Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

ፖለቲካ ሀጢአት የሆነባት አገር –ናትናኤል በርሔ

$
0
0

ኖርዌይ

unnamedሰሞነኛ በአለም ላይ ካሉት አበይት ክስተቶች አንዱ የሆነው የግሪክ መንግስት የኢኮኖሚ ውድቀት እና የፖለቲካ አለመረጋጋት የተከሰተበት ነው።አለም አሁን ለሰለጠነበት ዘመን ትልቅ አስተዋጽኦ ካበረከቱ አገሮች መሀከል በቀደምት ደረጃነት የምትመደብ ግሪክ ዲሞክራሲ የምንለውን ፅንሰ ሀሳብ በማምጣት እና ስራ ላይ በማዋል የሚቀድማት አገር የለም።የጥንታዊታ ግሪክ በ5ኛው መቶ ክርስቶስ ልደት በፊት ሀያል ልኡላዊት አገር ካደረጉዋት ነገሮች ውስጥ ዲሞክራሲ የሚለውን ቃል ዲሞ /Demo/ “people” እና ክራሲ “ power” በማለት በወቅቱ ፍችውን አስቀምጠውታል። ግሪክ በ21 ክፍለ ዘመን ከሀያላን አገራት የተበደረችውን ብድር መክፈል ባለ መቻልዋ ስር በሰደደ የመልካም አሰተዳደር ጉድለት በሙስና በዕዳ ቀውስ ምክንያት አሁን ላለችበት በአለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት /IMF/ ፤ አውሮፓ ህብረት እንዲሁም የአውሮፓ ሴንትራል ባንክ ዕዳ አጣብቂኝ ውስጥ ከቷቷል።

ወደ አገራችን ስንመለስ ኢትዮጵያም ለአለም አቀፍ አንድ ሚልዮን ዶላር Sovereign ቦንድ ሽያጭ ለገበያ አቅርባ ነበር ወለዱም 6% ነው አሁን ባለው የኢኮኖሚ ገባያ ከ 6% ወደ 7% አድጎዋል ይህም ማለት የመክፈል ዕዳችንም መጠን ጨምሮዋል ። ኢትዮጵያ ዛሬ ያለችበትን ጂዮግራፊያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ሌሎች ገጽታዎች ለመላበስ ያበቋት እጅግ በርካታ ክፉ እና በጎ ተበለው የሚጠቀሱ የታሪክ ክስተቶችን አስተናግዳለች ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ እንዲህ አሳሳቢ ሁኔታና ውድቀት አፋፍ ላይ ባለችበት ሁኔታውን ዝም ብሎ በመልከት በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር የምንኖር ኢትዮጵያዊያኖች ዛሬ ህወሃት/ኢህአዴግ ጨቋኝ አገዛዝ በገዛ ልጆቿ ወድቃ ልትፈርስ እየተንገዳገደች ነው፡፡ እርቀን ሳንሄድ የቅርብ ጊዜ ታሪካችንን እንኳን ብንፈትሽ ዛሬ ለምንገኝባቸው እጅግ ውስብስብ እና ፈታኝ ችግሮች መንስዔ የሆኑትን ነገሮች በቀላሉ ልንገነዘብ እንችላለን። የችግሮቻችንን ምንጮች እና ያስከተሉብንን መዘዝ በቅጡ መረዳት ከቻልን ከተዘፈቅንበት አረንቋ ውስጥ ለመውጣት ጊዜ ላይ ወስድንብ ይችላል።

ይህ አካሄድ በሌላ አንጻር በኢትዮጵያችን እየደረሰ ያለው ረሃብ፣ የዋጋ ግሽበት፣ የኑሮ ውድነት፣ ሙስና፣ ፍትሕአልባነት፣ አፈና፣ ግድያ ወዘተ የተወሰነ የኅብረተሰብ ክፍልን ብቻ ሳይሆን ከሲቪሉ ጀምሮ ጦር ሠራዊቱን፣ ደኅንነቱ፣ ተማሪውን፣ ገበሬውን፣ የመንግሥት ሠራተኛውን፣ ወዘተ ቤት ያንኳኳ በመሆኑ ለኢትዮጵያ አንድነትና ብልጽግና በሰላም የሚታገሉ ሀይሎችን በስውርና በአደባባይ አስሯል፥ ደብድቧል፥ ገሏል፥ የተረፉት አገር ጥለው እንዲሰደዱ አስገድዷል። ድምጻችን ይከበር በማለት ሠላማዊ ሰልፍ የወጡ ንጹህ ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ በአደባባይ በጥይት ተደብድበዋል። ህዝብን እርስ በርስ በማናከስ ሆድና ጀርባ ለማድረግ ሞክሯል። የአገራችን መሬት እየተሸነሸነ ለባዕዳን በመከፋፈል ላይ ይገኛል፡፡ የሀገሪቷን መዋዕለ ንዋይ ጨምሮ ዋና ዋና የኢኮኖሚ አውታሮች በወያኔ አባላትና የጎሳ ትስስር ባላቸው ባለሥልጣናት ተይዟል። ዜጎች በገዢው ፓርቲ ሰላዮች፥ ካድሬዎችና ታጣቂዎች እየተዋከቡ በገዛ ሀገራቸው ሰርተው መኖር አቅቷቸው ለመሰደድ እየተገደዱ ነው። ህወሃት/ኢህአዴግ ጨቋኝ አገዛዝ እንደመሆኑ ከእነዚህ አምባገነን መንግሥታት በላቀ መልኩ ኢትዮጵያውያንን አፍኖ ያለው ህወሃት አገዛዝ በሕዝባዊ ለውጥ ከሥልጣን መነሳት አለበት፡፡ ሕዝባችንም ለዘመናት የተጠማውን ነጻነትና ፍትሕ ለማግኘት ለለውጥ እንመካከር! እንዘጋጅ !! እንተባበር !! “በቅርብ ጊዜው የኢትዮጵያ ፖለቲካ አሣዛኝ የሆነው ጉዳይ መንግሥቱም፣ ገዥ ፓርቲውም፣ ሕግ አውጭውም ሁሉም አንድና እርሱው መሆኑ ነው፡፡ ባለፉት ዓመታት ጉዞ ውስጥ የጋራ አመራር የሚባል ነገር ተመናምኖ ህወሃት/ኢህአዴግ በፓርቲያቸው ውስጥ ብቻ ሣይሆን ዛሬ በደረስንበት ሁኔታ በሃገሪቱና በመንግሥቱ መዋቅሮች ውስጥ በሚከናወነው ሥራ ሁሉ ብቸኛ ፈላጭ ቆራጭ ሆነዋል፡፡”

ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችን የመደገ ፍልማድ አነስተኛ በሆነባት ሀገርና ተቃዋሚ ፓርቲዎችን መደገፍ መንግስትን እንደ መቃወም በሚቆጠርበት ሁኔታ ሊገኝ የሚችለው ድጋፍ አናሳነው:: “ምንም እንኳ ምዕራቡ የገንዘብ አቅም ቢኖረውም በሃገር ውስጥ ባለው ፖለቲካ ላይ ግን ጫና የማሣደር ጉልበት እንደሌለው የኢትዮጵያው ገዥ ፓርቲ የተረዳ ይመስለኛል ።ኢትዮጵያ አሁንም ቢሆን የምዕራቡን ድጋፍና የልማት እርዳታ ትፈልጋለች፤ ብቅ ብቅ እያሉ ያሉትን እንደ ቻይናና ሕንድ አይነቶቹን ኃያላን ቦታም ደግሞ ትገነዘባለች፡፡ ጉዳዩ መርህና ርዕዮተ ዓለም ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን የመመቻቸት ወይም የመጠቃቀምም ጉዳይም ነው፡፡” ጨቋኝ አምባገነኖች ከሌሎች አገሮች እየተወገዱ እኛ ዝም ብለን የምንመለከትበት ምንም ምክንያት ሊኖር አይገባም፡፡ በእነዚህ የሰሜን አፍሪካ አገራት የኑሮ ውድነት፣ የነጻነት ዕጦት፣ ጭቆና፣ ግድያ፣ ሕገወጥነት ወዘተ ያንገፈገፈው ሕዝብ የደረሰበትን የምሬት ደረጃ የኢትዮጵያ ሕዝብ አልደረሰበትም ማለት ፈጽሞ አይቻልም፡፡ ምናልባትም ግፉ ከዚህ የበለጠ ሊሆን ይችላል ። ለኢትዮጵያ ፖለቲካ መፍትሄው ራሱ የኢትዮጵያ ሕዝብና ከጠላቶቿ ጋር የማያብሩት የፖለቲካ ድርጅቶቿ ብቻ ናቸው። ወያኔንና ግብረአበሮቹን ከሥር መንግለው ኢትዮጵያን ነጻ የሚያወጧት ቆራጦቹ ልጆቿ ናቸው።
በአብዛኛው ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ከነመኖራቸው ራሳቸውን ለማህበረሰቡ የሚያስተዋውቁት ምርጫ የተወሰነ ጊዜ ሲቀረው ብቻ ነው:: ከምርጫ በኋላ እንቅስቃሴ ቢኖር እንኳን መሪዎቹ ጎልተው የሚወጡበትና እንደ ድርጅት ፖለቲካ ፓርቲዎች የማይታዩበት ነው:: “የምርጫ ፖለቲካ ፓርቲ” የሚለው አሰያየም በተለያዩ ሙሁራን እየተንጸባረቀ ያለው ለዚህ ነው:: በሌላ በኩል ደግሞ ከማህበረሰባዊው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የተገናዘበ ፖለቲካል ስትራተጂና ታክቲክ ያላቸው ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች በቁጥር እጅግ አናሳ ናቸው:: ፖለቲካል ስትራተጂና ታክቲክ ያላቸው እንኳን በማህበረሰቡ ውስጥ ዘልቀው ስላልገቡ አይደለም በአጠቃላይ ህዝቡ ይቅርና የፖለቲካ ንቃተ-ህሊናቸው ከፍ ብሏል በሚባለው የህብረተሰብ ክፍል እንኳን በተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ያለው ዋናዋና ልዩነቶች እንኳን አይታወቅም:: በሀገር ውስጥ ሆነ በውጭ የሚገኙ አብዛኞቹ ባለሃብቶችም አንድም ማህበራዊ ግዴታቸውን ጠንቅቀው የማይረዱ መሆናቸው፣ሁለትም ”ጎመንበጤና“ ብለው ከፖለቲካ ራሳቸውን የሚያገሉት አንድ ፖለቲካ ፓርቲ የመደራደርና የመገዳደር አቅሙን ለመገንባት በዋናነት ፖለቲካል ስትራተጂውንናታክቲኩንከማህበረሰባዊው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ያገናዘበና በማህበረሰቡ ውስጥ ዘልቆ በመግባት ማህበረሰቡን ማደራጀትና ማሰባሰብ አለበት:: በዚህ ሂደት ውስጥ አንደኛ ፖለቲካ ፓርቲው በማህበረሰቡ ውስጥ ተቀባይነትን ያተርፋል:: እንዲሁም ደግሞ በሌሎች ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋርም የመደራደር አቅሙንከፍ ያደርገዋል:: በተያየዘ መልኩም ከሌሎች ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመደራደር የጋራ ፖለቲካ አጀንዳ ነድፈው የጋራ ተጠቃሚነትን

The post ፖለቲካ ሀጢአት የሆነባት አገር – ናትናኤል በርሔ appeared first on Zehabesha Amharic.


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ አጭበርብረዋል የተባሉ እስራት ተፈረደባቸው

$
0
0

–የባንኩ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ የተቀጡት በሌሉበት ነው

መንግሥታዊ ሰነዶችን በሐሰት በማዘጋጀት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰባራ ባቡር ቅርንጫፍ፣ ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ ማጭበርበራቸው የተረጋገጠባቸው የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅና ሁለት ግለሰቦች፣

national bank of ethiopiaሰኔ 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ከአምስት እስከ 12 ዓመታት ከስድስት ወራት የሚደርስ ጽኑ እስራት ተፈረደባቸው፡፡

የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ በሙስና ወንጀል ክስ የመሠረተባቸው፣ የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅ አቶ መኳንንት አበጀ፣ ይፈመን ቲምበር ፕሮሰሲንግ የተባለ ድርጅት ተወካይ አቶ ብርሃኑ አዳፍሬና የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ይትባረክ አፈወርቅ ናቸው፡፡

የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያስረዳው፣ የባንኩ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ መኳንንት በ2005 ዓ.ም. የተለያዩ ሀሰተኛ የባንክ ዋስትና ሰነዶችን አዘጋጅተዋል፡፡ ያዘጋጁትን ሐሰተኛ ሰነድ ይፍመን ቲምበር ፕሮሰሲንግ ለተባለው ድርጅት በመስጠት ወንጀሉን መፈጸማቸውን ያስረዳል፡፡

በሥራ አስኪያጁ የተዘጋጀውን ሐሰተኛ ሰነድ የድርጅቱ ተወካይ አቶ ብርሃኑ በመቀበልና ሐሰተኛ የሽያጭ ዋስትና በማስያዝ፣ ከአንድ የማደያ ድርጅት ውል ተዋውለው 900,000 ብር የሚያወጣ የሞተር ዘይት፣ ቅባቶችና የነዳጅ ኩፖን ወስደው በወንጀሉ መሳተፋቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡

የይፈመን ቲምበር ፕሮሰሲንግ ሥራ አስኪያጅ ናቸው የተባሉት አቶ ይትባረክ፣ ከአቶ ብርሃኑ ጋር በመተባበር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ላደረጉት የእንጨት ምሰሶዎች አቅርቦት ውል፣ ሐሰተኛ ሰነዱን በዋስትና በማቅረብ 4,908,623 ብር ቅድመ ክፍያ ከኢትዮ ቴሌኮም በቼክ መውሰዳቸውን ይገልጻል፡፡ ገንዘቡንም ወደ ድርጅታቸው አካውንት በማስገባትና አውጥተውም ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውም በክሱ ተጠቁሟል፡፡

የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ሦስቱም ተከሳሾች ድርጊቱን መፈጸማቸውን በምስክሮችና በሰነድ በማረጋገጡ፣ የባንኩ ሥራ አስኪያጅ አቶ መኳንንት በሌሉበት በስምንት ዓመታት ጽኑ እስራት፣ አቶ ብርሃኑ አዳፍሬ በ12 ዓመት ከስድስት ወራት ጽኑ እስራትና አቶ ይትባረክ አፈወርቅ በአምስት ዓመታት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 18ኛ ወንጀል ችሎት ሰኔ 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ፍርድ ሰጥቷል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

The post የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ አጭበርብረዋል የተባሉ እስራት ተፈረደባቸው appeared first on Zehabesha Amharic.

የማለዳ ወግ…እየሳቁ ማልቀስ  ! –ነቢዩ ሲራክ

$
0
0

* የተሰራው ስራ ስኬት ፣
ባልተሰራው ስራ የሚያመው ህመም  !
neby===========================
* ወጣቱ አባወራ መሀመድ ሀሰን ሀገር ቤት ገባ  !
* ሁለቱ መሀመዶች ጉዳያችንና ተስፋው …
*  ያሰመረው ተስፋ
* ያልሰራነው የቤት ስራ …
* ባትደግፉ እንኳ  አታደናቅፉ
* እርዱ እረዳችኋለሁ  …

ሁለቱ መሀመዶች ጉዳያችንና ተስፋው …
=======================
ወጣቱ አባወራ መሀመድ ሀገር ቤት በሰላም ገብቷል ። ሰኞ ለማክሰኞ አጥቢያ ሰኔ 29 ቀን 2007 ዓም በሰላም መግባቱን የገለጸልኝ መሀመድ በሳውዲ ቆይታው በተለይም ሮመዳን በገባ ማግስት ተስፋው ጨልሞበት ሰዓት ድረሱልኝ ያላቸው ወገኖቹ በጸሎትና ትብብር ከምንም በላይ መደሰቱን ገልጾልኛል ።

…የሁለት መሀመዶችን የመሰንበቻ ወጋችን ነበር ።  በሀኪሞች ስህተት ዘጠኝ ዓመት የአልጋ ቁራኛ የሆነውን  ታዳጊ ብለቴናው መሀመድና ስደት ያሰናከለው ወጣት አባወራ መሀመድ ሁሴን እያልኩ በዙሪያው ባለው መረጃ ሳቀብላችሁ ከረሜያለሁ ።  የብላቴናው ጉዳይ ውስብስብ ያደረገው በደል አድራሹ ሆስፒታል ጉዳዮችን የማረቅና የማፈን አቅም ቢሆንም ግፍ ተሸፋፍኖ አይቀርምና ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ወደ መጨረሻዋ ሰዓት መዳረሻው የተጣጋን ይመስላል …ፈጣሪ ይርዳን  !

የወጣቱ አባወራ ያልኳችው የመሀመድ ሁሴን ጉዳይ ግን እነሆ ተከውኗል ። Mission Accomplished ብለናል  !  መሀመድን በደረሰበት የከፋ የመኪና  አደጋ በአዲት ጠባብ አልጋ ተወስኖ የመክረሙን አበሳ ፣ የወገን ናፍቆትና ህመሙን ቀድሜ ብረዳም በአካል ሔጀ ሳየው መስማት እንደማየት አለመሆኑን እያወቅኩት ደጋግሜ የተረዳሁነት አጋጣሚ ነበር ። ብርቱው ሰርቶአደር ገበሬ መሀመድ የወለዳቸውን ሁለት ፍሬ ልጆች ብሩህ ተስፋ ብሎ የገባበት ስደት ቢያሰናክለውም ሳገኘው ያየሁበት  በብሩህ ገጽታ ፊቱ በርቶ ነበር ። መሀመድን እንርዳ ካልኩበት ሰዓት ጀምሮ በጸሎትና በገንዘብ ያደረጋችሁለት እርዳታ አተርፍ ብሎ ያጎደለውን መሀመድ በወገን አለኝ ተስፋ አድሶት ተመልክቻለሁ ፣ ህመሙንም አስረስቶታል ።

መሀመድ ዛሬ ራሱን ችሎ መሮጥ  አይችልም። መሀመድ በሀገሩ የሸለለ የፎከረበትን መሬት መርገጥ አይችልም  ።  መሀመድ ትናንት ቤተሰቡን ለመታደግ  ገስግሶ ወደ ስደት የመጣበትን ምድር ይኖር እንደሁ እንጅ አይረግጠውም  ! በኩንፊዳ ሆስፒታል ሳገኘው ለዘጠኝ ወራት በአንዲት ጠባብ አልጋ ላይ የተገጠመለትን ብረትና ብረት ይዞ ጎንበስ ቀና እያለ ፣ ቀኝና ግራ እየተላወሰ ነበር …
ይህ ፈተና የገጠመው መሀመድ ግን ብርቱ ሞራል አለው ። ሲያገኘኝና ፣ አቅፎ ሲስመኝ ደስ አለው … ጽናትና ተስፋውን ተመልክቸ ተደመምኩ …በውስጤ ” ተመስገን ነው! ” ስለ ለፈጣሪ ምስጋና አቀረብኩ !   … መሀመድ በአጭሩ  የቁንፊዳ ቆይታየ ደጋግሞ  ፈጣሪው ስለሆነው ሁሉ ሲያመሰግን ያስታወሰኝ እያለን እና ስለተደረገልን ለፈጣሪ ምስጋና የማናቀርብ እኛም ሀጥኦቹን አስታወስኩ …

የሰመረው ተስፋ ….
=============
ትናንት ሰኞ ሌሊት ሰኔ 30 ቀን 2007 ዓም ሌሊት ሊሸኝ ቅዳሜ ከጅዳ 320 ኪሎ ሜትር ርቀት በአንዱ የቀይ ባህር ዳርቻ ጥግ ባለ ሆስፒታል ስንገናኝ እንዲህ ነበር ያለኝ ” አልሀምዲላህ ፣ ከፈጣሪ በታች በወገኖቸ ስለተፈረገልኝ ጸሎትና ያልጠበቅኩት እርዳታ የጨለመው በርቶልኛል  ፣ አሁን ባለ ተስፋ ነኝ ፣ አላለቅስም ። ነቢዩ ሮመዳን ለሀገሬ መግባት ከቻልኩ ደግሞ እሰየው ነው  ፣ ትሄዳለህ ካልከኝ በኋላ ድኛለሁ ፣ ኢንሻላህ አላህ አለ  !” ነበር ያለኝ

…እነሆ ተስፋው መሀመድ በሮመዳኑ የጸሎት ወር ድረሱልኝ እንዳለ ያሰበው ተሳክቶ ከናፈቃት ሀገሩ ደርሷል ። ታግሎ የጣለ ያደባየው የናፈቀው ወንድሙ አቅፎ ደግፎ ከወገኑ ሊያገናኘው ተቀብሎታል …ከናፈቃቸው ሁሉ ወገኖቹ የመገናኛው ቀን ደርሷል ….መሀመድ ልጆቹና ቤተሰቡ ጋር ሊገናኝ ሳይውል ሳያድር ተንቀባሮ ወዳደገባት ቀየው ሳይውል ሳያድር ወደ ባቲ ይገሰግሳል … ልጆቹ ናፈወቀውታላ !  ሚስቱ ናፍቃዋለቻ  ! እናት አባት ቤተሰብ ፣ ዘመድ አዝማድ ናፍቀውታላ  ! … ሳላስበው ነፍሴ በስሜት ተናጠች …ብዙ መሀመዶችን አሰብኳቸው  ! ብዙ ስም የለሾች በአዕምሮየ ተመለለሱ …

መሰራት ያለበት ፣ የሚያመው ያልሰራው የቤት ስራ …
================================
ወገን እያላቸው ፣ ወገን እንደሌላቸው በየበርሃው ወድቀው የቀሩት ይሁን ቢባል ፣ በየሆስፒታሉ ወድቀው ፣ በየቤቱ ህመማቸውን ህመም አድርገው ደብዛቸው እየጠፋ ያሉ ወገኖቸን ጨካኙ እኔ ላንዳፍታ አሰብኩት … መዲና ከተማ ውስጥ በመኪና አደጋ የተገጨች እህት አለች ፣ አትሰማም አታይም ፣ ማንነቷን እንኳ ከጣቶቿ አሻራ ወስዶ መለየት የቻለ የለም ፣ ያን ሰሞን “ማንነቷን ለዩና አሳውቁን  ” ብለን ነበር ። መጀመሪያ ከቅርብ ወራት ወዲህ ከፖለቲካ ወገንተኛነት ተላቆ ወገናዊ እየሆነ የመጣው ” ወገን ለወገን ” በጅዳ ከባቢ ያለ የፊስ ቡክ ቡድን መረጃውን አቅርቦታል  !  ” ከወገን ለወገን ” ያገኘሁትን መረጃ እኔም አቅርቤያለሁ  !

ያም ሆኖ እኔ በሁለቱ መሀመዶች ጉዳይ ትኩረት ሳደርግ ተሰናክላ ለአመታት የአልጋ ቁረኛ የሆነችቅን እህት ማንነት የሚያረጋግጥ መረጃ ደርሶኛል ። የአመታት የአልጋ ቁራኛ የመሆን አበሳና ስለ ወላጆቿ ያልሰመረ ፍለጋና ሞታለች ብለው ስለደመደሙበትን ሙሉ መረጃ ደርሶኛል …ላለፉት አመታት በተመሳሳይ ሁኔታ በመኪና አደጋ አዕምሮውን የሳተ እጁ ከብረት አልጋ ላይ ታስሮ የሚሰቃየውን ወንድም ደራሽ አጥቶ ለመክረሙ ብዙ መረጃ አለ … ጅዳስ ቢሆን ለአመታት ከሆስፒታል ወድቃ ያላየናት ፣ ከአመታት ያልነቃች እህት የለችምን  ?  ያማል …ያማል …ያማል  !

የምንሰራውን ባትደግፉ እንኳ  አታደናቅፉት …
=============================
የሚሰራውን ስላልሰራችሁ የምወቅሳችሁ ፣ የወገንን ጥቅም አስቀድሙ በማለቴ ጥቅማችሁ ያዛባሁባችሁ ፣ የምሰራውን ስራ የምትነቅፉኝ ሆይ  ! አዙራችሁ ራሳችሁን ጠይቁ  !  … እኔ ስላነሳሁት ብቻ ”  ውሾ ”  ብላችሁ ከማብጠልጠልና ለክብርና ዝና ፣ ብሎም የታመመን አይቶ ከመታመም ፣ የጨነቀውን አይቶ ከመጨነቅ ውጭ የማገኘው ጥቅም ያለ አይምሰላችሁ  ! ቸር  ደግ ሆኘ የማደርገው ልገሳም የለም … ዳሩ ግን እድሜው ሲገፋ ነው መሰል ” በእህቶቸና ወንደሞቸ ላይ የማየው ስቃይና ተለያይቶ መቅረት በልጆቸ ፣ በራሴና በቤተሰቤ ላይ ቢሆንስ ?” እያልኩ እየፈራሁ ወገን ለወገኑ እንዲደርስ  የማደርገውን መረጃ ቅበላን ማስተባበሩን ባትደግፉ እንኳ  አታደናቅፉት   ….  መከራችን አበሳችን ብዙ ነው ፣ በህብረ ት ከሆነ ግን ሊቀረፍ የሚቻለን ብዙ የወገን ችግር አለ  !

ወጣቱ አባወራ መሀመድን ወደ ሀገር ቤት እንዲገባ የሳውዲ መንግስት የትራንስፖርት ወጭን ሸፍኖለታል ፣ እናመሰግናለን  ! …  ከዚህ በተረፈ እኛ ለእኛ ፣ ለራሳችን ወንድም ስላደረግነው ደስተኞች ነን እንጅ ጀብድ አልሰራንም  ! ቆንስሉ ረዳው ኮሚኒቲው  ፣ ማህበራት ደገፉት ፣ ድርጅቶች ፣ አልያም ግለሰቦች ረድተውት እዚህ ደረሰ ፣ ይህ መከራከሪያችን መሆን የለበትም ፣  አይበጀንምና  !  መሀመድን ወደ ሀገር ቤት ለማስገባት ተቋማት ደገፉት ግለሰቦች ማንም ደገፈው ማን ቁምነገሩ  መሀመድ በሰላም ሀገሩ መግባቱ ነው ፣ በቃ አውነቱና የሚበጀን ይህው ነው  ! … ስሜት እዚህ ላይ ልገድበው …
እርዱ እረዳችኋለሁ  …
==============
ለመሀመድ 11.250 የሳውዲ ሪያል ካስረከብኩ በኋላ ተጨማሪ 1100 የሳውዲ ሪያል (700 ሪያል ከ400 ከስልክ ካርድ ጋር ተደምሮ) እርዳታ ሰብስቤያለሁ ። ” ጋን በጠጠር ይደገፋል! ” እንዲሉ በቀጣይ  ለመሀመድ የሚደረገው እርዳታ ቃል የገባችሁ ቃላችሁን እስትፈጽሙ ለቀናት ማሰባሰቡን እገፋበታለሁ ፣ መቋቋሚያ ቢሆነው ያቻልነውን እናድርግ … ፈጣሪም ያለው ” እርዱ እረዳች ኋለሁ!  ” ነውና አሁንም መሀመድን ለመደገፍ የቻልነውን እንሞክር  ! …

በተረፈ አነሰ በዛ ሳትሉ ከጎኔ ለቆማችሁ ስላደረጋችሁት ሁሉ ምስጋናየ እርካታየን ባይገልጸውም  ደጋግሜ አመሰግናችኋለሁ  !

ደስ የሚለውን ሁሉ ይስጣችሁ  !

ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 30 ቀን 2007 ዓም!

The post የማለዳ ወግ… እየሳቁ ማልቀስ  ! – ነቢዩ ሲራክ appeared first on Zehabesha Amharic.

ውጊያው ለ6ኛ ቀን ቀጥሏል * በወልቃይት ማይምቧ በተባለ አከባቢ ከበድ ያለ ውጊያ መደረጉን አርበኞች ግንቦት ሰባት አስታወቀ

$
0
0

(ኢሳት) ውጊያው ለ6ኛ ቀን ቀጥሏል:: በወልቃይት ማይምቧ በተባለ አከባቢ ከበድ ያለ ውጊያ መደረጉን ከአርበኞች ግንቦት ሰባት መረጃ ክፍል የደረሰን ዜና ያመለክታል:: በትላንትናው ዕለት ከአዲስ አበባ በ12 አውቶብሶች የተጫኑ ወታደሮች ወደ ወልቃይት በተለይም ውጊያው ወደበረታባቸው አከባቢዎች እንደተጓጓዙ ለማወቅ ተችሏል:: በቃፍቲያ እና አብርሃጅራር የማጥቃት እርምጃ ተውስዶ በመንግስት ሰራዊት ላይ ጉዳት መድረሱን የአከባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል:: በሰሜን ኢትዮጵያ የጦርነት እንቅስቃሴ እየታየ ነው::

photo file

photo file


በወልቃይት ማይምቧ በተባለ አከባቢ ከበድ ያለ ውጊያ መደረጉን ከአርበኞች ግንቦት ሰባት መረጃ ክፍል የደረሰን ዜና ያመለክታል:: በትላንትናው ዕለት ከአዲስ አበባ በ12 አውቶብሶች የተጫኑ ወታደሮች ወደ ወልቃይት በተለይም ውጊያው ወደበረታባቸው አከባቢዎች እንደተጓጓዙ ለማወቅ ተችሏል::

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የአርበኞች ግንቦት ሰባትን ጥቃት ለኤርትራ መንግስት ሸለሙት:: የኢትዮጵያን ህዝብ አስፈቅደን እርምጃ እንወስዳለን አሉ::የመከላከያ ሰራዊት አባላት አፈሙዛቸውን ወደ አፋኙ ስርዓት ማዞር አለባቸው የሚል ጥሪ እየቀረበ ነው:: ከኤርትራ መሬት ተነስቶ እየተፋለመ ወዳለው የኢትዮጵያ የነጻነት ሃይል ጥይት መተኮስ እንደሌለባቸው ከየአቅጣጫው ጥሪ እየቀረበ ነው::

The post ውጊያው ለ6ኛ ቀን ቀጥሏል * በወልቃይት ማይምቧ በተባለ አከባቢ ከበድ ያለ ውጊያ መደረጉን አርበኞች ግንቦት ሰባት አስታወቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

ሰበር ዜና:- ጦማርያንና ጋዜጠኞች ከእስር ተፈቱ

$
0
0

11728831_10207319600571747_797923304602753844_o-2
ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ፣ጋዜጠኛ አስማማው ሃይለጊዮርጊስ፣ ጦማሪ ዘላለም ክብረት፣ማህሌት ፋንታሁንና ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ ዛሬ ማምሳውን በፍትሕ ሚኒስቴር ውሳኔ መፈታታቸው የታወቀ ሲሆን ከቤተሰብ መቀላቀላቸው ከአዲስ አበባ የወጡ መረጃዎች ገለጹ።የቀሩት በእስርና በስደት ያሉ አምስት ጦማሪያን ጉዳኢ በተጀመረው የክስ ሂደት ይቀጥላል ቢባልም ቁርጥ አለ ውሳኔ አለመሰጠቱ ታውቋል። በክሱ ላይ ብኢን ለመስጠት ከመጪው ቀጠሮ ሐምሌ 13 ቀን 2007 በፊት ይፈቱ ዌኢ እንደተባለው ክሱ ቀጥሎ ብይን ይሰጥ አልታወቀም።

ከአስሩ ጦማሪያንና ጋዜጠኞች መካከል የክስ ሂደታቸው ይቀጥላል የተባለው የክሱ መዝገብ በስሟ የተከፈተውን ሶሊያና ሽመልስ ፣ አቤል ዋበላ ሱጌቦ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ በፍቃዱ ሃይሉ እና አጥናፉ ብርሃኔ ጉዳይ መታየቱ እንደሚቀጥል ከፍርድ ቤቱ የተገኘ መረጃ አመልክቷል።

የፍትህ ሚኒስቴር የፌደራል ተቋማትን ስልጣን እና ተግባር ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 691/2003 አንቀፅ 16 መሰረት በማናቸውም ሰዓት የተጀመረ ምርመራ እና ክስ የማቋረጥ እና የማንሳት ስልጣን እንዳለው ይታወቃል ያለው አንድ የአገዛዙ ሚዲአ ፍቺውን ሕጋዊ ላማድረግና በሕግ መሰረት የተሰራ ለማስመሰል ሞክሯል። በዚህ መዝገብ አቃቤ ህግ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ የወንጀል ችሎት ምስክሮችን ማሰማቱን ተከትሎ ችሎቱ ብይን ለመስጠት ለሀምሌ 13 ቀን 2007 መቅጠሩን አስቀድመን መዘገባችን ይታወሳል።

የዞን ዘጠኝ ጦማሪአንም ሆኑ ሌሎች በእስር ላይ ያሉ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ መሪዎች በፈጠራ መንግስትን በሀይል ለመታልና በሽብር በሚል ተከሰው ያለ በቂ ማስረጃ በትዕዛዝ የተፈረደባቸውና ጉዳያቸውን እተከታቱ ያሉት መጨረሻ ለጊዜው ባይታወቅም የፕ/ት ኦባማ የኢትዮጵያን ጉዞ ዕቅድ በምሳሌነት የሚያነሱ መደመጥ ጀምረዋል።

ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ግልጽ ደብዳቤ የጻፈውን ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀን ጨምሮ ክሳቸው ይቀጥላል የተባሉት አምስቱ ጦማሪያን ጉዳይ ከሐምሌ 13 ቀተሮ በፊት ይቋጭ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም።

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በርካታ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ድርጅት በተለያየ ደረጋ ያሉ መሪዎች፣ የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትና ሌሎችም ጉዳይ በተመለከተ አገዛዙ የሰጠው መግለቻ የለም።

ባለፈው ሰኔ 8/2007 ቀጠሮ አንደኛዋን ተከሳሽ ሲሊአና ሽመልስን ይመለከታል የተባለው <ሲ.ዲ >> በግልጽ ችሎት ይታያል ተብሎ ሲጠበቅ ዳኞች ያለ አንዳች ማብራሪያ በግልጽ ችሎት አይታይም በማስረጃነት ተቀብለነዋል ማለታቸው ይታወሳል።

የጦማሪያኑ መፈታት ከፕ/ት ኦባማ ጉዞ ጋር ይያያዝ ዌኢም በሌላ ምክንያት እስካሁን የሚታወቅ ባይኖርም አንዳንዶች የኦባማ ጉዞን እቅድ በምክንያትነት ያነሳሉ።

The post ሰበር ዜና:- ጦማርያንና ጋዜጠኞች ከእስር ተፈቱ appeared first on Zehabesha Amharic.

5ቱ የዞን 9 ጦማርያን አባላት እና ጋዜጠኞች ከአንድ ዓመት በላይ እስር በኋላ ተፈቱ :: የአፈታታቸው ሁኔታ ጠበቃውን ጨምሮ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል

$
0
0

5ቱ የዞን 9 ጦማርያን አባላት እና ጋዜጠኞች ከአንድ ዓመት በላይ እስር በኋላ ተፈቱ ::
የአፈታታቸው ሁኔታ ጠበቃውን ጨምሮ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል
zone 9 today

The post 5ቱ የዞን 9 ጦማርያን አባላት እና ጋዜጠኞች ከአንድ ዓመት በላይ እስር በኋላ ተፈቱ :: የአፈታታቸው ሁኔታ ጠበቃውን ጨምሮ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል appeared first on Zehabesha Amharic.

[ትንታኔ] የናይጄሪዉ ፕሬዝዳንት እና የቦኮ ሐራም አሸባሪ ቡድን ፍጥጫ –ሳዲቅ አህመድ (በድምጽ)

በሄኖክ ሰማእግዜር ላይ ለተፃፈ አስተያየቴ ፤ ይድረስ ለስርጉተ ስላሴና  ለቢላል አበጋዝ

$
0
0

ከጋዜጠኛ ደምስ በለጠ  

 

Voa-amharic-የተከበርሽው ወድ እህቴ  ሰርጉተ ስላሴ አንቺስ እንዴት ሰንብተሽልኛል ።   አዎ !በጋራ መድረካችን ዘ-ሃበሻ የሚወጡትን ፅሁፎችሽን እከታተላለሁ ። ይገርምሻል የጋራ ወዳጃችን ስላንቺ በጥቂቱም ቢሆን አውግተውኝ ስለነበር በተወሰነ ደረጃ የማውቀው ነገር አለ ። እህቴ ስርጉተ ስላሴ፤ እንደዛሬ ግን ውስጥሽን ለማየት አልቻልኩም ነበር። የሰዎችን ሰብአዊ መብት መከበር በተለይ ደግሞ እዚህ አሜሪካን እየኖርን ለምን እንደፈጥጣለን በሚል መሰረት ላይ ያጠነጠነውን ፅሁፌን አንብበሽ ለሰጠሽው የራስሽ አስተያየት፤ አክብሮቴን ልገልፅልሽ እወዳለሁ። አክብሮቴን እንድቸርሽ አቢይ ምክንያት የሆነኝ ደግሞ ከፅሁፍሽ “ውስጤ” መጀመሪያ እስከመጨርሻ ድረስ፤ እኔ በሄኖክ ሰማ እግዜር ላይ ካቀርብኩት የፅሁፉ መሰረታዊ ሃሳብ ሳትወጪ ወይም ሌላ ትርጉም ሳትሰጪ ወይም ሃሳቡን ወደምትፈልጊው አቅጣጫ ሳጥጠመዝዢ  መልስ በመስጠትሽ ነው ። ምን ለማለት እንደፈለግሁ ይገባሻል ብየ እጠብቃለሁ።

 

አንዳንድ ለፅሁፌ የሚሰጡ መልሶች እንደ አለሽበት አገር እንደ ስዊስ ቺዝ የተቀዳደዱ ስለሚሆኑ የትኛው ሐሳብ ላይ ላይ ቆመሽ በየትኛው ቀዳዳ ሾልከሽ የትኛውን እንደምትመልሺ ይቸግራል ። እህት አለም ተመልከቺ ስለሄኖክ ሰማእግዜር ስናገር እዚህ አሜሪካን ሃገር ስለተፈፀም ጉዳይ ብቻ ነው የተናገርኩት ። ኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔ ጋዜጠኞች አላሰረም ፤አላሳደደም፤ የሙስሊም አማኞችን የእምነት ነፃነት አልተጋፋም፤ ሰላማዊ ታጋዮችን አላሳነቀም የሚል ክርክር ውስጥ አልገባሁም ። ስለአንድ ነጥብ ስናገር የምናገረው ስለዚያ ነጥብ ብቻ ነው ። የማሰብና የመናገር ነጻነት ስል  ሌላ ትርጉም ሳይኖረው አንድና አንድ የማሰብና የመናገር ነጻነት ማለት ብቻ ነው ።

 

በምሳሌ ላስረዳ ። ስቴት ኦፍ አሪዞና ውስጥ አንድ ሰው ሌላውን ሰው በስለት ገደለና ለፍርድ ቀረበ ። ሟችን ለሞት የበቃው ሁለቴ መወጋቱ ነው ። ገዳይ ደግሞ ጠበቃ ቆሞሎት ጥፋተኛ አይደለሁም እያለ እየተከራከረ ነው ። “ጥፋተኛ ያልሆንክበትን ምክንያት አቅርብ” ሲባል፤

“ኢንዶኔዥያ ውስጥ በአንዲት ደሴት ላይ የሚኖሩ ጎሳዎች አሉ ። እነዚህ ሰዎች ጎሽ የሚመስለውን በሬያቸውን  በገመድ ዘርጥጠው ከጣሉት በኋላ  ሃምሳ የሚሆኑ ሰዎች ከየአቅጣጫው በአምሳ ጩቤ ወግተው ይገድሉታል ። ሰውነቱን ዘነጣጥለው ስጋውን እየቀቀሉ ይበሉታል ። እኔ የገደልኩትን ሰው በአንዲት አነስተኛ ጩቤ ሁለቴ ብቻ ነው የወጋሁት ። በገመድ አልዘረጠጥኩት፤ በአምሳ ጩቤ ወርሬ አላሰቃየሁት ፤ ስጋውንም ዘልዝየ አልበላሁት በምን ምክንያት ነው እነዚህ በጭካኔ የተሞሉ የኢንዶኔዥያ ሰዎች ሳይከሰሱና ጥፋተኛ ሳይባሉ እኔ ጥፋተኛ ተብየ የምከሰሰው?”

የሚል ክርክር አቀረበ ። ሳሙና ሌላ እንዶድ ሌላ !

 

እኔም እንዳቺው የራሴ ባህሪ አለኝ ። ምን መሰለሽ እመቤት!  አንድ ሰው ከፃፍኩት ርእስ ውጪ መሰረተ-ሃሳቡን ሳይሆን ቃሉን ብቻ ጎትቶ የራሱን ትርጉም ሰጥቶ ሊሞግተኝ ቢሻ መልስ ለመስጠት ይቸግረኛል ። መነሻው የራሱ ትርጉም እንጂ  የእኔ አይደለምና !

 

ሰው! ሰው! ሰው! እያልሽ የሰጠሽው ትንታኔ ለኔም ተመችቶኛል። የምንም ነገር መሰረቱ ሰው ነውና ። ሄኖክም ሰው ነው ። ሰዋዊ መብቱ ይከበርለት ነው ሙግቴ ። የጠላነውን የሄኖክን መብት  ስናከብር የኛንም መብት እያከበርን እንደሆነ መዘንጋት አያስፈልግም ።

 

በፅሁፍሽ ላይ “አያቶቼ የቤተ ክህንት ዓራት ዓይናማ ሊቃናት ነበሩና እናቴ ስትነግረኝ ሲያድጉ መሬትን ሲረገጡ መሬት የታመመች ያህል ወይንም የቆሰለች ያህል እንዲጠነቀቁላት ይቆጣጠሯቸው ነበር። መሬት ላይ መዝለል አይፈቅድላቸውም ነበር።” ብለሻልና በነገረ መለኮት ጥበብ ዘልቋቸው ፤ እውቀትን ተነክረውበት በፍልስፍናው ረቅቀውበት፤ አራት አይን የበራላቸው ፤ ለግኡዟ መሬት ህመም የሚጠነቀቁ ሰዎች የልጅ ልጅ የሆንሺው ስርጉተ-ስላሴ ፅሁፍሽ ላይ “እኛም ስናድግ ጠረኑ እንዲኖር ተደርጎ ቢሆንም፤ አሁን የሚገርምህ ነገር የበለጠ በላቀ ሁኔታ ተፈጥሮን እማይበት መንፈስ ያ የአያት ቅድመ አያቶቼ መንፈስ አፅመ ቅዱስ ቅርስ የላክልኝ – ይመስለኛል። መሬትን ስረግጥም – የበለጠ ከልጅነቴ ጊዜ ተጠንቅቄ ነው።” ያልሺው ድንቅ ነውና በአርአያ ስላሴ ለተፈጠረው ምንኛውም አይነት ለምትወጂውም ሆነ ለማትወጂው ሰው መብት መጠንቀቅ ይጠፋሽል ብዬ አልገምትም ።

 

ሔኖክ ጋዜጠኛ አይደለም ካድሬ ነው ብለሽዋል ።  ለመግባባት እንዲመቸን እኔም ካንቺ ጋር ልስማማና እንደገና ከፅሁፍሽ ልዋስ ። እንዲህ ይጠቀሳል፦ “የኢሠፓ ፓርቲ አባል ሆኜ በካድሬነት ስሠራ በነበረበት ጊዜ እማስበው የፓርቲዬን ፕሮግራም ዓላማና ግብ ተፈጻሚነት ብቻ ነበር። ጉዞዬ አንድ አቅጣጫ ግቤም አንድ ብቻ ነበር። ጋሬ – ዓይነት።”  እንግዲህ ሄኖክም ዛሬ ከዚህ በላይ እንደጠቀሽው አንቺ እህቴ ያኔ የነበርሽበት ደረጃ ላይ ያለ ቢሆንስ? አንቺ ያለፍሽበትን ደረጃና መብት ሊነፈገው ይገባል ? ሌላ ምንም አይነት ትርጉም ሳይሰጠው ማለቴ ነው ። እኔ ሳደርገው ልክ ነው እሱ ሲያደርገው ግን ስህተት ነው እንደማትይኝ ተስፋ አደርጋለሁ ።

 

“ሌላው ያነሳኽው ሰላማዊ ሰልፍን በሚመለከት ነው” ብለሽኛል ። እኔ ያነሳሁት ሰላማዊ ሰልፍን ሳይሆን  የሰላማዊ ሰልፉን አላማ ከሃዲድ መውጣት ወይም መንገዱን መሳቱን ነው ። ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው ።እንደገና ፅሁፌን ተመልከቺው ። እህቴ ስርጉተ  እዚህ ፅሁፍ ላይ ከላይ እንዲህ ብያለሁ እኔም እንዳንቺው ስለባህሪዬ ስገልፅ  ። “አንድ ሰው ከፃፍኩት ርእስ ውጪ መሰረታዊ-ሃሳቡን ሳይሆን ቃሉን ብቻ ጎትቶ የራሱን ትርጉም ሰጥቶ ሊሞግተኝ ቢሻ መልስ ለመስጠት ይቸግረኛል ። መነሻው የራሱ ትርጉም እንጂ  የእኔ አይደለምና !” ፅሁፍሽ ላይ ከዚህ ሌላ ከፅንሰ-ሃሳቡ የወጣ ሃሳብ አላገኘሁም ። ሆኖም ግን አስከትለሽ “ሰላማዊ ሰልፍ የተፈቀደ አመፅ ማለት ነው” ብለሻልና እኔም አንድ ነገር ጥያቄ አለኝ ላንቺ ። ሰላምና አመፅ እንዴት አድርጎ ነው አንድ  የሚሆነው? ሰላማዊ ሰላም ነው ፤ አመፅም አመፅ ነው ።

 

ይገርምሻል እዚህ ዋሽንግቶን ዲሲ ከ50 ሰዎች በላይ ለሰላማዊ ሰልፍ የምትጠብቂ ከሆነ ከዲሲ ገቨርንመንት ፈቃድ ማውጣት ይኖርብሻል ። የተፈቀደ አመፅ ላደርግ ነው የመጣሁት ብለሽ ብትነግሪያቸው እዚያው ነው ለእስር የሚዳርጉሽ ። ጠላትሽ ይታሰር ።

 

ስለአበበ በለው “እንዲህ ዓይነት ሰብዕና ሲያመጣ – አመመኝ።” ብለሻል ። ምን አይነት ሰብዕና ይሆን ያመጣው?  ለኔ ግልፅ አይደለም ።  “ስለ – አዋረደኝ” ያልሺውንም ልገምትና አንቺ ስለመንቶቹ ስትፅፊና በምናብሽ የሳልሺውን በወረቀቱ ላይ ስታወራርጂ አበበን የሳልሺው በራስሽ እይታ ይመስለኛል ። አበበም ፤ “ስርጉተ እባክሽ ስለእኔ ስትፅፊ እንዲህ፡ እንዲህ ብለሽ ፃፊልኝ” እንዳላለሽ እገምታለሁ ። ብሎሽ ከሆነ እውነት ነው አዋርዶሻል ፤ ካላላሽ ደግሞ ውዳሴ ከንቱው የቱጋ እንዳለ ፈልጊው እሱ አላዋረደሽም እላለሁ ። “አንድ ጋዜጠኛ በአድማ መግባት – በፍጹም የለበትም።”  ብለሻል ስለአበበ በለው ። የትኛው አድማ ላይ እንደገባ ግልፅ ስላልሆነልኝ  የምለው ነገር ይቸግረኛል ።

 

በተረፈ ፅሁፌን አንብበሽ የተሰማሽን በጨዋነት በመግለፅሽ አመሰግናለሁ ። በሰነዘርሻቸው ሃስቦች ላይ የምስማማባቸውም ሆኑ የማልስማማባቸው ሃሳቦች ቢኖሩም  የሃሳብ ነፃነትሽን አከብራለሁ ።

ለምወዳቸውም ሆኑ ለማልወዳቸው ሰዎች እኩል መብት እንዲኖራቸው ነውና ጥረቴ በዚህ እንደምንተጋገዝ  ተስፍጋ አደርጋለሁ ።

 

ደሕና ሁኝልኝ እህት አለም።

 

\\\\\\

 

 

ይድረስ ለአቶ ቢላል አበጋዝ በቅድሚያ የከበረ ሰላምታየ ይድረስዎ ። ከርስዎ ጋር በሃሳብ አልተለያየንም። የሄኖክ መብት መከበር እንደነበረበት፤ ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ነገሮች ከመስመር መውጣት እንዳልነበረባቸውና ያም ከብስጭት የመጣ እንደሆነ ገልፀው ልምድ ሊያርመው የሚችል ስህተት ነው ብልዋል ። እኔ መኖሪያየን ቀይሬ አሁን ወደምኖርበት ስቴት እስከተዛወርኩ ድረስ ለ15 አመታት ወያኔን በመቃወም በዋሽንግተን ዲሲ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቻለሁ። ያስታውሱ እንደሆነ በ2005 ኖበምበር 14 ቀን 30ሺህ ኢትዮጵያዊ ሰላማዊ ሰልፍ ውጥቶ ከአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት የተነሳው ሰልፍ እስከ ኮንግረሱ ፅህፈት ቤት ድረስ ተጉዟል ። ያን ሰላማዊ ሰልፍ ክጅምሩ እስከ ፍፃሜው ካስተባበሩትም ከመሩትም ሰዎች አንዱ እኔ ነበርኩ ። ለቨርጂኒያ ዲሲና ሜሪላንድን መገናኛ የሆኑት አውራ መንገዶች ሙሉ ለሙሉ ተዘግተው ነበር።  የሰልፉ አላማ ግብ በወያኔ ጥይት የተገደሉ ወገኖቻችንን መከራ ማሳየትና ብሎም እስር ቤት የተወረወሩት የቅንጅት መሪዎችን መስዋእትነት ማሰብ ነበር ። ታዲያ ሰላማዊ ሰልፉ በራሱ ግብ አልነበረም ። ስለዚህ የሚደረጉ ሰልፎች ሁሉ  በመሰረቱ ግቦች አይደሉም ። የአንድ ትልቅ አላማ ተጨማሪ ማሳያ   ብቻ መሆን ይገባቸዋል ።  ፅሁፍዎ ላይ  እንዳሉት ሄኖክ ወጥ እየዛቀ በላ አልበላ ቤቱ ችሎት ስለሚኖር የኔ ጉዳይ አይደለም ።

 

ሌላው አንዱ አረፍተ ነገርዎ ከቀጣዩ ጋር አልያያዝልኝ እያለ ተቸግሬ ነበር። ስሜት አልሰጥ ያሉኝን እያለፍኩ ግንዛቤ በሰጡኝ ላይ ብቻ ነው መልስ ለመስጠት የሞከርኩት ። እኔ እርስዎን ብሆን የሆሊውድን “ሴልማ” ፊልም የታሪክ ማጣቀሻ አድርጌ ላቀርብ አልደፍርም ነበር ፤ ፊልሙንም አላየሁትም ። ታሪኩ ግን በስቴት ኦፍ አላባማ ፤ ወደርዕሰ-ሰከተማይቱ ሞንትጎመርይ በደቡባዊ የአሜሪካ ስቴቶች ለሚኖሩ ጥቁሮች የመምረጥ መብት መከበር ላይ ያነጣጠረ ሰላማዊ ሰልፍ እንደነበር አውቃለሁ ። አቢይ አላማው ከሰልፉ በፊት ቀድሞ የታሰበበት  ለጥቁሮች የመምረጥ መብትን ማጎናፀፍ ሲሆን ለዚህ መብት መከበር ሰላማዊ ሰልፉን እንደማሳያ ተጠቅመውበታል ።  በአላባማ ስቴት ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኛና በባለስልጣናቱ ድጋፍ  መከራ የደረሰባቸውና ይተደበደቡት ጥቅሮቹ ሰላማዊ ሰልፈኞች ፤ የእርስዎን አባባል ከፅሁፍዎ ልዋስና በብሽቀት ፤ እልህና ምሬት፤ ደብዳቢዎቻቸውን ነጮቹን እነሱም መደብደብ ቢጀምሩ ኖሮ ፤ የሰልፉ አላማ መንገዱን ስቶ የዛሬው ታሪክ ሌላ በሆነ ነበር ።

 

አቶ ቢላል አበጋዝ ጨቋኞችን የማውረድ ስልጣን አለኝ አላልኩም ። ይህ እርስዎ ፅሁፌን ሲያነቡ በራስዎ ልምድ የተረጎሙት ነው ። ደሞ አያስጎምጁኝ ፤ ይህማ ስልጣን ቢኖረኝ ኖሮ በአለም ያሉትን የሰው መብት ገፋፊዎች ሁሉ ገንድሼ ገንድሼ እጥላቸው ነበር ። ወይ ነዶ !

በደጋፊም መልኩ ይሁን በተቃዋሚ ፤ እኔ ጨቋኝ በኔ ላይ እንዲነግስብኝ አልፈቅድም ነው ያልኩት ። ያ የኔ ምርጫና መብት ነው ።

 

“ለሄኖክ መብት የምከራከረውን ያህል ለኢሳትም እቆማለሁ ።” ብለዋል እኔም ከእርስዎ ጎን እቆማለሁ ። በተለይ የሚዲያ  መብት እንዲከበር ስለምጥር ፡ በነፃነት የመናገሪያና ሃሳብን መግለጫ መድረኮችን ሁሉ እደግፋለሁ ። ሁለት ነገሮች ደግሞ አልወደድኩልዎትም ። በምርጫ ይሁን በግዴታ ዝም በል የሚለኝን ሰው እንቀዋለሁ ። የኔ ትምህርቴም የግል ባህሪየም ዝም እንድል አይፈቅዱልኝም ። ስለዚህ ዝም እንደማልል እንዲያውቁልኝ ፍላጎቴ ነው ። በሰዎች መብት ላይ ስንስማማ ቆይተን  ስናበቃ አበበ በለው ላይ  “በሳምንት መጨረሻ አንድ ቀን ለሚመጣ ቱሪናፋ” ብለውታል ። አዘንኩብዎ በጣም አዘንኩ ። አበበ ላይ ቂም የያዙበት ነገር እንዳለ ተሰማኝ ። አዲስ ድምፅ ራዲዮም በነጻዋ አገረ አሜሪካ ፡ በነጻነት ሃሳብን መግለጫ መድረክ ነውና የእሱም መብት እንዲከበርለት መጣር ይኖርብናል  ።

 

አበበ በለው የጻፈውን ደብዳቤ በተመለከተ የጠቀስኩት አሁንም ከመብት ጋር የተያያዘ እንጂ እርስዎ እንዳሉት አርበኞች ግንቦት 7ን ለመጎሸም እንዳልነበረ ሊያውቁልን እፈልጋለሁ ፤ ይህ የርስዎ ትርጉም ነው ። እዚህ ላይ ፍንትው ብሎ እንዲታይዎ የምፈልገው አንድ ነገር አለ ።እኔ አርበኞቹን እንደቱሪስት መስህብ ለቀናት ብቻ አይደለም ጎብኝቻቸው የመጣሁት ። ወይም በሪሞት ኮንትሮል በቴሌቪዥን መስኮት አይደለም የማውቃቸው ። እኔ አርበኞቹን ደጋግሜ ተመላልሼ ፤ አንዴ እንዳውም ለስድስት ወራት ቆይቼ የሚበሉትን በልቼ የሚጠጡትን ጠጥቼ አብሬያቸው ኖሬ አውቃቸዋለሁ ። በኢሳትም ሆነ በሌሎች ሚዲያዎች የሚቀርቡትን ተዋጊዎች ፎቶዎች በስም እየጠቀስኩ ልነግርዎ እችላለሁ ።  የትኞቹ የድምሕት የትኞቹ ደግሞ የአርበኞች እንደሆኑም እየለየሁ ልነግርዎ እችላለሁ ።  ስለዚህ በኔ በኩል የምጎሻሸምበት ምንም ምክንያት የለም ።

 

እንዲያውም የኤርትራ ልምዴንና ያየኋቸውን ሁኔታዎች ሁሉ ፤ በቅርቡ በተከታታይ ካሉኝ የፎቶና የፊልም ክምችት ጋር እያያያዝኩ  አቀርባቸዋለሁና  እንዲከታተሉ እጋብዛለሁ ።

 

አዎ መብት ማክበርን ልማዳችን እናድርግ ። ሮም ሲሄዱ እንደሮማውያን እንደሚባለው የምንኖርበትንም አገር ህግ ማክበር የተገባ ነውና እናክብር ። አቶ ቢላል አበጋዝ ሆይ ፤ ጌታ ክርስቶስ ጤናዎን እንዲጠብቅልዎ  እፀልያለሁ ። ቸር ይግጠመን ።

 

 

 

ጁላይ 8 2015 ፡

ከላስ ቬጋስ ኒቫዳ ።

 

 

 

 

 

 

 

The post በሄኖክ ሰማእግዜር ላይ ለተፃፈ አስተያየቴ ፤ ይድረስ ለስርጉተ ስላሴና  ለቢላል አበጋዝ appeared first on Zehabesha Amharic.


የ ያ ትውልዱ አቶ ክፍሉ ምንድን ነው የሚሉ? –ይገረም አለሙ

$
0
0

 

kiflu tadesseአቶ ክፍሉ ታደሰ ወዴት እየሄድን ነው በሚል ርዕስ ኢህአፓ ሲፖዚየም ላይ ያቀረቡት ያለውን  ጽሁፍ ዘሀበሻ አስነበበን፡፡  ጽሁፉን ማንበብ ስጀምር አቶ ክፍሉ የያ ትውልድ ወኪል ናቸውና፣ ከጉልምስና እስከ እርጅና በፖለቲካው ያሳለፉ/ያሉ ናቸውና በጽሁፋቸው መነሻና መድርሻ የጠቀሱትን የእንቧይ ካብ መሰረት ካኖሩ ሰዎችም አንዱ ናቸውና ወዘተ ትናንትን አስታውሰው የ40 አመቱ ትግል መስዋእትነት እንጂ ድል ያልታየበትን ምክንያት ይነጉሩናል፣ ዛሬን ዳስሰው ከወያኔ አገዛዝ የመላቀቂያውን መንገድ ያመላክቱናል፣ ስለነገ አልመው ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መመስረት ስለመቻያው ዘዴ ይጠቁሙናል የሚል ጉጉት ነበረኝ፡፡ ግና በዚህ መልክ አላገኘሁትም፡፡  በአንድ ነገር ግን ከአቶ ክፍሉ እስማማለሁ፡፡ ኢህአዴግን ለማሸነፍ የሚደረገውን ትግል ያክል ከዛስ በኋላ ለሚለው ዛሬውኑ መስራት እንደሚገባ፡፡

አቶ ክፍሉ ምኒልክን  ለውይይት የቀረበ ጽሁፋቸው  አብይ ማጠንጠኛ የማድረጋቸው ምክንያት ባይገባኝምና ከጽሁፉም መረዳት ባይቻልም ምንሊክ፣ የተፋላሚ ሀይሎች አጀንዳ የሆኑበት ወቅት ነው በማለት ምኒልክን በተመለከተ አለ ያሉትን ልዩነት  ነግረውናል፡፡ ስለ ያ ትውልድ እንደ ሁልግዜአቸው ድክመት ስህተቱን ሳይነኩ አስታውሰውናል፡፡ እኛና እነሱ አንድነትና ልዩነታችን ብለው አንድነታቸውን ሳይነኩ  የልዩነቶቻቸው ማሳያ ያሉዋቸውን  አቅርበውልናል፡፡እንዲህ እንዲህ እያሉ ስጋት አጭረው ጥያቄ አስቀምጠው ሰባት ገጽ የሄዱበት ጽሁፍ በቅጡ ሲታይ  ለማስተላለፍ የፈለጉት ወቅታዊ ጉዳይ ሶስት መስመር በማይሞላ የሰፈረው ሆኖ እናገኘዋለን ፡፡  እንዲህ ነው የሚለው፡፡

“በአጠቃላይ፣ በአሁኑ ሁኔታ የኢትዮጵያን ችግር ባልተማከለና በተናጠል በሚካሄድ የትጥቅ ትግል ለመፍታት የሚደረገው ሙከራ፣ መፍትሄ በማምጣት ፈንታ አገሪቱ እንድትበታተን ተጨማሪና አጋዥ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል መገንዘብ ተገቢ ነው። ”

ጥያቄ አንድ፤ ይህን ለማለት ይህ ወቅት ለምን ተመረጠ?

እንደለመድነው ማለባበሱን ካልመረጥነው በስተቀር በግልጽ መረዳት የሚቻለው ይህ ወቅት የተመረጠው አርበኞች ግንቦት ሰባ ውጊያ ጀመርኩ በማለቱ ነው፡፡ሁለቱም ድርጅቶች አላማና የትግል ስልታቸው በውል ይታወቃል፤ ተዋሀድን ሲሉ እየተዘጋጀን ሲሉ ወራ ተቆጥረዋል፣ታዲያ አቶ ክፍሉ የአርባ አመት ልምዳቸው የሀገራችን ችግር በትጥቅ ትግል አይፈታም የሚል ድምዳሜ ላይ እድርሶአቸው ከሆነ ለምን ያኔ  ይህን ሀሳብ አላነሱም፡፡ ወይንስ አያደርጉትም ብለው ንቀዋቸው?

ጥያቄ ሁለት፣ ባልተማከለና በተናጠል ሲሉ የእነተባበርን ጥሪ አልሰሙም ማለት ነው?

ጥድቁ ቀርቶ በወጉ በኮነነኝ እንዲሉ በአንድ ማእከል እየተመሩ መታገሉ ቀርቶ  ተደጋግፎ መቆም እጅ ለእጅ ተያይዞ መራመድ ቢቻል መልካም ነበር፡፡ ግን ለዚህ አልታደልንም ፡፡ አሸነፈና አቸነፈ በሚል የፊደል ልዩነት ሳይቀር እስከ መገዳደል የደረሰው የእነ አቶ ክፍሉ ያ ትውልድ ያመጣው  ያለመስማማት በሽታ እስከ ዛሬ መድሀኒት አልገኝለት ብሎ  በግለሰብ ደረጃም ሆነ በፓርቲ መተባበሩ ቀርቶ መከባበሩ አይታይም ፡፡  የወያኔ አገዛዝ ሀያ አራት አመት የዘለቀውና መቶ በመቶ አሸነፍኩ እያለ ለመመጻደቅ የበቃውም በዚሁ ምንያት መሆኑን አሌ የሚል አይኖርም፡፡ ታዲያ ለበሽታው መድሀኒት መፈለግ ነው  የሚበጀው ወይንስ እንደምንም ብለው አንድ ርምጃ ለመሄድ የሚጥሩትን ለማሰናከል መሞከር?

ብዙዎች ቃልና ተግባራቸው አልገጥም እያለ በምንቸገርበት፤ብዙዎች ያልሆኑትን ነን እያሉ በሚያጭበረብሩበት  ብዙዎች ከተግባሩ ሳይኖሩ በቃላት እያደናገሩ በሚኖሩበት ወዘተ ወቅት ጥቂቶች  ቃላቸውን በተግባር ማሳየት ሲጀመሩ ያልተማከለና በተናጠል የሚካሄድ ትግል  በማለት ትግሉን ለማሳነስና ይበልጡንም በህብረተሰቡ ውስጥ ፍርሀት ለማንገስ መሞከር ተቢ አይሆንም፡፡  ትግሉን በተግባር የጀመሩት እነዚህ ወገኖች ትንሽ ትልቅ ሳንባባል፤ሰበብ ምክንያት ሳናበዛ ኢትዮጵያን ከወያኔ አገዛዝ ለማላቀቅ ነው የምንታገለው የምትሉ ሁሉ እንነጋገር እንተባበር በማለት ከመጠየቅ አልፈው ሲለምኑ ሰምተናል፤ምስክሮች ነን፡፡ አላማቸው ራስን ለቤተ መንግሥት ማብቃት ሳይሆን የኢትዮጵያን ሕዝብ የስልጣን ባለቤትነት ማረጋገጥ የሆነ ወገኖች ተጠራርተው በውህደትም በመተባበርም አቅም ፈጥረው አንድ ርምጃ መራመድ ሲጀምሩ ፈጥኖ ወጥቶ በተናጠል የሚካሄድ ያልተማከለ ትግል በማለት የአግድሞሽ መኮነንና በህብረተሰቡ ውስጥ ስጋት ለመጫር መመኮር የመጣንበት የሴራ ፖለቲካችን በአርባ አመቱም አለማረጀቱን ነው የሚያሳየው፡፡

ጥያቄ ሶስት አቶ ክፍሉ   ተቆርቋሪ የሆኑ ወገኖች አንድ ጥያቄ ሊያነሱ ይገባል፤ ከፊታችን የተደቀነው ትልቁና ሀገራዊው ግዴታ ኢህአዴግን መጣል ወይስ አገርን ማዳን የሚል ነው? ሲሉ ምን ማለታቸው ነው?

ኢህአዴገን ማሸነፍና አገርን ማዳን አንድ ላይ የሚታዩና የሚከናወኑ ሆነው ሳለ የተለያዩ ተግባራት ሆነው ሲበዛም ጥያቄ ተደርገው መቅረባቸው  በተለይ ደግሞ ከተነሱበት ወቅት አንጻር ሲታዩ በውስጣችን ስር ከሰደደው  የመደጋገፍ ሳይሆን የመጠላለፍ ፖለቲካ ዛሬም አለመላቀቃችንን  የሚያሳይ ነው፡፡ ወያኔዎች እኛ ከሌለን ኢትዮጵያ ትበታተናለች የሚሉት አይነት መልእክትም በውስጡ ይታያል፡፡ ወያኔን መጣል ሀገር የማዳን ከፊል ተግባር ነው ኢትዮጵያን የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት፤ ሰብአዊ መብት የተከበረባት ዴሞክራሲያዊት ሀገር ማድረጉ ደግሞ ቀጣይ ተግባር ነው፡፣ስለሆነም ሁለቱ ወይስ በሚል አማራጭ ተነጣጥለው መቅረብ አይኖርባቸውም፡፡ ኢህአዴግ በሥልጣን ላይ እያለ ኢትዮጵያን ማዳን የሚቻልበት ዘዴና መንገድ አለ ካተባለ በስተቀር፡፡

ያ ትውልድ ደርግን እየተቃወመ በአንጻሩ የእኔ ብቻ ትክክል በሚል አስተሳሰብ፤ ተደጋግፎ ማለፍን ሳይሆን ጠልፎ መጣልን በተካነ የሴራ ፖለቲካ  ርስ በርሱ እስከመገዳደል በደረሰ ጠላትነት እየተቀዋወመ እንዳይሆኑ ሆኖ መከራ አወረሰን፡፡

የኢህአዴግ ተቀዋሚዎችም(አርባ አመትም አራት አመትም የሚሆናቸው በውጪም በውስጥም የሚኖሩ በሰላማዊም በጠመንጃም እንታገላልን የሚሉ)  ወይ ተባብረው መታገል ወይ ተከባብረው አንተም በመንገድህ እኔም በመንገዴ ብለው መታገል ተስኖአቸው ከጥሎ ማለፍ ጨዋታ መውጣት፣ ከሴራ ፖለቲካ መላቀቅ አልሆንልህ ብሎአቸው  ወያኔ ተደላድሎ እንዲገዛን አበቁት፡፡አንድ ተቀዋሚ ፓርቲ ጠንክሮ ታግሎ ለስልጣን ከሚበቃ የወያኔ አገዛዝ ቢቀጥል የሚመርጡ ይመስል ቀና ብሎ መራመድ ሲጀምርና ጠንከር ብሎ መታገሉ ሲታይ ጠልፎ ለመጣል የተካኑበትን ስራ ይጀምራሉ  ሴራ ይጎነጉናሉ፡፡በዚህም ተያይዞ ዘፍ ይሆንና፡ለገዢው ምቹ ሁኔታ ይፈጥራሉ፡፡

እነ አቶ ክፍሉ በግዜአቸው ታግለዋል፣ከመሪዎቹ በላይ ያ ወጣት በድፍረቱ በጽናቱ በተግባር ሰውነቱ ይደነቃል፡፡ ትግላቸው ግን መሪዎቹን ለስደት ወጣቱን ለእልቂት ሀገሪቱን ለወታደራዊ አንባገነን አገዛዝ ከመዳረግና እስከ ዛሬ ለቀጠለው ፖለቲካዊ ችግራችን አንዱ ምክንያት ሆኖ ከመጠቀስ ባለፈ ያስገኘው ድል ያስመዘገበው ውጤት የለም፡፡ በመሆኑም ዛሬ በግል ከእነ አቶ ክፍሉ በወል ከኢህአፓ (በተግባር ካለ)የሚጠበቀው አቶ አሰፋ ጫቦ ደጋግመው ይሉት እንደነበረ የድርሻ ተጠያቂነትን በድፍረት ወስዶ የእንቧይ ካብ ያሉትን መሰረት ያቆሙ እነርሱ ናቸውና የእንቧይ ካቡ ወደ ድንጋይ ካብ የሚቀየርበትን መንገድ ማመላከት ነው፡፡ የአሸነፈና አቸነፈ ልዩነት ያመጣውን መዘዝና ያስከተለውን እልቂት ያውቃሉና ልዩነትን በውይይት መፍታት እንዲቻል ግንባር ቀደም ሆኖ በቃል ሳይሆን በተግባር መሰለፍ ነው፡፡ተነጣጥሎ ትግል ለየብቻ መውደቅን እንደሚያስከትል በተግባር አይተዋልና የተራራቀውን አቀራራቢ የተጣላውን አስታራቂ ሆኖ መቆም ነው፡፡

ትናንት ዛሬ አይደለም፣ የሀገሬ ገበሬ እንኳን ይህን ሲገልጸው በትናንት በሬ ያረሰ የለም ይላል፡፡እናም የትናንቱ አልጠቀመንምና ለዛሬ የሚበጀንን ለነገም ወንዝ የሚያሻግረንን  በጋራ ማየቱ መልካም ይሆናል፡፡ እኔ ከሌለሁበት፣ እኔን ለስልጣን የማያበቃኝ ከሆነ፤ እኔ ካልመራሁት ወዘተ ከሚል ለመተባር ጠንቅ ከሆነና ትግሉን ሲያኮላሽ ከኖረ አስተሳሰብ ወጥቶ ኢትዮጵያን ከወያኔ አገዛዝ በማላቀቅ የህዝብ የሥልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባት ሀገር ለማድረግ በግል፣ በድርጅት ብሎም በጋራ እንዴት እንንቀሳቀስ ብሎ ሁሉም የሚችለውን ለማበርከት መነሳቱ እንጂ ለማደናቀፍ ማለሙ ትናንትም አልበጀ ዛሬም ሆነ  ወደ ፊትም አይበጅም፡፡ ስለሆነም መጠላለፉ መወራረፉ ያለፈው ይበቃል፡፡  በዚህቺ የሎሬት ጸጋየ ገብረ መድህን ግጥም ሀሳቤን ልቋጭ፡

መተባበር የተሳነው ስንቱ ልቡ ቲአቲረኛ

ዲስኩር ፈታይ ላንቲከኛ

ቆምኩልህ ለሚለው ወገን ተአማኒነቱን ረስቶ

በትረ መንግሥት ለመጨበጥ ለነገ ሥልጣን ዋዥቶ

የዓለምን በደም መታጠብ እንዳላየ ሆኖ አይቶ

በተቃውሞ መተባበር ጥቅሜን ይጎዳል ሲል ሰግቶ

ልክ እንደ ገደል ማሚቶ

ይዋነያል በልሳኑ የራሱን ቃል ራሱ ሰምቶ፣

ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይጠብቅ፣

The post የ ያ ትውልዱ አቶ ክፍሉ ምንድን ነው የሚሉ? – ይገረም አለሙ appeared first on Zehabesha Amharic.

የህዝበ ሙስሊሙ ኮሚቴ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ የጥብቅና ሙያቸው ኮሚቴዎቹ የጥፋተኝነት ብይን በተላለፈበት ቀን መሰረዙ ታወቀ

$
0
0

ጠበቃ ተማም አባቡልጉ

ጠበቃ ተማም አባቡልጉ


ሰበር ዜና ቢቢኤን
ቢቢኤን ሃምሌ 2/2007

የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ጠበቃ የሆነው ጠበቃ ተማም አባቡልጉ በፍርድ ቤት ላይ በሚያደርጋቸው ክርክሮች በተለይም መንግስት ከጅሃዳዊ ሀረካት ጀምሮ የሰራቸውን ሸፍጦችና ኢትዪጲያዊ ውስጥ የፍትህ ስርአቱን ዝቅጠት በመረጃና በህግ በማጣቀስ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ በማጋለጣቸው ምክኒያት ከዚህ ክስ ተመስርቶባቸው እንደነበር ይታወቃል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ማስፈራሪያና ዛቻዎች ከመፈጸማቸውን ሌላ እብድ በሚመስል ሰው በመላክ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ይታወቃል፡፡

ይህ ሁሉ ግፍ ተፈጽሞባቸው በጀግንነት ከስራቸው ያልቆሙት እንዲሁም የህግ ክፍተቶችን ጭምር በማጋለጥ፤ ከኮሚቴዎቹ በተጨማሪ መንግስት የከሰሳቸው የነ አብራ ደስታ ጠበቃ የነበሩትን ተማም አባቡልጉን መንግስት በኮሚቴው ላይ የጥፋተኝነት ብይን ባስተላለፈበት እለት የጥብቅና ሙያቸውን ፍቃድ ፍትህ ሚኒስትር መሰዘረዙ ታውቋል፡፡
አቶ ተማም አባቡልጉ ያለ ምንም ፍርሃት እውነታውን በሚዲያዎች ላይ በማጋለጥ ታላቅ አስተዋጾ ያበረከቱ፤ በብዙዎች ዘንድ በጀግንነት የሚጠሩ ፤ ፤ለሙያቸው ያደሩ ጠበቃ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ቢቢኤን ጠበቃ ተማም አባቡልጉን በማነጋገር ተጨማሪ መረጃ ይዞ የሚቀርብ ይሆናል::

The post የህዝበ ሙስሊሙ ኮሚቴ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ የጥብቅና ሙያቸው ኮሚቴዎቹ የጥፋተኝነት ብይን በተላለፈበት ቀን መሰረዙ ታወቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

2 ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን እስር ቤት ሆና ያሸነፈችው ርዕዮት ዓለሙ

$
0
0

reyot
ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ተፈታች

(ዘ-ሐበሻ) ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት ዓለሙ ትናንት ጁላይ 9 ቀን 2015 ዓ.ም የ እስር ጊዜዋን አጠናቃ ተፈታች። የመንግስት ሚድያዎች ጋዜጠኛዋ የአመክሮ ጊዜ ተሰጥቷት እንደተለቀቀች አድርገው ቢዘግቡም እውነታው ግን ርዕዮት የአመክሮ ጊዜዋን ጨርሳ የነበረው ባለፈው ጥቅምት ወር ነበር።

በሽብር ወንጀል ተከሳ 14 ዓመት ተፈርዶባት የነበረችው ይህችው ጋዜጠኛ በይግባኝ ቅጣቱ ወደ 5 ዓመት ዝቅ ብሎላት የነበረ ሲሆን እነዚህን ዓመታት በእስር አሳልፋ ከቤተሰቦቿ ጋር ተቀላቅላለች።

በእስር በነበረችበት ወቅት በሚደርስባት የሰብአዊ መብት ጥሰት የርሃብ አድማ እስከማድረግ ደርሳ የነበረችው ርዕዮት እህቷ እስከዳር ዓለሙ ሳይቀር እንዳትጠይቃት ታግዳ እንደነበር የሚታወስ ነው።

ባለቤቷ ጋዜጠኛ ስለሺ ሃጎስ አንድነት በጠራው ስብሰባ ላይ ተገኝቷል በሚል በፖሊስ ጉዳት የደረሰበት መሆኑም ይታወሳል። ር ዕዮት እስር ቤት እያለችም የዩኔስኮን የፕሬስ ነፃነት አዋርድ እንዲሁም በዓለምአቀፉ የሴቶች የመገናኛ ብዙኃን ድርጅት – International Women’s Media Foundation – IWMF “በጋዜጠኝነት ለተሠራ ጀብዱ ሽልማት” የሚል አዋርዶችን አሸንፋለች።

The post 2 ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን እስር ቤት ሆና ያሸነፈችው ርዕዮት ዓለሙ appeared first on Zehabesha Amharic.

ጥቂት ስለአርበኞች ግንቦት 7 ተዋጊ አርበኛ ሃና –ከጋዜጠኛ መሳይ መኮንን

$
0
0

የርዕዮትን: የማህሌትንና የኤዶምን ከህወሀት ማጎሪያ እስር ቤት ነጻ መሆን ውስጤ የፈጠረውን ደስታ እያጣጣምኩ እያለ ድንገት በትዝታ አምስት ወራት ወደ ሁዋላ ሄድኩኝ- -ከኤርትራ በረሃ:: ይህቺን ኢትዮጵያን ከህወሀት እስር ቤት ነጻ ለማውጣት ብረት ያነሳችውን እህታችንን ላስተዋውቃችሁ::
arbegnoch
አርበኛ ሀና ትባላለች:: የ23 ዓመት ወጣት ናት:: የአርበኞች ግንቦት 7 ተዋጊ ወታደር ስትሆን በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ተሳትፋለች:: በኤርትራ በረሃ ስማቸው ከጀግንነት ጋር ከሚነሳላቸው አርበኞች መሃል ሀና ግንባር ቀደም ናት:: ስሟ በአርበኞች መንደር ገኖ ይነሳል::
………አንድ ጊዜ ላይ እንዲህ ሆነ::

ሀና የምትገኝበት ወታደራዊ ክፍል ግዳጅ ይሰጠዋል:: እስከ 30 የሚጠጋ አርበኛ የሚገኝበት ይህ ቡድን የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጦ በመግባት በአንድ የህወሀት ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት ፈጽሞ የመመለስ ግዳጅ ተሰጥቶት ይሰማራል:: ሀና መትረየሷን ታጥቃለች:: ጠዋት ከመነሻቸው ወደ ኢላማ ቦታው ገሰገሱ:: እንደታቀደው ድንገተኛ ጥቃቱ ተሰንዝሮ የታሰበውን ጉዳት አድርሰው ወደ ካምፓቸው ሊመለሱ እያለ ድንገት በህወሀት ሰራዊት ይከበባሉ:: ምን ይደረግ? ብዙ ቁጥር ያለውንና እስከአፍንጫው የታጠቀውን የህወሀት ሰራዊት መክቶ ወደ ካምፕ መመለስ ከባድ ሆነ:: የዚህን ጊዜ ነበር አንድ ጀግና ታሪክ የሰራችው:: ….ሀና::

መትረየሷን መተረች:: ገዢ መሬት ያዘች:: ቦታዋን አስተካከለች:: ….እሷ መስዋዕት ሆና የትግል ጓዶቿን ልታስመልጥ ወሰነች:: ምሽት እየመጣ ነው:: ጓዶቿ ተስናበቷት:: ዳግም በህይወት እንደማያገኟት ታወቃቸው:: …እሷ መትረየሷን ወደ ህወሀት ሰራዊት ለቀቀችው:: ለጓዶቿ ሽፋን በሚሰጥ ስልት አስካካችው:: …ፍልሚያው በአንዲት ሀና እና በህወሀት ሰራዊት መሃል ሆነ:: የሀና መትረየስ ያስካካል:: ጓዶች በዚያ ሽፋን ወደ ጦር ካምፓቸው እየተመለሱ ነው:: የሀና የመትረየስ ድምጽ እየራቃቸው ነው:: እነሱ ይተርፉ ዘንድ አንድ አርበኛ መስዋዕት መሆን ግድ አለ:: በተሰጣቸው ግዳጅ ውጤታማነት እየተደሰቱ የሃናን መስዋዕትነት እያወደሱ ከካምፓቸው ምሽት ላይ ደረሱ:: በአርበኞች መንደር ህይወት እንዲህ ናት:: ታጋይ ይሰዋል:: ትግል ይቀጥላል::

…እኩለ ሌሊት ከመድረሱ በፊት ነው:: ጭው ካለው የኤርትራ በረሃ አንድ ሰው ወደ አርበኞቹ መንደር ከኢትዮጵያ ድንበር አቅጣጫ ይገሰግሳል:: በርቀት የተመለከቱት የሌሊት የካምፕ ተረኛ ዋርዲያዎች(ጠባቂዎች) መሳሪያቸውን አስተካክለው ጣት ከቃታ አገናኝተው ወደ ካምፑ እየገሰገሰ ያለውን ሰው ይጠብቃሉ:: ውድቅት ሌሊት ስለነበር ማንነት መለየት አልተቻለም:: የሚገሰግሰው ሰው እየቀረበ ሲመጣ ዋርዲያዎቹም ኢላማቸውን አስተካክለው እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጁ:: ….ሰውዬው ቀረበ:: ሴት ናት::ሃና:: ዋርዲያዎቹ አላመኑም:: የዕለቱን የይለፍ ቃል ጠየቋት:: መለሰችላቸው:: ደክሟታል:: ተአምር የሚያሰኘው ከዚይ የህወሀት ሰራዊት ከበባ ማምለጧ አይደለም:: ሁለት የጦር መሳሪያዎችንም ማርካ ተሸክማለች:: ከሷ መትረየስ ጋር ሶስት:: ዋርዲያዎቹ በሚያዩት ነገር ተደንቀዋል:: በአርበኞች መንደር ስለ ሃና እርም ወጥቷል:: ጉድ ተባለ::

….ሃናን በአካል ሳገኛት በጣም ቁጥብ ነበረች:: ብዙ አትናገርም:: ታሪኳን እንድታጫውተኝ ያደረኩት ጥረት አልተሳካም:: ሲበዛ ዝምተኛ ናት:: ጀግና አይናገርም::
…ሃና ከሰሞኑ ውጊያዎች በአንዱ እንደተሰለፈች እገምታለሁ:: ልብን በኩራት በሚያሞቀው ጀግንነቷ ሁሌም አስታውሳታለሁ:: የጣይቱ ልጅ!!!!!

The post ጥቂት ስለአርበኞች ግንቦት 7 ተዋጊ አርበኛ ሃና – ከጋዜጠኛ መሳይ መኮንን appeared first on Zehabesha Amharic.

ትምህርት ሰጭ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ስብሰባ በዋሽንግተን ዲሲ * –ከእሸቴ ውለታው

$
0
0

ዘ-ሐበሻ ተከታታይ ቭዲዮዎችን እስከምትለቅ ድረስ ይህን ዘገባ ያንብቡ

ዘንድሮ ለ32ኛ ጊዜ በሰሜን አሜሪካ የስፓርት ፈዴሪሽን የተዘጋጀው የእግር ኮስ ጨዋታ በሜሪላንድ ግዛት ዋሽግተን ነበር ሜሪላንድ በውብ ኢትዪጵያውያን አምራና ተውባ ነበር የከረመች።
Elias Kifle

Kinfu Asefa

Soliana

Asegede Gebresilase

Aklog Birara

Dawit Tegegne
የዘንድሮ እግር ኮስ ዝግጅት እንደወትሮው ነገር ግን በጣም ባማረና በደመቀ ሁኔታ የእግር ኳስ ጨዋታው ፣ የንግድ ልውውጡ፣ባህላዊናዘመናዊ የሙዚቃ ፊስቲቫሉ ፣ኢትዪጵያን መሰረት ያደረገ ፓለቲካ ስብሰባዎችና ሰላማዊ ሰልፎች ወዘተ የተከናወነበት ነው።

በሁሉም ክንውኖች አቅም እንደፈቀደ ተሳታፊና ታዳሚ ሁኛለሁ ከሁሉ በላይ አቅሌን የሳበኝና የማረከኝ በአዲስ ድምፅ ራዲዪ በአበበ በለው አዘጋጅነት የነበረው የጋዜጠኞችና የሜዴያ አዘጆች ሚና በኢትዪጵያ የዲሞክራሲና የነፃነት ትግል ምን መሆን አለበት? በሚል የመወያያ ርእስ የቀረበው ውይይት እጅግ አስተማሪና ሚዲያዎች ያለባቸውን ችግር በግልፅ የተነጋገሩበት በመሆኑ በአይነቱ የተለየ ነበር።

በዚህ ስብሰባ በፓናል የውይይት አቅራቢ የነበሩት ታዋቂው፣ አንጋፋው ኢኮኖሚስትና አክትቢስት ዶ/ር አክሎክ ቢራራ ፣ የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ሶሊያና ሽመልስ፣የኢትዩጵያ ሪቭው አዘጋጅ ኢልያስ ክፍሌ፣የኢትዪጵያ ሜዲያ ፎረም (EMF) አዘጋጅ ክንፉ አሰፋ፣ ታዋቂው አክቲቭስት አበበ ገላውና የአዲስ ድምፅ አዘጋጅ አበበ በለው በየተራ ርእሱን መሰረት በማድረግ በሳልና ጠቃሚ ንግግር አድርገዋል።

የስብሰባው መሪ አቶ ዳዊት ተገኘ በመጀመሪያ ንግግራቸው ባለፈው ሀያ አራት ዓመት አምባገነኑን የወያኔን ኢህአደግ አስተዳደር በህዝባችን ላይ የሚደርሰውን ኢስብአዊ የሆነ ጭፍጨፋና ግድያ፣ ህዝባችንን በዘርና በኃይማኖት በመከፋፈል ማቆሚያ የሌለው እልቂትና ፍጅት በመፍጠር የሚሰራቸውን ሴራና ደባዎችን በማጋለጥና መረጃ በመስጠት፤ በተለይ በምርጫ 97 ኢትዪጵውያን ጋዜጠኞች የሰሩት ስራናያደረጉት አስተዋፅኦ በታሪክ የሚረሳ አይደለም።

እንደ እውነቱ ከሆነ ይህን ሥርአት ፊት ለፊት የታገሉትና እርቃነን ሥጋውን በማጋለጥ ለኢትዪጵያ ህዝብና ለዓለም ህብረሰብ ያሳወቁት ኢትዪጵያውያን ጋዜጠኞችና የሜዴያ ሰዎች ናቸው። በውጭም ማለት በዲያስፓራው ህዝቡን በማነቃነቅና በማደራጀት መረጃ በመስጠት፣ ትግሉና ምርጫ ለውጤት እንዲደርስ ከማንም በላይ ከፊት ሁነው የሰሩት በውጭ አገር ያሉ ጋዜጠኞች ና የሚድያ ሰዎች ናቸው። ለአብነት ያህል ከመሀላችን ካሉት የኢትዪጵያ ሪቭው አዘጋጅ ኢልያስ ክፍሌ፣ የኢኤምኤፍ (EMF) አዘጋጅ ክንፈ አሰፋ፣ የአዲስ ድምፅ አዘጋጅ አበበ በለው እነዚህ ወንድሞች በምርጫ 97 በተደረገው ትግልና ለቀጣዩ የዲሞክራሲ ና የነፃነት ትግል መሪ ተዋናይና ግንባር ቀደም አንቂና አስተባባሪዎች ናቸው ለእዚህ ነው አምባገነኑ የወያኔ ሥርዐት በለሉበት የረጅም አመት እድሜ የፈረደባቸው ዘረኛውን የወያኔ ከፋፋይና ፀረ ዲሞክራሲና አፋኝ ሥርዐት በሰላ ብእራቸው በማጋለጣቸውና በመታገላቸው በአምባገነኑ ሥርአት ሰለባ ሁነው በመከራ ቤት በእስር የሚገኙትን እነ እስክድር ነጋን፣ርእዪት አለሙ፣እነ ተመስገንን፣እነ ውብሸትን ወዘተ ስናስታውስ እና ለዲሞክራሲና ለነፃነት በመናገራቸው ና በመፃፋቸው ከግፈኛው ስርአት ደህንነቶች አምልጠው የሚወዶቸውን ልጆቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ተለይተው ሳድይወድ በግድ ተሰደው በባእድ ሀገር በአፍሪካና በመካከለኛ አረብ በስደትና በመከራ ያሉት ስናስውስ የኢትዩጵያ ጋዜጠኞችና የሚድያ ሰዎች ይህን ሥርአት ምን ያህል እንደታገሉትና ዋጋ እንደከፈሉበት የሚሳይ ነው።

አቶ ዳዊት ንግግሩን በመቀጠልበእስር፣ በግዞትና በስደት የሚገኙ ጋዜጠኞች መስዋአትነት የሚስተምረን ሁለት አደራ አለ። አንደኛው ለማይቀረው የነፃነት ትግል በርትተንናተጠናክረን እንድንታገል። ሁለተኛው ኢትዪጵውያን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሊኖራቸው ስለሚገባ የዲሞክራሲ መብት ማለት የመናገር፣የመፃፍ፣የመደገፍ፣ የመቃወምና የመተቸት ወዘተ.. እንደ ሰው ልጅ ማግኘት ማስከበርና ለዚህ የዲሞክራሲ መብትና ነፃነት በየትኛው ደረጃና በየትኛውም ቦታ መታገል እንዳለብን; በእነርሱ መስዋእትነት አስተምረውናል:: አደራ ብለውናል:: ከዚህ አንፃር እናንተ በውጭ ማለት በዲያስፖራ የምትገኙ ጋዜጠኞች ና የሜዴያ ሰዎች ምን ያህል ነፃ ናችሁ? ለህዝብ የምታቀርቡት ዘገባና ዜና ምን ያህል ከቀረቤታና ከፓለቲካ ድርጅት አፍቃሪነት ገለልተኛ ነው? የፓለቲካ ድርጅቶች ገለልተኛና ነፃ ሜዲያ መሆናችሁን አምነው ምን ያህል መብቶቻችሁን ያከብራሉ? የመሳሰሉት ጥያቄዎች በማቅረብ ለስብሰባው ታዳሚ ውይይቱን ክፍት አድርገውታል።

በቤቱ ተመሳሳይ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበዋል:: አብዛኛውን ከቀረቡት አስተያያቶች በአብዛኛው ያነጣጠረው የግለሰቦችን የመናገርናየመተቸት መብት እየተጋፋ ያለው ግንቦት ሰባት በሀገራችን ጉዳይ በተለይ ኤርትራና ሻዕቢያ በተመለከተ የሚደረጉትን ውይይቶች ህዝብ እንዳይወያይበትና አስተያየት እንዳይሰጥበት የሚደርገው የጉልቤና የአፈና አካሄድ መቆም አለበት በሀያ አራት አመት ትግል ፀንተው በፀረ ወያኔና ሻቢያ አቆም ታግለው ያታገሉ ወንድሞችን ስለ ሻቢያና ኢሳያስ አፈወርቂ አነሳችሁ በሚል እናንት የወያኔ ተላላኪዎች ተብለው እየተሰደቡ ነው።ይህን አካሄድም ትክክል አለመሆኑና ለማስቆም የድርጅቱ መሪዎች ያደረጉት ጥረት የለም ይልቁንም የድርጅቱ መሰረታዊ ፍልስፍ ናስድብ፣ ጩሆትና አድማ እስኪመስል ድረስ ቀጥለውበታል::

ታዳሜው ይህን አካሄድ ከምንትልገለው የወያኔ ሥርአት ተለይቶ ስለማይታይ አካሄድን እንታገለዋለን:: በተረፈ ትናንት በኢትዪጵያ ሪቭው አዘጋጅ በኢልያስ ክፍሌ ዛሬ በአዲስ ድምፅ አዘጋጅ በአበበ በለው እየተደረገና በመደረግ ላይ ያለው ጋጠ ወጥ ዘመቻ የተሰለፍበትን ድርጅት ሰብእና የሚሳይ ስለሆነ ሊታረም ይገባል። ኢልያስ ክፍሌ ሆነ አበበ በለውን ወያኔ ለማለት ቀርቶ ደጋፊዎች ሌላውም የሞራል ብቃት የላቸውም። በዚህ ጉዳይ በአጽኖኦት የተገለጠው ለግንቦት ሰባት ድርጅትና ለለውጥ ፈላጊው አባላት ከፍተኛ አክብሮት እንዳለው አስምሮበታል::

ድርጅቶችን አንተች የሚለው አባባል ስህተትና ወቅታዊ አለመሆኑ ተተችቶበታል:: ወያኔ ሀያ አራት አመት በግፍና በበደል ህዝባችንን እየከፋፈለና እያሰቃየ በአምባገነንነት መግዛቱን እኛም ያለመስልቸት በፅናት ሀያ አራት ዓመት አጋልጠነዋል:: ነገር ግን ህዝቡን መርተውና አደራጅተው ለድል ያበቁታል ያልናቸው የፓለቲካ ድርጅቶች ህዝቡን ለድልና ለነፃነት አለማብቃት ብቻ ሳይሆን ራሳቸው ወደህብረትና አንድነት ባለመምጣት የትግሉና የፖለቲካው አቅጣጫ ያጡ ይመስላሉ ስለዚህ ድርጅቶችን ራሳቸውን ሊያዩና እንዲፈትሹ ጥሪ ማድረግ እኛም ሆነ ህዝቡ ልንተቻቸውና ልንገመግማቸው ይገባል ይህ አካሄድ ለድርጅቶች ና ለትግሉ ብርታትና ጥንካሪ ይሰጣቸዋል:: የህዝብ ትችት የሚፈራ አምባገነን መንግስትና ራሱን በትእቢት ያሳበጠ ውስጡ በባዶ ጩኸት የሞላ ኃይል ብቻ ነው።

በመጨረሻ በፓናልአቅራቢዎችና በታዳሚው የተደረስበት መንፈስ
1ኛ/ የፓለቲካድርጅቶች፣አባሎቻቸ ውና ሊላው ማህብረተስብ የነፃ ሚድያን ሚና እንዲረድልን ጥረ ማድረግ፣ በሚድያ አቀራረብ በፅሁፍ ዘገባ፣ በዜና ሆነ በቃለ መጠይቅ የሚስራው ጥንቅር አቅራቢው ጋዜጠኛ ህዝብ ሊያውቀው ይገባል ብሎ ያመነበትን የማቅረብ ሙሉ መብት እንዳለው። አዘጋጅው ይህን ማቅረብ የእገሊን ድርጅት ያስከፋብኛል በሚል ስነ ልቦናዊ ሰቀቀን እንዲፈጠር የሚደረገው ዘመቻ መቆም አለበት ድርጅቶች ነፃ ሚዲያዎችን የእነርሱ ልሳን እንዲሆኑ በቀጥታ ሆነ በተዘዋሪ መሞከር ወንጀል ነው።ድርጅቶች የነፃ ሚድያዎችን ሽፋን ማግኘት የሚችሉት በሚሰሩት ሥራና መሪት ላይ በተግባር በሚደርጉት አስተዋፅኦ እንጅ ሚዲያዎችንና አዘጋጆችን በማንቆሸሽ ና በማሸበር አይደለም።

2/ኛ የሜዲያ አዘጋጆች የተመክሮ ልውውጥ ማድረግ አለብን በሚል የህሊና ራዲዮ አዘጋጅ ሳምሶም ውብሽት የሙያ ትንተና ትምህርት ሰጭ በመሆኑና በትክክል ከነፃ ሚድያነት አንፃር እየሰራን ስለመሆኑ ትምህርታዊ ግምገማ ለማድረግ አንድ ፎረም ማቋቋም ጠቃሚ በመሆኑ የአዲስ ድምፅ አዘጋጅ አበበ በለው በአስተባባሪነት ተመርጦ ሌሎች የሚዴያ ባለ ቤቶችን ጨምሮ አንድ ፎረም እንዲቆቆም ተወስኖአል።

3/ኛ በተለይ ዘ ሀበሻ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሄኖክ በሰጠው ማሳሰቢያ መሰረት ለሀገራቸው፣ ለህዝባቸው ነፃነት ሲሉ ሥርአቱን ተችታችኋል; ህዝብን አነሳስታችሆል በሚል በእስር ና በስደት የሚገኙ የጋዜጠኛ ቤተሰቦች ልንረዳቸውና ልናበረታታቸው ይገባል።ሄኖክ በመቀጠል በትናንት ቀን እኔና እዚህ ቤት ያለን የሚድያ ሰዎች የጀግናው ጋዜጠኛ ባለቤት ወ/ሮ ሰርካለምና ልጇን በማየታቸውና በመጎብኘታቸው ከፍተኛ የህሊና ደስታ እንደተሰማው ገልፆ እኛ በውጭ የምንገኝ ጋዜጠኞች፣ የፓለቲካ ድርጅቶችሆነ ዲያስፖራው እነዚህን ለህዝብ ልሳን በመሆን በወይኔ እስር ቤት ያሉ ፋኖ ቀዳጅ የሆኑ ትንና በስደት የሚገኙትን ልንረሳቸው አይገባም:: ስለዚህ የምንመሰርተው ፎረም በአገዛዙ እጅ የወደቁትንና ቧእድ ሀገር የተሰደድትን ጋዜጠኞችንና ቤተሰባቸውን የምረዳበት የምንደግፍበትና የምንዘክርበት መሆን አለበት ብሎል።

በአጠቃላይ ስብሰባው በጥሩ መንፈስና በበሳል አካሄድ የተካሄደ ነበር። ታዳሚው የሁሉንም ማህረሰብ አባላት ያካልተተ ሲሆን የቆየ የፓለቲካ ተመክሮ ያላቸው ፣ የፓለቲካ ንድፍ ፀሀፊዎች፣ ጦማርያንና የፓልቶክ ባለቤቶችን ያከተተ ነበር። በታዳሚነት ካየሆቸው መሀል ታዋቂው የሰብአዊ መብት ተማጎች ኦባንግ ሜቶና ታምረኛው ብእረኛ ተክሌ አበበ ነበሩ።

The post ትምህርት ሰጭ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ስብሰባ በዋሽንግተን ዲሲ * – ከእሸቴ ውለታው appeared first on Zehabesha Amharic.

“የኢትዮጵያ ዕድገት ውጤት የውጭ እርዳታ ነው”ዶ/ር አክሎግ ቢራራ (Video)

$
0
0

ባለፈው ቅዳሜ ጁላይ 4 በሜሪላንድ ደብል ትሪ ሆቴል በተደረገውና ጋዜጠኛ አበበ በለው (አዲስ ድምጽ ራድዮ) ባዘጋጀው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ታላላቅ ሰዎች ተገኝተው ነበር:: የሁሉንም ተናጋሪዎች ንግግር ዘ-ሐበሻ በቭዲዮ አስቀርታዋለች – በተከታታይ ለሕዝብ እናደርሰዋለን – ለዛሬው የዶ/ር አክሎግን ንግግር ያድምጡት::

Aklog Birara

The post “የኢትዮጵያ ዕድገት ውጤት የውጭ እርዳታ ነው” ዶ/ር አክሎግ ቢራራ (Video) appeared first on Zehabesha Amharic.

ጋዜጠኛ ኤዶም፣ርዮትና ማህሌት-ከተፈቱ በሁዋላ ሀብታሙ ምናለ ታፍኖ ተወሰደ

$
0
0

የጋዜጣው ስራ አስኪያጅ በአዲስ አበባ በደህነቶች ታፍኖ ተወሰደ

፣ከእነ ጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙ በተጨማሪ ሌሎችም የታሰሩ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ሲፒጄ ጠየቀ

የጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙ እና ከዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ሶስቱ ጋዜጠኞችና ሁለቱ ጦማሪያን መፈታት ለበርካታ ኢትዮጵያውያን ሰፊ መነጋገሪአ በሆነበት በአሁኑ ወቅት እንደ ሌሎች ሁሉ እንካን ከጠባቡ እስር ቤት ተፈታችሁ ያለውን የቀዳሚ ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለን የአገዛዙ ደህንነቶች ዛሬ ማምሻውን ከቤቱ አፍነው መውሰዳቸውን ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።
Habtamu Minale
የሀብታሙ ምናለን ከቤቱ ዛሬ ዕኩለ ሌሊት ላይ ታፍኖ መወሰድ ይፋ ያደረገው ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ ማንነታቸው ባልታወቀ የደህነት አባላት ታፍኖ ት እንደወሰዱት እንደማያውቁና ከዚህ በፊት ለአንድ ሙሉ ቀን ጥብቅ ምርመራ ሲደረግበት ውሎ አሻራ ሰጥቶ መውጣቱን አስታውሷል።

የቀዳሚ ገጽ ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ የነበረው ሀብታሙ ምናለ ዛሬ ማለዳ ከአራት ዓመት እስር በሁዋላ የአመክሮዋ ጊዜ አልፎ በአመክሮ ከእስር ወጣች የተባለችውን ጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙን አስመልክቶ በፌስ ቡክ ገጹ የርዮትን መፈታት የፈጠረበትን ስሜት በመግለጹ አይዘነጋም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙ መፈታትን አስመልክቶ ዓለም አቀፉ ጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅት ሲ.ፒ.ጄ ባወጣው መግለጫ አስቀድሞም መታሰር የሌለባት ርዮት በመፈታቱዋ ደስተኛ መሆኗንና የጤናዋን ጉዳይ ተጠይቃም የህመም ማስታገሻ እየወሰደች መሆኑን መግለጿን ጠቅሷል። መጀመሪያውኑ መታሰር እንደሌለባትና ከአራት ዓመት በላይ በእስር በልዩ ልዩ ክልከላዎች ጭምር መቆቷን፣ከእስር በሁዋላ የጡቷ ህመምን ጠቅሷል። ሁሉም ጋዜጠኞች ከእስር እንዲለቀቁ ጠይቋል።

በአሁኑ ወቅት የእነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ውብሸት ታዬ፣ተመስገን ደሳለኝ፣ የሱፍ ጌታቸው እና የሌሎቹም ፖለቲካና የህሊና እስረኞች የፕ/ት ኦባማን የኢትዮጵአ ጉዞ ዕቅድ ተከትሎ ከእስር ይፈቱ ወይም አይፈቱ ታወቀ ነገር የለም በሚባልበት በዚህ ወቅት የቀዳሚ ገጽ ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ የነበረው ሀብታሙ ምናለ በደህነቶች ታፍኖ መወሰድ አንዱን ፈቶ ሌላ ማሰር እንቅስቃሴ አስመስሎታል።

ትላንት ተፈቱትን ከዞን ዘጠኝ አባላት አምስቱ በስተቀር በቀሪዎቹ ላይ ክሱ ይቀጥላል ከመባል አልፎ የፖለቲካው ውሳኔ ምን እንደሆነ አልታወቀም። በትላንቱ ዘገባችን ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ፣ጋዜጠኛ አስማማው ሃይለጊዮርጊስ፣ ጦማሪ ዘላለም ክብረት፣ማህሌት ፋንታሁንና ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ ዛሬ ማምሳውን በፍትሕ ሚኒስቴር ውሳኔ መፈታታቸው የታወቀ ሲሆን ከቤተሰብ መቀላቀላቸው ከአዲስ አበባ የወጡ መረጃዎች ገለጹ።የቀሩት በእስርና በስደት ያሉ አምስት ጦማሪያን ጉዳኢ በተጀመረው የክስ ሂደት ይቀጥላል ቢባልም ቁርጥ አለ ውሳኔ አለመሰጠቱ ታውቋል። በክሱ ላይ ብኢን ለመስጠት ከመጪው ቀጠሮ ሐምሌ 13 ቀን 2007 በፊት ይፈቱ ወይ እንደተባለው ክሱ ቀጥሎ ብይን ይሰጥ አልታወቀም።

ከአስሩ ጦማሪያንና ጋዜጠኞች መካከል የክስ ሂደታቸው ይቀጥላል የተባለው የክሱ መዝገብ በስሟ የተከፈተውን ሶሊያና ሽመልስ ፣ አቤል ዋበላ ሱጌቦ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ በፍቃዱ ሃይሉ እና አጥናፉ ብርሃኔ ጉዳይ መታየቱ እንደሚቀጥል ከፍርድ ቤቱ የተገኘ መረጃ ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም።

The post ጋዜጠኛ ኤዶም፣ርዮትና ማህሌት-ከተፈቱ በሁዋላ ሀብታሙ ምናለ ታፍኖ ተወሰደ appeared first on Zehabesha Amharic.


የሕወሓት አገዛዝ ከኣርበኞች ግንቦት 7 ጋር ጦርነት መግጠሙን አመነ * 30 ወታደሮችን ደመሰስኩ አለ

$
0
0

war
ከደረጀ ሃብተወልድ

ኢሳት ከሳምንት በፊት ያወራውን ወሬ ፋና ትኩስ ወሬ አስመስላና ቆራርጣ አቅርባዋለች።
ዜናው “መቼ ነው ይህ የሆነው?” የሚለውን መጠይቅ በዚህ በዚህ ቀን ብሎ በትክክል አይመልስም። እንዲሁ ወደ መጨረሻው ላይ “ሰሞኑን” ብሎ ነው ያለፈው። “የት?” የሚለውንም እንዲሁ በደፈናው “ከኤርትራ በሚዋሰን ድንበር” ብሎ ነው ያለፈው። በየት አካባቢ በሚዋሰነው ድንበር? ምንም ዝርዝር የለውም። እንኳን ወታደራዊ ዜና፤ አንድ ተራ ዘገባ እነኚህን የዜና አበይት መጠይቆች ሊያሟላ ግድ ነው።
ምነው ፋናዎች! ግልጽነትን ሌላው ቢቀር ከወዳጃችሁ ከሪፖርተር ተማሩ እንጂ!
-ደግሞ ሪፖርተር ምን አለ?
ዘይቱ ድንጋይ ሆነ አለ።
-ከየት የመጣው ዘይት?
ከወዳጅ ቻይና!
-መቼ?
ሰኔ 23 ቀን 2007 ዓ.ም
-ኣሀ ኣሀ…ኣሀ…ለዚህ ነዋ አያቴ እንደዛ ያለችኝ?
ምን አሉሽ?
“አረ አያቴ ሆዴ ጥጥር ብሏል፤ድንጋይ ሆኖብኛል፤ ምን ሆኜ ይሆን?” ስላት ፦” እኔ ምናቅልሻለሁ የቻይና ዘይት በልተሽ ይሆናላ!” አለችኝ።
ህምም…

መንግስት ያመነበት ዜና የሚከተለው ነው

ከኤርትራ ጋር በሚዋሰን ምእራብ ትግራይ ድንበር አካባቢ ሰርጎ ለመግባት የሞከሩ ከ30 የማይልቁ የሻዕቢያ ተላላኪዎች መደምሰሳቸውን የፌደራል ፖሊስ ገለፀ
አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 3፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከኤርትራ ጋር በሚዋሰን ምእራብ ትግራይ ድንበር አካባቢ ሰርጎ ለመግባት የሞከሩ ከ30 የማይልቁ የሻዕቢያ ተላላኪዎች መደምሰሳቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል አሰፋ አብዩ ተናገሩ።

በሻዕቢያ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው ትንኮሳ ለመፈጸም ከሞከሩት ጸረ ሰላም ሃይሎች መካከል አብዛኞቹ ሲደመሰሱ ጥቂቶቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

እንደ ኮሚሽነር ጄነራሉ ገለጻ ከተንኳሾቹ አንድም ወደ ኋላ ያፈገፈገ ሳይኖር የትንኮሳ ዕቅዳቸው ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የሻዕቢያ ተላላኪዎች አልፎ አልፎ የትንኮሳ ድርጊት የሚያካሂዱ መሆኑን ገልፀው፥ ሰሞኑን የተደረገው ከዚህ ቀደም ከነበረው የተለየ አይደለም ብለዋል።

እነዚህ ሃይሎች ያደረጉት ትንኮሳ አነስተኛ እና በቀላሉ በቁጥጥር ስር ለመዋል የቻለ ነው ያሉት ኮሚሽነር ጄነራሉ፥ ፀረ ሰላም ሃይሎቹ ከጸጥታ ሃይሉ ጋር ውግያ ለመግጠም የሚያስችል አቅምም ብቃትም የላቸውም ብለዋል።

የኤርትራ መንግስት ኢትዮዽያ እና ሌሎች ሃገሮችን ለማተራመስ የያዘውን አቋም የማይቀይር ከሆነ ኢትዮዽያ ተመጣጣኝ እርምጃ እንደምትወስድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ሰሞኑን መናገራቸው ይታወቃል።

Source: FBC

አሜሪካ ላይ ጋዜጠኛ ሲደበደብ ፣ቃሊቲ ላይ ጋዜጠኞች  አብረው ያለቅሳሉ –ታምሩ ገዳ

$
0
0

ከታምሩ ገዳ ( የግል አስተያየት)

tamgeda@gmail.com

Voa-amharic-ባለፈው አርብ (ሃምሌ 4 /2015 እ ኤ አ ) ከመላው የአሜሪካ ግዛቶች  የተሰባስቡ  በሺዎች  የሚቆጠሩ  ዲሞክራሲ ፣ ፍትህ ፣ እኩልነት  እና ሰላም ናፋቂ ኢትዮጵያዊያን   በአሜሪካው መናገሻ ከተማ ዋሽንግተን  ዲሲ    በሚገኘው የዋይት ሃውስ ቤተ መንግስት  ደጃፍ ላይ  በመስባስብ  የፕ/ት  ባራክ ኦባማ  አስተዳደር  በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ  ውስጥ  እየተካሂደ  ያለውን ዘግናኝ  እና አሳሳቢ የሆነው  የስበዊ መብት ረገጣን ወደ ጎን በመተው    በምትኩ  ፕ/ት ኦባማ ለወቅቱ የኢህአዲግ  መንግስት ባለሰልጣናት ኣውቅና  እና “ቡራኪ ለመስጠት  “በተያያዝነው  የሃምሌ ወር  መባቻ ላይ  ወደ አ/አ ለመጓዝ ማቀዳቸውን   በመቃዎም  ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ በአይነቱ እና በይዘቱ ታላቅ የተባለ  ሰላማዊ  ሰልፍ አካሂደዋል።

ይህ አይነቱ  ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ይበል እና ወደፊትም ተቀናጅቶ ይቀጥል የሚያሰኝ ሲሆን፣ መቼም ሁሌም  ትላልቅ ፕሮግራሞች   ሲዘጋጁ እና  ሲካሄዱ መጠነኛ የሆኑ ግድፈቶች መከስታቸው የማይካድ  ሲሆን  በዚህ ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ   ላይም ሰልፉን በግንባር ተገኝቶ ለመዘገብ  የተላከው የአሜሪካ ራዲዮ  የአማሪኛው  ክፍል(ቬኦኤ) ባልደረባ የሆነው  ጋዜጠኛ ሄኖክ ሰማ እግዜር ከግዙፉ ስልፈኛ መካከል  አፈንግጠው የውጡ  ጥቂት ስልፈኞች አላሰፈላጊ ከሆኑ  ቃላት አንስቶ  እንደ እርሱ  ዜና ዘገባ “የጋዜጠኛ መታወቂያውን መንጭቆ መውሰድ እና መጣል፡ ኣርሱንም  ማዋክብ እና ከጀርባው  ለድብደባ ያደረስ” የሰነልቦና እና የአካል ጥቃት ፈጽመውበታል።ቪኦኤም  አሳዛኙ ገጠመኙን  በድህረገጹ ላይ በከፊል  በተነቀሳቃሽ ምስል አስደግፎ ለጥፎት  ይገኛል።

ጋዜጠኛ ሄኖክ  ስለ አሳዛኙ ገጠመኙ ለፖሊስ ሲያስረዳ

እዚህ ላይ ጋዜጠኛ ሄኖክ ምን አይነት ባለሙያ ነው?   ደካማ እና ጠንካራ  ጎኖቹ ምንድን ናቸው  ? ከሙያው አኳያ እነማንን አስከፋ እነማንንስ አስደስተ?  ወዘተ… የሚሉት እና መስል ተጠየቆች  እንደተጠበቁ እና ለ ቀጠረው (ለቬኦኤ ራዲዮ)  ፣ለራሱ ለጋዜጠኛው  ህሊና  እና  በዋንኛነት ደግሞ ለመላው የ ቬኦኤ አድማጮች  ፍርድ  የምተዋቸው  ጉዳዮች ሲሆኑ ጋዜጠኛ ሄኖክ “  ባድማጮቹ ዘንድ የቱን ያህል የተጠላ እና የዝሆን ያህል የገዘፉ ጉድለቶች  ቢኖሩበትም”  ጋዜጠኛው አቅርቧል ለተባለው  የተሳሳተ ዘገባዎች  የህግ አግባብነት ባለው መልኩ መቃወም፡  መክሰስ  እና  ለአንተ በጭራሽ መረጃ  አነስጥም (ለቃለ ምልልስ ፈቃደኛ  አይደለንም)  ማለት    እየተቻለ    “ ከራሷ ዜጎች  አልፋ እኛም ብንሆን  በአገራችን ያላገኝነውን  እና ሁሌም ኣንዲተገበር የምንናፈቀው  ሃሳባችንን በነጻ የመግለጽ፣ የመደራጀት ፣  በሰላማዊ መንገድ  የፈለግነውን የመደገፍ እና የመቃውም   ፍጹም መበት ባጎናጸፈችን  በምድረ አሜሪካ  እምብርት  ላይ  በአገሩ ልጆች  በተለይ ደግሞ ለ ፍትህ ፣ ለዲሞክራሲ ፣  ሃሳብን በነጻ ለመግለጽ እና  ለእኩልነት መብት መከበር ለመታገል  እንዲሁም የአምባገነኖችን   እኩይ ተግባራትን  በጽኑ ለመቃወም  እና ለአለም ህዝብ ለማጋለጥ   ቁሩ  እና ሃሩሩ ሳይበግራቸው  ለተቃውሞ ሰልፍ ወደ አደባባይ  ከወጡ  ሺዎች መካከል  በጣት የሚቆጠሩት  ሰልፈኞች  ያደረሱበት የማዋከብ ፣ የማሸማቀቅ ኣንደርሱ(ሄኖክ) ዘገባ “የጉሸማ ጥቃት  “ የትም ይሁን የትም   ፣በምንም መልኩ ተቀባይነት  ያለው  ሆኖ አላገኘሁትም ። ጥቃቱን የፈጸሙት ወገኖችም ቢሆኑ  በማወቅ ይሁን፣ በምንቸገርኝነት አሊያም   በስሜታዊነት  ከጋዜጠኛው ጋር  የፈጠሩት እሰጣ  እገባም ቢሆን   ከጋዜጠኛው ጀርባ  ኣለም አቀፍ ተደራሽነት  ያለው  ቪኦኤ የተባለ ግዙፍ ተቋም መኖሩን ፣ከዚህ ተቋም ጀርባም ነጻፕሬስን እንደ አይናቸው ብሌን የሚመለከቱት በብሊዮኖች የሚቆጠሩ  ወገኖች መኖራቸውን እና የእነርሱን አይኖችን  ለመጠንቆል መሞከር እንደሆነ ጠንቅቀው የተገነዘቡት አይመስለኝም ።ይህ ጥቃት በሌላ ጎኑ  በ አገር ቤት ጋዜጠኞችን ፣ጦማርያኖችን ፣ የፖለቲካ እና የሃይማኖት መሪዎችን እና  ተወካዮችን በማዋከብ ፣ በማሳደድ፣ በማሰር ፣ ቶረቸር በማደረግ ፣ ያለ ጥፋታቸው  በከባድ እስራት በመቅጣት እና በመበቀል  ፣  እድል   የገጠማችውንም እገር ጥለው  እንዲስደዱ ላደረጋቸው እና በማደረግ ላይ ለሚገኘው  ለወቅቱ የኢህአዲግ መንግስት የልብ ልብ የሚስጥ እና  “አበጀህ!”  የሚል መልእክት የሚያሰተላልፍ ነው ።

በተቃራኒው ደግሞ  ህገመንግስታዊ መብት የሆነው   ሃሳብን በነጻ የመግለጽ  መብታቸውን  ሲተገብሩ   በተለያዩ የህግ ሽፋኖች አማካኝነት  በቃሊቲ ፣በቂሊንጦ  እና በሌሎችም እስር ቤቶች   ውስጥ እየማቀቁ  የሚገኙ የነጻ ፕሬስ አባላትን እና የዲሞክራሲ ታጋዮችን  የማሳዛን  ፣አንገትን የማስደፋት እና የማስለቀስ  ድርጊት ሆኖ ተስምቶኛል ። ለምን ቢባል?  ሃሳብን የመግለጽ መብት  ለጥቂቶች ብቻ የማይስጥ  ወይም “እኛ የወደድነው ብቻ ይደመጥ”  የማይባልለት  ተፈጥሮአዊ እና የስብ አዊ መብት በመሆኑ ነው ።

ለዚህ አባባሌ ማጥቀሻ የሆነኝ ዘንድ ከተቋቋመ አራት አስር አመታት ያስቆጠረው  ታላላቅ የእምነት ተቋማት የሆኑት   የእስልምና፣የክርስትና  እና የአይሁድ  አባቶች ፣ የአገር እና የፖለቲካ መሪዎች፣  ታዋቂ ግለሰቦችን   በካርቱን  አማካኝነት  በፈርንፋይኛ ፣በእንግሊዘኛ  እና በአስፓኒሽ ቋንቋዎች  በማብጠልጠል  እና በመሳለቅ  የሚታወቀው ቻርሌይ  ኢብዶ(Charlie Hebdo) ጋዜጣ በእስልምና  ሃይማኖት በተለይ ደግሞ በነብዮ መሃመድ ዙሪያ ያወጣቸው ተከታታይ  ካርቱናዊ   ሰላቆቹን  ተከተሎ  በህትመቱ የተቆጡ  ታጣቂዎች   ባለፈው  ጥር 7 /2015 እኤ አ  ፓሪስ  (ፈረንሳይ) በሚገኘው  ቢሮው ላይ ባደረሱት ጥቃት  ዋና  አዘጋጁን  ጨምሮ 12 አባላቱ  እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ  እነደገደሏቸው  መዘገቡ  አየዝነጋም።ታዲያ  ምንም እንኳን  የጋዜጠኞቹ   ምጻታዊ ስላቆች  እና ፊዞች  ሁሉንም ወገን  ያስደስታል ባይባልም  በጋዜጠኞቹ ላይ የተቃጣው የጥቃት እርምጃ ግን  ሃሳብን በነጻ የመግለጽ መብት ላይ   ከተሰነዘረ ጥቃት   ጋር  በማያያዝ     በመሬት ይገባኛል ጥያቄ ካፈው ግማሽ ምእተ አመት  ጀምሮ  የሚፈጁት  የ ፍልስጤሙ  እና  የ እስራኤሉ  (ፕ/ት መሃመድ ሃባስ  እና ጠ/ሚ/ር ቢንጃሚን ናተኒያሁ)፣ ከድህረ የቀዝቃዛው የአለም ጦርነት በኋላ ግዙፍ የተባለ ውጥረት ውስጥ የገቡት   የሩሲያው እና የዩክሪኑ ፕ/ት  (የውጪ ጉ/ሚር ሰርጌ ላቫሮቭ  እና    ፕ/ት ፔትሮ  ፖሮሽአንኮ)  ጨምሮ  ከ40 በላይ የአገር እና የሃይማኖት  መሪዎች( እንደ አጋጣሚ  ከአውራ መሪዎች መካከል ፕ/ት ኦባማ ብቻ  አለተገኙም) በፓሪስ  ጎዳና ላይ ከ አንድ ሚሊዮን በላይ በሚገመቱ አፍቃሪ  ነጻ ፕሬሶች  በመታጀብ  እና  እጅ ለእጅ በመያያዝ “እኔም ቻርሊይ ኢብዶ ነኝ”(Je suis Charlie Hebdo)፣”ፍቅር ከ ጥላቻ ይጠነክራል”( Love is stronger than hate) …ወዘተ የሚሉ መፈክሮችን በማስማት  የነጻ ፕሬስ  ነጻነት  በየትም ስፍራ ገደብ ሊበጅለት እንደማይገባ  እና  ነጻ ፕሬስ በየትኛውም ስፍራ እና  ጊዜ በጭራሽ ለድርድር እንደማይቀርብ በማስረገጥ አቋማቸውን  ገልጸዋል።የሰብ ኣዊ መብት ተሟጋቾቹ  እነ ሁማን ራይት ዎች እና  አሚኒሲቲይ ኢንተርናሽናል ፣  የጋዜጠኞች  እንባ ጠባቂዎቹ እነ  ሲፒጂ(ከ ኒዮርክ) እና ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ማህበር(ከፖሪስ)ጥቃቱን በከፍተኛ ቃላት እና ቁጣ  አውግዘውታል።

 

ሰለ ፓሪሱ የቻርሊይ  ኢብዶ ጋዜጣ አሳዛኝ  ገጠመኝ  ለትውስታ ያህል ይህንን ያህል  ካልኩ  ወደ ሰሞነኛው  የዋይት  ሃውሱ ደጃፍ   በጋዜጠኛ  ሄኖክ    እና “ሰራው አይጥመንም” ባሉት  ወገኖች መካከል የተፈጠረውን  ግጭት በተመለከተ   ከተቃውሞ ስልፉ አዘጋጆች መካከል አንዱ  ለቬኦኤ ቀርበው  “ ሄኖክ በአብዛኛው  ኢትዮጵያዊ ዘንድ   የወቅቱን  ስርአት ይደግፋል  ተብሎ ሰለሚታመን  ፣በቅርቡም  በኢትዮጵያ  የተካሄደው እና ኢህአዲግ 100% አሸነፍኩ ያለው ምርጫን  ፍትሃዊ   ነው ብሎ በመዘገቡ በርካታ ኢትዮጵያዊያኖች በጥሩ አይን ሰለማያዩት   ፣ሄኖክ ለዘገባ ከሚመጣ ቪኦኤ በእርሱ ፈንታ  ሌላ ሰው ቢልክ የተሻለ መሆኑን መክሬው ነበር ።  በሄኖክ እና  በግለስቦቹ መካከል በተፈጠረው  ግጭት ላይ የታክስ ፎርሱ(የሰልፉ አዘጋጆች) እጆች  በፍጹም   የለበትም።” በማለት የታክስ ፎርሱ  ትላንትም ሆነ ወደፊትም ለሰላማዊ ትግሉ በጽናት  እንደሚቆም ሲናገሩ  ተደምጠዋል።  እዚህ ላይ   ግብረሃይሉ ለፍትህ እና ለዲሞክራሲ  መጎልበት የሚያደርጋቸው  ጥረቶች በማንኛውም  ወገን  የሚበረታታ እና የሚደገፍ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘ  የግብረሃይሉን መንፈስ እና  አላምን የሚያጎድፉ  እንደ ስሞነኛው አይነት አላስፈላጊ እና አሳዛኝ እንከኖች ሲፈጠሩ ግን ግብረሃይሉ  በግንባር ቀደምነት  ወጥቶ “ በእኛ ስም መደረግ የለበትም” በማለት የማጋለጥ እና የማውገዝ  ዲሞክራሲያዊ ሃላፊነት  የተጣለበት  ይመስለኛል። ይህንንም ማድረግ  ለወደፊቱ ትግሉ  መንገድ ይጠርጋል ። የአሜሪካ ህግም ይደግፋል  ።

የተጠያቂነት ነገር ካነሳሁ ዘንዳ   ቪኦኤም ቢሆን  በጋዜጠኞቹ  ስራዎች ዙሪያ  ስሞታዎች   እና ወቀሳዎች  ከየቱም አቅጣጫ ሲመጡ ጉዳዩን በግልጽነት  በመመርመር  የደረስበትን ጭብጥ ለአድማጮቹ  ውሎ ሳያድር የማሳውቅ እና  የጥርጣሬ  ዳመናዎችን የመግፈፍ  የሚዲያ ተቋማዊ ሃላፊነት እንዳለበት  እና በየትኛውም  ስፋራ  የሚሰማሩ  ጋዜጠኞቹ ደህንነትን በተመለከተም “የትም ፍጭው  ዱቂቱን  ብቻ አምጭው  ወይም ለዘብተኛ“ ከሚያስመስል  አካሂድ ወጥቶ  ሪፖርተሮቹ “ የፕረስ ፍቃዳቸው  ሲታገድ፣ ሲነጠቅ፣ሲዋከቡ  ወይም  በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አገር ጥለው እንዲሰደዱ ሲደረጉ “ እነ CPJ,RSF, HRW,AI  …ወዘተ የሚያወጧቸውን  ፕረስ ነክ ዘገባዎችን እና መግለጫዎችን   እየጠቀሰ ከሚያሰደምጠን  አዲስ  መጢዎቹ እነ አልጀዚራ ቲሊቭዥን  ስለባልደረቦቻቸው በግብጽ   መታስር እና መዋከብ በተመለከተ  ከ አንድ አመት በፊት ካደረጉት  የነጠረ ተከታታይ ሙያዊያዊ የተቃውሞ ፣የማውገዝ እና   የአቁዋም ጽናት  ሊማር ይገባዋል እላለሁ።

በስተመጨረሻም  ጋዜጠኛ ሄኖክ ስማ እግዚሄር  ከዘገባዎቹ ጋር በተያያዘ  ስሞኑን  ያጋጠመውን አካላዊ እና ሰነልቦናዊ  ወከባን ተከትሎ ሰሞኑን  የተነሱት አንዳንድ  የደጋፍ  እና የተቃውሞ  አሰተያየቶችን ስመለከት   በፈረንሳዩ  የቻርሊይ ኢብዶ ጋዜጠኞች  ላይ የደረሰውን  ጥቃት ለመቃወም  በመዲናይቱ ፓሪስ  ቻርልስ ደጎል አደባባይ  ዙሪያ ተሰባስበው  ከነበሩት  በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት  ሰልፈኞች  ውስጥ   ወደላይ ከፍ አድረገው  ካውለበለቧቸው  የነጻ ፕሬስ አፍቃሪዎች   መፈክሮች እና ፖስተሮች  መካከል” አንተ በምትለው አልስማማም ፣ነገር ግን ማለት የምትፈልገውን  ሁሉ  እንድትናገር እስከ ህይወት  መሰዋእትነት  ድረስ እዋደቅልሃለሁ።”(“ I don’t agree with what you say, but I will fight to the death to defend your right to say it.”   ) የሚለው መፈክር በቻርልይ ኢብዶ ጋዜጣ  የተለያዮ ፣  እወዛጋቢ እና አከራካሪ  ስላቃዊ ካርቱኖች እና መጣጥፎች   ነጋ ጠባ  ከሚፈለቀለቁት  ባለተናነስ በጋዜጣው  አድራጎቶች እርር እና  ድብን በማለት  ፈጣሪ ኣንዳች የሆነ  የማስታገሻ መአቱን  እንዲያወርደበት የተመኙ  ቢሊዮኖች (ጽረ- ቻርሊይ ኢብዶዎች )ሳይቀሩ ልባቸውን ነካክቶታል ፣ ቀልባቸውንም ስቧል ። እኔም  መፈክሩ ከፓሪስ  ውጭ የምንገኘነውን  በዙዎቻችንን ያስማማል ብዮ አምናለሁ።

 

በዚህ አጋጣሚ  የለጥፋታቸው እና  ያለማሰረጃ  ከአመታት በላይ  ከውህኒ ቤት  ተውርውረው ሲማቅቁ  ከሚገኙት  ከሃያ በላይ ጋዜጠኞች፣አምደኞች  እና ጦማሪያኖች  መካከል  አምስት ያህሉ ለእነ እነርሱ ጭምር ባስገርማቸው ሁኔታ የፕ/ት ኦባማን የአ/አ ጉብኝት ዋዜማን ተከትሎ  የኢሀአዴግ  መንግስት የ ኦባማን አፍ ለማዘጋት  ሲል  “ክሴን አንስቻለሁ”    በማለት   ምንም እንኳን ቀድሞውኑም  መከሰስ እና መታስር  ሳይገባቸው  ከእስራት ተለቀው ቢያንስ  ከሚወዳቸው ህዝብ እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመቀላቀል  በመብቃታቸው  በውስጤ ልዮ የደስታ  ስሜት ጭሮብኛል ። የተቀሩትም በ አስር ሺዎች የሚቆጠሩት የህሊና ኣሰረኞች  እና ወገኖቻችን  ከሰቆቃው ነጻ የሚሆኑበት  እና ማጎሪያ ቤቶቹም ቢሆን  ወደ ሆስፒታልነት ፣ወደ ት/ቤት ነት ወደ ሙዚዮምነት እና ወደ መዝናኛ ስፍራነት የሚቀየሩበት   ጊዜ እሩቅ እንደማይሆን ጽኑ እምነት አልኝ።

 

 

 

ከደስታው በስተጀርባ  –ይገረም አለሙ

$
0
0

 

justiceበቅድሚያ እንኳን ደስ አለን፡፡ የሌት ቅዥቱ የቀን ስቅይቱ ሥልጣንና ሥልጣን ብቻ የሆነው ወያኔ ያለ ስማቸው ስም ሰጥቶ ያለ ግብራቸው ወንጀል ለጥፎ ህሊናቸውን ለሆዳቸው አሳልፈው የሰጡ አቃቤ መንግስትና ዳኞች ሰይሞ  በውህኒ ያኖራቸው እህት ወንደሞቻችን ከእስር ተፈተዋል፡፡ እነዚህ ወጣቶች ወንጀላቸው አንድና አንድ ነው፤ እናት ሀገር ኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ጸሀይ ልትሞቅ የምትበቃበትን፣ልጆቿ በፍቅር በሰላም በእኩልነትና በአንድነት መኖር የሚችሉበትን ሥርዓት መፍጠሪያውን መንገድ ማመላከታቸው፡ አገዛዝ በቃን ማለታቸው፣ የወያኔን ማንነትና የአገዛዝ እንዴትነት ማጋለጣቸው ሀሳባቸውን መግለጻቸው ወዘተ ነው ወንጀላቸው፡፡

ወያኔ አምስት ዓመት እየጠበቀ ምርጫ ያካሂድ እንጂ መጀመሪያም ለሥልጣን የበቃው ሀያ አራት አመትም በሥልጣን የቆየው በምንና እንዴት እንደሆነ ያውቀዋል፡፡ የሚኖረው በጠመንጃ ቀስፎ፤ በአንድ ለአምስት ጠርንፎ ጆሮ ጠቢ አሰማርቶ ብዙ ሆድ አደሮችን ገዝቶ ቢሆንም ሕዝቡ አጋጣሚ ጠብቆ ከተነሳ ምን ሊያደርገው አንደሚችል በምርጫ 97 አይቷልና ኮሽ ባለ ቁጥር እየደነበረ ትንሽ ነገር ባየ በሰማ ቁጥር ይቺ ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም እያለ ያስራል ይገላል ያሰድዳል፡፡የረጋውን ማዕበል ይቀስቅሱታል ብሎ የሚፈራቸውን በአይነ ቁራኛ ይጠብቃል አስፈራቶ ላንበርከክ ወይንም ደልሎ ጸጥ ማሰኘት ይሞክራል፡፡ ይህ አልሰራ ሲል ወንጀል ፈብርኮ የሀሰት ምስክር አሰልጥኖ በህግ ካባ ስውር ደባ ይፈጽማል፡፡

ህገ ወጥ ተግባሩ  ተቃውሞ አስነስቶ ከዛም ከዚህም ጥያቄ ሲበዛበትና ይህም ለሥልጣኑ አስጊ መስሎ ሲታየው እንዲህ እንደ ሰሞኑ ክስ አቋረጥኩ ምህረት አደረኩ ወዘተ ይልና ያልፈጠረበትን ቅዱስ ለመምሰል ይሞክራል፡፡ስለሆነም በእህት ወንድሞቻችን ከእስር መፈታት የመደሰታችንን ያህል ከዚህ ደስታችን በስተጀርባ ይህ የሆነበትን ምክንያት መመርመር ማወቅና መዘጋጀት ብሎም የተጀመረው ትግል ይበልጥ እንዲቀጥል ማድረግ አለብን፡፡

ርእዮት አለሙ ለጋዜጠኞች ስትናገር ከእስር ቤት ውጪ ሲሉኝ አመክሮ አልሞላሁ ይቅርታ አልጠየቅሁ በምን መንገድና ምክንያት ነው ውጪ የምትሉኝ ተመልሼ የምመጣ ከሆነ አልወጣም አልኳቸው ያለችው ወያኔን በደንብ በማወቋ ነው፡፡ ሁላችንም እንዲህ አውቀን ከደስታችን በስተጀርባ ይህ ለምን ሆነ፣ወያኔ ምን ገጥሞት ምንስ አስቦ ነው ይህን ያደረገው ብለን ማሰብ መምከር ይኖርብናል፡፡ይህ ካልሆነ ግን የወያኔ የማስቀየሻ ስልቱ ሰራለት ማለት ነው፡፡ ስለ ወያኔ ሳስብ፣

ገደልን እንዳይሉ ሞተው አገኙዋቸው

ማረክን አንዳይሉ ሰው የለ በእጃቸው

ምን አሉ አንግሊዞች ሲገቡ ሀገራቸው

ለወሬ አይመቹም ተንኮለኞች ናቸው

የሚለው በአጼ ቲዎድሮስ ሞት  የተገጠመውና በተለያየ መጻህፍት የተገለጸው የለቅሶ ስንኝ ይታወሰኛል፡፡ ወያኔዎች ሥልጣናችንን ለማቆየት ይጠቅመናል ካሉ ምንም ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ አይሉም፡፡ የተናገሩትን መካድ የሰሩትን አይኔን ግንባር ያድርገው ማለት የገቡትን ቃል ማፍረስ ለእነርሱ ተራ ነገር ነው፡፡ ዋናው ጉዳይ ሥልጣን ነውና፡፡

ቅንጅቶችን አስረው በገጠማቸው ተቃውሞና ተአቅቦ ከገቡበት ማጥ ለመውጣት አቶ መለስ ፕ/ር ኤፍሬም ይስሀቅን አማልደኝ ሲሉ ከርመው እስረኞቹ ሲፈቱ 18 ወራት በፈጀ የሀገር ባህል ወግ መሰረት በሽምግልና አንደተፈቱ በመንግስት መገናኛ በብዙሀን ቀኑን ሙሉ ሲነገረን ውሎ በእሰረኞቹ መፈታት የፖለቲካው ትኩሳት በርዶ ወያኔዎች ሲረጋጉ የተፈቱት በሽምግልና ሳይሆን በህግና በህግ ነው ማለታቸውን የምንረሳ አይመስለኝም፡፡ ከዚህ አልፈውም አቶ መለስ ነብሳቸውን ፈጣሪ እንደፍላጎቱ ያድርጋትና ሽምግልና ብሎ ነገር አልነበረም ብለው በአደባባይ መካዳቸውን የማያወቅ ያለ አይመስለኝም፡፡ለብርቱካን ሚደቅሳ ዳግም መታሰር ምክንያት የሆነውም ይሄው ነው፡፡

ወያኔዎች ለሥልጣናቸው ሲሉ ርኩስ ተግባራቸውን  በራሳቸው ሰዎችም ላይ ከመፈጸም ወደ ኋላ እንደማይሉ አይተናል፡፡አቶ ታምራት ላይኔን ስኳር አታሎኝ የከተማ ኑሮ አማልሎኝ የጓደኞቼን ምክር አልሰማ ብዬ አጥፍቼአለሁ ካልክ አንተም ሆነ ቤተሰብህ ምንም አትደረጉም ብለው ቃል ገብተው ለህዝብ በቀጥታ በተላለፈ የፓርላማ ስብሰባ ላይ ካስለፈለፉዋቸው በኋላ እንደ አሰሩዋቸውና የራሳቸውን ንግግር እንደ ማስረጃ እየቆጠሩ ሲያብጠለጥሉ ሲወነጅሉዋቸው አይተናል ሰምተናል፡፡ወያኔ ስልጣኔን ያቆይልኛል ብሎ ካመነ መላእክትን ርኩስ ዲያቢሎስን ቅዱስ ከማለት የማይመለስ ለመሆኑ ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡

ወያኔ ማናቸውን ነገር ሲያደርግ ከሥልጣኑ አንጻር ነው፡የመንግሥትነት ስሜት ተሰምቶት፤ለህግ የበላይነት ለመገዛት ዳድቶት ፈሪሀ እግዚአብሄር አድሮበት ለሀገር ደህንነትና ለሕዝብ ጥቅም ተጨንቆ ወዘተ የሚፈጽመው አንዳችም ነገር አለመኖሩን በሀያ አራ አመታት አገዛዙ አሳይቶናል፡፡ ስለሆነም ጥሩ ሲያደርግ ከደስታችን መጥፎ ሲያደርግ ከሀዘን ቁጣና ጩኸታችን በስተጀርባ ረጋ ብለን ነገሮችን መመርመር ተገቢ ነው፡፡ ይህን ማድረግ ባለመቻላቻን ነው ወያኔ በስልት በእብሪትና በማን አለብኝነት በሥልጣን ለመቆየት ያስችሉኛል በማለት  የሚወስዳቸው እኩይና ሰይጣናዊ ተግባሮች ሁሌ አዲስ የሚሆኑብን፡፡

እስረኛን መፍታት መልካምና የተቀደሰ ተግባር ቢሆንም ወደዚህ ደረጃ የተደረሰው  በእምነት ሳይሆን በግፊት ድርጊቱ የተፈጸመው በሰይጣናዊ አስተሳሰብ በመሆኑ እህት ወንድሞቻችን ከአውሬዎች እጅ በመውጣታቸው እየተደሰትን ደስታችን የወያኔን ተንኮል ከማየት አንዳይጋርደን መጠንቅ ይኖርብናል፤ ወያኔዎች ለወሬ የማይመቹ ተንኮለኞች ናቸውና፡፡

 

 

 

በሰሜን የአገሪቱ ክፍል የሚታየውን ውጥረት ተከትሎ አየር ሃይል በጠንቀቅ እንዲቆም ታዘዘ

$
0
0

ሐምሌ ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት የአርበኞች ግንቦት7 በወሰደው ፈጣን ጥቃት በርካታ የኢህአዴግ ወታደሮች መገደላቸውን ፣ ይህንን ተከትሎ የወልቃይትና አካባቢው ህዝብ ያሳያው ድጋፍ እና ሽምቅ ተዋጊዎችን ለመቀላቀል የሚጠይቀው ወጣት መበራከት ያሰጋው ገዢው ፓርቲ፣ የአየር ሃይል አባላት በጠጠንቀቅ እንዲቆሙ ማዘዙን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።

Photo File

Photo File


የአየር ሃይል አባላቱ ካለፉት ሁለት ወራት ጀምሮ ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በሌሊት ፈረቃ እንዲሰሩ ሲደረግ ቢቆይም፣ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ስልጠናው ተጠናክሮ መቀጠሉን እንዲሁም አየር ሃይል አባላቱ ማንኛውም ግላዊ እንቅስቃሴያቸው እንዲገታ ተደርጓል።

የአየር ሃይል አባላቱ ” አንደኛ ደረጃ ተጠንቀቅ” የሚተላለፈው ፓርላማው የጦር አዋጅ ሲያውጅ ብቻ መሆኑን ለኢሳት ቢገልጽም፣ ጠ/ሚኒስትሩ ” ህዝብ አስፈቅደን በኤርትራ ላይ እርምጃ እንወስዳለን ከማለት ውጭ” የጦርነት አዋጅ እንዲታወጅ አላደረጉም።

አዲስ የጦር አውሮፕላኖች ተገዝተው መምጣታቸውንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በደፈጣ ውጊያ ፈጣን ጥቃት በመፈጸም ከፍተኛ ድል ያገኘው የአርበኞች ግንቦት7 ጦር ፣ በተለያዩ አካባቢዎች እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑንም የሚደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

የኢህአዴግ መንግስት ከአንድ ሳምንት ዝምታ በሁዋላ ሰሞኑን ጦርነት እንደነበር ለማመን ተገዷል። በምእራብ ትግራይና ሰሜን አማራ ድንበር ሰርገው ለመግባት የሞከሩ 30 የሻእቢያ ተላላኪዎች ተደምስሰዋል ሲል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄ/ል አሰፋ ተናግረዋል። ጄኔራሉ ጦርነቱ ከማን ጋር እንደተካሄደ ለመግለጽ ድፍረቱን አላገኙም። በደፈናው የሻእቢያ ተላላኪዎች ከማለት ውጪ አርበኞች ግንቦት7 ለማለት አለመድፈራቸው እንዲሁም “አንድም ያፈገፈገ ተንኳሽ የለም” ካሉ በሁዋላ፣ ተመልሰው “አብዛኞቹን ደምስሰናቸዋል ፣ ጥቂቶችም ይዘናቸዋል” ማለታቸው እርስ በርሱ የሚጋጭ እና የመገለጫውን ተአማኒነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ መሆኑን ዘጋቢያችን ገልጿል።
አሰማርቷል። ይሁን እንጅ ለጥበቃ ከተሰማሩት መካካል የተወሰኑ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጠፍተው ኤርትራ ገብተዋል።

ይድረስ ለነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያዊያን –ከያህያ ይልማ

$
0
0

አሁን ያለው የሕወሐት ሥርዓት ችግሮች ምን እንደሆኑ በውል ተመልክቶ በተቃራኒው ምን ዓይነት የትግል መስመር እንደሚያስፈልግ እኔ ያህያ ይልማ የሚከተሉትን ቁምነገሮች ሳስቀምጥ የሌሎቻችሁም አስተያየት ውሸት የሌለው እና ህሊናዊ ተጠየቅ ባለበት መልኩ እንዲሆን እያስገነዘብኩ በደስታ እጋብዛችኋለሁ::

1. የሕወሐት ሥርዓት ችግሮች

tplf-rotten-apple-245x300ሀ. የሕወሐት መስራቾች ወደ ትግል ለመግባት ያሰቡት እና የገቡት የንጉሱን ስርዓት ብሎም የአማራውን ገዥ መደብ በተለይም የሰሜን ሸዋን የበላይነት ተዋግቶ በማስወገድ የወልቃይትንና የራያን ለም መሬቶች አስገብቶ ታላቋን ትግራይ መመስረት አልሞ ሆኖ እያለ አምባገነኑን የደርግ ስርዓት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ በማውረድ በምትኩ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት አሰፈንኩ እያሉ ያጭበረብራሉ:: እዚህ ላይ የማይካድ ሐቅ አለ:: የሕወሐት ተራ ታጋዮች በቆራጥነት ተዋግተዋል፣ ስርዓጥ አልበኛ ከነበረው ከአምባገነኑ ደርግ አንጻር የሰራዊታቸው ዲስፕሊን የሚደነቅ ነበር፣ የመጨረሻ ደባቸው ምን እንደሚሆን በትክክል ባይታወቅም እንዲሁ በምንረዳው ሐሳባቸውን ከመገንጠል ወደ ኢትዮጵያን መምራት አስተሳሰብ ቀይረውም ነበር:: እነዚህ ሁኔታዎች በትግራይ እና በሌላው የኢትዮጵያ አካባቢ የሚኖሩ ገጠሬዎች እንዲደግፏቸውና አብረዋቸው እንዲሰለፉ ዳርጓቸዋል:: እየፈራረሰ የነበረውን የወቅቱን ሶሻሊስታዊ ርዕዮተ ዓለምን በብልጣብልጥነት የተው መስለው ከምዕራባዊያን ጋር ወዳጅነት መፍጠራቸውም በእጅጉ የጠቀማቸው አካሄድ ነበር::

ለ. የሀገር ድንበርን ከማስከበር እና የህዝቦችን አንድነት ከመጠበቅ አንጻር ሲነጻጻር የወረደ ቢሆንም ሕወሐት የአጼ ዮሐንስን ዘመን አምጥቸላችኋለሁ በሚል ስሜት ትግራዊያንን ተጠቀሙብኝ እያለ በሙስና የማይገባቸውን ሐብት እንዲያጋብሱ እያደረገ ይገኛል::

ሐ. የሕወሐት ስርዓት የለየለት ዘረኛ መሆኑን የራሱ አጋዥና ታዛዥ የሆኑት የብአዴን፣ የኦህዴድ፣ የደህዴንና ሌሎች አጋር ድርጅቶችም ተረድተውት ራሳቸውን ነጻ ለማውጣት ጊዜ እየጠበቁ ይገኛሉ:: ለዚህም ማስረጃ ጦሩና ደህንነቱ እንዲሁም ወሳኝ የመንግስት አውታሮች በሕወሐት ብቸኝነትና የበላይነት ተጨንፍረው ይገኛሉ::

መ. ሕወሐቶች በትግል ወቅት ያልነበራቸውን ጭካኔነት በአሁኑ በሰለጠነ ዘመን እንዴት ሊተገብሩት እንደቻሉ በሚያሳዝን ሁኔታ ዜጎችን ሲያስሩ፣ ሲያንገላቱና ሲገድሉ መመልከት የተለመደ ተግባር ሆኗል::

ሰ. የሕወሐት ስርዓት ለብዙሃኑ ኢትዮጵያዊያን ጨለምተኝነትንና ተስፋቢስነትን አስፍኗል:: መማር ትርጉም አጥቷል፣ የመኖር ዋስትና ጠፍቷል፣ ሀላፊነት ያላቸው ሰዎች በውሸት የተሞሉ በመሆኑ ውሸታቸውን እየነዙ በኢትዮጵያዊያን መካከል መተማመን ጠፍቷል፣ ከፋፍሎ የመግዛት ስልትን አጠናክረው ስለቀጠሉበትም ኢትዮጵያዊያን በጎሪጥ እንዲተያዩ ዳርጓል::

ረ. የሕወሐት ስርዓት ሉዓላዊነትን ከማስከበር እና ከማስጠበቅ ይልቅ ስልጣንን የሚያስቀድም በመሆኑ በድንበራችንና በህዝባችን ላይ እየደረሰ ላለው አሳፋሪ ውርደት ተጠያቂ ነው::

ሸ. የመሰረተ ልማት አውታሮች እየተዘረጉ ቢታዩም እንዴት ነው የሚዘረጉት፣ ጥቅሙስ ለህዝቡ እየደረሰ ነው ወይ ተብሎ ሲታይ መልሱ ተቃራኒ ነው:: የመሰረተ ልማት አውታሮቹ የሚገነቡት ኢትዮጵያ በረጅም ጊዜ እንኳ ልትከፍለው የማትችለው ወደ ፵ ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የብድር እዳ እንድትሸከም ሆና ሲሆን ከዚሁ እዳ ከግማሽ በላይ የሚሆነው በፖለቲካ ጉዳይ የሚንቀሳቀሱ ዜጎችን ለማፈኛ ሆኖ ከማገልገል በተረፈ በሕወሐት ባለስልጣናት እየተዘረፈ የሚገኝ መሆኑን የተለያዩ መረጃዎች ያሳያሉ::

ቀ. በአጠቃላይ የሕወሐት ስርዓት ለዚህ ዘመን የማይመጥን ፍጹም አምባገነን ዘረኛ ስርዓት ነው:: ህዝቡም ይህን በደንብ ስለሚገነዘብ ሕወሐትን እንደ ዘራፊ ቡድን እንጂ እንደ መንግስት አይመለከተውም::

በመሆኑም የሕወሐት ስርዓት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መወገድ ያለበት የኢትዮጵያዊያን ካንሰር ነው:: ከዚህ በመነሳት የሕወሐት ስርዓት በመሳሪያ የታጀበ ህዝባዊ አመጽን በማቀጣጠል ሊወገድ ይገባዋል::

2. ሕወሐትን ለማስወገድ የሚያስፈልጉ የትግል መስመሮች

ሀ. ሰላማዊ ትግል እያሉ ጊዜን ከማጥፋትና ዜጎች እንዲሰቃዩና እንዲገደሉ ከማድረግ አሁን ባለው ሁኔታ የሕወሐት ስርዓትን ለማስወገድ የሀይል አማራጭ መጠቀም ብቻ መሆኑን ማወቅና ከልብ ማመን ነው::

ለ. ከታሪክ እንደምንረዳው እንኳንስ አምባገነኑ ሕወሐት ይቅርና ዴሞክራስያዊ የሆኑ ስርዓቶችም ይወለዳሉ፣ ያድጋሉ፣ ይሞታሉ:: ከዚህ አንጻር ሕወሐት ተወልዶ ሲያድግ ተመልክተናል:: አሁን ደግሞ የህዝብ እሮሮ በርክቶ ወደመሞቻው ጉዞ ላይ ይገኛል:: ይህንን መረዳትና የኢትዮጵያ ካንሰር የሆነውን ሕወሐት ማስወገጃ ጊዜው አሁን መሆኑን መገንዘብና መነሳት ያስፈልጋል::

ሐ. ተስፋ ሰጭ ሆኖ እየተንቀሳቀሰ ያለውን የአርበኞች ግንቦት ሰባትን ሀይል ከሁሉም የኢትዮጵያ አቅጣጫ መደገፍ፣ ቅስቀሳ ማካሄድና መቀላቀል:: አርበኞች ግንቦት ሰባትን መቀላቀልና ማጠናከር የሚጠቅመው ሕወሐትን ለማስወገድ ብቻ ሳይሆን ሕወሐት ከተወገደ በኋላም ሳይታወቅ የሕወሐት ዓይነት ቡድን ሳይፈጠር ሉዓላዊነት የሰፈነባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት ስለሚጠቅም ነው:: የክርስትና እና የእስልምና ሀይማኖቶች እንዳይጨቆኑብን ካሰብን ክርስቲያኖችና እና ሙስሊሞች የሆን በሙሉ አርበኞች ግንቦት ሰባትን መደገፍና መቀላቀል ነው:: የብሔር ጭቆና አለ ብለን የምናምንም አላስፈላጊ የቃላት አተካራን ትቶ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሀይል መሆንና ውሳኔዎችን በጋራ የምናስኬድ መሆን:: ድጋፉ ከተለያየ አቅጣጫ የማይመጣ ከሆነ ግን አርበኛች ግንቦት ሰባት ጎንደሬ ወይም ሰሜን ሸዋ ወይም ጎጃሜ ወይም ወሎየ የበዛበት ወይም አንዱን ሀይማኖት ብቻ ከፍ አድርጎ የሚመለከት ይሆንና በጋራ ወሳኝ ከመሆን የቡድኑን ይሁንታ የምንጠብቅ እንሆናለን:: በዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብና በፍትህ የሚያምነው አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ መዳፍ እንደገባ ሁሉ አሁን በስም ከምናውቃቸው ታጋዮች የድሉን መጨረሻ ለማየት የሚታደሉት ጥቂቶች ሊሆኑ ይችላሉ:: ይህ ማለት የሁላችንም ተሳትፎ ከሌለ ከድል በኋላ የምናየው አርበኛች ግንቦት ሰባት መልኩን ቢቀይር ችግሩ አሁን ያለመሳትፋችን ውጤት ነው የሚሆነው:: ስለሆነም አሁን የምናደርገው ተሳትፎ ከኢትዮጵያችን ነጻ መውጣት ጋር ተያይዞ ለሚኖረው የህልውናችን፣ የማንነታችንና የአብሮነት ውሳኒያችን አካል መሆኑን ተገንዝበን ከአርበኛች ግንቦት ሰባት ጎን መቆም::

መ. አርበኛች ግንቦት ሰባት እንደ ድርጅት ትግሉን እያፋፋመ ጎን ለጎን ማኒፌስቶ ማዘጋጀት ይጠበቅበታል:: ማንፌስቶው የሚከተሉትን ሶስት ወሳኝ ጉዳዮች ቢያካትታቸው እሻለሁ::

1. ኢትዮጵያ ክብሯ ከፍ ያለች አገር ሆና እንድትቀጥል ህጋዊ ሰውነት ያለው ማንኛውም ተቋም መለሰ ዜናዊና ደቀመዝሙሮቹ እያላገጡ እንዳየነው የኢትዮጵያን ታሪክ የማንቋሸሽ ስራ ነውርና ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ ትኩረት ማድረግ::

2. ሕወሐት ብሔር ብሔረሰብና ህዝቦች እያለ ትርጉሙ ላገሬው ግልጽ ያልሆነን ማደናገሪያ እንደተጠቀመበት ሳይሆን በቀናነት ከምር ራስን በራስ የማስተዳደር ተግባራዊነት አስፈላጊ ነው:: ለዚህም ፕ/ር መስፍን ከጻፏቸው መጽሀፍት መካከል «ኢትዮጵያና የመንግስት አስተዳደር» [ካነበብኩት ጊዜው ስለረዘመ የመጽሀፉ ትክክለኛ ርዕስ የጠቀስኩት ስለመሆኑ እርግጠኛ አይደለሁም] በሚለው እንደተመራመሩት አካባቢያዊ ስሜቶች የሚንጸባረቁባቸው ማህበረሰቦች የራሳቸው አስተዳዳሪዎች ኖሯቸው ተጠሪነታቸው በቀጥታ ለማዕከላዊ መንግስት መሆን:: ለምሳሌ የተንቤን፣ የአድዋ፣ የመቀሌ፣ የራያና የጁ፣ የላስታና ዋግ፣ የደላንታና ደቡባዊ ወሎ፣ የከሚሴ፣ የአፋር፣ የኦጋዴን፣ የጎጃም፣ የጎንደር፣ የሸዋ፣ የሐረሪና ድሬዳዋ፣ የወላይታ፣ የጋሞ፣ የጎፋ፣ የአርሲ፣ የሀድያ፣ የጉራጌ፣ የስልጤ፣ የባሌ፣ የወለጋ፣ የቤንችማጅ፣ የሐመር፣ የሙርሲና የቱርሲ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ የጋምቤላ ወዘተ. የራሳቸው አስተዳደር ኑሯቸው ተጠሪነታቸው ለማዕከላዊ መንግስት እንዲሆን ማድረግ አንድ ነን በሚል ሽፋን የሚከሰቱ ዘረኛዊ የአስተዳደር በደሎችን በእጅጉ ለመቀነስ ይረዳል:: አካባቢን ለማልማትም ከልብ ተነሳሽነት እንዲኖር ይረዳል::

3. ታሪካዊ በደሎች እንደነበሩ አምኖ ሀገራዊ እርቅ እንዲኖር ቁርጠኝነትን ማሳየት::

ሠ. ሕወሐትን ለመጣል የሚደረገው ትግል ከተከማቸው መሳሪያ አንጻር አልጋ ባልጋ የሚሆን ባይሆንም እንደ ድሮው በቆራጥነት የሚታገል ታጋይ የሌላቸው መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል:: ቁርጠኝነት የነበራቸው አርጅተው በሙስና ተዘፍቀው ከመዋጋት ይልቅ ሁሉም አዛዦች ሁነው ያሉበት ወቅት ነው:: እንተማመንበታለን የሚሉት እንደ አግአዚ አይነት ያለው ጦርም ቢሆን እንኳ መሳሪያ ባልያዘ ሰላማዊ ዜጋ ካልሆነ በስተቀር መልስ የሚሰጥ ታጋይ ጋር የመዋጋት ሞራል የለውም:: መልቀምቀም የለመደ ስለሆነ ሞትን የሚጋፈጥ አይደለም:: ረባም አረባ ድሮ የሚሰብኩበት አይዲዮሎጂ ነበራቸው:: አሁን ግን እነሱን ግራ አጋብቶ ሌላውንም ግራ ያጋባው አብዮታዊ ዴሞክራሲ በማንም የተተፋ ስለሆነ የሞራል መቀስቀሻ የላቸውም:: አጭበርባሪና ውሸታም መሆናቸው ስለታወቀ አዲስ ሀሳብ እናምጣ ቢሉም የሚቀበላቸው የለም:: ከሕወሐቶችና ጥቅመኛ አለቆች ውጭ ያለው ተራው ወታደር እጅ ለመስጠት የሚዘጋጅና በነሱ ላይ አዙሮ መተኮስ የሚችል ሀይል ነው ያለው:: ስለሆነም የትግሉ መራራነት በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቅ ነው የሚሆነው::

ረ. ትግልን ለማካሄድ ምክኒያት ማብዛት ወደ ኋላ ያስቀራል:: ለምሳሌ አርበኞች ግንቦት ሰባት ከጅምሩ ህብራዊ እንደሆነ ብንረዳም መሰረቱ አማርኛ ተናጋሪ የሆነው ህዝብ ነው:: ድርጅቱን ኦሮሞዎችና ነጻነትን የሚሹ ሌሎች አካሎች መሰረቱ በአማርኛ ተናጋሪው በመሆኑ መሸሻ ምክኒያት ማድረግ የለባቸውም:: ከላይ እንደጠቀስኩት ካሁኑ መሳተፍ የራስን ሃሳብ ውጤት እንዲኖረው ለማድረግ ይጠቅማል:: ከዚህ በተጨማሪ አማርኛ ተናጋሪው በሕወሐትና ሆድ አደር አጋር ፓርቲዎች ሲገፋና ፍዳውን ሲያይ እንኳ እልህ ተጋብቶ የራሴ ሳይል ለኢትዮጵያ ብሎ ነው ሲጮህና ሲታገል የኖረው:: ታዲያ ስተት ካለ እንተራረም እንጂ ማለት ኢትዮጵያዬ ማለቱ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ነው የምቆመው ማለቱ ድጋፍ ያሰጣል፣ አይዞህ ያስብላል እንጂ በጥርጣሬ ያስተያያልን ? የሕወሐትን ከፋፍለህ ግዛ ፖለቲካን መቸም ሁላችንም ጠግበነው አንገሽግሾናል:: እና ለምኑ ብለህ ነው ወገኔ የሚልህን የምትርቅ:: ታሪካዊ ስህተቶችንም እንደምንተራረም መስመር እየዘረጋን ነው:: ያለፈው አልፏል፣ የሆነው ሆኗል ለኢትዮጵያ ህዳሴ፣ ለፍትህ፣ ለዴሞክራሲና ለነጻነት ስንል ዛሬ ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጎን ቆመን ለአገራችን ካንሰር የሆነውን ሕወሐትን እናስወግድ::

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>