድር። (ከሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

09.01.2014 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

Andargachew 1እንደ ሰው አለመሆንን ፍንትው አድርጎ ባሳዬው የሰሞናቱ የበደል ድርድር አብዛኛው የጭድ ክምር ሆኖ ነው እኔ በግሌ ያገኘሁት። በሌላ በኩል ግን ይህንን እጅግ የወረደ የቴሌቪዥን ቅንብር አይቶ ወያኔ መላእክ ሌላው ዓለም ጭራቅ ብሎ ብይን የሚሰጥ ሰው ይገኛል ብሎ መገመት እራሱ እውርነት ነው። ቀድሞ ነገር ለሰብዕዊ መብት ክብር ህጋዊነትን ለማብሰር የሃሳብ ነፃነት፤ የመደራጀት ነፃነት፤ የዕምነት ነፃነት፤ የመሰብሰብ ነፃነት፤ የመምረጥና የመመረጥ ነፃነት ዕውን መሆን አላባቸው – በጥቂቱ። ይህን ስለአደረጉ አስሮ – ደብድቦ – አፍኖና አሰቃይቶ „ሰብዕዊ መብታቸው ተጥበቆ ተዝናንተው ያልተጠዬቁትን ሳይቀር ተናገሩ¡“ ማለት እጭነት ነው። ለመሆኑ የወንድማቸውን ሁኔታ በአካል ተገኝተው ለማዬት ከሀገረ አሜሪካ ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ የሄዱትን እህታቸውንስ ስለምን በ24 ሰዓት ባዕታቸውን ዬእትብት መንደራቸውን ለቀው እንዲወጡ አደረገ ወያኔ? ይህም የወያኔ የነፃነት ገነት ተብሎ ሊወደስ ይሆን¡?
አዎን! የነፃነት አረበኞቻችን ሃሳባቸውን በመግለጻቸው ለምን ታሰሩ? የሚለውን ጥያቄም መመለስ ያስፈልጋል። ሃሳብን መግለጽ እኮ ወንጀል አይደለም። የማይገሰስ ሰማያዊ መብት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። በአንጻሩ ነፃነቱን የተነጠቀ ሰው በማናቸውም ሁኔታ ተደራጅቶ ለነፃነቱ የሚያደርገው ትግልም ቢሆን ህጋዊ ነው። ህገወጥ የሚሆነው ነፃነቱን የቀማው አካል ወንበዴው ወያኔ ሰብዕዊ መብትን እረግጦ፤ የሰው ልጅን ሰብዕዊ መብት ለማስከበር በተጉት ላይ የሚያካሂደው የህሊና ዘረፋ፤ ህሊናን አስገድዶ ድፈረት ነው- ወንጀሉ። አስገድዶ ህሊናን በመዳፈር በታሪክ ወያኔ የመጀመሪያውን ረድፍን ይይዛል።
ወያኔ በቀል ነው መርኹ። በቀል ደግሞ ምህረት የለሽ ነው። ምህረት የለሽ መሆን ደግሞ ከሰው ደረጃ አውርዶ አውሬነትን ያውጃል። ይህ ደግሞ የሚጨበጥ የሃቅ እንክብል ነው። በእያንዳንዷ ቀን፤ በእያንዳንዷ ሰዓት፤ በእዬአንዳንዷ ደቂቃ የዜጎቻችን ደም በህገወጡ ጎጣዊ ድርጅት በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በወያኔ ይፈሳል። በወገኖቻችን ላይ ኢ- ፍትሃዊ ተግባር ይፈጸማል። እያንዳንዷ የወያኔ የመኖር ስንቅ ቋሳን ሰንቆ አሪወሳዊ ተግባርን መፈጸም ነው። ይህ ደግሞ በሚታዩ ብቻ ሳይሆን ብዙ በማይታዩ የሰው ልጅ ሊደርስባቸው በማይችሉ ማናቸውም ስለታማ ጦር ጥቃት ይፈጸማል። ወገኖቻችን – ይቀቀላሉ። መፈተኛና መሞከሪያም ይሆናሉ – በገደል ውስጥ እያሉ ተቅብረው አንድ ሜትር በአንድ ሜትር በሆነ ዛኒጋባ ይሰቃያሉ። ወንድ ከሆነ ወያኔ ስለምን ያሉበትን ቦታ ሆነ የተሰወሩበትን ሁኔታ አደባባይ አያውለውም?!
ቀድሞ ነገር እስር ቤት ሆኖ ለዛውም በወያኔ እጅ ተወድቆ „ምቾት ላይ ናቸው¡“ ብሎ ማወጁ የወያኔን የማስተዋል ደረጃ ምን ያህል ቁልቁል እንደሆነ ያሳያል። ለምን? ሰው ሃሳቡን በመግለጹ፤ የተሻለ ሥርዓት እንዲኖር በማለሙ እኮ ለምን ይታሠራል? ለዚህ መልስ አለው ሽፍታው ወያኔ?! ከታሠሩ በኋላ እንኳን ባልተቋረጥ እገዳ ከቤተሰብ – ከጠያቂ ጋር እንዳይገናኙ፤ ስንቅ እንዳይገባላቸው ለምን ያደርጋል?! መልስ አለው ሽፍታው ወያኔ? ለነገሩ ወያኔ በሰብ ተፈጥሮ ማለትም እንደ ሰው በራሱ ተፈጥሮ የሸፈተ አሜኬላ እኮ ነው። እራሱን አያምንም ሌላውንም አያምንም። እራሱን ሆኖ መኖር አይችልም። ስለምን ሰብዕነትን የዘለለ እሾኽ በመሆኑ።
እንሆ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሁለት የግንቦት 7ትን ጥንካሬ ላነሳ ፈልግሁ። የታዘብኩትን – በእኔ ዕይታ። የጹሑፌ ሐዲድ ነውና። የመጀመሪያው የግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር አካላት የነገን መተንበይ ባልችልም እስከ አሁን ባለው ሁኔታ የመደማመጥ አቅማቸው አንቱ ነው። የሃሳብ ልዩነት በፓርቲ ህይወት ውስጥ እንደሚኖር ግድ ይላል። ነገር ግን ይህን የሀሳብ ልዩነት በበለጸገ የዴሚክራሲ መደማመጥ መምራት መቻል ሥልጡንነት ነው። ከፍተኛ አመራር አካላቱ ሲካሰሱ ወይንም የፈነገጡ ሃሳቦችን አደባባይ አውለው ማስተባበያ ድርጅቱ ሲሰጥባቸው አይታይም። ስለዚህ ግንቦት ጊዜውን በአግባቡ ማስተዳደር የቻለ፤ በጋራ አመራርና በግል ኃላፊነት መመራቱን ዕውነታው ይመሰክራል። ሁለተኛው ብርቱው የብቃት ሚስጢር ደግሞ ግንቦት ህጋዊ በሆነ የህዝብ መድረክ፣ የመገናኛ አውታር ወይንም ማህበራዊ ድህረ ገጽ አቻ የነፃነት ትግል ፓርቲዎችን ሲተች፤ ሲያቃልል፤ ሲያብጠለጥል ተደምጦ አያውቅም። ይህም የጥንካሬው ሌላው የተግባር ህንፃው ነው።
ይህ ደግሞ ለገዢው የጎጥ ድርጅት አይመችም – ፈጽሞ። ከጠጠር ላይ የመተኛት ያህል ይጎረብጠዋል፤ ከረመጥ ላይ የመጋደም ያህል ያርመጠምጠዋል – ከሹል ድንጋይ ላይ የመቆም ያህል ያቆነጠንጠዋል። ስለዚህ የተሰበረ የፍላጎት ድልዱዩን ለመጠገን ሌላ መንገድ ፈለገ። …. ግንቦት ካለተፈጥሮው፤ ከላአደገበት ተመክሮው ከሌሎች ፓርቲዎች ወይንም ድርጅቶች ጋር ማዋጋት ፈለገ። ይህ … ይቀጥላልም። በህልሙ የሚነስተው ነበላባላዊ የነፃነት አርበኛ መጠሪያ ሥም ከህዝብ ፍቅር ለማግለል ብዙ አሳቶች ነገም ይጫራሉ …. ነገር ግን እኛ ሆን የጉዳዩ ባለቤት የነፃነት ትግሉ አባዎራዎች በበሰለ ተምክሮና – ማስተዋል፤ በቀና እና ቀጥ ባለ ህዝባዊ ፍላጎት ትግሉን ሊመሩና ሊያስተዳደሩ ይገባቸዋል። የጠላት ሴራ ጉቶዎች ሆኑ ጉንጉኖች ጅማሯቸው … ይከታተላል። መሆን ያለበት መፈለግና ማሳካት የመቻልን አቅም ይለካልና … ከጫካ ዶክተሪን በልጠው መገኘት ይኖርባቸዋል – እያንዳንዱ የነፃነት ትግሉና መሪው። ። ህዝቡንም ድንቆችን ከነክብራቸው ሊጠበቅቻውና መንፈሱን ሳይሳሳ ሊለግሳቸው ይገባል። የሚቻልን – ለማስቻል ነገን በብቃት ማዬት ይጠይቃል።
ለዚህም ነው በጣም በተከደነ ሁኔታ ሥጋት ያለበት የወያኔ አመራር ኢትዮጵውያንን ቀንዲል ሥም በማስጠራት በዛ ላይ መጥፎ ምስል እንዲኖር ለማድረግ የተጋው። ግን ጥረቱ የበከተ – የበሰበሰና የዛገጠ አተላ ነው የሆነው። ከእሱ በላይ ህዝብ አካሎቹን የነፃነት ትግሉን ተስፋዎች ሆኑ መሪዎችን ልጆቹን ያውቃል – አሳምሮ። ነፍስ አስቶ – ሌላ ሰብዕና ፈጥሮ፤ በመርዝ አደንዝዞ – ይቀዳል። የተናገራችሁት ይህ ነበር ይባላሉ – እስረኞቻችን። በዝብርቅ ፊልም ቅንብር እሱ እንደሚያመቸው ያው በጫካ ተመክሮ ተለብዶ – ተለስኖ – በስሚንቶ ታሽጎ እንዳዬነው ይቀርባል። …. ፍላጎትን ጠንቅቆ የሚያውቀው የአስተዋዩ የኢትዮጵያ ህዝብ አብራክና ማህጸን ክፋይ ወገን ግን ይህን የቅጥፈት ድርድር በሚገባ በልቶ ያውቀዋል። ይልቁንም በምን የብቃት ልክ እዬተመራ መሆኑንም ይመዝንበታል። እንዲህ ማጣፊያ ሲያጥር – ወያኔ ግርድ ያበጥር። ሌላው ደግሞ በጣም ወያኔ ተንጠራራ – እኛ የምናስከፍለው የቋሳ ዋጋ ዝቅ ያለ ነው ይቀረናል —- ዓይነት …. ለሰው ልጆች የስቃይ መጠን ውድድር አሰኘው። – በዴሞክራሲ ትርጎሜና የተግባር ክንውን ከአደጉት ሀገሮች ጋር እራሱን አለካካ። ሽልማትም አሻው —- መካሬ የለሽ፤ ግራጫ የመከነበት ፍልስ ድርጅት – ነገ የሸሸው።
አዎን! የሚገርመው – ወያኔ በእጁ የገባውን ጀግና መንፈስ በጣም ከቀደመው በላይ በሰፋ ሁኔታ ይፈራዋል። በመንፈሱ ብቻ ይርበደበዳል። ያለውን እንኳን በተሰተካከለ ሁኔታ ለማቅረብ አቅም የለሽ እዲሆን ያደረገውም ይሄው ነው። በራሱ ፍርድ ቤት እንኳን ለማቅረብ ድፍረት ከድቶታል። ኮሽታው ሁሉ በድንጋጤ ያደናብረዋል። ስለምን የእኔ የሚለው ከጎኑ የቆመ አንድ ብጣቂ ሃቅ የለምና። በራሱ ድርጊት እፈረቱ በቀለሰለት ጎጆ ተደብቆ ይዳክራል።
ጎጠኛው ወያኔ ሃቅን እንደ ፈራ ኑሮ ከሃቅ ጋር ሳይገናኝ፤ ከሃቅ ጋር ሳይመክር እልፈቱን ያውጃል። ወያኔ ሲከስም ዘር አልባ ሆኖ ነው። ስለምን? የሰብዕነት ፍርፋሬ ተጠግቶት ስለማያውቅ። እውነት ስለ ራቀው። ህዝባዊ ፍቅር ስለ ፈለሰበት – ከባህር የወጣ አሳ ነው። የወያኔ መኖሪያው ዙ ቢሆን መልካም በሆነ ነበር። እንደ እንሰሳ ኑሮ – እንደ እንሰሳ ማለፍ። አዬንለት አዲስ የተባለለትን ቪዲዮ – አንድ የሚጨበጥ ነገር በሌለው ፍሬ ፈርስኪ የፋንድያ ክምር – ዜሮን ደመረ። እኔ እንኳን አዲስ ነው ለማለት በጣም ነው የተቸገርኩት። ምክንያቱም በተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው እጣት ላይ የነበረው ቁስለት ሆነ የጥፍራቸው ደሙ የተመጠጠው ግርጠት አሁንም እንደ አለ ነው። የሰውነት ላሂያቸውን በሚመለከት የፊልም ቅርበትና ርቀት ቀረጻ ካልሆነ በስተቀር እንደ ወቅቱ ተፈሪነት ሁኔታ ያን ጊዜ የተቀረጸውን ቆራርጠው ክፍል አንድ – ሁለት – ሦስት እያሉ ይቀጥላሉ ባይም ነኝ። በሌላ በኩል የዋሁም ደህና ነው የተሻለ ገጽ አለው እንዲል መንፈስ ለማዛል የተጠቀሙበት ነውም ባይ ነኝ። ምክንያቱም በጣም ነው የኖረውን ቁጫን ሁሉ በእሳቸው ላይ የተወጡት። ማንፌስቶውን ጽፎ ወያኔ ድርጅቱን ሲመሰርት የተሰማው ያህል ቁርሾ ነው በሂደቱ ማዬት የተቻለው። ስለዚህም የተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አገግመው ለመወጣት እንዲህ ቀላል አይሆንም ባይ ነኝ። ለዚህም ነው እሳቸውን በሚመለከት ቀዳዳዎች ሁሉ የተወታተፉት። ወያኔ ለፈጸመው ድርብርብ – ዘመን ይቅር ለማይለው ወንጀል አቅርቦ በአካል ለማሳዬት አቅም ያንሰዋል። ነፍስ ያለቀጠሮ ስለማትወጣ እንጂ የክርስቶስን መከራና ስቃይ እንደተቀበሉ መረዳት አያቅትም።
ወሳኝ
ከሰሞናቱ የቪዲዮ ይፋ መረጃ አንድ ዋሳኝ ጉዳይን ዘለግ ባለ ሁኔታ ማዬት ያለብን ይመስለኛል። ከወያኔ ኢንባሲዎች ውጪ የወያኔ ደጋፊ አከርካሪዎች ዘማች እጅ ምን ያህል ለብቅላ ሆነ ለጉርጉራ የመደመጥ አቅም እንዳላቸው እኔ በግሌ ማዬት ችያለሁ። በሌላ በኩል „የታላቋ ትግራይ ህልመኞችንም“ መስመር ተመልክቸበታለሁ። ወያኔ ከቅርቡ ያለውን ጉዳይ እንኳን ከተፈጸመ በኋላ ነው ማዬትና ማስተዋል የሚችለው። እንኳንስ የውጩን የማገናዘብ አቅም ሊኖረው ቀርቶ። ባናኝና ዕብን ነውና። ቀላሉ ምሳሌ የ97 ምርጫ ወያኔ በእጁ ያለውና የሌለውን የተረዳው መቼ ስለመሆኑ ጭብጥ ማስረጃ ነው። ከዚህ በኋላ ነቅቶ ስንት ነገሮችን እንደ ከለሰ ይታወቃል። ስለዚህ በዚህ ስሌት ሲኬድ የአሁኑ ቪዲዮ መንፈስ መነሻው የት እንደሆነ ለማገናዘብ ይቻላል ባይ ነኝ። እርግጥ የጠጠረና ረቂቅ ነው … እንዲህ በበሩ ዘው ተብሎ ተገብቶ የሴራውን ውስጥ ማዬት አይቻልም እንጂ ፍሬ ነገሩ ውጪ ያለው የወያኔ የድጋፍ መስመር የዳንኪራው ሁሉ ማሳረጊያ ሆኖ ነው – እኔ በግሌ ያገኘሁት። ውዶቼ የኔዎቹ ፈትሽቱት – ከልብ ሆናችሁ። ሌላ መልዕክት ያሰተላልፍላችኋል።
መቋጫ
የሆኖ ሆኖ ምንግዜም በጠላት እጅ የወደቀ ወገን ታሪካችን ነው። ምንጊዜም በጠላት እጅ የወደቀ ወገናችን አርበኛችን ነው። ምንጊዜም በጠላት እጅ ጥቃት የተፈጸመበት ህዝብ ሰንደቃችን ነው። ምንጊዜም በጠላት እጄ የተጎሳቆለ ተቋም ዓርማችን ነው። ምንጊዜም በጠላት እጅ የወደቀ መንፈስ ዝክራችን ነው። ምንጊዜም በጠላት እጅ ስቃይ የተፈጸመ ገላ ደማችን ነው። ምንጊዜም በጠላት እጅ የጥቃት ሰለባ የሆነ አካል መርሃችን ነው። ሲጠቃለል ታሪክም ዘመንም የነፃነት ትግሉን መጸሐፍ ይጽፋሉ። መጸሐፎቻችን ውስጦቻችን ናቸው። ታማኞቻችን ማተቦቻችን ናቸው – የወልዮሽ ብሄራዊ ሃይማኖታችንም።
ትናንትም ዛሬም ነገም የተከበሩ አቶ አንደርጋቸው ጽጌ መንፈሳቸው የነፃነት ደወል ነው። የከፈሉት መስዋዕትነት – የሚቀበሉት ስቃይ፤ ያዩት ፈተና የበለጠ እንድናከብራቸው – እንድንወዳቸው – አንድናደንቃቸው ያደርገናል። ሥማቸውን ስናሰብው በደማችን ሃዲድ ያበራል። ተግባራቸውን ስናሰላው በእዝነ ልቦናችን ያፈልቃል – ለምንግዜም። ግርማቸው – አንደበታቸው – ድርሳናችን ነው። የተግባር ሰውነታቸው የትም ይሁኑ የትም መንገዳችን ነው።
አንድ አስተዋይና ሳቂተኛ ንፋስ ይመጣል – አውሬን ለማሰናበት።
ሁሉን ለሰጠ ጀግና ክብራችን የሰንድቕዓላማችን ያክል ነው!
ጀግኖቻችን መርሆቻችንና መንገዶቻችን ናቸው።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ለጥምቀት ሰማያዊ ቲሸርት እንዳይለበስ ተከለከለ • ህዝብን ያነቃቃሉ የተባሉ መንፈሳዊ ጥቅሶች መጠቀም አይቻልም ተብሏል

$
0
0

semayawi(ነገረ ኢትዮጵያ) የክርስትና እምነት ተከታይ ወጣቶች ጥምቀት በዓል ላይ ሰማያዊ ቲሸርቶችን እንዳይለብሱ መከልከላቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ፈረንሳይ ሌጋሲዮን ጀምሮ እስከ ጃንሜዳ አካባቢ የሚኖሩ ወጣቶች በተለያዩ ማህበራት ስር ለጥምቀት በዓል ዝግጅት እያደረጉ እንደሚገኙ የገለጹት ምንጮቹ ከዝግጅታቸው መካከል ቲሸርት አሳትሞ መልበስ አንዱ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ሆኖም ወጣቶቹ ለጥምቀት በዓል የተለያዩ የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅሶች የታተሙበት ሰማያዊ ቲሸርት ማሳተማቸውም ተከትሎም ደህንነትና ሲቪል የለበሱ ፖሊሶች በየ ቤታቸው እየዞሩ ‹‹ጥምቅት በዓል ላይ ሰማያዊ ቲሸርት መልበስ አይቻልም፡፡›› እያሉ እያስጠነቀቁ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በነገው ዕለትም ካድሬዎች ከፈረንሳይ ሌጋሲዮን እስከ ጃን ሜዳ አካባቢ የሚገኙ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በጉዳዩ ላይ ለማነጋገር ስብሰባ መጥራታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተመሳሳይ ህዝብን ያነቃቃሉ ከሚል ስጋት አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በቲሸርት ላይም ሆነ ሌላ ለጥምቀት በዓል ላይ በማድመቂያነት በሚውል ነገር ላይ ማተም እንደማይቻል ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ወጣቶቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ለጥምቀት በዓል ማድመቂያነት እንዳይውሉ ከተከለከሉት ጥቅሶች መካከል ‹‹የጌታ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን፣ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚያብሄር ትዘረጋለች፣ የአባቶቻችን ርስት አንሰጥም….›› የመሳሰሉት ይገኙበታል ተብሏል፡፡ እነዚህን መንፈሳዊ ጥቅሶች መጠቀም እንደሚያስቀጣም ደህንነትና ፖሊሶች የበዓሉ አዘጋጅ ወጣቶችን አስጠንቅቀዋል፡፡

ወጣቶቹ ሰማያዊ ቲሸርትም ሆነ የተከለከሉትን መንፈሳዊ ጥቅሶችን በሐይማኖታዊ ፋይዳቸው ምክንያት ባለፉት የጥምቀት በዓላት ላይ ሲጠቀሙባቸው እንደቆዩ፣ አሁን ደህንነቶች እነሱ ካላሰቡት ፖለቲካ ጋር ማገናኘታቸው እንዳሳዘናቸውና ከሐይማኖታዊ ፋይዳቸው ውጭ ምንም አይነት ትርጉም እንዲኖራቸው ታስበው የተሰሩ ባለመሆናቸው በበዓሉ ላይ እንደሚጠቀሙባቸው ገልጸዋል፡፡

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ እሁድ ጥር 3 ቀን ጠቅላላ ጉባኤው ለማድረግ በዝግጅት ላይ ነው።

$
0
0

UDJየአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ እሁድ ጥር 3 ቀን ጠቅላላ ጉባኤው ለማድረግ በዝግጅት ላይ ነው። የጠቅላላ ጉባዔ መደበኛ ስብሰባ በየሶስት አመቱ ሲሆን አስቸኳይ ወይንም ልዩ የጠቅላላ ጉባኤ መጥራት እንደሚቻል የአንድነት ደንብ በግልጽ ያስቀምጣል፡ በአንድነት ደንብ መሰረት አስቸኳይ ወይም ልዩ ጠቅላላ ጉባዔ መጥራት የሚቻለው ከጠቅላላ ጉባኤ አባላት አንድ ሶስተኛው ሲጠይቁ ወይንም ምክር ቤቱ ሲወስን ብቻ ነው። የጠቅልላ ጉባኤ አባላት በፓርቲው የተመዘገቡ፣ የድርጅቱ አባልነት መታወቂያ ያላቸው ናቸው። የድርጅቱ የሥር አስፈጻሚ ኮሚቴ ፣ የቀድሞ ሊቀመንበር ሆነ የአሁኑ ሊቀመንበር ጠቅላል ጉባኤ የመጥራት ስልጣን በደንቡ መሰረት የላቸውም።
በዚህ መሰረት ከጠቅላላ ጉባኤ ቀጥሎ የድርጅቱ የበላይ አካል የሆነው ብሄራዊ ምክር ቤቱ፣ ሐሙስ ታህሳስ 30 ቀን ባደረገው ስብሰባ ነበር እሁድ የሚደረገዉን ጠቅላላ ጉባኤዉ የጠራው። በምክር ቤቱ ስብሰባ፣ “ቅሬታ አለን” ባለው አሁን ባለው አመራር ላይ ችግር ያላቸውና ምርጫ ቦርድ በመሄድ ከምርጫ ቦርድ ጋር አብረው ሲሰሩ ከነበሩት መካከል፣ ሶስት የምክር ቤት አባላት ( 5 %) ፣ ሐሳባቸውን እና ታቋዉሟቸውን ለማሰማት እድል ተከፍቶላችው የነበረ ቢሆንም፣ ዝምታን መርጠዋል። በስብሰባው የተገኙ ሌሎች 39 (78%) የምክር ቤት አባላት ግን የጋራ አቋም በመያዝ፣ በምርጫ ቦርድ እየተደረገ ያለውን ኢ-ሕገመንስግታዊ እንቅስቃሴ በማውገዝ አንድነት በፊቱ የተደቀነበትን መሰናክል ያልፍ ዘንድ ጠቅላላ ጉባዔዉ በተሎ እንዲጠራ የወሰነው።
መኢአድ እና አንድነት የዉህደት ስምምነት በሚፈርሙበት ጊዜ ኢሕአዴግ ዱርዬዎች ልኮ ስብሰባዉን ለመረበሽ ሞክሮ እንደነበረ ይታወቃል። በዚህም ምክንያት ተመሳሳይ ነገር እንዳይፈጠር፣ ፖሊስ ለምን አስቀድማችሁ አልነገራችሁኝ ነበር እንዳለይ፣ ፖሊሲ አስፈላጊዉን ጥበቃ እንዲያደርግ ከወዲሁ የማሳወቅ ሥራም ተሰርቷል። ምርጫ ቦርድ ሕጉ እንደሚጥይቀው ታዛቢዎች እንዲልክም ደብዳቤ እንዲደርሰው ተደርጓል።
– See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/3418#sthash.jqJccZ66.dpuf


የሕዝባችን አንድነት እና የአገራችን ታሪካዊ መልካአ-ምድር ለመጠበቅ ታሪካዊ ሃላፊነት ለሚሰማችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፦

$
0
0

Gondor Hibretእንደሚታወቀው የጎንደር ክ/ሀገር፤ የጋራ መመኪያችን ለሆነችው ኢትዮጵያችን የአንድነት መሰረት የታሪክ እምብርት በመሆን ትታወቃለች። በመሆኑም፤ ለሁላችንም ኩራት እና መመኪያ የሆነችውን ኢትዮጵያ አገራችን ለማጥፋት መሰሪ አላማን ይዘው የተነሱ አገር አጥፊዎች ሁሉ የመጀመሪያ የጥፋት ክንዳቸውን የሚሰነዝሩት፤ ጦራቸውን የሚወረውሩት አላማቸው በቀላሉ ይሳካ ዘንድ በቅድሚያ በጎንደር ላይ ነው። እንደምሳሌ የውጭ ወራሪዎችን ብንጠቅሥ፤ በእጅ አዙር ቱርኮች ከግብፃዊያን ጋር በመተባበር የሀገር ውስጡን ግራኝ መሃመድን በመሳርያነት በመጠቀም ከ1519-1535 ዓ. ም፤ እንዲሁም ድርቡሾች በ1880-81 ዓ. ም. በቀጥታ፤ በማዝመት፤ ስፍር ቁጥር የሌለው ወገኖቻችን ጨፍጭፈዋል፤ የታሪክ ቅርሶችን መዝብረው፤ ቀሪውን ለማሥረጃ እንዳይተርፍ ለቃቅመው አቃጥለዋል። —

ሙሉውን ጋዜጣ በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ—-

ዘ-ሐበሻ ሰበር ዜና –አንድነትን ፓርቲ ምርጫዉን መሳትፍ የለበትም የሚል የፖለቲካ ዉሳኔ እንደተወሰነ ፣ ከሕወሃት አመራሮች ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን ገለጹ

$
0
0

ሰበር ዜና – አንድነትን ፓርቲ ምርጫዉን መሳትፍ የለበትም የሚል የፖለቲካ ዉሳኔ እንደተወሰነ ፣ ከሕወሃት አመራሮች ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን ገለጹ

UDJ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ የበረራ ቁጥር ET -AQV አይሮፕላን በጋና አክራ ተከሰከሰ

$
0
0

ethiopian airlines 2

ethiopian airlines
Minilik Salsawi

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ አይሮፕላን በኮቶካ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ሜከስከሱ ከጋና አክራ የወጡ ዜናዎች አመለከቱ::

የመከስከስ አደጋው የተከሰተው ካርጎ አይሮፕላኑ በኤርፕርቱ ለማረፍ ሲንደረደር በነበረው መጥፎ አየር ምክንያት መሆኑን የአየር መንገዱ ባለስልጣናት ተናግረዋል::አደጋው የተከሰተው ጠዋት ሶን የጋና አየር መንገድ ባለስልጣናት ዘግይተው መረጃ መስጠታቸው ታውቋል::

የበረራ ቁጥሩ ET -AQV የሆነው አይሮፕላን ከቶጎ ሎሜ ተነስቶ አክራ ለማረፍ ሲሞክር አደጋው መድረሱን ባለስልጣናቱ ተናግረዋል::በአይሮፕላኑ ጋር የነበሩ 3 ሰዎች የተረፉ ሲሆን በአሁን ሰአት በወታደራዊ ሆስፒታል ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል::

ወያኔ ኢትዮጵያን አፍርሶ ወደ ጉሬው ለመግባት

$
0
0

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት     ቅዳሜ ጥር ፪ ቀን ፪ሺህ፯  ዓ.ም.                         ቅፅ ፫ ፣ ቁጥር ፰

የመጨረሻ መሠናዶውን እያደረገ ነው
· የትግሬ-ወያኔዎች ከተለያዩ ጎሣዎች እና ነገዶች ሰዎችን መልምለው እና አደራጅተው፣ እንዲሁም የወታደራዊ፣ የደህንነት፣ የአደረጃጀት፣ የአመራር እና የቁጥጥር ሥራ የሚሠሩ የትግሬ-ወያኔዎች መድበው በከፍተኛ ሚሥጢር ኢትዮጵያን የማፈራረስ ሤራ እየተዶለቱ መሆኑን በተጨባጭ መረጃዎች አረጋግጠናል።

moreshየትግሬ-ወያኔ የመጨረሻ ግብ ኢትዮጵያን በመበታተን፣ የትግራይ ረፑብሊክ መመሥረት መሆኑን በ1968 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው ፕሮግራሙ መሠረት ላለፉት ፵(አርባ) ዓመታት ያደረገው ጉዞ ያሣያል። በጉዞው የኢትዮጵያን የረጅም ዘመን ታሪክ ክዶ በመቶ ዓመት መገደቡን፣ የትግሬ-ወያኔ መሪዎች እና አባሎች በተደጋጋሚ በጻፉዋቸው መጻሕፍት እና በየአጋጣሚው ባደረጉዋቸው ንግግሮች ለሕዝብ ይፋ ማድረጋቸው ይታወቃል። «ኤርትራ በኢትዮጵያ በቅኝ ግዛትነት የተያዘች ናት፤ ስለሆነም ሻዕቢያ የሚያካሂደው የመገንጠል እና የነፃነት ጥያቄ ተገቢ እና ትክክል ነው።» ብለው፣ ከሻዕቢያ በላይ ሻቢያ ሆነው፣ የትግራይን ልጆች የጦር ማገዶ በማድረግ ኤርትራን ማስገንጠላቸው ማንም ሊያስተባብለው የማይችለው ሃቅ ነው። ኢትዮጵያውያንን እንደ አንድ ሕዝብ ያስተሳሰሩ የወል ዕሴቶችን፥ «የኢትዮጵያዊነት አገራዊ እና ብሔራዊ ስሜት የሁሉም በኢትዮጵያ የሚኖሩ ነገዶች እና ጎሣዎች ሳይሆኑ፣ የዐማራው ብቻ የማንነት መገለጫዎች ናቸው፤ ዐማራው ጨቋኝ እና በዝባዥ ነገድ ነው፤ እርሱን ሁሉም ነገዶች እና ጎሣዎች በወያኔ መሪነት ተባብረው ማጥፋት አለባቸው።» በማለት በከፈቱት የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ጦርነት፣ የኢትዮጵያዊነት የወል ዕሴቶችን፣ ተቋሞችን፣ ግንኙነቶችን፣ አሠራሮችን ወዘተርፈ በማጥፋታቸው ዛሬ አገሪቱ እና ሕዝቧ የሚገኙበት ሁኔታ በግልጽ ያሣያል። የአገሪቱ ዘመን-ጠገብ መልከዐ-ምድራዊ መለያ ስሞች እና ወሰኖች ተሽረው በተወሰኑ ነገዶች ማንነት ብቻ ላይ የተመሠረቱ ስሞች በመስጠት፣ የኢትዮጵያውያንን ተዘዋውሮ በፈለጉት ቦታ እና አካባቢ የመኖር እና የመሥራት ተፈጥሮአዊ፣ ታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ሰብአዊ መብቶቻቸውን ገፍፈው፣ አንድነታቸውን አሣጥተው፣ አብሮነታቸውን ክደው፣ በጠላትነት እንዲተያዩ አድርገዋቸዋል። ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ከሕዝቡ ስሜት ፈጽሞ እንዲጠፉ መጠነ ሠፊ የሆነ የሥነልቦና ጦርነት ከፍተው አገሪቱን ከመጨረሻው የጥፋት ጠርዝ ላይ አድርሰዋት ይገኛሉ።

የትግሬ-ወያኔ እና ተከታዮቹ በኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና ብሔራዊ ጥቅም፣ እንዲሁም በሕዝቧ ኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ ታሪክ፣ ትውልድ፣ ሕግ እና ማናቸውም ዓይነት ሥነ-ምግባር ይቅር ሊለው የማይችል የክህደት ተግባሮችን የፈጸሙ መሆኑን ከማንም ይበልጥ ራሣቸውም አይክዱም። ይህም በመሆኑ የኢትዮጵያ አንድነት ተጠብቆ ከዘለቀ በየትኛውም ጊዜ በአገር ክህደት ወንጀል ተጠያቂ እንደሚሆኑ ያውቃሉ። ከዚህ ተጠያቂነት ለመዳን እንችላለን ብለው የሚምኑት ሁለት ነገሮችን ጎን ለጎን ማከናወን ሲችሉ ብቻ ነው። እነዚህም፦ አንደኛ የወያኔ ትውልድ ለሚቀጥሉት መቶ ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሕይዎት ላይ የወሳኝነቱን ሚና ይዞ የሚቀጥልበት አስተማማኝ ሁኔታ ሲረጋገጥ፤ ይህ የመጀመሪያው ዕቅድ በተለያዩ ምክንያቶች ባይሣካ ሁለተኛው አማራጭ ዕቅድ ትግራይን ከኢትዮጵያ በመገንጠል የትግራይ ረፑብሊክ በመመሥረት ጎጆ መውጣት፤ የሚሉ ናቸው።

ሁለተኛውን ግብ ለማሣካት በኢትዮጵያ ላይ ሥልጣን ከተቆጣጠሩ ጊዜ ጀምሮ ለምትገነጠለው ትግራይ ቁሣዊ፣ ቴክኒካዊ እና ኅሊናዊ ሁኔታዎች እንዲሟሉ የሚያስችሉ ተግባሮችን ማከናወን እንዳለባቸው ታሣቢ አድርገው መንቀሣቀሣቸው ባለፉት ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት የሥልጣን ዘመናቸው ትግራይ ውስጥ አያሌ የመሠረተ ልማት ሥራዎች መሥራታቸው ይታወቃል። በዚህም መሠረት የትግራይ ክልል ከጎንደር እና ከወሎ ክፍለ ሀገሮች መሬት ነጥቀው በታሪክ የትግራይ አካል ሆነው የማያውቁ አካባቢዎችን አጠቃልለው ጥንተ-ነዋሪውን የዐማራ ነገድ አባላት የሚገድሉትን በመግደል፣ ቀሪውን በማሠር እና በማሰደድ ትግሬን አስፍረውበታል። ይህ የያዙት ግዛት ወደፊት ለምትገነጠለው ትግራይ ይጠብባል በማለት ከሰቲት ወደ ደቡብ ምዕራባዊ የጎንደር እና የጎጃምን የሱዳን አዋሳኝ ወረዳዎችን ከቤንሻጉል ጉምዝ እና ጋምቤላ ክልሎች ጋር በማገናኘት የታላቋ ትግራይን የመሥፋፋት ዓላማ ዕውን በማድረግ ላይ ይገኛሉ (አባሪ ካርታውን ይመልከቱ)።

በዚህም መሠረት ለወደፊቷ ትግራይ ለምትጠቀልለው ሠፊ ግዛት፣ ከውጭው ዓለም ጋር የሚያገናኙ የመገናኛ መሥመሮችን ዘርግተዋል፣ ተጨማሪ መሥመሮችንም በፍጥነትም በመገንባት ላይ ይገኛሉ። የትግራይን ምርት ወደ ውጭ ለመላክ እና ከውጭ የሚፈለጉ ሸቀጦችን ወደ ውስጥ ለማስገባት፣ ከጅቡቲ እስከ መቀሌ፣ ከሱዳን ጠረፍ እስከ መቀሌ የሚያገኛኙ የባቡር ሐዲድ ግንባታዎች በመፋጠን ላይ ናቸው። ሁለት ታላላቅ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ጣቢያዎች መቀሌ እና አክሱም ላይ ገንብተዋል። ቀበሌዎችን ከወረዳ ከተሞች፣ ወረዳዎችን ከአውራጃዎች (ዞኖች)፣ አውራጃዎችን ከዋና ከተማዋ ከመቀሌ ጋር የሚያገናኙ፣ ክረምት ከበጋ ያለምንም እንከን አገልግሎት የሚሠጡ መረብ-መሰል አውራ መንገዶች ተገንብተዋል። ድርቅን ለመቋቋም የክረምት ዝናብን ለማቆር የሚያስችሉ በርካታ ግድቦችን ሠርተው አገልግሎት ላይ አውለዋል። የትግራይን አዲሱን ትውልድ ከኢትዮጵያዊነት ስሜት አውጥቶ የትግራዊነት ስሜት እንዲገነባ የሚያስችሉ፣ በተቀነባበረ ሁኔታ ቅስቀሣ እና ትምህርት በማያቋርጥ መልኩ የሚሰጡ ተቋሞች ተገንብተዋል። በርካታ ትምህርት ቤቶች፣ ኮሌጆች፣ የቴክኒክ እና የሙያ ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርስቲዎች ተከፍተዋል። በኢንዱስትሪ ግንባታ ረገድ የነባሮቹን የኢትዮጵያ ፋብሪካዎች ሕልውና የሚያጠፉ የመድኃኒት፣ የጨርቃጨርቅ፣ የስሚንቶ፣ የመጠጥ እና የብረታ ብረት ፋብሪካዎች በሁሉም የትግራይ አውራጃዎች ተቋቁመዋል። ከእነዚህ መካከል፦ የአዲግራት መድኃኒት ፋብሪካ፣ እንዲሁም መቀሌ የተገነቡት የመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ፣ የአልሜዳ የጨርቃጨር ፋብሪካ፤ የመሥፍን ኢንጂነሪንግ የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ፣ ወዘተርፈ ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው። አሽጎዳ አካባቢ በአፍሪቃ በግዙፍነቱ ቀዳሚ የሆነ እና በነፋስ ኃይል ኤሌክትሪክ የሚያመነጩ ተርባይኖች በብዛት ተገንብተዋል።

የአገሪቱ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ መዋቅሮች ያላአንዳች ይሉኝታ በወያኔች የተያዙ ናቸው። የአገሪቱን የአየር እና የምድር ኃይል መከላከያ የማዘዣ ማዕከሎች ከአዲስ አበባ እና ከደብረዘይት በማስወጣት ማዕከላዊ ዕዛቸውን ትግራይ ላይ እንዲሆን በማድረግ ወሣኝ የሆኑት የመከላከያ መሣሪያዎች ትግራይ ውስጥ እንዲከማቹ ተደርጓል። የከባድ ሮኬቶች መተኮሻ መንኮራኩሮች ትግራይ ውስጥ ተገንብተዋል። የአገሪቱ የመከላከያ ኃይል ከጓድ እስከ ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ድረስ ያሉት ቁልፍ የአዛዥነት፣ የመገናኛ፣ የድርጅት፣ የሎጂስቲክ ኃላፊነቶችን በሙሉ በትግሬዎች በማስያዝ የወታደራዊ ተቋሙ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴው የትግራይን መገንጠል ዕውን በሚያደርግ መልኩ ወደፊት እየተባለ ይገኛል።

በአጠቃላይ የትግራይን ግንጠላ ዕውን መሆን ሂደቱ የተመቻቸ እንዲሆን፣ በ«ሽግግር ዘመን» ተብየው «ልማት ቅድሚያ በጦርነት ለተጎዱ ክልሎች» በሚል ስም የአገሪቱ አጠቃላይ በጀት ለትግራይ ልማት ተመድቦ ለአምስት ዓመታት ከላይ ለተጠቀሱት ተግባሮች እንዲውል መደረጉ ይታወቃል። ከሽግግር መንግሥቱ ፍጻሜ በኋላም የተዘጋጀው «ሕገመንግሥት» ተብየው የሽግግር መንግሥቱ ቻርተር ተከታይ ሆኖ በመዘጋጀቱ፣ አጠቃላይ ያለፉት ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት ሲሠራ የኖረው ከፍ ሲል የተጠቀሱትን ሁለት ግቦች ለማሟላት፣ ማለትም፦ የትግሬ-ወያኔ ትውልድ ለመቶ ዓመታት በኢትዮጵያ ሥልጣን ላይ የሚቆይበትን ሁኔታ እያረጋገጡ መጓዝ፣ ይህ የማይሆን ከሆነ ለምትገነጠለው ትግራይ ቁሣዊ፣ ቴክኒካዊ እና ኅሊናዊ መሠረት ሊሆኑ የሚችሉ የሁለንተናዊ ግንባታ ተግባሮችን በተጓዳኝ ማከናወን የሚለው በተደጋጋፊ መልኩ ሲሠራ መቆየቱ ይታወቃል።

ይህ ሁሉ ሤራ ቢጎነጎንም፣ የትግሬ-ወያኔ ባልጠበቀው መልኩ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ከሕዝቡ ኅሊና ውስጥ ከመፋቅ እና ከመደብዘዝ በተቃራኒ፣ የበለጠ እየጠነከረ መሄዱ የአደባባይ ምሥጢር ነው። ለዚህ ማረጋገጫዎች በተከታታይ በሚነሱ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች እና በተቃዋሚ ኃይሎች መበራከት ናቸው። ስለዚህ የትግሬ-ወያኔ ቡድን «ለመቶ ዓመታት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሥልጣን ላይ እቆያለሁ» የሚለው ዓላማው ሊሣካ የማይችል እንደሆነ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ በ፲፱፻፺፯ (1997) ዓ.ም. ብሔራዊ ምርጫ በማረጋገጡ፣ አጠቃላይ እንቅስቃሴውን «ትግራይን ከቀሪዋ ኢትዮጵያ መገንጠል» በሚለው ሁለተኛ ግቡ ላይ እንዲያተኩር ሁኔታዎች እንዳስገደዱት ይታያል። ለዚህ የግንጠላ ዓላማው ያጸደቀው «ሕገመንግሥት» ተብየው ዋናው መሣሪያው መሆኑ ይታወቃል። አንቀፅ ፴፱(ሰላሣ ዘጠኝ) ለማንም ጥቅም ተብሎ ሣይሆን፣ የትግራይን ግንጠላ ለማሣሳካት የተቀረጸ አንቀፅ እንደሆነ ማንም ይስተዋል አይባልም። ዛሬም ቢሆን የትግሬ-ወያኔ የተመሠረተበትን ዋናውን ስሙን (ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ) ያለመቀየሩ የሚያረጋግጠው ሃቅ ትግራይን ከቀሪዋ ኢትዮጵያ መገነጠል በይደር የቆየ የማይቀር አጀንዳው መሆኑን ነው። ይህ ዕውነት እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ አንቀፅ ብቻ ትግራይን ገንጥሎ በሰላም መኖር እንደማይችል የትግሬ-ወያኔ ጠንቅቆ ያውቃል። የትግሬ-ወያኔ መሪዎች ከተጠያቂነት መዳን የሚችሉት፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብ የዘረፉትን ንብረት መጠቀም የሚችሉት፣ የትግራይ መገንጠል ለጊዜውም ቢሆን ዕውን ሊሆን የሚመችለው፣ በቀሪዋ ኢትዮጵያ ነገዶች መካከል መበታተን ሲፈጠር፣ ከሁሉም በላይ ዐማራ የተሰኘውን ነገድ ሌሎች ነገዶች በጠላትነት ፈርጀው እርሱን ማዳከም ሲችሉ፣ እንዲሁም «ዐማራ» ሲል የከለለውን ክልል ከውጭ አገር ጋር እንዳይገናኝ ዝግ በማድረግ ብቻውን አቁሞ ኅልውናውን ማጥፋት ሲቻል እንደሆነ ብቻ መሆኑን ይህ ቡድን አቅዶ በተግባር ሲንቀሣቀስ ቆይቷል። ለዚህም ባለፉት ዓመታት ሁሉም በሚባልበት ደረጃ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙት ነገዶች ዐማራውን በአውራ ጠላትነት ፈርጀው የጥፋት እጃቸውን እንዲያነሱበት አድርጓል።

የትግሬ-ወያኔ ምዕራባዊውን «የዐማራውን ክልል» ለም እና ድንግል መሬቶች ለሱዳን በገጸበረከት ሰጥቷል። በቀረው ምዕራባዊ ዳርቻ የትግራይን ግዛት በማስፋት ከቦ፣ ከቤንሻጉል ጉምዝ እና ከጋምቤላ ክልሎች ጋር አገናኝቷል (አባሪ ካርታውን ይመልከቱ)። ከ5 ሚሊዮን የማያንስ ዐማራ ከምድረ ኢትዮጵያ አጥፍቷል። አያሌ ዐማሮች በአገር ውስጥ ሠርቶ የመኖር መብታቸውን በመገፈፋቸው ለስደት ሕይዎት ተዳርገዋል። በስደት በዓለም ዙሪያ ከሚኖረው ኢትዮጵያዊ መካከል ከመቶ ፷(ስድሣ) እጁ በላይ ዐማራ መሆኑ የሚያመለክተው፣ ዐማራው በገዛ አገሩ ሠርቶ የመኖር መብቱን የተገፈፈ መሆኑን ብቻ ሣይሆን፣ ዐማራው በመጥፋት ሂደት ላይ መሆኑን የሚያሣይ ነው።

ሰሞኑን ለሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ከደረሱት እጅግ አስተማማኝ መረጃዎች መካከል፣ ወያኔ በኢትዮጵያ ፖለቲካ አናት ላይ የመቆየት ዓላማው የማይሣካ መሆኑን ተገንዝቦ፣ ወደ ሁለተኛው እና የመጨረሻ ግቡ፣ ማለትም፦ ትግራይን ለመገንጠል በከፍተኛ ሚስጢር እየሠራ መሆኑን የሚያረጋግጡ ናቸው። ይህም የትግራይ ግንጠላ ዕቅድ ለማሣካት እንዲቻል፣ ከአገር ውስጥ ተቃዋሚ ኃይል እንዳይነሣ፣ ኢትዮጵያን በሽግግር ዘመኑ ከፋፍለዋት በነበረው ፲፬(አሥራ አራት) እና ከዚያም በላይ የሆኑ የክልል ወሰኖችን የሚያመለክቱ ካርታዎችን አዘጋጅተው፣ ከየጎሣው ሰዎችን መልምለውና አደራጅተው፣ ለነዚህ ሰዎች የወታደራዊ፣ የደህንነት፣ የአደረጃጀት፣ የአመራር እና የቁጥጥር ሥራ የሚሠሩ የትግሬ-ወያኔዎች ተመድበው በከፍተኛ ሚሥጢር ፀረ-ኢትዮጵያ ሤራ እየተዶለተ መሆኑን አረጋግጠናል። ይህም ከ1997 የምርጫ ሽንፈታቸው ማግሥት ጀምሮ በመከናወን ላይ ያለ ተግባር እንደሆነ የመረጃ ምንጮቻን ገልፀውልናል። «ይህ አይሆንም፣ አይደረግም፣ አይታሰብም» ሊባል የማይችል እንደሆነ የወያኔ ጉዞ እና ተግባር ከጥርጣሬ ውጭ በሆነ መንገድ ያስረዳናል። ለዚህ ሤራቸው ማረጋገጫዎቹ በነባር ኢትዮጵያዊ እምነቶች መካከል እየሰራ ያለው የማጥፋት ሥራ፤ በጎጃም፣ በጎንደር፣ በአዲስ አበባ፣ በሶማሌ፣ እየተካሄዱ ያሉት የጥፋት እርምጃዎች የዚህ ዕቅድ አካሎች መሆናቸውን ልብ ሊባል ይገባዋል።

ሌላው የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያን የማፈራረስ ተልዕኮው የማይቀር እና የፍጻሜው የመጨረሻ ደረጃ ላይ መድረሱን ማሣያው፣ የምዕራቡ ዓለም የመረጃ እና የስትራቴጂክ ጥናቶች ተቋም ባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት አጋማሽ ላይ በ2030 እ.አ.አ. ከዓለም ካርታ ላይ ከሚጠፉ አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን ይፋ ማድረጉን እናስታውሳለን። በተመሣሣይ ሁኔታ በኅዳር ወር ፪ሺህ፯ ዓ.ም. ሞስኮ ውስጥ የተካሄደ የዓለም አቀፍ ቀውሶች ጥናት ተቋም ባዘጋጀው ስብሰባ፣ በምሥራቅ አፍሪካ የሚታየውን ብጥብጥ ለዘለቄታው ለማስወገድ የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ኮንፌደሬሽን መመሥረት እንዳለበት ግፊት የሚያደርግ ጥናት ቀርቧል። የኮንፈደሬስሽኑ አባል አገሮች ጥንት እንግሊዝ «ከኢትትዮጵያ ተቆርሶ ወደ ሱዳን ይካተት» ትለው የነበረው የኤርትራ ምዕራባዊ ክፍል ወደ ሱዳን ተካልሎ ሱዳን ከሦስት እንድትከፈል፣ የኤርትራ ደጋማው ክፍል ከትግራይ ጋር ተቀላቅሎ ትግራይ ትግርኝ የተሰኘ ግዛት እንዲፈጠር፣ የአፋርኛ ተናጋሪዎች በአንድ ግዛት ተጠቃለው አንድ ግዛት እንዲሆኑ፣ በአምስቱ ዓመት የአርበኛነት ዘመን ፋሽስት ጣሊያን «ዐማራ» ብሎ ሰይሞት የነበረው ክልል አንድ የዐማራ ግዛት እንዲሆን፣ የቀሩት አካባቢዎች የፋሽስት ጣሊያንን ክፍፍል መሠረት አድርገው የየራሳቸውን ግዛቶች እንዲመሠረቱ እና በነዚህ አገሮች መካከል ኮንፌደሬሽን ይመሥረት የሚል ነው። የእነዚህ ጥናቶች ግብም ከወዲሁ ኢትዮጵያዊው የኢትዮጵያን መፍረስ አይቀሬነት እንዲለማመደውና «ድሮም ተብሎ ነበር» በማለት የአገሩን መፍረስ በፀጋ እንዲቀበል የሥነ- ልቦና ሰለባ ከወዲሁ መሠራቱን የሚያመለክቱ ናቸው።

ካርታ፦ ለወደፊቱ «የትግራይ ሪፑብሊክ» ተብሎ በትግሬ-ወያኔ የሚገነጠለው የኢትዮጵያ አካል በአረንጓዴ ቀለም የተቀለመው ነው።

የትግሬ-ወያኔ እና ዕኩይ ዓላማው ኅልው ሆነው የሚዘልቁት ኢትዮጵያውያን ሠፊውን ለቀን ጠባቡን፣ ኢትዮጵያዊነትን ትተን ጎሣዊ ማንነትን ስንላበስ፣ ዕውነትን ከድተን ከውሸት ጎራ ስንሰለፍ፣ ዘላቂውን ትተን አላቂውን እና ጠፊውን ስንይዝ፣ አኩሪውን ትተን ነገ የሚያሳፍረውን ስንከተል፣ ለኅሊና ሳይሆን ለጥቅም ስንገዛ ነው። እስካሁን የትግሬ-ወያኔ ያለ ልጓም የጋለበን በነዚህ ምክንያቶች ብቻ ነው። አሁን ግን የትግሬ-ወያኔ አጥፍቶን ሊጠፋ ከመጨረሻው ጠርዝ ላይ ቆሟል። የመጥፋቱም ያለመጥፋቱም ጉዳይ የሚወሰነው በእኛ ብቸኛ ምርጫ ነው። ምርጫችን በኢትዮጵያዊነታችን መቀጠል ከሆነ፣ ወያኔ ያጠመደልንን የመነጣጠል መንገድ ትተን በአንድነት በመቆም ኢትዮጵያን ከመጥፋት ለመታደግ ቁርጠኛ አቋም ልንይዝ ይገባል። ቢመሽም፣ እጅግ ብንዘገይም፣ ፈጽሞ ከመቅረት ይሻላል እና እጅ ለጅ ተያይዘን አገራችን እንድናድን ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ጥሪውን ያቀርባል።

ከሁሉም በላይ የትግሬ-ወያኔ ወደ መጨረሻ እርምጃው ሲያመራ አጥፍቶ የሚጓዘው፣ ከጽንሱ ጀምሮ በአውራ ጠላትነት ፈርጆ ላለፉት ፵(አርባ) ዓመታት ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሲገድለው፣ ሲያስረው፣ ሲያሰቃየው እና ሲያሳድደው የኖረውን ዐማራ እስትንፋስ ሳያቋርቋጥ ከጉሬው እንደማይገባ አውቀን፣ ከተደገሰልን ጥፋት እራሳችን መከላከል እንድንችል ከምንጊዜውም በላይ ነቅተንና ተደራጅተን ኅልውናችን ለማስጠበቅ ቁርጠኛ ሆነን እንድንቆም ሞረሽ-ወገኔ አደራ ይላል።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!
ኢትዮጵያ በጀግና እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ታፍራ እና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!

ከመላው አገሪቷ በአንድ ቀን፣ በአንድ ፊሽካ ጥሪ፣  የአንድነት ጉባኤተኞች ተሰባስበዋል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) “አንድነትን ለመታደግ ከየአቅጣጫው እየተመመ ያለው የአንድነት የሰላማዊ ትግል ሰራዊት፣ በጊዜ በዋናው ጽ/ቤት ከትመዋል፤ ይሄው ታሪክ ሊሰራ፣ የምርጫ ቦርዱ አሳፋሪነት፣ የስርዓቱ ሽፍትነት ሊመሰክር፤ ይህን የአንድነት ልጆች ተጋድሎ ለልጅ ልጅ ሊነግር ታድመዋል።

unnamed (1)ይህ ትልቅ ታሪክ ሲፈፀም በቦታው ተገኝቼ ለመመልከት በመቻል ኩራት ነው የሚሰማኝ”  ሲሉ አስተያየታቸዉን የሰጡት የአንድነት ተጠባባቂ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊው አቶ አስራት አብራሃ፣   ነገ እሁድ በሚደረገው ጠቅላላ ጉባኤ፣  አባላት፣  በአራት ቀናት ጥሪ ፣ በቁጭትና በቁርጠኝነት፣  በልባቸው የነጻነትን ደዉል እያቃጨሉ መምጣታቸው እንዳኮራቸው ይናገራሉ።

 

“በአሁኑ ሰዓት ከመላ ሀገሪቱ በአንድ ቀን፤ በአንድ ፊሽካ ጥሪ የአንድነት ጉባኤተኛ አንድነት ፓርቲን በኢህአዲግ ከሚመራው ምርጫ ቦርድና ተላላኪ ወንበዴዎች ሴራ ለመታደግ ብሎም ቀጣይ የትግሉ ምእራፎች ላይ ለመምከር በአሁኑ ሰዓት በአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት ከተን ገብተናል” ሲሉ አንድ የአንድነት አባል አስተያየት ሲሰጡ ፣ ሌላው አባል ደግሞ  “ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ አንድም ነፃና ፍትሀዊ ምርጫ አስፈፅሞ የማያውቀው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ፣ ኢህአዴግ ምርጫ እንዲያጭበረብር በመፍቀዱ ሳቢያ ምርጫን ተከትሎ በሚነሱ አለመግባባቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ደማቸው በየመንገዱ ፈሷል፡፡ ምርጫ ቦርድ ከገዳዮቹ ባልተናነሰ የእነዚህ ውድ ኢትዮጵያውያ የደም እዳ አለበት፡፡ ያለጥርጥር የምርጫ ቦርድ ሀላፊዎችም ከገዢው ቡድን ሹማምንት እኩል የደም ዕዳቸውን የሚያወራርዱበት ቀን ሩቅ አይሆንም፡፡” ሲሉ ምርጫ ቦርድ እያደረገ ባለው ነገር በታሪክ ተጠይቂ እንደሚሆን ገልጸዋል።

unnamed

“ምርጫ ቦርድ እየተባለ የሚጠራው የኢህአዴግ ተቀፅላ ተቋም አጅግ አስደማሚ ጠቅላላ ጉባኤ ባካሄድን ማግስት በአራት ቀናት ውስጥ ሌላ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርታችሁ እንደገና ፕሬዚደንቱ ካላስመረጣችሁ የመጨረሻ እርምጃ እወስዳለሁ በማለት ሱሪ በአንገት በሆነ ሁኔታ በድጋሚ ሌላ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ እንድንጠራ ተገደናል፤ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ከየቦታው ከአራቱም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች ክተት ብለው ሌሊትና ቀን ተጉዘው ፓርቲያቸው ለማዳን በጊዜ ደርሰናል” ሲሉ አንድ ሶስተኛ አባል ይናገራሉ።

 

ምርጫ ቦርድ ሕግ በሚጠይቀው መሰረት ታዛቢዎች እንዲልክ ደብዳቤ ቢደርሰውም፣ ራሱ ባደራጃቸው በነአየለ ስምኔህ፣ ዘለቀ ረዲ ቡድን “ሌላ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቷል” በሚል እንደማይገኝ በደብዳቤ አሳውቋል። ሆኖም የአንድነት አመራር አባላት “ምርጫ ቦርድ ተገኝም፣ አልተገኝም፣ ጠቅላላ ጉባዬያችንን እናደርጋለን።  በድጋሚ እንደገና ከቀበና ጽ/ቤታችን የዲሞክራሲ፣ የለወጥና የነጻነት ደዉል እንደዉላለን” ሲሉ በአገር እና ከአገር ዉጭ ያለው ኢትዮጵይዊ ሁሉ በዚህ ወሳኝ ወቅት ከጎናቸው እንዲሁን ጥሪ አቅርበዋል።

 

“በዚህ ስርዓት ስር ለአንድ ሌሊት እንኳ ቢሆን በሰላም ተኝቼ ካደርኩኝ ቀኜ ይረሳኝ፤ የረገጠኩት መሬት ይክዳኝ” እንዳሉት የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊው አቲ አስራት አብርሃ፣ በአንድነት አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ዘንድ ትልቅ ቁርርጠኝነትና ወኔ እየተያ እንደሆነ የሚደርሰን ዘገባ ያመለክታል።

 

እሁድ ለሚደረገው የጠቅላላ ጉባኤ ከመላው አገሪቱ እየተመሙ የመጡ የአንድነት ተወካዮች በአንድነት ጽ/ቤት

 

 

 

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>