Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

በነጆ የተገደለው ገመቹ ጥላሁንን ለመቅበር የወጣውን ሕዝብና ቁጣውን የሚያሳይ ቪዲዮ

$
0
0

በኦሮሚያ ክልል የተነሳው ሕዝባዊ ቁጣ በተለያዩ ቦታዎች በቀጠለበት ሁኔታ አሁንም የአጋዚ ሰራዊት ሰላማዊ ታጋዮችን መግደሉን ቀጥሏል:: ቀጣዩ ቪዲዮ የሚያሳየው በነጆ ከተማ በወያኔ ሠራዊት የተገደለው ገመቹ ጥላሁንን ለመቅበር የወጣውን ሕዝብ እና ቁጣውን ነው::

The post በነጆ የተገደለው ገመቹ ጥላሁንን ለመቅበር የወጣውን ሕዝብና ቁጣውን የሚያሳይ ቪዲዮ appeared first on Zehabesha Amharic.


ምናልባት ስለሞጋቾች ድራማ ምርጥ አርቲስቷ ፍቅርተ ደሳለኝ የማታውቋቸው ነገሮች

$
0
0

Screen Shot 2016-01-28 at 11.02.40 AM

አርቲስት ፍቅርተ ደሳለኝ  አዲስ አበባ ውስጥ ቀበና አካባቢ ነው ተወልዳ ያደገችው፡፡ ወደ ሙዚቃው አለም ስትገባም የብዙነሽ እና የሂሩት በቀለ ስራዎችን በማንጎራጎር ነበር፡፡ ይህ ግንኙነትም ተጠናክሮ በናይጄሪያ ሎጎስ እና በሱዳንም ስራዎቻቸውን አብረው አቅርበዋል፡፡ በ1958ዓ.ም የቀድሞው ቀዳማዊ ኃይለስላሴ (የአሁኑ ብሄራዊ ቲያትር) በድምፃዊነት ከመቀጠሯ አስቀድሞ በምሽት ክበብ ውስጥ ትሰራ ነበር፡፡ብሄራዊ ቲያትር የገባችውም በቴሌቭዥን ስትዘፍን የተመለከቷት የዛን ጊዜው የብሄራዊ ቲያትር ስራ አስኪያጅ ችሎታዋን አድንቀው ወደ ቲያትር ቤቱ እንድትመጣ በመጠየቃቸው ነበር፡፡በወቅቱ የተሰጣትን ፈተና በአጥጋቢ ሁኔታ በማለፏ በ100 ብር ደምወዝ ተቀጠረች፡፡
722fikirtedesalegnoldies

በአንድ ወቅት ስራዋን በቀጥታ ስርጭት ስታቀርብ የዘፋኝ ስም ሲፃፍ የአባቷን ስም ቀይራ ነበር፡፡ ከቤተሰቦቿ ለመደበቅ እና በወቅቱ በድምፃውያን ላይ ይሰነዘር ከነበረው ትችት ለመሸሽ ስትል እንደሆነም ትናገራለች፡፡ እናም በጊዜው ፍቅርተ ደሳለኝ የነበረ ስሟ ፍቅርተ ግርማ ተብሎ በቴሌቭዥን በመታየቱ በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሆና ነበር፡፡ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ቲያትር ቤትን በተቀላቀለችበት ጊዜ ቲያትር ቤቱ በስሩ 3 ኦርኬስትራዎች ነበሩት (ያሬድ፣ ዳዊት፣ እዝራ) ፡፡ አርቲስት ፍቅርተ ደሳለኝም በያሬድ ኦርኬስትራ ስር ሆና የተለያዩ የሀገራችን ክፍል ተዘዋውራ ሰርታለች፡፡
ከሰራቻቸው ዘፈኖቿ መካከል ጥቂቶቹን እናንሳ፡- የሻለቃ ግርማ ሀድጎ ግጥም እና ዜማ የሆነው የመጀመሪያ ስራዋ “የፍቅር ምድጃ”፣ “ሰው በናፍቆት አይሞትም”፣ “ኮተት” የተሰኘው የሲራክ ታደሰ ድርሰት፣ “ቤትም እኮ ነበር”፣ “የመኖሬ ተስፋ”፣ “የኔ አለኝታ”፣ በ1963ዓ.ም የተቀረፀው “ባሌ ነው ህይወቴ”፣ በጎዳና ተዳደሪ ልጆች ላይ የሚያተኩረው እና ከታምራት አበበ ጋር የተጫወተችው “ጠውላጋዋ አበባ”፣ እንዲሁም ከጌጡ አየለ ጋር በርካታ አስቂኝ የኮሜዲ ሙዚቃዎችን ተጫውታለች፡፡

10698681_10203742346733155_4838225161140564847_n   ፍቅርተ ደሳለኝ እና ጌጡ አየለ በሚሰሯቸው የኮሜዲ ሙዚቃዎች አቀራረባቸው ከስሜት ጋር ነበር፡፡ በጊዜውም ባልናሚስት፣ እጮኛሞች፣ ፍቅረኛሞች እና መሰል ገፀ ባህሪያትን ወክለው ስለሚጫወቱ በተመልካች ዘንድ ባልና ሚስት ተደርገው ይቆጠሩ ነበር፡፡ እንደ አርቲስቷ ገለፃ “አርቲስት ጌጡ አየለ የወንድ ጓደኛ እንኳን አልነበረውም፡፡ ሰርጉንም እኔ ነኝ ደግሼ የዳርኩት” በማለት በሁለቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ታስረዳለች፡፡
ቀደም ሲል ትምህርት ሳትማር የትራንፔት ተጫዋች የሆነው የመጀመሪያ ባለቤቷ አቶ ግርማ ገብረአብ እያስጠናት በግሩም ሁኔታ ዘፈኖቿን ታቀርብ ነበር፡፡ ባለመማሯ የተቆጨችው ፍቅርተ ደሳለኝ በየነ መርዕድ የማታ ትምህርቷን ጀምራ ፍሬህይወት 1ኛ ደረጃ ት/ቤት እስከ 8ኛ ክፍል ተማረች፡፡ ከዚያም በሌላ ት/ቤት እስከ 12ኛ ክፍል ትምህርቷን አጠናቃቀች፡፡
አርቲስት ፍቅርተ ደሳለኝ ከሙዚቃዎቿ ባሻገር በርካታ ትያትሮችና እና ፊልሞችን ሰርታለች፡፡ ከሰራቻቸው ትያትሮች ውስጥ የሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን የትርጉም ስራ የሆነው “የፌዝ ዶክተር ” የተሰኘው ትያትር የመጀመሪያ ስራዋ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ “ጥላ”፣ “የባላገር ፍቅር”፣ የዶ/ር አርቲስት ተስፋዬ አበበ ድርሰት የሆነው “አምታታው በከተማ” ላይም የገጠር ሴትን ወክላ ተጫውታለች፡፡ በ1992ዓ.ም ጡረታ ከወጣች በኋላ የአዜብ ወርቁ የትርጉም ስራ የሆነው “8ቱ ሴቶች” እንዲሁም “ፍቅር የተራበ” ትያትር ላይ ተውናለች፡፡

ከትያትሩ ወደ ፊልም ኢንዱስትሪው ተቀላቅላ በዛ ያሉ ፊልሞች ላይም ሰርታለች፡፡ ለአብነትም ፡- “ማራ፣ ማንነት፣ ታስራለች፣ ዱካ፣ የህሊና ዳኛ/ የመጀመሪያ የፊልም ስራዋ ነው/፣ ቫኬሽን ፍሮም አሜሪካ፣ ሰርፕራይዝ፣ ጥቁር ነጥብ፣ የልደቴ ቀን፣ ያ ልጅ፣ የትውልድ እንባ፣ ስሌት፣ ጓንታናሞ፣ ልዩነት፣ 400 ፍቅር፣ አይራቅ፣ ጉደኛ ነች የመሳሰሉትን በጥቂቱ መጥቀስ ይቻላል፡፡ አርቲስት ፍቅርተ ደሳለኝ በትያትርም ሆነ በፊልሞቹ ላይ ብዙውን ጊዜ የእናት ገፀ ባህሪን ተላብሳ ነው የምትቻወተው፡፡
ለመድረክ ከፍተኛ ክብር የምትሰጠው አርቲስት ፍቅርተ ደሳለኝ ሽቅር ቅር እና ሳቂታ ናት፡፡ ፈገግታ ከፊቷ የማይለያት አርቲስቷ እንባዋም ቅርብ ነው ይላሉ በቅርብ የሚያውቋት ጓደኞቿ፡፡ ጡረታ በ1992ዓ.ም ከወጣች በኋላ የፍቅር ዘፈን አልሰራም፤ ከሰራሁም ጠንከር ያሉና አስተማሪ ስራዎችን ነው የምሰራው የሚል አቋም አላት፡፡

Screen Shot 2016-01-28 at 11.07.04 AM
አርቲስት ፍቅርተ ደሳለኝ ከትራንፔት ተጫዋች ባለቤቷ ከአቶ ግርማ አንድ ልጅ ወልዳለች፡፡ ይህ ትዳር ባይዘልቅም አሁን ሌላ ትዳር መስርታ እና ልጆች ወልዳ እየኖረች ነው፡፡ የልጅ ልጅ ያየችው እና የአራት ልጆች እናት የሆነችው ፍቅርተ ደሳለኝ በቅርቡ የወጡ እና ሊወጡ የሚችሉም በርካታ ፊልሞችም አሏት፡፡ የተለያዩ የቴሌቭዥን ድራማዎች ላይም ተሳትፋለች፡፡
ለአንጋፋዋ ድምፃዊት እና ተዋናይት እድሜ እና ጤና ተመኘሁ፡፡

The post ምናልባት ስለሞጋቾች ድራማ ምርጥ አርቲስቷ ፍቅርተ ደሳለኝ የማታውቋቸው ነገሮች appeared first on Zehabesha Amharic.

“በአኮቦ ወረዳ ከ200 በላይ የሚሆኑ አኙዋኮች ህፃናት እና ሴቶች ተጨፍጭፈዋል”–ከታህሳስ ሶስት መታሰቢያ ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ የተሰጠ መግለጫ

$
0
0

ከታህሳስ ሶስት መታሰቢያ ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ የተሰጠ መግለጫ

(December 13 Commemoration Democratic Movement)

ጥር 16 ቀን 2008 ዓ.ም

ሁላችንም እንደምንገነዘበው ባለፋት 25 አመታት ወያኔ ሲጠቀምባቸው የነበሩ ስሌቶችና ጭካኔና በተሞላበት ድርጊቶች መካከል የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር በሀይማኖት እና በክልል እየከፋፈለ አንዱን ብሄረስብ በሌላው ላይ እያነሳሳና እያስታጠቀ ለመቆየት በመቻሉ ነው። በተናጠል ሌላውን ብሄረሰብ እያጠቃ በጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚፈፅመው የኢሰብዓዊ ድርጊቶች ከማንኛውም ግዜ በላይ በመቀጠል ላይ ነው ያለሁ። ለዘመናት በሰላም እና በፍቅር ይኖር የነበሩትን ብሄረሰቦች እርስ በእርስ በማጋጨት በሌላው ብሔረሰብ ላይ የዘር ማጥፋት ዘመቻም እያወጀና እየጨፈጨፈ ሲያንስም የሕዝቡን ነፃነት እየሸረሸረ ዛሬ በበለጠ ግዜ የሀገሪቷን ሉዓላዊነት አወዛጋቢ ሁኔታ ላይ ጥሎዋታል።

File Photo

File Photo

መላው የአለም ህዝብ እንደሚያውቀው ታህሳስ 3፣1996 ዓ.ም (December 13, 2003) በጋምቤላ ከተማና በተለያዩ ወረዳዎች ዉስጥ ከሶስት ሺህ በላይ የሚበልጡ እኙዋኮች እንደ እንስሳ በወያኔ የታደኑበት ቀን ነች። ይህን ድርግት በተመሣሣይ ሁነታ በሌላው የኢትዮጵያ ብሕረሰብ ላይ እንዳይደገምና መላዉ የአለም ሕዝብ ይህን ታርካዊ ቀን እንድያስታውሳትና እንዳይረሱት ምክንያት ተደርጎ ይህንን ድርጅት በዚቹ ቀን እንድሠየም ተደርጓል። አሁንም ቢሆን በአኙዋኮች ላይ በሌላ መልኩ ተመሳሳይ ግድያ እየተካሄደ ነው። ባለፈው ወር ብቻ በአኮቦ ወረዳ ከ200 በላይ የሚሆኑ አኙዋኮች ህፃናት እና ሴቶችን ጭምር ወያኔ ባስጣጠቃቸው ከባድ የጦር መሳሪያዎች በስደተኛው ንዋር ብሄረሰብ ተጨፍጭፈዋል። እንዲሁም አኮቦ ወረዳ አልፎ በተመሳሳይ ሁኔታ ደግሞ በኢታንግ ወረዳ የሚገኙ ቀበሌዎች በነዚህ የጦር መሣርያዎች በመደብደብ በርካታ በቶችና ንብረቶችን ተጋይተው 18 በላይ የሚበልጡ አኙዋኮች መገደላቸው እና በርካቶች መቁሰላቸው ለአለም ተገልፆዓል።

በተጨማሪ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝና የተቀሩት ከፍተኛ የወያኔ ባለሥልጣን በተገኙበት ለውሸት ፕሮፓጋንዳ ተብሎ በጋምቤላ የብሄርና ብሄረስቦች በሚከበርበት ቀን ለአኙዋኮች መግደያ እንዲሆን የታቀደው የጦር መሳሪያ የተከማቸበት ግምጃ ቤት እንዳይከፈት በትህዛዛቸው የተከለከለ ሲሆን ፣ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ እነዚህን መሳሪያዎች ለአጋሩ የንዋሩ ብሕረሰብ ለማከፋፈል ስሞክሩ የጫኑበት መኪና ላይ በኬላ ላይ በመያዙ እስከ ዛሬ ድረስ ማንም በዚሁ ሽብር የተጠየቀ እንዳልነበረ ነው። በአለፋት ቀናት በዜና ምንጮች ስዘገቡ የነበረው የጋምቤላ አሳሳቢ ሁኔታ የንዋሩና የወያኔ ሴራዎች በመሆናቸዉ የአኝዋክ ብሕረሰብ ለዘመናት በዘግነቱ የኮራ ለአገሪቷን ሉዑላዊነት ከሚገባው መጽዋትነት የከፈለ በወያኔ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ያልተበገረ አኩሪ ታሪክ ያለው ሕዝብ ነው። ይህን ሆኖ እያለ ወያኔና ግብረአበሮቹ የአቀዱትን የአኝዋኩ ብሕረሰብ የመጨፍጨፍ ሴራ ማንኛውም ኢትዮጵያዊና የአለም ሕብረተሰብ በጥብቅ እንድያወግዘውና እንድያከሽፍ ያስፈልጋል። በመቀጠልም በአዲስ አበባ አካባቢ የሚገኙ የታወቁ እና ያልታወቁ አስቃቂ እስር ቤቶች ክ200 በላይ የሚሆኑ አኙዋኮችና የመጀንገር ብሄረስብ ሀባላት በታህሳስ 3፣ 1996 ዓ.ም ወያኔ በፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጄል በግድያ ወቅጥ በመትረፋቸው ብቻ ተወንጅለው በእነዚህ እስር ቤቶች በመሰቃየት ላይ ናቸዉ።

ትላንት በአማራው በሱማሌው በኦሮሞው በአኙዋኩ በመጀንገር እና በሌሎችም የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሲፈፀም የነበረው ግድያ፣ አሁንም ደግሞ በአዲስ አበባ ማስተርፕላን ጋር የተያያዘው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ሰበብ በማድረግ የወያኔ አሸባሪ ሰራዊት የኢትዮጵያ ህዝብ ጭካኔ በተሞላበት ጭፍጨፋ የተፈፀመባቸዉ ናቸው። ከዚህም አልፎ የሀገሪቷን ንብረቶች እየዘረፈ፣ መሬቶችን እየነጠቀ እና ህዝቡን በማፈናቀል ለ25 ዓመታት ሁሉ የዘረጉትን የግድያ ስንስለቶች እንዲቆይ ያደረገው ህዝብን በመከፋፈል መሆኑ እየታወቀ አሁን ኦሮሞ ሕዝብ ለነፃነትና ለእኩልነት የሚያካሆደሁን እንቅስቃሴ የአንድ ብሄረሰብ ትግል ብቻ ሳይሆን የጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድነትን የተመረኮዘ ትግል እንደሆነ ሊታሰብበት ይገባል ።እስከ ዛሬ ድረስ ወያኔ በሌላውብሄረሰብ ላይ በጠናጥል ሲፈፅማቸው የነበሩትን ግድያዎች በጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እንዳልተፈፀመ ተደርጎ ባለመወሰዱ የወያኔ አረመኔነትን እንድያራዝም አድርገናል። በመሆኑም ይህች አገር ከገባችበት ሰቆቃ ለማላቀቅ የመላው የኢትዮጵያ ብሄረስቦች በአንድነት በዘር በሀይማኖት ሳይከፋፈሉ ሁሉን ያካተተ ውህደት በመፍጠር ወያኔ የሚወገድበትን አንድ አላማ መቀየስ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ጭምር ነው። ዛሬ በሁሉም አቅጣጫ ህዝቡ ታፍኖል ለነጌይቱ የሚያዘልቃቸውን የነፃነት ትንፋሽም ታግዷል ። ለዘመናት ኢትዮጵያ እንድትኖር ያበቁትን እነ አፄ ቴውድሮስ አፄ ምንሊክ እና ዘርዓይን እና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን በከፈሉት መስዋትነት ሲሆን በሀገሬ ውስጥ ባርነትን አንቀበልም ብለውነውሞትንየተጋፈጡት።

ስለዚህ ነፃነት በልመና በነፃ እንደማይጎናፀፍ  በመሆኑ፣ ከሰማይ የሰላምና ነፃነት አምላክ  እሲኪወርድ ድረስ የምንጠብቅ ከሆነ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ትኖራለች የሚል ግምት እንደማይኖር ነው።

በመቀጠል ደግሞ ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ለማስተላለፍ የሚንፈልገው፧ ወያኔ የሕዝቡን ደም ደፍቶ በዝርፊያ ያካበታቸውን ሀብቶች ፣ የንግድና የኢኮኖሚ አውታሮች [ትራንስፖርትና መገናኛ ዘርፎች]በዘረፋ የተገኙ በመሆናቸሁ በነፃነትና በሰብአዊነት የሚያምኑ በውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በወያኔና በደጋፊያቸ የንግድና የኢኮኖሚ አውታሮች ላይ ማእቀብ እንድጫንባቸው።

በተለያዩ ሀገሮች በድብቅ ያካበቱ የንግድ ዘርፎች የዉጭ ምንዛሬ ምንጭ በመሆናቸውና በነዚ ሀብት በሚሰበሰበሁ በመጠቀም ሕዝቡን የሚጨፈጭፋበትን የጦር መሣሪያ በመሆኑ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ አቅሙን በሚፈቅደው ሁነታ ከነዚህ ዘርፎች ጋር አንዳችም የንግድ ግንኙነቶችን እንዳይኖር እንድቆጠቡ።

መንግስት መንግስትነትን የሚያሰኘው ማሟላት የሚገባቸዉ አላፊነቶችና ድርግቶች በጥቂጡ ለመግለጽ፣ በሕዝቡን መካከል ሰላም እንድሰፍን መጣር፣ በሕብረተሰቡ መካከል የሚፈጠሩ አለመግባቶች በሰላማዊ እንድፈቱና በማድረግ፣ የአንድነት ስመት እንድኖርና የአገርቷን ደህንነትና ድምበር ማስከበር ሲሆን ወያኔ ግን በተቃራኒ ሕዝቡን በዘርና በጎሳ እየከፋፈለ፣ እየገደለና የአገርቷን ንብረቶችን እየዘረፈ፣ መሬቱን ለውጭ አገር እየለገሰ፣ ለሰውነት ለነፃነትና ለዲሞኪራሲ እሉኝታ የሌለው፣በጎሰኝነት በዘረኝነት በብሕረተኝነት አጥብቀው የሚያምኑበት በመሆኑ ይህን ስርኀት መንግሥት ባለመሆኑ በሕዝቡ ደምና አጥንት የነደፋቸው ፀረ ሰው ሕገ ወጥ ሕጎች ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንዳያከብራቸው ለጠቅላላው ሕዝብ ጥሪያችን እናስተላልፋለን።

በአንድነት በነፃነትና በእኩልነት በፍትህና በዲሞኪራሲ ላይ የተመሠረተ ስሪኀት እንድቋቋም የሚያስችል በጠቅላላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትብብር ብቻ ነው። በዚሁ በመነሳት ዘረኛዉ የአረመኔ ስብስብ ሊፋለሙት የሚያችላቸውን አንድ ዓላማ በመነሳት፣ የፓለቲካ ድርጅቶች ልዩነቶች በማስወገድ፣ በአገር ስሜት ለአሁኑ አጣዳፊ የአገር ማዳን ጉዳይ በጋራ እንድንወጣ በአስቸኳይ ጥሪያችን ስናስተላልፍ፣ ለብዙ አመታት በተናጠል የተሞከሩ የነፃነት እንቅስቃሴዎች የትም እንዳላደረሱን የሚታሰብ ሲሆን አሁንም ከተለያዩ ድርጅቶች እና ብሄረስቦች መካከል የተጀመረውን የመተባበር መንፈስ በሰፊው እንዲቀጥል እና የጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ ምኞት በመሆኑ ድርጅታችን በዘር እና በክልል የተገደበ ባለመሆኑ ከጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ተባብረን ለመስራት ዝግጁ መሆናችንን በዚህ አጋጣሚ ለመግለፅ እንወዳለን።

አንድ ኢትዮጵያ አንድ ህዝብ!

E‐mail: dec13codemo@gmail.com የታህሳስ ሶስት መታሰቢያ ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ

The post “በአኮቦ ወረዳ ከ200 በላይ የሚሆኑ አኙዋኮች ህፃናት እና ሴቶች ተጨፍጭፈዋል” – ከታህሳስ ሶስት መታሰቢያ ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ የተሰጠ መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአባይ ጸሃዬ ጦርነት በሚለው ላይ ምላሽ ለተስፋዬ ገብረአብ –ግርማ ካሳ

$
0
0

abay Tsehaye

ተስፋዬ ገበረአብ አንድ ወቅት የኢሕአዴግ ባለስልጣን የነበረ ሰው ነው። ጥሩ ጸሃፊ ነው። ከኦሮሞ ብሄረተኞች ጋር የቅርብ ግንኙነት አለው። አንድ ወቅት እንደዉም የኦሮሞ ተማሪዎች ማህበር ላይ የክብር እንግዳ ሆኖ ቀርቧል። በዚይ ወቅት “በሞጋሳ እኔም ኦሮሞ ነኝ” ነበር ይለው። ሞጋሳ አንድ ሰው “ኦሮሞ” ባይሆንም የኦሮሞን ባህልንና ቋንቋን ከተቀበለ፣ በኦሮሞ ሽምግሌዎች ፍቃድ “ኦሮሞ” የሚሆንብት ስርዓት ነው።፡(naturalized ኦሮሞነት)
ተስፋዬ “የአባይ ጸሐዬ ጦርነት” በሚል ርእስ አንድ ጽሁፍ አስነብቦናል። በጽሁፉ እነ አባይ ጸሃዬ አማራውን እና ኦሮሞውን በማጣላት በስልጣን ለመቆየት የማይፈነቅሉት ድንጋይ እንደሌለ ነው የገለጸው። ‘ከመነሻው በቋንቋ ላይ የተመሰረተ የፌደራል ስርአት ለመጠቀም ሲነሱ በህዝቦች መካከል በሚፈጠር አለመግባባት ስልጣናቸውን ለማቆየት እንደሚችሉ በማመን ነበር። በርግጥም ተጠቅመውበታል” ሲል ፣ በስልጣን ለመቆየት ሲባል ህዝብን በዘር ለመከፋፈል ከጠዋቱ ከጅምሩ የሕወሃት አጀንዳ እንደነበረ ነው የሚያስረዳን።

እዚህ ላይ ከተስፋዬ ገብረአብ ጋር በጣም እስማማለሁ። በተለይም አሁን ያለው በቋንቋ ላይ የተመሰረተው የፌዴራል ስርዓት ዋና አላማ፣ የብሄረሰቦችን መብት ለማስጠበቅ ታስቦ ሳይሆንን በሕዝብና በሕዝብ መካከል ግድግዳን በመፍጠር ከፋፍሎ ለመግዛት እንደሆን ብዙዎቻችን ደጋግምመን ስንጽፍፍበትና ስንናገረው የነበረ ጉዳይ ነው።

በነገራችን ላይ ተስፋዬ ራሱ የሕወሃት ባለስልጣን በነበረበት ጊዜ የዚህ በዘር የመከፋፈል እንቅስቃሴ አካል እንደነበረ መረሳት የለበትም። በተለይም የቡርቃ ዝምታ በሚል ርእስ የጻፈው፣ በፍጠራ ልአይ የተመረኮዘ መጽሐፍ ፣ ሆን ተብሎ በኦሮሞዎችን እን በሌላ ማህበረሰብ መካከል ትልቅ ጥላቻ እንዲኖር ያደረገ በጣም መርዛማ መጽህፍ ነበር።፡ታድዲያ አሁን ተስፋዬ፣ ከነርሱ ጋር ሲጣላ፣ ዞር ብሎ ስለ ወያኔ ዘረኘንት ሲነግረን ማየት ትንሽ ይያስቃል። ለምንኛውም፣ ግድ የለም ምናልብት የአመልክከት ለውጥ ተፈጥሮ ሊሆንን ስለሚችል የቡርቃ ዝማትን ለጊዜው ትቼ አሁን ወደጻፈው እመለሳለሁ።

ተስፋየ ለመግለጽ እንደሞከረው፣ ሕዝብን ክሕዝብ ለመለያየት ሆን ተብሎ ከመነሻው የተዘረጋው፣ በኦነግና በሕወሃት ተግባራዊ የሆነውን በቋንቋ ላይ የተመሰረተው የፌዴራል ስርዓት አንዱ ዉጤት “ኦሮሚያ” የምትባል ክልል መፈጥሯ ነው። ከዚይ በፊት ኦሮሚያ የሚባል ክፍለ ሃገር፣ ዞን፣ ወረዳ መንደር ኖሮ አያውቅም። ኦነግን የመንግስት አካል ለማድረግ ሲባል ብቻ የተፈጠረች ክልል ናት። ይች ክልል ፣ ለአስተድደር አመች ካለመሆኗ የተነሳ ለብዙ ግጭቶችና አለመስምማቶች ምክንያት ሆናለች።

ኦሮሚያን ጨመሮ አሁን ይሉት ዘረኛ የፌዴራል አወቃቀር የወለዳቸው ክልሎች፣ አሁን እንዳለው ቋንቋን ብቻ ሳይሆን፣ የአስተዳደር አመችነትን፣ የሕዝብ አሰፋፈርን፣ ባህልን፣ የህዝቡ ፍላጎትን፣ ኢኮኖሚን፣ ጂዮግርራፊን …ባካተተ መልኩ በጥናት፣ መስተካከል እንዳለባችው የብዙዎች እምነት ነው።

ተስፋዬ ገብረአብ ግን፣ ሕወሃት/ኢሕአዴግ ለከፋፍለህ ግዛ ከመነሻው የተጠቀመብት የፌዴራል ስርዓት እንደሆነ ግሩም በሆነ ሁኔታ በሳፈረበት ብእሩ፣ ወረድ ብሎ ደግሞ “የአማራ ልሂቃን ቢያንስ ኦሮሚያን እንደ ክልል በማወቅ የመቀራረቡን መንገድ መክፈት ይጠበቅባቸዋል” ሲል በኦነግና በሕወሃት በሃይል በሕዝቡ ላይ የተጫነን ፌዴራሊዝም መቀበል እንደሚገባ ይነግረናል። በቀኝ እጅ የተገነባን በግራ እጅ ማፍረስ ይሉታል ይሄ ነው።
ሌሎች ብዙ ተስፋዬ ጫር ጫር ያደረጋቸው ነጥቦች አሉ። በተለይም “አማራ” ስለሚለው ማህበረሰ የጻፋቸው ትንሽ መስመር የለቀቁ አባባሎችን አንብቢያለሁ። ብዙም እዚያ ላይ አሁን ለጊዜው አላጠፋም። ግን ሳልጠቅስ የማላልፈው አንድ ነጥብ አለ።

በኦሮሚያ የተነሳውን ተቃዉሞ በመደገፍ፣ በኦሮሚያ ባሉ ትላልቅ ከተሞችና በሌሎች ክልሎች ያለው ማህበረሰብ ተነስቷል ማለት አይቻልም። ይሄም የራሱ የሆነ ምክንያቶች አሉት። ዶር መሳይ ከበደ እንደጻፊት ላለፉት 25 በነበረው ሁኔታ ጥርጣሬ መኖሩ (ብዙዎች በኦሮሞ አክራሪዎች ጥቃት ሲፈጸምባቸው፣ ከቅያቸው ሲባረሩ ስለነበረ …) አንድ ምክንያት ነው። ሕዝቡ አለመደራጀቱ፣ የኦሮሞ ተቃውዋሚዎች ይዘዉት የነበረው አጀንዳ አገር አቀፍ አለመሆኑ እንደ ሌሎች አበይት ምክንያቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ። ሆኖም ተስፋዬ ገብረዓብ፣ ምክንያቶችን ከመረዳት ይልክ፣ የኦሮሞዎችን ተቃዉሞ አልደገፉም በሚል፣ ለሌላው ማህበረሰብ ማስጠንቀቂያ ቢጤም ለመስጠት የሞከረበት ሁኔታ ነው ያለው።

“በቅርቡ የወያኔ ነባር አባል ከሆነ የቀድሞ ወዳጄ ጋር በፅሁፍ ስናወጋ” ያለው ተስፋዬ፣ ይሄ ወዳጁ “የሞጋሳ ዘመዶችህ(ኦሮሞዎች ማለቱ ነው) አይሳካላቸውም። አማሮች ለታክቲክም ቢሆን ከኛ ጋር ናቸው።” እንዳለው ጽፏል። ሌላም ማህበረሰብ ከወያኔዎች ጎን እንደቆመ ነው ሊያመላክተን የሞከረው። አንድ ማህበረሰብ ዝም አለ ማለት አገዛዙን ደገፈወደ ማለት ድምዳሜ እንደመድረስ ነው። በአዲስ አበባ ከ200 በላይ ዜጎች ሲረገፉ ሌሎች አልተነሱም ነበር። በባህር ድዳር

ወረድ ብሎም “ የኦሮሞ ህዝብ አመፁን አጠናክሮ ቀጥሎ ብቻውን የወያኔን ስርአት ለማስወገድ ከበቃ ለሌላው ወገን ለፀፀት የሚያበቃ ታሪካዊ ስህተት ይሆንበታል። በአብሮ መኖር ሂደት ሌሎች የሚሉትን መስማት ቀዳሚ ጉዳይ ነው። የኦሮሚያን አመፅ ሌሎች ኢትዮጵያውያንም እንዲሳተፉበት ሲጠየቁ፤ ለነገ አብሮነት በማሰብ እንጂ የኦሮሞ ህዝብ ብቻውን ወያኔን ማንበርከክ አይችልም ከሚል አልነበረም። ይህን አብሮ የመታገል ጥያቄ በተሳሳተ መንገድ የተገነዘቡ ወገኖች ወያኔን ስልጣን ላይ በማቆየቱ ረገድ የማይናቅ ድርሻ እያበረከቱ ነው” ሲል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የኦሮሞዎችን ንቅናቄ ሌላው መደገፍ እንዳለበት ያስጠነቅቃል።

ይህ አይነትት አቀራረብ በጣም አደገኛ አቀራርብ። የኦሮሞ ብሄረተኞች ተስፋዬ እንዳለው የኦሮሚያ ትላልቅ ከተሞች ሳያቅፉ ፣ ሌላውን ማህበረሠብብ አግለው ለብቻው የሚያመጡት ዉጤት ይኖራል ብዬ አላስብም። ላለፉት ሁለት ወራት የተደረጉት እንቅሥቃሴዎች ለውጥ ካላመጡ ምንም አይነት እቅንስቃሴ ነው ለዉጥ የሚያመጣው ? መቼም የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እንዲሰረዝ ተደርጓል የሚል መልስ አይይቀርብም። ማስተር ፕላኑ በሌላ መልኩ መተግበርኡ አይቀሬ ነው።

ይህ የተጀመረውና በጣም ምመቅዛቀዝ እየታየበት የመጣው የኦሮሞዎችን እንቅስቃሴ በቶሎ ሌሎችን ባቀፈ መልኩ እንዲሰፋ ካልተደረገ ፣ በዚህ ረገድ የኦሮሞ ልሂቃን ምመሰረታዊ የሆነ የአካህእድ ለውጦችን ካላደረጉ፣ በጣም ትልቅ ታሪካዊ ስህተት ነው የሚሠራው። ሌሎችን ማስጠንቀቅና በልእሎ ላይ መዛት ሳይሆን፣ የሌሎች ጥያቄ ምንድን ነው ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል። ሌልአው ማህበረሰብ እኮ ላለፉት 25 አመታት በኦሮሚያ ዉስጥ ሲፈናቀል፣ ሲገደል፣ ኦሮሞ አይደለህም ትብሎ ከሥራ ሲባረር ..የነበረ ነው። ብዙ ግፍ የተፈጸመበት ነው። ይህ ማሀብረሰብብ ቢፈራና ቢጠራጠር በጭራሽ ሊወቀስ አይገባውም።

የኦሮሞ ልሂቃን “ኦሮሚያ፣ ኦሮሚያ..” የሚሉትን አቁመው፣ ጥያቄው የምብት፣ የፍትህ ጥያቄ ነው በሚል ለምን በኢትዮጵያ የዜጎችን ጣይቀእ ህኡሉ የምኢያከበር ዴሞክራሲያዊ ስር፤ዓት እንዲገነባ አይነሱም? የኦሮሞ መሬት የወሰደ ከሚሉ መሬቱ የሌሎቻ ያለሆነ ይመስል፣ ለምን ገበሬው የመሬት ባለቤት ይሁን አይይሉም ? የዲሞክራሲ ስርዓት ከተገነባ ፣ ሕዝቡ ከፈለገ በአጼ ጊዜ የነበረው አወቃቀር፣ ከፈለገ ዓሁን ያለውን፣ ከፈለገ ደግሞ ሌላ አዲስ ….ማዋቀር እንደሚችል ለምን ስምምነት ማድረግ ይሳናቸዋል ? ለምን ኦሮሚያ ወይንም ሞት የሚል አቋም ይይዛሉ ? ኦሮሚያ መኖር አለበት ካሉ በኦሮሚያ ዉስጥ መሆን የማይፈለገውስ ማህበረሰብ ? 75% የሚሆነው የአዳማ ህዝብ፣ 990% የሚሆነ የአዲስ አበባ ህዝብ፣ 60% የሚሆነው የጂማ ህዝብ፣ ከ80% በላይ ይየሚሆኑት የቢሾፍቱና የሻሸመኔ ነዋሪዎች ….

ይልቅ የሚያዋጣው ግትርነትት ሳይሆን ነገሮች በርጋታ ተመልክቶ፣ የሁሉንም መሰረታዊ ጥያቄ በመለሰ መልኩ መግባባቶች እንዲኖሩ ማድረግ ነው። ለዚኅም በዋናነት ቁልፍ ሥራ መስራት ያለባቸው የኦሮሞ ልሂቃን ናቸው።፡ሌላአ ማህበረሰብ በኦሮሞ ክራሪዎች ላለፉት 25 ሲገፋ የነበረ ነው። ይሄንን ሕዝብ ማቀፍ የግድ ያስፈልጋል። ሌላው ይቅር በኦሮሚያ ያሉትን ትላልቅ ከተሞች ማቀፍ ያስፈለጋል።፡በኦሮሚያ ያሉ ትላልቅ ከተሞች ደግሞ multi-ethnic ናቸው።

The post የአባይ ጸሃዬ ጦርነት በሚለው ላይ ምላሽ ለተስፋዬ ገብረአብ – ግርማ ካሳ appeared first on Zehabesha Amharic.

በጋምቤላ በኑዌር እና በአኝዋኮች መካከል በተፈጠረ ግጭት 6 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰማ

$
0
0

Zehabesha News

(ዘ-ሐበሻ) በጋምቤላ ከተማ በኑዌሮች እና በአኝዋኮች መካከል በተነሳ ደም ያፋሰሰ ግጭት የ6 ሕይወት ማለፉን የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች ከስፍራው ዘገቡ::

ባለፈው ሳምንት አንድ ሰው መሞቱን ተከትሎ ዛሬ በጋምቤላ ከተማ በተከሰተው ግጭት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች እንደቆሰሉ ምንጮቻችን ዘግበዋል::

በሁለቱ ብሔረሰብ ግጭቶች በስተጀርባ የሕወሓት እጅ እንዳለበት የሚጠቅሱ የፖለቲካ አክቲቭስቶች በተለይ የአኝዋክ አክቲቭስቶች ከኑዌር ማህበረሰብ በስተጀርባ ሕወሓት እንዳለበትና ጠመንጃ እንዳስታጠቃቸው ይከሳሉ::

ተጨማሪ መረጃዎችን ዘ-ሐበሻ ይዛ ትመለሳለች::

The post በጋምቤላ በኑዌር እና በአኝዋኮች መካከል በተፈጠረ ግጭት 6 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.

አቡነ ማትያስ መህበረ ቅዱሳንን አፈርሰዋለው ሲሉ የማፍረሻውን ትዕዛዝ ማን ሰጣቸው? ቅዱስ ሲኖዶስ? ወይንስ….? ። –ከተማ ዋቅጅራ

$
0
0

H_E_Abune_Matiyas_Archbishop_of_Jerusalem_Misaያልፈረሰን ማፍረስ ያልተነቃነቀን ማነቀነቅ በአንድነት ለዘመናት ተዋደው እና ተፋቅረው የኖሩትን ህዝብ መበተን የኢትዮጵያኖች የእለት ተእለት ዜና ከሆነ ስንብቷል። ዛሬም በአንድነት እና በጥንካሬአቸው  ለቤተ ክርስትያን እውቀታቸውን፣ ገንዘባቸውን፣ ጉልበታቸውን ሳይሳሱ በመስጠት የቤተክርስትያን ልጅነታቸውን በማስመስከር ያልተማረን እንዲማሩ በማርደግ፣  የአብነት ትምህርት ቤቶችን ህንጻዎችን በማነጽ እንዲጠናከር በማድረግ፣ ቤተክርስትያንን  በቅንነት በማገልገል ወጣትነት ሳያታልላቸው በጉብዝናህ ግዜ እግዚአብሔርን አስብ የሚለውን አምላካዊ ቃል እየፈጸሙ ያሉትን ወጣቶች የበለጠ ፍቅር፣ የበለጠ አባታዊ ምክር፣ የበለጠ ቤተ ክርስትያኗ ድጋፍ፤ ማድረግ ሲገባቸው የቤተክርስትያኗ መሪ በተባሉት በአቡነ ማቲያስ የሰላ ትችት እየተሰጣቸው እጅና እግራቸውን አስሬ ካላስቀመጥኳቸው ተብሎ ዛቻዎችን ስንሰማ እንደ ቤተክርስትያን ልጅነታችን የሚያም ጉዳይ ነው። ማን አይዞት ብሎዎት ነው የቤተክርስትያን ልጆችን ለማሰር የተነሱት? የየትኛውስ አካል ለማስፈጸም ነው ማህበረ ቅዱሳንን ለማፍረስ የተነሱት?

የማህበረ ቅዱሳን አባል ከአለማዊ ትምህርት የአለማዊ ትምህርታቸውን ጠንቅቀው የተማሩ ከመንፈሳዊ ትምህርታቸውም መንፈሳዊ ትምህርታቸውን በደንብ የተማሩ የተማሩትንም በስራ ላይ የሚያውሉ በአባቶች መሰረት ላይ የተመሰረቱ የቤተክርስትያን አገልጋዮች ናቸው። ማህበረ ቅዱሳን በቁጥር በጣም ብዙ የሚባል አባል እንዳለው የሚታወቅ ሲሆን አገልግሎታቸውም እንደ ቁጥራቸው በጣም ሰፊ ነው። በመላው ኢትዮጵያ የሲኖዶስ አባቶች ሊደርሱበት ያልቻሉትን ቦታዎች ጭምር በመድረስ የቤተክርስትያን ልጅነታቸውን በማስመስከር የተዘጉ ቤተክርስትያንን በማስከፈት፣ ሊዘጉ ያሉትን ሳይዘጉ በመድረስ በተጠናከረ ሁኔታ ቀጣይነት ባለው መልኩ አገልግሎት እንዲቀጥል በማድረግ ቋሚ መገልገያ በመትከል እራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩበትን ስራ በመስራት ከፍተኛ ተጋድሎ  እያደረጉ ያሉ የቤተክርስትያን ልጆች ናቸው።

የማህበረ ቅዱሳን እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ብቻ የተወሰነ  ሳይሆን በመላው አለም የተዘረጋ በግዜ እና በቦታ ሳይወሰኑ ለቤተክርስትያን ቅድሚያ በመድረስ አገልግሎት በመስጠት ያለ ስብስብ ነው። ቅዱሳኖች ግዜአቸውን፣ እውቀታቸውን፣ ጉልበታቸውን ለቤተክርስቲያን በመስጠት ከእግዚአብሔር የአገልግሎታቸውን ዋጋ የጽድቅ አክሊል ተቀብለዋል። የስሙ ስያሜውም እንደሚነግረን የማህበረ ቅዱሳን አገልግሎት ከዚህ የተለየ ባለመሆኑ ማህበረ ቅዱሳን ተብሏል። የቅዱሳንን ፈለግ ተከትለዋልና።

ታዲያ አቡነ ማቲያስ ማህበረ ቅዱሳንን ማፍረስ ለምን አስፈለጋቸው? እውነተኛ አባት ቢሆኑ ልጆቻቸው  በቤተ ክርስትያን ተሰብስበው ሲያዮ ደስ ሊላቸው ሲገባ… ልጆቻቸው  ተሰብስበው ስለቤተክርስትያን በአንድነት ሲቆሙ ሊያኮራቸው ሲገባ… ልጆቻቸው ገንዘባቸውን፣ እውቀታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ሳይሳሱ ለቤተክርስትያን ሲሰጡ ሊኮሩባቸው እና የበለጠ እንዲተጉ ሊያበረቷቷቸው ሲገባ አስሬአቸው እነሱን ሳላጠፋ እንቅልፍ አይወስደኝም ተብሎ መዛቱ ከፓትሪያሪክ የሚጠበቅ ነውን? ሲኖዶሱ ልጆቻቸው እጅና እግራቸው ታስሮ ከቤተክርስትያን መጥፋት አለባቸው ተብለው ሲዛትባቸው የማህበሩ አባላት ካልጠፉ እንቅልፍ እንደማይተኝ ሲነገርባቸው ምን ተሰምቷችሁ ይሆን?

ሲኖዶስ ከዚህ በፍት አቡነ ማትያስ ላይ በማህበረ ቅዱሳን እና በሌላ ቤተክርስትያናዊ ጉዳዮች ላይ አቡኑ በግላቸው ጥቂት ግለሰቦችን ሰብስበው ከሳቸው ጋር እንዲቆሙ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ላይ ጠንካራ አቋም በማሳየት የአቡኑን ሃሳብ በሙሉ ውድቅ በማድረግ ጥንካሬአቸውን አይተናል። እኛም በእውነተኛ አባቶች በሲኖዶሱ ውሳኔ እጅጉን ኮርተናል። ዛሬ ለምን ተመልሶ መጣ? ተመልሶ ሲመጣስ የሲኖዶስ ውሳኔ ምን ይሆን? ወደፊትስ ተመልሶ እንዳይመጣ ምን አይነት ውሳኔ ይሆን የሚወሰነው?

እንደ ቀልድ በሚሊዮን የሚቆጠር ስብስብን እግሩን እና እጁን አስረዋለው ብሎ  መናገር ከቤተክርስትያን አባት ይጠበቃልን? የአባቶች ድርሻ እኮ ያልተሰባሰቡትን ወደ ቤተክርስትያን መሰብሰብ እንጂ በቤተ ክርስትያን ስር የተሰበሰቡትን ከቤተክርስትያን ማባረር አይደለም። በእግዚአብሔር ቤት ላይ ሹመት የተቀበላችሁት በቤተክርስትያን ጥላ ስር የተሰበሰቡትን ለማፍረስ እና ለመበታተን ነው እንዴ? በእውነተኛዋ ቤተክርስትያን ስር በፍቅር ተሰብስበው በጥላዋ ያረፉትን እንደ ሰው ፍላጎት በቀላሉ ማፍረስስ ይቻል ይሆንን? በቤተክርስትያን  ስር ያለመለያየት በአንድነት የተሰበሰቡትን የቤተክርስትያን ልጆችን አፈርሳችኋለው ብሎ መናገር የቤተክርስትያን አባቶች ሃሳብ ወይንስ የሌላ አካል ሃሳብ?

አቡነ ማቲያስ መሐበረ ቅዱሳንን አፈርሰዋለው ብለው ይናገሩት እንጂ ከኋላቸው  ማን እንዳለ የታወቀ  ነው። ማህበረ ቅዱሳን ያሰባሰባቸው ሁሉም የቤተክርስትያን ልጆች መሆናቸው ብቻ ነው። የማህበሩ አባል የሚሆነው ወይንም የሆኑት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ  አማኝ የሆነ ብቻ ነው። ምንም አይነት የፖለቲካ አላማ  የሌለው ማህበር ነው። የዘር የቀለም ልዩነት የለም።በእርግጠኛነት ለመናገር ከሁሉም ብሄሮች ውስጥ የተዋህዶ ልጅ ከሆነ የማህበሩ አባል መሆን የፈለገ መሆን ይችላል። ወደዚህ ማህበር ሲመጣ ስለ ብሔር ወይንም ስላለህ ፖለቲካ አመለካከት ቦታ የለውም። ምክንያቱም የማህበሩ ምስረታ ምድራዊ መንግስትን ለማገልገል ሳይሆን ሰማያዊ መንግስትን መስበክ ስለሆነ። ምድራዊ ስልጣንን ለማስገኘት ሳይሆን የማታልፈውን የእግዚአብሔር መንግስት ለማውረስ ስለሆነ። ስለዚህ የሐጥያት ስር የሚባሉት ዘረኝነት፣ ወገኝተኝነት፣ገንዘብ ወዳድነት፣መለያየት የመሳሰሉት በማህበሩ ውስጥ ቦታ የሚሰጣቸው ጉዳዮች አይደሉም። ስለዚህ እውነተኛ ኢትዮጵያዊነት እና የእግዚአብሔር አገልጋዮች የሚገኙበት ማህበር ነው። ከየትም ይምጣ ከየት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጅ ከሆነ የዚህ ማህበር አባል መሆን ይችላል። ማህበሩን የማታውቁት አለ ብዬ መናገር ባልደፍርም ካላችሁ ግን ያለው እውነት ይሄ ነው።

ማህበረ ቅዱሳንን ማፍረስ የተፈለገበት ዋናው አላም ለመንግስት ፖሊሲ የተመቸ ስላልሆነ ነው። እንደ መንግስት ሃሳብ በዘር የተደራጀ ቢሆን ኖሮ አልያም የመንግስት ደጋፊ ሆነው መንግስት የሚፈልገውን የማለያየት ስራ የሚሰሩ ቢሆኑ ኖሮ ወይንም እንደ መንግስት ሃሳብ ኢትዮጵያን የማፍረስና  ታሪኳን የማጥፋት ስራ የሚሰሩ ቢሆኑ ኖሮ የኦርቶዶክስ አማኝ በሙሉ ወደዚህ ማህበር እንዲገቡ መንግስት ያስገድድ ነበረ። ይሄ ባለመሆኑ ዘረኝነት የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርስም ታሪካችንንም ለአፍሪካ ብሎም ለአለም ህዝብ ምሳሌ ነው በማለት አንድነት፣ ፍቅር፣ የእግዚአብሔር መንግስት የሚሰበክበት ማህበር በመሆኑ ዘረኝነት ነብሳቸው ትጸየፋዋለች ጥላቻንም አያስተምሩም ፍቅር ቤታችው፣ ፍቅር አገራችው፣ ፍቅር አምላካችው ነው በመሆኑ መንግስት ለማፍረስ ተነሳ። እንደተለመደው መንግስት እጄ የለበትም ለማስባል ሁሉንም በራሳቸው ሰዎች ከኋላ ሙሉ ድጋፍ በመስጠት  የሚያስመታው። ነገሮች አቅጣጫውን ስተው ጠንካራ ተቃውሞ ገጥሞት መቀልበሻው ሲጠፋውና ሲጨንቀው ደግሞ እርቅ ይላል። አቡነ ማቲያስ በማህበረ ቅዱሳን ላይ የመነሳታቸው ሚስጢር 100% የመንግስት መዶሻ ሆነው ማህበሩን ለመምታት የተነሱ አባት ናቸው እንጂ ለቤተክርስትያን በመቆርቆር ከቤተክርስትያን አባቶች ጋር ተማክረው  የቤተክርስትያንን መሰረቷን ለማጥበቅ የተነሱ እንዳልሆነ ጥንቅቀን እናውቃለን።

የቤተክርስትያንን ህልውና የሚፈታተንና ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነገር ከፊታችን ቀርቧል እኛ ልጆቿ ከእግዚአብሔር ዋጋ የምናገኝበት አልያም የምናጣበት።

ይሄንን ሁላ የምለው የማህበረ ቅዱሳን አባል ሆኜ አይደለም ነገር ግን እንደ ቤተክርስትያን ልጅኔቴ የቤተክርስትያን ጉዳይ ስለሚያገባኝ ነው። ስለ ቤተክርስትያን ጉዳይ ዝም ማለት አየር ሳትተነፍስ መኖር አንድ ነው። ስጋዊ ህይወትህ ማኖር ካለብህ ለደቂቃም ማጣት የማትችለው ነገር አየር ነው። ነፍስህን ለዘላለም በእግዚአብሔር እቅፍ ማኖር የምትችለው ቤተክርስትያን ስትኖር ብቻ ነው። ስለዚህ ስለ ቤተክርስትያን ዝም አንልም።

ከተማ ዋቅጅራ

28.01.2016

Email- waqjirak@yahoo.com

 

The post አቡነ ማትያስ መህበረ ቅዱሳንን አፈርሰዋለው ሲሉ የማፍረሻውን ትዕዛዝ ማን ሰጣቸው? ቅዱስ ሲኖዶስ? ወይንስ….? ። – ከተማ ዋቅጅራ appeared first on Zehabesha Amharic.

የኦሮሞን ሕዝብ ትግል ከመጠራጠር  ይልቅ ለሱዳን የሚሰጠውን መሬት ለማስቆም ሌላው ሕዝብ አሁን ይነሳ

$
0
0

ethiopia sudan Boarder

በኦሮሚያ የተነሳው ሕዝባዊ አመፅ አሁንም ተቀጣጥሎ በቀጠለበት በአሁኑ ሰአት በሌላው የኢትዮዽያ ክፍል ግን አልፎ አልፎ ጎንደር ላይ ከሚሰማው ውጥረት በስተቀር ይህ ነው የሚባል ምንም አይነት የአመፅ እንቅስቃሴ አይታይም። በተለያዩ ሚዲያዎች ወይም ድሕረ ገጾች ሌሎች ክልሎች ሕዝባዊ አመፁን እንደሚቀላቀሉና በኦሮሞ ህዝብ ያለዉ ጥያቄ በሌሎች ክልሎችም እንዳለና አንድ ቀን ሊፈነዳ እንደሚችል ሲነገር ቆይቷል ነገር ግን እስካሁን አመርቂ የሆነ እንቅስቃሴ በሌሎች ክልሎች የተደረገበት ሁኔታ የለም። አንዳንድ ከኦሮሚያ ክልል ውጪ ያሉ ፖለቲከኞች እንደሚሉት ከሆነ ሌላው ክልል አመፁን ያልተቀላቀሉበት ምክንያት በትግሉ ላይ ጥርጣሬ ስላላቸው ፣ ወይም አንድ ፀሀፊ እንዳስቀመጡት በኦሮሚያ እና በአካባቢዋ የተነሳውን ሕዝባዊ አመጽ ሌሎች ክልሎች ያልተቀላቀለበት ምክንያት በኦሮሞ ሕዝባዊ አመጽ ውስጥ የማያምኑት ንጥረ ብሔርተኝነት አለ ወይም ይኖራል ብለው በመፍራታቸው ነው። ስለዚህ ትግሉ Oromo Protest የሚለው Ethiopian Protest በሚለዉ መቀየር ይኖርበታል ይላሉ። ሌላው ደሞ በተለይ ስለ ርዕሰ መዲናዋ ፊንፊኔ ወይም አዲስ አበባ ሲነሳ አምስት ለአንድን መደራጀት እንደትልቅ ምክንያት ይጠቀሳል ነገር ግን ሁለቱም ምክንያት ውሃ የማይቁዋጥሩ ናቸው።

 

አምስት ለአንድ ከሚለው ከሁለተኛው ምክንያት ልነሳ። አምስት ለአንድ የሚባለው የስለላ መረባቸውን ፋሺስት TPLF በመላው ኢትዮዽያ ሲጠቀሙበት ቆይተዋል። ነገር ግን እንኩዋን የተማረው ያልተማረው ጀግናው የኦሮሞ ገበሬ አፈራርሶ ከጥቅም ውጪ አድርጎታል። ጉዳዩ ምንም የተለየ ሚስጥር የለወም ይህ ከታች ያለውን ምስል እንመልከት። ይች የምታዩዋት ፈረስ በመጀመሪያ ሰሞን ጠንካራና የማይነቃነቅ ግንድ ላይ ነበር ስትታሰር የቆየችው አሁን ግን አንድ ፕላስቲክ ወንበር ላይ ታስራ ሳትንቅሳቅስ እንደ ድሮው ጠንካራና የማይነቃነቀው ግንድ ላይ የታሰረች መስሏት ቆማለች። ይህ የሚያመለክተው የዚህች ፈረስ የታሰረው አእምሮዋ እንጂ አካሏ አይደለም። ስለዚህም የአዲስ አበባ ህዝብ ያልተነሳው የአምስት ለአንዱ አደረጃጀት ጥንካሬ ሳይሆን በውስጡ ባለው አላስፈላጊ የሆነ ጥርጣሬ እና ፍራቻ ነዉ። አምስት ለአንዱን እናፍርስ ከተባለ የሚያስፈልገው ቆራጥነትና ዋጋ መክፈል ብቻ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ ወያኔዎች ልጆቹን በገደሉበት ወቅት ቀብሮ ዝም ብሎ ወደቤቱ አልተመለሰም ይልቁንም ሞት አያቆመንም በማለት የቀብሩን ስነስረዓት እየቀየረ የተቁዋሞ መድረክ እያደረገው አመጹን ቀጥልዋል። ለውጥ ለማምጣት መስዋት መሆን የግድ ነው ብሎም ያምንል።

 

አሁን ደግሞ ትግሉ ብሔርተኝነት በውስጡ አለ በሚል ሌሎች ብሔሮች በጥርጣሬ ያዩታል ስለዚህ ትግሉ Oromo Protest የሚለው Ethiopian Protest ወደሚለው መቀየር ይኖርበታል ወደሚለው ልመለስ። በመጀመሪያ ደረጃ የ25 አመቱ ግፍና መከራ አንገሽግሾት አመጹን ያለምንም ማመንታት ውድ ልጆቹን መሰዋእት በማድረግ ከሁለት ወራቶች በላይ እያካሄደ ያለው የኦሮሞ ሕዝብ ነው። ስለዚህ Oromo Protest የሚለው የአመፁ መጠሪያ ብዙም የሚያከራክር አይደለም። ሲቅጥል 45 ምሊዮን ከሚሆን ህዝብ አንድ አይነት አመለካከት ብቻ መጠበቅ የለየለት ሞኝነት ይመስለኛል። ስለዚህ የኦሮሞ ሕዝብ እየሞተ ትግሉን በቀጠለበት ወቅት ሌላው ህዝብ የችግሩ ተጠቂ ሆኖ ዝምታን ሲመርጥ ብሄርተኝነት በተቁዋሞ ውስጥ መንፀባረቁ የሚገርም አይሆንም።

 

ትግሉን ከOromo Protest ወደ Ethiopian Protest መቀየር ከተፈለገ የቀረዉ ሕዝብ እንደ ኦሮሞ ሕዝብ መነሳት በቂ ይናሆል። እዚህ ጋር ሌላው ሕዝብ ለመነሳት የኦሮሞ ሕዝብ ትግል አጋር መሆን ወይም መቀላቀል ሳይሆን የሚያስፈልገው የራሳቸውን ችግር ማንሳት ብቻ በራሱ ከበቂ በላይ ነው። የትኛውም ክልል ወይም ብሔረሰብ በወያኔ መራሹ የወንበዴ ጥርቅሞች ላይ ለመነሳት እልፍ አእላፍ የሆኑ ከበቂ በላይ ምክያቶች አሉት። እስቲ ለአብነት ያህል ልክ እንደ ኦሮሚያው ለህዝባዊ እምቢተኝነት የሚያበቁ ምክንያቶችን በስፋት ሕዝባዊ ተቃውሞ ይነሳባቸዋል ተብሎ የሚጠበቁ የተወሰኑ ክልሎች ወስደን እንመልከት። በመጀመሪያ አማራ ክልል ቀጥሎ ደሞ ርዕሠ መዲናዋን ከዚያ ጋምቤላ ወስደን እንመለከታለን።አሁንም ወያኔዎች የሚያደርሱት ልክ የሌለው የ25 አመቱ ግፍና በደል እንዳለ ሆኖ ልክ ከኦሮሚያ ክልል ተነጥቆ ለአዲስ አበባ ሊሰጥ እንደነበረው ወልቃይት በሀይል ወደ ትግራይ አልተካለለም፧ ዋልድባ ገዳም በግፍ ለኢንቨስተሮች አልተሸጠም፧ ከሁሉ የሚብሰው ደሞ ከጎንደር ሰፊ መሬት ተነጥቆ ለባዕድ ሀገር ሱዳን ለመስጠት ወያኔ የካርታ የማንሳት ስራዋን እያጠናቀቀች አይደለምን፧ ካሉት አያሌ ምክንያቶች ለህዝባዊ እንቢተኝነት እነኝህ ከላይ የተጠቀሱት ከበቂ በላይ ናቸው።

 

አዲስ አበባ ከምርጫ 97 ጋር በተያያዘ በአንድ ቀን ከ 200 የሚበልጡ ዜጎችዋን አጥታ ደም ዕንባ አላነባችም፧ ነጋዴ በግፍ ከገበያ ሲስተም እንዲወጣ አልተደረገም፧ በአረብ ሀገር ግፍና በደል ለደረሰባቸው ወገኖች ሰልፍ የወጡ ዜጎች በአጋዚ ወታደሮች አልተቀጠቀጡም፧ በሊብያ በአሸባሪዎች ለተቀሉት ወገኖች መንግስት እራሱ በጠራው ሰልፍ ላይ የተገኙ ዜጎች በአደባባይ የዱላ ውርጅብኝ አልወረደባቸውም፧ የጋምቤላ ህዝብ ከመሬቱ በኢንቨስትመንት ስም አልተፈናቀለምን፧ የጋምቤላ ክልል ከ400 በላይ ዜጎቹን አጥቶ የፍርድ ያለህ አያለ እየጮኸ አይደለምን፧ ኡጋዴን ሲዳማ እያልን ብንቀጥል ለሕዝባዊ አመፅ የሚያበቁ በርካታ ምክንያቶች አሉ።

 

ታዲያ ይሄ ሁሉ መከራና ስቃይ እየደረሰበት ሌላው ብሔረሰብ ያለመነሳቱ ሚስጥር ምን ይሆን፧፧፧ ልክ ፀሀፊው እንዳስቀመጡት በኦሮሚያ እና በአካባቢዋ የተነሳውን ሕዝባዊ አመጽ የሌላ ብሄረሰብ ሰዎች ( በይበልጥም አማራው ) ያልተቀላቀለበት ምክንያት በዚህ በኦሮሞ ሕዝባዊ አመጽ ውስጥ የማያምኑት ንጥረ ብሔርተኝነት አለ ወይም ይኖራል ብለው በመፍራታቸው ከሆነ ገና ለገና የኦሮሞ ብሔርተኝነትን በመፍራት አማራው ለመብቱ መከበር ላይነሳ ነው፧ ወልቃይትንም አሳልፎ ሊሰጥ ነው፧ ሁሉም ይቅር የጎንደር መሬት ተቆርሶ ለሱዳን ሲሰጥ ዝም ብሎ ሊመለከት ነው፧ እምቢተኝነቱ በጥርጣሬ ታየ አልታየ የኦሮሞ ሕዝብ ከመቼውም በላይ ጥንካሬውን እያሳየ ተቃዉሞውን ሳያቁዋርጥ ወደፊት እየገፋ ነው። ዋናው ነገር እዚጋ የኦሮሞ ህዝብ እምቢተኝነት ፣ ብሔርተኝነት ይኑረው አይኑረው የሚወሰነው በሕዝቡ ነው። ስለዚህ የኦሮሞ ሕዝብ እንቢተኝነት በውስጡ ብሔርተኝነት አለበት ከማለት ይልቅ ሱዳን ድንበራን አካላ ሕጋዊ ከማድረጉዋ በፊት ወያኔ የማካለሉን ስራ ተግባራዊ እንዳታደርግ የአማራው ሕዝብ ሌላውን በማስተባበር ሕዝባዊ እምቢተኝነቱን ከዳር እስከዳር አንቀሳቅሶ ልክ እንደ ማስተር ፕላኑ ተግባራዊ እንዳይሆን ማስቆም አለበት።

 

አድ አዳማ(Norway)

The post የኦሮሞን ሕዝብ ትግል ከመጠራጠር  ይልቅ ለሱዳን የሚሰጠውን መሬት ለማስቆም ሌላው ሕዝብ አሁን ይነሳ appeared first on Zehabesha Amharic.

ወልቃይት ጠገዴ ማነው?

$
0
0

welkayet - satenaw

መግቢያ

ወልቃይት ጠገዴ ማነው? የሚለው “ሊበሏት ያሰቧትን ….” አይነት ጥያቄ በተደጋጋሚ የሚነሳው ከማን በኩል እንደሆነ ማወቅ “ሊበላን” ያሰፈሰፈውን አስቀድሞ ለማወቅ ይረዳል የሚል እምነት አለን። ከዚህም በመነሳት ባደረግነው ጥናትና ክትትል ጥያቄው ተደጋግሞ የሚነሳው በትግራይ ነጻ አውጭ ቡድን በኩል ሲሆን ይህ ወራሪና ተስፋፊ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ የወልቃይትን መሬት በረገጠ ወቅት በአቶ ስብሃት ነጋ አዛዥነትና በአቶ መኮንን ዘለለው አጥኝነት ጥያቄው ለወገናችን ቀርቦ ነበር። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ለዚህ እኩይ ቡድን በተንበረከኩና ባደሩ፤ ይልቁንም የዚህን ወንጀለኛ ቡድን በህዝባችን ላይ የፈጸመውን የዘር የማጽዳት ወንጀልና በሃይል ወደ ትግራይ የከለላቸውን የጎንደር ታሪካዊ ለም መሬቶች ህጋዊ ሽፋን ለመስጠት በሚዋትቱ ጥቂት ተንበርካኪዎች በኩል ጥያቄው ዳግም ሲነሳ እየሰማን ነው። 

በተለይም በቅርቡ አቶ ሃይሉ የሺወንድም የተባሉ የአካባቢው ተወላጅ በጃንዋሪ 6, 2016 “የወልቃይት ባህልና የማንነት ጥያቄ” በሚል በኢትዮሚዲያ ድረ-ገጽ ላይ ባሰራጩት ባለ 8 ገፅ ፅሁፍ ላይ ለአለፉት 37 ዓመታት ህወሃትን በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ማህበረሰብ ላይ ያደረሰውን የዘር ማፅዳትና በትግሪያዊነት የመተካት ወንጀል ለመግታት በታገሉና ለኢትዮጵያና ለመላው የዓለም  ህዝብ ባጋለጡ በስደት በሚገኙ የአካባቢው ተወላጆችና በሃገር ውስጥ ሆነው “የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት”ን ለማስከበር ለሚታገሉ ወገኖች ይህን የማንነት ጥያቄ ደጋግመው ሲጠይቁና እርስ በእርሳቸው የሚቃረኑ ሃሳቦችን በማንሳት አንባቢውን ግራ ለማጋባት ላይና ታች ሲዋትቱ ተመልክተናል።

ስለሆንም ይህን በጥቂት እውነትነት ያላቸው በሚመስሉና በፍፁም ክህደትና በህወሃታዊ ሴራ የተሞላ ፅሁፍ በአግባቡ መልስ መስጠትና እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ህወሃትና ተላላኪዎቹ በታጋዩና ጀግናው ህዝባችን መካከል ሊዘራ ያሰበውን መርዛማ እንክርዳድ ነቅሶ በማውጣት ማጋለጥና ለወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ትክክለኛውን ታሪካዊ መረጃ ከምንጩ ማቅረብ አስፈላጊነቱ ስለታመነበት ይህ ታሪካዊ ሰነድ እንደተለመደው በስደት በሚገኙ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች አማካኝነት ተዘጋጅቶ ቀርቧል።  

በቅድሚያ ግን ለጠቅላላ ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ እነዚህ ለህወሃት ፍርፋሪ የተንበረከኩና የወልቃይት ጠገዴን ማህበረሰብ ህወሃትን ለመሰለ “የቀን ጅብ” አሳልፈው የሰጡ ግለሰቦች እነማን እንደሆኑ ለአንባቢ በመጠኑም ቢሆን ግልፅ ማድረጉ አይከፋምና እነሆ ። ይህ ባንዳነት የባህሪው የሆነው የሆድ-አደሮቹ ቡድን የሚመራው በወ/ሮ አዜብ መስፍን ሲሆን፣ በእርሷ ገንዘብና ስልጣን ሙሉ ድጋፍና እንክብካቤ የሚደረግለት የአንድ ቤተሰብ ስብስብ ነው። አቶ ኃይሉ የሺወንድም ደግሞ ለረጅም ዘመናት በአውሮፓ ኖርዌይ አገር ነዋሪ የነበሩና ካለፉት ሁለት አመታት ወዲህ ግን ነዋሪነታቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉ ሲሆን በቅርቡ ሁለት ሰፋፊ የእርሻ መሬቶች በጋንቤላ ውስጥ እንደተሰጣቸውና አዲስ ባለሃብት ለመሆን እየተሯሯጡ የሚገኙ ናቸው።እኒህ ግለሰብ የወ/ሮ አዜብ መስፍን ወንድም (የወ/ሮ አዜብ ምስፍን እናትና የአቶ ኃይሉ እናት እህታማቾች) ሲሆኑ እንዲሁም የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር ባለስልጣን የሆነው የአቶ ፈረደ የሺወንድምና  በካርቱም ሱዳን ውስጥ ስደተኞችን በመጠቆምና በማሳሰር በሰፊው የሚታማው የአቶ ተስፉ የሺወንድም ወንድም እንደሆኑ ይታወቃል። 

አቶ ኃይሉ አገር ቤት ከመግባታቸው በፊት የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር እንደ ወራሪ ኃይል ይመለከቱ እንደነበርና ወልቃይት ወደ ነበረበት ግዛት ወደ ጎንደር ያለ ድርድር መመለስ እንዳለበትም እንደአቋም  በመውሰድ ያስተጋቡ እንደነበር ይታወቃል። ሌላኛው ግብረ-በላ ደግሞ አቶ ፀጋዬ አስማማው የሚባል ሲሆን የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ በመሆን የሚያገለግልና የህወሃት ቀንደኛ አሽከርና ተላላኪ በመሆን ከአቶ ፈረደ ጋር ሰሜን አሜሪካ ድረስ በመምጣት የወልቃይት ተወላጆችን ሰብስበው የ“እራስ ገዝ” አስተዳደር እንዲጠይቁ ሲያግባባ የነበረና አሁንም በተሰጠው የዳኝነት ሙያ ሽፋን ታጋዩን ህዝባችንን በማስፈራራት ግንባር ቀደሙን ሚና የሚጫወት እርሱ ነው።  በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይና በተለይም “የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት” አስከባሪ ኮሚቴ ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም እንግልት፣ እስር፣ ስቃይና፣ አደጋ ግንባር ቀደም ጠያቂዎቹ እነዚህ አራት ሆድ-አደሮች መሆናቸውን ለማሳሰብ እንወዳለን። 

 

መልካም ንባብ

ከአዘጋጆቹ

ወልቃይት ጠገዴ ማነው?

“የወልቃይት ባህልና የማንነት ጥያቄ” የሚለው ፅሁፋ በገጽ 4, 2ኛው አንቀጽ ላይ “ስለዚህ የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር ወልቃይትን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያለውን ታሪክ በዜሮ ብናባዛው፤ የህዝበ-ውሳኔው ውጤት ከትግራይ ጋር መኖር የሚሹ ወልቃይቴዎች በሰፊ ልዩነት ሊያቸንፉ መቻላቸውን ያበስር ነበር” ይላል። ነገር ግን ይህ የአቶ ሃይሉ የሺወንድም ምኞትና ድምዳሜ ወይም ህወሃታዊ ተልዕኮ ከታሪክና ከተጨባጩ የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ አቋምና ምርጫ ፍጹም እንደሚቃረንና እንደሚጋጭ በሁለት ቀደምት የህወሃት አባላት የቀረቡ ምስክርነቶች አጥጋቢ መልስ ስለሚሰጡ እነርሱን እንመልከት።

ኢትዮጵያውያን እንደ ዛሬው ህወሃት በለጠፈብን የብሔር ታርጋ ምክንያት የጎሪጥ መተያየት ሳንጀምርና ሃገራችን ጎጥ ጎጥ ከመሽተቷ 37 ዓመታት በፊት በትግራይ ነጻ አውጭ ቡድን በኩል ለወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ የቀረበው “ወልቃይት ጠገዴ ማነው?” ጥያቄ በወቅቱ የነበሩት ኩሩና በማንነታቸው ላይ ፍጹም ብዥታ ያልነበራቸው ወገኖቻችን የህወሃት ወኪል ለነበረውና ጥያቄውን ይዞ ለመጣው ለአቶ መኮንን ዘለለው በማያዳግም ሁኔታ መልሰውለት እንደነበር ታሪክ ህያው ምስክር ነው። በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ የህወሃት ነባር አባልና የፋይናንስ ኋላፊ የነበሩት አቶ ገብረመድህን አርአያ በዲሴምበር 22, 2015 ኢትዮ-ሚዲያና ጎልጉል ድረ-ገፅ ላይ “በወልቃይት ጠገዴ፤ ጠለምት በአማራው ላይ ህወሃት የፈጸመው የዘር ማጽዳት ወንጀል” በሚል ባወጡት ጥልቅ ሰነድ በገጽ 2 ላይ፤

“በሪጅን 1 የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረው፣ በአባቱ ወልቃይት ፀገዴ፣ በእናቱ ሽሬ የሆነው መኮንን ዘለለው፣ የተወጠነውን ትልእኮ ይዞ ወልቃይት ፀገዴ ፀለምት እየተዘዋወረ ህዝቡን በመሰብሰብ ይህ መሬት የትግራይ መሬት ስለሆነ እናንተ ከእንግዲህ ወዲህ የሰሜን ጎንደር ዜጎች አይደላችሁም፣ የትግራይ መሬት ስለሆነ እንኖራለን ካላችሁ ትግሬዎች መሆናችሁን አምናችሁ ተቀበሉ፤ የትግራይ ዜጎች አይደለንም፣ ሰሜን በጌምድር የትግራይ አይደለም ካላችሁ ደግሞ የድርጅቱን የህወሓትን ውሳኔ ተጠባባቁ፤ የምታምኑበትን አሁን ተናገሩ በማለት ሲያስጠነቅቅ፣ ከህዝቡ በኩል ያገኘው መልስ ግን አንድ ነበር። የቀረበውን ሃሳብ ከህፃን እስከ አዋቂ፣ የወልቃይት ፀገዴና የፀለምት ህዝብ፣ እኛ የሰሜን በጌምድር (ጎንደር) አማሮች እንጂ ትግሬዎች አይደለንም፣ የታሪካችን ስር መሰረቱ የበጌምድር አማሮች ነን። ይህ ቆመህ የምትናገርበት መሬት ሰሜን በጌምድር ይባላል። ከጥንቱ ታሪካችን 3 ብትነሳም ይህ መሬት ታሪካዊ ነው። ያለፉት የኢትዮጵያ ነገሥታት ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰአት በመንግሥት እውቅና ያገኘ የጎንደር፣«”የበጌምድር” ጠቅላይ ግዛት እየተባለ የሚጠራ ነው። ዋና ከተማችን ደግሞ ጎንደር ነው። የእናንተም ትግራይ ጠቅላይ ግዛት ይባላል፣ ዋና ከተማው ደግሞ መቀሌ ነው። ስለዚህ ኣናንተ የተሓህት ታግዮች ጉዳዩን ብታሱብበት ጥሩ ነው። ወደ እርስ በርስ ግጭ ያመራል።በተጨማሪም ታሪካዊ የወሰን ክልል አለን፣ እሱም ተከዜ ወንዝ ነው። የትግራይና በጌምድር የድንበር ክልሉ ተከዜ ወንዝ ነው። ከጥንት ጀምሮ የሁለቱ ኢትዮጵያውያን የድንበር ወሰን መሆኑን ልናረጋግጥ እንፈልጋለን በማለት በአንድነት ድምፅ ህዝቡ ራሱ አረጋገጠ።” በማለት ገልፀውታል።

ይልቁንም በአቶ መኮንን ዘለለው በኩል ለቀረበላቸው የማንነት ጥያቄ “የበጌምድር አማሮች ነን” የሚለውን የማያወላዳ ምላሽ የሰጡ የማህበረሰቡ ታላላቅና የተከበሩ መሪዎች በአቶ ስዩም መስፍንና በአቶ ግደይ ዘራፅዮን መሪነት ታፍነው ወደ ትግራይ መወሰዳቸውንና በሳሞራ የኑስ ትእዛዝ እንደተረሸኑ እራሳቸው አቶ መኮንን ዘለለው ለኢሳት ቴሌቭዥን በሰጡት ቃለ-መጠይቅ ላይ በዝርዝር አጋልጠዋል። በዚህ “ወልቃይት ጠገዴ ማነው?” በሚለው የህወሃት ያልተቋረጠ ጥያቄ ዙሪያና ህዝባችን በሚሰጣቸው አንድ፤ ግልፅና ቀጥተኛ መልስ ምክንያት ወገናችን የጅምላ ግርፋቶች፤ መፈናቀሎች፤ እስራቶች፤ ግድያዎች፣ ስደቶች፣ ቅስም ሰባሪና፣ ፀያፍ በደሎች ተፈፅመውበታል።

ታዲያ ይህ ሁሉ ሰቆቃ አሁንም ሳያባራ የትግራዩ ነጻ አውጭ ቡድን እነሆ ዛሬም እንደገና በእነ አቶ ሃይሉ የሺወንድም በኩል “ወልቃይት ጠገዴ ማነው?” ይለናል። አስቀድሞ በአቶ መኮንን ዘለለው በኩል ቀርቦ ህዝባችንን ለእልቂት የዳረገው ህወሃታዊ ጥያቄ ዳግም ለወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ መጠየቅ ማለት አንድም ወገኖቻችን በማንነታቸው ጸንተው በመቆማቸው ምክንያት የከፈሉትን መስዋእትነት እንደ “ውሻ ደም” በመቁጠር ለመሳለቅ ወይም በህዝባችን ላይ ለተደገሰው ቀጣይ ህወሃታዊ ፍጅት ሰበብ ለማዛጋጀትና የጥፋት መንገድ ለመጥረግ የታለመ ይመስላል።

የህወሃት ሆድ-አደሮች ምን እያሉን ነው?

ወልቃይት ጠገዴ ማነው? ለሚለው የህወሃት መላዘን ወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ምላሹ ከላይ በአይን እማኞችና በህያው ምስክሮች እንደተረጋገጠ አይተናል። ታዲያ ለምን የዛሬዎቹ ተላላኪዎች “ስለዚህ የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር ወልቃይትን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያለውን ታሪክ በዜሮ ብናባዛው፤ የህዝበ-ውሳኔው ውጤት ከትግራይ ጋር መኖር የሚሹ ወልቃይቴዎች በሰፊ ልዩነት ሊያቸንፉ መቻላቸውን ያበስር ነበር” እያሉ ሌላውን ህዝብ ለማደናገር ይሞክራሉ? ለምንስ በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ በደል ላይ ይዘባበታሉ? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም።

ከዚህ የሆድ አደሮች ዘመቻ የምንረዳው ነገር ቢኖር ተላላኪዎቹ ቀደም ሲል በተደጋጋሚ እንገልጸው እንደነበረው ሁሉ ከህወሃት የተሰጣቸውን “የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብን በማዳከምና በመከፋፈል ትግሪያዊነትን አሜን ብሎ እንዲቀበል” የማስቻል ተልእኮ ለማሳካት በሚል በመላው ኢትዮጵያ በተለይም እንደ ጋምቤላ ባሉ አካባቢዎች በሚደረጉ የመሬት ዘረፋዎችና ቅርምቶች (ወልቃይት ጠገዴ ለትግራውያን ብቻ ነው) ቢንበሻበሹም ውጤቱ ግን “ጉም መዝገን” ሆኖባቸዋል። ይልቁንም በሃገር ውስጥ የሚገኘው የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ከምንግዜውም በላይ ተደራጅቶና ከመላው የአማራ ህዝብ ጋር አንድ ሆኖ ማንነቱ ለማስከበር ቆርጦና አምርሮ ሲነሳ ከህወሃት ይልቅ የተጨነቁት በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ስም ድርጎ ሲቀበሉ የከረሙት ናቸው።

ከህወሃት በኩል ልምጭ የተቆረጠበት የሚመስለው ሆድ-አደሩ ቡድን መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ያንገሸገሸውንና ህወሃትን እስከ አንገቱ ያነቀውን፤ ይልቁንም በህወሃት/ኢህአዴግ መንደር እውቅና አግኝቶ ከጠ/ሚ እስከ ተራ ካድሬ እየተቀባበለ የሚዘምርለትን “የመልካም አስተዳደር እጦት” በምትባል “የጦስ ዶሮ” በመታከክ የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ያነሳውን ዘርንና ትውልድን ከጥፋት የመታደግና የአማራ ማንነቱን በትግሪያዊነት ከመተካት የማዳን ፈርጀ ብዙ ጥያቄ “የትግራይ ክልል ባለስልጣናት የአስተዳደር በደል ስለፈጸሙበት” ነው እያሉ ማፌዝ በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ቁስል በእሳት የጋለ ብረት እንደመስደድ ይቆጠራል።ያስተዛዝባልም።

ይልቅስ አቶ ሃይሉና የጥቅም ተጋሪዎቻቸው በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይ የደረሰው በደል የዘር ማፅዳትና በትግሪያዊነት የመተካት ዓለም-አቀፍ ወንጀል መሆኑን የምትስቱት አይመስለንም። ይህን በማንነታችን ላይ የተፈጸመና በዓለም-አቀፍ የፍርድ አደባባይ የሚያስጠይቅን ወንጀል በማኮሰስና “የትግራይ ክልል ባለስልጣናት የአስተዳደር በደል” አድርጎ በማቅረብ ከህወሃት ጋር የገጠማችሁን ኪሳራ ማወራረድ ወይም የሚቆረጥላችሁን ድርጎ ማሳደግ አትችሉም። ኪሳራችሁን ማወራረድም ሆነ ሌላም ማድረግ የምትችሉት ለጌቶቻችሁ እውነቱን በመናገር ብቻ ነው። ምክንያቱም የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ጎንደሬ-አማራ መሆኑን በአንድ ድምጽ ያረጋገጠውና በማንነቱም ምክንያት ለሚመጣ ማንኛውም ነገር ዋጋ ለመክፈል ዝግጁነቱንና ቁርጠኝነቱን በተግባር ያሳየው ገና “የትግራይ” የሚባሉ ገዥዎችና አስተዳደራቸው ከመፈጠሩ እጅግ አስቀድሞ እንደነበር ከወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ባልተናነሰ እነ ስብሃት ነጋ ጠንቅቀው ያውቃሉና እራሳችሁን አታታልሉ። ትዝብት ላይም አትውደቁ።

በሌላ በኩል ምንም እንኳ ዛሬ ህወሃት እስከ አፍንጫው ቢታጠቅና የሃገሪቱን መንግስታዊ ስልጣንና ሃብት እንዳሻው ቢያዝና ቢናዘዝበትም የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ዛሬም በማንነቱ ላይ ያለውን የቀደመ ጽኑ እምነትና የትውልዱን ምስክርነት ማስለወጥ አልተቻለውም። እንግዲህ ለህወሃትና ለእነ አቶ ሃይሉ የሺወንድም እውነታው እንደ እሬት መራራ ቢሆንባቸውም ታሪክ በደማቁ የመዘገበውና በእያንዳንዱ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ ህሊና ተጽፎ የሚገኘውና ለትውልድ የምናስተላልፈው እውነታ ግን የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ህወሃት ዕርስታችንን ከመርገጡ በፊትም ሆነ በወረራ በተቆጣጠረ ጊዜ በጎንደሬ-አማራነቱ ጸንቶ በመቆም መራር መስዋእትነት እንደከፈለ ሁሉ ወደፊትም በማንኛውም የከፋ ፈተና ውስጥ ቢያልፍም ከጎንደሬ-አማራነቱ ሊያናውጸው የሚችል ምንም አይነት ምድራዊ ሃይል ያለመኖሩን ነው። ምክንያቱም ወልቃይት ጠገዴ አይደለም ለማንነቱና ለዕርስቱ፤ አምነው ለተጠጉትም አንገት እንደማያስደፋ ትግራውያን ያውቃሉ!

ታዲያ ወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ማነው?

“በአፍ የመጣን በአፍ፣ በመጣፍ የመጣን በመጣፍ” መመለስ የቀደሙ አባቶቻችን ስርዓትና ብሂል በመሆኑና ታሪካዊ ጠላቶቻችንም እንደ አመጣጣቸው መመለስ ተገቢ በመሆኑ ህወሃት በተላላኪዎቹ በኩል በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ መካከል ሊዘራ የሞከረውን እንክርዳድና በኢትዮጵያ ህዝብና በታሪካችን ላይ ሊፈጠር የታሰብውን ብዥታ ለማጥራት ሲባልና ለታሪክም ምስክር ይሆን ዘንድ “የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ማነው?” የሚለውን ጥያቄ በአጭሩ እንደሚከተለው ስንመልስ ጥልቁንና ተነግሮ የማይጠገበውን የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ታሪክ ለታሪክ ፀሃፊዎችና ለባለሙያዎች በመተው ነው።

  1. የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ እንደ ማንኛውም የሰሜኑ ኢትዮጵያ ማህበረሰብ ሁሉ የአካባቢውን ስያሜ በመውሰድ የእራሱ መጠሪያ አድርጎ ኖሯል። ለምሳሌ የጎንደሬ ዘሩ ምንድነው? የሚኖርበት አካባቢ ስያሜ ማን ይባላል? የጎጃሜውስ? የወሎዬው? የጋይንቴው? የምንጃሬው? የስሜንኛው? … ወዘተ ለመሆኑ እነዚህ ወገኖቻችን እራሳቸውን ሲጥሩ “እኛ ማነን” ይላሉ? እኛስ እነርሱን እነማን ናቸው እንላለን?  ጎንደሬውን – ጎንደሬ ፤ ጎጃሜውን – ጎጃሜ ፤ ወሎዬውን – ወሎዬ፣ ደብረታቦሬውን – ደብረታቦሬ፤ ጋይንቴውን – ጋይንቴ፤ ስሜንኛውን – ስሜንኛ፤ በለሴውን – በለሴ፣ ወግሬውን – ወገሬ፣ ቋረኛውን – ቋሬ …. ወዘተ እያልን ወልቃይቴውን – ወልቃይቴ፣ ጠገድቼውን – ጠገድቼ፣ ጠለምቴውን – ጠለምቴ አላልንምን? እንላለን እንጂ!
  1. ታዲያ የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ አባቱ ማነው? የዘር ሐረጉስ ከየት ይመዘዛል ቢሉ?

ወልቃይት የሚለው ስም ከስር መሰረቱ የአማራ መስራች አባት የሚባለው የተጠቀሰበት አገር ነው። አማራው ከወልቃይት ወደ ጠለምት ከዚያም ወደ ላኮ መልዛ (የዛሬው ወሎ) እያለ ሌላውን አካባቢ እያስፋፋ እስከ ሞቃዲሾ ተጉዞ ሃገር ያቀና ታላቅ ነገድ ያረፈበት መሆኑ ታሪክ ሁሌም ይመሰክራል። ወልቃይት ጠገዴ አማራ የሆነው ዛሬ ትግሬ ሊያደርጉት እንደሚታትሩት በተዘዋዋሪ ሳይሆን የአማራ አባትና ግንድ በመሆን ነው። ለዚህ ፅሁፍ በሚስማማ መልኩ ታሪካዊ ማስረጃዎችን እንመልከት።

አለቃ ታዬ ወልደማርያም የተባሉ ሊቅና የተመሰከረላቸው ታሪክ ፀሃፊ “የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ” በተባለው ዝነኛ መፅሃፋቸው በገፅ 16 ላይ እንዲህ ፅፈዋል። “ከለው ከሳባ ወደ ምዕራብ ወደ ደቡብ ያለ ያማራ የወልቃይት የጠገዴ አባት ነው። ከእነዚህም የኢትዮጵስ ልጆች የወንድማማቾቹ ነገድ ህዝብ ሁሉ በመልካቸውና በቁርበታቸው ይመሳሰላሉ። እኒህም ህዝብ የያዙት አገር በጥቅሉ ባባታቸው ስም ኢትዮጵያ ተብሎ ይጠራል።” በመቀጠልም የአማራው አባት አስገዴ ግንዱ ከወልቃይት ጠገዴ አርማጭሆ ከዚያም እያደገና እየሰፋ አማራ ሳይንት ድረስ የደረስ መሆኑን ገልጸው ጽፈዋል።

አቶ አማረ አፈለ “ደም አይፍሰስ በቃ የህወሃት ማኒፌስቶ ያብቃ!” በሚለው መፅሐፋቸው በገጽ 27 ታሪካዊ ምስክርነታቸውን እንደሚከተለው አስፍረዋል።

“ከተከዜ ጀምሮ ወደ ደቡብ እስከ ሸላሎ በተዘረጋው ምድር ላይ ያሉት ወረዳዎች ሕዝቡ አፍ መፍቻ ቋንቋው አማርኛ ነው። ከትግራይ ጋር በተከዜ ወንዝ ድልድይነት ጎረቤት ስለሆነ ወዲያና ወዲህ ማዶ ያለው የዐማራና የትግራይ ቋንቋ ቃላት ቢያንስ 80 በመቶ ተመሳሳይ በመሆናቸው መናገሩ አዳጋች አይሆንባቸውም። ይልቁንም የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት መዘጋዎች ጥጥ ስለሚያመርት ብዙ የትግራይ ተወላጆች በጥጥ ለቀማ ወቅት በየዓመቱ ወደነዚህ መዘጋዎች ይመጣሉ። ዐማሮች ከእነርሱ ጋር ለመግባባት ሲሉ ትግርኛውን ይጠቀሙበታል። ከእንግዶች መካከል ሀገሬውን አግብተው የሚቀሩም አይጠፉም። ለዚህም ወደ ኋላ መለስ ብለን ታሪክ ስንመረምር ወልቃይት ጠገዴና ጠለምት በአክሱም፤ በላስታው በሽዋ ሆነ በጎንደር ዘመነ መንግሥት አንድም ግዜ የትግራይ ግዛት አካል ወይም ገባር የሆነበት የታሪክ ወቅት የለም። ይህን እውነት ለመረዳት ከጎንደር ዘመነ መንግሥት በፊት ጀምሮ 20ኛ ምዕተ ዓመት ሁለተኛ አጋማሽ ድረስ የታወቁ የውጭ ሀገር ጉብኝዎችና ታሪክ ፀሐፊዎች በተለያዩ ክፍለ ዘመናት ኢትዮጵያን እየተዘዋወሩ ካዩ በኋላ ስለ ብሔረስቦችና ስለ አስተዳደር ክፍሎች የተውልን ጹሑፎችና ካርታዎች ህያው የታሪክ ማስረጃዎች ናቸው።”

“ለአብነት ያህል ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ፤ ጅምስ ብሩስ፤ ዶክተር ሚካኤል ረሥል፤ ማንስፊልድ ፓርኪንስ፤ ስቨንረንሰን ወዘተ…….የተባሉ ታዋቂ ተመራማሪዎች ለትውልድ ያበረከቷቸውን መጻሕፍት መመልከት ይቻላል። ይልቁስ የኢጣሊያን መንግሥት ኢትዮጵያን በ1928 ዓ/ም ከመውረሩ በፊት በጐንደር ከተማና በሌሎች ከተሞች በከፈታቸው የቆንስል ቢሮዎች አማካይነት ባካሄደው ሰፊ የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ጥናት ባወጣው አስተዳደር መዋቅር ትግራይ ከኤርትራ ጋር ሲደርብ ጠገዴንና ጠለምትን የአማራ ክልል በማድረግ ትግሬ አለመሆናቸውን አረጋግጧል።”

ወልቃይት ጠገዴ ፡ ትግሬ 

የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ለመላው ኢትዮጵያዊ ይልቁንም ለድንበርተኛ የትግራይ ህዝብ ያበረከታቸው ታሪካዊና ዘመን ተሻጋሪ ውለታዎች በትግራይ ህዝብ ሁሌም እንደሚታወሱና ከትውልድ ትውልድም እንደሚዘክራቸው በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡ ለምን ቢሉ እነዛ የትግራይ ህዝብን ህልውና የተፈታተኑ ክፉ የረሃብና ዘመናትና በእነዛ የጭንቅና የስደት ዘመናት የታደገን ጎረቤት መርሳት የማይታሰብ ነውና፡፡

ይሁንና ወራሪውና ተስፋፊው የትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይ እያደረሰ የሚገኘውን የዘር ማፅዳት ወንጀል የበቀል ሽፋን ለመሰጠትና የትግራይም ህዝብ የዚህ እኩይ ሴራ አካል በማስመሰል እጅግ የተዛቡና አኩሪ ታሪካችንን የሚያጎድፉ  አሉባልታዎችና የፈጠራ ታሪኮች በህወሃት መንደር ከመወራት አልፈው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ለህወሃት በተንበረከኩና ባደሩ የአንድ ቤተሰብ አባላት ፊታውራሪነት ወደ ህዝብ በነጻ ሚዲያዎች አማካኝነት በፅሁፍ ሲሰራጩ ለመመልከት ችለናል፡፡

አበው “ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል” እንዲሉ ይህን እኩይ ሴራ ከወዲሁ በማጋለጥ በህዝቦች መካከል ሊፈጠር የታሰበውን ውዥንብርና ህወሃታዊ ትርፍ ማኮላሸት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

ውንጀላ 1. “የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ የትግራይን ህዝብ ይንቃል (ዝቅ አድርጎ ይመለከታል)” ስለመባሉ፤

ምንም እንኳ እነ አቶ ሃይሉ የሺወንድም በፅሁፋቸው በገፅ 4 ላይ የትግራይን ህዝብ በወልቃይት ማህበረሰብ እንደተበደለና በደሉን “ህወሃቶች መች እረሱ?” እያሉ በማጠየቅ ለህወሃት የፈጠራ ውንጀላ ማረጋገጫ መሰል ሃሳብ ቢያዋጡም እኛ ግን ይህን ሃሰተኛ ክስ በሁለት ዋና ዋና አቅጣጫ በማየት ለከሳሾቻችንና ለአጫፋሪዎቻቸው ምላሽ ለመስጠት እንሻለን።

“ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ፣ ይሏታል ጅግራ”

“የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ትግሬ ነው” ለዚህም ነው ወደ ትግራይ የከለልነው እያሉ አይናቸውን በጨው አጥበው ከ25 ዓመታት በላይ የሚያደርቁን ህወሃቶች፤ በሌላ በኩል ደግሞ “የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ የትግራይን ህዝብ ይንቃል” በማለት ደጋግመው ይከሳሉ።

ለመሆኑ ከመቼ ጀምሮ ነው አንድ ህዝብ እራሱን የሚንቀው ወይም የእራሱን ዘር ዝቅ አድርጎ የሚመለከተው? እውነት የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብና የትግራይ ህዝብ አንድ ዘር ነው ተብሎ ቢታመን ኖሮ ይንቀናል ወይም ዝቅ አድርጎ ይመለከተናል ሊባል ይቻል ነበርን? እውነታው ግን፦

  1. በትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን የትግራይ ህዝብ ጠላት ተደርጎ በተቆጠረውና ሃገር አቀፍ የዘር ፍጅት የታወጀበት የአማራው ነገድ አካል በመሆኑና የዘር ማፅዳቱ ዘመቻ የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብን የሚያካትት በመሆኑ ሲሆን፤
  1. በሌላ በኩል ደግሞ ለ“ታላቋ ትግራይ” መንግስትና ለ“ትግሪያዊው ወርቅ” ህዝብ የምግብ ዋስትና የሚያረጋግጥ ለም መሬትና ከቀሪው ዓለም  ከሱዳን ጋር የሚገናኙበት የየብስ መውጫና መግቢያ  መስመር ለማግኘት በመቋመጥ የተነደፈውን የ1968ቱን የህወሃት ማኒፌስቶ ስኬት ሊያደናቅፍ ይችላል በሚል እሳቤ ለፈጸሙት የወልቃይት ጠገዴን ዘር የማፅዳትና በትግሪያዊነት የመተካት ወንጃል ምክንያታዊ ለማስመሰል የተለጠፈ የበቀል ካባ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
  1. ይልቁንም ታሪክና ትውልድ ይቅር ለማይለውና ዓለም ለተፀየፈው የወልቃይት ጠገዴን ዘር የማፅዳትና በትግሪያዊነት የመተካት ወንጀላቸው በህዝባችን የተቀናጀ መራራ ትግል ሲከሽፍና ከተጠያቂነት እንደማያመለጡ ሲረዱት፤ በደሉን ለትግራይ ህዝብ ክብር ሲሉ የፈፀሙት ለማስመሰልና፣  የትግራይ ህዝብም የዚህ እኩይ ወንጀላቸው ተባባሪ እንደሆነ የማስመሰል ሴራ አካል ስትሆን፤ በላዩም ላይ ተላላኪዎቻቸው “ህወሃቶች መች እረሱ?….” በማለት ልክ የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ የትግራይን ህዝብ ይንቅ እንደነበርና አሁን ህወሃቶች በደሉን መርሳት ሲገባቸው ነገር ግን እንዳልረሱት በማስመሰል ማረጋገጫ ይሁን ትዝብትነቱ ያለየለት ለህወሃት የፈጠራ ክስ የሃሰት ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ፡፡

ውንጀላ 2.  “የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ በ50/60ዎቹ ዓ.ም አካባቢ ወደ አካባቢው ለተለያዩ የጉልበትና የግብርና ስራዎች ይመጡ    የነበሩትን የትግራይ ተወላጆች ያገለገሉበትን ገንዘብ ባለመክፈል ይበድላሉ” ስለመባሉ፤

ዛሬ በዚህ ጉዳይ ላይ መልስ መስጠት አላስፈላጊ እንደሆነ እናምናለን፡፡ ምክንያቱም ህዝባችን በፊውዳሉ ዘመን በአሰሪና ሰራተኛ መካከል ሊከሰቱ ከሚችሉ ከእንዲህ አይነቱ ተራና ታሳቢ ከሆኑ ክሶች በላይ እጅግ አንገብጋቢና አሳሳቢ በሆኑት የህወሃትና የተላላኪዎቹ ሴራዎች ላይ በናተኩርና በወገናችን መካከል በሚያሰራጯቸው በማር የተለወሱ መርዞች ላይ በማተኮር ከዘር ማፅዳቱ ወንጃል በብዙ መስዋዕትነት ያተረፈውን ትውልዱን ከብከላ እንድንከላከልለት ቅድሚያ እንደሚሰጥ ጠንቅቀን እናውቃለንና ነው፡፡

ነገር ግን ከ1969 ዓ.ም በኃላ ላለው አዲስና ለመጭው ትውልድ የአባቶቹንና የአያቶቹን አኩሪ ታሪክ እግረ መንገዱን እንዲያውቅና ከሁመራ የእርሻ ልማት ጋር ተያይዞ ለሚነሱ መጥፎም ይሁን ጥሩ ታሪኮች እውነተኛ ስንቅ ከምንጩ ማቀበል ተገቢ ነው በሚል በዚህ ውንጀላ ዙሪያ ትንሽ ለማለት ወደድን፡፡

የወልቃይት ጠገዴ አብዛኛው ህዝብ በግብርና ሙያ የሚተዳደር የነበረ ሲሆን የወባ በሽታን፣ ጊንጥና እባብን …ወዘተ ተቋቁሞ  መዘጋ ወልቃይትንና ሁመራን የመሰሉ ገናና የእርሻ ቦታዎችን አልምቷል። ያለማውን መሬትም “መውፈር ቀደም” ስርአት በመጠቀም ለሁሉም አራሽ ክፍት በማድረግ ከመላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ በተለይም ደግሞ ከኤርትራና ከትግራይ ህዝብ ጋር ተካፍሎ ሲያርስ ኖራል። በወቅቱም በብዙ ሺ ለሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ጥጥ ለቀማና ማሽላ ቆርጣ ከመሳሰሉ ዝቅተኛ ደረጃ የስራ እድሎች እስከ ባለ መሬትነት ባሉ የልማት ዘርፎች ይሳተፍ ነበር።

በሌላ በኩል ደግሞ የወልቃይት ጠገዴ  ማህበረሰብ ትግራይ ውስጥ በተደጋጋሚ ርሀብ በተከሰተባቸው በእነዛ ክፉ ዘመናት ነብሳቸውን ለማትረፍ በስደት ለሚመጡት በብዙ ሺዎች ለሚቆጠሩ የትግራይ ወገኖች ጊዚያዊ መጠለያና ምግብ በማቅረብ እንዲያገግሙ ካደረገ በኋላም ራሳቸውን መልሰው እንዲያቋቁሙ የስራ እድል በመስጠት ሲረዳ የቆዬ የወገን አለኝታ ነበር።

እንግዲህ በዚህ ወቅት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆችና የአካባቢው ህዝብ በሚሳተፍበት የእርሻ ልማት በግለሰቦች ደረጃ ለሚፈጠሩ የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነቶች እንዴት የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ተጠያቂ ሊሆን ይችላል?

እውነታው ግን እራሱን የትግራይ ነጻ አውጭ ብሎ የሰየመው ወራሪና ተስፋፊ ቡድን ለተዘፈቀባቸው የዘር ማፅዳት፣ የዝርፊያ፣ ኢትዮጵያን የማፈራረስና፣ አካባቢውን የማተራመስ ወንጀሎች በመላው የኢትዮጵያ ህዝብና በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከሚጠብቀው ፍርድ ለማምለጥ ከለላና ዋሻ በማድረግ የሚጠቀምበትን የትግራይ ህዝብ በመያዦነት ይዞ ለመቆየት በማለምና በተለይም አጎራባች ከሆኑት የጎንደርና የኤርትራ ህዝብ ጋር በጠላትነት እንዲተያይና በስጋት ውስጥ ሆኖ ህወሃትን ብቻ እያመለከና ለህወሃት ሹማምንት እየተገዛ እንዲኖር የተጠመደበት ወጥመድ አካል እንጂ ውንጀላው የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ከትግራይ ህዝብ ጋር የነበረውን ግንኙነት በትክክል ያላገናዘበና የግንኙነቱንም ልክ አቆሽሾ የሚገልፅ የሃሰት ውንጀላ ነው።

ለትግራይ ሲቆርሱ አያሳንሱ 

ይህ ለሆዱ ያደረ ቡድን የትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን  በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይ በመፈፀም ላይ የሚገኘውን የዘር ማፅዳትና አካባቢውን በትግሪያዊነት የመተካት ወንጀል መቃወምና ማውገዝ ሲሳናችውና ይልቁንም አገር ያወቀውንና ፀሃይ የሞቀውን የህወሃት ወንጀል በትግራይ ህዝብ የተፈጸመ በማስመሰል “የወልቃይትን ህዝብ ሰብአዊ ክብር የሚያዋርዱ ጥሰቶችን በዚህ መድረክ ላይ መግለፁ በህዝቦች መካከል አላስፈላጊ ቁርሾ ስለሚፈጥር እዛው ተከድኖ ይብሰል ብለናል” በማለት ከትግራይ ህዝብ ይልቅ ለህወሃት ሹማምንት ያላቸውን ወገንተኝነትና ታዛዥነት ያረጋግጣሉ።

በሌላ በኩል ግን በትግራይ ህዝብና በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ መካከል ጠላትነት እንዳይፈጠርና ቁርሾ ለትውልድ ላለማስተላለፍ በሚል ያደረጉትን “ጥንቃቄ” እና “አስተዋይነት” በእጅጉ አድንቀናል። አንድም ትላንት የፊውዳሉ ስርዓት ፈጸመ ለሚባለው ግፍና በደል ዛሬ ተከሳሽና እዳ ከፋይ የተደረገው ጭቁኑ የአማራ ህዝብ ነውና ነገም የትግራይ ህዝብ የህወሃት ሹማምንት እዳ ከፋይ እንዳይሆን ቅድመ ጥንቃቄ መደረጉ ተገቢ ነው ።

ለወልቃይት አባት ፍለጋ፡ ከትግሪያዊነት ወደ ኤርትራዊነት መንሸራተት

የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሠብ እንደ ማንኛውም የሰው ዘር መነሻዬ የሚለው አባት፣ የእኔ የሚለውና ቆጥሮ የሚደርስበት የዘር ሃረግ፣ ይልቁንም የእኔ የሚላቸውን ታሪኮቹንና ባህሎቹን የሚመዘግብበትና የሚጠብቅበት ብሎም ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚያስተላልፍበት የእራሱ መንገድ ያለው ታላቅና አስተዋይ ህዝብ ነው። በአጭሩ ወልቃይት ጠገዴ አባቱን ያውቃል።

ነገር ግን እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ማንነቱን ላይ ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባና የከፋ አደጋ ላይ የሚጥል ተግዳሮት የገጠመው በታሪኩ ለመጀመሪያ ግዜ በትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን በኩል ወረራ ከተፈፀመበት ግዜ ጀምሮ ነው። ይህን ታሪካዊ ፈተና ለማለፍና በድል ለመወጣት ይቻል ዘንድ ወገናችን እልህ አስጨራሽ የሆነ መስዋዕትነት ከፍሏል። በመክፈልም ላይ ይገኛል።

በእነዚህ የታሪካችን የጨለማ ዘመናት በዋናነት የተጋፈጥነው ተግዳሮት ትግሬነትን እንደ ማንነታችን በመቀበል ትግሬ መሆን እና ከህወሃት ጋር ተመሳስሎ በመኖር ትግሬነትን ለትውልድ ማውረስ ወይም በአማራ ማንነታችን ፀንተን በመቆም ያለልካችን በህወሃት የተሰፋልንን ትግሬነት ባለመቀበላችን ምክንያት በጠላት በኩል ሊመጣ ያለውን ሁሉ መከራና ችግር በመጋፈጥ በማንነታችን ላይ ያነጣጠረውን ጠላት ድል መንሳት ነበሩ።

ከዚህም በመነሳት እነሆ ወገናችን ለአለፉት 37 ዓመታት በህወሃት የጭካኔና የመከራ ወጀብ ውስጥ ለማለፍ ቢገደድም የህወሃት ትግሪያዊነት የአንድም ወልቃይቴ ወይም ጠገድቼ ልብ ማማለልና ትግሬያዊ ማድረግ አልተቻለውም። እንግዲህ ሁሉም ህወሃታዊ ሴራዎች ተጨፍልቀው በግለሠብ ደረጃ የአንድን ወልቃይቴ ወይም ጠገድቼ ቀልብ መማረክ ካልተቻለው እንዴትስ አድርጐ የዚህን ኩሩና ታላቅ ህዝብ ማንነት ማስለወጥ ይቻለዋል? እንዴትስ አድርጐ ወልቃይት ጠገዴ የትግራያዊነት ቀሚስ ማልበስ ይቻላል። ለዚህም ይመስላል ሆድ-አደሮቹ በፅሁፋቸው በገፅ 2/4 አንቀፅ 2 ላይ “ትግሪያዊነት በትግራይ ክልል ባለስልጣናት በኩል በወልቃይት ማህበረስብ የተጫነ…” መሆኑን በማለት ማስተባበያ አይሉት ማስተዛዘኛ ለመስጠት የሞከሩት። ይልቁንም አበው “የጨነቀው እርጉዝ ያገባል” እንዲሉ የትግራይ ጌቶቻቸውን ለማፅናናት በሚመስል ቃና የወልቃይት ጠገዴን ማንነት ከ“ትግራይ-ትግራያዊነት” ወደ “ኤርትራ-ትግሪያዊነት” ለማንሸራተት የተገደዱት። እንዲህም ይላሉ፦

“ከትግራይ ብሄረሰብ ጋር የሚመሳሰለው በቀጥታ ሳይሆን በተዘዋዋሪ መንገድ ነው። ይኅውም የወልቃይት ባህል የሚመሳሰለው ኤርትራ ነጻነቷን ስትቀዳጅ አብሮ ከተገነጠለው ትግርኛ ከተባለው የከበሳ አካባቢ ብሄረሰብ ባህል ጋር ነው። በቋንቋም ቢሆን የትግርኛ ዘዬ ወይም ዳያሌክት ተመሳሳይነቱ ከኤርትራ ትግርኛ ጋር ነው።”

እውነታው ግን ዛሬ ተከዜን አሻግረን አርቀን ወደ ኤርትራ-ትግሪያዊነት እንደ ወረወርናቸው ሁሉ በቀጣይ የህዝባችን ጠንካራና የተባበረ ብርቱ ክንድ ሲደቁሳቸውና አዲሲቷ ማንነታቸው ገዥ አጥታ እርቃኗን ስትቀር እንደ ሌሎቹ ቀይባህርን ተሻግረው “የወልቃይት ጠገዴ ዘር የመጣው ከማዳጋስካር ነው” እንደሚሉን አንጠራጠርም። ለምን ቢሉ እንደ ዛሬ አያድርገውና ታላላቅ የሚባሉት ብሄሮች ሳይቀር “ከማዳጋስካር ነው የመጣነው” የምትለውን የህወሃት የዘረኝነት ድርሳን እያነበነቡ ያደነቁሩን ነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።

ወልቃይት ጠገዴ ፡ አማራ

የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ባሳለፋቸው መራር የትግል ዘመናት እንደ ማንኛውም ትግል በተለያዩ የእድገት ደረጃዎች ውስጥ ማለፉ የግድ ነበር። ምንም እንኳ ትግላችን ከፊት ለፊቱ ከፍተኛና ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ የሚጠብቀው ቢሆንም በአሁን ሰዓት የህዝባችን ትግል ከፍተኛ የስኬት ደረጃ ላይ ይገኛል። ይሃውም ፦

  1. ህዝባችን ለአለፉት 37 ዓመታት በትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን ከደረሰበት ፈርጀ ብዙ የዘር ማፅዳትና አካባቢውን በትግሪያዊነት የመተካት የተቀነባበረ ወንጀል የተረፉትን ልጆቹን በማሰባሰብና ወጣት የልጅ ልጆቹን የትግሉ አካል በማድረግ ለህልውናውና ለማንነቱ መጠበቅ ተከታታይ የሞት ሽረት ትግል የሚያደርግበት ቀውጢ ሰአት በመሆኑ፣
  1. የትግራዩ ነፃ አውጭ ቡድን ለአለፉት 25 ዓመታት የሃገሪቱን መንግስታዊ ስልጣን በመጠቀም አካባቢውን ከጋዜጠኞችና መንግስታዊ ካልሆኑ ምግባረ-ሰናይ ድርጅቶች እይታና እንቅስቃሴ ዝግ በማድረግ በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይ ይፈጽም የነበረው የተቀነባበረ የዘር ማጽዳት ወንጀል ለህወሃት ፍርፋሪ ባልተንበረከኩ ፅኑ ልጆቹ ያላስለሰ ትግልና በኢትዮጵያ የቁርጥ ልጆች ሁለገብ ድጋፍ በኢትዮጵያ ህዝብና በመላው ዓለም እውቅና ያገኘበትና የአብዛኛው ጋዜጠኞች፣ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቶችና፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እንዲሁም ሌሎች በንቃት የሚከታተሉት ግንባር ቀደም ጉዳይ ለመሆን የቻለበት ወቅት በመሆኑ፣
  1. ኢትዮጵያ ሃገራችንና ህዝቧን እያሸበረና እየዘረፈ የሚገኘው የትግራዩን ነፃ አውጭ ቡድን ከስልጣን ለማስወገድ በሰላማዊም ሆነ ነፍጥ አንስተው የሚታገሉ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ድርጅቶች በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይ የደረሰበትን ፈርጀ ብዙ የዘር ማፅዳትና አካባቢውን በትግሪያዊነት የመተካት የተቀነባበረ ህወሃታዊ ወንጀል እውቅና የሰጡበትና ግንባር ቀደም የሚታገሉለት አጀንዳቸው በማድረግ በችግሩ አፈታትም ዙሪያ ግልጽ የሆነ አቋም የያዙበት ወቅት በመሆኑና፣
  1. በተለይም ከላይ የተዘረዘሩትንና በተለያዩ መድረኮች ያስመዘገባቸውን የተለያዩ ድሎች በማስጠበቅ መላውን የጎንደርና የአማራ ህዝብ ከጎኑ በማሰለፍ ለሚታገልለትና ለሚታገልበት የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ! መመለስ ከምንግዜውም በላይ ቆርጦ የተነሳበት ወሳኝ የትግል ወቅት ነው።

እንግዲህ በዚህ ወቅት ነው ሆድ-አደሩ ቡድን የህወሃት ጌቶቻቸውን ለማስደሰትና ከተቻላቸውም ጠራርጎ ሊወስዳቸው ከመጣው የህዝብ ቁጣ ለመታደግ መታተራቸውን በሚያሳብቅ መልኩ “ወልቃይት እና አማራ” በሚለው የመጣጥፋቸው 2ኛው አንቀጽ ላይ “ከቋንቋ ልዩነት ሌላ ወልቃይትን ከአማራ የሚያራርቅ ብዙ ግፍ ተፈጽሞል” በማለት ቀደም ሲል “ወልቃይት እና ትግራይ” በሚለው ክፍል “በህዝቦች መካከል ሰላም ለማውረድና አላስፈላጊ ቁርሾን ለትውልድ ላለማስተላለፍ” በማለት የተመፃደቁበትን ለህዝቦች ሰላም ያላቸው አርቆ አሳቢነታቸውንና ሚዛናዊ የሚመስለው ህሊናቸው ከመቅፅበት ከድቷቸው የጎንደር/አማራ ህዝብ በወልቃይት ላይ አደረሰ የሚሉትን ሁሉ በማተት የቆሙለትና ያደሩለትን ባንዳዊ አጀንዳ ምን ድረስ እንደሆነ ያሳዩናል፡፡

ይህ ሴራ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ! አጀንዳን ከታጋዩ ህዝባችን በማስጣልና እርስ በእርሱ በመከፋፈል ለከፋው የህወሃት አፀፋዊ ጥቃት ያለ አጋርና ደጀን አጋልጦ ለመስጠት የተጠነሰሰ ህወሃታዊ ሴራ መሆኑን ለመረዳት ህወሃት ቀደም ሲል በህዝባችን መካከል ሰረጎ በመግባት የሄደባቸውን መሰሪ የከፋፍለህ-ግዛ መንገዶች ወደ ኃላ መለስ ብሎ ማየቱ በቂ ነው፡፡

ስለሆነም ከነበረን ልምድና ከቀደመው ታሪካችን በመነሳት ይህን በተንበርካኪው ቡድን በኩል የቀረበልንን ህወሃታዊ ሴራ ለህዝባችንና ከጎናችን ለተሰለፈው ለኢትዮጵያ ህዝብና በተለይም ለጎንደርና ለአማራ ህዝብ ጠለቅ ብሎ በማሳየት ህወሃትን በተባበረ የህዝብ ክንድ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ በሚደረገው ትግል የበኩላችንን ለማበርከት እንሻለን።

1ሴራ፡  የአማራን ህዝብ በፈጠራ ክስ መወንጀል

የአማራ ማንነት ጥያቄ! አጃንዳን ማስጣል

  1. ፀሃፊው “ወልቃይትና አማራ” የሚለውን ርዕስ መጻፍ ሲጀምሩ “ሲጀመር ወልቃይት የጎንደር እንጂ የአማራ ሆና አታውቅም” በማለት ነበር። እኛም እውነት ነው ወልቃይት የጎንደር እንጂ የማንም ሆና አታውቅም!!!!

ለአለፉት 25 ዓመታት ወልቃይት ጠገዴ የትግራይ አካል ነው እያለ ሲያደነቁረን የነበረው እርስዎ ዛሬ የተንበረከኩለት የትግራይ ነፃ አውጭ ቡድንና ከእርስዎ ቀደመው ለህወሃት ያደሩት ቤተሰቦችዎ ናቸው። ይልቁንም ታላቋን ኢትዮጵያ በቋንቋ ሸንሽኖ በአራቱም ማእዘን የዘር ግጭት የለኮሰው እርስዎ ያደሩለትና የተወዳጁት ህወሃት ነው። ጎንደርንም አማራ ብሎ የከለለው የእርስዎ ህወሃት እንጂ ሌላ ማንም አይደለምና ከሰማዎት እንደ ወዳጅነትዎ ለደንቆሮው ህወሃት “ወልቃይት ጠገዴ የጎንደር እንጂ … ሆና አታውቅም” ብለዋል ይበሉልን።

 

  1. በ2ኛው አንቀጽ ላይም “ከቋንቋ ልዩነት ሌላ ወልቃይትን ከአማራ የሚያራርቅ ብዙ ግፍ ተፈጽሞል” ይላሉ።

ከዚህ ዓረፍተነገር ጀምሮ የተከተላችው አንባቢ ሁሉ በእርግጠኝነት አንድ እውነት ያስታውሳል። ይኅውም ህወሃት በአለፉት 25 ዓመታት የስልጣን ዘመኑ የአማራውን ህዝብ ከኤርትራው፣ ከኦሮሞው፣ ከሲዳሞው፣ ከወላይታው፣ ከትግሬው፣ ከጋምቤላው፣ …ወዘተ ለማፋጀት የቀሰቀሰበትና ብዙ የአማራ ተወላጆች ለከፋ እልቂትና ስቃይ የተዳረጉበትን የህወሃት በአማራ ህዝብ ላይ የከፈተውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ቅስቀሳ ያስታውሳል።

እንግዲህ ይህ በአቶ ሃይሉ የሺወንድም ፊታውራሪነት የቀረበው ደግሞ “የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ በአማራ ህዝብ ላይ …” በሚል ወደፊት ህወሃት በጎንደር ህዝብ ላይ በተለይም አማራነን ባሉ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች ላይ ለሚያካሂደው ጭፍጨፋ መንገድ እየተጠረገ መሆኑን እንረዳለን። ለዚህም ፍጅት ቅድመ ዝግጅት አቶ ሃይሉ በፅሁፋቸው የድርሻቸውን ተወጥተዋል።

  1. ጉደኛው ፀሃፊ “በሁመራ ዘመናዊ እርሻ ምክንያት ሲገኝ የነበረው ገቢ ለደብረታቦር ትምህርት ቤት መስሪያና ለሌሎች አካባቢዎች ጥቅም ይውል ነበር። አሁን እንደሚደረገው ማለት ነው” ይሉናል።

የሁመራ እርሻ ልማት የተጀመረው በ1950ዎቹ መጀመሪያ ሲሆን አገልግሎቱ የተቋረጠው “ገስጥ” ይባል የነበረው የደርግ ጦር በ1969 ዓ.ም ሁመራንና አካባቢውን በሃይል በወረረበትና ህዝባችንን በጀምላ በጨረሰበት ጊዜ ነበር።

በአንፃሩ ደግሞ ዛሬ በህወሃት የሚመራው የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር በሚያወጣው አመታዊ መጽሄት በአስተዳደሩ ስር የሚገኙ ት/ቤቶችን አስመልክቶ ያውጣውን መረጃ ምን እንደሚል በከፊል እንመልከት።

Screen Shot 2016-01-28 at 10.32.28 PM

ከላይ በተጨባጭ መረጃ እንደምንመለከተው የሁመራ እርሻ ልማት ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ እስከ ከሰመበት ጊዜ ድረስ  በደብረታቦር አውራጃ ምንም አይነት ት/ቤት እንዳልተገነባ የተረጋገጠ እውነት ሆኖ እናገኘዋለን።

ታዲያ የዚህ “ከሁመራ እርሻ በተሰበሰበ ግብር … ደብረታቦር ላይ ት/ቤት ይሰራ ነበር… ።አሁን እንደሚደረገው ማለት ነው።” የሚለው የሆድ-አደሩ ቡድን ውንጀላ መነሻው መሰረተ ቢስ እንደሆነ በተጨባጭ የተረጋገጠ ሲሆን ታዲያ የዚህ ውንጀላ ዋና አላማ ምን ሊሆን ይችላል ብሎ መመርመር ተገቢ ነው። ከህወሃት ባህሪና እስከዛሬ ካለፍንባቸው ተሞክሮዎች በመነሳት በእርግጠኝነት መናገር የምንችለው፦

  1. ህወሃት በአለፉት 25 ዓመታት የጎንደርን ህዝብ ሰሜንና ደቡብ ብሎ በመከፋፈል የማንወጣው የመጠላለፍና የመፋጠጥ አዙሪት ውስጥ ለመክተት አበክሮ ሰርቷል። አላማውም ይህ የታላቋ ኢትዮጵያ ጠባቂና ተቆርቋሪ የሆነውን ህዝባችን ከኢትዮጵያ ላይ አይኑን እንዲያነሳና ለህወሃት ዝርፊያና ኢትዮጵያን የማተራመስና የማፍረስ ሴራ እንቅፋት እንዳይሆን በማለም ነበር። ነገር ግን በህዝባችን አስተዋይነትና በታላላቆቻችን ብርቱ ጥረት ሴራው ለጊዜው ሊከሸፋና ውጤት ማምጣት ሳይችል ቀርቷል። እነሆ ይህ በሆድ-አደሩ ቡድን የሚቀርበው የፈጠራ ውንጀላ የሴራው ቀጣይ ክፍል ነው።
  1. የህወሃት የ37 ዓመታት የዘር ማፅዳትና በትግሪያዊነት የመተካት ወንጀል ያልተሳካውና ይልቁንም ህወሃትን እስከ አንገቱ ያነቀው የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ የአማራ ማንነት ትግል እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰው በመላው የጎንደር ህዝብ ድጋፍና ተሳትፎ ጭምር ነው። ይህ እውነታ በህወሃት መንደር ግልፅ ከሆነ ሰነባብቷል።  ስለዚህም ህወሃት በለመደው ከአያቶቹ በወረሰው የከፋፍለህ ግዛ ፈሊጡ ተላላኪዎቹን በመጠቀም የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብን ከአማራ ህዝብና በተለይም ከጎንደር ህዝብ ለመነጠልና ለማጥቃት የተደረገ ሴራ አካል ነው።
  2. “…አሁን እንደሚደረገው ማለት ነው።” ይላሉ።

ዛሬ ህወሃት የወልቃይት ጠገዴን መሬት በመውረር የሚፈፀመውን ለከት ያጣ ዝርፊያ ወንጃል በዘውዳዊው ስርዓት ወቅት እንደሚደረገው አይነት ነው ብሎ በንፅፅር ማቅረብ አንድም የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ በህወሃት አልጠግብ ባይነትና አይን ያወጣ ዝርፊያ ምክንያት ህዝባችን የገባበት የበይ ተመልካችነትና የድህነት አረንቋ ላይ መዘባበት ሲሆን ይህም እጅግ አሳፋሪም ነውረኛም ነው። ፍርዱንም የትግራዩ ነፃ አውጭ ቡድን ዕርስታቸውን በመውረርና ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የትግራይ ሰፋሪዎችን የእርሻ መሬታቸው ላይ በማስፈር ለማያውቁት ረሃብና ልመና ለተዳረጉ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች እንተዋለን።

  1. ፀሃፊው ውንጀላውን በመቀጠልም “በደጃዝማች አያሌው ብሩ ግዛት ዘመን በወገራ ደጋማና ቆላማ አካባቢ የሚኖሩ አማራዎች በወልቃይት ላይ ወረራዎችና ዝርፊያዎች እንዲያካሂዱ ተደርጓል።” ይሉናል።

እንደሚታወቀው የፊውዳሉ ስራአት አንድን ለስርአቱ አልገዛ ወይም አልገብር ያለን ወረዳ ለመቅጣትና ለማስገበር ይጠቀምበት የነበረው አይነተኛ ዘዴ ሌላውን አጎራባች ወረዳ እንዲዘምትበትና እንዲወረው ብሎም እንዲያስገብረው በማድረግ ነበር። ይህም ድርጊት በተለያዩ የጎንደር አካባቢዎች ስለመፈጸማቸው በህይወት የሚገኙ አባቶቻችንና እናቶቻችን ህያው ምስክር ናቸው። ነገር ግን ይህን ዘርንም ሆነ ማንነትን መሰረት ሳያደርግ ይደረግ የነበረን መንግስታዊ ቅጣት “የጎንደር አማራዎች” በተለይ በወልቃይት ላይ ሆን ብለው የፈጸሙት አድርጎ ማቅረብ ህወሃት የጎንደርን ህዝብ እርስ በእርሱ ለማጋጨት ከጠነሰሰው ሴራ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?

እዚህ ላይ አንድ የታሪክ ማስረጃን ጠቅሰን እንለፍ። በ1949 ዓ.ም አካባቢ አዲስ ዘመን/ይፋግ አካባቢ አቶ አግማሱ ወጤ የተባለ ግለሰብ ያምፃል (ይሸፍታል)። ከእለታት በአንዱ ቀን ሊይዙት ከመጡ ወታደሮች ጋር ይታኮሳሉ። በዚህ ጊዜ የወረዳው አስትዳዳሪ የነበሩት ፊታውራሪ (ደጃዝማች) በረደድ አስፋው አቶ አግማሱ ወጤ እንዲያዝ እርዳታ ስላልሰጡ እርሳቸው የሚያስተዳድሩት ወረዳ እንዲወረር ይደረጋል። እንዲወር የተላከውም የመናመቀጠዋ ወረዳ ነበር። ለወረራ የዘመተው ወታደር ቀለቡንም ሆነ ምኝታውን የሚያገኝው በወረራ ከያዘው ማህበረስብ ስለነበር ለዚህም ሲባል  በየአለቃው እየሆነ በየመንደሩ ይሰማራል። በዚህም ወረራ የከምከም ቃሮዳ ህዝብ ክፉኛ መጎዳቱ የታወቃል።ይህም ፊውዳላዊ የማስገበሪያ ዘዴ በሁሉም አካባቢ ሲተገበር የኖረ እንጂ የህወሃት ተላላኪዎች እንደሚሉት የወልቃይትን ማህበረሰብ ሆን በሎ ለማጥቃት የተደረገ አንድም ወረራ አልነበረም።

ይልቁንም ፀሃፊው ተወልደው ባደጉበት አካባቢ የልጅነትና የወጣትነት ዘመን ላይ የተፈጸመን ተመሳሳይ እውነተኛ ታሪክ ፍጹም አጣሞና አዛብቶ ለህወሃት ሴራ በሚመች መልኩ ማቅረብ፤ አንድም ህወሃት ማኒፌስቶ ቀርፆና አካባቢውን በሃይል ተቆጣጥሮ የወልቃይት ጠገዴን ዘር አፅድቶ በትግሪያዊነት ለመተካት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የትግራይ ሰፋሪዎች በማስፈር የተጓዘበትን  ዘግናኝ የዘር ማፅዳት ወንጃል በስመ “ወረራ” ለማቃለልና ለማድበስበስ የታለመ ሲሆን በሌላ መልኩ ደግሞ  ህወሃት በአማራ ህዝብ ላይ በቀጣይነት ለሚፈጽመው የዘር ማጽዳት ፍጅት መንገድ ጠራጊ ሆነው ለማገልገል ቆርጠው መነሳታቸውንና በአማራ ህዝብ ላይ ሊያካሂዱ ያቀዱትን ግጭት በፊታውራሪነት ለመምራት የሄዱበትን እርቀት ያመላክታል።

  1. አቶ ሃይሉ “ምዝበራው አልበቃ ብሎ አባወራውን አባርረው ሚስቲቱ አስገድዶ መድፈር የተለመደ ነበር” ይላሉ።

“የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም” እንዲሉ እዚህ ላይ እነ አቶ ሃይሉ የሺወንድም ቀስ በቀስ የገቡበት ህወሃታዊ የክህደትና የሸፍጥ ቁልቁልት ጥልቅና መውጫ ወደሌለው እንጦሮጦስነት ሲቀየር እናያለን።

የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ እንኳንስ በሚስቱና በዕርስቱ ለመጣበት ይቅርና በዋዛ በፈዛዛ ክብሩን ለነካ ሁሉ ምላሹ ጥይት እንደሆነ ጠላታችን ህወሃት ሳይቀር ጠንቅቆ ያውቃል። ይህን በታሪካችን ተሰምቶም ሆነ ታይቶ የማያውቅ ፀያፍ ምግባር በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይ እንደተፈጸመ አድርጎ ማቅረብ በቅድሚያ ከሁሉም በላይ ይህ ለሆዱ ያደረ ተንበርካኪ ስብስብ ለወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ያላችውን ንቀት የሚያሳይ ሲሆን፤ በመቀጠልም ድርጊቱን ፈጽሟል ብለው በሚከሱት የጎንደር-አማራ ህዝብ ላይ ያላቸውን ከልክ ያለፈ ጥላቻ ምን ድረስ ሊጓዝ እንደሚችል በተጨባጭ ያረጋገጠ ነው።

ለመሆኑ የትኛው ወልቃይቴ ወይም ጠገድቼ ነው ከወራሪ ወታደር የተወለደና አባቱን የማያውቅ? የትኛውስ አባወራ ነው ሚስቱን አስደፍሮ በማህበረሰቡ ውስጥ ተዋርዶ የኖረው? ከዚህ ከተዋረደ ቤተሰብ ውስጥ የተወለዱ ልጆች እነማን ናቸው? የልጅ ለጆቹስ እነማን ይሆኑ? እንግዲህ መልሱን ለእነ አቶ ሃይሉ የሺወንድም እንተዋለን።

እኛ ግን እንዲህ እንላለን። ይህን በታሪካችን ተሰምቶም ሆነ ታይቶ የማያውቅ ፀያፍ ምግባር በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይ እንደተፈጸመ አድርጎ ማቅረብና ማስተጋባት የማንም ሳይሆን ዕርስታችንን በወረራ ይዞ ዘራችንን እያጥፋና አካባቢያችንን በትግሪያዊነት እየተካ የሚገኘው ህወሃት በህዝባችን ላይ ያለውን ንቀትና ጥላቻ ያሳየበት ሲሆን እስከዛሬ በህዝባችን ላይ በዝግ ለፈፀማቸውና ነገ ታሪክ ለሚያወጣቸው ግፎችና ፀያፍ ድርጊቶች ፍንጭ የሰጠበት መንገድ ነው እንላለን።

እንዲህም እንመሰክራለን። ከህወሃት በፊት በነበሩ ስርዓቶች ሁሉ እንዲህ አይነት ፀያፍ ድርጊት በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይ አይደለም ሊፈፀም ይቅርና በወሬ ደረጃ ተሰምቶም እንደማያውቅ ምስክሮች ነን። ይህ የፈጠራ ክስ ህወሃት የወልቃይት ጠገዴን ማህበረሰብ ክብር ለማዋረድና አኩሪ ታሪኩን ለማንቋሸሽ የሄደበት ፀያፍ መንገድ ነው።

2ሴራ፡  የወልቃይት ጠገዴን ከአማራዊነት መነጠል

  1. ውንጀላ እና የሃሰት ምስክርነት

ፀሃፊው በመጣጥፋቸው እጅግ አደገኛ የሆኑ ሁለት የፈጠራ ውንጃላዎችን በማቅረብ የሃሰት ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ።

1ኛ. በስደት የሚገኙት የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች በአሁኑ ሰዓት በሀገር የተቀጣጠለውና የአማራ ምንነት እንቅስቃሴ የሚመሩ ወገኖችን አጀንዳውን ያገኙት የተሰጣቸው ከዲያስፖራው ነው የሚል ሲሆን፤

2ኛ. “የወልቃይት አማራ ማንነት እንቅስቃሴ በአጭር ጊዜ ተደማጭነት ያገኘው … የብአዴንን ቡራኬ ስላገኘ ” በማለት የወገናችንን የዘመናት ትግልና መስዋዕትነት ውጤት የሆነውን ይህን ታላቅ ድል እራሱን እንኳ ከህወሃት ቁንጥጫ ማዳን ለማይቻለው የብአዴን ባርኮት ያደርጉታል።

እነዚህ ሁለት ውንጀላዎች ህወሃት ከመጀመሪያው ጀምሮ የሚያላዝንባቸውና አሁንም ወገኖቻችንን ለማሸማቀቅና እንደለመደው አፍኖ ለማጥፋት የሚያደርገው ቅድመ ሁኔታ ነው። በተለይም በአለፉት የእንቅስቃሴው የመጀመሪያ ወቅቶች የነበረው ህወሃት ሌላውን ተላላኪውን አቶ ፈረደ የሺወንድምን ወደ ጐንደር በመላክ የእንቅስቃሴውን የኮሚቴ አባላት ለማስፈራራት መሞከሩ የሚታውቅ ሲሆን በእንቅስቃሴው አመራር አባላት መካከል አንዳችም አይነት ጉዳት ቢደርስ ተጠያቂ የሚሆነው አቶ ፈረደ እና ግብረ አበሮቹ እንደሆኑ የኮሚቴው አባላት ለቤተሰቦቻቸው መናገራቸውን ልብ ይሏል።

አሁንም ይህ ተመሳሳይ ውንጅላ በአቶ ኃይሉ የሺወንድም መደገሙ “አያ ጅቦ ሳታማኽኝ ብላኝ” ያለችው እንሰሳ ታሪክ ያስታውሰናል። ስለሆነም በኮሚቴው አባላት ላይና  የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ! ፊርማ ማስባሰቢያ ሰነድ ላይ በፈረሙ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች ላይ የሚደረሰው ማንኛውም ህወሃታዊ አፈና እና ጥቃት ግንባር ቀደም ተጠያቂ የሚሆኑት በመግቢያችን እንደገለፅነው በዋናነት ወ/ሮ አዜብ መስፍን፣ አቶ ፈረደ የሺወንድም፣ አቶ ሃይሉ የሺወንድም፣ አቶ ፀጋዬ አስማማው እና የጥቅም ታጋሪዎቻቸው መሆናቸውን ከወዲሁ ልናረጋግጥ እንወዳለን።

  1. ወልቃይትን ከጠገዴ መነጠል

ቡድኑ በመጣጥፉ በገፅ 5, 2ኛው አንቀጽ ላይ “ወረራውና ዘመቻው እንደ ባህል ሆኖ፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በጠገዴው ተወላጅ በክቡር ቢትወደድ አዳነ መኮንን አስተዳደር ሳይቀር በየምክንያቱ ተመሳሳይ ዘመቻዎች ተካሂደዋል። የቢትወደድ ቀብቲያ ላይ በጥይት መቁሰልና የጀግናው ወጣት አርበኛ ወልቃይቴ የመኮነን በርሄ (ጎንደሬ በጋሻውን ያንብቡ) መገደል ከዚህ አይነቱ ዘመቻ ጋር የተያያዘ ነበር።” ይለናል።

በክቡር ቢትወደድ አዳነ መኮንን የአስተዳደር ዘመን በወልቃይት ላይ የተፈጸመው ወረራ ከላይ በሰፊው እንደገለፅነው የፊውዳሉ ስርአት አንድን ለስርአቱ አልገዛ ወይም አልገብር ያለን ወረዳ ወይም አንገዛም ያሉ ግለሰቦች (ሽፍቶች)  ለመቅጣትና ለማስገበር ይጠቀምበት የነበረው አይነተኛ ዘዴ ሌላውን አጎራባች ወረዳ እንዲዘምትበትና እንዲወረው ብሎም እንዲያስገብረው የማድረግ አንዱ አካል ነው። ከዚህም በመነሳት በዘመኑ በወልቃይት ማህበረሰብ እንደ ጀግና በፊውዳሉ ስራአት ደግሞ እንደ አመፀኛ ይቆጠር የነበረው ወጣቱ አርበኛ መኮነን በርሄን ለመያዝና ለመንግስት ለማስረከብ የታዘዘው የክቡርነታቸው አስተዳደር ነበር።

ይሁን እንጂ ክቡር ቢትወደድ አዳነ መኮንን ምንም እንኳ በመንግስት መኮነን በርሄን ይዘው እንዲያቀርቡ ቢታዘዙም ወደ ወልቃይት ጦር አላዘመቱም። ይልቁንም እራሳችው ከጥቂት ወታደሮቻቸው ጋር ወደ አካባቢው በመሄድ የወልቃይትን ፊታውራሪዎች በማማከር  በሽምግልና ምህረት ተደርጎለት እንዲገባ ይስማማሉ። መኮነን በርሄንም እኛ ዋስ እንሆንሃለን በማለት የእራሱ ዘመዶች ፊታውራሪዎቹ ክቡር ቢትወደድ አዳነ መኮንን ዘንድ ይዘውት ይቀርባሉ። እሳቸውም አባታዊ ምክራቸውን ለግሰው ዋስ እንዲጠራ ይጠይቁታል። እርሱም በሽምግልና ያመጡትን ፊታውራሪዎች ለዋስትና ቢጠይቅ ከወንድሞቹ አንድም የሚዋሰው ሰው ያጣል። በዚህም ጊዜ በሽምግልና ባመጡት ዘመዶቹ ክህደት የተናደደው ጀግና መታሰሬም ሆነ መሞቴ አይቅርልኝም በሚል ደብቆ በያዘው ሽጉጥ ክቡር ቢትወደድ አዳነ መኮንን ያቆስላል። በወቅቱም ቢትወደድ ከወደቁበት ሆነው እንዳትገሉት በማለት ያስጠነቀቁ እንደነበርና ነገር ግን እዛው የነበሩት ሁሉ ተረባርበው እንደገደሉት ታሪክ ህያው ምስክር ነው።

እውነታው ይህ ሆኖ እያለ ሆን ተብሎ ታሪክን በማጣመም በጠገዴ ተወላጆች አማካኝነት በወልቃይት ማህበረሰብ ላይ የተፈፀመ ወረራ አድርጎ ማቅረብ ይልቁም አንድ አካል አንድ አምሳል ከሆነው የጠገዴ ህዝብ የተገኙት ጀግናው አባታችን ክቡር ቢትወደድ አዳነ መኮንን ሆን ብለው ወልቃይትን ለመበቀል የዘመቱና በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ዘንድ እንደ ጠላት ወይም በዳይ እንደሚቆጠሩ ተደርጐ መቅረቡ እጅግ የተሳሰተና ከእውነታውም የወጣ ነው። እርግጥ ነው ክቡር ቢትወደድ አዳነ መኮንን ወደ ወልቃይት የዘመቱበት ጊዜ አለ። ይኸውም ለጣሊያን ባንዳ ሆነው አገር የከዱትን ደጃዝማች ለመያዝና ለመቅጣት እንደነበር ታሪክ በደማቁ ፅፎታል።

ከዚህም በመነሳት ቀደም ሲልም ፀሃፊው “በህዝቦች መካከል ሰላም ለማውረድና አላስፈላጊ ቁርሾን ለትውልድ ላለማስተላለፍ” በማለት ስለትግራይና ወልቃይት ህዝብ ፍቅርና ሰላም የተጨነቁትና የተጠነቀቁትን ያህል በዚህኛው የፅሁፋቸው ክፍል በጠገዴና በወልቃይት ማህበረሰብ መካከል ምን አይነት ፍቅርና አንድነት ለመገንባት እንዳሰቡና እንደጣሩ ከወዲሁ መመልከት ይቻላል።

በመጀመሪያ አንድ የታሪክ ማስረጃ እናቅርብ። ጣሊያን ኢትዮጵያን ለቆ በወጣ ማግስት የስሜን አውራጃ ህዝብ ጣሊያን ባደረሰበት ግፍና መከራ የተነሳ እጅግ በከፋ ድህነት ውስጥ እንደሚገኝና እንደሚሰቃይ፤ የዘመኑንም ግብር የመክፈል አቅም እንደሌለውና ምህረት እንዲደረግለት ለአፄ ኅይለስላሴ መንግስት ጥያቄ ያቀርባሉ። ነገር ግን ጥያቄውን ያልተቀበለው የአፄ ኅይለስላሴ መንግስት የስሜን አውራጃ በሰላም እንዲገብርና ፈቃደኛ ካልሆነ በሃይል እንዲገብር ትእዛዝ ይተላለፋል። ይህንም እንዲያስፈፅም ከመንግስት የታዘዘው የክቡር ቢትወደድ አዳነ መኮንን አስተዳደር ነበር። እንደተለመደው የክቡር ቢትወደድ አዳነ መኮንን ጦር ፊታውራሪ አጥናፉ መሸሻ የሚገኙበትን የስሜን አውራጃን ለመቅጣትና ለማስገበር ይዘምታል። በዚህም ጦርነት የቢትወደድ አዳነ መኮንን ጦር ይሸነፍና ቢትወደድ አዳነም ቆስለው ይማረካሉ። ይሁን እንጂ ፊታውራሪ አጥናፉ መሸሻ የዘመቱባቸውን ቢትወደድ አዳነን በክብር ተቀብለውና ይቅርታ ጠይቀው፣ የራሳቸውን በቅሎ በመስጠት ወደ መጡበት መልሰዋቸዋል።

ከዚህ ታሪካዊ እውነታ የምንረዳው ነገር ቢኖር ከላይ እንዳየነው ወደ ወልቃይት የዘመቱት አማራው የጠገዴው ተወላጅ ክቡር ቢትወደድ አዳነ መኮንንና ጦራቸው ወደ ሌላኛው አማራ ወደሆነው የእነ ፊታውራሪ አጥናፉ መሸሻ የስሜን አውራጃ ግዛት ለማስገበር በማእከላዊው መንግስት ትእዛዝ መዝመቱን እንረዳለን። ይህም ድርጊት በመላው ኢትዮጵያ ሲሰራበት የነበረ አሰራር ነበር።

ከእነዚህ የታሪክ እውነታዎች በመነሳትና “በህዝቦች መካከል ሰላም ለማውረድና አላስፈላጊ ቁርሾን ለትውልድ ላለማስተላለፍ” በማለት ስለትግራይና ወልቃይት ህዝብ ፍቅርና ሰላም የተጨነቁትና የተጠነቀቁትን በማየት የእነ አቶ ኃይሉ የሺወንድም በክቡር ቢትወደድ አዳነ መኮንን ጦርና በጠገዴ ላይ ያቀረቡት ውንጀላና ክስ ስንመለከት አላማው ግልፅ ይሆናል። ይኸውም ወልቃይትና ጠገዴ የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ መሆናቸው አይደለም የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ወራሪው ጣሊያንም ያውቀዋል።

ነገር ግን አንድ የጠገዴን ህዝብ ከሁለት በመክፈል ግማሹን ወደ ጎንደር/አማራ ሌላውን ግማሽ ደግሞ ወደ ትግራይ በመከለል ሁለት ጠገዴ የፈጠረው ተስፋፊውና ወራሪው የትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን ከጠገዴ ማህበረሰብ በኩል የደረሰበትን “አንድ ጠገዴ እንጂ ሁለት ጠገዴ የለም!” የሚለውን የህዝብ ተቃውሞ ለማፈንና በወልቃይት ማህበረሰብ ከተቀጣጠለው የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ! ጋር የተፈጠረው የትግል አንድነትና ትብብር ለማዳከምና ነጥሎ ለማጥቃት ሲል ህወሃት በተላላኪዎቹ በኩል የከፈተው የመከፋፈል ዘመቻ አካል መሆኑን ወገናችን ጠንቅቆ ይረዳል።

የሆድ – አደሮቹ አጀንዳ

  1. “የወልቃይት አማራ ማንነት ኮሚቴ አባላትና ደጋፊዎቻቸው ከተመደበላቸው ስራ ጎን ለጎን ለስታተስ ኮ አንቲ ቅድመ ሁኔታ መሳካት ትርጉም ያለው ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።” በማለት ከ 7 ገፅ በላይ በመፃፍ ለከሰሱትና ለወነጀሉት ታጋይ ህዝብና ኮሚቴ የራሳቸውን አጀንዳ ሊጭኑበት ይሞክራሉ።

የዚህ አጀንዳ ምንጩና አላማው አንድና አንድ ነው። ይኸውም በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይ ከ37 ዓመታት በላይ የተፈፀመው ዘርን የማፅዳትና አካባቢውን በትግሪያዊነት የመተካት ወንጀል በዓለም አደባባይ መጋለጡ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎናችን መቆሙና፣ ይልቁንም ህዝባችን በጎንደርና በመላው የአማራ ህዝብ ደጋፍና ትብብር ታሪካዊ የተባለለትን ህዝባዊ ጥያቄ አንግቦ በአንድነት መነሳቱ ህወሃት በሃይል የወሰደውን የጎንደር ለም መሬት እንዲመልስ የሚይስገድድ ከሆነ፤ በስመ ምርጫ በሃይል የወረረውን ወልቃይት ጠገዴን ህጋዊ አድርጎ ለመጠቅለል የታለመ ቀጣይ ሴራ እንደሆነ እንረዳለን።

እኛ የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ማንነታችንን በሚመለከት “ህዝበ ውሳኔ” የምንሰጥበት መነሻም ሆነ መድረሻ ምክንያትና ግብ የለንም፡፡ ሊኖረንም አይችልም፡፡ መፍትሄውም እጅግ በጣም ቀላልና ግልፅ ነው፡፡ ይኸውም መሬታችንና ማንነታችን ከ1983 ዓ.ም በፊት ወደነበረበት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይመለስ፡፡ አራት ነጥብ!!!

  1. ህወሃት ዛሬ በተላላኪዎቹ በኩል “የትግራይ ሰፋሪዎችን ከወልቃይት ጠገዴ ማስወጣት” እያለ የሚያናፍሰው ወሬና የሚዘራው መርዝ፤ ትላንት በተመሳሳይ መልኩ ጠፍጥፎ በሰራቸው ተላላኪዎቹ አማካኝነት አባቶቻችን ውድ ህይወታቸውን ሰውተው በክብር ባቆዩልን ሃገራችን ውስጥ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን ለዘመናት ከኖሩባቸውና ጎጆ መስርተው፣ ልጆች ወልደው አሳድገውና ድረው፣ ሃብትና፣ ንብረት አፍርተው በሰላም ከሚኖሩባቸው የኦሮሚያ፣ የቤንሻጉል፣ የጋምቤላና፣ የደቡብ ክልሎች በጀምላ እንዲባረሩና ሜዳ ላይ እንዲወድቁ የተደረገበትን በእጅጉ ያሳዘነንና ያስቆጣንን እኩይ ድርጊት በትግራይ ተወላጆች ላይ እንዲደገም የታለመ ሴራ እንደሆነ ጠንቅቀን እናውቃለን። ይልቁንም “በህዝቦች መካከል ሰላም ለማውረድና አላስፈላጊ ቁርሾን ለትውልድ ላለማስተላለፍ” በማለት የተመፃደቁበትና ለህዝቦች ሰላምና ለትውልድ አርቆ አሳቢ ለመምሰል የሞከሩበት ብዕራቸው ነጥፎ “የትግራይ ሰፋሪዎችን ከወልቃይት ማስወጣት” በማለት በህዝቦች መካከል የማይበርድ እሳት ሲጭሩ እንመለከታለን።

እኛ ግን ከዚህ ቀደምም ባወጣናቸውና ለህዝብ ይፋ ባደረግናቸው ሰነዶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ደጋግመን በግልፅ እንዳስቀመጥነው ሁሉ ዛሬም በድጋሚ አቋማችንን እንደሚከተለው አቅርበናል።

ኢትዮጵያ ሃገራችን ሁሉም ኢትዮጵያውያን በሰላም፣ በፍቅር፣ በመከባበር፣ በእኩልነትና፣ በአንድነት የሚኖሩባት የጋራ ቤታችን ናት! መሆን አለባት የሚል ፅኑ እምነት አለን። ማንኛውም ኢትዮጵያዊ/ት በማንኛውም የኢትዮጵያ ክፍል በነፃነት ተንቀሳቅሶና የዜግነት መብቱ ያለአንዳች ገደብ ተከብሮለት፤ በሰላም ሰርቶ ሃብት የማፍራት፣ ጎጆ መስርቶ የመኖርና፣ ለጆች ወልዶ የማሳደግ ፍፁም እኩል መብት አለው፤ ሊኖረውም ይገባል የሚለው የቀደምት አባቶቻችን ኢትዮጵያዊ መርሆ ለወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረና እኛም በተግባር የኖርንበት ኢትዮጵያዊ ማንነታችንና እንደ አንገት ማተባችን የምንጠብቅው ቃልኪዳናችን ነው። ለዚህም ተቀዳሚው ምስክራችን የትግራይ ህዝብ ነው።

ስለሆነም ማንኛውም በህወሃት ሴራም ሆነ የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ተወናብዶ ወይም ሰርቶ ለመኖርና ልጅ ወልዶ ለማሳደግ ወደ ወልቃይት ጠገዴ በህወሃት የሰፈራ ዕቅድ ምክንያት የሰፈረ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ እንደ ቀድሞው ሁሉ የወልቃይት ጠገዴን የጎንደር-አማራ ብሄርተኝነትና አስተዳደር ተቀብሎ እስከኖረ ድረስ የዜግነት መብቱ ሙሉ በሙሉ ተከብሮለት ሊኖር ይገባል ይሚል ፅኑ እምነትና አቋም አለን። ለዚህም መብት መከበር አበክረን እንሰራለን።

ማጠቃለያ

እራሱን የትግራይ ነፃ አውጭ እያለ የሚጠራው ፀረ-ኢትዮጵያ፣ ፀረ-ሰላም ቡድን ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ በወረራ በያዘቸው የጎንደር ታሪካዊ መሬቶች ላይ በሚኖሩ የወልቃይት ጠገዴና የጠለምት አማራ ተወላጆች ላይ ያደረሰው የዘር ማፅዳትና በትግሪያዊነት የመተካት ዓለም-አቀፍ ወንጀል በአስቸኳይ እንዲቆምና አፋጣኝ የመፍትሄ እርምጃዎች እንዲወሰዱ የሁሉንም ሰላም ወዳድ የሰው ዘር ድጋፍ የምንሻበት ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን። በተለይም ላለፉት 37 ዓመታት የህወሃትን ህገ-ወጥ መስፋፋትና ወረራ ለመግታት በሁሉም አቅጣጫ ሲታገል የኖረው ህዝባችን፤ ዛሬም ያለውን ሃይል በማሰባሰብና ትግሉን በወጣት ልጆቹ በማጠናከር ከፍተኛ መሰዋዕትነት እየከፈለ ይገኛል።

በአንፃሩ ህወሃት ዛሬም ቢሆን በስግብግብነት የያዝውን በአያት ቅድመ-አያቶቻችንን ክቡር አፅም የተዋጀችውን ዕርስታችንን በሰላማዊ መንገድ ላለመልቀቅ እንደቆረጠ የሚያሳዩ ተጨባጭ መረጃዎች ይታያሉ። በተለይም የህወሃት  የ2 ዜግነት ጥቅማጥቅም ያንበረከከው  ቡድን አማካኝነት ታጋዩን ህዝባችን ለመከፋፈልና ለማዳከም ሲል ብቻ ጋምቤላውያንን ከመሬታቸው በሃይል በማፈናቀል ለነዚህ ሆዳሞች በገፍ እያከፋፈለና የሃገሪቷን ገንዘብ ሳይቀር እየረጨላቸው እንደሚገኝ በተጨባጭ መስረጃ ለማረጋገጥ ችለናል።

ይሁን እንጂ ይህ ከወራሪው የጣሊያን መንግስት የተቀዳ ህወሃታዊ ሴራ እጅግ ያረጀና ያፈጀ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ጠንቅቆ የሚያውቀው በመሆኑ ህዝባችን አንድነቱንና ፅናቱን ጠብቆ፣ ለሆድ አደሮች የማደናገሪያ ጩኸትና፣ የማዘናጊያ ድርድሮች ጆሮውን ሳይሰጥ፤ ያነገበውን የወልቃይት ጠግዴና ጠለምት የአማራ ማንነት ጥያቄ! ከግቡ ሳያደርስና፣ የጀመረውን ዘሩን የማዳንና የአባቶቹን ዕርስት የማስመለስ ትግል በድል ሳያጠናቅቅ እንደማይመለስ ፅኑ እምነታችን ነው።

በመጨረሻም የወልቃይት ጠግዴና ጠለምት የአማራ ማንነት ጥያቄ! በውስጡ የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎችና የመዳረሻ መፍትሄዎች ያካትታል።

1ኛ. ወደ ቀደመው የጎንደር ግዛት መመለስ

ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ታሪካዊና መልክዓምድራዊ አካላችን ወደሆነው ጎንደር/የበጌምድር ግዛታችን መመለስ! ይህም ማለት ማንኛውንም መሰረታዊ የማንነታችን መገለጫዎች የሆኑትንና በተለይም ባህላችንና ቋንቋችን በነፃነትና ያለምንም ገደብ መጠቀም ወደምንችልበት ሁኔታ መመለስን ያካትታል፡፡ እነርሱም፡-  በክልላችን ውስጥ በሚካተቱ በማንኛውም መንግስታዊም ሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፤ እንዲሁም በትምህርት ቤቶች አማርኛ ቋንቋችን የመጠቀም መብታችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መከበር፣ ታሪካዊ መጠሪያ ስማቸው ተቀይሮ በትግሪያዊ ስሞች የተተኩትን ት/ቤቶች፣ መንገዶችና፣ የአካባቢዎች ወደ ቀደመ ይዞታቸው መመለስና የመሳሰሉትን ጉዳዮች ያካትታል።

2ኛ. ዕርስት ለባለ ዕርስቱ

የተፈናቀሉትና የተሰደዱት የአካባቢው ተወላጆች ወደ ዕርስታቸውና ቀያቸው በመመለስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የርስታቸው ባለቤት ማድረግ፡፡ ከስደት ተመላሹ ወገናችን ከዜሮ የሚጀምረውን ታሪካዊ ኑሮ ብዙ የሚባልላቸው ጉድለቶች እንደሚያጋጥሙትና በጊዜ ሂደት ሊሟሉ የሚችሉ የመሆናቸው ነገር እርግጥ ቢሆንም መሰረታዊ የሆኑት የማህበራዊ ህይዎት ግብአቶች እንዲሟሉለትና አካባቢው ሰላምና መረጋጋት ሰፍኖበት ኑዋሪዎቹም ያለስጋት ሰላማዊ የዕለት ከዕለት ቀጣይ ኑሮዋቸውን በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲያከናውኑ ማስቻል ያስፈልጋል።

3ኛ. ወንጀለኞችን ለፍርድ ማቅረብ

አካባቢችን ከፍተኛ ወንጀል የሚፈፀምበትና እስከ አሁንም ድረስ ለማንኛውም ገለልተኛ አካላት ዝግ ነው። በተለይም መንግስታዊ ላልሆኑ የሃገር ውስጥና የውጭ ሃገር ድርጅቶች፣ ለጋዜጠኞች፣ ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በአካባቢው መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም አካባቢው  ለማንኛውም ገለልተኛ አካል ምርመራና እይታ ክፍት እንዲሆን በማድረግ የህወሃት አፈናና ወጥመዱ ተሰብሮ የወገናችን በደልና ስቃይ ለዓለም ሰላም ወዳድ ህዝቦች እንዲደርስ በማስቻል፣ የተፈፀመው ወንጀል በገለልኛና ነፃ አካላት እንዲጣራ በማድረግ ወንጀለኞቹን ለፍርድ ማቅረብ የግድ ይሆናል፡፡ በዚህም ለዘመናት የፈሰሰው የወገናችን እንባ ይታበሳል፤ ዓለማችንም ለወንጀለኞ ማምለጫ ቦታ እንደማይኖራት ይረጋገጣል።

4ኛ. የትግራይ ሰፋሪዎችን መልሶ ማቋቋም

በህወሃት የትግሪያናይዜሽን እኩይ ወጥመድ ተጠልፈው በወለቃይት ጠገዴና ጠለምት አካባቢዎች ሰላማዊና የተደላደለ ኑሮ መኖር የጀመሩትን የትግራይ ሰፋሪዎች ደህንነታቸውና ምቾታቸው ተጠብቆ ይኖሩ ዘንድ መርዳትና ማስቻል። ይኸውም እነዚህ ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ ከትግራይ አካባቢዎች በተለያየ መንገድ መጥተው በዕርስታችን የሰፈሩት የትግራይ ሰፋሪዎች እንደፍላጎታቸው ወደ ትግራይ የመመለስ ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል እንላለን፡፡

በመጨረሻም

ይህ ወቅታዊና ታሪካዊ ሰነድ እንዲዘጋጅ ከጅምሩ ግፊት ያደረጉ፣ በአዘጋጅነት ተመድበው የሰሩ፣ እጅግ ጠቃሚና አስፈላጊ የታሪክ ማስረጃዎችንና ሰነዶችን ያደረሱንና፣ በአጠቃላይ ሙሉ ድጋፋቸውን በመስጠት ከጎናችን ላልተለዩን በሃገር ውስጥና በውጭ የምትገኙ ወገኖቻችን ላቅ ያለ ምስጋናችን ይድረሳችሁ።

በሌላ በኩል በጉዳዩ ያገባናል ያሉ አያሌ ምሁራንና ድርጅቶች የህወሃትንና የተላላኪዎቹን ሴራ ለማጋለጥና ትክክለኛውን ታሪካዊ እውነታ ለኢትዮጵያውያን ለማድረስ ያዘጋጇቸውን ሰነዶች ለጊዜው እንዲያዘገዩልን በጠየቅናቸው መሰረት መልካም ፈቃዳቸውንና ቀና ትብብራቸውን ቸረውናልና ላቅ ያለ ምስጋናችን ይድረስልን።

ይልቁንም የህወሃትና ግፍና ጭካኔ ለወገንና ለዓለም ህብረተሰብ ለማጋለጥ በምናደርገው ትግል ከጎናችን ለተሰለፋችሁና መልእክቶቻችን በወቅቱ ለሚመለከተው ሁሉ ላደረሳችሁልን ድህረገጾች፣ ጋዜጣዎች፣ ሬዲዮኖችና ቴሌቪዥኖች ባጠቃላይ የህዝብ መገናኛ አውታሮች ሁሉ ከፍ ያለው ምስጋናችንና አክብሮታችን ይድረሳችሁ፡፡

ማንኛውንም አስትያየት፣ መርጃ፣ ወይም ጥያቄ በሚከተለው አድራሻ ለአዘጋጆቹ ሊያደርሱን ይችላሉ።

አባይ መንግስቱ፣ ቻላቸው ዓባይ፤ ጐሹ ገብሩና፣ አብዩ በለው

aamg50@yahoo.com

ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር!

ድል ለህዝባችን!

ጥር 19፣ 2008 ዓ.ም

The post ወልቃይት ጠገዴ ማነው? appeared first on Zehabesha Amharic.


ጉድ እኮ ነው! (አንዱዓለም ተፈራ –የእስከመቼ አዘጋጅ)

$
0
0

 

Eskemeche

ሐሙስ፣ ጥር ፲ ፪ ቀን፣ ፳ ፻ ፰ ዓመተ ምህረት

በዚሁ በሳተናው ገጽ፤ የተስፋዬ ገብረአብን፣ የግርማ ካሳን እና የአምሳሉ ገብረኪዳንን ጽሑፍ አነበብኩ። ያነበብኩበት ምክንያት ግልጽ ነው። አንድ ወዳጄ አንብበው ስላለኝ ነበር። በተጨማሪ ደግሞ በተደጋጋሚ በአንድ ርዕስ ላይ ልውውጥ ሲደረግ፤ እኔን ቀልቤን ሳበው። እናም አነበብኩ።

ተስፋዬ ገብረአብ፤ ምንም እንኳ ለኢትዮጵያዊያን አንድነትና ሰላም ቀና አመለካከት የለውም ብዬ አሁንም ባስብም፤ ጥቂት ቁም ነገሮችን ከመሰሪ ተንኮሉ ጋር ደርቶ አቅርቧል። እኒህ ጥቂት ያልኳቸው ቁም ነገሮቹ ሊታዩ የሚገባቸው ስለሆነ፤ እሱ ለኛ ነጋሪ ሆኖ መቅረቡ፤ ትኩረቱ ደርቶ ላቀረባቸው ነገሮቹ ነው ባይ ነኝ። ሆኖም አነበብኩት።

አቶ ግርማ ካሳ ያቀረበው የራሱን አመለካከትና ስለ ተስፋዬ ገብረአብ ጽሑፍ ነበር። የተስፋዬን ጽሑፍ በመተንተን ሂደቱን አሳይቶበታል።

የሠዓሊ አምሳሉ ግ/ኪዳንን ጽሑፍ ጓጉቼ ነበር ያነበብኩት። የግርማ ካሳን ወያኔነት ላውቅ በመቸኮል፤ ሁለቱን ቀድሜ ሳነብ በመጋለብ ነበር። ታዲያ ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ሆኖ አገኘሁት። ምነው ሠዓሊ አምሳሉ! ሊጽፉ የተነሱበት ግርማ ካሳ ለተስፋዬ ገብረአብ የጻፉትን በሚመለከት አልነበረም? ታዲያ ምነው ረሱትና ሌላ ቦታ ገቡ? ከዚህ በፊት ግርማ ካሳ ለጻፈው መልስ መሥጠት ከፈለጉ፤ ለምን በዚያ ርዕስ አላደረጉትም ነበር?

እዚህ ላይ ሁለት አጠቃላይ ችግሮቻችንን በሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን ጽሑፍ አነበብኩ። የመጀመሪያው፤ ማንኛውንም የማንወደውን ጽሑፍ ወያኔ ብሎ መለተሙ ነው። ያሳዝናል። ግለሰቦች ሃሳባቸውን በሚገልጹበት ጊዜኅ አስቀድመን ወያኔ በማለት፤ ግለሰቡንና ያቀረበውን ጽሑፍ አላትሞ መምታት! የደካማ ሰው ግንዛቤ።

ሁለተኛው ደግሞ፤ ፍጹም ግንኙነት በሌላቸው ሁለት ጽሑፎች መካከል፤ የሚፈልጉትን እየመረጡ እንደ አንድ አድርጎ ማቅረብ ነው። ለምን? አሁንም የደካማ ሰው ግንዛቤ። ሃሳብን ከጸሐፊው ጋር የምናያይዝበት ወቅት አለ። ለምሳሌ ተስፋዬ ገብረአብን በሚመለከት፤ በሥልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ አማራንና ኦሮሞን ለማጋጨት የደረሰው መጽሐፍ      ቋሚ ነቀርሳ ነው። እናም ሰውየውን ከዚህ ጽሑፍ አውጥቶ ለይቶ ማስቀመጥ፤ በተለይ ለአንድ ኢትዮጵያዊ ከባድ ነው። እናም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የሚጽፈውን፤ ከዚያ አመለካከቱ አንጥሮ ማውጣት እኔን ቸግሮኛል። በተለይም ኤርትራ ነኝ ብሎ ከወገነ ወዲህ፤ ይሄን ግለሰብ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ በሀገራችን ጉዳይ ቀና አመለካከት ኖሮት ጽሑፍን የማነብለት፤ አፍንጫየን ይዤ ነው።

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን በግርማ ካሳ ላይ የጻፉት አሳዝኖኛል። ግርማ ካሳ ትጥቅ ትግሉን አይደግፍም። ታዲያ ይሄ ወያኔ ያደርገዋል። ከሆነማ እኔንም ሁለት በለኝ። የኢሳያስ አፈወርቂን ተግባርነ ተንኮል ፈጽሜ ከልቤ አላወጣውም። ያ ብቻ አይደለም፤ በአሁኑ የሀገራችን የፖለቲካ ሀቅ፤ የትጥቅ ትግል አደገኛ ነው። በዚህ አመለካከቴ ወያኔ የምትለኝ ከሆነ፤ ይቅናህ።

ወደ ቁም ነገሩ ለመመለስ ይህል፤ ግርማ ካሳ ዶክተር መሳይ ከበደ የጻፉትን በመደገፍ አቅርቧል። በደንብ አንብቦት ከሆነ፤ ዶክተር መሳይ ከበደ እንደ ተስፋዬ ገብረአብ ተመሳሳይ አመለካከት ነው ያላቸው። በኢትዮጵያዊነት ጉዳዮችን ከመመልከትና ትግሉ አንድነት እንዲይዝ ከመጣር ይልቅ፤ ሌሎች የኦሮሞዎችን እንቅስቃሴ ይደግፉ ነው የሚሉት ሁለቱም። ኢትዮጵያዊያን ግን፤ ትግሉ በኢትዮጵያዊያንና በገዥው ቡድን መካከል ነው። እያንዳንዱ ጥያቄ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጥያቄ በመሆኑ፤ በአንድነት የምንነሳበት በመሆኑ፤ ከፋፋይ የሆኑና የኦሮሞ ጥያቄ፤ የሙስሊሞች ጥያቄ የምንለውን እናቁም። እዚህ ላይ ጠላታችን ገዥው ቡድን እንጂ፤ በትግሉ ዙሪያ የተሰባሰብነው እስር በርሳችን አይደለም። የሃሳብ ልዩነት ጠላትነትን ግድ አይልም። የምንለያይበት ከምንስማማበት አንጻር ሲታይ ኢምንት ነው። አሁን ሀገር አድን ላይ ነው ያለነው። አሁን እኔ ልግዛ፣ እኔ ልግዛ፣ እያሉ በድርጅቶቻቸው ዙሪያ ብቻ ተጠምደው፤ ሀገራዊ ጉዳዩን ከሌሎቹ ጋር አብሮ በመፍታት ላይ አለማተኮራቸው ሊያሳስበን ይገባል።

እናም   “ወያኔው ግርማ ካሳ ሆይ! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው” የተሳሰተና አስተማሪ ያልሆነ ጽሑፍ ነው።

 

The post ጉድ እኮ ነው! (አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ) appeared first on Zehabesha Amharic.

ሌሊት በመታን ድንጋይ ቀን አንደገምም! –የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ህብረት

$
0
0

Muslimsየወያኔ መንግሥት የጫነበት የመከራ ቁልል ትኬሻውን እጅግ አላሽቆና አቁስሎ ያንገፈገፈው መሆኑንና ከአሁን ወዲያ ለመሸከም ፈቃደኛ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ በግልጽ እያሳየ ነው። የተነጠቀውን ነፃነቱንና የተዋረደውን ክብሩን ለማስመለስ ቁጣ በተሞላበት እምቢተኝነት ወደ አንድ የፊልሚያ ሜዳ በመተመም ላይ ይገኛል።

የአገሪቱ የፖለቲካ ነፋስ ወትሮ እንደነበረው ወያኔ ወደ ሚፈልገው የሕዝብ ማጥፊያ አቅጣጫ መጓዙ ቀርቶ አሸዋ፣ ጠጠርና ግንድ አዝሎ አዙሪቱ የወያኔን መንግሥት የክፋትና የጭካኔ ድንኳን ካስማ እየነቀነቀ ነው። ከመሠረቱ የተነቃነቀ ደግሞ መገርሰሱ አይቀሬ ነው።

ሙስሊሙ ህብረተሰብ እየተደበደበ፣ እየታሠረና እየተገደለ በህዝባዊ እምቢተኝነት የወጠረውን የትግል ገመድ ሣያረግብ ለመብቱና ለነፃነቱ የሚያደርገው መዋደቅ ዓራተኛ ዓመቱን ዘልቆ ግቡን እስኪመታ ድረስ በመምዘግዘግ ላይ ነው። የኦሮሞ ወገኖቻችን በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ስም በእድገትና ብልፅግና ቋንቋ  ተሽሞንምኖ የቀረበላቸውን መሬት አስነጣቂ፣ ቋንቋና ባህል አውዳሚ የሆነውንና በውስጡ መርዝ የሰነገውን የስንቅ አገልግል አንቋደስም በማለት የወያኔን መንግስት የሚያስርድ የአመፅ እሳት እያቀጣጠሉ ነው። የኦሮሞ ወጣቶች በህልውናቸው ላይ የተቃጣውን አደጋ በነቂስ ወጥቶ በመጋፈጥ ክብራቸውን በደማቸው እየዋጁት ነው።

ሕዝብ ከፊቱ የተጋረጠውን የወያኔን የሃይማኖትና የዘር መለያና መከፋፈያ አጥር ደርምሶ አፍጥጦ የወጣው የተቃውሞ ማዕበል የወያኔን የተንኮል መፈብረኪያ ማዕከሎችን የፊትና የማጀት ሳንቃ መበረጋገድ ጀምሯል። የፍርሃትና የድንጋጤ ላብ እያላበው ያለው ወያኔ መራሹ መንግስት በሸፍጥ የተቆጣጠረውን በትረ- መንግስት ዕድሜ ለማራዘም “ከ50 በላይ የደህንነት አባላት” በተገኙበት “በማስተር ፕላኑ፣ በኑሮ ውድነቱና ከሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ጋር በተያያዘ ህዝቡ በድንገት ወደ አደባባይ ሊወጣ ይችላል” በሚል ፍርሃት የመንግሥት ጆሮ ጠቢዎች ቡድን በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ አስከፊ ደባ እየሸራረቡ የመሆኑ ሚስጥር በገሃድ በቅርቡ ወጥቷል። በዚህም ስብሰባ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ትግል የባቡር ጉዞ ሐዲዱን የሚያስት፣ የሚበትንና ሙስሊሙን ከኦሮሞ ወገኖቹ ጋር በጋራ እንዳይታገል፤ ተነጥሎ እንዲመታና እንዲሸመደመድ የሚያድርግ ቀውጢ የሆነ እቅድ አውጥቷል።

የወጣውም እስትራተጂ ሙስሊሙን ሕብረተሰብ ከኦሮሞ ወገኖቹ ትግል ለማራቅ የታሠሩቱን የሙስሊሙን መሪዎች መፍታትና ይህንንም ለማስፈፀም ከሃገር ውጭ ያለ የሙስሊም ድርጅት በመንግስት ተጋብዞ በታሣሪዎቹ ስም መንግስትን ይቅርታ እንዲጠይቅ ማድረግ ነው። እነዚህ የሚጋበዙ ሰዎች ከኮሙኒቲ ጋር ግንኙነት ያላቸው እንዲሆኑና በእስረኞቹም ላይ በፀጥታ ሃይሎች አልያም ታስረው በተፈቱ ሙስሊሞች በኩል ግፊት ተደርጎባቸው የይቅርታ ሰነድ እንዲፈርሙ። ይህ ጥንቅር የመንግስት እጅ አለበት እንዳይባል

 

ደግሞ የተዘጋጀው ዘጋቢ ደኩሜንታሪ – “የማስጠንቀቂያ ደወል” መሆኑ ነው – ቀደም ብሎ ለሕዝብ እንዲታይ የሚል ነው። በተጨማሪም ከወያኔ መንግስት ጋር ለመተባበር በሽምግልና የሚሄዱት  በዲያስፖራው ሙስሊም ተቀባይነት እንዲያገኙ ከፍተኛ መስተንግዶና አቀባበል በመንግስት እንዲድረግላችውና ጥሩ ሥራ እንደሠሩ ለማስመሰል ሠፊ የሚድያ ሽፋን ተሰጧቸው ብዙ ጋዜጣዊ መግለጫና ቃለ መጠይቅ እንዲያደርጉ ታቅዷል። ስለሆነም የወያኔ ካድሬዎች ይህንን ሴራ ተግባራዊ የሚያደርግ ተባባሪ የዲያስፖራ የሙስሊም ድርጅት በማፈላለግ ሥራ ላይ በዚህ በአካባቢያችን ተጠምደው ከርመዋል። ይህ ምስጢር ይፋ ከወጣ በኋላ በውጭ የሚኖሩ ሙስሊሞችን ብቻ ሳይሆን ክርስቲያን ወገኖቻችንንም ጭምር እያነጋገረ ነው። ይህን በመሰለ በእስልምናና በሙስሊሞች ላይ ሳይሆን በኦሮሞ ሕዝብ ትግል ላይ ጭምር ያነጣጠረ አደጋ ከወያኔ መንግስት ጋር በማበር ተግባራዊ ለማድረግ በዚህ ወጥመድ የሚገባ የሙስሊም ድርጅት ወይም ቡድን ማን ይሆን እያሉ ለትግሉ የቆሙ ወገኖች ሁሉ እያጠያየቁ ነው።

ከዚህ በፊት ሕዝብ ያልመከረበት፣ ያልተጠናና የዲያስፖራ ሙስሊሞች የተቃወሙት የሽምግልና ሙከራ በሚዘገንን ውርደት እንዳከተመ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው። ከዚያ እፍረት ሕዝቡ ሣያገግም ከውርደት አልፎ ጣራ የነካ ክህደት ለማሳካት ከወያኔ ሰላዮች ጋር የሚያብር ድርጅትም ሆነ ቡድን ወይም ግለሰብ በዚህ ሳቢያ በሙስሊሙ ህብረተሰብና በትግሉ ላይ ለሚደርሰው አደጋ ከተጠያቂነት እንደማያመልጥና በዝምታም ሕዝቡ እንደማያልፈው ከወዲሁ ቢያጤን  ይበጃዋል። ለዚህም ነው ሌሊት በመታን ድንጋይ ቀን አንደገምም የምንለው።

“ኮሚቴዎቻችን ነፃ ናቸው” የሚለው የሙስሊሙ ትልቁ መፈክር፣ ከመጀመሪያው መታሰር አልነበረባቸውም ከማለት የዘለለ ሌላ ትርጉም የለውም። ለአንዲት ጀምበር እሥር ቤት እንዲቆዩም አንሻም። ትልቁና ወሳኙ የወያኔ መንግስት መፍታት ያለበት ያለምንም ቅድመሁኔታ ኮሚቴዎቻችን የታሰሩባቸውን ሶስቱን ጥያቄዎች ሲሆን ማነጋገርም ያለበት አለአግባብ ያሰራቸውን የሕዝበ ሙስሊሙን ወኪሎች እንጂ ከዲያስፖራ የመለመላቸውን የአንድ ድርጅት አመራር አባሎች ወይም ግለሰቦች አይደለም። የኢትዮጵያ ሙስሊሞችም ሆነ የሌሎች ወገኖቻችን  ችግር ሊፈታ የሚችለው በአጠቃላይ በሃገሪቱ ላይ ያንሰራፋው “ብሔራዊ ጭቆና” ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት ሲያገኝ ብቻ ነው። የሙስሊሙ ሕብረተሰብ ችግር ተቀርፎ ለብቻው መፍትሄ ሊያገኝ ይችላል በሚል የቅዥት ባሕር ውስጥ እንዳንዋኝ ባለፈው አራት ዓመት ከትግላችን ብዙ ተምረናል። የመንግስት ትልቁ ልፋት የነበረው የተጠየቁትን ጥያቄዎች ወደ ጎን አሽቀንጥሮ ስለመሪዎቻችን ነታሰር ብቻ ትኩረት እንድንሰጥ ነበር። ያ ሁሉ መስዋእትነት የተከፈለው ለዘለቄታ ነፃነት ነው። አራት ዓመት ሙሉ አንዲት የሕዝብ ጥያቄ ሳይመልስ የደበደበውን፣ ያሠረውና የገደለውን ሕዝብ ይቅርታ ጠይቁኝ ማለት ገደብ የለሽ ድፍረት ከመሆኑም በላይ የሚያመላክተን ወያኔን ማመን ቀብሮ መሆኑን ነው።

የአገር ቤቱና የዲያስፖራው ሙስሊም ህብረተሰብ መልሶና መላልሶ አበክሮ የገለፀው ነገር ቢኖር የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የጠየቁትና ደማቸውን ያፈሰሱለት ሶስት ጥያቄዎችና ከዚያ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሁሉን አቀፍ የሆኑ የመብትና የነፃነት ጥያቄዎች እስካልተመለሱ ድረስ፣ በተለይም “ብሔራዊ ጭቆና” ከሙስሊሞች  ጫንቃ ላይ እስካልወረደ ድረስ ትግሉ እንደሚቀጥል ነው። በሽምግልና ሽፋን “ለብሔራዊ ነፃነት” የሚደረገውን የሞትና ሽረት ፊልሚያ ለመቀልበስ የተወጠነው ሴራ መክሸፍ ይኖርበታል። ከዲያስፖራ ሽማግሌ ሆነን ወደአገርቤት እንሄዳለን የሚሉ ካሉ ግን የሙስሊሙ መደብደቢያ ዱላ፣

 

ድንጋይና መቀፍደጃ ስንሠለት ለወያኔ የሚያቀብሉ፣ ራሳቸውን ፀረ ኢስላምና ፀረ ሙስሊሞች ጎራ የደባለቁ፣ ሽማግሌ ሣይሆኑ ሸንጋዮች፣ ከሀዲዎችና አደርባዮች ናቸው እንላለን። “ኮሚቴዎቻችን ነፃ ናቸው” ስንል ቅንጣት ያክል ወንጀል ያልፈፀሙ ንፁሐንና ኡስታዞዛችን እንቁዎቻችን ናቸው ማለታችን ነው። ግልፅና

ግልፅ ኣቋም። ሽማግሌ ይቅርታ የሚጠይቀው ለቀጠፈ፣ በሰራው ሥራ ላፈረና፣ ለዘረፈ ማጅራት መቺ ወንጀለኛ እንጂ ለሃቀኞች አይደለም። አሚሮቻችን ወንጀለኛ አልነበሩም፣ አሁንም አይደሉም። ይቅርታ ጠያቂ መሆን ያለበት ዜጎችን ደብድቦ፣ አስሮ፣ ንፁሕ ደም ያፈሰሰው ጨቋኙ የወያኔ መንግስት እንጂ የተገላቢጦሽ ሊሆን አይችልም።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጉዳይ የሁሉም ሙስሊም ጉዳይ ነው። የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጉዳይ ነው። በዚህ ዙሪያ የሚደረጉ ክንዋኔዎች ለሁሉ ግልፅና ሕዝብ ያወቀው መሆን አለበት። ሕዝቡም ማወቅ ያለበት፣ ነገሮች ተበላሽተው ከወደቅንና ከተዋረድን በኃላ ሊሆን አይገባውም። ካለፈው ተሞክሮ ትምህርት መገብየትና ላንደግመውም መጠንቀቅ አለብን።

ሐቁን ለመናገር፣ ይህ አዲሱ የወያኔ የሽምግልና ጥሪ የሰላም ፈላጊነት ሳይሆን የድረሱልኝ የጭንቀት ዋይታ ነው። ይህን የወያኔን የደባ አመጣጥ ለወገን ለአገርና ለእምነትና ነፃነት የሚቆረቆር ሁሉ በአይነ ቁረኛ መከታተል አለበት። የወያኔን የሥልጣን ዘመን ለማራዘም እየተደረጉ ባሉት ሙከራዎች እንዲተባበሩ ግብዣ የተደረገላቸው ወይም የሚደረግላቸው ካሉ ከዚህ ትልቅ ‘ፊትና’ ወይም ችግር ከሚያስከትል መቅሰፍት እንዲታቀቡና አካሄዳቸውንና አመለካከታቸውን  እንዲፈትሹ በጥብቅ እናሳስባቸዋለን። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በደልና ግፍን ለማስወገድና ሃቅን ለማንገሥ ከኦሮሞ ወንድሞቻችን ጎን ተሰልፈው ትግሉን በያሉበት የሚችሉትን በማበርከት እንዲያጧጥፉና እስከ ድል ደጃፍ እንዲገፉበት የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ሕብረት አጥብቆ የጠይቃል።

 

ትግላችን እስከድል ደጃፍ በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!

አላሁ አክበር!

የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ሕብረት

 

 

The post ሌሊት በመታን ድንጋይ ቀን አንደገምም! – የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ህብረት appeared first on Zehabesha Amharic.

በጆርጃ –አትላንታ እና አካባቢው ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ጥሪ ቀርቦላችኋል

ቴዲ አፍሮ እና አብይ ላቀው ለኮራ የሙዚቃ አዋርድ ታጭተዋል |የሁላችንንም ድምጽ ይፈልጋሉ –እንምረጥ

$
0
0

teddy afro and abby Lakew

(ዘ-ሐበሻ) አድናቂዎቹ የፍቅር ንጉሥ እያሉ የሚያሞካሹት ድምፃዊው ቴዲ አፍሮ እና በ ቅርቡ እንደገና ‘የኔ ሐበሻ’ አዲስ ነጠላ ዜማዋን የለቀቀችው ድምፃዊት አብይ ላቀው ለታዋቂው የኮራ የሙዚቃ አዋርድ እጩ ሆነው ቀረቡ:: ሁለቱ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች ለዚህ ክብር የበቁት ሃገራችን ኢትዮጵያን ወክለው በመሆኑ የሁላችንም ድምጽ አስፈላጊ ነው::

የሌሎች ሃገራት ሕዝቦች የራሳቸው አርቲስት እንዲመረጥ ቅስቀሳ ከማድረግም በላይ በመምረጥም ላይ ይገኛሉ:: ከጃንዋሪ 20, 2016 ጀምሮ ለሕዝብ ይፋ የሆነውና ሕዝቡም በመምረጥ ላይ የሚገኝበት ይኸው የኮራ አዋርድ ቴዲ አፍሮን በምርጥ ዝነኛ ድምጻዊ (LEGENDARY AWARD) የውድድር ካታጎሪ እንዲሁም አብይ ላቀውን በምርጥ የሴት የባህል ድምፃዊነት (Best Traditional Female Artist) ካታጎሪ አብይ ላቀው ታጭተዋል::

የኮራ አዋርድ ከ55 ቀናት በኋላ አሸናፊዎች የሚታወቁ ሲሆን ከዚያ በፊት ግን ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያውያን ወዳጆች ለሁለቱ ድምጻውያን በጽሁፍ መልዕክት ድምፃቸውን መስጠት ይችላሉ::

+248984000 ስልክ ቁጥሩ ሲሆን ለአብይ ላቀው KORA 74 የሚለውን ቴክስት በማድረግ መምረጥ ይቻላል::
እንዲሁም ለቴዲ አፍሮ በተጠቀሰው ስልክ ቁጥር KORA 156 በማለት ቴክስት በማድረግ መምረጥ ይቻላል:: አስታውሱ ለሁለቱም ድምፃውያን ድምጽ መስጠት ይቻላል – የዜግነት ግዴታዎን ይወጡ::

INTERNATIONAL VOTING, SMS YOUR ARTIST’S VOTING CODE TO +248984000

Teddy Afro: KORA 156

Abby Lakew: KORA 74

ለበለጠ መረጃ እንዴት መምረጥ እንደሚችሉ ለማወቅ
http://www.koraawards.com/en/news/how-to-vote-for-your-favourite-artists/#prettyPhoto

The post ቴዲ አፍሮ እና አብይ ላቀው ለኮራ የሙዚቃ አዋርድ ታጭተዋል | የሁላችንንም ድምጽ ይፈልጋሉ – እንምረጥ appeared first on Zehabesha Amharic.

በሾላ ገበያ የእሳት አደጋ ተነስቶ ሱቆች ነደዱ |አጭር የቃጠሎውን ቪዲዮ ይዘናል

$
0
0


(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ በተለምዶ ስሙ ሾላ ገበያ በሚባለው አካባቢ ዛሬ እኩለ ቀን አካባቢ በተነሳ ቃጠሎ ሱቆች መንደዳቸው ተሰማ:: እንደ ዘ-ሐበሻ የአዲስ አበባ ዘጋቢዎች ከሆነ በሾላ ገበያ ፍራሽ ተራ አካባቢ ሱቆች በቃጠሎው ነደዋል::

በተለይ ፍራሽ ተራ አካባቢ ያሉ አንዳንድ እሳቱን ሊያባብሱ የሚችሉ ነገሮች ለ እሳቱ መስፋፋት አስተዋጽኦ ቢያደርጉም የአካባቢው ነዋሪም እሳቱን ሊያባብሱ የሚችሉ አንዳንድ እቃዎች ሲያሸሽ እንደነበር ገልጸዋል:: የአዲስ አበባ እሳት አደጋ ሱቆች ከነደዱ በኋላ አደጋው እንዳይስፋፋ የማጥፋት ሥራ እንደሰራ የሚገልጹት የዓይን እማኞች በሰው እና በሕይወት ላይ ጉዳት ስለመድረሱ ማስረጃ እንዳላገኙ ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::

በሾላ ገበያ ፍራሽ ተራ አካባቢ የተነሳው ቃጠሎ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ንብረቶችን ቢያወድምም ትክክለኛው ቁጥር ግን አልታወቀም::

የዚህ የእሳት ቃጠሎ መነሻ አልታወቀም:: ሆኖም ግን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት አመራሮች ከዚህ ቀደም በተለያዩ ቦታዎች ሊያስነሳቸውና ለሌላ ሰው ቦታውን ሊሸጠው የሚፈልገውን ቦታ የ እሳት አደጋ በማስነሳት ወንጀል ሲወነጀሉ መቆየታቸው ይታወሳል::
shola

The post በሾላ ገበያ የእሳት አደጋ ተነስቶ ሱቆች ነደዱ | አጭር የቃጠሎውን ቪዲዮ ይዘናል appeared first on Zehabesha Amharic.

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት:- ፀረ-ወያኔ አቋም ለአላቸው የኢትዮጵያውያን የፖለቲካ፣ የሲቪክ እና የሙያ ማኅበራት በሙሉ –መነሻ የመግባቢያ ኃሣብ ስለማቅረብ

$
0
0

ሐሙስ ጥር ፲፱ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ.ም. (Thursday January 28, 2016)                                                                

ሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት፣ 

 ፀረ-ወያኔ አቋም ለአላቸው የኢትዮጵያውያን የፖለቲካ፣ የሲቪክ እና የሙያ ማኅበራት በሙሉ

በያሉበት

 

ጉዳዩ፦ መነሻ የመግባቢያ ኃሣብ ስለማቅረብ፦ እስከ አንድነት ለመድረስ የሚያስችል ውጤታማ ትብብር ለማድረግ መከተል ስለሚገባን አካሄድ፤ 

 moresh

ማናችንም እንደምንገነዘበው፣ ባለፉት 40 እና 50 ዓመታት ኢትዮጵያውያን ስንደራጅ የኖርነው በልዩነቶቻችን ላይ ባተኮሩ ዓላማዎች ዙሪያ ነው።ልዩነቶቻችን ደግሞ ከርዕዮተ-ዓለም ባሻገር፣ በነገድ፣ በጎጥ እና በኃይማኖት ጭምር ያጠነጠኑ በመሆናቸው፣ አንድነታችንን አሳሳቢ ደረጃ ላይ አድርሶታል። ከሁሉም በላይ፣ የትግሬ-ወያኔ በባዕዳን ድጋፍ ተበረታትቶ፣ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. የፖለቲካ ሥልጣን ሲጨብጥ፣ ያስተጋባው የዲሞክራሲ ቀቢፀ-ተስፋ እውነት መስሏቸው የተከተሉት ወገኖች አይጠፉም። ሆኖም ይህ ፀረ-ኢትዮጵያ ቡድን በተግባር ሲያከናውን የሚታየው፥ የቋንቋ ፣ የነገድ ፣ የጎሣ ፣ የዘር ፣ የኃይማኖት ፣ ወዘተርፈ ልዩነቶችን መሠረት አድርጎ ሕዝቡ ለዘመናት ገንብቶት በኖረው ኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ ግልጽ የጥፋት ዘመቻ ማካሄድን ነው። የትግሬ-ወያኔ ባለፉት 25 ዓመታት ውስጥ በአካሄደው የዘር ልዩነት ፖለቲካ ግፊት፣ ሕዝቡ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን ችላ እያለ፣ በቋንቋ ማንነቱ ዙሪያ ብቻ እንዲያስብ እና እንዲደራጅ አድርጓል። በዚህም ምክንያት ለሕዝቡ አንድነት ጌጥ እና ውበት፣ ጥንካሬ እና ልዩ መታወቂያ የሆኑት ነባራዊ ልዩነቶች የጠብ እና የብጥብጥ መነሻዎች ሆነዋል። በዚህ ረገድ የአያሌ ዜጎች ሕይዎት መጥፋቱን፣ ንብረት መውደሙን እናውቃለን። በተለይም ኢትዮጵያውያን ዐማሮች የአማርኛ ቋንቋ በመናገራቸው ብቻ ለዘመናት ከኖሩበት አካባቢ ተለይተው ሀብት ንብረታቸውን እየተዘረፉ መባረራቸውን ማስታወስ ይበቃል።  በዐማራ፣ በአኙዋክ ፣ በሶማሌ እና በሌሎች ነገዶች ተወላጆች ላይ የሚደርሰው የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ሊገታ አለመቻሉ  የአደባባይ ምስጢር ነው። ስለዚህ ይህ ድርጊት እየተባባሰ በመሄድ ላይ ስለሆነ፣ አፋጣኝ እና መሠረታዊ መፍትሔ የሚሻ ጉዳይ ነው።

የትግሬ ወያኔው አገዛዝ በሥልጣን ላይ ሊቆይ የሚችለው፣ ፍትሐዊ አስተዳደርን በማራመድ ሳይሆን፣ የጀመረውን  የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲውን እያራቀቀ በመሄድ ብቻ መሆኑ ከእንግዲህ ሊያጠያይቅአይችልም። ስለሆነም፣ ይህን  የትግሬ ወያኔውን አገዛዝ በጠመንጃ ኃይል ከጨበጠው የፖለቲካ ሥልጣን በእርግጠኝነት በማላቀቅ አሽቀንጥሮ  ለመጣል ከኢትዮጵያውያን አንድነት የተሻለ አስተማማኝ መሣሪያ አይኖርም። ለዚህ ደግሞ፣ እስካሁን የተጓዝንበትን የልዩነት ጉዞ መተው፣  በኢትዮጵያዊነት አገራዊ ስሜት በአንድነት መቆም ያስፈልጋል። ስለሆነም ከልዩነቶቻችን ይልቅ በአንድነታችን ላይ አትኩረን በኅብረት መንቀሳቀስ አማራጭ አይኖረውም  አንድነት ኃይል ነው፤ ጥንካሬ ነው፤ የማድረግ ብቃት ማረጋገጫ ነው።

 ሰሞኑን ከየአቅጣጫው የሚሰሙት የ«እንተባበር» እና የ«አንድነት» ጥሪዎች ወቅታዊ ስለሆኑ አዎንታዊ ምላሽ ሊያገኙ ይገባል። ለተግባራዊነታቸው አስተማማኝ መሠረት ለመጣል ደግሞ፣  «በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል» የሚሉ ወገኖችን ሁሉ አካትቶ፣ ለሚታሰበው አንድነት ጉዞ ፈር ቀዳጅ የሆነ የምክክር መድረክ ይዋል ይደር ሳይባል መፈጠር ይኖርበታል። ለዚህ ሂደት ውጤታማነት ተሞክረው ለግብ ካልበቁ የስምምነት ሙከራዎች ትምህርት ሊቀሰም ይገባል። እንዳለፉት ስምምነቶች ሁሉ የተፈረመባቸው ቀለም ሳይደርቅ ወደ ነበሩበት የመመለስ ሁኔታ እንዳይገጥም፣ የተስማሚ ወገኖችን ይሁንታ ያገኘ የመግባቢያ ሰነድ ሊዘጋጅ ይገባል። ይህ ሰነድ ወደ ዋናዎቹ የስምምነት ጉዳዮች ለመግባት ተስማሚዎቹ ወገኖች አምነውና ዐውቀው፣ የውዴታ ግዴታ የሚገቡበት አስገዳጅ እና ተፈጻሚነት ያለው ይዘት ሊኖረው ይገባል። ሰነዱ ከተዘጋጀ እና ሁሉም አንድነት ፈላጊዎች ተስማምተው ከፈረሙበት በኋላ፣ ለሕዝብ ይፋ ሆኖ ሂደቱን ሕዝቡ በባለቤትነት እንዲከታተለው እና ተስማሚ ወገኖችም የተጠያቂነትና የኃላፊነት ስሜት እንዲያድርባቸው  ማድረግ ይገባል። 

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት አገራችን ኢትዮጵያ የገባችበትን አሳሳቢ ሁኔታ በመግለጽ እና በአስቸኳይ ቢወሰድ አደጋውን ሊያስወግድ ይችላል ብሎ ያመነበትን የመፍትሔ ኃሣብ በመጠቆም ከዚህ በላይ የሰፈረውን አቅርቧል። ለአፈጻጸም ይረዳ ዘንድም፣ ከዚህ በታች የተመለከቱት አስፈላጊ እርምጃዎች በውል እየተጤኑ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያሳስባል።

1.         ስምምነቱን የሚመራ ኮሚቴ ሊመሠርት የሚችል የጋራ መድረክ መፍጠር

(ሀ)        ይህ መድረክ ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ መጠራት ይኖርበታል። 

(ለ)        መድረኩ ኃላፊነት በወሰዱ ወይም በሚወስዱ ድርጅቶች አማካኝነት ይጠራል።  

(ሐ)       ለመድረኩ እያንዳንዱ በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ የፖለቲካ፣ የሲቪክ ና የሙያ ማኅበራት በአምስት በአምስት ሰዎች ይወከላሉ፤ ታዋቂ ግለሰቦች እና የኃይማኖት ድርጅቶች እያንዳንዳቸው በአንድ  ሰው የሚወከሉ ይሆናል።

(መ)       የመድረኩ ኃላፊነትም ለቀረበው የአንድነት ጥሪ አዎንታዊ መልስ ለመስጠት የሚያስችል አስማሚ ኮሚቴ መመሥረት እና አስማሚ ኮሚቴው ሊያተኩርባቸው በሚገባቸው የመግባቢያ ሰነዶች ይዘት ላይ ለመወሰን ይሆናል።

2          የአስማሚ ኮሚቴ አባሎች አመራረጥ

(ሀ)        በተዘጋጀው መድረክ በተገኙ አባሎች አማካኝነት በሚደረግ ውይይት ቁጥራቸው ከአሥራ አምስት እስከ ሃያ አንድ የሚሆኑ የኮሚቴ አባሎችን የያዘ ኮሚቴ መመሥረት ።  

(ለ)        የኮሚቴ አባላቱም ከሚከተሉት አንዱን ወይም ከሁሉም በማቀላቀል መመሥረት ይቻላል። 

3        የኮሚቴው አባላት ይዘት

(ሀ)        በሁሉም ተስማሚዎች አመኔታና አክብሮት የተቸራቸው ታዋቂ ኢትዮጵያውያን ግለሰቦች፣ 

(ለ)        በኢትዮጵያ ካሉት ነገዶች እና ጎሣዎች ከአምስት መቶ ሺህ ሕዝብ በላይ ያላቸው የነገድ እና የጎሳ ተወካዮች፤

(ሐ)       ከኢትዮጵያ ታላላቅ ኃይማኖቶች ታዋቂ አባቶች ፤፤ 

 

4        የቴክኒክ የሥራ ቡድን ስለ ማቋቋም

(ሀ)        ለሚቋቋመው አስማሚ ኮሚቴ ሥራ መቃናት እና መቀላጠፍ የሚያግዙ በሁሉም ተስማሚ ወገኖች ይሁንታ ያገኙ፣ ወይም ከተስማሚ ወገኖች ተመጣጣኝ ውክልና ያላቸው የቴክኒክ የሥራ ቡድኖች መቋቋም አለባቸው።

(ለ)        የእነዚህ የሥራ ቡድኖች ተግባርና ኃላፊነታነታው በግልጽ የሰፈረ፣ ከአስማሚ ኮሚቴው ጋር ሊኖራቸው የሚችለው የሥራ ግንኙነት በማያሻማ መንገድ የተገለጸ መሆን ይኖርበታል። 

5          የኮሚቴው የሥራ ጊዜ እና የአፈጻጸም ጉዳዮች

(ሀ)        አስማሚ ኮሚቴው በሥራ ላይ የሚቆይበት ጊዜ የተወሰነ መሆን ይኖርበታል። 

(ለ)        ኮሚቴው ዝርዝር የሥራ አፈጻጸም መመሪያዎችን ያዘጋጃል።

(ሐ)       ኮሚቴው የተሳታፊ ድርጅቶችን እና ና ግለሰቦችን አመራረጥ መስፈርት ያዘጋጃል።

(መ)       የስምምነቱ ሥነሥርዓት የሚገዛበት ደንብ እና  የአሠራር ቅደም ተከተል መመሪያዎች በኮሚቴው ይዘጋጃሉ።     

6          ትኩረት የሚጠይቁ ሌሎች ጉዳዮች

(ሀ)        ተስማሚዎቹ ወገኖች ከስምምነት ከደረሱ በኋላ ማከናወን ያለባቸውን አንኳር አገራዊ ጉዳዮችን ለይቶ ማስቀመጥ፣

(ለ)        ከወያኔ ውድቀት በኋላ ኢትዮጵያ ልትከተለው ስለሚገባ የአስተዳደር እና የፖለቲካ ሥርዓት በአገር አንድነት ከተስማሙ ወገኖች  የቀረቡ ኃሣቦችን  ማቀናጀት፤

(ሐ)       ስምምነቱ የሚካሄድበት አገር፣ ከተማ እና ጊዜ መወሰን፤

(መ)       በመግባቢያ ሰነዱ የተስማሙ ድርጅቶችን፣ ቡድኖችን፣ ስብስቦችን እና ማኅበሮችን ማንነትና የሚወክሏቸውን ሰዎች ማንነት ለይቶ መመዝገብ፤

(ሠ)       የስምምነቱ ሂደት እና ውጤት የሚገለጽባቸውን ቋንቋዎች መወሰን፤

(ረ)        ስምምነቱ በሚገለጽባቸው ቋንቋዎች መካከል የትርጉም ልዩነት ቢከሰት፣ በዋናነት የሚወሰደውን ቋንቋ ለይቶ መወሰን፤

7            ተጨማሪ ማሳሰቢያ

(ሀ)        አንድነት የሚፈጥሩ ቡድኖች የሚለያዩባቸው አቋሞች ቢኖሯቸውም የአገር አንድነትን በተመለከተ የሚጋሯቸው እሴቶች ምን እንደሆኑ ተለይተው መቀመጥ ይኖርባቸዋል።

(ለ)        በመስማሚያው ወይም መግባቢያው ሰነዱ እና በአሠራሩም ቅደም ተከተል ስምምነት ከተደረገ በኋላ፣ ወደ ዋናው ጉዳይ ሲገባ፣ ስምምነቱ በቀና እና በታሰበው ጊዜ እንዲከናወን፣ ተሳታፊዎች «አሉኝ» የሚሏቸውን የአቋም ጥያቄዎች በክብደታቸው ቅደም ተከተል መሠረት አስማሚው ኮሚቴው በሚወስነው የጊዜ ገደብ ውስጥ በጽሑፍ እንዲያቀርቡ ማድረግ ሥራን ያቀላጥፋል። ከዚህ በተጨማሪ ስምምነቱም በእነዚያ ነጥቦች ዙሪያ ብቻ እንዲያተኩር መወሰኑ በውይይቱ ወቅት ሰጥቶ ለመቀበልም ሆነ፣ «ይህ ካልሆነ» ብሎ አቋምን አጠንክሮ ለመጓዝ ይረዳል።

እነዚህና መሰል ጉዳዮችን የሚያካትት ሰነድ መዘጋጀት ለሚታሰበው አንድነትና የትብብር ጥሪ ውጤታማነት ያገለግላል ብሎ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ያምናል።

The post ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት:- ፀረ-ወያኔ አቋም ለአላቸው የኢትዮጵያውያን የፖለቲካ፣ የሲቪክ እና የሙያ ማኅበራት በሙሉ – መነሻ የመግባቢያ ኃሣብ ስለማቅረብ appeared first on Zehabesha Amharic.

“ለጋዜጣ ጉዳዩን ማቅረብ የተፈለገው ከቀናነት በመነጨ ሳይሆን፤ በማር የተለወሰ መርዝ ነው” –አቶ አበራ ገብሩ

$
0
0

ሰንደቅ

ባሳለፍነው ሳምንት የሰማያዊ ፓርቲ የዲስፒሊን ኮሚቴ አንድ ሥራአስፈፃሚ እና በሶስት የምክር ቤት አባላት ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔ በመቃወም የፓርቲው ሥራአስፈፃሚ መግለጫ ማውጣቱ የሚብስ ነው። ይህንንም ተከትሎ የኦዲትና የምርመራ ኮሚሽን የመጨረሻ ውሳኔ እየተጠበቀ መሆንም መዘገባችን ይታወቃል።

ዝግጅት ክፍላችንም የሰማያዊ ፓርቲ የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን ሰብሳቢ የሆኑትን አቶ አበራ ገብሩ አነጋግረናቸዋል። ከሳቸው ጋር ያደረግነው ሰፋ ያለ ቃለ ምልልስን በዚህ መልኩ አቅርበነዋል።

ሰንደቅ፡- ባለፈው ሳምንት የፓርቲያችሁ ሥራአስፈፃሚ የዲሲፕሊን እርምጃ የተወሰደባቸውን አራት አባላት ውሳኔ እንደማይቀበል በይፋ አስታውቋል። በእነዚህ ሁለት አካላት የተፈጠረውን አለመግባባት ኦዲትና ምርመራ ኮሚሽኑ ለመፍታት ምን እያደረገ ይገኛል?

አቶ አበራ፡- በመጀመሪያ ደረጃ በዚሁ ጋዜጣ ላይ የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽኑ ውሳኔ እየተጠበቀ ነው በሚል የዘገባችሁት ዜና መነሻውን እናንተ ብቻ ነው የምታውቁት። መታወቅ ያለበት በአሁን ሰዓት ኦዲት ኮሚሽኑ እየተመለከተው የሚገኝ የይግባኝ አንዳችም ጥያቄ የለም። ይህ በሆነበት ሁኔታ ምንድን ነው እኛ የምንመለከተው።

ሰንደቅ፡- በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ሥራአስፈፃሚው እና በምክር ቤቱ መካከል ልዩነቶች ሲፈጠሩ የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጠው ኦዲትና ምርመራ ኮሚሽኑ መሆኑን ይደነግጋል። ስለዚህም ሥራአስፈፃሚው የዲሲፕሊን ኮሚቴውን ውሳኔ ውድቅ ማድረጉ እና የምክር ቤቱን የክስ ይዘት አልቀበልም ማለቱን የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽኑ ይግባይ ስላልቀረበለት ብቻ በዝምታ ያልፈዋል ማለት ነው?

አቶ አበራ፡- ሥራ አስፈፃሚው በማያገባውና በማይመለከተው ሥልጣን እና ተግባር ውስጥ ነው የተዘፈቀው። ምክንያቱም ሥራአስፈፃሚው ከሳሽም ተከሳሽም ባልሆነበት ሁኔታ ከሳሽም ተከሳሽም ራሳቸውን መከላከል በሚችሉበት ሁኔታ ውሳኔውን ተቀባይም ነሺም የሆነበት መንገድ ሕገወጥ ነው። በደንባችን መሰረት የዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ የመጨረሻ ውሳኔ ተደርጎ የሚወሰድ አይደለም። የይግባኝ አቀራረብ ደንብና ስርዓት በፓርቲው ውስጥ አለ። ይህ ሕጋዊ መስመር ብቻ ነው የተፈጠሩ የውሳኔ ልዩነቶች መመልከት የሚችለው። ከዚህ ውጪ ያለው አካሄድ በሕግም በሌላም መመዘኛ ተቀባይነት የለውም።

እዚህ ላይ ግልፅ መሆን ያለበት የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴውን ውሳኔ የማየት ስልጣን ብቻ ሳይሆን አስፈላጊ ነው ብሎ ካመነ በፓርቲው በየትኛውም መዋቅር ስር የሚገኙ ሰነዶችን ጠይቆ ምርመራ የማካሄድ ስልጣን አለው። ስለዚህም ሥራአስፈፃሚው በዲሲፕሊን ኮሚቴው አካሄዶች እና በክሱ ይዘት ቅሬታዎች አለኝ ቢል እንኳን ለኮሚሽኑ ጥያቄውን ማቅረብ ይችል ነበር። ምክንያቱን በማናውቀው መንገድ ይህን ሕገወጥ መንገድ ለምን እንደመረጡ ግን አልገባንም።

ሰንደቅ፡– እርስዎ ያሉት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በአሁን ሰዓት በፓርቲው ውስጥ የተፈጠረ ልዩነት መኖሩ የአደባባይ እውነት ነው። ይህ በሆነበት ሁኔታ ይግባኝ አልቀረበልንም በሚል ምክንያት ብቻ ጉዳዩን አቅርቦ አለመመልከት ከኃላፊነት መሸሸ ወይም በቀጣይ ሊያስጠይቃችሁ የሚችል ነገር አይኖርም ብሎ መውሰድ ይቻላል?

አቶ አበራ፡- መጠንቀቅ ያለብን እየተባለ ያለው ወይም ከሕግ አግባብ ውጪ ለአደባባይ የቀረበው ነገር ምን ያህል እውነትነት አለው? ይህንን ጥያቄ መመለስ ስንችል ነው ፓርቲው ውስጥ ችግር አለ ወይም የለም ለሚለው ምላሽ የሚቀርበው። በፓርቲው ውስጥ የተለመደ የቅሬታ አቀራረብ እያለ ጉዳዩን ወደ ጋዜጣ ይዞ መውጣት ለምን አስፈለጋቸው? ቅሬታ ያለው አካል ቅሬታውን ለኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን ለምን አላቀረበም?

ዲሲፕሊን ኮሚቴው ውሳኔውን የሰጠሁት ኮረም ሞልቶ ባደረግነው ውይይት መነሻ ነው የሚል ምላሽ አቅርቧል። የኮሚቴው ውሳኔ ምንም ይሁን ምንም ቅሬታ ያለው ወገን ለኮሚሽኑ ይዞ መቅረብ ነበረበት እንጂ፣ በጋዜጣ ላይ ጉዳዩን ይዞ ብቅ ማለቱ በራሱ የዲሲፕሊን ግድፈት ተደርጎ የሚወሰድ ነው። በነገራችን ላይ አይደለም በዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ ላይ በኮሚሽኑ ውሳኔን አሰጣጥ ላይ ቅሬታ አለኝ የሚል አካል ካለ ጉዳዩን ወደ መደበኛ ፍርድ ቤቶች አቅርቦ መዳኘት የሚችልበት አሰራር በፓርቲያችን ውስጥ አለ። ስለዚህም በእኛ አረዳድ ጉዳዩን በሕግ አግባብ ሳይኬድበት ለጋዜጣ ማቅረብ የተፈለገው ከቀናነት የመነጨ ሳይሆን፣ በማር የተለወሰ መርዝ አድርገን ነው የምንወስደው።

ሰንደቅ፡- በነገራችን ላይ በዚህ ጋዜጣ ከመስተናገዱ በፊት፣ በፓርቲያችሁ ልሳን ጉዳዩ መስተናገዱንስ እንዴት ያዩታል?

አቶ አበራ፡- በፓርቲያችን ልሳን ላይ የወጣበት እና በሌሎች ጋዜጦች ላይ የወጣበት ጊዜ በጣም ተቀራራቢ ነው። እያልን ያለነው በፓርቲያችን ልሳንም ሆነ በግል ጋዜጦች የተስተናገደበት ሁኔታ ሕግን የተከተለ አይደለም። ቁምነገሩ የአሰራር ጥያቄ እንጂ ጉዳዩ የተስተናገደበት መገናኛ ብዙሃን አይደለም። በሁለቱም መስተናገዱ ስህተት ነው።

ሌላው ከተሰጠው ሥልጣን ውጪ የዲሲፕሊን ኮሚቴውን ውሳኔ አልቀበልም በማለት ሥራአስፈፃሚው በፓርቲው ልሳንና በሌሎች መገናኛዎች የተዘገበው ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ኮሚሽኑ መግለጫ አውጥቷል። ለባለድርሻ አካላትም እንዲደርስም ይህ መግለጫ ተበትኗል። ፓርቲውም በሕግ እንጂ በተወሰኑ ሰዎች ፍላጎት እንደማይመራ መታወቅ አለበት።

ሰንደቅ፡- የአንድ ፖለቲካ ፓርቲ ከፍተኛው አስፈፃሚ አካል፣ ሥራአስፈፃሚው መሆኑ ይታወቃል። ይህ አካል ስራዎቹን በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ያከናውናል ተብሎ ይገመታል። ከዚህ አንፃር እርስዎም ከላይ እንዳሰፈሩት፣ ሥራአስፈፃሚ ከስልጣኑ በላይ በመሄድ የዲሲፕሊን ኮሚቴውን ውሳኔ አልቀበልም ያለበት ፍላጎት ምንድን ነው ብላችሁ ትወስዳላችሁ?

አቶ አበራ፡- ፍላጎታቸው የሚመስለኝ በቀጣይ በሌሎች አመራሮች ላይ የሚታዩ ክሶች አሉ። እነዚህ ክሶች ከመቅረባቸው በፊት በሕግ አሰራሩ ላይ አላስፈላጊ ጫናዎች ለማሳደር ነው። ይህም ሲባል ዲሲፕሊን ኮሚቴው በአራት የፓርቲው አባላት ላይ የወሰደው እርምጃ ይህንን ከመሰለ፣ ነገስ ምን ሊወሰድ ይችላል የሚል ድንጋጤ ክስ በሚጠብቃቸው አመራሮች ላይ ውሳኔው፣ ድንጋጤ ፈጥሯል። የትኛውንም ያህል ጫና ለመፍጠር ቢፈለጉም፣ ከሕግ በላይ መሆን የሚችል ግለሰብም ሆነ አካል በፓርቲያችን ውስጥ ሊፈጠር እንደማይችል ከወዲሁ ግንዛቤ መወሰድ አለበት።

ሰንደቅ፡- የዲሲፕሊን ኮሚቴው ውሳኔ ኮረም ባልሞላበት የተወሰነ ነው እየተባለ ነው። ይህ ከሆነ እውነቱ አላስፈላጊ ግፊት መፍጠር ተደርጎ ሊወሰድ እንዴት ይችላል?

አቶ አበራ፡- አለመታደል ሆኖ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሴራ ፖለቲካ ነው። በመከራከሪያት የቀረበው ኮረም አልሞላም አንድ ሰውም አልፈረመም የሚል ነው። በመተዳደሪያ ደንባችን መሰረት ከሰባት የዲሲፕሊን ኮሚቴዎች፣ አራትና ከዚያ በላይ ከተገኙ ኮረም ሞልቷል ሲል ይደነግጋል። በዚህ መሰረት የዲስፕሊን ኮሚቴው ጉዳዩን ለመመልከት ስብሰባ ሲቀመጡ አራት አባላት በመገኘታቸው፣ ስብሰባው ኮረም ሞልቶ መጀመሩን ያረጋግጣል።

በስብሰባ አሰራር ቃለ ጉባኤ የሚፈረመው፣ በቀጣይ ስብሰባ ላይ ተነቦ የነበሩ አባላት ካደመጡና ከተስማሙ በኋላ ነው። በቃለ ጉባኤው ላይ የልዩነት ሃሳብ ያለው ሰው፣ ስሙ ተጠቅሶ በቃለ ጉባኤው ላይ የልዩነት ሃሳቡ ይሰፍርለታል። በቃለ ጉባኤው ላይ የውሳኔ ሃሳብ የሚሰጥበት ከሆነ በስብሰባው ላይ የተካፈሉ አባላት ድምጽ ይሰጣሉ። በአብላጫ ድምጽ ውሳኔ በጉዳዩ ላይ ያርፋል። ስለዚሀም ኮረም ሞልቶ ስብሰባ ከተጀመረ ውሳኔ የሚሰጠው በነበሩ አባላት ብቻ መሆኑ መታወቅ አለበት። ለምሳሌ የዲስፕሊን ኮሚቴው ስብሰባውን ሲጀምር በአራት የኮሚቴ አባሎች በመሆኑ፣ ስብሰባው የተከፈተው በመተዳደሪያው ደንብ መሰረት ኮረም ሞልቶ መሆኑን ለመረዳት ይቻላል። በውሳኔ አሰጣጡም ላይ የተገኙት አራት አባላት ብቻ ናቸው ድምጽ መስጠት የሚችሉት። ከዚህ መነሻ ነው፣ አንዱ የዲሲፕሊን ኮሚቴ እኔ ባልፈረምኩት ሁኔታ ውሳኔ ተላልፏል በሚል የፓርቲው የውስጥ አሰራር ለአደባባይ የበቃው። የፖለቲካ ሴራውና ጠለፋውም እዚህ ላይ ነው የሚጀምረው። ቅሬታ ያቀረበው የኮሚቴው አባል በተቃውሞ እንኳን ድምጽ ቢያዝለት፣ አሁን የተሰጠው የውሳኔ ሃሳብ ሶስት ለአንድ በሆነ ድምጽ ያልፋል። ይህ እውነት ጠፍቷቸው አይደለም ወደ ጋዜጣ የሄዱት፣ የነገን ተከሳሽነት በአላስፈላጊ ጫናዎች ለማምለጥ ከመፈለግ እንጂ።

ሰንደቅ፡- የዲስፕሊን ኮሚቴው በተገቢው መንገድ ኃላፊነቱን ተወጥቷል እያሉኝ ነው?

አቶ አበራ፡- ላስረዳህ የሞከርኩት የፓርቲው የውስጥ አሰራር ከሕግ አግባብ ውጪ ለአደባባይ እንዲወጣ እንዴት እንዳደረጉት ነው። ከዚህ ውጪ የዲሲፕሊን ኮሚቴው የሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ውሳኔ አይደለም። በውሳኔው ላይ ቅሬታ ያለው ወገን ካለ በሚያቀርበው የይግባኝ ቅሬታ መሠረት የኦዲትና የምርመራ ኮሚሽኑ የሚመለከተው ይሆናል። ይግባኝ ባልቀረበበት ሁኔታ ግን ኮሚሽኑ ጉዳዩን ለማየት ምንም አይነት የህግ ድጋፍ አይኖረውም። በመተዳደሪያው ደንብ መሠረት በአስራ አምሰት ቀናት ውስጥ ይግባኝ ካላሉ ውሳኔው የጸና ይሆናል። በተለየ ሁኔታ እያየን ያለነው የአቶ ዮናታን ተስፋዬ ጉዳይ ነው።

ሰንደቅ፡- እስካሁን የተነጋገርነው ከአሰራር አንፃር ነው። ሥራአስፈፃሚው ሆነ እርምጃ የተወሰደባቸው አባላት በክሱ ይዘት ላይም ተቃውሟቸውን በይፋ ነው ያቀረቡት። ይህም ሲባል የክሱ ይዘት የግለሰቦችን የመናገር የመጻፍ መብቶችን የተጋፋ ነው ሲሉ ከሰዋል። በዚህ ላይ ኮሚሽኑ ምን አስተያየት አለው?

አቶ አበራ፡- አንድ ሰው የፓርቲ አባል የሚሆነው ከራሱ የተወሰነ ነፃነቱን ቀንሶ ነው። ይህም ሲባል ለፓርቲ ፕሮግራም እና ደንብ እገዛለሁ የሚል የውል ስምምነት ውስጥ ስለሚገባ ነው። ስለዚህም የአንድ የፓርቲ አባል አስተሳሰቡም ሆነ አፃፃፉ ከፓርቲው ደንብ እና ፕሮግራም ጋር አንድ የሆነ የሚመጋገብ መሆን አለበት። ከዚህ ውጪ በራስ ፍላጎት መነሻ የሚፈጸሙ ማናቸውም አይነት ተግባራት በዲስፕሊን ኮሚቴ የሚታዩ ነው የሚሆኑት።

የፓርቲውን የማዕዘን ድንጋይ የሆኑ የግለሰቦችን ነፃነቶች ወደ ቡድን መብት በመውሰድ አደባባይ ላይ አውጥቶ ለክርክር ማብቃት በፓርቲው ደንብ ያስቀጣል። በፓርቲው ውስጥ በዘር በሃይማኖት በቋንቋ እና በተለያዩ መንገዶች ከፋፋይ የሆኑ ነገሮች የሚሰራ በሕግ እንደሚቀጣ የፓርቲው ደንብ ይደነግጋል። ስለዚህም የፓርቲውን ደንብ አልፎ ስለአንድ ማሕበረሰብ በብሔር ወይም በሌላ መልኩ ለመከራከር አትችልም። አንዱን ማሞገስ ሌላውን ማንኳሰስ በግለሰቦች ነፃነት ስም የሚታለፍ ተግባር አይደለም። ፓርቲው በዜጎች ትስስር እንጂ በቡድን ፍረጃ ላይ የቆመ አይደለም።

ሌላው ይህ የክስ ይዘት ትክክለኛነት መነሳት ያለበት ክሱ ከመታየቱ በፊት ነበር። ክሱ መደመጥ ከጀመረ እና ውሳኔ በተወሰነ ደረጃ ከተሰጠው በኋላ፣ አሁን ላይ ስለክሱ ይዘት ማውራት ተገቢ አይደለም። ተቀባይነትም የለውም። ለዚህም ነው አካሄዳቸው ቀናነት የጎደለው ነው የምንለው። በጋዜጣ ላይ ያቀረቡትን የመከራከሪያ ነጥቦች በፓርቲው ደንብ ስርዓት መከራከር የተከለከሉ ይመስል በዚህ መሰል ተግባር መሰማራታቸው ኃላፊነት የጎደለው ስራ ነው።

ሰንደቅ፡- የኦዲትና የምርመራ ኮሚሽኑ ድምጽ የተሰማ ዛሬ ነው። በፓርቲያችሁ ዙሪያ የገንዘብ ምዝበራዎች እንዳሉ በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙሃን ሲገለጽ ነበር። ካለባችሁ ኃላፊነት አንፃር ይህን ጉዳይ እንዴት ነው የምትመለከቱት?

አቶ አበራ፡- ምርመራ የተጀመረባቸው ፋይሎች አሉ። ምርመራ ባልተጠናቀባቸው ፋይሎች ላይ ደግሞ ምንም አስተያየት መስጠት አልችልም። የምርመራው ውጤት ነው የሚወስነው። ይህ ባልታወቀበት ሁኔታ ምዝበራ አለ ወይም የለም ለማለት አደጋች ነው። አጣርተን ስንጨርስ የደረስንበትን የማጣራት ውጤት ይፋ እናደርጋለን።

ሰንደቅ፡- የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን በይግባይ አይቶ ውሳኔ የሰጣውቸው ፋይሎች አሉ?

አቶ አበራ፡- ከዚህ በፊት አሁን የዲሲፕሊን ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆነችው በሥራአስፈፃሚው ከፓርቲ ከኃላፊነቷ እንድትነሳ ተደርጋ ነበር። ቅሬታዋን ለኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን አቅርባ በይግባኝ ጉዳዩ ሲታይ ነበር። በምርመራ በተደረሰው ውሳኔ መሰረት ከሕግ አግባብ ውጪ መነሳቷ ተደርሶበት ወደ ኃላፊነቷ እንድትመለስ ተደርጓል። ሌላው የአባል ፎርም ሳይሞሉ ውሳኔ በተላለፈባቸው ሰዎች የተሰጠውን ውሳኔ ተገቢ ባለመሆኑ ፋይሉ እንዲዘጋና ክሱ ውድቅ እንዲሆን የተወሰነበት ሁኔታም አለ። በአጠቃላይ ከከፍተኛ አመራር እስከ ተራ አባላት ድረስ ውሳኔ ሰጥተን ቀጥተናል። ለጠቅላላ ጉባኤውም ሪፖርት አቅርበናል። ሌሎችም አሉ።

ሰንደቅ፡- አቶ ዮናታን ተስፋዬ በማረሚያ ቤት እያሉ ጉዳያቸውን መመልከት ተገቢ ተደርጎ የሚወሰድ ነው? በዚህ ላይ ኮሚሽኑ ምን ይላል?

አቶ አበራ፡- ባሰራጨነው መግለጫ ላይ በግልፅ እንዳሰፈርነው የአቶ ዮናታን ተስፋዬን ጉዳይ እየመረመርነው ይገኛል። ከምርመራው በኋላ ውሳኔ ያገኛል። ሆኖም ግን በዚህ ጋዜጣ ላይ አቶ ዮናስ በመከራከሪያት የአቶ የሸዋስ ጉዳይ አንስተው ያቀረቡት ፈጽሞ ሃሰት መሆኑ መታወቅ አለበት። አቶ የሽዋስ በማረሚያቤት እያሉ በሕግ የሚያስጠይቅ ክስም አልቀረበባቸውም። ይህ ባልሆነበት ሁኔታ የምክር ቤት ሰብሳቢውን አቶ ይድነቃቸውን ለመወንጀል መፈለጋቸው ኃላፊነት የጎደለው ተግባር መሆኑ ግንዛቤ መወሰድ አለበት። ውንጀላውንም ያቀረቡት ግለሰብ እውነትን በዚህ ደረጃ ለማዛባት ለምን እንደፈለጉ ለማንም የማይገባ አቀራረብ ነው።

ሰንደቅ፡- አሁን ካለው አጠቃላይ ሁኔታው ፓርቲው ሕጋዊ እና ሕገወጥ መስመሮችን በሚያጣቅሱ አመራሮች መካከል ላይ ይገኛል ማለት ይቻል ይሆን?

አቶ አበራ፡- ይህንን የሚወስነው በያዝናቸው ፋይሎች ላይ ምርመራዎችን ካጠናቀቅን በኋላ በሚገኘው ውጤት ነው። በርግጥ ሥራአስፈፃሚው መግለጫ እሰጣለሁ እያለ የተሰጠ ውሳኔን እስከመሻር የሄደበት ሁኔታ ነው ያለው። እነዚህ እና ሌሎች ጉዳዮችን ጠቅላላው ጉባኤ እንዲመለከታቸው ስራዎች እየተሰሩ ነው የሚገኙት። ከዚህ በፊትም ፓርቲው በርካታ ችግሮችን ያለፈ በመሆኑ አሁንም የተፈጠረውን ችግሮች በብቃት በጠቅላላው ጉባኤ ውሳኔ እንደምንፈታው እርግጠኞች ነን።

The post “ለጋዜጣ ጉዳዩን ማቅረብ የተፈለገው ከቀናነት በመነጨ ሳይሆን፤ በማር የተለወሰ መርዝ ነው” – አቶ አበራ ገብሩ appeared first on Zehabesha Amharic.


ድርቁ አስጨናቂና አሳሳቢ ሆኗል ተባለ –አለማየሁ አንበሴ

$
0
0

8acfa691a3312753b88f9cfa1ec4d485_M• በድርቁ አካባቢዎች 350ሺ ተጨማሪ ህፃናት ይወለዳሉ
• የነፍሰ ጡር እናቶች ቁጥር እየጨመረ ነው
• የእርዳታ እህል በፍጥነት እንዲጓጓዝ ተጠየቀ
በድርቅ በተጐዱ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በሚቀጥሉት 6 ወራት ውስጥ 350ሺህ ተጨማሪ ህፃናት እንደሚወለዱ የተባበሩት መንግስታት ያስታወቀ ሲሆን ለድርቁ የሚደረገው አለማቀፍ ድጋፍ የተቀዛቀዘ መሆኑ ችግሩን አስጨናቂና በእጅጉ አሳሳቢ አድርጐታል ተብሏል፡፡
አለማቀፉ የህፃናት አድን ድርጅት በበኩሉ፤ በአሁኑ ወቅት ከሶሪያ ቀጥሎ አሠቃቂ የሰብአዊ ቀውስ ያንዣበበው በኢትዮጵያ መሆኑን ጠቁሞ፤ 4መቶ ሺህ ህፃናት የአልሚ ምግብ በእጅጉ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጿል፡፡
ድርቁ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ባለሙያዎቹን በመላክ ተዘዋውረው እንዲጎበኙ ማድረጉን የጠቆመው የህፃናት አድን ድርጅቱ፤ በርካታ እናቶች ነፍሰ ጡር መሆናቸው አሳሳቢ እንደሆነ ገልጿል፡፡ ለእናቶች እንክብካቤ ማድረግ አስቸጋሪ በሆነበት እንዲሁም እናቶች አስፈላጊውን ንጥረ ምግብ ማግኘት ባልቻሉበት ሁኔታ የነፍሰ ጡር ሴቶች ቁጥር መጨመር ችግሩን አስጨናቂ ያደርገዋል ተብሏል፡፡ የሚወለዱት ህፃናት እጣ ፈንታም አሳሳቢ የህፃናት አድን ድርጅቱና የተባበሩት መንግስታት ጠቁመዋል፡፡
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግስት ድርቁን ለመቋቋም እያደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ከ10.5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ለማውጣት እንደሚገደድ የአለም የምግብ ፕሮግራም ከትናንት በስቲያ ያስታወቀ ሲሆን የገንዘብ ድጋፉም እስከ ሚያዚያ ወር ድረስ ተሰባስቦ ለተረጅዎች ድጋፍ መዋል እንዳለበት ገልጿል፡፡
በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የድርቁ ሁኔታ በ1977 ዓ.ም ከተከሰተውና የ1 ሚሊዮን ገደማ ዜጐችን ህይወት ከቀጠፈው የድርቅ ክስተት የባሰ መሆኑን የጠቆመው የአለም የምግብ ፕሮግራም፤ 10.5 ቢሊዮን ብሩን በመጪው ወር ከለጋሾች እንደሚያሰባስብም ገልጿል፡፡
በአጠቃላይ ለእርዳታው ያስፈልጋል ተብሎ ከተገመተው 1.4 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ በአሁኑ ወቅት 37 በመቶ ያህሉ መገኘቱን የተባበሩት መንግስታት የእርዳታ ማስተባበሪያ ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡
የብሔራዊ የአደጋና ስጋት ቅነሳ ስራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ፤ መንግስት ለተጐጂዎች በቂ እርዳታና ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልፆ እስካሁን ከተለያዩ አገራትና የረድኤት ተቋማት 431 ሚ. ዶላር ድጋፍ ቃል መገባቱን አስታውቋል።
የመንገድ ችግርና የመጋዘን እጥረት እርዳታ በማከፋፈል ሂደቱ የሚገጥሙ እንቅፋቶች እንደሆኑም ኮሚሽኑ ጨምሮ ገልጿል፡፡
የተባበሩት መንግስታት የእርዳታ ማስተባበሪያ ኤጀንሲ በበኩሉ በእርዳታ አሰጣጡ ላይ ዘይት፣ ስንዴና የማባያ የምግብ ግብአቶች በአንድነት ለተረጂዎች እየቀረቡ አለመሆኑ እርዳታ ፈላጊዎች ለእንግልት እየዳረገ መሆኑን ጠቅሶ፤ የምግብ ግብአቶች በአንድነት እንዲቀርቡ ጠይቋል፡፡
እስከ ሚያዚያ 2008 የሚበቃ እርዳታ መገኘቱን የጠቆመው ኤጀንሲው፤ እርዳታውን ከወደብ የማጓጓዝ ሥራ በፍጥነት መከናወን እንዳለበት አሳስቧል፡፡ በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በአጭር የሞባይል የጽሑፍ መልዕክት ስኬታማ የሆነ እርዳታ እያሰባሰበ መሆኑን  አስታውቋል፡፡ የማህበሩ የኮሚኒኬሽንና የሃብት ማሰባሰብ መምሪያ ሃላፊ አቶ ደግሰው አማኑ ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ በአጭር ጽሑፍ መልዕክቱ እርዳታ የሚያዋጣው የህብረተሰብ ቁጥር በየእለቱ እየጨመረ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀን እስከ 10ሺህ ሰው ከ5 ብር 50 ብር የሚደርስ የገንዘብ እርዳታ እየሰጠ እንደሆነ ተረጋግጧል ብለዋል፡፡

The post ድርቁ አስጨናቂና አሳሳቢ ሆኗል ተባለ – አለማየሁ አንበሴ appeared first on Zehabesha Amharic.

3 ህፃናት ሃዋሣ ዩኒቨርሲቲ ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ሞቱ –አለማየሁ አንበሴ

$
0
0

5 የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ

hawasa 4በሃዋሣ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የሃዋሣ ዩኒቨርሲቲ ፍሳሽ ማጠራቀሚያ ገንዳ ውስጥ የገቡ 3 ህፃናት ህይወታቸው አለፈ፡፡ ዕድሜያቸው 8‚ 12‚ እና 14 የሚሆናቸው ህፃናት፤ በሽቦ አጥር በተከለለው የዩኒቨርሲቲው የቆሻሻ ፍሳሽ ማጠራቀሚያ ገንዳ ውስጥ በአጥር ተንጠላጥለው በመግባት ለመዋኘት ሲሞክሩ ህይወታቸው አልፏል፡፡
ወደ ፍሳሽ ማጠራቀሚያው የገቡት አራት ህፃናት ሲሆኑ ከሁለት መንትያ ወንድማማቾች መካከል አንደኛው ወደ ማጠራቀሚያ ውስጥ ሳይገባ በመቅረቱ ህይወቱ የተረፈ ሲሆን፤  የስምንት አመቱ ህፃን መንትያ ወንድሙን ጨምሮ ሁለት ጓደኞቹ በገንዳው ውስጥ ገብተው በመቅረታቸው ሁኔታውን ለሰዎች ነግሮ፣ የህፃናቱ አስከሬን ከገንዳው ውስጥ ሊወጣ ችሏል፡፡
የህፃናቱ የቀብር ስነስርዓት ከትናንት በስቲያ በስላሴ ቤተክርስቲያን የተፈፀመ ሲሆን በህፃናቱ ሞት የአካባቢው ነዋሪዎች በእጅጉ አዝነዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ለፍሳሽ ማጠራቀሚያ ባዘጋጀው ገንዳ ውስጥ የተጠራቀመውን ፍሳሽ እያጣራ መልሶ ለአገልግሎት እንዲውል በሚያስችል ቴክኖሎጂ እየተጠቀመ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች፤ ማጠራቀሚያው ግን በበቂ ሁኔታ በአጥር ተከልሎና ጥበቃ ተመድቦለት ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባ ነበር ብለዋል፡፡
ስለጉዳዩ እንዲነግሩን ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ያደረግነው ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ምላሽ ሳያገኝ ቀርቷል፡፡
በሌላ በኩል ከሰሞኑ ርዕደ መሬት ጋር በተያያዘ አዋሣ ዩኒቨርሲቲ ለ15 ቀናት በመዘጋቱ ምክንያት ወደ ቤተሰቦቻቸው በመኪና ሲጓዙ የነበሩ 5 የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ትናንት ዝዋይ ላይ በተፈጠረ መኪና አደጋ ህይወታቸው አልፏል፡፡

The post 3 ህፃናት ሃዋሣ ዩኒቨርሲቲ ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ሞቱ – አለማየሁ አንበሴ appeared first on Zehabesha Amharic.

በጋምቤላ የሟቾች ቁጥር 8 ደረሰ |ውጥረቱ እንዳየለ ነው |በርካቶች በቦምብ ፍንዳታ ቆስለዋል

$
0
0

ዘ-ሐበሻ በሰበር ዜና ባለፈው ሀሙስ በጋምቤላ በኑዌር እና በአኝዋክ ብሄረሰቦች መካከል በተነሳ ግጭት የሟቾች ቁጥር 6 መድረሱን መዘገቧ ይታወሳል:: ግጭቱ እስከ ዛሬ ድረስ መቀጠሉ ተዝግቦ የሟቾች ቁጥር አሻቅቧል::

አዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደዘገበው በጋምቤላ ክልል በኑዌርና በአኝዋክ ብሔሮች መካከል በተፈጠረ ግጭት የክልሉ የፀጥታ ሃይል አባላትን ጨምሮ የ8 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በርካቶች በቦንብ ፍንዳታ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

gambela
የከተማዋ ነዋሪዎች ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ በግጭቱ ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን ከትላንት በስቲያ ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ጨምሮ ባንኮችና የንግድ ተቋማት የተዘጉ ሲሆን ትናንት ረፋድ ላይም በከተማዋ አንዳንድ አካባቢዎች ግርግር ተከስቶ እንደነበር ታውቋል፡፡
ለቀናት በዘለቀው ግጭት የክልሉ የትራንስፖርት ቢሮ ም/ኃላፊን ጨምሮ 8 ሰዎች መሞታቸውንና በከተማዋ ሁለት ቦታ በፈነዳ ቦንብም በርካቶች መቁሰላቸውን የጠቆሙት ምንጮች፤ የክልሉ ልዩ የፖሊስ ኃይልን ጨምሮ የመከላከያ ሰራዊት ግጭቱን ለማረጋጋት ጥረት ማድረጋቸውን ጠቅሰው በትናንትናው ዕለትም ከተማዋ በውጥረትና ግርግር ስትዋከብ መዋሏን ገልፀዋል፡፡
የግጭቱ መነሻ ከ15 ቀናት በፊት በክልሉ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ም/ዲንና በክልሉ ም/ፕሬዚዳንት ሹፌር መካከል በመኖሪያ ቤት መሬት ጉዳይ በተፈጠረ የግል ፀብ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮቻችን፤ ጠቡን ተከትሎ ም/ዲኑ የአኙዋክ ተወላጅ ሹፌሩን እጁ ላይ በጥይት መተው ማቁሰላቸውን ገልፀው በዚህም ሳቢያ ጉዳዩ የብሄር ግጭት መልክ እንደያዘና ወደ ተማሪዎች የቡድን ፀብ እንደተዛመተ አስረድተዋል፡፡
ግጭቱ ከእለት እለት እየተባባሰ ቀጥሎም አንዲት የኑዌር ተወላጅ ተማሪ በግጭቱ ጉዳት ደርሶባት ህክምና እየተከታተለች ሳለ ህይወቷ በማለፉ ግጭቱ መካረሩን የጠቆሙት ምንጮች፤ የኑዌርና የአኙዋክ ብሄር ተወላጅ ተማሪዎች የእርስ በእርስ ግጭት መፍጠራቸውን ገልፀዋል፡፡
የክልሉ ልዩ ሃይል ግጭቱን ለማርገብ ሙከራ ሲያደርግ ቢቆይም ሁኔታው ባለመረጋጋቱ የመከላከያ ሰራዊት በትናንትናው እለት በከተማዋ ተሰማርቶ ግጭቱን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገ መሆኑን ነዋሪዎች ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡
በጉዳዩ ዙሪያ ከክልሉ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ም/ኃላፊ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ጥረት ብናደርግም በትናንትናው ዕለት ኃላፊው አዲስ አበባ መምጣታቸውን ገልፀው፤ “መረጃ ለመስጠት እንደማይችሉ ገልፀውልናል ሲል አዲስ አድማስ ዘገባውን አጠናቋል::

The post በጋምቤላ የሟቾች ቁጥር 8 ደረሰ | ውጥረቱ እንዳየለ ነው | በርካቶች በቦምብ ፍንዳታ ቆስለዋል appeared first on Zehabesha Amharic.

በውጥረት ውስጥ ካለችው ጋምቤላ ፎቶዎች ደርሰውናል |ዛሬም ሰዎች እያለቁ ነው

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በጋምቤላ በኑዌር እና በአኝዋክ ብሄረሰቦች መካከል የተነሳው ግጭት እየተባባሰ ይገኛል:: ቀደም ባለው ዘገባችን ቦምብ ፈንድቶ በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን መዘገባችን ይታወሳል:: በጋምቤላ በተፈጠረው የ እርስ በ እርስ ግጭት የሟቾች ቁጥር 8 ደርሷል:: የዘ-ሐበሻ የጋምቤላ አካባቢ ያሉ በጎ ፈቃድ ዘጋቢዎች ይህን የቦምብ አደጋ እና ያደረሰውን ጥፋት የሚያሳዩ ፎቶዎች ልከውልናል:: ይመልከቷቸው::

Gambela 2 Gambela Gambela3 Gambela4

gambela 5

The post በውጥረት ውስጥ ካለችው ጋምቤላ ፎቶዎች ደርሰውናል | ዛሬም ሰዎች እያለቁ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

በጋምቤላ እስር ቤት የ20 ዓመቱ ኦካቺ ኦቡል ተገደለ |የሟች ፎቶን ይዘናል |ከ16 ዓመት በታች ያሉ እንዳይመለከቱት

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ሰሞኑን በጋምቤላ በተነሳው ብጥብጥ ጋር ተያይዞ እስር ቤት የነበረው ኦካቺ አቡል ዛሬ ተገድሎ መገኘቱ ተዘገበ:: ዘ-ሐበሻ ከስፍራው ያነጋገቻቸው የዓይን እማኞች ከሟች ኦካቺ አቡል ፎቶ ግራፍ ጋር አያይዘው በሰጡን መረጃ በሟች አስከሬን ላይ ከፍተኛ የጥይት እና የዱላ ምልክቶች አይተዋል::

gambela 5

በሕወሓት መንግስት የሚደገፈውና ጋምቤላን በስልጣን ላይ ተቆጣጥሮ የሚገኘው የኑዌር ብሄረሰብ ወታደሮች ይህን ወጣት ከ እስር ቤት አውጥተው እንደገደሉት ያስታወቁት እነዚሁ ዘ-ሐበሻ ያነጋገረቻቸው ወገኖች ከተማዋን ፌደራል ፖሊስ ተቆጣጥሯት ቢገኝም በተለይ የአኝዋክ ብሄረሰብ ሲገደሉ እያዩ ዝም ብለዋል ሲሉ ተቃውሟቸውን ያሰማሉ::

እንደ አይን እማኞች ገለጻ ኦካቺ በኑዌር ተወላጅ ወታደሮች ከ እስር ቤት ተወስዶ ሲገደል እነዚሁ የሕወሓት የፌደራል ወታደሮች እያዩ ነበር::

በአሁኑ ወቅት በጋምቤላ የአኝዋክ ብሔረሰብ አባላት እንዴት በስደት ወደ ክልላችን በስደት በመጡትና በስልጣን ላይ ባሉት የኑዌር ማህበረሰብ አባላት እንገደላለን በሚል የጋምቤላ ከተማን ውጥረት ውስጥ ከተዋታል::

ዘ-ሐበሻ ይህን ጉዳይ እየተከታተለች ትዘግባለች::

The post በጋምቤላ እስር ቤት የ20 ዓመቱ ኦካቺ ኦቡል ተገደለ | የሟች ፎቶን ይዘናል | ከ16 ዓመት በታች ያሉ እንዳይመለከቱት appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>