Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

ፖፕ ፓየስ 11ኛ አጼ ኃይለ ሥላሴን ለማስከዳት ስላደረጉት ሙከራ ኪዳኔ ዓለማየሁ


የጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ደብዳቤ ከቃሊቲ:- ‹‹የስልጣን ጥመኝነት የወለደዉ የፀረሽብር አዋጅ››

$
0
0

 ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ

ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ

የፀረሽብር አዋጁንና እየተተገበረ ያለበትን መንገድ ባሰብኩ ቁጥር  ወደአይምሮዬ የሚመላለሱ በርካታ ጥያቄዎች አሉ፡፡ ከነዚህ መሀከል አዋጁ ለምን ሰብአዊ መብትን የሚጥሱ አንቀጾች ኖሩት/  ከሽብር ጋር ምንም አይነት ንክኪ የሌለን ንጹሀን ሰዎችስ በአዋጁ መሰረት እየተባለ ለምን ይፈረድብናል የሚሉት ይገኙበታል፡፡ እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ አዋጁ የወጣበትን ምክንያት መመርመር ግድ ይላልና ይህንኑ አደረስኩ፡፡

 

የፀረሽብር አዋጁ ለምን ወጣ

 

ኢህአዴግ የፀረሽብር አዋጅ እንዲወጣ ያደረገዉ እዉተኛ የሽብር አደጋ ተደቅኖበት አለመሆኑን ለመረዳት ብዙ መጓዝ አያስፈልግም፡፡ በአሽባሪነት የተጠረጠርንና የተፈረደብንን ሰዎች ማንነት ማወቁ ብቻ ይበቃል፡፡ ኢህአዴግ ኢትዮጵያዉያን ላይ እየተፈጸመ ያለዉ ግፍ ይብቃ ብለዉ ስርዓቱ በሌላ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ይለወጥ ዘንድ በሰላማዊ መንገድ ሲታገሉ የነበሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላት፣ በመስርያ ቤታቸዉ ወይም ደግሞ በመኖርያ ቤታቸዉ አካባቢዎች የመንግስት ሀላፊዎች በሚጠሯቸዉ ስብሰባዎች ላይ ደፋር ጥያቄዎችን በማቅረባቸዉ ብቻ ጥርስ የተነከሰባቸዉ የነፃ አስተሳሰብ  ባለቤቶች፣ መንግስት ለአገዛዙ  አመቺ በመሰለዉ መልኩ ሀይማኖታቸዉን ለመበረዝና ለመከለስ ያደርግ የነበረዉን እንቅስቃሴ በሚያስገርም ጀግንነት የመከቱ የእስልምና ሀይማኖት መሪዎችና ተከታዮች እንዲሁም የህዝብ ድምፅ መሆናችንን አምነን ሀላፊነታችንን በአግባቡ ስንወጣ የነበርን  የነፃዉ ፕሬስ አባላት የፀረሽብር አዋጁ ሰለባ ሆነናል፡፡

 

ይህ የመንግስት ድርጊት አዋጁን ያወጣበት እዉነተኛ ምክንያት በስልጣን ወንበር ላይ ያለምንም ተቺ፣ ተቃዋሚና ተቀናቃኝ ተደላድሎ ለመቀመጥ መሆኑን የሚያሳይ ነዉ፡፡ ይህ አይነቱ አካሄድ ደግሞ ኢህአዴግ የጀመረዉ ሳይሆን እሱን ከመሰሉ አምባገነኖች የኮረጀዉ ያረጀና ያፈጀ አሰራር ነዉ፡፡ የአፍሪካዉያን የቀድሞ ቅኝ ገዢዎች አልንበረከክ ብለዉ ያስቸገሩዋቸዉን የነፃነት ታጋዮች የአሸባሪነት ታፔላ ይለጥፉባቸዉ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ዛሬ ደግሞ ኢህአዴግ ሰብአዊና የዜግነት ክብራችንን ለመጣል እምቢ ያልነዉን የገዛ ሀገሩን ልጆች እስር ቤት ለማጎርና ለማሰቃየት አመቺ ነዉ ብሎ ባመነበት በዚህ የቅኝ ገዢዎች አስቀያሚ መንገድ ላይ እየተጓዘ ነዉ፡፡

 

ምን ይሻላል?

 

የፀረሽብር አዋጁን በመታከክ ኢህአዴግ እየፈፀማቸዉ ያሉትን የመብት ረገጣዎች ለማስቆም ከባድ ትግል ይጠይቃል፡፡ አሁን ያለዉ  የፀረሽብር አዋጅ ተገቢ በሆነ በሌላ የፀረ ሽብር አዋጅ መተካት ይኖርበታል፡፡ ይህ ባይሆን እንኳን አሁን ያለዉ አይነት ለኢህአዴግ የገበረ የፍትህ ስርዓት እስካለ ድረስ ግን ንፁሀን ዜጎች በአሸባሪነት መታሰራቸዉ አይቀርም፡፡ አሁን ባለዉ የፀረሽብር አዋጅ መሠረት በትክክል ብንዳኝ ኖሮ እንኳን ጥፋተኛ ልንባል የማይገባን ምንም አይነት ወንጀል ያልፈፀምን ግለሰቦች አሸባሪ ተብለን በእስር ላይ መገኘታችን ይህንን መራራ እዉነት የሚያሳይ ነዉ፡፡ በመሆኑም አዋጁንና በይበልጥ ደግሞ አዋጁን ለስልጣኑ ማራዘሚያነት ኢፍትሀዊ በሆነ መንገድ እየተጠቀመበት ያለዉን ኢህአዴግን በማዉገዝ እየተደረጉ ያሉትን የተቃዉሞ ሰልፎችና ሌሎች ሰላማዊ የተቃዉሞ እንቅስቃሴዎች ጠንክረዉ መቀጠል ይኖርባቸዋል፡፡

 

የተቃዉሞ እንቅስቃሴዎች በዋናነት ኢህአዴግ ላይ ማተኮር እንዳለባቸዉ የማምነዉ በፀረሽብር አዋጁና በአተገባበሩ ብቻ ሳይሆን የሌሎች ለቁጥር የሚያዳግቱ የኢትዮጵያዉያን ችግሮች ምንጭ ራሱ ኢህአዴግ በመሆኑ ነዉ፡፡ ኢህአዴግ ስልጣኑን ለማራዘም የሚረዳዉ እስከመሰለዉ ድረስ ማንኛዉንም አይነት ተግባር ከመፈፀም ወደኃላ የማይል መሆኑን እስኪያንገሸግሸን ታዝበናል፡፡ በሌላ አነጋገር የኢህአዴግ ድርጊቶች ሁሉ ምክንያቶች ( motives ) ከዘረኝነት፣ ከስልጣን ጥመኝነት፣ ካለአግባብ ከመበልፀግና ከመሳሰሉት እኩይ ፍላጎቶች ጋር የተያያዙ ናቸዉ፡፡ “If one”s motives are wrong, nothing can be right” ከሚለዉ የአርተር ጎርደን አባባል እንደምንረዳዉ አንድ ነገር የሚደረግበት ምክንያት ስህተት ከሆነ ትክክል የሚሆን ነገር አይኖርም፡፡ በዚህም ምክንያት ከኢህአዴግ መልካም ነገር መጠበቅ አይቻልም፡፡ በመሆኑም የሚኖረን ብቸኛ አማራጭ የሰለጠነና ሰላማዊ ትግል የሚጠይቀንን መስዋዕትነት ከፍለን ስርዓቱን መለወጥ ነዉ፡፡

 

ስርዓቱን ስለመለወጥ ስናስብ አብረን ልናስባቸዉ የሚገቡ በርካታ ተያያዥ ጉዳዮች አሉ፡፡ ስርዓቱን ለመለወጥ በምንሄድበት መንገድ ላይ ገዢዉ ፓርቲ ያስቀምጣቸዉን በዘር፣ በሀይማኖት፣በፖለቲካ ርዕዮተ ዓለምና በጥቅም የመከፋፈል እንቅፋቶች እንዴት ማለፍ እንደምንችል በጥልቀት አስቦ መንቀሳቀስ ግድ ይላል፡፡  በየአቅጣጫዉ የተበታተኑ እንቅስቃሴዎችን ከማካሄድ ይልቅ በህብረት ሆነን መታገል መቻል ይኖርብናል፡፡ ከኢህአዴግ በኋላ ስለሚመሰረተዉ ስርዓትም በደንብ ማሰብና መመካከር የሀገሬ ጉዳይ ይመለከተኛል ከሚል ማንኛዉም ሀላፊነት ከሚሰማዉ ዜጋ በተለይም ደግሞ የተቃዉሞ እንቅስቃሴዎችን ከሚመሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ሌሎች አካላት ይጠበቃል፡፡ የሚጠበቅብንን ሁሉ እስካደረግንና በፅናት እስከቆምን ድረስ ደግሞ ብሩህ ቀን የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡

 

ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ከቃሊቲ

 

ፌደራል ፖሊስ በረመዳን ጾም ፍቺ በሙስሊሞች ላይ ድብደባ ፈጸመ

$
0
0

ከመሐመድ
ፖሊስ የኛ አይደለም ሊሆንም አይገባውም፡፡ “ፖሊስ” ለዚህ ጽሁፍ ሲባል “ኢህአዴግ” የተባለ የማፊያዎች ስብስብን ለመጠበቅ ህዝብን በአደባባይ ሊያሸብር ህጋዊ ፈቃድ የተሰጠው የደደቦች ስብስብ ነው፡፡ ፖሊስ ደደብ ነው፡፡ ማገናዘቢያውን በኢህአዴግ የሽብር ቡድን የተቀማ ህጻናት ፣ ሃረጋውያን ፣ ነብሰ ጡር ፣ ሴት ፣ ሰላማዊ ሰዎችን ፣ መንገደኛ መለየት የተሳነው እንሰሳ ነው፡፡ ፖሊስ ክብሪት ነው፡፡ አምጣ የወለደችውን እናቱን ለመደብደብ የማያቅማማ ቅል ራስ፡፡
ጉዞ በጦር ቀጠና….
ከብሔራዊ …በአዋሽ ወደ ኮሜርስ….. ቱርርር ድጋሚ ወደ አዋሽ ባንክ ፣ በአርቲስቲክ ወደ ብሔራዊ ባንክ ሆም መዘክር ፣ ታጥሯል መንገዱ ቱርርር ወደ ተገኘው ቅያስ ሰዎች ተደብድበዋል ፣ መስገጃ ፣ ጫማዎች ፣ አማይማ ፣ ኮፊያ ፣ የተፈነከቱ ሰዎች ፣ የተያዙ ወጣቶች ፣ ረጃጅም አጠና የያዙ የባንዳው ውሾች ፣ በፋራረሱት መንደሮች አቆራርጠን እዚያችው ትንሽ ፈቀቅ ብለን…
b_400_300_16777215_00_images_mejlisqebr

Addis_august8_2013_21

Addis_august8_2013_20

Addis_august8_2013_17

Addis_august8_2013_16
…አትሩጡ …አትሩጡ… ጥግህን ያዝ!! ጥግጥጉን ወደ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር … የተለያዩ የመንግስት መስሪያቤቶች የሙስሊሙ እስር ቤት ሆነዋል፡፡ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በብዙ ውሾች መሃል የተያዙ ወንድሞቼን ተመለከትኩኝ….አንዱ ውሻ ጋረደኝ ሁሉንም ለመቁጠር አልቻልኩም ……..አንድ ..እእ….ሁለት ተነጥለው ሌላ …ሁለት…. ወዲ…ያ ….ሌሎች የታሰሩ ግን በስንቱ መስሪያ ቤቶች ስንቱ ሙስሊም ታስሯል…! መስሪያ ቤቶች ባጠቃላይ (ያሲን ኑሩ በሆነው ሲዲው ላይ አጀልህ ከደረሰ ሁሉም ነገር አንተን ለመግደል ሰበቢያ መሆን ይችላል ብሎን ነበር) ሙስሊሙን ለማሰር አፋቸውን ከፍተው ሲጠብቁን አስተዋልኩ…ናሽናል ጂዎግራፊ ቲቪ ላይ በብዙ ነብሮች የተከበበችውን ሚዳቋ ትዝ አለችኝ… ከመንጋዋ የተነጠለችውን አንዷን ሚዳቋ ጥቂት የነብር መንጋ ከበው ሲበሏት ለመን መንጋው አይታደጋትም ስል ጠየኩ…..ዛሬም ከጀምአው እየነጠሉ የሚደበደቡትን ወንድሞቼን ለመርዳት ሳይሞክሩ ነብስን ለማዳን የሚራወጡት ወንድሞቻቸውን ለመርዳት ከሚናዝኑት ከብዙው የህዝን መንጋ ጥቂቱን ብቻ አስተዋልኩ…ጥቂት ናቸውና የባንዳው ሰራዊት በቀላሉ አጠቃቸው….
አንድም ባስ አልተሰበረም ፣ አንድም ድንጋይ ሲወረውር የተመለከትኩት ሰው አልነበረም፡፡ በእርግጥ …..መብትን መጠየቅ ሽብር አይደለም ፣ እራሱ ገዳይ እራሱ ከሳሽ ፣ በሃገራችን ሰላም አጣን ፣ መንግስት የለም ወይ ፣ እንትን የህዝብ ነው (ይሄን እኔ አላልኩም) ፣ ኢቴቪ ፣ዛሚ ፣ ፋና ፣ መንግስት ፣ ወዘተረፈዎች ሌባ ናቸው ብለናል፡፡ የህዝብን አደራ የበሉ ፣ ከህዝብ አብራክ ወጥተው ህዝብ ላይ ቁልቁል የሚተፋ ወሽካታ አድርባይነታቸውን ነግረናቸዋል፡፡ ጥፋታችን በግፍ የታሰሩብንን መሪዎቻችንን እንዲፈቱልን መጠየቃችን ነበር፡፡ በሃይማኖት ጣልቃ አትግቡብን ፣ ህገ መንግስቱ ካልተተገበረ የወረቀት ነብር ነው ብለን ብሶታችንን ማሰማታችን …….
በአጠና ተነረትን ፣ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ፊት ለፊት ግንቡ ጥግ ስር እራሱን ስቶ የወደቀው በግምት እድሜው ወደ ስልሳዎቹ የሚጠጋው አዛውንት መሃል አናቱ ተበርቅሶ ደሙ እየፈሰሰ ማንም እንዳይረዳው የባንዳው ሰራዊት ከበው ሞቱን ይጠብቃሉ ፣ ጉዞ ወደ ጥቁር አንበሳ!! ብሔራዊ ሜትሪዮሎጂ ፊት ለፊት ያለው የባንዳው ሰራዊት ጣቢያ ፊት ለፊት ባለው ሚዲያን/የአስባልት አካፋይ ተዘርግፈው የወደቁ ሰዎች ይታዩኛል ፣ አንድ አባት ከሁለት (በግምት የአስራ አራት እና ከአስራ ስምንት የማይበልጡ) ልጆቹ ጋር አፈር መስለው ሶስቱም በባዶ እግራቸው የሰውዬው ኮት በጭቃ ጨቅይቶ የሴቶቹ ልብሶች አፈር መስሎና ጸጉራቸው ተንጨባሮ በቢታንያ ክሊኒክ ቅያስ ብቅ አሉ፡፡ የሰራዊቱ ጣብያ በር ላይ ደም ረግጠን በቅያስ ወደ ሞሃ እድገት በስራ ት/ት ቤት ደረስን፡፡ ከጦር አውድማው ወጥተን መስሎን ጫማችንን ሱሪያችንን ልናነጻ ቀልባችንን ልናረጋጋ ሊስትሮ ፍለጋ ስንኳትን ከእናቱ ጋር የተለያየ አንድ ከአስራሁለት አመት የማይበልጥ ልጅ አይኖቹ ወዲያ ወዲህ ሲሉ አይን ለአይን ተገጣጠምን፡፡
እየተቅለሰለሰና እየተርበተበተ “ከእናቴን ጋር ተጠፋፋን ወደ መሳለሚያ 01 መንገዱን አሳዩኝ..” ሲል ልመናውን አቀረበ፡፡
እናቱ ታየችኝ!! ልክ ብሔራዊ ባንክ ጋር ጥጉን ካሰለፏቸው ሰዎች መካከል አንዲት ነብሰ ጡር ሁለት ልጆቿን ይዛ ርህራሄ የማያውቁትን እነዚህን የባንዳውን ሰራዊት ያዝኑላት ዘንድ ስትለምናቸው…ሚጣ በሚሯሯጡት ሰዎች ተረግጣ እሪሪሪ ስትል ከልጇ እኩል የምታነባዋ ብሔራዊ ቲያትር ጋር የየኋት እናት በአይኔ ይዞሩ ጀመር፡፡

“እናትህ ስልክ ይኖራታል..!” የኔ ጥያቄ ነበር ከልጁ ይልቅ የእናቱ ጭንቀት በአይኔ እየዞረ…

“የላትም!”

“ና” በል! ጉዞ በሞሃ ወደ በርበሬ በረንዳ…ከአብነት ፣ ከምራብ ፣ ከተክለሃይማኖትና ከሜክሲኮ ያሚመጡ መንገዶችን የሚያገናኘው መስቀለኛው መንገድ ላይ ሊስትሮ ስንፈልግ ከተክለሃይማኖት ቱርርር እያሉ አናታችን ላይ ሊወጡ … ወደ ጭድ ተራ ቱርር…ሃደሬ ሰፈር ውስጥ ውስጡን ሰዎች ይሯሯጣሉ ዞር ስል ልጁ ከአጠገቤ የለም!! የት ገባ!! በቃ አንድ ሰው ያሳየዋል ብዬ ጥሩውን ጠረጠርኩ!! ከጭድ ተራ ወደ ምናለሽ ተራ ምናለሽ ተራ ጋር የሰላም ቀጠና ነው ብለን እርግት ፣ ቅዝቅዝ ፣ ትክዝ ፣ ፍዝዝ እንዳልን…ከወደ ሰላም ባልትና አካባቢ ቱርርር ወይ ዛሬ!! ምናለሽ ተራ ያላትን ቁሶች ኁላ ቆሽ…ኮሽ…ስብር …ብረታብረቶችን ድስጣድስጦችን ፣ ማንኪያዎችን ምናምኖችን ሽክም ይዞ ቱርርር ….የጭንቅ ቀን አይመሽም!! በሃያሁለት ቀበሌ ወደ ድሬ ህንጻ ሰባተኛ፡፡ አሁን ሰላም ነው፡፡

ስለምን ይሄ ሁላ ውርጅብኝ….አንድም ጠጠር እንኳ ባላነሳ ህዝብ ላይ ግን ለምን!!

የመንግስትን መግለጫ ለማዳመጥ ሞባይሌን አውጥቼ ዛሚን ከፈትኩ …ኤንሶ ኤንሶ…ይላል…ወደ መስተዳድሩ ኤፍ ኤም….አይኬ ..ጫምባላላ ይላል…ወደ 97.1 የእስፖርት ዝውውር ይዘግባል አንዱን ሃገር በቀል ተጫዋች ጋብዘው….98.1 የአምስት ሰዓት ዜና ጀመረ…ጆሮዬን ሰክቼ ቀልቤን ሰብስቤ በትካዜ ማድመጥ ጀመርኩ፡፡
“የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤት አቶ እከሌ በአዲስ አበባ እስታዲየም በመገኘት መንግስት ድህነትን ለመቀነስ በሚያደርገው እርብርብ ህዝበ ሙስሊሙ እያደረገ ያለውን አስተዋጽዎ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገነዘቡ፡፡ የኢድ ሶላትም ህዝበ ሙስሊሙ በተገኘበት በአዲስ አበባ እስታዲየም በሰላም ተካሂዶ እንደተጠናቀቀ ከኢዜአ ባገኘነው መረጃ ለማወቅ ተችሏል” ብሎ ኩም አደረገኝ፡፡ አሁን አመመኝ፡፡ አሁን ጆሮዬን ጠዘጠዘኝ፡፡ /…./

አንድነት በአርባምንጭ ከተማ ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ክፍል 1, 2, 3, 4 and 5

$
0
0

አንድነት በአርባምንጭ ከተማ ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ክፍል 1

አንድነት በአርባምንጭ ከተማ ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ክፍል 2

አንድነት በአርባምንጭ ከተማ ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ክፍል 3

አንድነት በአርባምንጭ ከተማ ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ክፍል 4

አንድነት በአርባምንጭ ከተማ ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ክፍል 5

በአዲስ አበባ፣ በወልቂጤ፣ በአፋር፣ በደሴና በአዳማ ሙስሊሞች ላይ መንግስት እርምጃ ወሰደ

$
0
0

ሙስሊም 1
ሙስሊም 3
ሙስሊም(ዘ-ሐበሻ) ለኢድ ሶላት በወጡ ሙስሊሞች ላይ መንግስት ድብደባ መፈጸሙ ታወቀ። በአዲስ አበባ፣ በወልቂጤ፣ በአፋር፣ በደሴ፣ በአዳማና በሌሎችም ከተሞች ለኢድ ሶላት በወጡ ሙስሊሞች ላይ መንግስት ከአንድ ሳምንት በፊት በሰጠው ማስጠንቀቂያ መሠረት ዛሬ ድብደባውን ሲፈጽም በተለይም አዲስ አበባ የጥይት ድምጽ መሰማቱን እና አድማ በታኝ ፖሊሶችም አስለቃሽ ጭስ መጠቀማቸውን ከድምጻችን ይሰማ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የ1434ኛውን የኢድ አልፈጥር በዓል በዛሬው ዕለት በመላው ዓለም የሚገኙ ሙስሊሞች እያከበሩት ሲሆን በኢትዮጵያ የተከበረው በተቃውሞ፣ በእስር፣ በድብደባና በ እንግልት መሆኑ በርካታ ሙስሊሞችን እንዳስቆጣ ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች ከምናገኛቸው የሕዝብ አስተያየቶች መረዳት ችለናል። በአዲስ አበባ የፌደራል ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሙስሊሞች ድብደባ የደረሰባችው ሲሆን የተደብዳቢ ሰዎችም ፎቶ ግራፍ ከነደማቸው በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተለቋል።
“የመንግስት ታጣቂዎች የዒድ ክብረ በዓልን ለመፈጸም የወጡ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ከፍተኛ ኃይል የተቀላቀለበት ድብደባ ፈጽመዋል፡፡ መንግስት ለኢትዮጵያውያን ሙስሊም ዜጎቹ ያለውን ከልክ ያለፈ ጥላቻ በዛሬውም በኢድ በዓል ቀን አሳይቷል፡፡” ሲል ሁኔታውን የገለጸው ድምፃችን ይሰማ ፌዴራል ፖሊስ ሙስሊሞችን እስከቤታቸው ደጃፍ ድረስ እየተከተለ ጥቃት ሲዘነዝሩባቸው ውለዋል ብሏል።
በሙስሊሞቹ በዓል ላይ እንዲህ ያለው ተግባር ቢፈጸምም መንግስታዊ ሚዲያዎች ግን በዓሉ በሰላም መጠናቀቁን እየዘገቡ ነው። በተለይ የሕወሓት ራድዮ የሆነው ራድዮ ፋና የዛሬውን በዓል በማስመልከት የዘገበው የሚከተለውን ነው። “ሙስሊሙ ማህበረሰብም ከማለዳው ጀምሮ ወደ ስቴዲየም በማምራት በአሉን በሰላት ፣ በስግደት ተክቢራና ሌሎችንም ሀይማኖታዊ ስነ ስርአቶች በማካሄድ አክብሮታል። በበአሉ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸህ ኪያር ሙሀመድ አማን እንዳሉት ፥ በረመዳን ሙስሊሙ ፈጣሪው ያዘዘውን መልካም ነገሮች ሁሉ ሲከውን መቆየቱን አንስተዋል። መልካም ነገሮች የሚደረጉት በረመዳን ብቻ ባለመሆኑ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከረመዳን በኋላም መልካም ነገሮችን ማድረጉን እንዲቀጥል አሳስበዋል። በሀይማኖት ስም አንዳንድ አክራሪዎች ሰላምን የሚነሳ ድርጊት እየፈጸሙ መሆኑን ጠቁመው ፥ ይህም መላው ሙስሊሙ በየመስጊዱ ጸሎቱን በአግባቡ እንዳይከውን እያደረገ ይገኛል ብለዋል። ይህን ተቀባይነት የሌለውን ድርጊትም ሙስሊሙ መታገል አለበት የሚሉት ፕሬዝዳንቱ ፥ በአሉን ካጡና ከተቸገሩ ወገኖች ጋር በጋራ ማክበር ይገባል ነው ያሉት።
የመንግስት ሚድያዎች በዓሉ በሰላም መጠናቀቁን ቢዘግቡም ድምፃችን ይሰማ ደግሞ ተቃውሞውን በቪድዮ ለአደባባይ በማብቃት የመንግስትን ውሸት እርቃኑን እንዳስቀረው ታዛቢዎች የሚናገሩት።

“ኃይሌ ፕሬዘዳንት ከሚሆን የሪዞርቱ አስዳደር ቢሆን ይሻለዋል”–አቶ ግርማ ሰይፉ

$
0
0

በኢትዮጵያ ፓርላማ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ አባል የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ የኃይሌ ገብረስላሴን ወደ ፖለቲካው ዓለም መግባትና ለፕሬዚዳንትነት እወዳደራለሁ ማለቱን ተከትሎ ለላይፍ መጽሔት በሰጡት ቃለ ምልልስ “‹‹ሃይሌ ፕሬዘዳንት ከሚሆን የሪዞርቱ አስዳደር ቢሆን ይሻለዋል›› አሉ። በመጽሔቱ የቀረበው ቃለምልልስ እንደወረደ ይኸው፦

‹‹ለሚሚ ስብሃቱ የምሰጠው ምላሽ እንኳን ብቻ ነው››
‹‹መለስ በመሞታቸው ፓርላማው ተነቃቅቷል››

የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ በታሪክ አጋጣሚ በፓርላማው ብቸኛ የገዢው ፓርቲ ተቃዋሚ በመሆናቸው የሁሉን ትኩረት እንዲያገኙ ምክንያት ሆኗቸዋል፡፡እጅግ የተጣበበ ጊዜ ያላቸው ግርማ በቅርቡ የነጻነት ዋጋው ስንት ነው? የሚል መጽሀፍ ለንባብ አብቅተዋል፡፡ዳዊት ሰለሞን መጽሀፉን እንደመነሻ በመውሰድ ነገሮችን በተለየና በሰለጠነ መንገድ መመልከት የሚወዱትን ግርማን አነጋግሯቸዋል፡፡የፓርላማ አባሉ ጊዜያቸውን በማጣበብ ለቃለ ምልልሱ ፈቃደኝነት በማሳየታቸውም ምስጋናችን ይድረሳቸው ፡፡
ላይፍ– በቅርቡ የነጻነት ዋጋው ስንት ነው የሚል መጠይቅ ያለው መጽሐፍ ለንባብ አብቅተዋል፡፡በፓርላማ ንግግር በማድረግ፣በየሳምንቱ በጋዜጦች ላይ አርቲክሎችን ከመጻፍና አንድ ጥራዝ መጽሐፍ በማውጣት መካከል ያለው ልዮነት ምንድን ነው
ግርማ — ምንም ልዮነት የላቸውም፡፡በቀን ውስጥ ያለውን ጊዜ እንደየድርሻቸው ይከፋፈላሉ እንጂ ልዮነት የላቸውም ብዬ አምናለሁ፡፡እንደውም አንዱ ሌላኛውን ይደግፋል የሚል እምነት አለኝ፡፡
ላይፍ — የነጻነት ዋጋው ስንት ነው የሚለው መጽሐፍዎ በዋናነት ሊያስተላልፍ የፈለገው መልእክት ምንድን ነው
Girma-Seifu2ግርማ –ያው ሰዎች ለነጻነታቸው ምን ያህል ዋጋ እየከፈሉ እንደሆነ ለማሳየት ነው፡፡በመጽሀፉ ውስጥ በተለያየ ገጸ ባህሪ የተወከሉ ሰዎች አሉበት፡፡ነጋዴዎች፣የተማሩ የሚባሉ፣ሐይማኖተኞችና ባተሌዎች አሉበት፡፡ሁሉም በእጁ ላይ ያለውን ነጻነቱን ተደራድሮበት እየሸጠው ሳይሆን እንዲሁ እያጣው መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ልቦለድ ሳይሆን እውነተኛ ገጠመኝ ነው፡፡ሁሉም ሰው በእጁ ያለውን ነጻነት አሳልፎ እየሰጠ እንደሆነ መጽሐፉ ያሳያል፡፡በእርግጠኝነት መጽሐፉን የሚያነብ ሰው ራሱን አንድ ቦታ ያገኘዋል፡፡
ላይፍ— ‹‹እዚህ አገር ያለውን ፍርሃት 95 ከመቶ የፈጠርነው እኛው ራሳችን ነን›› የሚል መደምደሚያ ላይ በመጽሐፉ ደርሰዋል፡፡የሌለ ነገር ነው የምትፈሩት እያሉን ነው
ግርማ — የሚያስፈራራን ነገር የለም አላልኩም፡፡እኔ ሁልጊዜም 80 ከመቶ የሚሆነውን ፍርሃት የፈጠርነው እኛ ነን እል ነበር ፡፡ነገር ግን አንድ ቀን ጃዋር መሐመድ በሰላማዊ ትግል ዙሪያ ንግግር ሲያደርግ ነው ይህንን ቁጥር ያገኘሁት፡፡ማተኮር ያለብን ፐርሰንቱ ላይ አይደለም፡፡ለምሳሌ መቶ ሰዎች ቢኖሩ ሊያስፈራራው የሚችለው አንዱን ብቻ ነው፡፡ቀሪዎቹ አንዱ ሰው ላይ የደረሰውን በመመልከት የሚፈሩ ናቸው፡፡በተለያየ መንገድ ማስፈራራቱ ሊኖር ይችላል ነገር ግን ብዙዎቻችን የምንፈራው ሌሎቹን እየተመለከትን ነው፡፡በየቀበሌው የሚገኙ ሰዎች የሚበዙት ኢህአዴግ የሆነ ነገር ይጥልልኛል በማለት የተጠጉ ናቸው፡፡እነዚህ ሰዎች ናቸው ወደ የቤቱ እያመሩ ሊያስፈራሩ የሚሞክሩ፡፡ነጻነታችንን ነጻነት በሌላቸው ሰዎች እያስነጠቅን መሆኑን መመልከት አለብን፡፡እስኪ ተመልከት ከፍርሃት የወጡ አንድ ሚልዮን ሰዎች ቢኖሩን ኢህአዴግ እንዴት ነው አንድ ሚልዮኑን ሊያስፈራራ የሚችለው?
ላይፍ — በ2002 በተሳተፉበት ምርጫ ከጎንዎ ሊያገኟቸው ይፈልጓቸው የነበሩ የቅርብ ሰዎችዎን በመፍራታቸው የተነሳ ሊያገኟቸው አለመቻልዎን በመጽሐፍዎ ጠቅሰዋል፡፡እነዚህ ሰዎች መጽሐፉ ከወጣ በኋላ በአንድም በሌላ መንገድ የተናገሩት ነገር ይኖራል?
ግርማ –አይተውት ራሳቸውን ያገኙበት ይሆናል እንጂ እኔን እንዲህ አልነበረም ያለኝ የለም፡፡ደግሞም አይኖርም ምክንያቱም እውነት ነው፡፡እውነት ሲሆን እኮ ብዙም ክርክር አያስነሳም፡፡እነዚህ ሰዎች ብዙ ሚልዮኖችን የሚወክሉ መሆናቸውም መዘንጋት የለበትም፡፡
ላይፍ -ሰዎች የእኛን አገር ፖለቲካ ሲያስቡ ወደ አእምሯቸው የሚመጣው ሴረኝነት ነው፡፡በሴራ ፖለቲካ የተነሳ ብዙ ርቀት መጓዝ አልተቻለም፡፡እርስዎ ደግሞ ሐይማኖተኛ ለመሆንዎ በመጽሐፍዎ ደጋግመው የጠቀሷቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃላት በመመለከት መገመት አያስቸግርም፡፡ፖለቲከኛና ሐይማኖተኛ መሆን በእኛ አገር የሴራ ፖለቲካ ውስጥ ፈታኝ አይሆንም?
ግርማ — በጣም ለብዙ ሰው መናገር የምፈልገው ፖለቲከኛ ለመሆን ውሸታም ሴረኛ መሆን አለማስፈለጉን ነው፡፡ፖለቲከኛ መሆን የሚጠይቀው በመጀመሪያ ሐቀኝነትንና ሴረኛ አለመሆንን ነው፡፡እንደምታስታውሰው በፓርቲው ውስጥ ነጻ ውድድር መኖር አለበት የምለው በድርጅታዊ አሰራር ባለማመኔ ነው፡፡ድርጅታዊ አሰራር ማለት የሆነን ሰው በማንሳት የምታስቀምጥበት ነው፡፡ነገር ግን እችላለሁ የሚል ሰው ተወዳድሮ ማሸነፍ ይኖርበታል የሚል እምነት አለኝ፡፡ያን ያህል ሐይማኖተኛ አይደለሁም፡፡ክርስቲያን ነኝ፡፡ለእምነት ክብር እሰጣለሁ፡፡ሰው ሁሉ የእኔን እምነት መከተል አለበት አልልም፡፡ነገር ግን ከማያምን የሚያምን የተሻለ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ለምን ጠንቋይን አይሆንም እምነት ያለው ሰው የሆነ የሚፈራው ነግር እንዳለው አስባለሁ፡፡እግዚአብሄርን ወይም አላህን የሚያምን ሰው በጨለማ የምሰራውን ገልጦ የሚያይ አምላክ አለ ብሎ ስለሚያምን ክፉ ነገር የማድረግ ድፍረት አይኖረውም፡፡
ላይፍ– የፖለቲካ ህይወትዎን በጀመሩበት የኤዴሊ ፓርቲ ውስጥ በነበረ ሴራ ወደ ቅንጅቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ እንዳይመጡ መደረግዎን በመጽሀፍዎ በማስታወስ ወደ ማዕከላዊ ኮሚቴው ብመጣ ኖሮ ግን እታሰር ነበር ብለዋል፡፡ይህ በእኔ ያልተፈጸመው አምላክ ስለጠበቀኝ ነው ይላሉ፡፡ነገር በዚያ የ1997 ምርጫ ወቅት ለእስር የተዳረጉ የትግል ጓደኞችዎ እንደመሆናቸው መጠን እኔን አምላክ አስመለጠኝ ማለት ምን ያህል ተገቢ ነው?
ግርማ — እግዚአብሄር የሰው ልጆችን በንፍር ውሃ ባጠፋ ጊዜ በኖህ አማካኝነት በሰራው መርከብ እርሾ ማስቀረቱ አይዘነጋም፡፡መርከቡ ላይ የተሳፈሩ ሰዎች ግን በጠፉ ሰዎች ደስተኛ ነበሩ ማለት አይቻልም፡፡የእኔም እንደዚሁ ነው፡፡በመጽሀፉ ለማሳየት የሞከርኩት ይህንን ነው፡፡ሴራ የሚሰሩ ሰዎች ነበሩ፡፡እነዚህ ሰዎች ባላሰቡት መንገድ እንዲህ አይነት ነገር በመፈጠሩ ለእስር ተዳርገዋል፡፡እኔ አልታሰርኩም፡፡መቼም ብታሰር ጥሩ ነበር ይለኛል ብለህ እንደማትጠብቀኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ላይፍ –የአገሪቱ ህገመንግስት ፌደራላዊ ስርዓት መገንባቱን በማወጅ ሁለት የፌደራል ክልሎችንና ዘጠኝ ክልሎች እንዲቋቋሙ አድርጓል፡፡ስርዓቱ በብሄር ብሄረሰቦች የሚያምን በመሆኑም በዛ ያሉ ብሄር ተኮር ፓርቲዎች ተፈጥረዋል፡፡እርስዎ ደግሞ ብሄር ተኮር ፓርቲዎች ከፓርቲነት ወደ መንግስታዊ ወደልሆኑ ተቋማት እንዲወርዱ መፈለግዎን በመጻህፉ ጠቅሰዋል፡፡አባባልዎ ከነባራዊው የአገሪቱ ሁኔታ ጋር አይጋጭም?
ግርማ – እረ በፍጹም አይጋጭም፡፡በግልጽ መጽሀፉ ላይ እንዳስቀመጥኩት እነዚህ ድርጅቶች የሲቪክ ማህበራት መሆን ይችላሉ፡፡ለምሳሌ በኦሮሞ ላይ ህገ ወጥ ነገር ሲፈጸም እነዚህ ድርጅቶች ተጎዳ የሚሉትን የህብረተሰብ ክፍል በመያዝ ችግሩን ማሳየት ይችላሁ፡፡ፓርቲዎች መመስረት ያለባቸው በአስተሳሰብ እንጂ በብሄር መሆን የለበትም ምክንያቱም የኦሮሞ የአማራ የሚባል አስተሳሰብ የለም፡፡እንደዚህ ከሆነ እኮ አይሁዶች አንድ ፓርቲ ብቻ ይኖራቸው ነበር፡፡አረቦች ጋርም የምናገኘው አንድ ፓርቲ ብቻ ይሆን ነበር፡፡ኦሮሞ ላይ የሚደርስ ችግር እንዲሰማን የግዴታ ኦሮሞ መሆን አይጠበቅብንም፡፡ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው፡፡በብሄር ላይ ተመስሮቶ ፓርቲ መፍጠር የሰውን ልዮ አፈጣጠር አለመገንዘብ ነው፡፡
ላይፍ — ህብረ ብሄራዊነትን በመስበክ አንድነትን ለማጎልበት የሚጥሩት የፊውዳል ልጆችና የቀድሞ ስርዓት ናፋቂዎች ናቸው ይባላል፡፡እርስዎ የፊውዳል ልጅ ይሆኑ እንዴ ?
ግርማ — የፊውዳል ልጅ አይደለሁም፡፡ነገር ግን በባዮሎጂ መደራጀት የለብንም ብዬ አምናለሁ፡፡አይ መደራጀት አለብን የሚሉ ካሉም መብታቸው ነው፡፡ይህንን አከብራለሁ፡፡ሰው ከተሰጠው ነጻነት አንጻር መሳሳት መብቱ ነው የማይችለው ማሳሳት ነው፡፡እስኪ አስበው አንድ የኦሮሞ ልጅ ኦሮሞ ስለሆንኩ ምረጡኝ ቢል አያሳፍርም?፡፡አንድ አማራ እኔ አማራ በመሆኔ ልትመርጡኝ ይገባል በማለት ቢንጎማለል አያሳፍርም?፡፡ ኢትዮጵያ በጣም የተለየች ናት፡፡ኦሮሞ ወይም አማራ ስለሆንኩ ምረጡኝ ብለህ በክልልህ ብትመረጥ አገሪቱን መምራት አትችልም፡፡ኢትዮጵያን ለመምራት ኢትዮጵያዊ መሆን ያስፈልጋል፡፡እነዚህ ድርጅቶች ምንም አይነት ነገር መፍጠር አይችሉም እያልኩኝ አይደለም፡፡ነገር ግን አንድ የኦሮሞ ተወላጅ ከክልሉ ውጪ ያለውን ህዝብ ድጋፍ ለማግኘት ሁሉንም የሚወክል ሆኖ መቅረብ አለበት፡፡ይህን ለማድረግ ደግሞ ከብሄሩ ይልቅ የሁሉንም ልብ ሊያስገኝለት የሚችልን ሃሳብ መያዝ
ላይፍ — አሁን እርስዎ ከሚነግሩን በተቃራኒው ኢትዮጵያ ውስጥ መንደርተኝነት፣ብሄርተኝነትና ክልላዊነት እየተስፋፋ ይገኛል፡፡በዚህ ክበብ ውጪ በኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት ለሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ነገሮች አስቸጋሪ አይሆኑም?
ግርማ — የህብረ ብሄራዊፓርቲዎች ፈተናም ይህ ነው፡፡ሰዎች ስሜታቸው ተነክቶ የሚነሱት ሐይማኖታቸው ብሄራቸውን የተመለከቱ ነገሮች ሲነካባቸው ነው ይህ በጣም መጥፎ ነገር ነው፡፡ለምሳሌ አንተ የቡርጂ ህዝብ ተወካይ ነኝ ብለህ ብትነሳ በፓርላማው የምታገኘው አንድ ወንበር ነው፡፡ታዲያ እንዴት ነው በአንድ ወንበር በዚህች አገር ተጽእኖ ለመፍጠር የምታስበው? እኔም የወረዳ 6 ህዝባዊ ንቅናቄን በማቋቋም እንዴት ነው አገር መምራት የምችለው?፡፡ በትልቁ የፖለቲካ ሂደት ውስጥ ምንም ለውጥ እንደማያመጡ አልተረዱም፡፡
ላይፍ — በምክትል ፕሬዘዳንትነት የሚመሩት የፓርቲዎ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የፖለቲካ ፍልስፋና ወይም የሚከተለው ርዕዮት ምንድን ነው?
ግርማ — ይህ በግልጽ በፕሮግራማችን ላይ ተቀምጧል፡፡ጋዜጠኞች ስለማትመለከቱ ወይም ከእኔ ለመስማት ካልፈለግክ በስተቀር ማ ለት ነው፡፡አንድነት በግልጽ የሊበራል ዲሞክራሲ አራማጅ ነው፡፡ነገር ግን ይህንን የምንከተለው በኢትዮጵያ ነባራዊ እውነታ ነው፡፡ለምሳሌ ተማሪዎች በሙሉ እየከፈሉ መማር አለባቸው አንልም፡፡ይህ ቢሆን ብዙ ልጆች ትምህርት ቤት መሄድ አይችሉም፡፡ከስምምነት ዲሞክራሲም በተወሰነ ደረጃ የምንወስደው ነገር አለን፡፡እንደ አስተሳሰብ መውሰድ ያለብን ጠቃሚ የሆነውን ነገር ነው፡፡አንድነት ውስጥ በጣም ብሄርተኛ የሆነ ሰው በመግባት ፓርቲው የሆነን ብሄር ሆን ብሎ የመጨቆን አላማ እንደሌለው መመልከት ይችላል፡፡
ላይፍ — ይህንን ጥያቄ ያነሳሁት በቅርቡ የፓርቲው ፕሬዘዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ‹‹አንድነት ሊበራል ነኝ ካለ ችግር ይፈጠራል››በማለት በመናገራቸው ነው
ግርማ — እሱ እንግዲህ በቅርቡ ጠቅላላ ጉባዔ ስለምንጠራ ምላሽ ያገኛል፡፡በሌላ መንገድ ካልሆነ ጭልጥ ብለን ነጭ ሊበራል የምንሆንበት ምክንያት ስለሌለ እርሳቸውም የሚወጡበት ነገር የለም፡፡
ላይፍ — ወደ ፓርላማው እንመለስ፣በቅርቡ ባስነበቡን አንድ አርቲክል ፓርላማው በቀኝ ክንፍ ሲያጠቃ ዋለ ብለዋል፡፡ሌሎችም በፓርላማው ውስጥ መጠነኛ የሆነ መነቃቃት ስለመፈጠሩ ይናገራሉ፡፡ይህ መነቃቃት እውነት አቶ መለስ ዜናዊ ከሞቱ በኋላ የተፈጠረ ነው?
ግርማ — ምንም ጥርጥር የለውም እርሱ ስለመሆኑ፡፡ነገር ግን በፓርላማውም ይሁን ከመንገስት ባለስልጣናት ይህ የሆነው የእርሳቸውን ሞት ተከትሎ ነው ይላሉ ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡እነርሱ ሊሉት የሚችሉት ባለፉት ሶስት አመታት የአቅም ግንባት ተካሂዶ በመጨረሻዎቹ ሁለት አመታት ሰራንበት ነው፡፡ይህ ግን ትክክል አይደለም፡፡አቶ መለስ በነበሩበት ግዜ ፓርላማው ምንም አለ ምን እርሳቸው የሚሉት ነገር ብቻ ስለሚፈጸም ለምን እናገራለሁ የሚል ስሜት ነበር፡፡እርሳቸው ከሄዱ በኋላ ግን አቶ ሃይለማርያም ፓርላማውን እንደተቋም መጠቀም ግድ ይላቸዋል፡፡ምክንያቱም እርሳቸው እንደ ቀድሞው ሁሉን ሉጠቀልሉ አይችሉም፡፡እዚህ ላይ ካነሳህው አይቀር ፓርላማው በቀኝ በኩል ሲያጠቃ ውሎ በግራ በኩል ጎል አገባ ብዬ ነበር ነገር ግን አሁን ፓርላማው ያገባው ጎል ተሰርዟል፡፡በእግር ኳስ ጎል ካገባህ በኋላ ጎሉ የሚሰረዘው አመከልክተህ ነው አይደል?እዚህ ግን ጎሉ የተሰረዘው እንዲህ አይደለም፡፡የተሰረዘው ጎል የሚያመጣው ነገር አለው፡፡ፓርላማው በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ቢወስን በግምገማ ውሳኔው የሚታጠፍ ከሆነ ፓርላማው ወደ ቀድሞ ቦታው ሊመለስ ይችላል የሚል ስጋት አለኝ፡፡የአንድ የምክር ቤት አባል ያለመከሰስ መብት የሚነሳ ጥያቄው በፍትህ ሚኒስትር በኩል ነው፡፡ከዚህ በፊት የአቶ ያረጋል አይሸሹም አለመከሰስ ሲነሳ በህጉ መሰረት አልነበረም አሁንም እንዲህ ይደረግ ተብሎ ነበር ይህንን ለማድረግ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነበር ፓርላማው የወሰነው ግን አሁን ውሳኔው እንዲታጠፍ ተደርጓል፡፡ሰውዬውም ከአገር ወጥተዋል፡፡በእውነት የ500 ካሬ ጉዳይ አይደለም፡፡አባሉም መሬቱን ከአንዱ ወስደው ለሌላ ሰጥተዋል ነው የተባለው፡፡ለማን ነው የሰጡት ከማን ነው የወሰዱት የሚለውን ነገር እንደ ጋዜጠኛ ማጣራትና ለህዝብ ማሳወቅ የእናንተ ድርሻ ነው፡፡
ላይፍ — በፓርላማው የሚያደርጓቸው ንግግሮችና የሚያቀርቧቸው ሞሽኖች ተቀባይነት አጥተው ወይም የተለየ ትርጉም ተሰጥቷቸው ሲቀርቡ ሲመለከቱ ምን አለበት ፓርላማ ባልገባሁ ብለው አያውቁም?
ግርማ – አላውቅም፡፡ምክንያቱም ከመግባቴም በፊት የማቀርበው ሃሳብ ተቀባይነትን ያገኛል ብዬ አልጠበቅኩም፡፡ነገር ግን ተናድጄ አውቃለሁ ስትናደድ ንግግር ማቋረጥ ትችላለህ እኔ ግን ለመበጥበጥ አልገባሁምና ይህንን ማድረግ አልፈለግኩም፡፡እኔ እዛ ስገባ አማራጭ እንዳለ አውቀው እንዲወስኑ የታሪክ ጨዋታ ለመጫወት ነው የገባሁት፡፡ሁሉም ነገር በታሪክ የሚመዘገብ በመሆኑ በታሪክ ተጠያቂ እንሆናለን፡፡
ላይፍ — በተለያየ አጋጣሚ ከአገር ሲወጡ በውጪ የሚያገኟቸው የሌሎች አገራት የፓርላማ አባላት ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ አባል በፓርላማ መሆንዎን ሲሰሙ ምን ይልዎታል?
ግርማ — ያው መገረማቸው አይቀርም፡፡አብረውኝ የሚሄዱት የፓርላማ አባላትም እንዲህ አይነት ነገር ሲነሳ ይሸማቀቃሉ እኔ ግን አልሸማቀቅም የሚሸማቀቁት እነርሱ ናቸው፡፡በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ ኢህአዴግ ሜዳውን ክፍት በማድረግ ለመድብለ ፓርቲ ፖለቲካ የሚጠቅም ነገር ያደርጋል የሚል እምነት ነበረኝ ነገር ግን ምንም ቀዳዳ ሳይፈጥር ሁሉንም አሸንፊያለሁ አለ፡፡ዝግጁነት አለመኖሩን በዚህ አሳይቶናል፡፡ስለዚህ ለ2007 ምርጫ ነጥቀን ለመውሰድ ጠንክረን መስራት ይኖርብናል፡፡እንደ አንድነትም ይህንን ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምረናል፡፡
ላይፍ — አትሌት ሃይሌ ገ/ስላሴ በቅርቡ የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት መሆን እንደሚፈልግ ይፋ አድርጓል፡፡የአትሌቱን የፕሬዘዳንትነት ፍላጎት እንዴት አገኙት?
ግርማ –ከራሱ ከሃይሌ ጋር ተነጋግሪያለሁ፡፡በመጀመሪያ ሃይሌ ፕሬዘዳንት ለመሆን የፈለገው እንደ አሜሪካ መስሎት ነው፡፡ምንም ስልጣን የሌለው ፕሬዘዳንት ሃይሌ መሆን ይፈልጋል የሚል እምነት የለኝም፡፡አሁን ግን የፓርላማ አባል ሆኖ የሆነ ነገር ማበርከት ፈልጓል፡፡ነገር ግን በግሉ ተወዳድሮ ፓርላማ ቢገባ ምንም የሚጨምረው ነገር እንደሌለው ነግሬዋለሁ፡፡ሃይሌ ኢህአዴግ መሆን አይችልም ምክንያቱም አስተሳሰቡ የካፒታሊስት ነው፡፡ሃይሌ የአንድነት አባል መሆን ግን ይችላል፡፡የምችለውን በግሌ ማድረግ እችላለሁ ካለ መብቱ ነው፡፡አንዳንድ ሰዎች ሃይሌ ወደ ተቃዋሚዎች ቢመጣ በገንዘብ ይደግፋቸዋል ይላሉ ነገር ግን ይዞ መምጣት ያለበት ሊበራል የሆነ አስተሳሰቡን ነው፡፡ከዚህ ውጪ ግን ሃይሌን በኢህአዴግ መስመር ውስጥ አገኘዋለሁ ብዬ አልጠረጥረውም፡፡ ስልጣን የሌለው ፕሬዘዳንት ከሚሆንም የሪዞርቱ አስተዳዳሪ ቢሆን ይሻለዋል፡፡
ላይፍ — የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል መሪ ቃል ፓርቲዎ ህዝባዊ ንቅናቄ እያደረገ ይገኛል፡፡በአጠቃላይ ተቃዋሚዎች የሚገኙበትን መነቃቃት እንዴት ተመለከቱት?
ግርማ — ብዙዎች አንድነት ንቅናቄውን የጀመረው ከሌሎች ኮርጆ ነው ይላሉ ፡፡ነገር ግን ኮርጀንም ከሆነ ችግር የለብንም፡፡አውነታው ግን ይህ አይደለም እያደረግነው ያለው በስትራቴጂክ ፕላናችን መሰረት ነው፡፡ጎንደርና ደሴ ላይ ያደረግናቸው ሰላማዊ ሰልፎች በመዋቅራችን አማካኝነት የሰራነው ነው፡፡በቀጣይም ይህንን በተለያዮ ክልሎች እናደርጋለን፡፡ሚልዮኖች ከእኛ ጋር ሆነው የሚጠይቁት የተለያዩ መሰረታዊ ጥያቄዎችን ነው፡፡
ላይፍ — የፓርቲውን ንቅናቄ መጀመር ተከትሎ በዛሚ ሬዲዩ በጋዜጠኞች የክብ ጠረጴዛ ፕሮግራም ሚሚ ስብሃቱ አንድነት ይህንን ንቅናቄ የጀመረው ከውጪ በተለይም ከግንቦት 7 ከግብጽ ካገኘው ገንዘብ ፍርፋሪ እንዲደርሰው አስቦ ነው ብላለች ይህ አለመሆኑን እርስዎ በምን ሊያስረዱ ይችላሉ?
ግርማ — እንኳን ነው የምንላት፡፡በስተርጅና ሚሚ መሆኗን ከማሳየቷ ውጪ እርሷ እንዲህ ብላናለችና አይ እኛ እንዲህ ነን ማለት አንፈልግም፡፡አንድ ወቅት ላይ ሚዲያውን በተመለከተ የሆነ ካውንስል ለማቋቋም መንቀሳቀሷን በተመለከተ ለንባብ የበቃ ጽሁፍ አንብቤ ነበር፡፡ጽሁፉ ካውንስሉ መቋቋሙን ቢደግፍም የሚሚን መኖር ግን ክትፎ በፖፖ ብሎት ነበር፡፡እኔም ከዚህ ውጪ የምለው ነገር የለኝም፡፡
ላይፍ — ገዢው ፓርቲ ንቅናቄውን ከአክራሪነት እያቆራኘው ከመሆኑም በላይ ፖሊስ ወረቀት የሚበትኑ አባሎቻችሁን እያሰረ ነውና ንቅናቄው የሚሳካ ይመስልዎታል?
ግርማ — ንቅናቄው እኮ ይህንንም ለመታገል ታስቦ የተጀመረ ነው፡፡እያንዳንዱ ሰው አምባገነንነትን እምቢ ማለት አለበት፡፡ዋነኛው የንቅናቄው ግብ ከፍርሃት መውጣታችንን ማሳየት ነው፡፡ይህንንም እያደረግን እንደሆነ እናምናለን፡፡
ላይፍ –ህዝባዊ ንቅናቄው የሶስት ወር ዕድሜ እንዳለው ተነግሯል፡፡ከሶስት ወር በኋላ ምን ልታደርጉ ነው?
ግርማ — የሶስት ወሩ ንቅናቄ እንደ መነሻ ነው፡፡መስከረም ላይ ጠቅላላ ጉባዔ ይደረግና የሁለት አመት እንቅስቃሴያችን ይገመገማል፡፡ከዚያም 2007 ምርጫ የምናደርገውን ዝግጅት ህዝብን በሚያሳትፍ መልኩ እንገፋበታለን፡፡እናም ይህ የመጀመሪያ እንጂ በየትኛውም መንገድ የመጨረሻችን አይሆንም፡፡መጽሐፍስ የፈራ ይመለስ ይል የለምን?

የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ቃለ ምልልስ ከጀርመን ድምጽ ራድዮ ጋር

$
0
0

[jwplayer mediaid="6117"]

የጀርመን ድምጽ ራድዮ ጋዜጠኛ ሸዋዬ ለገሰ የዘ-ሐበሻ እና የጤና አዳም ድረ ገጽ ዋና አዘጋጅ ሔኖክ ዓለማየሁን አነጋግራዋለች። ቃለምልልሱ በጀርመን ድምጽ ራድዮ ላይ ተላልፏል። የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች እንድተከታተሉት እዚህ በማምጣት አካፍለናችኋል።

ስለጤና ጉዳይ የሚቀርቡ መረጃዎችን ምን ያህል ህዝብ እንደሚያገኛቸዉ፤ ወይም ለምን ያህል ህዝብ እንደሚደርሱ መገመት ይቸግራል። ነገር ግን አንድ ነገር ግልጽ ነዉ ሰዎች ለጤና ይዞታቸዉ ትኩረት መስጠትን ችላ ሊሉ አይገባም።
ጤና-ነክ ጉዳዮችን በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ለማቅረብ መጣር የእኛን ኅብረተሰብ ሊነቃ ይችላል የሚል እምነት ያላቸዉ ወገኖች ራሱን የቻለ የጤና ድረገጽ ከፍተዉ መረጃዎችን ሲያሰራጩ ወራት ተቆጥረዋል።
ዘመኑ የቴክኒዎሎጂ ነዉ የመረጃ፤ በአንዱ ጓዳ የተከሰተዉን ሌላዉ ባለበት ሆኖ ሊሰማዉ መንገዱ ተመቻችቷል፤ ለብዙሃኑ። በዘመነ ኢንቴርኔት ምስጢር የለም፤ ራዲዮና ቴሌቪዥን ዜናዎችን አልተከታተልኩም፤ የጤና ጉዳይ መረጃዎችን እንደልቤ አላገኝም ከሚባልበት ጊዜ ልንሻገርም ዳርዳር እያልን ይመስላል። አፍሪቃ ዉስጥም ቢሆን ይህ ዛሬ ብዙም የሚወራለት የራቀና ያልተደረሰበት ጉዳይ አይደለም።

ዛሬ ይላል የጤና አዳም ድረገጽ አንቀሳቃሽ፣ ዛሬ ሰዎች ለራዲዮና ቴሌቪዥኑ ጊዜ ቢያጡ እንኳ ከያሉበት በእጅ ስልካቸዉ በየመንገዱም ቢሆን የሚሹትን መረጃ ማንበብ ይችላሉ። የተለያዩ ወቅታዊ ዜናዎችን ከመዘገብ በተጓዳኝ ሄኖክ ዓለማየሁ ለጤና ጉዳይም ትልቅ ትኩረት መስጠቱን የሚያንቀሳቅሰዉ ድረ ገጽ ዘሃበሻ ይናገራል። ለጤና መረጃዎችን የምታጋራዉን ድረገጽም እዚያዉ ላይ ታዝላ ነዉ ያስተዋልኳት። አዘጋጅዋ ለጤና ጉዳዮችን ትኩረት መስጠት ይገባል በሚል ለኢትዮጵያዉያን አንባቢዎቹ መረጃ በመስጠት ለማበረታታት ታስቦበት የተጀመረ መሆኑን ነዉ የሚናገዉ፤
ጋዜጠኛ ሄኖክ እንደሚለዉ ባላቸዉ መረጃ መሠረት በርካታ የድረገጹ ጎብኚዎች የሚገኙት እዚያዉ ሰሜን አሜሪካ ነዉ። ከኢትዮጵያስ ጎብኚዎች ይኖሩት ይሆን? ዝርዝሩን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ፤
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ

(ምንጭ፡ የጀርመን ድምጽ ራድዮ)

40 የዓድዋ ተወላጆች ታሰሩ

$
0
0

Abrham Destaከዓመታት በፊት በእርሻ መሬት ማነስ ምክንያት ወደ 400 የሚሆኑ የዓድዋ ተወላጆች (ልዩ ስሙ ‘ወርዒለኸ’ ከሚባል ቦታ) በመንግስት አካላት ከቀያቸው ተነስተው በቃፍታ ሑመራ ወረዳ (ጣብያ ማይወይኒ፣ ቁሸት መንሼን) እንዲሰፍሩ ተደረገ። ቤት ሰሩ፤ ኑሯቸው እዛው መሰረቱ።

አሁን ግን አዲስ ነገር ተከሰተ። የሰፈሩበት፣ ኑሯቸው የመሰረቱበት መንደር ለከብቶች እርባታ ‘ተስማሚ ሁኖ ስለተገኘ’ በኢንቨስትመንት ስም ከብቶች ለሚያረባ ድርጅት እንዲሰጥ ተወሰነ። አርሶአደሮቹ ያለ ምንም ካሳ ቀያቸው ለቀው እንዲነሱ ታዘዙ። ካሳ ጠየቁ፤ እንደማይሰጣቸው ተነገራቸው። ለመኖርያ የሚሆን ቅያሪ ቦታ ጠየቁ። መልስ አልተሰጣቸውም። ቀያቸው ባጭር ግዜ ዉስጥ ለቀው እንዲወጡ ሲነገራቸው አርሶአደሮቹ ጠንከር ያለ ተቃውሞ አሰሙ።

ከነዚህ 400 የሚሆኑ የተፈናቀሉ አርሶአደሮች ‘የተቃውሞው አስተባባሪዎች ናቸው’ ተብለው የተጠረጠሩ 40 አባወራዎች ታሰሩ። ክስ መመስረት እንኳን አይችሉም። ምክንያቱም መሬት የመንግስት ነው።

መሬት የሌለው ዜጋ ሀገር የለውም። መሬት የመንግስት ከሆነ የመንግስት አካላት (የገዢው ፓርቲ አባላት) በፈለጉበት ግዜ ዜጎችን ማፈናቀል ይችላሉ።

 

ለትግራይ ተወላጆች በሙሉ ……. 
Abraha Desta
—————————————-
‘ዜጎች ነንና ፍትሓዊ ልማት ያስፈልገናል’ ሲንል አሰሩን። ‘ደማችን ገብረናልና ሰለማዊ ሰልፍ የመውጣት መብታችን ይከበርልን’ ስንል ደበደቡን። ‘ብዙ መስዋእት ከፍለናልና ነፃነታችንን አትንፈጉን’ ስንል ትጥቃችንን አስፈቱን። መብታችንን ለማስከበር ስንሞክር ገደሉን።

ግን ይህን ሁሉ ወላጆቻችን፣ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የከፈሉት መስዋእት ዓላማው ምን ነበር? ደርግን ደምስሶ ሌላ ደርግ መመስረት? ይሄማ ሊሆን አይችልም። ደርግ’ኮ ደርግ ያሰኘው ተግባሩ ነው።

ደርግን የምንጠላው ደርግ ስለሆነ አይደለም። መጥፎ ምግባር ስለነበረው ነው። ጨቋኝ ስለነበረ ነው። ገዳይ ስለነበረ ነው። ገዳዮቹ ቢቀያየሩ እንኳን ተግባራቸው ያው ግድያ መሆኑ አይቀርም። ገዳይ ማን ይሁን ምን ያው ገዳይ ነው። ደርግ እንዲጠላ ያደረገው ገዳይነቱ ነው። ለኛ የገደለ ሁሉ ደርግ ነው። መግደል፣ በሰው ልጅ ላይ ግፍ መፈፀም፣ መጨፍጨፍ ምን ያህል መጥፎ መሆኑ ከልምድ እናውቀዋለን። ስቃዩ ምን ያህል መራራ እንደሆነ ከራሳችን በላይ ማንም ሊያስረዳን አይችልም።

የኢህአዴግ ወታደሮች (ይቅርታ የመንግስት ወታደር ስለሌለ ነው) ኮፈሌ አከባቢ በህዝቡ ላይ ችግር መፍጠራቸው እየሰማን ነው። ወታደሮቹ ለሚወስዱት እርምጃ ምክንያት ያቀርቡ ይሆናል። የፈለገ ምክንያት ቢኖር እንኳን በሰለማዊ ዜጎች ላይ ግፍ መፈፀም ሊደገፍ አይችልም። መፍትሔም ሊሆን አይችልም። የኃይል እርምጃ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንደማይሆን ለመገንዘብ የደርግ ስርዓት ትግራይን ሲደበድብ የተከሰተውን ማስታወስ በቂ ይመስለኛል።

የኢህአዴግ ወታደሮቹ በኮፈሌ ሰለማዊ ህዝብ ላይ ችግር ሲፈጥሩ በተጎጂዎች ስነልቦና የሚፈጠር ስሜት ልክ የደርግ ወታደሮች እኛ ላይ ግፍ ሲፈፅሙ በኛ አእምሮ ዉስጥ የተከሰተው ሓዘንና የእልህ መንፈስ ነው። ደርግ የፈፀመው ግፍ በኛ ከባድ ጠባሳ ጥሎ አልፈዋል። በኮፈሌዎችም ተመሳሳይ ነው። ለኮፈሌዎች (በኛ ስሜት) ኢህአዴግ ደርግ ሁነዋል። ደርግ እኛን ገደለ፤ ኢህአዴግ እነሱን ገደለ። ያው የሁለቱም ግድያ ነው። ሁለቱም ስርዓቶች በየ አቅጣጫቸው ተመሳሳይ ናቸው። ገዳዮች ናቸው።

በሰዎች ላይ ግፍ ሲፈፀም መቃወም ይኖርብናል። ደርግ ሲገድለን ግድያው ለደገፉ፣ የደርግ ተግባር ደጋፊዎች ለነበሩ፣ ወይ ተቃውሟቸውን በግልፅ ላላሰሙ ወገኖች የሚኖረንን ስሜት በራሳችን እንገምግመው። ቤተሰቦቻችን ላይ በደል ወይ ግድያ ሲፈፀም ከጎናችን ለቆሙ ወገኖች ትልቅ ውለታ እንደዋሉልን የሚሰማንን ያህል በሌሎችም ተመሳሳይ ግብረመልስ ይኖራል። ጉዳት ከደረሰባቸው ዜጎች ጎን መሰለፍ የብሄር ወይ የሃይማኖት ጉዳይ አይደለም፤ የሰብአዊነት ጥያቄ እንጂ።

ስለዚህ ይህን የኢህአዴግ ዜጎች የመበደል ተግባር መቃወም ይኖርብናል። ፖለቲከኞች ስልጣናቸው ለማደላደል ሰለማዊ ሰዎች ላይ ግፍ ይፈፅማሉ። ሰለማዊ ሰው ሲበደል ሌላ የሚጠቀም ሰለማዊ ሰው ሊኖር አይችልም (ከፖለቲከኞች በቀር)። በስልጣን ላይ ያለው አካል ሰው የሚበድለው በስልጣኑ ለመቆየት ሲል ነው፤ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችም ሰው መንግስት ሲበደል ድጋፍ የሚያገኙበት ዕድል ይኖሯቸዋል። ስለዚህ ከህዝብ በደል ሊጠቀሙ የሚችሉ ፖለቲከኞች ብቻ ናቸው። ለሰለማዊ ሰው ግን (የሰለማዊ ሰዎች በደል) ጉዳት ብቻ ነው ያለው። ስለዚህ መቃወማችን ግድ ይላል።

ህወሓት ኢህአዴግ ከኛ ወጣ። እኛን ተመልሶ በደለ። ይባስ ብሎ ደግሞ በኛ ስም ሌሎችን ይበድላል። ይህ ህዝቦችን የመበደል ተግባሩ ሁላችን እንቃወመው።

ይህ የሰብአዊነት ድምፅ ነው።

It is so!!!

 

 


የችግሮች መንስኤ እኛ እራሳችን ነን –በይበልጣል ጋሹ

$
0
0

በይበልጣል ጋሹ

commnetዛሬ ከጊዜ ወደ ጊዜ ችግር እየጨመረ መምጣቱ ዓለምን ስጋትና ጭንቀት ውስጥ ከቷታል። ለአንዱ ችግር መፍትሔ ይሆናል ተብሎ የቀረበው ሃሳብ በሌላ በኩል ሊፈታ የማይችል ችግር ፈጣሪ ሲሆን መመልከት የተለመደ ነገር ነው። ምንም እንኳ /ከተለዩ ሰዎች በስተቀር/ ሰው በራሱ ችግር ለመፍጠር ተነሳሽ ባይሆንም ለመፍትሔም የዘገኘና ቆራጥነት የማይታይበት በመሆኑ ለችግሩ መበባስ መንስኤም ምክንያትም ነው። በዚህች አጭር ጽሁፍም የእኛ የችግር መንስኤነትን በአጭሩ ለማሳየት እሞክራለሁ። ሙህራን በዚህ ዙርያ ሰፊ ጥናት በማድረግ እንዲያቀርቡልን ግብዣየ በደስታ ነው።

 

  • እንደሚታወቀው እንደ አህጉራችን አፍሪካና አገራችን ኢትዮጵያ ሁላችንንም የሚያሳስበንና ጎልቶ የሚታየው የአስተዳደር/ፖለቲካዊ ችግር ነው። እንደሚታወቀው ሁሉም የፖለቲካ ድርጅት/ገዢው ፓርቲ/ ለነጻነት፣ ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለሰባዊ መብትና ለዲሞክራሲ እቆማለሁ ብሎ መነሳቱንና የህዝብ ድጋፍ ማግኘቱን ረስቶ የበፊቱንና የአለፈውን የአስተዳደር ዘመን በእጅጉ የሚያስመሰግን ሁኖ እናገኘዋለን። ዘረኝነትንና አድሎአዊነትን ለመዋጋት የተነሳ ድርጅት ከበፊቱ በበለጠ ችግር ፈጣሪ ሲሆን ጎልቶ ይታያል። ሙስናን ለመዋጋት የተነሳ ድርጅት ለሙስና መስፋፋት ዋነኛ ተዋናይ መሆኑ በእጅጉ ያሳስባል። ድህነትን ለማጥፋት የተነሳ ድርጅት ራሱን ከማበልጸግ ባለፈ የህዝቡን የኑሮ ደረጃ ከቲዮሪ/theory/ ባለፈ መቀየር አልቻለም። ዲሞክራሲን አሰፍናለሁ ብሎ የተነሳ ድርጅት ሚድያ ላይ ከመናገር ባሻገር ህብረተሰቡን የዲሞክራሲ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ ግን አልቻለም። ምን አልባት ኢትዮጵያ በዲሞክራሲዊ አስተዳድር ስርዓት ትመራለች፣ ድህነት ቀንሷል ልንል እንችል ይሆናል፤ እውነት ነው የእኛም ትልቁ ችግራችን ይህ ነው። በመካከላችን 100% ልዩነት መኖሩ የተወሰነው የህብረተሰብ ክፍል በምቾት፣ በሰላም፣ በደስታ፣ በነጻነትና ዲሞክራሲ ሲኖር አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል ደግሞ በእጅጉ በሚያሳዝን ሁኔታ በርሀብ፣ በችግር፣ በስቃይ፣ በአድሎአዊነትና በነጻነት እጦት ውስጥ መኖሩ ችግሩ ጎልቶ እንዲታይ አድርጎታል።

ለችግር መንስኤዎች እኛው ነን ያልኩበት ምክንያትም የፓርቲውን/የድርጅቱን ዓላም በሚገባ ሳንረዳና ሳንገነዘብ ከመጀመሪያው ጀምረን ይሁን ብለን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረጋችን ነው። ግማሾቻችን ደግሞ ሳይመቸን እንደ ተመቸን፣ ሳንጠግብ እንደ ጠገብን፣ ነጻነትና ዲሞክራሲ ሳይኖር በነጻነት እንደምንኖር ሁሉ እንደ ሄሮዶሳውያን ሺ ዓመት ንገስ፣ ከአለአንተ አገር ትገለበጣለች፣ ለህዝቡ ተቆርቋሪ የለም እያልን ችግሩን እንዲያስተካክል በግልጽ ከመናገር ይልቅ የማይገባውን የምስጋና ቅኔ ስለምናቀርብ፤ ከፊሎች ደግሞ በጊዜያዊ ጥቅም ተይዘው ችግሩን እንዳንመለከት ከለላ ስለሆነብንና መሰል ችግሮች ስላሉብን ለችግሩ መባባስ ዋነኛ ተጠያቂዎችም መንስኤዎችም እኛው እራሳችን ነን።

  • ለተለያዩ ችግሮች የመፍትሔ ሃሳብ ከምንጠብቅባቸው የእምነት ተቋማት ሳይቀር በመሪዎቻችን መካከል ዘርፈ ብዙ ችግሮችን እናገኛለን። ጥቂት የእምነት መሪዎች/አባቶች ነን ባዮች ከአለም ባለስልጣናት ባልተለየ መልኩ አስተዳደራዊ በደል በእምነት ተቋማቸው ላይ ሲያደርሱ መመልከት የተለመደ ነገር ሁኗል። ዘረኝነትንና ሙስናን ይዋጉልናል ያልናቸው ሰዎች ለችግሩ መፋጠን ዋነኛ አካል ሁነዋል። ቤተ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር በተሰጠችው መመርያ ተጠቅማ ለአለም ሰላም የማደል ፀጋ ቢኖራትም ዳሩ ግን እነዚያ ጥቅመኞች ፀጋዋን ለዓለም እንዳታድል አዚም ሁነውባታል።

ለዚህም ችግር መንስኤ  እኛው የእምነቱ ተከታዮች ነን። ለምን ቢባል በተለያየ ዘርፍ ላይ ለሚገኙ የእምነት ተቋም አስተዳዳሪዎች ፊት በሙስና፣ በስርቆትና በብልሹ አስተዳደር ስለበለጸጉ ሰዎች እናወራለን፣ እንተርክላቸዋለን። በእነዚህ ነውረኛ  ሰዎች ላይም ምንም አይነት የእምነት ሃላፊነታችንንና ግዴታችንን መወጣት ባለመቻላችን ሌሎች እንደማበረታቻ ቆጥረውታል። በእነዚህ እና መሰል ምክንያቶች ችግሮች እንዲበባሱ የእኛ አስተዋጾ ቀላል እንዳልሆነ መገንዘብ ይቻላል።

  • ወደ ባዕድ ሀገር በስደት የሚጎርፈው ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ ሀገር ቤት ሰው የማይኖር እስኪመስል ድረስ ፍላጎቱና ፍልሰቱ ከፍተኛ ሁኗል። ለዚህ ችግር በዋናነት የመንግሥት አስተዳደራዊ ድክመት ቢሆንም እኛም የበኩላችንን ድርሻ ባለመወጣታችን የመጣ ትልቅ ችግር ነው። በስደት የሚኖሩ ወገኖች የስደትን አስከፊነት እያወቁ ነገር ግን በሀገር ቤት ለሚኖሩ ወገኖቻቸው ችግሩን በሚገባ አለማስረዳት፣ ወደ ሀገር ቤት በሚሄዱበት ጊዜም የተለየ ለብሰውና መስለው መታየታቸው እና የሚሰሩትን የሥራ አይነት እንኳ በትክክል አድካሚነቱንና አሰልችነቱን አለመናገር ለሌሎች ከሀገር መውጣት ምክንያት ሁኗቸዋል። ስለዚህ የሆነውንና የሚሆነውን በትክክል መረጃ መስጠት ብንችል ወገኖቻችን በይሆናልና በማይሆን ተስፋ ከሀገር ወጥተው የስደትን አስከፊ ህይወት ተጠቂ ባልሆኑ ነበር።

ስደት ምንልባት በኢኮኖሚ የተሻለ ነገር ሊኖረን ይችል ይሆናል እንጂ የሰላም ኑሮ  ግን መኖር የሚቻለው ተወልደው በአደጉበት ሀገር ነው። በስደት ህይወት የባህል፣ የእምነት፣ የአለማዊነትና የቋንቋ ተፅዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ የተረጋጋና ሰላማዊ ህይወት መምራት በጣም አስቸጋሪና ከባድ ነው። በዚህም የተነሳ በጭንቀትና በውጥረት የሚኖሩ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። ስለዚህ ሰውን ወደ ስደት ህይወት መጋበዝ በጭንቀትና በሃሳብ እንዲኖር መፍረድ የሚል ድምዳሜ ቢሰጥ ያንሳል እንጂ ማጋነን አይሆንም።

በአጠቃላይ እኛ ሁላችንም ብንችል የችግር መፍትሔዎች እንድንሆን ባንችል ደግሞ የችግር መንስኤዎች እንዳንሆን የራሳችንን በጎ አስትዋጾ ማድረግ ይኖርብናል። ለችግር መፍትሔ ይሆናሉ ያልካቸውን 2 ላንሳና ሌላውን እናንተ ቀጥሉበት።

  1.  ችግሮችን በትክክል መረዳት፦ ችግሩን ከስር መሰረቱ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ በአጠቃላይ ሀገራዊ ጉዳቱን መረዳትና ችግሩ እንዳይበባስ የራሳችንን አስተዋጾ ለማድረግ ችግሩን በትክክል መረዳት ይጠበቅብናል። ሙህራን “ችግሩን ማዎቅ የመፍትሔ 50% ነው” እንዲሉ  ችግሩን በትክክልና በጥልቀት መረዳት ካልቻልን መፍትሔ በቀላሉ ለማግኘት አስቸጋሪ ስለሚሆን የችግሩን የት፣ መቼ፣ እንዴትና ወዴት የሚሉትን ጥያቄዎች በማንሳት ችግሩን ከመሰረቱ ማዎቅ ከሁላችን የሚጠበቅ ተግባር ነው።
  2. ችግሩን ለማሶገድ በቆራጥነት መነሳት፦ ችግሩን በትክክል ከተረዳን መፍትሔ ለማምጣት ደግሞ  በቆራጠነት መነሳት ይኖርብናል። ፍራትን፣ ቸልተኝነትን፣ አይሆንም ባይነትን፣ አድርባይነትን፣ ጥቅመኝነትንና ዘረኝነትን ከውስጣችን አሶጥተን ለሀገርና ለተተኪ ትውልድ በሁሉም በኩል የበለጸገች ሀገር ለማስረከብ ቆራጥነትና ሰማትዕነት ያስፈልጋል። የማንም ርዳታ ሳያሻን በራሳችን ተነሳሽነት ሀገራዊ ሃላፊነታችንን ለመወጣት እና ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ሁላችንም ቆርጠን መነሳት ይኖርብናል።…………………….+++

 

Sport: ቲኪ ገላና የኦሊምፒክ ድሏን በሩሲያ ለመድገም ተቃርባለች

$
0
0

ከቦጋለ አበበ

በሁለት ዓመት አንዴ የሚካሄደው የዓለማችን ትልቁ የአትሌቲክስ የውድድር መድረክ (የአትሌቲክስ የዓለም ዋንጫ ) በሩሲያዋ መዲና ሞስኮ ሊጀመር የሃያ አራት ሰዓታት እድሜ ይቀሩታል፡፡ ይህን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በርካታ የስፖርት አፍቃሪዎች በጉጉት እየጠበቁት ይገኛሉ፡፡
ውድድሩ ነገ ሲጀመር ማለዳ ላይ በጉጉት የሚጠበቀው የሴቶች ማራቶን ውድድር ይካሄዳል፡፡ በዚህ ውድድር ውጤት ያስመዘግባሉ ተብለው ከሚጠበቁ አትሌቶች መካከል የኦሊምፒክና የኢትዮጵያ የርቀቱ ባለ ክብረወሰን የሆነችው ቲኪ ገላና ግንባር ቀደሟ ነች፡፡
ባለፈው ለንደን ኦሊምፒክ ከወደቀችበት ተነስታ አስቸጋሪውን የማራቶን ውድድር በድንቅ የአጨራረስ ብቃት ማሸነፍ የቻለችው ቲኪ በዘንድሮው የዓለም ሻምፒዮናም የአሸናፊነት ግምት ያገኘች አትሌት መሆን ችላለች፡፡
tiki gelana
ቲኪ ባለፈው ዓመት በርቀቱ 2፡18፡50 የሆነ ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ የስፖርቱን አፍቃሪዎች ያስደነቀች አትሌት መሆኗ በነገው የዓለም ሻምፒዮና ትኩረት የሚሰጣት አትሌት እንድትሆን አስችሏታል፡፡ ቲኪ በዘንድሮው ዓመትም በርቀቱ 2፡36፡55 የሆነ ሰዓት ያስመዘገበች ጠንካራ አትሌት መሆኗ በውድድሩ የአሸናፊነት ግምት እንዲሰጣት አድርጓል፡፡
ቲኪ ገና በርቀቱ ብዙ ያልተጓዘች ወጣት አትሌት እንደመሆኗ መጠን በነገው የዓለም ሻምፒዮና ውድድሯ ብቻ ሳይሆን ወደ ፊት ብዙ ታሪኮችን ልትፅፍ እንደምትችል የስፖርቱ ተንታኞች እየተናገሩ ይገኛል፡፡ የነገው ውድድር ጠንካራ ፉክክር የሚደረግበት እንደሚሆን ቢገመትም ቲኪ በአይበገሬነቷ በድል ትወጣዋለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በውድድሩ የቲኪ ጠንካራ ተፎካካሪዎች ኬንያውያንና የሌሎች አገሮች አትሌቶች አይደሉም፡፡ በዚህ ውድድር ዓመት በተለያዩ ታዋቂና ጠንካራ የማራቶን ውድድሮችን አሸንፈው ከቲኪ ጎን ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶችም ነገ በውድድሩ ይጠበቃሉ፡፡
አበሩ ከበደ በነገው ውድድር ከቲኪ ያላነሰ የአሸናፊነት ግምት የሚሰጣት አትሌት ነች፡፡ አበሩ ባለፈው ዓመት በርቀቱ ባስመዘገበችው 2፡20፡30 ሰዓት በዓለም ሻምፒዮና አገሯን ለመወከል ሁለተኛዋ ተመራጭ አትሌት ለመሆን በቅታለች፡፡
አበሩ በዓለም አቀፍ መድረኮች የቲኪን ያህል የገዘፈ ስም ባይኖራትም በዛሬው ውድድር የአገሯንና የራሷን ስም የምታስጠራበት እድል አግኝታለች፡፡ አበሩ ይህን እድል ተጠቅማ ባለታሪክ ከሆኑ የአገሮቿ አትሌቶች ተርታ ለመሰለፍ ከቲኪ ጋር ተፋጥጣለች፡፡
በሌላ በኩል በዚህ የውድድር ዓመት በማራቶን ድንቅ ብቃት በማሳየት የተለያዩ ታዋቂ ውድድሮችን ማሸነፍ የቻለችው ፈይሴ ታደሰ የኦሊምፒክ ባለ ድሏን ቲኪን ልትፈትን የምትችል አትሌት ነች፡፡ ፈይሴ በርቀቱ ባለፈው ዓመት 2፡23፡07 የሆነ ሰዓት በማስመዝገብ በርቀቱ አሉ ከሚባሉ አትሌቶች ተርታ መሰለፍ ችላለች፡፡
ፈይሴ በዘንድሮው ዓመት በርቀቱ ቀድሞ የነበራትን ሰዓት ከሁለት ደቂቃ በላይ ያሻሻለች አትሌት መሆኗም በነገው ውድድር እንድትጠበቅ አድርጓታል፡፡ ፈይሴ ሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ የመግባት አቅም እንዳላት በዓመት ውስጥ ያሳየችው ድንቅ አቋም ምስክር ነው፡፡
መሰረት ኃይሉ ኢትዮጵያን ወክላ ከአገሮቿና ከሌሎች አትሌቶች ጋር ጠንካራ ፉክክር ታደርጋለች ተብላ ግምት የተሰጣት አትሌት ነች፡፡ መሠረት በውድድሩ ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን ለቡድን ጓደኞቿ የምታደርገው አስተዋፅኦ ቀላል እንደማይሆን ይጠበቃል፡፡
በለንደን ኦሊምፒክ የአስር ሺ ሜትር ውጤታማ የቡድን ሥራ በመሥራት ኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ እንድታሸንፍ ያደረገችው መሰለች መልካሙ በነገው ውድድርም ከጠንካራ ተፎካካሪነቷ ባሻገር የተለመደውን ውጤታማ የቡድን ሥራ ትሰራለች ተብላ ትጠበቃለች፡፡
መሰለች ከቡድን ሥራው ባሻገር ውጤት የማስመዝገብ አቅም ያላት አትሌትም ነች፡፡ ለዚህም ባለፈው ዓመት በማራቶን ያስመዘገበችው 2፡21፡01 የሆነ ፈጣን ሰዓት እንዲሁም በዘንድሮው ዓመት ያስመዘገበችው 2፡25፡46 ሰዓት ምስክር ነው፡፡
ኢትዮጵያ በዘንድሮው ሻምፒዮና በተለይም በማራቶን ባሰባሰበችው ቡድን ከምንጊዜውም በላይ ውጤታማ እንደምትሆን የተለያዩ የዓለም መገናኛ ብዙኃኖች እየዘገቡ ይገኛል፡፡ በማራቶን ስብስብ ውስጥ የተካተቱት አትሌቶች የኦሊምፒክና ሌሎች ታዋቂ የማራቶን ውድድሮች ማሸነፍ የቻሉ መሆናቸው በነገው ውድድር ምንም መፍጠር አይችሉም ብሎ ለመገመት ከባድ እንዲሆን አድርጓል፡፡

(ሰበር ዜና) የኢትዮጵያ ወታደራዊ አውሮፕላን ተከሰከሰ

$
0
0

Plane crash

(ዘ-ሐበሻ) በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃድሾ በማረፍ ላይ የነበረ አንድ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አውሮፕላን ዛሬ ማለዳ ላይ  መከስከሱን ከአዲስ አበባ የመጡ ዜናዎች አረጋገጡ። የኢትዮጵያ መንግስትም ይህንን ዜና ያረጋገጠ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 4 መድረሱንም አስታወቋል።

የወታደራዊ እቃ ማጓጓዣ አውሮፕላኑ አደጋ የደረሰበትለማረፍ በሚሞክርበት ወቅት እንደሆነ ዓለማቀፉ የሚዲያ ተቋም ሮይተርስ ሲዘግብ በአውሮፕላኑ ውስጥ ተጭነው ከበነበሩ 5 ሰዎች ውስጥ 4ቱ ሕወታቸው ማለፉም ተዘግቧል።

(ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እንመለሳለን)

ስንቅና ውሸታም እያደር ይቀላል! –ፈቃዱ ለሜሣ (ፕሮፌሰር)

$
0
0

የኮርስ ስም ፤ በኢትዮጵያ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ላይ የሚሠነዘሩ የፈጠራ ወሬዎችና ተጨባጩ ሃቅ
የኮርስ ቁጥጥር ፤ ‹hist101› (ልቦለድና ፈጠራ በኢትዮጵያ ኦሮሞዎች ላይ)
የኮርስ መምህር፤ ፕሮፌሰር ፈቃዱ ለሜሣ
ኮርሱ የተጀመረበት ወር፤ ሐምሌ 2005
ትርጉምና ቅንብር፤ ይነጋል በላቸው

ማሳሰቢያ፡- አሁን እዚህ ያቀረብኩት የትርጉም ሥራ ከወቅቱ የፖለቲካ ንፋስ አኳያ በጣም ጥንቃቄ የሚያስፈልገው መሆኑን አውቃለሁ፡፡ በቃላት የምንዛሬ ትርጉም ዜጎች እየተላለቁ በሚገኙባት ሆደባሻ ዓለም ውስጥ ይህን መሰሉን ጉዳይ በቀላሉ መተርጎም እንደማይቻል እረዳለሁና ማንኛውም ዓይነት በዋናው ጽሑፍ ላይ ያልተጠቀሰ ሃሳብ በዚህ ትርጉም ውስጥ በስህተት ቢገኝ ኃላፊነቱ ፕሮፌሰሩ ሣይሆን የኔ የተርጓሚው መሆኑን ለአንባቢያንና ለፕሮፌሰር ፈቃዱ ከታላቅ ይቅርታ ጋር በትህትና እገልጻለሁ፡፡ በተቻለኝ መጠን የዋናው የእንግሊዝኛ ጽሑፍ ወዘና እንዳይጠፋ ጥረት አድርጌያለሁ – የኔ የራሴ ሥነ ልሣናዊ ‹የተፈጥሮ ለዛ›ም እንዳይከፋብኝ ከሚል ቅን አስተሳሰብ በመነሣት የተጠጋጋ ግን ከዋናው እምብዝም የማያፈነግጥ ‹ኮዝሞቲክስ› እጅግ አልፎ አልፎ በጣም በስሱ ፈንጠቅ ለማድረግ ሞክሬያለሁ – ለዚህ ደግሞ ፕሮፌሰርን በድጋሚ ይቅርታ እጠይቃለሁ – እንዲህ የማደርገው እንግሊዝኛው ወዳማርኛ ሲመለስ ድርቅ እንዳይልብኝና መሸጋገሪያ ድልድዩ ቢጠናከር ትርጉሙ ይበልጥ እንደሚያምር ሳምንበት ነው ፤ ለማንኛውም ግን ሰው ነኝና ብሳሳት በቀናነት እዩልኝ እንጂ ልፋቴን በሚያጣጥል የከፋ ደረጃ እንዳታብጠለጥሉኝ አደራ እላለሁ፡፡ ዛሬም መልካም ንባብ፡፡

OLF rebels from the front-line hold their weapons as they return to their training camp in Southern Ethiopia near the border town of Moyale(ኦሮሞዎችንና የኢትዮጵያን ታሪክ በሚመለከት ዳሰሳ ለሚያደርጉ የውጭ ጋዜጠኞች የመነሻ ግንዛቤ መጨበጫ ይሆናቸው ዘንድ የተዘጋጀ) ኦሮሞና ኢትዮጵያ፤ ምሥጋና ለ: ayyaantuu.com ድረ ገጽ)

(ናዝሬት፣ ኢትዮጵያ) – መሠረቱን ኳታር ያደረገው የአልጀዚራ ቴሌቪዥን የኢትዮጵያ ኦሮሞዎችን በሚመለከት በርካታ ዝግጅቶችን በቅርቡ አየር ላይ ማዋሉ የሚታወስ ነው፡፡ የሕዝባችንን ገጽታ በመሰለው መልክ ለዓለም ማኅበረሰብ በስፋት በማስተዋወቅ ረገድ ይህ የሚዲያ ተቋም የመጀመሪያው በመሆኑና እያደረገ ያለውም አስተዋጽዖ ቀላል ባለመሆኑ ሊወደስ ይገባዋል፡፡
ይህ ዓይነቱ ሕዝብን የማስተዋወቅ ሥራ ከሚያስገኛቸው ጠቀሜታዎች ውስጥ አንደኛው፣ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት በነሱና በተከታዮቻቸው አማካይነት በሕዝቡ ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ግፍና በደል እንዲሁም የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች የሚከታተል ገለልተኛ ወገን መኖሩን ተገንዝበው የሚያካሂዷቸውን የሰብኣዊ መብት ረገጣዎች በቀላሉ እንዳይመለከቱ ማስገደዱና በዚያም ሳቢያ እነኚሁ ባለሥልጣናት የሚያስተዳድሩትን ሕዝብ የወቅት ሁኔታ የዓለም ሕዝብ በግልጽ እየተከታተለው መሆኑን እንዲያውቁት ማስቻሉ ነው፡፡ ኦሮሞዎችና ሌሎች ኢትዮጵያውያን በጋራ ሆነው ለእኩልነትና ለዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸው መከበር ላለፉት በርካታ አሠርት ዓመታትና አሁንም ድረስ ሲታገሉ ቆይተዋል፡፡ ስለኦሮሞ ሕዝብ ጥንተ አመጣጥና ታሪካዊ ዳራ የመዘገቡ አስፈላጊነት ጥያቄ ውስጥ የማይገባ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ይህ ሲደረግ ግን በትክክል መዘገብ እንደሚኖርበት መረዳት ለማንኛውም ወገን ጠቀሜታ አለው፡፡ ትክክለኛ ያልሆነና የተጣመመ መረጃን ወይም በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ወደ አንድ ወገን የሚያጋድል ዘገባን ማቅረቡ ለዴሞክራሲ የምናደርገውን ሁለንተናዊ ትግል ይጎዳብናልና ከዚህ መሠረታዊ ነጥብ አንጻር ሁላችንም ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል፡፡ ይህ የተንሻፈፈ አካሄድ ብሔራዊ መግባባትንና ሰላምን ከመፍጠር ይልቅ ቁጣንና አንዱ ባንዱ ላይ መንገፍገፍን እያስከተለ ቅራኔን ያባብሳል፡፡
በቅርቡ አልጀዚራ ትክክል ያልሆነ ወይም የተሳሳተ ዘገባ እንዲያርቀብ ከተገደደበት ምክንያቶች አንደኛው የመረጃ ምንጩ ግራና ቀኙን ያማከለ ሣይሆን በአንድ አቅጣጫ ብቻ ማለትም በአብዛኛው በዉጭ የሚንቀሳቀሱ ኦነግንና ኦ.ኤፍ.ዲ.ኤምን የመሳሰሉ የኦሮሞ ድርጅቶች መሆናቸው ነው፡፡ በዚህ ግን አልጀዚራ ብዙም ሊወቀስ አይገባውም፤ ምክንያቱም በኢትዮጵያ የሚገኙ ትክክለኛውን መረጃ የሚያውቁ ሰዎች ወይም ድርጅቶች የሚያውቁትን እውነት ቢናገሩ የሚደርስባቸውን ያውቃሉና ለደኅንነታቸው ይሰጋሉ፡፡ ስለዚህም አልጀዚራን የመሳሰሉ የውጪ የመገናኛ ብዙኃን የተሻለ አማራጭ ሲያጡ በመረጃ ምንጭነት ለመጠቀም የሚገደዱት በውጭ ሀገራት በስደትና በልዩ ልዩ ኢኮኖሚያዊም ይሁን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ተሠማርተው የሚገኙ ሰዎችን ወይም ቡድኖችን ነው፡፡ ይህ ደግሞ ኢትዮጵያን የመሳሰሉ የሦስተኛው ዓለም ሀገራትን ሁኔታ መዘገብ ለሚፈልጉ ለእንደነዚህ ዓይነቶቹ የውጭ የመረጃ ተቋማት ትልቁ የራስ ምታት ነው፡፡ ምክንያቱም ከአንድ ወገን የሚያገኙትን መረጃ ሊያረጋግጡ የሚችሉባቸው የሀገር ውስጥ በሮችና መስኮቶች በሚዲያ አፋኝ አምባገነን መንግሥታት ስለሚዘጉባቸው በአብዛኛው ያልተረጋገጠና የአንድ ወገን መረጃ ለመዘገብ ይገደዳሉና፡፡
ለዛሬው ለመማማር ያህል እንዲጠቅመን ሰሞኑን አልጀዚራ በኦሮሞ ሕዝብ ታሪክና ለዴምከራሲያዊ መብቶቻችን መከበር በምናደርገው ትግል ዙሪያ ያስተላለፋቸውን ዘገባዎች በሚመለከት መታረም የሚገባቸው ዋና ዋና ህፀፆችና እውነትነት ጨርሶውን የሚጎድላቸው አሳሳች ጉዳዮች ስላሉ በነዚያ ላይ አንዳንድ የማስተካከያ ነጥቦችን ከዚህ በታች እንመለከታለን፡፡ የሚከተሉት የማስተካከያ ሃሳቦች ከፖለቲካዊ አስተሳሰብ በጸዱ ሃቀኛ ምሁራን የሚደገፉ ቢሆኑም በፖለቲካ ጠበል የተጠመቁ የማንኛውም ጎራ ‹ምሁራን› ግን ላይደገፏቸው ወይም ተቀባይነት ሊያሳጧቸው ይችላሉ፡፡ ይሁንና እነዚህን ሃቆች ማንም ይገፍትራቸው ወይም ይቀበላቸው ዋናው ጉዳይ እውነታዎቹ ስሜት ወለድ ሳይሆኑ የታሪክ መዛግብትን፣ የአውሮፓ ተመራማሪዎች የደከሙባቸው የታሪክ መጻሕፍትንና በዕውቅ ምሁራን የተዘገቡ የታሪክ ማስታወሻዎችን መሠረትና ዋቢ ያደረጉ በመሆናቸው የትኛውም ወገን ሊጠራጠራቸው አይገባም፡፡

ልቦለድ ቁጥር አንድ:-

“ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ1868 እስከ 1900 ከጠቅላላው የኦሮሞ ሕዝብ መካከል ግማሹ የሚሆነውና ወደ አምስት ሚሊዮን አካባቢ የሚገመተው ሕዝብ ሙሉ በሙሉ [በሀበሾች ንጉሥ በአጤ ምኒልክ ጦር]ተገደለ፡፡”

ሃቅ ቁጥር አንድ፡-

ይህ መነሻና መድረሻ የሌለው ተራ አሉቧልታ እንጂ እውነት አይደለም፡፡ ይህንና ሌላም ይህን መሰል መሠረተቢስ ወሬ ተደጋግሞ የሚነገረውና እንደማለፊያ ዜማ ዘወትር የሚቀነቀነው በአብዛኛው የኦሮሞን መገንጠል በሚደግፉና ዓላማውንም በሚያራምዱ ‹ተምረናል› በሚሉ የተወሰኑ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላትና ውጪ ባሉ አክራሪ የጎሣ ፖለቲካ አቀንቃኞች እንዲሁም ‹gadaa.com›ን በመሳሰሉ የኦነግ ደጋፊ ድረ ገፆች አማካይነት ነው፡፡ የሆኖ ሆኖ ግን እነዚህ ወገኖች በዚያን ዘመን የተገደለው የኦሮሞ ቁጥር አምስት ሚሊዮን ማለታቸው የቁጥር ዕውቀታቸው ዜሮ መሆኑን ከማመልከቱ ባሻገር የሚያስተላልፈው መልእክት ሚዛን የሚያነሳ እንዳልሆነ ታሪክንና የሕዝብ ብዛት ዕድገትን የሚያውቅ ይረዳዋል፡፡ በዚያን የ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ አካባቢ 90 የሚደርሰውን የኢትዮጵያን ዘውጎች ሁሉንም ሥሌት ውስጥ ባካተተ የሕዝብ ቆጠራ ጠቅላላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ከአምስት ሚሊዮንም በጣሙን የሚያንስ እንደነበር በታሪክ መጻሕፍት ሠፍሮ ይገኛል፡፡ እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ታዲያ ከዘጠናው ዘውግ ውስጥ የኦሮሞው ማኅበረሰብ ብቻ ተነጥሎ “10 ሚሊዮን ይደርስ ነበር፤ ከዚያም ውስጥ አምስቱ ሚሊዮኑ በ‹ጨካኝ ንጉሥ ተጨፍጭፎ› ተገደለ” ማለቱ በራሱ የጤናማነት ጉድለት እንጂ አንድም ተጠየቃዊ አመክንዮ የለውም፡፡ ለመዋሸት ደግሞ ይህን ያህል ረጂም ርቀት መሄድ ለምን እንዳስፈለገ ለማንም ግልጽ አይመስልም፡፡ ስለዚህ አምስት ሚሊዮን ኦሮሞዎች በአፄ ምኒልክ ጦር ተገደሉ የሚለው የተሳሳተ መረጃ የማንንም ቀልብ የማይስብና የትኛውንም ዓላማ ለማራመድ የማያገለግል ተራ የፈጠራ ወሬ ነው፡፡ እውነቱ ግን በዚያን ዘመን በተቀሰቀሱ የገብር አልገብርም የርስ በርስ ግጭቶችና ጦርነቶች ሳቢያ በብዙ ሺዎች የሚገመቱ ኦሮሞዎችና ሌሎች ኢትዮጵያውን – በሁለቱም ጎራዎች – ለሕልፈት መዳረጋቸው ነው፡፡ አንዳንድ ፖለቲከኞች ለራሳቸው ጠባብ አጀንዳ ሲሉ የዚያን ጊዜውን ዕልቂት ‹ጄኖሣይድ› እንደሆነ ቢፈርጁም እውነቱ ግን ሌላ ነው፡፡ እውነቱ ታዲያ የጄኖሣይድ ሣይሆን በዘመኑ በአውሮፓ መሣሪያና በሰለጠነ የሰው ኃይል ተደራጅቶ የነበረው በንጉሠ ነገሥት ምኒልክ የሚታዘዘው የሸዋ ጦር በኋላቀር መሣሪያና ካለበቂ የጦር ልምድና ሥልጠና ለጦርነት ከተሰለፈው የደቡቡ ኃይል ጋር በተፈጠረ የኃይል ሚዛን መበላለጥ ምክንያት በተከሰተው ግጭት በተለይ በደቡቡ በኩል ብዙ ወገን ማለቁ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ባልተመጣጠኑ ኃይሎች መካከል የተከሰተን ጦርነት ወይም ግጭት ያመለክታል እንጂ አንድ የታጠቀ ዘመናዊ ጦር ለልዩ ተልእኮ ወደ አንድ መንደር ወይም ቀየ ገብቶ ባዶ እጃቸውን በቤታቸው የተቀመጡ ንጹሓን ዜጎች እንደፈጀ በማስመሰል የዚያን ጊዜውን የርስር በርስ ውጊያ ወደ‹ጄኖሳይድ›ነት ለውጦ የተለዬ ስዕል መፍጠር ተገቢ አይደለም ብቻ ሣይሆን ጥፋት ነው፡፡ ታሪካዊ እውነቱ የዚያን ዓይነት መልክና ቅርጽ የነበረው አይደለም፡፡ እንዲያውም በነዚያ ያለፉ የመከራ ዓመታት ኦሮሞ ባልሆኑ ሰዎች ከተገደሉ ኦሮሞዎች ይልቅ በኦሮሞዎች የተገደሉ ኦሮሞዎች ቁጥር በጣም ይበልጣል፡፡ ምክንያቱም በኦሮሞ የተለያዩ ነገዶች ውስጥ በሀብትም ይሁን በአስተዳደር የእኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ፉክክርና መቀናቀን ስለነበር ከጎረቤቶቻቸው ኦሮሞዎችና ከሲዳማዎችም የነበራቸውን ሽኩቻ በጠረጴዛ ዙሪያ የቃላት ድርድር ሳይሆን አንዱ አንዱን በኃይል በመጨፍለቅ የበላይነቱን ለማረጋገጥ ሲል በጦር መሣሪያ ይፋለሙ ስለነበር ነው፡፡የዚያ ዓይነቱ ወንድም በወንድሙ ላይ ‹የሚቀዳጀው› ግንጥል ጌጣዊ ድል ደግሞ በአፍሪካ የመጀመሪያው እንዳልሆነና የተፈጥሮ ሀብትንም ይሁን ሌላ ጥቅም የሚያስገኝን ነገር ለመቀራመት ሲባል በሚደረግ ፍልሚያ በሌሎች የኢትዮጵያ ጎሣዎችና ነገዶች መካከልም የከረሩ ግጭቶች ይካሄዱ እንደነበር ታሪክ ይመሰክራል፤ ስለሆነም በደቡቡ ይበልጡን ኦሮምኛ ተናጋሪ በነበረው ማኅበረሰብና በሸዋው ባመዛኙ አማርኛ ይናገር በነበረው የአንዲት ሀገር ዜጎች መካከል የታዩ ግጭቶችን በሀገሪቱም ሆነ በሌላው ዓለም እንዳልታዩ ልዩ ተዓምሮች በመቁጠር ይህን ያህል ግዘፍ ነስተው መራገባቸው ማንንም ስለማይጠቅም እውነቱን ከእውነተኛ ምንጮች መረዳት አይከፋምና በተለይ በዚህ ቅንነት በሚጎድለውና የተንኮል ሤራ በተሸረበበት የጥፋት ጎዳና የሚራመዱ ወገኖች በአፋጣኝ ወደቀናው መንገድ በጊዜ እንዲመለሱ ይመከራሉ፡፡ ይህን ሃሳብ ጠቅለል ለማድረግ፣ የጂማ ዩኒቨርስቲው ፕሮፌሰር ጳውሎስ መንግሥቱ የቀኝ ክንፍ የኦሮሞ ነጻነት ጎራን ፍልስፍና በሚመለከት ውብ በሆነ አገላለጽ በጽሑፍ ካስቀመጡት ሀተታ ውስጥ የሚከተለውን ቀንጨብ አድርገን እንመለክት፡-

የኦሮሞን ማኅበረሰብ ታሪክ በሚመለከት ሆን ተብለው ተንሻፍፈው የተጻፉ ወይም የሚነገሩ በርካታ የፈጠራ ድርሰቶችና ልቦለዶች አሉ፡፡ እነዚህ በሬ ወለደ ዓይነት አሉታዊ ጥላ ያነገቡ የውሸት ታሪኮችን በጭፍን ተቀብለውና እውነት እንደሆኑ አምነው በጭፍን የሚጓዙ ወገኖችም ሞልተዋል፡፡ የፖለቲካ ኪሣራ ያጋጠማቸውና ወደጎን የተተው እንደኦነጉ አሰፋ ጃለታን የመሰሉ አስመሳይ ‹የታሪክ ተመራማሪዎች›ና ‹ጸሐፊዎች› በቤተ ሙከራዎቻቸው የፈበረኳቸው እነዚህ የሀሰት ወሬዎች የየዋሃንን ቀልብ በመሳብና በማሳሳት ረገድ የተጫወቱትና እየተጫወቱ ያሉት አሉታዊ ሚና ቀላል አይደለም፡፡ ይህ በስም የተጠቀሰ ግለሰብ በተለይ፣ አንድን ነገር ሆን ብሎ በማጣመም ለራሱ በሚያመቸው መልክ በመጥቀስና ቃላትን ወይም አባባሎችን ከቆሙለት ዐውዳዊ ፍቺ ሌላ ያልተፈለገ ትርጉም በማሸከም ሰውን የሚያወናብድ አሳሳች ሰው ነው፡፡ አንድ ምሳሌ ወስደን እንይ፤ አሌክሳንደር ቡላቶቪች የተባለ የ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሩሲያዊ ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ ተከሰተ ባለው በሽታና ርሀብ እንዲሁም በኦሮሞ ጎሣዎች መካከል ተካሄደ የተባለን ግጭት ጨምሮ ኦሮሞዎች ከሌሎች የሀገሪቱ ጎሣዎች በተለይም ከአማራው ጋር አካሂደዋል በሚላቸው ጦርነቶች ሳቢያ የኢትዮጵያ ሕዝብ ግማሽ በግማሽ እንዳለቀ ‹ምሁራዊ ግምቱ›ን ሰጥቶ ነበር፡፡ አጅሬ አሰፋ ጃለታ ይህን ዘገባ ካነበበ በኋላ ከአንድ ጤናማ ሰው በጭራሽ በማይጠበቅ ሁኔታ አጣምሞ በመተርጎም “ግማሹ የኦሮሞ ሕዝብ በ‹ክፉዎቹ› አማራዎች ተጨፍጭፎ ተገደለ፡፡” በማለት በኦሮሞ ታሪክ ውስጥ የግል ፈጠራ ድርሰቱን ሰንቅሯል፡፡ ይህ ተራ ነገር አይደለም፤ የአንዲት ሀገር ዜጎችን ጥርስ ለማናከስ በተንኮል የታቀደ ትልቅ ወንጀል ነው፡፡ በዚህ ደግሞ ማንም አይጠቀምም፡፡ ይህ የልቦለድ ታሪክ በአቶ ጃለታ የተፈለሰፈው ኦሮሞና አማራን በማጣላት ይገኛል ተብሎ የሚገመትን የሥልጣንና የኢኮኖሚ ጥቅም ታሳቢ ያደረገ የጎሣ ፖለቲካ ውጤት ነው፡፡ ከመነሻው ሚስተር ቡላቶቪችም ቢሆን ያን በአኀዛዊ ግምት ያስቀመጠውን የኢትዮጵያውያን ዕልቂት ሊደርስበት የሚያስቸለው አንዳችም የሕግ ድጋፍም ሆነ በግሉ የሚታወቅባቸው አቅምና ችሎታ የነበሩት ሰው አልነበረም፡፡ በሁለተኛም ያ ሰው የኦሮሞው ማኅበረሰብ ይኖርባቸው በነበሩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ዝኆንና ሌሎች የዱር እንስሳትን እያደነ በዛ ቢባል ለሁለት ወራት ያህል ብቻ ተዘዋወረ እንጂ ያን ከፍተኛ ወጪና የተማረ የሰው ኃይል የሚፈልግ የሕዝብ ቆጠራና የዕልቂት መንስኤ ጥናት ለማካሄድ የሚያስቸለው መደላድል በነዚያን በ1990ዎቹ ዓመታት ውስጥ ፈጽሞውን ሊኖረው አይችልም፡፡

ልቦለድ ቁጥር ሁለት፡-

“… አብዛኛው ሙስሊም የኦሮሞ ሕዝብ”

ሃቅ ቁጥር ሁለት፡-

ይህ ሐረግ በጥቂት የመገናኛ ብዙኃን አውታሮች ዘወትር ባይሆንም ካለፍ ካገደም የሚስተዋል ነው፡፡ በመሠረቱ በኦሮሞ ሃይማኖታዊ ታሪክ ከጥንት እስከዛሬ መቼም ቢሆን ‹አብዛኛው ሕዝብ እስልምናን ተከታይ ነው› የሚባል ሕዝብ ሆኖ አያውቅም፡፡ እንደእውነቱ ክርስትናም ሆነ እስልምና ከጊዜ በኋላ የመጡ እንጂ የአያት የቅድመ አያት ጥንታዊ ሃይማኖቶቻችን አይደሉም፡፡ ለምዕተ ዓመታት ስንከተላቸው የነበሩና በትውልድ ሲወራረሱ የቆዩ ሀገር በቀል ባህላዊ እምነቶች ነበሩን፡፡ (አሁንም ሊኖሩ ይችላሉ፡፡) ቀስ በቀስ ግን በተለይ የኦሮሞ መስፋፋት በተጋጋለባቸው ዓመታት እነዚህ ሁለቱ እምነቶች ወደኦሮሞው ሕዝብ ይበልጥ እየሠረጉ ገቡ፡፡ ሥርገቱም በፈቃዳችንና በተፅዕኖም እንደነበር ከታሪክ ድርሳናት እንረዳለን፡፡ በፈቃዳችን የሆነው እኛ በሰላምም ሆነ በጦርነት መልክ በሄድንባቸው የኢትዮጵያ ግዛቶች ውስጥ ከነበረው የክርስቲያን ወይም የሙስሊም ሕዝብ ጋር ስንዋሃድ ሲሆን በተፅዕኖ የሆነው እነዚሁ ኃይሎች የኛን ግዛቶች በሚወርሩ ጊዜ በሚያሳድሩት ተፅዕኖ ነው፡፡ የሆኖ ሆኖ ግን ያን ክስተት አሁን የኋሊት ዞረን ስናየው ጉዳዩ የሁለትዮሽ እንጂ በብቸኝነት አንደኛው ሃይማኖት በሌላኛው ላይ የበላይነትን የሚጭንበት ሁኔታ ስላልነበረ አንዱ ከአንዱ ጎልቶ የወጣበትና የኦሮሞን ሃይማኖታዊ ማንነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይበት ሁኔታ አልተፈጠረም፡፡ በዚህ ረገድ አሁን እንኳን ብናይ በኦሮሞ ማኅበረሰብ ውስጥ ያለው የሁለቱ ሃይማኖቶች የተከታይ ብዛት ተካካይ እንጂ ያን ያህል አፍን ሞልቶ ሊያናግር የሚያስችል የቁጥር መበላለጥ የላቸውም፡፡ (የመጨረሻው የ2000 ዓ.ም የሕዝብ ቆጠራ እንደሚያሳየው 48 በመቶ የሚሆነው ኦሮሞ የ(ማንኛውም ዘርፍ) ክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ሲሆን 47 በመቶው ደግሞ ሙስሊም ነው፡፡ እንደሚባለው ከሆነ ግን የእስልምና ሃይማት ተከታዩ ቁጥር በፍጥነት እያደገና በአንጻሩም የክርስትና ሃይማኖት እየጫጫ በመሄድ ላይ ያለ በመሆኑ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በኦሮሞዎች ዘንድ የሙስሊም ማኅበረሰብ ቁጥር ከክርስቲያኑ ሊበልጥ እንደሚችል ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶታል፡፡

ልቦለድ ቁጥር ሦስት፡-

“ሀበሾች ኦሮሞዎችን ለማንቋሸሽ አሉታዊ ትርጉም ባዘለ ቃል ‹ጋላ› እያሉ ይጠሯቸዋል፡፡”

ሃቅ ቁጥር ሦስት፡-

ይህን እብለትና ቅጥፈት የተሞላበትን የፈጠራ አባባል የሚጠቀሙበት ከፍ ሲል የተጠቀሱት መገንጠልን የሚያራምዱ የኦሮሞ ኤሊቶችና አጫፋሪዎቻቸው ናቸው፡፡ ይህን የሚያደርጉት በአባባሉ እውነትነት አምነው ሣይሆን በኦሮሞው ውስጥ የመረረ ስሜት ለመፍጠርና ሕዝቡ ሴማዊ ሀበሾችን(አማሮችን፣ ትግሬዎችንና ጉራጌዎችን) ፈጽሞ እንዲጠላ ለማድረግ ነው፡፡ ይህን በማድረጋቸው ቅራኔውን ያከረሩና በአቋራጭ የመገንጠል ዓላማቸውን ያሣኩ ይመስላቸዋል፡፡ የዚህ ቃል ጥንተ አመጣጥና ትርጉሙ ግን እንደዚህ ነው፡- ይህ አንቋሻሽ የሚመስል ‹ጋላ› የሚባል ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት ላይ የዋለው በዐረቦችና በሙስሊም ሶማሌዎች ሲሆን ኦሮሞዎችን ‹ጋል› በማለት መጥራታቸው በቃሉ ትርጉም መሠረት ኦሮሞዎች ‹ሃይማኖት የሌላቸው›ና ከነሱ የተለዩ ‹ባዕዳን› መሆናቸውን ለመግለጽ ነው፡፡ በኦሮሞ መስፋፋት ወቅት ሙስሊሞች በዚህ ቃል ኦሮሞዎችን መጥራት የፈለጉት ኦሮሞዎች የነበራቸው ባህላዊ ሃይማኖት/እምነት ከተለመደው የእስልምና ወይም የክርስትና ሃይማኖቶች የሚያፈነግጥ ሆኖ ስላገኙትና ያንንም በግዑዝ ነገሮች እንደማምለክ ወይም ከነአካቴው እንደሃይማኖት የለሽነት ስለቆጠሩት ነበር ተብሎ ይገመታል፡፡ እየቆዬ ግን ይህ አሉታዊ ፍቺ እንዲይዝ ጫና የተደረገበት ‹ጋላ› የሚል ቃል የኦሮሞን ማኅበረሰብ አባላት በቡድንም ይሁን በተናጠል ለመጥራት ሌሎች ኢትዮጵያውያንም ይጠቀሙበት ጀመር፡፡

ልቦለድ ቁጥር አራት፡-

“(በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ አካባቢ) ኦሮሞዎች በአፄ ምኒልክ ቅኝ አገዛዝ ሥር ወደቁ፡፡”

ሃቅ ቁጥር አራት፡-

የኦሮሞ ተገንጣይ ቡድኖች ከሚያናፍሷቸውና አንዳንድ የውጭ ጋዜጠኞችም በጭፍን ተቀብለው በተደጋጋሚ ከሚያራግቡላቸው የፈጠራ ወሬዎች መካከል አንደኛው አንድ ኢትዮጵያዊ ዘውግ (አማራ) ሌላውን ኢትዮጵያዊ ዘውግ (ኦሮሞን)በቅኝ ግዛት ሥር አስገብቷል የሚለው አስቂኝ ድራማ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ብዙውን ጊዜ “ሀበሾች ኦሮሞዎችን በቅኝ ግዛት ያዙ” ወዘተ. እየተባለ እንደመፈክር ይስተጋባል፡፡ ይህ የቅኝ ግዛት ነገር በኦነግና በመሰል የኦሮሞ ድርጅቶች እንዲሁም በአሜሪካና በአውሮፓ ሀገራት በሚገኙ የኦሮሞን ብሔርተኝነት አቀንቃኞች ዘንድ እንደእውነት ተወስዶ ለትግል ማነሳሻነትና ማነቃቂያነት ሲባል በስፋት ይወሳል፤ በሕዝብ ውስጥም ውስጥ ውስጡን ይሰበካል፡፡ በተለዬ አገላለጽና የዕይታ አቅጣጫ ሊታይ በሚችል መልኩ ይህ አንዱ ሌላውን ለመቆጣጠር የመሻትና የመሞከርም ሁኔታ ጨርሶውን ሊካድ ባይችልም … እንደአጠቃላይ ግን የኦሮሞ ብሔር መቼም ቢሆን በሌላ (የኢትዮጵያ) ዘውግ ቅኝ ተገዝቶ አያውቅም፡፡ ይህ ዓይነቱ ወሬ ሰሚን ሣይቀር ግራ የሚያጋባ ተራ ወሬ እንጂ ቅንጣት እውነትነት የለውም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ሌላው ቀርቶ አንድ የተባበረ የኦሮሞ ብሔር፣ ተለይቶ ከሚታወቅ አንድ ወጥ የኦሮሞ ግዛት ጋር በነዚያ ሩቅ ጊዜያት አልነበረም፡፡ ፖለቲካዊ ተፅዕኖ የሌለባቸው የታሪክ መጻሕፍት ሁሉ የሚመሰክሩት አንድ እውነት አለ፡፡ ያም እውነት በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ቋንቋቸው አንድ በሆነ ነገር ግን የተለያዩ የጎሣ/የነገድ ስብጥር ባላቸው ማኅበረሰቦች መካከል ለዘመናት ጦርነቶች መካሄዳቸው ነው፡፡ በልማዳዊ አነጋገር የ“ሀበሾች” ሥፍራዎች ናቸው በሚባሉ የሰሜን ኢትዮጵያ ብዙ ቦታዎች ሳይቀር ኦሮሞዎች በመስፋፋት ከትግሬዎች፣ ከአማራዎች፣ ከአፋሮችና ከሌሎችም የክልሉ ነዋሪዎች ጋር በመቀላቀላቸውና በመዋሃዳቸው ይህ በአንዳንድ የዋሃን “የሀበሾች ምድር” እየተባለ አላግባብ የሚጠራው የሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ራሱ የአንዱ ወይም የሌላው ብሔር ወይም ዘውግ ብቸኛ መኖሪያ ሣይሆን የሁሉም እንደሆነ በታሪክ ምሁራን ዘንድ ይታመናል፡፡ እርግጥ ነው በ1700ዎቹ ገደማ ራያ ኦሮሞዎችና የጁ ኦሮሞዎች የተወሰኑ የትግሬና የአማራ ግዛቶችን ተቆጣጥረው በነበረበት ጊዜ ለተወሰኑ ዓመታት የኢትዮጵያን ኦፊሴል ቋንቋ ኦሮምኛ አድርገው እንደነበር ከታሪክ ማኅደር መገንዘብ ይቻላል፡፡ ይህም ማለት በኢትዮጵያ የተለያየ ቋንቋና ባህል ያላቸው ጎሣዎችና ነገዶች እየተፈራረቁ ሥልጣን ይናጠቁ እንደነበረና በታሪክ ግምዶሽ እየተቆራኙ እርስ በርስ እንደተዋሃዱ፣ በዚህ ሂደትም ይበልጥ ጉልበተኛ የነበረው ዘውግ ለአገዛዝ አመቺ ነው ብሎ የሚያስበውን ቋንቋም (ሆነ ባህል) በሌሎች ላይ ይጭን እንደነበር መረዳት አይቸግርም፡፡ የዚያን ዘመኑ የአንድ ቋንቋ የበላይነት ግን እንደዛሬው ዘመን አጨቃጫቂና ከመጠን በላይ በተለጠጡ የቅራኔና ቁርሾ መዘዞች የታጨቀ አልነበረም፡፡ ምክንያቱም በንግድም ሆነ በሌላ ሥራ ከቦታ ቦታ ይዘዋወሩ የነበሩ ዜጎች ለሥራቸው ስኬት ሲሉ በሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የሌሎች ጎሣዎችን ቋንቋዎች ይናገሩ ስለነበርና ቋንቋን ማወቅም ከግል ጥቅም ጋር በቀጥታ ስለሚያያዝ በዚያን ዘመን ይስተዋል የነበረው ሥነ ልሣናዊ ችግር እንዳሁኑ በፖለቲካዊ አስተሳሰቦች የተንኮል ድርና ማግ የተሸመነ አልነበረምና ያን ያህል ጎልቶ የሚታይ ለታሪክ መዝገብ ፍጆታም የሚበቃ ቋንቋ ነክ ችግር አልነበረም፡፡ ይህ እንግዲህ ኦሮሞ የሠፈረበትን ግዛት የሚጠቁመን የኋላ ታሪክ ነው፡፡ ታሪኩም የሚያሳየን ኦሮሞ ያልተዳረሰበት ኢትዮጵያዊ ሥፍራ እንደሌለና ነገር ግን በየሄደበት ባህልና ቋንቋ እየተዋጠ ከሁሉም ጋር እንደሰም ቀልጦ አንድ መሆኑን ነው፡፡ ወደኋለኛው የአፄ ምኒልክ ዘመን ስንመጣ እንግዲህ የሚስተዋል አንድ ሃቅ መኖሩን እንረዳለን፡፡ ይሄውም ብዙዎች የታሪክ ተመራማሪዎችና ጸሐፍት እንደሚከራከሩበትና አሳማኝም ነው ብለው በርካቶች እንደሚቀበሉት ጉዳዩ የአማራና የኦሮሞ ዝርያ ወይም የደም ትስስር ሣይሆን አማርኛን በዋናነት የሚናገር ማኅበረሰብ ኦሮምኛን በዋናነት የሚናገርን ማኅበረሰብ በጊዜ ሂደት ሊያሸንፍ የመቻሉ ታሪካዊ አጋጣሚ መከሰቱ ነው፡፡ ይህ ሲሆን አማርኛን በሚናገረው ማኅበረሰብ ውስጥ ኦሮሞ አለ፤ ኦሮምኛን በሚናገረው ማኅበረሰብ ውስጥም አማራ አለ ማለት ነውና ትግሉ ይበልጡን የኢኮኖሚና የሥልጣን እንጂ የዘርና የቋንቋ አለመሆኑን ልብ ይሏል፤ እርግጥ ነው ግጭቶች ሁሉ የሀሰትም ይሁን የእውነት አንዳች የሚነገርላቸው ምክንያት ስለሚያስፈልጋቸው በሁሉም ወገን የሚነገሩ ግን እውነት ውሸትነታቸው ሊጣራ የሚገቡ ሰበበ-ድርጊቶች መኖራቸው የሚካድ አይደለም፡፡ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው እንግዲህ በነዚህ ዓይነቶቹ የኋላ ዳፋ ሊኖራቸው በሚችል ጠንቀኛ ንግግሮችና ሰብቆች ላይ ነው፤ ምክንያቱም ‹አንድ ወሬኛ ያባረረውን ሺ ጦረኛ አይመልሰውም› እንዲሉ ተጣሞ የተነዛን ወሬ ለማቃናት አስቸጋሪ ከመሆኑም በተጨማሪ ወሬው እየተበጠሰ እየተቀጠለ ይሄድና ያልተጠበቀ ከፍተኛ ችግር ይፈጥራልና ነው፡፡ ይህ ከፍ ሲል የተገለጸው የግጭትና አንዱ ሌላውን እያሸነፈ የማስገበር ሁኔታ የሚያመለክተን አማራ ኦሮሞን ወይም ኦሮሞ አማራን የማሸነፍ ጉዳይ አለመሆኑንና ታሪካዊ አንድምታው ከዚህ የፊት ለፊት ሽፋን ረቀቅ ያለና የተለዬ መሆኑን ነው፡፡ በተቻኮለ ፍርደገምድልነት የተሳሳተ አመለካከት ከማዳበር በፊት እውነትን መረዳት ለሁሉም ይጠቅማል፡፡
ሰሜነኞቹ አማሮች ጎራ ለይተው እንደተጋጩና ለጉዳት እንደተዳረጉ ሁሉ ኦሮሞዎችም እንዲሁ ጎራ ለይተው ግጭት ውስጥ ገብተዋል፡፡ ለዚህ አንዱ ግልጽ ማስረጃ የሚሆነን አፄ ምኒልክ በወጣትነታቸው ዘመን በአፄ ቴዎድሮስ ተይዘው ታስረው በነበረበት ወቅት በጎንደርና በሸዋ የአማሮች መኳንንትና መሣፍንት መካከል የታየው ፍጥጫ ነው፡፡ ወጣቱ ምኒልክ በተፈቱ ሰሞንም የኦሮሞ ነገዶች ኃይለኛ የርስ በርስ ውጊያ ላይ ነበሩ፡፡ የተቀናቃኞቻቸውን አከርካሪ በመምታት ያን ግጭት በአሸናፊነት ለመውጣት የፈለጉ የተወሰኑ የኦሮሞ ጦር ቡድኖች ከሸዋ አማሮች ንጉሥ አፄ ምኒልክ ጋር ኅብረት ፈጠሩ፡፡ ቱለማ ኦሮሞ፣ ሊሙና ሜጫ ኦሮሞ የሚባሉት የኦሮሞ ጦሮች ከሸዋው ንጉሥ ከአፄ ምኒልክ ጦር ጋር በመተባበር ሌሎችን የኦሮሞ ጦሮች በተለያዩ አስከፊ ዐወደ ዉጊያዎች በማሸነፍ ብትንትናቸውን አወጡት፡፡ ባጭሩ ኦሮሞዎች በኦሮሞነታቸው በአንድ ኦሮሞ ያልሆነ ባዕድ አካል በቅኝ ግዛት አልተያዙም፡፡ እርግጥ ነው የኦነግ መሥራች አባላት ይህን የ”ቅኝ ግዛት” ተረት ተረት ስላላመኑበት በተለይ በመጀመሪያ አካባቢ ይህን ያህል አፍ ሞልተው ሲናገሩት አልተስተዋለም፡፡ ይሁንና በ1960ዎቹ አካባቢ የኦነግ አመራሮች በግማሽ ኦሮሞ በሆኑት የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት አፄ ኃይለ ሥላሴ ላይ ኦሮሞዎች እንዲያምጹባቸው ለማድረግ ስሜትን የሚማርክ አንዳች የመቀስቀሻ ዘዴ መቀየስ አስፈለጋቸው፡፡ ለዚያም ሲሉ ይህችን መናኛ የ‹ቅኝ ግዛት› ካርድ በማንሣት ‹ለኦሮሚያ ነጻነት› ሁሉም ኦሮሞ በትግሉ እንዲሣተፍና “ከኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት” ራሱን ነጻ እንዲያወጣ ይቀሰቅሱበት ጀመሩ፡፡ በዚህ የኦሮሞ ነጻነት ግምባር ድንገተኛ የአቋም ለውጥ ምክንያት ከኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ጋር ለበርካታ ምዕተ ዓመታት በሁሉም ረገድ ተዋህደን እንዳልኖርንና በደምና በአጥንት እንዳልተሳሰርን ሁሉ እኛ ኦሮሞዎች “በማያውቁንና በማናውቃቸው አማሮች” አማካይነት እንደከብት በቅኝ ግዛት በረት ውስጥ የመገኘታችንን ምሥጢር ኦነግ ይፋ አደረገልን፡፡ ይህ ዓይነቱ የመጨረሻ ውራጅና ከተስፋ መቁረጥ የሚመነጭ የትግል ሥልት በሌሎች ሀገሮች ውስጥ በሚካሄዱ የነጻነት እንቅስቃሴዎችም ዘንድ ሥራ ላይ ሲውል ታይቷል፡፡ የኛን ሀገር ሁኔታ በሚመለከት አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የሚረዱት ገሃዱ እውነታ ግን በታሪክ ጥንቃቄ የተሞላበት ልዩ ሙያ ተዳውረው የተሸመኑት የሸዋ አማሮችና ኦሮሞዎች ለዘመናዊት ኢትዮጵያ መፈጠር ዋና መንስኤ መሆናቸው ነው፡፡ “ሸዋዎች እነማን ናቸው?” በሚለው በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተጻፈ መጸሐፉ ላይ፣ የታሪክ ምሁሩና የሰው ዘር አመጣጥ ተመራማሪው ዶክተር ጌሪ ሳሎል ይህን የመሰለ ጠቅለል ያለ ድምዳሜ አስፍሯል፤ “ ዘር ቆጠራን በሚመለከት ሸዋ ውስጥ (ከዚያም በመላዋ ኢትዮጵያ) የፖለቲካ የበላይነትን የጨበጡትን ቡድኖች ብናይ ከአማራና ከኦሮሞ የተወለዱ ቅዩጣን ዜጎች ናቸው፡፡”
ወደማጠቃለያችን ስንመጣ እንግዲህ በዋናነት መገንዘብ የሚያስፈልገን ነገር ቢኖር ከፍ ሲል የተጠቀሱት አራት መሠረታዊ ስህተቶች የኦሮሞን ታሪክና ኦሮሞ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሕይወት የሚጫወተውን ሚና በሚመለከት መዘገብ የሚፈልጉ በተለይ የውጭ ሀገራት ጋዜጠኞችን በማሳሳትና እውነቱን እንዳይዘግቡ በማወናበድ እያደናቀፉ መሆናቸውን ነው፡፡ አልጀዚራን የመሳሰሉ ዕውቅ የመገናኛ ብዙኃን የኦሮሞንና የሌሎች ኢትዮጵያውያንን ችግርና እንግልት መዘገባቸው እሰዬው የሚያሰኝ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ነገር ግን ያለባቸውን ኃላፊነት በብቃት ይወጡ ዘንድ ዘገባው ሚዛናዊ እንዲሆን ተጨማሪና ከፍተኛም ጥረት ማድረግ እደሚገባቸው መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡ አለበለዚያ የሚሠሩት የተዛነፈ ሥራ በተለይ ወጣቱን ክፍል ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ይመራውና ለችግሮች መፍትሔ ከማግኘት ይልቅ ችግሮች እየተባባሱ እንዲሄዱ ያደርጋል፡፡ እንደውነቱ ከሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ እየመጡ በሚሄዱ የተለያዩ መንግሥታት አማካይነት ከፍተኛ የአስተዳደር በደልና ጭቆና የደረሰባቸውና የሚደርስባቸው ኦሮሞዎች ብቻ ሣይሆኑ ሁሉም ዜጎች ናቸው፡፡ ከዚህ አስከፊ የብረት አጥር ወጥተው ወደተሻለ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ዘመን ሊሸጋገሩ የሚችሉት ደግሞ የጎሣና መሰል ልዩነቶቻቸውን ትተው ለጋራ መብቶቻቸው መከበር በአንድነት ሲቆሙና በአንድነት ሲታገሉ ብቻ ነው፡፡ በጋራ ሲሰለፉ ደግሞ የጋራ ጠላቶቻቸው በማር ለውሰው በመሃከላቸው በረጯቸው መርዘኛ አሉቧልታዎችና የሀሰት ወሬዎች መበርገግና በነጭ ውሸት የመሠሪዎች መሠረተቢስ ወሬ መረታት የለባቸውም – ‹ተደጋግሞ የተነገረ ውሸት እንደ እውነት ይቆጠራል› የሚባለውን ምሳሌያዊ አባባል በማስታወስ የሚነገረው ሁሉ እውነት እንዳልሆነ ማጤንና ሁሉም ትኩረቱን ከባርነት አገዛዝ ነጻ ወደሚያወጣው የጋራ መንገድ ማዞር ይኖርበታል፡፡ የውጭ የመገናኛ ብዙኃንም ያልተረጋገጠ የሀሰት ዘገባ በማቅረብ በሕዝብ መሀል ጥርጣሬንና መፈራራትን ከማንገሥ ተቆጥበው ትክክለኛነቱ በሁሉም ወገኖች ዘንድ የተመሠከረለትን ዘገባ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤ ከዚህ ቀደም ኅትመት ወይም አየር ላይ ባዋሏቸው መሰናዶዎቻቸው ላይ ስህተት ካለም ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከተው አካል ማስተካከያ መቀበልና ማስተላለፍ፣ ለቀደመ ስህተታቸውም ይቅርታን መጠየቅ ይገባቸዋል፡፡ እነዚህ ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ከአሁን በኋላ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ከቀሪ ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጋር ለዴሞክራሲ፣ ለልማትና ለፍትህ የሚያደርገውን ትግል የሚያደናቅፉ ከፋፋይና መሠረተቢስ ዝግጅቶችን ከማቅረብ እንዲቆጠቡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪየን አስተላልፋለሁ፡፡

– ፈቃዱ ለሜሣ የናዝሬት ዩኒቨርስቲ የቀድሞ ፕሮፌሰርና ጸሐፊ ናቸው፡፡

ለማንኛውም አስተያየትና ሂስ የኔ አድራሻ፡- yinegal3@gmail.com
Original title of this translation:- History 101: Fiction and Facts on Oromos of Ethiopia
የኢትዮሚዲያ ምንጭ፡ Salem News
________________________________________
የኔ ምንጭ፡- Ethiomedia.com – An African-American news and views website.
Copyright 2012 Ethiomedia.com. Email: editor@ethiomedia.com

በማሸበር የሚኖሩ በመግደል የሚከብሩ የሰው አረሞች

$
0
0

ዳኛቸው ቢያድግልኝtplf

አረም ማለት ያልተዘራበት የሚበቅል ገበሬ የዘራውን ሰብል የሚሻማ፣ ውሀውን የሚጠጣበት፣ ለበሽታና ተባይ መጠለያ በመሆን ለሰብል ጉዳት ምክንያት የሚሆን እጽዋት ማለት ነው። አረም በስሮቹ አማካይነት የሰብሉን ስር አንቆ የሚገድል፣ አንዳንዱም እንደ ፓራሳይት ሰብል ላይ ተጣብቆ የሚበቅል እንደ አቀንጭራ ያለ ማለት ነው። አረሞች በፈጣን አስተዳደጋቸው ሳቢያ አልሚ ንጥረ ነገሮችን ከመሬት የፀሀይ ብርሃን ከሰማይ በመሻማት የሚያቀጭጩና የሚገድሉ ናቸው። የስንዴ ማሳ ውስጥ የበቀለ በቆሎም እንኳ ቢሆን አረም ነው፣ ገብስም ቢሆን አረም ነውና ተነቅሎ ይጣላል።Tigray People Liberation Front Split

አረም ዘሩን በማባዛትና የመኖር እድሉን ለማራዘም በርካታ ዘዴዎችን እየተጠቀመ በብዛት የሚንሰራፋና በወቅቱ ካልታረመ ሰብል የሚያጠፋ ነው። ጎበዝ ገበሬ አርሞና ኮትኩቶ ሰብሉን ካልተንከባከበ በሰብል ምርት ምትክ አረሙን ማፈስ ይገደዳል። ልክ እንደ ምሳሌው ኢትዮጵያዊነትን የሰው አረም ውጦታል። ፀረ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት አቋምን የያዘ በሌሎች ስም ይልቁንም በትግሬ ስም ኢትዮጵያዊነት ላይ ተጣብቆ አገር እያፈረሰ ያለ የዘራፊ ቡድን አገርና ሕዝብ እያቀጨጨ ነው። ወያኔ በቆሎና ማሽላ ላይ ተጣብቆ እንደሚበቅል አቀንጭራ (ፓራሳይት፣ ጥገኛ አረም) ኢትዮጵያዊነትን ተጣብቶ ኢትዮጵያን እየገደለ ያለ ቡድን ነውና ተነቅሎ መጥፋት አለበት። በምስሉ የተቀረጹ ‘ኦፖርቹኒስት’ ገንጣዮችና ከፋፋይ ድርጅቶችም እንዲሁ።

ስንዴ ማሳ ላይ የበቀለ ገብስ አረም የመሆኑን ያህል ኢትዮጵያዊነትን አቀጭጮ የሚገድል ኢትዮጵያዊም ቢሆን የሰው አረም ነውና ተነቅሎ ሊጣል ወይም ለፍርድ ሊቀርብ ይገባዋል። ምንጫቸው ትግራይ ስለሆነና የትግራይ ተገንጣይ ግንባር ነኝ ስላሉም የትግራይ ሕዝብ ውክልና የላቸውም። በመጀመርያ እኒህ የሰው አረሞች ጭካኔና ግድያን የተለማመዱት ኢትዮጵያዊነትን ከፍ ያደረጉ የትግራይ ተወላጆችን በማደን መሆኑን እናውቃለን። የታታሪ ገበሬን ምሳሌነት የመጠቀሚያ ጊዜው እየረፈደ ቢሆንም አረም ለማጥፋት በደቦ መጠራራት የመጨረሻው የመኖር ያለመኖር ተስፋችን ነው። እያዩ ማለቅንም እለት በእለት እየተለማመድነው ከብት ወደ መታረጃው እንደሚነዳው አቅመ ቢስነት ውስጥ ከገባን ያበቃልናል። ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን አምርረው በሚጠሉ ሰዎች ጥፋት ምክንያት ኢትዮጵያን ልንጠላ ግን አይገባም። ሰሞኑን ሰላማዊ ሕዝብ ላይ በሚደርሰው ጭፍጨፋ ኢትዮጵያዊነታቸውን እስኪጠሉ ድረስ የሚማረሩት ወገኖች ምሬታቸው ከፍቶ ሰው መሆናቸውን እስኪጠሉና የሚፈራውና ለብዙዎች ጥፋት ምክንያት የሚሆነው የአጥፎ መጥፋት እልቂት እስኪመጣ መጠበቅ ሞኝነት ነው።

በሀገራችን ገበሬው የአረም ማጥፊያ መርዝ የሚጠቀመው ጥቂቱ ነው። የገንዘብ አቅም ስለሚያንሰው መርዛማነቱም ለሌላው ስለሚተርፍ። ልክ እንደዚያው ወያኔን ለማጥፋት የድርጅት አቅም አንሶናል ወደ መሳርያ ማንሳቱ ሁሉም እየተገፋ ከመጣ ለብዙ ህይወት መጥፋትም ምክንያት ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ገበሬዎች አረምን ለማጥፋት አንድ ግሩም ባህል አላቸው። ያም ደቦ፣ ጅጊ ወዘተ የሚባልና ተጠራርቶና ተሰባስቦ በህብረት ማሳቸውን ከአረም ማጽዳት የሚችሉበት መንገድ። ተመሳሳይ ብልህነት ከጠፋንና እያማረርን ዘመን ከቆጠርን ተራ በተራ አንዴ የተበደሉ ጎሳዎች አንድ ሰሞን፣ የተፈናቀሉ ወገኖች በሌላ ሰሞን፣ ክርስቲያኖች አምና እስልምና ተከታዮች ዘንድሮ፣ ሴቶች ትናንት፣ ወጣቶች ዛሬ ልላ እያልን በወረፋ መታረድን ልንለማመደው የግድ ይሆናል። አንዱ በሌላው ሞት ዝም በመሰኘት አጥፊዎቻችንን ጉልበት እየሰጠ፣ እነርሱም እየናቁንና እያፌዙብን በመጨረሻም አገር እንዲያሳጡን መፍቀድ የለብንም። ሕዝቡና የፖለቲካ ድርጅቶች ተበታትነው እየሮጡ ሲያልቁ የሰው አረሞች እየተሰፋፉና እየተመቻቸው መኖር የሚችሉበትን ሁኔታ እያመቻቹ የመቀጠል መዘናጋት ሊያበቃ ይገባል።

ዛሬ ያስቸገረንና የከበደን ሀገር በቀል አረም ነው ነገ ግን ጉልበተኛና ጨካኝ አንዴ እግሩን ከተከለ ማጥፊያ መንገድ የሌለው መጤ አረም ይውጠናል። በዚህ ከቀጠልን የዛሬዎቹ አረሞች ነገ ስማቸውን ለኛ ሰጥተውን እኛ እንደ አረም በመርዝ እናልቃለን። በዚህ ከቀጠልን ካሁኑ በከፋ ሁኔታ እንሰደዳለን እንሳደደለንም። ተቆጥቶ ለመነሳት በጣም አርፍደናል ባለቀ ሰዐትም እንኳ ቢሆን ለመነሳቱ ዛሬ ከነገ ይሻላል። ወያኔዎች በማሸበር የሚኖሩ በመግደል የሚከብሩና ሀገሪቱ የጦርነት ቀጠና ሆና እነሱ ወታደራዊ ስርዐትን አስፍነው ያሻቸውን እየገደሉ ለመኖር እየጣሩ ነው። አምባገነኖች ሁሌም በጦርነትና በቀውስ ሁኔታ ውስጥ መኖርን ይመርጣሉ። ምክንያቱም ሰላም ሲሆን እነርሱ መመለስ የማይችሉአቸው የመብት ጥያቄዎች ስለሚነሱ በስልጣን መቆየት አያስችላቸውም።

በፖለቲካ ድርጅትም ይሁን በጎበዝ አለቃ ሕዝቡ መንደሩን ሊያጸዳ ገዳዮቹን ለፍርድ ሊያቀርብ የሚችል ሀይል እንደሆነ ጠላቶቹ ሊያውቁት ይገባል። ተደጋግሞ እንደተገለጸው ወያኔ እርጉም ጠላት እንጂ መጥፎ መንግስት አይደለም። የሕዝብ ክብርና የሰዎች ነጻነትም አይገባውምና ተነቃቅሎ ሊጣል የሚገባው አረም ሊወገድ የሚገባው የሀገር ጠላት ነው።

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ከነፃነት ሰንደቅዓላማችን ጋር ለዘለዓለም ይኑርልን!

biyadegelgne@hotmail.com

ግንቦት 7 “ሙስሊም ወገኖቻችን፤ ቁስላችሁን አስራችሁ ከወያኔ ጋር በምናደርገው ፍልሚያ ተቀላቀሉን”አለ

$
0
0

ginbot 7ግንቦት 7 ዛሬ ባወጣው መግለጫው ለመላው የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥሪ አቀረበ። ግንቦት 7 በመግለጫው “ሙስሊም ወገኖቻችን፤ ቁስላችሁን አስራችሁ ከወያኔ ጋር በምናደርገው ፍልሚያ ተቀላቀሉን!!!!” ሲል ጥሪውን አቅርቧል። ንቅናቄው ለዘ-ሐበሻ የላከው መግለጫ ሙሉ ቃል የሚከተለው ነው።
በእስልምና እምነት እጅግ በደማቅ ሁኔታ ከሚከበሩት በዓላት አንዱ የሆነው ኢድ አልፈጥር ለ1434ኛ ጊዜ ነሐሴ 2 ቀን 2005 ዓ. ም. በመላው ዓለም በደስታ ሲከበር ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ግን ለዚህ አልታደሉም። በእለቱ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የኢድ ሰላታቸውን ሰግደው ወደ የመኖሪያ ቤቶቻቸው ሲመለሱ ለድብደባ በሠለጠኑ የወያኔ ወታደሮች አሰቃቂ ሰቆቃ ተፈጽሞባቸዋል። በዚህ እለት በአዲስ አበባና እና ሌሎች ትላልቅና ትናንሽ ከተሞች በርካታ ወገኖቻችን ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ አሁን ሕፃናት የወያኔ የጥይት ሰለባ ሆነዋል፤ ከዚያ እጅግ አሰቃቂ ግድያና ወከባ ያመለጡት ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በአስር ሺዎች የሚገመቱ ሙስሊሞች በዓሉን ያሳለፉት በወያኔ ማጎሪያዎች ውስጥ በሕመምና በረሀብ እየተሰቃዩ ነው።
ይህ ለምን ሆነ?
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ጥንቃቄ የተሞላበት ተቃውሞ ሲያካሄዱ አንድ ዓመት አልፏቸዋል። እጅግ ጨዋ በሆነ መንገድ ላቀረቡት የመብት ጥያቄ በታላቁ በዓል ቀን ወያኔ የእንቢታ ምላሹን ወራዳ በሆነ መንገድ ሰጥቷል። ወያኔ ለሰላማዊ ተቃዉሞ ያለውን ንቀት እናቶችን፣ ሕፃናትንና አረጋዊያንን ጭምር በመደብደብ አሳይቶናል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሕይወታቸው ላለፈ ወገኖቻችን ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል፤ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖቻችን ሕመም ይጋራል። በባለጌ የወያኔ ወታደሮች የተገደለየ፣ የተረገጡ፣ በቆመጥ የተደበደቡ፣ የተሰደቡ፣ የተተፋባቸው ወገኖቻችን ሁሉ ሕመማቸውን ችለው፤ እልሃቸውን ውጠው ለመረረ ትግል እንዲዘጋጁ ግንቦት 7 ጥሪ ያደርጋል።
በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ የደረሰው በደል በሁላችን ላይ የደረሰ ጥቃት፣ በደል ነው። የሙስሊም ወገኖቻችን የመብት ጥያቄ የኢትዮጵያዊያን ተበዳዮች ሁሉ ጥያቄ ነው። እነዚህ ጥያቄዎች በወያኔ አገዛዝ ሥር ምላሽ አያገኙም። ስለሆነም ተባብረን ኢትዮጵያችንን ከወያኔ ፋሽስታዊ አገዛዝ ነፃ አውጥተን ሁላችንም የነፃነት አየር Addis_august8_2013_16የምንተነፍስባት አገር እናድርጋት ዘንድ ዛሬውኑ የጋራ የትግል ጉዞ እንጀምር።
“ሙስሊም ወገኖቻችን ሆይ! እልሃችሁን ውጣችሁ፤ ቁስላችሁን አስራችሁ ከወያኔ ጋር ለሚደረግ ፍልሚያ ተቀላቀሉን!!!” በማለት ግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ጥሪ ያደርጋል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ

ድምጻችን-ይሰማ፦ የመጀመሪያው በሳል ኢትዮጵያዊ ሰላማዊ ትግል (ከያሬድ አይቼህ)

$
0
0

ከያሬድ አይቼህ – ኦገስት 9፥2013

ህወሃት ደደብ ነው። ምንም የማይገባው ፡ ገደብ የማያቅ ፡ ግርድፍ ባዕዳዊ ድርጅት ነው። በአስተሳሰቡ ባዕድ ፡ በስነምግባሩ ባዕድ ፡ በግብረገቡ ባዕድ። ይሄን የህገ-አራዊት ድርጅት ፊት ለፊት የገጠመው የድምጻችን-ይሰማ ንቅናቄ ነው። የንቅናቄው ብስለት ፡ አርቆ አሳቢነት ፡ አገራዊነት እና ሰብዓዊነት ድንቅ ነው ፤ ድንቅ!

voice of peopleከ18 ወራት በፊት አካባቢ የጀመረው የድምጻችን-ይሰማ ንቅናቄን በመጠኑ ግራ በመጋባት እና በተደባለቀ ስሜት ስከታተል ቆይቻለሁ። በዩናይትድ ስቴትስ የምንኖር ሰዎች የአሜሪካንን ፊሪሃ-ኢስላም (islamophobia) ፕሮፓጋንዳ ሌት ተቀን ስለምንጋተው ፡ እኔም ፈሪሃ-ኢስላም ተጠናውቶኝ ነበር። “ለመሆኑ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችም አሸባሪነትን ያስተናግዱ ይሆን?” የሚለው ጥያቄ በአይምሮዬ ጀርባ ሲያንዣብብ ቆይቷል።

ልጅ ኢያሱ መሃመድ አሊ (100 ዓመት)

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ታሪካዊ የሆነ የመንግስታዊ ተቋም ጫና እና ጭቆና እንደ ደረሰባቸው አምናለሁ። ልጅ ኢያሱ መሃመድ አሊን እንዳይነግስ ያገደው መንግስታዊ ፈሪሃ-ኢስላም ፡ በሌሎች ታሪካዊ ክስተቶችም ጫናውን እና ጭቆናውን ማሳየቱ የሚካድ አይደለም።

ሆኖም ግን አራዊቱ ህወሃት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ፈሪሃ-ኢስላምን ተጠቅሞ መጅሊሱን (የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበርን) ለመቆጣጠር መፈለጉ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች አሁንም የመንግስት ተቋማዊ ጭቆና ቀንበር ፡ ከልጅ ኢያሱ መሃመድ አሊ ከስልጣን መባረር 100 ዓመት በኋላ ፡ ደግሞ መከሰቱ ሙስሊሞች መብታቸውን ካለስከበሩ ማንም እንደማያስከብርላቸው የሚያስረግጥ ሃቅ ነው።

የ18 ወራት ፈተና

ድምጻችን-ይሰማ ላለፉት 18 ወራት እንደ ወርቅ ተፈትኗል። መሪዎቹ ታስረዋል። ያልተለወጠው ነገር ቢኖር ግን የንቅናቄው ብስለት ፡ አርቆ አሳቢነት ፡ አገራዊነት እና ሰብዓዊነት ናቸው። ንቅናቄው በኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ ለመብታቸው ለሚታገሉ ዜጎች ፡ ቡድኖች ፡ ድርጅቶች ሁሉ ትልቅ አርአያ ነው።

ሙስሊምየድምጻችን-ይሰማን አርአያነት በመከተል ሌሎች ንቅናቄዎች ህገመንግስታዊ መብቶች እንዲከበሩ ፋና ወጊ ሰላማዊ ትግልን ማራመዳቸው አይቀሬ ነው። የንቅናቄው ራሱን መግዛት ፡ ለአራዊቱ ህወሃት ወጥመዶች ራሱን አሳልፎ አለመስጠት ፡ በጽናት ጥያቄዎቹን በአርብ ጸሎት ላይ ማሰማቱ እጅግ ድንቅ ነው። ፍርሃት የማይበግረው ፡ የአውሬው ወያኔ ሚዲያ የማያግደው ፡ የሰላማዊ ትግል ጀግኖች ንቅናቄ በኢትዮጵያ ባለፉት 18 ወራት ተወልዷል።

የራሷ ሲያርባት የሰው ታማስላለች

አንዳንድ መሰሪ ፡ መርዛም ግለሰቦች የድምጻችን-ይሰማን ንቅናቄ “ለምን ለሁሉም ጥያቄ አይታገሉም?” የሚል የጥገኛነት ትችት ሊያሰራጩ ሲሞክሩ ፡ በተለይ ‘ሲቪሊቲ’ በሚባለው የፓልቷክ የዉሃ ላይ ኩበቶች ስብሳቤ ክፍል አዳምጫለሁ። ለራሴ ነፃነት ሃለፊነቱ የእኔ ነው።

በዲያስፓራ ተቀምጠን ፊትለፊት ያለምንም ፍርሃት አራዊቱን ወያኔ የሚጋፈጡትን የሰላማዊ ታጋዮች መተቸት የሞራል ዝቅጠት ፡ የስነልቦናን ውርደት እና የሰብአዊነት ኪሰራን የሚያሳይ ነው። የዲያስፓራ ቱልቱላዎች እረፉ። ባታርፉም ምንም ስለማታመጡ እረፉ።

ድምጻችን-ይሰማን መቃወም አራዊቱን ወያኔን መደገፍ ነው። ፈሪሃ-ኢስላም ያላችሁ ሰዎች ፡ የድምጻችን-ይሰማን የትግል መስመር ፡ ፈተና እና ጽናት ብታጤኑ እንደ እኔ ከፍርሃታችሁ ነጻ ትወጣላችሁ።

ድምጻችን-ይሰማ ግፋ! ቀጥል! በአላማህ ጽና!

ክብር ለሰማዕታት!

ኢድ ሙባረክ።

- – -
አድራሻ፦ yared_to_the_point@yahoo.com


ከፖለቲከኞች በላይ ገኖ የወጣው “ድምጻችን ይሰማ”

$
0
0

በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

ኢህአዴግ አክራሪነትን እየጋበዘ ነው!!

dimpoli

”የሰላማዊ ትግል ምንነት ለማይረዱ ትልቅ ትምህርት የሰጠ፣ ኢህአዴግ ፍጹም የሆነ ልምድ ባካበተበትና ኤክስፐርት በሆነባቸው የትግል ስልቶች ብልጫ ወስዶ ለማንበርከክ እንደሚያስቸግር፣ ሰላማዊ ትግል ከራስና ከስሜት ጋር የሚደረግ ታላቅ አስተምህሮት መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል። የድምጻችን ይሰማ ትግል በዚህ መልኩ በኢትዮጵያ ቀዳሚ ሆኖ ይቆያል” በግል አድራሻ ከተላከ አስተያየት የተወሰደ።

በአሃዝ፣ ጉዳቱ በሚገለጽበት መጠን፣ ጉዳቱ የሚገለጽበት ደረጃና የቋንቋው አቅም ልዩነት ካልሆነ በስተቀር ሁሉም ወገኖች፣ የውጪ ታዛቢዎች፣ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት፣ ራሱ ኢህአዴግ፣ ህወሃትና መላው ወዳጆቹ በአንድ እውነት ይስማማሉ። እሱም ህወሃት ራሱ ባመጣው ጣጣ፣ ራሱ ትዕዛዝ ሰጪ ሆኖ ያደረሰው ሰብአዊና በቀላሉ ሊበርድ የማይችል መከራ እንደሆነ በየአቅጣጫው አስተያየት እየተሰጠ ነው።

ያለ ምንም ማጋነን ኢህአዴግ ደም አፍሷል፣ ህይወት ቀጥፏል፣ አስሯል፣ ገርፏል፣ ፈንክቷል፣ ጣጣው ለሌሎች የሚተርፍ አካሄድ በመከተሉ ችግሩን አወሳስቦታል። ኢህአዴግ ይህንን ሁሉ ርምጃ የሚወስደው “ከብዙ ትዕግስት” በኋላ መሆኑን “በመንግሥት ወግ” ቢገልጽም “የሚያምነው ያገኘ አይመስልም” የሚል ወቀሳም ይሰነዘርበታል። እንደውም “ለየትኛዋ የሚወዳት አገር” በሚል ለፕሮፓጋንዳ አፉን በከፈተ ቁጥር ዘለፋ እየወረደበት ነው።

“ኢህአዴግ ጉልበት አልባ ተደረገ!”

ኢህአዴግ አቅም አልባ ሆኗል የሚሉ ወገኖች አሉ። እነዚህ ወገኖች ገለጻቸው ለሌላው ግራ የሚያጋባ አባባል ሊሆን እንደሚችል ይገምታሉ። ግን በነሱ እምነት ኢህአዴግ አቅም አልባ ሆኗል። አቅም አልባ ያደረገው “የድምጻችን ይሰማ” የትግል ስልት ነው። ኢህአዴግ ያለውና 4የሚታወቅበት መለያው የታጠቀው መሳሪያ፣ ወታደሩ፣ የፌደራል ሃይሉ፣ የክልል ፖሊስ፣ ፈጥኖ ደራሹ፣ የሰላምና መረጋጋቱ ፣ የስለላ ሃይሉ፣ የአጋዚ ጦሩ፣ የአንድ ለአምስት አወቃቀሩ … ከሁሉም በላይ ደግሞ ጉልበተኛነቱን የሚቆጣጠሩለት የአንድ ብሔር “ታማኝ” ሃይሎች መሆናቸው እንደሆነ አብዛኞች ይስማማሉ።3

“ኢህአዴግ አለኝ የሚለውን ጉልበቱን መጠቀም ቢፈልግም መድረኩን ‘በተጠና’ የትግል ስልት በሚፈልገው ደረጃ ሊጠቀም አለመቻሉ በደጋፊዎቹና በራሱ ዘንድ ስጋት ፈጥሯል” የሚሉት አስተያየት ሰጪ “የሙስሊሞች እንቅስቃሴ፣ የዕዝ ሰንሰለታቸውን ጠብቀው የሚያካሂዱት ትግል ኢህአዴግ ጉልበቱን እንዳይጠቀም ከልክሎታል። አሁን እየወሰደ ያለውና የወሰደው የሃይል ጥቃት ሊወስድ ከሚፈልገው ጋር ሲነጻጸር ሃይሉ ሽባ መደረጉን ያሳያል፤ ይህ ደግሞ የሰላማዊ ትግል ውበት ነው” ሲሉ ኢህአዴግ በገባው ጭንቅ መጠን ርምጃ ባለመውሰዱ እንደሚቆጭ ይናገራሉ። በሌላ አነጋገር የሽብር፣ የማሸበርና የመግደል “ጠቢብ” ለሆነው ኢህአዴግ አሁንም ችግሩ የሚፈታው በሃይል፣ በባሰ ሃይል እንደሆነ ከማመን አላፈገፈገም ሲሉ ያብራራሉ።

ኢህአዴግ ነገሮችን እያባባሰ የሰላማዊ ትግሉን ወደ አመጽ ለማስቀየር ሃሳብ ቢኖረውም “የድምጻችን ይሰማ ህብረት አስቀድሞ መረጃ የማግኘትና በሰላማዊ ትግል ተክኖ መገኘት ኢህአዴግ ያሰበውን እንዳይፈጽም አድርጎታል” በማለት አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። እነዚህ ክፍሎች ኢህአዴግ “አክራሪነትን የሚሰብኩና የሚያቀነቅኑ አሉ” በማለት ለሚለፍፈው “እስካሁን የአክራሪ ሙስሊም እንቅስቃሴ ስለመታየቱ መረጃ የለም። ከተፈጠረም አክራሪነት እንዲፈጠር ምክንያት የሚሆነው ራሱ ኢህአዴግ ነው። ደም ማፍሰሱን አጠናክሮ በቀጠለና ዜጎችን ማሰሩ በገፋበት ቁጥር ለመሞት የሚዘጋጁ ዜጎች አገር ውስጥ የመኖራቸውን ያህል የወንድሞቻቸውን ጭፍጨፋ በመመልከት የመስዋዕትነቱ ተካፋይ ለመሆን ዓለምአቀፋዊ የሙስሊም ኅብረተሰብ ቁጣ ያስተባብርና ራሱን ችግር ላይ ይጥላል፤ ለአገርም መከራ ይሆናል፡፡”

በተቃራኒው አክራሪነት እየተስተዋለ የመጣው አሁን እንዳልሆነ የሚናገሩ ክፍሎች “በአሁኑ ሰዓት አገራችን ውስጥ ያለው የሃይማኖት ውህደት ቀደም ሲል እናቶቻችንና አባቶቻችን በየዋህነት ሲያደርጉት እንደነበር አይነት ነው ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው” በማለት ይናገራሉ። በማያያዝም እንዲህ ያለው ስጋት በሰላማዊ ትግል ጉልበት አልባ የሆነውን ኢህአዴግ ሃይል እንዲያገኝና ይህንን ሃይል እንዲተማመን አድርጎታል ሲሉ ይከራከራሉ።

“ኢህአዴግ ሰክሯል”

ኢህአዴግ መስከሩን፣ አንጎሉ መዞሩንና የሚያደርገው እንደጠፋው የሚናገሩ ክፍሎች እንደሚሉት የኢድ ቀን ኢቲቪ ያሰራጨውን ዜና ቀላል ምሳሌ አድርገው ያቀርባሉ። የድምጻችን ይሰማ መነሻ ምክንያት የሆኑትን አዲሱን የመጅሊስ መሪ በቴሌቪዥን መስኮት አቅርቦ 2“ሙስሊሞች ላይ የወሰዳችሁትና የምትወስዱት ርምጃ የሚደገፍ ነው፣ ትክክል ነው” በማለት ያቀረበው ቃለ ምልልስ “ከስካርም በላይ አዙሪት ነው” ሲሉ የኢህአዴግን የበሽታ መጠን ይገልጻሉ። ሙስሊሙን አንኳን አሰራችሁት፣ ደበደባችሁት፣ ገደላችሁት በሚል ደረጃ “ደግ አደረጋችሁ፣ ርምጃችሁ ትክከል ነው” በማለት ዜና ማሰራጨቱ ኢህአዴግ በራሱ ሚዲያ በችግሩ ላይ እሳት ማርከፉን የሚያመላክት  ስለመሆኑ በማሳያነት ያቀርባሉ።

አንድ ጤና ያለው መንግስት የህዝብ ቁጣ ሳይለሳለስ፣ የቁጣውን መንስዔ አደባባይ በማቅረብ “ተጎዳን በሚሉ የህብረተሰብ፣ በተለይም የአንድ እምነት ተከታዮች ፊት ማዘፈን ኢህአዴግን የያዘውን የስካር የዞረ ድምር  (ሃንግኦቨር) የማሽተት ያህል ነው” የሚሉት ክፍሎች ኢህአዴግ ቢያንስ ለራሱ፣ ህወሃትና ቁንጮው ላይ ሆነው ሃብት ለሰበሰቡት ሲል እርቅ ሊወርድ የሚችልበትን መንገድ እንዲያስብበት ይመክራሉ። ጉዳዩንም በጥበብ እንዲይዘው ይመክራሉ።

መተማመን ድሮ ቀረ!!

በሙስሊም ወገኖች አወሊያ የተጀመረው የድምጻችን ይሰማ ጥያቄ፣ የኢህአዴግ የጥያቄው አያያዝ ችግር ተዳምሮበት የእምነቱ ተከታዮች ባሉበት ቦታ ሁሉ ተቃውሞው እየተዳረሰ ይገኛል። የአገሪቱን ሙስሊሞች ከጫፍ እስከጫፍ በሚያስገርም የግንኙነት መረብ እያስተባበረ የሚነደው ሰላማዊ ቁጣ የሌሎች እምነት ተከታዮችን ድጋፍ አለማግኘቱን ለኢህአዴግ ሃይል እንደሆነው የሚናገሩ ወገኖች “ይህንን አስመልክቶ በሚቀርበው መረጃ ግራ ተጋብተናል” ይላሉ።

“እንኳን የሌላውን ሃይማኖት የራሳቸውን ሃይማኖትና ስርዓት ማስጠበቅ ያቃታቸው የክርስትናው ሃይማኖት ተከታዮች፣ የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ደገፉ ተብሎ ሲዘገብ ዘገባው ሚዛን የሚደፋ አይሆንም” በማለት የሚከራከሩ ክፍሎች “የክርስትና እምነት ተከታዮች ለእምነታቸው ሊሰጡ የሚገባውን ክብር ከድምጻችን ይሰማ እንቅስቃሴ መማር ከቻሉ ይህ ብቻ በራሱ ይበቃል” በማለት በተቃራኒ ወቀሳ ይሰነዝራሉ። እንደውም የራሳቸውን የእምነት ቤት ማጽዳት ባለመቻላቸው ሊወቀሱ እንደሚገባ መረጃ በማጣቀስ ይከራከራሉ።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ላይ ካለው የረዥም ጊዜ የተቀነባበረ ሴራና የምንገኝበት የጂኦ ፖለቲካ ካሸከመን ጣጣ ጋር በማዳመር “ሜዳዎች ሁሉ ሸራተን ሆነው አይዋቡም” የሚል አስተያየት የሚሰጡ ክፍሎች “መተማመን ድሮ ቀረ” ሲሉ የሌሎች እምነት ተከታዮችን ዝምታ ይገልጹታል።

“ሙስሊሞች አብዛኞች በሆኑበት ቦታ ያለ ችግር ቢፈልጉ አክርረው፣ ቢፈልጉ አለዝበው እምነታቸውን ያራምዳሉ። አነስተኛ በሆኑባቸው አገራት ደግሞ ያለውን የአስተዳደር መሰረት የመጋራት ፈተና ይፈጥራሉ”  የሚሉት እነዚህ ክፍሎች “እነዚህ በሌሎች አገሮች የታዩ ተሞክሮዎች ከምዕራቡ መገናኛ ውስወሳ ጋር ተዳምረው በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ላይ ያስቀመጡት ጠባሳ ቀላል አይሆንም። ኢትዮጵያ ውስጥም ይህ ችግር አለ” ባይ ናቸው። በሌላም በኩል በማህበራዊ ድረገጾች አርሲ አርባ ጉጉና ጅማ የተከናወነውን በማንሳት ሰሞኑንን ለመከራከር የሞከሩትን በመጥቀስ የፍርሃቻው ማሳይ አድርገው ያስቀምጡታል።

ፍጹም ሰላማዊ ትግል – ፍጹም የሚያስቀና ህብረት!!

መሰረታዊ የእምነትና አመራር ጥያቄ በማንሳት ትግላቸውን በተጠና መንገድ የሚያካሂዱት የ”ድምጻችን ይሰማ” የትግል መስመር አስገራሚ እየተባለ ነው። ህብረታቸውና በተዋረድ የሚያካሂዱት መናበብ አስደማሚ ሆኗል። አልፎ አልፎ ከሚሰራጩ ወፍ ዘራሽ5 መልዕክቶች በስተቀር መሪዎችን በመከተል የሚያሳዩት ትብብር የሚያስቀና እንደሆነ እየተነገረ ነው። ተመሳሳይ ዓላማ ይዘው እርስ በርስ የሚቧቀሱት የተቃዋሚ የፖለቲካ ሃይሎች ከድምጻችን ይሰማ “የሰላማዊ ትግል” ቀመር ሊማሩና ይሁንታ ካገኙ ስልጠናም ሊወስዱ እንደሚገባ የሚናገሩ ተበራክተዋል።

እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት የሙስሊም ወገኖች ጥያቄና ጥያቄያቸው መልስ ካላገኘ ወደኋላ እንደማይሉ በመደጋገም ይፋ እያደረጉ ነው። ኢህአዴግ ከተካነበት ድርጅቶችን የመሰንጠቅና “የእባቡን አንገት ቁረጥ” ከሚለው የአምባገነኖች መርሁ አንጻር ድምጻችን ይሰማ ውስጥ ዘልቆ መግባት አለመቻሉ አስገራሚ የሆነባቸው ጥቂት አይደሉም። ቅንጅት እንደ ሰደድ እሳት አገር አዳርሶ ኢህአዴግን ባስጨነቀ ማግስት “ሳሎኑ ተበርግዶ ኢህአዴግ ሲንቦጫረቅበት” የተመለከቱ፤ ዓመት ከመንፈቅ ያህል የዘለቀውንና ከዕለት ወደ ዕለት በብቃትም ሆነ የኢህአዴግን መሠሪነት በመመከት እንዲሁም የተጠና የትግል ችሎታ በማሳየት ወደር ያልተገኘለትን የድምጻችን ይሰማ ትግል ከማድነቅ ወደኋላ አይሉም። ለሌሎች ሲመክሩም የመስመርና የትግል አስተላለፍ ለውጥ ለማድረግ አሁንም ጊዜው እንዳላለፈ ሊገነዘቡት ይገባል በማለት ለሌሎች የሰላማዊ ትግል ምንነት ላልገባቸውና የገባቸው መስሏቸው ተስፋ ለቆረጡ ይመክራሉ፡፡

ማስታወሻ

ይህ ሪፖርታዥ የተቀናበረው የዝግጅት ክፍላችን ካነጋገራቸው ወገኖችና በኢሜል ከተላኩ መልክዕክቶችና አስተያየቶች በመመርኮዝ ነው። ለንባብ እንዲያመች የአርታኢ ስራ ከመሰራቱ ውጪ ሙሉ ሃሳቡ የተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች ያሰፈሯቸው ነው። አሁንም በዚህ ጽሁፍ ላይ የቀረቡትን ሃሳቦች በማስፋትም ሆነ በመቃወም የሚላኩ ጽሁፎችን ለማስተናገድ ዝግጁ ነን። (ፎቶዎቹ የተወሰዱት ከቢላል Tube Photos ድረገጽ ነው)

በረመዳን ደም ዕምባ! በየጐንቻው!

$
0
0

Download (PDF, 562KB)

<script type=”text/javascript”><!–
google_ad_client = “ca-pub-8555893555560582″;
/* Add 468 x 60 – Banner */
google_ad_slot = “5735223818″;
google_ad_width = 468;
google_ad_height = 60;
//–>
</script>
<script type=”text/javascript”
src=”http://pagead2.googlesyndication.com/pagead/show_ads.js”>
</script>

የሽብርተኝነት ምንጭ ጭቆና ነው!

$
0
0

Abrham Destaደርጎች ‘ወንበዴዎች’ አሉን፤ ኢህአዴጎች ‘አሸባሪዎች’ አሉን። ያው ነው፤ ገዢዎች ለስልጣናቸው አስጊ የሆነ ሰው (ወይ ቡድን) ሲያጋጥማቸው ስም ሰጥተው የማጥላላት ዘመቻ ያካሂዳሉ።

የማጥላላቱ ዘመቻ ዋና ዓላማ ለስልጣን ስጋት የሆኑ ሰዎች ከህዝብ ለመነጠል ነው፣ ድጋፍ እንዳያገኙ ለማድረግ።

ግን ‘ወንበዴዎች’ ወይ ‘አሸባሪዎች’ እንዴት ይወለዳሉ? እንዴትስ ያድጋሉ? የውንብድና ወይ ሽበራ ምንጭ ጭቆና ነው። የጭቆና ምንጭ አምባገነንነት ነው። አምባገነንነት በሰው ህይወት፣ አስተሳሰብና ሃይማኖት ጣልቃ መግባት ይጨምራል።

ሰው ለመግዛት ጣልቃ መግባት የህዝቦች ነፃነት ማፈን ያመጣል። የሰዎች ነፃነት ማፈን የህዝቦች መብት መጣስ ነው። ህዝቦች መብታቸው ሲጣስ መብታቸውን የሚስያከብሩበት መንገድ ያፈላልጋሉ።

መንግስት በማይፈቅደው መንገድ መብታቸው ለማስከበር ሲንቀሳቀሱ ‘ሕገወጥ’ ተብለው ‘ወንበዴዎች’ ወይ ‘አሸባሪዎች’ ይሰየማሉ። መንግስት ‘ሕግ ለማስከበር’ በሚል ሰበብ የሃይል እርምጃ ይወስዳል። መጀመርያ ሕግ የጣሰ አካል ግን መንግስት ነው፣ የዜጎችን መብት በመጣስ። እናም ችግሩ እየተባባሰ ይሄዳል። ከተባባሰ ደግሞ የሃይል ሚዛን እንጂ የመደገፍና መቃወም ጉዳይ አይሆንም።

ስለዚህ ውንብድና ወይ ሽበራ የሚወለደው ከጭቆና ሲሆን የሚያድገውም በመንግስታዊ ያልተፈለገ የሃይል እርምጃ ነው። መንግስት በያዘው መንገድ ከቀጠለ ሀገራችን ወዳልተፈለገ የብሄርና የሃይማኖት ብጥብጥ ልትገባ ትችላለች።

መንግስት ችግሩ የመፍታት ግዴታ እንጂ የማባብስ መብት የለውም። አሁን እየተወሰደ ባለው የሃይል እርንጃ ምክንያት ብዙ ሙስሊሞች ሳያስቡት ወዳልተፈለገ በሃይል መብትን የማስከበር ተግባር ሊገቡ ይችላሉ። በደርጋዊ እርምጃ ምክንያት ብዙ የትግራይ አርሶአደሮች ሳያስቡት ከህወሓት ጎን ተሰልፈው ለመዋጋት ወስነው ነበርና።

የሙስሊሞች ጉዳይ መፍትሔ ይሻል። ከሃይማኖት አልፎ የሀገር ጉዳይም ነው።

የሽብርተኝነት ምንጭ ጭቆና ነው። ስለዚህ ሽብተርኝነትን ለመዋጋት ምንጩ ማድረቅ አለብን፤ ጭቆናን መዋጋት አለብን። የሃይል እርምጃ ሽብርተኝነትን የሚያባብስ እንጂ የሚፈታ አይደለም።

It is so!!!

ተሸንፈን እንዳንቀር (ሉሉ ከበደ)

$
0
0

(ሉሉ ከበደ)

Commentአንባ ገነኖች ስልጣን ላይ የሚቆዩበት ጊዜ እየረዘመ በሄደ ቁጥር አሰራራቸውን እየገመገሙና ራሳቸውን እያረሙ፤ ስልጣን ላይ ለመዝለቅ ያበቋቸውን ስልቶች የበለጠ ማጠናክራቸው እንዳለ ሆኖ፤ ቆይታቸው አዳዲስ ስልቶችን ለመፍጠርና ለመሞከርም እድል ይሰጣቸዋል ። ለምሳሌ መለስ ዜናዊ አባይን እንገነባለን  ብሎ ድንገት  እየተጯጯኽ  ህዝብን ማሯሯጥ እንደጀመረው አይነት።

ይህ አባይን የመሰለ ብሄራዊ ጉዳይ ባልታሰብ ሁኔታና ጊዜ ድንገት ያነሳው ቡድን፤ ኢትዮጵያን እንደሀገር ሊያቆዩአት የሚችሉ ልዩ ልዩ ብሄራዊ ጥቅሞችን ለባእዳን አሳልፎ የሰጠ፤ ብሄራዊ እሴት ከኢትዮጵያዊ ብሄራዊ ስሜት ጋር እንዲጠፋ የሚታገል፤ በኢትዮጵያ ህዝብ ምኞት ቁማር ተጫውቶ ወደ ኢትዮጵያ ትመጣ ይሆናል  ያላትን የአረብ አብዮት ሊያሳልፍ እንጂ የሚጠላውን የኢትዮጵያ ህዝብ  ሊጠቅም አባይን እንደማይገነባልን እናውቀዋለን።

የኢትዮጵያ ህዝብ  የሚሾመው፤ የሚሽረው፤ የኔ የሚለው መንግስት ሲኖረው፤ በብሄራዊ ኢትዮጵያዊ ስሜትና አንድነት፤ በሀገር ፍቅር ስሜት ተገንብቶ የተደራጀ ብሄራዊ ጦር ሲኖረው፤ በሙያው የተካኑ የሀገር ልጆች ተሰብስበው፤  ከመንግስታቸው፤ ከህዝባቸው ጋር መክረው፤ የግንባታውን አይነትና መጠን ሰፊ ጥናት አካሂደው፤ በየትኛው ቦታ፤ መቼ፤ እንዴትና ለምን አላማ  በምን መጠን ብንገነባው በህዝቡ ኑሮ ላይ ቀጥተኛ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ትርፍ ያስገኛል  ብለው መክረው፡ በውትድርናውም በህጉም አቅጣጫ ሊከተል የሚችለውን ሁሉ  አጥንተው፤ ገምተው፤ ሁሉም ዝግጅት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ተደርጎ አባይ ለኢትዮጵያ በኢትዮጵያውያን ሊገንባ ይችላል። የኢትዮጵያ ህዝብ በማናቸውም መልኩ፤ የሚከፈለውን መስዋእትነት ከፍሎ ሊያስወግደው የሚገባ ጠላት፤ አባይን ከኢትዮጵያ ህዝብ በሰረቀው ገንዘብ ለመገንባት ፍቃደኛ ቢሆን  እንኳ ህዝቡ ባንድ እጁ ወንዙን እየገደበ ባንድ እጁ እየታገለ ሀገሪቱንና ራሱን ነጻ ማውጣት አለበት። ወያኔ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያደርገው ነገር በሙሉ በራሱ ጥቅም ዙሪያ የተሰላ እንጂ ለህዝብና ለሀገር ይጠቅማል ተብሎ አይደለም።

አለቃቸው ከሞተ በኋላም የተረፉት የወያኔ መሪዎች፤ ሌጋሲው እያሉ ህዝቡን ማደናቆርና የዘረፋና የስርቆት እስትራቴጂአቸውን ማጠናከሩን ቀጥለዋል። ሌጋሲ ጥሎ አለፈ የሚባለው መሪ፤ እንደ ኒልሰን ማንዴላ፤ ህይወቱን ሙሉ ለሰው ልጆች አንድነትና እኩልነት ሲታገል፤ ጥቅሙንና ህይወቱን ለመስዋእትነት አቅርቦ፤ ሀገር ለበቀሉባት ዜጎቿ ሁሉ እኩል መኖሪያ እንድትሆን፤ እኩል ሀብት እንድትሆን፤ ዜጎች በዘርና በቀለማቸው አንዱ ከፍ አንዱ ዝቅ ሳይል እኩል አይን ለአይን እየተያዩ እንዲኖሩ የሚያስችል ስርአት እንዲሰፍን አድርጎ የሚያልፍ መሪ ነው። እንደመለስ ዜናዊ አይነት በዘረኝነት የቆሸሸ፤ ያንኑ ካንሰሩን ህዝብ ላይ አራግፎ በሰላም የኖረን ህዝብ እንዲበጣበጥ አድርጎ የሞተ ሰው ጥሩ ሌጋሲ ሳይሆን ጊዜ ጠብቆ የሚፈነዳ ቦንብ በህዝብ መካከል ቀብሮ  አለፈ ነው የሚባለው። መሰረትና ምክንያት ከሌለው በቀልና ጥላቻ ጋር ተወልዶ፤ አማራ የሚባል ዘር ጨፍጭፎ ሳይጨርስ እግዚአብሄር ፍርዱን የሰጠውን ሰው፤ በተጨባጭ ሲጨፈጭፉት፤ ሲያስሩት፤ ሲያግዙት፤ ለኖሩት ነጮች ምህረት አድርጎ፤ ትውልድን አስታርቆ፤ ሰላም አውርዶ፤ የአምላክን ሚና ለተጫወተ ታላቅ ሰው ማንዴላ የሚገባውን ክብር ለወያኔ ቆሻሾች መዘከር በህዝብ ማላገጥ ነው።

እንደ ወያኔ አይነት የህዝባቸውንና የሀገራቸውን ጥቅም ለሌላ አገር ህዝብና መንግስት አሳልፎ ለመስጠት የተዘጋጁ ወገኖች ባሉበት ሀገር  እነዚህ ገዢዎች የተወዳጇቸው መንግስታት የጥቅም ቁርኝታቸውን ዘላቂነት ለማረጋገጥ በስልጣን ላይ እንዲዘልቁ የበኩላቸውን ምክር  መለገሳቸው የማይቀርና የተለመደ ነገር ነው። ባእዳኑ  ማናቸውንም የረቀቀ የአፈናና የጭቆና ዘዴ ስለሚመክሯቸው ስለሚያስተምሯቸው፤ ስልጣን ላይ እየቆዩ በሄዱ ቁጥር የኢትዮጵያ ህዝብ እራሱን ነጻ ለማውጣት የተወሳሰበ ችግር ሊገጥመው ይችላል።

 

በሀያ ሁለት አመታት ጉዞአችን እያየነው ያለ ነገር ወያኔ የነደፈው እቅድ ያለ አንዳች ሳንካ እየተሳካ እየተሳካ በመሄድ ላይ ሲገኝ የኛ የተገዢዎቹ ኢትዮጵያውያን እቅድ ጩኸት ብቻ ሆኖ እሱም ሰሚ የሌለው የምድረበዳ ጩኸት እየሆነ መምጣቱን ነው። መላውን የሀገሪቱ ጦር ሰራዊት  በራሱ የአማጽያን ቡድን ለውጦ፤ ወያኔ ፖለቲካውንም ኢኮኖሚውንም መቶ በመቶ በበላይነት ተቆጣጥሮ፤ በፈለገው አይነትና ሁኔታ ህዝቡን በዘር አጥሮ፤ ከፋፍሎ፤ ተቆጣጥሮ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ መተሳሰሪያ ያንድነቱን እትብት በጣጥሶ እየጨረሰ ነው። ህዝቡ አንድ ቋንቋ እንዳይናገር የአማርኛን  ብሄራዊ ቋንቋነት ሰርዞ፤ የህዝቡን ህጋዊና ታሪካዊ የባለቤትነት መብት በሀይል አግዶ የባህር በር እንዳይኖር አሰብን ለጠላት ሰቶ፤ ምእራቡን የኢትዮጵያ ክፍል አንድሺህ ስድስት መቶ ኪሎ ሜትር ርዝመት ከሰላሳ እስክ ስልሳ ኪሎሜትር ስፋት ለሱዳን ሰቶ፤  መላውን ህዝብ ከየቀየው እያፈናቀለ፤ እያሳደደ፤ እየገደለ፤ ወህኒ እያጎረ የሀገሪቱን ለም የርሻ መሬት ለባእዳን በርካሽ እየቸበቸበ፤ ገንዘቡን እንደፈለገው እያደረገ መኖሩን ቀጥሏል። መላውን የሀገሪቱን ሀብት በህውሀት ቡድን መዳፍ ውስጥ አስገብቶ፤ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት መለያ የሆኑ ባህላዊ፤ ታሪካዊ፤ ሀይማኖታዊ ውርስና ቅርሶችን ሁሉ አውድሞ፤  ገዳማትን አፍርሶ፤ ሀውልቶችን ነቅሎ፤ ታሪካዊና መታሰቢያ ስሞችን ሁሉ ለውጦ፤ ሀይማኖታትን አርክሶ ክልሶ፤ ከፋፍሎ  በጣብጦ፤ አበጣብጦ፤ የነበረውን ሊያጠፋ ያልነበረውን ሀይማኖት ከየትም ፈልጎ እያመጣ፤ ህዝብ ላይ እያጣበቀ እየጫነ፤ ሌላም ሌላ ….የጥፋት ጎዞውን ያለ እንቅፋት ቀጥሏል።

እርግጥ ነው ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ለወያኔ እጅግ የሚያስፈራውና የሚያሳስበው የማይናወጥ አንድ አቋም እንዳለው በተደጋጋሚ አጋጣሚውን ሲያገኝ አሳይቷል። ወያኔ እንደማናቸውም ቅኝ ገዢዎች ሁሉ ማናቸውንም ዋጋ ከፍሎ እየሰራበት ያለው ከፋፍሎ የመግዛት ዘይቤ፤ ይህ ቡድን በገመተው ልክ የኢትዮጵያን ህዝብ አልከፋፈለለትም። ከስምንት አመት አገዳ በሁዋላ በቅርቡ ለሙከራ የተጀመሩት ሰላማዊ ሰልፎች፤ ያዲስ አበባውም የወሎውም የጎንደሩም ሁሉም ያረጋገጠው ነገር ቢኖር የኢትዮጵያ ህዝብ ከሀያ ሁለት አመታት በፊት የነበረ አብሮነቱን፤ እንድነቱን ምንጊዜም ከልቡ እንደማያወጣው ነው።

አዎ  የኢትዮጵያ ህዝብ ለየብቻው እንዲሆን፤ ለየብቻው እንዲያስብ፤ ለየብቻው  እንዲናገር፤ በሀይል ተከልሎ ታጥሯል። ከስድስት መቶ አመታት በላይ የጋራ መግባቢያ የነበረውን የአማርኛ ቋንቋ ሁሉም ክልል እናዳይናገር ተከልክሏል። ህጻናት የራሳቸውን ቋንቋ ብቻ እየተናገሩ እንዲያድጉና እንዲማሩ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር የሚያገናኛቸው ሌላ ቋንቋ እንዳይማሩ ተደርገዋል። የወያኔ ትልሙ ከኢትዮጵያ ህዝብ በብዛቱ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘውን ወጣት በሀምሳ አመት ውስጥ እንደጋሪ ፈረስ አንድ አቅጣጫ ብቻ የሚያይ አድርጎ ከፈጠረው፤ የሚያስተሳስረው ቋንቋ፤ ባህል፤ ታሪክ፤ የጋራ ሀገር ካሳጣው በቀላሉ ይበተናል፤ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አትኖርም ነው። ኢትዮጵያ ግን በኢትዮጵያ ህዝብ ልብ ውስጥ አንድነቷን ጠብቃ ለዘለአለም ትኖራለች። በወያኔ ፋሺሽቶች ከርሰ መቃብር ላይም በልጆቿ አንድነት አንዲት ሀያል ኢትዮጵያ ዳግም ትነሳለች።

ወያኔ የያዘውን ስልጣን ተቆጣጥሮ እስከመጨረሻው ለመዝለቅ የሚያስችለው እርግጠኛ የሆነበት ሌላው በተግባር ያዋለው ዘዴ፤ ጦር ሀይሉን ደህንነቱና ፖሊሱን በራሱ ሰዎች ማስይዙ እንዳለ ሆኖ፤ የህውሀት የጦር አለቆች ቀጥተኛ የሀገሪቱ ሀብት ባለድርሻ መሆናቸው ነው። በዛሬዋ  ዓለም ምንም አይነት የተለየ ሞያ ሳይኖረው፤ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እያወጣ ለግሉ ህንጻ መገንባት የቻለ፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በኢንቨስትመንት የሚያንቀሳቅ ጀነራል፤ ኮሎኔል፤ ሻለቃ ወዘተ….የሚባል፤ ስራ ላይ ያለ ወታደር ያላት ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ነች። እነዚህ ባለሀብት መኮንኖች የኛ ነው የሚሉት መንግስት እንኳ ለለውጥ ቢነሳና ያ ለውጥ ይህን ያለ አግባብ  በጃቸው ያከማቹትን ሀብት ያሳጣናል ብለው ከሰጉ ፤ የወያኔ ጀነራሎች ከላይ ያለውን የወያኔ አካል በሀይል አስወግድው ራሳቸው ስልጣኑን እንደሚይዙት ልንጠራጠር አይገባም። ስለዚህ ሁሉም የህውሀት አመራር በየፈርጁ ለራሱ ህልውና ሲል በስነስርአት የሀገሪቱን ሀብት እየዘረፈና እየተከፋፈለ በመኖር ላይ ይገኛል። ህዝብ ለለውጥ ልነሳ ካለ እስካሁን እያደረገ እንዳለው ማናቸውንም ወታደራዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እየወሰደ ይቀጥላል። እነዚህን በሀገር ሀብት ዘረፋ የደለቡ ደናቁርት የወያኔ ነፍሰገዳይ የጦር አለቆች፤ ከታች ያለው የሰፊው ህዝብ ልጅ የሆነው መለዮ ለባሽ ካላመጸና እግር ተወርች እያሰረ ለፍርድ ካላቀረባቸው፤ ግደል ባሉት ቁጥር የራሱን ቤተሰብ እየገደለ፤ የወገኖቹን ደም እያፈሰሰ እነሱ እየበለጸጉ መኖር እንዲቀጥሉ፤ ስርአቱም በጥቂት የአንድ ጎሳ አባላት የበላይነት ተገንብቶ እንዲቀጥል ከፈቀደላቸው ይህች ሀገርና ይህ ህዝብ ፍዳቸው ይቀጥላል።

የጦር አዛዦቹ የሀብት ምንጭ ማእከላዊ መንግስቱ ብቻ አይደለም። የየክልል አሻንጉሊቶቻቸው ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛሉ። አሰራሩ እንዲህ ነው። በአራቱም የሀገሪቱ ማእዘናት የጦር እዝ ማእክሎች ይገኛሉ ። የዚያን አካባቢ እዝ የሚያዙት የህውሀት ጀነራሎች ስራቸው፤ ጦሩን ማንቀሳቀስና መምራት ማዘዝ ብቻ አይደለም። ባካባቢያቸው ያሉ ክልሎችን ለምልክት ካስቀመጧቸው የክልል ፕሬዚደንቶች ጀርባ ሁነው፤ ክልሉን ያስተዳድራሉ። ይመራሉ። ሹማምንቱን ይቆጣጠራሉ። ያዛሉ። ከማእከላዊ መንግስት የሚለቀቀውን በጀት ያውቃሉ፤ ይቆጣጠራሉ።

ምሳሌ…. ሀረር ከተማ መቀመጫውን ያደረገው የምስራቅ እዝ አዛዥ ጀነራል፤ የሀረሪ ክልላዊ መንግስትና የሱማሌ ክልላዊ መንግስት  ባለስልጣናትን ያዛል፤ ይቆጣጠራል።  በየአመቱ የክልሎች በጀት እንደተለቀቀ የህውሀት ኩባንያዎች በያቅጣጫው አብረው ይለቀቃሉ። በየክልሉ በበጀት አመቱ ይሰራሉ የተባሉትን አንዳንድ ነገሮች ተሻምተው ይከፋፈላሉ። ከባጀቱ የተወሰነውን ይወስዳሉ። ከዚያ የተወሰነ መጠን የክልልሉ ሹማምንት እንዲበሉ ይደረጋል። ይህም የሚደረገው በኮረብሽን እንዲነካኩና የሚታዘዙትን አንፈጽም ካሉ በቀላሉ እስር ቤት ተወርውረው ሌላ ማስቀመጥ እንዲቻል ነው። ይህን ሁሉ በንቃት ይሚያስፈጽመው የወያኔ ጀነራል፡ ኮሎኔል፡ ወይም ሻለቃም ሊሆን ይችላል። በክልሉ ለምልክት የሚሆኑ ጥቂት ስራዎች እንዲሰሩ ያ የወያኔ አዛዥ ከተከታተለ በኋላ የተጋነኑና የውሸት ሪፖርቶች እንዲዘጋጁ ይደረጋል። የዚያ ክልል ፕሬዚዳንት የተረፈውን ገንዘብ ይዞ ወደ ጀነራሉ  ቢሮ እንዲመጣ ይታዘዛል።  ያንን ገንዘብ የተረከበው ጀነራል የሚበቃውንና የሚፈልገውን ያህል ወደ ግል ባንኩ ካስገባ በኋላ፤ ለሌሎቹ ማካፈል ካለበትም የሚያደርገውን ራሱ ይወስናል።

ለዚህም ነው ኢትዮጵያን የወረሯት አዛዥ የትግራይ ታጋዮች  በሙሉ በኢንቨስትመንትና በግንባታ ላይ የተሰማሩት፡፡ ለዚህም ነው እስከመጨረሻው እየገደሉ ጥቅማቸውን ያስጠብቃሉ እንጂ ሰላማዊ ትግል  በሚል ጨዋታ እጃቸው የገባውን ስልጣን አሳልፈው የማይሰጡት።

ምንድነው መደረግ ያለበት?

ይህን በኢትዮጵያ ህዝብ ልብ ውስጥ ተዳፍኖ ያለውን የአንድነትና የትግል ስሜት ጎልቶ እንዲወጣ ማድረግ ከንግዲህ በኋላ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም። አብረው ሲጋፈጡት ሞትም አይከብድም። አንዱ አደባባይ ወቶ የተቃውሞ ጩኸቱን ሲያስማ ሌላው በፍርሀት ቤቱ ተሸሽጎ አጨንቁሮ በመስኮትና  በበሩ ቀዳዳ የሚያይበት ሁኔታ ዛሬ ላይ መቆም አለበት።

ከዚህ መንግስት ጋር በሙሉ ልብ ለስርአቱ እድሜ መራዘም እየሰራችሁ ያላቸሁ ምሁራን፤ በኢትዮጵያ ህዝብና በሀገሪቱ ላይ እየደረሰ ያለው አፈና፤ ሰብአዊ መብት ረገጣና ግፍ፤ ትክክል አለመሆኑ ሳይገባችሁ ቀርቶ ሳይሆን ህሊናን ለጥቅም አሳልፎ የመሸጥ ጉዳይ ነው ችግራችሁ። ግልጽ ነው። እርግጥ ተፈጥሮን ተመክሮ ላያድነው ይችላል። አንድ ሰው በተፈጥሮው ራስ ወዳድ፤ ውሸታም፤ ሌባ፤ መስሎ አዳሪ፤ ጥቅም እንጂ ሰብአዊ ርህራሄ የማያውቅ ከሆነ፤ ለራሱ የሚጠቅመውን ነገር ካተረፈ፤ ህዝብ ያስፈጃል፤ ግፍም ይፈጽማል። ስለዚህ እናንት ከወያኔ ጋር የተለጠፋችሁ ቅጥረኛ ምሁራን፤ አማራ፤ ኦሮሞ፤ ደቡብ ወዘተ….ወያኔ ባላሰባችሁት ሁኔታ እያንዳንዳችሁን በልቶ እንደሚጨርሳችሁ ከወዲሁ ተገንዝባችሁ፤ የተጠቀማችሁትን ተጠቅማችኋል፤ የያዛችሁትን ይዛችሁ እራሳችሁን ከወያኔ መንግስት አግልሉ። የነጻነቱን ትግል ተቀላቀሉ። የበደላችሁትን ህዝብ ካሱ።

ሌሎቻችሁ በተቃዋሚውም ወገን በደጋፊውም ወገን ሳትሆኑ፤ መሀል ላይ ተደላድላችሁ፤ ድምጣችሁን አጥፍታችሁ፤ አድፍጣችሁ፤ በቀጥታ እናንተ ላይ ስላልደረስ ብቻ በሀገር በወገን ላይ የሚደርሰውን ግፍ እንዳላየ እንዳልሰማ ሁናችሁ፤ በራሳችሁ ህይወትና ምቾት ዙሪያ  እየተሽከረከራችሁ ይህችን ቀውጢ ቀን ለማሳለፍ የምትፈልጉ ኢትዮጵያውያን ይህ መሀል ሰፋሪነት ያስገኘላችሁ ሰላም ነገ ጠዋት ይደፈርሳል። ህዝብን እየጨፈጨፍኩ መግዛቴን እቀጥላለሁ ብሎ የቆረጠ ነፍሰ ገዳይ መንግስት ባለበት ሀገር ውስጥ የናንተ ሰላም አይዘልቅም። በህዝባዊ ትግል የቆሰለ መንግስት እንዳበደ ውሻ ባጠገቡ ያየውን ሁሉ ነው የሚቦጭቀው። አካሉንም ሳይቀር ስለዚህ…. ስለዚህ ከመሀል ውጡና ህዝቡ እንደሚሆነው ሁኑ። የህዝቡን የተቃውሞ ድምጽ አበራክቱ።

በተራ ወታደርነትና የበታች መኮንንነት ደረጃ ያላችሁ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፤ ይህ እንደከብት እየነዳ የሚያዛችሁ የወያኔ ታጋይ አዛዥ ከናንተ የበለጠ አዋቂ፤ ከናንተ የበለጠ ጀግና አይደለም። ቀን ያነሳው የመሀይም ሽፍታ ጥርቅም ነው። የአንድ መንደር ምልምል ነው። እናንተ ግን የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ልጆች ናችሁ። የኢትዮጵያ ህዝብ ቤተሰባችሁን የኑሮ ውድነት እየጠበሰው፤ የወያኔ አመራሮችና ታጋይ ጀነራሎች እንዲሁም ቅጥረኞቻቸው በሚሊዮን ዶላር ንግድ ተሰማርተው የአለም ሀብታም ሰዎች እንደሚኖሩት ይኖራሉ። በናንተ ደምም ይነግዳሉ። ለምሆኑ እናንተ ለሰላም ማስከበር ተልኮ ሩዋንዳ፤ ሶማሌ፤ ሱዳን፤ እየሄዳችሁ ስትሞቱ የተባበሩት መንግስታት ለያንዳንዱ ወታደር የሚከፍለውን ወፍራም አበል ተቀብላችሁ ወደ ቤተሰብ ልካችሁ ታውቃላችሁ? ስንቶቻችሁስ ናችሁ የተባበሩት መንግስታት ለናንተ አበል እንደሚከፍል የምታውቁ? የወያኔ ታጋይ አዛዦች ተቀብለው ወዴት እንደሚያደርሱትስ የምታውቁት ነገር አለ?

አንድ ወታደር በህዝብ ላይ አደጋ እንዲያደርስ ቢታዘዝ ያለቃውን ትዛዝ አልቀበልም የማለት የሞራልና የህግ መሰረት እንዳለው ይታወቃል። ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ከአብራኩ በወጡ ልጆቹ እያስገደለ፤ እስከመቼ ድረስ ነው ረግጦ የሚገዛውና የሀገሪቱን ሀብት የሚያጋብሰው? ወጣቱ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት እንደ ግብጽ፤ እንደቱኒዚያ ሰራዊት ከሀገርና ከህዝብ ጎን መቆም ይጠበቅበታል። የአንባ ገነኖች ደህንነት ሳይሆን የሀገርና የህዝብ ደህንነት ነው የሀገር ፍቅር ላለው ሰራዊት ቅድሚያ የሚኖረው። ሀይል በጁ ነው። የህውሀትን ታጋይ አዛዦች ሰብስቦ ወደ እስር ቤት ማጎርና ስልጣኑ ላይ ያሉትን አሽመድምዶ፤ ለህዝቡ የምርጫ ነጻነት መስጠት ያስፈልጋል። ህዝቡ በቶሎ ጊዚያዊ የሽግግር መንግስት አቋቁሞ፤ ለመደበኛ ምርጫ ሰላማዊ ስራ እንዲሰራ ማድረግና ከውስጥም ከውጭም ለሚነሱ የሀገር ጠላቶች ምላሽ ለመስጠት መሰማራት ያስፈልጋል።

ተቃዋሚ ነን የምትሉ ድርጅቶም አንዱ ያንዱን ጥረትና ትግል እያንኳሰሰ፤ ራሱን እያወደሰ ፤ እርስ በርስ መናቆር ከቀጠለ አተካራችሁ የኢትዮጵያን ህዝብ ጥርጣሬና ውዥንብር ውስጥ ስለሚከተው አንዳችሁንም አያምን። አንዳችሁንም አይከተል። መጀመሪያ ለራሳችሁ ተከባበሩ። ተባበሩ። አንዲት ጎጆ ለመገንባት አብረው የተሰማሩ ሰዎች ሳር አይሻማሙም ይባላል። የሁላችሁም አላማና ግብ ወያኔን አስወግዶ አንዲት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት እስከሆነ ድረስ፤ የተለማችሁት ዘዴና አካሄድ መለያየቱ የሚጠበቅና መሆንም፤ መኖርም ያለበት አማራጭ ነው እንጂ፤ አንዳችሁን ካንዳችሁ የሚያባላ የማይታረቅ ልዩነት አይደለም። በማይረባ ጥቃቅን ልዩነት በህዝብ ፊት ስትናቆሩ፤ ህዝቡ ሁላችሁንም አንቅሮ ተፍቶ፤ ከራሱ ውስጥ የሚያታግሉትን ሰዎች አውጥቶ ትግሉን ይቀጥላል። ያከመሆኑ በፊት ግን ተከባብራችሁ፤ ተባብራችሁ ህዝቡን በማስተባበር የለውጥ እንቅስቃሴውን አፋጥኑ።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ወያኔ ሀገር እያሳጣችሁ፤ ተስፋ እያሳጣችሁ በመጓዝ ላይ መኖሩን ሳትዘነጉ፤ ራሳችሁንና ሀገራችሁን ህዝባችሁን ለማዳን ተነሱ።

በጫትና በሀሺሽ፤ በአልኮል ናላችሁን የምታዞሩ፤ ገሚሶቻችሁም የሀገር ፍቅርን ስሜትና የትግልን ስሜት በሚያኮላሹ ሀይማኖቶች ተተብትባችሁ፤ በእውን ለምትኖሩበት የምድር ፈተና መፍትሄ እንደመፈለግ ከሞት በኋላ ስለምታገኙት ህይወትና ሞቾት ስትቃዡ፤ ጌታ ጌታ እያላችሁ በየ አጥቢያው ስታላዝኑ ወያኔ ምድሪቱን በላያችሁ ላይ እየሸጣት ነው። ከጴንጤውም ከጆቫውም ከሌላውም የቅዥት አለም ውስጥ ውጡና እናት ሀገራችሁ ኢትዮጵያን ከአርባ ጊዜ በላይ የሚጠራት መጽሀፍ ቅዱሳችንን ይዛችሁ፤ ለትግል የቆረጡ ወጣቶችን ተቀላቀሉ።

ኢትዮጵያ ዳግም ትነሳለች!

ሞት ለወያኔ!

lkebede10@gmail.com

 

ኢሳት ያኣማራ ቊጥር የቀነሰበትን ምክንያት አጋለጠ:

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>