Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የተካሄደውን ድብደባና እስራት እናወግዛለን –

$
0
0

ህዳር 27፣ 2007
shengoዛሬ ቅዳሜ ህዳር 27 ቀን 2007 ዓ. ም (ዲሴምበር 6፣ 2014) በዘጠኝ ተቃዋሚ ድርጅቶች አስተባባሪነት በአዲስ አበባ ተጠርቶ በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የህወሀት/ኢህአዴግ አገዛዝ የጸጥታ ሰራዊት ህዝቡን በዱላ በመደብደብና ብዙዎችን ወደ  እስር በመወርወር ሰላማዊ ሰልፉን በትኗል። የዚህ ግፍ ሰለባ ከሆኑት ውስጥም የትብብሩ ሰባሳቢ ኢንጅነር ይልቃል  እነደሚገኙበት ታውቋል። ይህን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ሽንጎው አጥብቆ ያወግዛል። በግፍ የታሰሩት ሁሉ ባስቸኳይ እንዲፈቱም ይጠይቃል።  –-[ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—

 

Download (PDF, Unknown)


በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት ተዋናይት አረፈች

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ‹‹እኔ ቲያትር ከመጀመሬ በፊት፣ ወንዶች ጢማቸውን እየተላጩና ጡት እየቀጠሉ የሴትን ገጸባህሪ ይጫወቱ ነበር›› ትል ነበር የመጀምሪያዋ ኢትዮጵያዊት ሴት ተዋናይ:: ከ1944 እስከ 1986 ዓ.ም ድረስ እጅግ በርካታ ቲያትሮችን ሰርታለች። ዳዊትና ኦሪዮን፣ አልሞትም ብዬ አልዋሽም፣ ቴዎድሮስ፣ ጦጢት፣ ፍልሚያ፣ ንግስተ-ሳባ፣ የሺ በጉለሌ እና የመሳሰሉትን በብቃት ተውናለች፡፡ ሴት ተዋናይ ባልነበረበት ጊዜ ወንዶችን ሱሪ ያስታጠቀች ቀዳማዊት አርቲስትም ናት።
selamawit gebresilase
አገሯንና ባህሏን ለማስተዋወቅ ሩቅ ምስራቅ፣ ሶቪየት ህብረት፣ ካርቱም ኡጋንዳና በርካታ አገሮችን ረግጣለች። በዛን ወቅት አዘጋጆቹ ለትራጄዲ ስራ እየመደቡኝ እንጂ ጥሩ ኮሜዲያን ይወጣኝ ነበር የምትለው አርቲስት በአንድ ወቅት ከጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ ወደትወናው ዓለም እንዴት እንደተሳበች “ተዋናይ ለመሆን በጭራሽ ፍላጎት አልነበረኝም። በዛን ጊዜ ዘመናይ ዘለቀ ለተባለች ጓደኛዬ ስራ ፈልጊልኝ ስላት ወደዚህ ስራ ለመግባት ፍላጎት ስለነበራት መለስ ቀለስ ትል ኖሮ እኔንም ወደቴአትር ቤት ይዛኝ መጣች። እኔ ለራሴ ከዚያ በፊት ሙዚቃ አይቼ አላውቅ ሳክሲፎኑ፣ ፒያኖው ምኑ ቁጡ። የጎረምሳውስ መዓት ብትይ! ያኔ እነተስፋዬ ሳህሉ ከእኔ በእድሜ በሰል ያሉ ነበሩ። ይሄ ነገር ለእኔ አይሆንም አልኳት ለጓደኛዬ። ምክንያቱም እኔ እፈልግ የነበረው የእደ-ጥበብ ስራ ነበር፡፡ ጥልፍ መጥለፍ ዳንቴል መስራትና ሌላ ሌላውን እንጂ ጎረምሳ መሀል መዋል አልፈልግም ብዬ ወደ ቤቴ ሄድኩና በዚያው ቀረሁ:: በኋላማ መኮንን ሀብተወልድ የተባሉ ሰው ያቋቋሙት ፒያሳ ውስጥ ‹‹ዜንጎን›› የተባለ ድርጅት ነበር። ጥልፍ፣ የልብስ ስፌትና የተለያዩ የእጅ ጥበብ መማሪያ ነው። እዛ ለመማር ብዙ ደጅ ብጠናም ቦታው ሞልቷል ብለው መለሱኝ፡፡ በዚህን ጊዜ ትምህርቴን እየተማርኩ አርፌ ተቀመጥኩኝ። ታዲያ አንድ ቀን ቴአትር ቤት ያዩኝ የዘመናይ (ጓደኛዋ) ጓደኞች አኔን ፍለጋ መጥተው አገኙኝ። ብቻ ወደ ትወናው የኔን ልብ ለማሸፈት ሳይመካከሩ እንዳልቀሩ እገምታለሁ። ጋሽ ተስፋዬ ሳህሉ (አባባ ተስፋዬ) ጢሙን ይላጭልሽና በ‹‹ቴዎድሮስ›› ቲያትር ላይ እቴጌ መነንን ሆኖ ሲሰራ እንድመለከት ተደረገ። ይህን ስመለከት እነሱ ጡት አበጅተው፣ ቂጥ አበጅተው ሲተውኑ እኔ በተፈጥሮዬና በጾታዬ ብሰራው ክፋቱ ምንድነው አልኩና መንፈሴ ጭልጥ ብሎ ወደ ተውኔቱ ገባሁ እልሻለሁ። ” ብላለች::

ይህች ድንቅ አርቲስት ሰላማዊት ገብረሥላሴ ትባላለች:: ለመጀመሪያ ጊዜ ትያትር ስትሰራ ይከፈላት የነበረው ከወንዶቹም በላይ ነው:: በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ተከፋይ እንደሚባለው በወቅቱ ከፍተኛዋ ተከፋይ ሰላማዊት ነበረች:: 12 ብር በወር::

“በዛን ጊዜማ ዕጩ ተዋናይ ተብዬ ብርቅ ነበርኩ ሹሩባዬን እየተሰራሁ ዘናጭ ሆንኩኝ በቃ ከወንዶቹ በላይ የኪስ ገንዘብ ነበረኝ፡፡ የወንዶቹ ሰባት ብር ሲሆን የእኔ 12 ብር ነበር።”

ለዛሬዎቹ ሴት አርቲስቶች ፋና ወጊ የሆነችው አርቲስት ሰላማዊት ገብረስላሴ ፈጣሪ ገነትን እንዲያወርሳት ዘ-ሐበሻ ትመኛለች::

ግንቦት 7 በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አወገዘ * “የሠራዊቱ አባል እየደበደበ ያለው የራሱን ልጅ፣ ወንድሙን ወይም እህቱን እንደሆነ ይወቅ”

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ግንቦት 7 ወቅታዊ አቋሙን በሚገልጽበት ጽሁፍ ሰሞኑን በሰላማዊ ታጋዮች ላይ መንግስት የወሰደውን እርምጃ አወገዘ:: ንቅናቄው “በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ የደረሰውን ጥቃት እናወግዛለን” ሲል በበተነው ጽሁፍ በድጋሚ ለመከላከያ ሰራዊቱ እና ለፖሊስ ሃይሎች “የሠራዊቱ አባል እየደበደበ ያለው የራሱን ልጅ፣ ወንድሙን ወይም እህቱን እንደሆነ ይወቅ” በማለት ከሕዝብ ጎን እንዲቆሙ ጥሪውን አቅርቧል::
ወቅታዊውን ጽሁፍ ይመልከቱ:-
Ginbot-7-Top-logo_4

በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ የደረሰውን ጥቃት እናወግዛለን !!!

በአብዛኛው በወጣት ወንዶችና ሴቶች የተገነባው ሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነበት የዘጠኝ ፓርቲዎች ኅበረት፣ “ነፃነት ለፍትሃዊ ምርጫ” የተሰኘ የአንድ ወር መርሀ ግብር አውጥቶ፤ ችግሮችን ተጋፍጦ አብዛኛውን ተግባራዊ አድርጓል። የመርሀ ግብሩ አቢይ አካል የነበረውና በህዳር 27 እና 28 ሊከናወን ታድቆ የነበረው የ24 ሰዓት የአደባባይ ተቃውሞ ግን በአገዛዙ የኃይል እርምጃ ምክንያት በታቀደው መንገድ ሊከናውን አልቻለም። የህወሓት ቅልብ የሆኑት ሲቪል የለበሱ ሰላዮችና የፌደራል ፓሊስ በተቃውሞው ተሳታፊዎች ላይ ኢሰብዓዊ የሆነ ጥቃት ፈጽመዋል።

ከጅምሩ፣ የፓርቲዎቹ ኅበረት የተቃውሞ ማሳወቂያ ደብዳቤውን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለማስገባት የገጠመው ችግር የህወሓት አገዛዝ የመንግሥትን መዋቅር ለፓርቲ ሥራ፤ የመንግሥት ተቀጣሪዎችን ደግሞ እንደ ህወሓት አገልጋዮች የሚጠቀምባቸው መሆኑ አንዱ ማሳያ ሆኗል። ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርጉ ማሳወቅ የፈለጉት ፓርቲዎች ህወሓት የዘረጋውን አፋኝ ሥርዓት የሚታገሉ በመሆናቸው ብቻ ደብዳቤዓቸውን የሚቀበል እንኳን አጥተው ተጉላልተዋል። ለሰልፉ ቅስቀሳ ማድረግም በራሱ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ወጣቶች ተንገላተዋል፣ ተደብድበዋል፣ ታስረዋል። ያም ሆኖ ውጣ ውረዶች ታልፈው ቅዳሜ ህዳር 27 ቀን 2007 ዓ. ም. ደረሰ።

የኅበረቱ አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎችና ጥሪውን የሰማ ሕዝብ ወደ መስቀል አደባባይ ማምራት ሲጀምር ሲቪል የለበሱ የአገዛዙ ታጣቂዎች እና ፌደራል ፓሊሶች ከሰንደቅ ዓላማዎችና መፈክሮች ባለፈ አንዳች ነገር ያልያዙትን እድሜያቸው ከሃያዎች ያልዘለሉ ውድ የኢትዮጵያ ልጆችን ደብድበዋል፤ ብዙዎቹም አፍነው በአሰቃቂ ሁኔታ እያንገላቱ ወደ እስር ቤቶች ወስደዋል። ወጣቶች ተወልደው ባደጉበት አገር፤ ስሜታቸውን በነፃነት ለመግለጽ በመድፈራቸው ብቻ በጭካኔ ተረግጠዋል፤ ተፈንክተዋል፤ እጅና እግሮቻቸው ተሰብሯል።
ginbot 7
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ይህ የህወሓትን ፋሺስታዊ እርምጃ አጥብቆ ይቃወማል። ግንቦት 7፣ ህወሓት ከስልጣን እስካልተወገደ ድረስ እንዲህ ዓይነቱን ፋሺስታዊ ተግባር መፈፀሙን የማይተው እኩይ ኃይል እንደሆነ ያውቃል፤ በዚህም ምክንያት የትግላችን ግብ ህወሓትን ማስወገድና በምትኩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁንታ ያገኘ መንግሥት መመሥረት መሆን ይኖርበታል ብሎ ያምናል፤ ለዚህም ይታገላል።

ግንቦት 7፣ ህዳር 27 ቀን 2007 ዓ.ም. “መብቶቻችንን በህወሓት ዘረኛ አምባገነኖች አናስነጥቅም” በማለት አደባባይ የወጡ ወጣቶችን ጽናት ያደንቃል። ህወሓት የሚለውን ሳይሆን የይስሙላ ህጉ የፈቀደላቸውን ለማድረግ በመድፈራቸው በህወሓት የህግ ማዕቀፍ ውስጥ ሆኖ የሚደረገውን ትግል አንድ እርምጃ ወደፊት አራምደውታል።

እያንዳንዱ የፓለቲካ ድርጅት ከዚህ ኩነት የሚወስዳቸው ተጨማሪ ትምህርቶች ቢኖሩም የሚከተሉትን ነጥቦች ብዙዎችን ያስማማሉ ብለን እናምናለን።

1. ህወሓት በምንም ዓይነት ቢሆን የያዘውን ስልጣን ለሕዝብ ፈቃድ ማስገዛት አይፈልግም፤

2. ህወሓት አገራችን ወደ ትርምስ እየገፋት እንደሆነ ግልጽ እየሆነ መጥቷል፤

3. ስልጣኑን የሚያሳጣው ከመሰለው እና አቅሙ እስካለው ድረስ ዘግናኝ እርምጃዎችን ከመውሰድ አይመለስም፤

ከህወሓት አገዛዝ መገላገል የሚቻለው ተገዶ ሲወገድ ብቻ ነው። ህወሓት እንዲወገድ ደግሞ የመጨቆኛ አቅሙ መዳከም ይኖርበታል። ህወሓትን የማስወገጃ አማራጭ መንገዶች ብዙ ሲሆኑ ተቀናጅተው ቢሠሩ የበለጠ ውጤታማ ይሆናሉ ብለን እናምናለን፤ “ሁለገብ ትግል” የምንለው የትግል ስልት ጭብጥ ይህ ነው። “እምቢ ለነፃነቴ” ብሎ የተነሳ ሕዝብ ህወሓትን ምን ያህል እንደሚያስደነግጥ በተደጋጋሚ ታይቷል። ህዳር 27ን መንደርደሪያ አድርገን በመውሰድ ከዚህ በተሻለ ለተደራጀ ሕዝባዊ እምቢተኝነትና አመጽ ራሳችን እናዘጋጅ።

በዚህ አጋጣሚ ግንቦት 7፣ ለመከላከያ ሠራዊት እና ፓሊስ አባላት ተደጋጋሚ ጥሪዎችን ማድረግ ይሻል። የመከላከያ ሠራዊት እና ፓሊስ አባላት እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ በህወሓት ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ የተበደላችሁ መሆኑን እናውቃለን። የህወሓት ሹማምንት ከሆኑ አዛዦቻችሁ መላቀቅና ራሳችሁን ነፃ የማውጣት ኃላፊነት የወደቀው በእናንተው በራሳችሁ ላይ ነው። ሠራዊቱ ራሱን በራሱ ነፃ ማውጣት ይኖርበታል። የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ህወሓት መወገዱ የማይቀር በመሆኑ ሠራዊቱ ራሱን ነፃ አውጥቶ ከሕዝብ ጋር ካልወገደ እጣ ፈንታው የተሸነፈ ሠራዊት መሆን ነው። ከዚህ በላይ የሠራዊቱ አባል እየደበደበ ያለው የራሱን ልጅ፣ ወንድሙን ወይም እህቱን እንደሆነ ይወቅ። ይህ ወሳኝ ጊዜ ነው እያንዳንዱ የሠራዊቱ አባል በግል ኃላፊነት ያለበት መሆኑ ሊሰማው ይገባል።

በሁሉም ዓይነት የትግል ዘርፎች የኢትዮጵያ ወጣቶች በስፋት እየተቀላቀሉ መሆኑ ተስፋ ሰጪ ነው። ጊዜው የለውጥ ነው። የተለያዩ ስትራቴጂዎች ተደጋግፈው እንዲሄዱ መደረግ ያለበት ወቅት ላይ ነን። በህዳር 27 ቀን በህወሓት ቅልብ ሰላዮችና የፌደራል ፓሊሶች አማካይነት የደረሰው ጉዳትና የፈሰሰው ደም ለፍትህና ለነፃነት የተከፈለ ዋጋ ነው። ህመማችሁ ህመማችን፤ ትግላችሁ ትግላችን ነው። የተለያዩ መንገዶች ወደ ነፃነት አደባባይ እያመሩ ነው።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

ዋለልኝ መኮንን-አፈና ያልገታው የአመጽ ድምጽ

$
0
0

ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
—–
ተነገወዲያ ህዳር ህዳር 29/2007 ዘጠነኛው የብሄርና ብሄረሰቦች ቀን ሊከበር ነው፡፡ ይህ ቀን ለበዓሉ አከባበር የተመረጠው የኢፌዴሪ ህገ-መንግሥት የጸደቀበት ቀን ስለሆነ ነው ተብሏል፡፡ ታዲያ በዚሁ ቀን አንድ ታላቅ አብዮታዊ ተገድሎ ነበር፡፡ የሚገርመው ደግሞ በዚያች ቀን የሞተው ሰውዬ በኢትዮጵያ ውስጥ የብሄርና ብሄረሰቦች መብት መከበር አለበት በማለት ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ የጻፈ ሰው መሆኑ ነው፡፡
*****
walelignህዳር 29/1964፡፡ ረፋዱ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 708 ጄት አውሮፕላን ከአዲስ አበባ በአስመራ በኩል ወደ አቴንስ ሊበር ነው፡፡ በአውሮፕላኑ የሚጓዙ መንገደኞች ቦታ ቦታቸውን ይዘዋል፡፡ ሰባት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ከአውሮፕላኑ ውስጥ ተሳፍረዋል፡፡ የበረራው ሰዓት ሲደርስ አውሮፕላኑ ከመሬት ተነሳ፡፡ ከሰማዩ ገብቶ መብረር ሲጀምር ግን ያልታሰበ ሁኔታ ተከሰተ፡፡ እነዚያ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አውሮፕላኑን በቁጥጥራቸው ስር ማዋላቸውን አስታወቁ፡፡ እነርሱ ወደሚፈልጉት ሀገር እንዲበሩም አብራሪዎቹን አዘዟቸው፡፡ ተማሪዎቹ የጠለፋ እወጃውን ካሰሙ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ደግሞ ሌላ ያልታሰበ ነገር ተከሰተ፡፡ አውሮፕላኑን ከጠለፋ እንዲታደጉ የታዘዙ ኮማንዶዎች በቀጥታ በጠላፊዎቹ ላይ በማነጣጠር ተኮሱባቸው፡፡ ስድስት ጠላፊዎች ተገደሉ፡፡ አንዲት ጓደኛቸው ደግሞ በከባድ ሁኔታ ቆሰለች፡፡ የአውሮፕላኑ ወለል በሙታኑ ደም ታጠበ፡፡
*****
በዚያች ዕለት የሞተው ታዋቂው የተማሪዎች ንቅናቄ መሪ ዋለልኝ መኮንን ነበር፡፡ ከርሱ ጋር የተገደሉትም ማርታ መብራህቱ፣ ጌታቸው ሀብቴ፣ ተስፋዬ ቢረጋ፣ ዮሐንስ በፈቃዱ እና አማኑኤል ዮሐንስ ናቸው፡፡ እነዚያ ወጣቶች አውሮፕላኑን ለመጥለፍ የሞከሩት የስርዓቱ ክትትል መፈናፈኛ ስላሳጣቸው ነው፡፡ ዓላማቸው ወደ ውጪ ከኮበለሉት ጓደኞቻቸው ጋር በመቀላቀል ለስር-ነቀል ለውጥ የሚታገል ድርጅት መመስረት ነበር፡፡ ከድርጅቱ ምስረታ በኋላም ወደ ሀገር ቤት ተመልሰው ትግሉን በየአቅጣጫው ለማፋፋም አስበዋል፡፡ ሆኖም እንደተመኙት አልሆነላቸውም፡፡ አውሮፕላን ለመጥለፍ ማቀዳቸው ቀደም ብሎ ተጠቁሞ ስለነበር የጸጥታው ክፍል በአየር ላይ አፍኖ አስቀራቸው፡፡
*****
ከላይ በተገለጸው አሳዛኝ ገቢር (ትራጄዲ) ህይወቱ የተቋጨው ዋለልኝ መኮንን በወሎ ክፍለ ሀገር የሳይንት (ቦረና) አውራጃ ተወላጅ ነው፡፡ የአንደኛና ደረጃ ትምህርቱን በደሴው ንጉሥ ሚካኤል ትምህርት ቤት አጠናቀቀ፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱንም እስከ አስረኛ ክፍል ድረስ ደሴ ከተማ በሚገኘው ታሪካዊው ወይዘሮ ስሒን ት/ቤት ተከታለለ፡፡ አስራ አንደኛና አስራ ሁለተኛ ክፍልን ደግሞ የዘመኑ ምርጥ ተማሪዎች መማሪያ በነበረው በአዲስ አበባው በዕደማሪያም ትምህርት ቤት አገባደደ፡፡ በ1958 ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከገባ በኋላም እጅግ የተለየ አብዮታዊ ሆነ፡፡

ዋለልኝ በ1959 በዩኒቨርሲቲው በተደረገው የግጥም ውድድር “ሙት ወቃሽህ መጣው” በሚለው ግጥም አንደኛ ወጥቷል፡፡ በዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ህብረት ይዘጋጅ በነበረው የታገል መጽሔት ከማንም በላይ የነቃ ተሳትፎ ያደርግ ነበር፡፡ በህቡዕ የሚዘጋጁ ጽሑፎችንም እያዘጋጀ ያሰራጭም ነበር፡፡ በተለይ “አዞዎቹ” የሚባለው የስር-ነቀል ለውጥ ደጋፊ የተማሪዎች ስብስብ በአቋም ደረጃ የተስማማባቸውን ሀሳቦች በጽሑፍ እያቀናበረ የሚያዘጋጀው እርሱ እንደነበር በያኔው እንቅስቃሴ የተሳተፉትም ሆነ የዘመኑን ታሪክ ያጠኑ ምሁራን ይመሰክራሉ፡፡

ከዋለልኝ ጽሑፎች መካከል ዝነኛ የሆኑት ሁለት ናቸው፡፡ አንደኛው ከላይ የጠቀስኩትና ህዳር 10/1961 በታተመው “ታገል መጽሔት” ላይ የወጣው “የብሄረሰቦች ጥያቄ በኢትዮጵያ” የሚል ርዕስ ያለው ጽሑፍ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በ1962 የተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት የነበረው ጥላሁን ግዛው ሲገደል የአጼው ስርዓት በተማሪዎቹ ላይ ያደረገውን ዛቻ በመቃወም “ለአዋጁ አዋጅ” በሚል ርዕስ በህቡዕ ጽፎ የበተነው ጽሑፍ ነው፡፡ ዋለልኝ በጽሑፎቹ ሳቢያ በተደጋጋሚ ጊዜያት ታስሯል፡፡ በተለይ “ለአዋጁ አዋጅ”ን የጻፈው እርሱ መሆኑ ሲታወቅ በችሎት ፊት ቀርቦ አምስት ዓመት እስራት ተፈርዶበታል (ሆኖም ተማሪዎች ባደረጉት ከፍተኛ የተቃውሞ ጫና ከዓመት በኋላ ተፈትቷል)፡፡

ከ1962 በኋላ ሁለት ክስተቶች የተማሪውን ንቅናቄ አቅጣጫ ቀይረውታል፡፡ እነዚህም በስርዓቱ የሚደረገው አፈና መጠናከር እና የድርጅት ምስረታ ጥያቄ መቀስቀስ ናቸው፡፡ በዚህም መሰረት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደ ቀድሞው ጊዜ የተቃውሞ ሰልፍ ከማድረግ ይልቅ የጥናት ክበቦችን እየመሰረቱ መወያየቱን መረጡ (የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በተቃውሞ ቀጠሉ)፡፡ ዋለልኝም በውይይት ክበቡ በሚያደርገው ጥናት ላይ አተኮረ፡፡ ከሀገር ተሰደው በአልጄሪያ ከሚገኙት እነ ብርሀነ መስቀል ረዳ ጋር በሚያደርገው የደብዳቤ ልውውጥ አማካኝነትም ሰፊ መሰረት ያለው ድርጅት ለመመስረት በሚደረገው ውይይትም ውስጥ ይሳተፍ ነበር፡፡ ህዳር 29/1964 በውጪ ካሉት ጓደኞቹ ጋር ለመቀላቀል ሲል አውሮፕላን ጠለፈ፡፡ ሆኖም ካሰበው ስፍራ ሳይደርስ በአውሮፕላኑ ውስጥ ተገደለ፡፡
*****
ከያኔው የተማሪዎች ንቅናቄ መሪዎች መካከል ዋለልኝ መኮንን ልዩ የሚያደርገው አንድ ነገር አለ፡፡ ይኸውም የተለያየ አመለካከት ባላቸው የፖለቲካ ድርጅቶች እንደ ታላቅ ሰማዕት የሚታይ መሆኑ ነው፡፡ ደርግ፣ ኢህአፓ፣ ህወሐት፣ ኦነግ፣ ሻዕቢያ፣ መኢሶን፣ ወዘተ… ሁሉም ለርሱ በጎ አመለካከት ነው ያላቸው፡፡ ታዲያ በዋለልኝ ታሪክ ላይ የሚደረገው ሽሚያም በጣም የጠነከረ ነው፡፡ አንዳንዶቹ ታሪኩን ከራሳቸው ድርጅት ጋር ለማቆራኘት ይሞክራሉ፡፡ በወቅቱ የነበረው የርሱና የጓደኞቹ አሰላለፍ ሲገመገም ግን ዋለልኝ ኢህአፓን ከመሰረቱ ወጣቶች ጋር ተመሳሳይ የፖለቲካ መስመር የነበረው ሆኖ ነው የሚታየው፡፡ ኢህአፓን የመሰረቱትም የርሱ የቅርብ ጓደኞች ናቸው፡፡ በመሆኑም ዋለልኝ በህይወት ቢሰነብት ኖሮ የዚሁ ድርጅት አባል ይሆን ነበር ተብሎ ነው የሚገመተው፡፡
*****
ዋለልኝ መኮንን ከብዙ በጥቂቱ ይህ ነበር፡፡ ወደፊት ሰፋ ባለ ሁኔታ ስለርሱ እጽፋለሁ ብዬ አስባለሁ፡፡ እናንተም በበኩላችሁ የምታውቁትን እንድታጋሩን በአክብሮት እንጠይቃችኋለን፡፡
——
ሰላም
አፈንዲ ሙተቂ
ህዳር 29/2006

ዜሮን በሞራ፤ በሁሉም የወደቀ ዱለኛ። (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 10.12.2014 /ሲወዘርላንድ – ዙሪክ/

ዛሬ እንደ አውሮፓውያኑ አቋጣጠር ታህሳስ 10 ቀን 2014 ነው። ይህ ቀን በዓለምአቀፍ ደረጃ በአንባገነኖች ጫና ሥር የተሰዉ ሰምዕት በጸሎት የሚታሰቡበት፤ በህይወት እያሉ ሰብዕናቸው ለሚጠቀጠቅ ምልዕት አትኩሮት በአፅህኖት የሚሰጥበት ብሩክ ቀን ነው። እንዲሁም ዓመታዊ ክንውኖችና ምላሻቸው በተደሞ የሚቃኝበት – የ1948 ቅዱስ መንፈስን የተካኑ 30 ሁለንትናዊ የኑሮ ቃለ ወንጌላት የተወለዱበት ማዕልት።

Yenese Gebreእኛም ኢትዮጵውያን በሰብዕዊ መብት ጭፍለቃ የሚታወቀው አንባገነኑ የወያኔ ማንፌስቶና ማስፈጸሚያ መሳሪያዎቹ ሁሉ በወገን፣ በሀገር፣ በዳር ደንበር፣ በሰንደቅ፣ በታሪክ፣ በዕምነት፣ በባህል፣ በፍቅር፣ በአብሮነት፣ በማንነት፣ በዜግነት፣ ዙሪያ ያደረሰውን፤ በማድረስ ላይ ያለውን ጭቆና ለማስወገድ ለትጋት እራሳችን የምናሰናዳበት ልዩ ቀን ነው። ገና በዋዜማው የታዳጊ ሃና ዘግናኝ ግፍና በደል፤ የሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ በወያኔ ሠራዊት መወረር፤ የዘጠኙ ፓርቲ የትብብር መርሃ ግብር ግብር ሁሉም በዱላና እስር የገጣማቸው ግፍ በአርምሞ ይታሰባሉ። ስለዚህ ይህን ቀን እኛ የምናስታውሰው ቀደምት ሰማዕቶቻችን የእነአሰፋ ማሩ፤ ሺብሬ ደሳለኝ፤ ዶር. እምሩ ሥዩም፤  ዬእኔ ሰው ገብሬ፣ የህጻን ነብዩ፤ ከዚህ ባለፈ በዬስደት ሀገሩ ክልትምትም ሲሉ ላለፉ፤ እኛ ሳናወቃቸው በመርዝ ለተጨረሱት፤ እስር ቤት በድርብ በቀል መዶሻ ለሚቀጠቀጡት ወገኖቻችን ሁሉ ልባችነን ክፍት አድርገን የመንፈሳችነን ዓይን አብርተን ጥላቻን – ጥላቻ እንዳይወልደው፤ በቀል – በቀልን እንዳይወልደው እራሳችነን አን በንፁህ ልቦና እና መንፈስ ወደ አምላካችን ዕንባችን በመላክ ይሆናል – በቃችሁ እንዲለን። ድጋሚ ስደት፣ ድጋሚ መከራ፣ ድጋሚ ሰቀቀን፣ ድጋሚ ሰጋትና መጠቃቃት ከምንጩ የሚደርቅበትን አዲስ ንጹህ መንፈስ በመውለድ፤ ሰብዕዊ ህግትን በሥራ ለመተርጎም ህሊናችን ስንዱ በማደረግ ሊሆንም ይገባል – የመስዋዕት ሰማዕታት ውለታ።

የወመኔው ወያኔ ህግጋት እናት ህጉ፤ ህገ መንግሥቱ በሞራ የተጠቀለለ ዜሮ ነው። ለአፈጻጸም የሚያሰናዳቸው መመሪያዎች ቢሆኑ በሞራ የተጠቀለሉ ዜሮዎች በመሆናቸው ሰብዕዊ ህጋዊ መብቶችን ገዳይ ናቸው። በእናት ሀገር ኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፉ ህግ የተባባሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሀገሮች እንዲፈጽሙት የደነገጉት ድንጋጌዎች ቢሆን ሥራ ላይ ሊውሉ የማይችሉ በሞራ የተሸፈኑ የዜሮ ድምሮች ናቸው። ክብሪት ብቻውን ብርሃንን፤ ሻማ ብቻውን ብርሃን አይሰጡም። ስለሆነም ሁለንትናዊው ዓለም ዐቀፍ የህግ አንቀፃትና ወያኔ ፈተና ውስጥ ናቸው። ወያኔ ፈተናውን የማለፍ አቅም የለውም። ስለዚህ ውጤቱም ዜሮ ነው።

ፈተናውና ውጤቱ በጥቂቱ።

„አንቀጽ 1የሰው ልጅ ሁሉ ሲወለድ ነጻና በክብርና በመብትም እኩልነት ያለው ነው። የተፈጥሮ ማስተዋልና ሕሊና ስላለው አንዱ ሌላውን በወንድማማችነት መንፈስ መመልከት ይገባዋል።“ የወያኔ ማንፌስቶ ህሊና ካለው አልተወለደም። አስተዳደሩም እንዲሁ። ወንድማማችነትን ፍቆ ጠብን፣ ጥላቻን የዘራና ያዘመረ፤ በቤተሰብ የቆዩ ትውፊቶች ሁሉ ቀራኒዎ ያወጀ ስለሆነ ኢትዮጵያ ላይ ውጤቱ —- ዜሮ ነው።

„አንቀጽ 2፤ እያንዳንዱ ሰው የዘር የቀለም የጾታ የቋንቋ የሃይማኖት የፖለቲካ ወይም የሌላ ዓይነት አስተሳሰብ የብሔራዊ ወይም የኀብረተሰብ ታሪክ የሀብት የትውልድ ወይም የሌላ ደረጃ ልዩነት ሳይኖሩ በዚሁ ውሳኔ የተዘረዘሩት መብቶችንና ነጻነቶች ሁሉ እንዲከበሩለት ይገባል። ከዚህም በተቀረ አንድ ሰው ከሚኖርበት አገር ወይም ግዛት የፖለቲካ የአገዛዝ ወይም የኢንተርናሽናል አቋም የተነሳ አገሩ ነጻም ሆነ በሞግዚትነት አስተዳደር ወይም እራሱን ችሎ የማይተዳደር አገር ተወላጅ ቢሆንም በማንኛውም ዓይነት ገደብ ያለው አገዛዝ ሥር ቢሆንም ልዩነት አይፈጸምበትም።“ ይህ ደግ ድንጋጌ በጎሳ ምጥ ውስጥ ባለች ሀገር የማይታሰብ ነው፤ ብሄራዊነት ህም! ውጤቱ –  ዜሮ ነው።

„አንቀጽ 3፤ „እያንዳንዱ ሰው የመኖር፣ በነጻነትና በሰላም የመኖሩ መጠበቅ መብት አለው።“ መላ አካላቷ በጠበንጃ በታገተ ሀገር የሚኖሩ ህዝቦች ሰላምና ነፃነት አልባ ናቸው። እንዲያውም ፈጣሪ አምላክ ትቶልን የሄደው የውስጡን ሰላም ሆኖ ሳለ፤ በወያኔ ግን ስቅላት የተበዬነበት የፈጣሪ ሥጦታም ጭምር ነው። ስለሆነም …. ውጤቱ —- ዜሮ

„አንቀጽ 4፤ „ማንም ሰው ቢሆን በባርነት አይገዛም። ባርነትና የባሪያ ንግድም በማንኛውም ዓይነት ክልክል ነው።“ የወያኔ ማንፌስቶ ያቀፈው ምርጥ ዘር ገዢ ሌላው ደግሞ ተገዢ ባሪያ ነው። ከዚህ በተጨማሪ  ሰሞኑን እንደ ጀርመኑ ዬZDF ቴሌቪዢን ዶክመንተሪ ዘገባ  የዘመናዊ የሠራተኛ ባርነት በሲዊዲኑ አሰሪ ካንፓኒ H&M ኢትዮጵውያን የመጨረሻ ክፍያ የሚያገኙና ለዘመናዊ ባርነት የተጋለጡ ስለመሆናቸው ምስክርነቱን ሰጥቷል። እንዲያውም ለባርነት የተዳረጉት ዬንፁህን የጉልበት ብዝበዛ ወሸኔና ማለፊያ ብሎ ወያኔ የሸለማቸውን ሺክ አላሙዲን ጨምሮ  እስኪበቃው ድረስ ዘገበው ወርፏቸዋል። ሀገረ ሲዊድን የባሪያ ጭቆናን በአዋጅ ካስረች በኋላ በእስያና በአፍሪካ የምታደርገው የእጅ አዙር ዬባርነት አገዛዝንም ዘገባው እስኪበቃው ነበር የከተከተው። ድርብርብ ባርነት በዘረኝነት ፖሊሲ ኢትዮጵያ ላይ ዘውድ ጭኗልና። ስለዚህ ውጤቱ …. ዜሮ ነው

„አንቀጽ 5፤ ማንም ሰው ቢሆን የጭካኔ ስቃይ እንዳይደርስበት ወይም ከሰብዓዊ አፈጻጸም ውጭ የሆነ የተዋረድ ተግባር ወይም ቅጣት አይፈጸምበትም።“ ሩቅ ሳይኬድ በተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የተፈጸመው ኢ – ሰባዕዊ ድርጊት በስተጀርባው ካለው የጣር ድምጽ፤ የወንድማችን ዬአቡበከር የእግር ብረት ቃለ ምልልስ ከበቂ በላይ ነው … ስለሆነም የዚህ ድንጋጌ ተፈፃሚነት – ዜሮ ነው ኢትዮጵያ ላይ።

„አንቀጽ 6፤ እያንዳንዱ ሰው በሕግ ፊት በሰው ዘርነቱ የመታወቅ መብት አለው።“ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ሰው ለመታዬት ለጎሳ ማደግደግ ያስፈልጋል። ይለፍ ያለው ጎጥ፤ ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ የሰው ሰውነቱ የሚለካው በጎጡ ነው። ስለዚህ – ዜሮ ይሆናል ውጤቱ።

„አንቀጽ 7፤ ሰው ሁሉ በሕግ ፊት እኩል ነው። ያለአንዳች ልዩነትም ሕጉ ደህንነቱን እንዲጠበቅለት እኩል የሆነ መብት አለው። ይህንን ውሳኔ በመጣስ ከሚደረግ ልዩነት ለማድረግ ከሚነሳሳ እንዲጠበቅ ሁሉም የእኩል መብት አለው።“ ይህ አንቀፅ በአራዊት ጫካዊ ተመክሮ ፈጽሞ ሊታሰብ የማይችል፤ በክትና በዘወትር ዜግነት አሳሩን የሚያይ ድንጋጌ ነው። ስለሆነ – ዜሮ ነው።

„አንቀጽ 8፤ እያንዳንዱ ሰው በሕገ መንግስቱ ወይም በሕግ የተሰጡትን መሠረታዊ መብቶች ከሚጥሱ ድርጊቶች ከፍተኛ በሆኑ ብሔራዊ የፍርድ ባለስልጣኖች ፍጹም በሆነ መንገድ እንዲወገድለት መብት አለው።“ የትኛው ህገ መንግሥት? ያ ማባጨዬዋው። ህም። እያንዳንዱ የወያኔ ጀሌ ንጉሥ ነው። እሱ ያሰረውን ቢቀዬር – ቢሞት ሌላው አይፈታውም እንኳንስ ያደገውን አንቀጽ ተግባር ላይ ለመዋል ስለዚህ ያው – ዜሮ።

„አንቀጽ 9፤ ማንም ሰው ያለፍርድ ተይዞ እንዲታሰር ወይም በግዛት እንዲኖር አይደረግም።“ ይህ ዕለታዊ የኢትዮጵያ ህዝብ የፍዳ ክምር ምን ሆነና? – በውንብድና ሀገር እያስተዳደር ባለው በጭፍኑ ወያኔ እርግጫ የተደረመሰ አንቀፅ ነው ስለዚህ ውጤቱ  –  ዜሮ

„አንቀጽ 10፤ እያንዳንዱ ሰው በመብቶቹና በግዴታዎቹ አፈጻጸም እንዲሁም በሚከሰስበት ማንኛውም ዓይነት የወንጀል ክስ ነጻ በሆነና በማያዳላ የፍርድ ሸንጎ በትክክለኛና በይፋ ጉዳዩ እንዲሰማለት የሙሉ እኩልነት መብት አለው።“ ይህ ድንጋጌ ህግና መንግሥት ፍርድ ቤትና ዳኛ ላላቸው ሀገሮች እንጂ እንደ እኛ እረኛ አልባ፤ ባለቤት አልባ፤ ለሆነ ስላልሆነ … በህጉ ውስጥ መኖር አይደለም በአጠገቡም የወያኔ መንፈስ የለም ስለዚህ ያው —- ዜሮ።

„አንቀጽ 11፤  „1/፡ በወንጀል ክስ የተከሰሰ ማንኛውም ሰው ለመከላከያው አስፈላጊዎች የሆኑትን ሁሉ አቅርቦ በሚከራከርበት የይፋ ፍርድ ቤት በሕግ መሠረት ወንጀለኛ መሆኑ እስቲረጋገጥበት ድረስ ከወንጀል ነጻ እንደሆነ የመቆጠር መብት አለው።“ ይህ ሊሆን ይችላልን? እእ –  ኢትዮጵያ ላይ የህልም ሠርግ ነው ስለዚህ ውጤቱ — ዜሮ

„2/፡ ማንም ሰው በብሔራዊ ወይም በኢንተርናሽናል ሕግ አንድ ነገር ወንጀል ሆኖ ባልተደነገገበት ጊዜ በፈጸመው ወይም ባልፈጸመው ማንኛውም ሥራ ወንጀለኛ ሆኖ አይከሰስም። ወይም ወንጀሉ በተፈጸመበት ጊዜ ከተደነገገው ቅጣት ይበልጥ አይፈረድበትም።“ ወያኔ እኮ ወንጀል ነው የሚለውን ፈብርኮ እራሱ ቀርፆ፤ አስገድዶ አስፈርሞ እኮ ነው የነፃነት አርበኞቻችን ግዞት ውስጥ መንፈሳቸውን እያነደደ የሚገኘው — አፈጻጸሙ እራሱ ሰቅጣጭ፤ መቀጣጫ የሚያደርግ፤ ሰው መሆንን የሚፈትን ስለሆነ – ውጤቱ – ዜሮ

„አንቀጽ 12፤ ማንም ሰው በግል ኑሮው በቤተሰቡ ውስጥ በቤቱ ወይም በሚጻጻፈው ደብዳቤ በፍርድ ያልተለየ ጣልቃ ገብነት ወይም ክብሩን የሚነካና ስሙን የሚያጎድፍ ተቃውሞ አይፈጸምበትም። እያንዳንዱ ሰው ከእንደዚህ ያለ ጣልቃ ገብነት ወይም የሚጎዳ ተግባር ሕግ እንዲከላከልለት መብት አለው።“ በዜጎች ታሪክ ላይ ስንት ድርድር ተውኔት ነው ወያኔ የሚሠራው? … ክብርን እንዴት ነው የሚጥሰው? አይደለም ዜጋን ሀገርን እንደ ሀገር ማዬት የማይችል፤ በክብሯና በማንነቷ፤ በታሪኳና በሉዕላዊቷ ላይ በሚያላግጥ ብህዝቦቿ ሞራል ላይ ሞት የፈረደ ስለሆነ ከዚህ ድንጋጌ ጋር እንዴት ብሎ ወያኔ ሊወዳጅ ይችላል?! ስለሆነም – ዜሮ

„አንቀጽ 13፤  1/፡ እያንዳንዱ ሰው በየብሔራዊ ወሰን ክልሉ የመዘዋወርና የመኖር ነጻነት መብት አለው።“ ይቻላልን? አይቻልም። እንኳንስ ይሄ ከባዕቱ እትብቱ ከተቀበረበት እንኳን መቀመጥ አይፈቀድለትም። ስንቱ ነው መንፈሱ በጭቃኔ የታረሰው – በደሉ ረመጥ ነው። ግፉ ቋያ ነው። ስለዚህ የድንጋጌው ውጤት – ዜሮ

„2/፡ እያንዳንዱ ሰው ከማንኛውም አገር ሆነ ከራሱ አገር ወጥቶ እንደገና ወደ አገሩ የመመለስ መብት አለው።“ በ24 ሰ ዓት ዜጎች ሀገራቸውን ለቀው እንዲወጣ የሚያደርግ ግዑዝ ይቻላልን? ይሆናልን? ደንበር እዬዘለለ፤ ደንበር እዬጠሳ ስንት ወገኖቻችን ነው ወያኔ የበላው? በተሰደድንበት ሀገር እንኳን ሊያስቀምጡን አልቻሉም በሆድ የገዛቸው ደጋፊዎቹ …. እንኳንስ ሌላ። የተከበሩ ዬአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ታላቅ እህት ምን ነበር የተፈጸመባቸው?! …. ስለዚህ መንፈሱ በዘመነ ወያኔ እንዳአለ የታጠሰ አንቀጽ ነው። እናም — ዜሮ

„አንቀጽ፡ 14፤ „1/፡ እያንዳንዱ ሰው ከጭቆና ሸሽቶ በሌሎች አገሮች ጥገኝነትን የመጠየቅና በደህና የመኖር መብት አለው።“ ወያኔ እያለ እንዴት ተብሎ? …. በበቀል በተነከረ የደም ጥማቱ፤ በመርዝ በተገኘው ነገር ሁሉ እያደነ ሰላም ይነሳል እንጂ … ኢትዮጵያ ያሉት ብቻ ሳይሆን ተሰደንም አልተኛልንም ወያኔ ስለዚህ ውጤቱ – ዜሮ

„2/፡ ፖለቲካዊ ካልሆኑ ወንጀሎች ወይም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ዓላማዎችን ከሚቃረኑ ሥራዎች የተነሳ በሚደርሱ ክሶች ምክንያት ከሆነ ይህ መብት ሊያገለግል አይችልም።“ ወይ ጉድ ኢትጵውያን እኮ ፈርሃ እግዚአብሄር ያለን ለህገ እግዚአብሄር ሆነ ለሰው ሰራሽ ህግጋት ትሁትና ቅን መንፈስ ያለን ሰላማዊ ዜጎች ነን። አብዛኞቻችን ኢትዮጵውያን በተሰደድነብት ሀገር ጸጥ ለጥ ብለን ነው የምንኖረው። ለጎረቤት፣ ለሥራ ባልደራባዎች ሁሉ የምንመች። ህግ የማይገዛው ሥራዓት የማያስተደድረው ወያኔና ማንፌስቶው ብቻ ናቸው።

„አንቀጽ፡15፤  „1/፡ እያንዳንዱ ሰው የዜግነት መብት አለው።“ ዜግነት በኢትዮጵያ ከተሰረዘ 24 ዓመት ሆነው። ዜግነት ትግሬነት ሆኗል። ስለዚህ ኢትዮጵያዊ ዜግነት እራሱ „ጽንፈኛ ብሄርተኛ“ እዬተባለ በጎሰኛው ወያኔ የሞት ፍርድ የታወጀበት ነው። የዜግነት ክብር ግርማና ሞገስ ፈተና ላይ ናቸው። ዜግነት ታስሯል። ወያኔ እንደ ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሚፈራውም አንዳችም ነገር የለም። ስለዚህ ያለው ጡንቻ ሁሉ የሚያርፈው ከዜግነት ላይ ነው። ስለዚህ የአፈጻጻሙ ክብርና ሂደቱ  – ዜሮ ነው።

„2/፡ ማንም ሰው ያለፍርድ ዜግነቱ አይወሰድበትም ወይም ዜግነቱን የመለወጥ መብት አይነፈገውም።“ ህም ነው …. ድንጋጌውንና በደሉን ማጠጋጋት ወይንም ማቀራረብ እንኳን አይቻልም ስለሆነም ይህም ዜሮ፤

„አንቀጽ፡16፤  1/፡ አካለ መጠን የደረሱ ወንዶችና ሴቶች በዘር በዜግነት ወይም በሃይማኖት ልዩነት ሳይወሰኑ ጋብቻን የመፈጸምና ቤተሰብን የመመሥረት መብት አላቸው፤ ጋብቻ በመፈጸም በጋብቻ ጊዜና ጋብቻ በሚፈርስበትም ጊዜ እኩል መብት አላቸው።

2/፡ ጋብቻ የሚፈጸመው ጋብቻ ለመፈጸም በሚፈልጉ ሁለቱም ወገኖች በሚያደርጉት ነጻና ሙሉ ስምምነት መሠረት ብቻ ነው።

3/፡ ቤተሰብ በኀብረ ሰብ የተፈጥሮና መሰረታዊ ክፍል ስለሆነ በኀብረሰቡና በመንግሥቱም ደህንነቱ እንዲጠበቅለት ይገባል።“

አነኝህን ድንጋጌዎች በነጠለ ትርጉማቸው ስንወስዳቸው በሞራ የተሸፈነ ብልጭልጭ የሚል አስመሳይ ደወሎች አሉበት። ወደ ውስጥ ስንዘልቅ ግን በሀገራችን በሚፈጸሙት ሶስት የጋብቻ ሥርዓቶች በሃይማኖታዊ፤ በባህላዊ እና በብሄራዊ ጋብቻ የጋብቻ ቀደምት ባህል፤ ትውፊትና ታሪክ ጠቀራ ለብሰዋል። የወልቃይትና የጠገዴ ሴቶች ልጆቻቸው በእናታቸው ሥም ነው የሚጠሩት፤ በአማራው ብሄረሰብ ልጅ እንዳይወልዱ የተሰጠው ክትባት የትድርን ዶግማ በቀጥታ የሚጻረር ነው። ወያኔ የጋብቻ መንፈስ ሸቀጥ እንዲሆን የሚደረገው ግፊት ብቻ ሳይሆን ጋብቻን ፍቅር ሳይሆን ዞግ – መራሽ እንዲሆን ስውር ተጽዕኖ ያደርጋል። ተጽዕኖውም ሆነ ተጠቂነቱም ከፍ ያለ ነው። ከዚህ በላይ በግፍ ስደቱ — እስራቱ – ሞቶ የጋብቻን ተፍጥሮ ድራሹን ነው ያጠፋው። ስለዚህ ከዋናው አምክንዮ ህግና ከአፈጻጻሙ ስውር ደባ አንፃር የውጤቱ ዝንባሌ ወደ ዜሮ ይሸኛል ….

„አንቀጽ፡17፤  „1/፡ እያንዳንዱ ሰው ብቻውን ወይም ከሌሎች ጋር በኀብረት ሆኖ የኀብረት ባለቤትነት መብት አለው።“ በጎሳ መንፈስ፤ በባለ ጊዜነት ዕይታ ከሆነ አዎን። እንደ ዜጋ ሲሰላ ግን ኢትዮጵያ ላይ አንቀጹ ከቦታው ተስርዟል። ስለሆነም ውጤቱ — ዜሮ።

„2/፡ ማንም ሰው ያለፍርድ ንብረቱ አይወሰድበትም።“ ፍርድ ቤት ሲኖረን ነው። እኛ ፍርድ ቤት፤ ለህዝብ ጥቅም የቆመ ሚዛን፤ ለሙያው ኪዳን ራሱን የሰጠ ርትሃዊ ሥርዓት የለንም። ስለዚህ ይህም ዜሮ

„አንቀጽ፡18፤ እያንዳንዱ ሰው የሃሳብ የሕሊናና የሃይማኖት ነጻነት መብት አለው። ይህም መብት ሃይማኖቱን ወይም እምነቱን የመለወጥ ነጻነትንና ብቻውን ወይም ከሌሎች ጋር በኀብረት በይፋ ወይም በግል ሆኖ ሃይማኖቱን ወይም እምነቱን የማስተማር፣ በተግባር የመግለጽ የማምለክና የማክበር ነጻነትን ይጨምራል።“ ኢትዮጵያ ላይ የአንቀጹ ጭብጥ ተግባራዊነት መሃን ነው። ስለዚህ ቁልጭ ያለ — ዜሮ

„አንቀጽ፡19፤ እያንዳንዱ ሰው የሐሳብና ሐሳቡን የመግለጽ መብት አለው። ይህም መብት ያለጣልቃ ገብነት በሐሳብ የመጽናትንና ዜናን ወይም ሐሳቦችን ያላንዳች የድንበር ገደብ የማግኘትን የመቀበልን ወይም የማካፈልን ነጻነትም ይጨምራል።“ ታላቁ የወያኔ የጥቃት ኢላማ ምን ሆነና – ያውም ወደልዜሮ

„አንቀጽ፡20፤ „1/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ በሰላም፡ የመሰብሰብና፡ ግንኙነት፡ የማድረግ፡ ነጻነት፡ መብት፡ አለው።“ ኢትዮጵያ ላይ የለውም። የሰሞኑ  ዬሰማያዊ ቢሮ ፎቶ ብቻ በቂ ነው። ስንቱስ ተዘርዝሮ ያልቅና። ስለዚህ ውጤቱ – ዜሮ

„2/፡ ማንም፡ ሰው፡ የአንድ፡ ማኀበር፡ አባል፡ እንዲሆን፡ አይገደድም።“ ወያኔ አስገድዶ – በገንዘብ ገዝቶ ነው አባል የሚያደርገው፤ አባልነት በፈቃደኝነት መርሁ ተዘቅዝቆ የተሰቀለ ነው። ስለዚህ – ዜሮ

„አንቀጽ፡21፤ 1/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡በቀጥታ፡ ወይም፡ ነጻ፡ በሆነ፡ መንገድ፡ በተመረጡ፡ እንደራሴዎች፡ አማካኝነት፡ በአገሩ፡ መንግስት፡ የመካፈል፡ መብት፡ አለው:“ ወይ መዳህኒተ ዓለም አባቴ በጎጥ ሶሻሊዝም ይህ ቅዱስ መንፈስ በቢላዋ ነው ዓይኑን ወያኔ ያወጣው። ስለዚህ – ዜሮ

„2/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ በአገሩ፡ የህዝብ፡ አገልግሎት፡ እኩል፡ የማግኘት፡ መብት፡ አለው።“ ለባለወርቅ ሊሆን ይችላል። ለግዕፋኑ ግን አይሠራም። ስልሆነም – ዜሮ።

„3/፡ የመንግስት፡ ሥልጣን፡ መሠረቱ፡ የሕዝቡ፡ ፈቃድ፡ መሆን፡ አለበት። ይህም፡ ፈቃድ፡ ለሁሉም፡ እኩል፡ በሆነ፡ በምሥጢር፡ በሚደረግ፡ የድምፅ፡ መስጠት፡ ምርጫ፡ ወይም፡ በተመሳሳይ፡ ሁኔታ፡ በየጊዜውና፡ በትክክል፡ በሚፈጸሙ፡ ምርጫዎች፡ እንዲገለጽ፡ መሆን፡ አለበት።“ አውሬን የሚፈቅድ፤ አራጅን የሚፈቅድ፤ አግላይን የሚፈቅድ፤ ገዳይን የሚፈቅድ ህዝብ የለም። ስለሆነም ድንጋጌው መልካም ሆኖ ሳለ በጎሳ ገዢወች የታፈነው ዬኢትዮጵያ ህዝብ ፍርፋሪውን ወይንም የድንጋጌውን ጸበለ ጻዲቅ ሊያገኝ አልቻለም። በቃህኝ! ካለ እኮ ቆዬ። 97 እኮ ንቅንቅ ብሎ ወጥቶ ነበር ባዶውን ያስቀረው። ረሃብን የሚፈቅድ ማን አለና? ክብር መጣስን የሚሻ ማን አለና? ስለዚህ ዜሮን በሞራ ጠቅሎ የዓለምን ህዝብ የሚያባጭልበት የእዬአራት አመቱ ምርጫ ከህዝብ ፈቃድ ውጪ በተጎማጀ አውሬያዊ መንገዱ ያስፈጽመዋል። በመሆኑ የድንጋጌው ድርጊተኝነት ኢትዮጵያ ላይ … ጠፍጣፋ ዜሮ።

„አንቀጽ፡22፤ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ የኀብረ፡ ሰብ፡ አባል፡ እንደመሆኑ፡ በኀብረ፡ ሰብ፡ ደህንነቱ፡ እንዲጠበቅ፡ መብት፡ አለው። እንዲሁም፡ በብሔራዊ፡ ጥረትና፡ በኢንተርናሽናል፡ መተባበር፡ አማካይነትና፡ በእያንዳንዱ፡ መንግስት፡ ድርጅትም፡ የሀብት፡ ምንጮች፡ መሰረት፡ ለክብሩና፡ ለሰብዓዊ፡ አቅሙ፡ ነጻ፡ እድገት፡ የግድ፡ አስፈላጊ፡ የሆኑት፡ የኤኮኖሚ፡ የማኀበራዊ፡ ኑሮና፡ የባህል፡ መብቶች፡ በተግባር፡ እንዲገለጹለት፡ መብት፡ አለው።“ ህዝባዊ መንግሥት ሲኖር፤ በህዝብ ፈቃድ ሥልጣን የተሰጠው ሃላፊነት የሚሰማው ሥልጡን ሥርዓት ሲኖር ብቻ፤ በአስተሳሰብ ድህነት ለተወረረው ዬወያኔ ሥርዓት ግንዛቤ  ግን – ሳይፈጽመው ዜሮ ላይ አስክኖታል።

„አንቀጽ፡23  „1/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ የመሥራት፡ የሥራ፡ ነጻ፡ ምርጫና፡ ለሥራም፡ ትክክለኛና፡ ተስማሚ፡ የአሠራር፡ ሁኔታዎችና፡ ሥራም፡ እንዳያጣ፡ መብት፡ አለው።“ አለን ይሄ ኢትዮጵያ ላይ ….?! የድንጋጌው መሪ የጎጥ ድርጅት አባልነት ብቻ ነው። ስለዚህ ለምልዕቱ የድናጋጌው ትርፋማነት ኢትዮጵያ ላይ — ዝክንትል ዜሮ።

„2/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ያላንዳች፡ ልዩነት፡ ማድረግ፡ ለአንድ፡ ዓይነት፡ ሥራ፡ እኩል፡ የሆነ፡ ደመወዝ፡ የማግኘት፡ መብት፡ አለው።“ ኢትዮጵያዊነቱን ለሚያስቀድም ብቁ ዜጋ፤ ነፃነት ከ እኔ መጀመር አለበት ለሚል ብልህ፤ አቅም ላለው ዜጋ ይህ አንቀጽ አይሰራም። — ለድውያኔ፣ ለደካሞች፣ ለአቅመ ቢሶች  ዬአስተሳስብ ድህነት ለረበባቸው ግን ይሠራል። ስለዚህ ህገ – ትርጓሜው የእኩል ተጠቃሚነትን ስለማይተረጉም — አድሎዊ ስለሆነ ኢትዮጵያ ላይ ውጤቱ – ደጎስ ያለ ዜሮ።

„3/፡ በሥራ፡ ላይ፡ ያለ፡ ሰው፡ ለእራሱና፡ ለቤተሰቡ፡ ለሰብዓዊ፡ ክብር፡ ተገቢ፡ የሆነ፡ ኑሮን፡ የሚያስገኝለትና፡ ካስፈለገም፡ በሌሎች፡ የኀብረሰብ፡ ደህንነት፡ መጠበቂያ፡ ዘዴዎች፡ የተደገፈ፡ ትክክለኛና፡ ተስማሚ፡ ዋጋውን፡ የማግኘት፡ መብት፡ አለው።“ ያው ለጎሳው ሊሠራ ይችል ይሆናል። ለኢትዮጵያዊነት ግን ኢትዮጵያ ላይ ጣር ነው። ስለዚህ - ከዜሮም ጎባጣው።

„4/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ ጥቅሞቹን፡ ለማስከበር፡ የሙያ፡ ማኀበሮችን፡ ለማቋቋምና፡ ማኀበርተኛ፡ ለመሆን፡ መብት፡ አለው።“ በጎሳ መንፈስ ብቻ ለተደራጀ። በብሄራዊነትን ለመግደል ለሚተባባር ሃይል ብቻ አልጋ ባልጋ ነው መንገዱ ነው። ለነፃነት ዘንካቲት ግን የሀገራዊነትን መንፈስ ለፈቀደ አይሠራም ድንጋጌው ሽባ ነው ስለዚህ ማርኩ – ዜሮ።

„አንቀጽ፡24፤ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ የዕረፍትና፡ የመዝናናት፡ እንዲሁም፡ በአግባብ፡ የተወሰኑ፡ የሥራ፡ ሰዓቶች፡ እንዲኖሩትና፡ በየጊዜው፡ የዕረፍት፡ ጊዜያትን፡ ከደመወዝ፡ ጋር፡ የማግኘት፡ መብት፡ አለው።“ ይሄን ድንጋጌ አንባቢ ብቻ ሳይሆን በህይወቱ ያሉ ይለኩት።

„አንቀጽ፡25፤ 1/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ ለእራሱና፡ ለቤተሰቡ፡ ጤንነትና፡ ደህንነት፡ ምግብ፣ ልብስ፣ ቤትና፡ ሕክምና፡ አስፈላጊ፡ የማኀበራዊ፡ ኑሮ፡ አገልግሎቶችም፡ ጭምር፡ የሚበቃ፡ የኑሮ፡ ደረጃ፡ ለማግኘት፡ መብት፡ አለው። ሥራ፡ ሳይቀጠር፡ ቢቀር፡ ቢታመም፡ ለመሥራት፡ ባይችል፡ ባል፡ ወይም፡ ሚስት፡ ቢሞት፡ ቢያረጅ፡ ወይም፡ ከቁጥጥሩ፡ ውጭ፡ በሆኑ፡ ምክንያቶች፡ መሰናከል፡ ቢገጥመው፡ ደህንነቱ፡ እንዲጠበቅለት፡ መብት፡ አለው።“

„2/፡ ወላድነትና፡ ሕጻንነት፡ ልዩ፡ ጥንቃቄና፡ እርዳታ፡ የማግኘት፡ መብት፡ አላቸው፤ በጋብቻ፡ ወይም፡ ያለጋብቻ፡ የሚወለዱ፡ ሕጻናትም፡ የተመሳሳይ፡ የደህንነታቸው፡ መጠበቅ፡ መብት፡ አላቸው።“ ሁለቱም ንዑሳን ድንጋጌዎች ድምጽ የሚመራት ሀገር ስትኖረን ነው። ከዓለም ሶስት የመጨረሻ ደሃ ሀገሮች አንዷ ኢትዮጵያ ናት። ሟርቱ ተሳክቶለታል። ኢትዮጵያ ስንት ትውልድ ሊከፍለው እንደሚችል አይተወቅም በዕዳ የተዘፈቀች፤ በብዙ ውስብስብ ፈተናዎች ለመፍታት የሚፈልገው መዋዕለ መንፈስ እራሱ … ህም። ለማንኛውም በሁለመናዋ በወያኔ እስር ለተፈረደባት ሀገር የህልም ገነት የሆነ አንቀጽ ነው። ስለዚህ የወደቀ ለቅሞ ለመብላት ተራ፤ ለዛም የሚጥል በሌለበት ሀገር  ስለሆነ የድንጋጌው ተፈጻሚነት ለጥቂት ወንበዴዎችና ቤተሰቦቻቸው ብቻ ይሆናል – ዜሮ።

„አንቀጽ፡26፤ 1/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ የመማር፡ መብት፡ አለው። ትምህርት፡ ቢያንስ፡ ቢያንስ፡ በአንደኛ፡ ደረጃና፡ መሰረታዊ፡ ደረጃዎች፡ በነጻ፡ ሊሆን፡ ይገባል። የአንደኛ፡ ደረጃ፡ ትምህርት፡ መማር፡ ግዴታ፡ ነው። የቴክኒክና፡ የልዩ፡ ልዩ፡ ሙያ፡ ትምህርት፡ በጠቅላላው፡ የከፍተኛ፡ ደረጃ፡ ደግሞ፡ በችሎታ፡ መሠረት፡ ለሁሉም፡ እኩል፡ መሰጠት፡ አለበት።

2/፡ ትምህርት፡ ለእያንዳንዱ፡ ሰው፡ ሁኔታ፡ ማሻሻያና፡ ለሰብዓዊ፡ መብቶችም፡ መሠረታዊ፡ ነጻነቶች፡ ክብር፡ ማዳበርያ፡ የሚውል፡ መሆን፡ አለበት። እንዲሁም፡ የተለያየ፡ ዘር፡ ወይም፡ ሃይማኖት፡ ባሏቸው፡ ሕዝቦች፡ መካከል፡ ሁሉ፡ መግባባትን፡ ተቻችሎ፡ የመኖርንና፡ የመተባበርን፡ መንፈስ፡ የሚያጠነክርና፡ የተባበሩት፡ መንግሥታት፡ ድርጅት፡ ሰላምን፡ ለመጠበቅ፡ የሚፈጽማቸው፡ ተግባሮች፡ እንዲስፋፋ፡ የሚያበረታቱ፡ መሆን፡ አለበት።

3/፡ ወላጆች፡ ለልጆቻቸው፡ ለመስጠት፡ የሚፈልጉትን፡ ትምህርት፡ ለመምረጥ፡ የቅድሚያ፡ መብት፡ አላችው።“ እንኝህን የሥልጣኔ መሠረት የሆኑት የዕውቀት ግንባታና መሠረት በጥቅሉ ሲታይ፤ የትምህርቱ ደረጃም የሚለካውና የሚመዘነው ከሥርዓቱ ጥንካሬና ከጠንካራ ፖሊሲዎቹ ከሚፈልቁ ጉልበታም ተግባራት ነው። በዘመነ ወያኔ ታላቅ ውድቀት ከደረሰባቸው አንዱ ትምህርትና የትምህርት ተዋዖው ነው። የትምህርት ሥርጭቱ ያልተመጣጠነ አድሎ የዘፈነበትና ነገን ያሳረር፤ ዬትናንትን ታሪካዊ ሃብታትን ያለርህራሄ ያቃጠለ ነው። ዝርክርክ „የእነ ተሎ ተሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ“  ለዜሮም መቅኑ የፈሰሰ – ዜሮ

„አንቀጽ፡27፤ 1/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ በኀብረተ ሰቡ፡ የባህል፡ ኑሮ፡ በነጻ፡ መካፈልና፡ በኪነ፡ ጥበብ፡ ለመጠቀም፡ በሳይንስ፡ እርምጃና፡ በጥቅሞቹም፡ ለመሳተፍ፡ መብት፡ አለው።

2/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ ከደረሰው፡ ማንኛውም፡ የሳይንስ፡ የድርሰትና፡ የኪነ፡ ጥበብ፡ ሥራ፡ የሚያገኘው፡ የሞራሉንና፡ የሃብት፡ ጥቅሞች፡ እንዲከበሩለት፡ መብት፡ አለው።“ ዬትውልድ መጸሐፍ የሆነው አርቲስት ወጋዬሁ ንጋቱን ያልተካ የትውልድ ማገር የሆነውን አርቲስት ደበበ እሸቱን የህዝብ ሃብትነቱን ያሰረ፤ ጸጋውን የለጎመ። አዬ! በአንድ ባለቅኔ ቴዲ አፍሮ የሚደረሰው ፍዳና መከራ በቂ ነው። ከብሄራዊነት የሚነሱ ማናቸውም አምክንዮዎች የሚመጠብቃቸው ዱላ ነው። ስለዚህ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከጎሳ ማኒፌስቶ ወራጅ ውሃ የተጠለለ ከሆነ – ምን አልባት። በተረፈ ለዛውም ለሥነ ጥበብ ነፃነት የጋዜጠኞች የጸሐፍት ፍልሰት ምንጩ ምን ሆነና። የዚህ ዬፍትህ ሥርዓት የተስተካካለ ይሆናል ብሎ ማሰብ ጮርቃነት ነው። ለዚህም ነው ዬነፃነት ትግሉ ብጥቅጣቂ ነገሮችን ዘግቶ አጠቃላይና ሥር ነቀል በሆኑ ሁኔታዎች ላይ አቅሙንም ጉልበቱንም የመንፈስ ሃብታትም መፍስስ አለበት የሚባለው። ከአጠቃላዩ የጎጥ አስተዳደር መንፈስ የጥልቅ ግልጽ ጥቃቱና ከሥውር ደባው ስንነሳ የዚህ አንቀጽ ተፈጻሚነት ኢትዮጵያ ላይ – የተድበለበለ ዜሮ ነው።

„አንቀጽ፡28፤ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ በዚህ፡ ውሳኔ፡ ውስጥ፡ የተዘረዘሩት፡ መብቶችና፡ ነጻነቶች፡ በሙሉ፡ በተግባር፡ እንዲውሉ፡ ለሚደረግባቸው፡ የኀብረሰብና፡ የኢንተርናሽናል፡ ሥርዓት፡ የመጠቀም፡ መብት፡ አለው።“ ለመብቱ ባይታወር የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ግዴታውን ለመፈጸም ይችላል። ይህ ማለት ብዙሃኑ ነፃነቱን ተነጥቆ ለተነጠቀው ነፃነት ዘብ ቁሞ ያድራል። ከጣና የተሳባው የመብራት ሃይል ትግራይ እስኪደርስ ድረስ ያለፈባቸው መንገዶችን እንደጨለመባቸው ሲሆን፤ ነገር ግን የመብራቱን ወጋግራ ባለፈባቸው ቦታዎች ያሉ ንጹኃን ቁመው ሲጠብቁ ውለው ያደራሉ። ማለት ብዙሃኑ ለማይጠቀምበት ቁሞ መብራት ይዞ ቁርስ ራት ምሳ ያበላል – ለባለጊዜው። እሱ ግን እንደ ተራበ። ለዛውም አንጡራ ሃብቱ ሆኖ። የበደሉ ልክ እኮ የለውም። ለነጌቶቹ መብራት ይዞ –  ለብዙሃኑ ግን ምንም – ያው ዜሮ።

„አንቀጽ፡29፤  1/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ የራሱ፡ ነጻነትና፡ ሙሉ፡ መሻሻል፡ በሚያገኝበት፡ ኀብረሰብ፡ ውስጥ፡ የሚፈጽማቸው፡ ግዴታዎች፡ ይኖሩበታል።

2/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ በመብቶቹ፡ በነጻነቶቹ፡ በሚጠቀምበት፡ ጊዜ፡ የሚታገደው፡ የሌሎችን፡ መብቶችና፡ ነጻነቶች፡ በሚገባ፡ ለማሰከበር፡ ብቻ፡ በተደነገጉ፡ ሕጎችና፡ የግብረ፡ ገብነትን፡ የጠቅላላውን፡ ሕዝብ፡ ፀጥታና፡ ደህንነት፡ በዴሞክራቲክ፡ ማኀበራዊ፡ ኑሮ፡ ትክክለኛ፡ የሆነው፡ ተፈላጊ፡ ጉዳይ፡ ለማርካት፡ በተወሰነው፡ ብቻ፡ ነው።

3/፡ እነዚህ፡ መብቶችና፡ ነፃነቶች፡ በማንኛውም፡ ሁኔታ፡ የተባበሩት፡ መንግሥታት፡ ድርጅት፡ መሰረት፡ ዓላማዎች፡ ተቃራኒ፡ በሆነ፡ መንገድ፡ ሊፈጸሙ፡ አይገባቸውም።“ ህግ መተላለፍ ከወያኔ በስተቀር ኢትዮጵያዊ ተፈጥሮ አይፈቅደውም። ስለዚህ ህግ ጣሹ ወያኔ ለህግጋቱ ሳይገዛ እዬዳጠና እዬደፈጠጠ የሚሄደውን ነገር ማስቆም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግዴታ ነው።

„አንቀጽ፡30፤ በዚህ ውሳኔ ከላይ የተዘረዘረው ሁሉ በዚሁ ውስጥ የተጠቀሱትን ማናቸውም መብቶች ወይም ነጻነቶች ለማበላሸት በታሰበ ማንኛውም ዓይነት ተግባር ለማዋል ወይም ድርጊትን ለመፈጸም ለማንኛውም መንግሥት ወይም ድርጅት ወይም ሰው የተባሉ አይተረጎሙም“ ወገኖቼ  እነዚህ ድንጋጌዎች ለዬሀገሮች ማስተማሪያ ብቻ ሳይሆኑ እንዲፈጸሙ፤ የህግ ጥበቃና ድጋፍ፤ እንዲሁም ክትትልና ቁጥጥር ሊደረግባቸው የሚገቡ የነባቢተ – ነፍስ ንጹህ የአዬር መስጫ ቧንቧዎች ናቸው። የተባበሩት መንግሥታት አባል ሀገሮች አኃታዊ ህገ መንግሥት፤ እናት ህግ ብለው ይሻል ይመስለኛል።

ከ1948 በኋላም ቢሆን በተለያዩ ጊዜያቶች ብዙ የማጠናከሪያ፤ የማጉያ አትኩሮት ተስጥቷቸዋል። በተለይ በ2007 እና በ2008 ጥልቅ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሰፊ አምክንዮዊ መንፈሶች በተጨማሪነት አድገዋል፤ ግን በወያኔ ባዶ ናቸው። ወያኔ የመስሚያ ታንቡሩ የተነፈስ ነውና። በ2007 እና በ2008 ሰፊ አትኩሮት የተሰጣቸው ጥልቅ የሰብዕና ህላዊ ጉዳዮች Durban Declaration constitutes  – racism, racial discrimnation, xenophobia and related intolerance በመፈጸም የድርጊት ጀግኖች ተብለው ለናሙና ከተመረጡት ሀገሮች ጥቂቶችን እስኪ ላንሳ።

አንዷ አርመንያ ነበረች። አረመንያ በፆታ እኩልነት ፍጹም የሆነ ጥበቃና ክትትል የምታደርገው ህግ በማውጣት ብቻ ሳይሆን፤ ለወጣው ህግ ጠንከራ ጠበቂ ተጨማሪ ህግ አውጥታ ሥራ ላይ በማዋል ነው፤ ድንቋ አርመንያ የሥራ ባርነት በፍጹም ሁኔታ የተወገደባት ሀገር ናት። ስለ ሰብዕዊ መብት በህጋዊ ትምህርት ቤቶች፣ በክበቦች፣ በካንፓሶች በነፃ ውይይት ይደረግበታል። አብሶ ለወጣቶች በትጋት እንደ ሃይማኖታዊ ዶግማ ይሰበከል። በአርመንያ 8ኛ ክፍል ላይ እንደ አንድ የትምህርት ሳብጀክት የሰብዕዊ መብት (Human Rights) ትምህርት ለተማሪዎች ይሰጣል።

ለንጽጽር እንዲረዳም – ከእማማ አፍሪካ ውስጥም ቢሆን አልጀሪያ ለተምሳሌ የተመረጠች ሀገር ናት። በብዙ ፈተና ውስጥ ያለፈችው አልጀርያ ለዚህ ክብር የበቃች ሀገር ናት። ዬ60 ብሄረሰቦች እናት የሆነቸው ቡርኪናፋሶ ዘረኝነትን፤ ግለላን፣ የሰው ልጅ ጥላቻን፤ ንቀትን በአዋጅ ያስቀረች ለሰብዕዊ መብት መከበር ጥልቅ ፍላጎቶች የተስማማች ሀገር ናት። ቀደምቷ የሰው ልጅ መፈጠሪያ እናት ሀገር ፍርጃ ደግሞ በጎሳ መከታከት። ባለፈም ሰብዕዊ መብት ቃሉን መጥራት የማይፈቀድባት፤ የሰብዕዊ መብት አፈጻጸም የሲኦልና ዬሃሞት ሀገር አድርጓታል – ወያኔ። አንዲት ስንጥር ደግ ነገር ፈጽሞ ማግኘት አይቻልም። ሀገር ማለት እኮ የእኔ ውዶች ዓለም አቅፍ ዕውቅና ባለው ድንበር ውስጥ የሰዎች ማህበር ማለት ነው። ማህበሩ ከተጠቀጠቀ፣ ከፈረሰ፣ ከተዘለለ ሀገር የለም። የሀገር መነሻው ሰው ነው። ዬማናቸውም ፍላጎት መነሻው ከሰው ምቹ ተፈጥሮ መሆን አለበት። ወያኔ ግን ተነሳፎ ነው ያለው። መነሻ ቢስ – ከንቱ ስለሆነ። ቀድሞ ነገር ለሰው ልጅ ማህበራዊ እድገት ንቀት ብቻ ሳይሆን እድገቱን የሚጸዬፍ ወያኔ ብቻ።

ክብሮቼ ልክውነው ….  ቁምነገሩ እኛስ ህልማችን ምንድን ይሆን? እነዚህን ህግጋት በውስጣችን አድርገን፣ ነገ የምናልማት ኢትዮጵያን በመንፈሳችን ይዘን፣ የአርነት ትግሉን ስናጠነክር ብቻ ለውጤት እንበቃለን። ግን አራሳችን ማዘዝ ስንችል ብቻ ነው። እንደገናም እኛስ በሌሎቹ ላይ ህግን ተላልፈን ምን በደል ፈጸምን ይሆን? ይሄ ሌላው የነገ የኢትዮጵያ ጥልቅ ፈተና ነው። ዛሬ አረሙ ካልጸዳ ነገም ይህ በደል ይፈጸማል። ከዚህ ላይ አንድ ምሳሌትን ላንሳ አንቀጽ 13ን ንዑስ አንቀጽ  „2/፡ እያንዳንዱ ሰው ከማንኛውም አገር ሆነ ከራሱ አገር ወጥቶ እንደገና ወደ አገሩ የመመለስ መብት አለው።“  ወገኖቻችን ኢትዮጵያ ሀገራቸውን አይተው የሚመጡትን ወንጀለኛ እናደርጋቸዋለን። ሲያስፈልግም መረብ ዘርግተን ማህበራዊ ግንኙነታቸውን ሁሉ ጢስ እናለብሰዋለን። አቅማችን ከበላው መሰረታዊ ጉዳይ አውራው ስለሆነ ነው ይህን ያነሳሁት። ይህ የተገባ አይደለም። የሚችሉ መሄዳቸው ዓለምዓቀፍ መብታቸው ነው። ኢትዮጵያ እጅግ እንደ ሰው የምትናፈቅ ሀገር ናት። መቀመጫውን ፓሪስ ያደረገ አንድ ዓለማቀፋዊ ዬኢኮኖሚ እድገት አያያዝና አገልግሎትን ጥራት አበረታች ድርጅት Business Initiative Directions (BID) ጉባኤ የሽልማት ሥርዓት ላይ በሥርዓቱ የተገኙ አንድ አዛውንት ስለ ሀገር ናፍቆት ጠይቄያቸው እንዲህ ነበር ያሉኝ „መኪና ውስጥ ሆኖ ምግብ ታዞ፤ አስተናጋጅ መጥቶ የሚያሰተናግድባት ብቸኛ ሀገር እኮ ናት – ኢትዮጵያ ለምን አትናፍቅ?!“ ስለዚህ እውነት እኛ እራሳችን መለወጥ አለብን።

እምዬ ሀዘን ላይ ብትሆንም፤ ጉስቁልናዋን ሄዶ ማዬት የነፃነት ትግሉን ያጎለበተዋል እንጂ አያሰልለውም። ብዙ ዓይነት መረጃዎች፤ የዓይን ምስክሮች ይገኛሉ። በዚህ ዙሪያ እራሱን የቻለ ተከታታይ አቅም ያለው ተግባር ቢከውን ስንት ምርት ይታፈስበታል።  እርግጥ የወያኔን ባይረስ ተሸክመው የሚመጡ ሊኖሩ ይችላሉ። እኛ አቅም አለን። እውነት አለን። ቁጭ ብለን ሞግተን የእኛ ሃብት ማድረግ እንችላለን። ዝም ብሎ በጅምላ ማዋከቡ፤ ማግለሉ ግን እንደ ለእኔ ህግን መተላለፍ ይመስለኛል። „ህግ ተላላፊዎችን ጠላሁ“ አለ ነብዬ እግዚአብሄር ዳዊት። ህግ ወያኔ ጣሰ ለማለት እኛ እራሳችነን በህግ ሥር ማሳደርን ይጠይቅ ይመስለኛል። አንዳንድ ጊዜ ከሰብዕዊ መብት የተነሱ ሃይማኖታዊ ሆኑ ዓለምዓቀፍ ህግጋት ጋር የመራራቅ ችግርም ያለብን ይመስለኛል።

ይህም ብቻ አይደለም በኪነጥበብ ዘርፍም አንቀጽ 27 ሃብትነቱ የህዝብ ሆኖ ለጥበበኛው የሚጣለው ማዕቀብ የብዙሃኑ ታዳሚ መብትን ይገጣል። አንቀጽ 18፣ ቢሆን ሃስብን – ፍላጎትን – ዕይታን  – ተቃውሞን – ድጋፍን የመግልጽ ነፃነት በትክክል መፈጸም ካልቻልን ነገን ያቀጭጫል። አሁን እኔ ዘሃበሻ ነፃነቴን ባያውጅልኝ በምን እንገናኝ ነበር። ነፃነት የሰው ልጅ ባገኘ ቁጥር ውስጡን ገልጦ ያሳያል። ውስጡን ግልጦ ባሳዬ ቁጥር ደግሞ የመፍትሄው አቅጣጫ ይታወቃል። አይደለም ከሚያግዝ፣ ዬማያግዝ ሃሳብም ልግሞ በውስጥ ከሚያዝ ቢወጣ፤ ያበጠው መተንፈሻ ቧንቧ ይሠራለትን እና መግሉ እንዲወጣ፤ ቁስሉ እንደ አባት አደሩ እንዲድን መፈወሻ ያገኛል። የማይድን ሲሆን ደግም አገላብጦ አይቶ በማሰናበት ጊዜን በአግባቡ ማስተዳደር ይቻላል።። ግን ለማድመጥ ስንፈቅድ ብቻ ነው። እኛ እራሳችን ነፃነትን ለሌለው ነፃነት በመስጠት መደባችን የት ላይ ይሆን?!

አያድርግብኛ እንጂ አንድ ምሳሌ ባነሳ „እኔ ወያኔ ብሆን¡“ ሎቱ ስብሃት ስለቃሉ ይቅር ይበለኝ አምላኬ ጋዜጠኛ ተመስገንን አላስርም ነበር። ስለምን? „የቅርብ ሟዕት የቹቻ መንከሪያ ይሆናል“ ይላል ጎንደሬ ሲተርት። ትእግስቱ ተመስገን ትልቅ ዋርካ ነበር። ከትንሿ ሰቀቅን ተነስቶ የህዝብን የውስጥ ስሜት እንደ ሃኪም መርምሮ፤ ትችቱን – መፍትሄውን – ቁልፉን በድፍረት ይናገራል። ፈውሱ ነበር ለወያኔ ግን በምን አቅል? ሽንፍላ። የተሜ ትንተናው የተቋም ያህል ከልብ ነበር። ደፋር ትችቱ ነገን አቃንቶ የማምጣት ልዩ አቅም ነበረው። ከህዝብ ውስጣዊ የሞቀ ወይንም ለብ ያለ ወይንም የበረደው ስሜት ተነስቶ የሚሰጠው ትንተና ለወያኔ መዳኛው መፈወሻው ልዩ ማሰልጠኛው ነበር። ሌላው አዛውንቱ ብዕረኛ ጋዜጠኛ እስክንድር የመንፈስ ዓይን ነበር። ሌሎች የብዕር አርበኞቻችንም ዕድሉን ቢያገኙ መዳህኒትም – መዳኛ ነበሩ። ለአንድ ሥልጡን ማህበረሰብ ህዋሱ የደፋር ጋዜጠኞች መኖር ነበር። ግን አልተቻለም። የነፃነት እራህብን በራህብ ቆላው፤ የነፃነት እርሃብን በራህብ አንገረገበው ጆፌው አሞራ።

አብርሽም ቢሆን ወያኔ  ከሚመካበት ማህበረሰብ የወጣ ወጣት ስለነበር፤ ጭራቁ የጎጥ ዶክተሬን በአዲሱ ትውልድ ዕይታ ምን እንደሚመስል ሳዕሊው ነበር። አቅም ስሌለው ወያኔ ብዕርን ፈርቶ ሃሳብን ሸሽቶ አሰረ። ኢትዮጵያን ሻማ አልባ አድርጎ ጭጋጋማ ጨለማ አለበሳት። ስለዚህ የእኛ ትግል ነገም የሃሳብ ብልጫ የሚመራት፤ የጠራ የሃስብ ጭማቂ የሚያስተዳድራት ሀገር ለመፍጠር ከሆነ፤ በዚህ ዙሪያ መጠራቅቁን ይፍታህ ማለት ያለብን ይመስለኛል። አራሳችን ለራሳችን ካሜራ መሆን አለብን።

አንቀጽ 20. ንዑስ አንቀጽ 2 አባልነት በፈቃደኝነትን ያከበረ ስለመሆኑ አበክሮ ያስገነዝባል። ስለሆነም ፈቅዶ የአንድ ፓርቲ አባል ለሚሆን፤ ወይንም ፈቅዶም ለማይሆኑ እኩል አክብሮትና የቤተሰባዊ ፍቅር የመስጠት እቅምን አምጠን መውለድ አለብን። ይህ ለዛሬ ብቻ አይደለም – ለነገም። ዛሬ ተሞርዶ ጎባጣውን ካላቃናነው ነገንም ያበልዘዋል።

ይህን ታላቅ „የወንጌል ቃል ያነገሠ“  ቀን ስናከብር ድንጋጌዎችን የዕለት ህይወታችን እንዲመሩት መፈቀዳችን እያረጋገጥን መሆን አለብን። በስተቀር አስክንድር – እስክንድር፤ የእኔ ሰው የእኔ ሰው፤ እርዮት እርዮት፤ በላይነሽ ባላይነሽ፤ አቡቦከር አቡበከር፤ በቀለ በቀለ፤ ውብሸት – ውብሸት ማለቱ ብቻውን ነገን አብርቶ አያመጣም። ስለዚህ ህጎችን ከወዲሁ ከእራስ ጋር አዋህዶ አክብሮቱን ድርጊት ላይ ለማዋል መትጋት ግድ ይለናል – እኛ እራሳችነን፤ እኛ ከዛ ቦታ ብንሆን በማለት ፈታኝ ነገሮችን ሁሉ ዛሬ መልክ ካላስያዝናቸው ነገ እዬመረቀዙ ለዛ መከረኛ ህዝብ ዕንባ ቀጣይነት ማዳበሬያ ይሆናሉ። ማሸነፍ የሚነሳው ከራስ ነው። ለሚወዱት ፍላጎት አራስ ነብር ሳይሆኑ እራስን ማሸነፍ ጀግነንት ነው - ደስታ ነው – ብሩህ ተስፋም ነው። የኔዎቹ ረጅም ጊዜ አቆዬኋችሁ – የግድ ስለነበር። አመሰግንኳችሁ። ትእግስታችሁን አደንቅኩኝ። መሸቢያ የሥራ ቀናት ከመጪው ሰንበት ጋር እንዲሆን ተመኘሁ – በአክብሮት። ደህና ሰንብቱልኝ።

ህግ የሚመራው ተናፋቂና ተወዳጅ ሥርዓት አምላካችን መርቆ ይስጠን!

ለህገ – ልቦና ነፍሳችን ይገዛ ዘንድ ልቦናችነን አምላካችን ይክፈት – ይርዳንም። አሜን!

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

‹‹መንግሥት ባለበት አገር በጠራራ ፀሐይ ቤቴን ተቀማሁ›› ወ/ሮ ዘውዴ ወልደማርያም፣ የየካ ክፍለ ከተማ ነዋሪ

$
0
0

5ae05111c2dabb956f6e9581e765e020_Lየዛሬ ‹‹ምን እየሠሩ ነው?›› ዐምዳችን እንግዳ ወ/ሮ ዘውዴ ወልደማርያም ይባላሉ፡፡ ዕድሜያቸው 70 መሆኑን ይናገራሉ፡፡

የሚኖሩት በየካ ክፍለ ከተማ በቀድሞ ቀበሌ 11/12 ወይም በአሁኑ ወረዳ ሰባት ውስጥ ነበር፡፡ ወ/ሮ ዘውዴ በ2001 ዓ.ም. በ1,700,000 ብር የገዙትን ቤት ላለፉት ስድስት ዓመታት የኖሩበት ሲሆን፣ ሙሉ በሙሉም ባይሆን የተወሰነ ግንባታ አካሂደውበታል፡፡ በቆርቆሮና እንጨት ታጥሮ የነበረን ግቢ፣ በግንብ ዙሪያውን ከሠሩና ሰርቪስ ቤቶችን ካደሱ በኋላ፣ ዋናውን ቤት ለመሥራትም ዲዛይንና የግንባታ ፈቃድ አግኝተው ነበር፡፡ ቤቱን ሲገዙ አስፈላጊ ናቸው የተባሉ ሕጋዊ ሰነዶችን ከመንግሥት ተቋማት ያገኙ ቢሆንም፣ ከስድስት ዓመታት ቆይታ በኋላ ‹‹የገዙት ቤት ይዞታነቱ የሌላ ሰው ነው፡፡ ከእርስዎ ቀደም ብሎ በ1985 ዓ.ም. ለሌላ ሰው ተሸጧል፡፡ በመሆኑም አስረክበው እንዲወጡ›› የሚል የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይደርሳቸዋል፡፡ በሁኔታው የተደናገጡት ወ/ሮ ዘውዴ፣ ወደ ፍርድ ቤት ሄደው ቢያመለክቱም እንዲወጡ ይነገራቸዋል፡፡

‹‹በሕጋዊ መንገድ የገዛሁትን ቤቴንማ ዝም ብዬ አላስረክብም›› ያሉት ወ/ሮ ዘውዴ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ብለው ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይሄዳሉ፡፡ እዚያም ይወሰንባቸዋል፡፡ ተስፋ ባለመቁረጥ ወደ ሰበር ሰሚ ችሎትም ሄደዋል፡፡ ውሳኔው ግን ሊቀለበስ አልቻለም፡፡ የመጨረሻ ጉዟቸውን ወደ ሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ቢያደርጉም፣ ‹‹የሕገ መንግሥት ትርጉም የሚያስፈልገው አይደለም›› በሚል የሦስት መስመር ምላሽ ተስፋቸው ተሟጦ አለቀ፡፡ መንግሥትንና የመንግሥትን ተቋማት በማመን ከልጅነት እስከ ዕውቀት ያፈሩት ገንዘባቸው አግባብ ባልሆነ መንገድ እንደተነጠቁ የሚናገሩት ወ/ሮ ዘውዴ፣ እግዚአብሔርና የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፍረደኝ ይላሉ፡፡ ታምሩ ጽጌ አነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- የደረሰብዎት ችግር ምንድነው?

ወ/ሮ ዘውዴ፡- ቤቴን በጠራራ ፀሐይ፣ መንግሥት ባለበት አገር ተነጠቅሁ፡፡

ሪፖርተር፡- ማነው የነጠቀዎት? ለምንና በምን ሁኔታ ተነጠቁ?

ወ/ሮ ዘውዴ፡- በ2001 ዓ.ም. በሕጋዊ መንገድ ወ/ሮ ጽጌ ተሾመ ከሚባሉ ሴት መኖሪያ ቤት ገዛሁ፡፡ ከመግዛቴ በፊት ሕጋዊ መሆኑን አረጋገጥኩ፡፡ ሴትየዋ ባለትዳር ቢሆኑም ባለቤታቸው አብረዋቸው አይኖሩም፡፡ ነገር ግን ሕጋዊ ውክልና ያላቸው መሆኑንም ሰነድ ተመልክቼ አረጋገጥሁና ገዛኋቸው፡፡

ሪፖርተር፡- የት ክፍለ ከተማና ወረዳ ነው?

ወ/ሮ ዘውዴ፡- የካ ክፍለ ከተማ ድንበሯ የእናቶችና ሕፃናት ሐኪም ቤት አካባቢ ነው፡፡ ለገዛኋቸው ሴትዮ ክፍያ ከመፈጸሜ በፊት፣ ወደ ክፍለ ከተማው ሄደን ስናረጋግጥ፣ በቤቱ ላይ ዕዳም ሆነ እገዳ የለበትም፡፡ ካርታ የተሠራውም በወ/ሮ ጽጌ ስም ነው፡፡ መሬት ልማትና አስተዳደርም ስንሄድ ከዕዳና እገዳ ነፃ ነው፡፡ ውልና ማስረጃም ስንሄድ ከዕዳና እገዳ ነፃ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ አሹራ እንድከፍል ደብዳቤ ተሰጥቶኝ ለመሬት ልማትና አስተዳደር 103,000 ብር አሹራ ከፍዬ ካርታው በእኔ ስም ዞረልኝ፡፡

ሪፖርተር፡- በስንት ነው የገዙት?

ወ/ሮ ዘውዴ፡- ቤቱን የገዛሁት 1,700,000 ብር ነው፡፡ ስፋቱ 449 ካሬ ሜትር ነው፡፡ ሕጋዊነቱን አረጋግጨ፣ ይዞታነቱ የእኔ ለመሆኑ ማረጋገጫውን ማለትም ካርታውን በስሜ አዙሬ ስጨርስ፣ የነበረውን የቆርቆሮና የጽድ አጥር አፍርሼ ዙሪያውን በድንጋይ ግንብ አጠርኩ፡፡ የፍሳሽ ማስወገጃ ካስገባሁ በኋላ ግቢውን በድንጋይ አስነጠፍኩ፡፡ ይኸንን ሁሉ ያደረግኩት ዝም ብዬ ሳይሆን ቤቱ የሚገኝበትን ወረዳ ሰባት አስፈቅጄና የግንባታ ፈቃድ ወስጄ ነው፡፡ ዋናውን ቤት ተውኩና ሰርቪሶቹን አደስኳቸው፡፡ ሌላ ገቢ ስለሌለኝ እነሱን አከራይቼ እየኖርኩ እያለሁ ክስ መጣብኝ፡፡

ሪፖርተር፡- የምን ክስ ነው የመጣብዎት?

ወ/ሮ ዘውዴ፡- ‹‹የገዛሺው ቤት ለሌላ ሰው የተሸጠ ቤት ነው፡፡ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክስ ስለተመሠረተብሽ ትፈለጊያለሽ›› ተባልኩኝ፡፡ በደረሰኝ ጥሪ መሠረት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስሄድ፣ ‹‹ቤቱ በ1985 ዓ.ም. ተሸጧል›› ተባልኩኝ፡፡

ሪፖርተር፡- ለማንና በስንት ብር ነው የተሸጠው?

ወ/ሮ ዘውዴ፡- ቤቱ የተሸጠው ወ/ሮ አልማዝ ተሰማ ለሚባሉ ግለሰብ ሲሆን፣ ነዋሪነታቸው ጣሊያን አገር ለሆኑ የኤርትራ ዜጋ በ160,000 ብር ተሸጧል፡፡ ሻጭ ወ/ሮ ጽጌ ተሾመ ቀብድ 88,000 ብር ተቀብለዋል፡፡ 60,000 ብር ይቀራቸዋል ተባልኩኝ፡፡

ሪፖርተር፡- ምን ምላሽ ሰጡ?

ወ/ሮ ዘውዴ፡- እኔ ማጣራት ያለብኝን ሁሉ አጣርቼ ቤቱ ከዕዳና እገዳ ነፃ መሆኑን አረጋግጨ በ1,700,000 ብር ገዝቻለሁ፡፡ የመጨረሻው አጣሪ የመንግሥት ተቋም ውልና ማስረጃም ምንም ዓይነት ችግር እንደሌለበት አረጋግጦልኝ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በስሜ ዞሮ ቤቱ የእኔ ነው፡፡ አሁን የመጣብኝ ነገር ምንም የማላውቀው ዱብ ዕዳ በመሆኑ ቀጠሮ ይስጠኝ ብዬ አስቀጥሬ ተመለስኩኝ፡፡ ቤቱን ገዝተዋል የተባሉት ኤርትራዊቷ ወ/ሮ አልማዝ፣ የሚከራከሩት በወኪል ነው፡፡ በቀጠሮው ቀን ስንቀርብ፣ የፍርድ ቤቱ ዳኛ ወኪሎቹን ‹‹ምንድነው የምትፈልጉት?›› የሚል ጥያቄ አነሱላቸው፡፡ ‹‹ቦታውን የገዛነው በ1985 ዓ.ም. ከማኅበሩ ነው፡፡ ውላችንም በማኅበሩ አማካይነት የተደረገ ውል ነው፡፡ ቦታውን እንፈልጋለን፡፡ ቦታውን የማናገኝ ከሆነ የተሸጠበትን ዋጋ እንፈልጋለን›› አሉ፡፡

ሪፖርተር፡- ቤቱ የተሠራው በማኅበር ነው?

ወ/ሮ ዘውዴ፡- አዎ ቤቱ የተሠራው በማኅበር ነው፡፡ የሰማሁት ግን የወ/ሮ አልማዝ ወኪሎች በፍርድ ቤት ሲናገሩ ነው፡፡ የማኅበሩም ስም ዕድገት በኅብረት ይባላል፡፡ ወኪሎቹ ቤቱን ወይም የተሸጠበትን ዋጋ እንደሚፈልጉ ገልጸው ተከራከሩ፡፡ ፍርድ ቤቱ ካዳመጠ በኋላ ለፍርድ ቀጠረ፡፡ በቀጠሮው ቀን ስንቀርብ ‹‹ቤቱን ወይም የተሸጠበትን ዋጋ አስረክቡ›› ብሎ ፍርድ ቤቱ ፈረደብን፡፡

ሪፖርተር፡- ከእናንተ በኩል የቀረበው መከራከሪያ ሐሳብ ምን ነበር?

ወ/ሮ ዘውዴ፡- ምንም ዓይነት ክርክር አላቀረብንም፡፡ ፍርድ ቤቱም የጠየቀን ነገር የለም፡፡ የእኔ ጠበቃ ካርታ እንዳለን አስረዱ፡፡ ቤቱን የሸጡልኝ ወ/ሮ ጽጌም አብረው ስለተከሰሱ፣ የእሳቸው ጠበቃ ‹‹ይኸ ፍርድ ቤት የዚህን ዓይነት ጉዳይ የማየት ሥልጣን የለውም›› በማለት ተከራከሩ፡፡

ሪፖርተር፡- ፍርድ ቤቱ ምን አለ?

ወ/ሮ ዘውዴ፡- ‹‹እኛ የነገርናችሁ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የወሰነውን እንጂ ውሳኔውን እኛ አልሠራነውም›› አለን፤ ፍርድ ቤቱ፡፡

ሪፖርተር፡- ከፍተኛው ፍርድ ቤት የወሰነውን ውሳኔ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሚናገርበት የሕግ አግባብ መኖሩን ጠይቃችኋል?

ወ/ሮ ዘውዴ፡- እኔ በግሌ አላውቅም፡፡ ጠበቆቻችን ግን ጠይቀዋል፡፡ የሻጭ ወ/ሮ ጽጌ ጠበቃ በመጠየቃቸው ነው ፍርድ ቤቱ እንደዚህ ብሎ የተናገረው፡፡ አሠራሩ ትክክል አለመሆኑን በመገንዘባችን ወደ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ ጠየቅን፡፡ ይግባኝ ያስገባንበት የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኛ ‹‹ይኸ ነገር አያዋጣችሁም፡፡ ቢቀርባችሁ ይሻላችኋል›› አሉን፡፡ ለምን? ብለን ጠየቅን፡፡ ‹‹የተሸጠ ቦታ ስለሆነ እያዋጣችሁም›› አሉን፡፡

ሪፖርተር፡- ዳኛው ‹‹አያዋጣችሁም›› ያሏችሁ የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔን መርምረው ነው?

ወ/ሮ ዘውዴ፡- አይደለም፡፡ ይግባኙን ሳይመረምሩ ነው፡፡ እኛ ሕጋዊ ካርታ እንዳለን ገለጽንና ‹‹እንዴት ይኸ ሊሆን ይችላል›› በማለት ስንጠይቅ፣ ‹‹እኔ የዳኝነት 20,000 ብር እንዳትከስሩ ብዬ ነው›› አሉና የይግባኙን አቤቱታ ተቀበሉን፡፡ አቤቱታችን ገና በቀጠሮ ላይ እያለ፣ ባለመብት ነን ያሉት የሥር ፍርድ ቤት የወሰነላቸው የወ/ሮ አልማዝ ተወካዮች፣ አፈጻጸም አምጥተው በቤቴ ላይ ለጠፉ፡፡ ይግባኝ ጠይቀን ገና በቀጠሮ ላይ በመሆኑ፣ እግድ ለማምጣት ወደ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ስንሄድ፣ ያስገባነው የይግባኝ አቤቱታ ጠፍቷል፡፡ ወዲያውኑ ጉዳዩን ለሚያዩት ዳኛ ስናመለክት ‹‹እኔ አያገባኝም፡፡ መዝገብ ቤት ከሌለ አቤቱታ ስታስገቡ ባላችሁ ቀሪ አስገቡ›› አሉን፡፡ በድጋሚ ጽፈንና ቃለ መሀላ አድርገን አፈጻጸሙን አሳገድን፡፡ ክርክራችንንም ቀጠልን፡፡

ሪፖርተር፡- ቤቱ በ1985 ዓ.ም. ወ/ሮ አልማዝ ለሚባሉ ግለሰብ መሸጡን እያወቁ ወ/ሮ ጽጌ እንዴት ለእርስዎ በድጋሚ ሊሸጡልዎት ቻሉ?

ወ/ሮ ዘውዴ፡- ቤቱን እንደገዙትና 88,000 ብር ቀብድ እንደከፈሉ ለፍርድ ቤት የሚያስረዱት ተወካዮች፣ ክስ የመሠረቱት በእኔና በወ/ሮ ጽጌ ላይ ነው፡፡ ወ/ሮ ጽጌ በፍርድ ቤት ያቀረቡት ክርክር፤ ቤቱን መሸጣቸውን አምነው፣ ነገር ግን ገዢ ወ/ሮ አልማዝ ቀብዱን ከከፈሉ በኋላ፣ ለሁለት ዓመታት በመጥፋታቸው ክስ መሥርተው በፍርድ ቤት ውሳኔ ማግኘታቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡ ውሳኔ ያገኙትም በመጀመሪያና በከፍተኛ ፍርድ ቤት መሆኑንም ለፍርድ ቤቱ አረጋግጠዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ወ/ሮ ጽጌ የሥር ፍርድ ቤቶች የወሰኑላቸው ለመሆኑ የሚያስረዳውን የውሳኔ ሰነድ እርስዎ አይተውታል?

ወ/ሮ ዘውዴ፡- ለእኔ አላሳዩኝም፡፡ ለፍርድ ቤቱ ግን ‹‹አቅርቤያለሁ›› ብለውኛል፡፡ ባለይዞታ ነን ባዮቹ የወ/ሮ አልማዝ ተወካዮች፣ ሰበር ደርሰው ማስወሰናቸውንም የሰማሁት ቆይቼ ነው፡፡ እኔ በቀጠሮዬ ቀን ከፍተኛው ፍርድ ቤት ስቀርብ፣ መጀመሪያውኑ ገና አቤቱታውን ሳያዩ ‹‹አርፋችሁ ተቀመጡ›› ያሉኝ ዳኛ ‹‹አስረክቡ›› ብለው ወሰኑብኝ፡፡ ተስፋ ባለመቁረጥ ወደ ሰበር ሄድን፡፡ ቤቱ የተሸጠ መሆኑንና የተሸጠ ቤት እንዴት ልንገዛ እንደቻልን ሦስት ዳኞች ጠየቁን፡፡ መንግሥት ባስቀመጣቸው ተቋማት ማለትም በወረዳ፣ በመሬት ልማትና አስተዳደር እንዲሁም በውልና ማስረጃ አረጋግጠን፣ ከዕዳና እገዳ ነፃ መሆኑን ስናውቅ እንደገዛነው ሙሉና ሕጋዊ ሰነዱን አሳይተን ምላሽ ሰጠን፡፡ ሦስቱ ዳኞች ምላሻችንን አዳምጠው ‹‹ያስቀርባል›› በማለት አምስት ዳኞች እንዲያዩት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጡን፡፡ በቀጠሮው ቀን ስንቀርብ ቤቱን ከሸጡልኝ ከወ/ሮ ጽጌ፣ በ1985 ዓ.ም. ቤቱን ገዝተዋል የተባሉት ወ/ሮ አልማዝ፣ ቀሪውን 60,000 ብር እንዲከፍሉ፣ እኔ ደግሞ ለወ/ሮ አልማዝ የቤቱን ካርታ አስረክቤ እንድለቅ ውሳኔ ተሰጠብን፡፡ እኔ ከቤቴም ሆነ ከገንዘቤ ሳልሆን አስረክቢ ተባልኩኝ፡፡

ሪፖርተር፡- ቤቱን አስረከቡ?

ወ/ሮ ዘውዴ፡- እኔ በሌለሁበት ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. በግዳጅና በጉልበተኛ ዕቃዬ እየተወረወረ እንድለቅ ተደረገ፡፡ እኔ ሕገወጥ ሰው አይደለሁም፡፡ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንደሚያደርገው የመንግሥት ተቋማት የሚሰጡትን ማረጋገጫ ይዤ፣ ልጆቼን ለማሳደግ ያለኝን ጥሪት በሙሉ አሟጥጨ የገዛሁትን ቤት፣ እንዴት እነጠቃለሁ? ለስድስት ዓመታት በስሜ ግብር ከፍያለሁ፡፡ ቤቱን አልምቸዋለሁ፡፡ በዋናው ቤት ላይ ፎቅ ለመገንባት ዲዛይን አሠርቼና የግንባታ ፈቃድ ወስጄ ነበር፡፡ ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አውጥቼበታለሁ፡፡ ይኸንን ደግሞ የወረዳው ሹማምንት ያውቃሉ፡፡ ምክንያቱም እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ያደረግኩት እነሱን እያማከርኩና ፈቃድ እየወሰድኩ ነው፡፡ ግንባታ ለማካሄድ ድንጋይና አሸዋም አስገብቼ ነበር፡፡

ሪፖርተር፡- አሁን በምን ሁኔታ ላይ ነው ያሉት?

ወ/ሮ ዘውዴ፡- እኔ ቤቱን ከገዛሁት በኋላ ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ውጪ አውጥቼበታለሁ፡፡ የሸጡልኝ ሴትዮ ገንዘቤን እንዲመልሱልኝና ባለይዞታ ነን ባዮቹም በቤቱ ላይ ያወጣሁትን ወጪ እንዲከፍሉኝ ክስ መሥርቻለሁ፡፡ ክሱን የመሠረትኩት ሰበር የወሰነው ውሳኔ ወደ አፈጻጸም ሳይሄድ በመሆኑ፣ አፈጻጸም ይዘው መጥተው ንብረቴን ወደ ውጭ እየወረወሩ በጉልበት ሲያስወጡኝ፣ የፍርድ ቤት ክርክር ያለበት ንብረት መሆኑን በመግለጽ፣ ለፍርድ ቤት አመልክቼ ክርክሩ እስከሚጠናቀቅ ድረስ እንዳይሸጥ፣ እንዳይለወጥና ለሦስተኛ ወገን እንዳይተላለፍ ታግዳ በቀጠሮ ላይ ነን፡፡ ዕድሜዬ ገፍቷል፡፡ 70 ዓመቴ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ተሯሩጨ የማድር ሴት አይደለሁም፡፡ በመጦሪያዬ አሁን ያለሁት በዘመድ ላይ ነው፡፡ ወዴትስ ልሂድ? እኔ ዜጋ ነኝ፡፡ ከ20 ዓመት በኋላ እውነተኛ ሴት ትሁን አትሁን በማላውቃትና ኑሮዋን ጣሊያን አገር አድርጋለች በተባለች የኤርትራ ዜጋ አማካይነት፣ በሕገወጥ መንገድ በመንገድ ላይ ተጣልኩ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፍረደኝ፡፡ ሕጋዊ ካርታ በእጄ ላይ ይዤ እንዴት መንግሥት ባለበት አገር ቤቴን እነጠቃለሁ? የመጨረሻው የመንግሥት አካል የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ እንዲያይልኝ ባመለከትም የተሰጠኝ መልስ አሳዛኝ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ምን አልዎት?

ወ/ሮ ዘውዴ፡- ጉባኤው ጥቅምት 12 ቀን 2007 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ፣ አቤቱታውን ተመልክቶ የቀረበው ጥያቄ የሕገ መንግሥት ትርጉም የሚያስፈልገው እንዳልሆነ ገልፆ ውሳኔ ማሳለፉን አሳወቀኝ፡፡ አሁን ያለሁት ጐዳና ላይ ነኝ፡፡ ሕግና መመሪያ ተከትዬ ትልቅ ችግር ላይ ወደቅሁ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የቀበሌ ቤት በሌለበት፣ ኮንዶሚኒየም ለመግዛት አቅሜ በማይፈቅድበት ሁኔታ ላይ ሆኜ፣ ይኸ ተፈጸመብኝ፡፡ ልጆቼን ይዤ ጐዳና ላይ ተጣልኩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያምን ጨምሮ ይመለከታቸዋል ላልኩት ሰባት ሚኒስቴሮች በአፋጣኝ መልዕክት እየከፈልኩ በፖስታ ቤት ደብዳቤ ብልክም፣ ምንም ምላሽ አላገኘሁም፡፡ ሰባት የፖስታ ቤት ደረሰኝ በእጄ ላይ ይገኛል፡፡ እኔ አቅመ ደካማ ሴት ነኝ፡፡ ኢትዮጵያዊት ዜጋም ነኝ፡፡ ሁሉም ማስረጃዎቼ ትክክለኛና ከመንግሥት ተቋማት የተሰጡኝ መሆናቸው እየታወቀ፣ እንዴት ቤቴን አስረክቢ እባላለሁ? የሚያሳዝነኝ ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ሰበር ሰሚ ያሉት ፍርድ ቤቶች በአንድ ዓይነት ንብረቴን ልቀቂ ማለታቸው ነው፡፡ ይኸ ወገንተኝነት ነው፡፡ እንዴት አንዱ ዳኛ ቆም ብሎ ማስረጃዎቹን ተመልክቶ ለእኔ አይፈርድም፡፡ እኔ ወገን የለኝም፡፡ ሥልጣን ላይ የተቀመጠ ዘመድ ቢኖረኝ ኖሮ እንደዚህ አልሆንም ነበር፡፡ ምናልባት ቤቱን በ1985 ዓ.ም. ገዝተዋል የተባሉትና በጣሊያን ይኖራሉ የተባሉት ወ/ሮ አልማዝ ዘመድ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ እሳቸው ባልተገኙበትና አንድ ቀን እንኳን የፍርድ ቤትን ደጃፍ ሳይረግጡ፣ የተወሰነላቸው ምናልባት ባለሥልጣን ዘመድ ቢኖራቸው ይሆናል፡፡ በተለይ ሰበር ሰሚ ችሎት ጐድቶኛል (እያለቀሱ)፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ይፍረደኝ፡፡ በተደጋጋሚ በተወሰነብኝ ውሳኔ ላይ የአንድ ዳኛ ስም በማየቴ ምናልባት እኝህ ዳኛ የወ/ሮ አልማዝ ዘመድ ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ግምት አድሮብኛል፡፡ አለበለዚያ ከ20 ዓመት ቆይታ በኋላ፣ ግብር ባልገበሩበትና ይርጋ ባገደው ንብረት ላይ ወ/ሮ አልማዝ ባለንብረት ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ወ/ሮ ጽጌና ወ/ሮ አልማዝ ተካሰው የሥር ፍርድ ቤቶች ለወ/ሮ ጽጌ ወስነዋል፡፡ ወ/ሮ አልማዝ ደግሞ በይግባኝ ሰበር ሄደው አስወስነዋል፡፡ እኔ ጥያቄ ሲመጣብኝ ክስ ስመሠርት በሁለቱ ሰዎች ላይ የነበረው የፍርድ ቤቶቹ ውሳኔ ከእኔ ክስ ጋር እንዲያያዝ በማድረግ፣ ከሥር ጀምሮ እስከ ሰበር በእኔ ላይ የተወሰነው ውሳኔ በእነሱ ላይ የነበረው ውሳኔ እየተጠቀሰ አንድ ዓይነት ነው፡፡ ይኸ የተደረገው ክርክሩን ሕጋዊ ለማስመሰል ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ለእርስዎ ቤቱን የሸጡልዎት ወ/ሮ ጽጌ፣ ቀደም ብለው ቤቱን ለሌላ ሰው መሸጣቸውንና የፍርድ ቤት ክርክርም እንደነበረበት ነግረዎት ነበር?

ወ/ሮ ዘውዴ፡- በፍፁም፡፡ ባለቤታቸው ውክልና እንደሰጧቸው፣ ካርታው በእሳቸው የተሠራ መሆኑን ሰነድ እያሳዩ አረጋግጠውልኛል፡፡ ስንዋዋልም ማንኛውንም በመንግሥት በኩል የሚመጣን ተጠያቂነት ኃላፊነት እንደሚወስዱ ሁሉ አረጋግጠውልኛል፡፡ እኔን ሜዳ ላይ እንድወድቅ ያደረገኝ፣ ያታለለኝ ውልና ማስረጃ፣ ሁሉንም ነገር መርምሮ ከዕዳና እገዳ ነፃ መሆኑን ገልፆ የሰነድ ማረጋገጫ የሰጠኝ ጊዜ ነው፡፡ ለሴትየዋም ካርታ እንዲሰጣቸው ሁሉንም ነገር አረጋግጦ የሰጣቸው ውልና ማስረጃ ነው፡፡ ስገብርበት የኖርኩትን፤ ከልጅነት እስከ ዕውቀት የያዝኩትን ጥሪት ሙጥጥ አድርጌ የወጣሁበትን ቤት ተነጠቅሁ፡፡

ባለሥልጣን ዘመድና ወገን ቢኖረኝ ምላሽ እንዲሰጠኝ እንደዚህ አልሆንም፡፡ እናት ያለው ባለሥልጣን እንደ እናቱና እንደ እህቱ አይቶ፣ ሁኔታዬንና ሕጋዊነቴን ገልጨ ብጽፍ ማንም ምላሽ የሰጠኝ የለም፡፡ ኢትዮጵያውያን በአገር ውስጥ፣ ከአገር ውጭም ያላችሁ ፍረዱኝ፡፡ ፍረዱኝ፡፡ ባለቤት ነኝ ካሉ ግብር መገበር ነበረባቸው፡፡ መሸጡን ሲሰሙም ማሳገድ ይችሉ ነበር፡፡ የባለቤትነት መታወቂያ ሳይኖራቸው በአሁኑ ጊዜ ቢሸጥ ከአምስት ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ቤቴን፣ እሳቸው በውጭ አገር ተቀምጠው (ወ/ሮ አልማዝ) ወሰዱብኝ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍረደኝ፡፡ መብቴ ተገፈፈ፡፡ እኔ አርጅቻለሁ፡፡ ሠርቼ እንኳን መኖር አልችልም፡፡ ቀን ቀን ቤተ ክርስቲያን ውዬ እስካለሁ ድረስ ገብቼ እንዳላርፍበት ጉድ ሠሩኝ፡፡ ምን ልሁን፡፡ እኔ ተዘረፍኩ፣ ተነጠቅሁ እንጂ በሕግ አግባብ ተወሰነብኝ አልልም፡፡ እኔ እዚሁ ሆኜ ሽቅብና ቁልቁል ተሯሩጨ ፍትሕ ሳጣ፣ ወ/ሮ አልማዝ በውጭ ቁጭ ብላ ተወሰነላት (እውነት አልማዝ የምትባል ሴት ኖራ ከሆነ)፡፡ ፍትሕ አጥቻለሁ፡፡ ጥፋቴ ምንድነው? የውልና ማስረጃ ሥራ ምንድነው? ዜጐች እንዳይታለሉ የተጭበረበሩ ሰነዶችን በመለየት ዜጐችን ከአደጋ መጠበቅ አይደለም? እኔም ይኸንን አምኜ ሕጋዊነቴን ለመጠበቅ በመሔዴ ፍትሕ ማጣት አለብኝ?፣ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ይፍረደኝ፡፡ መሬት አስተዳደርስ ቢሆን ሥራው ምንድነው? ሕጋዊ ካርታ እንዳለኝ አምኖና አረጋግጦ፣ ያቀረብኩትን ዲዛይን ተቀብሎ የግንባታ ፈቃድ ከሰጠኝ በኋላ፣ እንዴት ለሌላ ሰው ሊሰጥ ቻለ? የግንባታ ግብዓቶች አስገብቼ ከጨረስኩ በኋላ አስቆፍሬ ግንባታ ለመጀመር ቀናት ሲቀሩኝ ተፈረደብኝ፡፡ ይኸ ምን ማለት ነው? ፍረዱኝ፡፡ ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ግፍ ነው የተፈጸመብኝ፡፡

ሪፖርተር፡- ቤቱን የሸጡልዎት ወ/ሮ ጽጌ ገንዘብዎን እንዲመልሱልዎት አልጠየቋቸውም?

ወ/ሮ ዘውዴ፡- ‹‹እኔ የሸጥኩልሽ በሕጋዊ መንገድና ሕጋዊ ቤት ነው፡፡ ሕጋዊ ለመሆኑም ውልና ማስረጃ እንዲሁም መሬት ልማት አስተዳደር አረጋግጠውልሻል፡፡ ከዚህ ውጭ የእኔ ጥፋት ምንድነው?›› ብለው ምላሽ ሰጡኝ፡፡ ገንዘቡንም ታመው እንደታከሙበት በመግለጽ እንደሌላቸው ነግረውኛል፡፡ እኔ ግን ክስ መሥርቻለሁ፡፡ ቢያንስ ቢያንስ አጥር ለማጠር፣ ሰርቪሶችን ለማደስና ግቢውን ለማስነጠፍ ያወጣሁትን ወጪ እንኳን ለማግኘት ብዬ፡፡ ምን ላድርግ? ግራ ግብት አለኝ፡፡ ወዴትስ ልሂድ? ማንስ ይቀበለኛል? እግዚአብሔር የኢትዮጵያ አምላክ ይፍረደኝ፡፡ ውልና ማስረጃ ያረጋገጠው ካርታ ሊሰረዝ አይገባም፡፡ ቤት ስታከራዩ፣ መኪና ስትገዙና ቤት ስትገዙ ውልና ማስረጃ ሄዳችሁ ተዋዋሉ ተብሎ በመንግሥት ተነግሯል፡፡ እኔም ይኸንን ፈጽሜ ኦርጂናል የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ተሰጥቶኛል፡፡ ይኸ ሊሰረዝ አይገባም፡፡ ለእሷም (ለወ/ሮ አልማዝ) እስካሁን የተቀመጠ ገንዘቧን ወ/ሮ ጽጌ ይመልሱላት፡፡ መንግሥት ይርዳኝ፤ ያስመልስልኝ፡፡ በሥር ያሉ ኃላፊዎች ወይም አስፈጻሚዎች እየሠሩ ያሉትን ግፍ መንግሥት ይመልከትልኝ፡፡ በጠራራ ፀሐይ ቤቴ ተወስዶብኛልና መንግሥትም፣ ሕዝብም የሁሉ የበላይ የሆነ እግዚአብሔር ፍረዱኝ፡፡ የኢሕአዴግ መንግሥት እኔን አልበደለኝም፡፡ እሱ ያስቀመጣቸው አንዳንድ ቦታ ላይ ያሉ የሕዝብን ኑሮሮ የሚያንቁ አሉ፡፡ እነሱን ይመልከትልኝ፡፡ መንግሥት ቤት ለሌለው ኮንዶሚኒየምና እንደየአቅሙ እየሰጠ ባለበት፣ እንዲሁም በተለይ ሴቶችን በማደራጀት እንዲበረታቱ እያደረገ ባለበት ሁኔታ፣ እኔንና እኔን መሰሎችን ከመኖሪያቸው እያስወጡ በጐዳና ላይ የሚጥሉ አሉ፡፡ በእነሱ ላይ መንግሥት ውሳኔ ሊሰጥ ይገባል፡፡ መንግሥት ቢያልፋቸው የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ እግዚአብሔር ፍርድ ይሰጣል (እያለቀሱ)፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

የጂቡቲ መንግሥት ኢትዮጵያ ላይ ትኩረት ያደረጉ የ9.8 ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክቶቹን ይፋ አደረገ

$
0
0

d8b51c865d4592b0c67a08a55db302e0_L

የጂቡቲ መንግሥት እ.ኤ.አ. ከ2015 ጀምሮ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ተግባራዊ የሚሆኑና የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መሠረት ያደረጉ የ9.8 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንቶቹን ይፋ አደረገ፡፡

ፕሮጀክቶቹ በአብዛኛው ወደብና ወደብ ነክ አገልግሎቶችን ያካተቱ ናቸው፡፡ ፕሮጀክቶቹን ይፋ ያደረጉት የጂቡቲ ፖርትና ፍሪ ዞን ባለሥልጣን ሊቀመንበር አቡበከር ኦመር ሃዲ ናቸው፡፡

ሊቀመንበሩ ከኢትዮጵያ ወደ ጂቡቲ የተጓዘውን የጋዜጠኞች ቡድን ባገኙበት ወቅት እንደተናገሩት፣ የጂቡቲ መንግሥት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ ከመጣውና በዚያው ዕድገት እየቀጠለ ካለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ተጠቃሚ ነው፡፡ ይህንኑ የጂቡቲ ጥቅም ለማሳደግ ከኢትዮጵያ ፍላጐት ቀድሞ መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት ኃላፊው፣ አብዛኛዎቹ ፕሮጀክቶች በዚሁ አግባብ መታቀዳቸውንም ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ዶራሌ ተርሚናል ወደ 60 በመቶ የሚሆኑትን በኮንቴይነር ብቻ ታሽገው የሚመጡ የኢትዮጵያ ዕቃዎችን ያስተናግዳል፡፡ ይህንን ተርሚናል ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት እንዲሁም ከሌሎች የአካባቢው ተጠቃሚዎች ፍላጐት ጋር ለማጣጠም በሚቀጥለው የአውሮፓውያን አዲስ ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ማስፋፊያ ለመጀመር የጂቡቲ መንግሥት አቅዷል፡፡

የመጀመሪያው ዙር የዶራሌ ተርሚናል በአሁኑ ወቅት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በዓመት 1.6 ሚሊዮን ባለ 20 ጫማ ኮንቴይነሮችን የማስተናገድ አቅም አለው፡፡ የዚህ ተርሚናል ሁለት ሦስተኛ ባለአክሲዮን የጂቡቲ መንግሥት ሲሆን፣ የተቀረው ድርሻ በ65 አገሮች ወደቦችን በማስተዳደር የሚታወቀው የዲፒ ወርልድ ነው፡፡

የማስፋፊያ ፕሮጀክቱንም ሆነ አሁን በሥራ ላይ የሚገኘውን ዶራሌ ወደብ ከፕሮጀክት ጥንሰሳው ጀምሮ ዲፒ ወርልድ ተሳታፊ ሆኗል፡፡

የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ አሁን ያለውን አቅም በ30 በመቶ በማሳደግ አጠቃላይ የተርሚናሉን አቅም በዓመት ሦስት ሚሊዮን ባለ 20 ጫማ ኮንቴይነሮችን እንዲያስተናግድ ያደርገዋል፡፡

ሌላኛው ፕሮጀክት የታጁራ ወደብ ሲሆን፣ ግንባታውም በቻይና ኩባንያ እየተከናወነ እንደሚገኝ ለመረዳት ተችሏል፡፡ የታጁራ ወደብ በጂቡቲ ሰሜናዊ ክፍል ግንባታው የተጀመረ መሆኑንና ዓላማውም የኢትዮጵያ መንግሥት ለማልማት የፈለገውን የፖታሽ ማዕድን በብቸኝነት ለማጓጓዝ መሆኑን የጂቡቲ ፖርትና ፍሪ ዞን ባለሥልጣን ሊቀመንበር ገልጸዋል፡፡

የታጁራ ወደብ በአጠቃላይ 160 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ሲሆን፣ በዓመት አራት ሚሊዮን ቶን ፖታሽ የማጓጓዝ አቅም እንዳለውና የፖታሽ ሀብቱን የሚያጓጉዙ ግዙፍ መርከቦችንም ማስተናገድ እንደሚችል ተገልጿል፡፡

የዚህን ወደብ ግንባታ የሚያከናውነው የቻይናው ኩባንያ ባኦ ዬ ሁቤ ሲሆን፣ በተቆጣጣሪነት ደግሞ የጣሊያኑ ቴክኒካል ኤስፒኤ ተቀጥሯል፡፡ የተቆጣጣሪ ኩባንያው የጂቡቲ መሐንዲስ ቶማስ ሪኮቦኒ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ወደቡ ለኢትዮጵያ የፖታሽ ሀብት የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል እንደመሆኑ መጠን የፖታሽ ማዕድኑን ወደ መርከብ የሚጭኑ ኮንቬዬር ቤልቶች ይኖሩታል፡፡ ከወደቡ ጋር የተገናኘ የባቡር ሐዲድ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚዘረጋም ገልጸዋል፡፡ ይህ የታጁራ ፕሮጀክት ከመቀሌ – አዋሽ – ወልዲያ – አሳይታ – ታጁራ የባቡር ፕሮጀክት ጋር የሚገናኝ ነው፡፡

ከወደብ ግንባታዎቹ ጋር የሚገናኙ የባቡር ፕሮጀክቶችን በሦስት ዓመት ውስጥ ለማጠናቀቅ ዕቅድ ተይዟል፡፡ እነዚህም ከጂቡቲ ከተማ ጋላሊህ ወደምትባለው የጂቡቲ የኢትዮጵያ ድንበር ድረስ የሚዘረጋው የ98 ኪሎ ሜትር እና ከታጁራ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ጋላፊ የሚዘረጋው 124 ኪሎ ሜትር ናቸው፡፡ እንደ ቅደም ተከተላቸውም 550 ሚሊዮን ዶላርና 600 ሚሊዮን ዶላር በጀት ተመድቦላቸዋል፡፡

ሌሎቹ በዕቅድ የተካተቱ ወደቦች እንደዚሁ የኢትዮጵያ የወጪና የገቢ ንግድ ዕቃዎችን ፍላጐት መሠረት አድርገው እንደሚገነቡ አቡበከር ኦመር ሃዲ አስረድተዋል፡፡

የድፍድፍ ነዳጅ ተርሚናል በ200 ሚሊዮን ዶላር ለመገንባትና የፈሳሽ ዘይቶች ማጠራቀሚያ ተርሚናል ለመገንባት በሦስት ዓመት ዕቅድ ውስጥ ተካቷል፡፡

የነዳጅ ማጠራቀሚያ ተርሚናሉ ሦስት ቢሊዮን ዶላር በጀት ተመድቦለታል፡፡ በአሁኑ ወቅት የነዳጅ ማጠራቀሚያ ዲፖውን 54 በመቶ የምትጠቀመው ኢትዮጵያ ስትሆን፣ የተቀረውን ደግሞ የጂቡቲ መንግሥትና በጂቡቲ የሚገኙ የአሜሪካ፣ የፈረንሳይና ሌሎች ወታደራዊ ካምፖች ይጠቀሙበታል፡፡

በአሁኑ ወቅት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘውን የአገሪቱ የመጀመሪያ የሆነው የጂቡቲ ወደብን ወደ ንግድ ማዕከልነት የመቀየር ዕቅድ በአገሪቱ መንግሥት ተይዟል፡፡ ይህንን ወደብ የሚተካ ጂቡቲ መልቲ ፐርፐዝ ፖርት በ525 ሚሊዮን ዶላር ለመገንባት የቦታ ዝግጅት መጠናቀቁ ታውቋል፡፡

ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ወደ ውጭ የሚላኩ የቀንድና እንደ ግመል ያሉ የጋማ ከብቶችን በብቸኝነት ለማጓጓዝ የሚያገለግል ወደብም በ5.5 ሚሊዮን ዶላር ለመገንባት ታቅዷል፡፡

ራስ ሲያን የሚል መጠሪያ የሚኖረው አየር መንገድ እንዲሁም ቢሲድሌ ዓለም አቀፍ የመንገደኞችና የዕቃ ማጓጓዣ አየር መንገድ ለመመሥረት በዕቅድ ደረጃ 730 ሚሊዮን ዶላር ተይዞላቸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የጂቡቲ መርከብ ድርጅትን ለማቋቋም እየተንቀሳቀሱ መሆኑንና ከጂቡቲ ውጪ የኢትዮጵያንና የአካባቢውን ትራንስፖርት ፍላጐት መሠረት ያደረጉ ወደቦችን በሶማሊያና በደቡብ ሱዳን ለማቋቋም እየሠሩ መሆናቸውን አቡበከር ኦመር ሃዲ ገልጸዋል፡፡ ወደቦቹን ለማቋቋም ቻይና መርቻንትስ ከተባለ የቻይና ኩባንያ ጋር በሽርክና እየሠሩ መሆኑንና ለታቀዱት ፕሮጀክቶች 58 በመቶ የሚሆነው ገንዘብ መገኘቱንም ገልጸዋል፡፡

በዮሐንስ አንበርብር (ጂቡቲ) Source:: Ethiopian Reporter

የዓለም ባንክና አይኤምኤፍ መንግሥት ከምዕራብ የፋይናንስ ተቋማት እንዲበደር አሳሰቡ

$
0
0

World-Bankየዓለም ባንክና የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ለኢትዮጵያ መንግሥት በጋራ በጻፉት ደብዳቤ፣ መንግሥት ለካፒታል ፕሮጀክቶች ከአንድ የገንዘብ ምንጭ ብቻ መበደር እንደሌለበትና ይልቁኑም ለምዕራብ የገንዘብ ተቋማት በሩን ክፍት ሊያደርግ እንደሚገባ ምክረ ሐሳብ ለገሱ፡፡

ሁለቱ ግዙፍ የገንዘብ ተቋማት በኅዳር ወር መጨረሻ ከዋሽንግተን ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በጋራ በጻፉት ደብዳቤ፣ በርካታ የአውሮፓ ባንኮች የኢትዮጵያ መንግሥት ለሚያካሂዳቸው ፕሮጀክቶች ብድር ለመስጠት ፍላጎት እያሳዩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ነገር ግን መንግሥት በቂ ድርድር በማድረግ የሚቀርብለትን ፋይናንስ መጠቀም ሲገባው፣ ፈጣን ምላሽ አለመስጠቱንና ከአንድ ምንጭ ብቻ መጠቀሙን (የቻይና መንግሥት) ደብዳቤው ጠቁሞ፣ አንድ የገንዘብ ምንጭ ላይ ብቻ ትኩረት ማድረጉ ጉዳት እንዳለው ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡

በአንፃሩ የጀርመን፣ የእስራኤልና የእንግሊዝ ባንኮች ለኢትዮጵያ ፋይናንስ ለማቅረብ ዝግጁ ቢሆኑም የመንግሥትን ትኩረት አለማግኘታቸው ተጠቁሟል፡፡

የሁለቱ የፋይናንስ ተቋማት ደብዳቤ መንግሥት በቅርቡ ቦንድ ለዓለም ገበያ ማቅረቡን መልካም ጅማሬ መሆኑን ጠቅሶ፣ ከዚህ በበለጠ ምዕራባዊ ባንኮችን ሊጠቀም እንደሚገባና አንድን የገንዘብ ምንጭ ብቻ መጠቀም ጉዳት ሊኖረው እንደሚችል ይገልጻል፡፡

ክሬዲት ስዊስ፣ በርክሌ፣ ጄፒ ሞርጋንና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የመሳሰሉ ግዙፍ የፋይናንስ ተቋማት ለኢትዮጵያ መንግሥት ፕሮጀክቶች ፋይናንስ ለማቅረብ ፍላጎት አሳይተዋል፡፡ ሁለቱ የገንዘብ ተቋማት በኢትዮጵያ የፋይናንስ ግኝቶች ላይ ግምገማ ማካሄዳቸውን ገልጸው፣ የንግድና የካፒታል ፕሮጀክቶች ብድሮች ሙሉ ለሙሉ ማለት በሚያስችል ሁኔታ በአንድ የገንዘብ ምንጭ ላይ ብቻ ያተኮሩ መሆናቸውን በግምገማቸው መረዳታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ተቋማቱ መንግሥት የዕዳ አስተዳደሩን መቀየጥ እንደሚኖርበት በጻፉት ደብዳቤ ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡ መንግሥት ለካፒታል ፕሮጀክት አብዛኛውን ብድር የሚያገኘው ከቻይና መንግሥት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገሪቱ እየተካሄደ ያለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከታዋቂ ዓለም አቀፍ ተቋማት ዕውቅና እየተቸረው በመሆኑ፣ የምዕራብ የፋይናንስ ተቋማት ብድር ለማቅረብ ፍላጎት እያሳዩ ነው፡፡ ነገር ግን ከቻይና ሲነፃፀር፣ የምዕራብ የፋይናንስ ተቋማት የወለድ ምጣኔ ከፍተኛ ስለሆነ መንግሥት ብዙም ትኩረት እንዳላደረገ ምንጮች ይናገራሉ፡፡

Source:: Ethiopian Reporter


አሳዛኙ ብሔራዊ ውርደታችን

$
0
0

ኢትዮጵያ መንግስት አላት ወይ? የአሜሪካ አምባሳደር ለኢትዮጵያ መንግስት በቀይ ባህር ለሞቱት ኢትዮጵያውያን የሃዘን መግለጫ ላኩ።ኢህአዲግ/ወያኔ እስካሁን አንዳች አልተነፈሰም።Statement by Patricia Haslach, U.S. Ambassador to Ethiopia

Patricia Haslach, U.S. Ambassador to Ethiopia

Patricia Haslach, U.S. Ambassador to Ethiopia

በያዝነው ሳምንት መጀመርያ ላይ ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች በየመን የባህር ዳርቻ፣ በቀይ ባህር ውስጥ ከሰባ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መስመጣቸው መሰማቱ ይታወቃል።ጉዳዩ በሀገር ቤት እና በመላው ዓለም በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ሃዘን አስከትሏል።

ከእዚህ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያውያንን ልብ ያደማው ጉዳይ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን ቢቢሲን ጨምሮ በርካታ የዜና አውታሮች የተቀባበሉትን ጉዳይ ላይ አንዳች የሃዘን መግለጫ አለማሰማቱ ነው።በትናንሽ አደጋ ለሞቱ ለሌላ ሀገር ዜጎች የሃዘን መግለጫ በማውጣት እና በመላክ የሚታወቀው ኢህአዲግ/ወያኔ ለኢትዮጵያውያን ሞት አንዳች አልመተንፈሱ ሌላው የብሔራዊ ውርደታችን መገለጫ ነው።በሳውዲ ጉዳይ መንግስት እንደሌለን አውቀን ነበር።ዘንድሮም በቀይ ባህሩ አደጋ አረጋገጥን።በፌስቡክ ገፃቸው የእየእለቱን ውሎ የሚለጥፉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ሰሞኑን ከ 300 ሚልዮን ብር በላይ ወጣበት ስለተባለው በአሶሳ ስለነበረው ብሔር ብሄርሰቦች በዓል ማውሳታቸው ኢትዮጵያ መንግስት አላት ወይ? ብለው ብዙዎች እንዲጠይቁ ማስገደዱ አልቀረም።

ከእዚህ በታች በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ከሰባ በላይ ለሚሆኑት በቀይ ባህር ሕይወታቸው ላለፈው ኢትዮጵያውያን የሃዘን መግለጫ አወጣ።የኢትዮጵያ መንግስት ስለጉዳዩ እስካሁን ድረስ ምንም አላለም።

”ትናንት በየመን የባህር ዳርቻ ቀይ ባህር ውስጥ በሰጠመችው ጀልባ ሕይወታቸው ባለፈው ኢትዮጵያውያን የተሰማኝን ትልቅ ሃዘን ለኢትዮጵያ መንግስት እና ለሟቾች ቤተሰብ እገልፃለሁ።ልባችን ከሟቾች ቤተሰቦች እና ወዳጆች ጋር ሁሉ ነው” በኢትዮያ የአሜሪካ አምባሳደር ወ/ሮ ፓትሪሽያ ሃስላች

Source – US EMBASSY ADDIS ABABA

http://ethiopia.usembassy.gov/latest_embassy_news.html

”I would like to offer my condolences to the government of Ethiopia and the families of the many victims, including Ethiopian citizens, who drowned in the tragic sinking of a boat off the coast of Yemen in the Red Sea yesterday. Our thoughts are with the families and friends of those who died.” Patricia Haslach, U.S. Ambassador to Ethiopia

ከእዚህ በታች ያለው ቢቢሲ አደጋውን አስመልክቶ የዘገበው ነው።

Yemen migrant boat carrying Ethiopians sinks killing 70

Source - BBC
A boat carrying African migrants has sunk off Yemen’s western coast, killing 70 people, Yemeni officials say.
The boat, carrying mostly Ethiopian migrants, sank off Yemen’s al-Makha port due to strong winds and rough waves, security officials said.
Tens of thousands attempt to cross the Red Sea into Yemen every year, often in rickety, overcrowded vessels. Hundreds have died making the journey.
Yemen is viewed by many migrants as a gateway to the Middle East or Europe.
The latest sinking occurred on Saturday, with reports of the incident emerging on Sunday.
The Red Sea crossing between the Horn of Africa and Yemen is one of the world’s major migration routes, BBC Arab affairs editor Alan Johnston says.
Migrants dream of finding jobs and better lives in rich places like Saudi Arabia – but they are in the hands of unscrupulous people smugglers and, too often, never reach the Yemeni shore, our correspondent adds.

 

In October, the UN refugee agency said that more than 200 people had died at sea in 2014 while attempting to reach Yemen.
“There have been frequent reports of mistreatment, abuse, rape and torture, and the increasingly cruel measures being adopted by smuggling rings seem to account for the increase in deaths at sea,” the UN said at the time.

 

 

Source:: gudayachn

ሚስጢረኛ መፅሐፍ ተናግሮ አናጋሪ (በላይ ገሰሰ)

$
0
0
Gebru Asrat

አቶ ገብሩ አስራት “

አቶ ገብሩ አስራት “ሉኣላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ” በሚል ዓቢይ ርእስ የፃፉትን ድንቅ መፅሐፍ ምክንያት በማድረግ በዋሽንግተንና አከባቢዋ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን በመተባበር ዲሰምበር 7, 2014 ዓ.ም ለአቶ ገብሩ አስራት ታላቅ የሽልማት” የአድናቆትና የምሳ ዝግጅት አድርጓል:: በዕለቱ ከተለያየ ቦታ የመጡ ምሁራንና ሌሎች ታዳሚዎች ተራ በተራ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ለአቶ ገብሩም ላደረጉት የላቀ አስተዋፀኦ የተዘጋጀውን የክብር ሽልማት ተሰጥቷቸዋል:: ከዚያም አቶ ገብሩ ንግግር በማድረግ ቤቱን አመስግኗል:: ስነ ስርዓቱ ከቀኑ 2 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 8 ሰዓት በመቀጠል የተለያዩ ዝግጅቶችን በማከናወን የበዓሉን ፍፃሜ ሆኗል::–--[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—-

Download (PDF, Unknown)

ግንቦት ሰባት ሆይ…. ከሄኖክ የሺጥላ

$
0
0

Henok Yeshitila

Henok Yeshitila


ውድ ወዳጆቼ ሆይ ፣ ዛሬ ተክሌን መሆን አምሮኛል ( ተክሌ ይሻውን ሳይሆን ተክለሚካዔል ሳህለ ማርያምን )። ልጅ ተክሌ መቼም እኔ’ነቴን ለምን ወሰድክብኝ እንደማትለኝ ነው ። እንኩዋን እኔነት ፣ የእኔነት መፈጠሪያ የሆነችውን ሀገርህን ወስደዋትስ የለ ።

የዛሬ ጽሁፌ የሚያጠነጥነው ትልቁንና እና ጠንካራውን ድርጅት ግንቦት ሰባትን ላይ ነው ። እንደውም ጽሁፌን ከማውጠንጠን ማነጣጠር ሳይሻል አይቀርም ( የታጠቀን እንዲያ ነው እንጂ !) ። እና የምወደውን ግንቦት ሰባት ፣ ባልሞትለት እንክዋ የምደማለት ግንቦት ሰባትን ፣ የኔ የምለውን ግንቦት ሰባት ፣ የ አንዳርጋቸውን ግንቦት ሰባት ፣ የብርሃኑ ነጋን ግንቦት ሰባት ፣ የዔፍሬም ማዴቦን ግንቦት ሰባት ፣ የአበበ ገላውን ግንቦት ሰባት ፣ አዎ ስለሱ ነው ።
andargachew
አንተ ግንቦት ሰባት ሆይ ፣ አንተን ካወቅኩበት ቀንና ሰዓት ጀምሮ ትቢት ትቢት ይለኛል ፣ ወያኔ ምን ለማስፈራራት ቢሞክር ፣ ነገራቸው ሁሉ ድንፋታ እንጂ አንዳች ፍርሃት ልቤን ይሁን ሆዴን ቅም አይለውም ፣ ስላንተ ሳስብ አባቱን ከሩቅ እንዳየ ህጻን እፈነድቅአለሁ ፣ ስምህ በክፉ ሲነሳ ፊቴ ደም ይለብሳል ፣ የባንክ ደብተሬ እንኩዋ ዜሮ እያሳየ ስላንተ ስሰማ ምን እንደሆነ ባላውቅም መንዝር መንዝር ይለኛል ፣ ዘርዝር ዘርዝር ይለኛል ፣ ያም ሆኖ አንዳርጋቸው ከታሰረ ወዲያ ላንተ ያለኝ ፍቅር ወደ ንዴት እየሄደ ነው ። ይሄም የሆነው አንዳርጋቸው በመያዙ ሳይሆን ፣ የአንዳርጋቸውን መያዝ ተከትሎ ይህ ነው የሚባል አጸፋዊ እርምጃ ባለመውሰድህ ነው ። ሰማያዊ እንኩዋ ነጭ እርግብ ጭንቅላቱ ላይ አድርጎ ሰላም ሰላም እያለም ፣ እየተገፈተርም ቢሆን ሰልፍ ወጥቶዋል ፣ “የምንገለው ባይኖረንም የምንሞትለት ሕዝብ ግን አለን” ብሎ ይሄው እሳት ከጨበጠ ጋ በ እስክርቢቶ ትግሉን ሀ ብሎ ከጀመረ ቆየ ፣ አረ እንደውም እስክርቢቶ መግዣውን እኔም ተባብሬያለሁ ( በሱም በጣም ደስተኛ ነኝ ) ። ኢንጂነር ይልቃልን ሳስብ ማህታማ ጋንዲ ወይም ማርቲን ሉተር ኪንግ ትዝ አይሉኝም ፣ ምክንያቱ ደሞ፣ ወዳጄ ይልቃል እንደነሱ ጠንካራ አይሆን ይሆን ብዬ ስለማስብ ሳይሆን ፣ መሃተማ ጋንዲና ማርቲን ሉተር ኪንግ መስዋት የሆኑላቸው አይነት ሕዝብ ከጎኑ ስለሌለ ብቻ ። ይልቃል እና ጉዋደኞቹ እንደውም ከማህታማ ጋንዲም ሆነ ከ ማርቲን ሉተር ኪንግም ይበልጣሉ ፣ ለምን ቢባል ፣ የሚታገሉት ስርዓት ምን ያህል ጨካኝ እንደሆነ እያወቁት ትግሉ ውስጥ በአስር ጣታቸው እንደገቡበት ሳስብ ። የብረት ትግል የሚል ነገር ባያነሱም ግን ከብረት ትግል እኩል የሕይወት መስዋትነት እየከፈሉ እንደሆነ ስገነዘብ እውነት እውነት እልሀለው ደግሜ ደጋግሜ አከብራቸዋለሁ ። እንደውም አንዳንዴ ግር የሚለኝ ፣ እነሱ ለተገረፉት ፣ እነሱ ለተሰቃዩት ፣ ” በሰላማዊ ትግል ወያኔ ይወድቃል ብሎ ማስብ ዘበት ነው !” እያልኩ እኔ ራሴ አወራ ነበር ። ግን ቆይቶም ቢሆን የገባኝ ለካ ለሀገር ሲሉ መሞቱን ነው ” ሰላም ” ያሉት እንጂ ትግሉማ መች ሰላም አለው ብለህ ነው ። መቼም በደንብ እንደምታውቀው እኔ ” ወያኔ ባሩድ አሽትተን እንጂ ፣ እርግብ አሳይተን እናሸንፈዋለን ማለት ዘበት የሚመስለኝ ሰው ነኝ ” እንዴት ሸለምጥማጥን እርግብ ሆነህ ትቀርበዋለህ ?

ወደ አብይ ጥያቄዬ ስመጣ ስለ ትግሉ ሳስብ ሆድ ይብሰኛል ፣ መቼ ይሆን ጦርነቱ የሚጀመረው እያልኩ ከራሴ ጋ አወራለሁ ፣ በይበልጥ በግንቦት ሰባት ስም የተገደሉ ፣ የታሰሩ ፣ ከስራ የተፈናቀሉትን ሰዎች ሳስብ ፣ በጣም የዘገየህ ይመስለኛል ፣ ይሄ የኔ ብቻ ጥያቄ እና መብሰልሰል እንዳይመስልህ ፣ ያው እኔ ስለማልፈራ ነው ጥያቄውን የጠየቅኩት እንጂ አሁን አሁን የብዙ ወዳጆቼ ጥያቄ እየሆነ ነው ። መቼ ነው አዲስ አበባ ላይ የወያኔ ባለስልጣን ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገደሉ ሲባል የምንሰማው ? መቼ ነው የወያኔ ባለስልጣኖች ሲንማ-ራስ መቃም የሚያቆሙት ፣ መቼ ነው ከህዝብ ጋ መተራመስ የሚያቆሙት ፣ መቼ ነው ቀን የግንቦት ሰባትን አባላት እና ሌሎች ንጹሃን ሰዎችን ማዕከላዊ ወፌ ላላ ሲገርፍ የዋለ የ ወያኔ ባለስልጣን ማታ አንገቱ ተቆርጦ የምናየው ? መቼ ነው ? የክርስቶስ ዳግም መምጣት እንኩዋ እንዳንተ ውጊያ መጀመር በዙም አልጉዋ-ጉዋ-ንኝም !

መልሱን በድርጊት ትመልሱልኝ ዘንድ ከወገቤ ዝቅ ብዬ እጠይቃለሁ ።

ደህንነቶች እስረኞችን ነጣጥለው እያዋከቡ ነው

$
0
0

10845983_625946774197651_3379754561679383547_nየገዥው ፓርቲ ደህንነቶች የአዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ (ሶስተኛ) የሚገኙትን የተወሰኑ እስረኞች ‹‹አብራችሁን ካልሰራችሁ አንለቃችሁም!›› እያሉ እያዋከቡ ነው፡፡ ሶስተኛ ታስረው ከሚገኙት መካከል ሳሙኤል አበበ፣ ምኞት መኮንን፣ ሜሮን አለማየሁና መርከቡ ሀይሌ ውጭ ሌሎቹ የመታወቂያ ዋስ አምጥተው እንዲለቀቁ የተጠየቁ ሲሆን አራቱን እስረኞች ‹‹አንራችሁን ካልሰራችሁ አንለቃችሁም!›› እያሉ እያዋከቧቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተመሳሳይ ፖፖላሬ እስር ቤት ከሚገኙት መካከል ዮናስ ከድርንና ተስፋዬ መርኔን ደህንነቶች ‹‹የእናንተን ምርመራ አልጨረስንም፡፡ ትቆያላችሁ!›› እንዳሏቸው ተገልጾአል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ገመና (ተመስገን ደሳለኝ)

$
0
0

ተመስገን ደሳለኝ  (ከዝዋይ እስር ቤት)

Temesgen Desalegn behindbarመሐሙድ የሱፍ የተወለደው በ1980ዓ.ም ከሶማሌ ክልል ርእሰ-መዲና ጅጅጋ 500 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘውዶሀን ከተማ ነው፡፡ ለቤተሰቡ ሰባተኛ ልጅ ሲሆን፤ አምስት እህቶችእና ሦስት ወንድሞች አሉት፡፡ በጅጅጋ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እስከ አስረኛ ክፍል ድረስ መዝለቁቢሳካለትም፤ ከዚህ በላይ ግን ሊቀጥል አልተቻለውም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የኢትዮጵያመንግስት የደህንነት ሠራተኞች የ1999ዓ.ም የግንቦት ሃያ በዓል በጅጅጋ ከተማ ስታዲዬም በተከበረበት ዕለት፣ የኦጋዴን ነፃአውጪ ግንባር (ኦብነግ) በሰነዘረው የቦንብ ጥቃት ተሳትፈሃል በሚል ለእስር በመዳረጉነው፡፡ ይህንን ተከትሎምከምድራችን አስከፊ ማሰቃያዎች መካከል ግንባር ቀደም በሆነውና የክልሉ

ነዋሪ “ጄል-አዳብ” (የገሃነም እስር ቤት) እያለ በሚጠራው ማጎሪያ ውስጥ እጅግ በጣም የከፋ ምድራዊ መከራ እንደተቀበለሀዘን በተጫነው ድምፅ ይናገራል፡፡ በሠውነቱ የተለያዩ ክፍሎች ላይ እንደ ፍም ቀልተው የሚታዩት ጠባሳዎቹም ያሳለፈውንሥቃይ አፍ አውጥተው ይመሰክራሉ፡፡ ለአራት ወራት ያህል አንድ ክፍል ውስጥ ለብቻው ተቆልፎበት፤ ሃያ አራት ሠዓታትሙሉ እጆቹ በካቴና ተቀፍድደው፣በቀን ከአምስት ጊዜ በላይ ለምርመራ እየተጠራ ያለዕረፍት ከባድ ስቅየት (ቶርቸር)ሲፈፀምበት ቆይቷል:፡ በመጨረሻም ለአንዲትም ቀን የፍርድ ቤት ደጅ ሳይረግጥ፣ ለኦብነግ አባላት አንድ ፓኬት ሲጋራሲያቀብል እጀ-ከፈንጅ ተይዟል በሚል ክስ የጅጅጋ ዞን ፍርድ ቤት በሞት እንዲቀጣ መወሰኑን እዛው እስር ቤት ሆኖከኢትዮጵያ ሬዲዮ የዜና እወጃ  እና ከቪኦኤ ሶማሊኛ ፕሮግራም ሠምቷል፡፡

ከፍርዱ በኋላም በተመሳሳይ ወንጀል ከተከሰሰ አንድ እስረኛ ጋር በካቴና ተጠፍሮ በቀን አንድ እንጀራ ለሁለት ተካፍሎእንዲበላ እንደ ውሻ እየተወረወረለት 60 ቀናትን አሳልፏል፡፡ መሐሙድ በተለይም በእንቅልፍ ወቅት እርሱ ወይምየሰንሰለት ደባሉ የተገላበጠ እንደሆነ ካቴናው የሚያደርስበትን የመለብለብ ቃጠሎ ሲያስታውስ ዓይኖቹ በእንባ ይሞላሉ፡፡በአሁኑ ወቅት በዝዋይ ማጎሪያ ከባድ ጥበቃ ለሚደረግባቸው ብቻ በተመደበ ‹‹ዘጠነኛ ቤት›› ውስጥ አስራ አንድ ሶማሊኛተናጋሪዎችን ጨምሮ በድምሩ ሰላሳ አራት ሰዎች ጋር ከዛሬ ነገ የግፍ ፍርዱ ተፈጻሚ ሊሆንብኝ ይችላል በሚል ሰቀቀንእየባነነ በስጋት ተጠፍንጎ መኖር ከጀመረ እነሆ ሰባት ዓመት ሊደፍን ሦስት ወራት ብቻ ቀርተውታል፡፡

የተዋረደው የፍትሕ ሥርዓት!. . .

ርግጥ ነው ይህ በጨረፍታ ያቀረብኩት አሳዛኝ ታሪክ የመሐሙድ የሱፍ ብቻ አይደለም፡፡ ሌሎች ሰባት ‹‹አባሪዎቹ››ስቃዩንም ሆነ የሞት ፍርዱን ይጋሩታል (በነገራችን ላይ በአንድ መዝገብ የተወነጀሉት እነዚህ ስምንት የሞት ፍርደኞች፡-መሐድ ኢብራሂም፣ አረብ ሰዋኔ ዱልባንቲ፣ ሐሰን መሐመድ ዑስማን፣ ሐሰን መሐመድ ዓሊ፣ ሙክታር መሐመድ ዓብዱላሂ፣ከድር ሽኩር ሙሳ እና ካሚል ዓብዱልናስር እንኳን በጋራ መንግሥት ላይ ሊያሴሩ ቀርቶ እርስ በርስም የተዋወቁት እስር ቤትውስጥ ነው፡፡ ከጅጅጋ ወደ ዝዋይ ‹‹ዘጠነኛ ቤት›› ተዘዋውረው በርካታ ዓመታትን ያሳለፉትም በጭካኔው ወደርእንደማይገኝለት የሚነገረው የክልሉ ፕሬዚዳንት አብዲ

በአደራ እንዲቀመጡ በመተላለፋቸው መሆኑን ነግረውኛል፡፡) እንደ መሐሙድ ሁሉ እነርሱም ፍርድ ቤት ቀርበውአያውቁም፤ ምንም ዓይነት የሰውም ሆነ የሰነድ ማስረጃ አልተቆጠረባቸውም፡፡ እዚህ ጋ የማነሳው አሳዛኝ ገጠመኝከመካከላቸው አንዳቸውም ራዲዮ ስላልነበራቸው የተጣለባቸውን የሞት ፍርድ ውሳኔ የሠሙት፣ ዜናው ከተላለፈ ከበርካታቀናት በኋላ ሬዲዮ ካላቸው እስረኞች መሆኑ

ነው፡፡ ይህ እጅግ አሳፋሪና አስደንጋጭ መንግሥታዊ ውንብድና በደንብ ይብራራ ዘንድ ለተከሳሶቹ ከተሰጣቸው ባለ አንድገፅ የክስ ቻርጅ የሁለቱን ብቻ በአዲስ መስመር እጠቅሳለሁ፡-‹‹በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ አቃቤ ሕግና ፍትሕቢሮ በሶማሌ ክልላዊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት

ጅጅጋ

የዐ/ሕግ/መ/ቁ 90/2000

ዝዋይ እስር ቤት ያለው

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከሳሽ፡- ዐ/ሕግ

ተከሳሽ፡- ሐሰን መሐመድ ዑስማን (ሐንን መድቤ)

ዕድሜ፡- 21

ሥራ፡- ተማሪ

አድራሻ፡- ጅጅጋ ከተማ፡- 06 ቀበሌ

ወንጀል

በ1996ዓ/ም የወጣውን የኤ.ፌ.ዴ.ሪ የመ.መ.ሥ.ሥ.ህ.ቁ. 240(3) እና 251(መ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፣

የወንጀል ዝርዝር

ተከሳሽ ከመስከረም 1999 ዓ.ም. ጀምሮ እራሱን ኦ.ብ.ነ.ግ. እያለ ከሚጠራው ተቃዋሚና አሸባሪ ድርጅት ጋር በራሱፈቃድ

በዚሁ በጅጅጋ ከተማ ከላይ በተጠቀሰው ዓመተ-ምህረት አባል በመሆን በጫካ በዚሁ አካባቢ ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ጋርበከተማም

ሆነ በጫካ በመገናኘት በኢኮኖሚ ረገድ የሚያስፈልጋቸውን፡- ጫማ፣ ልብስ የመሳሰለውን እዚያው ድረስ ሄዶ በማቀበልአብሮ

ሲንቀሳቀስ በመቆየቱ ተከሶ ቀርቧል፡፡››

ሁለተኛው የክስ ቻርጅ ደግሞ እንዲህ ይነበባል፡-

‹‹በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ አቃቤ ሕግና ፍትሕ ቢሮ

በሶ/ክ/መ/ ጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት

ጅጅጋ

የዐ/ሕ/መ/ቁ 90/2000

ከሳሽ፡- ዐ/ሕግ

ተከሳሽ፡- መሐድ ሼክ ኢብራሂም

ዕድሜ፡- 28

ሥራ፡- የለውም

አድራሻ፡- ጅጅጋ ከተማ፡- ቀበሌ 05

1ኛ ክስ

ወንጀሉ

በ1996 ዓ/ም የወጣውን የኤ.ፌ.ዴ.ሪ የመ/መ/ህ/ ቁ. 241 እና 251(መ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፣

የወንጀሉ ዝርዝር

ተከሳሹ በ1998 ዓ.ም. ወራትና ቀኑ በውል ካልታወቀ ጊዜ ጀምሮ እራሱን ኦ.ብ.ነ.ግ. እያለ ከሚጠራው ተቃዋሚ የፖለቲካ

ድርጅትና አሸባሪ ጋር በራሱ ፈቃድ አባል በመሆን ከዚህ ሕገ-መንግሥቱን ከሚፃረር ድርጅት በቀጥታ ፌዴሬሽኑእንዲከፋፈል፣ ክልሉን

የመገንጠል ዓላማ ለማሳካት ይህንኑ ድርጅት ከዚሁ በጅጅጋ ከተማ ለጊዜው ካልተያዘ ግብረ-አበሩ ጋር በመሆን ይህንኑአሸባሪ ድርጅት

በሚያስፈልገው ማቴሪያል ሁሉ፡- ጫማ፣ የፖሊስ የደንብ ልብስ፣ መድሃኒት. . . የመሳሰለውን በማቀበሉ፡፡

2ኛ ክስ

ወንጀሉ

በ1996ዓ/ም የወጣውን የኤ.ፌ.ዴ.ሪ የመ/መ/ህ/ ቁ. 36 (ለ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፣

የወንጀሉ ዝርዝር

ተከሳሹ ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ የተለያዩ መ/ቤቶች ማለትም፡- የክልሉ ት/ቢሮን፣ የቀብሪ-ደሐር ት/ቢሮን፣ እንዲሁም የMSF

እና የተለያዩ መሥሪያ ቤቶችን እና የትምህርት ተቋማትን ማህተም በማስመሰል አትሞ እና የኃላፊዎችን ፊርማ ዓይነትአስመስሎ

በማስፈር ሐሰተኛ ሰነድ አዘጋጅቶ በመገኘቱ ተከሶ ቀርቧል፡፡››

(ሁሉም የክስ ቻርጆች ማኅተም እና አንጋው አፈወርቅ ምንተስኖት የተባለ የክልሉ ዐቃቤ ሕግ ፊርማ አላቸው)

እነሆም ያለአንድ ምስክር፣ ያለምንም የሰነድ ማሰረጃ፣ አንድም ቀን ችሎት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃል ሳይጠየቁ እና

ሳይከራከሩ (ያውም የዞን ፍርድ ቤት) በነዚህ በስም በጠቀስኳቸው በስምንቱ ኢትዮጵያውን ላይ የሞት ቅጣትን የመሰለየመጨረሻ

ውሳኔ እንደቀልድ አስተላልፎባቸዋል፡፡ (በነገራችን ላይ ሌሎች 13 የኢትዮጵያ-ሶማሌ ተወላጆችም በተመሳሳይ የሐሰትውንጀላ የዕድሜ

ልክ እስር ተፈርዶባቸው ዝዋይ ይገኛሉ፡፡ የሚገርመው ጉዳይ ደግሞ ም ቢሆኑ መጀመሪያ ተጠርጥረው በተያዙበት ወንጀልአይደለምየተጠየቁት፡፡ ጉዳዩ ጭራሽኑ በምርመራም ወቅት አልተነሳም) መቼም በዚህ መልኩ በተቀናበረ የውሸት ክስ ከ20-27 ዓመት የሚገኙ

ወጣቶችን በሲኦላዊ እሳተ-ነበልባል ስቅየት ውስጥ እንዲያልፉ ከማድረግም በዘለለ፣ ብሩህ ቀናቸውን አጨልሞ ላይመለሱወደመቃብር

የሚሸኝ ቅጣት ሲጣል ከመመልከት የበለጠ የትኛውንም ዜጋ የሕሊና ስቃይ ውስጥ ከትቶ፣ አንገት አስደፍቶ፣ በቁጣ ቀስቅሶ

ወደአደባባይ የሚያወጣ ገፊ-ምክንያት አለ ብዬ አላምንም፡፡

 

ማነው ተጠያቂው?

በእነዚህ ንፁሃን ኢትዮጵያውያን ላይ ‹በጄል-አደብ› የደረሰባቸው በነውረኝነት የታጀለ ኢ-ፍትሐዊ ፍርድ እና ስቅየት፣

የሥርዓቱን እውነተኛ ማንነት ገሃድ የሚያወጣ ተጨባጭ ተግባር መሆኑ ባይካድም፡ ይህንን አረሜናዊ ድርጊት በፊት-አውራሪነት

የመሩት፡- ኮሎኔል ሞኒ መንገሻ በጊዜው የክልሉ የፀረ-ሽብር ግብረ-ኃይል ዋና ኃላፊ የነበረ አሁን ወደአዲስ አበባ ተቀይሮ‹ሕገ-ወጥ

የሠው ዝውውር ወንጀል መከላከል› ኃላፊ፣ ቢኒያም የተባለ የክልሉ የደህንነት ኃላፊ፣ ሻለቃ ዘገየ በክልሉ የፌዴራል ፖሊስኃላፊ፣

ወልደአራዌ የክልሉ ፖሊስ ም/ኮሚሽነር፤ እንዲሁም ሻለቃ ወንድሜ፣ ሻለቃ በለጠ እና ታሰረ የተባሉ ኃላፊነታቸውንለይተው

የማያስታውሷቸው ግለሰቦች መሆናቸውን ግፉአኖቹ በተሰበረ ልብ፣ ምሬት በሞላው ድምፅ፣ ተስፋ በቆረጠ ስሜትሲተርኩልኝ ዓይኖቼ

ላይ የተቋጠረው የእንባ ከረጢት ገንፍሎ እንዳይፈስ ብርቱ ትግል ማድረጌን አልሸሽግም፡፡

የሆነው ሆኖ እነዚህ የሥርዓቱ ሹማምንት የፍርድ ቤት ደጅ ሳይረግጡ፣ የሞት ቅጣት እንዲተላለፍባቸው ባደረጓቸው

ምስኪኖች ላይ የማሰቃያ ጥበቦቻቸውን በሙሉ ከሞከሩባቸው በኋላ፡- ‹‹ሞት እንፈርድባችኋለን!!›› እያሉ ያስፈራሯቸውናይዝቱባቸው

ነበር፤ እነርሱም፡- ‹‹እናንተ ፍርድ ቤት ናችሁ እንዴ?›› ብለው በግርምትና ባለማመን ሲጠይቋቸው፣ ማናአህሎኝነትያሳበጣቸው የፀጥታ

ኃላፊዎች እንዲህ በማለት አስረግጠው መልስ መስጠታቸውን ሰምቻለሁ፡-

‹‹አዎን! ፍርድ ቤት ማለት እኛ ነን!!››

በርግጥ ከዚህ ሁሉ መከራ በኋላ የተላለፈባቸው ውሳኔ፣ ያውም በሞት እንዲቀጡ የሚል መሆኑን ስናስተውል የዛቻውን

መነሾ መረዳቱ አዳጋች አይሆንብንም፡፡ በአናቱም በምርመራ ወቅት ዕድል ፊቷን ያዞረችበትን ተጠርጣሪ እዛው እስረኛ ፊትበሽጉጥ

ግንባሩን በርቅሰው እንደ መናኛ ነገር ሜዳ ላይ ይዘረጉት እንደነበረ የዓይን እማኞች ይመሰክራሉ፡፡

በጥቅሉ ይህ ሁነት በሀገሪቱ አለቅጥ የተንሰራፋውን የፍትሕ እጦት፣ የሠብአዊ መብት ጥሰት፣ ዳኞች ከሕግ ይልቅ ከቤተ-

መንግሥት በሚላክላቸው የፍርድ ውሳኔ ንፁሃኑን ለምድራዊ ስቃይ ከመዳረግም አልፈው ተርፈው በጭካኔሕይወታቸውንም

እንደሚነጠቁ በቂ ማስረጃ ይመስለኛል፡፡

 

‹‹ጄል-አዳብ››

የክልሉ ኗሪዎች ‹‹ጄል-አዳብ›› (የገሃነም እስር ቤት) እያሉ የሚጠሩት የጅጅጋው ማሰቃያ ቤት ክፍሎች የተሠሩት አራትመቶ

ታሳሪዎችን እንዲይዙ ታስቦ ቢሆንም፣ አብዛኛውን ጊዜ ከአራት ሺህ በላይ ታሳሪዎች እንደሚታጎሩበት አረጋግጫለሁ፡፡ይህም አንድ

ሰው ከአንድ ሰዓት በላይ በእንቅልፍ ማሳለፍ እንዳይችል አድርጎታል፡፡ ምክንያቱም ቦታውን ለተረኛው የመልቀቅ ግዴታአለበትና፡፡

ምናልባት እንቅልፍ ቢጥለው እንኳ ተረኞቹ ቀስቅሰው (ጎትተው) ያስነሱታል፡፡

ከ‹‹ጄል-አዳብ›› በሕይወት ተርፎ የሚወጣ ሰው ዕድለኛ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ በዚህ ቦታ ከቤተሰብ ጋር መገናኘት ጭራሽ

አይሞከርም፡፡ ማሰቡ እንኳ እንደ ቅንጦት ነው የሚታየው፡፡ በእስር ቤቱ አጥር ሦስት መቶ ሜትር ክልል ርቀት ዙርያ ውስጥመገኘትም

ለከባድ ስቃይ (አንዳንዴም ለሞት ቅጣት) ይዳርጋል፡፡ በሃያ አራት ሰዓት አንዴ፣ አንድ እንጀራ ለሦስት እየተቃመሱለአምስት ዓመት

በዛ እስር ቤት ያሳለፈ ምስኪን አጋጥሞኛል፡፡ ይህ ወጣት በ2004ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ሦስት ዓይነት ተላላፊ በሽታ(ተቅማጥ፣

ሰውነትን የሚያሳክክና ጉሮሮን አሳብጦ ለአዕምሮ መቃወስ የሚዳርግ) ተከስቶ በቀን እስከ አስራ አራት ሰው ድረስ ይሞትእንደነበር

ያስታውሳል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ሕክምና ብሎ ነገር አልነበረም፡፡ እንዲያውም በግልባጩ የክልሉ አስተዳዳሪዎችጭካኔያቸውን (ኢ-

ሠብአዊነታቸውን) ወለል አድርገው የሚያሳብቁ ድርጊቶች መፈፀማቸውን አላቋረጡም፡፡ ለማሳያ ያህልም እስረኛው ከሌሊቱስድስት

ሰዓት ላይ በአንድ ድምፅ እንዲህ የሚል መፈክር እንዲያሰማ መገደዱን እዚህ ጋ መጠቀስ ይቻላል፡-

‹‹መለስ ዜናዊ ሐኖላዶ!›› (መለስ ዜናዊ ለዘላለም ይኑር!)

‹‹አብዲ ሑመድ ዑመር ሐኖላዶ!››

‹‹ኢትዮጵያ ሐኖላዶ!››

ኦብነግ ሐዳኦዶ!›› (ኦብነግ ይውደም!)ሌላው አስገራሚ ጉዳይ ቤተሰብ ታሳሪ ልጁ በሕይወት ይኑር ይሙት የሚያውቀውከማጎሪያው በስንት ጊዜ አንዴ የሚፈታ

ሰው ሲገኝ ብቻ የመሆኑ እውነታ ነው፡፡ እናም ድንገት በአንዲት ‹ዕድለኛ› ቀን አንድ ታሳሪ ከ‹‹ጄል-አዳብ›› የተለቀቀእንደሆነ ወሬው

ከመቅጽበት ይዛመትና ለሳምንታት አሊያም ለወራት የእስረኛው ቤት በእንግዶች እስከ አፍ-ገደፉ ጢም ብሎ ይውላል፡፡የተለመደ

ነውና እሱም ያለመታከት የቀረበለትን ጥያቄ በሚከተለው መልኩ ሲመልስ ይከርማል፡-

‹‹ኦ!… እገሌ ከሞተ እኮ ሁለት ዓመት አለፈው›› ፤ “እገሌማ ሲያሳዝን! ካረፈ ገና አንድ ወሩ ነው”፤ “ኦ! እገሌ ለወደፊቱ

እግዜር ይጠብቀው እንጂ እስካሁን በሕይወት ይገኛል…” ወዘተ ወዘተ. . .

– See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/2924#sthash.TMbo2T7g.dpuf

ባለፈው ዓመት ከሳዑዲ አረቢያ ከተባረሩት ኢትዮጵያውያን መካከል 85ሺው ተመልሰው መሄዳቸው ተዘገበ

$
0
0

ባለፈው ዓመት ከሳውዲ አረብያ ከተባረሩት ከአንድ መቶ ሰባ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን 50% (ከ 85ሺህ በላይ የሚሆኑት) ተመልሰው ሳውዲ አረብያ መግባታቸውን አዲስ አበባ ላይ ዛሬ በወጣ አዲስ የዳሰሳ ጥናት ተገለፀ:: (የጉዳያችን አጭር ጥንቅር)

Photo File

Photo File


ኢትዮጵያ ውስጥ የኑሮ መክበድ፣የነፃነት ማጣት እና የስርዓቱን ማዋከብ፣እስር እና ግድያ እየሸሹ የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከእለት ወደ እለት እየጨመረ ነው።ሰሞኑን በየመን የባህር ዳርቻ በቀይ ባሕር ውስጥ ከሰባ በላይ ኢትዮጵያውያን መስመጣቸው ይታወቃል።

ዛሬ የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማኅበር (CRDA) በሳውዲ ተመላሾች አሁን ያሉበት ጉዳይ ላይ የሚወያይ አውደ ጥናት አዲስ አበባ ላይ የቀረበ አንድ ጥናት ባለፈው ዓመት ወደ ኢትዮጵያ ከተባረሩት ከአንድ መቶ ሰባ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን 50% (ከ 85ሺህ በላይ የሚሆኑት) ተመልሰው ሳውዲ አረብያ መግባታቸውን ይገልፃል።ቪኦኤ የአሜሪካ ራድዮ የአማርኛው አገልግሎት ዘጋቢ ከአዲስ አበባ አውደ ጥናቱን አስመልክቶ ባቀረበው ዘገባ የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማኅበር (CRDA) የስትራቴጂክ ቡድን መሪ እና በድርጅቱ ልዩ አማካሪ አቶ ክፍለ ማርያም ገ/ወልድን ባነጋገረበት ወቅት ”ሀቁን እንነጋገር ከተባለ ግማሾቹ ተመልሰው ሄደዋል” ብለዋል።

በአውደ ጥናቱ ላይ የተገኙ የስደት ተመላሾች ውስጥ ለቪኦኤ ሃሳቧን የሰጠች ወጣት ”ከችግር የተነሳ ነው።እዚህ ሆኘ እራሴን ከማጠፋ ሄጄ ልሙት ከማለት ነው” ብላለች።ለወገኖቻችን በአራቱም ማዕዘን መውጣት የሀገራችን አጠቃላይ የፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳዮች ከዋና ምክንያትነት አያመልጡም።የችግሩ ዋና መንስኤ እየተተወ ስደቱን ብቻ ብናወጋው መፍትሄ አይሆንም።

የተመላሾቹንም ሆነ የአዲሱን ትውልድ በሀገሩ ተመክቶ እና ተማምኖ እንዲኖር አልተደረገም።ይልቁንም የኢህአዲግ አባል ካልሆነ እና ከካድሬዎች እግር ስር ካለወደቀ መኖር አይችልም።በሥራ ዓለም ያለው ባለሙያንም ብንመለከት የነፃነት ማጣቱ እና ሃሳቡን እና ችሎታውን ለሀገሩ ማበርከት አልቻለም።መሃንዲሱ፣የህክምና ዶክተሩ እና የአይሮፕላን አብራሪው በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ተደረገ።ሁሉ ሃገሩን ጥሎ ለመሄድ አኮበኮበ የቀረው ቆርጦ ከኢህአዴግ/ወያኔ ጋር ተጋፈጠ።ለእዚህ አብነት የሚሆኑን የሰማያዊ ፓርቲ እና የዘጠኙ አጋሮቻቸው ድርጊት ተጠቃሽ ነው።

የኢትዮጵያ ጉዳይ በእንዲህ አይነት ሁኔታ እንደሀገር የመቀጠላችን አደጋ በራሱ በግልፅ ይታያል።ጥቂቶች በሙስና እና በጎሳቸው ብቻ በሀብት ሲናጥጡ ሌላው ዜጋ ሃገሩን በረሃ ለበረሃ እየተንከራተተ ሲወጣ አይኖርም።አንድ ቀን እዝያው ሀገር ውስጥ ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጭ የመውጣታቸው አደጋ አይኖርም ማለት አይቻልም።የወገኖቻችን ሀገር ጥለው የመሄድ ጉዳይ የሚያመለክተው ይህንን ነው።ቁጥር ደግሞ ከሁሉ በላይ የሀገራችንን የፖለቲካ መድረክ መቀየር እንዳለበት አመላካች ነው።”ከሰማንያ ሺህ በላይ የሚሆኑ ወደ ሀገር ቤት የተመለሱ ወገኖቻችን ተመልሰው መከራ ወደ አዩባት ሳውዲ ተመለሱ” የሚለው ዘገባ በእራሱ መጪውን አመላካች ነው።እናት ልጇ ተመልሳ እቤት ከገባች በኃላ ተመልሳ ስትሰደድ እንዴት ታዝን? ምን ያልደረሰብን አለ? ሱዳን ባቅሟ ኢትዮጵያውያንን አባረረች ስንባል፣የመን ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መንገዶቿን ሞሉ ሲባል፣ጅቡቲ ኢትዮጵያንን ስታስር፣ እራሳችንን መጠየቅ ያሉብን ሶስት ጥያቄዎች አሉ እነሱም –
ኢትዮጵያ ክብሯ እና ማንነቷ አልተዋረደም ወይ?
ያለውን አስከፊ ሁኔታ ለመቀየር የፖለቲካው ችግር አለመስተካከል ዋነኛው ምክንያት አይደለም ወይ? እና
ለእዚህም ተጠያቂዎች የእያንዳንዳችን ለስርዓቱ መቀየር የአቅማችንን አለማድረግ አይደለም ወይ? የሚሉ ጥያቄዎች።
በመሆኑም ሰቆቃ ስንሰማ የምንኖርበት ዘመን እንዲቆም፣ኢትዮጵያ የጎሳ ፖለቲካ አራማጅ፣በሙስና የተነከረው እና ክብሯን እና ማንነቷን ከሚመጥናት በታች የሆነ አስተሳስብ ያለው ኢህአዲግ/ወያኔ የበለጠ ሀገራችንን መቀመቅ ሳይከት የእያንዳንዳችንን ኃላፊነት እንወጣ።በዝምታችን ኢትዮጵያን ከሚገድሉ ጋር አንተባበር።

ከእዚህ በታች ያለው ማያያዣ የጀርመን ድምፅ ራድዮ ከጥቂት ወራት በፊት ከሳውዲ የተባረሩ ወገኖቻችን ተመልሰው ወደ ሳውዲ የመመለሳቸውን ሁኔታ አስመልክቶ በድምፅ ያቀረበው ዘገባ ነው።

የአንድነት ፓርቲ ልዩ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዬ ተጀመረ::

$
0
0

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የጠራው ጠቅላላ ጉባኤ የተጀመረ ሲሆን ተሳታፊዎች የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት አረንጓዴ ፤የአዲስ አበባ ምክር ቤት ቢጫ፤ የክልል ዞን ተወካዮች ቀይ ቲሸርቶችን በመልበስ ለጉባኤው ድምቀት ሰጥተውታል፡፡

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አርብ (03/04/07) ጠቅላላ ጉባኤውን ያደርጋል፡፡ ፓርቲው ከዚህ ቀደም በታህሳስ 19/20/2007 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን አመት ሳይሞላ ሌላ ጠቅላላ ጉባኤ ለማድረግ ለምን እንዳስፈለገ የጉባኤ ጠሪ ኮሚቴ የሆኑትን አቶ አስራት ጣሴን አነጋግረን ነበር፡፡ አቶ አስራት እንዳብራሩት በታህሳስ 2006 ዓ.ም ተካሂዶ በነበረው ጠቅላላ ጉባኤ ምርጫ ቦርድ ማብራሪያ ጠይቆ ነበር፡፡ አቶ አስራት በተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ማቋቋሚያ አዋጅ 573/2000 መሰረት ምርጫ ቦርድ የጠቅላላ ጉባኤ ሪፖርት ማብራሪያ መጠየቅ እንደሚችል ገልፀው በሀምሌ 25 ቀን 2006 ዓ.ም በፃፈው ባለ ሶስት ገፅ ደብዳቤ ዘጠኝ ማብራሪያ የሚፈልጉ ጥያቄዎችን አቅርቦ ነበር፡፡ by MINILIK SALSAWI

10698475_829409667117784_3680643737158512454_n

አንድነት ፓርቲ በበኩሉ ሀምሌ 30 ቀን 2006 ዓ.ም ለተጠየቁት ጥያቄዎች ማብራሪያ ላከ፡፡ ከተላከው ማብራሪያ በመነሳት ምርጫ ቦርድ ጥቅምት 19 ቀን 2007 ዓ.ም ጥያቄዎቹን ወደ 6 ዝቅ አደረገ፡፡ ፓርቲው በበኩሉ ጥቅምት 21 ቀን 2007 ዓ.ም ለተጠየቁት ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጠ፡፡ ከዚያ በመቀጠል ምርጫ ቦርድ ህዳር 10 ቀን 2007 ዓ.ም ሶስት ማብራሪያ ያስፈልጋቸዋል ያላቸውን ጥያቄዎች ያቀረበ ሲሆን ፓርቲውም ህዳር 11 ቀን 2007 ዓ.ም ማብራሪያ ሰጥቶባቸዋል፡፡

UDJ general meeting 1

 

UDJ general meeting 1 9

11

5 6 10698475_829409667117784_3680643737158512454_n UDJ general meeting 2 4 3 8


ስምንት ጠቃሚ ነጥቦች ከእስራኤላውያን -ክፍል 6 (ዮፍታሔ)

$
0
0

ከዚህ ቀደም በነበሩት 5 ክፍሎች የእስራኤልን ታሪክ በአጭር በመቃኘት ስለአንድ ማዕከላዊ ድርጅትና ስለተቋማት አስፈላጊነት፣ ትግሉን ዓለምአቀፋዊ ስለማድረግ፣ ስለዳያስፖራው ወሳኝ ሚና፣ የጋራ ቋንቋ ለአንድ አገር ያለውን ጥቅም በሚመለከትና በአገር ጉዳይ የሀይማኖት መሪዎችና አገልጋዮች ሊኖራቸው ስለሚገባው የመሪነትና የማስተባበር ሚና ተገልጿል። ቀጣዩ ክፍል 6 ስለማስረጃና ስለማስረጃ ተቋም አስፈላጊነት ያብራራል።

  1. ሁሉንም መዝግቦ መያዝ (Documentation & Archaiving)

Jewish+Ethiopians+Reunited+Families+Israel+o1h5oGhsf2Vlበእስራኤላውያን የትግል ጊዜም ሆነ እስራኤልን ከመሠረቱበት እ.ኤ.አ 1948 በኋላ ሕዝብን ለማሳወቅ፣ ወንጀለኞችን ወደፍትሕ ለማቅረብ፣ ችግሩ እንዳይደገም ዓለምን ለማስጠንቀቅና ለማስገንዘብ በከፍተኛ ደረጃ የጠቀሙት በራሳቸው በእስራኤላውያን እና እስራኤላዊ ባልሆኑ ሌሎች ሰዎች በጊዜው ይደርስ ስለነበረው ግፍና ሰቆቃ በጽሑፍ፣ በፎቶግራፍ፣ በቪዲዮና በድምፅ ተመዝግበውና ተቀርጸው የተያዙ ማስረጃዎች ናቸው።

ይልቁንም እስራኤላውያን ለዚህ ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም ካቋቋሙ በኋላ ይህ ተቋም በሕፃናት ከተሣሉ ሥዕሎች ጀምሮ ከ25 ሺህ በላይ የተለያዩ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ በማጥናትና ለማስረጃ፣ ለምርምርና ለሙዚየም እንዲመቹ አድርጎ በማዘጋጀት ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በጀርመኖች የማጎሪያ ካምፕ ውስጥ የነበረችው አነ ፍራንክ (Anne Frank) የተባለች ትንሽ ልጅ ከመሞቷ በፊት በየቀኑ ስትመዘግበው የነበረው የግሏ ገጠመኝ (Diary) እና ሌሎችም ተመሳሳይ ስብስቦች ከነዚህ መካከል ተጠቃሽ ናሙናዎች ናቸው።  እነዚህ ማስረጃዎች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ለ6 ሚሊዮን አይሁድ ሕይወት መጥፋት ተጠያቂ የሆኑት የናዚ ወንጀለኞች ወደፍርድ ቤት ቀርበው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ በእጅጉ ጠቅመዋል። ለመማሪያ፣ ለምርምርና በሕዝብ እንዲጎበኙ በሚዚየም ተቀምጠው እስከዛሬም በጥቅም ላይ እየዋሉ ነው። እነዚህ ተቋማትና ድርጅቶች በእስራኤል ብቻ የተወሰኑም አይደሉም። በመላው ዓለም በተለያዩ ከተሞች ይህን የሚሠሩ በርካታ የአይሁድ ተቋማት፣ ላይበራሪዎች፣ ሙዚየሞች፣ የማስረጃ ክምችት (Archivals) እና የምርምር ተቋማት ዛሬም ይገኛሉ። በአሜሪካን አገር ብቻ United States Haloucast Memorial Museum በሚል በሚታወቀው ተቋም ሥር ይህን ሥራ የሚሠሩ አያሌ ድርጅቶች በበርካታ የአሜሪካ ከተሞች ውስጥ ይገኛሉ።

እነዚህን ማስረጃዎች በመንተራስ የተዘጋጁ መጻሕፍት፣ ፊልሞች፣ ትያትሮችና ትእይንቶች (Exhibitions) ቁጥራቸው አያሌ ነው። ይህ በእስራኤላውያን የደረሰውን ዓለም እንዲገነዘበው፣ እንዲማርበትና ይህን መሰል ነገር በድጋሚ በማንም እንዳይደርስ ካለው አስተዋጽኦ በላይ ለእስራኤላውያን ጥንክሮ መሥራት፣ ብልጽግና፣ አይበገሬነትና የመንፈስ ኩራት አጎናጽፏል። ከወደቁበት መነሳትና አገራቸውን መልሰው ማቋቋም ብቻ ሳይሆን እንደ እንስሳት እያዩ የገደሏቸውን ጀርመኖች ይቅርታ ለማስጠየቅና እስራኤላውያን በዓለም ፊት አንገታቸውን ቀና አድርገው እንዲሄዱና እንዲከበሩ እነዚህ ማስረጃዎች ያበረከቱት አስተዋጽኦ ቀላል አይደለም።

ከዚህ ምን እንማራለን? በመጀመሪያ ማስረጃና መረጃን የሚያሰባስብ፣ የማያቋርጥ የመረጃ ዳሰሳ የሚያደርግ፣ ለሥራ እንዲመች አድርጎ የሚያከማች/የሚያደራጅ፣ ሳይበላሹ ተጠብቀው እንዲቆዩ የሚንከባከብ፣ የሚቆጣጠር፣ ማስረጃዎቹ ለሌሎች የሚደርሱበትን የሚያመቻች፣ የሚያጠናና የሚተነትን ጠንካራ ተቋም ያስፈልገናል። ይህ ተቋም ከአገዛዙ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን በጠቅላላ እና በግእዝ በአማርኛና በሌሎችም የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና የተለያዩ የዓለም ቋንቋዎች ስለኢትዮጵያ የተጻፉትን ማንኛውም መጻሕፍት፣ የተዘጋጁትን የፎቶግራፍ፣ የድምፅና የቪዲዮ ሥራዎች ከአገር ውስጥም ከውጭም በስጦታ፣ በግዢ እና ኮፒ በማድረግ የሚሰበስብ መሆን ይኖርበታል። በፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ጥረት በማይክሮፊልም የተሰባሰቡት ሥራዎች ቋሚ ምስክር ናቸው። በአርቲስት ታማኝ በየነ አስተባባሪነት ይህ ተቋም በቅርቡ መቋቋሙ ደግሞ የቡድኑን አርቆ አስተዋይነት የሚያመለክትና እጅግ የሚያስደስት ነው። በሰው ኃይል፣ በእውቀት፣ በአደረጃጀትና በገንዘብ አቅም እንዲጠነክርና ሥራውን በብቃት እዲወጣ የመላው ኢትዮጵያዊ ድጋፍ ያስፈልገዋል።  ይህ ተቋም ትንሽ ቀደም ብሎ ቢሆን ኖሮ በቅርቡ በአዲስ አበባ በኪሎ እየተሸጡ በነበሩት ታሪካዊ መዛግብት ላይ ሊደርስባቸው ይችል እንደነበረ መገመት ይቻላል። አሁንም በየሰው እጅ ያሉትን በስጦታና በግዢ ለመሰብሰብ ጥረት ቢያደርግ ለአገርና ለወገን ባለውለታ ይሆናል።

መረጃዎች ዕለት በዕለት እየሰበሰቡ ለዚህ ተቋም ማስተላለፍ ደግሞ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ኃላፊነት ነው። ይህ ሁለተኛው አስፈላጊ ተግባር ነው። ማንም ነፃነት ወዳድ ኢትዮጵያዊ በእጁ የገባውን መረጃና ማስረጃ ከቻለ ዋናውን ካልቻለ ኮፒ አድርጎ፣ ያጋጠመውን በጽሑፍ፣ በፎቶና በቪዲዮ መዝግቦ የማስቀረት ኃላፊነት አለበት። ሕፃናት ሳይቀር በገጠርና በከተማ በዚህ አገዛዝ ሲፈጸሙ ያዩትንና ስለአገዛዙና ስለኑሮአቸው የሚሰማቸውንና በቤተሰባቸው የደረሰውን በሥዕልና በጽሑፍ እንዲገልጹት መምህራንና ወላጆች ማበረታታት ብሎም ማስረጃውን በጥንቃቄ ቀን መዝግበው ማስቀመጥና በጊዜው ለተቋሙ ማስተላለፍ ይኖርባቸዋል።

ዛሬ በየሰው እጅ ያለው ተንቀሳቃሽ ስልክ ካሜራ አለው። ይህን ካሜራ በመጠቀም ብዙ መረጃዎች ወጥተዋል፤ አሁንም እየወጡ ነው። ነገር ግን ከዚህም በበለጠ እያንዳንዱ ዜጋ ያገኘውን አጋጣሚ ሁሉ በካሜራው ቀርጾ የማስቀረት ኃላፊነት ሲወስድ ከፍተኛ ሥራ ይሠራል። መሻሻል የሚያስፈልገው ነገር ቢኖር የምስሎቹን ጥራት በሚመለከት ነው። ለዚህ መፍትሔው በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትኩረት ሰጥተው የካሜራ ባለሙያዎችን ከመቅጠር ጀምሮ ለአንዳንድ የድርጅት አባላቶቻቸው በቂ የፎቶግራፍና የቪዲዮ ቀረጻ ስልጠና በመስጠትና ከካሜራ ጋራ በማሰማራት ከፍተኛ ሥራ ሊሠሩ ይችላሉ። አባላቶቻቸው አደጋ ላይ እንዳይወድቁ ሚስጥራዊ ጥቃቅን ካሜራዎችን እንዲጠቀሙ ማድረግ ይቻላል።  እዚህ ላይ ጠንካራ የሆኑት በውጭ የሚገኙ የኢራን አክቲቪስቶች በኢራን 2009 (እ. ኤ. አ) ምርጫ የተነሣ መንግስታቸው የወሰደውን ጭካኔ የተሞላበት ርምጃ ለማጋለጥ የተጠቀሙበትን ዘዴ መጥቀስ ይጠቅማል። በዳያስፖራ የሚገኙት አክቲቪስቶች ከምርጫው በፊት በርካታ ሚስጥራዊ ካሜራዎችን ገዝተው ወደአገር ውስጥ ማስገባት ችለው ስለነበረ ከምርጫው በኋላ በምርጫው ውጤት ያፈረው የኢራን መንግሥት የወሰደው ርምጃ በዓለም የቴለቪዥን መስኮት ሊናኝና ከፍተኛ ውግዘት ሊያደርስበት በቅቷል። በገንዘብ የተሻለ አቅም ያለውና ለቴክኖሎጂ ቅርብ የሆነው ኢትዮጵያዊው ዳያስፖራ በዚህ በኩል ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ማድረግ ይኖርበታል።

(ይቀጥላል)

 

ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆቿ ሥራ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!

 

  „ከአዞ ዕንባ –ከዝንብ ማር አይጠበቅም“ (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 11.12.2014 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

ውዶቼ – የእኔዎቹ አንድ ነገር ከተሳራ በኋላ ተከፍቶ ቢያድር ተወሳክ ይገባበታል። ለጤናም ይበክላል። ጹሑፉ ቅናዊ ቢሆንም ትንሽ ማነፃጸሪያዎችን በማቅረብ ሃስብን መሰብስብ የዘበኝነት ተግባሬ ግድ ስለሚለው ተፃፈ።

de
መቼም ቅጥል – እርር – ካሉ ቅን ወገኔ የተጻፈ „ አሳዛኙ ውርዴታችን“ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/37001 በሚል እርስ አንድ አጠር ያለ ጹሁፍ ከዘሃበሻ አሁን አነበብኩኝ። ወንድምዓለም / እህትአለም/ „ከአዞ ዕንባ – ከዝንብ ማር“ እኔ አልጠብቅም። ሃውዚ ላይ ዕልፎች ሲያልቁ ካሜራውን ደቅኖ ለፖለቲካ ትርፍ ወገኑን ከጨረሰ አረመኔ ተስፈኛ እኔይቱ አልሆንም። በራህብ ለሚያልቁት ወገኖቼ ብሎ ላገኘው ገንዘብ ወያኔ፤ ማወራራጃው አሽዋ ነበር። ለደምና ለሥጋዎቹ ብጣቂ ሳይራራላቸው ለእናንተ ነው እያለ፤ እዬማለና እተገዘተ አሸዋ ሰፍሮ ነው ሞታቸውን ያወጀው። በልግ፣ መህር ሲደርስ እልፎች ከቀያቸው ሲነቀሉ – ባለቤት የላቸውም። ከእርሻ ማሳቸው የሚነቀሉት እኮ ህይወታቸው ሞት ነው።

እስኪ አንድ ነገር ልጠይቅ ጸሐፊውን … ወያኔ እነዚህ ወጎኖቻችን ማለቃቸውን ምክንያት አድርጎ የሀዘን ቀን ቢያውጅ፤ ጥቁር ለብሶ ቢውል ከቶ ሆድ ይሆነዎት ይሆን?

የሚገርመዎት አደጋውን ያደረሰችው ጀልባ ብቻውን ብትመለስ ሞቱን የሰሙ ወጣቶች እኔ እቀድም እኔ እቀድም ብለው ተሳፍረው ወደ ቀጣይ መዋዕቲነት መሄዳቸው አይቀሬ ነው። ከዚህ ጋርም ሌላ ነገር ማንሳት እሻለሁ። እሰረኞችን ወያኔ ቢፈታ፤ ሌላ ባለተራ ግበቶ ደግሞ ይማቅቃል። የአረብ ሀገሩ ትዕይንት በሚመለከት በቅብ ወያኔ ሲያረገርግ የመሰላቸው ወገኖች ሊኖሩ ይችሉ ይሆናል። ነገር ግን ያን ሁሉ መከራ ተቀብለው ሀገራቸው ገቡ ተብሎ ከተደመጠው ዲስኩር ጀርባ እኛ ያላዬነውና ያልሰማነው፤ ያልደረስንበትም ስንት የበቀል እርምጃ ተወስዶ ይሆን?! ፊት ለፊት በወጡት ላይ …. ሆነ መጠጊያ ባጡት ላይ። ዋናው ልናተኩርበት የሚገባው መሰረታዊ አውራ ተግባር የችግሩ ምንጭ ምን እንደሆን ከጋራ ስምምነት መድረስን ነው። መርዛማ ምንጭ ከምንጩ ነው ሊደርቅ የሚገባው። በስተቀር ተፋሰሱ ሁሉ ብክል ስለሆነ – አይምሬ ነው። ይህ ማለት የችግሩን ምንጭ ማውቅ እስካልተቻለ ድረስ መፍትሄ ሊገኝ ከቶውንም አይቻልም። እንግሊዘች „የችግሩን ምንጭ ማወቅ ለችግሩ ግማሹ መፍትሄ እንደ ተገኘ ይቆጠራል“ ማለታቸው፤ የችግሩ ጥልቀት – ስፋትና መጠን፤ ልኩን መፍትሄውን ሆነ ጉልበታምና የማያዳግም መፍትሄ አምንጪ ያደርገዋል ለማለት ነው። በእኛም ሀገር „በሽታውን ያልተናገረ መዳህኒት አያገኝም“ ይባል የለ። እንደዛ ነው።

ሌላው የተነሳው „መንግሥት“ በሚመለከት ነው። ጎሳ ላይ የጎሳ አለቃ እንጂ መንግሥት እድገቱ አይፈቅድለትም። ከቤተሰብ ቀጥሎ ባለው ጎሳ ውስጥ መንግሥት አለ ከተባለ፤ ቤተሰብ ላይ የመንግሥት besement አለ ማለት ነው። ስለዚህ ትንሽ ወደ ውስጥ ዘልቀን እንመርምረው። እርግጥ ነው ከቀደሙ ሥርዓቶች የተወረሱት ኢትዮጵያዊ ተቋማትን አፍልሶ ከኢትዮጵያዊነት ጋር አይገናኙም ያላቸው መዋቅሮች ወያኔ አሉት። ቀድመው የተደራጁ ስለነበር። ነገር ግን ባዶ ግድግዳ ጣሬያ የሚሆነውን ቆርቆሮ ወይንም እሳር ካለበሰ – ቤት ሊሆን አይችልም። „ቤት“ የቤትነት መስፈርቱን ካላሟላ ህይወትን ሊያቆይ አይችልም። የወያኔም መዋቅራዊ ቅራቅንቦው ይሄው ነው። ግጭትና ስበቱም እኮ የማይገናኙ ነገሮች በግድ ተሳበቁ ተብለው ነው እኮ?!

d2በተያያዥነት የተነሳው ጉዳይ „አሳዛኝ“ መቼ አባርቶ አውቆ። መርዶ ነው ደመር* ነው ዕጣ ፈንታችን።  „ውርደት“ ለሚለው ግን አልተመቸኝም። እኛ ምን ሆነን እንዋረዳለን?! ፈጻሚው አንገቱን ይድፋበት፤ ቀልብ ተሰፋሪው አንገቱን ያቀርቅርበት? ይልቅ እኛ እንዲህ የነገ ተስፋ እዬተዳፋ ባህር ውስጥ የሚደፋበትን ሳቢያውን ሳይሆን፤ የአምክንዮውን ምክንያታዊ መቅኖ በማወቅ …. የዓለም ዕድገት ደረጃና ዘመኑ የፈቀደለት ሥርዓት በኢትዮጵያ እንዲሰፍን መንፈሳችን መሞረድ ነው – መፍትሄው። ሞቱ ይቀጥላል …. ግፉም ይቀጥላል ወያኔ አስካለ ድረስ። ተጠግኖም አይድንም – ነዳላው ብዙ ነውና። ስለዚህ ሊገፋ የሚገባው ነገር፤ የህዝብ ፈቃድ የሚገዛው፤ የሚያስተዳድረው  አዲስ ሥራዓትን ለመፍጠር „በቃንን!“ ወደ አደገ ደረጃ ማድረስ ነው ቁም ነገሩ።

በተጨማሪነት የተነሳው የአሜሪካ አንባሳደር ሃዘናቸው መግለጻቸው ነው። ይህ በሁለት መልክ ሊታይ ይችላል። አንደኛው ከሰብዕዊነት አንፃር ቀኑም የሰብዕዊ መብት ቀን መሆኑ፤ ሁለተኛው ደግሞ ባሉበት ሀገር ለሚፈጸመው ግፍ ቸል ቢሉ የዓለም – ዐቀፉን ማህበረሰብ ወቀሳ ሽሽትም ጭምር ነው። ወቀሳውን አይችሉትም። እንዲሁም በቀጣይ ምርጫውም ላይ የሥልጣን ሚዛኑ ላደላው ዲሞክራት ፓርቲ ከፍ ያለ ተጽዕኖም አለው – በስፋት ሲታይ ጉዳዩ። በተረፈ ቅርበታቸውና ሀዘናችን ሃዘናቸው መሆኑ ያስመስግናቸዋል። ነገር ግን  ዬአሜሪካ መንግሥት የነፃነት ቀማኛ ሥርዓትን ከማንቆለባበስ ተቆጥቦ እኛም ሰውነን እና አዲስ ዕይታ እንዲኖረው ተጽዕኖ ማሳደር የሚችሉበት ሁኔታ ሲፈጠር፤ ይሄ በቅብ የተሽቆጠቆጠው የወያኔ ምስል ቀርቶ ሃዘኑ ሃቁን የመግለጥና የማጋላጥ አቅም አንዲኖረው ከማደረጉ ላይ ነው ብልሃቱ ያለው። ለዚህ ተግተው ከቀጠሉበት – ማለፊያ ነው። በስተቀር ግን …..

ወያኔ እስከ አለ ድረስ የነገ ኢትዮጵያ ተስፋም እንዲህ አመድ ተላብሶ፤ አመድ ቅሞ፤ የተፈጥሮ ገላ ወዙ በጉስቁልና የሚኖሩበት ሥርዓት  ለአፍታ ለድርደር የሚቀርብ ሊሆን አይገባም። እንደ ህዝብ እረኛም ሊታይ አይገባም። ዛሬ እኮ እኛ ትተነዋል። መሰረታዊ የሰው ልጆች አስፈላጊ ጉዳዮችን። መጠለያ፤ ከፈን፤ ምግብ፤ ንጹህ ውሃ ት/ቤት …. እንደ ቅንጦት ከተቆጠሩ ዓመታት ተቆጠሩ። ስለምን? ወገን በባዕቱ ድህነቱን ችሎ መኖር አልቻለም። ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ እስረኛ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፤ የጭንቀት በሽታም ተጠቂም ነው። ከሥጋት፣ ከፍርሃት ቀጥሎ የመንፈስ ጫና ያለው በሽታ በዬጓዳው እንዳሻው እዬተወራኘ ነው። ለመሆኑ ለ90 ሚሊዮን ስንት የሥነ – ልቦና ባለሙያዎች ከቶ ይኖሩን?!

ክውና – የነገ ተስፋ እንዲህ ነው …. አሮ – ጠውልጎ  – አፈር …. ለብሶ፤ አይመስሉ መስሎ፤ አይሆኑቱን ሆኖ – አፈር ቅሞ፤ ትቢያ ተንተርሶ፤ ትቢያን ተማምኖ፤ ትቢያን መጠለያ አድርጎ፤ ትቢያን ጉርሱ አድርጎ፤ ትቢያን ከፈኑ አድርጎ፤ ልጆቻችን በዚህ ሁኔታ ላይ ነው የሚገኙት – እ! እም!

  • ደመር … ጠብቆ ነው የሚበበው። ደመረ ከሚለው ቃል የተራባ ነው። ደረበ- ጨመረ – ሰበሰበ ይሆንና በገጠር የጋራ የለቅሶ ቀን ተቀጥሮ በወል ዕንባ የሚፈስበት የዕንባ ምጥ ቀለበት ቀን ማለት ነው።

እልፍ ነን እና እልፍነታችን በተግባር እልፍ እናድርገው።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 

11ዱ የማዕከላዊ ገራፊዎችን እወቋቸው

$
0
0

ከዳዊት ሰለሞን

በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ጋዜጠኞችን፣ፖለቲከኞችን፣የሀይማኖት ምሁራንና ያለ ምንም ተሳትፎ ኦሮሞዎች በመሆናቸው ብቻ በኦነግነት ተጠርጥረው ታስረው የነበሩ መተኪያ አልባ ዜጎችን በማሰር ቃላት ሊገልጸውና የሰው ልጅ ሊሸከመው አይችልም ተብሎ የሚታሰብን ሰቅጣጭ ድርጊት በመፈጸም ረገድ ወደር የሌላቸው ገራፊዎች ስም ዝርዝር ይፋ ተደርጓል፡፡እነዚህ ሰዎች አሁንም በዚሁ ድርጊታቸው ጸንተው ወንድሞቻችንን እያሰቃዩ የሚገኙ በመሆናቸው ህዝብ ሊያውቃቸውና ቀን ሲወጣም ፍትህ ሊጠይቅባቸው ይገባዋል፡፡
ethiopia-torture-620
ስማቸው የተጠቀሱትን ሰዎች የምታውቁ አልያም በእነዚህ ሰዎች በማዕከላዊ ምርመራ ወቅት ስቃይ የደረሰባችሁ ዜጎች መረጃውን ልታዳብሩት ወይም ሊጨመሩ የሚገባቸውን ገራፊዎች ልታጋልጡ ትችላላችሁ፡፡

ገራፊዎቹ ነጭ ወረቀት በማቅረብ ተጠርጣሪዎች ፊርማቸውን እንዲያኖሩ የሚያስገድዱ፣ገልብጠው የሚገርፉ፣በወንድ ብልት ላይ ውሃ የተሞላ ላስቲክ በማንጠልጠል የሚያሰቃዩ፣ሴት እስረኞችን ጡታቸውን በበትር የሚደበድቡ፣ሰውን ካልደበደቡ ስራ ያልሰሩ የሚመስላቸው ቃሉ ከገለጻቸው ‹‹አረመኔዎች››ናቸው፡፡ምናልባት የፍትህ ጸሀይ ወጥታ ህዝብ አሸናፊ ሲሆን እነዚህ ሰዎች ይፈጽሙ የነበሩትን ግፍ በአደባባይ እንዲመሰክሩ ይደረጉ ይሆናል፡፡

ቤተሰብ፣ ዘመድ፣ወዳጆቻቸውም ስማቸውን ተመልክተው የህሊና ዕዳ ይፈጥሩባቸው ይሆናልና ስማቸውን ይፋ ማድረጉ ብዙ ጥቅም ይኖረዋል ባይ ነኝ፡፡

1. ታደሰ መሰረት የማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ኃላፊ
2. ዩሀንስ ኢንስፔክተር
3. ተዘራ ቦጋለ ኢንስፔክተር
4. ብርሃነ ኢንስፔክተር
5. ከተማ ኢንስፔክተር
6. ሰይድ አሊ ኢንስፔክተር
7. ገብረመድህን ኑር ኢንስፔክተር
8. ሙልጌታ ኢንስፔክተር
9. አሰፋ ትኩት ምክትል ኢንስፔክተር
10. ታደሰ አያሌው ኢንስፔክተር
11. በለጠ ኢንስፔክተር

ውይ! አምባሳደሩ ተናገሩ!

$
0
0

ወንድሙ መኰንን፣ ብሪታኒያ

የዛሬ 30 ዓመት ገደማ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሒሣብ መዝገበ አያያዝ ትምሐርት አስተምር ነበር። ዛሬም በሱው ነው እንጀራዬን በስደት ዓለም ከስቃይ ጋር እንደወጥ እያጣቀስኩ የምበላው። ታዲያ ያኔ፣ የመምሕራን ካፌቴሪያ ለምሳ በየጠረጴዛው ዙሪያ በቡድን በቡድን እየተሰበሰብን አንዳንድ ክፍል ውስጥ ያጋጠሙን ገጠመኞች እያነሳን እንስቅ ነበር። አንድ ዕውቅ የኢኮኖሚክስ መምሕር ነበሩ። እግዚአብሔር ይመስገንና፣ ዛሬም በሕይወት አሉ። ስማቸውን ግን አልጠቅስም። ታዲያ አንድ ቀን ከጎናችን ካለው ጠረጴዛ ላይ ሁነው ምሳ እየበሉ ከሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር በዕለቱ ያጋጠማቸውን አስቂኝ ክስተት ሲገልጹ፣ ጆሮዬን ጣል አድርጌ እንደዋዛ እሰማቸው ነበር። ነገሩ እንዲህ ነው። አንዳንድ ጠጠር ያሉ የኢኮኖሚክስ ጽንሰ-ሀሳቦችን አንስተው ሲያስተምሩ፣ አንድ ወጣት ተማሪ ነገሩ ከብዶት ነው መሰል፣ ሳያስበው እንቅልፍ ይዞት ለሽ ይላል። ያንን ያዩት ዕውቁ የኢኮኖሚክስ ባለሙያ፣ ድምጻቸውን በድንገት በጣም ክፍ በማድረግ፣ ጮክ ብለው ማስተማር ይጀምራሉ። እንቅልፉን ይለጥጥ የነበረው ተማሪ በርግጎ ተነስቶ ይቆማል። መምሕር ትኵር ብለው አይተውት፤ “ይቅርታ! ቀሰቀስኩኽ እንዴ? ምን ላድርግ ብለኽ ነው። እንጀራ ነው የሚያስጮኸኝ።” አልኩት ብለው ሲናገሩ ጠረጴዛቸው ዙሪያ የተኮለኮሉት በሳቅ አውካኩ። እኔ ባልስቅም፣ ነገሩን ልብ ብዪ ከጎናቸው ከነበረው ጠረጴዛ እሰማቸው ስለነበር እስካሁን አስታውሰዋለሁ። ታዲያ፣ ዛሬ ይኸንን ምን አስታወሰህ ትሉኝ ይሆናል። አምባሳደር “ብርሀኑ” ከበደ፣ ለሪፖርተር ጋዜጣ የሰጡትን ቃለ-ምልልስ አንድ ወንድሜ ከአገር ቤት አካባቢ አንብቦት እኔም እንዳነበው ስለጋበዘኝ፣ አንብቤ ስጨርስ፣ “ምስኪን! እንጀራ ሁኖባቸው ነው የሚጮኹት” ብዬ እርፍ።

ambassador birhanu kebede አምባሳደር “ብርሀኑ” ከበደን፣ ባልተረዱት ነገር ገብተው፣ አሳዳሪ ጌቶቻቸውን ለማስደስት አንዴ ጀርመን ሬዲዮ ድረስ ደውለው፣ ሌላ ጊዜ፣ ቪኦኤ የአማርኛ ዝግጅት ድረስ ደውለው፣ የሆነውን አልሆነም እያሉ ሲቀሉ ሰምቼአቸው፣ የወንድምነቴን ያክል፣ “ይኸ ነገር አይስማማዎትም። ባይሆን፣ ለመዋሸት – ለመዋሸት፣ ወያኔ ከትግራይ ያስመጣልዎትን ታኮዎች ይጠቁሙና፣ እነሱ ይዋሽልዎት። እርስዎ ምን በወጣዎት” ብዬ መከሬአቸው ነበር። በኔ ሞት፣ ያኔ የጻፍኩትን ምክር ከላይ ያለውን ማጣቀሻ፣ ወይም የግርጌ ማስታወሻው ጠቁመው፣ ወንድማዊ ምክሬን አንብቡልኝ። እንደማይከፉ ቃል እገባልዎታለሁ። ታዲያ ወያኔ ካልሆኑ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ፣ በዛሬ ጊዜ አሁን ማን እንዲህ ያለ ገንቢ ምክር ይለግሳል? ያአውም ለባላንጣችን ታማኝ አገልጋይ አሽከር! ያንን ምክሬን ሰምተው፣ ለብዙ ጊዜ ዝም በማለታቸው ከእንዲህ ዓይነት ቅሌት እራሳቸውን ቆጥበው ሥራቸውን ብቻ በመሥራት ላይ ነበሩ ብዬ አምኜ ነበር። ምን ያደርጋል! “ድመት መንኵሳ፣ ዓይጧን አትረሳ” ነው የሚባለው? ጠፍቶኝ እንዳይመስላችሁ! አውቄ አጣምሜው ነው።

አምባሳደር ብርሀኑ፣ ከደርግ ዘመን ጀምረው ቀጣሪዎቻቸውን በማስደስት በሥራ የታወቁ ናቸው። የቤልጀየሙ ሥራቸው እንዳለ ሁኖ፣ ለንደን ከመጡ በኋላ፣ ለወያኔ የሠሩትን ውለታ፣ በአውሮፓ ያሉት የወያኔ ጉዳይ አስፈጻሚዎች የሠሩት በሙሉ ተሰብስቦ ቢደመር የለንደኑን አያክልም። ስለዚህ እራሳቸው እንዲህ እያሉ ስለራሳቸው ይመሰክራሉ።

“ለዓለም ገበያ ለሽያጭ የቀረበውን ቦንድ በተመለከተ በውጭ የተሸጠ በጣም ጠቃሚ እንኳን ባይባል፣ የአውሮፓ አጠቃላይ ተደምሮ የዚህ የእንግሊዝ ይበልጣል፡፡ ወደ 1.4 ሚሊዮን ዶላር ቦንድ ሸጠናል፡፡” (ሪፖርተር ታኅሳስ ፩ ቀን ፳፻፯)

ጎበዝ ደላላ! አሻሻጭ! የጠባ የጠነባውን የወያኔ የዘር ፖሊቲካ፣ በአፍዝ አደንግዝ ኪስ ማውለቅ ፕሮፓጋንዳ ሕዝቡን አታሎ ገንዘ መሞሸልቅ፣ መሸጡን ደኅና አድርገው ተክነውበታል። ኧረ እኛም ምስክር ነን። በዚሁ በሪፖርተር ቃለ ምልልስ፣ የእንግሊዝን መንግሥት በማግባባቱ ሥራና የፈጸሙትን ጀብዱ እንዲህ ሲሉ ያስረዳሉ።

ትልቁ ነገር ግን በኢትዮጵያ ኢንቨስት የሚያደርጉ ኢንቨስተሮች ትልልቆች ናቸው፡፡ ለአብነት ለመጥቀስ ዲያጆ የሚባለው በኢትዮጵያ ውስጥ በ225 ሚሊዮን ዶላር ሜታ ቢራ ፋብሪካን ገዝቷል፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ 100 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት አድርጓል፡፡ ስለዚህ በአጠቃላይ 325 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት አለው ማለት ነው፡፡ ዩኒሊቨር የሚባለው ትልቁ የመልቲላተራል ኩባንያ በኢትዮጵያ ውስጥ የመጀመርያ የኢንቨስትመንት ኦፕሬሽን እየጀመረ ነው ያለው፡፡ ሦስተኛ ፒተርድ የሚባለው የቆዳ ውጤቶች አምራቾች ድርጅት ለሰባ ዓመታት ጥሬ ቆዳ ይገዛ የነበረው በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ሦስት ፋብሪካዎች ሠርቶ ከ1,500 እስከ 2,000 ሠራተኞች ቀጥሮ እያሠራ ይገኛል፡፡ ይኼም የታወቀ ብራንድ ስለሆነ የቆዳ ውጤቶቹ ብሪቲሽ ኤርዌይስ የሚጠቀምበት ትልልቅ ሱቆች ውስጥ እየገባ ነው፡፡ ሌላ በማዕድን ፍለጋ ስንሄድ ታሎ በነደጅ ፍለጋ ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቁ ካምፓኒ ነው፡፡

አሁንም ይሄ የሚያሳየው ሰውዬው በተሰለፉበት ሥራ ውጤታማ መሆናቸውን ነው። ነገር ማበላሸት የሚጀምሩት፣ ጋዜጠኛው ወደማይሸጠው የወያኔ ፖሊቲካ ሲመራቸው ነው። እኔ እሳቸውን ብሆን፣ “እዚህ ጋ ወራጅ አለ” እል ነበር።

ሪፖርተር፡ “ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ መንግሥት በቁጥጥር ሥር የዋሉት የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸውን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ በተመለከተ የእንግሊዝ መንግሥት ስሜት ምንድን ነው? ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን (በግላቸው) ለኢትዮጵያ መንግሥት የመማፀኛ ደብዳቤ መጻፋቸው ይነገራል፡” ለሚለው ጥያቄው መልስ ሲሰጡ፣  “ጉዳዩ ይህን ያህል ትልቅ ጫና የለውም፡፡ ነገር ግን ግለሰቡ የእንግሊዝ ዜጋ እንደመሆኑ መጠን በእንግሊዝ መንግሥት የሆኑ ዕርምጃዎች መወሰድ አለባቸው የሚሉ አሉ፡፡  ሰውየው ለምን ታሰረ የሚል አይደለም፡፡ በሕግ ይዳኝ የሚል ነገር ነው፡፡” ሲሉ አቃለው ተናግረዋል። አንዳርጋቸውንም ሲከሱ፣ ያላንዳች ሀፍረት እንዲህ ብለዋል።

ይኼ ሰውዬ የሽብር ተግባር ላይ ገብቷል፡፡ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ከሚፈልጉ ኃይሎች ጋር እጅና ጓንት ሆኖ ይሠራ ነበር፡፡ ሦስተኛ ራሱም ይህንን አምኗል፡፡ ብዙ ጊዜ እጅ ከፍንጅ የተያዙና የታሰሩ ሰዎች እሱ እንደሚያሠለጥናቸውና የቡድኑ መሪ እንደሆነ፣ ከኤርትራ መንግሥት ጋር አብሮ እንደሚሠራ በግልጽ ያስቀመጠው ነገር አለ፡፡ እሱ እንደተያዘ ግንቦት ሰባት የሚባለው ድርጅት ራሱ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጦርነት ነው ያወጀው፡፡ 

አዪዪዪ! “አይ አለማወቅሽ፣ አገርሽ መራቁ አለ ሰውዬው!” ለመሆኑ፣ የወያኔው ወኪል፣ አሳዳሪ ጌታቸው ወያኔ ትላንትና ከሻዕቢያ ጋር አብሮ ኢትዮጵያን ሲያደማ እንደነበሩ ያውቁት ኑሯል? እንዴታ! በድንብ ነው እንጂ! የኤርትራን “ናጽነት” ዕውን ለማድረግ የስንት ኢትዮጵያዊን ደም አብረው እንዳአፈሰሱ ዘንግተውታል ማለት አይቻልም። የደርግ ዲፕሎማት በነበሩበት ጊዜ የወያኔና የሻዕቢያን አደገኛ አካሄድ የሀገር ክህደት መሆን ሲያብራሩ አልነብሩምን? ለመሆኑ ዛሬዎቹ ወያኔ ባለሥልጣናት እና ሞት የገላገለን የኢትዮጵያ ጠቅልላይ ሥቃይ አልነበሩም፣ “የተገነጠለችውን የኢትዮጵያን ጠቅላይ ግዛት እንዳገር ዕወቁልን” ብለው በአፍሪካ አንድነትና በተባበሩት መንግሥታት ኮሪዶሮች ኮሮጆ ተሸክመው ሲሯሯጡ የነበሩት? እሱ ነው ድርጊት ነው በታሪክ ዓይን የአወጣ የአገር ክህደት! በዚህ ወራዳ ድርጊታቸው የዓለም መንግሥታትን አስደምመው አልነበረም። ለመሆኑ ኢትዮጵያን ያለወደብ ያስቀራት ከሀዲ መንጋ፣ አንዳርጋቸው ነው ወይስ የወያኔ ዘረኛ ወራሪ? አምባሳደሩ፣ ምን አለ ቁስል ያለበትን ቦታ እየመረጡ ባይነካኩ? ሻዕቢያን በተመለከተ፣ ወያኔ የሞራል ብቃት የለውም ማንንም ለመወንጀል። ነገሩ፣ “የትላንትናውን የወንጀል ባልደረባዬን አትቀሙኝ” ወይንም “ባሌን አትቀሚኝ” ዓይነት ቂመኝነት ነው። ትላንት ከሻዕቢያ ጋር “በአንድ አልጋ ካልተኛን፣ በአንድ ጉድጓድ ካ…” ብለው እነፕሮፌሰር አሥራትን የመሰሉትን ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጆች ያስገደሉ ገንጣይ አስገንጣይ አገር ሻጮች፣ ዛሬ ደርሰው ከኤርትራ ጋር የተጎዳኘን ሁሉ “ዓይንህን ላፈር” ማለት ሌብነት እንጂ ምን ሊባል ነው? አምባሳደር እዚያ አካባቢ ወያኔን የረከሰ ፖሊቲካ ለመሸጥ ባይሞክሩ ጥሩ ነበር። ለምን ቢሉኝ፣ ሰውየው “እናቴን ያገባ ሁሉ አባቴ ነው” እንዳለው ነገም ዴሞክራሲያዊ የሆነ መንግሥት ኢትዮጵያ ውስጥ በግድም ሆነ በውድ ቢቋቋም፣ በተማሩት ሙያና በአካበቱት ልምድ ገዢዎቹን ሳይሆን ኢትዮጵያን ሊያገለግሉ ይቻላሉና፣ እንዳናምርርብዎት፣ የብዙዎቻችንን ቆሽት ከሚያድብን ንግግር ራቅ ቢሉ ነገም የመሥራት ዕድል ይኖርዎት ነበር።

ሰውዬው ከዚያም አልፎ ተርፎ፣ እነ አመንስቲ ኢንተርናሽናል፣ እነ ሕይማን ራይትስ ዎትች አልቀሩአቸውም። እንዲህም እስከማለት በቅተዋል።

“ተፅዕኖ የሚፈጥሩ ድርጅቶች አሉ፡፡ እነ ሂውማን ራይትስ ዎች እና እነ አምኒስቲ ኢንተርናሽናል አሉ፡፡ እነሱ በመንግሥት ላይ የሚቀሰቅሱት ውንጀላ ይቀጥላል፡፡ ውንጀላቸው መሠረት የለውም፡፡ ዲሞክራሲ በአንድ ሌሊት የምትፈጥረው አይደለም፡፡ የእንግሊዝ ወይም የኖርዌይ ዓይነት ካልሆነ ብለህ ዲሞክራሲ አይደለም ብለህ ልትፈርጅ አትችልም፡፡”

“አወቅኩሽ ናቅኩሽ” አለ አሉ ሰውዬው። እነዚህ ግዙፍ ድርጅቶች በዓለም ዙሪያ በሰብዓዊ መብት ተሟጋችነታቸውና ተአማኒነታቸው እንደ ሐውልት የተተከሉ ናቸው። እነዚህን የትም አይደርሱም፣ አሉታዊ ተጽዕኖም አያደርሱም ማለት ጅልነት ነው። እነዚህ ድርጆቶች እኮ ናቸው ደርግ በጥይት ሐሩር ሲያራውጣቸው በዓለም ጥብቅና ቁመውላቸው ሲሟገቱላቸው የነበሩት። ያኔ ሲሰደዱ፣ ወዳጆቻቸው ነበሩ። ዛሬ እነሱ አሳዳጆች ሲሆኑ፣ ከጠላት ቆጠሩአቸው? ዓለም ተለዋዋጭ ናት። እንኳን እነዚህ በ17 መርፌ የተጠቀመ ቡቲቶ ለብሰው ልሥልጣን የበቁ ወንበዴዎችና፣ የሮም መንግሥትም ወድቋል። የማይበገር የሚመሰለው የሶብየት ሕብረትም መንግሥት ፈራርሷል። አሳዳጆቹ በተራቸው እንደሚሰደዱ ጥርጥር የለንም። የጊዜ ጉዳይ ነው። ያቺ ቀን እንደገና ብቅ ስትል፣ ዓይናቸውን በጨው አጥበው፣ “ጥብቅና ቁሙልን” ሊሉ ነው እነዚህ ዓይን አውጣዎች። የአሜሪካና የእንግሊዝ መንግሥታት ወያኔ የጸረ-ሽብር ዘመቻ የቃል ኪዳን አጋራቸው ስለሆነች እነዚህን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን ጩኸት ቦታ እንደማይሰጡአቸው ተናግረዋል። እንግሊዝን በተመለከተም እንዲህ ብለዋል።

“የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ የመጣ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ውስጥ አንደኛ ደረጃ ይዛ ትገኛለች፡፡ በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግንኙነቱ ዘርፈ ብዙ እየሆነ ነው የመጣው፡፡ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው ዕርዳታ እንግሊዞች ‹‹Value for Money›› [ገንዘብን ለታሰበለት ዓላማ ማዋል] በሚል መርህ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰጠው ዕርዳታ ለትክክለኛ ዓላማው እየዋለ መሆኑንና የሕዝብን ሕይወት በመለወጥ ተግባራዊ እየሆነ መሆኑን በደንብ አስቀምጠዋል፡፡ እንደ ምሳሌም ይጠቅሱታል፡፡”

ይኸ እንግዲህ፣ “እኛ አሽከራቸው እስከሆን ድረስ ንዋዩን ያለምንም ጥያቄ ያፈሱልናል” የሚል የሚመስል ድምዳሜ ነው። ግን አምባሳደሩም ሆነ የሪፖርተር ዘጋቢ አንድ ነገር ረስተዋል። በየዓመቱ የሚወጣው የዩኤስ ስቴት ደፓርትመንት የሰብዓዊ መብት ረገጣ በኢትዮጵያ ዘገባ፣ አለማንሳታቸው አይግርምም? ዘንድሮም ተመሳሳይ ዘገባ በዪኬ መንግሥት ወጥቱአል። የአውሮፓ ሰብዓዊ መብት ኮሚሺን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ሰፕቴምበር 24 ቀን 2014 የተወያየበት የወያኔ አፈና፣ የአንዳርጋቸው ጠለፋ፣ የጋዜጠኞች መታፈን፣ “የጸር-ሽብርተኝነት ሕግ”፣ የጋዜጠኝነት ሕግ፣ የመያድ ሕግን በተመለከተ፣ ኃላፊነት የሚሰማው መንግሥት ሳይሆን ጋጠ-ወጥ የሆነ ማፊያ ቡድን ኢትዮጵያን የሚያስተዳድር እስኪመስል ተወያይቶባታል። “እኔ አላይም” ለማለት ካልሆነ፣ እንደሰጎን አንገትን አሸዋ ውስጥ ቀርቅሮ፣ አደጋ ሲመጣ መሸሸግ መላ ሰውነትን ከሞት አያድንም። አምባሳደር “ብርሀኑ” ከበደ፣ ጸሐይ የሞቀውን፣ ዓለም ያወቀን የሰብዓዊ መብት ረገጣ በኢትዮጵያ “የለም” ብሎ ድርቅ ብሎ መሸፋፈን አይቻልምና፣ ያንን ለመከላከል መሞከር ትዝብት ላይ ይጥላል። አምባሳደር! 23 ዓመት እኮ አንድ ሌሊት አይደለም። ደግሞ ዴሞክራሲ በአንድ ሌሊት አይሠራም እያሉ የዘባነኑብናል። የሰው ልጅ መብት ረገጣ በኢትዮጵያ ውስጥ ከደርግ ዘመን በላይ አሁን ብሶበታል!

ሌላው በጣም የገረመኝ አንድ ነገር፣ ሳይጠየቁ የዘበዘቡት፣ የኛ ዲያስፖራ የተባልን፣ “የጥቂቶቹ” ወያኔ ቁጥጥር ሥር አንውልም ብሎ አሻፈረኝነት ጉዳይ ነው። አምባሳደር ሆዬ “አገር ቤት የሚካሄዱትን አዎንታዊ ለውጦችን፣ ልማቶችን ማየት አለባቸው” ካሉ በኋላ እንዲህ ነበር ያሉት።

ልንታሰር ይሆናል የሚል ፍርኃት ያላቸው አሉ፡፡ ኢሕአዴግ 90 ሚሊዮን ሕዝብ የሚመራ ድርጅት ነው፡፡ እገሌ ወጣ እገሌ ገባ ብሎ ለመቆጣጠር ጊዜም የለውም፡፡ አንድም የተሳሳተ አመለካከት ነው አልያም ለራስ የሚሰጡት ግምት ነው፡፡ ሰው ከገደሉ ወይም ሌላ ወንጀል ከፈጸሙ ኢሕአዴግም ማንም አያድናቸውም፡፡ ሕግ ነው የሚመለከታቸው፡፡ ኤርፖርት ላይ እንደሚታነቁ የሚያምኑ ሰዎች አሉ፡፡ ኢሕአዴግ ግን ስለመኖራቸውም አያውቅም፡፡ 

ወቸ ጉድ! ከተናግሮ አናጋሪ ይሠውራችኹ! ሪፖርተር ይኽቺን ‹‹ኤርፖርት ላይ እንደሚታነቁ የሚያምኑ ሰዎች ቢኖሩም ኢሕአዴግ ግን ስለመኖራቸውም አያውቅም›› የምትለዋን ሐረግ መዝዞ ነው እንደ አርዕስት የተጠቀመባት። አይ አምባሳደር! እሶም እንደ አሳዳሪ ጌቶችዎ እንደ ጅል ይቆጥሩን ገቡ እንዴ? እኛ እኮ ከዚያ በላይ ነቄ ነን! ለመሆኑ ወያኔ ሚሊዮን ዶላር አፍስሶ፣ እንደሌባ ሸምቆ፣ ኢትዮጵያ ኤርፖርት ሳይሆን፣ ሰናዓ ኤርፖርት ድረስ መሽጎ፣ ወንድማችንን አንዳርጋቸው ጽጌን የጠለፈው አለመኖሩን ባለማወቁ ኑሯል? ጃታኔ አሊን ኬኒያ ድረስ ቅጥር ነፍሰ ገዳይ ልኮ ሲያስረሽን፣ ውጪ የምንኖረው፣ ተቃዋሚ ዲያስፖራ መዘንጋቱ ነበር። የኢትዮጵያን ኤርፖርት ተውት፣ ከኬኒያ ስንቶቹ ስደተኞች ናቸው እየተፈኑ የተወሰዱት? አቶ ሱሉብ አህመድና አቶ ዓሊ ሁሴን እኮ ከኬኒያ የተጠልፉት በዚህ ዓመት ጃኑዋሪ 26 ቀን መሆኑን ዘንግተውት ይሆን? ለመሆኑ፣ US$23,000,000 ከፍለው የበፊቱን የጋምቤላ አስተዳዳሪ የነበሩትን ኦኬሎ አክዩዪን ከጁባ የጠለፉት አፋኞች፣ ማንንስ ይምራሉ! ክቡር አምባሳደር! ለመሆኑ ስንት የደኅንነት አባል ነው፣ የራስዎ ለንደን የሚገኘው ቢሮዎ የሚያሰማራብን? እነዚህ ጆሮ ጠቢዎች፣ ምን ለመሥራት ይሆን የዘመቱብን? እንዲያው እራስዎ ጅል ሁነው አያጃጅሉን ጃል!

አንድ መርዶ ለአምባሳደር ብርሀኑ ከበደ ልንገራቸው። አንዳርጋቸው ጽጌን መጥለፋችሁ ትልቅ ስሕተት ነው። እስክንድር ነጋን፣ ርዕዮት ዓለሙን፣ አንዱዓለም አራጌን፣  ውብሸት ደሳለኝን፣ ናትህናኤል መኰንንን፣ ምትኩ ዳምጠን፣ የሺዋስ ይሁናለምን፣ ኪንፈሚካኤል ደበበን፣ ኦልባና ሌሊሳን፣ የእስልምና ጉዳይ ተከታታዮችን ወያኔ ሲያስር ለጊዜው ተናደን ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተን ነበር፣ ግን እንደአሁን አላመረርንም። ገንዘብ ልመና የመጡትንም ባለሥልጣኖቻችሁን አሳፍረን መልሰናቸው ነበር፣ ግን አልቀጠልነበትም። አንዳንድ ሆዳሞችን በየማሕበረሰባችን እያስሰረጋችሁ አስገብታችሁ፣ ቤተክርስቲያናችን ሳይቀር በሆዳደር ልማታዊ መንኰሳት ልትቀሙን ስትነሱ እሱን ለማስጣል፣ በተለይ ለንደን ውስጥ ጌቶችዎ የሚሠሩትን ወንጀል ከማጋለጥ ትንሽ ረገብ ብለን ነበር። ወንድማችንን አንዳርጋቸውን ከየመን ያንን ሁሉ ገንዘብ አፍስሳችሁ ስትጠልፉት፣ የተዳፈነውን እሳት ቆስቁሳችሁ አነደዳችሁት። ያውላችሁ ትግሉ ተቀጣጥሎላችኋል። አሁን ሆይ-ሆይ ተበሎ ይብርዳል ብላችሁ እየጠበቃችሁ ነው። እንደ ቋያ እሳት እይተንቀለቀል፣ ነበልባሉ እየጦፈ ነው። እነዚህ “ጥቂት” የሚሉአቸው ሰዎች ናቸው ሎንዶን ላይ 5th September 2014 ከአውሮፓ ሁሉ ተሰብሰበው መንገዱን ያጨናነቁት። ከሁለት ወር በኋላ፣ 7th November 2014 እነዚህ ጥቂት ናቸው፣ የብራሰልሱን Schuman Square ቀውጢ ያደረጉአት! የድሮ መሥርያ ቤትዎ ባልደረቦች፣ ወያኔ እምባሲ ውስጥ የሚሠሩት ሠራተኞች አለንገሩዎትም እንዴ ምን እንደሆነ። ሆ ብሎ ያ ሁለ ሰልፈኛ ወደ ኤምባሲው ሲተም፣ ተደናግጠው፣ ባለአምባሻውን የወያኔ ባንዲራ ከተሰቀለበት አውርደው፣ እዚያ መሬት ላይ ጥለው ነብር ሩጠው ገብተው በራቸውን ዘግተው የተቀረቀሩት! “ድኃን አትናቁ፣ ድኃ እንዴት ይናቃል፣ ትኋን እንኳን በአቅሙ፣ አልጋ ያስለቅቃል!” ሲባል አልሰሙም እንዴ!

እሳቱ ገና አልቆመመ። በዚህ ብቻ መሽ አባርቶ! እነዚህ “ጥቂት” የሚሉአቸው ሰዎች ናቸው ባለሥልጣኖቻችሁን በአሜሪካና በአውሮፓ ከተሞች ሲያሯሩጡአቸው የነበሩት። ዋሽንግተን በየሁለቱ ሳምንት ሰኞ ሰኞ የእንግሊዝ ኤምባሲ ይሸበራል፣ በኢትዮጵያ ሰላማዊ ሰልፎች! በየሁለቱ ሳምንት፣ ዓርብ ዓርብ የለንድን የውጭ ጉዳይ መሥርያ ቤትን በሰላማዊ ሰልፍ ይናወጣል። “የጎዳና ነውጥ ነው የምትሉት? “ምንም ለውጥ” አያመጡም፣ ያሉት፣ እኛ በፈጠርነው ማዕበል እኮ ነው የዩኬ መንግስት £2 ሚሊዮን ፓወንድ የወያኔ ባለሥልጣኖች የሚሰለጥኑበትን ገንዘብ የያዘባችሁ። £20 ሚሊዮን ፓወንድ የደኅንነቶች ስልጠና ፕሮግራማችሁን የተሰረዘው እኮ በድምጻችን ነው!  የኛ እኮ ግፊት ነው፣ ትላልቅ ጋዜጦች፣ እንደ Independent, The Guardian, and The Daily Mail የመሳሰሉት ጋዜጦች መንግሥታቸውን በጥያቄ እንዲያጣድፉ የተገደዱት! በኛና፣ እነዚያ ምንም ለውጥ አያመጡም ያሉአቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ተሟጋቾች፣ እንደ Amnesty International, Human Rights Watch, the Frontline, Pen International, Reprieve, Redress መሆኑን የሚረዳ ጭንቅላት አለዎት? አስተዳዳሪ ጌቶችዎ ካዝና ውስጥ ያለውን የብር ምንዛሪ ደርቆባቸዋል። ለእርስዎና ውጪ ለበተናቸው የደኅንነት ወፈሰማይ የሚከፍለው ደሞዝ አይነሮውም። ያንን መርዶ የዓለም ባንክ ሰሞኑን ነግሮናል። ከዚህ በፊት እንደመከርኩዎት፣ ከስዎ በፊት እንደነበረው አምባሳደር እርስዎም አገር ፈልገው ቢኮበልሉ ከአሁኑ ይሻልዎታል። ዕድሜዎ እየገፋ ነው። እየጨለመብዎት ነው። አሁንም ጨለማው ከበደ። ካረጁ አይበጁ!

አንዳርጋቸው ፅጌ እንዴት ተያዘ? –ከተስፋዬ ገብረአብ (Gadaa)

$
0
0

Andargachew Tsigeአንዳርጋቸው ፅጌን ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት የ2014 የፋሲካ በአል በዋለ ማግስት ነበር። ወደ ለንደን መንገድ ስለነበረው ከተከዜ በረሃ ወደ አስመራ መጥቶ ሳለ ደወለልኝና ተገናኘን። ሳገኘው ታሞ ነበር። ከምግብ ወይም ከውሃ ጋር የተያያዘ ቀላል ህመም እንደሆነ ነገረኝና ወደ ፋርማሲ ሄደን መድሃኒት ገዛን። እየደወልኩ ስለ ጤንነቱ ስጠይቀው ቆየሁ። በሶስተኛው ቀን ተሲያት ላይ ይመስለኛል ወደ ቤቱ ብቅ አልኩ። የግቢውን በር ገፍቼ ስገባ አንዳርጋቸው በሁለት እጆቹ ልሙጥ የባህር ድንጋዮችን ተሸክሞ ቁጭ ብድግ እያለ ስፖርት ሲሰራ አገኘሁት። ማጅር ግንዱ በላብ ርሶአል። ግቢው ውስጥ ካለችው የብርቱካን ዛፍ ላይ ያንጠለጠለውን ፎጣ አንስቶ ላቦቱን ማደራረቅ ያዘ።

በረንዳው ላይ ቁጭ ብለን ጥቂት ካወጋን በሁዋላ ለመሄድ ተነሳሁ። በዚህ ጊዜ ከሶስት ቀናት በሁዋላ ወደ ለንደን ለመሄድ ትኬቱን እንደቆረጠ ገልፆልኝ በነጋታው ምሽት የራት ቆይታ እንድናደርግ ጠየቀኝ። ሁለታችንም በጋራ የምናውቀውን ሰው ስም ጠቅሶም በራት ቆይታው ላይ እንደሚገኝ ጠቆመኝ። ተስማማሁና ቀጠሮ ያዝን።
በነጋታው በቀጠሮአችን መሰረት ተገናኘን። ምንም ልዩ ርእሰ ጉዳይ አልነበረንም። ስለ አካባቢያችን ፖለቲካ ተጨዋወትን። ስለ ግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል አንስቶም ጥቂት ነገረን። በሰው ሃይልና በአንዳንድ አስፈላጊ ተሽከርካሪዎች በመጠናከር ላይ መሆናቸውን፣ ወያኔ ያዳከመውን የኢትዮጵያዊነት ስሜት ለመመለስ የሚሰራው የፖለቲካ ስራ ራሱን የቻለ ጊዜ የሚወስድ ስራ እንደሆነ፣ በጥቅሉ ግን ትግሉ ተስፋ እንዳለው ነበር ያጫወተን። ሞራሉ ጥሩ ነበር። ተስፋ የመቁረጥ ዝንባሌ አላየሁበትም።

ራት እስኪቀርብ፣ “የጀሚላ እናት” በሚል ርእስ ካዘጋጀሁት (በወቅቱ ካልታተመ) መፅሃፍ አንድ ትረካ አነበብኩላቸው። “የአዲሳባ ቀብር” የሚል ነበር። ትረካው ኮሜዲ አይነት ስለነበር እየሳቁ ነበር ያዳመጡኝ። ከእኩለ ሌሊት በፊት መለያየታችን ትዝ ይለኛል። አንዳርጋቸው መኪና ስላልያዘ ቤቱ አድርሼው፣ “መልካም መንገድ” ተመኝቼ ተሰናበትኩት።

ያቺ ምሽት ከአንዳርጋቸው ጋር የመጨረሻ የምተያይባት እለት ትሆናለች ብዬ ግን እንዴት ማሰብ ይቻላል?
አሁንም ቢሆን ለዘልአለሙ አንተያይም ብዬ አልደመደምኩም። ሌላው ቀርቶ ይህች መጣጥፍ እንኳ ካለበት ጉረኖ
ደርሳ ሊያነባት እንደሚችል ተስፋ አደርጋለሁ።

ስለነገ ማንም አያውቅም። መለስ ዜናዊ ከግርማ ወልደጊዮርጊስ ቀድሞ ይሞታል ብሎ ሊያስብና ሊገምት
የሚችል ማንም አልነበረም። ደካማና በቀላሉ ተሰባሪ የሆነች ነፍሳችን ከአስር ደቂቃ በሁዋላ ምን ሊገጥማት
እንደሚችል እንኳ አናውቅም። ተስፋ ግን በልባችን ሞልቶ ተርፎአል። ስለዚህም ሰዎች በተስፋ ይኖራሉ። ሰዎች
በተስፋ አሻግረው ያልማሉ። ሰዎች በተስፋ እርቀው ይጓዛሉ…

ደጋግሜ እንደገለፅኩት አንዳርጋቸው ከነሙሉ ችግሮቹ ብርቱ ሰው ነበር። አንዳርጋቸው አደጋ ላይ
በመውደቁ ኢትዮጵያውያን “የአንድነት ሃይል” ፖለቲከኞች ትልቅ ሰው ጎድሎባቸዋል። ርግጥ ነው፣ ከአንዳርጋቸውጋር ስናወጋ የኦሮሞ ጉዳይ ከተነሳ ተግባብተን አናውቅም። አንዳርጋቸው በያዘው የፖለቲካ አቋም ከሰፊው የኦሮሞ
ህዝብ ደጋፊ ሊያገኝ እንደማይችል መናገሬም አልቀረ። በተለያዩ ፅሁፎች የማንፀባርቀውን አቋም አነሳ ነበር። አንድ
ጊዜ በወግ መሃል፣

“የታሪክ እስረኛ ላለመሆን ምኒልክ የኦሮሞ ህዝብ ላይ ለፈፀመው ግፍ ይቅርታ ጠይቃችሁ አጀንዳውን
ለመዝጋት ለምን አትሞክሩም?” ብዬ ጠይቄው በአነጋገሬ በጣም መቆጣቱን አስታውሳለሁ።

አንዳርጋቸው ለአማራ ብቻ ሳይሆን፣ ለትግራዩም፣ ለኦሮሞውም በአጠቃላይ ለመላ ኢትዮጵያውያን
የሚጠቅም የፖለቲካ መስመር ተከትያለሁ ብሎ በጥብቅ ያምናል። ለነገሩ ወያኔም እንዲሁ ይላል። ኢህአፓም
ይህንኑ ይላል። ሞአ-አንበሳ እንኳ በአቅሟ የዘውድ መመለስ ለኢትዮጵያ አንድነት ፍቱን መፍትሄ መሆኑን
ትሰብካለች። ፈላስፋው ዘርአያእቆብ እንደጠየቀን ‘ሁሉም የኔ መስመር ትክክል ነው’ የሚል ከሆነ ‘በዚህ መካከል
ማነው ፈራጅ?’ የሚል ጥያቄ ይነሳል። ምላሹ ቀላል ነበር። ፈራጅ ሊሆን የሚችለው ህዝብ ነው። የምንመፃደቅበት
ህዝብ ግን የሚሻለውን የመምረጥ እድል አላገኘም…

ሌላ ቀን ደግሞ እንዲሁ ከአንዳርጋቸው ጋር ስንጨዋወት እንዲህ አለኝ፣

“የወያኔ መውደቅ የማይቀር ነው። ከወያኔ መውደቅ በሁዋላ በአገሪቱ ሊፈጠር የሚችለው ክፍተትና
መለያየት ግን በጣም ያሳስበኛል። ከባድ ፈተና ከፊታችን ተደቅኖአል። ለብሄርና ለቋንቋ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ
መስጠት ይጠበቃል። ከፊታችን የተደቀኑትን ቋጥኝ ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያበቃ በቂ ዝግጅት አለን ለማለት ግን
እቸገራለሁ። ችግሩ ምን መሰለህ? መሬት ላይ የሚሰራው ስራ ከፕሮፓጋንዳው ጋር አልተመጣጠነም።
ፕሮፓጋንዳው መቅደሙ አደገኛ ነው።”

አንዳርጋቸው ይህን መሰረታዊ ችግር የሚዳስስና መፍትሄ የሚያስቀምጥ አዲስ መፅሃፍ በመፃፍ ላይ ነበር።
የመፅሃፉን ርእስ “ነፃነትን የማያውቅ ነፃአውጪ – ክፍል ሁለት” እንዳለውም ነግሮኝ ነበር። የመጀመሪያው “ክፍል
አንድ” መፅሃፍ፣ የአርትኦት ስራ ያስፈልገው ስለነበር፣ በአጫጭር አረፍተነገሮችና በቀላል አማርኛ እንድነካካው
ጠይቆኝ በትርፍ ጊዜዬ እያገዝኩት ነበር። ሁለቱንም መፃህፍት አንድ ላይ የማሳተም አሳብ ነበረው።

ወያኔ አንዳርጋቸውን የመን ላይ አሸምቀው እንደያዙት የሰማሁ ቀን በድንጋጤ ደንዝዤ ነበር። ማመን
አቃተኝ። አንዳርጋቸው ከአራት አመታት በላይ ወደ ኤርትራ ሲመላለስ የሱዳንና የየመንን አየር መንገዶች ተጠቅሞ
እንደማያውቅ አውቃለሁ። እኔ አልፎ አልፎ የየመንን መንገድ እንደምጠቀም ስለሚያውቅ፣ “ተው፣ አትመናቸው”
ብሎ ጭምር መክሮኛል። የመን ላይ ‘መንግስት አለ’ ለማለት እንደማይቻል አንዳርጋቸው እያወቀ ምን ሊሆን የመን
ሄደ? ያልተመለሰ ጥያቄ ሆነብኝ።

ዜናውን ስሰማ የተደበላለቀ አሳብ ወደ አእምሮዬ መጣ። ሊሆን የማይችል ጥርጣሬ ነገሮች ጭምር
ረበሹኝ። ዜናውን በሰማሁበት ደቂቃ ስንቱን አወጣሁ፤ ስንቱን አወረድኩ። ማን ዘንድ ደውዬ ማንን እንደምጠይቅ
ግራ ገባኝ። በመጨረሻ ወደ አንዳርጋቸው ዘመዶች እየበረርኩ ሄድኩ።

አስመራ ላይ አንዳርጋቸው “ዘመዶች” አሉት። የስጋ ዘመዶቹ አይደሉም። አዲስአበባ ጎረቤቶቹ የነበሩ
ናቸው። ነገሩ እንኳ ከጉርብትና በላይ ነው። አንዳርጋቸው ወጣት የኢህአፓ አባል ሆኖ ሲንቀሳቀስ የደርግ አፋኞች
ሊገድሉት ያሳድዱት ነበር። ወንድሙንና አንድ ኤርትራዊ ጓደኛውን ጎዳና ላይ ሲረሽኑበት አንዳርጋቸው የሚገባበት
ቀዳዳ አልነበረውም። በዚህ ችግር መሃል፣ የእናቱ ጓደኛ የነበረች አንዲት ኤርትራዊት ሴት አንዳርጋቸውን ወደ
አስመራ በመውሰድ ከመኖሪያ ቤቷ ሸሸገችው። ስድስት ወራት ከቤት ሳይወጣ ከቆየ በሁዋላ ያቺ ሴት የሃሰት
መታወቂያ አውጥታለት፣ ትንሹን አንዳርጋቸው እንደ ገበሬ አልብሳ ወደ ገጠር በመውሰድ ለሻእቢያ አስረከበችው።
ሻእቢያ አንዳርጋቸውን በሱዳን በኩል ሸኘው። ከዚያም አንዳርጋቸው ወደ ለንደን አቀና። አንዳርጋቸው መፅሃፉን
ሲፅፍ የመፅሃፉን መታሰቢያ ከሰጣቸው መካከል ጓደኛው የነበረ የእነዚሁ የኤርትራውያኑ ልጅ የነበረ ነው። ይህን
የተከበረ ቤተሰብ አንዳርጋቸው ወስዶ አስተዋውቆኝ ነበር። ስድስት ወራት የተደበቀባትን ክፍል ጭምር
አይቻለሁ። አንዳርጋቸው ይህን ቤተሰብ እንደ ስጋ ዘመዱ ያያል። እነርሱም አንዳርጋቸውን ሲያዩ በደርግ የተረሸነ
ሟች ወንድማቸውን ያስታውሳሉ።

እንግዲህ አንዳርጋቸው የመን ላይ መያዙን ስሰማ ወደ እነዚህ ሰዎች ነበር የበረርኩት። እንደደረስኩ
የግቢውን በር ደበደብኩ። አንዲት ሴት ብቅ አለች። አላውቃትም። እንግዳ ሳትሆን አትቀርም። ማንን እንደምፈልግ
ነገርኳት። የፈለግሁዋት ሴት እንደሌለች ነገረችኝ። እና የእጅ ስልኳን ሰጠችኝ። ደወልኩ። የምፈልጋት ሴት ስልኩን
አነሳች። ማን እንደሆንኩ ከነገርኳት በሁዋላ፣

“ስለ አንዳርጋቸው ሰማሽ?” ስል ጮህኩ።
“አልሰማሁም። ምን ሆነ?” ስትል እሷም ጮኸች።
“አሁኑኑ ነይ። እነግርሻለሁ…”

ከአስር ደቂቃ በሁዋላ እዚያው ከቤታቸው በራፍ ላይ ቁጭ ብለን የሰማሁትን ሁሉ ነገርኳት። ቃል
መተንፈስ እንኳ ተቸገረች። ትንፋሿ ቆሞ ድርቅ ብላ ቆየች። በመጨረሻ ግን ጥቂት ጥያቄ አዘል ቃላት ተናገረች፣

“በየመን በኩል ለምን እንደመጣ አልገባኝም? በየመንያ እንደማይጠቀም ከዚህ በፊት ነግሮኝ ነበር?”

በመቀጠል ከአንዳርጋቸው “ዘመዶች” ወደሌላው ደወልኩ። ተገናኝተን ስናወጋ ዜናውን ሰምቶ ነበር
የጠበቀኝ። ግራ ተጋብቶ ነበር። ግራ በተጋባ ስሜትም፣

“አንዳርጋቸው ከለንደን ሲነሳ ደውሎልኝ ነበር።” አለኝ። አያያዘና አከለበት፣ “…ትኬቱ በኤርትራ አየር
መንገድ ከዱባይ በቀጥታ ወደ አስመራ የተቆረጠ ነበር። ለምን በየመን በኩል እንደቀየረው አልገባኝም?”

አንዳርጋቸው ከየመን ወደ አዲሳባ መዛወሩን እስከሰማሁባት እለት የነበሩት ቀናት ለኔ እጅግ አስጨናቂ
ነበሩ። ወሬው አስመራን አዳርሶ ነበር። ፖለቲካ የማይከታተሉ ሰዎች ሳይቀሩ የአንዳርጋቸውን ስም እያነሱ ሲነጋገሩ
ሰማሁ። የኔና የአንዳርጋቸውን መቀራረብ የሚያውቁ እየደወሉ ይጠይቁኝ ነበር። አንዳርጋቸውን በፖለቲካ አቋሙ
የሚቃወሙት የኦነግ ከፍተኛ አመራር አባላት ጭምር በየመን ድርጊት ክፉኛ ተቆጥተው ነበር። የኦነግ አመራር
ከመቆጣት አልፎ የመን ላይ ዛቻ የቀላለቀለ መግለጫ አወጣ። ዳሩ ግን ማንም ምንም ማድረግ በማይችልበት
ፍጥነት አንዳርጋቸው ተላልፎ ለወያኔ ተሰጥቶ ኖሮአል። ኦሮማይ!

አንዳርጋቸው እንዴት ከወያኔ እጅ ሊገባ እንደቻለ ዛሬም ድረስ ግልፅ መረጃ የለም። የተለያዩ መላ
ምቶችን እየሰማን፣ እያነበብን ቆይተናል። አንዳርጋቸውን በቅርብ ከሚያውቁት አንዱ እንደመሆኔ እኔም ካለኝ
መረጃ በመነሳት የራሴን ግምት መውሰዴ አልቀረም። የኔን ግምት ይፋ ከማድረጌ በፊት ሌሎች የሚሉትን
ለመስማት በሚል እስካሁን ድረስ በጉዳዩ ላይ ሳልፅፍ ቆይቼ ነበር። አሳማኝ መረጃ ሳይፃፍ ወይም ሳይገለፅ ጊዜው
ስለረዘመ እነሆ! እኔም የግል አስተያየቴን ለማኖር ወሰንኩ…

ኤልያስ ክፍሌ ethiopianreview ላይ የፃፈውን አንብቤያለሁ። ግንቦት 7 የኤልያስን መረጃና ትንታኔ
በደፈናው፣ “ውሸት” ሲል ማስተባበሉንም ተከታትያለሁ። ግንቦት 7 ከማስተባበል አልፎ አንዳርጋቸው እንዴት
ሊያዝ እንደበቃ መግለፅ አለመቻሉ ግን ማስተባበሉን ጎደሎ ያደርገዋል። ያም ሆኖ የኤልያስ ክፍሌ ዘገባ ለኔ
አሳማኝ አልነበረም። በተመሳሳይ ከአንዳርጋቸው መያዝ ጋር በተያያዘ ጥቂት ወሬዎችን ተከታትያለሁ።
ከሰማሁዋቸው መካከል፣

“አንዳርጋቸው ከዱባይ አስመራ በቀጥታ የሚወስደው የኤርትራ አየር መንገድ ትኬት ነበረው። ዱባይ
ላይ የኤርትራ አይሮፕላን ስላመለጠችው የየመንን ትኬት ገዛ።” የሚለው አንዱ ነው።

ለዚህ መረጃ ክብደት ልሰጠው አልቻልኩም። አንዳርጋቸው ተጨማሪ አንድ ቀን ዱባይ በማደር
የሚቀጥለውን የኤርትራ አይሮፕላን መጠቀም እየቻለ፣ እንዴት አስተማማኝ እንዳልሆነ በሚያውቀው የመኒያ
ለመጓዝ ይወስናል? አንዳርጋቸው በየመን አየር መንገድ የተጓዘው በግማሽ ቀን ውስጥ በራሱ ውሳኔ ብቻ ከሆነ፣
የወያኔና የየመን የፀጥታ ሰዎች በዚያችው ቅፅበት አንዳርጋቸውን ለማፈን መቀናጀት ችለዋል ብሎ ማመን
ይቸግራል። የመሆን እድሉ በጣም አናሳ ነው። ለንደንም ሆነ አስመራ የሚገኙ የአንዳርጋቸው ዘመዶች የማያውቁት
አንድ ጉዳይ ያለ ይመስላል። በርግጥም አንድ ምስጢር ሊኖር እንደሚችል እጠረጥራለሁ።

ነገሩ ወዲህ ነው…

በአንድ ወቅት ግንቦት 7 ከነ ነአምን ዘለቀ እና ከአንድ የሆነ የአፋር ድርጅት ጋር ውህደት ነገር
መፈፀማቸውን በዜና ነግረውን ነበር። ከውህደቱ በሁዋላ ብዙም የተወራ ነገር ሳይኖር ነገሩ ተድበሰበሰ። ነአምን
ዘለቀ ከግንቦት 7 ጋር አብሮ ሲሰራ ስመለከት ግን አፋሮቹም ሆነ እነ ነአምን ጠቅልለው ግንቦት 7 ውስጥ ገብተዋል
የሚል ግምት ወስጄ ነበር። የአንዳርጋቸው የመያዝ ሂደት ከዚያ ሳይጀምር አልቀረም።

አንዳርጋቸው ከአፋሮቹ የፖለቲካ ድርጅት ጋር ግንኙነቱን አጥብቆ ቀጥሎ እንደነበር አውቃለሁ። ምን
እንደሚሰራ ግን ፈፅሞ ነግሮኝ አያውቅም። በመካከሉ ሆላንድ ሳለሁ ከግንቦት 7 ሰዎች በኩል የሾለከ የሚመስል
ወሬ ሰማሁ። ይህም ወሬ ለስራ ተብሎ 30 ሺህ ዶላር ተሰጥቶት ወደ የመን የተላከ አንድ አፋር የመሰወሩ ወሬ
ነበር። ወሬው በሰፊው የተሰራጨ አልነበረም። እጅግ በጣም ጠባብ በሆነ ቀዳዳ ነበር የሰማሁት። ይህ ወሬ
ሲመዘን ተራ ወሬ ሊመስል ይችላል። አፋሩ ገንዘብ መያዙ በርግጥ መረጃውን ከፍ አድርጎታል። ከገንዘቡ በላይ ግን
“የመን” የሚለው መረጃ ክብደት ነበረው። ግንቦት 7 የመን ላይ ትኩረት ማድረጉ ትልቅ መረጃ ነበር። አፋሩ
የመን-ሰንአ ሲደርስ ተሰወረ። ከዳ ወይስ ተያዘ? አይታወቅም። ከድቶም ሆነ ተይዞ ወያኔ እጅ ገብቶ ሊሆን
እንደሚችል ግን መገመት ይቻል ነበር። ይህ ከሆነ የግንቦት 7ን የተደበቀ ፍላጎት ወያኔ አውቆአል ማለት ነው።

ግንቦት 7 ምን እንደሚፈልግ ወያኔ ካወቀ፤ የግንቦት 7ን ፍላጎት ለማጥመጃ ሊጠቀምበት ይችላል። ቀላል
ጉዳይ አይደለም። ግንቦት 7 የመን ላይ ምንድነው የፈለገው? ከስደተኞች መካከል ታጋዮችን መመልመል?
የተመለመሉትን ደግሞ ወደ ተከዜ በረሃ ማሻገር? ይህን ስራ ለማከናወን ብዙ ገንዘብ ይጠይቃል። ውድ ነው።
ከሁሉም በላይ ግን ይህን ስራ ለመስራት የሚችል፣ አላማ ያለው ብቁ ሰው የመን ላይ ማግኘትን ይጠይቃል።

አፋሩ ገንዘብ ይዞ የመን ላይ ከተሰወረ በሁዋላ አንዳርጋቸው ተስፋ ቆርጦ ጉዳዩን ይተወዋል ተብሎ
አይገመትም። እንደገና ይሞክራል። ወያኔዎች በዚህ በአንዳርጋቸው ዳግማዊ ሙከራ ጊዜ የራሳቸውን ሰው የመን
ላይ አስቀምጠው አንዳርጋቸውን እንዲገናኘው አድርገው ይሆን? አንዳርጋቸው በረጅም ሂደት ወያኔዎች
ያዘጋጁለትን ሰው እንደራሱ ሰው በማመን ለግንቦት 7 አባልነት በምስጢር መልምሎት ይሆን? እና በረጅም ጊዜ
ሂደት አንዳርጋቸው ወያኔዎች ባዘጋጁለት ወጥመድ ውስጥ ሰተት ብሎ ገብቶላቸው ይሆን? ማለትም አንዳርጋቸው
እነዚያ አባላቱን ለማነጋገር፣ አሊያም ታጋዮቹን ወደ ተከዜ ለማሸጋገር እንዲቻል አንዳንድ ጉዳዮችን ለመፈፀም
በምስጢር የመን ገብቶ ለመውጣት ሞክሮ ይሆን?

ጥያቄዎቹ “አንዳርጋቸው እንዴት ተያዘ?” ለሚለው ጥያቄ ፍንጭ ሰጪ ሊሆኑ ይችላሉ። ቀጥተኛ መረጃ
ያለው አካል የተፈፀመውን በዝርዝር እስካልነገረን ድረስ ከምናውቀው በመነሳት ለመገመት እንገደዳለን።

ከዚህ ሁሉ በሁዋላ፣ “ወያኔዎች አንዳርጋቸውን ይዘው በማሰራቸው አተረፉ ወይስ ከሰሩ?” የሚል ጥያቄ
ይነሳል። የወያኔ ሰዎች “አተረፍን” እያሉ ነው። ማትረፍና መክሰራቸውን ለማየት በርግጥ ጥቂት ጊዜ መጠበቅ
ያስፈልግ ይሆናል። “አትርፈናል” ባዮች ከበሮ ሲደልቁ ሰምተናል። በአንዳርጋቸው መያዝ ቆሽቱ የደበነ ወገን፣ ነገ
በቁጣ ምን ሊፈፅም እንደሚችል አለመገመት የፖለቲካ የዋህነት ነው። እነ በቀለ ገርባ፣ እነ እስክንድር ነጋ፣ እነ
ኦልባና ሌሊሳ፣ እነ ኢንጂነር መስፍን አበበ (ራሶ)፣ እነ ጫልቱ ታከለ፣ እነ ኢብራሂም ሱልጣን፣ እነ ሰይድ አሊ፣ እነ
ፊፈን ጫላ፣ እነ ኮሎኔል ኦላኒ ጃሉ፣ እነ ውብሸት ታዬ፣ ዛሬም ድረስ እስርቤት ናቸው። አንዳርጋቸው ፅጌ
ተጨምሮአል። ይህን ፅሁፍ እየጻፍኩ ሳለም በርካታ ነፃነት ጠያቂዎች እየታፈኑ ወደ እስር ቤት በመጓዝ ላይ ነበሩ።
እስርቤት የተወረወሩትን ዜጎች በቀን 24 ሰአት የሚያስታውስ በሚሊዮን የሚቆጠር ዜጋ በመላ ኢትዮጵያ አለ።

በደል ሲበዛ ወደ በቀል ይለወጣል። ብዙውን ጊዜ ተበዳዮች ጉልበት ሲያገኙ የማመዛዘን ችሎታቸውን
ያጣሉ። በቀል ከመጣ ከደሙ ንፁህ የሆነውን ከተጠቃሚው መለየት ሳይቻል ጊሎቲኑ ከፊቱ ያገኘውን ሊበላ
እንደሚችል ከታሪክ በተደጋጋሚ አይተናል። ወያኔ አንዳርጋቸውና መስፍን አበበን በመሳሰሉ ታጋዮች ላይ
እየፈፀመ ባለው የማፈን ድርጊት ከህዝቡ መራር ቂም በማትረፍ ላይ ነው። ጭፍን ደጋፊዎቹ አደጋ ላይ
እንዲወድቁም አጋልጦ እየሰጣቸው ነው። በመሆኑም ወያኔ አትራፊ ስለመሆኑ ማረጋገጥ አይችልም።

የፅጌ ልጅ – አንዳርጋቸው ከጠላቶቹ እጅ ላይ ወድቆአል። በወያኔ ቴሌቪዥን ላይ ቀርቦም ጥቂት ቃላትን
ተናግሮአል። አንዳርጋቸው በጨካኝ ጠላቶቹ እጅ ላይ ወድቆ ሳለ የተናገራቸውን ቃላት በቀጥታ መውሰድ ወይም
ንግግሩን እንደ መረጃ ተጠቅሞ በዚያ ላይ አስተያየት መስጠት ተገቢ አለመሆኑን እረዳለሁ። ያም ሆኖ
አንዳርጋቸው በንግግሩ፣ “እኔን ተክቶ በረሃ የሚወርድ ሰው ማግኘት ይቸግር ይሆናል” አይነት አባባል መጠቀሙ
በተዘዋዋሪ የትግል ጥሪ ይመስለኛል። መስማት የሚፈልግ ካለ ይህን ሊሰማ ይችላል…

ርግጥ ነው አንዳርጋቸው ከተያዘ በሁዋላ በመላ አለም የሚገኙ “የአንድነት ሃይሎች” በቁጣ የተቃውሞ
ሰልፎችን አካሂደዋል። “አንዳርጋቸው ነኝ!” የሚል መፈክር ይዘውም ታይተዋል። “ሁላችንም አንዳርጋቸው ነን!”
የሚለው መፈክር ለአንዳርጋቸው ተገልብጦ ስድብ እንዳይሆንበት ግን እሰጋለሁ። “አንዳርጋቸው ነኝ!” ለማለት
ቢያንስ አንዳርጋቸው የሞከረውን ለመሞከር ቁርጠኛነትን ማሳየት ይጠይቃል። “ሁላችንም አንዳርጋቸው ነን!”
የሚለው አባባል በአፍ ብቻ ተንጠልጥሎ ከቀረ፣ እንደተለመደው የአንድ ሰሞን የዳያስፖራ ጫጫታ ሆኖ እንደ
ቀዳሚዎቹ መፈክሮች ይህም ከተረሳ ለአንዳርጋቸው ስድብ እንጂ ክብር ሊሆነው አይችልም።

የቅዳሜ ማስታወሻ – December 13, 2014 – Tesfaye Gebreab (Gadaa) – Email: ttgebreab@gmail.com

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>