Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 8745

በኮ/ል አለበል አማረ የሚመራው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ “ከግንቦት 7 ጋር አልተዋሃድኩም”አለ

$
0
0

(ፎቶ ከፋይል)

(ፎቶ ከፋይል)

በኢሳት ራድዮና ቲቪ ነሐሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከስልጣናቸው እንደተነሱ የተዘገበላቸው ኮ/ል አለበል አማረ የሚመራው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ “እየተካሄደ ነው የሚባለው ውህደት ብዙ ችግር ያለበትና ከእውነትም የራቀ ነው” ሲል መግለጫ አወጣ።
(ፎቶ ከፋይል - የአማራ ዲሞክራቲክ ኃይል ጦር ኃይሎች መካከል የተወሰኑት)

(ፎቶ ከፋይል – የአማራ ዲሞክራቲክ ኃይል ጦር ኃይሎች መካከል የተወሰኑት)


በኮ/ል አለበል አበራ እንደሚመራው ንቅናቄው መግለጫ “የተወሰኑ የድርጅታችን ታጋዮች አሁንም በኤርትራ መንግስት እገታ ኤርትራ ይገኛሉ፤ እነዚሁን ታጋዮች የድርጅቱ አካል በማስመሰልና በማስገደድ ኢንተርቪው እንዲሰጡ በማድረግ የሕገ-ወጡ ተግባር ከማድረግ እንዲቆጠቡና የሂደቱንም አፈጻጸም የተቀዋወሙሙ የድርጅታችን የተወሰኑ ሶስት አመራሮችና ሁለት አመራሮችና ሁለት ካድሬዎች በኤርትራ መንግስት እስር ላይ መሆናቸውን የታወቀ በመሆኑ ይኸው አላስፈላጊ ሁኔታ እንዲስተካከል ለኤርትራ መንግስትና ለተባባሪዎቻቸው በጥብቅ ደጋግመን እናሳስባለን” ይላል።

ኢሳት “የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ መሪውን ከሃላፊነት ማንሳቱን አስታወቀ” በሚል የሌላኛውን ወገን የአማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ጠቅሶ በዘገበው ዘገባ ላይ “ኮ/ል አለበል አማረ የድርጅቱ መስራችና ሊቀመንበር ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸውን፣ ውጭ አገር ከሄዱም በሁዋላ ድርጀቱን በማጠናከር ከፍተኛ ሚና መጫወታቸውን” ካወሳ በሁዋላ፣ ድርጅቱ መስዋትነት እየከፈለበት ያለው የነጻነት ትግል በቶሎ ግቡን እንዲመታ መሬት ላይ ወርዶ መታገሉ የበለጠ ውጤታማ ያደርገዋል ተብሎ ስላሚታመን በተደጋጋሚ እንዲመጡ ቢነገራቸው ሊመጡ ባለመቻላቸውና አሁን ባለንበት ጊዜ ድርጅቱን ውጭ ሃገር ተቀምጦ መምራት ስለማይቻል ከድርጅቱ ሊ/መንበርነት ወርደው በአባልነት እንዲቀጥሉ በሙሉ ድምጽ ወስነናል ብለዋል።” ሲል መዘገቡን፤ የኮ/ል አለበል ወገን ይህን ዘገባ ተቃውሟል።

ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 8745

Trending Articles