Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

ኢትዮጵያዊያኑ የመን ውስጥ በጭንቅ እያነቡ ነው ያሉት

$
0
0

በግሩም ተ/ሀይማኖት

የመን ምጥ በቁና መሆኑን ትታ ምድራዊ ሲዖል እየሆነች ነው፡፡ ባስነጠሳት ቁጥር ግዙፍ ግዙፍ ሚሳኢሎቿን የሚያወድም ሚሳኤል ከአየር እየተወረወረላት ነው፡፡ ያኔ ማስነጠሱ ቀርቶ ይነስራታል፡፡ በዜጎቿ ደም ነስሯን ታንቦለቡላልች፡፡ ሰሞኑን ሰነዓ ከተማ ውስጥ ፈጂ አጣን የሚባለው ቦታ ላይ ያለ የመሳሪያ ክምችት በተከታታይ ተመታ፡፡ ፓለስቲክ ሚሳይሉ ያለው እዛ ውስጥ እንደሆነ ነው የሳዑዲ ባለስልጣኖች የሚናገሩት፡፡ በእርግጥ ትክክልም ይመስላል፡፡ በፍንዳታው አካባቢው በመጥፎ ኬሚካል ተበከለ፡፡ ከ1 ኪሎ ሜትር ራዲየስ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ሳል፣ ቋቅታ፣ ወደላይ ወደታች አናወጣቸው፡፡ በሳዑዲ የሚመራው ህብረ ሀይል አንድ መላ ቀየሱ….
yemen
ቦታውን ታርጌት አድርገው ከባህር ያስወነጨፉት ሚሳይል እየተመዘገዘገ ከተማውን አቋርጦ ሲያልፍ ጀት መስሏቸው ሲተኩሱበት እንደነበር የአይን እማኞች ተናግረዋል፡፡ ሚሳይሉ ግን ታርጌት የተደረገበትን ቦታ በሀይለኛው ድባቅ በታና ወደታች ይዞጥ ጦለመ፡፡ ከፍ ብሎ በቀጥታ ወደታች ቁልቁል ይዞት ሲወርድ ከላዩ አፈር አለበሰው የሚበነው ኬሚካል ተቀበረ፡፡ ለአካባቢው ሰላም ሰጠ፡፡

የመን ሰሞኑን ጫን በርታ ያለ ድብደባ እየደረሰባት ቤቶቻችንም አረገደች ምድር እያሉ እንቅጥቅጥ ድንከራቸውን ተያይዘውታል፡፡ በተመታ ቁጥር ቤቶቹ ያረግዳሉ፤ መስኮት ይከፈታል፣ ህጻናት በድንጋጤ ከተኙበት ተሳቀው ይነሳሉ፡፡ የልብ ምታችን በመቶ እጥፍ ይጨምራል፡፡ የሰነዓ ከተማና መብራት ከተገናኙ ዛሬ ስድስተኛ ቀናቸው ነው፡፡ ውሃ ዋጋው የወርቅ ሆኗል፡፡ ቆሻሻ በየቦታው ተከምሮ ይታያል፡፡ ነዳጅ ከወትሮው ዋጋ በ5 እጥፍ ጨምሯል፡፡ 3000 ሪያል የነበረው በአንዴ 15.000 እና 20.000 ሪያል ገብቷል፡፡ በዚህ ምክንያት ቆሻሻ የሚያነሱት ሰራተኞች መስራት አልቻሉም፡፡ የግማቱ ነገር የፈነዳ ሽንት ቤት ውስጥ የተቆረቆረች ከተማ ሊያስመስላት ነው፡፡

ርሃብም ብዙዎችን ለማጨድ አቆብቁቦ የሸመቀ ይመስላል፡፡ መንገዱ ላይ ውርውር የሚሉት መኪናዎች በጣት የሚቆር ነው፡፡ ሰዉም ቢሆን ከረመዳን ጊዜው የባሰ ጥፍት ብሎ ከተማዋ በጭርታ የተኩስ ድምጽዋን እያዳመጠች ነው፡፡ የሁቲይ ሚኒሻዎች ጄቶቹን ለመከላከል ተኩሱን ከየአቅጣጫው ያዳምቁታል፡፡ ግን ጀቶቹ ጋር የመድረስ አቅም የለውም፡፡

ኢትዮጵያዊያኑ በዚህች አይነቷ የመን ውስጥ ነው በጭንቅ እያነቡ ያሉት፡፡ በእስር የነበሩት 680 ኢትዮጵያዊያን ከሚግሬሽን እስር ቤት ከተፈቱ በተኩል ሰዓት ውስጥ አካባቢው በተኩስ ተናውጦ በአየር ተደበደበ ምንም እንኳን የእስር ቤቱ ባይመታም ዙሪያውን ያሉት ተቋሞች ተደበደቡ፡፡ የሚያሳዝነው ግን ከእስር የተፈቱትን 680 ኢትዮጵያዊያን 30 የሞላውን እንኳን ማግኘቱ ከባድ ሆነ በእውነት ልባችን እንደፈራው ሆኖም መሰለኝ፡፡

በድሮው ፕሬዘዳንት አብደላ ሳላህ ጊዜ ደቡብ የመን እና ሰሜን የመን ሲዋጉ ኢትዮጵያዊያኑን በጦርነት አሰልፎ የነበረው የሰሜን የመን ከጦርነት በኋላ ዜግነት የሰጣቸው ዘሬም ስንት ኢትዮጵያዊያን አሉ፡፡ ታሪክ ራሱን ይደግማል ይባላል፡፡ እኛ ላይ ግን መድገም ብቻ ሳይሆን መደጋገም ሆኖ ጢቢጢቢ እየተጫወተብን ነው፡

The post ኢትዮጵያዊያኑ የመን ውስጥ በጭንቅ እያነቡ ነው ያሉት appeared first on Zehabesha Amharic.


ሰው ማለት ሰው የሆነ ነው ሰው የጠፋለት! –ኤድመን ተስፋዬ

$
0
0

በመንቃት ላይ ባሉ ፍጡራን መሀከል ያረረው ይበስላል ጥሬው እስኪበስል (ጎሞራው)

የምልከታ መነሻ

” አምላክ ከፈጠራቸው ፍጡራኖቹ በተለየ ለሰው ልጅ የሰጠው የማሰብ ፀጋ (ማሰብ እና ማሰላሰል መቻሉ) በራሱ የሰውን ልጅ ክቡርነት አመላካች ነው’’:: ይህን የተናገሩት ይችን አለም በተፈጦሮአዊው ሞት የተለዩት የግብፅ ኦርቶዶክስ ፓትሪያርክ አቡነ ሺኖዳ ናቸው፡፡ እውቁ ህንዳዊው  ኢኮኖሚስት አማርታሲያን ሴን በበኩሉ የሰው ልጅ የማሰብ እና የማሰላሰል ፀጋውን ተጠቅሞ የራሱንም ሆነ የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት እንዲችል ከምንም በላይ ነፃነት ያስፈልገዋል ይላል፡፡ እንደ ሴን ሁሉ እውቁ ፊሎሰፈር በርናንድ ሾው ማሰብ የጀመረ ሰው ያለ ነፃነት መኖር ሞቱ ነው ይላል፡፡ ከላይ የጠቀስኩአቸውን የሴን እና የበርናንድን ዘመን ተሸጋሪ እይታዎች መነሻ ስናደርግ ማሰብ ማለት ነፃነት ስለመሆኑ የሚያመላክተን ይመስለኛል፡፡ በሌላ በኩልም ለዚህ ፅሁፍ መግቢያ ያደረኩትን የአቡነ ሺኖዳን መንፈሳዊ ትንታኔ ከሴን እና ከበርናንድ እይታዎች ጋር ስንገምደው የማሰብን ፀጋ አምላክ ለሰው ልጅ ከሌሎች ፍጡራን በተለየ የሰጠው እንደመሆኑ  የማሰብ ፀጋም ሆነ ነፃነት የሰው ልጅ ሰው መሆኑ ብቻ የሚያገኘው ነው እንደማለት ስለመሆኑ የሚያመላክት ይመስለኛል፡፡ከላይ እንደጠከስኩአቸው  ሴን፣በርናንድ እና አቡነ ሺኖዳ ሁሉ በሙያቸው እስከ አሁን ምትክ አናገኝላቸው ይሆን እያልን የምንጨነቅላቸው የአደባባይ ሙሁሩን የፕ/ሮ መስፍን ወልደማርያምን  አንባገነኖች አእምሮአቸውን ስተው በጡንቻቸው ማሰብ ሲጀምሩ የሰውን ልጅ ክቡርነት ረስቶ ፍትህን ማጉአደል የሚጀምሩበትን ሁነት የተነተኑባቸውን ዘመን ተሸጋሪ ፅሁፎቻቸውን ማእከል ስናደርግ የአንባገነኖች ክፋት ከፈጣሪ የተሰጠውን የማሰብ ነፃነት ለመገደብ መሞከራቸው ስለመሆኑ የሚያመላክተነት ይመስለኛል፡፡

ዘመን ተሸጋሪ ስራዎቻቸውን አስቀምጠውልን በህገ ሞት ይቺን አለም ለተሰናበቱት ለበርናንድ እና ለአቡነ ሺኖዳ ለነብሳቸው እረፍትን እየተመኘው እንዲሁም ዘመን ተሸጋሪ ስራዎቻቸውን ላበረከቱልን እና ገና ለሚያበረክቱልን ለፕ/ር መስፍን ወልደማርያም እና ለአማርታ ሲያን ሴን ረዥም እድሜን ከመልካም ጤንነት ጋር እየተመኘው የዚህ ፅሁፍ ትኩረት ወደሆነው በእስር ቤት በጀርባ ህመም በመሰቃየት ላይ የሚገኘው ሰው በጠፋበት ሀገር ሰው ስለሆነው የትውልድ ተጋሪዬ ወጣት ስመለስ  ወጣቱ ልጅ ሰው በጠፋበት ሀገር ሰው እንዲሆን ያስቻለውን ምክንያቶች ከሀገራዊ ፋይዳዎቻቸው (ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ)  አኩአያ ለማሳየት እሞክራለው፡፡

ግለሰብ Vs አንባገነናዊ ስርአተ መንግስት

በአንድ ሉአላዊ ሀገር የሚኖሩ ህዝቦች ውስጥ እንደ ግለሰብ ለማህበረሰቡ የሚያበረክተውን ፋይዳም ሆነ ሚና  እንዲሁም ማህበረሰቡ ደግሞ ለግለሰቦች የሚያበረክተውን ፋይዳ ከሀገራዊ ሀብት ክፍፍል እና ከፍትሀዊ ስርአተ መንግስት አኩአያ ለማየት  መንግስታዊውን ባህሪ መነሻ በማድግ መንግስታዊው ባህሪ በግለሰብ እና በማህበረሰብ ላይ ያለውን ተፅእኖ መነሻ ማድረግ ተገቢ ይመስለኛል፡፡ መንግስት ማለት እንደ እኔ እምነት ህዝቦች በሰጡት  የሚታደስ እና የሚነጠቅ ውክልና ህዝቦችን የሚያስተዳድር የግለሰቦች ስብስብ ሲሆን፣ በግለሰቦችም ሆነ በአንድ ግለሰብ  የሚዘወረው እና   የመንግስታዊው ባህሪ መገለጫ አንባገነናዊነት በሆነበት ስርአተ መንግስት የስርአቱ አንባገነንነት ስፋት ግለሰብንም ሆነ ህብረተሰብን ሳይለይ ሁሉንም ህዝቦች በአንባገነናዊ ስርአት መግዛት እንደመሆኑ አንባገነናዊ ስርአት የግለሰብንም ሆነ የህብረተሰቡን መብት የመደፍጠጡ ሁነት አይቀሬ ነው፡፡ ትልቁ ጥያቄ ግን አፍጦ አግጦ ለመጣ አንባገነናዊው ስርአት የግለሰቦች እና የማህበረሰቡ ምላሽ እስኬት ነው የሚለው ይመስለኛል፡፡

አፍጦ አግጦ ለመጣ አንባገነናዊ ስርአተ መንግስት እንደ ግለሰብም ሆነ እንደ ማህበረሰብ የሚኖርን (መፍራትም ሆነ መተቸት ሊሆን ይችላል) ምላሽ ለማየት የእውቁን ራሺያዊው  ፀሀፊ ቶልስቶይ አንድ ዘመን ተሸጋሪ ፅሁፍ እና የስሎቫኩን ፊሎሰፈር ዙዜክ እይታዎች በአስረጂነት ማቅረቡ ተገቢ ይመስለኛል፡፡

አንድ ግለሰብ ፊልም ለማየት ወደ ሞስኮ ቲያትር ቤት ገብቶ ወደ ሲኒማ ቤቶቹ ውስጥ ከሚገኙት ወንበሮች ውስጥ መጨረሻ ላይ ወደሚገኘው ወንበር ገብቶ ተቀመጠ፣ ከጥቂት ደቂቃዎች በሁአላ አንድ ጄነራል እንደ ግለሰቡ ሁላ ፊልም ለማየት ወደ ሲኒማ ቤቱ በመግባት መጀሪያው ረድፍ ላይ ከሚገኙት ወንበሮች ውስጥ አንዱ ላይ ይቀመጣል፣ ፊልሙ እንደተጀመረ ጂነራሉ  ወደ ሁአላ ዞር ሲሉ ጥግ ላይ የተቀመጠው ግለሰብ ጄነራሉ አብዮቱን እንደምደግፍ አወቁብኝ እንዴ በማለት ግራ ይጋባል፣ ጄነራሉ በድጋሚ  ወደሁአላ ዞር ሲሉ ጥግ ላይ የተቀመጠው ግለሰብ በቃ አለቀልኝ ጄነራሉ አብዮቱን እንደምደግፍ አውቀውብኛል በማለት ይደመድማል፣ ጄነራሉ ለሶስተኛ ጊዜ ዞር ሲሉ ጥግ ላይ የተቀመጠው ፈጠን ብሎ ወደ ፊልም ሲከታተሉ  በየ ሁነቱ ወደ ሁአላ ዞር ማለት አመላቸው ወደ ሆነው ጄነራል በመሄድ እግራቸው ስር በመውደቅ ለዛሬ ይማሩኝ ተሳስቼ ነው የአብዮቱ ደጋፊ የሆንኩት በማለት ተናዘዘ፡፡ ከላይ የገለፅኩት ረሺያዊው ጠሀፊ ቶልስቶይ አንባገነናዊ ስርአተ መንግስት ከሻፊ ግለሰቦች ላይ ስለሚፈጥረው መርበድበድ  የገለፀበት ስነፅሁፉ አንባገነናዊ ስርአተ መንግስት ግለሰቦች ላይ ስለሚፈጥረው ሽብር ማሳያ ይመስለኛል፡፡ ስሎቫካዊው ፈላስፋ ዚዜክ የግለሰቦች ንቃተ ህሊና ሚዛናዊ ሲሆን በንቃተ ህሊናው ልክ የሆነ ስርአተ መንግስት የመፈለጉን አይቀሬነት ይገልፃል፡፡ እንደ ዙዜክ እምነት በግለሰቦች ሚዛናዊ ንቃተ የተነሳ የሚፈጠረው  ግለሰባዊ ፍላጎት ከግለሰባዊ ንቃተ ህሊና በታች ለሆነው ግለሰቡ ለሚኖርበት ማህበረሰብ ያለው  ፋይዳ  አንባገነናዊ ስርተ መንግስትን በመጋፈጥ ህብረተሰቡን ለሚዛናዊ ንቃተ ህሊና ማድረስ እንደመሆኑ  ለግለሰቡ ከሚኖረው ፋይዳ በላይ ነው፡፡

ተመስገን !

አምላክ ለሌሎች ፍጡራኑ ያልሰጠውን ነገር ግን ለሰው ልጆች ብቻ  የሰጠውን የማሰብ ፀጋ ተግባራዊ በማድረጉ የተነሳ ነፃነቱን ለድርድር የማያቀርበው በፋክት መፅሄት ላይ የአምድ ባልደረባዬ የነበረው ተመስገን ደሳለኝ ለኔ ማሰብ የጀመረ ሰው ከምንም በላይ ለነፃነቱ ቅድሚያ እንደሚሰጥ ማሳያ የሆነ ግለሰብ ነው፡፡ በእኔ እምነት  የአባት እዳ ለልጅ እንዲሉ መጠላለፍ እና አሸናፊነትን እና ተሸናፊነትን ብቻ  ፖለቲካዊ ባህሉ ላደረገው  እና አሁንም የሀገሪቷን ፖለቲካ ከሚዘውረው የያ ትውልድ ፖለቲካ ባህል ውስጥ ከመጠላለፍ ውስጥ ህብረትን፣ ከአሸናፊነት እና ተሸናፊነት ውስጥ አሸናፊነትን እና አሸናፊነትን ብቻ ያሳየ የአዲሱ ትውልድ አፍ ነው ፡፡ ከጳጳስ እስከ ሼካ፣ ከሼካ እስከ ምሁር፣ከምሁር እስከ ኪነጥበብ ባለሞያ ወዘተ ሀገርን እና ህብረተሰብን ወደ ጎን በመተው ለጓዳው ብቻ በማሰብ ምናገባኝ ባይ በሆነበት ሀገር ውስጥ ከአንባገነናዊው ስርአተ መንግስት በላይ የሚያስጨንቀው እንደ እኔ እምነት አርአያ የሚሆን ግለሰብ ያጣችው እና የሞራልን ዋጋ የናዱ ግለሰቦች የሚፈነጩባት ሀገር እጣ ፈንታ ነው፡፡  እንደ እኔ እምነት ተመስገን ደሳለኝ   አርአያ የሚሆን ግለሰብ ላጣቸው እና  የሞራልን ዋጋ የናዱ ግለሰቦች መፈንጫ ለሆነቸው ሀገሩ ሀገሬ በግለሰቦች የግል ፍላጎት የተነሳ ህልውናዋ አደጋ ላይ ሊወድቅ አይገባም በሚል ብእሩን የግለሰቦች ስብስብ በሆነው ስርአት  እና የስርአቱ  አንቋላጮች ላይ  ያነሳ የሀገሩ እጣ ፈንታ ያስጨነቀው ግለሰብ ነው፡፡

ከህዝብ በሚሰበሰብ ቀረጥ የሚከናወነው የልማት እንቅስቃሴ ወደ ግለሰቦች ጓዳ በሚገባበት፣ ከኢህአዴግ አባልነት ውጪ ስራ ማግኘት ከባድ በሆነበት፣ የወጣት ጥቃቅን እና አነስተኛ ማህበራት የፋይናንስ ዋስትና አደጋ ላይ በወደቀበት፣ ባለሀብቱ ዛሬ ደግሞ ምን ሊሉን ይሆን በሚል በነጋ በጠባ በሚጨነቅበት፣ ባህል እና እሴቶቻችን ጠፍተው የህዝብን እና የሀገርን ሀብት የዘረፈ  ደሩትን ነፍቶበአደባባይ በሚሄድበት እና በሚከበርበት፣ ፍትህን ለገንዘብ ብሎ ያዛባ ያሻውን በሚያደርግበት፣  ከዲግሪ እስከ ፒኢች ዲ በዘረፈው ገንዘብ ገዝቶ በማን አለብኝነት በአስተዳዳሪነት በተቀመጠበት በዘመነ ኢህአዴግ ላይ ለአቅመ አዳም የደረሰው ተሜ የአዲሱ ትውልድ አካል እንደ መሆኑ ለአዲሱም ሆነ ለነባሩ ትውልድ በመረጃ የተደገፈ ሚዛናዊ ሂስ እና ትችት ከፍ ሲልም ማስጠንቀቂያና መፍትሄን ከድፍረት ጋር ማቅረብ እንደሚቻል ያሳየ ከመሆኑም በላይ ኢትዮጲያዊነትን ማንም መስጠትም ሆነ መንፈግ እንደማይችል በተግባር ያሳየ ሰላማዊ ባለሞያ ነው ለኔ፡፡

ተመስገን ደሳለኝ ከፍትሀዊ ሀብት ክፍፍል እስከ አንባገነናዊ የግለሰቦች ጭቆና በብእሩ መግለፁ በአንድ በኩል እንደ ህዝብ የደረሰበትንም ሆነ ወደፊት ስለሚጠብቀው አደጋ ለባለቤቱ በማሳወቅ ረገድ በሌላ በኩል ለጭቆናወቅም ሆነ ለሌብነቱ መንስኤ ለሆኑት ግለሰቦች በነሱ የተነሳ በህዝቡ እና በሀገሪቷ ላይ ስለደረሰው እና ስለሚደርሰው ሁነት በማሳየት ረገድ ከፍተኛ ሚና ያበረከተ ብቻ ሳይሆን ገና የሚያበረክት ስለመሆኑ ሳስብ ፊቴ ላይ ድቅን የሚለው እና የሚያሳስበኝ  ተሜ ሰው በጠፋበት ሀገር ሰው በመሆኑ የተነሳ  በዝዋይ እስር ቤት ታስሮ በጀርባ ህመም የመሰቃየቱ ነገር ነው፡፡  በመንቃት ላይ ባሉ ፍጡራን መሀከል ያረረው ይበስላል ጥሬው እስኪበስል ብሎ የገጠመው  ጎሞራው በህይወት ኖሮ  የተሜን ህመም ቢሰማ ምን ይል ነበር ?

Comment

The post ሰው ማለት ሰው የሆነ ነው ሰው የጠፋለት! – ኤድመን ተስፋዬ appeared first on Zehabesha Amharic.

በአሜሪካ የመሸገው የሳሙኤል ዘሚካኤል ደቀ-መዝሙር

$
0
0

senakriem1
ክንፉ አሰፋ

“አሜሪካ ይዞን ከሄደ በኋላ በዋሽንግተን ዲሲ አንድ የገበያ አዳራሽ (ሞል) ውስጥ ጥሎን ጠፋ…ፖሊስ ሁለት ግዜ ይዞን ነበር… በርሃብ ተቀጣን፣ ርሃብ ጸንቶበት ሆስፒታል የገባም ልጅ አለ። … በየሬስቶራንቱ እየዞርን ለምነናል።” ይላል አንድ የ 11 አመት ሕጻን ሳይንቲስት። ሂውስተን ቴክሳስ ያሚገኘውን ናሳ የጠፈር ምርምር ተቋም ለመጎብኘት ከአዲስ አበባ ሄደው ነው አስሩ ሕጻናት ዲሲ ላይ የሚሰቃዩት።

አስሩን ህጻናት በአንድ መኪና(ትራክ) ውጽጥ አጭቆ ነበር ወደ ሞሉ የወሰዳቸው። የያዘው መኪና ከአራት ሰው በላይ መጫን አይችልም። እመንገድ ላይ ፖሊስ እንዳያያቸው “ሁላችሁም ጎንበስ በሉ።” ይላቸው እንደነበርም ህጻናቱ አጫውተውኛል።

እነዚህ ሕጻናት ሀገሪቱ የምትመካባቸው የነገ ሳይንቲስቶችዋ ናቸው። ከአጠቃላይ ትምህርት ቤቶች ተወዳድረው ከፍተኛ፤ እጅግ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ታዳጊዎች። በነዚህ ታዳጊዎች እና በወላጆቻቸው ላይ የደረሰው በደል እጅግ ብዙ ነው። ታሪኩ አንድ አሳዛኝ ፊልም ይወጣዋል። ወላጆቹ አሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ደውለው ይህ በደል ለህዝብ ይፋ እንዲሆንላቸው ቢጠይቁም የራዲዮ ጣብያው ጉዳዩን ባልታወቀ ምክንያት አፍኖታል። ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለጻፉት የአቤቱታ ደብዳቤም ምላሽ ተነፍገዋል። ጉዳዩ ለሚመለከተው ክፍል ሁሉ አቤት ብለዋል። ሰሚ ግን አላገኙም።
senakriem-mekonnen

ይህንን በደል የፈጸመው ግለሰብ ከአዲስ አበባ እንዲሸሽ ተደርጎ በዚያው በዋሽንግተን ዲሲ በአንድ የፕሮቴስታንት ፓስተር ቤት መሽጓል። በአሜሪካ የመኖርያ ፈቃድ የለውም። የባንክ ሂሳብ ግን አውጥቶ ገንዘቡን እዚያው አከማችቷል።

የትንግርታዊው “ዶክተር” ሳሙኤል ዘሚካኤልን የሽወዳ ስልት ገና ከአእምሯችን ሳናወጣ፤ ሌሎች የእሱ ደቀ መዝሙሮች ብቅ እያሉ ነው። ስልታቸውን ይቀይሩ እንጂ የሁሉም ቁጭ በሉዎች አላማ አንድ ነው – ህዝብን ማታለል። አንዳንዶቹ ለሽወዳቸው ረቀቅ ያለ ዘዴ ሲጠቀሙ ሌሎች ደግሞ ዘርካካ በመሆን የዋሁን ህዝብ በዘረፋ ተያይዘውታል።

ዛሬ ይዤላችሁ የቀረብኩት አጭበርባሪ የረቀቀ ስልት ባይጠቀምም ለሌብነቱ የተለየ መንገድ ይዞ ነው ብቅ ያለው። ሰናክሪም መኮንን ይባላል። ይህ ሰው የገዥው ፓርቲ አባል በመሆኑ ለዝርፊያው ምቹ መንገድ እንደፈጠረለት ይነገራል።

የሰናክሬም መኮንን አንድ አዲስ ፕሮጀክት ነደፈ። ከመላው ትምህርት ቤቶች በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያመጡትን አወዳድሮ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ታዳጊዎችን አሜሪካ በመውሰድ ሂውስተን ቴክሳስ የሚገኘውን ናሳ የጠፈር ምርምር ተቋም ማስጎብኘት። ከዚህም ሌላ የላቀ ውጤት ላመጡ ህጻናት የላፕቶፕ እና የአይፓድ ልዩ ሽልማት እሰጣለሁ ብሎ ቃል ይገባል። በየትምህርት ቤቱ እየዞረ የትምህርት ቤቶቹን እና ልዩ ልዩ መገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም አላማውን አስፈጸመ። ወጪውን ሁሉ የሚሸፍኑ ስፖንሰሮች አገኘ። አዲካ ትራቭል፣ ኦሮሚያ ባንክ እና ኢትዮጵያ አየር መንገድ የህጻናቱን ወጪ በሙሉ የሚሸፍን በቂ የሆነ ስፖንሰር ተገኘ።
macdonalds
ሰናክሬም የስፖንሰሩን ድጋፍ እና የአስሩን ህጻናት ፓስፖርት ይዞ አሜሪካ ኤምባሲ ለቪዛ ሄደ። በቂ የስፖንሰር ድጋፍ ስለነበረው ያለምንም ችግር የልጆቹን ቪዛ አገኘ።

ጫወታው እዚህ ላይ ነው የሚጀምረው። ስፖንሰሩን እና ቪዛውን በእጁ ካስገባ በኋላ የህጻናቱን ቤተሰቦች በተናጥል እየጠራ እያንዳንዳቸው የህጻናቱን የትራንስፖርት እና የመስተንግዶ ወጪ እንዲሸፍኑ ጠየቃቸው። ሰውየው በቂ በጀት ከስፖንሰሮች እንዳገኘ በወላጆቹ ይታወቃል። በመጀመርያ የገባውን ቃል አጥፎ ወላጆቹ የልጆቻቸውን ወጪ እንዲሸፍኑ መጠየቁ ለሁሉም እንግዳ ሆነባቸው። ሁሉም አንከፍልም ሲሉ መለሱለት።

ሰናክሬም ግን አጭር መልስ ሰጣቸው። “ወጪውን የማትሸፍኑ ከሆነ እድሉል ሌሎች ልጆች እሰጠዋለሁ።” ሲል የባሰ መርዶ አመጣባቸው።
ወላጆች አጣብቂኝ ውስጥ ገቡ። በአንድ በኩል ልጆቻቸው ወደ ሂውስተን ለመሄድ ተነሳስተዋል። የልጆቻቸውን ስሜት መጠበቅ ግድ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ሰው እያጭበረበራቸው መሆኑን አውቀውታል። ከብዙ ማንገራገር በኋላ ግን ገሚሱ ወላጅ የአውሮፕላን ትኬት፣ የአምስት ኮከብ ሆቴል፣ የመስተንግዶ እና የኮቴ ከፍሎ ልጆቹን ወደ አሜሪካ ላከ። ሰናክሬም ከውጭ ሃገር ከተቀበለው ዶላር ውጭ ወላጆቹ የከፈሉት ገንዘብ በድምሩ አንድ ሚሊዮን ብር ይጠጋል።

ይህንን ወጪ መክፈል ያየልቻሉ ህጻናትን ተሰረዙ። የነሱ እድል ሌሎች ጥሩ ውጤት የሌላቸው ግን ገንዘብ ላላቸው ወላጆች ተሸጠ። ዘረፋው በዚህ መልኩ ተፈጸመ። አስሩ ህጻናትም ወደ አሜሪካ ተጓዙ።

ወደ ዋና ድራማው ደግሞ ልውሰዳችሁ። አሜሪካ ዋሽንግተን እንደገቡ ለአንድ ቀን ብቻ በማሪዮት ሆቴል ቆይታ ያደርጋሉ። በነጋታው ሁሉም በአንድ ትራክ ተጭነው እዚህ ግባ የማይባል ማረፍያ ውስጥ በቡድን በቡድን ታጎሩ።

የጉዞው ዋና አላማ በሂውስተን የሚገኘውን የናሳ ጠፈር ምርምር ተቋም መጎብኘት ነበር። እሱን እርሱት ብሏቸዋል ሰናክሬም። ለግዜው ወላጆችን ማታለያ አስሩንም በቡድን ፎቶ አነሳቸው። የናሳን ማስክ በፎቶሾፕ እያስገባ አለበሳቸው። ናሳ የሄዱም አስመሰላቸው። ፎቶውንም በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ለጠፈው።

አሁን ልጆቹም ስለናሳው ጉዳይ አያስቡም። ከወላጆቻቸው ተነጥለው ወጥተው በአንድ ሃላፊነት በጎደለው ሰው እጅ ላይ ወድቀዋል። በአንድ ክፍል ወስጥ ተቆልፎባቸው ይውሉና ለተወሰነ ሰዓት በገበያ አዳራሽ ውስጥ ይለቀቃሉ። በአሜሪካን ሃገር በርሃብና ጥማት እየተሰቃዩ ነው። ረሃብ ጸንቶባቸው ሆስፒታልም የገቡ አሉ።

ወላጆቹ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጻፉት ደብዳቤ*፣ “ሰናክሬም ከእያንዳንዱ ወላጅ የአምስት ኮከብ ሆቴል ሂሳብ ተቀብሎ ሳለ ህጻናቱ ግን ተገቢውን የሆቴል አገልግሎት አላገኙም። ሴቶቹ የማይታወቁ ሰዎች ቤት እንዲያርፉ መደረጉ እና ወንዶቹ ደግሞ በቡድን በአንድ ክፍል ውስጥ እንዲያድሩ አድርጓል።” ብለዋል።

ምግብን በተመለከተ ተገቢውን ምግብ ሳይመገቡ ለረሃብና ለህመም መዳረጋቸውና ከዚህም የተነሳ በምግብ ማጣት ጉዳት ሆስፒታል መግባታቸው፤ የተወሰኑት ከአቶ ሰናክሬም ተወስደው ወደ ዘመድ ቤት እንዳረፉ በደብዳቤው ላይ ተገልጿል። በመጀመርያዎቹ ቀናት ማክዶናልድ እየወሰደ ይመግባቸው እንደነበር ልጆቹ ተናግረዋል። ከዚያ በኋላ ነው የረሳቸው።

ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ ደግሞ እነዚህን በአደራ የተቀበላቸውን ህጻናት በዋሽንግተን ዲሲ ለልመና መጠቀሙ ነው። “ከሄዱበት አላማ ውጪ በአደራ የተቀበላቸውን ህጻናት በየቤተክርስትያኑ እያዞረ ‘ለችግረኛ የሚሆን’ በማለት ኩፖን በማሸጥ አሰማርቷቸውም ነበር።” ይላል ደብዳቤው። ልጆቹን በዚህ መልኩ በልመና በማሰማራት በሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ እንደሰበሰበ ህጻናቱ ይናገራሉ። በተለይ ዋሽንግተን ዲሲ ያለው ወንጌላዊ ቤተ-ክርስትያን ህጻናቱ በጉባኤው ፊት ቆመው የልመናውን ኩፖን እንዲያሳዩና እንዲሸጡ አድርጓቸዋል። ይህ የሆነው የቤተ-ክርስቲያኗን ፓስተር ሃንፍሬይን በማታለል ነው።

ሕጻናቱ በዚህ መልኩ ተንገላትተው ግን ለመጡበት አላማ ምንም ነገር ሳያደርጉ ሊመለሱ ነው። በአካባቢው ያሉ የቤተሰብ አባላት አንድ ሃሳብ አመጡ። ኢትዮጵያዊው ጠረፍ ሳይንቲስት የሆኑትን ዶ/ር ብሩክ ላቀውን በጉዳዩ አማከሩዋቸው። ዶ/ር ብሩክም ፈቃደኛ ሆኑ። በወላጆች ትውውቅ የመጡት እኚህ ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት ህጻናቱ ካረፉበት ስፍራ ድረስ በምሄድ ስለ ናሳ አስረዷቸው።

ህጻናቱም ይህችን እውቀት ይዘው፤ ናሳን በቴለቭዥን እንኳን ሳይመለከቱ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ። የሰናክሬም የናሳ ጉዞ ፕሮጀክትም በዚህ ላይ ተጠናቀቀ። ገቢው አጓጊ ነውና ሰናክሬም አሁንም ሌላ ዙር ሊሰራ ማሰቡ አልቀረም።
የህጻናቱ ቤተሰቦች ግን በመሰባሰብ የጋራ አቋም ላይ ደርሰዋል። ያላግባብ የተወሰደባቸው ገንዘብም እንዲመለስ ጠይቀዋል። ሰናክሬም ግን ሸሽቶ አሜሪካ መሽጓል።

ይህ መረጃ እንደደረሰኝ ሰናክሬም መኮንን በኢሜል አግኝቼው ነበር። ጉዳዩን እልባት እንዲሰጥ፤ የሰዎቹንም ገንዘብ እንዲመልስ በተደጋጋሚ ጠየቅኩት። ይህ ከልሆነ ታሪኩን ለህዝብ ይፋ እንደማደርገውም ነግሬው ነበር። ይህ ጉዳይ ሜድያ ላይ ከወጣ ታዋቂ እንደሚያደርገው ተናግሮ አሾፈብኝ።

ይህንን የማደርገው ለሌሎች ወላጆች ትምህርት እንዲሆን ነው። ጉዳዩን ለበርካታ የሜዲያ አካላት ማሳወቄም ግድ ነው። ለጥንቱ ወዳጄ ሰይፉ ፋንታሁንም የህጻናቱን በደል ነግሬው ነበር። ህጻናቱን አነጋግሯቸዋል። ጉዳዩን በቅርቡ እንደሚያቀርበው ነግሮኛል።
ወላጆች በጋራ በመሆን ለሚመለከተው አካል የጻፉትን አቤቱታ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።*
*

The post በአሜሪካ የመሸገው የሳሙኤል ዘሚካኤል ደቀ-መዝሙር appeared first on Zehabesha Amharic.

ISIL በሊቢያ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን በማረድ እና በጥይት ገደለ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ISIL ወይም ISIS በሚል የሚታወቀው ቡድን በሊቢያ 30 ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን ግማሹን በማረድ ግማሹን በጥይት መግደሉን በለቀቀ ቪዲዮ አስታወቀ::
ethiopian killed

Ethiopian killed by ISIL

ethiopian killed by isil 1

ethiopian killed by isil 3
ISIL በለቀቀው የ29 ደቂቃ ቪዲዮ በሊቢያ ሁለት ግዛቶች ውስጥ ማለትም ባርካ እና ፋዛን ከተሞች ውስጥ እነዚህን ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች በጥይት እንዲሁም ሌሎቹን ሲያርዷቸው አሳይቷል::

ማስክ ያጠለቁት እነዚሁ የISIL አባለት ኢትዮጵያውያኑን የያዟቸውና ከላይ በተጠቀሱት ከተሞች ሕይወታቸውን ያጠፉት ከምስራቅ እና ደቡብ ሊቢያ እንደተያዙ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል:: ክርስቲያኖቹ ሃይማኖታቸውን እንዲቀይሩ አልያም የተለየ ታክስ እንዲከፍሉ ከመታረዳቸውና ከመገደላቸው በፊት እንደተጠየቁ የዘገበው አሶሺየትድ ፕሬስ ኢትዮጵያዊያኑ በባህር ዳርቻ አካባቢ ሕይወታቸው ተቀጥፏል ብሏል::

በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሰሃራ በረሃን በማቋረጥ ሊቢያ በሚገቡበት ወቅት ለበርካታ ችግሮች በተለይም ለተገዶ መደፈር; ለኩላሊት መሰረቅ እንዲሁም ለመገደልና ለመታሰር ሲበቁ ቆይተዋል::

ISIL የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ በርካታ አስተያየቶች እየተሰጡ ሲሆን ጋዜጠኛና አክቲቭስት አበበ ገላው በፌስቡክ እጹ የሚከተለውን አስፍሯል::

ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ወያኔ ነው!
በየመንና በደቡብ አፍሪካ የተከሰተው ሰቆቃ ሳያንሰን ዛሬ ደግሞ በሊቢያ ISIS ኢትዮጵያዊያን ክርስቲያኖችን ሰብስቦ ማረዱን አረዳን። ኢትዮጵያዊው በአገሩ ክብርና መብት ተነፍጎ፣ በአስከፊ ድህነት ይሰቃያል፣ ከመሬቱ፣ ከቤቱ ከቀዬው ይፈናቀላል፣ ታፍኖ በየእስር ቤቱ ይታጎራል፣ ይገደላል፣ በሃሰት ይከሰሳል፣ ሰቆቃ ይፈጸምበታል። የተሰማኝ ሃዘን ጥልቅ ነው። ቸሩ አምላክ የነዚህን ምስኪን ሰማእታት ነፍስ ይታደግልን፣ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ይስጥልን።
በስደትና በሽሽት ምድር ተዋርዶ መኖር ሳይበቃው በቁሙ ይቃጠላል፣ እንደ በግ ይታረዳል። የዚህ ሁሉ ችግር ዋነኛ መንስኤ ወያኔዎች ኢትዮጵያን ለጥቂቶች ምድራዊ ገነት ለብዙሃኑ ደግሞ ምድራዊ ሲኦል በማድረጋቸው ምክንያት መሆኑ ህሊና ላለው ሁሉ ግልጽ ነው። ለአንድ ህዝብ ከዚህ የከፋ የቁም ሞት የለም። ኢትዮጵያዊ ሁሉ በያለበት በቃ ብሎ የሚነሳበት ግዜ አሁን ነው። አገሩን ያላስከበረ ትውልድ ከዚህም የከፋ ይገጥመዋል። ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ወያኔ ነው። በቃ ብለን በአንድነት የምንነሳበት ግዜ አሁን ነው። ሊነጋ ሲል ይጨልማል!

The post ISIL በሊቢያ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን በማረድ እና በጥይት ገደለ appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: ቡናን በባዶ ሆድ መጠጣት በጤና ላይ የሚያመጣውን ጉዳት ያውቁ ኖሯል?

$
0
0

በሙለታ መንገሻ

ቡና በውስጡ አንቲኦክሲዳንት በመያዙ በሽታን ይከላከላል በተለይም ለአንጀት ካንሰር እና ሎሌች በሽታዎች በቀላሉ እንዳንጋለጥ ያድርጋል።

በተጨማሪም ቡና በውስጡ ካፌን የተባለ ንጥረ ነገር ስላለውም ሰዎች ብዙ ጊዜ ለመነቃቃት ይጠቀሙበታል።

በቡና ውስጥ ያለው አንቲኦክሲደንት በአትክልት እና ፍራፍሬ ውስጥ ያለው ክሎሪን ጄኒክ አሲድ ስብስብ መሆኑ ይነገራል።
ethiopian coffee
ይህም ቡናን በባዶ ሆድ በምንጠጣበት ወቅት እኛ ላይ ጉዳት እንዲሚያስከትል ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው ይባላል።

ጠዋት ከእንቅልፋችን እንደነቃን በባዶ ሆድ ቡናን የምንጠጣ ከሆነም ምግብ በሆዳችን ውስጥ በቀላሉ እንዲፈጭ የሚያደርገውን ሀይድሮሊክ አሲድ ላይ ጉዳት በማድረስ በቀላሉ ጨጓራችንን እንዲያመን ያድርገናል።

ለምግም መፈጨት በሚረዳን ሀይድሮሊክ አሲድ ላይ በቡና አንቲከኦክሲደንት አማካኝነት ጉዳት ከደረሰበት ከበድ ያሉ እና ፕሮቲንነት ያላቸው እንደ ስጋ ያሉ ምግቦች ሆዳችን ውስጥ በቀላሉ መፈጨት ስለማይችሉ እንደ ሆድ መነፋት፣ የሰውነት መቆጣት፣ የአንጀት ቁስለት እና ለአንጀት ካንሰርም ሊያጋልጠን ይችላል ይላሉ ተመራማሪዎቹ።

ቡናን ከእንቅልፍ እንደተነሳን የምንጠጣ ከሆነ በሰውነታችን ውስጥ ያለ የኮርቲሶን ንጥረ ነገር መጠን እንዲጨምር በማድረግ ሆዳችን እንዲነፋ ያደርጋል እንዲሁም እንዲያስታውከን በማድረገ ሰውነታችን እዳይረጋጋ ያደርጋል።

ስለዚህም በተለያዩ ጊዜ የተሰሩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ቡናን ጠዋት መጠጣት ያለብን ከእንቅልፋችን ነቅተን ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ያክል ከቆየን በኋላ እና ቢያንስ አንድ ዳቦ ከበላን በኋላ መሆብን አለበት ይሉናል።

coffee-beans-story
በጠዋት ስንነሳ ቁርስ የመብላት ባህሪ ከሌለን ቡናን መተው የሚመከር ሲሆን፦ አይ እኔ ያለ ቡና ቀኔን መጀመር አልችልም የምትሉ ከሆነ ደግሞ ቡናው የሚደርስብንን ጉዳት ለመቀነስ ያክል ትንሽ ወተት ወይም ቅቤ ቡናው ላይ ጨምረን መጠጣት አይዘንጉም ይሉናል ተመራማሪዎች።

ምንጭ፦ homehealthyrecipes.com

The post Health: ቡናን በባዶ ሆድ መጠጣት በጤና ላይ የሚያመጣውን ጉዳት ያውቁ ኖሯል? appeared first on Zehabesha Amharic.

በዋሽንግተን ዲሲ የደቡብ አፍሪካ ኢምባሲ አጠገብ ነገ ሰኞ ጠዋት ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ሰሞኑን በደቡብ አፍሪካ በስደተኞች ላይ የተፈጸመውን ግድያና ማዋከብን በመቃወም የደቡብ አፍሪካ መንግስት ይህን ጉዳይ በቶሎ እንዲያስቆም የሚጠይቅ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ እንደሚደረግ አዘጋጆቹ ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::
south africa ethiopians
በደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያውያኑ እና በሌሎች የአፍሪካውያን ስደተኞች ላይ የተፈጸመውን አሳፋሪ ድርጊት በመቃወም የተለያዩ ሃገር ወዳድ አርቲስቶች በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ሃዘናቸውን ሲገልጹ ነበር:: ከነዚህም መካከል በቅርቡ ‘ወገኔ’ የሚል ትልቅ መልዕክት ያለው ሙዚቃ የለቀቀው አርቲስት ብርሃኑ ተዘራ ይጠቀሳል:: ብርሃኑ በደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያውያኑ ላይ የተፈጸመውን ድርጊት አውግዞ ከወገኖቹ ጋር እንደሚቆምና እስካሁንም ጉዳት ያልደረሰባቸው ወገኖች ሁኔታው እስኪረጋጋ ድረስ ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጠይቋል:: ብርሃኑ “ከዚህ በፊትም በአረብ ሃገር አሁንም በደቡብ አፍሪካ በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይ ያሳዝናል” ብሏል::

ታዋቂው ተወዛዋዥ አብዮት (ካሳነሽም) እንዲሁ በደቡብ አፍሪካ ሕይወታቸውን ላጡ ኢትዮጵያውያን ፈጣሪ በገነት ነብሳቸውን እንዲያኖር ጠይቆ በጉዳዩ በጣም ማዘኑን ገልጿል:: ወጣቱ ተወዛዋዥ አብዮት በደቡብ አፍሪካ በስቃይ ላይ ለሚገኙት ወገኖቹ በሙያው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጿል:: በተጨማሪም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በያለበት ሃገር የደቡብ አፍሪካ ኢንባሲ ደጃፍ በመገኘት ለወገኖቹ ድምጹን እንዲያሰማ ጥሪም አቅርቧል::

እንቆቅልሽ የተሰኘ ተወዳጅ አልበም በቅርቡ የለቀቀው ድምፃዊ ፋሲል ደመወዝም እንዲሁ በደቡብ አፍሪካ የደረሰውን ሲመለከት እንዳመመው ገልጾ ሁሉም ጸሎት እንዲያደርግ ጠይቋል:: በዋሽንግተን ዲሲ በነገው ዕለት በደቡብ አፍሪካ ኢምባሲ በሚደረገው ሰልፍ ላይም ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምጹን እንዲያሰማም ጥሪ አቅርቧል::

ሰኞ ኤፕሪል 20 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ በ9 ሰዓት በሚደረገው በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ታዋቂውን የሰብ አዊ መብት ተሟጋች እና አርቲስት ታማኝ በየነን ጨምሮ በርከት ያሉ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል::

Monday …April 20th @ 9:am
South African Embassy
3051 Mass Ave NW, Wash, DC

The post በዋሽንግተን ዲሲ የደቡብ አፍሪካ ኢምባሲ አጠገብ ነገ ሰኞ ጠዋት ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል appeared first on Zehabesha Amharic.

ሕወሓት የሚመራው መንግስት በአይሲኤስ የተገደሉ ኢትዮጵያውያንን ካደ * “የተገደሉት ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን አላረጋገጥኩም”አለ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ሁሌም በዜጎቹ ጉዳይ ከበዳይ ወገን ጋር አብሮ በመሰለፍ ዜጎቹን የሚያዋርደው የሕወሓት የሚያስተዳድረው የኢሕ አዴግ መንግስት በሊቢያ አይሲኤስ የገደላቸውን 28 ኢትዮጵያውያንን ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን ማረጋገጫ አላገኘሁም አለ::
ethiopian killed by isil 1

Ethiopian killed by ISIL
ሕወሓት የሚመራው መንግስት ባወጣው መግለጫው “አይሲኤስ የተባለው አለም ዓቀፍ አሸባሪ ቡድን በሊቢያ በሚኖሩ ስደተኞች ላይ ፈፅሜያዋለሁ በሚል በቪዲዮ ያሰራጨው ዘግናኝ የግድያ ተግባር የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚያወግዝ ሲገልጽ” ስደተኛ እንጂ ኢትዮጵያውያን ማለት አልፈቀደም::

ሕወሓት የሚመራው መንግስት ዜጎቹን በመካድ በአቶ ሬድዋን ሁሴን በኩል የሰጠው መግለጫ ላይ እንዲህ ይላል:-

“በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 11 ቀን 2007 ዓመተ ምህረት የተለያዩ አለም ዓቀፍ ሚዲያዎች ባሰራጩት ዘገባ አይ ኤስ የተባለው አሸባሪ ቡድን ግድያ የፈፀመባቸው ስደተኞች ኢትዮጵያውያን እንደሆኑ ቢገልፁም በግብፅ ካይሮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ግን ስደተኞቹ ኢትዮጵያውያን ስለመሆናቸው ማረጋገጫ እንዳልሰጠም ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
አሸባሪው ቡድኑ ለህልፈት የዳረጋቸው ዜጎች ኢትዮጵያውያን ቢሆኑም ባይሆኑም መንግስት በንፁሃን ላይ የሚፈፀም ይህን መሰል አፀያፊና ዘግናኝ የሽብር ድርጊት አጥብቆ ይኮንናል ብለዋል፡፡”

በግልጽ ኢትዮጵያውያንን የመሰሉ ሰዎች ታርደውና ተገድለው ባህር ላይ ተጥለው መንግስት ገና ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን አላረጋገጥኩም ማለቱ ዜጎቹን በመካድ የታወቀው የሕወሓት መንግስት ዳግም እርቃኑን ቀርቷል:: በቅርቡ እሳዑዲ አረቢያ በየመን እና በደቡብ አፍሪካ በዜጎቹ ላይ ክህደት የፈጸመው ይኸው አምባገነን መንግስት በሊቢያ የሚገኙ ዜጎቹን መካዱ ብዙዎችን አሳዝኗል::

The post ሕወሓት የሚመራው መንግስት በአይሲኤስ የተገደሉ ኢትዮጵያውያንን ካደ * “የተገደሉት ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን አላረጋገጥኩም” አለ appeared first on Zehabesha Amharic.

በሊቢያ በኢትዬጲያውያን ክርስቲያኖች ላይ የተፈፀመው ኢ ሰብአዊ ጭፍጨፋ እስልምናን አይወክልም!!

$
0
0

አቡ ዳውድ ኡስማን

በኢትዬጲያን ክርስቲያኖች ላይ በእስልምና ሽፋን የተፈፀመውን ጅምላ ጭፍጨፋ ሙስሊም በመሆኔ እቃወማለው ፡፡
በእስልምና ውስጥ የዚህ አይነት እርኩስ ተግባር ተቀባይነት የለውም፡፡በእስልምና ሽፋን የዚህ መሰሉ ጭፍን አስተሳሰብ ባለቤቶች በሚፈፅሙት አሳዛኝ እና አሳፋሪ ተግባራት ኢስላም ሲሰደብ ማየት እንዴት ያሳምማል፡፤በኢስላም ውስጥ የበደለህን እና ድንበር ያለፈብህን አካል ለመበቀል ስትል ደካሞችን መጉዳት አበክሮ ያወግዛል፡፡ethiopian killed by isil 3

ከጠላት ጋር በሚኖርህ ፍልሚያ ላይ እራሱ ከጠላት ወገን በኩል ያሉ ንፁሃንን፣ ህፃናትን፣ ሴቶችን፣ አረጋውያንን፣ የማንኛውንም ሃይማኖት አባቶችን መግደል፣ቤተ አምልኮዎችን እና ገዳማትን መድፈር፣ዛፎችን ያለአግባብ መቁረጥን እና እንስሶችን መግደል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ ይህ ሆኖ ሳለ በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ላይ የሚንቀሳቀሱ ፅንፈኛ ቡድኖች በሊቢያ የደረሰወን አይነት አሳፋሪ እና ዘግናኝ ጥፋት ሲፈፅሙ ይስተዋላሉ፡፡ ኢስላም ከነዚህ ሰዎች ተግባር የፀዳ ነው፡፤ ሌላውም ሙስሊም ማህበረሰብ ፅንፈኞቹ በፈፀሙት ተግባር በጅምላ አይወነጀልም፡፡
የአንዲትን ህያው ነፍስ ያለአግባብ ያጠፋ የአለምን ህዝቦች ሂወት እንዳጠፋ እንደሚቆጠርበት ቁርአን አስተምሮናል፡፡

مِنْ أَجْلِ ذَٰلِكَ كَتَبْنَا عَلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنَّهُ مَن قَتَلَ نَفْسًا بِغَيْرِ نَفْسٍ أَوْ فَسَادٍ فِي الْأَرْضِ فَكَأَنَّمَا قَتَلَ النَّاسَ جَمِيعًا وَمَنْ أَحْيَاهَا فَكَأَنَّمَا أَحْيَا النَّاسَ جَمِيعًا ۚ وَلَقَدْ جَاءَتْهُمْ رُسُلُنَا بِالْبَيِّنَاتِ ثُمَّ إِنَّ كَثِيرًا مِّنْهُم بَعْدَ ذَٰلِكَ فِي الْأَرْضِ لَمُسْرِفُونَ
በዚህ ምክንያት በእስራኤል ልጆች ላይ እነሆ ያለ ነፍስ (መግደል) ወይም በምድር ላይ ያለማጥፋት (ካልሆነ በስተቀር) ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው ማለትን ጻፍን፡፡ (ሱረቱል ማኢዳ 32)

በመሆኑም በሊቢያ በኢትዬጲያ ክርስቲያኖች ላይ በ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ በቅድሚያ እምነቴ ኢስላም ስልሚያወግዘው አወግዘዋለው፡:ቀጥሎም የጠፋው የሰው ሂወት ነው እና እንደሰበአዊነቴ ድርጊቱ በማንም አካል ይሁን የትም ቦታ ይፈፀም አወግዘዋለው፡፡

ሃይማኖትን አስገድዶ ማስቀየር፣የኔን እምነት በግዳጅ ተቀበል ብሎ መግደል ፅንፈኞች የፈጠሩት እሳቤ እንጂ በእስልምና ውስጥ ፈፅሞ የለም፡፡ በሃይማኖት ማስገደድ እንደሌለ በቁርአንም ሆነ በሃዲስ በግልፅ ተቀምጦ ይገኛል፡፡

لَا إِكْرَاهَ فِي الدِّينِ ۖ
በሃይማኖት ማስገደድ የለም(ሱረቱል በቀራ፡256)

እስልምና ሰዎችን በመግደል ትጸድቃላችሁ የሚል አስተምህሮ አላስቀመጠልንም፡፡ የሌላ እምነት ተከታይ የሆኑትን ሰዎች እስልምናን በግዳጅ ካልተቀበላችሁ በሚል መግደል ኢስላም ሊፈቅድ ይቅርና የትኛውም እምነት ተከታይ ይሁን የሚያመልከውን ፈጣሪ በክፉ መስደብ፣የሃይማኖት አባትን መግደል፣ገዳምን፣ቤተ አምልኮዎችን ማፈራረስ በእስልም በጥብቅ የተከለከሉ ወንጀሎች ናቸው፡፡

የሌሎችን እምነት መስደብ የከለከለ እምነት ዛሬ ላይ የሌላ እምነት ተከታዬችን በመግደል ይጸድቃል የሚል አስተምህሮ ሊኖረው አይችልም፡፡
በየትኛውም እምነት ተከታይ የሚፈጸምን ግድያ እና ኢ ሰብአዊ ድርጊት እንደ ሙስሊምነቴ አወግዛለው፡፡ የኢትዬጲያ ክርስቲያኖችም ሆኑ ሌላ እምነት ተከታዬች በሃገራችን ኢትዬጲያ ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጋር ተከባብረን ለብዙ አመታት ኖረናል፡፡ በሰላም እና በጋራ ስንኖር እስልምና ንፁሃን የሆኑ የሌላ እምነት ተከታዬችን መግደል የሚያፀድቅ ተግባር መሆኑን አስተምሮ ቢሆን ኖሮ ኢትዬጲያ ውስጥም ሆነ በመላው አለም አንድም የሌላ እምነት ተከታይ ባልኖረ ነበር፡፡ ምክንየቱን ሁሉም መፅደቅ እፈልጋለው በሚል ሰዎችን በገደለ ነበር፡፡ እውነተው ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡

ከ 1400 አመታት በፊት ጀምሮ ሙስሊሞች በፍትህ ለሌላ እምነት ተከታዬች ጋር በጋራ ኖረዋል፡፡ የእምነት ልዩነት መኖር ጉርብትናን፣መልካም መዋዋልን፣ መከባበርን እና በችግር ጊዜ መረዳዳት አልከለከለንም፡፡ እስልምናም በጥብቅ ያዘዘን ይህን እንድንፈጽም ነው፡፡

አልሃምዱሊላህ የኢትዬጲያ ሙስሊም ህብረተሰብ ከዚህ መሰሉ ፅንፈኛ አስተሳሰብ የፀዳ ነው፡፡ በአላህ ፈቃድ ድሮም ፣አሁንም፣ ወደፊትም የኢትዬጲያ ሙስሊም ማህበረሰብ ከፅንፈኝነት የፀዳ ሆኖ ኢስላም ባስቀመጠው መልኩ ከሌሎች ዜጎች ጋር ተከባብሮ ይኖራል፡፡
ንፁሃንን ማረድ፣መግደል፣ በአጥፍቶ መጥፋት ንፁሃንን መጨረስ፣ሴቶችን ማገት፣ ንብረት መዝረፍ እና ማቃጠል፣ቤተ እምነቶችን ማቃጠል፣የየትኛውንም ሃይማኖት አባት መግደል፣ ገዳማትን መድፈር፣ ቀሳውስትን መግደል እና ማጥቃት ወዘተ…. የእስልምና ጋር የሚያያይዛቸው አንዳችም ተግባር የለም፡፡

ንፁሃንን መጨፍጨፍ እምነት ቢኖረው ኖሮ በደቡብ አፍሪካ እየተፈፀመ የሚገኘው አሰቃቂ ወንጀል ባልተፈፀመ ነበር፣ በቡርማ፣በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ወ.ዘ.ተ…. የተፈፀሙት ኢ ሰብአዊ ጭፍጨፋዎች ባልተፈፀሙ ነበር፡፡ እውነታው ግን ሽብርተኝነት እና ሰዎችን መጨፍጨፍን እምነት የሌለው የዘመናችን አሰቃቂ የጥፋት ተግባር ነው፡፡

ጉዳዩን ወደ ሃገራችን ልመልሰው እና የኢትዬጲያ ሙስሊሞችም ለ 3 አመታት ስናካሂደው የቆው ሰላማዊ የመብት ትግል መንግስታዊ የሃይማኖት ጣልቃ ገብነትን መቃወም እንጂ የሌሎች እምነት ተከታዬችን መብት የመጋፋት ሂደት አይደለም፡፡ የኢትዬጲያ ሙስሊም በሰላማዊ መንገድ እምነትን በግዳጅ የማስቀየርን መንግስታዊ ውንብድና እና ጣልቃ ገብነትን ነው የተቃወመው፡፡

በሊቢያ እስልምናን በግዳጅ ካልተቀበላችሁ በሚል እንደተገደሉት ኢትዬጲያውያኖች ሁሉ የኢትዬጲያ መንግስትም ሙስሊም ኢትዬጲያውያንን አህባሽ የተሰኘውን ጸረ ህዝብ አሰተሳሰብ በግዳጅ ካልተቀበላችሁ በሚል ሲያስር፣ ሲደበድብ፣ ደማችንን ሲያፈስ፣ ሲገድለን እና በርካቶችን ለበርሃ ስደት ሲዳርግ ቆይቷል፡፡

የሁለቱ ልዩነት በሊቢያ የተፈጸመው በሽብር በተፈረጀ ቡድን ሲሆን የኛ የሃገራችን ደግሞ ህጋዊ ሽፋን በተላበሰ የሃገር መንግስት ነው፡፡ ከዛ በተረፈ ሁለቱም በግዳጅ እምነት ለማስቀየር እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ ይህንን መንግስታዊ እምነት የማስቀየር ዘመቻ በሰላማዊ መንገድ ስንቃወም ግን የሌላ እምነት ተከታዬችን መብትም ሆነ ክብር አልተዳፈርንም አልነካንምም ፡፡

በመሆኑም የኢትዬጲ ሙስሊሞችን እምነታቸውን ከበካይ አስተሳሰብ ለመጠበቅ ሲያደርጉት የቆየው ሰላማዊ ትግልን ከየትኛውም የሽብር ቡድንም ሆነ አካል ጋር ለማያያዝ መሞከር ህዝብን ከህዝብ በሃይማኖት ከፋፍሎ ለማፋጀት ለሚፈልገው የሃገራችን መንግስት ግብዓት ከመሆን የዘለለ ጥቅም አይኖረውም፡፡

በመጨረሻም በየጊዜው እስልምናን ሽፋን በማድረግ እየተፈፀመ ለሚገኝ አሰቃቂ ጭፍጨፋ መፍትሄው የሌላ እምነት ተከታዬች በእስልምና ተከታዬች ላይ ጥርጣሬ እና ፍርሃት እንዲያድርባቸው በፕሮፖጋንዳ ጭንቅላታቸውን ማዞር፣ ንፁሃን ሙስሊሞችን በየቦታው እያሰቃዩ ማሰር፣ መግደል እና መፍጀት ሳይሆን ሁሉንም ወገኖች በፍትሃዊነት በማስተዳደር ሁሉም የችግሩ ሰለባ በመሆኑ እምነት ሳይለዩ በጋራ በመሆን ችግሩን ለመቅረፍ እንዲቀሳቀሱ መስራት ነው፡፡

ለሀጋራችን ህዝብ አላህ ሰላሙን ያውርድልን!

በየቦታው በስደት ያሉ ዜጎቻችንን አላህ እየተሰማ ከሚገኘው ፈተና ሁሉ ይጠበቃቸው
በየቦታው በግፍ እየተገደሉ ለሚገኙ ኢትዬጲያውያን ወላጆችም አላህ ሰብሩን እና መፅናናቱን ይስጣቸው!
አሚን!!

The post በሊቢያ በኢትዬጲያውያን ክርስቲያኖች ላይ የተፈፀመው ኢ ሰብአዊ ጭፍጨፋ እስልምናን አይወክልም!! appeared first on Zehabesha Amharic.


   ህወሃት የመከላከያ ሠራዊቱን  የገቢ ምንጭ በማድረግ ይጠቀምበታል፦

$
0
0

tplfየቀዳማዊ ኃይለሥላሤ መንግሥት የኢትዮጵያን የጦር ኃይል ወደ ኮንጎና ኮርያ ልኮ እንደ ነበር ይታወቃል።የደርግ ወታደራዊ መንግሥት በገልፉ ጦርነት ወቅት ኢራቅ ግብጽን ጨምራ እንዳትመታ ግብጽን ለመታደግ ልኮ እንደነበር ሁላችንም የምናውቀው ጉዳይ ነው።የህወሓት ቡድንም ወደ ሩዋንዳ፤ሶማሌና ደቡብ ሱዳን የመከላከያ ሠራዊቱን መስደዱ ግልጽ ነው።የኔ አብይ መነሻ ማናቸውም ይሁኑ በመላኩ ወይም ባለመላኩ ጉዳይ አይደለም።ከበስተጀርባው ምንድን ነገሮችን አስከትሏል የሚለው እንጅ? የግል አስተያየቴን እንደሚከተለው ላቅርበውና ይህን ጹሑፌን የምታነቡ ለዚህ ታሪክ ቅርበት ያላችሁ ወይም ጉዳዩን በውል የተገነዘባችሁ በስፋት ሃሳባችሁን እንደምትሰጡበት ተስፋ አደርጋለሁ።

1/ የአጼ ኃይለሥላሤ ዘውዳዊ መንግሥት ጦሩን ወደ ኮንጎና ኮርያ ሲልክ ጥሩ ዝምድና ለማትረፍ ወይም መልካም ዝና ለማግኘት ይሆናል ብየ አምናለሁ ለዚያም ሊሆን ይችላል ድሮ ኮርያ ዘምተው የነበሩ የኢትዮጵያ የጦር ሠራዊት አባላት በኮርያ መንግሥት የጡረታ ጥቅማ-ጥቅሞችን እንዲያገኙ የተደረገው።በዚህ ጊዜ ኃይለሥላሤ መንግሥት ለጦሩ ይከፍለው የነበረው ክፍያ አነስተኛ ቢሆንም የገንዘቡ አቅም ከፍተኛ ነበር በዚህ ላይ የኢትዮጵያ ገንዘብ ከዶላር ጋር እኩል ክፍያ ይከፈለው ስለነበር በጦሩና በጦሩ አባላት ቤተሰብ ላይ ችግር አልነበረም ማለት ይቻላል።የኑሮ ሁኔታውም እንዲህ ጣራ ላይ የደረሰ ስለአልነበረ የኢትዮጵያ የጦር ሠራዊት ወደ ጎንጎም ሆነ ደቡብ ኮርያ ቢዘምት በቤተሰብ ላይ የሚያመጣው ተጽእኖ አልነበረውም።ይህን በእውነቱ በበጎ ልናየውና ኢትዮጵያ ከራሷ አልፎ ጣልቃ ገብነትን በማይነካ መንገድ እርዳታ መስጠቷ ተገቢ መስሎ ይታየኛል።

2/ በደርግ የወታደራዊ አገዛዝ ዘመን በአፍሪካ ቀንድ የገነነ ሠራዊት ገንብቶ የነበረ ደርግ ሲሆን ወደ ግብጽ የተላኩት የኢትዮጵያ የሠራዊት አባላትም ከሁለት መቶ እስከ ሁለት መቶ እንደማይልቅ አስታውሳለሁ።እዚህ ላይ ደርግ የነበረበት ሁኔታና የኢራቅን የጦር ኃይል ለመመከት ደርግ የላከው ጦር ሁኔታ ሲታይ ደርግ እያሾፈ ነው ወይስ ኃይል ስለሚያጥረው ነው የሚሉ ጥያቄዎችን አንስተን እንደነበር አስታውሳለሁ።ያም ሆነ ይህ ግን ኢራቅ ግብጽን ሳትዳፈር በመቅረቷ የደርግ ገቨን ተሸፍኖ አልፏል።እንዲያ ይፈራና በግዙፍነቱ ገንኖ ይታወቅ የነበረው የኢትዮጵያ የጦር ኃይል በተገንጣይ ኃይሎች፤ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እናመጣለን ብለው በተነሱ ኃይሎችና በራሱ በደርጉ ርእሰ ብሔር መንግሥቱ ኃይለማርያም እንዲዳከም እንዲበታተንና ለጥቃት ሰለባ እንዲሆን ተደረገ በመጨረሻም አብዛኛው የጎዳና ለማኝ እስከ መሆን ደረሰ ይህን የምልበት ምክንያት የአንድ አገር የጦር ሠራዊት ካለው አገራዊ ተልእኮ አንጻር ሲመዘን የአገርን ዳር ድንበርና ሉአላዊነት ማስከበር በመሆኑ እነዚህ ሳይስተካከሉ በመቅረታቸው አሁን ካለንበት ደረጃ ደርሰን እንገኛለን።

3/ የህወሃት የመከላከያ ሠራዊት፦በመጀመርያ ደረጃ ከድኻው አርሶ አደር፤ነጋዴና የመንግሥት ሠራተኛ በሚሰበሰብ ግብርና ታክስ ደመወዝ እየተከፈለው የኢትዮጵያ ሠራዊት ሊባል አለመቻሉ ምን ያህል በሕዝብ የተጠላና ሥነምግባር የጎደለው ሠራዊት መሆኑን አስረግጨ ማለፍ እወዳለሁ።በመቀጠል ይህ የህወሃት ሠራዊት ከኢትዮጵያ ህዝብ የተፈጠረና እያንዳንዱ እናት አባት ወዳጅ ዘመድ ያለው እንደሆነ ይታመናል ነገር ግን ዓላማው የኢትዮጵያን ሕዝብ አንገት አስደፍቶ የህወሃትን ሥርዓት እድሜ ማስረዘም በመሆኑ በሕዝብ ዘንድ አመኔታ የተጣለበት አይደለም።ምክንያቱም በደቡብ ኢትዮጵያ፤በኢትዮጵያ ሶማሌ፤በአፋር፤በሰሜን ምእራብ ኢትዮጵያ የፈጸማቸው ተግባሮቹ አጽያፊና ፀረ-ህዝብ ናቸው።ይህ በዚህ እንዳለ ከታች እስከ ላይ ያሉት የሠራዊቱ አለቆች ንብረት በማካበትና በንግድ ሥራ ሲጠመዱ እየተመለከተ የሚለብሰውን ዩኒፎርምና የሚጫማውን ጫማ ከደመወዙ እየተቆረጠ እንዲገዛ ሲደረግ በጋራ ለምን ብሎ ጥያቄ አያነሳም? የተወሰኑት የመብት ጥያቄ አንስተው ሲሞግቱ ከየካምፑ እየተለቀሙ ሲገደሉና ሲታሰሩ ዝምታን መምረጥ አስፈላጊ አልነበረም ይህም አልበቃ ብሎ ወደ ሩዋንዳ ፤ደቡብ ሱዳንና ሶማሌ ሲልኩት ገዥዎቹ ምን ሊያተርፉ እንደሆነ በንቃት የተመለከተው አይመስልም።የተግባር ሥምሪቱን የሚያገኘው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሥር ሆኖና እንደ አንድ የሚሊታሪ ኃይል ዓለማቀፋዊ ስታንዳርድን አሟልቶ አይደለም። ይህን ሊያሟላ የማይችልበትን ምክንያት ሁላችንም የሚገባን ይመስለኛል።በዚህ ሥርዓት ውስጥ አንድም በብቃቱ ያለበትን ቦታ እንዳልያዘም እናውቃለን በበርሃ አስተሳሰብና በጠመንጃ ኃይል ልግዛ ሲሉ አገርንና ሕዝብን የጎዱ መሆናቸውን የምናውቀው እኛ እንጅ እነሱ አይደሉም ለምን?አገራዊ ወይም ብሄራዊ ሞራል የላቸውም ልባቸው እንዳይራራና ፈሪሃ እግዚአብሄር እንዳይኖራቸው ደግሞ መንፈሳዊ ስሜት የላቸውም የመጡበት ቤተሰብም አገር ሲያጠፋና ህዝብን ሲያደማ የነበረ ነው።እነዚህ ሁሉ ተዳምረው እያጭበረበሩ መኖርን የመረጡ ናቸው ለአብነት፦እኛ የተናገርነው እውነት ነው ይላሉ አንዳንዴ ስብሃት ነጋ የህወሃትን የውሸት ጆንያ ሲከፍተው በጆንያው ውስጥ ያለውን ውሸት ሲነግረን ልብ ብላችሁ ከሆነ(የኤርትራን ጉዳይ አስመልክቶ አንድ ነገር ብሏል)ህወሃት ገና ሲጀመር ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ አንድም እውነትነት ያለው ተግባር ፈጽሞ አያውቅም ራሱ ገድሎ ራሱ ማርዳት እውነት ከሆነ ፍርዱን ለአገር መተው ይሻላል። ህወሃት ነብሰ ገዳይ ዘራፊ ነው ጠባብና ጎጠኛም ነው ይህን ለምን ትነግሩብኛላችሁ ለምንስ አጋለጣችሁኝ ብሎ መግደል በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ማሰር እያሳደዱ ኢትዮጵያውያን አገር ጥለው እንዲጠፉ ማድረግ የህወሃት አይነተኛ መገለጫ ነው።

ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት ህወሃት ሠራዊቱን ወደ የተለያዩ አገሮች ሲልክና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የመከላከያ ሠራዊቱን ሁለንተናዊ ጉዳዮችን ሲሸፍን ለአንድ የሠራዊት አባል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምን ያህል እንደሚከፍል ማስረጃው ሰነድ በእጀ ባይኖረኝም በግምት ከ5 እስከ 7 ሺ ዶላር ሊከፍል ይችላል የሚለውን ልውሰድና ህወሃት 5.000 ሠራዊት ቢልክ ወይም ቢያከራይ 7000ሲባዛ 5000ሲባዛ በ3አገሮች ምን ያህል ገቢ እንደሚያገኝ አስቡት ይህ ሁሉ ለመከላከያ ሠራዊቱ የሚሰጥ ገንዘብ እንዳይመስላችሁ በቀጥታ ወደ ህወሃት አመራርና የሠራዊቱ ከፍተኛ አዛዦች የግል ባንክ የሚገባና ፎቆች የሚገነቡበት የተለያዩ የንግድ ተቋማት የሚስፋፉበት የአየር-ባየር ንግድ ይሆናል የራሱን ሕዝብ ባነገበው ነፍጥ አንገት አስደፍቶ የሚያስገዛው የህወሃት የመከላከያ ሠራዊት ግን የሚከፈለው ደመወዝ የጫማና የዩኒፎርም ከተቆረጠ በኋላ የሚተርፈውንና በህወሃት ገንዘብ በመደበኛ የወር ገቢው የሚያገኛትን ብቻ ነው።

በአሁኑ ሰአት አገር ጥለው የወጡ በየትኛውም ዓለም የሚገኙ ውድ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ግፍና በደል እየተፈጸመባቸው ይገኛሉ ይገደላሉ፤ይታሰራሉ….ወዘተ ይህን የሚያስፈጽመው ራሱ የህወሃት ሥርዓት እንደሆነ ቅንጣትም ቢሆን መጠራጠር አይኖርብንም።የአገር ሀብት እየተዘረፈ ሦስተኛ ወገን የሆነ አፍ እየተገዛበት ነው።በሰሞኑ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚንስትር ቀደም ሲል በአምባሳደር ሱዛን ሲደረት የነበረውም ሌሎች አሽቃባጮቻቸው የሚሉትም ህወሃት ያለበት ሁኔታ ጠፍቷቸው ሳይሆን ውሻ በበላበት ይጮሃል ነውና በወፍራም ዶላር የተመታ አፍ ከዚህ በላይም ሊያናግር ይችላል ወደፊትም የአገር ሀብት እየተጠረገ ህወሃት አፍ ከመግዛት አይመለስም።እኛ ኢትዮጵያውያንም ከጥቂቶች በስተቀር እጅ እግራችን አጣጥፈን ችግሩ እኛ እስካለንበት እስከሚደርስ እየጠበቅን ነው።ደቡብ አፍሪካ፤የመን፤ሳውዲ የተደረጉት ጥቃቶች ነገ አሜሪካ፤እንግሊዝ፤ፈረንሳይ፤ጀርመን ላይደገሙ ምን ዋስትና አለን?

እነዚህን ምክንያቶች እንድጠቅስ የገፋኝ የህወሃት የመከላከያ ሠራዊት ሥርዓቱን እንዳይገረሰስ የጀርባ አጥንት ሆኖ እያገለገለ ያለ ስለሆነ በዚህ ላይ ምን አይነት ርምጃ ቢወሰድ ውጤት ሊያመጣ ይችላል በሚል ጉዳይ ውስጥ ገብቼ ስለነበር ነው።ይህ ሠራዊት ኢትዮጵያውያን ሲሰደዱ፤ሲታሰሩ፤ሲገደሉ፤በውሸት ክስ ሕገ ወጥ ፍርድ ሲፈረድባቸው፤የህዝብ ሀብት ሲዘረፍ፤የሀገሪቱ ሉዓላዊነት ሲደፈር፤የሀገር ድንበር ሲደፈር ጀሮ ዳባ ልበስ በማለቱ የህወሃት ሠራዊት የሚል ትርጉም እንዲሰጠው ሆኗል ስለዚህ ህዝቡ ትክክለኛውን ትርጓሜ ሰጥቷል።በህዝብ ግብርና ታክስ ደመወዙን እያገኘ ሕዝብ አንገቱን ደፍቶ ለህወሃት እንዲገዛ መሣርያ ከሆነ ከህዝቡ ሊሰጥ የሚገባው ምላሽ ምን ሊሆን ይገባዋል?

የህወሃት ከፋፋይና ጎጠኛ ሤራ እንዳለ ሆኖ ማለትም ህዝብን በዘር በጎሳና በሃይማኖት መከፋፈሉ አንዱ ጎሳ ሌላውን ጎሳ በጥርጣሬ እንዲመለከተው ፀንቶ የኖረ በጋራ ተሰስቦና ተከባብሮ በአንድነት የኖረው ዝህብ እንዚያን ሁሉ እሴቶቹን አጥቷል።በሌላ በኩል ደግሞ ህዝቡ በውስጡ ያለውን ብሶት ለማስወገድ ትግሉን እንዳይቀጥል የተቃዋሚ ድርጅቶች ደንቃራና እንቅፋት ሆነውበት ይገኛሉ ዛሬ ድርጅት መመሥረት ፋሽን የሆነበትና ህዝብን ከህወሃት ባልተናነሰ ሁኔታ እየጎዱ እንደሆነ ልብ ሊሉት ይገባል።ህዝብን ነፃ አወጣለሁ ብሎ ሕዝብን አደጋ ውስጥ መክተት ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው ዛሬም ደግሜ እናገረዋለሁ የተቃዋሚ ኃይሎች በየትኛውም የትግልት ገብታችሁ መታገል መብታችሁ ነው።ህዝብን ለአደጋ የሚዳርጉ ተግባሮችን ግን መለየት ያሻል ምክንያቱም ህዝብ አልመረጣችሁም ታገሉልኝ ብሎም አልጠየቃችሁም ያለው ነባራዊ ሁኔታ ወደ ትግሉ እንድተገቡ አድርጓችሁ ከሆነ የትግል ስልታችሁንና ግባችሁን መርምሩ ገና አንድ ጋት ወደ ፊት ሳይኬድ እያለቀ ያለውን ህዝብ ልታስቡት ይገባል።እንደእኔ ትግሉ አግባብ ባለው መንገድ እየሄደ አይደለም።ትግሉ በአግባቡ ቢመራ ኖሮ ህዝብ አንቅሮ የተፋውን ህወሃትን ይቅርና ሌላም ቢሆን ማስወገድ ይቻላል።

የህወሃት የመከላከያ ሠራዊት፦ባሳለፍካቸው ጊዚያቶች የህወሃትን ሥርዓት እድሜ ለማርዘም ሲባል ከህዝብ የሚነጥል ተግባር ፈጽመሃል፤ህወሃት እያከራየ የገቢ መሰብሰቢያ አድርጓሃል፤ህወሃት ያለበት ተጨባጭ ሁኔታ እንደሚያሳየው ግራ የተጋቡ መሪዎቹ ጨልሞባቸው ነው ያለው።እስከ አሁን የፈጸሙት ፀረ-ሕዝብ ተግባራቸው እያባነናቸውና በደም በመጨማለቃቸው በኃይል ሥርአቱን ማቆየት ካልቻሉ የሚጠብቃቸው ምን እንደሚሆን ስለተገነዘቡ ግፉ ከጽዋው ሞልቶ በመፍሰሱ ሁላችንም የሞት የሽረት ትግሉን እንድንገባበት ተገደናል አገሪቱ ይጋራችን ናት ለህወሃት ብቻ መርጦ የሰጠው የለም።ስለዚህ የመከላክያ ሠራዊቱ መሣርያህን እንደያዝክ ህዝቡን በትጥቅ ትግል ላይ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ድርጅቶችን ተቀላቀል ከህዝብ ጎን ልትቆም ይገባሃል ምክንያቱም የህዝብ ልጅ ነህና ወንድሞችህና እህቶችህ በየአረብ አገሩ አልቀዋል እያለቁም ናቸው አሁን ደግሞ በደቡብ አፍሪቃ በወገኖችህ ላይ እልቂት ጀምሯል ህይወቱንና የሥርአቱን እድሜ ለማራዘም እየተጠቀመብህ ያለው መንግስት ተብየ ችግሩ በየኤባሲዎች እንዲባባስ አደረገ እንጅ ለወገን ደራሽ ሆኖ አልተገኘም እኛም ህወሃት ለኢትዮጵያ ህዝብ ይቆረቆራል ብለን አንጠብቅም።በደርግ ሠራዊት ላይ የተፈፀመው አንተም ላይ ከመፈጸሙ በፊት ጥግህን ልትይዝና የህዝብ ልጅነትን ልታስመሰክር ይገባሃል።በግለጫ እየሰጠሁ ወይም እያስፈራራሁ አይደለም ሠራዊቱን ስለማውቀው አሁን ያለውን ተጨባጭ ሁኔታም ስለምከታተለው ነገ የሚከሰተውን ነው እየተናገርኩ ያለሁት።

ሕዝባዊ እምብኝተኝነቱ ይቀጥላል!!

ነብሮ ነኝ።

 

The post    ህወሃት የመከላከያ ሠራዊቱን  የገቢ ምንጭ በማድረግ ይጠቀምበታል፦ appeared first on Zehabesha Amharic.

Hiber Radio: በየመን ያሉም ኢትዮጵያውያን የአይሲስ በሊቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደው የግፍ ግድያ ይፈጸምብናል የሚል ስጋት ፈጥሮባቸዋል…በደቡብ አፍሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያን ጥሪ አስተላለፉ…በኬኒያ እስር ቤት ያሉ 62 ኢትዮጵያውያን የረሀባ አድማ መቱ…“በሊቢያ ወገኖቻችንን ያረዱት፣ በጥይት የገደሉት እነዚህ በየትኛውም የእስልምና አስተምህሮ የተወገዙ ሰይጣኖች ናቸው”–ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ…ጋዜጠኛ አበበ ገላው በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሰጠው ማብራሪያና ሌሎችም

$
0
0

Habitamu
የህብር ሬዲዮ ሚያዚያ 11 ቀን 2007 ፕሮግራም

ለኢትዮጵያውያን በሙሉ በሊቢያ ፣በደቡብ አፍሪካና በየመን ለሞቱ ወገኖቻችን ነፍስ ይማር ! መጽናናትን እንመኛለን !

< ...በሊቢያ፣ በደቡብ አፍሪካና በየመን በግፍ ለተገደሉ ኢትዮጵያውያን ማዘን ማልቀስ ብቻ በቂ አይደለም። በአገር ቤትም በውጭም በንጹሃን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ማስቆም የሚቻለው ተባብረን ይሄን ስርዓት ማስወገድ ስንችል ብቻ ነው…የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በኢትዮጵያ ጉዳይ አልተቀየረም የሴትዮዋ ንግግር መሰረተ ቢስ ነው ራሳቸው ማብራሪያ ይሰጡበታል…>

ጋዜጠኛ አበበ ገላው በሊቢያ ፣በደቡብ አፍሪካና በየመን ስለሞቱ ወገኖቻችንና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ባለስልጣንን መግለጫ አስመልክቶ ከሰጠን ማብራሪያ የተወሰደ

<… በሊቢያ ወገኖቻችንን ያረዱት፣ በጥይት የገደሉት እነዚህ በየትኛውም የእስልምና አስተምህሮ የተወገዙ ሰይጣኖች ናቸው…መፍትሄው በሀይማኖት ፣በጎሳ ሳንከፈል መከራ ሲደርስብን አብሮን የሚቆም መንግስት የሌለን በመሆኑ ለራሳችን ራሳችን እንነሳ…> ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ስለ የሊቢአው የአይ.ሲ.ስ የአሸባሪዎች ድርጊትና ተያያዥ ጉዳዮች ጠይቀነው ከመለሰው (ሙሉውን ያዳምጡት)

በሊቢያ በአይ.ሲ.ስ አሸባሪዎች የተገደሉት ኢትዮጵያውያን ፣ የስርዓቱ ግዴለሽነትና የግብጽ ከአሸባሪው ጋር መፋለም (ልዩ ጥንቅር)

<...ሁለት ወንድሞቼ ደቡብ አፍሪካ ናቸው እነሱ ያሉት እኛ ቢያንስ እየታገልን የምንሞት ነን በሊቢያ የታረዱ፣በጥይት በአሸባሪዎች የተገደሉ ወገኖቻችን ጉዳይ አስለቅሶናል ።የመንግስት ተብዬው ክህደት አሳዝኖናል እባካችሁ በመላው ዓለም የምትገኙ ወገኖቻችን ጸልዩ እያሉ ነው …>

አስተያየት ሰጪ ለህብር ከገለጹት

<…ኢትዮጵያውያንን በቁም ያቃጠሉትን ለፍርድ ለማቅረብ እየተንቀሳቀስን ነው…ችግር ላይ ያሉትን ለመርዳት ሩጫ ላይ ነን…>

አቶ ደረጄ መኮንን በደቡብ አፍሪካ ጆሐንስበርግ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ዋና ጸሐፊ ለህብር ከሰጡት

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በሚገኙበት በቬጋስ የተጠራው ስብሰባ ( ከስብሰባው አዘጋጆች አንዱ አቶ አሸብር ጋር የተደረገ ቆይታ)

<…በደቡብ አፍሪካ አሁንም ሕይወታችን አደጋ ላይ ነው ዙሉዎቹ ቀድሞም አጋጣሚ ነው የሚፈልጉት ወገኖቻችን ይጩህልን…> አቶ ታሪኩ ጀማል ከደርባን ደቡብ አፍሪካ አቅራቢያ ለህብር እንደተናገሩት(ሙሉውን ያዳምጡ)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በሊቢያ ተጨማሪ ኢትዮጵያውያን አደጋ ውስጥ ናቸው

በየመን ያሉም ኢትዮጵያውያን የአይሲስ በሊቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደው የግፍ ግድያ ይፈጸምብናል የሚል ስጋት ፈጥሮባቸዋል

በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በወገኖቻቸው ላይ እሳት በቁማቸው የለኮሱትን በህግ ለመፍረድ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ገለፁ

በደርባን በድርጊቱ የተጠረጠሩ 19 የዙሉ ጎሳ አባላት ተይዘዋል

በአሸባሪው አይ.ሲ.ስ ሊቢያ ላይ አንገታቸው ተቀልቶና በጥይት ተደብድበው በሞቱት 30 ወገኖቻችን ጉዳይ ቁጣቸውንና ሐዘናቸውን እየገለፁ ነው

አገዛዙ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን አላጣራሁም ማለቱ የተለመደ የስርዓቱ ጭካኔ ነው ተብሏል

በኬኒያ እስር ቤት ያሉ 62 ኢትዮጵያውያን የረሀባ አድማ መቱ

በደቡብ አፍሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያን ጥሪ አስተላለፉ

የሚሉና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

The post Hiber Radio: በየመን ያሉም ኢትዮጵያውያን የአይሲስ በሊቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደው የግፍ ግድያ ይፈጸምብናል የሚል ስጋት ፈጥሮባቸዋል… በደቡብ አፍሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያን ጥሪ አስተላለፉ… በኬኒያ እስር ቤት ያሉ 62 ኢትዮጵያውያን የረሀባ አድማ መቱ… “በሊቢያ ወገኖቻችንን ያረዱት፣ በጥይት የገደሉት እነዚህ በየትኛውም የእስልምና አስተምህሮ የተወገዙ ሰይጣኖች ናቸው” – ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ… ጋዜጠኛ አበበ ገላው በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሰጠው ማብራሪያና ሌሎችም appeared first on Zehabesha Amharic.

ጤናችን ይጠበቅ በሁላችን (ተፈራ ድንበሩ)

$
0
0

ethiopiaየወጣችሁትን ተራሮች ጥላችሁ

የሮጣችሁትን ሜዳዎች ትታችሁ

አፈር ሣር ቅጠሉ እየናፈቃችሁ

በምኞት በተስፋ ቀን እንዲያልፍላችሁ

በረሀ አቋርጣችሁ የተሰደዳችሁ

ከዘመድ አዝማዱ በመለየታችሁ

ሙሉውን ጋዜጣ በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ

 

The post ጤናችን ይጠበቅ በሁላችን (ተፈራ ድንበሩ) appeared first on Zehabesha Amharic.

በደቡብ አፍሪካ ሰሞኑን ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ግፍ በመቃወም በአሁኑ ሰአት ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ፊትለፊት ኢትዮጵያውያን ድምፃቸውን እያሰሙ ይገኛሉ። ኢትዮትዩብ በስፍራው ይገኛል በምስል እና ቪዲዮ የተደገፉ መረጃዎችን ማቅረቡን እንቀጥላለን ተከታተሉን።

$
0
0

(ሊያደምጡት የሚገባ) አለምነህ ዋሴ የዲ/ን ዳንኤል ክብረትን “የሊብያ ሰማዕታት”ጽሁፍ እንደሚከተለው አንብቦታል

$
0
0


ethiopian killed by isil 3

“ሁለተኛው የሚጎድለው ነገር ደግሞ ፍጥነት ነው፡፡ አትሌቶቻችን በኦሎምፒክ ሲያሸንፉ የባለሥልጣናቱ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት ሯጮቹ ቆርጠውት ካለፉት ሪቫን ቀጥሎ የሚመጣ ዜና ነበር፡፡ አትሌቶቹ ደክሟቸው ከመሬት ሳይነሡ የባለሥልጣናቱ መልእክት ለሚዲያ ይደርስ ነበር፡፡ በዚህ የሁላችንም ኀዘን በሆነው ጉዳይ ግን ለምን መዘግየት እንደተመረጠ ግልጽ አይደለም፡፡ ማጣረቱ፣ መረጃ መሰብሰቡ፣ ተጨማሪ የዲፕሎማሲ ሂደቶችን መሄዱ ጊዜ ይወስዳል፡፡ ማዘን ግን ጊዜ አይወስድም፡፡ ቪዲዮው ተለቅቋል፡፡ ሲሞቱ እያየን ነው፡፡ መልካቸው የኛው ነው፡፡ አይሲስ የገደላቸው ‹ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች› ብሎ ነው፡፡ የዓለም ሚዲያዎች ያንኑ እያስተጋቡ ነው፡፡ ይኄ ለኀዘን ያንሳል? አፈፍ ብሎ ተነሥቶ ‹በሆነው ነገር እናዝናለን፤ ልባችን ተነክቷል፤ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን፤ ዝርዝሩን በየጊዜው እንነግራችኋለን› ለማለት ስንት ሰዓት ይወስዳል? የደቡብ አፍሪካው ችግር ደረሰ እንደተባለ ሙጋቤን ለውግዘት የቀደማቸው የለም፡፡ የኛዎቹስ የት ሄዱ?”

The post (ሊያደምጡት የሚገባ) አለምነህ ዋሴ የዲ/ን ዳንኤል ክብረትን “የሊብያ ሰማዕታት” ጽሁፍ እንደሚከተለው አንብቦታል appeared first on Zehabesha Amharic.

ኳስ ጨዋታና ፖለቲካ (ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ)

$
0
0

ማስታወሻ፤

getachew

ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ

ፕሮፈሰር መስፍን ወልደማርያም የትግራይ ሕዝብ በወያኔ አገዛዝ አለመጠቀሙን ለማሳየት ኢትዮሜዲያ ላይ አንድ ጽሑፍ አውጥቶ ነበር። ይህ የኔ ድርሰት የዚያ ተቃራኒው አስተያየት ስለሆነ መውጣት የሚገባው፥ እዚያው ኢትዮሜዲያ ላይ ነበር። ግን የኢትዮሜዲያ ባለቤት “በዚህ ድርሰትህ የትግራይን ሕዝብና ሕወሐት/ኢሕአዴግን አንድ አድርገሃቸዋል (“. . . TPLF a synonym with the Tigrai people.”) ብሎ ሊያወጣው አልፈቀደም። በእኔ አስተሳሰብ ይኸ ድርሰት ወያኔንና የትግራይን ሕዝብ አንድ አያደርግም። —-ሙሉውን ጋዜጣ በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ —

The post ኳስ ጨዋታና ፖለቲካ (ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ) appeared first on Zehabesha Amharic.

“የኢትዮጵያ ሕዝብ ስደትን አቁሞ እንደችሎታው በሕዝባዊ አመጽ ወይም በሕዝባዊ እምቢተኝነት ሃገሩን ሳይለቅ ይሳተፍ”–አርበኞች ግንቦት 7

$
0
0

ሀያ ስምንት ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን አይ ሲስ በተሰኘ ህሊና ቢስ፣ ፀረ-ሰው እና ፀረ-ስልጣኔ ቡድን በሊቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ የመገደላቸው መርዶ ዛሬ ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓ.ም. ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ደርሷል። ይህ አሰቃቂ መርዶ ልብን የሚሰብር ነው። አይ ሲስ በጥንት በጭለማ ዘመን እንኳን ባልነበረ ጭካኔ ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ሰዎችን በማረድ የሚደሰት፤ በሰው ዘር ሁሉ ላይ የመጣ አውሬ መሆኑን ነብዩ መሐመድ አትድረሱባቸው ያሏቸውንም ኢትዮጵያዊያንን ጭምር በማረድ አረጋገጧል። ይህ አሰቃቂ ተግባር ምንም ዓይነት አመክኖ ሊቀርብለት የማይችል አረመኔዓዊ የሽብር ጥቃት ነው።

ginbot 7አርበኞች ግንቦት 7:የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በወገኖቻችን ላይ በደረሰው አሰቃቂ ግድያ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል፤ ለሟች ቤተሰቦችና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን ይመኛል። ኢትዮጵያዊያን ሁሉ አይ ሲስን በጥብቅ እንዲያወግዙ፤ በአመቻቸው መንገዶች ሁሉ እንዲታገሉት አርበኞች ግንቦት 7 ያሳስባል።

በዚህ አጋጣሚ የአይሲስን የሽብር ተግባራት ከእስልምና እምነት ጋር ማያያዝ ፈጽሞ ትክክል እንዳልሆነ፤ ብዙሃን ሙስሊሞች የአይሲስና መሰል ቡድኖችን አካሄድ የሚቃመው መሆኑን አርበኞች ግንቦት 7 ማስገንዘብ ይሻል። ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ከክርስቲያን ወገኖቻቸው ጋር ተዋደውና ተፋቅረው የኖሩና እየኖሩ ያሉ ሲሆን የሁለቱ ሀይማኖቶች ተከታዮች ተደጋግፎ መኖር ለሀገራችን ህልውና ወሳኝ ጉዳይ መሆኑ የአርበኞች ግንቦት 7 እምነት ነው።

በያዝነው ሣምንት በወገኖቻችን ላይ እልቂት ሲደርስ የሊቢያ ብቸኛ ክስተት አይደለም። በደቡብ አፍሪቃ ወገኖታችን ከነሕይወታቸው በእሳት ተቃጥለው ተገድለዋል፤ በስለት ተዘልዝለዋል፤ ንብረታቸውን ተዘርፈዋል። በዛሬው ዕለት 700 ዜጎች የሜዲተራኒያን ባህር በጀልባዎች ሲሻገሩ መስመጣቸው ተሰምቷል። በየመን ደግሞ በርካታ ወገኖታችን በጦርነት እሳት ውስጥ እየተማገዱ ናቸው።

ኢትዮጵያዊያን በአገራችን የሰፈነውን የነፃነት እጦት፣ የፍትህ መጓደልና የኑሮ መክበድ ሸሽተን በሄድነት አገር ሁሉ የሚጠብቀን አሰቃቂ ሞትና ውርደት ሆኗል። ኢትዮጵያ ለኑሮ ያልተመቸችን በህወሓት አገዛዝ ብሉሽነት መሆኑ ጥርጥር የለውም። ይህንን ብልሹ አገዛዝ አስወግደን በምንወዳት አገራችን ተከብረን መኖር እንችላለን። ለኢትዮጵያዊያን ከኢትዮጵያ የተሻለ አገር የለም።

አርበኖች ግንቦት 7: የኢትዮጵያዊያን መከራ እንዲያበቃ ስደት ይብቃ ይላል። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንደዝንባሌውና እንደችሎታው በሕዝባዊ አመጽ አሊያም የሥራ ቦታውና መኖርያው ሳይለቅ በሕዝባዊ እምቢተኝነት በተደራጀ መንገድ የህወሓትን አገዛዝን ይታገል። በሕዝባዊ አመጽና በሕዝባዊ እምቢተኝነት የህወሓት ፋሽስቶችን አስወግደን በአገራችን በነፃነትና በክብር እንድንኖር ሀይማኖትም ሆነ የዘር ሀረግ ሳይለየን በጋራ እንታገል የሚል ጥሪ ያቀርባል።

ዘላለማዊ ክብርና እረፍት ለግፍ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን

The post “የኢትዮጵያ ሕዝብ ስደትን አቁሞ እንደችሎታው በሕዝባዊ አመጽ ወይም በሕዝባዊ እምቢተኝነት ሃገሩን ሳይለቅ ይሳተፍ” – አርበኞች ግንቦት 7 appeared first on Zehabesha Amharic.


(ሰበር ዜና) የሊቢያውን ግድያ በመቃወም በአ.አ. ድንገተኛ ሰላማዊ ሰልፍ እየተደረገ ነው * ወደ ቤተመንግስት ያመራው ሕዝብን ፖሊስ ቢመልሰውም መስቀል አደባባይ እየተሰበሰበ ነው

$
0
0

cherkos addis ababa

* ፌደራል ፖሊስ ለሐዘን የወጣውን ሕዝብ መደብደብ እና ማሰር ጀመረ
* ሐዘናቸውን የመኪና ጡሩምባ የሚያሰሙ ሹፌሮችን እያዋከበ ነው
* ሕዝቡን ከመስቀል አደባባይ ለመበተን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሠራዊት ሰፍሯል

(ዘ-ሐበሻ) በሊቢያ አይሲኤል 28 ኢትዮጵያውያንን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደለ በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጣውን በተለያየ መንገድ እየገለጸ ይገኛል:: በስልጣን ላይ ያለው ይህ ሁሉ ሕዝብ በአሰቃቂ ሁኔታ ሕይወቱን አጥቶ ለጉዳዩ ትኩረት አለመስጠቱ ያንገሸገሸው ሕዝብ በአዲስ አበባ በራሱ አነሳሽነት ከቤቱ ተነስቶ ወደ ቤተመንግስት ያመራ ሲሆን የመንግስት ወታደሮች እየመለሷቸው ይገኛሉ:: ሰልፈኛው “ከቤተመንግስት የምታስመልሱን ከሆነ መስቀል አደባባይ ሆነን እናለቅሳለን… መንግስት የለንም” በሚል ተቃውሞውን እያሰማ ይገኛል::

ፖሊስ ለሐዘን የወጣውን ሕዝብ ወደ ቤቱ እንዲመለስ እያሰገደደ እንደሆነ የገለጹት የዘ-ሐበሻ ምንጮች
ተከብረሽ የኖርሽ በአባቶቻችን ደም፣
እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም
እያለ መዝሙር እንደሚያሰማም አስታውቀዋል:: ፌደራል ፖሊሶቹ መንግስት ሐሙስ የራሱን ሰልፍ ስለሚጠራ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ እያሉ ቢያግባቡም “እንዴት እስከ ሐሙስ ጠብቁ ትሉናላችሁ?” የሚል ጥያቄ እያነሳም እንደሆነ ታውቕል::
‹‹መንግስት የሌለው ኢትዮጵያ ብቻ ነው!››
‹‹መንግስት የሌለን እኛ ብቻ ነን!››
እያለ መፈከር እያሰማ ወደ መስቀል አደባባይ የሚተመው ሕዝብ ቁጥር እየጨመረ ነው::

ጉዳዩን ተከታትለን እንዘግባለን::

The post (ሰበር ዜና) የሊቢያውን ግድያ በመቃወም በአ.አ. ድንገተኛ ሰላማዊ ሰልፍ እየተደረገ ነው * ወደ ቤተመንግስት ያመራው ሕዝብን ፖሊስ ቢመልሰውም መስቀል አደባባይ እየተሰበሰበ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

በአ. አ. አይሲኤል እና ቸልተኛው የኢትዮጵያ መንግስትን በመቃወም ድንገት የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ቭዲዮ (Video + Text)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) አይሲኤል የተባለው አሸባሪ ቡድን 28 ኢትዮጵያውያንን በሊቢያ ሕይወታቸውን ካጠፋ በኋላ ዛሬ በአዲስ አበባ እየተደረገ ባለው ድንገተኛ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሐዘኑን ሊገልጽ ክወጣው ሕዝብ መካከል ወጣቶች እየተመረጡ በቆመጥ ተደበደቡ:: ሕገወጥ ሰልፍ አድርጋችኋል በሚልም ሕወሓት የሚመራው መንግስት ወጣቶችን እያሰረ ይገኛል::

28 ኢትዮጵያውያን ነብሳቸውን በአይሲኤል ሲነጠቁ ዜጎቼ መሆናችውን አላጣራሁም ሲል በሟቾቹ ጉዳይ ግድም እንደሌለው ያሳየው ሕወሓት የሚመራው መንግስት ወታደሮቹን በማሰማራት በመስቀል አደባባይ በመሰብሰብ ላይ የነበረውን ሕዝብ መደብደቡ የሃገር ፍቅርና የወገን ፍቅር ከሌለው መንግስት የሚጠበቅ ተግባር ነው ሲሉ የፖለቲካ ተንታኞች አስተያየታቸውን ይሰጣሉ::
addis ababa cherkos
ወደ መስቀል አደባባይ በአይሲኤል እና በዜጎቹ ላይ ቸልተኛ በመሆነው የኢትዮጵያ መንግስት ላይ ተቃውሞውን ለማሰማትና ለሞቱት ወንድሞች ሐዘኑን ለመግለጽ የወጣው የአዲስ አበባ ሕዝብን በመስቀል አደባባይ በብዛት እንዳይሰበሰብ የመንግስት ወታደሮች ወደ መስቀል አደባባይ በተቃውሞ የሚተመውን ሕዝብ ከየመጋቢ መንገዶች እየቆረጡ ሕዝቡን ለማስቅቅረት እየሞከሩ ነው ተብሏል::

ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እንመለሳለን

The post በአ. አ. አይሲኤል እና ቸልተኛው የኢትዮጵያ መንግስትን በመቃወም ድንገት የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ቭዲዮ (Video + Text) appeared first on Zehabesha Amharic.

“[ቅዱስ ሲኖዶስ በሊቢያ ስለተሰውት ሰማዕታት ያወጣው መግለጫ] የተጻፈበት ቋንቋ ቤተ ክህነት ቤተ ክህነት አይልም”–ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

$
0
0

ከዲ/ን ዳንኤል ክብረት

የቅዱስ ሲኖዶሱን መግለጫ አየሁት፡፡ መጀመሪያ ነገር ቋሚ ሲኖዶሱ ተሰብስቦ መክሮበታል ብዬ ለማመን ይቸግረኛል፡፡ የተጻፈበት ቋንቋ ቤተ ክህነት ቤተ ክህነት አይልም፡፡ ለመሆኑ ለሰማዕታት የሚሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አጥታችሁ ነው? ይበልጥ ያስገረመኝ ደግሞ የሰማዕታቱ ዜግነት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ምን እንደሚጠቅማት ነው፡፡ መንግሥት የዜግነትን ጉዳይ ቢያነሣ ኃላፊነቱ በዜጎቹ ላይ የተወሰነ ስለሆነ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን ‹መልዕልተ ኩሉ› የተባለቺውን ዘንግታው ነው የዜግነት ጉዳይ ያሳሰባት? ምንም ኢትዮጵያዊነታቸው የማያጠራጥር ቢሆንም፣ ጠላታቸው እንኳን የመሰከረላቸው ቢሆንም፣ ዓለም ያወቃቸው ቢሆንም፣ ለቤተ ክርስቲያን ግን ሱዳኖችም ሆኑ ሩዋንዳዎች፣ ሶማልያዎችም ሆኑ ጅቡቲዎች የተሠውትኮ ክርስቲያኖች ናችሁ ተብለው ነው፡፡ ለአንድ ክርስቲያን የሰማዕትነት ክብሩ የሞተለት ክርስቲያናዊ ምክንያት ነው፡፡ የሞቱት ደግሞ ክርስቲያኖች ናችሁ ተብለው ነው፡፡ በቃ፡፡
daniel
ደግሞስ ‹የዜግነትና የማንነት መረጃውን በተመለከተ ግልጽ መረጃ ለማግኘት ጥረት እየተደረገ ነው› የሚሉን ማነው ጥረት እያደረገ ያለው? መንግሥት ነው ካላችሁ ‹መንግሥት ጥረት እያደረገ ነው› በሉ እናንተም ጥረት እያደረጋችሁ ከሆነ ንገሩን፡፡ ቤተሰቦቻቸውኮ ኢትዮጵያ ውስጥ ናቸው፡፡ ለምን ለየሀገረ ስብከቱ መመሪያ በመስጠት ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ከበዳችሁ? እረኛ በጎቹን በሪሞት ይጠብቃል እንዴ?
እጅግ ያስገረመኝና ያሳዘነኝ ነገር ደግሞ ክርስቲያን በመሆናቸው በአሰቃቂ ሁኔታ ለተገደሉ ወንድሞች ከቤተ ክርስቲያን የምጠብቀውን ሦስት ነገር ከመግለጫው ማጣቴ ነው፡፡ የመጀመሪያው የመታሰቢያ ጸሎት ሊደረግ ይገባው ነበር፡፡ በምንም ለማናውቃቸውና ለማያውቁን የኢንዶኔዥያ ዜጎች ሱናሚ መታቸው ብለን በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጸሎተ ፍትሐት ያደረግን ሰዎች ለሚያውቁንና ለምናውቃቸው ክርስቲያን ወገኖች ጸሎት ለማድረግ ለምን እንደከበደን እንጃ፡፡ ለመሆኑ ከአንድ አባት ከጸሎት በላይ ምን ሊገኝ ይገባ ነበር?

‹ማንነታቸው ተረድተን በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት አስፈላጊውን እናድርጋለን› ይላል መግለጫው፡፡ ለመሆኑ ከክርስትና በላይ ምን ማንነት አለ? የብሔር፣ የብሔረሰብ ማንነት ነው የምታጣሩት? ከዚያ ይልቅ ሁኔታውን የሚከታተል፣ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚገናኝና ለቀጣዩ የቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊም ቀኖናዊም ተግባር ነገሮችን የሚያመቻች ሲኖዶሳዊ ኮሚቴ ይቋቋማል ብዬ ጠብቄ ነበር፡፡ ምነው በአንድ አጥቢያ ገንዘብ ተወሰደ ሲባል ሲኖዶሳዊ ኮሚቴ ይቋቋም የለምን?

ሦስተኛው ያሳዘነኝ ነገር ቤተ ክርስቲያን በልጆቿ ላይ የሚደርሰውን ኀዘን የምትገልጥበት ቀኖናዊና ትውፊታዊ ሥነ ሥርዓት የሌላት ይመስል ኀዘንን በሴኩላር መንገድ ስትገልጥ ማየቴ ነው፡፡ እኔ የጠበቅኩት ለአንዳንድ ክርስቲያን ላልሆኑ ‹ታላላቅ ሰዎች› ቀብር እንኳን የሚከፈተው የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከፍቶ፣ ለቢዮንሴ እንኳን ያልተነፈጋት ማኅሌት ተቁሞ፣ በፓትርያርኩ የሚመራ ጳጳሳቱ የሚገኙበት የጸሎት ሥነ ሥርዓት ተደርጎ፣ መግለጫው በጸሎቱ ፍጻሜ ይሰጣል ብዬ ነበር፡፡ የመግለጫው አሰጣጥ ግን የዕለት ተዕለት ተግባርን በተመለከተ የሚሰጥ ሳምንታዊ መግለጫ ነበር የሚመስለው፡፡ ኦርቶዶክስ ኦርቶዶክስ አይሸትም፡፡ የተወካዮች ምክር ቤት እንኳን የሦስት ቀን ብሔራዊ ኀዘን ሊያውጅ መሆኑን ሲገልጥ ቤተ ክርስቲያኒቱ ግን የጸሎት ሳምንት አለማወጇ የታሪክ ትዝብት ውስጥ የሚከታት ነው፡፡

እኔ የሲኖዶሱ መግለጫና አገላለጡ ወርዶብኛል፡፡ ሲኖዶሳዊም መስሎ አልታየኝም፡፡ ሊቃውንቱ ያዩት፣ ጳጳሳቱ የተወያዩበት፣ ቅዱሳት መጻሕፍቱ ያሹት፣ ቀኖናዎቹ የዳሰሱት፣ ትውፊቱ የነካው፣ ባሕሉ ያጠነው አልመስልህ አለኝ፡፡ ‹ወይ እንደ እስክንድ ተዋጋ ወይ የእስክንድርን ስም መልስ› አለ ታላቁ እስክንድር፡፡

The post “[ቅዱስ ሲኖዶስ በሊቢያ ስለተሰውት ሰማዕታት ያወጣው መግለጫ] የተጻፈበት ቋንቋ ቤተ ክህነት ቤተ ክህነት አይልም” – ዲ/ን ዳንኤል ክብረት appeared first on Zehabesha Amharic.

የማለዳ ወግ…. ሀዘን የወለደው ደካማ ስሜት ፍርሃት !

$
0
0

    * በጨለመው ሚያዝያ ፣ የጨነቀ እለት  …

Nebiyu Sirakበማለዳው አነሳሴ እንደለመድኩት በስደቱ ዙሪያ ገብ የሆነውንና እየሆነ ስላለው ልሞነጫጭር  ፣ ልብተከተክ አልነበረም …  ከትናንት ከትናንት በስቲያ ጠዋት ፣ረፋድና ተሲያት ፣ ምሽት ፣ በደረቁ ሌሊት እያቅበጠበጠኝ ስልኬን አንስቸ ወደ ሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፒሊ ወደ ማትረጋው ቢንጋዚና ሚስራታ የደዋወልኳቸውን ስልኮች ተመለከትኩ ። ከወዳጆቸ የደረሱኝን ሁለት ሶስት አድራሻዎችና እዚህ ጅዳ ያለ ሊቢያዊ ጓኛየ አድራሻቸውን አፈላልጎ የሰጠኝን ሌሎች ሰብሰብ ያሉ ወንድሞችን አግኝቻለሁና ደጋግሜ ቁጥሮችን አየኋቸው  …

የሰበሰብኳቸው  ስልኮችን ደጋግሜ የደወልኩባቸው ስለሆኑ መፈላለጉ ጊዜ አይወስድብኝም ፣  ከስልኬ ፊት ለፊት ተደርድረዋልና እየመራረጥኩ … እደውላለሁ … እንቅልፍ ለአመል ያህል ተኝቸ ብንን ብንን ማለቱ ቢያስቸግረኝ ይለይለት ብየ እንደ ቀደመው የማለዳ ወግ ለመጻፍ ሳይሆን ባለፉት መራራ ሁለት የሃዘን ቀናት ያነጋገርኳቸው ሊቢያ የሚገኙ እህት ወንድሞቸን ሳነጋግራቸው በመቅርጸ ድምጼ ያስቀረኋቸውን ድምጾች መልሸ መላልሸ ማደመጥ ይዣለሁ …

“ቤንጋዚ ውስጥ ነን !” ያሉኝ ሌሎች ወንድሞች ጋር ቃለ ምልልስ እያደረግኩ ከሊቢያ አውጡን የሚለውን የድረሱልን እተሰማሁ እያለ ይቆራረጥ የነበረው የስልክ መስመር እራሹን ተቋርጦብኝ ስብተከተክ ፣ ሌሎች በሊቢያ የሚገኙ እህቶችን በሌላ መስመር አገኘሁ  ! የአድራሻቸውን መስመር ያገኘሁት የሆነው ያንገበገበው ከእኔ ቢጤ ቅምጥል ኩዌት ከሚገኝ ስደተኛ ወዳጀ ነው ።  እንዲህ ይላል ” ሃይ ነብይ እንዴት ነህ በካይሮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አድራሻ ማግኝት የሚቻለው በምንድነው ልጆች ይፈልጋሉ ሊቢያ ያሉ …ካንፖኒ ውስጥ ነው የሚሰሩ ፣ ወደ 14 ልጆች መንቀሳቀስ መውጣት አልቻሉም ፣  ችግር በተፈጠረበር ቦታ ላይ ነው ያሉት ፣ ወደ ሀገር መግባት ይፈልጋሉ ”   ከመልዕክቱ በኋላ አድራሻቸውን ላከልኝ  …  ሁሉንም የሰበሰብኳውን አድራሻዎች ደዋወልኩ … አንዳንዴ ስልኩ ይነሳል ፣ አንዳንዴ አይነሳም ፣ አንዳንዴ እያወራን በመካከል ይቋረጣል ፣ አንዳንዴ ከአጠገቤ ያሉትን ያህል የቀረበ ድምጽ ይሰማኛል …

ጥርት ያለው ድምጽና መልዕክቱ …
===================

ንጹህ ድምጹ ከአመታት በፊት በስራ ኮንትራት መጥተው በስራ ላይ ካሉት እህቶቸ እንደሆነ አላጣሁትም ፣  ” እባክህ ከሊቢያ ወደ ሀገራችን የሚያወጣን አካል አፈላልግልን ?  ለሚዲያ ሽፋን ሳይሆን ከጭንቅ እንድንወጣ እርዳን  ? ምንም ቢሆን ሀገራችን መግባት ነው የምንፈልገውና እርዳን ? የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዜናውን ሲናገር በዚህ ቁጥር ደውላችው ተረዱ አላለም ፣ ያሳዝናል ፣ ለማን አቤት እንበል?  የምትችል ከሆነ እርዳን  ?   ” በሚለው ተማጽኖ  ድምጻቸውና አልፎ አልፎ እኔኑ አላምነን እያሉ በምናደርገው ያልተናበብንበት ውይይት እኒሱ መሆናቸውን  እለየዋለሁ  !

ተቆራራጩ ድምጽና የተቆራረጠው ተስፋ  …
==========================

ተቆራራጩ ድምጽ ደግሞ በሱዳን አድርገው የሰሃራን በርሃ በስቃይ ቆርጠው መጥተው ፣ ባንዷ ሁከት በማይለያት ከተማ  የተኮለኮሉ ወንድሞች ናቸው ።  በማይገኘው መስመር አልፊ ሳገኛቸው  ስሜቴን ይፈታተኑታል ፣ የሆነውን በተባራሪ ወሬ እንጅ እንደ ትርፖሊ ነዋሪ እህቶቸ ክፉ ደጉን አላዩትም ፣ ያ መሆኑ በጀ  !  …ብቻ ወደ እንሱ ተስፋ ምድር አውሮፖ ሊሄዱ አስበው ፣  በ28 ( ሰላሳ ናቸውም ይባላል)  በጽነፈኛው ደዕሽ ISIS ጨካኝ አራጆች ተፈጸመ የተባለውን ግድያ ሰምተው ተደናግጠው ባንድ አሳቻ ቦታ ተደበወቀዋል ”  ወደ ሰላሳ እንጠጋለን ” ብለውኛል  ! የሚቀመስ ምግቡ ቀርቶ በረሃ ቆርጠው ቀዝቃዛ ውሃ ጠግበው ያልጠጡ ችግረኞች ናቸው ።  የእኒህ ችግረኛ ወንድሞች ስልክ  ደከም ያለች ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ይመስለኛል ውይይታችን ብዙም አይሰማም ፣ ችግሩን መገመት አያዳግትም … ብቻ ” የት እንሒድ  ? ” ብለው ከሀገር ያስለቀቃቸውን ችግር ፣ ቸነፈርና ድህነት ሳይሆን የአስተዳደር በደልና ስራ አጥነት ለዚህች ቀን አደንዳደረሳቸው የቆመው ጀሮየ ሰምቷል … እኒህኞቹ ወደ ሀገር መግባት አይፈልጉም ፣ እዚያው መቆየት ደግሞ  አይፈልጉም … ብቻ ምርጫቸው አለም ችግራችን ሰምቶ ወደ ሶስተኛ ሀገር ያውጣን ባዮች ናቸው  ! የተቆራረጠው ተስፋ መልዕክትና ተስፋ … ሲናገሩት ያማል …

ሰማሁት …  ሰማሁት  ፣ ተስፋየ በተነው  !
===========================

ከሞቱት ሰማዕት በላይ ውስጤን ያወከውና ልብን የሚሰብር ሆነው ካገኘኋቸው መካከል በትሪፖሊ ውስጥ በአንድ ሆስፒታል በስጋት ላይም ሆነው ስራቸውን በመስራት ላይ ያሉ 14 የሚደርሱ እህቶች ይገኙበታል  ። ከመካከላቸው ያነጋገርኳቸው ከሶስት ባይበልጡም ፣ የሶስቱ ጭንቀት ገላጭ ደረቅ አስተያየት የሁሉንም ይገልጸዋል ፣  በሚወጡበት ጉዳይና ባሉበት ሁኔታ ስንወያይ አልፎ አልፎ ባንግባባም ፣ ስንለያይ ፍላጎቴን አስረድቸ ተግባብተን ነው … ” አየህ ወንድም እኛ ስለታረዱት ወንድሞቻችን የሰማነው በሚዲያ ነው ፣ ከሁለት አመት በፊት ወደ ሊቢያ ትሪፖሊ መጥተን ስራችን እየሰራን ነው ፣ ስራ ላይም ሆነ ቤት ውስጥ ሆነን ሁሌም የጥይት ድምጽ ከከተማ ውጭ ፣ በርቀት እንሰማለን … አሰሪዎቻችንን ወደ ሀገራችን ስደዱን ስንላቸው ከተማ ውስጥ ችግር የለም እያሉ ያጽናኑናል ፣ በእርግጥም እስካሁን ከስራ ቦታ ወጥተን በቅርብ ርቀት ባለው በተዘጋጀልን ቤት እናርፋለን ፣ እስካሁን ችግር የለብንም  ፣ አሁን ግን የወንድሞቻችን መታረድ መሪርና አስደንጋጭ ዜና ስንሰማ ሰግተናል ፣ ተሸብረን ጨንቆናል …አንተ ምን ትረዳናለህ  ?   ለሚዲያ ሽፋን ብቻ ከሆነ አይጠቅመንም ፣ እኛ የምንፈልገው በሰላም ከሊቢያ መውጣት ነው ፣ ጭንቅ ላይ ነን ፣  የሚረዱንን ሰዎች አገናኘን ፣ እባክህ እርዳን  ? ” ያሉበትንና የገለጹበትን ድምጽ ደጋግሜ እያዳመጥኩ ተጨናንቄያለሁ  !  ” ከሊቢያ እንድንወጣ ብቻ እርዳን !” ብለው ከፍቷቸው አዝነው እየተማጸኑኝ ነበርና እኔም የቻልኩትን ለማድረግ እሞክራለሁ በሚል ቃል ገብቸ ላበረታታቸው ስሞክር አልተቻለኝም …አንዳንዴማ የጨነቀ እለት ይከፋ የል …ከፍቷቸው የሚሰጡት ጥርጣሬ የሞላበት አስተያየት ውስጤን ያውከው ያስቸግረኝ ይዟል …  ግን ቻል አደርገዋለሁ   ! … ማድረግ መሆን አለመቻል በተስፋ ተሞልቸ ስኖር ተስፋየ በተነው  …

የግብጽ ኢንባሲና እህቶች  …
===================

ጨለማው ሚያዝያ 12 ቀን 2007 ዓም  ሰኞ ማለዳ እኩለ ቀን ገደማ ነው ፣  ከማለዳው እስከ እኩለ ቀን የብዙ ወገኖች ትጋት የታከለበት ጥረት ተሳክቶ ሊቢያ ያሉት   ወገኖቻችን ይረዳሉ የተባሉ ኃላፊዎች አድራሻ ተገኘ ፣ በአድራሻው ወደ ሃገረ ግብጽ ካይሮ ደወልኩ ፣ ኃላፊውን አግኝቸ ሀገር ቤት መግባት ለሚፈልጉት እያደረጉ ስላለው ጥረት ጠየቅኳቸው ” ጉዳዩ ገና እየተጣራ በመሆኑ መረጃ ልሰጠህ አልችልም ፣ ነገር ግን በተለያዩ የሊቢያ ክፍል ያሉ ወገኖቻችን እየተደዋወልን ነው! ” የሚል ድፍን ያለ መልስ ሰጡኝ ።  ያገኘሁትን አድራሻ ለመለጠፍ ባስፈቅድም  ፈቃደኛ አይደሉም  ! በኢንባሲው መደበኛ ስልክ መስጠት እንደምችል ግን መከረውኛል ። አዎ አለቆቻቸውን ማነጋገር አለባቸው  ! አለቆቻቸው ደግሞ የተቸገሩት የሚደውሉና እርዳታ የሚያገኙበት እስካሁን ግልጽ ያለ አድራሻ አላስተላለፉም …  ያነጋገርኳቸው ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉት የግብጽ ኢንባሲ ትሁቱን ዲፕሎማት በተለይም ወደ ሀገር ቤት ለመግባት ፍላጎት ያላቸውን ትሪፖሊ የሚገኙ እህቶች አድራሻ ሰጠኋቸውና  አደራ ብያቸው ተለያየን !

አመሻሹ ላይ ወደ ትሪፖሊ ደወልኩ ፣  ስልኩ ተነሳ  ! ከሰላምታ በኋላ አድራሻቸውን እንደሰጠሁ ተናግሬ ሳልጨርስ  ” አዎ ደውለውልን ነበር ፣ ትሪፖሊ ያሉ  አቶ … የሚባሉ ኢትዮጵያዊ አድራሻ ሰጠውናል  ፣ ግን የትም አይጥሉንም  ?  እንዴት ታምናቸዋለህ  ? ሁላችንም ተነጋገርንበት ግን  ፈራን  !”   አለችኝ ስልኩን ያነሳችው እህት ከትሪፖሊ …

ያልደረሰንላቸው በሽዎች የሚቆጠሩ በሱዳን አድርገው በርሃውን ቆርጠው ሊቢያ የገቡት የሚያጠቃ፣ ኢትዮጵያውን ክርስትያኖችን ለይቶ የሚያድን የሰው አውሬ በሊቢያ መሽጓል ።  አሸባሪው  ISIS ይባላል ፣ እንዳሻው አንገት እየቀላ የንጹሃንን  ደም በማፍሰስ የሚፎክር ፣ የሚኩራራ እኩይ አውሬ !  አሸባሪው  ትናንት በግብጽ ክርስትያኖች ጀምሮ ዛሬ በኢትዮጵያ  ክርስትያኖች ደም ማፍሰሱን ቀጥሎ ማን ይነካኛል ብሎ እየፏለለ ይገኛል ።  ኃያላኑ አሜሪካና ምዕራባውያን ዝም ጭጭ ብለዋል  ! አሸባሪው  ISIS የሚደፍረው ጠፍቷል ፣  አለያም ሆን ተብሎ እንዳበደ ውሻ ተለቆ ሰው መፍጀት ይዟል  !

ተስፋ መቁረጥ ፣ ስጋትና ፍርሃት …
=====================

የሰሃራ በርሃን ቆርጠው ሊቢያ የተኮለኮሉትን ኢትዮጵያውያን ቁጥር ማንም አያውቀውም ፣ መሸሻ መሸሸጊያ ቢጠባቸው ፣ ችግራቸው ችግር ቢሆንም በሃገር ቤት የመሳደድ መታሰር ፍርሃቻ  ሃገር መግባት እንዳላስቻላቸው አጫውተውኛል ፣ የተመዘዘው ስል ጩቤ አላስፈራቸውም .. ! ”  ሶስተኛ ሀገር እንጅ ወደ ሃገር አንገባም !” እያሉ ነው  ! አደጋውን በተጨባጭ መረጃ ስታስረዳቸው ” በራሴ ወገን ፣ በራሴ ሀገር በእስር ከምሰቃይ ፣ በርሃው ይብላኝ … ” ይሉሃል …ከበርሃው በላይ ያለውን ጨካኝ  አሸባሪ ስራ ቢያውቁትም የሀገር ቤቱ የፖለቲካ ትኩሳት ወደ ሀገር የመመለስ ተስፋቸውን አጨልሞታል  ! ሀገር ቤት መግባቱ እንኳን ለእነሱ በራሴ ላይ ምን ይፈጠርብኝ እንደሁ የማላውቀው ጎልማሳ  የፈለገው ቢያደርጉም ፣ በሰው ሃገር በጨካኞች እጅ ከመውደቅ በሀገር  መከራን መቀበል ይሻለል ! ስላቸው ወያኔያዊ መንፈስ የተጠናወተኝ እየመሰላቸው ” እሱ ያንተ ምርጫ ነው ፣ ብቻ ስማችንና ድምጻችን እንዳታወጣው አደራ ! ” ይሉኛል መልሰው  ይጠራጠሩና  … ፈርተው  ! እናም ፖለቲካው የፈጠረው ስጋትና ፍርሃት ታየኝ …

ክህደት ፣ ሸፍጥ ፣ አምነት ማጣት … የወለደው ፍርሃት  …
===================================

“ወደ ሃገር እንግባ ” ያሉት ሞልተው ተርፈዋል ፣ ያም ሆኖ  እስካሁም በግላጭ የሚታወቅ ለሁሉም ተደራሽ አድራሻ አልተላለፈም  !  … የተደረሰላቸው ጭንቀት ፍርሃቱ የራሳቸውን ወገን እስከ መጠራጠር አድርሷቸዋል አይተናል ፣ ለመረዳት ”  ፈራን !”  እያሉ ነው   !  … ክህደት ፣ ሸፍጥ ፣ አምነት ማጣት … የወለደው ፍርሃት ፈሪ አድርጓቸዋል  !

ወደ አውሮፖ በጣሊያንና ማልታ በኩል ለመድረስ   በአሳር በመከራ እዚህ ጫፍ የደረሰ የሀበሻ ልጅ ደምም ረክሷል ፣ ሃበሻ የሌለበት ፣ የሀበሻ ነፍስ  ረክሶ ፣ ነፍሱ የማይጠፋበት ቦታ  አይሰማም ። ይህ የባህር አደጋ ብዙ ባይነገርለትም ፣ ተደጋግሞ የእኛን ሰው ነፈወስ ነጥቆታል ፣  አጥፍቶናል  ።  ቢደደጋገምም ሀዘን ቁጭቱ አልለመድ ብሏል ። እነሆ በሃዘን ላይ ሃዘን ሰምተናል  !  የወንድሞቻችን አንገት በተቀላበት የሜዲትራንያን ውቅያኖስ በተሰናከለች የአሻጋጋሪዎች መርከብ / ጀልባ  “የሞቱት የተረፉት እነማን ናቸው ? ” ተብሎ ወደ  የማይመረመርበትን ትራጀዲ  ተፈጽሟል !  ይህን የሰማነው ትናንት ነው  ፣ በሀዘን ላይ ሆነን !

ካለሁበት ሳውዲ ኩታ ገጠሟ የመን የሀበሻ ልጅ የድረሱልኝ ድምጽ አባርቶ ባያውቅም  ፣ የመን ሰማይ ስር በጦርነት እየታመሰ በመሆኑ የከፋ ዋይታ ድምጽ ይሰማል ፣ ጭካኔያቸውም አይተን የአፍሪካዊ ISIS  ያልናቸው ደቡብ አፍሪካውያን ውለታችን ረስተው አመድ አፋሽ አድርገውን ብቻ አልቀሩም ፣  የለየለት የንቀት ግፍ ተፈጽሞብናል  !  ይህም ያም ሁሉም ያስፈራል  !

ሁለት አስርት አመታት በኩራትና ፍጹም በነጻነት የኖርኩባት ሳውዲ አረቢያ አሁንም እስከ ትናንት በስቲያ ድረስ ከሀገሬ ባልተናነሰ ከከተማ እስከ ገጠር ከተሞቿ  በነጻነት ብንቀሳቀስባትም ዛሬ የነጻነቱን ግርማ ከላየ ላይ የለም  ! … ቤቱ ፣  ስራ ፣ ቦታው ፣ መንገዱ … ሁሉም ያስፈራል  ! ” ፈራን  !” ብለው አስፈሩኝ …

ትናንት ማምሻውን ከልጆቸ ጋር ስንጨዋወት የወትሮው አባታቸው አለመሆኔን ተረድተዋልና  ” አቤ ምን ሆነሃል ፣ ፊትህ ደስ አይልም! ” እያሉ ጠየቁኝ ፣ ወደ ውስጥ ሳልገባ ” ከእናንተ የሚጠበቀው ጥናት ነው  አጥኑ! ” አልኳቸው ፣ መልሴ ያልጣመው የ13 ዓመቱ የበኸር ልጀ ” አቤ እስኪ ላንድ ሰሞን ይህንን የምትጽፈውን ተወውና ዘና በል ፣ ባህር መጫወቻ ቦታ ሁሉም አካባቢ ጥሩ ጥሩ ወዳጆች እያሉህ እዚያም ወስደህንኮ ትጽፋለህ  ? ለምን ለራስህ እረፍት አትሰጠውም  !” ሲል እህቱ ማሂን እንዳቀፈ ክችም ብሎ አፍጥጦ ጠየቀኝ እዮብ ፣ የመጻፊን ጥቅም ባስረዳውም  ” እኛም እኮ አንተ ስትረባበሽ እንረበሻለን ” ሲል ሞገተኝ ፣ መልስ የለኝም ”  ልጀ ምን ታይቶት ይሆን  ?  ” አልኩ ራሴ ለራሴ በውስጤ … ከነጎድኩበት እሳቤ ራሴን በተሎ ሰብስቤ  ” አዎ ትክክል ነህ  ፣  እስኪ አረፍ እላለሁ  ! ” አልኩትና ቃል ገባሁለት …ለአባቱ የፈራ ልጅ   !

ፍርሃቱ ባያሸሸኝ ፣ ለልጀ የገባሁትን ቃል ለማክበር ላፍታ ያህል ከማህበራዊ መገናኛ መስመሩ ዘወር ልል አስቤያለሁ ፣ አብራችሁኝ ለተጓዛችሁ  ፣ ለደገፋችሁኝ ፣ ለተረዳችሁኝ ፣ ” ራስክን አትቆልል! ” ስትሉ የድርሻችሁን ስታደርጉ የማላያችሁ ወቃሾቸ ጭምር ሁላችሁንም አመሰግናለሁ  !  የሰማሁት ሰሞነኛ ልብም ሰባሪ እማኝነት  እንዳይቀር አንድተነፍስና ለእረፍት የመሰናበቻ መልዕክቴን በተሰበረ ልብ ካስተላለፍኩ ምንም አልሻም  ! የጨለቀ እለት …  እንዲህ ነው  !

ብቻ ከመግፋት መገፋት ፣ መልካም ነገር ነው ፣ ለሚቀረው አለም  ለሚያምኑበት መሞት ደግሞ ሰማዕትነት  ነው  !  ነፍስ የሚያስምር  !

ነቢዩ ሲራክ
የጨለመው ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓም

The post የማለዳ ወግ…. ሀዘን የወለደው ደካማ ስሜት ፍርሃት ! appeared first on Zehabesha Amharic.

አ.አ ቡልጋሪያ ማዞሪያ አካባቢ ሐዘኑን ለመግለጽ አደባባይ የወጣው ሕዝብ በፖሊስ ተበተነ (ዜና ፎቶ)

$
0
0

addis ababa pro 7

addis ababa pro 4

addis ababa pro 3

addis ababa pro 2

addis ababa pro

addia ababa pro 1

“እኔም ዘ-ሐበሻ ነኝ” ያለ አንባቢያችን በፎቶ ግራፍ የላከልን መረጃ እው::
ዛሬ ጠዋት ሚያዝያ 13 2007 5፡30 ላይ በተለምዶ ቡልጋሪያ ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከጨርቆስ ወደ አፍሪካ ህብረት በሚወስደው መንገድ ላይ የጨርቆስ ወጣቶች በመሰባሰብ የISIS ጭካኔያዊ ተግባር እና በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን ግፍ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ቢሞክሩ በፀጥታ ኃይሎች በተፈጠረ ውክቢያ ሊበተኑ ችለዋል፡፡ ለማንኛውም በማያውቁት ጉዳይ ለተሰው ወገኖቻችን ነብስ ይማር!!

The post አ.አ ቡልጋሪያ ማዞሪያ አካባቢ ሐዘኑን ለመግለጽ አደባባይ የወጣው ሕዝብ በፖሊስ ተበተነ (ዜና ፎቶ) appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>