ከሥርጉተ ሥላሴ 26.09.2015 /ሲወዘርላንድ – ዙሪክ/
(„እነሆ እኔ የሥጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ ነኝ። በውኑ ለእኔ የሚያቅተኝ ነገር አለን“ ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፴፪ ቁጥር ከ፳፯ እስከ ፳፰)
መቼም ይህን ዘመን – ዘመነ ግራሞት የዘምን ሚስጥር ልበለው ይሆን? እንዴት ናችሁ ቤቶች – ደህና ናችሁ ደህና ናችሁን?
![ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)]()
ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)
ቸገረን እኮ 6ቱ ህዋሳታችሁ የሉም እየተባል ነው። ስድስት ያልኩት የቀደመውን አምስቱን እንዳለ ተቀብዮ የሁሉ ዓይነታ የሆነውንም ጭንቅላትን በማከል እንጂ – የሳይንስን ሊቃውንት ለመጋፋት አይደለም። ሞልቶ ጭላጭ ባልሰራለት ዙሪያ ብክንክን ስንል ሰነባበትን። ቆስቁስ የሚል ቅጥል ሥም የነበራቸው የአባባ የአባቴ የሥጋ ዘመድ – ልጅ እያለሁ ቤት ይመጡ ነበር። ሰሞናቱን የቆሰቆሱ – የቀሰቀሱም ሁኔታዎች ቸል ተብለው ተዳምጠው ቢታለፉ፣ እነዛ በዘረኝነት ክርኒ የደቀቁ ሰማዕታት ሆኑ፤ በጉስቁል ህይወት ያልፋልን የሚጠብቁ ምንዱባን መንፈስ የት ናችሁ እያለ ያፋጥጣል። ሊታለፋ የማይገቡ ጉዳዮች ተክለ ሰውነት ነጥረው መፈተሽ – ይኖርባቸዋል። ቢያንስ በድምስሱ አለመሄዳችን ህዋሶቻችን ከእኛ ጋር ያሉ ስለመሆናቸው ፊርማ ገጭ – ይደረግበታል።
ሰሞኑን በVOA እና በኢሳት ዶር አረጋይ በርኽ የህወሓት አንጋፋ መስራች፣ የትዴትም መሪ የሸንጎውም አባል ሰሞናቱና የኢትዮጵያ ፖለቲካ በተመለከተ በሰጡት ቃለ-ምልስ ዙሪያ ትንሽ ልል ወደድኩ። ሁለት አዲስ ዕሳቤም አምጥተዋል። መነካካት የማይፈልጉትንም የህወሓት አንጡራ ሃብት የሆነውን ጄኒራል ዘረኝነትን ሆነ ልጆቹን – የልጅ ልጆችን ሸወድ አድርገው አልፈዋል። ዛሬ እኔ በነዛ ዙሪያ የምለውን እላለሁ።
እርግጥ ነው በአንዲት ብጣቂ የዕስቤ ክርክር ከሟቹ ጋዜጠኛ ተፈራ አስማረ ጋር የነበረውን – ጊዜ የበላ የረጅም ጊዜ እሰጣ ገባ ባውቅም፤ ቋጭቼ ነው ላልመለስበት በዛሬው ፁሑፌ እምከውነው። ያን ጊዜ የፓለቲካው እጭጌ ስለ ነበሩ፤ በዛ ሰብዕና ውስጥ የነበረውን ሙግት ስንታዘበው፤ እኒህ ሰው የኢትዮዽያ መሪ ቢሆኑ ከፕሬስ ነፃነት ጋር እንዴት ሊታረቁ ይችላሉ? በሚለው ዙሪያ ከጓደኞቻን ጋር እንነጋገር ነበር። ከሰሞናቱም በተለይ ከጋዜጠኛ ፋሲል ጋር የነበራቸው ቆይታ ብስጩ ድባብ ነበረው። የትግራይ ነገር ከተነሳች በስጨት ይላሉ። ግርሻ። የሆነ ሆኖ የአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ ከእውነት የወጣ አይደለም በማለት ክፋኛ የኮነኑትን፤ ቁም ተቀመጥ በማለት ያጣጣሉትን – ተንተርሼ ልጀምረው፤ ጋዜጠኛ ሰለሞን አባተ መጀመሪያ ካነሳው ጥያቄ ለጥቆ እንዲህ ነበር የጠዬቃቸው ዶር አረጋይን ……
„ዶር አረጋዊ ሌላ አንድ ተጨማሪ ጥያቄ ማንሳት እምፈልገው አርበኞች ግንቦት ባወጣው በዚህው በሰሞኑ መግለጫ አንድ ያነሳው ጥያቄ አለ በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ትግል ታሪክ ውስጥ ባጠቃላይና በተለይ ደግሞ ሕወሓት/ኢሕአዴግ የፖለቲካ ስልጣኑን በተቆጣጠረባቸው ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ውስጥ ሕወሓት/ኢሕአዴግን እንቃወማለን በሚለው ወገን ገንነው የመጡ ሁለት አፍራሽና ኋላቀር የፖለቲካ አዝማሚያዎች (trends) አሉ። ከነኝህ ውስጥ አንደኛው ራስን በፖለቲካ አመለካከት ዙሪያ ከማሰባሰብ ይልቅ በጎጥና በዘውግ ደረጃ የመመልከትና ሀገራዊ ፖለቲካን በደም ቆጠራ የመመንዘር አባዜ ነው። እርስወ አሁን የተፈጠረው ሁኔታ በዚህ የተቃውሞ ትግል ውስጥ የዘር መራራቅ መሻከር መጠራጠር እንዲፈጠርና እንዲህ አይነት ሁኔታ እንዲባባስ ያደርጋል ብለው ያስባሉ ወይስ ስጋት የለወትም?
የዶር አረጋይ በርኽ ምላሽ „በውነቱ ለመናገር ግንቦት ይህን መግለጫ ብሎ ከሆነ በጣም ተሳስቷል። የኢትዮጵያ ህዝብ በእርግጥ ህወሓት የፈጠረው ህወሓት ማለትም አስቸጋሪ ነው። ምክንያቱም እነመለስ የፈጠሩት የዞግ ወይንም የጎጥ ፖለቲካ በእርግጥም ገፍተው ህጋዊም አድርገውታል። በህገ መንግስትም ጨምረውታል። እና ይሄ ነገር የጥቂቶች ጉዳይ እንጂ የመላው ህዝብ ጉዳይ አይደለም። ለማስፈጸም ሞክረዋል፤ ህዝቡን ለመከፋፈል ሞክረዋል። ግን ህዝቡ የደረሰበት ጭቆና አንድ እየሆነ ስለመጣ የደረሰበት ጭቆና አንድ አይነት መሆኑ እያዬው ስለመጣ ፤ገዢዎቹ ላይ ያለው ገዢው መደብ አንድ አይነት ጭቆና እየደረሰበት እንዳለ እየተገነዘበ ሲመጣ፣ የወለጋ ገበሬ የትግራይ ገበሬ የሚያሳልፈው ያለ ስቃይ፤ የይፋትና ጥሙጋ ገበሬ የብቸና ገበሬ የሚያሳልፈው ያለ ጭቆና እየተረዳ ስለመጣ፤ በዚህ በጎጥ ምክንያት የሚፈጠር ሁኔታ ያለ አይመስለኝም። በእርግጥ እነዚህ ሰወች በዛ ስለተከፉ፣ ሥልጣን ላይ ያሉ ሰወች በዚህ ስለተከፉ በዛ ሊቀጥሉበት ይጥራሉ። ህዝቡ ግን ተፍቶታል። ይሄ ነገር አይቀበለውም። እንዲያውም በጋራ ሆኖ ለመታገልና አንድነቱን ፈጥሮ በአገሪቱ ለሁሉም እኩል የሆነ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመፍጠር ነው፤ የሚይ ያለው፤ የሚተምን ያለ፣ ፕላን የሚያደርግ ያለ፤ ስለዚህ ይሄ የጎጥ ትንተናው የግንቦት 7 ዝም ብሎ ለጊዚያዊ ጥቅም፣ ካልሆነ ለጊዜያዊ ማናፈሻ አንድን ወገን በጀርባ ለማሰለፍ ካልሆነ በስተቀር፣ ዋጋ ያለው ትንተና አድርጌ አልወስደውም።“ ጋዜጠኛ ሰለሞን አባተ በተመስጦና በአጽህኖት ያዳመጠውን እህ በማለት ውስጡን እንድንቃኝ ለአክባሪ አድማጮቹ የቤት ሥራ ሰጥቶን፤ ወደ ቀጣዩ ጥያቄ አምርቷል። ከቅኔው ልዑል ትንሽ የሥንኝ ዘለላ ….
„ወንድ ብቻውን ነው እሚያለቅሰው።“
„ከወዳጅ ዘመድ ርቆ
አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ
ተሸሽጎ ተገልሎ፥ ተሸማቆ ተሸምቆ
ከቤተ – ሰው ተደብቆ
መሽቶ የማታ ማታ ሌት ነው የወንድ ልጅ እንባው
ብቻውን ነው የሚፈታው። …
ብቻውን ነው የሚረታው። …..
ብቻውን ነው፥ ብቻውን ነው …
የእንባ ጨለማ ለብሶ ነው
ወንድ ልጅ የሚነጥበው።“
የብላቴ ሎትሬት ጸጋየ ቅኝትን የዋጠ ነበር የጋዜጠኛ ሰለሞን አባተ „እህ“ ። ዘመኑን መከታ ያደረጉ መስቃዎች ጡሯዊ ገለጣዎች ወይንም ዝንባሌዎች – የኢትዮዽያውያንን ውስጥ እንዲህ ሲያከስሉ – ይታያል። እንባቸውን በውስጥ ለሚያፈሱ – ደጎች። ታመው እንደሚያድሩም አስባለሁ።
ዕይታ።
- ዶክተሩ አዲሱን ዶክትሪያቸውን ሲጀምሩ እንዲህ ብለው ቀደሱት „ህወሓት ማለትም አስቸጋሪ ነው። ምክንያቱም እነመለስ የፈጠሩት የዞግ ወይንም የጎጥ ፖለቲካ በእርግጥም ገፍተው ህጋዊም አድርገውታል። በህገ መንግስትም ጨምረውታል።“ ግርሻ።
አዲስ የተወለደው የዶር አረጋይ ዶክተሪን ሟቹን ሄሮድስ መለስ ዜናዊ ከህወሃት ማንፌስቱ ለይታችሁ ማየት ይገባል ነው የሚሉን። ይህም ማለት ደርሷል ለምትሉት ሰቆቃ የህወትን ማንፌስቶ ለቀቅ፤ መለስን ጠበቅ እያሉን ነው። አፈርን ጠይቁ ነው የሚሉን። ይህ መስቃ የት ሊያደርስ እንደሚችል፤ እግዜሩ ብቻ ነው የሚያውቀው። ዕጣ ፈንታችን ለህወሃት ማንፌስቶ ይስገድ እየተባልን ነው። ሎቱ ስብኃት። ለዚህ የተሃድሶ ዕሳቤ ነው ተጎዝጉዞ ተነጥፎ የምናቡ የሽግግር መንግሥት የሹመት ፍርርም። ሞፈር – ቀንበር፣ ገበሬ፣ የእርሻ ማሳ የለም። ጎታው ግን በረድፍ ተሰልፎ „ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ“ እያለ በባንድ – ይዘምራል።
- „ይሄ የጎጥ ትንተናው የግንቦት 7 ዝም ብሎ ለጊዚያዊ ጥቅም፣ ካልሆነ ለጊዜያዊ ማናፈሻ አንድን ወገን በጀርባ ለማሰለፍ ካልሆነ በስተቀር፣ ዋጋ ያለው ትንተና አድርጌ አልወስደውም።“
racism discrimination and genocide in the 21st century
ይሄንን ያዳምጡት በአክብሮት፤ ገለጣዎች ወይንም ዝንባሌዎች ግፉ ከእርከኑ በላይ አልፎ፤ የአውሮፓ ማህበረሰበ በዘመነ ጨለማ ለደረሰው የአንድ ዘር የበላይነት፤ በእውነት ላይ የተመሰረተ ወላዊ ውሳኔ በተደሞ – ሰጥቶበታል። የትግሬ መንግስት እያለ፤ ይህስ አርበኞች ግንቦት የሰራው አርቲፊሻል አንድምታ ነውን – ልትሉ ይሆን ?
http://ecadforum.com/ethiopianvideo/2015/02/03/u-s-policy-ethiopia-a-failed-state-documentary
- ኦሾቲዝም በኢትዮጵያ
(„የክፋት ምስክሮች ተነሱብኝ የማላውቀውን በእኔ ላይ ተናገሩ“ መዝ ምዕራፍ፴፬ ቁጥር ፲፩)
በዚህ በናንተው ወገኖች ዘመን ከተፈጸመው ኦሾቲዝም በኢትዮጵያ ለቅምሻ፣ ለእርሰወም ብቻ ሳይሆን የመከረኛው ቤተሰቦች የእርሰዎን መልስና የአርበኞች ግንቦት መግለጫ የእውነት አውደ ምህረት ይመዝኑት ዘንድ በትህትና አሳስባለሁ።
https://www.youtube.com/watch?v=9ylowukO6yQ
https://www.youtube.com/watch?v=RWVt6ZSmXR8
https://www.youtube.com/watch?v=-bw1CQxaVqg
https://www.youtube.com/watch?v=4f0kkHnB4H4
https://www.youtube.com/watch?v=jPDnEkQPUNk
https://www.youtube.com/watch?v=dDhbbXTU9zk
ከአራዊቶች፤ ከፋሽስቶች መካከል ግን አንድ ፃድቅ፣ አንድ መላክ፤ አንድ ቅዱስ አለ።
- ነገረ አርኞች ግንቦት ሰባት
የተከበሩ ዶር አረጋይ በርኽ – ለኢህአድግ የሰጡት እውቅና በዛች አጭር የሦስትዮሽ ቃለ ልልስ ወደ 14 ጊዜ ነበር። ይገርም። በሌላ በኩል ደግሞ ሁለት ጊዜ ግንቦት ሰባት እያሉ ነበር የተናገሩት። አንድ የፖለቲካ መሪ የብቃቱ አቅም ለሌሎች አቻ ፓርቲዎች ያለው አክብሮት ምጣኔ እሱ – እራሱ ይለካበታል። ይህ ሰሳ ብሎ የቀረበው ነገረ የጎሪጥ – የአርበኞችን እና የግንቦት ውህደት በህሊና ውስጥ ያለውን የዕውቅና አቅም ቁልጭ አድርጓል። ይሄ ታዝሎ ነው ስለ ትብብር ሆነ ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚሰበከው። ሚሊዎኖች ተስፋቸውን ያስጠለሉበት የታሪክን ምዕራፍ አላዬሁም ቢሉት ትርፋ ተደማጭነትን በላፒስ ማጥፋት ይሆናል።
በጠቅላላ ከአሜሪካው ድምጽ ራዲዮ ጋር በነበረወት ቃለ ምልልስ ስውሩን መንግስት የተጣፈበትን ቅርፊት ኢህድግ እያሉ እውቅና ሲሰጡ የሚሊዎኖችን ድምጽ የሆነውን ውህደት ሆን ብለው – ድጠውታል። ይሄ ነው የታላቋ ትግራይ ህልመኛ ማኒፌስቶ – ትሩፋት። የማከብራቸውን አቶ ገመድህን አርያን አይመለከትም። ክቡርነታቸው ትእቢትም – የለባቸውም። ሌላው በዚህ አመክንዮ ውህደቱን ለፈጠረው ድርጅት ለቀድሞው አርበኞች ግንባር ያለውን ዓይን ያወጣ ንቀት በጉልህ – አይቸበታለሁ። ስለሆነም ለአቶ ወንድም ለአቤ በለው እንኳን ይህን ውርዴት መሸከም የሚችል ደንዳና ትክሻ ሰጠህ – እላለሁ። ለማንኛውም የት ቦታ ላይ የቁስል ጥዝጠዛ እንዳለ በተመስጦ – ተመልክቸበታለሁ።
- እጥረት የሚዛን።
„ግን ህዝቡ የደረሰበት ጭቆና አንድ እየሆነ ስለመጣ የደረሰበት ጭቆና አንድ አይነት መሆኑ እያዬው ስለመጣ ገዢዎቹ ላይ ያለው ገዢው መደብ አንድ አይነት ጭቆና እየደረሰበት እንዳለ እየተገነዘበ ሲመጣ፣ የወለጋ ገበሬ የትግራይ ገበሬ የሚያሳልፈው ያለ ስቃይ፤ የይፋትና ጥሙጋ ገበሬ የብቸና ገበሬ የሚያሳልፈው ያለ ጭቆና እየተረዳ ስለመጣ፤ በዚህ በጎጥ ምክንያት የሚፈጠር ሁኔታ ያለ አይመስለኝም።“ ዋው¡ – ግርሻ።
አንድን ነገር ለማወዳር የሚቻለው ሊወዳደር ከሚችለው ጋር ብቻ ነው። ጨርቅና ድንጋይ አይወዳደርም። ወይንም ውሃ እና አፈር፤ ወይንም ወርቅና ብረት ለዚህ ነው የጎጃም ገበሬ ሴቶች እንዲመከኑ፤ የጎንደር – የወሎ – የአፋር ገበሬዎች ከእርስታቸው መነቀል ብቻ ሳይሆን በእርስተ ጉልታቸው ዜግነታቸውን ተቀምተው ሃያ አምስት ሙሉ ምጥ ላይ ያሉት፤ ሃያ አራት ሰዓት ሙሉ ለትግራይ ቁሞ እራት የሚያበላው የጎንደር ገበሬ። የጋምቤላ ገበሬ ከመሬቱ መነቀሉ ብቻ ሳይሆን እንደ ወልቃይት ጸገዴ ጀኖሳይድ የተካሄደበት፤ የመተከል፣ የጉራ ፈርዳ፤ የወተር፤ የአንቦ ወዘተ ገበሬዎች ምኑ ያልቃል፤ እነኝህ ወገኖች ሰው አይደሉንም?
አርበኞች ግንቦት የወገኖቹ ችግር በሚገባ በዝርዝር ስለሚያውቀው፤ ከመከራው ጠርን በመነሳቱም ነው ሌላው ሲያባንነው ውሎ የሚያድርበት የቤተ መንግሥቱ ጉዳይ ባእዱ የሆነው። የህዝብ የሥልጣን ምንጭነትን ለማረጋገጥ ነው ዱር ቤቴ ያለው። ስለሆነም በሥራም በኑሮም ለማያውቁት – የማየት አጋጣሚ ላለገኙት መግለጫውን ለማመሳጣር ዳታ ያበዙት። የተከበሩ ዶር አረጋይ በርኽ ከአመት በፊት ነው ይህን ህዝብ ያዩት – ለሥራ በደረሱበት ዘመን የኢትዮዽያን ህዝብ ሥነ ልቦና ጋር በቅርበት ለመደማመጥ አጋጣሚውን ባለማግኘተወት ይመስለኛል፣ እንዲህ መቀራረብ የማይችል ዕይታ ሊኖር የቻለ፤ ይመስለኛል። እንጂ የአርበኞች ግንቦት መግለጫ ለጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ ሳይሆን ከመከራችን ልብ፤ ከእውነት ማህደር፤ ከእንባችን ብሄራዊ ጥሪ ነው የተነሳው። መታመን የሚቻለውም ከመራራው ሃቅ ሲነሱ ነው።
አድሎና ዘረኝነት እንዲሁም የኢትዮጵያዊ ዜግነት ዕጣ ፈንታ፤
(„እግዚአብሄር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው“ መዝ ምዕራፍ ፴፫ ቁጥር ፩፰)
የተከበሩ ዶር አረጋይ በርኽ – በመቅድምነት ለቀረበለወት ጥያቄ ስለ ጉስቁሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ያለበትን ከመከራ፣ ስደቱን፣ እራህቡን፤ መከፋቱን ገልጸው፤ ምክንያቱን ዘለው በሳቢያው ላይ ነበር – ያተኮሩት። የዚህ ሁሉ ምንጭ የህወሓት ማኒፌስቶ ዘረኝነት ነው። ይህን ደግሞ ወደ ውስጥ ሳይገባ የደጀ ሰላሟን የዘረኝነትን ስልባቦት ያዳምጡት እስኪ – በአክብሮት። የጹሁፌ ታዳሚዎችም የአርበኞች ግንቦት መግለጫ የእውነት መሰረትነቱን ማገናዘብ – ትችላላችሁ። ኢትዮጵያ በሽምቅ ውጊያ ሚሊሺያዎች ትተዳደራለች፤ ሲቢል ሰርቢሱ ተልዕኮም ይሄው ነው። አሁንም በአማተር ወታደራዊ ሥርአት አሳሯን – ታያለች። እንዲህ …..
https://ethsat.com/video/2015/09/09/esat-yesamintu-engeda-capitain-kinde-damte-september-2015/
https://ethsat.com/video/2015/08/17/esat-bezhi-samint-colonel-derese-capitain-teshome-ermias-august-16-2015/
https://ethsat.com/video/2015/08/23/esat-bezhi-samint-colonel-derese-capitain-teshome-ermias-august-23-2015-part-2/
ይህ እንግዲህ ከገጠር እስከ ከተማ በተዘረጋው – መዋቅር፤ በየትኛውም ቀዳዳ የሥነ – ልቦና የበላይነቱ በህግ የጸደቀለት የበላይና የበታች፣ የባሬያ እና የጌታ፣ የክትና የዘወትር፣ ወርቅና ነሃስ የፈጠረው የቆሰለ፤ የመገለ ግፍ ባልታሰበ ቀን፤ ካልሆነ ቦታ ከፈነዳ እንደ ሰው ለምናስብ – ያስጨንቀናል። ይሉንታ በሌለው ጭካኔ – አድሎ የተጠቀጠቀው ወገን ኮቴው ቋያ ነው። ረመጥ ነው። ቢያንስ የዕዳው ባለ ዕዳ ባልበሉት ዕዳ ህፃናት ገና ለሚወለዱት – ትግራይ ላይ ለሚፈጠሩ ህፃናት ጉዳይ ገዶት ነው አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ በርሃ የወረደው። ስለዚህም ዘመናዮችን ተወት አድርገን – ነገን ለማሳደር በሰብዕዊነት ዙሪያ እንስራ፤
የኢትዮጵያዊነት ስብዕና ሰፊ የሆነ የምርምር ማሳ ነው። አልተሰራበትም ከምል – አልጀመርነውም። የኢትዮጵያዊነት ሰብዕና በፈረሃ እግዚአብሄር የተሟሸ ነው። ህዝባችን ትውፊቶቹን – የባህል ዕሴቶቹን – እንደ ሃይማኖቱ ነው የሚቀበላቸው። ለዚህም ነው እኔ ኢትዮጵያ ሀገራችን ባልተፃፈ ህግም ትተዳደራለች አዘውትሬ የምለው – ስለተፈቀደለትም በአፈፃጸሙ እጅግ ጉልበታምና ጉልህ ሆኖ የምናገኘው። ለፍትህ አዳሪነቱ እራሱ የፍትህ አካል መሆኑ ነው። ዛሬ ባደገው ዘመን መቻቻልን የሚያበረታቱ ቢሮዎች እልፍ ናቸው። ኢትዮጵያ ግን ስትፈጠር የተሰጣት ናት። እና ዶር አረጋይ በርኽ የዛሉት ከዚህ ላይ ነው። በሚታይ ግፍ ውስጥ የማይታይ – ግን ተመስጥሮ ከደም ጋር የተቀመመ መቻቻል። ሌላ ዓለም የሌለ ይሉኝታ፤
ከሁሉ በላይ የሰው ትክክለኛ ትርጓሜ ከፈጣሪ ስጦታ ጋር የማመሰጠር ብቃት። እነዚህ ነገሮች በአንድ ዘር የበላይነት የሚደርሰውን ሰቆቃ ለመሸከም ታጋሽነትና መጠን ያለፈ ትእግስቱ እንደምናያቸው የሌሎች ሀገሮች እልቂቶች የታዬ ነገር አለመኖሩ ግፉ ተዘለለ ማለት አይደለም። ስለዚህም የአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ ከምንዱባኑ ዕለታዊ የዕንባ መሃጸን የተነሳ ተጨባጭና እውነት ነው። ነፍስም ትንፋሽም ያለው መግለጫ ነው። የዚህ ረቂቅ ጸጋ ባለቤቶችን መምህርና ጋዜጠኛ ውዴ አብረሃም ደስታ ሆኑ አቶ ገብረመድህን አርያ ክብር ናቸው ለታሪክም – ለዘመንም። የኢትዮዽያን ህዝብ ማስተዋል የሚሰብል። ጌታችን መዳህኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ለሚሊዎን ተላላፊዎች የአንድ ጻድቅ ድንቅ ተግባር የምህረት፣ የይቅርታ፣ የሥርየት መልእክተኛ ይሆናል። ኢትዮጵያዊነት ማለት ይህ ነው።
ኢትዮዽያዊነት ሰው ሰራሽ ንጥረ ነገር አይደለም። ኢትዮዽያዊነት ሰማያዊ ነው እንጂ ዶር. አረጋይ እንደሚሉት “ጭቆናው አንድ አይነት ሆኖ አይደለም።“ የታላቋ ትግራይ ማኒፌስቶ ያልተሳካለት አምክንዮ ኢትዮዽያዊነትን ከደማችን ማውጣት አልተቻለም። የነፃነታችን አንባሳደር የሆነውን ብሄራዊ አርማችን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅዓላማችን የሰናፍጭ ያህል ከክብሩ ዝቅ ማድረግ አልቻለም እንዲያውም እንዲበረከክ እራሱን እያደረገ መሆኑን ዘመን ጥሩ ነውና እያዬን ነው። ከዚህ በተጨማሪ አማርኛ ቋንቋ የኢትዮዽያ ህዝብ አንጡራ ሃብት መሆኑን ሊያከስለው ያሰናዳለትን ደባ ሁሉ ድል ማድረጉን ማኒፌስቷችሁ እንዲቀበል ስለተገደደ ለመቀዬጥ እየተደረገ ያለው የስዋሰው ህግ ረገጣ እያዳመጥን ነው። የ25 አመት ሸር – ብንን።
የአምስተርዳሙ ኢሳትና ዶር አረጋይ በርኽ የዕይታ አንድምታ ጭማቂ።
ዶር አረጋይ በርኽ ከኢስት ጋር በነበራቸው ቆይታ ከጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ጋር ባደረጉት ቃለ – ምልልስ አዲስ ዶክተሪን አዳምጠናል፤ ቀደም ባለው ጊዜ „ትግራይ የተሰዋንላትን ያህል አልተጠቀመችም“ ይሉን ነበር። አሁን ደግሞ „ተበድላለች“ ያሉን ከውቅያኖስ በሾርባ ማንኪያ ውሃ እንደ መቅዳት ቢያስቆጥርም – ሊንኮችን የጹሁፌ ታዳሚዎች እንድታዩ እጋብዛለሁ። ግብዣ ያልኩት ያልተመጣጠነ የሃብት ስርጭት መኖሩ የተገባ ነው ለማለት ሳይሆን፤ የትግራይ ልጆችም ወገኖቻችን የእኛው ስለሆኑ ነው። ምነው የግለሰብ መደለቢያ የሆኑ የተዘረፉ አንጡራ ሃብቶች ለህዝብ ጥቅም በዋሉ – እዛው ትግራይ ላይ። ቱቦ የህወሓት ባለስልጣናት ከሚዘምኑበት – ትግራይ ላይ እንጀራ በሆነ። ሰው በውሃ እየተጠማ ከሚፈስ ትልቅ ወንዝ አፍ ያረጠበ ምንጭ የተባረከ ነውና።
“የእኔ ዓላማ የግሌ ማለት ነው” ይሉና “ብቻም አይደለም፤ የስብስብ ይሄ ደግሞ ዝም ብሎ ተራ ዓላማ አይደለም። ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሙሉ በእኩልነት የሚይ ሥርዓት ህግ የሚገዛው አስተዳደር፣ እንዲፈጠር የቆምኩለት ዓላማ ነው። ይሄ ዓላማ ገና ተማሪ ሆኜ አዲስ አበባ የጀመርኩት ስለሆነ በቀላሉ የሚፍረከረክ አይደለም።”
ዶር አረጋይ በርኽ እውን ለዚህ ነበር ወጣትነታቸውን የሸለሙት አሁንም እኮ ከህወሃት ማንፌስቶ ዞር በሉ መለስን ጠይቁ እያሉን ነው። ይሄም ብቻ አይደለም ውጪ ከወጡ በኋላ እስከ ዛሬዋ እለት ድረስ ትግራይ ዴሞክራሲ ትብብር (ትዴት) አለ። የአሁኑን አላውቅም ቀደም ባለው ጊዜ የኢተፖድህ የድጋፍ ድርጅት ጥቆማ ላይ አብረዋቸው መድረክ ላይ የተቀመጡት የማያደርጉትን እሳቸው ሲያደርጉ – ተመልክቻለሁ። እራሳቸው ሀጎስ፣ ተክላይ እያሉ ቦታ ሲሻሙ አይቻለሁ። እና “በጎሳ አስተሳሰብ ኋላቀሮች፤ የዘቀጡ – የተጋረዱ” እያሉ የሚዘልፏቸው ወገኖች ወይንስ ከልጅነት እስከ እውቀት የጎጥ ችግኝ አብቃይ ወይንም መሥራቹ ማነው ለጎጡ ጥብቅና ደፋ ቀና የሚለው? “የራስን ዕድል በራስ መወሰን የብሄረሰቦች መብት እስከመገንጠል” ትክክል እንዳልነበር ገልጸዋል፤ በሁለቱም በኩል ላለፈው ህይወት ተጠያቂነቱ የማን ነው? ካሳውስ?
ወይ መዳህኒተ አምላኬ – አዲስ መደብ ያሉት የሁሉምብሄረሰብ አባላት በማድረግ የስልጣን ክፍፍሉን ወዛማ አድርገውታል፤ ምድር ጦሩ፤ አየር ኃይሉ፤ ደህንነቱ፤ የፖሊስ ሠራዊቱ፤ የፍትህ ተቋማት፤ የወይን ቤቶች አስተዳደር፤ ቁልፍ የኢኮኖሚ ተቋማት በትግራይ ተወላጆች ተይዞ ነው፥ ሙሁሩ የእንቅልፍ ክኒን የሚጋብዙን። ፍርፋሪ የሚወረወርላቸው ግን በካስማ ጎብጠው የሚሄዱትን ነው፤ ሌላው የሥነ ልቦና የበላይነት የራስ ጌታ ያደርጋል። ይሄ ዜግነቱን የተነጠቀው ሰቆቆኛው የኢትዮዽያ ህዝብ አሳምሮ፣ አበጥሮ፣ አንተርትሮ ያውቀዋል። በራስ የመተማመን ተፈጥሮዊ ጸጋውን ነው በግፍ ያጣው።
ሌላው የህወሓትን ዘረኛና ሚሊሻዊ አስተዳር ለመጣል የተደረጉ ጥረቶችን አቃለውታል ዶር አረጋይ በርኽ፤ በድርጅትም በህብረትም ተጽዕኖ ፈጣሪ አልነበረም ብለውናል፤ ጉልበታም ተሳትፎና ታሪካችን እኮ ነው የብዕር አርበኞቻችን በአለም አደባባይ የህወሓትን ረገጣ በማጋለጥ የድርብርብ ሽልማት ባለሟል የሆኑት፤ ሌላም ልከል -ህወሓትን ለፈተና የጣለ ፤ እንደ ድርጅት ቅንጅት፤ አንድነት፤ ግንቦት 7 ማንሳት ይቻላል፤ እንደ ሰብአዊ መብት ተሟጋች የሰማእቱ የኔሰው ህልፈት፤ ጋዜጠኛ አበበ ገላው፤ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፤ ጋዜጠኛና መምህር ርዕዮት ዓለሙ፤ ጋዜጠኛ ውብሸት ታየ፤ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ ጋዜጠኛና መምህር አብረሃም ደስታ፤ የዞን ዘጠኝ አንበሶች፤ አቶ ኦባንግ ሜቶ፤ አቶ ኦኬሎ አኳይና አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ፤ ገናናው የድምፃችን ይሰማ እንቅስቃሴ እና የተከበረው የህወሃትን መፍረክረክ ብቻ ሳይሆን፤ ህወሃትን ምጥ ላይ አስቀምጦታል።
በዱር ቤቴ መስመርም የአርበኞች ግንቦት ሰባት ውህደት ህወሓት የእንብርክክ እያስኬደው ነው። ሰፊ አድማጭም አለው። ይህ እውነት ነው። በተለይም የመሪዎቹ ሁሉን ሆነው አርበኛውን መቀላቀላቸው – የአርበኞች ግንቦት ጅምር የዘሩን ዛር ቁንጮ ህወሃትን ትቅማጥ እንደያዘው – እያራወጠው ነው። ይህን የሚሊዎኖችን የተስፋ ሃዲድ ማቃለል አይቻልም። ጠንካራ መሪ ጠንካራ ድርጅት አለን። የመሪነት ብቃት ተጽዕኖ ፈጣሪነት እያዬን ነው። ተመስገን።
የኢትዮጵያ አገር አን ጥምረትም ብሄራዊውን ጥሬ በሩን ከርችሞ ሳይሆን ቧ አድርጎ ከፍቶ ፏ ብሎ እየጠበቃችሁ ነው። መወሰን የነፍስ ወከፍ፤ እንዲሁም የወል ጉዳይ ነው። አሁን ማመሃኛ የለም። ያደገ፣ የቀደመ በሳል መግለጫ ነው፤ ለራሱ ለህወሓት ሳይቀር፤ እንኳንስ ለአጋር ድርጅቶች። በመጨረሻ ንግግረዎት አበክረው ለሚዲያ ሰዎች ያስገነዘቡትም ቢሆን በሀገር ጉዳይ ፉታ አጥተው ካላነበቡት በስተቀር የአገር አድኑ ሚዲያዎች እንዲተጉበት ላሳሰቡት ጉዳይ — የአገር አድኑ ጥምረቱ የሚዲያን የቤት ሥራ አስቀድሞ ሠርቶታል። የነገ ኢትዮጵያን ቀና መንፈስ ንድፍ አሃዱ ብሎታል። ይህነን ዘሃ ግራው – ትብትብ ሁኔታ የመሻገሪያ አስኳሉን በጥንቁቅ ህሊና ተልሞታል።
የማከብረወት ዶር አረጋይ በርኽ ——ያስታውሳሉ የኢተፓድህ ሁለተኛ ጉባኤ ተውሎ – ታድሮ፤ ታድሮ – ተውሎ፤ እንደገናም ታድሮ አጀንዳ እንኳን ማጽደቅ እንዳልተቻለ፤ ያ … ከሀገር ቤት ሳይቀር የጉባኤ አባላት የተሳተፋበት ታላቁን ጉባኤ እድምታ ህዝብ ተሰብስቦ ሲጠብቅ ምን እንደነበር እኔው እራሴ – አይቸዋለሁ። ለዚህም ነው ዛሬ ፈተናን እየደፈሩ የሚገሰግሱ ተግባራት የመንፈሴ ዘውድ የሆኑት፤ ለተባ ተግባር ዕውቅና ለመስጠት ቆጥቋጣ ባይሆኑ መልካም ይመስለኛል – በትህትና። ቅንነቱ ካለ የጎደለውን እየሟሉ፤ ያነሰውን እያከሉ የወል ፍላጎትን ማሳካት ይቻላል።
የሁለቱ ቃለ ምልልሳ ሚዛናዊነት ከመሪነት ሰብእና አንፃር።
ዶር አረጋይ በርኽ ስለ አቶ ሞላ በአሜሪካው ራዲዮ አማርኛው ዝግጅት ላይ አቶ ሞላ አስገዶምን እንደማያውቁት ከእርሳቸው በርቀት አስቀምጠው ኢሳት አምስተርዳም ላይ ሻሩት፤
1 ሌላው ስለ አቶ ሞላ አስገዶም ከህወሓት ጋር መስራት ዕድሜ ጠገብ እንደሚሆን ግምታቸውን አስምረውበታል፤ ይህ ባንድ በኩል የሚያውቁት ነገር እንዳለ ቢጠቁምም፤ በሌላ በኩል ለደማለት ድል ባይተዋር ነህ ተብሎ ሲባረር የዛችን ወቅት እልህ – ቁጭት ላይ ሆኖ ለዚህ ተግባር ይሰለፋል ማለት ይቸግራል። የቀደመው ዋጋው ደጅ አዳሪ ሆኖ በተቀራረበ ጊዜ አብሶ ከሄሮድስ መለስ ዜናዊ ሞት በፊት ይህን ኃላፊነት ሊያስወስድ የሚያስችል አመክንዮ አላየሁበትም፤ ሰብዕናውም ለዚህ ረጅም ጊዜ ስውር ድርሻ ብቃት – ያንሰዋል። በዚህ የዶር አረጋይ በርኽ የግምት ጉዞ ሌላ ሁለት ነገሮችን ባነሳ አንደኛው የስለላ ተግባር ለመሐበረሰባችን ነውር ሳለሆነ ወንዱን ጆሮ ጠቢ፤ ሴቷን ደግሞ ቀልበጡሊ በማለት እንዲገለሉ ያደርጋል። ስለዚህ በዚህ አምክንዮ ዙሪያ ከዶር አረጋይ በርኽ ይልቅ ታጋይ መኮነን ተስፋዬ ለትግራይ ህዝብ የታሪክ ህልውና ዘብ መቆማቸው – ነገን የሚያበረክት ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ታጋይ መኮነን አላሟሟቁትም፤ ለቅኖች አብዝተው ጥንቃቄ ማድረጋቸው፤ ለእኔ ተመችቶኛል። ሌላው የስለላው መረብ ረጅም ዕድሜ ነበረው ለማለት ማሰቡ የአገር አድን ጥምረቱ በጥርጣሬ ስጋት እንዲወጠር ነቅንቅ አይነት ይመስላል፤ ነገም ቢሆን ይህ ሊፈጠር ይችላል በማለት ያለውን ዘመን ጠገብ የትስስር ሥነ ልቦናዊ ጋብቻ ትርትር የሚፈጥር ዓይነት ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ስለዚህም መድህናችነን ኢትዮጵያዊነትን እንዋጥ።
2 በአሉታ በጥላቻ መጀመር ለአንድ የጎሳ ፓለቲካ መሪ ሳቢነትን፣ ተእማኒነትን፣ ተቀባነትን፣ ተስፋነትን፣ ወላዊነት መፍቀድን፣ ከዘመን ጋር ለመጓዝ መፍቀድን በጥቅሉ የአመራር ደረጃ ብቃትን ጥራት ላይ ተጽእኖ ያሳድራል፤ ወደ ስድብ ከወረደ የመሪነቱ ደረጃ ይቀዘቅል „የተጋረዱ“ „በአንድ ጀሮ ተሰምቶ በሌላው ይፈሳል“ በእኛ በተራዎች አያምርም እንኳንስ በእርሰዎ። ዋጥ ተደርገው መሪ ሆደ ሰፊ መሆን አለበት፤ የሚንቁትም ሆነ የሚጠሉት የህዝብ አስተያዬት ከሚደፋት ቢያደምጡት ነው የሚበጀው፤ አሁንም እቀጥላለሁ እንደምፈልገው ከሆነ በሀገሬ ውስጥም እስካሉ ድረስ፥ ለህዝብ ቅሬታዊ ትችት አቅል። ከሚወርፉት ሰው ተሽሎ መገኘት ብልህነት ነበር።
3 „በውነቱ ለመናገር ግንቦት ይህን መግለጫ ብሎ ከሆነ በጣም ተሳስቷል። „ብሎ ከሆነ“ ወይ ጉድ፣ በአንድ በኩል በአቶ ሞላ አስገዶም ዙሪያ ሚዲያ ላይ የወጡትን እንዳዩ፣ እንዲሁም እንዳታደሙበት ይነግሩናል፣ በሌላ በኩል የጉዳዩን የኣናት ምንጭ መግለጫ እንዳላነበቡ – ይነግሩናል። ንቀት ነው? ማጣጣል ነው? ጉዳዬ አይደለም ነው ወይንስ ከፖለቲካው ውጭ ነኝ ነው? እኔ እንደ ሥርጉተ በኢተፓድህ ታሪክ ቤተኛ የነበሩት የዛሬው የሸንጎ ቤተኛ የሚተናነቃቸው የሃቅ የወርቅ ጓል እንዳለ ተመልክቻለሁ፣ ለውጥ ፈላጊው መንፈሱን የገበረለት ተወዳጅ አዲሱ ምእራፍ ለማድመጥ እንዳቃታቸው – እውነት እንዲህ ናት ትመራለች። ለአርበኞቿ ግን ትጣፍጣለች። የእውነት ሽሽት እራስን – ይገልጣል።
ልከውን – የማከብራችሁ ብልሁን ሚዛን ለማየት የተለጠፉ ሊንኮችን ጊዜ ሰጥታችሁ ብትመረምሩ መልካም ነው። በተረፈ ውዴ ዘሃበሻን በማመስገን መሸቢያ ሰንበት። እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሊንኮች …..
ዶር አረጋይ በርኽ ስለ ጥዴን ሁኔታ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46742
http://ethsat.com/video/2015/09/18/esat-eneweyay-with-dr-aregawi-berhe-sep-18-2015-ethiopia/
„የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተወልደ ገብረ ፃድቃን ሥራው እየተካሄደ መሆኑን ለሪፖርተር አረጋግጠው፣ ሥራው ባለመጠናቀቁ መረጃ ለመስጠት እንደማይችሉ ገልጸዋል፡፡ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46868#sthash.bSgpTko2.dpuf
የኢፈርት የገዢው ፓርቲ ንግድና ኢንዱስትሪ ዝርዝርና የካፒታል መጠን
http://ethioentertainment.tumblr.com/post/69174617650
የሞሃ 8ኛ ፋብሪካ በመቀሌ ተመረቀ
http://ajebnew.net/news/story-in-amharic
የምጥን ማዳበርያ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ
http://www.google.ch/
የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተ መንግስት – ክፍል 8
http://www.ethioaddislink.com/aggregator/categories/16
የትግራይ ክልል በብዙ መልኩ ከሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች የተሻለ ተጠቃሚ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ! ለምን የሌሎች ክልሎች ለውጥ እንዲህ አይታይም?
http://ethiopiaobservatory.com/2015/04/10
http://ethiopiaobservatory.com/2015/09/15/update