Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

በኢትዮጵያ የምግብ እጥረት በእጥፍ እንደሚጨምር UNOCHA ገለጸ

$
0
0

በኢትዮጵያ የሚታየዉ የምግብ ርዳታ ፍላጎትና የተመጣጠነ የምግብ እጥረት በመጪዉ ዓመትም በእጥፍ እንደሚጨምር ግምት እንዳለ OCHA በመንስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ትላንት ባወጣዉ ዘገባ ገለጸ።

በኢትዮጵያ የሚታየዉ የምግብ ርዳታ ፍላጎትና የተመጣጠነ የምግብ እጥረት በመጪዉ ዓመትም በእጥፍ እንደሚጨምር ግምት እንዳለ OCHA  በመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ትላንት ባወጣዉ ዘገባ ገለጸ።

የምግብ እጥረቱ የEl-Nino  የዓየር ንብረት ክስተቶች ያስከተለዉ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህ ዓመት ነሐሴ ወር ላይ በተመጣጠነ ምግብ እጦት የተጎዱ ህጻናት፣ ነፍሰጡር ሴቶችና የሚያጠቡ እናቶች ቁጥር ከቀድሞዉ ዓመት ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ መጨመሩንም OCHA ገልጿል።

Source- VOA

 


ኢትዮጵያዊቷ ብርቅዪ አትሌት እና አሳዛኙ የአሜሪካ ገጠመኟ –“ወደ ኢትዮጵያ ከምመለስ እራሴን እዚሁ ባጠፋ እመርጣለሁ”ሌላኛው አትሌት

$
0
0

Genet Lireከታምሩ ገዳ

የ18 አመቷ ገነት ሊሪ በ400 ሜትር ወድድር ብሄራዊ ሪኮርድ በመሰበር አገሪቱ ካፈራቻቸው እና ሰሟን ከሚያሰጠሯት ጥቂት ብርቅዮ አትሌቶች መካከል አንዷ ስትሆን በመጭው 2016 እኤአ ኢትዮጵያን በመወከል ወደ ብራዚል ትጓዛለች ተብላ ከፍተኛ ተሰፋ የተጣለባት አትሌት ነበረች።ይሁን እና ከወራት በፊት ወደ አሜሪካ ለውድድር ተጉዛ “በ አገሬ ኢትዮጵያ ውስጥ የፖሊቲካ አባል ካልሆንሺ በሚል ምክንያት የተለያዩ በድሎች ደረሰወብኛል” በማለት አዚያው አሜሪካ የቀረችው ብርቅየዋ አትሌት ገነት ኑሮ በአሜሪካ አልጋ በአልጋ አልሆንልሽ ብሏታል።

እንደ ሰሞነኛው ታዋቂው የዋሽንገተን ፖስት እና የአንግሊዙ ጋርዲያን ጋዜጣ ተመሳሳይ ዘገባዎች ከሆነ ከሰድሰት ወራት በፊት አሜሪካ ወስጥ የጥግኝነት ማመልከቻ አቅርባ አስካሁን ድረስ ምላሽ ያላገኘችው አትሌት ገነት የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ኑሮ በአሜሪካ እጅግ ፈተናዎች የተሞሎባት ነበር ። በወር 400 ዶላር የተከራየችውን ቤት ኪራይ መክፈል ባለመቻሏ ለተወሰኑ ቀናት ከ ደጃፍ አሰከ ማደር ደረሳለች።በአሁኑም ወቅት ቢሆን የምትጠጋው (የሚረዳት ባለመኖሩ) ጉዳይዋን ከያዘላት ግለሰብ አንሰተኛ ክፍል ወስጥ ከሶፋ ላይ በመተኛት ለመዳበል ተገደዳለች ። ምንም እንኳን አርሱዋን የመሰሉ ወደ 30 የሚጠጉ ኢትዮጵያዊይን አትሌቶች ዋሽንግተን ዲሰ አቅራቢያ ቢኖሩም የቤተሰብ ነገር ሲነሳ ገነት የቤተሰቦቿ ፎቶዎችን (ታሪኮቿን )በማየት ማንባት ይቀናታል። በዚህ ወጣ ውረድ ውስጥ ግን ገነት አንድ ትልቅ ህልም አላት አርሱም ለየተኛው አገር እንደ ሆነ በውል ባታውቀውም በኦሎምፒክ ውድድር ላይ በመወዳደረ የወርቅ ሜዳሊያ ለማጥለቅ እና ሰንደቃላማ ማውለብለብ ነው ።

አንደ አትሌት ገነት ሁሉ አርሱም የገዢው መንግሰት” የፓርቲ አባል ካልሆንክ” ተበሎ የተለያዩ በደሎች እንደደረሱበት የሚናገረው የ25 አመቱ የረጅም ረቀት ጀግናው አትሌት ሃይሌ መንገሻ በአሁኑ ወቅት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በአንድ የመጠጥ መሽጫ መደብር ውስጥ ተቅጥሮ ኑሮውን የሚገፋ ሲሆን “ምንም እንኳን ብዙ ቀናት ቢጨልምም ፣የወደፊቱ እድሌን በቁርጠኝነት ባላውቀውም ወደ ኢትዮጵያ ከምመለስ እራሴን እዚሁ ባጠፋ እመርጣለሁ።” በማለት ደረሰብኝ ካለው በደሉ የተነሳ ከፈጥረቱ አንስቶ ደጉን እና ክፉን ካየባት አናት አገሩ( ኢትዮጵያ) ለጊዜውም ቢሆን ጥላ ከለላ የሆነችው አሜሪካንን መርጧል።

በተለያዩ ጊዜያት ኢትዮጵያን በአለማቀፍ የአትሊቲክስ ወድድሮች ላይ የሚወክሉት ፡ የአውሮፓ፣ የአሜሪካ ፣ የቻይና የመሳሰሉት ጎዳናዎች ላይ አረንጓዴውን ፣ቢጫውን እና ቀዩ ሰንደቃላማችንን በማውለብለብ የሁሌም አምባሳደሮቻችን የሆኑት ብርቅየዎቹ አትሌቶቻችን በሰበበ ባሰባቡ በወጡበት በመቅረት ለተለያዩ ባእዳን አገሮች የመሮጣቸው ነገር ሁኔታውን በቅርብ ለሚከታተሉ በርካታ ወገኖች በእጅጉ ያሳዘናል፣እንደ አገርም እንደ ሕዝብም ያሳፍራል ። ችግሩን ችግራቸን አድርገን መፍትሔውን ን በጋራ ካለፈላለግን “ዛሬ ቁጭ ብለው የሰቀሉት ነገ ቆመው ለማውረድ ይከበዳል “እንዳይሆን ደጋግሞ ማሰቡ ትልቅ አዋቂነት ነው። እስቲ እኛም ለምን ብርቅዪ አትሌቶቻችን ይኮበለላሉ? ብለን እነጠይቅ።

በሽብርተኝነት የተከሰሱት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ለጥቅምት 3 ተቀጠረባቸው

$
0
0

Abrha-Desta-Yeshiwas-Assefa-Daneil-Shibeshi-Habtamu-Ayalew

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ሀምሌ 14/2007 ዓ.ም የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከተከሰሱበት የሽብር ወንጀል መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲለቀቁ ወስኖላቸው የነበሩት አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ የሽዋስ አሰፋ፣ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ ዳንኤል ሽበሽና አቶ አብርሃም ሰለሞን ላይ ተጠይቆባቸው የነበረው ይግባኝ ተቀባይነት በማግኘቱ ለጥቅምት 3/2008 ዓ.ም ለቃል ክርክር ተቀጥረዋል፡፡

አምስቱ ተከሳሾች የተጠየቀባቸው ይግባኝ ተቀባይነት ይኖረዋል አይኖረውም የሚለውን ጉዳይ ለመወሰን ዛሬ መስከረም 21/2008 ዓ.ም በጠቅላይ ፍርድ ቤት ተቀጥረው የነበር ሲሆን አቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ አብርሃም ሰለሞን ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሲቀርቡ አቶ የሽዋስ አሰፋ፣ አቶ አብርሃ ደስታና አቶ ዳንኤል ሽበሽ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሳይቀርቡ ቀርተዋል፡፡

አቶ የሽዋስ አሰፋ፣ አቶ አብርሃ ደስታና አቶ ዳንኤል ሽበሽ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሳይቀርቡ በውስጥ ይግባኙ ተቀባይነት አግኝቶ ቀጠሮ እንደተሰጠባቸው ከመዝገብ ቤት የታወቀ ሲሆን ሶስቱ መቀጠራቸው ከታወቀ በኋላ ዘግይተው ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደረሱት አቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ አብርሃም ሰለሞን በቢሮ ተመሳሳይ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ እነ ሀብታሙ በቀረቡበት ወቅት አቃቤ ህግ ያልተገኘ ሲሆን ስለ ቀጠሮው ምንም አይነት ምክንያት እንዳልተሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

በሌላ በኩል ከተከሳሾቹ መካከል በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኘው አቶ ዳንኤል ሽበሽ በጨለማ ቤት ታስሮ እንደሚገኝ ቤተሰቦቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የልብ ህክምና ስፔሻሊስት አስራለች

$
0
0

12106927_10205145682302555_7926962653447447435_nየልብ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት የነበሩትን ፕሮፌሰር አስራት ወ/የስን ለእስር ዳርጎ በልብ ህመም ይሰቃዩ በነበሩ ዜጎች ህይወት የፈረደው የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት ከአስራት በኋላ በኢትዮጵያ የታዩትን የዘርፉ ባለሞያ ዶክተር ፍቅሩ ማሩን በሙስና ወንጀል ጠርጥሪያቸዋለሁ በማለት ካሰረ አመታት ተቆጥረዋል፡፡
የገቢዎች ሚኒስትር ከነበሩት የብአዴኑ አቶ መላኩ ፈንታ ጋር ለእስር የተዳረጉት ፍቅሩ በልብ ህክምና ስፔሻላይዝድ ያደረጉት በስዊዲን አገር ቢሆንም አገሬን ማገልገል እፈልጋለሁ በማለት አዲስ የልብ ህክምና ማዕከልን ከፍተው ነበር፡፡ዶክተሩ በራሳቸው ወጪ ዶክተሮችን ወደ ስዊዲን በመላክም በዘርፉ ስፔሻላይዝድ የሚያደርጉ ባለሞያዎች እንዲፈጠሩ ማድረጋቸውም ይነገርላቸዋል፡፡


ዶክተሩ ከአንድ የሞያ አጋራቸው (ዶክተር በቀለ ጋር በሽርክና )በከፈቱት ሆስፒታል የልብ ምታቸው የቀነሰ ታካሚዎች ምታቸው እንዲስተካከልና የተዘጉ የልብ የደም ስሮችን የሚያፍታታ ህክምና መስጠት ጀምረው የነበረ ቢሆንም ከታሰሩ በኋላ ህክምናውን የሚሰጥ ባለመገኘቱ እየተመላለሱ ይታከሙ የነበሩ ህሙማን ችግር ውስጥ ወድቀዋል፡፡


አርቴፊሻል መሳሪያ ተገጥሞላቸው በየስድስት ወሩ እየተመላለሱ ህክምናቸውን ያደርጉ የነበሩ የልብ ህሙማን ፍቅሩን ማግኘት ባለመቻላቸው ለሞት የተዳረጉ መኖራቸውንም የሚናገሩ አልጠፉም፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሜዲካል ስኩል ፍቅሩ ያለ ክፍያ እውቀታቸውን ማካፈልም ጀምረው ነበር፡፡በስዊዲን ዩኒቨርስቲዎች ዳጎስ ያለ ገቢ ይዝቁበት የነበረን የመምህርነት ሞያቸውን ለአገር ፍቅር የገበሩትን ፍቅሩን በሙስና ማሰር ቤት እንደማይመታ የቅርብ ሰዎቻቸው ይናገራሉ፡፡
ዶክተሩ የህክምና አገልግሎት ሲሰጡባትና ሲያስተምሩባት ከነበረችው ስዊዲን ጋር ጠንካራ ግኑኝነት የነበራቸው በመሆኑም ስዊዲናዊያን የልብ ሐኪሞች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የልምድ ልውውጥ ሲያደርጉ ነበር፡፡ከዶክተሩ እስራት ጀምሮ ግን ስዊዲናዊያኑ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው አያውቁም፡፡
የዶክተሩ መታሰር ብዙ ችግር እንደፈጠረ የተረዳው የኢትዮጵያ የግል ሐኪሞች ማህበር ለፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ለፍትሕ ሚኒስቴር፣ ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና ለዳያስፖራ ዴስክ ደብዳቤ ደብዳቤ በመጻፍ ዶክተር ፍቅሩ እንዲፈቱ ተማጽኗል ፡፡
እንደ ሪፖርተር ዘገባ ከሆነ ደብዳቤው በማኅበሩ የተጻፈው ጳጉሜን 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ቢሆንም፣ እስካሁን ከማናቸውም ምንም ዓይነት ምላሽ አለማግኘቱ ታውቋል፡፡ዶክተር ፍቅሩ በስዊዲን ነዋሪ የሆነች አንዲት ሴት ልጅ አለቻቸው፡፡


የጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አሊ ሱሌይማን ለሪፖርተር በሰጡት ቃለ ምልልስ ትልልቆቹን አሳዎች የማናጠምደው ‹‹ልማቱ እንዳይደናቀፍ በማሰብ ነው››ማለታቸው አይዘነጋም፡፡በዶክተሩ መታሰር የስንቱ ህይወት እየተደናቀፈ መሆኑስ አልታያቸው ይሆን?


መቼም ወንጀል የፈጸመ ሰው መታሰር የለበትም በማለት ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው ሊከራከር ባይችልም እንደ ኢትዮጵያ ለፖለቲካ ገረድ የሆነ ፍርድ ቤት ባለበት አገርና ንጹሐን ለዓመታት እየታሰሩ ነጻ ናችሁ መባላቸውን እየተመለከትን የእስራታቸው መንስኤ ሙስና ነው ለማለት አንደፍርም፡፡
በሙስና ተብለው የታሰሩ የከተማችን ሐብታሞች እስር ቤቱን ማደሪያ ብቻ ሲያደርጉት እየተመለከትን በዶክተሩ ላይ በር ቆልፎ በቀጠሮ እየተመላለሱ ህክምና ያገኙ የነበሩ ህመምተኞችን (በሽታው ጊዜ እንደማይሰጥ እየታወቀ) በሞት መቅጣት ለዜጎቹ ዋጋ ከሚሰጥ አካል የሚጠበቅ አይደለም፡፡

የጅቡቲ ፐሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ ኤርትራን ባልተገባ ባሕርይና በነገረኛነት ከስሰዋል

$
0
0

(VOA) ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰባኛ ጠቅላላ ጉባዔ ባደረጉት ንግግር ፕሬዚዳንቱ ይህንን ክሣቸውን ያሰሙት ፕሬዚዳንት ጌሌ “ኤርትራ ለአካባቢውና በአጠቃላይም ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ አደጋ ነች” ብለዋል፡፡
gelle
በአውሮፓ አቆጣጠር ከ2008 ዓ.ም አንስቶ የኤርትራ ወታደሮች የሰሜናዊ ግዛቶቻቸውን አንዳንድ አካባቢዎች ያለአግባብ ከተቆጣጠሩ በኋላ በዚህም ዓመት ውጥረትና ውዝግቡ መቀጠሉን የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ተናግረዋል፡፡

የመንግሥታቸው ባለሥልጣናትና እራሳቸውም በተደጋጌሚ ጉዳዩን ለማስረዳት ወደ ኒው ዮርክ መመላለሳቸውን አመልክተዋል፡፡

ሃገራቸው በሰላም፣ በሽምግልናና በድርድር እንደምታምን የተናገሩት ፕሬዚዳንት ጌሌ “የተክለ ግዛታችን የማይደፈር መሆን ግን ለድርድር የሚቀርብ አይደለም” ብለዋል፡፡

የኤርትራ መንግሥት ቀደም ሲል ባወጣው መግለጫ “የአካባቢው ብቸኛና ዋነኛ ያለመረጋጋት ምክንያት የኤርትራን ሉዓላዊ ግዛቶች በኃይል ይዛ ያለችው ኢትዮጵያ ናት” ብሏል፡፡

ከጅቡቲ ጋር የገቡበት የድንበር ውዝግብ ጉዳይ በጋራ ለተስማሙባቸው ሦስተኛ ወገን አካላት የቀረበ መሆኑን የኤርትራ መንግሥት ባለፈው የካቲት መጀመሪያ አውጥቶት በነበረ መግለጫ ተናግሮ የነበረ ሲሆን ንግግሩ በጥሩ ሁኔታ ተይዞ እያለ ብስለት የሌለውና በጎ መንፈስ የራቀው የጅቡቲ አቋም ለማስረዳት አስቸጋሪ ነው ብሏል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰባኛ ጠቅላላ ጉባዔ ያደረጉትን ንግግር ለመስማት ከዚህ ሥር ያለውን ማገናኛ ተጭነው ይከተሉ፡፡

የ2017 ዳይቨርሲቲ ቪዛ ሎተሪ (ዲቪ) የምዝገባ መርሃግብር ተጀመረ

$
0
0

dv
U.S. Embassy Addis Ababa

የምዝገባ ሂደቱን አስመልክቶ ማወቅ የሚፈልጉት መረጃ ይኖርዎታል? እንግዲያውስ ሰኞ መስከረም 24 ቀን 2008 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 እስከ 10፡00 ስዓት የኤምባሲው ኮንሱላር ሃላፊ ለጥያቄዎቻችሁ በፌስቡክ በቀጥታ ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ ሆኖም ግን የግለሰብ ጉዳዮች ላይ ምላሽ የማይሰጡ መሆኑን አስቀድመን ልናስገነዝብ እንወዳለን፡፡ ለጥያቄዎቻችሁ ምላሽ ለማግኘት ሰኞ እለት በሰዓቱ መገኘትን አይርሱ!

የዚህ ዓመት ዲቪ ምዝገባ ጥቅምት 23 ቀን 2008 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡

Registration for the 2017 Diversity Visa (DV) Lottery is now open!

Do you have questions regarding application processes, eligibility and other related issues? Our consular officer will be online on Facebook on Monday, October 5, 2015 from 3:00 PM – 4:00 PM to respond to your questions on the DV 2017 registration process. Please note that our officer will not reply to questions related to personal cases. Make sure you will be online on Monday so that your questions will be answered!

Registration period ends on November 3, 2015. Apply at https://www.dvlottery.state.gov/

በዋሽንግተን ዲሲ በትግራይ ኮሚኒቲ ሽፋን በጥቂት የትግራይ ተወላጆች መካከል ትልቅ ውዝግብ ተፈጥሯል

$
0
0

ሌሎች ሞላ አስገደሞች በሰሜን አሜሪካ እየተደራጁ ነው::

ከገብረተንሳይ ወልደዓብዝጊ

በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ የህወሓት አንድ ለአምስት አደረጃጀት ፓሊሲ በትግራይ ተወላጆች ዘንድ ከተጀመረ ቆይቷል:: ዛሬም ህወሓት የራሱ የሆኑትን ሰላዩችን እያሰማራ በስደት ዓለም የሚኖሩትን የትግራይ ተወላጆች በአውራጃ ! በዘር ሐረግና በሀይማኖት እየከፋፈለ መበተንና እርስ በርስ የማናቆር ተግባር ስራዬ ብሎ ተያይዞታል:: ሰሞኑን የህወሓት ደጋፊዎች ማንም ሳያማክሩ የትግራይ ኮሚኒቲ በዋሽንግተን ዲሲ እናቋቁማለን በሚል ሽፋን የራሳቸው ሕገ ደንብን ይዘው በመምጣት ህዝቡን እያተራመሱት ይገኛሉ::
Molla Asgdom 3
ህወሓት የትግራይ ህዝብን እንደ ከለላ በመጠቀም በህዝቡ ስምና ደም እየነገደ እስከ መቼ ይኖራል? የሚለው አንገብጋቢና የህልውና ጥያቄ በሚሊዮኖች ኢትዮ}ያውያን በተለይም በየዋሁ ፣ ጨዋውና ሀገር ወዳዱ የትግራይ ህዝብ ዘንድ በይፋ የማይነገር የአጀንት ቁስል ሆኖ ቆይቷል:: አሁንም የህዝቡን ብሶት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በመሄድ ሊፈነዳ እንደተቃረበ የሚያሳዩ ጭብጥ ምልክቶች እያየን ነው:: በቅርቡ አቶ ዳዊት ገብረእግዚኣብሄርን ጨምሮ በተለያየ መልኩ በህወሓት የይስሙላ ጉባኤም ሳይቀር በይፋ ሲስተጋባ የነበረው የህዝቡን እሮሮ “ ጆሮ ያለው ይስማ ” የሚያሰኝ መልእክት የሚያስተላልፍ ነው::

ነገር ግን ስልጣንና ገንዘብን ደመ ነብሳቸውና የዓይን ብሌናቸው የሆነውን የህወሓት መሪዎች በተለይም የመለስ ዜናዊ ራእይ ጠባቂዎች ነን የሚሉና ከሻዕቢያ ጋር የጥቅምና የዘር ሐረግ ንክክ ያላቸው የህወሓት መሪዎች በመካከላቸው የጤፍን ያህል ክፍተት እንዳይፈጠር በመፍራት “ስልጣን እስከ መቃብር ” በሚል የጋራ መፈክር የህዝቡን ጥያቄ ጆሮ ዳባ በማለት በጉባኤ ስም በህዝቡ ፊት የውሸት ድራማ ሲሰሩ አይተናል::

ለዚህም ነው የህወሓት መሪዎች ቀኑንና ጊዜውን እየመሸባቸው መሆኑን ፣ በአንፃሩ ደግሞ የህዝቡን ተቃውሞና ትግል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጋጋለና እየገነፈለ መሄዱን በውል ስለተገነዘቡ ዛሬ አልሞት ባይ ተጋዳይ በመሆን ከማንም ጊዜ በላይ የትግራይ ተወላጆችን የስልጣናቸውን መሳሪያና ማስረዘሚያ አድርገው ለመጠቀም ሲባል የህወሓት አረሜናዊ አገዛዝ አንገሽግሾት ሀገሩን ጥሎ በመሰደድ በባህር ማዶ የሚኖረውን ትግራዋይ ሳይቀር አንድ ለአምስት ለማደራጀት በብዙ ሚሊዮን የሚገመት የሀገሪትዋን አንጡራ ሀብት (ገንዘብ) በመርጨት በከፍተኛ ደረጃ እየተሯሯጡ የሚገኙት:: በዋሽንግተን ዲሲ ሰሞኑን የተነሳው ውዝግብም መነሻው ይኽው ነው::
የህወሓት 12ኛው ጉባኤ በመቀሌ ከተማ ለማካሄድ አንድ ሁለት ሳምንት ሲቀረው የህወሓት ፓሊት ቢሮ አባልና የአቶ አባይ ወሉ ሚስት ወይዘሮ ትርፉ ሶስት አባላት ያለው ከፍተኛ ሉኡክ በመምራት በሲያትል የጀመሩትን ጉብኝት በተለያዩ ከተሞች የሚገኙትን የትግራይ ተወላጆች ሰብስበው ለማነጋገር ሙኮራ አድርገው እንደ ነበር የሚታወቅ ነው:: የጉብኝታቸው አላማም አንዱ የአባይ ወሉ ቡድን በ12ኛው የህወሓት ጉባኤ በአሸናፊነት ለመውጣት ድጋፍ ለማሰባሰብ ነበር:: ሁለተኛው የጉብኝቱ አላማቸው ደግሞ በስደት ዓለም የሚገኘው የትግራይ ተወላጅ ለፍትሕና ለዲሞክራሲ በሚደረገው ህዝባዊና ሀገራዊ እንቅስቃሴ በመሳተፍ የለውጥ አጋር እንዳይሆን ለብቻው ነጥሎ አንድ ለአምስት በማደራጀት የልጅ ልጆቹንም ጭምር ለህወሓት ዘላለማዊ ስልጣን መሳሪያ ሆኖ እንዲኖር ለማድረግ በውጭ ለሚገኙት ደጋፊዎቻቸው መመሪያ ለመስጠት ነው:: ነገር ግን የጉብኝታቸውን ሰሞን አቶ ዳዊት ገብረእግዚኣብሄር የትግራይ ህዝብ ሰቆቃን አስመልክቶ ያደረገውን ቃለ ምልልስ የህዝቡን ቀልብንና ልብ ትርታን የሚነካ ንግግር አየሩን ተቆጣጥሮት ስለነበር ለወይዘሮ ትርፉ ጥሩ አጋጣሚ አልነበረም::
የወይዘሮ ትርፉን ጉብኝት በዚሁ ፅሑፍ ለመጥቀስ የፈለግኩበት ምክንያት ሰሞኑን በዋሽንግተን ዲሲ በተነሳው ውዝግብ ጋር ተያያዝነትና ትስስር ስላለው ነው:: ወይዘሮ ትርፉ በዋሽንግተን ዲሲ በኢትዮ}ያ ኤምባሲ አዳራሽ የተወሰኑት የትግራይ ተወላጆችን ጠርተው ባደረጉት ሰብሰባው ላይ ካሰሙት ንግግር ውስጥ እንዲህ ብለው ነበር:: “ባለፈው ጊዜ ወደ ጋምቤላ ክልል ለስራ ጉዳይ ሂጀ ነበር:: በጉብኝቴ ወቅትም እግረ መንገዴን በጋምቤላ ክልል የሚኖሩ አንዳንድ የትግራይ ተወላጆችን አግኝቼ አነጋግሬ ነበር:: አብዛኞቹ ማን መሆኔን አያውቁም ነበርና እንዴት እዚህ ድረስ መጣችሁ ብዬ በተራ አነጋገር ስጠይቃቸው የሰጡኝ መልስ እንዲህ የሚል ነበር:: “እኛ ወደዚህ ክልል ተሰደን የመጣንበት ዋና ምክንያት ሀገራችንን ጠልተን አይደለም:: ነገር ግን በትግራይ አካባቢ ያለው የአገዛዝ ስርዓት ፈርተን ነው ሳንወድ በግድ ቤት ንብረታችንን ጥለን እዚህ የወጣነው:: ሌሎቹ ከኛ ጋር የወጡ ጓደኞቻችን ወደ ሱዳንና ሌሎች አጓራባቸው ሀገሮች ተሻግሯል:: እኛ ግን እንደ ዕድል ሆኖ እዚህ እንኖራለን” በማለት በምሬት ሲገልፁልኝ በውስጤ ሳቄን መቆጣጠር አልቻልኩትም ነበር:: እነዚህ ሰዎች እንዲህ ብለው የገለፁልኝ ምክንያት ህወሓት ወደ ማይቆጣጠረው ወደ ሩቅ ቦታ የሄዱትና ከህወሓት እጅ ያመለጡ መስሏቸው ነው:: እኔም በንግግራቸው በመገረም በሉ እንተያያለን!! ህወሓት በጓዳችሁ ውስጥ እንዳለ እናሳያችሗለን ብዬ በሆዴ እየሳቅኩኝ ተሰናበትኳቸው::” በማለት ንቀት! ትእቢት! ፌዝና ድንቁርና የተቀላቀለበት ንግግር አቅርቧል::
የወይዘሮ ትርፉ ንግግር ለደጋፊዎቻቸውና ታማኞቻቸው እንደ ጀግንነት የሚቆጥሩት ቢሆንም ሌሎቹ ግን ፀያፍ አነጋገር ሲሉ ትዕዝብታቸውን ገልፀዋል:: ቀደም ብለው ራሳቸው እንደገለፁትም የወይዘሮ ትርፉ ንግግር በተግባር ሲታይ “ ትግራዋይ የህወሓት አገልጋይና ታማኝ ካልሆንክ የትም ብትሄድ ከእጃችን አታመልጥም:: ስለዚህ ያለህ አማራጭ የኛ አገልጋይ መሆን ወይም የቁም እስረኛ ሆነህ አርፈህ መቀመጥ ነው:: አሊያም ትመታለህ“ የሚል የማስፈራሪያ መልእክት ለማስተላለፍ የተጠራ ስብሰባ እንደነበር የሚያሳይ ነው:: ዛሬ በዚሁ በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ በትግራይ ተወላጆች መካከል የተነሳው ውዝግብም ከወይዘሮ ትርፉ ዕቅድ የቀጠለ መሆኑን ሳይታለም የተፈታ ነው::
መንግስት በቅርቡ ከሞላ አስገዶም ጋር በተያያዘ የሰጠው መግለጫም ከወይዘሮ ትርፉ ንግግር ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው:: ዋናው ቁም ነገር ሞላ አስገዶም ለምን ወደ ሀገሩ ተመለሰ ወይም ለምን ወደ ኤርትራ ሄደ የሚል አስተያየት ለመስጠት አይደለም:: መሄድም መመለሰም የራሱ ጉዳይ ነው:: ነገር ግን ሆን ተብሎ ከህወሓት መሪዎች ጋር በመመሳጠር ለጋ የትግራይ ወጣቶችን እየመለመለ በመውሰድ የእሳት ራት እንዲሆኑ በማድረግ በትግራይ ህዝብ ላይ የፈፀሙትን በደል ግን ታሪክ ይቅር የማይለው አሳፋሪና ወራዳ ተግባር ነው:: ከላይ ወይዘሮ ትርፉ እንደገለፁት የሞላ አስገደምና የህወሓት መሪዎች ድራማም ዋና መልእክቱ “የትም ብትሄዱ ከኛ አታመልጡም:: እጃችን ረጅም ነው በውስጣችሁ መልምለን ያስገባናቸው የህወሓት ሰላዮች አሉ” የሚል ነው::
ሰሞኑን በዋሽንግተን ዲሲ በጥቂት የትግራይ ተወላጆች መካከል የተነሳው ውዝግብም መነሻና መድረሻው የሞላ አስገዶም ዓይነት ባህርይና ተልእኮ የተላበሱት ጥቂት ሰዎች የጠነሰሱት ሴራ ነው:: በነገራችን ላይ በጥቅም ተደልለው በህዝባዊ ትግል ላይ ጥቁር ታሪክ እየጣሉ እጃቸውን ለህወሓት መሪዎች እየሰጡ ያሉት እነ ሞላ አስገዶም ብቻ አይደሉም:: ሌሎቹ ሞላዎችም በየጊዜው የትግል ጎራውን ጥቅርሻ እየቀቡ ወደ ህወሓት እጃቸውን ለመስጠት እንደ እጅ መንሻ የተጠቀሙበት ብዙዎች ናቸው:: ቀደም ሲል ስብሓት ነጋ የቀየሰውን ከህወሓት ያፈነገጡትን የቀድሞ ታጋዮች ወደ ቀድሞ እናት ድርጅታቸውን የማስመለስ ፕሮጀክት ነው ዛሬ ስራ ላይ እየዋለ ያለው:: በዚሁ የስብሓት ነጋ ፕሮጀክት ምክንያት ጥቂት ጀነራሎችንና ኰለኔሎችን ጨምሮ ከትግል ሜዳ እየፈረጠጡ ለነ አባይ ወሉ እጃቸውን የሰጡት ህወሓት ነበር ታጋዮች ቁጥራቸው ቀላል አይደለም:: ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ በትግራይ ኮሚኒቲ ስም እየተሰራ ያለው ድራማም የአቶ ስብሓት ነጋ ፕሮጀክት ነው ተግባር ላይ እዋለ ያለው::
ከዚህ ሁሉ ድራማ የምንረዳው ቁም ነገር በአንድ በኩል የህወሓት ስርዓት በተዳከመና አደጋ ላይ በወደቀ ቁጥር የትግራይ ህዝብም አብሮ አጥፍቶ ለመጥፋት መፍጨርጨር የተለመደ ስራቸው መሆኑን ነው:: በሌላ በኩል ደግሞ የትግራይ ተወላጆችን እርስ በራሳቸው አናቆሮና በታትኖ በማዳከም በአንፃሩ በትግራይ ምድር ለነፃነቱ፣ ለመብቱና ለሀገሩ ቀና ብሎ የማያይ ፣ የደነቆረና የደነዘዘ ትግራዋይ እንዲኖር በማድረግ ፀጥ ረጭ ብሎ የሚገዛ ትውልድ ለማፍራት ነው:: ስለዚህ ህወሓት በሀገር ቤትም ሆነ በስደት ዓለም ያለው ትግራዋይ ከቁጥጥሩ ውጭ እንዳይወጣ በመካከሉ ሰርገው በመግባት በታኝ ተልእኮ የሚፈፅሙለትን አስመሳይ ምልምሎችን አስቀምጧል:: የዋሽንግተኑ የትግራይ ተወላጆች ውዝግብም ከላይ ላዩ ሲታይ የኪሚኒቲ ጥያቄ ይምሰል እንጂ በስተጀርባው ያለው አላማ ግን ሌላ ነው:: አላማውም ትግራዋይ ለመብቱና ለነፃነቱ እንዳይነሳ በታትነህ፣ አናቁረህ፣ አሸብረህና አደንቁረህ ግዛ የሚል ለአርባ ዓመት የቆየ መሰሪ የህወሓት ፓሊሲ ውጤት ነው::

ጉዳዩን አስመልክተን በሌላ ነጥብ እመለሳለሁ ደህና ሰንብቱልኝ

የመንግስትና የግል ሚዲያዎች የአመለካከትና የክህሎት ችግሮች አለባቸው ተባለ

$
0
0
  • የመንግሥት ሚዲያዎች “የመንግሥት ቃል አቀባይ” ከመሆን የዘለለ ተግባር የላቸውም
  • አድርባይነትና የመንግሥት ልሳንነት በመንግስት ሚዲያዎች ላይ ጐልቶ ይታያል
  • ፅንፈኛ የግል ሚዲያዎች መንግሥትን መለወጥ ግባቸው አድርገው የተነሱ ናቸው

State-of-MediaAddis Admass – በአገሪቱ የሚገኙ የመንግሥትና የግል ሚዲያዎች የአመለካከት፣ የክህሎትና የአደረጃጀት ችግር እንዳለባቸው የተጠቆመ ሲሆን በህዝቡ ዘንድ ተአማኒነትን እያጡ እንደሆነም ተገለፀ፡፡በአገሪቱ ተፅእኖ ፈጣሪ ሚዲያ ለመገንባት ባሉ ፈተናዎችና መፍትሄዎች ላይ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ለሁለት ቀናት ባዘጋጀውና በትናንትናው እለት በጁፒተር ሆቴል በተከፈተው የሁለት ቀናት ሲምፖዚየም ላይ እንደተገለፀው፤ የአገሪቱ ሚዲያዎች ላይ የተአማኒነት ቀውስ እንደሚታይና ሚዲያው ከጠንካራነት ወደ አቅመቢስነት እያመራ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የመንግሥት ሚዲያዎች የመንግሥትን ፖሊሲ በራሱ በመንግስት ቋንቋ ከማቅረብ ውጪ ህዝቡ ጉዳዩን እንደራሱ እንዲቀበለው አድርጐ በማቅረብ ረገድ ደካማ እንደሆኑና የክህሎትና የአመለካከት ችግር በስፋት እንደሚታይባቸው ተገልጿል፡፡
በመንግሥት ሚዲያዎች በአመራርነት ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች የዘመናዊ ሚዲያ ማኔጅመንት ክህሎትና ልምድ እጥረት ያለባቸው ሲሆን ጋዜጠኞቹም የሙያ ብቃት ማነስ እንደሚታይባቸው ተገልጿል፡፡ አድርባይነትና የመንግሥት ልሳንነት፣ በመንግሥት ሚዲያዎች ላይ ጐልቶ እንደሚታይ ጥናቱ አመልክቷል፡፡ የመንግሥት ሚዲያ ባለሙያዎች የህዝባዊ ወገንተኝነት ችግር እንዳለባቸው የገለፀው ጥናቱ፤ የመንግሥት ሚዲያው የመንግሥት ልሳንነቱ የበዛ፣ የህዝቡን ብሶት የመቀበል አቅሙ ደካማ የሆነና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ፈትሾ በማቅረብ ረገድ የአቅም ውስንነት እንደሚታይበት ተገልጿል፡፡
በግል ሚዲያዎች ላይ የሚታዩ ችግሮች ተብለው ከተገለፁት መካከል ለዘብተኝነትና ፅንፈኝነት ተጠቅሰዋል፡፡ ለዘብተኛ የግል ሚዲያዎች ሚዛናዊ የመሆን ሙከራ ሲኖራቸው ፅንፈኛ የግል ሚዲያዎች ደግሞ መንግሥትን መለወጥ ግባቸው አድርገው የተነሱና ለፖለቲካዊ ተልእኮ ማስፈፀሚያነት የተመሰረቱ ናቸው ብሏል – ጥናቱ፡፡
ሚዲያን እንደ መንግስት መገልበጫ አድርጐ ማሰብና ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ መሞከር በግል ሚዲያዎች ላይ በስፋት እንደሚታይ ጠቁሞ ይሄም ለፕሮፌሽናል ጋዜጠኝነት ቦታ መንሳቱን ገልጿል፡፡
እነዚህን ችግሮች በማስወገድ ሚዲያው ኃላፊነት ባለው መልኩ ሙያዊ ተግባሩን እንዲወጣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩሉን አስተዋፅኦ ማድረግ ይጠበቅበታል ያለው ጥናቱ፤ መንግስት የመረጃ ነፃነትን ማረጋገጥ፣ የሚዲያ ተቋማትን እንደ ሁነኛ የህዝብ ድምፅ ማዳመጫ መቁጠርና በሚዲያው ለሚዘግቡና የመንግሥትን ውሳኔ ለሚፈልጉ ጉዳዮች አፋጣኝና ቁርጠኛ እርምጃ መውሰድ ይገባዋል ብሏል፡፡የሚዲያ ባለሙያዎችም አቅማቸውን በማጐልበት፣ ስራቸውን ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ ሊወጡ እንደሚገባም ተገልጿል፡፡ ፖሊስና ፍርድ ቤት በጋዜጠኞች ላይ የማሰር ስልጣናቸውን እንደልባቸው እንዳይተገብሩ የሚያደርግ የተለየ የህግ ጥበቃ እንደሚያስፈልግም በጥናቱ ተገልጿል፡፡
ውይይቱ ዛሬም የሚቀጥል ሲሆን የግል ሬዲዮና የማህበረሰብ ሬዲዮ ስለሚስፋፋበት፣ የግል የቴሌቭዥን ፈቃድ አሰጣጥ፣ በብሮድካስት ሚዲያዎች ላይ ስለሚሰራጩ ማስታወቂያዎችና የህትመት ሚዲያው ስለሚጠናከርበት ሁኔታ ሰፋ ያለ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡


በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኞቹ: “ታዖሎጐስ” እና “ቃለ ዐዋዲ” የኢ.ቢ.ኤስ ፕሮግራሞች ላይ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ተጋግሎ ቀጥሏል

$
0
0
  • የአ/አበባ ጎልማሶችና ወጣቶች ማኅበራት ኅብረት ተቃውሞውን ያስተባብራል
  • ለተቃውሞው፣ በሰባት ቀናት ከ100 ሺሕ በላይ የድጋፍ ፊርማዎች ተሰባሰቡ
  • የጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ እንዲወስንበት ለማድረግ ታቅዷል
  • “በማስረጃ ተደግፎ የሚቀርብ ነገር ካለም እርምት እንወስዳለን” /የጣቢያው ሓላፊ/

(ምንጭ: አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፮ ቁጥር ፰፻፳፤ ቅዳሜ መስከረም ፳፪ ቀን ፳፻፰)

tao logos and kale awadiBegashaw and Assegid
ኢትዮጵያን ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ (EBS) ቴሌቪዥን በሚተላለፉት “ታዖሎጐስ” እና “ቃለ ዐዋዲ” በተሰኙት የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አቀንቃኝ ፕሮግራሞች ላይ ሰሞኑን ከፍተኛ ተቃውሞ ተነሣ፡፡ ፕሮግራሞቹ እንዲዘጉና በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም እንዳይጠቀሙ ለመጠየቅ የሚያግዝ የሕዝባዊ ተቃውሞ ድጋፍ ፊርማም እየተሰባሰበ ነው፡፡

በ7 ቀናት ከ100ሺሕ በላይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች መፈረማቸውን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ጐልማሶች ማኅበራት ኅብረት ሰብሳቢ ፌቨን ዘሪሁን ለአዲስ አድማስ ገልጸዋል፡፡

“ኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ሕጋዊ ዕውቅና ለሌለው አካል ፈቃድ እየሰጠ ጥንታዊቱንና የተከበረችውን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዶግማ እና ቀኖና እንዲኹም ያሬዳዊ ዝማሬን እያንኳሰሱ ይገኛሉ፤” ያሉት ወ/ሮ ፌቨን፤ “ይህ ትውልድን ከመተካት እና የቀናችውን ሃይማኖት ከማስቀጠል አንጻር ትልቅ አደጋ አለው፤” ብለዋል፡፡

የአገራችን ሕገ መንግሥት ማንኛውም ሰው ወይም ተቋም የፈለገውን ሃይማኖት የመከተልና የሀገሪቱ ሕግ በሚፈቅደው መሠረት የእምነቱን አስተምህሮ ማስተማር እና ማስፋፋት እንደሚችል ያስታወሱት ሰብሳቢዋ፤ ነገር ግን የሌሎችን የእምነት ተቋማት ስም በማናለብኝነት በመዝለፍ በሃይማኖቱ ስም ስብከትም ኾነ ትምህርት በብዙኃን መገናኛ ማስተላለፍ ወንጀልም ኃጥያትም ነው፤ ሲሉ ኰንነዋል፡፡

“ታዖሎጐስ” እና “ቃለ ዐዋዲ” የተባሉት የጣቢያው ፕሮግራሞች፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሥርዐት እና ደንብ የተዘጋጁ መኾናቸውን ቢገልጹም የሚተላለፉት መልእክቶች ግን ከኦርቶዶክሳዊ ትምህርት፣ ሥርዐት እና ትውፊት ፈጽሞ የሚቃረኑና የቤተ ክርስቲያኗን ክብር የሚጋፋ በመኾናቸው ፕሮግራሞቹን ለማዘጋት በበርካታ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በመዘዋወር ከ100 ሺሕ በላይ ምእመናንን ማስፈረማቸውን ወ/ሪ ፌቨን ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ “በነዚኽ መርሐ ግብሮች አፋቸውን የሚያላቅቁት ጥቂት የማይባሉ ሰባክያን ነን ባዮች ኦርቶዶክሳዊ ያልኾነ ኑፋቄ ሲጽፉና ሲያስተላልፉ የነበሩ ውስጠ ሌላዎች መኾናቸው በግልጽ ይታወቃል፤” ብለዋል ሰብሳቢዋ፡፡

ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እና ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጋር ግንኙነት አላችኹ ወይ? ፊርማውንስ አስባስባችሁ ስትጨርሱ ለማን ነው የምታቀርቡት? በሚል ላነሣንላቸው ጥያቄ፤ ወ/ሪት ፌቨን ሲመልሱም፤ “አኹን እንቅስቃሴውን እያደረጉ የሚገኙት ከምእመናን ጋር እንደኾነ ገልጸው፤ ውሳኔውን ግን በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል ለቅዱስ ሲኖዶስ እንዲቀርብ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡ ከዚያ በፊት ግን ከቅዱስ ሲኖዶስ በታች በተዋረድ ካሉ ጽ/ቤቶች ጋር እንነጋገራለን፤” ብለዋል፡፡

ለኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን ቅሬታ አቅርበው እንደኾን የተጠየቁት ሰብሳቢዋ፤ “የጣቢያው ባለቤቶች ስሕተት እንደሚሠራ በርግጠኝነት ያውቃሉ፤”ካሉ በኋላ የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰቡን በ10 ቀናት ውስጥ በአፋጣኝ አጠናቀው ጥቅምት ላይ የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ለሚቀመጠው ቅዱስ ሲኖዶስ ለማቅረብ እየተጣደፉ መኾኑን ጠቁመዋል፤ ከዚያም በላይ ለጣቢያውም ጥያቄ እናቀርባለን፤ ብለዋል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ ምላሽ ለማግኘት በአዲስ አበባ ለሚገኘው የኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን ተወካይ ኢንኮም ትሬዲንግ ደውለን፤ እነዚህ ፕሮግራሞች ፈቃድ የሚያገኙት አሜሪካ ከሚገኘው ዋናው መሥሪያ ቤት ስለኾነ በጉዳዩ ላይ አስተያየት መስጠት እንደማይችሉ ነግረውናል፡፡

logo_finalአሜሪካ ከሚገኙት የጣቢያው ሥራ አስፈጻሚዎች አንዱ፤ አቶ ነቢዩ ጥዑመ ልሳን፤ ለአዲስ አድማስ በስልክ እንደተናገሩት፤ ከቅዱስ ሲኖዶሱም ኾነ ከሌሎች የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕጋዊ ተቋማት በይፋ የደረሳቸውና በአካልም ቀርቦ ያመለከተ ባይኖርም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚካሔደውን እንቅስቃሴ ተረድተነዋል፤ ብለዋል፡፡ በማስረጃ ተደግፎ የሚቀርብ ነገር ካለም አስፈላጊውን እርምት እንደሚወስዱም አስታውቀዋል፡፡

*               *               *

“ታዖሎጎስ” እና “ቃለ ዐዋዲ” በተባሉ የኢ.ቢ.ኤስ ቲቪ ፕሮግራሞች በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም እንዳይጠቀሙ ስለ መጠየቅ፤

Petition Background (Preamble):

የሀገራችን ሕግ መንግሥት ማንም ሰው የፈለገውን ሃይማኖት የመከተል መብት እንዳለው በግልጽ አስቀምጧል:: ስለዚህ ማንም የፈለገውን ሃይማኖት ያለተጽዕኖ እና ግፊት መከተል ይችላል፤ የሚያምንበትንም ሃይማኖት፣ የሀገሪቱ ሕግ በሚፈቅደው መሠረት ለማስተማርና ለማስፋፋት የሚከለክለው የለም፤ ነገር ግን የሌሎችን የእምነት ተቋማት ስም በማናለብኝነት በመዝለፍ እና በዚያ እምነት ስም ስብከትም ኾነ ትምህርት በብዙኃን መገናኛ ማስተላለፍ ግን ወንጀልም ኃጥአትም ነው::

ለዚኽም መነሻ የኾነን፣ በኢ.ቢ.ኤስ ላይ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስም የሚተላለፉ “ታዖሎጎስ” እና “ቃለ ዐዋዲ” የተባሉ የቴሌቪዝን መርሐ ግብሮች ናቸው:: እኒኽ መርሐ ግብሮች፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ደንብ መሠረት የተዘጋጁ እንደኾኑ ይገልጻሉ፤ የሚተላለፉት ዝግጅቶች ግን፣ ከኦርቶዶክሳዊ ትምህርት አንጻር ከፍተኛ ጥያቄ የሚያሥነሱና የብዙውን ኦርቶዶክሳዊ ምእመን ግንባር የሚያስቋጥሩ ናቸው:: በነዚኽ መርሐ ግብሮች የሚራቀቁት ጥቂት የማይባሉት ሰባክያንም ኦርቶዶክሳዊ ያልኾነ የኑፋቄ ትምህርት ሲጽፉና ሲያስፋፉ የነበሩውስጠ – ሌላ ሰዎች መኾናቸው በተለያዩ ሚዲያዎች በስፋት ተዘግቧል፤ እየተዘገበም ነው::

በቅርቡ በኢ.ቢ.ኤስ በሚተላለፈው የቴሌቪዥን መርሐ ግብርም ላይ በግልጽ የቤተ ክርስቲያኒቱን ዘመን ጠገብ ያሬዳዊ ዜማዎች እና የተከበሩ ዘማርያንን “መንደርተኛ” ብለው እስከ መዝለፍ ማለት ደርሰዋል:: ይህ በሃይማኖት ነጻነት ስም የሚደረግ ጠብ አጫሪነት በጊዜ ካልተፈታ በኋላ ሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊ እና ሀገራዊ ችግር መፍጠሩ አይቀርም::

ስለዚህ እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ጥያቄዎቻችንን ከዚህ በታች አቅርበናል፡-

1. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ራሱን የቻለ ሃይማኖታዊ እና አስተዳደራዊ መዋቅር አላት:: ማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱን ስም ይዞ የሚወጣ የአየር ፕሮግራም የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕጋዊ ፈቃድ ወይም ይኹንታ ማግኘት አለበት:: የቤተክርስቲያኒቱ ሕጋዊ መዋቅር ውስጥ ያለ አካል መኾን ይኖርበታል:: ቤተ ክርስቲያኒቱ ያላከችው ማንም አካል ግን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ስም ይዞ መንቀሳቀስ አይችልም::

በዚኽም መሠረት “ታዖሎጎስ” እና “ቃለ ዐዋዲ” የተሰኙት መርሐ ግብሮች ከቤተ ክርስቲያኗ ሕጋዊ ፈቃድ እስካልተሰጣቸው ድረስ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያንን ስም መጠቀም አይችሉም:: ስለዚኽም ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ሕጋዊ ማስረጃ ካላመጡ በስተቀር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስም መጠቀም እንዲያቆሙ ቴሌቪዝን ጣቢያው አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስድልን እንጠይቃለን::

2. በነዚሁ የቴሌቪዝን መርሐ ግብሮች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስም የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀኖና በሚጥስ መልኩ የሚተላለፉ መልእክቶች እና ድርጊቶች እየተበራከቱ መጥተዋል:: ይህም የአንድን ሃይማኖት ክብርና ልዕልና የሚነካ ነው:: በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስም የሚከናወኑ ኢ – ኦርቶዶክሳዊ የኾኑ ስብከቶች እና ድርጊቶች የሃይማኖቱ ተከታዮች ላይ የሞራልና የሥነ ልቡና ጫና እያስከተለ ነው:: ሕዝቡ ወደ ሕጋዊ ጥያቄ ከመሔዱ በፊት የኢ.ቢ.ኤስ አስተዳደር አስፈላጊውን እርምት እንዲሰጥልን እንጠይቃለን::

3. በነዚኹ ሰባክያን፣ በነዚሁ የቴሌቪዥን መርሐ ግብሮች ላይ በዐደባባይ “መንደርተኛ” በሚል የተዘለፈው የቤተ ክርስትያኒቱ ዘማሪ ይልማ ኃይሉ በይፋ ይቅርታ እንዲጠየቅ፤ በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮም ኾነ መምህራን ላይ ተመሳሳይ ዘለፋ እንዳይከናወን አስፈላጊውን መመርያ እንዲሰጥልን የኢ.ቢ.ኤስን አስተዳደር በኢትዮጵያዊ እና ክርስቲያናዊ ትሕትና እንጠይቃለን::

4. በመጨረሻም እነዚሁ ስብስቦች ለቲቪ ፕሮግራሞቻቸው ማስፈጸሚያ ይኾኑ ዘንድ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ስም የሚያደርጓቸው የስፖንሰር ጥያቄዎችና ልመናዎች በአስቸኳይ እንዲታገዱ እንጠይቃለን::
በዚሁ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደርም፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ስለሚተላለፉት መርሐ ግብሮች ግልጽ መግለጫ እንዲሰጥ እንጠይቃለን:: ከኹሉም በላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖና እና ታሪክ ከመጠበቅ እና ከማስጠበቅ አንጻር በዚኽ ጉዳይ ላይ ሰፊው ምእመን ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡

Source:: haratewahido

የአውሮፓ ሕብረት አባሎች ወደ 160 ሽህ ስደተኞችን በአባል ሀገሮች ለማስፈር ተስማሙ

$
0
0

[jwplayer mediaid=”47366″]

የአውሮፓ ሕብረት 28 አባሎች ወደ 160 ሽህ የሚጠጉ ስደተኞችን ወደ ሌሎች አባል ሀገሮች ለማስፈር ተስማሙ። በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ከግሪክና ጣሊያን የስደተኞችና የፍልሰተኞች ማቆያ ስፍራዎች፤ ወደ ሌሎች የአውሮፓ ሀገሮች የሚሰፍሩት፤ ጉዳያቸው ተቀባይነት ያገኘ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎችና ስደተኞች ይሆናሉ።

BF9974C9-AA37- Satenaw Newsሜዲትራንያን ባህር ዳርቻ የሚገኙ የአውሮፓ ሀገሮች፤ በተለይ ጣሊያንና ግሪክ፤ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በርካታ ሰዎች የሚፈናቀሉበትና የሚፈልሱበት ዓለም አቀፍ ቀውስ ቀዳሚ ተቀባይ ሀገሮች ሆነዋል።

ከነዚህ የባህር ዳርቻ ሀገሮች የፍልሰተኞችና ስደተኞች ወደ ሌሎች ሐገሮች እንዲሰፍሩ፤ የአውሮፓ ህብረት አባላ ሀገሮችም ጉዳዩን በጋራ ሃላፊነት እንዲወጡት ተግባራዊ ጥረት ተጀምሯል። የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት (UNHCR) የደቡብ አውሮፓ ቃል አቀባይ ካርላታ ሳሚ (Carlotta Sami) ስደተኞችና ፍልሰተኞችን የማስፉር እቅድ በቅርብ ወራት ስምምነት ያገኘ እንደሆነ ገልጸዋል።

“በርካታ አባል ሀገሮች የተወሰኑ ስደተኞችን ተቀብለው ለማስፈር ተስማምተዋል። ሰፈራው የሜዲትራንያን ባህርን አቋርጠው ወደ ጣሊያንና ግሪክ የሚገቡትን ስደተኞች ይመለከታል” ካርላታ ሳሚ ብለዋል።

የተወሰነው160 ሽህ ስደተኞችን ለማስፈር ነው። ሆኖም ቁጥሩ አባይን በጭልፋ አይነት፤ ችግሩን የማይቀርፍ ነው።

ግሪካና ጣሊያን እንዲሁም ሌሎች የስደተኞችና ፍልሰተኞች ቀዳሚ መዳረሻ የአውሮፓ ሀገሮች፤ የህብረቱ አባላት እንዲያግዟቸው ጥሪ ሲያሳልፉ ቆይተዋል። ሆኖም የተቀናጀ የስደተኞችና ፍልሰተኞች አቀባበል ስልት እንዲሁም ስምምነት ስላልነበረ፤ አፈጻጸሙ ተጓቶ ሰንብቷል።

ባለፈው ሚያዝያ ወር የአውሮፓ ህብረት ሀገሮች አስቸኳይ ጉባዔ ጠርተው የስደትና ፍልሰትን ጉዳይ በ28ቱ አባል ሀገሮች መሪዎች ውይይት ተደርጎበት ባለ 10 ነጥብ የስምምነት ሰንድ ቀርቦ ነበር።

ከነዚህም መካከል አንዱ በባህር ላይ ፈልጎ የማዳን አቅምን ማጠናከር ሲሆን፣ ትሪተን (Triton) እና ፖሲዶን (Poseidon) ለሚባሉት በሜዲትራንያን ባህር ሰዎችን ፈልጎ የማዳን መርሃ ግብሮች፤ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት በጀታቸው በእጥፍ እንዲያድግ ተወስኗል።

ሌላኛው ጉዳይ የህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎችን ንብረቶች፤ በተለይ ጀልባዎችን በመቀማት፤ ከጥቅም ውጭ እንዲሁኑ ማድረግ የሚል ነው። የብርታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካምሮን፤  በጉባዔው በር ላይ ባደረጉት ንግግር የዛሬው ስብሰባ አትኩሮት ህይወት ማዳን ሊሆን ይገባዋል ካሉ በኋላ ያደረጉት ንግግር ቀጥተኛ ነበር።

ህይወት ማዳን ማለት እነዚህን ችግረኞች መታደግ ነው። ከዚያም በተጨማሪ ወሮበላ አዘዋዋሪዎችን መደቆስና የአካባቢው ሃገሮች እንዲረጋጉ ማድረግ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካምሮን በወቅቱ ኤች ኤም ኤስ ቡልዋርክ (HMS Bulwark) የተባለች የብርታንያ የጦር መርከብን በሜዲትራንያን ባህር እንደሚያሰማሩ ተናግረው ነበር። ሁለት ሄሊኮፐሮች፡ 67 መኪኖች፣ ሶስት አውቶማቲክ ማሳሪያዎችና ከ400 በላይ ወታደሮች የመጫን አቅም አላት ኤች ኤም ኤስ ቡልዋርክ (HMS Bulwark)።

አርብለት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በብርታንያ የቀረበውን ረቂቅ ውሳኔ አጽድቋል። በዚህም መሰረት የአውሮፓ የባህር ሀይል የህገወጥ አዘዋዋሪ ጀልባዎችና መርከቦች ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወስዱ ስልጣን ሰጥቷል። መርከቦችን በዓለም አቀፍ የውሃ ክሎች መያዝ፣ መፈተሽና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ማስወገድን ያካትታል።

ሆኖም በሊቢያ የባህር ክልል እንዲሁም የባህር ዳርቻዎች የሚገኙ ጀልባዎችን ለማውደም በብርታንያና በአውሮፓ ህብረት የቀረበውን ሃሳብ፤ የመንግስታቱ ድርጅት አላጸደቀውም።

የአውሮፓ ህብረት በዓለም አቀፍ የባህር ክልሎች የሚንቀሳቀሱ ህገወጥ አዘዋዋሪ ጀልባዎችን የሚቆጣጠር የባህር ሃይል አሰማርቷል። የአውሮፓ ህብረት ባለፈው ሮብ “ዘመቻ ሶፍያ” የተባለ ሶስት የአፈጻጸም እቅድ ያለው ወታደራዊ ትብብር ለማድረግ ከሊብያ ጋር ተስማምቷል። አላማውም ህይወትን ማዳን፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርንና የወሮበሎችን ስራ ማስቆም ነው።

ከተሰነይ ኤርትራ ተሰዶ ወደ አውሮፓ የገባ መሆኑን የገለጸው የ20 ዓመት ወጣት በጣሊያን ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢዎች የተሰደደበትን ምክንያት ሲያስረዳ “የኤርትራ መንግስት በአሁኑ ወቅት ወጣቶችን በመጨቆን በውትድርና ስለሚያሰልፍ” ከሀገሩ ለመውጣት መወሰኑን ገልጿል።

ባለፈው 10 ወራት ብቻ፤ 3,092 ሰዎች ለህይወት አደገኛ በሆነው የጀልባ ጉዞ በሜዲትራንያን ባህር ላይ ሰምጠው ሞተዋል። ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ደግሞ ወደ አውሮፓ ለመሻገር በቅተዋል። የሚበዙት በግሪክና ጣሊያን ሰፍረው እንደሚገኙ የዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ገልጿል። የአውሮፓ ህብረት የሰዎች ፈልጎ ማዳን መርሃ ግብርም ከ100ሽህ በላይ ሰዎችን ህይወት እንዳተረፈ ተመዝግቧል።

ባለፈው አርብ የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት በስደተኞችና ፍልሰተኞች ጉዳይ ላይ ያሳለፈው ውሳኔ ላይ ቬኔዙዌላ ተአቅቦ ስታድርግ ሌሎቹ 14 አባላት በሙሉ ድምጽ አጽድቀውታል።

ሳሌም ሰለሞንና ሄኖክ ሰማእግዜር አቀናብረው ያዘጋጁትን ሙሉ ዝርዝር የተያያዘውን የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

የአውሮፓ ሕብረት አባሎች ወደ 160 ሽህ ስደተኞችን በአባል ሀገሮች ለማስፈር ተስማሙ/ርዝመት – 6ደ54ሰ/

The post የአውሮፓ ሕብረት አባሎች ወደ 160 ሽህ ስደተኞችን በአባል ሀገሮች ለማስፈር ተስማሙ appeared first on Zehabesha Amharic.

በሶማልያ 8 ኢትዮጲያውያን ፍልሰተኞች በመኪና አደጋ ሞተዋል

$
0
0

አዳነች ፍሰሀ

የዋሽንግተን ዲሲ

ኢትዮጵያውያን ፈላሾችን የጫነ የጭነት መኪና ፑንትላንድ በተባለው የራስ ገዝ ክልል ኳርድሆ ከተማ አጠገብ ተገልብጦ ቢያንስ 8 ሰዎች ተገድለው 40 እንደቆሰሉ የአይን ምስክሮችና የሆስፒታል ምንጮች ገልጸዋል።

ኢትዮጵያውያን ፈላሾችን የጫነ የጭነት መኪና ፑንትላንድ በተባለው የራስ ገዝ ክልል ኳርድሆ ከተማ አጠገብ ተገልብጦ ቢያንስ 8 ሰዎች ተገድለው 40 እንደቆሰሉ የአይን ምስክሮችና የሆስፒታል ምንጮች ገልጸዋል።

ጀማል አሕመድ ኡስማን የተባለ ከአደጋው የተረፈ የ 25 አመት እድሜ ወጣት ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ የሶማልኛ አገልግሎት በተናገረው መሰረት የጭነት መኪናው ከአቅሙ በላይ 120 ሰዎችን ጭኖ ነበር። ተሳፋሪዎቹ በሙሉም ኢትዮጵያውያን ነበሩ። ፋዱሞ ያሲን ጃማ የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ጋዜጣኛ ሆስፒታል በመሄድ ሶስት እዛው የሞቱ ሰዎች አስከሬኖችን እንደነበሩ ገልጸዋል።

ዝርዝሩን የተያያዘውን የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

[jwplayer mediaid=”47372″]

 

51C86376-CBC7-411A-B9BA-FE47805EA8BD_w640_r1_s_cx4_cy3_cw90

 

 

The post በሶማልያ 8 ኢትዮጲያውያን ፍልሰተኞች በመኪና አደጋ ሞተዋል appeared first on Zehabesha Amharic.

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሕገመንግስቱ እንዲሻሻል ያቀረቡትን ጥናት ምክንያት አስረዱ

$
0
0

የቀድሞው ፕሬዝዳንት እና በተቃውሞ ፖለቲካውም ውስጥ የአንድነት ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከተጻፈበት ወረቀት በላይ ዋጋ የለውም የሚባለውና ስርዓቱ ለፖለቲካ አርጩሜ ይጠቅሰው ካልሆነ ተግባራዊ ያላደረገውን ሕገ መንግስት የተወሰኑ አንቀጾች እንዲሻሻሉ ጥናት አቅርበዋል። በዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከህብር ሬዲዮ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርገዋል።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሕገመንግስቱ እንዲሻሻል ያቀረቡትን ጥናት ምክንያት አስረዱ

The post የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሕገመንግስቱ እንዲሻሻል ያቀረቡትን ጥናት ምክንያት አስረዱ appeared first on Zehabesha Amharic.

የ1966ቱ/የ77ቱ ዓይነት የረሃብ እልቂት ከመድረሱ በፊት መንግሥትም ሆነ ሰብአዊ ርኅራኄ የሚሰማን ዜጎች ሁሉ የበኩላችንን ጥረት ማድረግ ይገባናል!!

$
0
0

ክፍል-፩
በዲ/ን ኒቆዲሞስ

እኛ ኢትዮጵያውያን ለረሃብ ክሥተት በፍጹም እንግዶች አይደለንም፡፡ ጠኔ-ችጋር ደግሞ ደጋግሞ የጎበኘን፣ ረሃብ ስማችንን ያጎደፈብን፣ በሃፍረት አንገታችንን ያስደፋን፣ ቅስማችንን የሰበረን፣ ታሪካችንን ያጠለሸብን፣ የእልቂት፣ የሰቆቃ፣ የደም ምድር- ‹‹አኬል ዳማ›› በሚል የሚያሰቅቅ ስያሜ የተጠራን፣ መላው ዓለም በኀዘን ከንፈሩን የመጠጠልንና እንባ የተራጨልን ምስኪን ሕዝቦች ነን፡፡ ከዚህ አገራችን ለዘመናት ከተጎናጸፈችው እጅጉን ከምናፍርበትና ከምንሳቀቅበት ዓለም አቀፋዊ ገጽታ ጋር በተያያዘ በዛሬው መጣጥፌ ይዋል ይደር ሳንል ጊዜ ሰጥተን እንመካከር ዘንድ ዘንድሮ በዝናም እጥረት በአገራችን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ለረሃብ ስለተጋለጡት ሚሊዮኖች ወገኖቻችን እስቲ አብረን ትንሽ እንቆዝም፡፡
famine
በዚህች ቅጽበት ምናልባት አውቀነውም ይሁን ሳናውቅ በብዙ ትርፍና ባላስፈላጊ ወጪ በመዝናናት በጥሩ ምቾትና ድሎት ላይ ያለነውንና በማንኛውም ልኬት ሰዎች ለተባልን ሁሉ ፊታችንን መለስ አርገን ሚሊዮኖች ወገኖቻችን ለረሃብ ስለተጋለጡበትና በየአሥር ዓመቱ ብቅ እያለ ቤተኛው ስላደረገን የረሃብ ጉዳይ ላይ በጋራ እንወያይ ዘንድ ወደድኹ፡፡ እንደ መግቢያም ዛሬም ድረስ ሳስታውስው እጅጉን ከሚያሳዝነኝ ከአንድ ገጠመኜ ጽሐፌን ልጀምር፡፡

በደቡብ አፍሪካ የአርትና የባህል ሚ/ር፣ ማንዴላና የትግል ጓዶቻቸው ለ፳፯ ዓመታት በተጋዙበትና በዩኔስኮ በዓለም አቀፍ ቅርስነት በተመዘገበው በሮቢን ደሴት የነጻነት ሙዚየምና እና በኔልሰን ማንዴላ ፋውንዴሽን ትብብርና የገንዘብ ድጋፍ የሚሰጠውን ‹‹የአፍሪካ ቅርስና ቱሪዝም ጥናት የድኅረ ምረቃ/የፖስት ግራጁየት የትምህርት ፕሮግራም›› የስኮላር ሺፕ ዕድል አግኝቼ ትምህርቴን በተከታተልኩባት በኬፕታውን ከተማ በሮቢን ደሴት ሙዚየም የሆነ ገጠመኜ ነው፡፡

የዩኒቨርሲቲ ትምህርታችንን ከመጀመራችን በፊት የትምህርት ክፍላችን አስተባባሪ የሆነው ናይጄሪያዊው ጎልማሳ ከተለያዩ አገራት የመጣን ተማሪዎችን እርስ በርሳችን እንድንተዋወቅና እንዲሁም ይህን የነጻ የስኮላር ሺፕ ትምህርት ዕድል ለሰጠን ማንዴላና የትግል አጋሮቻቸው ለጥቁር ሕዝብ ነጻነት፣ ለሰው ልጆች መብትና እኩልነት ሲሉ ለበርካታ ዓመታት ቃላት ሊገልጸው የማይችለውን መከራና ግፍ በተቀበሉባት ለሮቢን ደሴት ወኅኒ/ግዞት ቤት ከነጻነት በኋላ ደግሞ ሺህዎች በየዕለቱ የሚጎርፉበት የነጻነት መታሰቢያ ሙዚየም ለመጎብኘትና ምስጋናችንን ለመግለጽ በሚል ነበር በደሴቲቱ የተገኘነው፡፡

የትምህርት ክፍላችን አስተባባሪ ከጉብኝታችንና ከቀኑ ውሎአችን በኋላ በሮቢን ደሴት በሚገኘው መኖሪያው የእራት ግብዣ አድርጎልን ነበር፡፡ ከኬፕታውን ሲ ፓይንት- ከኔልሰን ማንዴላ ጌት በመርከብ ለ፵፭ ደቂቃ ያህል ቀዝቃዛውንና ማዕበል የሚንጠውን የአትላንቲክ ውቅያኖስን በማቋረጥ፣ ውብ በሆነችው የደቡብ አፍሪካ እናት ከተማ በኬፕታውን ድንቅ ተፈጥሮ እየተደመምን፣ ከአድማሱ ጋራ የተጋጠመ የሚመስለውን ባለ ልዩ ግርማ ተራሮቿን በርቀት እየቃኘን፣ እንዲሁም በዓለማችን የመርከብ ቴክኖሎጂ ታሪክ ተወዳዳሪና አቻ የሌላት የተባለችውን የእንግሊዟን ታይታኒክ መርከብ ከ1800 ተጓዦቿ ጋር ያሰጠመውን በባለ ግርማ ሞገሱን የአትላንቲክ ውቅያኖስ የመርከብ ላይ ጉዞና የዶልፊኖችን የውኃ ላይ አስገራሚ ትእይንትና በሮቢን ደሴት ጉብኝታችን የፈጠረብንን ልዩ ደስታ ስሜታችንን ከፍ እንዳደረገው ነበር የትምህርት ክፍላችን አስተባባሪ በሆነው በሮቢን ደሴት መኖሪያ ቤቱ ለእራት የታደምነው፡፡

ታዲያ እራት ተበልቶ አልቆ የደቡብ አፍሪካውያኑን ወይን እየተጎነጨን ስንጨዋወት በጨዋታችን መካካል በትምህርት ክፍላችን አስተባባሪ ቤት ጠረጴዛ ላይ የተቀመጠውን የኔልሰን ማንዴላን የትግል ሕይወት የሚተርከውን መጽሐፍ አንስቼ ሳገላብጥ፣ ማንዴላ ለወታደራዊ ሥልጠና ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በነበሩበት ጊዜ በወቅቱ ከኢትዮጵያ መንግሥት የተሰጣቸውን ፓስፖርት በመጽሐፉ ላይ በአባሪነት መካተቱና የኢትዮጵያ ቆይታቸውን የሚያትተውን አስደናቂ ትረካ በማየቴ እጅጉን ደስ አለኝ፡፡

በአጠገቤ ለነበረችው ከዩኔስኮ ተወክላ ከሀገረ ናምቢያ ለመጣች የክፍል ጓደኛዬ መጽሐፉን እያሳየኋት ማንዴላ ስለ አገሬ ኢትዮጵያ የሰጡትን ድንቅ ምስክርነት በኩራት ካነብበኩላት በኋላ አገራችን ኢትዮጵያ ለደቡብ አፍሪካው የነጻነት ታጋይ ለኔልሰን ማንዴላና በአጠቃላይ ለጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ትግልና ተጋድሎ ያደረገችውን አስተዋጽኦ ከአንጸባራቂው ከዓድዋው ድል ጋራ በአጭሩ ተረኩላት፡፡

‹‹Oh really! እኔ ይሄን አላውቅም፤ ብዙዎች አፍሪካውያንም ይሄን የሚያውቁ አይመስለኝም፡፡ ስለ ኢትዮጵያ አብዛኛው የአገሬ ናምቢያ ሕዝብም ሆነ እኔ የምናውቀው ኹለት ነገሮችን ነው፡፡ አንደኛው በርካታ ተከታይ ያላቸውን ንጉሣችሁን ኃይለ ሥላሴን/ራስ ተፈሪውያንን ሲሆን ኹለተኛው ግን Sorry to say this …! ይሄን ስልህ እያዘንኩ ነው፤ በአገራችሁ ተከስቶ በነበረው አስከፊው ድርቅ/ራብ ስላለቁት ወገኖቻችሁን ነው የሰማሁትም፣ የማውቀውም፡፡ እውነቴን ነው የምልህ እንዲህ ዓይነት ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ ኩራት የሆነውን ታሪካችሁን፣ ሥልጣኔያችሁንና የአፍሪካ ጫፍ በሆነችው ደቡብ አፍሪካ ድረስ የዘለቀ አኩሪ የነጻነት ተጋድሎ ታሪክ ያላችሁ ታላቅ ሕዝቦች መሆናችሁን አላውቅም፡፡››

‹‹እንደ ቢ.ቢ.ሲ ባሉ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ያስተላለፉልንና ስለ አገራችሁ የምናውቀው የራብ፣ የጦርነትና የሰቆቃ ምድር መሆናችሁን ነው፡፡›› እንደውም አለችኝ ይህቺ ናምቢያዊት የክፍል ጓደኛዬ፤ ‹‹እንደውም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በአገራችሁ ደርሶ የነበረው ረሃብ ባደረሰባችሁ አሰቃቂ እልቂት ልባቸው ክፉኛ ያዘነባቸው የአገሬ የናምቢያ አዛውንቶች አንዳንድ ሰዎች ምግብ ያለ አግባብ ሲጥሉ ሲያዩ ‹Hey please Think the Starved People in Ethiopia››› እንደሚሉ ስትነግረኝ ያ የነበረው የቀኑ ውሎ ደስታዬና በአገሬ የነጻነት ታሪክ ተጋድሎ ኩራቴ በአፍታ ወደ ኀዘን ተቀየረ፡፡ ምነው ይሄን መጽሐፍ ባላነሳሁት-በቀረብኝ በሚል ጥፍሬ ውስጥ የመግባት ያህል ሃፍርትና ውርደት ተሰማኝ፡፡ ከዛች ቅጽበት በኋላ ከዚህች ሴት ጋራ ብዙም ማውራት አልቻልኩም፡፡

ሺህ ዘመናትን ካስቆጠረው ረጅሙ ታሪካችን፣ ቅርሳችንና ሥልጣኔያችን፣ በእጅጉ ከምንኮራበት የነጻነት ተጋድሎ ታሪካችን፣ ከአምላክ ከተቸረን የተፈጥሮ ጸጋችንና ውበታችን ይልቅ ክፉ ክፉው ታሪካችን እንዲህ ከጫፍ እጫፍ መሰማቱና መናኘቱ፣ መተረቻና መጠቋቆሚያ፣ የረሃብ መዝገበ ቃላት ፍቺ ማድመቂያ፣ የእርስ በርስ ጦርነትና የእልቂት፣ የደም ምድር ‹‹አኬል ዳማ›› መገለጫ ሕዝቦች መሆናችን ግራ እያጋባኝ ይሄው ዛሬም ድረስ ይሄ ክፉ ትዝታዬ ከእኔ ጋራ ይኖራል፡፡

በእርግጥ ይህ ዓይነቱ ገጠመኝ የእኔ ብቻ ገጠመኝ ነው ብዬ አላስብም፡፡ በርካታ ኢትዮጵያውያን በሔዳችሁበት አገርና ምድር ሁሉ ተመሳሳይም ብቻም ሳይሆን እንዳውም ከኔም ገጠመኝ ካልኩትም የከፋ ብዙ አንገታችሁን ያስደፋና ያሳቀቀን ገጠመኝ እንዳለን አውቃለሁ፡፡ በዛው በደቡብ አፍሪካ የነጻ ትምህርት ዕድል አግኝቶ ከሔደ ጓደኛችን መካከል ከሌሎቻችን ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ወፈር ያለና የሌሎች አፍሪካውያን ወንድሞቻችን ዓይነት በስፖርትና በምግብ የዳበረ ሰውነት ያለውን ወገናችንን አንዲት ደቡብ አፍሪካዊት የክፍሉ ተማሪ፣ ‹‹አንተ ረሃብ ከሌለበት የኢትዮጵያ ክፍል የመጣህ መሆን አለብህ …!?›› እንዳለችው በቁጭትና በኀዘን ሆኖ አጫውቶናል፡፡

ከጥቂት ዓመታት በፊትም አንጋፋው አዲስ ዘመን ጋዜጣ አንድ ለትምህርት ወደ ደቡብ ኮሪያ ሄዶ የነበረ ኢትዮጵያዊ ወጣት በዩኒቨርስቲው መምህራንና የክፍል ጓደኞቹ ከረሃብ እልቂትና ጦርነት ተርፎ ለዚህ ዕድል መብቃቱ ኩራት ሊሰማው እንደሚገባው በነጋ ጠባ ሲነግሩትና ሲያስረዱት እርሱም ይሄን ይረዱኝ ይሆን በሚል ስለ አገሩ ያለውን እውነታ ቢነግራቸውም ሊያምኑት ባለመቻላቸው ባጋጠመው የሥነ-ልቦና ቀውስ፣ ብቸኝነትና ባይተዋርነት እጅጉን ተማሮ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ትምህርቱን ጥሎ ወደ አገሩ እንደተመለሰ የሚተርክ ጽሑፍ እንዳስነበበን ትዝ ይለኛል፡:

በሄዱበትና በተሰደዱበት አገር በነጋ ጠባ ስለ ኢትዮጵያ የሚወራው የረሃብ፣ የእርስ በርስ ጦርነትና የእልቂት ታሪክ ቅስማቸውን ሰብሮት በባእድ ምድር ቀና ብለው መራመድ እያቃታቸው በኀዘን፣ ሰቀቀንና በቁጭት አንጀታቸው እያረረ፣ እግዚኦ የኢትዮጵያ አምላክ ሆይ መቼ ነው ስማችንና ታሪካችንን የምትለውጠው!? በሚል ተማኅጽኖ እንባቸውን እያፈሰሱ ከአምላካቸው ጋራ የሚሟገቱ በርካታ ወገኖች ዛሬም ድረስ አሉን፡፡ ስለ አገራቸው፣ ስለ ወገኖቻቸው በቁጭት የሚንገበገቡ፡፡

ይህን ለዘመናት አንገታችንን ያስደፋንን የረሃብ፣ የእርስ በርስ ጦርነት የውርደት ታሪካችንን ለማደስ ጉልበቴ በርታ በርታ እያልንበት ባለንበት ዘመን ረሃብ በራችንን ዳግመኛ ማንኳኳቱና በተከታታይ ምልክቱ ቢታይም በተለየ ግን በዘንድሮው ወርኻ ክረምት በዝናም እጥረት ምክንያት በተከሰተው ድርቅ ለረሃብ ለተጋለጠው በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝባችንን ከረሃብ፣ ከችጋር እልቂት ይታደጉልን ዘንድ መንግሥታችን ለጋሽ አገራትንና ዓለም አቀፍ የዕርዳታ ድርጅቶችን እየተማጸነ ነው፡፡

ከእንግዲህ ወዲህ የሚሠሩ ወርቅ እጆችን ይዘን ስንዴ ልመና እንዴት ይታሰባል፣ ሕልማችን ሕዝባችንን በቀን ሦስት ጊዜ ማብላት ነው፣ ረሃብን ታሪክ እናደርገዋለን፣ በምግብ እህል ራሳችንን እየቻልን ነው … ዕድገታችንን የኢኮኖሚ ግሥጋሤያችን ዓለም ሁሉ እጁን በአፉ ላይ እንዲጭን እያደረግነው ነው … ወዘተ እንዳልተባልን፣ እንዳላስባልን ዛሬ ግን ይኸው ዓይናችንን በጨው አጥበን በምዕራባውያኑ ደጃፍ ምግብ ልመና አኩፋዳችንን ይዘን መሰለፋችን እጅጉን ያሸማቅቃል፣ ያሳፍራልም፡፡

መንግሥት በቅርቡ ባወጣው መግለጫ ባለፈው ወርኻ ክረምት የዝናም ስርጭቱ ዝቅተኛና የተጠበቀውያን ያህል ባለመሆኑ የተነሣ ከ፬.፭ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ለረሃብ እንደተጋለጠና አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው አሳውቆአል፡፡ ለረሃብ የተጋለጡትን ወገኖቻችንን ቁጥር በተመለከተ መንግሥት ይፋ ያደረገው ቁጥር የተዛባ መሆኑን የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት እየገለጹ ነው፡፡ እነዚሁ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትና የዕርዳታ ድርጅቶች ለረሃብ የተጋለጠው ሕዝባችን ቁጥር ወደ ፯ ሚሊዮን እንደሚጠጋና ይህ ቁጥርም ወደፊት ሊያሻቅብ እንደሚችል እየተናገሩና እያስጠነቀቁ መሆናቸው ሌላኛው በፊታችን የተጋረጠብን ክፉ ዜና/መርዶ መሆኑ ማወቅ ሁላችንንም ግድ ይለናል፡፡
ሰላም!
ይቀጥላል፡፡

The post የ1966ቱ/የ77ቱ ዓይነት የረሃብ እልቂት ከመድረሱ በፊት መንግሥትም ሆነ ሰብአዊ ርኅራኄ የሚሰማን ዜጎች ሁሉ የበኩላችንን ጥረት ማድረግ ይገባናል!! appeared first on Zehabesha Amharic.

የቀድሞው ኢነጋማ ፕሬዚደንት ከፋለ ማሞ ከዚህ ዓለም በህልፈተ ሕይወት ስለተለዩት ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ የሙያ ሕይወት ዘመን ይዘክራሉ

$
0
0

SBS Amharic Radio: ከፋለ ማሞ፤ የቀድሞው የኢትዮጵያ ነፃ ጋዜጠኞች ማኅበር – ኢነጋማ ፕሬዚደንት፤ ከዚህ ዓለም በህልፈተ ሕይወት ስለተለዩት ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ የሙያ ሕይወት ዘመን ይዘክራሉ።

የቀድሞው ኢነጋማ ፕሬዚደንት ከፋለ ማሞ ከዚህ ዓለም በህልፈተ ሕይወት ስለተለዩት ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ የሙያ ሕይወት ዘመን ይዘክራሉ

The post የቀድሞው ኢነጋማ ፕሬዚደንት ከፋለ ማሞ ከዚህ ዓለም በህልፈተ ሕይወት ስለተለዩት ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ የሙያ ሕይወት ዘመን ይዘክራሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

ሐብታሙ አያሌው በኩላሊት ጠጠር መታመሙ ተገለጸ * እነ አብርሃ ደስታ ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

$
0
0

habtamu ayalew
(ዘ-ሐበሻ) በ እስር ቤት የሚገኘው ታዋቂው ፖለቲከኛ ሃብታሙ አያሌው ዛሬ በድንገተኛ ህመም ዘውዲቱ ሆስፒታል ተወስዶ እንደነበር ተዘገበ:: በአዲስ አበባ የሚገኙ የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንዳሉት ሃብታሙ ከ እስር ቤት ወደ ዘወዲቱ ሆስፒታል የተወሰደበት ምክንያት በሁለቱም ጎኖቹ ላይ የህመም ስሜት ስለተሰማው ነበር::

የዘውዲቱ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች ምርመራ ካደረጉለት በኋላ ህመሙ የኩላሊት ጠጠር መሆኑን ለባለቤቱ ወ/ሮ ቤተልሄም መናገራቸውን እነዚሁ ምንጮች አብራርተዋል:: ሃብታሙ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የተመለሰ ሲሆን በነገው ዕለትም ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ተገልጿል::

ከሃብታሙ አያሌው ጋር አብረው የተከሰሱትና በቅርቡ በከፍተኛው ፍርድ ቤት በነፃ የተለቀቁት አብርሃ ደስታ; ዳንኤል ሺበሺና የሺዋስ አሰፋም በነገው ዕለት አቃቤ ሕግ ይግባኝ በጠየቀባቸው ክስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርበው የቃል ክርክር ያደርጋሉ ሲሉ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል::

The post ሐብታሙ አያሌው በኩላሊት ጠጠር መታመሙ ተገለጸ * እነ አብርሃ ደስታ ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ appeared first on Zehabesha Amharic.


ኢህዴግ በሚጠራው መድረክ አለመገኘት ማንን ይጠቅማል? (ግርማ ሠይፉ ማሩ)

$
0
0

girmaseifu32@yahoo.com, www:girmaseifu.blogspot.com
Girma-Seifu2ቅጥ አንባሩ የጠፋው የኢትዮጵያችን ፖለቲካ በዋነኝነት የሚጎድለው ልክ ያልሆነን ነገር ልክ አይደለም ማለት ያለመቻል ነው፡፡ በግል አስተያየት ልክ አይደለም ብሎ መቆም ደግሞ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ የተሳሳተ ውሳኔ ባለቤቶች በድጋሚ ጥፋታቸውን በጥፋት ለማረም ሌላ ስህተት ይደግማሉ፡፡ አሰተያየትን በአሰተያየት ለመመለስ ይከብዳቸዋል፡፡ የዚህ ደግሞ ዋነኛው ሰለባ የተቃዋሚው ጎራ ነው፡፡ ለነገሩ አሁን ይህ ነው የሚባል ተቃዋሚ አለ ባይባልም፤ ያሉትም ቢሆኑ ከልምድ የሚማሩ ዓይነት ሆነው አልተገኙም፡፡

ለዛሬ ፅሁፌ መነሻ የሆነኝ አንድ ሰሙ “የአንዳርጋቸው ፅጌ ብርሃን” በሚል የብዕር ሰም የሚከተለውን መልዕክት በፌስ ቡክ ገፄ የውስጥ መልዕክት ማስቀመጫ

“ግርማ ካሳ (ልብ በሉ እኔ ግርማ ሠይፉ ነኝ) ወረድክብኝ በጣም። ተፈጭቶ ተቦክቶ ተጋግሮ ሊበላ የቀረበውን ነገር ድጋሚ ወፍጮ ቤት ይሂድ ብለክ እየተከራከርክ ነው። 24 አመት ሲያታልል የኖርን መንግስት ዛሬ 25ኛው አመት ላይ ሆነክም እንዴት አልገባክም? ስንት አመት ነው የሚፈጀው እንዳንት አይነት ሰዎችን ለማብሰል? ተወያየተክ ምን ታተርፋለክ ? ወያኔ ተቃዋሚዎችን  የሚፈልገው ለተራ ፕሮፖጋንዳው ሊጠቀምባቸው እንጂ ለነሱ ሀሳብ ጆሮ ለመስጠት አደለም። መንግስት እራሱ ያወጣውን ህግ ጥሶ ያሰራቸውን የፓርቲ አባሎችን ለማስፈታት ከወያኔ ጋር ስብሰባ መቀመጥ አያስፈልግም። እንዲ የምታስብ ከሆነ ከአልም ሁሉ ተለይተክ ከሀይለማርያም ደሳለኝ ብቻ የተሻልክ ጅላጅል ነክ ማለት ነው። ወያኔ ለ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተጻፈውን ድብዳቤ ልብ ብለክ አንብበከዋል ? እንዲ የሚል አርፍተ ነገር አለበት። “በሀገራችን የሚገኙ ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች “እንደ መላው የሀገራችን ህዝቦች ” እያለ ይቀጥላል። ሲጀመር ወያኔ እነዚ ፓርቲ ብሎ የሚያውቃቸው ድርጅቶች ከህዝብ ተለይተው ያሉ እና የህዝብ ድጋፍ የሌላቸው አርጎ ነው የጠራቸው። ፀረ ህዝብ አርጎ ነው የሚስላቸው። አንደ ህዝብ አካል አርጎ አይቆጥራቸውም አያከብራቸውም። አንዳንተ ዓይነት አሟሟቂ ሰው ነው ወያኔ የሚፈልገው።ኢቢሲን አሟሟቂ”

የሚል መልዕክት አስቀመጠልኝ፡፡

መልዕክቱ የተፃፋው በዚህ ጉዳይ አስተያየት ለሰጠው ወዳጄ ግርማ ካሣ ይመስላል ነገር ግን  የተላከው ለእኔ በእኔ አድርሻ እና እኔን በዓይነ ልቦናው እየሳለ እንደሆነ ያስታውቃል፡፡ በእኔ እይታ ደግሞ የግርማ ካሣን ሃሳብ መደገፍ ብቻ ሳይሆን በግል ለደወሉሉኝ አቋሜን ገልጬ ነበር፡፡ በዚህ ጉዳይ  ግን ሚዲያ ላይ ወጥቶ አስተያየት መስጠት ብፈልግም፤ ብዙ ምቾት አልተሰማኝም ነበር፡፡ ለማነኛው የዚህ አሰተያየት ሰጪን ሃሳብ መነሻ አድርጌ የግሌን አስተያየት ላቅርብ፡፡

በመጀመሪያ ማነኛውም ግብዣ ላይ የተጠራ ሰው ግብዣ የሚሄደው በመከባበር ሰሜት መሆን አለበት፡፡ ጠሪ አክባሪ በሚል እንጂ ግብዣው ላይ ምን ድግስ አለ በሚል መሆን የለበትም፡፡ በእኔ እምነት ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገራዊ አጀንዳ ላይ ከዚህ በፊት ጥሪ ተደርጎላቸው የማያውቁ የፖለቲካ ፓርቲውች መድረክ፣ ሰማያዊ እና መኢህአድ ግብዣ ተደርጎላቸዋል፡፡ ለምሳሌ በመጀመሪያው የአምስት ዓመት ዕድገትና ትራንሰፎርሜሸን ዕቅድ እና በአባይ ግድብ ወቅት ጥሪ ስለ አልተደረገላቸው አልተጠራንም ሃሳባችንን መስጠት እና የጋራ ማድረግ አልቻልንም ሲባል ነበር፡፡ በዚህ ወቅት የፖለቲካ ምዕዳሩም ሆነ አጠቃላይ ሀገሪቱ ያለችበት ሁኔታ ተመሳሳይ ነበር፡፡ በዛን ጊዜ ተቃዋሚዎች አልተጠራንም ሲሉ የነበረው ተጠርተው ለመቅረት አይመስለኝም፡፡ ተገኝተው ሃሳባቸውን ለማካፈል ይመስለኛል፡፡

በእኔ እምነት አሁን በተደረገው ጥሪ መስረት ከላይ ሰማቸውን የጠቀስኩት ፓርቲዎች ተገኝተው የሚከተለውን ማከናወን ይችሉ ነበር፡፡ መጀመሪያ ያለፈው አምስት ዓመት ክንውን ሲቀርብ ከመነሻው ጀምሮ በጋራ ከተቃዋሚዎች ጋር በጋራ ለመስራት መንግሰት እርምጃ ባለመውሰዱ የእቅዱ ዋና ዋና ምሶሶ የሆኑት ተግባራት ያለመሳካታቸውን በተጨባጭ ማስረጃ ለማስረዳት እድሉን ሊጠቀሙበት ይችሉ ነበር፡፡ ለምሳሌ የባቡር ዝርጋታ ከታቀደው 30 ከመቶ ያለመሰራቱ፣ በኤሌትሪክ ሀይል በተመሳሳይ 20 ከመቶ እንኳን ያለመሳካቱ፤ በመንገድ በውጭ ንግድ፣ በዋጋ ማረጋጋት፣ በግብርና በተለይ በሰፋፊ እርሻ ወዘተ.. ያሉትን መሰረታዊ ችግሮች በማሳየት ለዚህ ዋነኛው ችግር በጋራ በመስራት ሊገኝ የሚችለውን ሀገራዊ ሀይል ወደ ጎን ማድረጋቸውን ለህዝብ ይፋ ማድረጊያ መድረክ ይሆን ነበር፡፡ በተለይ የአባይ ግድብን ገዢው ፓርቲ የፖለቲካ መጠቀሚያ እንዲሆን በማድረጉ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ሊያደርጉ የሚችሉት ከፍተኛ አሰተዋፅኦ መገደቡን ለመናገር ከዚህ የተሻለ ትክክለኛ መድረክ የሚያገኙ አይመስለኝም፡፡ ይህንን መድረክ ለመጠቀም ባለመቻላቸው ትልቅ የፖለቲካ ኪሣራ ይመስለኛል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ገዢው ፓርቲ እራሱ ያመነውን የመልካም አስተዳደር መፍቻው ቁልፍ መንገድ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ግንባታ እና በተለይ ደግሞ የሚዲያዎች ተሳትፎ መኖር ተዓማኒነት የሚጣልባቸው የፍትህ ስርዓት መሆኑን በሰብሰባው በሚፈጠሩ አጋጣሚዎች ሁሉ በማንሳት ዕቅዱ ያልተሳካው ይልቁንም ሙስና የተንሰራፋው ስርዓቱን የሚተቹ ጋዜጠኘኞችና አምደኞች በመታሰራቸው፣ እምነት የሚጣልበት የፍትህ ስርዓት ባለመኖሩ እንደሆነ አጋጣሚውን መጠቅም ይቻል ነበር፡፡ ለዚህ ደግሞ ተመሳሳይ አቋም ያላቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ዝግጅት አድርገው መሳተፍ እንጂ አድማ አድርጎ ከግብዣ በመቅረት ውጤት የሚገኝ አይመስለኝም፡፡ ይህ ትልቅ ሰህተት ይመስለኛል፡፡

ከዚህ ውይይት በማስከተል “የፈሰሰ ውሃ አይታፈስም” በሚል ተረት ከገዢው ፓርቲ ጋር ተመራርቆ ለመውጣት ሳይሆን በቀጣይ ዕቅድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለያዩ ሀገራዊ አጀንዳዎች በምን መልክና ደረጃ ስንሳተፍ ይህ ዕቅድ ተግባራዊ ይሆናል በሚል መነሻነት የድርጊት መርዓ ግብር በመንደፍ የጋራ ኮሚቴ አቋቈሞ መውጣት፣ በተለይ የፖለቲካ ምዕዳሩ ለማስፋት የሚቻልበት መንገድ መቀየስ ሊሞከር የሚገባው ትልቅ ስራ ነበር፡፡ ይህ ከገዢው ፓርቲ ባህሪ አንፃር ተቀባይነት ባያገኝ እንኳን እንቢተኝነቱን ለማጋለጥ ይረዳ ነበር፡፡ እንደ ፓርቲ ሰርተፊኬት ይዞ ዓመት ከመቁጠር በዘለለ መንግሰት በተገኘበት ሁሉ እየተገኙ ድምፅ ማሰማት (ባይሰሙም መጮኽ) ግዴታቸው ነበር የሚል የግል አቋም አለኝ፡፡

እውነቱን ለመናገር በቁጥር እስከ ሃያ የሚደርሱ የፓርቲ አባላትን (ለምሳሌ ሶስቱ ፓርቲዎች 60 አባላትን) በአንድ መድረክ ላይ እንዲገኙ የተሰጠን እድል ያለመጠቀምን ያክል ደካማ ውሳኔ አይታየኝም፡፡ እያንዳንዳቸው ሁለት ደቂቃ መልእክት ቢያስተላልፉ የሁለት ሰዓት መልዕክት በመንግሰት ጆሮ ላይ ማስቀመጥ ይቻል ነበር፡፡ እነዚህን አጋጣሚዎች በእስር የሚማቅቁ ጓዶቻችንን በማንሳት ልንዘክራቸው ይገባ ነበር፡፡ አሸባሪ ያሏቸውን “ጀግኖች” ብለን ልናወደስ የምንችልበት መድረክ ያለመጠቀም በምን መመዘኛ ልክ እንደሚሆን አይታየኝም፡፡

ገዢው ፓርቲ ከአሁን በኋላ ለማነኛውም ዓይነት ውይይት ሳይጠራ ዳተኛ ቢሆን ሰበብ አግኝቷል፡፡ ቢጠሩም አይገኙም ይልቁንም በሚጠሩበት መድረክ ከመገኘት ይልቅ ውጪ ሆነው መግለጫ በማውጣት ላይ ይገኛሉ ብሎ ለሀጋሮቹ ማስረጃ ያቀርባል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከኢህዴግ መንግስት ባልተናነሰ ካድሬ የሆኑ የአሜሪካን እና አውሮፓ ህብረት ድጋፍ ሰጪዎች ይህን ለመስማት እና ለማመን ብዙ አይቸገሩም፡፡

በእኔ አረዳድ ፓርቲዎቹ በግብዣው ላይ ተገኝተው በምን ጉዳይ አተኩረው እንደሚናገሩ እንዴት አድርገው የፖለቲካ ጥቅም እንደሚያገኙበት መካሪ አላገኙም፣ በውስጥም በቅጡ አልመከሩበትም፡፡ የሚያሳዝነው እነዚህ ፓርቲዎች የአሜሪካ ኤምባሲ ለስዕል ኤግዚቢሽን ምረቃ ቢጠራቸው በግብዣው ላይ ይገኛሉ፡፡ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባል ሊያነጋግራችሁ ይፈልጋል ቢባሉ ይገኛሉ፡፡ መገኘት ብቻ ሳይሆን አነጋገሩን ብለው ዜና ይሰራሉ፡፡ እንግዲህ አንባገነኑ ኢህአዴግ ዲሞክራት እሰኪሆን ጠብቀው ለመወያየት ከሆነ ወደፊት የሚታይ ይሆናል፡፡ ባለፈው ፕሬዝዳንት ኦባማ ጉብኝት ሲያደርጉ ለግንኙነት በሚመቸው የእራት ግብዣ ላይ ላለመገኝት ወስነው በብዙ ሜትር ርቀት በቴሌቪዥን በተሻለ ለመከታተል በሚቻልበት የአዳራሽ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ሲወስኑ ዝም ማለታችን አበጃችሁ ያልን የመሰላቸው መሪዎች፤ ይህንንም ግብዣ ለፖለቲካ ጥቅም ማዋል አለመቻላቸውን ዝም ማለት ተገቢ አይደለም ለማለት ሲባል የቀረበ አስተያየት ነው፡፡ በእኔ እምነት በሰላማዊ ትግል በሀገር ውስጥ ለመንቀሳቀስ የወሰነ ማንኛውም አካል መንግሰትን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እያገኙ መልዕክት ማስተላለፍ ተገቢ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ጭምር ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ እና መንግሰት በሚጠሩት ማንኛውም ስብሰባ ላይ ላለመገኘት መወሰን የሚጠቅመው ገዢውን ፓርቲ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ሃሣብ ያለው በመቅረት የሚገኘውን ጥቅም ቢያስረዳኝ፣ በተለይ አሁን በተደረገው የሁለተኛው የእድገት እና ትራነስፎርሜሽን እቅድ ለመወያየት በተደረገው ጥሪ ላይ ያለመሳተፍ ያስገኘውን ጥቅም ለሚያስረዳኝ ለመማር ዝግጁ መሆኔን እገልፃለሁ፡፡ በደፈናው ገዢውን ፓርቲ እውቅና መንፈግ የሚል መልስ ግን አልቀበልም፡፡ በሀገር ውስጥ ሆኖ በዚሁ መንግሰት ስር እየተዳደሩ እውቅና መንፈግ የሚባል ፖለቲካ አይገባኝም፡፡

ቸር ይግጠመን!!!!

 

 

 

The post ኢህዴግ በሚጠራው መድረክ አለመገኘት ማንን ይጠቅማል? (ግርማ ሠይፉ ማሩ) appeared first on Zehabesha Amharic.

ዶሮን ስያታልሏት በመጫኛ ጣሏት የሚለዉን ተረት፣ ዶሮን ስያታልሏት በሬ ነቃባቸው ብሎ የቀየረው ኮሚዲያን ማን ነበረ ? ልጅ ያረድ ሊበል ?

$
0
0

 

ከአኩ ኢብን አፋር

mekele 1 Satenaw Newsኢህአዴግ የአጉላዕ፡ በራህሌ፡ዳሉል መንገድ መመረቁን ትናንት ከምሽቱ በሁለት ሳዓቱ ዜና ላይ በልሳኑ ኢብኮ አሳውቆናል።

ለመሆኑ የዚህ መንገድ ላማና ለአፋር ዝብ የሚያስገኘው ጥቅም (ወይም ጉዳትምንድነው ?

አጉላዓ ማለት ከመቀሌ ወደ ዓዲግራት ሲኬድ ዉቅሮ ከመድረሳችን በፊት የምናገኛት ትንሽ መንደር ናት።

በአፋር ክልል ባራሕሌ፣ ኤርታአሌ፣ የዳሉል ማዓድንና ፖታሽ ለመጎበኘት ወይም ለማምረት፣ ከአጉላዓ አቋረጠን እስከ ዳሉል ድረስ ዘልቀን እንገባለን።

የዚህ መንገድ ዋናው ዓላማም ወያኔ ለባእድ ኩባንያ የሸጠዉን የፖታሽ ሃብት ወደ መቐሌ ወስደው ከጀቡቲ ታጎሪ እስከ መቐሌ ከተገነባው የባቡር ሓዲድ መንገድ ጋር ለማገናኘት ብቻ ሳይሆን፣ በሰሜን አፋር አከባቢ የሕዝብ አለኝታ የሆነውን የጨው ምርት የህወሀት ባለ ሃብቶች መበልጸጊያ ብቻ እንዲሆን የተሰራ መንገድ መሆኑን ከወዲሁ የገባው ገብቶታል (ያልገባው ያለ አይመስለኝም)

ወያኔ እንደ አስተዳደሩ ሁሉ ልማቱም ፀረ ሕዝብ እየሆነ ከመጣ ቆይቷል።

አንዳንድ አፍቃረ ወያኔ የሆኑ የውጭ ድርጅቶች ሳይቀሩ በኢትዮጲያ ውስጥ ፈጣን ልማት እየተሰራ መሆኑን ሲመሰክሩ እናያለን።

ይሁን እንጂ ልማት ሲባል አጥፊና ጎጂ የይስሙላ ልማትም እንዳለ በተግባር እያየን ነው።

ለምሳሌ የዚህ የአጉላዓ፣ዳልል ፣ባራሕሌ መንገድ ሲንወስድ መንገዱ እስከ ዳሉል ይባል እንጂ ዳሉልን አይደርስም።

ዳሉል ማለት ከ80 ሺ እስከ 100 ሺ ሕዝብ ሚኖርባት ትልቅ ወረዳ ነ። 

በዚህ ወረዳ ባሉ ሁሉም ቀበሌዎች የመኪና መንገድ ባለመኖሩ በወሊድ ላይ የሚሞቱ ሴቶች፣ መንገድ ባለመኖሩ ዉሃ ያልተቆፈረላቸው፣ መንገድ ባለመኖሩ ት/ቤት ያጡ ስንቶች እንደሆኑ ከእኛ በላይ ወያኔ ራሱ ያውዋል።

የዚህ መንገድ ግንባታም እስከ ዳሉል ሲባል ከአጉላዓ እስከ ፖታሹ ቦታ ብቻ እንጂ የዳሉል ወረዳ መላው ህዝብን ያጣቃለለ አለመሆኑን እንድታውቁት እፈልጋለሁ (ያስፈልጋል?)

Mekele 2- satenaw Newsበዳሉል ወረዳ እና ባራሕሌ ፓታሽ፣ ማዓዲንና ጨው ያለበት ቦታ ሕዝብ የሚኖርበት አከባቢ አይደለም።

ባራሕሌም ብሆን እንዳጋጣሚ ሆኖ መንገዱ በመሃል ባራሕሌ ስለሚያልፍ እንጂ ብዙ ቀበሌዎች እርስ በርስ የሚያገናኛቸው መንገድ የላቸዉም።

ኧረ ባጣቃላይ በአፋር ክልል ወረዳ ከወረዳ፣ ቀበሌ ከቀበሌ የሚያገናኙ መንገዶች የሉም ማለት ይቻላል።

ባለፉት አስር አመታት ውስጥ የባለ ራዕዩ ራዕይ በሚል ስም በአፋር ሕዝብ ላይ የደረሰው ፋናቀል ብዙ ያልተወራለት ግን ታሪክ የማይረሳው፣ ልማት ሳይሆን (ህግ ቢኖር )ሽብር ነው።

ወያኔ እና ተላለኪዎቹ ከደቡብ  እስከ ምስራቅ  የአፋር ክልል (አከባቢዎችበስኳር ልማት ስም ያፋናቀሉት ሕዝብ ዛሬ ኻ ኖ እንግዳ ሲመጣባካል አርዶ ጋብዝ የነበረው ሕዝብ ዛሬ ላይ ወተት ላይ ዉሃ ጭምሮ ሲሸጥ ማየት (መመልከትበእነት ሆድን ያቆስላል።

በመጨረሻ ወያኔ ምንም እንኳን ሕዝብ ዝምታ ቢመርጥም አንድ ቀን ግን ዝምታው ፈንድቶ ከምንም በላይ የሚወደውን ሥልጣን ሊያሳጣው እንደሚችል ሊገነዘብ ይገባል።

The post ዶሮን ስያታልሏት በመጫኛ ጣሏት የሚለዉን ተረት፣ ዶሮን ስያታልሏት በሬ ነቃባቸው ብሎ የቀየረው ኮሚዲያን ማን ነበረ ? ልጅ ያረድ ሊበል ? appeared first on Zehabesha Amharic.

የቀድሞ ዴምሕት አባላት በወያኔ ፎቶገጭ ቤት

$
0
0

ነፃነት ዘለቀ
እንደምን ሰነበታችሁ፡፡ እንኳን ለአዲሱ ዓመት የ2008 ዓ.ም ሁለተኛ ወር “ለጥቅምት አንድ አጥንት” በሰላም አደረሳቹ፡፡ ጥቅምት ብርዳምና ንፋሳም ነው፡፡ ዘንድሮም እንደዛው ነው፡፡ የአዲስ አበባ የሰሞኑ ብርድ ሚስት ያሳቅፋል፡፡ ግን ስንገናኝ ሰላምታ የማንለዋወጠው ለምንድነው? ብዙ መጣጥጥፍ ጸሐፊዎች ይህን ወግ ልማድ ረስተው በቀጥታ ሊያስተላልፉት ወደሚፈልገጉት ቁም ነገር ይገባሉ – ያበሳጩኛል፡፡ “እንዴት ሰነበታችሁ” ማለት ማንን ገደለ? ኧረ ሳልረሳው – በመግቢያየ “አደረሳቹ” የሚል ቃል ሆን ብዬ ጽፌያለሁ፡፡ አማርኛ ቋንቋ በጣም ቅጥ አምባሩ እየጠፋ መምጣቱን ለመጠቆም ፈልጌ ነው እንዲያ ያልኩት፡፡ ትልልቅ የመሥሪያ ቤት ደብዳቤዎችን ብታዩ – አማርኛ አፍቃሪው ሕወሓት እንዳይቆጣኝ እንጂ – አማርኛው እንዴት እንደተመሰቃቀለ ልገልጽላችሁ አልችልም፤ በስማም! ውጥንቅጡ ወጥቶላቹሃል – እምልክ ገባክ? እንዲክም ስልክ በአንድ ወይ በሁለት አካባቢውች ብቻ እንዳይመስልክ – በሁሉም ቦቶችና ሥፍሮች ነው አማርንኛ እየተቀጠቀጠ ያለልክ፡፡ ምን እንደነካን አይታወቅም – ደግሞም “ዋናው መግባባት ነው” የሚል ፈሊጥ ተስፋፍቶልካል – ደካማ ጎንንና ስንፍናን መሸፈኛ ፈሊጥ ነው፡፡ “ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ …” ‹ጨው ነጋዴ መልሶ ገዛው› እንዲሉ ነው ነጎሩ፡፡ ምን ይሻላል? “ እዚህም እሳት…እዚያም እሳት … እሳት.. እሳት” አለ ያ ታሪካዊ የኪነ ጥበብ ሰው ቴዲ አፍሮ በ17 መርፌ ዘፈኑ (“ጃን ያስተሰርያል” ለማለት ፈልጌ ርዕሱ ለጊዜው ተሰውጦብኝ ነው)፡፡
Mola asgedom
ዋናው ሥራ አሥኪያጅ ወይም ሚኒስትር “…አስታውቃለሁ” መባል የሚገባውን “ …አስታውቃለው፡፡” የሚል ማሣረጊያ ቃል ያለው ደብዳቤ ላይ ፊርማውን አስቀምጦ በተላላኪው ሲሰድ ታያላችሁ – ዘመነ ድንቁርና ነው የገጠመን፤ ዘመነ ግዴለሽነትም ጭምር፡፡ እንዲያውም ይህ ዓይነቱ ስህተትማ ቀላልና ሊታገሱት የሚቻል ስህተት ነው፡፡ ይህን መሰል ከየቢሮው የሚወጣ ደብዳቤና በየቦታው የተለጠፉና የተሰቀሉ የማስታወቂያ ጽሑፎችን ብናይ አማርኛና እንግሊዝኛ በእግራቸው እየሄዱ እንደሆነ ማረጋገጥ እንችላለን፤ የጉራማይሌው ድረታ – የሆሄያት አጻጻፍ ችግር (የእስፔሊንግ ስህተት) … ግዘፍ ነስቶ “የቋንቋ መምህር ያለህ!” እያለ ነው – የቋንቋ መምህራኑ ራሳቸው ለምሳሌ “How is yours childs?” ወይም “ከአርዕስቶቹ ጋር የማይሄዱ ከባባድ ቃላቶችን ካለመጠቀም ተቆጠቡ” የሚሉ በሰዋስው ስህተት የታጨቁ ዐረፍተ ነገሮችን ሲናገሩ ልትሰማ ትችላለሀ – ጊዜው ነው፤ ጊዜውም ስህተትንና ነውረኝነትን እንደመልካም ዕሤት የሚቀበልና ሰዎችን ሳይወዱ በግድ የሚያባልግ ነው፡፡ ዕውር ለዕውር እየተማራ ሀገር ገደል ገባች! ወይ ወያኔ፤ በምን ዓይነት የሥኬት ጉዞ እየተምበሸበሹ እንደሆነ በጣም ጥቂቶች ብቻ ነን የምናውቀው፤ ዶግሞ’ኮ ይህ አደገኛ ሁኔታ የሚያሳስበውም ሆነ የሚያስጨንቀው አካል የለም፡፡ ተዓምር ነው፡፡ እንዲያው ለመግቢያ ያህል እንዲህ አልኩ እንጂ አነሳሴ ሌላ መሆኑን ርዕሴ በግልጽ ይናገራል፡፡ በዚህ በጠቀስኩት የቋንቋ አጠቃቀም ስህተት ልጻፍ ብልማ ወረቀት አይበቃኝም፤ የነገ ሰው ይበለኝ ግን፡፡ እንደሞትን ካልቀረን መገናኘታችን “ግድ ይላል”፡፡ ወይ አማርኛ! ኤርምያስ ለገሠ “ባለቤት አልባ ከተማ” ብሎ መጽሐፍ መጻፉን አትርሱ፡፡ “ባለቤት የሌለው እየጠፋ ያለ ቋንቋ” በሚል ‹አርዕስት› – ማለትም ርዕስ – ደግሞ አንዱ ይጻፍ፡፡
ዛሬ የወያኔን ቴሌቪዥን ድንገት አየሁ፡፡ ቤተሰቦቼ የቲቪ ጣቢያ (ቻናል) ሲቀያይሩ ድንገት EBC 1 የሚባለው የወያኔ ቱሪናፋ መስመር ላይ ይደርሳሉ(የስም መለዋወጥ የተፈጥሮ ጠባይን የሚለውጥና ውሸታምነትን በሕዝብ ዘንድ የሚያስረሳ ይመስል በኩረጃ የሚስተካከለው የሌለው ጦጣው ወያኔ ቲቪውን EBC አለና ወደ BBC, CBC, CNN,… ለማጠጋጋት ሞከረ – ማፈሪያዎች! ለመሆኑ “ኮርፖሬሽን” ምን ማለት ነው? አንድ የወያኔ ካድሬ እንደፈለገው ለሚያሽከረክረው ጥሩምባ መሥሪያ ቤት ይህ ስም ይከብደዋል፤ ነገሩ “ሲወልዱ አይታ ..” እንደሚባለው ነው፡፡ አሃ፣ ለስምማ “የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አይተ ማነው ብፃይ ኃይለማርያም ደሳለኝ” ይባልስ የለም? ቂቂቂቂ…. እኔን ጠ/ሚኒስትር ያድርገ..ኝ!) ዝኮነ ኮይኑ የወያኔን ቲቪ እንደማላይ የምታውቀው ባለቤቴ ፊቴን አየት አድርጋ ልትቀይረው ስትል ተይው አልኳት – አለወትሮየ ተይው በማለቴ እየገረማት ተወችው፡፡ ቀርቦ የነበረው ዝግጅት የሞላ አስገዶም ልጆች በወያኔ ጋዜጠኞች ቃለ መጠይቅ እየተደረገላቸው የሚያሳይ ዶኩመንተሪ የሚመስል ፊልም ነበረ፡፡ እንደምንም ጨክኜ ለመከታተልና ምን እንደሚሉ ለመስማት የትግስት ፈረሴን ቼ አልኩና ማዳመጤን ቀጠልኩ፡፡
“የቀድሞ የዴምሕት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የ… ግንባር መሪ” የሚል የማዕረግ ቅጥያ በምስላቸው ግርጌ የተለጠፈላቸው ፍጹማን ባላገሮች ናቸው የሚጠየቁት፤ ባላገር ስል ያልተማሩና ሥልጣኔ ያልዳሰሳቸው ደናቁርት ማይማን ለማለት ፈልጌ እንጂ በሌላ መልክ እንዳትተረጉሙብኝ አደራችሁን – ፀጉር ስንጠቃ አልወድም፡፡ አነጋገራቸው፣ (የተሰጣቸው ሊሆን ቢችልም) አለባበሳቸው፣ የሰውነት መላ አኳኋናቸው፣ የቋንቋና የሃሳብ ግንኙነታቸው፣ እንኳንስ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ሊመስሉ የዕድር ቤት ዘበኛም ሊሆኑ የማይችሉ ፋርጤዎች ናቸው – (ውይ ጉዴ – “ፋርጤ” ለካንስ “ፋርጣ” ከሚል የቦታ ስም የወጣ የወገን ቅጽል ነው፡፡ ግን ግዴለም “ባላገር” ለማለትም በፈሊጣዊ አገባብ ስለምንጠቀምበት እንደዚያ ተረዱልኝ – በቦታ አመልካችነቱ ከሆነ ብዙ ፋርጤ ጓደኞች አሉኝና በቃሉ ፈሊጣዊ አገባብ ቅር እንደማይሰኙብኝ አምናለሁ፡፡) እናም እነዚህን የመሰሉ ሰዎች በርግጥም ነፃ ሊያወጡን በረሃ ወርደው ከሆነ ከበፊቱ ስህተት ነበር ብቻ ሣይሆን እነሱን ፊደል ለማስቆጠርና ቀለም ለማስለየት እንዲሁም መጠነኛ የፖለቲካ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ እኛ ነበርን እነሱ ወደሚኖሩባቸው አካባቢዎች መውረድ የነበረብን፡፡ ሀገርንና ሕዝብን ነፃ ማውጣት ለካንስ እንዲህ ቀላል ኖሯል እንዴ? ቼጉቬራና ሆቺሚን እንደነዚህኞቹ ማይም ባላገሮች ነበሩ ይሆን? እኔማ ሣቄን መቆጣጠር አቃተኝ፡፡ ደግሞም ሁሉ ነገር ተወነባበደብኝና ግራ ገባኝ፡፡ ነፃ አውጪ መጀመሪያ ራሱ ነፃ የወጣ መሆን አለበት፡- ከተራው ዜጋ በበለጠ ወይም በተሻለ የነቃ፣ የተማረና የተመራመረ፣ ለማንኛውም ዓይነት ግልብና ህንፍሽፍሽ አስተሳሰብ በቀላሉ የማይንበረከክ፣ የጠንካራ አቋም ባለቤት፣ የጠንካራ ዲስፕሊን ጌታ … መሆን ይገባዋል እንጂ እንደነዚህ ዓይነት ልፋጭ ዜጋ ነፃ አውጪ ቢባል የነፃነትን ዋጋ ከዜሮ በታች ማውረድ ነው፤ እውነቴን ነው የምለው – ደግሞም አሁን እነዚህን የመሰሉ ማፈሪያዎች ስላየሁ አይደለም – ነፃ አውጪ እንደዚህ ከሆነ ባፍንጫዬ ይውጣ፡፡ ስለነፃነት ምንነትና አስፈላጊነት ምን አውቀውና ምን ገብቷቸውስ ነው ዘጠና ሚሊዮን ሕዝብ “ነፃ ሊያወጡ” በረሃ የወረዱት? ሞላ ራሱን ባለፈው ሰሞን ሳየው የተሰማኝ ስሜትም ይሄው ነበር፤ ከኔ የማይሻል ሰው ምን መሆኔንና እንዴት እንደምኖር ሣይረዳ ነው ነፃ ሊያወጣኝ የሚነሣ? ይህማ ልክ እንደወያኔ የወታደር አመላመል ማለት ነው፡፡ ወያኔና ወታደር ምልመላው ዓለምን ጉድ የሚያሰኝ ነው – ቢታወቅለት፡፡ አንድ አንቀጽ ጣልቃ ላስገባና እመለስበታለሁ፡፡
ይቺ “የሻቢያን ሜካናይዝድ ጦር፣ እግረኛ ጦር፣ .ቲሪሪም ቲሪሪም ‹እየጠራረግን› ከስምንት ሞቶ በላይ ሠራዊት ይዘን ከኤርትራ ምድር ወጣን” የሚሏት የነአስገዶም ንግግር በጣም ትገርመኛለች፡፡ እንዴት ነገሩ – ያን ጠረጋና የሰገሌን ጦርነትና ገና ወደፊት እንደሚደረግ የሚጠበቀውን ›ስፔስወር› የሚያስንቅ ድንቅ ጦርነት አንዳቸው እንኳን በሞባይላቸው ቀርጸው ያላሳዩን ለምን ይሆን? እንደዚህ ዓይነት ታላቅ ወታደራዊ ‹ኦፐሬሽን› ሲታቀድና ሲፈጸም ኮብላዩ የቀድሞ የዴምሕት ሠራዊት ይህን ታላቅ ጀብድ ቀርፆ እንዴት ለታሪክ አያስቀምጥም ወይንስ ገና በወያኔ ስቱዲዮ እየተቀናበረ ይሆን? ከማንም ወገን ሆኜ ሣይሆን እንደ አንድ ነፃ ታዛቢ ይህን “እየጠራረግን ወጣን” የሚሉትን ቀልድ ስሰማ ከማሣቅ አልፎ በጣም ያስገርመኛል – በውነትም ጠራርገው ከሆነ ከካርን የተሠሩ ወታደሮች በየበረሃው አርቲፊሻል ጠበንጃና የካርቶን ተዋጊ ጀቶችን ይዘው ቀሞው ነበር ማት ነው – እነዚህ ጀለንፎዎች ናቸው አንድን የሠለጠነና የታጠቀ ጦር ጠራርገው የሚወጡት፤ መሪዎቹ እነዚህ ከሆኑ ተመሪዎቹ ምን ዓይት ይሆኑ? ለምን በአግባቡ አይቀለድም? የቀልድም እኮ ጡር አለው፡፡ ደግሞም “ጄኔራል” ሞላ አስገዶም እጁን እያወናጨፈ እንዴት እንደጠራረጓቸው በሰውነት እንቅስቃሴ ተደራቢ “ቋንቋ” ሲገልጽ አንድም የሻቢያ ጦር የቀራቸው አይመስልም፡፡ እነሞላ በጣም ጀግኖች ናቸው ማለት ነው፡፡ ግን ግን ማስረጃ ስላላቀረቡ የሚሉት ሁሉ ከወታደር ቁጥር አንስቶ እስከ ግዳይ መጣሉ ድረስ ውሸት እንደሆነ መረዳት አይቸግረኝም – በበኩለይ፡፡ የወታደር ቁጥርን ካነሳሁ ዘንዳ ደግሞ ይህ ከዴምሕት አፈነገጠ የተባለ ጦር ከ70 እስከ 900 መሆኑ የሒሣብ ችሎታየን በእጅጉ ተፈታትኖብኛል(ለነገሩ ሀገራችን በዚህ የስታትስቲክስ አኀዛዊ መረጃ ጉዳይ አትታማም፡፡ ፈገግ በሉ፡- መንጌ የተጋነነ ቁጥር ይወድ ነበር አሉ፡፡ እናላችሁ በዘመቻ ፕላን ቀጠና ጽ/ቤት – ስድስት ኪሎ አ.አ.ዩ. ዋና በር ፊት ለፊት የሚገኘው – በተካሄደ አንድ ስብሰባ ላይ በኢትዮጵያ ለእርሻ ምቹ የሆነ(arable land) የቦታ ስፋት በካሬ ኪሎ ሜትር ተመንዝሮ በግብርና ሚኒስትሩ ሲነገር ከተሰብሳቢዎቹ ብዙዎቹ በሣቅ ፈነዱ አሉ – ነገሩ የገባቸው፡፡ ለካንስ ሞኙ ሚኒስትር ጓድ መንጌን ማስደሰቱን እንጂ የተናገረው አኀዝ ከኢትዮጵያ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት መብለጡን ልብ አላለውም ኖሯል! እኛ እንዲህ ነን እንግዲህ!) በውቀቱ ሥዩም በአንዲት ዚቀኛ ጭውውቱ “የቁጥር ችሎታየ እንኳን እስከዚህም ነው ግን በአዳራሹ ውስጥ የተሰበሰቡት ሰዎች ብዛት ከ7 እስከ 700 ይሆናል፡፡” ብሎ ነበር፡፡ እንግዲህ ይታያችሁ የነሞላ አስገዶም ቁጥር እንደወያኔና እንደነሞላ ከ800 በላይ ማለትም 900 ገደማ መሆኑ ነው፡፡ በሌላ መረጃ ደግሞ ከ70 የማይበልጡ ሲባል ሰምቻለሁ፡፡ እውነቱ የትኛው ነው? እውነት ከማን ጋር ናት? ሌሎች እንዲህ ሰኞ ማክሰኞ የእንክሻ ጨዋታ የሚጫወቱባት ከሆነ ለምን እውነት ራሷ እውነቱን አትነግረንም? ሁለቱን ደምረን አማካዩን እንውሰድ ወይንስ ቀን እንጠብቅ? … ውሸት ከዚህች ምድር የምትጠፋበትን ወቅት በጉጉት ከሚጠብቁ የዓለም ምሥኪን ዜጎች መካከል አንዱ መሆኔን ብገልጽ ጉረኛ ትዕቢተኛ ትምክህተኛ … ምናምነኛ እባል ይሆን? ልባል፡፡ ምን ቸገረኝ፡፡ እናም ሀሰት በእውነት የምትሸነፍበትንና ሁሉም ለኅሊናው ተገዢ የሚሆንበትን ቀን በከፍተኛ ጉጉት እጠብቃለሁ፡፡
ወያኔ ወታደር የሚመለምልበት የተለዬ መሥፈርት አለው፡፡ “ካጠናቀርኩት መረጃ” ውስጥ ከቃል ፈተናው አንደኛውን ጥያቄ ልንገራችሁ፡- “ዕንቁላል የጓሮ አትክልት ነው፤ እውነት ወይንስ ሀሰት?” ለዚህ ጥያቄ “እውነት” ብሎ የሚመልስ ተመልምሎ የሚቀጠርና እንደነገሩ ሠልጥኖ ወያኔ ለፈለገው ግዳጅ የሚሠማራ ሲሆን “ሀሰት” ብሎ የሚመልስ ግን አንጎሉ ስለሚሠራ የወያኔን የውትድርና መሥፈርት አያሟላምና አይቀጠርም፡፡ በተረፈ የወያኔ ወታደር ከመጠነኛ የመግባቢያ ደረጃ ባለፈ አማርኛ ቋንቋ እንዲያውቅ አይጠበቅበትም – ብዘውን ጊዜም ከአማራው አካባቢ ወታደር አይቀጠርም ከደቡብና ከጋምቤላ ነው ይበልጡን የሚመለመለው፤ የትምህርት ደረጃም ምናልባት ከማንበብና መጻፍ ባለፈ አይፈቀድለትም፤ ከዜጎች ጋር ተግባብቶ መኖር ምሕረት የለሽ ቅጣት ያስቀጣዋል፤ በአንድ ቦታ ግፋ ቢል ከሦስት ወር በላይ እንዲቆይ አይደረግም (ከሕዝብ ጋር እንዳይግባባና የርህራሄ መንፈስ እንዳይኖረው)፣ ከወታደሮችም ጋር ሆነ ከሲቪሎች ጋር እንዲገናኝና ብሶቱንም ሆነ ሌላ ነገር እንዲያወራ አይፈቀድለትም – በቡድን ሆኖ መቆምና መቀመጥም ሆነ ማውራት በወያኔ የጦር ሠፈር ነውር ነው(የነሱው ምርጥ ሰው ማለትም ዘውጋዊ ቁርኝት ያለህ የውድቡ አባል ከሆንክ ይህ ህግ አይመለከትህም)፣ አንድ የወያኔ ወታደር ግደል ሲሉት እነማንንና ስንት ብሎ ካልሆነ በስተቀር ለምን ብሎ መጠየቅ አይችልም – ቢጠይቅ ከጭፍን እንስሳዊ ታዛዥነት ወደሰውነት ደረጃ እንደተለወጠ ተቆጥሮ መፈጠርን የሚያስረግም እርምጃ ይወሰድበታል ወይም ዕድል ከቀናው ይባረራል – ለዚህም ነው ፌዴራል ሲባል ተግባሩ ሁሉ በአረመኔነት የተሞላው – ደግሞም ተከታታይና ታዛቢ ስለሚመደብበት ቢራራ ራሱን ችግር ውስጥ ይከታልና ሳይወድ በግዱ ይጨክናል – ጥሎ ካልጠፋ በስተቀር ሕይወቱ እንደዚህ ባለ መርገምት ውስጥ የታጠረ ነውና ብዙም አንፍረድበት – ይህም ሥራ ሆኖ ሥራውን ቢለቅ ሌላ መኖሪያ የለውም፤ ድህነት ያጨክናል፤ ድህነት የለዬለት ጭራቅ ያደርጋል፤ የመኖር ጉጉት ከሰውነት ተራ ያወጣል፡፡ ስለዚህም በየከተማው የምናያቸው መለዮ ለባሾች ሰው ሣይሆኑ በሰው አምሳል የሚንቀሳቀሱና ማኅበረሰቡን ወያኔ እንደሚፈልገው አንቀጥቅጠው ለመያዝ የተመደቡ ሥጋ-በል ዐውሬዎች ናቸው፡፡ ወታደር ስናይ የኛ ስለማይመስሉን እንሸሻቸዋለን፤ ፖሊስ እንደሚሻለን በእግረ መንገድ መጠቆሙ ግን አግባብ ነው፡፡ የወፓንና የፌዴራል ተብዬውን ወታደር ግን ተውት፤ እነሱን ስታስብ ጥሩ እንቅልፍ ላይዝህ ይችላል – ያቃዥሃል፡፡ አንተ ቀንቶህ ባትገረፍና ባትደበደብም ሌላው ወንድምና እህትህ ስለሚሰቃይ ቁስላቸው አንተንም ይጠዘጥዝሃል – ሰው ከሆንከ፡፡ ግን ስንታችን እንሆን ሰው? ይህም አጠያያቂ ነው፡፡
ፋርጤዎቹ የሞላ ልጆች አሳዘኑኝ፡፡ ደግሞም ወያኔ በተለመደ ቅጥፈቱ “የብሔር ብሔረሰቦችንና ሕዝቦችን” ተዋፅዖ ለማሟላት ከሚል ከንቱ ልፋት አንዱን ከደቡብ አንዱን ከሰሜን አንዱን ከምሥራቅ አንዱን ከምዕራብ እያደረገ ነው ቃለ መጠይቅ ያካሄደው፡፡ ሌላውና ለዚህ አጭር መጣጥፍ መጻፍ የወዲያው ምክንያት የሆነኝ እነዚህ የቀድሞ የዴምሕት “ከፍተኛ ባለሥልጣናት” (አላውቅም- ሊሆኑም ይችሉ ይሆናል፤ ማረጋገጫ እስካገኝ ግን ማላገጤም ይቀጥላል) ቃለ ምልልሱን ያካሄዱት ልክ እንደፎቶ ገጭ የመታወቂያ ፎቶ ማንሻ ወንበር አንድ ወንበር ላይና አንድ ግድግዳ አጠገብ ነው፡፡ በጣም ገረመኝ፡፡ ለባለቤቴ እያሳየሁ ሳቅንባቸው፡፡ ከ25 ዓመት የሥልጣን ዘመን በኋላም ፋራነቱን ሊቀርፍ ያልቻለ የመንግሥትን ሥልጣን የያዘ የወንበዴ ቡድን በዚህ የቴክኖሎጂ ዘመን ማየት የሚደንቅ ነገር ነው፡፡ አንድ ሰው እንኳን እንዴት አይነቃምና ይህን ቀላል ችግር ማስተካከል አልተቻለም? አምስት ይሁኑ ስድስት ተጠያቂዎች ሁሉም የተቀመጡበት ወንበር አንድ ነው፡፡ ቦታውም አንድ ነው፡፡ በራስጌያቸው መስኮት አለ፤ በግራ ጎናቸው በር አለ፤ በቀኛቸው መረብ የለበሰ በር ይሁን ጣሪያ አለ፡፡ እንዳልዋሽ ያህል ሰውዬው ሲቀመጥ ወዲያና ወዲህ ስለሚገፋውም ሊሆን ይችላል ወንበሩ ከመስኮቱ ወዲህ ወይም ወዲያ እየሆነ በጣም መጠነኛ ለውጥ በአንዳንዶቹ ተጠያቂዎች ላይ ይስተዋላል እንጂ አቀማመጣቸው የሁሉም አንድ ዓይነት ነው – የኛ የቀድሞ ነፃ አውጪዎች፣ የአሁን የወያኔ ባሮች፡፡ ወያኔ ማለት “አታምሪ ወይ አታፍሪ” የሚባል ዓይነት የክፍለ ዘመኑ ጉድ ነው – “ወላድ አይይህ” የሚባል ጉድ፡፡ ግን ግን ይህን ያህል የአገዛዝ ዘመን ለዚህ የወያኔ ግሪሣ የሰጠው ማን ይሆን? እኛ? ሰይጣን? ድግምትና መተት? ምዕራባውያን? የገዛ ኃጢኣታችን? እግዚአብሔር? ብልጣብልጥነታቸው? የአስተዳደር ዕውቀትና ጥበባቸው? ጭካኔያቸው? ጉልበታቸው? የኛ ሞልፋጣ ባሕርይ? ወይንስ ማን? በአርምሞ አስቡት፡፡ በጥቂት ሽፍቶች አገር ሲታመስ ማየት፣ ብዙ ዜጋ በእግር አውጪኝ አገር ጥሎ እየተሰደደ ራሱንና ቤተሰቡን ብቻ ከሽፍቶቹ የእሳት ጨንገር ነፃ ለማውጣት ሲሯሯጥ መታዘብ የማያመልጡት የክፍለ ዘመናችን እርግማን ሆነ፡፡ ማን ለሐዝብ ያስብ? ማን ለሀገር ይቆርቆር? ማን ለትውልድና ለታሪክ ይጨነቅ? ይህን በስብሶ ሊወድቅ የደረሰ የወያኔ ቤተ መንግሥት ማን ይግፋው? መቼስ በራሱ አይወድቅ፡፡ ትንሽም ቢሆን ገፊ ኃይም ያስፈልጋል፡፡ ራስ ወዳድነት በነገሠበት ዘመን ያ ከየት ይምጣ? እኔም አንተም አንቺም … የምንጨነቀው ስለራሳችን ሆነ፡፡ ነገን ትተን ዛሬ ላይ ብቻ አተኮርን፡፡ የጋራ ህልምና ራዕይ አጣን፡፡ ምን ይዋጠን?
ታስታውሳላችሁ መቼም – አንዳርጋቸውን በቲቪ ሲያቀርቡ ከበስተጀርባው የነበረው “ሳውንድ ትራክ” የታይታኒክን ፊልም ያጀበው የሴሌንዲዎን ዘፈን ወይም የቦብ ማርሊ “stand up for your right” ሣይሆን የሚገረፍ ሰው የሚያሰማው የስቃይ ድምፅ ነበር፡፡ አቡበከርን አንድ “ ምሁር ፈላስፋ”ና “ግሩም አንባቢ” የወያኔ ካድሬ ከካሜራ ተደብቆ በግዳጅ ቃሉን ሲቀበል በዓለም የእሥረኞች ምርመራ ታሪክ (በቲቪ ለሕዝብ በሚቀርብ ማለቴ ነው) ምናልባት የመጀመሪያው ሊሆን በሚችል መልኩ እጆቹን በካቴና አሥረው ነበር – የግፍ ግፍ፤ ወያኔዎች ምንም ዓይነት ሥነ ምግባር (ethics) እንደሌላቸው በዚያች ልይት ኹነት ብቻ ለዓለም አስመስክረዋል፡፡ በቅርቡም የ“ዓለምን መሪ” በኢትዮጵያ ሲቀበሉ ያደረጉት መስተንግዶና መሪውን ለማየት ሲተራመሱ ያሳዩት የፋርጤ ድርጊት ሲታይ የእነዚህ ሰዎች ሁኔታ አለማወቅ ብቻ ሣይሆን ሀገሪቱን ለማዋረድ ሆን ብለው ታጥቀው የተነሱ ይመስላሉ – እርግጥ ነው ከእረኞች ከዚህ የበለጠ መጠበቅ የዋህነት ነው፤ አብዛኞቹ ሞፈር ቀምበር ሰቅለው የመጡ ገበሬዎች ወይም ከፍየል ጥበቃ በቀጥታ ወደ መንግሥት ሥልጣን ያመሩ እረኞች ናቸው፤ በዚያ ላይ ነባር አሠራርን – ዓለም አቀፋዊም ቢሆን – የመጠየፍና ያለመቀበል ጠባያቸው የጎላ ነው፡፡ እንዲያው ለመሆኑ ግና እነዚህን የዮዲት ጉዲት ውላጆች ሊያጠፋ የሚችል በሀገራችን እንዴት አንድ ወንድ ይጥፋ? እነሱስ ምን ዓይነት “ዕድለኞች” ይሆኑ? ለነገሩ ከ1.2 ሚሊዮን ሕዝብ 11 ጀግና ልጆች ተገኝተው ትሪንዳድና ቶቤጎን አንድ ወቅት ለዓለም ዋንጫ ሲያበቁ ከ90 ሚሊዮን ሕዝብ መካከል 11 ሰው ጠፍቶ ለአፍሪካ ዋንጫ እንኳን አለመብቃታችን … ግን ይህን ለምን እዚህ አመጣሁት በል? አስፖርትና ፖለቲካስ ምን አገናኛቸው … ስለዚህ ወሬ አለቀብኝ ማለት ነውና ሌላ ነገር ሳልዘባርቅ በጊዜ ልሰናበት ምዕመናን፡፡
ለማንኛውም አስተያየት nzeleke35@gmail.com

The post የቀድሞ ዴምሕት አባላት በወያኔ ፎቶገጭ ቤት appeared first on Zehabesha Amharic.

የአቶ ግርማ ካሳ ነገር –ይገረም አለሙ

$
0
0

ማስታወሻ፤ ለዚህች አስተያየት መጻፍ ምክንያት የሆነውን የአቶ ግርማ ካሳን ጽሁፍ ያነበብኩት በዚህ መድረክ በመሆኑ አስተያየቱ የተላከው ለዘሀበሻ ብቻ ነው፡፡

ለመደገፍም ሆነ ለመቃወም የነገሩን ምንነት የአድራጊውን ማንነት የአፈጻጸሙን እንዴትነት ወዘተ ማወቅ ይጠይቃል፤ እውነትን መሰረት አድርጎ መቆም ያስፈልጋል፡፡ አቶ ግርማ ካሳ ግን ከሀገር ርቀው እየኖሩ በስማ በለው ወይንም ስሜታቸው በሚነግራቸው ብቻ እየተመሩ በማይጨበጥና በየግዜው በሚዋዥቅ አቋማቸው እየተቃወሙና እየደገፉ ሲጽፉ አመታት አስቆጥረዋል፡፡ እንደ ግዜው ርዝመት አንደሚሰጣቸው አስተያየት ምንም ለውጥ ሳያሳዩና የአቋም ማስተካከል ሳያደረጉ እስካሁን አሉ፡፡ አንድነት ከተመሰረተበት ገዜ ጀምሮ ከመሪዎቹ በላይ መሪ ለመሆን በሚቃጣ ስሜት የአቃፊ መሳይ ገፍታሪ ተግባር ሲጫወቱ የነበሩትና አንድነትን ለሞት ካበቁት ሰዎች አንዱ የሆኑት አቶ ግርማ አሁን ደግሞ መንጠላጠያ ፍለጋ ኢዴፓ መኢአድ መድረክ እያሉ ነው፡፡
2053fountain_pen
ኢሕአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር ስብሰባ ጠርቷል- መልካም ጅማሬ በሚል ርዕስ በቅርቡ ያስነበቡን ጽሁፍ አቶ ግርማ ምን አንደሚደግፉም ሆነ ምን እንደሚቃወሙ ለራሳቸውም የማያውቁ ወይንም ሆነ ብለው የማደናገርና አቅጣጫ የማስለወጥ ስራ የሚሰሩ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ ጽሁፉን እንዳነበብኩ አስተያየት በመስጠትና ባለመስጠት መሀል ሀሳቤ ሲዋልል የመድረካችን እንቁ ብቸኛዋ ሴት ጸኃፊ (ሌሎች ካሉ ባለማወቄ ይቅርታ) እህት ስርጉተ ተገቢ መልስ ሰጠች፡፡ እኔም ትንሽ አንድል መነሳሳት ፈጠረችብኝ፡፡

አቶ ግርማ እውነትና አንድነት፤ ለእውነት የቆመ ሰው ነገሮችን የሚመዝነው ከነገሩ ምንነትና እንዴትነት እንጂ ከአድራጊው ጋር ባለው ፍቅር ወይም ጥላቻ አይደለም፡፡ ወይንም ጉዳዩ ለግል ከሚያስገኘው ጥቅም አንጻርም መሆን የለበትም፡፡ አንዱ ሲሰራው ህገ ወጥ ብለው ያወገዙትን ድርጊት ሌላው ሲፈጽመው ማድነቅ አልያም በዝምታ ማለፍ ካለ ከእውነት ጋር ሆድና ጀርባ ተኩኗል ማለት ነው፡፡ ህግ ከሚጥሱ፤ ሥርዓት ከሚያፋልሱ፤ ስራን ሳይሆን ሴራን ምርጫቸው ካደረጉ ወዘተ ጋር የግል ጥቅምን እያሰቡ መተባበር ካለ በእውነት ላይ መሸፈት ብቻ ሳይሆን ከሰዋዊ ባህርይም መወጣት ነው፡፡

አቶ ግርማ በተለይ አንድነትን አስመልክቶ ከርቀት ሆነው በብዕራቸው ሲፈጽሙት የነበረው ተግባር ከእውነት ጋር ሆድና ጀርባ መሆናቸውን ብቻ የሚያሳዩ አልነበሩም፡፡ በአንዱ ጽሁፋቸው ያነሱት ሀሳብ ከቀጣዩ ጽሁፋቸው ሀሳብ ጋር የሚቃረን፤ በአንዱ ጽሁፋቸው ያሞገሱትን ሰው በሌላኛው ጽሁፋቸው የሚኮንኑት በመሆናቸው ከራሳቸውም ጋር የተጣሉ መሆናቸውንም ያሳብቃሉ፡፡

ራሳቸውን አንደ መሪ የቆጥሩበት አንድነት (በተወሰነ ተሳክቶላቸው በርቀት ሆነው የጎንዮሽ አመራር ለመስጠት እስከመቻል የደረሱበት ወቅት ነበር) ሲመሰረት መሪ ሆና የተመረጠችው ወጣቷ የህግ ባለሙያና የጠላለፉ ፖለቲካ ያልነካካት ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ነበረች፡፡ የብቱካን የመጀመሪያዋ ሴት የፖለቲካ ፓርቲ መሪ ሆና ወደ መድረክ መምጣት ስጋት የሆነው ለወያኔ ብቻ ሳይሆን በተቃውሞው ጎራ ላሉ ያለእኛ ፖለቲካ ለሚሉትም ነበር፡፡ ለዚህ ደግሞ ዳግም ለእስር በተዳረገችበት ዋዜማና ማግስት የተፈጸመባት ክህደትና ድጋፍ መንሳት በቂ ማረጋገጫ ነው፡፡ ይህንም መለስ ብሎ በወቅቱ የተጻፉትን በማየት ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ይሄው አድራጎት አመራሩ ለፓርቲው ሊቀመንበር በህገ ወጥ ሁኔታ መታሰር ትኩረት አልሰጠም የሚል ጥያቄ አስነስቶ በፓርቲው አባላት ዘንድ ቅራኔ ሲፈጠር አቶ ግርማና መሰሎቻቸው ጥያቄ አንሺዎቹን ሲዘልፉ ሲያወግዙ ከዛም አልፈው በወያኔነት ሲፈርጁ ነው የሰማን ያነበብነው፡፡ ቅራኔው ሰፍቶ ነገሩ ተስፋፍቶ በርካታ አባላት ሲባረሩና አንዳንዶችም አመራሩን በመጥላት ራሳቸውም ሲለቁ ( ሰማያዊ ፓርቲን የመሰረቱ) እነ አቶ ግርማ ችግራችሁን በውይይት ፍቱ ከማለት ይልቅ አመራሩን በማበረታታት የርምጃው ደግፊ ነው የሆኑት፡፡

አቶ ግርማ አንድነትና መድረክ፤ አንድነት ከመድረክ ጋር የሚኖረው ግንኙነት የተጠና የተመከረበት ሊሆን ይገባል በማለት አባላት የጥድፊያውን መቀላቀል ሲቃወሙ አቶ ግርማና መሰሎቻቸው ለፓርቲው ከአባላቱ በላይ ሀሳቢ ሆነው ተቀዋሚዎቹን ሲያወግዙ ነበር፡፡አንድነት ለአምስት ዓመታት ያህል የመድረክ አባል ሆኖ ራሱም ሳይጠቀም መድረክንም ሳይጠቅም አንካሰላንትያ ውስጥ ሲገባና በመድረክ የእገዳ ርምጃ ሲወሰድበት መድረክ ወይንም ሞት ያሉት አቶ ግርማ መድረክን ኮንነው አንድነት ከመድረክ እንዲፋታ መካሪና አመራር ሰጪ ሲሆኑም ታዝበናል፡፡
አቶ ግርማ አንድነትና ምርጫ 2002፤ አንድነት በምርጫ 2002 የሚሳተፍ ከሆነ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ሊቀመንበሩ አንድትፈታ ይጠይቅ፤እሱ ብቻም አይደል አባል የሆነበት መድረክም በምርጫው የምንወዳደረው ብርቱካን ከተፈታች ብቻ ነው በማለት እንዲጠይቅ ያድርግ በማለት አባላቱ ጠየቁ፡፡ የአንድነት አመራሮች ግን በመድረክ ተወዳድረን ስየና ነጋሶን ይዘን የሚያቆመን የለም በማለት በምርጫው እንደሚያሸንፉና ራሳቸውን ፓርላማ አንደሚገኙት ርጠኛ በመሆን “የብርቱካንን እስር የምርጫ 2002 ቅድመ ሁኔታ እርጎ ማቅረብ ፖለቲካውን ያስነሰዋል አንኳን አንድነት አንድነት አባል የሆነበት መድረክም ይህን አያደርግም በማለት በድፍረት በአደባባይ ተናገሩ፡፡ አነ አቶ ግርማም ሰልፋቸውን ከእነዚህ ሰዎች ጎን አድርገው ቀጠሉ፡፡ ከምርጫው የተገኘው ግን አንድ ወንበር ብቻ ሆነ፡፡

አቶ ግርማ አንድነትና ኢ/ር ግዛቸው፤ በብርቱካን መታሰር ምክንያት የፓርቲው ሊቀመንበር የሆኑት ኢ/ር ግዛቸው ዶ/ር ነጋሶ በተመረጡበት ጉባኤ ፊት “ወኔየ ሞቷል ሞራሌ ወድቋል በአመራርነት አይደለም በፓርቲ አባልነትም አልቀጥልም ብለው” ተሰናበቱ፡፡ እነ አቶ ግርማም አድንቀው ደገፉ ለፈፉ፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላ ፓርቲው ጉባኤ እያዘጋጀ ከመሆኑ ዜና ጋር ኢ/ር ግዛቸው ለሊቀመንበርነት እንደሚወዳደሩ ሲገለጽ እነ አቶ ግርማ አንዴት ሆኖ ለምንስ ተብሎ የሚል ጥያቄ አላነሱም፡፡ ኢ/ር ግዛቸውም በከፍተኛ ድምጽ ተመረጡ ተብሎ ሊቀመንበር ሆኑ፡፡ የእነ አቶ ግርማ ድጋፍም ተቸራቸው፡፡አስገራሚውና ለአንድነት ሞት ምክንያት የሆነውን የመጨረሻውን በር ለወያኔ ብርግድ አድርጎ የከፈተው ከዚህ በኋላ የሆነው ነው፡፡

ከላይ በገለጽኩት መልኩ ተመረጡ የተባሉት ኢ/ር ግዛቸው ስድስት ወር ሳይሞላቸው የሚደርስባቸውን ጫና መቋቋም እንዳልቻሉና በተለይ ከዲያስፖራው የገጠማቸው ተግዳት ሊያሰራቸው አንዳልቻለ ለምክር ቤቱ ገልጸው ሥልጣናቸውን ለቀቁ፡፡ (ዲያስፖራ ማለት እነ አቶ ግርማ መሆናቸውን ልብ ይሏል፡፡) የዲያስፖራው ግፊት ኢ/ር ግዛቸውን በመቃወም ከሥልጣን ማስነሳት ብቻ ሳይሆን ሌሎቹን በመደገፍም አስቷል፤አሳስቷል፡፡ሊቀመንበር የመምረጥ ሥልጣን የጠቅላላ ጉባኤ ብቻ መሆኑ ተዘንግቶ በእነ አቶ ግርማ ሆይ ሆይታ ምክር ቤቱ አቶ በላይን ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ፡፡ የእነ ግርማም የብእርም የብርም ድጋፍ ተቸረ፡፡ የሚያሳዝነው ከኋላ ሆኜ መስራት ነው የምፈልገው በማለት በተደጋጋሚ የቀረበለትን የሊቀመንበርነት ጥያቄ ሲገፋ የኖረው አቶ በላይ በውጪም በውስጥም ግፊት በመጨረሻ ሰአት ሊቀመንበር ሆኖ ለመከራ መዳረጉ ነው፡፡ ምነው አንድነት መሞቱ ካቀረ በኢ/ር ግዛቸው እጅ ላይ ቢሞት ኖሮ፤

ዛሬ የኢህዴግ መልካምነት የታያቸው አቶ ግርማ፤ ዛሬ ተቀዋሚዎችን ወደ ኢህአዴግ ግብዣ ሂዱ በማለት የሚመክሩት አቶ ግርማ በእነርሱ ግፊት የተፈጠረን ስህተት አንደመልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ ወያኔ አንድነትን ለማፍረስ ቢሮው ደጃፍ ላይ ጉድጓድ በሚቆፍርበት ሰአት ረጋና ሰከን ተብሎ ለወያኔ መግቢያ ሊሆኑ የሚችሉ ቀዳዳዎችን የመድፈን ስራ እንዲሰራ ለምን አይመክሩም ነበር፡ በቅርብ እንደታዘብነውና ከጽሁፎቻውም አንደተረዳነው እነ አቶ ግርማ በዛን ሰአት ይገፉና ያደፋፍሩ የነበረው የውግዘት መግለጫ እንዲወጣና እንኳን በዛን ሰአት ከዛ በፊት ያልሆነ ያልተቻለው ሰላማዊ ሰለፍ እንዲጠራ ነበር፡፡ አንድነት እንዲህ መሆኑ ላይቀር ሰልፍ ተብሎ ቢሮአቸው በር ላይ የተደበደቡት አባላት ያሳዝናሉ፡፡ እነ አቶ ግርማ ይህን ያደረጉት አንድነትን በመግለጫና በሰላማዊ ሰልፍ ማዳን ይቻላል ብለው አምነው ነው ወይንስ አንድነት እንዲሞት ከመፈለግ?
አቶ ግርማና የተባበሩ ጥያቄአቸው፤ አበው ከአንድ ብር ሁለት መድሀኒቱ፤ድር ቢያብር አንበሳ ያስር ወዘተ በማለት የመተባበርን አስፈላጊነትና ጠቃሚነት ይገልጻሉ፡፡ አልሆን እያለ ተቸገርን አንጂ ፓርቲዎች መተባበር አይደለም ተጨፍልቀው ከሶስትና ከአራት ባይበልጡ የብዙው እምነት ነው፡፡ ተለያይቶ በመቆም ከሚያተርፈው ውጪ፡፡ አቶ ግርማ ስለ ፓርቲዎች ትብብር የሚጽፉትን ከምር የሚያምኑበት አይመስለኝም፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ርሳቸውም አንደ ፖለቲከኞቹ ትብብርን ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ነው የሚያውሉት ብሎ መጠርጠር ይቻላል፡፡ ከዚህ ሲያልፍም ለወቅታዊ ትኩረት ማስቀየሻ ይሆናል ማለትም ይቻላል፡፡

የፓርቲዎችን መተባበር ከምር የሚፈልግ ሰው የተወጠነው ሲጨነግፍ፤ የተመሰረተው ሲፈርስ እያየ ዝም ብሎ ተባበሩ አይልም፡፡ መተባበር ያልተቻለበትን ምክንየት መርምሮ መፍትሄ ይጠቁማል፤ ፖለቲከኞቹን ሆድና ጀርባ የሚያደርጋቸውን በሽታ አጥንቶ መድሀኒት ያዛል፤ ከዚህ ሲያልፍም የመተባበር እንቅፋት የአብሮ መስራት ጋሬጣ የሆኑ ፓርቲዎችንም ሆነ መሪዎችን በተጨባጭ ማስረጃ ይኮንናል ያጋልጣል፡፡አቶ ግርማ ግን ለተቃውሞአቸውም ሆነ ለድጋፋቸው ስሜት አለያም የማናውቀው ምክንያት እንጂ የእውነት መሰረት ስለሌላቸው ሾላ በድፍን ተባበሩ ይላሉ እንጂ ማን ከማን ጋር እንዴትና በምን ሁኔታ በምንስ ደረጃ መተባበር እንደሚችሉና አንዳለባቸው አያመላክቱም፡፡

ወያኔን የሚገዳደር ጠንካራ ትግል ለማድረግ የሚበቃ መተባበር ለመፍጠር መጀመሪያ የፖለቲካውን መድረክ የሙጢኝ ባሉት ሰዎች ዘንድ የአስተሳሰብ ለውጥ ያስፈልጋል፤ከዛ በየፓርቲው ተሀድሶ ማድረግና ፓርቲዎቹን ከግለሰብ ድርጅትነት ወደ ትክክለኛ ፓርቲነት ማሳደግ፤ከዛ በኋላ መተባበሩም ሆነ ቅንጅት ግንባርም ይሁን ውህደት የመፈጸሙ ንግግር በፓርቲዎች መካከል ይሆናል፡፡ አቶ ግርማ የተባበሩ ጩኸተዎ ከምር ከሆነ በዚህ መንገድ ተግተው ይጻፉ፡፡ ሾላ በድፍን ተባበሩ ግን የጤና አይደለም፡፡

ስለ ሰላማዊ ትግሉም ቢሆን መጀመሪያ ትግሉን ሊመራ የሚችል ጠንካራ ፓርቲ መኖር ያስፈልጋል፡፡ አቶ ግርማ ደግሞ ከላይ ለማሳየት የሞከርኩት ተግባራቸው እንደሚያረጋግጠው እንደ መሪ ይቃጣቸው በነበረው ፓርቲ ውስጥ ውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲ ጎልብቶ ውይይት ባህል ሆኖ፤ የሀሳብ ልዩነት ተከብሮ ድርጅታዊ አንድነት ጎልብቶ ፓርቲው አንዲጠናከር ሳይሆን የጥቂት ግለሰቦች ቤት አንዲሆን ሲሰሩ የነበሩ ናቸው፡፡ ይህን ደግሞ ያኔ መርህ ይከበር ይባሉ ከነበሩት ወጣች ጋር ይመላለሱዋቸው የነበሩት ጽሁፎችዎ ያሳያሉ፡፡እባክዎን አቶ ግርማ መጀመሪያ ከእውነት ጋር ታረቁ፤ ከዛም የተቃውሞዎንም ሆነ የድጋፍዎን ምክንያት ይወቁ፤ ከቻሉም መለስ ብለው የጻፉዋቸውን ጽሁፎች በማየት ራስዎን ይጠይቁ፡፡

The post የአቶ ግርማ ካሳ ነገር – ይገረም አለሙ appeared first on Zehabesha Amharic.

የወያኔ ስራ  በቤተክርስትያናት ላይ!! በዘመናችን ያለ የቤተክርስቲያን ትልቁ ፈተና –ጉዞ ወደ እናት ቤተክርስቲያን (እንቀላቀል) ለምን ትልቅ ፈተና ሆነ ስንል?

$
0
0

 

ከጌታቸው ካሳሁን

          የእስከዛሬዎቹ  ጥቃቶች የሚፈፀሙት ከቤተክርስቲያን ውጪ በሆኑ ሰዎችና ተመሳስለው በገቡ ማንነታችውን በደበቁ ሰዎች ሲሆን ይህኛው ግን ለየት የሚያደርገው የሃይማኖት ሽፋን ያለው እንዲሁም እውቅና በሰጠናችውና በፈቀድንላቸው ጥፋታቸውን እራሳቸውን ሳይደብቁ በግልፅ እያሳዩን እንኳን ዝም ብለን የተቀበልናቸው የቤተክርስቲያን አማሳኞች  አባቶችና ምዕመናን የሚከናወን በመሆኑ ነው።እንግዲህ ወደ ጉዳዩ ስንገባ በመጀመሪያ ቤተክርስቲያን አንዲት ናት ርትዕት ናት በዶግማ ምንም ችግር የለባትም ነገር ግን በአስተዳደር ችግር ምክንያት ለሶስት ቦታ ተከፍላለች ። ልብ በሉ በዶግማ አላልኩም በአስተዳደር ምክንያት ነው ያልኩት።

በአስተዳደር  ለ3 ( ሶስት) ቦታ የተከፈሉትን እንደዚህ እናያቸዋለን

  1. በኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ ስር የሚተዳደሩ
  2. በአሜሪካን ሀገር ባለው ቅዱስ ሲኖዶስ ስር የሚተዳደሩ ሲሆኑ፡
  3. ገለልተኛ ቤተክርስቲያን፡-የሚባሉት ደግሞ በአሁን ግዜ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ሁለት ፓትርያርክ ስለሆነ ያላት ለየትኛውም ፓትርያርክ አንወግንም  የሚሉና ገለልተኝነታቸው ከሁለቱ አባቶች እንጂ ከቤተክርስትያኒቱ ያልሆነ እንዲሁም  እርቀ ሰላም ወርዶ አንድ ሲኖዶስ በቦታው እስኪመለስ ድረስ ለየትኛውም አንወግንም የሚሉ ናቸው።

ነገር ግን በሶስቱም  አስተዳደር  ስር ያሉት ቤተክርስቲያኖች መተዳደሪያ ደንባቸው በቅዱስ ሲኖዶስ የተዘጋጀው ቃለ ዓዋዲ ሳይሆን ከቤተክርስትያኑ አባላት በተውጣጡ ጥቂት ሰዎች በሚቀርጹት መተዳደሪያ ደንብ ነው። ቤተክርስቲያንነታቸው የአንዲት (እናት) ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲሆን፤  አንዱ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ሌላው ደግሞ እንጀራ ልጅ ሊባሉም አይችሉም።  እንዲሁም ምእመኖቻቸው የአንዲት እናት የኢ/ ኦ/ተ ቤተክርስቲያን ልጆች ናቸው። ጊዜ ያመጣው ፖለቲካ አስተዳደሩን ለሶስት ከፈለው እንጂ  ሁሉም አሃዱ አብ ቅዱስ ብለው የሚቀድሱ እና የሚያመሰግኑ ልዩነት የሌላቸው በአንድ አምላክ የሚያምኑ ናቸው።

በዚህ ጊዜ በአንድነት ስም ቤተክርስቲያንን መክፈል ያስፈለገበት ምክንያት

ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለው መንግስት ከጫካ ጀምሮ አንግቦ በመጣው የኢ/ኦ/ተ ቤተክርስቲያንን የማፍረስ ዓላማ በተለያዩ ጊዜያት ቤተክርስቲያንን ሲያቃጥል፣ ሲያስፈርስ፣ ሲያርስ፣ ታሪኳን በጠራራ ፀሀይ ሲያጠፋ የሀይማኖት ቦታዋን እየነጠቀ ለሌላ ሲሰጥ ስለ ቤተክርስቲያን ብሎ አንድም የተናገረላት አባትም ሆነ  የበላይ አካል ዝም ብሎ ከማየት ወጭ ያደርጉት አስተዋፆ የለም። በትንሹ ቢሆን በየአካባቢው ያሉ ምእመናን አትንኩ ቤተክርስቲያኔን ሲሉ በአፀፋው እስር፣ እንግልት፣ መገደል  ደርሶባቸዋል።  በእኛ ዝምታ መንግስት ተግባራዊ አድርጎታል ነገር ግን በተቻለው ፍጥነት የማፍረስ ሂደቱ እንዳይከናወን ሁለት ነገሮችን ይፈራል።

  1. ማህበረ ቅዱሳንን፡- ማህበሩን ለምን ይፈራዋል ስንል የቤተክርስቲያን የጀርባ አጥንት ነው በሎ ስለሚያስብ  ስለዚህ ማህበሩን ለማፍረስ በተለያየ ጊዜ ብዙ ሙከራ ቢያደርግም አልሳካ  በማለቱና ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ የሚደረገውን እሩጫ ማህበሩ ባያቆመውም ወደ ኋላ ስለጎተተበት እንዲሁም ውጤቱ እንዲያዘግም ስላደረገና መዋቅሩም በጣም ጥልቅና እስከ ታች ድረስ ዘልቆ ስለገባ ማፍረስ ባለመቻሉ በዚህ ጉዞ ወደ እናት ቤተክርስቲያን በሚል ከተቻለ ለማፍረስ አለበልዚያም ለማዳከም ነው።

ይህ አቅጣጫ እንዴት ማህበሩን ያፈርሳል   ?

 

ጉዞ ወደ እናት ቤተክርስቲያን በሚል እውነትነት ያለው በሚመስል የሃይማኖት ሽፋን ነገር ግን ህዝብን ከህዝብ፤ ባልን ከሚስት፤ በአጠቃላይ የምእመናንን ልብ ለሁለት ከፍሎ እስከመለያየት የሚያደርሰውን አጀንዳ የማህበረ ቅዱሳን አጀንዳ አድርጎ  በምእመን ዘንድ ሰርጾ እንዲገባ በማድረግ ማህበሩ በምእመናን እንዲጠላ ማድረግና ከተቻለ በዚህ አጋጣሚ ማህበሩን አፍራሽ አድርጎ በይፋ በማውጣት ማፍረስ ወይም ከምእመናን ልብ ውስጥ ማውጣትና ማዳከም ነው።  እዚህ ጋር ግን የሚያሳዝነው የማህበሩ አባል በሆኑ ነገር ግን የማህበሩ ዓላማ ባልሆነው ነገር እነርሱን ከፊት በማሳየት መጠቀምና ተአማኒነትን ለማግኘት በመሞከር የማህበሩን ተልእኮ እያስፈፀሙ አስመስሎ በማሳየት በእነርሱ መጠቀም ነው።

  1. ብዙ ህዝብ የተሰበሰበበት በዘር በጎሳ ያልትከፋፈለና ስርዓተ ቤተክርስቲያንን የጠበቀ አገልግሎት የሚሰጥበትን ቤተክርስቲያንን  ፦   እነዚህን ለምን ይፈራል ስንል አንድነትን አጥብቆ ስለሚፈራ ለስልጣኔ ያሰጋኛል ስለሚል። እንደዚህ ዓይነት ቤተክርስቲያኖች የሚገኙት ደግሞ በገለልተኛ ቤተክርስቲያን ስር ያሉት ጋር ነው። እነዚህ ቤተክርስቲያኖች አንድነታቸውን ጠብቀው ፍፁም ኢትዮጵያዊነት ስለሚታይባቸውና በቂ ባይሆንም ቤተክርስቲያን ላይ የሚደርሰውን አደጋ በመግለጫም ቢሆን በጥቂቱ ይቃወማሉ። እንዲሁም በሰው ኃይል፣ በፋይናንስ እና ከእዳ ነፃ የሆነ ቤተክርስቲያን ባለቤትና በአገልግሎትም ጠንካራ ስለሆኑ መንግስት በስጋት ያያቸዋል።                                                                      ይህን ቤተክርስቲያንን የመክፈል (የማዳከም) ስራ ማን ይስራው

እንግዲህ በአሁን ግዜ በቤተክርስትያኒቱ ውስጥ ሁለት አይነት ሰዎች ዲያቆናት፣ካህናትና እንዲሁም ጳጳሳት ከታች እስከ ላይ በተዋረድ ከስር አጥቢያ ቤተክርስትያን አንስቶ እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ ድረስ አሉ። እነርሱም፦

1.  የመጀመሪያዎቹ ፡- በመንግስት ተመልምለው ለዚህ ለቤተክርስቲያን የማፍረስና የማዳካም ስራ ስልጠና ወስደው ከድቁና እስከ ጵጵስና ደረጃ ተምረው ወይም የነበሩትን በዘር፣ በስልጣን፣ በጥቅማ ጥቅም ተደልለው ቤተ ክርስቲያኒቱን ከአጥቢያ ቤተክርስትያን እስከ ቤተክህነት እንዲሁም ጵጵስና ደረጃ የያዙት ሲሆኑ

2.ሁለተኞቹ፡- ደግሞ በታማኝነት፣ በፍፁም ፍቅር ፣በፍጹም እምነት በቤተክርስቲያኒቱ ያደጉና ለቤተክርስቲያኒቱ ዘብ የሚቆሙ ህመሟ ህመማቸው የሆነ ችግሯ ችግራቸው የሆኑ ከአጥቢያ ቤተክርስቲያን እስከ ጵጵስና ያሉ ሲሆኑ እነዚህኞቹ ግን በአጥፊዎቹ ተውጠው በፍፁም እንዳይንቀስቀሱና ድምፃቸው ወደ ውጭ እንዳይወጣ ታፍነው የተያዙ ናቸው። እንግዲህ ይህን ያህል ካልን ይህን የማፍረስ ስራ በበላይነት እንዲመሩ የተመረጡት ደግሞ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ናቸው።
abune-matyas
ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ፦ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን እንደዚህ ሳትከፋፈል በአንድ አስተዳደር ስር በነበችበት ግዜ ማለትም ሲኖዶስ አንድ መንጋውም እረኛውም አንድ በነበረበት ወቅት አቡነ ማትያስና አቡነ ጳውሎስ በገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን ሆነው አሁን ለአለው መንግስት ገንዘብ እየሰበስቡ ይረዱ የነበሩ፤ እንዲሁም በአሁን ጊዜ በስርዓት ቤተክርስቲያን ያልተሾሙና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የፕትርክና አሿሿም ስርዓትና ደንብ ያልተሾሙ በመንግስት ፊት አውራሪነት ስራዬን ይሰሩልኛል ብሎ በመንግስት ፈቃደኝነት የተሾሙ ፓትሪያርክ ሲሆኑ ይህን ደግሞ የቤተክርስትያኒቱ ፍትሃነገስት እንደሚቃወም ኤጲስቆጶሳት አንቀጽ 5 ቁጥር 175 ረስጠብ 21<< በዚህ አለም መኳንንት ቢረዳ ከእነርሱም ዘንድ ለቤተክርስትያን ቢሾም ይሻር እርሱና ግብረአበሮቹ ሁሉ ይለዩ ብሎ ይነግረናል>> ቤተክርስቲያንን የማፍረሻ (የመክፈያ) ዋና አጀንዳቸው ደግሞ ስርዓት ቤተ ክርስቲያን ፈርሷል የሚል ነው

ስለ ስርዓት ከመነሳቱ በፊት የቤተክርስቲያንን ስርዓቶችና እና አገልግሎቶች በጥቂቱ እንመልከት

  1. ሠዓታት መቆም
  2. ማህሌት መቆም
  3. ቅዳሴ መቀደስ
  4. ስብከት ወንጌል ካሉት ግልጋሎቶች በጥቂቱ እነዚህን ስናይ

እንግዲህ እነዚህ አማሳኞች የሚጠቀሙት አንዱን ቅዳሴን በማጉላት (በማዉጣት) ሌላው አገልግሎት ላይ ሥርዓት እንደሌለ በማድረግ ያውም የፓትርያርክ ስም አለመጥራትን እንድ ትልቅ ክህደት (ዶግማ) የተጣሰ ያህል በማራገብ ቤተክርስቲያን መክፈልን ተያይዘውታል። እነርሱን የሚያስጨንቃቸው የፓትርያርክ ስም መጠራት አለመጠራቱን እንጂ የቤተክርስቲያኒቱ አገልግሎቶች ሰዓታቱ፣ ማህሌቱ፣ ስብከተ ወንጌሉ ፣ ቀኖናው፤ዶግማው ስርዓት የጠበቁ አገልግሎቶች መሆናቸው ላይ ግድ የላቸውም። ይህ ማለት በቅዳሴ ጊዜ ስም አለመጥራት ችግር አይደለም ሥርዓት አልፈረሰም ማለት አይደለም። ነገር ግን በቅዳሴ ጊዜ ስም  መጥራት የቤተክርስትያኒቱን ስርአት ሙሉ ያደርገዋል ማለት አይደለም የቤተ ክርስቲያኒቱን ስም የማይጠራበት ምክንያት እልባት ቢያገኝ የቤተክርስትያኒቱ ዘርፈ ብዙ ችግሮችና  የቤተ ክርስቲያኒቱ ሥርዓትና አገልግሎቶች ሙሉና አንድ ወጥ ይሆናሉ። የቤተክርስቲያኒቱ ሰላም አንድነት እንዲሁም አስተዳደር አንድ ይሆናል። አባቶች በቅዳሴ ጊዜ የፓትርያርክ ስም እንዲጠራ ሲደነግጉ በስርዓተ ቤተ ክርስቲያን የተሾመ ስርአቷንና ዶግማዋን ቀኖናዋን ጠብቀው የተሾሙ የፓትርያርክ ስም እንዲጠራ እንጂ ከቤተክርስትያን የፓትርያርክ አሿሿም ስርዓት ውጭ ማለትም በመንግስት የተሾሙትን እንዲጠራ የሚል አይደለም ስርዓት ከተባለ ደግሞ አንድ ፓትርያርክ ፓትርያርክ ሊባል የሚችለው የቤተክርስቲያን ስርዓትዋንና ደንቧን የጠበቀ የእግዚአብሔርን ህዝብ በስርዓት የሚጠብቁ ኃይማኖቷን ቀኖናዋን ዶግማዋን ተከትሎ በእኩል የእግዚአብሔርን ህዝብ የሚመሩ አባትን እንጂ ከእግዚአብሔር ህዝብ ጡንቻ ያለውን መንግስት የሚያስቀድምን አባት አይደለም።ለዚህ ፍትሃ ነገስቱ ኤጲስቆጶስ  አንቀጽ 5 ቁጥር 175 ረስጠብ 21 <<በዚህ አለም መኳንንት ቢረዳ ከነርሱም ዘንድ ለቤተክርስትያን ቢሾም ይሻር እርሱና ግብራበሮቹ ሁሉ ይለዩ >>ነው የሚለው።

ለአብነት ያህል የኤርትራውን ፓትርያርክ እንመልከት። የኤርትራው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ አንቶኒዮስ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከጥር 13/ 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ከመንበራቸው አንስቶ የቁም እስረኛ ያደረጋቸው የኤርትራው መንግስት ነው። ምክንያቱም ደግሞ መንግስት ገዝቱ ያላቸውን 3000 ምእመናን አልገዝትም በማለታቸውና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ በመጠየቃቸው ሲሆን እርሳቸውም ከመንግስት ጡንቻ የእግዚአብሔር ይበልጣል በማለት አስካሁን በቁም እስር ላይ ይገኛሉ። መንግስትም አሳቸውን አስሮ በምትካቸው የመንደፈራውን አቡነ ዲዩስቆሮስን መሾሙ ይታወቃል።ይህን መረጃ በድሬቲዩብ January 22 2015 ላይ ተገልጾ እናገኛለን ልብ በሉ እውነት አሁን አባቶች ሥርዓቱን ሲሰሩ በቅዳሴ ሰዓት በመንግስት የተሾሙትን የአቡነ ዲዮስቆሮስ  ስም እንዲጠራ ነውን? አይደለም። ትክክለኛው ስርዓት በእስር ላይ ያሉት የአቡነ አንቶኒዮስ ስም እንዲጠራ እንጂ በመንግስት የተሾሙትን አለመጥራት እንደውም ስርዓትን መጠበቅ ነው።በመንግስት እንደተሾሙ እየታወቀ መጥራት ስርአት ማፍረስ ነው። እንደ ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ቀኖና መሰረት በአሁን ሰአት ቤተክርስትያን ፓትርያርክ የላትም ምክንያቱም ፓትርያርክ ይሰደዳል መንበር ግን አይሰደድም በስደት ላይ ያለው ሲኖዶስ ግን መንበር አቋቁሟል እንዲሁም የሃገር ውስጥ ሲኖዶስም በመንግስት በተሾመ ፓትርያርክ ተሰይሟል ቀኖና ቤተክርስትያን ደግሞ በመንግስት የተሾመ ይሻር ይላል እኔ ሳልሆን ቀኖናው ይሽራል ስለዚህ የትኛው ስም ይጠራ ?

እነዚህ አማሳኞች እውነት አንድነት ከሆነ ዓላማቸው ለምን ቃለ አዋዲውን አይቀበሉም? ለዚህ የሚመልሱት ደግሞ ከአሜሪካን ሀገር ጋር የማይስማማ ስላለው ነው ባይሎ የምንቀርፀው ይላሉ። ምክንያቱም የተነሱበት ዓላማ ያ ስላልሆነ ነው፤ እንጂ ከአሜሪካን ሃገር ጋር የማይስማማ ቢሆን እንኳን ጥያቄ ለቅዱስ ሲኖዶስ አቅርበው ቅዱስ ሲኖዶስ ከአሜሪካ ሃገር ህግ ጋር የሚስማማ ሊያወጣላቸው ይገባል እንጂ ማንም ሰው ተነስቶ ቃለ አዋዲውን ሊያሻሽል አይችልም። ምክንያቱም የማሻሻልም ሆነ የማስተካከል ስልጣን ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ ስለሆነ ። እንዲሁም እነዚህ በኢትዮጵያ ስር ነን ብለው ቃለ አዋዲውን የማይቀበሉት አንድ ባይሎ(መተዳደሪያ) እንኳን የላቸውም። ለምሳሌ በአንድ እስቴት ውስጥ 10 ቤተክርስቲያን ቢኖር እንኳን 10 የተለያየ ባይሎ(መተዳደሪያ) ነው ያላቸው እንጂ ለአስሩ እንኳን አንድ ባይሎ(መተዳደሪያ)  የላቸውም ምክንያቱም ዓላማው  መለያየት ስለሆነ ባይሎው አንድ ከሆነ አንድነትን ስለሚያመጣ አያስፈልግም። ይህን ደግሞ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ፓትርያርኩን ጨምሮ በማፍረስ ስራ ላይ የተሰማሩት አንድም ምእመናንን በመከፋፈል በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት እድሜ ማራዘም ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የራሳቸውን  የወደፊት መውደቂያ እያመቻቹ ነው። መንግስት ተቀይሮ ወይም በሆነ ምክንያት የቤተክርስቲያን አንድነት ቢመለስ እነዚህን ቤተክርስቲያኖች ገለልተኛ ለማድረግና ሸሽተው መጥተው በቁጥጥራቸው ስር አድርገው የቤተክርስቲያናችን ትንሳኤ እንደገና ወደ ኋላ ለመጎተት የታለመ ነው። ስለዚህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ምእመን ሆይ  ይህ ሁሉ ደባ በቤተክርስቲያን ላይ ሲሰራ ከዚህ ነገር ላይ ጥቂት ተጠቃሚዎች ካህናትና ግለሰቦች ስላሉ ጉዳዩን በደንብ አጢነን ዝም ብለን ከምንከተል ተው ልንላቸው ይገባል።

ይህ የአስተዳደር ችግር በምእመን የሚፈታ ችግር አይደለም የጀመሩትም አባቶች ናቸው የሚፈቱትም አባቶች ናቸው። ሁለቱ አባቶች ከፈለጉ አንድ ያደርጉታል ከፈለጉ እንደበተኗት ያስቀሯታል። ሁለቱ ከታረቁ  ሁሉም መንጋውም ግን እረኛውም አንድ ይሆናል። ምእመን ቤተክርስትያንን አንድ እናድርግ ቢል ግን ሁከትና እረብሻ  ነው የሚፈጠረው ምክንያቱም አባቶች አይፈልጉማ። አንድነት እንዳይመጣ እጃቸውን ያስገባሉ። ስለዚህ እኛ ምእመናን ግን ስደተኛ ገለልተኛ በኢትዮጵያ ሳንል አንድነታችንን ጠብቀን በያለንበት ቤ/ተክርስትያን እየተገለገልን በፍጹም ወንድማማችነት መፍትሔ እስኪመጣ ድረስ እግዚአብሔርን እየጠየቁ መኖር ያስፈልጋል።

እነዚህ አማሳኞች በተለያዩ ቦታዎች ከሰሯቸው የማፍረስ ስራዎች ውስጥ ለኣብነት ያህል በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ ቤተክርስቲያን ያደረጉትን እንመልከት

በመጀመሪያ የሜኒሶታ ደ/ሰ/መ/ቤተክርስትያን ማን ናት?በሜንሶታ ካሉ አብያተክርስቲያናት አንዱ                     ላይ ያዉም ደብረሰላም መድኃንያለም የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ለምንተመረጠ?

ደብረሰላም መድኃኒዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ከተመሰረች ከ1993 እ. ኤ. አ.በገለልተኝነት የምትታወቅ ሲሆን በተለያዩ ጳጳሳት የተባረከችና በአሁን ጊዜም የተለያዩ ጳጳሳትና የቤተክርስትያን ታላላቅ አባቶች ከኢትዮጵያ ድረስ በመምጣት ምክር ትምህርትና ቡራኬ ያልተለያት እንዲሁም በአሜሪካን ሀገር አሉ ከሚባሉት ታላላቅ አድባራት በአሁን ሰዓት ግንባር ቀደም ናት ቢባል ማጋነን አይሆንም በአሁን ግዜ አገልግሎቷን በማስፋት በአመት 365 ቀናት ማለትም አመቱን በሙሉ ለተገልጋዮች ክፍት በመሆን የተለያዩ አገልግሎቶችን በመስጠት ብቸኛዋ ቤተክርሰትያን ናት ቢባል ማጋነን አይደለም።

በደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን የሚሰጡ አገልግሎቶች

  • (1)ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 6am – 10am ለጸሎት ክፍት ሆኖ የእጣን ጸሎት እና የኪዳን ጸሎት ይደረጋል።
  • (2)ዘወትር እሁድ የሰንበት ቅዳሴ ከነግህ ጸሎት ጋር  ከንጋቱ 5am ጀምሮ ይሰጣል።
  • (3)ዘወትር የአዘቦት ቅዳሴ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ባሉት ቀናት ወር በገባ የሚካኤል ፣ ፣ የኪዳነምህረት፣ የገብርኤል

የማርያም እና  የመድኃኒዓለም ቀን ይቀደሳል።

  • (4) በአመት 8 ግዜ አመታዊ በአለ ንግስ ይደረጋል።በሁሉም በዓላት የዋዜማ አገልግሎት ከ3pm ጀምሮ ይሰጣል።

እንዲሁም በበዓሉ ቀን በማህሌት ከ2am ጀምሮ እስከ በዓሉ ፍጻሜ በድምቀት ይከበራል። እንዲሁም ከዓመታዊ

በዓላት በተጨማሪ የጽጌ ፤ የደብረታቦር ፤የስብከት፤የኖላዊ፤የልደት፤ የጥምቀት፤የሆሳእና፤የትንሳኤ፤ የዳግማ ትንሳኤ እና የጰራቅሊጦስ ማህሌት ይቆማል።

  • (5)በዓብይ ጾም 5 ቀን ሙሉ ስርአተ ሰሙነህማማት ከጠዋቱ 6am ጀምሮ ይከናወናል።
  • (6)14 ቀን የፍስለታ ሱባኤ በለሊት ሰዓታት፤በውዳሴ ማርያም ትርጓሜ እና በቅዳሴ አገልግሎት ይሰጣል።
  • (7)የመስቀል በዓል በየዓመቱ ኢትዮጵያዊ በሆነ መልኩ በድምቀት ይከበርል።
  • (8)ዘወትር ሐሙሰ ከምሽቱ 5pm ጀምሮ የስብከተ ወንጌል ትምህርት ይሰጣል ።
  • (9)ዘወትር እሁድ ከቅዳሴ በሁዋላ ማህበረ ካህናቱ እና የሰንበት ት/ቤት መዘምራን በህበረት የየእለቱን እና የየባእላን ያሬዳዊ ዜማ (ወረብ) ይዘመራል።እንዲሁም ከአገልግሎት በሁዋላ የባእላቱ ቀለም ይጠናል።
  • (10)ዘወትር እሁድ ከቁርባን በሁዋላ ለህጻናትና ወጣቶች መንፈሳዊ እና የቋንቋ ትምህርት ይሰጣል።
  • (11)ለቤተክርስትያን ዓባላት መረዳጃ እድር ይሰጣል።
  • (12) በኢትዮጵያ ለሚገኙ የተለያዩ አድባራትና ገዳማት በተለያዩ ጊዜያት ከፍተኛ የገንዘብ እርዳታ ያደርጋል።

በተጨማሪም ቤተክርስትያኒቱ ከእዳ ነጻ ፤የዘር፤የጎሳ፤ልዩነት ሳይኖራት ከሁሉም አይነት የብሄር ተዋጽኦ በእኩል ፍጹም ኢትዮጵያዊነትን በተሞላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ህጉዋን፣ ስርአቷን፣ ቀኖናዋንና ዶግማዋን የጠበቀ አገልግሎት በመስጠት እስከ አሁን ድረስ በመድኃኒዓለም ሃይል ያለች እና ወደፊትም የምትኖር በተጓዳኝም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የህንጻ ዲዛይን አሰራር መሰረት በእዚህ በሜንሶታ ለቤተክርስቲያኒቱና ለሃገራችን እንዲሁም ለተተኪ ትውልድ አሻራ ጥሎ ለማለፍ ባለ 3 ጉልላት ያለው የተለያዩ የአገልግሎት ዘርፍ መስጠት የሚችል ካቴድራል ለመገንባት እንዲሁም ቤተክርስትያኒቱን በውጭው ዓለም ከፍ አድርጎ ሊያሳይ የሚችል እና  ዶግማዋና ቀኖናዋ ተጠበቆ ሳይበረዝ ለተተኪ ትውልድ ለማስተላለፍ የሚደረገው ርብርብ ለቤተክርስትያኒቱ እጅግ ጠቃሚና ለመንግስት ደግሞ እራስ ምታት ስለሆነበት የመንግስት አይን አረፈበት ።

እስቲ ልብ በሉ ይህን ሁሉ አገልግሎት እና ስርአት ጠብቃ የያዘች ቤተክርስትያን ልትደገፍና ልትበረታታ ይገባታል እንጂ  ይህንን ሁሉ ስርአተ ቤተክርስትያንን እና አገልገሎትን ወደጎን ትቶ የአቡነ ማትያስን ስም አልተጠራም ተብሎ በአንድ ቀን ቤተክርስትያንን አፍርሶ መሔድ ባልተገባ ነበር። ይሁን ስህተት እንኳ ተገኝቶም ከሆነ በምክር በትምህርት መስተካከል ሲችል  በክፉ መተያየትን እና መለያየትን ባላመጣን ነበር። እዚህ ጋ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የተናገሩትን ጠቅሼ ልለፍ [በዘልማድ ሆኖ ገለልተኞች ብለው ፈረጇቸው እንጂ በሀገረ ስብከትም እንተዳደራለን የሚሉ የራሳቸውን ባይሎ ቀርጸው የሚተዳደሩ እንጂ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቃለ አዋዲን አንድም የሚተገብር ቤተክርስቲያን በመላው አሜሪካ አለ ብዬ አልጠብቅም………እንዲሁ ገለልተኛ ብሎ ማራቅ ለቤተ ክርስቲያን ጉዳት እንጂ ጥቅም የለውም በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ ያልተወገዙና ያልተለዩ አካላት መሆናቸው እየታወቀ ገለልተኛ ብሎ ማራቅ አይገባም። ልዩነት ሊኖር ይችላል ይህን አምነን መቀበል አለብን። የአስተዳደር እንጂ የሀይማኖት ልዩነት የለንም ሁሉም በስርዓት የሚቀድሱ ማህሌት የሚቆሙ ክርስትና እየተነሳባቸው ሰው እየተዳረባቸው ፍታት እየተፈታባቸው አስፈላጊው መንፍሳዊ ነገር ሁሉ ሚስጥራተ ቤተክርስቲያን እየተፈጸመባቸው እየታወቀ ገለልተኛ ብሎ መጥራት ምን ማለት ነው? ሊታረም የሚገባው ነው……..ወግድ ብሎ ማራቁ ክርስቲያናዊ ተግባር አይደለም በቅዳሴ ላይ የፓትርያርክ ስም አለመጠራቱ ችግር አይደለም አልልም ችግር ነው። ነገር ግን በዚህ ምክንያት ሊለያየን አይገባም ብዬ አምናለሁ] እኚህ አባት ይህንን ያሉት ጁን 12,2012 ላይ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ላይ ነው።

በተጨማሪም በፋይናነስ በአካውንት ውስጥ ሚሊየን ዶላር አለ የሚባል ነገር ሲመጣማ በጣም ትኩረት ተሰጠው ስለዚህ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድበት ከመንግስት ትእዛዝ ተላለፈበት ።

መንግስትም ይሰሩልኛል ብሎ ባስቀመጣቸው አባት መሪነትና በተላላኪዎቻቸው አንድ ተብሎ ተጀመረ  ይህንንም የማፍርስ ስራም እንዲሰሩ ሰዎች ተመለመሉ።

የተመለመሉት እነማን ናቸው?

  1.   ብጹዕ አቡነ ዘካርያስ የኒወርክና አካባቢው ሀገረስብከት ጳጳስ፦ የጎጃም ሃገረስበከት  ጳጳስ የነበሩና የፓትርያርክ የበላይ ቅዱስ ሲኖዶስ ሆኖ ሳለ ነገርግን አቡነ ጳውሎስ ከቅዱስ ሲኖዶስ በላይ  በመሆን  ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ ትእዛዝና ፍቃድ በአቡነ ጳውሎስ ትእዛዝ ለኒዎርክና አካባቢው ሃገረ ሰብከት የተዘዋወሩና በፍትሃነገስት ላይ ኤጲስቆጶሳት አንቀጽ 5 ቁጥር 158  ኒቅያ 77<<ኤጲስቆጶስ በአገሩ መስፋትና መጥበብ በህዝቡ ማነስና መብዛት ምክንያት ኤጲስቆጶስነት ከተሾመበት አገር ወጥቶ ወደ ሌላ አገር አይሂድ ስለዚህም ከእርሷ የሚሻለውን ሊፈልግ አይገባውም ይህ ለእርሱ አይገባውምና።ለሰው ሁሉ ድርሻው ከእግዚአብሄር ተሰጥቶታል እንጂ ይህ ከህዝባውያን ወገን ሚስት ያገቡ ሰዎችን ይመስላል ያለዝሙት ምክንያት ሰው ከሚስቱ ቢሰነካከል ከእርሷ በምትበልጥ ሊለውጣት ቢፈልግ እርሱ በጣም በደለኛ ነው።ከአገራቸው የተሻለ አገርን የሚፈልጉ ኤጲስቆጶሳትም ካህናትም እንደዚሁ ናቸው ስለዚህም አውግዘን ለየናቸው ።ይህ ልማድ መጥፎ ነውና ።>>የሚለውን በመተላለፍ የተሾሙበትን ሃገረ ስብከት ትተው የመጡ ፤  ኤጲስቆጶሳት አንቀጽ 5 ቁጥር 167 ድስቅ 30<<ከነውር ወገን አንዲቱ ነውር በኤጲስቆጶስ ላይ ብትታወቅ ከመዓርጉ የሚዋረድበትን ከሹመቱ  የሚሻርበትን ምክንያት ይናገራል።>>ይህንን በመተላለፍ እምነት ያጎደሉ እንዲሁም በኤጲስቆጶስ አንቀጽ 5 ቁጥር 172<<አንድ ሊቀጳጳስ በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ አልመጣም አይበል የታወቀ ምክንያት ካላገኘው በቀር ወደኋላ አይበል የቀረበትንም ምክንያት ይጻፍ ፈቃድም ይቀበል>> የሚለውን በመተላለፍ እዚህ ሀገር ከገቡ ጀምሮ ከ10 ግዜ በላይ አንድም ስብሰባ ያልተካፈሉ እንዲሁም   እንደ ቤተክርስትያን ቀኖና ህግና ስርአት  ቅዱስ ሲኖዶሱ የማያውቃቸውና ጵጵስናቸው የተሻረ አባት ናቸው።እንዲሁም በፓትርያርክ ቀብርም ሆነ ሹመት ላይ ያልተገኙ  አባት ናቸው።ለዚህ ስራ ሲመረጡ ስልጣናቸውን ተገን በማድረግና በመጠቀም በማውገዝና በማስፈራራት ከቀኖና ውጭ በሆነ መንገድ እንዲያስፈጽሙ ማድረግ ነው።
  2.   በእዚህ በሚንሶታ እስቴት ውስጥ የሚገኙ በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ስር ነን የሚሉ ነገር ግን ያይደሉ ከመንግስት ጋር በቅርበት የሚሰሩ ካህናትና ግለሰቦች ናቸው።
  3.   በዛው በደብረሰላም መድሃንያለም ለብዙ ግዜ አገልጋይ የነበሩ እንዲሁም ተገልጋይ የነበሩ ካህናትና ዲያቆናት ቤተክርስትያኒቱ የነበረባቸውን ስጋዊ ችግር በገንዘብም ሆነ በተለያየ ነገር የቀረፈችላቸው በችግራቸው ግዜ የቀረቧት ዛሬ ደግሞ ሲሞላላቸውና ጊዜ ፊቷን ዞር ስታደርግላቸው የተነሱባት የእናት ጡት ነካሾችና እንዲሁም ለዚህ ስራ የተመረጡ ጥቂት የቤተክርስትያን ተቆርቁዋሪ መስለው ቤተክርስትያን የማፍረስን ስራ የሚሰሩ ግለሰቦችና እግዚአብሄርን የማያውቁ ነገር ግን የእግዚአብሄር አገልጋዮች የነበሩ የሰንበት ት/ቤት አገልጋዮች ናቸው።

እነዚህ ከላይያየናቸው አማሳኞች ለስራቸው መጀመሪያ የተቀበሉዋቸው                                          ሁለት መመሪያዎች

  1. አንደኛው በሰላምና በተረጋጋ ሁኔታ ቤተክርስትያኒቱን ከነሙሉ ንብረቷ በመንግስት ቁጥጥር ስር ማዋል ይሄኛው  በጣም  አዋጭ ሲሆን ብዙ ጊዜ ፤ገንዘብና ጉልበት ቆጣቢ እንዲሁም በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቅ ነው።
  2. ሁለተኛው ደግሞ ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር ያችን ትልቅ የኢ/ ኦ/ተ/ቤተክርስትያንን ዶግማዋንና ቀኖናዋን እንዲሁም ስርዓተ ቤተክርስትያን ጠብቃ የምትሄደውን ለሁለት ከፍሎ ከተቻለ ማጥፋት ካልሆነም ማዳከም የሚል ነው ይህ ደግሞ ግዜ ይወስዳል። እንግዲህ እነዚህ አማሳኞች በመመሪያቸው መሰረት ኔትወርካቸውን ዘርግተው ከኢትዮጵያ ድረስ መመሪያ ሲያስፈልግ በይፋ በቡራኬ መልክ አይዟችሁ በርቱ ከጎናችሁ ነን በማለት እንደየ አስፈላጊነቱ ደግሞ ከሃገረስብከቱና ከቅዱስ ፓትርያርኩ በሚመጡ ፍጹም መንፈሳዊነት በሌላቸው ቤተክርስትያንን የሚከፍሉና የሚበትኑ መልእክቶችን በመጻጻፍ የክርስቲያኑንና  የቤተክርስትያኑን ክብር ያላገናዘበና የኢትዮጵያን ኦ/ተ/ቤ አማኙን አንገት ያስደፋ እንዲሁም የሚያሸማቅቅ ደብዳቤዎችን በመላላክና  ግልጽ በሆነና በድብቅ የስልክ ግንኙነቶች በማድረግ ቤተክርስቲያኒቱ ላይ ጥቃታቸውን ቀጠሉ።

 

የአጀንዳቸው መሠረት ስርአተ ቤተክርስቲያን ፈርሷል

እንግዲህ እነዚህ ለማፍረስ በተመለመሉ ኅይሎች አማካኝነት ከ20 ዓመት በላይ ቤተክርስትያኒቱ ሰላሙዋንና አንድነቷን ጠብቃ የኖረችበትን አቋሟን ወደጎን በመተው የቤተክርስትያን አገልግሎት ቅዳሴ ብቻ በማስመሰል ስርአተ ቤተክርስትያን ተጥሷል በማለት በቅዳሴ ግዜ የፓትርያርክ ስም አልተጠራም መጠራት አለበት በሚል በሰፊው ማራገብ ጀመሩ ።ጥያቄአቸውንም አቀረቡ ጥያቄአቸውም አግባብ፤ተገቢና መብታቸውም ስለሆነ መልስ መሰጠት አለበት በሚል በቤተክርስትያኒቱ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ ውሳኔ እንዲሰጥበት ተደረገ በአብዛኛው አባላት ከጠቅላላ አባላቱ ከ50+1 በላይ የሆነው አባል አንድነቷ ተጠብቆ በአለችበት አቋሟ እንድትቀጥል የሚል ውሳኔ ተሰጠ። እነርሱ ግን አላማቸው ሌላ ነበርና ተስማምተው ድምጽ የሰጡበትን በማጠፍ ጠቅላላ ጉባኤ አልተሟላም አሉ እሺ ካልተስማማች እንደገና ጠቅላላ ጉባኤ ይጠራ ሲባሉ በፍጹም እኛ በመረጥነው መንገድ ብቻ ነው መሆን ያለበት አሉ።

እነዚህ አማሳኞች በመጀመሪያ ደረጃ ያስቀመጡት አልሳካ ሲላቸው ሁለተኛ አማራጫቸውን በመጠምዘዝ በሁከትና በረብሻ ቤተክርስትያኒቱን ማወክ ተያያዙት ጠቅላላ ጉባኤ ይጠራና አባላቱ ይወስንበት ሲባሉ በህጋዊና በሰላማዊ መንገድ እንደማይሆንላቸው ስላወቁት በፍጹም ጠቅላላ ጉባኤ ሳይጠራ እኛ የፈለግነውን ነገር ብቻ ካልተደረገ አሉ ። ይህን ግዜ ነበር ህግ ያለበት ሀገር ስለሆነ በህግ እንዲዳኝ ወደ ፍርድ ቤት ጉዳዩ ያመራው ።  ጉዳዩም በፍርድ ቤት እያለ በዘረጉት ኔትዎርክ በመታገዝ እንዲያስታርቁ ሳይሆን ከተቻለ አስፈራርተውም ሆነ አውግዘው ወደ እራሳቸው አላማ ማለትም መንግስት ወደ ሚቆጣጠራት ቤተክርስትያን የማስገባት ስራ እንዲሰሩላቸው ካልሆነም የተፈለገውን የመክፈል ሰራ እንዲሰሩላቸው ሁለት ጳጳሳትን አመጡ

  1. አቡነ ማርቆስን ከኢትዮጵያ
  2. አቡነ ዘካርያስን ከአሜሪካን

በማስመጣት በአዳራሽ ባደረጉት ስብሰባ ላይ ያውም በአርምሞ ሱባኤ በሚያዝበት በታላቁ አብይ ጾም ህዝብን ከሚመራ ጳጳስ የማይጠበቅ የስድብ አፍ በቤተክርስትያኒቱ፤በንዋያተ ቅዱሳቱ፤አላማቸውን በማይደግፉት ካህናትና ዲያቆናት እንዲሁም ምእመናን ላይ ሲሳደቡ፤ሲሳለቁና ሲስቁ ውለው እና አድረው እንዲሁም በማግስቱ የመጋቢት መድኃኒዓለም በዓለ ንግስ ላይ በአቡነ ማትያስ እየተመሩ የመጡት ልዑካን ከነግብራበሮቻቸው በጣም ከአቅም በላይ የሆነ ትእግስት እና እልህ አስጨራሽ ትእይንት በቤተክርስትያኑ ዓውደ ምህርት ላይ በማሳየታቸው ምእመኑ ከአቅሙ በላይ ስለሆነበት አግባብ ያልሆነ ስድብ በጳጳሳቶቹ ላይ እንዲሳደብ አድርገውታል የእነርሱም አላማ በአውደምህረቱ ላይ ያልተገባ ትእይንት በማድረግ ምእመኑን ንዴት ውስጥ በመክተት ያልሆነ ቃል እንዲናገር ማድረገ ነበረና እነዚህ አፍራሽ ሃይሎች ይህችን አጋጣሚ በመጠቀም ጳጳሳቶች ተሰደቡ እያሉ ምእመኑ ላይ ተጽእኖ ለመፍጠር ሞክረዋል ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ማንነታቸው ተጋለጠ። እዚህ ጋር አንድ ልብ ልንለው የሚገባ ነገር አለ ጳጳስ ይሰደባል ግን አይሳደብም ፣ይመታል ግን አይማታም፣ይገደላል ግን አይገድልም፣ያስታርቃል ግን አያጣላም፣ ምእመንን ይሰበስባል ግን አይበትንም ፣ፍቅርን ይዘራል ግን ጥላቻን አያበቅልም እንዲሁም አንድ ጳጳስ ገና ሲመነኩስ እንደሞተ (የሞተ)ስለሆነ በቁሙ ተስካሩን  ያወጣል የጵጵስናውን አስኬማ ሲደፋ ደግሞ ለሃይማኖቱ፣ለህዝቡ፣ለተበደለ፣ለተገፋ፣ፍትህ ላጣ ፣ለተጨቆነ ፣ለቤተክርስትያን ለመሳሰሉት ሊሰደብ፣ሊገረፍ፣ሊታረዝ፣ሊታሰር፣ ብሎም ሞትም ከአስፈለገ ሊሞት ነው እንጂ ሹመቱ እንደ አለማዊ ሹመት አይደለም። እነዚህ ጳጳሳት ግን እንደነርሱ ፍላጎት ከፍለውት ነው የሄዱት ሆኖም ግን በመድኃኒዓለም ቸርነት ምእመኑ ለቤተክርስትያኑ ጠንክሮ እንዲቆም ነው ያደረጉት ቆሞም ተገኘ ።ከዛም ጳጳሳቶቹ ለአፍራሽ ካህኖቻቸው መመሪያ ሰጥተው የአቡነ ማትያስን ስም ሳትጠሩ ከእንግዲህ እንዳትቀድሱ ብለዋቸው ለሰሩት ሁከትና ብጥብጥ ተመራርቀው እና ተመሰጋግነው ጳጳሳቶቹም ወደ መጡበት ተመለሱ።

እለተ ሆሳዕና፦

እነዚህ አማሳኞች የሆሳዕና በዓል ከመደረሱ ከቀናት በፊት አንድ ቤተክርስትያኒቱን በእጃቸው የሚያስገቡበት የመሰላቸውን ተንኮል(ዘዴ) ቀይሰው ያች ቀን እስክትደርስ መጠባበቅ ጀመሩ። ድንጋዮች ያመሰገኑበት ሻጮችና ለዋጮች በጅራፍ እየተገረፉ ከቤተመቅደስ የወጡበት ክርስቶስ ቤቱን ያጸዳበት ቀን እለተ ሆሳህና በታላቋ የምስጋና ቀን ሆሳህና በ2006  በሚንሶታ በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ ቤተክርስትያን አሳዛኝ ነገር ተከሰተ።

የሚገርመው ደግሞ እርስ በእርሳቸው ስለማይተማመኑ እንዳይካካዱ ተፈራርመው በሌሊት ወደ ተከበረችው የእግዚአብሄር ቅዱስ ስጋው እና ክቡር ደሙ ወደ ሚፈተትበት ቅድስት መቅደስ ገቡ። ህዝበ ክርስትያኑ ለአገልግሎት መጡ ነው ያለው እነርሱ ግን ለአሰቡት አላማ ነው የመጡት እቅዳቸውም ከቅዳሴ በፊት የሚከናወኑ ስርአቶች ከተከናወኑ በሁዋላ በቅዳሴ ጊዜ የአቡነ ማትያስ ስም ከተጠራ እንቀድሳለን ካልተጠራ አንቀድስም ብለው አቋማቸውን በፊርማቸው በይፋ አሳወቁ በዚህን ግዜ በሆሳዕና እለት ድንጋዮች በአመሰገኑበት ዕለት  እኛ ካልቀደስን እንዲሁም የሰንበት ተማሪዎች ካልዘመሩ ቤተክርስትያኑ ይዘጋል ሳይወዱ በግዳቸው የእኛን ፍላጎት ያሟላሉ ብለው የእግዚአብሄር ቤት መሆኑን እረስተው የትዕቢት ስራን ሰሩ። በዚህን ጊዜ ነበር መድኃኒዓለም ጅራፉን ያነሳው መድኃኒዓለም ከተነሳ ያውም በሆሳዕና ዕለት እስከ መጨረሻው ካላጸዳ አይመለስም እናም የማጽዳቱን ስራም ጀመረ።

እነሆ ከወደ ቤተመቅደስ አንድ ድምጽ ተሰማ “ እባካችሁ በዚህ በታላቅ ቀን በሆሳዕና ድንጋዮች ባመሰገኑበት ቀን የጳጳስ ስም ካልተጠራ ብለን የእግዚአብሔርን ስም አንጠራም አይባልም እውነት ከእግዚአብሔር ምስጋና የሰው ምስጋና ይበልጣልን ? በረከት ያስወስድብናል በጅራፍም ያስገርፈናል ከቤቱም ያስባርረነናል አሁን ምእመኑን ከምንበትን ቤተክርስትያኑንም ከምንዘጋ እስከዛሬ ድረስ ለብዙ ዘመን የጳጳስ ስም ሳንጠራ የቀደስንበትን ቤተክርስትያን አንቀድስም ከምንል እንቀድስና ጥፋትም ሆኖ ቢገኝ እንኳን ይቅርታ እንጠይቅበት’’ የሚል ቃል መጣ እነርሱ ግን ከበላይ ነው የታዘዝነው ብንቀድስ ክህነታችን ይያዛል መቀደስ አንችልም ብለው አቋማቸውን ገለጹ በዚህን ግዜ ነበር መድኃኒዓለም ያዘጋጃቸው ካህናትና ዲያቆናት ቅዳሴ  መቀደስ ሲጀምሩ የአማሳኞቹ ካህናትና ዲያቆናት ተከታይ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች እንዲሁም ጥቂት የእነርሱ አጀንዳ የእውነት የቤተክርስትያን አንድነት የመሰላቸው ወደ 50 የሚጠጉ ንጹሃን የቤተክርስትያን ምእመን አንድ በአንድ በየተራ ቤተመቅደሱን ለቀው ወደ ፓርክ በማመራት የሆሳእና እለት እግዚአብሔር መድኃኒዓለም በእየሩሳሌም ለቤቱ አልታዘዝ ያሉትን ጠራርጎ እንዳስወጣ ሁሉ በዳግማዊቷ እየሩሳሌም በሚንሶታ ደብረ ሰላም መድኃኒዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ ተደገመ።  እግዚአብሔር በቤተመቅደሱ ተመሰገነ ከበረ ተወደሰ አቡነ ማትያስ በፓርክ ተመሰገኑ ከበሩ ተወደሱ ።

ከሁሉም በጣም ለየትና ግርም የሚለው ደግሞ እሁድ እሁድ ሁልጊዜ  ከቅዳሴ በሁዋላ የዕለቱ ያሬዳዊ ዜማ (ወረብ) ይወረባል (ይዘመራል) ያን ግዜ ግን ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች በሙሉ ወጥተው ፓርክ ሄደው ስለነበር ማን ሊዘምር ነው ሲባል  ለካ እግዚአበሔር እኛ ስናምጽ ለራሱ የሆነ ሰው ለቤቱ ያዘጋጃል፤ ከምእመን እርሱ መረጠ አንድ አንድ እያሉ አውደ ምህረቱን ሞሉት እግዚአብሔር እንዲያመሰግኑት ከመረጣቸው መካከል አንዲት ልትወልድ የደረሰች እህት የመድኃኒዓለምን ድምጽ በሰማች ግዜ ከተቀመጠችበት ብድግ ብላ ልታገለግል ልትዘምርለት መጣች የአምላካችን ስራው ድንቅ ነው ።አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ትዝ አለኝ በሉቃስ ወንጌል ላይ ምዕ 1 ቁጥ 41 እንዲህ የሚል ቃል አለ  “ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ግዜ ጽነሱ በማህጸኗ ውስጥ ዘለለ በኤልሳቤጥም መንፈስቅዱሰ ሞላባት   ………… ኤልሳቤጥም እነሆ የሰላምታሽ  ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ግዜ ጽንሱ በመሃጸኔ በደስታ ዘሏልና’’ ብላ እንዳመሰገነች አንዲት ልትወልድ የደረሰች ነብሰጡር የመድኃንያለምን ድምጽ በሰማች ግዜ ከተቀመጠችበት በድግ ብላ መቁዋሚያውንና ጽናጽሉን አነሳች በዚህን ግዜ በማህጸኗ የነበረው ጽንስ ዘለለ ፤ሰገደ፤አመሰገነ እግዚአብሄር በሆሳዕና እለት በድንጋዮችና በህጻናት ተመሰገነ ማለት ይህ አይደል።

እንግዲህ ምእመናን እሺ ብንል ለእግዚአብሔር ብንታዘዝ የምንከብረው የምንባረከው እኛው ነን እምቢ ብንል ደግሞ የምንጎዳው እኛው ነን እግዚአብሔር እንደው ምንም የሚጎልበት አንዳች ነገር የለውም ቢፈልግ በመሃጸን ያሉትን ያስነሳል ቢፈልግ ህጻናትን ያስነሳል ቢፈልግ ድንጋዮችን ያስነሳል ይህንንም ደግሞ በሚንሶታ ደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስትያን አይተነዋል ።

የአውጋዡንና የተከታዮቹን ማንነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ውግዘት አውጋዡም ሆነ ተከታዮቹ በእውነት የኢ/ኦ/ተ ቤተክርስትያን አማኞች ናቸውን?

እዚህ ጋር ተከታዮቹ ብዬ የገለጽኩት ይህንን ተግባር ተቀብለው የሚያስፈጽሙትን እንጂ ምዕመኑን አይወክልም ምክንያቱም ምዕመኑ በንጹህ ልቡ የእውነት አንድነት መስሎት ስለሚከተል በበመጀመሪያ በኢትዮጵያ  ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ቀኖና መሰረት ስልጣኑ የተሻረ አባት ሊያወግዝም ሆነ ሊለይ አይችልም የተወገዘ እንዴት ያወግዛል ሲቀጥል በሰሞነ ሕማማት ማለትም ከሆሳእና እስከ ትንሳኤ ባሉት ቀናት ውስጥ እንኳን ማውገዝ ፤ማሰርና መለየት ቀርቶ መፍታት እንኳን በማይቻልበት ቀን አቡነ ዘካርያስ የደብረሰላም መድኃንያለም የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ካህናት ፤ዲያቆናት እንዲሁም ምእመንን በፍትሐነገሥት አንቀጽ 15 ቁጥር 600 <<በሰሞነ ሕማማት ክርስትና ማንሳት፤ ክህነት መስጠት፤ለሞቱ ሰዎች መጸለይ አይገባም በእነዚህም ቀኖች ውስጥ ፈጽሞ ማገልገል ይገባል እንጂ በሰሞነ ሕማማት ስለሚሞቱት ሰዎች የሙታን ግንዘትና የሃዋርያት ስራ ወንጌላት የሙታን ፍታት በሆሳዕና በዓል ይነበብ እንጂ በጸሎተ ሐሙስ ጸሎተ ተአምኆ እግዚአ ሕያዋን የቡራኬ ጸሎት  አይባልም(አይጸለይም)ቅዳሜ ግን እግዚአ ሕያዋን ይባላል ፍትሃት ይፈታል ከመሳለም በቀር ጸሎተ እጣንም ይጸለያል በእለተ እሁድ ግንዘት ማድረግ በፋሲካ ቀንም ማልቀስ አይገባም >> የሚለውን በመተላለፍ በሰሞነ ሕማማት ቀኖናውን ጥሰው አናገለግልም ብለው የወጡትን ምንም ሳይሉ ቀኖናውን ጠብቀው ምንም ሳያጉዋድሉ ያገለገሉትን በሙሉ  በጸሎተ ኅሙስ ካህናቱና ዲያቆናቱ ቅዳሴ ቀድሰው ሲወጡ እነዚህ አማሳኞች ከአቡነ ዘካርያስ የመጣ የውግዘት ደብዳቤ ነው ተቀበሉ ብለው ፎቶና ቪዲዮ ደግነው ደብዳቤውን ለመስጠት ሞከሩ የተቀበለውም ተቀበለ ያልተቀበለም አልቀበልም ብሎ ወደ ቤቱ ሄደ።የተላለፈውንም ውግዘት እንደሚከተለው እናያለን፦

  1. ቤተክርስትያኒቱ ፦ከተመሰረተች ከ20 ዓመት በላይ የሆናት በጳጳሳት ተባርካ ብዙ ክርስትያን የተጠመቀባት ፤የቆረበባት ፣የተዳረባት ፣ሰው ሲሞት ፍትሃት የተደረገባት፣ብዙ መንፈሳዊና ሚስጥራዊ ግልጋሎት የተሰጠባት ቤተክርስትያን እግዚአብሔር አምላክ የምእመኑን ጸሎት የተቀበለባትና የፈጸመባት ቤተክርስትያንን ከዛሬ ጀምሮ አሮጌ ህንጻና የአሳማ(የከብቶች) ማርቢያ ትሁን ብለው በህንጻ ቤተክርስትያኒቱ ላይ እንዲሁም በንዋያተ ቅድሳቱ ላይ የውግዘት ቃል ተላለፈ።
  2. ካህናቱና ዲያቆናቱ ፦ከሆሳዕና ቀን ጀምሮ በደብረ ሰላም ቤተክርስትያን ብቻ የአቡነ ማትያሰን ስም ሳይጠሩ የቀደሱ ካህናትና ዲያቆናት ተወገዙ ልብ በሉ በሌላ ቤተክርስትያን ስም ሳይጠሩ መቀደስ ግን አያስወግዝም ቤተክርስትያን ሁሉንም በእኩል የሚዳኝ አንድ አይነት ህግ ያላት እንጂ አንዱን የሚኮንን አንዱን የሚያጸድቅ ህግ የላትም አለመጥራት የሚያስወግዝ ቢሆን እንኳን አይደለም እንጂ በዓለም ላይ ያሉት ገለልተኞች በሙሉ በተወገዙ ነበር ። ነገር ግን አላማው ጠንካራና ስርአተ ቤተክርስትያንን የጠበቁ ቤተክርስትያንን እየተከታተሉ የማጥፋት ዘመቻ ስለሆነ በደብረሰላም ብቻ ያሉት ተወገዙ ።
  3. ምእመኑ(ህዝበ ክርስትያኑ)፦በዚህች ቤተክርስትያን ውስጥ ቅዳሴ ያስቀደሰ ፣የቆረበ ፣ክርስትና ያስነሳ፣የተዳረ፣ቤተክርስትያን ውስጥ አገልግሎት የሰጠውን ካህን መስቀል የተሳለመ እንዲሁም ማንኛውንም አገልግሎት የተገለገለ በሙሉ ተወገዘ ።

እንግዲህ በኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርዓትና ደንብ ውግዘት እንዲሁ በቀላሉ የሚመጣ ነገር አይደለም በጣም ከባድ ነገር ነው እንደው በአሁን ግዜ ግን በጣም ያሳዝናል ። እንደ አንድ ኢ/ኦ/ተ/ቤ ምእመን ሆኜ ስመለከተው  አንገቴን እንድደፋ አድርጎኛል። ስለውግዘት በፍትሃነገስት ላይ አንድ ካህን ስለ ሁለት ነገር ይወገዛል እርሱም ቢሆን ተመክሮ አልመለስ ሲል ነው።

  1. በነውር ምክንያት        2. በምንፍቅና (በሃይማኖት ክህደት) ናቸው

እዚህ ግን የሆነው የሊቀጳጳሱን ፍላጎት ስላላሟሉ ለምን ቀደሳችሁ ተብለው ነው የተወገዙት መወገዝ ከነበረባቸውም አንቀድስም ብለው  የሄዱት ነበር መወገዝ የነበረባቸው እንዲሁም በፍትሃነገስት ላይ ኤጲስቆጶስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 184 ረስጠብ 24<< አንድ ሊቀጳጳስ በቂም በበቀል ቢያወግዝ ከሹመቱ ይሻር በተጓዳኝ የተወገዘው ካህንም ይቋቋመው ነው የሚለው >>።ደግሞ ካህናቱ አጥፍተው ተወገዙ ቢባል እንኩዋን ቤተክርስትያኒቱንና መዕመኑ በምን ጥፋታቸው ነው የሚወገዙት ቤተ ክርስትያን በሄደ ፣ በቆረበ ፣ በአመሰገነ መቼም ይህንን ለቤተክርስትያኒቱ ትልቅ ውርደት ስለሆነ አንድ ሊባል ይገባዋል።

 

ስቅለት(ዕለተ አርብ)

እነዚህ አማሳኞች ቤተክርስትያኒቱ ተወግዛለች አንሄድም እንዳትሄዱ ብለው ለምእመኑ ቤት ለቤት በመሄድና በስልክ እየደወሉ ይናገሩ ጀመር እዚህ ጋር ልብ ልንለው የሚገባው ነገር በእለተ ሃሙስ ከቅዳሴ በሁዋላ ለካህናቱና ለዲያቆናቱ በደበዳቤ ነው ውግዘቱ የደረሳቸው ታድያ ምነው በዕለተ ዓርብ መጥተው አገለገሉ ። ዕለተ ዓርብ ውግዘቱ ተነስቶ ነበር ወይስ ለእነርሱ የማፍረስ ስራ ሲሆን እንዳይሰራ ቤተክርስትያንን የሚያንጽ ሲሆን ውግዘቱን እንዲሰራ ተደረጎ ነው የተወገዘው ነገሩ እንዲህ ነው ጸሎተ ሃሙስ ዕለት ወደ 300 የሚሆኑ የቤተክርስትያኒቱ አባላቶች እነዚህ አፍራሽ ካህናትና ዲያቆናት በራሳቸው ግዜ በዕለተ ሆሳዕና ስራቸውን እረግጠው ስለወጡ ከዛሬ ጀምሮ የቤተክርስትያናችን አገልጋዮች አይደሉም የሚል በፊረማ የተደገፈ ወረቀት ለዳኛው ስለተሰጠው የአሜሪካን ህግ ደግሞ ተፈጻሚ እንደሚሆን  ስለሚያውቁት ሌላ ነገር መፈለግ ነበረባቸው እርሱም፦

  • ሌላ ቤተክርስትያን
  • ለቤተክርስትያኑ መገለገያ የሚሆን ነዋያተ ቅድሳት

ስለዚህ አዳራሽ ተከራይተው የትንሳኤን በዓል በአዳራሽ ብለው አወጁ  በቤተክርስትያኒቱም ምንም አይነት አገልግሎት አይሰጥም ብለው ምእመኑን ለማወናበድ ሞከሩ እንዲሁም ለእኛ ወፈ ግዝት ለእነርሱ ደግሞ ግዝት የሆነውን ተላልፈው ቤተክርስትያን መጥተው ንዋያተ ቅድሳቱን ዘርፈው ከእንደገና ውግዘቱን አውጀው ላይመለሱ ወጥተው ሄዱ።ከዚህም ቀን ጀምሮ በድምጽም በሁከትም እንደማይሆንላቸው  እንዲሁም በመድኃኒዓለም ቸርነትና በምእመኑ ያላሰለሰ ጥረትና ብርታት እንዳልተሳካላቸው ስላወቁት ቤተክርስትያን ለመክፈት አንድ ብለው ጀመሩ።

ሜይ 11  ወሳኙና አሳዛኙ ቀን

ለቤተክርስትያኒቱ በጣም አሳዛኝ ነበር ፤ የፍርድ ቤቱ ዳኛ በተገኙበት ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ ድምጽ ተሰጥቶ  የቤተክርስትያኒቱ አቋም የተገለጸበት ቀን ነበር። እዚህ ጋ ሳልጠቅሰው የማላልፈው ነገር ትላንት አባቶች ጳጳሳት ተሰደቡ ብለው ሲናገሩ የነበሩ በዚህ ቀን ከ8 አመት በላይ የማይጠገበውን የቤተ ክርስቲያንን ያሬዳዊ ዜማ ያስተማሯቸውን፣ንስቸውን የተቀበሏቸውን ፣ በእጃቸው የተባረኩት እና የቆረቡትን አባት በአደባባይ መሳደብ የማይረሳና አሳዛኝ ትእይንት ነበር። ይህች ቀን ለአማሳኞቹ የደስታ ቀን ነበር ምክንያቱም ከሆነላቸው ቤተክርስትያኒቱን ከነ ሙሉ ንብረቷ መረከብ ካልሆነላቸው ደግሞ ለሁለት መክፈል  ሁለቱም ውጤት ለእነርሱ የአሸናፊነት ነው ። ለቤተክርስትያኒቱ ምዕመን ግን የሃዘን ቀን ነበር ምክንያቱም ሁለቱም ውጤት የሃዘን ነበር ውጤቱ አፍራሾች ቢወስዱት በመንግስት ቁጥጥር ስር አውለው ቤተክርስትያኒቱን ባለቤት አልባ አድርገው የመንግስት ፍላጎት ማስፈጸሚያ ሊያደርጉአት  ስለሆነ ውጤቱ በ ተቃራኒውም ቢሆን ከእህት ከወንድሞቻቸው በመለየታቸው ምክንያት የሃዘን ቀን ነበር ያም ሆነ ይህ ውጤቱ የመድኃንያለምና የምዕመኑ ሆነ ቤተክርትያኒቱ  በነበረችበት አቋሟ እንድትቀጥል ሆነ ።ቤተክርስቲያኔ ብለው ደፋ ቀና እንዳላሉባት በአፋቸው ሞልተው ለመጥራት እንኳን የሚሳሱላትን ቤተክርስቲያንን ከዚህች ቀን ጀምሮ እንደ ቤተክርስትያን ሳይሆን 4401 ሕንጻ እያሉ የእግዚአብሔርን ቤት ማዋረዳቸውን ቀጠሉ።

 

ደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስትያን ለሁለት ተከፈለች ፦   አብዛኛው ምእመን ደብረሰላም መድኃኒዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያንን ይዘው እንደበፊታቸው ሲቀጥሉ በሌላው ወገን ያሉት ደግሞ ጽርሃርያም ቅድስት ስላሴ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ብለው ሌላ ቤተክርስትያን መክፈታቸውን በይፋ አወጁ ሁለቱም በየአሉበት አገልግሎታቸውን ማከናወን ጀመሩ።

ከተከፈሉ በሁዋላ ደብረሰላምን የማዳከሙ ሂደት

ደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ከተከፈለችበት ጊዜ ጀምሮ የመድኃኒዓለም ጥበቃ ያልተለያት ቤተ ክርስቲያን በመሆኗ እግዚአብሔር ለራሴ የሚለውን እራሱ በፍቃዱ እያመጣ አገልግሎቱ ከዱሮ በበለጠ እየሰፋ በመሄዱ   መንግስት በፖለቲካው ይጠቀምበት የነበረውን አሰራር ማለትም ለመንግስቴ ያሰጉኛል የሚላቸውን ጠንካራ ተቃዋሚዎችን የሚያዳክምበትን አሰራር በቤተክርስትያን ውስጥ በእነዚህ አፍራሽ ሃይሎች አማካኝነት እየተጠቀመበት እንዳለ እናያለን።  እስቲ የሚንሶታ ደብረሰላም መድኃኒዓለምን ለሁለት ከተከፈለ በኋላ ለማዳከም የተጠቀሙበትንና እየተጠቀሙበት ያለውን ነገር በዝርዝር እንመልከት

  1. የሚንሶታው ደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ቤተክርስትያኒቱ ከተመሰረተች ጀምሮ ላለፉት 19 ዓመት  የነበረውና ያለው የሰንበት ትምህርት ቤት  መጠሪያ ስም ቤዛ ኩሉ ሰንበት ት/ቤት ነው። አሁን ደግሞ ጽርአርያም ቅድስት ስላሴ ስደተኛው  ቤዛ ኩሉ ሰንበት ት/ቤት በማለት ሰይመውታል በጣም የሚገርመው ጽርአርያም ስላሴ ከተመሰረተ ገና አንደኛ አመቱ ሆኖ ሳለ እነርሱ ግን  ጽርአርያም ስላሴ ስደተኛው ቤዛ ኩሉ ሰንበት ት/ቤት አስራ ዘጠነኛ አመት ብለው ለሰሚው ግራ የሆነ  ዓመታዊ በዓል አክብረዋል እዚህ ጋር ስሙ ላይ ችግር የለበኝም እውነት ለሃይማኖት ከሆነ ቤዛ ኩሉ ሰንበት ት/ቤት አንደኛ አመት ነበር መባል የነበረበት። ለዚህ ደግሞ የሚሰጡት ምክንያት አብላጫዎቹ ዘማሪዎች ከቤተክርስትያን ስለወጣን ነው ይላሉ ልብ በሉ አብላጫዎቹ ምእመናን አይደለም ያሉት ምእመንም ቢባል እንኳን ስህተት ነው  ሰንበት ት/ቤት ከመቼ ወዲህ ነው የግለሰቦች ሆና የምታውቀው ቤተክርስትያን ከ2000 ዘመን በላይ በኖረችበት በታሪኳ የዚህ አይነት ውርደት የቤተክርስትያን ልጆች  ነን በሚሉት ልጆቿ ሰንበት ት/ቤት የኛ የተወሰንን ሰዎች ነው የሚል የተነሳባት የመጀመሪያዎቹ ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም ። የሰንበት ት/ቤቱ ባለቤቶች ነን የሚሉት ደግሞ ሰንበት ት/ቤቱ በደብረሰላም መድኃንያለም ቤተክርስትያን ሲመሰረት እንኩዋን ያልንበሩ ናቸው።ልጅ ያቦካው ለራት አይበቃም ይባል የለ አባቶች ካላችሁ ስደተኛ ሰንበት ት/ቤት በሚንሶታ የተጀመረው በሌላውም እንዳይስፋፋ አንድ ልትሉ ይገባል ጅብ በቀደደው እንዳይሆን ስል የእኔን ሃሳብ እናገራለሁ።የሲኖዶስ መቀመጫ ኢትዮጵያ እንደሆነ ሁሉ የሰንበት ት/ቤቶችም መቀመጫቸው የተመሰረቱበት ቤተክርስትያን ነው የቤዛ ኩሉ ሰንበት ት/ቤትም መቀመጫ በተመሰረተበት ደብረሰላም ቤተክርስትያን ነው እንጂ በሌላ ሊሆን አይችልም።ሰው ይመጣል ይሄዳል እንጂ ሰንበት ት/ቤት ሰው ተከትሎ አይሄድም እንዲሁም ታሪክ ታሪክ የሚባለው ጊዜን እና ቦታን ሲገልጽ እንጂ የሰውን የሙቀት መጠን እየተለካ አይደለም የሚመለከተው አካል ካለ ኅይማኖታዊ ማስተካከያ ሊሰጠው ይገባል።
  2. ደብረሰላም ቤተክርስትያን ውስጥ ያሉት ታቦታት (ሀ)የመድኃኒዓለም (ለ)የኪዳነምህረት (ሓ)የሚካኤል (መ)የገብርኤል  ሲሆኑ እነዚህ አማሳኞች የመድኃኒዓለምን ታቦት በማስመጣት ሁለቱ ቤተክርስትያኖች ተለያይተው እንዲቀሩ ምዕመን   ከምዕመን እንዳይገናኝ የማድረግ ስራ ሰርተዋል ለቤተክርስትያኒቱና ለህዝበ ክርስትያኑ ቢያስቡ ኖሮ በአንድ  ከተማ ውስጥ ያለን ታቦት ባላስመጡ ነበር ። የሌለውን ነበር ማምጣት የነበረባቸው እግዚአብሔርም  በአንድነትና በፍቅር እንዲከብር በተደረገ ነበር ። እነዚህ ሰዎች ለስርዓት የሚጨነቁ በማስመሰል በሃይማኖት ሽፋን ነበር ቤተክርስቲያኗን ለሁለት የከፈሏት እነርሱ ግን ዶግማውን እስከማፍረስ ሲደርሱ ተው ያላቸውም የለም ምክንያቱም ደግሞ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን  አስተምሮ ስላሴ ማለት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው መድኃኒዓለም ማለት ወልድ ነው። ሁለቱም አንድ ናቸው ብላ ነው የምታስተምረው እንደ ቤተክርስትያን አስተምህሮ በስላሴ ታቦት ላይ የመድኃኒዓለም ታቦት አይገባም ምክንያቱም ሁለቱም አንድ ናቸውና በስላሴ ላይ እመቤታችን ፤ጻድቃን፤ ቅዱሳንሰ ናቸው የሚገቡት እንጂ በየትኛውም አስተምሮ መድኃኒዓለም አይገባም እነዚህ አማሳኞች አላማቸው ስለስርአት ጥሰት ሳይሆን የመንግስትን አላማ ማስፈጸም ስለሆነ አስገብተውታል።አራት መለኮት ሊባል ይሆን እግዚአብሔር ይሰውረን አንድ ሊቀ ጳጳስ እንደተናገሩት “እንደዚህ አይነት ድርጊት አራት አምላክ አለ ብለን እንደ ማመን ነው የሚቆጠረው ይህ አይነት ድርጊት በቅዱስ ሲኖዶስ ላይ ቢቀርብ እና ቢታይ ጵጵስናን እስከ ማሻር እንደሚደርስ” ገልጸዋል ። በመቀጠልም ለምእመኑ ለገብርኤል ንግስ መድኃኒዓለም ሄደው እንዳያነግሱ ከዚህ በፊት ዞር ብለው አይተውት የማያውቁትን የኤርትራ ገብርኤል ቤተክርስትያን ሄዳችሁ አንግሱ ብለው ለህዝቡ አስታወቁ ሔደውም አንግሰው ጥሩ ቀን እንዳሳለፉ ገለጹ እውነት ንግሱን ፈልገው ቢሆን ችግር አልነበረውም ነገር ግን ደብረሰላም መድኃኒዓለምን ለማዳከም የተደረገ ነው። እንጂ  የሚደረገው ስራ አሁንም አላቆመም የቤተክርስቲያኗ አባት ከኢትዮጵያ የሚካኤልንም ታቦት ይዘው መጥተዋል። የሚቀራቸው የገብረኤል እና የኪዳነምህረትን ታቦት ነው ወደፊት ምን እንደሚሆን እናያለን፤   ስለዚህ ምእመናን ሆይ ይህ አስተምሮ የኢ/ኦ/ተ/ቤ አስተምሮ እንዳልሆነ ልንገነዘብ ይገባል ዝም ብለን ተከታዮች ከምነሆን ቆም ብለን ልናስብ ይገባናል በተለይ ደግሞ ጉዞ ወደ እናት ቤተ ክርስትያን(እንቀላቀል) የሚለው ስሙ እና ከእላዩ ሲታይ  መልካም የሚመስለልና የሃይማኖት ሽፋን ያለው ውስጡ ግን ዶግማውን የሚንድ የዘመናችን የቤተክርስትያን ፈተና አስተምሮው የቤተክርስትያን ያልሆነ የመንግስትና የእነርሱን ተልኮ ለማስፈጸም የሚሮሯሯጡ ሰዎች ያስገቡብን ስለሆነ በእውነተኞቹ የቤተክርስትያን አባቶች እርምት ሊወሰድበት ይገባል። ምዕመናንም ማንም ተነስቶ ቤተክርስትያንን አንድ ላደርግ ነው ተከተሉኝ ቢል ልንከተለው አይገባም የበላይ አካል የሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰጠውን መመሪያ ብቻ ነው መከተል ያለበን። የቤተክርስቲያንም ክብር ሊጠበቅ ይገባል።

3 ደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስትያን ለምዕመኖቿ ወንጌልን ለማስፋፋት በምታደርገው መምህራንንና ዘማርያን    ከተለያዩ ደብራት የምትጋብዛቸውን እየተከታተሉ ደብረሰላም መድኃኒዓለም ብትሄዱና ወንጌልን ብታስተምሩም ሆነ ብትዘምሩ ትወገዛላችሁ በማለት በማስፈራራት እንዲሁም አቡነ ዘካርያስ እዚያ ቤተክርስትያን አወግዝሃለሁ በሚል ማስፈራርያ ለመምጣት የአየር ትኬት ከተቆረጠላቸው በሁዋላ በዛቻው ምክንያት የሰረዙ መምህራን  እንዳሉ በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እወዳለሁ ለዚህ ደግሞ ኤጲስቆጶስ አንቀጽ 5 ቁጥር 182 እንዲህ ይለናል <<ፈጽሞ ቂመኛ የሆነ ወይም በየጊዜው ሁሉን እስከማሰርና እስከ ማውገዝ ድረስ ፈጥኖ ለማውገዝ ቂሙን የማይረሳ ቢሆን ይሻር >> ይለናል እንዲሁም ምንም እንኳን ቤትክርስትያን የሰጠቻችሁ ሃላፊነት ቢሆንም ይህንን ሁሉ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ተቋቁማችሁ ሃይማኖታዊ ግዴታችሁን ለተወጣችሁ ሰባክያንና ዘማርያን በሃያሉ በመድኃኒዓለም ስም  ምስጋናዬን  አቀርባለሁ።

ሽልማት

እንግዲህ እንደሚታወቀው ከዋልድባና ከመሳሰሉት ታላላቅ ገዳማትና አድባራት የመጡ አባቶች ተገፍተው፤ ተበድለው፤ፍትህ አጥተው፤ ቤተክርስትያን ሲቃጠልባቸው፣ ሲፈርስባቸው አቤት ለማለትና ለማሳወቅ በአሁን ግዜ ወደ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቢሮ ለመግባት በፍጹም ዝግ በሆነበትና በማይቻልበት ሁኔታ እንዲሁም ደግሞ በሌላ በኩል የመንግስት ጉዳይ አስፈጻሚዎች የቤተክርስትያን አፍራሽ ሃይሎች ለእነርሱ ደግሞ ክፍት ሆኖ እንደፈለጉ የሚወጡበትና የሚገቡበት በሆነበት በአሁን ጊዜ የሚንሶታው ደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስትያን አፍራሽ ሃይሎች እንደ ፈለጉ ሲወጡና ሲገቡ እንዲሁም ላደረጉት(ላበረከቱት) ቤተክርስትያንን የመክፈል ስራ ሽልማታቸውን ከአቡነ ማትያስ ጋር ፎቶ በመነሳት አሳይተውናል።

ማጠቃለያ

እንግዲህ ይህ ሁሉ ሲፈጸም እነዚህ ቤተክርስትያንን በማፍረስ(በመክፈል) ላይ የሚገኙ አማሳኞች እራሳቸውን ንጹህ፣ ቅዱስ ፣ጻድቃን ፣ሃይማኖተኞች በማድረግ ሌላውን ለማዳከምና ለማፍረስ የሚፈልጉትን ቤተክርስትያንና ምእመናንን  ፖለቲከኛ ፣ሃጥያተኛ ፣ በማድረግ በድፍረት የናገራሉ እንዲሁም ከእነርሱ ጋር የሚሰሩትን ጳጳሳት ትክክለኛ ናቸው ሲሉ የእነርሱን ሃሳብ የማይደግፉትን ፣የሚያስታርቁትን፤የሚመክሩትን ያውም የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑትን እውነተኛ አባቶችን ይሳደባሉ፤ያንቋሽሻሉ ትክክለኛ አባት እንዳልሆኑ ለደጋፊዎቻቸውና ለምእመን ይናገራሉ ደግሞ ልዩ መለያቸው ዓይን ያወጣ ውሸት ነው ።ይህን ደግሞ በሚንሶታ ደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስትያን አይተነዋል።

እንግዲህ ውድ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ምዕመን ሆይ አንድ ልናጤነው የሚገባ በአሜሪካን አገር በሲኖዶስ ስር ነን የሚሉት በሙሉ በስም ብቻ በሲኖዶስ ስር ነን ይላሉ እንጂ  አንድም ቅዱስ ሲኖዶስ የአዘጋጀውን መመሪያ ማለትም ቃለ ዓዋዲ ተግባራዊ የሚያደርግ የለም የሲኖዶሱን መመሪያ ተግባራዊ ሳያደርጉ (በሲኖዶስ ማዕቀፍ) ውስጥ ሳይገቡ ሌላውን መወንጀል ከፈረሱ ጋሪውን ማስቀደም ነው እንዲሁም  ለግለሰቦች መጠቀሚያ መሆን እንጂ ለቤተክርስትያኒቱ የሚያስገኘው ነገር ስለሌለ እርምት ሊወሰድበት ይገባል።  ደግሞም ቅዱስ ሲኖዶሱ ከስርአት ውጭ ነው ብሎ ምንም አይነት ተግሳጽም ሆነ ውግዘት ያላደረገበትን ቤተክርስትያን እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን የሚጠይቅ ጉዳይ አንድ ጳጳስ በግሉ ተነስቶ ሊለየው (ሊያወግዘው) አይችልም ተቀባይነትም አይኖረውም እንደውም  ቅዱስ ሲኖዶሱ ስርአትን በመጠበቃቸው የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያንን ቀኖናና ዶግማ  በመከተላቸው ህዝበ ክርስትያኑን በደንብ በስርአትና በኃይማኖት መምራት ይችላሉ ብሎ፦

  1. አቡነ ዳንኤልን ከሚንሶታው ደብረሰላም መድኃኒዓለም ገለልተኛ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶሱ ለጵጵስና ሲሾማቸው እንዲሁም
  2. አቡነ ፋኑኤልን ከዲሲ ሚካኤል ገለልተኛ ቤተክርስትያን ያን ቅዱስ ሲኖዶሱ ለጵጵስና ሲሾማቸው እነዚህ ስርአት አስከባሪዎቹ የት ነበሩ ?

ቅዱስ ሲኖዶስ ከገለልተኛ ቤተክርስትያን እየጠራ ሹመትን ሰጣቸው እንጂ አልለያቸውም ቅዱስ ሲኖዶስ ሲሾም ሌላው የቅዱስ ሲኖዶስ የበላይ ሆኖ ሊያወግዝም ሆነ ሊለይ እንደማይችል ለመግለጽ እወዳለሁኝ ስለዚህ በአሁን ግዜ እንደወረርሽኝ እየተስፋፋ የመጣውን  ጉዞወደ እናት ቤተክርስትያን(እንቀላቀል)የሚለው የተሞከረባቸውን የተለያዩ አብያተ ክርስትያናትና ምእመናን ላይ ያስከተላቸውን ችገሮች ስንመለከት እንኩዋን አንድነትን ሊያመጣያ ቀርቶ በአንድነት የነበሩትን ምእመናን የበተነ፣ዘመዳማቾችን የለያየ ፣ባልና ሚስትን ያለያየ ፣በኢኮኖሚና በማህበራዊ ምዕመኑን ያቃወሰ እነዲሁም ስለቤተክርስትያን በጋራ ሆኖ ይሰራና ይነጋገር የነበረውን እንዳይሰራና እንዳይነጋገር ያደረገ ነው። ስለዚህ ማንኛውም የኢ/ኦ/ተ/ ቤተክርስትያን አማኝ ሊያደርገው የሚገባው ጥንቃቄ ማንም ተነስቶ እንቀላቀል ቢል ቤተክርስትያንን የሚያፈርሱና የሚያዳክሙ አማሳኞች መሆናቸውን ማወቅ አለብን ይህ ጉዳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የሚጠይቅ ስለሆነና ማንም ጳጳስም ሆነ ፓትርያርክ በግል የሚጽፉት ደብዳቤም ሆነ መልእክት የቤተክርስትያን ድምጽ አለመሆኑን በማወቅ ልንቃወመው ይገባል የቤተክርስትያን የበላይ አካል ቅዱስ ሲኖዶስ ስለሆነ ከቅዱስ ሲኖዶስ የሚመጡት መልእክቶች ብቻ የቤተክርስትያን ድምጽ መሆናቸውን መረዳት ይኖርብናል ።

በመጨረሻም በመንግስት የምትመኩ ፤በዘርና በጎሳ የተመካችሁ፤ በስልጣን ጥማት የሰከራችሁ፤በፍቅረ ነዋይ የታወራችሁ፤ክርስቶስን የማታውቁ ግን የክርስቶስ አገልጋዮች ነን የምትሉ በሙሉ ቤተክርስትያንን በማወክና ሰላሟን በማደፍረስ በመክፈል እንዲሁም በማዳከም ላይ የተሰማራችሁ  ጳጳሳት ፤ካህናት፤ዲያቆናት ፤ግለሰቦች እስቲ ለአንድ ሰከንድ ቆም ብላችሁ የተሰቀለውን ክርስቶስን አስቡት ያን ግዜ እውነትን ታይዋታላችሁ እውነት ደግሞ የተሰቀለው ክርስቶስ እንጂ መንግስት አይደለም መንግስትም ይቀየራል፤ስልጣንም ይቀራል፤ገንዘብም ይጠፋል  ሁሉም ያልፋል የማያልፈው እውነት ብቻ ስለሆነ ስለ እውነትን መስክራችሁ ሰማእት ለመሆን ሞክሩ።ከቻላችሁ እውነትን ተናገሩ ካልቻላችሁ ሃሰትን አትናገሩ ይህንንም ካልቻላችሁ ዝም በሉ።

ስለ እውነት ምንነት ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ ከጻፉት ላይ በማቅረብ ጽሁፌን ልደምድም

እውነት ማለት የኔ ልጅ

እውነት ጽድቅ እንዳይመስልሽ ኩነኔ ነው እውነት ያማል

አይታከሙት ደዌ ያከሳል ያጎሳቁላል

ሁሌ አያስከብርሽም አንድ አንዴ ህይወት ያስከፍላል

ልጄ እውነት ከህይወት ይከብዳል

በመኖር ከህይወት ተገኝቶ መልሶ ህይወት ይበላል ።

__

<< እግዚአብሄር አምላክ ፍቅርን ይስጠን >>

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

The post የወያኔ ስራ  በቤተክርስትያናት ላይ!! በዘመናችን ያለ የቤተክርስቲያን ትልቁ ፈተና – ጉዞ ወደ እናት ቤተክርስቲያን (እንቀላቀል) ለምን ትልቅ ፈተና ሆነ ስንል? appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>