Quantcast
Channel: ዘ-ሐበሻ – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 8745 articles
Browse latest View live

Sport: ኤፍ ኤ ካፕ 6ኛው ዙር: ማን.ዩናይትድ ከአርሰናል (ልዩ ትንታኔ ስለ ፍልሚያው)

$
0
0

በየሳምንቱ በመላው ዓለም የሚገኙ ስፖርት አፍቃሪያን በጉጉት የሚጠብቁት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በዚህ ሳምንት በኤፍ ኤ ካፕ 6ኛ ዙር ውድድር ተተክቷል፡፡ በእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር (ኤፍ ኤ) አዘጋጅነት ከሚደረጉ የሀገር ውስጥ ውድድሮች ከፕሪሚየር ሊጉ ቀጥሎ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው የኤፍ ኤ ካፕ ውድድር በርካታ ክለቦችን ጥሎ ስድስተኛ ዙር ላይ ደርሷል፡፡ በስድስተኛው ዙር የኤፍ ኤ ካፕ ውድድር አራት ጨዋታዎች በተለያዩ የእንግሊዝ ከተሞች ይካሄዳሉ፡፡
FA Cup Final 2015
የመጀመሪያው ጨዋታ ቅዳሜ በእንግሊዞች የምሳ ሰዓት ጨዋታ 9፡45 ላይ የሊግ አንዱ ተወዳዳሪ ብራድፎርድ ሲቲ የሻምፒዮንሺፑን ሬዲንግ በሜዳውና በደጋፊው ፊት በሚፋለምበት መርሐ ግብር ይጀመራል፡፡

ብራድፎርድ ሲቲ በሊግ አንድ ውስጥ በ48 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ተጋጣሚው ሬዲንግ በበኩሉ በሻምፒዮንሺፑ በ41 ነጥብ በአሥራ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ የሊግ አንድ የደረጃ ሰንጠረዥን ብሪስቶል ሲቲ በ73 ነጥብ፣ ፕሪስተን በ63 ነጥብ እና ማክዶንስ በ62 ነጥብ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ይዘዋል። የሻምፒ ዮንሺፑን የደረጃ ሰንጠረዥ ደግሞ ሚድል ስቦሮው በ66 ነጥብ፣ ደርቢ ካውንቲ በ65 ነጥብ እንዲሁም ዋትፎርድ በግብ ተቀድሞ በተመሳሳይ 65 ነጥብ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ በሚቀጥለው ዓመት ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ለማደግ የሚደረገውን ሩጫ እያገባደዱ ይገኛሉ፡፡ ሁለቱ ክለቦች ለስድስተኛ ዙር ጨዋታ የደረሱት ብራድፎርድ ሲቲ ቼልሲና ሰንደርላንድ ጥለው ሲሆን፤ ሬዲንግ በበኩሉ ካርዲፍ ሲቲንና ደርቢ ካውንቲን በጥሎ ማለፍ አሸንፎ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ጨዋታው ቀጥሎ ምሽት 2፡30 ላይ አስቶንቪላ በሜዳው ቪላ ፓርክ ላይ ዌስትብሮሚች አልቪዮንን ይገጥማል፡፡ ይህ ጨዋታ ሁለቱ ክለቦች ባለፈው ማክሰኞ በቪላ ፓርክ በ28ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በተገናኙ ሳምንት ሳይሞላቸው ለሁለተኛ ጊዜ የሚገናኙበት ጨዋታ ይሆናል፡፡ አስቶንቪላዎች የቀድሞ አሠልጣኛቸውን ፖል ላምበርትን አባረው በምትኩ የቶትንሃም ሆትስፐር ዋና አሠልጣኝ የነበሩትን ቲም ሽሩድን በአሠልጣኝነት ከቀጠሩ በኋላ መጠነኛ የሚባል ለውጥ ያመጡ ሲሆን፤ ሽሩድም የመጀመሪያ ሦስት ነጥባቸውን አግኘተዋል፡፡ ባለፈው ማክሰኞ የቶኒ ፑሊሱን ዌስትብሮሚች አልቪዮን አስተናግደው ምስጋና ለዳኛው ይግባውና በባከነ ሰዓት በተሰጣቸው የፍጹም ቅጣት ምት ማሸነፋቸው እና የመጀመሪያ ሦስት ነጥባቸውን ማግኘታቸው ከፍተኛ መነሳሳት ፈጥሮላቸዋል፡፡ ዌስትብሮሚች አልቪዮኖች በበኩላቸው በከፍተኛ ግብ አስቆጣሪያቸው በራሂኖ ታግዘው ከፍተኛ የፕሪሜር ሊጉን ሽንፈታቸውን ለመበቀል ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡

መርሐ ግብሩ ዕሁድ ቀጥሎ ምሽት 1፡00 ላይ የመርሲሳይዱ ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ሮድ ስታዲየም የሻምፒዮን ሺፑን ብላክበረን ሮቨርስን ያስተናግዳል፡፡ ሊቨርፑሎች በፕሪሚየር ሊጉ ባደረጓቸው ተከታታይ ጨዋታዎች በማሸነፍ ከነበሩበት የ12ኛ ደረጃ ወደ አምስተኛ ደረጃ መምጣታቸው እና ይህንን ጨዋታ በሜዳቸው የሚያደርጉ መሆኑ ከፍተኛ የማሸነፍ ዕድል ተሰጥቶታል፡፡ ብላክበርን በበኩሉ አሁን ያለበት ደረጃ ሊቨርፑልን ሙሉ ለሙሉ ማቆም የሚያስችል ባይሆንም ለጨዋታው ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው በመግባት ለሊቨርፑል ከፍተኛ ፈተና እንደሚሆኑባቸው ይጠበቃል፡፡

አራተኛውና በጉጉት የሚጠበቀው የመጨረሻው ጨዋታ ሰኞ ምሽት 4፡45 ማንቸስተር ዩናይትድንና አርሰናልን ያገናኘው ጨዋታ ነው፡፡ ሁለቱ ክለቦች በተገናኙ ቁጥር ከጨዋታው በላይ በአሠልጣኞችና በተጫዋቾች መካከል የሚደረገው እሰጥ አገባ ሁሌም የሚናፈቅ ነው፡፡ በዚህ ዓመት ደግሞ አርሰናል ከተፋላሚው ማንችስተር ዩናይትድ በፕሪሚየር ሊጉ በአንድ ነጥብ ከፍ ብሎ በሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ሲሆን፤ ማንችስተር ዩናይትድ በበኩሉ ከአርሰናል በመቀጠል በአራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ እንደሚታወሳው ሁለቱም ክለቦች ባለፈው ረቡዕ በፕሪሚየር ሊጉ ከሜዳቸው ውጪ ያደረጓቸውን ጨዋታዎች በድል ተወጥተዋል፡፡ ማንችስተር ወደ ጄምስ ፓርክ ስታዲየም አቅንቶ ኒውካስል ዩናይትድን ገጥሞ በ89ኛው ደቂቃ በኒውካስትሉ ግብ ጠባቂ ቲም ክሩል ስህተት ተጠቅሞ አሽሊ ያንግ ባስቆጠራት ግብ 1ለ0 ሲያሸንፍ አርሰናል በበኩሉ ወደ ሎፍተስ ሮድ በማቅናት ኪውፒአርን ገጥሞ ኦሊቬ ጅሩድና አሌክሲስ ሳንቼዝ ባስቆጠሯቸው ሁለት ተከታታይ ግቦች 2ለ1 አሸንፎ መመለሱ አይዘነጋም፡፡

በአራት የተለያዩ ጨዋታዎች ቀጥሎ የሚውለው የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ 6ኛ ዙር ውድድር አራት ክለቦችን ወደ ግማሽ ፍጻሜ ሲያሳልፍ አራት ክለቦችን በማሰናበት ይቋጫል፡፡ የፍጻሜው ውድድር በመጪው ግንቦት መጀመሪያ አካባቢ በታላቁ ዌምብሌይ ስታዲየም የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል፡፡

The post Sport: ኤፍ ኤ ካፕ 6ኛው ዙር: ማን.ዩናይትድ ከአርሰናል (ልዩ ትንታኔ ስለ ፍልሚያው) appeared first on Zehabesha Amharic.


Health: የጥብስ ቅጠል የጤና ጥቅሞች Health Benefits of Rosemary

$
0
0

Rosemary
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)
✔ ካንሰርን ይከላከላል
ሮዝመሪ(የጥብስ ቅጠል) በውስጡ የያዘው ካርኖሶል የተባለ ንጥረ ነገር ካንሰርን የመከላከል አቅም እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
✔ የማስታወስ ችሎታን ይጨምራል
ከጥንት ጀምሮ ስለዚህ ጥቅሙ የሚነገርለት የጥብስ ቅጠል በውስጡ የያዘዉ ካርኖሲክ አሲድ የአንጎል ነርቮችን የመጠበቅ አቅም ስላለው በህመም ወይም ከእድሜ ጋር በተያያዘ ምክንያት ለሚመጣ የመርሳት ችግር እንዳንጋለጥ ይረዳል፡፡
✔ የማይግሬን ህመምን ያስታግሳል
የጥብስ ቅጠልን በሞቀ ውሃ ዉስጥ በመጨመር ለ 10 ደቂቃ መታጠን ማይግሬን ህመምን ያስታግሳል፡፡
✔ የፀረ ባክቴሪያነት ጥቅም
ጥናቶች እንደሚያሣዩት ከሆነ የጥብስ ቅጠል እንደ ጨጓራ ባክቴሪያ (H. pylori) እና ሌሎችንም ይዋጋል፡፡
✔ የአፍ ጠረንን ለማስወገድ
የጥብስ ቅጠል ተፈጥሮአዊ የሆነ የአፍ ጠረን ማስወገጃ ነዉ። ትንሽ የጥብስ ቅጠልን በሞቀ ዉሃ ዉስጥ አድርጎ መጉመጥመጥ መጥፎ ጠረንን ያስወግዳል።
✔ የቆዳ መሸብሸብን ይከላከላል
የጥብስ ቅጠል በተለያዩ የቆዳ ማለስለሻ ክሬሞች ዉስጥ የሚገባ ሲሆን ቆዳን እንዳየሸበሸብ እና ጤናማ እንዲሆን ይረዳል።
✔ በሽታን የመከላከል አቅምን ያዳብራል
የጥብስ ቅጠል በዉስጡ ያለዉ አንቲ ኦክሲደንት፣ አንቲ ኢንፍላማቶሪ እና አንቲ ካርሲኖጄኒክ ንጥረ ነገር የሰዉነታችንን በሽታ የመከላከል አቅምን እንዲዳብር ይረዳል።
በአብዛኛው ጠቀሜታዉ የሚያመዝነው የጥብስ ቅጠል ነፍሰጡር ሴቶች እና የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች ግን በብዛት እንዲወስዱ አይመከርም።
ጤና ይስጥልኝ

The post Health: የጥብስ ቅጠል የጤና ጥቅሞች Health Benefits of Rosemary appeared first on Zehabesha Amharic.

ያሬድ ጥበቡ ይናገራሉ: የኢትዮጵያ አየር መንገድ 85% የሚቀጥረው ትግሬዎችን ነው * አዲሱ ለገሰ ይህን ተቃውመው የቦርድ ሊቀመንበርነቱን ለቀዋል…ሌሎችም

$
0
0

Yared Tibebu zehabeha

(ዘ-ሐበሻ) የቀድሞው የኢህዴን ታጋይ ጌታቸው ጀቤሳ (ያሬድ ጥበቡ) በፌስቡክ ገጻቸው በጻፉት መረጃ አዳዲስ የኢትዮጵያ አየር መንገድን እና የብአዴንን ገመናዎች ለሕዝብ ይፋ አድርገዋል:: ይህ የአቶ ጌታቸው ጀቤሳ (ያሬድ ጥበቡ) ወቅታዊ መረጃ ከአቶ መለስ በኋላ በተለይ ሕወሓት በኢህ አዴግ ውስጥ ነጥሮ ለመውጣት እያደረገ ያለውን ሴራ ያጋለጠ በመሆኑ በፌስቡክ ገጻቸው ያቀረቡትን ዘ-ሐበሻ እንደወረደ እንደሚከተለው አስተናግዳዋለች::

ከቤተ መፃህፍቴ መስኮት ውጪ የማርች አቦ ጥጥ በረዶ ይነሰነሳል ። ጎረቤቴ ውሻዋን ለማናፈስ ወጥታለች ። እኔ እንኳንስ የውጪውን በረዶ የውስጤንም መቋቋሙ ከብዶኛል ። ውስጤን የበረደኝ ያለምክንያት አይደለም ። ትናንትና ማታ አዲስ ከተሰደዱ ወጣቶች ጋር በሲልቨር ስፕሪንጉ የሉሲ ሬስቶራንት ራት እየበላን ሳለ፣ በኢትዮጵያ አየርመንገድ ውስጥ እየተከናወነው ስላለው ዘረኝነት የሰማሁት እንቅልፍ ነስቶኝ አደረ ። እንቅልፍ ባጣ፣ በዚያውም የሰማሁትን ከማምናቸው ምንጮች ለማጣራት፣ ባህርዳር ደውዬ ሃሎ አልኩ ። ማታ የሰማሁትንም አረጋገጥኩ ። ከመለስ ሞት ወዲህ እየተጠናከረ በመጣው የወያኔ ዘረኝነት የተነሳ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 85 በመቶ የሚቀጥረው ትግሬዎችን ብቻ መደረጉንና ፣ ይህንንም የአቶ ተወልደ ወያኔያዊ እርምጃ በመቃወም አዲሱ ለገሰ ከቦርድ ሊቀመንበርነት መልቀቁንና በቦታውም አባዱላ መተካቱ ተነገረኝ ።

ይህ ለምን አስፈለገ? ለሚለው ጥያቄዬም፣ ከመለስ ሞት ወዲህ ላደረባቸው የበታችነት ስሜትና ፍርሃት፣ አማራጭ አድርገው የወሰዱት ወያኔን እንደ ድርጅት ማጠናከር ፣ ከድርጅቱ ተባረው የነበሩትን መመለስ ፣ ትግሬዎችን በሁሉም መንግስታዊ ድርጅቶች የበላይነታቸውን ማረጋገጥና፣ በአይን አውጣነት በስፋት ትግሬዎችን እንዲቀጥሩ ማድረግ ፣ የተያዘው ስልት ይሄ መሆኑን አጫወተኝ ። ከተባረሩት መሃል ለመመለስ በሚደረገው ጥረትም፣ ለምሳሌ የትግራይ ፕሬዚደንት የአቶ አባይ ወልዱ ታላቅ ወንድም የሆኑት አምባሳደር አውአሎም ወልዱ፣ በአቶ መለስ ዘመን የተባረሩ ቢሆንም፣ በቅርቡ የመንግስት ቪላ እንዲሰጣቸው ተደርጓል ። የሚያሳዝነው በቪላው ውስጥ ላለፉት 20 አመታት ነዋሪ የነበሩት አንድ የቀድሞ ረዳት ሚኒስትር በ3 ቀናት ውስጥ ቤቱን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል አለኝ ።

ይሄ ሁሉ ሲሆን ብአዴኖች ምን እያደረጋችሁ ነው ስለው፣ እኛማ የአማራ ክልልን መሬት ለመንጠቅ የሚጋፉንን የትግራይ ክልል ወራሪዎች ስንከራከርና የህዝቡን ቁጣ ለማብረድ ላይ ታች ስንል፣ እነርሱ ፌዴራል መንግስቱን ትግራዋይ የማድረግ ስራቸውን እያፋጠኑ ነወደ አለኝ ። ከወልቃይት ሌላ ምን መሬት ፈለጉ? ብዬ ስጠይቅ፣ “ወልቃይት ትላለህ ጠገዴን አልፈው ሳንጃ እኮ ደርሰዋል ። ችግሩ በጣም ስለተባባሰ፣ ሃይለማርያም ደሳለኝ ራሱ መጥቶ ካድሬዎችን ሰብስቦ እስከማናገር ደርሷል ።

The post ያሬድ ጥበቡ ይናገራሉ: የኢትዮጵያ አየር መንገድ 85% የሚቀጥረው ትግሬዎችን ነው * አዲሱ ለገሰ ይህን ተቃውመው የቦርድ ሊቀመንበርነቱን ለቀዋል… ሌሎችም appeared first on Zehabesha Amharic.

የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ ጭምብል ባጠለቁ ግለሰቦች ተደበደቡ

$
0
0

blue partyበጉጅ ዞን አዶላ ወረዳ ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ለክልል ምክር ቤት በዕጩነት የቀረቡት አቶ ኤልያስ ጣሂር የካቲት 25/2007 ዓ.ም ጭምብል በለበሱ ግለሰቦች ከፍተኛ ድብደባ እንደደረሰባቸው የጉጂ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ አቶ ግርጃ ገቦ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡

በተመሳሳይ የካቲት 21/2007 ዓ.ም ቦረና ዞን ተልተሌ ወረዳ የጤና ጥበቃ ሰራተኛ የሆኑት አቶ ታሪኩ በሀይሉ ‹‹የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ነህ›› በሚል በፖሊሶች ከፍተኛ ድብደባ ከደረሰባቸው በኋላ ለእስር መዳረጋቸውን የቦራ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አቶ ጌታቸው በቀለ ለነገረ ኢትዮጵያ ተገልጾአል፡፡ አቶ ታሪኩ በሀይሉ ስብሰባ ላይ የመብት ጥያቄ ባነሱበት ወቅት በፖሊስ ከስብሰባው እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸው ለእስር መዳረጋቸውን አቶ ጌታቸው ገልጸዋል፡፡

The post የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ ጭምብል ባጠለቁ ግለሰቦች ተደበደቡ appeared first on Zehabesha Amharic.

እጩ ተወዳዳሪዎቻችን እየታሰሩ ናቸው –አምዶም ገብረስላሴ

$
0
0

ኣቶ ብርሃን ንጉስ ተክለዝጊ የተባሉ የዓረና-መድረክ የክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ከነ ሚስታቸውና ታላቅ ልጃቸው ታሰሩ።

ኣቶ ብርሃን ንጉስ ተክለዝጊ በቖላ ተምቤን ወረዳ የወርቃ ኣምባ ምርጫ ክልል ዓረና-መድረክ ወክለው ለክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ሁነው ቀርበዋል።

ይህ እስር የተፈፀመው በወረዳው ኣስተዳዳሪዎች፣ የሃይማኖት ኣባቶች፣ የቅርብ ዘመዶች ከውድድሩ እንዲወጡ የተሞከረው ልመናና ማባበል ሊቀበሉ ባለመቻላቸው ነው።

1545648_786839981400938_395658053806875682_nኣቶ ብርሃን ንጉስ ተኽለዝጊ በቖላ ተምቤን ወረዳ ስምረት ቀበሌ ለበርካታ ዓመታት ዋና ኣስተዳዳሪና የምሊሻ ኮማንደር ሁኖው ኣገልግለዋል። ኣስተዳዳሪ በነበሩበት ወቅት ከፍተኛ የህዝብ ፍቅር ያሳደሩ ሲሆን ከስልጣናቸው ሲወርዱም ያለ ህንዝብ ፍቃድ ከወረዳ የመጣ ትእዛዝ የተደረገ ነበር።

የወረዳው ኣስተዳዳሪዎች “.. ይህ ህዝባዊ ቅቡልነቱ ተጠቅሞ ዓረና-መድረክ እንዲያሸንፍ ያስችለዋል..” የሚል ስጋት በመፍጠሩ በማሳደራቸው በራሳቸው ትእዛዝ ዛሬ ዓርብ 27 / 06 / 2007 ዓ/ምኣቶ ብርሃን ንጉስ ተኽለዝጊ፣ ባለቤቱና ታላቅ ልጁ በጉያ እስር ቤት እንዲታሰር ኣድርገዋል።

የህወሓት መንግስት የመድረክ በኣፅቢ ወንበርታ እጩ ተወዳዳሪ የሆነው ኣቶ ወልደገብርኤል ሃይሉም “..የኣስር ወር እስር ተፈረደብህ..” በማለት ውቕሮ ወህኒ ቤት ማስገባታቸው የሚታወስ ነው።

የመድረክ እጩ ተወዳዳሪዎች እጅግ የከፋ የእስር ዛቻና እንግልት እያደረሱ ያሉ ወረዳዎች ጣንቋ ኣበርገለ፣ እምባ ኣላጀ፣ ኣፅቢ ወንበርታ፣ ቖላ ተምቤን፣ ታሕታይ ማይጨው፣ ዓዲ ግራት ናቸው።

በነዚህ ወረዳ የሚገኙ እጩ ተወዳዳሪዎቻችን ድብደባ፣ እስር፣ ወከባና እንግልት እየደረሰባቸው ይገኛል። እነዚህ ወረዳዎች ግፉ ያበዙት ብለን የገለፅናቸው እንጂ እንደ ደጉዓ ተምቤን የመሰሉ ወረዳዎችም “..ያለ የወረዳ የድጋፍ ደብዳቤት ቅስቀሳ የሚያካሂድ፣ በራሪ ወረቀት የሚያድል ሰው ካገኛቹ እርምጃ ውሰዱበት..” የሚል ትእዛዝ ለሚልሻዎች ያስተላለፉም ኣሉ።
ያሁሉ የምሊሻ የተኩስ ልምምድ ሲያካሂ የከረመው ዓረና-መድረክ ኣባላት ቅስቀሳ ሲያካሂዱ ኣልሞ ለመምታት ታሳቢ ኣድርጎ ነበር ማለት ነው።

በኢትዮዽያ ያለው የይስሙላ ምርጫው በትግራይ ያለው ሁኔታ ግን ጭራሽ የምርጫ ጭላንጭል እንዳይታይ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።

ነፃነታችን በእጃችን ነው..!

IT IS SO..!

The post እጩ ተወዳዳሪዎቻችን እየታሰሩ ናቸው – አምዶም ገብረስላሴ appeared first on Zehabesha Amharic.

አርቲስት ብርሃኑ ተዘራ ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹ወገኔ›› የተሰኘውን ሙዚቃ እንዲቀሰቅስበት ፈቀደ

$
0
0

(ነገረ ኢትዮጵያ) አርቲስት ብርሃኑ ተዘራ በቅርቡ ‹‹ወገኔ›› በሚል ያወጣውን ዜማ ሰማያዊ ፓርቲ ለቅስቀሳ እንዲጠቀምበት መፍቀዱን ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ ገልጾአል፡፡ ኤፍ ኤም 96.3 ሰማያዊ ፓርቲ ለቅስቀሳ በላከው መልዕክት ላይ በማጀቢያነት የተጠቀመበት ሙዚቃ የባለ መብቱን ፈቃድ አላገኘም በሚል የቅስቀሳ መልዕክቱን መመለሱ ይታወሳል፡፡ በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ) የሰማያዊ ፓርቲን የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ‹‹እንደገና አስተካክሎ ካልላከ ለማስተላለፍ እቸገራለሁ›› በሚል መመለሱን ለፓርቲው በፃፈው ደብዳቤ አስታወቀ፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹በ2007 ዓ.ም አዲስ ላወጡት ‹‹ወገኔ›› የተሰኘው ነጠላ ዜማ ያለውን አክብሮት እየገለፀ፣ እርስዎ በስራዎ የገለጹትና ፓርቲውም የሚታገልላት አንድነቷ የተጠበቀላት ኢትዮጵያ እንድትኖር ለሚሰራው ስራ ይጠቀምበት ዘንድ ሙዚቃውን እንዲፈቅዱልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡›› ብሎ በደብዳቤ በጠየቀው መሰረት አርቲስቱ ፓርቲው ‹‹ወገኔ›› የተሰኘውን ዜማ ለቅስቀሳ እንዲጠቀምበት መፍቀዱን ገልጾአል፡፡

አርቲስት ብርሃኑ ተዘራ ለሰማያዊ በፃፈው ደብዳቤ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ‹ወገኔ› የተሰኘውን ሙዚቃዬን ለመጠቀም የጠየቀኝን ፈቃድ በሙሉ ፍላጎቴ መፍቀዴን በፊርማዬ አረጋግጫለሁ፡፡›› ሲል ገልጾአል፡፡

The post አርቲስት ብርሃኑ ተዘራ ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹ወገኔ›› የተሰኘውን ሙዚቃ እንዲቀሰቅስበት ፈቀደ appeared first on Zehabesha Amharic.

ዛሬም ታጥቦ ጭቃ … !!!! ወያኔም የሚፈልገው ይህንን እኮ ነው::

$
0
0

ትላንትና የአንድነት ሃይል ነን ሁላችን ለኢትዮጵያችን ሲሉን የነበረ ስለኦሮሞ ሕዝብ መበደል አቤት ሲባል ኦሮሞ መሆኔን ወደ ኢትዮጵያዊ መሆኔ/ሰው መሆኔ ይቀየር ብለው የሰብዐዊነት ዘመቻዎችን በጥፊ ለማላጋት የተንደረደሩ ኦሮሞ አሊያም ሌላው ብሄር ሲጠራ ጀመሩ ዘረኝነት የሚሉ አተፍታፊዎች ኢትዮጵያ ብለው በስሟ የሚነግዱ ጥቂቶች ዛሬ ላይ አማራው ይደራጅ አሊያም ይገንጠል እያሉ ማራገባቸው የፖለቲካ ስትራቴጂ አይሉት የድል ግብ ምን ያህል ማንነታቸውን ገልጸው እንዳወጡ በይፋ አይተናል::በእምነቶች ዙሪያ የሚደረጉ ትግሎችን ውስጥ ውስጡን ለማክሰም ሲራወጡ ያየናቸው አዛኝ ቂቤ አንጓቾች ድፍርስ የፖለቲካ ባህሪያቸውን አደባባይ ላይ እያስነበቡን መሆኑ ለሽሙጥ ዳርጓቸዋል::

ራሳችንን ወደ አንድነት እንምራ አምባገነኖችን ታግለን ሕዝቦችን እይመራን ነጻ እንውጣ…መስመራችን ለአንዲት ኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያውያን ጥርጊያ እያበጀን እሾህ እና አሜኬላ እየነቀልን ወያኔን ከነግሳንግሱ በጋራ ተባብረል በአንድነት ሃይላችን እናስወግድ የጎሳ ፖለቲካ ከቅኝ ገዢዎች የተወረሰ የመከፋፈያ እና ሕዝቦችን የመርገጫ መሳሪያ ነው እያልን ባለንበት ሰአት እየተወያየን ለትግላችን በምንተባበርበት እና የዳበረ የሰለጠነ ሃሳብ በምናፈልቅበት ወሳኝ ወቅት ላይ የወያኔን የጎሳ ፖለቲካ ልዩ መርዛዊነት ታከን ለመደራጀት ሲከፋም ለመገንተል ማሰባችን የምንሄድበት መንገድ አለማወቅ ብቻ ሳይሆን ከጭቃ ወደ እሾሃማ ሽቃ እያዘነበልል መሆኑን ልንረዳው ግድ ይላል:: ትላንት የአንድነት ሃይል ነን የሚሉ ግሳንግሶች ዛሬን ስለመገንጠል እና ስለ ጎሳዊ መደራጀት ሊሰብኩን ሲሞክሩ ምሞከራቸው ጤነኝነታቸውን እንድንጥራጠር አድርጎናል::

ወያኔ የሚፈልገው እኮ የታገለለትም አላማ እኮ ይህ ነው:: በጎሳ ምከፋፈል ማደራጀት ማስገንጠል ማገነጣጠል በይፋ በፖለቲካ ፕሮግራሙ እና ግልባጩ በሆነው ህገመንግስቱ ላይ በግልጽ ሰፍሮ ከመታየቱም በላይ ከአመት እስከ አመት የሚሰበከው በውጪም በሃገር ውስጥም ለኢትዮጵያውያን የተሰጠው የቤት ስራ ይሕው በጎሳ እንደራጅ ንገንተል የሚለው መርዘኛ ፕሮፓጋንዳ ሲሆን ህዝብንም እየለያየ የሚያፋጀው የሚያፈናቅለው የሚያሰድደው መኖሪያ አሳጥቶ የሚያንከራትተው የሚያሳስረው የሚያስገድለው ወዘተ ይኸው ከይሲ አስተሳሰብ ነው::ኢትዮጵያውያን በጋራ በአንድነት ተያይዘን የወያኔን አምባገነን ዘረኛ መንግስት እናስወግድ ብለን ከዳር እስከዳር እያስተባበርን እየቀሰቀስን ባለንበት ወቅት ላይ አደፍራሽ ሃሳቦችን በማራገብ የወያኔን የቤት ስራ ለመስራት መራወጥ ወንጀለኝነት እና የትግል አደፍራሽነት ቢሆንም የዚህ ሃሳብ ባለቤቶች ሩጫ ወንዝ እንዳማያሻግራቸው እና እንደማይሳካላቸው አስረግጠን ልንነግራቸው ይገባል::የወያኔ መደምሰስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የወያኔ ሃሳቦችን ሆኖ ቦምቦች አብረው የሚከሽፉበት ጊዜ ሩቅ አይደለም:: ድል የሕዝብ ነው::መነጣተል አሊያም መገነጣጠል ብሎም በጎሳ ፖለቲካ መደራጀት የምትሉ እናንተ በፖለቲካ እና በኢኮኖሚ እየተበደለ በገዢዎች አለንጋ ለሚገረፈው ደሃው ወገናችን እዘኑለት::

‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Comment

The post ዛሬም ታጥቦ ጭቃ … !!!! ወያኔም የሚፈልገው ይህንን እኮ ነው:: appeared first on Zehabesha Amharic.

[የቴዎድሮስ አድሃኖም ቅሌት ጉዳይ] “ተበርቼ ሰላም!”አለ ያገሬ ሰዉ…ከ ሳዲቅ አህመድ

$
0
0

tewedros

የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በሶሻል ሚዲያ ላይ እኔን ለቀቅ አርጉ ልጅቱ ያለችዉን ነዉ ያልኩት ለህጻን ንጹህ ህሊና እምነትን መቸር አለብን ሲሉ ያለማቅማማት ተናገሩ። የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ከገቡበት ኪሳራ ለመዉጣት ምጸትን ሲጠቀሙ፥ ምጸትን መጠቀሙ ግድ አለን።

ትንሽ ከቴዲ ጋር እንፎጋገር።

ማረግ፣ክብር፣ፈገግታ፣ጊታር፣መዝፈን፣የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያዉም ዶክተር…አቤት አቤት ያንተ ያለህ (ያ-ሳትር-ያ-ረብ!) http://en.m.wikipedia.org/wiki/Tedros_Adhanom ዶክተር ልጅቱን ለቀቅ ያርጓት::

ይህ ስለ ልጅቱ ሳይሆን የርሶን የወደፊት አገርን የመምራት፣ጠቅላይ ሚኒስቴር የመሆን ብቃት አመላካች ነዉ።እንኳን ደስ አሎት!ሌላዉ ቀርቶ የህወሃት ቁኝጮ የነበሩት ለገሰ ነበር ስማቸዉ? መቼ አላህ ብለዉ ያዉቃሉ? መቼ ኢንሻ አላህ ብለዉ ያዉቃሉ? መቼ ገለቱማ ብለዉ ያዉቃሉ? እንደዉ እርሶ እንደ እርሳቸዉ ጫካ አልገቡም እንጂ የሚመቹ ጠቅላይ ሚኒስቴር ይሆኑ ነበር።

አዩ በህወሃትኛ ስህተት የሚታረመዉ በሌላ ስህተት በመሆኑ ችግር የለዉም።ደግነቱ ማስቀየስ የሚችል የተዋጣለት የፕሮፓጋንዳ ሰዉ የላቹም። ያዉ አትላንታ ቅንድቡን የመሳሰሉ ሰዎች ጥሩ አድርገዉ ደረጃቹን ከፍ ያደርጉታል።ሲዲ አልሽጥም ያለዉ ዘፋኝ በሙሉ መጠጊያ ማግኘቱ የ አርቲስቶቻችን ሞራል ለመጠበቅ አሌ-የማይባል ጠቀሜታ ስላለለዉ ያንድ ወቅት የሲልቨር እስፕሪንግ ሜሪላድ ጎረቤታችን (በከፊል ጀመዓችን) ከሙሴ በትር (አሳ ሙሳ) እስከ ደደቢት የጥበብ ልማትን ማስመዝገቡ እሰየዉ የሚያስብል አይመስሎትምን?

ግን ዶክተር ምን አልባት የጫካዎቹ ህወሃቶች እርሶን ማኖ ለማስነካት ይህንን ገጸባህሪ በፖለቲካ ድርሰት ደርሰዉት ቢሆንስ? ‘ያልጠረጠረ ተመነጠረ!’ ነዉ? ወይስ ከእነ ኦባማ የተኮረጀዉ የሶሽል ሚዲያ አጠቃቀም የዞረ ድምርን አምጥቶ ‘የለመዱት ልማድ ያሳዳል ከማእድ ሆነ ነገሩ?

አንዳንዴ እኮ ስለ እኛ ሳይሆን ስለወለድናቸዉም ልጆች ስንል ክብራችንን እንጠብቃለን።ዉይ!.. ልጆቻችንን አንገት የሚያስደፋ ነገር ምነኛ ከፋ።የተጠቀለሉት ጠቅላይ ሚኒስቴር ቦታዉን ከያዙ በሗላ ዘላለማዊ ክብር ምናምን ብለዉ በመናገራቸዉ በልጆቻቸዉ መተቸታቸዉን ተናግረዋል። ግን ችግር የለዉም ልጆች ከተኙ በሗላ የፌስ ቡክና የትዊተር ዘመቻ ስለሚጀምሩ ምን ችግር አለዉ?

ዶክተር በዲሲዉ ሌላኛዉ ቅንድቡ በኩል ያች የተነፈሷት የጓንታናሞ አስተያየት እርሶ ምነኛ የመጠቁ መሆኖን አመላካች ቢሆንም አንድ በምናምናዊ ሐረካት ያሳያቹት የዲሲ አካባቢ ጋዜጠኛ እርሶ ከመጠቁበት ቦታ መረጃ በሚሉት አዉጫጪኝ አዉርዶ ለመፈጥፈጥ ሳዓታት ነበር የፈጁበት። በልጅቱም ጉዳይ ላይ ለመድገም አስቦ አበበ ገላዉ ስራ ስላቀለለት ትቶታል። እባኮትን ባንዳንድ የድረ-ገጽ አስተያየቶች የሚያደርጉትን ከማድረግ አይቦዝኑ።

እርሶ እኮ የተለያዩትን ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከተቻለ ለማዋሃድ ካልተቻለ በጋራ ጥቅም ተከባብረዉ እንዲኖሩ ለማድረግ… ያሎትን ትስስር በመጠቀም ….ሚና ያሎት ኖት። ግን በጫኮቹ ህወሃቶች መቼ እለት ያገኙት “ኤ”… “ሲ” እናዳይሆን ብዙ በሪቱዎች ከያሉበት ያምጡ። በነገራችን ላይ “ልብ ያለዉ ልብ ይበል!” የሚለዉንም ነገር ይረዱ።ለዛሬ በዚህ ይብቃ።

The post [የቴዎድሮስ አድሃኖም ቅሌት ጉዳይ] “ተበርቼ ሰላም!” አለ ያገሬ ሰዉ… ከ ሳዲቅ አህመድ appeared first on Zehabesha Amharic.


ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፣ አቶ ኤርሚያስ ለገሰና ኢህአዴግ

$
0
0

Ermias Legesseከጀማል ሙሳ

«አክራሪ እስልምና የኢትዮጵያ ክርስትና አስቸጋሪው ፈተና» ብለህ ያዘጋጀኸውን ጥናታዊ ጽሁፍ አዳመጥኩት። አቶ ኤርሚያስ ለገሰ የሰጠህን ምላሽም እንዲሁ አነበብኩት። አንተም «ኤርሚያስ ሆይ!» ብለህ የጻፍከውን ምላሽ አንብቤ እንደጨረስኩ «ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት የመጨረሻ አስተያየት» የሚለውን የኤርሚያስን ጽሁፍም አነበብኩት። ሁሉንም ካነበብኩ በሗላ ግን ባንተ ብቻ ሳይሆን ባገሬ መንግስትም በጣም አዘንኩኝ።

በርግጥ ኤርሚያስ ለገሰ በሰጠህ መልሶች ብዙዎችን የማውቃቸውን እውነታዎች ባገኛቸውም ካንተን ጥናታዊ ፅሁፍና የመልስ ፅሁፎች ግን አንተና የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለኢትዮጵያ ሙስሊም ያላችሁን ትልቅ ጥላቻ ለመገንዘብ ችያለሁ። ያነሳሃቸውን ነጥቦች ስመለከት ከመጀመሪያው ጀምሮ ያቀረብከው ታሪክ ስለቁራአን ፤ስለነጃሽ ፤ስለኢትዮጵያውስጥ እስልምና ፤ለአጼ ሃንስ እለፈት ምክኒያት ሆኑ፤ሞሶሎኒ እንዃን ሳይቀር ለሙስሊም ያደላ ዕንደነበር፤የክርስቲያን ሴቶች ራሱ በሙስሊሞች እንደሚደፈሩ፤የቤተክርስተያን ቅርሶች በሙስሊሞች እንደሚዘረፉ፤ ባጠቃላይ ከድሮ ጀምሮ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ለክርስቲያኖች ፈተና እንደነበሩ፤ወደፊትም ትልቅ ጠላት መሆናቸውን፤በአገሪቱ የሂጃብ መስፋፋት፤ የመስጊዶች ፤የቁርአን ትምህርት ቤቶች ፤ የኢስላማዊ ድርጅቶች ፤የሃጅ እና ዑምራ ተጓዦች፤ኢስላማዊ መፅሃፍትና ሌሎችም የሙስሊሙ እንቅስቃሴ አንተ ከምተፈልገው ቁጥር በላይ መብዛቱ እንዳሳሰበህ ከመግለፅና በሙስሊሙናክርስተያኑ መሃከል ጥላቻን ከመዝራት ባሻገር የገለፅካቸው ሁሉ ነገሮች ከጥናታዊ ፅሁፍነት ወደ ተራ የቡና ወሬነት ያደላሉ።

ጥናታዊ ፅሁፍህ ላይ ያቀረብካቸውን መረጃዎች እንዴት እንዳሰባሰብካቸው የተገለፀ ነገር የለም? ብሎ ኤርሚያስ ለጠየቀህ ጥያቄም መልሱን «ኤርሚያስ ሆይ!» ብለህ በጀመርከው የመልስ ፅሁፍም ፕሮጀክተር ላይ ለሰወች እንዳሳየሃቸው ነገርከን እንጅ ለኛ ልታሳየን ስላልቻለክ ዳታወ ቪዲዮ ወይም አኒሜሽን ሊሆን ይችላል ብየ አልፍሃለሁ፡፡

ጥናታዊ ፅሁፍህን አስመልክቶ ኤርሚያስ ለገሰ ለጠየቀህያቀረብከውን መረጃዎችህን እንዴት እንዳሰባሰብካቸው፤ በጥናታዊ ጵሁፍህ ላይ በአሁን ሰአት ያለውን የኢትየጵያ ሙስሊሞች ” ኢትዬጲያዊነት የተላበሰ፣ ሰላማዊና ፍትሐዊ ጥያቄ” ማንሳት እነዳልፈለክ፤ ለምን አሁን?፣ ምን አዲስ ነገር ተገኝቶ ነው ይሄን ጥያቄ ይዘህ ብቅ እንዳለክ የጠየቀህ ቢሆንም ጽሑፉ ነሐሴ 25 ቀን 1999 ዓም አሜሪካ እንደቀረበ የሚገልፅ ነበር ዳሩ ግን «አክራሪ እስልምና የኢትዮጵያ ክርስትና አስቸጋሪው ፈተና Published on Feb 20, 2015 Deacon Daniel Kibret https://www.youtube.com/watch?v=4u6ItFJeG4A »

50ኛው ደቂቃ 39ኛ ሰከንድ ላይ በ1987 ዓም ከተደረገው ሀገርአቀፍ ቆጠራ በሗላ የአምና በ2006ጥናትህን የኢቶጵያን ህዝብ በክልሎች ከፍለህ ስታበራራ ነበር፡፡ጥናቱ የቀረበው በ1999 ዓም፣ አንተ ጥያቄውን ያነሣኸው ደግሞ በ2007 ነው ብለህ ኤርማስን መቸ እነደቀረበ ሳያጣራ ብለህ ከመወንጀልህ በፊት ከላይ በተጠቀሰው ደቂቃና ሰከንድ እንደገለፅከው 2006ን አምና እያለክ ኤየገለፅክ «ስሜ ነው እንጂ እኔኮ ነቢይ አይደለሁም» እያለክ በማፌዝ ኤርሚያስን ለመዝለፍና ለመወንጀል ሞከረሃል ለመሆኑ የትኛውን 2006 ይሆን ፅሁፍህ ላይ «አምና2006» ብለህ የምትጠራው የፈረንጆችን እንዳልል «በ1987 ዓም ከተደረገው ሀገርአቀፍ ቆጠራ » ብለህ ከጠራህ በኋላ ስለሆነ 2006 ዓ.ምን ያበራራሀው ይሄንንም እዛው ፐሮጀክተሩ ላይ ይሆን ምናገኘው እንደዛ ከሆነ የፕሮጀክተሩ ማሳያ ብትር በተረ-ሙሴ መሆነ አለበት።

አንተና የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለኢትዮጵያ ሙስሊም ያላችሁን ትልቅ ጥላቻ በድጋሚ ለመገንዘብ ችያለሁ አንተ (በ2000 ዓም ጥናቱን ካቀረብኩት በኋላ ነው ‹ሽመልስ ከማል ሠራው› ያልከው ጥናት ለመንግሥት የቀረበው፡፡ ያ ጥናት ለመንግሥት አካላት ሳይለዋወጥ መቅረቡን በወፍ በረር እናውቅ ነበር፡፡ ስለዚህም የተከተለ ከቀደመ ይወስዳል እንጂ የቀደመ ከተከተለ አይወስድምና ‹ቃላት ሳይቀየሩ የቀረበው› እኔ ያቀረብኩት ጽሑፍ እንጂ በእናንተ ስብሰባ ላይ የቀረበው ጽሑፍ ወደ እኔ መጥቶ ሊሆን አይችልም ) ስትለን
ኤርሚያስ ደሞ በጥናቱ ውስጥ ያሉትን መረጃዎች እንደወረደ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማው በ2001 አም ከሽመልስ ከማል ነበር ፤ከግማሽ በላይ የአንተ ዶክመንት አባሪ እነደረገበት፤ ከአራት ሚሊዬን በላይ በሆኑ የኢህአዴግ አባላት ውይይት እንደረገበት እነደተቃወሙት ይገልፅልናል።

በስተመጨረሻ ወደ ዋናው ቁም ነገር ስመጣ ግን አነተም ቀደምክ ኢህአዴግ የሁለታችሁም ጥናታዊ ፅሁፍ ተብሎ የቀረበው ከጭፍን የሙስሊም ጥላቻ የመነጨና ኢስላምን የማጥፋት ድብቅ አጀንዳውን ከነማን ጋር አሲሮ የተነሳ ፤በአክራሪነት ስም ሆን ተብሎ ክርስቲያንና ሙስሊሙን ለማጋጨት የታቀደ መሆኑና የሙስሊሙና እርስቲያኑ አንድ መሆን እነደእግር እሳት የሚያቃጥላቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች እነዳሉ ለማንም የተደበቀ አደለም ሆኖም እነዚህ ራሳቸውን እነደ ፀረ-አሸባሪ የሚያዩ አክራሪ ፀረ-ሰላሞች ሰላማዊ ዜጋን በማን አለብንነት የአሸባሪ ስም በመለጠፍ በየወህኒ ቤቱ በማጎርና በማሰቃየት ለታሪክ አስነዋሪ ለነገዋ ኢትዮጵያም የሚያሳፍረና የሚያወቃቅስ እየሰራችሁ የነፃነትን ትረጉም ሳታውቁ ራስን የነፃነት አረጎ ልደቴን አክብሩልኝ እያሉ መቀባጠር የረከሰ ፖለቲካ ነው።

የጥናት አቅራቢዎችም የጥላቻና እነቶፈንቶ ወሬ በመያዝ ከፀረ-ኢስላም የመንግስት ባለስልታናት ጋር ወግኖ የህዝበ ሙስሊሙን ደም መፍሰስ፣መሰቃየትና በእስር መማቀቅ ከማሴር ይልቅ ሃይማኖት በሚያዘው መልኩ በፍቅር፣በሰላም፣በመተዛዘን፣በመከባበር፣በመቻቻል ብትሰበኩ በፈጣሪ ዘንድ የተወደደና የተቀደሰ ደግ ሃሳብ ነው። ለሰው ደግ ሆናችሁ ስለደግነት ብታወሩና ብተሸልሙ ኢትዮጳ ውስጥ የምታዘጋጁት«የአመቱ ደግ ሰው» የተሰኘው አመታዊ ሽልማት በአለምአቀፍ ደረጃ አሳድጎ ሽልማቱ ቅድሚያ ለናነት በተገባችሁ ነበር።

The post ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፣ አቶ ኤርሚያስ ለገሰና ኢህአዴግ appeared first on Zehabesha Amharic.

አቶ ቶውድሮስ አድሃኖም ሂሳቸውን ሊወጡ ነው! እናበረታታቸው እስቲ…ይዋጡ…. አይዝዎ.. (አቤ ቶኮቻው)

$
0
0

አቶ ቶውድሮስ አድሃኖም ሂሳቸውን ሊወጡ ነው! እናበረታታቸው እስቲ… ይዋጡ…. አይዝዎ…. ዋሽቻለሁ፣ ቀጥፌያለሁ…. ይበሉን መቅጠፉም መዋሸቱም ዛሬ የተጀመረ አይደለም።
ይልቅ በነካ እጅዎ… ልጅቷን ወደ ትምህርት ቤትዎ ይመልሷት፣ ትምህርቷን ጥላ የመንግስት ፕሮፖጋንዳ ሰለባ መሆኗ ነውር ነው። የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ ይቁም! … ለመሆኑ መንግስት ለጋራ ሙለታ ህዝቦች የሚሆን በጀት እንዴት አጣ! ? የመንግስት ዋና ሃላፊነት እኮ ልክ ማስገባት ሳይሆን ልጆችን ትምህርት ቤት ማስገባት ነው!

እነሆ አቶ ቴውድሮስ… የ ሃያ ሚሊዮኑን ጉዳይ በበሪቱ ላይ ሲያሳብቡ!

11015071_902189619825781_2601891041881579942_n

11015071_902189619825781_2601891041881579942_n

The post አቶ ቶውድሮስ አድሃኖም ሂሳቸውን ሊወጡ ነው! እናበረታታቸው እስቲ… ይዋጡ…. አይዝዎ.. (አቤ ቶኮቻው) appeared first on Zehabesha Amharic.

አዲሱ የወያኔ ዘመቻ!

$
0
0

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

Amsaluበመጽሐፈ ገጽ (በፌስ ቡክ) ጓደኝነት ጥቂት የማልላቸው የኢትዮጵያዊነትን የሀገር የወገን የማንነት የቅርስ ተቆርቋሪነትን ስሜት የተላበሱ የሚያስቀናና የሚንቀለቀል ወኔ የተሞሉ እኅቶች ወንድሞች የመጽሐፈ ገጽ ጓደኝነት እየጠየቁኝ እየተቀበልኳቸው በተቻለኝ መጠንም እያበረታታሁ በጉድኝነታችንን እስከአሁን ቀጥለን ነበር፡፡ ለካ እነኝህ ኢትዮጵያዊነትን የተላበሱና ወኔ የተሞሉ ቁጭት የሚበላቸው እያልኩ የማወድሳቸውና የተቻለኝን ያህልም ሳበረታታቸው የነበሩ ወንድሞችና እኅቶች ወያኔዎች ያሁሉ ስሜትና ተቆርቋሪነታቸውም ጭንብል ወይም ሽፋን ኖሯል ለካ ሰሞኑን እነኝህ ሰዎች በዘመቻ በየአቅጣጫው “ከአሁን በኋላ አማራ ስለ ራሱ ብቻ ማሰብ ይኖርበታል፣ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ ስለራሱ ማሰብ ትቶ ለ80 ምናምን ብሔረሰብ ሁሉ ማሰብ ለድንበር መበላሸት አለመበላሸት ማሰብ የለበትም፣ አሁን 30 ምናምን ሚሊዬን አማራ ሕዝብ እስከ መኖሩም ለተዘነጋው በችግር በዘረኝነት በረሀብ በሥደት አለንጋ ለሚገረፈው የራሡ ቤተሰብ ብቻ ማሰብ መቻል አለበት፣ ሀገር ማንነት ምናምን እያለ የራሱን ህልውና አደጋ ላይ መጣል የለበትም” ከማለትም አልፈው ካርታ ሠርተው ጎንደር ጎጃም ወሎንና ሸዋን አካለው “መገንጠል ይኖርብናል” በማለት መገኝጠልን በማቀንቀን የምትገነጠለዋንም ሀገር “አማራ፣ ቤተ አማራ፣ አቢሲኒያ፣ ኢትዮጵያ፣ ግዮን” የሚሉ ስሞችን ለምርጫ አቅርበዋል፡፡ ስለ ወደብ አገልግሎት ጥያቄ ሲመልሱም “እኛ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሀገር ድንበር ማንነት ምንትስ የሚለውን ትተን እራሳችንን ብቻ ካሰብን በራሳችን ጉዳይ ላይ ብቻ ካተኮርን ከሌሎች ጋር ሰላም ስለምንሆን የወደብ አገልግሎትን በጎንደር በኩል ከኤርትራ ማግኘት እንችላለን” ይላሉ፡፡ አንዳንድ ወገኖችንም ይሄ ሴራ የወያኔ መሆኑን ካለማወቅና የጨነቃቸው ወገኖች ያቀረቡት ሐሳብ መስሏቸው ለመደገፍ የዳዳቸው ሁሉ ነበሩ፡፡ ለአንደኛው ምን አልኩት፡-
ወንድሜ ምን ነካህ? ምን ሆንክ? ይሄ እኮ ተሸናፊነት ነው እጅ መስጠት እኮ ነው፡፡ እስኪ አሁን አንተን ከወያኔ ምን እንደሚለይህ ንገረኝ? ኢትዮጵያን ስለተውክ እንዴት ነው እራስህን ልታድን የምትችለው? ውጊያው እኮ አማራ ኢትዮጵያን እስኪተው እስኪጥል ማንነቱን ማለትም አማራነቱን እስኪክድ ድረስ ብቻ ሳይሆን ጨርሶ ዘሩ እስኪጠፋ ድረስ እኮ ነው፡፡ ምን ነው ሲበዛ የዋህ ሆንክብኝ? የትኛውንስ ክፍል ነው የምትገነጥለው? ወያኔ ከጎንደር ከጎጃም ከወሎ ውስጥ አገዎችን ቅማንቶችንና ሌሎች ወገኖችን እያነሣሣ ምን እንዲሉ እያደረገ እንደሆነ አታውቅም? ይሄ አስተሳሰብ የመጨረሻዎቹ የደናቁርቱ የድንቁርና የድንቁርና ብቻም ሳይሆን የጠላትነት አስተሳሰብ ነው የኢትዮጵያ ጠላት አስተሳሰብ፡፡ አንድነት ወይም የኢትዮጵያ ህልውና በምንም ተአምር ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም፡፡ ለሱም እንደ እናት አባቶቻችን ሁሉ የማንከፍለው የመሥዋዕተነት ዓይነት ሊኖር አይገባም፡፡ የኢትዮጵያ ነፍስ ያለው በአንድነቷ ውስጥ ነው አንድነቷ ከፈረሰ በድን ትሆናለች ትሞታለች፡፡ ኢትዮጵያ ከሞተች በኋላ ደናቁርቱና የጠላት ቅጥረኞች ይመስላቸዋል እንጅ በየትኛውም የፈራረሰ አካሏ ላይ ሰው መኖር የሚችልበት ዕድልና ሁኔታ አይኖርም፡፡ ለኢትዮጵያ መፈራረስ ተባባሪ የሆነ ሰው የሚጠየቀው በታሪክ ፊት ብቻ ሳይሆን በቅዱስ ቃሉ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ ከ70 ጊዜያት በላይ በክብር በፍቅር በሞገስ በሚጠራት በእግዚአብሔር ፊትም ነው፡፡ ለኢትዮጵያ (ለእግዚአብሔር ሀገር) ጠላት መሆን ያስኮንናልና ተጠንቀቅ፡፡ አልኩት፡፡
ብቻ ምን አለፋቹህ በመጽሐፈ ገጽ ሰሞኑን እያያቹህት እንዳላቹህት ይህ ዘመቻ እንደኛ ናቸው ብለን እናስባቸው በነበሩ አሁን ግን ባልጠበቅነው መንገድ በራሳቸው ጊዜ ማንነታቸውን በገለጡት በወያኔ ካድሬዎች በሰፊው የተያዘ ዘመቻ ሆኗልና እንዳትሳሳቱ እንዳትሰናከሉ ማስጠንቀቅ እወዳለሁ፡፡ ይህ ዘዴ ወያኔ እስከዛሬ የያዘው የአማራን ብሔራዊና የባለአደራነት ስሜት ለማጥፋት የደከመው ድካም በፈለገው ፍጥነትና መጠን ውጤት እንዳላመጣለትና ብዙም ውጤታማ እንደማያደርገው ካወቀ በኋላ አዲስ የቀየሰው ስልት ነው፡፡ ነገር ግን በእኔ እምነት ይሄ የወያኔ አዲሱ የኢትዮጵያዊነትንና የባለአደራነትን ስሜት ከአማራ የማጥፋትና ሀገሪቱን ባለቤት ባለአደራ ተቆርቋሪ የማሳጣት እኩይና ሰይጣናዊ ዘመቻ እንደቀደመውና ሲሠራበት እንደቆየው ዘመቻው ሁሉ ይከሽፋል እንጅ ይሠራለታል ብየ አላስብም፡፡ ወያኔ የኢትዮጵያዊነትን ስሜት ከሌሎቹ ብሔረሰቦች በተሳካ መልኩ አጥፍቻለሁ ብሎ ያስባል የቀረኝና ያቃተኝ አማራ ብቻ ነው ብሎ ያስባል፡፡ መስሎት እንጅ የኢትዮጵያዊነትን ስሜት ከኢትዮጵያዊያን አጠፋለሁ ማለት ቅዠት ነው፡፡ ከደሙ ጋር ተቀላቅሎ ያለ ነውና፡፡

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

The post አዲሱ የወያኔ ዘመቻ! appeared first on Zehabesha Amharic.

አንድነት ፓርቲና ውለታው –ከሃቅ ማህደር። –ከሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 08.03.2015 /ሲዊዘርላንድ ዙሪክ/

Womansday

የ2015 ዓለምዓቀፍ ሴቶችን ቀን እኔ በግሌ ዕለቱን ያሰብኩትን መጠነ ሰፊ አቅም ዬነበረውን በወንበዴው በወያኔ ትእቢት በቀላጤ የፈረሰውን የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲን፤ እስረኛዋን እናት ሀገሬን፤ እስረኛ እህትና ወንድሞቼን፤ በራህብ – በመፈናቀል ሰቆቃ ላይ ያሉ ወገኖቼን አስቤ ነበር። አንድነት ፓርቲ ዬብሄራዊነት ምንጩ ከቅንጅት መንፈስ የተነሳ ብቻ ሳይሆን የሴቶችን አቅም ያዳመጠ በኽረ ፓርቲ በመሆኑም ጭምር ነው።

አንድነት ለእኛ  ትውልድ፤ እኛ ለተፈጠርንበት ትውልድ፤ የመጀመሪያዋን ሴት የፓርቲ መሪ ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳን በብሄራዊ ደረጃ እንድትመራ፤ እንድታስተባብር የፈቀደ ብቸኛው ፓርቲ ነው። አንጋፋነቱን ሆነ የትውልድ ልዑቅ ፓርቲ መሆኑን ማመሳከር የሚችለው ሃቅም ይኼው ነው። የሴቶችን አቅም ፍሰት በዚህ ዙሪያ ቆጥቦልናል።  ለአንድነት ፓርቲ ስለ ሴቶች የማድረግ ሙሉ አቅምና ሥጦታ ቅስቀሳ አያስፈልገውም ነበር። ዛሬ አንድነት የለም። አፍርሰዉታል። ንደውታል፤ ዘርፈውታል፤ መንፈሱን ቀምተውታል፤ ብቃቱን አራቁተውታል። እንዲህ እንደ ሚታየው ፎቶ ዕንባችን ከውስጥ ሞልቶ ውጩንም አርሶታል። የምር መራራ ቀን ነበር ….

እኔ የአንድነት መፍረስ የሰማሁ ዕለት ሰውነቴ ተቆረሰ፤ መንፈሴ ተናዳ፤ ህሊናዬ ቆሰለ። አንድ ብሄራዊ ፓርቲ ፈቃድ ተሰጥቶት ከተደራጀ በኋላ፤ ጊዜውን፣ አቅሙን፤ ጉልበቱን አፍስሶ ከሁሉ በላይ መሪዎቹን በተለያዬ ጊዜ ለካቴና – ለስለት፤ ለድብደባ – ለመደፈር ሰውቶ እንዲህ መስዋዕትነቱን ሁሉ መና በማደረግ ሲፈርስ ማዬት ከዚህ የበለጠ የሃዘን ቀን አልነበረም ለእኔ። ሁላችሁም እንደምታውቁት 90 ሚሊዮን ህዝብ ልሰደድ ቢል አይችልም፤ ጫካ ልግባ ቢልም እንዲሁ፤ ስለሆነም ነበር አንድነት አቅሙ የፈቀደውን የህዝብ አንጡራ ፍላጎት መርሁ በማድረግ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ከባርነት ለመላቀቅ፤ ቀጥሎም ዴሞክራሲን ለማስፈን ትግል ማደረግ ግድ ይለው ስለነበር አብዝቶ መስዋዕትነቱን የተቀበለ።

ሰላማዊ በሆነ መንገድ የታገሉ መሪዎቹ ሲታሰሩበት አዲስ በመምረጥ፤ ሲደበደቡበት በመንፈስ ከጎናቸው በመሆን፤ ሲሳደዱበት በማበረታታ፤ በሆደ ሰፊነት የአመራር ተካታታይነቱ በወያኔ ጣልቃ ገብነት ባልተቋረጠ ሁኔታ ቢደፈርስበትም ሳይታክት እርግብን አምኖ፣ ዘንባባን ተደግፎ ብዙ በጣም ብዙ ጥረት አድርጓል። ይቻላል – ይቻላል ይቻላል እያለ …. ጣረ ታገለ ታተረ …. ግን …. ሞት ተበዬነበት።

ከሁሉ በላይ ለእኔ መንፈስ እጅግ ቅርብ የሆነው የአንድነት ጉዳይ የኢትዮጵያ ሴቶችን ልዩ ብልህ አቅም ዕውቅና የሰጠ ብቸኛው ብሄራዊ ፓርቲ መሆኑ ነበር። 40 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ፓርቲዎች ሁሉ ያለደረጉትን ነገር ነበር አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ደፍሮ ያደረገው። በሌላ በኩልም አስተውላችሁት ከሆነ የአውሮፓ ኮሚሽን ዕንባችን የተጋራው ወላዊ የነፃነት ትግል ብርቱ ዕውቅና ዓርማው ሴት ነበረች። ክብርት ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ። ጋዜጠኛ ርዕዮትም የአንድነት ፓርቲ የምክር ቤት አባል ነበረች። ምንም እንኳን ከተገለሉት ውስጥ የነበረች ብትሆንም መነሻ ቤቷ አንድነት ነው። የእውነት መጨረሻው እውነት ነውና እውነተኞች ነጥረው አሁንም ጥቃት ስፈጸምባቸው ክብርት ጋዜጠኛ ርዕዮትና ሌሎች ቀደምት የአንድነት መሪዎች የተገለሉበት ሃቅ ዘመን ሰጠው።

40 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ፓርቲዎች ወይንም 23 ዓመት ዕድሜ ያላቸው የጎሳ ድርጅቶች አንድ ዓለም ዓቀፍ ዕውቅና ያላት ሴት ወይንም መሪ ወይንም ጋዜጠኛ አላፈሩም። አንድነት ግን አለው። በእኛ የሴቶች ታሪክ ውስጥ ልዩ ማህደረ – ዝክረ ነው። የአንድነት ሚስጢር ያለው ከዚህ ላይ ነው። አንድነት የመጀመሪያ የህይወት ትምህርት ቤት የሆነችውን እናት – ሴት – እህት – ሚስት – ጓደኛን፤ ጸጋ አልተላለፈም። ይህን ሃቅ የደፈረ- ያስተማረ – በተግባር አንድነት ብቻ ነው። ሴት እኔን ትምራኝ ብሎ መፍቀድ ከውሳኔዎቹ ሁሉ እጅግ ፈታኙ ነው። ይህን ጀርመኖችም ሲዊዞችም አድርገውታል። ውጤቱንም አዬተውታል።

ስለሆነም የኢትዮጵያ ሴቶች አትኩሮት፤ አክብሮት፤ ልቅና የሰጣቸውን ፓርቲያቸውን በማንለኝበት ወያኔ በቁሙ ሲያፈርስባቸው መቆጣት አለባቸው፤ መበሳጨት አለባቸው፤ ስለምን? ብለው መንገብገብ አለባቸው፤ ጉዳያችን ነው ብለው በባለቤትነት ስሜት ፊት ለፊት ወጥተው በሰላማዊ መንገድ ተራጋጩን የወያኔ ሃርነት ትግራይን ማንፌስቶ አስፈጻሚዎች መጠዬቅ አለባቻው። ትእቢተኛውን የጎሳ ድርጅት መልስ እንዲሰጣቸው በተከታታይነት መጠዬቅ አለባቸው።

ቢያንስ የትዕቢተኛውን ትብትብ መንፈስ ክፍተት ከውስጡ መፍጠር አለባቸው። ንፋስ አብጠልጥሎ አናቱን እንዲፈርሰው ተግተው መጠዬቅ አለባቸው። በፌስ ቡክ፣ በቲተር፣ ወይ በጉጉል ወይ በግልጽ ደብዳቤ ሊሆን ይችላል። እርግጥ የብሄራዊ ነፃነት መፍጫው የምርጫው ክፍለ ጊዜ ሲያልፍ የሚኖር አዲስ የድብብቆሽ ትወና ሊኖር ይችላል። የሆነ ሆኖ ለዘለቄታ – ከባርነት ወደ ነፃነት፤ ከጭቆና ወደ ዴሞክራሲ መሸጋገር ብቻ ሳይሆን የሴቶችን የመሆን አቅም በእኩልነት እስኪሰፍን ድረስ መትጋት ግድ ይላል። የአንድ ሀገር ዴሞክራሲ መጠን የሚለካው ለሴቶች ከሚሰጠው ዕውቅና ስፋትና ጥበት ይወሰናልና።

እኛ እንዳለፍነበት ዘመን የኢትዮጵያሴቶች አቅም መባከን ወይንም ከከርሰ ምድር ውስጥ እንዳለ ሃብት አፈር ለብሶ መቅረት የለበትም። አዲሱ ትውልድ ሴቶች ከወንዶች ጋር ተወዳድረው በሴትነታቸው ሳይሆን በመጠነ ሰፊ ብቃታቸው፤ በእናታዊ ጸጋቸው፤ በድርጁው መንፈሳቸው፤ በሚስትነት ስጦታቸው፤ በመምህርነት ክህሎታቸው፤ በማህበራዊነት መክሊታቸው ማሸነፍ አለባቸው። ዘመኑንም – መምራት። የእኔ ህልምና ናፍቆት ዬአፍሪካ አንድነት ድርጅት፤ የተባባሩት መንግሥታት ድርጅት፤ የአውሮፓ ኮሚሽን አሜሪካን ጨምሮ የበርካታ ሀገሮች መሪዎች ሴቶች እንዲሆኑ ነው። ከሴቶች ውስጥ ያለውን ሚስጢር ማንም ፈላስፋ ወይንም ሳይንቲስት ተመራምሮ እስካሁን አልደረሰበትም። ለነገሩ በሴቶች የብቃት ልክ ምን የምርምር ሥራ ተሰርቶ በፍጹም ሁኔታ የተዘለለ አምክንዮ ክስተትም ነው። ሴቶች ፍቅር ናቸው። ፍቅር ደግሞ ሁሉንም ነው መሬት ….

ኢትዮጵያ ሀገራችን በነገው የሴቶች ዓለም ትደምቅ ዘንድ፤ ተጠቃሚ ትሆን ዘንድ፤ ሴቶች ዛሬን አብረው መሆን አለባቸው ነገን ለማግኘት። ግፊያው አለ፤ ግን ስልቱም ስላለ ማሸነፍ ይችላሉ – አይበገሬነት ከጠጡ፤

ሰሞናቱን ጀርመኖች በሁሉም ፓርቲዎቻቸው ጉልህ አጀንዳው በሴቶች እኩል ተሳትፎና ውጤት ግምገማ ላይ ነበሩ። ለዛውም በተመጠነ የቁጥር ተዋፆ በአኩልነት ላይ የተመሰረተ ተሰትፎ ባለበት ሀገር … እኔ ንጉሥ ዳዊት „የቤትህ ቅናት በላኝ“ እንዳለው ነበር ያደረገኝ ….

ወደ ኢትዮጵያ ጎራ ሲባል ደግሞ የትውልድ ፈርጦች የነገ ፍሬዎች „ነፃነት“ ባሉ የጣይቱ ልጆች ባለፈው ዓመት ምን እንደደረሳባቸው ይታወቃል። ዱላ፤ እስር …. መደፈረ ….  የዓለም ሴቶች የ2014 ቀናቸውን በፍሰሃና በደስታ ሲያሳልፉ የኢትዮጵያ ሴቶች ደግሞ በወያኔ ርግጫና ፍጥጫ ….

የብሎገር ጸሐፍት ታታሪዎች እንዲሁም የድምጻችን ይሰማ የካሜራ ታታሪ ሴት እህታችንም ጨምሮ ሊበረታቱ፣ ሊደነቁ፣ ሊደገፉ፣ ሊሸለሙ ሲገባቸው፤ በተመሳሳይ ሁኔታ የደረሰባቸው ፍዳና መከራ ነው። በጥቅሉ ዕለቱን ኢትዮጵያ ላይ ሲታሰብ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ዘር ተከል ጨለማዊ አገዛዝ ተወግዶ፤ በልቡ የታበዬው ገዢ ፓርቲ ተወግዶ፤ አቅማችን – ችሎታችን፤ ሊደመጥ የሚችልበት ሥርዓትን መናፈቅ፤ ለናፍቆት „በቃንን“ ማስታጠቅ አንገብጋቢው መስመራችን ሊሆን ይገባል።

በተረፈ „በድምጻችን ይሰማ“ ያለው ጉልበታም እንቅስቃሴ ሆነ ጉልህ ድንቅ የሴቶች ተሳትፎ ለዛላቂ የነፃነት ትግል ከሚደረገው ጋር አቀናጅቶ የሴቶችን ሰማያዊ ሚስጢር ኢትዮጵያ ላይ ጥቅም ላይ ለመዋል – እንትጋ። እግዚአብሄር አምላክ ለአፈራችን ያብቃን አሜን! እግዚአብሄር ይስጥልኝ ዘሃበሻ ማህበራዊ ድህረ ገጽ። ለሰጣችሁኝ የማያልቅ ጣፋጭ የብዕር እኩልነት ነፃነት ምልክቴ ናችሁ – ኑሩልኝ። አድማጪዎቼም – ኑሩልኝ!

 

ሴት የአቅም ፈላስፋ ናት!

ዓለም ዓቀፍ ሴቶች ቀን የካቲት 29 ለዘለዓለም ይኑር! ….

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 

The post አንድነት ፓርቲና ውለታው – ከሃቅ ማህደር። – ከሥርጉተ ሥላሴ appeared first on Zehabesha Amharic.

(ዜና ፎቶ) መርካቶ አካባቢ ያሉ ወጣቶች አዛውንቶችን እና የአእምሮ ህመም ያለባቸው የጎዳና ተዳዳሪዎችን ገላቸውን ሲያጥቡና ጸጉራቸውን ሲላጩ ዋሉ

$
0
0

የዘ-ሐበሻ ወዳጅ ከአዲስ አበባ የላከው ፎቶ ነው:: ጸሐፊው የመንግስት ባለስልጣናት ቀይ ቀረባት አስረው በአደባባይ ሲዋሹ ወገን ለወገኑ እንዲህ ያደርጋል ሲሉ ፎቶውን ልከውልናል:: ዛሬ ከጠዋቱ 4 ሰዓት አካባቢ አዲስ አበባ አንዋር መስጊድ አካባቢ የሚገኘው ቶታል አጠገብ ወጣቶች በአካባቢው የአእምሮ ህመም ያለባቸውንና በእድሜ የገፉ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ገላቸውን ሲያጥቡ እና ጸጉራቸውን ሲላጩላቸው ውለዋል:: ይህን ደስ የሚል በጎ ተግባር ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎች እንዲደርስ ፎቶውን የላከልን ወዳጃችን “መንግስት ከዚህ ምን ይማራል?” ሲል ይጠይቃል::
addis ababa

merkato addis ababa copy

The post (ዜና ፎቶ) መርካቶ አካባቢ ያሉ ወጣቶች አዛውንቶችን እና የአእምሮ ህመም ያለባቸው የጎዳና ተዳዳሪዎችን ገላቸውን ሲያጥቡና ጸጉራቸውን ሲላጩ ዋሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢሕአዴግኣዊ ዴሞክራሲ እና ሊብራሊዝም – ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ

$
0
0

አዲስ አድማስ ጋዜጣ ቅፅ 15 ቁጥር 789፣ የካቲት 28 ቀን 2007 ዓ.ም)

መግቢያ

ኢሕአዴግ፣ የዐፄውን ሥርዐት ርዝራዥና የደርግን አስከፊ ሥርዐት አፈራርሼ አገሪቱን በተሻለ የዴሞክራሲ ጎዳና እየመራኹ ነው በማለት ያለመታከት እያበሠረና እየወተወተ ይገኛል። ካለፈው ሥርዐት አላቅቄኣችኋለኹ የሚለው የራሱ እውነታ ቢኖረውም፣ በአንጻሩ ግን ኢሕአዴግ ራሱ የሚያበጅልን ዐዲስ ቀንበር መልክ አውጥቶ ዐደባባይ ወጥቶ መታየቱ አልቀረም፡፡ ያረጀውን አገዛዝ በዐዲስ አሠራር ከሚጭንብን ከዚኽ ዐይነቱ ቀንበር መላቀቅ የኢሕአዴግ ችግር ሳይኾን፣ የእኛ የአገሪቱ ዜጎች ችግር እና የቤት ሥራ መኾኑን መረዳት ይኖርብናል።
የዚኽ መጣጥፍ ቀዳሚ ዓላማ÷ ከኹለት ዐሥርት ዓመታት በላይ የቆየው የኢሕአዴግ አገዛዝ ከዴሞክራሲ፣ ከዜጎች ነጻነትና መብት አኳያ ምን ዐይነት መንገድ ይዞ እየኼደ እንደኾነና ኢሕአዴግ በጥቂቱም ቢኾን ከጀመረው የዴሞክራሲ መንገድ ስቶ የኋላ ኋላ ራሱን ወደ ኢ-ዴሞክራሲ አገዛዝ እንደምን እንደቀለበሰ በተወሰነ መልኩ ለማሳየት ነው። መጣጥፉ በሦስት ንኡሳን ርእሶች የተከፈለ ነው፡፡ በክፍል አንድ፣ የዴሞክራሲ እና የሊብራሊዝም ፅንሰ ሐሳቦችን ከአገራችን ኹኔታ ጋራ በማያያዝ የመንደርደሪያ ሐሳብ እሰጣለኹ። በክፍል ኹለት፣ በሰው ልጆች የቅርብ ታሪክ ውስጥ ዴሞክራሲ እና ነጻነት ለመጎናጸፍ ይበጃሉ የሚባሉት ተቋማት÷ ለምሳሌ፣ እንደ ፓርላማ፣ የፍትሕና የሚዲያ፣ የመድበለ ፓርቲና የምርጫ ሥርዐት እንዲኹም ሲቪል ማኅበራትን ኢሕአዴግ እንደምን መንፈሳቸውን ቀይሮ የራሱ የፖለቲካ መገልገያ እንዳደረጋቸው፤ የምርጫ ሥርዐቱን በምሳሌነት በማንሣት ሐተታና ትችቴን አቀርባለኹ። በክፍል ሦስት፣ በአገራችን የፖለቲካ ሕይወት ውስጥ የሚገኘውን አፍራሽ የኾነ የፍትሕ አቀራረብ በማሳየትና በመጨረሻም፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ዐጭር ማስታወሻ በማኖር መጣጥፉን እቋጫለኹ።
dr dagnachew Assefa
፩. የዴሞክራሲ እና የሊበራሊዝም ነገር

እንደ ዕውቁ የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ምሁር ሳሙኤል ፒ. ሃንቲንግተን እይታ፣ በቅርብ የሰው ልጅ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ በተለያዩ ጊዜዎች ሦስት የዴሞክራሲ ሞገዶች ተከሥተዋል። ከፍጹማዊ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት የተደረጉትን ሽግግሮች ምሁሩ በሞገድ አምሳል ያቀርቧቸዋል። እንደእርሳቸው ትረካ፣ የመጀመሪያው ሞገድ ከፈረንሳይና ከአሜሪካ ዐብዮት በኋላ በ19ኛው ምእት መባቻ የተነሣው ሲኾን ተከታዩ ደግሞ ከኹለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በብዙ አገሮች ውስጥ የታየው ነው፤ ሦስተኛው ደግሞ ከ1974 እስከ 1990 (እ. አ. አ.) ሠላሳ ያኽል አገሮች ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት የተሸጋገሩበት ነው፤ ምሁሩ ይህን የሽግግር ወቅት “ሦስተኛው የዴሞክራሲ ሞገድ” የሚል ስያሜ ሰጥተውታል።
ከሦስተኛው ሞገድ በኋላ ግን ሒደቱ የዴሞክራሲ ልምላሜን እያጠወለገ፣ በአንዳንድ አገሮች ውስጥ ወደ ኋላ ይቀለበስ ጀምሯል፡፡ ከእኒኽ አገሮች መካከል ኢትዮጵያ አንድዋ ናት። የአገሮቹ መንግሥታት ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት ግንባታ ገብተናል ብለው ሲያውጁ፣ ነጻነት እና የመብት ጥያቄዎች ቀዳሚ ቦታ ይይዛሉ ተብሎ ተገምቶ ነበር። ኾኖም ግን፣ እነዚህ መንግሥታት የዴሞክራሲን መዋቅር ሌጣውን ተቀበሉ እንጂ በባሕርያዊነት አብሮት የሚሔደውን የሊብራሊዝም ጎዳና ስላልተከተሉ፣ በአሉበት እየረገጡ ወደፊት መራመድ ተስኗቸዋል።

በዚህ ዙሪያ ወሳኝ ጥናቶችን ያደረጉ ሰዎች እንደሚናገሩት፣ የዴሞክራሲ እና የሊብራሊዝም ፖለቲካዊ መርሕ ከፍልስፍና አንጻር ሲታዩ አንድነትም ልዩነትም አላቸው። የሰው ልጅ ምሉዕ የኾነ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ፍትሐዊ ነጻነት ይኖረው ዘንድ የዴሞክራሲ እና የሊብራሊዝም መስተጋብር የግድ ይላል። ዴሞክራሲ የሚለው ቃል በዋናነት ሕዝብን ከዓምባገነናዊ ኀይል የሚከላከል ጋሻ (Demo-protection) ሲኾን፣ ሊብራሊዝም ደግሞ የሕዝብ ሉዓላዊነት (Demo-power) ነው። ዐዲሶቹ “ዴሞክራሲያዊ” መንግሥታት በተወሰነ ደረጃ የዴሞክራሲን አንዳንድ ፈለጎች ለመከተል ባይቸገሩም፣ የሊብራል ጥሪዎችን ማድመጥ ግን በእጅጉ ተስኗቸዋል።

ምናልባት፣ በዴሞክራሲ እና በሊብራሊዝም መሀል እንዴት ወይም ምን ዓይነት ልዩነት ሊኖር ይችላል ብለው የሚጠይቁ ሰዎች ስለሚኖሩ በዚኽ ዙሪያ ጥቂት ብለን ማለፉ ተገቢ ነው። አንደኛ፣ ዴሞክራሲ የሚያተኩረው በሥልጣን ክፍፍል፣ በየጊዜው በሚደረጉ ምርጫዎች፣ በብዙኃን መገናኛ፣ በመድበለ ፓርቲ፣ በሲቪል ማኅበራት… ወዘተ ተቋማዊ አያያዝና አሠራር ላይ ነው። በአንጻሩ ሊብራሊዝም በሕግ የበላይነት፣ በመሠረታዊ የሰው ልጆች ነጻነትና መብት ላይ ያተኩራል።

ኹለተኛ፣ ዴሞክራሲ የመንግሥት ሥልጣን በሚያዝበት መዋቅር ላይ ሲያተኩር፣ ሊብራሊዝም ደግሞ የሥልጣን ወንዝ ከገደቡ ወጥቶ ዜጎችን እንዳያጥለቀልቅ ለመከላከል፣ በምን መንገድ እየተቀየሰና እየተገራ መሔድ እንዳለበትና እንደሚገባው ይደነግጋል። ይኸውም ዴሞክራሲ ተሳትፎ ላይ ሲያተኩር ሊብራሊዝም ደግሞ ተጠያቂነት ላይ ያተኩራል። በአንዲት አገር መልካም የነጻነትና የፍትሕ ሕይወት መንገድ ተይዟል የሚባለው፣ ዴሞክራሲ የሚጠይቀው ሕዝባዊ ተሳትፎና ሊብራሊዝም የሚሻው መንግሥታዊ ተጠያቂነት በአንድነት ተባብረው ሲገኙ ነው።
በፅንሰ ሐሳብ ደረጃ የዴሞክራሲ እና የሊበራሊዝም የአጽንዖት ልዩነት እንደተጠበቀ ኾኖ፣ ወደ ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ኹኔታ ስንመጣ፣ ሥርዐቱ የኹለቱንም መሠረታዊ ጥሪዎች ማስተናገድ የተሣነው ኾኖ እናገኘዋለን። የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ከደርግ በኋላ፣ በተወሰነ መልኩ የዴሞክራሲ ጭላንጭል ቢያገኝም፣ ሕገ መንግሥቱ እንደሚደነግገው የሥልጣን ባለቤትነትን አልተጎናጸፈም። ይህን ለማለት የሚያስደፍረው፣ የአገራችንን ፖለቲካ ከሕዝባዊ ተሳትፎና ከመንግሥታዊ ተጠያቂነት አንጻር ስንመለከተው ትልቅ ጉድለት በመኖሩ ነው፡፡

(፩) ሕዝባዊ ተሳትፎ፦

ዜጎች በሕይወታቸው፣ በንብረታቸው፣ በማኅበረሰባዊ ኹኔታዎቻቸው ወሳኝ በኾኑ ጉዳዮች ላይ የምክክርና የውሳኔዎች አካል ባልኾኑበት ሥርዐትና አሠራር ውስጥ የዴሞክራሲ መሠረታዊ ጥሪ የኾነው ሕዝባዊ ተሳትፎ አልተወለደም ማለት ነው። ለኢሕአዴግ ግን ተሳትፎ ማለት (ሀ)አስቀድሞ የወሰነውን ነገር ሥልጠና በሚል ፈሊጥ ወደ ሕዝብ ማውረድ፣ (ለ)ባለድርሻ በሚል ፈሊጥ የራሱን ወኪሎች መርጦ ውሳኔዎች በተሳትፎ የተገኙ ማስመሰል ነው። ለሐቀኛ ተሳትፎ ግን የንግግር ነጻነት እና የመሰብሰብ ነጻነት ያስፈልጋል። መንግሥት እና ዜጎች በእኩል ደረጃ መወያየታቸው ቀርቶ፣ መንግሥት አቀባይ ሕዝብ ደግሞ ተቀባይ ኾነዋል።

(፪) ተጠያቂነት፦

መረጃ ከመንግሥት ወደ ሕዝብ የማይወርድበት አገር ውስጥ የተጠያቂነትን ሥርዐት ማሟላት በእጅጉ አስቸጋሪ ይኾናል። ሥርዐቱን ለማሟላት ከመንግሥት ቁጥጥር ውጭ የኾነ ሚዲያ ይኖር ዘንድ ግድ ይላል። ዜጎች መረጃ የሚያገኙበት መንገድ እስከሌላቸው ድረስ መንግሥትን ተጠያቂ ሊያደርጉባቸው የሚችሉባቸው መንገዶች ኹሉ ይዘጋሉ።
አንዳንድ የፖለቲካ ምሁራን፣ ዴሞክራሲ ለማበብ ረዘም ያለ ጊዜ ይጠይቃል፤ በመኾኑም ኢሕአዴግን የበለጸገ ዴሞክራሲ አላመጣም ብሎ መተቸት አግባብነት የለውም፤ የሚል መከላከያ ያቀርባሉ። የአፍሪቃ ዴሞክራሲ ገና ለጋ በመኾኑ ለመቶዎች ዓመታት ከቆየው ምዕራባዊ ዴሞክራሲ ጋራ ሊነጻጸር አይገባም፤ ሲሉም ይሞግታሉ። ለዚኽ ዓይነቱ አስተያየት ተገቢ መልስ ሰጥተዋል ብለን የምናምነው የ20ኛው ምእት ትልቁ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ጂዮቫኒ ሳርቶሪ (Giovanni Sartori) ናቸው። በእርሳቸው አመላለስ፣ ዴሞክራሲ የተለያዩ ክፍሎች ያሉት መዋቅር እንጂ አንድ ወጥ ባለመኾኑ፣ አንድ መንግሥት ቢያንስ የዜጎችን የንግግር፣ የመሰብሰብና ሐሳብን የመግለጽ ነጻነትን ለማክበር ምን ያኽል ጊዜ ያስፈልገዋል? ጋዜጠኛን ላለማሰር፣ የፖለቲካ ስብሰባዎችንና ሰላማዊ ሰልፎችን ላለመከልከል ሥርዐቱ ስንት ዘመን መቆየት ይኖርበታል?
በእኔ በኩል በዴሞክራሲ ፍላጎትና በገዢዎች ፍላጎት መሀል የተዘረጋው ቅራኔ እንደተጠበቀ ኾኖ፣ ከዚህ ቀደም ለማሳየት እንደሞከርኹት፣ የአገራችን የዴሞክራሲ ሥርዐት ግንባታ ለችግር የተጋለጠበት አንዱ ምክንያት፣ አውሮጳውያን በዘመነ አብርሆ ለመቶ ዓመታት ያኽል እንደአደረጉት፣ በሊብራሊዝም ባህል ላይ የተመሠረተ የሐሳብና አመለካከትን የመግለጽ ነጻነት፣ የኅትመት ነጻነት፣ ሃይማኖታዊ መቻቻልና በጥቅሉ በመሠረታዊ የሰው ልጆች የነጻነት ጥያቄዎች ላይ አስቀድመን ብርቱ ሥራ ባለመሥራታችን ነው።

፪. ዐዲሶቹ የኢ-ዴሞክራሲያዊ ኀይሎች ሥርዐተ ተቋማት

በዚህ ርእስ ሥር በከፊል የማቀርበው ሐሳብ በዋናነት የተመረኮዘው፣ በቅርቡ የጀርመኑ የፖለቲካ ሳይንቲስት ፕሮፌሰር አንድሪያስ ሺድለር (Andreas Schedler) በ2009 (እ. አ. አ.) በዴሞክራሲ ስያሜ ስለሚንቀሳቀሱት ዐዲስ መንግሥታት በአጠኑት ጥናት ላይ ነው።

ቀደም ባለው ክፍል ለማሳየት እንደሞከርኹት፣ ፕሮፌሰር ሳሙኤል ፒ. ሃንቲንግተን “ሦስተኛው የዴሞክራሲ ሞገድ” ወደፊት መገስገሡን ትቶ፣ የቀኝ-ኋላ ዙር መንገድ መከተሉን መግለጻቸውን አውስቻለኹ። ሌሎች ጸሐፍትም፣ ከዚኹ የገለጻ መንፈስ ጋራ በሚሔድ መልኩ፣ ይህን ፕሮፌሰሩ ‘ቅልበሳ’ ያሉትን ፅንሰ ሐሳብ፣ አንዴ ‘ኢ-ሊብራል ዴሞክራሲ’፣ አንዳንዴ ‘ኦተሪቴሪያን ዴሞክራሲ’ የሚሉ ስያሜዎች እየሰጡ ለመግለጽ ሞክረዋል። ፅንሰ ሐሳቡ በተለያዩ ስያሜዎች ቢገለጽም፣ በዋና ጭብጣቸው፣ የሥርዐቶቹን ‘ኢ-ዴሞክራሲያዊ’ ባሕርይ የሚያሳዩ መኾኑ ላይ ግን ሙሉ ስምምነትና አንድነት አላቸው።የዴሞክራሲ ሞገድ ውስጥ የተፈጠሩት ዐዲስ ሥርዓቶች፣ በውጣኔአቸው የነጻነትና የመብት ፍንጣቂ ቢታይባቸውም፣ ከሰብአዊ ነጻነት አኳያ ሲመዘኑ ግን የተመናመነ የተሰፋ መንገድ ላይ እንዳሉ መረዳት አዳጋች አይኾንም።

“ፍጹማዊ የሥልጣን አገዛዝ” ወይም ደግሞ “የጭቆና አገዛዝ” በሚል ቀደም ብሎ የሚታወቀው ስያሜ በዐዲሶቹ ሥርዐቶች ዐውድ ውስጥ “ዴሞክራሲያዊ” የሚል ቅጽል ተለጥፎለት እናገኘዋለን። እዚኽ ላይ ማንሣት የሚገባን መሠረታዊ ጥያቄ፣ “ዴሞክራሲያዊ” የሚለው ቃል ከእኒኽ ሥርዓቶች ስያሜ ጋራ ለምን አብሮ ተያይዞ ይቀርባል? የሚል መኾን ይኖርበታል። ይህን ጥያቄ የምናነሣበት ዋነኛ ምክንያት በቀደመው ዓምባገነናዊ አገዛዝ (Dictatorship) እና በዛሬው ጠቅላይ አገዛዝ (Authoritarianism) መካከል መሠረታዊ ዝምድናና ልዩነት ይኖር እንደኾን መፈተሽ ስላለብን ነው።

ፍተሻው በቀጥታ ወደ አገራችን ተጨባጭ ኹኔታ ያመጣናል። ለመኾኑ፣ በደርግ ሥርዐትና በኢሕአዴግ ሥርዐት መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? ደርግን “ዲክቴተርሺፕ”፣ ኢሕአዴግን ደግሞ “ኦተሪቴርያን” የምንላቸው ለምንድን ነው? የኹለቱ ሥርዐቶች ልዩነት ሲቀርብ፦ አንዱ ገዳይ፣ ጨፍጫፊ፣ አረመኔ ተደርጎ ይተነተናል፤ ሌላው ደግሞ፣ በወዳጆቹ ዘንድ፣ እንደ ነጻ አውጪ፣ የዴሞክራሲ አራማጅ ተደርጎ ሲቀርብ፣ በተቃዋሚዎቹ በኩል ደግሞ፣ እንደ ኢ-ዴሞክራሲያዊና ጎሰኛ ተደርገው እንደኾነ ዘወትር እንሰማለን። ኹለቱም አቀራረቦች ላይ ላዩን ሲታዩ በተወሰነ መልኩ እውነታ ቢኖራቸውም፣ በፅንሰ ሐሳብ ደረጃ ግን፣ የኹለቱን ሥርዐቶች መሠረታዊ ልዩነት በበቂ አይነግሩንም። በመኾኑም የቀድሞውንና የዐዲሱን መንግሥታዊ ሥርዐቶች ልዩነት በምንመረምርበት ጊዜ፣ ፕሮፌሰር ሺድለር የሚያቀርቡት ሐሳብ የበለጠ ጠቃሚ ኾኖ እናገኘዋለን።

ቀዳሚ የሚኾነው የኹለቱም ሥርዐቶች ተልእኮ ሥልጣንን ማካበት እና ሥልጣን ላይ መቆየት ነው። ከዚኽ አንጻር፣ ኹለቱም ሥርዐቶች ግባቸው አንድ ነው፡፡ ከግቡ ለመድረስ የሚጠቀሙባቸው መንገዶች ግን የተለያዩ ናቸው። እንደ ፕሮፌሰር ሺድለር አቀራረብ፣ የቀድሞዎቹ ዓምባገነኖች ሥልጣን ላይ ለመቆየት የሚጠቀሙባቸው ተቋማት ወትሮውንም በታሪክ ውስጥ የሰውን ልጅ ነጻነት በመፈታተን የሚታወቁትን፣ እንደ ‘የጦር ኀይል’፣ ‘ፖሊስ’፣ ‘ጸጥታ’፣ ‘ደኅንነት’፣ ‘ሲቪል ታጣቂዎች’ ናቸው። በሌላ በኩል፣ ዐዲስ የመጡት ዴሞክራሲያዊ ነን የሚሉት ሥርዐቶች ደግሞ የድሮውን የመጨቆኛ ተቋማት ትተው፣ የሰውን ነጻነትና መብት ያስከብራሉ የሚባሉትን የፍትሕ፣ የሕግ አውጪ፣ የምርጫ፣ የብዙኃን መገናኛ ተቋማትን ወዘተ… በጭቆና መሣሪያነት ይጠቀማሉ።

እዚህ ላይ ተገቢ የሚኾነው ጥያቄ፣ ለነጻነት የታሰቡ ተቋማት እንደምን ተቀልብሰው የመንግሥት መጠቀሚያ ለመኾን በቁ? የሚል ነው። በመኾኑም በዚህ ጉዳይ ላይ ትንሽ ገለጻ ከሰጠን በኋላ፣ የፍትሕ ተቋማትን፣ የብዙኃን መገናኛ ተቋማትንና የምርጫ ተቋማትን በምሳሌነት እናነሣለን።

ከኹሉ አስቀድሞ፣ ዐዲሱ ሥርዐት ሥልጣን በሚይዝበት ጊዜ የሚረከበው “ባዶ የፖለቲካ ተቋማዊ መሬት” (institutional tabularasa) አያገኝም። እንዲያውም ካለፈው ሥርዐት የቀጠሉ ርዝራዥ ተቋማት ተፎካካሪ ሊኾኑበት ስለሚችሉ የሚጠቅመውን ተቋም ዐቅፎና አስቀጥሎ አይበጀኝም የሚለውን ያፈርሰዋል።

በኹለተኛ ደረጃ፣ ዴሞክራሲን ሊያራምዱ ይችላሉ የሚባሉትን ዐዲስ ተቋማት ይገነባል፤ ኾኖም ግን፣ ተቋማቱ በመጀመሪያ እንደ ሥርዐት የቆሙበትን መንፈስ ሽሮ ሕይወት አልባ በማድረግ ለታይታ፣ በቅርፃቸው ብቻ እውናዊ እንዲመስሉ ያደርጋቸዋል። በዚኽም ሳይገታ በራሱ ቁጥጥር ሥር ከአዋላቸው በኋላ፣ ተቋማቱን እንደ ለማዳ እንስሳ እዚያው ሥርዐቱ ግቢ ውስጥ ይለቃቅቸዋል፤ ነገር ግን እነኚኽ የተሽመደመዱና ለአገዛዙ የተገሩ ተቋማት እንዲኹ ተቀላቢ ኾነው አይቀመጡም። ሥርዐቱ እስከአለ ድረስ ትጉሃን የጭነት ፈረስ ኾነው አገልግሎታቸውን ያበረክታሉ።

በሦስተኛ ደረጃ፣ ሥርዐቱ ሲጀምር ሕገ መንግሥት ተቀርፆ በአንድ በኩል ከአሐዳዊ ወደ ፌደራላዊ ሥርዓት ሽግግር መደረጉ ተገልጧል፤ በሌላ በኩል ከአንድ ወጥ የሥልጣን ዘርፍ ወደተለያየ የሥልጣን ዘርፍ ሔዶ የሥልጣን ክፍፍል እንዲኖር በሕገ መንግሥቱ በሕግ ተደንግጓል፡፡ አሁን ምን ደረጃ ላይ ደርሰናል ብለን በምንመለከትበት ጊዜ ግን የምናገኘው የሚከተለውን እውነታ ነው። ሕግ አስፈጻሚው ክፍል ወደ ጎን (Horizontal) እና ወደ ላይ (vertical) የሥልጣን ሽሚያ በማድረግ በአንድ በኩል ፌደራል ተቋሙ ላይ በሌላ በኩል የሕግ አውጪው እና የሕግ ተርጓሚው ላይ ትልቅ ጫና በማሳረፍ ሥልጣናቸውን በእጅጉ ገድቦታል። በመኾኑም፣ በእኒኽ ኹለት ዐሥርት ዓመታት ውስጥ፣ ሕግ አስፈጻሚው ተቋም ከሌሎቹ የመንግሥት ክፍሎች ኹሉ በበለጠ እየተጠናከረ እንዲኹም ሌሎቹን ተቋማት እያመነመነ ሔዷል።

ሀ) የፍትሕ ተቋማት፡-
በማንኛውም ሀገር ታሪክና በእኛም ነባራዊ ኹኔታ እንደምንረዳው፤ ያለሕግ ነጻነት የለም። እንዲኹም ሕግን ለመተግበር የፍትሕ ተቋማት ወሳኝ ድርሻ አላቸው። ኾኖም ግን የአንድን አገር ፍትሕ ለማስከበር የሕግ ተቋማት ራሳቸው በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ የግድ ይላል። ይኸውም የራሳቸውን ልዕልና ያላስከበሩ ተቋማት የዜጎችን ነጻነት ያስከብራሉ ማለት ዘበት ስለኾነ ነው።
አንዳንድ ጸሐፍት እንደሚነግሩን፣ የጠቅላይነት ሥርዓቶች የፍትሕ ተቋማትን ልዕልናና አቋም ለመቦርቦርና ለማዳከም ሕጉን ለመጨቆኛ በሚኾን መልኩ ደጋግመው በማመቻቸት (Judicialization of repression) ሲተገብሩ ይስተዋላሉ። ይህን ለመተግበር ከሚከተሏቸው መንገዶች የተወሰኑትን እንደሚከተለው ማየት ይቻላል።

I. የፍትሕ ተቋማትን ሥልጣን መገደብ (disempowerment)፤
የፍትሕ ተቋማትን መገደብ በምንልበት ጊዜ፤ የተለያየ እመቃ ደረጃ ያለው ነው። በመጀመሪያ፣ የተሠየሙትን ዳኞች ሥልጣን መገደብና ማሳነስ ነው፤ በተጨማሪም ለመመርመር የሚችሉበትን ወሰን በእጅጉ ማጣበብና በመጨረሻም ዳኞች ሊኖራቸው የሚገባውን የውሳኔ ነጻነት (ዲስግሬሽን) ማሳጠር ማለት ነው።

II. ለመንግሥት “ይበጃሉ” የሚባሉ ሰዎችን መሠየም፤
በዚህ ረድፍ የሚታየው ኢ-ፍትሐዊ ጉዞ የሚጀመረው በዳኝነት ወንበር ላይ የሚሠየሙት ዳኞች እየተመረጡ የሥርዐቱ ወዳጆች እንዲኾኑ መደረጉ ነው። የሕዝብ አስተዳደር ጥናት ያጠኑ አንዳንድ ምሁራን እንደሚነግሩን፤ አንደኛው የመንግሥት ችሎታ፣ ለጥቅማጥቅም ቀልባቸውን ሊሰጡ የሚችሉትን ነቅሶ የማውጣት ስልት ነው። እነኚኽም ለጥቅማጥቅምና ድጎማ የተመቻቹ ሹመኞች (incentive compatibility) ናቸው። በጥቅም የማይደለሉትን ደግሞ ቀጥተኛውን መንገድ ተከትለው እንዳይሔዱ በማስፈራራት ሐሳብን የማስፈጸም ጫና (dissuasive punishment) እንዲደርስባቸው ይደረጋል። ከዚኽም በተጨማሪ የፍትሕ ሒደቱን ረጅምና ውሳኔውን ለመሻር በሚያመች መልኩ ከታች ወደ ላይ እንዲሔድ፤ እልባቱ በረጅም የአቤቱታና የውሳኔ መሻርያ ሰንሰለት እንዲፈጸም ይደረጋል።

III. የተበታተነ የፍትሕ ሥርዐት፤
ሕጉን ለመጨቆኛ በሚኾን መልኩ ማመቻቸት (Judicialization of repression) በአንድ ሀገር ያለ የፍትሕ ሥርዓት አንድ ወጥ የኾነ ቅርጽ እንዳይኖረው፣ መደበኛ ከኾነው የሕግ ተቋም ተፎካካሪና በሕግ አስፈጻሚው ቁጥጥር ሥር የኾነ መንታ ተቋም በመፍጠር የመደበኛውን ፍርድ ቤት ተግባር ወደ ተቀጽላው ተቋም ማሸጋገር ነው።

ለ) የሚዲያ ቁጥጥር፤
ሚዲያን በሚመለከት ተቀዳሚው የኦተሪተርያን መንግሥታት ዓላማ፤ ፖለቲካዊ መረጃዎችን የማምረቻ ኃይልን መቆጣጠርና በአገሩ ውስጥ ብቸኛ አምራች ኾኖ መቅረብ ነው። ዜጎች በተለይ የፖለቲካ መረጃን በአማራጭ እንዳያገኙና ተፎካካሪ የኾነ የፖለቲካ ምልከታ እንዳይኖር ፍጹማዊ ሥልጣንን የተጎናጸፉ መንግሥታት ከሚያደርጓቸው ዕቀባዎች መካከል የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል።

የመገናኛ ምንጮች ብዝኃነት በመከልከሉ ዜጎች የመገናኛ አውታር ባለቤት የመኾን ዕድል የላቸውም። በመኾኑም በአገሪቱ የሚገኙት ሚዲያዎች በመንግሥት ሥር በመኾናቸው፤ የዝግጅቱን ይዘት ለመወሰን፣ ሕዝቡ ምን መስማት እንዳለበትና ምን መስማት እንደሌለበት በቁጥጥራቸው ሥር ማድረግ ይችላሉ። አንዳንድ የሚዲያ ተቋማት ለግለሰቦች በባለቤትነት የተሰጡ ቢኾንም የትኩረት አቅጣጫቸው ጠንከር ያሉ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በማንሣት ወይም ወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮችን በትኩረት በመዘገብ እንዲሠሩ ስለማይፈቅድ ብዙ ጊዜ በመዝናኛ፣ በስፖርታዊ ዘገባዎችና ይህን በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ የታጠሩ ፕሮግራሞችን በማስተላለፍ እንዲጠመዱ ያደርጓቸዋል። ይህ ዐይነቱ የመገናኛና ሚዲያ የትኩረት አቅጣጫ ለሥርዐቱ ብዙም አስጊ ባለመኾኑ ከጫና ለመገላገል የሚጠቅም መላ ኾኖ ሲያገለግል ይስተዋላል።

ሐ. የምርጫ ሥርዓት፡-
ወደ ዴሞክራሲ ጎዳና ገብተዋል የሚባሉት አገሮች ተቀዳሚ ሥራ የሠሩት በምርጫ ተቋማት ላይ ነው። መንግሥታት በአገራቸው ሕዝብ ፊትም ኾነ በዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ፊት በፍትሐዊ ምርጫ ሥርዐትና ሒደት ውስጥ ማለፋቸው የቅቡልነት መሠረታዊ ጥያቄ ኾኗል። የምርጫ አስፈላጊነት በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌ ላይ እንኳን የሕግ ዕውቅና አግኝቶ ወቅታዊ እና እውነተኛ ምርጫ ማካሔድ የአገሮች ተቀዳሚ ሓላፊነት እንደኾነ ተቀምጧል።

በኢትዮጵያም በሕገ መንግሥቱ፣ እንደ አንድ የዴሞክራሲ ሽግግር ሒደት ውስጥ እንዳለ አገር፣ በየአምስት ዓመቱ አገሪቱን ለማስተዳደር ተፎካካሪ ፓርቲዎች በብሔራዊ ምርጫ ለመንግሥት ሥልጣን የሚወዳደሩበት ሥርዐት ተደንግጓል። ከዚኽም በመነሣት፤ የመጪው ግንቦት ወር 2007 ዓ.ም. ውድድር ብሔራዊ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሐዊና የሕዝብ ተአማኒነት ባለው መልኩ እንዲካሔድ አቅጣጫ ተቀምጧል። የሕዝብ ተአማኒነት የሚለው እንደ መሥፈርት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጠ ስላልሆነ ለጊዜው እንተወውና፣ “ነጻ” እና “ፍትሐዊ” በሚሉት ስያሜዎች ላይ እናተኩር። ከኹሉ አስቀድሞ፣ ቃላት በመስጠትና ቃላቱን በመደጋገም ብቻ እውንና ተጨባጭ ማድረግ ይቻላል ወይ? በአኹኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ልትጎናጸፍ ትችላለች ወይ? ስለ ነጻና ፍትሕዊ ምርጫ በመጠኑ ከአብራራኹ በኋላ፣ የጥያቄዎቹን ምላሽ ለአንባቢ እተዋለኹ።

“ነጻ” እና “ፍትሐዊ” የሚለው ቃል በመጀመሪያ ብቅ ያለው እ.ኤ.አ. በ1927 ዓ.ም. የአሜሪካን ካልቨን ኮሌጅ ልኡክ ኒኳራጓ ለምትባለው አገር “አሜሪካ ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ እንድታካሂድ ቃል እሰጣለኹ፤” የሚል ንግግር ሲያደርግ ቃሉ የመጀመሪያ ዕውቅናውን አግኝቷል። ቀጥሎም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የ1956 ዓ.ም የቶጎ ላንድን የወደፊት ኹኔታ በሕዝበ ውሳኔ ለማረጋገጥ ባወጣው ሪፖርት ላይ ይኸው ቃል ተደግሟል። በሦስተኛ ደረጃ፤ በ1978 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔና ቁጥጥር የናሚቢያ ነጻነት፣ ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ከተካሔደ በኋላ ምክር ቤቱ የሒደቱን ፍትሐዊነትና ነጻ አካሔድ ለዓለም ሲያበሥር ቃላቱ ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት ለማግኘት በቅተዋል።
ኹለቱ ስያሜዎች አብዛኛውን ጊዜ በአንድነት ቢጠቀሱም፤ ይዘታቸውንና ትርጉማቸውን በተናጠል ለማየት እሞክራለኹ፡፡

(ሀ) የምርጫ ነጻ ሒደት ሲባል፡-
ከኹሉ አስቀድሞ ነጻ የሚለው ቃል ዜጎች የማይሸራረፍ የመምረጥ መብት እንዳላቸው የሚጠቁም ነው። የዜጎችን በነጻ የመምረጥ መብት ለመተግበር የሚከተሉት ኹኔታዎች መመቻቸት አለባቸው።
1. የመሰብሰብ እና የመመካከር ነጻነት፣
2. ማኅበራትን የማቋቋም መብት፣
3. የመንቀሳቀስ መብት፣
4. የመናገር መብት፣
5. የፖለቲካ ድባቡ ከዘለፋ፣ ከማስፈራራትና ከመዋከብ የጸዳ መኾን ይኖርበታል።

(ለ) ፍትሐዊ ምርጫ ስንል ደግሞ፡-
1. ተአማኒ በኾነ የምርጫ ቦርድ ሥር የድምፅ ቆጠራው መካሔዱ፣
2. ከምርጫው በፊትም ኾነ በኋላ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አለመግባባት ሲከሠት ፍትሐዊ የግጭት መፍትሔ የሚሰጥ ተቋም መኖሩ፣
3. ኹሉም የፖለቲካ ፓርቲዎችና ግለሰቦች ውድድር ውስጥ እንዲገቡ ያልተጨናነቀና እኩል ዕድል መስጠት፣
4. ኹሉንም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚያስተናግድ እኩል የሚዲያ አቅርቦት ማመቻቸት፣
5. የውድድሩ ሜዳ ለኹሉም ፓርቲዎች የተስተካከለ እንዲኾን ማድረግ ሲቻል፣
6. በዋናነት የመንግሥትና የፓርቲ የምርጫ ወጪ የሚወጣበት ቋት ሲለይ ነው።
ከላይ የጠቀስናቸው አንዳንድ ነጥቦች እንደሚያሳዩት፣ ነጻና ፍትሓዊ ምርጫ የሚሟላው በአንድ ቀን የድምፅ መስጫ ኮሮጆ ውስጥ ካርድ በማስገባት ሳይኾን ሦስት የምርጫ ሒደትን ሲያካትት ነው። (ሀ)ከምርጫ በፊት ያለው የአገሪቱ የፖለቲካ ድባብና የመወዳደሪያው ሜዳ መስተካከል፤ (ለ)የምርጫው ቀን ውሎ እና ገለልተኛ አወዳዳሪ ተቋም፤ (ሐ)ከምርጫው ዕለት በኋላ በተወዳዳሪዎች መካከል ጭቅጭቅ ቢነሣ ዳኝነትን የሚሰጥ ገለልተኛ ተቋም። ከላይ ላነሣነውም ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ለማግኘት፣ አንባቢ፣ የጠቀስናቸውን መስፈርቶች ከአገራችን ነባራዊው ኹኔታ ጋራ በማነጻጸር የራሱን ፍርድ መስጠት ይችላል።
(ይቀጥላል)

The post ኢሕአዴግኣዊ ዴሞክራሲ እና ሊብራሊዝም – ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ appeared first on Zehabesha Amharic.

ማስታወቂያ ለህጻን ኢንቨስተሮች ከዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም –ክንፉ አሰፋ

$
0
0

Tewodros adhanom
አሁን የምጽፈውን በደንብ አንብቡ። መቶ በመቶ እውነተኛ ነው። እውነተኛ ኩሸት።

“ያልተገባ ነገር እየፃፍን ልጆችን አንጉዳ። ሕጻናት የምታስቡት ፕሮጀክት የተቀደሰ ነው። እንደሚሳካም እምነቴ የፀና ነው። አሁን ዋናው ጉዳይ ህጻናት ህልማቸውን እንድናሳካ የማበረታታትና የመደገፍ ነው። ሕጻናት ሆይ 20 ሚሊዮን ዶላር ባትይዙም ቢሮዬ ብቅ በሉ!”

አይቴ ቴድሮስ በፌስ ቡክ ገጻቸው የለቀቁት መልእክት ይህ አልነበረም። ይህ አሸባሪዎች በርዘው የለቀቁት እንጂ፣ የዶ/ር ቴድሮስ ትክክለኛው መልእክት እንዲህ ይነበባል።

“ያልተገባ ነገር እየፃፍን ልጅቷን ባንጐዳ፡፡ ያሰበችው ፕሮጀክት የተቀደሰ ነው እንደሚሳካም እምነቴ የፀና ነው፡፡ አሁን ዋናው ጉዳይ በሪቱ ጃለታ አሕመድ ህልሟን እንድታሳካ የማበረታታትና የመደገፍ ነው፡፡ Galatoomaa በሪቱ፡፡ አላህ ይባርክሽ፡፡ Rabbi si haaeebbisu በርቺ፡፡ Jabaadhuu”

በማህበራዊ ድር-ገጾች ብዙ ፉገራዎች ከተራው ሰው ሲሰራጩ ቢታዩም፤ ነጭ ፉገራን በሚንስትር ደረጃ ስናይ ግን የመጀመርያው መሆኑ ነው።

በፌስቡክ ላይ “የጀርመን ነዋሪ ነኝ” ያለችው ልጅ ፒያሳ ባር ስታስተናግድ ተገኘች። የፌስቡክ ጓደኞችዋ በድንገት ሲያገኟት ልጅት ምንም አልመሰላት። “ለምን ዋሸሽ?” ቢሉዋት። አይኗን በጨው አጥባ መልስ ሰጠች።

“መዋሸት ብርቅ ነው እንዴ?” አለች። የሷን ፉገራ በመቶ እጅ የሚበልጡ ፉገራዎች ስለሚያጽናኗት ቅንጣት ያህል አልደነገጠችም። ጣትዋን በቴድሮስ አድሃኖም ላይ እያነጣጠረች ጓደኞችዋን አረጋጋች።

የዚህችን ወጣት ውሸት ማካበድ እንደማያስፈልግ የተረዱት ጓደኞችዋ፣ ከውቅያኖስ የጠለቀውን፣ ከባህር የሰፋውን የቴድሮስ ውሸት ከሰሙ በኋላ ነበር።

“አበስኩ ገበርኩ… የባሰ አታምጣ።” ይላሉ እናቶች።

በአጼ ምኒሊክ ግዜ ለፍርድ ሙግት የቀረበ አንድ ሰው እጁን እያወራጨ ሲናገር ብብቱ ይታይ ነበር። እብብቱ ስር ያለ ጸጉሩም አጎፍሮ ነበር። የብብቱን ጸጉር ያስተዋሉ ዳኛ፣ ችሎት በመድፈር ወንጀል 50 ጅራፍ ቀጡት። ሰውየው ቅጣቱን ሳይግደረደር ተቀበለ። ይህንን 50 ጅራፍ ለምን ሳይከላከል እንደጠቀበለ በጓደኛው ሲጠየቅ፣ ለብብቴ 50 የቀጡኝ የታችኛውን (የሃፍረተ ስጋዬን) ጎፈር ቢያዩ 100 ይሉኝ ነበር አለ።

“… የባሰ አታምጣ።” ነው ነገሩ።

ከዚህች ተራ ወጣት የባሰው ነጭ ውሸት በተጋለጠ ጊዜ፣
“የ14 አመትዋ ልጅ በአውስትራሊያ የ8ኛ ክፍል አስደናቂ ውጤት በማምስመዝገብ ያገኘችውን 20 ሚሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ ለልማት ለማዋል ወሰናለች ያልኩት ፍጹም ስህተት ነው። ስለ ጥፋቴ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ።” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ተናገሩ።

የሚል ዜና ብንጠብቅ፣ ብንጠብቅ፣ ብንጠብቅ እስካሁን ልንሰማ አልቻልንም። አቤ ጎርጉሮ ያወጣውን ቅሌት በፌስቡክ ከተለቀቀው የልደት ውስኪያቸው ጋር አወራርደውታል። ውሸቱ አሸማቆ፣ አሸማቆ፣ ይገድላቸዋል… ድንጋጤው ይጥላቸዋል ብሎ የገመተ ጥቂት አይደለም። ግን እንዴት አይነት ፈጣጣ ናቸው። ያንን ጉድ ይዘው ቢሮ ሲገቡ ምንም እንዳልተፈጠረ መስለው ብቻ አይደለም። ውሸታቸውን ስልቅጥ፣ዋጥ አድርገዋት ሌላ ጥፋት ደረቡበት።
“ህጻናትን ወደኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው።” የሚለውን የክርስቶስ ጥቅስ ቀየር አድርገው የራሳቸውን ፈንጠዝያ ሊነግሩን ሞከሩ።

“…ህፃናትና ታደጊዎች የዋሆች እንደሆኑ ክፋት እንደሌላቸው ከኔ ጋር የምትስማሙ ይመስለኛል። በዚህ ምክንያትም ህፃናትና ታዳጊዎች የሚነግሩኝን ማመን እመርጣለሁ። ስህተትም ቢኖራቸው ከየዋህነት ካልሆነ ከክፋት አይመነጭም። ህፃናትን ማመን ስህተት ከሆነ መሳሳትን እመርጣለሁ።…”

አይቴ ቴድሮስ በዚያ በልካቸው ባልተሰራ ወንበር ላይ ተቀምጠው ከሰሞኑ በርካታ ህጻናትን እንደሚያስተናግዱ ይጠበቃል። ከውጭም ከሃገር ውስጥም ኢቨስተር ህጻናት ወደ ቴድሮስ ቢሮ ይጎርፋሉ። በሚሊዮን እና በቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት እናደርጋለን ብለው ይዋሻሉ። ቴድሮስም በፌስ ቡክ ገጻቸው ታሪኩን ይለቀልቁልናል…ውሸቱንም ይለቁልናል። እነሆ ህጻናትን ማመን ስህተት አይደለምና እንዲዋሹ ተፈቅዶላቸዋል።

አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል የሚባለው እውነት ነው። ጭንቅላት ሲገለጥ ደግሞ ገመና ይወጣል። በህወሃት መዋሸት አዲስ ነገር አይደለም። ሰዎቹ በቀን ከመቶ ግዜ በላይ ይዋሻሉ። በስነልቦና ተመራማሪዎች እነዚህን ሰዎች ፓቶሎጂካል ውሸታሞሽ ይላቸዋል። ይህ በሽታ ሰዎች ካሉበት ችግር ለማምለጥ ወይንም ከተቆራኛቸው የበታችነት ስሜት ይመጣል። ውሸት መናገር፥ አንዳች ጥቅም ለማግኘት ሲባል ሆን ተብሎ የሚፈፀም ድርጊት ነው። ለዚህ የስነ ልቦና ችግር ከጥቅሙ ይልቅ የረጅም ጊዜ ጉዳቱ ያመዝናል። የሚዋሸው ሰው በሰዎች ዘንድ የሚኖረውን ተቀባይነትን የሚያሳጣ ስብዕናም ያላብሳል። ችግሩ የስነልቦና ነውና መፍትሄውም የስነ-ልቦና ህክምና ነው።

አንድ አባት ልጁን ይጠራውና “ልጄ፣ ጥፋት ካጠፋህ የቤታችን ውሻ ስለሚነግረኝ ተጠንቀቅ።”ይለዋል። ልጁ ውሻ የሚሰማ እና የሚናገር ይመስለው ኖሮ ውሻውን እየቀረበ ያናግረው ነበር። ነብስ እስኪዘራ ድረስም ይህንን ውሽት አምኖ ተሸወደ።

የቴዎድሮስ አድሃኖም ግን ተገላቢጦሽ ሆነብን። ነብስ እስኪዘራ ድረስ… ህዝቡን መሸወድ ተያይዞታል። በዚህ የመረጃ ዘመን ነጭ ውሸት ዋሽቶ ሲያበቃ፣ ውሸቱ ሲነቃ ሌላ ታሪክ መፍጠር ህዝቡን ዝቅ አድርጎ መመልከት አይመስልም? 20 ሚሊየን ዶላር እኮ ከ20ሺ ዶላር ይበልጣል። 20 ሚሊዮን ዶላር ከ 200 ሺም ይበልጣል። 20 ሚሊዮን ከ 2 ሚሊዮንም በ10 እጥፍ ይበልጣል። 20 ሚሊዮን በጣም ተጋነነ። ከአንድ ጀምረው ቀስ በቀስ እያሳደጉ ወደዚያ ቢደርሱም አንድ ነገር ነው።

ጃፓኖች እንዲህ ይላሉ። “የሚታመን ውሸት ለመዋሸት ከፈለግህ የማይታመን እውነት አትናገር።”
አይቴ ቴድሮስ በቅድሚያ ውሸትን በማንኪያ… ውሸትን በትንሹ ያለማምዱን! … ታዲያ እንደጀመሩ ይጨርሱልን።

The post ማስታወቂያ ለህጻን ኢንቨስተሮች ከዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም – ክንፉ አሰፋ appeared first on Zehabesha Amharic.


ሶስት ሚሊየን ብር የሚጠጋ ወጭ የወጣበት ድልድይ የጥራት ችግር አለበት ተባለ

$
0
0

downloadየካቲት ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአባይ ወንዝ ላይ የተሰራዉ 108 ሜትር ርዝመት እና አንድ ነጥብ ስድስት ሜትር ስፋት ያለው ተንጠልጣይ ድልድይ በሃገሪቱ ብቸኛዉ የተንጠልጣይ ድልድይ በመስራት በሚታወቀው ሄልቬታስ ሲዊዝ ኢንተርኮኦፕሬሽን በተሰኘ መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት ባለፈው ታህሳስ ወር መጨረሻ በይፋ ተመርቆ ስራ ቢጀምርም፣ በምረቃው ስነስርዓት የተገኙ ባለሙያዎች ድልድዩ የጥራት ችግር እንዳለበት መናገራቸው ነዋሪዎችንና በቦታው ተገኙ አመራሮችን አስደንግጧል፡፡

በአማራ ክልል ገጠር መንገድ ስራዎች ድርጅት የቁጥጥርና ክትትል ኬዝ ቲም ባለሙያ የሆኑት አቶ ይገርማል ታምር በዝርዝር ያቀረቡት የጥራት ችግር በምረቃ ስነስርዓቱ ለታደሙ የክልል እና የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ኃለፊዎች፣ ግንባታውን በኃላፊነት የሰራው ባለሙያ እና የአካባቢውን ነዋሪዎችን ያስደነገጠ እንደነበር በምረቃው ስነስርዓት የተገኙ ታዛቢዎች ተናግረዋል፡፡

40 በመቶ በሄልቬታስ ፤60 በመቶዉ ደግሞ ከዓለም ባንክ የግብርና እድገት ፕሮግራም በተገኘ ገንዘብ ወጭዉ የተሸፈነው ይህ ድልድይ ለሃምሳ አመታት እንዲያገለግል ታስቦ የተሰራ ቢሆንም የተሰራበት የድንጋይ አይነት፣የውሃ አጠጣጡ እና ገመዶችን ወጥሮ የያዘው የግንባታ አካል ስጋት ያለበት መሆኑን ባለሙያው ተናግረዋል፡፡

የዳስራ ማርያም እና የጭስ አባይ እንዲሁም በደቡብ ጎንደር ዞን ደግሞ የደራ ወረዳ የተወሰኑ የገጠር ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደሮችን የዘመናት ጥያቄን የፈታ ሁኗል የተባለለት ታንኳ በር ተንጠልጣይ ድልድይ እንዲሰራ ላለፉት ሁለት ዓመታት አርሶ አደሮች በተደጋጋሚ ለሚመለከተዉ አካል ጥያቄ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡

ሄልቬታስ ስዊዝ ኢንተርኮርፕሬሽን የተባለው የግብረ ሰናይ ድርጅት በክልሉ በተለያዩ ቦታዎች የሚሰራቸውን ተንጠልጣይ ድልድዮች ስራ በብቸኝነትና ማንም ተቆጣጣሪ በሌለበት ሁኔታ እንደሚሰራና ማኔጅመንቱም በአንድ አካባቢ ሰዎች ብቻ የተያዘ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። ድርጅቱ በአምስት ክልሎች ከስልሳ በላይ ተንጠልጣይ ድልድዮችን እንደሰራ በእለቱ የምረቃ ስነስረአት ላይ ተገልጿል፡፡

Source:: Ethsat

The post ሶስት ሚሊየን ብር የሚጠጋ ወጭ የወጣበት ድልድይ የጥራት ችግር አለበት ተባለ appeared first on Zehabesha Amharic.

ማስተርስ/ዶክተሬት እንደ መለዋወጫ እቃ! (ታሪኩ አባዳማ)

$
0
0

ታሪኩ አባዳማ | የካቲት 2007

ልጄ አስራ ሁለተኛ ክፍል ስለጨረሰ የደስታዬ ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ… የሚል ግብዣ ደርሷችሁ አያውቅም? እናንተም ፋሽኮ ቪኖ ወይንም እናትና ልጅ አረቄ ይዛችሁ ድግሱን ለማድመቅ ሳትሄዱ አልቀራችሁም – የዚያን ዕለት ጎረምሶቹ የቀለጠ ፓርቲ ደግሰው እስኪነጋ ይጨፍራሉ አሉ… ይህስ ይሁን።Fake-Indian-degrees-abound

ድህረ ምረቃ ፕሮግራም ላይ መሆኑን አንድም ቀን ሲናገር ሰምታችሁ የማታውቁት በቅርብ የምታውቁት ሰው ፣ እንዲያውም በመደበኛ ትምህርት ከስንተኛ ክፍል ነበር? አቋርጦ ወደ ሄደበት ሄዶ (ጫካ ወይንም ምርኮ) ግን የዛሬ ‘ሹም’ ‘የማስተርስ ፣ ዶክትሬት ዲግሬዬ በፖሰታ ስለደረሰኝ የደስታዬ ተካፋይ እንድትሆን ብሎ ቢጠራችሁስ? ይኼ ሰው ድሮ ትምህርት ቤት የተመዘገበበት ስም ሌላ ነበር… አሁን ደግሞ አዲስ ስም ብቻ ሳይሆን አዲስ ማዕረግ ፣ አዲስ ቤት ፣ አዲስ መኪና… ምኑ ቅጡ… ባናቱ ላይ ዲግሪ ሸምቶበታል።

ይድረስ ለተከበሩ… አስፈላጊውን ክፍያ ስላጠናቀቁ የ ማስተርስ ዲግሪዎን አያይዘን ልከናል – ለዶክተሬት ዲግሪዎ ተመልሰው እንደሚመጡ ተስፋ እናደርጋለን – የዋጋ ቅናሽም እናደርግሎታለን – ስለ ደንበኝነታችን ሲሉ አገልግሎታችንን ለስራ ባልደረቦችዎ እንዲያስተዋውቁልን ትብብሮን እንጠይቃለን – ለዚህም ተገቢውን ወሮታ እንከፍላለን – ያስታውሱ ‘ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ’ – ሴንቸሪ ዩንቨርሲቲ

ታዲያ እርሶም ለምርቃቱ ተጋብዘዋል – በተጠራው ድግስ ላይ ‘…ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትህን የት ነበር የጨረስከው ፣ ማትሪክ ውጤትህስ ስንት ነበር ፣ የመጀመሪያው ዲግሪህስ… ያጠናኸው ፣ የተመራመርከው እና መቸ ያዘጋጀኸው መመሪቂያ ቴሲስ ነው ለዚህ ያበቃህ?…’ ብላችሁ ትጠይቃላችሁ ወይስ ድግሱን ተቋድሳችሁ …እንኳን ለዚህ አበቃህ ብላችሁ መርቃችሁ ትመለሳላችሁ?

አነሳስቶ ላስጀመረን ፣ አስጀምሮ ላስጨረሰን ተብሎ ባደባባይ በግልፅ ሳይተያዩ ማስትሬት እና ፒኤችዲ እንደ መለዋወጫ እቃ ‘…ኦን ላይን ኦርደር…’ ማድረግ የወቅቱ የወያኔ ሹማምንት ልዩ መታወቂያ መሆኑን ስናይ ‘ኦ ዲግሪ ሆይ ከስምሽ ጀርባ ስንት ደደብ መሸገ’ እንድንል ያስገድደናል። ባንድ ጀምበር ሚሊየነር ፣ ባንድ ጀምበር ጄነራል እናም ባንድ ጀምበር ዶክተር እገሌ መባል ወያኔአዊ ተፈጥሮ ያመጣብን በሽታ ነው። እነኝህ ሰዎች በየመስኩ በሚፈጥሩት ስፍር ቁጥር የሌለው የተዛባና ህገ ወጥ አሰራር ጉዳቱ ውሎ አድሮ አገሪቱ ላይ በሁለንተናዊ መልኩ እየተንፀባረቀ መሆኑን ለመናገር የሚያስቸግር አይመሰለኝም። አዲሱ ሚሊየነር በሙስና እና ነጠቃ ላይ የተገነባ መሆኑ ፣ ጄነራሉ ችግር ሁሉ የሚፈታው በጠመንጃ ብቻ ነው ሲል የቁጩ ማስተርስ እና ዶክተርም የነሲብ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ መፍትሔ ሲያረቅ ሲያማክር… እንዲያው ተያይዞ ገደል መግባት መሆኑ ቁልጭ ብሎ አይታያችሁም?

‘…ለኢህአዴግ ታማኝ እስከሆነ ድረስ ማይም እንኳ ሚኒስትር መሆን ይችላል…’ ያለው ማን ነበር? ሙት ወቃሽ እንዳልሆን ብዬ እንጂ ይኼ ድኩም ራዕይ የተሰነቀው ገና ከጠዋቱ እንደነበር አትዘንጉ ለማለት ነው። የአሳ ግማቱ ከወደ አናቱ!!

አንኳንስ ዶክተሬት ስምንተኛ ክፍል ሲጨርሱ ካባ ለብሶ ፎቶ መነሳት ፣ የምርቃት ቀን ደግሞ ሽክ ባለ ልብስ ፣ ባጌጠ አደራሽ ፣ ሞቅ ደመቅ ባለ ስነስርዓት ዘመኑን መቋጨት እዚህ በምእራቡ አለም ጭምር የተለመደ ነው። ከዩንቨርሲቲ ሲመረቁ ደግሞ ስርዓቱ ለየት ይላል – ይኼ ሁሉ የሚደረገው ግን አንድም ትምህርት በአግባቡ የተሰጠ ለመሆኑ ይፋዊ ማረጋገጫ ለመስጠት ሲሆን – ሽፍንፍን ፣ ድብቅብቅ ተመርቂያለሁ ማለት ባካዳሚው አለም ሆነ በህብረተሰቡ ውስጥ ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ መሆኑን ለማሳየት ጭምር ነው። ይህን ስል በወያኔ ተቋማት አደባባይ የተመረቀ ሁሉ ብቃቱ ተረጋግጧል ማለቴ አይደለም።

ወያኔ ሁሉንም ዘዴ እንደ አስፈላጊነቱ ይጠቀምበታል። ከገበያ መሸመት ያለባቸው ሹሞች በጀት ተይዞላቸዋል – በተጠረቡ ቤቶች ውለው አድረው ‘የሚመረቁ’ ደግሞ አሉ… ከሲቪል ኢንሲቲትዩት… ከዚህ ሰፈር ከዚያ ሰፈር ኮሌጅ… ከዚህ ከዚያ ህዝቦች ዩንቨርሲቲ… ኮብል ስቶን ጠራቢ ምሩቃን ከታማኝ የወያኔ ካድሬ ምሩቃን ጋር ተማክረው ስለጉዳዩ የበለጠ ሊነግሩን ይችላሉ።

በምዕራቡ የትምህርት አለም ግን ልጆቻችሁን አስተምረን እዚህ አድርሰናል ፣ አዘጋጅተናል ፤ ኑ ተረከቡን የሚል ጥሪ ለወላጆች ሲቀርብ – ወጣቶቹ ለመጪው የከፍተኛ ትምህርት ዘመን ወይንም ለላቀ ሀላፊነት መዘጋጀታቸውን ለማብሰር ብቻ ሳይሆን ጠንክረው በጥሩ ውጤት ያጠናቀቁትን በአርአያነት በአደባባይ በመሸለም ሌሎችም እንዲተጉ ለማበረታታት ጭምር ነው። ይህም የሚደረገው አለምክንያት አይደለም።

የትምህርት ደረጃ የማይዛነፍ ራሱን የቻለ እርከን ፣ አድማስ እና ጥልቀት አለው – በትምህርት ገበታ የተወሰነ አመታት ማሳለፍ በራሱ የተጠና ፣ የተወጠነ ግብአት ያለው መሆኑንም መረዳት አያዳግትም። እያንዳንዱ እርከን ከዕድሜና የአይምሮ መጎልመስ ጋር ተቀናጅቶ ፣ በጥንቃቄ ተመጥኖ እየተለካ ዕውቀት የመመገብ ዘዴ ተዘርግቷል – መደመር እና መቀነስ ብለው ሳይጀምሩ ፣ ረጅሙን የሂሳብ ጎዳና ሳይጓዙ ካልኩለስ ስሌት ውስጥ መግባት እንደማይቻል ሁሉ ወግ ያለው መደበኛ ትምህርት በተገቢው መንገድ ሳይታለፍ ባቋራጭ ማስተርስ እና ፒኤችዲ አገኘሁ ማለት ራስን ከማጃጃል አልፎ ጦሱ የት እየለሌ ነው።

የረባ ዕውቀት ሳይጨብጡ ድሀ አገርን ያህል ለመምራት መድፈር ፣ ‘ድህነትን ታሪክ እናደርጋለን’ ከሚል ባዶ መፈክር የዘለለ ፋይዳ የለውም – ውጤቱ ከባዶ ጣሳ ወደ ተቀደደ ጣሳ ውሀ አገላብጥኩ እንደ ማለት ያህል ነው። ይሄም ባዶ ያም ባዶ – ከባዶ ለባዶ!! Blank of blank ይሉታል ፈረንጆቹ።

በመጀመሪያ ዲግሪ ለመመረቅ አራት ዓመታት የሚፈጀው በሚሰጡት ኮርሶች የሚገኘው ዕውቀት ብቻውን ያን ያህል ዘመን ይፈጃል ተብሎ አይመስለኝም። ተማሪው አራት ዓመታት በዚያ የእውቀት ማዕከል ሲመላለስ ከመደበኛው ትምህርት ሌላ ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊ ፣ አለም አቀፋዊ እና ቤተሰባዊ ልምድ እና እውቀት አጣምሮ በመቅሰም አይምሮውን ያጎለምሳል። ካንድ ደረጃ ወደሚቀጥለው ለመሻገር የትናንቱ ለዛሬው ፣ የዛሬው ለነገው የሚያወርሱት መሰረት እጅግ አስፈላጊ ናቸው። መደበኛ ትምህርት ወደ ስራ አለም ሲሰማሩ ሀላፊነትን በብቃት ለመወጣት የሚያስችል ስንቅ መደቆሻ አምባ ነው። በወጉ ሳይሰንቁ ሩቅ ለመጓዝ አይታሰብም ፣ በድፍረት የመጣው ይምጣ ብሎ መጓዝ ይቻል ይሆናል ውጤቱ ግን ባዶ መፈክር እያመረቱ ማደናገር ይሆናል – ከባዶ ጭንቅላት የሚመነጩ መፈክሮች መሬት ላይ ካለው ውነት ጋር የሚጣረሱ ለመሆናቸው ያለፉትን 23 ዓመታት ብቻ ማስተዋል ይበቃል – በቀን ሶስት ጊዜ ትበላለህ አይነት!!

ትምህርት እውቀት ነው ፣ እውቀት ደግሞ ሀይል ነው። የትምህርት ማዕረግ ሸምቶ ባልሰለጠኑበት ደረጃ እና ብቃት ሀላፊነት ላይ መቀመጥ ‘ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት ዳገት ላይ ይለግማል’ እንዲሉ ፈታኙን የህብረተሰብ ሁለንተናዊ ችግሮች ለመጋፈጥ እና ለማቃለል ከቶውንም ማጠፊያው ይቸግራል። ይህንነም በተጨባጭ እያየነው ነው – እቅድ ተነደፈ ተብሎ ወረቀት ላይ የሚለቀልቁት ቅዠት ከዕውቀት ማነስ የሚመነጭ መደናበር ነው። በየዘመኑ ማክተሚያ ‘እቅዳችን ያልተሳካው …’ 99 ሰበብ መደርደር።

በቅርቡ ይፋ ሆነው ባነበብናቸው የምርመራ ዘገባዎች እንደተገነዘብነው አገራችን ከቶውንም የዩንቨርሲቲ ደጃፍ መርገጥ ቀርቶ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በወጉ ያላጠናቀቁ ባለስልጣናት የተሸከሙትን የሙያ ማረጋገጫ ምስክር ሰነድ እያየን ነው። ሳይማሩ የጠመጠሙ ዳውላ ሹማምንት እየበረከቱ መሆኑን በማስረጃ ተደግፎ የቀረበው ዘገባ አረጋግጧል። ይኼ ዜና አሳፋሪነቱ ድርጊቱን ለፈፀሙት ቱባ ባለስልጣናት ብቻ ሳይሆን እነዚህን ታቅፎ ተመርኩዞ አገር እየገዛ ላለው የወያኔ ስርአት ጭምር ነው።

ወያኔ ግን ሀፍረት ያውቃል እንዴ?

ይችን አስተያየት ለመክተብ ያነሳሳኝ ዋና ምክንያት ድንቅ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ባቀረበው በዚህ ጥናታዊ ዘገባ ከተጋለጡት (ቅሌት ከተከናነቡት ብል ይሻላል) ግለሰቦች አንዱ አቶ ቆስጠንጢኖስን ባንድ አገጣሚ የማውቀው በመሆኑ ነው። ሰውዬውን ያገኘሁት እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር 1971 – 72 አብረን ማዕከላዊ ብሎም ከርቸሌ በቆየንባቸው የእስር ዘመናት ነበር። ያንን የእስር ዘመን በሚመለከት በቃለ መጠይቅ የተናገረውንም ሰምቻለሁ… ቆስጤ ያው እንደ ጥንቱ ነው – ሲናገር ሳግ አያንቀውም – የሴንቸሪው ዶክተሬት በባህሪው ላይ ለውጥ አላመጣም።

በሰኔ ወር 1971 ዓም በደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢ ደርግን የሚያሰጋ አንዳች ህቡዕ እንቅስቃሴ በደህንነት መስሪያ ቤት የተደረሰበት መሆኑ ይወራል። በዚህ እንቅስቃሴ ተሳትፈዋል የተባሉ አስራ ዘጠኝ ያህል የጂጌሳ እና ሰንቀሌ እንጨት መሰንጠቂያ ወዛደሮች (በደን ልማት ባለስልጣን ስር የነበሩ ፋብሪካዎች ናቸው) የፋብሪካዎቹ ዋና ስራ አስኪያጅ አለማየሁ ዘውዴ እንዲሁም በሻሸመኔ እና አካባቢው በልዩ ልዩ መስክ የተሰማራን ግለሰቦች በአካባቢው የደርግ ተጠሪ ኮሎኔል አባተ መርሻ አዝማችነት ከያለንበት ታድነን ደቡብ ጦር ሰፈር በሚገኝ እስር ቤት ገባን። በማግስቱ በከፍተኛ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች አጀብ አዲስ አበባ ተጓጉዘን ማዕከላዊ እስር ቤት እንታጎራለን። የተከሰስንበት ጉዳይ መንግስትን በወታደራዊ ሀይል ለመገልበጥ ዝግጅት ማድረግ የሚል ነበር። ‘… ጦር መሳሪያ አከማችታችሁዋል ፣ ወታደራዊ ስልጠና እየወሰዳችሁ ነው..’ ይላል የክሱ ቻርጅ። ከታሰርነው መካከል አንድም ወታደር የለም – እርግጥ ነው እሳት ከሌለ ጭስ የለም… እሳቱ ግን የነደደው ሌላ ሩቅ ሩቅ ሰፈር ነበር… ዝርዝሩ ወደ ሌላ ታሪክ ስለሚወስደን ለጊዜው እዘለዋለሁ።

ይህ በንዲህ እንዳለ አዲስ አበባ የደን ልማት ሰራተኞች ማህበር ሊቀመንበር ሀይሉ ዳኜ ተይዞ በኛ የክስ ሰነድ ተካተተ ፤ ብዙም ሳይቆይ ቀንደኛው ተጠርጣሪ ቆስጠንጢኖስ በረኼ ነው በሚል እሱም ተይዞ መጣ።

ቆስጤን በዝና እንጂ እስከዚያ ድረስ በአካል አላውቀውም ነበር… ደን ልማት ውስጥ ማለፊያ ስልጣን ያለው ሰው ሲሆን ተወዳጅ ተክለሰውነትም ነበረው… ረጋ ብሎ መናገር… ግን ሳያቋርጥ የመናገር ችሎታ አለው። ምንም ርዕስ ስጡት ቆስጤ እንደ ልዩ ባለሙያ ይተነትነዋል ፣ ያብራራዋል… ልዩ ተስጥኦ ነው። ታዲያ ከሚናገራቸው ነገሮች ውስጥ አብላጫው መጨበጫ መያዣ የሌለው ነገር ነበር… የቱ ውነት የቱ ውሸት መሆኑን እንኳ ለመለየት ይቸግራል። ያኔ እኔ ገና የ12ኛ ክፍል የህብረተሰብ ትምህርት ተማሪ ስለነበርኩ ቆስጤ የሚተነትነው የፊዚክስ ንድፈ ሀሳብ ሚስጥር ሆኖብኛል። በዚህ የተነሳ በጣም አደንቀዋለሁ – በብዙሀኑ እስረኛ ዘንድ በዚያን ዘመን ማዕከላዊ ከነበሩ ምሁራን እንደ አንዱ ይቆጠር ይከበርም ነበር።

አወይ ማዕከላዊ! እኛ በታሰርንበር ዘመን እስር ቤቱ ተጨናንቆ እና ገንፍሎ ከቤት ውጭ መተላለፊያው ላይ ሰሌን ዘርግተን መተኛት ነበረብን። ማዕከላዊ ስንገባ እነ ጋሼ አሰፋ ጫቦ በጨለማ ቤት እንደታሰሩ ነው ፣ እኔ የደረሰኝ ላይኛው ግቢ 8 ቁጥር ሲሆን ብዙ ሰዎችን የመተዋወቅ ዕድል አጋጥሞኛል። እዚህ አሜሪካ ባለፈው ዓመት ዋይት ሀውስ ተጋብዞ ከፕሬዘደንት ኦባማ ልዩ ክብር የተቸረው ሳይንቲስቱ ዶር ሰለሞን ቢልልኝ የ8 ቁጥር ባልደረባዬ እንደነበረም አስታውሳለሁ።

የቼዝ ጨዋታ ስልት አስተምሮ ለውድድር እንድሰለፍ ያበቃኝ ሙባረክ ሸሪፍ (የሸሪፍ ላውንደሪ ባለቤት ልጅ) ከዚያው ከ8 ቁጥር ነበር ሌሊት ሌላ ክፍል ታስረው ከነበሩ ጓዶቹ ጋር ተወስዶ የተረሸነው (ከብርሀነመስቀል ረዳ ጋር ከጫካ የተያዙ ወጣቶች ናቸው)። እስከዛሬ ድረስ በቤተሰብ ደረጃ ግነኙነታችን ተጠብቆ የሚገኝ የዚያን ጊዜ የ8 ቁጥር እስረኛ ባልደረባዬ በቀለ ተፈራ ዛሬ ከነቤተሰቡ ጀርመን አገር ይኖራል… አዲስ አበባ ታዋቂ ኮማሪቶች ፔጆ 504 ወርቅና ውድ ጌጣ ጌጥ እየሸመተ ሲያንቆጠቁጣቸው የነበረው የመንግስት እርሻ ልማት ሀላፊ የነበረውን በርሔ ተመልሶንስ ታስታውሱታላችሁ? እሱም 8 ቁጥር ነበር። ስንቱ ይነገራል።

አለም በቃኝ ሲወስዱን ደግሞ የልጅነት ጓደኛዬን የሽመልስ ኦላና ታናናሽ ወንድሞች ሀይለልዑል እና ዳኜ አገኘሁዋቸው። ሽመልስ ኦላና አምቦ አካባቢ በግፍ መገደሉ ሳይበቃ ደርግ መላ ቤተሰቡን ለረጅም ጊዜ በእስር አሰቃይቷል ፣ ቤት ንብረታቸውን ቀምቶ ባዶ አስቀርቷቸዋል። አባቱ አንጋፋው ኦቦ ኦላና ባቲ በወያኔ ዘምንም ቢሆን ከመንገላታታት አላመለጡም። አንዳንድ ቤተሰብ ላይ የወረደውን ግፍ ሲያስቡት ይዘገንናል።

ከርቸሌም ቢሆን በየቤቱ ከታጎረው እስረኛ ሌላ አለም በቃኝ ክልል ሜዳው ላይ የላስቲክ ጎጆ ቀይሶ የሚያድረው ቁጥሩ እጅግ ብዙ ነበር። የመጀመሪያ ቀን አዳሬን ያደረኩት የ8 ቁጥር ባልደረባዬ ከነበረው ከመሐመድ ኢዛም ጋር ሲሆን – (መቸም 8 ቁጥር ኖሮ መሀመድ ኢዛምን የሚዘነጋው ያለ አይመስለኝም)። ተናግሮ የሚያስቅ ፣ ፈገግታ ከፊቱ የማይለይ ፣ ጨርሶ እስር ቤት መሆኑን ለመዘንጋት እና ሌሎችም እንዲዘነጉ ለማድረግ የነበረው ተሰጥኦ የሚገርም ነው። የኮሜርስ ምሩቅ እና የባንክ ሰራተኛ ነበር – ታዲያ የዚያን ዕለት ሜዳ ላይ አነጣጥፈን ከመተኛታችን ዝናም መንጠባጠብ ይጀምራል – መጠለያ የሚሉት ነገር የለም ምክንያቱም ቤት ውስጥ የሚተኙት በሙሉ ተቆልፎባቸዋል – መሀል ላይ ያለው በረንዳ ለጠጠር መወርወሪያ የሚሆን ክፍተት አንኳን የለውም – እስረኛው እንደ ርስቱ የሚቆጥረው የመኝታ መደብ አጨናንቆታል። እናማ ከዝናም መሸሻ ቦታ የለም። መሐመድ ኢዛም ግን እንዲህ አለኝ ‘አይዞህ አትስጋ ዝናም በአስማት የማቆም ችሎታ አለኝ… ብቻ የሚሆነውን ጠብቅ’ ሲል በማይገባኝ ቋንቋ መለፍለፍ ጀመረ…. ውነትም አስገምግሞ የመጣው ዝናብ በመንጠባጠብ ቀስ በቀስ በረደ – እኛም አንቀላፋን። ሁዋላ ውጭ ከመተኛት የታደጉኝ የሸመልስ ወንድሞች ናቸው።

ብዙ ትዝታ ያተረፍንበት ዘመን። … ወደ ቆስጤ ልመልሳችሁ።

እንዳልኩት በዚህ ጉዳይ ላይ ለመፃፍ ያነሳሳኝ የቆስጤ ነገር ነው። ትምህርቱን ከአዲስ አበባ ዪንቨርሲቲ ያውም በአፄው ዘመን ያጠናቀቀ ማለፊያ ጭንቅላት የነበረው ቆስጤ ምን ሲያደርግ የዩንቨርሲቲ ደጃፍ ረግጠው ከማያውቁ እነ አባዱላ ገመዳ ተርታ የሚያስልፈው ድርጊት እንደ ፈፀመ ሳስበው ይገርመኛል? በውነቱ በፖለቲካ እምነቱ ከወያኔ ጎን ቢሰለፍ ፣ እሱም እንደነሱ የዘር ሐረግ መዝዞ ይህን እና ያንን ስልጣን ቢጨብጥ ለምን ይህን አደረክ ብሎ መጠየቅ ተገቢ ላይሆን ይችላል – ሰልጣን በዘር መስፈርት እንደ ቆሎ በሚታደልበት ዘመን እሱም ከዚያ ሰልፍ ውስጥ መግባቱ ቢያስቆጭም ትምህርትን ያክል ታላቅ ነገር የዘረኞች ማላገጫ ሲደረግ ግን ለምን እሱ ራሱ ግንባር ቀደም አድራጊ ፈፃሚ ሆነ? ውሻ በቀደደው…

ቆስጤ ይበልጥ ትዝ የሚለኝ ከርቸሌ ወደኛ ክፍል ተዳብሎ መኖር ከጀመረ በሁዋላ የሆነው አጋጣሚ ነበር። ዘመኑ 1972 ወሩ ትዝ አይለኝም ለሆነ የእስልምና ብሔራዊ በአል ቀን ወህኒ ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ ጫት በይፋ እንዲገባ ይፈቀዳል – በዕለቱ ከውጭ በገባልን ጫት ምርቃና ሞቅ ደመቅ ያለ ውይይት ተከፍቶ ብዙም ሳይቆይ መድረኩ ለቆስጤ ይሰጠዋል። የንግግሩ ርዕስ ስለ ፊዚክስ የትምህርት መስክ ሲሆን በወቅቱ በመስኩ ስለተገኙ አዳዲስ ግኝቶች ምን ሊነግረን እንደሚችል ከቤቱ ጥያቄ ቀረበ። ቆስጤ ትንተናውን ጀመረ – ያኔ እኔ የ12ኛ ክፍል የሶሻል ሳይንስ ተማሪ ስለነበርኩ ስለፊዚክስ ብዙም ዝንባሌ አልነበረኝም። ይሁንና ቆስጤ ከሚሰጠው ትንታኔ በተለይ ስለ ህዋ ምርምር የተደረሰበትን ጭብጥ ሲያብራራ ሁላችንም ፈዘን በተመስጦ ‘በምርቃና’ መንፈስ እንከታተለው ነበር። አገላለፁ ቴክኒካል ተርም የሚበዛበት በመሆኑ ይመስለኛል አብዛኛው ነገር አልገባኝም – ሁላችንም ግን ባድናቆት ተከታትለነዋል። ያን ያህል ራሱን መግለፅ የሚችል ሰው ፣ የመጀመሪያ ዲግሪውን አንቱ ከተባለው የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ለፍቶ ደክሞ ያገኘ ሰው እንዴት መደበኛ ትምህርታቸውን በወጉ እንኳን ካላገባደዱት እነ አባዱላ ገመዳ ተራ ለመሰለፍ መረጠ? መልሱን በጨዋ ደንብ ሊሰጠን የሚችለው ቆስጤ ብቻ ነው።

ዛሬ አለም ያለበትን የቴክኖሎጂ ዕድገት ደረጃ ስናይ የሰውን ዘር ለዚህ ምጥቀት ያበቁ ሳይንቲስቶች በየዘመኑ ተጠበው በምርምር ባስገኙት ውጤት መሆኑ ግልፅ ነው። ከጥንት እስከ አሁን ደረጃ በደረጃ እየበለፀገ እየዳበረ ዕውቀት ይበልጥ እየረቀቅ ብሎም እያንዳንዱ መስክ ዳብሮ ልዩ የሙያ ዘርፍ መፍጠር አስፈላጊ የሆነበት ዘመን ላይ ነን። የስራ ክፍፍል ለብቃት መጎልበት አይነተኛ መሣሪያ እንደሆነ ሁሉ ካንድ የጠቅላላ ዕውቀት ዘርፍ ወደ ሰፔሸላይዜሽን ሽግግር የሚደረገው ያው ብቃትን ለማጎልበት ሲባል ነው። ይኼ ደግሞ በድህረ ምርቃ የትምህርት ዘርፍ ስልጠና እና ምርምር በማድረግ የሚጨበጥ ውጤት ነው። ታዲያ ከምድር ተነስቶ የድህረ ምረቃ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት መሸመት ባጠቃላይ ባገሪቱ እና በተለይ በትምህርት ገበያ ዘንድ ያለውን ሚዛን ምን ያህል እንደሚያዛባው የሚጠፋው ማነው? ቆስጤ ኦን ላይን ኦርደር የተደረገ ዲግሪ መሸመት ትምህርትን በቁሙ ለመግደል ከተሰለፉ ማይማን ተርታ እንደሚያሰልፈው እንዴት ጠፋው?

አገርን ለመግደል የትምህርት ስርዓቱን መግደል ፣ የትምህርትን ብቃት ዋጋ ማሳጣት እና ስልጣንና ሀላፊነት ዘር መዝዞ ለተጠጋ ሆዳም ማስታቀፍ – ይኼ ነው ከወያኔ አንቀፅ 39 ያተረፍነው – ትምህርት እና በተግባር የተፈተነ የሙያ ብቃት ሳይሆን ከዚህ ከዚያ ዘር መምጣት… እናም ስለ ዲግሪው ሴንቸሪ ዩንቨርሲቲ ይጨነቅበት።

ዶክተሬት በፖሰታ ልኬልሀለሁ
የድሮ ስምህን ደልዠዋለሁ…. አጅሬ ዶክ…

The post ማስተርስ/ዶክተሬት እንደ መለዋወጫ እቃ! (ታሪኩ አባዳማ) appeared first on Zehabesha Amharic.

አፈረች ዲያቆን –ቀስቶ ወተረ

$
0
0

daniel-kibret-300x207ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በሰባኪነት የታወቀ እንደ ሆነ ይነገርለታል ። በአንድ ወቅት እዚህ አሜሪካ ሳሉ የአሁኑ የአዲስ አበባው መንግሥት ሹመኛ የሆኑ አባ ማርቆስ ፥ ያገለግሉበት ከነበረው ቤተ ክርስቲያን የነበሩ ወጣት ክርስቲያኖች ፥ ዲያቆን ዳንኤል መጥቶ ማስተማር አለበት እያሉ ያስቸግሯቸውና ይጋበዛል ። ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ለማስተማር መዘጋጀቱን እንጂ ከዚያ ያለፈ ነገር አለ ብሎ አላሰበም ። ካህኑ በል ነገ የምታስተምረው አንተ ስለ ሆነክ ፥ ቀደም ብለህ መጥተህ በዲቁና ቀድሰህ ታስተምራለህ ይሉታል ። ዳኒ ትንሽ ያቅማማል ። አሁንም ይጫኑታል አይ ቅዳሴ እንኳን አልችልም ይላል ። በዚህ ጊዜ “አፈረች ዲያቆን” ታዲያ የዲቁና ቅዳሴ ሳትችል በየት አልፈህ አስተማሪ ሆንክ በማለት “አፈረች ዲያቆን” ብለው ተርተውበታል ። -–[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ—–

The post አፈረች ዲያቆን – ቀስቶ ወተረ appeared first on Zehabesha Amharic.

የቴሌቭዥን ድራማዎች በስድስተኛውም የስሜት ህዋሳችንም መቃኘቱን አንርሳ; የትኞቹ ያስተምራሉ? የትኞቹ መታረም ይፈልጋሉ? ”ቤቶች”እና ”ሞጋቾች”ድራማ

$
0
0

Mogachoch
(የጉዳያችን አጭር ማስታወሻ)

ከጌታቸው በቀለ

በቴሌቭዥን የሚተላለፉ መርሐ ግብሮች አነሰም በዛም በሕዝብ ላይ የሚፈጥሩት የእረጅም ጊዜ ተፅኖ ቀላል አይደለም።በተለይ በታዳጊ ወጣቶች እና ልጆች ላይ ለነገ እነርሱነታቸው የሚጭረው ስሜትም ሆነ አለማቸውን እና አካባቢያቸውን የሚመለከቱበት ዕይታ የጠበበ አልያም የሰፋ ወይንም የተንሸዋረረ የመሆን እድሉ ትልቅ ነው።እዚህ ላይ ወላጆች ለልጆቻቸው ከቴሌቭዥን መርሃ ግብር በኃላ የሚሰጡት የማስተካከያ ሃሳብ ወይንም ልጆችም ሆኑ ወጣቶች ጉዳዩን የሚያዩበትን እይታ ቀላል አይደለም።

የኢትዮጵያ ተለቭዥንን በሀገር ውስጥ የመረጃ ምንጭነት ተአማኒነቱ የወረደበትን ደረጃ ለመግለፅ ህዝቡ ”የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እውነት የምናገረው ሰዓት ብቻ ነው” የሚለውን አባባል መግለፁ ብቻ በቂ ነው።ከግማሽ ክ/ዘመን በላይ በመገናኛ ብዙሃንነት የቆየ የቴሌቭዥን ጣብያ በእዚህ አይነት ደረጃ የወረደ የመረጃ ምንጭ መሆኑ እንደ ኢትዮጵያዊነት በጣም ያሳዝና።ዛሬ ቢልልን ኖሮ ኢቲቪ በመላው ዓለም ባሉ ከተሞች ወኪሎች በኖሩት እና በቀጥታ የሚዘግቡ ዘጋቢዎች በኖሩት ነበር። ይህ ደግሞ ከወጭም አንፃር ብዙ አለነበረም።ምክንያቱም በመላው ዓለም እንደመበተናችን በነፃ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ማግኘት ከባድ አይደለም።ነገር ግን አለመታደል ሆኖ አምባገንነት፣ጎሰኝነት እና ሙስና መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደጠረነፈ ሁሉ የኢትዮጵያ ቴሌቭዝንም አንዱ ሰለባ ነው።ኢትዮጵያውያን ግን በሀገር ቤት የታፈነ ድምፃቸውን በቸልታ አላዩትም።በጥቂቶች አስተባባሪነት የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን በመላው ዓለም እና በሀገር ቤት ላሉ ወገኖቻችን ብቸኛው ነፃ የመገናኛ ብዙሃን ለመሆን በቅቷል።

የእዚህ አጭር ማስታወሻ አላማ ስለ ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ታሪክ ለማውራት አይደለም።ስለሚያቀርባቸው ሳምንታዊ ድራማዎች ግን ትንሽ ማለት ፈለኩ።የቴሌቭዥን ድራማዎቹን ምግብ እየበላሁም ሆነ መንገድ ላይ ባለኝ ክፍት ጊዜ እመለከታቸዋለሁ።ይህንን የማደርገው መዝናኛ ስለሆኑ ብቻ ሳይሆን አሁን ያለውን የሀገር ቤትን ማኅበራዊ፣ስነ-ልቦናዊ፣ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ሁኔታ ስለሚያንፀባርቁልኝ ነው።የድራማዎቹን የመሃል እንቡጥ መልእክት ፈልፍላችሁ ለማግኘት ስትሞክሩ (በስድስተኛው የስሜት ህዋስ ማለቴ ነው) ብዙ ጠቃሚ እና ጎጂ ጎኖቹን ለማየት አያስቸግራችሁም።
በስድስተኛው የስሜት ህዋስ የሶስቱ ድራማዎች እይታ

እዚህ ላይ በቴሌቭዥን ከሚቀርቡት ድራማዎች ውስጥ የሁለቱ ማለትም ”ቤቶች” እና ”ሞጋቾች” ላይ የማነሰው የጠለቀ ሂስ አለመሆኑን እና ያንን ለማድረግ የሙያው ክህሎት እንደሌለኝ ለመግለፅ እፈልጋለሁ።ነገር ግን ድራማዎቹ በህብረተሰባችን ላይ ያላቸው አሉታዊ እና በጎ ተፅኖ ላይ ሃሳብ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
1/ ”ቤቶች” ድራማ

ይህ በየሳምንቱ ቅዳሜ ምሽት የሚቀርበው ድራማ በብዙዎች ዘንድ በአስቂኝነቱ የሚጠቀስ እና በርካታ ተመልካች ያለው መሆኑ ይታወቃል።አመታዊ ዝግጅቱን ሲያዘጋጅም የሚመለከቱት ተመልካቾች በርካታ መሆናቸውን ያሳያል።እንደ እኔ አስተያየት ድራማው ከማዝናናት ባለፈ ሊያስተምር የሚገባው በርካታ ነገሮች ይቀሩታል።በመጀመርያ ደረጃ ታሪኩ አንድ በግንብ በታጠረ ቪላ ቤት ውስጥ የሚኖር ቤተሰብ ዙርያ ያጠነጥናል።ቤተሰቡን መካከለኛ ገቢ ያለው ቤተሰብ ለማለት ይከብደኛል።ምክንያቱም መካከለኛ ገቢ የሚባለው ሕብረተሰብ አሁን በራሱ ጠፍቷል።ከሃያ ሶስት አመታት በፊት አንድ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር መሬት ተመርቶ ቤት የመስራት አቅም ነበረው።ዛሬ ቤት ለመስራት ከፍተኛ ገቢ ካላቸው ውስጥ የሚመደብ ካልሆነ አይታሰብም።እናም ድራማው ውስጥ የሚተውኑት ቤተሰብ አባላት ቢያንስ ባለ ሁለት ሰራተኛ እና አንድ የጥበቃ ግለሰብ የሚተዳደሩ ናቸው እና መካከለኛ ከሚለው እናውጣቸው።እዚህ ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከ95% በላይ በእንደዚህ አይነት ኑሮ የሚኖር አይደለም።አዲስ አበባ ብቻ የግል መፀዳጃ የሌለው የሕዝብ ብዛት ከ70% በላይ እንደሆነ ከተገለጠ እሩቅ አይደለም።በመሆኑም ድራማው ተጨባጩን የሀገራችንን ሕዝብ ኑሮ አይወክልም።ይህ ግን ድራማውን ያስወቅሰዋል እያልኩ አይደለም።ጥቂቶችም ብዙሃኑ ግብር በሚከፍልበት ቴሌቭዥን እርስ በርስ ሲጨዋወቱ መመልከት በራሱ ድራማ ነውና።
Tilahun Gugsa
በእዚህ ድራማ ላይ ”ይቤ” ገፀ ባህሪ ይዞ የሚጫወተው ወጣት የዩንቨርስቲ ተማሪ ለወጣቱ ምን ያስተምራል? ብዬ ስጠይቅ በገፀ ባህሩ ላይ ባብዛኛው አሁን በዘመነ ኢህአዲግ/ወያኔ አንድ የዩንቨርስቲ ተማሪ የሚኖረውን መልክ ይዞ ታገኙታላችሁ።ይቤ በድራማው ላይ ይጠጣል፣ይቅማል፣የተለያዩ የሴት ወዳጆች አሉት፣የሚናገረው የተደበላለቀ ማለትም ”ከአራዳ አነጋገር” እስከ እንግሊዝኛ የተደባለቁ፣ኢትዮጵያዊነት በሙሉ የጠፉበት ሆኖ እናገኘዋለን።በነገራችን ላይ ይቤ መሃንዲስ ነው እና የነገ ኢንጅነሮቻችን የሚቅሙ፣የሚያጨሱ ናቸው በመሆኑም መስርያቤቶች ከመሃንድሶች ጋር ሲሰበሰቡ የጫት በጀት መያዝ አለባቸው ማለት ነው።

ቤቶች ድራማ ሶስት መስተካከል ነበረባቸው የምላቸው አቀራረብ አይቼበታለሁ

የመጀመርያው በቅርቡ የታየው ነው ታሪኩ እንዲህ ነው።ሁለቱ የቤት ሰራተኞች ቡና እያፈሉ ሳሉ የቤት ጠባቂው ዘበኛ ያገኘውን ዱቄት መሰል ነገር ፍሙ ላይ ሲጨምሩት እና በቤቱ ውስጥ የነበሩት በሙሉ ሲሰክሩ ያሳያል።እንደ ድራማው አገላለፅ ለካ የጨሰው አደገኛ ዕፅ ነበር።ሙሉ ድራማው በወቅቱ ቀጥሎ ያሳየን ነገር ቢኖር አንድ እፅ የወሰደ ሰው ምን እንደሚታየው፣ለምሳሌ ድመት ዘንዶ እንደሚመስለው፣ሰዎች ትልቅ ሆነው እንደምታዩት በተግባር እያሳየ ትውልዱን አሰለጠነ።የሚገርመው ድራማው የእፅን አስከፊነት ሳይሆን አዝናኝነት ነው እስኪበቃን የነገረን።እፅ ያጨሱት በፖሊስ ሲያዙ እና ሲቀጡ ሳይሆን የአደገኛ እፅን አዝናኝነት ለታዳጊ ወጣት ሁሉ ተነገረው።ይህንን የተመለከተ ወጣት ”አንድ ቀን ልሞክረው” እንዲል አድረገው አቀረቡለት።ይህ ክፍል ከታየ ገና ወራት አልተቆተሩም።በአድዋ በዓል ላይ ሸለላችሁ ብሎ ያገደ ፖሊስ ያለው መንግስት በተለቭዝኑ የእፅ አወሳሰድ ስልጠና ሲሰጥ ማየት ያሳምማል።

ሁለተኛው፣ ቤተሰቡ ለሽርሽር ከሄደባቸው ቦታዎች አንዱ ቅዱስ ላሊበላን ያሳየናል።በቅዱስ ላሊበላ ቅፅር ውስጥ በአካል ቤተሰቡ ቆሞ የሚሰጠውን ገለፃ ያዳምጣል።በእምነት ቦታ በመሰረቱ የቀልድ ድራማ መስራት አስቸጋሪ ነው።ድራማው ላይ ግን ሃይማኖታውም ሆነ ታሪካዊ ገለፃ ሲሰጥ በመሃል የፌዝ እና የቀልድ ንግግሮች ይሰሙ ነበር።ይህ እንግዲህ በመሃል ከሚገባው የሳቅ ጋጋታ ጋር አብሮ ነው።የእምነት ቦታዎች የሚሰጣቸው ቦታ እና በአማኙ ዘንድም ሆነ በታዳጊ እና ወጣቶች ዘንድ የሚያሳድረው ተፅኖ ፈፅሞ አልተጤነም።ቅዱስ ላሊበላ ከመጎብኘቱ ባለፈ የከበረ ቀልድ የማይነገርበት ቦታ መሆኑን ማሰብ ተገቢ ነበር።በሌላ በኩል ግን የድራማው አላማ ሀገርህን እወቅ በሁሉም ቤተሰብ መለመድ አለበት የሚለውን ሃሳብ በማንፀባረቁ የሚደገፍ አይደለም እያልኩ አይደለም።ለእምነት ቦታዎች የማይባሉ ቀልዶች ቀላቀለበት እንጂ።

ሶስተኛው የድራማው አቀራረብ የገጠሩን የሀገራችንን ገበሬ ለከተማው ወጣት የሚስልበት የተሳሳተ አቀራረብ ነው።የቤቱ ዘበኛ ሁል ጊዜ እንቅልፍ በጣም ወዳጅ፣ምግብ የሚወድ፣ሥራ የማይወድ እና ግዴለሽ አድርጎ የሚስልበት ገፀ ባህሪ የኢትዮጵያን ገበሬ ፈፅሞ አይወክልም።የኢትዮጵያ ገበሬ እንቅልፍ የለውም ከማለዳ እስከ ምሽት ሲለፋ ውሎ ማታ የቀረውን ሥራ በመስራት የሚጠመድ፣ንቁ፣በሥራ የሚያምን፣ላመነበት የሚሞት እና ለወዳጁ ሟች ነው።ይህንን የህብረተሰብ ክፍል ነው እንግዲህ ለሕዝቡ ”ሎሽ ማለት ብቻ የሚወድ” ተብሎ የሚቀርበው።ይህ በእራሱ ከቀልድ ባለፈ ብዙ ማህበራዊ ነገሮችን የሚነካ ነው።በኮሜዲ ፊልሞች ላይ ገፀ ባህርያት የተለያዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን እያነሱ ያስተምራሉ እንጂ በኢትዮጵያ ገበሬ ላይ የሚሳለቅ አቀራረብ ይዘው እና ከገበሬው የምንማረው እንቅልፍ ብቻ የመሰለ አቀራረብ ማንንም አይጠቅምም።

እዚህ ላይ የቤቶች ድራማን አንዳንድ ግድፈቶች እና ማስተካከል የሚገባቸውን አቀራረቦች ላይ ሃሳብ ለመስጠት ፍለግሁ እንጂ በደፈናው ድራማውን ለማጣጣል እንዳልተነሳሁ ይታወቅልኝ።ድራማ ከአዝናኝነቱ ባለፈ ወጣቶችን በስነ-ምግባር፣በሀገር ፍቅር ስሜት እና በቅን ለሀገር መስራትን የሚያስተምር ካልሆነ በሳቅ ማንከትከትን ብቻ አላማዬ ብሎ ከተነሳ ስለ እፅ አወሳሰድ የሚያሰለጥነን ከሆነ አደገኛ ነው።ላሰምርበት የምፈልገው ለሕዝብ የሚቀርቡ ድራማዎች በተለያየ ሙያ ላይ ያሉ አማካሪዎች ያስፈልጋቸዋል።ደራሲው ”ህዝብን ካሳቀ እና መንግስትን እስካላሳቀቀ ድረስ መንገዱ ሰላም ነው” በሚል አስተሳሰብ ብቻ አየር ላይ ማዋል የለበትም።

”ሞጋቾች” ድራማ

ከእዚህ በአንፃሩ በ”ኢቢኤስ”ቴሌቭዥን የሚቀርበው ”ሞጋቾች” የተሰኘው ድራማ ጥሩ፣አስተማሪ እና ትውልድን የሚያንፅ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።ሞጋቾች በአንድ ሆስፒታል ውስጥ የሚሰሩ የህክምና ዶክተሮች እንዴት ህዝባቸውን በታማኝነት እንደሚያገለግሉ እና በማህበራዊ ኑሮአቸው ውስጥ የሚገጥማቸውን ተግዳሮት ያሳያል።የሞጋቾች ድራማ በፊልም አቀራረፅ እና የድምፅ ጥራቱ ብቻ ሳይሆን የመረጡት ሆስፒታል ተራው ሕዝብ የሚገለገልበትን እና እታች ያለው ሕዝብ የሚላቸውን አባባሎች፣ስሜቶችን ሁሉ የሚያንፀባርቅ አቀራረብ ይታይበታል።እዚህ ላይ ማስታወሻዬ አጭር ከመሆኑ አንፃር ባጭሩ ”ሞጋቾች”ድራማ ሶስት ነገሮችን ለአዲሱ ትውልድ እንደሚያስተምር ጠቅሼ ሃሳቤን ልግታ።

1/ ተምሮ በሀገር መስራትን እና ወገንን ማገልገልን
በድራማው ብዙ ክፍሎች ላይ የሚታዩት አቀራረቦች በዶክተር ደረጃ ያሉ የህክምና ባለሙያዎች ምን ያህል እታች ላለው ሕዝብ እንደሚጨነቁ እና ኃላፊነት እንደሚሰማቸው ያሳያል።

2/ የዩንቨርስቲ ሴት ተማሪዎች ጥንቁቅ እንዲሆኑ ይመክራል
የድራማው ዋና ገፀ ባህሪ በአንድ ወቅት የዩንቨርስቲ ተማሪ ሆና ሳላ አንድ ምሽት በተፈጠረ የምሽት ዳንስ ይመሽባትና ከሰው ቤት ታድራለች።ሆኖም በእዚችው ምሽት ተደፍራ ልጅ ትወልዳለች።ድራማው ባብዛኛው የወለደቻትን ልጅ አባት በመፈለግ ስትደክም ያሳያል።ይህ አሁን ላሉት ወጣቶች እያንዳንዱ ምሽት የምትሰራ ስህተት እና ከዋልጌ ተማሪዎች ጋር መግጠም የሚያስከፍለው ዋጋ ለአመታት የሚተርፍ መሆኑን ያሳያል።ይህም በተለይ ሴት ወጣቶች ጥንቁቅ እንዲሆኑ ይመክራል።

3/ በአንድ ወቅት ችግር ቢያጋጥምም መልሶ መነሳት እንደሚቻል ያስተምራል
የድራማው ዋና ገፀ ባህሪ ባንድ ወቅት ተደፍራ ልጅ ለመውለድ ተገደደች።ሆኖም ተመልሳ ጠንክራ በመማሯ ዛሬ ለህክምና ዶክተርነት በቃች።ይህ በራሱ የሚያስተምረው ትምህርት አለ።ወጣቶች ስህተት ላይ ሊወድቁ ይችላሉ ግን ከስህተታቸው ተመልሰው እንደገና ተነስቶ ለቁም ነገር መብቃት ነው ዋናው ቁም ነገር ይለናል የድራማው መልእክት።

ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ድራማዎች የረቀቀ የፕሮፓጋንዳ መስርያ አውድማ ወይንም የተበላሸ ትውልድ ማፍርያ ማሽን እንዳይሆኑ በስድስተኛውም የስሜት ህዋሳችንም መቃኘቱን አንርሳ።

ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
የካቲት 26/2007 ዓም (ማርች 5/2015)

The post የቴሌቭዥን ድራማዎች በስድስተኛውም የስሜት ህዋሳችንም መቃኘቱን አንርሳ; የትኞቹ ያስተምራሉ? የትኞቹ መታረም ይፈልጋሉ? ”ቤቶች” እና ”ሞጋቾች” ድራማ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአባይ ግድብ በግብጽ ፍላጎት ላይ ተመስርቶ መገንባቱ ወያኔ ምን ያህል አጣብቂኝ ውስጥ እንደገባ ያሳያል

$
0
0

Blue Nile 2
(ምንሊክ ሳልሳዊ) የአባይም ግድብ እንደ ባድመ ድል ለጭፈራ አቀባብሎ እንዳይሰጠን .. መቸም ወያኔ በሰው መቀለድ ለምዷል::የአባይ ቦንድ የገዛህ የገዛሽ ሁሉ ነገሮች ሁሉ ባዶ ጭብጨባ ሆነዋል:: ለሕዝብ የማይጨነቀው ወያኔ በኢኮኖሚ ከደቀቀው የመንግስት ሰራተኘው ጀምሮ እስከ ጎንበስ ቀና ብሎ ደክሞ እስከሚሰራው ምስኪን ኢትዮጵያዊ ድረስ በአባይ ቦንድ ስም ከፍተኛ ገንዘብ ሲሰበስብ ቆይቷል::በውጪዉም አለም ቦንድ ለመሸጥ ቢዘምትም ሳይሳካለት ቀርቷል::ሻእቢያ እና በአከባቢው ያሉ ጉዳዮች ወያኔን ውጥረት ውስጥ ጨምረውታል::ይህ የትግሉ አንድ አካል የሆነ የድል ጥርጊያ መንገድ ለፖለቲካ ድል ልንጠቀምበት ይገባል::የአባይ ግድብ ትከትሎ የመልስን መሞት አስታኮ ግለሰቡን አባይን የደፈረ መሪ በማለት እስከማላዘን ተደርሷል::የቅርብ ጊዜ ታሪክ እንደሚያሳየን ከሆነ የኢትዮጵያ የመጨረሻእ ንጉስ ሃይለስላሴ አባይን ለመገደን ይህንኑ የግድብ ዲዛይን አሰርተው ነው ዲዛይኑ በገንዘብ ኖቶች ላይ ሳይቀር ታትሟል; በጊዜው..ወያኔ ያንን ዲዛይን በዘመናዊ መሃንዲሶች አሻሻለው እንጂ አዲስ ነገር አልፈጠረም::

አሁን እየሰማንው ያለነው ደሞ አባይ የሚገደበው ሱዳን እና ግብጽ በፈለጉት መንገድ መሆኑ እየተነገረን ነው:: አስቀድመን እንደተናገርነው የህዝብ መብቶች ሳይረጋገጡ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሳይገደቡ ህዝብን በግዳጅ ከጉሮሮው በቦንድ ስም እየነጠቁ ሕዝብ ያተዋጠለትን ሕዝብን ያላሳተፈ ግድብ እገነባለሁ ብሎ መነሳት ከባት የፖለቲካ ኪሳራ ያስከትላል ይህንንም ኪሳራ እያየነው ነው::ወያኔ ከሱ በላይ አዋቂ እና ከሱ በላይ ልሃገር ለህዝብ ጠበቃ የልማት ቡድን አድርጎ ቢንጠራራም ራሷን ከፍ ከፍ ያደረገች ማሽላ አንድም ለወንጭፍ አንድም ለውፍ .. የሚለውን ያስታውሰናል::
ወያኔ የሰበሰበው ቦንድ ለንግድ ድርጅቶቹ ካፒታል ማሳደጊያ ካደረገው በኋላ እየተሰራ ያለው ስራ ሁሉ በእኩይነት የተከበበ ከመሆኑም ባሻገር በውስጡ ያለውን መፈረካከስ ሙስና እና የፓርቲ ካድሬዎች መበስበስ እንዲሁም የተቃዋሚው ጎራ መጠናከር በጣም ስላሰጋው በተጨማሪም የኤርትራ ጋር ያለው አለመግባባት እየሰፋ መምጣቱ በአባይ ግድብ ላይ ያለው ልፍስፍስ አቋሙ የባሰ ሽባ በመሆኑ እጁን ለግብጽ እና ሱዳን እንዲሰጥ ተገዷል::ከኤርትራ ጋር ጦርነት ብንገጥም ሱዳን እና ግብጽ በተዝዋዋሪ ሊያጠቁን ይችላሉ የሚለው የወያኔ ጭንቀት እንዲሁም ለአባይ ግድብ ያሰበው ሁሉ ሳይሳካ በባዶ ስላስቀረው በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ የገነባው ኢኮኖሚም በባዶ ካዝና ስለቀረ መጣፊያው ያጠረው ወያኔ አጣብቂኝ ውስጥ በመግባቱ የአባይን ግድብ ለግብጽ እና ሱዳን አስረክቧል::አሁንም የኢትዮጵያውያን ጥያቄ ከአባይ ግድብ በፊት የሰብአዊ መብት ጥሰት ይገደብ::የሰባዊ መብት እና የህዝቦች ነጻነት ባሌለበት አገር በልማት ስም ራስን መቆለል እንደምናየው ውርደቱ በአደባባይ ያጋልጣል::ኢትዮጵያውያን ወሳኝ ወቅት ላይ መሆናችንን አውቀን በወያኔ መቃብር ላይ ነጻነታችንን ማረጋገጥ አለብን:

The post የአባይ ግድብ በግብጽ ፍላጎት ላይ ተመስርቶ መገንባቱ ወያኔ ምን ያህል አጣብቂኝ ውስጥ እንደገባ ያሳያል appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 8745 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>